መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.pdf

40
ኩር መረጃ ለሁለንተናዊ ለውጥና ልዕልና! 22ኛ ዓመት ቁጥር 17 መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር “ኦዲቱ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት በጽናት ይሰራል!!” የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ስልክ፡ 0582200634 ፋክስ፡ 0582201694 ፖ.ሣ.ቁ፡ 479/ባሕር ዳር ወደ ገጽ 20 ዞሯል በውስጥ ገፆች ገጽ 7 ገጽ 40 - የግዮን ትሩፋት - የቁልቁለት ጉዞ ገጽ 21 ገጽ 3 ገጽ 10 - ባይ ሸለቆ ስልጣኔዎች - ያለውን በቁጭት - የውኃ ሽታ የሆነው ውኃ ገጽ 18 - የ”ጃምቦ ወንዝ” ዘንገናን ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ነው ሙሰኞች ከህግ አያመልጡም! የአብክመ የ ነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ) Frequency- 27500 ) Symbol rate - 12341 ) FEC- 3/4 ) Polarization – hori- zontal መከታተል ይችላሉ፡፡ ስርጭቱን በናይል ሳት የሆስፒታሉ ግንባታ መቋረጥ ችግር ሆኗል ፀጋዬ የሽዋስ በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የተጀመረው ሆስፒታል ግንባታው መቋረጡ ለበርካታ ችግሮች እየዳረጋቸው መሆኑን ተናገሩ:: የወረዳዋ ነዋሪ አቶ ጋሻው ዋለልኝ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ መዘግየቱ ሳያንስ አሁን ደግሞ መቋረጡ ህብረተሰቡን ለተለያየ ችግር እየዳረገው ነው:: ነዋሪዎች ወደ አቅስታ፣ መካነሰላምና ደሴ ሆስፒታሎች በመሄድ ህክምና ለማግኘት ሲሞክሩ እስከ ሞት የሚደርስ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀዋል:: ወይዘሮ ጉዝጉዝ ገረመውም በቅርቡ ወደ አቅስታ አምርተው በህዳር 11 ሆስፒታል ሲገላገሉ በመንገድ ርቀት ሳቢያ በርካታ እንግልት እንዳስተናገዱ ገልፀዋል:: ከደጃቸው የተጀመረው ሆስፒታል ቢጠናቀቅ ኖሮ ከዚህ እንግልት መዳን ይችሉ እንደነበር ይገልፃሉ:: እናቶች ወደ ሆስፒታሎች ሳይደርሱ በመንገድ ለህልፈት እየተዳረጉ እንደሆነ የሚገልፁት ደግሞ የወግዲ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ፈንታው ናቸው:: የተጀመረው ሆስፒታል ቢጠናቀቅ የበርካታ እናቶችን ህይወት መታደግ ይቻል እንደነበርና የጤና ጣቢያውንም ጫና መቀነስ ያስችል እንደነበር ይገልፃሉ:: በጤና ጣቢያ የማይፈቀዱና በሆስፒታሉ ብቻ የሚገኙ መድሃኒቶችን ለማግኘትም ህብረተሰቡ እየተንገላታ ነው ይላሉ:: የሆስፒታሉን ግንባታ ሲቆጣጠሩ የነበሩት የወረዳው የጤና ጥበቃ ጽ/ ቤት ሰራተኛ አቶ አወቀ ጫኔ ሆስፒታሉ በ2005 ዓ.ም በ33 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር እንዲገነባ ለተቋራጩ ሲሰጥ በ500 ቀናት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ነበር ውል የተያዘው:: ሆኖም ግን ግንባታው እስከተቋረጠበት ቀን ድረስ አንድ ሺህ ቀናትን ወስዷል:: በተቋራጩ በኩል መጠናቀቅ ያለባቸው ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ክፍያ እንዳይከፈል በመወሰኑ ግንባታው መቋረጡንም አስረድተዋል:: በአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የጤና መሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ ክንድይሁን እገዘው እንደገለፁት ግንባታውን ሌላ ተቋራጭ እንዲጨርሰው ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል:: ለልማት ድርጅት በመስጠት ድርድር ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ያቀረቡት ዋጋ የተጋነነ በመሆኑ ለግል ተቋራጮች ጨረታ ለማውጣት ጥረት መጀመሩን ገልፀዋል:: (ሙሉ ዘገባውን በገጽ 4 ይመልከቱ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚገኘውን የዘንገና ሐይቅ ለጐብኝዎች ምቹ ለማድረግ ከ13 ሚሊዮን ብር በሚልቅ ወጪ ባለሐብቶች ሎጂዎችን እየገነቡ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ:: ከብሔረሰቡ መዲና እንጅባራ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የዘንገና ሐይቅ ለበርካታ አመታት በቱሪዝም ዘርፍ በቂ ገቢ ሳያስገኝ ቆይቷል:: ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በሐይቁ ዳርቻ ለቱሪስቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሎጂዎች፣ ማረፊያ ቦታዎችና ሌሎች መዝናኛዎች ባለመሟላታቸው መሆኑን በመምሪያው የቱሪዝም ልማት ፕሮሞሽን ባለሙያ አቶ በሪሁን አጥናፉ ተናግረዋል:: በዚህ አመት ግን ሆህያትና ኢኤም የተሰኙ ድርጅቶች በሐይቁ ዳርቻ በ13 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር ሎጂዎችንና ለቱሪስቶች ማረፊያ የሆኑ ግንባታዎችን በማፋጠን ላይ በመሆናቸው ዘንገና ሐይቅ ለዞኑ ገቢ ለማስገኘትና ለወጣቶችም የስራ እድል ለመፍጠር እየተቃረበ ነው ብለዋል፤ የሆህያት ሎጅ በዚህ አመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ በማስታወስ:: በዞኑ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የልማታዊ ባለሐብት መሳብና መደገፍ የሰራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው አያሌው በበኩላቸው በዘንገና ሐይቅ ላይ ሎጂዎችን እየገነቡ ያሉት ሁለቱ ድርጅቶች ቱሪስቱን የበለጠ ለመሳብና ክልሉን ተጠቃሚ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ጀምረው እስከ ጐንደር ድረስ (ዓባይ ሸለቆና ዘንገናን ጨምሮ) የቱሪስቶች ማቆያ ለማድረግ አስበዋል ብለዋል:: ይህ ደግሞ የቱሪስቱን የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ስለሚያደርገው ገበያ የማግኘት እድል ሊኖር እንደሚችል ገልፀዋል:: አቶ ጌታቸው አያይዘውም በዘንገና ሐይቅ ዳርቻ ሎጂዎች መገንባታቸው የአካባቢው ነዋሪ እንደ ጭራ፣ ዋንጫ፣ የቀርቅሐ ውጤቶችንና ሌሎች የእደ ጥበብ ስራዎችን ለቱሪስቱ እየሸጠ ገቢ እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል:: ከዚህ በተጨማሪም የአካባቢው መልክዓምድር ለእይታ ሳቢ ስለሆነ ነዋሪውን በአካባቢያዊ ቱሪዝም እንዲሰማራ ማድረግ ይቻላል ብለዋል:: በሐይቁ አካባቢ የሚገነቡ ሎጂዎች አካባቢያዊ ተጽዕኖ እንዳይኖራቸውም የፍሳሽ እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገዳቸው በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንቷል ብለዋል:: ሆሄያት የተባለው ድርጅት የቱሪስቶችን ቆይታ ለማራዘም አዲስ አበባ፣ አባይ በረሐ፣ ዘንገና ሐይቅ፣ ባህር ዳርና ጐንደር ተመሳሳይ ሎጂዎችንና የእንግዳ ማረፊያ ቦታዎችን ለመገንባት ማቀዱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል:: ወንዶች ብቻ በመጫኛ ተጎትተው የሚወጡበት ደብር ማርያም ገዳም የሚገኝበት ተራራ ባሏቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የመስህብ ሀብቶች ልክ ከቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የበየዳ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ:: ከወረዳው ነዋሪዎች መካከል አቶ አበባው አስካል እንደተናገሩት ወረዳቸው በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶች የታደለ በዚህ ዓመት መጨረሻ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ሎጅ ገጽ - 5 “የልጅነት ሕልሜ መዝረፍ ነበር” አቶ አቡሀይ ውብሸት ተማሪና ተመራማሪ በሀብታችን እየተጠቀምን አይደለም - ኗሪዎች አብርሃም በዕውቀት ጌትነት ድልነሳ

Upload: lamkhuong

Post on 31-Jan-2017

440 views

Category:

Documents


20 download

TRANSCRIPT

በኩርመ ረ ጃ ለ ሁ ለን ተ ና ዊ ለ ው ጥ ና ል ዕ ል ና !

22ኛ ዓመት ቁጥር 17 መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ዕትም ዋጋ 2 ብር

“ኦዲቱ ኪራይ ሰብሳቢነትን ለመዋጋት በጽናት ይሰራል!!”

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት

ስልክ፡ 0582200634 ፋክስ፡ 0582201694

ፖ.ሣ.ቁ፡ 479/ባሕር ዳር

ወደ ገጽ 20 ዞሯል

በውስጥ ገፆች

ገጽ 7

ገጽ 40

- የግዮን ትሩፋት

- የቁልቁለት ጉዞገጽ 21

ገጽ 3

ገጽ 10

- የዓ ባይ ሸለቆ

ስልጣኔዎች

- ያለውን በቁጭት

- የውኃ ሽታ የሆነው ውኃ

ገጽ 18

- የ”ጃምቦ ወንዝ”

ዘንገናን ለቱሪዝም ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ነው

ሙሰኞች ከህግ አያመልጡም!

የአብክመ የሥነ-ምግባርና

የፀረ ሙስና ኮሚሽን

) Frequency- 27500 ) Symbol rate - 12341 ) FEC- 3/4 ) Polarization – hori-zontal መከታተል ይችላሉ፡፡

ስርጭቱን በናይል ሳት

የሆስፒታሉ ግንባታ መቋረጥ ችግር ሆኗል ፀጋዬ የሽዋስ

በደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የተጀመረው ሆስፒታል ግንባታው መቋረጡ ለበርካታ ችግሮች እየዳረጋቸው መሆኑን ተናገሩ::

የወረዳዋ ነዋሪ አቶ ጋሻው ዋለልኝ እንደገለፁት ሆስፒታሉ ይጠናቀቃል ከተባለበት ጊዜ መዘግየቱ ሳያንስ አሁን ደግሞ መቋረጡ ህብረተሰቡን ለተለያየ

ችግር እየዳረገው ነው:: ነዋሪዎች ወደ አቅስታ፣ መካነሰላምና ደሴ ሆስፒታሎች በመሄድ ህክምና ለማግኘት ሲሞክሩ እስከ ሞት የሚደርስ ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ገልፀዋል::

ወይዘሮ ጉዝጉዝ ገረመውም በቅርቡ ወደ አቅስታ አምርተው በህዳር 11 ሆስፒታል ሲገላገሉ በመንገድ ርቀት ሳቢያ በርካታ እንግልት እንዳስተናገዱ ገልፀዋል:: ከደጃቸው የተጀመረው ሆስፒታል ቢጠናቀቅ ኖሮ ከዚህ እንግልት መዳን ይችሉ እንደነበር ይገልፃሉ::

እናቶች ወደ ሆስፒታሎች ሳይደርሱ በመንገድ ለህልፈት እየተዳረጉ እንደሆነ የሚገልፁት ደግሞ የወግዲ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ፈንታው ናቸው:: የተጀመረው ሆስፒታል ቢጠናቀቅ የበርካታ እናቶችን ህይወት መታደግ ይቻል እንደነበርና የጤና ጣቢያውንም ጫና መቀነስ ያስችል እንደነበር ይገልፃሉ:: በጤና ጣቢያ የማይፈቀዱና በሆስፒታሉ ብቻ የሚገኙ መድሃኒቶችን ለማግኘትም ህብረተሰቡ እየተንገላታ ነው ይላሉ::

የሆስፒታሉን ግንባታ ሲቆጣጠሩ

የነበሩት የወረዳው የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሰራተኛ አቶ አወቀ ጫኔ ሆስፒታሉ በ2005 ዓ.ም በ33 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር እንዲገነባ ለተቋራጩ ሲሰጥ በ500 ቀናት ውስጥ ግንባታው እንደሚጠናቀቅ ነበር ውል የተያዘው:: ሆኖም ግን ግንባታው እስከተቋረጠበት ቀን ድረስ አንድ ሺህ ቀናትን ወስዷል:: በተቋራጩ በኩል መጠናቀቅ ያለባቸው ስራዎች ባለመጠናቀቃቸው ክፍያ እንዳይከፈል በመወሰኑ ግንባታው መቋረጡንም አስረድተዋል::

በአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የጤና መሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ ክንድይሁን እገዘው እንደገለፁት ግንባታውን ሌላ ተቋራጭ እንዲጨርሰው ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል:: ለልማት ድርጅት በመስጠት ድርድር ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ያቀረቡት ዋጋ የተጋነነ በመሆኑ ለግል ተቋራጮች ጨረታ

ለማውጣት ጥረት መጀመሩን ገልፀዋል::

(ሙሉ ዘገባውን በገጽ 4 ይመልከቱ)

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚገኘውን የዘንገና ሐይቅ ለጐብኝዎች ምቹ ለማድረግ ከ13 ሚሊዮን ብር በሚልቅ ወጪ ባለሐብቶች ሎጂዎችን እየገነቡ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ::

ከብሔረሰቡ መዲና እንጅባራ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የዘንገና ሐይቅ ለበርካታ አመታት በቱሪዝም ዘርፍ በቂ ገቢ ሳያስገኝ ቆይቷል:: ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት በሐይቁ ዳርቻ ለቱሪስቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሎጂዎች፣ ማረፊያ ቦታዎችና ሌሎች መዝናኛዎች ባለመሟላታቸው መሆኑን በመምሪያው የቱሪዝም ልማት ፕሮሞሽን ባለሙያ አቶ በሪሁን አጥናፉ ተናግረዋል:: በዚህ አመት ግን ሆህያትና ኢኤም

የተሰኙ ድርጅቶች በሐይቁ ዳርቻ በ13 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር ሎጂዎችንና ለቱሪስቶች ማረፊያ የሆኑ ግንባታዎችን በማፋጠን ላይ በመሆናቸው ዘንገና ሐይቅ ለዞኑ ገቢ ለማስገኘትና ለወጣቶችም የስራ እድል ለመፍጠር እየተቃረበ ነው ብለዋል፤ የሆህያት ሎጅ በዚህ አመት መጨረሻ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ በማስታወስ::

በዞኑ ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የልማታዊ ባለሐብት መሳብና መደገፍ የሰራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጌታቸው አያሌው በበኩላቸው በዘንገና ሐይቅ ላይ ሎጂዎችን እየገነቡ ያሉት ሁለቱ ድርጅቶች ቱሪስቱን የበለጠ ለመሳብና ክልሉን ተጠቃሚ ለማድረግ ከአዲስ አበባ ጀምረው እስከ ጐንደር ድረስ (ዓባይ ሸለቆና ዘንገናን ጨምሮ) የቱሪስቶች ማቆያ ለማድረግ አስበዋል

ብለዋል:: ይህ ደግሞ የቱሪስቱን የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ስለሚያደርገው ገበያ የማግኘት እድል ሊኖር እንደሚችል ገልፀዋል::

አቶ ጌታቸው አያይዘውም በዘንገና ሐይቅ ዳርቻ ሎጂዎች መገንባታቸው የአካባቢው ነዋሪ እንደ ጭራ፣ ዋንጫ፣ የቀርቅሐ ውጤቶችንና ሌሎች የእደ ጥበብ ስራዎችን ለቱሪስቱ እየሸጠ ገቢ እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል:: ከዚህ

በተጨማሪም የአካባቢው መልክዓምድር ለእይታ ሳቢ ስለሆነ ነዋሪውን በአካባቢያዊ ቱሪዝም እንዲሰማራ ማድረግ ይቻላል ብለዋል::

በሐይቁ አካባቢ የሚገነቡ ሎጂዎች አካባቢያዊ ተጽዕኖ እንዳይኖራቸውም የፍሳሽ እና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገዳቸው በሳይንሳዊ መንገድ ተጠንቷል ብለዋል::

ሆሄያት የተባለው ድርጅት የቱሪስቶችን ቆይታ ለማራዘም አዲስ አበባ፣ አባይ በረሐ፣ ዘንገና ሐይቅ፣ ባህር ዳርና ጐንደር ተመሳሳይ ሎጂዎችንና የእንግዳ ማረፊያ ቦታዎችን ለመገንባት ማቀዱን አቶ ጌታቸው ተናግረዋል::

ወንዶች ብቻ በመጫኛ ተጎትተው የሚወጡበት ደብር ማርያም ገዳም የሚገኝበት ተራራ

ባሏቸው የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ የመስህብ ሀብቶች ልክ ከቱሪዝም ገቢ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የበየዳ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ::

ከወረዳው ነዋሪዎች መካከል አቶ አበባው አስካል እንደተናገሩት ወረዳቸው በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ቅርሶች የታደለ

በዚህ ዓመት መጨረሻ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ሎጅ

ገጽ - 5

“የልጅነት ሕልሜ መዝረፍ ነበር”

አቶ አቡሀይ ውብሸትተማሪና ተመራማሪ

በሀብታችን እየተጠቀምን አይደለም - ኗሪዎች

አብርሃም በዕውቀት

ጌትነት ድልነሳ

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 2

ርዕሰ አንቀፅ

ይድረስ ለበኩር

በኩር

መ ረ ጃ ለ ሁ ለን ተ ና ዊ ለ ው ጥ ና ል ዕ ል ና !

ዋና አዘጋጅ፡- ጥላሁን ቸሬ ስልክ፡- 0918 70 60 08 E mail– [email protected]

ምክትል ዋና አዘጋጆች ፡- መዝናኛ አምዶች ፡- አብዮት ዓለም Email- [email protected] ትምህርታዊ አምዶች፡- ይህዓለም መለሰ

በኩር በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በየሳምንቱ የሚታተም የሰኞ ጋዜጣ

አዘጋጆች፡-

ጌታቸው ፈንቴ አባትሁን ዘገየ Emial [email protected] ጌትነት ድልነሳ [email protected] ሙሉ አብይ [email protected]

ህትመት ክትትልና ስርጭት፡- ደምሴ ሃሰን

አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ዋጋው አድማሱ አድራሻ ፡- አማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዋናው መ/ቤት - ባህር ዳር

ፖ ሳ.ቁ 955 ስ.ቁ /+251/ 058 226 50 18 E-mail [email protected] Web www.amma.gov.et

በጽሁፍ መልዕክት(sms) ab. በማስቀደም 8200

የማስታወቂያ አገልግሎት ፡ ስልክ ቁጥር 05 82 26 49 88 05 82 26 57 32 ፋክስ ቁጥር 05 82 20 47 52

[email protected] [email protected]አታሚ፡- ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

አዲስ አበባ

ታህሳስ 7 1987 ተመሰረተ

በአንድ ሀገር ወይም ከተማ ግንባታ ለማካሄድ ድርጅቶች /የስራ ተቋራጭ/ የግንባታ ቁሳቁስ የሚያስቀምጡበት ቦታ ማመቻቸት የግድ ይላል:: ይህን ታሳቢ በማድረግም የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ለቻይና መንገድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ቦታ አመቻችቶለታል፤ ይህ ይበል የሚያሰኝ ነው::

ችግሩ ግን ለቻይናው ኮንስትራክሽን ድርጅት የተሰጠው ቦታ ከመንታ መንገድ ፊት ለፊት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ቦታው በሊዝም ይሁን በምደባ ከፍተኛ የስራ እድል ለሚፈጥሩ ግለሰቦች መስጠት ነበረበት:: ይህ ችግር ህዝቡን እያንገበገበው እያለ የቻይናው መንገድ ኮንስትራክሽን ድርጅት የስራ ባልደረቦች በተለምዶ ቻይና ካምፕ በሚባለው ቦታ መኖሪያ ቤት ሰርተው የመኖራቸው ጉዳይ ነው::

ሰዎቹ የሚከታተላቸው አንድ የከተማ አስተዳደር ባለሙያ ባለመኖሩ የቤት ኪራይ ላለመክፈል መኖሪያ ቤታቸውን በካምፑ ውስጥ

ውድ በኩሮች ፁሁፋችሁን ሁሌም አነባለሁ:: ግን የታሪክና የጥበብ አምዳችሁ ውስጤን ይገዛዋል:: የራስ አሉላ ታሪክ፣ የአለማየሁ ቴዎድሮስ፣ ጥቁር አሞራ (2004/05) ዓ.ም በውስጠ ማህተሜ የተቀመጡ ናቸው:: ከጥበብ አምድም ብዙ የምጠቅሳቸው አሉ::

ነገር ግን ከመጽሃፍት ገጾች ላይ ድርሰትን መመልከት ላይ ትንሽ ደከም ብላችሁብኛልና ቢሻሻል!

ችሎቱ ከጐንጂ ነኝ

ርብ የመስኖ ግድብ ከአራት ዓመት በላይ ተጓቷል:: የሰራባ መስኖ ግድብም ተጓቷል:: የአዘዞ ጐርጐራ መንገድ ግንባታም ተጓቷል:: የባህር ዳር - አዴት ዘማ - ወንዝ - ሞጣ ፈለገ ብርሃን - ደጀን መንገድም ተጓቷል:: የእንጅባራ ዞናል ሆስፒታል ለረጅም ዓመት ተጓቷል:: የሐይቅ ሆስፒታል ተጓቷል:: ብዙ ብዙ ግንባታዎች ነገሮች ተጓተዋል::

ብዙ ግንባታዎች ከተቀመጠላቸው የማጠናቀቂያ ጊዜ በላይ እየተጓተቱ በህብረተሰቡም፣ በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይም ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ነው:: ለመሆኑ በአገራችን አንድ ግንባታ በታቀደበት ጊዜ የሚጠናቀቀው መቼ ነው? የሚለው እስከአሁን መልስ አላገኘም:: ከረጅም ዓመታት በፊት ለግንባታዎቹ መጓተት ሲጠቀሱ የነበሩ ምክንያቶችም ዛሬም ሳይለወጡ ሳይቀነሱ ይቀርባሉ::

የግንባታ ስራዎችን የማስተዳደር እና የመምራት አቅም ማነስ፣ የግንባታ እቃዎች አቅርቦት፣ የዲዛይን ክለሳ እና ጥራት ችግሮች ትላንትም የሚጠቀሱ ዛሬም ያልተሻሻሉ እንዲያውም ጐልተው የሚጠቀሱ ሰበቦች ሆነው ቀጥለዋል::

ከዚህ ባሻገር በስንት ስቃይ የተጠናቀቁትም ለግንባታ የወሰዱትን አመት ግማሽ እንኳን ሳያገለግሉ መሰነጣጠቅ፣ ቀለማቸው መልቀቅ መፈራረስ ይጀምራሉ:: እናስ ከዚህ ክፉ ልክፍት የምንወጣው መቼ ነው:: በእርግጥስ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ማጓተት ከአቅም ማነስ፣ ከግንባታ ቁሳቁስ አለመሟላት የሚመጣ ብቻ አይደለም:: ዋናው ችግር በአስተሳሰብ የሚመጣ እንጅ::

በእኛ እምነት ሁሉም መሰረተ ልማት የሚጓተተው፣ የጥራት ደረጃ ችግር የሚከሰተው በግንባታ ስራዎች ልምድ ማነስ፤ የተሟላ ቁሳቁስ አለማግኘት የሚለው ሙሉ በሙሉ አሳማኝ አይደለም:: ይልቁንም ሳይሰሩ፣ ሳይለፉ ሳይደክሙ 100 በመቶ አትራፊ ለመሆን ከሚመጣ ፍላጐትና ስግብግብነት የተነሳ ነው::

የሚገነባው መንገድ፣ የሚገነባው ሆስፒታል፣ የሚገነባው ግድብ ከራሱ እና ቤተሰቦቹ አልፎም መላ የአገሩን ህዝቦች የሚለውጥና ኑሯቸውን የሚያሻሽል መሆኑን ካለመገንዘብ የመጣ የሀሳብ ድህነት ነው:: በዚህች አገር ስንት ግንባታዎች ተከናወኑ ስንቶቹስ ተጠናቀቁ ስንል መልሱ የተለያየ ይሆናል:: መማር… የግንባታ ስራዎች ልምድ መቅሰም ካስፈለገ እነዚህ ትምህርት ቤቶች መሆን ነበረባቸው:: ዋናው ችግር ያለው እዚያ ላይ አይደለም የምንለውም ለዚሁ ነው::

ለመማር እና አቅሙን ለማሳደግ የፈለገ እኮ! ከትላንቱ ብቻ ሳይሆን ከዛሬው ብዙ ትምህርቶችን መውሰድ ይቻለዋል:: ይህ የሚሆነው ግን በሙሉ ፍላጐት ለአገር እና ለወገን ለመስራት ዝግጁ እና ቅንነት ሲኖር መሆኑን ልብ ሊባል ይገባዋል::

ትላንትም ለግንባታው መጓተትና ጥራት ችግር “የግንባታ ስራዎች ልምድ ማነስ … የግንባታ እቃዎች አለመሟላት ነው” የሚል ሰበብ መደርደር ነበር:: ዛሬም ይሄንኑ ሰበብ ለመደርደር አላፈርንም:: ታዲያ ከትላንት ችግር ልምድ የሚወሰደው… ቁሳቁስ የሚሟላውስ መቼ ይሆን?

የዛሬ 10 ዓመት ስንደረድረው የነበረውን ሰበብ ዛሬም ከጠቀስን ነገም በዚሁ መቀጠላችን አይቀርም:: እናም ለዚህ ነው በየቦታው ለሚጀመሩ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መጓተት ዋናው የአስተሳሰብ ድህነት ነው የምንለው:: ለራስ ብቻ በልቶ ማደር፣ ለህዝብና ለአገር ደንታ ካለመስጠት የመጣ አስተሳሰብ በመሆኑ የምናንደረድረው ሰበበ “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” መሆኑ ሊቆም ይገባል::

የአገር እና የህዝብ ሀብት በአስፈሪ የጥቅም ሰንሰለት በተያያዙ ማፍያ ቡድኖች እንዳልሆነ ሲሆን እንደተለመደ ተግባር መቁጠሩ በህዝብ ከመወቀስ አያድንም::

ለዚህ ደግሞ መንግስት ከፍተኛውን ድርሻ ሊወስድ ይገባል:: መንግስት ከህዝቡ ጐን ሆኖ ግንባታ የሚያጓትቱን… የጥራቱን ደረጃ እንደፈለጋቸው የሚወስኑትን … ከተቋራጭ እስከ የመንግስት አመራሩና ባለሙያው ድረስ ያለውን የጥቅም ገመድ መበጠስ ይገባዋል:: ሶስት እና አራት ግንባታዎችን ያከናውናል ተብሎ የተመደበው በጀት ለአንዱ ብቻ እየሆነ በአገሪቱ ምጣኔ ኃብት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በጣም ከፍተኛ ስለሚሆን አሁንም ገመዱ በደንብ መቆራረጥ ይገባዋል እንላለን! የማጓተትና የማቋረጥ መገለጫነት ምዕራፍም ሊዘጋ ይገባዋል!

ከፍተኛ ሪፖርተሮች፡- ታምራት ሲሳይ ፀጋዬ የሽዋስ [email protected] አዲሱ አያሌው አብርሃም አዳሙ አብርሃም በዕውቀት ሙሉጌታ ሙጨ

ደረጀ አምባውሱራፌል ስንታየሁ

ሪፖርተር፡-ጌትሽ ኃይሌ[email protected]

ፎቶ ሪፖርተር፡- ሰለሞን ሀዲስተባባሪ የካርቱን ባለሙያ፡- ብርሃኑ ክንዱ

የኮምፒዩተር ፅህፈት እና ግራፊክ ዲዛይነር፡- የኔሰው ማሩእመቤት አህመድአለምፀሐይ ሙሉደጊቱ አብዬ

ቢሻሻል!ለቦታ ሰጭው ማን

ይቀርባል?

ማጓተት እና ማቋረጥ መገለጫ

መሆናቸው ሊቆም ይገባል!

ሰርተው መኖር ከጀመሩ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው:: ይህ ደግሞ ዜጋው መኖሪያ ቤት አጥቶ እየተሰቃየ ባለበት ከተማ የውጭ ዜጋ የሆነ ሰው መኖሪያ ቤት ገንብቶ ሲኖር ከተማዋ ለዜጐቿ ወይስ ለውጮች የሚል ጥያቄ ያስነሳልና አንድ ቢባል እላለሁ:: ከመኖሪያ ቤት ኪራይስ የውጭ ምንዛሬ አይገኝም ያለው ማን ነው?

ከባህር ዳር ጣና ክፍለ ከተማ

ገጽ 3በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ኢኮኖሚና ልማትኢኮኖሚና ልማትኢኮኖሚና ልማት

ሱራፌል ስንታየሁ

ወደ ገጽ 40 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

ትሩፋትየግዮንየአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት

/አመልድ/ ከሁለት ሺህ አምስት መቶ በላይ በገጠር የሚኖሩ ቤተሰቦችን በአማራጭ የሀይል አቅርቦት ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ:: ድርጅቱ ከፓዎር አፍሪካ ባገኘው 2.5 ሚሊዮን ብር በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፉን በአመልድ የምዕራብ አማራ የተፈጥሮ ደን ጥበቃና ዘላቂ እንክብካቤ ኘሮጀክት ኃላፊ አቶ መኳንንት ዳኛው ተናግረዋል::

እንደ ኃላፊው ገለጻ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ የመጣውን የምዕራብ አማራ የተፈጥሮ ደን በዘላቂነት ለመጠበቅ እንዲያስችል አማራጭ የታዳሽ ሀይል በአርሶ አደሩ ቀየ እያቀረበ መሆኑን አስታውቀዋል::

በአለፋ ወረዳ የጣራ ኮዘን ብርጌ ጎጥ አርሶ አደር የሆኑት አቶ ይሰማው ዘመነ ላለፉት ስድስት ወራት ያለማቋረጥ ታዳሽ ሀይል መጠቀማቸውን ተናግረዋል:: አርሶ አደሩ ቀደም ሲል ለመብራት አገልግሎት ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ነዳጅ ይጠቀሙ የነበረውን ሙሉ በሙሉ አስቀርቶላቸዋል::

ባለቤታቸው ወይዘሮ የምክር ሞላ በበኩላቸው ታዳሽ ኃይሉ የዓይናቸው ጤና እንዲሻሻል ከማድረጉ በተጨማሪ የሚያባክኑትን ጉልበትና የሚያጠፉትን ጊዜ እንደቀነሰላቸው ተናግረዋል::

መረጃውን ያደረሰን የአመልድ የኮሙኒኬሽን ባለሙያ እሱባለው ድረስ ነው::

የገጠር መንገድ መስፋፋት ሁለገብ

አስተዋፆኦ እያበረከተ ነው

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር ዞን በ2008 በጀት ዓመት እየተገነቡ ያሉ መንገዶች እየተሰራ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለማህበራዊ ኑሮ መሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የአበርገሌ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ::

በተያዘው ዓመት በወረዳችን ከፍተኛ የመንገድ ማስፋፋት ስራ ተሰርቷል የሚሉት ነዋሪዎቹ ከተከዜ ሃይቅ የሚያስግሩትን አሳና የሰሊጥ ምርት ወደ ገበያ ለማድረስ እየረዳቸው መሆኑን አርሶ አደር ገሽይ ሃይለ ሚካኤል ተናግረዋል::

የመንገዱ መገንባት በወሊድ ወቅት የሚከሰተውን የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚሰራው ስራ ተጠቃሚ እንድንሆን ከማድረጉ ባሻገር የአጎራባች ወረዳዎች የገበያ ትስስር የተጠናከረ እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል አርሶ አደር ገሻይ ሃይለ ሚካኤል፡፡

የአበርገሌ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ኪሮስ እንዳሉት በአየር ንብረት መዛባት የተከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በመደበኛ የገጠር መንገድ ግንባታዎች ሃምሳ አራት ኪሎ ሜትር በህብረተሰቡ ትብብር እየተሰራ ነው::

አቶ ዋሊ ፈንታው የዋልታ ገጠር መንገድ ህብረት ስራ ማህበር አስተባባሪ በክልል መንግስት ድጋፍ የሚሰሩ ድልድይ እና ቀድመው ማለቅ የነበረባቸው ሌሎች ስራዎች ግን ባለመጀመራቸው የትራንስፖርት አገልግሎቱን የተሟላ እንዳይሆን ማድረጉን ገልፀዋል:: በበጀት ዓመቱ 1080 ኪሎ ሜትር መንገድ እየተገነባ መሆኑን ሪፖርተራችን ግርማ ተጫነ ዘግቧል::

አርሶ አደሮች የታዳሽ ሀይል ተጠቃሚ ሆኑየሠሞኑ የባህር ዳር ሙቀት ከወትሮው

የተለየ ሆኖብናል:: እኩለ ቀን ላይ በከተማዋ በእግር የሚንቀሳቀስ ሠው

‘ፀሀይዋ ዝቅ ብላለች እንዴ?’ ማለቱ አይቀርም:: እኔም እንደ ሌሎች ኗሪዎች ሙቀቱን እያማረርኩ የተከለከለ በመሰለው ሰዓት ወደ ቀበሌ 11 /አባይ ማዶ/ ጉዞ እያደረኩ ነው:: የማልቀርበት ጉዳይ አለኝና ድልድዩን እንደተሻገርኩ መቶ ሜትር ያህል ከተጓዝኩ በኋላ ወደ ግራ ታጥፌ መቶ ሃምሳ ሜትር ያህል ሄድኩ::

የአባይን ወንዝ ዳር ተከትሎ ጫካ ይታያል:: ወደ ውስጥ ዘልቄ ሥገባ ሥታቃጥለኝ የነበረችው ፀሀይ በዚህ ጫካ ውስጥ መግቢያ አጥታለች:: ንፁህ አየር፣ የተፈጥሮ ቅዝቃዜ፣ ፀጥታ የነገሠበት አካባቢ፣ በአዕዋፋት ዝማሬ የታጀበ ሆኖ አገኘሁት::

ይህንን ቦታ ጫካ ያሰኙት ግራርና ብሳና፣ ዋርካና ዋንዛ፣ ፅድና ባህር ዛፍ… አይደሉም:: የጊዬንን ውሃ እየጠጡ ያደጉ የአቦካዶ፣ የፓፓያ፣ የቡና፣ የጌሾ… ዛፎች እንጂ:: በዚህ የፍራፍሬ ዛፍ በነገሠበት ጫካ ውስጥ ሥገባ አርሶ አደር ወርቁ እንዳለ በአንደኛው የማንጐ ዛፍ ላይ ዘንቢል አንግተው ወጥተው በለቀማ ላይ እንዳሉ አገኘኋቸው:: ከማንጎው ዛፍ ላይ የደረሠውን ፍሬ እየቆረጡ ወደ ዘንቢላቸው ውስጥ ይጨምራሉ::

የሚበቃቸውን ያህል ማንጎ ከለቀሙ በኋላ ከዛፉ ላይ ወርደው እዚያው የማንጎውን ዛፍ ተደግፈን ቁጭ አልንና ሥለ አትክልትና ፍራፍሬ ልማታቸው ማውራት ጀመርን:: አርሶ አደር ወርቁ ከዛሬ ሃያ አመት በፊት ጀምረው ነው የተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች ማልማት የጀመሩት:: በ1987 ዓ.ም ሰላሳ እግር የማንጎ ችግኝ ተክለው መንከባከብ ያዙ::

ጎን ለጎን ደግሞ ከስልሳ እግር በላይ ቡና ተክለው በየጊዜው ከአባይ ወንዝ በጀሪካን ውሃ ተሸክመው እያጠጡ፣ እየኮተኮቱ ቦታውን ከቁጥቋጦ ወደ ፍራፍሬ ጫካነት ቀየሩት::

ከ1990ዎች መጀመሪያ ጀምሮ እነዚህን አትክልትና ፍራፍሬዎች ለቤት ፍጆታም፣ ለገበያ በማዋልም የድካማቸውን ዋጋ ማግኘት ጀመሩ:: ከጊዜ ወደ ጊዜም የማንጎ ምርቱ እየጨመረ ሂዷል:: እሳቸውም ሠላሳ እግር ብቻ የማንጎ ዛፍ እንዲኖራቸው አልፈለጉም:: ከአመታት በኋላ ተጨማሪ ሠላሳ እግር ማንጎ ተከሉና የጓሯቸውን የማንጎ ጫካነት ከፍ አደረጉት::

ከአንድ ሄክታር በላይ የሚሆነው መሬታቸውን በየጊዜው በአትክልትና ፍራፍሬ እየሸፈኑት ሄዱ:: ከማንጎና ከቡና ተክላቸው በተጨማሪ ፓፓየ፣ አቦካዶ፣ ዘይቱን፣ ጌሾ… በመትከል ከአባይ ወንዝ ውሃ በማመላለስ እያጠጡ፣ እየተንከባከቡ ማሳደግ ቻሉ:: የአትክልትና ፍራፍሬው ቁጥር በማሳቸው ላይ እያደገ ሲሄድ፤ የሚያገኙት ገቢም በየጊዜው በዚያው ልክ እያደገ መጣ::

ምንም እንኳ እሳቸው የዛሬ ሁለት አስርት አመታት አካባቢ በሁለት ዙር የተከሏቸው ስልሳ እግር የማንጎ ችግኞች ቢሆንም፤ በአሁኑ ጊዜ ከመቶ በላይ እግር የማንጎ ዛፎች በማሳቸው ውስጥ ይገኛሉ:: ፍሬው ከማሳው ላይ ሲወድቅ እዚያው አፈር እየለበሠ በራሱ ጊዜ እየተባዛ እንደሆነ አርሶ አደር ወርቁ አጫወቱኝ::

እነዚህን የማንጎ፣ የፖፖያ፣ የዘይቱንና… ችግኞች ተክለው እያሳደጉ ተጠቃሚ በመሆን ብቻ እጃቸውን አጣጥፈው መቀመጥ አልፈለጉም:: ይልቁንስ ከማሳቸው ላይ አነስተኛ መሬት በመቀነስ ቆፍረው፣ መደብ አደላድለው ድሮ ገዝተው የተከሉትን ችግኝ አሁን ራሳቸው እያፈሉ መሸጥ ጀመሩ::

የችግኝ ማፍያ ላስቲክ በመግዛት ባዘጋጁት መደብ ላይ ማንጎ፣ ፖፖያ፣ ቡና፣ ዘይቱን… እያፈሉ ከፍራፍሬ በተጨማሪ ፍል እየሸጡ ተጠቃሚ ሆነዋል:: አርሶ አደር ወርቁ በጀሪካን ከአባይ ወንዝ በማመላለስ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማታቸውን ቢጀምሩም በዚያው ግን አልቀጠሉም::

ከማንጎ፣ ከጌሾና ከቡና… ሽያጭ ካገኙት ገንዘብ ቀንሰው በ1995 ዓ.ም በዘጠኝ ሺህ ብር የውሃ መሳቢያ ጄኔሬተር በመግዛት ከአባይ ወንዝ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከጀሪካን ወደ ኘላስቲክ ቦይ ቀየሩት:: ከአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በሚያገኙት ገንዘብ ቤተሠቦቻቸውን በጥሩ ሁኔታ እንደሚመሩ፣ መኖሪያ ቤታቸውን እንዳደሱ አጫወቱኝ::

በየጊዜው ጌሾ፣ አቦካዶ፣ ማንጎ… ስለሚሸጡ ጥርት ያለውን አመታዊ ገቢ ለማወቅ እንደሚቸግራቸው የገለፁሉኝ አርሶ አደር ወርቁ “በትንሹ እስከ ሃምሳ ሺህ ብር ድረስ በአመት አላጣም” ይላሉ::

ወ/ሪት ማስተዋል ወርቁ የአርሶ አደር ወርቁ ልጅ ናት:: የአባቷን የከተማ ግብርና ልማት በተመለከተ “አባቴ ሁሌም ከአትክልትና ፍራፍሬው ልማት ጋር ተቆራኝቶ ነው የሚውል:: ሲቆፍር፣ ሲኮተኩት፣ ውሃ ሲያጠጣ፣… ነው የሚውለው:: የቤተሠባችን ህይወት የሚመራው አባታችን በሚያለማው አትክልትና ፍራፍሬ ነው:: ከዚህ በተጨማሪ አሁን የራሴን ሻይ ቤት ከፍቼ እየሠራሁ እገኛለሁ:: ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ አባቴ ስሪበት ብሎ በሠጠኝ ሰባ ሺህ ብር ካፒታል ነው፤ ይህ ብር የተገኘው ጠዋት እና ማታ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በግብርና ልማት ሠርቶ ባገኘው የድካሙ ዋጋ ነው” አለችኝ::

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

አርሶ አደር ወርቁ እንደለ

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 4 ዜና ትንታኔ

ፀጋዬ የሺዋስ

ወደ ገጽ 38 ዞሯል

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው የወግዲ ሆስፒታል በ2005 ዓ.ም ነበር

ግንባታው የተጀመረው:: ከመቶ ኪሎ ሜትሮች በላይ አቅስታ፣ መካነሰላምና ደሴ እየሄዱ የሚታከሙት የአካባቢው ነዋሪዎች ሆስፒታል ሊገነባላቸው እንደሆነ ሲሰሙ እጅግ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸው እንደነበር የአካባቢው ነዋሪ አቶ ጋሻው ዋለልኝ ያስታውሳሉ:: ግንባታው ሲጀመር የሚመረቅበትን ቀን በጉጉት መጠባበቅ የጀመሩት ነዋሪዎቹ የሆስፒታሉን የግንባታ ሂደትም በቅርብ ርቀት ይከታተሉ ነበር:: ሆስፒታሉ ግን እስከ 74 በመቶ ከተገነባ በኋላ መቀጠል አልቻለም:: ይህም ህብረተሰቡ በጤና ተቋም እጥረት ሳቢያ ያስተናግዳቸው የነበሩ ችግሮች እንዲቀጥሉ አደረገ::

አቶ ጋሻው እንደተናገሩት የተጀመረው ሆስፒታል ግንባታ በፍጥነት አለመጠናቀቁ ያስጨነቀው ነዋሪ ጭራሽ ሲቋረጥ መደናገጡንና ከፍ ያለ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን በርካታ ኪሎሜትሮችን እያቆራረጠ ለእንግልት፣ ለወጪና ለሞት መጋለጡን ይናገራሉ:: የግንባታው ተቋርጦ መቆየት ነዋሪዎችን ግራ እንዳጋባና ለምን እንደዘገዬ የህዝቡ የመረረ ጥያቄ እንደሆነ ነው የሚናገሩት::

ወ/ሮ ጉዝጉዝ ገረመው በወግዲ ወረዳ የሚኖሩና ሆስፒታሉ ባለመጠናቀቁ ምክንያት ከሚኖሩበት ከ100 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው በአቅስታ ሆስፒታል በቅርቡ የወለዱ እናት ናቸው:: ነፍሰጡር ሆኖ ረዥም መንገድ ተጉዞ መውለድ እንግልቱ ከባድ መሆኑን አውስተዋል:: አጠገባቸው ላይ የተጀመረው

ሆስፒታል ቢገነባ ኑሮ የቤተሰባቸውን ድካምና ጭንቀት የሳቸውንም እንግልት ማስቀረት ይቻል እንደነበር ነው የሚገልፁት:: ይህ ሆስፒታል ተጠናቆ ማየትና በመንደራቸው መታከም ትልቅ ምኞታቸው መሆኑን ይናገራሉ::

ግንባታውን እንደሚመለከተው አካልም እንደ አካባቢው ነዋሪም ከመሰረቱ ጀምሮ ሲከታተሉ እንደነበር የሚናገሩት አቶ ይማም ሙህዬ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሰራተኛ ናቸው::

የአካባቢው ህብረተሰብም ወደ ደሴ፣ መካነሰላምና አቅስታ ከተሞች ለህክምና ሲጓዝ ለከፍተኛ እንግልት እየተዳረገ መሆኑን እንደሌሎች ሁሉ እርሳቸውም ታዝበዋል:: አንዲት ነፍሰጡር እናት ወደ መካነ ሰላም ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላት በመጓዝ ላይ እንዳለች

ህፃኑ ታፍኖ መሞቱን እንደሚያስታውሱና ይህም ሆስፒታሉ ባለመጠናቀቁ የተከሰተ ችግር መሆኑን ይገልፃሉ:: በገንዘብ እጦት ምክንያትም ወደነዚህ አካባቢዎች ሄደው መታከም የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በሆስፒታሉ አለመጠናቀቅ ሳቢያ ተጎጂ እንደሆኑ ይጠቁማሉ:: የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስም በወረዳው ዓቅም የሚቻል ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል በቶሎ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ይላሉ::

የወግዲ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ጥጋቡ ፈንታውም የሆስፒታሉ አለመጠናቀቅ በስራቸው ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ይገልፃሉ:: የአካባቢውን ህዝብ ቁጥር ከግምት በማስገባት ሆስፒታል እንዲሰራ የክልሉ መንግስት ቢፈቅድም በሚፈለገው ጊዜ ካለመጠናቀቁ ባለፈ ግንባታው በመቋረጡ ጤና ጣቢው ላይ ያለውን ጫና መቀነስ እንዳላስቻለና የታካሚው

የሆስፒታሉ ግንባታ መቋረጥ

ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መቸገራቸውን ይናገራሉ:: ጤና ጣቢያው በመከላከሉ ተግባር ላይ መስራት የሚጠበቅበት ቢሆንም በጫና ሳቢያ አለመስራቱን ገልፀዋል:: ከጤና ጣቢው አቅም በላይ የሆኑ ህሙማን ሲኖሩ መካነሰላም፣ አቅስታና ደሴ ሆስፒታሎች ሪፈር በሚጽፉበት ጊዜ ታካሚዎቹ በመንገድ የሚሞቱበት አጋጣሚ እንዳለ ነው የሚናገሩት::

አንዲት እናት ወደ አቅስታ ሆስፒታል ሪፈር ከተፃፈላት በኋላ እንደገና ወደ ደሴ ሪፈር ተጽፎላት በመንገድ ማረፏንም ያስታውሳሉ፤ ይህም ሆስፒታሉ ስራ ባለመጀመሩ ሳቢያ የተፈጠረ ክፍተት መሆኑን ያስረዳሉ:: በጤና ጣቢያ እንዲገኙ የማይፈቀዱና በሆስፒታል ደረጃ ብቻ የሚቀርቡ መድሀኒቶችን ጤና ጣቢያው ማቅረብ አለመቻሉም ህብረተሰቡን ለእንግልት እየዳረገው ነው::

የሆስፒታሉ ግንባታ መቋረጥ የህብረተሰቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መሆኑን የሚናገሩት ደግሞ የወግዲ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አዳነ ዋልተንጉስ ናቸው:: “አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም!” እየተባለ ቢሆንም በሆስፒታሉ አለመጠናቀቅ ሳቢያ እናቶች ለተለያየ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ይናገራሉ::

የወረዳው አምቡላንሶች ቁጥር ሁለት ብቻ ቢሆንም በቀን አምስትና ከዚያ በላይ እናቶች ሪፈር በሚባሉበት ጊዜ ሁለቱ አምቡላንሶች እየተመላለሱ አገልግሎት ለመስጠት ቢሞክሩም ትልቅ ክፍተት እየተፈጠረ መሆኑንም ያብራራሉ:: የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ችግሩን በመገንዘብ ግንባታው በአፋጣኝ የሚጠናቀቅበትን ስልት ሊቀይስ ይገባል ይላሉ::

ህብረተሰቡን ለችግር ዳርጎታል

በ500 ቀን ግንባታው ይጠናቀቃል የተባለው ሆስፒታል ከ1 ሺህ 200 ቀን በላይ ቢያስቆጥርም አሁንም ገና 74 በመቶ ላይ ነው

ገጽ 5በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እንግዳችን

ወደ ገጽ 26 ዞሯል

አብርሃም በዕውቀት

አቶ አቡሀይ ውብሸት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ተማሪና ተመራማሪ

“የልጅነት ሕልሜ መዝረፍ ነበር”

አቡሀይ ውብሸት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ተማሪና ተመራማሪ ነው:: ከዚህ ቀደም በኬሚስትሪ የትምህርት ዘርፍ በዲፕሎማ ደረጃ በመምህርነት ተመርቆ በጃናሞራ ወረዳ አስተምሯል:: በአስተማሪነት እየሠራ በግሉ በሠራቸው ሙከራዎች ከተለያዩ ነገሮች ነዳጅ ማምረት ችሏል፤ በዚህም የባለቤትነት መብት ጭምር አግኝቷል:: አሁንም በፈጠራው ላይ ተጨማሪ ምርምሮችን እያካሄደ ይገኛል:: የበኩር እንግዳችን ሆኖ ተሞክሮውን ሊያካፍለን ፈቅዷልና መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ ተመኘሁ::

ነዳጅ ለማምረት መነሻ ምክንያትህ ምንድን ነው?

ትውልድና ዕድገቴ ሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ ነው:: ከአንደኛ ክፍል እስከ መሰናዶ ድረስ የተማርኩትም እዚያው ጃናሞራ መካነ ብርሃን ነው:: በኋላም በኬሚስትሪ ዲፕሎማ ተመርቄ በአስተማሪነት በዚያው በመካነ ብርሃን ተቀጥሬ አገለግል ነበር:: በዚያን ጊዜ በአካባቢው ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ኃይል አልነበረም:: ለብርሃን ምንጭነት የሚያገለግለው ኩራዝ ሲሆን ነጭ ጋዝ ደግሞ በሊትር እስከ 20 ብር ድረስ ይሸጥ ነበር:: እና ይህንን ችግር የሆነ አማራጭ ፈልጌ መፍታት እንዳለብኝ አሰብኩ::

አነሳሴ ነዳጅ መሥራት ሳይሆን ቢያንስ በባዮ ጋዝም ቢሆን ሠርቼ የራሴንና የጓደኞቼን ችግር መፍታት ነበር ምኞቴ:: በወቅቱ ነጭ ጋዝ መግዣ

ብቻ ሳይሆን ነጭ ጋዝ የሚሸጠውም በአብዛኛው ደባርቅ ስለሆነ ለማምጣት እንቸገር ነበር:: በክፍል ውስጥ ሳስተምር ደግሞ በተደጋጋሚ ሙከራዎችን የመሥራት ዝንባሌ ስለነበረኝና ሙከራዎቼም ስኬታማ ስለነበሩ በዚህ የተነሳ ነጭ ጋዝን የሚተካ ነገር መስራት እንደምችል እምነት አደረብኝ::

ምርምሩን ለመጀመር እንደ መነሻ የሆነህ ንድፈ-ሀሳብ (ቲዮሪ) ነበር?

አዎ! በርካታ የኬሚስትሪ ንድፈ ሀሳቦች አሉ፤ የኬሚስትሪ መጻሕፍትን አነባለሁ፤ በተለይ ካርቦናማ (ኦርጋኒክ) ኬሚስትሪን በሚመለከት የተጻፉ መጻሕፍት በጣም ጠቅመውኛል:: “ኃይድሮካርቦን” የሚባለውን የካርቦናማ ኬሚስትሪ ክፍል ሳነብ ነዳጅ እንዴት በተፈጥሯዊ ሁኔታ እንደሚመረት በሚገባ ተረዳሁት:: በኃይድሮካርቦን ንድፈ ሀሳብ መሠረት ነዳጅ በተፈጥሯዊ መንገድ የሚፈጠረው ሚሊዮን ዓመታትን የእፅዋትና እንስሳት ቅሪተ አካላት በከፍተኛ ኃይል በመሬት ውስጥ በመታመቃቸው ነው::

እኔም ለመጀመሪያ ጊዜ ከዕፅዋት ቅሪተ አካላት ነዳጅ ለማምረት ነበር የሞከርኩት:: ሙከራውም በመጠኑ የተሻለና የተሳካ ነበር::

በመጀመሪያ ነዳጅ ለማምረት የሞከርከው ከምን ነበር?

የመጀመሪያ ሙከራዬ ከበቆሎ ነበር፤ በቆሎን የመረጥኩት ከራሴ ምልከታ ተነስቼ ነው:: ከበቆሎ የሚዘጋጅ ጠላ ለቀናት በተለይም ከ10 ቀን በላይ ሲሰነብት እፍግታው እየቀነሰና ከውኃው በላይ እየተንሳፈፈ ሲጠል የነጭ ጋዝ ባሕሪን ሲያሳይ ትመለከታለህ:: ያንን የሚንሳፈፈውን ፈሳሽ ስትለኩሰውም ከላይ ይቀጣጠላል:: ከዚህ በመነሳት የነዳጅነት ባሕርይ እንዳለው ግምት ወስጀ ነው ወደ ሙከራ የገባሁት::

በነገራችን ላይ ከዶሮ ኩስም ነዳጅ አምርቻለሁ:: ለዚህም እንደ መነሻ የወሰድኩት የራሴን ምልከታ ነው:: ቤንዚን እና ሌሎችም ነዳጆች የመትነን ባሕርይ አላቸው፤ ሲተኑ የምታየው የራሱ የሆነ ቀለም አለ:: ዶሮ ወዲያውኑ ስትኮሳም ኩሱ ላይ የሚነሳ ትነት አለ፤ ጠረን ያለው ትነት ነው የሚታዬው:: ይህ የሚተን ነገር ነው ከዶሮ ኩስ ነዳጅ ማምረት እንደሚቻል ያስገነዘበኝ፡፡ ከዚህ ተነስቼ ከዶሮ ኩስ ነዳጅ ማምረት እንደሚቻል ገመትኩና ሞከርኩት፤ ተሳካልኝ::

ቡናንም ሞክሬዋለሁ፤ ቡና ሲቆላና ከእሳቱ ሲወርድ ከምጣድ ላይ እንዳለ የሚያሳየው እንፋሎት መሰል ጭስ ከነዳጅ ትነት ጋር ይመሳሰላል::

የቡናው ቅባት መሬት ላይ ፈስሶ ሲታይም ነዳጅ ከፈሰሰበት መሬት ጋር ስለተመሳሰለብኝ ሞከርኩት:: ከሙከራዬም ነዳጅ ማምረት እንደሚቻል አረጋግጫለሁ:: ነዳጅ ሊመረትባቸው ይችላል ብዬ ከጠረጠርኳቸውና ከሞከርኳቸው ነዳጅ ያላገኘሁበት ገብስ ብቻ ነው:: በእርግጥ ገብስ ከመጀመሪያውም የነዳጅነት ባሕርይ የሚያሳይ አልነበረም::

ከዶቤ (በደጋ አካባቢ ከሚገኝ ጥቁር

የጓሳ) አፈር ነዳጅ ይገኛል ብለህ እንዴት አሰብክ?

አንደኛው ምክንያት በቆሎና ሌሎችም ሰብሎች ዋጋቸው እየጨመረ በመሄዱ በዚያው ልክ የነዳጁ ዋጋም እየጨመረ ስለሚሄድ አዋጭ አለመሆኑን መረዳቴ ነው:: ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ሌላኛው መነሻዬ የአካባቢው ችግርና ልማድ ነው:: እንደነገርኩህ ጃናሞራ አካባቢ የመብራት ችግር በሰፊው አለ፤ ምንም እንኳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተማው መብራት ማግኘት የጀመረ ቢሆንም:: ከችግሩ መኖር ባሻገር ደግሞ በተለይ ወደ ደጋው አካባቢ ያሉት ነዋሪዎች “ዶቤ” የሚባለውን ጥቁር አፈር እንደ ኩበት እየቆሰቆሱ ያነዱታል:: በተለይ ጃናሞራ፣ ደባርቅና በየዳ ደጋማው አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ዶቤ አፈርን ለማገዶ በስፋት ይጠቀማሉ:: ይህንን ስመለከት አፈሩ የነዳጅነት ባሕርይ እንዳለው ተገነዘብኩ::

በዚህ መሠረት ተደጋጋሚ ነዳጅ የማምረት ሙከራዎችን ሠራሁ:: ከ18 ያልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ በመልኩ ነጭ ጋዝ የሚባለውን ነዳጅ የሚመስል የሚቀጣጠል ነገር አመረትኩ:: ትክክለኛ ነዳጅ ግን አልነበረም:: ነገር ግን ማምረቻ ማሽኑ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠይቅ ስለነበረ ዞሮ ዞሮ ከኤሌክትሪክ ጥገኝነት አልወጣሁም:: ያም ሆኖ ምርምሬን ቀጥዬ ከመሬት ውስጥ ጉድጓድ ቆፍሬ ማሽኑን በእመቃ ኃይል በማሠራት ነዳጅ የማምረት ሥራ ጀመርኩ:: በ16 ቀን ከሦስት እስከ አራት ሊትር ነዳጅ መሰል ነገር ማምረት ቻልኩ:: የጉድጓዱ ጥልቀት በጨመረ ቁጥር የሚወጣው ነዳጅ መጠንም ይጨምራል::

ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ውጤትህን ይዘህ እንዴት መጣህ?

መጀመሪያ ላይ ከበቆሎና ከዶሮ ኩስ የማመርተውን ነዳጅ መሠል ነገር ለቡታጋዝና ኩራዝ ተጠቃሚዎች መካነ ብርሃን ውስጥ በሊትር ስድስት ብር እሸጥ ነበር:: ከዚያ ትክክለኛ ነዳጅ ለነዋሪዎቹ ይሸጥ የነበረው ነጋዴ ገበያ ስሻማው ቅሬታ አደረበት::

ከ18 ያልተሳኩ ሙከራዎች በኋላ በመልኩ ነጭ ጋዝ የሚባለውን ነዳጅ

የሚመስል የሚቀጣጠል ነገር

አመረትኩ:: ትክክለኛ ነዳጅ ግን አልነበረም:: ነገር ግን ማምረቻ ማሽኑ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠይቅ ስለነበረ

ዞሮ ዞሮ ከኤሌክትሪክ ጥገኝነት

አልወጣሁም::

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 6 መዝናኛ ቅምሻደረጀ አምባው

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በእጥፍ ዓይናቸውን ያርገበግባሉ::

ኩላሊታችን አንድ ነጥብ ሶስት ሊትር ደም ያጣራል:: በየቀኑ አንድ ነጥብ አራት ሊትር ሽንት ከሰውነታችን ያስወጣል::

ደማችን ከውሃ ስድስት እጅ ይወፍራል::

አንጎላችን ክፍል 80 በመቶው ውሃ እንደሆነ ያውቃሉ?

ከአካላችን ውስጥ ካሉት ክፍሎች ጠንካራ ጡንቻ ያለው ምላስ ነው::

ከቀን ይልቅ የበለጠ ማሰብ የምንችለው በምሽት ነው::

5ቱ በዓለማችን በወታደራዊ ታሪክ ወንጀለኛ ተብለው ታድነው የተገደሉ ሰዎች

ጥያቄና መልስ

የ15ኛ ሳምንት ጥያቄ መላሾች ቴዎድሮስ ማሩ ከደብረታቦር ሶስት ጥያቄ፣

ምናለ ሰውየው፣ ይላቅ ስንሻው፣ በለጠ መዝገቡ ሶስቱም ከሰከላ ግሽዓባይ እንዲሁም ዝነኛው ሻምበል ከብራቃት፣ ጥላሁን ባይህ ከፍኖተሰላም እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ጥያቄዎችን መልሰዋል:: እናመሰግናለን፣ በተሳትፏችሁ ግፉበት::

የ17ኛ ሣምንት ጥያቄ1. በአምስተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ

የአማራ ክልል በኦሎምፒክ ስፖርት ስንት ሜዳሊያ በማግኘት አጠናቀቀ (ወርቅ፣ ብር፣ ነሐስ)?

2. የዚካ ቫይረስን አስተላላፊ ትንኝ ማን ትባላለች?

3. በፍል ውሃ አቅራቢያ በዘመናዊ መልክ አዲስ የተሰራው ኢዮቤልዩ (በአሁኑ አጠራር ብሔራዊ) ቤተ መንግስት መቼ ተመረቀ?ጥያቄ መላሾች 0918 70 60 08 ስልክ ቁጥርን ተጠቀሙ

የ15ኛ ሣምንት ጥያቄ

1. የኢትጵያ ህዋ ሳይንስ ማህበር የምርምር ፕሮጀክቱን በቅርቡ ለአራት የሃገራችን ዩኒቨርሲቲዎች አስረክቧል:: እነማን ናቸው?

2. የእስራኤል የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስቴር ማን ናቸው?

3. የመጀመሪያው የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታ መቸና የት ተካሄደ?

የ15ኛ ሳምንት ጥያቄ መልስ

1. ባህርዳር፣ ወልዲያ፣ ጐንደር፣ መቀሌ ዩኒቨርሲቲዎች ናቸው፡፡

2. ጎልድ ሜይር - በ1961 ዓ.ም

3. ከመጋቢት 2 እስከ 16/1999 ዓ.ም አዲስ አበባ

1. ኦሳማ ቢን ላደን

የሩሲያ ድንበር ጠባቂዎች ድንበራቸውን በአስተማማኝ ለመጠበቅ የሚያስችል አጋጣሚ ተፈጥሮላቸዋል:: ቮልኮሶቢ የተባለው ከፍተኛ ስልጡን የተኩላ ዝርያ ያለው ውሻ ደግሞ ለዚሁ ተግባር ተዘጋጅቷል:: ኢሮፔሲስ በድረ ገጹ እንደዘገባው ቮልኮሶቢ የተኩላን ቁመትና ጥንካሬ የያዘ ነው:: ሰዎች

ባህሪ በመጋራት የሩሲያ ወታደራዊ ተቋም አባላት ሆኑ:: በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑት እነዚህ ውሾች ከሁለት ሺህ እሰከ ሶሰት ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያወጣሉ:: ከነዚህ ልዩ ዝርያዎች የሚገኘውን ጥቅም ብቻቸውን ማግኘት የፈለጉት የሩሲያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ግን መሸጥን አግደዋል::

እነዚህ ውሾች በመጀመሪያ የሰለጠኑት ተቀጣጣይ ነገሮችን እንዲለዩ፣ ያልተቀረጡ እቃዎችን እንዲይዙ እና በወንጀለኞች ዙሪያ የሚደረጉ የማነፍነፍ ስራን እንዲያከናውኑ ነበር:: ስልጠናው በሚሰጥበት ጊዜም ስራቸውን በፍቅር መስራታቸው ለአሰልጣኞች ቀና ሆኖላቸዋል::

የመንገድ ላይ ትምህርት ቤት

ላለፉት 15 ዓመታት ያህል የፋብሪካ ባለቤት የሆኑት ከማል ፓርማር ማንበብና መጻፍ የማይችሉ ህጻናትን ከትምህርት ሰዓት በኋላ መሰረታዊ ትምህርት በመስጠት ለትምህርት ቤት ፈተና ማዘጋጀታቸው የሰሞኑ አነጋጋሪ ወሬ መሆኑን የኦዲቲ ሴንትራል ድረ-ገጽ አስነብቧል::

ድንበር ጠባቂ ውሾች

የፓርማር ታሪክ የሚጀምረው ከ15 ዓመት በፊት አንድ ቀን ከሰዓት በኋላ ነው:: ከብረታብረት ፋብሪካው አካባቢ ቆመው እያለ በአጠገባቸው የሚያልፉ ህፃናት ስለ መጨረሻው ፈተና ሲነጋገሩ ሰሙ:: በአካባቢው ካለው የመንግስት ትምህርት

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

በፈረንጆች ብልህ ከሚባሉና “ከኋላ ሆነው የፊታቸውን የሚመሩ” ከሚሏቸው ሰዎች ይመድቡታል:: የማይጨበጥ የአመጻ መሪነቱም ብዙዎችን ያስደነቀ ነው:: ኦሳማ ቢላደን በ1957 ከየመኑ የህንፃ ስራ ከበርቴ ሼክ መሀመድ ቢን አውድ ቢን ላደን 17ኛ ልጅ ሆኖ ተወለደ:: የህይወት ታሪኩ እንደሚለው እስልምናን ሙሉ በሙሉ የተቀበለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበረበት ወቅት ነው:: ከዚህ በኋላ ፂሙን ማሳደግ ጀመረ:: የኦሳማን ህይወት እንዲህ የለወጠው ከሙስሊም ወንድማማቾች ጋር የፈጠረው ቁርኝት ነው::

ጽንፈኛውን አልቃይዳን በመምራት ምዕራባውያንና አሜሪካን ሲያስጨንቅ የኖረው፤ በዓለም መንግስታት በወታደራዊ ወንጀለኝነት የተፈረጀውን ኦሳማን ለመያዝ የተደረገው ሙከራ በመጨረሻ ውጤት አገኘ:: በፓኪስታን ውስጥ በነበረው ድብቅ መኖሪያ ቤት በአሜሪካ የባህር ኃይል ከኮማንዶዎች ሚያዚያ 2003 ዓ.ም ለመገደል በቅቷል::

2. ኤርኔስቶ ቼጉቬየራ

አርጀንቲናዊው ኤርኔስቶ ቼጉቬየራ በትምህርቱም ሆነ በሙያው ሐኪም ቢሆንም ዓለም በብዙ የሚያውቀው በግራ ክንፈኛ ተዋጊነቱ ነው:: ሰኔ 1920 ዓ.ም የተወለደው ቼጉቬየራ የቤተሰብ መሰረቱም ሲበዛ ለድሆች፣ ለተገፉና ለተጨቆኑ ተቆርቋሪ ነው:: ቼጉቬራ በብዙ የላቲን አሜሪካ አገራት ተዛውሯል:: በዘመኑ በየአገሩ መንግስታት ጭቆና የሚፈፀምባቸውን የተገፉ፣ ፍትህ የራቃቸውና የተበደሉትን ዜጐች በቅርበት ለማየትም አስችሎታል::

በሜክሲኮ በሙያው እየሰራና በዩኒቨርሲቲ እያሰተማረ በነበረበት ወቅት ከኩባውያኑ ወንድማማቾች ራውልና ፊደል ካስትሮ ጋር ተዋወቀ:: ከሁለቱ ወንድማማቾች ጋር በመሆንም የጀኔራል ባቲስታን ጨቋኝ አስተዳደር ከኩባ ሲያስወግዱ ቼጉቬየራ አብሮ ተዋግቷል:: ከኩባ አብዮት በኋላ ለነፃነት የሚታገሉ ፋኖዎችንም ረድቷል::

ቦሊቪያ ውስጥ እንደ ወንበዴ ይቆጥሩት የነበሩ የዓለም ተፃራሪዎቹ፤ ከአሜሪካ ልዩ ኃይል ባገኙት ልምምድ ሊማርኩት ችለዋል:: ከተያዘ በኋላም

በአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት ቦሊቪያ ውስጥ በጥቅምት 1960 ዓ.ም ተገደለ:: የዓላማ ተፃራሪዎች እንደሽፍታ የሚቆጥሩት ቼጉቬየራ፣ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የነፃነት ተዋጊና ዓለም አቀፍ አርበኛ ተደርጐ ይቆጠራል::

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

ደግሞ ለሰው ልጅ ታዛዥና ወዳጃዊ አመለካከት እንዲኖረው አድርገው ቀርፀውታል:: የዚህን ውሻ ዝርያ ለማግኘት በርካታ ዓመታት ያሳለፉት ሩሲያውያን ከ200 በላይ የተኩላ ዝርያን በማዳቀል ምርምር አድርገው አልተሳካላቸውም ነበር::

እነዚህ የእንስሳት ባለሙያዎች በመጨረሻ በ2000 (እ.ኤ.አ) አንድ ግኝት አገኙ:: ይህንን ስኬታቸውንም “ናይዳ” በማለት ሰየሙት:: የካስፔያን ባህር ተኩላ የሆነችው ይህች ግኝት ከሰዎች ጋር ታላቅ መግባባትን የፈጠረች ነበረች::

በምርምሩ ወቅት ተኩላዋ ከውሻ ጋር ተዳቅላለች:: በ10 ዓመታት ውስጥ ‘ናይዳ’ 40 ያህል የተኩላ ውሾችን ማፍራት ችላለች:: የተገኙት ዝርያዎችም የአባታቸውን ታዛዥነት እና የእናታቸውን የተኩላነት

ገጽ 7በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ትዝብትትዝብት

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

አብዮት ዓለም

አገር እየጠጣች ነው! ብል “አታጋነው ባክህ” አትበሉኝ:: እኔ አገር እና ህዝብ እየጠጡ ናቸው እላለሁ:: እናም ምንም

ግነት የለበትም ባይነኝ:: ካላመናችሁ ትላልቅ ከተሞቻችንን ተዋቸው እና ትንሾቹን ተመልከቱ:: የንግድ ሀሣቡ ሁሉ ሂዶ የሚያርፈው ወይ ድራፍት ቤት መክፈት ነው! ወይ ደግሞ ቡና ቤት ከፍ ሲል ደግሞ ዊስኪ መጠጫ ጐሮኖዎች መክፈት ነው … ከዚህ ያለፈ የሚያስቡት ከመጠጥ ቤት ጋር ሲነፃፀር ጥቂት ናቸው::

እስኪ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ በሙሉ ዓለም የባህል ማዕከል ፊት ለፊት ጐራ በሉ:: ህዝብ ምን እያደረገ እንደሆነ ግልጥልጥ ብሎ ይታያችኋል:: እዚህ አካባቢ አልኮል ሲመሽ ነው የሚለው ቀርቷል:: ገና በማለዳው የድራፍት ብርጭቆዎች “ለጤናችን! ለደስታችን/ችርሥ/! በሚሉ ግጭቶች ድምፅ ሁከት መፍጠር ይጀምራሉ::

ድሮ ቀረ የምትለዋ አባባል በደንብ የሠራችው በመጠጥ ሰዓት መጀመሪያ ላይ ነው:: እኔ ሳውቀው በፊት ከማለዳው አንድ ሰዓት መጠጥ ቤት መገኘት ሲሰርቁ ከመያዝ እኩል ነበር:: ዛሬ ግን ከማለዳው 12፡ዐዐ ሠዓት መጠጥ ቤቶች ይጥለቀለቃሉ:: ደግሞ የሚገርመው በዚህ ሰዓት የሚመጡት ጃምቦኛዎች ገና ወጣቶችና ከ30ዎቹ እና 40 ዎቹ የመጀመሪያ ዕድሜ አካባቢ የሚገኙት መብዛታቸው ነው:: ወሳኝ የትውልድ ምዕራፍ ላይ የሚገኙ ብለን ልንወሰዳቸው እንችላለን፤ የሚገርመው ፆም ባልሆነ ቀን የሚታዬው ትዕይንትም በሰውና በአንበሳ መካከል ያለውን አመጋገብ ለመለየት ያስቸግራል:: በተለይ በወር የመንግሥት ደሞዝ ጠብቆ ለሚኖር ሰው ድርጊቱ “እየኖርኩ ነው?” ያሰኛል::

በእነዚህ ቦታዎች ብር እንደ ቅጠል ይበተናል:: ቁርጥ ሥጋ እንደ ቆሎ የሚዘገንበት፤ ድራፍት የውሃ ያህል ቁብ የማይሠጠው ሆኖ ይታዘባሉ:: እናም የገንዘቡ የት መጣነት በምን ጊዜያቸው ሰርተው ነው? ሳይሰሩ ቁጭ ብለው እንደዚህ ለቁርጥ ሥጋና ለድራፍት እቅፍ ብር መድፋት እንዴት ይቻላል? የሚለው ሀሣብ ይመጣብዎትና ምስኪን የመንግሥት ሰራተኛ ከሆኑ በዚህ አካባቢ ድርሽ ላለማለት ይወሥናሉ:: በቃ የበታችነት… ሆድ የመባስ ስሜት ስለሚሰማዎትና የኪሥዎትን አቅመ ቢስነት ሥለሚያሥታውሥዎ ወደ እነዚህ አካባቢዎች ብቅ ላለማለት ይገደዳሉ:: ከቻሉ መጠጥ እርም ይላሉ፤ ካልቻሉ የጣሳ ችካልና በሰባራ ጭልፋ የሚሰፈር በቆልት ያማትራሉ::

ወን

ዝ” አስተዋይ ካለ በየአካባቢው ቀኑን ሙሉ ድራፍት ሲጋቱ የሚውሉት ሰዎች የገንዘብ ምንጫቸው ሊጣራ ይገባል! ሊፈተሽ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ይገነዘባል:: እኔ በበኩሌ ጤነኛ አይመሥለኝም:: ቀኑን ሙሉ ድራፍት ሲያንደቀድቁ… ጮማ ሥጋ ሲዘነጥሉ እየዋሉ…በሥልክ ብቻ ሥለ “ቢዝነስ” ሲነጋገሩ እየዋሉ እንዴት እንዲህ ዓይነት የገንዘብ ባለቤቶች ሊሆኑ ይችላሉ:: ፍትሀዊነት እየጐደለው ነው:: ይጠቅማል፣ ህዝቤን ይበጀዋል ብሎ ወገቡን አጥፎ ላቡ ጠብ እስኪል ድረስ ሲሠራ የሚውለው ዜጋ አይደለም የእነሱን ያህል ቀርቶ ከወር ወር ምግብ በልቶ ለመዝለቅ እንኳ እየተሣነው ሲመለከቱ በሥልክ ብቻ በሚደረግ ድለላ ቢጤ “ሥራ” ቦርጭን ተራራ አሣክሎ የድራፍት እና የጮማ መክተቻ ሲሆኑ ማዬት ቀና ሠራተኛን ያሳምማል::

በተንቀሣቃሽ ሥልካቸው “ቢዝነስ” በማለት የሚያወሩት በእርግጥ ከሥራ ከተቆጠረ እነዚህ የጃምቦ ወንዞችና የበሬ ሥጋ ማጠራቀሚያ የሚመስሉት “ዝሆኖች” ሥራ እየሠሩ ነው እንበል:: “ቢዝነስ መሥራት” በተሣሣተ መንገድ እንደተተረጐመ ይሰማኛል:: ጠልፎ መጣል፣ ያልተገባን ጥቅም ማግኘት፣ በተጭበረበረ ሰነድ ሚሊዬነር መሆን፤ የጨረታ ሰነዶችን ማጭበርበር… ወ.ዘ.ተ የዘመኑ የሥራ ሥም የተሰጣቸው “ቢዝነስ” የሚባሉት ናቸው:: እናም እነዚህ በየአካባቢው ያለሥሥት… ገንዘባቸውን ሳይጨንቃቸው ጃንቦ ሲደፉ ሥጋውን ያለሥሥት ሲተለትሉ የሚውሉ ዜጐቻችን በዚህ “የቢዝነሥ ሥራ” ውስጥ የተሰለፉ መስለው ይታዩኛል::

ወደ ቀድሞው ነገሬ ልመለስ:: አዎ በመነሻየ እንዳልሁት አገር እና ህዝብ ጃምቦ ቤት እየመሠሉ ነው:: የንግድ ሥራ በሙሉ ወደ ጃምቦ ቤትነት እየተቀዬረ ይመስላል:: አገር የጃንቦ ቤቶች መፈጠሪያ ሆናለች:: ህዝቦቹም በመነጨው የጃምቦ ወንዝ ውስጥ የሚዋኙ ሆነው ታዝቤያለሁ::

የጥበብ ማዕከል … የባህል ማሣያ እና ማንፀባረቂያ ይሆናል ተብሎ በተቋቋመው የባህር ዳሩ ሙሉ ዓለም ባህል ማዕከል ፊት ለፊት እኮ ከዳር ዳር የተዘረጉት የጃምቦ ወንዞች ናቸው:: ምናልባት አንድ ወይም ሁለት ትኩሥ ነገር የሚሸጡ ቤቶች ቢኖሩ እንጅ ከዳር ዳር ማሥከሪያ ቤቶች ናቸው:: ይሄን መሥመር ይዘን በታላቁ መስጊድ አድርገን ወደ

ብሔራዊ ሎተሪ ሥናመራ እየባሰ ነው የሚሄደው:: የጃምቦ አድናቂ ከሆኑ ኪስዎትን ፈትሸው ጐራውን ይቀላቀላሉ፤ እንደቀልድ አንድ ሁለት ልበል ያሉት በዚያው የጃምቦ ባህር ውስጥ ሲዋኙ ውለው ምናልባትም ቤትዎን ሊረሱት ይችላሉ::

በባህር ዳር ቀበሌ አራት የሚባለውን አካባቢ መቁጠር ቢቻል በንግድ ሥራዎች ላይ ከተሰማሩት ውስጥ የጀምቦ ቤቶችን ቁጥር የሚያስንቅ ያለ አይመስልም አካባቢው በሙሉ በጃምቦና ዊስኪ ቤትነት የተጥለቀለቀ ነው:: እነዚህን ለማግኘት የአንድ እና ሁለት እርምጃ ልዩነት ብቻ ነው የሚጠይቀው::

ከባህር ዳሩ ሙሉዓለም ባህል ማዕከል አካባቢ ጀምሮ የሚዘረጋው የጃምቦ ወንዝ በውስጥ እስከ ቀበሌ አራት ትራፊክ መብራቱ ድረሥ ይዘልቃል:: በውስጥ ለውስጥ የጥርብ ድንጋይ በተነጠፈባቸው መንደሮችም የመጠጥ ግሮሰሪዎችና ጃምቦ ቤቶች በብዛት ይገኛሉ:: እናም ሲነጋ ጀምሮ መገጫጨት የጀመረው የጃምቦ ብርጭቆ ረፍት ሳይኖረው እስከ ሌሊቱ ድረስ ይዘልቃል:: በየቀኑ ብትመላለሱ ዘወትር የማይቀየሩ ፊቶችንም ያገኛሉ::

‘ታዲያ እነዚህ ሰዎች በየትኛው ጊዜያቸው ሠርተው ነው ገንዘቡን የሚያመጡት?’ ብለው ደግመው ለመጠየቅ ይገደዳሉ:: “ቢዝነስ እየሠሩ ነው” የሚል በምሥኪኑ ሥራ ሥም የተጀቧቦነ መልሥም ያገኙለታል::

ለጃምቦ ወንዛችን ትዝብቴ ባህር ዳር ከተማን በማሣያነት መርጫለሁና ወደሌላው አካባቢ ላቅና:: ከመነሐሪያው ጀርባ ያሉትን ሰፈሮች እንቃኝ:: የጃምቦ ባህሮች ናቸው:: ምድረ ሾፌር እና ረዳት እየተሠባሠበ በቡድን የሚዋኝባቸው ጃምቦ ባህሮች:: በዚህ አካባቢ ጠዋትም፣ ቀንም፣ ማታም ብትመላለሱ የጃምቦ ብርጭቆዎች ሲፋጩ… ደስታቸውን በግጭት ሲገልፁ ነው የሚታዘቡት::

ምናልባትም ረዳትና ሹፌር በተሣፋሪው ላይ ምን ያህል ግልምጫ፣ ሥድብና ዱላ ቀረሽ ጩኸት የሚያወርዱበት በጃምቦ ባህሩ ውስጥ ሲዋኙ ቆይተው ሥለሚመጡ ሳይሆን ይቀራል:: እኔ የማውቀው ቁርስ ተበልቶ ሻይ ወይም ውሃ ሲጠጣ ነው፡… እዚህ ሰፈር ግን የቁርስ ማወራረጃ ድራፍት ነው… ከአንድም፣ ሁለት ሦስት፤ ቀተር ሲል ደግሞ ጫት፣ መሸት ሲል ደግሞ ጠንከር ያለ አልኮል፤ ነገም እንዲህ፤…

በዚህ ሁሉ ታጅቦ የሚሽከረከረው መኪና ቢጋጭ፣ ቢገለበጥ፣… ያስገርማል! ቢወቀሩ ቢወቀሩ ልባቸው ላይ የመራራትና የሰብዓዊነት ሥሜት እንዳይኖር ያደረጋቸው ይሄ በጃንቦ ላይ ጫት፣ በጫት ላይ ሲጃራ በሲጃራ ላይ ደረቅ አልኮል… አይደለም ትላላችሁ? እስኪ ከፓፒረሥ ሆቴል ፊት ለፊት ጀምሮ ቀጥታ ወደ ፔዳ መሥመር እንጓዝ፤ የጠጠር መጣያ ቦታ የለውም በሚባል ደረጃ እኮ ጃምቦ ቤቶች “ እጅ” ለ “ እጅ” ተያይዘው ነው የምናገኛቸው:: እኔ የሚገርመኝ ይሄን ያህል ቤቶች ተደርድረው ጠጪ አለማጣታቸው ነው::

እኔ በነዚህ አካባቢዎች መጓዝ ፈታኝ እንደሆነም ይሰማኛል:: የትኛው እንደሚያወራ፣ የትኛው እንደሚያዳምጥ መለየት ያስቸግራል:: ሁሉም አፋቸውን ከፍተው የሰጧቸው ይመሥል ከሚያንደቀድቁት ድራፍት ጋር የሚያንደቀድቁት ወሬ እኩል ነው:: ከድራፍቱ ብርጭቆ ግጭት ጋር ወሬዎችም እየተገጫጩ አድማጭ ባይኖራቸውም ይቀጥላሉ::

የሚገርመው እነዚህ ከፓፒረሥ ሆቴል ፊት ለፊት ካሉት ጀምሮ የተዘረጉት የጃምቦ ወንዞች የዕውቀት ቤት ወደሆነው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማድረሣቸው ነው:: ምንም ርህራሔ ሳይኖራቸው እስከ ተማሪው ደጃፍ ያደርሣሉ:: ተማሪው በዕውቀት ሳይሆን በመጠጥ ባህር ውሥጥ ዋኝቶ እንዲወጣ ለማድረግ ዓላማ ያላቸው ይመስላሉ:: ለወትሮው በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ፣ መፅሐፍ ሻጮች ሲበዙ ነበር የምናውቅ:: ዛሬ አድራሻቸው ጠፍቶ ወደ ጃምቦ ወንዝነት እየተለወጡ ነው::

የ”ጃምቦ

የጃምቦ ወንዞች ተማሪው በዕውቀት ሳይሆን በመጠጥ ባህር ውሥጥ ዋኝቶ እንዲወጣ ለማድረግ ዓላማ ያላቸው ይመስላሉ::

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 8 ዜና ትንታኔ

አብርሃም በዕውቀት

ወደ ገጽ 34 ዞሯል

በሀብታችንእየተጠቀምንአይደለም

ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መስህብ ሀብት ባለቤቶች ቢሆኑም ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ጥቅም እያገኙ እንዳልሆነ የበየዳ ወረዳ ነዋሪው አቶ አበባው አስካል ይናገራሉ:: አቶ አበባው እንደሚሉት ጥንታዊና ታሪካዊ ገዳማት፣ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት፣ ከተለያዩ ነገሥታት ለአብያተ ክርስቲያናቱ የተበረከቱ ልዩ ልዩ ስጦታዎችና የግድግዳ ላይ ስዕሎች ቢኖሩም እየተጎበኙ አይደለም::

ቅርሶቹን በዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ብቻ አከማችቶ በመጠበቅ ሀብት ማግኘት እንደማይቻል ያስረዱት አቶ አበባው የሚመለከተው የመንግሥት አካል ካለን የመስህብ ሀብት ተጠቃሚ የምንሆንበትን መንገድ ሊያመቻችልን ይገባል ይላሉ:: “በወረዳችን ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች ጭላዳ ዝንጀሮ አለ፤ ቀይ ቀበሮ፣ እስከ 20 ሜትር ርዝመት ያለው የፈረስ ጭራ፣ እንደ ቅዱስ ያሬድ ያሉ የዋሻ ውስጥ ገዳማትም አሉን፤ ነገር ግን ጎብኝ ከወረዳችን ካሉ የመስህብ ሀብቶች ሁሉ የሚያዘወትረው ራስ ደጀን ተራራን ብቻ ነው” በማለት አቶ አበባው ይናገራሉ::

በ1414 ዓ.ም የተተከለው የበየዳ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ሳሕል ጌትነት ወንድሙነኝም የአቶ አበባውን ሀሳብ ይጋራሉ:: “በቤተ ክርስቲያናችን እጅግ ብዙ የሆኑ ሊጎበኙ የሚገባቸው ቅርሶች አሉን፤ ነገር ግን በዓመት አንድ ጎብኝ እንኳ አይመጣም:: እስካሁን ባለው እውነታ ከቅርሶቹ ያተረፍነው ነገር ቢኖር ስም

ኗሪዎች

ብቻ ነው” ይላሉ:: የወረዳው ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከአስጎብኝ ድርጅቶች ጋር ትስስር በመፍጠር ወረዳው ከቱሪዝም ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝ ሊሠራ እንደሚገባውም ያሳስባሉ::

ወ/ሮ አስማሩ ካሳ የተባሉ የወረዳው ነዋሪ በበኩላቸው አካባቢው ከቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚ ያልሆነው ከማስተዋዎቅ እጥረት እንደሆነ ያስረዳሉ:: እርሳቸው እንደሚሉት ወረዳው ካለው የመስህብ ሀብት ብዛት የተነሳ ከቱሪዝም ይበልጥ ተጠቃሚ መሆን ይችል ነበር:: “በወረዳችን ከ10 በላይ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት አሉ:: አብያተ ክርስቲያናቱ ደግሞ በያዙት ተንቀሳቃሽ ቅርስ፣ በኪነ-ሕንጻ ጥበባቸውና በግድግዳ ላይ ስዕሎቻቸው አማካኝነት መጎብኘት የሚገባቸው ናቸው” ይላሉ ወ/ሮ አስማሩ::

የበየዳ ወረዳ ከቀበሌ ቀበሌ የሚያገናኝ መንገድ ስለሌለው የአካባቢውን ሕብረተሰብ ከቱሪዝም ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ አለመቻሉንም ወ/ሮ አስማሩ ያስረዳሉ:: “መንገድ ባለመኖሩ ምክንያት አልፎ አልፎ ብቅ የሚሉ ጐብኝዎች የሚንቀሳቀሱት በእግር ነው:: ለምሳሌ ከፊንዝራራ ተክለሃይማኖት ወደ በየዳ ኢየሱስ፣ ከበየዳ ኢየሱስ ወደ አሾረና ኪዳነምሕረት፣ ከድል ይብዛ ቅዱስ ያሬድ፣ ከድል ይብዛ ቤተ ሐዋርያት ፍልፍል ቤተ ክርስትያን፣… ለመንቀሳቀስ ጎብኝዎች ከአካባቢው ሕብረተሰብ በቅሎ ይከራያሉ:: ዕቃ የሚጭኑላቸው ሰዎችንም ይቀጥራሉ፤ መንገዱ ግን ለእንስሳት ጉዞ እንኳ ምቹ አይደለም” በማለትም ያብራራሉ::

በበየዳ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቅርስና የመስህብ ሀብቶች ጥናት ቁጥጥር ባለሙያ አቶ

ሙሉጌታ ዳምጤም የአስተያዬት ሰጭዎችን ሀሳብ ይጋራሉ:: ወረዳው ከራስ ደጀን (4543 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ) በተጨማሪ የግልገል ደጀን (4510 ሜትር)፣ አናሎ (4473 ሜትር)፣ ወይኖ በር (4465 ሜትር)፣ አባ ያሬድ (4453 ሜትር)፣ ጠፋው ለዘር (4409 ሜትር)፣… የመሳሰሉ ከፍተኛ ተራሮች መገኛም መሆኑን የሚያስረዱት ባለሙያው በጎብኝዎች ዘንድ ግን የሚታወቀው የራስ ደጀን ተራራ ብቻ መሆኑን ገልፀዋል::

የበየዳ ወረዳ “የቅርስ ክምችት ጓዳ” በሚል የሚታወቅ፤ እጅግ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ የግድግዳ ላይ ስዕሎች፣ የደንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ ከብር፣ ከወርቅና ከዕንቁ የተሠሩ ውድ ጌጣጌጦችና ቁሳቁሶች የሚገኙበት እንደሆነም አቶ ሙሉጌታ ያብራራሉ:: “ይሁን እንጅ …” አሉ አቶ ሙሉጌታ፤ “ይሁን እንጅ በየዳ ከቱሪዝም ዘርፉ በመጠቀም ደረጃ ገና አልጀመረም፤ ጎብኝዎች ራስ ደጀንን ብቻ አይተው እየተመለሡ ነው:: ሌሎች በወረዳው ያሉት ውድ ቅርሶች፣ የተፈጥሮ መስህቦች፣… እየተጎበኙ አይደለም:: በሰወሬ ጊዮርጊስ የሚገኘውና 40 ክንድ የሚረዝመው የፈረስ ጭራም ጎብኝ አላገኘም” ብለዋል::

አቶ ሙሉጌታ እንደሚሉት ከበየዳ ወረዳ 17 ቀበሌዎች ውስጥ 15ቱ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አዋሳኝ ናቸው:: “ቀይ ቀበሮ የመጀመሪያ መነሻው በወረዳችን አርባ ረግረግ የሚባል አካባቢ እንደሆነ ከ80 ከመቶ በላይ በጥናት የተረጋገጠ ነው” ሲሉም ባለሙያው ገልጸዋል::

አቶ ሙሉጌታ “ወረዳው የማይጎበኘው ከቱሪስት ግብዓቶች ውስጥ መስህብ የሚባለውን ብቻ በመያዙ ነው፤ በተለይም ደረጃቸውን የጠበቁ ምግብ ቤቶች፣ መብራት፣ ሆቴል፣ ትራንስፖርት፣ ባንክ፣… አለመኖራቸው ነው:: እነዚህን ችግሮች በጥናት ለይተን አውቀናል፤ የመፍትሔ ሀሳቦችንም ጠቁመናል” ብለዋል:: በጥናቱ መሠረትም ባለሀብቶች በተለይ በሆቴል ዘርፍ እንዲሠማሩ ለማድረግ የወረዳ አስተዳደር ምክር ቤቱ አቅጣጫ እንዳስቀመጠም አቶ ሙሉጌታ አስረድተዋል::

ነገር ግን እንደ መብራት፣ መንገድና ባንክ ያሉ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ባለመኖራቸው የተነሳ ባለሀብቱ ደፍሮ በወረዳው መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ አልቻለም:: ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ሆቴል ለመገንባት 11 ያህል ባለሀብቶች ጥያቄ አቅርበው ቦታ የተሰጣቸው ቢሆንም ወደ ግንባታ ግን እንዳልገቡ ያስታወሱት አቶ ሙሉጌታ ከአስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ውስጥ በመንግሥት ምላሽ እየተሰጠ ያለው በመንገድ ዘርፍ ብቻ እንደሆነም ያብራራሉ::

በበየዳ ወረዳ ለሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ከነገሥታት

የተበረከተ የወርቅና ዕንቁ ለምድ

ደጃች ካሣ ኃይሉ “ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ንጉሠ ነገሥት

ዘኢትዮጵያ” ሆነው የነገሡበት ዘውድ በየዳ ወረዳ ካሉ

አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ ይገኛል

ከነገሥታት የተበረከተ የወርቅ ጋሻ በበየዳ ወረዳ በሚገኝ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገኛል

ከአማራ ክልል ገጠር መንገዶች ጋር በመነጋገርም

በገጠር መንገድ ተደራሽነት ቅድሚያ ሊሰጣቸው

የሚገቡ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለይተው

መስጠታቸውን ያስረዱት አቶ ሀብቱ የበየዳ

ወረዳም ቅድሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተለዩት

የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል::

ገጽ 9በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ማህበራዊ

ወደ ገጽ 31 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

ከአምስት አመታት በፊት በለጋምቦ ወረዳ ዙሪያ ይኖሩ የነበሩ አካል ጉዳተኛ ህፃናት ፀሀይ እንኳን እንደልብ አያገኙም

ነበር:: በተለይ የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ህፃናት ከቤት እንዲወጡና ሰው እንዲያያቸው ቤተሰብ አይፈልግም ነበር:: ለዚህ ችግር ዋነኛው ምክኒያት አመለካከት ሲሆን አመለካከታቸው እንደዚህ ሆኖ ዘመናትን እንዲቆይ ያደረገው ደግሞ በቀዬው ህፃናቱን የሚያስተምርና ለወላጆቹ ግንዛቤ የሚፈጥር ተቋም ባለመኖሩ ነበር:: የአቅስታ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ትምህርት መስጠት ከጀመረ በኋላ ግን ችግሩ በተወሰነ መልኩም ቢሆን እየተቃለለ የመጣ ይመስላል::

ወ/ሮ አየለች አህመድ ካሏቸው ልጆች መካከል አንዱ የአእምሮ እድገት ውስንነት አለበት:: ይኖሩ የነበረው በአቅስታ ከተማ ዙሪያ ካሉ የገጠር ቀበሌዎች በአንዱ ነበር:: ሆኖም አቅስታ ከተማ ላይ ለአካል ጉዳተኞች የሚሆን ትምህርት ቤት ተከፍቷል ሲባል ሲሰሙ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ለልጃቸው ሲሉ ወደ አቅስታ ከተማ አቀኑ::

ልጃቸውን ወደ ትምህርት ቤት ከመውሰዳቸው በፊት የነበረው ባህሪ ለእሳቸው ፈታኝ እንደነበረ ይናገራሉ:: ያገኘው መሬት ላይ መተኛት፣ አቧራ ከራሱ ላይ መበተን፣ እንግዳ ሰው ተከትሎ መጓዝ፣ እና መሰል ባህሪያትን ያሳይ ነበር:: ትምህርት ቤት መዋል ከጀመረ በኋላ እነዚህ ነገሮች መስተካከላቸውን ወ/ሮ አየለች ይናገራሉ:: አንደበቱ መፍታታት መጀመሩን፣ ልብስና ጫማ ራሱ መልበስና መጫማት መጀመሩን፣ ሰው አታድርግ የሚለውንም እንደሚሰማ በደስታ ይገልፃሉ::

በየእለቱ ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርሱት እሳቸው ሲሆኑ ይህም በልጃቸው ዙሪያ ከመምህራኖቹ ጋር ውይይት ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮላቸዋል:: ባዩት ለውጥ በእጅጉ እንደተደሰቱ የሚናገሩት ወ/ሮ አየለች ከዚህ በኋላም ልጃቸው እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተስፋ አላቸው::

በትምህርት ቤቱ የልዩ ፍላጎት ትምህርት እየተማሩ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል አንዱ ሙሃመድ ያሲን ነው:: የአራተኛ ክፍል አይነስውር ተማሪ ነው:: የአርሶ አደር ልጅ በመሆኑ እንደሱ ላሉ ተማሪዎች ትምህርት እንደሚሰጥ ቤተሰቦቹ ባለማወቃቸው መግባት ባለበት እድሜ ወደ ትምህርት ሳይገባ ቆይቷል:: አቅስታ ላይ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መጀመሩ ግን ዘግይቶም ቢሆን እድሉን እንዲያገኝ እድል ፈጥሮለታል:: ለትምህርት ያለው ፍላጎት ላቅ ያለ ነው:: በከፍተኛ ፍላጎት ስለሚማር በትምህርቱም ውጤታማ ነው:: ከመምህራኖቹ ጋርም ያልገባውን በመጠየቅና በመረዳዳት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ይናገራል:: አንደኛ

ወጋገን

ፀጋዬ የሽዋስ ለተዘነጉት

ደረጃ እየወጣ አራተኛ ክፍል ደርሷል:: በቀጣይም በትምህርቱ በርትቶ አስተማሪ መሆን ይፈልጋል:: አስተማሪ መሆን የሚፈልገውም እንደሱ አካል ጉዳተኛ የሆኑና እድሉን ያላገኙ ህፃናትን ለማስተማር ነው::

መሬም ቻሌም በትምህርት ቤቱ የአራተኛ ከፍል አይነስውር ተማሪ ስትሆን ለረዥም ጊዜ ትምህርት እየናፈቃት ትምህርት ሳታገኝ የኖረች ተማሪ ናት:: ቤተሰቦቿ አርሶ አደር በመሆናቸው ለአይነ ስውር ተማሪ ትምህርት ስለመኖሩ የሚያውቁት ነገር አልነበረም:: ዘጠነኛ ክፍል የደረሰ የአጎቷ ልጅ አቅስታ ላይ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መኖሩን ይሰማና ለቤተሰቦቿ ይነገራል:: ብተሰቦቿም መረጃውን ቢሰሙም ልጃቸውን ልኮ ለማስተማር ፈቃደኛነት አላሳዩም:: ይሄን ያስተዋለው የአጎቷ ልጅ ሀላፊነቱን ወስዶ መሬምን ወደ አቅስታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይዟት ሄደ::

መማር ስትናፍቅ የኖረችው መሬምም ከፊደል ጋር የመገናኘት እድሉን አገኘች:: በትምህርት ቤቱ ባላት ቆይታ በጣም ደስተኛ መሆኗን ትናገራለች:: መምህራኖቿም በጥሩ ሁኔታ ድጋፍ እያደረጉላት መሆኑን ትገልፃለች:: መሬምም እንደሙሃመድ ሁሉ አስተማሪ መሆን ትፈልጋለች:: አካል ጉዳተኞች ከጓዳ ወጥተው የሚማሩበት እድል እንዲፈጠርላቸው እሷም የበኩሏን ማበርከት ትፈልጋለች:: መምህር በሚስተምርበት ጊዜ የሚናገረውን ተከታትሎ ማስታወሻ መያዝ ፈታኝ በመሆኑ መቅረፀ ድምፅ እንደሚያያስፈልጋቸው አይነስውራን ተማሪዎቹ ያምናሉ::

ሁለቱ ተማሪዎች እስከ ሶስተኛ ክፍል ድረስ በልዩ ፍላጎት ከተማሩ በኋላ ዘንድሮ አራተኛ

ክፍል ላይ በአካቶ ትምህርት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተቀላቅለው እየተማሩ ነው ያገኘኋቸው:: እስከሶስተኛ ክፍል በልዩ ፍላጎት የሚማሩት ተማሪዎች እንደ አካል ጉዳታቸው የተለያየ ዘዴን በመጠቀም ይማራሉ:: ማየት የተሳናቸው፣ መስማት የተሳናቸውና የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎች እንደየ ችግራቸው በተለያየ መንገድ ነው የሚማሩት::

ወ/ሮ የሺሃረግ አባተ መስማት ለተሳናቸውና የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎች ትምህርት ይሰጣሉ:: በዚህ የስራ መስክ ከተሰማሩ አራት አመታት አልፈዋል:: እንደልጆቹ የአካል ጉዳትና ባህሪ በተለያየ መንገድ ተማሪዎቻቸውን ያስተምራሉ:: በጨዋታ ምልክ የሚያስተምሩበት መንግድ እንዳለም ይናገራሉ:: መስማት የተሰናቸው ተማሪዎች በምልክት ይማራሉ፤ ለዚህም የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ከትምህርት ቤቱ ጋር በመሆን አዘጋጅተዋል:: የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎች ራሳቸውን መንከባከብና አካባቢያቸውን መገንዘብ እንዲችሉ በትኩረት ይሰራሉ:: በሚሰሩት ስራም ለውጦችን በየጊዜው ስለሚያስተውሉ በእጅጉ ደስተኛ ናቸው:: ከተማሪ ወላጆች ጋርም ቢያንስ በየሳምንቱ እየተገናኙ ይመክራሉ:: ልጆቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ይዘው የሚሄዱ ወላጆች ልጆቻቸው የትምህርት ቤቱን ድባብ እስከሚላመዱ ድረስ አብረዋቸው እንደሚውሉ መምህርቷ ይናገራሉ::

“እንደየልጆቹ የጉዳት አይነት በአንድ ለአምስት አደረጃጀት ከፍለን እያስተማርናቸው ነው”

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመምህሩን ጥቅማ ጥቅም ማሟላት ይገባል ሲሉ አንዳንድ መምህራን ጠየቁ::

በምዕራብ ጐጃም ዞን ቋሪት ወረዳ መምህራን ማህበር 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባከበረበት ወቅት የገነት አንደኛ ደረጃ ት/ቤት መምህር አቶ ባለው አባትነህ እንደገለፁት የመምህራን ማህበር መቋቋሙ ቀደም ሲል የነበሩብንን የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችንና በመምህሩ ላይ ያሉ ቅሬታዎችን ለመፍታት በር ከፍቷል ሲሉ ተናግረዋል::

ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ራሄል አለማየሁ በበኩላቸው በዓሉ መከበሩ የነበሩብንን ችግሮች በግልፅ አውጥተን እንድንወያይ መደረጉ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል:: ከዚህም ባሻገር የመምህሩን የመኖሪያ ቤት፣ የትምህርት ዕድልና የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን በማሟላት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አስተያይታቸውን ሰጥተዋል::

የመምህራን ማህበር ሊቀመንበር መምህር ያሬድ መንግስቴ የመምህራን 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መካሄዱ አላማው የሙያ ማህበሩ ያለበትን ችግር በግልፅ በማቅረብ ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር መፍትሄ በማፈላለግ ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ለማድረስ ነው:: ቀጣይም የመምህሩን ቅሬታዎች ተቀብሎ ለመፍታት የበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አስገንዝበዋል::

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ

እየተሰራ ነውጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለማስወገድ

ተግተው እንደሚሰሩ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ::

በአካባቢያችን ያለዕድሜ ጋብቻ፣ የበዓል ቀናትን ማብዛትና ንቅሳት አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ ጐጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው ያሉት አርሶ አደር ወርቅነህ ወለልኝ ናቸው:: እነዚህን ጎጂ ድርጊቶች ለማስወገድም ባለሙያዎች በሚሰጡን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መሠረት ተግተን እንሰራለን ብለዋል::

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በአካል ፣ በስነ- ልቦናና ገንዘብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራሉ ሲሉ የተናገሩት የዛላ ዙሪያ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉዓለም በላይ ናቸው:: ተፅዕኖውን ለማስወገድም በአደረጃጀታቸው እየመከሩ መሆኑን በማስታወስ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ለ18 ሺህ 500 ሰዎች ግንዛቤ ለመስጠት ታቅዷል:: በዚህም መሠረት ለ18 ሺህ 550 ሰዎች ግንዛቤ ተሰጥቷል ያሉት በወረዳው የሴቶች እና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት የሴቶች ማደራጃ፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዋና የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ ጌትነት ባይህ ናቸው:: ግንዛቤ ካገኙት ውስጥም ዘጠኝ ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል:: የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን እንደዘገበው::

የትምህርትን ጥራት ለማስጠበቅ

ጥቅማጥቅም ማሟለት ይገባል

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 10

ሳምንቱ በታሪክ

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

ታሪክ

መሰረት ቸኮል

(ክፍል አንድ)

ምድር ስትፈጠር፤ የቆመችበትን መሰረት እንዲያጠናክሩ ኃላፊነት ከተሰጡ አራት ወንዞች መካከል ግዮን አንዱ ነው::

ዓባይ በዓለም ላይ እንደ ርዝመቱ ዕድሜውም ረጅም ነው:: ከስድስት ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ይጓዛል:: ብሩንዲ፣ ኮንጎ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ኡጋንዳ በዓባይ ተፋሰስ ውስጥ ይካተታሉ:: አስር አገራትን ያቆራርጣል ማለት ነው::

የዓባይ ወንዝ ከሁለት የተለያዩ ምንጮች የሚነሱት ጥቁር ዓባይና ነጭ ዓባይ ውህደት ከፈጠሩ በኋላ ናይል በሚል መጠሪያ ዓለም ያውቀዋል:: ነጩ ዓባይ… ኡጋንዳ ከምትጋራው የአራት አገሮች ንብረት ከሆነው ቪክቶሪያ ሐይቅ በመነሳት፣ አምስት ሺህ 584 ኪሎ ሜትር ወደ ሰሜን አቅጣጫ ተጉዞ ካርቱም ውስጥ ኡምዱሩማን ከሚጠብቀው ጥቁር ዓባይ ጋር ይገናኛል::

ጥቁሩ ዓባይ ከኢትዮጵያ ሰከላ ተነስቶ እስከ ኡምዱሩማን አንድ ሺህ 529 ኪሎ ሜትር በመጓዝ ከወንድም ወንዙ ጋር ይቀላቀላል:: እናም ካርቱም ኡምዱሩማን ላይ ናይል ተብሎ ወደ ግብፅ በመፍሰስ መጨረሻውን ሜዲትራኒያን ባህር ያደርጋል::

ናይል አስገራሚ ተፈጥሮ ያለው ወንዝ ነው:: በእኛ ዘመን ያልተዳሰሰ የፕላኔታችን ክፍል ዓለም፣ የምድር ጣራዎቹ የሒማሊያ ተራሮች፣ በበረዶ የተሸፈነው አንታርክቲክ፣ የጨረቃ ምስጢር ሳይቀር

የዓባይ ሸለቆ

ስልጣኔዎችሁሉም ታስሰው፣ ተዳሰው፣ ተነክተዋል:: ከሁሉም ግን የናይልን ወንዝ ምንጮች ምስጢር እንቆቅልሹን የመፍታቱን ያህል ስሜት አያክሉም::

የዓባይን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ለ2000 ዓመታት ያህል ሲያጨቃጨቅና መፍትሔ ሳያገኝ ለዘመኑ ታላላቅ አሳሾች ትልቅ ራስ ምታት ሆኖ የቆየ የፕላኔቷ ታላቅ ሚስጢራዊ ወንዝ ነበር::

ከግብጽ በኩል ይህን ብቻየን ልጠቀም የሚል አስተሳሰብ የተሸከሙ ብዙ የአሳሾች ቡድኖች ያደረጓቸው ዘመቻዎች ሁሉም ሳይሳካላቸው ተመልሰው ነበር - ታሪክ እንደሚጠቁመው:: ከዛሬ 160 ዓመታት በፊት የዓባይ ምንጭ የትነት፣ ሀሪ ጀንሰን የተባለው የዘመኑ አሳሽ፣ “የዓባይ ወንዝ ምንጭ የአሜሪካ አህጉር ከተገኘ በኋላ ትልቁ የዓለማችን መልክዓምድራዊ ምስጢር ሆኗል” ብሎ ነበር::

ይሁን እንጂ ግብጽ ውስጥ የሚገኝ አንድ ፀሃፊ ሞክሮ ነበር፤ ሰውየውም “በቴቤስ አቅራቢያ በሲየን እና በኤልፋንታይን መካከል ክፎፌና ሞፌ የሚባሉ እንደዋንጫ ቅርጽ የመሰሉ ሁለት ተራሮች ነበሩ፣ ለጥልቀታቸውም ወሰን የሌላቸው የዓባይ ምንጮች ከእነዚህ ተራራዎች መካከል ይወጣሉ፣ ግማሹም ውሃ በሰሜን አቅጣጫ ወደ ግብጽ ይፈሳል፣ ግማሹም ደግሞ በደቡብ አቅጣጫ አድርጐ ወደ ኢትዮጵያ

ይፈሳል፤ ብሎ ነገረኝ፤ ከዚህ በላይ ሌላ መግለጫ ከማንም ማግኘት አልቻልኩም:: በዓይኖቼም የተቻለኝን ያህል ለማየት እስከ ኤሌፋንታይን ድረስ ሄድኩ፤ ነገር ግን ያገኘኋቸውንም ስጠይቅ የተለያዩ ነገሮች ነገሩኝ፤ ሁሉም ግን አሳማኝ አይደሉም:: ብቻ ዓባይ ከግብፅ ማዶ ካሉ ሩቅ አገሮች እንደሚመጣ አምናለሁ:: ከዚህ ሌላ ንግግር አልቀጥልም::” በማለት ጽፎታል::

ዳሩ “ውሀ እንደልማዱ ቁልቁለት ወረደ” የሚለውን ሽምጥጥ አድርጎ የሚክድና ለጥቅም የተደረገ አሰሳ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በመልክዓምድራዊ አቀማመጥ ብናሰላው እንኳ ዓባይ ከዝቅተኛው የግብፅ እና ሱዳን አቀማመጥ የአፍሪካ የውሀ ማማ ወደተባለው የኢትዮጵያ ተራሮች የመፍሰስ ዕድል የለውም።

በዓለም ካሉ ወንዞች ለየት የሚያደርገው በደረቃማውና ጭቃማው ወቅት ላይ ዓባይ ብቻ ሞልቶ መፍሰሱ ነው:: የዚህን ምስጢር እንዲህና እንዲህ ነው እያሉ መላምቶችን ከመደርደር ባለፈ ምክንያቱን የደረሰበት የለም:: ከዚህም ባለፈ አንድ ሺህ ማይል ርቀትን አንድም ገባር ወንዝ በማይመግበውና ዝናብ አይቶ በማያውቀው ጭው ባለ አስፈሪ በረሃን ተቋቁሞ እስከመዳረሻው ሳይቋረጥ /ሳይደርቅ የሚፈስ ወንዝ የመሆኑን ምስጢር ማወቅ አልተቻለም::

አለን ሙርሄድ እንደፃፈው፤ ከሄሮዳተስ በኋላ በነበሩት ዘመናት አውሮፓውያን ከቻይና ጋር ተዋውቀው ነበር፤ አሜሪካና አውስትራሊያ ተገኝተዋል:: የዓለም የብስና ውቂያኖሶች ዛሬ ድረስ ባላቸው ዓይነት ካሮታና ቻሮት ሊሰራላቸው ተችሎ ነበር:: ነገር ግን እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ የአፍሪካ ትምህርትና ውስጠ ምስጢራቷ በሄሮዳተስ ዘመን እንደነበረው ሁሉ እንቆቅልሽ መሆኑን ቀጥሎበት ብዙዎችን እልህ አጋብቷል፣ እልህም አስጨርሷል::

በ1770ዎቹ ጀምስ ብሩስ ጥቁር ዓባይን ከምንጩ ኢትዮጵያ እስከ ካርቱም ያለውን አስሶታል:: ነገር ግን በ1856 ነጩን ዓባይ ለማሰስ ቁርጠኛ ሆነው ለሞከሩት አሳሾች እንኳ ከጁባ አልፎ መሄድ አልተቻላቸውም:: የነጭ ዓባይ ምንጭን ማግኘት ከባድ ነበር:: አረንቋው፣ በፓፒረስ የተሞሉ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች፣ ወባ፣ አስከፊው ሀሩርና ሌሎችም

መጋቢት 26• 1941 ዓ/ም - አሥራ ሁለት ምዕራባውያን

አገሮች፤ የአሜሪካ ኅብረት፣ ታላቋ ብሪታንያ፣ ፈረንሲስ፣ ቤልጂግ፣ ሆላንድ፣ ዴንማርክ፣ ኢጣልያ፣ ሉክሳምቡርግ፣ ኖርዌይ፣ አይስላንድ፣ ካናዳ እና ብርቱጋል በስምምነት የሰሜን አትለንቲስ የውል ድርጅት (North Atlantic Treaty Organization (NATO)መሠረቱ

መጋቢት 27• 1937 ዓ/ም - ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ

ከስደት ዘመን በኋላ በኢትዮጵያ አርበኞች ትግል እና በብሪታኒያ ሠራዊት እርዳታ የጣሊያንን ሠራዊት ድል እየመቱ ደብረ ማርቆስ ከተማ ገቡ:: በምሥራቅ ኢትዮጵያ የተንቀሳቀሱ አርበኞችም አዲስ አበባን በዚሁ ዕለት ያዙ::

መጋቢት 30• 1938 ዓ/ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ በረራውን ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል በምስር ርዕሰ ከተማ ካይሮ ላይ አከናወነ።

• 1945 ዓ/ም - በኬንያ ‘የአፍሪቃ ኅብረት እንቅስቃሴ’ መሪ የነበሩት ጆሞ ኬንያታ ድርጅቱ በቅኝ ገዝዎቻቸው ላይ የ’ማው ማው’ ሽብርን አካሂዷል በሚል በተሰነዘርበት ክስ ኃላፊነት አለብዎ ተብለው ለሰባት ዓመት የጽኑ እሥራት ቅጣት ተፈረደባቸው።

ሚያዝያ 1• 1908 ዓ/ም - የጥቁር አሜሪካዊው

የሰብዓዊ መብት መሪ የዶክቶር ማርቲን ሉተር ኪንግ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በተወለዱበት ከተማ በአትላንታ ተከናወነ። የጆርጂያ ክፍለ-ሀገር ገዥ ሌስተር ማደክስ ዶክቶር ኪንግ የ’ሀገር ጠላት’ ነበሩ በሚል አቋም እቀብሩ ላይ አልሳተፍም ብለው መቅረታቸው ሳይበቃ ለሟቹም ክብር የክፍለ ሀገሩን መንግሥታዊ ቢሮዎች እንደማይዘጉ አስታወቁ።

ሚያዝያ 2• 1928 ዓ/ም - የፋሺስት ኢጣልያ ሠራዊት

ኢትዮጵያን አጥቅቶ ወረራ በመጀመሩ የብሪታኒያ መንግሥት በኢጣልያ ላይ ቅጣት እንዲጣል በመገፋፋትና እና በራሱ በኩልም በአውሮፓ ጦርነት የሚያቀጣጥል ቢሆንም እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።

• 1937 ዓ/ም ለአሥራ ሁለት ዓመታት አገራቸውን በፕሬዚደንትነት የመሩት አሜሪካዊው ፍራንክሊን ዴላኖ ሩዝቬልት በዛሬው ዕለት አለፉ። ሩዝቬልት የአሜሪካ 32ኛው ፕሬዚደንት ነበሩ።

• 1953 ዓ/ም - የሶቪዬት ሕብረት የመጀመሪያውን ጠፈርተኛ፣ የ27 ዓመት የአየር ኃይል አባል ዩሪ ጋጋሪንን በመኖራኩር ተኮሰች። ጋጋሪን በጠፈር በረራ ምድርን ለአንድ ሰዓት ከአርባ ደቂቃ ያህል ከዞረ በኋላ ወደመሬት ተመልሷል።

• 1943 ዓ.ም. ሁለት ሺህ 188 ወታደር ያሰለፈው የኢትዮጵያ የክቡር ዘበኛ ሠራዊት፣ ቃኘው የሻለቃ ጦር ወደ ኮርያ ዘመተ። ከዘማቾቹ ማህል አንዱ የነበረው ‘የክራሩ ጌታ’ የሀመሳ ዐለቃ ካሣ ተሰማ “እልም አለ ባቡሩ” በሚለው ዘፈኑ ይሄንን ዕለት አወድሶታል።

ገጽ 11በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ጥበብ

ወደ ገጽ 36 ዞሯል

ከመፃሕፍት ገፆች

አባትሁን ዘገየ

ልብን በሚያቀልጥ ሙቀቷ ፍጥረታትን ስታነድ የዋለችው የሚያዝያ ፀሐይ ውሎዋን ጨርሳ ከተሰናበተች ከአንድ ሰዓት በላይ ሆኗታል:: ቀኑም ቦታውን ለምሽቱ ሊያስረክብ ለዓይን ያዝ ማድረግ ጀምሯል:: በባህር ዛፍ ፍልጥ ግጥም ተደርጐ ከታጠረው የቤቱ ግቢ ውጪ ድንገት “ቤቶች!... ቤቶች!... ኧረ ቤቶች! …” የሚል ቁጣና ችኮላ የተቀላቀለበት የጥሪ ድምጽ ተሰማ::

ትህትና ሀብቴ ራት ለማቅረብ ጓዳ ውስጥ ጉድ ጉድ ስትል ድምፁ ገዝፎ ተሰማት:: አንዳች የድንጋጤ ስሜት ሽው አለባት:: “እሱ ነው ወይስ?…” ብላ ለማረጋገጥ ማዳመጧን ቀጠለች:: ጥርጣሬዋ እውነት መሆኑን ስትረዳ “ጉድ ፈላ!... ደግሞ ብሎ ብሎ ቤት ድረስ መጣ?!…” ስትል አሰበችና ድካም ስለተጫጫነው ጋቢውን ለብሶ መደብ ላይ የተኛውን ባሏን በእምነት ተረፈን ገልመጥ አድርጋ አየችው:: በረዥሙ ሲተነፍስ እንቅልፍ እንደወሰደው ተረዳችና “ተመስገን…” ስትል አንሾካሾከች:: በእምነት ነቅቶ ከሰውየው ጋር አተካራ እንዳይገጥም በመስጋትም ሮጣ ከቤት ወጣችና የግቢውን የጭራሮ በር በከፊል ከፍታ ድምጿን ዝቅ አድርጋ “በኃይሉ ለምን አትተወኝም… በማልፍ በማገድምበት የምታስቸግረኝ ሳያንስህ ብለህ ብለህ ቤቴ ድረስ መጣህ?!…” አለችው::

“ከዚህ በኋላ ጉዳየ ካንቺ ጋር ሳይሆን ከዚያ ምናምን ካስነካሽ ምናምንቴያም ባልሽ ጋር ነው!” አለና ሊገባ ተንደረደረ::

“ምን ልታደርግ ነው? እሱ በሌለበት የምትገባው?…” ላለማስገባት ታገለችው:: “…ልትዋሺኝ አትሞክሪ!… ቀጣፊ!… ሲገባ አይቸዋለሁ! በህግ አምላክ አህያየን አምጣ!… በህግ ይዠሃለሁ!…” እየለፈለፈ ገፍትሯት ወደ ቤት ገባ::

በእምነት በድንጋጤ ከመኝታው ተነስቶ መደቡ ላይ ቁጭ ብሎ ዓይኖቹን ሲያሻሽ በኃይሉ፣ “ጓደኝነት!፣ ወዳጅነት!፣ አብሮ አደግነት እንዲህ ነው?!… ንጥቂያ!… ሌብነት!…” ፊት ለፊቱ ቆሞ ደነፋበት::

በእምነት ጓደኛው በኃይሉ ታገለ ሰሞኑን መንገድ ላይ ሲያገኘው ሰላምታ በመስጠት ፋንታ “እ!...” እያለ በክፉ ዓይን እያየው ሲያልፍ ደጋግሞ ታዝቦታል:: “ይሄ ሰው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፀባዩ እንዲህ የተቀያየረው ምን ሆኖ ነው?” በማለትም ሲያውጠነጥን ሰንብቷል:: ዛሬ ይባስ ብሎ ቤቱ ድረስ ገስግሶ መጥቶ ከላይ ከላይ እየተናገረ ከፊት ለፊቱ ሲገተር ለነገር እንደመጣ ተገነዘበ:: “ካልደፈረሰ አይጠራም!” ብሎ አሰበና ሊጋፈጠው ወስኖ ከተቀመጠበት ተነስቶ ፈንጠር ብሎ ቆመ::

እንደቆመ ከበኃይሉ ጋር ያሳለፉትን የልጅነት ህይወት እያስታወሰ በሀሳብ ባህር ሰጠመ::

ሁለቱም በዕድሜ ተመጣጣኝ ናቸው:: ተወልደው ያደጉትም ባንድ ሰፈር ነው:: ይህም የልጅነት ጊዜያቸውን በጓደኝነት አብረው እንዲያሳልፉ አድርጓቸዋል::

በኃይሉና በእምነት አብሮ አደግ ጓደኛሞች ቢሆኑም በባህይ ፈጽሞ ተቃራኒዎች ነበሩ:: በእምነት ቅንና ተግባቢ ሰው ነው:: ባንፃሩ በኃይሉ ደግሞ መሰሪ፣ ተንኳሽ እንዲሁም ቀናተኛና ሁሉንም የእኔ ላድርግ ባይ ስግብግብ ነው::

ሁለቱ አብሮ አደጐች በባህርይ እንዲህ የተቃረኑ በመሆናቸው የተነሳም ብዙ ጊዜ ሲጋጩና ሲናጩ ኖረዋል::፡ በእምነት ነገሮችን በቅንነትና በይቅር ባይነት ሲያልፍ፣ ባንጻሩም በኃይሉ በሞገደኛ ባህሪው ሲያሸንፍ ማየት የተለመደ ነበር:: በእምነት በጨዋታ ላይ “እገሊት የእኔ ሚስት ናት” ሲል በኃይሉ አባብሎም አታሎም ሲወስድበት ኖሯል:: በመጫወቻ ሲጣሉም የማታ ማታ ነጣቂውና በእጅ አድራጊው ሞገደኛው በኃይሉ ነበር::

ይህ ሁሉ ይፈፀም የነበረው በልጅነት ህይወት ውስጥ ስለነበር ከልጅነታቸው ጋር አብሮ አልፏል:: ሁለቱ አብሮ አደግ ጓደኛሞች እድሜያቸው በጨመረ ቁጥር አብረው የሚውሉ የሚያመሹበት ጊዜ እያጠረ… እያጠረ… የሚለያዩበት ጊዜ እየረዘመ… እየረዘመ… ሄዶ የየራሳቸውን ህይወት በተናጠል ወደ መምራት ተሸጋግረዋል:: ታዲያ ዛሬ…

በኃይሉ “ትሰማኛለህ በእምነት?!…” ብሎ የነገር ዘገር በመስበቅ እንደብራቅ ሲጮህበት በእምነት ደንግጦ ከሰጠመበት የሀሳብ ባህር ወጣ::

“ጤፍህን ጭነህ ካስገባህ በኋላ እንዴት አህያየን አትመልስም?!…” በጥያቄ አፋጠጠው::

“ጤፍም አላስገባሁ… አህያም አላየሁ…” አለ በእምነት በተረጋጋ ሁኔታ::

“ከቤትህ ፊት ለፊት የተከመረው የጤፍ ክምር ታዲያ የት ገባ?!... ማን ወሰደው?!...” በኃይሉ ተጭኖ ጠየቀ::

“እኔ ለአንድ ሳምንት ያህል ከቤቴ ተለይቼ

በሰነበትኩበት ጊዜ ባለቤቴ አስወቅታ አስገብታዋለች… ብየ ስለገመትኩ… ሳልጠይቅ ገብቼ ቁጭ አልኩ:: አንተ ግን እኔ ስላልተጨነቅሁለት ጤፍ እያነሳህ ትጨነቃለህ!...” በጥርጣሬ ዓይን እያስተዋለው በእምነት መለሰለት::

“እኔን ያስጨነቀኝ ያንተ ጤፍ አይደለም:: አህያየ ነው:: አህያየን አምጣ!... እምቢ ካልህ ትቀፈደዳታለህ! ከዚያ እኔ …” ምፀታዊ ፈገግታ ፈገግ አለ፤ በኃይሉ::

“ከዚያ አንተ ምን?!...” አሁንም በእምነት በጥርጣሬ ዓይን እያስተዋለው ጠየቀው::

“የማደርገውን ታያለህ!...” የሁለቱን ምልልስ ከጓዳዋ በር ላይ ቆማ

ስታዳምጥ የቆየችው ትህትና በብስጭት ፀጉሯ ሲቆም፣ ደሟ በደም ስሯ ሲራወጥ ተሰማት:: ቁጣዋን መግታት ስለተሳናት፣ “አንተ እንኳን ባሌን ቀርቶ እኔን ቀና ብሎ የማየት ጥፍር ታህል አቅምና ወኔ የለህም!... ተመኝተህ፣ አውርተህ ትቀራለህ!... አንተን ብሎ ወ…” ንግግሯን እንደምንም ገታችው::

በእምነት ባለቤቱ ጓደኛውን ይሄን ያህል አዋርዳ ለመናገር የደፈረችበት አንዳች ውስጠ ምስጢር ቢኖራቸው ነው እንጂ በሚል የቅናት ስሜት ሽው ሲልበት ተሰማው:: “ዘለህ እነቀው… እነቀው!...” የሚል ስሜት እያደረበት ቀና ብሎ በቁጣ በሚንተገተጉ ዓይኖቹ ሲያፈጥበት በኃይሉ “ቆይ ባልሠራልህ!... አንቺ ደግሞ…” ብሎ እየተወራጨ ወጥቶ ሄደ::

* * *“ስም!...” አሉ፤ የመሀል ዳኛዋ ዛጐልማ

ዓይኖቻቸውን ተከሳሹ ላይ ተክለው::“በእምነት!... በእምነት ተረፈ!...”“መኖሪያ?...”“ማንኩሳ!”“የተከሰስክበትን ጉዳይ ታውቀዋለህ?”“አውቀዋለሁ እንጂ ሳላውቅ እዚህ ምን ማረግ

ነኝ? አህያ ሰርቀሀል ተብየ ነው! ወይ የማንኩሳው ሚካሄል?!...”

“ያልተጠየቅኸውን አትቀባጥር::” ዳኛው አስጠነቀቁ::

“የጠየቁኝን መለስኩ እንጂ እንኳን ልቀባጥር ቀባጣሪም አልወድ!... ጥዩፍ ነኝ!...” አለ በእምነት አሮጌ ጋቢውን ከትከሻው አውርዶ እንደገና አስተካክሎ እየለበሰ::

“ወንጀሉን ፈጽመሀል ወይስ

ሲልቪላይ ላዩን

ተመስገን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብዬ ስሰራ አንዳንዴ ውቢቱ ሲልቪ ትመጣና “Salut, Castro noire” ትለኛለች:: (“ሰላም፣ ጥቁር ካስትሮ”) (ፂም ስላለኝ ነው::)

“Que la paix soit avec toi, O, Scheherazade Blanche,” እላታለሁ (“ሰላም ላንቺ ይሁን፣ ፃእዳይቱ ሻህራዝድ ሆይ”)

ትስቃለች:: በምስራቃውያን አነጋገር እንቀጥላለን:: አብረሀት ስትሆን ሳቅ ቀልድ ታበዛለህ፣

“ዠማንፉቲዝሟ” ይጋባብሀል፤ ስለምንም ነገር ደንታ አይኖርህም

አንድ ቀን ግን “ምንድን ነው ሁልጊዜ ስትጽፍ ‘ማገኝህ?” አለችና

ደብተሬን አየችው:: “የምን ጽህፈት ነው ይሄ? ያገራችሁ ነው?” አለችኝ::

“አዎን”“ምኑም አይገባም”“ቀላል ነው:: ሁለት መቶ አርባ የሚሆኑ ፊደላት

አሉት”“Quel horreu! (ኧረ የጉድ ያለህ!) እንግዲያው

አታስረዳኝ ይቅርብኝ… ምንድን ነው ‘ምትፅፈው?”“ምንም አይደለም…”“ልብወለድ ነው?”“ብጤ ነው”“እንዴት ማለት -ብጤ?”“እንዴት ልበልሽ? ልብወለድ ነው፣ ግን ፈጥሬው

አይደለም፣ ያየሁትን የሰማሁትን ነገር ሰብስቤ ቅርጹን እለዋውጣለሁ ‘ንጂ፣ ላንባቢ እንዲጥም”

“ቆይ …ቆይ:: አሁን መፃፍ አለብህ ወይስ ለጊዜው ልትተወው ትችላለህ”

“ልተወው እችላለሁ”“እንግዲያው ከዚህ እንሂድና ቡና ልጋብዝህ:: እና

ስለድርሰት እናውራ:: ይስማማሃል?”“Malin Castro noir, va!” (“ሂድ ወድያ! ጮሌ

ጥቁር ካስትሮ!”) deux Chevaux መኪናዋ ውስጥ ከገባን በኋላ “ኤክስ ውስጥ የምወደው ካፌ የለኝም:: ማርሰይ እንሂድ?” አለችኝ

እየቀለድን እየሳቅን ደጋግማ “Moi, tu sais, je m’en fous!” እያለች፣ በሆዴ ውበቷን እያደነቅኩ፣ ማርሰይ ደረስን::

ትኩሳት ሰብሊት ገብረእግዚዓብሔር

በቡልጋ እና ሸንኮራ የተካሄደ ትግልየቡልጋ ሕዝብ የኢትዮጵያን መሸነፍ ሲሰማ

ደንግጦ፣ የንጉሠ ነገሥቱን ወደ አውሮፓ መሄድ ሲሰማ ደግሞ ተገረመ:: የአንድ ጥቁር ሕዝብ ጉዳይ በነጭ አደባባይ ተሰምቶ ትክክለኛ ፍርድ ይገኛል ብሎ አላመነም:: የንጉሠ ነገሥቱንም ጉዞ ከሽሽት ለይቶ አላየውም:: ጠላት አንዳች ተቃውሞ ሳያጋጥመው አዲስ አበባን መያዙ አስቆጣው:: ስለዚህ የበኩሉን ትግል ጀመረ::

ንጉሠ ነገሥቱ ከአዲስ አበባ በወጡበት ቀን ማግስት፣ ማለትም ሚያዝያ 25 ቀን 1928 ዓ.ም ቅዳሜ እለት፣ የሀገር ሽማግሌዎቹ ሕዝቡን በጥሩምባ በመቀስቀስ ኮረማሽ ዋሻ ውስጥ ተደብቆ የነበረውን የጦር መሳሪያ አስነሱ:: የመሳሪያ ማንሳቱ ሥራ ከአፄ ምኒልክ አደራ በተቀበሉ ሽማግሌዎች ኃላፊነት ተካሄደ:: እነሱም ግራና ቀኝ ቁመው ሕዝቡን በተራ እያስገቡ፣ የየመስክህን የሚል ምክር እየሰጡ በሥነ ሥርዓት መሳሪያ እንዲያነሳ አደረጉ:: ስራው ቅዳሜ ቀንና ሌሊት፣ እንደዚሁም እሁድ ቀንና ሌሊት በሰላም ተካሄደ:: ሚያዝያ 27 ቀን ሰኞ ወደ ማታ ዋሻው ተቃጠለ:: በቃጠሎው የዋሻው በር ስለተደረበ በየዋሻው የነበረው ሰው አብሮ ተቃጠለ:: አንድ ቄስ ከሳጥን ላይ ለጥፎት የሄደው ጧፍ ሳይታይ ሳጥኑን እሳት በማቀጣጠሉ ነበር:: እሳቱን ለማጥፋት ያልተቻለው ደግሞ ሳጥኑ ዲናሚት ተቀምጦበት ስለነበር በመፈንዳቱ ነው:: ብዙ ሰው አለቀ:: መሳሪያውን ያስነሱ የነበሩ ሽማግሌዎች ጭምር ገና ካልተነሳው መሳሪያ ጋር አብረው ተቃጠሉ::

የኢትዮጵያ ታሪክ ኢጣሊያ በኢትዮጵያ ከወልወል እስከ ጐንደር ከተድላ ዘ ዮሐንስ

ምስክሮቹ

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 12 ማስታወቂያ

ባህር ዳርአቶ ያሲን ኢሣ በባህር ዳር ከተማ በቀበሌ ህዳር 11 ውስጥ ላላቸው ቤት የማይንቀሣቀስ ንብረት የስጦታ ግዥ ማዛወሪያ ቅጽ የውል ቁጥሩ A/ህ11/052 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የህዳር 11 ክ/ከተማ አስ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ለአቶ ኑርልኝ ሰጥአርጌ ባሉበት በከሣሽ እናትነሽ አያሌው በተከሣሽ እርስዎ መካከል ባለው ገንዘብ ክስ ጉዳይ መከሰስዎን አውቀው ለመጋቢት 30 ቀን 2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡3ዐ እንዲቀርቡ፡፡ ባይቀርቡ ግን ጉዳዩ በሌሉበት የሚታይ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

በከሣሽ የጐንጅ ቆለላ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በተከሣሽ የአዲስ አለም ጥበብና ጓደኞቻቸው የህ/ሸ/ማ/ተወካይ የሽዋስ ታረቀኝ መካከል ስላለው የአካል ጉዳት ካሣ ክስ ክርክር ጉዳይ የተዘጋው መዝገብ የተንቀሣቀሰ መሆኑን በማወቅ ለሚያዚያ 11 ቀን 2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባ/ዳርና አካ/ከፍ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ክበበው ደምሴ በባህር ዳር ከተማ ህዳር 11 ክ/ከተማ ውስጥ ላላቸው ቤት የማይንቀሣቀስ ንብረት የስጦታ ግዥ ማዛወሪያ ቅጽ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የህዳር 11 ክ/ከተ/አስ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

በከሣሽ ይርጋለም አባይ በተጠሪ ሃምሣ አለቃ ኪሮስ ገ/እግዚአብሔር መካከል ስላለው የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ አቤቱታ ጉዳይ ተጠሪ ለመጋቢት 30/2008 ዓ/ም 3፡ዐዐ ላይ እንዲቀርቡ፡፡ የማይቀርቡ ከሆነ ግን ጉዳዩ በሌሉበት ታይቶ ውሣኔ የሚሰጥ መሆኑን እንዲያውቁት ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባህር ዳር ከተማ ወ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

ምዕራብ ጐጃምአቶ ኢይሃልቅ መንግስቱ በመርዓዊ ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ የቀበሌ ቤት፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን ወ/ሮ ፀሐይ ጌታሁን፣ በደቡብ ሁነኛው ማስረሻ አዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታቸው ካርኒ ቁጥር 004303 የሆነ ካርኒ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመርዓዊ ከተ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ካሴ አካላት መርሻ በግሽ ዓባይ ከተማ 01 ቀበሌ ውስጥ በሰሜን ሙሉ ካሴ፣በደቡብ ይርገድ፣ በምስራቅ መንገድ፣በምዕራብ ሙሉዬ ብዙየ መካከል ተዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታ ካርኒ ቁጥር 1035 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የግሽ አባይ መሪ ማዘጋጃ ቤት------------------------------------------------

ወ/ሪት ማስተዋል ጌትነት በፍ/ሰላም ከተማ ቀበሌ 01 በአዋሣኝ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ አያና ተክሌ፣በምዕራብ አያሌው ያረጋል፣ በምስራቅ ንብረት ጥሩነህ በካርታ ቁጥር 70325/270-94 ተመዝግቦ የሚገኘው የምሪት ካርኒ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አመልካች ወ/ሮ ውባለም ሽፈራው ተፈላጊ አቶ ታገለ ስንሻው ይኖርበት ከነበረው ሰከላ 01 ቀበሌ ከቤት እንደወጣ ስላልተመለሰ የመጥፋት ውሣኔ ይሰጠኝ ብለዋል፡፡ ተፈላጊው በህይዎት ካሉ ወይም ያሉበትን የሚያውቅ ካለ ለመጋቢት 29/2008 ዓ/ም ይቅረብ፡፡

የጃቢ ጠህናን ወ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

በአመልካች ወ/ሮ የሽወርቅ ዘለቀ ወኪል መ/ታ አያሉ ዘለቀ ስላቀረቡት የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ ጥያቄ ጉዳይ ወ/ሮ ስንታየሁ አብየ የተባለችዋ ግለሰብ በመቅረጫ ሰጐዲት ቀበሌ ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የሄደችበት አድራሻዋ ያልታወቀ ስለሆነ በህይዎት ካለች ለሚያዚያ 04 ቀን 2008 ዓ/ም 3፡ዐዐ እንድትቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የጃቢ ጠህናን ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------------

አባ ዘሪሁን አዲስ በአዴት ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ 18 ቁጥር ፣በምዕራብ 16 ቁጥር ፣በሰሜን 27 ቁጥር

፣በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት ካርታ ቁጥር 00110/04 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ጥላሁን መንግስት በአዴት ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ 117 ቁጥር ፣በምዕራብ መንገድ፣በሰሜን 135 ቁጥር ፣በደቡብ 137 ቁጥር የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት ካርኒ ቁጥር 209005 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አመልካች እነ ቄስ ሞላ ዳኛው ተጠሪ አቶ አበበ መኮነን መካከል ስላለው የመጥፋት ውሣኔ ይሰጥልኝ ጥያቄ ጉዳይ አስመልክቶ ፍ/ቤቱ የመጥፋት ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት ተጠሪ በህይዎት ካለ ወይም አሁን አየሁ የሚል ወገን ካለ ለሚያዚያ 05 ቀን 2008 ዓ/ም ለሆነው ቀጠሮ ችሎት እንድትቀርቡ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ መስከረም አለሙ በአዴት ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ እሸቴ ጓዴ፣ በሰሜን ሙሉ እንየው ፣በደቡብ ገነት አለሙ የሚያዋስነው መኖሪያ ቤት የምሪት ካርኒ ንምራ ቁጥር 199949 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዴት ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

በይግባኝ ባይ ወጣት ቢያድግልኝ አሣየ ይግባኝ መልስ ሰጭ 1ኛ አስረሣች ወርቁ 2ኛ ተክለወር ብሩ 3ኛ አውራጃው ሰውነት መካከል ስላላው የጉዳት ካሣ ክስ ክርክር ጉዳይ 2ኛ ተከሣሽ አቶ ተክለወር ብሩ መከሰሱን አውቆ ሚያዝያ 04 ቀን 2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡3ዐ ቡሬ ተዘዋዋሪ ችሎት ቀርቦ እንዲከራከር ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት------------------------------------------------

አቶ አንቲገኝ አላምር ላቀ በመርዓዊ ከተማ ቀበሌ 02 በምስራቅ መሐሪው አበበ፣ በምዕራብ ወ/ሮ ዘርትሁን ደመላሽ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ ወ/ር ዋሴ መንገሻ ተዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታቻው ካርኒ ቁጥር 854427 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመርዓዊ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ገረመው ደመላሽ አድገህ በፍ/ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 በአዋሣኝ በሰሜን የማነ ብርሃን ፣በደቡብ እመየነሽ ፣ በምዕራብ መንገሻ ፣በምስራቅ መንገድ በካርታ ቁጥር 70348/252/94 ተመዝግቦ የሚገኘው የቤታቸው ኘላን ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የፍ/ሰላም ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ የቻለ አለሙ አድማስ በመርዓዊ ከተማ ቀበሌ 03 ውስጥ በምስራቅ ሲገርመኝ ዋለ፣በምዕራብ አለኸኝ የኋላ፣በሰሜን ዘውዲቱ ተስፋ፣ በደቡብ መንገድ አዋስኖ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታቸው ካርኒ ቁጥር 135257 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመርዓዊ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ምስራቅ ጐጃምአቶ እንደሻው ውበቴ በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 03 ላላቸው መኖሪያ ቤት ካርታ ቁጥር K/81274 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደ/ማርቆስ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ ውብሊቀር ተዋበ የህግ ባለቤቴ አቶ ወርቁ አዛገው ይኖርበት ከነበረው ከባሶ ሊበን ወረዳ ከየላምገጅ ቀበሌ ከጥቅምት 21/2001 ዓ/ም ጀምሮ እንደወጣ ስላልተመለሰ የመጥፋት ውሣኔ ይሰጠኝ ብለዋል፡፡ ስለዚህ አቶ ወርቁ አዛገውን አየሁት ወይም እዚህ ቦታ ይገኛል የሚል ካለ ለሚያዝያ 7 ቀን 2008 ዓ/ም እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባሶ ሊበን ወረዳ ፍ/ቤት------------------------------------------------

አመልካች ወ/ሪት አዝመራ በቀለ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት አቶ በቀለ ደምስ ስለጠፍ የመጥፋት ውሣኔ

ይሰጠኝ ብለዋል፡፡ ስለሆነም በህይዎት ካሉ ለሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ/ም ከጠዋቱ በ3፡ዐዐ እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የደ/ኤልያስ ወ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

አዊሰይድ ኡመር በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ሰፈራ ፎረንቅ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤታቸው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 1147/2001 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቻግኒ ከ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ውበት ገላው በፈንድቃ ከተማ በ2001 ዓ/ም የከተማ ቦታ የተመሩበት ደረሰኝ ቁጥር 1697 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ አንድ ወር ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የፈንድቃ ከተማ ማ/ቤት------------------------------------------------

መሪጌታ አምበሉ አናጋው እንዳለው በቻግኒ ከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ሰፈራ ፎረንቅ የሚገኘውን የመኖሪያ ቤታቸው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 1012/97 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቻግኒ ከተ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

አቶ አሣዬ አበራ ይመኑ በዳንግላ ከተማ ቀበሌ 03 የሚገኝ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር 2573/አ/1252 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ተቃዋሚ ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የዳንግላ ከተማ አስ/አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ዋግኽምራወ/ሪት ትግስት መኮነን በኒሯቅ ከተማ ቀበሌ 01/በቀጠና 3 ካርታ ቁጥር ኒ 87 በደቡብ ቄስ ተክሌ አማርጊስ ፣በሰሜን አጓች ማከያ ፣በምስራቅ መንገድ ፣በምዕራብ ኪዴ በላይ አዋስኖ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው የይዞታ ካርታ ማረጋገጫ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የኒሯቅ ከተማ ማ/ቤት------------------------------------------------

ሰሜን ጐንደርአመልካች ወ/ሮ አታክልት አናውጤ ተጠሪ አቶ ሆነ ገብሬ መካከል ስላለው በባልና ሚስት ክስ ተጠሪው ለሚያዝያ 04 ቀን 2008 ዓ/ም እንዲቀርቡ ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የጎንደር ከተማ ወ/ፍ/ቤት------------------------------------------------

አቶ ብርሃን በለጠ ጐባቸው በሰሜን አ72 በደቡብና በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አ69 የሚያዋስነው የካርታ ቁጥር 155/88 የመኖሪያ ቤት ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የአዘዞ ድማዛ ክ/ከ/አስ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ደቡብ ጐንደርአቶ መንጌ እምሬ በመ/ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 01 በአዋሣኝ በምስራቅ አዳምጤ ዋለ፣ በምዕራብ መለሰ ውብነህ፣በሰሜን ወንድም ጣሰው እና አዳምጤ ዋለ ፣በደቡብ መንገድ የሚያዋስነው 108 ካሬ ሜትር የድርጅት ቦታ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የመ/ኢየሱስ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ ባንች ፈንቴ በነፋስ መውጫ ከተማ በካርታ ቁጥር 016/11/76 ተመዝግቦ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት

ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ አታላ ባይለየኝ በደ/ታቦር ከተማ በስማቸው የሚገኘው በካርታ ቁጥር 1704/58/75 ተመዝግቦ የተሰጣቸው ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ሰሜን ወሎመ/ታ መንገሻ ሰማው በሪሁን በሮቢት ከተማ 01 ቀበሌ ያለው የይዞታ ማረጋገጫቸው ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የሮቢት ከተማ መሪ ማ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ ሙሉ ፈቃዴ በቆቦ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው የመኖሪያ ቦታ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር መ2-2/774/2002 ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቆቦ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ደቡብ ወሎዘቢባ አብዱ ጐሻም በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 05 ክልል ላላቸው የመኖሪያ ቤት በስሜ የተመዘገበ ቁጥር 6423/ኮ/ቴ/አገ/ቀ/05/1999 ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 22 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ ሰአዳ የሱፋ በደሴ ከተማ በቧንቧ ውሃ ክ/ከተማ በቀጠና 5 ክልል በቁጥር A-16008 የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የቧንቧ ውሃ ክ/ከተማ አገ/ጽ/ቤት------------------------------------------------

ወ/ሮ በድርያ መሐመድ ሣኒ በደሴ ከተማ በቀድሞው 19/09 በሮቢት ክ/ከተማ ክልል የቤት ቁጥር 1235 በካርታ ቁጥር A-6376 የተመዘገበ ካርታ ስለጠፋባቸው በማንኛውም ምክንያት ይዠዋለሁ ወይም ይገባኛል የሚል ካለ ማስታወቂያው ከወጣበት ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ ተቃውሞውን ካላቀረበ በምትኩ ሌላ ይሰጣቸዋል፡፡

የደሴ ከተማ አስ/ከ/ል/ኮን/መምሪያ------------------------------------------------

ትግራይከሣሽ ዐቃቢ ሕግ ተከሣሽ አቶ ሣሙኤል ምህረቴ አስራት አድራሻ አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ጣና ክ/ከተማ ቀበሌ 16 ስልክ ቁጥር 0925466567 በተከሰሱበት የሐሰት ገንዘብ መያዝ ወንጀል ክስ ለሚያዚያ 13 ቀን 2008 ዓ/ም ከቀኑ 3፡ዐዐ እንዲቀርቡ፡፡ ካልቀረቡ ግን ጉዳዩ በሌሉበት የሚታይ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የምዕራብ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ሁመራ ምድብ ችሎት------------------------------------------------

አፋልጉኝ እናቴ ወ/ሮ መቅደስ ትዕዛዙ ትኖርበት ከነበረው ጐንደር ከተማ ቀበሌ 03 በ1997 ዓ/ም ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም፡፡ እኔ በዚያን ወቅት የአንድ ዓመት ህፃን ነበርኩ፡፡ አሁን እድሜየ 13 ዓመት ነው፡፡ እናቴን የምትኖርበትን የሚያውቅ ካለ በስልክ ቁጥር 058111 11 38 ወይም 0918776618 ደውሎ ያሣውቀኝ ይላል፡፡

ፈላጊ ህፃን አቤል ተክሌ እንግዳወርቅ------------------------------------------------

ገጽ 13በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ፍትህ/መልካም አስተዳደር

ወደ ገጽ 31 ዞሯል

ፍትህ ነክ ዜናዎች

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር

የተሳተፉ ግለሰቦች ተቀጡ

ጥፋተኞች ተቀጡ

ሙሉጌታ ሙጨ

በአራጣ ብድር ወንጀል የተከሰሱ ግለሰቦች በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፍትህ ቢሮ ገለፀ፡፡

በቢሮው የወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ አቶ ዳኘ አድማሱ እንደገለፁት የሰሜን ወሎ ዞን ነዋሪ የሆኑት ተከሳሽ ዋለ አማረ እና ሲሳይ ንጉሴ እንዲሁም የምዕራብ ጐጃም ዞን ነዋሪ የሆነው ምስጋናው ከበደ አራጣ በማበደር ህገወጥ ድርጊት በመፈፀማቸው የሰሜን ወሎና የምዕራብ ጐጃም ዞን ፍትህ መምሪያ ክስ መስርተውባቸው ነበር፡፡

ክሱን የተመለከተው የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸውና ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው መጋቢት 12/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ዋለ አማረን በአንድ አመት እስራት እና በአምስት ሺህ ብር፣ ተከሳሽ ሲሳይ ንጉሴን ደግሞ በሁለት አመት ከአምስት ወር እስራት ቀጥቷቸዋል፡፡ የምዕራብ ጐጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 2/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ምስጋናው ከበደን በሁለት ዓመት ጽኑ እስራት እና የሁለት ሺህ ብር ቅጣት ወስኖበታል፡፡

የስራ ሂደት መሪው ግለሰቦችን ለስደትና ለከፋ ችግር የሚዳርግ ብሎም ለቤተሰብ መበተን ምክንያት የሆነውን ህገወጥ ተግባር የሚፈጽሙ ህገወጦችን ህብረተሠቡ ለፍትህ አካላት ጥቆማ በመስጠት እና ምስክር ሆኖ በመቅረብ ተገቢው የቅጣት ውሳኔ እንዲያርፍባቸው እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፊት

በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል የተከሰሱት ሦስት ግለሰቦች በጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጣታቸውን ፍትህ ቢሮ ገለፀ፡፡

በቢሮው የወንጀል ጉዳዮች ዋና የስራ ሂደት መሪ ዐቃቤ ህግ ዳኘ አድማሱ እንደገለፁት ተከሳሾቹ ፈቃድ ሳይኖራቸው በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ አገራት እንልካችኋለን በማለት ተበዳዮችን ለከፋ እንግልትና ስቃይ በዳረጉት በአቶ ሙሀመድ ጫኔ፣ በአቶ አብዱ ሞላና በአቶ ጀማል ሙሀመድ ላይ የሰሜን ወሎ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ህግ በማስረጃ የተደገፈ ክስ መስረቶባቸዋል፡፡

በመሆኑም የሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹ በዐቃቤ ህግ የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ባለመቻላቸውና ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው የካቲት 16/2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ መሀመድ ጫኔን 14 ዓመት እና ሦስት ሺህ ብር፣ ተከሳሽ አብዱ ሞላን 13 ዓመትና 10 ሺህ ብር እንዲሁም ተከሳሽ ጀማል ሙሀመድን በ12 ዓመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡

የስራ ሂደት መሪው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በርካታ ወጣቶችን ለከፍተኛ እንግልትና ስቃይ የሚዳርግ ስለሆነ ይህን ህገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች ህብረተሠቡ በማጋለጥ ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ የዜግነት ድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የመጨረሻ ክፍል

በመጋቢት 12 ቀን 2008 ዕትም የፍትህና መልካም አስተዳደር አምድ “ፊት ለፊት”

በሚል ርዕስ በሸዋ ሮቢት ከተማ የተደረገ ውይይት ማስነባባችን ይታወሳል:: ያልተዳሰሱ ዘርፎችን በመጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ.ም ልናስነብባችሁ ቃል ገብተንም ነበር:: ይሁንና በልዩ ዕትም ምክንያት ቃላችንን ጠብቀን ለንባብ አልበቃንም:: በመሆኑም ተከታዩን የውይይት ክፍል በዚህ ዕትም ይዘን የወጣን በመሆናችን እንድታነቡት ከይቅርታ ጋር እንጋብዛለን::

የመብራት አቅርቦትወይዘሮ አይናለም ጐላ ይባላሉ:: በሸዋ ሮቢት

ከተማ የዜሮ አራት ቀበሌ ነዋሪ ናቸው:: እርሳቸው እንደገለፁትም የ03 እና የ04 ቀበሌ ነዋሪዎች የመብራት ተጠቃሚዎች አይደሉም:: በመብራት እጦት ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ እየደረሰባቸው ነው:: በርካታ ግለሰቦች በተለያዩ የንግድ ዘርፎች መሰማራት ቢሹም መብራት ባለመኖሩ አልቻሉም:: ለአብነት መጠጥ ለመሸጥም ሆነ ምግብ አዘጋጅቶ ለገበያ ለማቅረብ የግድ ማቀዝቀዣ ያስፈልጋል:: የመብራት እጦት ግን በዚህ ዘርፍ እንዳይሰማሩ አድርጓቸዋል:: በተለይ ተማሪዎች በምሽት አጥንተው ተወዳዳሪ ሆነው መውጣት አልቻሉም::

የችግሩን ስፋትም ወ/ሮ አይናለም ሲያብራሩ “በዚህ ዘመን የ03 እና 04 ቀበሌ ነዋሪዎች ፋኖስና ኩራዝ እንዲጠቀሙ ተገደዋል:: ለምን? ብለን ስንጠይቅ ‘ለመስመር ዝርጋታ የሚሆን ገንዘብ ያስፈልጋል’ ተባለ:: እናም የቀበሌው ነዋሪ ድሀ- ሀብታም ሳይባል የተጠየቀውን እንደየአቅሙ አዋጣ:: በጠቅላላውም 64 ሺህ 600 ብር ገቢ ተደረገ:: ይሁን እንጅ ገንዘቡ ገቢ ከሆነ ሦስት አመት ተቆጠረ- ነገር ግን ብልጭ ያለ ነገር የለም::

“ገንዘቡ ተዋጣ፤ አሁንስ መብራቱ የማይገባበት ምክንያት ምንድን ነው? ስንልም ‘ምሰሶ የለም’ ተባለ:: በሌላ በኩል በሌሎች ከተሞች የመስመር ምሰሶ ይተከላል፤ ገመድ ይዘረጋል፤ በየግለሰቡ ቤት ቆጣሪ ይሰጣል… እናም አጐራባች ከተሞች ከቤት ባለፈ በመንገድ መብራት ሲንበሸበሹ እኛ ጨለማ የሆንበት ምክንያት አልገባንም”

አቶ አበበ አጋ በከተማዋ የ01 ቀበሌ ነዋሪ ናቸው:: “በክረምት በአካባቢው የኤሌክትሪክ መስመር ይወድቃል፤ ገመድ ይበጠሳል፤ እንጭት ገመድ ላይ ያርፋል፤ በአጠቃላይ መብራት ላይ ችግር ሲገጥም የድረሱልኝ ጥሪ በስልክ እናሰማለን::

ታዲያ የመብራት ሰራተኞች ‘ቅድሚያ ለፖሊስ አመልክቱ’ ይላሉ:: ጠቅለል ባለ አገላለጽ የመስመር ሠራተኞች ስልቹ ናቸው:: አንድ ሰው መብራት ተበላሽቶበት በአፋጣኝ ከተሰራለት “ጠርጥር ነው ነገሩ”፤ ለምን? ከተባለ ‘በእጁ’ ያልሄደ የዋህ ግለሰብ ሲለፈልፍ ውሎ ይሰነብታል እንጅ፤ ምላሽ አያገኝም:: የመስመር ሰራተኞች ሳይፈሩና ሳይቸሩ ‘የደንቡን ክፈሉ’ ማለት ጀምረዋል”

ውሀየሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪ ህዝብ ቁጥር በ2008

ዓ.ም 54 ሺህ መድረሱ ይነገራል:: ይህ ህዝብ ንፁህ የመጠጥ ውሀ የሚያገኘው በ1977 ዓ.ም ከተገነባ ጉድጓድ ነው:: ቧንቧው የተሰራው በወቅቱ በነበረው ህዝብ ቁጥር ነው::

አቶ ብርሀኑ ገረም የ02 ቀበሌ ነዋሪ ናቸው:: በቤታቸው የቧንቧ መስመር ከተዘረጋ ከ15 ዓመት በላይ ሆኖታል:: ነገር ግን ውሀ የሚያገኙት በሳምንት ከአንድ ቀን አይበልጥም፤ ለዚያውም በውድቅት ሌሊት ነው:: ሌሊት ጠብቀው ካልቀዱ የወንዝ ውሀ መጠቀማቸው ግድ ነው::

አቶ ብርሀኑ ጨምረው እንደገለፁት የአካባቢው ህፃናት እና ታዳጊዎች በተደጋጋሚ ይታመማሉ:: ምክንያቱ ደግሞ ከውሀው ንጽህና መጓደል ጋር የተያያዘ ነው:: ፊደል የቆጠረው ሰው ውሀውን አፍልቶ ይጠጣል:: ህፃናት ግን ያገኙትን ስለሚጠቀሙ ለውሀ ወለድ በሽታ ይጋለጣሉ::

በሸዋ ሮቢት ከተማ አንድ ሰው ገላውን በየሳምንቱ መታጠብ አይታሰብም:: “ለምን?” ካሉ ውሀ የለምና::

ጤናአቶ ብርሀኑ ገረም ጤናን በተመለከተም

በከተማዋ አንድ ግለሰብ የግል ሆስፒታል መክፈታቸውን አድንቀው በመንግስት የተገነባው ሆስፒታል ግን ለምን ስራ እንዳልጀመረ ጠይቀዋል::

መንገድየሸዋ ሮቢት ከተማን ከሁለት ሰንጥቆ ወደ አዲስ

አበባ የሚወስደው የአስፋልት መንገድ ነጠላ ነው:: የከተማዋ ነዋሪ አቶ ቀፀላ ተገኘ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ ያለው ዋናው መንገድ ነጠላ ከመሆኑ

በተጨማሪ ጠባብ ነው:: በአንድ ጊዜ ሁለት ተሽከርካሪዎችን ያለ ስጋት አያሳልፍም:: በመሆኑም በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ የመጣውን የተሽከርካሪ ፍሰት ማስተናገድ አልቻለም:: በከተማዋ የእግረኛ መንገድ የሚባል ነገር ባለመኖሩ ችግሩን “በእንቅርት ላይ…” አድርጐታል:: ቀደምቶቹም ሆኑ አዲሶቹ የመኖሪያና የንግድ ቤቶች የተገነቡት በአስፋልት ዳርቻ በመሆኑ ችግሩን የተወሳሰበ አድርጐታል ይላሉ::

ለፊት

የሸዋ ሮቢት ከተማ ነዋሪ ፊት ለፊት ሲወያይ፤

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 14 ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያየምስራቅ ጎጃም ዞን የደባይ ጥላት ግን ወረዳ የቁይ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በ2008 ዓ/ም በጀት ዘመን የቅጥር ግቢውን ዙሪያ አጥር ሎት 01 /ጤና ጣቢያው የአጥሩን ቆርቆሮ ፣ሚስማር ፣ያልተፈጨ ድንጋይ፣ ስሚኒቶና ቀለም አቅራቢ አሟልቶ ሌሎችን ደግሞ ተቋራጩ አሟልቶ/ ለማስገንባትና ሎት 02 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን / ጀኔሬተር ፣ ላውንደሪ ማሽን ፣ ኘሪንተር ፣ ፎቶ ኮፒና የመሣሰሉትን/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡1. ከላይ ለተጠቀሱት የስራ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው እንዲሁም የግዥ መጠናቸው ከብር 50,000.00/ሃምሣ ሺህ ብር/ በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት

ከፋይነት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡3. በህንፃ ግንባታው በደረጃ GC/BC 10 እና በላይ የሆኑ የህንፃ ተቋራጮች መሆን አለባቸው፡፡4. ለግንባታውና ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ መግኘት ይችላሉ፡፡5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00/አንድ መቶ ብር/ለሎት 01 እና ብር 50.00/ሃምሣ ብር/ ለሎት 02 በመክፈል ከቁይ ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በመምጣት

መግዛት ይችላሉ፡፡6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለሎት 01 ብር 1200.00/አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር/ እና ለሎት 02 ብር 1500.00/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በሲፒኦ ፣በጥሬ ገንዘብ

ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡7. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል/ሎት/ስለሆነ ከተጠቀሱት እቃዎች ውስጥ አንዱንም ካላሟሉ ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡8. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01 እስከ 21ኛው ቀን ከ2፡3ዐ እስከ 11፡3ዐ ድረስ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለሎት 02 ደግሞ እስከ 15ኛው ቀን ከ2፡3ዐ

እስከ 11፡3ዐ ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቁይ ጤና አጠ/ጣቢያ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂ/ቢሮ ቁጥር 18 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ

ሣጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህን ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለሎት 01 ለ21 ቀናት እና ለሎት 02 ለ15 ቀናት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡3ዐ እስከ 11፡3ዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡10. አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈባቸውን ጠቅላላ እቃዎች በቁይ ጤና አጠ/ጣቢያ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ንብረት ክፍል ቢሮ ቁጥር 21 ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡11. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ለሎት 01 በ22ኛው ቀን 4፡ዐዐ ተዘግቶ 4፡3ዐ እንዲሁም ለሎት 02 በ16ኛው ቀን 8፡ዐዐ ተዘግቶ 8፡3ዐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት የሚከፈት ሲሆን

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘታቸው ጨረታውን የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በላይ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

12. ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የአንድ ዓመት ዋስትና ያላቸውና እቃዎች ሲገቡ በባለሙያ ተረጋግጠው የሚገቡ ይሆናል፡፡

13. የጨረታ መክፈቻውና መዝጊያ ቀን የበዓላት ቀን፣እሁድና ቅዳሜ ከሆነ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡

14. የጨረታ ፖስታው ስርዝ ካለበት ፓራፍ መደረግ አለበት ይህም ሆኖ በስርዝ ድልዝ ምክንያት የማይነበብ ከሆነ ውድቅ ይሆናል፡፡

15. ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በቢሮ ስልክ ቁጥር 0582570137 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሣሰቢያ፡- የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ሲባል በመ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ አስገብቶ የደረሰኙን ኮፒ ከሰነዱ ጋር በፖስታው ውስጥ ማያያዝ አለባቸው ለማለት እንጅ በጥሬ ገንዘብ ፖስታው ውስጥ መያያዝ የለበትም፡፡

የቁይ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

ድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ፣ በውስጥ ገቢ እና በጅኪዩኘ በጀት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚገዛቸው እቃዎችን አገልግሎቶች 1. የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያ እቃዎች 2. የተለያዩ የስፖርት እቃዎች 3. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 4. የኤሌክትሪክ እቃዎች 5. ኢምፖርትድ የሆኑ ጠረጴዛና ቁምሣጥኖች 6. የሰራተኞች የደምብ ልብስ ማለትም ቆዳ ጫማ እና ቦት ጫማ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በጋዜጣ በግልጽ የጨረታ ዘዴ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ያላቸውና የሚያቀርቡ፣

2. የምዝገባ የምስክር ወረቀት የንግድ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግዥ መጠኑ ከ50,000.00/ሃምሣ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ከላይ በተራ ቁጥር 5 የተገለፀው ኢምፖርትድ በሆኑት ፈርኒቸሮች ተወዳዳሪዎች የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው እንጅ የማምረት ወይም የመፈብረክ ፈቃድ ያላቸውን አይመለከትም፡፡

7. ተጫራቾች ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር 20.00/ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒውን ማስያዝ አለባቸው፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡3ዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡ዐዐ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡3ዐ ጨረታው ይከፈታል፡፡

11. ውድድሩ በሎት ወይም በተናጠል ለማወዳደር ኮሌጁ የተሻለውን አማራጭ የሚጠቀም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

12. እቃዎቹን ከኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581410031 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

15. ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡

16. አድራሻ ደ/ጎ/አስ/ዞን ደ/ታቦር ከተማ

በጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

ደብረ ታቦር

የጨረታ ማስታወቂያየደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ለደራ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ኢንተርኘራይዞች ልማት ጽ/ቤት በአንበሣሜ ከተማ አንድ የከብት በረት ሸድ ግንባታ እና በሃሙሲት ከተማ ሁለት የእንጨትና ብረታ ብረት ሸድ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ያላቸው፣

4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ

5. ደረጃ 9 እና በላይ የሆኑ መጫረት ይችላሉ፣

6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

7. የግንባታ ዝርዝር መግለጫ(ስፔስፊኬሽን ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሣ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 06 ማግኘት ይቻላል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ወይም የግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታው ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 06 ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡3ዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን 2008 ዓ/ም ጠዋት 4፡ዐዐ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ጠዋት 4፡3ዐ ይከፈታል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ፣ በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058258

0140 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

ገጽ 15በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ኪንና ባህልኪንና ባህል

አማርኛ በአማርኛ

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

የራስጌ ፅሑፎችና ሌሎች አጫጭር ልብ ወለዶችና ወጐች መድብል ተመረቀ:: በማህበራዊ ሒሶች ላይ ያተኮረው መፅሐፍ፡- ከመቃብር ላይ የሙገሳ ቃላት ይልቅ በህይወት እያለን የመረዳዳት ባህል እንዲዳብር አስተዋጽኦው የጐላ ነው ተብሏል::

በወጣቷ ደራሲ መቅደስ አብይ ተደርሶ ለአንባብያን የበቃው ይህ መፅሐፍ 12 ክፍሎችን የያዘ ሆኖ ማህበራዊና ፍልስፍናዊ ይዘት ያላቸው ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል::

በሙሉ ዓለም የባህል ማዕከል በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ሠዎች በህይወት እያሉ የመረዳዳት ባህልን በመዘንጋት ከሞቱ በኋላ የሚደረግ ሙገሳና የመቃብር ላይ ፅሑፎች ለሥራዋ መነሻ እንደሆናት ደራሲዋ ተናግራለች:: በእለቱ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ዋና ፀሐፊ አርቲስት አንዱዓለም አባተ እና በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር የባህር ዳር ቅርንጫፍ ሊቀመንበር ሊቀ ህሩያን በላይ መኮንን በእንግድነት ተገኝተዋል::

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከመፅሐፉ የተወሰዱ ማራኪ አንቀጾች ለታዳሚዎች የተነበቡ ሲሆን የደራሲዋን ጨምሮ የእለቱ የክብር እንግዶች ፊርማ ያረፈበት መፅሐፍ ለጨረታ ቀርቦ በአምስት ሺህ ብር ተሽጧል :: በርካታ ገጣሚያን የግጥም ሥራዎቸውን ለታዳሚዎች አቅርበዋል:: በስነ ስርዓቱ ላይ ከጎንደር የመጡትና “ግጥም በማሲንቆ” በተሰኘው ወርሃዊ የግጥም ምሽት ስራቸው የሚታወቁቱን አባላት ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል::

ሌላው አስተያየት የሰጡት ሊቀህሩያን በላይ መኮንን በከተማዋ የስነ ፅሑፍ እድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀው የወጣቷን ድርሰትም በማሳያነት አንስተዋል::

140 ገፆችን የያዘው መፅሐፍ 35 ብር የመሸጫ ዋጋ ተተምኖለታል:: ወጧቷ ደራሲ ከዚህ ቀደም በመድረክ ላይ የግጥም ሥራዎቿ ትታወቃለች::

ማህበራዊ ጉዳዮችን

የሚዳስሰው መፅሐፍ ተመረቀ

ደረጀ አምባው

ሕዝበናኝ

አፄ

(ጌትሽ ኃይሌ)

አስደሳቹ እንበለው ወይም አስፈሪው ፈተና የሚጀምረው በአካባቢው በሚደረገው ጉዞ ነው:: ከሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና ከተማ እነዋሪ በ10 ያህል ኪሎ ሜትር የሚርቀውን የአፄ ሕዝበናኝ ቤተመንግስት ፍርስራሽ ለመመልከት በጠዋቱ ተነስተናል::

መኪና መግባት እስከ ሚችልበት የጉዞአችን አጋማሽ ደረሰ ከተጓዝን በኋላ ቀሪው ጉዞ በእግር ነበር:: በግራና ቀኝ ያሉት መንደርተኞች ሰብላቸውን ሰብስበው አውድማ ላይ ዘርግተው ‘ሆ! በሬ!’ እያሉ ሲያበራዩና ከእንስሳቱ ጋር ዙሪያ ክብ በመስራት ፍሬውን ከገለባው ለመለየት ሲደክሙ የሚያሳየው ትዕይንት እስከ ገደሉ ጫፍ ድረስ ይከተለናል::

በመጨረሻ የሜዳማው መልክዕ ምድር ተጠናቆ ሁሉንም በርቀት የምናይበት በሦስቱም አቅጣጫ ያለውን ሃገር በግልጽ የምንቃኝበት አፋፍ ላይ ደረሰን:: ምንም ዓይነት መከላከያ ባለመኖሩ የገደሉን ጫፍ ለመጠጋት ያስፈራል:: ከጫፍ አንድ ሁለት ሜትር ራቅ ካላሉ ሊያዞረዎትም ይችላል::

በዚህ አፋፍ ላይ ቆመን ዙሪያ ገባውን በማየት ስንደነቅ በድንገት ከአፋፍ ስር እያለከለኩ የሚወጡ የከተማ ሰዎች ብቅ አሉ:: ላባቸውን በነጠላቸው ጫፍ የሚጠርጉት ሁለቱ እናቶች ከባዱን መንገድ በማጠናቀቃቸው እንደተደሰቱ በሚያሳይ ፈገግታ ተሞልተው በአጠገባችን በሚገኙ ዲንጋዮች ላይ አረፍ አሉ::

“ከውዴት ነው?” ጠየቅን:: ድካሙ ያልበረዳላቸው እናቶች “ከገዳሙ” አሉ ከላይ ከላይ እየተነፈሱ::

ገዳሙ ከርቀት ይታያል “የአቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም:: ከሱ አለፍ ብሎ ደግሞ የጉዟችን መዳረሻ የሆነው የዳይ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ቆርቆሮ በዛፎች ተከቦ ይታየናል::

የእነርሱን ድካም ስናይ እኛም እንደመድከም ብንልም የማይቀር ስለሆነ ጉዞውን ለመጀመር ስንሰነባበት፤ እናቶች የያዙትን ዱላ እያቀበሉን “ለምርኩዝ ይረዳችኋል:: ያዙት! “አሉን:: አመሰገንንና ተሰነባብተን ወደ ቁልቁለቱ መውረድ ጀመርን::

ቁልቁለቱ አጭር ቢሆንም ለየት ያለ የፍርሃትና የደስታ ስሜት ውስጥ ያስገባል:: በታላቅ ጥንቃቄ የጀመርነውን ከዲንጋይ ወደ ዲንጋይ የመዝለል ጉዞ ሳናጋምስ በድንገት ከኋላችን የመጣ የአካባቢው ወጣት ዱብ! ዱብ! በማለት ሰላምታ ሰጥቶን የሩጫ ያህል እየዘለለ ተጓዘ:: ‘ለካ መንገድም ይለመዳል!’ ፍርሃታችን መገፈፍ ያዘ:: በግራና ቀኝ ከርቀት በመናየው ድንቅ መልከዓ ምድር እየተደሰትን ጉዟችንን ቀጠልን:: አፋፉ ላይ ያገኘናቸው እናቶች የሰጡን ምርኩዝም በእጅጉ ጠቀመን ፈታኙን ቦታ ከወረድን በኋላ ግን ተራራዎችን ወደ ጐን በመተው ወደ መንደሮች የሚወስደውን መንገድ ስንከተል ጉዞአችን በለሰለሰው አየር የታገዘና ቀና ሆነ::

ከአንድ ሰዓት በኋላ ዳይ ጊዩርጊስ ያለበት ቦታ ስንደርስ በእጅጉ ተዳክመን ነበር:: እድሜ ጠገብ በሆኑ አፀዶች ስር በተዘጋጀው የመቀመጫ ቦታ አረፍ በማለት ድካማችንን ካስታገስን በኋላ አካባቢውን ለመመልከት ዘወር ዘወር ማለት ጀመርን::

የታሪካችን ማጠንጠኛ የሆነው የአፄ ህዝበናኝ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ በዳይ ጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል:: በዚሁ ግቢ የሚታዩት ፍርስራሽ ድንጋዮች ቤተ መንግስቱ በስርዓት ተጠርበው በተዘጋጁ ጌጠኛ ድንጋዮች የታነፀ ግንብ ቤት እንደነበር ይጠቁማሉ:: ዲንጋዮቹ በአስደናቂ ጥበብ በአራት ማዕዘን ቅርፅ ተጠርበው በደረጃ መልክ የተደረደሩበትን ትዕይንት በቤተክርስቲያኑ ቅፅር ግቢ ውሰጥ እናየዋለን::

14 ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር ስፋት ይዞ ከሚታየው ደረጃ ውጪ ቀሪው የቤተ መንግስቱ ፍርስራሽ ግን በመሬት ውስጥ እንደተቀበረ አባቶች ይናገራሉ:: የፍርስራሹ የውስጥ ግድግዳ የተሰራው፣ ደረጃው የተሰራበት ዓይነት ዲንጋይ ሳይሆን ባልተጠረበ ነገር ግን ሃረግ በመሰለ ጌጥን በፈጠሩ ያማሩ ድንጋዮች መሆኑና ሕንፃው የንጉሱ ግብር ማብያ አዳራሽም እንደነበር በቦታው ለረዥም ጊዜ የኖሩት ቄስ የማነ ብርሃን ይናገራሉ::

ከ500 ዓመት በፊት ኢትዮጵያን ለአራት ዓመታት የገዙት አፄ ሕዝበናኝ በዘመነ መሳፍንት ጊዜ ብቅ ያሉ ንጉስ ነበሩ::

ሐገሪቱ በባላባቶች ስትገዛ፣ ባላባቶቹ በአንድ የአካባቢ ንጉስ ሥር ይመሩ ነበር:: በዚህ ዓይነት በሚያስተዳድሩት ነገስታት ላይ የበላይነት የሚኖረው ንጉሰ ነገስት ወይም በኢትዮጵያ ነገስታት ንጉስ ተብሎ ይጠራል:: የጠቅላይ ግዛቱ ገዢዎችን የሚሾም ንጉሱ ነው:: እነዚህ ገዥዎች በየጠቅላይ ግዛቱ የጦር መሪነቱንም ስልጣን የሚይዙና ራስ ወይም ሹም በተባሉ የማዕረግ ስሞች የሚታወቁ ናቸው:: ለዋናው ንጉሰ ነገስት ግብርን የሚሰበስቡ እነርሱ ሲሆኑ ከህዝቡ ልብስ ጨው ብረትና እህል በመሰብሰብ ወደ ማዕከላዊ መንግስት ያስተላልፋሉ:: ወቅቱ ህዝቡ በገንዘብ ፋንታ መገልገያ ከሚጠቀምባቸው ጨው /አሞሌ/ና ብረት ባሻገር የዕቃ በዕቃ መለዋወጥም በብዛት የተሰራበት ዘመን ነበር::

ነገስታቱ ዘውድ የሚጭኑት በአክሱም ሲሆን የሚኖሩት ግን በተለያዩ ዋና ከተማዎች ነበር:: ታዲያ አፄ ሕዝበናኝ ወንድማቸው አፄ ይሰሐቅ በ1414 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ ቦታውን በመረከብ ስርዓተ ንግሳቸውን በአክሱም ከፈፀሙ በኋላ ሀገሪቱን ለማቅናት ሲወጡና ሲወርዱ የቆዩ ንጉስ ናቸው::

በንጉሱ ዙሪያ በጽሑፍ የተገኙ ታሪክ ባይኖራቸውም በአካባቢው ከአያት ቅድመ አያት ሲወርድ ሲወራረድ የመጣ ታሪክ እንደሚያስረዳው

ኣርቦን = ቀብድ፣ ዋስትና

ወይም መያዥ

/ነገር/

ቀንዘ = የዛፍ፣ የተክል

ቅርንጫፍ

ዠጠዠጠ = ገጠገጠ፣ በብዛት

ተከለ፣ ደረደረ

ሰሪሳራ = በግንባር ግራና ቀኝ

ከጉንጭ በላይ

ያለ የሰውነት ክፍል

ሃመልማል = ልምላሜ፣

አረንጓዴነት

ዛህርት = ትልቅ ሆድ

ኪን ዜናዎች

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 16 ማስታወቂያ

ግልፅ የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያየአዊ/ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ት/ዋና መምሪያ ለአዊ/ብሔ/አስ/ መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ በመናኸሪያ በጀት የቢሮ እና የአዳራሽ ኮርኔስ ሥራ፤ የቢሮ እና የካፍቴሪያ ግንባታ እንዲሁም የመናኸሪያዉን አጥር እድሳት እና ግንባታ ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዉ ጋር ዉል በመያዝ ማስገንባት እና ማሳደስ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፤3. የቫት ሠርተፊኬት እና የታደሰ የደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የብቃት ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡ በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች

ወቅታዊና ለገ/ኢ/ት/ ዋና መምሪያ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ ከ50,000.00 ብር በላይ ስለሆነ የሚወዳደሩት የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ ናቸዉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ግልጽ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20.00 /ሀያ ብር ብቻ/ በመክፈል በገ/ኢ/ት/ዋ/መምሪያ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡

6. የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በሎት ሆኖ የቢሮ እና የአዳራሽ ኮርኔስ ሥራ ሎት-1 የካፍቴሪያ እና የቢሮ ግንባታዉ ሎት-2 እንዲሁም የአጥር እድሳትና ግንባታ ሎት-3 ሆኖ ዉድድሩ በየሎቱ 3ቱም ሎት ለየብቻ ይወዳደራል፡፡

7. አሸናፊዉ ተቋራጭ የግንባታ ግብአቶችን በሥራ ዝርዝሩ መሠረት ራሱ በማቅረብ ግንባታዉን ዉል በያዘ በ60 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ አጠናቆ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡

8. የግንባታዉ የሥራ ዝርዝር መግለጫ /Bill of Quantity/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ድምር 1 % በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም

በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በገ/ኢ/ት/ ዋና መምሪያ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በአዊ ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ት/ መምሪያ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰአትጨረታዉ

በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ከጥዋቱ 4፡0ዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዊ ገ/ኢ/ት/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በ22ኛዉ ቀን ከጥዋቱ 4፡45 ይከፈታል ፤ ነገርግን 22ኛዉ

ቀን ብሔራዊ በዓል /አሁድ ቅዳሜ/ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፤12. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት የተከለከለ ነዉ፡፡13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡14. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 0582270065 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582270066 በመደወል

ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአዊ ብሔ/አስ/ገ/ኢ/ል/ ዋና መምሪያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበቋሪት ወረዳ የሚገኘው የገ/ማርያም ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ሽንት ቤት

ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከደረጃ ዘጠኝና በላይ የሆናችሁ የህንፃ ስራ ተቋራጮችን መወዳደር

እንደምትችሉ እየገለጽን የግንባታውን ዲዛይንና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት

የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

2. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሣ ብር/በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ8፡ዐዐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአርቲሜቲክ ስሌት በኋላ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በሲፒኦ ፣በደረሰኝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ፎቶ ኮፒ ከዋጋ መሙያ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡

7. ዋጋው የሚሞላው ኮሌጁ ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡8. በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ከተሰረዘ ለመሰረዙ ፓራፍ

መደረግ ይኖርበታል፡፡

9. በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም፣ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት፡፡10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ ሙሉ በሙሉ የተጠበቀ

ነው፡፡

11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በማስያዝ በፍትህ ውል መፈፀም ይኖርበታል፡፡

12. ተቋራጮች ፈቃዳቸውን ያወጡት ከፌደራል ከሆነ በአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት የአጭር ጊዜ ምዝገባ ያደረጉበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13. የግንባታ ስራው የቦታ ርክክብ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ6ዐ ካላንደር ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡

14. ጨረታው ተከፍቶ እያንዳንዱ ተጫራች ያቀረበው ዋጋ አርቲሜቲክ ከተሰላ በኋላ የሚገኘው ውጤት በመጀመሪያ ሲከፈት ከተነበበው በተጫራቹ የቀረበ ዋጋ ያለው

ልዩነት ከ2 በመቶ በላይ ከሆነ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡

ማሣሰቢያ፡- በዚህ ጨረታ ያልተካተቱ ህጎችና መመሪያዎች ሁሉ ተፈፃሚ

ይሆናሉ፡፡

የገ/ማርያም ቴ/ሙ/ማሰልጠኛ ኮሌጅ

የጨረታ ማስታወቂያ ማሻሻያድርጅታችን የG.W.D ትሬዲንግ አ/ማህበር በባ/ዳር ከተማ ለሚያስገነባው የገበያ ማዕከልና አፓርትመንት አገልግሎት የሚውል ብረት ለመግዛት መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ/ም በጋዜጣ ላይ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሣል፡፡ ይሁን እንጅ በጨረታው ላይ “የቱርክ ስሪት” የሚለው ተሰርዞ የጥንካሬ መጠኑ(Tensil Strength) 400 Mpa የሆነ ተብሎ እንዲስተካከልና የጨረታ ማስገቢያ ቀኑም ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ1ዐኛው ቀን በ9፡3ዐ ተዘግቶ በዕለቱ በ1ዐ፡ዐዐ ይከፈታል፡፡

የG.W.D ትሬዲንግ አ/ማህበር

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ የሰ/አቸ/ወ/ጤ/ጥ/ጽ/ቤት ለህ/ጤ/ጣ አገልግሎት የሚውል የእንግዳ ማቆያ ክፍል ለማሰራት

ከደረጃ /8/ በላይ የሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ1. ማንኛውም የህንፃ ተቋራጭ በዘመኑ የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ወይም የዘመኑን ግብር የከፈለበት

ማስረጃ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም ቲን ካርድ ያለው፡፡

2. የግንባታ የምስክር ወረቀት ከመሰረተ ልማት ሚኒስቴር /ክፍል/ስራና ከተማ ልማት ቢሮ ማቅረብ የሚችለው ፣የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችልና ለደረጃው የሚያስፈልጉ መረጃዎችን የጨረታ ሰነዱን ሞልተቶ ሲያቀርብ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውጭ አያይዞ ማቅረብ የሚችል ሆኖ ተጫራቹ ለግንባታ ስራ የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል ማቴሪያልና ማሽኔሪች ሙሉ በሙሉ ራሱን ችሎ ማሰራት የሚችል፡፡

3. ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00/ሰላሣ ብር/ በመክፈል ሊበን ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት እስከ ጨረታው ቀን ማጠናቀቂያ በስራ ሰዓት መግዛት ይችላል፡፡

4. የሚሰራውን የግንባታ አይነት ዝርዝር /ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡፡5. ተጫራቾች ስራውን ለመስራት ከፈረሙበት ቀን ጀምሮ ለደረጃ /8/ እና በላይ 50 የካለንደር ቀናት ውስጥ

ሰርተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 5,000.00/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ በሲፒዮ

፣በጥሬ ገንዘብ ፣በሌላ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ኮፒዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት

በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግና አድራሻውን በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 3፡45 ድረስ ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑም በዚሁ ቀን 4፡ዐዐ ህዳሴ ጤና ጣቢያ ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሣቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የሚያስተጓጉል ከመሆኑ ተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሣኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/ በሌላ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

9. አሰሪው መስሪያ ቤት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡10. ለበለጠ መረጃ 0582311432 ወይም 0918128813 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሰሜን አቸፈር ወ/ህዳሴ ጤና ጣቢያ

የጨረታ ማስታወቂያ

በከሣሽ እንጅባራ ከተማ ራዕይ እቁብ ማህበር ጠበቃ ሽታነህ እያሱ ተከሣሽ እነ ሙሉ ሃይሉ 2ቱ ራሣቸው መካከል ባለው የአፈፃፀም ገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኘው የድርጅት ቤት በአዋሣኝ በምስራቅ ግርማ ይስማው ፣ በምዕራብ አዲሴ አለነ፣ በሰሜን ውብነህ ዳኛው ፣በደቡብ መንገድ እና የአቶ ያዘው ዘለቀ መካከል የሚገኘውን በ1ኛ ተጠሪ ሙሉ ሃይሉ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋው 216,800.00/ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ብር/ ስለሚሸጥ ሚያዚያ 14 ቀን 2008 ዓ/ም ከቀኑ 3፡ዐዐ እስከ 6፡ዐዐ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቀርቦ እንዲጫረት ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

ማሣሰቢያ፡- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ስትመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ ኛውን ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሣስባለን፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት

ገጽ 17በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ለወጣቶችከዚህም ከዚያም

የራስዎትን የሥራ ዕድል እንዲህ

ቢፈጥሩስ?

አብርሃም በዕውቀት

ስለመስኖ ጥቂት እውነታዎች

ወደ ገጽ 31 ዞሯል

• በቅድሚያ ዕውቀት፣ ክህሎትና መነሻ ካፒታል ካለዎት የሚያዋጣዎትን የሥራ መስክ ይምረጡ::

• በመረጡት የሥራ መስክ ዙሪያ ስልጠናዎችን ይውሰዱ፤ ስልጠናውንም ከተቋማት፣ ኮሌጆች ወይም የግል አሰልጣኞች ማግኜት ይችላሉ::

• ያሉትን ዕድሎች ሁሉ አሟጠው ለመጠቀም ይጣሩ፤ የሚያገኟቸውን ሰዎች ሁሉ ካሰቡት ሥራ ጋር በተገናኘ እንደግብዓት ይጠቀሟቸው፤ በደንበኛነት፣ በመረጃ ምንጭነት፣ በአስተዋዋቂነት፣ …:: ይህ ማለት ግን አጉል ስግብግብ በሚያስብል መልኩ አይደለም::

• ግትር አይሁኑ፤ በሚያመርቱት ምርት ጥራት፣ ዓይነት፣ … ከደንበኞች የሚደርስዎትን አስተያዬት በፀጋ ተቀብለው ለመመርመር ዝግጁ ይሁኑ:: ራስዎትንና ድርጅትዎን ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማስማማት ይጣሩ::

• በድርጅትዎ ውስጥ የሚቀጥሯቸውን ሠራተኞች የትምህርት፣ የዕውቀትና ክህሎት ደረጃ እንዲሁም የስነ-ምግባር ሁኔታ አስቀድመው ይለዩ::

• ይህንን ሁሉ ሂደት ካለፉ በቃ ፈቃድ አውጥተው ወደ ሥራ ይግቡ፤ መልካም የሥራ ጊዜ ይሁንልዎት!ምንጭ፡ www.monster.com

• መስኖ በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የዓለም ሕዝብ የተለመደና እ.ኤ.አ በ2050 የዓለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቀዳሚ አማራጭ ሆኖ ተቀምጧል::

• በአሜሪካ በአብዛኛው ለመስኖ ሥራ የሚውለው የከርሰ ምድር ውኃ ሲሆን በቀን 53 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ጋሎን ውኃ ከ407 ሺህ 923 ጉድጓዶች ይወጣል::

• በአሜሪካ ለመስኖ የሚውለው ውኃ እ.ኤ.አ ከ1950 እስከ 1980 ባሉት 30 ዓመታት ብቻ በ68 በመቶ አድጓል:: ነገር ግን ከ1980 እስከ 1985 የመስኖ ተጠቃሚነት በአሜሪካ ጭማሬ ሳያሳይ ቆቷይል:: ከ1985 ወዲህ ግን በፈጣን ሁኔታ የመስኖ ሥራ እያደገ መሆኑ ተነግሯል::

• ከዋሽንግተን የውኃ ጉድጓዶዎች 80 ከመቶ ያህሉ ለመስኖ ሥራ ይውላሉ::

• ሕንድ ከአገራዊ የኃይል ፍጆታዋ 20 ከመቶው የሚውለው የጉድጓድ ውኃን ለመስኖ ለማውጣት ነው::

• ከዓለም የእርሻ መሬት በመስኖ እየለማ ያለው 20 በመቶ ብቻ ሲሆን 40 ከመቶውን የዓለም የምግብ ፍጆታ ይሸፍናል::

• ሕንድ 90 ከመቶ ውኃዋን ለመስኖ ስትጠቀም ቻይና ግን 65 ከመቶ ብቻ ነው ለመስኖ እየተጠቀመች ያለችው::

• በዓለም ላይ ከሚከናወነው የመስኖ ሥራ ከ15 እስከ 35 በመቶው ጊዜያዊ ነው::

• በአሁኑ ወቅት ያለው የመስኖ ውኃ አጠቃቀም ሳይሻሻል ከቀጠለ በ2030 ላይ የሚኖረውን ሕዝም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ተጨማሪ ሁለት ሺህ ኪሎ ሜትር ኩብ ውኃ ያስፈልጋል:: ምንጭ - http://www.seametrics.com

5?መርሻ እንየው በዳባት ወረዳ ደቋ ቀበሌ በ1982 ዓ.ም ነው የተወለደው:: መርሻ እንደ ታላላቆቹ የመሬት ሽግሽግ በተደረገበት ዘመን ባለመወለዱ ወይም ለአቅመ አዳም ባለመድረሱ የእርሻ መሬት አላገኘም:: ወላጆቹ ግን ልጃቸውን በወግ በማዕረግ ድረው ጎጆ እንዲመራ ሩብ (አንድ ቃዳ) መሬት ሰጥተውታል::

ወላጆቹ የሰጡትን ሩብ መሬት ይዞ ትዳር የመሠረተው መርሻ ዓይኑን በዓይኑ ማየት ሲጀምር ግን ያች ሩብ ሄክታር መሬት አልበቃችውም:: “እንኳን ልጅ ተጨምሮ ሩብ ሄክታር መሬት ለቤት መሥሪያና ለባልና ሚስት መተዳደሪያም አትበቃም:: መቸም መሬትን ጫፍና ጫፉን ይዘህ በመለጠጥ አታሰፋውም:: እና ኑሮ እየከበደኝ፣ የማደርገው እየጨነቀኝ፣ ትዳር መያዜንም እየጠላሁት መጣሁ” ይላል መርሻ ያለፈ ኑሮውን ሲያስታውስ::

በዚህ የተነሳ ተጨማሪ የእርሻ መሬት ባለማግኘቱ የሚሠራውና ቤተሰብ የሚመራበት መተዳደሪያ ግራ ገብቶት የአንዳንድ አቅመ ደካሞችን መሬት በመከራዬት ለእኩል በማረስ ሕይወቱን መምራት ጀመረ:: “መሬት በጣም ውድ ስለሆነ አንዳንዴ ለእኩል ያረስኩትን መሬት ሌላው ‘በሲሶ ወይም በሩብ አርስላችኋለሁ’ እያለ ይወስድብኛል:: በዚህ ሁኔታ ለእኩል ማረስም እየከበደ መጣ” ሲል የአቅመ ደካሞችንና በሬ የሌላቸው ሰዎችን መሬትም ለማረስ መቸገሩን ያስታውሳል::

በ2004 ዓ.ም ግን ለመርሻ እንየውና ለሌሎችም የዳባት ወረዳ ወጣቶች አንድ አዲስ ተስፋ ብቅ አለ፤ በአካባቢው የሚገኙ መሬት አልባ ወጣቶች ከወል መሬቶች ላይ የተወሰነ የእርሻ ቦታ እንዲያገኙ በማድረግ በመስኖ የማሰማራት ተግባር በወረዳው አነሳሽነት ተጀመረ:: “በቀበሌ አመራሮችና በነዋሪዎቹ መሬት አልባ ወጣቶች ተመለመልን፤ የተወሰነ ስልጠናም ተሰጠን:: ከዚያ በመስኖ ሥራ ለመሠማራትና ኑሯችንን ለማሻሻል ያለን ፍላጎትና ችግራችን ታይቶ ዛሪካርና ወንዝ አካባቢ ለ46 ወጣቶች 15 ሄክታር የወል መሬት ተሰጠን” ብሏል መርሻ::

ለእነመርሻ የተሰጣቸው መሬት ጥቁር አፈር በመሆኑ ለመስኖ ሥራ የተመቼ ሆነ፤ ጥቁር አፈር ውሀ የመቋጠር ፀባይ ስላለውና በቀላሉ ስለሚረጥብ:: የቢራ ገብስ፣ ሽንኩርትና ድንች ያመርታሉ:: የግብርና ባለሙያዎች ተከታታይ ምክርና ትምህርት እየሰጧቸው፣ ምርጥ ዘርና

ሌሎችም የግብርና ግብዓቶች እየቀረቡላቸው በቦታው ላይ በዓመት ሦስት ጊዜ ማምረት ጀመሩ:: “በአጠቃላይ በ15 ሄክታሩ መሬት በዓመት ከ300 እስከ 400 ኩንታል እንደ ግብዓት አጠቃቀማችን እናመርታለን” የሚለው ወጣቱ መርሻ በዚህ መስኖ ላይ ተመርኩዞ አሁን ላይ አምስት ቤተሰብ በበቂ ሁኔታ ያስተዳድራል::

ሌሎችም እንደርሱ የእርሻ ቦታ ያገኙ ወጣቶች በተሰጣቸው ውስን ቦታ ላይ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ለመምራት የሚያስችላቸውን ገቢ እንዲያገኙ ከዛሪካርና ወንዝ መለስተኛ የመስኖ ፈለግ

(ቦይ) በመንግሥት ወጭ ተሰርቶላቸው ውኃው እስከ ማሳቸው አብዛኛው ክፍል መድረሱን ገልጿል:: በዚህም በተለይ የቢራ ገብስ በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውን መርሻ ነግሮኛል:: “ድሮም ሩብ ሄክታር መሬት ነበረኝ፤ አሁን የተጨመረን የመስኖ ቦታም ድርሻዬ ከሩብ ብዙም አይበልጥም:: ግን የማመርተው የቢራ ገብስ ስለሆነና በመስኖ በዓመት ሦስት ጊዜ ስለማመርት ጥሩ ጥቅም እያገኘሁ ነው፤ አምስት ቤተሰቦቼን በበቂ ሁኔታ እያስተዳደርኩበት ነው” ብሏል::

የተለመደውን ገብስ በሚያመርትበት ጊዜ የምርታማነት ደረጃው አነስተኛ እንደነበር የሚናገረው መርሻ የቢራ ገብሱ ግን በምርታማነት ደረጃም በገበያ ያለው ተፈላጊነትም በእጅጉ ያደገ በመሆኑ ተጠቃሚ እንደሆነ ያስረዳል:: “በመስኖ ስናመርት ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ በአግባቡ እንጠቀማለን፣ አረም በወጣ ቁጥር ደጋግመን እናርማለን :: ምርጥ ዘሩ በሄክታር ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ይሰጣል:: በዚህም የተሻለ ምርት እያገኘን ነው:: የገበያ ትስስርም ከግብርና ምርት አቅራቢ ድርጅቶችና ከጎንደር ብቅል ፋብሪካ ጋር ተፈጥሮልናል” በማለትም ተጠቃሚነታቸው

እያደገ እንደሆነ ያብራራል::መርሻ አሁን ያገኛትን የመስኖ

ቦታ ተጠቅሞ ጥሪት መቋጠር እንደጀመረ ሲናገርም “በ2007 ዓ.ም 50 ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት ሠርቻለሁ፣ ሁለት ላሞች፣ አንድ በሬ እና ስድስት እናት በጎች አሉኝ፤ ወደ ዘጠኝ ሺህ ብር ደግሞ ባንክ አስቀምጫለሁ:: አሁን ማሳ ላይ ካለው ገብስም ጠቀም ያለ ገንዘብ አገኛለሁ ብዬ እየጠበኩ ነው:: አሁን ያለውን ገብስ እንዳነሳሁ ደግሞ ሚያዝያ ላይ ሽንኩርት እተክልበታለሁ፤ በአጠቃላይ በመስኖው በጣም ተጠቃሚ ነኝ፤ ሕይወቴንም እየለወጠው ነው” ብሏል::

ሩብ + ሩብ =

መርሻ እንየውበመስኖ የቢራ ገብስ በማምረት የተሰማራ ወጣት

በመስኖ የቢራ ገብስ ከሚያመርቱ ወጣቶች ከተሰበሰበው 89 ኩንታል የቢራ ገብስ ምርጥ ዘር ከፊሉ

(አብርሃም በዕውቀት)

በደቋ

ቀበሌ

ዛሪካ

ርና ወ

ንዝ ዳ

ር የተ

ደራጁ

ወጣ

ቶች

በመ

ስኖ ያ

ለሙት

የቢ

ራ ገብ

ስ በየ

ካቲት

ወር

2008

ዓ.ም

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 18 ከተማ ልማትከአብክመ ከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረበ

አብርሃም በዕውቀት

በየካቲት 14 ቀን 2008 ዓ.ም የበኩር ጋዜጣ ዕትም በዚህ ዓምድ “የአዲ አርቃይን ውኃ ውኃ በላው” በሚል ርዕስ የአዲ-አርቃይ ከተማን የንጹሕ መጠጥ ውኃ እጥረት፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ያደረገውን ጥረትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን መዘገባችን ይታወሳል:: በዘገባው ላይ ምላሽ የሰጡት በተለይ ግንባታውን እያከናወነ ያለው የአማራ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) የአዲ-አርቃይ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ኃላፊ “ሥራው በየካቲት ወር መጨረሻ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል” ብለውን ነበር::

የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን የሚያከናውነው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ተወካይ አቶ አማኑኤል መኬም ሥራው በአግባቡ እየተሠራ ቢሆንም የማጠናቀቂያ ጊዜ በውል ባለመገደቡ መጓተቱን ገልፀው የአጠቃላይ ሥራው 82 ከመቶ መጠናቀቁንና የቀረው ሥራም በአንድ ወር ውስጥ ማለቅ የሚችል እንደሆነ አስረድተው ነበር:: የአዲ-አርቃይ ከተማ ነዋሪዎችና አመራሮች ግን “በአንድ ወር ይጠናቀቃል የሚለው ነገር ለሚዲያ ፍጆታ ካልሆነ በቀር ሥራውን አያጠናቅቁትም፤ መንግሥት መፍትሔ ሊሰጠን ይገባል” ብለው ነበር::

በያዝነው የመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ስለአዲ-አርቃይ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር በተለይ ስለከሸፈውና ስለተጓተተው ሁለተኛ ፕሮጀክት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይመር ሀብቴን አነጋግረናቸው ነበር:: አቶ ይመር እንዳሉት ለአዲ-አርቃይ ከተማ ነዋሪዎች በእንስያ ወንዝ ላይ በ11 ሚሊዮን ብር ወጭ ተገንብቶ በሚያዝያ ወር ተመርቆ ሐምሌ ላይ ጎርፍ የወሰደው ግንባታ የዲዛይን ችግር አልነበረበትም::

የአዲ-አርቃይ ከተማ የውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ ጌትነት እንደሚሉት ግን ግንባታው ከመጀመሪያም የዲዛይን ችግር የነበረበትና የአካባቢው ሰዎችም ያልተቀበሉት በኋላም አንድ ክረምት ማለፍ ሳይችል በውኃ የተወሰደ ነው:: የከተማዋ ውኃ አገልግሎት ጽ/ቤትም የንጹሕ መጠጥ ውኃ ግንባታውን እንዳልተረከበ ያስረዳሉ::

ያም ሆነ ይህ ግን በ2003 ዓ.ም ሚያዝያ ወር የተመረቀው የአዲ-አርቃይ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ውኃ በልቶት ማንም ሳይጠየቅበት ቀርቷል:: ይህንን ተከትሎም መንግሥት የዜጎቹን የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግር ለመቅረፍ በ2007 ዓ.ም እንደ አዲስ ግንባታ በእንስያ ወንዝ ላይ እንዲካሄድ አድርጎ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውኃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አሠሪነትና በአውስኮድ ሥራ ተቋራጭነት ሥራ ተጀምሯል:: የተጀመረው ሥራም መጓተቱን ያመኑት ምክትል ኃላፊው አቶ ይመር “የቀረው ሥራ በጣም ትንሽ ነው፤ ከዚህ በፊት መዘግዬት የተፈጠረው የኤሌክትሮ ሜካኒክ ዕቃዎች ከውጭ ሲገቡ ረዥም የግዥ ሂደትና ጊዜ በመፍጀታቸው ነው:: አሁን ግን የቀረው አሸዋ ማንጠፍ ብቻ ስለሆነ ሥራው እስከ መጋቢት 20 ይጠናቀቃል” በማለት በመጋቢት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ገልፀውልን ነበር::

ውኃሽታ የሆነው

የውኃ

ነገር ግን ቃል እንደተገባው የአዲ-አርቃይ ከተማ ነዋሪዎች እስካሁን ውኃ አላገኙም:: በዚህ ሁኔታ መቼ እንደሚያገኙም አይታወቅም:: ነዋሪዎች አሁንም ውኃ በወረፋና በኮታ በተሽከርካሪ እየታደላቸው

እንደሆነ የውኃና ፍሳሽ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጁ አቶ ደረጀ ጌትነት ከሰሞኑ በስልክ ነግረውናል:: እርሳቸው እንዳሉት በየካቲት ወር መጨረሻ እንደሚጠናቀቅ የተነገረለት የእንስያ ወንዝ ፕሮጀክት አሁንም ዳር አልደረሰም:: “ፕሮጀክቱ ላይ ለውጥ አለ ከተባለ አሸዋ በአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር ተገዝቶ ከወንዙ ዳር ለአደጋ ተጋልጦ መቀመጡና ሁለቱ ጀነሬተሮች ውኃ መግፋት እንደሚችሉ መሞከሩ ብቻ ነው:: በላቦራቶሪ ተፈትሾ ጥራቱ ገና ያልተረጋገጠ በመሆኑ አሸዋውን ወደ ማጣሪያው የማስገባት ሥራው አልተጀመረም:: አሸዋውም እንዲመጣ የታዘዘው በከረጢት ታሽጎ ነበር፤ ግን እንዲሁ በክፍት መኪና ተጭኖ ገብቷል:: ያም ሆኖ በበልግ ዝናብ ምክንያት ለሚከሰት ጎርፍ ተጋልጦ

አሸዋው ወንዝ ዳር ይገኛል” ብለዋል አቶ ደረጀ::የአዲ-አርቃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ

ሰርካለም ወርቄም የሥራ አስኪያጁን ሀሳብ ይጋራሉ:: እርሳቸው እንደሚሉት የክልሉ ውኃ መስኖና ኢነርጂ

ልማት ቢሮ ፕሮጀክቱ እንዲጠናቀቅ ከማድረግ ይልቅ ሰበቦችን እየደረደረ በዚያ ላይ ሕዝቡን የማይሆን ተስፋ እየሰጠ ነው:: “በየካቲት ወር መጨረሻ እናጠናቅቃለን ብለው መጋቢት 20 ድረስ በፕሮጀክቱ ላይ ለውጥ አለማምጣት የሚገርም ነው፤ ይህንን እያየም ሕብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እያጣ ነው:: ችግሩ ሰፊ የመልካም አስተዳደር ችግር ከመሆን አልፎ የማህበራዊ ቀውስ ምንጭም እየሆነ ነው” ብለዋል::

በአማራ ውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውሥኮድ) የምዕራብ አማራ ኮንሥትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ዶክተር ደረጀ ተስፋሁንም ልክ እንደ አቶ ይመር ሁሉ የአዲ-አርቃይ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት እስከ መጋቢት 20 ቀን 2008 ዓ.ም ይጠናቀቃል

በማለት በመጋቢት ወር መጀመሪያ ቃል ገብተው ነበር:: ዶክተር ደረጀ የሲቪል ሥራው በነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም ተጠናቅቆ የኤሌክትሮ ሜካኒክ መሳሪያዎች እስኪመጡ እስከ ጥር 2008 ዓ.ም ድረስ ሥራ ቆሞ መቆየቱንም አስታውሰዋል::

አሁን ግን የኤሌክትሮ ሜካኒክ ሥራውም ተጠናቅቆ የማጣሪያ አሸዋውም ከአዲግራት መጥቶ ከቦታው እንደደረሰም ዶክተር ደረጀ ተናግረዋል፤ (ምንም እንኳ በየካቲት 14 ዕትማችን ላይ ያነጋገርናቸው የፕሮጀክቱ የአውሥኮድ ተጠሪ

አሸዋው ከድሬዳዋ ሊመጣ መኪና መላኩን ነግረውን የነበረ ቢሆንም):: ዶክተር ደረጀ እንዳሉት የአሸዋው ጥራት መፈተሽ ስላለበት ለአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ተሰጥቷል፤ ውጤቱ እንደደረሰም በቀናት ውስጥ አሸዋ የማንጠፉ ሥራ ተሠርቶ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለው ነበር::

የማማከር ሥራውን እያከናወነ የሚገኘው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች ድርጅት የእንስያ ወንዝ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የማማከር አገልግሎት ሰጭ አቶ አማኑኤል መኬ ባለፈው ረቡዕ በስልክ ስለአሸዋው ሁኔታ ጠይቀናቸው “አሸዋው መጥቶ ከግንባታ ቦታው ደርሷል፤ ነገር ግን የጥራት ፍተሻ ውጤቱ እስካሁን አልደረሰንም፤ ስለሆነም ሥራውን ማከናወን አልተቻለም” ብለዋል::

የአዲ አርቃይ ከተማ ነዋሪዎች ከ77 ዓመት በፊት ጣሊያን ከሰራው ቧንቧ ከእንባ ባልበለጠ መጠን የሚወርድ ውኃ በወረፋ ሲቀዱ

ገጽ 19በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ከዓለም አካባቢ

አጫጭር ዜናዎች

ወደ ገጽ 29 ዞሯል

(ጌትነት ድልነሳ)

አብርሃም አዳሙ

ወደ ገጽ 29 ዞሯል

ቻይና ከሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደምትፈልግ ተነገረ::

ቻይና ምጣኔ ሀብቷን የበለጠ ለማፋጠንና ፖለቲካዊ ተሰሚነቷንም ከፍ ለማድረግ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በተናጠልና በጋራ እያጠናከረች ነው:: ከሰሞኑም ከጐረቤት ሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ የእርሻና የደን ሚኒስትሯን ወደ ካርቱም ለመላክ መዘጋጀቷን ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል::

እንደ ዘገባው ከሆነ ሚኒስትሩ

የፓኪስታን ባለሀብቶች በታንዛኒያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት መፈለጋቸው ተነገረ::

በቀደሙት ዓመታት በተለያየ ምክንያት የዓለምን ባለሀብቶች ቀልብ መግዛት ያልቻለው ምስራቅ አፍሪካ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የባለሀብቶች መዳረሻ እየሆነ ነው:: ከሰሞኑ የአሶሼትድ ፕሬስ ዘገባ ይፋ እንዳደረገው የፓኪስታን ባለሀብቶች በምስራቅ አፍሪካዊቷ ታንዛኒያ በኃይል ልማት፣ በቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በሰፋፊ የእርሻ ልማት ለመሳተፍ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል::

የፓኪስታን ባለሀብቶች በታንዛኒያ ኢንቨስት ሊያደርጉ ነው

ቻይና ከሱዳን ጋር ያላትን ግንኙነት ልታጠናክር ነው

መ ቀ መ ጫ ቸ ው ን ሶማሊያ አድርገው በህንድ ውቅያኖስ ላይ የባህር ላይ ውንብድና ሲፈጽሙ የነበሩ ዘራፊዎች ጉዳያቸው በፈረንሣይ ፍርድ ቤት መታየት ጀመረ::

ጐረቤት ሶማሊያ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1900 መባቻ ጀምራ በትርምስ ውስጥ ትገኛለች::

በሱዳን በሚኖራቸው ቆይታ ሁለቱ ሀገራት በግብርናው ዘርፍ በጋራ በሚሰሩባቸው መስኮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል:: ይህ ደግሞ ሱዳን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በምታደርገው ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተነግሯል:: ሚኒስትሩ ከዚህ ጐን ለጐን የሁለቱ ሀገራት ምጣኔ ሀብት በሚጠናከርበትና ልምድ በሚለዋወጡበት ዙሪያ ከካርቱም ባለስልጣናት ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል::

በታንዛኒያ የፓኪስታን ተወካይ አሚር ካህን የፓኪስታን ባለሀብቶች ወደ ዳሬ ሰላም በማቅናት ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከንግድና ኢንዱስትሪ ኃላፊዎች ጋር በሚሰማሩባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች መወያየታቸውን ተናግረዋል:: ከውይይቱ በኋላም “ባለሀብቶቹ በእርሻ፣ በሀይል ልማትና በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ለመሰማራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል“ ብለዋል:: የታንዛኒያ መንግስትም ለባለሀብቶች የተቻለውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል መግባቱን ካህን ተናግረዋል::

የባህር ላይ ወንበዴዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ጌትነት ድልነሳ

ቱሪዝም

ቀይ መብራት

የበዓለም አቀፍ ደረጃ በየቀኑ ከ100

ሺህ በላይ በረራዎች ይደረጋሉ:: ይህ አሀዝ በድግግሞሽ የሚደረግ በረራን የሚያካትት ሲሆን የአንድ ጊዜ በረራ ቁጥሩ ግን ከ50 ሺህ እስከ 80 ሺህ እንደሚገመት የብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ መረጃ ያመለክታል:: በየቀኑም በእነዚህ በረራዎች ከስምንት ሚሊዮን በላይ መንገደኞች ይስተናገዳሉ:: በዚህ ምክንያት የአየር በረራ ኢንዱስትሪውን ከሌሎች የትራንስፖርት ዘርፎች ተመራጭና ግዙፍ ያደርገዋል::

በተመሣሣይም የባቡር የመጓጓዣ ስልት ተጠቃሚ በሆኑ ሀገራት ዘንድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጐች ድንበርና

ከተማ ያቋርጡበታል:: እነዚህ ሁለት የመጓጓዣ አይነቶች ደግሞ በዓለም ላይ ተመራጭና ፈጣን በመሆናቸው በየቀኑ የሚያጓጉዙት ህዝብ ቁጥር እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አይደለም:: በተለይም ጐብኝዎች እና የንግድ ሠዎች የእነዚህ የመጓጓዣ ዘርፎች ዋነኛ ደንበኞች እንደሆኑ ይነገርላቸዋል:: በየአመቱም ከአንድ ቢሊዮን በላይ ጐብኝዎች በተለያዩ ሀገራት ይንቀሣቀሣሉ:: የአውሮፓ ሀገራት ደግሞ ዋነኛ የጐብኝዎች መዳረሻ ናቸው:: በተለይም እንደነ ፓሪስና ሮም ያሉት ከተሞች ለመስህብ ብቻ የተፈጠሩ ይመስላል:: በየአመቱ በርካታ ጐብኝዎችን በማስተናገድ ተጠምደው ያሣልፋሉና::

ዓለም አቀፉ የቱሪዝም ድርጅት እንደሚለው በቱሪዝሙ ዘርፍ በየዓመቱ

ከአንድ ትሪሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ይንቀሣቀሣል:: ይህ መጠን ድርጅቱ በፈረንጆቹ 2030 ካስቀመጠው የአንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን የጐብኝዎች ቁጥር ትንበያ አንፃር ሲታይ በየአመቱ ከፍተኛ ዕድገት እያሣየ መሄዱ እንደማይቀር እሙን ነው:: የዚህ እድገት ከፍተኛው ተጠቃሚ ደግሞ የመጓጓዣው ኢንዱስትሪ ነው::

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት እነዚህ ሁለት የአለማችን ግዙፍ የምጣኔ ሀብት መሠረቶች ከፍተኛ ሥጋት ተደቅኖባቸዋል:: በአለም ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሠደደና መልኩን እየቀያየረ በመጣው የሽብር ጥቃት ውስጥ ጉዞና ጉብኝት ተመራጭ የጥቃት ኢላማ እየሆኑ መምጣታቸውን እየታዘብን ነው::

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 20 ማስታወቂያ

በአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅትና በክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ትብብር የሚዘጋጅ

የግንባታውን ኢንዱስትሪ ከሙስና በመከላከል ማዘመንና ማሣደግ

ክፍል አስራ አንድ

ይህም በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ ሂደት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ፖሊሲውም ሆነ ስትራቴጂዎቹ እንዲሁም ተያያዥ ህግጋት እንዲሻሻሉ የሚያግዙ ሀሣቦችን በማመንጨት ሠነዶቹ ይበልጥ ኪራይ ሰብሣቢነትን እንዲከላከሉና ተገልጋዩን የህብረተሰብ ክፍል የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ እድል መፍጠር ይገባቸዋል:: በርካታ መረጃዎች እንደሚጠቁሙትም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ መሠረት የሚያደርጋቸው የህግ ማዕቀፎችና ስትራቴጂዎች በሂደት ሊሻሻሉና ይበልጥ ጠቃሚ የሚሆኑት በሰነዶቹ ይዘት፣ አተገባበርና አጠቃቀም ዙሪያ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤው ኑሮአቸው የራሳቸው ሲያደርጉት ብቻ ነው::

7.2. ተያያዥ የህግ ማዕቀፎች ስለማስፈላጋቸው

ከላይ ለመግለፅ እንደተሞረው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ፖሊሲ ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገው፣ የወጣው ፖሊሲ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን ከተፈለገ ተያያዥነት ያላቸው የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችም ያስፈልጋሉ:: እንደሚታወቀው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እጅግ ሰፊና ዘርፈ ብዙ በመሆኑ እንደየዘርፉ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ያሹታል:: የህግ ማዕቀፎች የተባሉትም አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ማለታችን ነው:: በመሆኑም የኢንዱስትሪውን የተለያዩ ዘርፎችን የሚመለከቱ በፌዴራልም ሆነ በክልሎች የተለያዩ አዋጆች፣ ደንቦችን መመሪያዎች ወጥተውና ፀድቀው በተግባር ላይ ይገኛሉ::

የክልል መንግሥታት ያዘጋጅዋቸው ኮንስትራክሽንን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎች ቢኖሩም በዋናነት መሠረት ተደርገው የሚወሠዱት

በፌዴራል የሚጋጁት ህጐች ናቸው:: ለአብነት ያህል የሚተሉትን አዋጆች መጥቀስ ይቻላላ:: ይኸውም የኢትዮጵያ የህግ አዋጅ ቁጥር 624/2ዐዐ1 አንዱ ሲሆን ይህንኑ ተከትሎ የወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የህንፃ ደንብ ቁጥር 243/2ዐዐ3 በዋናነት ይጠቀሳሉ:: የግንባታ ተግባራት መሬት ላይ በመሆኑ የመሬት አጠቃቀምን በተመለከተም የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ አዋጅ ቁጥር 731/2ዐዐ4 ወጥቶና ፀድቆ ወደሥራ እንዲገባ ተደርጓል:: ከኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በተያያዘም ሌሎች አዋጆች ከመውጣታቸው በተጨማሪም የአዋጆቹ ማስተግበሪያ ደንቦችና መመሪያዎች ተዘጋጅተውላቸዋል:: ከዚህ አልፎም የየዘርፎቹ ባለሙያወች ሊገለገሉባቸው የሚችሉ ማንዋሎችና ስታንዳርዶችም ተዘጋጅተውላቸዋል::

የሁሉንም የህግ ማዕቀፎች ይዘትና ገፅታ በዝርዝር መዳሰስ ባይቻልም በቀጥታ ከኢንዱስትሪው ጋር ግንኙነት ያለውን አዋጅ የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2ዐዐ1ን እንደሚከተለው መቃኘት እንችላለን:: ይህ አዋጅ በሰባት ክፍሎችና በ6ዐ አንቀጾች የተከፋፈለ ሲሆን በተለዩ አበይት አንቀጾች ሥርም በርካታ ንዑሣን አንቀጾች ተካተው ይገኛሉ::

በአዋጁ ክፍል አንድ “ጠቅላላ” በሚለው ርእስ ሥር የአዋጁ አጭር ርእስ እና በአዋጁ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉ ቃላትና ሀረጎችን የሚፈታው “ትርጓሜ” የሚለው ሁለተኛው አንቀጽ ይገኛሉ:: በዚህ ክፍል ከሚገኙት ሦስት አንቀጾች መካከልም የመጨረሻውና

በአንቀጽ ሦስት የተቀመጠው የአዋጁ የተፈፃሚነት ወሠን ነው::

የአዋጁ ክፍል ሁለት “አስተዳደር” በሚለው አብይ ርእስ ሥር ደግሞ ከ4-28 የሚገኙትን 25 አበይት አንቀጾች ተካተው ይገኛሉ::

በክፍል ሁለት ሥር ከተዘረዘሩት አስተዳደር ነክ አንቀጾች መካከልም፡-• ማመልከቻና ኘላን ስለማቅረብ፣• የኘላን ስምምነትና ኘላንን ስለማፅደቅ፣• ስለ ኘላን መገምገሚያ ጊዜና ኘላንን ውድቅ

ስለማድረግ፣• ስለ ግንባታ ፈቃድና ኘላን ፀንቶ ስለሚቆይበት

ጊዜ፣• ስለ ህንፃ ሹም፣ ውክልናና ስለ ይግባኝ፣• ትእዛዝ ስለማስከበርና ስለማስታወቂያ፣• ስለ ተቆጣጣሪወችና ስለ ህንፃ መጠቀሚያ

ፈቃድ፣• ስለ ኘላን መገምገሚያ ክፍያና ኘላን ማፅደቂያ

ክፍያ ወዘተ የሚሉ ነጥቦች ተቀምጠዋል::በአዋጁ ክፍል ሦስት “የመሬት አጠቃቀም

ተጓዳኝ ጥናቶችና ዲዛይኖች” በሚለው ዋና ርእሰ ጉዳይ ሥርም ከአንቀፅ 29 እስከ 34 ሰባት ዋና ዋና/አበይት/ አንቀጾች ተካተውበታል:: በዚህ ክፍል ስር ያሉት አንቀጾች ከያዟቸው ነጥቦች መካከልም፡-• ስለ መሬት አጠቃቀምና ስለ ተጓዳኝ ጥናቶች

እንዲሁም ስለ ዲዛይኖች፣• በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው

ጥንቃቄዎችና በግንባታ ቦታ ላይ ስለሚናወኑ ሥራዎች፣

• ስለ አርኪቴክቸርና ስለ ስትራክቸር፣ ወዘተ የሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች ተዘርዝረዋል::

የአዋጁ ክፍል አራት “የውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን” በሚለው አብይ ርእስ ጉዳይ ሥር ከ36-43 ያሉትን 8 አንቀጾችን ይዟል::

በዚህ ክፍል ሥር ከተጠቀሱት ዋና ዋና አንቀጾች መካከልም፡-

• የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ስለሚደረጉ ዝግጅቶችና ስላለው አቅርቦት፣

• ስለ ፍሳሽ አወጋገድና ተቀባይነት የሌላቸውን ፍሳሾች ስለመቆጣጠር፣

• ስለ ኢንዱስትሪ ዝቃጭና ስለ ውሃ አልባ ቆሻሻዎች ማስወገጃ፣

• የጐርፍ ውሃ ስለማስወገድና የመሣሠሉት ነጥቦች ተዘርዝረዋል::

በክፍል አምስት “እሳት መከላከልና የእሳት ማጥፊያ ተከላ” በሚለው ዋና ርእሰ ጉዳይ ሥር እንዲሁ ከአንቀጽ 44 እስከ 46 የተዘረዘሩት ሦስት አንቀጾች ይገኛሉ:: በነዚህ 3 አንቀጾች የሚመለከቱት የሚከተሉት ነጥቦች ናቸው::• ስለ ጠቅላላ መስፈርት፣• ስለ እሳት ማጥፊያ ተከላና• ስለ እሳት መከላከያ የውሃ አቅርቦት::

በአዋጁ ክፍል ስድስት “የሕንፃ ሥራ ህጐችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ስለመጣስ” በሚለው አብይ ርእስ ሥር ደግሞ ከአንቀጽ 44-55 ያሉትን 1ዐ ነጥቦች /አንቀጾች/ ተካተዋል:: በዚህ ክፍል ሥር የተዘረዘሩት አበይት አንቀጾችም የሚከተሉትን ነጥቦች ይዘዋል::• ስለ ወንጀል ህጉ ተፈፃሚነትና የግንባታ ፈቃድን

አለአግባብ ስለመስጠት፣• የመቆጣጠር ግዴታን ባለማክበር ህገወጥ

ግንባታ እንዲከናወን ስለመርዳት እና ባለ ጉዳይን አለአግባብ ስለማጉላላት፣

• መረጃ ስለመደበቅና የሳሳተ መረጃ ስለመስጠትና ደረጃው የማይፈቅድለት ግንባታ ስለማከናወን፣

• ደረጃውን ያልጠበቀ ግንባታ ስለማከናወን እና የአማካሪነት የሙያ ሃላፊነትን ስለመጣስ፣

• በመንግሥት ሠነዶች አለአግባብ ስለመገልገል አና ስለሙያና ሥራ ፈቃድ እገዳ የሚሉ አንኳር አንቀጾች ይገኛሉ::

ይቀጥላል

ቢሆንም ከቱሪዝም ሀብት ግን ተጠቃሚ አይደለም::ወ/ሮ አስማሩ ካሳ የተባሉ ሌላዋ የወረዳው ነዋሪ

እንደሚሉት ደግሞ የመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ በሰፊው የማስተዋዎቅ ሥራ አለመስራትና ለዘርፉ ትኩረት አለመስጠት ተጠቃሚ ላለመሆናቸው ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው:: የበየዳ ወረዳ በርካታ የስሜን ተራሮች፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ ቀይ ቀበሮና ሌሎችም ብርቅዬ የተፈጥሮ መስህቦች እንዲሁም ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶች መገኛ ቢሆንም ተጠቃሚ አለመሆናቸው እንዳሳዘናቸው ወ/ሮ አስማሩ ተናግረዋል::

ወረዳው በ15ኛው ክፍለ ዘመንና ከዚያ በፊት የተሠሩ ገዳማት፣ የራስ ገብሬና ጣይቱ ብጡል ቤተ-መንግሥት፣ እስከ 40 ክንድ ርዝመት ያለው የፈረስ ጭራ መገኛ ሲሆን ዓመታዊ የቱሪስት ፍሰቱ ግን ዝቅተኛ መሆኑን በበየዳ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የቅርስና የመስህብ ሀብቶች ጥናት ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ሙሉጌታ ዳምጤ ይናገራሉ:: የበየዳ ወረዳ “የቅርስ ክምችት ጓዳ” በሚል የሚታወቅ፤ እጅግ በርካታ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት፣ የግድግዳ ላይ ስዕሎች፣ የደንጋይ ላይ ጽሑፎች፣ ከብር፣ ከወርቅና ከዕንቁ የተሠሩ ውድ ጌጣጌጦችና ቁሳቁሶች የሚገኙበት ቢሆንም የዚያን ያህል ግን ከዘርፉ

ተጠቃሚ እንዳልሆነ አቶ ሙሉጌታ ያብራራሉ::

እርሳቸው እንደሚሉት ወረዳው በቱሪስቶች በብዛት የማይጎበኘው ለጉብኝት የሚሆን መሠረተ ልማት የሌለው በመሆኑ ነው:: ችግሮቹንም በመለዬት ለሚመለከተው አካል አሳውቀው መፍትሔዎችን እየጠበቁ እንደሆነም አቶ ሙሉጌታ ያስረዳሉ::

የሰሜን ጎንደር ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ባለሙያው አቶ ሀብቱ ዓለሙ በበኩላቸው ዞኑ የበየዳ ወረዳን ከቱሪዝም ሀብት ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ይናገራሉ::

(ዝርዝር ዘገባውን በገጽ 8 ይመልከቱ)በ1414 ዓ.ም የተተከለው እና በርካታ ቅርሶችን የያዘው የበየዳ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

ከገፅ 1 የዞረ

በሀብታችን ...

ገጽ 21በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. የሔዋን ገጽየሔዋን ገጽከዚህም ከዚያም

ወደ ገጽ 28 ዞሯል

ሙሉ ዓብይ

ቁጭትያለውንበ

የምንገኘው በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጤ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀርባ በተንጣለለው ሜዳ

ልምላሜን ተላብሰው ዝርፍፍ ብለው ከሚገኙት ዛፎች ጥላ ስር ነው:: የመገኘታችን ምስጢርም የበጤ ቀበሌ ሴቶችንና የአርብ ከስአት በኋላ ቁርኝትን አይተን ለሌሎች ለማካፈል ነው::

በቀበሌዋ የሚገኙ አንድ ሺህ 43 ሴቶች በ175 አንድ ለአምስት እና በ37 የልማት ቡድን ተደራጅተዋል:: እናም ዘወትር አርብ ሴቶች የከፋ ችግር ካልገጠማቸው በቀር ከበጤ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀርባ አይለዩም፤ ሴቶቹ በዚህ ቦታ በመገናኘት በችግሮቻቸው ዙሪያ ይመክራሉ፣ ሳምንታዊ ቁጠባ በሳጥናቸው ያስገባሉ፣ በጐልማሶች ትምህርት እውቀት ይቀስማሉ፣… ለነዚህ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎችም ሴቶቹ ከየጐጣቸው ሀሩሩ ሳይበግራቸው ተከታትለው በሰዓቱ ተገኝተዋል::

እኛም ሴቶቹ የቁጠባ ገንዘባቸውን ሲያስገቡ፣ ሲማሩ፣… አስተዋልን:: ከአባላቱ መካከል ወይዘሮ ሀዋ ኢብራሂምን ትምህርት እንዴት ነው? ስንል ጠየቅናት:: “ጥሩ ነው፤ በፊት ምንም አላውቅ ነበር፤ ስልክ ለመደወል በልመና ነበር:: አሁን ግን ከስልኬ የሰው ስም አንብቤ ማውጣት፣ ቁጥር ሲሆንም ጽፌ መደወል ችያለሁ” አለችን::

በቁጠባ በኩልም የቀበሌዋ ሴቶች በየሳምንቱ አርብ እንደ አቅማቸው ከሁለት ብር እስከ 40 ብር ይቆጥባሉ:: ገንዘቡም ከመካከላቸው ባስ ያለ ችግር ያለባቸው ሴቶች ተለይተው በሦስት ወር ሰርተው እንዲመልሱ ይሰጣል:: በዚህ ሁኔታ ገንዘቡ እየተዘዋወረ ችግራቸውን ያቃልላል፤ የመቆጠብ ልምዳቸውንም ያዳብራል::

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከልም ወይዘሮ ሀሊማ አሊ አንዷ ናቸው:: የነ ወይዘሮ ሀሊማ የልማት ቡድን “ቢፍቱ” /ፀሐይ/ ይሰኛል:: የልማት

ማህበሩ አባል ከሆኑ አንድ ዓመት ከሰባት ወራት ያስቆጠሩት ወይዘሮ ሀሊማ ባለፈው ዓመት 550 ብር ብድር ወስደዋል:: በሚኖሩበት የኪራይ ቤት ውስጥ ዘይትና ብስኩት በመሸጥ የቤተሰቦቻቸውን የእለት ጉርስ መሸፈን ችለዋል::

ወይዘሮ ሀሊማ በመደራጀታቸው ተበድረው ሰርተው ከነበሩበት የችግር ኑሮ ከመውጣታቸው ባለፈ “በፊት መስራት እየፈለግሁ በገንዘብ እጦት የሚያጋድደኝ በማጣት እጅና እግሬን አጣጥፌ እውል ነበር:: በዚህም ለእለት ችግሬ እንጨት ለቅሜ በመሸጥ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ እገፋ ነበር:: አሁን ግን ያለምንም ሰቀቀን 80 ብር የቤት ኪራይ እከፍላለሁ:: ለቸገረው አበድራለሁ:: ለወደፊትም የራሴን ቤት የመስራት አላማ አለኝ” ይላሉ::

የቀበሌዋ ሴቶች ተደራጅተው የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከማሳደግና በጐልማሶች ትምህርት ከመሳተፍ ባሻገር በጤናው ዘርፍ ስር ሰዶ የቆየውን የአመለካከት ችግር መፍታት እንደቻሉም አመላካች ሁኔታዋች አሉ:: በተለይም በጤና ተቋም በሀኪም እርዳታ መውለድን እንደ መልካም አጋጣሚ መቁጠር መቻላቸው አንዱ ነው::

የበጤ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ ከዶ አህመድ አንደኛዋ በአደረጃጀቱ ተጠቃሚ ሴት ናቸው:: በቤትና በህክምና እርዳታ የመውለድን ሁኔታም እርሳቸው ልዩነቱን ሲገልጹ “ታላቅ እህቴ የልምድ አዋላጅ ነበረች:: አራት ልጆቸን እስከ ሶስትና አራት ቀን በማማጥ በቤት ውስጥ እህቴ አገላግላኛለች:: አራተኛዋ ልጄ ግን በአራተኛው ቀን ስትወለድ ታፍና ሙታ ነበር የወጣቸው” በማለት በቁጭት ዛሬ ላይ ያስታውሳሉ::

ወይዘሮ ከዶ ተደራጅተው ባገኙት ግንዛቤ አምስተኛ ልጃቸውን ደግሞ በጤና ተቋም በሀኪሞች እርዳታ በሰላም ተገላግለዋል:: የበፊቱንና የአሁኑን በማነፃፀርም ወይዘሮ ከዶ ሲናገሩ “አራተኛዋ

ልጄ ማደግ እየቻለች ታፍና ሞተችብኝ:: አሁንማ ቅድመ ወሊድ ምርመራ ሳደርግ ቆየሁ:: መውለጃየ ሲደርስ ደግሞ አምቡላንስ መጣና ጤና ጣቢያ ወሰዱኝ:: ከዚያም ቡና እየጠጣሁ “ወዲያውኑ ነው የተገላገልሁ፤ ከዛ በኋላም ገላየን ታጠብሁ፣ ምግቡ፣ ቡናው፣… የሚደረገው እንክብካቤ ያስደስታል:: በፊትማ ከቤት ስወልድ ሰውነቴን የምታጠብ ከሳምንት በኋላ ነበር:: አሁንማ በርግዝና ወቅት በሚደረግልን ምርመራ ደማችን ቢቀንስ፣ የጽንሱ አቀማመጥ ባይስተካከል፣… ሀኪሞች በህክምና ያስተካክሉልናል፤ ይመክሩናል:: የበፊቱን ሳስበው ተጐድተን ነው የኖርን:: አሁንማ ወልጀ፣ ገላየን ታጠቤ፣ ለልጅ ልብስ ተሸልሜ ነው ወደ ቤቴ የተመለስሁ!”

የበጤ ቀበሌ ሴቶች አደረጃጀት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት በርካታ ስራዎች ለማከናወን በትምህርት፣ በቁጠባ፣ በጤና፣… እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ማሳያ ነው:: እነዚህን የተገኙ ለውጦች ለማስቀጠልም ህግና ደንብ እንዳለው ለመገንዘብ ችለናል:: ለነዚህ ተግባራት እውን መሆንም የወንዶች አጋርነት ሌላው በጐ ጐን ነው::

የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ አልዩ አበጋርም ለሴቶች አደረጃጀቶች እንደ አመራርነታቸው እገዛ እንደሚያደርጉ አረጋግጠውልናል “አንድም እናት በወሊድ ምክንያት እንዳትሞት የቀበሌው አመራሮችና ሁሉም የቀበሌው ኗሪዎች በተገኙበት ወደ ጤና ተቋም ለማድረስ በሚደረገው ሂደት ሁሉ ከጐናቸው እንድንቆም ተስማምተናል:: አንዲት ሴት ከቤት ከወለደች አባዎራው በገንዘብ እንዲቀጣ የሚለውን ህገ ደንብም ተስማምተን ተፈፃሚ እንዲሆን አጽድቀናል” ይላሉ:: በዚህም “ምጥ ድንገት መጥቶነው፤ መንገድ ስንጀምር ነው”

ያለ ዕድሜ ጋብቻ ከ18 ዓመት በታች ያሉ ሁሉንም ፆታዎች ያጠቃልላል:: ዕድሜያቸው ለጋብቻ ሳይደርስ በቤተሰብ ፍላጐት የማጋባት ተግባር የተለመደ ቢሆንም ባሁኑ ወቅት እየቀረ ይገኛል::

ያለ ዕድሜ ጋብቻ ከትምህርት ገበታ ከማስቀረቱም በላይ በስነ - ተዋልዶ ስርዓት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ከፍትህ፣ ከፖሊስ፣ ከጤናና ከትምህርት ሴክተሮች ጋር በመሆን ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር መከላከል መቻሉን የግዳን ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት የህፃናት መብት ደህንነት እንክብካቤ ባለሙያ አቶ አብርሃም ሽመልስ ተናግረዋል::

ያለዕድሜ ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ባይባልም የሚሰጠው የግንዛቤ ትምህርት ህብረተሰቡ ጉዳቱን በመረዳት የዕድሜና የጤና ምርመራ በማድረግ ሲፈቀድለት የጋብቻ ስርዓት እንደሚፈፀም ገልፀዋል::

ከወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚህ ዓመት ከመጡ 29 የጋብቻ ይፈቀድልን ሴት ልጃ ገረዶች መካከል ስድስቱ እድሜያቸው ለጋብቻ የደረሰ ባለመሆኑ አልተፈቀደላቸውም ሲል የግዳን ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል::

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ

ሴት ተማሪዎች ተሸለሙ

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የቀበሌ 16 ሙሉ ሳይክል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ሽልማት ሰጠ::

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ እሸቴ አበራ እንደገለፁት በትምህርት ቤቱ ከሚማሩ ተማሪዎች

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ከወጡት 58 በመቶው ሴቶች ናቸው:: ለውጤቱ መምጣት የራሳቸው ተነሳሽነት፣ የመምህራን ልዩ ድጋፍና የቤተሰቦቻቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ርዕሰ መምህሩ ገልፀዋል::

አቶ አሊ ሙሃመድ የተባሉ የት/ቤቱ መምህር በሰጡት አስተያየት የተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ ዘዴና የተማሪዎች አደረጃጀት ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋፆኦ እንደነበራቸው ገልፀዋል:: ከተሸላሚ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ቤተልሄም ተስፋዬ በሰጠችው አስተያየት ትምህርት ቤቱ አጋዥ መጽሀፍትን በማቅረቡና ባደረገችው የዕለት ተዕለት ክትትሎች ውጤቷን እንዳሻሻለች ተናግራለች:: ሌላዋ ተሸላሚ ተማሪ ጽጌሬዳ እያሱ በበኩሏ “የትምህርት ቤቱ፣ የመምህራንና የቤተሰቦቼ ድጋፍ ለሽልማት አብቅቶኛል” ብላለች:: ዘገባው የጎንደር ከተማ አስተዳዳር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው::

ያለ ዕድሜ ጋብቻን ለመከላከል ካጋር

አካላት ጋር እየተሰራ ነው

የበጤ ቀበሌ ሴቶች እንዲህ ዘወትር አርብ ተሰብስበው ገንዘብ ይቆጥባሉ በጉዳዮቻቸው ዙሪያም ይነጋገራሉ

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 22 ለህፃናት ለህፃናት ከዚህም ከዚያምደረጀ አምባው

እንቆቅልሽ

1. ቀን ቀን ኩሊ ማታ

ማታ ጆሊ

2. ቀይ በሬ አዟሪ ነጭ

በሬ ቦርቧሪ

3. ትንሽ ልጅ ጢም

አጢማ

4. በልቶ የበላውን

የሚረሳ

የእንቆቅልሽ መልስ

1. ጫማ2. ምላስና

ጥርስ3. ብቅል4. ሆድ

ስዕሉን

በመሣል

ተለማመዱ

አንድ ለማኝ በመልካም አትክልት ውስጥ ብቻውን ሲመላለስ ሳለ እንዲህ አሰበ

“ሀብታም ሰዎች ከቶ እንዴት እብዶች ናቸው:: ብዙ ገንዘብ እያላቸው ስለ ምን በቃን አይሉም? እንደገናም ይፈልጋሉ፤ ለኔ እኮ አሁን አንድ ከረጢት ወርቅ ቢኖረኝ ይበቃኝ ነበር::” እያለ ያጉረመርም ጀመር:: እንዲህም እያለ ሲናገር ወዲያው አንዲት የተዋበች መልካም ሴት ወይዘሮ ታየችውና “እኔ ስሜ ዕድል ይባላል:: አሁን አንተን ላበለጽግ መጥቻለሁና ከረጢትህን ከፍተህ ያዝ ወርቅም እሞላዋለሁ፤ ግን ባንድ ነገር ብቻ እንድትጠነቀቅ አስታውቅሀለሁ::

ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? ትምህርትስ እንዴት ይዟችኋል? ከአሁኑ ጥናትን

ጠበቅ አድርጐ መያዝ የሰኔ ፈተና ሲመጣ ላለመደናገር ስለሚያግዝ የዕለቱን በዕለቱ ማጥናትና መከለስን አትረሱም አይደል? ጐበዞች!

ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ግንቦት 20 ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው አዲስ አምባ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያገኘናትን የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እናስተዋውቃችሁ::

ሰዊተ ካሴ ትባላለች:: የተወለደችው ጐንደር ከተማ ሲሆን ወላጆቿ ለስራ ወደ ባህር ዳር ሲመጡ ይዘዋት በመምጣት ትምህርቷን እዚሁ ባህር ዳር ጀምራለች:: ሰዊተ እስከ አምስተኛ ክፍል ድረስ ደረጃ በመያዝ ከክፍል ክፍል ተዘዋውራ አታውቅም ነበር:: ነገር ግን ጐበዝ ተማሪ የነበሩት ታላላቅ እህቶቿን ስታይና ሲደነቁ ስትሰማ እርሷም ጐበዝ በመሆን መደነቅ እንዳለባት ወሰነች::

ታላላቅ እህቶቿ እንዲያስጠኗት በመጠየቅ በየዕለቱ እህቶቿ ባወጡላት መርሀ ግብር /

• ሁሉም ህፃናት እንደተወለዱ የሚለዩት የቀለም ዓይነት ጥቁርና ነጭ ብቻ ነው::

• አንድ ደረጃ ስንወጣ ሁለት መቶ ጡንቻዎችን እናንቀሳቅሳለን::

• የአንድ ሰው የዓይን ኳስ እስከ 28 ግራም ይመዝናል::

• ከእያንዳንዱ ሰከንድ በኋላ አይናችንን እናርገበግባለን:: በለቅሶ ጊዜ አይናችን ሲርገበገብ እንባን ካይናችን ኳስ ላይ ይጠርጋል:: ይህም አይናችን በጥራት እንዲያይ ይረዳዋል::ምንጭ - ሲ ኤን ኤን

ሀሣብን መግለጽ

በበለጠ ሁኔታ በማጥናቷ 92 አማካይ ውጤት በማምጣት ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ መዛወሯን አጫውታናለች::

በትምህርት ቤቷ ልዩ ልዩ ክበባት ተሳትፎ የምታደርገው ሰዊተ በጐበዝ ተማሪዎችና በሴቶች ክበብ ስነ ጽሁፎችን በማቅረብ ትታወቃለች::

“በልዩ ልዩ የትምህርት ቤት ክበባት መሳተፍ ተማሪዎች ድፍረት ይዘው በሰው ፊት መቅረብ እንዲችሉ ይረዳል” የምትለው ሰዊተ በሰዎች ፊት ሀሣቡን በነፃነት መግለጽ የለመደ ተማሪ ወደፊትም ሀሣቡን ለመግለጽ እንደማይቸገር ትናግራለች::

የቴሌቪዥን ድራማ መመልከትና ኳስ መጫወት የሚያዝናናት ይሁን እንጅ “ብዙውን ጊዜ ፊልም በማየት ማሳለፍ በትምህርት ሰነፍ ስለሚያደርግ መዝናኛን እየመጠኑ በትምህርት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል” ትላለች::

ለወደፊቱ የሕክምና ዶክተር መሆን እንደምትፈልግ ራዕይ ያላት ሰዊተ ሕሙማንን መርዳት እንደሚያስደስታት ገልፃ፤ ራዕዯን ለማሳካትም ከአሁኑ ጀምራ ጊዜዋን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርቷ ጥሩ ደረጃ መድረስ እንዳለባት ታምናለች::

ቤተሰቦቿ በየጊዜው የተማረችውን በመመልከት ጥያቄ እንደሚጠይቋትና

ክትትል እንደሚያደርጉላት የተናገረችው ሰዊተ የወላጅ ክትትል ለልጆች ትልቅ ቦታ መድረስ ዋና ጉዳይ መሆኑን በታላላቅ እህቶቿ ማየቷን አጫውታናለች:: ታላላቅ እህቶቿ በከፍተኛ ውጤት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም (ዩኒቨርሲቲ) ገብተው በመማር ላይ ለመሆናቸው ዋናው ምክንያት የወላጅ ክትትልና ድጋፍ መሆኑንም አጫውታናለች::

ልጆች ካነባችሁት ታሪክ ቁም ነገር አገኛችሁ? ጐበዞች! በትምህርት ቤት ውስጥ በልዩ ልዩ ክበባት በመሳተፍ ንግግርን መልመድ ሀሣብን በነፃነት ለመግለጽ ይረዳልና እናንተም ንግግር ማድረግን ተለማመዱ::

ዕድል እና ለማኝ

ከወርቁ አንዳችም ሽራፊ ወደ ምድር ቢወድቅ አፈር ሆኖ ይቀርብሀል” አለችው::

ለማኙም ከረጢቱን አቀረበና ዕድል ወርቁን እየዘገነች ትወረውርለት ጀመር:: ወዲያውም “ምናልባት ከረጢቱ ሞልቶ ወርቅ ሊወድቅ ይችላልና ይብቃህ” አለችው::

ለማኙም “እመቤት ሆይ ከረጢቱ ጠንካራ ነውና አይቀደድም ቢያንስ አንድ እፍኝ ይጨምሩልኝ” አለ:: ዕድልም “እኔስ አንድ የወርቅ ሽራፊ ብቻ እንጂ ሌላ የሚችል አይመስለኝም!” አለችው::

ለማኙ ግን “ግድ የለም እመቤቴ አንድ ጊዜ ይጨምሩልኝ” አለ:: ዕድልም እንደገና ሌላ አንድ እፍኝ ወርቅ ጨመረችለት፤ ከረጢቱም ፈነዳ ወርቁም በመሬት ላይ ፈሰሰና አፈር ሆኖ ቀረ::

በዚያ ጊዜም ዕድልን ቀና ብሎ ቢያይ ከዐይኑ ተሠወረችበት:: እርሱም እንደ ወትሮው ወደ ድህነቱ ተመለሶ ይኖር ጀመር::

ልጆች- መጠንን /አቅምን/ አውቆ መኖር መልካም ስለሆነ በአቅም መኖርን እንልመድ::

ምንጭ - ታሪክና ምሳሌ

ፕሮግራም/ መሠረት ማጥናት ጀመረች:: በዚህም መሰረት ከአምስተኛ ወደ ስድስተኛ ስታልፍ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ አለፈች:: ከስድስተኛ ወደ ሰባተኛ ክፍልም ከበፊቱ

ገጽ 23በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ጤናችንጤናችን

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

አጫጭር ዜናዎች

ወደ ገጽ 30 ዞሯል

ፀጋዬ የሽዋስ

ወይዘሮ ጥሩወርቅ ሞላ በማህፀናቸው ለዘጠኝ ወራት የተሸከሙት ልጅ መወለጃው ቀን ሲደርስ ጭንቅ ሆነባቸው:: በሰላም አምጨ እገላገላለሁ ብለው በሚኖሩበት የተንታ ወረዳ ውስጥ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ሲያመሩ ነገሩ የሚታሰበውን ያህል ቀላል አልሆነላቸውም:: በቶሎ ወደ አቅስታ ከተማ ማምራትና በህዳር 11 ሆስፒታል በሚገኙ ሀኪሞች እገዛ ማግኘት እንዳለባቸው ተነገራቸው:: አምቡላንስ ተጠራ፣ ጉዞ ወደ አቅስታ ሆነ:: አቅስታ እስኪደርሱ ድረስ ቤተሠብ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ ፀሎቱን ለፈጣሪ ያደርሳል:: እሳቸውም ቢሆን ለፈጣሪያቸው ፀሎት ማድረሱን ከህመማቸው ጋር እየታገሉም ቢሆን አልረሱትም:: ከአንድ ሰዓት በኋላ አቅስታ ከተማ ወደሚገኘው የህዳር 11 ሆስፒታል ደረሱ:: “ሆስፒታሉ እንደደረስኩ በአልጋ ተቀበሉኝ” ይላሉ::

የሆስፒታሉ ሰራተኞች የወይዘሮ ጥሩወርቅንም ሆነ የህፃኑን ህይወት ለመታደግ ርብርብ ማድረግ ጀመሩ:: ቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልግ በመወሰኑ ወደ ቀዶ ህክምና ክፍል ከሀኪሞቹ ጋር ገቡ:: በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀዶ ጥገናው ተሰርቶላቸው ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ አስታቀፏቸው:: ባለሙያዎችን፣ ሆስፒታሉን፣ ዘመድ ወዳጃቸውን አመሰገኑ::

እኔም ቀዶ ህክምናው ተጠናቅቆ ልጃቸውን ከታቀፉ 24 ሰዓት ሳይሞላቸው ነበር በሆስፒታሉ ያገኘኋቸው፤ ከፊታቸው ላይ የንቃትና የደስታ ስሜት ይነበባል:: ከአልጋቸው ላይ መጋረጃ ስላለ በነፃነት ልብስ መቀየርም ሆነ ልጃቸውን መንከባከብ እንዲችሉ እድሉን ፈጥሮላቸዋል:: እሳቸው በተገኙበት ክፍል ወደ አራት እናቶች የተኙ ቢሆንም አራቱም አልጋ በመጋረጃ የተከፋፈለ ነው::

ወይዘሮ እመቤት አሊ ደግሞ የሚኖሩት በአቅስታ ወረዳ ውስጥ እንደመሆኑ በሆስፒታሉ ቅድመ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተዋል:: የመውለጃ ጊዜያቸው ሲደርስ ወደ ሆስፒታሉ በማምራት በቀዶ ህክምና ነው የተገላገሉት:: የባለሙያዎች ድጋፍና እንክብካቤ በእጅጉ እንዳስደሰታቸው ይናገራሉ::

እናቶች ወደ ሆስፒታሉ ሲያመሩ ከአቀባበል ጀምሮ በልዩ ትኩረት እንክብካቤ እንደሚሰጡ የገለፁልን አቶ መንግስቱ ኤባ የማዋለጃ ክፍሉ

እንዲሰምርኬዝ ቲም አስተባባሪ ናቸው:: እናቶችን በስትሬቸር/ የሚንቀሳቀስ አልጋ ወይም በተንቀሳቃሽ ወምበር /ዊልቸር ነው አቀባበል የሚያደርጉላቸው:: ከዚያም የማረፊያ አልጋ እንዲይዙ በማድረግ ምርመራ ይደረግላቸዋል:: በምርመራው ውጤት መሠረት አስፈላጊው ሁሉ እገዛ ተደርጎላቸው እንዲወልዱ ይደረጋል:: ከጤና መቃወስ ጋር የተያያዘና ትክክለኛ ምጥ ካልሆነም አስፈላጊውን ሁሉ ህክምና አግኝተው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ይደረጋል::

አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና እንክብካቤ ተደርጎ ከወለዱ በኋላ የህፃኑን/ኗን ጤንነት በተመለከተ ምርመራ ይደረጋል:: ህፃኑን/ኗን ማሞቂያ ክፍል ማስገባት የሚያስፈልግ ከሆነ ወደ ማሞቂያ ክፍል እንዲገባ/ትገባ ህክምና የሚያስፈልግ ከሆነም ህክምና እንዲያገኝ ወይም እንድታገኝ ይደረጋል:: ህፃኑ/ኗ አስፈላጊውን ሁሉ ህክምና አግኝቶ/ታ እስከምትወጣ/ሚወጣ ድረስ እናት በሆስፒታል እንድትቆይ ይደረጋል::

የህዳር 11 ሆስፒታል ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ ለእናቶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የሚናገሩት ደግሞ አቶ እስክንድር አበበ በሆስፒታሉ የእናቶችና ህፃናት ክፍል ኬዝ ማናጀር ናቸው:: አንድ እናት ቢያንስ በእርግዝና ወቅት ለአራት ጊዜ የቅድመ ወሊድ ክትትል ታደረጋለች:: ለእናትም ለህፃኑም ሙሉ የሆነ ክትትል፣ ይደረግላቸዋል ይላሉ:: ከእርግዝና ጋር የተያያዙ የጤና መታወኮች፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አሳሳቢ የሆኑ የጤና መታወኮች፣ የፅንሱ ደህንነት፣ የሚሰጡ መድሃኒቶች በቅድመ ክትትል ወቅት ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ናቸው::

ኤች.አይ ቪ በደሟ ለሚገኝ እናትም ቫይረሱ ወደ ፅንሱ እንዳይተላለፍ አስቀድሞ ዝግጅት ይደረጋል:: ቫይረሱ በደሟ የሚገኝ እናት የትዳር አጋሯም ድጋፍ ሊያደርግላት ስለሚገባ የቅድመ ክትትሉ አካል ይደረጋል:: ስለዚህ ከነፍሰጡር ባለቤቱ ጋር ወደ ሆስፒታሉ በየጊዜው እየሄደ ክትትል ያደርጋል:: ከክትትሉ በኋላ የወሊድ ወቅት ሲደርስም አስፈላጊው ሁሉ ዝግጅት ተደርጎ እንድትወልድ ይደረጋል:: በማህፀን መውለድ የምትችል ከሆነ በማህፀን እንደትወለድ ይደረጋል፣ ካልሆነ ደግሞ በቀዶ ህክምና እንድትገላገል ይደረጋል:: ከወሊድ በኋላም ክትትሉ ይቀጥላል:: ያለቀዶ ህክምና የወለደች እናት በትንሹ 24 ሰዓት ክትትል ይደረግላታል::

በ24 ሰዓት ውስጥ በህፃኑም ሆነ በእናቲቱ ምንም አይነት ችግር እንደሌለ ከተረጋገጠ ወደ ቤት ሲሄዱ መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች ምክር ይሰጣል:: በቀዶ ህክምና የወለደች እናትም ጤንነቷ እስኪረጋገጥ ክትትል ይደረግላትና በተመሳሳይ ምክር ተሰጥቷት ወደ ቤቷ እንድትሄድ ይደረጋል::

አንድ እናት ከወለደችና ወደ ቤቷ ከሄደች ከስድስት ቀናት በኋላ ወደ ሆስፒታሉ በማምራት ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባታል:: በዚህ የድህረ ወሊድ ምርመራ ወቅት የእናትና የልጅ ጤንነት ሁኔታ ተመርምሮ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና እንክብካቤ ይደረግላቸዋል:: እናት ራቅ ካለ ስፍራ ከመጣች ደግሞ በስድስተኛው ቀን በአቅራቢያዋ በሚገኝ የጤና ተቋም ምርመራ እንድታደርግ ይነገራታል::

ወሊድ

በጤና መድህን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የተነሱ የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች መፈታታቸው ተገለፀ::

የምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጤና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አለሙ ይበልጣል እንደገለፁት በወረዳችው በሚገኙ 12 ጤና ጣቢያዎች ለህብረተሰቡ የጤና መድህን የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል:: በዚህ ጊዜም በአንዳንድ የህክምና ባለሙያዎችና የድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ላይ የስነ ምግባር ችግሮች እንደሚታይ ባለፈው በተካሄደው የመልካም አስተዳደር ውይይት ህብረተሰቡ ጥያቄውን አቅርቧል ብለዋል::

ይህንንም ለማስተካከል የጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ህብረተሰቡ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እያገኘ ነው ብለዋል:: በቀጣይም ይህንን ተግባር አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ መግለፃቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሙኑኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል::

የእናቶችንና ህፃናት ሞት

ለመቀነስ እየተሰራ ነው

በምዕ/ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ በወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት አስታወቀ::

የጤና ስራዎች የንቅናቄ ውይይት ሲካሄድ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አዕምሮ ተናኘ እንደተናገሩት ነፍሰ ጡር እናቶች የጤና ክትትል በማድረግ ዘጠኝ ወር ሲሞላቸው ወደ ጤና ተቋማት ሂደው እንዲወልዱ በማድረግ የእናቶችንና የህፃናትን ሞት መቀነስ ተችሏል::

ለእናቶች አገልግሎት የሚውል አምቡላንስ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ለመግዛትም እስከ አሁን 434 ሺህ 195 ብር መሰብሰቡን የተናገሩት አቶ አዕምሮ ነፍሰ ጡር እናቶች በጤና ተቋማት በሚቆዩበት ጊዜ ለምግብ አገልግሎት የሚውል አንድ ሺህ 470 ኩንታል እህል ለማሰባሰብ ታቅዶ አንድ ሺህ 337 ኩንታል እህል መሰብሰቡንም ተናገረዋል::

የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የእናቶችና ህፃናት ክትትል ባለሙያ አቶ ሙላው ከበደ እንደተናገሩት ደግሞ ነፍሰ ጡር እናቶች የጤና ክትትል እንዲያደርጉና በጤና ተቋማት እንዲወልዱ በማድረግ በኩል አመራሩ ግንባር ቀደም ሊሆን ይገባዋል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ዘግቧል::

የጤና መድን ችግሮች እየተፈቱ

ነው

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 24 ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰ/ወሎ ዞን የወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት በ2008 በጀት አመት በአለም ባንክ በጀት እና በከተማ አስ/ሩ በጀት በከተማው ውስጥ ለሚያሰራቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች ማለትም፡-1ኛ ዶዘር ኪራይ 2ኛ ግሬደር ኪራይ 3ኛ 12 ካልቨርት1 ፓይፕ ካልቨርት 3 ስላቭ ካልቨርት እና ድጋፍ ግንብ 1 4ኛ የውሃ ተፋሰስ 5 5ኛ የጋቢዮን ሽቦ ግዥ የመሳሰሉትን ለግንባታ ስራው የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ማቴሪያሎች አቅርበው /ችለው/ የሚሰሩ በደረጃ 9 እና በላይ ሙያ ያላቸው የስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ 2. የማሽነሪዎችን ሊቭሪና በስሙ የተመዘገበ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለበት፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( ቲን ነበር) ማቅረብ የሚችሉ፤

4. ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. ከአማራ ክልል ውጭ የሚመጡ ተጫራቾች በሚንስተር መ/ቤቱ የኮንስትራክሸንና ኢንዱስትሪ ልማት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዝገባ ሰርተፈኬት ማቅረብ የሚችሉ፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለዶዘርና ለግሬደር ብር 50.00 ሃምሳ ብር / ለካልቨርት ሰራ ለ12ቱም ብር 60.00 /ስልሳ ብር/ ፓይፕ ካልቨርት ፣ ስላቭ ካልቨርት እና ድጋፍ ግንብ ብር 30.00 /ሰላሳ ብር/ ለውሃ ተፋሰስ ግንባታ ለእያንዳንዱ ሳይት ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ ለጋቢዮን ሽቦ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል በሰ/ወሎ/ዞን/ወልዲያ/ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ማግኘት ይቻላል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናልና በኮፒ በማዘጋጀት የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ የሚወዳደሩበትን የግንባታ ስራ ሳይት በመምረጥ በፖስታው ላይ ጽፈው በተለያየ ፓሰታ አሽገው በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚሆኑት ከተደራጁ ጀምሮ አምስት አመት ያልሞላቸው ስለመሆኑ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው፡፡

1ኛ ዶዘር ኪራይ እና ግሬደር ኪራይ ተወዳዳሪዎች

መስሪያ ቤቱ ለሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ፣ የአፈር ቆረጣ ወይም ጠረጋ ስራዎች አገልግሎት የሚውል ዶዘር D8R እና ግሬደር 140 እና ከዚያ በላይ የፈረስ ጉልበት ያለው ለእያንዳንዳቸው 300 ሰዓት እና በላይ ለሆነው ጊዜ የሚሰሩበትን ዋጋ ፣ የትራንስፖርት ፣ የነዳጅና የጥበቃ አገልግሎት ወጭዎችን ችሎ በማቅረብ መስራት የሚፈልግ የዶዘርና የግሬደር ባለንብረቶች ሁሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን 26/07/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10/08/2008 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ11/08/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

2ኛ የጋቢዮን ግዥ ተወዳዳሪዎች

መስሪያ ቤቱ ለሚያሰራቸው የአፈር መሸርሸር መከላከል ስራ አገ/ት የሚውል የተለያየ መጠን ያላቸው ብዛት 310 የጋቢዮን ሽቦ በተሰጠው የስራ ዝርዝር መሰረት ከጋቢዮን አምራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በሚፈለገው መጠንና ጥራት መሰረት ማቅረብ ለሚችሉ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 26/07/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 10/08/2008 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሰራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን በ8፡00 ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

3ኛ 12 የካልቨርት ተወዳዳሪዎች

በከተማው ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ ሳይቶች ላይ ለሚገነባው ካልቨርትስራ ለግንባታው የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ማቴሪያሎች እና የእጅ ዋጋ ችሎ /አቅርቦ/ በተዘጋጀው ፕላንና የስራ ዝርዝር መስራት ለሚፈልጉ የስራ ተቋራጮች በሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮማስራትይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 26/07 /08 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 17/08/08 ዓ.ም የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዘወትር በሰራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም 17/08/ 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

4ኛ ፓይፕ ካልቨርት እና ስላቭ ካልቨርት ሰራ ተወዳዳሪዎች

በኢንዱስትሪ መንደር አካባቢ ለሚገኙበት 3 ስላቭ ካልቨርትና 1 ፓይፕ ካልቨርት የግንባታ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማንኛውንምማቴሪያሎችንእናየእጅዋጋችሎ/አቅርቦ/ለሚሰሩየስራ ተቋራጮች በሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 26/07/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 17/08/ 2008 ዓ.ም ድረስ ከቀኑ 8፡00 ድረስ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዘወትር በሰራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም 17/08/2008 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውበተገኙበት ይከፈታል፡፡

5ኛ ለውሃ ተፋሰስ ግንባታ ተወዳዳሪዎች

በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማው ውስጥ ለሚያሰራቸው ልዩ ልዩ የውሃ ተፋሰስ ግንባታዎች አገልግሎት የሚውሉ ማንኛውንም ማቴሪያሎችን እና የእጅ ዋጋ ችሎ /አቅርቦ/ መስራት ለሚፈልጉ የስራ ተቋራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡ በኢንዱስትሪ መንደር አካባቢ ለሚገኙ ሳይት 1 125 ሜትር ሳይት 2 100ሜትር ሳይት 3 130 ሜትር ለሆኑት የውሃ ተፋሰስ ግንባታዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ27/07/2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/08/08 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ድረስ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዘወትር በሰራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም 18/08/ 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጧዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ደፈርጌ ቀበሌ አስ/ር አካባቢ ከብት ተራ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ግቢ እስከ እንኳይ ሰፈር ጎርጅ ድረስ 260 ሜትር የውሃ ተፋሰስ እና አድማስ ባሻገር ለ20 ሜትር መንገድ ለኮብልስቶን የተዘጋጀው 260 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ማንኛውንም ማቴሪያሎችን እና የእጅ ዋጋ ችሎ /አቅርቦ/ መስራት ለሚፈልጉ የስራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 29/07/ 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 19/08/2008 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ድረስ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዘወትር በስራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጧቱ 3፡00 ታሽጎ 19/08/ 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

1. የድጋፍ ግንብ ስራ ተወዳዳሪዎች

ኢንዱስትሪ መንደር አካባቢ ለሚሰራው የድጋፍ ግንብ 48.5 ሜትር ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚውል ማንኛውንም ማቴሪያሎችን እና የእጅ ዋጋ ችሎ /አቅርቦ/ በሚሰጠው የስራ ዝርዝርና ፕላን መሰረት መስራት ለሚፈልጉ የስራ ተቋራጮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 30/07/ 2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 20/08/ 2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላት ዘወትር በስራ ሰአት በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 20/08/2008 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ከዚህ በላይ ከቀረቡት የስራ ዝርዝር ውስጥ በሎት ከተቀመጡት 1ኛ 12 ካልቨርት ፣2ኛ 3 እስላቭ ከልቨርት ፣3ኛ አንድ ፓይፕ ካልቨርት ፣4ኛ የጋቢዮን ግዥ 5ኛ ዶዘርና ግሬደር ኪራይ በስተቀር ሌሎች ኢንዱስትሪ መንደር አካባቢ ከሚገኙት ሳይት ቁጥር 1እና 2 225 ሜትር ፣ሳይት 3 130 ሜትር ደፈርጌ ቀበሌ አስ/ር አካባቢ ከሚካኤል ቤተክርስቲያን እስከ እንኳይ ሰፈር ድረስ 260 ሜትር የውሃ ተፋሰስ አድማስ ባሻገር 260 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ፣6ኛ ድጋፍ ግንብ ስራ 48.5 ሜትር ለሆኑት የግንባታ ስራዎች የሚፈልጉትን አንድ የግንብ ስራ ብቻ በመምረጥ ሞልተው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 03 33 31 13 31 እና 03 33 31 03 22 ወይም 03 33 31 18 61 በመደወል ማግኘት ይቻላል

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወልድያ ከተማ አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት

ገጽ 25በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ሰሞነኛ ዜናዎችጌትሽ ሐይሌ

የኤች.አይ.ቪ./

ኤድስ ፈዋሽ መድሃኒት

አዲስ ተስፋ

የምንመገበው ምግብ ይዘት ለሁሉም የሰውነት ክፍሎቻችን መደበኛ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው:: የምንመገበው ምግብ ይዘትም በምናከናውናቸው እንቅስቃሴዎች የተመሰረተ ነው:: ከዚህም ጋር ተያይዞ የሙያው ጠበብቶች በቀን ማግኘት የሚገባንን የጉልበት መጠን እድሜን፣ ፆታንና ሌሎች ነጥቦችን መሰረት በማድረግ ሙያዊ ትንታኔ ይሰጣሉ::

ሰሞኑን ኦዲቲ ሴንትራል በቴክኖሎጂ አምዱ ይዞት በወጣው ዘገባ አንገት ላይ የሚታሰር መሳሪያን በመጠቀም የምንመገበውን ምግብ የጉልበት /ካሎሪ/ መጠን ማወቅ ተችሏል ይለናል::

ሰው አልባው የገበያ አዳራሽ

ባለፉት ጊዜያት በኮምፒዩተር እገዛ ያለአንዳች የሰዎች ጥበቃ አገልግሎት ስለሚሰጡ ተቋማት

የሳይንሱ ምጥቀት በእጅጉ በተራቀቀበት በአሁኑ ወቅት ከጥቂት ቫይረስ ወለድ በሽታዎች ውጪ ሌሎች በሽታዎች ፍቱን መድሃኒት እንዳላቸው የሙያው ጠበብቶች ይናገራሉ::

ከነዚህ ቫይረስ ወለድ በሽታዎች ውስጥ የሰውን ልጅ ብቻ ኢላማ ያደረገውና ዘር፣ ፆታ፣ ሀይማኖትና እድሜ ሳይለይ ነጭ የደም ህዋሳትን የሚያጠቃው ኤች.አይ.ቪ. እስካሁን ምንም ፈዋሽ ክትባት አልተገኘለትም::

ተመራማሪዎቹ የክትባት ጥረታቸውን ጥግ ድረስ ቢያደርሱትም ከተስፋ በዘለለ ቫይረሱን መግደል የሚችል የፈውስ ብስራት አላስደመጡንም::

ቴክኖሎጂ ዶት ኦርግ በሳይንስ አምዱ ሰሞኑን ይዞት የወጣው ዘገባ ግን ዝምታውን የሰበረ ይመስላል:: ተመራማሪዎቹ የኤች.አይ.ቪ.ን ፈዋሽ መድሃኒት ለማግኘት መቃረባቸውንም ድረ ገፁ አስነብቧል::

ዓለምአቀፉ የኤድስ መድሃኒት ኢኒሼቲቭ (IAVI)፣ ላጆላ የተባለ ተቋምና ስክሪፕስ ሪሰርች ኢንስቲትዩት (TSRI) በጋራ ባደረጉት ጥናት ነው የቫይረሱ ፈዋሽ መድሃኒት አዲስ ተስፋ ይፋ የተደረገው::

ግኝቱ በቫይረሱ ላይ የሚደረገውን ጥናት በእጅጉ እንደሚያግዝና ፈዋሽ መድሃኒቱን እውን ለማድረግ መቃረባቸውን የሚያመላክት ነው ተብሏል::

የጥናት ቡድኑ መሪና የTSRI ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዊሊያም ሸፍ፡- “ሁሉም ሰው እንግዳ አካልን ማግለል የሚችል ፀረ እንግዳ አካል እንዳለው አረጋግጠናል” ብለዋል::

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ይህንን አገልግሎት የሚያከናውኑት ፀረ እንግዳ አካላት ከኤች.አይ.ቪ. ጋር የተላመዱና የቫይረሱን መራባት የሚያፋጥኑ እንግዳ አካለትን (antibodies) ማስወገድ ይችላል:: ይህም ግኝት የቫይረሱን ፈዋሽ መድሃኒት ለማግኘት በር የከፈተ ነው ተብሏል::

ይህ አዲስ ተስፋ የተጣለበት ግኝት ቫይረሱ የሚያጠቃቸው የቤታ (Beta cells) ህዋሳት እንዲነቃቁ በማድረግ ህዋሳቱ እንግዳ አካላትን የሚገድሉ ፀረ እንግዳ አካል እንዲያመነጩ ያደርጋል:: በመሆኑም ቫይረሱ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች እንዳይሰራጭ ያደርገዋል::

እንደ የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት 35 ሚሊዮን ሰዎች ከቫይረሱ ጋር ይኖራሉ::

(ጌትሽ ኃይሌ)

የ”ካሎሪ” መጠን ነጋሪው መሳሪያ

በኒውዮርክ ባፋሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዩተር ሳይንቲስት በሆነው ዌንያኦ ዙ የፈጠራ ውጤት የሆነው ግኝቱ ምግብ በምናኝክበት ወቅት የሚወጣን ድምጽ መሰረት በማድረግ የምግቡን የጉልበት መጠን ይናገራል::

አውቶዳይተሪ (Autodietary) የሚል መጠሪያ የተሰጠው መሳሪያው የተለያዩ የምግብ አይነቶች በሚታኘኩበት ጊዜ የተለያዬ ድምጽን ማውጣት የሚችል ነው::

ከዚህ በተጨማሪም ምግብ በሚዋጥበት ጊዜ የሚያወጣውን ድምፀት ለማወቅ ሙከራውን አጠናክሮ እየሰራ እንደሆነ የሚናገረው ዙ ይህንንም

በቻይና ሰሜን ምስራቅ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጋር በጋራ እያከናወነ ነው::

መሳሪያው አንገት ላይ የሚታሰር ሆኖ ምግብ በምናኝክበት ወቅት በተገጠመለት እጅግ አነስተኛ ማይክሮፎን አማካኝነት የሚወጣውን ድምጽ ይመዘግባል:: የምግቡን የጉልበት መጠንም ይናገራል:: በዚህም መሳሪያው ላይ በተደረገው ሙከራ 85 በመቶው ውጤታማ መሆኑ ተነግሯል::

መሳሪያው ለጤናማ አመጋገብ አስተዋጽኦው የጐላ እንደሆነ እየተነገረለት ነው::

ይሁን እንጂ መሳሪያው ተመሳሳይ ገጽታ ላላቸው የተለያዩ ምግቦች ተመሳሳይ ድምፀትን ያሰማል:: በመሆኑም ይህንን እጥረት ለመቅረፍ አሁንም እየሰራ እንደሆነ የፈጠራው ባለቤት ይገልፃል:: የባዬሞኒተሪንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀምም የደም ስኳር መጠንንና ሌሎች አመልካቾችን መሰረት በማድረግ የምግቡን የጉልበት መጠን ለማወቅ እየሰራ እንደሆነ ተመራማሪው ተናግሯል::

መሳሪያው በተለይ የስኳር ህሙማን፣ በአንጀት ህመም ለሚያሰቃያቸውና በሌሎች ተያያዥ በሽታዎች ለሚሰቃዩ ተመራጭ መሆኑን ዘገባው ያመለክታል::

በተደጋጋሚ ሲነገር እንሰማለን:: ይህም ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ምጥቀት አንፃር የሚያስገርም አይደለም::

ኦዲቲ ሴንትራል ከወደ ስዊድን አገኘሁት ብሎ ባሰራጨው ዘገባ ደግሞ “ያለ ምንም የሰዎች ጥበቃ አገልግሎት በሚሰጠው የእቃ ግምጅ ቤት ስማርት ስልካችንን በመጠቀም የትም ቦታ ሆነን የምንፈልገውን ነገር መገበያየት እንችላለን” ይለናል::

በሁሉም ቀናት ክፍት በመሆን 24 ሰዓታትን አገልግሎት የሚሰጠው የእቃ ግምጃ ቤቱ ሁሉም እንቅስቃሴዎቹ ስማርት ቀፎ ላይ በተጫነ አፕሊኬሽን ቁጥጥር ስር ናቸው::

የስዊድን ዜጋ በሆነው ሮቤርቶ ኢሊጀሰን የፈጠራ ውጤት የሆነው ይህ አዲስ የመገበያያ ዘዴ፡- ባለፈው ጥር ወር በግዙፉ አፕል ኩባንያ እውቅና ተችሮታል::

የፈጠራ ስራው ማንኛውም ተጠቃሚ ወርሃዊ የደንበኝነት የአገልግሎት ክፍያን በመክፈል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም ባሻገር በእቃ ግምጃ ቤቱ የሌሉ እቃዎችንም በትዕዛዝ ማግኘት የሚያስችል ነው::

ተጠቃሚዎች ስዊድን ውስጥ ባለ የራሳቸው የሆነ የባንክ መለያ ካርድ ሊኖራቸው እንደሚገባ የሚገልፀው ሮቤርቶ ይህም ስርቆትን ለመከላከል ያስችላል::

ከዚህ በተጨማሪም “ማንኛውም እንቅስቃሴ በካሜራ ቁጥጥር ስር በመሆኑ ስጋት አይግባችሁ” ሲል የፈጠራው ባለቤት ያብራራል:: በቅርቡም በብዙ የስዊድን ከተሞች ለማስፋፋት ለተጠቃሚዎች የማድረስ እቅድ እንዳለው ዘገባው አስታውሷል::

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 26

ከገጽ 5 የዞረ

“የልጅነት ሕልሜ ...

በእርግጥ እኔ የምሸጠው ከእርሱ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር በጣም ዝቅተኛ ነበር፤ በዚህ የተነሳ ደንበኞቹ ሁሉ ወደኔ ኮበለሉበት::

በሁኔታው ያልተደሰተው ነጋዴ ለአካባቢ ጥበቃ “ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ነዳጅ እያለ እየሸጠ ነውና ተቆጣጠሩት” ብሎ አመለከተ:: አካባቢ ጥበቃዎችም መጥተው አናገሩኝ፤ “ፈጠራህን እናደንቃለን! እናበረታታለን፤ ነገር ግን ያመረትከው ነዳጅ መሠል ነገር በትክክል ምንነቱ መታወቅና በአካባቢም በጤናም ላይ ጉዳት አለማድረሱ እንዲረጋገጥ ብታደርግ መልካም ነው” የሚል ምክር ሰጡኝ::

ከዚያ ሐሙስ ነግረውኝ ዓርብ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያመረትኩትን ነዳጅ ይዤ መጣሁ:: ግን የዩኒቨርሲቲው የጥበቃ ሠራተኞች ሊያስገቡኝ አልቻሉም:: ከጥበቃዎቹ ጋር በር ላይ እየተነጋርን እያለ ባጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ደረሱ:: ከዚያ ከጥበቃዎቹ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት አርግበው ይዘውኝ ወደ ቢሯቸው ገቡና ስለጉዳዩ ተነጋገርን:: በጣም ተገረሙም ተደሰቱም::

በቀጣይም ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተነጋገርንና በጀት ተመደበልኝ፤ ለሙያው ቅርበት ያላቸው ዶክተር ብርሃኑ እንዲያግዙኝ ተመደቡልኝ:: ዩኒቨርሲቲው በተለይ ፕሬዝዳንቱ ትልቅ ድጋፍ አደረጉልኝና ሥራ ጀመርኩ:: ምርምሬን የጀመርኩት ከዚያ በፊት ሥሠራ እንደነበረው ከበቆሎና ከሌሎችም ሰብሎች ነበር:: በዚህ ሁኔታ እኔ ማምረቱን ቀጥዬ ሳይንሳዊ ጥናቱን ደግሞ ዶክተር ብርሃኑ አጠኑ:: መጨረሻ ላይ ከበቆሎ የተገኘው ነጭ ጋዝ፣ ከዶሮ ኩስ የተመረተው ቤንዚንና ከቡና የተገኘው ናፍጣ ሆኖ ተገኜ::

ወደ ዶቤ አፈር እንዴት ተመለስክ?ከዚያ በኋላ የዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ተጠናክሮ

ቀጠለ፤ ቀደም ብዬ እንደነገርኩህ ደግሞ በስሜን አካባቢ ዶቤ አፈር ለማገዶነት ይውላል:: መንደዱ ብቻ ሳይሆን አፈሩ ስታየው ቅባትነት ያለው ነው፤ እፍግታውንም ስለካው ከሌላው አፈር ያነሰ ነው:: ስለዚህ ነዳጅ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አደረብኝ:: በዚያ ላይ የሰብል ምርቶቹ ዋጋ እየጨመረ መሄዱ አዋጭነቱን አነስተኛ ያደርገዋል፤ በተለይ ከቡና የሚመረተው ነዳጅ በጭራሽ አዋጭ አይደለም:: አፈሩ ግን የተሻለ አዋጭ እንደሚሆን ገመትኩ፤ ጥናቱንም ጀመርኩ::

ለምሳሌ ከአዋጭነት አንጻር ያለውን እውነታ በአሀዝ ልግለፅልህ፤ ከአንድ ኪሎ ግራም በቆሎ ከሁለት ሊትር በላይ ነዳጅ ይወጣል:: ከዶሮ ኩስ ደግሞ ከሁለት ኪሎ ግራም አንድ ሊትር የማይሞላ ነዳጅ ነው የሚመረተው:: ከቡና ደግሞ ከሦስት ኪሎ ግራም አንድ ሊትር ብቻ ነዳጅ ነው የሚወጣው፤

የአፈሩን ግን ስናይ ከአንድ ኪሎ ግራም አፈር ከሦስት ሊትር በላይ ነዳጅ ይገኛል:: በዚያ ላይ አፈሩ በተለያዩ አካባቢዎች አፋርን ጨምሮ በስፋት መገኘቱ ደግሞ በእጅጉ አዋጭ ያደርገዋል::

አፈር በባሕርይው ቶሎ የማይተካ፣ ውድ የተፈጥሮ ሀብት መሆኑ አዋጭነቱን አይቀንሰውም?

በእርግጥ ሰፊ ጥናት ያስፈልገው ይሆናል፤ ገና እያጠናነውም ነው:: ነገር ግን አፈሩ እኛ ባንጠቀምበትም በነፋስና በጎርፍ እየተወሰደ መባከኑ አልቀረም:: በተጨማሪም ጥቅሙን ማነፃፀር ነው፤ አፈሩን ለነዳጅ ማምረቻነት ከመጠቀምና ካለመጠቀም የሚገኘውን ጥቅምም ማወዳደር ነው:: እንዲሁ ሳየውም ዶቤ

አፈርን መጠቀም አሉታዊ ተፅዕኖ የለውም፤ ጓሳ አካባቢ ያለ አፈር ስለሆነ ጓሳው ቶሎ በስብሶ ወደ አፈርነት የሚቀየርም ይመስለኛል::

ሙሉ በሙሉ ነዳጅ ከዶቤ አፈር ለማምረት ምን ያህል እርቀት ሄደሃል?

ገና ጅምር ላይ ነኝ:: የበርካታ ምሁራንን ተሳትፎም የሚጠይቅ ነው፤ አፈሩን ብቻ ለማጥናት ሰፊ ጊዜ የሚወስድ ነው:: የተለያዩ ባለሙያዎችን ከስነ-ህይወት፣ ከኬሚስትሪ፣ ከፊዚክስና ከሌሎችም የትምህርት መስኮች የተውጣጡ ምሁራንን ይዞ

ማጥናት ይጠይቃል:: ቢበዛ ግን ከስድስት እስከ ስምንት ዓመታት ሙሉ በሙሉ ወደ ማምረት የምንገባ ይመስለኛል::

ከተለያዩ ነገሮች ያመረትካቸው ነዳጆች በተግባር ተሞክረዋል?

አሁን በዩኒቨርሲቲው ትብብር ሳይንሳዊ ጥናቱን ያካሄዱት ዶክተር ብርሃኑ ነጭ ጋዙ ለአውሮፕላን ነዳጅነት የሚውል መሆኑን አረጋግጠውታል:: ቤንዚንና ናፍጣም ለተጠቃሚዎቹ ሞተሮች ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው:: ቤንዝኑን ለሞተር ሳይክል ሞክረነዋል ያጋጠመን ችግር የለም:: ስለዚህ ለማንኛውም ቤንዝን ተጠቃሚ መሆን የሚችል ነው:: እንደ ጎንዮሽ ጉዳት ያየነው የተወሰነ አሲድነት ባሕርይ መኖሩ ነው፤ እሱም መፍትሔ ይፈለግለታል::

በምርምር ሥራዎችህ ያገኘኸው የባለቤትነት መብት አለ?

አዎ! በሦስቱ የባለቤትነት መብት ከአዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት ተሰጥቶኛል:: መብቱን እንዳገኝ አስፈላጊውን እገዛ ያደረገልኝም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው:: ከአፈር፣ ከበቆሎና ከዶሮ ኩስ ነዳጅ የማምረት ባለቤትነት መብት ተሰጥቶኛል:: አሁንም ምርምሮቹን ጫፍ ለማድረስ ዩኒቨርሲቲው እገዛ እያደረገልኝ ነው፤ የበጀት እጥረት ግን አለ:: ኢንጅነር ሰሎሞን የተባለ የዩኒቨርሲቲው መምህርም እያገዘኝ ነው::

የምፈልጋቸው ቁሳቁሶች እየተሟሉልኝ ነው፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዟዙሬም የአፈር ጥናት እንዳደርግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተሽከርካሪ መድቦልኛል:: ይህ ሁሉ ለሕልሜ መሳካት ትልቅ አስተዋፅዖ እያበረከተልኝ ነው::

አቡሀይ በልጅነቱ ምን መሆን ይመኝ ነበር?

የልጅነት ሕልሜ መዝረፍ ነበር፤ የተመሠከረለት ቅኔ ዘራፊ የመሆን ፅኑ ሕልም ነበረኝ:: የአብነት ትምህርት እየተከታተልኩ በነበርኩበት ጊዜ እጅግ የማደንቃቸው ቅኔ ዘራፊዎች ነበሩ፤ ችሎታቸውና ፈጠራቸው በልጅነት አዕምሮዬ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ቀላል አልነበረም:: ትምህርቱን እስከ ቅኔ ቆጠራ አድርሸው ነበር፤ ዲቁናም ተቀብያለሁ፤ መግፋት ግን ሳልችል ወደ ሳይንሱ መጣሁ:: በኋላ ወደ መደበኛው ትምህርት ስገባና በተለይ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስደርስ ደግሞ ወደ ምርምር ማዘንበል ጀመርኩ:: የማስበው ነገር ደግሞ እየተመቻቸ መጣ::

ምርምርህን ከዚህ ደረጃ ለማድረስ እንድትገፋበት ያደረገህ ማበረታቻ ነበር?

መጀመሪያ ላይ ሥራዬን ያቀረብኩት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ሳቀርበው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ እነአቶ በረከት ስምዖን፣ እነአቶ አያሌው ጐበዜ፣ … ተገኝተው ጎበኙልኝ፤ በጣም አበረታቱኝ:: ይህ ለእኔ የመጀመሪያው ትልቅ ማበረታቻና ጉልበቴ ነበር:: በሰሜን ጎንደር ዞን በፈጠራ ተሸላሚ ስሆን ይበልጥ ሞራሌ አደገ:: ሥራዬም በእጅጉ ተሞካሸ:: አዲስ አበባም ሄጄ በአገር አቀፍ ደረጃ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋባዥነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እጅ ስሸለም በቃ የሕልሜ ጫፍ ላይ እንደምደርስ በራስ የመተማመን ደረጃዬ ከፍ አለ:: ለዚህም ነው በቀጣዮቹ ስድስትና ሰባት ዓመታት ወደ ሙሉ ማምረት በእርግጠኝነት እገባለሁ ብዬ የምናገረው::

ልምድህን ስላካፈልከኝ በአንባቢዎች ስም አመሰግናለሁ::

እኔም በጣም አመሰግናለሁ::

ግን የዩኒቨርሲቲው የጥበቃ ሠራተኞች ሊያስገቡኝ

አልቻሉም:: ከጥበቃዎቹ ጋር በር ላይ የእየተነጋርን

እያለ ባጋጣሚ የዩኒቨርሲቲው የምርምር

ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ደረሱ:: ከዚያ

ከጥበቃዎቹ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት

አርግበው አብረው ይዘውኝ ወደ ቢሯቸው ገቡና

ስለጉዳዩ ተነጋገርን::

አቡሀይ በምርምር ያመረታቸው የተለያየ ዓይነት የጥራት ደረጃ ያላቸው ነዳጆች ናሙና (ላንቲካ)

አቡሀይ በምርምር ነዳጅነቱን ያረጋገጠው የዶቤ አፈር ናሙና (ላንቲካ)

ገጽ 27በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. እጽዋት/እንስሳት

አማያዊሻርክ

ሙዋሊሙ

ሰማያዊ ሻርክ ከ400 በላይ ዝርያ አለው:: እንደ ስሙ ቀለሙ ሰማያዊ ነው:: ይህ የአሣ አይነት በተንጣለለና በጥልቅ ባህር ውስጥ ይኖራል::

ሰማያዊ ሻርክ ከ400 ሚሊዮን አመታት በፊት መኖር እንደጀመረ ይነገራል:: ከአሳ አይነቶች መካከል ቀድሞ በመፈጠር ሰማያዊ አሳን የሚስተካከለው የለም::

አጥንቱና ጅማቱ ጠንካራ ነው:: በተለይ የአፉ የላይኛውና የታችኛው ክፍል ጥንካሬ ወደር የለውም:: ሰውን ጨምሮ ታዳኝ እንስሳትን ከነከሰ አይለቅም:: ነክሶ ካቆሰለ በኋላ ቢለቅ እንኳ ቁስሉ በቀላሉ አይድንም::

የሰማያዊ ሻርክ ጭንቅላት በአጥንት የደነደነ ነው:: በመሆኑም ሌሎችን የአሳ አይነቶች በጭንቅላቱ ከገጨ በምቱ የሚያሳርፈው ጉልበት ከፍተኛ ነው:: በሰማያዊ ሻርክ የተነረተ አሳ የመዳን እድል የለውም::

የተለያዩ የሰማያዊ ሻርክ ዝርያዎች የተለያየ የጥርስ ቅርጽ አላቸው:: ለአብነት የአንዳንዱ በጣም ሹል ሲሆን፣ የሌላው ባለሶስት ማዕዘን ነው:: ጠፍጣፋ ጥርስ ያለውም አለ:: ታዲያ እንደ አመጋገቡ ባህርይ የጥርሱ ጥንካሬም የተለያየ ነው:: ሁሌም ጠንካራ ነገር የሚመገብ በመሆኑ ጥርሱ ጠንካራ ነው::

በሌላ በኩል ይህ የአሳ አይነት ጠንካራ ነገር እንደመቆርጠሙ ጥርሱ በአፋጣኝ መልሶ አዳዲስ ጥርስ ያበቅላል:: ሰማያዊ ሻርክ በእድሜ ዘመኑ የተለያዩ ጊዜያት ጥርስ ስለሚያበቅል በሺዎች የሚቆጠር ጥርስ ያወጣል::

አብዛኛው የሰማያዊ ሻርክ ዝርያ ስጋ በል ነው:: የተለያዩ የአሳ አይነቶችንም ይመገባል:: በራበው ጊዜ ደግሞ የራሱን ግልገል ሳይቀር አባሮ ይበላል:: እርግጥ ነው፤ ሁሌም ሰማያዊ ሻርኮች ጥቃት አድራሾችና ስጋ በል ብቻ አይደሉም:: የባህር ውሰጥ ሳር፣ ቅጠላቅጠል፣ ጭቃ የሚመገቡ አሉ:: ካልነኳቸው የማይተናኮሉም ይገኙባቸዋል::

ሰማያዊ ሻርክ ለአሳ አስጋሪዎች ቶሎ እጅ አይሰጥም:: በየትኛውም የአስጋሪዎች መረብ ውስጥ አይገባም:: መተናኮል ሲሻ ደግሞ አስጋሪዎችን ካገኘ ወደ ማጥመጃ መርከባቸው በመዝለል ነክሶ ወደ ባህር ውስጥ ይዘፍቃቸዋል፤ ቀረጣጥፎም ይበላቸዋል:: እናም ሰማያዊ ሻርክ “ሰው አጥማጅ ነው” ቢባል ይቀላል::

አብዛኛው የአሳ ዝርያ የሚራባው እንቁላል ጥሎ በመፈልፈል ነው:: ሰማያዊ ሻርክ ግን በሶስት አይነት ዘዴ ራሱን ያራባል:: የመጀመሪያው እንቁላሉን በባህር ውስጥ በመጣልና በመፈልፈል ይራባል:: አንዲት እንስት ሰማያዊዋ ሻርክ በአንድ የርቢ ጊዜም 100 እንቁላል ትጥላለች:: ሁለተኛው የመራቢያ ዘዴ እንቁላሉን በእንስቷ ሆድ ውስጥ እየጣለ በመሰብሰብ ብሎም በመፈልፈል ዝርያውን የሚያስቀጥልበት ነው:: ሶስተኛው በጽንሰት አማካኝነት ይወልዳል:: ታዲያ አንዲት ሰማያዊ ሻርክ ፀንሳ ለመውለድ ከዘጠኝ እስከ 12 ወራት ይፈጅባታል::

ፆታዊ ተራክቦ ያልፈፀመች ሰማያዊ ሻርክ ምንም እንቁላል መጣል አትችልም::

ተባዕቱ ሰማያዊ ሻርክ ግልገሎቹን ተንከባክቦ የማሳደግ ኃላፊነት አለበት::

ሰማያዊ ሻርክ የተዋጣለት አዳኝ ነው:: ለዚህ ስኬቱ አንዳኛው ምክንያት የላቀ የስሜት ህዋስ መታደሉ ነው:: የአብዛኛው የሰማያዊ ሻርክ የማሽተት አቅም ከፍተኛ ነው:: አንድን ባዕድ እንስሳ በ60 ሜትር ርቀት አሽትቶ መለየት ይችላል:: ይህም ለማጥቃትም ሆነ ለማድፈጥ ይረዳዋል:: በመሆኑም ሰማያዊ ሻርክ በአደፈጠ ፍጡር አይጠቃም::

በዚህ እሳቤ መሰረት የአሜሪካ የባህር ኃይል አካዳሚ ሰማያዊው ሻርኮችን በየጊዜው እያሰለጠነ ለቅኝት ተግባር ይጠቀምባቸዋል:: ከአካላቸው ላይ ቦምብ በማጥመድም የታሰበውን ኢላማ እንዲመቱ ይደረጋል:: ይህ አይነቱ ተግባር በባህረ ሰላጤው ጦርነት ወቅት በኢራቅ የጦር ሀይል ላይ ተሞክሮ ውጤታማነቱ ተረጋግጧል::

ታዲያ ሰማያዊ ሻርክ በአሜሪካ የጦር ሀይል በልዩ ሁኔታ እየሰለጠነ ጥቃት ማድረሱንና የስለላ ተግባር መፈፀሙን የተረዱ አገሮች ሁኔታውን አልወደዱትም:: ስለሆነም ሩሲያ፣ ስካንድኒቪያን

አገሮች፣ ኩባ… በባህራቸው ሰማያዊ ሻርክ ዝር እንዳይል እያደረጉ ነው፤ በመርዝ እስከመግደልም ደርሰዋል::

የሰማያዊ ሻርክ አሳ ዓይን መስታወት የመሰለ ነው:: ይህም በውሃ ውስጥ ጥርት ያለ እይታ እንዲኖረው አድርጓል::

በተጨማሪም ሰማያዊ ሻርክ በውስጡ ከጠፍጣፋ የራስ ቅሉ እስከ ጭራው ድረስ የሚደርስ ትልቅ ቱቦ አለው::

በዚህ አካሉ ውስጥም የውሃ ውስጥ እንቅስቃሴን የሚለይበት መጠቆሚያ አለው:: ይህም በቀላሉ ታዳኞቹን ለመያዝ ንቁ ሆኖ ለመጠበቅ ያስችለዋል:: በሌላ በኩል በታዳኞቹ ላይ የሚለቀው የኤሌክትሪክ ሞገድ ከፍተኛ በመሆኑ አፍዞ አደንዝዛ ማጥቃት ይችላል-www.Prionace Shark.com እንደዘገበው::

ከ400 በላይ ከሰማያዊ ሻርኮች መካከል ዌል ሻርክ አንዱ ነው:: ዌል ሻርክ 12 ሜትር ርዝመት

ሲኖረው 150 ኪሎ ግራም ይመዝናል:: እንቅስቃሴው በቡድን በመሆኑ ለምንም ሆነ ለማንም አይበገርም::

ደም መጣጩ ሻርክ ሌላው አይነት ነው:: ቀለሙ ከሌሎች የተለየ ነው፤ ግራጫ:: 10 ሜትር ቁመት አለው፤ ክብደቱ ደግሞ 100 ኪሎ ግራም ተለክቷል:: ከሌሎች የሰማያዊ ሻርኮች በተለየ ምግቡን ደም በመምጥመጥ ብቻ ያገኛል::

የሰማያዊ ሻርክ አማካይ ርዝመት ተባዕቱ ከአንድ ሜትር ከ82 እስከ ሁለት ሜትር ከ82 ሜትር ይደርሳል:: እንስቷ በአንፃራዊነት በሁሉም መመዘኛ ትልቅ ነች:: ሁለት ሜትር ከሁለት እስከ ሶስት ሜትር ከሶስት ሴንቲ ሜትር ተለክታለች:: በክብደት ረገድ ተባዕቱ 182 ኪሎ ግራም፣ እንስቷ ደግሞ 391 ኪሎ ግራም ይመዝናሉ::

አንዲት ሰማያዊ ሻርክ በአንድ ጊዜ ከ25 እስከ 100 ጫጩቶችን ትወልዳለች፣ የእርግዝና ጊዜዋ ደግሞ አንድ አመት ነው:: ግልገሎቹ ለርቢ የሚደርሱት በስድስተኛ አመታቸው ነው::

በዓለም ላይ በየአመቱ 20 ሚሊዮን ሰማያዊ ሻርክ ተይዞ ለምግብነት ይውላል:: በአብዛኛው የሚታደነው ደግሞ በጥይት ወይም በሌላ ኬሚካል በመግደል ወይም በማስከር ሩህን አስቶ በመያዝ ነው::

ሰማያዊ ሻርክ ከምግብነት ባለፈ በዘመናዊ የህክምና ኢንዱስትሪ በመግባት የካንሰር መድሃኒት ይሰራበታል:: የአዕምሮ ማበረታቻ እንክብልም ይዘጋጅበታል:: የቲቢ መድሃኒት ይሰራበታል:: ለደረቅ መርፌ ህክምና ግልጋሎት የሚውል ፈሳሽ ይቀመምበታል:: የስንፈተ ወሲብ መድሃኒት ይዘጋጅበታል:: የማደንዘዣ ፈሳሽ መድሃኒት ይቀመምበታል:: ቫይታሚን “ቢ ኮምፕሌክስ 12” ይፈበረክበታል::

የሰማያዊ ሻርክ ዋነኛ ጠላት ሰው ነው:: አማካይ እድሜው 20 አመት ነው::

አለው:: በእድሜውም 18 ሜትር ድረስ ማደግ ይችላል:: በአማካይ 13 ቶን ወይም 130 ኩንታል ይመዝናል:: 130 ሜትር ጥልቀት ድረስ ገብቶ ያደፍጣል፤ ይዋኛልም::

ሌላው የሻርክ አይነት ካራኪዳ ይባላል:: ይህ የሻርክ ዝርያ ቁጡና ጉልበተኛ ነው:: ሰውንም በውሃ ውስጥ ካገኘ አባሮ በመያዝ አዝለፍልፎ ይገለዋል:: 20 ሜትር ቁመት

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 28

ያለውን በቁጭት...ከገፅ 21 የዞረ

የሚል የማጭበርበሪያ መልስ ያቀረበ በ600 ብር፣ መውለጃዋ ቀን እየታወቀ ቀድሞ ወደ ጤና ጣቢያ ያላመጣ ደግሞ በ500 ብር ይቀጣል::

የቀበሌው አመራሮችም ሆነ ሌላው “እርጉዝ ማን ናት?፣ ከወለደችም የት ወለደች?” እያሉ ክትትል ያደርጋሉ:: ባለፉት ስድስት ወራትም 62 ሴቶች በጤና ተቋም፤ ሁለቱ በቤት ተገላግለዋል:: የሁለቱ ሴቶች ባለቤቶቻቸው በቀበሌው በኩል ተጠርተው በደንቡ መሠረት ቅጣታቸውን ከፍለዋል:: በዚህ ሁኔታም ሁለት አባወራዎች የ600 ብር እና የ500 ብር ቅጣት ከፍለዋል::

የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ አልዩ የራሳቸውን ተሞክሮም የባለፈውን ካሁኑ እያነፃፀሩ አጫውተውናል:: ባለቤቴ ስምንተኛ ልጃችንን ልትወልድ ምጥ ሲጀምራት የልምድ አዋላጆች ‘ገና ነው ቆይ፣ ገና ነው ቆይ’ እያሉ ብዙ አምጣ ስትወልድ ህፃኑ ሞቶ ወጣ:: በዛ ምክንያት ከአምስት ዓመት በፊት እንዳትወልድ ነገሩን:: አምስት አመት ከሞላት በኋላ አምና ሰኔ ላይ ደግሞ ልትወልድ ቀኑ ሲደርስ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ወደ ጤና ጣቢያ ሄደች:: ከቀኑ አምስት ሰዓት በሰላም ተገላገለች:: በዛ ሰዓት ግን ብዙ ደም ፈሰሳት:: ከቤት ቢሆን ኑሮ ችግሩ የከፋ ይሆን ነበር” በማለት ያስታውሳሉ::

እንደ አቶ አልዩ ማብራሪያ ቀደም ባሉት ጊዜያት ሴቶች ምጥ ሲደርስባቸው ወንዶች እርሻ፣ ገበያ፣… ከሄዱ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሴቶች ብቻ ነበሩ:: በዚህም በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን እርግፍ አድርገው ሞተዋል::አሁን ግን ሴቶችም “ምንስቃይ እኛ ብቻችንንም ብንሆን ወደ ሀኪም እንሄዳለን” በማለታቸው ሁሉም የቀደሞውን የተሳሳተ አመለካከት አስወግደዋል::

ነፍሰጡር እናቶች በጤና ተቋም በመገልገል

እና በሌሎች መስፈርቶችም የበጤ ቀበሌ ሴቶች አደረጃጀት ከወረዳው ቀዳሚ እንደሆኑ የቀበሌው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ዘሀራ ሙሀመድ አጫዎቱን:: እርሳቸው እንዳሉት በቀበሌዋ የሚኖሩ አንድ ሺህ 43 ሴቶች በ175 የአንድ ለአምስትና በ37 የልማት ቡድን ተደራጅተዋል::

ከነዚህም ግማሽቹ የሴቶች ማህበር አባል ሲሆኑ በአደረጃጀት ግን ሁሉም አባል ናቸው::

ሴቶች በመደራጀታቸው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግራቸውን ማቃለል እንደቻሉ የጠቆሙት ኃላፊዋ በተለይ በአካባቢው ስር ሰዶና የኖረውን በልምድ አዋላጅ ይፈፀም የነበረውን በቤት

የመውለድ ችግር መፍታት ችለዋል::“ነፍሰጡሮች ወደ ህክምና መሄድን እንደ ነውር

ይቆጥሩት ነበር:: ‘እንዴት ውጭ ሂጀ እጋልጣለሁ’ ይላሉ:: በዚህም ሰባትና ስምንት ልጆቻቸውን ትተው የሞቱ በርካቶች ናቸው:: እናታቸውን በሞት ያጡ

ልጆችም ለችግር ይደረጉ ነበር” ይላሉ::አሁን ግን በቀበሌው በየ15 ቀኑ ሴቶች

በአደረጃጀታቸው የወሊድ ቅድመ ምርመራ አለማድረግ፣ በቤት ውስጥ ያለ ሀኪም መውለድ፣… በሴቷም ላይ ሆነ በጽንሱ የሚያስከትለውን እስከ ሞት የሚደርስ ጉዳት በጤና ባለሙያዎች ግንዛቤ ይፈጠርላቸዋል:: በዚህም ሁሉም በሚባል ደረጃ ዛሬ የበጤ ሴቶች በጤና ተቋም እየተገላገሉ ነው::

የወረዳው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ወርቅነሽ ዘነበ በበኩላቸው በወረዳው

ሁለት ሺህ 53 የሴት አንድ ለአምስትና 532 የልማት ቡድን መመስረቱን ጠ ቁ መ ዋ ል : : በዚህም በጐልማሶች ትምህርት፣ በቁጠባና በጤና ተቋም በመውለድ እና በልማት ባላቸው ተሳትፎ የበጤ ቀበሌ ሴቶች ከወረዳው ግንባር ቀደም

መ ሆ ና ቸ ው ን አረጋግጠዋል::

እኛም የሌሎችን ባናይም የበጤ ቀበሌ ሴቶች በአደረጃጀታቸው ተገኝተው በጋራ ለመምከር፣ ዕውቀት ለመቅሰም፣… ዘወትር በሚገኙበት እለተ አርብ ሰዓታቸውን አ ክ ብ ረ ው በ መ ድ ረ ስ ፣ ከደረሱ በኋላም ወደ ተግባራቸው ለ መ ሰ ማ ራ ት

ያላቸው ተነሳሽነት ምስክር ነው:: የበጤ ሴቶች ተሞክሮ በሌሎችም ቢሰፋ በተለይ የእናቶችን ሞት መቀነስ የሚያስችል መሆኑ አያጠራጥርም::

ከገጽ 9 የዞረ

ለተዘነጉት...

የሚሉት ደግሞ ወ/ሮ ብዙሃን አሊ ሌላዋ የልዩ ፍላጎት መምህርት ናቸው:: ለሁሉም የጉዳት አይነት ትምህርት ይሰጣሉ:: ለአይነስውራን ዳስሰው ቅርፁን ሊያውቁ የሚችሉበት የትምህርት መርጃ መሳሪያ አዘጋጅተዋል::

የትምህርቱ ርእስ በሚያዘው መሰረት በየምእራፉ መርጃ መሳሪያዎችን ለመጠቀም ጥረት ያደርጋሉ:: መስማት ለተሳናቸው ከምልክት ቋንቋ በተጨማሪ በስእል ነገሮችን እንዲለዩ ያደርጋሉ:: ምምህሯ ከሚሰጡት ትምህርት ባሻገር ተማሪዎቹ እርስ በርስ እንዲረዳዱ ያደርጋሉ:: የአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ተማሪዎችም በመመሪያው መሰረት ድግፍ እንደሚያደርጉላቸው መምህርቷ ይናገራሉ:: ለእይነስውራን ተማሪዎች ማስተማሪነት የሚያገለግል ብሬል ወረቀት ውስንነት መኖሩን መምህርቷ ይገልፃሉ::

የአእምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ተማሪዎችንም ለማስተማር የሚረዱ መርጃ መሳሪያዎች አለመኖር ስራቸውን ፈታኝ እንዳደረገው ይገልፃሉ:: በመምህራኑ የሚዘጋጁ መርጃ መሳሪዎች ቢኖሩም በቂ ናቸው ማለት እንደማይቻል ይናገራሉ:: ምንም አይነት የተማሪዎች የመማሪያ መፅሃፍ የላቸውም:: የመምህሩ መምሪያ መፅሃፍም አንድ ብቻ እንደሆነ ወ/ሮ ብዙሃን ይገልፃሉ::

ህብረተሰቡ አካል ጉዳት ያለባቸውን ህፃናት በእርግማን እንደመጣ በማሰብ ቤት ውስጥ ያውላቸው እንደነበር የሚናገሩት የአቅስታ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር

አቶ ሁሴን እንድሬ ናቸው:: ትምህርት ቤቱ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መስጠት ሲጀምር ይህንን የተሳሳተ የህብረተሰብ አመለካከት ማስተካከል ነበረበት:: ስለዚህም የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን አመቻችተው ለውጥ ለማምጣት

መሞከራቸውን ርዕሰ መምህሩ ይናገራሉ:: የተወሰኑ ልጆች ወደ ትምህርት ቤቱ በማምራት መማርና መለወጣቸውን ሲያዩ ህብረተሰቡ አመለካከቱ እየተቀየረ መምጣቱንና ጉዳት ያለበትን ልጁን መላክ መጀመሩን ይናገራሉ:: ዛሬ ላይ ራሳቸው

ወላጆች በባለቤትንት ትምህርት ቤቱን መደገፍ መጀመራቸውንም ይገልፃሉ::

የግብአት አቅርቦቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ቢመጣም ሙሉ በሙሉ ማሟላት አለመቻሉን ያምናሉ::

አቶ አንዱአለም አሰፋ በለጋምቦ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የትምህርት ተቋማት ማስፋፋትና የትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት ዋና የስራ ሂደት ባለሙያ ናቸው:: በወረዳው በአራት ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ይናገራሉ:: ለነዚህ ተማሪዎች የሚያስፈልገውን ድጋፍ ወረዳው በተቻለ መጠን ለማገዝ ሙከራ እየተደረገ ነው ይላሉ:: ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጥ እንደሚደረግም ተናግረዋል:: አቅስታ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ያለው እ ን ቅ ስ ቃ ሴ የተሻለ የሚባል እንደሆነ ገልፀዋል:: ከጂኩዊፕ በትምህርት ጥራት የሚሰጥ ገንዘብን የሚመለከት ነው በተገኘ ከአርባ

አራት ሺህ ብር በላይ ገንዘብ የተለያዩ ቁሳቁሶችን እንዲገዙ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል:: ወረዳው ካለው በጀት አንፃር ሁሉንም ነገር በአጭር ጊዜ ማሟላት አለመቻሉንም ያምናሉ::

ተማሪዎቹ ት/ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ የትምህርት መርጃ መሳሪያ እየተማሩ ነው

ገጽ 29በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.

የቱሪዝም ቀይ ...ከገፅ 19 የዞረ

ከገፅ 19 የዞረ

የባህር ላይ ...በተለይም በውንብድና ተግባር ላይ የተሰማሩ የባህር ላይ

ወንበዴዎች መፈንጫ ሆና ቆይታለች:: ወንበዴዎቹ ከዚህም በተጨማሪ በህንድ ውቅያኖስ የሚያቋርጡ መርከቦችን በማገትና በመዝረፍ የዓለም የንግድ ሚዛን እንዲዛባና ችግር ውስጥ እንዲገባ አድርገው ቆይተዋል::

ይህን የተመለከቱት ምዕራባዊያን ሐገራት የባህር ላይ ወንበዴዎችን ለመቆጣጠር ግብረ ሐይል በማቋቋም መፍትሔ እንዲመጣ አድርገዋል:: በዚህ ሒደት ተሳታፊ የነበሩ ሰባት የባህር ላይ ወንበዴዎች በ2011 እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በህግ ጥላ ስር ውለው ሰሞኑን ጉዳያቸው እየታየ ነው:: የሮይተርስ ዘገባ እንደሚያስረዳው ከሰባቱ የባህር ላይ ወንበዴዎች መካከል ሁለቱ በእድሜ ልክ እስራት ቀሪዎች ደግሞ ከበድ ያለ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ዘገባው ጨምሮ ገልጿል::

በቀደሙት ጊዜያት የባቡር ጉዞዎች ለእንዲህ አይነቱ የሽብር ጥቃት ተመራጭ የነበሩ ቢሆንም አሁን አሁን ግን የአየር በረራዎችም አሣሣቢ በሚባል ደረጃ የስጋት ጥላ አጥልቶባቸዋል::

በቅርብ አመታት እንኳ ደብዛቸው ከጠፋ የመንገደኞች አውሮፕላን አንስቶ አየር ላይ እስከ ጋዩት ድረስ ዓለም እጅግ አሣዛኝ የበረራ የሽብር ጥቃቶችን አስተናግዳለች:: በዚህ ረገድ የአውሮፓ ሀገራትን የሚስተካከላቸው የለም:: በስፔን፣ በእንግሊዝ፣ በጣሊያን፣ በግሪክ፣ በፈረንሣይ፣… ሠሞኑን ደግሞ በቤልጂየም ብራሠልስ የተፈፀሙት የሽብር ጥቃቶች የዘርፉን ደህንነት ምን ያህል አደጋ ላይ እንደወደቀና በሽብር ፈፃሚዎች ዘንድ ዋነኛ ማነጣጠሪያ እየሆነ መምጣቱን ያመላክታል:: በአህጉራችን አፍሪካም ግብጽን በመሣሠሉ ሀገራት ዘግናኝ ጥቃቶች ተፈጽመዋል::

ባለፈው አመት 224 መንገደኞችን የጫነው የሩሲያ አውሮፕላን ፍንዳታ (አብዛኞቹ ጐብኝዎች መሆናቸውን ልብ ይሏል) የዚህ አንዱ ማሣያ ነው:: ይህ ጥቃት በግዙፍነቱ ይጠቀስ እንጅ ሀገሪቱ ቀላል የማይባል የባቡርና የአውቶቡስ ጥቃቶችን በተለያዩ ጊዜያት አስተናግዳለች::

በአንፃሩ በመስህብ መዳረሻዎች የሚፈፀሙት የሽብር ጥቃቶች መጠናቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ መምጣቱን ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያሣየው:: በተለይም የአውሮፓ ጐብኝዎች የሚበዙባቸው መዳረሻዎች ለሽብር ጥቃት ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል:: ቢቢሲ ለማሣያነት ባቀረበው የቱኒዝያ የባህር ዳርቻ ጥቃት አብዛኞቹ ሟቾች እንግሊዛውያን እንደነበሩ ገልጿል:: በተመሣሣይ በግብጽ በደረሡ አደጋዎችም እንግሊዛውያን ሠላባዎች እንደነበሩ አስታውሷል::

ቱሪዝምን መሠረት ያደረገ የሽብር ጥቃት ምንም እንኳ በአካባቢ የተወሠነ ነው ባይባልም ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የሚያስተናግዱ አህጉራት ከሌሎቹ አንፃር ደህንነታቸው በሽብርተኝነት እየተፈተነ ነው:: የዚህ ጥቃት ሠለባ የሆነው የአፍሪካ አህጉር በተለይም የምዕራብና የሠሜን አፍሪካ ሀገራት በአመታት ውስጥ ተመሣሣይ የሽብር ጥቃቶችን አስተናግደዋል:: በዚህ ወር መጀመሪያ በኮትዲቯር የባህር የመዝናኛ ስፍራ በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ላይ 18 ሰዎች ሲገደሉ አብዛኛዎቹ ሟቾች ፈረንሣውያን ነበሩ:: ባለፈው ህዳር ወር ማሊ ባማኮ ውስጥ በሚገኝ ዓለም አቀፍ ሆቴል ውስጥ በደረሠ ፍንዳታ 22 ሠዎች ሲገደሉ ምዕራባውያን ጐብኝዎች ዋነኛ ማነጣጠሪያ ነበሩ:: ቡርኪናፋሦ ኦጋዱጉ ውስጥም በደረሠው ተመሣሣይ ጥቃት አላማው ከዚህ የተለየ አልነበረም::

ከምንም በላይ ግን ቱሪዝም የሽብር ጥቃት ዋነኛ ኢላማ እየሆነ ሥለመምጣቱ ከፈረንሣይ በላይ አሣማኝ ማረጋገጫ አናገኝም:: በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ትልልቅ የሽብር ጥቃቶችን ያስተናገደችው ፓሪስ ከሌሎች አቻ ከተሞች ተነጥላ ሀዘን ያጠላባት እጣ ፈንታዋ ሆኖ ሣይሆን ቁጥር አንድ የቱሪስት መዳረሻ ከተማ በመሆኗ ነው:: ጥቃቱ በመዝናኛ እና በመጓጓዣ ሥፍራዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ስንመለከት ደግሞ ሽብር ይበልጥ የቱሪዝም ቀይ መብራት መሆኑን ያሣየናል:: የሠባ ሠዎችን ህይወት የቀጠፈው የሠሞኑ የፓኪስታን ጥቃትም ከዚህ ተነጥሎ የሚታይ አይደለም::

ዎል ስትሬት ጆርናል በፈረንጆቹ 2010 ባወጣው ሪፖርት በየአመቱ ከሦስት ሚሊዮን ጐብኝዎች ውስጥ አንድ ምዕራባዊ ዜጋ በሽብር ጥቃት እንደሚገደል ዘግቧል::

አብዛኞቹ የሽብር ድርጊቶች በሆቴሎች ፣ በመዝናኛ ሥፍራዎች፣ በባህር ዳርቻዎችና በመጓጓዣ

መንገዶች ብቻ ተወስነው የቀሩ አይደሉም:: ይልቁንም አብዛኛዎቹ የሽብር ቡድኖች ጥንታዊና እጅግ ውብ የሆኑ የቅርስ ሀብቶችን ማውደም ሌላኛው አጀንዳቸው ነው እንጂ:: የማሊ የእስልምና ሀይማኖት ማስተማሪያ ሆነው ሽህ አመታትን የኖሩት ውድ ቅርሦች ሲወድሙ ሽብርተኞች እንደ ቅዱስ ተግባር ቆጥረውታል::

ከአምስት አመታት በኋላ ከአይ ኤስ እጅ የወጣችው ጥንታዊቷ የሶሪያ ከተማ ፓልሜራም ወደ ሶሪያ ስትመለስ እኒያን የሁለት ሺህ ዘመናት ድንቅ የኪነ ህንፃ ውበት ይዛ ሳይሆን በአቧራ ተሸፍና ነው:: ምንም እንኳ ፓልሜራ ዛሬ ነፃ ብትወጣም ነገ የሚጐበኛት ስለመኖሩ ግን በእጅጉ ያጠራጥራል:: እናም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ወደፊት የጉብኝት መዳረሻዎች በሽብርተኞች በጐ ፍቃድና የዋጋ ተመን የሚጐበኙበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን የኢንዲፔንደንቱ ጉዞ ዘገባ አርታኢ ሲሞን ካልደር ይናገራል::

“የቱሪዝም ዘርፍ በግብጽ፣ በፈረንሣይ፣ በሊባኖስ፣ በቱኒዝያ፣ በማሊና መሠል መዳረሻዎች ፈተናው ቢበዛም ይበልጥ ደህንነታችንን እንድናጠናክርና የተሻለ አለም እንድንፈጥር የሚያደርገን ነው” ሲሉ ደግሞ የቀድሞው የዮርዳኖስ የቱሪዝም ሚኒስትር ለቢቢሲ ተናግረዋል::

“ይህ የግብጽ፣ የፈረንሣይ፣ የቱኒዝያ፣ የቱርክ፣ የታይላንድ አሊያም የኢንዶኔዥያ ችግር አይደለም፤ ይህ የሁላችንም ስጋት ነው:: በዚህም ውስጥ ሆነን ጉብኝታችን ይቀጥላል” ሲሉ አክለዋል::

ቱሪዝምን ከሽብር ነፃ ማውጣት የሚቻለው ግን መንግስታት ለጉዞና ለጉብኝት ደህንነት ይበልጥ ትኩረት ሲሠጡ እንደሆነ ነው ብዙዎችን የሚያስማማው:: አለበለዚያ ግን እንደ ኢንዲፔንዳንቱ የጉዞ ዘገባ አርታኢ ሲሞን ካልደር አባባል ዘርፉ በአሸባሪዎች እጅ ስር የመውደቁ ዕድል ሠፊ ይሆናል::

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 30

የ“ጃንቦ...”

ከገፅ 23 የዞረ

ወሊድ...የድህረ ወሊድ እና የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት

ሌላው በሆስፒታሉ የሚሰጥ አገልግሎት ነው:: እናት አስፈላጊው ሁሉ ምክር ተሰጥቷት ፈቃደኛ ከሆነችና በማህፀና የወለደች ከሆነች በ48 ሰዓት ውስጥ በማህፀን የሚገባ “ሉኘ” የተባለ የወሊድ መቆጣጠሪያ እንድትጠቀም ይደረጋል:: ሌሎችን አማራጮችንም በማቅረብ በእናት ምርጫ መሰረት የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ እንድትሆን ይደረጋል::

በህዳር 11 ሆስፒታል የእናቶችና ህፃናት አገልግሎት በአንድ ብሎክ ውስጥ ነበር የሚገኘው፣ በቅርቡ ግን ሆስፒታሉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ወደ ሁለት ብሎክ ለማሳደግና አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል:: ይህም የነበረውን መጨናነቅ በመቀነስ ለእናቶችና ህፃናት የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል እድል መፍጠሩን አቶ እስክንድር ይናገራሉ::

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ዳዊት ይፍሩ እንደሚሉት ሆስፒታሉ ለእናቶችና ህፃናት ጤና ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነው:: ሆስፒታሉ አስራሩን በማሻሻልና ለእናቶችና ህፃናት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር እናቶች የበለጠ ወደ ጤና ተቋም ሄደው እንዲወልዱ ለማድረግ አስቦም ነው እየሰራ የሚገኘው፣ ይህም ዛሬ ላይ የእናቶችን እርካታ በመጨመር ውጤት እያሳየ መሆኑን ዶክተር ዳዊት ይናገራሉ::

በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ሆስፒታሎች ማሟላት አለባቸው ተብለው የወጡ መስፈርቶች /ስታንደርድ ሆስፒታሉ ከ95 በመቶ በላይ ማሟላቱንም ዳይሬክተሩ ያብራራሉ:: በየመንፈቅ አመቱ ቅኝት በማድረግም የእናቶችን እርካታ ለመለካት ጥረት ያደርጋሉ:: እንደ አጠቃላይም የሆስፒታሉ አገልግሎት በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ያመጣውን ለውጥ ይመዝናሉ::

ሆስፒታሉ ከዚህም ባሻገር በዙሪያው የሚገኙ አምስት ጤና ጣቢያዎችን በቋሚነት

ይደግፋል:: ለጤና ጣቢያዎቹ ከእናቶችና ህፃናት ጤና አንፃር ሆስፒታሉ በትኩረት ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን በየሶስት ወሩ ድጋፋዊ ጉብኝት ያደርጋል:: በጉብኝቱ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይም ለጤና ጣቢያዎቹ አስተያየት ከመስጠት ባለፈ ስልጠና ይሰጣል:: ለጤና ጣቢያዎቹ የሚደረገው ድጋፍ በተዛዋዋሪ የሆስፒታሉንም ስራ ማቅለል እንደሆነም ሜዲካል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል::

አርሶ አደር ወርቁ ከማንጎም ሆነ ከፖፖያ፣ ከዘይቱንም ሆነ ከቡና ሽያጭ ከሚያገኙት ብር ይልቅ የበለጠ አስደስቶኛል የሚሉት የአካባቢያቸውን የአየር ሁኔታ መቀየራቸውን ነው፤ ነፋሻ አካባቢ ውስጥ መኖሩ መንፈሳቸውን እንደሚያረካው፣ ልጆቻቸው በነፃነት የዛፍ ጥላ ሥር ሲጫወቱ ማየቱ

ከገፅ 3 የዞረ

የግዮን...መሬት ላይ ተንጠባጥበው ይስተዋላሉ:: ረዥም ዕድሜ ያስቆጠሩ የማንጎ፣ የፖፖያና የዘይቱን ዛፎች፣ አካባቢውን ነግሠውበታል:: እነዚህን የለመለሙ የፍራፍሬ ዛፎች ተዟዙሬ እያየሁ በአዕምሮየ ‘አርሶ አደር ወርቁ ካለሟቸው ፍራፍሬዎች ለኪሳቸው ገንዘብ እንደሚአገኙት ሁሉ ለአእዋፍ ምግብ፣ ለባህር

እንደሚያስደስታቸው ይናገራሉ:: ከጊዮን ወንዝ እየጠለቁ ካበቀሉት የማንጎ፣

የፖፖያ፣ የዘይቱን፣ የጌሾ… ጫካዎች ውስጥ ከአርሶ አደር ወርቁ ጋር ዛፍ ጥላ ሥር ቁጭ ብለን ከአወራን በኋላ የአትክልትና ፍራፍሬ ማሳቸውን ተዟዙሬ ጎበኘሁ:: ወፍ እየገመጠ የጣላቸው የማንጎ ፍሬዎች

ዳር ህዝብ ደግሞ በዋጋ የማይተመን ንፁህ አየር መለገሳቸውን ያውቁት ይሆን’ እያልኩ ከሰዓታት በፊት በጊዮን ትሩፋቶች አምልጨው የነበረውን የፀሐይ ሀሩር እንደገና ተቀበልኩት::

ንጉሱ ለአጭር ጊዜም ቢሆን ህዝቡ በቤተ ክርስቲያን አማካኝነት ትምህርት እንዲማር ያደርጉ ነበር:: በዚህም በርካታ መኳንንት፣ የቤተክህነት ሰዎችና ሌሎች ማንበብና መጻፍ የቻሉበት ጊዜ እንደነበር ይነገራል::

አፄ ሕዝበናኝ የመኖሪያ ቦታቸውን በዳይ ጊዩርጊስ በማድረግ ቤተ መንግስታቸውን ያሰሩ እንጅ ከቦታ ቦታ በመዘዋውር የተለያዩ የአስተዳደር ስራዎችን ይሰሩ ነበር:: በሚዘዋወሩበት ጊዜም ያርፉ የነበረው በድንኳን ሲሆን ንጉሱን በስራ የሚረዱ የጦር ሰራዊቱ መሪ፣ ዋና ፈራጆች/ዳኞች/፣ ፀሐፊዎችና ብዙ አሽከሮችም አብረው ይንቀሳቀሱ ነበር::

አፄ ህዝበናኝ …ከገፅ 15 የዞረ በኢትዮጵያ መጻሕፍት በብዛት ተደርሰውበታል

በሚባለው መካከለኛው ዘመን ለተፃፉት ልዩ ልዩ መጻሕፍት መገኘት የሽዋ ምሁራንን በማፍራት አፄ ሕዝብናኝ ተጠቃሽ ንጉስ ነበሩ::

ከአፄ ይስሐቅ በኋላ ለአጫጭር ጊዜ የነገሱት የንጉስ ዳዊት ልጆች እርስ በርስ ባለመስማማትና በሽኩቻ እንዳሳለፉ በታሪክ ይነገራል:: እርስ በርስ ከነበረው የውስጥ ለውስጥ ግጭት በተጨማሪ ከአረብ ሐገር በመምጣት የእስልምናን ሐይማኖት ዋና የሀገሪቱ እምነት ለማድረግ ከጣሩት የመሐመድ አቡል ባራካት ወታደሮች ጋር በየጊዜው የነበረው ጦርነትም የተሻለ ሊሰሩ የሚችሉበት ፋታ አልሰጣቸውም:: ከአፄ ይሰሐቅ የንግስና ጊዜ በኋላ ሁለት ወንድሞቻቸው አፄ በድልናኝ ለአንድ ዓመት ቀጥሎም አፄ አምደ እያሱ ለሰባት ዓመታት የስልጣን

መንበሩን በመያዝ አፄ ዘርያ ያዕቆብ ገናና በመሆን ስልጣነ መንበሩን ለ34 ዓመታት ይዘው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያመላክታሉ::

በአፄ ዳዊት ወገን ብቅ ካሉት ነገስታት ለአጭር ጊዜም ቢሆን ኢትዮጵያን የመሯትን አፄ ሕዝበናኝ ታሪክ የምንደመድመው በባህል አምባነቷ ተቀባይነት እያገኘች በሄደችው የሞርትና ጅሩ ወረዳ የሚገኘውን የቤተ መንግስት ፍርስራሽና ሌሎች የነገስታት ዙፋን እንዲሁም አፄው ከ500 ዓመት በፊት ያሰሩትን የዳይ ጊዬርጊስ ቤተክርስቲያን እንዲጐበኙ በመጋበዝ ነው::

ወ/ሮ ጥሩወርቅ ሞላ በሆስፒታሉ ያገኙት አገልግሎት በእጅጉ እንዳስደሰታቸው ይናገራሉ፡፡

ከገፅ 7 የዞረ

በዚህ እስከ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በሚዘረጋው የጃምቦና ውስኪ ባህር ከዕውቀት በር ለሚወጡት ተማሪዎች እግር በእግር እየተከተለ የሚሸኛቸው የመጠጥ ወንዙ ነው:: በራፋቸው ላይ የተዘረጋው የጃምቦ ወንዝ ተማሪዎችን እያባበለ አሥገብቶ ወደ ደራሽ ወንዝነት በመቀዬር ወስዶ ቀበሌ ስድስት “ኮሸኮሽ ሰፈር” እና ቀበሌ 1 ይቀላቅላቸዋል:: ኮሸኮሽ ሰፈር ምን እንዳለ ልብይሏል፤ ይህ ደግሞ ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው::

እዚህ ላይ ቆም ብለን ማሰብ አለብን:: የባህር ዳርን እንደማሣያ አቀረብሁ እንጅ ጐንደርም፣ ደሴም፣ ደብረ ታቦርም፣ ደብረ ማርቆሥም፣ ወልድያም፣ ደብረ ብርሐንም ብትሔዱ የጃምቦው ወንዝ ጉልበቱ የማይጋፉት ነው:: ጐንደር ዩኒቨርሲቲ ከዋናው ግቢ እንደወጡ ቁልቁል በአሥፋልቱ ወደመሀል ከተማ ሲዘልቁ በግራና በቀኝ በጃምቦ ወንዞች ተከበው ነው:: ወንዙ በረጅም ጉዞው ሳይደነቃቀፍ እስከ መሀል ፒያሳ በሙሉ ጉልበቱ ይዘልቃል:: በድራፍት ባህር ውስጥ እየጠመቀ መላ ከተማዋን ያዳርሳታል::

ወልድያ የባሰባት ሆና ታገኟታላችሁ:: ቀጭኗ አሥፋልት ከአቅሟ በላይ የጃምቦ ወንዝ ግራና ቀኝ አጅቧታል። ደሴ ከጃምቦው መፈጠሪያ በቅርብ ርቀት ላይ ተገኝታ እንዴት የወንዙ ተካፋይ አትሆንም፤ የደሴ ጐዳናዎችም የጃምቦ ወንዞች የሚጓዙባቸው ናቸው:: የጃምቦው ወንዝ እስከ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ሽቅብ ወጥቶ ወደ ተማሪዎች ይደርሳል::

እንዳትቀየሙኝ ደብረ ብርሐን፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮሰበር እና ፍኖተሠላም ብቻ ሳይሆኑ የጃምቦ ወንዝ በትንንሽ ከተሞች ሁሉ በአሥደንጋጭ ፍጥነት ተሥፋፍቷል:: ፅፌው ሥለማልጨርሰው ነው እንጂ በየከተሞች ከዚህ የተለዬ የመጠጥ ማዕበል የለም::

እግር ኳስ ሜዳዎች ዙሪያቸውን በጃምቦ ቤቶች የተከበቡ ናቸው:: የአዲስ አበባውን ስታደዬም ያየ ሰው በቂው ነው:: በሜዳው ላይ ለጤናም ለውጤትም ተጫዎቾች ኳሥ ይጫወታሉ:: በስቴዲዮሙ የንግድ ቤቶች ደግሞ ለመግለፅ በሚያሥቸግር፣ ለማዬት በሚከብድ ሁኔታ ስፖርት አፍቃሪው የአዲስ አበባ ህዝብ ጃምቦ ሲያጋጭ ታገኙታላችሁ::

እናም የጃምቦው ወንዝ ሊገደብ አይገባም ትላላችሁ? ወንዙ ተጠራቅሞ ማዕበል አሥነሥቶ ሁላችንንም ከመጠራረጉ በፊት ሊገደብ አይገባም? በዚህ የጃምቦ ወንዝ ውስጥ ተዘፍቆ የሚውል ሰካራም ዜጋሥ አገሪቱን እንዴት ብሎ ሊያራምዳት ይችላል? ሊገደብ ግድ ነው!

ገጽ 31በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.

ከገፅ 13 የዞረ

ፊት ለፊት...ከገፅ 17 የዞረ

ሩብ + ...ወጣቱ አርሶ አደር መርሻና ከእርሱ ጋር የመስኖ

ቦታ የተሰጣቸው ወጣቶች በተደረገላቸው ድጋፍ ደስተኛ መሆናቸውንና ሕይወታቸው መለወጡን ይናገራሉ:: ከተደረገላቸው ድጋፍ ባሻገር ግን የመስኖ ፈለጉ ተጠናቆ አለመሠራቱና የብቅል ፋብሪካውና የምርጥ ዘር ሕብረት ሥራ ማኅበሩ የመግዣ ዋጋቸውን አለማሻሻላቸው ለሥራቸው እንቅፋት በመሆናቸው እንዲስተካከሉላቸው ጠይቀዋል::

አቶ አስችለኝ ተገኘ የዳባት ወረዳ የሰብል ዘር ብዜት ባለሙያ ናቸው:: በደቋ ቀበሌ ዛሪካርና ወንዝ ዳርቻ በሚገኙት የእነመርሻ የመስኖ ሥራዎች ቦታ ተገኝተው የሚያደርጉትን ድጋፍና ክትትል በሚመለከት ሲያብራሩ “ወጣቶቹ በመስኖ ሥራ በጣም ተጠቃሚ እየሆኑ ነው:: እኛም በተቻለ አቅም የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስፈላጊውን የግብርና ኤክስቴንሽን ሥራ እየሠራን ነው:: ወደ ፊትም ከዚህ የተሻለ ድጋፍ ማድረጋችንን እንቀጥላለን” ብለዋል::

በተያዘው የበጋ ወቅት ወጣቶቹ በመስኖ እያመረቱ ያለው የቢራ ገብስ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለምርጥ ዘር የሚውል እንደሆነ የተናገሩት አቶ አስችለኝ “በዳባት ወረዳ በ13 ቀበሌዎች የቢራ ገብስ ለማልማት የሚያስችል ዕድል አለ፤ በዚህ ዓመት አሁን ማሳ ላይ ካለው ውጭ ብቻ 675 ኩንታል የቢራ ገብስ ተመርቷል፤ ከዚህ ውስጥ 586 ኩንታሉ

ያስታወሱት አቶ አስችለኝ የቢራ ገብስ ግን አንድ ኪሎ ግራም 10 ብር ከ90 ሳንቲም ሒሳብ ለማኅበራትና ለብቅል ፋብሪካው እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል:: “የምርጥ ዘር ዋጋ ለኪሎ እስከ 17 ብር ከ60 ማሻቀቡ ግን ሙሉ በሙሉ አርሶ አደሩ የቢራ ገብስ እንዳይዘራ እንቅፋት ነው:: ያም ሆኖ ሙሉ ግብዓት እና ለአንድ ሄክታር መሬት እስከ አንድ ኩንታል ተኩል ዘር ከተጠቀሙ የቢራ ገብስ በወረዳችን ምርታማነቱ በሄክታር እስከ 56 ኩንታል ስለደረሰ አዋጭ ነው:: ግን አርሶ አደሩ ሙሉ በሙሉ በምክረ ሀሳቡ መሠረት አለማምረቱ በዚህ ልክ ሁሉም ተጠቃሚ እንዳይሆን አድረጎታል” ሲሉ አቶ አስችለኝ አስረድተዋል::

ከዋጋ ጋር በተያያዘ ወጣቶቹ የሚያነሱትን ማስተካከያ ጥያቄ በተመለከተ ሲያብራሩም “በእርግጥ ከተራው ገብስ ጋር ሲነፃፀር የቢራ ገብስ ጥሩ ዋጋ ያስገኛል፤ ነገር ግን አርሶ አደሩ ዘር የሚገዛው በ17 ብር ከ60 ነው፤ ለማኅበራቱ የሚያስረክበው ግን በ10 ብር ከ90 ሳንቲም ነው:: ይህ መስተካከል አለበት:: የብቅል ፋብሪካውም ከአርሶ አደሮቹ የሚረከብበት ዋጋ እንደገና ሊጤን የሚገባው እንደሆነ ተረድተናል:: ለማሻሻልም እንጥራለን” ብለዋል::

የዳባት ወረዳ ግብርናና ገጠር ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረሕይወት መኳንንት ደግሞ በወረዳው መሬት ያልነበራቸው 304 ወጣቶች ተደራጅተው በመስኖ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ:: ከእነዚህም

“በተለያዩ ጊዜያቶች ተሽከርካሪዎች በምሽት ሲሄዱ ከመኖሪያ ቤቶች አጥር ጋር በተደጋጋሚ ይጋጫሉ:: በምሽት መኪናዎች ሲተላለፉ አደጋ ይደርስባቸዋል:: በከተማዋ በ2008 ዓ.ም ከ20 በላይ አደጋዎች ደርሰዋል::

“የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ገንዘብ አውጥቶ የመንገዱን ፕላን በየጊዜው ይከልሳል:: ለዚህም በ2007 ዓ.ም ብቻ 55 ሺህ 500 ብር ወጪ አድርጓል:: በዚህም ከገንዘብ በተጨማሪም ጉልበትና እውቀት ባክኗል:: ቀስ ብሎ የተሻሻለው ፕላንም ጠመዝማዛ ሆነ ተብሎ ተሰረዘ:: እናም ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ‘አፈር ያነሳ ሥጋ’ ሆኖብናል በማለት አቶ

ቀፀላ የችግሩን ስፋት ዘርዝረዋል::

የፍጆታ ምርትበሸዋ ሮቢት ከተማ የስኳርና ዘይት አቅርቦት

ተደራሽ አይደለም ያሉት ወይዘሮ አምበልነሽ ተካ ናቸው:: “በየቀበሌው አልፎ - አልፎ አቅርቦቱ ቢመጣም በቤተሰብ የሚሰጠው አንድ ኪሎ ግራም ስኳርና አንድ ሊትር ዘይት ብቻ ነው:: በገጠር ቀበሌዎችማ ጭራሹን የለም፤ በመንግስት መስሪያ ቤትም አቅርቦቱ የለም:: ለምን? ስንል ደግሞ ‘የመንግስት አቅርቦት አነስተኛ ነው’ እንባላለን::

“በሌላ በኩል ከቸርቻሪዎች በብዛት ይገኛል:: መንግስት በየቀበሌው የሚልከውን የፍጆታ ምርት በስውር ይቸበቸባል:: እናም ህብረተሰቡ ላላስፈላጊ ወጪ ተዳርጓል” ብለዋል::

ደንአቶ እንደሻው ከፍያለው ይባላሉ:: የእኒህ

ግለሰብ ጥያቄ ተናጠላዊ አይደለም:: ህይወት ላለው ሁሉ የሚበጅ ነው- የደን ሀብትን ይመለከታል:: “በሸዋ ሮቢት ዙሪያ የሚገኘው የህዝብ ደን እየተጨፈጨፈ ነው:: ቀደም ሲል የነበሩት ጠባቂዎች ‘አታስፈልጉም’ በሚል ተሰናብተዋል:: ይህን ክፍተት ተጠቅመውም ግለሰቦች እየመነጠሩት ይገኛሉ:: ‘ሀይ!’ ባይ በመታጣቱም ትናንት አረንጓዴ ሸማ ለብሰው የነበሩት ተራሮች እርቃናቸውን ቀርተዋል:: እናም መላ ይፈለግለት” የሚል ነበር::

ገቢዎችበሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች “አላግባብ

ግብር ተጣለብን፣ የሰነድ ማበላለጥ አለ፤ ፍቃድ ተከለከልን፣” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሳሉ:: ከነዚህም መካከል አቶ አሊ ሙሀመድ እንደተናገሩት የሴቶች፣ የወንዶችና የህፃናት የልብስ መሸጫ ሱቅ አላቸው:: ይሁን እንጅ፤ የንግድ ፈቃዳቸውን ወደ ጫማ መሸጫ ለመቀየር አሰቡ:: ጥያቄያቸውንም ለሸዋ ሮቢት

የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቀረቡ “ይሰራላቸው” ተባለ:: በመጀመሪያም “ፍቃዱን ያሳድሱ” ተባሉ:: ሁለት ሺህ ብር ከፍለው አሳደሱ:: በመጨረሻም “የጫማ መሸጫ ፈቃድ ይሰጠኝ?” ሲሉ አመለከቱ:: በቀነ ቀጠሮ አሰናበቷቸው:: ይሁንና ላለፉት ሦስት ወራት ቢመላለሱም ፍቃዱ አልተቀየረላቸውም:: “በሦስተኛ ወገንም 10 ሺህ ብር ጉቦ ተጠየቅሁ” ብለዋል::

መልስየአማራ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ከሸዋ ሮቢት

ከተማ አስተዳደር ጋር ባዘጋጀው የከተሞች መድረክ ውይይት ላይ አመራሩና ነዋሪው ፊት ለፊት ተገናኝተዋል:: ለተነሱ ጥያቄዎችም የሚከተለው ምላሽ ተሰጥቷል::

በመብራት ጉዳይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና አስተያየት የሰጡት የሸዋ ሮቢት ከተማ የኤሌክትሪክ ዲስትሪክት ሀላፊ አቶ ደረጀ ተስፋዬ ናቸው፤ “በህብረተሠቡ የተነሱ ጥያቄዎች ትክክል ናቸው፤ ነገ፣ ዛሬ ሳይባል መፈታት አለባቸው:: ህብረተሰቡ ባዋጣው ገንዘብ ተጠቃሚ አልሆነም:: እርግጥ ነው፤ ጥያቄያቸው የዘገየው በምሰሶ፣ በገመድና በትራንስፎርመር እጥረት ነው:: በቅርቡ ሁሉም እየተሟላ በመሆኑ ለጥያቄያዎች ተገቢው ምላሽ ይሰጣል” ብለዋል::

በንፁህ መጠጥ ውሀ ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሰጡት ደግሞ የከተማዋ የውሀ አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ መንግስቱ ናቸው:: እንደ እሳቸው ገለፃ የከተማዋ ነዋሪ በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ ነው:: እናም በ1977 ለ15 ሺህ ህዝብ ተብሎ ከተቆፈረ ጉድጓድ ውሀ ያገኛል:: አሁን የከተማዋ ህዝብ 50 ሺህ ደርሷል:: በመሆኑም የህብረተሠቡን ቁጥር ከአቅርቦቱ ጋር ለማጣጣም መንግስት ጥልቅ ጉድጓድ ቆፍሯል:: 48 ኪሎ ሜትር መስመርም ዘርግቷል:: የክልሉ መንግስት ደግሞ የኤሌክትሪክ ውስንነቱን ግምት ውስጥ አስገብቶ የጀኔሬተር እርዳታ አድርጓል፤ እናም ችግሩ በቅርቡ ይቃለላል::

የአንድ ከተማ ዕድገት የሚለካው በህዝቡ ኑሮ ነው:: ለዚህ ደግሞ የመንገድ ምቹነት ዋነኛው ነው:: የሸዋ ሮቢት ከተማ የአስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምናለ መዓዛ እንደገለፁት በመንገድ በኩል የባለሙያ እጥረት አጋጥሟል:: ያሉትም ቢሆን ካርታ በአግባቡ ማንበብ ባለመቻላቸው ጽ/ቤቱን ለተለያዩ ኪሳራ ዳርገውታል:: ስለዚህ በቂ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን ባለሙያዎች ለመቅጠር ጥረት እየተደረገ ነው::

የከተማዋን መንገድ ለማስፋት የግድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ይሁንታ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ምናለ ከዚህ ባለፈ ግን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ደረጃውን በጠበቀ የጌጠኛ ድንጋይ እየተገነባ ነው ብለዋል::

ለብቅል ፋብሪካው ተልኳል፤ 89 ኩንታል ደግሞ በምርጥ ዘርነት ለዘር ተሰብስቧል፤ አሁን ማሳ ላይ ያለውንም በዘር ብዜት ማኅበራት በኩል ተረክበን መልሰን ለአርሶ አደሩ የመኸር ግብዓት አድርገን እናስረክበዋለን” ብለዋል::

የጎንደር ብቅል ፋብሪካ እና የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጄንሲ የቢራ ገብስን ለማምረትና የተሻለ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በስልጠና፣ በግብዓት፣ በአቅርቦትና በገበያ ትስስር ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነም አቶ አስችለኝ አብራርተዋል:: በዳባት ወረዳ በቢራ ገብስ መልማት የሚችል ሰፊ ማሳ እንዳለ የሰብል ዘር ብዜት ባለሙያው ቢናገሩም በ2007/2008 የምርት ዘመን በመኸር በዘር መሸፈን የተቻለው ግን በምርጥ ዘር እጥረት 116 ሄክታር መሬት ብቻ ነው:: በተለይ ከፍተኛ የቢራ ገብስ አምራችነት አቅም ባለው የወቅን ዙሪያ ቀበሌ ብቻ በቀጣይ መኸር (2008/2009 የምርት ዘመን) 300 ሄክታር ማሳ ለመሸፈን መታቀዱን አስረድተዋል::

በበጋ ወራት ሌሎች የአካባቢው ዝርያ ያላቸው የገብስ ዓይነቶችን ሲያመርቱ አርሶ አደሮቹ ለአንድ ኪሎ ግራም አምስት ብር ብቻ እንደሚሸጡ

ውስጥ 46ቱ እነመርሻ ያሉበት የደቋ ቀበሌ አንዱ እንደሆነ ገልፀዋል::

ከብቅል ፋብሪካው ጋር አስቀድሞ የገበያ ትስስር ውል ተሠጥቶ ወጣቶቹ ተጠቃሚ እንደሆኑ የገለፁት የጽ/ቤት ኃላፊው ያልተጠናቀቀውን የውኃ ፈለግ በተመለከተም “ሥራው ተጠናቅቆ ርክክብ ያልተፈፀመ ስለሆነና ውል ከወሰደው አካል ጋርም ተነጋግረን ሥምሪት የሰጠንበት ስለሆነ ሥራው ይቀጥላል:: ተጨማሪ ወደ 28 ሄክታር የሚያለማ የመስኖ ተፋሰስ ሥራ በዛሪካርና ወንዝ ላይ ለመሥራትም አቅደናል:: የውኃ አቅርቦቱም የተጠና ስለሆነ ወጣቶቹ ስጋት አይግባቸው” ብለዋል::

በዳባት ወረዳ ከዛሪካርና በተጨማሪ ከ300 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚችል ጃንበለው የሚባል ወንዝም ይገኛል:: በወረዳው ከመስኖ ጋር በተያያዘ ብቻ በተያዘው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዓመታት እስከ አንድ ሺህ ወጣቶችን የወል መሬቶችን በመስጠት ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም አቶ ገብረሕይወት አስረድተዋል::

በዳቋ ቀበሌ ዛሪካርና ወንዝ ዳር መርሻና ሌሎች ወጣቶቹ በመስኖ ያለሙት የቢራ ገብስ ዘር

ወደ ገጽ 39 ዞሯል

ሀሣብን መግለጽ፣ መዳመጥ እና ለችግሮች የመፍትሄ ሀሣብ የተንሸራሸረበት ውይይት፤

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 32 ማስታወቂያ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበደቡብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የእስቴ ወረዳ የግብርና ጽ/ቤት በለዋየ ቀበሌ ልዩ ስሙ መንበርያ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ የሚገኘውን የህዝብ ደን ባህር ዛፍና የፈረንጅ ጽድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ ያላቸው፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማየት ይቻላል፡፡

6. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሣ ብር/ ብቻ ከፍሎ በስራ ቀን መግዛት ይቻላል፡፡

7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን አይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የእስቴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡3ዐ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡

9. ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡3ዐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ላይ ይከፈታል፡፡

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 447 0888 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእስቴ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

የአጥር ግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያየባህር ዳር አይ ሲ ቲ ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የማዕከሉን አጥር ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን

በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. ደረጃ GC/BC 10 እና ከዚያ በላይ የሆነ የህንፃ ተቋራጭ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር

ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. በንግድ ኢዱስትሪ ቢሮ የተሰጠ የታደሰ የዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. የክልሉ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ለ2008 ዓ/ም የስራ ዘመን የተመዘገቡ ስለመሆኑ

የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ፈቃዳቸውን በፌደራል ላወጡ ተቋራጮች በአብክመ ጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ልማት

ቢሮ የተሰጠ የአጭር ጊዜ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡

6. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች ለደረጃው የሚያስፈልገውን የሰው ኃይልና ማቴሪያል ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ከማዕከሉ ግዥ

ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 114 በመቅረብ የማይመለስ ብር 30.00/ሰላሣ ብር/

በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

9. በአንዱ ተጫራች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት ከጨረታ የሚያሰርዝ ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ

ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ከጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ ጋር በማድረግ በጥንቃቄ በሰም

በታሸገ ፖስታ እስከ 22ኛው ቀን 4፡ዐዐ ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ማስገባት

ይኖርባቸዋል፡፡

12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በ22ኛው ቀን

በ4፡ዐዐ ታሽጎ በዚያው ቀን በ4፡3ዐ በማዕከሉ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር

114 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 22ኛው ቀን የበዓላት ወይም መደበኛ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን

በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

13. ተጫራቾች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ላይ የድርጅቱ ስምና ፊርማ ማህተም

ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582264135 ወይም በአካል ቀርበው

ማግኘት ይችላሉ፡፡

15. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በማንኛውም የመንግስት ተቋም ስራን በማጓተት ወይም ባለመጨረስ

ያልታገዱ እንዲሁም ያልተከሰሱ፤ በክስ ላይ ያልሆኑና የመልካም ስነ-ምግባር ስራ አፈፃፀም

ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት የስነ-ምግባር ጉድለቶች ማለትም በተሣተፈበት ግንባታ

ስራውን ያቋረጠ ያጓተተ የታገደና በክስ ላይ ያለ መሆኑን ከተረጋገጠ አሰሪው መ/ቤት ከውድድር

ወጪ ያደርጋል፡፡

16. አሰሪው መ/ቤት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአብክመ የኢ/ኮሙ/ል/ኤጀንሲየባህር ዳር አይ ሲ ቲ ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል

አድራሻ፡- ባ/ዳር ቀበሌ 03 ከሙሉዓለም የባህል ማዕከል ጐን

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕ/ጎጃም ዞን የሰ/አቸ/ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ የሊበን ለግዲያ መንገድ ለማስጠገን

ግሪደር፣እስካቫተር፣ሮሎ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ባለንብረቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ናምበር/ ያላቸው፡፡

3. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50000.00/ሃምሣ ሺህ ብር/እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይንም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ከሰ/አቸ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ በመክፈልና የከፈሉበትን ማስረጃ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡3ዐ ድረስ ተሽጦ በ16ኛው ቀን 4፡ዐዐ ታሽጐ በዚሁ ቀን 4፡3ዐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ስዓት ታሽጐ በተመሣሣይ ስዓት ይከፈታል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዛት ሲመጡ የንግድ ስራ ፈቃዳቸውን የጨረታ ሰነድ ለሚሸጠው አካል ማሣየት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሰነዶችን ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን በሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ስለሆነ በአንድ ሎት /ምድብ/ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ዋጋ መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡ እንዲሁም የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ እና የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት ውጭ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00/ሰላሣ ብር/ በመክፈል ከሰ/አቸ/ወ/ግ/ን/አስ/የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ከ20 በመቶ ቀንሶም ይሁን ጨምሮ ማሰራት ይችላል፡፡

14. ተጫራቾች ዋጋ በሚያስቀምጡበት ጊዜ የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ ከሁሉም የጨረታ ሰነዶች እና ፖስታው ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ መሆን የለበትም ሆኖም ግን ስርዝ ካለው ፊት ለፊት ፓራፍ ወይም መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ካልሆነ ግን ተጫራቾች ሙሉ በሙሉ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ፡፡

15. በጨረታው ለመሣተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 02 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

16. ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡

የሰሜን አቸፈር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ገጽ 33በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰዎች ምን ይላሉ?ሰዎች ምን ይላሉ?አብርሃም በዕውቀት

የሕዳሴው ግድብ

ለቁጠባ ባሕላችን ምን አስተዋጽኦ አለው?

የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ለሀገራዊ ቁጠባ ያበረከተው አስተዋፅዖ በጣም ከፍተኛ ነው:: ከዚህ ቀደም የነበረብን ችግር

ድህነት ብቻ ሳይሆን የሥራ ባሕል አለመዳበርና የቁጠባ ባሕላችን ዝቅተኛ መሆን ጭምር ነበር:: ከተረፈን እንጅ ከምንጠቀመው ቀንሰን መቆጠብ አልለመድንም ነበር::

የሕዳሴው ግድብ ግንባታ ሲጀመር ግን ብዙ ነገሮች መቀዬር ጀምረዋል፤ በተለይ የቁጠባ ባሕላችን በጣም ተሻሽሏል:: ግድቡ ትልቅ ሕዝባዊ መነሳሳትን ፈጥሯል፤ ሕብረተሰቡ ለግድቡ ያለውን ድጋፍ ደግሞ በአብዛኛው የገለፀው የቁጠባ ቦንድ በመግዛት ነው:: ሰው ቦንድ ሲገዛ ደግሞ ግድቡን ከመደገፍ ባለፈ የእያንዳንዱ ዜጋ የቁጠባ ልምድ አብሮ እያደገ ነው::

ቁጠባ በመሠረቱ የአንድ ማሕበረሰብ የለውጥ መሠረት ነው:: የኢንቨስትመንት ፍሰትም

የሚጨምረው ሕብረተሰቡ በሚኖረው የቁጠባ አስተዋፅዖ ልክ ነው:: ይሁን እንጅ የቁጠባ ልምዳችን በጣም አነስተኛ ነው:: ከዚህ በፊት ከነበረው ልምዳችን ጋር አነጻጽረን ስናየው አሁን ላይ በጣም ተለውጧል:: ለዚህ ለውጥ ደግሞ ትልቁን ሚና የተጫወተው የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የድጋፍ ቦንድ ነው:: ግድቡ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ አስተሳሰብ ያነቃነቀ፣ ንቅናቄው ደግሞ በቦንድ ግዥና በስጦታ በተግባር የታገዘ ነበር::

ይህም ለቁጠባ ባሕል መጎልበት የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል:: ከድጋፉም ባሻገር ግድቡ የፈጠረው የሥራ ዕድል ለቁጠባ መሻሻል የራሱ ድርሻ አለው:: የተፈጠረው የሥራ እድል ቀላል አይደለም፤ ያንን ተከትሎ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎችም የተወሰነ መቆጠብ ጀምረዋል:: የባንኮች የተደራሽነት ሁኔታም በእጅጉ አድጓል፤ የባንኮች ወደ ሕብረተሰቡ መቅረብም የቁጠባ ባሕል እንዲያድግ አስተዋፅዖ አድርጓል፤ መሠረታዊ

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ለእኔ ቁጠባ ባሕል መሻሻል አስተዋፅዖ ማድረጉን በውል አላወኩም:: ቦንድ በመግዛት ግን

ተሳትፌያለሁ፤ ግድቡ ከተጀመረ አንስቶ በየዓመቱ ቦንድ አቅሜ በፈቀደ ልክ እየገዛሁ ነው:: ዘንድሮ ግን የተወሰነ ድርቁ ተፅዕኖ ስላሳደረብኝ አልገዛሁም፤ ምናልባት እግዜር ከታረቀንና ወቅቱን ጠብቆ ዝናብ ከጣለ በሚቀጥለው ዓመት እጥፍ አድርጌ እገዛለሁ፤ እኔ ቦንድ የምገዛው ለመቆጠብ ብዬ ሳይሆን አገሬ ከምትሠራው ታሪክ ተሳታፊ ለመሆን ነው:: በመቆጠብ ደረጃም እንደገቢዬ መጠን በየወሩ እቆጥባለሁ፤ በቋሚነት በየወሩ መቆጠብ ከጀመርኩ ወደ አራት ዓመት ሆኖኛል:: አሁንም መቆጠቤን እቀጥላለሁ::

የቁጠባ መጠን በማይክሮ ባንኮቻችን በጣም አድጓል፤ በእርግጥ ለውጡ “በሕዳሴ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የመጣ

ነው? አይደለም?” የሚለው ጥናት ያስፈልገዋል:: መንግሥትም የቁጠባ ባሕል እንዲያድግ ትኩረት ሰጥቶ መሥራቱ ለተገኘው የቁጠባ ልምድ ማደግ አስተዋፅዖ እንዳበረከተ ይሰማኛል:: በእኛም በኩል የሕብረተሰቡ የቁጠባ ባሕል እንዲጎለብት በሰፊው የሠራነው ባለፉት አራትና አምስት ዓመታት ነው፤ በተለይም ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የቁጠባ ልምድ እንዲያድግ ቤት ለቤት ሳይቀር ትምህርት እንዲሰጥ ተደርጓል::

በዚህም በየቤቱ ይቀመጥ የነበረ ገንዘብ ወደ ፋይናንስ ተቋማት መምጣት ጀምሯል:: የፋይናንስ ተቋማቱ ወደ ህብረተሰቡ ቀዬ መሄዳቸውም ለቁጠባ ባሕል ማደግ አስተዋፅዖ አበርክቷል:: እንዲያውም እንደ አብቁተ ስናዬው ባለፉት 18 ዓመታት ከነበረው የቁጠባ አቅም ይልቅ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሰበሰበው በእጅጉ ይበልጣል:: ይህም የሚያሳየው የቁጠባ አቅምም ልምድም ማደጉን ነው::

በሕዳሴ ግድብ ቦንድ ከ177 ሚሊዮን ብር

የቁጠባ ባህል ለውጥ እንዲመጣ ግን የሕዳሴው ግድብ ቦንድ ሽያጭ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል:: አሁንም ግንዛቤ የመፍጠሩና ቁጠባን የማበረታታት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፤ ያለቁጠባ ኢንቨስትመንት ሊኖር አይችልም::

በሕዳሴ ግድብ ቦንድ ምክንያት ብቻ የቁጠባ ደብተር የከፈቱ ግን ደግሞ በአቅማቸው ልክ ከቦንድ ግዥ በተጨማሪም መቆጠብ የጀመሩ ዜጎች በጣም ብዙ ናቸው:: እኛም እንደ ባንክ ሠራተኛም እንደ ኢትዮጵያዊም ቦንድ ለሚገዙ ሰዎች የተለዬ ፈጣን መስተንግዶ እንሰጣለን:: እንደ መደበኛው የባንክ ደንበኞች የመስተንግዶ ወረፋ አይጠብቁም፤ የተሻለ ወለድም እንዲያገኙ እናደርጋለን፤ ይህም ስኬታማ እንደሆነ እየታዘብን ነው::

የቁጠባ መጠን በእጅጉ ማደጉን በርካታ ማሳያዎች አሉ:: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመታዊ የቁጠባ መጠን በእጅጉ አድጓል፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት 50 ዓመታት ከነበረው የአጠቃላይ የቁጠባ መጠን ይልቅ ያለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በብዙ እጥፍ ይበልጣል:: አሁንም ይህ የቁጠባና የድጋፍ ሥራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ የሕዝቡ ተነሳሽነትም ግለቱን ጠብቆ የሚቀጥል ይመስለኛል::

በላይ ከአርሶ አደሩ በቦንድ ሽያጭ ተሰብስቧል:: ከዚህ በላይ ግንዛቤ ቢፈጠር የበለጠ የቁጠባ አቅም እንዳለ ማየት ይቻላል:: በተለይ የገንዘብ ተቋማት ተደራሽነት ማደግ ለቁጠባ ልምድ መሻሻል ስላለው አብቁተ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው:: ካሉት 413 መደበኛ ጽ/ቤቶች በተጨማሪ በምዕራብ አማራ ብቻ ከ800 በላይ ሳተላይት ጽ/ቤቶች በተጨማሪነት ከፍተናል፤ በየቀበሌው ደርሰናል፤ ይህም የቁጠባ ልምድን እያሰዳገ ነው::

አቶ ኢሳያስ ሰይፉየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሕር ዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅአቶ ጋሻው ወርቅነህ

የአብቁተ የሪሶርስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ

አቶ እሸቴ የማታየዳሸን ባንክ ባሕር ዳር

ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅአቶ አምባቸው ተካስማዳ ወረዳ አርሶ አደር

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 34

ከገፅ 6 የዞረ

5ቱ በዓለማችን ...ከገፅ 8 የዞረ

በሀብታችን...በወረዳው ያሉ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች በሙዚዬም

ውስጥ ሳይሆን በየገዳማቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ተቆልፈው የሚኖሩ መሆናቸውም ላለመጎብኘታቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ባለሙያው ያስረዳሉ:: “ችግሩን ለመቅረፍ ገዳማቱ በራሳቸው አቅም ሙዚዬም እየገነቡ ነው፤ ለአብነትም በበየዳ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን ሙዚዬም ተገንብቶ ተጠናቅቋል፤ የፊንዝራራ ተክለሃይማት ደግሞ ባለፈው ታህሳስ 24 ቀን 2008 ዓ.ም የመሠረት ድንጋይ ተጥሎለታል:: እስካሁን ሙዚዬም የመገንባት ሥራ ትኩረት ባለመሰጠቱና በጀት ባለመያዙ ግን ተጠቃሚነታችን ዘግይቷል” በማለት ተጠቃሚነቱ ወደፊት ሊጨምር እንደሚችል ያስረዳሉ::

የበየዳ ወረዳ ባሕልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረሕይወት በላይነህ በበኩላቸው የቱሪስት መዳረሻ ሀብቶችን በአግባቡ ያለመጠበቅና ያለመከለል ችግሮችም እንዳሉ ያብራራሉ:: ከበየዳ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን አቅራቢያ የሚገኘው የእቴጌ ጣይቱ ቤተ-መንግሥት ዙሪያውና ውስጡ እየታረሰና እየፈረሰ መቆየቱን ጭምርም ያነሳሉ:: አቶ ገብረሕይወት እንዳሉት የእቴጌ ጣይቱ ቤተ መንግሥት በቅርቡ ተከልሎ እንዲጠበቅ ይደረጋል፤ ለባለይዞታዎቹ አርሶ አደሮችም ትክ የእርሻ ቦታ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው::

የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አክለውም “የበየዳ ወረዳን ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ ለማድረግ ለአስጎብኝዎች በራሪ ጽሑፎችን አዘጋጅተን ሰጥተናል፤ የተወሰኑም ቢሆን ጐብኝዎች እየመጡ ነው:: ነገር ግን የጎብኝዎች ቁጥርና ያለን የቱሪስት መስህብ ሀብት በእጅጉ የተመጣጠነ አይደለም” ብለዋል:: የበየዳ ወረዳ ከ60 በላይ የድንጋይ ክምሮች፣ ከ10 በላይ ከ600 ዓመታት የሚበልጥ ዕድሜ ያላቸው ገዳማት፣ የተለያዩ ጥንታዊ የነገሥታት አልባሳትና ስጦታዎች እንዲሁም የተፈጥሮ የመስህብ ሀብቶች መገኛ የመሆኑን ያህል ቱሪስቶች እንደማይጎበኙትም ኃላፊው ተናግረዋል::

የሰሜን ጎንደር ዞን ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ የቱሪዝም ልማትና ፕሮሞሽን ባለሙያው አቶ ሀብቱ ዓለሙ ደግሞ የበየዳ ወረዳን ከቱሪዝም ኢንዱስትሪው ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን ጥናት እንዲካሄድ መደረጉን ያነሳሉ:: ከጎንደርና ካይሮ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ከሁለት ዓመታት በፊት የአካባቢውን የመስህብ ሀብቶች የመለዬት ሥራ በጃፓን ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት አጋዥነት መሠራቱንም በአብነት አንስተዋል:: በጥናቱ መሠረት ፊንዝራራ ተክለሃይማኖትና በየዳ ኢየሱስ ዋነኛ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ መለዬታቸውንና እነሱንም በመምሪያው ድረ-ገፅና የፌስቡክ ገፅ የማስተዋዎቅ ሥራ መሠራቱን አብራርተዋል::

“ቅርሶቹን ማስተዋወቅ ብቻውን መስህብ ቢሆንም ቱሪስት አያመጣም፤ ማልማት ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ሀብቱ ከፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የቅዱስ ያሬድ እና የፊንዝራራ ተክለሃይማኖት ገዳማትን ለማልማት ፕሮጀክት ቀርፀው በመላክ ምላሽ እየተጠባበቁ መሆኑንም አስረድተዋል:: ማልማት ሲባል ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መጠገን፣ ሙዚዬም መገንባትና መሠረተ ልማት እንዲኖራቸው ማድረግ መሆኑንም አቶ ሀብቱ አብራርተዋል::

መምሪያው ከዚህ ቀደም ደንቢያ ውስጥ የሚገኙትን “ማን እንደአባና ደብረ ሲና” ገዳማት ሙዚዬም እንዲገነባ ተደርጓል:: ከአማራ ክልል ገጠር መንገዶች ጋር በመነጋገርም በገጠር መንገድ ተደራሽነት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ የቱሪስት መዳረሻዎችን ለይተው መስጠታቸውን ያስረዱት አቶ ሀብቱ የበየዳ ወረዳም ቅድሚያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተለዩት የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል:: ከክለላና ወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘም ከዞኑ አካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ጋር በመሆን የቅርሶቹ ክልል በአውሮፕላን ፎቶግራፍ እንዲነሱ እየተደረገና የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል::

3 ሳዳም ሁሴን

በሚያዝያ 1929 ዓ.ም የተወለዱት ኢራቅን ለ24 ዓመታት አንቀጥቅጠው የገዟት ሳዳም ሁሴን በአገዛዝ ዘመናቸው እጅግ የተፈሩ አምባገነን ሆነው አሳልፈዋል:: ፍፁም አምባ ገነን የነበሩት ልጆቻቸው ኡዴይና ቁሴይ ሁሴን ከአባታቸውም በላይ የተፈሩ ነበሩ ይባልላቸዋል::

ከታላቋ አሜሪካ ጋር እልክ የተጋቡት አምባገነኑ መሪ ኩዌትን በመውረራቸው ከአሜሪካ ጋር የነበራቸውን ፀብ አከረሩት:: ለጠላት የማይተኙት አሜሪካውያንም ሕዝብ ጨራሽ መሳሪያ ስላላችሁ አስፈትሹ በሚል ፀቡን አባባሱት:: ፀቡም ከመክረርና ከቃላት ጦርነት አልፎ ወደ ጦርነት ተቀየረ:: እናም የአሜሪካና የግብረ አበሮቿ ጦር በሳዳም ላይ አየለባቸው:: ሳይም ተሸሸጉ:: አገር ምድሩ ሲፈራቸው ሲርድላቸው የነበሩት ልጆቻቸውም ምድር ቁና ሆነባቸው:: እነርሱም እንደ አባታቸው ከአንዱ ቪላ ተሸሸጉ:: ከአሜሪካ መራሹ ኃይል ራሳቸውን ለጥቂት ወራት ሰውረው ቆዩ:: በመጨረሻ ግን በብዙ የአሜሪካ ኮማንዶዎች ተከበው በተኩሱ ልውውጥ ከነ ጠባቂዎቻቸው ተገደሉ:: ሳዳም ሁሴንም ከልጆቻቸው መገደል ጥቂት ወራት በኋላ ያ ሁሉ ግርማ ሞገሳቸው ተገፎ፣ ተጐሳቁለው ከሰውነት ጐዳና ወጥተው ከተደበቁበት ጉድጓድ ተያዙ:: ከሶስት አመት በኋላ በታህሳስ ወር 1999 ዓ.ም በስቅላት የሕይወታቸው ምዕራፍ ተዘጋ::

4 ማትዌል አንቶኒዮ ኖሪጋ

አብዛኛውን ትምህርቱን በወታደራዊ ሳይንስ ላይ አተኩሮ የተማረው ማትዌል የተወለደው በፓናማ ከተማ የካቲት ወር 1926 ዓ.ም ነው:: አሜሪካኖችም በስለላ እና ስነ ልቦና ጥበብ በራሳቸው ትምህርት ቤት ያሰለጠኑት መሆኑ ለያዘው ማንነት አስተዋጽኦ አድርጓል::

በጥቅምት 1960 ዓ.ም በፓናማ ብሔራዊ ዘብ ውስጥ በመስራትም ሌትናል ኮሎኔል ማዕረግ ደርሷል:: ከአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ ጋር ይሰራ የነበረው ማትዌል በዕፅ ዝውውር ተሳትፎ እና ተቃዋሚ ቡድኖችን በማዋከብ ተግባሩ ይታወቅ ነበር::

እናም ማትዌል በአሜሪካ ጥርስ ውስጥ ገባ:: ለሀገሩ በርካታ ስራዎችን ሲያበረክት የነበረው ማትዌል ጐን ለጐን በሰራቸው የዕፅ ማዘዋወር፣ በህገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በመጠቀምና በመዝረፍ ወንጀሎች ተከሶ የ20 ዓመታት እስራት ተፈርዶበት እስሩን በመፈፀም ላይ ይገኛል::

ብሔራዊ ሕብረት ሊቀመንበር በመሆን የአዛዥነቱን ቦታ ይዘው ነበር:: አይዲድ የጦር አለቃ ከመሆን ባሻገር በርካታ ታጣቂ ወታደሮች ነበሯቸው:: በወቅቱ የተባበሩት መንግስታትን ሰላም አስከባሪ ጦር በማባረራቸው አሜሪካውያን አይዲድን ይቃወሙ ጀመር::

5 ሞሐመድ ፋራህ ሃሰን አይዲድ

እናም ጦረኛውን ሰው ለመያዝ በርካታ እርምጃዎች ተሞክረዋል:: 1984 ዓ.ም ጀምሮ የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች ወጥተው ወርደው እጃቸው ውስጥ ለማስገባት ያልቻሉበትና በአንድ ተራ የሚሊሺያ መሪ የተፈተኑበት ሆኖ ሳይሳካ ዓመታትን አስቆጥሯል:: ይህም የአሜሪካ መንግስት በአንድ በስልጣኔ እጅጉን በሚያንስ የጦር መሪ ተዋርዷል::

በሐምሌ ወር 1988 ዓ.ም ከቅርብ አጋራቸው ጋር ሽኩቻ ውስጥ የገቡት አይዲድ በመቁሰላቸው ለህልፈት በቅተዋል::

ትውልዳቸው ሶማሊያ ውስጥ በታህሳስ ወር 1927 ዓ.ም ነው:: ከ ዚ ያ ድ ባ ሬ ውድቀት በኋላ የተባበሩት ሶማሊያ በኋላም የሶማሌ

ከገፅ 6 የዞረ

ድንበር ጠባቂው...በአሁኑ ወቅት ግን የቮልኮሶቢ ዝርያዎች

በሩሲያ ወታደራዊ ተቋም ትልቅ አገልግሎት እንዲሰጡ ሰልጥነው ስራቸውን በብቃት እየተወጡ ነው:: በሩሲያ ድንበሮች የሚንቀሳቀሱትን ዕፅ አዘዋዋሪዎችና ወንጀለኞች አድነው በመያዝ ትልቅ ውጤት አስመዝግበዋል::

ከአሁን በፊት ከነበሩት ስልጡን ውሻች እጅጉን የሚበልጡት እነዚህ ዝርያዎች የማሽተት ብቃታቸው ከተራው ውሻ ስድስት እጥፍ

ይበልጣል:: ወንጀለኞችን ክንዳቸው ላይ ነክሰው ከያዙ በኋላ በፍፁም አይለቁም:: ሽፈርድ የተባለው ታዋቂ የጀርመን ዝርያ ያለው ውሻ ወንጀለኞች የተደበቁበትን ቦታ በሽታ የሚያገኘው በአራት ደቂቃ ውስጥ ነው፣ አዲሶቹ ዝርያዎች ግን ከ15 እስከ 20 ሰኮንድ ብቻ ነው የሚወስድባቸው::

ዛሬ የሩሲያ ድንበር ጠባቂዎች እረፍት ተሰምቷቸዋል:: ቻይናና ሞንጐልያን በሚያዋስነው ድንበራቸው ሲያስቸግሩ የነበሩ ወንጀለኞችን በቀላሉ በእጅ ማድረግ ጀምረዋልና::

ከገፅ 6 የዞረየመንገድ ላይ...

ቤት የወጡትን ተማሪዎች በማስቆም አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቁ:: ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መመለስ ባልቻሉት ተማሪዎች በጣም ደነገጡ:: ከመካከላቸው በእድሜ የገፉት እንኳን በአግባቡ ማንበብ አይችሉም፤ ይንተባተባሉ::

“የፈተና ወረቀታቸውን በመውሰድ አንዳንድ ጥያቄዎችን ጠየቅሁ::” የሚሉት አቶ ፓርመር “ከመካከላቸው አንዱም ጥያቄዎችን ለመመለስ አልቻለም:: እንዲያነቡም ጠየቅሁ ሆኖም እንዴት እንደሚነበብ አያውቁም:: በጣም ተደነቅሁ ‘በፈተና ወረቀቱ መልስ ላይ ምን ፃፋችሁ?’ በማለት ስጠይቃቸው የሚያውቁት ነገር ፊደል መለየት ብቻ መሆኑን አወቅሁ:: ለነዚህ ልጆች አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝም ወሰንኩ::” በማለት ከ15 ዓመታት በፊት እንዴት ማስተማር እንደጀመሩ ይናገራሉ::

ከዚህ በኋላ አቶ ፓርመር በቀበሌው የሚኖሩ ህፃናትን ሰብስበው ሲጠይቁ ከመካከላቸው አምስቱ ብቻ የተማሩ መሆኑን አወቁ:: ከዚህ በኋላም በራሳቸው ፋብሪካ የጥገና ክፍል የተሰሩ ወንበሮችን በማዘጋጀት ህፃናቱ በምሽት ወደ እርሳቸው እየመጡ እንዲማሩ አደረጉ:: ፈቃደኛ ሆነው የመጡትን አስር ያህል ተማሪዎችን በመንገድ ዳር ባዘጋጁት ቦታ ከፊደል ማስቆጠር ጀምሮ የሚያውቁትን ነገር በሙሉ በማስተማር ተጠመዱ::

“በቀን ለሁለት ሰአት አስተምራለሁ:: ከዚያም ሁላችንም በጋራ ራት እንመገባለን” በማለት ታሪካዊ ግኝቶችን በማህበራዊ ድረ ገጽ ለሚጽፈው የህንዱ ሂውማንስ ኦፍ አምዳቫድ የገለፁት አቶ ፓርመር “ራቱ ቀለል ያሉና ጣፋጭ ምግቦችን ያካተተ በመሆኑ በርካታ ተማሪዎችን እየሳበልኝ መጥቷል:: በዓመት አንድ ጊዜ ከተማሪዎች ጋር ሽርሽርም እንሄዳለን::”

በማለት ይናገራሉ::ዛሬ ይህ የመንገድ ላይ ትምህርት ቤት ተማሪዎች

155 ሲደርሱ በርካታ ተማሪዎች ወደ ኮሌጅና ዩኒቨርሲቲ በጥሩ ውጤት አልፈው እንደሄዱ መረዳቱን ዘገባው አስነብቧል::

“አንዷ የቀድሞ ተማሪዬ ዛሬ የባንክ ቤት ስራ አስኪያጅ ሆናለች:: የኮምፒዩተር ኢንጂነር፣ ሌላው መካኒካል ኢንጂነር እና አንድ ሴት ደግሞ ለህክምና ትምህርት አመልክታለች:: ተመልከቱ ምንም ማንበብ ካለመቻል ተነስተው እዚህ ደረጃ የደረሱ ልጆችን ከማፍራት የበለጠ ስኬት የት አለ?” በማለት አቶ ፓርመር ይጠይቃሉ::

“ከኔ ጋር አብረው ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች አንዱም 10ኛ ክፍልን አላለፈም::” የሚለው የቀድሞው የአቶ ፓርመር ተማሪ ሮናክ ስላንኪ “እርሱ ግን ችግራችንን በመመልከት ረድቶን ለዚህ ታላቅ ደረጃ ደርሰናል:: የ11ኛና 12ኛ ክፍል ወረሃዊ ክፍያችንን የሚሸፍንልን እርሱ ነበር የእርሱ ዓይነት ሰዎች ዓለማችን ያስፈልጓታል::” በማለት ስለ አቶ ፓርመር ለኢንዲያ ኤክስፕረስ ጋዜጣ ተናግሯል::

የአቶ ፓልመር ቤተሰቦች ፕሮጀክቱን በመደገፍ ህፃናቱን ቤተሰብነት እንዲሰማቸው ማድረጋቸው ለስኬት አብቅቷቸዋል::

ዛሬ በእርሳቸው የተማሩ አስር ያህል ተማሪዎች ፕሮጀክቱን በመደገፍ ህፃናቱን በማስጠናት ሲያግዙ፤ ተጨማሪ በጐ ፈቃደኞችም ዓላማውን በመደገፍ የራት ስነስርዓቱ የሚጠይቀውን ወጪ የሚሸፍኑ ከ20 እስከ 25 ባለሃብቶች አግኝተዋል::

“ሁልጊዜም ቢሆን ህፃናት ትክክለኛውን ዕውቀት ይዘው እንዲያድጉ ከመጀመሪያው ጀምሮ መንከባከብና ማገዝ ከሁሉም የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባራችን ሊሆን ይገባል::” በማለት የመንገድ ላይ መምህሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

ገጽ 35በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ማስታወቂያ

ለአግሮቢግ ፕሮግራም የድጋፍ ፈንድ ተጠቃሚዎች ፕሮፖዛል ለማቅረብ የወጣ የጥሪ ማስታወቂያበኢትዮጵያ መንግስትና በፊንላንድ መንግስታት በተደረገ የሁለትዮሽ የልማት ትብብር በአማራ ክልል የተቋቋመው የግብርና ተኮር የንግድ ልማት ፕሮግራም (የአግሮቢግ ፕሮግራም/AgroBIG Programme) የሦስት ዓመት ፕሮግራም ሲሆን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ሦስት ዓይነት የድጋፍ ፈንዶች በተመረጡ የምርት እሴት ሰንሰለቶች ብቁ ለሆኑ አምራቾች፣ አቀነባባሪዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ማለትም፤

• ለጥቃቅንና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች• ለመሠረታዊ ሕብረት ሥራ ማሕበራትና ዩኒዬኖች• በህጋዊ መልክ ለተደራጁ የአርሶ አደር አደረጃጀቶች• በዘርፉ ለተሰማሩ ሕጋዊ የግል ቢዝነስ ተቋማት• አግሮ እንዱስትሪዎች• የምርምርና ጥናት ማዕከላት፤ ዩኒቨርሲቲዎችና የመሳሰሉ ተቋማት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ የፕሮጀክት ሃሳቦችን ተቀብሎ ለመደገፍ ቅድመ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡

የድጋፍ ፈንዱ ተግባራዊ የሚሆንባቸው ሜጫና ፎገራ ወረዳዎች ሲሆኑ በዋነኛነት በሽንኩርት፣ ድንች ፣ ሩዝና በቆሎ እሴት ሰንሰለት ልማትን የሚያፋጥኑና ተወዳዳሪ ፣ ትርፋማና ዘላቂነት ያለው ልማትን የሚያረጋግጡ የፕሮጀክት ሃሳቦችን ለመደገፍ ተዘጋጅቷል፡፡

ሦስቱ የድጋፍ ፈንድ ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. የፈጠራ ፣ ሠርቶ ማሳያና ምርምር ድጋፍ ፈንድ (Innovation, demonstration & Research Fund /IDRF-FUND)፡-

ይህ ፈንድ ለእሴት ሰንሰለት ልማት ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ ፈጠራ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅና የተሻሉ የምርምር ውጤቶችን ለማላመድ ለሚደረጉ ጥረቶች የሚሰጥ የፋይናንስ ድጋፍ ሲሆን፡- ለአንድ የፕሮጀክት ሃሳብ (Business Plan Proposal) ከፍተኛው 1.14 ሚሊዮን ብር ሲሆን ዝቅተኛው ደግሞ 45,600 ብር ነው፡፡ አመልካቹ የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪ 15% አስተዋፅዖ ማድረግ ይጠበቅበታል፡

፡ይህ የፋይናንስ ድጋፍ ከግለሰብ አመልካች በስተቀር ለሁሉም ክፍት ነው፡፡ የመንግስት ድርጅቶች ፣ የግል ሽርክና/አክሲዮን ማህበራት፣ የተመዘገቡና ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው አደረጃጀቶች፣ የሕብረት ሥራ

ማህበራት፣ ካምፓኒዎች፣ የምርምር ማእከላትና ዩኒቨርሲቲዎች ሊያመለክቱ ይችላሉ፡፡2. የእሴት ሰንሰለት ድጋፍ ፈንድ (Value Chain Fund /VCF-FUND)

ይህ ፈንድ በአካባቢው ከድንች፣ሽንኩርት፣ በቆሎና ሩዝ አመራረትና ግብይት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ የእሴት ሰንሰለት ልማት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍና ያሉትን እምቅ አቅሞችን ሥራ ላይ ለመተግበር የሚሰጥ ድጋፍ ሲሆን

በአነስተኛ ይዞታ የማምረት ተግባር ኢንቨስትመንቶችን አካባዊ የሆኑ የድንች፣ ሽንኩርት፣በቆሎና ሩዝ አሴት ሰንሰለት ላይ ለሚከናወኑ ሥራዎችና የግብይት እንቅስቃሴዎችን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ለአንድ የፕሮጀክት ሃሳብ (Business Plan Proposal) ከፍተኛው 205,000 ብር ሲሆን ዝቅተኛው 22,800 ብር ነው፡፡ አመልካቹ በተመሳሳይ የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪ 15% መሸፈን ይጠበቅበታል፡፡ተጠቃሚ የሚሆኑት በሜጫና ፎገራ ወረዳዎች የሚገኙ ከግለሰብ በስተቀር ህጋዊ ሰውነት ያላቸው የተመዘገቡ አርሶአደሮች፣ የግል ተቋማት፣ የህብረት ሥራ ማህበራት፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች

ሊሆኑ ይችላሉ፡፡3. የመቀናጆ ድጋፍ ፈንድ (Matching Grant Fund /MG-FUND)

ይህ ፈንድ ከፍተኛ ወጪ ለሚጠይቁ ኢንቨስትመንቶች ማለትም በከፍተኛ ደረጃ ጥራትን መሠረት ያደረገ በተመረጡ ምርቶች ላይ የማቀነባበር ሥራዎችን ለማከናወን ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ ለአንድ የፕሮጀክት ሃሳብ (Business Plan Proposal) ከፍተኛው 2.2 ሚሊዮን ብር ሲሆን ዝቅተኛው 205,000 ብር ነው፡፡ አመልካቹ ቢያንስ የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ወጪ 50% መሸፈን ይጠበቅበታል፡፡ አመልካቾች የዚህ ፈንድ ተጠቃሚ ለመሆን ሕጋዊ ሰውነት ያላቸውና የተመዘገቡ እንዲሁም የተሰማሩበት ተግባር በአማራ ክልል በሁለቱ ወረዳዎች ማዕከላት በ100 ኪ/ሜ ራዲዬስ ውሰጥ የሚገኙና

በተመረጡት ምርቶች እሴት ሰንሰለት ጋር ቀጥተኛ ትስስር ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ወይም ድርጅቶች መሆን አለባቸው፡፡የማመልከቻ ቅፅን በተመለከተ ከላይ በተገለጹት የድጋፍ ፈንዶች ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉና መሥፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ቅፁን፡-

ከአግሮቢግ ፕሮግራም ማስተባባሪያ ዩኒት፣ ባሕርዳር ሹም አቦ ክፍለ-ከተማ አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም አዲሱ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ወይም ከአግሮቢግ ዌብ ሳይት፡- www.agrobig.org/ ወይም ከሜጫ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፤ መራዊ ከተማ ወይም ከፎገራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፤ ወረታ ከተማ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አመልካቾች ከማመልከቻቸው ጋር ሕጋዊ ሰውነታቸውን የሚያረጋግጡ ማሰረጃዎችን (የታደሰ የንግድ/የሙያ ፈቃድ ሌሎችንም) ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የማመልከቻ ማቅረቢያ ቦታ፡- የፕሮጀክቱን ንድፈ-ሃሣብ -Concept Note (ለፈጠራ፣ሠርቶ ማሳያና ምርምር ድጋፍ ፈንድና የመቀናጆ ድጋፍ ፈንድ) እና ዝርዝር የፕሮከት ሃሳብ - Full Project Proposal (የእሴት ሰንሰለት ድጋፍ ፈንድ) ከማመልከቻ ጋር በሁለቱ ወረዳዎች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤቶች ወይም አግሮቢግ-ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ባሕርዳር በግንባር መቅረብ ይኖርበታል፡፡የማመልከቻ ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ፡-ግንቦት 8 ቀን 2008 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ስዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡

የአግሮቢግ ማስተባበሪያ ዩኒትባህርዳር

ስ.ቁ፡- 058-220-9238 ወይም 058-220-9195 ዌብ ሳይት፡- www.agrobig.org

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2008የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ቀበሌ 13 አየር መንገድ መሄጃ ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ አዲስ ያስገነባውን ህንፃ በአጠቃላይ የህንፃውን የስራ ክፍሎችን፣ የፎቅ ደረጃዎችን ፣ በረንዳዎችን ፣ መፀዳጃዎችን፣ መጋረጃዎችን፣ የህንፃውን አካባቢ፤ ደረጃና ምድር ግቢውን ዓመታዊ ውል በመያዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማፀዳት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች፡- 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት መረጃ የሚያቀርቡ፣ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 2. በተጨማሪም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነታቸውን የሚያረጋግጥ የቫት ሰርተፍኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ የማይመለስ

30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ የሚቻል ሲሆን ሰነዱን በመሙላት በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 15ኛው ቀን 11፡3ዐ ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡

4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ የተመሰከረለት /ስፒኦ/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 3፡30 ይዘጋና 4፡0ዐ ሰዓት ይከፈታል፡፡7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡8. የሚጸዳው ህንጻዎችን ፤ብዛት ያላቸው ክፍሎች ፤ስቱዲዮዎች ፤መጸዳጃ ቤቶች እና ምድር ግቢውን እንዲሁም ለግዥ የሚቀርቡ የፅዳት ዕቃዎችን አይነትና ብዛት እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ

የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡9. ጨረታ ሰነዱን ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደው አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለው ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡

ማሣሠቢያ፡- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918706738/0918781476 ደውሎ ወይም ፋክስ ቁጥር 0582204752 በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አብክመ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 36

ከገፅ 10 የዞረ

የዓባይ... ምስክሮች ...ከገፅ 11 የዞረ

ተደማምረው የአሳሾችን ጉዞ አወሳሰበው፣ ከመንገድ የመለሷቸው ምክንያቶች ነበሩ::

የሆነ ሆኖ የዓባይን ወንዝ ምንጮች ማግኘት ብዙ ፈትኗል:: የማታ ማታ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ መነሻዎቹ መሆናቸው ታውቋል::

ዓባይ የስልጣኔ ምንጭ ከሆኑት የዓለማችን ጥቂት የወንዝ ሸለቆ ስልጣኔዎች ውስጥ አንዱ ነው:: ከዛሬ አምስት ሺህ ዓመታት በፊት ማለትም ከሶስት ሺህ እስከ ሁለት ሺህ ዓመተ ዓለም ባለው ጊዜ ውስጥ ጥቂት የወንዝ ሸለቆዎችን ተከትሎ በግማሹ የደቡባዊ የእስያ ክፍልና ሰሜናዊ አፍሪካ አካባቢዎች የተደራጁ ስልጣኔዎች በቅለዋል::

በኢንደስ፤ ናይል፣ ቲግሪስና ኤፍራተስ እና

የሎው ወንዞች የሸለቆ ስልጣኔዎች ይጠቀሳሉ:: ሁሉም የየራሳቸው ባህሪ ያላቸውን የስልጣኔ በሮችን ለዓለም ከፍተዋል፤ ጨለማውን ገፈዋል::

የዓባይ ሸለቆ ስልጣኔዎችም ዓባይን ተከትለው ተመስርተዋል:: ቀደምት ከሚባሉት ዓባይ ሸለቆ ስልጣኔዎች ሁለቱ ጥንታዊ ግብጽና ኑቢያ ስመ ገናናዎቹ ነበሩ:: ከዓባይ የበቀሉ የስልጣኔ ፈርጦች… ከሌሎቹ የሚለየውም የብዙ ዓይነት ስልጣኔዎች አባት መሆኑ ነው::

የዓባይ ወንዝ የእነዚህን ሁለቱን ታላላቅ አፍሪካዊ ስልጣኔዎች ለእርሻ ሥራ አስተማማኝ የውሃ ምንጭ በመሆንና ከመካከለኛው ሰሐራ የአፍሪካ ክፍልና ከሜዲትራኒያን ባህር ጋር አገናኝ ድልድይ በመሆን የሁለቱን ስልጣኔዎች እድገት ቅርጽ አስይዞታል::

ሁለቱም የሸለቆው ስልጣኔዎች መሰረታቸው ዓባይ ወንዝ ይሁን እንጂ የራሳቸውን መንገድ ተከትለው ነበር ያደጉት:: ዓባይ ለእነዚህ ስልጣኔዎች የሕይወት ምንጭ ነበር:: አልፎም የስልጣኔ መገኛ በመሆን ከመነሻው እስከ መድረሻው ታላላቅ አገራትን፣ ሕዝቦችንና ከተሞችን ፈጥሯል::

ምድር ሁሉ ሳይሰለጥን የዓባይን ወንዝ ሸለቆ ተከትለው የተቋቋሙት ሕዝቦች ወንዙን ተማምነው እልም ባሉት በረሀዎች ነበር የሰፈሩት:: የዓባይን ወንዝ በመንተራስ ሸለቆውን አለሙት:: እርሻ የተጀመረው በዓባይ ሸለቆዎች እንደነበር ጥንታዊ የታሪክ ማስረጃዎች ያሳያሉ::

ጥንታዊት ግብፅና ኑቢያ /የአሁኗ ሱዳን/ ቀደምት ከሚባሉት ስመ ገናና የሸለቆው ስልጣኔዎች በተጓዳኝ ሜሮኤ፣ ደግሪት፣ አክሱም፣ ኩሽ እና ሌሎቹም የዓባይ

ፈርጥ ጥቁር ስልጣኔዎች በየጊዜው ተነስተዋል::በረኸኛው ዓባይ ሰው ለኑሮ በማይደፍራቸው

እና ዝናብ ዓይተው በማያውቁ በርሀዎች መሀል ለመሃል ብቻውን በመጓዝ ግብፅ የሚደርስ ለየት ያለ ወንዝ ነው:: እናም በረኸኛውን ብርቱ ወንዝ ተጠልለው የተመሰረቱት ብርቱ ህዝቦች ብርቱ ስልጣኔዎችን ገንብተዋል::

ከኢትዮጵያና ከኡጋንዳ የሚነሱት ሁለቱ ዓባዮች በሱዳን ካርቱም ኡምዱሩማን በረሀ ላይ ተገናኝተው ኑብያን እያለሙ በአንድ ዓባይነት አንድ በመሆን ብዙ ሺህ ኪሎ ሜትር ወደ ሰሜን ይጓዛሉ:: ዓባይ ከሩቅ አገር ተሸክሞ ያመጣቸውን ስጦታዎች በግብፅ በረሀ ላይ ያራግፋል:: በረሀማውን የግብፅ ምድር እጅግ ለም በሆነ አፈር ደልድሎ ስልጡን መናገሻው አድርጐ መስርቷታል::

ዓባይ ከአፍ እስከ ገደፉ ጢም ብሎ ሞልቶ በግብፅ ምድር ሲንጐማለል የሚታይበት ወቅት ለግብጽ የበጋ ወራት ነው፤ መስከረም:: በነዚህ ወራት

የግብፅ በረሀው ወበቅ፣ ደረቅ አየር በሚነፍስበት ምድር የዓባይ ከሶስት ሺህ ዓመት ዓለም ጀምሮ የሚቆጠረው የጥንታዊት ግብፅ ስልጣኔ በዓለም በዘመኑ ደምቀው ከታዩ በጣት የሚቆጠሩ ኃያላት ተርታ ይሰለፋል:: ዓባይ የስልጣኔዋ ምንጭ ነው፣ ሔሮዳተስ እንዲያውም “የዓባይ ስጦታ!” ብሎ እስከመጥራት ተገዷል::

ከዓባይ ግርጌ ላይ የተመሰረተችው ጥንታዊቷ ግብጽ በሶስት ስርዎ መንግስታት ትከፋፈላለች። አሮጌው ስርዎ መንግስት (ከ2660 እስከ 2160) ይደርሳል። መካከለኛው ስርዎ መንግስት ደግሞ (ከ2040 እስከ 1640) እና አዲሱ ስርዎ መንግስት (ከ1550 እስከ 1070) ይባላሉ:: በእነዚህ ረጅም ዘመናት ውስጥ የተለያዩ ፈርኦኖች የየራሳቸውን አሻራዎች እያሳረፉ ያለፉባት ምድር ናት::

ግብፅ ለፈርኦኖቿ መቃብር እንደመታሰቢያ በምትገነባቸው ፒራሚዶች ትታወቃለች:: የፈርኦን ኃያልነቱና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱ ጣሪያ ላይ የደረሰበት አሮጌው ስርዎ መንግስት በሚባለው ዘመን ነው እነዚህ ፒራሚዶች የተገነቡት:: በጣም ታዋቂዎቹ ግዙፍ ፒራሚዶች የንጉስ ኩፋ ታላቁ ፒራሚድና ታላቁ ሲፊኒክስ ከ2600 እስከ 2500 ቢ.ሲ.ጂ. በግብፅ ጊዛ በተባለ ቦታ የተገነቡ ናቸው:: በአጠቃላይ ግብፅ ውስጥ 72 ፒራሚዶች ይገኛሉ::

ፒራሚዶች የዓባይ ሸለቆ ስልጣኔዎች የከፍታ ዘመን ነፀብራቅ እንደመሆናቸው ከግብፅ ባለፈ ሱዳን ውስጥም ይገኛሉ:: ሱዳን ውስጥ 32 ፒራሚዶች ቢገኙም በግዙፎቹ የግብፅ ፒራሚዶች መግነን ተውጠው ብዙም የመታወቅ ዕድሉን

አልተሰጣቸውም::ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የታሪክ

ተመራማሪዎች ግብጽ ውስጥ ያሉት ፒራሚዶች ግዙፍና ለዓይን አስገራሚ ድንቅ የዘመኑ ስልጣኔ ውጤቶች መሆናቸው እንዳለ ሆኖ በአፍሪካ

የመጀመሪዎቹ ፒራሚዶች ግን አይደሉም ይላሉ:: በናይል ሸለቆዎች ስልጣኔ ከላይኛው ወደ ታችኛው እንደተስፋፋ በማስረዳት ግብፅ የመጨረሻዋ የሸለቆው ስልጣኔ መሆኗን ያወሳሉ::

ይቀጥላል

አልፈፀምህም?!...” “እሯ!... ሚካሄል አባቴ ድረስ! እኔ በእምነት ነኝ

ባህያ ስርቆሽ የምጠረጠር!… እመይቴ እንደ ስሜ የታመንሁ ነኝ!… ይሄን ባህሪየን በጥሞና አይተው ነው ወላጆቼ ‘በእምነት፣ በእምነቴ’ ያሉኝ!...” በተደፈርሁ ስሜት በሁለት እጆቹ ወገቡን ይዞ ጣሪያ ግድግዳውን፣ ወለሉን፣ ዳኞቹን … አንድ ባንድ አስተዋለ::

“ወንጀሉን ለመፈፀምህ ማስረጃ ቢቀርብብህ? ቢመሰከርብህስ?…” የመሀል ዳኛዋ በጥርጣሬ ዓይን እያስተዋሉት ጠየቁት::

“አይ እመይቴ… እንደ ጨቅላ አያስፈራሩኝ!…ባንዳች ነገር ሊጣላኝ ቢፈልገኝ ነው እዚህ የገተረኝ:: አለመስረቄን እሱም አሳምሮ ያውቀዋል:: የሆነው ሁኖ ንጥህናየ ነው ሚወጣኝ…” አለ፤ የመሀል ዳኛዋን እያስተዋለ:: ዳኛዋ ወደ ዓቃቤ ህግ ዓይኖቻቸውን ወርውረው፡- “ምስክሮች ተዘጋጅተዋል?” ሲሉ ጠየቁ::

ዓቃቤ ህጉ ሁለት እጆቹን ወደ ኋላው ሸርቦ እጅ እየነሳ “አዎ ክቡር ፍርድ ቤት…” አለ::

“ይቅረቡ” ሲሉ ዳኛዋ አዘዙ::***“ስም” አሉ ዳኛዋ የመጀመሪያውን ምስክር

እያስተዋሉ:: “ዓባይ አስፈራው”“የመጡበትን ጉዳይ ያውቃሉ?”“አዎ! ያ ልማደኛ ሌባ አህያ በመስረቁ ልመሰክር

ነው::”“ተጠርጣሪውን ቢያዩዋቸው ያውቋቸዋል?”“አዎ! አውቀዋለሁ! ደሞ እሱ ጠፋኝ?!”“እስኪ ከእነሱ ከአምስቱ ሰዎች መካከል

ተጠርጣሪው ካሉ ለይተው ያሳዩኝ” አሉ መሀል ዳኛዋ፤ አንዴ ወደ ምስክሩ አንዴ ወደ ሰዎቹ እየተመለከቱ::

በእምነት የምስክሩን ሁኔታ በአንክሮ ይከታተላል:: ምስክሩ ሰዎቹን አንድ ባንድ ተመለከቷቸው:: ተከሳሹ በእምነት በግራ እጁ አፉን ሸፍኖ ዳኛዋን ያስተውላል:: ሳቁ የመጣበት ይመስላል::

ዳኛዋ በበኩላቸው የምስክሩ ሁኔታ እየገረማቸውና እንዲጠራጠሩ እያደረጋቸው ጥያቄያቸውን ቀጠሉ::

“ሰውየው በምን ሥራ ነው የሚተዳደሩት?”“ማን? ሌባው?” በድፍረት ምስክሩ ጠየቁ:: “ተጠርጣሪው!” በማለት አባባላቸውን አርመው

መለሱላቸው፤ ዳኛዋ::“ምን የማይገባበት አለ ደሞ እሱ!”“እኮ ምን ምን?!...”“አንድ ጊዜ ‘አናጢ ነኝ!’ አንድ ጊዜ ‘ግንበኛ ነኝ!’

ይላል:: እሱ ምን ቅጥ አለው::”“አህያውን ሲሰርቅ ያዩት ምን ሰዓት ነው?”ምስክሩ ድንግጥ ብለው “ከጠዋቱ 12 ሰሀት”

አሉ::“አህያው ምን ዓይነት ነው?” ዳኛዋ ጥያቄቸውን

አስከተሉ:: ምስክሩ ይሄኔ ይበልጥ ተደናግጠው “ቡ… ቡ… ቡላ!... አዎ! ቡላ!” አሉ::

“እስኪ በግራ ጐንዎ በኩል የቆሙትን ሰው ይመልከቷቸው::”

ምስክሩ ሰውየውን እያስተዋሉ አንገታቸውን በ’አላውቃቸውም’ ስሜት ነቀነቁ::

“ሲሰርቁ ያዩዋቸው ሰው ናቸው?” ዳኛዋ ጠየቁ::“እሮ!... አይ… አይደሉም!” ምስክሩ መለሱ:: ዳኛዋ ከዚህ በላይ መቀጠል አልፈለጉም::

በምልክት ፖሊስ ጠሩና ምስክሩ እንዲቆዩ አዘው ሁለተኛው ምስክር እንዲቀርቡ ጠየቁ::

“ስም!...” ምስክሩ መደንገጣቸው ከፊታቸው ይነበብባቸዋል:: ግራ ቀኝ፣ ወደ ፊት ወደ ኋላ መልከትከት ካደረጉ በኋላ፣

“አዳሙ… አ… አ… አታላይ” አሉ::“አቶ አዳሙ የቀረቡበትን ጉዳይ ያውቁታል?”“አዎ ክቡር ዳኛ ልመሰክር ነው፤ በአህያ ሌባው

ላይ” ምስክሩ አቀርቅረው መለሱ::“አቶ አዳሙ ሰውየው አህያውን የሰረቁት በስንት

ሰዓት ነው?”“ከቀኑ በስድስት ሰሀት:: ሰው ቤቱ ሲከተት

ሰረቀው…” ድክም ባለ ድምጽ አንጠልጥለው ተውት::“አህያው ቀለሙ ምን ዓይነት ነው?”“ጥቁር!”“የሰረቁትን ሰውስ ያውቋቸዋል?”“አ… አውቀ… አውቀዋለሁ” እየተንተባተቡ

መለሱ::“ሥራቸው ምንድን ነው?”“እሮ ሥራውስ ብዙ ነው:: አናጢ ነኝ ይላል::

ግንበኛ ነኝ ይላል:: ሌላ ግዜ ደሞ ገበሬ ነኝ ይላል:: ምኑ ቅጡ!”::

“እስኪ እዚህ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀል ሰውየውን ያሳዩኝ” ዳኛዋ እስክርቢቷቸውን በሁለት እጆቻቸው የአውራ ጣትና ሌባ ጣት መሀል አጋድመው እያሽከረከሩ ጠየቁ::

ምስክሩ በግራም በቀኝም፣ በፊትም በኋላም ያሉትን ሰዎች አስተዋሉ:: “እዚህ የለም” ሲሉም እያመነቱ ተናገሩ:: በዚህ ጊዜ በእምነት እጁን አውጥቶ ክቡር ፍርድ ቤት ይፈቀድልኝ ልናገር

ሲል ጠየቀ:: ዳኛዋ ግን ምስክሮች ተሰምተው ሳያልቁ መጠየቅ እንደማይችል በመግለጽ ከለከሉት::

ፖሊስ ምስክሩን በቁጥጥር ስር እንዲያቆያቸው በምልክት አዘው ሶስተኛ ምስክር እንዲቀርብ ጠየቁ::

“ስም?...” ጠየቁ ዳኛዋ::ምስክሯ መሬት መሬት እያዩ“ካሳነሽ ባያብል” አሉ::“አህያው ሲሰረቅ አይተዋል?”“አዎ! አይቻለሁ…” “በስንት ሰዓት ነው ሲሰረቅ ያዩት?”“ተቀኑ ስምንት ሰሀት::”“አህያው ቀለሙ ምን ዓይነት ነው?”“ከሆዱ ነጭ፤ ከጀርባው ጥቁር::”“የሰረቁትን ሰውስ ያውቋቸዋል?”“አ… አው… አውቀዋለሁ!... አውቀዋለሁ እንጂ…”“እሳቸው በቀኝዎ በኩል የቆሙት ናቸው?”

ጠየቁ ዳኛዋ፤ የሶስቱም ምስክሮች ቃል መለያየት እያበሳጫቸው::

ምስክሯ ሰውየውን ከላይ እስከ ታች ተመለከቱና ሰውየው ነው መሰለኝ:: ግን የለበሰው ልብስ የእሱ አይመስለኝም:: የፖሊስ ልብስ ሆነብኝሳ!...” አሉና ወደ ዳኛዋ ተመለከቱ::

“እሳቸው የሚለብሱት ልብስ ምን ዓይነት ነው?”“እሱ ደሞ እንዲህ ያለ ልብስ ተየት አግኝቶ፤

ታልሰረቀው በቀር!... እሱ የቆሸሸ ቱታ ነው የሚለብስ…” ዳኛዋ “የተሰረቀው አህያ መልኩ ምን ዓይነት ነው?” ሲሉ በድጋሚ ጠየቋቸው::

“ነጭ… እህ!... ቡላ… የለም ነጭና ቡላ…” ተንተባተቡ::

ችሎቱን የሞላው ሰው በሳቅ አውካካ::“ሥነ-ስርዓት!... ፀጥታ!… ፀጥታ!…” ዳኛዋ

ጠረጴዛውን በእስክርቢቷቸው እየቆረቆሩ ፀጥታ እንዲሰፍን ጠየቁ::

በዚህ ቅጽበት ምስክሯ ቀልባቸው ተገፎ፣ ሰውነታቸው እየተንቀጠቀጠ፣ እሮ እኔ ይቅርብኝ… ይቅር… እመይቴ… አባቴ ሚካሀል ይቅር በለኝ… እ… እኔ… ሲሰርቅም ሲሰረቅም አላየሁ:: ሌባውንም አላውቀው…

“ሌባውን ካላወቁት፣ ሲሰረቅ ካላዩ ታዲያ ለምን ምስክር ሆነው ቀረቡ?!...” ዳኛዋ ቆጣ ብለው ጠየቁ::

“አምስት መቶ ብር እሰጥሻለሁ:: እንዲህ ብለሽ መስክሪ ብሎ አስጠንቶኝ ነው ልመሰክር የመጣሁ! ይቅር በሉኝ ይቅር በሉኝ” እያሉ አስሬ እጅ ነሱ::

ዳኛዋ ፈገግ ብለው ፖሊሱን በምልክት ምስክሯን ወደ ማረፊያ ቤት እንዲያስገባቸው ሲያዙት አዳራሹ በህምህምታ ተዋጠ::

ገጽ 37በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ማስታወቂያ

የቅጥር ማስታወቂያየደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች ባለው ክፍት የስራ መደብ ላይ ከስራ ፈላጊዎች መካከል አወዳድሮ መደቡን በቅጥር መሸፈን ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የስራ መደቡ መጠሪያ

ደረጃ መ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ፆታ የትምህርት ደረጃ እና ለመደቡ አግባብ ያለው የስራ ልምድ

ተፈላጊ የትምህርት መስክ

1. ሴክሬታሪ II ጽሂ-9 8-40/ደታ-15-

37-790-25 2,008 4 አይለይም 12ኛ/10ኛ ክፍል ያጠናቀቁና 10 ዓመት፣ 10+1 ያጠናቀቁና 8

ዓመት፣ 10+2 ያጠናቀቁና 6 ዓመት ፣10+3 ያጠናቀቁና 4 ዓመት ፣ ደረጃ 4 ያጠናቀና 2 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

የጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ፣ሴክሬታሪያል ሣይንስ፣ ሴክሬታሪያል ሣይንስ ኤንድ ኦፊስ ማኔጅመንት፣አድሚኒስትሬትቭ ኦፊስ ኤንድ ሴክሬታሪያል ሣይንስ

2. ከፍተኛ የሂሣብ ባለሙያ I

ኘሣ-7 8.40/ደታ-1497 4,461 1 አይለይም የባችለር ዲግሪና 8 ዓመት የስራ ልምድ፣ የማስተርስ ዲግሪና 6 ዓመት የስራ ልምድ፣ የዶክትሬት ዲግሪና 4 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት

አካውንቲንግ፣ ማኔጅመንት ቢዝነስ ኢዱኬሽን፣ ባንኪንግና ፋይናንስ ፣ ፋይናንሻል አካውንቲንግ ፣ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ፣ ፋይናንሻል ማኔጅመንት ፣ ፐብሊክ ሴክተር ፋይናንስ ፣ ቢዝነስ ማኔጅመንት ፣ ሰርቲፋይድ አካውንቲንግ፡፡

3. በጀት ባለሙያ II/ለ3ኛ ጊዜ የወጣ/

ኘሣ-5 8.40/ደታ-847 3,425 1 አይለይም የባችለር ዲግራና 6 ዓመት የስራ ልምድ የማስተርስ ዲግሪና 4 ዓመት የስራ ልምድ የዶክትሬት ዲግሪና 2 ዓመት የስራ ልምድ ያለው /ያላት

ኢኮኖሚክስ ፣ ትምህርት እቅድና ስራ አመራር ፣ ማኔጅመንት ፣ አካውንቲንግ ፣ ስታትስቲክስ

4. ከፍተኛ የውስጥና የውጭ ግንኙነት ባለሙያ II /በድጋሜ የወጣ/

ኘሣ-8 8.40/ደታ-850 5,081 1 አይለይም የባችለር ዲግሪና 9 ዓመት የስራ ልምድ የማስተርስ ደግሪና 7 ዓመት የስራ ልምድ የዶክትሬት ዲግሪና 5 ዓመት የስራ ልምድ ያለው /ያላት፡፡

አማርኛ ፣ እንግሊዝኛና ስነ ጽሁፍ ፣ ፖለቲካል ሣይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ፣ ጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን ፣ቋንቋና ፎሪን ላንጉጅ ሊትሬቸር ፣ ሊትሬቸር

5. ከፍተኛ የስርዓተ ትምህርት ባለሙያ /ለ3ኛ ጊዜ የወጣ/

ኘሣ-8 8.40/ደታ-1480 5,081 1 አይለይም የባችለር ዲግሪና 9 ዓመት የስራ ልምድ የማስተርስ ዲግሪና 7 ዓመት የስራ ልምድ የዶክትሬት ደግሪና 5 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት፡፡ የስራ ልምዱ ሙሉ በሙሉ በስርዓተ ትመህርት ቀረፃ በስርዓተ ትምህርት ግምገማና ጥናት በስርዓተ ትምህርት ባለሙያ /አስተባባሪነት/በመንግስት ዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች ላይ በመምህርነት የሰራ/ች/

የስርዓተ ትምህርት መማር ማስተማር ዝግጅትና ክትትል፣ ፔዳጐጅካል ሣይንስ ፣ በትምህርት እቅድና አመራር

6. ግንበኛ II /ለ4ኛ ጊዜ የወጣ/

እጥ-8 8.40/ደታ-1462 1,743 2 አይለይም 5ኛ ክፍል ያጠናቀቁና 12 ዓመት፣6ኛ ክፍል ያጠናቀቁና 1ዐ ዓመት ፣7ኛ ክፍል ያጠናቀቁና 8 ዓመት ፣8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ 6 ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ያላት/

ቢዩልዲንግ ኮንስትራክሽን፣ ኮንክሬት ወረክ፣

1. እድሜ 18 ዓመት እና በላይ

2. የስራ ቦታ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

3. የምዝገባ ጊዜ ማታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት

4. ከተወዳዳሪያዎች የሚፈለግ

4.1. የትምህርት ማስረጃ እና የስራ ልምድ ኦርጅናል ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር

4.2. ሲኦሲ ለወጣላቸው የትምህርት ዝግጅቶች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.3. በፈተና ወቅት ተወዳዳሪዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5. የምዝገባ ቦታ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሰው ሃብት ስራ አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ህንፃ ቁጥር 039 ቢሮ ቁጥር 7

6. የፈተና ቀን ወደፊት በማስታወቂያ ይገለፃል፡፡

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበአዊ ብሔረስብ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ በመ/ቤቱ ውስጥ የሚገኙ የህግ ታራሚዎች የምግብ አገልግሎት በራሣቸው የምግብ ማብሰያ እቃ ችለው አብስለው /አዘጋጅተው/ የሚመግቡ ግለሰቦችን ወይም ድርጅቶችን ከግንቦት 1/2008 ጀምሮ ለአንድ አመት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ የተጫራቾች ግዴታዎች፡-

1. ህጋዊና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡3. ከእህል አቅርቦት እስከ ማብሰልና መቀለብ በራሣቸው ወጭ ሸፍነው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የግብር ከፋዮች/ቲን ናምበር/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

5. የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረላቸው ቼክ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋጋው 1 በመቶ ማስያዝ የሚችል፡፡ 6. ጥራቱን የጠበቀ በአንድ ሰዓት ቁርስ በስድስት ሰዓት ምሣ በአስር ሰዓት እራት ሰርቶ ማቅረብ የሚችል፡፡7. የጤና ችግር ያለባቸው የህግ ታራሚዎች የምግብ ለውጥ እንዲያደርጉ የህክምና ማስረጃ ሲያቀርቡ የዋጋ ለውጥ ሣያደርጉ በአሸነፉበት ዋጋ ለውጠው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

8. የውሃ ፍጆታ በራሣቸው ወጭ መሸፈን የሚችሉ፡፡

9. ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ 30.00/ሰላሣ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ማለትም 26/07/08 ዓ/ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የአዊ ብሄ/ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

10. የእንጀራና የዳቦ አቅርቦት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆንን አይጠይቅም፡፡11. ከምግብ ጋር የተያያዙ ወጭዎችን በሙሉ አቅራቢው ይሸፍናል፡፡12. የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻው ቀን 10/08/2008 ዓ/ም ይሆናል፡፡13. ጨረታው የሚከፈተው በቀን 11/08/2008 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡ዐዐ ነው፡፡14. የተጫራቾች ዋጋ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም፡፡15. የአንድ ታራሚ የአንድ ቀን የምግብ ሂሣብ ከነቫቱ 14 ብር ሲሆን ከዚህ በታች ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡16. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን ፣ ማህተም እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡17. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበት ዋጋ 1ዐ በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ፡፡18. አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት 5 ቀን በኋላ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው፡፡19. ቀርበው ውል ያልያዘ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ለመንግስት ገቢ ተደርጐ ለተፈጠረው ችግር በህግ ተጠይቆ ድጋሜ በወጣው ጨረታ አይሣተፍም፡፡20. በጨረታው ላይ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0582270070 ደውለው ይጠይቁ፡፡21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአዊ ብሔ/ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 38

የሆስፒታሉ ግንባታ...ከገፅ 4 የዞረ

አቶ አወቀ ጫኔ የወግዲ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሰራተኛና የሆስፒታሉን ግንባታ ተወክለዉ ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው:: ሆስፒታሉ በ2005 ዓ.ም በ33 ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ብር እንዲገነባ ኮንትራት ለተቋራጩ ሲሰጥ በ500 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ነበር ውል የተያዘዉ:: ሆኖም ግን ግንባታው እስከተቋረጠበት እለት ድረስ አንድ ሺ ቀናትን መውሰዱን አቶ አወቀ ይናገራሉ:: በነዚህ ቀናት ውስጥ በክልሉ መንግስትና በተቋራጩ መካከል ልዩነቶች ተፈጠሩ:: መጠናቀቅና መስተካከል ያለባቸዉ ስራዎች በመኖራቸው ክፍያ እንዳይከፈለው ተወሰነ:: ክፍያዉ ባለመከፈሉም ተቋራጩ ድርጅት ግንባታውን በራሱ ወጪ ማስቀጠል አልቻለም:: የግንባታው ሂደት 74 በመቶ ሲሆን የበጀት አጠቃቀሙ 79 በመቶ ደርሶ ነበር::

ግንባታው በሚከናወንበት ወቅት ወረዳው ከክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በየጊዜው መረጃ ይለዋወጥ ነበር:: በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ጥረቶች ሲደረጉ እንደነበርና በመጨረሻ ግን ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱን አቶ አወቀ ይገልፃሉ:: በመሀልም ቢሆን ከጥራት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተመለከተ ከጤና ጥበቃ ቢሮ ጋር በመነጋገር ተቆጣጣሪ መሀንዲሶች እንዲቀየሩ ለማድረግ ተሞክሯል::

ሁለት የአማራ ዲዛይናና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት መሀንዲሶች በቋሚነት ግንባታውን እንዲቆጣጠሩ ቢመደቡም ጥራቱን በአግባቡ መቆጣጠር ባለመቻላቸዉ እስከ ሰባት ጊዜ እንዲቀየሩ ሆኗል::

መሀንዲሶቹ ወደስፍራው እንደገቡ የግንባታ ጥራት ችግር እንዳለ አምነው ስራ ይጀምሩና እየቆዩ ሲመጡ ችግር እንደሌለበት መናገር ይጀምራሉ ይላሉ:: በአዲስና ነባር መሀንዲሶች መካከል አለመግባባት ይከሰት እንደነበር ያስታውሳሉ:: በመጨረሻ ግንባታው እንዲቋረጥ ሲወሰንም ባለሀብቱ ቀድሞ መረጃ ደርሶት ስለነበር አንድም የግንባታ እቃ በቦታው አለመገኘቱን ይገልፃሉ:: የጤና ጥበቃ ቢሮ መሀንዲሶችም አንዳንድ ጊዜ ወደ ስፍራው በመሄድ የግንባታውን ሂደት የሚጎበኙ ቢሆንም የጥራት ችግር አለመኖሩን መመስከራቸውን አቶ አወቀ ይናገራሉ::

የወግዲ ሆስፒታል አለመጠናቀቅ ህዝቡን ከማጉላላቱና ለተለያዩ ችግሮች ከማጋለጥ ባለፈ በተጎራባች ወረዳዎች ለሚገኙ ሆስፒታሎችም ጫናን እየፈጠረ ነው:: በለጋምቦ ወረዳ ሚገኘው የህዳር 11 ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ዳዊት ይፍሩ እንደሚናገሩት የወግዲ ወረዳ ሆስፒታል በፍጥነት አለመጠናቀቅ በሆስፒታላቸው ላይ ጫና ፈጥሯል:: ከወረዳው ሆስፒታሉ ድረስ ለመድረስ ጊዜ የሚፈልግ እንደመሆኑ በተለይ ነፍሰጡር እናቶች ላይ ይህ መዘግየት ከፍተኛ ችግር ሊፈጥር ይችላል ይላሉ::

ለምሳሌ ከወሊድ በኋላ የሚከሰት የደም መፍሰስ ችግር ሲኖር አንድ እናት ግፋ ቢል እስከ ሁለት ሰአት ብቻ ነው መቋቋም የምትችለው:: ስለዚህ አምቡላንስ ተፈልጎ ሆስፒታል እስከምትደርስ ከዚያ በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል:: ይህም እናቶች በጊዜ አገልግሎት

እንዳያገኙና ለተለያየ ችግር እንዲጋለጡ ያደርጋል ይላሉ:: አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ሆስፒታሉ መሸከም ከሚችለው በላይ ታካሚ በሆስፒታሉ የሚጠራቀምበትና ሆስፒታሉን ከፍተኛ ጫና ውስጥ የሚከትበት ጊዜ አለ ይላሉ:: ስለዚህ እንደወግዲ ያሉ በአጎራባች ወረዳዎች የሚሰሩ ሆስፒታሎች በቶሎ ቢጠናቀቁ የነሱንም ሆስፒታል ስራ የሚያግዙና ጫና የሚቀንሱ መሆኑን ያምናሉ::

በደቡብ ወሎ ዞን በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ሆስፒታሎች ቁጥር ወደ ዘጠኝ እንደሚደርሱ የሚናገሩት የዞኑ ጤና ጥበቃ መምሪያ ኃላፊ አቶ ልዑልሰገድ ንጉሴ በበኩላቸው ከዘጠኙ ውስጥ ሁለቱ ተጠናቀዋል፣ ሁለቱ በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ፣ ቀሪዎቹ ግን የተቋረጡና በእጅጉ የተጓተቱ መሆናቸውን ይገልፃሉ:: የሆስፒታሎቹ ግምባታ መጓተትም የመልካለም አስተዳደር ችግር እየሆነና ህብረተሰቡንም ለተለያየ እንግልትና ችግር እየዳረገ መሆኑን ተገንዝበዋል::

በግንባታ ሂደቱ ላይ ከተቋራጮች ጋር ወርሀዊ ስብሰባ እንደሚደረግ የሚናገሩት አቶ ክንድይሁን ግንባታዎቹ የደረሱበትን ደረጃ በተመለከተ ውይይት እንደሚካሄድ አብራርተዋል:: በውይይቱም ከቢሮው የሚጠበቀው እንዲሟላና ከተቋራጮቹም የሚጠበቀው እንዲስተካከል ውሳኔ ያስተላልፋሉ:: በዚህ መንገድ ችግሮችን ለማስተካክል ይሞከርና ለውጥ የማይመጣ ከሆነ ውሉን ወደማቋረጥ ይሄዳል ብለዋል::

ተቋራጮች ትልቅ ችግር አድርገው የሚያነሱት የገንዘብ አቅምንና በውጭ ምንዛሬ ምክንያት ከውጭ የሚያስመጡት እቃ መዘግየት መሆኑንም ተናግረዋል:: እንዚህን ነገሮች ከግምት ውስጥ በማስገባት ተጨማሪ ጊዜ ቢሰጥም በሚፈለገው መንገድ መስራት ስላልቻሉ ተቋራጮች ግንባታ እንዲያቋርጡ ለማድረግ እንደሚገደዱ አብራርተዋል:: የተቋራጮችና የተቆጣጣሪ ድርጅቶች የእውቀት ክፍተትም ትልቅ ችግር መሆኑን ያነሳሉ:: ግንባታዎቹ የሚፈልጉትን ግብአት ጠንቅቆ ካለማወቅ ወደስራ ከተገባ በኋላ የእቃዎቹ ዋጋ ከጠበቁት በላይ ይሆንና ለመዘግየት ብሎም ግንባታውን ለመቋረጥ እንደሚገደዱ ይገልፃሉ::

አፈፃፀማቸው ለተመረጡ የግል ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ እንዲሰሩ ለመስጠት እንቅስቃሴ ተጀምሯል:: የነዚህ ድርጅቶች ዋጋ አዋጭ ከሆነ እንዲገነቡት ካልሆነ ግን የክልሉ መንግስት እልባት እንዲሰጠው ይደረጋል ብለዋል::

የአማራ መንገድና ህንፃ ግንባታ ስራዎች ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ጥላዬ ቢተው በበኩላቸው ድርጅቱ በክልሉ እየተገነቡ ያሉ ወደ 60 ያህል ሆስፒታሎችን እንደሚቆጣጠር ገልፀው፤ ሆስፒታሎቹን ለመከታተል በየዞኑ አንድ የፕሮጀክት አስተባባሪ ተመድቧል ብለዋል:: አንድ አስተባባሪ እስከ 10 ፕሮጀክቶችን ያስተባብራል:: ግንባታዎች በሚካሄዱበት ስፍራ ሁለት ሁለት ባለሙያዎች ተመድበዋል:: ባለሙያዎቹ ዋና ተቆጣጣሪና ረዳት ናቸው:: የወግዲ ሆስፒታል ሲገነባ የጥራት ልኬቱን ሳያልፍ የተሰራ አንድም ስራ የለም ይላሉ:: እያንዳንዱ የግንባታ ቁስ ወደስራ ከመግባቱ በፊት ጥራቱ ተፈትሾ ስለመሆኑ እርግጠኛነታቸውን ይገልፃሉ::

አቶ ደምሴ ሀይለማርያም በአማራ መንገድና ህንፃ ግንባታና ቁጥጥር ስራዎች ቁጥጥር ድርጅት

ከግንባታ ጥራት ጋር በተያያዘ ያለውን ሁኔታ የሚከታተለው የቀድሞው የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት የአሁኑ የአማራ መንገድና ህንፃ ግንባታ ቁጥጥር ስራዎች ድርጅት መሆኑን ይገልፃሉ:: ስለዚህ የመቆጣጠሩንና የግንባታው ሁኔታ በሚፈለገው መንገድ ስለመገንባቱ በዋናነት የሚመለከተው ይህንኑ ድርጅት ነው ይላሉ::

ወግዲ ላይም ለተቋራጩ ጊዜ ለመስጠት ተሞክሮ እንደነበርና ጊዜውን መጠቀም ባለመቻሉ ግንባታው እንዲቋረጥ ተደርጓል ብለዋል:: ግንባታው ከተቋረጠ በኋላ የተሰራውና ቀሪው ስራ ተለቅሞ ተጠናቋል:: ስለዚህ ለሌላ ተቋራጭ መሰጠት ስላለበት መቅደላ ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር በዋጋው ዙሪያ ህጋዊ ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል::

የልማት ድርጅቶቹ ማትረፍ ሳይሆን መደገፍ እንዲችሉ ታስቦ ይህ ውሳኔ መወሰኑንም ያብራራሉ::

አቶ ክንድይሁን ይህንን አስተያዬት ከሠጡን ከሳምንት በኋላ ተመልሰን ስንጠይቃቸው ድርጅቱ ያቀረበው ዋጋ የተጋነነ በመሆኑ ድርድሩ መቋረጡን ገልፀዋል:: ስለዚህ በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ በተሻለ

የደቡብ ወሎ ፕሮጀክት አስተባባሪ ናቸው:: በወግዲ ሆሲፒታል ግንባታ ላይ እንደተባለው ሰባት ጊዜ ያህል ባይሆንም የተወሰነ ጊዜ የባለሙያ ለውጥ ተደርጓል ይላሉ:: ይህም የተደረገው በባለሙያዎቹ ላይ በተስተዋለ የአቅም ክፍተት ምክንያት መሆኑን ይገልፃሉ:: የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ባለሙያዎች ከጠንካራ ባለሙያዎች ጋር በመመደብ ስራ እንዲለምዱ የማድረግ አሰራር ይከተሉ እንደነበርም ይናገራሉ:: በባለሙዎቹ መካከል በስራ ሂደት አለመግባባቶች የሚፈጠርበት ጊዜ መኖሩንና ለዚህም አፋጣኝ ርምጃዎች በመውሰድ ባለሙያዎቹ የሚሰሩበትን ቦታ የማቀያያር ስራ እንደሚሰራ ይናገራሉ::

በተቋረጠ ግንባታ ላይ ተቆጣጣሪ መሀንዲሶች እውቅና ሳይሰጧቸው የሚሰሩ ስራዎች ውድቅ እንደሚደረጉ የሚናገሩት አቶ ደምሴ በወግዲ ሆስፒታልም እንደዚህ አይነት ነገሮች መኖራቸውን ገልፀዋል:: የብረት በሮች፣ የውሃ መገደቢያ፣ የውሃ መፋሰሻና መሰል ግንባታዎች ላይ ክፍተት በመኖሩ አዲሱ ተቋራጭ ድርጅት የሚሰራቸው መሆናቸውን ያስረዳሉ:: እነዚህ ግንባታዎች መጀመሪያ ከባለሙያዎቹ ፈቃድና እውቅና ውጭ ( ግንባታው ሊቋረጥ አካባቢ) የተሰሩና እንደአዲስ የሚሰሩ የተባሉ ናቸው::

ዋነኛው የችግሩ ምክንያትም የተቋራጮች አቅምና የቁርጠኝነት ችግር መሆኑን ይናገራሉ:: ከክልሉ አመራሮች ጋር በመነጋገር ችግሮቹን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነውም ብለዋል:: ውሉ እንዲቋረጥ ከተደረገ በኋላ ጨረታ ወጥቶ ለሌላ ተቋራጭ እስከሚሰጥ ድረስ ጊዜ እንደሚፈልግና እየተፈጠረ ያለው መዘግየትም ከዚህ ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልፀዋል::

ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል 64 የተለያየ ደረጃ ያላቸው ሆስፒታሎች ይገኛሉ፤ ወደ 45 ያህሉ ደግሞ መጠናቀቃቸውንና ከነዚህም ውስጥ 22 ያህሉ ስራ መጀመራቸውን የገለፁልን በክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የጤና መሰረተ ልማት ኃላፊ አቶ ክንድይሁን እገዘው ናቸው::

ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች ላይ ሆኖ በርከት ያሉ ሆስፒታሎች መጓተታቸውን የሚናገሩት አቶ ክንድይሁን ትልቁ ምክንያት የቦታዎቹ አቀማመጥ ነው ይላሉ:: ተቋራጮቹም የቦታዎቹን አቀማመጥ ምክንያት በማድረግ ግንባታዎቹን የሚያጓትቱበት ዕድል መኖሩን ይገልፃሉ:: ቢሮውም ችግሩን ከግምት በማስገባት ጊዜ ለመስጠት ይሞከርና በሚፈለገው መልኩ የማይሄዱ ከሆነ ውሉ እንዲቋረጥ እንደሚደረግ ተናግረዋል::

ሆስፒታሉ እስከ 74 በመቶ ተገንብቶ ነው የተቋረጠው

ገጽ 39በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.

ከገጽ 40 የዞረ

የፊፋ...

ከገጽ 40 የዞረ

የቁልቁለት...በዓመቱ በ1995 ሚያዝያ ወር ላይ አልጀሪያ

2 ለ0 አሸነፈች። ከዚያ በኋላ ሁለቱ ሃገራት የዛሬ ሁለት ዓመት ባደረጓቸው የደርሶ መልስ ጨዋታዎች አሸናፊዋ አልጀሪያ ብትሆንም፤ ከ3 ግብ በላይ ማስቆጠር ግን አልቻለችም ነበር። 3 ለ1 እና 2 ለ1 ነበር አልጀሪያ ያሸነፈችው። ከሰሞኑ ግን ያልተጠበቀውና ያልታሰበው ሆነ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ብሊዳ አልጀሪያ ውስጥ 7 ለ1 ተሸነፈ።

የአልጀርያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ክሪስቲያን ጉርኩፍ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 3ኛ ጨዋታ ኢትዮጵያ ላይ የ7ለ1 ድል ካስመዘገቡ በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ተቃርበዋል::

ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ በቡድናቸው ድል ዙርያ ለጋዜጠኞች የሰጡትን መግለጫ ከተለያዩ የአልጄርያ የብዙሃን መገናኛ አውታሮች በማጣቀስ ሶከር ስፖርት ዘግቧል ::

አሰልጣኝ ክሪስቲያን ጉርጉፍ ‹‹ሁሉንም ነገር ባቀድነው መሰረት ተግባራዊ አድርገናል:: በፈጣን እንቅስቃሴ ተጋጣሚያችን በራሱ የግብ ክልል ተገድቦ እንዲጫወት ማድረግና ጨዋታውን ራሳችን በምንፈልገው ፍጥነት እንዲሄድ ነበር ዓላማችን:: የጨዋታው መጀመርያ አካባቢ እንስቃሴያችን ዝግ

ያለ ቢሆንም የኋላ ኋላ ተጋጣሚወቻችንን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከተናቸዋል::

‹‹ከዚህም በላይ ልዩነት ለመፍጠር ትኩረት እና ትዕግስት የታደሉ ጥራት ያላቸው ተጫዋቾች ይዘናል:: ያመከንነው የፍፁም ቅጣት ምት እና ያልተጠቀምንባቸው በርካታ የግብ እድሎች ባይኖሩ ኖሮ ውጤቱ ከዚህም በላይ ይሰፋ ነበር:: ነገር ግን ጨዋታው ልዩ ነበር:: ትልቅ ግብም አሳክተናል:: ፍፁም የሆነ ምሽት አሳልፈናል::”

‹‹በጨዋታው ላይ ቅር የሚለኝ ነገር ቢኖር የተቆጠረብን ግብ ነው:: ግብ ሳናስተናግድ ለመውጣት ተመኝቼ ነበር:: ቡድኔ በመጨረሻዎቹ 15 ደቂቃዎች ባሳየው እንቅስቃሴ ደስተኛ አይደለሁም:: ሁልጊዜም በትኩረት እና ንቃት ለ90 ደቂቃ መንቀሳቀስ አለብን:: ቡድኔ በተሰጥኦ የተሞላ ነው:: ነገር ግን ጨዋታዎችን በብስለት ማሸነፍም ይኖርብናል” ሲሉ ተናግረዋል::

የአልጀሪያ ቡድን በአዲስ አበባ ስታዲየም በመልሱ ጨዋታ 3 ለ3 በመለያየቱ ነጥቡ 10 ሆኗል:: ኢትዮጵያ በምትገኝበት የአፍሪቃ ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አልጀሪያ በ10 ነጥብ እና በ12 ንፁህ ግብ እየመራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ በ5 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የቀድሞው ዝነኛና የወቅቱ የባቫሪያኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ የክብር ፕሬዚዳንት ቤከንባዎር ባለፈው ጥቅምት ወር በወቅቱ ስህተት መስራቱን

ግብ...ከገፅ 40 የዞረ

«የአይፍል ማማን በእኔ ሐውልት ከቀየሩት ያኔ እዚሁ እቀራለሁ» ሲል ፈረንሣይ የመቆየቱ ነገር የማይታሰብ መሆኑን በማያሻማ መልኩ ገልጿል።

ዝላታን ኢብራሒሞቪች አውሮጳ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ አራት ሃገራት የሊግ ክለቦች ተሰልፎ ለአራቱም ዋንጫ ማስገኘት ችሏል። የሆላንዱ አያክስ ሁለት ጊዜ ዋንጫ እንዲያገኝ ካደረገ በኋላ፤ በጣሊያን ሴሪ አም ጁቬንቱስ ሁለት ጊዜ ዋንጫውን እንዲወስድ አስችሏል። ነገር ግን ጁቬንቱስ ሁለቱንም ዋንጫዎች በሀገሪቱ በተከሰተው እና ካልቾፖሊ በተሰኘው የእግር ኳስ ቅሌት የተነሳ ተነጥቋል።

በነገራችን ላይ ካልቾፖሊ የዛሬ ዐሥር ዓመት ገደማ በጣሊያን ፖሊስ ይፋ የሆነ የእግር ኳስ ቅሌት ነው። በወቅቱ ዋነኞቹ የጣሊያን ቡድኖች የሚፈልጉት ዳኛ እንዲያጫውታቸው በተደጋጋሚ የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በፖሊስ መጠለፉ ቅሌቱ ይፋ እንዲሆን አስችሏል። እዛው ጣሊያን ውስጥ ዝላታን ኢብራሒሞቪች ከኢንተር ሚላን ጋር ተሰልፎ ሦስት ዋንጫዎችን ማንሳትም ችሏል።

ከዚያም ወደ ስፔን በማቅናት የላሊጋውን ዋንጫ ከባርሴሎና ጋር ድል አድርጎ በመሳም ተሳክቶለታል። የድል መዝሙሩንም እየዘመረ ተመልሶ ያቀናው ወደ ጣሊያን ነበር። ጣሊያን ውስጥ እንደ ጎርጎሪዮሳዉያኑ አቆጣጠር ከ2011-2012 በተደረገው የሴሪኣ ግጥሚያ ኤሲ ሚላንን ለዋንጫ ባለቤትነት አብቅቶታል። ያኔ

ለእሱ በተከታታይ ስምንተኛ ዋንጫው ነበር።ከአንዱ ሀገር ወደሌላኛው ሀገር ክለብ እያቀያየረ

በሄደበት ሁሉ የዋንጫ ባለቤት የሚሆነው ስዊድናዊ አጥቂ፤ በመቀጠል ከጣሊያን ወደ ፈረንሣይ ነበር ያቀናው። እዚያም የፓሪስ ሴንጄርሜይን መለያን ለብሶ በመሰለፍ ቡድኑ ላለፉት አራት የፍፃሜ ጨዋታዎች አሸናፊ በመሆን አራት ዋንጫዎችን በተከታታይ እንዲሰበስብ አብቅቶታል።

ኤ.ኤፍ.ፒ እንደዘገበው፤ በዘንድሮው የፈረንሣይ ሊግ ቡድኑ ፓሪስ ሴንጄርሜይን ትሮይን 9 ለ0 በረመረመበት ጨዋታ አራቱ ግቦች የዝላታን ኢብራሒሞቮች ናቸው። ታዲያ ይህን ድንቅ ግብ አዳኝ ነው እንግዲህ የእንግሊዞቹ እነ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቸልሲ እና አርሰናል ለማስፈረም እየተረባረቡበት የሚገኙት። የ34 ዓመቱ አጥቂ ዝላታን ለአንደኛው የእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ ቡድን ፊርማውን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል:: «በፓሪስ ሴንጄርሜይን ውስጥ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን አልቆይም። እዚህ የአንድ ወር ተኩል ጊዜ ይቀረኛል» ሲል ተናግሯል። የዝላታን ኢብራሒሞቪች ቀልብ የትኛው የእንግሊዝ ቡድን ላይ እንደሚያርፍ ባይታወቅም በቅርቡ ግን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ በግዙፍ ሰውነቱ እየተሯሯጠ ግብ ሲያድን ማየታችን አይቀርም። ቸር ያሰማን!

መናገሩም ይታወሳል። ከተጠርጣሪ ግለሰቦች መካከል ፍራንዝ ቤከንባዎር፤ የቀድሞ የሃገሪቱ እግር ኳስ ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የ2006ቱ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ፕሬዚዳንትና የቀድሞ የፊፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ነበር::

ሄልሙት ሳንድሮክ፤ የቀድሞ የሃገሪቱ እግር ኳስ ማህበር ዋና ጸሃፊና የወቅቱ የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ዳይሬክተር በመሆን ሰርቷል::

ቲዎ ዋንዚንገር፤ የቀድሞ የሃገሪቱ እገር ኳስ ማሀበር ፕሬዚዳንት፣ የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትልና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንዲሁም የፊፋ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግሏል::

ሆርስት ሺሚት፤ የሃገሪቱ እግር ኳስ ማህበር ዋና ጸሃፊና የወቅቱ የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዚዳንት ነበሩ::

ስቴፈን ሃንስ፤ የሃገሪቱ እግር ኳስ እና

የወቅቱ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ኮሚቴ ፋይናንስ ኦፊሰር በመሆን ሰርተዋል::

በፈረንጆቹ ሃምሌ 2000 ላይ በተካሄደው የአስተናጋጅነት ምርጫ ጀርመን በ12 ለ 11 ድምጽ ደቡብ አፍሪካን ማሸነፏ ይታወሳል።

ቤከንባዎር በ1974ቱ የአለም ዋንጫ ምዕራብ ጀርመንን በአምበልነት በመምራት፥ እንዲሁም ከ16 ዓመታት በኋላ በጣሊያኑ የዓለም ዋንጫ ደግሞ በአሰልጣኝነት የዓለም ዋንጫን ማንሳቱ አይዘነጋም።

አቶ ወንድዬ እደግልኝ የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ናቸው:: በከተማዋ ሥርአት ያለው የገቢ አሰባሰብ አልነበረም:: በመሆኑም ነጋዴዎች ላልተፈለገ ወጪ ተደርገው ቆይተዋል:: በቅርቡ ግን የገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሰው ሀይልና በአሰራር ራሱን በማዘመኑ የገቢ አሰባሰብ ስርአት ተበጅቶለታል:: ከአንድ ሺህ ብር በላይ ግብር የሚከፍልም የግድ ወደ ገቢዎች መሄድ ሳይጠበቅበት በባንክ በኩል እንዲከፍል እድሉ ተመቻችቶለታል::

“ቀደም ሲል አሰራሩ የተዝረከረከ ስለነበር አንድ የመስሪያ ቤቱ ባልደረባ ደረሰኝ በማበላለጥ 800 ሺህ ብር መመዝበሩ ተደርሶበታል፤ በህግም በቁጥጥር ስር ውሏል” ብለዋል::

አቶ አዲሱ ዘለቀ የከተማ አስተዳደሩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሀላፊ ናቸው:: ስለስኳርና የምግብ ዘይት ለተነሱ ጥያቄዎች “የስኳርና የምግብ ዘይት አቅርቦት በአገር አቀፍ ደረጃ እጥረት አለ:: ስለሆነም አንድ ሰው የፈለገውን ያህል ሊያገኝ ባለመቻሉ

ከገፅ 31 የዞረ

ፊት ለፊት... ቢያማርርም በየወሩ በተወሰነ ደረጃ ይሰጣል:: ይህም ሆኖ ባቋራጭ ለመበልፀግ የሚሹ ስግብግቦች ለህብረተሠቡ ፍጆታ የቀረበን ሲመዘብሩ ተይዘዋል:: ለአብነት በ2008 ዓ.ም 186 ኩንታል ስኳርና 6 ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ውሎ ለህዝብ ተሰራጭቷል:: በተረፈ የስኳርና የዘይት ጥያቄ መቶ በመቶ የሚፈታው በአገር አቀፍ ደረጃ አቅርቦቱ ሲሟላ ነው” ብለዋል::

በደን ሀብት ዙሪያ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አልተገኘም::

የሸዋ ሮቢት ከተማ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አየለ መሠለ ደግሞ በዘርፉ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ የሆስፒታል ግንባታው ተጓቷል:: በአሁኑ ወቅት ግን ግንባታው ተጠናቆ የሰው ሀይል ወደ መመደቡ ተደርሷል፤ በቅርቡም ስራ ይጀምራል ብለዋል::

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግርማ የሽጥላ ደግሞ “ህዝቡ ባነሳቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ዙሪያ ከአመራሩ ጋር ለመምከርና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀት እንዳለብን ውይይቱ አመላክቶናል:: ሁኔታውንም በመገናኛ ብዙሀን እናሳውቃለን” ብለዋል::

ለ2006ቱ የጀርመን ዋንጫ የማዘጋጀት ዕድል በማጭበርበር የተጠረጠሩት፤

አይበገሬው ዝላታን፤

በኩር መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም.ገጽ 40 በኩር ስፖርትበኩር ስፖርት

ወደ ገጽ 39 ዞሯል

ሙዋሊሙ

አማራ ክልል አሸናፊነቱን አስጠብቋል

የቁልቁለት ጉዞ

ወደ ገጽ 39 ዞሯል

ግብ

ኢትዮጵያ ሶማሊያን 7 ለ0 አሸነፈች። ይህ የሆነው

እንደ ጎርጎርዮሳዊዉ አቆጣጠር በ1969 ዓመት ነበር፤ የዛሬ 47 ዓመት:: ዘመኑ በብዙዎች ዘንድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ወርቃማ የሚባልበት ነበር። ከሰሞኑ ደግሞ በተራዋ አልጀሪያ 7 ለ1 አሸነፈች። “ማንን?”፤ ኢትዮጵያን። በርካቶች የወቅቱን የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ደረጃ ሲገልጹ ከምንጊዜውም በላይ የቁልቁለት ጉዞ እየተጓዘ እንደሆነ ይደመጣሉ።

ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ከ48 ዓመት በፊት አንስቶ ለአፍሪቃ ዋንጫ ያደረጓቸውን ሰባት ጨዋታዎች ብንመለከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንደ ዘንድሮው ከባድ ሽንፈት ገጥሞት አያውቅም። እንደ ጎርጎሪዮሳዊዉ አቆጣጠር በ1968 መስከረም ወር ላይ ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ ተገናኝተው፤ አሸናፊዋ ኢትዮጵያ ነበረች፤ ለዚያውም 3 ለ0። ሁለቱ ሃገራት በ1982 መጋቢት ወር ላይ ዳግም ተገናኙ፤ አልጀሪያ የኢትዮጵያን መረብ መድፈር አልቻለችም፤ ጨዋታው ያለምንም ግብ ነበር የተጠናቀቀው።

በ1994 መስከረም ወር ተገናኝተውም ሁለቱም ግብ ሳይቆጠርባቸው እንደተከባበሩ መለያየታቸውን ታሪክ መዝግቦታል።

ዝላታን ኢብራሒሞቮች የስዊድን ብሄራዊ ቡድን አጥቂ ነዉ። ከሰሞኑ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተሰልፎ ከሚጫወትበት የፈረሳዩ ፓሪስ ሴንጀርሜይን ቡድን አፋተዉ ሊያስፈርሙት መፈለጋቸው ተሰምቷል። የ34 ዓመቱ አጥቂ ከማንቸስተር ዩናይትድ፣ ከቸልሲ አሊያም ከአርሰናል ለአንዱ ሊፈርም እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው።

5ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች በሐዋሳ ከተማ ከመጋቢት 6 እስከ 18/2008 ዓ.ም ሲደረግ ሰንብቶ ተጠናቋል፤ የአማራ ክልልም

ጨዋታውን በአንደኛነት ፈጽሟል::ከ640 በላይ የስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት

ያሳተፈው የአማራ ክልል በ18 የስፖርት አይነቶች ተሳትፎ አንደኛ በመውጣት ተመልሷል:: ቡድኑ ባስገኘው ድል የተደሰተው የክልሉ ህዝብም ከደጀን ከተማ ጀምሮ ባህር ዳር እስኪገባ ደማቅ አቀባበል አድርጐለታል::

ፊፋ ከ2006ቱ የጀርመን የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅነት የምርጫ ሂደት ጋር

በተያያዘ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ ቀጥሏል ።በዚህም ጀርመን አስተናጋጅነቱን እንድታገኝ

ተፈጽሟል ከተባለው ሙስና ጋር ተያያዥነት እንዳላቸው በጠረጠራቸው ስድስት ጀርመናውያን ላይ ያካሄደውን ምርመራ ውጤት ፊፋ አቅርቧል። የቀድሞው የሃገሪቱ ዝነኛ ተጫዋችና አምበል ፍራንዝ ቤከንባወርም ተጠርጣሪ በመሆን ምርመራ

የልዑካን ቡድኑ በዘመናዊ የስፖርት አይነቶች 58 ወርቅ፣ 45 ብርና 67 ነሀስ በድምሩ 170 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ መውጣቱን የልዑካን ቡድኑ መሪ አቶ እማኘው ይግዛው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልፀዋል::

በፓራሊምፒክ ስፖርት አይነትም በ25 የወርቅ፣ በ32 የብርና በ20 የነሀስ ሜዳሊያ ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ በሁለተኛነት አጠናቋል::

መስማት በተሳናቸው ኦሊምፒክ ስፖርት ሰባት የወርቅ፣ ሰባት የብርና ስምንት የነሀስ ሜዳሊያ

በማግኘት በሁለተኛነት ፈጽሟል:: በአጠቃላይ ውጤትም በአምስተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች አንደኛ በመውጣት በአራተኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ያገኘውን ድል መድገም ችሏል::

ስድስተኛውን የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች የመቀሌ ከተማ እንድታስተናግድ መመረጧ ተነግሯል::

ወደ ገጽ 39 ዞሯል

እየተደረገበት ይገኛል።ባለፈው ዓመት የጀርመኑ ኒውስ ዊክሊ

ጋዜጣ፣ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዩሮ የአስተናጋጅነት ድምጽ ለማግኘት ጥቅም ላይ መዋሉን ዘግቦ ነበር። ስድስት ግለሰቦችም ከዚህ ጋር ተያያዥነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው ነው ተቋሙ ምርመራውን እያደረገባቸው የሚገኘው።

የፊፋ የማጣራት ሂደት ተጫዋቹ ከፓሪስ ሴንጀርሜይን ቡድን ጋር

የገባው ውል ሊጠናቀቅ አንድ ወር ከግማሽ ብቻ ነው የሚቀረው።

ውሉ እንዳበቃም ከፓሪስ ሴንጀርሜይን እንደሚለቅ ፈረንሳይ ውስጥም እንደማይቆይ ፈረንሣዮች የሚታወቁበትን እና የሚኮሩበትን በመዲናይቱ ፓሪስ ውስጥ የሚገኘውን የአይፍል ማማን በማጣቀስ አስረግጦ ተናግሯል።

አዳኙ

በጠንካራ የኳስ ምቱ የሚታወቀው ዝላታን