reporter issue 1229

36
|ገጽ 1 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004 FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPIRIT ነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ ጥር 30 ቀን 2004 የረቡዕ እትም ቅፅ 17 ቁጥር 22/ 1229| አዲስ አበባ ኢትዮጵያ | ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ |ዋጋ ብር 7.00 በውስጥ ገጽ 2 ወደ ገጽ ዞሯል 33 እንደ ሸንበቆ ወጥቶ እንደ ሙቀጫ አልንከባለል ያለው የኑሮ ውድነት በውድነህ ዘነበ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባለፈው እሑድ ባካሄደው ስብሰባ፣ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ የዜጎችን ሀብት የማፍራት መብት የሚፃረር በመሆኑ እንዲሻር ጠየቀ:: ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው እየሩሳሌም ሆቴል በተካሄደው የግማሽ ቀን ስብሰባ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል:: ጥናቱን ያቀረቡት የፓርቲው የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ ኢነጂነር ዘለቀ ረዲና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው:: ሁለቱም ጽሑፍ አቅራቢዎች አዋጁ ሕገ መንግሥቱን የሚፃረርና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት የሚጋፋ ብለውታል:: ኢንጂነር ዘለቀ ባቀረቡት ጽሑፍ ሕገ መንግሥቱ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ነው አንድነት ፓርቲ የሊዝ አዋጁ እንዲሻር ጠየቀ ወደ ገጽ ዞሯል 4 በታምሩ ጽጌ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በደቡብ ክልል በስድስት ወረዳዎችና በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የታሰሩበት 112 አመራሮችና አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ መንግሥትን ጠየቀ:: በደቡብ ክልል በደንባ ጎፋ ወረዳ፣ በዛላ ወረዳ፣ በአይዳ ወረዳ፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ በአባ ደብረ ፀሐይ ወረዳና በኦባ ወረዳ ከጥር 14 ቀን መኢአድ የታሰሩ 112 አመራሮቹና አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ ‹‹በአባሎቻችን ላይ እየጨመረ የመጣው እስራት አሳስቦናል›› ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘው የአልቃይዳ ሕዋስ ለሕዝብ ይፋ ሊደረግ ነው በታምሩ ጽጌ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተደራጅቶ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ በብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተነገረለት የአልቃይዳ ሕዋስ፣ ሰሞኑን ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል:: ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የግብረ ኃይሉ አባል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሽብሩን ለመፍጠር ሲንቀሳቀስ የነበረው ሕዋስ በሶማሊያ ውስጥ ካሉት የአልሸባብና የአልቃይዳ አሸባሪ ቡድኖች፣ በኬንያ፣ በሱዳን፣ በፊሊፒንስ፣ በሳዑዲ ዓረቢያና በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ካሉ የአልቃይዳ ሕዋሶች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተረጋግጧል:: አንዳንድ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ቀናት ውስጥ ተጠናቀው የአሸባሪ ሕዋሱ ማንነት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የገለጹት የግብረ ኃይሉ አባል፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተሰሙ ካሉ አላስፈላጊና ውዥንብር ፈጣሪ አሉባልታዎች ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል:: ከትናንት በስቲያ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ባወጣው አጭር መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአሸባሪው የአልቃይዳ ድርጅት ውስጥ አባል የሆኑና ኢትዮጵያ ውስጥ በመደራጀት ሽብር ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል:: እንደ ግብረ ኃይሉ ገለጻ፣ ተጠርጣሪዎቹ ዜጎችን ለማደራጀት፣ ለመመልመልና ለሥልጠና ለማዘጋጀት ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው የአልቃይዳ ቡድን ዕርዳታ እየተደረገላቸው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ታስረዋል:: አልቃይዳ ዓለም አቀፍ መሠረት ያለው የአሸባሪዎች ቡድን ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ1988 መጨረሻ አካባቢ በቅርቡ በአሜሪካ ኮማንዶዎች ፓኪስታን ውስጥ በተገደለው በኦሳማ ቢን ላደን መደራጀቱ ይታወቃል:: የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት አልሸባብን፣ አልቃይዳንና ሦስት የኢትዮጵያ ድርጅቶችን በሽብርተኝነት መሰየሙ ይታወሳል:: ፎቶ በሪፖርተር/ፋይል የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉና የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

Upload: sombremato

Post on 01-Dec-2014

341 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

Page 1: Reporter Issue 1229

|ገጽ 1 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com FREE PRESS FREE SPEECH FREE SPIRITነፃ ፕሬስ ነፃ ሐሳብ ነፃ መንፈስ

ጥር 30 ቀን 2004

የረቡዕ እትም

ቅፅ 17 ቁጥር 22/ 1229| አዲስ አበባ ኢትዮጵያ | ጳጉሜን 6 ቀን 1987 ተመሠረተ |ዋጋ ብር 7.00

በውስጥ

ገጽ 2

ወደ ገጽ ዞሯል33

እንደ ሸንበቆ ወጥቶ እንደ ሙቀጫ አልንከባለል ያለው

የኑሮ ውድነት

በውድነህ ዘነበ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባለፈው እሑድ ባካሄደው ስብሰባ፣ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ የዜጎችን ሀብት የማፍራት መብት የሚፃረር በመሆኑ እንዲሻር ጠየቀ::

ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው እየሩሳሌም ሆቴል በተካሄደው የግማሽ ቀን ስብሰባ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል:: ጥናቱን ያቀረቡት የፓርቲው የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ ኢነጂነር ዘለቀ ረዲና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው:: ሁለቱም ጽሑፍ

አቅራቢዎች አዋጁ ሕገ መንግሥቱን የሚፃረርና የዜጎችን ንብረት የማፍራት መብት የሚጋፋ ብለውታል::

ኢንጂነር ዘለቀ ባቀረቡት ጽሑፍ ሕገ መንግሥቱ መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ነው

አንድነት ፓርቲ የሊዝ አዋጁ እንዲሻር ጠየቀ

ወደ ገጽ ዞሯል4

በታምሩ ጽጌ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በደቡብ ክልል በስድስት ወረዳዎችና በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የታሰሩበት 112 አመራሮችና አባላት

በአስቸኳይ እንዲፈቱ መንግሥትን ጠየቀ::በደቡብ ክልል በደንባ ጎፋ ወረዳ፣ በዛላ

ወረዳ፣ በአይዳ ወረዳ፣ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ በአባ ደብረ ፀሐይ ወረዳና በኦባ ወረዳ ከጥር 14 ቀን

መኢአድ የታሰሩ 112 አመራሮቹና አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠየቀ

‹‹በአባሎቻችን ላይ እየጨመረ የመጣው እስራት አሳስቦናል››ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

ኢትዮጵያ ውስጥ የተያዘው የአልቃይዳ ሕዋስ ለሕዝብ ይፋ ሊደረግ ነው በታምሩ ጽጌ

ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተደራጅቶ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ በብሔራዊ መረጃ ደኅንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተነገረለት የአልቃይዳ ሕዋስ፣ ሰሞኑን ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል::

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የግብረ ኃይሉ አባል ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ሽብሩን ለመፍጠር ሲንቀሳቀስ የነበረው ሕዋስ በሶማሊያ ውስጥ ካሉት የአልሸባብና የአልቃይዳ አሸባሪ ቡድኖች፣ በኬንያ፣ በሱዳን፣ በፊሊፒንስ፣ በሳዑዲ ዓረቢያና በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ካሉ የአልቃይዳ ሕዋሶች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተረጋግጧል::

አንዳንድ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ቀናት ውስጥ ተጠናቀው የአሸባሪ ሕዋሱ ማንነት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የገለጹት የግብረ ኃይሉ አባል፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተሰሙ ካሉ አላስፈላጊና ውዥንብር ፈጣሪ አሉባልታዎች ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ አሳስበዋል::

ከትናንት በስቲያ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ባወጣው አጭር መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በአሸባሪው የአልቃይዳ ድርጅት ውስጥ አባል የሆኑና ኢትዮጵያ ውስጥ በመደራጀት ሽብር ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ የተደረሰባቸው ስምንት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል::

እንደ ግብረ ኃይሉ ገለጻ፣ ተጠርጣሪዎቹ ዜጎችን ለማደራጀት፣ ለመመልመልና ለሥልጠና ለማዘጋጀት ምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው የአልቃይዳ ቡድን ዕርዳታ እየተደረገላቸው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ታስረዋል:: አልቃይዳ ዓለም አቀፍ መሠረት ያለው የአሸባሪዎች ቡድን ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ1988 መጨረሻ አካባቢ በቅርቡ በአሜሪካ ኮማንዶዎች ፓኪስታን ውስጥ በተገደለው በኦሳማ ቢን ላደን መደራጀቱ ይታወቃል::

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ዓመት አልሸባብን፣ አልቃይዳንና ሦስት የኢትዮጵያ ድርጅቶችን በሽብርተኝነት መሰየሙ ይታወሳል::

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ፋይል

የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉና የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲ

ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል

Page 2: Reporter Issue 1229

በጳጉሜን 6 1987 ተጀመረ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተም አድራሻ፡- ከቦሌ መድኃኒዓለም ወደ ብራስ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ከቦሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል አጠገብ ስልክ 0910-885206/ 011-661 61 79/85/87/011-8614339 ፋክስ: 011-661 61 89

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 03 የቤት ቁጥር 2347 ፖስታ 7023 አ.አ ኢትዮጵያ

ማስታወቂያ ሽያጭና ስርጭት 0910 885206/ 011 6 61 61 79/ 85

[email protected] E-mail: [email protected]

Website: www.ethiopianreporter.com

ዋና ሥራ አስኪያጅ፡ አማረ አረጋዊዋና አዘጋጅ፡ መላኩ ደምሴአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 13/14 የቤት ቁ. 481ምክትል ዋና አዘጋጅ፡ ዘካሪያስ ስንታየሁከፍተኛ አዘጋጅ፡ ዳዊት ታዬ አዘጋጆች፡ ሔኖክ ያሬድ ጌታቸው ንጋቱ

ምሕረት ሞገስ ኃይሌ ሙሉ

ረዳት አዘጋጆች፡ ታደሰ ገ/ማርያም ምሕረት አስቻለው ታምሩ ጽጌ የማነ ናግሽ

ዋና ግራፊክ ዲዛይነር፡ ይበቃል ጌታሁንከፍተኛ ግራፊክ ዲዛይነር፡ ቴዎድሮስ ክብካብግራፊክ ዲዛይነሮች፡ ፀሐይ ታደሰ ፋሲካ ባልቻ እንዳለ ሰሎሞን ስሜነህ ሲሳይ ቢኒያም ግርማ ነፃነት ያዕቆብ ቤዛዬ ቴዎድሮስ

ዋና ፎቶ ግራፈር ናሆም ተሰፋዬፎቶ ግራፈሮች፡ ታምራት ጌታቸው መስፍን ሰሎሞን

ካርቱኒስት፡ ኤልያስ አረዳ

በሚዲያና ኮምዩኒኬሽንስ ሴንተር (ኤም.ሲ.ሲ) ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር

እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ

ረቡዕ ጥር 30 ቀን 2004

ርእሰ አንቀጽ

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡ ደረጀ ጠገናው ብርሃኑ ፈቃደ ውድነህ ዘነበሪፖርተሮች፡ ምዕራፍ ብርሃኔ፣ እስከዳር አስማረማርኬቲንግ ማናጀር፡ እንዳልካቸው ይማምሴልስ፡ ቤዛዊት ፀጋዬ' Hና Ó`T' w\¡ S<K<Ñ@�' IK=ና ከuደ፣ ብሩክ ቸርነትማስታወቂያ ፕሩፍሪደር፡መሳይ ሰይፉ፤ ኤፍሬም ገ/መስቀል፤ ዳዊት ወርቁኮምፒውተር ጽሑፍ፡ ብርቱካን አባተ፣ ሄለን ይታየው፣ አፀደ ካሳዬ፣ ፍሬሕይወት ተሰማ፣ ገነት ፀሀይማስታወቂያ ፅሁፍ እስከዳር ደጀኔ፣ ብፅአት ተረፈ መሠረት ወንድሙ፣ ራሔል ሻወልሕትመት ክትትል፡ ተስፋዬ መንገሻ፣ የየሱስወርቅ ማሞ፣ ገዛኸኝ ማንደፍሮዌብ ሳይት፡ ቤዛዊት ተስፋዬ፣ ቢኒያም ሐይሉ

እንደ ሸንበቆ ወጥቶ እንደ ሙቀጫ አልንከባለል ያለው የኑሮ ውድነት

‹‹ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ›› የሚለውን ተረት እያስታወስን፣ የኑሮ ውድነቱ እንደ ሸንበቆ በየቀኑ ወደላይ ቢወጣም አንድ ቀን ይወርዳል፤ እንደ ሙቀጫም ይንከባለላል ብለን ጠብቀን ነበር:: እንደ ተረቱ ግን አልሆን አለ:: የኑሮ ውድነት እንደ ሸንበቆ ወጣ ወጣ እንጂ እንደ ሙቀጫ አልንከባለል ብሏል::

ኑሮ እየከበደ ነው:: በዝቅተኛና በመካከለኛ ደረጃ ያለውም የኅብረተሰባችን ክፍል ለዕለታዊ ኑሮ የሚያስፈልገውን መሠረታዊ ነገር ለመግዛት አቅም ባጣበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን::

እንዴት ነው ነገሩ; ሁሉም ነገር እየጨመረ ነው:: እውነት ሁሉም ጭማሪ ከውጭ ምንዛሪ ጋር የተያያዘ ነውን? እውነት ግሽበት ያስከተለው ነውን? እውነት ከነዳጅ ዋጋ የተያያዘ ነውን? ስግብግብነት ያስከተለው ነው ተብሎስ የሚታለፍ ነውን?

ዋናው መንግሥትን፣ ሌላ የሚመለከተው አካል ካለም እሱን፣ ኢኮኖሚስቶች የሚነገሩን ከሆነ ደግሞ እነሱን የምንጠይቀው ጥያቄ ግልጽ ነው:: የአቅርቦቶች ዋጋ በየቀኑ መናር ዋናውና ትክክለኛ ምክንያቱ ምንድን ነው?

ኑሮ መወደዱ ብቻ ሳይሆን ምክንያቱ በግልጽ በሚመለከተው አካል በየሁኔታው አለመነገሩና ሕዝቡ እንዲያውቀው አለመደረጉ ራሱን የቻለ ሌላ ችግር እየሆነ ነው:: ወቅታዊውና እውነተኛው ምክንያት ይነገረን::

መፍትሔውስ? ለኑሮ ውድነቱ በየቀኑ መናር መፍትሔው ምንድነው; አንድ ቀን ይወርድ ይሆናል እያሉ ብቻ በተስፋ መጠበቅ? በቂ የአገር ውስጥ ምርት ባይኖርም ለሞራል ‹‹በአገሬ ምርት እኮራለሁ›› እያሉ መዘመር; ወይስ በተጨባጭ መፍትሔ ሊሆን የሚችል ዕርምጃ ይኖራል;

ይህም ቢሆን ከመንግሥትም ከሚመለከተው አካልም ሊብራራልንና ሊነገረን ይገባል:: መፍትሔ አለው ወይ; አንዳንድ የዋጋ ማሻቀቦችና ጭማሪዎች ሊታወቁም ሊገመቱም ይችላሉ:: ከዓለም አቀፋዊ ሁኔታ፣ ከምንዛሪ ለውጥና ከነዳጅ ዋጋ ጋር ሊያያዙ ይችላሉ:: የንብረት ስም የማዛወር ክፍያ ከሁለት በመቶ ወደ 15 በመቶ አድጓል ሲባል ግን ከውጭ ምንዛሪና ከነዳጅ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም:: ምናልባት መንግሥት ለያዛቸው የልማት ዕቅዶች ተጨማሪ ገንዘብ ስላስፈለገው ነው ሊባል ይችላል:: ነገር ግን ግምታዊ ትንተና እንጂ ተጨባጭ ምክንያቱን የሚወስነው አካል ነው የሚያውቀው::

በአሁኑ ጊዜ አንዳንድ አስደንጋጭ ሁኔታዎች እየታዩ ናቸው:: አገር ለቀው በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች፣ በሱዳንና በሌላ አገር ለመሥራት እየተጓዙ ያሉት ወጣት ኢትዮጵያውያን ቁጥር የሚያስደነግጥ ነው:: የፓስፖርትና የቪዛ ክፍሎች ሥራ በእጅጉ ተደራርቦባቸዋል:: ሠልፉ ያስደነግጣል:: የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ፖሊሲና የእኛ አገር ፖሊሲ ስለተለወጠና ስለሚያበረታታ የተፈጠረ ዕድል ነው? ወይስ የኑሮ ውድነት የፈጠረው ችግር? ይህንንም በበቂ ሁኔታ ማጥናት ያስፈልጋል::

ደጋግመን የምንለው ነገር አለ:: በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ሁሌም ተቀራርቦ መወያየት ቢኖር ኖሮ ሕዝብም ምክንያቱን እያወቀ መረጋጋት ይችላል:: መንግሥትም ያለውን ችግር በተጨባጭ አሳውቆ የሕዝብ ትብብርም ሊያገኝ ይችላል:: ይህ ስለማይደረግ ግን መራራቅ መጠራጠርን እያስከተለ ይገኛል::

የኑሮ ውድነቱ ግን እያስከተለ ያለው የስደት ጎርፉን ብቻ አይደለም:: የወንጀል ብዛትንም ጭምር እንጂ:: የስርቆትና የዝርፊያ ወንጀል እየበዛ ነው:: በየመንገዱ ቀማኛዎች አሉ:: የማይደፈሩ ግቢዎች በዘራፊዎች እየተደፈሩ ናቸው:: ይህም አደገኛ ሁኔታ ብቻ ተብሎ የሚታለፍ ሳይሆን፣ ገንዘብ ያለው ወንጀለኛ ገንዘብና የሚበላው ያጣን ደሃ የሚቆጣጠርበት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል የሚያስብል ነው:: ወንጀሉም ግለሰባዊ መሆኑ ቀርቶ የተደራጀ ወደ መሆን ይሸጋገራል፤ እየተሸጋገረ እየታየም ነው::

የኑሮ ውድነት መናር ሙስናንም እያጠናከረ ነው:: ሙስና እየተስፋፋ ያለው የቅንጦት ኑሮ በሚፈልጉት ኃይሎች ብቻ አይደለም:: በዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ጠባቂዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ተላላኪዎችና የመሳሰሉት ተቀጥረው ለሚሠሩበት ሥራ ሳይቀር ጉቦ እየጠየቁ ነው:: ‘ስጡን እንጂ ደመወዝ ምን ይሸፍናል?’ ተብሎ በግልጽ የሚነገርበት ዘመን ላይ ደርሰናል::

በመሆኑም የኑሮ ውድነት ሊያስከትላቸው የሚችሉ ስደት፣ ሙስና፣ ሌሎች ወንጀሎች፣ የትምህርት ማቋረጥ፣ ለመጥፎ ባህል መዳረግ፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ትኩረትና መፍትሔ ያስፈልጋል::

ዋናው መፍትሔ በቂ ምርት ማምረት ነው:: የአገር ውስጥ አቅርቦትን ማሳደግ ነው:: ይህ ደግሞ የመንግሥት ፍላጎት ቢሆንም፣ ለተግባራዊነቱ ልዩ የማበረታቻ፣ የማስፈጸሚያ ፖሊሲና መመርያ ያስፈልገዋል::

ዜጎች ቶሎ ወደ ሥራ እንዲገቡ፣ ቢሮክራሲው የድርሻውን በተቀላጠፈ መንገድ እንዲያቀርብ፣ ባንኮች፣ የመሬት ይዞታዎችና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች ጥረታቸውን አቀናጅተውና አቅማቸውን አጠናክረው ለዚህ ተግባር ምንጊዜም ዝግጁ መሆን አለባቸው::

በዚህ ላይ ከመንግሥት፣ ከንግዱ ኅብረተሰብና ከሸማቹ ማኅበረሰብ የተውጣጣ ቋሚ የቲንክ ታንክና የመመካከሪያ መድረክ ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ሲታይ ችግሩ ከፍተኛ ነው:: በኑሮ ውድነት ምክንያት ትምህርት የሚያቋርጡ ወጣቶች አሉ:: ወደ ዝሙት እያመሩ ያሉ አሉ:: ወደ ወንጀል ተደራጅተው እየገቡ ያሉም አለ:: አገር ጥለው የሚሄዱ ዜጎች እየተበራከቱ ናቸው:: ሕፃናትን ማሳደግ እያስቸገረ ነው:: ትዳር መመሥረት ከባድ አጀንዳ እየሆነ ነው:: ሌሎች ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም ዋነኛው ማጠንጠኛ የኑሮ ውድነቱ እየናረ መምጣቱ ነው:: ያልታሰበ አደጋ ሊከሰት እንደሚችልም እንገምት::

የኑሮ ውድነት እንደ ሸንበቆ ሲወጣ እንጂ እንደ ሙቀጫ ሲንከባለል አልታይ ብሏል:: በችግሩ ላይ እንወያይና ለመፍትሔው እንረባረብ:: በጋራ! በአስቸኳይ! በኃላፊነት ስሜት!

Page 3: Reporter Issue 1229

|ገጽ 3 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

በታምሩ ጽጌ

መንግሥት ከሊዝ ኪራይ ማግኘት የሚገባውን 419,827 ብር እንዲያጣ በማድረግና ሥልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም ወንጀሎች ተከሰው ከነበሩት አምስት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት መካከል፣ የመሬት ልማት ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ግለሰብ በሰባት ዓመታት ፅኑ እስራትና በአሥር ሺሕ ብር ተቀጡ::

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ዓቃቤ ሕግ በመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኝነታቸው በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የተረጋገጠባቸው አቶ አብዲ ዓሊ ቅጣቱ የተጣለባቸው ጥር 24

ቀን 2004 ዓ.ም. ነው:: መዝገቡን መርምሮ ቅጣቱን የጣለው

ድሬዳዋ የሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን፣ በግለሰቡ ከህዳር 2001 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 2003 ዓ.ም. ድረስ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት፣ በሕዝብና በመንግሥት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በመዘንጋት፣ የተሰጣቸውን ከፍተኛ ሥልጣን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል መፈጸማቸው በሰዎችና በሰነድ ማስረጃዎች መረጋገጡን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል::

ፍርደኛው አቶ አብዲን ለቅጣት የዳረጋቸው ጉዳይ፣ የአስተዳደሩ የሊዝ ቦርድ

ውሳኔ ሳይኖር የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ፈቃድ ሳይኖርና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ፣ የአንድን ግለሰብ የቦታ ጥያቄ በቀጥታ እሳቸው ወደሚያዟቸው የመምርያ ኃላፊዎች በመምራት፣ ካርታ እንዲዘጋጅ በማዘዝና በመፈረም 1920 ካሬ ሜትር ቦታ መፍቀዳቸውን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያስረዳል::

በሰባት ዓመታት ፅኑ እስራትና በአሥር ሺሕ ብር እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው አቶ አብዲ ዓሊ ጋር ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ክስ የተመሠረተባቸው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት አቶ ባህር አሜ፣ አቶ ዘይኑ ሸሪፍ፣ አቶ ከተማ ተሰማና አቶ አብዱራህማን አሜ መሆናቸው ታውቋል::

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባል በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ

በውድነህ ዘነበ

ሁለት የቻይና ኩባንያዎች ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን 1.9 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በትናንትናው ዕለት ተረከቡ::

ፕሮጀክቶቹ በኦሮሚያና በትግራይ ክልል የሚገኙ ሲሆን፣ በኦሮሚያ ክልል ከነቀምት እስከ በደሌ ድረስ ያለውን መንገድ ሲጂሲ ኦቨርሲስ ሲረከብ፣ በትግራይ ክልል ከሐውዜን እስከ ፍሬወይኒ ያለውን መንገድ ቻይና ሬልዌይ ነምበር ስሪ ኩባንያ ወስዷል::

የነቀምት በደሌን መንገድ መገንባት

ለግብርና ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑን፣ በአካባቢው የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች በመካሄድ ላይ መሆናቸውንና ከዚህ በተጨማሪም በያዩ ወረዳ የማዳበርያ ፋብሪካ የሚገነባ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ባለሥልጣኑ አስታውቋል::

የሐውዜን ፍሬወይኒ መንገድ ፕሮጀክት የሚከናወነው በአካባቢው የመንገድ አውታር ባለመኖሩ መሆኑ ተጠቅሶ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር በመንገድ ማገናኘት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ተብሏል:: አራተኛው የመንገድ ዘርፍ ልማት መርሐ ግብር ሕዝብን ከሕዝብ

ጋር በመንገድ ማገናኘት ዓላማው መሆኑ ተገልጿል::

ሁለቱ ፕሮጀክቶች በሦስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃሉ ተብሎ የታቀደ ሲሆን፣ ሁለቱም መንገዶች በጠቅላላው ሁለት መቶ ኪሎ ሜትር ርዝመት አላቸው::

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በተያዘው የበጀት ዓመት በ17.4 ቢሊዮን ብር በጀት የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ ይገኛል:: በርካታ የቻይና ኮንትራክተሮችም የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ይታወቃል::

ሁለት የቻይና ኩባንያዎች የ1.9 ቢሊዮን ብር የመንገድ ፕሮጀክቶችን ተረከቡ

በኃያል ዓለማየሁ

በዓለም ላይ የታወቁ የቡና አቅራቢዎች፣ ገዥዎች፣ ቆዪዎችና የቡና ገበያ አጥኚዎች ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ስብሰባ አዳራሽ በሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ቡና አብቃዮች ማኅበር ኮንፈረንስና ኢግዚቢሽን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ::

ቁጥራቸው ከ700 እስከ 1,000 የሚገመቱ የጉባዔው ተሳታፊዎች አዲስ አበባ እንደሚመጡ ይጠበቃል:: ጉባዔው ከአሜሪካ ልዩ ቡና ማኅበር፣ ከጃፓን ልዩ ቡና ማኅበርና ከአውሮፓ ልዩ ቡና ማኅበር ተወካዮችና አባላትን እንደሚያካትት፣ በኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ቡና አብቃዮች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ አብደላ ባገርሽ ለሪፖርተር ገልጸዋል::

ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ቡና አብቃዮች ጉባዔና ኤግዚቢሽንን ከአምስት ዓመት በፊት ማስተናገዷ የሚታወስ ቢሆንም፣ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜ የሚጀመረው ጉባዔ ካለፈው በተለየ በዓለም ላይ ዕውቅና ያላቸው ቡና ገዥዎችንና ቆዪዎችን፣ እንዲሁም የቡና ገበያ አጥኚዎችንና ሌሎች የገበያው ተሳታፊዎችን እንደሚያካትት ታውቋል::

በጉባዔው ላይ ከልዩ ቡና ምርት ጋር በተያያዘ በዘላቂነት ቡና የሚበቅልባቸውን የቡና ደኖች የቱሪስት መስህብ ለማድረግ፣ እንዲሁም በዓለም ገበያ በልዩ ቡና ላይ የተለያዩ ጥናቶችና ንግግሮች እንደሚቀርቡ የገለጹት አቶ አብደላ፣ በቀጣዩም ቀን የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ቡና አብቃዮች ምርታቸውን የሚያሳዩበት ኤግዚቢሽን እንደሚካሄድ አስታውቀዋል:: በኤግዚቢሽኑ ላይ የአፍሪካ ባሪስታዎች ውድድርና የቡና ቅምሻም እንደሚካተት ታውቋል::

ጉባዔውና ኤግዚቢሽኑ ከመካሄዱ በፊት በሚቀጥለው ሳምንት ዓርብ ዕለት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ሳይንሳዊ የቡና ኮንፈረንስ የሚካሄድ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል::

የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ ቡና አብቃዮች ማኅበር 11 የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪካ አገሮችን የሚያካትት ሲሆን እነሱም ኢትዮጵያ፣ ብሩንዲ፣ ኮንጎ፣ ኬኒያ፣ ማላዊ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያና ዙምባቡዌ ናቸው::

በዓለም የታወቁ የቡና ነጋዴዎች የሚሳተፉበት ጉባዔ

በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Page 4: Reporter Issue 1229

ገጽ 4|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

ከገጽ 1 የዞረ

2nd TIME CALL FOR CONSULTANCY- ON MIS AUTOMATION (LICENSEd FIRM CONSULTANT)

Introduction and Background

Omo Micro Finance Institution (OMFI) was established on Aug. 14/1997 and registered on Oct. 01/1997 as a share company. The

institute serves more than 380,000 loan clients and 492,000 saving clients through 14 branch offices located in all Zones and 154 sub

branch offices located in all Woredas and different city administrations of SNNPR region.

Currently, OMFI intends to automate its MIS system. As such the institution seeks to recruit a competent licensed firm consultant who

support and serve advisory role for the entire period of its MIS automation.

Objective of the consulting Assignment

a. Support and advise the identification and implementation of appropriate MIS system which meets the requirements for

the institute’s overall business objectives.

b. Support and serve advisory role for the identification and implementation of suitable infrastructure to inter connect the

institute’s operational branches and sub branches with central data base (namely head office).

c. Strengthen the MIS department and build the capacity of the institute’s community (management and staff especially MIS

staff) through Knowledge transfer and training.

Scope of the Consultancy Assignment

Develop a transition plan from the current working environment to the new environment with due consideration for OMFI’s

resources, technology, and caliber of staff.

Capacitate the MIS team to handle the whole MIS automation scheme and create awareness for management members.

Review and enrich OMFI’s request for proposal (RFP) document.

Follow up of the bidding process, from release to evaluation with appropriate team.

Work with the vendor to develop an implementation plan for users’ training, for the targeted system installing, testing, and

rolling out.

Assess readiness of system implementation sites (identify and recommend necessary hardware, suitable high level network

architecture, appropriate communications, electricity, and the like).

Assess and propose advanced Trainings to strength the MIS staffs to handle new system administrations and other related

technical tasks.

Assess vendor’s user manual for completeness and understandability.

In collaboration with MIS staff closely monitor and control the system implementation process to check with desired standards.

Conduct performance audit to determine full compliance of the new MIS with law and regulations.

Enable smooth commissioning process develops and conduct system commissioning milestones, project closure and

maintenance plans. As well all activities performed after the commissioning of the system, like, usage monitoring and

identification of gaps

deliverables

Transition plan, Reviewed Request for Proposal (RFP),

Vendors’ proposal Evaluation report.

Implementation plan for installing, testing, and rolling out the new software system wide

Technical guideline for the MIS department to oversee data migration and data transfer risk information

Appraisal of vendor’s training plan on system use.

Assessment of user’s manual

Facilitate the process of addressing user comments and requests for modification in a timely manner

performance audit

Report(Inception, Progress, Interim, and Final Report)

Qualifications and experience

An individual(s) who provide a consultancy/advisory service to the institution needs to posses the following experiences and skills:

The consultant (An individual(s)) is expected to possess an at least MA/MSC degree qualification which has close connection

with the subject at issue.

Proven experience in consulting projects of similar nature for large corporate organizations or government institutions especially

banks or microfinance institutions.

Relevant qualifications and experience of key staff(s), to be assigned to tasks listed here, in projects of a similar nature.

Proven technical capacity in system requirements gathering and software tasting (preferable).

Technical ability in advanced data base management system, high level network architecture, security system and devices

(preferable).

Ability to communicate in national language is advantageous.

Proven business and management skills in microfinance or banks (is advantageous).

How to apply:

A. Interested Consultants can purchase detailed TOR starting from the first date which the advertisement issued on the newspaper

up to 15/fifteen/ calendar days from Omo micro finance head office, Finance department, Bureau no. 11. by providing:

1) Non-refundable fee of Ethiopian birr 100.00(one hundred birr only)

2) Certified copy of certificate of registration/renewed trade license/

3) Copies of VAT and Tax payers’ registrations certificate

B. The consultant(s) must submit physically two separate hard copies of Wax-sealed technical and financial proposals to our

Head Office of Omo microfinance Institution S.C., Located in, Hawassa, infront of the gate of Meskel Square at the 16TH

calendar day from 10:00 am _12:00 am .

C. If the 16TH day is not a working day the submission date will be the next working day and the qualification document will be

opened on the same day at 3:00 pm in the presence of interested bidders/representatives.

D. When submitting the proposal; the following information/ document must be included

Proposed work plan that indicates all envisaged activities to the end of the final report

Consultant’s profile(history, experience as a firm consultant in the relevant field

Similar previous experience of services carried out for large corporate organizations or government institutions. References

from those organizations/institutions and name of contact person must be provided.

Academic and professional qualifications of consultant(S)

Cost proposal that covers all consultant’s costs and envisioned costs the study will incur- where data is not available narrate

the cost.

E. The institute reserves the right to reject any or all bids.

Further information can be obtained from the following addressOmo Micro Finance Institution S.C Head Office

P.O.Box: 353Tel: +251-046-220-2053 or +251-046-220-2051

Fax: +251-046-2202052Email: [email protected]

Hawassa, Ethiopia

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም Omo Micro Finance Institution S.c.

እስከ ጥር 21 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ 112 የድርጅቱ አባላት መታሰራቸውን የገለጸው መኢአድ፣ ተጠናክሮ የቀጠለው ዜጎችን ከሥራና ከቀያቸው የማፈናቀልና የማሰር ተግበር እንዲቆምና የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል::

አዲስ አበባ የሚገኘው የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ትናንት ባወጣው መግለጫ፣ ገዢው ፓርቲ በደቡብ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ የመኢአድ አባላትና ደጋፊዎች ላይ እየፈጸመ ያለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ሰላማዊ ትግሉን ለማቀጨጭና ለማኮላሸት መሆኑን አመላካች ነው ብሏል::

በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በአባላቱ ላይ በደሎች መፈጸማቸውን የገለጸው መኢአድ፣ የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች በጥይት መትተው በማቁሰል፣ ሕክምና እንዳያገኙ በመከልከልና ለኢንፌክሽን እንዲጋለጡ በማድረግ፣ መሬታቸውን በመንጠቅና ለቀበሌው ባለሥልጣናት በመስጠት፣ በሆነ ባልሆነው በማሰርና በሕገወጥ መንገድ በገንዘብ በመቅጣት የመሳሰሉትን በደሎች እየፈጸሙባቸው እንደሚገኙ አስታውቋል::

መሬታቸውን የተቀሙና የተለያዩ በደሎች የሚፈጸምባቸው የድርጅቱ አባላት ቤተሰቦቻቸውንና ቀያቸውን ትተው በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የገለጸው መኢአድ፣ በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ በሰበታ አካባቢ ማስፈራራት፣ ድብደባና እስራት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ጠቁሟል::

መኢአድ መንግሥት በፓርቲው የወረዳና የቀበሌ አመራሮችና አባላት ላይ በየክልሉ እየወሰደ ያለውን የጅምላ እስር እንደሚቃወም አስታውቆ፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በተቃዋሚ ፓርቲ አመራርና አባላት፣ በጋዜጠኞችና በንፁኃን ዜጎች ላይ ታፔላ በመለጠፍ ማሰር፣ ማዋከብና ማስፈራራትን እንዲያወግዝና በመንግሥት ላይ ጫና እንዲፈጥር ጠይቋል::

የመኢአድ ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል፣ ‹‹በአባሎቻችን ላይ በየቀኑ እየጨመረ የመጣው እስራት አሳስቦናል:: በሕዝብ ላይ ስቃይ፣ መከራና እንግልት በማብዛትና በማስፈራራት

ለውጥ ማግኘት አይቻልም፤ የሚያስፈልገው ሕዝብ የሚወደውንና የሚያምንበትን መሥራት ብቻ ነው፤›› ብለዋል::

በደቡብ ክልል የደንባ ጎፋ ወረዳ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ

(ደኢሕዴን) ተጠሪ አቶ እያሱ ጣሰውን ለማነጋገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም::

መኢአድ የታሰሩ...

በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በእናርጅ እናውጋ ወረዳ በአባላቱ ላይ በደሎች መፈጸማቸውን የገለጸው መኢአድ፣ የገዢው ፓርቲ ታጣቂዎች በጥይት መትተው በማቁሰል፣ ሕክምና እንዳያገኙ በመከልከልና ለኢንፌክሽን እንዲጋለጡ በማድረግ፣ መሬታቸውን በመንጠቅና ለቀበሌው ባለሥልጣናት በመስጠት፣ በሆነ ባልሆነው በማሰርና በሕገወጥ መንገድ በገንዘብ በመቅጣት የመሳሰሉትን በደሎች እየፈጸሙባቸው እንደሚገኙ አስታውቋል::

Page 5: Reporter Issue 1229

|ገጽ 5 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያየኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት አነስተኛ የቁጠባና ብድር አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሲሆን ከዚህ በታች ባሉ ክፍት የሥራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾችን አወዳድሮ ብልጫ ውጤት ያመጡትን በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል::

ተ.ቁ የክፍት ሥራ መደቡ መጠሪያ

ብዛት የሥራ ቦታ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና አግባብ ያለው የሥራ ልምድ

ደረጃ ደመወዝ ምርመራ

1 ሲኒየር ኦፕሬሽን ኦፊሰር

2 ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት በኢኮኖሚክስ’በማርኬቲንግ’uT’@ÏS”ƒ ወይም u}Sddà ¾ƒUI`ƒ Se¡ ›?U ›? Ç=Ó]“ 4 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ¨ÃU u=›? Ç=Ó]“ 6 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ

XIV

በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

በድጋሚ የወጣ

2 ፕላንና ፕሮጀክት ዝግጅትና ትንተና ኦፊሰር

3 ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት በኢኮኖሚክስ’uT’@ÏS”ƒ’e ƒe+¡e “ u}Sddà ¾ƒUI`ƒ Se¡ ›?U ›? Ç=Ó]“ 4 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ¨ÃU u=›? Ç=Ó]“ 6 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ

XIV

በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

በድጋሚ የወጣ

3 ጥናትና ዶክሜንተሸን ኦፊሰር

3 ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት በኢኮኖሚክስ’uT’@ÏS”ƒ’e ƒe+¡e “ u}Sddà ¾ƒUI`ƒ Se¡ ›?U ›? Ç=Ó]“ 4 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ¨ÃU u=›? Ç=Ó]“ 6 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ

XIV

በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

በድጋሚ የወጣ

4 ሲኒየር ዳታቤዝ አድሚኒስትሬተር

1 ሀዋሳ ዋናው መ/ቤት በኮምፒውተር ሳይንስ’በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ’ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተም’ በኢንፎርማ+¡e’ በኢንፎርሜሽን ሲስተም’ በe ƒe+¡e “ u}Sddà ¾ƒUI`ƒ Se¡ u=›?ስሲ Ç=Ó]“ 4 ¯Sƒ ›Óvw ÁK¨< ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ

_ በስምምነትበድጋሚ የወጣ

5 ጁኒየር የህግ ባለሙያ

3 ሶዶ’Jd°“ “ T>³” p/ê/u?„‹ በህግ አድቫንስ ዲፕሎማና 4 ዓመት አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ወይም የኮሌጅ ዲፕሎማና 6 ዓመት አግባብ ያለው የሥራ ልምድ ያለው/ላት

X በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

በድጋሚ የወጣ

6 ሂሳብ ሰራተኛ 67 በተቋሙ ሥር ባሉ ን/ቅ/ጽ/ቤቶች በአካውንቲንግ ¾ƒUI`ƒ Se¡ ቢ ›? Ç=Ó]“ 0 ¯Sƒ ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ VI

በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

7 ኦፕሬሽን ኦፊሰር 139 በተቋሙ ሥር ባሉ ን/ቅ/ጽ/ቤቶች በኢኮኖሚክስ ወይም በአካውንቲንግ ¾ƒUI`ƒ Se¡ ቢ ›? Ç=Ó]“ 0 ¯Sƒ ¾Y^ MUÉ ÁK¨</Lƒ

VI

በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሠረት

ማሳሰቢያ፡- የምዝገባ ቦታ፡- ዋናው መ/ቤት የሰው ሀብት ሥራ አመራርና ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 19

የምዝገባ ጊዜ፡- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት

አመልካቾች የትምህርና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውንና ኮፒውን በመያዝ በአካል ወይም በፖ.ሳ.ቁ. 353 ወይም በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በፋክስ ቁጥር 046-220-20-51/52 በመላክ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

ለሁሉም ክፍት የሥራ መደቦች አመልካቾች ከታወቀ ዩኒቨርሲቲ/ኮሌጅ የተመረቁ መሆን ይኖርባቸዋል::

በተራ ቁጥር 6 እና 7 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች አመልካቾች በ2003 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የተመረቁ መሆን ይኖርባቸዋል::

በተራ ቁጥር 6 እና 7 ለተጠቀሱት የሥራ መደቦች አመልካቾች ሀዋሳ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መ/ቤት ወይም እንደአመቺነቱ በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ማዕከል ባሉ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች መመዝገብ ይችላሉ::

ተ ቋ ሙ !

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም Omo Micro Finance Institution S.c.

በሔኖክ ያሬድና በታምሩ ጽጌ

የቀድሞው የሕፃናት ኮሚሽን ኮሚሽነር፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊ የነበሩት ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ ሽመልስና የኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ ሥርዓተ ቀብር ከትናንት በስቲያ ተፈጸመ::

ላለፉት አምስት አሠርት በተለያዩ ሰብዓዊና አገራዊ ጉዳዮች ከመንግሥት ከፍተኛ ሹምነት እስከ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪነት ያገለገሉት ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ፣ በተለይ በ1960ዎቹና 70ዎቹ በአገሪቱ ተከሥቶ የነበረውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቋቋም ከተሰማሩት ግንባር ቀደምት መካከል አንዱ እንደነበሩ ከሕይወት ታሪካቸው ለመረዳት ተችሏል::

በቀይ መስቀል ማኅበር ዋና ጸሐፊነት ዘመናቸው የደም ባንክን ያቋቋሙት አቶ ተሠራ ወርቅ፣ ከነበሩባቸው ኃላፊነቶች መካከል የልጆች፣ ወጣቶችና ቤተሰብ ደኅንነት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የቴርዴስ ሆምስ የምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ፣ የዓባይ (ናይል) ተፋሰስ አገሮች የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ሰብሳቢ ሆነው ያገለገሉበት ይገኙባቸዋል::

ከአባታቸው አቶ ሽመልስ ዘነበወርቅና ከእናታቸው ወ/ሮ አፀደማርያም ቸርነት ጥቅምት 30 ቀን 1939 ዓ.ም. በሐረር ከተማ የተወለዱት ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ፣ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ስዊድን ሚሽን፣ ሁለተኛ ደረጃን በአዲስ አበባ ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ሲከታተሉ፣ ከንግድ ሥራ ኮሌጅ በ1957 ዓ.ም. ተመርቀዋል::

ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥና

ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ ሽመልስና ኢንጂነር መስፍን

ኃይሌ አረፉ

በውጭ አገር ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩት ኮሚሽነር ተሠራ ቀብራቸው ጥር 28 ቀን 2004 ዓ.ም. በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል:: ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ የአንዲት ሴትና አንድ ወንድ ልጆች አባት ነበሩ::

በተያያዘ ዜና በሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም የተቋቋመው የኢትዮጵያ መንገዶች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ኢንጂነር መስፍን ኃይሌ፣ ጥር 27 ቀን 2004 ዓ.ም አርፈው ጥር 28 ቀን 2004 ዓ.ም የቀብር ሥርዓታቸው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል::

ኢንጂነር መስፍን ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ ወር 2003 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በተለያዩ ከፍተኛ ኃላፊነቶች የሠሩ መሆናቸውን ከሕይወት ታሪካቸው ለመረዳት ተችሏል:: በቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ላይ አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል::

ኮሚሽነር ተሠራ ወርቅ ሽመልስ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ በተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ቅንነትና ግልጽነትን የተላበሰ፣ ከጸበኛነትና ባላንጣነት መንፈስ የፀዳ የመልካም ግንኙነት መንፈስ እንዲፈጠር የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ጥሪ አቀረበ::

የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማት ዕድገት ባለቤትነትና የማንነት ዓይነተኛ መገለጫዎች ናቸው ከሚባሉት መሠረታዊ ጉዳዮች መካከል የፖለቲካ ቂም በቀልና ቁርሾ ስለማስወገድና ብሔራዊ መግባባትን ስለመፍጠር በአምስት ዓመቱ ዕቅድ አለመካተቱ፣ በእጅጉ የሚያሳስብ ጉዳይ መሆኑን ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ያስታወቀው ኢራፓ፣ ገዥውንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ጨምሮ ማንኛውም ሰላም ወዳድ ዴሞክራትና ቅን አሳቢ ዜጋ ያለ ልዩነት ለብሔራዊ መግባባት መሳካት ሁለንተናዊ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል::

ምርጫ 2002ን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በምክር ቤት ወንበር ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም፣ በሁሉም ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለማማከርና ለማሳተፍ የሰጡት መሪ ቃል ሥራ ላይ እንዲውልም ጥሪ አቅርቧል::

በአንድ አገር ሕዝብ እንደ ሕዝብ በብልሹ የአስተዳደር ሥርዓት ላይ የሚያቀርባቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሞራላዊ የፍትሕና የዴሞክራሲ፣ የመብትና የነፃነት ጥያቄዎችና የሚወስዳቸው ዕርምጃዎች ሁልጊዜ ሰላማዊ ይሆናሉ ወይም እንዲሆኑ ይገደዳሉ በማለት ኃይልን መጠቀም ወይም በኃይልና በጡንቻ መመካትና መተማመን ጤናማ መፍትሔ ነው ለማለት እንደማያስደፍር የገለጸው ፓርቲው፣ ተራማጅና ዴሞክራት የውጭ አገር መንግሥታት፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የግጭት አስወጋጅ ድርጅቶችና ሌሎችም በሚሰጡት የትብብር መስኮች ሕጋዊ መስመሮች ተዘርግተው

ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠይቋል::

‹‹ትልቁ ስጋታችን ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን ነው፤›› ያሉት የኢራፓ ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮ፣ ጊዜው ሳይመሽና ሳይጨልም ገዥው ፓርቲና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በቅንነት ውይይት በማካሄድ ብሔራዊ መግባባት የሚፈጠርበት መድረክ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ለሪፖርተር ገልጸዋል::

የሊዝ አዋጁን ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት የወጡት ሕጐች፣ ደንቦችና መመርያዎች በዜጐች ተቀባይነት ያገኙ አለመሆናቸውን የጠቆሙት አቶ ተሻለ፣ ችግሮች ከቁጥጥር ውጪ ከመሆናቸው በፊት መፍትሔ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል::

ራዕይ ፓርቲ የብሔራዊ መግባባት ጥሪ አቀረበ

ምርጫ 2002ን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በምክር ቤት ወንበር ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም፣ በሁሉም ወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለማማከርና ለማሳተፍ የሰጡት መሪ ቃል ሥራ ላይ እንዲውልም ጥሪ አቅርቧል::

Page 6: Reporter Issue 1229

ገጽ 6|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

የስብሰባ ጥሪየአፄ ዮሐንስ ት/ቤት የቀድሞ

ተማሪዎች ማህበር እሁድ የካቲት

4 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠቅላላ ስብሰባ

የሚያካሂድ ስለሆነ፣ በአፄ ዮሐንስ

ት/ቤት የተማራችሁ ሁሉ በዚሁ

ዕለት ከጥዋቱ 2፡30፣ በተግባረ

ዕድ ት/ቤት አዳራሻ እንድትገኙልን

ጥሪያችንን በማክበር እናቀርባለን::

ኮሚቴው

የስብሰባ ጥሪThe World Bank

BId FOR SALE OF USEd OFFICE FURNITURE

The World Bank Ethiopia Country Office would like to sale different used office furniture through competitive bid on an “as-is, where-is” basis. The World Bank does not give warranty and guaranty for any of its properties being disposed. Interested bidders are therefore invited to submit their bids according to the following bid instructions.

1. Prospective bidders can inspect the furniture on February 18, 2012 and February 25, 2012 from 9:00am to 12:00pm at the World Bank compound (Worbek House).

2. The last day for submission of bids is February 28, 2012, 4:30pm. 3. Bids must be accompanied with bid bond of 5% of the value of the bid

amount in CPO written to the International Bank for Reconstruction and development ( IBRd ). The bid bonds will be later returned to unsuccessful bidders.

4. Bid winners are required to pay the full amount of the winning price and collect the furniture within ten days after they are notified.

5. Bid winners are responsible to settle any government taxes and duties as they may be applicable.

6. World Bank reserves the right to reject any or all bids.

Interested bidders can collect bid document from the World Bank Ethiopia Office at Africa Avenue ( Bole Road – Worbek House ) during working hours starting from February 08, 2012. Sealed bids should be submitted to:

Resource Management OfficerWorld Bank Ethiopia Country Office

Africa Avenue (Bole Rwanda) Worbek HouseAddis Ababa

በኃይሌ ሙሉ

ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ቀደም ባሉት ዓመታት ሲከተለው በነበረው አሠራር አንድን ሕግ በፓርላማ ከማስፀደቁ በፊት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያካሂድ ነበር:: ምንም እንኳን አንዳንድ ታዛቢዎች መንግሥት ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገው ውይይት የይምሰል መሆኑን፣ በውይይት ወቅት ከኅብረተሰቡ የሚቀርቡ ግብረ መልሶችን ተቀብሎ ማሻሻያ ለማድረግ ከመሞከር ይልቅ፣ በፓርቲ ደረጃ የተላለፉ ውሳኔዎችና የተያዙ አቋሞችን በኅብረተሰቡ ላይ ለመጫን እንደሚንቀሳቀስ በመጥቀስ የመንግሥትን አካሄድ ቢተቹም፣ የመንግሥት ፍላጐት ምንም ይሁን ምን አንድ ሕግ ከመፅደቁ በፊት ውይይት እንዲካሄድበት መደረጉን በበጐ መልኩ የሚመለከቱት ብዙዎች ናቸው::

ባለድርሻ አካላት ያልተወያዩበትና ያልተከራከሩበት ሕግ ዱብ ዕዳ ሆኖ በሚቀርብበት ወቅት፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚፈጥረው ብዥታ ቀላል አለመሆኑን የሚናገሩት እነኝሁ ተንታኞች፣ በአፈጻጸም ላይ ችግር እንዳይከሰት ከተፈለገ ሕጉ ከመፅደቁ በፊት ኅብረተሰቡ በጉዳዩ ላይ በቂ መረጃ ሊኖረውና ሕጉ የሚያስገኝለትን ጠቀሜታ ጠንቅቆ እንዲያውቀው ማድረግ እንደሚገባ ያስረዳሉ::

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ አወዛጋቢ ሕጐች ፀድቀዋል:: ከእነዚህ አወዛጋቢ ሕጐች መካከል የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ሕግ፣ የሚዲያ ሕግና የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው:: በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር ተደጋጋሚ ትችቶች የሚሰነዘሩባቸው እነኝህ ሕጐች ከመፅደቃቸው በፊት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ውይይት ተካሂዶባቸዋል:: ከላይ የተጠቀሱት ሕጐች መፅደቅ የፖለቲካ ምኅዳሩን እንዲጠብ ያደርጋል በሚል ባለድርሻ አካላትና ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በወቅቱ ስጋታቸውን ቢገልጹም፣ ከያዝኩት አቋም ወይ ፍንክች ያለው ገዥው ፓርቲ ሕጐቹን በፓርላማ አስፀድቋል:: የተወሰኑ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ይህ የተለመደ የኢሕአዴግ አሠራር ነበር:: በአንድ ጉዳይ ላይ አቋም ይይዛል፣ ቀጥሎም በጉዳዩ ላይ ኅብረተሰቡን ያወያያል፣ ከዚያም በውይይቱ ላይ ኅብረተሰቡ ይህንን አቋም ደግፏል ብሎ ውሳኔ ያስተላልፋል፤ ሕግ ያፀድቃል::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአብዛኛው ኅብረተሰብ ዘንድ የመወያያ አጀንዳ የሆነው የሊዝ አዋጅ የፀደቀው ግን ከዚህ በተለየ መንገድ ነው:: በጉዳዩ ላይ ማንም ምንም ሳይሰማ፣ የዓመቱ የተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በተከፈተ ማግስት ለቋሚ ኮሚቴ ሳይመራ፣ በአስቸኳይ የፀደቀው ይህ ሕግ ከዚህ ቀደም እንደፀደቁት ሕጐች ሁሉ የአንድ ሰሞን መነጋገሪያ አጀንዳ ብቻ ሆኖ የሚቋጭ አይመስልም:: አወዛጋቢነቱ አሁንም ቀጥሏል:: የሕጉን መፅደቅ ተከትሎ

የሊዝ አዋጁ ውይይት ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ?

የሊዝ አዋጁ ላይ ከሚቀርቡ ክርክሮች አንዱ ነባር ይዞታዎች በሊዝ ሥሪት ውስጥ የገባሉ መባሉ ነው

Page 7: Reporter Issue 1229

|ገጽ 7 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

Invitation for bids (Tender No. 15/2004)

Addis Ababa Abattoirs Enterprise hereby invites all interested and eligible bidders for the implementation of Integrated information management system.

The Bid documents can be obtained from the Procurement & Property Administration Process of the Enterprise against payment of non-refundable fee of Birr 100.00 (One Hundred Birr) during working hours.

Bidders are requested to submit their bid proposals in accordance with the objectives and scope as specified in this document and the work to be performed as defined in the Term of reference (TOR).

Bids must be accompanied with a bid security of 20,000 (Twenty Thousand Birr) in the form of CPO and must be delivered to the Enterprise before the bid opening time.

All sealed offers should be delivered on or before March 6, 2012 (27/06/2004 E.C 10:00 A.M or 4:00 local time) to Procurement & Property Administration Process of the Enterprise.

Bids will be opened in the Enterprise on March 6, 2012 (27/06/2004 E.C. at 10:30 AM or 4:30 local time) in the presence of bidders or their legal representative.

The Enterprise reserves the right to accept or reject all or part of the bid without assigning any reason thereof, for more information please call or contact.

Addis Ababa Abattoirs Entreprise Tel. No. 0114652294, 0114667501 Fax No.: 0114654223 P.O.Box 1908 Addis Ababa

የኦዲት ሥራ አገልግሎት ማስታወቂያ

ኤንዳ ኢትዮጵያ በበጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው:: ድርጅታችን የ2011 (እ.ኤ.አ) ሂሳቡን በተመሰከረላቸው የሂሳብ አዋቂዎች ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል::

ስለዚህ ለ2004 ዓ.ም. የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ኦዲተሮች ሂሣቡን ኦዲት ለማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 ቀናት ውስጥ ማመልከትና መወዳደር ይችላሉ:: ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች ባለው አድራሻ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

ኤንዳ ኢትዮጵያ

ፖ.ሳ.ቁ. 25718 ኮድ 1000

ስልክ ቁጥር 011-4168895/011-4162004

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ከባለድርሻ አካላት ተቃውሞ የገጠማቸው [ሕግ አርቃቂው] የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ በመንግሥትና በግል ሚዲያዎች የሰጡት ማብራሪያም በኅብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረውን መደናገር ከማባባስ ውጭ ያመጣው ለውጥ እንደሌለ ታዛቢዎች ይገልጻሉ::

የመንግሥት ባለሥልጣናቱ በተለያዩ ጊዜያት በሰጡት መግለጫ በሊዝ አዋጁ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ወገኖች በኪራይ ሰብሳቢነት ተሰማርተው የቆዩ ጥቂት የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ አዋጁ አብዛኛውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ቢገልጹም፣ ይህ የእነሱ ድምዳሜ በአብዛኛው ኅብረተሰብ ተቀባይነት ያገኘ አልነበረም:: ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ውይይት ሳያደርግ አዋጁ መፅደቁ ስህተት እንደነበረ በመንግሥት ባለሥልጣናት ቢነገርም ተቀባይነቱ ውኃ የሚቋጥር አልሆነም::

የተለያዩ ምንጮች እንደሚገልጹት የሊዝ አዋጁን ተከትሎ በሕዝቡ ዘንድ የተፈጠረውን ብዥታ ለማጥራት በሚል በርካታ የመንግሥት ባለሥልጣናት የአዲስ አበባን ነዋሪዎችን በየወረዳው በመሰብሰብ ቢያወያዩም የጠበቁትን ውጤት ማግኘት አልቻሉም:: የተወሰኑት ስብሰባ ረግጠው ሲወጡ አብዛኛዎቹ ተሰብሳቢዎች ደግሞ የሊዝ አዋጁን እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል:: እነኝህ የሪፖርተር ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ፣ የሊዝ አዋጁ በቀጣዩ ዓመት በሚካሄደው የአዲስ አበባ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል የሚል ስጋት ያደረባቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር ኃላፊዎች፣ ኅብረተሰቡን በማሳመን ረገድ ካድሬዎቻቸው ጠንክረው እንዲሠሩ እየወተወቱ ነው:: የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ኃላፊዎችም ባለድርሻ አካላትን በየጊዜው እየሰበሰቡ ማወያየታቸውን ቀጥለውበታል:: ‹‹በፀደቀ ሕግ ላይ መወያየቱ ምን ይጠቅማል?›› የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው::

አዋጅን መሠረት በማድረግ የሚወጡት ደንብና መመርያዎች የኅብረተሰቡን ፍላጐት በሚያሟላ መልኩ እንዲስተካከሉ ይደረጋል የሚለው ማባበያም ለሕግ ባለሙያዎች የሚዋጥ ሆኖ አልተገኘም:: በአዋጅ ላይ በግልጽ የተቀመጠን ጉዳይ በመመሪያና በደንብ ማስተካከል እንደማይቻል የሚገልጹት የሕግ ባለሙያዎች፣ መንግሥት ስለደንብና መመርያ ከሚያስረዳ ይልቅ አዋጁ የሚስተካከልበትን መንገድ ቢፈልግ የተሻለ መሆኑን ይናገራሉ::

ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ባለፉት ሃያ ዓመታት በፓርላማ የፀደቀ ሕግ ወዲያውኑ እንዲስተካከል የተደረገበት ክስተት ታይቶ አይታወቅም:: ገዥው ፓርቲ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የቀረበለትን ቅሬታ መሠረት አድርጐ የሕግ ማስተካከያ ቢያደርግ ክስተቱ ለኢሕአዴግ እንደ ውድቀት ይታይ ይሆን? ሕጉ ማሻሻያ ሳይደረግበት ተፈጻሚ ከሆነስ በቀጣይ በሚካሄዱ ክልላዊና

ብሔራዊ ምርጫዎች የሚፈጥረው ተፅዕኖ ምን ይሆን? የሚለውም ሌላው መነጋገሪያ ጉዳይ ነው::

ክስተቱ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መልካም አጋጣሚን ሳይፈጥርላቸው አይቀርም:: የገዥው ፓርቲ ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆነው መድረክ በአገሪቱ ውስጥ አንድ ዓይነት የመሬት ሥሪት ሊኖር አይገባም በማለት ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል:: ይህንን የተቃዋሚዎች አቋም ትኩረት ውስጥ ስናስገባ በሊዝ አዋጅ የተከፋው የኅብረተሰብ ክፍል ተቃዋሚዎችን ሊመርጥ የሚችልበትን ዕድል ሰፊ ያደርገዋል:: አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ከመጪው የአዲስ አበባ ምርጫ ጋር በተያያዘ ኢሕአዴግ አደጋ ላይ የወደቀ መሆኑን ታዛቢዎች ይናገራሉ:: የመንግሥት አሞጋሽና አወዳሽ የሆነው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ሳይቀር በቅርቡ ታትሞ በወጣው ርዕሰ አንቀጹ መንግሥት በቂ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ባለመሥራቱ በደላሎች ሁለት ለአንድ እየተመራ ነው በማለት መግለጹ በአሁኑ ወቅት ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ያሳያል::

ከዚህ ቀደም ከፀደቁት ሕጐች በተለየ ሁኔታ መንግሥት የሊዝ አዋጁን በቂ ውይይት ሳያካሂድ በችኮላ ያፀደቀበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ነው:: የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ እንደሚሉት፣ መንግሥት የሊዝ አዋጁን በጥድፊያ እንዲፀደቅ ያደረገው ከዚህ ቀደም እንደፀደቁት ሌሎች ሕጐች ሁሉ ብዙም ትኩረት ሳይሰጠው ተምታቶ ያልፋል፣ ኅብረተሰቡም እንደተለመደው ውሳኔውን ዝም ብሎ ይቀበላል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ይዞ ሳይሆን አይቀርም:: መንግሥት አዋጁ ከመፅደቁ በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ቢያካሂድ ኖሮ በአዋጁ ላይ የተካተቱ አወዛጋቢ አንቀጾች የሚለወጡበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችል እንደነበር የሚናገሩት አቶ ግርማ፣ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ ውይይት ማካሄዱ ትርጉም አልባ መሆኑን ይገልጻሉ::

አቶ ግርማ እንደሚሉት መንግሥት የሊዝ አዋጁን ካላሻሻለ በስተቀር ምን ያህል ውይይት ቢያካሂድ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመለካከት መቀየር አይችልም:: ኢሕአዴግ የሕዝቡን ድጋፍ ማግኘት ከፈለገ የሊዝ አዋጁን ማሻሻል አለበት የሚሉ ወገኖች የመኖራቸውን ያህል ሕጉን ማሻሻል ለኢሕአዴግ ውድቀት ይሆናል የሚሉ ወገኖችም አልጠፉም:: እነኝህ ወገኖች እንደሚሉት ኢሕአዴግ ለሕዝብ ይጠቅማል ብሎ ያወጣውን ሕግ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያስተካክል ከሆነ ሕዝቡ ‹‹በደመነፍስ ነው የምንመራው›› በማለት በመንግሥት ላይ እምነት ያጣል:: አቶ ግርማ ግን በዚህ አይስማሙም:: እርሳቸው እንደሚሉት ኢሕአዴግ አዋጁን የማያስተካክል ከሆነ በሊዝ አዋጁ የተከፋው ሕዝብ በሙሉ በቀጣዩ ምርጫ በድምፁ ይቀጣዋል:: መንግሥት ሕጉን የሚያሻሽል ከሆነ የተወሰነውን ኅብረተሰብ ድጋፍ ሊያገኝ የሚችልበት አጋጣሚ እንደሚኖር የሚናገሩት አቶ

ግርማ፣ ‹‹አዋጁን ሳያስተካክል ቢቀር ውጤቱን ያገኘዋል›› ሲሉ ያስጠነቅቃሉ::

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ ታዋቂ የሕግ ምሁር በበኩላቸው፣ የሊዝ አዋጁ በቂ ውይይት ሳይደረግበት በጥድፊያ እንዲፀድቅ መደረጉ የሕግ አወጣጥ ሥርዓቱ በሚያስደንቅ ደረጃ የተመሰቃቀለ መሆኑን ያመላክታል:: ሕጉ ከመፅደቁ በፊት መንግሥት ጉዳዩን በትክክል ስለማየቱም ይጠራጠራሉ::

‹‹የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጁን ዝም ብሎ አቀረበ፤ ፓርላማው አፀደቀለት›› በማለት አዋጁ የፀደቀበትን የተሳሳተ መንገድ ይናገራሉ:: ሕጉ ከፀደቀ በኋላ የመንግሥት ኃላፊዎች ሕዝብን በማወያየት ስህተታቸውን ለማስተባበል የሚያካሂዱት ዘመቻ በተጨባጭ ያለውን ችግር ይቀርፋል የሚል እምነት የላቸውም:: እርሳቸው እንደሚሉት መንግሥት ለጉዳዩ እልባት መስጠት ካስፈለገ የተወሰኑ የፓርላማ አባላትን ፊርማ በማሰባሰብ ፓርላማው ሕጉን እንደገና አይቶ ማሻሻያ የሚደረግበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል:: መንግሥት አወዛጋቢዎቹን የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ፣ የሚዲያ ሕግና የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ሕግ ሲያፀድቅ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም በጉዳዩ ላይ የጠራ አቋም የነበረው መሆኑን የሚያስረዱት ምሁሩ፣ በሊዝ አዋጅ ላይ ግን ሕጉን ካዘጋጁት የመንግሥት ኃላፊዎች ውጪ ‹‹የመንግሥት አቋም ይኼ ነው›› ብሎ መናገር እንደሚያስቸግር ይገልጻሉ:: አልፎ አልፎ የሚታዩ መለሳለሶችም ለዚህ ዓይነተኛ መገለጫዎች መሆናቸውን ያስረዳሉ::

በሊዝ አዋጁ ላይ ተቃውሞ የሚያቀርቡ ወገኖች ጥቅማቸው የተነካና ኪራይ ሰብሳቢዎች ናቸው የሚለውን የመንግሥት ኃላፊዎችን ሐሳብም የሕግ ምሁሩ አይቀበሉትም:: በእርሳቸው እምነት ነባር ይዞታዎች በሙሉ ወደ ሊዝ መግባት አለባቸው መባሉ ይዞታዎችን በማናጋት መፈናቀልን የሚያስከትሉ በመሆኑ በአዋጁ ተጐጂ የሚሆኑት ሰዎች በርካቶች ናቸው:: አዋጁን የሚቃወሙት ጥቅማቸው የተነካባቸው ሰዎች ናቸው የሚለው ማስተባበያ ውኃ የማይቋጥር መሆኑን ሲያስረዱም፣ በአንድ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተናገሩትን ተረት በምሳሌነት ያቀርባሉ::

በአንድ ወቅት አንድ ንጉሥ አንድ ዓባይ ጠንቋይ ጠርተው መቼ ነው የምሞተው? ብለው ሲጠይቁት ዓባይ ጠንቋዩ ‹‹እርስዎ የሚሞቱት እኔ በሞትኩ በማግስቱ ነው›› የሚል ምላሽ መስጠቱን፣ ንጉሡም ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ‹‹ይኼንን ሰውዬ እንዳይሞት ተንከባከቡት›› ብለው ትዕዛዝ መስጠታቸውን አቶ መለስ የገለጹበት ሁኔታ መኖሩን የጠቆሙት የሕግ ምሁሩ፣ ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ መሥራታቸው እንደ ወንጀል ሊቆጠር እንደማይገባ ያስረዳሉ::

የመንግሥት ባለሥልጣናቱ በተለያዩ ጊዜያት በሰጡት መግለጫ በሊዝ አዋጁ ላይ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ወገኖች በኪራይ ሰብሳቢነት ተሰማርተው የቆዩ ጥቂት የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ አዋጁ አብዛኛውን ኅብረተሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ቢገልጹም፣ ይህ የእነሱ ድምዳሜ በአብዛኛው ኅብረተሰብ ተቀባይነት ያገኘ አልነበረም:: ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ውይይት ሳያደርግ አዋጁ መፅደቁ ስህተት እንደነበረ በመንግሥት ባለሥልጣናት ቢነገርም ተቀባይነቱ ውኃ የሚቋጥር አልሆነም::

Page 8: Reporter Issue 1229

ገጽ 8|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

Page 9: Reporter Issue 1229

|ገጽ 9 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

Page 10: Reporter Issue 1229

ገጽ 10|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

ቶታል ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀውን ማደያ ሊያስመርቅ ነው

ቶታል ኢትዮጵያ ሐያት አካባቢ 10.6 ሚሊዮን ብር የፈጀበትን ማደያ የፊታችን ሐሙስ ሊያስመርቅ ነው::ድርጅቱ በአዲስ አበባ ያለውን የማደያ ቁጥር 36 ያደረሰው ይህ የነዳጅ ማደያ፣ ካፌ፣ የመኪና ማጠቢያ፣ የጐማ አገልግሎት መስጫና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጥ ይሆናል::ቶታል ኢትዮጵያ በመላ አገሪቱ 186 የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች አሉት::

በብርሃኑ ፈቃደ

አዋሽ ወንዝ መነሻውን ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ በኩል በኦሮሚያዋ ምዕራብ ሸዋ ኢጀሬ ወረዳ አድርጎ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ዝቋላ ተራራን እያካለለ ሦስት ተጨማሪ ክልሎችን አረስርሶ፣ ሲብሰው ደግሞ ገነዳድሶ ውሎ ያድራል:: እንደ ዓባይ ሁሉን ጠራርጎ ሳይወስድ የአንዱን ለአንዱ እያካፈለ እዚሁ ጂቡቲ ድንበር አፋፍ ላይ 1,200 ኪሎ ሜትር አካልሎ እፎይ ይላል::

ኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ሶማሌ ክልሎችን በውኃ ሲሳይ እያቋደሰ የሚኖረው አዋሽ፣ አሁን ደግሞ አራት የስኳር ፋብሪካዎችን፣ የእርሻ ማሳቸውን፣ እንዲሁም ግድቦቻቸውን ጭምር በውኃው እያጠገበ ያገለግል ጀምሯል:: ገባሮቹን የሎጊያ፣ የቦርከና፣ የሚሌ፣ የአጣዬ፣ የሐዋዲ፣ የቀበናና የዱርከም ወንዞችን አስተባብሮ መተሐራን፣ አዋሽ፣ ገዋኔንና አሳኢታ ከተሞችን እየሰነጠቀ የአገር ሲሳይነቱን ያስመሰክራል:: በንዳዱና በሐሩሩ ጊዜ ለጥም፣ ለነፍስ ሐሴት ከመሆኑ በላይ በየደረሰበት አትክልትና ፍራፍሬውን፣ ሰብልና አዝርዕቱን ሁሉ እያለማ ይነጉዳል::

ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በአንድ ኪሎ ሜትር ዙርያ እየተሽከረከሩ የሸንኮራ አገዳ እርሻውን የሚያጠጡለት ዘጠኝ ዘመናዊ ውኃ ማጠጫዎቹ የአዋሽ ወንዝ ተጠልፎላቸው ሳያቋርጡ ተግባራቸውን ያከናውናሉ:: በሰኮንድ 500 ሜትር ኩብ ውኃ ከአዋሽ ሆድ እየተቀዳ በየሰርጡ አቆራርጦ ሰፋፊዎቹን እርሻዎች ያጠጣል:: ወንጂ ሸዋ ስኳር በዚህ አኳኋን በቀን ከ8,100 ሔክታር በላይ የሸንኮራ አገዳ ተክል ያለው ሲሆን፣ ዓመታዊ የስኳር ምርቱም በዓመት 75,000 ቶን ሆኖለታል:: እንደ ወንጂ ሸዋ ሁሉ መተሐራ ስኳር ፋብሪካም አንጋፋና 46 ዓመታትን የፈጀ የስኳር ምርት ተሞክሮ አለው:: አዋሽን ጠልፎ ሸንኮራ የሚያለማው መተሐራ በሰኮንድ ስምንት ሜትር ኩብ ውኃ በመስኖ እያጠጣ፣ አባድር በሚባለው አዲሱ ያገዳ ማሳውም አራት ሜትር ኩብ ውኃ በሰኮንድ እየጠለፈ በቀደዳቸውና 1,200 ኪሎ ሜትር በሚሸፍኑት ቦዮቹ ከአዋሽ ያጠጣል::

መተሐራ በ1962 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መንግሥትና በደቹ ኤችቪኤ ኩባንያ መሠረቱን ሲጥል፣ በቀን 17 ሺሕ ኩንታል አገዳ እየፈጨ ወደ ስኳርነት የሚለውጥበት አቅሙ አሁን ላይ 50 ሺሕ ኩንታል ደርሶ፤ በቀን አምስት ሺሕ ኩንታል ስኳር ለማምረት አስችሎታል:: በስኳር ተረፈ ምርቱም (አገዳ ገለባ፣ ጭቃና ሞላሰስ) በቀን 10 ሺሕ ሌትር ኢታኖል ለማምረት የሚያስችለውን ፕሮጀክት ተክሎ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል:: 10 ሺሕ ሔክታር መሬትም ለአገዳ ልማት አውሏል:: በአሁኑ ወቅት ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙበት ቤንዚን ከዚሁ 10 በመቶ የኢታኖል ድብልቅ ያለው ነው:: መተሐራ የኢታኖል ማምረቻ ፕሮጀክቱን ለመገንባት 11 ወራት የፈጀበት ሲሆን፣ ለግንባታው ደግሞ 225 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል:: 55 በመቶውን ኢታኖል መተሐራ ሲያመርት ቀሪውን ፊንጫኣ ይሸፍናል:: ከኢታኖል የሚወጣው ተረፈ ምርትም ለአፈር ማዳበርያነት እየዋለ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል::

በሁለት ወገን የማስፋፋት ሥራ የመረጠው መተሐራ፣ አሁን በቀን 50 ሺሕ ኩንታል

የሚፈጭበት አቅሙን ወደ 65 ሺሕ ኩንታል የሚያሳድግበት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከሰም በሚባለው የአፋርና የኦሮሚያ አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገነባው ነው:: ሆኖም መንግሥት ከሰም ለብቻው ራሱን ችሎ የሚቋቋቀም ፕሮጀክት እንዲሆንለት እያሰበ ሲሆን፣ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ከስኳር ኮርፖሬሽን እንደተመደበለትም ታውቋል:: በከሰም 1100 ሔክታር መሬት በአገዳ ተሸፍኖ፣ የፋብሪካ ተከላ ሥራውም እንዲሁ መንገዱን ጀምሯል:: ከሰም በመተሐራ ሥር መሆኑ ከጠለ ደግሞ መተሐራ አሁን በዓመት የሚያመርተውን 1.3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር በእጥፍ ጨምሮ ወደ 2.6 ሚሊዮን እንደሚያሳድገው ይታሰባል::

የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብዙነህ አሰፋ፣ ፋብሪካቸው ከዚህም በላይ ለገበሬዎች ማኅበራት 920 ሔክታር ያህል መሬት አልምቶ እንደሰጠ ሲናገሩ፣ ይህም ማለት 1,800 አባወራ የሚያስተናግድ መሆኑን የኦሮሚያን የመስኖ መሬት ክፍፍል አሠራርን ማጣቀሻ

አድርገው ነው::

የመተሐራ ሠራተኞች ጥያቄ

በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ 8,500 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞችን የሚያስተዳድር ግዙፍ ፋብሪካ ነው:: ጋዜጠኞች ፋብሪካውን በጎበኙበት አጋጣሚ ግን በርካታ የተከፉ ሠራተኞች ብሶታቸውን ለማሰማት ከሥራ ገበታቸው ነቅለው የወጡበት አጋጣሚ ተከስቶ ነበር:: ሠራተኞቹን ባነጋገርንበት ወቅት ለመረዳት እንደቻልነው፣ ቢያንስ 1,500 ያህል ሠራተኞች በፋብሪካው ሪፎርም ሰበብ መቀነሳቸውን ይናገራሉ:: በርካቶቹ በጡረታ ምክንያት እንደሚቀነሱ ቢነገራቸውም፣ ውጡ የተባሉበት መንገድ ግን እጅግ አስከፍቷቸዋል::

አቶ ዋቤ ዴዳቾ፣ በመተሐራ 23 ዓመታት አገልግለዋል:: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደመወዛቸው 1,050 ብር ቢደርስም አምስት ልጆቻቸውን ለማስተዳደር ይፍጨረጨሩባታል:: ፋብሪካው የቤት፣ የመብራት፣ የውኃ፣ የሕክምናና መሰል

ሽፋን ስለሚሰጥ አንዳንዱን በዚያ እንደሚያቻችሉት ቢታመንም፣ ድንገተኛው የስንብት መርዶ ግን ግራ የሚያጋባ ሆኖባቸዋል:: በራሳችሁ ከሥራ ገበታችሁ መልቀቃችሁን በፊርማችሁ አረጋግጡልኝ የሚለው የፋብሪካው ጥያቄ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ እንደሚባለው ሆኖባቸው አበሳጭቷቸው ተቃውመውታል:: ተቋውሟቸው ግን ከቀድሞው የሥራ ገበታቸው ዝቅ ብለው በማጽዳት ተግባር ላይ እንዲሠማሩ እንጂ እንደ መብት ጥያቄ እንዳልታየላቸው ተናግረዋል::

በርካታ ሠራተኞች የስኳር ኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር የቅርብ ጊዜ ጉብኝት በክፍያ፣ በአስተዳደር፣ በሠራተኛ መብትና በጥቅማጥቅም መከበር ላይ ጥያቄ አንስተውላቸው መፍትሔ እንደሚያገኙ ሲጠባበቁ በተቃራኒው ግን ውጤቱ ከሥራ መባረር መሆኑ ተስፋ ቢስ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል:: ‹‹እናንተስ ምን ልታመጡልን ነው የምታደክሙን? እርሳቸው በመጡበት ወቅት እየሆነ ያለውን፣ እውነቱን የተናገሩ እኮ ዛሬ ምን

አዋሽ ወንዝ የሚመግባቸው ግድቦችና ስኳር ፋብሪካዎች

መተሐራ ስኳር ፋብሪካ 8,500 ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞችን የሚያስተዳድር ግዙፍ ፋብሪካ ነው

Page 11: Reporter Issue 1229

|ገጽ 11 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

በዳዊት ታዬ

የሃይላንድ ውኃ አምራች የሆነው ኢትዮጵያ ቬንቸር ሊሚትድ አፔክስ ቦትሊንግ ኩባንያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የድርጅቱን ሠራተኞች በሙሉ ከሥራ ማገዱን ተከትሎ በሠራተኞችና በድርጅቱ መካከል የተፈጠረው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው::

ኢትዮጵያ ቬንቸርስ ሊሚትድ ባሳለፍነው ጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ሠራተኞቹን በሙሉ ሰብስቦ ከሥራ ማገዱን ያስታወቀው ከመንግሥት ግብር ጋር በተያያዘ የሥራ ፍቃዱን ማደስና መሥራት ባለመቻሉ እንደሆነ ገልጿል::

ይህንን ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ ግን ወደ 40 የሚጠጉ ሠራተኞችን መልሶ ወደ ሥራ እንዲገቡ ማድረጉና ቀሪዎቹ ሠራተኞች ደግሞ በሕግ አግባብ ሊከፈላቸው የሚገባ ጥቅማጥቅም ያልተሰጣቸው በመሆኑ፣ ድርጅቱ ከሕግ ውጭ ያልተገባ ተግባር እየሠራ ነው ብለው ከሰዋል::

የድርጅቱ የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር ወ/ሮ ትዕግሥት ተፈራ፣ ‹‹ድርጅቱ ያለምንም ማስጠንቀቂያና በሕግ ልናገኝ የሚገባንን ጥቅማጥቅም ሳይሰጥ መሰናበታችን ሳያንስና ሁሉም ሠራተኛ መታገዱን አሳውቆ በጐን የተወሰኑ ሠራተኞችን መርጦ ማስገባቱ፣ ድርጅቱ ሕገወጥ አካሄድ እየተጓዘ መሆኑን ያሳያል፤›› ብለዋል::

ሥራዬን ለመቀጠል ፍቃድ አልታደሰልኝም እያለ አዲስ የሠራተኛ ቅጥር ለማድረግ ማስታወቂያ ጭምር ለጥፎ ነበር የሚሉት የሠራተኛ ማኅበሩ ሊቀመንበር፣ እንዲህ ዓይነት አካሄዱ አሳዛኝ ነውም ይላሉ::

በድርጅቱና በሠራተኞቹ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ከመጀመርያው ጀምሮ ሲከታተል እንደቆየ የገለጹት የኢትዮጵያ የምግብ፣ የመጠጥና የመሳሰሉት ሠራተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ገብረሥላሴ ተስፋዬ፣ የድርጅቱ አካሄድ ግራ የሚያጋባና ሕግን የተከተለ አለመሆኑን ያስረዳሉ::

የድርጅቱ አካሄድ አግባብ አለመሆኑንና ጉዳዩን

በሰላማዊ መንገድ ለመጨረስ የተደረገው ጥረት ያለመሳካቱን ያስረዱት አቶ ገብረሥላሴ፣ ድርጅቱ ሥራዬን መሥራት ያልቻልኩት ፍቃዴን ማደስ ባለመቻሌ ነው ብሎ ይህንንም ያደረኩት ለሁሉም ሠራተኛ ነው በማለት እንደገና የተወሰኑ ሠራተኞችን መርጦ እንዲገቡ ማድረጉ በራሱ ትክክል አለመሆኑን ያስረዳሉ::

ሠራተኞቹ የታገዱበት ምክንያት አግባብ ባለመሆኑም ጉዳዩ የሚመለከተው የአዲስ አበባ ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲያውቀው ተደርጐ ቢሮው ሠራተኞችን ያገደበት ምክንያት አሳማኝ አለመሆኑን ገልጿል::

ድርጅቱ እገዳውን ሲያደርግ ምክንያቱን ቢሮው በደብዳቤ ጭምር ያስታወቀ ቢሆንም፣ ቢሮው በበኩሉ ‹‹በአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ድንጋጌዎች መሠረት ከሥራ ውል የሚመነጩ የመብትና ግዴታዎች ለጊዜው ታግዶ የሚቆይበት ሁኔታ አንቀጽ 18/6 የአሠሪው ጥፋት ባልሆነ ምክንያት ከ10 ተከታታይ ቀናት ላላነሰ ጊዜ የድርጅቱ ሥራ የሚያቋርጥ ያልታሰበ የገንዘብ

ችግር ሲያጋጥም የሚፈቀድ ቢሆንም፣ ድርጅቱ የፈጸመውን እገዳ በጥልቀት ሲመረምር አዋጁን መሠረት ያላደረገ ስለሆነ ቢሮው እገዳውን ያልተቀበለ መሆኑን እየገለጽን ድርጅቱም ሠራተኞችን አግዶ ላቆየበት ጊዜ ደመወዝ እንዲከፍል እናሳስባለን፤›› ይላሉ::

ከዚህ ደብዳቤ በኋላም ቢሆን ፌዴሬሽኑ ከድርጅቱ ማኔጅመንት ጋር ውይይት ቢያደርግም፣ ሠራተኞችን ለመመለስ ወይም በሕግ የሚፈቀድላቸውን ክፍያ ባለመስጠቱ ጉዳዩን ወደሕግ ለመውሰድ መገደዳቸውን አቶ ገብረ ሥላሴ ገልጸዋል::

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ መሠረት አንድ ድርጅት እገዳ ሲያደርግ የስድስት ወር ደመወዝ ለሠራተኞች መክፈል አለበት:: ከ145 በላይ የሚሆኑት ሠራተኞች በሕግ አግባብ ሊከፈላቸው የሚገባቸው ወደ 800 ሺሕ ብር በመሆኑ ይህንኑ ክፍያ እንዲያገኙ አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል::

ማንኛውም በድርጅቱ ላይ ገንዘብ የሚፈልግ አካል ንብረቱን በማሳገድ ጭምር ይህ ክፍያ እንዲከፈልና ቅድሚያ ሠራተኞቹ እንዲያገኙ እናደርጋለንም ብለዋል::

ድርጅቱ በራሱ አነሳሽነት ሠራተኞችን በማባረሩ ሠራተኞች ተገቢውን ጥቅም የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ ነው ይላሉ:: እንደ ሠራተኛ ማኅበሩ ገለጻ፣ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ በሆነ መንገድ 106 ሠራተኞችን ማባረሩና በፍርድ ቤት የስድስት ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው ተወስኖላቸው እንደነበር ያስታውሳሉ::

ድርጅታችን ለሚያመርተው የታሸገ ውኃ ከመንግሥት የሚፈለግበትን ግብር በወቅቱ እየከፈለ የቆየ ቢሆንም፣ ከ1996 እስከ 2000 ዓ.ም. ድረስ ላመረተው የታሸገ ውኃ የማሸጊያ ወጪውን በማካተት የተሰላውን ኤክሳይዝ ታክስ 52.04 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል የግብር ማስታወቂያ የደረሰው መሆኑ ይታወቃል:: ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 307/95 አንቀፅ 2(8) እና 5(1) መሠረት በማምረቻ ወጪ ውስጥ የሚካተት ባለመሆኑ የማሸጊያ ወጪ

ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የመክፈል ኃላፊነት አለበት ብሎ ስለማያምን ታክሱን አልከፈለም:: በአዋጁ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው በማሸጊያ ወጪ ላይ ኤክሳይዝ ታክስ መክፈል የሌለበት ለመሆኑም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ብሎ ለሚያምነው የመንግሥት መሥርያ ቤቶች በሙሉ አቤቱታውን ሲያቀርብ የቆየ ቢሆንም፣ አዋጁ ሲወጣ የሕግ አውጪው ሐሳብ ለኤክሳይዝ ታክስ መሠረት የሆነው የማምረቻ ወጪ የማሸጊያ ወጪንም የሚያጠቃልል በመሆኑ በማሸጊያ ወጪ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ ሊከፈል ይገባል በሚል ምክንያት ጥያቄው ውድቅ ተደርጓል::

በሌላ በኩል ግን በአዋጅ ቁጥር 686/2002 መሠረት የድርጅቱ የንግድ ሥራ ፈቃድ ካልታደሰና የፀና የንግድ ፈቃድ ከሌለው በቀር ድርጅቱ የንግድ ሥራውን መሥራት አይችልም:: የንግድ ሥራ ፈቃዱን ለማደስ ደግሞ በቅድሚያ የተወሰነበትን የኤክሳይዝ ታክስ ዕዳ መክፈል ይጠበቅበታል:: ከፍ ሲል እንደተገለጸውም፣ ገንዘቡ ከድርጅቱ አቅም በላይ በመሆኑ ዕዳውን ሊከፍል ስላልቻለ የንግድ ፈቃዱን ለማደስ አልተቻለም:: ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ያቀረብነው የዕዳ ምህረት ጥያቄው እስከሚታይ ድረስ የድርጅቱ የንግድ ፈቃድ ታድሶ ሥራውን እንዲቀጥልና ሠራተኞች እንዳይበተኑ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ያቀረብነው ጥያቄም ተቀባይነት ባለማግኘቱ ፈቃዱን ለማደስ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም::

በመሆኑም ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ምክንያቶች ድርጅቱ የንግድ ሥራ ፈቃዱን ማደስ ባለመቻሉ የንግድ ሥራውን ሊሠራ የማይችልና ፈቃዱ ሳይታደስ ሥራውን መሥራትም ከባድ የወንጀል ኃላፊነት የሚያስከትል በመሆኑ እንዲሁም ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ያቀረብነው የዕዳ ምህረት ጥያቄም ምላሽ ለማግኘት ጊዜ የሚወስድ ስለሆነ ድርጅቱ ላልተወሰነ ጊዜ ሥራውን እንዲያቆም ተገዷል::

በመሆኑም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 18(6) መሠረት ከጥር 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የድርጅቱ ሠራተኞች የሥራ ውል መታገዱን እንገልጻለን::

አፔክስ ቦትሊንግ ከሠራተኞቹ ጋር እየተወዛገበ ነው

እንደተደረጉ እያየን ነው፣›› የሚለውን አስተያየት የሰነዘሩም ነበሩ::

የሠራተኞቹ ጥያቄ በእነዚህ ጉዳዮች ይጀምርና፣ በቀን ሥራ የሚከፈለው 23 ብር ዝቅተኛነት፣ በዓመት የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ 40 ሳንቲም የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳለና ከሁሉ በላይ ደግሞ 15 እና 20 ዓመት አገልግለው የቋሚ ሠራተኛነት መብት መነፈጋቸው፣ የእያንዳንዱን ሠራተኛ የሥራ ሒደት ጥራት፣ የማምረት አቅምና ብቃት ሁሉ እንደማይታዩላቸው የተናገሩት ደግሞ በመተሐራ 30 ዓመት ሲያገለገሉ፣ 15ቱን ዓመት በጊዜያዊነት ማሳለፋቸውን፣ ሆኖም ግን ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያና ገለጻ ከሥራ መሰናበታቸውን የሚገልጽ ጽሑፍ በሰሌዳ ላይ ተለጥፎ ከበርካታ ስም ዝርዝሮች መካከል እርሳቸውም መካተታቸውን ተናግረዋል::

የእርሻ ሥራዎች ሥራ አስኪያጁ አቶ አብዱላዚዝ የሱፍም ሆኑ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ብዙነህ ፋብሪካው ባካሄደው ሪፎርም ከሚገባው በላይ ሠራተኛ መሸከሙ እንደተረጋገጠ ተናግረዋል:: እንደ አቶ አብዱላዚዝ ገላጻ፣ በእርሻ ሥራ ብቻ ከሚሳተፉ 7,000 ሠራተኞች አምስት ሺሕ ያህሉ ጊዜያዊ ሆነው፣ ከስድስት እስከ አሥራ አንድ ወራት ለሚደርስ ጊዜ የሚቀጠሩ ናቸው:: ሁለት ሺሕ ያህሉ ደግሞ ቋሚ ሆነው የሚሠሩ ናቸው:: ከእነዚህም ግን የሚቀነስ ሠራተኛ እንደሚኖር አረጋግጠዋል::

አብዛኞቹ ሠራተኞቹ የቁርጥ ሥራ የሚሠሩ እንደሆኑ ይታወቃል:: ይህም ሠራተኞቹ በሠሩት የሥራ መጠን ልክ የሚከፈላቸው ነው:: ለአብነት አንድ የአገዳ ቆረጣ ሠራተኛ ፋብሪካው ደህና አድርጎ ሲፈጭ እስከ 40 ብርና ከዚያም በላይ ሊያገኝ ይችላል ያሉት አቶ አብዱላዚዝ፣ ይህን ያህን ባልፈጨ ጊዜ ግን በቀን 23 ብር የጆርናታ ክፍያ እንደሚፈጸም አረጋግጠዋል:: ይህ ዝቅተኛው ክፍያ ግን ለሠራተኛው ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ብዙነህ ተጫማሪ ማብራርያ መስጠት ግድ ሆኖባቸው ነበር:: በክፍያና በቋሚ ቅጥር ዙርያ ሠራተኞች ላነሱት ቅሬታ ማስተባበያ የሰጡት አቶ ብዙነህ፣ በኮንትራት ሥራ በጊዜያዊነት እስከ 20 ዓመት እንድናገለግል ተገደናል ለሚለው የሠራተኞቹ ጥያቄ፣ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሠራተኞች የቋሚነት ቅጥር እንደሚፈጸም፣ ለክፍት ቦታዎች አስፈላጊውን መስፈርት ያሟሉ ሠራተኞች እስካሉ ድረስም ቋሚ ቅጥር እንደሚሰጣቸው ተናግረዋል::

የ‹‹አርባ ሳንቲም ጭማሪ››

ሠራተኞቹ እንደሚናገሩት አንድ ዓመት ላገለገሉበት አርባ ሳንቲም በደመወዛቸው ላይ ሊጨመር እንደቻለና በምን እሳቤ እንደሆነ ግራ የገባቸው፣ አንዳንዶቹ ጭርስኑ ይህችኑ ጭማሪ ሳያገኙም ሁለት ዓመት እንደሚቆዩ ሲናገሩም ተደምጠዋል::

አቶ ብዙነህ ይህንን ጥያቄ የሚመልሱት ጭማሪው ከሁለት ዓመትም በላይ ወይም ከሦስት ዓመት በኋላ ሊደረግ የሚችል እንደሆነ በመግለጽ ምላሻቸውን ሲጀምሩ፣ ለቋሚ ሠራተኛ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ ሳይሆን ለቁርጥ ሥራ የሚደረግ የሥራ ዋጋ ጭማሪ መሆኑን በማብራራት ነበር:: ለቁርጥ ሥራ በተሠራው መጠን የሚከፈል በመሆኑ በአገር አቀፍ ደረጃ ጭምር ታይተው ጭማሪ እንደሚደረግበት ገልጸዋል:: በፋብሪካው ሠራተኞች የሚያነሷቸው ጥያቄዎች በርካታ ናቸው:: ለየት ካሉት መካከል ግን ከደመወዝ ጭማሪና ከቅጥር ጋር የሚገናኙ ነበሩ:: የቀን ክፍያ 23 ብር መሆኑ ከመንግሥት ዝቅተኛ ክፍያ ጋር ሲታይ በቂ ሊባል እንደሚችል የሚናገሩት አቶ ብዙነህ፣ የሠራተኛ ማኅበሩም ተገኝቶበት የተቀመጠ ስለመሆኑ ተናግረዋል:: ይህንን የቁርጥ ሥራ ክፍያ የሚያገኙት ሠራተኞች፣ በሥራ ለሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ የቤት፣ የውኃ፣ የመብራት፣ የሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ ሲገልጹም፣ ዓመታዊ የሕክምና ወጪው 12 ሚሊዮን ብር ከመሆኑም በላይ ለጊዜያዊ ሠራተኛ ሐኪም እስካዘዘ ድረስ እስከ 70 ሺሕ ብር ድረስ ለሕክምና ያወጣል ብለዋል::

በሪፎርሙ የሚቀነሱትን የሠራተኞች ጉዳይ በተመለከተ ሲናገሩ፣ የኢትየጵያ ስኳር ፋብሪካዎች ከሚገኙበት ዘልማዳዊ አሠራርና ከአቅም በላይ የሠራተኛ መጠን መሸከም መገለጫቸው ሆኖ መገኘቱን፣ በዚህም ቁጥራቸው ለጊዜው ያልተገጸ መጠን ሠራተኞች ከመተሐራ እንደሚቀነሱና በአብዛኛው ከዕድሜያቸው ጋር እንደሚያያዝ ገልጸዋል:: በቅርቡ ለመከታተል እንደተቻለውም በተለያዩ የሥራ መስኮችም የቅጥር ማስታወቂያ እየለቀቀ ይገኛል:: ቦታ ያጡ ሠራተኞችን በተለይ ጡረታ ይወጣሉ የተባሉቱ 55 ዓመት ዕድሜ ያለፋቸው፣ 25 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ወዲያውኑ የጡረታ መብት አግኝተው ይሰናበታሉ:: 50 ዓመት የሞላቸውና 25 ዓመት ያገለገሉትን ከሥራ ለማሰናበት በሕጉም ስላልቻለ በሚኒስትሮች ምክር ቤት አስወስኖ፣ ቋሚ የጡረታ

አበል እንዲያገኙ ለማድረግም ያስባል:: ነገር ግን ነባሮቹ ሠራተኞች ስጋታቸው ከ25 ዓመታት በላይ በፋብሪካው ሲሠሩ የቤትና መሰል ጥቅማጥቅም ያገኙ ስለነበር የክፍያውን ማነስ በዚያ ሲያካክሱ እንደቆዩ ገልጸው፣ የአሁኑ ስጋታቸው ግን በምትከፈላቸው 800 ብር ወይም 1,000 ብር ቤት ተከራይተው፣ አምስትም ስድስትም ልጆቻቸውን ቀልበውና አስተምረው ለመኖር የመቻላቸው ጉዳይ ያስፈራቸዋል:: በዚህ ምክንያትም ተመርጠው እንደተጣሉ፣ ጉልበታቸው ሲያልቅ እንደተወገዱ የሚሰማቸው አንጋፋ ሠራተኞች ብሶታቸው ገንፍሎ ሲወጣ መመልከት ችለናል:: አቶ ብዙነህ ግን የሚቀነሱት ሠራተኞች ፈቃደኞች እስከሆኑ ድረስ አዳዲስ በሚቋቋሙት ግዙፍ ፋብሪካዎች ቦታ እንደማያጡ ተስፋ አለኝ ባይ ናቸው::

ከሰም ፕሮጀክትና ለተነሺ ኗሪዎች የቤቶች ግንባታ

ከሰም ፕሮጀክትን የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን በተቋራጭነት የሚመራው ሲሆን፣ በሚገነባው ግድብ 20 ሺሕ ሔክታር ለሸንኮራ አገዳ ልማት ውኃ የማጠጣት አቅም ይኖረዋል:: በተጨማሪም ለአርብቶ አደሩ የሰፈራና የልማት ቦታ ስለሚሰጥም ያንንም እንዲያለማ የሚጠበቅ ነው:: ለመስኖ ልማት በሚውለው ደቡባዊ ክፍል ላይ ሰፍረው ይገኙ የነበሩ አርብቶ አደሮች የተነሱ ሲሆን፣ ይህም አምስት ሺሕ ሔክታር የሚሸፍን ቦታ ነው::

በልማት ምክንያት ለሚነሱ አርብቶ አደሮች 300 ሔክታርና 250 የሚደርሱ መኖርያ ቤቶች ተገንብተው ለአርብቶ አደሮች ይሰጣሉ:: እስካሁን 88 አርብቶ አደሮች ተነስተው ቤትና ቦታ እየተሰጣቸው እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል:: አርብቶ አደሮቹ በመሬታቸው ላይ የራሳቸውን አዝርዕቶች ማምረት ቢችሉም፣ ከፕሮጀክቱ ጋር በመሆን አገዳ ለማምረት ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸው ተነግሯል::

በፕሮጀክቱ ከሚቀጠሩት ውስጥ 30 በመቶው አርብቶ አደሮች እንደሚሆኑም ይጠበቃል:: ተጨማሪ 550 ቤቶችን ለመገንባት ጨረታ ወጥቷል:: ለእነዚህ ደግሞ 705 ሔክታር መሬት እንደሚከፋፈልም በውኃ ሥራዎች ዲዛይንና ቁጥጥር፣ የከሰም ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ነገዎ ገልጸው፣ 20 ሺሕ ሔክታሩ መሬት በሚለማበት ጊዜ እንዲነሱ የሚደረጉት ሦስት ሺሕ ያህል አርብቶ አደሮች መሆናቸውንም ተናግረዋል::

ግማሾቹ በሰፈራ ግማሾቹም በመንግሥት ቤት የሚሠራላቸው ይሆናሉ::

የከሰም ፕሮጀክት የግድብ ሥራውን ከጀመረ ስድስት ዓመታትን አስቆጥሯል:: ይህ ደግሞ የሆነው ግድቡ ሲሠራ በጂኦሎጂካል ጥናቱ ያልታሰበ የፍል ውኃ በማጋጠሙ ነው:: በመሆኑም ከስድስት ዓመታት ቆይታ በኋላ መፍትሔ የተገኘለት ይህ ችግር 220 ሜትር ቱቦ ተሠርቶለት ከግድቡ ራቅ እንዲል ተደርጓል:: የከሰም ፕሮጀክት የእርሻ ማስፋፊያ ሥራዎች ሥራ አስኪያጅ አቶ ምሩጽ ወልዳይ እንደሚገልጹት ከሆነ፣ የከሰም ግድብ ከአዋሽ በመጥለፍ 500 ሚሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ የሚይዝና ሥራውም በዚህ ዓመት የሚጠናቀቅ ይሆናል:: ውኃውን መሠረት በማድረግም በቀን 10 ሺሕ ቶን አገዳ የሚፈጭ ስኳር ፋብሪካ ለማቋቋምም ደፋ ቀና እያለ የመስኖ ሥራውና የውኃ ማከፋፈያ መስመሮች ዝርጋታም እንዲሁ በመገባደድ ላይ የሚገኙበት ባለተስፋ ፕሮጀክት ነው::

ከሰም በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልቃል ተብሎ ሲጠበቅ በመጀመርያው ዙር በቀን ስድስት ሺሕ ኩንታል የሚያመርትበትና 13 ሺሕ ሔክታር አገዳ የሚያለማበት በመሆኑ ዘንድሮ ከአንድ ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት በዘር አገዳ እንደሚሸፍን ይታሰባል:: የፋብሪካውን ሥራ የብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽንና አንድ የቻይና ኩባንያ እያካሄዱት ሲሆን፣ በኢታኖል ማምረቻው በቀን 2500 ኪሎ ሊትር ሲያመነጭ 35 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ለማቅረብ የሚችል ይሆናል::

አቶ ሰሎሞን በከሰም የመስኖ ግድብ ሥራ በአብዛኛው እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ አስረድተዋል:: በከሰም ፕሮጀክት ግራውተር የሚባልና ለኢትዮጵያውያን የመስኖ ግድብ መሐንዲሶች አዲስ አሠራር በቻይናውያን የተዋወቀ ቴክኖሎጂ የተተገበረበት ነው:: ይህም በባህር ጠለል በታች 70 ሜትር ጥልቀት በመቆፈር መሠረት የመደልደልና የማጠናከር ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ ለዚህ ተግባር ብቻ ሲባል ከቻይና 3,500 ቶን ልዩ ሲሚንቶ እንዲመጣና እንዲገነባበት መደረጉን ገልጸዋል:: 96 ሜትር ቁመት የሚኖረው ሆኖ እየተገነባ ያለ ሲሆን፣ የ50 ዓመት ዕድሜ በትንሹ ተተልሞለታል:: 1.2 ቢሊዮን ብር የተመደበለት የከሰም ፕሮጀክት እንደ አቶ ሰሎሞን ማብራሪያ 50 በመቶ ሥራው የተጠናቀቀ ነው:: 500 ሠራተኞችን በቋሚና ጊዜያዊ ይዞ እየሠራ ይገኛል::

አቶ ገብረሥላሴ ተስፋዬ

Page 12: Reporter Issue 1229

ገጽ 12|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

አሰናጅ፡-ሔኖክ ያሬድና ምዕራፍ ብርሃኔ

ፍለጋው የመሳሳብ ሕግ ሁሌም የሚሰጥህ የምታስበውን ነው::ግን ቢሆን አልፈልግም ለሚሉት ቃላት

ግን ቦታ የለውም::ዩኒቨርስ የምትሰማው አጣርታ ነው የሚል አንድምታ ሊፈጥር ይችላል::ነገር ግን የበለጠ

የሚመሳሰለው በተወሰኑ ቁልፍ ቃላት ላይ ትኩረት ከማድረግ ጋር ነው::ጉግል፣ ያሆ፣ አይቲዩንስ የመሳሰሉት የኀሠሣ ገጾች እንደሚያደርጉት ነው::

እንበልና ኢንተርኔት ላይ ሙዚቃ እየፈለግህ ነው::ነገር ግን የፖፕ አድናቂ አይደለህም::እናም ‹‹ፖፕ ያልሆነ›› የሚል የመፈለጊያ ቃል ታስገባለህ::

የፍለጋህ ውጤት ሲመጣ ታዲያ የኀሠሣ ገጹ ያልሆነ የሚለውን ቃል ትቶ ፖፕ በሚለው ላይ ብቻ ማተኮሩን ትረዳለህ::በሺዎች የሚቆጠሩ የፖፕ ሙዚቃ ድረ ገጾች ይዘረዘሩልናል፤ ሙሉ በሙሉ የማትፈልጋቸውን ብቻ ውጤት ያስገኘው ቁልፉ ቃል ነው::

ሒደቱ ከመሳሳብ ሕግ ጋር አንድ ዓይነት ነው::ሁሌም ወዳንተ የምትስበው ቁልፍ ቃላትን፣ የሐሳቦችህን ቁልፍ ጉዳይ ነው::እንዲከሠት የማትፈልገውን ነገር ደጋግመህ በማሰብ ትጨነቃለህ፤ ዞሮ ዞሮ ግን መከሠቱ አይቀርም::ለምን ይመስልሃል? በማትፈልገው ነገር ላይ ሙሉ ትኩረትህን በማድረግህ የተነሣ ነው::ዩኒቨርስም ያንኑ ነገር ለአንተ ለመስጠት ተግታ ሠርታለች::በሕይወትህ ውስጥ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ለማግኘት ብቸኛው መንገድ በምትፈልጋቸው ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ነው::

- ከብርሃኑ በላቸው ‹‹ታላቁ ምስጢር›› መጽሐፍ የተወሰደ (2011)

‹‹ብድሯን ያልከፈለች ወፍ››ገጣሚ ወ/ሮ ውዳለት ገዳሙ ‹‹ብድሯን ያልከፈለች ወፍ›› ብለው ያወጧት የተረት መጽሐፍ

አለች::ብድራቸውን ያልከፈሉ ኢትዮጵያውያን በሚልም ርእስ መተካት የሚችል ሐሳብ የያዘ ይመስላል::

ወፏ ብዙ ብድር ነበረባት::አበዳሪዎቿ እንዳያገኟት ቀን ቀን ተኝታ እየዋለች ሌሊት ሌሊት መብረር በመጀመሯ የሌሊት ወፍ እንደተባለች ተረቱ ይነግረናል::

አባቶቻችን ለነፃነት ሲዋደቁ ኖረው አገር ድንበር አስከብረው ሰጡን::ዛሬምኮ ዳር ድንበራቸው ያልተሰመረላቸው፣ የተረጋገጠ ድንበር የሌላቸው አገሮች አሉ::በድንበራቸው ምክንያት ብዙ ጊዜ የሚዋጉ አገሮች አሉ::

ኢትዮጵያ ጥንታዊ የሆነ ድንበሯን በልጆቿ መስዋእትነት አስከብራ አስረክባን፣ በዜግነታችን ኰርተን የምንኖርባት አገር ነች::ይህችን ዳር ድንበር አስከብረው የሰጡንን አገር ግን አሁን ያለነው ልጆቹ አላበለጸግናትም፤ ኋላቀር የሆነች አገር ለትውልድ ልናስረክብ ብዙዎቻችን አሁንም ተኝተናል::ብድሯን ያልከፈለች ወፍ መሐፍፍ ላይ ወ/ሮ ውድላት ገዳሙ ሊነግሩን የፈለጉት ለቤተሰብ፣ ለአገር፣ ለደንበኛ፣ ለባንክ ያለብንን ብድር መክፈል እንዳለብን ነው::አለበለዚያ ብድሯን ያልከፈለች የሌሊት ወፍ ቀን ትበር የነበረችው ዕዳዋን ባለመክፈልዋ ባለዕዳዎቹ እንዳይዟት ሲተኙላት በረራዋን ወደ ሌሊት የቀየረችዋን ወፍ እንሆናለን::በግል ቢዝነሳችን፣ በቤተሰብና በአገር ከመወቀስ እንድንድን ልዑል እንግዚአብሔር ሁላችንም በትጋት፣ ለዕድገትና ለብልጽግና እንድንሠራ ከልብ ያነሣሣን::

- ከዶ/ር ወሮታው በዛብህ ‹‹በኢንተርፕረነርሽፕ መበልፀግ›› የተወሰደ (2003)

ጐለጐታዛቲ ይእቲ ኆኅታ ለአርያም ብዬ ካንቺ ወዲያ ሌላ ልቤ ልብ ብትል ዓይኔ ብትማትር የአንቺን ገላ አልፈው ከሌላ ሊያርፉ ክንዶቼ ተመዘውእንደዚያ መምህር እንደ ሊቁ ጌታ ጀርባዬን በጅራፍ እልፍ ጊዜ ቧጪ ከግንባሬዬ በላይ የሾህ አክሊል ድፌ እርቃኔንም አርቀሽ በአደባባይ መሀል ከመስቀል ላይ ሰቅለሽ ደሜን አንዠቅዢቂው ጐኔን በጦር ወግተሸ ደግሞ በሁዋላ ላይ…. ስትጨርሻት ነፍሴን ከስጋዬ ከፍለሽ ውዴ! አትቅበሪኝ መቃብሩን ምሰሽ ይልቁን ውዴዋ! ለሰማይ አሞራ ረሀብ ማስታገሻ በድኔን ወርውሪው እንደግም ቆሻሻ!!

- ቢኒያም መኰንን (ጌቲ) ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ እንደገጠመው

ገራገር

የራሱን እግር ተኩሶ ያቆሰለው

ዜናው የተሰማው ከወደ ጆርጂያ ነው::የ26 ዓመቱ ፖሊስ የሽጉጥ ትርዒት ይታይ በነበረበት ጊዜ ነው እግሩን ተኩሶ ያቆሰለው::

ቻርልስ ሌክ በመባል የሚጠራው ይህ ወጣት ፖሊስ፣ ሳቫና ሲቪክ ሴንተር የሚባል ቦታ ላይ የሽጉጥ ትርዒት ሲዘጋጅ የትርኢቱ ተካፋይ ለመሆን በቦታው ታድሞ ነበር::ለትርዒቱ የቀረቡት ሽጉጦች አልተቀባበሉም ነበር::በመሆኑም ቻርልስ ቀልቡ ያረፈበትን ሽጉጥ ገዝቶ መኪኖች በብዛት የቆሙበት ስፍራ በመሄድ የሽጉጡን አፍ ወደ መሬት ዘቅዝቆ ሲያቀባበል ነበር የራሱን እግር የመታው::

ዜናውን ያስነበበው አሶሺየትድ ፕሬስ፣ ሳቫና ሞርኒንግ ኒውስን ጠቅሶ ወጣቱ ፖሊስ በወቅቱ ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደና የአካባቢው ፖሊስም ጉዳዩን እያጣራው እንደሆነ ከትናንት በስቲያ በድረ ገጹ ላይ አስነብቧል::

ራሱን እረኛ ያደረገው ጥንቸል

በሰሜናዊ ስዊድን በምትገኝ በትንሽ የእርሻ ግዛት ውስጥ አንድ ጥንቸል ራሱን የበጎች እረኝነትን አስተምሮ ሥራውንም በሚገባ በማቀላጠፍ ታዋቂነትን እያገኘ እንደሆነ ኤም ኤስ ኤን ቢ በድረ ገጹ አስነብቧል::

ጥንቸሉ እረኝነትን ከአካባቢው ውሾች እንደ ተማረ የጥንቸሉ ባለቤት ግሬታ ቫይግሬን እዚያው ስዊድን ለሚገኝ ዘ ሎካል በሚባል ድረ ገጽ ላይ ተናግረዋል::

የጥንቸሉን የእረኝነት መላ እንቅስቃሴ የግሬታ ጓደኛ የሆኑት ዳን ዌስትማን በቪዲዮ ቀርጸው ዩ ቲዮብ የሚባል ማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ በመልቀቃቸው፣ ቪዲዮው ባለፈው ሳምንት ብቻ ከ650,000 ጊዜ በላይ ታይቷል::

ዌስትማን አክለውም ጥንቸሉ ራሱን የእርሻው ንጉሥ አድርጎ የሚያይና በጎቹም የእርሱ እንደሆኑ እንደሚሰማው ተናግረዋል::

የአሜሪካዋ ሚያሚ ከተማ ‹‹ለኑሮ የማትመች›› ተብላ

ተሰየመች

ሞቃታማ ፀሐይ፣ በነጫጭ አሸዋዎች የተሞሉ የባሕር ዳርቻዎችና በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ዶላሮች የሚገመቱ የተንጣለሉ ቤቶች በሚያሚ ከተማ ቢገኙም፣ በየቦታው በሚሰሙት ድምፆች ሳቢያ ከተማዋ ለመኖር ፍጹም የማትመች መባሏን ሮይተርስ በድረ ገጹ ላይ አስነበበ::

በከተማይቱ የሚገኙት ሀብታሞችና ታዋቂ ሰዎች እጅግ ትላልቅ የሆኑ ቤቶች ቢኖሯቸውም፣ በተቃራኒው ደግሞ ከሪል ስቴት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ቀውስ ያጋጠማት ከተማ በመሆኗ ስያሜው ለመሰጠቱ አንዱ ምክንያት ሆኗል::

ለከተማይቱ ስሙ ሲሰጣት ከግምት ውስጥ ከገቡ እውነታዎች መካከል በከተማዋ ያለው የሥራ አጥነት፣ የሚፈጸመው ወንጀል፣ የሚወጡ ሐራጆች፣ የገቢና የንብረት ግብር፣ ከተማዋ በሠራተኞችና በጎብኝዎች መጨናነቋንና በግዛቷ ውስጥ ሰፍኖ ያለው የፖለቲካ ሙስና እንደሚገኙበት ታውቋል::

የከተማዋ ሞቃታማ ፀሐይና ጥሩ የአየር ንብረት የበርካቶችን ቀልብ የሚስብ ቢሆንም፣ አንድ በመቶ ከሚሆነው የከተማይቱ ነዋሪ በስተቀር የተቀረውና በዓመት 72ሺሕ ዶላር ገቢ የሚያገኘው ሕዝብ በሚያሚ ለመኖር እጅግ እንደሚቸገር ተገልጿል::

ልጅነትና ርግብቲቲ ውሻዬ በኩዳዴ ጾም ሰሞን የዓሣ

አጥንት በልታ ጉሮሮዋ ላይ በመሰንቀሩ ትንሽ ታማ ሞተችብኝ::በጣም አዘንኩኝ::ኃይሉ ዶሮ ሊያጽናናኝ ቤት መጣና ‹‹ለምን እኔና አንተ ርግብ አናረባም?›› አለኝ::

የእኛ ቤት መንገድ ዳር በመሆኑ አይመችም ስለው፣ ‹‹እኛ ግቢ ውስጥ እኮ ነው የምናረባው::ፍራንክ አዋጥተን ርግቦቹን እንገዛለን::ከዚያ ቤታቸውን ሠርተን እናኖራቸዋለን::››

ሁለት፣ ሁለት ብር አዋጥተን ወንድና ሴት የሆኑ አራት ርግቦች ከእንግዱ ላይ ገዛን::እንግዱ ከመንደራችን ወረድ ብሎ ከጨነቀው ሱቅ በታች ነው የሚኖረው::በርካታ ርግቦች አሉት::ርግብ ከሚያረቡ ሌሎች ሰዎች ጋር ግንኙነት አለው::ወንጭፍና ትንንሽ ድብልብል ድንጋዮች በኪሱ ይይዛል::ቤቱ ተወልደው ያደጉ፣ እጁን በደንብ የለመዱ ርግቦች አሉት፣ በእነዚህ ርግቦች አማካይነት ሌሎች ርግቦች ጠለፋ የሚያካሂድበት ጊዜም አለ::ይህን ለማድረግ ሌሊት ነው የሚነሳው::የቤት ርግቦቹን በሰሪያን ኮት ኪሱ ይይዝና አሰበው አካባቢ ሲደርስ ወደ ሰማይ ይለቃቸዋል::በአየር ላይ ይበርሩና ታች ሰው ግቢ ውስጥ ሌሎች ርግቦች ሲያዩ ያርፋሉ::ርግቦቹ ያረፉባቸው ሰዎች ይይዟቸዋል::ላባቸውን ይነቅሉታል::ለዕለታት እዚያው ይቆያሉ::ላባቸው እንዳደገ አንድ ሁለት ርግቦችን አስከትለው ወደ ሰፈራችን ይመጣሉ::

እንግዱ አበበ እንዲህ ዓይነት ዝነኛ ርግቦች ስላሉት አንዱን ርግብ ወደ ሰማይ ለቅቆት ሲበር ‹‹ይመለሳል›› ይላል በእርግጠኝነት::

‹‹ለማየት ያብቃህ አይመለስም›› ይላል፤ አንዱ የሰፈር ልጅ::

‹‹እንወራረድ::››‹‹በስሙኒ! በስሙኒ!››‹‹እሺ::››ያስይዛሉ::ከጥቂት ቀናት በኋላ ሲላ የተባለው

ርግቡ በአያሌ ርግቦች ታጅቦ ከች ይላል::ሰፈራቸው በጭብጨባና በጩኸት ይደምቃል::

እንግዱ ርግቦቹን ከሸጠልን በኋላ ለሳምንታት የተረጋጋ ሕይወት ኖርን::ላባቸው የተነጨው ርግቦች መንቀሳቀስ ሲጀምሩ አንዳንድ ስጋቶችን ፈጠሩብን::ከነኃይሉ ዶሮ ቤት ጓሮ ከእነ አደባይ ሰፈር አንድ ዱርዬ ድመት እየመጣ ቋሚ ጠላታችን ሆነ::እሱን ሌት ተቀን ስንጠብቅ፣ ብቅ ሲል በድንጋይም በዱላም ለመከላከል በምናደርገው ጥረት መንደሩን በጩኸት እናምሰዋለን::ትንሽ አሟቸው የተኙ አሮጊቶች እየተራገሙ ከየቤታቸው ይወጣሉ::

ድመት የገደለ እጁ ይንቀጠቀጣል የሚል እምነት ስለዘሩብን ዱሮዬውን ድመት ከማባረር ፈቅ ያለ ድፍረት አልነበረንም::ዱርዬው ድመት ግን ጨክኖ አንዱን ወንድ ርግብ በላብን::በዚህም ይሙት በቃ ፈረድንበት::ኃይሉ ዶሮ ጥሩ አላሚ ስለነበረ አነጣጥሮ የወረወራት ድንጋይ አንዴ ጆሮግንድን ብትለው ዱሮዬው ድመት ሲንደባለል በጣም ደስ ብሎኝ ጨኽኩኝ::ኃይሉ ዶሮም አብሮኝ ጮኾ፣ ‹‹ወይኔ ፋንጋይ! እጄን እየው፣ መንቀጥቀጥ ጀመረ›› አለኝ::

ሳይ እጁ ምንም አይንቀጠቀጥም::ዞር ስንል ድመቱ ተነስቶ ጥሻ ውስጥ ገብቷል::‹‹ይኼውልህ! ባለመሞቱ ነው እጄን ያንቀጠቅጠኝ የነበረው የተወኝ::››

አመንኩት::- ዘነበ ወላ ‹‹ልጅነት›› በሚለው መጽሐፉ

የተረከው (2004)

አማራጭ ወቅታዊ መረጃ ፍለጋ

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

Page 13: Reporter Issue 1229

|ገጽ 13 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

Page 14: Reporter Issue 1229

ገጽ 14|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

z ¡ Wü VACANCY ANNOUNCEMENT Concern Worldwide is an Irish-based non-governmental, international, humanitarian organisation dedicated to the reduction of suffering and working towards the ultimate elimination of extreme poverty in the world’s poorest countries.Concern-Ethiopia would like to invite dynamic and creative applicants for the following positions:

Position: Emergency Preparedness & Response ExpertDuty station: Addis Ababa, with frequent travel to Regions

Terms of employment: Indefinite Period Contract

Job PurposeThe Emergency Preparedness and Recovery Manager is responsible for developing emergency preparedness and response plans as per the objectives and actions plans of the Concern Ethiopia Strategic Plan. In addition, the post holder will be responsible to produce reports, provide training to staff, and the collection and analysis of early warning data, both local and national, to respond to emergencies in Ethiopia.

Main duties & Responsibilities:

a) Emergency preparedness, response planning and project implementation1. the Concern Ethiopia Preparedness for Effective Emergency Response (PEER) 2. Consolidate the early warning data collection system that include revising checklists,

reporting schedules and feedback systems3. Coordinate and lead assessments and verification missions in hotspot areas4. Lead/ support in development of concept notes/ project proposals on recovery,

preparedness and rehabilitation5. Participate in the preparation of emergency response project proposals and budgets to

donors and government.6. Assist project/field teams to develop objectives and work-plans (weekly and monthly) for

the respective project and ensure that all planned activities are met. 7. Ensure that Concern’s emergency rehabilitation and DRR projects are of good quality and

reaching national and international standards for performanceb) Financial Management

1. Assist the emergency programme coordinator, project teams and finance/logistics departments in budget preparation and revision as necessary

2. Monitor the under and/or over spending of project budget and advise field teamsC) HR

1. Prepare staffing needs in line with preparedness and response plans and assist the recruitment of local staff

d) Reporting1. Compile monthly, quarterly, and project end reports to Concern, government and donors,

and or regularly check quality of reports produced by the field teams and provide feedback.2. Provide brief internal monthly reports to the Emergency programme Coordinator and

regular updates and/or reports to Addis based department heads and advisors on project developments.

e) Networking1. Represent Concern at Federal and Regional l level coordination/ sectoral cluster meetings

pertaining to the emergency preparedness and recovery and other meetings when requested by senior management

2. Ensure good collaboration and participation of government and other relevant partners.3. Liaise with national and international bodies to ensure information sharing, co-ordination

and linkages where appropriate.f) Monitoring & Evaluation

1. Conduct frequent supervision and monitoring visits to programme and project areas and identify issues related to programmes, donor compliance and other programme quality issues.

Qualification and Experience Essential:

Masters Degree in relevant discipline (development studies, DRR, health/nutrition etc) with minimum of three years relevant work experience in emergency response project implementation and designing, or

First degree in relevant discipline (economics, sociology etc) with minimum of 6 years relevant work experience in emergency response project implementation and designing

Desirable: Previous experience working in wider emergency response programmes Management experience Experience with international NGOs, especially WASH or food security

Special Skills, Aptitude or Personality Requirements: Ability to work as part of a team Flexibility, adaptability, and patience Facilitation and interpersonal skills Analytical and problem solving skills Ability to work under pressure often to strict deadlines Ability to assess problems and recommend solutions Methodical and thorough Training coaching and mentoring skills Cross cultural awareness and sensitivity to cultural differences Awareness of gender issues Empathy with organisational goals Good knowledge and competence of computer applications i.e. Microsoft, Word, Excel

Email Excellent English writing skills Ability to motivate and develop skills of others

“Women are strongly encouraged to apply”

Salary : As per the organization scale

Closing date : 17th February 2012

Concern has a Staff Code of Conduct and Programme Participant Protection Policy which has been developed to ensure the maximum protection of programme participants from exploitation and to clarify the responsibilities of Concern staff, consultants, visitors to the programme and partner organizations, and the standards of behaviour expected of them. Any candidate offered a job with Concern Worldwide will be expected to sign the Programme Participant Protection Policy and the Staff Code of Conduct as an appendix to their contract of employment and conduct themselves in accordance with the provisions in these two documents

Interested applicants should send their C.V., application letter outlining how their experience and skills fit this vacancy and copy of supporting documents to:

Concern EthiopiaHuman Resource Department

P.O. Box 2434Addis Ababa.

Only short listed candidates will be contacted

ለደሃ የሚሆን አይጠፋም?ዛሬ የምንጓዘው ከሸዋ ዳቦ መርካቶ ነው። መቼም ወደ መርካቶ ጉዞ የጀመረ ማንም ሰው በአፍሪካ ሰፊው

የገበያ ሥፍራ መሆኑን ማሰብ ይጀምራል። በተለይ ይህ ስሜት የሚሰማው ሰው ታሪክ ሠርቶ የማለፍ ሕልም ካለው ውስጡ በመካለብ ይርመሰመስበታል። ዳሩ ታሪክ መሥራት ለእነ ዓፄ ምኒሊክ፣ ለእነ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ምን ጠቀመና? አሁንማ ወደ መርካቶ መጓዝ እየቀረ በየአቅራቢያው የፈለጉትን እየሸመቱ መኖር ተችሏል። ‹‹መንገዶች ሁሉ ወደ መርካቶ ያመራሉ›› የሚለው የመርካቶ ነጋዴዎች አባባል እየተረሳ የመጣ ይመስላል። ያም ሆነ ይህ ሦስት ተሳፋሪ ብቻ የጎደለው ታክሲ እኔንና ሌሎች ሁለት ተሳፋሪዎችን ጨምሮ ሲሞላ ወያላው ‹‹ሳበው›› አለው።

እኔ ከመግባቴ በፊት የተጀመረው ጭቅጭቅ ወዲያው ቀጠለ። የጭቅጭቁ መነሻ ከእኛ በፊት የተሳፈሩ ሰዎች ለረጅም ጊዜ በመቆየታቸው ነው::አንዱ የተበሳጨ ተሳፋሪ፣ ‹‹ሦስት ሰው ለመሙላት ብለህ ከስንት ጉዳያችን ስታስተጓጉሉን አታፍርም?›› ብሎ ወያላው ላይ አፈጠጠበት::ወያላው በጣም እየሳቀ፣ ‹‹ለየቱ ጉዳይህ ነው? መርካቶ ከረንቦላ ቤት መሄድን እኮ መርሰዲስ ወይም ቮልቮ ፋብሪካ እንደመሄድ አደረግከውሳ?›› ሲለው ብዙዎች የታፈነ ሳቅ አሰሙ::ሰውዬው በጣም ተናዶ፣ ‹‹የትም ልሂድ በገዛ ጉዳዬ ምንአገባህ? ስታስረፍደኝ የመጠየቅ መብት አለኝ፤›› አለው::ወያላው ከሾፌሩ በላይ የተሰቀለውን ጥቅስ በአገጩ ጠቆመው::ሰውየውና ሌሎች ተሳፋሪዎች ጥቅሱን ተንጠራርተን ስናይ፣ ‹‹ራስዎ አርፍደው እኛን አያስቸኩሉን›› ይላል::እኛም ሰውየውም አቀርቅረን ቀረን::ወይ ጊዜ?

ሕይወትን እየታዘብን ማጣትን እየረገምን ጉዟችን ቀጥሏል። በዚህ መሀል አንዱ ተሳፋሪ ለታክሲ የምከፍለው አዋጡልኝ አለ::ሁላችንም የማነው በሚል ስሜት ስንዘጋው ልመናውን ገፋበት::አንድ በዕድሜ ጠና ያሉ ሰው፣ ‹‹አንተ ሰውዬ እባክህ ስለ ጉልበትህ ስትል ዝም በል አታደንቁረን፤›› አሉት። በትዝብትና በቅሬታ ውስጥ ሆኖ ሲያያቸው ቆይቶ ያልተዋጠለትን ንግግር ደገመላቸው። ‹‹በጉልበትህ አምላክ ይላሉ? እርስዎን ብሎ ትልቅ ሰው›› ብሎ መዘርጠጥ ሊጀምራቸው ሲል፣ ተሳፋሪዎች በአንድነት ጮኹበት። እሱ ግን የሰውን ጩኸት የሚፈራ አይመስልም::ዓይኑን እያጉረጠረጠ ያማትረናል::

‹‹አጥቼ እንጂ የምጠይቀው ኖሮኝ መሳላችሁ? ምድረ ኪራይ ሰብሳቢ ሁሉ የሕዝብን ሀብት ለራሱ ጥቅም እያግበሰበሰ ያደኸየን ሳይበቃው በጉልበትህ አምላክ ይለኛል። ዝም አትበሉ ፍረዱኝ! ያጣ ጉልበተኛና ሰላም አደፍራሽ ሲባል ውስጥ ለውስጥ እየተሽሎከሎከ የሚያሽሎከልከው ግን በሰላም ይኖራል። አንቺ አገር እውን ዓይን አለሽ?›› ብሎ የታክሲዋን ጣርያ ሲያይ ቆየና፣ ‹‹አባት እኔ ሳልሆን በሂትለር ሒሳብ መሰላት ያለብኝ ምድረ ጉበኛና ኪራይ ሰብሳቢ ነው። እኔ በግልጽ ለመንኩ። ለምኑ ይሰጣችኋል ነው የሚለው ቃሉ፤›› ብሎ እንደደከመው ዝም ሲል ሾፌሩ እንዲወርድ ነገረው። ‹‹እሺ የድሃ አምላክ ያያል የእምዬ ኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል›› እያለ ያለምንም ማንገራገር ሲወርድ ታክሲዋ ለጊዜው እፎይ አለች። ሁላችንም ውስጥ ግን ልናምነው የማንፈልገው እውነት ቀርቶልናል። በሕዝብ ሀብት የሚንደላቅቁና የሚበለፅጉ ሞልተው በተረፉበት ሁኔታ ድሃው እስከመቼ ሰሚ አጥቶ ይኖራል? እስከመቼ ላቡንና ደሙን ይገብራል? ‹‹ሳስበው ታከተኝ›› ያለው እረኛ እውነቱን ነበር ለካ?

ቀልባቸው ተገፎ የቆዩት አዛውንት መውረዱን አይተው መረጋጋት እንደጀመሩ፣ ‹‹ወይ ጉድ አሁን ይኼ ጤነኛ ይባላል; እብድ እንጂ፤›› ብለው ሁላችንንም በየተራ ተመለከቱን። ወያላው ቀበል አድርጎ ‹‹ይኼማ አንዱ ሌባ ነው፤ በዚህም በዛም ብሎ እኮ ሳይከፍለኝ ነው የወረደው፤›› ሲል አዛውንቱ ደግሞ፣ ‹‹አንተ ሒሳብህ መጉደሉን ነው የምታየው; አይ የልጅ ነገር የሰው ጤና አያሳስብህም? አንተ ምን ቸገረህ ሆድህ ከሞላ?›› ብለው በነገር ሲወጉት ግራ ተጋብቶ አያቸው። እንዲያ ሲናገሩት ንዴታቸውን እሱ ላይ እየተወጡበት ይመስል ነበር። ጋቢና የተቀመጠ ወጣት እጁን ሰዶ ሒሳቡን እየከፈለ፣ ‹‹በዚህም ተባለ በዚያ ሰውዬው የተናገረው ልክ ነው። ሙሰኛው በአገርና በሕዝብ ሀብት ላይ እየተጫወተ ነው። እኛ ግን በዕዳ እንዋኛለን። እንኳን እኛ የልጅ ልጆቻችን ከፍለው የማይጨርሱት ዕዳ እላያችን ላይ ያናጥራል። ኧረ አንዳንዴስ ያስመርራል፤›› ብሎ ተንገፍግፎ ተናገረ::የወጣቱን ንግግር የሚያዳንቀውና ‘እውነት እውነት’ የሚለው ደግሞ ታክሲዋን ተንጫጫባት። የሰውን ሁካታና ጭቅጭቅ ወደ ጎን ብዬ ከሾፌሩ በላይ የተሰቀለ ሌላ ጥቅስ ላይ ዓይኔን ጣል አደረግኩ::‹‹ፍቅር ለአፍቃሪው ዕዳ፣ ለተፈቃሪው ዲቪ፣ ለተመልካቹ ደግሞ ዲኤስቲቪ ነው፤›› ይላል::የታክሲ ሾፌሩና ወያላው በጥቅስ ሲዝናኑ የአበሻ ልጅ በነገር ይባላል::

በዚህ መካከል ድንገት አንድ ጎረምሳ በንዴት የታክሲውን ግድግዳ ሲደበድብ ደንግጠን ዞረን አየነው::ሾፌሩም ታክሲዋን አቆማት::‹‹ምን ሆነህ ነው አባቱ?›› አለው ወያላው::ጎረምሳው፣ ‹‹ምን የማልሆነው አለኝ በፈጠረህ?›› እያለ ማልቀስ ቃጣው::‹‹እኮ ተናገራ›› አልነው በኅብረት::‹‹በቃ ተለያየን›› አለ ቀስ ብሎ በሹክሹክታ::የሰማነው ደግሞ ምን አለ እያሉ ለሚጨቀጭቁን እንደግምላቸዋለን። ‹‹ከማን?›› አለው ወያላው አሁንም እንደ መርማሪ::‹‹ከእጮኛዬ ነዋ›› ሲል በዚህ ጊዜ አዛውንቱ፣ ‹‹አይ የልጅ ነገር አይዞህ ገና ስንቱን ታየዋለህ? ምን አባቷ እሷ ብትሄድ ሌላ ትተካለች፤›› ብለው ጉዳዩን ቀለል ለማድረግ ሲሞክሩ፣ አንድ ወጣት አቋረጠቻቸውና ‹‹አይ የእርስዎ ነገር እንዴት ፍቅርን ያህል ነገር ተንዶ አይዞህ ገና ብዙ ታያለህ ይሉታል ፋዘር?›› ብላ ወደ ወጣቱ ዞረች። ሾፌሩ እየተነጫነጨ፣ ‹‹ለዚህ ነው?›› እያለ ታክሲዋን ማንቀሳቀስ ጀመረ። በዚህ መሀል ወያላው ሾፌሩን እያስቆመው አዳዲስ ተሳፋሪዎችን ከታክሲዋ መጠን በላይ ይጭን ጀመር::ታክሲዋ በትርፍ ተሳፋሪዎች ሞልታ ጭንቅ ውስጥ ሆነን ወያላው እየሳቀ፣ ‹‹የዓባይ ቃል ስላለብን ጠጋ ጠጋ በሉ›› ሲለን ሳንወድ ሳቅን::

‹‹እንዲያው የሚያንገበግበው እኮ ያጣላን ነገር ነው፤›› አለን ጎረምሳው በመሀል እንደ መረጋጋት ብሎ::‹‹ምንድነው እሱ?›› አልነው አሁንም ሁላችንን ጓጉተን::‹‹ቴሌ ተብዬው ነዋ። ሌላማ ማን ይሆናል? በዚህ ፍቅርም እንደ ኑሮ በተወደደበት ዘመን የቴሌ ካርድ አልገባ ብሎኝ ስልኬ መደወል እርም ካለ ሦስት ቀን ሆነው፤›› ሲል፣ ‹‹ኧረ እኔ አለሁ አምስት ቀን የሞላኝ›› አለ ሌላው። ‹‹ታዲያ ካርድ እንደሌለህ በአዲሱ ዘዴ አትነግራትም? ምነው ነፃ አይደል እንዴ?›› አልኩት ጣልቃ ገብቼ::‹‹ዳሩ ብነግራትስ እሷስ ምኑን ሞልታ ታናግረኝ?›› አለን ተክዞ። ‹‹ታዲያ ይኼ ያጣላል እንዴ? ለመሆኑ የፍቅራችሁን ጥም የምትወጡት በስልክ ነው?›› ሲል አንዱ ሊቀልድ ሞከረ። የሳቀው ስቆ ያልሳቀው ገላምጦት ‹‹ቴሌን እግዜር ይይልህ›› ማለት ያዝን። አንድ ዕርምጃ ወደፊት ሦስት ወደኋላ እስከመቼ?

ታክሲያችን እየከነፈች ጥቁር አንበሳ ደርሳለች። ወራጅ ተብሎ ወያላው ወራጆችን አውርዶ ሁለት ዕቃ የያዙ ጎልማሶች ገቡ። እነሱም ኢሚግሬሽኝ በራፍ የተገተረውን ዕልፍ አዕላፍ ሕዝብ አይተው ስለ ስደት ይከራከራሉ። ‹‹ኧረ ለመሆኑ ለምድን ነው መሰደድ የሌለብን? ንገረኝ እስኪ?›› ይለዋል አንደኛው ሰውዬ። ‹‹ነገርኩህ እኮ ከዳር ቆሞ አስተያየት መስጠት ቀላል ነው። ለመሻሻል ግን አብዛኞቻችን በአገራችን ላይ መሥራትና መኖር ይገባናል፤›› አለው ረገጥ አድርጎ። ‹‹ፓ አብራርተህ ሞተሀል? መቀላመዱንማ ሁሉም ተክኖታል። ዋናው ግን ሀቁ ላይ ነው። ሜዳውም ፈረሱም ያው ቢባል ድፍን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማቄን ጨርቄን ሳይል ነቅሎ ይሰደዳል። እውነቴን አይደል? አንቺ አሁን አትሄጂም?›› ብሎ ያችን ወጣት ሲጠይቃት በድፍረቱ አፍራ አንገቷን ደፋች። ሁላችንም እየሰማናቸው አንዳቸውንም መደገፍ የፈለግን አንመስልም።

‹‹ትሰማለህ?›› ይለዋል አንደኛው ሰውዬ::‹‹የዚህች አገር ዋነኛ ችግር ምንም እንዳይመስልህ ሽሽት ነው። ሁላችንም ለተግባር ጊዜ ወደኋላ እንሸሻለን::እናማ እንዴት እንድንለወጥ ትጠብቃለህ?›› አለው። ልክ ነው የሚሉ አንገታቸውን እያወዛወዙ ይደግፉታል። ጓደኛው ግን ሳያስጨርስ ጣልቃ ይገባል። ‹‹ምን ሰለቸህ ብትሉኝ ወሬ ነው። ኪራይ ሰብሳቢነትን በጋራ እንከላከል፣ ኤድስን በጋራ እንከላከል፣ ሽብርተኝነትን በጋራ እንከላከል፤ መፈክሩ ሁሉ በጋራ ስለተሞላ ብቻ ስንጠየቅም በጋራ መሆን አለበት እንዴ? ለዚህ መድኃኒቱ መሸሽ ነው ወንድሜ::አንተ እዚህ ተንጋለህ እየተፋህ መልሰህ ዋጥ፤›› ብሎት እንደ መቀላለድ እያሉ ርዕስ ሲቀይሩ ቀልባችን ወደ ራሳችን ተመለሰ። ተናግሮ አናጋሪ፣ ቆርጦ ቀጥልና ጀምሮ የማይጨርስ እንዴት በዝቷል እናንተዬ? ወያላው የሰዎቹ ነገር አላማረውም መሰል፣ ‹‹ምነው ምነው? ይህችም እንጀራ ሆና ሚጥሚጣ በዛባት›› ብሎ በፌዝ ፈገግታ ሰዎቹን አያቸው::

መድረሻችን ሲቃረብ እኛም ለመውረድ ስናኮበኩብ መርካቶ ተተረማምሷል። ‹‹እንዲህ ስንተረማመስ መሽቶ ይነጋል፤›› አለ አጠገቤ ተቀምጦ እስካሁን በዝምታ ውስጥ የነበረው ተሳፋሪ። ‹‹ምን እሱ ብቻ እንዲህ ስንተረማመስ ነው ተወልደን የምንሞተው፤›› ብሎ ወያላው ጨመረለት። ‹‹አዎ ሰሞነኞች ነን፤ ሰሞን ያናወዘን ወረተኞች። ጉዳያችን የምንለው በሰሞነኝነት ለያዝነው ነገር ብቻ እንጂ መሠረታዊ አካሄድና የተጠና ጉዞ አልፈጠረብንም፤›› ብለው አዛውንቱ ጨመሩልን። በማያቋርጥ የሕይወት እንቅስቃሴ ውስጥ ተሁኖ ጉዳዮቻችንና ጭንቀቶቻችን ግን ምነው ሰሞነኛ ሆኑ? ሙስናን፣ ኢሰብዓዊነትን፣ ስደትን፣ የመስተንግዶ ቀርፋፋነትን፣ በሽታንና ድህነትን ከሥራቸው ገንድሰን የምንነቅላቸው መሠረት በያዘ አካሄድ ስንመራ ብቻ ነው። ወያላው ለሾፌሩ የምሣ እንብላ ጥያቄ እያቀረበለት ነው::የት እንብላ መባባል ጀምረዋል::አዛውንቱ እየሳቁ፣ ‹‹መርካቶ ምን ጠፍቶ?›› አሉ::ወያላው ተክዞ፣ ‹‹የአቅም ጉዳይ ሆኖብን እኮ ነው፤›› አላቸው::አዛውንቱ፣ ‹‹እባክህ አታስብ ለደሃ የሚሆን አይጠፋም::ባይሆን ደሃ ምግብ ባያዘጋጅ ኖሮ ሀብታም ገንዘቡን ይበላ ነበር የሚለውን አልሰማችሁም?›› አሉ::ወያላው እየሳቀ መጨረሻ ሲለን ከተጠቀጠቅንበት ታክሲ በግፊያ ወርደን ተበታተንን። መልካም ሰንበት!

Page 15: Reporter Issue 1229

|ገጽ 15 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

የጨረታ ማስታወቂያየደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተር፣ የፋክስ ማሽን፣ ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ኤል ሲ ዲ ፕሮጀክተር እና ላፕቶፕ ኮምፒዩተር አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል:: በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከታች የተገለፀውን መሰፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል:: 1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑ የመንግስት ግብር ያጠናቀቁ እና የገ/

ኢ/ል/ሚ የአቅራቢዎች ምዝገባ ያከናወኑ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብ 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ከኢንስቲትዩቱ ቢሮ ቁጥር 104 መውሰድ ይቻላል፣

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል::

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋችሁን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 104 ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

5. የመጫረቻ ዋጋውን 5/% የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል የጨረታው አሸናፊ ሲታወቅ የተያዘው ሲፒኦ ወዲያውኑ ለተሸናፊው ተጫራች ተመላሽ ይደረጋል::

6. ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- ደቡብ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ስ.ቁጥር 0912017942ፋክስ ቁጥር 0462204000/0462204521

ፖ.ሣ.ቁ. 06ሀዋሳ

INVITATION FOR BIDBid NO. NCB 3/2012

Save the Children Norway-Ethiopia is an international NGO engaged in the fulfillment of the well-being of children. It works for a World which respects and values each child, a world which listens to children and learns from them, and a world where all children have hope and opportunity.

Save the Children Norway-Ethiopia invites eligible and qualified bidders or contractors /preferably local/Category WC/GC-6 & above to submit sealed bids for the works of 9 hand dug wells and 1 spring development in Gendawuha Town Administration & Metema Woreda North Gondar zone Amhara region. Intersected eligible bidders may obtain further information from Save the Children Norway Ethiopia country office and inspect the bidding documents at the address given below in weekdays from 8:30 am- 4:30 pm local time.

A complete set of bidding documents in English may be purchased by interested bidders on the submission of written application to address below and upon payment of non-refundable fee Ethiopian Birr 100.00. The method of payment will be in cash and the bidding document will be submitted in hard copies.

Bids must be delivered to the address below at or before February 17, 2012; 4:30 pm local time. Electronic bidding will not be permitted. Late bids will be rejected. All bids must be accompanied by bid security of 2 % of its offer or an equivalent amount in freely convertible currency. Bids shall be submitted in two copies with technical and financial offers in two separate envelopes. Bids shall be opened in presence of bidders and /or their legal representative’s who wish to attend on February 20, 2012 at 10:00 am local time. Bidders must submit their bid only for one lot SCNE reserves the right to reject any or all bids

Address Save the Children Norway- Ethiopia

Administration and Finance Department8th floor Dire Complex Building, Old Airport, opposite to Victory

SupermarketTelephone: 0113206381-84

P.O. Box 6589, Addis Ababa.Or

Gondar Field Office P.o. box 1057, Gondar

At the compound of North Gondar Zone Education Department

(ጥንቅር- ብሩክ ቸርነት)

ጨረታ እና ንብረት (ጥንቅር- ዳዊት ወርቁ)

ግዥጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የሲዳማ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- ወንበር፣ ጠረጴዛ እና የጽምፅ ማጉያ መሣሪያዎች:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 221 44 94 ይደውሉ::------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በአማራ ብ/ክ/መንግስት የፖሊስ ኮሚሽን:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- ጉርድቦት ጫማዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና የከባድና ቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማ:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 226 21 11/058 220 14 53 ይደውሉ:: ------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች፣ የተለያየ መጠን ያላቸው LCD ቴሌቪዥኖችና ወዘተ:: ጨረታው የሚከፈተው፡- የካቲት 12 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 320 40 07/ 011-371-7114 ይደውሉ:: ------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት

የሚፈልገው፡- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ ዕቃዎችና እንዲሁም ዲጂታል የማስታወቂያ ሰሌዳ:: ጨረታው የሚከፈተው፡- የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046/221-21-26/ 220-96-76 ይደውሉ:: ------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- ፕላዝማ ቴሌቪዥኖች:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0111-22-64-56/0111-22-38-84 ይደውሉ:: ------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በአማራ ብ/ክ/መንግሥት የደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል:: በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- የበሰለ ምግብ፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ የጽህፈትና የጽዳት መሣሪያዎች:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ይደውሉ:: ------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የቴ/ሙ/ት/ትና ስልጠና ኤጀንሲ፡ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልገው፡- የሥልጠና ጥሬ ዕቃና ቋሚ የሥልጠና ዕቃዎች:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 046 224 01 01/046 221 14 487 ይደውሉ:: ------------------------------------

ሽያጭጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር:: በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ የሚፈልገው፡- ልዩ ልዩ ያገለገሉ ፋይል ካቢኔቶች፣ ወረቀቶች፣ መጽሔቶች፣ ቅጻቅጾች፣ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች ቁምሳጥኖችና ወዘተ ... ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0115 51 70 80 ይደውሉ::------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ:: በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ የሚፈልገው፡- ያገለገሉ የቢሮና ሌሎች ዕቃዎች:: ጨረታው የሚከፈተው፡- የካቲት 28 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 553 89 35/ 011 5 51 18 88 ይደውሉ::------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የኢትዮጵያ ቅርስ ባለደራ ማህበር:: በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ የሚፈልገው፡- የባህር ዛፍ :: ጨረታው የሚከፈተው፡- የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 515 88 02/011 515 37 77 ይደውሉ::------------------------------------

ኮንስትራክሽንጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ:: በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት የሚፈልገው፡- የኮብል ስቶን ግንባታ ሥራ::

ጨረታው የሚከፈተው፡- የካቲት 14 ቀን 2004

ዓ.ም.:: ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-

22 59 57/ 24 90 30/ ይደውሉ::

------------------------------------

ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የኢትዮጵያ

ንግድ ባንክ:: በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት

የሚፈልገው፡- የማስታወቂያና የፕሮሞሽን

አገልግሎት /ባነሮች፣ ቢልቦርዶች፣ ተለጣፊ

ማስታወቂያዎች የሬዲዮና የቴሌቪዥን

ማስታወቂያዎችና ወዘተ ..../ ለበለጠ መረጃ፡-

በስልክ ቁጥር 0111 22 89 10/ 0111-22

86 97 ይደውሉ::

------------------------------------

ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በደ/ብ/ብ/

ሕ/ክ/መንግስት:: በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት

የሚፈልገው፡- የገበያ ማዕከል:: ለበለጠ መረጃ፡

- በስልክ ቁጥር 046-331 26 98 ይደውሉ::

------------------------------------

ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- በጉጂ ዞን

ቦሬ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት:: በጨረታ አወዳድሮ

ማሰራት የሚፈልገው፡- የሕዝብ አዳራሽ:: ለበለጠ

መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0466-67 02 61/23

ይደውሉ::

------------------------------------ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤት፡- የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት:: በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት የሚፈልገው፡- G+0 የቢሮ ግንባታ፡ ለበለጠ መረጃ፡- ------------------------------------

Page 16: Reporter Issue 1229

ገጽ 16|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

ሪፖርተር፡- ናሽናል ሴንተር ኦፍ ኮምፒተንስ ኢን ሪሰርች ኖርዝ ሳውዝ የትኩረት አቅጣጫው ምንድነው?

አቶ ብርሃኑ፡- ናሽናል ሴንተር ኦፍ ኮምፒተንስ ኢን ሪሰርች ኖርዝ ሳውዝ በስዊስ ናሽናል ሳይንስ ፋውንዴሽን አማካይነት የስዊዘርላንድ መንግሥት በለገሰው 100 ሚሊዮን ፍራንክ የተመሠረተ፣ የሰሜንና ደቡብ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ምርምሮችን በጥምረት የሚያኪያሂዱበት ፕሮግራም ነው::በመላው ዓለም ባሉ ዘጠኝ ቀጣናዎች ሥር በሚገኙና ከ40 በላይ የሚሆኑ መካከለኛ ገቢ ያላቸውና ደሃ አገሮች የሚያካሂዱት የልማት እንቅስቃሴ ከራሳቸው ችግር በተጨማሪ፣ የእነሱ ባልሆኑ ችግሮች ሳቢያ ወይም በዓለም አቀፍ ሁኔታ ምክንያት ተጓትቷል::የእነሱ ካልሆኑት ችግሮችም መካከል የአየር ንብረት ለውጥ እንደ አብነት ሊጠቀስ ይችላል::እነዚህ አገሮች ይህንን ችግራቸውን የሚፈቱት ምን ቢደረግላቸው ነው? የሚለውን ጥያቄ ከፍ ብሎ የተጠቀሰው ፕሮግራም ይመልሳል፤ ወይም መፍትሔ ይጠቁማል::

ሪፖርተር፡- ፕሮግራሙ ችግሩን የሚፈታው እንዴት ነው?

አቶ ብርሃኑ፡- አንደኛው ችግሩ ላይ ያተኮረ ምርምር አድርጎ መፍትሔ የሚሆን ሐሳብ በማመንጨት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ አገሮች ለችግሮቻቸው በራሳቸው መፍትሔ የሚፈልጉበትን የአቅም ግንባታ የማሳደግ ሥራ በማከናወንና ማኅበረሰቡም በራሱ ጉዳይ ላይ መፍትሔ የሚሻበትን መንገድ በማገዝ ነው::

ሪፖርተር፡- በስዊዘርላንድ የሚገኙና የጥምረቱ አባል የሆኑ ተቋማት እነማን ናቸው?

አቶ ብርሃኑ፡- በስዊዘርላንድ ካሉት የጥምረቱ አባል ተቋማት መካከል በስዊስ ዩኒቨርሲቲ ሴንተር ፎር ዴቨሎፕመንት ኤንድ ኢንቫይሮመንት፣ ስዊስ ፒስ ፋውንዴሽን፣ በዙሪክ ዩኒቨርሲቲ የዴቨሎፕመንት ስተዲ ግሩፕ፣ በጄኔቭ ግራጁዌት ኢንስቲትዩት ኦፍ ኢንተርናሽናል ኤንድ ዴቨሎፕመንት ስተዲስ፣ እንዲሁም ስዊስ ትሮፒካል ኤንድ ፐብሊክ ሔልዝ ኢንስቲትዩት፣ ዲፓርትመንት ኦፍ ወተር ኤንድ ሳኒቴሽን ኢን ዴቨሎፒንግ ካንትሪስ ናቸው::ናሽናል ሴንተር ኦፍ ኮምፒተንስ ኢን ሪሰርች ኖርዝ ሳውዝ የሚመራው የጥምረቱ አባል የሆኑ የስዊስ ተቋማት ተወካዮችና የቀጣናው አስተባባሪዎች በሚገኙበት ቦርድ አማካይነት ነው::ጥምረቱ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኘው ከስዊስ ናሽናል ሳይንስ ፋውንዴሽንና ከስዊስ የልማትና የትብብር ኤጀንሲ ነው::

ሪፖርተር፡- ከስዊዘርላንድ ውጭ የሚገኙ የጥምረቱ አባል ተቋማት አሉ?

አቶ ብርሃኑ፡- አዎ ከስዊዘርላንድ ውጭ የጥምረቱ አባላት የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችና የልማት

ድርጅቶች ይገኛሉ::ከእነዚህም መካከል በአፍሪካ፣ በእስያ፣ በላቲን አሜሪካና በአውሮፓ የሚገኙ 190 ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ተጠቃሾች ናቸው::ከዚህም ሌላ በመላው ዓለም የሚገኙ 400 የሚጠጉ ተመራማሪዎች ለፕሮጀክቱ እንቅስቃሴ የየበኩላቸውን እገዛና አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸው::

ሪፖርተር፡- በየትኞቹ ቀጣናዎች ውስጥ በታቀፉ አገሮች ነው ፕሮግራሙ የሚካሄደው?

አቶ ብርሃኑ፡- ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያና ኤርትራ የሚገኙበት የአፍሪካ ቀንድ አንደኛው ቀጣና ነው::ኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳና ቡሩንዲ የተካተቱበት ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ነው::ኮትዲቯር፣ ቡርኪናፋሶ፣ ሞሪታኒያ፣ ማሊ፣ ቻድ፣ ሴኔጋል፣ ጋና፣ ካሜሩንና ሴራሊዮን ያሉበት የምዕራብ አፍሪካ ቀጣናም ይገኝበታል::ሌሎች 30 ያህል አገሮች ያሉበት የአውሮፓ፣ የመካከለኛው፣ የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ የካሪቢያንና የመካከለኛው አሜሪካ ቀጣናዎችም ተጠቃሾች ናቸው::በእነዚህ ቀጣናዎች የሚከናወነው ፕሮግራም የቆይታ ጊዜው ለ12 ዓመት ብቻ ነው::በእነዚህ ዓመታት በቂ የሆነ ሥራ ተሠርቶ በቂ የሆነ መልስ መገኘት መቻል አለበት::ከዚህ አንፃር የአፍሪካ ቀንድ ፕሮግራም ከተጀመረ 10 ዓመት ተኩል ሆኖታል::ፕሮግራሙ ሊዘጋ አንድ ዓመት ተኩል ብቻ ቀርቶታል::የማስተባበርያው ጽሕፈት ቤት በምን መልኩ ይቀጥላል በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገበት ነው::

ሪፖርተር፡- በአፍሪካ ቀንድ ለልማትና ዕድገት እንቅፋት በሆኑት ችግሮችና ስለተከናወኑት ምርምሮች ቢያስረዱን?

አቶ ብርሃኑ፡- በቅድሚያ ከፍ ብሎ በተጠቀሱት ዘጠኝ ቀጣናዎች ውስጥ የሚገኙና ዋና ዋና ናቸው የተባሉ 30 ችግሮችን የመለየት ሥራ ተከናውኗል::ይህ ዓይነቱ ሥራ ከተከናወነባቸው ቀጣናዎች መካከል ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ጂቡቲ፣ ሶማሊያና ኤርትራ የሚገኙበት የአፍሪካ

ቀንድ አንዱ ነው::በዚህም የተነሳ በአፍሪካ ቀንድ ለልማትና ዕድገት ማነቆ በሆኑ ችግሮች ላይ ምርምሮች ተከናውነዋል::ምርምሮቹም የተከናወኑት የፒኤችዲና የማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ባላቸው 65 ተመራማሪዎች ነው:: አብዛኛዎቹ ወይም 85 ከመቶ ያህሉ ምርምሮች የተሠሩት በኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችና በኢትዮጵያ ላይ ነው::በፒኤችዲ ደረጃ ያሉ ተመራማሪዎች ምርምራቸውን የሠሩት በስዊዘርላንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን፣ በማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ያሉት ደግሞ የሠሩት በኢትዮጵያ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነው::ለሁሉም ተመራማሪዎች እንደ ደረጃቸው የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል::

ሪፖርተር፡- ምርምሮቹ በምን ላይ የተደረጉ ናቸው?

‹‹መረጃ የሌለው ፖሊሲ ፋይዳ የለውም››

አቶ ብርሃኑ ደበሌ በናሽናል ሴንተር ኦፍ ኮምፒተንስ ኢን ሪሰርች (ኤንሲሲአር) ኖርዝ ሳውዝ የአፍሪካ ቀንድ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ናቸው::በጎሃ ፅዮንና በአምቦ ከተሞች የአንደኛና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል::በስዊድን ኦፕስላ ዩኒቨርሲቲ በፊዚካል ጂኦግራፊና ሶይል ሳይንስ የመጀመርያ ዲግሪ፣ እንዲሁም በቤልጂየም ጌንት ዩኒቨርሲቲ በሶይል ሰርቬይ ኤንድ ላንድ ኢቫሉዌሽን ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል::በሥራ ዓለምም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፎረስት ሪሰርች ኢንስቲትዩት በአፈር ላብራቶሪ ቴክኒሽያንነትና በሆለታ እርሻ ምርምር በተመራማሪነት ሠርተዋል::በቀድሞው የሸዋ ክፍለ ሀገር ግብርና መምርያ ኃላፊ፣ የማዕከላዊ ፕላን ቀጣና ኮሚሽን ኮሚሽነርና የግብርና ምክትል ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል::አሁን በአስተባባሪነት እየሠሩ ባሉበት ድርጅት የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ታደሰ ገብረ ማርያም አነጋግሮአቸዋል::

አቶ ብርሃኑ ደበሌ፣ የኤንሲሲአር ኖርዝ ሳውዝ የአፍሪካ ቀንድ አስተባባሪ

አቶ ብርሃኑ፡- የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠቀም በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ላይ በሚከሰቱ ውዝግቦች፣ በጤናው ዘርፍ፣ በተለይ ጫት ከኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊና ከፖለቲካ አንፃር የሚኖረው አንድምታ ምን እንደሚመስል ተካቷል::በውኃ እንዲሁም ከከተማ ዕድገት ጋር ተያይዘው በሚመጡ የአካባቢ ለውጦች ጋር የተያያዙ ይገኙባቸዋል::

ሪፖርተር፡- በአፍሪካ ቀንድ ለልማት ማነቆ በሆኑ ችግሮች ላይ የምርምሩ ሥራ የተከናወነው በኢትየጵያና በሱዳን ብቻ ነው ይባላል::በቀሩት አገሮች ላይ ለምን ይህ ዓይነቱ ምርምር አልተከናወነም?

አቶ ብርሃኑ፡- በኤርትራ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ልንሄድ አንችልም::እነሱም እዚህ ሊመጡ አይችሉም::በቆላማ አካባቢ ያለው የኢትዮጵያ አየር ንብረት ከጂቡቲ ጋር ይመሳሰላል::ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተሠራ የጂቡቲንም ችግር ሊወክል ይችላል::በሶማሊያ የፀጥታ ችግር ከመኖሩ ባሻገር የኦጋዴን አካባቢ የሶማሊያን አካባቢ ስለሚመስል ኦጋዴን ላይ የተሠራው ለሶማሊያ ሊያገለግል ይችላል::ሱዳንን ደግሞ ስንመለከት የዓባይን ወንዝ አስመልክቶ የተሠራው ሥራ ደቡብ ሱዳንንና ግብፅን አካቶ የተከናወነ ነው::በተለይ ደግሞ ዓባይን አስመልክቶ ኢትዮጵያን፣ ግብፅንና ሱዳንን በመሸፈን አቅምንና አወቃቀርን በሚመለከት ተሠርቷል::ግብፆች በመስኖ ልማት ዙርያ የማስፈጸምና የአደረጃጀት ሥራዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ አቅም እንዳላቸውና በኢትዮጵያ በኩል ግን በጣም ደከም ያለ መሆኑን የተሠራው ሥራ ያሳያል::ይህ ዓይነቱ ጥናትና ምርምር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለኃይድሮ ፖለቲክስ ትምህርት መቋቋም መንስዔ ለመሆን በቅቷል::

ሪፖርተር፡- ብዙ ገንዘብ ወጥቶባቸውና ጉልበት ፈስሶባቸው የተከናወኑ ምርምሮች ከነግኝታቸው ወይም ውጤታቸው መደርደሪያ ላይ ቀርተዋል? ወይስ ለተግባራዊነታቸው የተወሰደ ዕርምጃ አለ?

አቶ ብርሃኑ፡- ማንኛውም ምርምር ጠቀሜታ የሚኖረው የምርምሩ ውጤት ተግባራዊ ሲሆን ወይም በአፈጻጸም ላይ ሲውል ብቻ ነው::ከዚህ በፊት ባለን ልምድ ምርምርን በአንድ በኩል፣ አፈጻጸምን የሚከታተሉና ፖሊሲ የሚያመነጩ በሌላ በኩል ወይም በየራሳቸው ካምፕ ተቀምጠው ነው ያሉት::አንዱ ከሌላው ጋር ያለው ግንኙነት ይህን ያህል አመርቂ አይደለም::አሁን እኛ አንድ የጀመርነው ባህል አለ::እሱም ምንድነው ያገኘነውን ውጤት ይዘን ዝም ብሎ መቀመጥ ወይም ሼልፍ ላይ መደርደር ሳይሆን፣ ውጤቱን ተግባራዊ ሊያደርጉ ይችላሉ ወይም የፖሊሲ ነክ ነገሮች አሉትና በፖሊሲ አመንጪዎችና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሊታዩ ይገባል እንላለን::ያመንባቸውን ደግሞ በተናጠል አውጥተን የፖሊሲ መግለጫ አዘጋጅተን በዚያ ላይ ውይይት እንዲካሄድበት እናደርጋለን::ሌሎችም በዚህ መልክ ተከትለው መሄድ አለባቸው ብለን እናምናለን::የፖሊሲ ሰዎችም በጥናቶቹ ላይ ተመሥርተው ፖሊሲያቸውን ማመንጨትና ማስተካከል አለባቸው እንላለን::መረጃ የሌለው ፖሊሲ ፋይዳ የለውም::በመረጃ ላይ የተመሠረተ ፖሊሲ ግን ጠንክራና ትክክለኛ ፖሊሲ ነው የሚሆነው::

ሪፖርተር፡- በውጤቱ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ለማካሄድ ምን ዓይነት ስልት ወይም ዘዴ ነው የምትጠቀሙት?

አቶ ብርሃኑ፡- በውጤቱ ላይ ያተኮረ ውይይት ለማካሄድ ሁለት ዓይነት ስልቶችን እንጠቀማለን::ይኼውም የሳይንስ ፖሊሲ ፎረምና የቀጣና ዓውደ ጥናት ወይም ወርክሾፕ በማዘጋጀት ነው::የሳይንስ ፖሊሲ ፎረም ፖሊሲ አስፈጻሚዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከተመራማሪዎቹ ጋር ተገናኝተው ፖሊሲ ነክ ወይም ይዘት ባላቸው ውጤቶች ላይ የሚወያዩበትና ሐሳብ ለሐሳብ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው::ቀጣናዊ ዓውደ ጥናት ደግሞ የተገኙትን የምርምር ውጤቶች ቴክኒካዊ ይዘታቸውን ጭምር በዝርዝር በመወያየት የሚግባቡበትና የሚስማሙበት ነው::በመሠረቱ ከዚሀ በፊት በዚህ ዓይነቱ ዓውደ ጥናት ላይ ቀርቦ ውይይት ይደረግባቸው የነበሩት በጅምር ወይም በሥራ ላይ ያሉ ምርምሮች ብቻ ነበሩ::ይህም ሁኔታ ተመራማሪዎቹ ትክክለኛውን መስመር እንዲከተሉ፣ ወይም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከመርዳቱም በላይ፣ ትኩረት የሚያሻውን አቅጣጫ በማስገንዘብና በመጠቆም ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል::አሁን ግን ያለቀላቸውን የምርምር ውጤቶች በዓውደ ጥናቱ ላይ ቀርበው እንደዚሁ ውይይት እንዲደረግባቸው እያደረግን ነው::

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/ታምራት ጌ

ታቸው

የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠቀም በሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች ላይ በሚከሰቱ ውዝግቦች፣ በጤናው ዘርፍ፣ በተለይ ጫት ከኢኮኖሚ፣ ከማኅበራዊና ከፖለቲካ አንፃር የሚኖረው አንድምታ ምን እንደሚመስል ተካቷል::በውኃ እንዲሁም ከከተማ ዕድገት ጋር ተያይዘው በሚመጡ የአካባቢ ለውጦች ጋር የተያያዙ ይገኙባቸዋል::

Page 17: Reporter Issue 1229

|ገጽ 17 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

የማነ ግርማይ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል::

ተራ የሥራ መደቡ መጠሪያ ብዛት የትምህርት ደረጃ የሥራ ልምድ እና ተጨማሪ ክህሎት

1

የሠዉ ኃይል አስተዳደር ኃላፊ 1

ከታወቀ ዩንቨርስቲ/ኮሌጅ በማኔጅመንት ወይም በተመሳሳይ የሙያ ዘርፍ በዲግሪ የተመረቀ/ች

በሙያዉ 5ዓመት እና ከዛ በላይ የሰራ/ች በኮንስትራክሽን ድርጅት ዉስጥ ብቻ ቢያንስ ለ3ዓመት ያገለገለ/ች

2ሲኒየር አካዉንታንት

1በአካዉንቲንግ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሌጅ በዲግሪ የተመረቀ/ች

በሙያዉ 4 አመት እና ከዛ በላይ በኮንስትራክሽን ድርጅት ዉስጥ የሰራ/ች በፒችትሪ አካውንቲንግ ሶፍትዌር እውቀት ያለው/ት በሂሳብ የመዝጋት ስራ ላይ በቂ ልምድ ያለው/ት

3 ኳንቲቲ ሰርቬየር 1ከታወቀ ዩንቨርስቲ/ኮሌጅ በሲቪል ኢንጂነሪንግ በዲግሪ/በዲፕሎማ የተመረቀ/ች

ለዲግሪ በኳንቲቲ ሰርቬየርነት 2ዓመት እና ከዛ በላይ የሰራ/ች ለዲፕሎማ በኳንቲቲ ሰርቬየርነት 4ዓመት እና ከዛ በላይ የሰራ/ች

4 ሰርቬየረ 1ከታወቀ ቴክኒካል ኮሌጅ በሰርቬይንግ የሙያ ዘርፍ በዲፕሎማ የተመረቀ/ች በሙያው 6ዓመትና ከዛ በላይ የሰራ/ች

5ኧርዝወርክ ፎርማን

1

በማንኛውም የኮንስትራክሽን ሙያ ዘርፍ በዲፕሎማ የተመረቀ ወይም 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ

ለዲፕሎማ 6ዓመት የስራ ልምድ እና ከዛ በላይ የሰራ12ኛ ክፍል ለጨረሰ 10ዓመትየስራ ልምድና ከዛ በላይ በመንገድ ሥራ ላይ የሰራ

6 ጉዳይ አስፈጻሚ 1 በማንኛዉም የሙያ ዘርፍ በዲፕሎማ የተመረቀ/ች በሙያዉ 4ዓመት እና ከዛ በላይ በኮንስትራክሽን ድርጅት ዉስጥ የሰራ/ች 3ኛ መንጃ ፈቃድ ያለው/ት ቢሆን ይመረጣል

7 ገንዘብ ያዥ 1 ከታወቀ ዩንቨርስቲ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ በዲፕሎማ የተመረቀች በሙያዉ 1 ዓመት የሰራች የካሽ ሪጅስተር መጠቀም የምተችል እንዲሁም መሠረታዊ የኮምፒዉተር እዉቀት ያለት

8ፀሐፊ

1በሴክሬትሪያል ሳይንስና የቢሮ አስተዳደር በዲፕሎማ የተመረቀች

በፀሐፊነት ሙያ 1 ዓመት እና ከዛ በላይ የሰራች አማርኛና እንግሊዘኛ ጽሑፍ የመጻፍና የማንበብ ችሎታ የመግባባት ክሎት እንዲሁም የጸሐፊነት ሌሎች ተባራትን በሚገባ የማከናወን ችሎታ ያላት

9የንብረት ክፍል ሰራተኛ

1

በንብረት አያያዝ ወይንም በተጓዳኝ ዘርፍ ዲፕሎማ የተመረቀ/የተመረቀች

በሙያዉ 2 ዓመትና ከዚያ በላይ በኮንስትራክሽን ድርጅት ዉስጥ ያገለገለ/ች ስለንብረት አያያዝ በቂ ዕዉቀት ያለዉ/ት እንዲሁም ከንብረት ክፍል ሰራተኛ የሚጠበቁ ተግባራትን በሚገባ የማከናወን ችሎታ ያለው/ት

10 የከባድ መኪና ሹፊር 10 8ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 4ኛ መንጃ ፍቃድ እና ከዛ በላይ ያለዉና በሙያዉ 3 አመት እና ከዛ በላይ የሰራ

11 የቀላል መኪና ሹፊር 1 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ 3ኛ መንጃ ፍቃድ ያለዉና በሙያዉ ቢያንስ 2 ዓመትና ከዛ በላይ የሰራ

የሥራ ቦታ:- አዲስ አበባደሞዝ:- በስምምነት

አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃቸዉን ከግለታሪክ(CV) ጋር በማያያዝ ማስታወቂያዉ ከወጣ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ ከታች በተገለፀዉ አድራሻ መላክ ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 251 115 50 65 81 ይደውሉ::

የማነ ግርማይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭየፖስታ ሳጥን ቁጥር 41985

አ.አ

ተ.ቁየሥራ መደቡ

መጠሪያተፈላጊ ችሎታና የት/

ደረጃተፈላጊ የስራ ልምድ ብዛት

የሥራ ቦታ

1 ፕሮጀክት ሥራ

አስኪያጅ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና በመጀመሪያ ዲግሪ

የተመረቀ/ች

በሙያው 8 ዓመት የሠራ/ች ከዚህ ውስጥ 4 ዓመት በፕ/ሥራ አስኪያጅነት የሠራ/ች

ቢቻል በሕንጻ ላይ የሠራ/ች

1 አ/አ (ካዛንቺስ)

2 ፕሮጀክት ሥራ

አስኪያጅ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ በሲቪል ምህንድስና በመጀመሪያ ዲግሪ

የተመረቀ/ች

በሙያው 12 ዓመት የሠራ/ች ከዚህ ውስጥ 6 ዓመት በፕ/ሥራ አስኪያጅነት የሠራ/ች

ቢቻል በሕንጻ ላይ የሠራ/ች

1 አዲስ አበባ

3 ኦፕሬተር ደረጃ 2/ዳንፐር

ኦፕሬተር/

10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና በመሣሪያዎች ኦፕሬሽን ስልጠና ሠርተፊኬት እና ልዩ መንጃ ፈቃድ

ያለው/ት

በሙያው 3 ዓመት የሠራ 1 ዓለምገና

4 ኳሊቲ ኮንትሮል

ከታወቀ ተቋም ከሕንጻ ኮንስትራክሽን

በዲፕሎማ የተመረቀ/ች

በሕንጻ ግንባታ ፊኒሺንግ ሥራ ላይ ከ6 ዓመት በላይ

የሠራ/ች

1 አዲስ አበባ

5 ወጥቤት ሠራተኛ

ማንበብና መፃፍ የሚችል

በተመሳሳይ ሙያ 6 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ት

3 ሐርገሌ ዶሎባይ መ/ሥራ ፕሮጀክት /ሶማሌ ክልል/

6 ካምፕ አስተዳደር

10ኛ/12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች

በተመሳሳይ ሙያ 6 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ት

1

• ደመወዝ፡- ለሁሉም የሥራ መደቦች በስምምነት • የማመልከቻ ቦታ፡- አዲስ አበባ ጅማ መንገድ ከካራቆሬ ፍተሻ 50 ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ግራ

በሚወስደው መንግድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ወይም በፖ.ሣ.ቁ. 11161 መላክ ይቻላል:: • የማመልከቻ የጊዜ ገደብ ማስታወቂያው በወጣ በሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዋናውን ማስረጃ

እና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::

ስልክ ቁጥር 011-3-48-19-12/13

እንይ ኮንስትራክሽንክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

ተ.ቁ የስራ መደቡ መጠሪያ

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ መመዘኛ

ብዛት የስራ ቦታ

ደመወዝ

1 ቴክኒሽያን በኤክትሮኒክስ መሣሪዎች በዲፕሎማ የተመረቀ/ች/ና የ3 ዓመት የስራ ልምድ ያለው /ያላት/

3 አዲስ አበባ

በስምምነት

2 አካውንታንት በአካውንቲንግ ከታወቀ ኮሎጅ በዲፕሎማ የተመረቀ/ች/ና የ3 ዓመት የስራ ልምድ

ያለው /ያላት/

2 አዲስ አበባ

በስምምነት

3 ሴልስ ማን እና

ማርኬቲንግ

በሙያው ከታወቀ ኮሌጅ በዲፕሎማ የተመረቀ/ች/ና የ3 ዓመት የስራ ልምድ ያለው /ያላት/

4 አዲስ አበባ

በስምምነት

4 ሴክረታሪ በሙያው ከታወቀ ኮሌጅ በዲፕሎማ የተመረቀችና የ3 ዓመት የስራ ልምድ

ያላት

2 አዲስ አበባ

በስምምነት

5 ሹፌር እና ጉዳይ አስፈፃሚ

10ኛ ክፍል ያጠናቀቀ እና በሙያው ሶስት ዓመት የሰራ ሶስተኛ መንጃ ፈቃድ ያለው

1 አዲስ አበባ

በስምምነት

ማሳሰቢያ፡- ከላይ ከተዘረዘሩት የስራ ዓይነቶች ለመቀጠር የምትፈልጉ ያሉአችሁን የትምህርት ማስረጃ፤ የስራ ልምድና ተዛማጅ የሆኑትን ማስረጃዎች ኮፒ CV ጋር አያይዛችሁ ለዋና ስራ አስኪያጅ በፖ.ሣ.ቁ. 1224 አ.አ ብላችሁ ላኩልን::

Page 18: Reporter Issue 1229

ገጽ 18|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

Page 19: Reporter Issue 1229

|ገጽ 19 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

Page 20: Reporter Issue 1229

ገጽ 20|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

መ/ቤታችን ባዮኢኮኖሚ አፍሪካ ለ2ዐዐ4 ዓ.ም. የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል:: ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ::

2. ከዚህ በፊት የሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ከሰጡአቸው ድርጅቶች የተሰጣቸውን ማረጋገጫና ለኦዲት ሥራው የሚመድቧቸውን ባለሙያዎች የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ::

3. ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚወስደውን ጊዜና የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ በማያሻማ ሁኔታ የሚያቀርብ::

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ዋናው መ/ቤት አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ ማስገባት አለባቸው::

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ፣ ፈረንሳይ ኤምባሲ ከፍ ብሎ ብረት ድልድይስልክ ቁጥር ዐ111 142765 / ዐ111 1435ዐ1 ዐ911 12ዐ88ዐ

ሂሣብ ምርመራ አገልግሎት ጨረታ

በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ አያት አክሲዮን ማኅበር ከዚህ በታች ለተጠቀሰው ክፍት የሥራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል::

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የመስክ ሽያጭ ሠራተኛ

የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ፡- ከታወቀ የትምህርት ተቋም በማርኬቲንግ ወይም በቢዝነስ አድኒስትሬሽን በዲፕሎማ ተመርቆ/ተመርቃ በመስክ ሽያጭ ወይም በደንበኞች በመስተንግዶ ቢያንስ አንድ ዓመት የሠራ/የሠራች::

ብዛት፡- 10 (አሥር)

የቅጥር ዓይነት፡- ኮንትራት ሆኖ በየጊዜው የሚታደስ

ደመወዝ፡- በድርጅቱ ስኬል መሠረት

ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅም፡- የኮሚሽን ክፍያና አበል

የሥራ ቦታ፡- አዲስ አበባ

ማሳሰቢ፡-1. የማመልከቻ መቀበያ ጊዜ፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት

10 ተከታታይ የሥራ ቀናት 2. የማመልከቻ ማቅረቢያ ቦታ፣

አመልካቾች የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን የሚገልጸውን ዋናውን ሰነድና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከማመልካቻቸው ጋር ለገሐር ማሪታይም ፊት ለፊት ሳካ ሕንፃ አያት አክስዮን ማኅበር የቤቶች ሽያጭ ቢሮ ማቅረብ አለባቸው::

3. አመልካቾች ቶሎ ሥራ ሊጀምሩ የሚችሉበትን ጊዜ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል::4. የአመልካቾች አመራረጥ፣

መስፈርቱን የሚያሟሉ እና በአጭር ጊዜ ሥራ መጀመር የሚችሉ አመልካቾች ብቻ ለቃለ መጠይቅ በስልክ አድራሻቸው ይጠራሉ::

አያት አክሲዮን ማኅበር ፖ.ሣ.ቁ 3372አዲስ አበባ

ለሥራ ፈላጊዎች

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን

1. 5 Desk Top Computer, Optiplex above 790, Processor Speed 4 GB, Intel board 64 & excutedisable bit, RAM 4 GB or above, dual core, expandability upto 8 GB, LCD Monitor 19 inch እና፣

2. 7 Toshiba Laptop i5, core 4 GHZ, Processor Speed atleast 4 GB, RAM HD – 500 GB or above, 19 inch Screen size.

በጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈፀም ይፈልጋል::

በመሆኑም ከላይ የተገለጹትን ኮምፒውተሮች የምትሸጡ ድርጅቶች በፖስታ የታሸገ የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ፕሮፎርማችሁን ሠሜን ሆቴል ጀርባ ወደ ናይጄሪያ ኤምባሲ በሚገነጠነው መንገድ ድልድዩን ተሻግሮ ከኢትዮጵያ የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ ፊት ለፊት በስተግራ በሚገነጠለው አስፓልት 7ዐ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን::

ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 011 – 155 74 62 ወይም 0911 – 86 71 41

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን

Invitation for Audit FirmUniversity of California San Diego-Ethiopia (UCSD-E), in collaboration with partners, has been scaling up a comprehensive HIV/AIDS program to assist with HIV prevention, treatment, care and support to the Uniformed Services of Ethiopia (USE).

UCSD-E would like to engage an Authorized and Certified Audit Firm to undertake the audit of its accounts preferably for the current fiscal year 2010/2011 as per the guideline of the Charities and Societies Agency (CSA). UCSD-E would like to invite Audit Firms preferably classified as Grade A and B and the firms should submit:-

• A profile of the firm including its• Qualification and experience of the Audit firm • Certificate of compliance from the office of the Federal Audit• Relevance and renewed trade license • Testimonials from clients preferably for conducting audit of

NGO accounts• Annual Audit fee for the regular audit fee we require

If interested, you can assess the volume of our financial documents by visiting our offices during office hours.Interested Audit firms should submit their expression of interest and audit fee in a separate sealed envelope in person to UCSD-E finance office within 10 days after this announcement is made.

UCSd – EthiopiaP.O. Box 20734 code 1000

Tel: 011-554-4444, Fax: 011-554-4200Wollo Sefer, In front of Tebaber Berta, Four Storey Grey

building

Page 21: Reporter Issue 1229

|ገጽ 21 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

y ሃሎ

y አቤት?

y እኔው ነኝ ክቡር ሚኒስትር፣ የስልኬ ባትሪ አልቆ የወዳጆቼን ሞባይል ተጠቅሜ ነው::ብዙ ወዳጆችዎ እዚህ በጋራ ተሰብስበን ዕቅድ እያወጣን ነው::

y ጥሩ ነው::ሁልጊዜም የምለው ይህንን ነው::የቢዝነስ ዕቅድ አውጡ፣ ተወያዩ፣ በዘፈቀደ አትሂዱ ነው የምለው::ኢንቨስትመንት ሲርየስሊ መወሰድ ያለበት ሥራ ነው::ምን ዓይነት ኢንቨስትመንት ነው ያሰባችሁት?

y የዛሬ ስብሰባችን ስለ ኢንቨስትመንት አይደለም::ያለነውም ኢንቨስተሮች ብቻ አይደለንም::ነጋዴዎች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ሌሎችም አለን::በአጠቃላይ የድርጅትዎም የእርስዎም ደጋፊዎችና አድናቂዎች ነን::ልማታዊ ኃይሎች ነን::

y አጀንዳችሁ ከኢንቨስትመንት በላይ ነው በለኛ::

y አዎን ብል ማጋነን አይሆንብንም::የእርስዎን በርዝ ዴይ ለማክበር እየተወያየን ነው::

y በ - ር - ዝ - ዴ - ይ - የእኔ በርዝ ዴይ?

y አዎን::

y መቼ እንደሆነ እንኳን እኔ ራሴ በቅጡ አላውቀውም::

y እኛ እናውቀዋለን::ፓስፖርትዎ ላይ አይተነዋል::

y ፓስፖርቴ ላይ ያለውማ የግድ ቀን መጻፍ ስላለበት ይጻፍበት እንጂ ትክክለኛ ላይሆን ይችላል::

y ግን የለም - በዓሉ ይከበራል - ይዘጋጁ::

y ኧረ እኔ እንዲህ ዓይነት ነገር አልወድም::

y ክቡር ሚኒስትር የኢትዮጵያ ሕዝብ ይወድዎታል::ባለውለታችን ነዎት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይከበር ብሏል፣ ይከበራል::በእርስዎ ቤት በሚቀጥለው ሳምንት ታሪካዊ የበርዝ ዴይ ድግስ እውን ይሆናል፣ ለታሪክ ይዘጋጁ::

y ኧረ . . . .

y የኢትዮጵያ ሕዝብ የወሰነውን እምቢ አይባልም::

y ስማ. . .

y በቃ ቻው - ተወስኗል - ዝግጅቱ አልቋል::ሰዎች ተመድበዋል፣ ስፖንሰሮች ተገኝተዋል::ተጠናቋል::ቻው::

y እ. . .

y ክቡር ሚኒስትር በቀኑ የሚለብሱት ልብስ አዘጋጅተናል::ቀደም ብለን እንልክልዎታለን::ቻው::

[ቅዳሜ ምሽት ነው::ክቡር ሚኒስትሩ መኖርያ ቤት ግቢ ውስጥ ነው::አንድ ሺሕ የሚሆን ሰው የበርዝ ዴይ በዓል ለማክበር ተሰብስቧል::ቀደም ብሎ የመጣውን ልብስ ለብሰው ክቡር ሚኒስትሩ አምሮባቸዋል::የበዓሉ ኮሚቴ አስተባባሪ ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ለክቡር ሚኒስትሩ በጓሮ በኩል እያስረዳ ነው]

y ከእርስዎ የሚጠበቅ ነገር አጭር ንግግርና ፈገግታ ብቻ ነው::ጭፈራውና መጠጡ ሲጀመር እየዞሩም እንግዶችን ያነጋግራሉ::

y አንዳንዱ የተጠራው ሰው እውነት ወዶነው የመጣው?

y ወዶ ብቻ ሳይሆን ለምኖ እባካችሁ እወዳችኋለሁና ልገኝ ብሎ ጠይቆና ተማጥኖ ነው የመጣው::

y ብዙ ሰዎች ያቀረቡት ማመልከቻ ጠረጴዛዬ ላይ አለ::አሁን ነገ እንዴት የጠየቁትን አይቻልም እላቸዋለሁ?

y አይቻልም ከማለት መፍቀድና መደገፍ ነዋ::ወዳጅማ ማስቀየም አይገባም::አሁን በዓሉ ሊጀመር ነው ይዘጋጁ::የመድረኩ መሪ የታወቀ አርቲስት ነው::በዝግጅቱ ይኮራሉ፣ ሊጀመር ነው::

[የመድረኩ መሪ ወደተዘጋጀለት መድረክ ወጣ::ክቡር ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ያደረጉት ትግልና አስተዋጽኦ

ሁለት ገጽ ሙሉ የተዘጋጀ ጽሑፍ አነበበ::ግቢው በጭብጨባ ተደበላለቀ::የመድረክ መሪው ቀጠለ]

y “ክቡር ሚኒስትር - የተከበራችሁ እንግዶች ይህንን ታሪካዊ በዓል የተሳካ እንዲሆን ያደረጉ በርካታ ስፖንሰሮች አሉ::በአንዴ ሳይሆን አለፍ አለፍ እያልኩ ስፖንሰሮቹን አስተዋውቃለሁ::በመጀመርያ ውኃውን፣ ቢራውን፣ ውስኪውንና ዋይኑን ስፖንሰር ላደረገው ደማቅ ጭብጨባ እንድታደርጉለት እጠይቃለሁ::የስፖንሰሩን ስም እጠራለሁ - እጠራለሁ - ወደ መድረክ እንዲመጡልኝ እጠይቃለሁ - ፒንኮ ትሬዲንግ - ለፒንኮ ትሬዲንግ ደማቅ ጭብጨ”

[ደማቅ ጭብጨባ ለስፖንሰሩ ከተደረገ በኋላ የመድረክ መሪው ቀጠለ]

y “የተከበራችሁ እንግዶች - ክቡር ሚኒስትር ለበዓሉ ድምቀትና ለክቡር ሚኒስትሩ መልካም ልደት የሚመኙ በርካታ ቅኔዎችና ግጥሞች በአርቲስቶች ተዘጋጀተው ለክቡር ሚኒስትሩ ተሰጥተዋል::እንኳን ሁሉንም የአንዱን አርቲስት ግጥም ለማንበብም ጊዜ ስለማይበቃን አንድና ሁለት ስንኝ ብቻ ቀንጨብ ቀንጨብ እያደረግን አልፎ አልፎ እናሰማለን::የመጀመሪያዋን እነሆ፡-”

y “ተራ ሰው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ

y ኪራይ አይሰበስብ ልማታዊ

y የኒዮ ሊበራሊዝም ፀር

y ሃፒ በርዝዴይ ክቡር ሚኒስትር”

[ጭብጨባው ቀጠለ ተቀጣጠለ የመድረክ መሪውም ቀጠለ]

y “ክቡር ሚኒስትር - የተከበራችሁ እንግዶች - ስፖንሰሮቹ ብዙ ናቸው::አሁን የማስተዋውቀውና ደማቅ ጭብጨባ እንዲያገኙ የምጠይቀው ክትፎውን ስፖንሰር ያደረገውን ነው::ወደ መድረክ ይውጡልን - እሳቸው ናቸው አመሰግናለሁ::ደማቅ ጭብጨባ - ቲ - ፒ- ኤስ ቢዝነስ. . .”

y “ሌላ ስፖንሰር ደግሞ ላስተዋውቅ - በሬውን ራሳቸው መርጠው ገዝተው አሳርደው ጎድንና ደቢት ልዩ ቀይ ሥጋውን ራሳቸው እየመረጡ ለተጋባዥ ያቀረቡት ሊፎ - ፒ - ኤል - ሲ ደማቅ ጭብጨባ ለሊፎ. . . .”

[የመድረክ መሪው ቀጠለ]

y “ክቡር ሚኒስትር የተከበራችሁ እንግዶች ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ቀንጨብ ቀንጨብ እያደረግን ግጥሞችን እናነባለን::እኔ ከማነበው ራሱ ገጣሚው ወደ መድረክ ወጥቶ ቀንጨብ አድርጎ እንዲያነብ እጋብዛለሁ”

[ገጣሚው ወደ መድረክ ወጣ ቀንጨብ አድርጎ የሚከተለውን አነበበ]

y “የመልካም መስተዳድር ዳኛ

y የዲሞክራሲ ዘበኛ

y የዓባይ ግድብ ጠበቃ

y የልማት ዕድገት አለቃ

y የብሔር ብሔረሰቦች ድልድይ

y ክቡር ሚኒስትር . . . . ሃፒ በርዝ ዴይ”

[ጭብጨባው ቀጠለ - ገጣሚው ወረደ የመድረክ መሪው ቀጠለ]

y “ከዚህ ቀጥሎ ሌላና ልዩ ስፖንሰር አስተዋውቃለሁ::ጮማው ቢቆረጥም፣ ደቢትና ጎድን ቢበላም፣ በውስኪ ብንታጠብም ውኃ ብንጎነጭም አንዳንድ ተንኮለኛ የሥጋ አካል ተደብቆና ተቀርቅሮ ሊቀር ይችላል::የተደበቀና የተቀረቀረም የኋላ ኋላ ሊተናኮልና ሊጎዳ ይችላል::ስለዚህ ለጤንነትም ለፈገግታም የተቀረቀረና የተሸሸገን ፈልቅቆ ማውጣትና መጣል ያስፈልጋል::የማስተዋውቃችሁ ስፖንሰርም ይህንን ሥራ እሠራለሁ ብለው የተነሱ ናቸው::ክቡራን እንግዶች፣ ክቡር ሚኒስትር በየጠረጴዛው የምታዩትን የጥርስ እንጨት ስፖንሰር ያደረጉትን ወደ መድረክ እጋብዛለሁ::ደማቅ ጭብጨባ . . . የጥርስ እንጨት ስፖንሰር ያደረገው ሜትዎር ትሬዲንግ . . . ደማቅ ጭብጨባ”

[ደማቅ ጭብጨባ ለጥርስ እንጨት ስፖንሰር ተሰጠ::ተደበላለቀ::የመድረክ መሪው ቀጠለ]

y “ክቡር ሚኒስትር ኬክ የሚቆረስበትና

ሻማ የሚጠፋበት ሰዓት ላይ እየተቃረብን ነን::ክቡር ሚኒስትሩን ወደ መድረክ እጋብዛለሁ::አስተናጋጆች ሻምፓኙን እንዲያዘጋጁ እጠይቃለሁ::ከኬክ ቆረሳ በኋላ ሌሊቱን ሙሉ ጭፈራ ይኖራል::አለመጨፈር ያስቀጣል::ወደ ኬክ ቆረሳ ከመግባታችን በፊት ሌላ ገጣሚ ቀንጨብ አድርጎ ስንኞችን ያሰማናል::”

[ገጣሚው ወደ መድረክ መጣ የሚከተለውን አነበበ]

y “የኢትዮጵያ ውዳሴ

y . . . . . . ሕዳሴ

y ፀረ ድህነት ሞተር

y . . .. ካሽ ሬጂስተር

y እንዴትስ ላድንቅህ . . . ምን ብዬስ ልናገር

y ሃፒ በርዝዴይ ዕድሜህ ይርዘም ከማለት በቀር

y . . . . . . . . ክቡር ሚኒስትር”

[ክቡር ሚኒስትሩ በተደበላለቀ ስሜት የምስጋና ንግግር አደረጉ::ኬክ ተቆረሰ፣ ሻምፓኙ ተከፈተ::ርችት ተተኮሰ፣ ጭፈራው ቀጠለ፣ ጦፈ፣ ሰው ተሳከረ፣ ሊሆን የሚችለው ሁሉ ሆነ::በጧቱ ቤተሰብ ለቁርስ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጧል::ክቡር ሚኒስትሩ የልጃቸው ፊት ደስ አላላቸውም ጠየቁ]

y የልጄ ፊት ደስ አላለኝም::ምን ሆነሽ ነው?

y ምንም::

y የማስተርስ መመረቂያ ጽሑፍ እያዘጋጀሽ እንደሆነ አውቃለሁ::ለአንቺ ጊዜ ውድ ነው::ለአባትሽ በርዝ ዴይ ተብሎ ለአንድ ቀን ብትረበሺ ምን ቅር ያሰኛል?

y አባዬ ጥያቄው የጊዜ ችግር አይደለም::

y ታዲያ ሌላ ችግር አለ?

y አዎን ሌላ ችግር አለ::ችግሩ ሌላ ነው::

y ምንድን ነው ችግሩ ንገረኝ?

y በግልጽ የምትመልስልኝ ከሆነ በግልጽ እነግርሃለሁ::

y በግልጽ እመልስልሻለሁ::

y ምን የሚሉት ድግስ ወይም ፓርቲ ነው በቤታችን የተካሄደው?

y በርዝ ዴይ ፓርቲ ነዋ!

y ከመቼ ወዲህ ነው በርዝ ዴይ አክባሪ የሆንከው? ስልሳ ዓመት ሙሉ አክብረህም አታውቅም::ዘንድሮ ያከበርከው ለምንድን ነው? የሐኪም ትዕዛዝ ወይስ የኢሕአዴግ ውሳኔ?

y እ- - - እንኳን ሐኪም ሊያዝና ኢሕአዴግ ሊወስን፣ እኔ ራሴም አልፈለኩም ነበር::

y ካልፈለከው ታዲያ ለምን ተደረገ?

y ገፍተው መጡ::እምቢ ማለት አፈርኩ::

y በዚህ ጉዳይ ላይ አቋም ወስደህ መወሰን ካቃተህ በአገር ጉዳይ ላይ እንዴት ብለህ ነው የምትወስነው? የአገር ጉዳይ አይከብድም? በቀላሉ ከተንበረከክ በከባዱ እንዴት ትቋቋማለህ?

y የፖለቲካ ጉዳይኮ አይደለም የድግስ ጉዳይ ነው::የፖለቲካ ቢሆን ኖሮማ ጠንካራ አቋም እወስድ ነበር::የአባትሽን ጠባይ የምታውቂው ይመስለኛል::

y የአባቴን አቋም ጠንካራ ነው እያልኩ ነበር፣ አሁን አሁን ግን እንኳን የአባቴን የሁላችሁንም መጠራጠር ጀመርኩ::

y የሁላችሁንም ስትይ?

y የሌሎች ባለሥልጣኖችም ጭምር እያሳሰበኝ መጣ::

y ምንድን ነው የሚያሳስብሽ?

y የድግስና የበዓል መጫወቻ እየሆናችሁ ነው::

y እንዴት?

y እውነቱን ልንገርህ ዳዲ . . . . ክብራችሁን እየጠበቃችሁ አይደለም::85 ሚሊዮን ሕዝብ እያስተዳደራችሁ መሆናችሁንና ሕዝብም እያያችሁ መሆኑን የዘነጋችሁት ይመስለኛል::

y አልገባኝም?

y ልንገርህ፣ እስቲ ምን ትለዋለህ ቤተሰብ እያለህ ዘመድ እያለህ አንዱን የክትፎ፣

ሌላውን የጥሬ ሥጋ፣ ሌላው የውኃ ስፖንሰር እየተባለ ሲነገርና የቀልድ ቀልድ ደግሞ የጥርስ እንጨት ስፖንሰር እየተባለ ሲቀለድ . . . ማክበር ብትፈልግስ ባለህ አቅም ከቤተሰብ ጋር አታከብርም?

y እንግዶቹ እኮ ወዳጆቼ ናቸው::

y ወዳጆችህ ሊኖሩ ይችላሉ::ሁሉም ግን ወዳጆችህ አይደሉም::እኔን ስለማያውቁኝ ከእነሱ መሃል ገብቼ የሚያወሩትን አዳምጥ ነበር::በአንተ ይቀልዳሉ፣ በኢሕአዴግ ይቀልዳሉ፣ በመንግሥት ይቀልዳሉ፣ ሰኞ ጧት ሄደን እምቢ ያለንን እናስፈርማለን እያሉ ይቀልዱብሃል፣ ይህ ተራ ድግስ አልነበረም ሌላ ድግስ ነው::

y ምን ሌላ ድግስ?

y የፖለቲካ ድግስ - የሙስና ድግስ::

[ክቡር ሚኒስትሩ የልጃቸውን ንግግር መቀበልም መቃወምም አቃታቸው::መጣሁ ብለው አቋርጠው ተነሱ::መኝታ ቤት ገቡ፣ ተረበሹ፣ እሑድ ቀኑን ሙሉ እንደተረበሹ ውለው አድረው ሰኞ ጧት ቢሮ ገቡ::ቆይተው ቆይተው ጸሐፊያቸውን ጠሩ]

y አቤት ክቡር ሚኒስትር?

y በጣም ደክሞኛል ቅዳሜና እሑድ በጣም ቢዚ ነበርኩ እና. . .

y አውቃለሁ::

y ምንድነው የምታውቂው?

y ቢያንስ ቅዳሜ ቢዚ ሆነው እንደዋሉና እንዳደሩ አውቃለሁ::

y ምን ታውቂያለሽ?

y የበርዝ ዴይ ፓርቲ እንደነበር አውቃለሁ::

y ማን ነገረሽ?

y ፌስ ቡክ ላይ ነው ብዙ ፎቶግራፎች ያየሁት፣ መዓት ቀልድም፣ ግጥምም እዛ ፌስ ቡክ ውስጥ አለ::

y ፌስ ቡ . . . . ክ . . . . ጋዜጠኞችም ሌላ የማይፈለግ ሰውም አልነበረም::ለማስታወሻ ብለን የቀጠርነው የራሳችን ካሜራ ማን ካልሆነ በቀር::

y አይ ክቡር ሚኒስትር - ሁሉም ሞባይል ካሜራ አለው አይደል?

y እና በዛ ቀርፀው ሊያሰራጩ?

y ይኸው ተሰራጨኮ - ምርቃቶችም፣ ድግሶችም፣ ስብሰባዎችም በአሁኑ ጊዜ መጠንቀቅ ያስፈልጋል::ሁሉም ይቀርፃል፣ ሁሉም ያሰራጫል::ሰሞኑን በየኢንተርኔቱና በየፌስቡኩ ያለው ይህ በድብቅ የተቀረፀ ድምፅና ምስል ነው::የሚሰራጨው ያለውም ደስ አይልም::

y እንዴት ደስ አይልም?

y ባለሀብቶች ሲቀልዱና ሲያፌዙ፣ ባለሥልጣኖች ሲያፍሩና ሲያሳፍሩ ነው እየታየ ያለው::አያምርባችሁም::

y ወይ ጣጣ . . .

y [ጸሐፊዋ ቢሮዋ ሰዎች ሲገቡ ሰማችስና ቶሎ ወጥታ ወደ ቢሮዋ ሄደች::ሰዎቹን አነጋገረችና ወደ ክቡር ሚኒስትሩ ቢሮ ተመለሰች]

y ሰዎች መጥተዋል ክቡር ሚኒስትር

y ነገርኩሽ በጣም ደክሞኛል::እንቅልፍም አልተኛሁም::ሰዎች ዛሬ ማነጋገር አልችልም::ጉዳይ ያላቸው ሰዎች ናቸው?

y አዎን ከአሁን በፊት እርስዎ እንዲፈርሙላቸው ደብዳቤ ያስገቡ ሰዎች ናቸው::

y አሁን ማነጋገር አልችልም ወስኛለሁ::

y ልመልሳቸውማ አልችልም::አገናኝን እንጂ እሳቸው ይፈርሙልናል ብለው ሙጭጭ አሉ::

y ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው እንዲህ የሚሉት?

y የእርስዎ ወዳጆች ነን እያሉ ናቸው::

y ምን ዓይነት ወዳጆች?

y የእርስዎን በርዝ ዴይ ያዘጋጁት::

y ወይ . . . ጣጣ . . . . .

Page 22: Reporter Issue 1229

ገጽ 22|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

Chemonics International Inc., a leading international consulting firm based in Washington, D.C., seeks experienced professionals for USAID’s Famine Early Warning Systems Network (FEWS NET III), the world’s premier provider of high quality food security analysis and early warning. Created in response to the 1984 famines in East and West Africa, this $200 million, five-year activity (2012-2016) aims to collaborate with international, regional, and national partners to provide timely and rigorous early warning and analysis of potential, emerging, and/or evolving food security issues in order to inform appropriate humanitarian response. The project currently covers 31 countries, with plans to expand over the coming five-year phase. This position is based in Addis Ababa, Ethiopia.

Chemonics International Inc. is looking for individuals who have a passion for making a difference in the lives of people around the world and demonstrate leadership, versatility, and integrity in their work. Interested candidates should send their CV and cover letter to: [email protected] by Wednesday, February 15, 2012.

Position descriptionThe National Technical Manager (NTM) serves as the technical and administrative head of the Ethiopia office. The NTM is responsible for activities in four areas:• Efficient, focused food security monitoring, early warning analysis, and response planning, including maintaining a knowledge base composed of, at a minimum, livelihood zone profiles, commodity trade flow maps, sub-national seasonal monitoring calendars, and technical databases covering commodity prices, rainfall, agricultural production, population, historical assistance flows, and nutrition/health; and developing and updating seasonal monitoring plans;

• Effective communication of this analysis to partners and decision-makers through high

National Technical Managerquality reports and briefings;

• Capacity strengthening and network management, including collaborating with national, regional and international partners;

• Project administration and management, including regular reporting requirements;• S/He will collaborate with a team of regional technical experts and other technical

mangers of the area. The NTM will be required to conduct regular field assessments of food security conditions and travel intensely within his/her country of posting, and some international travel in sub-Saharan Africa, Europe, and the United States may be required.

Qualifications• At minimum, a degree in a discipline that is directly relevant to food security analysis• At least five years of relevant country or regional experience in early warning/food security information systems, food security analysis, as well as other related fields;• GIS applications and mapping skills;• Excellent computer skills;• Excellent communication and interpersonal skills, coordinating with partners and stakeholders;• Supervisory, management, and donor coordination experience; and• Excellent analytical and report-writing skills. • Excellent command of English; • Ability to speak local languages other than the national language will be an asset.

Only candidates qualified for the position will be contacted.

VACANCY ANNOUNCEMENTMetaferia Consulting Engineers PLC has vacancy for the following positions:

1. Senior Irrigation EngineerQualification: Msc in Irrigation Engineering or related field Expereince: Minimum of 8 years of relevant expereince on

study and design of irrigation schemes and supervision works

2. Irrigation EngineerQualification: Msc in Irrigation Engineering or related fieldExpereince: Minimum of 5 years of relevant expereince on

study and design of irrigation schemes and supervision works

3. Hydraulic EngineerQualification: MSc in Civil/Hydraulic EngineeringExpereince: Minimum of 8 years of relevant expereince in design of hydraulic structures.

4. Hydrologist Qualification: Msc in Hydrology Expereince: Minimum of 8 years of relevant expereince in hydrological studies, water resources and IWRM

For all positionsOther Skills: Computer Literate with knowledge of different design software and good command in spoken and written English

Work place: Addis Ababa with duty travel to different project sitesDuration: PermanentSalary: Negotiable

Interested applicants are invited to submit their non-returnable application accompanied with CV and copies of educational and expereince testimonials up to 29th February 2012 to our office at Bole Road next to Sabit Building House No. 988/29, 6th floor or send through the following address:-

Metaferia Consulting Engineers PlcP.O.Box 3192Tel: 011 551 56 47Addis Ababa

ክፍት የስራ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሰን ኦፕቲክስ ኀ.የተ.የግል ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የስራ መደቦች አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል::

ተ.ቁ የስራ መደቡ መጠሪያ

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ

ብዛት የአገልግሎት ዘመን

1 ስራ አስኪያጅ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በማኔጅመንት ቢ.ኤ ዲግሪ

ወይም ማስተርስ

2 3/1

2 ኤክስኪዩቲቭ ሴክሪተሪ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በሴክሪተሪ ቢ.ኤ ዲግሪ ወይም

ኦፊስ አድሚኒስትሬሽን

2 2 አመት እና ከዚያ በላይ

3 እቃ ግዥ እና አቅርቦት ኃላፊ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በእቃ ግዢና አቅርቦት ቢ.ኤ

ዲግሪ

3 2 አመት እና ከዚያ በላይ

4 የሂሳብ ሰራተኛ ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በአካውንቲንግ ቢ.ኤ ዲግሪ

ወይም ዲፕሎማ

3 1/2 አመት

5 ኤሌክትሪክ ባለሙያ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በኤሌክትሪሽያን ዲፕሎማ

2 1/2 አመት

6 ማርኬቲንግ ኤክስኪዩቲቭ

ከታወቀ ዩኒቨርስቲ/ኮሎጅ/ በማርኬቲንግ ቢ.ኤ ዲግሪ

3 2 አመት እና ከዚያ በላይ

7 ሞተረኛ 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና 1ኛ ደረጃ መንጃ ፈቃድ ያለው

3 1 አመት እና ከዚያ በላይ

ለስራ መደቡ የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርትና የስራ ልምድ ማስረጃችሁን ዋናውን ከሚነበቡ የማይመለስ ፍቶ ኮፒ ጋር በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት የስራቀናት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::

አድራሻ፡- ፒያሳ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት አጠገብ በሚኘው ቅርንጫፋችን ስልክ፡- 0115-567578/75

Page 23: Reporter Issue 1229

|ገጽ 23 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

ል ና ገ ር

በአየለ ከበደ

የማንም አገር ኤምባሲ የአገሩን ጉዳይ የማስፈጸም ተልዕኮ እንጂ አንድን ዜጋ በገዛ አገሩ የዜግነት መብቱን የመጣስ ሥልጣን አይኖረውም!

አየለ ከበደ እባላለሁ፤ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ነኝ::በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለፒኤችዲ በመማር ላይ እገኛለሁ::ጉዳዬን በአንድ የኦሮሞ ተረት ልጀምር::‹‹ከውጭ የመጣች አይጥ የቤቷን አሳደደች›› ይባላል::እኔን የገጠመኝ ጉዳይ እንዲህ ነበር::

ባለፈው ዓርብ ጥር 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 11፡30 በአሜሪካ ኤምባሲ ጀርባ ባለው መንገድ ወደ ሽሮ ሜዳ በቀስታ እጓዛለሁ::በዚያን ሰዓት አንድ የኤምባሲ የሴኩሪቲ ሠራተኛ ከላይ ቆሞ ወደ ታች ጠራኝና የጥበቃ ፖሊሱ ወዳለበት ቦታ እንድሄድ አዘዘኝ::እርሱም ተከትሎኝ ወደ ፖሊሱ ሄደ::በመቀጠል መታወቂያህን አሳየኝ አለኝ::በእጄ የነበረውን በተለምዶ ‹‹የቀበሌ›› መታወቂያ የሚባለውን ከወረዳዬ የተሰጠኝን አወጣሁ::አምጣው አለኝ::እኔም ሳለመነታ ሰጠሁት::

በመቀጠል ‹‹ሌላ ተጨማሪ መታወቂያ ለዚህ ማረጋገጫ የሚሆን ማየት እፈልጋለሁ›› አለኝ::ለጊዜው ከዚህ ሌላ አልያዝኩም አልኩት::በመቀጠል ሌላ ጥያቄ አቀረበልኝ::‹‹በተደጋጋሚ በዚህ መንገድ ስታልፍ በካሜራችን ተቀርፀሃል::ለምን ጉዳይ በዚህ እንደምታልፍና የመኖሪያ ሠፈርህስ የት እንደሆነ ንገረኝ?›› የሚል ነበር::እኔም አንዳንድ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሌላ ጊዜ ደግሞ ለመናፈስ አልኩት::ከዚያ በኋላ በፖሊሱ ጥበቃ ሥር ትቆያለህ አለኝና መታወቂያዬን ወስዶ ወደ ኤምባሲው ቅጥር ግቢ ገባ::ከ20 ደቂቃ በኋላ መታወቂያዬን በሌላ የሴኩሪቲ ሠራተኛ ላከልኝ::

በተደጋጋሚ ትሄድበታለህ የተባልኩት መንገድ ያልተከለከለና ሰውም ሆነ ተሽከርካሪ የሚጓዝበት ነው::ያለሁትም አዲስ አበባ እንጂ ኒውዮርክ ወይም ዋሽንግተን አይደለም::የሚገዛኝም የኢፌደሪ ሕገ መንግሥት እንጂ የዩኤስ አሜሪካ ሕገ መንግሥት አይደለም::የሚገዛኝን ሕገ መንግሥት መቶ በመቶ የተቀበልኩት ከመሆኑም በላይ ከውስጡ አንዲት አንቀጽ ብትወጣ እንኳን አይዋጥልኝም::ስለዚህ እንደ ሸማኔ መወርወሪያ

እየፈጠንኩ በቀን ሺሕ ጊዜ ብመላለስ፣ ወይም እንደ ኤሊ እያዘገምኩ በመንገዱ ለማለፍ 24 ሰዓት ቢፈጅብኝ ጠያቂውን ምን አገባው? ባልተከለከለ መንገድ ላይ የሚሄደውን መንገደኛ ለመጠየቅ መታወቂያ ወስዶ ፎቶ ኮፒ የማድረግ ወይም የመመዝገብ ሥልጣን የሰጠው ማነው?

‹‹ጠጅ በብርሌ ነገር በምሳሌ›› እንደሚባለው አንድ የአማርኛ ተረት ልጨምር:: ‹‹ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች›› ይባላል::እንዲህ ዓይነቱን ክብረ ነክና ማንነትን የሚፈታተን ተግባር የፈጸመው የሴኩሪቲ ሠራተኛ የአሜሪካ ኤምባሲ ተቀጣሪ በመሆኑ ማን ይጠይቀኛል በሚል ይመስላል::እንደዚያ አስቦ ከሆነ ግን ተሳስቷል::የፓርላማ አባላት እንኳ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ወደ መታረሚያ ስፍራ እንደሚላኩ መዘንጋት የለበትም::

ምናልባት መንገዱ ስጋት ሆኖባቸው ከሆነ መፍትሔው ከመንግሥት አካላት ጋር ተነጋግሮ ማዘጋት ነው::ይህም ሊሆን የሚችለው ስጋት መሆኑን መንግሥት ካመነበት ብቻ ነው::ከዚያ ውጭ ግን በመንገዱ መሄድን አላቆምኩም::ለወደፊት ማንም ሳይጠይቀኝ መሄዴን እቀጥላለሁ::ለመሆኑ ከሁለት ዓመታት በላይ በዚያ መንገድ ስመላለስ ለምን አልተጠየቅኩም? አሁን ለሴኩሪቲ ሠራተኛው ምኔ ተለውጦ ታየው? ካሜራው ሊቀርፀኝ አልቻለም ወይስ እኔን መለየት አልቻለም?

ማንም ሰው መታወቂያውን እንዲያሳይ የሚጠየቀው የትና ለምን ጉዳይ ነው? ባለጉዳይ ሆኜ ወደ ኤምባሲው አልሄድኩም፤ ለወደፊቱም ለመሄድ ዓላማ የለኝም::ሕግን አልተላለፍኩም::ስለዚህ ካሜራውስ ባልተከለከለ መንገድ የሚጓዝን ሰው የሚቀርፀው ከማን በተሰጠው ፈቃድ ወይም ሥልጣን ነው? እኛ እነ አፄ በጉልበቱ ነንና እንዳሻን እናደርጋለን ነውን? ኤምባሲው በመንገድ ላይ የሚጓዝን ሰው በካሜራው እንደፈለገ የሚቀርፅ ከሆነ ራሱ ስለምን ‹‹ፎቶግራፍ ማንሳት የተከለከለ ነው›› የሚል ማስታወቂያ አቆመ? አንድ ክስተት ቢፈጠርስ በተደጋጋሚ በዚህ መንገድ ተመላልሷል የሚለው መላምት ምን ሊሠራለት ነው? ይህን መላምት እንደ መነሻ መጠቀም መቶ በመቶ የተሳሳተ ከመሆኑም በላይ ባለ መላምቱ ደካማ ዕውቀት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል::

ሳይኮሎጂስት እንደመሆኔ ለ20 ደቂቃ ያህል በፖሊስ ጥበቃ ሥር በነበርኩበት ጊዜ አንድ አሳዛኝ ነገር ተነገረኝ::ፊቴ ሲታይ ‹‹ኦሮሞ›› ወይም ‹‹ሶማሌ›› መምሰሌ እንዳስጠረጠረኝና መታወቂያዬም ሲታይ ‹‹ብሔረሰብ ኦሮሞ›› ስለሚል በመሆኑ ነው::ይህ ግን ስንት ሚሊዮን ሕዝብን የሚያስቆጣና እንደ እመጫት ነብር የሚያደርግ አደገኛና መጥፎ አስተሳሰብ መሆኑን በግልጽ ለመጠቆም እፈልጋለሁ::አፍሪካዊ፣

የኩሽና የኦሮሞ ልጅ መሆኔን ወድጄው የራሴ መገለጫ አደርገዋለሁ::ሌላው ጉዳይ አማፂ የሚወጣው ከኦሮሞና ከሶማሌ ብሔሮች ብቻ አለመሆኑን መረዳትም አስፈላጊ ነው::

አንድ ኤምባሲ ዜጋን በገዛ አገሩ ያለምንም ምክንያት የማንከራተትና የማስፈራራት ሥልጣን ይሰጠዋል የሚል እምነት የለኝም::የምኖርባት አገሬ ሕገ መንግሥትም በነፃ መንቀሳቀስን ይፈቅድልኛል::በተደጋጋሚ በዚህ መንገድ ታልፋለህ ያለው የሴኩሪቲ ሠራተኛ በቀን፣ በሳምንት፣ በወርና በዓመት ስንት ጊዜ ማለፍ እንደሚፈቀድልኝ አልነገረኝም::ፖሊሱና መታወቂያዬን መልሶ ያመጣው የሴኩሪቲ ሠራተኛ በፈለግኩ ሰዓት የማለፍ መብቴ ያልተገደበ መሆኑን ገልጸውልኛል::ከዚያም በተጨማሪ እንዲህ ዓይነት ድርጊት የተፈጸመበት የመጀመሪያው ሰው እንዳልሆንኩ ለመረዳት ችያለሁ::ሳልገልጸው ማለፍ የማይገባኝ ፖሊሱ በንግግሩ በሳል፣ በሥርዓት የተሞላ፣ በራስ መተማመን ያለው፣ ሰው አክባሪና አስተዋይ መሆኑን ነው::የመብት መጣስ ወንጀል ፈጽሟል የምለውም የሴኩሪቲ ሠራተኛም ቢሆን እንደ አንድ ሰው እንጂ ሌሎችን እንደማይመለከት መግለጽ እፈልጋለሁ::

የሽብርተኝነት ጉዳይም ከሆነ የተባበሩት መንግሥታት ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ሽብርተኞችን እኔም እቃወማለሁ፤ አወግዛለሁ::ሆኖም ግን ሽብርተኝነት በቦምብ ናዳ ብቻ ይጠፋል ብዬ አላምንም::መርዘኛ የሆነው የሽብርተኝነት አይዲኦሎጂ እንዲከስም የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት መሥራት የበለጠ ውጤት እንደሚያስገኝ እምነቴ ነው::

ጽሑፌን ከመቋጨቴ በፊት ልገልጸው የምፈልገው ነገር ቢኖር በድህነት ብንኖርም ክብራችንን በጣም እንፈልገዋለን::መጠነኛና ጊዜያዊ ችግርን ከመቅረፍ ከማያልፈው የማንም አገር ዕርዳታ ይልቅ መከበሬ ለእኔ ትልቅ ቦታ አለው::በእኔ እምነት ዕርዳታ ዘለቄታዊ ዕድገትን ሊያመጣ አይችልም::ቢያመጣ እንኳ ክብሬን የሚነካ ከሆነ ይቅርብኝ::ስለሆነም ኤምባሲው የአገሩን ጉዳይና ተልዕኮ ይፈጽም እንጂ የዜግነት መብትን ከመግፈፍ ይቆጠብ እያልኩ ጉዳዬን ቋጨሁ::ጤና ይስጥልኝ!

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በ[email protected] ማግኘት ትችላላችሁ::

አሸባሪው ማን ነው?

በተደጋጋሚ ትሄድበታለህ የተባልኩት መንገድ ያልተከለከለና ሰውም ሆነ ተሽከርካሪ የሚጓዝበት ነው::ያለሁትም አዲስ አበባ እንጂ ኒውዮርክ ወይም ዋሽንግተን አይደለም::የሚገዛኝም የኢፌደሪ ሕገ መንግሥት እንጂ የዩኤስ አሜሪካ ሕገ መንግሥት አይደለም::የሚገዛኝን ሕገ መንግሥት መቶ በመቶ የተቀበልኩት ከመሆኑም በላይ ከውስጡ አንዲት አንቀጽ ብትወጣ እንኳን አይዋጥልኝም::

በአበዱልአዚዝ በህሩ

በዓለማችን በየዓመቱ በትራፊክ አደጋ የሚሞተው ሰው ቁጥር በጦርነት ከሚሞተው ሰው አንፃር ወደ አራት እጥፍ ይሆናል። አብዛኛው የአደጋው ሰለባዎች ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ዜጎች ናቸው። ለንፅፅር ያህል ዝቅተኛ የትራፊክ አደጋ የሚከሰትባትን አይስላንድ የምትባል አገርን እንውሰድ። ኢትዮጵያ ውስጥ በአማካይ አንድ መኪና የሚያደርሰው የሞት አደጋ አይስላንድ ውስጥ 2,000 መኪኖች ከሚያደርሱት በላይ ነው (በ2009 የተመድ ሪፖርት መሠረት)።

ኢትዮጵያ ውስጥ ተሽከርካሪዎች አደገኛ ገዳዮች ናቸው ማለት ይቻላል። የንብረት ውድመቱም በዚያው ልክ ነው። የተሽከርካሪዎች ብዛት በጨመረ ቁጥርም የአደጋዎች አስከፊነት እየጨመረ ነው የሚሄደው። የሞት አደጋውና የአካል ጉድለቱ ያሳዝናል። ከድህነታችን አንፃር ደግሞ የሚወድመው ሀብትም ብዙ ነው። በዚህ ጽሑፌ የኢንሹራንስ ገበያው አደጋ ለመቀነስ አስተዋጽኦ የሚያደርግበትን አሠራር ለመጠቆም እሞክራለሁ።

አሠራሩ የሚያተኩረው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተሽከርካሪዎችንና አሽከርካሪዎችን የጀርባ ታሪክ (background history) የሚያሳይ መረጃ ማግኘት እንዲችሉ በማስቻል ላይ ነው። የማስፈጸም ኃላፊነቱም የመንገድ ደኅንነት መሥርያ ቤቶችን የሚመለከት ይሆናል። በቅርቡ ተግባራዊ መሆን የጀመረው የሦስተኛ ወገን ኢንሹራንስም ለምጠቁመው አሠራር ውጤታማነት ገንቢ ሚና ይኖረዋል። የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የተሽከርካሪዎችንና አሽከርካሪዎችን ታሪክ የሚያሳይ መረጃ ማግኘት መቻላቸው አደጋን ለመቀነስ ለምን ያግዛል? እንደሚታወቀው ኢንሹራንስ የሚገቡ የአሽከርካሪ ባለቤቶች ለኢንሹራንስ ኩባንያው በየዓመቱ

የተወሰነ መጠን ያለው ክፍያ (ፕሪሚየም) ይፈጽማሉ።

አደጋ በደረሰባቸው ጊዜም የኢንሹራንስ ኩባንያው ካሳ ይከፍላል ማለት ነው። የካሳው መጠንም ባለአሽከርካሪዎችና የኢንሹራንሱ ኩባንያ ቅድሚያ በገቡት ውል መሠረት ይሆናል። የፕሪሚየሙን መጠን ከሚወስኑት ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ተሽከርካሪው አደጋ የማድረስ ዕድሉ ነው። ተሽከርካሪው አደጋ የማድረስ ዕድሉ ከፍተኛ ከሆነ የኢንሹራንስ ኩባንያውም ከፍተኛ ፕሪሚየም ይጠይቅበታል። በአንፃሩ ተሽከርካሪው አደጋ የማድረስ ዕድሉ ዝቅተኛ ከሆነ የሚከፈለው የኢንሹራንስ ፕሪሚየም ዝቅተኛ ይሆናል ማለት ነው። ይህም የሚሆንበት ምክንያት አደጋ የማድረስ ዕድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ተሽከርካሪዎች ካሳ የማስከፈል ዕድላቸውም ከፍተኛ ስለሆነ ነው። የኢንሹራንስ ኩባንያውም ከፍ ያለ ፕሪሚየም ካላስከፈለ በቀር ለእንዲህ ዓይነቶቹ ተሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ መስጠት አያዋጣውም። ሁሉም ተሽከርካሪዎች ደግሞ አደጋ የማድረስ ዕድላቸው እኩል አይደለም።

ለምሳሌ ያህል በአማካይ ሲታይ በጎልማሶች ከሚሽከረከሩ ተሽከርካሪዎች ይልቅ በወጣቶች የሚሸከረከሩት ይበልጥ አደጋ ያደርሳሉ። የመኪኖች የቴክኒክ ብቃትም እንዲሁ። የአሽከርካሪዎች ባህርይና ግንዛቤም አደጋ የመከሰት ዕድል ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። የተሻለ ግንዛቤ ያላቸውና ጠንቃቃ አሽከርካሪዎች አደጋ የማድረስ ዕድላቸው ያነሰ ነው።

ባለተሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ መግባት ሲፈልጉ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ስለተሽከርካሪዎች/አሽከርካሪዎች በቂ መረጃ ካላቸው፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑት ላይ ከፍ ያለ ክፍያን ይጠይቃሉ። ለምሳሌ ያህል አይሱዙ የጭነት መኪኖችና የቤት መኪኖችን እናነፃፅር። በለጋ ወጣቶች የሚሽከረከሩት

አይሱዞዎች ብዙውን ጊዜ አደጋ በማድረስ በአገራችን ዕውቅናን አትርፈዋል። የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም አይሱዙዎችን ከፍ ያለ ፕሪሚየም ያስከፍሉዋቸዋል፤ ለቤት መኪኖች ከሚያስከፍሉት አንፃር።

በአገር አቀፍ ደረጃም የእያንዳንዱ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ የአደጋ ታሪክ ተመዝግቦ ከተቀመጠና ይህም መረጃ ለኢንሹራንስ ድርጅቶች ከተሰጠ፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶችም መረጃውን በመጠቀም ዋጋቸውን ይተምናሉ። ብዙ ጊዜ እየጠጣ ሲያሽከርክር የተያዘ አሽከርካሪም ኢንሹራንስ መግባት ሲፈልግ ብዙ ዋጋ ይጠየቃል::ግድ የለሽ አሽከርካሪ ነውና አደጋ አድርሶ ካሳ የማስከፈል ዕድሉም ከፍተኛ ስለሆነ። ብዙ ጊዜ መብራት የሚጥስ፣ ከፈተቀደው ፍጥነት በላይ የሚነዳ፣ ወዘተ አሽከርካሪም የሚጠብቀው ዕጣ ፈንታ ከፍ ያለ የኢንሹራንስ ፕሪሚየም መክፈል ይሆናል። እንደዚህ ዓይነቱን አሽከርካሪ በቅናሽ ፕሪሚየም ደንበኛ አድርጎ መያዝ ለኢንሹራንስ ኩባንያዎች አያዋጣም።

ይህ መረጃ መኖሩ አደጋን ከመቀነስ አንፃር በሁለት መንገድ አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል። አንደኛ ጥፋት የሚፈጽሙ ሰዎች የሚከፍሉት የኢንሹራንስ ፕሪሚየም ስለሚበዛበቸው ጥፋት ላለመፈጸም ይጠነቀቃሉ። ሁለተኛው ጥፋት የሚያበዙ አሽከርካሪዎች የሚቀጥራቸው ባለተሽከርካሪ ለማግኘት ይቸገራሉ። ምክንያቱም ጥፋት የሚያበዛ አሽከርካሪ በቀጣሪው ላይ የኢንሹራንስ ፕሪሚየም ወጪ እንዲበዛ ያደርጋልና።

ስለዚህ ባለንብረቶች ይበልጥ ጠንቃቃ የሆኑና ልምድ ያላቸውን አሽከርካሪዎች ብቻ እንዲቀጥሩ ጫና ይፈጥርባቸዋል። ግድየለሽ አሽከርካሪዎች ከገበያው መውጣታቸው ደግሞ አደጋን ለመቀነስ ያግዛል። አሁን ካለው የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕድገት አንፃርም እንደዚህ ዓይነቱን መረጃ ማመቻቸት ብዙ ወጪን የሚያስወጣ

አይሆንም። ኮምፒዩተሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋጋቸው እየቀነሰ ነው የሚሄደው። እያንዳንዱ የትራፊክ ጽሕፈት ቤት በራሱ ክልል የተከሰቱ የትራፊክ ጥፋቶችን በኮምፒዩተር ይመዘግባል። አሽከርካሪዎች ጥፋት ሲፈጽሙ በመንጃ ፈቃድ ቁጥራቸው፣ በስማቸው፣ በምስላቸው፣ ወዘተ መሠረት ለይቶ ይመዘግባል። ተሽከርካሪዎችንም በሰሌዳ ቁጥራቸው መለየት ይቻላል።

በፌደራል ደረጃ ኃላፊነት የሚወስድ አካል ደግሞ እነኚህን መረጃዎች አጠናቅሮ ለኢንሹራንስ ድርጅቶች ይሰጣል። የተሽከርካሪ ባለቤቶችም ኢንሹራንስ መግባት ሲፈልጉ፣ የኢንሹራንስ ድርጅቶች የአሽከርካሪውንና የተሽከርካሪውን የጀርባ ታሪክ አመሳክረው የፕሪሚየም ክፍያ መጠየቅ ይችላሉ ማለት ነው። ብዙ የትራፊክ ጥፋት የሚፈጽሙትንም ብዙ ፕሪሚየም ይጠይቃሉ። በዚህም መሠረት ብዙ ጥፋት የሚፈጽሙት በገበያው እየተቀጡ፣ ሕግ አክባሪዎቹና ጠንቃቃዎቹ ደግሞ በገበያው ይበረታታሉ ማለት ነው። ግድ የለሾችን የሚቀጣና ጠንቃቃዎችን የሚያበረታታ ሥርዓት መኖሩ ደግሞ ሰዎች ይበልጥ ጠንቃቃ እንዲሆኑ በማበረታታት አደጋን ለመቀነስ ያግዛል። የፌደራል መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣናትም ለዚህ አሠራር ተፈጻሚነት ኃላፊነት ወስደው መሥራት ይኖርባቸዋል፤ የመንገድ ደኅንነትን መጠበቅ ዋነኛው ኃላፊነታቸው ነውና።

አሠራሩ መንግሥት ላይ ብዙ ወጪን በማያስከትል ሁኔታም መተግበር ይቻላል። የፌዴራል መሥርያ ቤቱ በዚህ መልክ የሰበሰበውን መረጃ ለኢንሹራንስ ድርጅቶች በሽያጭ ማቅረብ ይችላል። ከሽያጩ የሚያገኘውን ገቢም መረጃውን ለመሰብሰብ የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ይጠቀምበታል።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል::

የኢንሹራንስ ድርጅቶች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ ይችላሉ

Page 24: Reporter Issue 1229

ገጽ 24|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004 ማህበራዊ ማህበራዊ

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ፣

አክስዮን ማኅበራችን ለ2004 ዓ.ም. ምርት ሥራ የሚሆን ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ የተዳመጠ ጥጥ በቀጥታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል::

ስለሆነም የድርጅታችንን ጥጥ ፍላጎት ማሟላት የሚችል ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈለ ማንኛውም ጥጥ አምራች የጥጥ ናሙና በቅድሚያ ከዚህ በታች በተገለፀው የድርጅታችን አድራሻ ማቅረብና ማነጋገር የምትችሉ መሆናችሁን እንገልፃለን::

አዋሣ ጨርቃጨርቅ አ.ማኅበር

ፓፓሲኖስ ህንፃ አንደኛ ፎቅየቢሮ ቁጥር 149

ስልክ ቁጥር 011 551 89 00 /011 553 75 12

አዲስ አበባ

VACANCY ANNOUNCEMENTChina Gezhouba Group Company Ltd would like to employee qualified applicants for the following positions for our office.

1. Position: Secretary Educational Background: College diploma in Secretarial Science. Sex: Female 2. Position: Supervisor Sex: Both3. Position: Mechanic Sex: Male4. Position: Lawyer Sex: Male5. Position: Small Vehicle Driver Sex: Male6. Position: Electrician Sex: Male

N.BExperience: two up to three years relevant experience. Language: Requirement: Must speak fluent English.Preference: Hard working and dedicated applicant.Number: for all position OneWorking Place: Wolkite-Hossaina (Endiber Town)

All qualified applicants should submit their CV and testimonials in person within Ten working days from this vacancy announcement at our office located in Wolkite Emdiber Town Kebele 02, P.O.Box 29Only short listed applicants will be contacted.

China Gezhouba Group Company LimitedOffice Tel: 0113310570

Mobile: 0923128105

በእስከዳር አስማረ

ቅዳሜ ጠዋት በጃንሜዳ ሲጫወቱ ያስተዋልናቸው ጐልማሶች የተጫሙት ቡትስ ጫማ፣ የፈረስ ላይ የገና ጨዋታ ጊዜ የሚደረግ ሄልሜት ወይንም ቆብና በመጠናቸው ገዘፍ ያሉና በእንክብካቤ መያዛቸውን የሚመሰክር አቋም ያላቸው የፈረሶች ሞገስ ለጨዋታው የተለየ ውበት አጐናጽፎታል::

እንደ ገና ጨዋታ፤ አነስተኛና ከእንጨት የተሠራች ኳስና ዘንግ ለጨዋታው ያስፈልጋሉ:: ሳራማ የሆነና 300 ያርድ ወይንም የአንድ የእግር ኳስ ሜዳን ሦስት እጥፍ የሚሆን ቦታም እንዲሁ:: ጨዋታው በቡድን ፈረስ ግልቢያ የሚከናወን ነው::

ጥንት እንግሊዛውያኑ ከመዝናናትም ባለፈ ፈረሶቻቸው ይሰለጥኑላቸው ዘንድ ፖሎ ወይንም የፈረስ ጉግስ እንዲጫወቱ ያደርጓቸው እንደነበር ይነገራል:: አንድ ፈረስ ወደ ጦር ሰፈር ከመዝመቱ ቀደም ብሎ የፈረስ ጉግስ መጫወት አለበት የሚል እምነትም ነበራቸው::

በመሆኑም ፈረሶቻቸውን በፈረስ ጉግስ ጨዋታ በደምብ ካሰለጠኑ በኋላም ወደ ጦር ሰፈር ይሸኙዋቸው ነበር:: የንጉሣውያኑ ቤተሰቦችና ሚስቶቻቸው፣ እንዲሁም ከደንገጡሮቻቸው ጋር ይጫወቱ እንደነበር ይታወቃል:: ፖሎ የሴትም የወንድም ጨዋታ ሲሆን በእንግሊዞች ዘንድ የጨዋታዎች ንጉሡ እየተባለ የሚወደስ ስፖርታዊ ጨዋታ ነው::

በጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በውጭ ዜጎች አማካይነት ወደ አገራችን እንደገባ የሚነገርለት ፖሎ ከአገራችን የገና ጨዋታ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን እንደ የገና ጨዋታ ሁሉ በአገራችን የገና ቀን ይዘወተርም ነበር::

አሁን አሁን ፈረስ ላይ የገና ጨዋታ በባለፀጐች እንደሚዘወተር ያጫወቱን መቶ አለቃ ደጉ ጃፋር ናቸው:: እሳቸው እንደሚሉት፣ በፊት በፊት በተለይም በገና ዕለት እንደ ገና ጨዋታ ሁሉ የፈረስ ላይ ገናን የሚጫወቱ ሰዎች በርካታ ነበሩ:: አሁን አሁን ግን የፈረስ ላይ ገና እንደሌላው ስፖርታዊ ጨዋታ እንብዛም አይዘወተርም:: ቢሆንም ግን በየጊዜው

በተለያዩ ቦታዎች የፈረስ ላይ የገና ጨዋታ ውድድር በአገራችን በቡድን ተደራጅተው የሚያካሂዱ አካሎች አሉ:: የፖሎ ገና ጨዋታ ማኅበርም ተቋቁሟል::

የፈረስ ላይ ገና ለመጫወት እያንዳንዱ ቡድንም ውስጥ አራት ፈረሰኞች ለዳኝነቱም ሁለት ፈረሰኛ ዳኛዎችም ይኖራሉ::

የአንድ ጨዋታ ጊዜ ወይም “ቻተር” ከሰባት እስከ አሥር ደቂቃ ይወስዳል:: እንደ እግር ኳስ ጨዋታ ሁሉ በደቂቃዎች ውስጥ የበለጠ ነጥብ ያስቆጠረ አሸናፊ ይሆናል:: የፈረስ ጉግስ ጨዋታን ከዘጠኝ ዓመታት በፊት መጫወት እንደጀመረ ያጫወተን የ39 ዓመቱ ጐልማሳ ሚሊዮን ድጉማ ነው:: በአንድ ጓደኛው

አማይነት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ወደ ጃን ሜዳ መጥቶ የሚጫወቱትን ሰዎች ካየ በኋላ እስከ ዛሬ ከፈረስ ላይ ገና ጨዋታ አልተለያየም:: በጣም የሚያስደስትና የሚያዝናና ጨዋታ እንደሆነም ይናገራል::

ያዝናናል ብለን በምናስበው ነገር ራሳችንን ማዝናናት ይኖርብናል ሲል የሚናገረው ሚሊዮን፣ በተለይም በስፖርታዊ ጨዋታዎች እንደ ፖሎ፣ ጎልፍ፣ ቤዝ ቦል ጊዜን ማሳለፍ ከማዝናናቱም ባሻገር ለጤንነት ጠቃሚ እንደሆነ አጫውቶናል:: በሳምንት ሁለቴ ከጓደኞቹ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ጃን ሜዳ በመሔድ ይጫወታል:: ጨዋታውን ለማካሔድ ቢያንስ ለሁለቱም ቡድኖች ከስምንት በላይ ፈረሰኞች

በማስፈለጋቸው ከጓደኞቹ ጋር በሳምንት ሁለት ቀኖችን በመመደብ ተገናኝተው በጨዋታው ይዝናናሉ::

አብዛኞቹ በራሳቸው ፈረሶች እንደሚጫወቱ ያወጋን አቶ ሚሊዮን አራት የግል ፈረሶች አሉት::

ሰው ጤንነቱን ጠብቆ የሚያዝናናውን ወይንም የሚያስደስተውን ነገር ከውኖ ማለፍ እንደሚገባ የሚመክረው አቶ ሚሊዮን፣ በግል የንግድ ሥራ ውስጥ ተሰማርቷል:: ሳምንት ለእያንዳንዱ ፈረሶች ከአንድ ሺሕ ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግና ወጪያቸው ትንሽ በዛ ቢልም ለመዝናናት የሚያወጣው ወጪ እምብዛም እንደማይከብደው ይናገራል::

ከሁለት ሕፃናት ልጆቹ ጋር ለመዝናናት መጥቶ ያገኘነው አቶ ሚሊዮን፣ በተቻለው አቅም ለሥራው፣ ለመዝናናትና ለቤተሰቦቹ የሚሆን ጊዜ እንዲኖረው እንደሚያደርግ፣ ለመኖር የተፈቀደለትን ጊዜ ማድረግ የሚገቡትን ወይም የሚፈልጋቸውን ነገሮች ከውኖ እንደሚያሳልፍ በተለይም ረቡዕና ቅዳሜ ከቀኑ ከስምንት ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት የፈረስ ላይ ገና ጨዋታን ከውጭ አገር ዜጐች ጓደኞቹ ጋር እንደሚጫወት ገልጿል::

የፈረስ ላይ ገና ጨዋታ ለጤንነት ከሚሠሩ ሌሎች ስፖርቶች እኩል ስለሚገለገልበት “ጂም መግባት አያስፈልገኝም” በማለት ከማዝናናቱ ባለፈ ከጤንነት ጋር በተያያዘ እጅግ ጠቃሚ ስፖርታዊ ጨዋታ መሆኑንም ያብራራል::

“በሥራ የደከመንና በሌሎች የሕይወት ጥያቄዎች ሲባዝን የሚውለውን አዕምሮአችንን ፈታ ለማድረግና የመስራት፣ የመኖር ፍላጐታችን፣ በአጠቃላይ ጤንነታችን መልካም ለማድረግ እንዲህ ያሉ ጨዋታዎች ይጠቅማሉ:: ሁሉም ሰው ለመዝናናት ዋጋ ሰጥቶና ጠቀሜታውን ተረድቶ ለመዝናናት ጊዜ ሊኖረው ይገባል፤” ሲልም ያስረዳል::

እጅግም ያልሰለጠኑት የአገር ውስጥ ፈረሶች እስከ 4000 ብር የሚሸጡ ሲሆን የሰለጠኑና በአግባቡ የተያዙት ፈረሶች ግን እስከ 20,000 ብር እንደሚያወጡ ጨምሮ ይገልፃል:: በጣም የሰለጠኑና ከውጭ አገር ፈረሶች ጋር የተዳቀሉ ፈረሶችም እስከ 200,000 ብር ያወጣሉ::

ፖሎ የፈረስ ላይ ገና ጨዋታ

የፈረስ ላይ ገና ጨዋታ ለጤንነት ከሚሠሩ ሌሎች ስፖርቶች እኩል ነው

Page 25: Reporter Issue 1229

|ገጽ 25 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

ፍ ሬ ና ፍ ርከ

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ:: ጎዳ ጠርሙዝና ብርጭቆ አክሲዮን ማህበር::

ጎዳ ጠርሙዝና ብርጭቆ አ.ማ በትግራይ ክልል በዕዳጋ-ሓሙስ ከተማ ትልቅና ዘመናዊ የጠርሙዝና የብርጭቆ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የተቋቋመ ሲሆን ለፕሮጀክት ስራ ከስር ለተመለከቱት ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች አመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል::

ተ/ቁ የስራ ዝርዝር በአጭሩ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ

1 የግዥና አቅርቦት ሃላፊ ----------- ብዛት 1(አንድ)

የቴክኖሎጂና የማሽን አቅራቢ ድርጅቶችን የማፈላለግ፣ የመምረጥና የግዥ ስራ መስራት::የህንፃ ግንባታ አማካሪና የህንፃ ተቋራጭ ድርጅቶችን የመምረጥ ስራ መስራት::ከስራው ጋር ግንኙነት ያላቸው የጨረታና የኮንትራት ውል ሰነዶች ማዘጋጀት::የውጭና የአገር ውስጥ ግዥ ጋር የተያያዙ ስራዎችን በማከናወን ንብረቶች በተፈለገው ጊዜ፣ በደህንነትና በተመጣጣኝ ዋጋ

ተገዝተው ወደ ፕሮጀክቱ እንዲደርሱ ማድረግ::ተገዝተው የመጡ ንብረቶች ምንም ጉዳት እንደሌለባቸው አረጋግጦ መረከብ እንዲሁም ከመጥፋት፣ ከመቀላቀል፣ ከብልሽትና

ከአደጋ ተከላክሎ ማስቀመጥና ለተጠቃሚው አካል በአግባቡ እንዲደርሱ ማድረግ::ምርት ለማስጀመር የሚያስፈልጉ ግብአቶች በወቅቱ እንዲዘጋጁ ማድረግ::

ከታወቀ ዩንቨርስቲ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስ፣ በኢንደስትሪያል ኢንጂነሪንግ ወይም በተመሳሳይ ሞያ በመጀመርያ ዲግሪ ወይም ከዛ በላይ የተመረቀ/ች::

ለመጀመርያ ዲግሪ ቢያንስ በሞያው/ዋ 10ዓመት የሰራ/ች ከዚህ ውስጥ 4ዓመት በከፍተኛ ሃላፊነቶች በትላልቅ ፕሮጀክት የሰራ/ች::

ከውጭ ግዥ ጋር በተያያዘ ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ያሉ ማንኛውም ስራዎች የማከናወን እውቀትና ልምድ ያለው/ት::

2 የፋይናንስ ሃላፊ ----------- ብዛት 1(አንድ)

አክሲዮን በመሸጥ ስራ ላይ መሳተፍና የአክሲዮን ክፍያዎች በአግባቡና በወቅቱ መፈፀማቸውን መከታተልና ማረጋገጥ::ከባንክ ብድር በወቅቱ እንድናገኝ ማድረግ::ለፕሮጀክት ግንባታና የምርት ስራ ለማስጀመር የሚያስፈልግ በጀት ዝግጁ ማድረግ:: ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር በመከተል የአክሲዮን ማህበሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ማስተዳደር እንዲሁም ይህን

ለመተግበር የሚያስችሉ አሰራሮች ማውጣትና መተግበር::ከፕሮጀክት ጅማሮ እስከ ፋብሪካ እውን መሆን ድረስ ያሉ ጠቃሚ መረጃዎችን በአግባቡ በማሰባሰብና በመያዝ ለፋብሪካ ማሸጋገር::

ከታወቀ ዩንቨርስቲ በአካውንቲነግ ወይም በተመሳሳይ ሞያ በመጀመርያ ዲግሪ ወይም ከዛ በላይ የተመረቀ/ች::

ለመጀመርያ ዲግሪ ቢያንስ በሞያው/ዋ 8ዓመት የሰራ/ች ከዚህ ውስጥ 4ዓመት በከፍተኛ ሃላፊነቶች በትላልቅ ፕሮጀክት የሰራ/ች::

3 በኤክስኩቲቭ ሴክረተሪ ----------- ብዛት 1(አንድ)

የዋና ስራ አስኪያጅ ቢሮ ማደራጀትና ማስተዳደር እንዲሁም የፅህፈት ስራዎችን ማከናወን::የስራ አስፈፃሚ (የማኔጅመንት) ስብሰባ ፀሃፊ ሆኖ መስራት::

ከታወቀ ዩንቨርስቲ በሴክረተሪያል ሳይንስ እና የቢሮ አስተዳደር በዲፕሎማ ወይም በመጀመርያ ዲግሪ የተመረቀች::

ለዲፕሎማ ቢያንስ በሞያው 8ዓመት የሰራች ከዚህ ውስጥ 4ዓመት በኤክስኩቲቭ ሴክረተሪ የሰራች::

አስፈላጊ መረጃዎች፤1) የስራ ቦታ ----------- ዕዳጋ-ሓሙስ / ትግራይ (ለተወነ ጊዜ የስራ ቦታ አዲስ አበባ ይሆናል)::2) የቅጥር ሁኔታ------------- -- በቋሚነት:: 3) ደመወዝ -- በስምምነት:: 4) የማመልከቻ ቀን እስከ የካቲት 17ቀን 2004ዓ/ም::5) የአክሲዮን ማህበሩ አድራሻዎች፤

5.1) የቢሮ አድራሻ፤ ቦሌ መንገድ ሜጋ ህንፃ ቢሮ ቁጥር-5015.2) የቢሮ ስልክ፤ 011 554 90 50 5.3) የፖስታ ሳጥን ቁጥር፤ 1114/ኮድ1110

6) አመልካቾች የማይመለስ ማመልከቻና ሲ.ቪ.(C.V.) እንዲሁም ቅጅ(Copy) የትምህርትና የስራ ማስረጃዎቻቸውን እና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በማያያዝ በስራ ሰዓት በአካል ወይም በፖ.ሣ. ቁጥራችን በመላክ ማመልከት ይችላሉ::

ቅንብር፣ በምዕራፍ ብርሃኔ

ሥራ አጥነት፣ በቂ ያልሆነ ትምህርት፣ አናሳ የሥራ እድልና ወጣቱን በተመለከተ በቂ ያልሆነው የመንግሥታት ኢንቨስትመንት ተደማምረው፣ በዓለም ላይ ያሉ ወጣቶች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዲወድቁ ማድረጉን፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ክፍል ባወጣው የወጣቶች ሪፖርት ላይ ከትናንት በስቲያ በዩ ኤን ኒውስ ሰርቪስ ድረ ገጽ ላይ ተነቧል::

የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ጉዳዮች ክፍል፣ ወጣቱን መሠረት አድርጎ በኢንተርኔት ባደረገው ምክክርና ውይይት ሥራ አጥነት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ራስ ምታት እንደሆነ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ተችሏል::

አንድ ወር የፈጀው ይህ ውይይት ዕድሜያቸው ከ15 አስከ 30 የሚደርስ ወጣቶች ተሳትፈውበታል::እነዚህ ወጣቶች ሐሳባቸውን፣ መልእክታቸውን፣ ልምዳቸውንና ቢሆን የሚመርጧቸውን አስተያየቶች በውይይቱ ሰንዝረዋል::ከዚህ በተጨማሪም ወጣቶቹ የሥራ ዕድልን አግኝተው በዚያው ዕድልም ለረዥም ጊዜ ለመቆየት ያስችላል ብለው ያመኑባቸውን ነጥቦችንም አስቀምጠዋል::በዚህም ምክንያት የተባበሩት መንግሥታት ስለወጣቶች ያወጣው ሪፖርት ወጣቶቹ ሲያንሸራሽሯቸው ከነበሩት ሐሳቦች በመነሣት እንደሆነ በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል::

እነዚህ ወጣቶች ካነሷቸው ሐሳቦችና በዋነኝነት ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የትምህርት ሥርዓት አማካይነት ወጣቱ በሚሰማራበት የሥራ ዘርፍ ላይ ጥሩ በሆነ ብቃትና ተገቢ በሆነ ዕውቀት መሳተፍ አለመቻላቸው ይጠቀሳል::

ወጣቶቹ እያገኙት ያሉት የትምህርት ጥራት አጠያያቂ እንደሆነና አሁን የሚወስዱት ትምህርትም ባሁኑ ጊዜ ላሉት የሥራ ዕድሎች አስፈላጊ ስለመሆናቸው ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል::አክለውም ወጣቶቹ ያላቸው ዕውቀትና ልምድ ለረዥም ጊዜ እንዴት እንደሚያገለግላቸውና ውሳኔ አስታላላፊ የሆኑ ግለሰቦች፣ በወጣቶቹ ብቃት ላይ ተመርኩዘው ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎታቸውን እንደሚጠራጠሩ ወጣቶቹ እንደሚሰማቸው በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል::

ወጣቶቹ እንዳሉት ከሆነ እያገኙት ያለው ትምህርት አብዛኛውን ጊዜ ንድፈ ሐሳብ ላይ ያተኮረ ነው::በመሆኑም ወጣቶቹ በራሳቸው ሰዓትና ግፊት የተማሩትን ለመተግበር እየተገደዱ እንደሆነም አክለዋል::

በውይይቱ ከተሳተፉ ወጣቶች መካከል ሴኔጋላዊ የ24 ዓመቱ አማዱ፣ ‹‹በዚህ ጊዜ ያለው ትውልድ ከመቼውም በላይ የተማረ ትውልድ ነው::በመሆኑም ሥራ ማግኘት ከመቼውም ጊዜ በላይ

ሊቀል ይገባ ነበር::ይሁንና እየተሰጠ ያለው ሥልጠናና ገበያ ላይ ያለው ሰው የመቅጠር ኃይል ተመጣጣኝ አይደሉም፤›› ሲል ሐሳቡን ሰንዝሯል::

ከትምህርት ጥራት ባሻገር በርካቶች እንደሚስማሙበት ከሆነ፣ መንግሥታት በየአገሮቻቸው ላሉ ሥራ አጥ ወጣቶች ያለባቸውን ችግር ለመፍታት በቂ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳልሆነም ወጣቶቹ ተናግረዋል::

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሕንዳዊው የ16 ዓመቱ ምሪዱላ ጥያቄውን ‹‹ዕውቀታችንንና ልምዳችንን የምንተገብርበት የሥራ ዕድል ካልተሰጠን የመማራችን ጥቅሙ ምን ላይ ነው?›› ሲል አቅርቧል::

የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ ወጣቶች ከትምህርት ቤት ወጥተው ሥራ ለማግኘት ያደርጉት በነበረው እንቅስቃሴ፣ ከባባድ የሆኑ ሁኔታዎችን ሲጋፈጡ ነበር::ሐቻምና በተከሰተው የዓለም የኢኮኖሚ ቀውስ አማካይነት፣ ዓለም ላይ የተመዘገበው የወጣት ሥራ አጥ ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ያሻቀበ እንደነበርና ቁጥራቸውም 75.8 ሚሊዮን እንደደረሰ ተመዝግቧል::

ሌላው እውነታ ደግሞ የሥራ አጥነቱ ልዩነት ከጎልማሳው ማኅበረሰብ ይልቅ በወጣቱ መካከል ያለው እንደሚጎላም ተጠቁሟል::ይህን በምሳሌ ያስደገፈው ሪፖርት እ.ኤ.አ በ2010 ወጣት ሥራ አጥ 12.6 በመቶ የነበረ ሲሆን፣ የጎልማሳዎች ደግሞ 4.8 በመቶ እንደነበር ተመልክቷል::

‹‹በዓለም ላይ እስከዛሬ ያልነበረና ብዛት ያለው በርካታ ወጣት ባለበት ዘመን ላይ እንገኛለን::ይህ ትውልድ መብቱን የማስከበርና በኢኮኖሚውም ሆነ በፖለቲካው ዘርፍ ከፍተኛ ድምፅና አስተዋጽኦ እንዲኖረው የሚፈልግ ነው::ከዚህ በፊት የተባበሩት መንግሥታት ተንቀሳቅሶና ሠርቶ ከሚያውቀው በላይ ሠርቶ ሰፊ የሆነ የሥራ ዕድልና ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት ልናመጣ ይገባል::ይህ እንዲሆን ደግሞ ከወጣቱ መጀመራችን

የግድ ነው፤›› ሲሉ ወጣቱ እየተጋፈጠ ያለውን ችግር የተጋሩት የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላይ ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ናቸው::

ሪፖርቱ ወጣቶቹ ዕድል ቀንቷቸው እንኳን ሥራ ቢያገኙም፣ በሥራቸው ረግተው የመቀመጥ ሁኔታ እንደማይታይባቸው ጠቅሷል::ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የመጨረሻ ተቀጣሪዎች ወይንም ደግሞ የመጀመሪያ ተባራሪዎች በመሆናቸው እንደሆነ ሪፖርቱ ያስረዳል::

በሌላ በኩልም ወጣት ሴቶች ከዕድሜ አቻዎቻቸው ከሆኑ ወንዶች ጋር ሥራ የማግኘት ዕድላቸው ሲነፃፀር እጅግ አናሳ እንደሆነ፣ ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ አብዛኛዎቹ በትርፍ ጊዜያቸው ስለሚሠሩ ወይም ደግሞ ዝቅተኛ ተከፋዮች በመሆናቸው እንደሆነ ተብራርቷል::

በዚህ ሁሉ እውነታ ግን ወጣቶች ሥራ የማግኘት ተስፈኞች ብቻ ያልነበሩ ሲሆን፣ ነገሮችን በበጎ ተመልክተው ላሉበት ማኅበረሰብ ወሳኝ የሆነ ለውጥና አስፈላጊ የሆነ አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ያምናሉ::በመሆኑም አሁን ባለው የዓለም ኢኮኖሚ ሁኔታ በርካታ ወጣቶች በድርጅቶች ወይም በተቋሞች ውስጥ የመቀጠር ሐሳባቸውን ወደ ጎን በመተው ሥራ ወደመፍጠሩ እያዘነበሉ ይገኛሉ::

ሪፖርቱ እንደሚጠቅሰው ከሆነ ወጣቶች እያደገና ጥሩ ተስፋ ባለው ኢንቫይሮመንት ነክ የሆኑ ዘርፎች ውስጥ የመሰማራቱ ዝንባሌ እያሳዩ ይገኛሉ::‹‹ባሁኑ ጊዜ ያሉት ወጣቶች ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ጉዳዮችን ጠንቅቀው ያውቃሉ::የአየር ንብረት ለውጥንና የማኅበራዊ ጉዳዮችንም ጨምሮ::ስለሆነም ወጣቶቹ ኢንቫይሮመንት ነክ የሆኑ ጉዳዮች ላይ መሰማራታቸው አሸናፊ የሚያደርጋቸው ይመስለኛል፤›› ያለው የ ዎርልድ ኤስፔራናቶ ዩዝ ኦርጋናይዜሽን አባል የሆነው የ23 ዓመቱ ማይክል ነው::

ለአራት ሳምንታት በቆየው በዚህ የኢንርኔት የምክክር መድረክ ላይ 1,100 ተሳታፊዎች ከነፎቶዋቸውና ከነቪዲዮአቸው ስለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ተወያይተዋል::

የዓለም ወጣቶችን ያስጨነቀው ሥራ አጥነት

‹‹መላው ዓለም ውስጥ ካሉት ዙፋናዊ መንግሥታት መሐከል የአንዱ ንጉሠ ነገሥት ግዛት መናገሻ ከተማ የሆነችው አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕጋዊ

ጉዳዮች ከፍተኛ መወያያ መንበር ለመሆን

የበቃችው እንዲያው በዋዛ አይደለም::››

ዠን አፍሪክ መጽሔት እ.ኤ.አ. ጁን 17 ቀን 1973 (ሰኔ 10

ቀን 1965 ዓ.ም.) እትሙ ‹‹አዲስ አበባ የአፍሪካ ዋና ከተማ›› ብሎ

ያንፀባረቀው ጽሑፍ

Page 26: Reporter Issue 1229

ገጽ 26|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

1ኛ/ የሥራ መደብ……………… አስተዳደር /Human Resource Manager/ ተፈላጊ ችሎታ……………… ዲግሪ በአስተዳደር ወይም የሆቴል ማኔጅመንት ምሩቅ የሥራ ልምድ………………… በተመሳሳይ ተቋም ቢያንስ 2 ዓመት የሠራ/የሠራች 2ኛ/ የሥራ ልምድ……………… ሆቴል ሱፐርቫይዘር ተፈላጊ ችሎታ……………… ዲፕሎም በሆቴል ሱፐርቫይዘር ማኔጅመንት የሥራ ልምድ………………… በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም ቢያንስ 2 ዓመት የሠራ/የሠራች3ኛ/ የሥራ ልምድ……………… ምግብና መጠጥ ቁጥር ኃላፊ ተፈላጊ ችሎታ……………… በሆቴል ማኔጅመንት ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ የተመረቀ/ች የሥራ ልምድ………………… በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በኃላፊነት ቢያንስ የ2 ዓመት የሥራ ልምድ ያላት/ያለው4ኛ/ የሥራ ልምድ…………………ምግብና መጠጥ ቁጥጥር ሠራተኛ ተፈላጊ ችሎታ……………… በምግብና መጠጥ ቁጥጥር ሙያ ከታወቀ ተቋም የተመረቀ/ች የሥራ ልምድ………………… በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በምግብና መጠጥ ቁጥጥር ቢያንስ 1 ዓመት የሠራ/ች5ኛ/ የሥራ መደብ……………… የቤት አያያዝ ኃላፊ ተፈላጊ ችሎታ……………… በቤት አያያዝ ሙያ ከታወቀ ተቋም የተመረቀች የሥራ ልምድ………………… በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በኃላፊነት ቢያንስ 4 ዓመት የሠራች6ኛ. የሥራ መደብ……………… የእንግዳ መቀበያ ኃላፊ ተፈላጊ ችሎታ……………………ዲፕሎም በሆቴል ማኔጅመንት ወይም በፍሮንት ኦፊስ ኦፕሬሽን ያለው/ት የሥራ ልምድ………………….. በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በኃላፊነት ቢያንስ 2 ዓመት የሠራ/ች 7ኛ. የሥራ መደብ……………… የእንግዳ መቀበያ ካሸር ተፈላጊ ችሎታ ……………… በእንግዳ አቀባበል ከታወቀ ተቋም የሰለጠነችና በአካውንቲንግ ቢያንስ አድቫንስ ሰርተፍኬት ያላት የሥራ ልምድ…………………….በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በእንግዳ መቀበያ ካሸርነት የ2 ዓመት ልምድ ያላት8ኛ/ የሥራ መደብ……………… የመስተንግዶ ኃላፊ ተፈላጊ ችሎታ……………………..ዲፕሎም በመስተንግዶ ሙያ ያለው/ት ወይም በሱፐርቫይዘር ማኔጅመንት አድቫንስ ሰርተፍኬት የተመረቀ/ች የሥራ ልምድ……………………. በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በመስተንግዶ ኃላፊነት ቢያንስ 3 ዓመት የሠራ/ች9ኛ/ የሥራ መደብ………………… የጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ ተፈላጊ ችሎታ…………………….. ዲፕሎም በአስተዳደር ወይም ከሥራው ጋር በተዛማጅነት ሙያ የተመረቀ/ች

የሥራ ልምድ……………………. በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በጠቅላላ አገልግሎት ወይም በፐርሶኔል ሙያ ቢያንስ 3 ዓመት የሠራ/ች

10ኛ/ የሥራ መደብ………………… ዶርማን /ፖርተር/ ተፈላጊ ችሎታ…………………….. በእንግዳ አቀባበል ሙያ የተመረቀ ወይም 12ኛ ክፍልን አጠናቅቆ ተመሳሳይ ሙያ የወሰደ

የሥራ ልምድ……………………. በፖርተርነት ወይም በዶርማንነት ሙያ በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም ቢያንስ 1 ዓመት የሰራ

11ኛ/ የሥራ መደብ………………… ሼፍ ስቲዋርድ ተፈላጊ ችሎታ……………………..በሆቴል ሙያ /ቤት አያያዝ/ ወይም መስተንግዶ የተመረቀ/ች የሥራ ልምድ……………………. በተመሳሳይ የሆቴል ተቋም በሼፍ ስቲዋርድነት ቢያንስ 3 ዓመት የሰራ/ች12ኛ/ የሥራ መደብ………………… ቱር ጋይድ ተፈላጊ ችሎታ…………………….. ከታወቀ የሙያ ማሰልጠኛ በሙያው የተመረቀ

የሥራ ልምድ…………………….. ዕውቅና ባላቸው ቱር ትራቭል ኤጀንቶች በቱር ጋይድ የሠራ13ኛ/ የሥራ መደብ………………… የቱር ኦፕሬሽን ትኬት ኤጀንት ተፈላጊ ችሎታ……………………..በቱርና ትኬቲንግ ኤጀንት ሥራ ሙያ ከታወቀ ሙያ ማሰልጠኛ የተመረቀ/ች የሥራ ልምድ…………………… በቱር ኦፕሬሽን ትኬቲንግ ሙያ በታወቀ ተቋም ቢያንስ 2 ዓመት የሠራ/ች 14ኛ/ የሥራ መደብ………………… ቺፍ ቴክኒሽያን ተፈላጊ ችሎታ…………………….. በኢንጅነሪንግ ዲግሪ ወይም በኤሌክትሪክሲትና ፕላምበር ዲፕሎም ያለው/ላት የሥራ ልምድ…………………… በተመሳሳይ ተቋም በቺፍ በቱር ቴክኒሽያንነት /ኃላፊነት/ ቢያንስ 4 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው

ማሳሰቢያ፡- ሀ/ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-14 ለተገለጹት ክፍት ሥራ ቦታዎች ደመወዝ በስምምነት ይሆናል::

ለ/ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ7 የሥራ ቀናት

አመልካቾች ቃሊቲ

በሚገኘው ክራውን ሆቴል በግንባር አስተዳደር ቢሮ መስጠት ወይ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 100135 መላክ ይቻላል::

ሐ/ አድራሻ ደብረዘይት መንገድ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት

ስልክ 011 4 39 14 44 ወይም 011 4 39 14 45

ክራውን ሆቴልየፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ባሉት ክፍት የሥራ መደቦች አመልካቾችን አወዳድሮ በፈተና ብልጫ ያመጡትን ለመቅጠር ረቡዕ ህዳር 20/2004 ዓ/ም በሪፖርተር ጋዜጣ ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ከዚህ በታች ላለው የሥራ መደብ ማለትም፡-

1. ለንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኦዲተር፡- ክፍት የሥራ መደብ ብዛት 35

2. ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጁኒየር አይቲ ኤክስፐርት ፡- ክፍት የሥራ መደብ ብዛት 11

ቀርባችሁ ከተመዘገባችሁና የፈተና ጥሪውን በመከታተል ላይ ከምትገኙ አመልካቾች መካከል ለፈተና የተመረጣችሁ ተወዳዳሪዎች የስም ዝርዝራችሁን ከተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በመመልከት ማክሰኞ የካቲት 06 ቀን 2004 ዓ/ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ በፈተናው ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::

ተቋሙ!

ዱግዳ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግ ማህበርክብሪት ፋብሪካ

ከዚህ በታች ላሉት ክፍት የሥራ ቦታዎች አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል::

1. የሥራ መደቡ፡ ሲኒየር አካውንታንትየትምህርት ደረጃ፡ በአካውንቲንግ በቢኤ ዲግሪ ወይም በዲፕሎም የተመረቀየሥራ ልምድ፡ በፋብሪካው ውስጥ የሠራ ሆኖ በቢኤ ዲግሪ ለ6 ዓመት

በሂሳብ ክፍል የሠራ ሆኖ ከዚህ ውስጥ 2 ዓመት በሲኒየርነት የሰራ/ች

በዲፕሎማ ለ8 ዓመት በሂሳብ ክፍል የሠራ ሆኖ ከዚህ ውስጥ ለ3 ዓመት በሲኒየርነት የሰራ/ች

ጾታ፡ አይለይምብዛት፡ 1

2. የሥራ መደቡ፡ ካሸር አካውንታንትየትምህርት ደረጃ፡ ዲፕሎማ በአካውንቲንግ የተመረቀየሥራ ልምድ፡ 2 ዓመት በካሸርነት፣ በካሽ ሪጂስተር፣ እንዲሁም ቢቻል

በጀማሪ ሂሳብ ሰራተኝነት የሰራችጾታ፡ ሴትብዛት፡ 1

3. የሥራ መደቡ፡ ምርትና ቴክኒክ መምሪያ ኃላፊየትምህርት ደረጃ፡ በመካኒካል ወይም በኬሚካል ኢንጂነሪንግ በዲግሪ የተመረቀየሥራ ልምድ፡ በምርትና ቴክኒክ መምሪያ የሥራ ክፍል ውስጥ ለ10 ዓመት

የሰራ ከዚሁ ውስጥ ለ2 ዓመት በመምሪያ ኃላፊነት የሰራጾታ፡ ወንድብዛት፡ 1የሥራ ቦታ፡ ተራ ቁጥር 1 አዲስ አበባ ›› ›› 2 እና 3 ቃሊቲደመወዝ፡ በስምምነት

ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ቀጥሎ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ከቃሊቲ ቶታል ወደ ውስጥ ገብቶ በሚገኘው ጌት አስ ኢንተርናሽናል ትራንስፖርት ግቢ የክብሪት ፋብሪካው አስተዳደር ቢሮ የትምህርት ማስረጃና የሥራ ልምድ ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል::

ስልክ፡ 0114 35 17 40

Page 27: Reporter Issue 1229

|ገጽ 27 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

INVITATION TO BIDThe African Medical and Research Foundation (AMREF) is an international non-for-profit, non-governmental organization that was founded in 1957 in East Africa, seeking to provoke health care improvements of significance important in Africa. Headquartered in Nairobi, Kenya, AMREF has country offices in Ethiopia, Kenya, Tanzania, Uganda and South Africa and field offices in Southern Sudan.

Although AMREF has been formally registered in Ethiopia in 1998, a full-fledged country program was started in 2002. Since then, the country program has grown from one project in Addis Ababa to over 20 projects in four regions (Addis Ababa, Afar, Oromia and Southern Nation, Nationalities and People Region). AMREF in Ethiopia (AMREF ET) is working in health development with the motto of providing better health for the people of Ethiopia.

AMREF Ethiopia would like to invite potential bidders for the following:

• The supply of standard office furniture for our newly constructed health post at South Omo in SNNPR regional state.

S.No. description Specification Unit Quantity

1 Office desk (150X60)Three drawers

Pcs 28

2 Lab bench type

(90X85)Without drawer

Pcs 14

3 Stool Chair ( 32X32) Pcs 28

4 Cupboard (200X120X40) Pcs 14

5 Book Shelf (120X80X40) Pcs 28

6 Store Shelf (200X100x40) Pcs 14

7 Office chair (40X35) Pcs 568 Notice board With two

doors(80X120X20)Pcs 14

Therefore, all bidders shall provide the following:• Registration with Ministry of Finance

• Currently Renewed Business License

• Evidence for settlement of current tax obligation

• Bids must be submitted to AMREF Ethiopia Office on or before February 15, 2012 at 2.30 P.M accompanied by a bid security of Birr. 5,000.00 (Insurance bond is not acceptable).

• Bidders can give their offer by Wax sealed envelope to AMREF Ethiopia Country office.

The bid shall be opened at AMREF’s HR & Administration Office on the 15th February 2012 at 2:30 P.M. in the presence of bidders or their representatives.

AddRESS: AFRICAN MEDICAL AND RESEARCH FOUNDATION,

HEAD OFFICE, ADDIS ABABA, ETHIOPIA.P.O.Box 20855 code 1000

Tell. 0116627851ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Environmentalists Development Association - Ethiopia (EDAE) invites eligible and competent contractors for small scale rehabilitation of Jarre Water Supply System in East Wollega Zone, Gudeyya Bila District. The main components of the work are rehabilitating/maintaining pipeline, reservoir, collection chamber, public water points, spring box and construction of one cattle trough and one water point.

Interested Bidders may obtain bid documents from the office of EDAE in Bole Sub City Kebele 12/13 House No. 316/3, Office No. 402 during office hours upon presentation of valid legal documents.

Bidders should submit their financial and technical proposals separately in a sealed envelope on or before February 15, 2012 until 5 pm local time. Bids received after the closing date will not be considered.

EDAE reserves the right to accept or reject in part or full any or all the offers without assigning any reason whatsoever.

The bid will be opened on February 16, 2012 at 10 am local time in the presence of bidders or their legal representatives. .

Further information can be obtained through the telephone numbers 0911 615171, 0910 462829, 0911411255

Invitation to Bid

የኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪት አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች አሰሪ ማህበር በስሩ ያሉት አባል ኤጀንሲዎች በውጭ ሀገር በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ለስራ ለሚያሰማሯቸው ሠራተኞች ሙሉ የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጡ የኢንሹራንስ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ መግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ ማናቸውም መንግሥታዊም ሆኑ የግል ኢንሹራንስ ተቋማት የሚሰጡትን የሕይወት መድህን ሽፋን እና የአደጋ ጊዜ የኢንሹራንስ አገልግሎት ፓኬጅ የያዘ ፕሮፖዛል በተጨማሪም የመድህን ሰጪውን ኩባንያ ፕሮፋይልና የጠለፋ ዋስትና (Reinsurance arrangement) ያካተተ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 29793 አዲስ አበባ ወይም ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፊት ለፊት ባለው ኪዳኔ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ ላይ ባለው ቢሮአችን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ::

ማኅበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው::

የኢትዮጵያ የውጭ ሥራ ስምሪት አገልግሎት ሰጪ ኤጀንሲዎች ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

Page 28: Reporter Issue 1229

ገጽ 28|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

Page 29: Reporter Issue 1229

|ገጽ 29 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለጎዳ ጠርሙዝና ብርጭቆ አክሲዮን ማህበር ባለ አክሲዮኖች በሙሉ

የጎዳ ጠርሙዝና ብርጭቆ አክሲዮን ማህበር ባለ-አክሲዮኖች ባሳዩት ፈጣን የአክሲዮን ግዥና የክፍያ አፈፃፀም መሰረት የፋብሪካ ግንባታ ማከናወን የምንችልበት ምዕራፍ ላይ ደርሰን የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ በመቻላችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ለመላው ባለ-አክሲዮኖች እንኳን ደስ አላችሁ ይላል፡፡

፡፡

ሚያዝያ 23ቀን 2002ዓ/ም በተደረገው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች መሰረት የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራውን በተሳካ ሁኔታ ስላጠናቀቀና የሚቀጥለው ስራ በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከናወን በመመስረቻ ፅሑፍ፣ በመተዳደርያ ደንብና በአገራችን የንግድ ሕግ መሰረት ከስር በተመለከቱት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት የዳይሬክተሮች ቦርድ አስቸኳይ ጠቅላላ የባለ አክሲዮኖች ስብሰባ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሀ) ጠሪ አካል -------- የዳይሬክተሮች ቦርድለ) ተጠሪ አካል ---------

፡፡ ሁሉም ባለ አክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው

ሐ) አጀንዳዎች፤ ፡፡

1) የስራ ክንውን ሪፖርት ማድመጥ፡፡ 2) የካፒታል ማሳደግና የተሸጡ አክሲዮኖችን ማፅደቅ፡፡ 3) በመመስረቻ ፅሑፍ እና በመተዳደርያ ደንብ ላይ ማሻሻያዎችን ማድረግ፡፡ 4) አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ መምረጥና የሚከፈላቸውንም የስራ ዋጋ መወሰን፡፡

መ) ጠቅላላ የአክሲዮን መጠን ---- 1,175,000 አክሲዮኖች እያንዳንዳቸው 50ብር ዋጋ ያላቸውሠ) የስብሰባ ቀን ---

፡፡ ቅዳሜ መጋቢት 1ቀን 2004ዓ/ም

ረ) ስብሰባው የሚጀመርበት ሰዓት ---

ሰ) የስብሰባ ቦታ ------ ከጥዋቱ 3፡00

ሸ) የዋና መስርያ ቤት አድራሻ -- አዲስ አበባ አክሱም ሆቴል፣ ኃይሌ ገብረስላሴ ጎደና፡፡

ቦሌ መንገድ፣ ሜጋ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 501 ነውሁሉም ባለ አክሲዮኖች በጠቅላላ ጉባኤው እንዲገኙ በአክብሮት እየጠራን በስብሰባው የማትገኙ አባላት ሕጋዊ ወኪሎቻችሁ የስብሰባው ቀን ከመደረጉ ሶስት ቀን በፊት ሕጋዊ ውክልናቸውን በመያዝ በአክሲዮን ማህበራችን ዋና መስርያ ቤት ሪፖርት እንዲያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

፡፡

በተጨማሪ በገባችሁት ቃል መሰረት ክፍያችሁን በጊዜው ከፍላችሁ ያላጠናቀቃችሁ የካቲት 10ቀን 2004ዓ/ም የመጨረሻ ጊዜ ገደብ መሆኑን አውቃችሁ ክፍያችሁን እንድትፈፅሙ በትህትና

እናስታውቃለን

፡፡

ቦሌ መንገድ ሜጋ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 501 +251 115 54 90 50, 1114/code 1110, Fax +251 11554 90 52

Page 30: Reporter Issue 1229

ገጽ 30|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

JOBS and CONSULTANCIES In UNITED NATIONS DEVELOPMET PROGRAMME (UNDP)

No. POSTCONTRACT

TYPE REFERENCE NO.Brief Job/Consultancy description & Web-link

for detailed advert Submission deadline

1 Team Leader – Climate Change and Vulnerabilities

Fixed Term Appointment UNDP/ICS-11/01/2012 Please visit the UNDP Country Office website

visit the UNDP Country Office website http://www.et.undp.org/index.php?option=com_vac&Itemid=107, the UN Country Team website: www.unethiopia.org/job Opportunities.aspx and http:///www.ethijobs.net for details of the vacancy. Click on the position to access the full vacancy announcement and apply.

15 February 2012

2 Executive Associate to the RR/RC

Fixed Term Appointment UNDP/ICS-7/02/2012 18 February 2012

Important information on UNDP employment modalities.1. Individual Contract (IC): A procurement modality for individual consultancies. Application (CV, brief technical proposal and financial proposal will be submitted to our secured email: [email protected] or online application through www.jobs.undp.org; 2. Fixed Term Appointment (FTA): is a modality of hiring individuals under a staff contract for a period of one year or more.3. Temporary Appointment (TA): is a modality of hiring individuals under a staff contract for a period of less than one year.4. Service Contract (SC): is a modality for hiring individuals under a non-staff contract for a period of six months or more.5. Firm consultancy: a procurement modality for inviting firms to conduct consultancy assignments.

For Consultancy services: UNDP Ethiopia Consultancy Service: [email protected]

Tel: off 0113 72-54-09/0113 72-78-22 0113 72-57-62/0113 72-71-74 Fax: 0113 71-33-80 P.O.Box 41781 Addis, Ababa, Ethiopia E-mail: [email protected]

ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ተ.ቁ የሥራ መደብ የትምህርት ደረጃ የሥራ ልምድ

1 መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ

ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና በተመሳሳይ የሥራ መስክ 8/ስምንት/ ዓመት የሠራና ከዚህ ውስጥ 2/ሁለቱን/ ዓመት በኃላፊነት የሠራ

2 ኮንስትራክሽን ኢንጂነር ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና በተመሳሳይ የሥራ መስክ 5/አምስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ በመንገድ ሥራ ፕሮጀክት የሠራ

3 ስትራክቸራል ኢንጅነር ቢኤስሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

4 ማቴሪያል ኢንጂነር ቢ.ኤስ.ሲ በጂኦሎጂ ወይም በኧርዝ ሳይንስ በሙያው ከ4 ዓመት ያላነሰ ያገለገለ/ች

5 የቢሮ ምህንድስና ኃላፊ ቢ.ኤስሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና ወይም በኧርዝ ሳይንስ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 6 /ስድስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሰራ

6 ኦፊስ ኢንጂነር ቢኤስ.ሲ በሲቪል ምህንድስና 4 /አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ በቢሮ ምህንድስና የሰራ

7 የመሳሪያዎችና ተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ኃላፊ

ቢ ኤስ ሲ ዲግሪ በመካኒካል ምህንድስና በተመሳሳይ የሥራ መስክ 6/ስድስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

8 ቺፍ ሰርቬየር በሰርቬይንግ ሙያ በዲፕሎማ የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 6/ስድስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

9 ኳንቲቲ ሰርቬየር ዲፕሎም በምህንድስና ያለው በሙያው ቢያንስ 4/አራት/ ዓመት ያገለገለ /በመንገድ ፕሮጀክት/

10 ረዳት ኳንቲቲ ሰርቬየር በሰርቬይንግ ሙያ በዲፕሎማ የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 1/አንድ/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ11 ሳይት ኢንጂነር ቢ.ኤስ.ሲ ዲግሪ በሲቪል ምህንድስና በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

12 ሱፐር ኢንቴንዳንት በኮንስትራክሽን ከሙያና ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 8/ስምንት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

13 አውቶ ኤሌክትሪሽያን በአውቶ ኤሌክትሪሽያንንት የኮሌጅ ዲፕሎማ ያለው በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

14 የብረት ፎርማን በብረታ ብረት ሥራ ከሙያና ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ15 ስትራክቸር ፎርማን በኮንስትራክሽን ሙያ ከሙያና ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

16 መሳሪያዎች መካኒክ በአውቶ መካኒክ /በጠቅላላ መካኒክነት/የኮሌጅ ዲፕሎማ ያለው/ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 6/ስድስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

17 አውቶ መካኒክ በአውቶ መካኒክነት ከሙያና ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

18 ኤክስካቫተር ኦፕሬተር 8ኛ ክፍል ያጠናቀቀና በኤክስካቫተር ኦፕሬተር የአጭር ጊዜ ሥልጠና ያለው በተመሳሳይ የሥራ መስክ 3/ሶስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

19 የክለርክ ላብራቶሪ ቴክኒሽያን በላብራቶሪ ቴክኒሺያንነት ከታወቀ የጤና ተቋም የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 2/ሁለት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

20 ካምፕ አስተዳደር 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

21 ኢንዱስትሪያል ኤሌክትሪሽያን በኤሌክትሪክ ሲቲ ከሙያና ቴክኒክ ት/ቤት የተመረቀ በሙያው 3/ሶስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሰራ

22 አካውንታንት በአካውንቲንግ በዲፕሎማ የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 4/አራት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

23 ካሸር 12ኛ ክፍል የተጠናቀቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 2/ሁለት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

24 ንብረት ክፍል ሠራተኛ በሰፕላይ ማኔጅመንት በዲፕሎማ የተመረቀ በተመሳሳይ የሥራ መስክ 3/ሶስት/ ዓመትና ከዚያ በላይ የሠራ

ደመወዝ፣ በስምምነትየሥራ ቦታ፣ በየፕሮጀክቱ

ከዚህ በላይ በተመለከቱት የሥራ መደቦች ለመወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5/አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃ እና የሥራ ልምዳችሁን በመያዝ አስተዳደር ክፍል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን::

አድራሻ፡- ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ደቡብ አፍሪካ ጀርባ ሳትኮን ዋናው መ/ቤት ስልክ ቁጥር 011 372-78-22 ወይም 011 372-71-74

Page 31: Reporter Issue 1229

|ገጽ 31 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

በጥበበሥላሴ ጥጋቡ

የኢትዮጵያ ሙዚቃም ይሁን ጥበብ ሲወሳ የ1960ዎቹን ጊዜ ማወደስ የተለመደ ነው:: በተለምዶ “ወርቃማው ዘመን” የሚባለው ጊዜ ብዙ ታሪክ የማይረሳቸውን ሙዚቀኞችን ያወጣ ሲሆን፣ ከብዙ ሙዚቀኞች ጀርባ መድረክ ላይም ብዙ ሙዚቀኞች፣ ትላልቅ ኦርኬስትራዎች፣ የሚታዩበት የማይረሳ እንደነበር የመድረክ ላይ ትዝታቸውን አሁንም ብዙዎች ያስታውሱታል ይኼ ጊዜ አሁንም ቢሆን የሚከበሩና የሚወደዱ ሙዚቀኞችን ማፍራት ችሏል:: ከእነዚህም ውስጥ ታዋቂዎቹ ዓለማየሁ እሸቴና ማሕሙድ አሕመድ ይጠቀሳሉ:: እነዚህ ሙዚቀኞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ሲሆኑ በተለያዩ አውሮፓ አገሮችም የተለያዩ ኮንሰርቶችን በማቅረብ ይታወቃሉ:: ከኢትዮጵያ መድረክ ራቅ ያሉት እነዚህን ሙዚቀኞች ማየት በብዙ ተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ነበር::

ከጥር 24 እስከ ጥር 27 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ የተካሄደው ሦስተኛው የአኬሽያ ጃዝና ዓለም አቀፍ ሙዚቃ ፌስቲቫል ላይ መዝፈን መቻላቸውም ብዙዎችን አስፈንጥዟል:: ለሦስተኛ ጊዜ የተካሄደው ዓመታዊው ፌስቲቫል የተጀመረው ሐሙስ ሲሆን ጃዝ አምባ፣ ፈንዲቃና ትሮፒካል ጋርደን ተካሂዷል:: በመጀመርያው ቀን አዲስ አበባ ውስጥ ጃዝ፣ ፈንክ የተባሉትን የሙዚቃ ዓይነቶች ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር በመቀላቀል ታዋቂ ባንድ ከሆኑት ውስጥ ኑቢያን አርክ፣ አሁን እየታወቀች ያለችው ሳባ ካሕሣይ፣ ሐሴት አኩስቲክ ባንድ ምሽቱን አድምቀውት አልፈዋል:: በዛው ምሽት ፈንዲቃ ውስጥ ሙኒት መስፍን እና ዮርግ እንዲሁም ዘና በል ባንድ ዘፍነዋል::

ዓርብ ምሽትም በተመሳሳይ የ1950ዎቹንና የ60ዎቹን የዱሮ ሙዚቃዎች ለአሁኑ ትውልድ ለማምጣት የሚጣጣሩት አዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት፣ ተከትሎም ጃዝ ሙዚቃ ከኢትዮጵያ ሙዚቃ ጋር ሲቀላቀል ምን ይመስላል የሚለውን ኧርባን ቫይብስ፣ የሚንቆረቆር ድምፅ ያላት ኢቦኒ ጄ ጣይቱ ሆቴል ውስጥ የሚገኙትን የጃዝ አምባን ተመልካቾች ሲያስደምም አምሽቷል:: የዓርብ ማጠናቀቂያ የሆነው ፈንዲቃ የነበረው ኢትዮ ከለር የባህላዊ ባንድ ዘፈን ነበር::

አዲስ አበባ ውስጥ ምንም እንኳን ብዙ የሙዚቃ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም በትልቅ ደረጃ ኮንሰርት ወይም

ፌስቲቫል ብዙ አይታይም:: ዓመታዊ የሆኑ ፌስቲቫሎች ከጣት ቁጥር አይበልጡም::

ከነዚህም በቁጥር ትንሽ ከሆኑት ዓመታዊ ፌስቲቫሎች አንዱ የሆነው አኬሽያ ብዙ ሙዚቀኞችንም አንድ ላይ በማምጣት ተወዳጅ መሆን ችሏል:: ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ሙቀት ቢጨምርም የብዙ ዛፎች መኖር ትሮፒካል ጋርደንን የሙቀት መጠን ቀዝቀዝ ያደረገ ነበር:: በትልቁ ትሮፒካል ጋርደን ውስጥ ተመልካቹ ተሰባጥሮ የተቀመጡ፣ የቆሙ፣ የዝግጅቱ አካል የነበሩትን የተለያዩ ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ዕቃዎች፣ መጠጥና ምግብ የሚሸምቱም ነበሩ::

ከእኩለ ቀን ጀምሮ ኢርስ አፕ፣ ዳንኪራ፣ ውዳሴ ባንድ የተጫወቱ ሲሆን ለዚህ ዝግጅት ብለው ከስፔይን የመጡት ዴድ ካፓ፣ ኤምሲ ሲያምረኝ ለተመልካቹ ልዩ ስሜት ሰጥተውት አልፈዋል::

ከኪዩባ የሙዚቃ ተፅዕኖ ያለበት እሺ ሀቫና፣ ጃዝንና ኢትዮ ጃዝን ቀላቅለው የሚጫወቱት ጃዝ ማሪስ እና ከሉቴንያ የመጣው ዳይኒየስ ፑላ ስካስ ባንድ አመሻሹን ያደመቁት ነበሩ:: የቅዳሜ መዝጊያ የነበረው ዓለማየሁ እሸቴ ወደ መድረኩ ሲመጣ በትሮፒካል ጋርደን የነበረው ተመልካች ጩኸቱን አቀለጠው::

ለየት ባለ የመድረክ ችሎታው የሚታወቀው ዓለማየሁ እሸቴ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉትን፣ እስካሁን ከሕዝብ አእምሮ ሊጠፉ ያልቻሉትን እንደ “ተማር ልጄ”፣ “ያጥቁር ግስላ” ዘፈኖችን ሲያቀርብ የሕዝቡ ጩኸትም ተከተለው::

ብዙዎቹን ዘፈኖቹን ብሔራዊ መዝሙር ይመስል ተመልካቹ አብሮት ይዘፍን ነበር:: በቦታው የነበሩ ተመልካቾች ዓለማየሁ እሸቴን በማየታቸው ደስታቸውን በመዝለል፣ በመጨፈር፣ እስክስታ በማለት ምሽቱን ለየት ያለ አድርገውታል::

ብዙዎቹ ዘፈኖች ዓለማየሁ ራሱ ከመዝፈኑ በፊት ተመልካቹ ራሱ ይዘፍን ነበር:: በተለይም “አዲስ አበባ ቤቴ” የሚለውን ዘፈን ሲዘፍን የሰው ስሜት ለየት ያለ ነበር::

ይኼ ዘፈን የመዝጊያ ዘፈን የነበረ ቢሆንም ተመልካቹ ይደገም በማለቱ ከመድረክ ከሄደ በኋላ ተመልሶ መጥቷል:: የቅዳሜ ማጠናቀቂያም ነበር::

የፌስቲቫሉ የመዝጊያ ቀን በነበረው ኮንሰርት በሙዚቃ ተማሪዎች ዝግጅቱ ተጀምሮ፣ ኬኒ

አለን፣ ታዳሚው አብሮ መድረኩ ላይ እንዲሳተፍ የምታደርገውና የዝግጅቱ መሪ የነበረችው ሙኒት ከ ዮርግ ጋር፣ ከሆላንድ የመጡት ዩሪ ሆኒንግ ኳርቴት የዝግጅቱ አካል ነበሩ::

ከዚህ በተጨማሪ የከሰዓቱን ውሎ ያደመቁት ባሕታ ገብረሕይወትና ግርማ ነጋሽ በአዲስ አኩስቲክ ፕሮጀክት ባንድ ታጅበው ዝግጅታቸውን አቅርበዋል::

በዚህ የሙዚቃ ፌስቲቫል ብዙ ባንዶችና ሙዚቀኞች ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ከውጭ አገር መጥተው የተሳተፉ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ከአሜሪካ የመጣው ታዋቂው አሜሪካዊው ሙዚቀኛ ቴዎድሮስ አንዱ ነው:: ከብዙ ታዋቂ ሙዚቀኞች ጋር በጥምረት የሠራው ቴዎድሮስ ከባንዱ ጋር ሆኖ በሣክስፎኑ ምሽቱን ለየት አድርጐታል:: የመጨረሻውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የምሽቱ ፈርጥ ማሕሙድ አሕመድ መጨረሻ ላይ ሲመጣ ተመልካቹ ወደ መድረኩ በጩኸት መጠጋት ጀመረ:: ሰዎች ካሜራቸውን፣ ቪዲዮ ካሜራቸውን ስልካቸውን በመጠቀም ይኼንን ለየት ያለ ኮንሰርት ለማስቀረት ሲታገሉ ታይተዋል::

በመድረክ ላይ ረዥም ጊዜውን ያሳለፈው ማሕሙድ አሁንም እንደ ዱሮው መዝፈንና መንቀሳቀስ እንደሚችል ያሳየበት ኮንሰርት ነው:: ብዙ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘው ማሕሙድ ምሽቱን ለየት ያለ አድርጐት አልፏል::

በጉራጊኛ “አሽቃሩ” ሲል ሰው በጉራጊኛ፣ በአማርኛ እስክስታውን ሲያወርደው ተመልካቹ ቦታው ጠቦት ነበር:: መድረኩን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ከሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾቹ ጋር በመጣመር ምሽቱን በብዙዎች እንዲታወስ አድርጐታል::

ዘፈኑን ከመዝፈኑ በፊት ተመልካቹ እንዲዘፈንላቸው የሚፈልጉትን ዘፈን ጮክ ብለው በአንድነት በመዝፈን ለዘፋኙ ያላቸውን አድናቆት ቸረውታል:: “ተረሳሽ ወይ” የሚለውን ዘፈኑን አብረው በመዝፈንም “እንዴት ይረሳል” በማለትም እንደ ብሔራዊ መዝሙር አጅበውታል:: ከመድረኩ ላይ ተመልካቹ ሊያስወርደው ያልቻለው ማሕሙድ ከመድረክ ከወረደም በኋላ በሕዝቡ ጩኸት እንደገና መድረክ ላይ ተመልሶ መጥቷል:: “አቤት አቤት” እያለ ሰውም ይጮህ ነበር:: በመጨረሻም ላይ መጥቶ አንድ ዘፈን ከተጫወተ በኋላ ምሽቱ ተጠናቅቋል::

“አኬሽያ” አንጋፋዎቹ ያደመቁት ፌስቲቫል

የሜክሲኳውያን ዐውደ ርዕይ ዛሬ ይከፈታል

የሜክሲኳውያኑ ማርታ ዴልጋዶ ፖንቼና ካሳንድራ ሳባ ሒሌ የሥዕል ዐውደ ርዕይ ዛሬ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ እንደሚከፈት በኢትዮጵያ የሜክሲኮ ኤምባሲ አስታወቀ::

የኤምባሲው የአስተዳደር ረዳት ወ/ት ፌቨን አብርሃ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ዐውደ ርዕዩ ‹‹Signs of History›› (የታሪክ አሻራዎች) የሚል ርእስ ያለውን ዐውደ ርዕይ በጋራ ያዘጋጁት የሜክሲኮ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሜክሲኮ ናሽናል ዩኒቨርሲቲ ናቸው:: ዐውደ ርዕዩ ከነገ የካቲት 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ወ/ት ፌቨን ገልጸዋል::

ፎቶ በ

ማሪዮ

ዲባሪ

ፎቶ በ

ሪፖርተ

ር/መስፍ

ን ሰሎ

ሞን

የኢትዮጵያና ኮርያ የባህል ልውውጥ ምሽት ጥር 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተካሂዷል::

በምሽቱ በኮርያዊው ዳንኤል ሙን የሰለጠኑ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት በአማርኛና በሌሎች ስድስት ቋንቋዎች መልካም ገጽታን የሚያወሱ መዝሙሮች አቅርበዋል:: በተጨማሪም

ለሕፃናቱ የተዘጋጁና ከጣሩ ሁሉንም ነገር ማግኘት እንደሚቻል የሚገልጹ መልዕክት ያላቸው ተረቶችና አጫጭር

ድራማዎችም የዝግጅቱ አካል ነበሩ::

Page 32: Reporter Issue 1229

ገጽ 32|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

የአገር ውስጥ ዜና

የዓለም ዜና

የዛሬ 60 ዓመት አባታቸው ንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛ ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በወጣትነታቸው የእንግሊዝ ንግሥት የሆኑት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት፣ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ለአምስት ወራት የሚዘልቀውን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓላቸውን ማክበር ጀምረዋል::በ25 ዓመታቸው በአባታቸው እግር ተተክተው በምድረ እንግሊዝ የነገሡት የ85 ዓመቷ ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ የእንግሊዝን ሕዝብ ለማገልገል አሁንም ቃል ኪዳናቸውን እንደሚያድሱ በመልዕክታቸው አረጋግጠዋል::እ.ኤ.አ በ1952 የአባታቸው የንጉሥ ጆርጅ ስድስተኛን ሥልጣን ተረክበው ላለፉት 60 ዓመታት በመልካም ጤንነት የዘለቁት ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ የእንግሊዝ ሕዝብ ለእሳቸውና ላለፉት 64 ዓመታት አብረዋቸው ለኖሩት ባለቤታቸው ለልዑል ፊሊፕ የሰጠውን ድጋፍና ማበረታታት አወድሰዋል::ባለቤታቸው በአሁኑ ጊዜ የ90 ዓመት አዛውንት ናቸው::

ምንም እንኳ የንግሥቷ የአልማዝ ኢዮቤልዩ እጅግ በደመቀ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው በመጪው ሰኔ ወር ቢሆንም፣ ከትናንት በስቲያ ንግሥቷ ከወትሮው ብዙም ባልተለየ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን እየጎበኙ ለተወዳጁ አባታቸው ያላቸውን ክብር አሳይተዋል ተብሏል::በሚቀጥሉት አምስት ወራት ንግሥቷ በእንግሊዝ ውስጥ ተወስነው የሚቆዩ ሲሆን፣ የተቀሩት የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት ግን በቀድሞ የእንግሊዝ ግዛቶች ማለትም ከአውስትራሊያ እስከ ካናዳ፣ ከአፍሪካ እስከ ፓስፊክ ውስጥ እስከምትገኘው ትንሿ ቱቫሉ ድረስ ይንቀሳቀሳሉ::በጋራ ብልፅግና አባል አገሮች ውስጥ ለንግሥቷ ክብር በሚደረጉ ሥነ ሥርዓቶች ላይ ይገኛሉ::

እ.ኤ.አ በ1952 ንግሥት ኤልሳቤጥ የ25 ዓመት ወጣት ነበሩ::በአንድ ድንገተኛ ቀን የአባታቸው ሞት መርዶ ሲነገራቸው በወቅቱ የእንግሊዝ ቅኝ በነበረችው ኬንያ በጉብኝት ላይ ነበሩ::ባለቤታቸው ልዑል ፊሊፐ አባታቸው በተኙበት በዚያው ማሸለባቸውን ሲያረዱዋቸው የያኔዋ ወጣት ልዕልት የደረሰባቸው ድንጋጤ እስካሁን ድረስ እንደሚሰማቸው ይናገራሉ::በድንጋጤ ከኬንያ በርረው እንግሊዝ የገቡት ወጣቷ ልዕልት አቀባበል የተደረገላቸው በእንግሊዝ ዝነኛ ጠቅላይ ሚኒስትር ዊንስተን ቸርችልና በካቢኔያቸው ነበር::ለረዥም ዘመናት ሲወርድ ሲወረድ የመጣው የእንግሊዝ የንግሥና ኃላፊነትም ወዲያው በእሳቸው ትከሻ ላይ ወደቀ::ሥርዓተ ንግሣቸው እ.ኤ.አ ሰኔ 2 ቀን 1953 ተካሂዶ በይፋ የእንግሊዝ 40ኛዋ ንግሥት ሆኑ::

የ60ኛ ዓመት የንግሥና የአልማዝ ኢዮቤልዩዋቸውን የሚያከብሩት ንግሥት ኤልሳቤጥ በመልዕክታቸው ለሕዝባቸው እንዲህ ብለው ነበር::‹‹ቤተሰባዊነትና ወዳጅነት እጅግ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፤ ወደመጪው ጊዜ ደግሞ በንፁኅ አስተሳሰብና በጥሩ ልቦና ማየት ያስፈልገናል፤›› ሲሉ ተናግረዋል::እሳቸውና ባለቤታቸው በእንዲህ ዓይነቱ ጥልቅ እሳቤ ውስጥ ሆነው የአልማዝ ኢዮቤልዩውን እንደሚያከብሩም አስታውቀዋል::

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሮን እንዳሉት፣ ንግሥቷ አገራቸውን በልምድ፣ በክብርና በሙሉ ሥልጣን የመሩ ናቸው::‹‹ንግሥቷ የሚያብለጨልጩ ጌጥ ናቸው›› የሚሉ ተቺዎች እሳቸው ሥልጣን እንደሌላቸው በማስመሰል የሚያወሩትን ያጣጣሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ‹‹እንዲህ ዓይነቱ አባባል ሕገ መንግሥታችንን ካለማወቅ ወይም ንግሥቷን አናንቆ ከማየት የመነጨ ነው፤›› ብለዋል::‹‹ሁሌም ትጉህ፣ ሁሌም ወሳኝ፣ ሁሌም የሚከበሩ ንግሥት ሲሆኑ፣ እሳቸው የዕውቀትና የቀጣይነታችን ምንጭ ናቸው፤›› በማለት አወድሰዋቸዋል::ለሕዝቡና ለአገሪቱ ምንጊዜም ደራሽ በማለት ጭምር::

ንግሥት ኤልሳቤጥ በየዓመቱ ከመንግሥት ግምጃ ቤት የተመደበ 36.2 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ በጀት

ሲኖራቸው፣ ከዚህ ውስጥ 359 ሺሕ ፓውንድ ስተርሊንግ ለባለቤታቸው ለልዑል ፊሊፕ በደመወዝ መልክ የሚታሰብ ነው::ንግሥቷ እ.ኤ.አ ከ1952 ጀምሮ የእንግሊዝ ፓርላማን 3,500 ድንጋጌዎች አፅድቀዋል::ንግሥት ኤልሳቤጥ እንግሊዝ ውስጥ ላሉ 600 ያህል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የበላይ ጠባቂ ናቸው::

በ60 ዓመታት የንግሥና ዘመናቸው ዓለምን ከጫፍ እስከ ጫፍ የዞሩት ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ ከእንግሊዝ ነጋሢያን መካከል የሦስት ልጆቻቸውን የጋብቻ ፍቺ ያዩ ብቸኛዋ ንግሥት መሆናቸው ይነገራል::ምንም እንኳን የኔዘርላንድ ንጉሣዊ ቤተሰብ ገቢ ተቀራራቢ ነው ቢባልም፣ የእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰብ ወጪ በአውሮፓ ውስጥ ከፍተኛው ነው ይባላል::የስፔይን ንጉሣዊ ቤተሰብ ከእንግሊዝ ጋር ሲነፃፀር ዓመታዊ ገቢው ትንሽ ሲሆን፣ እሱም ከሰባት ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ያንሳል ነው የሚባለው::በዚህም ንግሥት ኤልሳቤጥ እንግሊዝ ውስጥ ካሉ ባለፀጋዎች መካከል በ257ኛ ደረጃ ላይ ሲገኙ፣ ጠቅላላ ሀብታቸው 300 ሚሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ ይገመታል::

ንግሥት ኤልሳቤጥ በንግሥና በቆዩባቸው 60 ዓመታት ውስጥ የካንተርበሪ ስድስት ሊቃነ ጳጳሳት የተለዋወጡ ሲሆን፣ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በርካታ የዓለም መሪዎችና ነገሥታት ተለውጠዋል::ብዙዎችም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል::ንግሥቲቱ ከሚታወቁባቸው ባህርያት መካከል አንዱ መጠጥ ሲሆን፣ ጂን፣ ዱቦኔት፣ ወይን፣ ማርቲኒና ሻምፓኝ በየቀኑ ከምግብ በፊትና በኋላ ስለሚቀማምሱ በሥልጣን ላይ አሉ ከሚባሉ ሰዎች ዋነኛዋ መጠጥ ደፋሪ ይባላሉ::

የአርሰናል እግር ኳስ ክለብ ደጋፊ መሆናቸው የሚነገርላቸው ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ የእንግሊዝን ንግሥና ለመጀመርያ ጊዜ አሸንፈው ከተቆጣጠሩት ንጉሥ ዊሊያም ጀምሮ 40ኛዋ ንግሥት ናቸው::የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የበላይ ኃላፊ የሆኑት ንግሥት ኤልሳቤጥ፣ እ.ኤ.አ በ2002 ለመጀመርያ ጊዜ በሊንከንሻየር የሚገኘውን መስጊድ መጎብኘታቸው በታሪክ ተመዝግቦላቸዋል::

ንግሥት ኤልሳቤጥ በጣም ተጓዥ መሆናቸውን

የሚረጋግጠው ደግሞ ባለፉት 60 ዓመታት 261 ይፋዊ የባህር ማዶ ጉብኝት በማድረጋቸው ነው::በ116 አገሮች 78 መንግሥታዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይወሳል::እ.ኤ.አ ከ1952 እስከ 2011 መጨረሻ ድረስ 102 የጉብኝት ጥያቄ የቀረበላቸው ሲሆን፣ የመጨረሻው በህዳር ወር 2011 ከቱርክ የቀረበላቸው ነው::

ንግሥት ኤልሳቤጥ የተወለዱት እ.ኤ.አ ሚያዝያ 21 ቀን 1926 ቢሆንም፣ የልደት ቀናቸው በይፋ የሚከበረው ግን በሰኔ ወር ውስጥ ነው::የአገሪቱ 150 ሺሕ ቅቦችና ስዕሎች በአደራ የሚቀመጡት ንግሥቷ ዘንድ ነው::ንግሥቷ ራሳቸው 129 ጊዜ ለሰዓሊያን ቀርበው ምስሎቻቸው በተለያዩ ሰዓሊያን ለዕይታ ቀርበዋል::

ባለፉት 60 የንግሥቷ ዓመታት ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን ሕዝብ በባኪንግሐም ቤተ መንግሥት የአትክልት ሥፍራ የተጋበዘ ሲሆን፣ በየዓመቱ ስምንት ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ንግሥቷን ይጎበኛሉ::ባለፉት 60 ዓመታት ንግሥቷ ከ404 ሺሕ በላይ ሽልማቶችንና ክብሮችን አግኝተዋል::ንግሥቷና ባለቤታቸው በግምት 45 ሺሕ የገና ካርዶችን ለወዳጆቻቸው መላካቸው ይነገራል::ንግሥቷ በንግሥና ዘመናቸው ከሰር ዊንስተን ቸርችል እስከ ዴቪድ ካሜሮን ድረስ 12 ጠቅላይ ሚኒስትሮችን አይተዋል::እ.ኤ.አ በግንቦት 2011 በአየርላንድ ጉብኝት ያደረጉት ንግሥት፣ በእንግሊዝ ነገሥታት ታሪክ የመጀመሪያዋ ተብለዋል::ምክንያቱ ደግሞ አየርላንድ ነፃ ከወጣች በኋላ በማንም እንግሊዛዊ ንጉሥ ወይም ንግሥት ተጎብኝታ ስለማታውቅ ነው::

ከትናንት በስቲያ በስኮትላንድ በኤደንበርግ ካስል 21 ጊዜ ለክብራቸው ዕኩለ ቀን ላይ መድፍ የተተኮሰ ሲሆን፣ በመቀጠል ለንደን ላይ 41 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል::በታወር ኦፍ ለንደን 62 ጊዜ እንዲሁ የመድፍ ተኩስ ተሰምቷል::በርካታ እንግሊዛውያን ንግሥቷ ለአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓላቸው በመድረሳቸው በተለያዩ የእንግሊዝ ሚዲያዎች የደስታ መግለጫቸውን እያጎረፉላቸው ነው::በተለይ ደግሞ ለእንግሊዝ ንጉሣዊ ቤተሰቦች በታክስ መልክ ከሚገብሩት ከካናዳ፣ ከአውስትራሊያና ከኒውዚላንድ እንዲሁ እንኳን አደረሰዎት የሚሉ የመልካም ምኞት መግለጫዎች እየተሰሙ ናቸው::

የንግሥት ኤልሳቤጥ የ60 ዓመታት ንግሥና ክብረ በዓል ተጀመረ

የንግሥቷ የአልማዝ ኢዮቤልዩ እጅግ በደመቀ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው በመጪው ሰኔ ወር ቢሆንም፣ ከትናንት በስቲያ ንግሥቷ ከወትሮው ብዙም ባልተለየ ሁኔታ ትምህርት ቤቶችን እየጎበኙ ለተወዳጁ አባታቸው ያላቸውን ክብር አሳይተዋል

የባራክ ኦባማ ቅድመ አያት ከመኪና አደጋ ተረፉ

የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ቅድመ አያት ሳራ ኦባማ ኬንያ ውስጥ ከደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ መትረፋቸውን የዘገበው ግሎብ ኤንድ ሜይል ነው::የ90 ዓመት አዛውንቷ ሳራ ኦባማ ባለፈው ቅዳሜ ይጓዙበት የነበረው የቤት አውቶሞቢል በድንገት በመገልበጡ መጠነኛ ጭረት ቢያጋጥማቸውም፣ በሆስፒታል የመጀመርያ ዕርዳታ ተደርጎላቸው ወዲያው ወደቤታቸው ሄደዋል::ኬንያ ውስጥ ኪሱሙ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ከከባድ ተሽከርካሪ ሲሸሽ ከተገለበጠው አውቶሞቢል ውስጥ በሰላም የወጡት የባራክ ኦባማ ቅድመ አያት፣ ‹‹እግዚአብሔር አብሮኝ ነበር፤›› ማለታቸው ተሰምቷል::ከደረሰው አደጋ አንፃር ያለምንም ጉዳት መትረፋቸውን የእግዚብሔር ሥራ መሆኑን ጠቁመው፣ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል::የፕሬዚዳንት ኦባማ ቅድመ አያት ሑሴን ኦንያንጎ ኦባማ ሁለተኛ ሚስት የሆኑት ሳራ ኦባማ፣ ከአሜሪካና ከመላው ዓለም ለጎረፈላቸው የእንኳን አተረፈዎት የመልካም ምኞት መግለጫ ከምሥጋና ጋር ምላሻቸውን መስጠታቸው በዘገባው ተመልክቷል::ምንም እንኳን በአስተርጓሚ ቢነጋገሩም ባራክ ኦባማና ቅድመ አያታቸው ከፍተኛ መቀራረብ እንዳላቸው ይነገራል::

* * * *

የሶሪያ መንግሥት የተቃውሞ ከተሞችን በከባድ መሣርያ ደበደበየሶሪያ መንግሥት የሕዝባዊ አመፁ መነሻ የሆነችውን

ሖምስንና ሌሎች ከተሞችን በከባድ መሣርያ ሲደበድብ መሰንበቱን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል::የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ የሶሪያ መንግሥት የሕዝቡን ሰላም የማረጋገጥ ኃላፊነት ማለታቸውም ተነግሯል::ሰሞኑን በተለይ በሖምስ ከተማ ላይ በከባድ መሣርያ በታገዘው ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል::የሶሪያ መንግሥት ግን የተገደሉት ንፁኃን ዜጎች ሳይሆኑ አሸባሪዎች ናቸው እያለ ነው::ሩሲያና ቻይና በሶሪያ ላይ ሊተላለፍ የነበረውን ውሳኔ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸው ውድቅ በማድረጋቸው ተቃውሞ እየተሰማባቸው ነው::በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የአሜሪካ አምባሳደር ሱዛን ራይስ ሁለቱ አገሮች ከአምባገነን ጋር ወግነዋል ሲሉ ወርፈዋቸዋል::የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ መንግሥት ባለፉት 10 ወራት ውስጥ ከሰባት ሺሕ በላይ ዜጎችን ገድሏል እየተባለ ነው::በትናንትናው ዕለት በሖምስ ከተማ ከ30 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የመንግሥት ተቃዋሚዎች ገልጸዋል::

* * * *

ኢራን የአሜሪካን አዲሱን ማዕቀብ የሥነ ልቦና ጦርነት ስትል አጣጣለችው

አሜሪካ በኢራን መንግሥት ንብረቶችና የፋይናንስ ተቋማት ላይ የጣለችውን አዲሱን ማዕቀብ የሥነ ልቦና ጦርነት ነው ስትል ኢራን ማጣጣሏን የብሉምበርግ ዘገባ አመልክቷል::አሜሪካ ጠንካራ ያለችውንና በራሷ ይዞታ ሥር ተግባራዊ የሚደረገውን አዲሱን ማዕቀብ ይፋ ካደረገች በኋላ፣ ኢራን ትርጉም ላለው ውይይትና ድርድር በሯ ክፍት መሆኑን አስረድታ፣ ከዚያ ውጭ ያለውን ግን እርባና ቢስ ብላዋለች::በኑክሌር መርሐ ግብሯ ላይ ከማንም ጋር

ለመደራደር ፈቃደኛ መሆኗን አስታውቃ፣ ከዚህ ውጭ በኢራን ላይ የሚደረጉ ማዕቀቦች ምንም አይፈይዱም ማለቷ በዘገባው ውስጥ ተካቷል::ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከትናንት በስቲያ ባስተላለፉት ትዕዛዝ የኢራን መንግሥት ንብረቶች፣ የኢራን ብሔራዊ ባንክና የፋይናንስ ተቋማት ማዕቀብ ተጥሎባቸዋል::ከዚህ ቀደም አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት በኢራን ነዳጅ ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ይታወሳል::ኢራን ለኑክሌር ግንባታ የሚሆነውን ዩራኒየም እያበለፀገች ሲሆን፣ አሜሪካና ተባባሪዎቿ ደግሞ ኢራን ከዚህ ድርጊቷ እንድትታቀብ እያስጠነቀቁ ናቸው::

* * * *

የኖርዌይ የጭፍጨፋ ተዋናይ በነፃ መለቀቅ አለብኝ አለ

ባለፈው ሐምሌ 2003 ዓ.ም. 77 ኖርዌጂያንን በአውቶማቲክ ጠመንጃ የጨፈጨፈው አንድረስ ቤሪንግ ብሬቪክ ከትናንት በስቲያ ፍርድ ቤት ሲቀርብ በነፃ መለቀቅ አለብኝ አለ::እንደ ቫንኩቨር ሰን ዘገባ፣ ያንን መሰል ዘግናኝ ጭፍጨፋ ያከናወነው ብሬቪክ ድርጊቱን በአገሪቱ ጠላቶች ላይ የተፈጸመ ነው ብሏል::ጠላቶች ያላቸው ስደተኞችን በመቀበል ላይ ተቃውሞ የሌላቸውን ነው::‹‹መታሰር የለብኝም፤ የምጠይቀውም በአስቸኳይ መፈታትን ነው፤›› ያለው የጭፍጨፋው ተዋናይ፣ ኖርዌይ የመጤ አናሳዎች መኖሪያ መሆን የለባትም በማለት የቀኝ ክንፍ ጽንፈኝነት መገለጫ የሆነውን ሰላምታ አሰጣጥ አሳይቷል::በቅርቡ በተደረገለት ምርመራ ግለሰቡ ወንጀል ከመፈጸም የማይመለስ ወፈፌ መሆኑ መረጋገጡን ዘገባው አስረድቷል::

* * * *

አርባ ሚሊዮን ሕዝብ ለመመገብ የሚያስችል እህል ሊከማች ነውበቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ 40 ሚሊዮን

ሕዝብ የሚመግብ የመጠባበቂያ እህል ለማከማቸት የሚያስችሉ ዕርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት አስተዳደር ማስታወቁን ኢዜአ ዘገበ:: በአሁኑ ወቅት በሰባት መጋዘኖች ውስጥ 410 ሺሕ ሜትሪክ ቶን የመጠባበቂያ የምግብ እህል ክምችት እንዳለው፣ ክምችቱም ሦስት ሚሊዮን ሕዝብ ለስድስት ወራት መመገብ የሚያስችል ነው ተብሏል:: አሁን ያለውን የምግብ እህል ክምችት አቅም ለማሳደግ አሥራ አንድ ተጨማሪ አዳዲስ መጋዘኖች ለማስገንባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስተዳደሩ ያስረዳል:: መጋዘኖቹ 2.6 ሚሊዮን ቶን እህል የመያዝና የማከማቸት አቅም እንዲኖራቸው አሁን ያለውንም የምግብ እህል ክምችት ወደ ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ያሳድገዋል:: ይህም 40 ሚሊዮን ሕዝብ ለስድስት ወራት ያለምንም እንከን መቀለብ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ተጠቁሟል:: የመጀመሪያዎቹ ሁለት መጋዘኖችም 400 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ምግብ የመያዝ አቅም እንዳላቸውና ግንባታቸውም ለማከናወን ዲዛይናቸው ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን መላኩን ዘገባው ተመልክቷል::

* * * * * * * * * * *

በደቡብ ክልል 110 ሺሕ ሔክታር መሬት ለቡና ልማት ሊውል መሆኑ

ተነገረበደቡብ ክልል 110 ሺሕ ሔክታር መሬት በቡና

እንደሚለማ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ:: እንደ ኢዜአ ዘገባ፣ አሁኑ ወቅት በክልሉ 300 ሺሕ ሔክታር መሬት በቡና የተሸፈነ መሆኑን፣ ሰፊ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች በነፍስ ወከፍ ከአንድ ሺሕ የቡና ችግኝ፣ መካከለኛ መሬት ያላቸው ከ750 እስከ አንድ ሺሕ ችግኝ፣ እንዲሁም አነስተኛ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች ከ250 እስከ 500 የቡና ችግኝ እንዲተክሉ በማድረግ፣ በዓመቱ መጨረሻ በተያዘው እቅድ ለማሳካት እየተሠራ መሆኑን የክልል ግብርና ቢሮ ገልጿል:: በክልሉ በሚገኝ 14 ዞኖች በአራት ልዩ ልዩ ወረዳዎች የሚለሙ መሆኑንና በተያዘው ዓመት በቡና ለሚሸፈነው 110 ሺሕ ሔክታር አዲስ መሬት ከ273 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን፣ በቡና የተሸፈነውን መሬት 20 በመቶ እንደሚያሳድገውም ዘገባው ያስረዳል::

* * * * * * * * * * *

የመጀመሪያው የመርከብ መሐንዲሶች ማሠልጠኛ ተከፈተ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው በመርከብ ላይ

የሚሠሩ መሐንዲሶች ተቋም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቆ መከፈቱን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል:: በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተቋቋመው በመርከብ ላይ የሚሠሩ መሐንዲሶች ማሠልጠኛ ተቋም አግባብነት ጥራትን ከማረጋገጥ አኳያ በምሳሌነት መጥቀስ እንደሚቻልና የማሪታይም አካዳሚው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ባለሞያዎችን በማፍራት ረገድ የማይተካ ሚና እንደሚኖረው የትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ተገልጿል:: እንዲሁም በመርከብ ኢንዱስትሪው ዘርፍ የአገሪቱን ዜጎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ በመሆኑ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሮግራሙን ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት አስፈላጊ የሆኑ የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ዘገባው ጨምሮ ያስረዳል:: በአሁኑ ወቅትም አካዳሚው የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ባለሙያዎችን ተቀብሎ በማሠልጠን ላይ እንደሚገኝ ዘገባው አመልክቷል::

* * * * * * * * * * *

በ120 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባው የንፁህ ውኃ ፕሮጀክት

በመጠናቀቅ ላይ ነው በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅ ወለጋ ዞን ግንባታው

ከ120 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመካሄድ ላይ ያለው የነቀምቴ ከተማ የንፁህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት፣ ከ97 በመቶ በላይ መጠናቀቁን የዞኑ የውኃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽሕፈት ቤት ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል:: በ1998 ዓ.ም የተጀመረው ይኼው ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት አብዛኛው ሥራ መጠናቀቁም ተነግሯል:: ፕሮጀክቱ በአሁኑ ጊዜ የውኃ መስመር ዝርጋታ ከ100 እስከ ሁለት ሺሕ ሜትር ኪዩብ ውኃ የመያዝ አቅም ያላቸው የአራት የውኃ ታንከሮች ግንባታ አጠናቋል:: የጄኔሬተርና የሌሎች አገልግሎት መስጫዎች ግንባታም የተጠናቀቀ በመሆኑ፣ ለነዋሪዎቹ በከፊል ንፁህ የመጠጥ ውኃ ማቅረብ መቻሉ ተገልጿል:: በተጨማሪም በመጪው ግንቦት ወር 2004 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር፣ ከ100 ሺሕ በላይ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ዘገባው ያስረዳል::

* * * * * * * * * * *

Page 33: Reporter Issue 1229

|ገጽ 33 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

Call for consultancy Service African Development Aid Association (ADAA) is an Ethiopian Resident Charitable Organization established in 1988. Since then, the organization has been partaking in various development endeavors in different parts of the country. Currently, ADAA is looking to recruit a competent and qualified consultancy firm that can undertake the following tasks:

1) Organizational strategic plan development2) Organizational restructuring and benefit package

manual development

Therefore interested , qualified and legally registered consultancy firms are invited to collect Terms of Reference (ToR) from the organization and submit their technical & financial proposals within five days from the date of this announcement

Address: African Development Aid Association (ADAA)

Bole sub-city, CMC road, Gurd-shola area, G&B Building 2nd floor

PoBox: 100061

Tele: 0116-466896/95

African Development Aid Association (ADAA)

Amendment on the advertisement published on Sunday Tir 20, 2004 or January 29, 2012 on Invitation to Bid For

Developing Strategic Document by the Young Women Christian Association in Ethiopia

We would like to first request an apology for the erroneousness made on the date of submission of the advertisement made on Invitation to Bid For Developing Strategic Document published on Sunday Tir 20, 2004 or January 29, 2012.

We would like now to inform all applicants that we have changed the date of submission extending for 10 consecutive days from Wednesday, February 8, 2012.

VACANCY ANNOUNCEMENTNew Millennium University College

1.Position: Managing Director

2.Qualification: MA/MSc or PhD 2.1 Educational Planning and Management or 2.2 Business Administration or 2.3 Economics and Relevant fields

3.Experiences: At least 6 years for MA/Msc and 4 years for PhD in Relevant positions

4.Types of Employment: Permanent

5.Duty Station: Mekelle

6.Salary: Negotiable

7.Application deadline: 10 days after the announcement of this notice.

Applicants can submit their non returnable CV and relevant documents to the personnel in Mekelle Campus Room No. 1.

New Millennium University College

ቢልም፣ የሊዝ አዋጁ መሬት የመንግሥት ብቻ እንደሆነ የሚያሳይ ሆኗል:: የሕዝብ የመሬት ባለቤትነት በወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ጉዳይ ሆኗል ይላል የኢንጂነር ዘለቀ ጽሑፍ::

“ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት ሕዝብ ሊወያይበት ይገባ የነበረ ቢሆንም፣ መንግሥት ሕዝብ ለመረጣቸው የፓርላማ አባላት እንኳ ጊዜ ሳይሰጥ ነው በአፋጣኝ ያፀደቀው:: ይህ ደግሞ ሕገ መንግሥቱ ሕዝቦች የሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ናቸው:: በመረጧቸው ወኪሎች ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ በማድረግ መብታቸው ይገለጻሉ የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ይፃረራል፤” ሲሉ ኢንጂነር ዘለቀ በጽሑፋቸው አስረድተዋል::

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊም በ2002 ዓ.ም. ከተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ በኋላ ባደረጉት ንግግር ተቃዋሚች ባይመረጡም በወሳኝ አገራዊ ጉዳዮች ዙርያ እናወያያቸዋለን ሲሉ ቃል መግባታቸውን ኢንጂነር ዘለቀ አስታውሰው፣ ከዚህ የሊዝ አዋጅ የበለጠ አገራዊ ጉዳይ ምንድን ነው? ሲሉ ምክር ቤቱ፣ ሕዝቡና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሊዝ አዋጁን በተመለከተ ለውይይት ያልተጋበዙበትን ምክንያት ይጠይቃሉ::

አንድነት ፓርቲ ሥልጣን ቢይዝ ግን ዜጎች መሬት መሸጥና መለወጥ እንደሚችሉ ኢንጂነር ዘለቀ አስታውቀዋል::

አቶ ግርማ በበኩላቸው፣ መሬት የመሸጥና የመለወጥ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ፓርቲያቸው አንድነት መሬት ሳይሸጥና ሳይለውጥ ልማት ማምጣትም ይችላል ሲሉ የአንድነትን አቋም አስረድተዋል::

አቶ ግርማ ባቀረቡት ጽሑፍ አዋጁ ሕገ መንግሥቱን ከመፃረሩም ባሻገር ለልማት እንቅፋት፣ የዜጎችንም መብት የሚያፍን ሲሉ አብጠልጥለውታል::

በአገሪቱ የሚገኙ ከተሞች በአዋጅ ወደ ሊዝ ሥሪት እንደሚገቡ ተደንግጓል:: ከተማ ማለትም ከሁለት ሺሕ በላይ ነዋሪዎች የሚኖሩበትና ከነዋሪዎችም ከ50 በመቶው በላይ የሚሆነው ከግብርና ሥራ ውጭ የሚተዳደር ነው ይባላል::

አቶ ግርማ እንዳሉት፣ በሊዝ ሥሪት የሚጠቀሙ አገሮች ሊዝን የሚጠቀሙት በቦታ ጥበትና ከኢኮኖሚ ዕድገት አንፃር አንዱ ከተማ ከአንዱ ከተማ የሚወዳደርበት ሁኔታ በመኖሩ ነው::

አንደኛው ከተማ መጨናነቅ ሲታይበት መሬት የሚያቀርበው በሊዝ ሊሆን ይችላል:: ሌላኛው ከተማ ደግሞ አልሚዎችን ለመሳብ መሬት በነፃ ሊያቀርብ ይችላል ብለዋል::

ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ግን ትናንሽ ከተሞችን በሊዝ ሥሪት ማስገባት ኢንቨስተሮች እንዲሸሹ የሚያደርግ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ከተሞቹ እንዳያድጉ የሚያደርግ ነው ብለውታል አቶ ግርማ በጽሑፋቸው::

በሌላ በኩልም በሊዝ አዋጁ አንድ ባለይዞታ

500 ካሬ ሜትር ነባር ይዞታ ኖሮት፣ ከጎኑ ተጨማሪ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ተረክቦ ልማት ማካሄድ ቢፈልግ፣ ነባሩን ጨምሮ አንድ ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታው ሊዝ ይሆናል ተብሎ መደንገጉ አግባብ አይደለም ሲሉም ይከራከራሉ::

“ለምሳሌ እኔ አልሚ ብሆን ላልተወሰነ ጊዜ የያዝኩትን ነባር ይዞታ ስለምን ለተወሰነ ጊዜ (ሊዝ) ከምጠቀምበት ቦታ ጋር እቀላቅላለሁ?” ሲሉ የሚጠይቁት አቶ ግርማ፣ አዋጁ ልማት እንዳይካሄድ እንቅፋት ነው ሲሉ ለጥያቄያቸው ምላሽ ሰጥተዋል:: ነባር ይዞታም ሲሸጥ ሊዝ ይሆናል መባሉ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ ሁሉም ነባር ይዞታ በሊዝ ሥሪት ይገባል ተብሎ መደንገጉ አግባብ አይደለም በማለት አቶ ግርማ ይቃወማሉ::

የሊዝ መብት ለሦስተኛ ወገን ከተላለፈም መንግሥት አለሁበት ማለቱ አግባብ አለመሆኑን ገልጸው፣ መንግሥት ማድረግ ያለበት ከተሸጠው ገንዘብ ታክስ መቁረጥ ብቻ መሆን አለበት ይላሉ::

አዋጁ ባለንብረቶች ንብረታቸውን አስይዘው ብድር እንዲያገኙ የማያመች ከመሆኑም በላይ፣ ባንኮች ንብረት ይዘው እንዲያበድሩ የማይገፋፋ ነው ሲሉ በአዋጁ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አቅርበዋል::

አዋጁ የመሬት ሥሪትን እንደሁኔታው ለያይቶ የማይመለከት ብሎም ሕዝብን የመንግሥት ጭሰኛ የሚያደርግ በመሆኑ፣ አዋጁ መሻር እንዳለበት አቶ ግርማ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል::

ሰብሰባውን የመሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራር ዶ/ር ኃይሉ ዓርአያ መሬት በመንግሥት ይዞታ ሥር መሆኑ ተፈጥሯዊ አይደለም ብለዋል::

እንደ ዶ/ር ኃይሉ ገለጻ፣ በዓለም ላይ ከሚገኙ 194 አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት አገሮች ብቻ ናቸው መሬት በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያዋሉት እነዚህም አገሮች ሰሜን ኮሪያ፣ ቬትናም፣ ቻይናና ኩባ ሲሆኑ እነዚህም አገሮች በችግር የተሞሉና ጥሩ ምሳሌዎች እንዳልሆኑ አብራርተዋል::

ቻይና 186 ሚሊዮን ሕዝቦች ከድህነት ወለል በታች የሚገኙባትና በቅርቡ የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃን ለመመረቅ ወደ አዲስ አበባ የተገኙት የቻይናው ፕሬዚዳንት ወኪል፣ ቻይና በማደግ ላይ ያለች አገር መሆኗን መግለጻቸውን ዶ/ር ኃይሉ ዋቢ አድርገዋል:: “የቻይና ኢኮኖሚ ሆርሞን እንደሚሰጠው እንስሳ የሚደልብ እንጂ ተፈጥሯዊ ባለመሆኑ ጤነኛ አይመስለኝም፤” ሲሉ ተችተዋል::

በስብስባው ወት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በወቅቱ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ለመድረሱ ቀርበዋል:: ዶ/ር ኃይሉ ለተሰብሳቢዎች በዚህ የሊዝ አዋጅ ላይ ወደፊት ተከታታይ ስብሰባዎች እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል::

አንድነት ፓርቲ...

Page 34: Reporter Issue 1229

ገጽ 34|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

ATIONS UNISHAUT COMMISSARIATPOUR LES REFUGIES

UNITED NATIONSHIGH COMMISSIONER

FOR REFUGEES

OFFICE OF THE UNITED NATIONS HIGH COMMISSIONER FOR REFUGEES

UNHCR Representation Office in EthiopiaINTERNAL/EXTERNAL VACANCY NOTICE No.

ETHAS/012/2012

Title of Post : Shelter Construction CoordinatorLocation : Assosa, Sherkole and Tongo( Three post)Duration : Initially for six monthsDate of Entry on Duty : As soon as possibleCategory and Level : Individual Contractor Agreement (ICA):3(Under UNOPS) Closing Date : 15 February 2012

Summary of Job description

Under the direct supervision of the Shelter Construction/Physical Planning office in Assosa of UNHCR, the incumbent performs the following functions:

1. Plan, organize and coordinate skills training programme to refugees to enable them build their own shelters.

2. Ensure that refugees receive construction materials on time at the camps by working closely with logistics and supply officers on material supply and delivery arrangements.

3. Ensure that masons and carpenters are readily available to train as well as assist refugees to build their own shelters.

4. Manage construction activities in the camps so that the schedule is respected, cost remains within budgetary limits and the quality of the work meets standards.

5. Report regularly to the co-ordinator in Assossa on all construction related matters, as well as resolve problems encountered in the field.

6. Ensure that technical norms and standards are respected during the construction phase; and the shelter guidelines are fully implemented.

7. Ensure that the construction of social infrastructures in the camps progresses as planned to meet beneficiaries’ expectations.

8. Co-ordinate the inputs of sub-contractors, implementing partners and beneficiary groups in the camps to enhance and facilitate the construction activities in the camps in a cost-effective and efficient manner.

9. Meet refugee leaders and community representatives to resolve outstanding matters and cross cutting issues.

10. Identify and recruit skilled carpenters and masons from within the refugee community to assist in project implementation.

11. Assist the office in allocating land plots to refugees to build shelters.12. Ensure that the needs of the vulnerable groups are addressed and given a high

priority in the construction phase of the shelters.13. Manage the masons and carpenters hired in the camps to train and assist the

refugees in building shelters.14. Assist in other construction activities in the camps as deemed necessary by the

field office.15. Perform other duties as required.

Required Competencies

•A Working knowledge of Arabic is an asset.•Applied skill on project management.•Problem solving capacity.•Working capability under stressed environment

Qualification and Experience:

• A diploma or degree in construction management/ project management/ civil engineering from a recognized university or college.

• At least three years of experience as a construction manager or as a construction site supervisor or as site engineer.

Address for Applications

Applications should carry the number of this vacancy notice and should be sent to:

Human Resources Unit

UNHCR Representation Office in Ethiopia

P.O.Box 1076

Addis Ababa

All applicants should submit their applications together with a complete Personal

History (P-11) form which is available at the gate of UNHCR offices or retrieve

from UNHCR website http://www.unhcr.org/recruit/p11new.doc

ATIONS UNISHAUT COMMISSARIATPOUR LES REFUGIES

UNITED NATIONSHIGH COMMISSIONER

FOR REFUGEES

OFFICE OF THE UNITED NATIONS HIGH COMMISSIONER FOR REFUGEES

UNHCR Representation Office in EthiopiaINTERNAL/EXTERNAL VACANCY NOTICE No. ETHAD/011/2012

Title of Post :Health Information System Associate (HIS Associate)Location :Addis AbabaType of Appointment :Temporary Appointment(TA)Duration :Initially for six monthsDate of Entry on Duty :As soon as possibleCategory and Level :GL-6Closing Date : 15 February 2012

Summary of Job description

Under the direct supervision of the Health and nutrition coordinator of UNHCR representation office in Addis Ababa, the incumbent performs the following functions:

1. Act as a focal point for implementation of quality HIS in all the refugee camps in Ethiopia.

2. Ensure that HIS is timely received from all the camps and follow up with those that delay weekly/monthly submissions.

3. Enter the health and nutrition information in the data base and generate summary reports.

4. Screen the data for errors and missing information and share the findings with the relevant agencies for correction and improvement of data collection.

5. Compile, analyze and generate draft reports for interpretation by the public health officer.

6. Prepare monthly, quarterly and annual reports and ensure that appropriate feedback is given to agencies and other stakeholders.

7. Send the HIS reports to UNHCR Branch Office as well as the RSH and Headquarters.

8. Ensure that HIS materials are properly distributed to the camps9. Provide on job training and technical support on HIS to health and

nutrition staff. 10. Provide formal training and capacity building as necessary for

implementing partners using standardized training materials.11. Assist in the development of data collection tools for the Public Health

and HIV unit.12. Compile quarter and annual health sector reports.13. Undertakes other duties as required

Required Competencies•Good organizational and interpersonal skills.•Good knowledge of Microsoft Office applications and Statistical software

CSPro Epi-info, SPSS is an asset.•Good written and spoken English •Strong report writing and data analytical skills and ability & willingness to

work under stressful conditions and remote areas

Qualification and Experience:

•University degree in Medicine or Public Health or Nutrition or related technical fields.

•At least 3 years experience in public health, preferably with management of Health Information System (HIS) and Monitoring and Evaluation

.Address for Applications

Applications should carry the number of this vacancy notice and should be sent to:

Human Resources Unit

UNHCR Representation Office in Ethiopia

P.O.Box 1076

Addis Ababa

All applicants should submit their applications together with a complete Personal History (P-11) form which is available at the gate of UNHCR offices or retrieve from UNHCR website http://www.unhcr.org/recruit/p11new.doc

Page 35: Reporter Issue 1229

|ገጽ 35 | ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

www.ethiopianreporter.com

ስ ፖ ር ት ስ ፖ ር ት

ኦ ሊ ም ፒ ክ

ቀን ቀ ረ ው

ለን ደ

ንየጄኔራል ኃየሎም መታሰቢያ ሩጫ በመቐለ እሑድ ይካሔዳል

ዓመታዊው የሜጀር ጄኔራል ኃየሎም አርአያ መታሰቢያ የጎዳና ሩጫ የካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም. በመቐለ ከተማ ይካሔዳል፡፡

ብሔራዊ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የፊታችን እሑድ በመቐለ የሚካሔደው 13ኛው የሜ/ጄ ኃየሎም መታሰቢያ 15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ነው፡፡

በደረጀ ጠገናው

የሐቻምናው የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ አሸናፊው ደደቢት እግር ኳስ ክለብ ከአሠልጣኙ ገብረመድኅን ኃይሌ ጋር መለያየቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ::

ከአገር ውስጥ አሠልጣኞች ከፍተኛውን ክፍያ 20 ሺሕ ብርና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ለገብረመድኅን በመክፈል ሪከርዱን የያዘው ደደቢት፣ ከአሠልጣኙ ጋር የመለያየቱ ሰበብ ቡድኑ ምርጥ ተጫዋቾችን እንደማሰባሰቡ ውጤታማ ባለመሆኑ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ::

ደደቢት በዘንድሮው የፕሪምየር ሊግ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው በ17 ነጥብና ስድስት ግብ ክፍያ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ፣ ከመሪው መብራት ኃይል ያለው ልዩነት ስምንት ነጥብ ነው::

ደደቢትና ገብረመድኅን ኃይሌ ተለያዩ

ገብረመድኅን ኃይሌ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ከአልጀርያ እስከ ደቡብ አፍሪካ የሁሉንም አፍሪካውያን ትኩረት ያገኘው የዘንድሮው 28ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ ዛሬ ይካሔዳል::

አ ስ ተ ና ጋ ጆ ቹ ን ኢኳቶሪያል ጊኒና ጋቦንን ሩብ ፍጻሜው ላይ ያቆመው የአፍሪካ ዋንጫ ግጥሚያ ለፍጻሜው ለማለፍ አይቮሪኮስት ከማሊ፣ ጋና ከ ዛ ም ቢ ያ ይፋለማሉ::

ቡ ድ ኖ ቹ ለግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ የ በ ቁ ት አይቮሪኮስት ኢኳቶሪያል ጊኒን 3ለ0 በመርታት፣ ዛምቢያም በተመሳሳይ ውጤት ሱዳንን ከውድድሩ በመሸኘት ነው::

ለአይቮሪኮስት ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው የቼልሲው ኮከብ ዲዲየር ድሮግባ ነው:: ድሮግባ ፍጹም ቅጣት ሳተ እንጂ ሦስታ (ሐትሪክ) የሚሠራበት ዕድል አጋጥሞት ነበር::

የዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጫዋቹ

ድ ሮ ግ ባ አ ገ ሩ ባ ገ ኘ ች ው ው ጤ ት የተሰማውን ደስታ የ ገ ለ ጸ ው ጓደኞቹን በማመስገን ነው:: ዶቸቬሌ በድረገጹ እንደጻፈው፣ ‹‹ፍጹም ቅጣት ምቱን ከሳትኩ በኋላ ጓደኞቼ ስላበረታቱኝ በጣም ነው የማመሰግነው:: ዛሬ ማሸነፋችን በጣም ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ:: አንድ፣ ሁለት ወይም ሦስት ግብ ማስገባት ያን ያህል ትልቅ ነገር አይደለም:: ትልቁ ነገር ግን ከአስተናጋጇ አገር ጋር ተጫውቶ ማሸነፉ ነው:: እነርሱ ቀዳሚ ግጥሚያዎቻቸውን ስላሸነፉ ሜዳ የገቡት በሙሉ ልብ ነበር:: እናም በጥቅሉ በኔ ግቦች ብቻ ሳይሆን በማለፋችን ደስ ብሎኛል::››

በእሑድ የሩብ ፍጻሜ ግጥሚያ በተደጋጋሚ የአፍሪካ ዋንጫን ያነሣችውና ከ30 ዓመታት ወዲህ ዳግም ዋንጫውን ለመሳም የቋመጠችው ጋና ቱኒዝያን 2ለ1 ለማሸነፍ የቻለችው በተጨማሪ ሰዓት ውስጥ

ባገኘችው ሁለተኛ ግብ ነው::

ዛሬ በኢኳቶሪያል ከተማ ባታ ላይ ዛምቢያ ከጋና፣ በጋቦኗ ሊቨርቪል ደግሞ

ማሊ ከአይቮሪኮስት ወሳኙን ግጥሚያ ያደርጋሉ:: ተሸናፊዎች ለሦስተኛነት ቅዳሜ፣ ፍጻሜው ደግሞ እሑድ እ ን ደ ሚ ካ ሔ ድ ይ ጠ በ ቃ ል : : ገማቾች ዋንጫው ከጋና ወይም አይቮሪኮስት

እ ንደማያልፍ ቢያወሱም፣ በ1966 እና 1986 ዓ.ም. ለፍጻሜ ደርሳ ዋንጫ ያጣችው ዛምቢያም ለዋንጫ አለሁኝ እያለች ነው::

ውጤታማ የነበሩት ሞሮኮ፣ ቱኒዝያ፣ ሴኔጋልና ጋምቢያ በየምድባቸው በየጊዜው በመሰናበታቸው ባለድሎቹ ግብፅ፣ ካሜሩን፣ አልጀሪያና ናይጄሪያ በዘንድሮው ውድድር ባለመገኘታቸው ለፍጻሜው ዛምቢያ ደርሳ ዋንጫውን ለማንሣት ዕድል አላት የሚሉት አሠልጣኙ ሄርቭ ሬናርድ ናቸው::

ለካፍ ኦን ላይን ቃል የሰጡት ፈረንሣዊው የዛምቢያ አሠልጣኝ፣ ስለፍልሚያው ያወሱት ነጥብ አለ፣ ‹‹የዘንድሮውን ዋንጫ ለማሸነፍ ዕድሉ አለን:: ዛምቢያ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ለፍጻሜ ደርሳ (1966 እና 1986 ዓ.ም.) ተሸንፋለች:: የአሁኑ ትውልድ ግን ከነዚያ አልፎ መሔድ አለበት::

የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ተፋላሚዎች ዛሬ ይታወቃሉ

1 7 7

በጋዜጣው ሪፖርተር

በአሜሪካዋ ከተማ ቦስተን ባለፈው ቅዳሜ በተካሔደው 17ኛው የኒው ባላንስ የአዳራሽ ውስጥ ሩጫ ኢትዮጵያውያቱ ጥሩነሽ ዲባባና መሠረት ደፋር ድል ቀናቸው:: ጥሩነሽ የሁለት ማይል ሩጫዋን በ9 ደቂቃ 21.60 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ስታሸንፍ፣ መሠረት በበኩሏ በሦስት ሺሕ ሜትር አሸናፊ ለመሆን የበቃችው በ8 ደቂቃ 33.57 ሰከንድ መስመሩን ቀድማ በማለፍ ነው:: ጥሩነሽን ተከትለው በሁለተኛነትና ሦስተኛነት የፈጸሙት አሜሪካውያቱ ጃኪ አርስንና ደሊላህ ዲክሬሴንዞ ናቸው::

መሠረትን ተከትላ ሁለተኛ የሆነው ደግሞ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ጎይተቶም ገብረሥላሴ ስትሆን፣ ሞሮኳዊቷ ሲሃም ሊላሊ ሦስተኛ ሆናለች:: በወንዶች 3000 ሜትር ከአንድ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ኬንያውያንና ኢትዮጵያውያኑ ተቆጣጥረውታል::

ኬንያውያኑ ካሌብ ንዲኩና ሲላስ ኪፕላጋት

አንደኛና ሦስተኛ ሲወጡ፣ ኢትዮጵያውያኑ ደጀን ገብረመስቀልና ሐጎስ ገብረሕይወት ሁለተኛና አራተኛ ሆነው መፈጸማቸው ከቦስተን የተሰራጨው ዜና ያስረዳል::

በሌላ በኩልም ባለፈው እሑድ በሆንግ ኮንግ ከተማ በተካሔደው የማራቶን ሩጫ በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያውያኑ እንዳሸነፉ ዶቸቬሌ በድረገጹ ዘግቧል::

ሰባ ሺሕ ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት 16ኛው የሆንግ ኮንግ ማራቶን በወንዶች ደረጀ አሊ፣ በሴቶች ምስክር ደምሴ አሸንፈዋል:: በዚሁ ሩጫ የ26 ዓመት ወጣት መግቢያ መስመሩ ላይ ከደረሰ በኋላ ራሱን ስቶ ወድቆ ሆስፒታል ውስጥ መሞቱን ዘገባው አክሎ ገልጿል::

ኢትዮጵያዊው ያዕቆብ ጃርሶ ሦስተኛ በወጣበት የጃፓን የቤኙ ኦኪታ ማራቶን ኬንያዊው ሐሩን ኞሮጌ አሸናፊ መሆኑን፣ ሞንጎሊያዊው ኦቺር ሁለተኛ መሆኑን ታውቋል::

ጥሩነሽ ዲባባና መሠረት ደፋር በቦስተን ድል ቀናቸው

ጥሩነሽ ዲባባ መሠረት ደፋር

Page 36: Reporter Issue 1229

ገጽ 36|

www.ethiopianreporter.com

| ረቡዕ | ጥር 30 ቀን 2004

የዲዛይንና ዝግጅት በሚዲያ ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አሳታሚ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ሴንተር አታሚ፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡ አራዳ ቀበሌ፡ 17 የቤት ቁጥር፡ 984

ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ጎንደር ሲጓዝ በነበረው የስካይ ባስ አውቶቡስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ላለቁት 43 ተሳፋሪዎች፤ ጥር 27 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎተ ፍትሐት ተደርጎላቸዋል:: ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ ከአደጋው ሰለባዎች ሕይወታቸውን ባጡበት ስፍራ ማስተማርያ ይሆን ዘንድ መታሰቢያ እንዲቆምላቸው ጥሪ አቅርበዋል:: በአደጋው ሕይወታቸው ካለፈው መካከል የአንድ ቤተሰብ አራት አባላትና ባለፈው ኅዳር ጎጆ የወጡ ሙሽሮች ይገኙበታል:: (በሔኖክ ያሬድ)

ለዓባይ በረሃ ሰለባዎች ጸሎተ ፍትሐት ተደረገ

በጋዜጣው ሪፖርተር

ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ዓርማውን ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል ይፋ ያደርጋል:: ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ዓርማውን ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ በሳር ቤት የሚገኘውን አዲሱ የኩባንያው ሞዴል የአገልግሎት መስጫ ማዕከል የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል በሚገኙበት ይመረቃል::

በዓለማችን ግዙፍና ታዋቂ የሆነው የፈረንሣይ ቴሌኮም (France Telecom) የኢትዮ ቴሌኮምን ማስተዳደር ከጀመረ ዓመት ያለፈው ሲሆን፣ ድርጅቱ ኢትዮ ቴሌኮምን የተረከበው የአገልግሎት ብቃቱን ለማሳደግ ነው:: የፈረንሣይ ቴሌኮም የኢትዮ ቴሌኮምን መዋቅር ከኤን 1 እስከ ኤን 5 በመከፋፈል ያደራጀ ሲሆን፣ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሥር

የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ማሰናበቱ ይታወሳል::

የፈረንሣይ ቴሌኮም ኢትዮ ቴሌኮምን ለማስተዳደር የተዋዋለው ለሁለት ዓመት ሲሆን፣ ለአገልግሎቱም 30 ሚሊዮን ዩሮ ይከፈለዋል:: የፈረንሣይ ቴሌኮም አስተዳደር ግን በኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በርካታ ደንበኞች ያላቸውን ቅሬታ እምብዛም ሊያስወግድ እንዳልቻለ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎችና አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

የኢትዮ ቴሌኮም የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አብዱራሂም አህመድ ስለዓርማው ይዘት አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው፣ “ስለዓርማው ዓላማና ዝርዝር ጉዳዮች በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሚሰጥ በመሆኑ ከወዲሁ አስተያየት መስጠት ይከብደኛል፤” ብለዋል::

ኢትዮ ቴሌኮም አዲሱን ዓርማ ዛሬ ይፋ ያደርጋል

በዓለማችን ግዙፍና ታዋቂ የሆነው የፈረንሣይ ቴሌኮም (France Telecom) የኢትዮ

ቴሌኮምን ማስተዳደር ከጀመረ ዓመት ያለፈው ሲሆን፣ ድርጅቱ ኢትዮ ቴሌኮምን የተረከበው

የአገልግሎት ብቃቱን ለማሳደግ ነው::