the image of son of god

22
የልጁ መልክ ራዕይ. ምዕራፍ .1 Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

Upload: tlcfan-international-ministry

Post on 18-Dec-2014

349 views

Category:

Education


8 download

DESCRIPTION

 

TRANSCRIPT

Page 1: THE IMAGE OF SON OF GOD

የልጁ መልክ

ራዕይ. ምዕራፍ .1

Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

Page 2: THE IMAGE OF SON OF GOD

መግቢያ ጥቅሶች • ‘’29.ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ

ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ 30 አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤

ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው። 31 እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን

ይቃወመናል?’’ ሮሜ.8፥29-31

• ‘’እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው’’ 1.ጢሞ.3፥16

• ‘’ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ

ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።” 1.ጢሞ.4፥8

Page 3: THE IMAGE OF SON OF GOD

ኢየሱስ አራት ዋና መልኮች

1. በመጀመሪያ በአብ ቀኝ በክብር ያለው መልክ

2. ሁለተኛው የሰው ልጅን ለማዳን ስጋ ለብሶ የተገለጠበት መልክ

3. ሦስተኛው ከሁለቱ ለየት ያለ ነው። ይህም ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ለ40 ቀናት የተመላለሰበት የማንነት መልክ

4. በክብር ሲመለስ ያለው መልክ

Page 4: THE IMAGE OF SON OF GOD

የቃል ኪዳን (Bond-servants)

• ይህ ባሪያ ወይም በእንግሊዘኛው “bond-servants”የሚለው ቃል በዘጸ.21፥1-6 ላይ በእግዚአብሔር ሕግ ላይ ተጽፎ የምናገኘውን ባሪያ የሚያመለክት ነው።

• ምሳሌ፦ ንጉስ ዳዊት መዝ.40፥ 6-8 • ሌላ ቅሶች፦ ሮሜ.1፥1, 6፥16-18, ዮሐ.10፥9 • አንድ ሰው ወደ ጌታ ሲመጣ ምንም እንኳን እግዚአብሔር

እንደ ልጅ ቢቀበለውም ትክክለኛ ልጅነትን ስፍራ አይዝም ነገር ግን ሕጻን ስለሆነ የባሪያን ስፍራ ይይዛል። ገላ.4፥1-3

Page 5: THE IMAGE OF SON OF GOD

(Bond-servants) ባሪያው ዮሐንስ

• የክርስቶስን የሰማያዊ ውበት ከነሙሉ ክብሩና ግርማዊነቱ በፍጹም ግልጽነት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል የተመልከተው ሽማግሌው የጌታ ባሪያ ሐዋርያው ዮሐንስ ነው።

• ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ያናገረው ባሪያ ነው።

“የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል:: ከመከራ ስጋት ያርፋል::” ምሳሌ.1:32

• 2.ቆሮ.12፦1-11

Page 6: THE IMAGE OF SON OF GOD

የክርስቶስ ራዕይ • የራዕይ መጽሐፍ የክርስቶስ መገለጥ መሆኑን በመናገር ይጀራል፣” The

Unveiling of Jesus Christ” በእንግሊዘኛው “revelation” ሲሆን በግሪኩ ደግሞ apokalupsis, ይህም ቀጥታ ሲተረጎም የተሸፈነውን መግለጥ ማለት ነው፣

Galatians 1:12 “12 For I neither received it from man, nor was I taught it, but I received it

through a revelation [apokalupsis, “unveiling”] of [i.e., from] Jesus” “19 For the anxious longing of the creation waits eagerly for the revealing

[apokalupsis, “unveiling”] of the sons of God.” Romans 8:19,

• “ The Revelation of Jesus Christ, which God gave unto him, to show unto his servants things which must shortly come to pass; and he sent and signified it by his angel unto his servant John:”

‘’1 ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ

እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥”

Page 7: THE IMAGE OF SON OF GOD

በውስጡ የተጻፈውን

“የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው፣” ራዕይ.1፦2

• ዳንኤል. 5 •

Page 8: THE IMAGE OF SON OF GOD

ፍጥሞ ደሴት • ዮሐንስ እንደሚነግረን እርሱ በመከራ ውስጥ ነበር፣

ራዕይ1፦9,2፦9,10,22,7፦14 ዳን.10፦1-11 ዮሐንስ የሰምርኔስም ቤተክርስቲያን በዚያውን ወቅት በመከራ ውስጥ ነበረች፣ ትያጥሮም በኤልዛቤል የተነሳ በታላቅ መከራ ውስጥ ነበረች፣ ዮሐንስ ግን ስለ ጌታ ምስክርና ቃል በመከራ ውስጥ ነበር፣

Page 9: THE IMAGE OF SON OF GOD

የመልከት ድምፅ • የመለከትን ድምጽ የድል ድምፅን የያዘ ሲሆን በእግዚአብሔር ሕግ

መሰረት መለከት ለብዙ ምክንያቶች የነፋል፣ ዘሁ.10፦1-10

Page 10: THE IMAGE OF SON OF GOD

በመቅረዞች መካከል

• የመለከትን ድምጽ የድል ድምፅን የያዘ ሲሆን በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት መለከት ለብዙ ምክንያቶች የነፋል፣ ዘሁ.10፦1-10

• መቅረዞቹን ከተመለከተ በኃላ በመካከሉ የሰውን ልጅ የሚመስለውን ተመለከተ፣ ሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፣ ራዕ.1፦20

Page 11: THE IMAGE OF SON OF GOD

የሰው ልጅ የሚመስለው

• ኢየሱስ በምድር በሥጋው ቆይታው ወቅት የሰው ልጅ ይመስል ነበረ፣ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅም ነበር፣ በአብ ቀኝ ሲቀመጥ አሁንም መንፋሳዊ ቅርጹን ሳይቅይር የሰውን ልጅ ይመስላል፣ ሁለት እግር፤ ሁለት እጅ፤ አይን፤ ጆሮ፤ ፀጉር….ወዘተ ያለው ነው፣ ኢየሱስን በሰው ልጅነቱ ስንመለከተው ሰው ይመስላል፣

• ይህ በመቅረዞች መካከል የተገለጠበት የሰው ልጅ መልክ የሰው ልጆች የሚደርሱበት የመላካቸው ጣራ ነው፣

• እግዚአብሔር የሰው ልጆችን የጠራው ይህን መልክ እንዲመስሉ ነው፣ • ዮሐንስ የሰው ልጅ የሚመስለው ማየት የቻለው በመንፈስ በመሆኑና

ለሚስማው ድምጽ ፍቱን ከሚሄደት መንገድ መልሶ እሺ ብሎ በመታዘዙ ነው፣

Page 12: THE IMAGE OF SON OF GOD

አለባበሱ

• እግዚአብሔር ለዮሐንስ እንዳሳየው ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ሲታይ ልብሱ እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ሆኖ ነው፣ የለበሰው የጽድቅ ልብስ ከተቆራጠ ጨርቅ የተሰራ ሳይሆን ከአንድ ወጥ ከሆነ ጨርቅ የተሰራ ነው፣

Page 13: THE IMAGE OF SON OF GOD

የደረቱ መታጠቂያ

• በቁጥር 13 ላይ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነው ይለዋል፣ ጌታ ኢየሱስ እግሩ ድረስ በለበሰው ልብስ ላይ አንድ ውስብ መታጠቂያ አለው፣ ይህ ውብ የሆነው የወቅ መታጠቂያ ያለው በወገቡ ሳይሆን በደረቱ ላይ ነው፣ ደረቱ እንዳለ በወርቅ ተለብጧል፣ ደረት የልብ መገኛ ስፍራ ሳይሆን ልብ በምሳሌ ሲጠራ የእግዚአብሔር ሕግ የተፃፈበት ስፍራ ነው፣ እግዚአብሔር ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ በማለት ደግሞም ልጄ ሆይ ሕጌን በልብ ሰውር በማለት ብዙ ጊዜ ይናገራል፣ ዕብ.8፦10-12

Page 14: THE IMAGE OF SON OF GOD

ፀጉሩ

• የኢየሱስ የጸጉር ቀለም ለዮሐንስ በራዕይ ላይ ተገለጠለት፣ ዮሐንስ የኢየሱስን ፀጉር ሲመለከተው እንደ በግ ፀጉር እንደ በረዶም ነጭ ነበር፣ ዳንኤልም ኢየሱስን በተመለከተው ወቅት የተመለከተው እንደ ጥጥ ነጭ ጸጉር ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆኖ ነው፣ ዳን.7፦9

• በዘመናት የሸመገለ የሚለው ቃል ከፀጉሩ ንጣት ጋር አብሮ ይሄዳል፣ በዓለም ላይ ብዙ የፀጉር ቀለም አለ፣ ቡኒ፤ ጥቁር፤ ግራጫ፤ ነጭ ….ወዘተ ናቸው፣ የሚደንቀው ግን ሁሉ የጸግር አይነቶች መጨረሻቸው የሆነው ነጭ ፀጉር ነው፣

• የእግዚአብሔር ቃል በሽበታሙ ፊት ተነሳ ሽማግሌውን አክብር አምላክህንም ፍራ እኔ እግዚአብሔር ነን ይላል፣ ዘሌ.19፦32

• የጎበዛዝት ክብር ጉልበታቸው ናት የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው፣ ምሳሌ.20፦29

Page 15: THE IMAGE OF SON OF GOD

ራሱ

• እንደ በረዶ እንደ ባዘቶ ጥጥ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር የሆነ ራስ አለው፣ ይህ ብርሃን አስተላላፊ አብጸባራቂ ነው፣ ጌታ በመቅረዞቹ መካከል ሲገለጥ ይህ ራስ ይዞ ተገለጠ፣ ብርሃን እንዳያስተላልፍ የሚያደርግ ወይም የጨለማ መገኘት የሚያመለክት አንድስ እንኳን ጥቁር ነገር በራሱ ላይ አልታየም፣

Page 16: THE IMAGE OF SON OF GOD

ዓይኖቹ

• ብዙ ሰዎች እግዚአብሔር እንዲመለከታቸው ይፈልጋሉ፣ በእርግጥም ሁለት አይነት መመልከት አለ፣ የመጀመሪያው ፍጥረትን የሚቆጣጠርበት አስተያየት ሲሆን በዚህ መልኩ ሁሉን ይመለከታል፣ ሁለተኛው አሰተያየቱ ደግሞ የሰው ልጆችን የሚመለአትበት አስተያየቱ ነው፣

“እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንጽ አይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉ፣”2.ዜና.16፦19

• የእግዚአብሔር አይኖች ወደ ምድር የተላኩ የሚንበለበሉ መናፍስት ናቸው በሰባት ይመሰላሉ፣ ራዕ.5፦6 ይህ ደግሞ ፍጹም መሆናቸውን ያሳያል፣ እነዚህ አይኖች በፊቱ መሆናቸው ራሱ ላይ እንዳሉ ያመለክታል፣ የቤተክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነው እነዚህ በሰባት አይን የተገለጡ የእግዚአብሔር አይኖች በክርስቶስ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ነብዮ ዘካርያስ ይናገራል፣ ዘካ.3፦9 እነዚህ አይኖች በደልን ያቃጥላሉ፣

Page 17: THE IMAGE OF SON OF GOD

እግሮቹ

• እግሮቹ በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፣ ዳንኤል ሲመለከተው ደግሞ ክንዶቹና እግሮቹ የጋለ ባስ ይመስሉ እንደ ነበር ይናገራል፣ ብረት ነክ ይሆኑ ነገሮች ሁሉ ወደ ተፈለጉበት ቅርጽ ላማስያዝ ሲያስፈልግ ወደ እሳት ውስጥ ይገባሉ፣ የጌታ እግሮች በዚህ መልኩ መመስላቸው ለምን ይሆን? በእግዚአብሔር እሳት ውስጥ የገባ እርምጃና ሥራ ለእግዚአብሔር በሚመች መኩ የተገራ ነው፣ የእግዚአብሔር ሥራና እርምጃ ያደርጋል፣

• ኢየሱስ የብርሃን አለቃ ሲሆን ዲያቢሎስ ደግሞ የጨለማ ገዢ ነው፣ ሁለቱ በእግዚአብሔር ፊት በጠላትነት የተቀመጡ ሲሆን ብርሃን ግን ሁሉ ጊዜ ጨለምን ያሸንፋል፣ ዘፍ.3፦15

• እግዚአብሔር እባቡንና ጊንጡን እንድንረግጥ ልጣን ሰጥቶናል፣ ሉቃ.10፦19 ይሁንና ባልጋለ እግር መርገጥና በጋለ እግር መርገጥ አንድ አይነት ውጤት የለውም፣

Page 18: THE IMAGE OF SON OF GOD

ቀኝ እጁ

• ቀኝ እጅ የስልጣንና የሃይል ምልክት ነው፣ እኛንም ያስቀመጠን በቀኙ ነው፣ ነገርግን በቀኝ እጁ ስለ ያዛቸው ስለ ሰባቱ ከዋክብት ልናገር እወዳለሁ፣ እነዚህ ሰባት ከዋክብት በከዋክብቱ ስብስብ ዓለም Pleiades, “the seven sisters.” በመባል ይታወቃሉ፣ መዝ.147፦4 እግዚአብሔር ሁሉን ከዋክብት ብሰማቸው እንደሚጠራ ይነግረናል፣ ዘፍጥረት.1፦14-19 ላይ እግዚአብሔር ከዋክብትን የፈጠረው ብርሃን ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለምልክትና ለዘመኖች እንደ ሆነ ይናገራል፣ “for signs and for seasons.” ስለዚህም ከዋክብት ስለሚመጣው ነገር ትንቢት የሚናገሩ ናቸው ማለት ነው፣ ዘመንና ወቅት በእነርሱ ሊታወቅ ይችላል ማለት ነው፣

Page 19: THE IMAGE OF SON OF GOD

ድምፁ

• ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበር፣ ዳንኤል በትንቢቱ ድምፁ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር፣ ውሃ ከላይ ወደታች ሲወረወት ድምጽን ይፈጥራል፣ የሕዝቅኤልን ትንቢት ስንመለከት ስለዚህ ድምጽ የበለጠ እንረዳለን፣

“ሲሄዱም የክንፎቻቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ እንደ ሁሉን የሚችል የአምላክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅም ሠራዊት

ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆሙም ክንፎቻቸውን ዝቅ ያደርጉ ነበር።” ሕዝ.1፦24

Page 20: THE IMAGE OF SON OF GOD

የአፉ ስይፍ

• በሁለት ወገን የተሳለ ሰለታም ሰይፍ ወጣ፣ በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፣ ዕብ.4፦12 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን በሁለት በኩል የተሳለ ሰይፍ ይዞ የነበረ ግራኙ አዳኝ የናዖድን ታሪክ እናገኛለ፣ ይህ ሰው ይህን ሰይፍ ተጠቅሞ እስራኤልን ከአስገባሪ ነጻ አወጣቸው፣ መሳ.3፦15-23 ይህ ሰው ሕዝብ ነጻ ለማውጣት ይህ ሰይፍ ብቻ በቂ መሆኑን የተረዳ ታላቅ አሰተዋይ የሆነ በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳ የዛን ዘመን አዳኝ ነበር፣

• ጠላታችንን የምንገጥምበትና የምናጠፋበት ይህ ሰይፍ ነው፣ ኤፌ.6፦10-17 • ሕያው በመሆኑ ሕያው የሆኑ ስራዎችን ያከናውናል፣ በቅዱሳን ውስጥ ሲገባ

መንፈስንና ነፍስ እስኪለይ ድረስ ይወካል፣ የልብን ሃሳብ ይመረምራ፣ ዕብ.4፦12

Page 21: THE IMAGE OF SON OF GOD

ፊቱ

• ሐዋርያው ዮሐንስ በኢየሱስ ፊት ላይ ካሉት ግልጽ ነገሮች መካከል የጠቆመን ጸጉሩን፤ ራሱን፤ ዓይኑን፤ አንደበቱን ሲሆን የአፍንጫውንና የጆሮው ምስያ ምን እንደሚመስል መገንዘብ ያስቸግራል፣ ምናልባት የዮሐንስ የትኩረት አቅጣጫና አድናቆት የጣለበለበት ስፍራዎችን በጠቅላላው በፊቱ ይጠቀለላሉ፣ ፊቱም በሃይል እንደሚያበራ እንደ ፀሐይ ነበረ፣ የልጁ መልክ ከላይ እስከ ታች የተሟላ በመሆኑ ድል ነሺ አማኞች የልጁን መልክ ለመምሰል የሚበቃቸውን ያህል ልጁን ገልጦታል፣ እርሱን በመንፈስ ሆነን በመመልከት እርሱ እንዳየነው ለመምስል ራሳችንን እናስለምዳለን፣

• ዮሐንስም ሆነ ጳውሎስ ኢየሱስ ሲገናኛቸ ይህን ታልቅ ብርሃን ነጸብራቅ ተመልክተዋል፣ ሐዋ.22፦6-11 ክብር ብርሃን በመሆኑ በቀትር ሲያበራ ጨለማ ፈጽሞ ከእግር በታች ይሆናል ጥላ የሆነ ነገር ሁሉ ይወገዳል፣ ይህን ብርሃን የሚቋቋ ምንም አይነት ጨለማ የለም፣

Page 22: THE IMAGE OF SON OF GOD

“28 እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። 29 ልጁ በብዙ

ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ 30

አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም

እነዚህን ደግሞ አከበራቸው፣” ሮሜ.8፦28-30

Justification – Sanctification – Glorification