2,3,9,10 - ethiopian observerethioobserver.net/finote_nesanete issue9_092711.pdf · ፡...

16
www.andinet.org.et 1 ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም. 2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም. 2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.9 የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ! ከርዕዮት እስከ ደበበ መስፍን ነጋሽ ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ ቢከሰት እንታገላለ ን፡፡ ሽብርተኝነትን በጥንቃቄ እንታገላለን፡፡ በአንዳንድ አገሮች ሽብርተኝነትን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙ አሉ፡፡ 2,3,9,10 12 14 5 የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአገር ቤት እና በውጭ አገር! የሰላም ትግል - መቼ ተጀመረ? ከዝንጀሮዎቹ ጌታ ታሪክስ ምን እንማራለን? 13

Upload: ngodiep

Post on 27-Jul-2018

237 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

PB2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 1ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.9

የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!

ከርዕዮት እስከ ደበበ መስፍን ነጋሽ

ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ ቢከሰት እንታገላለን፡፡ ሽብርተኝነትን በጥንቃቄ እንታገላለን፡፡ በአንዳንድ አገሮች ሽብርተኝነትን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙ አሉ፡፡

2,3,9,10

12 14

5የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአገር ቤት እና በውጭ አገር!

የሰላም ትግል - መቼ ተጀመረ? ከዝንጀሮዎቹ

ጌታ ታሪክስ ምን እንማራለን?

13

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

22ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 3ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

22ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 3ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ርእዮት ዓለሙርእዮት ዓለሙ ማናት? የትስ ተወለደች? የትስ ተማረች? በመጨራሻስ ምን ደረሰባት? ለሚሉት ጥያቄዎች ላንባቢያንና በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ ጧት ማታ ለምትታገልለት ሕዝብ ሰለማንነቷ በመጠኑ ሐሳብ ለመፈንጠቅ እንሞክራለን፡፡ርእዮት ዓለሙ የተወለደችው በ1972 ዓ.ም ናዝሬት ከተማ ነው፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በተለያዩ ት/ቤቶች ብትማርም በመጨረሻ ያጠናቀቀችው በነፋስ ስልክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ርእዮት ዓለሙ የማስተማር ዝንባሌ ስለነበራት ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በመግባት በሠርቲፊኬት ተመርቃለች፡፡ በምትፈልገው ሙያ በማስተማር ላይ ተሠማርታ እያስተማረች ከዚሁ ጎን ለጎን ትምህርቷን በማታው መርሃ ግብር በመግባት በዚያው በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በዲፕሎም ተመርቃለች፡፡ አሁንም የመማር ጉጉት ስላላት በማስተማር ሥራዋ ላይ እንዳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመግባት በእንግሊዘኛ ቋንቋ በ2001 ዓ.ም በዲግሪ ተመርቃለች፡፡ በዚያው ዓመት በሚያስደንቅ ሁኔታ በቴአትር ጥበባት የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች፡፡ ርእዮት ዓለሙ መደበኛ ሥራዋ ማስተማር ይሁን እንጂ የጋዜጠኝነት ሙያን አጥብቃ ስለምትወድ ከማስተማሩ ጎን ለጎን ወርክ ሾፖች፣ አጫጭር ኮርሶችን በመውሰድ የጋዜጠኝነት ሙያን ክህሎት አዳብራለች፡፡ በመሆኑም በተለያዩ ጋዜጦች ዓምደኛ እና አዘጋጅ በመሆን አመርቂና አይረሴ ሞጋች የሆኑ መጣጥፎችን

በማቅረብ ትታወቃለች፡፡ ለምሳሌ የፍትሕ ሳምንታዊ ጋዜጣ አምደኛ ነበረች፡፡ በኋላም የማስተማር ሥራዋን ትታ አዲስ ፕሬስ ጋዜጣ ተቀጥራ በምትሠነዝራቸው የሰሉ ሂሶች ጎልታ ትታወቃለች፡፡ በቅርብ የሚያውቋት የእስር ሰለባ የሆነችው በጻፈቻቸው ጽሑፎች ሳይሆን እንደማይቀር ግምታቸውን ይሠጣሉ፡፡

የፖለቲካ አቋምርእዮት ዓለሙ ለውጥን ከሚፈልጉት ወጣቶች አንዷ በመሆኗ ላመነችበት ነገር ከመከራከር ወደ ኋላ አትልም፡፡ በተለይም በምትጽፋቸው መጣጥፎችና ግጥሞች በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፋለች፡፡ ርእዮት ፀባየ መልካም፣ ጭምት፣ ሲበዛ ብዙ ከመናገር ቁጥብ ነች፡፡ ባንፃሩም ሌሎች ሲናገሩ በሰከነ መልኩ የማዳመጥ ችሎታዋ የላቀ ነው፡፡ በዚህ ምግባሯም በጓደኞቿ ተወዳጅና ተከባሪ ወጣት ነች፡፡ አባቷ አቶ ዓለሙ ጌቤቦን ልጃቸው በሽብርተኝነት ተጠርጥራ ስትያዝ ምን ስሜት እንደተፈጠረባቸው ጠይቀናቸው የሰጡን መልስ፡- “ልጄን ስለማውቃት በሽብርተኝነት ተጠርጥራ በተያዘችበት ወቅት ምንም አልደነቀኝም፡፡ በሽብርተኝነት ተጠርጥራ መባሏ ግን አሳዝኖኛል፡፡ ልጄ የሕዝብ ልጅ ነች፡፡ ለሕዝብ ጥቅም የቆመች ሆና እንዴት የሕዝብን ጥቅም ለመጉዳት በሽብር ተግባር ውስጥ ትሳተፋለች? በፍፁም ሥራዋ አይደለም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ገልፀዋል፡፡

ስለሺ ሐጎስ የተወለደው መቂ ከተማ በ1972 ዓ.ም ነው፡፡ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በዚያው በመቂ ከተማ በካቶሊክ ት/ቤት ተምሯል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው በዝዋይ ከተማ ነው፡፡

ስለሺ ሐጎስ በኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በመግባት በሥነ ጽሑፍ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በመግባት በቴአትር ጥበብ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡

ስለሺ ሐጎስ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት ከሚጥሩ ወጣቶች አንዱ ነው፡፡ በሚያቀርባቸው ግጥሞች ካነባበብ ስልቱ ጋር ተዳምረው ቀልብን የመሳብ ተሰጥኦ ነበረው፡፡

ስለሺ ሐጎስ በቴአትር ጥበባት ዲግሪውን ያግኝ እንጂ የሥነ ጽሑፍ ትኩሳት ስለነበረው “ቼንጅ” ወይንም ለውጥ የሚል መጽሔት ማሣተም ጀምሮ ነበር፡፡ በሁኔታዎች አስገዳጅነት ግን ርቆ ሊራመድ አልቻለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ መሥረዳድር የኤፍ ኤም 96.3 የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ የአየር ሰዓት

በመውሰድ የመዝናኛ ፕሮግራም ያዘጋጅ ነበር፡፡ በዚህም በርካታ ደንበኞችን ለማፍራት ችሏል፡፡

ስለሺ ሐጎስ በምን ምክንያት በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የቅርብ ጓደኛው የሆነውን ወጣት ሀብተማርያምን አግኝተን ስለ ሁኔታው ጠይቀነው ነበር፡፡ “እኔ ጓደኛየን የማውቀው በቁምነገረኛነቱ ነው፡፡ ካልሆነ ቦታ ይገኛል የሚል እምነት የለኝም፡፡ ለጊዜውም በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋለ አላውቅም፡፡ በመንግሥት በኩል እስካሁንም በሽብር ተጠርጥሮ የሚል መግለጫ አልሰማሁም፡፡ ያላንዳች ምክንያት ተይዞ መታሰሩ ግን አሳዝኖኛል” ብሏል፡፡ ሌላው ጓደኛው ወርቅነህ የተባለው “የስለሺ መታሰር ገርሞኛል፡፡ ጓደኛዬን የማውቀው በቁምነገረኛነቱና በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዲመጣ መፈለጉን እንጂ ከዚህ ውጭ ሌላ ፀባይና ክፋት አላውቅበትም ” ሲል በመታሰሩ ማዘኑን ገልፃልናል፡፡

እንግዲህ ርእዮት ዓለሙና ስለሺ ሐጎስ እነማን እንደ ሆነ ላንባቢያንና ለሚታገሉለት ሕዝብ በመጠኑ ለመፈንጠቅ ሞክረናል፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በ1954 ዓ.ም በወለጋ ክፍለ ሀገር ልዩ ቦታው ቦጂ ድርመጂ በሚባል አካባቢ ተወልደው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በዚያው አካባቢ አጠናቀዋል፡፡ ከዚያም በጤና ረዳትነት በመማር አሁን ደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን በሚባል ቦታ ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንግሊዘኛ ቋንቋ በመማር የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪያቸውን (BA&MA)አግኝተው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በእንግሊዘኛ የፍልስፍና ዲግሪ (PhD) እያጠኑ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡ በሥራ ዓለምም ለ20 ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ጨምሮ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ አገልግለዋል፡፡

የቤተሰብና ማህበራዊ ህይወትአቶ በቀለ ገርባ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ

አንድ ሴትና ሦስት ወንድ ልጆች አሏቸው፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ስትሆን የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ ጨርሳ በ2003 ዓ.ም ተመርቃለች፡፡ የሁለተኛ ልጃቸው ወንድ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ጨርሶ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርስቲ

ምደባን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ ሦስተኛ እና አራተኛ ልጆቻቸው መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ይገኛሉ፡፡

ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐና ረጋሳ ይባላሉ፡፡ አቶ በቀለ ምንም እንኳ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢሰሩም የመኖሪያ አድራሻቸውና ቤተሰቦቻቸው የሚገኙት ናዝሬት ከተማ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸውንም ከአዲስ አበባ እየተመላለሱ እንደሚጠይቋቸው ባለቤታቸው ተናግረዋል፡፡ በማህበራዊ ህይወታቸውም ከሰው ጋር ተግባቢና ሐሳባቸውን በነፃነት የሚገልፁ፣ በተለይ በተማሪዎቻቸው እጅግ የሚወደዱና እንደ ልጆቻቸው እንደሚያቀርቡ፤ የሰውን ሐሳብ በቀላሉ የሚረዱና ቀና አመለካከት ያላቸው ናቸው ይላሉ ባልደረቦቻቸው፡፡ ከማንኛውም ደባል ሱስ ነፃ መሆናቸው ደግሞ ይበልጥ እንዲወደዱ አድርጓቸዋል ይላሉ፡፡

የፖለቲካ ህይወታቸውፓለቲካን መቼ እንደጀመሩ በግልፅ ባይታወቅም

ከወጣትነታቸው ጀምሮ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይበልጥ ግን የኦሮሞ ፌደራሊስት ዴሞክራሲያዊ

ንቅናቄን (ኦፌዲን)ን ከተቀላቀሉ በኋላ ጐልተው እንደወጡ ይነገራል፡፡ በድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመሆንና በመድረክ ፓርቲ ውስጥም የሥራ አስፈፃሚ አባል በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ከኦነግ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ መጠርጠራቸው ከእውነት የራቀ ነው፡፡ ምክንያቱም እንደማንኛውም ጨዋ ኢትዮጵያዊ በኃይማኖት ታንፀው ያደጉ በመሆናቸው እንኳን የኦነግ አባል ሊሆኑ ቀርቶ ኦፌዲንን እራሱ ቀስ ብለው ነው የተቀላቀሉት ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ለሰላማዊ ትግል ትልቅ ቦታ ስለሚሰጡ ነው ሲሉ ዶ/ር ሞጋ ተናግረዋል፡፡ ሌላው “ሽብር ለተባለው እሱ እኮ በባህልና በኃይማኖት ታንፆ ያደገ እና ከተለያዩ የሀገራችን ማህበረሰቦች ጋር በተለያየ ቦታ በጥሩ መግባባትና ፍቅር አብሮ እየኖረ ነው፡፡ ስለዚህ ማን ላይ ሽብር ያስባል? እንኳን ማሰብ በሌሎች ሀገሮች ላይ የሚፈፀመውን የሽብር ተግባር በመገናኛ ብዙኃን ሲያይና ሲሰማ የሚሳቀቅና የሚናደድ ሰው ነው፡፡ እኛ አሁን በጋብቻ ዓለም ውስጥ ሰንኖር 21ኛ ዓመታችን ነው ከተጠረጠረበት ተግባር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው ጠንቅቄ አውቀዋለሁ” ሲሉ ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐና ይናገራሉ፡፡ የመድረክ በተለይም የኦፌዴን አጋሮቻቸውም የወ/ሮ ሐና ረጋሳን ሐሳብ ይጋራሉ፡፡

አቶ ኦልባና ሌሊሳ በምዕራብ ሸዋ ጨሊ ወረዳ በ1966 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም በተወለዱበት አካባቢ አጠናቀው ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በመግባት በግብርና ዲፕሎማ አግኝተዋል፡፡ ከዚያም በመንግሥት ግብርና ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በሚተዳደር መስሪያ ቤት ተቀጥረው ለዓመታት አገልግለዋል፡፡ በማታው መርሐ ግብር በአምቦ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል እየተማሩ እንደነበርና በተደረገባቸው የፖለቲካ ጫና ምክንያት ሥራቸውን በፈቃዳቸው ሲለቁ የጀመሩትንም ትምህርት ለማቋረጥ እንደተገደዱ ባልደረቦቻቸው ይናገራሉ፡፡

የቤተሰብ ሁኔታን በተመለከተ እስካአሁን ትዳር ያልያዙ ሲሆን መተዳደሪያቸውም ሙሉ በሙሉ የፖለቲካ ሥራ ስለሆነ ከኦህኮ ጽ/ቤት በሚያገኙት አባል ነው፡፡

የፖለቲካ ህይወት ከ1992 ዓ.ም ምርጫ በፊት የተወለዱበት ጨሊያ

ወረዳን በመወከል ለፓርላማ ተወዳድረዋል፡፡ 1997 ዓ.ም ደግሞ ለኦሮሚያ ም/ቤት ድርጅታቸውን ወክለው በመወዳደር ተመርጠው ለ5 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በተጨማሪም በወቅቱ የህብረት ዋና ተጠሪ ነበሩ፡፡ በምርጫ 2002 ደግሞ ለኦሮሚያ ም/ቤት ተወዳድረዋል፡፡ ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ የኦህኮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ “በሥነ -ምግባርና በኃይማኖት ታንፀው ስላደጉ ከማህበረሰቡ ጋር ጥሩ መግባባት ያላቸው ሲሆን ትዕግስተኛ እና ከሰዎች ጋር በሰላም መወያየትና ችግርን በመግባባት መፍታት ስለሚያምኑ በሰላም መነጋገር አንዱ መለያ ባህሪያቸው ነው” ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡

“የተጠራጠሩበት ጉዳይ ዛሬ የመጀመሪያ ሳይሆን

በተደጋጋሚ አምቦ ላይ ይፈፀምባቸው እንደነበርና ነፃ ሆነው እንደተለቀቁ ይታወቃል” በማለት ከምርጫ 97 በኋላም ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስባቸው እንደነበርና ከዚህ በፊት እንጦጦ ጫካ ተወስደው ከባድ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የትግል አጋሮቻቸው አስታውሰዋል፡፡

“አሁን በሽብር መጠርጠራቸው ሆን ተብሎ ትግሉን ለማዳከም እንደሆነ እንጂ አቶ ኦልባና ሰላማዊ ትግልን እንደ መርሃቸው የሚቆጥሩና የቆዩ ፖለቲከኛ ናቸው እንጂ የሽብር ዓላማማም ሆነ ትብብር እንደሌላቸው ይታወቃል” ሲሉ ዶ/ር መረራ ለዝግጅት ክፍሉ ተናግረዋል፡፡ በዚህ ወቅት የኦህኮ /መድረክ አመራር ውስጥም ጉልህ ተሳትፎ የሚያደርጉና ከሥራ ባልደረቦቻቸውም ሆነ ከሌሎች ጓደኞቻቸው ጋር ጥሩ የሆነ ማህበራዊ ግንኙነት ያላቸው ናቸው ሲሉ የትግል አጋሮቻቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ስለሺ ሐጎስ

አቶ በቀለ ገርባ

አቶ ኦልባና ሌሊሳ

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

22ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 3ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

22ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 3ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

በ2003 ዓ.ም ለ10 ቀናት ትምህርትን አስመልክቶ ከመምህራን ጋር ንግግር ያደረጋል በሚል የት/ቤቱ መዝጊያ ወቅት ለአንድ ሳምንት ወደ ኋላ ተጐትቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ መምህራን ሰኔ 30 ቀን 2003 ዓ.ም ማቆም የነበረባቸውን ትምህርት ወደኋላ ለአንድ ሣምንት ቢያሳጥሩትም የታሰበው ስብሰባ አልተካሄደም፡፡ ያለፈውን የትምህርት ዓመት ያደናቀፈውን ስልጠና ፤ በ2004 ዓ.ም መስከረም ወር ይሰጣል ተብሎ የተነገረ ቢሆንም፤ ጉዳዩ ዘግየት ብሎ ’’ የግል ት/ቤት መምህራንና የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ’’ በሚል ርዕስ መስከረም 14 ቀን 2004 ዓ.ም መምህራኑ በየሚገኙበት ወረዳ የአንድ ቀን ስልጠና ተሰቷል፡፡የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ በሚል ርዕስ መምህራን በተመረጡ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ በተዘጋጀ ክፍል ተሰብስበው በቴሌቪዥን ወይም በፕላዝማ ገለጻ ተከታትለዋል፡፡ በአንዳንድ ት/ቤቶች መብራት ባለመኖሩ በተወከሉ የየወረዳው የትምህርት ኃላፊዎች በግንባር በመገኘት ሥልጠናውን ሰጥተዋል፡፡በስልጠናው በ2004 ዓ.ም የትምህርት ጥራት የሚያረጋገጥ መሆኑን የተዘጋጁ አዲስ ፓኬጆች እንዳሉና ትምህርትም ከዚህ በኋላ በከፍተኛ የጥራት ደረጃ እንደሚሰጥ አበክረው ገልፀዋል፡፡ በመምህርነት የሚሣተፉ ሠዎች ከአሠለጣጠን ጀምሮ ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ መልኩ እንደሚሠለጥኑ ገልፀው ነበር ፡፡የተማሪ መምህራን ጥምረት ለውጥ ያመጣ

- እስካሁን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አልቻልንም (አንድነት ፓርቲ)

- ቤተሰብ፣ የትግል አጋሮቻቸውና የህግ አማካሪ እንዲያገኛቸው ተከልክለዋል (ቤተሰብ)

- የእስር አያያዛቸው አሳስቦናል

በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት የሆኑት መ/ር ናትናኤል መኮንንና መ/ር አሳምነው ብርሃኑ እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጐስ የመኢዴፓ ዋና ፀሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ ከታሰሩ በኋላ ቤተሰብ፣ የትግል አጋሮቻቸውን የሕግ አማካሪዎቻቸው ለማግኘት ሞክረው በመከልከላቸው የእስር አያያዛቸው አሳስበናል ሲል የፓርቲው ጽ/ቤት ለዝግጅት ክፍላችን ገለፀ፡፡ ጉዳዩን የሚከታተል በፓርቲው ሊቀመንበር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የሚመራ አራት ኮሚቴዎችን ያቀፈ የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተል አንድ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ከህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቀዋል፡፡

ከፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ክፍል በደረሰን መረጃ መሠረት በእ/ር ግዛቸው ሽፈራው የሚመራ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ኮሚቴ፣ በተከበሩ አቶ ግርማ ሴይፉ የሚመራ የህዝብ ግንኙነት ጉዳዮች ኮሚቴ፣ በወ/ሮ ላቀች ደገፉ የሚመራ የማህበራዊ ጉዳዮች ኮሚቴ በአቶ ሽመልስ ሀብቴ የሚመራ የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳዮች ኮሚቴ ተቋቁሞ ኃላፊነትና ተግባሩን በዝርዝር ከተገለፀለት በኋላ ሥራቸውን እያከናወኑ ናቸው ተብሎአል፡፡ ስለ ጉዳዩ አጠቃላይ ሁኔታ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደገለጹልን “እስረኞች ከታሠሩበት ጊዜ ጀምሮ ማንም ሰው እንደገለጹልን “እስረኞች ከታሠሩበት ጊዜ ጀምሮ ማንም ሰው እንዳያገኛቸው በመደረጉ የእስረኞቹ አያያዝ አሳስበናል፡፡ ህገመንግስታዊ መብታቸውን ለማስከበር ጉዳዩን የሚከታተል አንድ ግብረ ኃይል አቋቁመን እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ እስረኞቹ ተጠርጥረው በተሰሩበት ፍ/ቤት ቀርበው ተመስክሮባቸው ሳይረጋገጥ የመንግስት ሚዲያዎችና ከመንግስት ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው አንዳንድ ሚዲያዎች ወንጀለኛ እንደሆኑ አስመስለው የፕሮፓጋንዳ ሥራ እየተከናወነባቸው ነው፡፡ ይህ በአስቸኳይ መቆም አለበት፡፡ የአገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 19 ስለ እስረኞች አያያዝ የሚደነግገው አንቀጽ እየተጣሰ ነው” ብለዋል፡፡

በመቀጠልም ዶ/ር ነጋሶ ሲናገሩ “እስከ አሁን ድረስ

ከእስረኛ ቤተሰቦች ባለኝ መረጃ መሠረት ስንቅ ከማቀበልና ዕቃ ከመቀበል ውጪ እስረኞቹ ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ አለመቻላቸውን ገልጸውልኛል፡፡ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የድጋፍ ሰጪ ፓብተሮቻችን ጉዳዩን በንቃት ከመከታተላቸውም በላይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ ናቸው፡፡ አንዳንድ ኢንባሲዎችም ስለ ጉዳዩ ከጠየቁን በኋላ ጠ/ሚኒስትሩን እንደሚያነጋግሯቸው ገልፀውልናል፡፡ የፍርድ ሂደቱንም በቅርብ እንደሚከታተሉት ለየመንግስታቸውም ያለውን ሁኔታ እንደሚያስታውቁ አረጋግጠውናል፡፡ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ሂውማን ራይትዎች በአገሪቱ ውስጥ እየተፈፀመ ያለውን ሁኔታ ጠይቀውን አስረድቼአቸዋለሁ፡፡ የሽብርተኝነት ህጉን በመጠቀም ህጋዊና ሠላማዊ ታጋዮችንና ጋዜጠኞችን የማፈን ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡ ፀረ -ሽብር ህግ ህገመንግሥቱን የሚቃረን ስለሆነ አዋጁ ውድቅ መደረግ አለበት፡፡ ህዝብ ብሶቱን በነፃነት የሚገልጽበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል ፓርቲው በዚህ በተጀመረው የእስር ዘመቻ ላይ አባላቱን በየደረጃው ለማወያየት እቅድ ይዟል፡፡ በመቀጠልም ህዝባዊ ስብሰባዎችን ለማከናወን እያስብን ነው፡፡ የአገራችንን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ውጪ አገር በአማርኛ ቋንቋ ከሚተላለፉ ሬዲዮኖች ውስጥ አውስትራሊያ አትላንታና ካናዳ የሚገኙ ሬዲዮ ጣቢያዎች አነጋግረውን ዘግበውታል” በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከተቋቋሙት ኮሚቴዎች መካከል የህግና ሰብአዊ መብት ጉዳዮች ኮሚቴ ስብሳቢን አቶ ሽመልስ ሀብቴን ኮሚቴያችሁ እስከ አሁን ድረስ ምን ምን ተግባራትን አከናወናችሁ ወደፊትስ ምን ለመስራት አቅዳችኃል በማለት ጠይቀን በሰጡን መልስ “እስከ ዛሬ ድረስ እስረኞቹን ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ሞክረን ተከልክለናል፡፡ አሁን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በጽሑፍ ለማወቅና በህግ ለመጠይቅ እየተንቀሳቀስን ነው” ብለውናል፡፡ በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት እስረኞችን ለመጠየቅ ሄደው የተከለከሉት የፓርቲው አመራሮች ኢ/ር ግዛቸው አቶ ዳዊት አስራደ፣ አቶ ሽመልስ ሀብቴና ጠበቃ ዳንኤል ካፌ መሆናችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን አብረዋቸው ከሄዱት ውስጥ አቶ አስራት ጣሴ አቶ ሰለሞን ታደሰ የሚገኙበት ሲሆን በአሁኑ ሳምንት ደግሞ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚውና የብሔራዊ ም/ቤት አባላት ሄደው መከልከላቸውን መረዳት ተችሎአል፡፡

በተያያዘ ዜና የቀድሞ የኢህዲሪ ፕሬዝዳንትና የወቅቱ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከትላንት በስቲያ እስረኞችን ለመጠየቅ ሄደው መከልከላቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ግልፀዋል፡፡ በዕለቱ ከተወሰኑ ግለሰቦች ጋር

በመሆን በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ እስር ቤት እንደደረሱ በእስር ላይ የሚገኙትን የፖለቲካ አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ማግኘት እንደሚፈልጉ ገልጸው ጠይቀዋል መዝጋቢ ፖሊሶች በስም ማንን ብለው ሲጠይቁ ዶ/ር ነጋሶ አቶ አንዱዓለም አራጌን ሲሉ መዝጋቢ ፖሊሶች አንድ የፖሊስ ኃላፊን ጠርተው አቶ አንዱዓለምን እንጠይቅ እያሉ ናቸው ብለው ሲያመለክቱ ፖሊሱ በንዴትና በቁጣ “ዋ አይቻልም፡፡ እዚህም መቆም አይቻልም በግቢው ውጡ” በማለትና በማመናጨቅ ለማስወጣት ሞክሮአል፡፡ ለምን እንድጠይቅ አይፈቀድልኝም ብለው ሲጠይቁ ፖሊሱ የከለከለው የበላይ አካል ነው፡፡ በማለት መልሷል፡፡ የከለከለው የበላይ አካል ማነው በማለት ዶ/ር ነጋሶ ሲጠይቁ ፖሊሱ አላውቅም በማለት መልሷል፡፡ በሥፍራው የነበሩት እ/ር ዘለቀ ረዲ ፖሊሶችን ኃይለ ቃልና ማመናጨቅ ለምን ያስፈልጋል፡፡ እኚህ ሰውዬ ቢያንስ በአንድ ወቅት የአገሪቱ ፕሬዝደንት የነበሩ ናቸው፡፡ በዕድሜም አዛውንት ናቸው፡፡ እየጠየቁ ያሉት ህጋዊ ጥያቄ ነው፡፡ እስረኛ መጠየቅ እፈልጋለሁ ለምን ትከለክሉኛላችሁ? ነው ያሉት፡፡ “ቁጣን መወራጨትን ምን አመጣው”? ሲሉ ፖሊሶቹን ሲያነጋግሩ ተደምጧል፡፡ “የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ይውጣ ይውጣ” ሲሉ ፖሊሶች በቁጣ እና በኃይለ ቃል መልሰዋል፡፡ በመጨረሻም እንደ ማንኛውም ጠያቂ ያመጡትን ስንቅ ላይ የተጠያቂውን ስምና ያመጡትን ሦስት ሰዎች ስም በመጻፍ ስንቁን ሲያስረክቡ የሌሎች ጠያቂዎች ሲገባ የዶ/ር ነጋሶ የእ/ረ ዘለቀና አብሮአቸው ያለው አንድ ጠያቂ ስም ያለበትን ወረቀት ፖሊሱ ተቀብሎ የጠያቂዎቹን ስም ቀዳዶ ጥሎታል፡፡ እነ ዶ/ር ነጋሶም ግቢውን በመልቀቅ ወጥተዋል፡፡

ስለነበረው አጠቃላይ ሁኔታ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው እ/ር ዘለቀ ረዲ እንዳሉት “እኔ በዜግነቴ ካዘንኩባቸው ቀናቶች ዛሬ አንዱ ነው፡፡ ፖሊሶቻችን የተገነቡበት ሥነ ምግባር በእጅጉ ያሳዝናል፡፡ አንድ ሰው ወንጀል እስካልሠራ ድረስ ህጋዊ መብቱን መጠየቅ ጥፋት አይደለም፡፡ ሰው በዕድሜው በትምህርቱ በኃላፊነቱ ይከበራል፡፡ የማታውቀውን ሰውም ታከብረዋለህ እዚህ የምትመለከተው ግን ያሳፍርሃል፡፡ ጥላቻን ምን አመጣው? ቁጣን ድንፋታ ለምን አስፈለገ? በትህትና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መነጋገርን ምን ከለከለን፡፡ ፖሊሶች ዜጐችን በጥላቻ፣ በጠላትነት መንፈስ ለምን ይመለከቱናል? የቆሙትም ለአገርና ለህዝብ አይደለምን? አገልጋይነታቸውስ ለማነው? በእውነት እኔ እንደግለሰብ በእጅጉ አዛኜአለሁ” በማለት ቅሬታቸውን በሀዘን ገልፀዋል፡፡ ከፍተኛ ሁኔታ የማመናጨቅ ተግባር የተፈፀመባቸው ዶ/ር ነጋሶ በተረጋጋ መንፈስ ወጥተው ሲሄዱ መመልከት ተችሎአል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተል ግብር ኃይል መቋቋሙ ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የግል ት/ቤቶችመምህራን

የትምህርት ጥራትን ያመላከተ የአንድ ቀን ስልጠና ተሠጠ

ስለ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔርወ/ት ሊዲያ ዘሪሁን ትባላለች፡፡ በእስር ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝደንት የአቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር ልጅ ናት፡፡ በአባቷ ዙሪያ ባልደረባችን ብዙአየሁ ወንድሙ አነጋርሯታል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡

አባትሽ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር በእስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ በመጀመሪያ አቶ ዘሪሁን የት ተወለዱ?ዘርዬ የተወለደው እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ልዩ ሥፍራው መርከቶ የሚባል አካባቢ ነው፡፡

ስለ ትምህርታቸው አጠቃላይ ሁኔታ ብትገልጪልኝ ከ1-12ኛ ክፍል ተመሮ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ጉለሌ በሚገኘው መድኃኔዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ ከኢትዮጵስ ኮሌጅ በዲፕሎማ ተመርቋል፡፡ ከእንግሊዝ አገር በተልዕኮ ትምርት ተመሮ መመረቁን አውቃለሁ፡፡

አቶ ዘሪሁን ስንት ልጆች አሏቸው? አንቺ ስንተኛ ልጃቸው ነሽ? ከቤተሰባቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት ትገልጪዋለሽ?

ሁለት ልጆች ነው ያለው፡፡ እኔ ሁለተኛ ልጅ - ነኝ፡፡ በአኔና በታላቄ መካከል ያለው ልዩነት አንድ ዓመት

ነው፡፡ ታላቅና ታናሽ ሳይሆን አኩዮች ነን፡፡ አንደንድ ሰዎች መንታዎች ናችሁ እያሉ ይጠይቁናል፡፡ እናትና አባታችንም በልጅነታቸው ስለወለዱን አብረን ስንታይ ወላጆቻችን ሳይሆኑ ጓደኞቻችን ይመስላሉ፡፡ የማያውቁን አብረውን ሲያዩን ጓደኞቻችን አድርገው ይወስዱታል፡፡ በመልክና በዕድሜ ብቻ ሳይሆን በመቀራረብም አንደ ጋደኛ ነን፡፡ ዘርዬ ያሳደገን አቅርቦ በፈቅር ነው፡፡ እኛም ለአባታችንና ለእናታችን ልዩ ፍቅር አለን፡፡ አስከ ዛሬም ከአጠገባችን ተለይቶን አያውቅም፡፡

አቶ ዘሪሁን መደበኛ ሥራቸው መንድነው? አነስተኛ ንግድ ሥራ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በፖለቲካው ሥራ ያሳልፋል፡፡

ሥራውን አሁን እናንተ ቀጥላችሁበታል?ሥራው ቆሟል፡፡ ከአባታችን አናገኝ የነበረው -

ገቢ ተቋርጧል፡፡ከልጆቹ ሥራ የያዘ ሰው አለ?

የለም፡፡ለምን የእሳቸውን ሥራ እናንተ

አልቀጠላችሁም? ሥራውንም አናውቀውም፡፡ በመስመሩ ውስጥ -

አልገባንም፡፡ እሱ ሲሰራ የነበረው ከዱባይና ከቻይና ዕቃ የሚያመጡ ነጋዴዎችን እየተቀበለ ለቸርቻሪ ነጋዴዎች ማከፋፈል ነው፡፡ እኛ እንዳንቀጠልበት በመስመሩ ውስጥ አልገባንም፡፡ ይህንን ሥራ ለመስራት መተዋወቅ መግባባትና መተማመንን ይጠይቃል፡፡

አሁን በምን ትተዳደራላችሁ? እናታችን በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ -

በአነስተኛ ደሞዝ ትሠራለች፡፡ በአሁኑ ጊዜ በእሷ ገቢ ነው የምንኖረው፡፡

አቶ ዘሪሁን ከጓደኞቻቸውና ከአካባቢ ሕብረተሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዴት ትገልጪዋለሽ? ያደገው መርካቶ በመሆኑ ከሰው ጋር ለመግባባት ጊዜ

አይወስድበትም፡፡ ፈጣን፣ተጫዋች፣ሩህሩህና ከሰው ጋር መሥራት የሚችል፣ከሰው ጋር ተካፍሎ መብላት የሚወድ ሰው ነው፡፡ ኪሱ ውስጥ ያለው ገንዘብ አስኪያልቅ ድረስ ሰው የሚጠግብ አይመስለውም፡፡ አብረን መንገድ ላይ ስንሄድ ብዙ ጊዜ ስለሚያቆመን እንቸገራለን፡፡ መንገድ ላይ ያገኘው ሁሉ ዘርዬ፣ዘሬ እያለው ትልቁም ትንሹም ሲንጠላጠልበት ማየት የተለመደ ነው፡፡ ዘርዬ ፍቅር የሆነ አባት ነው፡፡

አባትሽ ወደ ፖለቲካው ሕይወት መቼና እንዴት እንደገቡ የምታውቂው ነገር ይኖራል?

አዎ ዘርዬ ለእኛ የሚደብቀው ታሪክ የለውም፡- ፡ እንደነገረን ወደ ፖለቲካው ሕይወት ያዘነበለው በቀድሞ መንግሥት ነው፡፡ ገና በ15 በ16 ዓመቱ በቀድሞ መንግሥት በአብዮታዊ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር/አኢወማ/ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያደርግ እንደነበር፤ኢህአዴግ አገሪቱን ተቆጣጥሮ ፓርቲዎች ሲቋቋሙ በመላው አማራ ሕዝብ /መአህድ/ ውስጥ ተደራጅቶ ታግሏል፡፡ ከፕ/ር አስራት ሞት በኋላ በመአህድ ውስጥ አለመግባባት በመፈጠሩ መአህድን ለቆ በመውጣት በመውጣት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት/ኢዲህ/ ገብቶ ነበር፡፡ ኢዲህ ከኢዴፓ ጋር ሲቀላቀል ቅልቅሉን በመቃወም ራሱን ከድርጅቱ አገላለ፡፡ በመጨረሻ ከተወሰኑ የትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲን /ኢብአፓ/ን መሠረቱ፡፡ ፓርቲው ከተመሠረተበት ጀምሮ በፕሬዝደንትነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

በመታሰራቸው ምን ይሰማሻል?ዘርዬ ተነጥሎን ስለማያውቅና ከታሰረም -

በኋላ የተፈጸመበትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በማየቴ እጅግ አዝኛለሁ፡፡ ለአገርና ለሕዝብ የሚከፈል መስዋዕትነት በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል፡፡

አባትሽ ታሰሩ የተባሉት “በሽብርተኝነት” ነው፡፡ “በልማት አውታሮች ላይ አደጋ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው ነው” ተብሏል፡፡ ታዲያ ይህ እንዴት

እኔ ይህንን አላምንበትም፡፡ በሽብር ተግባር ውስጥ ይገባል ይሳተፋል -

ብዬም አላስብም፡፡ አባቴን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ በሐዝብ ሀብትና ንብረት ላይ ውድመት ለመፈጸም በሰው ሕይወት አደጋ እንዲፈጠር ሊተባበር አይችልም፡፡ ሽብርተኞች እኮ ከሰብአዊ አመለካከት ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ስለ ሰው ልጅ ደንታ የሌላቸው ሱሰኞቹ ናቸው፡፡ ዘርዬ ግን አይደለም፡፡ ለሰው ፍጡር ትልቅ ክብር ያለው ነው፡፡ ወንጀልን በመከላከል ሥራ የሚሳተፍ እንጂ ወንጀል ለመፈጸም ተፈጥሮውም ባህርዩም አይፈቅድም፡፡

ወደ 9 የዞሯል

ወደ 6 የዞሯል

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

42ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 5ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

42ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 5ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ሽብርተኝነት ከ20ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ጀምሮ እየጎላ የመጣ አደገኛ ክስተት ነው፡፡ አደገኛነቱ በግልጽ የታየው እ.ኤ.አ መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም በኒውዮርክ ከተማ የንግድ ማዕከል ላይ በደረሰው ጥቃት ነው፡፡ በዚህ ጥቃት በሺዎች የሚቆጠር ህይወት ጠፍቷል፡፡ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዓለም ሕዝብ ላይ ይህ ነው የማይባል ድንጋጤና የመንፈስ ጭንቀት ፈጥሯል፡፡

ተንታኞች ሽብርተኝነትን በተለያየ መንገድ ገልጸውታል፡፡ የሥልጣኔዎች ግጭት ውጤት ነው ብለውታል፡፡ የምዕራቡ ሥልጣኔ በምሥራቅ ሥልጣኔ ላይ በአሳደረው መንፈሳዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ጥቃት ምክንያት ብሶት የወለደው ነው ብለውታል፡፡ በአንድ በኩል የራስን እምነት፣ የራስን ፍላጎት በሌላው ላይ በግድም ሆነ በውድ ለመጫን ከመፈለግ የሚመነጭ አምባገነናዊና አረመኔአዊ ድርጊት ነው ብለውታል፡፡ በሌላ በኩል የተነፈገ መብትን ለማስመለስ የሚጠቀሙበት የትግል መሣሪያ ነው የሚሉም አሉ፡፡

የሽብርተኝነት ጥቃት ዋና ኢላማዎች የምዕራቡን ዓለም ይወክላሉ የተባሉ ታላላቆቹና የለሙት አገሮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ከእነዚህ አገሮች ጋር የቅርብ ንኪኪ አላቸው የተባሉ አገሮች የሽብርተኝነት ሰለባ ሆነዋል፡፡ የሽብርተኝነት ዋና ሰለባዎች የለሙና የክርስትና ዕምነት ተከታይ የምዕራብ አገሮች ይሁኑ እንጂ ሌሎችም አገሮች በተለያየ ምክንያት በተለያየ ደረጃ የሽብርተኝነት ሰለባ ሆነዋል፡፡

የሽብርተኝነት ተጠቂ የሆኑ የምዕራብ ሀገሮች ሽብርተኝነትን ለመቋቋም የተለያዩ ርምጃዎችን ወስደዋል፤ በመውሰድ ላይም ናቸው፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ አስተባባሪነትና በሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅት (NATO) ጃንጥላ ሥር ተሰባስቡ ሌሎች አገሮች የሽብርተኝነት ምንጭ ነህ ብለው በፈረጁት አገርና አካባቢ ሄደው የማጥቃትም ይባል የመከላከል ጦርነት ከፍተዋል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ እነዚያ የ “ኔቶ” ሃገራት የፀረ -ሽብርተኝነት ጦርነታቸውን ለማሳካት እንዲያግዛቸው ከሌሎች በርካታ አገሮች ጋር የፀረ -ሽብርተኝነት ቃልኪዳን ተገባብተዋል፡፡ ሁለንተናዊ አቅማቸውን በማስተባበር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ተስማምተዋል፡፡ ከአሜሪካ ጋር በመተባበር ሽብርተኝነትን በጋራ ለመዋጋት ከተስማሙት ሀገሮች አንዷ ሃገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡

እነዚህ የሽብርተኝነት ሰለባ የሆኑ አገሮች የወሰዱት ሌላው ርምጃ ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚረዳቸውን ልዩ የፀረ -ሽብርተኝነት ሕግ ማውጣት ነው፡፡ የዛሬው ትኩረትታችንም እዚህ ላይ ነው፡፡ ሕግን በተመለከተ ሁለት አስተሳሰቦች አሉ፡፡ አንደኛው አስተሳሰብ ሽብርተኝነትን አገሩ በአለው መደበኛ ሕግ መከላከል ይቻላል፤ ስለዚህ ሌላ የተለየ ሕግ ማውጣት አያስፈልግም የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው አመለካከት ሽብርተኝነት ከዚህ በፊት ከተለመዱት ተራ ወንጀሎች የተለየ ባህሪ ስላለውና የተለየ አካሄድ፣ አያያዝና አሠራር ስለሚጠይቅ ልዩ ሕግ ያስፈልገዋል የሚል ነው፡፡ ለማንኛው ሁለተኛውን አመለካከት በመከተል የፀረ -ሽብር ሕግ ያወጡ በርካታ አገሮች አሉ፡፡

ዴሞክራሲ በሰፈነበትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ እንደይወድቅ እንደቆቅ ነቅተው የሚጠብቁ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም የነቃ ሕዝብ በአለበት፤ የመከላከያና የደህንነት ኃይሎች የገለልተኛና የዓለም አቀፍ ሰብአዊ ሕግ የዘለቃቸው በሆኑበት ሁኔታ የፀረ -ሽብርተኝነት ሕግ መውጣት ብዙም አያሰጋም፡፡ የተሳሳተ ርምጃ እንኳን ቢወሰድ ነፃነቱ፣ የሙያ ብቃቱና ገለልተኝነቱ ያለው የፍርድ ሥርዓት ርቆ ሳይሄድና ጉዳት ሳይደርስ ያስተካክለዋል፡፡

ፀረ -ሽብርተኝነት ሕግ አደገኛ የሚሆነው በአምባገነን ሥርዓቶች በሚመሩ አገሮች ውስጥ ነው፡፡ በዳበረ የዴሞክራሲ ሥርዓት በሚመሩ አገሮች ፀረ -ሽብርተኝነት ሕጉ የሚያተኩረው የውጭ አደጋን በመከላከል ላይ ነው፡፡ ከሥርዓቱ አሳታፊነትና ፍትሐዊነት የተነሳ በዘላቂነት የሚፈራ አደገኛ የውስጥ ጠላት የሚሉት ኃይል አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህ ሕጉ ሲወጣ የዜጎቻቸው ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለአግባብ እንዳይነኩ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ በአምባገነን ሥርዓት በሚመሩ አገሮችን ግን አምባገነኖቹ ኃይሎች የውጭ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ጠላትም እንዳላቸው ያምናሉ፡፡ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግበው ሕጋዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና ነፃ ጋዜጦችን የሚያይዋቸው እንደጠላት ነው፡፡ ማንኛውም ቆንጠጥ የሚያደርግ ትችት እንደ ጠላትነት መግለጫ ተደርጎ ይወሰዳል፤ ለአደጋም ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ አዋጁን የሚያወጡት የውጭ ጠላትን ብቻ ሳይሆን የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውንም ለማጥቃት በሚያመቻቸው መልክ ነው፡፡ አምባገነን መሪዎች የሚቀርፁት ሕግ ለደህነትና ለፖሊስ ከሞላ ጎደል ያልተገደበ የመያዝ፣ የመፈተሸ፤ የማሰር ሥልጣን ይሰጣል፡፡ አንቀጾች ለገዢዎች በሚያመች መልክ ለመተርጎም እንዲያመቹ አሻሚ ባህሪ የሰጣቸዋል፡፡ አንድ ድርጊት የሚያስቀጣ ወይም የማያስቀጣ መሆኑ በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ ስለዚህ ፓርቲዎች፣ ጋዜጦች ሕዝቡ በአጠቃላይ ዘወትር በስጋት ላይ ይሆናሉ፡፡ የፍርድ ሥርዓቱ በቁጥጥራቸው ሥር ስለሆነ የተፈለገውን የርምጃ ትዕዛዝ ለመስጠት ወይም ሥርዓቱ በሚፈልገው መንገድ ለመፍረድ ታዛዥ ይሆናል፡፡

ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ሁለት ጥቅም ያስገኝላቸዋል፡፡ አንደኛ በፀረ- ሽብርተኝነት ስም ከምዕራባውያን ኃያላን ጎን በአጋርነት በመቆማቸው በጥሬ ገንዘብም ሆነ በዓይነት (ለምሳሌ በመሣሪያ፣ በፖለቲካ ድጋፍ) ዳጎስ ያለ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ ሁለተኛ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም የሚያወጡት ሕግ የውስጥ የሥልጣን ተቀናቃኞቻቸውን ለማጥቃት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሽፋን ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ ነው ፀረ -ሽብርተኝነት ለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደ የተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ ነው የምንለው፡፡

ሽብርተኝነትን በጽናትና በቁርጠኝነት እንቃወማለን፤ እናወግዛለን፡፡ በፀረ -ሽብርተኝነት ሽፋን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚሰጥ አገዛዝንም በተመሳሳይ ጽናትና ቁርጠኝነት እንቃወማለን፤ እናወግዛለን፡፡

ፀረ-ሽብርተኝነትለአምባገነኖች ከሰማይ የወረደየተቀናቃኝ ማጥቂያ መሣሪያ

ከሰንደቅ ዓላማው ጋር የሚወክለው ህዝብ

ይከበር!

ፍኖተ -ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2ዐዐ3 ዓ.ምተመሠረተ፡፡ ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲናለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ሥር የሚታተምበፖለቲካዊ፣ በማህበራዊ፣ በመዝናኛ፣ በኢኮኖሚያዊናበወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የፓርቲው ልሣን ነው፡፡

ጋዜጣችን እንደ ፓርቲ ልሳን ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ ሚዛናዊ የግል ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል ይፈልጋል የማንኛዉም ሰዉ ሀሳብና አመለካከት የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት እንዲሆን እንሻለን ሰፊና ረዝም የሚዲያ ሽፋን ያለዉ ኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ አቋሙንና ፖሊሲዉን ለማቅረብ ቢፈልግ ክፍት ነዉ

ዋና አዘጋጅ፡- አንዳርጌ መሥፍንአድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 የቤ.ቁ አዲስ

አዘጋጆች፡- ብዙአየሁ ወንድሙ ብስራት ወ/ሚካኤል

አምደኞች፡- ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ኢ/ር ዘለቀ ረዲ አንዱዓለም አራጌ ግርማ ሠይፉ ዳምጠው አለማየሁ ተስፋዬ ደጉ በላይ ፍቃደ ወንድሙ ኢብሳ

ኮምፒውተር ጽሑፍ፡- የሺ ሃብቴ ብርትኳን መንገሻ

አከፋፋይ፡- ነብዩ ሞገስ

አሣታሚው፡- አንድነት ለዴሞክሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤ.ቁ አዲስ

አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትአራዳ ክ/ከተማ ቀበሌ 07 የቤ.ቁ 984

የዝግጅት ክፍሉ

ስልክ +251 922 11 17 62 +251 913 05 69 42 +251 118-44 08 40

ፖ.ሳ.ቁ፡ 4222

ኢሜይል፡- [email protected] [email protected]

ፋክስ ቁጥር፡- +251-111226288

ነፃ አስተያትርዕሰ አንቀፅ

ከዳዊት አስራደ

በህገ-መንግስቱ አንቀጽ ፰ ንዑስ አንቀጽ ፩ የኢትዮጵያ ብሔሮች፡ ብሔረሰቦች፡ ህዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸዉን ይደነግጋል። ንዑስ አንቀጽ ፪ እና ፫ ደግሞ ህገመንግስቱ የሉዓላዊነትታቸዉ መገለጫ እንደሆነና ይኸዉም በህገመንግስቱ መሰረት በሚመርጧቸዉ ተወካዮቻቸዉና በቀጥታ በሚያደርጉት ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ እንደሚረጋገጥ ያስረዳሉ። ነገር ግን ገዥዉ ስርአት ሲፈልግ ህገመንግስቱን ከቁብ ያልቆጠሩ ህጎችን በማዉጣት፤ሲያሻዉ ደግሞ ምንም አይነት ህግ ማዉጣት ሳያስፈልገዉ ህገ-መንግስቱን ሲረግጥና ሲጥስ ይታያል። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ በህገ-መንግስቱ እንደተደነገገዉ የሚወክሉትን እንደራሴዎች በነፃነት በመምረጥም ሆነ በሌላ ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ ሉዓላዊነቱን ለማስከበር ባደረጋቸዉ እንቅስቃሴዎች ምክንያትነት ከመሰደድ፣ ከመታሰር፣ ንብረቱን ከመወረስ፣ ታፍኖ ከመሰወር፣ከስራ ከመፈናቀልም ሆነ ባደባባይ በጅምላ ከመገደል ህገ-መንግስቱ ሲያስጥለዉ አልታየም። ይህ ስርአት በዴሞክራሲና በዚሁ መከረኛ ህግ ስም ሲምልና ሲገዘት በተደጋጋሚ የሚሰማ ቢሆንም አርቅቆ ላጸደቀዉ ህገመንግስትና የሉዓላዊነቱ መገለጫ ለሆነዉ ህዝብ ለመገዛት ፍቃደኛ አለመሆኑ በየቀኑ በመረጋገጥ ላይ ያለ ሀቅ ሆኗል።ለዚህም በየጊዜዉ በፖለቲካ አቋማቸዉ ምክንያት ለስደት የተዳረጉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች፤በመላ ሀገራችን የሚገኙ እስር-ቤቶችን ያጨ ናነቁት እስረኞች፤ ቢያንስ ቢያንስ በምርጫ 97 ማግስት ባደባባይ በጥይት የተቆሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች፤በየጊዜዉ ከስራ እየተፈናቀሉ ያሉት ዜጎች እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማን አለብኝነት ስርአቱ በብቸኝነት እንደፈለገ በሚሆንበት ፓርላማ ያፀደቀዉን “የፀረ-ሽብርተኝነት” አዋጅ ተከትሎ በስመ አሸባሪ በጅምላ ታፍሰዉ በማዕከላዊ እስር ቤት በግፍ ታስረዉ የሚሰቃዩ የፖለቲካ እስረኞችና ነፃ-ጋዜጠኞች አብይ ማረጋገጫ ሆነዉ ሊቀርቡ ይችላሉ።ከዚህም በተጨማሪ በመካከለኛዉ ምስራቅ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስደተኞች ያሉበትን አሰቃቂ ሁኔታና እየደረሰባቸዉ ያለዉን ኢ- ሰብዓዊ ግፍ የሚከታተል መንግስታዊ አካል አለመኖሩ የኢህአዴግ መንግስት ለህዝባችን ደህንነትና ክብር ግድ እንደሌለዉ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነዉ።በአርሲ ዞን “ኤራ ማኛ መቻራ” በተሰኘ የቻይና የመንገድ ስራ ድርጅት ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለዉን ግፍና እንግልት ለማስቆም 720 አባላት ያሉት የሰራተኛ ማህበር ቢመሰርቱም፤ ካለ አበልና ደሞዝ በፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ተደብድበዉ ተባረዉ ከስራም መታገዳቸዉ፤ የምትተዳደሩት በቻይና ህግ መሰረት በመሆኑም ምንም አይነት ጥያቄ ማንሳት እንደማይችሉ መገለፁ፤ በሀገራቸዉ ላይ በዉጭ አገር ዜጎች እየደረሰባቸዉ ያለዉን ግፍ መንግስት እንዲያስቆምላቸዉና መብታቸዉን እንዲያስጠብቅላቸዉ ጥያቄ ቢያቀርቡም ጆሮ ለማግኘት አለመቻላቸዉ ኢትዮጵያዉያን በሀገራችን የገዥዉን ስርዓት የሚረዱ የዉጭ ዜጎችን ያህል ክብርና ቦታ አለማግኘታችንን የሚያሳይ ተጨ ባጭ ሀቅ ነዉ። የባንዲራ ቀን መከበሩ እጅግ በጣም የሚመሰገን ተግባር ነዉ። ብሄራዊ ክብርንና የሀገር ፍቅርን ከትዉልድ ወደ ትዉልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አስተዋጽኦ አለዉና። ነገር ግን የህዝብ ሉዓላዊነት እንደፈለጉት በሚረግጥባትና ነፃነት ከመጥፋቱ የተነሳ ህዝብ በፍርሀት ቆፈን መንፈሱ ታስሮ በሚሰቃይባት ሀገር የባንዲራ ቀን ሰይሞ ባሸሼ ገዳሜ ማክበር በህዝብና በባንዲራ ከመቀለድ በቀር ሌላ ምን ትርጉም ሊሰጠዉ ይችላል? ባንዲራ የሚወክለው ሕዝብን ነውና፡፡ በርሀብና ካለማቋረጥ በመናር ላይ ባለዉ መልህቅ-አልባ የኑሮ ዉድነት የሚማቅቀዉን ህዝብ ማክበር፤ እንዲሁም በየጊዜዉ ለሚያነሳቸዉ የፍትህ፤ የመልካም አስተዳደር፣ የዴሞክራሲና የነፃነት ጥያቄዎች መልስ መስጠት ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ አጥብቄ አምናለሁ። በበለጸጉት አገራት እንደሚታየዉ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ ሁኔታና ማንነት ከፍ ሲል፤ ዴሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶቹ ሲከበሩና በስልጣኔ ጎዳና ሲራመድ ህዝቡን የሚወክለዉ ባንዲራ ክብር አብሮ ከፍ ይላል። የዜጎች የባንዲራና የሀገር ፍቅርም እንዲሁ። በተቃራኒዉ የህዝብ የኑሮ ሁኔታና ማንነት ዝቅ ሲል የባንዲራ ክብርና የሀገር ፍቅር አብሮ ይወድቃል። በመሆኑም የኢህአዴግ መንግስት ከማንኛዉም የፖለቲካ ጥቅምና ፕሮፓጋንዳ በፊት የህዝብ ክብር ቅድሚያ ሊሰጠዉ እንደሚገባ በአንክሮ ማጤን ይኖርበታል። ለዚሁ ቅዱስ ዓለማ በጽናት የቆመው የኢትዮጵያ ሕዝብ እምነቱ መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ ህዝብም ለማንነቱ ክብርና ለወደቀችዉ ባንዲራዉ ከፍ ማለት ከራሱ ሌላ ማንም ሊቆምለት እንደማይችል ተገንዝቦ ሰብዓዊ ክብሩን፤ ዴሞክራሲያዊ መብቱንና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ በታሪካዊዉ አንድነቱ አብሮ እንደሚቆም እምነቴ የፀና ነው፡፡

ጋዜጣችን “ፍኖተ-ነፃነት” ብለናታል፡፡ “ፍኖት” ማለት መንገድ ማለት ሲሆን ከነፃነት ጋር ሲጣመር “የነፃነት መንገድ” ማለት ነው!!

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

42ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 5ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

42ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 5ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ የደርግ አሃዳዊነትንና የኢህአዴግ ፌደራላዊነትን በተመለከተ ውይይት ለመክፈት ነው፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ እኔ አንድ አቋም አለኝ፡፡ ይህ አቋም የኢህአዴግ ፌደራላዊነት ከደርግ አሃዳዊነት የሚለየው በቅርጽ ብቻ ነው፡፡ በይዘት ወይም በአፈጻጸም ወይም በተግባር ግን ሁለቱም ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ናቸው የሚል ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የኢሕዴግ ስርዓት ፌደራላዊ ያልሆነ ፌደራሊዝም ነው ማለት ነው፡፡በውይይቱ ሂደት ይህ አቋም ትክክል ሆኖ ከወጣ አሁን አለን የምንለው ፌደሬሽን በቅርጽ ፌደራላዊ በይዘት ግን አሃዳዊ መሆኑን እንገነዘባለን ማለት ነው፡፡ እኔ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ አይደለሁም፡፡ የተግባር ፖለቲካ ግን የዕለት ተዕለት ሥራዬ ሆንዋል፡፡ በተለይ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፍ አሁን የምንከተለው የፌደራል ሥርዓት እውነተኛ ባህሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ፌዴሬሽን ምንድን ነው? ወደ ዝርዝር ሳይገባና በአጭሩና በተራ ቋንቋ ፌደሬሽን ማለት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ በተወሰነ መልክአ ምድራዊ ክልልና በግልጽ በተቀመጠ የመንግሥትነት ባህሪ ባለው የአስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች ወይም ስቴቶች ከሉአላዊነታቸው ቀንሰው በመስጠት በሚፈጥሩት ማከላዊና የጋራ የሆነ ሥልጣን አካል የሚተዳደሩበት ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ወይም ስቴቶች እያንዳንዳቸው መሠረታዊ ሉዐላዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ሕገ መንግሥት አላቸው፡፡ የዚሁ ሉዐላዊነት ሌላ መገለጫ የሆነ ሰንደቅ ዓላማም አላቸው፡፡ በቋንቋቸው ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አጠቃላይና የጋራ ሉዐላዊነታቸውን የሚያረጋግጥ ፌደራላዊ ሕገ-መንግሥትና ሠንደቅ ዓላማም አላቸው፡፡ ስለዚህ ሥልጣን በማዕከልና በፌደሬሽኑ አባላት መካከል የተከፋፈለ ነው፡፡ የፌደሬሽኑ አባላት ለፌደራሉ በፈቃዳቸው ከሰጡት ሥልጣን ውጭ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን አላቸው፡፡በአንጻሩ በአሐዳዊ መንግሥት ሥርዓት ሙሉ

ሥልጣን የሚያዘው በአንድ ማዕከላዊ አካል ነው፡፡ ክልሎች ሕግ የማውጣትም ሆነ ፖሊሲ የመቅረጽ ሥልጣን የላቸውም፡፡ ሆኖም ማዕከላዊው መንግሥት በሕግ የተመጠነ ሥልጣን ለክልሎች በውክልና ሊሰጠ ይችላል፡፡በኢህአዴግ አሐዳዊ ሥርዓት የፌዴራሉ መንግሥት አባላት ዘጠኝ ሲሆኑ እነዚህም የትግራይ፣የአፋር፣የአማራ፣የኦሮሚያ፣የሱማሌ፣የቤንሻጉል/ጉሙዝ፣የደቡብ ብሔሮች/፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣የጋምቤላ ሕዝቦችና የሐረሪ ሕዝብ ክልሎች ናቸው፡፡የደርግ አሐዳዊ ሥርዓት በ5 ራስ ገዝ አካባቢዎችና በ24 የአስተዳደር አካባቢዎች በድምሩ በ29 አካባቢዎች የተዋቀረ ነበር፡፡

አምስቱ ራስገዝ አካባቢዎች የሚከተሉት ነበሩ፡-1. ኤርትራ ራስገዝ 2. የትግራይ ራስገዝ 3. የአሰብ ራስገዝ4. የድሬደዋ ራስገዝ5. የኦጋዴን ራስገዝ

የአስተዳደር አካባቢዎች፡-1. የሰሜን ጎንደር 2. የደቡብ ጎንደር 3. የሰሜን ወሎ 4. የደቡብ ወሎ 5. የምስራቅ ጎጃም 6. የምዕራብ ጎጃም 7. የመተከል 8. የአሶሳ 9. የወለጋ 10. የሰሜን ሸዋ 11. የዲስ አበባ 12. የምዕራብ ሸዋ13. የደቡብ ሸዋ14. የምዕራብ ሐረርጌ15. የመሥራቅ ሐረርጌ16. የአርሲ17. የባሌ18. የጋምቤላ19. የኢሉባቦር

20. የከፋ21. የጋሞጎፋ22. የሲዳሞ23. የኦሞ 24. የቦረና አካባቢዎች ነበሩ፡፡

ራስ ገዝ የተባሉት 5 አካባቢዎች የጠረፍ አካባቢዎች፣የፀጥታ ችግር ያለባቸውና በጂኦ ፖለቲካዊ ባህሪያቸው ምክንያት ለሃገሪቱ ደህንነትና ሠላም ሲባል ከሌሎቹ አካባቢዎች በተለየ ዓይን ሊታዩና የተለየ ሥልጣን ሊሰጣቸው ይገባል ተብለው የታሰቡ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ሆኖም የኢሕዲሪ ሕገ-መንግሥት ፀድቆ ሲወጣ በራስ ገዝና በአስተዳደር ክልሎች መካከል የረባ የመብትም ሆነ የሥልጣን ልዩነት አልነበረም፡፡ የኢህዲሪ ሕገ-መንግሥት ራስ ገዝ አካባቢዎች የሚኖራቸው መብትም ሆነ ሥልጣን በሕግ ይደነገጋል በማለት አልፎታል፡፡ ሆኖም የተባለው ሕግ ሳይወጣ ሥርዓቱ ፈረሰ፡፡የኢህአዴግ የፌደራል መንግሥት አባላት በወረቀት ላይ ያላቸው መብትና ሥልጣን የደርግ ሥርዓት ራስ ገዝና የአስተዳደር አካላት ከነበራቸው መብትና ሥልጣን እጅጉን የላቀ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ሆኖም ሁለቱን ሥርዓቶች አንድ የሚያደርጋቸው አንድ ነገር አለ፡፡ ሁለቱም እጅግ የተማከለ፣የመቆጣጠሪያ መዋቅሩ ከማዕከል እስከ ቀበሌ ድረስ የወረደ የፓርቲ ሥርዓት ሰለባዎች ናቸው፡፡ የደርግ ራስ ገዝና የአስተዳደር አካባቢዎች የኢሠፓ የቁጥጥር ሥርዓት ሰለባዎች ነበሩ፡፡ የአሁኑ የፌደራል መንግሥት አባል መንግሥታትም የኢህአዴግ ቁጥጥር ሥርዓት ሰለባዎች ናቸው፡፡ የደርግ ራስ ገዝና የአስተዳደር አካላት በአሃዳዊ መንግሥት ፈቃድ በውስጥ አስተዳደራቸው ትንሽ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት (autonomy) ቢኖራቸውም ከማዕከል እስከ ቀበሌ የተዋቀረው ኢሠፓ የአለቻቸውን ትንሽ ነፃነት ይወስድባቸዋል፡፡ የራስገዝም ሆነ የአስተዳደር አካባቢዎች የኢሰፓ ከፍተኛ ካድሬዎች ነበሩ፡፡ በአጠቃላይ የራስ ገዝና የአስተዳደር አካባቢዎች እንቅስቀሴ የሚኖሩትና ፕሮግራሞችን ተግባራዊ የሚያደርጉት የኢሠፓ መሪዎች ነበሩ፡፡ ራስ ገዝና

የአስተዳደር አካባቢዎች ተግባራዊ የሚያደርጉት የኢሠፓን ፕሮግራም ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ድሮውንም ሥርዓቱ ከስም (ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ) በስተቀር ዴሞክራሲያዊ ስላአልነበረ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር መዋሉ አያስደንቅም፡፡የአንድ ፓርቲ ቁጥጥር አለአግባብ መሆኑ ጎልቶ የሚታየው ከፌደራላዊ ሥርዓቱ ጎን ለጎን ሲታይ ነው፡፡ ፌደራላዊ ሥርዓት በአግባቡ ከተተገበረ ለኢትዮጵያ ተስማሚና ተገቢ ሥርዓት ነው፡፡ ሕገ መንግሥት ጸድቆ ፌደራላዊ ሥርዓት ተመሠረተ ሲባል የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ ቀን መጣ ብሎ ተስፋው ለምልሞ ነበር፡፡ ሆኖም የተያዘው ተስፋ ሁሉ ከወረቀት ባለፈ በተግባር ወደ ዕለት ተዕለት ሕይወት አልሸጋገር አለ፡፡ በተለይ የፌዴራል ሥርቱ እንደተጀመረ አብዛኛዎቹ ክልሎች በኢህአዴግ የተመደቡ የቅርብ ተመልካቾች ነበሯቸው፡፡ የእነዚህ ተመልካቾች ዋና ሥራ እነዚህ አዳዲስ ባለሥልጣን ክልሎች ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ እንዳይሄዱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ መቆጣጠርና የተፈለገውን መሥመር እንዲይዙ ማድረግ ነበር፡፡ ይህ አሠራር አሁንም እንደቀጠለ ነው የሚታመነው፡፡ ምናልባት አሠራሩ ይበልጥ የተራቀቀ ይመስላል፡፡ ዘጠኙ የፌደራሉ መንግሥት ራሳቸውን በራሳቸው ለማስተዳደር የሚያስችላቸው ሙሉ ሥልጣን የሚሰጣቸው ሕገ መንግሥት አላቸው፡፡ ሠንደቅ ዓላማም አላቸው፡፡ በቋንቋቸው ወይም በመረጡት ቋንቋ ራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ሆኖም ይህ ያልተማከለ የአሠራር ዕቅድ፣እጅግ በተማከለና መዋቅሩን እስከ ቀበሌ በዘረጋ የአውራ ፓርቲ አሠራር ሥርዓት ተጠፍሯል፡፡ ስለዚህ ያልተማከለው የፌዴራል ሥርዓት እንደታሰበው በነፃነት ሊሠራ አልቻለም፡፡ ግልጽ ሆኖ የሚታየው የፌደራልና የተማከለ የአውራ ፓርቲ ሥርዓት አብረው ሊሄዱ እንደማይችሉ፡፡የፌዴራል ሥርዓት የሚሠራው ነፃነትና የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት በሰፈነበት ሁኔታ ነው፡፡ ነፃነት በሌለበት፣የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ባልሰፈነበት እውነተኛ የፌዴራል አሠራር ሊኖር አይችልም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የፌደራል መንግሥቱ

ፌደራላዊ ያልሆነ ፌደራሊዝም

ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ

ፋና ወጊነታቸው ዘመናዊውን ትምህርትና ህሳቤ በመቅሰም ይጀምራል፡፡ የ14 ዓመት ልጅና የ6ኛ ክፍል ተማሪ እያሉ ከሐረር በ1937 ዓ.ም ከሌሎች ሦስት ተማሪዎች ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ መጡ፡፡ ለመምጣትም ምክንያት የሆናቸው በጊዜው በአካባቢያቸው ከ6ኛ ክፍል በላይ የሚያስተምር ት/ቤት ባለመኖሩ ነበር፡፡

አዲስ አበባ ደርሰውም መጀመሪያ በሊሴ ገብረማርያም ት/ቤት ቀጥሎም በኮልፌ ዕደ ጥበብ ት/ቤት በአዳሪነት በመግባት ትምህርታቸውን መከታተል ያዙ፡፡ የፈተና ውጤታቸውም በደረጃ ከሚያልፉ ተማሪዎች ተርታ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ታዋቂ እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡ ቢሆንም ግን በዚህ ት/ቤት ሃሳባቸው ሊሰክን ባለመቻሉ ወደ ት/ሚኒስቴር በመሄድ በጊዜው የሚንስትሩ አማካሪ አሜሪካዊው ዶ/ር ሩክሜክ ዘንድ በመቅረብ የሚፈልጉትን አስረዱ፡፡ ዶክተሩም ብላታ ጌታዬ አስፋው የሚሹትን ለማግኘት ፈተና እንዲወስዱ አደረጓቸው፡፡ እሳቸውም ፈተናውን በጥሩ ውጤት አልፈው በ1933 ዓ.ም ወደ ተከፈተው ተግባረ-ዕድ ት/ቤት በአዳሪነት ተመዝግበው ገቡ፡፡ በግቢው 1ኛ ፎቅ ላይ የሚኖሩት ዶ/ር ሩክሜክም እያበረታቷቸው ትምህርታቸውን በትጋት ቀጠሉ፡፡

ብላታ ጌታዬ አስፋው ዝንባሌያቸው ማስተማር በመሆኑ ወደ መምህራን ማሠልጠኛ እንዲዛወሩ በመጠየቅ በ1939 ዓ.ም በወቅቱ ጉለሌ ይገኝ ወደ ነበረው መምህራን ማሠልጠኛ ገብተው በ1943 ዓ.ም ትምህርታቸውን አጠናቀቁ፡፡ ትምህርታቸውን እንደጨረሱም ደብረብርሃን ኃ/ማርያም ማሞ 1ኛ ደረጃ ለ10 ወራት እንዳስተማሩ አዲስ አበባ አርበኞች ት/ቤት ተዛውረው እንዲያስተምሩ ከት/ሚኒስቴር ትዕዛዝ ይደርሳቸዋል፡፡ ትዕዛዙንም ተቀብለው ቀን እያስተማሩ በማታው የትምህርት ክፍለ ጊዜ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ በነበረበት ጊዜ ሎንዶን የነፃ ትምህርት ዕድል አግኝተው በ1947 ዓ.ም ወደዚያው አቀኑ፡፡

ሎንዶን ደርሰውም “School of Oriental and African study” በሚባለው ተቋም ገብተው በአፍሪካ ጥናት ቢኤ ዲግሪያቸውን አገኙ፡፡ ወደ አገር ቤት ተመልሰውም ክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል በሚመሩት ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ ከዩኔስኮ የሚሰጡ መጽሐፍትን መተርጎም ጀመሩ፡፡

የስነ-ጽሑፍ ጉዞብላታ ጌታዬ በውስጣቸው ያለውን ተሰጥኦ የበለጠ

ለማውጣትና ለመጠቀም እንደያመቻቸው በ1940ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በ1939 ዓ.ም የተመሰረተው የደራሲያን ማህበር አባል ሆኑ፡፡ በጊዜው የማህበሩ አባል ለመሆኑ የሚያስፈልገው መስፈርት በዘርፉ አንድ ሥራ ለተደራሲያኑ ወይም ለተመልካቹ ማቅረብን ግድ ይል ስለነበር እሳቸውም የ “ፍቅር ጮራ” የተሰኘውን የፍቅር ታሪክ ደርሰው ለሕዝብ አቅርበው ነበር፡፡

ይህ ትያትር የመጀመሪያው ዘመናዊ የፍቅር ታሪክ ሆኖም ይታወቃል፡፡ የ “ኤርትራ ጉዳይ” ን የፃፉት አምባሳደር ዘውዴ ረታ በፍቅር ተመርኩዘው የፃፉትን ትያትር ቀዳሚ ሣይሆን አይቀርም የሚሉ አንዳንድ ግለሰቦች ቢያጋጥሙኝም አብዛኞቹ ግን ከፋሽስት ወረራ በኋላ በ1944 ዓ.ም በቀድሞው የማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የቀረበው የብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ በፍቅር ላይ የተመሰረተው ትያትር ቀዳሚ መሆኑን ይስማማሉ፡፡ ከእሳቸው በፊት አገርንና ጀግንነትን በተመለከተ እነ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ትያትሮችን ይጽፉና ያዘጋጁ የነበር ሲሆን “አፋጀሽኝ” ትያትርም የዚሁ አካል ነበረች፡፡

በጊዜው የማሕበሩ አባላቶች ጸሐፊና ገጣሚ የነበሩት ከፍተኛ የሃገሪቷ ሚንስትሮች ነበሩ፡፡ ቀዳሚ የማሕበሩ ፕሬዝዳንት ክቡር ራስ ቢትወደድ መኮንን እንዳልካቸው (በዝነኛው “አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም” ድርሰታቸው ይታወቃሉ) ሲሆኑ ቀጥለውም ደጃዝማች ግርማቸው ተ/ሐዋርያት ማሕበሩን መርተዋል፡፡ ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራም በጸሐፊነት ተመርጠው አገልግለዋል፡፡

ብላታ ጌታዬ የደራስያን ማሕበርን መመስረት ለምን እንዳስፈለገ ሲናገሩ “ . . . የኢትዮጵያ ደራስያን ታሪክ ሲነሳ ዘመኑ የትየለሌ ነው፡፡ በጊዜው ማሕበር ባይቋቋምም እነ ማን ይጽፉ እንደነበር በአብዛኛው መረጃ ባይኖርም በየገዳማቱና ቤተ-ክርስቲያኑ የሰማዕታቱን ገድል ጨምሮ የፀሎት መጽሐፍንና ሌሎች ሐይማኖታዊ መጽሐፍትን የዕህል ዘርና ቅጠላቅጠል እየጨመቁ የተለያዩ የቀለም ዓይነቶችን በማውጣት በቀሰምና በላባ እየፃፉና እየሳሉ ለተከታታይ ትውልድ ያስተላልፉ የነበሩ ሁሉ መረሳት የለባቸውም. . .፡፡” የሚሉት ብላታ ጌታዬ ማሕብሩ በጊዜው ሲመሠረት በዋናኘት አላማው አድርጎ የተነሣው በሃገሪቷ ያሉት የጽሑፍ ቅርሶች በዋናኝነት ተሰባስበው እንዲታተሙና ሌሎች አዳዲስ ጸሐፍትን ለማፍራት እንደነበር ይገልፃሉ፡፡ የአሁኑ የሃገሪቷ

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የደራስያን ማሕበሩ ገንዘብ ያዥ በነበሩበት ጊዜም መንግሥት የመጽሐፍ ህትመትን ወጪ ¼ኛ እንዲሸፍን ካደረጉት መሃል አንዱ እንደነበሩ ያስታውሳሉ፡፡ ምንአልባትም ከቀደምቶቹ የማሕበሩ አባላት በአሁኑ ጊዜ በሕይወት የምንገኘው ሁለታችን ብቻ ሣንሆን አንቀርም ይላሉ፡፡

ይኸንኑ ¼ መንግሥት ይሸፍነዋል የሚባለውን ወጪ ብርሀንና ሠላም ህትመቱን ካከናወነ በኋላ ያልተሸጠው ት/ሚኒስቴር እንዲገዛው ተደርጐ ት/ቤቶች ለሪፈረንስ (ማጣቀሻ) እንዲጠቀሙበት ይደረጋል፡፡ ንጉሱም (ቀ.ኃ.ሥላሴ) ለመጽሐፍ ትልቅ ፍቅር ስለነበራቸውና አርአያ ለመሆን ቲያትርን እንደሚመለከቱና እንደሚገመግሙ ሁሉ ወመዘክር (ብሔራዊ ቤተ- መዛግብትና መጽሐፍት ማዕከል) በመገኘት በመጽሐፍ ሒስና ውይይት ላይ ይካፈሉ እንደነበርም ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ ያን ዘመን በአድናቆት ያስታውሱታል፡፡ብላታ ጌታዬ ሀገራችን በእኛ አቆጣጠር በ1940 የዩኔስኮ ኃላፊ የነበሩት ክቡር አቶ አካለ ወርቅ ሀ/ወልድ ፈረንሣይ ፓሪስ ለስብሰባ በተገኙበት ጊዜ ሃገራችን በየአመቱ 40 ሺ ዶላር ለመክፈል በመስማማት ግዴታዋን ስትወጣ በአንፃሩም በአባልነታቸው በርካታ መጽሐፎችን ያገኙ እንደነበር ይመሰክራሉ፡፡

የማህበሩ ፕሬዝዳንት ክቡር እንዳልካቸው መኮንን በነበሩበት ወቅት በርካታ መጽሐፍትን አሣትመዋል፡፡ እንዳልካቸው መኮንን ፒያሣ ኪንግ ጆርጅ ቡና ቤት አጠገብ “ጆና ፕሎስ” ከሚባል አርመናዊ መጽሐፍ ነጋዴ መደብር ቀጥሎ “መድሐኔዓለም” የተባለ የመጽሐፍ መሸጫ በመክፈት ለንባብ ባህል መዳበር ከፍተኛ ዕገዛ እንዳደረጉ የሚናገሩት ብላታ ጌታዬ አስፋው ፀሐፊ ተውኔት መንግስቱ ለማ ማህበሩን በፀሀፊነት ለረዥም ጊዜ እንዳገለገሉና ከሣቸው ጋርም እነ ክቡር አበበ ረታን የመሣሠሉ ግለሰቦች እንደነበሩ ያስታውሣሉ፡፡

ብላታ ጌታዬ ስለ-ሥነ ፀሐፍትና መጽሐፍት ይኸን ይላሉ፡፡ “ሥነ ጽሑፍ አፍቃሪ ለብቻው፤ ባለሙያው ወይም የተፈጥሮ ስጦታ ያለው ለብቻ ተከፋፍለው መታየት አለባቸው፡፡ አፍራሪና ተሰጥኦ ያለው ሁሉ ተደበላልቆ ፀሐፊ ወይም ደራሲ እየተባለለ ሊጠራ አይገባውም፡፡” ሲሉ አጥብቀው ያሰምሩበታል፡፡

አያይዘውም የሥነ ጽሑፍ ሰው ቅኔን የተቀኘ (የዘረፈ) ቢሆን ይመረጣል፡፡ ቅኔ አእምሮ አስፍቶ ሀሣብን ያዥጐደጉዳል፡፡ አንዳንዴም ቅኔ ባይዘረፍም ሊሣካ ይችላል፡፡ ምሣሌ መጥቀስ

ቢያስፈልግ ቆዳ ነጋዴና የትምህርት ሚኒስቴር ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ቅኔ የዘረፉ አልነበሩም ይላሉ፡፡ የበርካታ መጽሐፍት ፀሀፊና ተርጓሚ የነበሩት መኮንን ኃ/ወልድም በቤተ ክህነት ትምህርታቸው ክድቁና እንዳልዘለሉ ያስታውሣሉ፡፡

ስለ ክቡር ዶ/ር ሀዲስ አለማየሁ ሲነሣም ክቡር ዶ/ር ደጃዝማች ዘውዴ ገ/ህይወት ሞት ቀደማቸው እንጂ እሳቸው ዘንድ የሚገኘውን የዶ/ር ሀዲስ አለማየሁን ሥራዎች ሊያስረክቧቸው እንደነበርና እንዲሁም ፕላዛ ሆቴል ጀርባ ያለው መኖሪያ ቤታቸውን ታሪካዊ በማድረግ የሥነ ጽሑፍ ባለውለታነታቸውን ለመዘከር አስበው እንደነበር ብላታ ጌታዬ ይናገራሉ፡፡

በጊዜው የነበሩት ፀሀፍት ለህዝብ ታሪክና ዕውቀት ቅድሚያ የሚሰጡና የሚጨነቁ በመሆኑ ለጽሑፋቸው አንድም ጊዜ እንዲከፈላቸው ሲደራደሩ ሆነ ሲናገሩ አይደመጡም የሚሉት ብላታ ጌታዬ በደርግ ጊዜ በግፍ የተገደሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቴዎፍሎስ ለህዝቡ ማስተማሪያ የሚያገለግል 12 ሺህ ኮፒ መጽሐፍ ተንሣኤ ዘ- ጉባኤ ማተሚያ ቤት እንዲያሣትሙ አዘዋቸው እንደፈፀሙ ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜም ከ40 አመት በላይ ያስቆጠረው ቼምበር ማተሚያ ቤትን ለማቋቋምም ከጣሊያን ወረራ በፊት የነበረ “ሱርማኒያ” የተሰኘ ማተሚያ ቤትን ከተመለከቱ በኃላ የሚፈልጉትን እንደልባቸው ለማተም በመፈለጋቸው ያቋቋሙት መሆኑን ይገልፃሉ፡፡

ãረ አይደረግም!የሀገሪቷን መንፈሣዊ እሴቶችን ጠብቆ ለማቆየትና

ለትውልድ ለማስተላለፍ እንዲቻል በፀሐፊነት አንድ ይደረግ የነበረው ታላቅ ጥራት ለዛሬ መሠረት መሆኑ የማይካድ ነው፡፡ ያ ! ትውልድም ይሔ ይደረግልኝ የሚል ቅድመ ሁኔታ ሳያስቀምጥ ሀገራዊና ሞራላዊ ግዴታውን ተወቷል፡፡ ይህ ዓላማውም ዘላቂ እንደሆነ ትውልዳዊ ራዕይ ወሣኝ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡

ከዚህ በመነሣትም የአንጋፋውን ታሪካዊ ድምፃዊ ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠን የህይወት ታሪክ ለመፃፍ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በገንዘብ ተደራድሮአል የሚባለውን ብላታ ጌታዬ እንደሰሙ ክፉኛ መደንገጣቸው አስታውሣለሁ፡፡

ቀጣዩ ክፍል ሣምንት

ወደ 13 የዞሯል

ከገፅ 8 የዞረከ” ኮ”ና “ካ” የፈለቀች ...

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

62ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 7ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

62ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 7ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ተመስጦ (meditation) በሆነ ነገር ላይ ትኩረት መፍጠር ነው፡፡ አንዲት እናት ልጇን ለማስተኛት አሊያም መነጫነጩን እንዲተው የማደንዘዣ ዘዴ አላት፡፡ “እሽሩሩ….” የሚለውን ቃል መደጋገም ብቻ ነው፡፡ ልጇም በመጨረሻ ወደ ፀጥታው የእንቅልፍ አለም ይሄዳል፡፡ “እሹሩሩ” ማለት ማንቃት አይደለም፡፡ የማስተኛ ማደንዘዣ ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስማችንን/ የምናውቀውን ሰው ስም ለተወሰነ ጊዜ በተደጋጋሚ ብንጠላው ከዚህ በፊት የሰጠነው የአይነት፣ መጠን ቀለምና የመሳሰሉት ተመሳስሎሾች ይጠፋብናል፡፡ ከዚያም ብሶ ራሳችንን/ የጠራነውን ሰው ወደ አለማወቅ የሚደርስ ብዥታ ይጠፋብናል፡፡ ከዚያም ብሶ ራሳችንን /የጠላነውን ሰው ወደ አለማወቅ የሚያደርስ ብዥታ ይፈጥርብናል፡፡ እንደነዝዛለን፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ሕዝብ “እሹሩሩ”ን በመደጋገም ያደነዝዛል፡፡ በመደንዘዛችን ደግሞ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ አካባቢ እንዳለን ጭምር ይጠፋብናል፡፡ የቃሉ ድግግሞሽ የፈጠረብን ውዥንብር፣ በህልም አለም

ስለሚያሰክረን ድህነት ላይ ሆነን ድህነትን እንረሳለን፡፡ አሊያም ድህነትን “በልማት” ስም የበለጠ እንላመደዋለን፡፡ እየተለማመድነውም ነው፡፡ “የቸኮለ ሰው ሲቆም የሄደ ይመስለዋል” በድህነት የኖረ ደግሞ ሲያወራ የበለፀገ ይመስለዋል፡፡ ጉንጭ አልፋ የማይላቀቀን የድህነት ኑሮ በልማታዊ በፕሮፓጋንዳ ድህነት ተጭኖን ደህነትን ረስተነዋል፡፡ “ባለፉት አምስት አመታት በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅና እጅግ የምንኮራበት ልማት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ የዚህን ድል ታላቅነት አቃሎ ማየት ፍፁም አይችልም” (አዲስ ራዕይ መጋቢት ሚያዚያ 2000 p. 33) ህዝቡ ለአመፅ እንደማይነሳሳ ለማሳመን ከ2 ዓመታት በኋላ አዲስ ራዕይ እንዲህ ትላለች፤ “… “በአገራችን የለውጥ ጉዞ ርካታ ሊያገኝ በመቻሉ የቀለም አብዮት መሳሪያ የሚሆንበት እድል ከቶውንም ሊከሰች አይችልም!!”(አዲስ ራዕይ -መጋቢት ሚያዝያ -2002 p. 10)

“ስለልማት ሲነሳ ኢትዮጵያ እንደ አገር …. ለምሳሌ የሚጠቀስ እንኳን የሚኖርባት አገር ነበረች፡፡ ዛሬ ምሳሌዎችን ጠቅሰን አንዘልቀውም፡፡ እድገቱና ልማቱ

ደግሞ ልዩ ባህሪ አለው” (ህዳሴ -ልዩ ዕትም -መጋቢት 2002 p.27)ይህ ዘዴ፣ ለነገሮች ያሉን የመጠን እና አይነት ግንዛቤን ያደበዝዛል፤ ያደነዝዛል፡፡ ለምሳሌ ደርቅና ርሃብ ማለት የ1966ቱ እና የ1977ቱ መጠን እና ዓይነት መሆን አለበት ብለን ካሰብን እውነትም የችጋርን አለንጋ ለምደናል፡፡ በችጋር ውስጥ ሆነን ችጋር ማለት ልክ እንደ 19977ቱ ሁሉ የሚላስ የሚቀመስ ሙሉ በሙሉ የሚጠፋበት ጊዜ እንጂ ቁርስ በልቶ ምሳ እና እራት ያለመድገም ወይም ያልተመጣጠነ ምግብ መጠረቅ ስለማይመስለን “ዲማ ከዚህ መንደር ይርቃል?” በማለት ባሰብነው ግዝፈት ልክ እንጤቃለን፡፡ ይህን ሲል ሌላ ነገር ትዝ አለኝ፤ “ላላዋቂ ፎገራ ዱሩ ነው” የሚል ተረት፡፡

ያን ባሰብኩ ቁጥር አለማወቅ ምን ጨለማ፣ ምን ከባድ፣ ምን የተምታታ ድፍን ያለ ነገር ነው? እላለሁ፡፡ ፒያሳ፣ ጥቁር አንበሳ ቡና ቤት ቁጭ ብዬ ሻይ እየጠጣሁ ሽንት ቤት መጠቀም ፈለግሁ፡፡ አንድ ሁለቴ በመጠማዘዝ ሄጄ በመኝታ ክፍሎች መሃል ላይ ስደረስ ግራ ገብቶኝ ቆምኩ፤

አሰብ አረኩኝና ወደ ኋላ ተመልሼ “ሽንት ቤት ወዴት ነው?” ብዬ የመኝታ ቤት ተቆጣጣሪዋን ጠየቅኋት፡፡ “ላላዋቂ ፎገራ ዱፋ ነው፡፡” ብላኝ ተንከትክታ ሳቀች፡፡ ለካ በሩ ላይ ደርሼ ወደ ኋላ ተመልሼ ኑሯል፡፡ እኔ የማወቃቸው ሽንት ቤቶች በሆነ ጥግ የተውሸለሸሉ እንጂ በዚህ አይነት የተገጠገጡ አልነበሩም፡፡ ሽንት ቤት በር ቆሜ ሽንት ቤት መጠየቄ ከተረታችን ጋር ምን ያገናኘው እንደሆነ ጠየቅኋት፡፡ እንዲህም አለችኝ “ብዙ ሰዎች ወደ ጎንደር ሲሄዱ አንድ እጅግ አውላላ የሆነ የከብት ሰራዊት የወረረው ሜዳ ላይ ይደርሱና ለመሆኑ ፎገራ ወዴት ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በእነርሱ ቤት ፎገራ ዱር መሆኑ ነው፡፡ ፎገራ ገደላ ገደል፣ ፎገራ ማለት ሩቅ መሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን ቆመው የጠየቁበት ውብ ሜዳ ራሱ ፎገራ ኑሯል፡፡” በማለት አስደመመችኝ “እንጨቆረር ግባ” እንደሚባለው ይሆን? በጣም ቅርብ የሆነውን ቦታ ሩቅ አድርጎ መሳል? እየራበን ከችጋር ላይ ቁመን፣ ችጋር እየጠበሰን “ልማት ልማት” በሚለው ፕሮፓጋንዳ ደንዝዘን ርሃቡ ጥጋቡ፣ ደህነታችን ልማት እየመሰለን በቁማችን ሙተን ኖርን እንላለን!!

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ኢሕአዴግ ይነግረናል:: ኢቲቪም አይታክትም፡፡ ከአንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች… ጀምሮ እስከ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ድረስ የፖለቲካውን ቀጥ ያለ እድገት የማያንቆለጳጵስ የለም፡፡ ቀጣዩን ከአቶ መለስ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ካየን ግን እውነታው ሌላ ይሆናል፡፡

“ጥያቄ- የበኩር ልጅዎ ለኃላፊነት የምትበቃበት እድሜ እየደረሰ ነው፡፡ እርስዎ ወደ በረሃ የሄዱት በ19 ዓመትዎ ሲሆን የእርሷ እድሜ ከዚያ በላይ ነው፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው ምኞትና ፍላጎት ተፅዕኖ ማድረግ ባይችሉም ሁሌም መልካሙን ነው የሚመኙላቸው፡፡ ስለዚህ የእርሷን ምርጫና ውሳኔ ወደ ጎን በመተው ፖለቲካ ውስጥ እንድትገባ ይፈልጋሉ፣ ይመኛሉ?”

“አቶ መለስ፡- እንደ መታደል ሆኖ እኔ አልወስንላትም፡፡ መወሰን ብችል ኖሮ ግን ከዚህ ዓይነቱ ህይወት እንድትርቅ በመከርኳት፤ ሆኖም እንዲህ ዓይነቱን ህይወት ለመኖር የሚያስችል ፅናት በውስጧ ካለ ፅናቱን ይስጥሽ እላታለሁ፤ ምክንያቱም እንዲህ አይነቱን ህይወት ለመኖር ፅናቱ ከሌለ መቀጠል ስለማይቻል፡፡ ስለዚህ ውስጧ የሚንቀለቀል ስሜት ከሌለ ፖለቲካ ውስጥ ለመግባት ፈፅሞ ማሰብ የለባትም፡፡(ሰረዝ የራሴ) ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ልጆች መምከር የሚፈልገውም የሚከተለውን ነው፡፡ ከውስጥ የሚንቀለቀል ስሜትና ፅናት አለን ብላችሁ ከገመታችሁ ፖለቲካ ውስጥ ግቡ፡፡ ይህ ፅናት ከሌላችሁ ግን ለራሳችሁ ጤንነት ስትሉ ከፖለቲካ ራቁ፡፡(ሰረዝ የራሴ)

(ትኩእ:መለስ ከልጅነት እስከ እዉቀት: 58 & 59)

በዚህ የአቶ መለስ አነጋገር አብዛኛውን እስማማለሁ፡፡ ሙያ (Profession) ያዝናናል፤ በእውቀት እና ልምድ ያበለፅጋል፡፡ አሰራርና

ስርዓት ስለሚገዛው በያንዳንዱ ቀናችን ጎልባች ያደርገናል፡፡ ኢ-ሙያዊ (non- professinal) የሆነ ጉዳይ ግን ካንሰር ነው፡፡ ምርታማነትን፣ ጉልበትን፣ ውጤታማነትን እና ጤናን ይበላል፡፡ ይባስ ብሎ ነፍስን ይበላል፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካም እንዲሁ ነው፡፡ ለዲፕሎማሲና ለምርጫ ሰሞን እንደሚባለው አይደለም፡፡ ስራ ለመቀጠር አባል በሆን ማግስት እንደምንለውም አይደለም:: ለነገሩ እሱ “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ነው፡፡ ሙያዊነት የሌለው በመሆኑ የሚርቁት ተፋጂ ነበልባል ነው፡፡ በመሆኑም አቶ መለስ ገና እውነት መክረውናል፡፡ ነገር ግን ይህ ከምን እንደመጣ የሚጠቁም ምክንያት ላቀርብ፤ ለዚህ ችግር መነሻ የሚሆኑ ምክንያቶችን ሳውጠነጥን ዐቢይ ተ/ማሪያም “የአባት ውርስ” ያለው ፅሑፍ ተከሰተልኝ፡፡ ዐቢይ አቶ መለስ ልጃቸው ፖለቲካ ውስጥ እንዳትገባ የተመኙበትን ለመተንተን ሁለት መሰረተ ሀሳቦችን አኑሮ ነው፡፡ “አንደኛ፡- አቶ መለስ ለልጃቸው ከሁሉም የላቀውን ይፈልጋሉ፡፡ ሁለተኛ አቶ መለስ መልካም አባት ናቸው” የሚሉ፡፡

“ምክንያት አንድ” 19 ዓመት እንኳን ያልሆነው ለግላጋ ፣ለገሰ

ዜናዊ ትግል ጀመረ፡፡ ነገር ግን ወይ አስቦ አሊያም እንዲሁ፣ ልክ እንደቀድሞዎቹ ሁሉ፣ ፍፁማዊ የስልጣን የበላይነትን አረጋገጠ- መለስ ዜናዊ፤ የልጁ አባት፡፡ በመሆኑም ፖለቲካ ውጥኖች የማይሳኩባት ሜዳ ሆና ታየችው፡፡ “በአፍሪካ በ`M` የሚጀምር ስም ያላቸው አምባገነኖች መንግሥቱና ሞቡቱ ናቸው” ብሎ ያሰበው ለገሰ ዜናዊ በመለስ ዜናዊ ስም የነዚህን ጎራ ለመቀላቀል መንደረደሩ አብሽቆት ሊሆን ይችላል፡፡ የሙያ እጥረት እንዳለበት ሁሉ “ልጃቸው እርሳቸው ባለፉበት ሞያ እንዳታልፍ ቢፈልጉ የፍቅር ነው፡፡“ምክንያት ሁለት”

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሙያዊ ያልሆነ እና “የማይከበር” መሆኑን ተረድተዋል ማለት ነው፡፡ ወይም ቀድሞውኑም ለፖለቲካዊ አነጋገር እንጂ በደንብ አድርገው ያውቁታል፡፡ በአፍሪካ ደረጃ እንኳ ወደ ፖለቲካው የሚመጡ ሰዎች በአቋራጭ ለመክበር የቆረጡ፣ ለራሳቸውም ለሌሎችም ክብር የሌላቸው፣ ለመዋሸት፣ ለማታለል፣ ለመሸፈጥ፣ ለመወንጀል፣ ለመፍለጥ ለመቁረጥ ያሰቡ ናቸው፡፡ ይህን በድህረ ምርጫ 97 ኢሕአዴግን መታዘብ እንችላለን፡፡ ራሳቸውን ያስቀደሙና ከሆድ እንጂ ከጭንቅላት ያልተሰሩ ስለመሆናቸዉ የአብዛኛዎች ምሁራን የጥናት ዉጤት ነበር፡፡ መራጮች ባለዝቅተኛ መረጃ መራጮች የሆኑ ናቸዉ:: ሚዲያዉ ፅንፈኛና የገዥዎች ፍላጎተ የሚዘዉረዉ ነዉ:: (ለምሳሌ ኢቲቪ ለመሪዎች መቆሙን ዛሬ የጀመረው እንዳይመስላችሁ፡፡ በደርግ ዘመነ መንግስትም እንዲሁ::ጓድ መንግስቱ ሀይለ ማሪያም የሜዳ ቴኒስ ይወዱ ነበር አሉ፡፡ ስለዚህ ETV መንጌን ማስደሰት እንደነበረበት ተረዳ፡፡ በመሆኑም በወቅቱ ከኤዴንቤርግ ይተላለፍ የነበረን የሜዳ ቴኒስ የሻምፒዮና ውድድር ለ’ኢትዮጵያውያን’ በሙሉ በቀጥታ (live) አስተላለፈ፤ የአድማጭ ተመልካች ፍላጎት የመንግሥቱ የመለስ፡፡) እንግዲህ በአጠቃላይ የብሄር ፖለቲካ የጦዘበት እና የሴራ እና “ፖለቲካን እንደ ሙያ ክብረ ቢሲ” የሆነች አድርገው የሚያስቡ ናቸው፡፡ ስለዚህ “ወደዚያ እንዳትገባ ቢፈልጉ የአባትነት ነው፤ እርሳቸው ውስጡ እንኳ ቢኾኑ፡፡”

“ምክንያት ሦስት”በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ

በእንግሊዝ ወይም በኔዘርላንድ ፖለቲካ መሳተፍ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ተሳታፊነት የጊዜ፣ የነፃነትና የእኩልነት እና በዋነኝነት የህይወት መሰዋዕትነት የሚጠይቅ ነው፡፡ ይህን ምስክርነት

መስጠት የሚችሉት ራሳቸው አቶ መለስ ናቸው፤ መለስ ተክሌን በመግለፅ፣ ስዬ አብረሃን በመጥቀስ፣ በትግል ባሳለፈው ጊዜያት (አቶ መለስ አሁንም ትግል ላይ ነኝ ይላሉ፡፡ ለነገሩ ባየነው አካሄድ እውነትም ፖለቲካው ትግል ነው) ዘግናኝ ክንውኖችን ቢያንስ ታዝበዋል ፤አሊያም ተሳትፈውበታል፡፡ ‹‹ሥልጣን ላይ ለመውጣትም ሆነ ለመቆየት የሚደገረውን የፊት እና የጀርባ መወጋጋት፣ አሻጥር እና ጭካኔ ከርሳቸው በላይ የሚያውቀው የለም፡፡” ስለዚህ ይህን በየኩርባው መልአከ ሞት የመሸጉበት ህይወት ለልጅ መመኘት “የጥሩ አባት ወግ አይደለም፡፡” የሚለው ዐቢይ ሲያሳርግ እንደሚቀጥለው ነው፤

“ነገር ግን ….በአቶ መለስ ቦታ ሆኜ ሳስበው ከአንድ ሀቅ

ማምለጥ አልቻልኩም፡፡ የአትዮጵያ ፖለቲካ አደገኛ ቢሆን፣ ውሉን ቢሆን፣ ክብረ ቢስነት ቢበዛው፣ በከፊል ቢሆንም እንኳ አቶ መለስ ራሳቸው ተጠያቂ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ ለመሀል ፖለቲከኛ ሆናም ይሁን ሳትሆን የምታልፍበት የፖለቲካ ሁኔታ የአባት ውርስ እንጂ የተፈጥሮና የአምላክ ውርስ አይደለም፡፡”

እኔ ደግሞ የራሴን ሁለት መሰረተ ሃሳብ ይዤ ላጠናቅ–አንደኛ፤በተለየ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከልጅ በላይ ለአባቱ የሚቀርብ የለም፤ሁለተኛ፡- ወቅታዊዉ የአለም ስርአት የበለጠ ስላቀራረበን ተጎዳድተን አንራራቅም::ስለዚህ ሰምሀል ሆይ ! እኔ እልሻለሁ ኢትዮጵያን የሚመራው አባትሽ አቶ መለስ እንጂ የእስራኤላውያኑ ሚካኤል አይደለም፡፡ ሙሴም አይደለም፡፡ ስለዚህ አንች ለአባትሽ ቅርብ ነሽ- መና ሲያወርድም ከኛ ትቀርቢያለሽ -መዓት ሲወርድበትም ከኛ ትቀርቢያለሽ ! የጃንሆይ ልጆችና የልጅ ልጆች የነበሯቸዉን ያክል እድል እንኳ የለሽም፤የመለስ ልጅ እንኳ ብትሆኚ::

ልማት ልማት…= እሹሩሩ

“የአባት ውርስ”

መሆኑን ለወደፊትም ከዚህ በተሻለ መልኩ እንደሚለወጥ ተማሪዎችም በአግባቡ እንደሚፈፅሙ ተንግሩአል ፡፡ለወደፊቱ በተለያየ ፈተና ወቅት የሚኮርጁ ተማሪዎች ጨርሶ እንደማይኖሩና የተማሪዎች መኮረጅ መልመድ በወደፊት ሕይወታቸው በኪራይ ሰብሳቢነትና ጥገኛ አመለካከት ሥር መውደቅ እንደሚያስከትል ገልፀዋል፡፡ዛሬ ኪራይ ሰብሳቢዎች በስፋት ሊታዩ የቻሉት ባለፉት ሥርዓቶች የመኮረጅ ባህል የነበረ በመሆኑ እንደሆነ ከየመድረኮቹ ሲገለጽ የዋለ ሃሳብ ነበር፡፡ በቀጣዩ ዓመት የትምህርት መሻሻል መርሀ ግብር ትኩረት የሚያደርግባቸው ተብለው አራት ጉዳዮች ተገልፀዋል፡፡ እነዚህም፡-ተከታታይ ግምገማ፣ተማሪ ተኮር የትምህርት አሰጣጥ ፣የተማሪ መምህራን ጥምረት ሚዛናዊነትና መሆኑ ተጠቅሶ ባለፉት ሁለት ሥርዓቶች ተማሪዎች፤ የንጉሱን ዘለዓለላማዊነትና በደርግ ዘመን ደግሞ የሶሻሊስት ሥርዓትን አሸናፊነት ከመማር ውጭ መሠረታዊ የሆነውን የዴሞክራሲ ሥርዓትን ጨርሰው ሣይማሩ አልፈዋል ተብሏል፡፡ ዛሬ ግን አስራ አንዱን የዲሞክራሲ መርሆች መሠረት ያደረገ ትምህርት እየተሰጠ ነው ፡

፡ተማሪዎች የዴሞክራሲ ጽንሰ ሐሳብን ጠንቅቀው የተረዱ በመሆናቸው በዴሞክራሲ አግባብ የተማሪዎችን ካውንስል የመሠረቱና ያለ ምንም መድሎ መሪዎቻቸውን እንደሰየሙ በየት/ቤቱ እየታየ መሆኑን ተነግሯል፡፡የሥነ-ምግባርና የሥነ-ዜጋ ትምህርት የገዢውን ፓርቲ (ኢሕአዴግ) ፕሮግራምን የሚጭን አለመሆኑን በየወረዳው ስብሰባውን ሲመሩ የነበሩት የሥርዓቱ ቁጮዎች ሲገልፁት የዋሉት ጉዳይ ነው፡፡በየመድረኩ የነበሩ አወያዮች ትልቅ አፅንኦት በመስጠት ሲወተውቱ የዋሉት ሐሳብ ደግሞ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “በዚህም ምክንያት በሀገሪቱ የት/ቤት ሥራ የተለየ ትኩረት ተደርጐበት ከብዛት ወደ ጥራት የሚሸጋገር መሆኑን ያለማመንታት ገልፀዋል፡፡ ከሃያና አርባ ዓመታት በኋላ የትምህርት ጥራት በተሰጠው ትኩረት ሃገሪቱ በዓለም በመካከለኛ ደረጃ ከሚገኙ ሀገሮች ተርታ ትደርሳለች፡፡’’ ይላል ፡፡ሌላው በአወያዮቹ የተገለፀው ሐሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ የሥራ-አጥ ቁጥር በጣም እየቀነሰ መሆኑንና የከተማው ወጣቶችም ከአጉል ሱሰኝነት ተላቀው ወደ ስኬታማነት እየተለወጡ መሆኑን አበክረው አስረድተዋል፡፡ እንደ አጠቃላይ

በሚል አባባል ተመሳሳይነት ያላቸው የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በቀጣይ ዓመታት የመምህራንን ኑሮ ከመሠረቱ እንደሚለወጥ፣የኮንዶሚንየም ቤት ለመምህራን 40% ብቻ እንዲከፍሉ በማድረግ የቤት ባለቤት ለማድረግ እንደሚሠራ ገልፀዋል፡፡ በሀገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ጉዳይ ላይም ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ የኑሮ ውድነቱ ኢትዮጵያን ብቻ ሣይሆን ዓለምን ሁሉ እያወከ እንደሆነ ከገለፁ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሩ እንዳይባባስ ለመቆጣጠር ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ ቀኑን ሙሉ የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች (የትምህርት ቢሮ ሹማምንት) ይናገሩ በነበሩት ሐሳብ ላይ የተናገሩ መምህራን “ዕውነታው በአዲስ አበባ ከተማ በተጨባጭ ከሚታየውና ከምንሰማው እውነት ጋር ጨርሶ የማይገጣጠምና ዕውነቱን ገልብጦ የሚያሳዩ ከመሆናቸውም በላይ በተጨባጭ አዲስ አበባን የሚያውቅ ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችለው ነው፡፡” ሲሉ አንዳንድ መምህራን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በሌላ በኩል የት/ቢሮ ባለሥልጣናት እንደገለፁት “መምህራን ሞያቸውን መውደድ፣ሀገራቸውን ማክበር እንዳለባቸውና ጠንክረው ሊሠሩ አንደሚገባ

በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ የማይጠነክሩ ከሆነ ግን ዕድገት ማጣት ብቻ ሣይሆን ከሞያው እንዲወገዱ ይደረጋል፤የማስተማር ፍቃድ አይሠጣቸውም” በማለት ደምድመዋል፡፡ለግል ት/ቤት መምህራን የትምህርት ማሻሻያ ሥልጠና መስጠት እንደማይቻልና፤ነገር ግን የመንግሥት መምህራን በተመለከተ ከሰርትፊኬት ወደ ዲፕሎማ፣ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪና ወደ ሁለተኛ ዲግሪ የማሸጋር ሥራ ቢሮው እንደሚሠራ ስብሰባውን የሰበሰቡት ባለሥልጣናት አስረድተዋል፡፡ የሙያ ዕድገት ማሻሻያ ትምህርት ዕድል ጠንክሮ ለሚሠራ መምህር ሁሉ ክፍት መሆኑንና አንድ መምህር የግድ የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆነ ዕድሉ አይሰጥውም የሚለው መሠረተ ቢስ ወሬ እንደሆነ፤ይህንንም በየዩኒቨርስቲው ለከፍተኛ ትምህርት በተለይም ለማስተርስ ፕሮግራም እየተመለመሉ ያሉትን መምህራን በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፤ማንም የገዢው ፓርቲ አባል ስለሆነ የማስተርስ ፕሮግራም የመማር ዕድል እየተሰጠው አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰለሞን ስዩም[email protected]

ከገፅ 3 የዞረበአዲስ አበባ ከተማ ....

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

62ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 7ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

62ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 7ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

“የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሐፍ አጠበች”

አሽናፊ ደስታ ወንድምአገኘሁ

ዓለም ከተፈጠረ፣ዘመን ከተቆጠረ፣አንስቶ አሁን እስከ አለንበት ዘመን ድረስ፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ሕፃናት፣ ጐበዛዝት፣ አሮጊቶች እና ሽማግሌዎች፣ የዚያኛው ትውልድ የዚህኛው ትውልድ የዚያኛው ትውልድ ሳይባባሉ፣ተከባብረው እና ተመሳስለው ከአንድ ላይ ኑረዋል፡፡

አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች፣ አህቶች፣ አሮጊቶች እና ሽማግሌወች፣ የዚያጨኛው ትውልድ የዚህኛው ትውልድ ሳይባባሉ ክአንድ ላይ ኖረዋል፡፡ አሁንም እየኖሩ ነው፡፡

የማይገሰስ የተፈጥሮ ሕግ ነውና ማንኛውም ፍጡር ይወለዳል፣ያድጋል፣ ያረጃል፣ ይሞታል ፡፡ ከዚህ ውጭ የዚያኛው ትውልድ፣የዚህኛው ትውልድ የሚለው ፈሊጥ፣ተቀባይነት የሌለው የጥራዝ ነጠቆች አጉል ፈጠራ ነው፡፡

ለዚህ ጽሑፍ የሰጠነው ርዕስ እንደተጠበቀ ሁኖ ሕወሓት ኢሕአዴግ አወኩ አወኩ ብሎ አንድ አካል፣አንድ አምሣል ሁኖ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ በጐሣ፣ በሃይማኖት፣ በክልል፣ በቋንቋ፣ በብሔርና በብሔረ-ሰብ

ከፋፍሎ እርስ በርስ የሚያናቁረው አልበቃ ብሎ፣የዘመኑ ፈላስፋ ደግሞ፣አርብ ነሐሴ 27 ቀን 2003 ዓ.ም ታትሞ በወጣው ፍትሕ ጋዜጣ ገጽ 8 ያሁኑ ትውልድ ከዚያኛው ትውልድ ሊወርሳቸው የማይገባ ጠቂት ነጥቦች” በሚል ዐቢይ ርዕስ ሥር፣ “… እንዲሁ ግን የአባቶች ትውልድ፣ የያኔው ትውልድ፣የስድሳዎቹ ትውልድ፣ የድሮው ትውልድ፣የአሁኑ ትውልድ፣ . . . እየተባለ ሲነገር መስማታችን አልቀረም፡፡ አንዳንድ ምሁራን ግን የአንድ ትውልድ ዘመን ከ30 ዓመት ያለውን ያሁኑ ትውልድ ብንላቸው ከሰላሳ በላይ ያሉትን ደግሞ የዚያኛው ትውልድ ወይም በተለይ የ60ዎቹ ልንል እንችላለን ማለት ነው፡፡ ለጊዜው በዚሁ እንግባባና እንቀጥል፡፡” ይሉና ጽሑፋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እኔ ግን፣ አበቃሁ፡፡

እንደተረገመው ወይም በሥልጣኔ ወደኋላ እንደቀረው እንደ አፍሪቃ አሕጉር በዝምድናወይም በትውውቅ ሣይሆን በችሎታ ወይም በመልካም ሥራ በሚሠራበት በሰለጠነው ዓለም የጄኔራልነት ወይም

ከዚያ በላይ ማዕረግ የሚሰጠው በጦር አመራሩ፣በጦር ሥልት አዋቂነቱ፣በአዋጊነት ችሎታውና በዕድሜ ብስለቱ ተገምግሞ ነው፡፡ ምሣሌ ፊልድ ማርሻል ሞንትጐሞሬ፡፡

የሲቪሎን ትክክለኛ አሻEEሻEም ወይም ማዕረግ አሰጣጥ የወሰድን እንደመሆኑም፣ቀድሞ በሚመጣው የዕድሜ ብስለት፣የትምህርት ደረጃ፣የሥራ ልምድ፣የአመራር ብቃት ጠባየ መልካምነት ከአድሏዊነት እና ከጉቦ የነፃ ሰው መሆኑ ተገምግሞ ነው፡፡ አንድ ሰው ለከፍተኛ ማዕረግ የሚበቃው፡፡ ለምሣሌ ጠንካራዋ ወይም ብርቱዋ የተባሉት ሚስስ ታቸር ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የበቁት ልክ በ50 ዓመታቸው ነው፡፡

ሕፃኑ፣ወጣቱ፣ባለማዕከላዊ ዕድሜው፣ ሽማግሌው፣ አዛውንቱ ጉራማይሌ ሕዝብ የሚኖርባት ዓለም፣ከ60 በላይ ያለውን የዜያኛው ትውልድ፣ወይንም የአሁኑ ትውልድ እያልን እንጥራው ማለት “ሥራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል” እንደሚባለው ተረት ነው፡፡ ከዚህ በላይ አንብበን በመጣነው

ጋዜጣ ከሰው ዕድሜ ውስጥ ገብተው ያዳበሩትን ፈላስፋ ተከትለን እንሂድ ብንልም እንኳን፣ያ የተባለው ትውልድ አልቆ፣ከምድረ ገፅ ጠፍቶ፣ይህ የተባለው ትውልድ መተካት አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ሁኖ የማያውቅ ሊሆንም የማይችል ስንኩል ወይም ዕኩይ አስተሳሰብ ነው፡፡

ከነ ሶክራትስ ባፊት የነበሩትን ፈላስፋዎች ወደ ጐን እንተዋቸውና እነ ሶክራተስ፣እነ ፑላቶና እነ አርስቶትል ሲፈላሰፉ የነበሩት ኦእኮ በዘመናቸው የነበረውን ብልሹ አስተዳደር ወደ ፀዳ እና እድሏዊ ወደ አልሆነ ዴሞክራቲክ አስተዳደር ለማምጣት ነው እንጂ ከሰው ዕድሜ ውስጥ ገብተው ከ30 ዓመት በታች ያለውን ያሁኑ ትውልድ፣ ከ60 በላይ ያለውን ያኛው ትውልድ እንበለው ከሚለው የዕድሜ መለኪያ ውስጥ ገብተው ለመዳከር አይደለም፡፡

ምክንያቱም የነእከሌ ትውልድ ለማለት ያትውልድ ከምድረ ገፅ መጥፋት እንዳለበት ያውቃሉና፡፡ ትውልድ የማያቋርጥ የተፈጥሮ ሕግ ነው፡፡ ሺህ ፍጡር ይሞታል በዚያኑ ዕለት

የጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል ንብረቶች

እስከአሁን አልተመለሱም

ብስራት ወ/ሚካኤል

ባለፈው መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም በ “ሽብር” ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዕለቱ ሲያሽከረክሯት የነበረች የቤት መኪና እና መተዳደሪያቸው የሆነውን የቤት ኪራይ ገንዘብ እንዲመለስላቸው ጋዜጠኛ ሰርክዓለም ፋሲል ቢጠይቁም እስከአሁን እንዳልተመለሰላቸው ገለፁ፡፡

ወ/ሮ ሰርክዓለም ንብረቶቹ በተያዙበት ማዕከላዊ እስር ቤት ሄደው የመኪናውን ሊብሬ በእሳቸው ስም እንደሆነ ለማስረጃነት ቢያቀርቡም “ከአንቺ እጅ አልያዝንም” የሚል መልስ እንደተሰጣቸውና መተዳደሪያቸው የሆነው የቤት ኪራይ ገንዘብንም ሲጠይቁ “ሁሉንም ከአንቺ ስላልወሰድን አጣርተን ስንጨርስ ደውለን እንጠራሽና ትወስጃለሽ” ብለው እንደመለሷቸው በተለይ ለዝግጅት ክፍሉ ገልጸዋል፡፡

የትራንስፖርት ታሪፍ ዋጋ እያወዛገበ ነው

ብስራት ወ/ሚካኤልበአዲስ አበባና ክልል በሚገኙ ከተሞች ባልታወቀ

ምክንያት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ሲሉ ተጠቃሚዎች ይናገራሉ፡፡ በተለይም በአዲስ አበባ ከቦሌ ድልድይ 22 ማዞሪያና ከካዛንችስ ቦሌ መድኃኔዓለም እያንዳንዳቸው በፊት 1.25 (አንድ ብር ከሃያ አምስት) ሳንቲም የነበረው ታሪፍ አሁን 2.8ዐ (ሁለት ብር ከሰማኒያ) ሳንቲም እንዲከፍሉ መገደዳቸውን ተጠቃሚዎች ገልፀዋል፡፡ ይህን አስመልክቶ የታክሲ ባለንብረቶችና ሾፌሮች አሁን መንግሥት ያደረገው የዋጋ ማሻሻያ በቂ አይደለም፤ ያንሳል ሲሉ እነሱም ቅሬታቸውን ይናገራሉ፡፡ ለዚህም ምክንያት ብለው የሚገልፁት የመለዋወጫ ዕቃ እጅግ በጣም በመጨመሩና የነዳጅ ዋጋውም ቢሆን ከፍተኛ ስለሆነ ጭማሪው በቂ አይደለም ይላሉ፡፡

በተመሳሳይም ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 230 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የምትገኘው ሆሣዕና ከተማ ድረስ በመንግሥት በተደረገው ማሻሻያ 71 (ሰባ አንድ) ብር የነበረው ታሪፍ ባለፈው ሳምንት 110 (አንድ መቶ አስር) ብር እንደነበርና አሁን ደግሞ ወደ 140 (አንድ መቶ አርባ) ብር እንደሆነ የዝግጅት ክፍሉ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡ ምክንያቱን ግን ለማጣራት መርከቶ የሚገኘው አውቶቡስ ተራ ስምሪት ክፍሎችን ብንጠይቅም አሳማኝ ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም፡፡ ተጠቃሚዎችም ጉዳዩን መንግሥት በአስቸኳይ እንዲያይልን እንፈልጋለን በማለት ጠይቀዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY(UDJ)ቁጥር፡-አንድነት /437/2ዐዐ4ቀን 15/01/2004 ዓም

ግልጽ ደብዳቤለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊአዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በሽብርተኝነት ስም የታሰሩ አባሎቻችንና ሌሎች ዜጎች ሕገ-መንግሥታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው ስለመጠየቅ፣

በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ በግልጽ እንደሚታወቀው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በሕገ-መንግሥቱ በተደነገገው የመደራጀት መብት መሠረት ሕጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ ለዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እውን መሆን፣ ለሕገ-መንግሥታዊነትና ለሕግ የበላይነት በጽናት ለመታገል የተቋቋመ የፖለቲካ ፓርቲ ነው፡፡

አንድነት ከሠላማዊ የትግል ስልት ውጭ በሀገራችን ዘላቂ ልማትም ሆነ የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት ማስፈን እንደማይቻል ያምናል፡፡ አሁን ባለው አስቸጋሪ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ እንኳ ሠላማዊ ትግል ብቸኛው አማራጭ መንገድ መሆኑን እምነታችን ነው፡፡ አባሎቻችንም ለትግሉ መርሆዎችና ዓላማዎች ተገዢዎች መሆናቸውን እናውቃለን፡፡

ከነዚህ ዓላማዎችና መሠረታዊ እምነቶች በመነሳት አንድነት ሽብርተኝነትን አጥብቆ ያወግዛል፡፡ ሽብርተኝነት የንፁሀንን ህይወት የሚቀጥፍ፣ የሀገርንና የሕዝብን ሀብትና ንብረት የሚያወድም፣ የሀገር ልማትና መረጋጋትን የሚያናጋ ድርጊት በመሆኑ ይህን አስከፊ አደጋ ከመቃወም ባለፈ ለመከላከል በጽናት እንቆማለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም ሕግን የሚጥስና በሕዝብ ዘንድ ሽብርና ፍርሀት የሚያሰርጽ ሥርዓትን በጽናት እንቃወማለን፡፡

አሁን በሀገራችን ባለው ሁኔታ መንግሥት በሽብርተኝነት ስም እየወሰደ ያለው እርምጃ ሽብርተኝነትን ከሕዝብ ጋር ሆኖ ከመከላከል ይልቅ በዜጎች ላይ የሚፈጥረው የሽብር፣ የፍርሀትና የመሸማቀቅ ድባብ፣ የበለጠ አመዝኖ ይገኛል፡፡ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የፖለቲካ ምህዳሩን ይበልጥ የሚያጠብ፣ ከሕዝብ ጋር መቃቃርን የሚፈጥርና ሽብርተኝነትን ከመቆጣጠር ይልቅ የሕዝብንና የፖለቲከኞችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ያለመ ነው የሚል እምነት አለን፡፡

በቅርቡ በተከታታይ በሽብርተኝነት ስም በርካታ ዜጎች መታሠራቸው የሚታወቅ ሲሆን ባለፉት ሳምንታትም የፓርቲያችን ም/ሊቀመንበና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ የኦፌዴን ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦሕኮ የጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ የመኢዴፓ ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ ዘመኑ ሞላ፣ እንዲሁም የፓርቲያችን ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት የሆኑነት አቶ ናትናኤል መኮንን እና አቶ አሳምነው ብርሃኑ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ፣ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስ እንዲሁም አርቲስት ደበበ እሸቱ መታሠራቸው ይታወቃል፡፡ አንድነት ፓርቲ በሕገ-መንግሥታዊነትና በሕግ የበላይነት የሚያምን ፓርቲ እንደመሆኑ መጠን ሰዎች በወንጀል ለምን ተጠረጠሩ የሚል ጥያቄ ባይኖረውም ዜጎችን በገፍ ማሰር ለችግሩ መፍትሔ ይሆናል የሚል እምነት የለውም፡፡ ከዚህም ባሻገር በመንግሥት የሚወሰዱ እርምጃዎች ሥርዓትን የተከተሉና ሕጋዊነትን የተላበሱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ በሽብርተኝነት ስም በአባሎቻችንም ሆነ በሌሎች ዜጎች ላይ እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች የዜጎችን ሕገ-መንግሥታዊ መብቶች የሚጋፉና የሚጥሱ በመሆናቸው፡-

ሀ) ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ ለ) በጥርጣሬ የተያዙት ሰዎች በፍ/ቤት ውሳኔ እስኪያገኙ ድረስ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 19/6 መሠረት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ፤ሐ) የሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ሰብዓዊ-መብት መከበሩ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉ ሰዎች ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣

ከኃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር የመገናኘትና የመጎብኘት መብታቸውን ጨምሮ በአስቸኳይ እንዲከበር፤ መ) በ‹‹ፀረ-ሽብርተኝነት›› ሕግ ስም የሚደረገው የሕዝብ መብት ረገጣና እስራት በአስቸኳይ እንዲቆም፤ ሠ) ህዝብን አፍኖ ለመግዛት ታስቦ የተዘጋጀው ‹‹ የፀረ-ሽብርተኝነት›› አዋጅ ከበርካታ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ጊዜ ሳይሰጠው እንዲሻሻል፤ረ) በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 2ዐ/3 መሠረት ማንኛውም ዜጋ በወንጀል ተጠርጥሮ እስካልተፈረደበት ድረስ እንደወንጀለኛ ያለመታየት ሕገ-መንግሥታዊ መብት እንዳለው ይታወቃል፡

፡ በመሆኑም የመንግሥት የመገናኛ ብዙሃን ፍርድ ባልተሰጠባቸው ዜጎች ላይ እንደተፈረደባቸው ወንጀለኞች በመቁጠር የሚያሰራጩትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እንዲደረግ፤

ሰ) በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ 2 በተደነገገው መሠረት የዜጎች የግል ሕይወት መከበርና የመጠበቅ መብት በተለይም፤ ማንኛውም ሰው በግል የሚጽፋቸውና የሚፃፃፋቸው ደብዳቤዎች እንዲሁም በቴሌፎን፣ በቴሌ ኮሙኒኬሽን እና በሌሎች በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች የሚያደርጓቸው ግንኙነቶች ያለመደፈር መብት እንዲከበር፤ እንዲሁም፤

ሸ) በህገ-መንግሥቱ አንቀጽ 29 በተደነገገው መሠረት የዜጎች የአመለካከትና ሀሳብን በነፃ የመያዝ መብት እንዲከበሩ እንጠይቃለን፡፡ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥትዎ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጠው መልስ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ሠላምና መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው እናምናለን፡፡ በመሆኑም

የጥያቄዎቻችንን ተፈፃሚነት በቀናነት ተመልክተውና ከየትኛውም ሀገራዊ ጉዳይ ቅድሚያ ሠጥተው እንዲያረጋግጡልን በኢትዮጵያዊ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታ ጋር ነጋሶ ጊዳዳ (ዶ/ር) ሊቀመንበር

ግልባጭ- ለኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት- ለኢፌዲሪ የሕ/ተወካዮች ም/ቤት- ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ- ለኢፌዲሪ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን- ለመድረክና ለመድረክ አባል ድርጅቶች- ለሌሎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉ- ለሁሉም የፕሬስና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች- ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ሁሉ- ለዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ማህበር

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

82ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 9ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

82ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 9ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

መዝናኛየአደባባይ ምስጢሮች

መዝናኛሰሞኑን የገጠመኝ ነገር አስቤውም አልሜውም አላውቅም፡

፡ መቼም ዛሬ በአገራችን የተከሰተውን የኑሮ ውድነት ሁላችሁም የምታውቁት ነው፡፡ እናት ልጃEን የምታቀምሰው አጥታ ቤቷን ዘግታ የምታፈስውን እንባ ቤት ይቁጠረው፡፡ በየመንገዱ ብቻውን እየተነጋገረ የሚሄደው ወላጅ አባት እግዚአብሔር ጽናቱን ይሰጥህ የሚያሰኝ ነው፡፡ በዜጎች ላይ የመጣ የሥርዓቱ ውጤት መሆኑ የገሃድ ሃቅ ነው፡፡ በጥቂት የዘመኑ ገዢዎቻችን ደግሞ በተቃራኒው የቅንጦት ኑሮአቸውን ቀጠለዋል፡፡ ስለረሃብና ስለችግር ሲወራ የፈጠራ ወሬ ነው” ይሉናል፡፡ በተቋማዊ ኔትዎርክ የተንሰራፋው ሙስና ከልካይ በሌለበት የአገሪቱን ሀብት እየመዘበሩ ተደላድለው የኖራሉ፡፡ የሕዝብ ብሶት ከዕለት ወደ ዕለት ቀጥሏል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ለአንድ ጉዳይ ከቤቴ ወጥቼ በመንገድ ላይ እንዳለሁ ንፋስ የቀላቀለው ዝንብ ገጠመኝ፡፡ ጃንጥላዬን ዘርግቼ ልከላከል ብሞክርም አልቻልኩም፡፡ ጃንጥላውን ንፋሱ ገነጣጠለብኝ፡፡ ዝናቡም ክፉኛ ጐዳኝ፡፡ ልጠለል ብዬ ታዛ ቢጤ ፈልጌ ቆምኩ፡፡ በዝናብ የበሰበሰውን ሰውነቴን አኮማትሬ ከሰውነቴ ውስጥ ከሚሰማኝ ብርድ ጋር የምነጋገር የመስል አስላስላለሁ፡፡ በድንገት አንድ የተዝረከረከ ልብስ የለበሰ፣ ፀጉሩ የተንጨባረረ፣በባዶ እግሩ የሚሄድ ግዙፍ ሰውዬ በዝናቡ እየበሰበሰ ወደ እኔ መጣ፡፡ በአንድ እጁ ያለቀበቶ የለበሰውን ሱሪ ጨብጦ ይዟል፡፡ አብድ መሆኑን አልተጠራጠርኩም፡፡ በቀጥታ እኔን እየተመለከተኝ በፈጥነት መምጣቱንም አልወደድኩትም፡፡ በሴትነቴም ፍርሃት ተሰምቶኛል፡፡

ልክ አጠገቤ እንደደረሰ ቆም አለና “ችግር አለ? ምንድነው ችግሩ?” ሲል አይኑን በአኔ ላይ አፍጥጦ ጠየቀኝ፡፡ እኔም የበለጠ ፍርሃት ፈጥሮብኝ “ምንም ችግር የለም፡፡ “ሰላም ነው አልኩት እንዴ? ችግር የለም? እንዴት ነው ችግር የማይኖረው? ምን ማለትሽ ነው? ችግር የለም ስትይ እያለ ጥያቄውን ደረደረ፡፡ የበለጠ እያፈጠጠና እጁን እየጨበጠ ተጠጋኝ፡፡ የምስጠው መልስ ጠፍቶኝ በመለማመጥ መልክ ዝም ብዬ አይን አይኑን ተመለከትኩት፡፡ “አንቺ ከአሜሪካን ነው የመጣሽው? ኬክ ነው የምትመገቢው? ከማርስ የመጣሽ ዩፎ ነሽ? ምን ስለሆንሽ ነው ችግር የለም የምትይው? በርቀት በአንድ በረንዳ ላይ ዝናብ ለመጠለል ማዳበሪያቸውን እየለበሱ የተቀመጡትንና የተኙትን ጐዳና ተዳዳሪዎች አያሳየኝ ይህ ሁሉ ሰው በየቀኑ በረሃብ ሲያልቅ የሰው ሕይወት ሲረግፍ አያየሽ ችግር የለም ትያለሽ እያለ ሲጮህ ይህ ሰውዬ አይለቀኝም ብዬ ሽሽቴን ጀምርኩ፡፡ እሱም ተከተለኝ ሩጫዬን ጀመርኩ፡፡ ችግር የለም!! እያለ ይከተለኛል፡፡ ጫማዬ ተበጠሰብኝ፡፡ ጐንበስ ብዬ ጫማዬን እያነሳሁ ዞር ብዬ ተመለከትት፡፡ እሱም ሱሪውን በእጁ እንደያዘ የወርደውን ጐርፍ እያንቦጫረቀ ይከተለኛል፡፡ ጭንቀቴን የተመለከቱ መኪና አቁመው በሩን ከፈቱልኝና እንዴት እንደገባሁም አላውቀውም፡፡ ያዘኝ አመለጥኩ እያልኩ ሳዳምጥ መኪናው በሩን ዘግቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር አሁንም ድምጹን ከፍ አድርጎ እንዴት ችግር የለም ትላለች? ይህ ሁሉ ሰው እየተረፈረፈ ችግር የለም ይባላል ሲል ይሰማኛል፡፡ ጐበዝ ዘንድሮ አብዱም ጭምር ኑሮ መሮታል ማለት ነው?!! ኸረ ፈጣሪ ደግ ጊዜ ያምጣ!!

መጽሐፍ . . . ! መጽሐፍ ! . . . ! መጽሐፍ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለንባብ የሚያገለግል እንዲሁም የጥናትና ምርምር ማዕከል የሚሆን ቤት መጽሐፍት ለማቋቋም በሂደት ላይ ይገኛል፡፡ ስለዚህ እርስዎ

የሚያበረክቱልን አንድ መጽሐፍ ለእኛ ጠቃሚያችን ነውና ከምስጋና ጋር ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡

ኑ! የሚያነብ ትውልድ እንፍጠር

የመረጃና ዶክመንቴሽን 0911 035035

ለመላው የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ

በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

በብሩክ ከበደ

የሀገራችንን ምስራቃዊ አቅጣጫ ሳስብና ህሳቤዬን ወደ ተለያዩ ጉዳዮች ስመነዝረው ሁል ግዜ የሚገርመኝ ልበለው የሚደንቀኝና መልስ የማጣለት አንድ ወሳኝ ጥያቄ በውስጤ የጭርብኛል፡፡ “ለኢትዮጵያ በስፓርቱ፣በስእሉ፣በድርሰቱ፣በሙዚያው፣በውትድርናው፣በሳይንሱ፣በጋዜጠኝነቱ፣በዲፕሎማቱ፣በሚኒስትርነቱና አልፎ ተርፎም በእስከ ዛሬው እውነት በዋናነት ኢትዮጵያን የሚመሯት ሁሉ የሚገኙት ከወደዛው አቅጣጫ መሆኑ ነው ጥያቄዬን ሁልግዜ ላገኘሁት ሁሉ የማነሳው፡፡ አንዳንዴም ምስራቅ (ጀምበር) የጎህ መውጫ ስለሆነ እውቀቱም፣ፍቅሩም፣ በአያሌው ተሰጥቷቸው ይሆን? እያሉኩ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ ለምን ቢሉ አሁንም ምንጩ አልነጠፈምና!፡፡

እነ ራስ መኮንን ወ/ሚካኤል ወ/መለኮት፣ንጉስ ተፈሪ መኮንን፣ሐረር ባይወለዱም ኮ/ል መንግሥቱ ኃ/ማርያም፣ፕ/አስራት ወ/የስ፣ዶ/ር ጌታቸው ጐሎዲያን፣ብዙነሽ በቀለ፣ገ/ክርስቶስ ደስታ (ሰዓሊና ገጣሚ)፣ረ/ት ፕ/ተስፋዬ ገሰሰ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ፣ጀ/ል ተስፋዬ ገ/ኪዳን፣ወጋየሁ ደግነቱ፣ደምሴ ዳምጤ (ጋዜጠኛ) ወዘተ ኧረ! ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል?፡፡

ስለዚህ ጉዳይ በዛሬው ጽሑፌ የማነሣቸውን ምስራቃዊ ግለ ሰብ በአንድ ወቅት የዚህ ተፈጥሮአዊ ምስጢር ምን ይሆን? ስል ጠይቄአቸው የሚከተለውን እንዳሉኝ አስታውሳለሁ፡፡ “. . . ወደ ምስራቅ ብትሄድ ጎንደሬው፣ጎጃሜው፣ትግሬው፣ሸዌው፣ወለጋው በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሠላምና በፍቅር እየተጋገዘና እየተረዳዳ በፍቅር ለረዥም አመታት የኖረበት ክልል ነው፡፡ የሃኪሙ፣የደራሲው፣የሣይንቲስቱ፣የጀነራሉና የሌላውም ቤተሰብ ወደ ሐረርጌ የመጣው ከተለያዩ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ ሐረርጌ ከተወለድክ በቃ ሐረርጌያዊና ኢትዮጵያዊ ነህ፡፡ ሐረርጌ ከኖርክ እንደ ልብ ነው የምትናገረው፡፡ ይህ ደግሞ ለእውቀት ትልቅ ቦታ አለው፡፡ የፈለከውን ትጠይቃለህ ይመለስልሀል፡፡ ልጅ ነው፣ሴት ናት የሚባል ነገር ቦታ የለውም፡፡ ሐረርጌ የራሱ ነፃነት አለው፡፡ ሐረርጌ “አቦ!” ካለ ስለሚናገረው አይጨነቅም፡፡ አንቱታን እንኳን የለመድንው እዚህ ከመጣን ነው፡፡ ሌላው ቢቀር እስላምና ክርስቲያን የሚለው የሃይማኖት ልዩነት ለማንም ሐረርጌያዊ አይገባውም፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ቤት የእያንዱንዱ ነው፡፡ የግሌ ብሎ ነገር ብዙም ቦታ የለውም. . .፡፡” ነበር ያሉኝ፡፡ ለዚህም

ይሆናል ይህችን የፍቅር፣የሠላምና የመከባበር ሃገር ዩኒስኮ የሠላምና የመቻቻል እንዲሁም ጥንታዊና ታሪካዊ ብሎ መሸለሙ ቢያንሳት እንጂ አይበዛባትም ሲል ያሽሞነሞናት፡፡ ከፍ ከፍ ያደረጋት፡፡

የዛሬው የጋዜጣው አምድ ተጋሪ በቀድሞ አጠራር በሐረር ጠቅላይ ግዛት በጨርጨር አውራጃ ጉሮቆሬ በተባለው መንደር ሚያዝያ 12 ቀን 1922 ዓ.ም የተወለዱትና የማዕረግ ስማቸው ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ ወ/መስቀል ናቸው፡፡ ፀሐፊ ተውኔት ደራሲና ገጣሚ ለሆኑት ብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ ይህን የቤተ ክህነት ማዕረግ የሰጧቸው የአዲስ ዓለም ርዕሰ አድባራት ደብረ ፅዮን ማርያም አስተዳዳሪ ንብረ ዕድ አባ ገ/ሕይወት መልሴ እንደሆኑ የተሰጣቸው ማስረጃ ያሳያል፡፡

ንብረ ዕድን ለሌሎች ግለሰቦች የተሰጣቸው ማዕረግ ይኖር ይሆን? ስል በስልክ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ “ . . . አዎን ሌሎችም ለሃገራቸው ቁም ነገር ላበረከቱ ወገኖች የተለያየ ስያሜ ያላቸውን የቤተ ክህነት የማዕረግ ስሞችን ሰጥተናቸዋል፡፡ ከተሰጣቸው መሃል ፕ/ር ታደሰ

ታምራት፣ዶ/ር ኃ/ገብርኤል ዳኜ፣አቶ አለሙ ታፈሰን የመሳሰሉት ይገኙበታል. . .፡፡” ሲሉ መልሰውልኛል፡፡ ብላታ ጌታዬ አስፍው ተፈራም የተሰጣቸው የክብርና የማዕረግ ሥም የከረመ ቢሆንም እስከአሁን አልተጠቀሙበትም፡፡ በክብር ስማቸው ሲጠሩም በዚህ ጋዜጣ ላይ የመጀመሪያው ይሆናል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ፊርማቸው፣ቲተራቸውና ማህተማቸው ሁሉ በሥራና በሙያ በበቁበት ሙሉ የክብር ስማቸው እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡

በአሁኑ ጊዜ የታሪክ፣የስምና የመሳሰሉት ሽሚያዎች በገንዘብና በጥቅማጥቅም ልጥቀምህ ጥቀመኝ በሚል አካሄድ እየነጎደ ባለበት ወቅት ያ! ትውልድ ለሃገር እድገትና ጥቅም እንጂ አጉል ዝናና ክብር ያልቆመ ለመሆኑ የግለሰቡ ድርጊት ብዙ የሚያስተምር ይመስላል፡፡

የስልጣኔ ሀሁብላታ ጌታዬ አስፋው ተፈራ በሃገራችን የዘመናዊ

ትያትርና የመጽሐፍ ድርሰት ተቋዳሽ ብቻ አልነበሩም፡፡ የሌላም ፋና ወጊ ታሪክ ባለቤት ናቸው፡፡ ይህም

የአዕምሮ ህመምተኛው ሆድባሰው

እንዴ?

ለዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የልደት በዓል ነገ ይከበራልበኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ ሚና የተጫወተው ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ የልደት በዓል ሮብ መስከረም 17 ቀን 2004 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞ ች እንደሚከበር ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የአርቲስቱ ቤተሰቦችና ጓደኞች በገራ በመሆን የአርቲስቱ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን በዙ አርቲስት ተስፋዬ አበበ፣ አርቲስት የፊል ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ በገራ በሰጡት ጋዜጣዊ

መግለጫ በሮቡ ፕሮግራም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ሙዚቃ፣ ግጥም፣ መነባንብ፣ አጫጭር ተውኔቶችና ሌሎችም ዝግጅቶች ያቀርባሉ ተብሏል፡፡የአርቲስቱ የአንደበት ስራና የሙዚቃ እንዲሁም ዶክመንተሪ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀው በተጨማሪ በየዓመቱ የልደት በዓሉ ይከበራል ብለዋል፡፡ዘንድሮ 71 ዓመቱ ሲሆን ለ3ተኛ ጊዜ ከሞተ በኋላ እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡

በትያትር መቀዝቅና መዳከም ዙሪያ ውይይት ተካሄደ መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ትያትሮች የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከትያትር ባለሙያዎች አርቲስቶችና ከአዲስ አበባ ባህልና ትያትር አዳራሽ ከሀገር ፍቅር፣ ከራስ ትያትር ባለሙያዎች ባካተተው ስብሰባ አርቲስት ሕይወት አራጌ የስብሰባ ቡድን መሪ አቶ ሙሉ ገበየሁ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ የተነሳ ዋነኛ ምክንያቶች የአርቲስቱ የገቢ

ደረጃ ተጠቃሚ ያለመሆን ልማታዊ ጭብጥ ያላቸው ስራዎች የመቅረብ የፊልም አንደስትሪ መብዛትና አርቲስቱ ከትያትር ይልቅ ወደ ፊልም ስራ ላይ ማተኮሩ አዳዲስ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ያለመኖር ለትያትር መዳከም አይነተኛ ምክንያቶች መሆናቸው በዚህ ዙሪያ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሊያስብበት እንደሚገባና ተገቢው ትኩረት ሰተው መስራት እንዳለባቸው ተገልፆል፡፡

“ብድራት” ፊልም ሊመረቅነውበሩም ፊልም ፕሮዳክሽን የተሰራውና በደራሲና ዳሬክተር ምኒሊክ አራጋው አበበ የተዘጋጀው “ብድራት” በአይነቱ ለየት ያለና እስካሁን ከተሰሩት ፊልሞች በጭብጡ የባለስልጣን ስልጣናቸው ተገን አድርገው የሙስና ተግባር ሲፈፅሙ የሚያሳየው ፊልም የፊታችን መስከረም 21 በመላው አገሪቱ ይመረቃል፡፡ በማግስቱ መስከረም 22 በኢትዮጵያ ብሐየራዊ ትያትር በ11፡00 ሰዓት ላይ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ይመረቃል፡፡ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣

አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ጋዜጦች በሚገኙበት እንደሚመረቅ ታውቋል፡፡ “ብድራት” ፊልም ከአንድ ዓመት ከ6 ወር ጊዜ ወስዶል ከ380.000 ብር በላይ ወቶበታል፡፡ በዚህ ፊልም ላይ ወጣትና አንጋፋ ተዋናያዮች ተውነውበታል፡፡ ተዋናኝ ጌታቸው ስለሺ ትግስት ባዩ፣ ሃይማኖት ደበበ፣ መሠረት መኮንን፣ መሳይ ሙሉጌታ ፊልሙ ላይ ሰርተዋል፡፡

ከ” ኮ”ና “ካ” የፈለቀች አርቲስት“የፍቅር ጮራ” ደራሲ ማነው?

ወደ 5 የዞሯል

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

82ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 9ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

82ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 9ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ስለ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬወ/ሮ ብርሃኔ ተስፋዬ በእስር ላይ የሚገኘው የጋዜጠኛ ውብሸት

ታዬ ባለቤት ናት፡፡ በባለቤቷ ዙሪያ ባልደረባችን ብዙአየሁ ወንድሙ አነጋግሯታል፡፡

ውብሼት የት ተወለደ? አስተዳደጉስ? - ውብሼት የተወለደው ፊቼ አካባቢ ነው፡፡ ለቤተሰቦቹ

11ኛ እና የመጨረሻ ልጅ በመሆኑ በነጻነት ነው ያደገው፡፡ ታላላቆቹም እየተቀባበሉትና እያቀማጠሉት በምቾት ነው ያሳደጉት፡፡

ትምህርቱስ?- የመጀመሪያ ደረጃ ትምህረቱንና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ

ትምህርቱን ፊቼና ነው የተማረው፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ዝዋይ ተምሮ አጠናቀቀ፡፡ ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በጋዜጠኝነት ተመርቋል፡፡

የሥራው ህይወቱ ምን ይመስላል?- ዩኒቲ ዩኒቨርስቲ በትምህርት ላይ እያለ የሚማርበት ዩኒቲ

ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ የሚያሳትመው አንድ ጋዜጣ ነበር፡፡ በዚያ ጋዜጣ ላይ ተሳትፎ ያደርግ ነበር፡፡ ተመርቆ እንደወጣ ሓዳር ጋዜጣ ሥራ ጀመረ፡፡ ከዚያም በመሰናዘሪያ፣ በነጋድራስ፣ በጐግል፣ በአውራምባ ታይምስ ጋዜጦች ላይ ሠርቷል፡፡

የውብሼትን ተፈጥሮ ወይም ከጓደኞቹ፣ ከሥራ ባልደረቦቹ ከጐረቤቶቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዴት ትገልጪዋለሽ?

- ውብሼት በተፈጥሮው ለሰው ይጨነቃል፡፡ ከራሱ ጥቅምና ችግር ይልቅ የሰው ጉዳይ የሰው ችግር ያስጨንቀዋል፡፡ ሰው ሲቸገር ማየት አይፈልግም፡፡ ሰውንም ማስቸገር አይፈልግም፡፡ የማስታውሰው አንድ ጊዜ የልጃችን ልደት ይከበር ነበር፡፡ ምሽት ቤተዘመድና ጓደኞቻችን ሙዚቃ ከፍተው መጫወት ፈለጉ፡፡ ጐረቤት ሰው ሞቷል ሐዘን ነው አይቻልም ይላል፡፡ ለቅሶው ቆይቷል እኮ እያለ ዘመድም ጐረቤትም ይጫወቱ ሲሉ 40 ቀን አልሞላም ይከለከላል፡፡ የሐዘኑ ባለቤቶች ሰምተው በመምጣት ችግር የለውም ተዋቸው ይጫወቱ ሲሉት አይቻልም ብሎ ቅሬታ በማሰማቱ ጫወታው ቀርቷል፡፡ በማህበራዊ ጉዳይ ይህንን ያህል የሚጨነቅ ነው፡፡ በሀዘንም በደስታም ቀድሞ ይገኛል፡፡ ከጓደኞቹና ከሥራ ባልደረቦቹም ቢሆን ጥሩ ግንኙነት አለው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሰው ሲቆጣ ሲናደድ የማብረድ የማቀዝቀዝ ችሎታ አለው፡፡ እኛ የምንኖረው ከግለሰብ ቤት ተከራይተን ነው፡፡ ተከራይተን በገባንበት ሠፈርና ጐረቤት ጋር ለመግባባትና የሰፈሩን ፀጥታ ለማክበር ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡ ቤታችን ውስጥ ድምጻችንን ከፍ አድርገን ስንናገር እንኳን ጐረቤት ትረብሻላችሁ እያለ ይቆጣል፡፡ አንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ስንሄድ አንድ ወጣት ከአንዷ ወጣት አንገት ላይ ወርቋን በጥሶ ይዞ ይሮጣል፡፡ ጮሃ ስታለቅስ፤ ውብሼት ሮጦ ሮጦ ልጁን ከያዘው በኋላ ወርቁን ተቀብሎ ለልጅቱ ይመልስለታል፡፡ ልጁ ያመልጣል፡፡ ልጅቱ የአንገት ወርቋን ተቀብላ ዝም ብላ ትሄዳለች፡፡ ምናለ አመሰግናለሁ፤ እግዜር ይስጥልኝ፡፡ ብትል እንኳን፤ እንዲህ መከራ አይቼ ተደባድቤ ተቀብዬ ከእጄ ምንትፍ አድርጋ ሄደች እያለ ሁሌ ያስቀናል፡፡ ራሱን ለሰው ሲል ይህንን ያህል አሳልፎ የሚሰጥ ነው፡፡

አሁን በእስር ቤት ውስጥ ስትመለከቺው ምን ይሰማሻል?

- በራስ መተማመኑ በጣም ደስ ይለኛል፡፡ አይዞሽ እያለ የበለጠ እኔን ያጽናናኛል፡፡

በሚዲያ እንደሰማነው እኮ ውብሸት ተጠርጥሮ የታሰረው “በሽብርተኝነት” ነው፡፡ በልማት አውታሮች ላይ አደጋ

ለማድረስ በቡድን ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ማስረጃ ተገኝቷል” እየተባለ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሲታይ በራስ የመተማመን መንፈስ ተገቢ ነው ትያለሽ?

- ው ብ ሸ ት ን የማውቀው ባለቤቴ ስለሆነ አይደለም፡፡ የተወለድነው አንድ አካባቢ ነው፡፡ አብረን ነው ያደግነው፡፡ ባህርዩንም ተፈጥሮውንም ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡ የሚናገረውንና የሚሰራውን ብቻ ሳይሆን ሊሠራ ያሰበውንም ጠንቅቄ አውቀዋለሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ውብሸት እኮ እንኳን የህዝብ የልማት አውታር ሊያጠፋ የግለሰብ ንብረት አላግባብ ሲባክን የሚጣላ ሰው ነው፡፡ ምግብ ቤት ገብቶ እጁን ሲታጠብ ውሃ ያለአግባብ ሲፈስ ሲያይ ለምን ይፈሳል ብሎ የሚጣላ ነው፡፡ ቤተሰቡን፣ ተከራዮችን ብቻ ሳይሆን የአከራዩን የቤቱን ባለቤቶች መብራትና ውሃ አላግባብ አባከናችሁ የሚል ሰው እኮ ነው፡፡ እኔ አንዳንድ ጊዜ እያፈርኩና እየደነገጥኩ በቤታቸው በንብረታቸው አንተምን አገባህ ስለው “ይሄ የነሱ የግል ንብረት ብቻ አይደለም፡፡ የአገርና የህዝብ ንብረት ነው፡፡ መብራቱም ውሃውም የሚመጣው በውጪ ምንዛሪና ወጪ ነው፡፡ የሚጐዱት ወይም የሚከስሩት እነሱ ብቻ አይደሉም፡፡ መንግስትና ህዝብ ጭምር ነው፡፡ የእኔም የልጄም ሀብትነው” የሚል ነው፡፡ ምግብ ቤት ገብቶ ያለአግባብ ውሃ ሲፈስ መብራት ሲበራ ቢያይ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ የለውም ብሎ አስጠርቶ የሚያነጋግር ነው፡፡ ሌላም ሌላም በርካታ ምሳሌዎችን ልጠቅስልህ እችላለሁ፡፡ በጥቅሉ ውብሸት የመንግስትንና የህዝብን ንብረት ይቅርና የግለሰብን ንብረት ከግል ንብረቱ በላይ የሚቆረቆር ሰው ነው፡፡ በምንም መልኩ በሽብር ተግባር ንብረትና ልማት ለማውደም ይንቀሳቀሳል ብዬ አላምንም፡፡ ለዚህ ነው ዛሬም በራስ መተማመኑን የማየው፡፡

በአንቺ እምነት በምን ምክንያት ታሰረ ብለሽ ነው የምታምኚው?

- በጋዜጠኝነቱ በሚጽፈው ነው ፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በጋዜጠኝነቱ እየታሠረ ተፈቷል፡፡ ውብሸት ሙሉ ጊዜውን የሚያጠፋው በማንበብና በመጽሐፍ ነው፡፡ ሀብቱም ንብረቱም መጽሐፍ ነው፡፡ ያለንበት ቤት ቀይረን ወደ ሌላ ቦታ ዕቃችንን ስናጓጉዝ ትልቁ ጓዛችን የእሱ መጽሐፍ ነው፡፡ ልጁን ለማጫወትና ለማዝናናት እና ለማህበራዊ ጉዳይ ከሚያጠፋው ውስን ሰዓት ውጪ ረጂሙን ሰዓት በማንበብና በመጽሐፍ ያሳልፋል፡፡ የሚጽፋቸው ጽሑፎች መንግስትን አስከፍቶት ይመስለኛል፡፡

የውብሸት ልዩ ባህርይ የምትይው ምንድነው? - መብቱን ማንም እንዲነካበት አይፈልግም፡፡ የሰውን

መብትም አይነካም፡፡ የሰው መብት ሲነካና ሲደፈር ቀድሞ የሚጋፈጠው እሱ ነው፡፡ ሁል ጊዜ የሚናገረው ልጄ የተሻለ ህይወትና ሥርዓት ማየት አለበት፡፡ ልጄ እንዲኖር የምፈልገው እኔ የኖርኩትን

ኑሮ ሳይሆን ከእኔ የተሻለ ነው የሚል ምኞት አለው፡፡ ለዚህ ነው የልጁንም ስም ፍትህ ብሎ ስም ያወጣለት፡፡ ውብሸት ከቢሮው ሲወጣ ሮጦ ቤቱ ነው፡፡ ትንሽ ከዘገየ እንኳን እዚህ ደርሻለሁ እያለ አስሬ ይደውላል፡፡ ከሥራው ውጪ ከቤቱና ከልጁ ተነጥሎ ማሳለፍ አይፈልግም፡፡ እኛም ስለ አስለመደን ትንሽ ከዘገየ እንሰጋለን፡፡

አሁን እሱ በመታሰሩ ምን የተፈጠረባችሁ ችግር አለ?- አሁን እሱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገብቷል፡፡ ማዕከላዊ

ወንጀል ምርመራ እያለ ድብደባ ተፈጽሞበት የግራ ጆሬዬን ያመኛል ይል ነበር፡፡ አሁን እየተሻለው ነው፡፡ እኔን እንደ ግል ፖሊሶች የማዋከብና የማስፈራራት ነገር ነበር፡፡ አሁን ማንም አይናገረኝም፡፡ ማረሚያ ያሉ ፖሊሶች በሥርዓቱ ያስተናግዱናል፡፡ ቃሊቲ ከገባ በኃላ በፖሊስ እስከ አሁን የገጠመኝ ግልምጫም፣ ስድብም፣ ማስፈራራትም የለም፡፡ በእርግጥ የሁለት ዓመት ልጅ ይዞ ቃሊቲ መመላለስ ችግር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደሞዙ ተቋርጧል፡፡ የገቢ ምንጭ በተቋረጠበት፤ የኑሮ ውድነቱ እየባሰበት በሄደበት ወቅት ያሉትን ችግሮች መገመት ይቻላል፡፡ የቤት ኪራይ ሌላው ችግር ነው፡፡ ከደሞዙ ውጪ ሌላ ተጨማሪ ገቢ አልነበረንም፡፡

ቅድም ስትገልጪ በራስ መተማመኑ ደስ ይለኛል ብለሽ ነበር፡፡ አሁን ባለበት ሁኔታ እንዴት ነው?

- ቅድም እንደነገርኩህ አሁን ያለበት ቦታ ፊት ከነበረበት ቦታ የተሻለ ነው፡፡ ፖሊሶችም ሥነ ሥርዓት አላቸው፡፡ አቀባበላቸውም ስብአዊ ነው፡፡ ስትሄድም በጥላቻ ወይም በጠላትነት ዓይን አይቀበሉህም ደስ ይልሃል፡፡ ማዕከላዊ ያሉ ፖሊሶች ከጥበቃ እስከ ምርመራና ኃላፊነት ቦታ እስካሉት ድረስ ምንም ነገር መናገር አልፈልግም፡፡ አብረን መኖር ከጀመርን ጊዜ ጀምሮ ከሁለትና ከሦስት ቀን በላይ ተለያይተንም አናውቅም፡፡ ለቤቱ ትልቅ ዋጋ የሚሰጥ ነው፡፡ በየሰዓቱ እየደወለ እኔንና ልጁን ያለንበትን ሁኔታ ማወቅ የሚፈልግ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ በማይችልበት ወቅት የገቢ ምንጫችን ሙሉ በሙሉ መቋረጡን በሚያውቅበት ሁኔታ መጨነቁ ማሰቡ የማይቀር ነው፡፡ እኔ በተቻለኝ መጠን ምንም ችግር እንደሌለ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ ከዚያ በተረፈ ጥሩ ነው፡፡

ሊያኮራሽ ይችላል? እኔ ይህንን አላምንበትም፡፡ በሽብር -

ተግባር ውስጥ ይገባል ይሳተፋል ብዬም አላስብም፡፡ አባቴን በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ በሐዝብ ሀብትና ንብረት ላይ ውድመት ለመፈጸም በሰው ሕይወት አደጋ እንዲፈጠር ሊተባበር አይችልም፡፡ ሽብርተኞች እኮ ከሰብአዊ አመለካከት ውጪ የሆኑ ናቸው፡፡ ስለ ሰው ልጅ ደንታ የሌላቸው ሱሰኞቹ ናቸው፡፡ ዘርዬ ግን አይደለም፡፡ ለሰው ፍጡር ትልቅ ክብር ያለው ነው፡፡ ወንጀልን በመከላከል ሥራ የሚሳተፍ እንጂ ወንጀል ለመፈጸም ተፈጥሮውም ባህርዩም አይፈቅድም፡፡

አንቺ በምን ምክንያት ታሰረ ብለሽ ታምኛለሽ?

የአባቴ ፓርቲ የምርጫውን ሥን ምግባር አልፈርምም ብሎ አቋም ከወሰዱት ፓርቲዎች የመጀመሪያው ተቃዋሚ ፓርቲ ነው፡፡ የምርጫውን ውጤትም አልቀበልም ብሎ አቋሙን በግልጽ የወሰደ ፓርቲ ነው፡፡ ከምርጫው በኋላ በርካታ የፓርቲው አባላት ከሥራ ታግደዋል፡፡ እርዳታ ተከልክለዋል፡፡ ወከባ ዛቻ ይፈፀምባቸው እንደነበረ በተደጋጋሚ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ የፓርቲውን መግለጫዎች አንብቤአለሁ፡፡ ግንቦት 2ዐን ቀን በመቃወም ሕዝባዊ ሠለማዊ ሠልፍ ለማድረግ ፈቃድ ጠይቀው ነበር፡፡ የአሜሪካን የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂላር ክሊንተን አዲስ አበባ ሲመጡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታና የሚፈጸመውን ኢ-ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ ጥሰት

ለመግለጽ እንዲችሉ ፕሮግራም አንደያዝላቸው ኢንባሲውን በጽሑፍ ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የተፈፀመበት ጥቃት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በእርግጠኝነት ዘርዬ የታሰረው ኢህአዴግን አምርሮ በመታገሉ ነው፡፡ የታሠረው በአመለካከቱ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ይህንን ሁሉ አንቺ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?

እኔ የዕለት ተዕለት ሁኔታ እከታተላለሁ፡- ፡ የፓርቲውንና የአባቴን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

አቶ ዘሪሁን አሁን ያሉበት ሁኔታ እንዴት ነው?

አሁን ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ነው፡፡ - እንደ አንድ እስረኛ ተይዟል፡፡ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ በነበረበት ጊዜ ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት ተፈጽሞበታል፡፡ ሁለት ቀን ሙሉ እጁ ታስሮና ተሰቅሎ የማያውቀውንና ያልፈፀመውን እንዲያምን ሲደበደብ እንደነበር ለፍ/ቤት ሲያስረዳ ሰምቻለሁ፡፡ የተፈጸመበትን ግፍ ለቤተሰቡም ገልጿል፡፡ ለህግ ቆሜአለሁ፣ህግ አስከባሪ ነኝ ከሚል አካል ህግ እናውቃለን ህገ-መንግሥትን እናከብራለን ከሚሉ ወገኖች እንዲህ ዓይነት ግፍ በማየቴ አዝናለሁ፡፡ ስለ ህግ የበላይነት ስለ ፍትህ ስለ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ ለማውሪት ምን ሞራል አላቸው? ጠባሳውን አሁንም ማየት ይቻላል፡፡

ፍ/ቤቱ ይህንን ሲሰማ ምን አለ? ድብደባው ይቁም፡፡ ህክምና ይደረግለት ብሏል፡፡ በዚህም አዝኜአለሁ፡፡ አንድን በሕግ ቁጥጥር ሥር ያለን ሰው እንዲህ አይነት ግፍ የፈጸመ ለምን በህግ አይጠየቁም? ለምን እርምጃ አይወስዱም? ይህ ድርጊት ከተፈጸመ ሁለት ወር አልፎታል፡፡ ህክምና አላገኘም፡፡ ህመሙ ዛሬም ይሰማዋል፡፡ድብደባው ይቁም ብሎ ብይን በቂ አይደለም፡፡

ፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ይህ ሁሉ አይገጥመውም ነበር አሁን ላይ ሆነሽ ስታስቢው በፖለቲካ ውስጥ ባይገባ ኖሮ ብለሽ አታስቢም? በፍፁም አላስብም፡፡ ፖለቲካ ውስጥ የገባው አገሪቱ ውስጥ ያለው ፖለቲካ ሁኔታ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እየከፈለ ያለው መስዋዕትነት አንድ ክቡር ዜጋ ለአገሩ የሚከፍለው ነው፡፡ ለአገርና ለህዝብ የሚከፈል ዋጋ ከምንም በላይ ክብር አለው ብዬ አስባለሁ፡፡ የእሱ መታሰር መደብደብ መሰቃየት የእኛም መጉላላትና ለችግር መጋለጥ ከሕዝብና ከአገር ጥቅም ጋር ሲወዳደር ሚዛን የሚጻፉ አይደሉም፡፡

አባትሽ በመታሰሩ በኑሮአችሁ ላይ የፈጠረው ችግር አለ?የቤተሰብ የገቢ ምንጭ ሲቋረጥ የሚፈጠረውን ለማንም ግልጽ ነው፡፡ የኑሮ ውድነቱ ከዕለት ተዕለት የምትመለከተው ነው፡፡ ችግራችንን ተቋቁመን አቅማችን በፈቀደው ሁሉ ዘርዬን ባለበት ለመርዳት እየሞከርን ነው፡፡

ስለ ዘሪሁን ... ከገፅ 3 የዞረ

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

102ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 11ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

102ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 11ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ዛሬ መንግሥት እንደ ፋሽን የያዘው በሚመስል መልኩ ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚታገሉ የሠላማዊ ትግል አርበኞችን በሽብርተኝነት መወንጀል ሆኗል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድት) መስከረም 5 ቀን 200 ዓም ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡ ፓርቲው ይህንን መግለጫ የሰጠው ‹‹ሕዝብን የሚያሸብር ሁሉ ራሱ በማያቋርጥ ፍርሃትና ሽብር የተዋጠ ነው!›› ሲል ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ ፓርቲው ባለሦስት ገጽ መግለጫው በርካታ ነጥቦችን በመዳሰስ አብራርቷል፡፡ መግለጫ አያይዞም ‹‹ሽብርተኝነትን በሚያደርሰው ጉዳት ብቻ ሳይሆን ዓላማውም የራስን ፍላጎት በሌሎች ላይ መጫን በመሆኑ ተቀባይነት የሌለው የእቢተኞችና የጉልበተኞች ድርጊት በመሆኑ አጥብቀን እንኮንነዋለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሽብርተኝነት ስም ሽብር የሚነዛ አካልን አጥብቀን እናወግዛለን›› ብሏል፡፡ ‹‹መስከረም 3 ቀን 2ዐዐ4 ዓም በፓርቲያችን ከፍተኛ የአመራር አባል ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በሆኑት በአቶ አንዱዓለም አራጌ፣ በፓርቲያችን የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት በአቶ ናትናኤል መኮንን እና በአቶ አሳምነው ብርሃኑ ላይ የተወሰደው የእስር እርምጃና መታሠራቸውን ተከትሎ ከመንግሥት የተሰጠው መግለጫ ይህንኑ ሀቅ የሚያረጋግጥ አንድ ተጨማሪ ማስረጃ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ የማን አለብኝነት እርምጃ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ሁሉ የመጨረሻውም እንደማይሆን ከኢህአዴግ የ2ዐ ዓመታት የአገዛዝ ሥርዓት ባህሪ የምናውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ነፃ ጋዜጠኛ እስክራንድ ነጋ በሽብርተኝነት መታሰር ከዚህ ተለይቶ አይታይም፡፡ በመግለጫው ላይ የተገኙ ጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከጥያቄዎቹም ጥቂቶቹ ‹‹የታሠሩት አባሎቻችሁ እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደ ግለሰብ ነው፡፡ እያንዳንዱ አባላችሁ በሽብርተኛ ቡድን ውስጥም ይሁን በሌላ ድርጅት ውስጥ አለመኖሩን እንዴት እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ? ለወደፊት ምን ማድረግ አስባችኋል? እናንተ ሽብርተኝነትን እንዴት ትገልፁታላችሁ? እናንተ አሁን ለኢህአዴግ ምክር እየሰጣችሁ ነውን? የህዝብ አመጽ ይቀሰቅሳል እያላችሁ ነው? የታሠሩት እስረኞች የት እንዳሉና በምን ሁኔታ ላይ

እንዳሉ የምታውቁት ነገር አለ?; የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ፓርቲውን ወክለው መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የጥናትና ምርምር ኃላፊው ዶ/ር ኃይሉ አርአያ፣ የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ አስራት ጣሴ የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ዳዊት አስራደ ጥያቄዎቹን በጋራ መልሰዋል፡፡››

ዶ/ር ነጋሶ በሰጡት መልስ ‹‹አንዱዓለም አራጌ ሠላማዊ ትግልን እንደ ኃይማኖት አምኖ የተቀበለ ነው፡፡ ቆራጥና የዓላማ ጽናት ያለው ለወደፊት ለመሪነት ተስፋ የሚጣልበት ወጣት ነው፡፡ ከምርጫ 2ዐዐ2 ክርክር ጀምሮ ጎልቶ የወጣ ለነፃነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ለሰብአዊ መብት የሚሟገት ነው፡፡ ኢህአዴግ ደግሞ የሚከራከረውንና የሚቋቋመውን ማየት አይፈልግም፡፡ በኦሮምኛ አንድ አባባል አለ፡፡ በአንድ ቦታ እኩል ጉልበት ያላቸው ወይፈኖች በአንድ ላይ አይኖሩም ይባላል፡፡ አንዱ አንዱን አሸንፎ ካላሳመነው በስተቀር አይላቀቁም ይባላል፡፡ ኢህአዴግም በጠንካራ አስተሳሰብ የሚቋቋሙትን የማጥፋት ሥራ ይሰራል፡፡ እኛ ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ አንዱ ዓለምና ሌሎች የብሔራዊ ም/ቤት አባሎቻችን ነፃና ህጋዊ ሰዎች ናቸው፡፡ ሌሎች የታሠሩ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችም እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡ ህዝቡ የሉዓላዊ ሥልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንታገላለን፡፡ ሽብርተኝነትን በየትኛውም መልኩ እንቃወማለን፡፡ በአገራችን ያለው ችግር አፍንጫችን ላይ ደርሷል፡፡ ችግር ሲበዛ ህዝብ መንቀሳቀሱ አይቀርም፡፡ አንድነት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ አይሰራም፡፡ አይተባበርም የሚሉት ትክክል አይደለም፡፡ 121 የኦፊዴንና የኦህኮ አባላት ሲታሰሩ አውግዘናል፡

፡ በመድረክ ላይ የጠላትነት ወሬ የሚያወሩትን ተው በሏቸው ማንኛውም ሰው አባላቶቻችንንም ጨምሮ ህጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ መብቴን አስከብራለሁ ብሎ ቢሄድ አንቃወምም፡፡›› በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡

ኢ/ር ግዛቸው በበኩላቸው ሲመልሱ ‹‹ የገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲፈጠር አይፈለግም፡፡ አንድ አምባገነን ግዙፍ ፈላጭ ቆራጭ ፓርቲ ለመመስረት ይፈልጋል፡፡ ሽብርተኝነት ዓለም አቀፋዊ ችግር ነው፡፡ ሽብርተኝነትን በማንኛውም መልኩ ቢከሰት እንታገላለን፡፡ ሽብርተኝነትን በጥንቃቄ እንታገላለን፡፡ በአንዳንድ አገሮች ሽብርተኝነትን እንደ ፖለቲካ መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙ አሉ፡፡ አንድነት ፓርቲ ይህንን አይደግፍም፡፡ አይደግፍም ብቻ ሳይሆን ያወግዛል፡፡ ሽብርተኝነት ለሰው ልጅ ሁሉ አደጋ ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አባሎቹን ሲመለምል ህግና ደንብ አለው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ አባሉ የሚመለመለው አንድ አባል አረጋግጦና ፈርሞ ነው፡፡ በመቀጠል ለሦስት ወር በእጩ አባልነት ይቆያል፡፡ በዚህ ሦስት ወር ውስጥ የክትትል ጥናት እናደርጋለን፡፡ የፓርቲውን ደንብና ፕሮግራም አምኖ መቀበሉን እናረጋግጣለን፡፡ ከዚህ በኋላ ነው በአባልነት የምንቀበለው፡፡ አባል ከሆነም በኋላ የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን እንከታተላለን፡፡ በዚህ ምክንያት አባሎቻችን ከሽብርተኝነት ሆነ ከሌላ ማንም ድርጅት ጋር ግንኙነት የላቸውም ብለን በእርግጠኘነት የምንናገረው ለዚህ ነው፡፡ ዜጎችን ለማሸማቀቅና ለማስፈራራት ማሰርና ማስፈራራት መፍትሔ አይደለም፡፡ እኛ የምንፈልገው የሠላምና ብልጽግና ዘመን እንዲሆንልን እንጂ ክትትልና አፈና አይጠቅምም፡፡ ኢህአዴግ የሰለጠነ መንገድን መከተል አለበት፡፡ ስልጡን ንግግር የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት መከተል አለበት፡፡ በማለት ሃሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡

አቶ አስራት ጣሴ በበኩላቸው በሰጡት መልስ ‹‹ጠ/ሚኒስትሩ በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ ጠይቋቸው መልስ ሲሰጡ ሰምቼአለሁ ‹‹በሰሜን አፍሪካ ያለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ወደ አገራችን ቢመጣስ; ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ለአምስት ዓመታት

የኮንትራት ውል ፈርሞልናል ብለዋል፡፡ ግን እሳቸው ያልተረዱት ነገር አንድ ውል በተከናወነው ውል መሠረት ካልተፈፀመ ውሉን ማፍረስ እንደሚቻል አልተረዱትም፡፡ እኛ ቤት አልባና ህዝብ አልባ የሆነች አገር እንዲፈጠር የሚፈልግ ጤነኛ አዕምሮ የለም፡፡ ኢህአዴግ ወደ ውስጥ ወደ ራሱ ለማየት ፍቃደኛ ይሁን፡፡ ህዝብን መተንፈሻ ለማሳጣት መሯሯጥ ተገቢ አይደለም፡፡ ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረ እለት ለመጀሪያ ጊዜ ዜና ሲያስተላልፉ ያሉት ትዝ ይለኛል፡፡ ‹‹ብሶት የወለደው›› ብለው ነበር፡፡ ብሶት የሚወልደው ኢህአዴግን ብቻ ነው እንዴ? ህዝብ በብሶት ተነስቶ ያልተፈለገ ችግር እንዳይፈጠር የህዝብ ጥያቄን መልስ ነው የምንለው ኢህአዴግ ደጋግሞ የሚናገውና ነገር አለ፡፡ ‹‹እኛ ተቃዋሚዎች እግር እንዲያወጡ እናግዛለን፡፡›› ይላሉ እግር ሲያበቅሉ እግራቸውን እንቆርጣለን ይላል፡፡ አንድ ፓርቲ ወይም ግለሰብ ጠንከር ብሎ ሲወጣ የፖለቲካ ስብእናውን እያዳበረ ሲመጣ የሚጠብቀው ይኸው ነው፡፡ ለአንዱ ኦነግ፣ ለአንዱ ግንቦት ሰባት ለሌላውም ደግሞ ሌላ ይዘጋጅለታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከሜዳ ላይ እያነሱ ሰውን ሽብርተኛ እያሉ መለጠፍ አስነዋሪ ሥራ ነው፡፡ በሽብርተኘነት ላይ መቀለድ ነው፡፡ በየአገሩ በሽብርተኝነት በሚሰቃዩ የሰው ፍጡራን ላይ ማላገጥ ነው፡፡ ለሰው ልጅ ክብር አለመስጠት ነው፡፡ ኢትዮጵያ እኮ የሽብር አደጋዋ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ አንድነት እንደ ፓርቲ እያንዳንዱ የአንድነት ፓርቲ አባል እንደግለሰብ አገራችን የሽብር ሰለባ እንዳትሆን የሚፈለግብንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ሠላማዊ ትግሉ አንድ እርምጃ ወደፊት በተራመደ ቁጥር በሽብርተኝነት ስም ሠላማዊ ዜጎችን እየፈረጁ እስር ቤት መክተት እጅግ ጥፋት ነው፡፡ ተቀፍድደን መያዛችንን

እንቃወመዋለን፡፡ አንዱዓለም ከመታሠሩ ጥቂት ሰዓታት በፊት እኔ ቢሮ ነበር፡፡ የመጨረሻ ሰዓት ያነጋገረኝ ‹‹ዛሬ እኮ ለመጀመሪያ ቀን መዋለ ህፃት ልጄን አስገብቼው መጣሁ፡፡ ጥዋት ሳስገባው ለማስታወሻ ፎቶ ግራፍ አስነስቼ ነው ት/ቤት ያደረስኩት፡፡ ማታ ሲመጣ ውሎውን እንዴት እንዳሳለፈ እንዴት ብሎ እንደሚተርክልኝ ለመስማት ቸኩዬአለሁ ብሎኝ ነበር፡፡›› እንግዲህ አንዱዓለም እንዲህ ዓይነት ሩህ ሩህ የፍቅር አባት ነው፡፡ እንግዲህ በዚያን ሰዓት የልጁን አንደበት ለመስማት የሚጓጓውን ሰው ነው በሽብርተኝነት የሚይዙት እስክንድር ነጋም የ6 ዓመት ልጁን ከት/ቤት አውጥቶ ወደ ቤት ለመውሰድ ሲሄድ ነው የያዙት፡፡ ይህ ህፃን ልጅ እስር ቤት የተወለደ ነው፡፡ ልጁን ቤት እስኪያደርስ ጊዜ እንኳን ጊዜ አልሰጡትም፡፡ ከህፃን ልጁ ነጥለው እጁን በካቴና አሠሩት፡፡ ህፃን ልጁ እያለቀሰ ሲንፈራፈር ከበው ፊልም ይቀርፁታል፡፡ እነዚህ ሰዎች ናቸው ሽብርተኞች?፡፡ ታዲያ ይህ በሽብርተኝነት ላይ መቀለድ አይደለም፡፡ ሽብርተኞች እኮ የት እንደሚውሉ ምን ዓይነት ስብዕና፣ ሳይኮሎጂ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ ስብዕናቸው የተጠና ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ስብዕና ያላቸውን አባቶች፣ የሠላም አርበኞች እንዲሁ ዝም ብሎ ተነስቶ ‹‹ሽብረተኛ›› ብሎ የሬዲዮና የቴሌቪዥን አቅም አለኝ ብሎ መለጠፍ እጅግ ነውር ሥራ ነው፡፡ በእውነት በታሪክም፣ በህዝብም፣ እምነትም ካላቸው በእምነትም የሚያስጠይቅ ነው፡፡ እኛ የኢህአዴግን ባህርይ አጥንተነዋል፡፡ ሠላማዊ ትግል ይፈራል፡፡ የሠላማዊ ትግል ፈሪ ነው፡፡ የሚፍልገው ሽብር ፈጣሪ ብሎ ጦርነት ሊገጥም ነው፡፡ እኛ ደግሞ እያልን ያለነው የምንፈልገው ሠላማዊ ትግል ነው፡፡ አንተ በያስከው መትረየስ፣ አንተ በያዝከው ቦንብ አንገጥምህም፡፡ እኛ እምንገጥምህ ህጋዊና ሠላማዊ በሆነው ትግል ነው፡፡ አንባገነኖች ሠላማዊ ትግልን ይፈራሉ፡፡ ምክንያቱም የነሱ የጉልበት ምንጭ ታንክ ነው፡፡ የነሱ የጉልበት ምንጭ ወታደር ነው፡፡ ፖሊስ ነው፡፡ የሠላማዊ ትግል ጉልበት ግን እነዚህ አይደሉም፡፡ ስለዚህ ይንገሩን፡፡ ሠላማዊ ትግልን ተው ይበሉን፡፡ ሠላማዊ ትግልን ይቅር ይበሉን፡፡ እኛ ደግሞ የምንላቸው የዚህችን አገር ሠላማዊ ትግልን ተስፋ ለማስቆረጥ የምታደርጉት ትግል ነው እያልን ነው፤ እኛ እኮ ስለ ሠላማዊ ትግል ስንታገል ከጀርባችን ብዙ ጫና አለብን፡፡ የማይቻል ነገር ይቻላል ትላላችሁ ይሉናል፡፡ መድረኩን ይዛችሁ ሰውን ማስደብዳብ ነው፡፡ ማስቀጥቀጥቀጥ ነው፡፡ ማሳሰር ነው፡፡ እየተባልን እየተከሰስን ነው፡፡ የለም ወደ ኋላ አንመለስም፡፡ ሠላማዊ ትግል ይቻላል፡፡ ዛሬ ባይቻል ነገ ይቻላል፡፡ ነገ ባይቻል ተነገወዲያ ይቻላል፡፡ እያልን ነው፡፡ አሁንም የምንለው ይህንኑ ነው፡፡

ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ለጥያቄዎቹ ተጨማሪ መልስ ሲሰጡ ‹‹ሽብር ማለት ምን ማለት ነው? አሸባሪ ማለት ምን ማለት ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ይህ ጥያቄ የሁሉም ሰው ጥያቄ ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በአንድ ቤት በአሸባሪዎች ፈንጂ ቢፈነዳ የአካባቢው ሰዎች ወይም የቤቱ ባለቤት ለምን ብሎ ይጠይቃል?፡፡ ለምንድነው እንዲህ ዓይነት ኢ-ሰብዓዊ የሆነ ተግባር የተፈፀመው ብሎ ይጠይቃል፡፡ ምክንያቱም ሊያስረዳው የሚችለው ነገር አይደለም፡፡ መልስ የሌለው ነገር ስለሆነ ነው፡፡ መንግሥት በሚወስዳቸው ትርጉም የለሽ ተግባሮች ለምን እያልን እንጠይቃለን፡፡ እዚህ ደረጃ ድረስ ወደቅን እንዴ? ብለን እንጠይቀለን፡፡ ምክንያቱ ስውር አይደለም ግልጽ ነው፡፡ ይህ መንግሥት አውራ ፓርቲ ነኝ ብሎ ወስኖ በሥልጣን ላይ ለመቆየት መህልቁን ጥሎአል፡፡ ይህንን ቦታ እንዲያጣ አይፈልግም፡፡ እዚያ ቦታ ላይ ለመቆየት የሚያደርገው ነገር የለም፡፡ ሥልጣን ነው፡፡ በሦስተኛው ዓለም ሥልጣን ማለት ቢዝነስ ነው፡፡ በደሀው ዓለም ሥልጣን ቢዝነስ ነው፡፡ በትላልቁ በለሙ አገሮች የፖለቲካ ሥልጣን የዓላማ ማስፈፀሚያ ነው፡፡ ወደ ፖለቲካ ሥልጣን የሚመጡት አገራዊና ህዝባዊ ዓላማ አላቸው፡፡ ራእይ አላቸው፡፡ ዓላማቸውንና ራእያቸውን ለማስፈፀመ ይጠቀሙበታል፡፡ የፖለቲካ ህልማቸውን እውን ለማድረግ ነው ወደ ሥልጣን የሚመጡት፡፡ በእኛ አገር ግን የፖለቲካ ሥልጣን የመክበሪያ ቦታ ነው፡፡ በዚያ በሥልጣን በሚቆይበት ጊዜ የድርሻውን ይዞ ለመሄድ ነው፡፡ አሁን ይህ መንግሥት እኮ ኢንፖየር እየገነባ ነው፡፡ ያልገባበት የኢኮኖሚ ዘርፍ የለም፡፡ ይህንን ሁሉችንም እናውቀዋለን፡፡ በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት እየገነባነው፡፡ ይህንን ማጣት አይፈልግም፡፡ እሱ ብቻ አይደለም፡፡ ደጋፊዎችም አፍርቷል፡፡ ይህ አሁን የያዝነው ተግባር እንጀራችን ነው፡፡ ህልውናችን ነው ብለው አምነዋል፡፡ ምናልባትም መስዋዕትነት የሚከፍሉበት ደረጃ ላይ የደረሱ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ እዚህ ካሉት ፊልም ቀራጮች፣ የካሜራ ሰዎች ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ ካሉት ባለሥልጣናት ድረስ ሥራ ነው፡፡ ቢዝነስ ነው፡፡ አትፈርዱባቸው፡፡ የእንጀራ ጉዳይ ነው፡፡ መልሱ ይኸ ነው፡፡ በአንድ ዝቅተኛ ተቋማት ውስጥም ብትወርዱ ሲንደፋደፉ ትመለከቱታላችሁ፡፡ ገብቶአቸው አይደለም፡፡ የገባቸው የቅርብ እንጀራቸው ነው፡፡ ሌላ የፖለቲካ፣ የርዮተ-ዓለሙ ጉዳይ፣ የአገር ህልውና ጉዳይ ገብቶአቸው አይደለም፡፡ የዓለማችን ጉዳይ ገብቶአቸው አይደለም፡፡ ‹‹እንጀራህ ነው፡፡ ኢህአዴግ ካለ እንጀራህን ታገኛለህ፡፡ ኢህአዴግ ከሌለ እንጀራህን ታጣለህ›› እያሉ

‹‹መንግሥት እንደ ፋሽን. . . የሠላማዊ ትግል አርበኞችን በሽብርተኝነት መወንጀል ሆኗል›› አንድነት ፓርቲ

‹‹አንድነት የያዘው የትግል መስመር ግልጽ ነው፡፡ ህጋዊና ሠላማዊ የትግል መስመር ነው፡፡ በአንድነት ጥላ ሥር የተሰባሰቡት ታጋዮች በሙሉ የነፃነት ጥማት ያሰከራቸው ነፃነታቸውን በነፃ ምርጫ ለማስከበር በተደጋጋሚ ደፋ ቀና ሲሉ የሚታዩ ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ልባቸውን የሞላው፣ በማንነት ፍለጋ የናወዙ ንፁህ የኢትዮጵያ

ልጆች መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ሥም ማውጣት ታርጋ መለጠፍ ለምን አስፈለገ ብለን ስንመለከት ግልጽ የሆነ ነገር ነው፡፡ ኢህአዴግ በኢኮኖሚ ረገድ እያደረገ እንዳለው ነገር የጠቅላይ ገዢ ሂደት ሞኖፖላይዝም እንቅስቃሴ በፖለቲካው ዘርፍም በብቸኝነት ለመቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ እሱን የሚመስሉ አሚን አሚን የሚሉ ትናንሽ ፓርቲዎች ሰብስቦ መድብለ ፓርቲ ያለ ለማስመሰል እሽሩሩ እያለ እና እያባበለ ጉርሻ እየሰጠ ይዞ መራመድ እንጂ ህገ-መንግሥት በደነገገው መሠረት በአገሪቱ ውስጥ

እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲመሠረት ፍላጎት የለውም፡፡ ለሥልጣኑ የሚያሰጋ ምንም ዓይነት ኃይል እየመጣበት መሆኑን ሲያውቅ በምንም ዓይነት መንገድ ትግሉን በማኮላሸት በብቸኝነት አምባገነን ሆኖ የፈላጭ

ቆራጭ አገዛዝን ማስፈን ነው፡፡

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

102ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 11ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

102ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 11ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

ስለሚነግሩት ነው፡፡ መልሱ አጭር ነው፡፡ ለምን ለሚለው ጥያቄ መልሱ ኢህአዴግ በገጠር በጨለማ የሚጓዝ መንገደኛ ነው፡፡ ጨለማ ደግሞ ክፋት ነው፡፡ ቁጥቋጦ ሁሉ ዘሎ የሚያንቀው አውሬ ይመስለዋል፡፡ ስለዚህ ሁሌ ይደነብራል፡፡ በተራመደ ቁጥር ሁሉ እንደደነበረ ነው፡፡ ፓርቲዎችን ባየቁጥር፣ ጠንካራ ግለሰቦችን ባየቁጥር ይደነብራል፡፡ ጠንካራ ግለሰቦች በታዩት ጊዜ ሁሉ የሚታየው የሚያጣውን ነገር ነው፡፡ የአውራ ፓርቲ ነኝ ብሎ ራሱን ያስቀመጠበትን ኢምፓየርነቱን፣ በቢሊዬን የሚቆጠረውን ሀብቱን ማጣቱ ያስፈራዋል፡፡ ያስደነግጠዋል፡፡ ይህ ከሆነማ ኪሳራ ነው፡፡ ሊመጣ የሚችለው ሁሉ መወገድ አለበት ብሎ ያስገባል፣ የህልውና ጉዳይ ነው ብሎ ያስባል፡፡ ይህ የተሳሳተ ህልውና ነው፡፡ የሚያሳፍር የሚያሳዝን አመለካከት ነው፡፡ እያንዳንዷ እርምጃ እያንዳንዷ አፍራሽ የኃይል እርምጃ አመፁን ያስከትላል፡፡ አመጽን የሚቀሰቅስ ነው፡፡ አመጽን የሚያነሳሳ ነው፡፡ እኛ እኮ የምንፈራው ይህንን ነው፡፡ በእንግሊዝኛው ‹‹ For every action there is on equal reaction›› እንደምተውቁት እኛ ደግሞ በፖለቲካ ስንተረጉመው ደግሞ ‹‹ For every action is a greater reaction›› የበለጠ አጥፊ ነው፡፡ የበለጠ አውዳሚ ነው፡፡ በመጨረሻ የሚሆነው ይኸው ነው፡፡ ይህ ከመጣ ደግሞ ማንም አይተርፍም፡፡ ሁላችንም ተያይዘን እንጠፋለን፡፡ እኛ የምንታገለው ከዚህ አደጋ እንድንተርፍ ነው፡፡ ቆንጆ አገር አለን፡፡ ኩሩ ህዝብ፡፡ ሀብትም እግዚአብሔ በመጠኑ አድሎናል፡፡ እባካችሁ እንቀመጥና ስለ አገራችን እንወያይ፡፡ ስለአገርና ስለ ህዝብ ጥቅምና መብት እንነጋገር፡፡ ያሉብንን ችግሮች ፈተን ልማታችንን በጋራ እናልማ፡፡ ልማታችን የጋራችን ነው፡፡ ልማት እንፈልጋለን፡፡ አሁን እንደምንሰማው ይህ መንግሥት የልማት አባት እንደሆነ፤ ሌላው ደግሞ ተቃራኒ እንደሆነ፤ እንዲው ትልቅ ሸክም እንደተሸከመ አስመስሎ መናገር ይሞክራል፡፡ የልማት ጉዳይ የሠላም ጉዳይ የሁሉም ዜጋ የጋራ ጉዳይ ነው፡፡ የሁላችንም ሸክም መሆን አለበት፡፡ ሽብርተኝነትን መዋጋት የጋራችን ጉዳይ ነው፡፡ ይህንን መንግሥት የሚመክረው ማነው? የመካሪ ያለህ እያልን ነው፡፡ በአገር ውስጥም ያላችሁ ከአገር ውጭም ያላችሁ አዛውንት እስቲ ምከሩት፡፡ አያስኬድህም፤ የትም አያደርስህም፤ በመጨረሻም ውድቀት ያስከትልብሀል በሉት፡፡ ሩቅ ሳንሄድ በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ ውጤቱን እያየነው ነው፡፡ እኛ ይህ በአገራችን እንዲፈጠር አንፈልግም፡፡ እባካችሁ ልብ ግዙና እንመካከር ለአገራችን መፍትሔ እንፈልግ ነው፡፡ መልስ እኛ አመጽ ይቀሰቀሳል ብለን እየቀሰቀን አይደለም፡፡ በዓለም ላይ የተከሰተውን እናውቃለን፡፡ በአገራችንም ተፈጽሞአል፡፡ በ1966 ዓም የተከናወነውን አብዮት ማንሳት ይቻላል፡፡ ሰው አቅዶት ስው ፈልጎት ጠርቶት የመጣ ነገር አይደለም፡፡ ገዢው ፓርቲ ራሱ በወቅቱ የነበረው ፊውዳሉ ሥርዓት ያመጣው ችግር ነው፡፡ ሌሎችን ታሪኮችንም ብናይ፡፡

አቶ ዳዊት አስራደም ሲመልሱ ‹‹አንድነት የያዘው የትግል መስመር ግልጽ ነው፡፡ ህጋዊና ሠላማዊ የትግል መስመር ነው፡፡ በአንድነት ጥላ ሥር የተሰባሰቡት ታጋዮች በሙሉ የነፃነት ጥማት ያሰከራቸው

ነፃነታቸውን በነፃ ምርጫ ለማስከበር በተደጋጋሚ ደፋ ቀና ሲሉ የሚታዩ ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ልባቸውን የሞላው፣ በማንነት ፍለጋ የናወዙ ንፁህ የኢትዮጵያ ልጆች መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ታዲያ ይህ ከሆነ ሥም ማውጣት ታርጋ መለጠፍ ለምን አስፈለገ ብለን ስንመለከት ግልጽ የሆነ ነገር ነው፡፡ ኢህአዴግ በኢኮኖሚ ረገድ እያደረገ እንዳለው ነገር የጠቅላይ ገዢ ሂደት ሞኖፖላይዝም እንቅስቃሴ በፖለቲካው ዘርፍም በብቸኝነት ለመቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ ደግሞ እሱን የሚመስሉ አሚን አሚን የሚሉ ትናንሽ ፓርቲዎች ሰብስቦ መድብለ ፓርቲ ያለ ለማስመሰል እሽሩሩ እያለ እና እያባበለ ጉርሻ እየሰጠ ይዞ መራመድ እንጂ ህገ-መንግሥት በደነገገው መሠረት በአገሪቱ ውስጥ እውነተኛ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት እንዲመሠረት ፍላጎት የለውም፡፡ ለሥልጣኑ የሚያሰጋ ምንም ዓይነት ኃይል እየመጣበት መሆኑን ሲያውቅ በምንም ዓይነት መንገድ ትግሉን በማኮላሸት በብቸኝነት አምባገነን ሆኖ የፈላጭ ቆራጭ አገዛዝን ማስፈን ነው፡፡

- ጠለቅ ባለ ሁኔታ እንመልከተው ብለን ካልን ለምንድነው በመድረክ እና በአንድነት ላይ ይህ ሁሉ ወከባ፣ ዛቻ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ እስር የሚፈፀመው? በሌሎች አንዳንድ ፓርቲዎችስ ላይ ለምንድነው የማበጣበጥ እስር የሚፈፀመው ? መልሱ ግልጽ ነው፡፡

- ህገ-ወጥ ስለሆኑ አይደለም፡፡ በወንጀል ተግባርም ስለተሳተፉ አይደለም፡፡ ህጋዊና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በምርጫ ሥልጣኑን እንደሚነጥቁት ስለሚያውቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በአንድነትና በመድረክ ላይ ለምን እንዲህ እየጠነከረ መጣ ለምን እንዲህ ዓይነት አረመኔያዊ ሥራ ይፈፀምብናል፡፡ ብለን ካልን ሦስት ነገሮች አበክረን ልንመለከት ይገባል፡፡

1ኛ የሠላማዊ ትግል ለኢህአዴግ እጅግ የሚከብደው መሆኑ፤ ቋንቋው ባለመሆኑ ትግሉ ወደሚገባው ቋንቋ እንዲገለበጥለት ስለሚፈልግ ነው፡፡ ቋንቋው ጦርነት ነው፡፡ ቋንቋው ግድያ ነው፡፡ የትግሉን መስመር እጅን ጠምዝዞ ለማስቀየር ስለሚፈልግ ነው፡፡ ህዝቡም በሠላማዊ ትግል እምነት አጥቶ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ ለማድረግ ነው፡፡ 2ኛ የውሰጥ ሥራ ሰጥቶንበውስጥ ሥራችን ደፋ ቀና ስንል ከትግል አጀንዳችን እንድንዘናጋ ነው፡፡ እያጠናከርን ትግሉ ወደፊት ከማራመድ ባለበት ቆመን ስንደነባበር ማየት ነው፡፡ እሱ ደግሞ የፖለቲካውን መስመር በብቸኝነት ተቆጣጥሮ እንደፈለገ የአገዛዝ ምህዳሩ እንዲሰፋለት ነው፡፡ 3ኛ ህዝብን ከትግል በፍርሃት ማራቅ ነው፡፡ ኢህአዴግ አንድ ነገር ጠንቅቆ ሊረዳ ይገባል፡፡ እኛ የምንከተለው ሠላማዊ ትግልን ነው፡፡ ሠላማዊ ትግል ደግሞ መንፈስ ነው፡፡ መንፈስ ስለሆነ ነው የቅንጅት መንፈስ ያልተቀበረው፡፡ የነፃነት ትግል መንፈስ ነው፡፡ የሠላማዊ ትግል ታጋዮች በተሸከሙት መንፈስ ቢታሰሩ ሥጋቸው ይታሰራል እንጂ መንፈሳቸው አይታሰርም፡፡ የነፃነት ታጋዮች ሲታሰሩ መንፈሱ የበለጠ እየገነና እየተባዛ ወደ ሌሎች በርካታ ሰዎች ላይ ያርፋል እንጂ መንፈሱ ታስሮ አይሟሟም፡፡ አይሞትም ‹‹የእስረኛ መንፈስ ያታግላል፡፡ ህዝባዊ መንፈስን ለማሰር መሞከር የዋህነት ነው›› የነፃነት የትግል መንፈስን በምንም ዓይነት ማሰር አይቻልም፡፡

የትግል ጉዞውን የበለጠ ያፋጥነዋል፡፡ ይህንን እውነት ኢህአዴግ ወደደም ጠላም ጠንቅቆ መረዳት አለበት፡፡ ሽብርተኝነት ለእናንተ ምንድ ነው? የሚል ጥያቄ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ ወ/ሮ ሠላም የተጠየቀ ጥያቄ አለ ሽብር ማለት በሠላም ወጥቶ በሠላም የማይገባበት ማለት ነው፡፡ ለህይወት ለንብረት ለቤተስብ ለአገር ዋስትና ማጣት ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ለነዚህ ጉዳዮች መፈጠርም ምክንያት ሆኖ መገኘት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሠላም የህግ ማእቀፍ ተደርጎለታል፡፡ ከዚህ የህግ ማእቀፍ የሚወጣ ሁሉ በሽብርተኝነት ያስፈርጃል፡፡ ከሽብር ለመራቅ ህገ-መንግሥቱን ማክበር ይገባል፡፡ በወ/ት ብርቱካን መታሠር ብቻ 36 የህገ-መንግሥቱ አንቀፆች ተጥሰዋል፡፡ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻችን በሚነኩ 36 አንቀፆች ተጥሰዋል፡፡ ሰው የነፃነት ስሜት ሳይማረው ሲቀር እራሱን ሳንሱር እያደረገ እንዲኖር ሲፈረድበት በገዛ አገሩ ዜጋው ግራና ቀኙን ተመልክቶ እንዲናገር ሲበየንበት፤ ብዕሩ መርጣ ለመትፋት ስትጨነቅ፤ ወጥቶ እስኪገባ ምን ያጋጥመኛል እያለ ሲጨነቅ የሚውል ሥርዓት ሲገነባ ሽብርተኝነት ማለት ያ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ግልጽ የሆነ ሀቅ ነው፡፡ በአባሎቻችን ላይ አየተፈፀመባቸው ያለው ወከባ፤ እስር . . . በሎች ወገኖቻችን ላይ ሁሉ እየተፈፀመ ያለው ወከባና እንግልት ለተመለከተ በተለይ ለሰብአዊ መብት ለዴሞክራሲና ለነፃነት ለቆመ ሰው ሁል ጊዜ ራስ ምታት ነው፡፡

በመሆኑም የአንድነት አባላት ብቻ ወይም የተወሰኑ ግለሰቦችን ብቻ ለማስፈታት ሳይሆን በአደዋም የታሠሩትን ወገኖቻችንን ለማስፈታት እንታገላለን፡፡ ዘለቄታ ያለው የፍትሕ ሥርዓት እንዲዘረጋ ዘሬም ትግላችንን አጠክረን እንቀጥላለን፡፡ መቼም ቢሆን ወደ ኋላ አንልም፡፡ በዚች አገር የሽብርተኝነት ነገር ሲነዛ ሁል ጊዜ አንድ በጭንቅላቴ የሚመላለስ ነገር አለ፡፡ ለመሆኑ ይህች አገር የማናት? የማን ሆኖ ነው ማን ማን የሚያሽብረው? ይህች አገር እኮ የሁላችንም ናት፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚመለከተው ነው፡፡ በበሰለና በሰከነ ሁኔታ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ያለን ነው፡፡ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተገነባን ነን፡፡ ባህላችን ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሥጋት የሚሆነው ካለ እሱ ፈሪ ኢትዮጵያዊ መሆን አለበት፡፡ አንድን ኢትዮጵያዊ ሽብርተኛ ብሎ መሰየም በራሱ እጅግ የሚያሳዝንና የሚያሸብር ነው፡፡ የኢትዮጵያዊነትን ታሪካዊ ማንነት ያለመረዳት የማንነት መገለጫ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የትግል መንፈሳችንን እስከ ቀራኒዮ አደባባይ ድረስ ይዘን እንቀጥላለን፡፡ እኛ ሠላማዊ ትግላችንን አጠናክረን ስንቀጥል ኢህአዴግ ይሸበራል፡፡ በገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ አመለካከት ህጋዊና ሠላማዊ ትግል የሚሸበር ከሆነ እኛ ደግሞ በህጋዊና ሠላማዊ ትግል ብቻ ጠንክረን እናሸብራለን፡፡›› በማለት አቶ ዳዊት መልስ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መልኩ ትግሉን ይዘን መራመድ እንድንችል ሠፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግሉ የእርሱ ነውና የትግላችንን ዓላማና ግብ ተመልክቶ ወደፊት መቀጠል እንድንችል ከጎናችን እንዲቆም በዚህ አጋጣሚ መልእክቴን ማስተላለፍ እፈልጋለሁ፡፡›› በማለት ሃሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ የፓርቲውን ሙሉ መግለጫ በገጽ 13 ይመልከቱ፡፡

የመጀመሪያዋ የአፍሪካ ሴት ኖቤል ተሸላሚ አረፉ

የአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ፣ በሴቶች መብትና ግልፀኝነት የመንግስት አሰራርን አስመልክቶ ላበረከቱት አስተዋፅኦ እ.ኤ.አ. በ2004 የዓለም ሰላም ኖቤል ተሸላሚ የሆኑት ኬንያዊ ፕሮፌሰር ዋንጋሪ ማታኢ አረፉ፡፡

ከአፍሪካ የመጀመሪያ ኖቤል ተሸላሚ ማታኢ ከ20-30 ሚሊዮን ዛፎችን በአፍሪካ በማስተከል የአረንጓዴ መቀነት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደነበሩና በሀገራቸው የ2002 ምርጫ በመሳተፍ አሸንፈው በኬንያ መንግስት ሚኒስትርነትም አገልግለዋል፡፡ በዚህም ወቅት መንግስት ግልፀኝነት የተሞላበትን አሰራር እንዲከተልና ለሀገሪቱ ሁሉ አቀፍ ለውጥ የአርዓያነት ድርሻን በመጫወት ከፍተኛ ሚና ነበራቸዉ ሲሉ የቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዘዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ተናግረዋል፡፡ እዚህ ደረጃ ለመድረስም በተለያዩ ጊዜያት ለእስር እንደተዳረጉ በማስታወስ፡፡

ኖቤል ሎሬት ዋንጋሪ ማታኢ ባደረባቸው የካንሰር ህመም ምክንያት በናይሮቢ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሳለ እሁድ መስከረም 24 ቀን 2011 ዓ.ም በ71 ዓመታቸው ህይወታቸው አልፏል፡፡ በኬንያ የሚገኙ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንም ሀገራቸው “ኬንያ አንድ ታላቅ ሴት አጣች” ሲሉ ሌላው ማህበረሰብ ደግሞ “የአፍሪካ ሴቶች የለውጥ አርአያ አረፉ” ሲሉ በሀዘን አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

በትሪፖሊ ከ1,200 በላይ ሰዎች በጅምላ እስር ላይ

ተገኙበሊቢያዋ ዋና ከተማ ትሪፖሊ በተለምዶ ማዕከላዊ

እየተባለ በሚጠራው አቡሳሊም እስር ቤት 1,270 የሚሆኑ እስረኞች ተገኙ፡፡ እስረኞቹም በሙዓመር ጋዳፊ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ ሲያስነሱ የነበሩ ሲሆን ቀሪዎቹ እስረኞች ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ይቃወሙ የነበሩት ደግሞ አቡሳሊም በሚባለው ማዕከላዊ እስር ቤት በፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ይላሉ የዓይን እማኝ እስረኞች፡፡

የተገደሉት እስረኞችም የአጥንት ሽርፍራፊ በረሃማው ስፍራ ላይ ተበትኖ እንዳለም በጥናት ተረጋግጦ ተለይቷል፣ የተለያዩ የአጥንት ስብርባሪዎችና የልብስ ቁርጥራጮች የላይኛው ለም አፈር ላይ ይገኛል፡፡ ይህም አምባገነኖች ምን ያህል ጨካኞች እንደሆኑና ለህዝባቸው ንቀት እንዳላቸው ያሳያል ሲል የብሔራዊ ሽግግር ምክር ቤት ተናግሯል፡፡ አምባገነን መሪዎች የፀጥታ ኃይሎችን በመጠቀም የሚቃወሟቸውን ሰዎች ማሰራቸው አንዱ መገለጫቸው እንደሆነ ገልፆ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ግን በህይወት እስካሉ መቼም ከተጠያቂነት አያመልጡም፣ በህግ ፊትም ይቀርባሉ ለዚህም አዲሱ የሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት መንግስት ይህ አስከፊ ድርጊት እንዴትና በማን በትክክል እንደተፈፀም ለማረጋገጥ የውጭ እገዛ እንሻለን ሲል ጠይቋል፡፡

ሳውዲ ዓረቢያ ሴቶች የመምረጥና የመመረጥ መብት ተፈቀዳላቸው

በሳውዲ ሴቶች የግል ህይወትና የስራ ሁኔታ ገደብ ተጥሎባቸው ነበር፡፡ አሁን በሚቀጥለው የከተማ አስተዳደር ምርጫ ሴቶች የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብት እንደተፈቀደላቸው የሀገሪቱ ንጉስ አብዱላህ አስታውቀዋል፡፡ ይህም ከሚቀጥለው ሐሙስ በኋላ ለውጡ እውን ይሆናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሴቶች በሀገሪቱ ከፍተኛው “ሹራ ምክር ቤት” አማካሪም እንዲሆኑ ጠቁመዋል፡፡ ንጉሱ እንደተናገሩት ከሆነ ከአዲሱ የ” ሹራ ም/ቤት” ህጋዊ አካላት ሁሉም ሊቀበሉት ይገባል፡፡ ምክንያቱም ሴቶች በተጣለባቸው ገደብ ከሼርያ ጋር በተያያዘ ቅሬታ ማቅረባቸውና በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸው ሚና ጉልህ ስለሆነ ወስነናል፡፡ ይህንንም በትክክል ከከፍተኛ ፀሐፊዎቼ ጋርና ከሌሎችም በ”ሹራ ም/ቤት” ተሳትፎ ከሚያደርጉ ሴቶች ጋር ከሚቀጥለው የስራ ዘመን ጀምሮ እውን ይሆናል ሲሉ ንጉሡ ተናግረዋል፡፡

ሌላ ሺህ ፍጡር ይተካል፡፡ ወይም ይወለዳል፡፡ “አባት ያበጀው ለልጅ ይበጀው”በሚለው ብሒል

መሠረት፣አባቶቻችን እርስ በርስ መከባበር፣ የሕግ የበላይነትን፣ ተአማኒነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ትህትናን፣ ታዛዥነትንና አዛዥነትን አስተምረውን አልፈዋል፡፡ እኛ ግን የነርሱን አርአያነት አልተከተልንም፡፡

አባቶቻችን ስለ ሀገር እና ስለ ወገን ፍቅር ሲሉ፣እግራቸውን ለጠጠር፣ደረታቸውን ለጦር ዳርገው፣ከአገር ዳርቻ እስከ አገር ደርቻ በእግራቸው ተጉዘው፣ዘምተው ደማቸውን አፍስሰው፣አጥንታቸውን ከስክሰው፣ጦር ሜዳ የተሰውት ከሞት የተረፉትም የተፈጥሮ ሞት ሙተው ይህችን ቅድስት አገር አስረክበውን አልፈዋል፡፡

አባቶቻችን ሳይማሩ አስተምረው ከነ አጥንቷና ከነጉልጥምቷ ያስረከቡንን ይህችን የወላድ መካን የሆነች ቅድስት ሀገር ያልነበረ፣ሊኖርም የማይገባው አዋልድ ከየትም እየቃረምን እያመጣን እያስገባን አገራችንን ኢትዮጵያ ወደ ጥፋት ጐዳና እየመራናት ነው፡፡

ሕወሓት ኢሕአዴግ የግዛት ዘመኑን ለማራዘም ሲል የማይቆፍረው ጉድጓድ፣የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ዓይኑ እያየ እንዳላየ፣ጆሮው እየሰማ እንዳልሰማ፣ህሊናው እያወቀ እንዳላወቀ በመምሰል፤የሕጐች የበላይ ወይም ቁንጮ በሆነው ሕገ መንግሥት እስከ መገንጠል ድረስ የሚፈቅድ አንቀጽ በማስፈር ዓለም የተቀበለውን

የአገሩን ቋንቋ ወደ ጐን በመግፋት አንድ አካል አንድ አምሣል በመሆን፣ልዩነቱን አጥብቦ፣አንድነቱን አስፍቶ ተዋልዶ የኖረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆድና ጀርባ አድርጎታል፡፡

ለአሕያ ማር እንደማይጥመው ሁሉ፣ለሕወሓት ኢሕአዴግም፣ኢትዮጵያን የሚመለከት ነገር ሁሉ አይጥመውም፡፡ ይሁን እንጂ፣የባዕዳን ሀሳብ እየተቀበሉ፣የአገርን ቅርስ እና ታሪክ አንዳልነበረለማድረግ መሞከሩ፣ያጠፋል እንጂ አያለማም፡፡

ብሔር እና ብሔረሰብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙን ጠንቅቀን ሳናውቅ፣አውራጃዎችን እና ወረዳዎችን ሁሉ ብሔር ብለዋቸዋል፡፡ በየአውራጃዎቹ፣ በየወረዳዎቹና በየቀበሌዎቹ ተሰባጥረው የሚኖሩትን የሕብረተሰቡ አካል የሆኑትንም ብሔረሰብ ብለናቸዋል፡፡ አያስኬድም፡፡

አገር ማለት ኢትዮጵያ ናት፡፡ ኢትዮጵያ ወጥነት የሌለው ድብልቅ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ የሚኖርባት አገር እንጂ የብሔር ብሔረሰብ አገር አይደለችም፡፡

ከቀድሞ ፀሐፍትና ገጣሚያን መካከል አንዱ የነበሩት በሰማይ ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ ከበደ ሚካኤል (የክብር ዶ/ር) በ2ኛው ታሪክና ምሣሌ መጽሐፋቸው በገጽ አንድ፣ስለ አገር ምን ብለው እንዳለፉ እስኪ እንመልከት፡፡

“አገር”“አገር በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በልማድ፣

በተስፋ፣በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው፡፡

“አገር ማለት አያት ቅድመ አያት የተወለዱበት አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም ሠራ ሠርተው ዕድሜያቸው ሲደርስም ልጆቻቸውን ተክተው የሚቀበሩባት ጉድጓድ ነው፡፡

አገር አባት እናት ዘመድ ምግብ ጌጥና ሀብት በመሆኑ፣ድህነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድመ አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው፡፡” ብለዋል በስም ተጠቃሹ፡፡

አገር በክልል፣ በሃይማኖት፣ በጐሣ፣ በቋንቋ፣ በብሔረና በብሔረሰብ ወይም በጥቅማጥቅም የማይሸጥና የማይለወጥ መሆኑን ከዚህ በላይ በጥቅስ ውስጥ አስገብተን ያስቀመጥነው መሠረተ ሀሳብ ስለሚነገረን፣አገር እንደቀላል ዕቃ አንዬው ልብ እንበል፡፡ ከአፍሪቃ አሕጉር፣ፊደል፣የጽሑፍና የንግግር ቋንቋ ያለን እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን፡፡ ፊደላችን መኩሪያችን፣መመኪያችን፣አለኝታችንና ክብራችን ነው፡፡ ልንፍቀው፣ልንሰርዘውና ልንክደው አንችልም፡፡ ታሪካችን ነውና፡፡

“የቄስ ሚስት አወቅሽ አወቅሽ ... ከገፅ 7 የዞረ

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

122ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 13ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

122ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 13ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት የጀርመን ባህር ኃይል መርከቦች እንግሊዝን ከበዋል፡፡ የአሜሪካ መርከቦች ሲቀርቡ፣ በቀላሉ በጀርመን ሰብማሪንስ (በባህር ላይ ሳይሆን በባህር ውስጥ የሚሄዱ መርከቦች) እየተጠቁ በብዛት ይሰምጡ ጀምር፡፡ ጀርመኖች በባህር ላይ ጦርነት በበርካታ መስፈርቶች የበላይነት ነበራቸው፡፡ አሜሪካኖች ግን መርከቦች በሰጠሙባቸው ቁጠር፣ ሽንፈት ተቀብለውና ተስፋ ቆርጠው አልተቀመጡም፡፡ ሌሎች መርከቦች በብዛት ማሰማራት ጀመሩ፡፡ ወደ እንግሊዝ የሚላኩት የአሜሪካን መርከቦች፣ ጀርመኖች ሊያሰጥሟቸው ከሚችሉት በላይ በመሆናቸው የተወሰኑቱ የእንግሊዝ ወደቦች መድረስ ጀመሩ፡፡

ይሄን ምሳሌ ያነሳሁት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ምንም እንኳን አሜሪካኖች ከጀርመኖች ጋር ያደርጉት እንደነበረው የባህር ኃይል ወታደራዊ ትንቅንቅ ባናደርግም፣ በአገራችን እኩልነት፣ መልካም አስተዳደር፣ ፍትህ፣ የዜጎች ሰብአዊ መብት መከበር እንዲሰፍንና የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ የሚደረግ፣ አባታችን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፣ እህታችን ሽብሬ ደሳለኝ፣ ወንድሞቻችን ባይሳ ዳባና አረጋዊ ገብረዮሐንስ የመሳሰሉ በርካታ

ወገኖቻችን በሕይወታቸው ዋጋ የከፈሉበት ብዙዎች የታሰሩበትና ከፍተኛ መከራና እንግልት የተቀበሉበት፣ የሰላማዊ ትግል ትንቅንቅ አለ፡፡

አዎ ያኔ ጀርመኖች ለተወሰነ አመታት አይለው እንደነበር፣ ሕዝባችንን በዘር ከፋፍለው የመከራ፣ የድህነት፣ የረሃብ ቀንበር የጫኑበት ጥቂት አምባገነኖች ለጊዜው አይለው ሊሆን ይችላል፡፡

የግንቦት ሰባት ምርጫ ከተደረገ ስድስት አመታት አልፈዋል፡፡ ያኔ በአገር ቤት፣ ቅንጅት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አራት ድርጅቶችን አሰባስቦ ተንቀሳቀሰ፡፡ በነዶ/ር መረራ ጉዲና የሚመራው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረት በውጭ ያሉትን በአገር ቤት ያሉትን ድርጅቶች አገናኝቶ የሰላማዊ ትግል ዘመቻውን ቀጠለ፡፡ በውጭ አገር ያለው ኢትዮጵያዊ፣ አገር ቤት ካለው ኢትዮጵያዊ ጋር በቅርበት፣ በጋራ የሰራበት፣ በርግጥ የኢትዮጵያውያን ትብብርና አንድነት የታየበት ታሪካዊ ወቅት ነበር፡፡ የኢሕአዴግን የስልጣን አገዛዝ ከፍፃሜ ለማድረስ ጫፍ የተደረሰበትም ጊዜ !

በተለያዩ ማዘናጊያ ታክቲኮች፣ በምእራባውያንም ትልቅ ርዳታ፣ በኋላም ዜጎችን በጥይትና በጭካኔ እንደ ቅጠል በማርገፍ፣ አገዛዙ እስካሁን ድረስ ስልጣን ላይ ተፈናጦ ይገኛል፡፡ የቅንጅት መሪዎች ታሰሩ፡፡ አገር ቤት ያሉ የሕብረት መሪዎች ፓርላማ ገቡ፡፡ ውጭ አገር ያሉት የሕብረት መሪዎች አገር ቤት ባሉት አጋሮቻቸው አኮረፉ፡፡ (ኩርፊያቸው አገር ቤት ካለው ወገናቸው ለይቷቸው ወደ መረሳት አደረሳቸው እንጂ ምንም ያመጣላቸው ነገር የለም) ወደ ቅንጅት ስንመለስ፣ አገር ቤት ያሉ መሪዎቹ በመታሰራች በውጭ አገር ያሉ የድጋፍ ድርጅቶች፣ ትግሉን የመምራት ሃላፊነት ተጣለባቸው፡፡ ከቅንጅት የሰላማዊ ትግል ስልት አማራጭ ውጭ፣ የትጥቅ ትግልን እናራምዳለን ከሚሉ ከኦነግ፣

ኦብነግ፣ አርበኞች ግንባርና ከሲዳማ ነፃ አውጭ ግንባር ትብብር ፈጠሩ፡፡ ትኩረቱ ከአገር ቤቱ ትግል ወደ ውጭ አገሩ ትግል ዞረ፡፡

የቅንጅት መሪዎች ከቃሊቲ እስር ቤት ሲፈቱ፣ ዲያስፖራ በቀል በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በመካከላቸው ልዩነቶች ተፈጠሩ፡፡ የመጀመሪያው ተመራጭ የአዲስ አበባ ከንቲባ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የቅንጅት ዋና ጸሐፊ አቶ ሙሉነህ እዮኤልን የመሳሰሉ አንጋፋ የቅንጅት አመራር አባላት “ሰላማዊ ትግል አይሰራም” በሚል የስደት ኑሮ ጀመሩ፡፡ ግንቦት ሰባት የተሰኝን ድርጅት አቋቁመው፣ ያዋጣል በሚሉትና በሚያምኑበት ትግል መስክ ተሰማሩ፡፡ የግንቦት ሰባት መሪዎች አገር ቤት መዋቅር እንዳላቸው ይናገራሉ፤ ግን እስከ አሁን፣ በሕዝብ የሚታየው እንቅስቃሴያቸው፣ ከሞላ ጎደል በውጭ አገር ሰብሰባዎች መጠራት ላይ ብቻ ያተኮረ ይመስላል፡፡

በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ይመራ የነበረውና አብዛኛውን የቅንጅት ከፍተኛ አመራር ያቀፈው ቡድን፣ ገዢው ፓርቲ የቅንጅትን ስም ለአየለ ጫሚሶ ቡድን፣ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ስለሰጠ፣ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በሚል ስም መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ድርጅቱ በሕዝብ ያለው

ተቀባይነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ እያለ ሲመጣ የአንድነት ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን በግፍና በጭካኔ ወደ ቃሊቲ ተወሰደች፡፡ በነፍስ ገዳዮች ላይ ያልታየ ቶርቸር ደረሰባት፡፡ ለስድስት ወራት ጨለማ ቤት ውስጥ እንድትቀመጥ ተደረገ፡፡

በርካታ የሕብረትና የቅንጅት ደጋፊ የነበሩ፣ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “አገዛዙ በሰላም አይወርድም” የሚል አቋም መያዝ ጀመሩ፡፡ ብዙዎች ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ ታየባቸው፡፡ በመሆኑም በአገር ቤት የሚደረገውን ትግል ለመርዳት ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው አይነት ትጋትና ፍላጎት እየመነመነ መጣ፡፡ ይልቅስ “ከሰላማዊ ትግል ውጭ ሊኖር የሚችል ሌላ አማራጮች ካለ?” በሚል “የትጥቅ ትግል እናደርጋለን” የሚሉ ቡድኖች አካባቢ የመሄድና ስብሰባዎቻቸውን የመሳተፍ ሁኔታ ተጀመረ፡፡ አብዛኛው የዲያስፖራ ኢትዮጵያው ትኩረቱን አገር ቤት ከሚደረገው ትግል አንስቶ በውጭ አገር ባሉ ድርጅቶች ላይ ያውም ደግሞ በአስመራ ላይ እያደረገ መጣ፡፡

በአገር ቤት የአንድነት ለዲሞከርሲና ለፍትህ ፓርቲ የተለያዩ ኃይሎችን በአንድ ላይ በማምጣት፣ ትግሉ አገር አቀፍና ሥር የሰደደ እንዲሆን ጥንቃቄ፣ ብስለት፣ ትእግስትና ቁርጠኝነት በተሞላበት ሁኔታ ትግል እያደረገ ነው፡፡ በቅርቡ በአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል፣ አገር ውስጥ የሚታተም፣ የጠለቀ የፖለቲካ ይዘት ያላቸው ፅሁፎችን ያዘለ፣ ሕዝቡን የሚቀሰቅስና ገዢው ፓርቲ እያደረገ ያለውን የስልጣን መባለግ የሚያጋልጥ፣ ሳምንታዊ ጋዜጣ አውጥቶ ለሕዝብ እንዲደርስ እያደረገ ነው፡፡

ይህ ጋዜጣ ቢያንስ ቢያንስ ለማተሚያ ብቻ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ብር (ወደ 640 ዶላር) ያወጣል፡፡ ጋዜጣው ከአዲስ አበባም አልፎ በሌሎች ግዛቶች

ለማዳረስ ትልቅ እቅድ አለ፡፡ ይህም ሕዝቡን ለማንቃትና ለማደራጀት ትልቅ ሚና ሊጫወት የሚችል ቁልፍ የሕዝብ ግንኙነት መሳሪያ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአንድነት ፓርቲ አባል የሆነበት፣ መድረክ ከአራት አምስት ወራት በፊት በመቀሌ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ሕዝባዊ ስብሰባ ማድረጉ በሰፊው ተዘግቧል፡፡ ለስብሰባው ወደ 16000 ብር (950 ዶላር) ነበር የተከፈለው፡፡ “ከመቀሌው ስብሰባ ውጭ ሌሎች በርካታ ሕዝባዊ ስብሰባዎች በስፋት ለምን አይደረግም?” የሚል ጥያቄ ለአመራር አባላቱ ሲቀርብላቸው በዋናነት እንደምክንያት የሚያቀርቡት የገንዘብን ችግር ነው፡፡

አረና ትግራይና አንድነት ፓርቲ በጋራ ሆነው ስድስት ጽ/ቤቶች በትግራይ ነበሯቸው፡፡ አሁንም በገንዘብ ችግር ምክንያት በማይጨውና በሽሬ የሚገኙ ጽ/ቤቶች ተዘግተዋል፡፡ “ለመታገልና መስዋእትነት ለመክፈል ሕዝቡ ዝግጁ ነው፡፡ የሰው ኃይል ችግር የለንም፡፡ ችግራችን ገንዘብ ነው” ይላሉ የአረና አመራር አባላት፡፡

በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ደገፈም አልደገፈም፣ አገር ቤት ያሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሕይወታቸውን አሳልፈው በመስጠት አምባገነንነት እየታገሉ ነው፡፡ ጠንካራ ናቸው? ጠንካራ አይደሉም፡፡ ብዙ ይቀራቸዋል ? አዎን ብዙ ይቀራቸዋል፡፡ አገዛዙን መቋቋም ይችላሉ ? አሁን ባሉበት ሁኔታ መቋቋም አይችሉም፡፡ ነገር ግን መልካም ጅማሬ ላይ ነው ያሉት፡፡ ተጨባጭ የሆኑ ሥራዎች እየሰሩ ነው፡፡ ሕዝቡን ባላቸው የገንዘብ አቅምና መጠን እያደራጁት ነው፡፡ ከሕዝቡ ጋር ሆነው ብሶቱን በድፍረት እያሰሙለት ነው፡፡ ዛሬ አንድ ተብሎ ነው ነገ ሁለት የሚባለው፡፡

በውጭ አገር የምትኖሩ ውድ ወገኖቼ፡እንግዲህ በውጭ አገር የምንኖር እኛ፣ በአገር

ቤት ያሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እየታሰሩ፣ እየተደበደቡ፣ ከሥራ እየተባረሩ፣ እንግልትና ወከባ እየደረሰባቸው ተስፋ ሳይቆርጡ ትግሉን ተያይዘው ባሉበት ሁኔታ፣ እኛ በአንጻራዊነት ሲታይ በምቾት የምንኖር፣ ተስፋ ቆርጠን ፊታችንን ልናዞርባቸው ይገባልን ? በጭራሽ አይገባም!!!

የኢሕአዴግ ትልቁ የአፈና ስትራቴጂ በአገር ቤት ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር ማድረግ ነው፡፡ የአሜሪካ መርከብ እንግሊዝ እንዳይደርስ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን መርከቦች አብዝተን ልናሰማራ ያስፈልጋል፡፡ በሌለላ አባባል ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ በዘጠና ሰባት፣ እንደጠበቅነው ውጤት ባይገኝም፣ ከኛው ጋር የነበሩ መሪዎቻችን የምንላቸው አንገታችንን ቢያስደፉንም፣ ፊታችንን ውጤት ሊያመጣ ከሚችለው ከሰላማዊው ትግል ማዞር የለብንም፡፡ የበለጠ እንዳውም በእልህና በብርታት መነሳት ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ትኩረታችን ወደ ኢትዮጵያ መሆን አለበት፡፡ በዚያ ያሉ ወገኖቻችን ጎን መሰለፍ አለብን፡፡

የፈለገ የተለያዩ ስብሰባዎች በውጭ አገር ብናደርግ፣ የፈለገ ሰልፎች ብንወጣ፣ የፈለገ ጠዋትና ማታ ገዢውን ፓርቲ እየረገምን ብንጽፍ፣ የፈለገ ከውጭ አገር በራዲዮና በቴሌቪዥን ዜናዎች ብናሰራጭ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍርሃት ካልወጣና በራሱ መተማመን ካልጀመረ በቀር ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ለዚህም ሕዝቡን ማደራጀት ያስፈልጋል፡፡ ኢሕአዴጎችን በውጭ ያለነው ኢትዮጵያውያን ለብቻችን በባዶው የምናሰማቸው ጫጫታዎች ያሰቃቸዋል እንጂ አያስፈሯቸውም፡፡ የሚያስፈራቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀና ማለት ብቻ ነው፡፡

ትላንት ወድቀን ቆስለናል፡፡ ግድ የለም “እህ” እያልን፣ እያማረርን፣ ቁስላችንን እያሻሸን አንቀመጥ፡፡ እንነሳ፣ እንንቀሳቀስ፡፡ ነገም ተመልሰን ልንወድቅ እንችላለን፡፡ ነገር ግን እየወደቅን፣ እየተነሳን የፍትህ አምላክ የሆነው የእግዚአብሄር መልካም እርዳታ ተጨምሮበት ለድል መብቃታችን አይቀርም፡፡

ግርማ ካሳ([email protected])

የኢትዮጵያ ፖለቲካ በአገር ቤት እና በውጭ አገር!

ኢህአዴግና ግብረአበሮቹ በተከታታይ በተቀዋሚ ድርጅቶች አመራርና አባላት፤ በግል ጋዜጠኞችና አርቲስቶች ላይ ባጠቃላይ በተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት ላይ እያካሄዱ ያለውን የማሰርና የአፈና ዘመቻ በጥብቅ እናወግዛለን። በቅርቡም ያለአንዳች ማስረጃ በፍርሃት ላይ በተመሠረተ ስሌት ብቻ የግል ኑሮአቸውን በሰላም ከሚያከናውኑበት ቦታ በሽብርተኝነት በመወንጀል በግፍ ያሰሯቸውን፤

1. አቶ ደበበ እሽቱ፤ አርቲስት፤ 2. አቶ አንዱአለም አራጌ፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ም/ፕሬዝደንትና የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ፤ 3. አቶ በቀለ ገርባ፤ የኦፍዴን ም/ሊቀመንበርና የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ 4. አቶ ኦልባና ሌሊሳ፤ የኦህኮ ሥራ አስፈጻሚና የጽ/ቤቱ ኃላፊ5. አቶ ናትናኤል መኮንን፤ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ብ/ም/ቤት አባል6. አቶ ዘመኑ ሞላ፤ የመላው ኢትዮጵያዊያን ዲሞክራሳዊ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ7. አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚሐብሄር የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ /ኢብአፓ/ ፕሬዝዳንት8. አቶ አሣምነው ብርሃኑ የአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ ተለዋጭ ብ/ም/ቤት አባል9. አቶ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛ10. ወ/ት ርዕዮት ዓለሙ፤ ጋዜጠኛ 11. አቶ ውብሸት ታዬ፤ ጋዜጠኛ12. አቶ ስለሺ ሃጎስ ፤ጋዜጠኛ

ሌሎችም እንደዚሁ በሥር ላይ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ እንዲለቅ በጥብቅ እናሳስባለን። እነዚህን ግለስቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቅርና የዓለም ሕብረተስብም ጭምር በተለይም የዓለም አቀፍ ስብአዊ መብት አስጠባቂ ድርጅቶችና የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ደህንነት ማህበር ለሀገሪቱ ደህንነት ተቆርቁረው በነፃ ሃሳባቸውን ከመግለጽ ሌላ በሽብርተኝነት የሚያስከስስ ወንጀል እንደሌለ ባወጡአቸው መግለጫዎች አስታውቀዋል። ጐሰኛው አምባገነን መንግሥት ዓይን ባወጣ መልኩ ፈጥሮ ያቀረበው ክስ የሚያስገርም ከመሆኑም በላይ በዓለም ሕዝብ እይታም አሳፋሪ ተግባር ነው። ዋነኛ ዓላማው ግን በተቃዋሚ ድርጅቶች፤ አባላትና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ፍርሃት ፈጥሮ ብሶቱን እንዳይገልጽና ለጐሰኛ አምባገነን አገዛዙ እንዲንበረከክ ለማድረግ እንደሆነ አያጠራጥርም።በመሠረቱ ኢህአዴግ በመሣሪያ ሀይል በሕዝባችንና በሀገራችን ላይ የተጫነ ሲሆን እነሆ ላለፉት ሀያ ዓመታት እንደፈለግው ሲያስር፤ ሀገር ቆርሶ፤ ሕዝባችንን በረሀብ ሲጐሳቆል፤ ለዘመናት ተሳስረው የኖሩ ወገኖቻችንን ጐሳ ከፋፍሎ ለዘመናት የሚቆይ ውዝግብ ውስጥ ለመክተት ያላሰለስ ጥረት እያደረገ ፤ያለ ሀይሉን በመጠቀም የሕዝቡን የምርጫ ድምጽ በጉልበት በመንጠቅ በሥልጣን የቆየ ነው። በኢህአዴግ የሚመራው አምባገነን መንግሥት የሚያወጣቸው ሕጎች፤ የሚፈጥራቸው መ/ቤቶች የጦርና የፖሊስ ሀይሎችን ጨምሮ ሁሉም የአገዛዙን ደህንነት የሚጠብቁና ዕድሜውን የሚያራዝሙ ተግባሮች እንዲፈጽሙ ታቅደው የተፈጠሩና የተዋቀሩ መሆኑን ለአንድ አፍታም መዘንጋት የለብንም።

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ማህበር፤ 1. ከፍ ብሎ ስማቸው የተጠቀሱትና ሌሎችም በየክፍለ ሀገሩ የታሰሩ የፓለቲካ እሥረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቀ ለዚህም መሠረተ ቢስ ክስና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደረግ የስብዓዊ መብት ረገጣ አቶ መለስና ግብረ አበሮቻቸው ተጠያቂ መሆናቸውን በጥብቅ እናስታውቃለን። 2. የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደረሰበት ስላለው መራራ የኑሮ ሁኔታና ለዚህም መፍትሄ የሚላቸውን ሀሳቦች በሰላማዊ መንገድ በአደባባይ ወጥቶ ለመግለጽ የጠየቀው ጥያቄ እገዳው ተነስቶ ብሶቱን መግለጽ እንዳለበት እናምናለን። ሰልፍ የማድረግ መሠረታዊ መብቱ ስለሆነም ከማንም ፈቃድ አያስፈልገውም እንላለን፤ በነቂስ በአደባባይ ወጥቶም ብሶቱንና ፍላጎቱን መግለጹን የምንደግፍ መሆኑን እንገልጻለን። ይህ መብቱ እስኪረጋገጥለት ድረስ በሚቻለን አቅም ባገኘነው መድረክ ሁሉ ካለማሰለስ የምንታገል መሆኑን እንገልጻለን።

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑርበሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ሰጭ ማህበር

ኢህአዴግና ግብረ አበሮቹ በተቃዋሚዎች ላይ በሚያካሂዱት

የእሥር ዘመቻ በመቃወምከሰሜን አሜሪካ የመኢአድ ድጋፍ ማህበር

የተሰጠ መግለጫ(መስከረም 11፤ 2004 ዓ ም)

የኢሕአዴግ ትልቁ የአፈና ስትራቴጂ በአገር ቤት ጠንካራ ተቃዋሚ እንዳይኖር ማድረግ ነው፡፡ የአሜሪካ መርከብ እንግሊዝ እንዳይደርስ ማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን መርከቦች አብዝተን ልናሰማራ ያስፈልጋል፡፡ በሌለላ አባባል ተስፋ መቁረጥ

የለብንም፡፡ በዘጠና ሰባት፣ እንደጠበቅነው ውጤት ባይገኝም፣ ከኛው ጋር የነበሩ መሪዎቻችን የምንላቸው አንገታችንን ቢያስደፉንም፣ ፊታችንን ውጤት ሊያመጣ

ከሚችለው ከሰላማዊው ትግል ማዞር የለብንም፡፡ የበለጠ እንዳውም በእልህና በብርታት መነሳት ያለብን ጊዜ ነው፡፡ ትኩረታችን ወደ ኢትዮጵያ መሆን አለበት፡፡

በዚያ ያሉ ወገኖቻችን ጎን መሰለፍ አለብን፡፡

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

122ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 13ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

122ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 13ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

መስፍን ነጋሽ

አንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶችን ጥያቄ የፖለቲካ ጥያቄ ነው!! ድርጅቶቹን አሁን በተያዘው ፋሽን “ማዳከም ይቻላል” ተብሎ ታስቦ ይሆናል፤ ጥያቄዎቹን ማጥፋት ግን አይቻልም። የኢሕአዴግን ዘመቻ

በተቃራኒው ካየነው ለእነዚህ ድርጅቶች የማያገኙት ድጋፍ እየሰጣቸው እንደሆነ መረዳት አይከብድም። በዚህም ልክ ኢሕአዴግ እንደደርግ በራሱ አንገት ላይ ገመድ እየጠመጠመ ይገኛል። የእነአቶ መለስ ትንቢትና ፍርሐት የሮበርት መርቶንን “ራሱን የሚፈጽም ትንቢት” (self-fulfilling prophesiy) ያስታውሰኛል። መርተን እንደሚለው እነዚህ ትንቢቶች የሚደርሱት ዋናዎቹ ባለቤቶች “እውነት ናቸው፤ ይደርሳሉ” ብለው ስለሚያምኑ፤ በዚሁ እምነታቸው ላይ በመመሥረትም ተግባራዊ ምላሽ ስለሚሰጡ ነው። ለኢሕአዴግም በአጠቃላይ ተቃዋሚዎቹ በተለይ ደግሞ ተቃዋሚዎች የሚፈጸሙ ትንቢቶች ሆነውበታል። ኢሕአዴግ እነዚህና ሌሎቹም ቡድኖች የሚያነሱትን የፖለቲካ ጥያቄ በፖለቲካዊ መንገድ ቢፈታ ቡድኖቹ/ጥያቄዎቹ እውነት ሆነው እንደሚያከስሩት፣ የጭቆና ስርአቱ ከስሩ እንደሚናድ ያውቃል። እነአቶ መለስ የዘነጉት ነገር እነዚህ ቡድኖች “በሕገ ወጥ” መንገድ ሊገለብጡዋቸው እንደሚችሉ መተንበይና ለትንቢቱም ምላሽ መስጠት በመጀመራቸው ከኪሳራው ሊያመልጡ የሚችሉበት እድል መዘጋቱን ነው። በሁለቱም በኩል ኢትዮጵያ አምባገነንነትን ከትከሻዋ አሽቀንጥራ ትጥላለች። ትንቢቱ ይደርሳል፤ ቀርቶም አያውቅም። እስከዚያው “የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች” አሸብሩ፣ ክበቡ፣ እሰሩ፣ ግደሉ።

የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!ከርዕዮት እስከ ደበበ

“ካዛብላንካ” የተባለውን ታዋቂ ፊልም አይታችሁት ይሆናል። በሞሮኮ የከተመው አሜሪካው ነጋዴ ሪክ (ዋናው ገጸ ባህርይ) ፊት ለፊት ባይገልጸውም ናዚዎችን ይጠላል፣ የጣልያኑን ፋሺስት ይጸየፋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መግቢያ (1941 እ.አ.አ) ላይ በፈረንሳዮች ስር የነበረችው ካዛብላንካ ወደጀርመኖቹ ልትተላለፍ በጭንቅ ተይዛለች። ከናዚ አምልጠው ወደ አሜሪካ የሚሄዱ ስደተኞች ከተማዋን ሞልተዋታል። የጀርመኑ ናዚ ተወካይም ወደከተማዋ መጥቷል። በሙስና የተዘፈቀው ፈረንሳዊው የከተማዋ አስተዳዳሪ ሉዊስ ሬኖ ናዚዎችን ቢጠላም ሙስናውን ቀጥሏል። ሪክ የአንድ ወቅት ፍቅረኛውና ባሏ ከካዛብላንካ በአውሮፕላን እንዲወጡ ይረዳቸዋል። ሁለቱ የሚያመልጡት ሪክ ሉዊስን በመሣሪያ አስፈራርቶት የማምለጫ ጊዜ ስለሚያገኙ ነው። በዚህ መጨራሻ የጀርመኑ ተወካይ ወደ አውሮፕላን ጣቢያው ይደርሳል። ሪክ ጀርመናዊውን ይገለዋል። የሬኖ ወታደሮች ትእዛዙን ይጠብቃሉ። ለጥቅስነት የበቃ ትእዛዝ ይሰጣቸዋል፤ ገዳይ እፊቱ እያለ “Round up the usual suspects”።

“የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች” በገፍና በግፍ ማሰር ግራ የገባቸው አምባገነኖች ሁሉ የጋራ ጠባይ ነውን? ዛሬ በአገራችን ሁሉም ሰው “የተለመደ ተጠርጣሪ” ሆኗል። አገሪቱ በሽብርተኞች የተሞላች እስክትመስል ድረስ የሚያዙ “ሽብርተኞች” ዜናና ጉዳይ መነጋገሪያ እየሆነ ነው። ለመሆኑ መንግሥት ይህን ያህል “ሽብርተኞችን” መያዝ ከቻለ፣

ያልተያዙት “ሽብርተኞች” ስንት ይሆኑ?በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ዜጋ

በድንገት “ሽብርተኛ” ሊባል የሚችልበት ፖለቲካዊ ሁኔታ ተመቻችቷል። ይህን ለማስፈጸም የሚችል ሕግ ከነዳኞቹ፣ ሠራዊት ከነመሣሪያው ተዘጋጅቷል። የአቶ መለስ መንግሥት በብዙ መልኩ የመንግሥቱ ኀይለማርያምን ስትራቴጂ ቃል በቃል መድገም ጀምሯል። እርግጥ መንጌ ሕግን የመለስን ያህል መጠቀሚያ የማድረግ ብቃት አልነበራቸውም። አንዱ ማሳያ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን እስከመጨረሻው የመምታት፣ ከስራቸው ነቅሎና ገድሎ የመጨረስ ፖሊሲ ነው። በዚህ የደርግ ፖሊሲ ሕዝብና አገር ቢጎዳም ሕወሓት እና ሻእቢያ ግን ተጠቃሚዎች ነበሩ። ደርግ ተቃዋሚዎቹን ያጠፋልኛል ያለው ፖሊሲ “ከሕወሃትና ከሻእቢያ ጋራ በማንኛውም መንገድ ይገናኛሉ፣ የአማጽያኑን ሐሳብ የመደገፍ አዝማሚያ ሊኖራቸው ይችላል” ያለቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች ማሰርና መግደል ነበር። በመጨረሻ ውጤቱ ይህ ፖሊሲ እነሕወሓትን የሚጠቅም፣ ደርግን ደግሞ ከሕዝብ ፈጽሞ የሚነጥል ነበር፤ በተለይም ከትግራይና ከኤርትራ ሕዝብ። አምባገነኖች ከታሪክ ለመማር ስለማይችሉ ታሪክን የደገሙ ሳይመስላቸው ታሪክን ይኖራሉ።

አሁን መለስ ተቃዋሚዎቻቸውን ለማጥፋት “በሽብርተኝነት” ስም የጀመሩት ዘመቻ የደርግ ግልባጭ ነው፤ በአፈጻጸሙም በውጤቱም። ደርግ “ዓሳን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ” ይል ነበር። አቶ መለስም ኦነግን እና ግንቦት 7ን ለማጥፋት “ባህራቸውን” ለማድረቅ ተነስተዋል። አቶ መለስ ባህሩን ለማድረቅ የተከተሉት መንገድ አገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎችን በሐሳብም ይሁን በተግባር፣ በሕልምም ይሁን በቅዠት መደገፍ አደገኛ ወንጀል እንዲሆን ማድረግ ነው። ደርግም እንዲሁ ነበር ለማድረግ የሞከረው። ትግሬ (ትግራዋይ) መሆን በራሱ በሕወሓት/ሻእቢያ ደጋፊነት ለመጠርጠር የሚያበቃበት ጊዜና ሁኔታ ነበር። አሁንም ስትራቴጂው አልተቀየረም። ኦሮሞ መሆን በራሱ የኦነግ አባልና ደጋፊ ተደርጎ ለመጠርጠር የሚበቃ እየሆነ ነው። የኦነግ አባል የሆነ ዘመድ ያለው ሰው ዘመዱ ከአሜሪካ ደውሎለት ስለአካባቢው ሁኔታ ካወራ፣ ምሬቱን ከገለጸለት፣ ስለ አቶ መለስ ካድሬዎች ድራማ ካወራለት አለቀለት። ለአሸባሪው ድርጅት መረጃ ሲያቀብል ተገኘ ማለት ነው። የስልክ ንግግሩ ቅጂ ይቀርባል፤ ማስረጃ አለን ይባላል። “ማስረጃ” ለማግኘት ሰማይ ምድሩ ይቧጥጣል፡፡ የግንቦት 7 አባል የሆነ፣ ባይሆንም የሚጠረጠር የድሮ የትምህርት ቤት ጓደኛ ካላችሁ እንዳይደውልላችሁ መጸለይ አለባችሁ። ራስህ ደውለህ “እንዳትደውልልኝ” እንዳትለው ይህን ማድረግ በራሱ የሚያስጠረጥር ነው፤ “የሚደብቁት ነገር ከሌለ ‘አትደውልልኝን’ ምን አመጣው?” ብለው የሚጠይቁ አዳማጮች አሉ። አገር ውስጥ የሚገኝ ተቃዋሚ አባል ብትሆንም እንዲሁ እንደ እንቅስቃሴህ የዚሁ ወጥመድ ሰለባ ልትሆን ትችላለህ። ጋዜጠኛ መሆንም እንዲሁ ከመቅሰፍቱ ላይሰውርህ ይችላል። (ከመቅሰፍቱ የሚሰውረውን ታውቀዋለህ!) አንድ ቀን ከቢሮ ወይም ከቤት አጅበው ሊወስዱህ ይችላሉ። ክምር መረጃ አላቸው፤ ካስፈለገም ክምር መረጃ ይፈጥራሉ ወይም አንተ ራስህ በራስ ላይ ማስረጃ ትፈጥራለህ። ማእከላዊ በገባህ በአራተኛው ቀን “24” የተባለውን ፊልም የሚያስንቅ የሽብር ድራማ ደርሰህ፣ ዋናው ገጸ ባሕርይም አንተ ራስህ ሆነህ ትገኛለህ። ልክ እንደአገራችን ፊልመኞች ደራሲውም፣ ፕሮዲውሰሩም፣ ዋና ገፀ ባህርይውም አንተው ራስህ ሆነህ በቲቪ ትቀርባለህ።

ፊልሙን የተሟላ ለማድረግ ደግሞ ሌሎች “የባለሞያ” እገዛ ያደርጉልሃል።

የማእከላዊ ምርመራ ምን ማለት እንደሆነ በቅርብ የተረዳሁት ለጥቂት ቀናት እዚያ ታስሬ በነበረበት ወቅት ነው። በታሰርኩበት ክፍል አጠገብ አንድ ቢበዛ 13 ዓመት የሚሆነው ልጅ አያለሁ። ከሌላው ታሳሪ በሙሉ ተለይቶ ይታያል፤ በጣም ልጅ በመሆኑ። በገባሁ ማግስት ስለልጁ ስጠይቅ ከልጁ በላይ የሚያሳዝን ታሪክ ሰማሁ። ነገሩ እንዲህ ነበር። አቃቂ/ቃሊቲ አካባቢ አንድ ሰው ተገድሎ፣ ሰውነቱ ተቆራርጦ በማዳበሪያ ተደርጎ ተጥሎ ይገኛል። ከዚያ በፊት የሟች ሚስት ባሏ እንደጠፋ፣ ከሦስት ጓደኞቹ ጋራ ተጣልቶ እንደነበር አመልካታ ነበር ይባላል። ነገሩ እንደተሰማም እነዚህ ሦስት ወጣቶች ይታሰራሉ፤ ማእከላዊ። ከዚያም የሠራችሁትን አውጡ ይባላሉ። “ከሟች ጋራ መጣላታችን እውነት ነው፤ ነገር ግን እንኳን ልንገድለው አልተደባደብንም” ይላሉ። እንደሚባለው በሟች ሚስት ገፋፊነትና እጅ መንሻ ጭምር የፈረደባቸው ወጣቶች ወደተለመደው የምርመራ ምእራፍ ይገባሉ። በመጨረሻ ድብደባው ሲበዛባቸው “አዎ፣ ጓደኛችንን ገድለነዋል” ብለው ይናዘዛሉ። ልብ በሉ፣ “ገድለነዋል” ብቻ አይደለም፤ “ገድለን፣ ቆራርጠን ጥለነዋል” ብለው ነው የሚናዘዙት። በስራው ጥራት ዘወትር የሚተማመነው ፖሊስም ምርመራውን ጨርሶ (ምርመራ ተጨረሰ የሚባለው እንዲህ ሲሆን ይሆን?) ለአቃቤ ሕግ ለመላክ ዝግጅት ይጀምራል።

ይህ ሁሉ ሲሆን በእውነተኛው ግድያ የተሳተፈ አንድ ሕሊና ሲረበሽ ይከርማል። ያ ሕሊና፣ የዚያ እስር ቤት ውስጥ ያየሁት ጨቅላ ልጅ ሕሊና ነበር። ልጁ የሟች ሚስት፣ የቀድሞዋ ከሳሽ እኅት ነው። ሟች የተገደለው በጓደኞቹ ሳይሆን በገዛ ሚስቱና በሁለት ወንድሞቿ ነበር። ይህ ትንሽ ልጅ ድርጊቱን ስላየ፣ በኋላ እንዳይናገር በማለት በግድ የክፋታቸው ተባባሪ አድርገውታል (የሰማሁትን ዝርዝር እዚህ መናገር አልፈለኩም)። ልጅ ነውና ከሕሊና የመደበቅን ክፋት በቅጡ አልተማረም፤ በመጨረሻ ነገሩን ለሌላ ሰው ተናግሮ ፖሊስ አዲስ ምርመራ ይጀምራል። ቤታቸውም ውስጥ የሟች ደም ፍንጣሪ ሁሉ ተገኝቷል አሉ። በአዲሱ ምርመራ (በቀድሞው መንገድ የተካሄደ ይሆን?) የሟች ሚስት፣ ትንሹን ልጅ ጨምሮ ከሁለት ወንድሞቿ ጋራ ታስረው አይቻቸዋለሁ።

ዛሬ “ሽብርተኛ” እየተባሉ የሚያዙት የብዙዎቹ ሰዎች ታሪክ ከዚህ የምርመራ ሂደት ድራማ የተለየ ስለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም። ጋዜጠኛ ውብሸትን ጨምሮ “በሽብርተኝት” የተጠረጠሩ ሰዎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቶች ተናግረዋል። (የፍርድ ቤቶቹ ምላሽ አያስቃችሁም? “ከተፈጸመ እንዳይደገም”፣ ወይም ራሱ ደብዳቢው አካል ጉዳዩን እንዲያየው እግረ መንገድ ጠቅሶ ማለፍ።) ደርግ አገርን ከሚጎዳ፣ ሕዝብን ከሚያሰቃይ ይልቅ “ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ መፍታት ነበረበት” እየተባለ እንደቀለድ ይነገራል። ይህ ጥፋት የአገር ጥፋት፣ የትውልድ ጥፋት ነበር። ያቺው አገር፣ ያው ራሱ ትውልድ ግን ይህንኑ ጥፋት በባሰ መልኩ እየደገሙት ነው። ዛሬም መመሪያው “የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች ክበቡ” ነው። ድሮ ደርግ “የተለመዱ ተጠርጣሪዎች” ነበሩት። በአገሪቱ ለሚያጋጥሙ ማናቸውም ችግሮች ተጠርጣሪዎቹ እነዚሁ አካሎች ነበሩ። በሬዲዮ፣ በኢቲቪ፣ በአዲስ ዘመን፣ በፓርቲ ልሳን፣ በቀበሌ ስብሰባ፣ በሞያ ማኅበራት፣ በጾታ ማኅበር…አብዮት/መስቀል አደባብይ፣ ናዝሬት፣ ነቀምት፣ ባህር ዳር፣ ድሬዳዋ፣ መቀሌ…ሁሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚወገዙት እነርሱው ነበሩ።

ዛሬም የማውገዣ ቦታዎቹና ተቋማቱ እንኳን አልተቀየሩም። የውግዘቱ ይዘትና ቋንቋም እንዲሁ። የይዘት ሳይሆን የቃላት ለውጡን በምሳሌ እናስታውስ። ኢምፔሪያሊዝም ወደ ኒዎ ሌበራሊዝም፣ ሕወሃት/ሻእቢያ ወደ ኦነግ/አብነግ/ግንቦት 7፣ ተገንጣይ/አስገንጣይ ወደ ጠባብ/ትምክህተኛ፣ አልቱራቢ/በሽር ወደ ኢሳያስ..ተቀይረዋል።

የሚመራውን መንግሥት ከልቡ ያወጣ ሕዝብ ገበያ አይሄድም፣ ቢሮ አይገባም፣ በኢኮኖሚ አይሳተፍም፣ ለልማት ስራ አያዋጣም ማለት ቂልነት ነው። በመንግሥቱም ጊዜ እኮ “ለእናት አገር ጥሪ” (ስሙ እንዴት ደስ ይላል!) ሕዝብ አዋጥቱዋል፤ ለልማት ዘመቻ ዘምቷል፤ እረ ለጦርነትም ዘምቷል። እነዚህ ሁሉ ግን ሕዝቡ በሙሉ ልቡ እስከ መጨረሻው ከመንግሥቱ ጋር ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሊሆኑ አይችሉም። አሁንም ልክ እንደድሮው ሕዝቡ በውድም በግድም ለአባይ ግድብ ስላዋጣ ወይም ቦንድ ስለገዛ ለመለስ አገዛዝ የሕዝብ ፍቅር ማሳያ ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። “ለእናት አገር ጥሪ” አለማዋጣት እና ለአባይ ግድብ አለማዋጣት በመሠረቱ ውጤታቸው ተመሳሳይ ነው። ደርግም ኢሕአዴግም የየራሳቸው መቅጫ አላቸው። ለጊዜው መዋጮው ከቅጣቱ የተሻለ እስከሆነ ድረስ ሕዝቡ የሚመርጠው መዋጮውን ነው። በተጨማሪ ደግሞ “የእናት አገር ጥሪውም” ይሁን “የአባይ ግድብ” በመሠረቱ ሊደገፉ የሚገባቸው ዓላማዎች ናቸው። አቶ መለስ እና ኮሎኔል መንግሥቱ ሕዝቡ ለአገሩ ወይም ለግል ጥቅሙ ብሎ የሚያደርገውን ሁሉ ለእነርሱ ፍቅር ሲል ያደረገ እየመሰላቸው ሳይሞኙ አልቀሩም።

ወደ ተነሳንበት ጉዳይ ስንመለስ፣ ተቃዋሚዎችን ወይም የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ሁሉ በጥርጣሬ የሚመለከት ፖለቲካ ፈጽሞ ሊረጋጋ አይችልም። የዴሞክራሲያዊ ስርአት መነሻ መሰረት መተማመን እና ይህንኑ ተቋማዊ የሚያደርግ አመራር ነው። አሁን የምንታዘበው ግን እርስ በርስ መጠራጠርን የፖለቲካ ሥርአቱ መለያ የሚያደርግ፣ መጠራጠርን ተቋማዊነት የሚያላብስ ፖለቲካነው።

በነገራችን ላይ!ቢያንስ ለወጉ ያህል “እንኳን አደረሳችሁ” መባባል

ነበረብን መሰለኝ። “ለምኑ?” ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር መልሱ ብዙ ነው። የአዲስ ዓመት በዓል ከሕዝባዊና ባህላዊ በዓልነት ወደ መንግሥታዊ ፕሮፓጋንዳ መድረክነት መለወጡን ለማየት እንኳን አደረሳችሁ! የአምናና የዘንድሮ የዘመን መለወጫ በዓላት ፍጹማዊ አምባገነን መንግሥታችን አንድም እርሱ የማይወደስበት የጋራ መድረክ እንዳይኖረን የሚያደርገው ወረራ አውራ ማሳያዎች ናቸው። ከብዙ ስሕተቱና መዘዙ ጋራ፣ ደርግ እንኳን ይህን ያህል ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላትን የፕሮፓጋንዳ መጠቀሚያ ለማድረግ አልቻለም ነበር። ፕሮፓጋንዳው በጥቅስ እየታከከ፣ በካድሬ ሰባኪያን እየተዋበ በዐርብ ስግደት፣ በእሑድ ጸሎት እንኳን አልተው ብሎናል። አሁን ደግሞ ብሔራዊውን የአዲስ ዓመት በዓላችንን ከአዝማሪዎቹ ጋራ ተቆጣጥሮታል። በዚሁ ከቀጠልን ብዙም ሳንቆይ ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓሎቻችን ሁሉ “ለሕዝብ ጥቅም” በቁጥጥር ስር መዋላቸው አይቀርም፤ ሙከራው ተጀምሯል። ምናልባትም እንቁጣጣሽ የሚለው “የትምክህተኞች” ስያሜ ሊቀየር ይችላል። እባካችሁ፣ በበዓል ቀን እንኳን እረፍት ስጡን። በናታችሁ አንዳንድ ጊዜ እንኳን ተዉን! የመተንፈሻ ጊዜ ስጡን!

አባላት የፋይናንስ አቅማቸውን አስካላጎለበቱ ድረስ ነፃነታቸውን የማረጋገጥ አቅማቸውም ደካማ ይሆናል፡፡ የሚንቀሳቀሱት ከሞላ ጎደል ከማዕከል በሚሰጣቸው ድጎማ ነው፡፡ በራሳቸው ፋይናንሳቸውን የማጠናከር አቅማቸው ገና አልዳበረም፡፡ ጠባያቸውን ካላሳመሩ፣ እንደ ውሃ በተቀዳላቸው ቦይ ካልፈሰሱ የድጎማቸውን ሁኔታና የክልላቸውን ልማት አደጋ ላይ ከመጣላቸውም በላይ በቁልፍ ቦታዎች ላይ የተቀመጡ የክልል ሹማምንትም ቦታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቁልፍ የሹመት ቦታ ማጣት ደግሞ በተለመደው ባህላዊ አነጋገር “የአንጀራ ገመድን መበጠስ” ማለት ነው፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመበልጸግ ዕድልን ማጣት ማለት ነው፡፡በሰለጠነውና በበለጸገው ዓለም ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለፖለቲካ ሥልጣን የሚወዳደርበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመበልጸግ አይደለም፡፡ ፖለቲካ ዓለምና ውስጥ የሚገቡት እምነት፣ዓለማና ራይዕይ ስላላቸውና ያንን እምነት፣ዓላማና ራዕይ እውን ሆኖ ማየት ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ብዙዎቹ ሚሊየነሮች ናቸው፣ከፖለቲካ ውጭ ሠርተው የሚያገኙትን ገንዘብ በሥልጣን ቦታ ተቀምጠው ከሚያገኙት ገንዘብ እጅጉን ይበልጣል፡፡ እንደ እኛ ባሉ የሦስተኛ ዓለም አገሮች ግን ሰዎች ከጥቂት ሰዎች በስተቀር ለሥልጣን የሚወዳደሩት በሃገራቸው ውስጥ ከሚገኘው የሃብት ዳቦ ላይ የቻሉትን ያህል በጭቀው ለመውሰድና በአጭር ጊዜ ውስጥ ከድህነት ለመላቀቅ ነው፡፡ ስለዚህ የእኛ አገር የፌደራል አካላት ሹማምንት የፌደራሉ ሥርዓት በትክክል እንዲሠራ የሚከፈለውን መስዋዕትነት እየከፈሉ በሕጋዊና ሠላማዊ መንገድ ከመታገል ይልቅ

ታዛዥ መሆንንና የራሳቸውን ሕይወት ማመቻቸትን የመረጡ ይመስላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ፌደራሊዝም ፌደራላዊ ሊሆን አልቻለም፡፡ፌደራሊዝምን ፌደራላዊ አንዳይሆን የሚያደርገው ሌላው ችግር የሰው ኃይል አቅም ማነስ ነው፡፡ ፌደራሊዝም እንደማንኛውም የመንግሥት አወቃቀር ረቂቅ ሥርዓት ነው፡፡ ዕውቀት፣ልምድና ከፍተኛ የሥራ ዲስፕሊንና ቁርጠኝነቱ ያለው ከፍተኛ የሰው ኃይል ይጠይቃል፡፡ የዚህ ዓይነት የሰው ኃይል በብቃት የለም፡፡ ይህ የሁሉም ክልሎች ችግር ቢሆንም በተለይ ተረስተው በነበሩ የጠረፍ አካባቢዎች ይብሳል፡፡ ዕውቀት ያለው የሰው ኃይል በራሱ ይተማመናል፣ ሥራውን በጥራት ይሠራል፡፡ ዕውቀት ያለው፣በራሱ የሚተማመንና ሥራውን በጥራት የሚሠራ የሰው ኃይል መብቱን ያስከብራል፡፡ የማይሆነውን አይሆንም ይላል፡፡ ነፃነትን ይጠይቃል፡፡ በዚች አጭር ጽሑፍ የአገራችንን ፌደራሊዝም በተመለከተ ሦስት ችግሮችን አንሰተናል፡፡ አንደኛው ችግር በመሠረቱ የነፃነት እጦት ነው፡፡ በአንድ በኩል በፌደራሊዝም፣የሥልጣን ክፍፍል ነው፡፡ በሌላ በኩል የዚህ ዓይነት ፌደራሊዝም ክፉኛ በተማከለና መፈናፈኛ በሌለው አምባገነን አውራ ፓርቲ ሥርዓት ውስጥ ነው ለመሥራት የሚሞክረው፡፡ በቅርጽ ፌደራላዊ ነው በተግባር ግን የተማከለ ወይም እንደ ደርግ ኢሠፓ ሥርዓት አሃዳዊ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ሊቀጥሉ አይገባም፡፡ የሚያሳዝነው ግን ኢህአዴግ አሁን በአለው መልኩ በሥልጣን ላይ እስከቀጠለ ድረስ፣ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ እስካልሰፈነ ድረስ ለውጥ ሊመጣ የማይችል መሆኑ

ነው፡፡ ሁለተኛው የፌደራል መንግሥት አባላቱን እጅ የሚያስረው ደግሞ የፋይናንስ አቅማቸው መዳከምና ለድጎማ መዳረጋቸው ነው፡፡ ለድጎማ መዳረግ በኢህአዴግ እጅ ላይ መውደቅ ዓላማ ነው፡፡ ሦስተኛው የቆየ ሰው ኃይል አቅም ማነስ ችግር ነው፡፡ ወደ ውስጥ ሲገባ ደግሞ ሌሎች ችግሮችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡በሃገራችን ፌደራሊዝም ከተመሠረተ አሥራ ስድስት ዓመት ያህል ሆኖታል፡፡ ሥርዓቱን በተመለከተ ብዙ ምሁራን ብዙ ብለዋል፡፡ በቅርቡ አዲስ አበባችን ፌደራሊዝምን በተመለከተ ዓለምአቀፍ ጉባኤ አካሂዳለች፡፡ በዚህ ጉባኤ ብዙ ጽሑፎች ቀርበዋል፣ብዙ ሰዎች ብዙ ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያም በፌደራሊዝም ሞዴልነትም ምስጋናዎች ተችረዋል፡፡ ጥያቄው አመስጋኞቹ እነማን ናቸው? ስለኢትዮጵያ ምን ያህል ያውቃሉ? የሚለው ነው፡፡ ያም ሁሉ ሆኖ፣ተብሎም በሃገራችን በመሬት ላይ ለውጥ የለም፡፡ ድመት እንዳለችው “ያው በገሌ” ነው፡፡ እውነተኛ ፌደራሊዝም በሃገራችን እውን ሆኖ ማየት እንፈልጋለን፡፡ ከፓርቲ ቁጥጥር፣ከፓርቲ ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ እውነተኛ ፌደራሊዝም ማየት እንፈልጋለን፡፡ ኢህአዴግ በአሁኑ መልኩ ሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ግን ይህ ምኞታችን እውን ሊሆን አይችልም፡፡ ምኞታችን እውን እንዲሆን የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ መኖር አለበት፡፡ መድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲን ለማምጣት በሕጋዊና ሠላማዊ መንገድ ጠንክረን መታገል አለብን፡፡በመጨረሻም ስለመንግሥት አወቃቀር ወይም ቅርጽ ስንነጋገር ዋናው ቁምነገር ያለው ቅርጽ

ላይ አለመሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡ ስለ አሃዳዊነትና ስለፌደራላዊነት አንስተናል፡፡ ብዙ ጊዜ ፌደራላዊነት ዴሞክራሲያዊነት፣አሃዳዊነት ደግሞ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት እንደሆነ ይታሰባል፡፡ በዓለማችን አሐዳዊ ሆነው በሚያጠግብ ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ብዙ አገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ሩሲያ ፌዴራላዊት ነች፡፡ የዴሞክራሲ ተምሣሌት ግን አይደለችም፡፡ አሜሪካ ፌደራላዊ ናት፡፡ እንግሊዝ ደግሞ አሃዳዊ ናት፡፡ ሁለቱም የዴሞክራሲያዊነት ተምሳሌቶች ናቸው፡፡ ኖርዌይ፣ስዊድንና ሆላንድ ለምሳሌ አሃዳዊ ናቸው፡፡ ከዚያም አልፈው ዘውዳዊ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህም አገሮች በዴሞክራሲያዊነታቸው በአርአያነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡እርግጥ ቅርጽ ለአፈፃጸም ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ ሆኖም ቅርጽ ሁሉ ነገር አይደለም፡፡ ታዲያ ቁምነገሩ ያለው ምኑ ላይ ነው? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡ ቁምነገሩ ያለው የአንድ አገር ሕዝብ የተማረ፣በአስተሳሰብ የሠለጠነ፣በኢኮኖሚ የበለጸገ፣በዴሞክራሲያዊ ባህሉ የዳበረ፣የሰው ልጅ ሕይወት ክቡርነትን የተገነዘበ፣ለሕግ የበላይነት ከፍተኛ አክብሮት ያለው፣እውነትን፣ቅንነትን፣ ታማኝነትን፣ተጠያቂነትን የዕለት ተዕለት ህይወቱ መመሪያ ያደረገ እመሆኑ ላይ ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ ባህሪያት ያሉት ሕዝብ የሥርዓቱ ቅርጽ አሃዳዊም ይሁን ፌደራላዊ ሥርዓትን ማደጊያውና መበልጸጊያው ሊያደርገው ይችላል፡፡ለውይይት መነሻ ይህን ካልኩ ይበቃል፡፡ መድረኩም ይኸው፡፡ እንወያይና የፌደራል ሥርዓታችን እውነተኛ ባህሪ ግልጽ እናድርግ፡፡

የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ!

ከገፅ 5 የዞረፌደራላዊ ያልሆነ ...

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

142ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 15ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

142ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 15ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

የዚህ ጽሑፍ ግብ በሰው ልጅ ታሪክ የሰላም ትግል መቼ እንደተጀመረ መመርመር እና የሰላም ትግል ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ቀላል በሆነ ምሳሌ ማብራራት ነው። በሰው ልጅ ታሪክ የሰላም ትግል መቼ እንደተጀመረ ስንመረምር በኢትዮጵያም የተመዘገበ የሰላም ትግል ታሪካችንን መለስ ብለን ባጭሩ እናስተውላለን። እንደሚታወቀው የሰው ልጅ ታሪክ በአብዛኛው የእርስ በርስ ጦርነት እና መጨራረስ ታሪክ ስለነበር በተሻለ ሁኔታ ተጽፎ ወደ እኛ ዘመን የተላለፈውም ይሄው አስከፊ ታሪክ ነው። አብዛኛው የሰው ዘር በጦርነት ላይ ከነበረው አምላኪነት የተነሳ የሰላም ትግልን በመናቅ ተጽፈው የሚገኙ የሰላም ትግል ታሪክ መረጃዎች ሳይቀሩ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በቅጡ አይሰባሰቡም ነበር። ስለዚኽ የሰላም ትግል ሲነሳ በብዙዎች አዕምሮ ፈጥኖ ብቅ የሚለው በ78 አመቱ በ1940 ዓመተ ምህረት የሞተው ጋንዲ ነው። የሰላም ትግልን የጀመረው ጋንዲ ነው ብለው የሚገምቱ ጥቂት አይደሉም። ርግጥ ጋንዲ ለሰላም ትግል ታላቅ እውቅናን ያስገኘ የሰላም ትግል ስትራተጂስት (ስኬታማ የሰላም ትግል ፕላን ቀያሽ) ሲሆን የሰላም ትግል የተጀመረው ግን ከጋንዲ ረጅም ዘመን ቀድም ብሎ እንደሆነ ታሪክ ያመለክታል። በያዝነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ፍልስፍና አለም አቀፍ እውቅናን ያገኙት ምሁራን እነ ጅን ሻርፕ እና ሌሎች እንደዘገቡት ከሆነ የሰው ልጅ ጭቆናን እና የፖለቲካ ግጭትን ለመፍታት ሰላማዊ ትግልን ከክርስቶስ ልደት ቀደም ብሎ ጀምሮ ተጠቅሟል። ጅን ሻርፕ “ክፍል አንድ፡ የፖለቲካ ኃይል እና ትግል” (The Politics of Nonviolent Action, Part One: Power and Struggle) በሚለው መጽሐፉ ገጽ 75-76 ላይ በጥንታዊት ሮም ፕሌቢያኖች (Plebeians) የተባሉት የሮም ኗሪዎች በ494 ዓመተ ዓለም ስኬታማ የሰላም ትግል አድርገዋል። የታሪክ መጽሐፎች እና ድረ ገጾች እንደሚያመለክቱት ፕሌቢያኖች ባሮች ሳይሆኑ ከቀረው ሮማዊ ጋር እኩል የፖለቲካ መብት ያልነበራቸው ተጨቋኝ ዜጎች ነበሩ። ለገዢዎቻቸው (ቆንሲሎች/consuls) ወታደር በመሆን እና ተጨማሪ ግልጋሎቶች ይሰጡ ነበር። ግብር ጨምሮ። በ494 ዓመተ ዓለም ፕሌቢያኖች ይፈጸምባቸው የነበረውን የፖለቲካ ጭቆና ለማስወገድ የወሰዱት ርምጃ የዘመናቸውን ገዢዎች (ቆንሲሎች/consuls) መግደል አልነበረም። መቼም በዚያን ጊዜ የህዝቡም ቁጥር ብዙ ስላልነበር ፕሌቢያኖች ከተማውን ለጨቋኞቹ ገዢዎች ትተው በቅርብ በሚገኝ ተራራ ላይ ለተወሰኑ ቀናት በመስፈር ቀደም ሲል ለከተማዋ እና ለገዢዎቻቸው (ቆንሲሎች/consuls) ይለግሱት የነበረውን ትብብር እና አስተዋጽኦ በሙሉ ነፈጉ። ፕሌባውያን ጥያቄያቸው ተገቢውን መልስ ካላገኘ በሰፈሩበት ተራራ ላይ የራሳቸውን ከተማ እንደሚመሰርቱ ለገዢዎቻቸው አስታውቀው ነበር። ይኽ የፕሌባውያን ሰላማዊ ትግል (የፖለቲካ እንቢታ እና ትብብር መንፈግ) ገዢዎቹን ያለ ፕሌባውያን ሙሉ ትብብር መኖር እንደማይችሉ እንዲገነዘቡ

አደረገ። ይኽ የፕሌባውያን የሰላም ትግል ለጨቋኞቹ ገዢዎች በፍራቻ የሚገዛላቸው ህዝብ ከፍራቻ ነፃ ወጥቶ ትብብር ከነፈጋቸው የሚመሩት መንግስት እና የሚኖሩት የድሎት ኑሮ እንደማይኖር ወለል ብሎ እንዲታያቸው አደረገ። ባጭሩ የጥንታዊ ሮማ ገዢዎች ምድር ሰማዩ ጨለመባቸው። ድርድር ለማድረግ ተገደዱ። ወደው ሳይሆን በስልጣናቸው ለመቆየት የነበራቸው የተሻለ አማራጭ የፕሌባውያንን ጥያቄ ተቀብሎ በፕሌባውያን ላይ ይፈጸም ለነበረው የፖለቲካ ጭቆና መፍትሄ መስጠት ብቻ እንደነበር በግልጽ ስለገባቸው ነበር። ስለዚህ በርካታ የፖለቲካ ለውጦች አደረጉ። በ494 ዓመተ ዓለም የተደረገው የፕሌባውያን ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የተገባደደው በዚኽ አይነት ስኬታማ ፍጻሜ ነበር። ይኽ ፕሊቢያኖች ላንድ ሰሞን የሰፈሩበት ተራራ “የተባረከው ተራራ” (“The Sacred Mount”) የሚል መጠሪያ አግኝቶ እንደነበር ታሪክ ያመለክታል።እንደገና በ258 ዓመተ ዓለም ግድም የጥንታዊት ሮማ ወታደሮች ከውጊያ ሲመለሱ ይፈጸምላችኋል የተባሉት የኑሮ መሻሻል ሁኔታ በገዢዎች ታገደ። የመንግስት ባለስልጣኖች የገቡትን ቃል ማፍረሳቸው ጦሩን ቢያናድደውም የጦር ኃይሉ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ገዢዎቹን አልገደለም። ትብብር እና ግልጋሎት የመንፈግ ሰላማዊ ትግል ነበር ያደረገው። ሰላማዊ ትግሉ ተፈጻሚ ለማድረግ ሰራዊቱ መሬቷ ለም ወደሆነው ክሩስቱመሪያ (Crustumeria) ወረዳ ዘምቶ “በተባረከው ተራራ” ላይ ሰፈረ እና አዲስ ከተማ በመቆርቆር ከቀድሞ ገዢዎቹ እራሱን ነጻ እንደሚያወጣ አወጀ። በዚህን ጊዜም የሮማ ገዢዎች ለሰራዊቱ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት መልሰው የሰራዊቱን ትብብር ለማግኘት ችለዋል። እንግዲኽ እስከዚህ ድረስ እንዳስተዋልነው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ መለስ ስናደርግ ደግሞ በኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ላይ ቱርኮች የጋረጡትን እንቅፋት ለማስወገድ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩት ታላቁ እያሱ (1674-1698/9) ያደረጉትን ሰላማዊ ትግል እናገኛለን። የምጽዋን ወደብ በመያዛቸው ቱርኮች ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ቀረጥ እየጨመሩ የኢትዮጵያ ነጋዴ እንዳይጠቀም አደረጉ። ይኽ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ እንዳያድግ አደረገ። በዚህን ጊዜ ታላቁ ኢያሱ ከኢትዮጵያ ወደ ወደቡ ምንም አይነት ምግብ ነክ ሸቀጥ እንዳይሄድ ዐዋጅ አስነገሩ። ቱርኮች የምግብ ምንጫቸው ተዘጋ። ጦርነት ከተደረገ ደግሞ የሚሆነው በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚሆን ቱርኮች ያን አይፈልጉም። ታላቁ ኢያሱ በዐዋጅ የንግድ ልውውጥ እገዳ (እቀባ) በማድረግ ቱርኮች ከወደቡ የሚያገኙት ጠቀሜታ ዝቅ እንዲል አደረጉ። ቱርኮች የሚበሉትም ተቸገሩ። በደረሰባቸው ችግር ተገደው ወደ ድርድር መጡ። ከዚህ በፊት የዘረፉትን ሸቀጥ መልሰው እና የጫኑትን ቀረጥ አንስተው ካፄ ኢያሱ ጋር ስምምነት አደረጉ። በዘመናችን የዚህ አይነት የንግድ እቀባ በመንግስታት መካከል የሚደረግ የሰላም ትግል ነው። የሰላም ትግል በሚል ባይፈርጀውም የተደረገውን ዝርዝር ሁኔታ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ “የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ካፄ ልብነ ድንግል እስከ ዐፄ ቴዎድሮስ” በሚለው መጽሐፍ ገጽ 179 ላይ በሰፊው ይተርካል። ባጭሩ እንመልከት።ናይብ ሙሳ የተባለው በምጽዋ እና በአርኪቆ የነበረው የቱርኮች ሹም ብዙ ሸቀጥ እየነጠቀ እና ቀረጥ እያበረከተ የምጽዋ እና የሐማሴን ህዝብ ንግድ እንዳይነግድ አደረገ። በዚህን ጊዜ ንጉሱ ወዲያው ወደ ሐማሴን አውራጃ ገዢዎች እና ባላባቶች መልክተኛ ልከው፥“ቅቤ፣ ማር፣ እህል ይዞ ከሐማሴን ወደ ምጽዋ ለንግድ ማንም እንዳይሄድ፣ የሄደ ግን ብርቱ ቅጣት ያገኘዋል” ሲሉ ዐዋጅ ነገሩ። በዚህ ዐዋጅ ቱርኮች ታላቅ ችግር ላይ ወደቁ። የአርኪቆ ገዥ ናይብ ሙሳም ወታደራዊ ዘመቻ አድርጎ ዐዋጁን በኃይል እንዳያስፈርስ ያፄ ኢያሱ ጦር ሰራዊት ቀደም ብሎ በአክሱም እና በሐማሴን መስፈሩን አስተውሏል። ምንም እንኳን በመዳፉ

ቢተማመንም ጦርነት በኢትዮጵያ ምድር ቢጀምር ኢትዮጵያውያን የሽምጥ በፈረስ ጋልበው በመደፉ መካከል በመግባት ውጊያውን ወደ ጨበጣ ውጊያ እንደሚቀይሩበት ያውቃል። ስለዚህ ናይብ ሙሳ በቀረጥ ምክንያት የዘረፈውን ሸቀጥ ይዞ ንጉሱ የነበሩበት አክሱም ድረስ መጣ። የጨመረውን ቀረጥ እንደሚያነሳ ቃል ገብቶ ከንጉሱ ጋር እርቅ አደረገ። የዘረፈውን ሸቀጥ ለንጉሱ አስረከበ። ከዚህ በኋላ የሐማሴን ህዝብ ወደ ምጽዋ፣ የምጽዋ ህዝብም ወደ ሐማሴንም ወደ ትግራይም እየመጣ እንደቀድሞው እንዲነግድ ስምምነት አደረጉ። ከስምምነቱ በኋላ ናይብ ባሻ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ንጉሱም ከአክሱም ተነስተው ወደ ጎንደር ተጓዙ። በዘመናችን የዚህ አይነት የንግድ እቀባ በመንግስታት መካከል የሚደረግ የሰላም ትግል እንደሆነ የታወቀ ነው።ርግጥ ይኽ በታላቁ ኢያሱ የተደረገው የሰላም ትግል በኢትዮጵያ የተደረገ የመጀመሪያ የሰላም ትግል ነው ከሚል ድምዳሜ አያደርሰንም። ነገር ግን በኢትዮጵያ የሰላም ትግል መደረጉን ያረጋግጥልናል። ለጥቆ የምናነበው አጭር ታሪክ በጎ ያልሆኑ ተግባሮችን ለቻይናውያን ለማስተማር ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የግብረገብ (የሞራል) ታሪክ መጽሐፍ የተወሰደ ሲሆን ይህ አጭር ታሪክ መጀመሪያ “በብልጥነት መግዛት” (“Rule by Tricks”) በሚል ርዕስ ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ የተተረጎመው በሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ነበር። ይኽ አጭር ታሪክ ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ከአልበርት አነስታይን ተቋም ይታተም በነበር የዜና ጋዜጣ ላይ ታትሞ ለንባብ ቀርቧል (The translation was originally published in Nonviolent Sanctions: News from the Albert Einstein Institution (Cambridge, Mass.), Vol. IV, No. 3 (Winter 1992-1993), p. 3.]። በቅርብ ደግሞ ጂን ሻርፕ ይኽን ታሪክ ከአምባገነን ወደ ዲሞክራሲ በሚለው መጽሐፉ ገጽ 17-18 ላይ አቅርቦታል። ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) የተባለው ጸሐፊ ዩ ሊ ዚ (Yu-li-zi) በሚል ስምም ይታወቃል። ወደ ታሪኩ እናምራ።በ14ኛ ክፍለ ዘመን በቻይናዊው ሊዩ ጂ/ by Liu-Ji (1311-1375) በተጻፈው የሞራል ትምህርት ማስተማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ከየት እንደሚመጣ ግልጽ ተደርጎ ቀርቧል። በዚኽ መጽሐፍ ውስጥ በፊውዳላዊቱ ቹ (Chu) ግዛት ውስጥ አንድ ሽማግሌ ዝንጀሮዎች እንዲያገለግሉት በማድረግ ይኖር እንደነበር እና የቹ (Chu) ግዛት ህዝብ ይኼን ሽማግሌ ሰው የዝንጀሮዎቹ ጌታ (“ju gong”/monkey master) ብሎ ይጠራው እንደነበር ተጽፏል። ይኽ ሽማግሌ ሰው ሁልጊዜ ማለዳ እየተነሳ በቁጥጥሩ ስር የነበሩትን ዝንጀሮዎች በግቢው ውስጥ እያሰለፈ ትልቁ ዥንጀሮ የቀሩትን ዝንጀሮዎች መርቶ ወደ ተራሮች እንዲወስድ እና ፍራፍሬ እንዲለቅሙ እንዲያደርግ ትዕዛዝ ይሰጠው ነበር። እያንዳንዱ ዝንጀሮ በተራራዎች ውሎው ከለቀመው ፍራፍሬ ውስጥ አንድ አስረኛውን (1/10) ለሽማግሌው መለገስ ህግ ነበር። ይኽን ማድረግ የተሳናቸው ዝንጀሮዎች ርህራሄ የሌለው ቅጣት ይደርስባቸው ነበር። እያንዳንዱ ዝንጀሮ ተገርፎ ያውቃል። ኑሮ ለዝንጀሮዎቹ እጅግ መሪር ነበር። እያንዳንዱ ዝንጀሮ ብቃወም የከፋ ይደርስብኛል የሚል ፍራቻ ስለነበረው ግፉን ተቀብሎ ይኖር ነበር። ለረጅም ጊዜ ተቃውሞ የሚያሰማ አንድ ዝንጀሮ ቢገኝ ብርቅ ነበር። በዚህ አይነት ዝንጀሮዎቹ የሽማግሌውን አገዛዝና ቅጣት ተቀብለው ለረጅም ዘመን ግልጋሎታቸውን እየለገሱት አብረው ይኖሩ ነበር በማለት ሊዩ ጂ (Liu-Ji) የሞራል ትምህርት ለጋሹን ታሪኩን ይጀምራል ። ከእለታት አንድ ቀን በተራሮች ውለው የሚጠበቅባቸውን አንድ አስረኛ (1/10) ፍራፍሬ ለሽማግሌው ከገበሩ በኋላ ወደ ታጠረ ማደሪያቸው ገብተው ሳለ ትንሽ ዝንጀሮ፡ “ እነዚህን በተራራ ላይ ፍራፍሬ የሚያፈሩ ተክሎች እና እጽዋቶች የተከላቸው ይኽ ሽማግሌ ሰው ነውን?” በማለት የቀሩትን ጭቁን ዝንጀሮዎች ጠየቀ።

ሌሎቹ ዝንጀሮዎች፡ “ አይደለም። የሚበቅሉት በራሳቸው ነው” በማለት መልሳቸውን አቀረቡ። ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጥያቄ በትላልቆቹ ዝንጀሮዎች አዕምሮ መጥቶባቸው አያውቅም ነበር። ትንሽቱ ዝንጀሮ ጥያቄዋን በመቀጠል፡ “ታዲያ፣ ፍራፍሬዎቹን ካለሽማግሌው ፈቃድ መውሰድ አንችልምን?” ስትል ወገኖቿን ጠየቀቻቸው። በዚኽን ጊዜ ዝንጀሮዎቹ ነቃ ብለው ጋል ባለ ስሜት እና ከፍ ባለ ድምጽ፡ “ አዎ፣ ሁላችንም ካለሽማግሌው ፈቃድ የለቀምነውን ፍራፍሬ መውሰድ እንችላለን” የሚል መልስ ሰጡ። አሁንም ትንሽቱ ዝንጀሮ ጥያቄዋን በመቀጠል፡ “ታዲያ፣ ለምን የሽማግሌው ጥገኞች እንሆናለን?” ብላ ጥያቄዋን ሳትጨርስ ዝንጆሮዎቹ ድንገት ሁሉም ነገር ገባቸው። ነቁ። የሽማግሌው አለቃነት (ገዢነት) ካለነሱ ትብብር ሊሆን እንደማይችል ወለል ብሎ ታያቸው። ነፃነታቸውን መነጠቃቸው ገባቸው። ሽማግሌው ነፃነት ከሰጣቸው የሚበላው ፍራፍሬ ስለሚያጣ ነፃነታቸውን እንደማይሰጣቸውም ቁልጭ ብሉ ታያቸው። ነፃ አውጪ ነኝ የሚል ሌላ ሽማግሌ ሰው ቢመጣም ነፃነታቸውን ማግኘታቸው አስተማማኝ ሊሆን እንደማይችል ተረዱ። የተነጠቁትን ነፃነት የማስመለስ ኃይል በእጃቸው እንዳለ ተገለጸላቸው። ፍራቻ ድንገት ለቋቸው ሄደ። የተነጠቁትን ነፃነት ለማስመለስ በአንድነት ተነሱ። በዚያኑ ሌሊት ሽማግሌው እንቅልፍ ላይ ሳለ ዝንጀሮዎቹ የማደሪያቸውን አጥር ነቃቅለው ሽማግሌው ከእነሱ እየተቀበለ በጎተራው ያጠራቀመውን ፍራፍሬ በሙሉ ወስደው ባካባቢ ወደሚገኝ ጫካ ሄዱ። ከዚያ በኋላ ዳግም አልተመለሱም ዝንጀሮዎቹ። ሽማግሌው የሚበላው አጥቶ በረሃብ ሞተ። በመጨረሻ ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375)፡ “በአለም ውስጥ የተወሰኑ ሰዎች ህዝባቸውን የሚገዙት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ሳይሆን በብልጥነት ነው። እንደነዚያ አይነቶቹ ሰዎች ልክ እንደ ዝንጀሮዎቹ ጌታ አይደሉምን? አንዴ ህዝባቸው ካወቀ እና ከነቃ በኋላ ግን ብልጥነታቸው መስራቱ ያበቃል” በማለት ታሪኩን ይደመድማል። ከዚኽ አጭር የሞራል ታሪክ አንደኛ የሽማግሌው (የዝንጀሮዎቹ ጌታ) ኃይል ምንጭ የራሳቸው የዝንጀሮዎቹ ትብብር እንደነበር እና ሁለተኛ የዝንጀሮዎቹ ከፍራቻ ነፃ ወጥቶ ትብብር መንፈጋቸው የሽማግሌውን የፖለቲካ ኃይል ምንጭ አድርቆ ሽማግሌውን እንደገደለው እንማራለን። የሰላም ትግል እምነትም የሚነሳው ህዝብ አድርግ የተባለውን ሁልጊዜ እሺ ብሎ ላያደርግ እና አታድርግ የተባለውን ደግሞ አንዳንዴ ሊያደርግ ይችላል ከሚል ቀላል ፅነሰ አሳብ ነው። ህዝብ የጠላውን መንግስት ሁልጊዜ በፍራቻ ያከብራል ማለት አይቻልም። ሰራተኞች ኢኮኖሚን የሚያሽመደምድ የስራ ማቆም ርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ። ቢሮክራሲው እንዲፈጽም የተሰጠውን መመሪያ እሺ ላይል እና ገዢው ቡድን ማስተዳደር ሊያዳግተው ይችላል። ወታደሩና ፖሊሱ በህዝብ ላይ እንዲፈጽሙ የታዘዙትን ወከባ፣ ስለላ፣ እስር፣ ግድያ ሁል ጊዜ እሺ ብለው ላይፈጽሙ ይችላሉ። እንግዲህ ህዝብ ገዢውን ቡድን ካላከበር፣ ሰራተኞች ስራ ካቆሙ፣ ቢሮክራሲው መመሪያ የማይፈጽም ከሆነና ወታደሩ ህግ ማስከበሩን ቸል የሚል ከሆነ የገዢው የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ደረቁ ማለት ነው። ስለዚህ አምባገነን ገዢዎች በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ወከባ፣ እስር፣ እና ተመሳሳይ ህገመንግስታዊ ያልሆኑ ርምጃዎች ህዝቡ ሁልጊዜ በዝምታ ተቀባይ ይሆናል ብለው ራሳቸውን ባያታልሉ ይሻላቸዋል። በለውጥ ላይም ሁልግዜ ጋሬጣ መሆን እንደማይቻል የአረቡ አለም የነጻነት እንቅስቃሴ የቅርብ ጊዜ ምስክር ነው። የሆነው ሆኖ ከፍ ብለው የአምባገነን ገዢ ቡድኖችን የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ለማድረቅ የሚያስችሉ ሰላማዊ እና ህገ-መንግስታዊ ትግሎች ሲደረጉ እርስ በርስ መገዳደል አይኖርም። ከተሞች አይፈርሱም። የፋብሪካዎችና የመንገድ አገልግሎቶች ሙሉ አቅማቸው አይጎድልም። የመንግስት ህንጻዎች አይደመሰሱም። ትምህርት ቤቶች አይፈርሱም። መንገዳችን የሰላም ትግል ነው።

የሰላም ትግል - መቼ ተጀመረ? ከዝንጀሮዎቹ ጌታ ታሪክስ ምን እንማራለን?

ግርማ ሞገስ ([email protected])

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

142ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 15ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

142ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 15ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

በሰላማዊ ትግል ዴሞክራሲያዊ የመንግስት ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ሰላማዊ ዜጎችን አግባብ ባልሆነና ባልተጨበጠ ክስና ዉንጀላ ማሰር፣ አፍኖ መሰወር፣ ንብረትን ማዉደምና መዉረስ እንዲሁም የአደባባይ ግድያ ባለፉት 20 የኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመናት የተለመዱ ተግባሮች ሆነዉ ቆይተዋል። አሁን ደግሞ ይህ አምባገነናዊና ኢፍትሀዊ ተግባር በህግ ሽፋን ተጠናክሮ ቀጥሏል። ለገዥዉ ስርአት የአፈናና የጥርነፋ መዋቅር ተባባሪ ያልሆኑና ለመብታቸዉ መከበር የሚታገሉ ዜጎች በአሸባሪነት ስም በጅምላ እየታፈሱና እየታሰሩ ይገኛሉ። ታፍነዉ የተወሰዱና ያሉበት ቦታ የማይታወቀዉም ጥቂት አይደሉም።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሽብርተኝነት ተወንጅለዉ ታስረዋል። ሰብአዊ መብታቸዉም በማንአለብኝነት እየተረገጠ ይገኛል። ከነዚህ ንፁሀን ዜጎች ዉስጥ ብዙዎቹ የመድረክ አባላቶችና ለሞያቸዉ ታማኝ የሆኑ ጋዜጠኞች መሆናቸዉን ስናይ ደግሞ ዘመቻዉ በሀገራችን ተጠናክሮ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረገዉን ሰላማዊ ትግል ለመጨፍለቅና ህዝብን ከትክክለኛ መረጃ አርቆና አፍኖ ለመግዛት ታስቦበትና ሆነ ተብሎ የተያዘ ስልት መሆኑን እንገነዘባለን።

የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ፣ የኦፌዴን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ፣ የኦህኮ የጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ ኦልባና ሌሊሳ፣ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ናትናኤል መኮንንና አቶ አሳምነዉ ብርሀኑ፣ ታዋቂዉ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ዉብሸት ታየ፣ ጋዜጠኛ ሪዮት አለሙ፣ ጋዜጠኛ ስለሽ ሐጎስ እንዲሁም አርቲስት ደበበ እሸቱ የአንባገነናዊዉ ስርአት ጅምላ እስራት ሰለባ ከሆኑት ጥቂቶቹ ናቸዉ።

እነዚህ ዜጎች በሀገራችን በሚደረገዉ ፈታኝ ሰላማዊ ትግል ዉስጥ በህገመንግስቱ ጥላስር ግንባር ቀደም ተዋናይ የሆኑ ፖለቲከኞችና ሞያዊ ግዴታቸዉን አክብረዉ ለህዝብ ትክክለኛና ያልተዛባ መረጃ ለማድረስ የሚተጉ ጋዜጠኖች መሆናቸዉን መድረክ አጥብቆ ያምናል። ለእስር የዳረጋቸው መንግስትም በሽብርተኝነት ወንጀል ስለመታሰራቸው በመገናኛ ብዙሃን ፕሮፖጋንዳ ሲያሰራጭ እንጂ ስለፈፀሙት የሽብር ተግባር ተጨባጭ ማስረጃ ሲያቀርብ አልታየም፡፡

በመሆኑም፦1ኛ. ሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤2ኛ. የሁሉም የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ሰብዓዊ-መብት መከበሩ በአስቸዃይ እንዲረጋገጥ፤3ኛ. በፀረ-ሽብርተኝነት ህግ ስም የሚደረገዉ የህዝብ መብት ረገጣና እስራት በአስቸዃይ እንዲቆም፤ 4ኛ. ህዝብን አፍኖ ለመግዛት ታስቦ የተዘጋጀዉ “የፀረ-ሽብርተኝነት” አዋጅ ከብርካታ የሕገ መንግስቱ አንቀፆች ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ጊዜ ሳይሰጠዉ እንዲሻር፤ እንዲሁም5ኛ. ማንኛውም ዜጋ በወንጀል ተጠርጥሮ እስካልተፈረደበት ድረስ እንደወንጀለኛ ያለመታየት ሕገ መንግስታዊ መብት እንዳለው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ፍርድ ባልተሰጠባቸው ዜጎች ላይ እንደተፈረደባቸው ወንጀለኞች በመቁጠር የሚያሰራጩትን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ለሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት ሁሉ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማስከበር ከፓርቲያችን ጎን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።መንግስት በፈረጠመ አምባገነናዊ ክንድ ህዝብን በማፈን የስልጣን ዘመንን ለማራዘም መሞከር አወዳደቅን ማክፋት መሆኑን ካለፉት አምባገነናዊ ስርአቶች ሊማር ይገባል!

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)መስከረም 09 ቀን 2004 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ሁኔታ ለሶስተኛው አብዮት “ሶስተኛ መንገድ የለም”ሶስተኛ አብዮት የሚመራው በምልዓተ-ሕዝቡ ነው

በሽብርተንነት ስም የህዝብ መብቶችን ማፈን ይቁም!

ከኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የተሰጠ መግለጫ

በ 1987 ዓ.ም በዝነኛዋ የጦቢያ መጽሄት ላይ ”ሦስተኛ መንገድ የለም” በሚል ርእስ አንድ መጣጥፍ እንዳስነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡ በትራፊክ ስርዓት ሶስተኛ መንገድ የለም፡፡የግራ ወይም የቀኝ መስመር ይዞ ከማሽከርከር በቀር ሌላ ሶስተኛ መንገድ የሚፈልግ ሰው ለትራፊክ አደጋ ከሚጋለጥ በስተቀር የትም አይደርስም፡፡ ይህንን ያሉት በቀዝቃዛው የአለም ጦርነት ማብቂያ ወ/ሮ ማርጋሬት ታቸር ለዘመኑ ሶቭየት ህብረት መሪ ለሚስተር ሚካኤል ጎርቫቾቭ የተናገሩት የማስጠንቀቂያ ሃሳብ ነበር፡፡

አዲሱን የዓለም ስርዓትና ግሎባላይዜሽንን በማዋለድ ረገድ እንዲሁም ቀዝቃዛው የአለም ጦርነት በሰላም እንዲያበቃ መሪ ተዋንያን የነበሩት የአሜሪካኑ ፕሬዝዳንት ሚስተር ሮናልድ ሬገን፤ የሶቭየት ሕብረቱ መሪ ሚስተር ሚካኤል ጎርቫቾቭ፤የእንግሊዟ ጠ/ሚኒስትር ሚስ ማርጋሬት ታቸር በጋራ እየተሰበሰቡ በሚወያዩበት ወቅት የተናገሩት ሃይለ ቃል ነው፡፡ሚስተር ጎርባቾቭ፣ ፕሪስቶሪካና ግላስ ኖትስ በተባሉ ፍልስፍናዎቻቸውን ይዘው በመውገርገር ላይ መሆናቸውን ሴትዮዋ ከተረዱ በኋላና ይልቁንም ከካፒታሊስታዊው እና ከሶሻሊዝሙ የእድገት ጎዳና አንዱን መምረጥ በተሳናቸው ጊዜ የተናገሩት የማስጠንቀቂያ ሀሳብ ነው፡፡ እኔም በግዜው ይህንን ጉዳይ ያነሳሁትና በኢትዮጵያ ዴሞክራቶች ዘንድ ያለውን ምርጫ ሁለት ብቻ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ አንደኛው መንገድ ኢትዮጵያ ከተቃጣባት የጥፋት መንገድ ሁሉ ድና እንደ ሃገር እንድትቀጥል የማድረግ ተልእኮ ሲሆን ሁለተኛው መንገድ በብሄረሰቦች የይስሙላ መብት ዙሪያ ተሰባስቦና ኢትዮጵያን በታትኖ የቡድን ህልውና ብቻ አክብሮና አጠቃላይ የዜጎችን መብትና ነጻነት ረግጦ መግዛት ነበር፡፡ ከዚህ ሌላ በዚያን ወቅት ከ 20 ዓመታት በፊት ሌላ የፖለቲካ መንገድ ማሰብ አስቸጋሪ ነበር፡፡

በዛሬው የኢትዮጵያና የዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ሶስተኛ መንገድ የለም ማለት ትርጉሙ እጅግ የላቀ ነው፡፡ ዛሬ እየገሰገሰ በመምጣት ላይ ያለው ሶስተኛው አብዮት የፖለቲካ ፍልስፍና፣ የታወቀ አይዶሎጂና በታመነ ንድፈ ሃሳብ የሚመራ አይደለም፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት በሰሜን አፍሪካና በአንዳንድ የእስያ አገሮች የታየው ህዝባዊ ንቅናቄ ያስገኘው ድል አርያነቱ እንደኛ ሀገር ላሉት ሁሉ ነው፡፡ ይህ ሕዝባዊ አመጽ እንደተፈጥሮአዊ የጥፋት ክስተት እየነቀለና እየመነገለ የሚጓዝ ማዕበል ነው፡፡ ሕዝቦች በሰላማዊና በተረጋጋ መንፈስ ሲጠይቋቸው የኖሩትን አጠቃላይ የሰው ልጅ መብቶች በአንድ ጀምበር የሚጨበጡ ሆኑ፡፡ ይህንን ጊዜ ያመጣውን ጎርፍ በስርአትና በአክብሮት ካላስተናገዱት ጠራርጎ የሚወስደው ማንን እንደሆነ መግለጽ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ሰላም ያላስገኘውን ነጻነት በህዝባዊ ንቅናቄ እንደሚጨበጥ ታይቷል፡፡ አምባገነኖች ምን ያህል ቢፈረጥሙ ፤ የቱንም ያህል የተንኮል ሴራ ቢያውጠነጥኑ በራሱ ጊዜና ዘመን እየመጣ ያለውን ሶስተኛውን አብዮት መቀልበስ አይቻላቸውም፡፡ ምክንያቱም ሶስተኛው ሕዝባዊ አብዮት የሚመራው ወይም ፊት አውራሪው ምልአተ ህዝቡ ነው፡፡

ባለፈው ግንቦት ወር2003 ዓ.ም በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ በሰጠሁት ቃለ ምልልስ ሦስተኛው አብዮት ከመፈንዳቱ በፊት መንግስት ዴሞክራሲያዊ ለውጦችን ማድረግ አለበት በማለት ተማጽኖዬን ማቅረቤ አይረሳም፡፡ ለሰላማዊ ጥያቂያችን ሀላፊነት የተመላ መልስ አለመስጠት መጭውን የጥፋት ጎርፍ መጋፈጥ የግድ ይሆናል፡፡ በሶስኛው አብዮት ሶስተኛው መንገድ የለም ለማለት የደፈርኩት በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡

1. የዜጎች የፖለቲካ እና የሲቪል መብቶች እንዲሁም የዴሞክራሲ፤ የሰብአዊ መብቶችና ነጻነቶች ባልተከበሩበት እና ታፍነው በተያዙበት ሀገር በተቃውሞ ጎራ ከአንድነት ይልቅ ወደ ብትንትንነት ማምራቱ የሚያስቆጭ መሆኑን ለማመልከት፡፡

2. በአባላት መበራከት መብዛትና መራባት ሳይሆን እነደ አሜባ ራስን በመከፋፈል የቁጥር መብዛት ፋይዳ የሌለው ጉዞ መሆኑን ማመልከት

3. ወትሮም ከታወቁት የፖለቲካ መስመሮችና መርሆች ላይ በመቆም ከመታገል ይልቅ በዳበሳና በሽኩቻ መጓዝ ለህዝብ ፋይዳ ያልሰጠ መሆኑን በማጤን፡፡

4. በታወቁ የፖለቲካ መርሆች ከመመራት ይልቅ በስልጣን ተቀናቀኝነትና በባለ አንጣነት የገዢውን ፓርቲ የስልጣን ፍርፋሪ መቀላወጥ

5. በፓርቲ ወይም በድርጅት አባላት መካከል ሊኖር

የሚገባው እኩልነት፤ የጋራ አመራርና በስራ ክፍፍል መርህ መገዛት መሆኑ ቀርቶ በግለሰብ ጣኦቶች ዙርያ በመቆም የጌታና የሎሌ ግንኙነት በማስፈን ዴሞክራሲያዊ ሂደቱ እንዲጨናገፍ በማድረግ የመከራ ዘመናችንን በማራዘም እራስን እየሰዉ መቃተት እጣ ፈንታችን መሆኑ፡፡

6. የሕዝቡ ተጨባጭ ድጋፍ እጅግ በሳሳበት ሁኔታ የመገኘታችን እንቆቅልሽ በመስዋትነቱ የተገኙትን ድሎች መጠበቅና ማስከበር ባለመቻላችን አምኖ የመቀበል ችግር፡፡

7. በተቃዋሚዎችና በመንግስት መካከል ብሔራዊ መግባባት ተፈጥሮ የአገራችን ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችን ለመመለስ ባለመቻሉ ዛሬም ሁለት ያፈጠ የልዩነት መስመሮች በመኖራቸው የሶስተኛውን አብዮት መምጣት አስፈላጊ አድርጎታል፡፡ ወዘተ ናቸው፡፡

ተደጋግሞ እንደሚገለጸው በአንድ ሐገር የህዝብ ነጻነት ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት ባልተከበረበት ሁኔታ የተቃዋሚ ድርጅቶች በብሄራዊ የጋራ ግንባር(united front) በመሰባሰብ የህዝብን ንቅናቄ በመምራት የሚፈለገውን ዴሞክራሲና ነጻነት በምልዓት ሳይጎናጸፉ በፊት ፓርቲ በሚል ስያሜ መጠራት አልነበረባቸውም፡፡ ሁሉም ተቃዋሚዎች በአንድነትና በውህደት ቆመውና ዴሞክራሴያዊ ንቅናቄውን ከዳር አድርሰው ሲያበቁ ይልቁንም የዜጎች የፖለቲካና የሲቪል መብት ሁሉ ሲረጋገጥ እያንዳንዱ እነደየዝንባሌውና እንደየእምነቱ ጎጆ እየወጣ ፓርቲ መመስረት ይቻላቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኛ ሀገር ሁኔታ ከፈረሱ ጋሪውን ያስቀደመ ነው፡፡

ስለሆነም ሦስተኛው አብዮት የሚመራው በህዝቡ ነው ቢባልም የህዝቡን ትግል ቴክኒካዊ ቅርጽ ለማስያዝ የተቃዋሚዎች በዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ዙሪያ መደራጀትና መሰባሰብ በእጅጉ በፍጥነት ይጠበቅባቸዋል፡፡

እንደሚታወቀው 1966 ዓ.ም የተቀጣጠለው ህዝባዊ አብዮት ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ቢያደርስም ለዘመናት ተንሰራፍቶ የኖረውን የገባር ስርዓት (የጭሰኝነት) ከማስወገዱም በላይ የመሬት-ላራሹን ጥያቄ ከመፍታት አንጻር የብሄር ብሄረሰቦችን ዋነኛ የሆነው መደባዊ ጭቆና ለመፍታት አስችሏል፡፡

ይህ የመጀመሪያው አብዮት ያስገኘው ድል ታላቅ ታሪካዊ ርምጃ መሆኑ ባይካድም ሁለት መሰረታዊ ችግሮች ፈጥሮ አልፏል፡፡ አንደኛው በዓምሳዎቹ መጨረሻ እና በስድሳዎቹ መጀመሪያ አከባቢ በገጠር ማቆጥቆጥ ጀምሮ የነበረው ካፒታሊስት ርሻ እንዲመክን በማድረጉ እስከዛሬ ለቀጠለው አጠቃላይ ድህነትና የምግብ ዋስትና እጦት አንዱ ተጠቃሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡

ሁለተኛው በአዋጁ የታጣው ጉዳይ የመሬት የግል የይዞታ መብት መነፈጉ ነው፡፡ በመሰረቱ በሀገራችን ለረጅም ዘመናት የቆየው የመሬት ይዞታ ቅራኔ ምንጩ መሬት በግል መያዙ ሳይሆን በግለሰቦች እጅ ያለገደብ መከማቸቱ ነው፡፡

የመጀመሪያው አብዮት ካስገኛቸው ዴሞክራሲያዊ ለውጦች አንዱ ”ሶሻሊስት ዴሞክራሲ” ሌላው የከተማ ቦታና የትርፍ ቤት አዋጅ ነው፡፡ በነዚህ አዋጆች በመጠቀም የኢትጵያን የገዢ መደቦች መደባዊ ፍላጎት የደመሰሰ ሆኖ ተቆጥሯል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ወያኔ ሁሉ ነገር ካብቃ በኋላ በፈርሱ ላይ እያጎራ እና የነፍጠኛኛውን ስርአት እደመስሳለሁ እያለ በከንቱ ይደክማል፡፡ በሀገራችን የአብሮነት ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልክ የዝርያ ብሄረተኝነትን እስከ ጥግ ድረስ በመቀስቀስና እኩይ የቁርሾ እና የበቀል ስሜት በማነሳሳት በኢትዮጵውያን መካከል የደም መፋሰስ መጥፎ ታሪክ እንዲጻፍ አድርጓል፡፡ ወያኔዎች አልታደሉም እነጂ በዘመኑ የኢትዮጵያ ተማሪዎች መምህራንና ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ”በእድገት በህብረት ዘመቻ” በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ተሰማርተው እና ከደሃው ገበሬ ጋር በጋራ ሆነው የፊውዳሊዝመን ቅሪቶች ከማስወገድ ጋር ዴሞክራሲያዊ ለውጡን በማስፋፋት ወደር የማይገኝለት ታሪክ ሰርተዋል፡፡ በዚህ ወቅት ሰሜነኞቹ ጸረ-ኢትዮጵያ ሀይሎች እስከዝሬ የቀጠለውን እትዮጵያን የማዳከምና የመበታትን ሴራ በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ለምድ ቀጥለዋል፡፡ ለመሆኑ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ምንድን ነው?

አብታዊ ዴሞክራሲ እንደፍልስፍና የተከሰተው ሁለተኛውን አብዮት በመምራት ረገድ ነው፡፡ እንደሚታወቀው በአለማችን የኖረውና ያለው የመንግስት አወቃቀር ሁለት አይነት እነደሆነ

ይታመናል፡፡ እነሱም አሃዳዊና ፌደራላዊ በመባል በዋናነት ይታወቃሉ፡፡ ይበልጥ የተስፋፋው ግን ፌደራሊዝም የተባለው መንግስት አወቃቀር ነው፡፡ ፌደራሊዝምም የሚታወቀው የጋራና የግል አስተዳደርን የሚወስን ደንብ ወይም ስርዓት Covenant for shared and self rule ነው፡፡

በዘመናችን ያለው የዴሞክራሲ ስርዓት ዓይነቱና ስያሜው ብዙ ነው፡፡ በስም ተለይተው የሚታወቁት እንኳን ከአስር የሚበልጡ ናቸው፡፡

ዋና ዋና የሚባሉትሊበራል ዴሞክራሲሶሻል ዴሞክራሲ ናቸው፡፡ይሁንና በነዚህ ሁሉ ዝርዝር ውስጥ አብዮታዊ

ዴሞክራሲ የሚባል ቅርጽ የለም፡፡1. Representative - የውክልና ምርጫ መንግስት

ባለሥልጣናትንና አመራሩን መሰየም 2. Parliamentary democracy- ፕሬዝዳንታዊውን

ሥርዓተ አመራር የሚቃወም ነው3. Liberal democracy- የግለሰብ መብትና

ነጻነትን ለመንከባከብ የቆመ ህገ-መንግስት ልዩ መታወቂያው ነው፡፡

4. Direct democracy - ለቀጥተኛና ርትዑ ምርጫ የሚቆም ነው፡፡ ዜጎች በግል በቀጥታ በመንግስት ውሣኔ አሰጣጥ ላይ የመሳተፍ መብት የሚያከብር ነው፡፡

5. Socialist democracy - በልዩ ልዩ ቅርጽ የሚዋቀሩ ሶሻል ዴሞክራሲና ዴሞክራቲክ ሶሻሊዝም ሥርዓቶችን ሁሉ አጠቃሎ የያዘ ነው፡፡

6. Anarchist Democracy “Majority rule” - ለብዙሃን አገዛዝ መቆም

7. Iroquols Democracy - ለተሳትፎና ለውክልና ዴሞክራሲ የቆመ

8. Sortition “Democracy without election” choosing decision makers through a random process

9. Consensus Democracy - አልፎ አልፎ ከሚያጋጥም የብዙሃን ድምጽ የልቅ የጋራ የስምምነት ውሳኔ የብዙሀን ድምጽ በአናሳዎች ላይ የበላይነት ጥሩ አይደለም የሚል አመለካከት የሚያራምዱ ናቸው፡፡

10. Interactive Democracy- መራጮች ሕግ በማውጣት ረገድ እንዲሳተፉ በመረጃ መረብ (Information technology) በመጠቀም መስራት ጠቃሚ ነው ብለው ያምናሉ፡፡

11. Aggregative Democracy - የፖሊሲ ሃሣቦች ለህዝብ ምርጫ የሚቀርቡበትና አብላጫውን ድምጽ ያገኘው የፖሊሲ ሃሣብ በሥራ ላይ የሚውልበት ሥርዓት ነው፡፡

12. Deliberative Democracy - የመንግስት ባለሥልጣናትና ሕዝብ በመደማመጥና በመስማማት የአዕምሮ ለውጥ በማድረግና ምክንያታዊ ውሳኔ ላይ በመድረስ የዜጎችን ይሁንታ ማግኘት

13. Radical Democracy - በጨቋኝና በተጨቋኝ ሕብረተሰብ መካከል የቆየውን ቅራኔ ለመፍታት ተብሎ የቆመ ሥርዓት ነው፡፡

እንግዲህ ከዚህ በላይ የዘረዘርናቸው የዴሞክራሲ ቅርፆች አንድን ዴሞክራሲያዊ መንግስታዊ አወቃቀር በተጨባጭ እንዲከሰት በዘመናችን የማይታለፉ የህዝብ መብቶች ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የኢህአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ በነዚህ ተቃራኒ ሆኖ የቆመ በመሆኑ በሰላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄ መወገድ ይኖርበታል፡፡ የኢትዮጵያ ምልዓተ-ህዝብም በዴሞክራሲያዊ ንቅናቄው በአጭር ጊዜ መብቶቹን የሚጎናጸፍ ከመሆኑም በላይ ለግማሽ ምዕተ አመታት በቡቃያው እየታጨደና ድሉንም ለአንምባገነኖች እያስረከበ ወደ ቤቱ የሚገባበት ዘመን ያከትማል በውጤቱም መሰረታዊ እና የሚከተሉትን ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ይቀዳጃል፡፡

መሰረታዊ የዴሞክራሲ መርሆዎች Basic principle of democracy 1. Free election /ነፃ ምርጫ/2. An Independent Judiciary /ነፃ የዳኝነት

ስርዓት/3. Freedom of expression/ሀሣብን በነጻ

መግለጽ/4. Independent political parties /ነጻ የፖለቲካ

ፓርቲዎች/5. A written constitution/የተፃፈ

ሕገመንግስትመኖር/ ናቸው፡፡እነዚህ ሲተነተኑ በርካታ የዴሞክራሲ ሥርዓት

ግኝቶችና ውጤቶችን ማግኘት ይቻላል፡፡

ከዳምጠው አለማየሁ

www.andinet.org.et www.andinet.org.et

162ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8 PBፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.

2ኛ ዓመት ቅጽ.2 ቁ.8

ፍኖተ ነፃነት ማክሰኞ መስከረም 16 2004 ዓ.ም.