save the children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ...

146
Save the Children

Upload: others

Post on 10-Apr-2020

12 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

Save the Children

Page 2: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 3: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

3

መግቢያ

አያ ሙላት፡- ጤና ይስጥልኝ፤ እንደምን ዋላችሁ!

በቅድሚያ ወደ መጀመሪያው የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለ ጊዜ እንኳን በደህና መጣችሁ፡፡ አቶ ቢራራ መለሰ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስርዐተ ምግብ ቡድን መሪ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ሲናገሩ እንዳደመጣችሁት፤ የብሄራዊ የእናቶች ምግብ አለመጣጠንና የህጻናት መቀንጨር ትልቅ የሀገር ችግር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በዚህም ዙሪያ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎች አዘጋጅተናል፤ በእነዚህ ክፍለጊዜዎች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናቶችና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋናና ቁልፍ የሆኑ ትምህርቶችን እንማራለን፡፡ የዚህ ትምህርታዊ ውይይት ዋናው ዓላማ፤ በቂ እውቀትና ክህሎት ገብይታችሁ፤ ጠንካራ፣ ጤናማ እና ብሩህ ህጻናት አሳድጋችሁ ለቁምነገር እንዲበቁ ማድረግ ነው፡፡

እንግዲህ ዛሬ የመጀመሪያ ክፍለጊዚያችን እንደመሆኑ፤ የምንተዋወቅበትና ቀጣዮቹ የውይይት ክፍለጊዜዎች ምን እንደሚመስሉ ባጭሩ የምናይበት ይሆናል፡፡

አያ ሙላት፡- ስሜ ሙላት ይባላል ፤ብዙ ሰዎች አያ ሙላት ብለው ይጠሩኛል፡፡ የተወለድኩት ከገበሬ ቤተሰብ ሲሆን፤ በልጅነቴ በአባቴ ትንሽ ማሳ ላይ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት አባቴን አግዘው ነበር፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ግብርና አትኩሮቴን ይስበው ነበር፤ አንድ የፍሬ ዘር ተዘርቶ አድጎ ከፍሬው ስንበላ ስመለከት፤ የተፈጥሮ ነገር ሁልጊዜ ይደንቀኛል.

(ትንፋሽ ይወስዳል)

ካደግኩም በኋላ ስለግብርና ስራ የማወቅ ፍላጎቴ እያደገ በመሄዱ በጎጣችን ለግብርና ባለሞያዎችና ለገበሬዎች የሚሰጠውን ስልጠና ተከታትዬ ብዙ ነገር ለመማር ችያለሁ፡፡ ባገኘሁት እውቀትም አባቴን በማገዝ ከኋላቀር አስተራረስ በበለጠ ሁኔታ እንዴት የተሻለ አዝመራ እንደሚያገኝ፣ ማሳውን ከወቅቱ ጋር የእያስማማ፤ ሰብል እያፈራረቀ እንዲያርስ አግዤዋለሁ፡፡ የተሻለ ውጤት በማግኘቱ አባቴም ደስተኛ ነበር፡፡ ያን ጊዜ ነበር በግብርና ስራ ለመሰማራት የወሰንኩት፡፡ ሞዴል ገበሬ በመሆኔም ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ገበሬዎች የተሻለ ምርት እንዲያገኙ በመርዳትና በማማከር የምወደውን የግብርና ስራ ስሰራ ቆይቼአለሁ፡፡ አሁን እንደ ድሮው የግብርና ስራ ባልሰራም ገበሬዎችን በምክር ከመርዳት ወደኋላ አላልኩም፤ አሁን ባለችኝ ትርፍ ጊዜዬ ከልጅ ልጆቼ ጋር በመጫወት አሳልፈዋለሁ፤ ባለቤቴ ብርቱካን ግን አታሳርፈኝም፤ ገና ጎረምሳ ነህ፤ ገና ብዙ መስራት አለብህ እያለችኝ ነው፡፡ ባለቤቴ ብርቱካን እዚህ ጎኔ ትገኛለች፤ እሷም አሁን እራሷን ታስተዋውቃለች፡፡ በቀጣይ በሚኖረን ዘጠኝ የመማማሪያ ክፍለጊዜያት ውስጥ እኔ እና ብርቱካን እየተጋገዝን የማህበረሰብ ውይይቱን እንመራለን ማለት ነው፡፡

Page 4: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

4

እቴ ብርቱካን፡-(እየሳቀች)፡- እውነቴን ነው፤ እቤት ከዋለ ባሌ ቶሎ ያረጅብኛል፡፡ ገና ነው መስራት አለበት፡፡

አያ ሙላት፡- (እየሳቀ) የሷን ምክር በመስማቴ ይሄው ዛሬ ከናንተ ጋር ውይይቱ ላይ ተገኝቼአለሁ፡፡ እስኪ የእኔ ብርቱካን እራስሽን አስተዋውቂ፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አመሰግናለሁ ሙላት! በድጋሚ እንደምን ዋላችሁ! በተደጋጋሚ ባለቤቴ ስሜን ሲጠቅስ ሰምታችኋል፤ ላልሰማችሁት ብርቱካን እባላለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች እቴ ብርቱካን ብለው ይጠሩኛል፡፡ እስኪ ከየት ልጀምር.. እኔ ለቤተሰቦቼ የመጀመሪያ ልጅ ነኝ፤ ሁለት ወንድምና አንድ እህት ነበሩኝ፡፡ የልጅነት ጊዜዬን ሳስታውስ የመጀመሪያ ልጅ እንደመሆኔ ታናናሽ ወንድሞቼንና እህቴን የምንከባከበው ትዝ ይለኛል፡፡ ትምህርቴን ለመከታተል የነበረኝ ጊዜ ትንሽ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ምንም እንኳ ወላጆቼ ያልተማሩና ደሃ ቢሆኑም በትምህርቴ እንድገፋ ያበረታቱኝ ነበር፡፡ ልጅነት ደጉ እንደሚባለው እናቴን በስራ ማገዙንና ታናናሾቼን መንከባከብ በጣም የሚያስደስተኝ የልጅነት ትዝታዬ ነው፡፡ እንግዲህ ያኔ ነበር በውስጤ ሰው መርዳትና መንከባከብ የወደፊት ሞያዬ እንዲሆን የፈለግኩት፡፡ የምመኘውን የነርሲንግ ትምህርት ተምሬ ነርስ ሆንኩ፡፡ ቆይቼም አዋላጅ ሆንኩ፤ አዋላጅ በነበርኩበት ጊዜ በህብረተሰቡ ውስጥ በመዘዋወር እያዋለድኩ ስለ ጤናማ አመጋገብና ስለ ንፅህና አስተምር ነበር፡፡ ተማሪ በነበርንበት ጊዜ ትምህርት ለመስጠት ወደተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች እንሄድ ነበር፡፡አጋጣሚውን ልንገራችሁ፤ ስለጤና አጠባበቅና እጅን መታጠብ ስላለው ጥቅም ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ልናስተምር በምንዘዋወርበት ጊዜ ነው የልጆቼን አባት ሙላትን የተዋወቅኩት ፡፡ አስታውሳለሁ በምሰጠዉ ትምህርት በጣም ከመደሰቱ የተነሳ ከኛ ጋር እብሮ እየተዘዋወረ ገበሬዎችን ያስተምር ነበር፡፡

አያ ሙላት፡- (እየሳቀ) አንቺን ለመቅረብ ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ስለገባኝ ነው እንደዛ አብሬያችሁ የደከምኩት፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ተሳክቶልሃል (እየሳቀች) ድካምህ መና አልቀረም፤ እኔን የመሰለች አመለሸጋ ሚስት አገኘህ፡፡ ለማንኛውም ወደተነሳሁበት ፍሬ ነገር ልመልሳችሁና፤ ቀደም ብዬ እንዳልኩት በነርስነት ቆይቶም በአዋላጅነት ብዙ ነገር ልማር ችያለሁ፡፡ ከተማርኳቸው በርካታ ነገሮች መካከል የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናቶች እና የህጻናት ስርዐተ ምግብ ጠቃሚነት አንዱ ነው፡፡ እኔ ባደግኩበት ቤተሰብ ውስጥ ወላጆቼ ስለእንደዚህ አይነት ነገር ምንም አያውቁም ነበር፡፡ እኔና ባለቤቴ ተጋብተን የመጀመሪያ ልጃችንን ባረገዝኩ ጊዜ የእናቶች ስርዐተ ምግብ ማለትም የምበላዉን ምግብ ማመጣጠን ጀመርን፡፡ ጀመርን ያልኩበት ምክንያት ባለቤቴ እኔን በመደገፍ፣ በመወያየት እና እኔን በመንከባከብ ምንጊዜም ከጎኔ የማይለይ በመሆኑ ነው፡፡ ፈጣሪ ይመስገን፤ የሚያማምሩ፣ ጠናካራ፣ ጤናማ እና ብሩህ አእምሮ ያላቸው ሁለት ልጆች ወልደን አሳድገናል፡፡ አንዷ ዶክተር ስትሆን አንደኛዋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አስተማሪ ሆናለች፡፡ የመጀመሪያዋ ልጃችን ከአንድ

Page 5: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

5

ዓመት ተኩል በፊት የአያትነት ጸጋን አሳይታናለች፡፡ ታናሿም አሁን ነፍሰጡር ነች፡፡ እንግዲህ እኔና አባታቸው አያት እንደመሆናችን መጠን ለልጆቻችን ድጋፍና ምክር ጠቃሚ መሆኑን በመረዳታችን ከጎናቸው ባለመለየት የሚቻለንን እያደርግን ነው፡፡ መቼም እንደምትገምቱት ሁለቱም ልጆቻችን የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናቶች እና የህጻናት ስርዐተ ምግብ ተግባራትንን በደንብ ይከተላሉ፡፡

ጡረታ ከመውጣቴ በፊት፤ በነርስትነትና በአዋላጅነት ባገለገልኩበት ረዥም ዘመን ውስጥ ብዙ ሴቶችና እናቶችን ስለዚህ የእናቶች እና የህጻናት ስርዐተ ምግብ እቅድ እና አጠቃቀም አስተምሪያለው፡፡ ሆኖም ምኞቴ ሰፋ ባለ መድረክ ለብዙ ሴቶችና እናቶች ትምህርቱ እንዲደርሳቸው ነበር፡፡ ይህው ዛሬ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት መድረክ ላይ ብዙ ሴቶችና እናቶችን የማስተማር እድል በማግኘቴ ምኞቴ ተሳክቷል፡፡ እኔና ባለቤቴም በዚህ መድረክ ላይ አንድ ላይ በመሳተፋችን ደስ ብሎኛል፡፡ ባለቤቴ በግብርና እኔ በጤናው ዘርፍ ባካበትነው የረዥም ጊዜ ልምድና እውቀት እንዲሁም፤ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናትን የእናቶች እና የህጻናት ስርዐተ ምግብ ጠቀሜታን ስለምናውቅ ከዛም አልፎ፤የልጅ ልጅ ያደረስን ወላጆች በመሆናችን እውቀትና ልምዳችንን ለእናንተ ለማካፈል ብቁ ያደርገናል ብዬ አምናለው፡፡

አያ ሙላት፡- አመሰግናለሁ ብርቱካን! አሁን እንግዲህ ማንነታችንን ካወቃችሁ እስኪ ብርቱካን ስለጠቀሰችው የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት ምንነት ልንገራችሁ፤ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት አዲስ አይነት የማስተማሪያ ዘዴ ሲሆን በርካታ ቁምነገሮችን የምንወያይበት፤እና ሃሳብ የምንለዋወጥበት መድረክ ነው፡፡ ምናልባት እስከዛሬ ከተሳተፋችሁበት የማህበረሰብ ውይይት በሚከተሉት ይለያል፤ በዚህ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት፡-

• የሚሳተፉት ሠዎች ከ15 እስከ 20 አይበልጡም፡፡

• ተሳታፊዎች በሦስት ቡድኖች ይከፈላሉ፤ እነሱም ለየብቻቸው ይሰበሰባሉ

1. የነፍሰጡር ሴቶች እና የሚያጠቡ እናቶች ቡድን፣

2. የባሎችና አባቶች፤ ማለትም የነፍሠጡር ሴቶችና የሚያጠቡ እናቶች ባሎችና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት አባቶች ቡድን

3. የሴት አያትና ምራት ማለትም የነፍሠጡር ሴቶችናየሚያጠቡ እናቶች እናት ወይም ምራት እና ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት አያቶች ቡድን

• በእያንዳንዱ ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች በርካታ የሚጋሩዋቸው ጉዳዮች ስላሉ እርስበርስ መረዳዳትና በነጻነት ሃሳባቸውን መለዋወጥ ይችላሉ፡፡

• በዚህ መድረክ ቀልብን የሚገዙ ውይይቶች፣መዝሙሮች፣ ጨዋታዎች፣ ቀልዶች እና ልዩልዩ ታሪኮች ይኖሩናል

• በእነዚህ አስር የዳበሩ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለጊዜዎች ህጻናት ልጆቻችን፣ ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው ሊያድጉ የሚችሉባቸውን መንገዶች እንማራለን፡፡

Page 6: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

6

በእነዚህ ክፍለጊዜዎች በርካታ የምንወያይባቸው ቁምነገሮች ይኖሩናል፡፡ እየተዝናናን የምንማርበት በመሆኑ ዘና የሚያደርጉን ቀልድና ታሪኮች፣ አስተማሪ የሆኑ ጨዋታዎች እና ዘፈኖችን እንሰማለን፤ የመነጋገር እና ሃሳብን የመግለጽ አቅማችንን የሚያሳድጉ ትምህርቶችን በጨዋታ መልክ እንማራለን፤ እንዲሁም ደጋፊ ቁሳቁሶችና መረጃዎችን እቤት በመውሰድ ከቤተሰቦቻችን ጋር ሃሳብ እና መረጃ የምንለዋወጥበት አስደሳች የመማሪያ ጊዜ ይሆናል፡፡

አያ ሙላት፡- አንድ ላይ በሚኖረን ቆይታ አንዳንድ ጊዜ የእኛን ድምፅ ትሰማላችሁ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከናንተ ጋር ያሉት አስተባባሪ ያወያያችኋል፡፡ በየመሃሉም ለሚኖራችሁ ውይይትና የቡድን ስራዎች አስተባባሪ ቴፑን ዘግተው እኛ እንቀጥላለን፡፡ ስለዚህ እየተቀያየርንና እየተተካካን የትምህርት ክፍለ ጊዜውን እንመራለን ማለት ነው፡፡ ይሄን የደውል ድምጽ ስትሰሙ (የደውል ድምጽ ይሰማል) ቴፑ የሚጠፋበት ጊዜ ነው ማለት ነው፡፡ የምትሰሩትን የቡድን ስራ ወይም ውይይት ስትጨርሱ አስተባባሪ ቴፑን መልሰው ይከፍቱታል፡፡ እኔና ብርቱካን እንደገና እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡

እስቲ እንሞክረው! ‹ኪልልል› የሚለውን የደወል ድምጽ ስንሰማ አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉት፡፡ በዚህ አጋጣሚ እስኪ ከራስዎ ጀምሮ ሁሉም ተሳታፊዎች እራሳቸዉን ያስተዋውቁ፤ ተዋውቃችሁ ስትጨርሱ፤ አስተባባሪ እባክዎን መልሰው እንደገና ቴፑን ይክፈቱት፡፡

የደውል ድምጽ (ይሰማል) እቴ ብርቱካን፡እንኳን ደህና መጣችሁ! አሁን ሁላችንም በደንብ የተዋወቅን ይመስለኛል፡፡

የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ምን ያህል ወሳኝ ቀናት እንደሆኑ ደግሜ ላስታውሳችሁ እፈልጋለሁ፡፡ እነዚህ አንድ ሺህ ቀናት ስንል አንዲት እናት ከጸነሰችበት እለት ጀምሮ የወለደችው ህጻን ሁለት ዓመት እስከሚሞላው ያለውን ጊዜ ማለታችን ነው፡፡ በእነዚህ የመጀመሪያ አንድ ሺህ ቀናት ነፍሰጡርና አጥቢ ሴቶች የተለያዩ አይነት ጠቃሚና የተመጣጠኑ ምግቦችን ከተመገቡ፤ እስከ 6 ወር ድረስ ያሉ ህፃናት የእናት ጡት ብቻ ከጠቡ፤ከ 6 ወር እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህፃናት ከእናት ጡት በተጨማሪ የተለያዩ አይነት ጠቃሚና የተመጣጠኑ ምግቦችን ከተመገቡ ጤናማ፤ጠንካራና ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ልጆች መፍጠር ይቻላል፡፡ እነዚህ ልዩ አንድ ሺህ ቀናት እጅግ ወሳኝና ጠቃሚ የሆኑበት ምክንያት ህጻናት በፍጥነት የሚያድጉበትና የሚቀረጹበት ጊዜያት በመሆናቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ይሄ ወርቃማ እድል ለልጆቻችን ጥሩ መሰረት የሚጣልበትና ጥሩ የህይወት ጅማሬ የምንሰጥበት ጊዜ ነው ያልነው፡፡

ብርቱካን እስኪ በቀጣይ አስር የውይይት ክፍለጊዜያችን ምን ምን ርዕሰ ጉዳዮችን እንደምንመለከት በአጭሩ ንገሪን

እቴ ብርቱካን፡-እሺ እንግዲህ በዚህ በመጀመሪያው ክፍለጊዜ፤ ማለትም የዛሬው ውይይታችን ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ምንነት አጠቃላይ ግንዛቤ የምንጨብጥበት ይሆናል፡፡ ከሁለተኛው እስከ ዘጠነኛው ባሉት የውይይት ክፍለጊዜያት ውስጥ፤

Page 7: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

7

በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ አንድ ቤተሰብ ጠንካራ፣ጤናማ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ህጻን እንዲኖረው ደረጃ በደረጃ መደረግ ስለሚገባቸው ነገሮች ዘርዘር አድርገን በጥልቀት እንወያያለን፡፡ የመጨረሻውና አስረኛው ክፍለ ጊዜ፤ በአጠቃላይ ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት በዘጠኙ የውይይት ክፍለጊዜያት ውስጥ ምን ፍሬነገሮች እንደተማርን ለማስታወስ ደግመን የምንከልስበት እና ይህን ትምህርት ለመውሰድ እድል ላላገኙ ሁሉ ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ያገኘነውን እውቀትና ክህሎት የምናካፍልበት ጊዜ ይሆናል ማለት ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት አራት ደረጃዎች አሏቸው፤ የመጀመሪያው ህፃኑ ተፀንሶ እስከሚወለድበት፤ ሁለተኛው ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ 6 ወር እስከሚሞላው፤ ሶስተኛው ከ 6 ወር ጀምሮ 12 ወር እስከሚሞላው፤ የመጨረሻውና አራተኛው ደረጃ ከ12 እስከ 24 ወር ያሉት ጊዜያት ናቸው፡፡

ሙላት እንግዲህ ካለህ የግብርና ልምድ ተነስተህ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናቶች እና የህጻናትን ስርዐተ ምግብ ጥቅም በግብርና ለሚተዳደሩት ቤተሰቦች በሚሆን ምሳሌ ልታብራራልን ትችላለህ?

አጠቃላይ መግለጫ

አያ ሙላት፡- እሺ፤ ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስንነጋገር፤ ቀደም ብለው የተጠቀሱትን አራት የህፃናት እድገት ደረጃዎች ከሱፍ ተክል የእድገት ደረጃዎች ጋር ብናነፃፅረው ለግንዛቤ ይረዳናል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ይህን ሂደት የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎች ብለን እንጠራዋለን፡፡

አስተባበሪ እባክዎ ለውይይት እንዲረዳ የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎች ምስል በፍሊፕ ቻርት ገፅ ያሳዩ፡፡

እንደምታዩት የመጀመሪያው የእድገት ደረጃ ዘር እንለዋለን፡፡ ይሄ ጊዜ አንድ ህጻን ከተጸነሰበት ቀን ጀምሮ እስከሚወለድ ድረስ ማለትም በእናቱ ማህጸን ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ነው፡፡ አንድን ዘር መሬት ውስጥ ስንዘራ፤ ምን ያህል ለዘሩና ለአፈሩ እንክብካቤ እንደምናደርግ ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቀዋለን፤ ልክ እንደዛውም ነፍሰ ጡር እናት በእርግዝና ወቅት የምትመገበው የተመጣጠነ ምግብ፤ ለእርሷም ለፅንሱም እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም ነፍሰጡር እናቶች ጠንካራና ጤናማ እንዲሆኑ ማታ ማታ ከመተኛታቸው በፊት የአይረን ኪኒን መውሰድ ይኖርባቸዋል፤ ይህ ፅንሱንም ይረዳዋል

አያ ሙላት፡- ሁለተኛውን የእድገት ደረጃ ችግኝ እንለዋለን፡፡ ይሄም የእድገት ደረጃ አንድ ህጻን ልጅ ከተወለደበት እስከ ስድስት ወር ያለውን ጊዜ ይይዛል፡፡ መቼም እንደምታውቁት እንደ ገበሬ የዘራናት ዘር ከመሬት ብቅ ስትል፣ መብቀል ስትጀምር ልባችን በተስፋ አብሮ ማደግ ይጀምራል፤ ተንከባክበን ጠብቀን ጥሩ ሆና እንድትበቅል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ልክ እንደምናበቅላት ዘር፤ ችግኝ በምንለው የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ስድስት ወራት የእናታቸውን ጡት ብቻ ነው መጥባት ያለባቸው ይህ ማለት ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብ ወይም ውሃ በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም ማለት ነው፡፡

Page 8: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

8

አያ ሙላት፡- ሦስተኛውን የእድገት ደረጃ እምቡጥ እንለዋለን፡፡ ይሄ የእምቡጥ ደረጃ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ያለውን የአንድ ህጻን ልጅ እድሜ ይይዛል፡፡ በዚህ ወቅት ወላጆች በህፃኑ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያዩበት ጊዜ ነው፤ እምቡጥ ልጆች ንቁ ሆነው መቀመጥ፣ መዳህ የሚጀምሩበት፣ ነገሮች ሁሉ አዳዲስ ስለሚሆንባቸው፤ ለማወቅ ያገኙትን ነገር ሁሉ ወደ አፋቸው የሚያደርጉበት ጊዜ ነው፡፡ ለዚህ ነው አካባቢያቸው ንፅህናውን የጠበቀ ቦታ መሆን አለበት፤ የሚጠጡትም የተፈላ፤ ወይም የተጣራ ውሃ መሆን አለበት፡፡ እምቡጥ ልጆች ማለትም ስድስት ወር የሞላቸው ህፃናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ወፍራም፤ ለስላሳ ገንፎ፣ የተፈጬ/ እና ልመው የተቦኩ ለስላሳ ምግቦች መመገብ የሚጀምሩትበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ለአካላቸውም ሆነ ለአይምሯቸው እድገት ሃይል የሚሰጣቸውን ተጨማሪ ምግብና ፕሮቲን የሚፈልጉበት እድሜ ነው፡፡

አያ ሙላት፡- አራተኛውን የአንድ ህጻን ልጅ የእድገት ደረጃ አበባ እንለዋለን፡፡ ይሄ የእድገት ደረጃ ወይም የእድሜ ክልል ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ያለው የአንድ ህጻን እድሜ ነው፡፡ በአበባ እድሜ ያሉ ህጻናት መጠኑ ከቀድሞ በርከት ያለና በትንሹ ተከታትፈው የተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ የሚችሉበት ጊዜ ነው፡፡ ጡት መጥባት ማቆም የለባቸውም፡፡ አካባቢያቸው ንፁህና የሚጠጡትም ውሃ የተፈላ፤ ወይም የተጣራ መሆን አለበት፡፡

አሁን ደግሞ በሱፍ አበባ የመሰልነውን የአንድ ህጻን ልጅ እድገት ደረጃዎች በደንብ ለመገንዘብ እንዲያስችለን አራቱን የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎች በመጠቀም ትምህርታዊ ጨዋታ እንጫወታለን፡፡ ጨዋታውን እኔ እጀምራለሁ ስሜ ሙላት ይባላል፤ እኔ የዘር አያት ነኝ ይህን ያልኩበት ምክንያት አንደኛዋ ልጄ ነፍሰጡር በመሆንዋ ዘር ማህፀኗ ውስጥ ስላለ ነው፡፡ በተጨማሪም የአበባ አያት ነኝ ማለት ሁለተኛዋ ልጄ አንድ ዓመት ከመንፈቅ የሞላት ልጅ ስላላት ነው፡፡ ግልጽ ነው? እስኪ እናንተ ደግሞ ሞክሩት፡፡

አስተባባሪ ቴፑን ይዝጉትና ሁሉም ተሳታፊ እራሱን ያስተዋውቅ፡፡ እንግዲህ እራሳችሁን ስታስተዋውቁ ስማችሁን እየተናገራችሁ የዘር፣ ችግኝ፣ እምቡጥና አበባ ወላጅና አያት መሆናችሁን አስተዋውቁ፡፡ ለምሳሌ፡- ስሜ ገነት ይባላል፤ የችግኝ እናት ነኝ፡፡(ይህም ማለት ገነት ጨቅላ ህፃን ወይም ስድስት ወር ያልሞላት ልጅ አላት ማለት ነው፡፡) እስኪ በዚህች ምሳሌ ተጠቅማችሁ ትውውቁን ቀጥሉ ስትጨርሱ አስተባባሪ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡ደወል ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! አራቱን የሱፍ አበባ እድገት ደረጃዎች በመጠቀም እራሳችሁን እንዳስተዋወቃችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዘር፣ ችግኝ፣ እምቡጥ እና አበባ በአንድ ህጻን እድገት ላይ በልዩ አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ የሚታዩበት ወሳኝ የእድገት ደረጃዎች ናቸው፡፡ የዘራነውን ሰብል ከመጀመሪያው ዘር ከዘራንበት ጊዜ አንስቶ መንከባከብና ማሳደግ እንዳለብን ሁሉ፤ ህጻናት ልጆቻችንንም ከእለተ ጽንስ ጀምሮ መንከባከብና ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ልዩ ቀናት ናቸው፡፡ ምክንያቱም በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ህጻን ሰውነት እና አዕምሮ በፍጥነት/ቶሎ የሚያድግበት ወቅት በመሆኑ ነው፡፡

Page 9: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

9

ስለዚህም በዚህ ጊዜ ውስጥ ለነፍሰጡር ሴት፣ ለምታጠባ እናት እንዲሁም ለህጻናት የተመጣጠኑ ምግቦችን የመገብናቸው እንደሆነ ህጻናቱ ደስተኛ፤ ጠንካራ፤ ጤናማ፤እና በአዕምሮ ብሩህ ከመሆናቸውም አልፎ በአዋቂነታቸው ዘመን ስኬታማ ህይወት እንዲኖራቸው እንረዳቸዋለን ማለት ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አመሰግናለሁ ሙላት! ገበሬ ስለሆንክ የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎችን የገለጽክበት መንገድ ደስ የሚል ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትንሽ ለየት ያለ ነገር እንሞክር፤ መቼም መካከላችን ሙዚቃ የማይወድ ሰው የለም፤ አይደለም እንዴ? እስኪ እስካሁን ስለተወያየንባቸው አንድ ሺ ቀናት የሚገልፅ አንድ ጥሩ መዝሙር እንስማ፤ ቃላቶቹን በደንብ አድርጋችሁ አድምጡ፤ አብሮ መዘመርንም ይቻላል፡፡

የመጀመሪያ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡- (ከመዝሙሩ ጋር አብራ እያንጎራጎረች) መዝሙሩ ደስ አይልም? እኔ ወድጄዋለሁ! እናንተስ? መልዕክቱን እንደሰማችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እስኪ በዘፈኑ ዙሪያ ሃሳብ ተለዋወጡበት፡ ቴፑ ከመዘጋቱ በፊት ግን የምትወያዩባቸውን ጥቂት ነጥቦች እነሆ፡-

1. ከመዝሙሩ ምን ተገነዘባችሁ? ዘፈኑ ምን አይነት መረጃዎችን ወይም መልእክቶችን ይዟል?

2. ከመዝሙሩ በጣም የወደዳችሁት ምኑን ነው?

3. ይሄን መዝሙር ለቤተሰባችሁ ማስተማር የምትችሉ ይመስላችኋል?

ጥያቄዎቹ ግልጽ ናቸው አይደል? እሺ አስተባበሪ ቴፑ ይዘጋና ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር የተጠቀሱት ሦስት የመወያያ ሃሳቦች ላይ ተሳታፊዎቹ እንዲወያዩ ይርዷቸው፡፡ ስትጨርሱ አስተባባሪ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

የደወል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህን መጣችሁ፡፡ የመዝሙሩን መልዕክት በደንብ ተወያያችሁበት አይደል? ዘፈኑን እንደተከታተላችሁት አንድ ህጻን ከተጸነሰበት ዘር ብለን ከምንጠራው የእድሜ ደረጃ ጀምሮ አድጎ ሁለት ዓመት እስከሚሞላውና አበባ ብለን እስከምንጠራው የእድሜ ደረጃ ድረስ ያለውን የህይወት ጉዞ በደንብ የሚያስገነዝበን ጥሩ መልክት ያዘለ ዘፈን ነው፡፡ እስኪ አጠር ባለ መልኩ የመዝሙሩን መልዕክት እንየው፡፡

• ይህ ልዩ የህይወት ጉዞ የሚጀምረው በደንብ ተመግባ ጠንካራ የሆነችው እናት ጠንካራና ጤናማ ዘር ከጸነሰች ጀምሮ ከዘጠኝ ወር በኋላ ልጁ የሚወለድበትን ጊዜ ያካትታል፡፡ የተወለደውም ህጻን ችግኝ ብለን እንጠራዋለን፡፡

• ችግኝ ህፃን ከተወለደ ጊዜ አንስቶ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ የሚጠባበት ጊዜ ሲሆን ተጨማሪ ምግብም ሆነ ፈሳሽ ወይም ውሃ መስጠት የተከለከለ ነው፡፡

• ከስድስት ወር በኋላ እምቡጥ የምንለው የእድገት ደረጃ ላይ ይደርሳል፤

Page 10: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

10

በዚህ ጊዜም ከእናት ጡት በተጨማሪ ወፍራም ገንፎና ለስላሳ የተፈጩ የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ መጀመር አለበት፡፡

• ህፃኑ አንድ አመት ሞልቶት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያለው ጊዜ የአበባ ጊዜ ይሆናል ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከእናት ጡት በተጨማሪ ጠቃሚና ገንቢ ምግቦችን መመገብ አለበት፡፡

የህጻናት ልጆቻችንን የወደፊት እድል ብሩህ የሚያደርግ ጥሩ መንገድ አይመስላችሁም? የሚያምር የህይወት መንገድ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የሰማነው መዝሙር ይህን እድል ያላገኙ ህጻናት ምን እንደሚደርስባቸው በደንብ ገልጾልናል፡፡ ምክንያቱም የተመጣጠነና ገንቢ ምግብ ያላገኙ ህፃናት ጠንካራ፣ ጤናማ እና በአዕምሯቸውም ብሩህ አይሆኑም፤ ደካማ፣ ፈዛዛ በትምህርታቸውም ደካማ ይሆናሉ፡፡ አድገውም በአዋቂነት ዘመናቸው ደስተኛና ስኬታማ ህይወት ለመምራት ያላቸው እድል በጣም ያነሰ ነው፡፡

ይሄ ግን እንዳይሆን ማድረግ ይቻላል፡፡ ደስ የሚለው ነገር ማንኛውም ቤተሰብ ለልጁ ይህን መልካም እድል መፍጠር ይችላል፡፡ ከተወለደ በኋላ ዘግይተን ብንጀምርም ህፃኑ ሁለት ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ጠንካራ፣ጤናማ እና ብሩህ አዕምሮ ያለው ሆኖ እንዲያድግ እድሉ አለን፡፡ በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ የልጆቻችንን የወደፊት ህይወት ጥሩ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን፡፡ ደሃም ሆነ ሃብታም፣ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖር ማንኛውም ቤተሰብ ይህን በማድረግ ጥሩ መሰረት መጣል ይችላል፡፡

እቴ ብርቱካን፡-በጣም ጥሩ፡፡ ጥሩ መዝሙር ነው፤ እነዚህን ሁሉ ፍሬ ነገሮች አስተምሮናል፡፡ መዝሙሩን ወደኋላ መልሰን እንሰማዋለን፡፡ በቀጣዮቹ አስር የውይይት ክፍለጊዜያችን ስለ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ ትምህርትን በተመለከተ ብዙ ቁምነገሮችን እንቀስማለን፡፡ ቀደም ሲል ሙላት የረዥም ዘመን ሞዴል አርሶአደር በመሆኑ ካለው እውቀትና ልምድ ጠቃሚ ነገሮችን አካፍሎናል፡፡ እኔም በበኩሌ ለብዙ ዓመታት የጤና ባለሞያና ነርስ በመሆኔ ያለኝን ልምድና እውቀት ላካፍላችሁ እፈልጋለሁ፡፡

እስኪ ስለ ጉልቻ አንዳንድ ነገር ላጫውታችሁ፡፡ መቼም ሁላችንም ጉልቻ ምን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ጉልቻ ለዘመናት አብሮን የኖረ በየቤታችን በየማእድቤታችን የምናገኘው በየእለቱ የምንገለገልበት ሲሆን ጉልቻ የቤተሰብ ተምሳሌትነት አለው፡፡ መቼም እንደምናውቀው አንድ ሰው ‘’ሦስት ጉልቻ መሰረተ’’ ሲባል፤ ሚስት አገባ፣ ጎጆ ወጣ፣ ቤተሰብ መሰረተ ማለት ነው፡፡ ሙላትን ሳገባ እናቴ የመጀመሪያዬን ጉልቻ ቤት መመስረቴን በማስመልከት ሰጥታኛለች፡፡ ከዚህ ውጪ እንግዲህ በጥሬ ትረጉሙ ጉልቻ የወጥ ማብሰያ ድስትን ወይም የእንጀራ ምጣድን ደግፎ የሚይዝ/ የሚያስቀምጥ ሦስት ከፍ ክፍ ያሉ ድንጋዮች ወይም የሸክላ አምዶችን ይወክላል፡፡

ምጣዱ ሚዛኑን ጠብቆ እንዲቀመጥ ሦስቱም ጉልቻዎች በጣም ጠቃሚ ናቸው፤

Page 11: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

11

አንዱ ጉልቻ ከመሃል ቢወጣ ምጣዱ በቅጡ መቀመጥ አይችልም፤ ምጣዱ በትክክል እንዲቀመጥና እንጀራው እንዲጋገር ሦስቱም ጉልቻዎች ተስተካክለው፣ በቁመት ተመጣጥነው መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስለ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ ስንወያይ ከጉልቻ ሃሳብ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እንማራለን፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ የእናቶች ስርዐተ ምግብ ጉልቻ ምስልን እኔ የጉልቻ ሀሳቡን ሳስረዳ ለተሳታፊዎቹ አሳዩዋቸው፤ እስቲ ከእንጀራ ምጣዱ ልጀምር፡፡

• ምጣዱ የዘወትር ምግቦችን በምሳሌነት ይወክላል፡፡ የዘወትር ምግቦች የምንላቸው ምግቦች በየእለቱ አዘውትረን የምንመገባቸውን ምግቦች ሲሆን፤ እንጀራ፣ ሽሮ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ገብስ፣ እንሰት/ቆጮ፣ ባቄላ፣ ሽምብራ፣ አተር ክክ፣ ምስር፣ በቆሎ፣ እና ማሽላ የመሳሰሉት በተለያየ መልክ አዘጋጅተን የምንመገባቸው ናቸው፡፡

• ከእንጀራ ምጣዱ ስር ምን እንዳለ አስተዋላችሁ? ሦስቱ ጉልቻዎች ምጣዱን ደግፈው ተሸክመውታል ወይም አቁመውታል፡፡ እነዚህ ጉልቻዎች የዘወትር ምግባችን ላይ የምንጨምራቸውና እናትና ህፃናትን የሚገነቡ ዋነኛ ምግቦችን ይወክላሉ፡፡ እነዚህን ዋነኛ ምግቦች ኮኮብ ምግቦች ብለን እንጠራቸዋለን፡፡

የእናቶች ስርዐተ ምግብ ጉልቻ፡-

• ቀይ አምድ፡- ባለ ሶስት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል እነዚህም ከእንሰሳት ተዋጽኦ የምናገኛቸውን የምግብ አይነቶች ማለትም እንቁላል፣ወተት፣ ስጋ፣ ዶሮ፣ አይብ፣ እርጎ፣ እና አሳ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ነፍሰ ጡርና አጥቢ እናቶች ባለ ሶስት ኮከብ ምግቦችን ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ መብላት አለባቸው፡፡

• አረንጓዴው አምድ፡- ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል እነዚህም አረንጓዴ ቅጠላቅጠልና አትክልት ምግቦችን ማለትም የአበሻ ጎመን፣ቆስጣ፣ ዱባ፤ ካሮት፣ ስኳር ድንች፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ አታክልቶች የተለያዩ፤ ገንቢ በቫይታሚን የታመቁና ሀይል ሰጪ ምግቦች ናቸው፡፡ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ባለ ሁለት ኮከብ ምግብ ጨምረው መመገብ አለባቸው፡፡

• ቢጫው አምድ፡- በድጋሚ ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል፡፡ እነዚህም ፍራፍሬን ማለት ብርቱካን፣ፓፓያ፣ አቦካዶ፣ ማንጎ፣ፓም፣ አናናስ፣ ሙዝ እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች በየቀኑ በሚመገቡት ምግብ ላይ ቢያንስ አንድ ባለ ሁለት ኮኮብ ፍራፍሬ ምግብ ጨምረው መመገብ አለባቸው፡፡

አስተባበሪ እባክዎን ከመማሪያ መርጃው መሳሪያ ላይ የህጻናት የተመጣጠነ ምግብ የጉልቻ ስእላዊ ማሳያውን ገልፀው ያሳዩዋቸው፡፡

የህፃናት ስርዐተ ምግብ፡-

Page 12: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

12

• ቀዩ አምድ፡- ልክ እንደ በፊቱ ባለ ሶስት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል፡፡ እነዚህም ከእንሰሳት ተዋጽኦ የምናገኛቸው የምግብ አይነቶች ማለትም እንቁላል፣ወተት፣ስጋ፣ ዶሮ፡ አይብ፣ እርጎ፣ እና አሳ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ከስድስት ወር ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ላይ ያሉ ህጻናት ተገቢውን እድገት ለማግኘት ቢያንስ አንድ ባለ ሦስት ኮከብ ምግብ በየቀኑ መመገብ አለባቸው፡፡

• አረንጓዴው አምድ፡- ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል፤ ማለትም አትክልትና ፍራፍሬን፡፡ የአትክልት ምግቦች የአበሻ ጎመን፣ቆስጣ፣ ዱባ፣ ካሮት፣ ስኳር ድንች፣ ቲማቲም፣ ጥቅል ጎመን የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ አትክልቶች፤ ገንቢ በቫይታሚን የታመቁና ሀይል ሰጪ ምግቦች ናቸው፡ በተጨማሪም የህፃናት ስርዐተ ምግብ ፍራፍሬን እንደ ብርቱካን፣ፓፓያ፣ አቦካዶ፣ ማንጎ፣ፓም፣ አናናስ፣ ሙዝ እና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡ ከስድስት ወር ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ያላቸው ህጻናት ቢያንስ አንድ አትክልትና ፍራፍሬ ባለ ሁለት ኮኮብ ምግብ በየቀኑ መመገብ አለባቸው፤ ይሄንን ካላደረጉ የቫይታሚን እጥረት ህፃናቱ ላይ ይፈጠራል፡፡

• ቢጫው አምድ፡- ባለ አንድ ኮኮብ ምግቦችን ይወክላል፤ እነዚህም ቅባትና ዘይቶች ናቸው፡፡ ቅቤ፣ የሱፍ፣ የኑግ፣ የተልባ ሌሎችንም የአትክልት ዘይቶች ይወክላል፡፡ እነዚህን ቅባትና ዘይቶች የህፃናት ምግብ ውስጥ ጨምረን ስናበስል ተጨማሪ ሀይል ይሰጣቸዋል፡፡ የህፃናት ሆድ ትንሽ በመሆኑም ቅባትና ዘይቶች ምግቦችን ለማለስለስና ለማጣፈጥ፤ ምግቡም እንዲፈጭ ይረዳቸዋል፡፡ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ላላቸው ህጻናት ምግብ በምናዘጋጅበት ጊዜ ከእነዚህ ምግቦች በቂውን መጠን መጥነን መጨመር ይኖርብናል፡፡

የተመጣጠነ ምግብ ስንል አሁን የገለጽናቸውን የምግብ አይነቶች ማለታችን ነው፡፡ እነዚህን ምግቦች ኮከብ ምግቦች እንላቸዋለን፡፡ እነዚህን ኮከብ ምግቦች ዘወትር በሚዘጋጀው ምግብ ላይ እየጨመርን መመገብ እጅግ ጠቃሚ መሆኑንም መርሳት የለብንም፡፡

ማርባትና ማብቀል

እቴ ብርቱካን፡-እንግዲህ ኮከብ ምግቦችን በደንብ አውቀናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ነፈሰጡር እና አጥቢ እናቶች፤ እንዲሁም ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት እድሜ ያሉ ህጻናት ኮከብ ምግቦችን ከእለት ምግቦች ወይም መክሰስ ጋር ጨምረው ምንጊዜም እንዲመገቡ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህንን ግን እንዴት ማድረግ ይቻላል? እስኪ ሙላት የእዚህን መልስ አብራራልን፡፡

አያ ሙላት፡- መልሱ ቀላል ነው፤ ብዙዎቻችን አርሶ አደር/ገበሬ እንደመሆናችን መጠን እነዚህን ምግቦች በማርባትና በማብቀል በቀላሉ ልናገኛቸው እንችላለን፡፡ እስቲ ከእናንተ መሃል ስንቶቻችሁ ናችሁ ኮከብ ምግቦችን እያረባችሁና እያበቀላችሁ የምታገኙ? እስኪ እጃችሁን እያወጣችሁ ንገሩን፡፡ አስተባባሪ እባክዎ ሃሳባቸውን እንዲገልጹና እንዲወያዩ ይርዷቸው፡፡ ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው

Page 13: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

13

ይክፈቱት፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ! መቼም ሁላችሁም ለቤተሰባችሁ በቀላሉ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ኮከብ ምግቦችን እንደምታረቡ ወይም እንደምታመርቱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እንደሙላት አይነት ሞዴል የግብርና ባለሞያ በመካከላችን መገኘቱ ኮኮብ ምግቦችን እንዴት እንደምናረባና እንደምናመርት በምክር ሊረዳን ይችላል፡፡ ሙላት በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ የምታብራራልን ነገር ይኖራል?

አያ ሙላት ፡- በደንብ እንጂ፤ ይሄማ ጥርሴን የነቀልኩበት ሞያዬ ነው፡፡ እንደምታውቁት አርሶአደሮች እና የግብርና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ግብርናን በተመለከተ ሰፊ ልምድ አለን፡፡ ስለምርጥ ዘር አጠቃቀም፣ ስለማዳበሪያ አጠቃቀም፣ ስለተሻሻለ አስተራረስ ዘዴ እና ስለመሳሰሉት ጠቃሚና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ ምክሮችን እና እውቀቶችን እንለግሳለን፡፡ ጠቃሚ ትምህርቶችን በመውሰድ ኮከብ ምግቦችን በየእለቱ የምትመገቡበትን መንገድ መፍጠር ይቻላል፡፡ በአስሩ የአንድ ሺ ቀናት የውይይት ክፍለጊዜያችን ኮኮብ ምግቦችን እንዴት እንደምናረባና እንደምናበቅል እንማራለን፡፡

ማግኘትና መግዛት

እቴ ብርቱካን፡- አመሰግናለሁ ሙላት! እንግዲህ ለነፍሰጡር እናትም ሆነ ለምታጠባ እናት እንዲሁም ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ላሉ ህጻናት በየእለቱ ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ ከሚያስችለን አንዱ መንገድ ከገበያ ገዝተን በማቅረብ ነው፡፡ በቆሎ፣ ስንዴ፣ገብስ፤ ጤፍ፤ ሰሊጥ፣ ሽንብራ፣ ማር፣ ቡና የመሳሰሉት ለቤተሰባችን በቂ ገንዘብ የሚያስገኙ ምርቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ሸጠን ከምናገኘው ገንዘብ የተወሰነውን ብር ኮከብ ምግቦችን ለመግዛት ያስችለናል፡፡ እስቲ ስንቶቻችን ነን የእርሻ ምርቶቻችንን በመሸጥ ገንዘብ የምናገኘው? እባክዎ አስተባባሪ ውይይቱን ያመቻቹላቸው፡፡ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት እንዲወያዩ ይርዷቸው፡፡ ውይይቱን ሲጨርሱም ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

የደወል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እሺ፤ እንኳን ደህና መጣችሁ! መቼም ሁላችሁም እህልና ሌሎች የእርሻ ውጤቶችን በመሸጥ/ገበያ በማውጣት ገቢ እንደምታገኙ እገምታለሁ፡፡ ቀደም ሲል እንደጠቀስኩት ከዚህ ላይ የሚገኘው የተወሰነ ገንዘብ ለቤተሰባችን ኮኮብ ምግቦች መግዣ ልናውለው እንችላለን፡፡ በቀጣዩ ተከታታይ የውይይት ክፍለጊዚያችን፤ ለእናቶችና ለህጻናት በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት በቂ ኮከብ ምግቦችን ለመግዛት የሚያስችለንን ተጨማሪ ገቢ ከግብርና ስራ እንዴት ማግኘት እንደምንችል እንማራለን፡፡

Page 14: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

14

ማዘጋጀት ሳይበላሽ ማቆየትና መከማቸት

እቴ ብርቱካን፡-ቀደም ሲል እናንተ ስትወያዩ፤ ሙላት አንድ የሚያስቅ ታሪክ እየነገረኝ ነበር፡፡ እስኪ ሙላት ለእነሱም ንገራቸው፡፡

አያ ሙላት፡- እሺ ብርቱዬ፡፡ ታሪኩ በአንድ ምሽት አንድ ወዳጄ ቤት የሆነ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ሁሌም እንደሚደረገው እዚህ ወዳጄ ቤት ቤተሰቡ በሙሉ ለእራት አንድላይ ገበታ በመቅረብ የመብላት ልምድ አላቸው፡፡ አንድ ቀን ታዲያ የጓደኛዬ ባለቤት እንደተለመደው ቀኑን ሙሉ በስራ ተወጥራ እዚህና እዚያ ስትል ቆይታ በመዋሏ ደክሟት ከመሸ እራት ለማብሰል ትጣደፍ ጀመር፡፡ ባለቤቷና ሦስቱ ልጆቿ ግን ካለወትሮው እራት በመዘግየቱ ቢርባቸውም ችለው እየጠበቁ ነው፡፡ በመጨረሻም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሽሮ ወጥ በስሎ ከጉልቻው ወረደ፡፡ ሽሮው ትኩስ በመሆኑ ቶሎም እንዲበርድ ብላ የድስቱን ክዳን ከፍታ መሬት ላይ ሽሮው እንዲበርድ ከፍታ ተወችው፡፡

መለስ ብላ ፊቷን ወደ ሌማቱ በማዞር እንጀራ በገበታ እያዘጋጀች ባለችበት ጊዜ ከቅጽበት ከውጪ ስትንደረደር የገባች እንቁራሪት፤ ዘላ እንዲበርድ የተከፈተው ድስት ውስጥ ጥልቅ ትላለች፡፡ ጉዷን የማታውቀው እናት ገበታውን አሰናድታ በጉጉት የሚጠብቋት ባለቤቷና ሦስት ልጆቿ ፊት እንጀራውን በትሪ ታቀርባለች፡፡ በቤተሰቡ ከምግብ በፊት የመጸለይ ልማድ ስለነበራቸው ሁሉም ተነስቶ ይፀልዩ ጀመር፡፡ ልክ አባትየው ምግቡን ባርኮ ቁጭ ሲል፤ እንቁራሪቷ ከድስቱ ዘላ የእንጀራው ትሪ ላይ ዱብ ስትል አንድ ሆነ፡፡ ሁሉም ተደናገጡ፤ እናት እሪታዋን ለቀቀች/ ጮህች፣ ልጆች ሲዘሉ ሽሮው ተደፋ፡፡ ያልታሰበ አስደንጋጭ ትርኢት ሆነ፡፡ ከዚያም ትልቁ ልጅ ቀስ ብሎ እንቁራሪቷን አንስቶ ከበር አውጥቶ ጣላት፡፡ እናትየው ክው እንዳለች ቀረች፤ እንዴት ሆኖ ወጡ ውስጥ እንቁራሪቷ እንደገባች ሊገባት አልቻለም ነበር፤ ወዲያው ነገሩ ተገለጠላት፡፡ ሽሮው እንዲበርድ ብላ ድስቱን ክፍት አድርጋው እንደነበር አስታወሰች፡፡ ሁሉም በተፈጠረው ነገር መሳቅ ጀመሩ፡፡

ልጆቹ እርቧቸው ስለነበረ የተረፈውን ሽሮ መብላት ፈለጉ፤ አባታቸው ግን አይሆንም አለ፤ የምግብ መመረዝ ሊያስከትል እንደሚችል በመረዳቱም ልጆቹ እንዳይበሉ ከለከላቸው፡፡ ያም ሆኖ ሁሉም በነገሩ ስቆ ሳይጨርስ እናትየው ወዲያው ቆንጆ ፍርፍር አደረሰችላቸው፡፡ ይሄ ታሪክ ሁልጊዜ ባስታወስኩት ቁጥር ያስቀኛል፡፡ (ሙላት በትንሹ ሲስቅ ይሰማል)፡፡

እቴ ብርቱካን፡-(እየሳቀች) አመሰግናለሁ ሙላት! ያካፈልከን ታሪክ አስቂኝ ቢሆንም አንድ የሚያስተምረን ነገር አለ፡፡ እናትየው እየተጣደፈች ድስቱን ክፍት በማድረጓ እንዳጋጣሚ ሆኖ እንቁራሪት ሆነች እንጂ በደንብ የማይታዩ ጥቃቅን ነፍሳት ወይም ዝንብ ቢሆኑ ኖሮ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ስለዚህ ምግብ ማዘጋጀት እና በአግባቡ በንጽህና ማቆየት ከአንድ ሺህ ቀናት ስርዐተ ምግብ ትምህርታችን አንዱ መሆኑን መረዳት አለብን፡፡

Page 15: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

15

በድሮ ጊዜ ሰዎች ከቦታ ወደ ቦታ፤ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ሲጓዙ ረጅም ጊዜ ስለሚወስድባቸው ስንቅ ይዘው ይጓዙ ነበር፡፡ ስለዚህም የሚይዙትን ስንቅ ማዘጋጀትና ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ ማቆየት የሚያስችል ብልሃት ነበራቸው፡ ፡ በተለያየ ምክንያት ኮከብ ምግቦችን በፈለግነው ሰዓት ማግኘት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ስለዚህም በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ በየእለቱ እንድናገኝ ምግባችንን በደንብ ማዘጋጀት፣ ሳይበላሽ በንጽህና መጠበቅና ማቆየት የሚያስችለንን ብልሃት መማር /ማወቅ ያስፈልገናል ማለት ነው፡፡ በቀጣዩ የውይይት ክፍለጊዜያችን እነዚህን አንዳንድ ብልሃቶች እንማራለን፡፡

ማረፍ ማገዝና መብላት

እቴ ብርቱካን፡-እስካሁን የተነጋገርንባቸውን ማለትም የተጠመጣጠነ ምግብ አርብተንም ዘርተንም፤ ሸጠንም ገዝተንም፤ በንጽህና አብስለን እና ሳይበላሽ እንዲቆይም አድርገን፤ ጣጣውን ጨርሰን ስናበቃ፤ ነፍሰጡር ወይም የሚያጠቡ እናቶች በቀን በቂ ኮከብ ምግቦችን ላይመገቡ ይችላሉ፡፡

እዚህ ላይ ማስታወስ ያለባችሁ ነገር አንድ ነፍሰጡር ሴት ሆድዋ ውስጥ ፅንስ ማለትም ዘር ስላለ እንዲሁም አጥቢ እናቶች ጨቅላ ህፃን ወይም ችግኝ ልጅ ስለሚያጠቡ ለሁለት ነው የሚበሉት ማለትም ለራሳቸውና ለልጃቸው ማለት ነው፡ ፡ የጤና ባለሞያ እንደመሆኔ መጠን አንዱ ስራዬ፤ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች ተጨማሪ ምግብ እንዲበሉ ማስተማር ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ቤት ለቤት በመዘዋወር እንዲሁም ጤና ጣቢያ የሚመጡትን ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ተጨማሪ ምግብ እንዲበሉ የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡ ብዙ ጥረት ብናደርግም ብዙ ሴቶች ግን ተጨማሪ ምግብ አይመገቡም፡፡ ጥቅሙ ሳይገባቸው ቀርቶ ወይም የኛን የባለሞያዎችን ምክር ሳይሰሙ ቀርተው አይደለም፤ ተጨማሪ ምግብ መመገብ ለምን እንደሚጠቅም በደንብ ያውቃሉ፡፡ ምንአልባት ላለመመገባቸው የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

መቼም ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት አንድ እናት በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወቅት የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ ስሜት ይሰማታል፡፡ እንዲያውም ይሄ ምልክት ብዙ ሴቶች ማርገዛቸውን የሚለዩበት ነው፡፡ ወዲያውም የተወሰነ ምግብ እና ሽታ መጥላት እንጀምራለን፡፡ አንዳንድ እናቶች ደግሞ በእርግዝና ወራታቸው መገባደጃ ልጁ ትልቅ ሆኖ በምጥ ጊዜ ለመውለድ እንዳንቸገር በሚል ስጋት ሆነ ብለው በቂ ምግብ አይመገቡም፡፡ አንዳንድ ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እየራባቸውም ቢሆን እራስ ወዳድና ስግብግብ መስሎ ላለመታየት ሲሉ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ በበቂ አይመገቡም፡፡

ሌሎቹ እናቶች ደግሞ ለባሎቻቸውና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ቅድሚያ በመስጠት ተገቢውን ምግብ አይመገቡም፡፡ ብቻቸውን ቤት በሚውሉበት ጊዜም አይመገቡም ምክንያቱም አንዲት ሴት ብቻዋን መብላት በሀገራችን ባህል እንደነውር ስለሚታይ ነው፡፡ አንዳንድ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ስራ ስለሚበዛባቸው እራሳቸውንና

Page 16: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

16

ህፃናቶችንም ለመመገብ ወይም ለማጥባት በቂ ጊዜ የላቸውም፡፡ እነዚህ እናቶች የቤት ውስጥ እና የእርሻ ስራ ላይ ተጠምደው ስለሚውሉ ለራሳቸው ለመብላት፣ በበቂ ሁኔታ ለማረፍና ህጻናት ልጆቻቸውን ለመመገብ በቂ ጊዜ የላቸውም፡፡ እንደሰማችሁት አንዳንድ ጊዜ እናቶች ተጨማሪ ምግብ እንዲበሉ ማድረረግ አስቸጋሪ ነው፡፡

እነዚህ ችግሮች ነፈሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው በየቀኑ የሚያጋጥሟቸው እውነተኛ ችግሮች ናቸው፡፡ ቤተሰቦቻችን እነዚህን ችግሮች እንድንወጣ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በቀጣይ ውይይት ክፍለጊዚያችን እንወያይባቸዋለን እንዴትም ችግሮቹን መቅረፍ እንደምንችል ትምህርት እንማራለን፡፡

አስረኛውንና የመጨረሻውን የውይይት ክፈለጊዜያችንን ስናጠናቅቅ ሁላችንም የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ፤ ገንቢና በአይነቱ የተለያየ የምግብን ጥቅም በመገንዘብ፤ ጤናማ፣ ጠናካራና ብሩህ የሆኑ ህጻናትን ማሳደግ የሚያስችለን በቂ ችሎታና ክህሎት እንደሚኖረን እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለው፡፡ የተናገርኩት ጥሩ ዜና አይመስለችሁም?

አያ ሙላት፡- በጣም እንጂ፤ እስኪ በጭብጨባ እንግለፀው፡፡

SFX: ሁሉም ያጨበጭባሉ፤ የጭብጨባ ድምጽ ይሰማል

መወያየትና በጋራ መወሰን

እቴ ብርቱካን፡-ወዳጆቼ አንድ ጥያቄ አለኝ፤ እስቲ በእናንተ አስተያየት ለህጻናት እና ለእናቶች ጠቃሚውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚረዳ ብቸኛው መንገድ ወይም ዘዴ ምን ይመስላችኋል? እስቲ ወደመልሱ ሊያቀርበን የሚችል አንድ ጨዋታ እንጫወት፤ በነገራችን ላይ ይህ ጨዋታ የምንነጋርባቸውን አንዳንድ ጉዳዮች በቀላሉ እንዲገባን ስለሚረዳን እወደዋለሁ፡፡ ይሄ ጨዋታ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእንቆቅልሽ ጨዋታ ማለትም የሚገጣጠሙ ካርዶች ያሉት ማለት ነው እንደምትወዱት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የጨዋታው ህግ እንደዚህ ነው፡፡ አስተባበሪ እባክዎን ተሳታፊዎች በሦስት ቡድን እንዲከፈሉ ያደርጉ፤ ለእያንዳንዱ ቡድን የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት የእንቆቅልሽ ጨዋታ ይስጧቸው፡፡ የጨዋታው አላማ እያንዳንዱ ቡድን የተሰጡትን ካርዶች በአግባቡ እየገጣጠመ አንድ የተሟላ ምስል ማግኘት ነው፡፡ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ አስተባባሪ እባክዎ እየተዘዋወሩ ያስረዱ፡፡ ስትጨርሱ እንደ ቀድሞው አቀማመጣችሁ አንድላይ በሰፊው ተቀመጡ፡፡ አስተባባሪ እያንዳንዱ ቡድን ለሌላው ቡድን አባላት ከጨዋታው ምን እንደተማረ እንዲያስረዳ ይርዷቸው፤ በሚያስረዱበትም ጊዜ የሚከተሉትን ነጥቦች ወይም ጥያቄዌዎች ለውይይት መነሻ እንዲሆኑ እባክዎ በማስተባበር ይርዷቸው፡፡

• ካርዶቹን በመገጣጠም ምን ተማራችሁ?

Page 17: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

17

• ስለ ሱፍ አበባ እድገት ደረጃ የተያያዘ ነገር አገኛችሁበት?

አስተባባሪ የእንቆቅልሽ ጨዋታው እስኪያልቅ ድረስ ቴፑን ያጥፉት፡፡ ጨዋታውን እና ውይይታችሁን ስትጨርሱ ከኔ ጋር መልሰን እንገናኛለን፡፡ ስትጨርሱ አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይክፈቱት፡፡

የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ! መቼም ሁላችሁም የአንድ ሺህ ቀናት የእንቆቅልሽ ጨዋታውን እንደወደዳችሁት ተስፋ አለኝ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ከጨዋታው የቀሰምነው አንድ ትልቅ ቁም ነገር፤ የሱፍ አበባ ብለን ከሰየምነው የአንድ ህጻን ልጅ የእድገት ደረጃ፤ ከጽንስ ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያለው የእድገት ደረጃ እና ያላቸውን ዝምድና በደንብ አስተምሮናል ብዬ አስባለሁ፡፡ በተጨማሪም ይሄ ጨዋታ፤ ለህጻናት እና ለእናቶች ጠቃሚውን የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚረዳ ብቸኛው መንገድ ወይም ዘዴ ምንድነው? ለሚለውም ጥያቄ መልስ እንድናገኝ አስችሎናል፡፡ ለማንኛውም መልሱ፡-

• በጨዋታው የተማርነው አንድ ትልቅ ቁም ነገር የቤተሰብ አንድነትን አስፈላጊነት ነው፡፡ ሁሉም የቤተሰብ አባላት ለእናትና ለህፃኑ በመጀመሪያው አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በመርዳት ትልቅ አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላሉ፡፡

• እናንተ ቤተሰብ ውስጥ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል? ህጻናት እና እናቶች በአንድ ሺህ ቀናቱ ውስጥ የተመጣጠኑ ምግቦችን እንዲያገኙ መተጋገዝ አለ? ከሌለስ እንዴት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል?

እናቶች፣ አባቶች፣ ሴት አያቶች እና የቅርብ ዘመዶች ለዘር፣ ችግኝ፣ እምቡጥ እና አበባ ልጆች እድገትና ብልፅግና ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ካለ ቤተሰብ ድጋፍ የእናቶችና የህፃናት በቂ ኮከብ ምግቦችን የማግኘትና በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺ ቀናት በቂ እርዳታ እንዲያገኙ ማድረግ አስቸጋሪ ነው

በቀጣዮቹ የውይይት ክፍለጊዜዎች ከላይ የዘረዘርናቸው የቤተሰብ አባላት እያንዳንዳቸው ምን አይነት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ እንደሚችሉና ስለተመጣጠነ ምግብ ከቤተሰባችን ጋር እንዴት መወያየት እንዳለብን በዝርዝር እንማራለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከባለቤታችን ጋር በግልጽ ለመወያትና ስለተመጣጠነ ምግብ ተገቢውን ውሳኔ እድንሰጥ የሚረዳንን ክህሎት እንማራለን፡፡ አዎ እነዚህ ነገሮች ጤናማ፣ ጠናካራ፣ እና ብሩህ ልጆች እንዲኖሩን የሚጠቅሙን ወሳኝ ቁም ነገሮች ናቸው፡፡

እንግዲህ እስካሁን ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስለተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊነትና ተገቢነት የተነጋገርነው ሁሉ ፍሬ እንዲያፈራ እና እንዲሳካ፤ የባልና ሚስት መግባባትና ግልፅ የሆነ ውይይት ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ቀደም ብዬ እንደነገርኳችሁ በእኔና በሙላት እንዲሁም በቤተሰባችን መካከል ጤናማ፤ መተሳሰብ ያለበት ነፃ ውይይት ስለነበረ ምን ያህል እኔና ልጆቼን እንደረዳን የእኔን ቤተሰብ ምሳሌ ልትወስዱ ትችላላችሁ፡፡ በነጻነት መነጋገርና መግባባት ለሁላችንም

Page 18: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

18

ቤተሰብ ይጠቅማል፡፡ በሚቀጥሉት የውይይት ክፍለጊዜያት፤ እኔና ሙላት እንዴት በባልና ሚስት ከዛም አልፎ በቤተሰብ ውስጥ በሚደረጉ ነፃ ውይይቶች ውሳኔ ላይ እንዴት እንደምትደርሱ ልምዳችንን እናካፍላችኋለን፡፡ ከልምዳችንም ተምራችሁ ጤናማ፤ ብሩህ እና ስኬታማ ህይወት ያላቸው ልጆች እንደምታፈሩ ታረጋግጣላችሁ፡፡

ጠይቁና አግኙ

አያ ሙላት፡- እንግዲህ በዚህ በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜ ብዙ ቁም ነገሮችን የተማማርን ይመስለኛል፡፡ የዛሬውን ክፍለጊዜያችንን ከማጠናቀቃችን በፊት ግን፤ እስካሁን ከተማርነውና ከተወያየንባቸው ነጥቦች ውስጥ መጠየቅ የምትፈልጉት ነገር ወይም ግልጽ ሆኖ ያልተረዳችሁት ነገር ካለ እንድትጠይቁ እጋብዛለሁ፡፡ ወዳጄ አስተባባሪ ጥያቄያችሁን ለመመለስ ይሞክራል፤ ካልሆነም በቀጣዩ የውይይት ክፍለጊዜያችን መልሶቹን አዘጋጅተን ለመመለስ እንሞክራለን፡፡

አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉትና ጥያቄዎች ካሉ ተነጋገሩባቸው፤ ምናልባትም ከተሳታፊዎች መካከል ለጥያቄዎቹ መልስ መስጠት የሚፈልጉ ስለሚኖሩ ለእነሱም እድል ይስጧቸው፡፡ ጥያቄዎቹን ተወያይታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ መልሰን እንገናኛለን፡፡

የደውል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- ጥሩ የጥያቄና መልስ ውይይት ጊዜ እንደነበራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በቀጣዮቹ

የውይይት ክፍለጊዜያችን በርካታ ቁምነገሮችን እንደምንማማር እምነቴ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ዛሬ በተቻለ አቅም ብዙ ነገሮችን ተምረናል/ ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ በአንድ ቀን መቼም ሁሉን ነገር መጨበጥ ቢያስቸግርም፤ ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተማማርነውን ፍሬ ነገር እንደማትረሱ ተስፋ አለኝ፡፡ እስቲ ዋና ዋናዎቹን ፍሬ ሃሳቦች መልሰን አብረን ለመከለስ እንሞክር፡፡ ሙላት ምን ይመስልሃል?

አያ ሙላት፡- ጥሩ ሃሳብ ነው፤ ከተማርንባቸው ነጥቦች አንዱ፤ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት፤ማለትም አንድ ህጻን ከተጸነሰበት እለት ጀምሮ ሁለት ዓመት እስከሚሞላው ያለውን ጊዜ፤ በሱፍ አበባ መስለን (ዘር፣ችግኝ፣ እምቡጥ እና አበባ) ለነፍሰጡር እናት እና ለአንድ ህጻን ጤና ብሎም የተስተካከለ እድገት ስርዐተ ምግብ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተምረናል፡፡

ሁለተኛው ፍሬ ነገር፤ስለ ጉልቻ የተማርነው ነው፡፡ የእንጀራ ምጣዱ የዘወትር ምግቦችን በምሳሌነት ይወክላል፡፡ የዘወትር ምግቦች የምንላቸው ምግቦች በየእለቱ አዘውትረን የምንመገባቸውን ምግቦች ሲሆን በጉልቻ የመሰልናቸውን ኮከብ ምግቦችንና አይነታቸውንም ተምረናል፡፡ ቀይ አምድ ከአንሰሳት ተዋጽኦ የምናገኛቸው የምግብ አይነቶች ሲሆኑ

Page 19: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

19

ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች ይባላሉ፡፡ ጉልቻው ስር የምታዩት አረንጓዴው አምድ ቅጠላቅጠል / አትክልት ባለሁለት ኮከብ ምግቦችን ይወክላል፡፡ የጉልቻው ቢጫው አምድ ፍራፍሬን የሚወክል ሲሆን ባለሁለት ኮኮብ ምግብ ይባላል፡፡ ለልጆች ስርዐተ ምግብ ግን ሶስቱ አምዶች አንደኛው ቀዩ አምድ የእንሰሳት ተዋፅኦ ባለ ሶስት ኮከብ ምግቦችን ሲወክል፤ አረንጓዴው አምድ ደግሞ አትክልትና ፍራፍሬን ባለ ሁለት ምግቦችን ይወክላል ሶስተኛው ቢጫው አምድ ቅባትና ዘይትን ማለትም ባለ አንድ ኮከብ ምግቦችን ይወክላል፡፡

ነፍሰጡር እና የምታጠባ እናት እንዲሁም ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህጻናት በየእለቱ ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ ማድረግ የምንችልባቸው ዘዴዎች፤

አንድ፡- ኮኮብ ምግቦችን ማርባትና ማብቀል

ሁለት፡- ከእርሻ/ከግብርና ከምናገኘው ገንዘብ ላይ ኮኮብ ምግቦችን ከገበያ ገዝቶ ማቅረብ

ሦስት፡- ኮኮብ ምግቦችን ማዘጋጀትና ሳይበላሹ እንዲቆዩ ማድረግ

አራት፡- ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች በቂ እረፍት እንዲያገኙና ተጨማሪ ምግብ እንዲመገቡ መርዳት

አምስት፡- ከሁሉም በላይ ደግሞ የእናቶችና የህጻናት የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብን በተመለከተ በተለይም ባልና ሚስት በመመካከር የጋራ ውሳኔ ማድረግ እንዳለባቸው ተምረናል፡፡

ወደ ቤት የሚወሰድ ቁሳቁሶችና የቤት ሥራዎች

አያ ሙላት፡- አዎ የባልና ሚስት ውይይትና ስምምነት በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ከዛሬ ጀምሮ መወያየት አለባቸው

በዚህ በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜያችን የተማርነውን ለማስታወስ እንዲረዱን እቤታችሁ የምትወስዷቸውን ማስታወሻዎች አዘጋጅተናል፤ እቤትም ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ እቅድ እንደምትነጋገሩ፣ እንደምትወያዩና ያወቃችሁትንም እንደምታካፍሉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብ እቅድን/ ትምህርት የሚያስታውሱ ስእላዊ መግለጫ የያዘ የቁልፍ መያዣ ካርድና እና የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ግድግዳ ላይ የሚሰቀል ፖስተር ይወስዳሉ፡፡

አስተባባሪ እባክዎን ያከፋፍሏቸው እና ስለ አጠቃቀማቸው ያስረዷቸው፡፡ እስቲ ትንሽ ጊዜ ወስዳችሁ አሳዩዋቸው፡፡

የደውል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! የቁልፍ መያዣ ካርድ እና ፖስተሩን አያችኋቸው? እንዳያችኋቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ቤት ስትሄዱም ለባለቤታችሁ፤ ለቤተሰባችሁና ለጓደኞቻችሁ እንደምታሳዩ እና እንደምትማሩባቸው፤ በተለይም ቁልፍ መያዣው ላይ ያሉ ምስሎች የአራቱን የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃና በመጀመሪያው አንድ

Page 20: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

20

ሺ ቀናት የእናቶትና የህፃናት ስርዐተ ምግብን ለማስታወስ እንደ ዘር፤ ችግኝ፤ እምቡጥና፤ አበባ ምሳሌ ተቀምጠዋል፡፡ በነገራችን ላይ ፖስተሩን ግድግዳ ላይ ለጥፉት፡፡ ሌላው መርሳት የሌለባችሁ፤ ነፍሰጡር እና የምታጠባ እናት እንዲሁም ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ያሉ ህጻናት ኮከብ ምግቦችን በየእለቱ መመገብ እንዳለባቸው መዘንጋት የለባችሁም፡፡

የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር ይጀምራል

እቴ ብርቱካን፡-ይህን ዜማ የማውቀው መሰለኝ፤ አዎ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር ነው፡፡ ይህን የመጀመሪውን የውይይት ክፍለጊዚያችንን በዚህ ባማረ መዝሙር ብንጨርሰዉ፤ ምን ይመስላችኋል?

መዝጊያ

አያ ሙላት፡- በጣም ጥሩ፤ከመለያየታችን በፊት፤ ሁላችንም አንድ ላይ በድጋሚ እንዘምረው፡፡

የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር ይሰማል

አያ ሙላት፡- ደስ ሲል! ብርቱካን እዚህ ላይ ብናበቃ ምን ይመስልሻል?

እቴ ብርቱካን፡-በጣም ጥሩ፤ እንግዲህ በዚህ በመጀመሪያው ክፍለጊዜያችን ብዙ ቁምነገሮችን ተምረናል፤ በጣም ደስ ብሎኛል! የሚቀጥለውና ሁለተኛው ክፍለጊዜያችን እስከምንገናኝ በጣም ጓጉቻለሁ፡፡

አያ ሙላት፡- ቀጣዩ ክፍለጊዜያችን መቼ እንደሚሆን አሰተባባሪ እባክዎ ለተሳታፊዎች ይንገሯቸው፡፡ እስከዚያው ደህና ሁኑ፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ደህና ሁኑ፡፡

Page 21: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

21

Page 22: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 23: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

23

መግቢያ

እቴ ብርቱካን፡-ጤና ይስጥልኝ፤ እንደምን ሰነበታችሁ? ለሁለተኛው የመማማሪያ ክፍለጊዜያችን እንኳን በደህና መጣችሁ!

አቶ ቢራራ መለሰ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስርዐተ ምግብ ቡድን መሪ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ሲናገሩ እንዳደመጣችሁት፤ የብሄራዊ የእናቶች ምግብ አለመጣጠንና የህጻናት መቀንጨር ትልቅ የሀገር ችግር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በዚህም ዙሪያ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎች አዘጋጅተናል፤ በእነዚህ ክፍለጊዜዎች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናትና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋናና ቁልፍ የሆኑ ትምህርቶችን እንማራለን፡፡ የዚህ ትምህርታዊ ውይይት ዋናው ዓላማ፤ በቂ እውቀትና ክህሎት ገብይታችሁ፤ ጠንካራ፣ ጤናማ እና ብሩህ ህጻናት አሳድጋችሁ ለቁምነገር እንዲበቁ ማድረግ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ብርቱካን እባላለሁ። በሚኖሩን የውይይት ክፍለጊዜያት በርቀት ሆኜ እመራለሁ። በቆይታችን አንዳንድ ጊዜ የእኔን ድምፅ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የባለቤቴን የሙላትን ድምጽ ትሰማላችሁ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ቀጥታ ከናንተ ጋር ያሉትን አስተባባሪ ትሰማላችሁ፤ እየተቀያየርንና እየተተካካን የትምህርት ክፍለጊዜውን እንመራለን። በየመሃሉም ለሚኖራችሁ ውይይት አስተባባሪ ቴፑን በመዝጋት እንድትወያዩና የቡድን ስራ እንድትሰሩ ይረዷችኋል። ይሄን የደውል ድምጽ ስትሰሙ (የደውል ድምጽ ይሰማል) ቴፑ ይጠፋል ማለት ነው። የምትሰሩት የቡድን ስራ ወይም ውይይት ሲያበቃ ቴፑ ይከፈትና እኔና ሙላት ካቆምንበት እንቀጥላለን ማለት ነው።

እስቲ እንሞክረው! ‹ኪኪልልል› የሚለውን የደወል ድምጽ ስንሰማ አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉትና ከርስዎ ጀምሮ ሁሉም ሰው እራሱን አስተዋወቆ ሲጨርስ፤ እባክዎን መልሰው እንደገና ቴፑን ይክፈቱት።

የደውል ድምጽ (ይሰማል)

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን በደህና መጣችሁ! ሁላችሁም በደንብ እንደተዋወቃችሁተስፋ አደርጋለሁ። የዛሬውን ውይይት ከመጀመራችን በፊት ባለፈው ክፍለጊዜ የተነጋገርንባቸውን ጉዳዮች እስኪ አንዴ ደግመን እንመልከታቸው።

በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ ልጆቻችን ጠንካራ፤ ጤናማና ብሩህ እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብን እንደምታስታውሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለመሆኑ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስንል ምን ማለታችን ነው? ማነው ሊነግረን የሚችለው? ስንቶቻችሁ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎችን ማለትም ዘር፤ ችግኝ፤ እምቡጥና አበባን ታስታውሳላችሁ።

አስተባባሪ፤ እባክዎ ለማስተማሪያ የተዘጋጀውን የሱፍ አበባ ደረጃዎች ምስል ለሁሉም ያሳዩ፤ እስኪ እነዚህን አራቱን የእድገት ደረጃዎች በየተራ እየተነሳችሁ ለማስረዳት ሞክሩ። ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: ደወል

Page 24: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

24

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ፤ ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ጥሩ ውይይት እንዳደረጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ እንግዲህ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የምንለው ከፅንስ ጀምሮ አንድ ህፃን ሁለት ዓመት እስከሚሞላው ድረስ ያለውን ጊዜ ነው።

የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት አራት የሱፍ አበባ እድገት ደረጃዎች ያላቸው ሲሆን እነሱም ዘር፣ችግኝ፣ እምቡጥ እና አበባ ይባላሉ። በእነዚህም የእድገት ደረጃዎች ማንም ቤተሰብ ሀብታምም ይሁን ደሃ፤ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ ህጻናትና እናቶችን የተመጣጠነ፤ የተለያየ ምግብ እንዲያገኙ ማገዝ ይችላል። የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት በጣም ወሳኝ ጊዜያት ናቸው፤ ልጆቻችን ጤናማ እድገትና ጥሩ ህይወት እንዲኖራቸው ጥሩ መሰረት የምንጥልበት ወርቃማ እድል ነው። በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜያችን የአንድ ሺህቀናትን መዝሙርን አዳምጠናል፤ አብረንም ዘምረናል። ለባለቤታችሁና እቤት ላሉት ቤተሰቦቻችሁም መዝሙርን እንዳስተማራችኋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።

አስተባባሪ እስኪ ለእነዚህ ጥያቄዎች ስንቶቻቸው እጃቸውን እንዳወጡ መዝግቡ

• የአንድ ሺህ ቀናት መዝሙርን እቤት ስንቶቻችሁ ዘመራችሁ?

• የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ቁልፍ መያዣ ካርድ እና የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት ፖስተርስ ስንቶቻችሁ ለባለቤታችሁና ለቤተሰብ አባላት አሳያችሁ፤ ቁልፍ መያዣውንስ አሳያችኋቸው? ።

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ፖስትርን እቤታችሁ ግድግዳ ላይ የለጠፋችሁ?

እቴ ብርቱካን፡-አመሰግናለሁ! እስኪ አሁን ደግሞ ትንሽ ጊዜ ወስዳችሁ እቤታችሁ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያጋጠማችሁን ሁኔታ ተወያዩበት። እነዚህ ጥያቄዎች ለውይይታችሁ መነሻ ሊረዷችሁ ይችላሉ፡ ይሄ በቤታችሁ ውስጥ ስለተካሄደው ወይይት መረጃ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ አስተባባሪ መረጃዎቹን ሪፖርት ቅፁ ላይ መዝግበው ይያዙ። ።

• አንደኛ፤ መቼም ሁላችሁም ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የተማራችሁትን ጥሩ ዜናና መልካም ትምህርቶች ለቤተዘመዶቻችሁ እንዳካፈላችሁ፤ የወሰዳችኋቸውንም የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች እንዳሳያችኋቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ለመሆኑ ስለተማራችሁት ትምህርት ስትነግሯቸው ምን አሉ?

• ሁለተኛ፤ ለቤተሰቦቻችሁ ስለአራቱ የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎች ስታስረዷቸው እንዴት ተቀበሉት? ዋናው ፍሬ ነገሩስ ገባቸው ወይስ ያልገባቸው ነገር ነበር?

• ሦስተኛ፤ የአንድ ሺህ ቀናት የእናቶች እና የህጻናት ስርዐተ ምግብ እቅድን ማለትም የተመጣጠነ ምግብ አጠቃቀምን በቤታችሁ ለማሻሻል ከቤተሰባችሁ ጋር ወሰናችሁ?

እስኪ ሁላችሁም በቤታችሁ የገጠማችሁን እነዚህን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ተወያዩበት፤ አስተባባሪ እባክዎ ቴፑን ይዝጉትና በጥያቄዎቹ ላይ እንዲወያዩ ያግዟቸው። ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት

Page 25: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

25

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን በደህና መጣችሁ፤ አንዳንዶቻችሁ ስለ አንድ ሺህ ቀናት ቤታችሁ ውይይት ስታደርጉ አንዳንድ ችግሮች ገጥሟችሁ ይሆናል፤ ለችግሮቹም አሁን ካደረጋችሁት ውይይት ወይም ከአስተባባሪ መፍትሄ አግኝታችሁ ይሆናል። ግን ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ካላገኛችሁ አስተባበሪ በቀጣዩ የውይይት ክፍለጊዜያችን መልሶቹን አዘጋጅተው ይጠብቋችኋል።

የዛሬው ሁለተኛው የውይይት ርእሰ ነገር ዘር ብለን የምንጠራው የእድገት ደረጃ ነው። ይሄም በእናት ማህፀን የሚገኘው ፅንስ ማለት ነው፡፡ ይሄ ዘር ጤናማ፣ ጠናካራ እና ብሩህ ህጻን ሆኖ እንዲያድግ ነፍሰጡር እናትና ቤተሰብ ምን ምን ማድረግ እንዳለበት እንማራለን።

በእርግዝና ወቅት፤ ነፍሰጡር እናት የምትመገበው ለሁለት ሰው ነው። ይህም ማለት ለራሷም በሆዷ ላለው ጽንስም ጭምር ነው። ቀደም ሲል በክፍል አንድ የውይይት ጊዜያችን ኮከብ ምግቦች ብለን በጠቀስናቸው ምግቦች ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ነፍሰጡር እናቲቱም በማህጸኗ ያለውን ጽንስም ይገነባሉ ያጠነክራሉ ፤ አንዲት ነፍሰ ጡር እናት በቂና ተመጣጣኝ ምግብ ያልተመገበች እንደሆነ ግን ጤናዋ ያልተስተካከለ ደካማ ትሆናለች፤ በማህጸኗ የሚገኘውም ጽንስ የተሟላ እድገት አይኖረውም።

በእርግዝና ወቅት፤ ነፍሰጡር እናት የምትመገበው ለራሷ ብቻ ሳይሆን በሆዷ ላለው ጽንስም ጭምር መሆኑን ስላለው ጥቅም በዝርዝር ከመነጋገራችን በፊት፤ እስቲ ቀደም ሲል በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜ የሰማነውን የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙርን በከፊል አብረን እንስማው።

SFX: የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-የመዝሙሩን ግጥም በደንብ አዳመጣችሁት? በተለይ ስለ ዘር ማለትም እንዴት እናቶች ልዩ እንክብካቤና ድጋፍ በእርግዝና ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸውና ይሄም በማህፀኗ ላለው ዘር ማለትም ፅንስ ጤናማ እድገት እንዲኖረው ወሳኝ መሆኑን የመዝሙሩ መልእክት ያስታውሰናል። ቀደም ብለን እንዳልነው ነፍሰጡር ሴት ለሁለት ነው የምትበላው ማለትም ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለጽንሱም ጭምር ስለምትበላ የተመጣጠኑና ባለ ከኮከብ ምግቦች ጋር መመገቧ በጣም ወሳኝ ነው።

በነገራችን ላይ አንድ ነፍሰጡር እናት የሠውነት ክብደቷ በቂና የተመጣጠነ ምግብ መመገቧንና ያለመመገቧን አመላካች ነው፡፡ የነፍሰጡር ሴት ክብደት ከስታንዳርድ በታች ከሆነ በማህጻኗ ያለው ህጻን በቂና የተመጣጠነ ምግብ አያገኝም ማለት ነው። በተጨማሪም ክብደቷ ከስታንዳርድ በታች የሆነች ነፍሰጡር ሴት ጊዜው ያልደረሰ ህጻን የመውለድ እድሏ ከፍ ያለ ነው።ይህም አስፈላጊውን ጊዜ በእናቱ ማህፀን ሳይቆይ ለመወለድ ዝግጁ ያልሆነ ልጅ ትወልዳለች ማለት ነው። ።

እስቲ ነፍሰጡር ሴቶች የክብደታቸው ሁኔታ እንዴት እንደሆነ እንይ፤ በ2003 ዓ.ም

Page 26: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

26

በተደረገ የዴሞግራፊክ የጤና ጥናት፤ በሀገራችን

• ከ 4 ነፍሰጡር ሴቶች መካከል አንዷ የምግብ አለመመጣጠን ችግር አለባት

• ከ 6 ነፍሰጡር ሴቶች መካከል አንዷ የደም ማነስ ሲኖርባት፤ በእርግዝና ጊዜ ከ 6ቱ አንዷ ብቻ ነች የአይረን ኪኒን የምትወስደው

• ይሄ ለነፍሰጡር ሴቶች ጥሩ ዜና አይደለም፤ ማንኛዋም ነፍሰጡር እናት ክብደቷ ከስታንዳርድ በታች መሆን የለበትም፡፡

በእርግዝና ወቅት አንድ እናት የምትመገበው ለሁለት ሰው ስለሆነ ለእራሷና በሆዷ ላለው ዘር የተመጣጠነ ምግብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። ስለዚህ ነፍሰጡር እናት ሌላ ጊዜ ከምትመገበው ምግብ በዛ አድርጋ መመገብ አለባት። ምግቧ ላይም የምትጨምራቸውን ኮከብ ምግቦችንም እንደዚሁ ጨመር አድርጋ መመገብ ይኖርባታል።

በተጨማሪም ነፍሰ ጡር ሴቶች ከመደበኛው የገበታ ሰዓት በተጨማሪ ቀለል ያሉ ምግቦች ወይም መክሰሶችን እንዲሁም ኮከብ ምግቦችንም ጨመር አድርገው እንዲመገቡ በጣም ይመከራሉ። ይሁን እንጂ ነፍሰጡር እናቶችና ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ምክንያቶች ይሄን አያደርጉም። በዛሬው የውይይት ክፍለጊዜያችን ነፍሰጡር ሴቶችና ቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ምግብ እና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን የሚበሉት ምግብ ላይ የማይጨምሩበትን ዋና ዋና ምክንያቶችና ችግሮች እንመለከታለን። እነዚህንም ችግሮች እንዴት እንደምንወጣና ማሸነፍ እንደምንችል እንወያያለን።

ኤንጂን በሀገራችን ባደረገው ጥናት፤ ነፍሰጡር እናቶች ከተለመደው የምግብ ሠዐት ውጪ ተጨማሪ ምግብ ወይም የተሻለ የምግብ አይነት የማይመገቡበት ዋናው ምክንያት ሴቶች በባህላችን እራስ ወዳድ ላለመሆን፤ ከራሳቸው ይልቅ ቢርባቸው እንኳን ልጆቻቸውን፣ ባለቤታቸውን እና ሌሎችን የማስቀደም መስዋዕትነት ወይም ለሌላው መኖር ምክንያት ነው። ነፍሰጡር እናቶች ብቻቸውን መብላት፣ ከቤተሰብ የተለየ ወይም የተሻለ ምግብ መመገብ ወይም ለራሳቸው ጨመር አድርጎ መብላት ሆዳም የሚያስብል ትልቅ ነውር አድርገው እንዲያዩት ከባድ የባህል ተጽእኖ አለባቸው።

እስቲ ለዚህ ማስረጃ ይሆነን ዘንድ የተለያዩ አካባቢ የሚኖሩ ነፍሰጡሮች፣ አባወራዎች እና ሴት አያቶች በዚህ ሃሳብ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት/አመለካከት እንስማ።

(የተዋናዮች ድምጽ)

• በጭራሽ፤ እንዴት ያንን ልታደርግ ትችላለች፤ አትችልም። ለራሷ የሚሆን የተለየ ምግብ ማዘጋጀት አትችልም፤ ለዚያውስ ለእሷ የሚሆን ተጨማሪ ምግብ ከየት መጥቶ። የምትበላው ቤት ያፈራውንና ቤተሰቡ የሚበላውን ነው። ለሷ ለብቻዋ ምግብ ማዘጋጀት አስቸጋሪና የማይሆን ነገር ነው። (ሴት አያት፣ ከኦሮሚያ)

Page 27: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

27

• እንዲህ አይነት ነገር የለም፤ ለነፍሰጡር ብሎ የተለየ ምግብ ማዘጋጀት፤ ብቻዋን ከቤተሰቡ ተለይታ መመገብ የኢትዮጵያ ልማድ አይደለም። በባህላችንም የተለመደ ነገር አይደለም። ያለንን በጋራ ተካፍለን መብላት አለብን። እሷም አታደርገውም፤የሚበላ ነገር ብሰጣት ብቻዋን አትበላም። (አባወራ/ባል፤ ከትግራይ)

• በኛ አካባቢ ሚስቶች ከራሳቸው ይልቅ ባላቸውን ያስቀድማሉ። ወተተ ለባሎቻቸው ይሰጣሉ። እኔ በበኩሌ ግን ይሄንንን አልደግፍም ምክንያቱም ያለውን እውነት ስመለከት ሴቶቹ ተገቢውን እንክብካቤ አያገኙም። (አባወራ/ ባል፤ ከደቡብ)

• እኛ ወንዶች ለሚየጠቡ ሴቶቻችን ሳይንሱ ከሚያስተምረን በጣም ያነሰ ምግብ ነው የምንሰጣቸው። በቀን አራት ወይም አምስት ጊዜ የተለያየና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባቸው። ይህን ለማድረግ ግን ጊዜው የለም። ይሄ ደግሞ በተማረው የህብረተሰብ ክፍልም ያለ ነገር ነው። ገና አሁን በቅርቡ ነው ያውም በትንሹ ለሴቶቻችን ማሰብ የጀመርነው። (አባወራ/ባል፤ ኦሮሚያ)

እቴ ብርቱካን፡-አሁን ያዳመጣችሁት፤ በተለያየ ቦታ የሚኖሩ አባወራዎችና አያቶች በኤንጂን ጥናት ላይ ከተናገሩት በቀጥታ የተወሰደ ነው። ባዳመጣችሁት ጉዳይ ላይ የእናንተ አስተያየት ምንድን ነው? በዚህም ጉዳይ የገጠማችሁን ነገር እስኪ ተወያዩበት፤

እቴ ብርቱካን፡-አስተባባሪ እባክዎ ቴፑን ያጥፉትና በጋራ ተወያዩበት፤ እስኪ እነዚህን ጥያቄዎችም ለመመለስ ሞክሩ

• ከላይ ያዳመጣችኋቸው አይነት ችግሮች ወይም አስተሳሰቦች በእናንተ ቤተሰብ ውስጥ ገጥሙዋችሁ ያውቃሉ ?

• ከእናንተ መካከል የሴቶች መስዋዕትነት ወይም ለራስ አለመኖር በነፍሰጡር ሴቶች ላይ የሚያስከትለውን ችግር መፍትሄ አግኝታችሁ ለሁለት ሠው መብላት እንዳለባት ያደረጋችሁትን ተመክሯችሁን ለሌሎች እባካችሁ አካፍሉ።

• ከተሳታፊዎች መካከል በበቂ ሁኔታ ተጨማሪ ምግቦችን እና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን የምትመገብ ወይም በእርግዝናዋ ወራት የተመገበች ነፍሰጡር የሚያውቅ ካለ፤ እባክዎን ተመክሯችሁን ወይም ልምዳችሁን ለሌሎቹ አካፍሉ።

አስተባበሪ ፤ ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

(SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል)

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ! በውይይታችሁ ጥሩ ጥሩ ሃሳቦችንና ልምዶችን እንደተካፈላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ነፍሰ ጡር እናቶች ከራሳቸው በፊት ልጆቻቸውን፣ ባላቸውን እና ሌሎች የቤተሰብ አባላትን በማስቀደማቸውና በራባቸው ሰአት እንኳ ብቻቸውን መብላት ስለማይችሉባቸው ችግሮችና ምክንያቶች በበቂ ሁኔታ እንደተወያያችሁና ሃሳብ እንደተለዋወጣችሁ ተስፋ አድርጋለሁ።

Page 28: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

28

ድራማ

ቀደም ሲል እንዳልኩት ከደቂቃዎች በፊት የሰማችኋቸው በተለያየ ክልል እና አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች አስተያየቶች ነበሩ። መቼም ከእናንተ መካከል ተመሳሳይ አስተያየት ያላቸው ሰዎች እና ቤተሰቦች ሊኖሩዋችሁ እንደሚችሉ እገምታለው። በውይይታችሁ ወቅትም አንዳንዶቻችሁ እነዚህን ችግሮች በቤታችሁ እንዴት መፍታት እንደቻላችሁ ጠቃሚ ምክር እንዳካፈላችሁም ተስፋ አደርጋለሁ።

በሃገራችን ቤተሰብ በአንድ ገበታ ቀርቦ አብሮ የመብላት ባህል አለን። በተለይም እናቶች ከባልና ከልጆቻቸው ጋር በአንድ ገበታ ሲመገቡ ማየት ያስደስታቸዋል። ቤተሰብ በአንድ ማእድ/ገበታ የመመገቡ ልማድ የቤተሰብን ፍቅርና መቀራረብ የሚያጠናክር ከፍተኛ ማህበራዊ ፋይዳ ያለው መሆኑን እንገነዘባለን። እናቶች ከራሳቸው በፊት ባላቸውን፤ ልጆቻቸውን፣ እና ሌሎችን እንደሚያስቀድሙም ይታወቃል። ይሁን እንጂ እነዚህ ነገሮች ነፍሰጡር እናቶች ተጨማሪ ምግብና የተለየ ምግብ እንዳይመገቡ የሚያግዷቸው ምክንያቶች ሆነው ይታያሉ።

ቀደም ብለን እንደተነጋገርነው አንድ ነፍሰ ጡር ሴት ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ባለሶስት ኮከብ ምግብ መመገብ ይኖርባታል፤ ለዚህ ደግሞ የግድ የቤተሰብ ድጋፍ ያስፈልጋታል።

በተለይም ነፍሰጡር እናቶች የሚመገቡት ምግብ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን በማህጸናቸው ላለው ጽንስም ጭምር መሆኑን ምንጊዜም ቤተሰብ መረዳት ይኖርበታል። እናቲቱ ከምትመገበው የተመጣጠነ ምግብ በሚያገኘው ነው የጽንሱ /ዘሩ አካልና አዕምሮ እድገት የተሟላ የሚሆነው። ለዚህ ነው አንድ ነፍሰጡር የተመጣጠነ ምግብ በተመገበች ቁጥር የሚወለደውም ህጻን ጤናማ፣ ጠናካራና፣ አዕምሮው ብሩህ የሚሆነው እድሉም ከፍ እያለ የሚመጣው። ልክ መሬት ውስጥ እንደተዘራ ፍሬ ፤ ዘሩ/ፅንሱ በእንክብካቤና የሚያስፈልገውን ገንቢ ምግብ ካገኘ ወደ ሚቀጥለው ችግኝ የሚያድግልን።

ነፍሰጡር ሴት ከቤተሰብ ጋር ገበታ ስትቀርብ ተጨማሪ ምግብ መብላት ይኖርባታል። ከዚህም ውጪ መክሰስ መብላት አለባት። ይሄንንም እንድታደርግ የባሏና የቤተሰቦቿ ድጋፍ ያስፈልጋታል። እስካሁን ከላይ የተነጋገርንባቸውን ፍሬ ነገሮች የሚያጠናክር አጭር ድራማ እስቲ አብረን እንከታታል፤ ድራማው ነፍሰጡሯ አቻምና ቤተሰቧን ያስቃኘናል።

ውስጥ - አቶ በለጠ ቤት - ጠዋት

SFX: (የላሞች እምቧታ፤ የዶሮዎች አኩኩሉ ይሰማል) አቶ በለጠ፡- እንደምን አደርሽ አቻም፤ ዛሬ የጤና ጣቢያ ቀጠሮ አለብሽ መቼም አልረሳሽውም?

በይ እንዳናረፍድ በጊዜ እንሂድ።

አቻም፡- ኧረ እኔ አልረሳሁትም ። ይልቅ ከመሄዳችን በፊት ቁርስ ቅመስ፤ ቡናም ጠጣ

Page 29: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

29

በባዶ አፍ እንዴት ትወጣለህ በለጥዬ። ቀርቧል…

አቶ በለጠ፡- አይ አቻም የኔ ቁርስ ይደርሳል የት ይሄዳል፤ይልቅ በጠዋት ጸሀዩ ሳይከር ብንሄድ ይሻላል፤ እንዴ ወተቱን በሙሉ ለኔ ቀድተሽዋልና፤ ላንቺ የቀዳሽው የታለ? ለመሆኑ ከነጋ እህል ቀምሰሻል?

አቻም፡- እኔ እንደነገሩ ቀምሻለሁ፤ ይልቅ ጉረስና እንሂድ

አቶ በለጠ፡- ያንቺን ነገር መች አጣሁት አቻም፤ ይሄኔ ለልጆቹ ቁርስ ስትንደፋደፊ ለራስሽ ምንም አልቀመስሽም። ይሄን ሁሉ ወተት አልበሽ ብቻዬን ልጠጣው ነው፤ የማይሆነውን፤ በይ ነይ አብረን እንብላ፤ ያንን ኩባያም ወዲህ በይ ከወተቱ ላካፍልሽ።

አቻም፡- (በመሰልቸት ቃና የቀልድ ሳቅ እያለች ) በለጠዬ ገበታ በቀረበ ቁጥር እንዲያው እኔን እንደህጻን ልጅ ብዪ አትብዪ አይሰለችህም፤ ለምን አታምነኝም በላሁ አልኩህ እኮ።

አቶ በለጠ፡- አንቺን እኮ መንከባከብ ግዴታዬ ነው አቻም። አንቺ እኮ አሁን የምትበይው ላንቺ ብቻ አይደለም በሆድሽ ላለው ፅንስ ጭምር መሆኑን አትርሽ። ጠዋት የቀመሽ እንደሆን አሁን ደግሞ ከኔ ጋር ትንሽ ብትቀምሺ ይጠቅምሻል እንጂ አይጎዳሽም። በይ ነይ ቁጭ በይ፤ ፍርፍሩ ሳይበርድ እንጉረስ።

አቻም፡- እሺ በል ይሁን እቀምሳለሁ፤ መቼም አንተ ያልከው ካልሆነ ሰው አትለቅም።

አቶ በለጠ፡- ጎሽ የኔ ወርቅ፤ እንዲህ ነው እንጂ፤ በይ ያዥ… ጉረሽ…

SFX: (ቡና ሲቀዳ፤ ምግብ ሲበላ ድምጽ ይሰማል)

ትእይንት ክፍል 2

ውስጥ - ጤና ጣቢያ ተራ መጠበቂያ፤ ጠዋት

የሰዎች ድምጽ ይሰማል።

አቶ በለጠ፡- አቻም ዛሬ እድለኞች ነን ብዙም ሰው የለም፤ ቶሎ ከጨረስን እኔም ወደማሳዬ በጊዜ እሄዳለሁ።

አቻም፡- በለጥዬ እንዲያው ዝም ብለህ እኮ ነው ከእኔ ጋር እዚህ ቀጠሮ ባለኝ ቁጥር የምትለፋው፤ አንተ እኮ ስራ ፈታህ፤ እኔ ምን እሆናለሁ ብለህ ነው። እርግዝና ለኔ እኮ አዲስ ነገር አይደለም፤ የሁለት ልጆች እናት እኮ ነኝ በለጥዬ። ይልቅ ወደ ስራህ ሂድ

አቶ በለጠ፡- ኧረ እኔ አልሄድም። ምነካሽ አቻም፤ ለኔ እኮ እያንዳንዱ ልጅ ልክ እንደ አዲስ ነው፤ እኔ አብሬሽ ሆኜ በተቻለኝ መርዳቱ ነው የሚያስደስተኝ።

SFX: (የነርሷ ወደነሱ ስትቀርብ ኮቴ ይሰማል)

ነርስ፡- ወ/ሮ አቻም፤ እንደምን አደርሽ፤

Page 30: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

30

አቻም፡- ደህና እግዚያብሄር ይመስገን፤ ደህና ነሽ ሲስተር ሠናይት።

ነርስ፡- ደህና ነኝ ፤ በይ ነይ እኔን ተከተይኝ።

አቻም፡- እሺ ሲስተር።

አቶ በለጠ፡- ጎሽ፤ እኔ እዚሁ እጠብቅሻለሁ ሂጂ።

ትእይንት 3

ውስጥ - ነርስ ሠናይት የምርመራ ክፍል - ጠዋት ነርስ ሰናይት፡-አቻም ቀጠሮ ቀንሽን አክብረሽ በመምጣትሽ ደስ ብሎኛል ።

አቻም፡- እድሜ ለባለቤቴ ልቅር ብልም መች ያስቀረኛል። እሱ እዚህ በመጣሁ ቁጥር ከጎኔ መለየት አይፈልግም።

ነርስ ሰናይት፡-አቶ በለጠ ጥሩ ባል ናቸው ማለት ነው።

አቻም፡- ልክ ነሽ እኔም እድለኛ ነኝ እሱን በማግኘቴ።

ነርስ ሰናይት፡-እሺ ለመሆኑ ጤናሽን እንዴት ነሽ?

አቻም፡- አሁን በጣም ደህና ነኝ፤ የሚያቅለሸልሸኝና አልፎ አልፎ የሚያስመልሰኝም አሁን ትቶኛል።

ነርስ ሰናይት፡-ለመሆኑ የታዘዘልሽን አይረን ኪኒን ማታ ከመኝታ በፊት እየወሰድሽ ነው?

አቻም፡- አዎን እየወሰድኩ ነው፤ አላቋረጥኩም። እኔ ብረሳ ባለቤቴ ያስታውሰኛል፤ እሱ አይረሳም።

ነርስ ሰናይት፡-(እየሳቀች) አቶ በለጠ ጥሩ ባል ነው። ንግስት ንብን በጥሩ ሁኔታ እየተንከባከበ ነው። እኔ አሁን ሚዛንሽን እለካሻለሁ፤ ከዛ ደምሽንና ሌላ ነገሮች እለካለሁ፤ ሚዛኑ ላይ ቁሚልኝ….SFX: (ሚዛኑ ላይ ስትቆም ይሰማል ነርሷ ካርድ ስታገላብጥ፤ ስትጽፍ ደምጽ ይሰማል)

ነርስ ሰናይት፡-ቁጭ በይ፤(በስጋት ድምፅ) አቻም ባለፈው ጊዜ ከነበረው ክብደትሽ ብዙም አልጨመርሽም፤ አንቺ እኮ አሁን የአምስት ወር ነፍሰጡር ነሽ፤ ኪሎሽ ከዚህ ከፍ ማለት ነበረበት።

አቻም፡- እንጃ እኔ ምናውቃለሁ፤ ምናልባት በተፈጥሮዬ ቀጭን ስለሆንኩ ይሆናላ ብዙም ያልጨመርኩት።

ነርስ ሰናይት፡-አቻም በተፈጥሮሽ ቀጭን ስለሆንሽ አይደለም ክብደት ያልጨመርሽው። አንቺ ሆድ ውስጥ እኮ እያደገ የመጣ ፅንስ አለ፤ ስለዚህ አንቺም ክብደትሽ መጨመር ነበረበት፤ ግን አንቺ አልጨመርሽም፤ባለፈው ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ እንዴት መመገብ እንዳለብሽ ትምህርት ሰጥተንሽ ነበር፤ ለመሆኑ ታስታውሺዋለሽ ወ/ሮ አቻም?

አቻም፡- ከሞላ ጎደል አሳታውሳሁ፤ የምበላው ምግብ ላይም የነገራችሁኝን ኮከብ ምግቦች ጨምሬ ለመመገብ እሞክራለሁ።

ነርስ ሰናይት፡-ኮከብ ምግቦችን መመገብሽ ጥሩ አድርገሻል። የምትበይውን መጠንስ ከበፊቱ ጨምረሻል? መክሰስስ ትበያለሽ?

Page 31: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

31

አቻም፡- እሱን እንኳን አላደረኩም፤ ሀሳቡ ምንም አልተዋጠልኝም። ሰው እንደ ባህሉ፣ እንደወጉ ነው የሚኖረው። እኔ በሆዴ መገመት አልፈልግም፤ክብሬን መጠበቅ አለብኝ። የማከብረው ባለቤት የምወዳቸው ልጆች አሉኝ፤ ቅድሚያ ለነሱ ነው፤ መልካም ሚስት እና መልካም እናት እንዲህ ነው የምታደርገው። ከቤተሰቤ ተደብቄማ ለብቻዬ አህል ባፌ አይዞርም። እንዴት አድርጌ…ሠውስ ምን ይለኛል?

ነርስ ሰናይት፡-አሁን የተናገርሽው ሁሉ በደንብ ይገባኛል፤ አንድ ነፍሰጡር ሴት ለጤናዋ ተገቢ የሆነውን ተጨማሪ ምግብ በመመገቧ ክብሯ አይነካም። ነፍሰጡር ሴት የምትመገበው ለራሷ ብቻ ሳይሆን በሆዷ ላለው ህጻን ጭምር መሆኑን መረዳት አለብሽ። ለራስሽም ሆነ በሆድሽ ላለው ህጻን ጤና የምመክርሽን በቅጡ መስማት አለብሽ ወ/ሮ አቻም። እርግጠኛ ነኝ ባለቤትሽ የእኔን ሃሳብ ይደግፈዋል።

አቻም፡- ሲስተር አንቺ ለእኔ አስበሽ እንደሆነ አውቃለሁ። ግን ለእኔ ይሄ ሶስተኛው እርግዝናዬ ነው። ይቅርታሽን እንጂ የማደርገውን በደንብ አውቃለሁ ግዴለሽም።

ነርስ ሰናይት፡-ጥሩ፤ ከመሄድሽ በፊት የሚቀጥለውን የምርመራ ቀጠሮ ቀን እነግርሻለሁ እስከዛው እስኪ አንዴ ባለቤትሽን ወደ እዚህ ጥሪልኝ፤ አንዴ ላነጋግረው። እስከዛ አንቺ ውጪ ጠብቂኝ።

አቻም፡- ባለቤቴን ፈለግሽው? ኧረ እሱ ወደ እርሻው ለመሄድ ቸኩሏል ።

ነርስ ሰናይት፡-ግድ የለም አታስቢ፤ ለአጭር ደቂቃ ነው የምናወራው።

አቻም፡- እሺ ቆይ ልጥራው።

SFX: (አቻም ስትወጣ ኮቴ ይሰማል፤ በር ሲከፈት እና ሲዘጋ ይሰማል፤ በር ይንኳኳል)

ነርስ ሰናይት፡-አቤት.. ይግቡ።

አቶ በለጠ፡- (በሩ ይከፈትና ይዘጋል) እንደምን አረፈድሽ ሲስተር፤ ፈለግሺኝ እንዴ?

ነርስ ሰናይት፡-አዎ አቶ በለጠ ስለአንድ ጉዳይ ላነጋግርህ ነበር፤ አይዞህ ጊዜህን አልወስድብህም፤አረፍ በል

አቶ በለጠ፡- በደህና ነው? ምነው አቻም ደህና አይደለችም?

ነርስ ሰናይት፡-ደህና ነች፤ አቶ በለጠ በቅድሚያ ለባለቤትህ ስለምታደርገው ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ላመሰግንህ እፈልጋለሁ። ለዚህም ነው ደፍሬ በአሁኑ ሰአት ለባለቤትህ እጅግ አስፈላጊ ስለሆነው የተመጣጠነ ምግብ ጉዳይ ላነጋግርህ የደፈርኩት።

አቶ በለጠ፡- እሺ።

ነርስ ሰናይት፡-አቶ በለጠ፤ አንዲት ሴት ስታረግዝ አመጋገቧ ከወትሮው መቀየር አለበት። ለራሷ ብቻ ሳይሆን በሆዷ ላለውም ህጻን ጭምር ስለምትመገብ በሌላ ጊዜ ከምትመገበው ምግብ መጠን በላይ መመገብ አለባት፤ ከቤተሰቡ ጋር ከምትመገበው ተጨማሪ ምግብና መክሰስ መብላት አለባት። እንዲሁም ኮከብ ምግቦች ከምንላቸው እየጨመረች መመገብ አለባት።

አቶ በለጠ፡- ኮከብ ምግቦች ደግሞ ምን አይነት ምግቦች ናቸው?

Page 32: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

32

ነርስ ሰናይት፡-ከእንሰሳት ተዋፅኦ የሚገኙ ለምሳሌ፤- ስጋ፣ እንቁላል፣ ዶሮ፣ አሳ፣ ወተት እና አይብ የመሳሰሉትን የምግብ አይነቶች ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች ብለን እንጠራቸዋለን። እነዚህ ምግቦች ለአንድ ነፍሰጡር እናት እንዲሁም በሆዷ ላለው ጽንስ ገንቢና ጥንካሬ የሚሰጡ የምግብ አይነቶች ናቸው።

አትክልትና ፍራፍሬ ምግቦችን ደግሞ ባለሁለት ኮከብ ምግቦች ብለን እንጠራቸዋለን። እነዚህ ምግቦች ለሰውነት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች እና በቫይታሚኖች የበለጸጉ በመሆናቸው ለተጨማሪ እድገት በጣም ጠቃሚ ናቸው።

አቶ በለጠ፡- እኔ ይሄንን አላውቅም ነበር፤ በጣም ትልቅ ትምህርት ነው ያስተማርሽኝ ሲስትር፤ የሆነስ ሆነና ፤የተጠራሁበት የአቻም ጉዳይ ምንድን ነው?

ነርስ ሰናይት፡-አቻም እነዚህን የተመጣጠኑ ምግቦችን ለራሷና ለጽንሱ በሚጠቅም መንገድ እየተመገበች አይደለም። ለራሷ ተጨማሪና የተለየ ምግብ አዘጋጅታ መመገብ ራስ ወዳድነት ነው ብላ ስለምታምን ብቻዋን መብላት ነውር አድርጋ ታስባለች። በዚያላይ ለባሏና ለልጆችዋ ቅድሚያ ስለምትሰጥ ለራሷ በቅጡ አትመገብም።

አቶ በለጠ፡- እኮ የኔው አቻም፤ በኛ ምክንያት በደንብ አትበላም እያልሺኝ ነው?

ነርስ ሰናይት፡-አዎን በደንብ አትመገብም። ለዚህም ነው ከአምስት ወር ነፍሰጡር የሚጠበቀውን ያህል ክብደት የሌላት። ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ የራሷም ሆነ የህጻኑ ጤንነት ይጎዳል።

አቶ በለጠ፡- (በሃዘን ቅላጼ) እኔ እንግዲህ ምን አባቴ ላድርግ፤ ትምህርት የለኝ፤ ትምህርቴን ከአራተኛ ክፍል በማቋረጤ፤ የኔ እጣ እንዳይገጥማቸው ልጆቼን በተቻለኝ አቅም እያስተማርኩ ነው። የምተዳደረው በግብርና ነው፤ እግዚያብሄር ይመስገን ከቤታችን ምን ጠፍቶ፤ እሷም ታውቃለች። ካልጠፋ እህል በደንብ አትበላም ማለትሽ በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው ሲስተር። እንግዲህ ምን ማድረግ እችላለሁ ሁሉ ነገር ሞልቶ ካልበላች በግዳጅ አላበላት። ወይ ጉድ….

ነርስ ሰናይት፡-ልክ ነህ አቶ በለጠ፤ ይገባኝል። አቻም ብቻ አይደለችም የብዙ ሴቶች ችግር ነው። ከቤተሰቡ ተነጥላ ለራሷ ተጨማሪ ምግብ መብላት ያሳፍራታል፤ እራሷን ከቤተሰብ ያስቀደመች ስለሚመስላት ነውር አድርጋ ትቆጥረዋለች። ክብሯን መጠበቋ ደግሞ ላንተ ያላትን አክብሮት ማሳየቷ ነው።

አቶ በለጠ፡- ባለመብላቷ ነው እኔን የምታከብረኝ! መከባባር እራስን እየጎዱ አይደለም። አንድም ቀን አትብይ ብዬ ተናግሬም አላውቅ። ጨመር አድርጋ ብትበላ ደስ ይለኛል እንጂ ምን ይከፋኛል፤ ካልጠፋ ምግብ። እኔው ነኝ ምንጊዜም ካልበላሽ ብዬ የምጨቃጨቀው።አቻም የጥሩነቷን ያህል የግትርነት ጠባይ አላት፤ ሰው እሚላትን አትሰማም።

ነርስ ሰናይት፡-አቶ በለጠ እስካሁን የሆነው ሆኗል። አንተ ከኛ ከህክምና ባለሞያዎቹ በተሻለ እሷን መከታተል፤ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ እንድትመገብ መርዳትና ማሳመን ትችላለህ። ይሄውልህ ..ይሄ አንዲት ነፍሰጡር እናት የተመጣጠነ ምግብ እንዴት መመግብ እንዳለባት የሚገልጽ አጭር ጽሁፍ ነው፤ በዚህ መሰረት ለመከታተል ይረዳሀል፤ እንካ ቤት ውሰደው። ያንተ እገዛና ክትትል ካለ አቻምም ሆነች ህጻኑ ጤናማ ይሆናሉ።

Page 33: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

33

አቶ በለጠ፡- አመሰግናለሁ። እኔማ መድከሜ እነሱ ጤነኛ እንዲሆኑልኝ ነው፤ ሌላማ ምን እፈልጋለሁ ብለሽ ነው ሲስተር። እግዜር ይስጥልኝ፤ አመሰግናለሁ፤

ነርስ ሰናይት፡-ምንም አይደል

አቶ በለጠ፡- ደህና ዋይ

ነርስ ሰናይት፡-እሺ ደህና ዋል

SFX: (በር ሲከፍት እና ሲዘጋ ይደመጣል)

ትእይንት 4

ውስጥ - የወ/ሮ አቻም እና አቶ በለጠ መኖሪያ ቤት ነው - ረፋዱ ላይ፤

የከብቶችና የዶሮዎች ጩህት ይሰማል

አቻም፡ ስራ አለብኝ ብለኸኝ አልነበረም እንዴ? ለምን ከእኔ ጋር ቤት እንደተመለስክም አልገባኝም፤ ምንሆነሃል በለጥዬ? በመንገድም ሳናግርህ እንዳኮረፈ ሰው ሳትናገር ነው እዚህ ቤት የደረስነው።

አቶ በለጠ፡- ዛሬ ወደ እርሻ የመሄድ ፍላጎት የለኝም አልኩሽ እኮ ።

አቻም፡- በኔ ላይማ አንድ የተቀየምከው ነገር አለ፤ ምንድን ነው ንገረኝ።

አቶ በለጠ፡- (በንዴት ድምጽ) እኔ ለቤቴ አሳንሼብሽ አውቃለሁ!? ንገሪኝ በቤታችን የሚበላ ጠፍቶ ያውቃል!?

አቻም፡- ኧረ አያውቅም፤ አንተ ምንም አጓድለህብን አታውቅም፤ እኛ ቤት እድሜ ላንተ ተርፎ ለሌሎች የሚተርፍ ምግብ ነው ያለው፤ እኔ አማርሬም አላውቅም።

አቶ በለጠ፡- ምነው ታዲያ ባደባባይ መዋረዴ፤ ባለቤቴን ምግብ እንደምከለክል፤ ለባቤቴና ለቤተሰቤ አንሼ መታየቴ ምነው፤ ምነው እንደ ንፉግ ሠው አዋረድሺኝ! አመድ አፋሽ አደረግሺኝ።

አቻም፡- ባለቤቴ ምግብ ይከለክለኛል የሚል አልወጣኝም። እንደማንኛውም ሴት ቤት ያፈራውን ከቤተሰቤ ጋር እበላለሁ ብያለሁ፤ ሌላ ምንም ያልኩት ነገር የለም።

አቶ በለጠ፡- ለአንቺና ለልጆቼ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል እለፋለሁ። ። ያንቺም ሆነ የህጻን ልጃችንን ጤና የሚጠብቅ ቀላል የምግብ እቅድ መከተልና እራስሽን መጠበቅ ካቃተሸ የኔ ድካም ለማን ነው እስቲ ንገሪኝ? ምን አድርጌሽ ነው እንዲህ ያለ ውርደት ወስጥ የምትከቺኝ አቻም? በጣም ነው ያዘንኩብሽ

አቻም፡- (ሲቃ እየተናነቃት) እንዲህ ትበሳጭና ታዝንብኛለህ ብዬ አላሰብኩም። ካጠፋሁ እንግዲህ ይቅርታ አድርግልኝ። ሚስት እንደመሆኔ አንተን፤ እናት በመሆኔ ልጆቼን ማስቀደሜ መስዋትነት ነው። እንዲህ በማድረጌ አንተን አስደስታለሁ እንጂ አስቀይማለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር።

Page 34: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

34

አቶ በለጠ፡- ያንቺና የልጄ ጤንነት ሲስተጓጎል? እኔ አሁን እሱ ምኑ ያስደስተኛል በጭራሽ አያስደስተኝም። አንቺ እኮ ሁለት ነፍስ ነሽ፤ ቶሎቶሎ ይርብሻል፤ የዚያን ያህል ደግሞ መብላት አለብሽ። ጾምሽን ውለሽ ማታ እቤት ስገባ ጠብቀሽ ከኔ ጋር ገበታ በመቅረብሽ እንዴት እደሰታለሁ አቻም? ጥሩ አላደረግሽም።

አቻም፡- እኔ ይሄንን ባህል ብቻዬን አላመጣሁት፤ ባደኩበት ቤተሰብ እናቴም ሆነች ሌሎቹ ሴቶች የሚያደርጉት ነው።

አቶ በለጠ፡- ቤተሰቦቻችን ስላላወቁ ነው፤ የነሱን ወደኋላ ተመልሶ እንዲህ ነው እንዲያ ነበር ቢሉት ምንም ዋጋ የለውም። አንቺ እድሜ ለእነ ሲስተር ሰናይት እና ሌሎች የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ያስተማሩሽን መፈጸም ምን ይገድሻል?

አቻም፡- እኔ እንጃ ፤

አቶ በለጠ፡- እንጃ ምን ማለት ነው? እኔ በላሽ ወይ ብዬ ስጠይቅሽ ሁልግዜ መልስሽ አዎን በልቻለሁ ነው። ይሄው ሚዛኑ እንደሆነ አይዋሽ አሁን እኮ ጉዱ ወጣ።

አቻም፡- (እየፈራች እያመነታች) ብቻ እንዲያው…እንዲህ ነው ብዬ መናገሩ ከብዶኝ እንጂ፤ ንገሪኝ ካልክ ግልጡን ልናገር …በቤቱ በቂም ምግብ የለ፤ እንደምንም እያብቃቃው ነው ላንተም ሆነ ለልጆቼ የማቀርበው። ልጆቹ በቅጡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ደህና ነገር መመገብ አለባቸው፤ አንተም እርሻ ላይ ስለምትውል ጥሩ ነገር መብላት አለብህ። አለበለዚያ በምን አንጀትህ ስራውን ትገፋዋለህ። እንግዲህ እኔ ምን አደርጋለሁ፤ መቼም ከቤተሰቤ ተለይቼና ተደብቄ ያገኘሁትን ሁሉ አላግበሰብስም። ያላደኩበትን ጠባይ ከየት አመጣዋለሁ።

አቶ በለጠ፡- (ቁና እየተነፈሰ) የምትይው ነገር አሁን ገብቶኛል አቻም። ከኔና ከልጆቻችን ተርፎ ላንቺ የሚሆን በቂ ምግብ በቤታችን የለም ማለት ነው። እንግዲህማ ለቤተሰቤ የማልበቃ ሆኛለሁ ማለት ነው።

አቻም፡- እኔ ባንተ አልፈርድም፤ አንተማ የምትችለውን እያደረግክ ነው፤ ምናልባት…

አቶ በለጠ፡- ምናልባት ምን?

አቻም፡- ከጠየከኝማ አንዳንድ ሃሳቦች ነበሩኝ (በማመንታት ትተነፍሳለች) ለምሳሌ አምርተን ገበያ አውጥተን የሸጥንበት ገንዘብ የት እንደሚገባ አላውቅም። እውነቱን ለመናገር አምርተን ከሸጥነው የምናገኘው ገንዘብ ሌላ ነገር ላይ ከሚውል በከፊል ምግብ ግዢ ላይ ቢውል ጥሩ ሀሳብ መሰለኝ። ምናልባት ከሽያጭ ከምናገኘው ገንዘብ ላይ ቀንሰን ለምግብ መግዣ ብናጠራቅም ጥሩ ነው። የምንፈልጋቸውንም የምግብ አይነቶች በርካሽ የሚሸጥልን መፈለግ እንችላለን። ወደ ግዢም መሄድ ካልፈለግን ደግሞ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን በማሳችን እኛው እራሳችን ማምረት፤ ያመረትነውን ሁሉ ከመሸጥ ደግሞ የተወሰነውን ለራሳችን ማስቀረት ይኖርብናል። አልያም ደግሞ ተጨማሪ ገቢ የምናገኘበት መንገድ ካለ እኔም መርዳት እፈልጋለሁ። ቢረባም ባይረባም እንግዲህ ይሄው ነው የኔ ሃሳብ።

አቶ በለጠ፡- (በጸጥታ ይቆያል) ይሄማ ትልቅ ሃሳብ ነው አቻም። ለምንድነው እስከዛሬ እንዲህ ያለ ሀሳብ እያለሽ ሳታማክሪኝ የቀረሽው?

Page 35: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

35

አቻም፡- እንግዲህ አንተነህ የቤቱ አባወራ። የተገኘችውን ፍራንክ ቦታ ቦታ የምታስይዘው አንተው ነህ፡ እኔ ከአንተ በላይ እውቃለሁ ብዬ ለመናገር ይከብደኛል።

አቶ በለጠ፡- ‹ድር ቢያብር አንበሳ ያስር› ይባላል ከነተረቱ። እኔና አንቺማ በቤታችን ጉዳይ መመካከር አለብን። ያመረትነውን ሸጠን በምናገኘው ገንዘብ ላንቺ ተጨማሪ ምግብ የምንሸምትበት መንገድ ካለ እኔ ደስ ይለኛል፤ ወይም እነዚሁን ላንቺና ለልጆቹ የሚጠቅሙ ምግቦችን እኛው ማርባትና ማብቀል ከቻልን እሱም ጥሩ ሀሳብ ነው። ቆይ እኔም አንዳንድ ሀሳቦች ይኖሩኛል እንዴት ይሄን ጉዳይ ማስተካከል እንደምንችል። ብቻ የቤተሰብን ገቢና ወጪ መቆጣጠር እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም። ለማዳበሪያ፣ ለግብር፣ ለትምህርት ቤት፣ ለመሬት ኪራይ፤ ለልጆች መጽሃፍ እና ለትራንስፖርት የሚወጣውን ወጪ ሁሉ መቆጣጠር አለብኝ።።

አቻም፡- እንዳልከው ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ፤ አንተም እንዲህ ግልጽ ሆነህ ካማከርከኝ እኔም ያለንን እንዴት አብቃቅተን መጠቀም እንዳለብን ለማገዝ እችላለሁ።

አቶ በለጠ፡- አቻም፤ እንደሱ ብታግዢኝማ ትልቅ ሸክም አቀለልሽልኝ ማለት ነው። አሁን አንገብጋቢው ነገር ያንቺ የተመጣጠነና ተጨማሪ ምግብ የመመገብሽ ጉዳይ ነው። ተገቢውን ምግብ የምናሟላበትን መንገድ መመካከር አለብን። ተጨማሪ ገቢ የምናገኘው ምን ማምረት ብንችል እንደሆነ እኔም የግብርና ኤከስቴንሽን ባለሞያውን አማክረዋለሁ። እስከዚያው ግን ያለውን በደንብ መብላት አለብሽ ነፍሰጡር ለሁለት ነፍስ ነው የምትመገበው ልብ አድርጊ።

አቻም፡- እንደዚህ ስላሰብክልኝ በጣም ነው የማመሰግነው በለጥዬ። እኔና አንተም ግልፅ ሆነን ስለተነጋገርን ደስ ብሎኛል። ያንተንም ሆነ የሲስተር ሠናይትን ምክር በሙሉ ተቀብዬዋለሁ። የኖረ ጠባይ ለመተው ቢያስቸግርም፤ እራሴን ለመቀየር ፈቃደኛ ነኝ።

አቶ በለጠ፡- እኔም በግልጽ ስለተመካከርን ደስ ብሎኛል። በተለይም የተመጣጠነ ምግብ ላንቺም ሆነ ለጽንሱ ጠቃሚ መሆኑን በመረዳትሽ አቻም መቼም ዛሬ ኮርቼብሻለሁ። እራስሽን ለመቀየር ፈቃደኛ ከሆንሽ በቂ ነው። በቂ ምግብ መብላት አለብሽ፤ ተጨማሪ ምግብ መብላት ምንም የሚያሳፍር ነገር የለውም፤ የገበታ ሰአት እስኪደርስ በየመሃሉ ቤት ያፈራውን መቅመስ አትርሺ። ባለ ኮከብ ምግቦችንም በምግብሽ እየቀላቀልሽ መብላትም እንዳትረሺ። አንቺ ብቻ አይደለሽም እኔም እራሴን መቀየር አለብኝ። በግልጽ ተነጋግሮና ተመካክሮ ማደር ጠቃሚነቱን ዛሬ በደንብ አስተምረሺኛል የኔ ውድ። ተመካከረን ላንቺም ሆነ ለልጃችን የተሻለ የተመጣጠነ ምግብ የምታገኙበትን መንገድ እናመቻቻለን።

አቻም፡- አመሰግናለሁ በለጥዬ። እንግዲህ በሚቀጥለው ሲስተር ስታየኝ በክብደቴ ትደሰት ይሆናል።

አቶ በለጠ፡- (እየሳቀ) በጣም ነው እንጂ ደስ የሚላት።

አቻም፡- (በጣም እየሳቀች) ወፍሬ ደግሞ ብዘረጠጥ አደራ ማሾፊያ እንዳታደርገኝ፤ ካሁኑ ነግሬሃለሁ።

Page 36: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

36

አቶ በለጠ፡- ወፈርሽም ቀጠንሽም ለኔ ምንጊዜም ውብ ነሽ አታስቢ። አሁን ወደ እርሻ ልሂድ። ካዛ በፊት ግን ሃኪሟ የሰጠችንን የተመጣጠነ ምግብ መግለጫ ወረቀት እናንብበው እስቲ…

አቻም፡- እንዳንተ ያለ ባል በማግኘቴ እድለኛ ነኝ።

(SFX: የድራማ ሙዚቃ ይሰማና ሙዚቃው ቀስብሎ ይሞታል)። እቴ ብርቱካን፡-ደስ የሚል ድራማ ነው አይደል? አስተባባሪ እባክዎን በድራማው ዙሪያ ለሚደረገው

ውይይት የሚከተሉትን ነጥቦች እንዲወያዩባቸው ይርዷቸው፡-

• በተከታተላችሁት አጭር ድራማ የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው?

• ባለታሪኮቹ ምን ችግር አጋጠማቸው?

• ላጋጠማቸውንስ ችግር ምን መፍትሄ አገኙለት?

• በድራማው የተከታተላችሁትን አይነት ታሪክ በቤተሰባችሁ አልያም በአካባቢያችሁ ሊፈጠር የሚችል ታሪክ ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?

አስተባበሪ እባክዎ የደውሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን ያጥፉትና ውይይቱን ይምሩ፤ ስትጨርሱም ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን በደህና መጣችሁ! በድራማው ባለታሪኮች አቶ በለጠና ባለቤቱ ወ/ሮ አቻም

ዙሪያ መልካም ውይይት እንዳደረጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። በመጀመሪያ በባልና ሚስቱ መካከል ያለመግባባትና ግጭት ቢፈጠርም በስተመጨረሻ እንዳደመጥነው ታሪኩ በመግባባትና በደስታ አልቋል።ይህም የሆነበት ምክንያት አቶ በለጠ የሚስቱን የአቻምን እርግዝና በመረዳት፤ ተጨማሪ ምግብ መክሰስ መመገቧን፣ በየቀኑ የምትበላው የተመጣጠነ ምግብ ላይ ጨመራ መብላትዋን፣ ተጨማሪ ኮኮብ ምግቦችንም መብላቷን ስለተገነዘበ ነው። እንክብካቤ እንድታገኝና በህይወታቸው ለሚገጥማቸው ችግሮች ተመካክሮ ለመወሰን መስማማታቸውንም አይተናል።

ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ልክ እንደ ንግስት ንብ ናቸው። በቀፎው ውስጥ ያሉ ንቦች ሁሉ ንግስት ንብን በመንከባከብ ተባብረው ይኖራሉ ምክንያቱም ያለ እሷ በቀፎው የጋራ ህይወት ሊኖር አይችልምና ። ልክ እንደንቦቹ፤ የአንድ ነፍሰጡር ቤተሰቦች ተጨማሪ ምግብና እና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንድትመገብ ማበረታታት ይኖርባቸዋል። ንግስት ንብ ከቤተሰቡ ተነጥላ ብቻዋን መመገብ የማይቻላት ቢሆን እንኳ፤ ከቤተሰቡ ጋር ማእድ በቀረበች ጊዜ ተጨማሪ ምግብ እንድትመገብ ማበረታታት አለባቸው። ከዚህም በተጨማሪ ከመደበኛ የገበታ ሰዓት ውጪ መክሰስ መብላት ለነፍሰጡሯም በማህጸኗ ላለው ህጻንም ጠቃሚ በመሆኑ፤ ንግስት ንብ ይህንን እንድታደርግ ቤተሰብ ማበረታታት ይኖርበታል።

አሁን ደግሞ እዚህ መሀላችን ለሚገኙ ነፍሰጡር ሴቶች አንድ ነገር መናገር እፈልጋለሁ። እህቶቼ፣ ከጥልቅ ፍቅርና ከልብ በመነጨ ስሜት ልምከራችሁ፡

Page 37: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

37

እባካችሁን አደራ፤ ስግብግብ ወይም ራስ ወዳድ እንባላለን በሚል መሳቀቃችሁን ትታችሁ፤ ከገበታ ሰዓት ውጪ ተጨማሪ ምግብ መመገብ በማህጸናችሁ ላለው ጽንስ የተስተካከለ ጤንነት እንዲሁም የአካልና የአእምሮ እድገት እንደሚጠቅም በመረዳት፤መክሰስ፣ ተጨማሪ ምግብ እና ኮከብ ምግቦችን አዘውትራችሁ መመገብ እንዳለባችሁ አስታውሱ። ይህ፣ በጭራሽ ራስ ወዳድነት አይደለም። እንዲያውም ለልጃችሁ ያላችሁን ፍቅር ያሳያል፤ ለልጇ እንደምታስብ ጥንቁቅ እናት፣ እናንተም ገና ከመነሻው ልጃችሁን መንከባከብ አለባችሁ።

አያ ሙላት፡- እኔም በቀጥታ ላባወራዎች በተለይም ነፍሰጡር ሚስት ላላቸው መናገር የምፈልገው ቁምነገር አለኝ። ወንድሞቼ የቤተሰብ ሃላፊ መሆን፣ ትልቅ ክብር እንደሆነ ይገባኛል። ከአክብሮት ጋር መናገር የምፈልገው፤ ነፍሰጡር ሚስቶቻችሁ የሚመገቡት ለሁለት ሰው ስለሆነ በደንብ እንዲበሉ፣ አደራ አበረታቷቸው። ነፍሰ ጡር ሴቶች ንግስት ንቦቻችሁ ናቸው ስለዚህ ተንከባከቡዋቸው፡፡ቀደም ሲል ባደመጥነው ድራማ የአቶ በለጠን ታሪክ ምሳሌ አድርጋችሁ ውሰዱ።

አቶ በለጠ ከነፍሰጡር ባለቤቱ ከወ/ሮ አቻም የመጣውን ሃሳብ ተወያይተውበት በመቀበሉ ወጪና ገቢያቸውን በቅጡ ተቆጣጥረው በቂ ምግብ እንድታገኝ አቅደዋል። በእርግጥ፣ አባወራዎች የቤተሰብ ጠባቂና አለኝታ ናቸው፤ ቢሆንም አቶ በለጠ እንዳለው ‹ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ› ነውና ሚስቶቻችሁን በማወያየት በቂ ምግብ የሚያገኙበትን መላ መፍጠር ይቻላል። የቤተሰቡን ገቢ በተቻለ አቅም አብቃቅታችሁ ባለቤታችሁ ተጨማሪና ተገቢ ምግብ እንድታገኝ አድርጉ።

እቴ ብርቱካን፡-እኔም ለሴት አያቶችና አማቶች የማስተላልፈው አንድ ተጨማሪ መልእክት አለ። እንደናንተ አያት በመሆኔ፣ ለየቤተሰባችን ጤንነት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደምናበረክት አውቃለሁ። ለነፍሰጡር ልጃችን እንዲሁም ለልጃችን ሚስት ጠቃሚ ምክርና የህይወት ልምድ መስጠት እንችላለን። ጎጆ የወጡ ወንዶች ልጆቻችንም የኛን ምክር ይሰማሉ።

የአቶ በለጠና የወ/ሮ አቻምን ታሪክ ሰምተናል።እንደተረዳነው ነፍሰጡር ሴት የተመጣጠነ ምግብ ጨመር አድርጋ መብላት እንዳለባት፤ ከገበታ ሰዓት ውጭ መክሰስ መብላት እንዳለባት፤ እንዲሁም ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን መመገብና በቂ እረፍት ማግኘት እንዳለባት ከድራማው ተረድተናል። እኛም ሴት አያቶች እና አማቾች፤ ነፍሰጡሮቹ ይህንን ሳያሰልሱ እንዲያደርጉ መርዳትና ማገዝ ይኖርብናል። ወንድ ልጆቻችንንም እንመክራቸዋለን። አይደለም እንዴ? ከሚስቶቻቸው ጋር ስለቤተሰቡ ገቢና ወጪ ተወያይተው፤ በቂ ምግብ የምታገኝበትን ዘዴ እንዲፈጥሩ መምከር አለብን። ነፍሰጡር እናት የምትመገበው ለራሷ ብቻ ሳይሆን በሆዷ ላለው ህጻንም ጭምር እንደሆነ አውቀን ሁልጊዜ መርዳት እንዳለብን መርሳት የለብንም።

እቴ ብርቱካን፡-‹ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም› ነውና፤ አሁን ደግሞ ትንሽ ዘና የሚያደርገንን ስለ ንግስት ንብ የተዘጋጀ መዝሙር እናዳምጣለን። እስኪ እናንተም አብራችሁን ለመዝፈን ሞክሩ።

Page 38: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

38

SFX: የንግስትን ንብ መዝሙር ይደመጣል። እቴ ብርቱካን፡-(ዘፈኑን ስታንጎራጉር ይሰማል) ሁላችሁም መዝሙሩን እንደወደዳችሁት ተስፋ

አደርጋለሁ። እኔ በጣም ወድጄዋለሁ። እናንተስ?

አሁን በሰማነው መዝሙር ዙሪያ እንድትወያዩ እንፈልጋለን። አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በማስቆም፣ ውይይቱን ቀጥሉ። ከዚያ በፊት ግን እስቲ ለውይይት የሚረዳችሁን አንዳንድ ፍሬ ነገሮች ላካፍላችሁ።

• ከመዝሙሩ ምን ተረዳችሁ? ምን ምን መረጃዎች አገኛችሁ?

• ከመዝሙሩ የወደዳችሁት ምንድነው?

• እቤት ስትሄዱ ይሄንን መዝሙር ለቤተሰቦቻችሁ ልታስተምሩ ትችላላችሁ?

እሺ፤ አሁን አስተባባሪ ቴፑን ይዝጉትና ተሳታፊዎች በሦስቱ ፍሬ ነገሮች ላይ እንዲወያዩ ይርዷቸው፤ ውይይቱ ሲያልቅቴፑን ይክፈቱት።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፤ ብዙ ቁምነገር የሚነግረን ቆንጆ መዝሙር ነው አይደል?

ነፍሰጡሯ ሴት በመዝሙሩ ብዙ መልእክት አስተላልፋለች። በቀን ውስጥ በትንሽ በትንሹ በቶሎ በቶሎ ደጋግማ እንደምትመገብ ነግራናለች። በተጨማሪም በዘፈኑ፣ የእንሰሳት ተዋጽኦ ከሆኑ ምግቦች በየቀኑ መመገብ በሆዷ ላለው ዘር (ፅንስ) የተስተካከለ እድገት እንደሚበጅ ነፍሰጡሯ እናት ነግራናለች። ምክንያቱም የምትመገበው ለራሷ እና ለፅንሱ ነው። በቂ እረፍትና ምግብ እንድታገኝ ባለቤቷ እና እናቷ በቤት ስራ ማገዛቸው ደስ አይልም? የሚተሳሰብ ቤተሰብ ያስደስታል። በዘፈኑ እንደሰማችሁት፣ ጠንካራ ቤተሰብ በመተባበር ንግስት ንብን ይንከባከባል፤በቂ ምግብ እንድታገኝ ያግዛል። ነፍሰጡሯ ሴት ለቤተሰቡ ንግስት ንብ ናት፤ ቤተሰቦቿም ሰራተኛ ንቦች ናቸው። በጣም የሚያምር መዝሙር ነው!።

ቀደም ሲል ባዳመጣችሁት ድራማ ውስጥ፤ አቶ በለጠ፣ ባለቤቱ አቻምን እንደ ንግስት ንብ እንክብካቤ ሲያደርግላት አይተናል። አቻምም በፋንታዋ የጥሩ ነፍሰጡር ምሳሌ ነች። ምክንያቱም እራሷን በመንከባከብ በማህጸኗ ያለው ጽንስ በአእምሮና በአካል ፈጥኖ እንዲጎለብት ተጨማሪ ምግብና ተጨማሪ ኮኮብ ምግቦች ለመመገብ፣ ፈቃደኛ በመሆን በተግባር አስመስክራለች። ባልና ሚስት በመመካከርና በመወሰን በጋራ መፍትሄ እንደሚያገኙ ያሳዩን የጥሩ ጥንዶች ምሳሌ ናቸው። ‹ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ› እንደሚባለው፤የተማከሩት ነገር ምንጊዜም ውጤቱ ጥሩ ነው። እኔም እስኪ የባለቤቴን ድጋፍ ልጠይቅ። ሙላትዬ እዚህች ላይ ብትረዳኝና ትንሽ ምክር ብታክልበት ምን ይመስልሃል?

አያ ሙላት፡- (እየሳቀ) ደስ ይለኛል ውድ ባለቤቴ፤ ምንጊዜም ከጎንሽ ነኝ። የሚገርምሽ ነገር፤ መዝሙሩ ከጭንቅላቴ አልወጣም፤ እስካሁን ሳንጎራጉረው ነበር።

እቴ ብርቱካን፡-እኔ የምልህ ሙላት፤ቀደም ሲል በሰማነው የድራማ ታሪክ ውስጥ፤ ወ/ሮ አቻምና አቶ በለጠ ለቤታቸው በቂ ምግቦችን ለማብቀል ለማርባት ሲነጋገሩ ነበር። በዚህ ጉዳይ ምን ትመክረናለህ?

Page 39: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

39

አያ ሙላት፡- እንግዲህ ብዙዎቻችን የአርሶ አደር ቤተሰብ እንደመሆናችን፣ እንደ ንግስት ንብ የምናያት ነፍሰጡሯ፤ ኮከብ ምግቦች እንድታገኝ የምናደርግበት አንዱ መንገድ፤ ኮከብ ምግቦችን በማብቀልና በማርባት ነው። ብዙዎቻችን በየቤታችን ከምናበቅላቸውና ከምናረባቸው ኮከብ ምግቦች መካከል አንዳንዶቹን እያነሳን በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜያችን ተነጋግረናል።

እንደምታውቁት የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች የምርጥ ዘር አጠቃቀም፣ የተሻሻለ የአስተራረስ ዘዴ እና ሌሎች ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ጠቃሚ ምክሮችን በመለገስ ኮከብ ምግቦችን በብዛት ለማምረትና በየእለቱ እንድንመገብ የሚያስችለንን መንገድ ሊያስተምሩን ይችላሉ።

በዛሬው የውይይት ክፍለጊዜያችን፣ ብዙዎቻችን በየቤታችን ስላለው የዶሮ እርባታ እንነጋገራለን። የዶሮ እርባታ፣ ንግስት ንብ የእንስሳት ተዋፅኦ ምግቦችን ወይም ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦችን የምታገኝበት ዋነኛ መንገድ ነው፤ ለምሳሌ እንቁላል ባለ ሦስት ኮከብ ምግብ ነው። አንድ ነፍሰጡር እናት በቀን አንድ እንቁላል ከበላች፤ እራሷንና በሆዷ ያለውን ዘር ጠንካራ እና ጤናማ እንዲሆን ማድረግ ትችላለች።

አያ ሙላት፡- እስቲ የዶሮ ቤት እንዴት እንደሚገነባ እንነጋገር። የእጅ ሞያ እወዳለሁ፣ የዶሮ ቤቴን ስሰራ በጣም ደስ እያለኝ ነበር። ለነገሩ የዶሮ ቤት መስራት ቀላል ነው። ። የሚያስፈልጉን ቁሳቁሶች፣ ለቋሚ እና ለማገር የሚሆን እንጨት፣ ጥቂት ሚስማር፣ ለጣሪያ የሚሆን ቆርቆሮ ፣ ከፊት ለፊት አየር የሚያስገባ የሽቦ ወንፊት፣ ለግድግዳ የእንጨት ፍልጥ እና ለመምረግ በጭድ የተቦካ ጭቃ ናቸው።

ከፊት በኩል በሽቦ ወንፊት የተከለለ የዶሮ ቤት መስራት፣ ሁለት አገልግሎቶች አሉት። ወንፊቱ አየር እንደልብ እንዲንሸራሸርና አውሬ እንዳይገባ ለመከላከል ይረዳል። ዶሮዎቹ ቀን ቀን እንደልባቸው ይንቀሳቀሱበታል። ዋናው አገልግሎቱ ግን፣ እንስሳትንና ሰውን ለመለየት ነው - በተለይ ሕፃናት ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ። ይህም፣ ጀርሞች (የበሽታ ተሕዋሲያን) እንዳይተላለፉ ይረዳል። ይህንን ጉዳይ ወደፊት በሚኖረን የውይይት ክፍለጊዜ እንነጋገርበታለን። የቤቱን ዋነኛ ክፍል ስንሰራ፣ ከምድር ከፍ አድርጎ ክፍተቶች ያሉት ወለል (ቆጥ) ማበጀት ያስፈልጋል፤ ኩሳቸው ወለሉን ሳይነካ ወደ ምድር ስለሚወድቅና ዶሮዎቹ ስለማይረጋግጡት፤ በቀላሉ ለማጽዳትና በሽታ ለመከላከል ይረዳል። በቂ ውሃ እና የዶሮ መኖ በመስጠት እንዲሁም ቤታቸውን በማፅዳት፣ ጤናቸውን መጠበቅ እንችላለን። ጤናማ ዶሮ ብዙ እንቁላል ትጥላለች፤ረጅም እድሜ ይኖራታል። በዚህ መንገድ፣ ለንግስት ንብ፣ ለእንቡጥና ለአበባ ህጻናት በየቀኑ አስፈላጊውን እንቁላል ማግኘት እንችላለን።

የራሳችሁን የዶሮ ቤት በቀላሉ ለመስራት የሚረዳችሁ፣ ደረጃ በደረጃ የሚያብራራ፣ አጭርና ግልፅ መመሪያ አዘጋጅተናል።

አስተባባሪ፣ እባክዎን የዶሮ ቤት አሰራር መመሪያውን ለተሳታፊዎች ያድሏቸው።

እቴ ብርቱካን፡-አመሰግናለሁ ሙላት። ሌላው ትልቅ ነጥብ፤ ነፍሰጡር እናቶች የተመጣጠነ ምግብ የመመገብ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ የገንዘብ እጥረት ሲፈታተናቸው መፍትሄ

Page 40: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

40

እንደሌለው ያስባሉ። በተለያየ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ነፍሰጡር ሴቶች በገንዘብ እጥረት ጉዳይ ላይ ያላቸውን አስተያየት እስቲ እንስማ።

የተዋንያን ድምጽ

• “እጅ ያጥረናል። ዋጋው አይቀመስም። ለምሳሌ ፍየል አርደን ለመብላት ብንፈልግ፣ ዋጋ በጣም ይወደድብናል። ወተት አንዳንዴ በገበያ ይኖራል፤ ግን ውድ ነው። ስለዚህ ወተት መጠጣት አንችልም። አቅማችን ስለማይፈቅድ መግዛት አንችልም።” (ነፍሰጡር ሴት፤ ትግራይ)

• “በአቅማችን የምንችለውን እንድንበላማ ነግረውናል፤ እኔ ግን የተመጣጠነ ምግብ ለራሴ ማዘጋጀት አልችልም፤ ምክንያቱም አቅሜ አይፈቅድም። ይሄ ሁሉ በገንዘብ ችግር ምክንያት ነው።” (ነፍሰጡር ሴት፤ኦሮሚያ)

• “አቅሟ ስለማይፈቅድ እነዚህን ምግቦች ልትመገብ አትችልም። እነዚህን ምግቦች ማግኘት ካልቻለች ምን ታደርጋለች፤ ቤት ያፈራውን ትበላለች። ችግሩ ድህነት ነው።” (ነፍሰጡር ሴት፤ ጢሶ ስዴቻ፣ ጎማ፣ ኦሮሚያ)

እቴ ብርቱካን፡-የገንዘብ ችግር የብዙዎቻችን ችግር ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ገንዘቡ እያለ፣ ገንዘቡን ለኮከብ ምግቦች እንዴት እንደምንጠቀም መወሰን ያስቸግረናል - የቱን እንሽጥ፣ የቱን እንግዛ እና ምን እንብላ ነው ጥያቄው።

አያ ሙላት፡- ጥሩ ነጥብ ነው ያነሳሽው፤ እስኪ ለራሳችን ለመመገብ ሳይሆን ለገበያ አስበን የምናመርታቸውንና የምንሸጣቸውን የግብርና ውጤቶች እንመልከት። ለምሳሌ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ በአንዳንድ ክልሎችም ሰሊጥ ወይም ቆጮ፣ ማር፣ ሽምብራ እና ቡና ወደ ገበያ አውጥተን እንሸጣለን። ለሽያጭ ብለን የምናረባቸው እንስሳትስ አሉን?። እስኪ በነዚህና ገበያ አውጥተን በምንሸጣቸው ሌሎች ምርቶች ዙሪያ ትንሽ እንወያይ።

አስተባባሪ፣ እባክዎ ተሳታፊዎች የሚከተሉትን ጥያቄዎች መነሻ አድርገው እንዲወያዩ ያግዟቸው።

1. በቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ቆጮ፣ ሰሊጥ፣ ማር፣ ሽምብራ፣ ቡና፣ የቤት እንስሳት እና የመሳሳሉትን የገበያ ምርቶች ሸጠን በምናገኘው ገንዘብ ለቤተሰባችን ምንድነው የምንገዛው?

2. እነዚህን ምርቶቻችንን ሸጠን ከምናገኘው ገንዘብ ላይ የተወሰነውን ገንዘብ ለምሳሌ እንቁላል፣ ወተት፣ እርጎ፤ ስጋና እና ሌሎች ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦችን ገዝተን ነፍሰጡሯ ሴት ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ ከነዚህ ምግቦች እንድትመገብ ማድረግ አንችልም? ካልተቻለስ ለምንድነው የማይቻለው?

3. ከገቢያችን ላይ የተወሰነውን ቀንሰን ተጨማሪ ምግቦችን በመግዛት ንግስት ንብ ለራሷ እና በማኅፀኗ ላለው ህፃኑ ዘር በየቀኑ ከወትሮው የበለጠ ምግብ እንድትመገብ እንዲሁም መክሰስ እንድትጨምር ማድረግ እንችላለን? አይደለም እንዴ? ካልተቻለስ ለምን?

Page 41: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

41

አስተባባሪ እባክዎ ደውል እንደሰሙ ቴፑን ይዝጉና ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱ ሲጠናቀቅ ቴፑን መልሰው ይክፈቱ።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! ግሩም የውይይት ጊዜ እንዳሳለፋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ - በተለይ ለወንድ ተሳታፊዎች። በውይይታችሁም አንዳንድ የኑሮ ችግሮች እንደተነሱና የመፍትሄ ሃሳቦችም እንደተሰነዘሩ እርግጠኛ ነኝ። በውይይታችሁ ወቅት መፍትሄ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎችን አስተባባሪ በማስታወሻ ላይ ስለሚፅፏቸው፣ በቀጣይ ሳምንታት በሚኖሩን የውይይት ክፍለጊዜዎች መልስ እንዲያገኙ እናደርጋለን።

ትንሽ የልምምድ ጊዜም ይኖረናል። የቤተሰባችንን ገቢ በማብቃቃትና ሌሎች የገንዘብ ምንጮችን በመጠቀም፣ ንግስት ንቦቻችን ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችንና መክሰሶችን እንዲመገቡ ማድረግ ይቻላል። ለዚህም፣ ጥንዶችና ቤተሰብ በገንዘብ አጠቃቀም ላይ በተቃና መንገድ ለመወያየትና ለመወሰን የሚያገለግሉ አንዳንድ ክህሎቶችን በተግባር እንለማመዳለን። አሁን ለዛሬ ወዳሰናዳነው ቀጣዩ ርዕሰ ጉዳይ በመዝለቅ፣ ስለ ምግብ አዘገጃጀት እንወያያለን። እውነቱን ለመናገር፣ የሚያኩራራ የምግብ አዘገጃጀት ሙያ የለኝም። ደግነቱ፣ ውዷ ባለቤቴ የተዋጣላት የምግብ ባለሞያ ናት። ብርቱካኔ፣ ልትረጂን ትችያለሽ?።

እቴ ብርቱካን፡-እንዴታ! በነገራችን ላይ ውድ ባለቤቴ፣ ጥሩ ምክር ስላካፈልከን አመሰግናለሁ።። በፋንታዬ፣ አባይነሽ ስለምትባል ወዳጄ፣ አንድ ታሪክ ላጫውታችሁ። አባይነሽ ነፍሰጡር መሆኗን ያወቀች ጊዜ ትዝ ይለኛል። እንደዚያ ጊዜ ተደስታ አታውቅም። ታዲያ፣ በእርግዝናዋ የመጀመሪያዎቹ ሳምንታት እያቅለሸለሻት የምግብ ፍላጎቷ ቀነሰ። አንዳንድ ምግቦችንማ ከነአካቴው አልቀምሳቸውም አለች። ባለቤቷ አቶ ንጉሴ አባይነሽ በፊት በጣም የምትወዳቸውን ምግቦች በመጥላቷ በጣም ግራ ይጋባ ነበር። ከጊዜ በኋላ የሚያቅለሸልሻት ስሜት ጋብ ሲልላት ነው በትንሹ መብላት የጀመረችው።

አንድ ምሽት፤ በእኩለ ሌሊት፤ በራችን ሲንኳኳ ሰማን። በሩን ስንከፍት አቶ ንጉሴ ነው። ‹ምነው? አባይነሽ ደህና አይደለችም እንዴ?› ብለው፤ “በውድቅት ሌሊት እንቅልፍ ነሳኋችሁ እንጂ በደህና ነው” አለን። “በደህና ከሆነስ ደግ!” ብለን የመጣበትን ምክንያት ስንጠይቀው፣ ለመናገር አመነታ። “እንዲያው ትንሽ ጎመን ይኖራችሁ እንደሆን ብዬ ነው። አባይነሽ ድንገት ጎመን አማረኝ፤ አሁን ካላመጣህ፣ ካልወለድክ ብላ ብታስጨንቀኝ እናንተ ወዳጆቼ ዘንድ መጣሁ› አለኝ። ባለቤቱ ደርሳ ጎመን አማረኝ ብላ ያስጨነቀችው ለምን እንደሆነ ምክንያቱ አልገባውም። እንዲያውም፣ ለመሞላቀቅ ብላ ያደረገችው መስሎት ትንሽ በስጨት ብሏል። መች እንደዚያ ሆነና ብዬ ነገሩን አስረዳሁት፤ ሰውነታችን አንዳንድ ጠቃሚ ንጥረነገር ሲጎድልበት ፣ የአንዳንድ ምግቦች አምሮት ይጠናብናል። ጎመን በውስጡ ለደማችን የሚያስፈልግ አይረን የተሰኘ ንጥረነገር የያዘ ምግብ ነው። ነፍሰጡር ሴት እና

Page 42: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

42

በማህጸኗ ያለው ጽንስ ደግሞ ንጥረነገሩን ይፈልጋሉ፤ ለዚህ ነው ባለቤትህ ጎመን ያማራት ብዬ አስረዳሁት። እግረመንገዴንም፣ ለነፍሰጡር እና ለጽንሱ የሚያስፈልጉ ኮከብ ምግቦችንና (የአይረን ኪኒን) እንዲሰጣት ነገርኩት። ነገሩ ሁሉ ገባው። የባለቤቱ የጎመን እና የሌሎች ምግቦች አምሮት ከምን የመጣ እንደሆነ ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደበትም። ደግነቱ ከእራት የተረፈ ጎመን ከቤታችን ስለነበር አውጥቼ ሰጠሁት። አመስግኖኝ ይዞላት ሄደ። ለነፍሰጡር የሚያስፈልጉ የተመጣጠኑ ምግቦችና (አይረን ፎሊክ አሲድ ወይም በተለምዶ አይረን ኪኒን) ምንነትና ጠቀሜታ በዝርዝር ስላወቀ በማግስቱም ከባለቤቱ ከአባይነሽ ጋር ጤና ጣቢያ ሄዶ የአይረን ኪኒን እንዲሰጣት አደረገ፡፡።

አያ ሙላት፡- (እየሳቀ) እኔም ያችን ምሽት አልረሳትም። እንቅልፍ በዓይኔ ሳይዞር ነው የነጋው።

እቴ ብርቱካን፡-እንደ ንግስት ንብ የምንንከባከባቸው ነፍሰጡር እናቶችና ህጻናት በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት በየእለቱ በምግብ ሰዓትና በመክሰስ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ የሚረዱ ዘዴዎች አሉ። ከእነዚህም መካከል፣ በአግባቡ ምግብ ለማዘጋጀት፣ በንህጽና ሳይበላሽ ለማቆየትና ለማስቀመጥ የሚጠቅሙ ዘዴዎች ናቸው። እስቲ በመጀመሪያዎቹ እርግዝና ወቅቶች፣ ለነፍሰጡር ሴት የሚስማሙና ሳይበላሹ የሚቆዩ የመክሰስ አይነቶችን አስቡ። አንዳንዶቹን ልንገራችሁ።

• ቋንጣ - ለደም በሚያስፈልግና አይረን በተሰኘ ንጥረነገር የበለፀገ ግሩም መክሰስ ይሆናል፡፡ ታዲያ ትንሽ እሳት ቢነካው ጥሩ ነው፡፡

• እንዲሁም፣ ቆሎ

• ባቄላ

• ሽንብራ

• ፍራፍሬዎች

• የተቀቀለ እንቁላል የመሳሰሉት ጥሩ የመክሰስ ምግቦች ናቸው።

በሚቀጥለው የውይይት ክፍለጊዜያችን፣ የእራሴን የቋንጣ አዘገጃጀት አካፍላችኋለሁ። በተለይም ትኩስ ስጋ እንደልብ በማይገኝበት ወቅት፣ ቋንጣ አዘጋጅቶ ማስቀመጥ ብልህነት ነው።

ለዛሬ ግን እንድታስታውሱ የምፈልገው ሙዝ፣ ፓፓያና አቦካዶ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ዝግጅት የማያስፈልጋቸው መክሰስ መሆን የሚችሉ ቀላል ምግቦች መሆናቸውን ነው፡፡ ነፍሰጡሯ ዘወትር ማታማታ አይረን ኪኒን ከመውሰዷ በፊት የፍራፍሬ መክሰስ መብላት ትችላለች። ቆሎ እና ሽምብራም በደረቅ ስፍራ ካኖሩት ስለማይበላሽ፣ በተፈለገ ጊዜ ጥሩ መክሰስና የቡና ቁርስ ይሆናል። የቡና ነገር ከተነሳ በዚህ አጋጣሚ፣ አንድ ነገር ልንገራችሁ። ቡና ወይም ሻይ የምትጠጡ ከሆነ፣ የአይረን ክኒን ከመውሰዳችሁ አንድ ሰዓት በፊት ወይም የአይረን ክኒን ከወሰዳችሁ አንድ ሰዓት በኋላ ነው ቡና ወይም ሻይ መጠጣት የምትችሉት። ወደፊት በዝርዝር እንነጋገርበታለን።

Page 43: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

43

እቴ ብርቱካን፡-ነፍሰጡር በነበርኩ ጊዜ፤ በተለይም የመጀመሪያዎቹን የእርግዝና ወቅቶች ተጨማሪ ምግብ መመገብ እንዳለብኝ ስላወቅኩ፣ ለመብላት እፈልግ ነበር። ምግብ ከቤት አልጠፋም። ባለቤቴም ከጎኔ ሆኖ ያበረታታኝ ነበር። እንዲህም ሆኖ፣ መብላት አልቻልኩም። በጣም ያቅለሸልሽኝ ነበር፤ አንዳንድ ምግቦችንማ ገና ከሩቁ ሲሸቱኝ ወደላይ ይለኛል። ብዙዎቻችሁ በእርግዝና ወቅት እንደኔ እንደተቸገራችሁ እርግጠኛ ነኝ።

እስቲ በተለያየ አካባቢ የሚኖሩ ነፍሰጡር ሴቶች፣የተናገሩትን እንስማ። በአራት ክልሎች በተካሄደ ጥናት ላይ የተሳተፉ ሴቶች ናቸው ተመክሯቸውን የነገሩን። አንድ ሁለቱን እናዳምጥ።

(የተዋናዮች ድምጽ)

• “እያስመለሰኝ ተቸግሬ ነበር፤ በተለይም ጥቅል ጎመንና ገንፎ ስበላ እረፍት አይሰጠኝም ነበር።”

• “የምጠላቸው ምግቦች ነበሩ፤ ምግብ ሲያስጠላኝ፣ እርግዝናዬ የመጀመሪያ ወራቶች ላይ መሆኔን አውቃለሁ። ምግብ ሳዘጋጅና ስበላ ያስመልሰኛል። በተለይ ወደ አራት ወር ገደማ ሲሆነኝና ጽንሱ መንቀሳቀስ ሲጀምር፣ ያኔ ምግብ ያስጠላኛል።”

እቴ ብርቱካን፡-የወለዳችሁ ሴቶች፣ እነዚህ የእርግዝና ወቅት ምልክቶችን ታስታውሳላችሁ። ወይም ደግሞ፣ ሌላ ነፍሰጡር ሴት በእነዚህ ምልክቶች ስትቸገር አይታችሁ ይሆናል። በተለይም በመጀመሪያዎቹ የእርግዝና ወራት እያቅለሸለሸ ሲያስቸግረኝና ምግብ ሲያስጠላኝ፣ በምን አይነት መላ እንደተቋቋምኩት ልንገራችሁ። የምግብ ሰዓት እየጠበቅኩ አብዝቼ ለመብላትና ለመገላገል መሞከር አይበጅም። እስከነጭራሹ ከምግብ መራቅ ደግሞ የባሰ ይጎዳል። በየሰዓቱ ትንሽ ትንሽ እየደጋገምኩ መመገቤ ነው የጠቀመኝ። ብዙ ነፍሰጡር ሴቶችም፣ በዚህ እንደሚስማሙ አልጠራጠርም። ለኔ በጣም ጠቅሞኛል። የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እና የቅድመወሊድ ክትትል ባለሞያዎች ይህንን ዘዴ ይመክራሉ። ነፍሰጡር ሴት የምትመገበው ለሁለት እንደሆነ አትርሱ። ስለዚህ በገበታ ሰዓት ከምትመገበው መደበኛ ምግብ በተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን በማከል በየሰዓቱ ትንሽ ትንሽ ደጋግማ ለመብላት መጣር አለባት። ያቅለሸልሸኛል ወይም አስጠልቶኛል በሚል ሰበብ ከምግብ መራቅ ግን ለሁለቱም የከፋ ጉዳት ያመጣል።

እቴ ብርቱካን፡-እስቲ አሁን ደግሞ ብዙ ጊዜ በእርግዝናና በወሊድ ወቅት ስለሚከሰተው የደም ማነስ ህመም እንነጋገር። ነፍሰጡሮች እንዲሁም አባወራዎች፣ የደም ማነስ ምንነትንና መከላከያውን በቅጡ ማወቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም በሀገራችን፣ ከ6 ሕፃናት አንዱ የደም ማነስ ችግር አለባቸው። ነፍሰጡሮችም ከስድስትት ሁለቱ የደም ማነስ ችግር ያጋጥማቸዋል። በክልል ደረጃም ስንመለከት፡ በትግራይ ከከስድስትት አንዷ፤ በአማራ ከስድስት ሁለቱቱ፣ በኦሮሚያ ከስድስት ሁለቱ በደቡብ ክልል ከስድስትት አንዷ የሚሆኑ ነፍሰጡሮች የደም ማነስ ችግር ተጎጂ ናቸው።

Page 44: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

44

እቴ ብርቱካን፡-ለመሆኑ የደም ማነስ ችግር ምንድነው?

የደም ማነስ ችግር ተፈጥሯል ስንል፣ በደም ውስጥ አይረን የተሰኘው ንጥረነገር ጎድሏል ማለታችን ነው። ነፍሰጡር ሴት በደም ማነስ ችግር የምትጠቃው፤ በማህፀኗ ውስጥ ላለው ሕፃን ተጨማሪ ደም ስለምትፈጥር ነው። ነፍሰጡሯ፣ለራሷና ለሕፃኑ የሚበቃ ተጨማሪ የአይረን ንጥረነገር ያስፈልጋታል ማለት ነው።

የደም ማነስ ምልክቶችን ልንገራችሁ። ድካምና ስራ ላይ የመዛል ስሜት፣ የማዞርና የብዥታ ስሜት፣ መገርጣት፣ የእጅና የእግር መቀዝቀዝ፣ በአጠቃላይ ጤና የማጣት ስሜት፤ የደም ማነስ ምልክቶች ናቸው።

ደግነቱ፤ በአይረን ንጥረነገር ጉድለት የሚከሰተው የደም ማነስ ችግርን በቀላሉ ልንከላከለውና ልናስተካክለው እንችላለን። በአይረን ንጥረነገር የበለጸጉ ምግቦችን በመመገብና ሁል ጊዜ ማታ ከመኝታ በፊት የአይረን ክኒኖችን በመውሰድ የደም ማነስን መከላከል ይቻላል።

በአይረን ንጥረነገር ከበለፀጉት ምግቦች መካከል፣ ስጋ፣ በተለይም ጉበት እንዲሁም ባቄላ ይገኙበታል። እንደ ጎመን የመሳሰሉ አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች የአይረን ንጥረ ነገር ይይዛሉ። በቂ አይረን ለማግኘት ግን በጣም ብዙ ጎመን መመገብ ያስፈልጋል ማለት ነው።

የደም ማነስ ችግር መከላከያ ዋነኛው ፍቱን ዘዴ፤ የአይረን ክኒን በእርግዝናና ወቅት መውሰድ ነው። አንዲት ሴት ልክ ነፍሰጡር መሆንዋን እንዳወቀች ያለማቋረጥ ዘወትር ማታ ማታ ከመኝታ በፊት ቢያንስ ለ3 ተከታታይ ወራት ይህንን ክኒን መውሰድ አለባት። ከወሊድም በኋላ እናቶች የአይረን ክኒን ለሶስት ወራት ያህል መውሰዳቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል። ስለዚህ ደም ማነስን ለመካከል የሚሻለው ምርጫ የአይረን ኪኒን መውሰድ ነው፡፡ የአይረን ክኒን በጤና ተቋማት ሁሉ ይገኛል። እዚህ ላይ አንድ የምስራች ልንገራችሁ። መንግስት ይህን ክኒን ያለክፍያ በነጻ ይሰጣል። ነፍሰጡር ሴቶች የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ለማግኘት በእርግዝናቸው ወቅት ቢያንስ አራት ጊዜ ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ ስላለባቸው፣ ከቤተሰብ የመጓጓዣና ሌሎች ድጋፎች ያስፈልጋቸዋል።

እነዚህ ትናንሽ ክኒኖች፣ በእርግዝና ወቅትና ከወሊድ በኋላም ቢያንስ ለ ሶስት ወራት ያህል ያለማቋረጥ ማታ ማታ ሊወሰዱ ይገባል። የአይረን ክኒን መጠነኛ የሆድ ድርቀትና የአይነ ምድር መጥቆርን የመሳሰሉ አነስተኛ የጎንዮሽ ችግሮች ስለሚኖረው፣ እንዲሁም ክኒኑን ሲወስዱ የማቅለሽለሽ ስሜት ስለሚፈጥር፤ አንዳንድ ነፍሰጡሮች ክኒኑን አይወዱትም። ነገርግን፤ እነዚህ ችግሮች ብዙ ሊያስጨንቁን አይገባም። ምክንያቱም ችግሮቹን በቀላሉ መቅረፍ እንችላለን።

• በመኝታ ሰዓት ክኒኑን ከመውሰዳችን አስቀድመን ትንሽ ምግብ ከበላን የማቅለሽለሽ ስሜቱ በጣም ይቀንሳል።

Page 45: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

45

• የሆድ ድርቀት ከተሰማንም የአትክልት ምግቦችን በርከት አድርጎ በመመገብ እንዲሁም አብዝቶ ውሃ በመጠጣት ልናስወግደው እንችላለን።

• ደረት ላይ ይፍቀኛል ወይም ጨጓራዬን ይነካኛል የሚል ስሜት የሚፈጠር ከሆነም፤ ከክኒኑ በፊት ምግብ መውሰድ ብልህነት ነው።

ነፍሰጡሮች ክኒኑን መውሰድ ከጀመሩ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የጤንነት ስሜታቸው ይመለስላቸዋል። የድካም ስሜታቸው ይጠፋና ብርታት ይሰማቸዋል። የዚህን ጊዜ፤ ብዙ ሴቶች ከእንግዲህ ክኒኑ የማያስፈልጋቸው ይመስላቸዋል፤ ክኒን ለማምጣት ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ የለብኝም ብለው ያስባሉ። ነገር ግን ይሄ ስህተት ነው። አደራ አስታውሱ፡ ንግስት ንቦች በእርግዝና ወቅትና ከወሊድ በኋላም ዘወትር ማታ ማታ ይህንን ክኒን መውሰድ ይኖርባቸዋል። አባወራና ሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ ንግስት ንብ በእርግና ወቅትና ከወሊድ በኋላ ሁልጊዜ ማታ ማታ ክኒኑን እንድትወስድ በማስታወስና ክኒኑ ምንጊዜም ከቤት ውስጥ እንዳይጠፋ በማድረግ መርዳት አለባቸው።

ክኒኑን በየቀኑ ለመውሰድ እንዲያስታውሰን ግድግዳ ላይ የሚሰቀል የቀን መቁጠሪያ ለነፍሰጡሮች አዘጋጅተናል።

አስተባባሪ፣ እባክዎን የአይረን ክኒን ቀን መቁጠሪያውን ለተሳታፊዎች ያሳዩዋቸው። የቀን መቁጠሪያው ለሁሉም ነፍሰጡሮችና እመጫቶች ይታደላል።

አስተባበሪ፣ እባክዎን ቴፑን ይዝጉና የክኒኑን ቀን መቁጠሪያ ለነፍሰጡሮች፣ ለእመጫቶች እንዲሁም ለዘር ሴት አያቶች ወደ ቤታቸው ወስደው እዲጠቀሙበት ያድሏቸው።

የቤተሰብ አባላት፣ የአይረን ክኒን አወሳሰድን ለማስታወስ የተዘጋጀውን የቀን መቁጠሪያ በመጠቀም፣ ንግስት ንብ ዘወትር ማታ ማታ ከትንሽ መክሰስና ፍራፍሬ ጋር ክኒኑን እንድትወስድ ያስታውሷት። ተሳታፊዎቻችን የቀን መቁጠሪያውን እስኪያዩ ድረስ፣ እኔ ውሃ ለመጠጣት ወጣ ልበል! (እየሳቀች) ብዙ ከማውራቴ የተነሳ ጉሮሮዬ ደርቋል። እመለሳለሁ።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! ባለቤቴ ገና ውሃ እየጠጣች ስለሆነ፣ እኔ ልቀጥል። እንደተመለከታችሁት የአይረን ክኒኑ ቀን መቁጠሪያ ለአጠቃቀም ቀላል ነው። ዘወትር ማታ ማታ ንግስት ንብ ክኒኑን ስትወስድ፣ በቀን መቁጠሪያው ላይ እለቱን የሚያመለክተውን ባዶ ክብ በስክሪፕቶ በመቀባት እናጠቁራለን። ንግስት ንብ ክኒኑን በወሰደች ቁጥር በየእለቱ ማታ ማታ ይሄን እናደርጋለን። ንግስት ንብ፣ ባለቤቷና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ቀን መቁጠሪውን በማየት፣ ከመኝታ በፊት የአይረን ክኒኑን እንድትወስድ ያስታወሷት።

እስካሁን ክኒኑን መውሰድ ያልጀመራችሁ ነፍሰጡሮች፣ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ አባወራዎች ጭምር በመሄድ በቂ ክኒኖችን ማግኘት ይኖርባችኋል።

Page 46: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

46

ክኒን አልቆ ከቤት መጥፋት ስለሌለበት፣ ንግስት ንብ የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ወደሚሰጥ ጤና ተቋም በመሄድ ክኒኖችን እንድታገኝ ባለቤቷ ሊያግዛት ይገባል።

ነፍሰጡር ሴቶችና እመጫቶች፣ ክኒኑ በአግባቡ እንዲሰራና የአይረን ንጥረነገሩ ከሰውነታቸው ጋር እንዲዋሃድ፣ ክኒኑን ከመውሰዳቸው አንድ ሰአት በፊትና በኋላ ሻይ ወይንም ቡና ከመጠጣት መቆጠብ ይኖርባቸዋል።

አስተባባሪ፣ እባክዎን ቴፑን ይዝጉና፤ ንግስት ንብ ክኒኑን በአግባቡ እንድትወስድ ባለቤቷ ዘወትር ማታ ማታ እንዴት እንደሚያስታውሳትና እንደሚረዳት የሚያሳዩ የግለሰብ ተመክሮ ካርዶችን ለተሳታፊዎች ያሳዩዋቸው።

አያ ሙላት፡- እስቲ በእነዚህ የግለሰብ ተመክሮ ካርዶች ፍሬ ነገርና ምን ትምህርት እንደቀሰምን ትንሽ እንወያይ። ለመወያየት ይረዳን ዘንድ ጥቂት ጥያቄዎችን እናንሳ።

• ምን ተገነዘባችሁ?

• ስለእርግዝናና ስለ አይረን ኪኒን የባልና ሚስት በግልጽ መወያየት ለምን አስፈላጊ ይመስላችኋል?

• እርስዎና ባለቤትዎስ አሁን እንዳየናቸው ጥንዶች፣ እርግዝናን በሚመለከትና በእርግዝና ወቅት የሚከሰተውን የደም ማነስ ችግር ለመከላከል መወያየት ትችላላችሁ? የማትችሉ ከሆነስ ምክንያቱ ምንድነው?

አስተባባሪ፣ እባክዎን ደወሉን ሲሰሙ ቴፑን ይዝጉና ተሳታፊዎች እንዲወያዩ ያግዟቸው። ውይይቱ እንዳለቀ፣ ቴፑን ይክፈቱ።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ። በእማኝነት ካርዶቹ ዙሪያና በቀሰምነው እውቀት ላይ

እንደተወያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። በእርግዝና ወቅት በሚከከሰተው የደም ማነስ ችግርና በመፍትሄው ዙሪያም እንደተነጋገራችሁ አስባለሁ። የባልና የሚስት ውይይት እንዲሁም የባል ድጋፍ፣ የመፍትሄው ዋና አካል ናቸው

እቴ ብርቱካን፡-በህብረተሰባችን ውስጥ ብዙ ሴቶች በእርግዝና ጉዳዮች ላይ ከባሎቻቸው ጋር ከመወያየት የሚታቀቡት፤እፍረት ስለሚይዛቸውና ባሎቻቸው ለመነጋገር ፍላጎት የላቸውም ብለው ስለሚያስቡ ነው። እርግዝናቸውን ለብቻቸው ይዘው መቀጠልንና ዝምታን ይመርጣሉ። ብዙ አባወራዎች በበኩላቸው፣ የእርግዝና ጉዳይ የሴቶች ጉዳይ ነው ብለው ያስባሉ። እንዲያውም፤ የሚስቱን እርግዝና በቅርበት የሚከታተልና ለቅድመ ወሊድ አገልግሎት አብሯት ወደ ጤና ተቋም የሚሄድ ባል፣ ሌሎች ወንዶች ይስቁብኛል ብሎ ይሳቀቃል። ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ ለወንዶች አይመጥንም የሚል ስሜት ይጫናቸዋል።

ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ወሳኝነት ከተረዳችሁ፤ ባልና ሚስት ፅንስ/ዘር ልጃቸው ጤናማ ሆኖ እንዲያድግ ሁለቱ አንድ ሆነው በትብብር ተገቢውን ክትትልና እንክብካቤ መስጠት አለባቸው፡፡ ስለዚህም ነፍሰጡር እናቶች እፍረታቸውን ትተው ተጨማሪ ምግቦችን፣ ኮከብ ምግቦችን እና የአይረን ኪኒን እንዲወስዱ ባሎቻቸው

Page 47: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

47

ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው መጠየቅና መወያየት አለባቸው ማለት ነው። ባሎችም በፋንታቸው ሚስቶቻቸው ባለኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ፤ በተገቢው ሰአት የእናቶችና ህጻናት ህክምና በሚሰጥበት ጤና ጣቢያ አይረን ኪኒን እንዲያገኙ ማበረታታት ይኖርባቸዋል። ባልና ሚስቶች ይህን በማድረጋቸው ጤናማ፣ ጠናካራ እና ብሩህ አእምሮ ያለው ህጻን ልጅ ወልደው በማሳደግ ውጤታማ ይሆናሉ ማለት ነው።

አያ ሙላት፡- ቀደምሲል ደጋግመን እንደገለጽነው ስለተመጣጠነ ምግብ ባልና ሚስት እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር በግልጽ መነጋገር ጠቃሚ መሆኑን አይተናል። በተለይም የእናቶችና የህጻናትን የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስርዐተ ምግብ እንዲሻሻል የባልና ሚስትና የቤተሰብ ግልጽ ውይይተት ወሳኝ ነው፡፡ ግን ከላይ እንደተወያየንበት ባልና ሚስት ተስማምተው መወያየት ለብዙዎች ቀላል አይደለም። በሰላምና በግልጽነት ለመነጋገር በባልም በሚስትም በኩል ጥረት እና ልምምድ ማድረግን ይጠይቃል።

እስኪ ነፍሰጡር ሚስታችን የአይረን ክኒን ማታ ማታ እንድትወስድና ተጨማሪ ኮከብ ምግብ እንድትበላ ለመርዳት ምን ብለን አንደምናወራት ልምምድ እናድርግ፡፡ ምን ይመስላችኋል?

በባልና ሚስቶች መካከል ተወያይቶ/መወሰንን የሚያስተምረንን ጨዋታ ባለቤቴ ብርቱካን በደንብ ታብራራልናለች።

እቴ ብርቱካን፡- ይሄ ጨዋታ እንግዲህ ስለንግስት ንብና እንዴት የተመጣጠነ ምግብ እንደምታገኝ ስለ ሚደረገው ውይይት የምናካሂደው ልምምድ ነው፡፡ እንዴት እንደምንነጋገር፤ እንዴት እንደምንወያይ ከተለማመድን በኋላ ቤታችን ከባለቤታችን ጋር ልንሞክረው እንችላለን።

አስተባባሪ እባክዎን ተሳታፊዎቹን በሥስት ቡድን ይከፋፍሉዋቸው፡፡ እያንዳንዱ ቡድን አራት ወይ አምስት አባላት ይኑረው። ለእያንዳንዱ ቡድን የባል፣ የሚስት እና የሴት አያትን የሚወክሉበት የመጫወቻ ካርድ አንገታቸው ላይ እንዲያንጠለጥሉ ይርዷቸው።

በያንዳንዱ ቡድን ሁሉም ሰው የሚከተሉትን ነጥቦች በየቤቱ ለመነጋገር እና ለመወያየት እንዲችል ልምምድ ያደርጋል ማለት ነው፡-

• ንግስት ንቦች ለሁለት ሠው ስለሚመገቡ እንዴት መክሰስና ለቤተሰባቸውም ምግብ ሲሰሩ መቀማመስ፤ ገበታም ላይ ከቤተሰብ ጋር ሲቀርቡ ተጨማሪ ምግብ እንዴት እንደሚበሉ ቤተሰብ እንዴት ሊረዳቸው ይችላል፡፡ አንድ ቤተሰብ ንግስት ንቦች በየቀኑ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንዲመገቡ እንዴት መርዳት ይችላል?

• ንግስት ንቦች በየቀኑ የአይረን ኪኒን እንዲወስዱ አንድ ቤተሰብ እንዴት መርዳት ይችላል?

አሁን ደግሞ የጨዋታውን ህግ ላብራራላችሁ፡፡

Page 48: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

48

አስተባባሪ እባክዎን እያንዳንዱ ቡድን የሚመለከተውን መመሪያ በመከተል ጨዋታውን ይቀጥሉ፡

• ለባሎች/አባቶች ቡድን፤ እያንዳንዳችሁ የዚህ ቡድን አባላት በተራ ይህንን ጉዳይ ከባለቤታችሁ ጋር እንዴት አንደምትወያዩ ልምምድ ታደርጋላችሁ፡፡

• ለሚስት/እናቶች ቡድን፤ እያንዳንዳችሁ የዚህ ቡድን አባላት በተራ ይህንን ጉዳይ ከባለቤታችሁ እና ከባላችሁ እናት ጋር እንዴት እንደሚትወያዩ ልምምድ ታደርጋላችሁ፡፡

• ለሴት አያቶች ቡድን፤ እያንዳንዳችሁ የዚህ ቡድን አባላት በተራ ይህንን ጉዳይ ከልጃችሁ ሚስትና እና ከልጆቻችሁ ጋር እንዴት እንደምትወያዩ ልምምድ ታደርጋላችሁ፡፡፡

አስተባበሪ እባክዎን ለእያንዳንዱ ቡድን የባል፣ የሚስት እና የሴት አያትን ቦታ ወክለው የሚጫወቱበት ካርድ ይስጧቸው፡፡ በሦስት ከተከፈሉት ቡድኖች ውስጥ ሁለት ሰዎች የደረሳቸውን የባል፣ የሚስት እና የሴት አያት ቦታ ወክለው ይወያያሉ፤ ሌሎቻችሁ በጽሞና ውይይታቸውን ትከታተላላችሁ፡፡ ከአምስት ደቂቃ ውይይት በኋላ የቀራችሁት ተሳታፊዎች ሁለቱ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ፡፡

ጨዋታው እንዲቀላጠፍ አስተባበሪ በቡድኖች መሃከል እየተዘዋወሩ ውይይቱም ሆነ አስተያየቶቹ በስርዐት እንዲካሄዱ ያግዛሉ፡፡ በዚህ ጨዋታ የምታገኙት ልምምድ እቤታችሁ ከባለቤታችሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ለምታደርጉት ውይይት በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በትጋት ተሳተፉ፡፡

• ከአምስት ደቂቃ ውይይት በኋላ ቡድኖቹ የተሰጣቸውን የመጫወቻ ካርድ እየተቀያየሩ ሁለት ያልተጫወቱ ሠዎች ደግሞ ቡድናቸውን ወክለው ለአምስት ደቂቃ እንደገና ውይይት ያደርጋሉ፡፡

• ከአምስት ደቂቃ ውይይት በኋላ የቀራችሁት ተሳታፊዎች ሁለቱ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ እንደበፊቱ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ ማለት ነው፡፡

ዋናውና የዚህ ጨዋታ አላማ ንግስት ንብ ተጨማሪ ምግብና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንድትበላ ከዚህ በተጨማሪም የአይረን ኪኒን ዘወትር ማታ ማታ እንድትወስድ እቤት ከባለቤታችሁና ከሌላው የቤተሰብ አባል ጋር ግልጽ ውይይት እንዴት እንደምታደርጉ እንድትለማመዱ ነው

ሁላችሁም እድል አግኝታችሁ ከተጫወታችሁ በኋላ፤ አስተባበሪ ሁላችሁም አንድ ቡድን እንድትሆኑ ያደርጋሉ፡

እንጀምር?

አስተባባሪ አሁን በቡድን ይከፋፍሏችኋል፤ አስታውሱ የዛሬው ልምምድ ቤታችሁ ስትሄዱ ከባለቤታችሁና ከቤተሰባችሁ ጋር እንዴት መወያየት እንደምትችሉ የሚያስተምር ነው፡

Page 49: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

49

• ንግስት ንቦች ለሁለት ሠው ስለሚመገቡ እንዴት መክሰስ መብላት ለቤተሰባቸውም ምግብ ሲሰሩ እንዲቀማምሱ፤ ገበታም ላይ ከቤተሰብ ጋር ሲቀርቡ ተጨማሪ ምግብ እንዲበሉ ቤተሰብ እንዴት ሊረዳቸው ይችላል?፡፡

• አንድ ቤተሰብ ንግስት ንቦች በየቀኑ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንዲመገቡ እንዴት መርዳት ይችላል?

• ንግስት ንቦች በየቀኑ የአይረን ኪኒን እንዲወስዱ፤ የአይረን ኪኒን የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ አጠቃቀምን እንዲያውቁ ቤተሰብ እንዴት አድርጎ መርዳት ይችላል?

በሉ እንግዲህ፤ በጨዋታው እንደምትደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ!!!

ጨዋታውን እና ውይይታችሁን ስትጨርሱ ከኔ ጋር መልሰን እንገናኛለን። አስተባበሪ ጨዋታው እንዳለቀ እባክዎን ቴፑን መልሰው ይክፈቱት። መልካም ጨዋታ

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ ጨዋታው መቼም እንዳዝናናችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ። አስተባባሪ እባክዎን የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ይርዷቸው።

• ከጨዋታው ምን ተማርን?

• ከቡድናችን አባላት በቤታችን ለመነጋገርና ለመወያየት የሚያግዙ ምን ጠቃሚ ምክሮችን አገኘን

ንግስት ንብ ለሁለት ሠው በቂ ምግብ እንድታገኝና የአይረን ኪኒን እንድትወስድ ከቤተሰብ ጋር ለመናጋገርና ለመመካካር ጨዋታው ዝግጁ አድርጎናል?

አስተባባሪ ውይይቱን ስትጨርሱ፤ በቂ መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች ካሉ እባክዎን ማስታወሻ በመያዝ ከአለቃዎ ወይም ከጤና ኤክሽቴንሽን ሰራተኛ በቂ መልስ ወይም ማብራሪያ አምጥተው ለተሳታፊዎቹ በቀጣይ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት ለተሳታፊዎች ያካፍሉ ፡፡

አስተባበሪ እባክዎ ቴፑን ይዝጉና ውይይቱን ይጀምሩ፤ ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፡፡ መልካም የልምድ ልውውጥ እንዳደረጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። በቤታችን ውስጥ በግልጽነት ለመወያየት እና ለመግባባት ትልቅ ልምድ የምናገኝበት ጨዋታ እንደሆነ አምናለሁ። በግልጽ የመወያየት ችሎታ በአንዴ የሚመጣ ነገር አይደለም እያደር የምናዳብረው ክህሎት እንጂ። አንዳንድ ጊዜ ላይሳካ ይችላል፤ ግን በግልጽ መወያየትና መነጋገር ለንግስት ንብ እና ለዘር ህጻናት የተሻለ ጤና በር ስለሚከፍት ተስፋ ሳንቆርጥ የመግባባት ጥረታችንን መቀጠል አለብን።

Page 50: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

50

አያ ሙላት፡- ጥሩ የውይይት ክፍለ ጊዜ ያሳለፍን ይመስለኛል፡፡ ስለ መጀመሪያ የእርግዝና ወቅት የነፍሰጡር ሴት ስርዐተ ምግብ ብዙ ተምረናል፡ ዛሬ የተማማርናቸውን ዋና ዋናዎቹን ፍሬ ሃሳቦች መልሰን አብረን ለመከለስ እንሞክር።

• በቅድሚያ አንድ ነፍሰጡር ሴት ለሁለት እንደምትመገብ ብዙ ሴቶች ከመደበኛው የገበታ ሰዓት ውጪ መመገብን፣ ጨመር አድረገው መብላትን እንደነውር ይወስዱታል፤ ስለዚህም የነፍሰጡር ቤተሰቦች በገበታም ሰዓት ጨመር አድርጋ በደንብ እንድትመገብ ማበረታታት አለባቸው። በተጨማሪም ነፍሰጡር እናቶች በቤት ውስጥ እንደልብ የሚበላ ነገር እጥረት ያጋጥማቸዋል፤ ይሄም ሲሆን ነፍሰጡር ሴቶች ከአባወራዎች ጋር በቤተሰቡ ገቢ እና ተጨማሪ ምግብ ገዝቶ ሊቀርብ የሚችልበትን መንገድ መወያየትና መመካከር እንዳለባቸው ተምረናል። ‹ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሀኒቱ› በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ተመካክሮ ተባብሮ የመወሰንን አስፈላጊነት ተምረናል።

• የንግስት ንብ መዝሙርን ሰምተናል ተምረናል። የዚህ መዝሙር መልዕክቱም ነፍሰጡር ሴት የምትመገበው ለራሷ ብቻ እንዳልሆነ፤ በመሆኑም ሳታፍር በደንብ መብላት እንዳለባት ማበረታታትና መደገፍ እንደሚያስፈልግ ነው።

• አይረን በተሰኘው ንጥረ ነገር ጉድለት ወይም ማነስ ምክንያት የደም ማነስ ህመም በነፍሰጡርና በጡት አጥቢ እናቶች ላይ እንደሚከሰት ተምረናል።

• ሌላው ትልቅ የተማርነው ነገር፤ አንድ ነፍሰጡር ሴት ስለእርግዝናዋ፤ በተጨማሪም የደም ማነስ በሽታን እንዴት እንደምትከላከል ከባለቤቷ ጋር በግልጽ መነጋጋር ጠቃሚ መሆኑን ነው። ይህም ማለት አንድ ሴት ልክ መፀነሷን እንዳወቀች ወዲያውኑ ለባለቤቷ ማሳወቅ አለባት፡፡ ይህንንም በማድረጓ ባለቤትዋ ሀላፊነት ተሰምቶት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግላት፤ ከጎኗ እንዲቆም ነው፡፡ በተጨማሪም የነፍሰጡር እናት እና የባሏ እናት/ አማቷ ነፍሰጡሯን በመርዳት ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርጉ በመሆናቸው፤ ተገቢውን ኮከብ ምግቦች እንድትመገብ እንዲሁም አይረን ኪኒን በየእለቱ እንድትወስድ ይረዷታል፡

• ነፍሰጡር ሴት ከባለሦስት ኮከብ ምግቦች ቢያንስ አንዱን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ይኖርባታል። ባለሦሰት ኮከብ ምግቦች ከእንሰሳት ተዋፅኦ የምናገኛቸው እንደ ፣ እንቁላል፣ ወተት፣አይብ፣ እርጎ፤ ስጋ፤ኩላሊት፤ጉበት እና አሳ የመሳሳሉት ናቸው። እነዚህ ባለሦስት ኮከብ ምግቦች ነፍሰጡሯን ሴትና በሆዷ የሚገኘውን ዘር/ፅንስ የሚገነባና ጠንካራ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ምግቦች ናቸው።

• ነፍሰጡር ሴትና ቤተሰቦቿ ለደም ማነስ ችግር የሚሆነውን መድሃኒት የእናቶችና የህጻናት ህክምና ከሚሰጥበት ጤና ጣቢያ በቀላሉ ማግኝት እንደሚችሉ ተምረናል።

• ሌላው ነፍሰጡር እናቶች ወደ መኝታ ከመሄዳቸው በፊት መክሰስ በልተው የአይረን ኪኒን ከወሰዱ የማቅለሽለሽ ስሜቱ እንደሚቀንስ ተምረናል።

Page 51: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

• ከዚህ ጋር በተያያዘ ግድግዳ ላይ የሚሰቀል የአይረን ኪኒን የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ አጠቃቀምን ተምረናል፡፡ ለማስታወስ ያህል ንግስት ንባችን የአይረን ኪኒን ስትወስድ ቀን በቀን መቁጠሪያው ላይ ማጥቆር እንዳለባት ተምረናል፤ ኪኒኑን መውሰድ ያለባት በሙሉ የእርግዝና ጊዜዋና ከወለደች በኋላም ለሶስት ወር ማለት ነው፡፡።

ከዚህ በተጨማሪም አንድ ቤተሰብ ንግስት ንብን ለመንከባከብና ተገቢውን ኮከብ ምግቦች እንድታገኝ ለማድረግ የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠር አድርገን ተነጋግረናል። እነዚህም፡-

1. ኮከብ ምግቦችን ማርባትና ማብቀል

2. ከግብርና ምርቶች ከሚገኘው ገቢ ላይ ኮከብ ምግቦችን ከገበያ ገዝቶ ማቅረብ

3. ኮከብ ምግቦችን ማዘጋጀት፣ ሳይበላሹ ማቆየት፤ና ማከማቸት

4. ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች በቂ እረፍት እንዲያገኙና ተጨማሪ ምግብ እንዲመገቡ፤ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንዲበሉና አዘውትረው መክሰስ እንዲበሉ መርዳት

5. ከሁሉም በላይ ደግሞ የእናቶችና ህጻናት የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስርዐተ ምግብን በተመለከተ በባልና ሚስት መሃከል እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር በግልጽ ለመነጋገርና ለመወያየት የሚያደፋፍረንን ጨዋታ ዘና ባለ መንገድ ተጫውተናል።

የዛሬውን ትምህርታችንን ከመጨረሳችን በፊት እስካሁን ከተማርናቸውና ከተወያየንባቸው ነጥቦች ውስጥ መጠየቅ የምትፈልጉት ነገር ወይም ግልጽ ሆኖ ያልተረዳችሁት ነገር ካለ እንድትጠይቁ እጋብዛለሁ። አስተባባሪ ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ ይሞክራሉ፡፡፤ጥያቄያችሁ ዛሬ መመለስ ካልቻለ፤ በቀጣዩ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት ክፍለጊዜያችን መልሶቹን አዘጋጅተን ለመመለስ እንሞክራለን።

አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉትና ምናልባት ጥያቄ ካለ ጠያቂዎች እድል እንዲያገኙ ይርዷቸው፤ ጥያቄዎቹን ተወያይታችሁ ከጨረሳችሁ በኋላ መልሰን እንገናኛለን።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ! ጥሩ የጥያቄና መልስ ውይይት ጊዜ እንደነበራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። በቀጣዮቹም ስምንት የውይይት ክፍለጊዜዎች ብዙ ነገር እንደምንማር ተስፋ አደርጋለሁ።

አያ ሙላት፡- በባልና ሚስት መሀከል እንዲሁም ከቤተሰብ ጋር በግልጽ መነጋገርና መወያየት ምን ያህል ለንግስት ንብ እና በሆዷ ላለው ዘር/ጽንስ ጤንነትና እድገት ጠቃሚ እንደሆነ አይተናል። ይሄ በጣም ትልቅ ትምህርት በመሆኑ በዚህ ዙሪያ አንዳንድ ማስታወሻ አዘጋጅተንላችኋል

51

Page 52: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

52

እነዚህን የተማርናቸውን ነገሮችየሚያስታውሷችሁ እቤታችሁ ይዛችሁ ምትሄዱት የአይረን ኪኒን መውሰጂያ ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ እና ሌሎች ስጦታዎች አዘጋጅተናል።

የአይረን ኪኒን መወሰጂያ ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ቤታችሁ ግድግዳ ላይ ብተሰቅሉት በጣም ይረዳችኋል፡፡ አጠቃቀሙንም ለቤተሰብ አባላት አሳዩዋቸው፡፡

ለዘር ወላጆች ማለትም ነፍሰጡር ሴቶችና ባለቤቶቻቸው እንዲሁም ነፍሰጡር ልጅ ያላቸው ሴት አያቶች ለእናንተ የዘር ምስል ያለው ግድግዳ ላይ የሚለጠፍ ማስታወሻ ትወስዳላችሁ፡፡ እነዚህ ስጦታዎች ብዙ የሚያነጋግሩ ስለሆኑ ለቤተሰቦቻችሁ አሳዩ፡፡ስለ ዶሮ ቤት አሰራር የሚያስተምር በራሪ ወረቀትም አዘጋጅተናል፡፡ እንግዲህ ከዶሮ የሚገኘው እንቁላል ባለሦሰት ኮከብ ምግብ በመሆኑ ለነፍሰጡሯም ሆነ በማህፀኗ ላለው ጽንስ ጤና ጠቃሚ መሆኑን ደጋግመን ተነጋግረናል።

አስተባባሪ እባክዎ ለሚመለከታቸው ተሳታፊዎች ወደ ቤት ይዘዋቸው የሚሄዱትን ስጦታዎች ያድሏቸውና እንዴት እንደሚጠቀሙባቸው ያስረዷቸው። አስረድተው ከጨረሱ በኋላ መልሰን እንገናኛለን።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፤ መቼም የዘር ልጅ ያለው፤ ወይም እመጫት የሆነች

ሴት፤ እንዲሁም ከሶስት ወር በታች የልጅ ልጅ ያላት አያት የአይረን ኪኒን መወሰጂ ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ እንደተሰጣችሁ እና አጠቃቀሙም እንደገባችሁ አምናለሁ።

ሁሉም የዘር ቤተሰብ ማለትም ነፍሰጡር ሴቶች ወይም እርጉዝ ሴት ቤታቸው ያላቸው ባልም ሆነ አያት የዘር ምስል ያለውን ግድግዳ ላይ የሚለጠፍ ስቲከር እንደተሰጣችሁ አምናለሁ፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ሳቅ ብላ መቼም የችግኝ፤ የእንቡጥና የአበባ ልጆች ወላጆች ምን እንዳሰባችሁ አውቃለሁ፤ የእኛስ ስጦታ የታለ እንደምትሉ አውቃለሁ፤ ሀሳብ አይግባችሁ፤ አልረሳናችሁም፤ ለእያንዳንዳችሁ የሚሆን ወደ ቤት የምትወስዷቸው ስጦታዎች በቀጣዮቹ ክፍለ ግዜዎች እንደድርሻችሁ ይሰጣችኋል፤ የዛሬው ውይይት ስለ ዘር ብቻ ስለሆነ ነው፤ ለዘር ወላጆች ብቻ ያደልነው፤ እሺ?

• እሺ፤ እስቲ ስንቶቻችሁ ናችሁ እቤት ስትሄዱ ለቤተሰቦቻችሁ ስጦታችሁን የምታሳዮ? እስቲ እናሳያለን የምትሉ እጃችሁን አውጡ?

• እሺ ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለንግስት ንቦች ተጨማሪ እና ኮከብ ምግቦችን መመገብ እንዳለባቸው የተማርነውን ለቤተሰባችሁ የምታካፍሉ? እስቲ የተማርነውን እናካፍላለን የምትሉ እጃችሁን አውጡ?

• ከናንተ ውስጥ ስንቶቻችሁ ናችሁ ስለ አይረን ኪኒን ከባለቤታችሁ ጋር ለመነጋገርና ለመወያየት የተዘጋጃችሁ? እስቲ እጃችሁን አውጡ?

Page 53: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

• ከእናንተ መካከል የንግስት ንብ መዝሙርን ከቤተሰቡ ጋር ፤ አብሮ የሚዘምርና የሚያስተምር እጁን ያውጣ?

በጣም ጥሩ፤ እሺ መቼም ሁላችሁም እንዳወጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።እሺ ለሁላችሁም አንዴ እናጨብጭብ። (የጭብጨባ ድምጽ)

SFX: የንግስት ንብ መዝሙር ይጀምራል አያ ሙላት፡- ቆይ እስቲ፤ ምንድነው የምሰማው ዜማ? የንግስት ንብ መዝሙር ዜማን

ይመስላል….የዛሬውን ውይይታችንን መደምደሚያ በንግስት ንብ መዝሙር ብንጨርስ ምን ይመስላችኋል? እስኪ አንድ ላይ እንዘምረው አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት…

SFX: የንግስት ንብ መዝሙር ይደመጣል እቴ ብርቱካን፡- በጣም ጥሩ ደስ አይልም ፤ ቆንጆ አድርገን ነው የዘፈንነው፤ አመሰግናለሁ።

ሁለተኛውን የመማማሪያ ክፍለጊዜያችንን ጥሩ አድርገን ስላጠናቀቅን እስቲ ለራሳችን አንዴ እናጨብጭብ። (የጭብጨባ ድምጽ)

አስተባባሪያችሁ የሚቀጥለው የውይይት ክፍለጊዜያችን መቼ አንደሚሆን ይነግሯችኋል፡፡ ለዛሬው ንቁ ተሳትፉችሁ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ፡፡ በሦስተኛው የውይይት ክፍለጊዜያችን ስለ ቀጣዩ እርግዝና ክፍል እስክንወያይ ድረስ ደህና ሁኑ።

አያ ሙላት፡- ደህና ሁኑ።

53

Page 54: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 55: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

መግቢያ

እቴ ብርቱካን፡-ጤና ይስጥልኝ፤ እንደምን ሰነበታችሁ? ለሶስተኛው የዳበረ የማህበረሰብ ውይይት እንኳን በደህና መጣችሁ ።

አቶ ቢራራ መለሰ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስርዐተ ምግብ ቡድን መሪ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ሲናገሩ እንዳደመጣችሁት፤ ሀገር አቀፍ የእናቶች ምግብ አለመጣጠንና የህጻናት መቀንጨር ትልቅ ብሄራዊ ችግር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በዚህም ዙሪያ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎች አዘጋጅተናል፤ በነዚህ ክፍለጊዜዎች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናትና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋናና ቁልፍ የሆኑ ትምህርቶችን እንማራለን፡፡ የዚህ ትምህርታዊ ውይይት ዋናው ዓላማ፤ በቂ እውቀትና ክህሎት ገብይታችሁ፤ ጠንካራ፣ ጤናማ እና ብሩህ ህጻናት አሳድጋችሁ ለቁምነገር እንዲበቁ ማድረግ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-እቴ ብርቱካን እባላለሁ። በሚኖረን የውይይት ክፍለጊዜ በርቀት ሆኜ እመራለሁ። በቆይታችን አንዳንድ ጊዜ የእኔን ድምፅ፤ አንዳንድ ጊዜ የባለቤቴን የሙላትን ድምጽ ትሰማላችሁ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ቀጥታ ከናንተ ጋር ያሉትን አስተባባሪ ባልደረባችንን ትሰማላችሁ፤ እየተቀያየርንና እየተተካካን የትምህርት ክፍለጊዜውን እንመራለን። በየመሃከሉም ለሚኖራችሁ የውይይት ሀሳብ አስተባባሪያችው ቴፑን በመዝጋት እንድትወያዩና የቡድን ስራ እንድትሰሩ ይረዷችኋል። ይሄን የደውል ድምጽ ስትሰሙ (የደውል ድምጽ ይሰማል) ቴፑ ይጠፋል ማለት ነው። የምትሰሩት የቡድን ስራ ወይም ውይይት ሲያበቃ ቴፑ ይከፈትና እኔና ሙላት ካቆምንበት እንቀጥላለን ማለት ነው።

እስቲ እንሞክረው! አስተባባሪ የደወል ድምጽ ሲሰማ አባክዎ ቴፑን ይዝጉትና ከእርስዎ ጀምሮ ሁሉም ሰው እራሱን አስተዋውቆ ሲጨርስ፤ እባክዎ መልሰው እንደገና ቴፑን ይክፈቱት።

የደውል ድምጽ (ይሰማል) እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፤ ሁላችንም በደንብ እየተዋወቅን ይመስለኛል፡፡

ለዛሬ ሌላ አስደሳች ክፍለጊዜ ይኖራችኋል፡፡ የዛሬውን ርዕሰ ጉዳይ ከመጀመራችን በፊት ባለፉት ሁለት ክፍለጊዜያት የተወያየንባቸውን ጽንሰ ሃሳቦች በፍጥነት እንከልሳቸው፡፡

ብዙዎቻችሁ በመጀመሪያው ክፍለጊዜ የተማርነውን እንደምታስታውሱ እርግጠኛ ነኝ፡

አስተባባሪ እባክዎ ፣እርስዎ ለመማማሪያ እንዲረዳ ከተዘጋጀው ከተገላጭ ሰሌዳ ላይ የሱፍ አበባን የዕድገት ደረጃዎች ምስል ለተሳታፊዎች ሲያሳዩ እኔ ባለፈው የተወያየንባቸውን ጉዳዮች እከልሳለሁ፡፡

55

Page 56: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

56

የመጀመሪያውን የእድገት ደረጃ ዘር እንለዋለን፡፡ ይህ ጊዜ ጽንሱ ከተጸነሱበት ቀን ጀምሮ እስከሚወለድ ድረስ ማለትም በእናቲቱ ማህጸን ውስጥ የሚቆይበት ጊዜ ነው፡፡ ነፍሰጡር እናት በእርግዝና ወቅት የምትመገበው የተመጣጠነ ምግብ ከኮከብ ምግቦች ጋር፤ ለእርሷና ለዘር ፅንሱም እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተጨማሪም ነፍሰጡር እናቶች ጠንካራና ጤናማ እንዲሆኑ ዘወትር ማታ ከመተኛታቸው በፊት የአይረን ኪኒን መውሰድ ይኖርባቸዋል፤ ይህም ዘር/ፅንሱንም ጠንካራና ጤናማ እንዲሆን ይረዳዋል፡፡

SFX: JINGLE

ሁለተኛውን የእድገት ደረጃ ችግኝ እንለዋለን፡፡ ይሄም የእድገት ደረጃ አንድ ጨቅላ ህጻን ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ወር እስኪሞላው ያለውን ጊዜ ይይዛል፡፡ ችግኝ በምንለው የእድሜ ደረጃ ላይ ያሉ ህጻናት ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ወራቸውን እስኪጨርሱ የእናታቸውን ጡት ብቻ ነው መጥባት ያለባቸው፡፡ ይህ ማለት ምንም አይነት ተጨማሪ ምግብና ፈሳሽ ወይም ውሃ በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም፡፡

SFX: JINGLE

ሦስተኛውን የእድገት ደረጃ እምቡጥ እንለዋለን፡፡ ይሄ የእድገት ደረጃ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት ያለውን የህጻን ልጅ እድሜ ይይዛል፡፡ ስድስት ወር የሞላቸው ህጻናት ከእናት ጡት በተጨማሪ ለስላሳ ገንፎ፣ የተፈጩና ልመው የተቦኩ ለስላሳ ምግቦች ከኮከብ ምግቦች ጋር መመገብ መጀመር አለባቸው፡፡

SFX: JINGLE

አራተኛውን የእድገት ደረጃ አበባ እንለዋለን፡፡ ይሄ የእድገት ደረጃ ወይም የእድሜ ክልል ከአንድ ዓመት እስከ ሁለት ዓመት ያለው የአንድ ህጻን እድሜ ነው፡፡ አበባ ልጆች መጠኑ ከቀድሞ በርከት ያለና ከኮከብ ምግቦች ጋር በትንሹ ተከታትፈው የተዘጋጁ ምግቦችን መመገብ የሚችሉበት ጊዜ ነው፡፡ ጡት መጥባትም ማቆም የለባቸውም፡፡ ባሎችና ሌሎች የቤተሰብ አባላት ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶችን እንደ ንግስት ንብ ሊንከባከቧቸው፣ በቂ የእረፍትና የመመገቢያ ጊዜ እንዲያገኙም በቤት ውስጥ ሥራ ሊያግዟቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም የሚመገቡት ለሁለት ነውና፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ባለፈው ክፍለጊዜ ስለጉልቻ ጽንሰ ሃሳብና ኮከብ ምግቦች ተወያይተናል፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ እኔ የ“ጉልቻን ጽንሰ-ሃሳብ” ስከልስ፣ እርስዎ ተገላጭ ሰሌዳዎ ላይ የእናቶች ስርዐተ ምግብ ጉልቻን ምስል ለተሳታፊዎቹ ያሳዩዋቸው፡፡ የእንጀራ ምጣድ ሚዛኑን ጠብቆ የሚቀመጥባቸው ሦስት ጉልቻ አምዶች ኮከብ ምግቦችን ይወክላሉ፡

• ቀይ አምድ፡ ከእንሰሳት ተዋጽኦ የሚገኙ የምግብ አይነቶችን የሚወክል ሲሆን እነዚህም ባለሦስት ኮከብ ምግቦች ይባላሉ፡፡

• አረንጓዴ አምድ፡ አረንጓዴ ቅጠላቅጠልና አትክልቶችን የሚወክል ሲሆን

Page 57: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

57

እነዚህም ባለሁለት ኮከብ ምግቦች ይባላሉ፡፡

• ቢጫው አምድ፡ ፍራፍሬን የሚወክል ሲሆን እነዚህም ባለሁለት ኮከብ ምግቦች ይባላሉ፡፡

• ልብ ይበሉ ለህጻናት ስርዓተ ምግብ ቢጫው አምድ የሚወክለው ዘይትና ቅባትን ሲሆን ለበለጠ ሀይልና የሚበሉት ምግብ ለመፈጨት የሚያስፈልጋቸው ስለሆነ ነው፡፡ በተጨማሪም ለሕፃናት የአመጋገብ ስርዓት አረንጓዴው አምድ የሚወክለው አትክልትንና ፍራፍሬን ነው፡፡ ፡

በመጀመሪያው የውይይት ክፍለጊዜያችን የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺ ቀናት መዝሙር ተምረናል፤ እርግጠኛ ነኝ አሁን ሁላችሁም ግጥሙን ታውቁታላችሁ፡፡

በሁለተኛው የውይይት ክፍለጊዜያችን ደግሞ የንግስት ንብ መዝሙርን የሰማንና የተማርን ሲሆን እነዚህን ዘፈኖች ለባለቤቶቻችሁ፣ እና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ለማስተማር እንድትሞክሩ ተነጋግረን ነበር፡፡ ሁላችሁም አስተምራችኋል ብዬ አምናለሁ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ለእያንዳንዱ ጥያቄ እጃቸውን ያወጡትን ሰዎች ብዛት ይመዝግቡልን፡፡

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘፈናችሁ?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የንግስት ንብን መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘፈናችሁ?

• የአይረን ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተርን ለቤተሰቦቻችሁ አሳያችኋቸው? እነርሱስ ምን አሉ?

• ስንቶቻችሁ የአይረን ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተርን በቤታችሁ ግድግዳ ላይ ሰቀላችሁ? ክኒኑን መቼ መውሰድ እንዳለባችሁ እንዲያስታውሳችሁ ቀን መቁጠሪያውን መጠቀም ጀመራችሁ?

• ስንቶቻችሁ የዘር ተምሳሌት ስቲከር ለባለቤታችሁና ለቤተሰብ አባላት አሳያችሁ? እነርሱስ ምን አሉ?

• ስንቶቻችሁ የዘር ተምሳሌት ስቲከርን ግድግዳችሁ ላይ ለጠፋችሁ ?

• ስለ መጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት እንደ ቤተሰብ የወሰናችሁት ውሳኔ ወይም እርምጃ አለ?

እዚህ ጋር ስለተመክሯችሁ ለመወያየት ጥቂት ጊዜ እንውሰድ፡፡ አስተባባሪ፣ እባክዎ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት፣ ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

Page 58: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

58

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! ተመክሯችሁን ከሁሉም የቡድኑ አባላት ጋር በመካፈላችሁ አመሰግናችኋለሁ፡፡ ሁላችሁም ስለንግስት ንብ መዝሙርና ወደቤት ስለወሰዳችኋቸው ቁሳቁሶች ከቡድኑ ጋር ጥሩ ተመክሮ ተጋርታችኋል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁላችሁም የአይረን ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያውን ከባለቤቶቻችሁና ከቤተሰብ አባላት ጋር እንደተወያያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከቤተሰብ ጋር ስትነጋገሩ ያጋጠማችሁ ፈተና ካለ ከአስተባባሪዎችሁና ከቡድኑ አባላት አንዳንድ የመፍትሄ ሃሳቦችንና ጥቆማዎችን እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ይሄ ካልሆነም አስተባባሪ በሚቀጥለው ስብሰባ ለጥያቄዎቻችሁ መልሶች ለማፈላለግ ይሞክራሉ፤ ወይም ደግሞ አንዳንድ ተጨማሪ ድጋፎችን ያደርጉላችኋል፡፡

አሁን ክለሳችንን እንቀጥል፡፡ የምታስታውሱ ከሆነ፣ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ክፍለጊዜዎች፣ ንግስት ንቦች ለራሳቸውና በማህፀናቸው ውስጥ ላለው ዘር/ጽንስ ዘወትር ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ ለመርዳት ስለሚወሰዱ አንዳንድ የቤተሰብ ተግባራት ተወያይተን ነበር፡፡ ይሄንን ለማድረግ በርካታ መንገዶች ያሉ ሲሆን እነዚህ የቤተሰብ ተግባራትም የሚከተሉት ናቸው፡

• ኮከብ ምግቦችን ማርባትና ማብቀል

• የግብርና ምርቶቻችንን በመሸጥ ለኮከብ ምግቦች መግዣ ገንዘብ ማግኘት፤

• ኮከብ ምግቦችን ማዘጋጀት፣ሳይበላሹ እንዲቆዩ ማድረግና በንፅህና ማከማቸት፤

• ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ እናቶች በርከት ያለ ምግብ እንዲመገቡ መርዳት፣ በመደበኛ ምግባቸው ላይ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን ማከል፣ ቶሎ ቶሎ ምግብ በማቅረብ ለሁለት ስለሚበሉ እንዲመገቡ ማበረታታት፤

• የእናቶችና ህጻናት የመጀመሪያዎቹ 1000 ሺህ ቀናት የተመጣጠነ ምግብን በተመለከተ ከባለቤታችሁ ጋር መወያየትና መወሰን፡፡

ባለፈው ክፍለጊዜያችን ስለ ደም ማነስ፣ በሰውነት ውስጥ ስለሚያጋጥም የአይረን እጥረት፣ ስለ አይረን ክኒን አወሳሰድ ፣እንዲሁም ማቅለሽለሽንና ለሁለት መመገብን የተመለከቱ መረጃዎችን ተወያይተናል፡፡

• ነፍሰጡሮችና የሚያጠቡ እናቶች ራሳቸውን ከደም ማነስ ለመከላከል ትክክለኛው መንገድ ዘወትር ማታ ማታ ከመኝታ በፊት ከትንሽ መክሰስ ጋር የአይረን ክኒን መውሰድ እንደሆነ

• በመጀመሪያ የእርግዝና ወቅት ላይ የሚከሰትን ማቅለሽለሽ ለመቆጣጠር በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ከመብላት ይልቅ ትንሽ ትንሽ በቶሎ ቶሎ በመብላት ይረዳል፡፡

• ማቅለሽለሽንና ማስመለስን ለመቆጣጠር ከጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ምክርና ፣ከጤና ጣቢያ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡

• ነፍሰጡር ሴቶች ለሁለት ሰው ነው የሚመገቡት፡፡ ስለዚህ ከመደበኛ ምግባቸው በተጨማሪ ትናንሽ መክሰሶችን በተደጋጋሚ ለመብላት የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡ መደበኛ ምግባቸው ላይ ኮከብ ምግቦችንም መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡

Page 59: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

59

ባለፈው ክፍለጊዜያችን በመጀመርያ የዘር/ጽንስ ወይም የእርግዝና ወቅት ዙርያ የተወያየንባቸውን ጉዳዮች ሁላችሁም ታስታውሳላችሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

እቴ ብርቱካን፡ አሁን ወደ ዛሬው ርእሰ ጉዳያችን እንግባ፡፡ በዚህ በሶስተኛ ውይይታችን ስለ መጨረሻ የእርግዝና ወቅት እና ደረጃ እንዲሁም የዘር/ጽንስ እናቶችና ቤተሰቦች ይሄ ጽንስ ህጻን ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆኖ እንዲያድግ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንወያያለን፡፡ በእርግዝና ወቅት እናትየው ለሁለት መብላት ብቻ ሳይሆን ለራሷ ጥንካሬም ጭምር መብላት አለባት፡፡ ነፍሰጡር እናት ለጥንካሬ ብላ መመገቧ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ልጅ በምትወልድበት ጊዜ ለማማጥ ጥንካሬ ሊኖራት ይገባል፡፡ ነፍሰጡር ሴት ጠንካራ ስትሆን ማህጸኗ ውስጥ ያለው ሕጻንም ጠንካራ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም እናትየዋ በየቀኑ ከምትመገባቸው ኮከብ ምግቦች የምታገኛቸው አልሚ የምግብ ንጥረነገሮች እሷንና በማህጸኗ ውስጥ ያለውን ጽንስም ጠንካራ ያደርገዋል፡ ፡ ነፍሰጡር ሴት በቂ ምግቦች የማትበላና የምግብ ንጥረነገሮች እጥረት ያለባት ከሆነ፣ህጻኑም ለችግር ይጋለጣል፡፡

ለጥንካሬ መብላት ያለውን ፋይዳ በዝርዝር ከመወያየታችን በፊት እስቲ ባለፈው ሳምንት ያደመጥነውን የንግስት ንብ መዝሙርን እንስማ፡

SFX: የንግስት ንብ መዝሙር ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡ የመዝሙሮቹን ቃላት በደንብ አዳመጣችሁ? እናትየዋ ስትዘምር በተለይ እናቶች ትንሽ ትንሽ በተደጋጋሚ መብላት እንደሚያስፈልጋቸው፣ በእርግዝና ወቅት በቂ እረፍት ማግኘት እንዳለባቸው፣ እንዲሁም በተለይ ለእናትየዋ እና ለዘር/ፅንስ ጠንካራ መሆን የቤተሰብ ድጋፍ እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ ለሚጠቅሰው ክፍል ትኩረት ሰጥታችሁ አድምጣችኋል? ነፍሰጡር ሴቶች ለሁለት ሰውና ለጥንካሬ ብለው መብላት ያለባቸው ሲሆን እናቶች ኮከብ ምግቦችን በመብላት ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘታቸው አስፈላጊ መሆኑን ልብ በሉ፡፡

• በንግስት ንብ መዝሙር ውስጥ ቤተሰቧም ንግስት ንባቸውን የሚደግፉና የሚመግቡ ቤተሰቦች ጠንካራ ቤተሰቦች ናቸው ብለው ይዘምራሉ፡፡

• ለነፍሰጡር ሴቶች በመጨረሻ የእርግዝና ወቅት ጥሩ የአመጋገብ ልማድን መጠበቅ ለእናቶችና ለዘር ህጻናት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች ጥንካሬ እንዲያገኙ ከሌላው ጊዜ የበለጠ የሚበሉትን የምግብ መጠን በመጨመር መመገብ አለባቸው፡፡ በመደበኛ የምግብ ሰዓት የሚመገቡትን የኮከብ ምግቦች መጠንም መጨመር ይገባቸዋል፡፡

• ነፍሰጡር ሴቶች ቀኑን ሙሉ ትንሽ ትንሽ ቀላል ምግቦች እንዲሁም ብዙ ኮከብ ምግቦችን እንዲመገቡ በጣም ይመከራል፡፡ በርካታ ነፍሰጡር ሴቶችና ቤተሰቦቻቸው በምግባቸው ውስጥ በቂ ኮከብ ምግቦችን ለማግኘት የተለያዩ ዓይነት ችግሮች ይገጥሟቸዋል፡፡ በዚህ ክፍለጊዜ ነፍሰጡሮች የሚመገቡትን የምግብ መጠን ለመጨመርና በአመጋገብ ሥርዓታቸው ውስጥ ኮከብ ምግቦችን ከማካተት አንጻር የሚያጋጥሟቸውን አንዳንድ የተለመዱ

Page 60: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

60

ችግሮች እንወያይባቸዋለን፡፡ እነዚህን ችግሮች የምንፈታባቸውን መንገዶችም እንማራለን፡፡

• የኤንጂን ጥናት፣ በመጨረሻው ሶስት ወር ነፍሰጡር ሴቶች ሆን ብለው የሚበሉትን ምግብ እንደሚያሳንሱ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች ህጻናት ሲወለዱ ክብደታቸው ዝቅ ያለ እንዲሆን በሚል ሆን ብለው የምግብ አወሳሰዳቸውን ይቀንሳሉ፡፡ ይሄ ምጣቸውን ቀላል እንደሚያደርግላቸውም ያምናሉ፡፡ ይሄ ልማድ ‹‹ምግብን መቀነስ›› የሚባል ሲሆን አንዳንድ ነፍሰጡር ሴቶች የሚመገቧቸውን ምግቦች ከመቀነስም ባሻገር እንደ ፍራፍሬ ያሉ የተወሰኑ ምግቦች ሕጻኑን ያወፍረዋል ብለው ስለሚሰጉ ምጣቸውን ፈታኝ ያደርገዋል ብለው ያምናሉ፡፡

እስቲ የነፍሰጡር ሴቶች ‹‹ምግብን መቀነስ›› በተመለከተ አንዳንድ ባሎች፣ሚስቶች እና ሴት አያቶች የሚሉትን እንስማ-

(የተዋንያን ድምጽ)

o “እሷ እንደገለጸችው፤ ብዙ ምግብ ከተመገበች ህጻኑ ይወፍራል፤ትንሽ ከተመገበች ግን እሷም ጤናማ ትሆናለች፤ ምጧም ይቀልላታል፡፡” (ባል፣ዎሻሶያማ፤ ወነዶ ገነት፣የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት)

o “ሚስቴ በእርግዝና ወቅት ብዙ ምግቦች ከመመገብ ትታቀባለች፡፡ ማንም ሰው በደንብ እንዳትመገብ አይከለክላትም፡፡ ነገር ግን ሯሷን ብዙ ከመብላት ወይም አንዳንድ የምትወዳቸውን የምግብ ዓይነቶች ከመመገብ ታቅባለች፡፡ በምጥ ወቅት ከመቸገር ይልቅ የምትመገበውን ምግብ ለመቀነስ ትወስናለች----ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ጡቷ በቂ ወተት እንዲኖረው በደንብ ለመብላት ታስባለች፡፡ አሁን ግን በቂ ምግብ ከመመገብ ራሷን ታቅባለች፡፡” (ባል ከኦሮሚያ)

o “ችግር የሚፈጥርብን በምጥ ወቅት ነው፡፡ በእጃችን ያሉ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬዎች ብንመገብ ማህጸን ውስጥ ያለው ህጻን ሊወፍር ይችላል፡፡ ያለንን ቀስ በቀስ በመጠኑ ብንመገብ ነው የሚጠቅመን፡፡ ያገኘነውን ሁሉ ከተመገብን ግን ህጻኑ በጣም ይወፍርና ወሊድ ላይ ያስቸግረናል፡፡” (ነፍሰጡር ሴት ከጢሶ፣ሴዴቻ፣ጎማ፣ኦሮሚያ)

እነዚህ ከኤንጂን ጥናት የተወሰዱ አስተያየቶች ናቸው፡፡ አሁን በሰማችኋቸው ዙሪያ ያላችሁን አስተያየትና ተመክሮ እንወያይ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን ያጥፉትና በሰማናቸው አስተያየቶች ዙሪያ የቡድን ውይይት እናካሂድ፡፡ ውይይቱ በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ የሚያጠነጥን እንዲሆን ለማድረግ ይሞክሩ፡

o የቀረቡትን አስተያቶች የሚመስሉ በእናንተ ቤተሰብ ያጋጠሙተመሳሳይ ችግሮች አሉ?

o ከቡድኑ አባላት ውስጥ ምግብን መቀነስ የሚለውን ፈተና የተወጡ ይኖሩ ይሆን ? ካሉ ለተቀሩት የቡድኑ አባላት ተመክሯቸውን ማካፈል ይችላሉ?

Page 61: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

61

ከመካከላችሁ ምጣችንን ያቀልልናል በሚል እምነት ሆን ብለው ትንሽ ትንሽ የሚመገቡ ነፍሰጡር ሴቶች አሉ? ይህን የሚያደርጉ ካሉ ለተቀሩት የቡድኑ አባላት ተመክሯቸውን ሊያካፍሉ ይችላሉ? አስተባባሪ፤ እባክዎ ውይይቱን ሲጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! ነፍሰጡሮች ማህጸን ውስጥ ያለው ሕጻን ክብደቱ አነስተኛ ሲሆን ምጡን ቀላል ያደርገዋል በሚል እምነት ሆን ብለው ‹‹ምግብን መቀነስን›› በተመለከተ እነርሱም ሆኑ ቤተሰቦቻቸው በሚገጥሟቸው ተጨባጭ ችግሮች ዙሪያ ሁሉም ተሳታፊ በቂ ውይይት አድርጓል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

ቀደም ሲል እንደተናገርኩት፤ እነዚህ የተወያያችሁባቸው አስተያቶች ከተለያዩ ክልሎች የተገኙ ሰዎች የተናገሯቸው ናቸው፡፡ ምናልባት ብዙዎቻችሁ በቤተሰባችሁ ውስጥ ተመሳሳይ ችግሮች አጋጥሟችሁ ይሆናል፤ ወይም ያጋጠመው ቤተሰብ ልታውቁም ትችላላችሁ፡፡ እነዚህን ችግሮች እንዴት እንደተወጣችኋቸው አንዳንድ ሃሳቦችን ለቡድኑ አባላት እንዳካፈላችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡

• አብዛኞቹ ቤተሰቦች እነዚህ አባባሎች ትክክለኛ እንደሆኑ የሚያምኑ ሲሆን ነፍሰጡር ሴት በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት ትንሽ ትንሽ መመገቧ ማህፀኗ ውስጥ ያለው ህጻን ክብደቱ አነስተኛ እንዲሆን በማድረግ ምጧን ያቀልላታል ብለው ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ምግብን መቀነስ ነፍሰጡር እናቶችንና ዘር ህፃናትን ለችግር የሚያጋልጥ አደገኛ ልማድ ነው፡፡

• ምግብን መቀነስ ነፍሰጡር እናቶችም ሆነ ዘር ህፃናት የሚያስፈልጋቸውን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እንዳያገኙ በማድረግ፣ እናትየዋ ብርቱ እንዳትሆንና ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ አዕምሮ ያለው ህጻን እንዳትወልድ ያደርጋታል፡፡

• ቀደም ሲል እንዳብራራሁት፣ ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወራት ሁሉ በተለይም በመጨረሻዎቹ ወራት በደንብ መመገባቸውን መቀጠላቸው ወሳኝ ነው፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች በምጥ ወቅት የሚያስፈልጋቸውን ጥንካሬ የሚያጎናጽፏቸውን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች ለማግኘት ቢያንስ በቀን አንድ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች መመገባቸውን መቀጠል አለባቸው፡፡

• ነፍሰጡር ሴቶች የሚመገቡት ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን የአእምሮና የሰውነት እድገታቸው በእናትየዋ የአመጋገብ ሁኔታ ለሚወሰነው በማህጸን ውስጥ ላለው ዘር ህፃንም ጭምር እንደሆነ አይዘንጉ፡፡ ነፍሰጡር እናቶች በንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦችን መብላታቸው ህጻናት ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ አዕምሮ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ምክንያቱም የህጻናት መመገብ የሚጀምረው በማህጸን ውስጥ በመሆኑ ነው፡፡ መሬት ላይ እንደሚዘራ ዘር ሁሉ በማህጸን ውስጥ ያለውም ዘር/ ህጻን፣ እንዲጎነቁልና እንዲበቅል ችግኝ ህፃን እንዲሆን በቅጡ መመገብና ተገቢውን እንክብካቤ ማግኘት አለበት፡፡

Page 62: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

62

• ነፍሰጡር ሴቶች በቤተሰብ የገበታ ሰዓት ተጨማሪ ምግብ እንዲሁም ከመደበኛ የምግብ ሰአቶች ውጪም መክሰሶችን መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሄኛው ለነፍሰጡር ሴቶች ‹‹ምግብ ከመቀነስ›› ይልቅ በቤተሰባቸው ውስጥ ሊተገብሩት የሚችሉት የተሻለ መፍትሄ ነው፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች ‹‹ጥንካሬ ለማግኘት እንዲመገቡ›› ከ ከባለቤታቸውና ከቤተሰብ አባላት ብዙ ማበረታታትና ድጋፍ ማግኘት አለባቸው፡፡

የምጥ ሂደቱን ቀላል ያደርግልኛል በሚል እምነት ሆን ብላ አነስተኛ ምግብ ስለምትመገበውና ፍራፍሬዎችን ከመመገብ ራሷን ስላቀበችው ወርቄ የተሰራውን ድራማ እናዳምጥ፡፡

SFX: የበር መንኳኳት ድምጽ ይሰማል ወርቄ፡- ማነው? ይግቡ

ሙሉ፡- ደህና ዋልክ ደረጄ

ደረጄ፡- እማዬ እንዴት ዋልሽ

ሙሉ፡- ወርቄ፤ አያት ልታደርጊኝ ነው እኮ… ለመሆኑ እንዴት ነሽ? በሞትኩት! ክስት ብለሻል እኮ፤ ባለፈው ካየሁሽ ምንም ለውጥ የለሽም

ወርቄ፡- አይ ወይዘሮ ሙሉ- በተፈጥሮ ቀጭን ስለሆንኩ ይሆናላ፤ ምንድነው ደግሞ ይሄ ሁሉ የተሸከሙት?

ሙሉ- ምሳና ጥቂት ፍራፍሬ አምጥቼልሻለሁ፡፡ ወርቄ፤ እኔ የሰራሁትን ምግብ ምን ያህል እንደምትወጂ አውቃለሁ፡፡ እኔ እጄን ታጥቤ እስክመጣ ለምን ምግቡን ጠረጴዛ ላይ አታደርጊውም፡፡

SFX: ወይዘሮ ሙሉ ሲሄዱ የእግር ኮቴ ይሰማል፡፡ ወርቄ፡- እናትህ እንዴት ጥሩ ሠው ናቸው፤ ሁልጊዜ ምግብ ያመጡልናል፡፡

SFX: ትሪው ጠረጴዛ ላይ ሲቀመጥ ይሰማል ደረጄ፡- በጣም ልዩ ነው፤ ዶሮ ወጥ፣አይብና ጎመን በእንጀራ፡፡ ፓፓያውና ሙዙም ደስ

ይላል፡፡

SFX: የአግዳሚ ወንበር መሳብ፣የትሪና የመብላት ድምጽ ይሰማል

ወርቄ፡- እትዬ ሙሉ ይሄን ሁሉ ምግብ ተሸክመው ማምጣት አያስፈልግም ነበር እኮ

ሙሉ፡- ከኮከብ ምግቦች ጥቂቱን ላመጣልሽ ፈልጌ ነው- የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ባለ 3 ኮከብ እንደሆኑና ለነፍሰጡርና ለሚያጠቡ ሴቶች ተመራጭ መሆናቸውን ታውቂያለሽ? ስለዚህ ነው ዶሮ አርጄ ዶሮ ወጥ የሰራሁልሽ፡፡ ጥቂት ፍራፍሬዎችና አትክልቶችም አምጥቼልሻለሁ፡፡

ደረጄ፡- እማዬ፤ ስለዚህ ጉዳይ እንዴት ይሄን ሁሉ ልታውቂ ቻልሽ ?

Page 63: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

63

ሙሉ፡- ደረጀ ! ባለፈው ዓመት እህትህ እርጉዝ የነበረች ጊዜ የ1000 ቀናት የማህበረሰብ ውይይትን ስካፈል ትዝ ይልሃል? ያኔ ነው የተለያዩ ምግቦችን መመገብና ምግብን ማመጣጠን ስላለው ፋይዳ የተማርኩት፡፡

ሙሉ፡- (ግንባራቸውን ቋጥረው) ወርቄ እየበላሽ አይደለም እኮ? ምነው አልጣፈጠሽም እንዴ?

ወርቄ፡- ኧረ ወድጄዋለሁ! እርስዎ የሰሩትን ምግብ በጣም እንደምወደውማ ያውቃሉ፡፡ አሁን ግን በቅቶኝ ነው፡፡

ሙሉ፡- ምን? አልነካሽውም እኮ፡፡ አሁንም ያቅለሸልሻል እንዴ?

ወርቄ፡- የለም! የለም! እሱማ በእርግዝናዬ መጀመርያ ላይ ነበር፤ አሁን የእርግዝናዬ የመጨረሻ ወቅት ላይ ነኝ፤ስለዚህ መወፈር አልፈልግም፡፡

ደረጄ፡ እማዬ፤ ምንም እኮ አትበላም፤ ዛሬ ጠዋት ቁርሷን ቁራሽ ዳቦ ብቻ ነው የበላችው፡፡ በቃ፡፡ በደንብ ብይ ብላትም አትሰማኝም ፡፡

ሙሉ፡ ወርቄ፤ ለምንድን ነው ሆን ብለሽ ትንሽ ትንሽ የምትበይው? አይርብሽም እንዴ?

ወርቄ፡ መራብማ ይርበኛል፤ እየቻልኩት ነው እንጂ ዝም ብዬ ከበላሁ ሆዴ ውስጥ ያለው ፅንስ ክብደት ይጨምራል፣ ምጤንም አስቸጋሪ ያደርገዋል ብዬ እየፈራሁ ነው እንጂ፡፡

ሙሉ፡ ይሄ በጣም የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ነፍሰጡር እኮ ነሽ፤አንቺና ፅንሱ ከምትመገቢያቸው ምግቦች የሚገኙት ንጥረ ነገሮች ያስፈልጓችኋል፡፡ ለሁለት እንደምትመገቢ አትርሺ፡፡ ጥንካሬ ለማግኘትም መመገብ አለብሽ፤ በምጥ ወቅት አንቺና ፅንሱ መጠንከር አለባችሁ፡፡

ደረጄ፡- አይ እማዬ፤ ፍራፍሬውንማ ባትደክሚ ይሻልሽ ነበር፤ እሱንማ ንክች አታደርገውም፡፡

ሙሉ፡- ለምን ወርቄ! ፍራፍሬ የምትወጂ መስሎኝ ነበር፡፡

ወርቄ፡- እወዳለሁ፤ ግን አሁን ነፍሰጡር ስሆን መብላት አልፈልግም፡፡ ፍራፍሬ ህጻኑን ያወፍረዋል ፤ በሁዋላ በወሊድ ግዜ ወፍሮብኝ መጨናነቅ አልፈልግም፡፡

ሙሉ፡- ምን? የምትይው ሁሉ ትክክል አይደለም፤ ፍራፍሬ ህጻናትን አያወፍሩም፡፡ ደግሞ ይሄን ከየት ነው የሰማሽው?

ወርቄ፡¬- ጎረቤቴ ትዝታ ነግራኛለች፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት እርጉዝ ሳለች ብዙ አትበላም ነበር፤ፍራፍሬ የሚባል ነገርም አልቀመሰችም ፤ለዚህ ነው ምጧ ቀላል የሆነላት፡፡

ሙሉ፡- (እያሽሟጠጡ) ኡሁ ድንቄም ቀላል ሆነላት! ምጡ ቀላል የሆነላት ህጻኑ ቀጫጫና ከተገቢው ክብደት በታች ስለነበረ ይመስልሻል? ያን ምስኪን ልጅ ሰሞኑን አይቼዋለሁ፤አሁን ያለው ሰውነት ለእድሜው የሚመጥን አይደለም፤ምናልባትም ተቀንጭሯል ፡፡ በጣም አደገኛ ነገር ነው ያደረገችው፤ ነገሩ ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር፡፡

ወርቄ:- እንዴት ማለት?

Page 64: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

64

ሙሉ:- በአግባቡ ስላልተመገበች ህጻኑ ማህጸኗ ውስጥ ሞቶ ሊወለድ ይችል ነበር፤ እሷም በወሊድ ሰዐት አቅም ስላልነበራት የጤና ችግር ሊገጥማት ይችል ነበር፡፡ የምትበላውን ምግብ በመቀነስ እራሷንም ሆነ ህጻኑን ለአደጋ አጋልጣለች፡፡

ወርቄ:- ወይኔ ሳስታውሰው ከወለደች በኋላ በእግሯ ቆማ ለመሄድ ብዙ ጊዜ እንደወሰደባት ትዝ አለኝ፤አራስ እንኳን አትመስልም ነበር፡፡ በደንብም አላገገመችም፡፡

ደረጄ:- እማዬ፤ጤናማ ህጻን እንዲኖረን እንፈልጋለን፤ ወርቄም ምንም ችግር እንዲደርስባት አልፈልግም፤ስለዚህ እባክሽ በመጀመርያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናቶች ስብሰባ ላይ የተማርሽውን አካፍይን፡፡

ሙሉ:- ደስ ይለኛል፡፡ ያውም ለልጅ ልጄና የልጄ ሚስት! ይሄውልሽ ወርቄ፤ አሁን በደንብ አዳምጪኝ፡ ለሁለት መብላትሽን አትርሺ አንቺና ልጅሽ ጤናማና ጠንካራ የምትሆኑት አንቺ በደንብ ስትበይ ነው፡፡ የምትመገቢውን የምግብ መጠን መቀነስ የለብሽም፡፡ እንደውም ወትሮ ከምትበይው የበለጠ መብላትና ደጋግመሽ መክሰስ መውሰድ አለብሽ፡፡

ወርቄ:- እንዴት ነው ያንን የማደርገው?

ሙሉ:- ኮከብ ምግቦችን ማለትም የእንስሳ ተዋጽኦ፣አትክልትና ፍራፍሬዎችን በእለት ተእለት ምግቦችሽና መክሰሶችሽ ላይ መጨመር አለብሽ ፡፡ በቤተሰብ የምግብ ሰዓቶችም በዛ አድርገሽ መመገብም አስፈላጊ ነው፡፡

ወርቄ:- ብቻዬን ልበላ? መክሰስ ለብቻዬ? በምግብ ሰዓት ብዙ ልበላ? ኧረ ሴት ልጅ እኮ እንዲህ አታደርግም፡፡

ሙሉ:- እንደሱ ማድረግ ምንም የሚያሳፍር ነገር አይደለም፡፡አንቺ እኮ ንግስት ንብ ማለት ነሽ፡፡ ስለ ንግስት ንብ ታውቂያለሽ? እሷ ከሌለች ሌሎቹ ሰራተኛ ንቦች እንደማይኖሩ አታውቂም? ለአንቺ ደህንነት የቤተሰቡ አባላት በሙሉ ሃላፊነት አለብን፡፡ ስለዚህ አንቺም ሆንሽ በማኅጸንሽ ውስጥ ያለው ዘር/ህጻን ሲወለድ ጤናማና ጠንካራ ይሆን ዘንድ ባለቤትሽ፣ቤተሰብሽና እኔ እንረዳሻለን፡፡ ልጄ፤ለመሆኑ በቤት ውስጥ ሥራዎች እያገዝካት ነው?

ደረጄ:፡- አዎ እያገዝኳት ነው፡፡ እማዬ አንቺ እኮ በደንብ ነው ያሳደግሺኝ፡፡ በደንብ እንድታርፍና በደንብ እንድትመገብ እፈልጋለሁ፡፡ እንደ ውሃ መቅዳትና የማገዶ እንጨት መሸከም ያሉ ሥራዎችን ከጫንቃዋ ላይ አውርጄላታለሁ፡፡ ማታ ማታ አይረን ኪኒን መውሰዷንም አረጋግጣለሁ፡፡ መቼ መውሰድ እንዳለባት ለማወቅ የአይርን ኪኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያውን የምከታተለው እኔ ነኝ፡፡

ወርቄ:- በጣም ነው የሚያግዘኝ፡፡ እሱ ባይኖር ምኑን ከምኑ አደርገው እንደነበር አላውቅም፡፡

ሙሉ:- እንዲህ ነው እንጂ ልጄ፤ አኮራኸኝ፡፡ እኔም እንግዲህ እስክትወልጂ ድረስ እናንተ ጋር ተቀምጬ ምግቦችና መክሰሶችን አዘጋጅጅልሻለሁ፡፡ በምግብሽ ውስጥ ባለኮከብ ምግቦችን እንዴት እንደምታካትቱአስተምራችኋለሁ፡፡ እኔ ያመጣሁትን የምግብ ዓይነት አያችሁ---የእንስሳት ተዋጽኦ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች፣እንደ ስጋና ዶሮ የመሳሰሉ፣ እንዲሁም ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦች እንደ ጎመንና ፍራፍሬ ያሉ ማለቴ

Page 65: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

65

ነው፡፡ እንደተለመደው እንጀራ፣ ዳቦና ጥራጥሬ ብቻ መብላት ሳይሆን የተለያዩ ምግቦችን ማሰናዳት አለባችሁ፡፡፡፡ በየቀኑ ኮከብ ምግቦችን በማከል ብዙ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ አለባችሁ፡፡

ወርቄ:- ዛሬ ብዙ ተምሬአለሁ አመሰግናለሁ እትዬ ሙሉ፡፡ ከእንግዲህ ምክርዎትን ተግባራዊ አደርጋለሁ፡፡ በእርስዎና በውዱ ባለቤቴ ድጋፍ ጤናማ፣ጠንካራና ብሩህ አዕምሮ ያለው ህጻን እንደምወልድ እርግጠኛ ነኝ፡፡፡፡ እስኪ ካመጡት ምግብ ልብላ መሰል፤ ራሴን በረሃብ ጎድቼአለሁ ለካ፡፡

ሙሉ፡- (በፈገግታ) እንደዚህ ነው የእኔ ልጅ! ሌላው በመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ስብሰባ ላይ የተማርኩት ነገር፣ ለወሊድ ወቅት በጋራ የማቀድን አስፈላጊነት ነው፡፡ ደረጄ፤ለወርቄ የትራንስፖርት ወጪ ማስቀመጥ ይኖርብሃል፤ በመጨረሻዎቹ የእርግዝናዋ ወራት ጤና ተቋም ሄዳ የቅድመ ወሊድ ክትትል መቀጠል አለባት፡፡ የምጥ ጊዜዋ ሲደርስም በፍጥነት ወደ ጤናተቋም መውሰድ ይኖርብናል፡፡

ደረጄ፡ ይሄንን በእርግጠኝነት አደርገዋለሁ፡፡ ጤናማና ጠንካራ ልጅ ወልደን ለማየት ጓጉቻለሁ፡፡

እቴ ብርቱካን፡- ለማራኪ ታሪክ ድንቅ ማለቂያ ማለት ይሄ ነው! እናንተም እንደኔ በታሪኩ እንደተደሰታችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እስቲ አሁን ደግሞ ጥቂት ጊዜ ወስደን ስለታሪኩ የተሰማችሁን እንወያይ፡፡

አስባባሪ፤ አሁን ውይይቱን ይመሩልናል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች እንደመነሻ ልብ ይበሉ፡

o መጀመርያ ላይ ወርቄ የምትመገበውን ምግብ በመቀነስና ፍራፍሬ ከመብላት በመታቀብ ለወሊድ ለመዘጋጀት እየሞከረች ነበር እንደዚህ ዓይነት ልማድ ከዚህ በፊት ሰምታችኋል?

o የወርቄ አማት ወርቄን በጤናማና አስተማማኝ ሁኔታ ለወሊድ እንድትዘጋጅ ምን አደረጉ?

o የወርቄ ባለቤት ሚስቱ ለአስተማማኝ ወሊድ እንድትዘጋጅ ምን አደረገ ?

o በመጨረሻም፣ ይሄ ታሪክ በቤተሰቦቻችን እና በማህበረሰባችን ውስጥ በተጨባጭ ሊከሰት የሚችል ነውን? ለምን? ካልሆነስ ለምን?

አስተባባሪ፤ እባክዎ ተሳታፊዎችን ከ4-5 ሰዎች እያደረጉ ይከፋፍሉዋቸውና በታሪኩ እንዲወያዩበትና ከላይ የቀረቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲሞክሩ ያድርጉ፡፡

Page 66: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

66

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ በውይይቱ ወቅት የሚከተሉት ሃሳቦች

እንደተወያያችሁባቸው ተስፋ አደርጋለሁ

• የወርቄ አማት ወርቄ በምግቦቿና መክሰሶቿ ውስጥ ብዙ ኮከብ ምግቦችን እንድታካትት እንዲሁም በቤተሰብ የምግብ ሰዓት በርከት ያለ ምግብ እንድትመገብ ገፋፍተዋታል፡፡ ይህም ንግስት ንብና ዘሩ/ህጻን በወሊድ ሠዐት ጠንካራ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡ ከኮከብ ምግቦች እንዴት ልዩ መክሰሶችንና መደበኛ ምግቦችን አሰናድታ መብላታ እንደምትችል ለማስተማርና በቤት ውስጥ ሥራዎችም ለማገዝ ቃል ገብተውላታል፡፡

• የወርቄ ባል ውሃ መቅዳትና የማገዶ እንጨት መሸከም የመሳሰሉ የሥራ ጫናዎችን አቃልሎላታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቂ እረፍት እንድታገኝና በደንብ እንድትመገብ እንዲሁም ማታ ማታ አይረን ኪኒን እንድትወስድ አበረታቷታል፡፡

• የወርቄ አማት ወርቄንና ባለቤቷን በመጎብኘት ለወሊድ ወቅት በጋራ እንዲያቅዱ ነግረዋቸዋል፡፡ ባለቤቷ ለወሊድ ወቅት ገንዘብ እንዲያስቀምጥም ገፋፍተውታል፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ሁሉም ተሳታፊ ስለ ወርቄ፣ ስለባለቤቷ እንዲሁም ከችግር ስላዳኗቸውና አዋቂ ስለሆኑት ግሩም ሴት አያት ወይዘሮ ሙሉ ጥሩ ውይይት አድርጋችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ወይዘሮ ሙሉ በእርግዝና ጊዜ የምግብን መጠን መቀነስ ምጥን ከማቅለል ይልቅ እሷንና ህጻኑን እንደሚጎዳ በማስረዳት፣ ወርቄ እውነቱን እንድትገነዘብ አድርገዋታል፡፡ በምጥ ወቅት ጠንካራ እንድትሆን በምግቧ ውስጥ ኮከብ ምግቦችን እንዴት እንደምታክል ለማሳየትና ለወሊድ እንድትዘጋጅ ለመርዳት እሷ ጋ መቆየታቸው ደግነታቸውን አያሳይም?

ለጥንካሬ ኮከብ ምግቦችን የመመገብ ፋይዳውን ሁላችሁም እንደተገነዘባችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ጠንካራ እናት ማለት ጠንካራ ህጻን ማለትም ነው፡፡ በተለይ ለነፍሰጡር ሴቶች ባለሦስት ኮከብ ምግቦች የሆኑትን የእንስሳ ተዋጽኦ እንደ ሥጋ፣ እንቁላልና ዶሮ የመሳሰሉትን መመገብ ወሳኝ ነው፡፡ በተጨማሪ እንደ ፍራፍሬና አትክልት ያሉ ባለሁለት ኮከብ ምግቦችም እናቶችን ጠንካራ ያደርጋቸዋል፡፡ መክሰስ በተደጋጋሚ መመገብ ጥንካሬያችሁን ለመጠበቅ ቀላሉ መንገድ እንደሆነ ልብ በሉ፡፡ ማታ ማታ አይረን ኪኒን መውሰዱንም እንዳትዘነጉ፡፡ ይሄ ክኒን የድካምንና የብዥታን ስሜት የሚቀንስ ሲሆን ነፍሰጡር ሴቶች እንዲሁም ዘር/ፅንሱንም ጠንካራ እንዲሆኑ በቂ አይረን ይሰጣቸዋል፡፡

ነፍሰጡር ሴቶች በቂ ምግብ ካልበሉና ኮከብ ምግቦችን ካላገኙ፣በቂ ንጥረነገሮች ባለማግኘት ለሚመጡ የጤና ችግሮች እንደሚጋለጡ ማስታወስ ይገባችኋል፡፡ በወሊድ ወቅት ምጣቸውን ቀላል ከማድረግ ይልቅ ለጽንስ ማስወረድ ወይም ሌሎች ችግሮች የመጋለጥ እድላቸውን በመጨመር የራሳቸውንና የህጻኑን ህይወት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡

Page 67: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

67

• ንግስት ንቦች በመጨረሻው የእርግዝና ወቅት ለራሳቸው እንዲሁም በማህጸን ውስጥ ላለው ዘር/ፅንስ ጥንካሬና ጤንነት ሲሉ በርከት ያለ ምግብ መመገብ ያስፈልጋቸዋል፤

• በዚህ ወቅት የህጻኑ አእምሮና አካል በፍጥነት ስለሚያድግ ተመጣጣኝና ተገቢው ምግብ ይስፈልገዋል፤

• በቂ ምግብ የማትመገብና ኮከብ ምግቦች ከሆኑት ፍራፍሬዎች ራሷን የምታቅብ ሴት፣ ራሷም ሆነች ህጻኑ ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲቆዩ የሚያስችላቸውን የተመጣጠነ ምግብ እንዳያገኙ እየነፈገች ነው፡፡

• አንድ ነፍሰጡር የምትበላውን ምግብ መጠን መጨመር፣ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን መመገብ፣ አይረን ኪኒን መውሰድ፣ ቅድመ ወሊድ ክትትል ማድረግና ስለወሊድ እቅድ ቀደም አድርጎ ከትዳር አጋር ጋር መወያየት ለአስተማማኝና ጤናማ ወሊድ ተመራጭ መንገዶች ናቸው፡፡

በእርግዝና የመጨረሻዎቹ ደረጃዎች ላይ የምትበላውን ምግብ ሆን ብላ በመገደብ ፋንታ እነዚህን ነገሮች ብታደርግ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ለጥንካሬ መመገብን በተመለከተ በበቂ የተነጋገርን ይመስለኛል፡፡ አሁን ለንግስት ንቦች የሚሆን ዕለታዊ የአመጋገብ ማስታወሻ ጨዋታ እየተጫወትን ዘና እንላለን፡፡

አስተባባሪ ለቡድኑ አባላት የንግስት ንብ የዕለታዊ አመጋገብ ማስታወሻ መጫዋቻውን ፣ ከማሽከርያውና ከምግብ ካርዶች ጋር አድርገው ያሳዩዋቸው፡፡ እኔ አጨዋወቱን አስረዳለሁ፡

አስተባባሪ፤ እባክዎን ተሳታፊዎቹን በሶስት ቡድን ከፋፍሉዋቸው፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ቡድን የንግስት ንብ ማስታወሻ ጨዋታ ቁሳቁሶችን ያከፋፍሉ፡፡

ሁሉም ተሳታፊ ጨዋታውን የማየት ዕድል አግኝቷል?

አስተባባሪ፤ ተሳታፊዎቹን በቡድን ሲከፋፍሉና መጫወቻዎቹን ለማደል ቴፑን መዝጋት ካስፈለግዎ አሁኑኑ ይዝጉት፡፡ ዝግጁ ሲሆኑ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX የደወል ድምጽ ይሰማል፡፡

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ! ሁሉም ፊት ለፊት ያለውንየመጫወቻ ምንጣፍ፣ ማሽከርከርያና የምግብ ካርዶች የማየት ዕድል እንዳገኘ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አሁን አጨዋወቱን አስረዳለሁ

• በጨዋታው ምንጣፍ ላይ ያሉት ሦስት ትላልቅ ሰሃኖች ለአንድ ቀን የቤተሰብ መደበኛ የምግብ ሰአት የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ቁርስ፣ ምሳና እራት በሚል ተሰይመዋል፡፡

• ሁለቱ ትናንሽ ሳህኖች ለአንድ ቀን መክሰሶች ሲሆኑ አንደኛው ለረፋድ ጠዋት መክሰስ ሌላኛው ለከሰዓት መክሰስ ነው፡፡

Page 68: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

68

• ቡድኑ የተለያዩ የምግብ ካርዶችን ይመለከትና በቤታቸው ውስጥ ላለችው ንግስት ንብ የዚያን ቀን በመደበኛ የምግብ ሰአትና ለመክሰሶቿ ምን መብላት እንዳለባት አማራጮችን ይወያያሉ፡፡

• አራት ዓይነት የምግብ ካርዶች አሉ፡፡ የዘወትር ምግቦች ካርድ ቡናማ ነው፡፡ የእንስሳት ተዋጽኦ ወይም ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች ካርድ ቀይ ነው፡፡ የአትክልት ካርድ አረንጓዴ ሲሆን የፍራፍሬ ካርድ ቢጫ ነው፡፡ እነዚህ የምግብ ካርዶች የጉልቻውንና የሦስቱን አምዶች ቀለማት ይወክላሉ፡፡

• ዋናው ሃሳብ ከእያንዳንዱ ቀለም/የምግብ ቡድኖች ለእያንዳንዱ መደበኛ የምግብ ሰአት ከአራቱም ዓይነት ካርድ እና አንድ ወይም ሁለት የምግብ ካርድ ለመክሰስ እንድትመርጡ ነው፡፡ ይሄ ማለት ለእያንዳንዱ መደበኛ የምግብ ሰአት (ለምሳሌ ቁርስ) አንድ የዘውትር ምግብ ካርድ፣ አንድ የእንስሳ ተዋጽኦ ምግብ ካርድ፣ አንድ የአትክልት ካርድና አንድ የፍራፍሬ ካርድ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ምርጫዎ የተመጣጠነና ንግስት ንብ በእርግዝና ወቅት ጥንካሬዋን ጠብቃ ለመቆየት የሚያስችላትን የምግብ ንጥረ ነገሮች ሁሉ የያዘ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

እያንዳንዱ ቡድን በንግስት ንባቸው የዕለት የአመጋገብ እቅድ ላይ ተወያይተውና የምግብ ካርዶችን በማስተያየት ሊተገበሩ የሚችሉትን ምርጫዎች ወስነው በእያንዳንዱ ትላልቅ የምግብ ሳህኖችና ትናንሽ የመክሰስ ሳህኖች ላይ ያድርጉ፡፡

• አስታውሱ ንግስት ንቦች ወይም ነፈሰጡር ሴቶች በመደበኛ የምግብ ሰአት ወይም በመክሰስ መልክ በየቀኑ ቢያንስ አንድ ባለ ሦስት ኮከብ ምግብ ማለትም የእንስሳት ተዋጽኦ መመገብ አለባቸው፤ አስታውሱ - ንግስት ንቦች በእያንዳንዱ መደበኛ የምግብ ሰአት ቢያንስ አንድ ባለ ሁለት ኮከብ ምግብ መመገብ አለባቸው፡፡ እነዚህም አትክልቶችና ፍራፍሬ ናቸው፡፡

• በተጨማሪም ንግስት ንቦች በየቀኑ በዛ አድርገው መመገብ አለባቸው - በመደበኛ የምግብ ሰአት ላይ ብዙ በመብላት፣ ምግብ ሲያበስሉ በመቅመስና በየቀኑ ደጋግመው መክሰስ መብላትም ይኖርባቸዋል፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አስተባባሪ አሁን እንጀምር፤ መጫወቻውን ካከፋፈሉ በኋላ እያንዳንዱ ቡድን እንዴት እንደሚጫወት ይመለከታሉ፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ለዚህ ጨዋታ 20 ደቂቃ ይመድቡ፡፡ ከዚያም ስትጨርሱ እያንዳንዱ ቡድን ወደ ትልቁ ቡድን እንዲመለስ ያድርጉ፡፡

አስተባባሪ፤ አሁን ቴፑን ያጥፉና ተሳታፊዎች ጨዋታውን እንዲጀምሩ ይርዷቸው፡፡ ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX : የደወል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ! ጨዋታውን እንደወደዳችሁት ተስፋ አደርጋለሁ፡ አስተባባሪ

እባክዎ ከእያንዳንዱ አነስተኛ ቡድን አንድ ሰው መርጠው ጨዋታው እንዴት እንደተካሄደ እንዲሁም በቡድናቸው ውስጥ ስለጨዋታው ያደረጉትን ውይይት

Page 69: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

69

በተመለከተ ተመክሯቸውን እንዲያጋሩ በመጠየቅ ውይይቱን ያካሂዱ፡፡

በትልቁ ቡድን ውይይት ወቅት፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይጠይቁ

1. የንግስት ንብ የእለታዊ አመጋገብ ማስታወሻ ጨዋታን ወደዳችሁት ?

2. የእለታዊ አመጋገብ ማስታወሻ ውስጥ የቀለላችሁ ምኑ ነበር?

3. የእለታዊ አመጋገብ ማስታወሻ ውስጥ የከበዳችሁ ምኑ ነበር?

4. በጨዋታው ላይ ከቡድናችሁ ተሳታፊዎች ሊተገበሩ ስለሚችሉ ምርጫዎች ምን ምክር አገኛችሁ?

አስተባባሪ፤ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን ያጥፉና ውይይቱን ያስተባብሩ፡፡ ውይይቱን ሲጨርሱ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! በሚቀጥሉት ጥቂት ክፍለ ጊዜያት የየዕለት አመጋገባችሁን ለማቀድ ለመለማመድ በቂ ግዜ ይኖረናል፡፡፡

በተጨማሪም ልጆቻችሁ 6 ወር ሲሞላቸውና እንቡጥ ሆነው ከእናት ጡት ጋር ወፍራም ገንፎና የተፈጩ ምግቦች መመገብ ሲጀምሩ እለታዊ የአመጋገብ ማስታወሻ ላይ እንዴት እንደምታቅዱ ትማራላችሁ፡፡

ይሄ ሌላ ጊዜ የምትማሩት ሌላ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ ለዛሬ ንግስት ንቦች ጠንካራና ጤናማ እንዲሆኑ መመገብ የሚያስፈልጋቸው ምግቦች ላይ እናተኩራለን፡፡

አያ ሙላት፡- ብዙዎቻችን የገበሬ ቤተሰቦች ስለሆንን፣ ነፍሰጡር ሴቶች- ንግስት ንቦቻችን - ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ ማድረግ የምንችልበት አንደኛው ዘዴ በማርባት ወይም በማብቀል ነው፡፡ ባለፈው ስብሰባ፣ ብዙዎቻችን ያሳደግናቸውንና ያበቀልናቸውን ጥቂት ኮከብ ምግቦች በተመለከተ ተወያይተናል፡፡

የግብርና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች የተሻሻሉ የዘር ዓይነቶችና ዘመናዊ የአዘራር ዘዴዎችን በተመለከተ የእርሻ ምክር በመለገስ እንዲሁም በየቀኑና በእያንዳንዱ ምግባችን ውስጥ ኮከብ ምግቦች የመጨመር አቅማችንን ለማሳደግ የሚረዱ ሌሎች ሊተገበሩ የሚችሉ እርምጃዎችን በማሳየት ማገዝ ይችላሉ፡፡

• በዛሬው ክፍለጊዜያችን፣ ብዙዎቹ ቤተሰቦቻችን እየሰሩት ስላለው የዶሮ እርባታ እንነጋገራለን፡፡የዶሮ እርባታ፤ ንግስት ንቦቻችን ከእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች ጋር ያላቸውን ቅርበት ለማሳደግ ሁነኛ መንገድ ነው፡፡ ምክንያቱም እንቁላል ባለሶስት ኮከብ ምግብ ነው፡፡ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት በቀን አንድ እንቁላል መብላት ከቻለች፣ እራሷ እንዲሁም በማህፀኗ ውስጥ ያለው ዘር ጠንካራና ጤናማ እንዲሆኑ ታደርጋለች፡፡

ዛሬ ዶሮዎችን እንዴት እንደምናረባ የምንወያይ ሲሆን በተለይም ለቤተሰቡ ብዙ እንቁላሎችን መስጠት የሚችሉ ጤናማ ዶሮዎች መሆናቸውን ለማረጋገጥ የዶሮ

Page 70: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

70

መኖ አዘጋጃጀት ሂደት ላይ እናተኩራለን፡፡

የምታስታውሱ ከሆነ፣ ባለፈው ክፍለጊዜያችን ስለ ዶሮ ቤት አሰራር ነግሬያችኋለሁ፡፡ ስንቶቻችሁ ናችሁ ለቤተሰቦቻችሁ የዶሮ ቤት ለመስራት ያቀዳችሁት? ሁላችሁም ያቀዳችሁትን እንደምትፈጽሙ ተስፋ አደርጋለሁ!

አሁን አስተባባሪ፤ የዶሮ መኖ አዘገጃጀት፣ እንክብካቤና አያያዝን የሚመለከት ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ለቡድኑ አባላት ያከፋፍሉልናል፡፡

1. ጥሩ ባሎች ንግስት ንቦቻቸው በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜእንደ አንቁላል ያለ አንድ ባለ 3 ኮከብ ምግብ እንድትመገብ ያደርጋል፡፡

2. ባሎች ጥራት ያለው የዶሮ ምግብ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ነገሮችን በዝርዝር የያዘውንና ስለ አያያዝና እንክብካቤ መረጃ የሚሰጠውን በራሪ ወረቀት ማንበብ አለባቸው፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን ያጥፉና ተሳታፊዎች በዶሮ እርባታ ዙሪያ ስላላቸው ተመክሮ ውይይት እንዲካሄድ ያድርጉ፡፡ ውይይቱን ለማቀላጠፍ እባክዎ ተከታዮቹን ጥያቄዎች ይጠይቁ

1. ንግስት ንቦች፣ ባሎች/አባቶች ወይም ሴት አያቶች ስለዶሮ እርባታ ያላቸውን ተመክሮ ለቡድኑ አባላት እንዲያካፍሉ ይጠይቁ፡፡

2. ስንቶቻችሁ ዶሮዎች አሏችሁ?

3. ስንቶቻችሁ በቤታችሁ የዶሮ ቤት አላችሁ?

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል አያ ሙላት፡ እንኳን ደህና መጣችሁ! በንግስት ንቦቻችን ምግቦች ውስጥ ተጨማሪ ኮከብ ምግቦች

እንዲካተቱ የማድረግ አንዱ መንገድ እነዚህን ምግቦች ከገበያ መሸመት ነው፡፡ የእርሻ እህሎችን በገበያ ሸጠን ከምናገኘው ገንዘብ ጥቂቱን እነዚህን ኮከብ ምግቦች ለመግዛት ልናውለው እንችላለን!

ባል ሚስትና የቤተሰብ አባላት ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ሲያደርጉ እንዲሁም ከቤተሰቡ ገቢ ወይም ሌሎች የሃብት ምንጮች ጥቂቱን ለንግስት ንቦቻችን ኮከብ ምግቦችን ለመግዛት የሚደረጉ ውሳኔዎችን ሂደት ቀላል የሚያደርጉ አንዳንድ የተግባቦት ክህሎቶችን የምንለማመድበት ጥቂት ጊዜ ወደፊት ይኖረናል፡፡

አሁን ተሳታፊዎችን ጥቂት ጥያቄዎች መጠየቅ እፈልጋለሁ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን ያጥፉትና ተሳታፊዎች ስለዶሮ እርባታ ባላቸው ተመክሮ ዙሪያ ውይይት ያመቻቹ፡፡ ውይይቱን ለማቀላጠፍ እባክዎ ተከታዮቹን ጥያቄዎች ይጠይቁ፡፡

1. ዶሮ የማያረቡ ከሆነ ስለ እንቁላል ግዢ ልምዳቸውን ያካፍሉ

2. ዶሮዎችን ወይም እንቁላሎችን የት ነው የምትገዙት? በአካባቢያችሁ የዶሮ ወይም የእንቁላል ዋጋ ምን ያህል ነው?

Page 71: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

71

አስተባባሪ፤ ውይይቱን ሲጨርሱ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን በደህና መጣችሁ! የእንቁላልንና የዶሮ ዋጋን በተመለከተ ጥሩ ውይይት እንዳደረጋችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ በተለይ በበዓል ጊዜያት ምንም እንኳን ዋጋቸው ቢንርም፣ ሁልጊዜ ዶሮ ለመግዛት አቅም ባይኖራችሁም፣ ለብዙ ቤተሰቦች እንቁላል በንፅፅር ርካሽና መግዛት የሚቻል ነው፡፡ እንቁላል ባለሦስት ኮከብ ምግብ እንደመሆኑ ለንግስት ንቦች አስፈላጊ ነውው፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ቋንጣን ማዘጋጀት በጣም ቀላል ነው፡፡ ሁላችሁም ቋንጣን የምታዘጋጁበት የራሳችሁ መንገድ እንዳላችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ሆኖም እስቲ ፈጣን የምለውን የእራሴን የአዘገጃጀት መንገድ ላካፍላችሁ፡፡ እንደ ሁልጊዜው፣ ምንም አይነት ምግብ ከመንካታችሁ ወይም ማዘጋጀት ከመጀመራችሁ በፊት እጃችሁን በውሃና በሳሙና መታጠባችሁን እንዳትዘነጉ፡፡

1. ጥቂት ስጋ መግዛት ወይም ቤት ውስጥ የተረፈ ስጋ ካለን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ሥጋውን በረዥሙ መዘልዘል፤

2. በርበሬ ወይም አዋዜ፣ ትንሽ ዘይት፣ ጥቂት የሎሚ ጭማቂ፣ የተፈጨ ጥቁር አዝሙድና ጨው በአንድ ላይ ደባልቁት፤

3. ሥጋውን በበርበሬው ውህድ ማሸትና ውህዱ ውስጥ ማቆየት፤

4. በቂ አየር በሚገባበት ክፍል ውስጥ ህፃናት ወይም የቤት እንስሳት እንዳይደርሱበት አርቆ ገመድ ላይ መስቀልና ለጥቂት ቀናት እንዲደርቅ መተው፤

5. ቋንጣ በክረምት ወራት መዘጋጀት የለበትም፤ አየሩ ርጥበታማ ስለሆነ ቋንጣን ለማድረቅ አይሆንም፡፡

ቋንጣ ለመድረቅ ጥቂት ጊዜ ሊፈጅ ይችላል፤ አንድ ጊዜ ከደረቀ ግን ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ ሊቀመጥና በተፈለገ ጊዜ ሊበላ ይችላል፡፡ ለነፍሰጡር ሴቶችና ለህፃናት ትክክለኛ (ተመራጭ) መክሰስ ነው፡፡

ቋንጣን ሽሮ ውስጥ ወይም ፍርፍር ላይ አሊያም በማንኛውም ሌላ ዓይነት ወጥ ውስጥ መጨመር ወይም ደግሞ እንደመክሰስ ደረቁን መብላት ትችላላችሁ፡፡ ለልጆች ደግሞ አንድ ዘለላ ቋንጣ ተወቅጦ የሚበሉት ገንፎ ላይ ነስንሶ አብሮ ማብሰል ይቻላል፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ብዙ ሴቶች በእርግዝና የመጨረሻ ወራት ላይ እንደበፊቱ የማቅለሽለሽ ስሜት አይሰማቸውም፡፡ በዚህ ወቅት ነፍሰጡር ሴቶች የረሃብ ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችሁ ይሄ ነገር ደርሶባችኋል፤ ወይም ደግሞ ተመሳሳይ ነገር የደረሰባት ነፍሰጡር ሴት ታውቃላችሁ፡፡ ነገር ግን የምግብ አወሳሰዳቸውን ሆን ብለው የሚቀንሱ በርካታ ነፍሰጡር ሴቶች አሉ፡፡

Page 72: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

72

ምክንያቱም ማህፀን ውስጥ ያለው ህፃን ካልወፈረ በምጥ ሰዓት ያለችግር በቀላሉ እንገላገላለን ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡ ነፍሰጡር ሴቶች ለሁለት ሰው እንደሚመገቡ ማስታወስ ተገቢ ነው፤ ስለዚህም የተለመዱትን ዋና ምግቦች ጨምሮ ትንሽ ትንሽ መክሰሶችን ደጋግሞ ለመብላት የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው፡፡ ኮከብ ምግቦችንም ማከል ይኖርባቸዋል፡፡ አንዲት ነፍሰጡር በራሷ ላይ ልትፈጽመው የምትችለው የከፋ ነገር ቢኖር መመገብን ከእነአካቴው መተው ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡- ንግስት ንቦች በእርግዝና የመጨረሻ ወራት ላይ ብዙ የእረፍት ጊዜ ማግኘታቸውን ማረጋገጫ አንዱ መንገድ የምግብ ማብሰያና የቤት ውስጥ ሥራዎች መስሪያ ሰዓቶችን ለመቀነስ መላ መፈለግ ነው፡፡ የቤተሰቡ አባላት ሁሉ ንግስት ንቦችን በቤት ውስጥ ስራዎች ለማገዝ መተባበር አለባቸው፡፡

አንዱ መንገድ ግን በአሁኑ ወቅት በመተዋወቅ ላይ ስላለው የተሻሻለ (ዘመናዊ)፣ ጊዜ ቆጣቢ የማብሰያ ምድጃ ለቤታችሁ እንዴት እንደምታገኙ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ ወይም የግብርና ኤክስቴንሽን ሰራተኛን መጠየቅ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡ የባልና ሚስት ተወያይቶ/መወሰንን የሚያስተምረንን በተለይ የቤተሰብን ገቢና ለንግስቲቷ ንብ የሚያስፈልጋትን ምግቦች ለማርባትና ለማብቀል የሚረዳንን ጨዋታ አሁን እንለማመዳለን፡፡

ባለፈው ክፍለጊዜያችን እንዴት ሌሎችን ወክሎ መጫወት (መተወን) እንደሚቻልና የባሎችን፣ የእናቶችንና የሴት አያቶችን የሚወከልበት የመጫወቻ ካርድ እንዴት እንደምንጠቀም ተምረናል፡፡

ንግስት ንቦችና ህፃናቶቻቸው ብዙ ምግብ እንዲመገቡ፣ ብዙ እረፍት እንዲወስዱና ብዙ ኮከብ ምግቦችን እንዲያገኙ ለመርዳት እንዴት ከቤተሰቦቻችን ጋር እንደምንወያይ ለመለማመድ በትናንሽ ቡድኖች በመከፋፈል ጥቂት ተጨማሪ የውክልና ትወናዎችን እንሰራለን፡፡ መጀመሪያ ግን በትልቁ ቡድን ውስጥ እንዳላችሁ ፈጣን ትወና እንስራ፤ አሁን የምንሰራው የእንስሳትን የውክልና ካርድ በመጠቀም ነው፡፡

አሁን ደግሞ አስተባባሪ ለሁላችንም የአህያን፣ የአንበሳን እና የማርና ውሃ/ ጉሬዛን የሚወክሉ የሚና ጨዋታ መጫወቻ ካርዶችን ለሁሉም ያሳዩዋችኋል፡፡ እባክዎን ካርዶቹን በአንገታቸው ላይ እንዴት እንደሚያንጠለጥሉት ያሳዩዋቸው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-እስቲ መጀመሪያ እኔ ላስረዳችሁ፡ ስለእያንዳንዱ የእንሰሳት ገጸባህሪ ሳስረዳ አስተባባሪ በካርዱ ላይ ያለውን ምስላቸውን ያሳዩዋችኋል ማለት ነው፡፡

እባክዎን የአንበሳውን ምስል የያዘውን ካርድ ለሁሉም ያሳዩዋቸው፡፡

• አንበሳ በጣም ቁጡና በጣም የሚጮህ/ የሚያገሳ እንስሳ ነው፡፡ አንበሳ ሌላው ስለሚያስበውም ሆነ ስለሚናገረው ግድ አይሰጠውም፡፡ አንበሳ ንጉስ መሆንን አጥብቆ ይሻል፤ ሌላው ሰው ስለሚኖረው አስተያየትና ሃሳብ ለማዳመጥ ትእግስት የለውም፡፡ በመሆኑም ስለንግስት ንብም ሆነ ስለ

Page 73: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

73

የተመጣጠነ ምግብ ጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ሃሳቦችን ለመስማት ትዕግስት የሌላቸውና ሙግትና ጩህት የሚቀናቸው ሰዎች ልክ እንደ አንበሳ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ስለንግስት ንብም ሆነ ስለተመጣጠነ ምግብ በቂ እውቀት ያላቸው፤ ነገርግን አዲስ ሃሳብን እና ጠባይን በቤተሰቦቻቸው ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከውይይትና ከማግባባት ውጪ በጉልበት ለማሳመን የሚሞክሩ ሰዎች ልክ የአንበሳው አይነት ገጸባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡

አስተባባሪ እባክዎ የአህያውን ምስል የያዘውን ካርድ ለሁሉም ያሳዩዋቸው፡፡

• አህያ ቸልተኛ እንስሳ ነች፡፡ አህያ ለማንም ለምንም ግድ የላትም/አትጨነቅም፡፡ አህያ ሀሳብም ሆነ አስተያየት ለማንም አታካፍልም፤ ይልቁንም ምንም ነገር ቢፈጠር ስህተት መሆኑን እያወቀች እንኳ ለማረም ከመሞከር ይልቅ ዝም ብላ ትቀበላለች፡፡ ስለዚህም ስለንግስት ንብም ሆነ ስለተመጣጠነ ምግብ በቂ ትምህርት ተምረው ፤ከቤተሰባቸው ጋር ስለተማሩት ትምህርት የማይወያዩና እሚያውቁትን ለቤተሰባቸው የማያካፍሉ ሰዎች ልክ የአህያዋ አይነት ገጸባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡

እባክዎን የማርና የውሃ ወይም የጉሬዛውን ምስል የያዘውን ካርድ ለሁሉም ያሳዩዋቸው፡፡

• ማርና ውሃ/ጉሬዛ የተከበሩና እራሳቸውን የሚያከብሩ ናቸው፡፡ ጉሬዛ/ማርና ወሃ ሃሳብን ማካፈልና ሁሉም ሰው የሚመስለውን ሃሳብ እንዲያበረክት በሚያስችል በንግግር ያምናል፡፡ ማርና ውሃ/ጉሬዛ ትዕግስተኛ እና የተረጋጋ ከመሆኑም ባሻገር፤ ሲናገር ቁጡነት የማይታይበት በራስ መተማመን የሚታይበት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት የማርና ውሃ/ጉሬዛ ያላቸው ሰዎች ብዙ ሰዎች ያደንቁዋቸዋል፡፡ ስለ ንግስት ንብ እና ስለተመጣጠነ ምግብ የተማሩትን እና አዳዲስ ሃሳቦችን ከቤተሰባቸው ጋር የሚወያዩና የሚማማሩ፤ በተግባርም ለመለወጥ የሚያስችሉትን መልካም ትምህርቶችን የሚያካፍሉ ሰዎች የማርና ወሃ/የጉሬዛ ጠባይ/ገጸ ባህሪ ያላቸው ናቸው፡፡

አሁን ደግሞ አስተባበሪ ሶስት ፈቃደኞች ከፊትለፊት እዲወጡ ያድርጉና በእያንዳንዳቸው አንገት ላይ አንድ ካርድ ያንጠልጥሉላቸው፡፡

የመጀመሪያው በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊ አንገት ላይ የአንበሳ ምስል የያዘውን ካርድ ያንጠልጥሉ ከዚያም ተሳታፊው ፤ ልክ እንደአንበሳ ገጸባህሪ አስመስሎ እንዲጫወት ይንገሩዋቸው፡፡፡፡

ሁለተኛው በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊ አንገት ላይ የአህያ ምስል የያዘውን ካርድ ያንጠልጥሉ ከዛም ተሳታፊው ፤ ልክ እንደ አህያ ገጸባህሪ አስመስሎ እንዲጫወት ይንገሩዋቸው፡፡፡፡

ሶስተኛው በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊ አንገት ላይ የየማርና ውሀ/ጉሬዛ ምስል የያዘውን ካርድ ያንጠልጥሉ ከዛም ተሳታፊው ፤ ልክ እንደ ማርና ውሀ/ጉሬዛ ውሀ ገጸባህሪ አስመስሎ እንዲጫወት ይንገሩዋቸው፡፡

Page 74: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

74

እቴ ብርቱካን፡-የአንበሳ ምስል ካርድ በአንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉት በጎ ፈቃደኞች እንደ እራሳቸው ሆነው እንደ አንበሳ ገፀ ባህሪ ድምፃቸውን ቁጡና ትግስት በሌለው ስሜት እየጮሁ አረፍተነገሩን ይናገራሉ፡፡

• በአንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉት በጎ ፍቃደኞች እንደ እራሳቸው ሆነው እንደ አህያው ገጸባህሪ በግዴለሽነት፣ በጣም በቀስታ እና በደንታቢስነት አረፍተነገሩን ይናገራሉ፡፡ በአንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉት በጎ ፍቃደኞች እንደ እራሳቸው ሆነው እንደ ማርና ውሃ/ጉሬዛ በራስ በመተማመን፣ በደግነት እና ለሌሎች በመጨነቅ የሌሎችንም አድናቆት በሚስብ መልኩ አረፍተነገሩን ይናገራሉ፡፡ ፡፡

እሺ ሁላችሁም ከተዘጋጃችሁ ፤ እንጀምር፡፡

• አስተባባሪ የባሎችን ቡድን ጨዋታ እያስተባበሩ ከሆነ፤ ማለት የሚገባቸው የሚከተለውን አረፍተነገር ነው፤ ‹‹ ሚስቴ በየእለቱ ተጨማሪ ኮኮብ ምግቦችን የምታገኝበትን መንገድ እስቲ አንነጋገር፡፡››

• አስተባባሪ የሚስቶችን ቡድንን ጨዋታ እያሰተባበሩ ከሆነ፤ ማለት የሚገባቸው የሚከተለውን አረፍተነገር ነው፤ ‹‹ባሌ በየእለቱ ተጨማሪ ኮኮብ ምግቦችን ስለማገኝበት መንገድ እስቲ እንነጋገር፡፡››

• አስተባባሪ የሴት አያቶችን ቡድን ጨዋታ እያስተባበሩ ከሆነ፤ ማለት የሚገባቸው የሚከተለውን አረፍተነገር ነው፤ ‹‹ የእኔ ምራት በየእለቱ ተጨማሪ ኮኮብ ምግቦችን ስለምታገኝበት መንገድ እስቲ እንነጋገር፡፡››

አስተባባሪ፤ ቴፑን ይዝጉትና ተሳታፊዎች ጨዋታውን አንዲጫወቱ ይርዷቸው፡፡ ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ያብሩት

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ! ሁሉም ተሳታፊዎች ተናግረውና ተጫውተው ሲጨርሱ

፤ ተሳታፊዎች ምን እንደተመለከቱና ምን እንዳደመጡ እንዲያብራሩ ይጠይቋቸው፡፡

ተሳታፊዎች በጨዋታው ዙሪያ ያገኙዋቸው ተመክሮዎች እንዲወያዩባቸው በማስተባበር ይርዷቸው፡፡ ውይይቱም የተቃና አንዲሆን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይጠይቋቸው፡፡

ሀ እንደተመለከታችሁት፤ ሦስቱም በጎ ፈቃደኛ የተሰጣቸውን ገጸባህሪ ጥሩ አድርገው ተጫውተዋል ?

ለ ለመሆኑ እነዚህ ሶስት የአነጋገር አይነቶች የምታውቋቸው ሠዎችና ከእነሱ ጋር ያደረጋችሁትን ውይይት ያስታውሳችኋል?

ሐ ከሶስቱ የአነጋገር አይነቶች ማለትም ከአንበሳው፣ ከአህያ ወይም ከጉሬዛው/ ማርና ውሀ ፣ በባልና ሚስት እና በቤተሰብ መካከል መፍትሄ ለመፈለግና ሃሳብ ለመለዋወጥ በይበልጥ ውጤታማ ነው የምትሉት የትኛውንነው?

አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉና እነዚህን ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ጋር ተወያዩ፤ ስትጨርሱ ቴፑን ያብሩት

Page 75: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

75

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፡ የማርና ውሃ/ጉሬዛ የአነጋገር አይነት ልናዳብረው የሚገባን ጥሩ ክህሎትነው፤ እኛም በፋንታችን እዚህ የተማርነውንና ያወቅነውን እቤታችን ስንሄድ ከቤተሰባችን ጋር ለመወያያየትና ለመማማር የሚያግዘን ልምድ ነው፡፡

አያ ሙላት፡- ጥሩ ብለሻል፤ አሁን ደግሞ ልክ እንደ ማርና ውሃ/ጉሬዛ በመሆን በትንንሽ ቡድን በመሆን እንለማመዳለን፡፡ አስተባባሪ እባክዎን ሦስት ቡድኖችን በመፍጠር ለጨዋታው እንዲዘጋጁ ያድርጉ

እባክዎን የባል፣ የሚስት እና የሴት አያት መጫወቻ ካርዶችን በማውጣት ለእያንዳንዱ ቡድን ያድሏቸው፡፡

አያ ሙላት፡- በሦስት ከተከፈሉት ቡድኖች ውስጥ ሁለት ሰዎች የደረሳቸውን የባል፣ የሚስት እና የሴት አያት ቦታ ወክለው ይጫወታሉ፤ ሌሎቻችሁ በጽሞና ውይይታቸውን ትከታተላላችሁ፡፡ ከአምስት ደቂቃ ውይይት በኋላ የቀራችሁት ተሳታፊዎች ሁለቱ በተነጋገሩበት ጉዳይ ላይ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ፡፡

ጨዋታው እንዲቀላጠፍ አስተባበሪ በቡድኖች መሃከል እየተዘዋወሩ ውይይቱም ሆነ አስተያየቶቹ በስርዐት እንዲካሄዱ ያግዛሉ፡፡ በዚህ ጨዋታ የምታገኙት ልምምድ እቤታችሁ ከባለቤታችሁና ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ለምታደርጉት ውይይት በጣም ጠቃሚ ስለሆነ በትጋት ተሳተፉ፡፡

የቤተሰብ ማለትም የባል፤ የሚስት፤ የአያትን ወክለው በሚጫወቱበት ጊዜ የአነጋገራችሁን አይነት ልክ አንደ ማርና ውሃ/ጉሬዛ አድርጉ፤ በተቻላችሁ መጠን በራስ በተማመን፤ በትዕግስትና በደግነት የተሞላ ሲሆን ሌሎች የሚናገሩት ነገር ሌሎች የሚናገሩት ማዳመጥ አትዘንጉ፡፡

ይህ ዘና የሚያደርግ ጨዋታ ስለሆነ እነዚህን የንግግር ክህሎቶችን ከቤተሰብ ጋር ለመነጋገር ይረዳችኋል፡፡

ከአስር ደቂቃ በኋላ ሶስቱ ተሳታፊዎች ሠው ቀይረው፤ አዳዲስ ሠዎች እንዲጫወቱ ያድርጉ፡፡

ዋናውና የዚህ ጨዋታ አላማ ንግስት ንብ ተጨማሪ ምግብ እንድትበላና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦችን እንድትመገብ እንዲሁም የአይረን ኪኒን ዘወትር ማታ ማታ እንድትወስድ እቤት ከባለቤታችሁና ከሌላው የቤተሰብ አባል ጋር ግልጽ ውይይት እንዴት እንደምታደርጉ እንድትለማመዱ ነው፡፡

ሁላችሁም እድል አግኝታችሁ ከተጫወታችሁ በኋላ፤ አስተባባሪ ሁላችሁም አንድ ቡድን እንድትሆኑ ያደርጋሉ፡፡

አስተባባሪ ቴፑን ያጥፉትና ተሳታፊዎች ጨዋታውን እንዲጫወቱ ይርዷቸው፤ ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

Page 76: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡ እንኳን ደህና መጣችሁ፤የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች በማሰብ ተሳታፊዎቹን ያወያዩዋቸው

1. በዚህ ጭውውት ምን ተማራችሁ

2. ከእያንዳንዱ ቡድን ያገኘነው አስተያየት ንግግራችንን ልክ አንደ ማርና ውሃ/ ጉሬዛ እንዲሻሻልልን ያገኘነው ምክር ምንድን ነው

3. ከዚህ ጭውውት በኋላ ከቤተሰብ አባላት ጋር ለመወያየት በቂ ክህሎት ያገኛችሁ ይመስላችኋል፤ ያገኛችሁትስ ልምድ ንግስት ንቦችን በቂ ምግብና እረፍት እንዲያገኙ፤ የአይረን ኪኒን እንዲወስዱ እንዲሁም ለወሊድ እንዲሰናዱ ለማነጋገር ለመምከር የሚረዳችሁ ይመስላችኋል

አስተባባሪ ቴፑን ያጥፉና በእነዚህ ጥቄዎች ላይ ተወያዩበት፤ ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ያብሩት፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ፤ መቼም ጨዋታውና ውይይቱ ዘና የሚያደርግ ሆኖ እንዳገኛችሁት እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከባለቤታችን ጋር በግልጽ የመነጋገርና የመወያየት ልምድ/ችሎታችንን ለማዳበር መለማመዱ ጠቃሚ ነው፡፡ መርሳት የሌለብን ልክ እንደ ማርና ውሃ/ጉሬዛ ጥሩ አድርጎ መናገርን መማርና ከባለቤታችን ጋር በግልጽ መነጋገር እና መግባባት መለማመድን ይጠይቃል፡፡ እያደር የምናዳብረው ክህሎት በመሆኑ ለምን በአንዴ አልሆነልንም ብለን ተስፋ መቁረጥ የለብንም፡፡ ምንም እንኳ በቤታችን ከባለቤታችን ጋር በግልጽ መነጋገርና መወያየት እነዲሁም መግባባት ቀላል ባይሆንም መለማመዱ ጠቃሚ ነው፡፡ እንዲህ በማድረጋችን ዘር ብለን የሰየምነው ህጻን ልጃችን በተመጣጠነ ምግብ አማካኝነት የእድገት እርምጃው መልካም ጅማሬ ያገኛል፤ ንግስት ንቦቻችንንም እንደግፋቸዋለን ማለት ነው፡፡

እኛ ነፍሰጡር ሴቶች የምንመገበው ለመበርታትና ለመጠንከር ሲሆን በማህጸናችን ያለው ፅንስ አብሮ ይጠነክራል ማለት ነው፡፡

እንግዲህ የዛሬውን የውይይት ክፍለጊዚያችንን ወደማገባደዱ ተቃርበናል፡፡ ፡፡ በዛሬው የውይይት ክፍለጊዚያችን፤ ነፍሰጡር ሴቶች ሆን ብለው ምግብ መቀነስንና ለምን ለመበርታት እና ለመጠነከር መመገብ እንዳለባቸው ተምረናል፡፡

እስቲ የተማርናቸውን ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች እንከልስ፡፡

• አንድ ነፍሰጡር ሴት በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ባለሦስት ኮከብ ምግብ መመገብ ይገባታል፡፡ ባለሦስት ኮከብ ምግቦች የምንላቸው የእንስሳት ተዋፅኦ ምግቦችን ሲሆን እነዚህም እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ፣ እርጎ፣ ስጋ፣ ጉበት እና አሳ የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች ነፍሰጡር እናትን እና በማህጸኗ ያለውን ጽንስ ጠንካራና ጤናማ ለማድረግ የሚረዱ ምግቦች ናቸው፡፡

76

Page 77: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

77

• ንግስት ንቦችም በቀን ቢያንስ አንድ ባለሦሰት ኮከብ ምግብ መመገብ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም በየገበታው ባለሁለት ኮከብ ምግቦችን ጨምረው መመገብ ይኖርባቸዋል፡፡

• ንግስት ንቦች በቤተሰብ የገበታ ሰዓት ጨመር አድርገው መመገብ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም ከገበታ ሰአት ውጪ ማቆያ ምግብ መመገብ እና እንዲሁም ምግብ በሚያዘጋጁ ሰዓት ጨለፍ አድርገው መቅመስ ይኖርባቸዋል፡፡

• የቤተሰብ አባላት ንግስት ንቦች በደንብ እንዲመገቡ ማበረታታት አለባቸው፡፡

• የቤተሰብ አባላት ንግስት ንብ በቂ እረፍት እና ምግብ እንድታገኝ በስራ መርዳት አለባቸው፡፡

• በቤተሰብ መካከል በተለይም በባልና ሚስት መካካል በግልጽ ለመነጋገርና ለመግባባት ሁሉም ተገቢውን ልምምድ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

እንግዲህ በዚህ በሦስተኛው የውይይት ክፍለጊዜያችን በርካታ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል ፡፡ እስካሁን በተማርናቸው ፍሬ ነገሮች ዙሪያ ግልጽ ያልሆነ ነጥብ ካለ ጥያቄ እንድትጠይቁ እጋብዛለሁ፡፡ አስተባባሪ ጥያቄዎቻችሁን ለመመለስ ይሞክራሉ፤ ጥያቄያችሁ ዛሬ ካልተመለሰ ደግሞ ማስታወሻ በመያዝ ተገቢውን መልስ በማዘጋጀት በሚቀጥለው ክፍለጊዜ ስንገናኝ እንመልሳለን ማለት ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አስተባባሪ እባክዎን ወደቤታቸው የሚወስዷቸውን የእናቶችን ሥርዓተ ምግብ የሚያሳየውን የግርግዳ ፖስተር ለነፍሰጡር ሴቶች፣ለዘር አባቶች እና ለዘር ሴት አያቶች ያድሏቸው፡፡

• በተጨማሪም የዶሮ መኖ አዘገጃጀት የሚያሳየውን በራሪ ወረቀት ለሁሉም ያድሉ፡፡

እነዚህን ለቤተሰቦቻችሁ አሳዩዋቸው፤ በተጨማሪም ንግስት ንብን ስለመርዳት ተወያዩ፤ ንግስት ንብ በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ባለሦስት ኮከብ ምግብ፤ እንዲሁም ደግም ብርታትና ጥንካሬ እንድታገኝ በእያንዳንዱ የገበታ ሰዓት ባለ ሁለት ኮከብ ምግብ መመገብ እንደሚገባት መነጋገርና መወያየት ይኖርባችኋል፡፡

ስንቶቻችሁ ናችሁ በሚቀጥለው ስብሰባችን ላይ እቤት የምትወስዷቸውንን ቁሳቁሶች ለባለቤታችሁ፤ ለእናቶቻችሁ ወይም ለአማቾቻችሁ የምታሳዩና የምትወያዩት ይሄን ለማድረግ ፍቃደኛ የሆናችሁ እጃችሁን አውጡ፡፡

• ስለ ንግስት ንብ የተመጣጠነ ምግብ የግድግዳ ፖስተር/ምስል

• ስለ ንግስት ንብ የተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊነት እና ንግስቷ ንብ በየእለቱ ኮከብ ምግቦችን ስለምታገኝበት ሁኔታ

• ንግስት ንብ በቂ እረፍት እንድታገኝ የስራ ጫና እንዲቀነስላት ስለ መርዳት፤

ባልና ሚስት በጽሞና መነጋገር እና መደማማጥ፤ ከቤተሰባችን ጋር ንግስት ንብ እና ዘር ያልነውን ህጻን ለመርዳት መወያየትና መነጋገር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ እዚህ የተማርናቸውን ቁም ነገሮች የሚያስታውሱ ስጦታዎችን ሰጥተናችኋል፡፡

Page 78: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ለቤተሰቦቻችሁ እንደምታሳዩዋቸውና እንደምትወያዩባቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

SFX: የንግስት ንብ መዝሙር ቀስ እያለ ይሰማል አያ ሙላት፡- አሃ! የምሰማው ምንድነው ብርቱካን፤ አዎ የንብ ንግስት መዝሙርን ይመስላል፤

ስለ ንግስት ንብ በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት እና ስለ ዘር ፅንስ የተማርንበትን ይሄን ሶስተኛውን ክፍለጊዜያችንን በመዝሙሩ እንደምድመው፤ ምን ይመስላችኋል፤

አስተባባሪ፡- ከመለያየታችን በፊት እስቲ የንግስት ንብን መዝሙር አብረን እንዘምር

SFX: የንግስት ንብ መዝሙር ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-በጣም ጥሩ! በጣም ደስ የሚል ነበር፤ ቆንጆ መዝሙር ነው፡፡ አመሰግናለሁ፤

ሦስተኛውን የመማማሪያ ክፍለጊዜያችንን በጥሩ ሁኔታ ስላጠናቀቅን፤ እስቲ አንዴ ለራሳችን እናጨብጭብ፡፡

አስተባባሪ የሚቀጥለው ክፍለጊዜያችን መቼ እንደሚሆን ይነግሯችኋል፡፡ እስከዚያው ግን ሁላችሁም በንቃት ስለተሳተፋችሁ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ ችግኝ ብለን ስለሰየምነው የህጻን እድሜ በደንብ እንማራለን፡፡ እስከዚያሠው ደህና ሁኑ፡

78

Page 79: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

79

Page 80: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 81: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

81

መግቢያ

አያ ሙላት፡ ጤና ይስጥልኝ፤ እንደምን ዋላችሁ

ወደ አራተኛው የዳበረ የማሕበረሰብ ውይይታችን እንኳን በደህና መጣችሁ። ከሥርዓተ ምግብ ቡድን መሪ ከአቶ ቢራራ መለሰ የመክፈቻ ንግግር እንደሰማችሁት፣ በመላውአገራችን የእናቶች የምግብ አለመመጣጠንና የሕፃናት መቀንጨር ትልቅ ብሔራዊ ችግር ሆኖብናል። የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናትና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋና ዋና ትምህርቶችን ለመቅሰም፣ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎችን አዘጋጅተናል። ከዚህ ትምህርታዊ ውይይት በምትገበዩት እውቀትና ክህሎት አማካኝነት፤ በቁመናና በጠንካሬያቸው የሚያኮሩ፣ ጤናማና ብሩህ ህጻናትን በማሳደግ ለቁምነገር ማብቃት ትችላላችሁ፡፡ ይሄ ነው አላማችን።

እኔ አያ ሙላት እባላለሁ፡፡ ከውዷ ባለቤቴ ከብርቱካን ጋር እየተጋገዝን፣ እናንተው ዘንድ በአካል ባይሆንም በድምፃችን ተገኝተን ውይይታችሁን እናስተናብራለን። እኔና ባለቤቴ እየተፈራረቅን ድምጻአችንን ትሰማላችሁ። በየጣልቃው ደግሞ፣ ከናንተ ጋር ያለው አስተባበሪ ውይይታችሁን ያስተባብራሉ። ቴፑን ዘግተው፣ እንድትወያዩና የቡድን ስራዎችን እንድታከናውኑ ያግዟችኋል፡፡ ይሄን የደወል ድምጽ ስትሰሙ (የደወል ድምጽ ይሰማል)፣ ቴፑን የሚጠፋበት ጊዜ ነው፡፡ የቡድን ስራችሁን ወይም ውይይታችሁን ስትጨርሱ፣ አስተባበሪ ቴፑን መልሰው ይከፍቱታል፤ ያኔ እኔና ብርትኳን እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡

እስቲ አሁን እንሞክረው! አስተባባሪ እባክዎን የደወል ድምጽ ሲሰማ ፣ ቴፑን ይዝጉት፡፡ ፣ አሁን ተሳታፊዎች በሙሉ ስማቸውን በመናገር ራሳቸውን ያስተዋውቁ ። ተዋውቃችሁ ስትጨርሱ፤ እባክዎን አስተባባሪ ቴፑን ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስ

እቴ ብርትኳን፡-ጤና ይስጥልኝ። እንኳን ደህና መጣችሁ። እስካሁን፣ ሁላችሁም በደንብየተዋውቃችሁ ይመስለኛል፡፡ ሰላምታም ለመለዋወጥ ጊዜ ያገኛችሁ ይመስለኛል።

ወደ ዛሬው ርዕሰ ጉዳይ ከመዝለቃችን በፊት፣ በመጀመሪያዎቹ 3 ክፍለጊዜያት የተወያየንባቸውን ፍሬ ነገሮች እንዳስሳቸው።

በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት፣ ህፃናት ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው እንዲያድጉልን ምን ማድረግ እንዳለብን፣ በአንደኛው የውይይት ክፍለጊዜያችን ላይ የተማርናቸውን ነገሮች ሁላችሁም እንደምታስታውሱ እርግጠኛ ነኝ።

Page 82: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

82

የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ቁምነገር ምንድነው? ስንቶቻችሁ ናችሁ የሱፍ አበባ ተምሳሌትን ማለትም የዘር፣ የችግኝ፣ የእምቡጥ እና የአበባ ደረጃዎችን የምታስታውሱት ።

በመጀመሪያው ክፍለጊዚያችን፣ የጉልቻ ተምሳሌት ላይ ተነጋግረናል። የሶስቱን ጉልቻ አምዶች የትኛዎቹን ኮከብ ምግቦች እንደሚወክሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ የምታስታውሱት፡፡ የእንጀራውንስ ምጣድ ስንቶቻችሁ ናቸው ምን ምን የምግብ አይነቶች እንደሚወክል የምታስታውሱት? ለባለቤታችሁ እና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ የጉልቻን ተምሳሌት አስረድታችኋል? ንግስት ንብ በየእለቱ ቢያንስ አንድ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች እና በየገበታው ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችንእንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለባለቤታችሁና ለቤተሰብ አባላት አስተምራችኋል ወይ?

ንግስት ንቦች፣ በእርግዝና ወቅት በተለይም በመጨረሻዎቹ ወራት፣ በየእለቱ ተጨማሪ ምግብ ስለሚያስፈልጋቸው፣ በገበታ ሰዓት ላይ ምግቦችን መጨመርና እንዲሁም በመክሰስ ሰዓት ትናንሽምግቦች መብላት አለባቸው፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ባለፉት ሦስት ክፍለ ጊዜያት፣ ሁለት መዝሙሮችን በማዳመጥ ተምረናል። መዝሙሮቹ ስለምን እንደሆኑ የምታስታውሱ ስንቶቻችሁ ናቸው እስቲ የምታስታውሱ እጃችሁን አውጡ። የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናትን በሚመለከት ባለፉት ሦስት ክፍለጊዜያት የተማርናቸውን ቁምነገሮች ስንቶቻችሁ እንደምታስታውሱ ለማየት፣ ትንሽ ውይይት እናድርግ አስተባባሪ ፣ በያንዳንዱ ጥያቄ ስንት ሰው እጁን እንዳወጣ እየመዘቡ ውይይቱን ያስተባብሩ።

• ስንቶቻችሁ ናችሁየመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የንግስት ንብን መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ

• የአይረን ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተር እና የዘር ተምሳሌት ስቲከር ለቤተሰቦቻችሁ ያሳያችሁ ስንቶቻችሁ ናችሁ ?

• አጠቃቀሙን ለቤተሰቦቻችሁ ያስረዳችሁስ ስንቶቻችሁ ናችሁ?

• ስንቶቻችሁ የአይረን ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተር እና የዘር ተምሳሌት ስቲከርግድግዳ ላይ ለጥፋችኋል?

• ባለፈው ሳምንት፣ የእናቶች ሥርዓተ ምግብ ፖስተር እንዲሁም የዶሮ መኖ አዘጃጀትን የሚያስረዳ ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ተሰጥቷችኋል። እነዚህን ለባለቤታችሁ እና ለቤተሰብ አባላት በማሳየት፣ ስንቶቻችሁ የዶሮ መኖ አዘገጃጀት መመሪያውን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው አስረድታችኋል?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የእናቶች ሥርዓተ ምግብ ፖስተሩን በቤታችሁ ግድግዳ ላይ የለጠፋችሁ ?

Page 83: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

83

አስተባባሪ፣ እባክዎ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት፣ ውይይቱን ያስተባብሩ ። ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱ።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ውይይታችሁ ግሩም እንደነበረና እርስበርስ የቤት ተሞክሯችሁን እንደተጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ባለፉት ሁለት ክፍለጊዜያት ደግሞ፣ ለቤት ውስጥ ውይይት የሚያገለግሉ የተለያዩ የመግባቢያና የሃሳብ ማስተላለፊያ መንገዶችን በመማር፣ በትወና መልክ ተለማምደናል።

ሃሳብ የምንለዋወጥበትና የምንግባባበትን መንገድ የሚያሻሽሉ አንዳንድ ድንቅ ዘዴዎችን ሞካክረናል። ከባለቤታችንና ከቤተሰብ አባላት ጋር ስንነጋገር፣ እንደ አንበሳ ቁጡ ወይም እንደ አህያ ቸልተኝነትን በማዘውተር ሳይሆን፣ በራስ ከመተማመንና በአቋም ከመፅናት ጋር እንደ ማር እና ውሃ /ጉሬዛ በርህራሄና በትዕግስት በመሆን ነው፡፡

አያ ሙላት፡ ከባለቤትዎና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር፣ ንግስት ንቦች ተጨማሪ ምግብ እና ባለ ኮከብ ምግቦችን በእለት ምግባቸው እንዴት እንደሚያክሉ የወሰናችሁት ሃሳብ ወይም ያከናወናችሁት ድርጊት አለ? አዎ የምትሉ ከሆነ፣ ምን አደረጋችሁ?

ባለቤቶቻችሁ እና ሌሎች የቤተሰብ አባላት የእናቶች ሥርዓተ ምግብ ፖስተር ስታሳዩቸው ምን አሉ?

እቴ ብርቱካን፡ ለቤተሰብ አዲስ ሃሳብ ለማካፈልና ለመወያት ስንሞክር፣ አንዳንዴ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ለምሳሌ፣ ንግስት ንቦች ተጨማሪ ምግብ እንዲበሉና ተጨማሪ ኮከብ ምግቦች እንዲያገኙ እንዴት መርዳት እንደሚቻል ከቤተሰብ ጋር ስትነጋገሩ ያጋጠማችሁ ፈተና ካለ ልትነግሩን ትችላላችሁ?

እስቲ ሁላችሁም በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ስትወያዩ፣ እባካችሁ እርስበርስ ተሞክሯችሁን ተለዋወጡ። አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ በተሳታፊዎች የቤተሰብ ገጠመኝ ላይ ያተኮረውን ውይይት ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ ቴፑን ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። እርስበርሳችሁ ተሞክሯችሁን በመጋራታችሁ ምስጋና ይድረሳችሁ። በንግስት ንብ መዝሙር ላይና ወደ ቤት በወሰዳችኋቸው ትምህርታዊ ቁሳቁሶች ዙሪያ ቤተሰብ ውስጥ ጥሩ ተሞክሮ እንደገጠማችሁ ተስፋ አለኝ። አንዳንዴ ለቤተሰብ አዲስ ሃሳብ ለማካፈልና ለመወያየት ስንሞክር፣ ፈተናዎች ይገጥሙናል፡፡ ደግነቱ እንዲህ እንደናንተ በቡድን ውስጥ ተሳታፊ ስንሆን፣ የተለያዩ ሃሳቦች፣ ፍንጮችና ጥቆማዎች ሊሰጡን የሚችሉ ሰዎች ከአጠገባችን እናገኛለን፤ እናም እርስበርስ እንማማራለን፡፡

Page 84: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

84

• የእናቶች ወይም የንግስት ንብ ሥርዓተ ምግብን ለቤተሰብ በመናገር ለመወያየት ሲሞክሩ ፈተና የገጠማቸውን ተሳታፊዎች ሊረዳ የሚችል ሃሳብ ያለው ሰው አለ?

• እነዚህን ፈተናዎች ለማለፍ፣ የመግባቢያና የሃሳብ ማስተላለፊያ ምክሮችን የተጠቀመ ሰው አለ ወይ?

አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ ተሳታፊዎች በየቤታቸው የገጠሟቸውን ፈተናዎች በመግለፅ ተሞክሯቸውን ተወያይታችሁ ስትጨርሱ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት በተመለከተ ከቤተሰብ ጋር ስትወያዩ ፈተና የገጠማችሁ ተሳታፊዎች፣ ከአስባባሪያችሁ እና ከሌሎች ተሳታፊዎች አንዳንድ ጠቃሚ ሃሳቦችንና ጥቆማዎችን እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። ካልሆነም፣ አስተባባሪያችሁ በሚቀጥለው ክፍለጊዜ እስክንገናኝ ድረስ፣ ለጥያቄዎቻችሁ መልስ ለማግኘትና ተጨማሪ እገዛ ለማዘጋጀት ይጥራሩ።

አጠቃላይ መግለጫ

አያ ሙላት፡ አስታውሱ፤ ንግስት ንቦች ነፍሰጡር ወይም የሚያጠቡ እናቶች እንደመሆናቸው፣ የሚመገቡት ለሁለት ነፍስ ነው ይህ ማለት- ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለልጃቸውም ጭምር በየእለቱ ባለ ኮከብ ምግቦችን መብላት አለባቸው። ለሁለት ነፍስ መመገብ እንዲሁም ለጥንካሬ መመገብ ያስፈልጋቸዋል በተለይም፣ ለወሊድ በሚቃረቡበት ወራት በጣም አስፈላጊ ነው። ያኔ ንግስት ንቦችና ዘር ህፃናት፣ ያለ አንዳች ችግር በሰላምና በጤና ለወሊድ ይበቃሉ።

እቴ ብርቱካን፡ ትክክል ብለሃል ሙላት። በዚህ አራተኛ ክፍለጊዜያችን፣ የችግኝ የእድገት ደረጃ እና በማህፀን ውስጥ የነበረው ዘር ህፃን፣ ተወልዶ ወደ ችግኝ ህፃን ሲሆን፣ እናቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንወያያለን። የወሊድ ጊዜ፣ በተለይ በሴቶች ሕይወት ውስጥ ከሁሉም የላቀ ስሜት ከሚፈጥሩ ድንቅ ጊዜያት አንዱ ነው።

አያ ሙላት፡ እንዴ ለወንዶችም ድንቅ ጊዜ ነው! ባል እንደመሆኔ መጠን ሁለቱ ሴት ልጆቻችንን የወለድሽ ጊዜ እኔም እንዳንቺው ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ባሎች ስሙኝ ከልቤ ልንገራችሁ ገና በማህፀን ውስጥ የዘር ደረጃው አንስቶ በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የህፃኑን እድገት ሳታቋርጡ እየተከታተሉ ትክክለኛ ነገር ሁሉ በአግባቡ መፈፀምን የመሰለ ነገር የለም። ልጃችሁ ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ይሆንላችኋል።

እቴ ብርቱካን፡ ትክክል ብለሃል ሙላትዬ። መቼም የተናገርከው ነገር መሬት ጠብ አይለም። እንግዲህ፣ ህፃኑ ተወልዷል። ይህን ጊዜ፣ ሁለት ነገሮችን ማስታወስ ያስፈልጋል። አንደኛ ነገር፣ እናቶች ወዲያው እንደወለዱ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ጡት ማጥባት መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡ አዎ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ማጥባት የግድ ነው። ይህን ስንል አንዳንዶቻችሁን ሊያስገርማችሁ ይችላል። ግን፣ ጨርሶ የማይታለፍ

Page 85: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

85

ቁምነገር ነው። ሁለተኛ ነገር፣ እናቶች ከጡታቸው የሚወጣውን የመጀመሪያ ወርቃማ ወተት ለህፃናት ማጥባት እንዳለባቸው መረሳት የለበትም። ይህ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ወርቃማው ወተት እንገር ይባላል። አንዲት እናት ለህፃን ልጇ የምታበረክተው ከሁሉም የላቀ ስጦታ ምንድነው ቢባል፣ እንገርን ማጥባት ነው። እንገር፣ የተለያዩ በሽታዎችን በሚከላከሉ ብዙ ንጥረነገሮች የበለፀገ በመሆኑ፣ ለህፃናት ወደር የለሽ የህመም መከላከያ የጤንነት ጋሻ ይሆንላቸዋል፡፡ የበሽታ መከላከያ ንጥረነገሮችን በብዛት ስለያዘም ነው፣ ከወርቃማነቱ በተጨማሪ ከጡት ወተት ወፈር ዘለግ የማለት ባሕርይ የሚታይበት።

አያ ሙላት፡ አባወራዎች፣ አደራ ሚስቶቻችሁ ከወለዱ አንድ ሰአት ሳይሞላ ህፃኑን እንዲያጠቡ የእናንት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ የምጥ እና የወሊድ ጊዜ አድካሚ ስለሆነ፣ ሰአቱን ሊዘነጉት ይችላሉ። ትዝ ይለኛል፤ የእኔ ብርቱካን ሁለተኛ ልጃችንን ስትወልድ በጣም ስለደከማት፣ ወዲያውኑ እንቅልፍ ወሰዳት። ከድካም እፎይታ አግኝታ ከተኛችበት እንድትነሳ ማድረግ ቢከብደኝም፣ በአንድ ሰዓት ውስጥ ህፃኗን እንድታጠባ ከእንቅልፏ መቀስቀስ ነበረብኝ። አዋላጅ ባለሙያ ስለሆነችና ለምን እንደቀሰቀስኳት ስለምታውቅ ከደስታ በቀር ቅሬታ አልተሰማትም። ሌላ ጊዜ ግን በተኛችበት ሰዓት መጥቶ የሚረብሻት ሰው ጠላቷ ነው (በከፊል እየሳቀ)

እቴ ብርቱካን፡ (እየሳቀች) እናንተዬ ጊዜው እንዴት ይገሰግሳል፤ አመታት ቢያልፉም የትናንት ያህል ቅርብ ሆኖ ይታወሰኛል። ሙላት፣ ውድ ባለቤቴ፣ ሁልጊዜ ሳመሰግንህ እኖራለሁ። ባትቀሰቅሰኝ ኖሮ፣ ለህፃኗ ልጃችን አንድ ሰዓት ሳይሞላ እንገር ሳላጠባትና የፍቅር ስጦታዬን ሳልሰጣት ሰዓቱ ያልፍብኝ ነበር። እና ወገኖቼ፣ አደራ አስታውሱ፣ ከወሊድ በኋላ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ለጨቅላው ህፃናችሁ ጡት ማጥባትና እንገር መስጠት አለባችሁ። ከወሊድ በኋላ ከሁለት እስከ አራት ቀን ባለው ጊዜ እንገሩ እየተለወጠ ቀስ በቀስም እየቀጠነ ወደ ጡት ወተትነት ይሸጋገራል።

እቴ ብርቱካን፡ ነገርን ነገር ያነሳዋል ነውና፣ ለሚጠቡ ህፃናት የእሽሩሩ መዝሙር አዘጋጅተናል። እንደምትወዱት እርግጠኛ ነኝ። ረጋ ያለ መዝሙር ስለሆነ፣ ህፃናትን ለማባባል ተስማሚ ነው። ሁሉም የቤተሰብ አባላት ለችግኙ ጨቅላ ሊዘፍኑለት ይችላሉ። ወላጆችና ሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ ለችግኙ ጨቅላ ምን አይነት እንክብካቤ ማድረግ እንዳለባቸው ለመገንዘብ፣ መዝሙሩ ጥሩ ማስታወሻ ይሆንላቸዋል። እስቲ ለአፍታ መዝሙሩን እናዳምጥ።

SFX: የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙር ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ (እያንጎራጎረች)እሰይ ደስ ሲል! መጣ። እንዲህ ነው፣ ማራኪየጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙር! አይደለም እንዴ ሙላት? ሙላት? .... (እየሳቀች) እንቅልፍ ወሰደህ እንዴ? የኔ ጀግና! እውነቱን እኮ ነው መቼስ ምን ይደረግ። የሆነ ሆኖ፣ መዝሙሩ ጭልጥ አድርጎ የሚወስድ ትልቅ የማባበል ሃይል ስላለው፤ ህፃናትን እሽሩሩ እያለ የሰላም እንቅልፍ እንዲተኙ ያደርጋል። መቼም እናንተ እንዳልተኛችሁናሁላችሁም፣ እንደኔና እንደ ሙላት በመዝሙሩ እንደተማረካችሁ

Page 86: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

86

ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እስቲ የእሽሩሩ መዝሙራችን ላይ ትንሽ እንወያይ፡፡

አስተባባሪ ውይይቱን ያስተባብሩልናል። በመዝሙሩ ላይ ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን እንዲካፍሉ፣ እባክዎ የደወል ድምፅ እንደተሰማ ቴፑን ይዝጉት። ውይይቱ እንደጨረሳችሁ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት። ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጥቂት ጥያቄዎችን እነሆ፡

o አንደኛ፣ መዝሙሩ ምን ተገነዘባችሁ? ምን ምን መረጃዎችን አገኛችሁ?

o ሁለተኛ፣ ከመዝሙሩ የወደዳችሁት ነገር ምንድነው?

o ሦስተኛ፣ ይህንን መዝሙር ለቤተሰባችሁ ማስተማር የምትችሉ ይመስላችኋል ?

SFX፡ የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ህፃናትን የእናት ጡት ስለማጥባት በተለይም አራስ እናት ከባለቤቷ ብዙ ድጋፍ ማግኘቷም ጭምር በአድናቆት የሚገልፅልን የእሽሩሩ መዝሙር፣ ጥሩ መወያያ እንደሆነላችሁ አምናለሁ። ህፃናትን በእሽሩሩ መዝሙር ሲያስተኙ እንዴት ደስ ይላል እናንተዬ። እንዲያው፣ በመዝሙሩ ላይ አንዳንድ ጉዳዮችን ለማብራራት ትንሽ ልናገር።

• እናቲቱ ለህጻኗ ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ወርቃማውን እንገር ለልጇ ማጥባቷ ደግ አድርጋለች።

• ባለቤቷ ደግሞ፣ ችግኝ ህፃናት የጡት ወተት ብቻ መጠጣት እንዳለባቸው አስታውሷታል። የእናት ጡት ወተት ለህፃናት የሚያስፈልጋቸውን ሁሉንም ነገሮች ያሟላል። ስድስት ወር እስኪሞላቸው ሌላ ምግብ ወይም ፈሳሽ መውሰድ የለባቸውም።

• ችግኝ ህፃናት ለስድስት ወራት ምንም ውሃ መጠጣት አያስፈልጋቸውም። የጡት ወተት ብቻ ይበቃቸዋል።

• እናቶች ብዙ ባጠቡ ቁጥር ብዙ የጡት ወተት ማምረት ይችላሉ፡፡ አስታውሱ እናቶች ለሊትም ተነስተው ማጥባት አለባቸው፡፡

• ባሎች፣ ንግስት ንቦችን ተጨማሪ ምግብና ተጨማሪ እረፍት እንዲያገኙ እና ህጻናትን የማጥቢያ ጊዜ እዲኖራቸው ማገዝ አለባቸው።

እቴ ብርቱካን፡ የሰማነው መዝሙር ስለ እናት ጡት ወተት በርካታ ጠቃሚ ፍሬ ነገሮችን ይዟል። እስቲ እያንዳንዱን ፍሬ ነገር ላይ እንወያይ። አንደኛው ፍሬነገር፣ እንገር ወይም የመጀመሪያው ወርቃማው ወተት ነው። አንዳንድ እናቶች ለህፃናት እንገር የመስጠት ጥቅምን ይጠራጠራሉ። ነገር ግን፣ እንገር የተፈጠረው፣ ለጨቅላ ህፃናት ነው። እንገር፣ ለጨቅላ ችግኝ ህፃናት በጣም ጠቃሚ የሆነበትን ምክንያት የሚያውቅ አለ?

እቴ ብርቱካን፡ እስቲ በእንገር ጉዳይ ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተሞክሯችሁን በመጋራት ትንሽ ተወያዩ። አስተባባሪ ውይይቱን ያስተባብሩልናል። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

Page 87: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

87

የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። በደንብ እንደተወያያችሁ አምናለሁ። በዚህ አጋጣሚ፣ የእንገር መልካምነትንና ለጨቅላ ህፃናት ጠቃሚ የሆነበትን ምክንያት ላስታውሳችሁ።

• እንገር ህፃናት በቫይረስና በባክቴሪያ እንዳይታመሙ ይከላከላል። እንገር ለህፃናት የመጀመሪያው ክትባት ነው ።

• የህፃናትን ጨጓራ ያፀዳል፤ ሆዳቸውና አንጀታቸው እንዳይታወክ ይከላከላል።

• ለህፃኑ የሚያስፈልጉ ሁሉም የምግብ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን አጣምሮ የያዘ ነው።

አያ ሙላት፡ ብርቱካን እናትየዋና ህፃኑ ገላ ለገላ የመነካካታቸውንም ጥቅም መናገር አትርሺ። ለኔ ብዙ ጊዜ ነግረሺኛል።

እቴ ብርቱካን፡ አመሰግናለሁ ውዴ። እንኳንም አስታወስከኝ። ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ጨቅላ ህጻናት ከእናታቸው ደረት ላይ ገላ ለገላ እንዲነካኩ ማድረግና አንድ ሰአት ሳይሞላ ከእናታቸው ጡት እንገሩን እንዲጠቡ ለህፃኑም ለእናቱም ጤንነትና ደህንነት ይበጃል። ለምን እንደሆነ ምክንያቱን የሚያውቅ ከመሃላችሁ አለ ?

እቴ ብርቱካን፡ ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ስለማጥባት፣ ተሳታፊዎች ተሞክሮና ገጠመኛችሁን እያነሳችሁ ትንሽ እንወያይ። አስተባባሪ ውይይቱን ያስተባብሩልናል። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ውይይታችሁ ጥሩ እንደነበረ አምናለሁ። ችግኝ ህፃናት ከተወለዱ አንድ ሰአት ሳይሞላ ከእናቲቱ ጡት ጋር መገናኘታቸው ምን ምን ጥቅሞች እንዳሉት ላስታውሳችሁ።

• አራሷ እናት ከወሊድ በኋላ በብዛት ደም እንዳይፈሳት ይረዳል።

• ህፃኑ ቶሎ ከእናቱ ጡት ጋር ከተገናኘ፣ እናት በፍጥነት ወተት ታመነጫለች፤ ህፃኑ የጡት ወተት ይጠባል። ሌላ ምግብ አያስፈልገውም።

• ህፃኑ ጡት በጠባ ቁጥር ፣ እናቱ ተጨማሪ ወተት ታመነጫለች።

• ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ጡት እንዲጠቡ ማድረግ የህፃናትን የሞት አደጋ ይቀንሳል።

አደራ አስታውሱ። ችግኝ ጨቅላ ህፃናት፣ እንገር ካገኙ በኋላ ስድስት ወር እስኪሞላቸውና ወደ እንቡጥ ደረጃ እስኪያድጉ ድረስ ከእናት ጡት ወተት በስተቀር ሌላ ምግብና ፈሳሽ አያስፈልጋቸውም። ይህ ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ?

እቴ ብርቱካን፡ ህፃናትን ለስድስት ወር በእናት ጡት ወተትን ብቻ ስለማጥባት አጭር የተሞክሮና የሃሳብ ውይይት እናድርግ። አስተባባሪ ውይይቱን ያስተባብሩልናል፡፡ እባክዎ፣ ከውይይቱ በኋላ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

Page 88: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

88

SFX፤ የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ጥሩ እንደተወያያችሁ አምናለሁ። ችግኝ ህፃናት ለስድስት ወራት፣ ወደ እንቡጥ ደረጃ እስኪያድጉ ድረስ ከእናት ጡት ወተት በስተቀር ሌላ ምንም አይነት ፈሳሽ ወይም ምግብ አያስፈልጋቸውም። ለምን መሰላችሁ?

• የጡት ወተት፣ ለችግኝ ህፃናት ምትክ የሌለው ወደር የለሽ ምግብ ነው። ችግኙ ህፃን በአካልና በአእምሮ ለማደግና ለመጎልበት የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ የያዘ ነው።

• የጡት ወተት፣ የህፃኑ አንጎል፣ አይኖች እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን በሙሉ በአግባቡ የሚያሳድጉ ንጥረ ነገሮች አሉት።

• የጡት ወተት፣ ለህፃኑ የሚያስፈልግ በቂ ፈሳሽ የያዘ ነው። በሞቃት ጊዜም ቢሆን ችግኝ ህፃናት ውሃ አያስፈልጋቸውም።

• የጡት ወተት ህፃናትን ከበሽታ ይከላከላል። ተቅማጥ፣ የሳንባ ምችና ሌሎች የመተንፈሻ አካል ህመሞች፣ የጆሮ ቁስለት፣ ማጅራት ገትርና ሌሎች በሽታዎችን ስለሚከላከል፣ የጡት ወተት ለህፃናት የህይወት መድህን ነው።

• የጡት ወተት፣ ለህፃናት አይከብዳቸውም። በቀላሉ ከሰውነታቸው ጋር ይዋሃዳል።

• ህፃናትን፣ ስድስት ወር ሳይሞላቸው የእንስሳት ወተትና ውሃ እንዲሁም ሌላ ምግቦችን መመገብ አደጋ ያመጣል። ምክንያቱም፣ ችግኝ ህፃናት በማይቋቋሙት ጀርሞች የተበከሉ ሊሆኑ ይችላሉ።

• የጡት ወተት ብቻ የሚመገቡ ችግኝ ህፃናት በፍጥነት እየጠነከሩ ያድጋሉ። በሽታ አይመላለስባቸውም። ከዚያም በትምህርት ጎበዝ ይሆናሉ።

አያ ሙላት፡ ይሄ ምን ያህል ቁልፍ ጉዳይ እንደሆነ ለመገንዘብ፣ እስቲ በወጉ የተቆጠሩና የተረጋገጡ የአገራችን መረጃዎችን እንመልከት። ከአገራችን እናቶች መካከል፣ ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ማጥባት የሚጀምሩት ስንቶቹ ይሆኑ? 52 በመቶ ብቻ ናቸው። ይህ ማለት ከሁለት እናቶች አንዷ ብቻ፣ አንድ ሰአት ሳይሞላ ማጥባት ጀምራለች ማለት ነው፡፡

እስቲ ደግሞ፣ ከክልል ክልል እየተዟዟርን፣ ስንት እናቶች አንድ ሰአት ሳይሞላ ማጥባት እንደጀምሩ እንታዘብ።

Page 89: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

89

ክልል

አንድ ሰአት ሳይሞላ የሚጀምሩ እናቶች ከመቶ እናቶች

1 ትግራይ 45 ከመቶ (2 ከ 1) 2 አማራ 37 ከመቶ (3 ከ 1) 3 ኦሮሚያ 53 ከመቶ (2 ከ 1) 4 ደብብሕ 67 ከመቶ (3 ከ 2) 5 አዲስ አበባ 62 ከመቶ (3 ከ 2)

እንደምታዩት፣ ቁጥሮቹ ገና ዝቅተኛ ናቸው። ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ማጥባት የማይጀምሩ እናቶች አሉ ማለት ነው። ህፃናት ስድስት ወር እስኪሞላቸው ድረስ (ሌላ ምግብና ውሃ ሳይቀላል) በእናት ጡት ወተት ብቻ የሚያሳድጉ የአገራችን እናቶችስ ስንት ናቸው? 52 ከመቶ ብቻ ናቸው - ከሁለት እናቶች መካከል አንዷ እንደማለት ነው። ከአገራችን ህፃናት መካከል ግማሾቹ ብቻ ናቸው፣ እስከ ስድስት ወር በእናት ጡት ብቻ ያደጉት።

አያ ሙላት፡ አንዳንድ ተሳታፊዎች፣ ህፃኑን በጡት ወተት የማሳደግ ሃላፊነት የእናትየው ድርሻ ነው ብላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። እንደዚህ የሚያስቡ ብዙ ወንዶች አጋጥመውኛል። ወገኖቼ፣ ሁላችንም ለልጆቻችን ጤንነትና እድገት በትጋት መሳተፍ አለብን። ይሄ የእናትየዋ ብቻ ሳይሆን የመላው ቤተሰብ ጉዳይ ነው።

እቴ ብርቱካን፡ የቤተሰብ አባላት በሙሉ፣ አዲሱን ችግኝ ህፃን በመልካም ተቀብለው ለመንከባከብ፣ የየራሳቸው ልዩ ድርሻ አላቸው። እስቲ፣ በቤተሰብ ውስጥ ህፃን ሲወለድ ምን እንደሚመስልና የቤተሰብ አባላት እንዴት መተባበር እንደሚችሉ እንመልከት። ከእናት በተጨማሪ ሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ ጨቅላው ችግኝ ህፃን በአግባቡ የጡት ወተት እንዲያገኝ እንዴት ይተጋገዛሉ? አስተባባሪው በዚህ ጉዳይ ላይ የሚቀጥሉትን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎች እንዲወያዩ ያስተባብሩልናል።

• በወሊድ ወቅት ከወላዷ አጠገብ አብሯት የሚሆነው ማን ነው?

• ጨቅላውን ችግኝ ህፃን የሚያዋልድ ማን ነው?

• እናት ህፃኑን የምትታቀፈው መቼ ነው?

• ችግኙ ህፃን እንደተወለደ፣ ምን አይነት ምግብና ፈሳሽ ይሰጠዋል? ለምን? የሚሰጠውን ማን ነው?

• እናት ህፃኑን ማጥባት የምትጀምረው መቼ ነው? ጡት እንድታጠባ የሚያግዛትና የሚመክራትስ ማን ነው?

• እንገር የተሰኘውን የመጀመሪው የጡት ወተት ለህፃኑ ይሰጠዋል? ወይስ እንገሩ እንዲወገድ ይደረጋል? ለምን?

Page 90: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

90

እቴ ብርቱካን፡-እነዚህ ጥያቄዎች በጣም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። ተሳታፊዎች፣ ሃሳባችሁንና ተሞክሯችሁን በነፃነት እንደልብ እንድትናገሩ አደራ እላለሁ። አስተባባሪ፣ እባክዎ ውይይቱን ስትጨርሱ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX፡ የደውል ድምፅ

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ጥሩ እንደተወያያችሁ አምናለሁ።

አያ ሙላት፡ አባወራዎችና አባቶችም ጉዳዩ በጥሞና በማሰላሰልና ተሞክሯቸውን በማካፈል እንደተወያዩ ተስፋ አደርጋለሁ።

እቴ ብርቱካን፡ አመሰግናለሁ ሙላት። እስቲ ከራሴ ተሞክሮ ጥቂት ልንገራችሁ። አዋላጅ ሆኜ በሰራሁባቸው በርካታ አመታት፣ በወሊድ ጊዜ እነማን ከነፍሰጡሯ አጠገብ አብረዋት እንደሚገኙ ታዝቤያለሁ።

• ሴት አያቶች ብዙውን ጊዜ አብረዋት ይሆናሉ። ሴት አያቶች፣ ማለትም የነፍሰጡሯ እናት ወይም አማት በወሊድ ጊዜ ከአጠገቧ አይርቁም። አንዳንዴም በማዋለድ ይረዳሉ።

• እናት መቼና እንዴት ህፃኑን ጡት መጥባት እንዳለባት ምክር የሚሰጡም ሴት አያቶች ናቸው።

• እዚህ ላይ፣ አንድ ጎጂ ልማድ አለ። ለህፃኑ ጨጓራና አንጀት ጥሩ እየመሰላቸው፣ ሆድ ያለሰልሳል እያሉ፣ ችግኙ ህፃን የጡት ወተት መጥባት ከመጀመሩ በፊት ቅቤ ወይም ስኳር በውሃ በጥብጠው ያጠጡታል።

• ይህን ጎጂ ልማድ ባህል ሆኖ እንዲዘወተር የሚያደርጉት ደግሞ በአብዛኛው ሴት አያቶች ናቸው።

• ከዚህም በተጨማሪ፣ በርካታ የቤተሰብ አባላት፣ ከየመጀመሪያው ወርቃማ ወተት ወይም እንገር፣ የደፈረሰና የተመረዘ ነው ብለው ስለሚገምቱ፣ ብዙውን ጊዜ ያስወግዱታል እንጂ ለህፃኑ አይሰጡትም።

አያ ሙላት፡- ሴት አያቶች በጨቅላው ችግኝ አስተዳደግ ላይ ትልቅ የሃላፊነት ድርሻ እንደሚይዙ ማንም ይመሰክራል። የልጅ ልጆቻቸውን ከልብ ይወዳሉ፤ በጎ በጎውን ሁሉ ይመኛሉ።

እቴ ብርቱካን፡ ትክክል ብለሃል። ነገር ግን፣ አንዳንድ ሴት አያቶች፣ ስለመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የምስራች አልሰሙ ይሆናል፤ ወርቃማው ወተት ወይም እንገር ለህፃናት እጅጉን በጎ እንደሆነ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችና የጤና ጣቢያ ሰራተኞች ሲያስተምሩ አልሰሙም ማለት ነው። የእንገር መልክ ወደ ቢጫ ያደላ በመሆኑ አንዳንድ ሰዎች የደፈረሰ ነገር ይመስላቸዋል። ነገሩ ወዲህ ነው። የእንገር ቢጫማ መልክ፣ እንደ ወርቅ ብርቅ ድንቅ መሆኑ ያመለክታል። በጠቃሚ ንጥረነገሮች የበለፀገው እንገር፣ ለጨቅላ ችግኝ ከሁሉም የላቀ የአፍቃሪ ቤተሰብ ውድ ስጦታ ነው።

እናቶች እንገር ለጨቅላ ችግኞች ምንኛ ጠቃሚና አስፈላጊ እንደሆነ በውል

Page 91: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

91

እንደተገነዘባችሁ እርግጠኛ ነኝ። እንዲያም ሆኖ፣ ለችግኝ ህፃናት እንገር መስጠትና በጡት ወተት ብቻ ማሳደግ ጠቃሚ እንደሆነ በቅጡ ብንገነዘብም፣ ይህንን ቁምነገር ለባሎችና ለሴት አያቶች ማስረዳት ሊቸግረን ይችላል።

እቴ ብርቱካን፡ እስቲ እንነጋገርበት። ለጨቅላ ችግኝ ህፃናት እንገር ለመስጠት፣ ከዚያም በኋላ በጡት ወተት ብቻ ለማሳደግ ስትሞክሩ፣ ምን አይነት እክሎች እንደሚያጋጥሟችሁ እየተነጋገርን ጥቂት እንወያይ።

አስተባባሪ፣ ውይይቱን ያስተባብሩልናል። ተወያይታችሁ ስትጨርሱ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ውይይታችሁ መልካም እንደነበረ እገምታለሁ። እስቲ በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙን ችግሮች ላይ እንነጋገር።

አያ ሙላት፡- በወንዶች ብንጀምር እወዳለሁ፣ ብርቱካኔ። ለነፍሰጡሯና ከዚያም በኋላ ለምታጠባው እናት አፍቃሪ ባለቤት፤ ለህፃኑ ደግሞ አፍቃሪ አባት እንደመሆናችን፣ የወንዶችን ድርሻ መዘንጋት የለብንም። እኛ ወንዶች ላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ በርካታ ችግሮችን ስለማውቅ፣ ዋና ዋናዎቹን ነቅሼ ልናገር።:

• በመጀመሪያ፣ የጡት ወተትና የህፃኑ አመጋጋብ ጉዳይ፣ የሴቶች ጉዳይ ስለሚመስለን፣ የህፃኑ እናት ከሆነችው ባለቤታችንና ከሴት አያቶች ጋር መወያየት ሊከብደንና ሊያሳፍረን ይችላል።

• ከሴት አያቶች ጋር መነጋገር የዋዛ አይደለም። በጥንቱ ልማድና ወግ አሳድገው ለቁም ነገር እንዳበቁን ይነግሩናል። ልጆቻቸውን ያሳደጉበት ልማድ፣ አሁን በልጅ ልጆች ላይ የሚቀየርበት ምክንያት እንደሌለም እየነገሩ ይሞግቱናል።

• ሴት አያቶች፣ ታላላቆቻችንና ወላጆቻችን ስለሆኑ፣ በክብር ምክራቸውን ሰምተን መታዘዝ ግዴታ ይሆንብናል።

እቴ ብርቱካን፡-ትክክል ብለሃል ውድ ባለቤቴ። ወንዶች የሚገጥማቸውን ችግር ስለነገርከን አመሰግናለሁ። እኔ ደግሞ፣ በእናትነቴና በሚስትነቴ፣ ብዙ ሴቶች ላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥሙ ችግሮችን አንድ ሁለት ብዬ ላካፍላችሁ።

• የህፃኑ እናት አንድ ቁምነገር ተምራ ከባለቤቷ ጋር ብትወያይ፣ ባለቤቷ በሷ ሃሳብ ላይስማማ ይችላል። እኔ የህፃኑ አባት ነኝ ይላታል። ‘ወላጆቻችን እኛን ባሳደጉበት ልማድ ነው ልጃችን ማደግ ያለበት’ ይላታል።

• የህፃኑ ሴት አያቶች... እናቶቻችንና አማቾቻችንም፣ ‘እናንተን ወልደን በደህና ያሳደግንበት ወግና ልማድ አሁን በልጅ ልጆቻችን ላይ የሚለወጥበት ምክንያት የለም’ ይሉናል።

• ሴት አያቶች ታላላቆቻችን ስለሆኑ፣ በባህላችን እነሱን ማክበርና ምክራቸውን ሰምተን መታዘዝ ግዴታ ይሆንብናል።

• አሳዛኙ ነገር፣ የብዙዎቻችን ቤት ቢታይ፣ የሴቶች ደርሻ ሁሉንም ነገር እሺ

Page 92: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

92

ብሎ መቀበልና መታዘዝ ብቻ ስለሆነ፣ ትክክለኛና ጠቃሚ ሃሳብ ቢኖረን እንኳ በግልፅ ለመናገርና ለማስረዳት እንቸገራለን።

• እንዲህ መናገሬ፣ ባሎችን፣ ሴት አያቶችንና ሌሎች የቤተሰብ አባላትን ብቻ ጥፋተኛ ለማድረግ አይደለም። እኛ እናቶች ዘንድም ጉድለት አለ። ባለቤታችን እና ሴት አያቶች በሃሳባችን ቢስማሙልንም፣ ራሳችንን በስራ ስለምንጠምድ ችግኙን ህፃን ለቤተሰብ አባላት አደራ ሰጥተን እንሄዳለን። ከሄድንበት እስክንመለስ ድረስ ህፃኑ ሲርበው የሚጠባው አይኖርም። እስከዚያው ቢጨንቃቸው ነው፣ ውሃ ወይም ሌላ ምግብ ለህፃኑ የሚሰጡት።

አያ ሙላት፡ የሴት አያቶች ተሞክሮስ? ምንም አይነት ችግር ይገጥማቸዋል?

እቴ ብርቱካን፡ ወደ ሴት አያቶች ልመጣልህ ነው ውዴ። እንግዲህ ልጆች ወልደን፣ የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተናል። ስለዚህ በሴት አያትነቴ መናገር እችላለሁ።

• መቼም ጎጂ ልማድ ክፉ ነው፤ ከልማድ መላቀቅ ይቸግራል። እንገርን ማስወገድ እንዲሁም፣ ለህፃናት ቅቤ ወይም ስኳር በውሃ በጥብጦ ማጠጣት የመሳሰሉ ጎጂ ልማዶችን መተው ይቸግረናል፡፡ በዚያ ላይ ልጆቻችንን ያሳደግንበት ልማድ ጉዳት የሚያመጣ ስለማይመስለን፣ በልጅ ልጆቻችን ላይ የድሮውን ልማድ የምንቀይርበት ምክንያት አይታየንም።

• ደግሞ፣ እኛ ሴት አያቶች እንደታላቅነታችን ወግና ልማድ መጠበቅ አለብን። ልማድ አፍርሰን አዲስ ነገር ብንጀምር ሰው ምን ይለናል ብለን እናስባለን?

አያ ሙላት፡- ይገባኛል ብርቱካኔ። የቆየውን ልማድ መቀየር ይከብዳል። ልማዳችንን መቀየር እንዳለብን ከነጥቅሙ ብንገነዘነብ እንኳ፣ ዳገት ሆኖ ይታየናል። ግን ይሄ ጉዳይ የልጆቻችንን ሕይወትና ጤንነት የመጠበቅ ጉዳይ ነው። ጎጂ ልማዶችን መቀየር የሚኖርብን፤ ችግኝ ህፃናት ወደፊት ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው እንዲያድጉ፣ ጥሩ መሰረት ልንሰጣቸው ስለምንፈልግ ነው።

አያ ሙላት፡- ብዙ ከተነጋገርን ዘንዳ፣ በዚሁ ስንወያይበት በነበረው ጉዳይ ዙሪያ የፅጌን ውሎ የሚተርክ ድራማ ብናዳምጥ ምን ይመስልሻል ብርቱካኔ?

እቴ ብርቱካን፡-ወርቅ ሃሳብ ነው ውዴ። አብረን እናዳምጥ።

ድራማ

ድምፅ:- የጤና ጣቢያ፤ የሚከፈት በር፣ ከዚያም እየቀረበ የሚመጣ የኮቴ ድምፅ።

ነርስ:- ጤናማ ሴት ህፃን ወልደሻል ፅጌ። እንኳን ደስ ያለሽ።

ፅጌ:- ውይ ፈጣሪዬ ተመስገን በጣም ደስ ብሎኛል። ነርስ... ልጄን ልታቀፋት?

ነርስ፡- እንዴታ፤ ይሄው፣ ያዢያት...

SFX: ድምፅ፡- የሚያለቅስ ህፃን

ነርስ:- ርቧታል ማለት ነው። እኔ ላግዝሽ። የጡትሽን አግኝታ መጥባት እንድትጀምር...

Page 93: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

93

ደረትሽ ላይ ወደ ጡትሽ አስጠግተሽ ያዣት?

SFX: ድምፅ: የሚከፈት በር እና እየቀረበ የሚመጣ ኮቴ

ነርስ:- ጤና ይስጥልኝ አቶ ኪዳኔ። የጤናማ ሴት ልጅ አባት ሆነሃል። እንኳን ደስ ያለህ።

ኪዳኔ:- በጣም ደስ ብሎኛል ነርስ። አመሰግናለሁ። እንዴት ነሽልኝ ፅጌ?

ፅጌ:- ደህና ነኝ ውዴ። ለማጥባት ስዘገጃጅ መጣችሁ... ነርስ፣ ቅድስት፣ እትዬ ትርንጎ የባለቤቴ የኪዳኔ እናት ናቸው።

ትርንጎ:- እንዴት ነሽ ልጄ?

ፅጌ:- በጣም በጎ ነኝ። ምጡ እንደፈራሁት አልከበደኝም። ብዙም የድካም ስሜት የለኝም። እንዲህ የብርታት ስሜት ይኖረኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ገርሞኛል።

ትርንጎ:- እኔኮ ብያለሁ። ተጨማሪ ምግብ መመገብና መክሰስ መብላት፣ ከተጨማሪ ኮከብ ምግቦች ጋር በማግኘትሽ፣ እንዴት ስንቅ እንደሆነልሽ አየሽ! ብርታት አግኝተሽ ጤናማ ልጅ ለመውለድ በቃሽ። የልጅ ልጄን ለመታቀፍ ጓጉቻለሁ። ደግሞ ማማሯ። ሰውነቷም ጠንካራ ይመስላል። ስንት መዘነች ነርስ?

ነርስ:- ሦስት ኪሎ ነው ሚዛኗ። የጤናማ ህፃን ክብደት እንደዚህ ነው። አሁን ደግሞ የጡት ወተት ያስፈልጋታል። ፅጌ አሁን አጥቢያት?

ፅጌ:- ከጡቴ የሚወጣው ፈሳሽ ግን፣ - ወፍራም ብጫ ነገር ነው፡፡ ቆሻሻ ይመስላል፡፡ ይህን የደፈረሰ ነገር! እንዴት ብዬ አጠባታለሁ? ኧረ አላደርገውም። የጡቴ ወተት እስኪጠራ የላም ወተት ባጠጣት አይሻልም? የጡቴ ወተት ሲጠራ እንደ ወተት መንጣቱን አይቼ አጠባታለሁ።

ነርስ:- አይደለም አይደለም፤ ተሳስተሻል። ከጡትሽ የሚወጣው የመጀመሪያ ወፍራም ፈሳሽ እንገር ይባላል። በተፈጥሮው ወፈር ዘለግ ብሎ ወደ ቢጫ ያደላ መልክ አለው። እንገር ለህፃኑ በጣም አስፈላጊ ነው።

ትርንጎ:- እኮ ለምን? እንገር ለህፃኑ ምን ይበጀዋል?

ነርስ:- ህፃን ሲወለድ በመጀመሪያዎቹ ቀናት፤ ለህፃኑ የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ንጥረነገሮችን በሙሉ የያዘ ነው - እንገር። በተፈጥሮ ጥበብ ለህፃኑ የተዘጋጀ ነው።

ትርንጎ:- አንዳንድ እናቶች ግን ዞር ብለው እንኳ አያዩትም። መልኩን አይወዱትም። የደፈረሰ ይመስላል። እንዲያው እርግጠኛ ነሽ ነርስ፣ ይሄ ነገር ለህፃኑ ጥሩ ነው?

ነርስ:- እርግጠኛ ነኝ ወ/ሮ ትርንጎ። እንገር ለህፃናት ፍፁም አስፈላጊ እንደሆነ ቅንጣት አይጠራጠሩ። ህፃኑን ከበሽታዎች የሚከላከሉ ብዙ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው። ብዙ ጠቃሚ ንጥረነገሮች ስለያዘ ነው፤ ከጡት ወተት በመልኩና በውፍረቱ ልዩ ሆኖ የሚታየን

SFX: ድምፅ: የሚያለቅስ ህፃን።

ፅጌ:- እኔ የምልሽ ነርስ፣ ግን ልጄ እንገሩን ባትወደውስ። ይሄው ደረቴ ላይ ዝም ብላ ተኝታ ታለቅሳለች እንጂ መጥባት አልጀመረችም።

Page 94: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

94

ነርስ:- ምንም አትጨነቂ። መጥባት ስትጀምር ትወደዋለች። ደረትሽ ላይ ወደ ጡትሽ ስታስጠጊያ የእንገሩን መዓዛ ማሽተት ትችላለች። ብዙም ሳትቆይ አፏን የጡትሽ ጫፍ ላይ አድርጋ መጥባት ትጀምራለች። ይህ የተፈጥሮ ጥበብ ነው። ወደ ጡትሽ አስጠጊያት በተወለደች አንድ ሰአት ሳይሞላ መጥባት አለባት አንቺም አዲስ እናት፣ እሷም አዲስ ህፃን... አሁን የመላመጃ ጊዜያችሁ ነው። ትንሽ ታገሺና ታያለሽ።

ፅጌ:- እሺ ግን ነርስ፤ ይሄ እንገር እስከመቼ ይቆያል ትያለሽ?

ነርስ:- ሁለት ሶስት ቀን፣ ካልሆነም አራት አምስት ቀን ልጅሽ ስትጠባ፣ ቀስ በቀስ ወደ ተለመደው የወተት መልክ እየተለወጠ ይመጣል።

ፅጌ:- እሰይ! እሰይ ! መጥባት ጀመረችኮ ነርስ። አመሰግናለሁ - ላደረግሽልኝ እገዛ ሁሉ

ነርስ:- ለኔም እርካታ ነው። እንግዲህ ፅጌ አትርሺ፤ አፍቃሪ እናት ለህፃኗ የምታበረክተው ከሁሉም የላቀ ስጦታ እንገር መሆኑን አስታውሺ። ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ህፃኑን ማጥባትና እንገር እንዲያገኝ ማድረግ፣ ላንቺና ለህፃኗ ልጅሽ እጅጉን በጣም አስፈላጊ ነው። ሁለታችሁንም ይጠቅማል።

ፅጌ:- ስትጠባ እንዴት ልዩ ስሜት ይፈጥራል መሰለሽ ነርስ።

ነርስ:- ህፃኗ ደጋግማ ስትጠባ፣ አንቺም እየለመድሽው ቀለል ይልሻል። ለስድስት ወራት የጡት ወተት ብቻ ትሰጪያታለሽ አደራ። ለልጅሽ የወደፊት ሕይወት ጥሩ መሰረት ይሆንላታል።

አያ ሙላት፡- ድንቅ ታሪክ ነው። ፅጌ በጎውንና ቀናውን ነገር አድርጋለች። በምክር ያገዘቻት ነርስ ቅድስት ምስጋና ይገባታል፡፡

እስቲ በሰማነው ታሪክ ላይ ትንሽ እንወያይ። አስተባባሪ፣ የተሳታፊዎችን ወይይት በሚያስተባብሩበት ወቅት፣ እነዚህን ጥያቄዎችን ልብ ይበሉ።

o አንደኛ፣ በታሪኩ ውስጥ የተፈጠሩ፣ የተወሩና የተደረጉ ነገሮች ምንድናቸው?

o ሁለተኛ፣ በታሪኩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ምን ችግር አጋጠማቸው?

o ሦስተኛ፤ ችግሮቹን እንዴት ተወጧቸው?

o በመጨረሻም፣ እንዲህ አይነት ታሪክ፣ በቤተሰባችን ወይም በአካባቢያችን ማህበረሰብ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ታሪክ ነው? ሊከሰት የሚችል ከሆነ ለምን? ሊከሰት የማይችል ከሆነስ ለምን?

አያ ሙላት፡- አስተባባሪ፣ ደወሉን እንደሰሙ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ። በፅጌ ታሪክ ላይ ጥሩ እንደተወያያችሁ እገምታለሁ። ከወሊድ በኋላ አንድ ሰአት ሳይሞላ ለልጇ እንገር መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ፣ ከነርስ ቅድስት በሰማችው ጥሩ ምክር ተገንዝባለች፡፡

Page 95: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

95

እቴ ብርቱካን፡-እስቲ አሁን ደግሞ ሌላ ቁምነገር እናንሳና እንነጋገር። ይህም በጣም ጠቃሚና ወሳኝ ርእስ ነው፡፡ ስለ ንፅህና እንወያይ እያልኩ ነው። ችግኝ ህፃናት ከተወለዱ በኋላ፣ እንዴት በንጽህና ተንከባክበን ጤናቸውን እንደምንጠብቅ መነጋገር አለብን።

ጨቅላ ችግኝ ህፃናት፣ ከወላጆች፣ ከሴት አያቶች፣ ከታላላቅ እህትና ወንድሞች፣ በፍቅር የተሞላ የዘወትር እንክብካቤ ያገኛሉ። የቤተሰብ አባላት በሙሉ፣ ህጻናትን በመያዝና በመንከባከብ የየራሳቸው ጠቃሚ ድርሻ አላቸው።

ቀደም ሲል፣ ህፃናት በአግባቡ የጡት ወተት እንዲያገኙ የቤተሰብ አባላት ሁሉ ድጋፍ መስጠት እንዳለባቸው ተነጋግረናል። የችግኝ ህጻናትን ንጽህና ለመጠበቅ እንዲሁም የሚተኙበትንና የሚጫወቱበትን ቦታ ለማፅዳት፣ ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸው ድርሻ ይኖራቸዋል።.

እቴ ብርቱካን፡ሁሌም የሚያስገርመኝ ነገር ምን ይመሰላችሁ? ብዙ ሰዎች፣ ህፃናት አይነ ምድር ጉዳት የሌለው ይመስላቸዋል። ይህ ለምን ይመስላችኋል? እስቲ በዚህ ጉዳይ ላይ እንወያይበት ፡፡ ብዙ ሰዎች፣ ምን አልባት አንዳንዶቻችሁ የህጻናት አይነ ምድር ምንም ጉዳት የለዉም ብላችሁ የምታስቡ ትኖራላችሁ፡፡ ሊያስረዳኝ የሚችል ሰው ይኖር ይሆን?

• እሰቲ በመጀመሪያ እኔ ለምን ሰዎች እንደዚህ እንደሚያስቡ አንዳንድ ነጥቦችን ልንገራችሁ ህፃናት የጡት ወተት ብቻ ስለሚጠጡ፣ አይነ ምድርቸው ጉዳት አያመጣም ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ።

• አንዳንድ ሰዎችደግሞ፣ የህፃናት አይነ ምድር ያን ያህልም ጠረኑ ለአፍንጫ ስለማይከብድ ጉዳት የለውም ብለው ያምናሉ።

• ወይም ደግሞ፣ ህፃናት ክፋት የማያውቁ የዋህ ስለሆኑ፣ የህፃናት አይነ ምድርም ጉዳት የለውም የሚል እምነትም ይኖራል።

እቴ ብርቱካን፡-ብዙዎቻችሁ እንዲህ አይነት ሃሳብ የነበራችሁ ልትሆኑ ትችላላችሁ። ወይም ደግሞ፣ እንደዚያ የሚያምኑ በርካታ ሰዎችን ታውቁ ይሆናል። ግን ልንገራችሁ። ህፃናት ክፋት የማያውቁ የዋሆች ቢሆኑም፣ የጡት ወተት ብቻ ቢጠጡም፣ የአይነ ምድርቸው ጠረን ባይከብድም፣ የህፃናት አይነ ምድር ጉዳት አልባ አይደለም። ምክንያቱም፣ የህፃናትም ሆነ የአዋቂ አይነ ምድር ውስጥ፣ ለበሽታ የሚዳርጉ ብዙ ጀርሞች አሉ። ቅንጣት ታክል ድንገት በንክኪ ወደ አፋቸዉ ወይም ወደ አፋችንና ሆዳችን ከገባ በሽታን ያስከትላል።

አያ ሙላት፡- የህፃናት አይነ ምድር ጉዳት እንደሚያመጣ ስትሰሙ ለብዙዎቻችሁ አዲስ ሊሆንባችሁ ይችላል። ጀርሞች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ፣ ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው እንዴት በቀላሉ እንደሚዛመቱ በተጨባጭ ለመገንዘብ የሚረዳን አንድ ጨዋታ ላሳያችሁ።

እኔ የጨዋታውን አይነት አብራራለሁ። አስተባባሪ፣ ሁለት ፈቃደኛ ተሳታፊዎች ከተቀመጡበት ተነስተው እንዲቆሙ በመጋበዝ ጨዋታውን ያስተባብሩልናል። አስተባባሪ ከእርድ ማስቀመጫ እቃ ውስጥ ትንሽ እየቆነጠሩ፣ በሁለቱ ፈቃደኛ

Page 96: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

96

ተሳታፊዎች የቀኝ መዳፍ ላይ ይነሰንሳሉ - መዳፋቸው በእርድ እስኪሸፈን ድረስ ማለት ነው።

አስተባባሪ፣ የሁለቱ ፈቃደኞች የቀኝ መዳፍ ላይ እርድ እስኪነሰንሱ ድረስ፣ ቴፑን መዝጋት ይችላሉ። ከተዘገጃጃችሁ በኋላ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

የደወል ድምፅ

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ። አሁን ሁለቱ ፈቃደኞች፣ ከሌሎች ተሳታፊዎች ጋር ይጨባበጣሉ። አንደኛው ፈቃደኛ፣ ከግማሾቹ ተሳታፊዎች ጋር በቀኝ እጁ ይጨባበጣል። ሁለተኛው ፈቃደኛም፣ ከቀሪዎቹ ተሳታፊዎች ጋር በቀኝ እጁ ይጨባበጣል። ሁሉም ተሳታፊዎች ከሁለቱ አንዱ ፈቃደኞች፣ጋር ተጨባበጣችሁ?

መልካ፤ እባካችሁ ሁላችሁም የቀኝ መዳፋችሁን ተመልከቱ (እየሳቀ)። በጣም አስቂኝ ጨዋታ አይደለም ብርቱካኔ? ሁሉም ሰው በመገረም መዳፉን ሲመለከት ይታይሽ!

አያ ሙላት፡- እሺ ጨዋታዉን እንቀጠል። እስቲ መዳፋችሁ ላይ ምን እንዳያችሁ ንገሩን።

የሁላችሁም ቀኝ መዳፍ በእርድ ዱቄት ተነካክቷል? አስተባባሪ፣ ተሳታፊዎች በየመዳፋቸው የእርድ ዱቄት ማየታቸውን በመጠየቅ ያረጋግጡ።

አያ ሙላት፡- በጣም ጥሩ

• አስታውሱ፤ ጀርሞች በአይን አይታዩም፤ ጀርሞች በሽታን ያስከትላሉ። በአይን ልናያቸው አንችልም። ነገር ግን፣ በህፃናት አይነ ምድር ውስጥ ይገኛሉ። በታዳጊ ልጆችና በአዋቂዎች አይነ ምድር እንዲሁም በእንሰሳት አይነ ምድር ውስጥም ጀርሞች አሉ።

• አይነ ምድር በእጃችን ከነካን፣ እጃችን በጀርሞች ይበከላል። ከሌላ ሰው ጋር ስንጨባበጥ፣ ልክ እንደ እርድ ዱቄት እንዳየነዉ ጀርሞችም ከመዳፍ ወደ መዳፍ ይተላለፋሉ።

• በመዳፋችን ፊታችንን እንዳብሳለን። አይናችንን እናሻሻለን። ከንፈርና አፋችንንም እንነካካለን - ምግብ ስንበላ።

• በተለይ ህፃናት ፣ ያገኙትን ነገር ሁሉ በመዳፋቸውና በጣታቸው መነካካት እናም ወደ አፋቸው ማስገባት ይወዳሉ።

• ህፃናትና የቤተሰብ አባላት፣ የህፃን አይነ ምድር ከነኩ፣ አይነ ምድር ውስጥ ያሉ ጀርሞች ወደ አይን እና ወደ አፍ እየተዛመቱ በሽታ ይፈጥራሉ።

እቴ ብርቱካን፡-ትክክል ብለሃል ሙላት። ትንሽ ላክልበት። የህፃነት አይነ ምድር፣ ጉዳት የሌለው የሚመስላቸው ሰዎች፣ አይነ ምድሩን በፍጥነት ለማፅዳትና ለመጣል እንዲሁም እጃቸውን ለመታጠብ ደንታ ላይኖራቸው ይችላል። ነገር ግን፣ አሁን ጉዳቱን ስላወቅን፣ የህፃናትን አይነ ምድር፣ እንደ ታዳጊ ልጆችና እንደ አዋቂዎች አይነ ምድር፣ በፍጥነትና በአግባቡ አስወግዶ ማፅዳት እንደሚያስፈልግ ተገንዝበናል።

በተለይ የችግኝ ህፃናት ሰውነት በቀላሉ በጀርም ስለሚጠቃ፣ ከጀርምና ከበሽታ

Page 97: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

97

ልንጠብቃቸው ይገባል። ለዚህ፣ ማንኛውን አይነ ምድር ወደ መፀዳጃ ስፍራ መድፋትና ማፅዳት፣ ወይም ጉድጓድ ውስጥ መቅበር አለብን። ታዲያ ጉድጓዱ፣ ከቤታችን ከጓሯችን፣ እንዲሁም ከማንኛውም ምንጭ እና ወራጅ ውሃ የራቀ መሆን ይኖርበታል።

እቴ ብርቱካን፡ የህፃናትን አይነ ምድር በአግባቡ ካስወገድን በኋላ፣ ቀሪ ስራ መኖሩን አትርሱ፡

• የችግኙ ህፃን ከተፀዳዳ በኋላ፣ መቀመጫውንና እጆቹን በሳሙናና በውሃ ማጠብ አለብን።

• የራሳችንንም እጅ በውሃና በሳሙና መታጠብ እንዳለብን አስታውሱ።

• ሳሙና ከሌለ፣ እጆቻችንን በንፁህ አመድና በውሃ መታጠብ እንችላለን። ነገር ግን፣ በአሁን ጊዜ ግን ፣ ሳሙና በየሱቁ ሞልቷል። ስለዚህ ለንፅህና ሲባል፣ ሳሙና ገዝተን ሁሌም ከቤት እንዳይጠፋ ማስቀመጥ አለብን።

አያ ሙላት፡- ህፃናትን የምናስቀምጥበት ቦታም ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ጨቅላ ችግኝ ህፃናት፣ በንፁህ ጨርቅ ወይም ምንጣፍ ላይ መቀመጥ አለባቸው። የእንሰሳት አይነ ምድር በአቅራቢያቸው መኖር የለበትም። ምክንያቱም፣ የእንሰሳት እበት ወይም በጠጥ ጀርም ይዘው የሚመጡ ዝንቦችም፣ ህፃናት ላይ መድረስ የለባቸውም።

አያ ሙላት፡ አሁን ደግሞ፣ ለቤተሰቦቻችን በቂ ምግብ ለማሟላት የሚጠቅሙ የማሳደግና የማርባት ዘዴዎች ላይ በትኩረት እንነጋገራለን። በዚሁ አጋጣሚ መታለፍ የሌለበት ጉዳይ አለ። በግብርና የመንተዳዳር ቤተሰቦች፣ ውሎአችን ከእርሻ ላይ ነው። ለስራ ሲታትሩ እጆቻችንና እግሮቻችን ከአቧራና ከጭቃ ጋር ነው የሚውሉት። ደክሞን ወደ ቤት ስንመለስ አቧራና ጭቃዉም አብሮን ወደ ቤታችን ይዘነዉ እንመጣለን፣ በዚህ ጊዜ ቤተሰባችን ለጀርም ልናጋለጥ እንችላለን። በተለይ ጨቅላ ችግኝ ህጻን ወይም አምስት አመት ያልሞላቸው ልጆች ካሉን ወደ ቤት ጀርም ይዘን እንዳንመጣ በደንብ መጠንቀቅ አለብን።

በእጃችንና በጫማችን፣ ከእርሻ መሳሪያዎቻችን ጀርሞች እንዳይዛመቱ እንጠንቀቅ። ከዚህም በተጨማሪ፣ እንስሳት መነካካታችን ስለማይቀር፣ ከእንሰሳት ጀርም ልናዛምት እንችላላን። ለራሳችንና ለቤተሰብ ጤንነት በማሰብ፣ እጃችንን በሳሙናና በውሃ በመታጠብ፣ መልካም የንጽህና ልማዶችን ተግባራዊ የማድረግ ሃላፊነት አለብን። ሌላው ነገር፣ ቤት ውስጥ ስንራመድ፣ እያየን እያስተዋልን ይሁን - በተለይም ህፃናት በሚቀመጡብትና የሚጫወቱበት አካባቢ።

አያ ሙላት፡- ንግስት ንባችን የእንሰሳት ተዋፅኦ ምግቦችን እንድታገኝ የምናደርግበት አንዱ ዘዴ፣ በጎችን ወይም ላሞችን ማርባት ነው። ባለቤታችሁ እንደወለደች፣ ከጤና ጣቢያ ወደ ቤት ስትመለስ የደስ ደስ መቀበያ አቅማችሁ ከፈቀደ በግ ወይም ዶሮ ታርዳላችሁ። ከወሊድ በኋላ፣ እንድትበረታና ጨቅላውን ችግኝ ህፃን ጥሩ የጡት ወተት በአግባቡ እንድታጠባ፣ ሴት አያቶች፣ ማለትም የአራሷ እናት ወይም አማች፣ ቅቤ ያለው ወፍራም አጥሚት እንድትጠጣ ታዘጋጃላችሁ። አጥሚት ለመስራት ደግሞ የላም ወተት አስፈላጊና ጥሩ ነገር ነው።

Page 98: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

98

እቴ ብርቱካን፡-ትክክል ብለሃል ሙላቴ። ለዚህም “ላሞችን የመንከባከብና ወተት የማለብ ዘዴዎችን’ የሚያስተምር ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት አዘጋጅተናል። አስታባባሪ፣ እባክዎ፣ የማስተማሪያ ወረቀቱን ለሁሉም ተሳታፊዎች ይስጡ።

አያ ሙላት፡- አስተባባሪ ይሄንን ጨዋታ ለመጫወት ተሳታፊዎችንበሦስት ቡድን ይከፋፍሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ቡድን ‘’ገቢ ማግኘትና የመግዛት’’ የተሰየመውን ጨዋታ ማለትም የመጨዋወቻ ሰሌዳና 56 የገንዘብ ካርዶች ይስጧቸው፡፡ ጨዋታን ለመጫወት የቡድኑ አባላት በመጨዋወቻዉ ሰሌዳ ዙሪያ መቀመጥ ይችላሉ - መሬት ወይም ወንበሮች ላይ፡፡

በጨዋታው ሰሌዳ ዙሪያ ያሉት የተለያዩ የቤትና የግብርና ቁሳቆሶች እንዲሁም ኮከብ ምግቦች ከነዋጋቸው በዝርዝር ተቀመጠዋል፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች ቤተሰቦች የሚገዟቸው ናቸው፡፡ በሰሌዳው መሀከል ላይ ክብ ዙሪያ ውስጥ ገንዘብ የሚቀመጥበት ሲሆን እንዲሁም ቤተሰቦች ያመረቱትን እህል የሚሸጡበት የገበያ ማዕከልን ይወክላል፡፡

1. ጨዋታውን ለመጫወት በየቡድኑ የተካፋፈሉ ተሳታፊዎች ተራ በተራ ምርቶቻቸውን ገበያ በመውሰድ ለሽያጭ በማቅረብ የምርታቸውን የሽያጭ ዋጋ መጠን በገንዘብ መልክ ይወስዳሉ፡፡ ሸጠው ባገኙት ገንዘብ ተሳታፊዎች በሰሌዳው ዙሪያ ከሚገኙ የቤትና የግብርና ቁሳቁሶች መርጠው የሚፈልጉትን ይገዛሉ፡፡

2. የመጀመሪያው ተጫዋች ተራቸውን ከጨረሱ በኋላ የገንዘብ ካርዶችን ወደነበረበት በመመለስ ተራውን ለሚቀጥለው ተጫዋች ይለቃሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጫዋች ምርቶቻቸውን ሸጠው ባገኙት ገቢ የገንዘብ ካርድ በመውሰድ እንደፊቱ የሚፈልጉትን ሰሌዳው ላይ የተደረደሩ ቁሳቁሶች መግዛት ይችላሉ፡፡ የቀሩት ተሳታፊዎች ጨዋታውን ይመለከታሉ፤ ተራቸውም ሲደርስ እንደበፊቱ ጨዋታውን ይቀጥላሉ፡፡

3. ሁሉም ተሳታፊዎች ተራ በተራ ከተጫወቱ በኋላ እያንዳንዱ የቡድን አባላት ተጫዋቾች ባገኙት ገንዘብ ምን እንደሸመቱበት በትኩረት ይወያዩበት እና የምርጫቸውን ምክንያት ይወያዩበታል፡፡

4. አስተባባሪ ተሳታፊዎች ምን አይነት ምግቦችን ለንግስት ንቦቻቸው እንዲሁም ለእምቡጥ ልጆቻቸው እንደገዙ እየተዘዋወሩ ይመልከቱ፡፡ በተጨማሪም የትኛዎቹን የቤት ቅሳቁሦች እንደገዙ ይመልከቱ፡፡

በዚህ አዝናኝ ጨዋታ ላይ የትኞቹ ቁሳቁሶችና ኮከብ ምግቦችን ቤተሰቦች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ውይይት ያድርጉ፡፡ ምርጫቸው አቅማቸውን ያገናዘበ መሆኑንና የትኞቹን ምርቶች ሸጠው ቅድሚያ ለኮከብ ምግቦች ግዢ እንዲያውሉ አሳስቧቸው፡፡

Page 99: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

99

ማዘጋጀት ሳይበላሽ ማቆየትና መከማቸት

እቴ ብርቱካን፡-ንግስት ንብ እናቶች ከወሊድ በኋላ ብርታት እንዳይጎድላቸው፣ በንጥረ ነገሮች የበለፀጉ ምግቦችን ልናዘጋጅላቸዉ ይገባል። ለአራስ ሴት አጥሚት ስንሰራ፣ ባለ ሦስት ኮከብ ምግብ የሆነውን ወተት በመጨመር፤ እንዲሁም በማገገቢያ ወቅት የዶሮና የበግ ስጋ የመሳሰሉ የእንሰሳት ተዋፅኦ ምግቦችን በማቅረብ ስናግዛት፣ የንግስት ንባችን ጤንነትና ብርታት አስተማማኝ ይሆናል። ያኔ ለጨቅላው ችግኝ ጥሩና በቂ የጡት ወተት ማጥባት ትችላለች።

አትርሱ፤ አራስ እናቶች ተጨማሪ ምግብ መብላት እንዳለባቸው አስታውሱ፡፡ በተለይ ስጋ በማይኖርበት ወቅት፣ እንደ አትክልትና ፍራፍሬ የመሳሰሉና በደህና ዋጋ የሚገኙ ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን በብዛት እንዲመገቡ ማድረግ አለብን። ለምን ቢባል፣ የሚመገቡት ለሁለት ነፍስ ነውና። እንዲሁም ለጨቅላው ችግኝ ህፃናት የጡት ወተት ያጠባሉ።

ማረፍ ማገዝና መብላት

እቴ ብርቱካን፡ ንግስት ንብ እናት ብርቱ ሆና እንድትዘልቅ፣ ባለቤቷና የሴት አያቶች በተቻላቸው መጠን ባለ ኮከብ ምግቦችን በማዘጋጀት፣ ማገዶና ውሃም በማምጣት፣ እንዲሁም ሌሎች የቤት ውስጥ ስራዎችን በማከናወን ሊያግዟት ይገባል። ንግስት ንብ እናቶች ከወሊድ በኋላም የሚመገቡት ለሁለት ነፍስ መሆኑን አትዘንጉ፤ ለጨቅላ ችግኝ ህፃናትን የጡት ወተት የሚያጠቡ ናቸውና።

ከወሊድ በኋላ፣ አራስ እናት ለመመገብና ህፃኗን ለማጥባት በቂ ጊዜ እንድታገኝ አስበው፣ ለሚስቶቻቸው ድጋፍ በመስጠት የተመሰከራላቸው ምስጉን አባቶች አሉ። አስተባባሪ፣ እባክዎ፣ የአባወራዎች ድጋፍ የተዘጋጁ የምስክርነት ካርዶችን ለተሳታፊዎች መስጠትን እንዳይዘነጉ አደራ።

መወያየትና በጋራ መወሰን

አያ ሙላት፡- አስደሳቹ ነገር ምን ይመስላችኋል? አባቶች፣ እናቶች፣ ሴት አያቶች ሁሉ፣ ችግኝ ህፃናት እንዲያብቡ፣ ብርቱና ብሩህ ሆነው እንዲያድጉ፣ ከዚያም በትምህርትና በኑሮ ስኬታማ እንዲሆኑ በጣም ይፈልጋሉ። አሁን ጊዜው የትወና ጨዋታ ነው። አስተባባሪ፣ በአራት ወይም በአምስት እያደረጉ ተሳታፊዎችን በቡድን ከከፋፈሉ በኋላ፣ ዛሬ የተማርነውን ቁምነገር እንዴት ለባለቤታችን ወይም ለሴት አያቶች እንደምናስተላልፍ እንለማመዳለን። የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለማሸነፍ የሚያስችሉ ብልሃቶችንም ከዚህ የትወና ጨዋታ እናገኛለን።

እቴ ብርቱካን፡-በቅድሚያ ግን፣ ከባለቤታችን እና ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥና ለመነጋገር የሚያገለግሉ የመግባቢያ ዘዴዎችን በተመለከተ፣ ባለፈው የውይይት ክፍለጊዜያችን የተማርናቸው ዋና ዋና ፍሬነገሮችን መልሰን እናስታውሳቸው። እንደ አንበሳ ወይም እንደ አህያ አልያም ደግሞ እንደ ማርና ው/ ጉሬዛ መሆን እንችላለን።

Page 100: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

100

• ከሰዎች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥ እንደ አንበሳ ባህሪ መሆን ማለት እንዴት እንደሆነ ሊያስታወሰን የሚችል ተሳታፊ አለ?

• ከሰዎች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥ እንደ አህያ ባህሪ መሆን ማለት እንዴት እንደሆነ ሊያስታወሰን የሚችል ተሳታፊ አለ?

• ከሰዎች ጋር ሃሳብ ለመለዋወጥ እንደ ማርና ው/ጉሬዛ ባህሪ መሆን ማለት እንዴት እንደሆነ ሊያስታወሰን የሚችል ተሳታፊ አለ?

እስቲ ተሳታፊዎች እነዚህን ያስታውሷቸው እንደሆነ እንመልከት። አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ ተሳታፊዎች ሁሉንም የመግባቢያ ዘይቤዎች አንድ በአንድ ያውቁ እንደሆነ በመጠየቅ ያረጋግጡ። ወይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። የመግባቢያ ዘይቤዎቹን በማስታወስ ሃሳብ እንደተለዋወጣችሁ እገምታለሁ። ጥቂት ፍሬ ነገሮችን ላክል።

• አንበሳ ቁጣ ያበዛል፤ ትዕግስት የለውም። በጩኸት ሃሳባቸውን በሌሎች ሰዎች ላይ በሃይል ይጭናሉ። ሁሌም ጠብ ጠብ ይሸታቸዋል - ጠብ ያለሽ በዳቦ እንደሚባለው ነው።

• አህያ አለቅጥ ዝምተኛና ግድ የለሽ ነው፤ ቸልተኝነትን ያበዛሉ። ሃሳባቸውንና መረጃዎቻቸውን ለሌሎች ሰዎች አያስተላልፉም። አንገታቸውን ደፍተው በመቀበል ሌሎች ሰዎች የወሰኑትን መታዘዝ ያዘወትራሉ።

• ማርና ውሃ/ጉሬዛ በራሳቸው ተማምነው ሃሳባቸውን ያጋራሉ፤ በትዕግስትና በደግነት መንፈስ። በብልህነታቸውና በግርማ ሞገሳቸው የሚከበሩና የሚደነቁ ናቸው።

እቴ ብርቱካን፡-አሁን ወደ ትወና ጨዋታው በመዝለቅ እንለማመዳለን። አስተባባሪ እባክዎ በሦስት በቡድን ተሳታፊዎችን ይከፋፍሉ። ለትወና የተዘጋጁትን የአባት/አባወራ፣ የእናት/ ሚስት፣ የሴት አያት ካርዶች ለእያንዳንዱ ቡድን ይስጡ፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ባለፈው ክፍለ ጊዜ እንዳደረግነው፣ በጥንድ በጥንድ ትወናውን እንጫወታለን። በቡድን ውስጥ ሁለት አባላት ትወናውን ሲጫወቱ ሌሎች የቡድን አባላት ተመልካችና ታዛቢ ይሆናሉ።

• ሁሉም ተሳታፊዎች የራሳቸውን ማንነት በመወከል (ማለትም አባት/ አባወራ፣ እናት/ሚስት፣ ወይም ሴት አያት ሆነው) ትወናውን የመጫወት ተራ ይደርሳቸዋል። በትወና ጨዋታውም፣ የእንገርን ጠቃሚነት እንዲሁም ህፃኑ 6 ወር እስኪሞላው ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻ የመስጠት አስፈላጊነት ለባለቤታቸው ወይም ለሴት አያቶች በማስረዳት ይለማመዳሉ።

• ችግኝ ህፃናትን በእናት ጡት ወተት በአግባቡ ለማሳደግ የቤተሰብ አባላት እንዴት መደጋገፍ እንዳለባቸው በቅጡ የመወያየት ብልሃትን ስትለማመዱ፤ ዛሬ ስለ ችግኝ ህፃናት የተማራችሁትን ቁምነገር በሙሉ ለመናገር ጥረት አድርጉ።

Page 101: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

101

እቴ ብርቱካን፡- በቡድኑ ውስጥ አንድ ሰው የራሱን ማንነት በመወከል ትወናውን ሲጫወት፣ ሌላ የቡድኑ ባልደረባ እንደ ባለቤት ወይም እንደ ሴት አያት ሆኖ ይጫወታል። ለምሳሌ፣ በሴቶች ቡድን ውስጥ፣ አንዷ ሴት በእናትነቷ የራሷን ማንነት ለመወከል የእናትነት ካርድ በአንገቷ አጥልቃ ትወናውን ስትጫወት፣ ሌላ የቡድኑ ሴት የአባወራ ካርድ በአንገቷ አጥልቃ እንደ አባወራ አስመስላ ለመጫወት ትተውናለች።

• ሁለቱ ሰዎች ለ5 ደቂቃ ትወናውን ተጫውተው ያቆማሉ። በተመልካችነት ሲታዘቡ የነበሩ የቡድኑ አባላት አስተያየትና ምክር ይሰጣሉ።

• ምክርና አስተያየቱ ካለቀ በኋላ፣ ከቡድኑ ሌላ አዲስ ጥንድ ለ5 ደቂቃ ትወና በመጫወት ከቡድኑ ባልደረቦች ምክርና አስተያየት ይቀበላል።

• ሁሉም የቡድኑ አባላት የራሳቸውን ማንነት በመወከል ትወናውን የመጫወት ተራ እስኪደርሳቸው ድረስ ጨዋታው ይቀጥላል። የእንገርን ጠቃሚነት እንዲሁም ህፃኑ 6 ወር እስኪሞላው ድረስ በእናት ጡት ወተት ብቻ የማሳደግ አስፈላጊነት ለቤተሰብ አባላት የማስረዳት ብልሃትን የምትለማመዱበት ጨዋታ ነውና።

አስተባባሪ፣ ደወሉን ተከትለው ቴፑን በመዝጋት የትወና ጨዋታውን ያስተባብሩ። ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ። የትወና ጨዋታውን እንደወደዳችሁትና ከባለቤታችሁ ወይም ከቤተሰብ አባላት ጋር ሃሳብ በመለዋወጥ የመግባባት ብልሃትን እንደተለማመዳችሁ አምናለሁ።

አስተባባሪ፤ አሁን ሁሉም ተሳታፊዎች በጋራ ሆነው የየቡድናቸውን ተሞክሮ እርስበርስ መጋራት እንዲችሉ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመሰንዘር ለውይይት ይጋብዟቸው፡

• ከትወና ጨዋታው ምን ተማርን?

• ችግኝ ህፃናት በጡት ወተት የማሳደግ ብልሃት ላይ ከቤተሰብ አባላት ጋር በቀና ተወያይተን ለመግባባትና ድጋፋቸውን ለማግኘት የቡድናችን ባልደረቦች ያበረከቱልን ጠቃሚ ምክሮች ምንድናቸው?

• ስለ ችግኝ ህፃናት ጡት ወተት ማጥባት ብልሃቶችን ለቤተሰብ ለማጋራትና ለመወያየት ተጨማሪ ልምድ ያገኛችሁ ይመስላችኋል?

አስተባባሪ፣ በዚህ ውይይት ምላሽና መፍትሄ ሳያገኙ የቀሩ ጥያቄዎች ካሉ ከውይይቱ በኋላ መዝግበው ይያዟቸው። በሚቀጥለው ክፍለጊዜ ምላሽና መፍትሄ ይዘው እንደሚቀርቡም ለተሳታፊዎች ይግለፁላቸው።

አያ ሙላት፡- እሺ ፣ የትወና ጨዋታው ምን ይመስል እንደነበረና ምን እንደተማራችሁበት እየተነጋገራችሁ ለመወያየት ተዘጋጃችሁ? ውይይቱን ስትጨርሱ አስተባባሪ ቴፑን መልሰው ይከፍቱት። ተመልሼ እመጣለሁ። እስከዚያው የሚያረካ ውይይት ይሁንላችሁ።

Page 102: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

102

SFX: የደወል ድምፅ

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን ደህና መጣችሁ። በትወና ጨዋታውና ውይይቱ አዝናኝ እንደነበረ እርግጠኛ ነኝ። ከባለቤታችሁ ጋር ሃሳብ የምትለዋወጡበት ጥሩ የመግባቢያ ክህሎት ለማዳበር፣ የትወና ጨዋታዉ ጥሩ መላ ነው። ከባለቤታችሁ ጋር መልካም መግባባትን ለመፍጠር፣ የተወሰነ ልምምድና የተግባር ሙከራ ያስፈልጋል። የሂደት ጉዳይ ስለሆነ፣ አንዳንዴ እንደተመኛችሁት ሳይሳካ ቢቀርና ተስፋ መቁረጥ አይኖርባችሁም። ከባለቤታችሁ ጋር በቀና ተወያይቶ የመግባባት ልምድ በአንድ ቀን ሙከራ ብቻ የሚፈጠር ባይሆንም፣ ለችግኝ ህፃናችን የወደፊት ህይወቱ አስተማማኝ መሰረት ለመስጠት ስንል አሁኑኑ የመግባባት ጥረቶችን መጀመር አለብን።

አያ ሙላት፡ ግሩም ነው፤ ደስ የሚል ቆይታ ነበር፡፡እንግዲህ የክፍለ ጊዜያችን መገባደጃ ላይ ለመድረስ እየተቃረብን ነው። በዛሬው ክፍለጊዜያችን ስለ ወሊድና ችግኝ ህፃናት፡ እንዲሁም ስለ ጡት ማጥባት ብዙ ተምረናል። እስቲ የተማርናቸውን ፍሬነገሮች በአጭሩ መልሰን እንቃኛቸው፡

1. የ“እኛ” ባህርያት፡ እኛ (የምናጠባ እናቶች) ከወሊድ በኋላ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ለችግኝ ህፃፃናት እንገር እንሰጣለን።

2. እንገር ህፃናትን ከቫይረስና ከባክቴሪያ ይከላከላል። የህፃኑ የመጀመሪያ ክትባት ነው ልንል እንችላልን።

3. እንገር የህፃናትን ጨጓራ ያፀዳል፤ አንጀታቸውንም ከህመም ይከላከላል።

4. እንገር ለህፃናት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ንጥረነገሮችና ውሃን አሟልቶ ይዟል።

5. የ“እኛ” ባህርያት፡ እኛ (የምናጠባ እናቶች) ችግኝ ህፃናችን ስድስት ወር እስኪሞላቸዉ ድረስ በጡት ወተት ብቻ እናጠባዋለን።

6. የጡት ወተት፣ ለችግኝ ህፃናት ምትክ የሌለው ወደር የለሽ ምግብ ነው። ችግኝ ህፃናት በአካልና በአእምሮ ለማደግና ለመጎልበት የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ የያዘ ነው።

7. የጡት ወተት፣ የህፃናት አንጎል፣ አይኖች እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎችን በሙሉ በአግባቡ የሚያሳድጉ ንጥረነገሮች አሉት።

8. የጡት ወተት ህፃናትን ከበሽታ ይከላከላል። ስለዚህ የጡት ወተት ማጥባት ለህፃናት የህይወት መድህን ነው።

እቴ ብርቱካን፡ ችግኝ ህፃናት ከተወለዱ አንድ ሰዓት ሳይሞላከእናቲቱ ጡት ጋር መገናኘታቸው ምን ምን ጥቅሞች እንዳሉት ላስታውሳችሁ፡

• አራሷ እናት ከወለደች በኋላ በብዛት ደም እንዳይፈሳት ይረዳል።

• ህፃናት ቶሎ ከእናታቸዉ ጡት ጋር ከተገናኙ፣ እናቶች በፍጥነት ወተት ያመነጫለሉ፤ ህፃናት የጡት ወተት ይጠባሉ። ሌላ ምግብ አያስፈልጋቸዉም።

• ህፃኑ ጡት ሲጠባ፣ እናቱ ተጨማሪ ወተት ታመነጫለች።

Page 103: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

103

• የ“እኛ” ባህርያት፡ እኛ (የምናጠባ እናቶች) በየእለቱ በገበታ ሰዓት በለ ኮከብ ምግቦችን ጨምረን እንመገባለን።

ወደ ቤት የሚወስዱ ቁሳቁሶችና የቤት ሥራዎች

አያ ሙላት፡- ንግስት ንቦችንና ጨቅላ ችግኝ ህፃናትን ለመደገፍ የወላጆች መግባባትና የቤተሰብ ውይይት ቁልፍ ጉዳይ በመሆናቸው፣ ጥቂት የማስታወሻ ስጦታዎችን አዘጋጅተናል። ማስታወሻዎቹን ወደ ቤት ወስዳችሁ ለቤተሰባችሁ በማሳየት ስለ ወሊድ እና ስለ ችግኝ ህፃናት፣ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ አንድ ሰዓት ሳይሞላ የጡት ወተት ማጥባት አስፈላጊነትንና የእንገር ጠቃሚነትን ንገሯቸው። ንግስት ንቦች ከወሊድ በኋላ ቤታችን ውስጥ በሚያገግሙበት ወቅት እንዴት ልንደግፋቸው እንደሚገባን አስረዷቸው።

እቴ ብርቱካን፡ ሁሉም የችግኝ ህፃናት ወላጆችና ሴት አያቶች፣ በቤታቸው ግድግዳ ላይ የሚለጠፍ የችግኝ ህፃን ምስል ሊስጣቸዉ ይገባል። ሁነኛ የውይይት መነሻ ስለሚሆኑ፣ ንግስትን ንብ እና ችግኙን ህፃን ለመደገፍ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከጎረቤቶች ጋር የመነጋገሪያ እድል ይፈጥሩልናል። የብዙ ሰው ትኩረትን መሳባቸው የማይቀር ነው።

• ሁሉም ተሳታፊዎች፣ “ላሞችን የመንከባከብና ወተት የማለብ ዘዴ” የሚለውን የማስተማሪያ ታጣፊ ወረቀት ማግኘት ይገባቸዋል። ምክንያቱም። ላሞች ባለ ሶስት ከኮብ ምግብ የሆነውን ወተት ይሰጡናል፤ ወተት መጠጣት ለምታጠባ እናት በጣም ጠቃሚ ነው። እናት ስትበረታ ደግሞ፣ ችግኝ ህፃኗን በጡት ወተት ብቻ በማጥባት ታሳድጋለች።

• የጨቅላ ችግኝ ህፃን እናቶች እንዴት ጡት ማጥባት እንደሚጀምሩ የሚያብራራ ሌላ ማስተማሪያ ወረቀትም አዘጋጅተናል። የችግኝ እናቶች፣ አባቶችና ሴት አያቶች ወረቀቱን ወደ ቤታቸው ወስደው ቤተሰብ ይጠቀምበታል።

• አስተባባሪ ፣ እነዚህን ማስተማሪያ ወረቀቶችና ቁሳቁሶች እንደ አግባብነቱ ለሁሉም ተሳታፊዎች በማከፋፈል አጠቃቀማቸውን ያስረዳሉ። እስቲ ለአፍታ ያህል ተመልከቷቸው፤ ስትጨርሱ ተመልሼ እመጣለሁ።

SFX: የደወል ድምፅ

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ። ሶስት ወር ያልሞላው ችግኝ ህፃን የሚያሳድጉ ወላጆችና፣ ሴት አያቶች የችግኝ ህፃን ተለጣፊ ምስል እና የእናት ጡት ወተት ተጣጣፊ ማስተማሪያ እንደደረሳቸው አምናለሁ።

Page 104: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

104

አያ ሙላት፡- እስቲ ንገሩኝ፣ ስንቶቻችሁ እነዚህን የጨቅላ ህፃናት ስጦታዎችን ለቤተሰባችሁ ታሳያላችሁ? እባካችሁ እጃችሁን አንሱ፡፡ መልካም፤ መቼም ሁላችሁም እጃችሁን እንዳነሳችሁ እገምታለሁ።

ጨቅላ ችግኝ ህፃናት በጡት ወተት ብቻ ማደግ እንዳለባቸው፣ ንግስት ንብ እናቶች ከወሊድ በኋላ በሚያገግሙበት ወቅት ለሁለት ነፍስ እንደሚመገቡና ተጨማሪ ባለ ኮከብ ምግቦችን መብላት እንዳለባቸው በመዘርዘር ዛሬ የተማራችሁትን ቁምነገር ለባለቤታችሁና ለቤተሰባችሁ ለማካፈል ስንቶቻችሁ ቃል ትገባላችሁ? እባካችሁ እጃችሁን ከፍ በማድረግ አሳዩ።

የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙርስ? ስንቶቻችሁ መዝሙሩን ቤት ውስጥ በመዝፈን ባለቤታችሁንና ቤተሰባችሁም እንዲዘፍኑ ለማለማመድ ቃል ትገባላችሁ? ቃል የምትገቡ እባካችሁ እጃችሁን ከፍ አድርጉ።

ዛሬ የተማርነው ለባለቤታቸውና ለቤተሰባቸው ለማጋራት ፈቃደኛ ለሆኑት ሁሉ፤ እስቲ አንዴ እናጨብጭብላቸው!

የጭብጨባ ድምፅ

የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙር (fade in)

አያ ሙላት፡- እንዴ! ምንድነው የምሰማው? የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙር ይመስላል። በንግስት ንብ እና በችግኝ ህፃን ላይ ያተኮረውን አራተኛው ክፍለጊዜያችንን ለመደምደም፣ ምርጥ የመዝጊያ መዝሙር!

አያ ሙላት፡- ከመሰነባበታችን በፊት፤ የጡት ማጥባት የእሽሩሩ ዘፈናችንን አንዴ እንዝፈን።

የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙር

እቴ ብርቱካን፡ ድንቅ ነው! እያባበለ የሚወስድ ድንቅ መዝሙር! ድንቅ አዘማመር! ምስጋና ይድረሳችሁ። አንዴ ለራሳችን እናጨብጭብ፤ አራተኛን ክፍለጊዜያችንን በድንቅ መዝሙር አጠናቀቅን!

አስተባባሪ ለቀጣዩ ክፍለጊዜያችን የት እንደምንገናኝ ለሁሉም ተሳታፊዎች ያስታውሷቸው። ሁላችሁንም፣ ለንቁ ተሳትፎአችሁ ምስጋናዬን እገልፃለሁ። በመጪው ክፍለጊዜ፣ ለእንቡጡ መዘጋጀትን በተመለከተ ለመወያየት፣ ከእናንተ ጋር የምንገናኝበትን ጊዜ በጉጉት እጠብቃለሁ። ደህና ቆዩ ወገኖቼ

Page 105: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

105

Page 106: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 107: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

107

መግቢያ

እቴ ብርቱካን፡- ጤና ይስጥልኝ፤ እንደምን ሰነበታችሁ? ለሁለተኛው የመማማሪያ ክፍለጊዜያችን እንኳን በደህና መጣችሁ!

አቶ ቢራራ መለሰ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የስርዐተ ምግብ ቡድን መሪ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ሲናገሩ እንዳደመጣችሁት፤ የብሄራዊ የእናቶች ምግብ አለመጣጠንና የህጻናት መቀንጨር ትልቅ የሀገር ችግር መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በዚህም ዙሪያ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎች አዘጋጅተናል፤ በእነዚህ ክፍለጊዜዎች ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የእናትና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋናና ቁልፍ የሆኑ ትምህርቶችን እንማራለን፡፡ የዚህ ትምህርታዊ ውይይት ዋናው ዓላማ፤ በቂ እውቀትና ክህሎት ገብይታችሁ፤ ጠንካራ፣ ጤናማ እና ብሩህ ህጻናት አሳድጋችሁ ለቁምነገር እንዲበቁ ማድረግ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡- ብርቱካን እባላለሁ። በሚኖሩን የውይይት ክፍለጊዜያት በርቀት ሆኜ እመራለሁ። በቆይታችን አንዳንድ ጊዜ የእኔን ድምፅ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የባለቤቴን የሙላትን ድምጽ ትሰማላችሁ፤ በሌላ ጊዜ ደግሞ ቀጥታ ከናንተ ጋር ያሉትን አስተባባሪ ትሰማላችሁ፤ እየተቀያየርንና እየተተካካን የትምህርት ክፍለጊዜውን እንመራለን። በየመሃሉም ለሚኖራችሁ ውይይት አስተባባሪ ቴፑን በመዝጋት እንድትወያዩና የቡድን ስራ እንድትሰሩ ይረዷችኋል። ይሄን የደውል ድምጽ ስትሰሙ (የደውል ድምጽ ይሰማል) ቴፑ ይጠፋል ማለት ነው። የምትሰሩት የቡድን ስራ ወይም ውይይት ሲያበቃ ቴፑ ይከፈትና እኔና ሙላት ካቆምንበት እንቀጥላለን ማለት ነው።

እስቲ እንሞክረው! ‹ኪኪልልል› የሚለውን የደወል ድምጽ ስንሰማ አስተባባሪ እባክዎን ቴፑን ይዝጉትና ከርስዎ ጀምሮ ሁሉም ሰው እራሱን አስተዋወቆ ሲጨርስ፤ እባክዎን መልሰው እንደገና ቴፑን ይክፈቱት።

ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስ

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ፤ መቼም አሁን ሁላችሁም በደንብ እንደተዋወቃችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የዛሬውን ርዕሰ ነገር ከመነጋገራችን በፊት እስኪ ያለፉት አራት የውይይት ክፍለግዜ የተነጋገርንባቸውን ጉዳዮች መለስ ብለን እንያቸው፡፡

በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ውስጥ ልጆቻችን ጠንካራ፤ ጤናማና ብሩህ እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብን እንደምታስታውሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ለመሆኑ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ስንል ምን ማለታችን ነው? ማነው ሊነግረን የሚችለው? ስንቶቻችሁ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት የሱፍ አበባ የእድገት ደረጃዎች ማለትም ዘር፤ ችግኝ፤ እምቡጥና አበባ ታስታውሳላችሁ? ስለ ሶስቱ የጉልቻ አምዶችና ስለሚወክሉት የኮከብ ምግቦችም ተምረን ነበር፤ ምን እንደሆኑ ከመካከላችሁ የሚነግረን አለ?፤ ምጣዱስ ምን እንደሚወክል የሚነግረን አለ?፤

የጉልቻው ምስል ምን ምንን እንደሚወክል እና፤ ንግስት ንቦች በቀን ውስጥ ባለ ሶስት ኮከብ ምግብ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ፤ ባለ ሁለት ኮከብ ምግብ ደግሞ በመደበኛ የምግብ ሰዓት ወይም መክሰስ ላይ መጨመር እንዳለባቸዉ ለባለቤታችሁና

Page 108: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

108

ለቤተሰቦቻችሁ አስረድታችኋል ?

እቴ ብርቱካን፡-ባለፉት አራት የውይይት ክፈለግዜያችን ሶስት መልእክት ያዘሉ ዘፈኖች ሰምተናል፤ ዘፈኖቹ ስለምን እንደነበሩ ሊነግረን የሚችል ካለ እጃችሁን አውጡ!

ስለ መጀመሪያ አንድ ሺህ ቀናት ባለፉት አራት የውይይት ክፈለጊዜ የተማርነው ምን ያህሉን እንደምታስታውሱት አጠር ያለች ውይይት እናድርግ፤ አስተባባሪ ውይይቱን በመምራት ለሚቀጥሉት ጥያቄዎች እጃቸውን ያወጡትን ሰዎች ቁጥር መዝግቦ ይያዙ፡፡

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የንግስት ንብን መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የጡት ማጥባት የእሹሩሩ መዝሙር አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ?

• የአይረንና ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተር እና የዘር ተምሳሌት ስቲከር ስንቶቻችሁ ናችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ያሳያችሁ አሳይታችኋል?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የእናቶች ሥርዓተ ምግብ ፖስተሩን በቤታችሁ ግድግዳ ላይ ለጥፋችኋል?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የችግኝ ተምሳሌት ስቲከር ግድግዳ ላይ የለጠፋችሁስ?

አያ ሙላት፡- ባለፉት አራት ክፍለ ጊዚያችን የተለያዩ ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ሰጥተናችሁ ነበር፤ የዶሮ ቤት አሠራር፣፤ የዶሮ መኖ አዘገጃጀት፣ ላሞችን መንከባከብና አስተላለብ እንዲሁም ጨቅላ ህፃናት ጡት መጥባት እንዲጀምሩ ማስለመድን የሚያስተምሩንን መረጃዎች ተሰጥቷችኋል፤

• ስንቶቻችሁ እነዚህን በራሪ ወረቀቶች ለባለቤታችሁና ለቤተሰባችሁ አሳይታችሁዋል?

አስተባባሪ፣ እባክዎ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት፣ ውይይቱን ያስተባብሩ ። ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱ።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ ! ጥሩ ውይይት እንዳደረጋችሁና የቤት ተሞክሯችሁን እንደተጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ባለፈው የውይይት ክፈለጊዜ፤ ስለ ችግኝ የእድገት ደረጃ ብዙ ጠቃሚ ትምህርቶች ተምረናል፤ የሚያጠቡ ንግስት ንቦች እና ጨቅላ ችግኝ ሕፃናትን እንዴት እንደምናግዛቸው አይተናል

የሚያጠቡ ንግስት ንቦቻችንን እንዴት እንደምናገዛቸው የሚያስታውስንአለ?

• ንግስት ንቦችን በቤት ስራ ብናግዛቸው፤ ለማረፍ፤ ለመብላት፤ እንዲሁም ጨቅላ ችግኝ ህፃናትን ለማጥባት ግዜ ያገኛሉ፡፡

Page 109: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

109

• ንግስት ንባችን ለሁለት ስለምትበላ፤ ተጨማሪ ምግብ መብላቷን እና ተጨማሪ ኮከብ ምግብ ፤ በየቀኑ እንድትመገብ የእኛ እገዛ ያስፈልጋታል፡፡

አያ ሙላት፡ የችግኝ ጨቅላ ሕፃናትጠንካራ፤ ጤናማና ብሩህ እንዲሆኑ ምን ማድረግ እንዳለብን ታስታውሳላችሁ?፤

1. ችግኝ ጨቅላ ሕፃናት እንደወለዱ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ጡት መጥባት መጀመር ይኖርባቸዋል፡፡እናቶች ከጡታቸው የሚወጣውን የመጀመሪያ ወርቃማ ወተት ማለትም እንገር ለህፃኑ ማጥባት አለባቸው

2. ለመጀመሪያ 6 ወራት ከእናት ጡት በስተቀር ውሃም ሆነ ሌላ ምግም በምንም አይነት መውሰድ የለባቸውም

3. የችግኝ ጨቅላ ሕፃናትአይነምድር ወዲያውኑ በስርዐት ሌላ ነገር ሳያነእዳሪ መጣል አለበት

4. የችግኝ/ጨቅላ ሕፃናት ከተፀዳዱ በኋላ መቀመጫቸውን፣ እጃቸውን በውሃና በሳሙና በደንብ ማጠብ አለብን

የችግኝ ጨቅላ ሕፃናትን አይነምድር ጠርገን ከጣልን በሁዋላ እኛም እጃችንን በውሃና በሳሙና በቅጡ መታጠብ አለብን፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ባለፈው የውይይት ክፈለጊዜአችን የጡት ማጥባት የእሽሩሩ መዝሙርዘምረናል ችግኝ ሕፃናት ላላቸው ተሳታፊዎች የችግኝ ተምሳሌት ስቲከር ሰጥቼ ነበር

ከተሳተፊዎች መካከል የቤት ውስጥ ተሞክሯችሁን ልታካፍሉን የምትችሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ? እኒህን ሁሉ መረጃዎች ለባለቤታችሁና የቤተሰብ አባላት ስታሳዩ፣ ሁኔታቸው እንዴት እንደነበር? አስተባባሪ፤ እባክዎ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ውይይቱን ያስተባብሩ፡፡

• ስንቶቻችሁ ናችሁ ለባለቤታችሁና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ጡት የሚያጠቡና ቤት ውስጥ የሚያገግሙ ንግስት ንቦችን መደገፍ ስለሚቻልባቸው መንገዶች ያስረዳችሁ? ስንቶቻችሁ ናችሁ ለባለቤታችሁና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ጨቅላ ችግኝ ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ እንዲሆኑ ስለሚያግዙ መንገዶች ያስረዳችሁ?ስንቶቻችሁ ናችሁ ለባለቤታችሁና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት የጡት ማጥባት የእሹሩሩ መዝሙርን እቤታችሁ ውስጥ የዘምራችሁ?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ ለባለቤታችሁና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት የችግኝተምሳሌት ስቲከርን ያሳያችሁና እቤታችሁ ግድግዳ ወይም ላይ የለጠፋችሁ?

አያ ሙላት፡- ብርቱካኔ ፤ለተሳታፊዎች እነዚህንም ጥያቄዎች ልንጠይቃቸው ይገባል

1. ከቤተሰቦቻችሁ ውስጥ የህጻናትን አይነምድር በፍጥነትና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ማስወገድ የጀመራችሁ ስንቶቻችሁ ናችሁ?

2. ህጻናት ከተፀዳዱ በኋላ መቀመጫቸውን እና ()እጃቸውን በሳሙናና በውሃ ማጠብ የጀመራችሁ ስንቶቻችሁ ናችሁ?

Page 110: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

110

3. የህጻናትን አይነምድር ከነኩና በአግባቡ ከጣሉ በኋላ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ የጀመራችሁ ስንቶቻቻችሁ ናችሁ?

4. አስተባባሪ፤ እባክዎ ጥቂት ሰዎች እነዚህን ጥያቄዎች እንዲመልሱና የቤታቸውን ተሞክሮ እንዲያካፍሉ በመጠየቅ ውይይቱን ይምሩት፡፡ ሲጨርሱ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

አያ ሙላት፡- ተመክሯችሁን ስላካፈላችሁን እናመሰግናለን! ለቤተሰብ አዲስ ሃሳብ ለማካፈልና ለመወያት ስንሞክር፣ አንዳንዴ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። ለምሳሌ፣ከቤተሰብ ጋር ስትነጋገሩ ያጋጠማችሁ ፈተና ካለ ልትነግሩን ትችላላችሁ?

እስቲ ሁላችሁም በእነዚህ ጥያቄዎች ላይ ስትወያዩ፣ እባካችሁ እርስበርስ ተሞክሯችሁን ተለዋወጡ። አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ በተሳታፊዎች የቤተሰብ ገጠመኝ ላይ ያተኮረውን ውይይት ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ ቴፑን ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

እቴ ብርቱካን፡-እንኳን በደህና መጣችሁ! አሁን የዛሬ ርዕሰ ጉዳያችንን እንጀምር፤ አምስተኛ ክፍለ ጊዜያችንን ማለት ነው፡፡ አዲስ እናት መሆን አስደሳች ነገር ነው! ችግኝ ህጻናት ወደ እንቡጥነት ሲያድጉ ተከትለው የሚመጡትን ትላልቅ ለውጦች እንነጋገራለን፡፡

ችግኝ ህጻናትና እንቡጥ ህጻናት ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚስታውሰን ይኖራል ?

• ችግኝ ህጻናት የሚባሉት ከተወለዱበት ጊዜ አንስቶ 6 ወር እስኪሞላቸው ድረስ ያሉ ሕፃናት ናቸው፡፡

• እንቡጥ ህጻናት የሚባሉት ደግሞ ከ6 ወር እስከ 12 ወር እድሜ ያሉ ህጻናት ናቸው፡፡

በዛሬው ክፍለ ጊዜያችን፤ እናቶችና ቤተሰቦች ለእዚህ ለውጥ ራሳቸውን ለማዘጋጀት እንዲሁም ችግኝና እንቡጥ ሕፃናትን ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ይሆኑ ዘንድ በአግባቡ እንዲያድጉ ምን ማድረግ እንደምትችሉ እንማራለን፡፡

እቴ ብርቱካን፡ እርግጠኛ ነኝ በችግኝ ህጻናት ላይ ብዙ ለውጦችን አይታችኋል፡፡ ይግርማል በጣም ቶሎ እኮ ነው የሚያድጉት! እናንተን እንኳን እንዴት እንደሚለዩዋችሁና አስቂኝ ፊት ስታሳዩዋቸው ወይም አስቂኝ ድምጽ ስታሰሟቸው እንዴት እንደሚደሰቱ አጢናችኋል? እቃዎችን እንዴት አፈፍ እንደሚያደርጉና ያገኙትን ነገር ሁሉ ወደ አፋቸው እንደሚከቱስ አስተውላችኋል? በዚህ መልክ ነው መዳሰስን የሚማሩት፤ ሆኖም ቆሻሻ የሆነ ነገር ወደ አፋቸው እንዳይከቱ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባችኋል!

• የህጻናት አዕምሮና አካል ከፅንስ ወይም ዘር ከሆኑበት ጊዜ አንስቶ ማደግ ይጀምራሉ ፡፡ ሲወለዱም፣ ችግኝ ህጻናት የሚማሩት በሚነኩት፣በሚቀምሱት፣በሚያሸቱት፣ በሚሰሙትና በሚያዩት ነገር ነው፡፡

Page 111: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

111

• ቤተሰቦች፤ በሕጻናት የእድገት ሂደት ፣ የችግኝ እድሜያቸውን ከሚያጠናቅቁበት ጊዜ አንስቶ እንቡጥ እስኪሆኑ ብዙ ለውጦች እንደሚከሰቱ ሊጠብቁ ይገባል፡፡

እቴ ብርቱካን፡ ችግኝ ህጻናት ወደ እንቡጥ ሲያድጉ ምን አይነት ለውጦችን እንደምንጠብቅ ለመወያየትና የእናንተን ሃሳብ ለመስማት ጥቂት ጊዜ እንውሰድ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ በየተሳታፊዎች ተሞክሮዎች ላይ ውይይት ያድጉ፡፡ ሲጨርሱ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

አያ ሙላት፡ ውዴ፤ እስኪ አንቺ ደግሞ ትንሽ እረፊና እኔ ልተካሽ ፡፡ የእኛ ልጆች ባደጉበት ወቅት የማስታውሳቸውን ትዝታዎችና ያየኋቸውን ትላልቅ ለውጦች ልነግራቸው ፡ ሁሉም ህጻናት የሚያድጉት በራሳቸው ሂደት ነው ፤ነገር ግን አብዛኞቹ ቤተሰቦች እንቡጥ ህጻናት የሚከተሉትን ነገሮች እንደሚከሰቱ መጠበቅ አለባቸው፡

• የመጀመሪያ ጥርሳቸውን ያበቅላሉ

• የተለያዩ እቃዎችን ይነካሉ፣ይጎትታሉ፣ ያነሳሉ እንዲሁም ይጫወቱበታል

• በርካታ የተለያዩ ነገሮችን ወደ አፋቸው ይከታሉ

• ራሳቸውን ችለው መቀመጥን ይማራሉ

• በሆዳቸው ሲተኙ ከጭንቅላታቸውና ከደረታቸው ቀና ይላሉ

• በራሳቸው መነሳትና በድጋፍ መቆምን ይማራሉ

• በወላጆች ድጋፍ መራመድን ይለማመዳሉ

በጣም ትልቁ ነገር ደግሞ ከእናት ጡት በተጨማሪ ወፍራም ገንፎና ሌሎች ለስላሳ የተፈጩ ምግቦች መብላት መለማመድ አለባቸው፡፡

1. ከ7 እስከ 12 ወር ባላቸው እድሜ ህጻናት ወደፊት የሚሳቡ ሲሆን ለመዳህ ይጓጓሉ፡፡ እንቡጥ ህጻናት ሁሉን ለማወቅ በጣም ጉጉ ናቸው፡፡ እቃዎችን መነካካት፣ ማንሳትና ያገኙትን ነገር ሁሉ ወደ አፋቸው መክተት ይወዳሉ፡፡ እንቡጥ ህጻናት አካባቢያቸውን የሚፈትሹበትና የሚማሩት ዋነኛው መንገድ ይህ ነው፡፡

2. በዚህም ምክንያት እንቡጥ ሕፃናት ለብዙ ጀርሞች ይጋለጣሉ ማለት ነው፤ ይህም ለህመም ይዳርጋቸዋል፡፡

አያ ሙላት፡-፡ እስኪ አሁን ደግሞ በጣም የሚያስገርም ነገር ላጫውታችሁ። በቅርቡ፣ በኤንጂን ፕሮጀክት የተላከ የአጥኚዎች ቡድን በተለያዩ መንደሮች እየተዘዋወረ የታዘበው ነገር፣ ጉድ ያሰኛል። የቡድኑ ሥራ ምን መሰላችሁ? እንቡጥ ህፃናት ምን ሲያደርጉ እንደሚውሉ ቁጭ ብሎ መከታተልና ማጥናት! የአጥኚዎች ቡድን 24 እንቡጥ ህፃናትን ከጠዋት እስከ ማታ በቤታቸው ውስጥ በመገኜት የሚያደርጉትን ነገር በሙሉ ተመልክተው መዘገቡ፡፡ እስኪ፣ የአንዲት የዘጠኝ ወር ህፃን ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ ቀኑ ሰባት ስዓት ድረስ፣ ወደ አፏ ያስገባቻቸው ነገሮች በዝርዝር ልንገራችሁ።

Page 112: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

112

• የእናቷ ልብስ

• የጎረቤት ልብስ

• የእህቷ ጣቶች (በሶስት ተደጋጋሚ ጊዜያት)

• ቡና ለመሸፈን የሚያገለግለውን ጨርቅ

• የጎረቤት ፀጉር

• የእናቷ ጡት (በበርካታ ተደጋጋሚ ጊዜያት)

• የጎረቤት ልጅ የሰጣትን ዳቦ

• ሴት አያቷ እጃቸው ላይ እየፈሰሱ ያጠጧትን ን የላም ወተት

• የእንጨት ቁራጭ

• ስትጫወትበት የነበረ ማንኪያ

• አጠገቧ ተኝታ የነበረችውን የድመት ጭራ

• የእናቷን ጣቶች

• ከቅድሙ የተለየ ሌላ የዳቦ ቁራሽ

• የእንጨት ብትር

• መሬት የወዳደቁ ቅጠሎች (ቢያንስ ቢያንስ ለሰባት ተደጋጋሚ ጊዜያት)

• ድንች በእንቁላል (እናቷ እጆቿን በውሃ ብቻ ታጥባ ሳይደርቅ፣ በእርጥብ እጇ እያጎረሰቻት)

አያ ሙላት፡ (እየሳቀ) ይሄ ሁሉ በአንድ ቀን ነው። በማግስቱም አልቀረም፤ እንቡጧ ህፃን፣ እንደልመዷ ቀጠለች፣ አጥኚዎቹ በማግስቱ ጠዋት እየተከታተሉ የመዘገቡትን ይቺው ሕፃን ወደ አፏ ያስገባቻቸው ነገሮች ዝርዝር እነሆ፡

• ከእህቷ እጅ የወሰደችው የብረት ስፕሪንግ

• የሚያንቃጭል የፕላስቲክ መጫወቻ

• የድስት ማስቀመጫ ስፌት(ለ10 ተደጋጋሚ ጊዜያት ወደ አፏ አስገብታዋለች)

• የጫማ ቀለም ቆርቆሮ

• ስትጫወትበት የነበረ ማንኪያ (ለ5 ተደጋጋሚ ጊዜያት)

• የእናቷን ጫማ

• መሬት ላይ የነበረ ገለባ

• አባቷ ከእርጥብ ሳህን በማንኪያ ያጎረሳትን እንቁላል

• እህቷ የሰጠቻትን ስክርቢቶ

• አፈር

• የአሻንጉሊት ጭንቅላት

Page 113: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

113

• ተርፎ የነበረና እናቷ በማንኪያ ያጎረሰቻትን እንቁላል

• ከምንጭ የመጣ ያልተፈላና ያልተጠራ ውሃ በኩባያ

• የእናቷን ጡት (ለበርካታ ተደጋጋሚ ጊዜያት የጡት ወተት ጠብታለች)

• የሴት አያቷ እጃቸውን ሳይታጠቡ እጃቸው ላይ እያፈሰሱ ያጠጧትን የላም ወተት

• የሌላ ልጅ ከንፈር

• እንጀራ

• መሬት ወድቆ የነበረ ሳር

አይገርምም! እረፍት የሌላት አስገራሚ ህፃን! ስንቱን አዳረሰች! ነገር ግን፣ አስታውሱ ወደ አፏ ያስገባቻቸው ብዙዎቹ ነገሮች፣ ንፅህና ስለሚጎድላቸው፣ ለሷም ሆነ ለሌሎች እምቡጥ ህፃናት ጥሩ አይደሉም። ለዚህም ነው ህፃናት የሚታመሙት።

እቴ ብርቱካን፡ ትክክል ነህ ሙላትዬ። እንቡጥ ህፃናት በእጅጉ እንቅስቃሴ ያበዛሉ። ስድስት ወር ከሞላቸው በኋላ፣ ለአእምሮና ለአካል እድገታቸው፣ ከጡት ወተት በተጨማሪ ሌሎች አጋዥ ምግቦችን ይፈልጋሉ። ከጡት ወተት በተጨማሪ፣ የተፈጩና የላሙ ምግቦች ከወፍራም ገንፎ ጋር እየደጋገሙ መብላት እንዲሁም ንፁህ የተፈላና የተጣራ ውሃ መጠጣት አለባቸው።

በህፃናት ላይ የሚታዩ ትልልቅ የእድገት ለውጦች፣ ለቤተሰብ ድንቅና ብርቅ ናቸው። ደግሞም አስታውሱ፤ በዚህ የእድገት ደረጃቸው ህፃናት ብዙ ነገር ስለሚነካኩና እያነሱ ወደ አፋቸው ስለሚያስገቡ፣ ለበሽታ እንዳይጋለጡ ከወትሮው በበለጠ በትጋት ልንንከባከባቸውና ልንጠብቃቸው ይገባል። ወደ አፋቸው የሚያስገቧቸው ነገሮች፣ በጀርም የተበከሉ ናቸው።

እቴ ብርቱካን፡ እስኪ፣ የአገራችንን ሁኔታ በመቃኘት፣ ጀርሞች ምን ያህል ችግኝ እና እንቡጥ ህፃናትን እንደሚያጠቁ እንመልከት። የኢትዮጵያ መንግስት፣ ከየአካባቢው መረጃዎችን በመሰብሰብ ባካሄደው ጥናት ምን አይነት ውጤት እንደተገኘ እንይ። በሁለት ሳምንት ውስጥ፡

• ስድስት ወር ያልሞላቸው መቶ ህፃናት መካከል፣ 10 ያህሉ ተቅማጥ ይዟቸዋል።

• ከስድስት እስከ 11 ወር እድሜ ካላቸው መቶ ህፃናት መካከል፣ 25ቱ ተቅማጥ ይዟቸዋል።

• ከ12 እስከ 24 ወር እድሜ ካላቸው መቶ ህፃናት መካከል፣ 23ቱ ተቅማጥ ይዟቸዋል።

• ከ2 እስከ 3 ዓመት እድሜ ካላቸው መቶ ህፃናት መካከል ደግሞ፣ 14ቱ ተቅማጥ ይዟቸዋል -ይሄ ውጤት የተገኘው በሁለት ሳምንት ውስጥ በተረደገ ጥናት ነው፡፡

Page 114: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

114

እነዚህ ቁጥሮች፣ ቤተሰቦች እና በአጠቃላይ አገራችን ከባድ ችግር ውስጥ እንዳሉ ያሳያሉ። እስቲ፣ ከእነዚህ ቁጥሮች በመነሳት የችግሩን ስፋት መገንዘባችንን ለማረጋገጥ ትንሽ እንወያይ። አስተባባሪ ፣ እባክዎን በሚቅጥሉት አራት ጥያቄዎች ላይ ተሳታፎዎች እንዲወያዩ ያግዟቸው፡፡

• የተቅማጥ ችግር በይበልጥ የታየባቸው በየትኛው የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናት ላይ ነው?

• ይህ ለምን የሆነ ይመስላችኋል?

• በተቅማጥ ችግር በትንሹ የታየበት በየትኛው የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ህፃናት ላይ ነው?

• ይህስ ለምን የሆነ ይመስላችኋል?

አስተባባሪ፣ እባክዎ ቴፑን በመዝጋት፣ ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ፣ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ ይሰማል።

አያ ሙላት፡ እንኳን ደህና መጣችሁ! ጥሩ ውይይት እንዳደረጋችሁ እገምታለሁ። በእንቡጥ ህፃናት ላይ የተቅማጥ ችግር ለምን ከፍ እንዳለ አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት እውዳለሁ? እንቡጥ ህፃናት ወዲህ ወዲያ እየተንቀሳቀሱ አካበቢውን ያዳርሱታል። ከቦታ ቦታ ይንፏቀቃሉ፤ ዙሪያቸውን እያሰሱ ያገኙትን ሁሉ ይነካካሉ፤ የያዙትን ሁሉ ወደ አፋቸው ያስገባሉ። በዚያ ላይ፣ ከጡት ወተት በተጨማሪ፣ ሌሎች ምግቦችን ይበላሉ፤ ሌሎች ፈሳሾችን ይጠጣሉ።

ማስታወስ ያለብን ሌላው ጉዳይ፣ እንቡጥ ህፃናት ጥርስ እያወጡ ሊሆን ይችላል። ጥርስ ማውጣት ሲጀምሩ የድዳቸውን ስሜት ለማርገብ ሲሉ፣ ብዙ ነገሮችን ወደ አፋቸው ማስገባት ይበልጥ ያምራቸዋል።

• ከጡት ወተት በተጨማሪ፣ ሌሎች ምግቦችን መብላትና ፈሳሾችን መጠጣት መጀመራቸው፤ ጣቶቻቸውንና ሌሎች ነገሮችን ወደ አፋቸው ማስገባት ማዘውተራቸው፣ ተቅማጥ ለሚያስከትሉ ጀርሞች ይበልጥ ያጋልጣቸዋል።

• ችግኝ ህፃናት፣ የእንቡጥ ህፃናትን ያህል ወዲህ ወዲያ ብዙ አይንቀሳቀሱም። ብዙውን ጊዜ፣ በቤተሰብ አባላት ጭን ላይ ታቅፈው፣ ወይም በጀርባ ታዝለው አልያም ተኝተው ስለሚውሉ፣ ብዙ ነገር እየነካኩ ወደ አፋቸው አያስገቡም ማለት ነው።

አያ ሙላት፡- አስታውሱ፤ ከእንሰሳት አይነ ምድር ወይም ከሰው አይነ ምድር የሚዛመቱ ጀርሞች ለተቅማጥ ይዳርጋሉ፤ ጀርሞች ህፃናት ከጡት ወተትና ከሌሎች ምግቦች የሚያገኙትን ንጠረነገር ከሰውነታቸው ጋር እንዳይዋህዱም ያግዳሉ ። ተቅማጥ የእንቡጥ ህፃናትን ጉልበት በማሟጠጥ ለበርካታ ቀናት ህመም ላይ ሊጥላቸው ይችላል።

3. በጣቶቻቸውና በአፋቸው ብዙ ነገር መነካካት፣ አካባቢያቸውንም ዙሪያ ገባውን

Page 115: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

115

ማሰስ ስለሚያዘወትሩ፤ እንቡጥ ህፃናት ለብዙ ጀርሞች ይጋለጣሉ - በተለይ ደግሞ ከእንሰሳት እዳሪና ከሰው አይነምድር ለሚዛመቱ ጀርሞች ይጋለጣሉ።

እቴ ብርቱካን፡ አያችሁ! እንቡጥ ህፃናት፣ በንጥረነገር የበለፀጉ ምግቦችንና የእናት ጡት ወተትን በብዛት ቢመገቡም እንኳ፣ በአይነ ምድር ጀርሞች የተበከለ ነገር ወደ አፋቸው የሚያስገቡ ከሆነ፣ አንጎላቸውና አካላቸው በተሟላ ጤንነት ሊያድጉ አይችሉም። የህፃናት ሰውነት ገና ለጋ ስለሆነ በሽታዎችን የመቋቋም አቅም ስለሚያንሰው በቀላሉ በጀርም ይጠቃሉ፤ የሚመገቡትን ንጥረነገር ከሰውነታቸው ጋር እንዳይዋህዱም ስለሚያግዳቸው የሕፃናት ጉልበት ይሟጠጣል። የተቅማጥ ህመም እና የሕፃናት መቀንጨር ዝምድና እንዳላቸው በተደጋጋሚ ታይቷል። በህፃናት የእንቡጥነት እድሜ ላይ፣ ትክክለኛ የንፅህና ብልሃቶችን ተግባራዊ ማድረግ ዋነኛ ነገር ስለሆነ፣ ወላጆችና ቤተሰቦች፣ እንቡጥ ህፃናትን ከጀርሞች ለመከላከል ከወትሮውም በላይ በእጅጉ መጠንቀቅ አለባቸው።

እቴ ብርቱካን፡ እስቲ ዛሬ ባነሳናቸው ፍሬነገሮች ላይ ለአፍታ እንወያይ። ለውይይታችሁ መነሻ የሚሆኑ ጥያቄዎችን እነሆ፡

1. የእንሰሳት እዳሪ እና በሽታ ግንኙነት ያላቸው ይመስላችኋል?

2. ህፃናት በእንሰሳት እዳሪና ሽንት በተበከለ አካባቢ፣ ሽታው ካልደረሰባቸው ካልሸተታቸው በቀር ቢጫወቱ፣ አይጎዳም ብላችሁ ታምናላችሁ ?

3. የዝንቦች ነገርስ? ዝንቦች ጉዳት የላቸውም ብላችሁ ታምናላችሁ ?

4. በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ፣ የግል ተሞክሯችሁ ምንድነው?

አስተባባሪ፣ በነዚህን ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይቱን ያስተባብሩልናል። እባክዎ ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት።

SFX: የደወል ድምፅ

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን ደህና መጣችሁ! ጥሩ እንደተወያያችሁና ተሞክሮ እንደተለዋወጣችሁ አምናለሁ። እንግዲህ፣ ብዙ ከተነጋገርን ዘንዳ፣ አሁን ደግሞ ለለውጥ ያህል አጭር ድራማ እናዳምጥ።

ድራማ

አለሚቱ፡- ደህና አድረሽ ምንትዋብ፤ ልጅሽን ምን ነካብሽ? ሌሊቱን ሙሉ ሲያለቅስ ቤት ድረስ ይሰማ ነበር።

ምንትዋብ፡- እንዴት አደርሽ አለሚቱ ! ልጄ ምን እንደነካው እንጃ ታሞብኛል ። ፋታ በማይሰጥ ተቅማጥ ድክምክም ጉስቁልቁል ብሏል። በጭራሽ ሊገባኝ አልቻለም። በንጥረነገር የበለፀጉ ምግቦች አላሳነስኩበትም፤ የጡት ወተት አልከለከልኩትም።

አለሚቱ፡- ትናንትኮ፣ አንቺ ምሳ ስታበሳስይ፣ ልጅሽ ግቢውን ሁሉ ሲንፏቀቅበት ነበር። የሆነ ነገር ወደ አፉ አስገብቶ ይሆናል።

Page 116: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

116

ምንትዋብ፡- ምን ላድርግ ብለሽ ነው። ቀኑን ሙሉ እሱን ስጠብቅ መዋል አልችልም። ልጄ አርፎ አይቀመጥም፤ የማይነካካው ነገር የማያዳርሰው ቦታ የለም። እኔ እሱን ተከትዬ አልችለውም። አፉ ውስጥ ምን ምን እንዳስገባ ፈጣሪ ይወቀው። ከንጋት እስከ ምሽት እሱን አዝዬ መዋል አልችልም።

አለሚቱ፡- መቼም ከሚታመምብሽ ማዘሉ ይሻላል፡፡ ህፃናት በዚህ እድሜያቸው ወዲህ ወዲያ ዙሪያቸውን ማሰስ፣ ሁሉንም ነገር መነካካት ተፈጥሯቸው ነው። ግን ደግሞ ደህንነቱንና ጤንነቱን ለመጠበቅ የጥንቃቄ ብልሃቶችን ማበጀት አለብሽ። የልጅሽ ፊት በብዙ ዝንቦች ሲወረር አያለሁ። ይሄ ጥሩ ምልክት አይደለም!

ምንትዋብ፡- ዝንቦች ደግሞ ምን ክፋት አላቸው? ሁሉም ቦታ፣ ሁሉም ነገር በዝንቦች የተወረረ ነው።

አለሚቱ፡- እንዴ፤ ምንትዋብ ምን ነካሽ ዝንቦች ዋና የጀርም አስተላላፊዎች እንደሆኑ አታውቂም? ከሰው አይነምድር እና ከእንሰሳት እዳሪ የሚዛመቱ ጀርሞች ተቅማጥን ያስከትላሉ። በንጥረነገር የበለፀጉ ምግቦችንና የእናት ጡት ወተትን ለህፃኑ ብትመግቢውም፣ ከእነዚህ የሚያገኛቸው ንጠረነገሮች ከሰውነቱ ጋር እንዳያዋህድ ተቅማጡ ያግደዋል።

ምንትዋብ፡- አዬ ጉዴ! ታዲያ፣ ያረባናቸውን ፍየሎች፣ በጎችና ከብቶች ምን ልናደርጋቸው ነው። መቼም አውጥተን አንጥላቸው!

አለሚቱ፡- ኧረ በጭራሽ! አውጥቶ መጣል ምን አመጣው! ለእንስሳቱ የተለየ በረት መስራት ትችላላችሁ።

ምንትዋብ፡- አንዳንድ ሰዎች በረት ሲሰሩማ አይቻለሁ። ግን አሁን እኛ በረት ለመስራት አቅሙ የለንም።

አለሚቱ፡- በረት መስራት ባትችሉ እንኳ፣ ዘወትር ቤታችሁንና ግቢውን በማፅዳት በመጥረግ የልጅሽን ጤንነት መጠበቅ ትችያለሽ። የልጅሽንም ፊት አዘውትረሽ፣ እጅና እግር በሳሙናና በውሃ ማጠብ አለብሽ። በዚህ ዘዴ፣ በእንሰሳት እዳሪና በሌሎች ነገሮች የሚመጣበትን ብክለት ማቃለል ትችያለሽ።

ምንትዋብ፡- ውይ! ይህን ይህንስ ማድረግ እችላለሁ። ልጄ ወዲህ ወዲያ ሲንፏቀቅ፣ እንዲህ ለበሽታ ይጋለጣል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።

አለሚቱ፡- ህፃናት ስንቱን ነገር ወደ አፋቸው እንደሚያስገቡ ብትቆጥሪ ይገርምሻል። የሰዎች ፀጉር፣ ብረታብረት፣ ጨርቃጨርቅ ፣ ጣቶች... ምናለፋሽ፣ እጃቸው የገባ ነገር ሁሉ ወደ አፋቸው መክተት ነው።

ምንትዋብ፡- እሱስ፣ እውነት ብለሻል። በቀደም እለት፣ ቤት የማፀዳበትን ቆሻሻ ጨርቅ ይዞ ሲያኝክ አግኝቼዋለሁ። ጨርቁን ነጥቄ ዞር ከማለቴ፣ እንደገና ሳንቲሞች ወደ አፉ ሲያስገባ አገኘሁት። ቀኑን ሙሉ እሱን ስከታተል መዋል አልችል ነገር!

አለሚቱ፡ ግንኮ፣ ለምሳሌ ለሱ ብቻ የተዘጋጀ ንፁህ ላስቲክ ወይም ምንጣፍ ቢጤ ላይ ልታስቀምጪው ትችያለሽ። ከላስቲኩ ወጣ ሲል፣ አንስተሽ ትመልሺዋለሽ። አንዳች ንፁህ መጫወቻ ነገር ብትሰጪው ጥሩ ነው፤ ያለጉዳት መጫወት ይችላል። የምታነጥፊለት ነገር ሰፊ መሆን አለበት፤ እንደልቡ ወዲህ ወዲያ ይልበታል፤

Page 117: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

117

መጫዎቻም ካለሽ አጥበሽሁሉን ምንጣፉ ላይ ልታስቀምጪለት ትችያለሽ። በመመገቢያው ጊዜም እዚያው ልትመግቢው ትችያለሽ የፕላስቲክ ምንጣፍ የለሽም?

ምንትዋብ፡- ኧረ አለኝ። እህል የማሰጣበት ላስቲክ ነው፤ ግን አሁን አለቅልቄዋለሁ። ከባለቤቴ ጋር ተነጋግሬ ለህፃኑ ለብቻው አዲስ የላስቲክ ምንጣፍ እስክንገዛ ድረስ፣ ለጊዜው ይህንን እጠቀማለሁ።

አለሚቱ፡- ማለቅለቅ ብቻማ አይበቃም። ምንጣፉንና መጫወቻዎቹን ሙልጭ አድርገሽ በሳሙናና በውሃ ማጠብ አለብሽ። በዚህ መንገድ ህፃንሽ አካባቢው ከጉዳት የራቀ ምቹ ቦታ ይኖረዋል፤ አንቺም በቀላሉ ልትከታተይው ትችያለሽ።

ምንትዋብ፡- መቼም ምክርሽ መሬት ጠብ አይልም። እንዳንቺ አይነት ጥሩ ጎረቤት ማግኘት መታደል ነው። ሌሎች ጎረቤቶችማ... ይኸኔ እያዩ ዝም ነው የሚሉት፡፡ አመሰግናለሁ!

አለሚቱ፡- ምንም ችግር የለም። አሁኑኑ፣ ዳዊትን ወደ ጤና ጣቢያ ወስደሽ አሳክሚው። ለተቅማጡ መድሃኒት እንደሚሰጡሽ እርግጠኛ ነኝ።

ምንትዋብ፡- አመሰግናለሁ! እወስደዋለሁ። ባለቤቴ አሁኑኑ ስለሚመጣ አብረን እንሄዳለን።

ፍፃሜ

እቴ ብርቱካን፡ ድንቅ ድራማ ነው! ምንትዋብ ዳዊትን ወደ ጤና ጣቢያ ከወሰደችው በኋላ ምን ተፈጥሮ ይሆን እያላችሁ እንደምታስቡ አውቃለሁ። ወደ በኋላ የድራማውን ሁለተኛ ክፍል እናዳምጣለን። እስከዚያው፣ አሁን በሰማነው ድራማ ላይ ጥቂት እንወያይ።

እስቲ በሰማነው ታሪክ ላይ ትንሽ እንወያይ። አስተባባሪ፣ የተሳታፊዎችን ወይይት በሚያስተባብሩበት ወቅት፣ አራት ጥያቄዎችን ልብ ይበሉ።

o አንደኛ፣ በታሪኩ ውስጥ የተፈጠሩ፣ የተወሩና የተደረጉ ነገሮች ምንድናቸው?

o ሁለተኛ፣ በታሪኩ ውስጥ ያሉ ሰዎች ምን ምን ችግር አጋጠማቸው?

o ሦስተኛ፤ ችግሮቹን እንዴት ተወጧቸው?

o አራተኛ፣ እንዲህ አይነት ታሪክ፣ በቤተሰባችን ወይም በአካባቢያችን ማህበረሰብ ውስጥ ሊከሰት የሚችል ታሪክ ነው? ሊከሰት የሚችል ከሆነ ለምን? ሊከሰት የማይችል ከሆነስ ለምን?

እቴ ብርቱካን:-አስተባባሪ፤ እባክዎ የደወል ድምጽ ሲሰማ ቴፑን ያጥፉና ውይይቱን ያካሂዱ፡፡ ሲጨርሱ እባክዎን ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

Page 118: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

118

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! ሁሉም ተሳታፊዎች ስለምንትዋብ፣ ስለጎረቤቷ አለሚቱ እና ስለ ህጻኑ ዳዊት ጥሩ ውይይት እንዳደረጉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

እስቲ በሰማነው ታሪክ ላይ አንዳንድ ነጥቦችን ላክል።

• ለከብቶች ለሌሎች እንስሳት የተለየ አጥር ወይም ክፍል መገንባት እንዲሁም ለዶሮዎች የዶሮ ቤት መሥራት እንቡጥ ህጻናትን ከእንስሳ እዳሪ ይጠብቃቸዋል፡፡

• እንቡጥ ህጻናትን በጀርባ ማዘል፣ ጭን ላይ ማስቀመጥ ወይም በንጹህ አካባቢ አሊያም በንጹህ ምንጣፍ ላይ እንዲጫወቱ ማድረግ ከተበከሉ ስፍራዎች ይጠብቃቸዋል፡፡

• የእርሻ መሣሪያዎችንና አቅርቦቶችን እንቡጥ ህጻናት በማይደርሱበት ሥፍራ ማስቀመጥ፡፡

• ቤትንና መላ ግቢን ከከብቶችና ዶሮዎች እዳሪ፣ኩስና ቆሻሻ መጥረግና ማጽዳት፡፡

የቤተሰብ አባላት ለእንቡጥ ህጻናት ማድረግ የሚችሏቸው አንዳንድ የቤት ውስጥ የንጽህና እርምጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

• ከብቶችንና ዶሮዎችን እንቡጥ ሕፃናት ከሚመገብበት፣ ከሚጫወቱበትና ከሚኖሩበት መለየት

• ቤቱንና የግቢውን አካባቢ ከከብቶችና ዶሮዎች እዳሪና ኩስ የጸዳ ማድረግ

• እንቡጥ ህጻናትን ለማብላት ጭናችን ላይ ወይም በንጹህ ምንጣፍ ላይ ማስቀመጥ

• እንቡጥ ህጻናት የተበከሉ ነገሮችን እንዳያነሱ እና ወደ አፋቸው እንዳይከቱ መከላከል

• በእነዚህ ጊዜያት የራስን እጅና የእንቡጡን ህጻን እጆች በሳሙናና ውሃ ማጠብ፡

• ምግብ ከማዘጋጀታችን እና እምቡጥ ሕፃናትን ከማብላታችን በፊት እንዲሁም ራሳችን ከመብላታችን

• የእንቡጥ ህጻናትን አይነምድር ካስወገድን በኋላ

• *ከብቶችን ወይም ዶሮዎችን ከደባበሱ ወይም ከተንከባከቡ ወይም የእርሻ ሥራ ካከናወኑ በኋላ

• *የመመገቢያ እቃዎችን (ጎድጓዳ ሳህን፣ ስኒ፣ ማንኪያ ወዘተ) እንቡጥ ህጻናት ለመመገብ ከመጠቀም በፊት በሳሙናና በውሃ ማጠብ

• *እንቡጥ ሕፃናት ከተፀዳዱ በኋላ እጃቸሁንና እንዲሁም የህጻናትን መቀመጫቸውንና እጃቸውንበሳሙናና ውሃ ማጠብ

Page 119: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

119

• *እቃዎችን ለእንቡጥ ህጻናት እንዲጫወትበት ከመስጠታችሁ በፊት በሳሙናና በውሃ ማጠብ

• የእርሻ መሣሪያዎችንና አቅርቦቶችን እንቡጥ ህጻናት ከሚደርስበት አካባቢ ማራቅ

• የእንቡጥ ህጻናት ከጀርሞችና ከበሽታ ለመጠበቅ እንዲያግዙ የህጻናትን ታላላቆች ስለ ውሃ፣ ስለ ንጽህና አጠባበቅና ስለ አካባቢ ንጽህና ማስተማር

• ወላጆች የቤተሰብ ወጪና ገቢ ጉዳዮችን በጋራ በመወያየት ጥቂት ገንዘብ አንዳንድ ነገሮችን ለመግዛት እንዲውል ሊስማሙ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ፡

• *ሳሙና

• የውሃ ማከሚያ ክኒኖች ለእንቡጥ ሕፃናት ለሚጠጡት ዉሃ

• *ከተቻለ- ለእንቡጥ ሕፃናት የምግብ መመገቢያ ልዩ ጎድጓዳ ሳህን ቢኖራቸው

• *ከተቻለ- ለእንቡጥ ሕፃናት ውሃ መጠጫ ልዩ ኩባያ ቢኖራቸው

• *ከተቻለ- እንቡጡ ህጻን የሚመገቡበትና የሚጫወትበት የፕላስቲክ ምንጣፍ

አያ ሙላት፡- እንቡጥና አበባ ህጻናት ያላቸው ቤተሰቦች፤ ልጆቻቸውን ከበሽታ ለመጠበቅና ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው ማደጋቸውን እንዲቀጥሉ ለማገዝ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ማድረጋቸውን እርግጠኛ መሆን አለባቸው፡፡

እቴ ብርቱካን፡ አሁን የድራማውን ሁለተኛ ክፍል እናዳምጥ፡፡

ድራማ ክፍል 2

ውስጥ: የጤና ማእከል - ቀን

ነርስ:- ሰላም ምንትዋብ አቶ አካሉ፤ እንደምን አሉ?

አካሉ፡- ጤና ይስጥልኝ ነርስ አረጋሽ

ምንትዋብ፡- ሲስተር እንደ ምን አለሽ?

ነርስ፡- ተመልከቺው ይሄ ሸጋ ልጅሽ -- ምነው ምን ሆነብሽ? ደስተኛ አይመስልም

ምንትዋብ፡- ልጄን ትላንት ማታ ተቅማጥ ይዞታል፤ ከዚያን ሰዓት ጀምሮ እንደቀፈፈው ነው፡፡ የምታደርጊለት ነገር ይኖራል?

ነርስ፡- እንዴታ! እንኳንም በቶሎ ወደዚህ አመጣሽው፡፡ ሃኪሙ አሁኑኑ ያየዋል፡፡ እስከዚያው ዳዊትን ለህመም የዳረጉት ነገሮች ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ልነግርሽ እፈልጋለሁ፡፡

ምንትዋብ፡- እሺ

ነርስ፡- በእሱ እድሜ ለህጻናት ህመም ዋናው ምክንያት በተቅማጥ መያዝ ሲሆን ይሄ ደግሞ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው ህጻናቱ ከእንስሳ አዳሪና ከሰው አይነምድር ጋር ንኪኪ ሲኖራቸው ነው፡፡ ለህጻኑ ንጹህ ስፍራ ለማዘጋጀት አንዳንድ እርምጃዎች ወስደሻል?

Page 120: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

120

ምንትዋብ፡- እንደዛስ አላደረግሁም፡፡ ለዚህ ነው ለካ ጎረቤቴ አለሚቱ ስለዚህ ጉዳይ ስትነግረኝ የነበረው፡፡ የሰውንና የእንስሳን መኖሪያ መለየት፣ ግቢን ዘወትር መጥረግ እና ህጻኑ የሚጫወትበት ንጹህ የፕላስቲክ ምንጣፍ ማድረግ ስላላቸው ጥቅም አስረድታኛለች፡፡

ነርስ፡- በጣም ጥሩ! በጣም ጠቃሚ ምክሮችን ለግሳሻለች፤ ግን ይህ ብቻ አይደለም፡፡ የንፅህና በጣም አስፈላጊው ክፍል መታጠብ ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ አነጋግርሻለሁ፡፡ ዋናው የህፃኑ ተንከብካቢ እንደመሆንሽ መጠን አንቺና ሌላው ህፃኑን የሚይዙየቤተሰብሽ አባላት እጃችሁን በሳሙናና በውሃ ለመታጠብ ትኩረት መስጠት አለባችሁ፡፡ ለመሆኑ ለልጅሽ ምግብ ከማሰናዳትሽ በፊት እጅሽን እንዲሁም የምግብ እቃዎቹን በሳሙናና በውሃ ታጥቢያለሽ?

ምንትዋብ፡- እጄን እታጠባለሁ፤ ግን ብዙ ጊዜ ሳሙና አልጠቀምም፡፡

ነርስ፡- አቶ አካሉ፤ እርስዎስ-- ልጅዎትን ሲይዙ ወይም ከእሱ ጋር ሊጫወቱ ሲሉ እጅዎትን ይታጠባሉ?

አካሉ፡- በፍጹም፤ አድርጌው አላውቅም፡፡ እጄን የምታጠበው ልመገብ ስል ብቻ ነው፡፡

ነርስ፡- እጅን በሳሙና መታጠብ ለእራሳችሁና ለልጁ ጤንነት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

ምንትዋብ፡- በሳሙና መታጠብ ስላለው ጠቀሜታ ሰምተናል፤ ነገር ግን ብዙም ትኩረት ሰጥቼው አላውቅም፡፡

ነርስ:- መስጠትማ አለብሽ፡፡ ሳሙና ጀርሞችን ይገድላል፡፡ ልጅሽ በተቅማጥ የታመመበት ምክንያት የተበከለ ምግብ ሊሆን ይችላል፡፡

አካሉ:- በሳሙና መታጠብ በእኛ ቤተሰብ ውስጥ ልማድ ሆኖ እንደማያውቅ እቅጩን መናገር አለብኝ፡፡

ነርስ:- በተለይ የህጻኑን ምግብ ከማዘጋጀታችሁ በፊት በሳሙናና በውሃ መታጠብ አለባችሁ፡፡ ለምግብ ማዘጋጃ የምትጠቀሙባቸው እቃዎችም በሳሙና መታጠብ ይገባቸዋል፡፡ በተለይ ደግሞ መጸዳጃ ቤት ከተጠቀማችሁ በኋላ፣ የህጻኑን ካጸዳችሁና እንስሳት እዳሪ ከነካችሁ እንዲሁም የእርሻ ሥራ ላይ ከዋላችሁ በኋላ እጃችሁን በሳሙናና በውሃ መታጠብ አለባችሁ፡፡ ይሄንን ዘወትር ካደረጋችሁ በቤተሰቡ ውስጥ ልማድ ይሆናል፡፡

ምንትዋብ:- ወቸ ጉድ-- ከእንግዲህማ በደንብ ነው ሳሙና የምንጠቀመው፡፡ ልጄ እንዲህ ታሞ ማየት አልፈልግም፡፡

ነርስ፡- አቶ አካሉእርስዎም ቀኑን ሙሉ እርሻ ላይ ሲሰሩ ነው ስለሚውሉ እቤት ሲመጡ እጅዎትን በሳሙናና በውሃ መታጠብ እንዳለብዎ ማስታወስ ይገባዎታል፡፡

አካሉ፡- (በረዥሙ ይተነፍሳሉ)ለምን ያህል ጊዜ ከልጄ ጋር ለመጫወት እጓጓ እንደነበር ትዝ አለኝ፡፡ ከእርሻ በቀጥታ ወደ ቤት እመጣና ሚስቴ እራት እስክታዘጋጅ እኔ እይዘዋለሁ፡፡ ከዚያም እጄን ይነካካል፣ ጣቶቼን ሊነክሳቸው ይሞክራል፡፡ በመታቀፍ ብቻ ይታመማል ብዬ አስቤ አላውቅም!

ነርስ፡ ከልጁ ጋር ጊዜዎትን ማሳለፍዎ ድንቅ ነው፡፡ ብቻ ልጁን ከመያዝዎ በፊት እጅዎትን በሳሙናና በውሃ መታጠብዎን ያረጋግጡ፡፡ ቀደም ብዬ ከጠቀስኩት

Page 121: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ዋናው እጅን የመታጠብ ልማድ በተጨማሪ ቤትዎ ውስጥ ውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ መገንባትም ይችላሉ፡፡ እሱን ለመሥራት በጣም ቀላል ነው፡፡ ይሄ ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት እንዴት ውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ እንደሚገነባ ያሳይዎታል፡፡ ይሄው እንኩ፡፡ (SFX: የበር መከፈት ድምጽ ይሰማል) ሃኪሙ ልጅዎትን ለማየት ዝግጁ ነው፡፡

ምንትዋብ: አመሰግናለሁ ነርስ

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! በቀሪው ታሪክ እንደተደሰታችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እስቲ በታሪኩ ዙሪያ አጭር ውይይት እናድርግ፡፡ አስተባባሪ፤ በውይይቱ ሰዓት ተሳታፊዎቹ በተከታዮቹ ጥያቄዎች ላይ መወያየታቸውን ያረጋግጡ፡፡

• የእንቡጥ ሕጻኑ አባት አካሉ በታሪኩ ውስጥ ምንድነው ያደረጉት?

• የእንቡጥ ሕጻኑ እናት ምንትዋብ በታሪኩ ውስጥ ምንድነው ያደረገችው?

• ነርሷ በታሪኩ ውስጥ ምንድነው ያደረገችው?

• የትኛው የታሪኩ ክፍል ነው ሊተገበር የሚችል የሚመስለው? ለምን ?

• ሊተገበሩ የሚችሉ የማይመስሉ የታሪኩ ክፍሎች አሉ? ለምን?

• የቤተሰባችሁ አባላት እነዚህን ነገሮች በቤታቸው የሚፈጽሟቸው ይመስላችኋል?

አስተባባሪ፤ ውይይቱን ሲጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

እቴ ብርቱካን፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! ጥሩ ውይይት እንዳደረጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ነርሷ ስለ ንጽህና አጠባበቅና ሌሎች የመታጠብ ልማዶች ትልቅ ነጥብ አንስታለች፡፡ ልብ በሉ፡

• መዳህ መማር ሲጀምሩ እንዲሁም ነገሮችን በጣታቸው እየነኩና ወደ አፋቸው እየከተቱ ለመፈተሽ በሚጥሩበት ወቅት፣ ሁሉም የቤተሰብ አባላት የእንቡጥ ህጻናትን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የሚጫወቱት ሚና አላቸው፡፡

• አበባ ህጻናት ያላቸው ቤተሰቦችም ህጻናናትን ከአደጋ ለመከላከል ተመሳሳይ ነገሮችን ማድረጋቸውን ማረጋገጥ እንዲሁም ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው ማደጋቸውን እንዲቀጥሉ ሊደግፏቸው ይገባል፡፡

እስቲ በአገራችን ከውሃ ጋር ከተያያዙ የቁጥር መረጃዎች ጥቂቶቹን እንመልከት፡

• በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ ቤተሰቦች የተሻሻለ የውሃ አቅርቦት አላቸው፡፡ (ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ፤ 2011)

• የኤንጂን ጥናት የተሻሻለ የውሃ አቅርቦት የላቀ ተደራሽነት ዝቅተኛው እስከ 12 በመቶ፣ ከፍተኛው እስከ 79 በመቶ እንደሚደርስ ያሳያል፡፡ በአገሪቱ አማካይ ተብሎ እንደቀረበው፤ ጥናት ከተደረገባቸው 42 ወረዳዎች ውስጥ 50 በመቶና ከዚያ በላይ የንጹህ ውሃ ሽፋን ያላቸው 15ቱ ብቻ ነው፡፡

121

Page 122: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ውሃ የመቅጃ ጊዜ፡

ጥናት ከተካሄደባቸው ወረዳዎች ውስጥ ውሃ ለመቅዳት 30 ደቂቃና ከዚያ በታች የሚወስድባቸው ቤተሰቦች መጠን ዝቅተኛው እስከ 19 በመቶ፣ ከፍተኛው እስከ 93 በመቶ ሲሆን ከ42ቱ ወረዳዎች በ33ቱ ግማሹ ቤተሰቦች በ30 ደቂቃ ውስጥ ውሃ መቅዳት የሚችሉ ናቸው፡፡

የመጠጥ ውሃ ማከም፡

በጥናቱ በተቃኙት ወረዳዎች በሙሉ በቤተሰብ ደረጃ የመጠጥ ውሃን የማከም ልማድ በጣም ዝቅተኛ ሲሆን የልማዱ ስርጭት ከፍተኛው 16 በመቶ ብቻ ሲሆን በአብዛኖቹ ወረዳዎች (ከ42ቱ በ37ቱ) የውሃ ማከሚያ ዘዴዎችን የሚጠቀሙት ከመቶው ሰው 5ቱ ብቻ ናቸው፡፡

የህጻናትን አይነምድር ማስወገድ ከወረዳ ወረዳ የሚለያይ ሲሆን ዝቅተኛ የሚባለው እስከ 4 በመቶ፣ ከ42 ወረዳዎች በ13ቱ ብቻ ናቸው በግማሽ የሕፃናትን አይነምድር ያስወገዱ፡፡ በደቡብ ህዝቦችና ብሄር ብሄረሰቦች ክልላዊ መንግስት ውስጥ የተቃኙት ወረዳዎች በአጠቃላይ ከሌሎች ክልሎች ወረዳዎች የበለጠ የሕጻናት አይነምድርን የማስወገድ ልማድ የሚተገብሩ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቤተሰቦችን ይዘዋል፡፡

ማርባትና ማብቀል

አያ ሙላት፡ በዛሬው ክፍለ ጊዜያችን ስለ እንቡጥ ህጻናት ብዙ ጉዳዮችን የዳሰስን ሲሆን እጁቸውን ሳይታጠቡ በሚይዟቸው ሰዎች (በአብዛኛው እናቶች) እና በእንስሳ እዳሪ በተበከሉ አካባቢዎች ሳቢያ እንዴት ከእዳሪ ጋር ለተገናኘ የአንጀት መመረዝ እንደሚጋለጡም ተወያይተናል፡፡

አብዛኞቻችን የገበሬ ቤተሰቦች እንደመሆናችን መጠን ከብቶች፣ ፍየሎች፡ በጎችና ዶሮዎች ያሉን ሲሆን እኒኝህ እንስሳት ለኢትዮጵያ የቤተሰብ ኢኮኖሚ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡ እንስሳት የገቢና የምግብ ምንጮች ከመሆናቸውም ባሻገር በአብዛኞቻችን ቤት ከእነዚህ እንስሳ ጋር ቅርብ ግንኙነት ያለን ሲሆን ብዙ ጊዜም በአንድ ጣራ ሥር አብረን እንኖራለን፡፡

ምንም እንኳን አብዛኛው የከብቶች እዳሪ ያለው በግቢ ውስጥ ቢሆንም በህጻኑና በቤተሰቡ መኖሪያ ውስጥም ጥቂት የከብት እዳሪ አይጠፋም፡፡ የሚድሁ ህጻናት ለመሬት ቅርብ በመሆናቸው የከብቱን እዳሪ በእጃቸው ሊነኩት፣ ወደ አፋቸውም ሊከቱት ይችላሉ፡፡ እናቶች የከብቶችን እበት ቤት ለመለቅለቅና ጠፍጥፈው በማድረቅ ኩበቱን ለማገዶነት ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህም የተነሳ ለአብዛኛው ሰው የከብት እበት ጉዳት- ያለው ይመስላቸዋል ፡፡

ህጻናት አካባቢያቸውን ለማወቅ ባላቸው ጉጉት እንዲሁም ነገሮችን በመነካካትና ወደ አፍ በመክተት ልማዳቸው የተነሳ የከብቶች እዳሪንም ወደ አፋቸው

122

Page 123: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ሊከቱት ይችላሉ፡፡ ብዙ ሰዎች የእንስሳት እዳሪ ጎጂ አይደለም ብለው ያስባሉ፡ ፡ የሚያሳስባቸው ሽታው ነው፤ ህጻናትን የሚያሳምማቸው ሽታው ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ይሄን ጉዳይ በተመለከተ እስቲ አንዳንድ ሰዎች ምን እንዳሉ እንስማ፡፡

የተዋናዮች ድምጽ

“ በእንስሳት እዳሪ አጠገብ መጫወት ለከፋ ችግር አይዳርግም፡፡ ለጉንፋን ሊያጋልጣቸው ይችላል፤ ከባድ በሽታ ግን አያመጣባቸውም፡፡ በተለይ እዳሪው በሚሸትበት በቀትር ሰዓት ላይ እዚያ አካባቢ ካልተጫወቱ ምንም አይላቸውም፡፡” - እናት፤ አላማጣ፣ትግራይ

“ የእንስሳት እዳሪ ትልቅ ችግር አይደለም፡፡ ችግሩ ያለው ከሽንታቸው ነው፤ ይህም መጥፎ ጠረን ስላለው፤ ጠረኑ በሽታ ያስተላልፋል፡፡ ህፃኑ ግን በእዳሪ ይጫወታል፤ ምንም ችግር የለውም፡፡” አባት፤ ኢፍራታ፣አማራ ክልል

አያ ሙላት፡ አንዳንድ ሰዎች እንደውም በከብት እዳሪና በበሽታ መካከል ጨርሶ ምንም ዓይነት ግንኙነት የለም ብለው ያምናሉ፡፡ ህጻኑ ሊገጥመው የሚችለው ብቸኛ አደጋ ከብቶቹን በመቅረቡ የሚከሰት የአካል ጉዳት ነው የሚል ሃሳብ አላቸው፡፡ ምክንያቱም ከብቶቹ ህጻኑን ሊወጉት ወይም እላዩ ላይ ሊወጡበት ይችላሉ ብለው ስለሚፈሩ፡፡ የእንስሳና የሰው አይነምድር ዝንቦችን ይሰበስባል፡፡ በህጻናት ፊት ላይ ብዙ ዝንቦችን እንዳያችሁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ዝንቦች ችግር የላቸውም ብለው ያስባሉ፤ እናም በህጻናት ልጆቻቸው ላይ አደጋ ያመጣሉ ብለው አያምኑም፡፡

ቀደም ሲል እንደተገለጸው፤ ለእንስሳ እዳሪና ለሰው አይነምድር የተጋለጡ ህጻናት፣ ለበሽታዎች ቅርብ ናቸው፡፡ እንስሳት የቤተሰባችን አስፈላጊ አካል ናቸው፡፡ ስለዚህ እንዴት ነው የመመረዝ አደጋን የምንቀንሰው ወይም የምናጠፋው?

• ይሄን የምናደርገው የሰዎችንና የእንስሳትን መኖሪያ በመለየት ነው፡፡ ከእንስሳት ጋር በፈጠርነው ቅርብ ትስስርና በስርቆት ስጋት የተነሳ ይሄ ፈታኝ ሊሆንብን ይችላል፡፡ ነገር ግን የከብቶች በረት እና የዶሮ ቤትን ከዋናው ቤት አርቆ መስራት ሰዎችንና እንስሳቱን ለመለያየት ሁነኛ መላ ነው፡፡ ባለፈው ክፍለ ጊዜ የዶሮ ቤት አሰራርን የሚያሳዩ በራሪ ወረቀቶች አከፋፍለናል፡፡ ለትላልቅ ከብቶች በረት መስራት ወይም ለእንስሳት ሌላ ክፍል መጨመር ህጻናትን ከእንስሳት እዳሪ ለመታደግ ጥሩ ዘዴ ነው፡፡

• ዘወትር ግቢያችንንና ቤታችንን ማጽዳት እንዲሁም የእንስሳት እዳሪን በአግባቡ ማስወገድ አለብን፡፡ የእንስሳት እዳሪ ግሩም ማዳበሪያ ይሆናል፤ ነገር ግከመኖሪያ ቤት ርቆ መቀመጥ አለበት፡፡ የእንስሳት እዳሪን ካስወገድን በኋላም እጃችንን መታጠብ ይኖርብናል፡፡

123

Page 124: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ማግኘትና መግዛት

እቴ ብርቱካን፡ በአሁኑ ወቅት ሳሙና በአገሪቱ የትኛውም ሱቅ ውስጥ ይገኛል፡፡ ብዙ አማራጮችም አሉን፡ የእጅ ሳሙና፣ የገላ ሳሙና እንዲሁም የልብስ ሳሙና፡፡ የቤት እቃዎችን ለማጠብ ደግሞ ፈሳሽ ሳሙናና አጃክስ መጠቀም ይቻላል፡፡ ሳሙና በጣም ውድ አይደለም፤ ቤተሰብ መግዛት የሚችለው ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ቤተሰቦች ለራሳቸውና ለህጻናት ልጆቻቸው ጤና ሲሉ ሳሙናን መግዛት ቅድሚያ ሊሰጡት ይገባል፡፡ ውሃ ማከሚያ ክኒኖችም ገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡ በባለ 20 ሊትር ጀሪካን ውሃ ውስጥ ጥቂት “ውሃ አጋር” መጨመር ውሃውን ያለስጋት ለመጠጣት አስተማማኝ ያደርገዋል፡፡

እቴ ብርቱካን: እስቲ ጥቂት ጊዜ ወስደን እነዚህ ነጥቦች ላይ እንወያይባቸው፡፡ አስተባባሪ፤ እባክዎ የቡድኑ አባላት ሳሙና የሚገዙበትን ቦታ፣ እንዲሁም ምን ዓይነት በምን ያህል ዋጋ እንደሚገዙ መረጃ እንዲለዋወጡ ይጠይቋቸው፡፡ በውይይቱ ወቅት በአንዳንድ የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ መነጋገራቸውንም ያረጋግጡ፡

1. እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ አስፈላጊ ቢሆንም አንዳንዴ የሳሙና ዋጋ አቅምን የሚፈታተን ሊሆን ይችላል፡፡

2. ከሌሎች የቡድኑ አባላት ጋር ሳሙና የሚገዙበትን ቦታ፣ እንዲሁም የሚገዙትን የሳሙና አይነት በምን ያህል ዋጋ እንደሚገዙ መረጃ መጋራት አለባችሁ፡፡

3. በወሳኝ ጊዜያት እጅን ለመታጠብ እንቅፋት የሚሆኑ አንዳንድ የተለመዱ ችግሮችን ተወያዩ፡፡

አስተባባሪ ውይይቱን ሲጨርሱ፣ እባክዎ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

እቴ ብርቱካን: እንኳን በደህና መጣችሁ! የቤት ውስጥ ወጪና ገቢ ላይ መወያየትና ለእንቡጥና አበባ ህጻናት ልጆቻቸው ሳሙናና የመጠጥ ውሃ ማከሚያ ለመግዛት ምን ያህል ገንዘብ መመደብ እንደሚችሉ ስምምነት ላይ መድረስ ለወላጆች ጠቃሚ ነው፡፡ በውይይታችሁ ወቅት አንዳንዶቻችሁ አንስታችኋቸው ሊሆኑ የሚችሉ ጥቂት የተለመዱ ችግሮች ልናገር፡፡

• አንዳንዴ ውሃ በቀላሉ አይገኝም ወይም ውድ ነው

• ሳሙና በጣም ሊወደድ ይችላል

• አንዳንዴ ውሃና ሳሙና እኛ በምንፈልግበት ቦታ አይገኙም

• አንዳንዴ እንረሳለን

• አንዳንዴ በጣም ሥራ ይበዛብናል

• አንዳንዴ ቸልተኝነትን እናበዛለን፤ መጨነቅ አንፈልግም

124

Page 125: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

ማዘጋጀት ሳይበላሽ ማቆየትና መከማቸት

እቴ ብርቱካን: የእጅ መታጠብ ልማድን ለማሻሻል የሚጠቅሙ አንዳንድ ቀላል መፍትሄዎችን ልጠቁማችሁ፡

• በቀላሉ ከሚገኙ ቁሳቁሶች ውሃ ቆጣቢ የእጅ መታጠቢያ መስራት ቀላል ነው

• ውሃ ቆጣቢ የእጅ መታጠቢያ ውሃ እንዳይባክን ያደርጋል ስለአሰራሩ ከጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞችን ምክር መጠየቅ እንችላለን፤

• እጃችንን መታጠብ በሚያስፈልጉን ቦታዎች ሁሉ በርካታ የእጅ መታጠቢያ ጣቢያዎችን መስራት እንችላለን፡ ለምሳሌ - መጸዳጃ ቤት በር ላይ ፣ ወጥቤት ውስጥ፣ መመገቢያ ሥፍራዎች አቅራቢያና የህጻናት መጫወቻ ስፍራ አጠገብ

• በእጅ መታጠቢያ ጣቢያዎች ላይ ውሃ ቆጣቢ የእጅ መታጠቢያ ወይም ተንቀሳቃሽ ጆጎች አካባቢ በሲባጎየታሰረ ሳሙና ማስቀመጥ ይቻላል፡፡

• የእጅ መታጠቢያ ጣቢያዎች የሚሰሩበትን የተለያዩ መንገዶች እንዲያሳዩን ከጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች መጠየቅ እንችላለን

• ቤተሰብ ሳሙና ለማግኘት የማይችልበት አጋጣሚዎች ቢፈጠርና እጅን በውሃና በንጹህ አመድ መታጠብ ውጤታማ ነው

• ትላልቅ ልጆቻችንና ሌሎች የቤተሰብ አባላት እጃችንን በውሃና በሳሙና እንድንታጠብ አስታውሱ

ሁልጊዜ ምግብ ልታዘጋጁ ስትሉ እጃችሁን በሳሙናና በውሃ መታጠብ እንዳትዘነጉ፤ ለቤተሰባችሁ አባላት ከምግብ ዝግጅት በፊትና በኋላ እጅን መታጠብን አለማምዱ፡፡

አያ ሙላት፡ እንግዲህ የምሥራቹ ምን መሰላችሁ--- ወደ ቤታችሁ የምትወስዱት ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት አዘጋጅተንላችኋል፤ ስለ “ውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ አሰራር የሚያሳይ ነው፡፡ አስተባባሪ፤ እባክዎ አብረን የምንቆይበት ክፍለ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት እነዚህን ለተሳታፊዎቹ በሙሉ አከፋፍሉልኝ፡፡

ማረፍ ማገዝና መብላት

አያ ሙላት፡ አሁን አንድ ነገር ላጋራችሁ፡፡ አንድ ጨዋታ አብረን እንጫወታለን፡፡ ይሄንን ጨዋታ ከማንኛውም የቤተሰባችሁ አባላት ጋር በመሆን መጫወት ትችላላችሁ፡፡ ምናልባት አስተባባሪ ትንሽ ውሃና ሳሙና እንዲሁም የውሃ ጆግና ጎድጓዳ ሳህን ካለው ጨዋታውን አብረን ልንጫወት እንችላለን፡፡

1. አንድ ሰው እጃችሁ ላይ ውሃ እንዲጨምርላችሁ ጠይቁ፡፡ የእጃችሁ እጣቢ ከስር የተደቀነ ማጠራቀሚያ ወይም ባልዲ ላይ መፍሰሱን አረጋግጡ፡፡

2. እጃችሁን በንጹህ ውሃ ካራሳችሁ በኋላ ሳሙና ተጠቀሙ፡፡

125

Page 126: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

3. እጃችሁን በደንብ ሳሙና ምቱት፡፡ መዳፎቻችሁን እንዲሁም ጀርባውን፣ በጣቶቻችሁ መሃል እና ጥፍሮቻችሁ ስር ሳሙና መምታታችሁን አረጋግጡ፡፡

4. እጃችሁን ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች እሹት፤ ከዚያም በቀኝ እጃችሁ መዳፍ የግራ እጃችሁን ጥፍሮች፣ በግራ እጃችሁ መዳፍ ደግሞ የቀኝ እጃችሁን ጥፍሮች እሽት አድርጉት፡፡

5. በዝግታ እስከ 20 ድረስ ቁጠሩ ወይም አንድ የምትወዱትን መዝሙር ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ ዘምሩት፡፡ (በጣም አጭር መዝሙር ከሆነ ሁለቴ ዘምሩት) እኔ ሁልጊዜ የመልካም ልደት መዝሙር ነው የምዘምረው፤ ምክንያቱም ልደት እወዳለሁ!

6. እጃችሁን ሳሙናው እስኪለቅ ድረስ በንጹህ ውሃ በደንብ ተለቃለቁት

7. በንጹህ ጨርቅ ወይም ፎጣ እጃችሁን አድርቁት፡፡ ሁለቱም ከሌላችሁ፣ ነፋስ ያደርቅላችኋል

ጠይቁና አግኙ

አያ ሙላት፡ እንግዲህ ወዳጆቼ፤ የክፍለጊዜያችን ማጠናቀቂያ ላይ ደርሰናል፡፡ ከመሄዳችን በፊት ግን መጸዳጃ ቤት እንዴት እንደሚገነባና የውሃ ማከሚያ ክኒን የት እንደሚገኝ የጤና ኤክስቴንሽንናs የግብርና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ዘንድ መረጃ መጠየቁን እንዳትዘነጉት፡፡

ወደ ቤት የሚወስዱ ቁሳቁሶችና የቤት ሥራዎች

አያ ሙላት፡ እነዚህን ነገሮች ከቤተሰባችሁ ጋር መወያየትና ቤታችሁ ውስጥ መሞከር እንዳትዘነጉ፡

1. ዘወትር ግቢን ማጽዳትና እንስሳትን ለብቻ ማስቀመጥ

2. ሳሙና መግዛትና ሁልጊዜ እጅን ለመታጠብ ሳሙናና ውሃ መጠቀም

3. የውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ በራሪ ወረቀት ወደ ቤት መውሰድና ከቤተሰብ ጋር መጋራት

4. ከቤተሰብ አባላት ጋር በመሆን ውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ መስራት

መዝጊያ

አያ ሙላት፡- ከትዳር ጓደኛ ጋር መነጋገርና ቤተሰቦቻችን ራሳቸውን ለእንቡጥ ህጻናት እንዴት እንደሚያዘጋጁ በጋራ መወያየት፡፡

ሁሉም እዚህ ያለ ተሳታፊ “የውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ አሰራርን የሚያሳየውን በራሪ ወረቀትም ተቀብሏል፡፡

አስተባባሪ፤ ወደ ቤት የሚወሰደውን የመረጃ ቁስ መቀበል ለሚገባው ሁሉ አሁኑኑ ያከፋፍላሉና አጠቃቀሙን ያሳዩዋችኋል፡፡

126

Page 127: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

አሁን የመረጃ ቁሶቹን በጥሞና ለመመልከት እባካችሁ ጥቂት ደቂቃዎች ውሰዱ፤ስትጨርሱ እንደገና አገኛችኋለሁ፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል አያ ሙላት፡ እስቲ ንገሩኝ:

• ስንቶቻሁ በራሪ ወረቀቱን ለቤተሰቦቻችሁ ታሳያላችሁ?

• ስንቶቻችሁ ሳሙና ትገዛላችሁ?

• ስንቶቻችሁ ውሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያትገነባላችሁ? እናደርጋለን የምትሉ እባካችሁ እጃችሁን አውጡ!

መልካም! ሁላችሁም እጃችሁን አውጥታችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ

እቴ ብርቱካን፡ ረዥም የድካም ቀን ነው ያሳለፍነው፤ ስለዚህ ይሄን ክፍለጊዜ ዘና በሚያደርግ ነገር መቋጨት ያለብን ይመስለኛል፡፡ የጡት ማጥቢያ እሹሩሩ መዝሙር ቢሆን ምን ይመስላችኋል? ለእንቡጥ ህጻን ዝግጁ ስለመሆን፣ እናት ችግኝ ህጻኗ ወደ እንቡጥነት እስኪሸጋገር እንዴት በጉጉት እንደምትጠብቅ፣ እንዲሁም ወፍራም ገንፎና ኮከብ ምግቦችን በሙሉ ለመመገብ የቱን ያህል እንደምትቸኩል ---ብዙ ነገሮችን ያስታውሰናል፡፡

ዛሬ ከተማርናቸው ውስጥ ጥቂቶቹን ከትዳር አጋሮቻችንና ቤተሰቦቻችን ጋር እንጋራለን ብለው ፈቃደኛ ለሆኑት ሁሉ እናጨብጭብላቸው!

SFX: የጭብጨባ ድምጽ ይሰማል

SFX: የጡት ማጥቢያ እሹሩሩ መዝሙር (ድምጽ ይሰማል) አያ ሙላት፡ እንዴ! ምንድነው የምሰማው? የጡት ማጥቢያ እሹሩሩ መዝሙርን ይመስላል!

ይሄን ለእንቡጥ ህጻን ዝግጁ ስለመሆን የተሰናዳ አምስተኛ የዳበረ የማህበረሰብ ውይይታችን ለመቋጨት ትክክለኛው መንገድ ነው! ግሩም ውይይት በግሩም መዝሙር ይቋጫል፡፡

አያ ሙላት፡ እሺ! ከመሄዳችን በፊት --- ስንቶቻችሁ ናችሁ ቤታችሁ ውስጥ ለመዘመርና ለባለቤቶቻችሁእንዲሁም ለቤተሰቦቻችሁ እንዲዘምሩት ለማስተማር ፈቃደኛ የሆናችሁት? እንሞክራለን የምትሉ እባካችሁ እጃችሁን አውጡ!

እቴ ብርቱካን: ማለፊያ ነው! እውነትም ዘና የሚያደርግ ሙዚቃ! ግሩም አዘማመር ነው ! አመሰግናለሁ!! 5ኛውን ክፍለጊዜ በድንቅ መዝሙር በማጠናቀቃችን አሁን ለራሳችን እናጨብጭብ!

አስተባባሪ የሚቀጥለው ስብሰባ መቼ እንደሚሆን ለተሳታፊዎች ይንገሯቸው፡፡

ለዛሬው ንቁ ተሳትፎአችሁ ሁላችሁንም አመሰግናችኋለሁ፡፡ ዳግም ተገናኝተን ስለ ትንሽ እንቡጥ ህጻን የበለጠ የምናወራበትንና አብረን የምንሆንበትን ጊዜ በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡

እስከዚያው ደህና ሰንብቱ!

127

Page 128: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት
Page 129: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

መግቢያ

አያ ሙላት፡ ጤና ይስጥልን፤ እንደምን ዋላችሁ

ወደ ስድስተኛው የዳበረ የማሕበረሰብ ውይይታችን እንኳን በደህና መጣችሁ። ከሥርዓተ ምግብ ቡድን መሪ ከአቶ ቢራራ መለሰ የመክፈቻ ንግግር እንደሰማችሁት፣ በመላ አገራችን የእናቶች የምግብ አለመመጣጠንና የሕፃናት መቀንጨር ትልቅ ብሔራዊ ችግር ሆኖብናል። የመጀመሪያዎቹ የአንድ ሺህ ቀናት የእናትና የህጻናት ስርዐተ ምግብን በሚመለከት ዋና ዋና ትምህርቶችን ለመቅሰም፣ አስር የውይይት ክፍለጊዜዎችን አዘጋጅተናል። ከዚህ ትምህርታዊ ውይይት በምትገበዩት እውቀትና ክህሎት አማካኝነት፤ በቁመናና በጠንካሬያቸው የሚያኮሩ፣ ጤናማና ብሩህ ህጻናትን በማሳደግ ለቁምነገር ማብቃት ትችላላችሁ፡፡ ይሄ ነው አላማችን።

አያ ሙላት፡- ሙላት እባላለሁ፡፡ ከውዷ ባለቤቴ ከብርቱካን ጋር እየተጋገዝን፣ እናንተው ዘንድ በአካል ባይሆንም በድምፃችን ተገኝተን ውይይታችሁን እናስተናብራለን።እኔና ባለቤቴ እየተፈራረቅን ድምጻአችንን ትሰማላችሁ። በየጣልቃው ደግሞ፣ ከናንተ ጋር ያሉት አስተባባሪ ውይይታችሁን ያስተባብራሉ። ቴፑን ዘግተው፣ እንድትወያዩና የቡድን ስራዎችን እንድታከናውኑም ያግዛችኋል፡፡ ይሄን የደወል ድምጽ ስትሰሙ (የደወል ድምጽ ይሰማል)፣ ቴፑን የሚጠፋበት ጊዜ ነው፡፡ የቡድን ስራችሁን ወይም ውይይታችሁን ስትጨርሱ፣ አስተባበሪ ቴፑን መልሰው ይከፍቱታል፤ ያኔ እኔና ብርቱካን እንቀጥላለን ማለት ነው፡፡

እስቲ አሁን እንሞክረው! አስተባባሪ እባክዎን የደወል ድምጽ ሲሰማ፣ ቴፑን ይዝጉት፡፡ አስተባባሪ፣ አሁን ተሳታፊዎች በሙሉ ስማቸውን በመናገር ራሳቸውን ያስተዋውቁ ። ተዋውቃችሁ ስትጨርሱ፤ እባክዎን አስተባባሪ ቴፑን ይክፈቱት፡፡

የደወል ድምጽ ይሰማል

ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስ

አያ ሙላት:- እንኳን በደህና መጣችሁ! ሁላችሁም እርስ በእርስ እንደምትተዋወቁ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ከእድሜ አቻዎቻችሁ ጋር የመወያየትና ተመክሯችሁን የመጋራት መልካሙ ነገር ይሄ ነው፡፡

የዛሬውን ርዕሰ ጉዳይ ከመጀመራችን በፊት ባለፉት አምስት ክፍለጊዜያት የተወያየንባቸውን ጉዳዮች በፍጥነት እንከልሳቸው፡፡

በመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት፣ ህፃናት ጠንካራ፣ ጤናማና ብሩህ ሆነው እንዲያድጉልን ምን ማድረግ እንዳለብን፣ በአንደኛው የውይይት ክፍለ ጊዜያችን ላይ የተማርናቸውን ነገሮች ሁላችሁም እንደምታስታውሱ እርግጠኛ ነኝ። የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት ቁምነገር ምንድነው? ስንቶቻችሁ ናችሁ የሱፍ አበባ ተምሳሌትን ማለትም የዘር፣ የችግኝ፣ የእምቡጥ እና የአበባ ደረጃዎችን የምታስታውሱት?

129

Page 130: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

130

ከዚህም በተጨማሪ፣ የጉልቻ ተምሳሌት ላይ ተነጋግረናል። የሶስቱን ጉልቻ ተምሳሌት የትኛዎቹን ኮከብ ምግቦች እንደሚወክሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ ምታስታውሱት፡፡ የእንጀራውስ ምጣድ ስንቶቻችሁ ናቸው ምን የምግብ አይነት እንደሚወክል የምታስታውሱት ለባለቤታችሁ እና ለሌሎች የቤተሰብ አባላት፣ የጉልቻን ምሳሌት አስረድታችኋል? ንግስት ንብ በየእለቱ ቢያንስ አንድ ባለኮከብ አብ ምግቦች እና በየገበታው ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን እንድታገኝ ምን ማድረግ እንደንችልስ ለቤተሰብ አስተምራችኋል ወይ?

እቴ ብርቱካን፡-ባለፉት 5 ክፍለ ጊዜያት፣ ሶስት መዝሙሮችን በማዳመጥ ተምረናል። መዝሙሮቹ ስለምን እንደሆኑ የሚያስታውሰን አለ? ስንቶቻችሁ ናቸሁ የምታስታውሱት? እስቲ የምታስታውሱ ከሆነ እጃችሁን አውጡ። የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናትን በሚመለከት ባለፉት 5 ክፍለ ጊዜያት የተማርናቸውን ቁምነገሮች ስንቶቻችሁ እንደምታስታውሱ ለማየት፣ ትንሽ ውይይት እናድርግ አስተባባሪ፣ በያንዳንዱ ጥያቄ ስንት ሰው እጁን እንዳወጣ እየመዘገቡ ውይይቱን ያስተባብሩ።

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት መዝሙርን አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የንግስት ንብ መዝሙርን አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የጡት ማጥባት የእሹሩሩን መዝሙርን አስታውሳችሁ እቤታችሁ የዘመራችሁ?

• የአይረንና ክኒን ማስታወሻ ቀን መቁጠሪያ ፖስተር እና የዘር ተምሳሌት ስቲከር ስንቶቻችሁ ግድግዳችሁ ላይ ለጥፋችኋል?

• ስንቶቻችሁ ናችሁ የእናቶች ሥርዓተ ምግብ ፖስተሩን በቤታችሁ ግድግዳችሁ ላይ የለጠፋችሁ ?

• የችግኝ ተምሳሌት ስቲከር ስንቶቻችሁ ግድግዳችሁ ላይ ለጥፋችኋል?

አያ ሙላት፡- ለጠቀስናቸው ጥያቄዎች ሁላችሁም እጃችሁን እንዳወጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ! አሁን በተለይ እንደኔ ገበሬዎች ለሆኑት ወንዶች የማቀርባቸው ጥያቄዎች አሉ፡፡ ባለፉት አምስት ክፍለጊዜያት አምስት ተጣጣፊ በራሪ ወረቀቶችን ወደ ቤታችሁ እንድትወስዱም ተሰጥቷችሁ ነበር፡፡ እነዚያ በራሪ ወረቀቶች ስለምን እንደሚያወሱ ስንቶቻችሁ ታስታውሳላችሁ? አስተባባሪ ውይይቱን ይመራሉ፤ ለእያንዳንዱ ጥያቄዎች ምን ያህል ሰዎች እጃቸውን እንደሚያወጡም ይመዘግባሉ፡፡ስንቶቻችሁ ለባለቤታችሁ ወይም ለቤተሰብ አባላት “የዶሮ ቤት አሰራር” ተጣጣፊ በራሪ ወረቀትን አሳይታችኋል?

• ስንቶቻችሁ ለቤተሰባችሁ የዶሮ ቤት ለመስራት አቅዳችኋል?

• “የዶሮ መኖ አዘገጃጀት” ተጣጣፊ በራሪ ወረቀትስ? ይሄንን ስንቶቻችሁ ለባለቤታችሁ ወይም ለቤተሰባችሁ አሳይታችኋል?

• ስንቶቻችሁ ዶሮዎቹ ጤናማ እንዲሆኑና ለቤተሰቡ ብዙ እንቁላሎች እንዲጥሉ ለዶሮ መኖ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ገዝታችኋል?

Page 131: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

• “የወተት አስተላለብና የላም አያያዝ እንክብካቤ” ተጣጣፊ በራሪ ወረቀትስ ስንቶቻችሁ ከባለቤታችሁና ከቤተሰባችሁ ጋር ተጋርታችሁታል?

• ስንቶቻችሁስ “የእናት ጡት ማጥባት እንዴት እንደሚጀመር” የሚያስተምረውን ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ከባለቤታችሁና ቤተሰባችሁ ጋር ተጋርታችሁታል? ይሄ በተለይ ችግኝ ህጻናት ያላቸው ቤተሰቦችን ለማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ጨቅላ ችግኝ ህጻናት ከተወለዱ አንድ ሰዓት ሳይሞላ ወርቃማውን እንገር መስጠት ወሳኝ መሆኑን የሚያስታውስ ነው፡፡

• ስንቶቻችሁ ናችሁ “የዉሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ አሰራር”ን የሚያሳየውን ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ለባለቤታችሁና ለቤተሰባችሁ ያሳያችሁት?

• ስንቶቻችሁ ለቤተሰባችሁ የዉሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ ገንብታችኋል? ወይም ለመገንባት አቅዳችኋል?

እባካችሁ እነዚህን ያደረጋችሁ እጃችሁን አውጡ!

አስተባባሪ፤ እባክዎ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት፣ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱ።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን:-እንኳን በደህና መጣችሁ! ግሩም ውይይት እንዳደረጋችሁና ተሞክሯችሁን ከቤተሰብ

ጋር እንደተጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አሁን ሁላችንም በአለፈው ክፍለ ጊዜያችን ላይ እንድናተኩር እፈልጋለሁ- ለእንቡጥ መዘጋጀት የሚለው ላይ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም በጣም ብዙ አስፈላጊ ቁምነገሮችን ተምረናል፡፡ ለእንቡጦቻችን ዝግጁ እንድንሆን የሚረዱንን በርካታ መንገዶችና እንቡጦች ያገኙትን ሁሉ ወደ አፋቸው መጨመር ሲጀምሩ ማድረግ ስላለብን ነገሮች ተምረናል!

• እንቡጥ ሕጻናት ነገሮችን ለማወቅ እንዴት ጉጉ እንደሆኑና ለምን ያገኙትን ወደ አፋቸው እንደሚከቱ ስንቶቻችሁ ተወያይታችኋል?

• እንቡጦችን በተመለከተ የተማራችሁትን ስንቶቻችሁከባለቤቶቻችሁና ከቤተሰብ አባላት ጋር ተጋርታችኋል?

አስተባባሪ፤ እባክዎ የደወሉ ድምጽ ሲሰማ ቴፑን በመዝጋት፣ውይይቱን ያስተባብሩ። ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱ።

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን:-በድጋሚ እንኳን በደህና መጣችሁ! ግሩም ውይይት እንዳደረጋችሁና ተሞክሯችሁን

እንደተጋራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እስቲ ባለፈው ሳምንት የተወያየንባቸውን አንዳንድ አስፈላጊ ጉዳዮች ልከልስላችሁ፡፡

1. እንቡጥ ህጻናት በጣም ንቁዎች ናቸው፤ 6 ወር ከሞላቸዉ ጀምሮ ከእናት ጡት በተጨማሪ የተፈጩ ምግቦችና ለስለስ ያለ ገንፎ መብላት ለአዕምሯቸውንና ለአካላቸውን እድገት ያስፈልጋቸዋል፡፡

131

Page 132: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

132

2. እንቡጥ ሕፃናት በዚህ የእድገት ደረጃ ብዙ ነገሮችን ስለሚለቃቅሙና ወደ አፋቸው ስለሚከቱ ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ ነገሮች ደግሞ በጀርሞች የተበከሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

3. በእንስሳት እደሪ ወይም በሰዎች አይነምድር ላይ የሚገኙ ጀርሞች እንቡጦቹን ለተቅማጥ ሊዳርጓቸውና ሰውነታቸው ከእናት ጡትና ከሌሎች ምግቦች ማግኘት የሚገባቸውን ንጥረ ነገሮች እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል ተቅማጥ የእንቡጦቹን አቅም ሊያዳክምና ለብዙ ቀናት ለበሽታ ሊዳርጋቸው ይችላል፡፡

4. በዚህ የእንቡጥ የእድገት ደረጃ ላይ ተገቢው የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓት ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህም ወላጆችና ቤተሰቦች እንቡጥ ሕጻናትን ከጀርሞች መጠበቃቸውን ለማረጋገጥ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማስታወስ አለባቸው!

5. ዘወትር ቤትንና ግቢን መጥረግና ማጽዳት እንቡጥ ሕፃናት ለጀርሞች እንዳይጋለጡ ያደርጋል፡፡

6. ሳሙና ገዝታችሁ እጃችሁን በውሃና በሳሙና መታጠብ - ይሄም ምግብ ከማዘጋጀት በፊት፣ ከመብላት ወይም ህጻናትን ከማብላት በፊት እንዲሁም መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ፣ በተለይም የሰውን አይነ ምድር ወይም የእንስሳትን እዳሪ ካጸዱ በኋላ እጃችሁንን መታጠብ አለባችሁ፡፡

እቴ ብርቱካን:-እነዚህን ነገሮች በሙሉ ማስታወስ የእንቡጥ ልጆችን ጤንነትና ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡

ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስ

እቴ ብርቱካን፡-አሁን የዛሬውን ርዕሰ ጉዳያችንን እንጀምር- 6ኛውን ክፍለ ጊዜያችንን ማለት ነው፡፡ ጊዜው እንዴት ነው የሚበረው! እኛ እኒህን የመጀመሪያዎቹን አንድ ሺህ ቀናት ክፍለ ጊዜዎች መረጃዎች ለእናንተ ማስተማርና ማካፈል እንዳስደሰተን ሁሉ እናንተም እንደተደሰታችሁባቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

አያ ሙላት፡- አዎ፤ ትክክል ነሽ ብርቱካኔ፤እኔ ስለ ንግስት ንቦች፣ ዘሮች እንዲሁም ችግኝና እንቡጥ ሕፃናት ማውራት በጣም ነው ያስደሰተኝ፡፡ እንግዲህ ገበሬም አይደለሁ፤ ነገሩ በደንብ ይገባኛል!

እቴ ብርቱካን፡-አውቃለሁ ዉዴ፤ የዛሬው ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ ስለ ትንሽ እንቡጥ ነው፡፡ባለፈው ሳምንት ስለ እንቡጥ ዝግጅት የተወያየነው፣ ለዛሬዉ ክፍለ ጊዜ እንዲያዘጋጀን ነበር፡፡ ትንሽ እንቡጥ ማለት ስድስት ወር የሞላቸው ህጻናትን ሲሆኑ ሰባት ወር እስኪሆናቸው ድረስ ማለት ነው፡፡ ልብ ይበሉ የእንቡጥ እድገት ደረጃ አንድ ነው፡፡ ነገር ግን በሦስት ክፍለ ጊዜያት መከፋፈል አለብን፤ ምክንያቱም በእያንዳንዱ የእንቡጥ ርእሶች የምንማራቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት ስለንጽህና አጠባበቅና እንቡጥን እንዴት ከጀርሞች ብክለት መጠበቅ እንዳለብን ነበር የተማርነው፡፡ በዛሬው ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ ስለምግብና እንዴት ለእንቡጥ ተጨማሪ ምግቦችን እንደምንጀምር ነው የምንወያየው፡፡ ይሄ የእንቡጥ ደረጃ የምንማረው ቀጣዩ አስደሳች ምዕራፍ ነው፡፡

Page 133: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

133

ባለፉት ሳምንታት ስለ ንግስት ንብቦች ስርአተ ምግብ ተወያይተንበታል፡፡ ዛሬ ደግሞ ከ6 ወር በኋላ ለእንቡጥ ሕፃናት ልዩ ልዩ ምግቦችን ቀስ በቀስ ማስጀመር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንወያያለን፡፡ ይህ ማለት የተለያዩ ምግቦችን በአንድ ላይ በመፍጨት ማሰናዳትና ባለኮከብ ምግቦችን በማከል ለእንቡጥ ህጻናት ማብላት ይኖርብናል፡፡ ኮከብ ምግቦች እንቡጥ ህጻናት ጠንካራ፣ጤናማና ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ሆነው እንዲያድጉ ያደርጉቸዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ኮከብ ምግቦች ልጆቻችን በትምህርታቸው ጎበዝና ከክፍላቸው አንደኛ እንዲወጡና እንዲሁም ስኬታማ ህይወትን እንዲመሩ ያግዛቸዋል፡፡ ኮከብ ምግቦች ለንግስት ንቦች ለምንላቸው ነፍሰጡሮችና አጥቢ እናቶችም በጣም አስፈላጊ ናቸው!

እቴ ብርቱካን፡-ልጆቻችን ስድስትኛ ወራቸውን ከጨረሱ በኋላ የእድገታቸው አዲስ ምዕራፍ ላይ ይደርሳሉ፡፡ ችግኝ መሆናቸው ይቀርና ወደ እንቡጥነት የእድገት ደረጃ ይሻገራሉ፡፡ አንጀታቸው ይጠነክራል፤ ትንሽ እንቡጥ አካላቸው ያድጋል፡፡ በምግባቸው ውስጥ ተጨማሪ ምግቦችን ቀስ በቀስ መጀመር የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው፡፡ የእናት ጡት አሁንም ዋናው የምግባቸው ክፍል ቢሆንም ስድስተኛ ወራቸውን ከጨረሱ በኋላ ተጨማሪ ምግቦች ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይሄ ማለት እንደገንፎ ያለ ከተለያዩ እህሎች (ምጥን) የተሰናዳ ዋና ምግባቸው ሲሆን በተጨማሪ የተፈጩና የላሙ ምግቦች ለምሳሌ እንደ ሙዝ፣ የተቀቀለ ስኳር ድንች፣ ቆስጣ የመሳሰሉ ባለ ሁለት ኮከብ ምግቦችን ወይም የላም ወተት፣ እንቁላል የመሳሰሉ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦች እንዲሁም እንደዘይትና ቅቤ ያሉ ባለአንድ ኮከብ ምግቦችን (ለስላሳና ጣፋጭ ለማድረግ) በአንድ ላይ ደባልቀን እንደአንድ ምግብ ማዘጋጀት አለብን፡፡

ይህን ስንል ስድስትኛ ወራቸውን የጨረሱ ሕፃናት ሆዳቸው በጣም ትንሽ ስለሆነ ተጨማሪ ምግቦችን በትንሽ በትንሹ ማለማመድ ይስፈልጋል፡፡ ይህም ማለት ለመጀመሪያ ሳምንት በቀን ሦስት ጊዜ በወተትና ኪቤ የተሰራ ለስላሳ ገንፎ አንድ አንድ የሾርባ ማንኪያ ብቻ በመሠጠት ማለማመድ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሕፃን ከሌላ ሕፃን የምግብ አቀባበሉ ይለያል፡፡ ስለዚህ እናቶች በትግስት ጠዋት አንድ የሾርባ ማንኪያ ማብላት ሞክሩ፤ እንቢ ቢል ቆይታችሁ መሞከር ይኖርባችዋል፡፡ ምግብ ለትንሽ እምቡጥ ሕፃናት አዲስ ነገር ስለሚሆንባቸው በመጀመሪያ ሙከራቸው ሊተፉትም ላይቀበሉትም ይችላሉ፡፡ ይህ ሲሆን ግን ከነጭራሹ የምግብ ፍላጎት የላቸውም ብሎ መደምደም ወይም ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም፡፡ ደጋግሞ በመሞከር ማለማመድ አስፈላጊ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከምግቡ በተጨማሪ ጡት ማጥባት ማቋረጥ የለባቸውም፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ጡት ብቻ ማጥባት መቀጠል የለባችሁም፡፡ ለመጀመሪያዉ አንድ ሳምንት እምቡጥ ሕፃናትን በየቀኑ 3 የሾርባ ማንኪያ ማብላት ይኖርባችዋል፡፡

ምግብ መብላት በጀመሩ በሁለተኛው ሳምንት ላይ ለስላሳ ገንፎ፤ ተፈጭተው ከላሙ ኮከብ ምግቦች ጋር ግማሽ የቡና ሲኒ (ፍንጃል) በቀን ሶስት ጊዜ መብላት ይችላሉ፡፡

በሦስተኛው ሳምንት ግማሽ ሲኒ ላይ ትንሽ በመጨመር በቀን ሶስት ጊዜ ማለትም በዚሁ የሲኒ ልክ ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት ማብላት ይኖርባችኋል፡፡ ጡት

Page 134: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

134

ማጥባትም ማቋረጥ የለባችሁም፡፡

በአራተኛው ሳምንት ትንሽ እንቡጥ ሕፃናት አንድ ሙሉ የላመ ምግብ የቡና ሲኒ መብላት ይችላሉ፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎን እኔ በማስረዳበት ወቅት የህጻናትን ሥርዓተ ምግብ ጉልቻ ምስል ለተሳታፊዎች ያሳዩ፡

ኮከብ ምግቦች የእንቡጡ ህጻን አዕምሮ እንዲዳብር የሚያግዙ ሲሆን ጠንካራ፣ ጤናማና በጣም ብሩህ አዕምሮ ያላቸው እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡

1. ቀዩ ዓምድ የሚወክለው ባለ 3 ኮከብ ምግቦች የእንስሳ ተዋፅዎን ነው፡፡፡ ለምሳሌ - ዶሮ፣ ጉበትና ኩላሊት ፣ ሥጋ፣ እንቁላል፣ ወተትና ዓሳ፤ ህጻናት ሲመገቡ በደንብ ልስልስ እንዲልላቸው ስጋው ወይም ዓሳው በትናንሹ ተከትፎ መፈጨት ይኖርበታል-፡፡

2. አረንጓዴው አምድ የሚወክለው አትክልትና ፍራፍሬን ነው፡፡ እነዚህ ባለ2 ኮከብ ምግቦች እንቡጥ ህጻናትን ከጉንፋንና ሌሎች ህመሞች ለመከላከልና ጤናማ ሆነው እንዲዘልቁ ለመጠበቅ ይረዳሉ፡፡ ባለሁለት ኮከብ ምግቦች እንደ ፓፓያ፣ ማንጎ፣ ሙዝና ፖም ፍራፍሬዎችን እንዲሁም እንደ ቲማቲም፣ ካሮት፣ ስኳር ድንች፣ ቆስጣና ጎመን ያሉ አታክልቶች ናቸው፡፡

3. ቢጫው አምድ የሚወክለው ቅባትና ዘይት ባለ1 ኮከብ ምግቦችን ነው፡፡ ይህም እንደ ሱፍና ኑግ ያሉ የአትክልት ዘይቶች ወይም ቅቤ ናቸው፡፡ እነዚህ የህጻናቱን ምግቦች ለማለስለስና ጣፋጭ ለማድረግ ይረዳሉ፡፡ እንቡጦች ቅባትና ዘይቶችን ኃይል ለማግኘትና የሚበሉትን ምግብ ለመፍጨት ያስፈልጋቸዋል፡፡

አያ ሙላት፡- አሁን ደግሞ በአገራችን እናቶች ልጆቻቸውን ስድስት ወራቸውን ከጨረሱ በኋላ ስለሚመግቧቸው ምግቦች እንወያይ፡፡ ይሄ መረጃ ከኤንጂን ጥናት የተገኘ ሲሆን እስቲ ለህጻናት የሚሰጣቸው የመጀመሪያ ምግቦች ምን እንደሆኑ እንስማ፡፡

እናቶች ለልጆቻቸው ከስድስት ወር በኋላ በአብዛኛው እስከ ስምንትና ዘጠኝ ወር ወይም አስረኛ ወር ድረስ እንደመጀመሪያ ምግብ የሚሰጡት በዋናነት የላም ወተትና አጥሚት ነው፡፡ ለእንቡጥ ሕፃናት የሚሰጠው አጥሚት እንደ ውሃ ቀጥኖ የተሰናዳ ሲሆን ይሄም የሚሆነው እናቶች ህጻናት ይታነቃሉ ብለው ስለሚሰጉ ነው፡፡ በተጨማሪም እናቶች ቀጪን አጥሚት ተጨማሪ ለህፃናት ምግብ ይሆናቸዋል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡

ሁላችሁም ሰማችሁ አይደል? አይገርም! ማንም ሰው ለህጻናት ከስድስት ወር በኋላ ወፍራም ገንፎ ያበላ የለም፤ ለልጆቻቸው ቀጭን አጥሚት የሰጡትም ጥቂት እናቶች ናቸው! እሺ አሁን ደግሞ ለልጆቻቸው ኮከብ ምግቦችን የሰጡ እናቶች ካሉ እስቲ እንይ፡፡

Page 135: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

135

• በአጠቃላይ እናቶች፤ ህጻናት ከእናት ጡትና አጥሚት በቀር ሌላው ቤተሰብ የሚበላውን መብላት አለባቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ እናቶች ለህጻናት ልጆቻቸው ብለው በተለየ ሁኔታ የሚያሰናዷቸው ምግቦች የሉም፤ አዋቂ የሚመገበውን እንጀራ በወጥ ነው የሚሰጡዋቸው፡፡ ነገር ግን እናቶች ሌላው ቤተሰብ የሚበላውን በርበሬ ያለባቸውን ምግቦች ለህጻን ልጆቻቸው አይሰጡም፡ ፡

• እናቶች ለልጆቻቸው እንደ ሽሮና ክክ ያሉ እህሎችንና ጥራጥሬ የመሳሰሉ የዘወትር ምግቦችን የሚመግቡ ሲሆን የእንስሳት ተዋጽኦ እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎችን የሚመግቡ ከስንት ጊዜ አንዴ ነው፡፡ ህጻናት በአብዛኛው የሚመገቡት የእንስሳት ተዋጽኦ ምግቦች እንቁላልና የላም ወተት ሲሆኑ ሥጋ ግን በበዓላት ጊዜያት ብቻ የሚያገኙት ምግብ ነው፡፡

• በበዓላት ጊዜም ቢሆን ብዙ እናቶች ለህጻን ልጆቻቸው ስጋ ከማብላት ይቆጠባሉ፤ምክንያቱም በጣም ይከብዳቸዋል ብለው ስለሚያምኑ ህጻኑን ያንቀዋል ብለው ያስባሉ፡፡ ይሄ መረጃ ያስገረማችሁ አንዳንድ ተሳታፊዎች ትኖራላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንቡጥ ህጻናት ኮከብ ምግቦችን እንዲመገቡ አይደረግም፡፡ እስቲ ስለእናንተ ተመክሮዎች ለመወያየት ጥቂት አፍታ እንውሰድ፡፡ የእንቡጥ ወላጆችና አያቶች አሁን ስለሰሙት መረጃ የሚያስቡትን ሊነግሩንና ከቡድኑ ጋር ተመክሮዎቻቸውን ሊጋሩ ይገባል፡፡

አስተባባሪ፤ እባክዎ ደወሉን ሲሰሙ ቴፑን ያጥፉና ውይይቱን መምራት ይጀምሩ፡፡ ሲጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

አያ ሙላት፡- እንኳን ደህና መጣችሁ! ግሩም ውይይት እንዳደረጋችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ለትንሽ እንቡጥ ህጻናት ስድስት ወር ከሞላቸው በኋላ ወፍራም ገንፎ ከኮከብ ምግቦች ጋር መስጠት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተረድታችኋል ብዬ አምናለሁ፡፡

• አንድ ምስጢር ላካፍላችሁ፤ ገንፎው ለስለስ ያለና ወፍራም መሆን አለበት- ለእንቡጥ ህጻናቱ በእጃችን ማጉረስ እስከምንችል ድረስ መወፈር ይኖርበታል፡ ፡ እንደአጥሚት ቀጭንና እንደ ውሃ ፈሳሽ ከሆነ ምግብ እንዴት እንደሚዋጥ አይማሩበትም፡፡ ከዚያም በላይ በቂ የምግብ ንጥረ ነገር አያገኙበትም፡፡ የትንሽ እንቡጦች ሆድ ከምግብ ይልቅ በውሃ ትሞላል!

እቴ ብርቱካን፡-ለጊዜው ወጋችን እናቋርጥና ትንሽ ለለውጥ ያህል መዝሙር ደግሞ እናዳምጥ! መዝሙሩ “ተጨማሪ ምግቦች” የሚል ሲሆን ስለ ሕፃናት አመጋገብ የሚያወሳ ነው! በጥሞና አዳምጡና ከቻላችሁም አብራችሁ ዘምሩ!

SFX: ‘“ተጨማሪ ምግቦች” መዝሙር

እቴ ብርቱካን፡-(የማንጎራጎር ድምጽ) እንኳን በደህና መጣችሁ! እንዴት ደስ የሚል መዝሙር ነው! በመዝሙሩ እንደተደሰታችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እርግጠኛ ነኝ ተደስታችኋል! ተሳታፊዎች ስለ መዝሙሩ ያላቸውን ሃሳብ መጋራት እንዲችሉ አስተባባሪ እባክዎ ለውይይት መነሻ የሚሆኗቸውን ጥቂት ጥያቄዎች ያቅርቡ፡፡

Page 136: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

136

• አንደኛ፤ ከመዝሙሩ ምን ተረዳችሁ? የሰማችኋቸው አንዳንድ መረጃዎች ምንድን ናቸው?

• ሁለተኛ፤ ከመዝሙሩ የወደዳችሁት ምኑን ነው?

• ሦስተኛ፤ ይሄን መዝሙር ለቤተሰቦቻችሁ ማስጠናት የምትችሉ ይመስላችኋል?

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን ያጥፉና ተሳታፊዎች ውይይቱን ያስተባብሩስትጨርሱ ቴፑን መልሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል እቴ ብርቱካን፡-እንኳን በደህና መጣችሁ! ስለመዝሙሩ ግሩም ውይይት እንዳደረጋችሁ ተስፋ

አደርጋለሁ፡፡ ይሄ መዝሙር ስለኮከብ ምግቦችና ምንን እንደሚወክሉ ለማስታወስ ያግዛችኋል፡፡ መዝሙሩን በቃላችሁ ለማወቅና ለቤተሰብ አባላቶቻችሁ ለማስተማር ሞክሩ፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አሁን አንዳንዶቻችሁ እንቡጥ ሕጻናት፤ ወፍራም ለስላሳ ገንፎ መዋጥ ይችላሉ ብላችሁ ላታምኑ እንደምትችሉ አውቃለሁ፡፡ እኔ ግን መቻላቸው ሃቅ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ፡፡ ትናንሽ እንቡጥ ሕፃነት ከ6ወር በኋላ እንደመጀመሪያ ምግባቸው ለስለስ ያለ ወፍራም ገንፎ መመገብ መጀመራቸው ወሳኝ ነው፡፡ በእርግጥ ንግስት ንብ እናቶችም ጡት ማጥባታቸውን መቀጠል አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከ6 ወር በኋላ ለስለስ ያለ ወፍራም ገንፎ ለህጻናት ልጆቻችሁ ማስጀመር አለባችሁ፡፡

ከመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት እናቶች መካከል ጌጤ የተባለችውን ጎበዝ እናት ምስክርነት እንስማ፡፡

ምስክርነት x 1

ጌጤ እባላለሁ፤ የ26 ዓመት ባለትዳር ሴት ነኝ፡፡ ከስድስት ወር በፊት ወንድ ልጅ በሰላም ተገላግያለሁ፡፡ ልጄ ከተጸነሰበት ቀን አንስቶ ለቅድመ ወሊድ ክትትል ጤና ጣቢያ እሄድ ነበር፡፡ በእርግዝናዬ ወቅት የአይረን ኪኒን ዘወትር ማታ ማታ ወስጃለሁ፣ በየቀኑ በዘወትር ምግቤና መክሰስ ላይ ኮከብ ምግቦች በማከል በልቻለሁ፣ ስለዚህ ጤናማ ልጅ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ፡፡ ለመጀመሪዎቹ ስድስት ወራት ልጄን ጡት ብቻ ነበር ያጠባሁት፡፡ አሁን ልጄ ስድስት ወሩን ስለጨረሰ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ይሄ ለልጄ አዲስ ምዕራፍ ነው፤ ምክንያቱም ተጨማሪ ምግብ መብላት መጀመር ይችላል፡፡ ለልጄ የምመግበውን ሳዘጋጅ በጣም እጠነቀቃለሁ፡፡ እንዲታመምም አልፈልግም፤ ስለዚህ ምግቡን ከማዘጋጀቴ በፊት ሁልጊዜ እጄን በሳሙናና በውሃ ሙልጭ አድርጌ እታጠባለሁ፡፡

መጀመሪያ አካባቢ ልጄ የመዋጥ ችግር ይገጥመዋል ወይም የአዲሱን ምግብ እንግዳ ጣእም ስለሚሆንበት አይወደውም ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ስለዚህ ልጄን ቀጭን አጥሚት መመገብ ጀመርኩኝ፡፡ ያንን ሳደርግ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ ልትጎበኘኝ ቤቴ መጣች፡፡ ለልጄ ወፍራም ገንፎ ማብላት እንዳለበትና ገንፎውም ሲዘጋጅ ውፍረቱ በእጅ የሚያዝ መሆን እንዳለበት ነገረችኝ፡፡ መዋጥ የሚማረውም ወፍራም ከሆነ

Page 137: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

137

ብቻ እንደሆነ፣ አለበለዚያ ፈሳሽ እንደመጠጣት እንደሚሆንበትም አስረዳችኝ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ ወፍራም ገንፎ ከላሙ ኮከብ ምግቦች ጋር ነው የምመግበው፡፡ አዲሱን እንግዳ ጣዕም እስኪለይ ድረስ ፊቱን ኩምትርትር አድርጎት ነበር፣ ፡፡ ነገር ግን እንዲለሰልስና መዋጥ እንዳያስቸግረው ገንፎውን በዘይትና ወተት እንዲሁም እንቁላል ጨምሬ ስላበሰልኩት አልተቸገረም፡፡ ደግሞም የሚጣፍጥ መሰለኝ፤ ምክንያቱም ትንሽዬ አፉን በምላሱ ሲጠራርግ ነበር፡፡

በየዕለቱ ልጄ ላይ ለውጥ አያለሁ፡፡ ለልጄ ትክክለኛውን ነገር እያደረግሁ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ምክንያቱም ሁልጊዜ ደስተኛ ነው፡፡ በፍጥነትም እያደገ ነው፤ እንዲሁም ጤናማም ነው፡፡ የልጄ የህይወት ጉዞው በግሩም ሁኔታ እንዲጀምር አድርጌአለሁ፡፡

አያ ሙላት፡- ጌጤ በእርግጥም ድንቅ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ -ቀናት እናት ናት! እንቡጥ ሕጻኗ ጠንካራና ብሩህ አዕምሮ ያለው ሆኖ እንዲያድግ የሚያግዘው ለስለስ ያለ ወፍራም ገንፎ እንዴት እንደሚዘጋጅ ታውቃለች፡፡ እናንተስ? በምግብ ንጥረ ነገሩ የዳበረ ገንፎ እንዴት እንደሚዘጋጅ ታውቃላችሁ? እንቡጥ ሕፃናት ገንፎ ላይ እንዴት ኮከብ ምግቦች እንደሚጨመሩ እቤታችሁ ወስዳችሁ የምታሳዩት ነገር ለእናንተ አዘጋጅተናል፡፡ አስተባባሪ የህጻኑ ገንፎ ለስላሳ፣ ወፍራምና ጣፋጭ ይሆን ዘንድ እንዴት ባለ1፣2 እና 3 ኮከብ ምግቦች እንደሚጨመሩ የሚያሳየውን ይሄን ተጣጣፊ በራሪ ወረቀት ያከፋፍፍሉል! በተጨማሪም ትንሽ እንቡጥ ህጻናትን በምን ያህል የጊዜ ልዩነት እና ብዛት መመገብ እንዳለባችሁ ለማስታወስ የሚረዳችሁ ፖስተርም አዘጋጅተንላችኋል!

እቴ ብርቱካን፡-አሁን ምግብ ከማዘጋጀታችንና እንቡጥ ልጆቻችንን ከመመገባችን በፊት እጃችንን በሳሙናና በውሃ መታጠብ እንዳለብን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ይሄ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ ህጻናት በንጽህና ጉድለት የተነሳ በተቅማጥ ተይዘው ይታመማሉ፣ የፈዘዙናና የተቀነጨሩም ይሆናሉ፡፡ ማንኛውም የቤተሰብ አባል ከምግብ ዝግጅት በፊት ህጻናትን ከመመገብ በፊት መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ ወይም ሕፃናትን ካጸዳዱ በኋላ እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ አለባቸው፡፡

አያ ሙላት፡- ብዙዎቻችሁ እጃችሁን እንደምትታጠቡ አውቃለሁ፤ነገር ግን አንዳንዶቻችሁ እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ላትገነዘቡት ትችላላችሁ፡፡ እስቲ ጥቂት ጊዜ ወስደን ስለእነዚህ ሃሳቦች እንነጋገር፡፡ እባካችሁ በቡድን ሆናችሁ ተከታዮቹን ጥያቄዎች ተወያዩበት፡

1. እጅን በውሃና በሳሙና መታጠብ እምቡጥ ሕፃናትን ጠንካራና ጤናማ ከማድረጉ ባሻገር በተቅማጥና በሌላ በሽታ ምክንያት ከሚከሰተው መቀንጨር እንደሚከላከል ቢያውቁ ኖሮ ብዙ ሰዎች እጃቸውን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ይጀምሩ ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ?

2. ምግብ ከማሰናዳታችን ወይም ህጻናትን ከመመገባችን በፊት፣ መጸዳጃ ቤት ከሄድን ወይም እዳሪ ከነካን በኋላ እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ የዘወትር ልምዳችን እንዲሆን ቤተሰቦች ምን ማድረግ አለባቸው?

Page 138: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

138

አስተባባሪ፤ እባክዎ ቴፑን ያጥፉትና በእነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ተሳታፊዎች እንዲወያዩበት ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ፡፡ ውይይቱን ስትጨርሱ ቴፑን ይክፈቱት፡፡

SFX: የደወል ድምጽ ይሰማል.. አያ ሙላት፡ እንኳን በደህና መጣችሁ! እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ የዘወትር ልማድ

ለማድረግ የሚቻልበትን መላ በማፈላለግ ረገድ አንዳንድ ጥሩ ሃሳቦችን በመለዋወጥ፣ እርስ በእርስ እንደተረዳዳችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የልጆቻችሁን ምግብ ከማዘጋጀታችሁና ከመመገባችሁ በፊት እጃችሁን በሳሙናና በውሃ መታጠባችሁን መዘንጋት የለባችሁም፡፡ በተለይ ከመጸዳጃ ቤት መልስ ወይም የህጻኑን የሽንት ጨርቅ ከቀየሩ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ልብ ይበሉ የእሙቡጥ ህጻናት በሽታን የመቋቋም አቅም እንደአዋቂዎች የጎለበተ አይደለም፡፡ ለጀርሞችና በሽታዎች የበለጠ የተጋለጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ እንቡጥ ህጻናትን ስንይዝ ወይም ምግባቸውን ስናዘጋጅ በጣም በንፅህና መሆን አለበት፡፡

አንዳንዴ በዕለት ተእለት ህይወታችን ውስጥ እጃችንን በሳሙናና ውሃ እንዳንታጠብ እንቅፋት የሚሆኑ ሌሎች ፈተናዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ፈተናዎች መካከል በቂ ውሃ እና ሳሙና ቤት ውስጥ አለመኖር እንደልብ እንዲሁም ለመታጠብ ሳሙናና ውሃ በአመቺ ቦታ ያለመኖር በዋናነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ባለፈው ክፍለ ጊዜያችን እንዴት የዉሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያ መገንባት እንደምትችሉ አሳይተናችኋል፡፡ ይሄ ውሃ ቆጣቢ የእጅ መታጠቢያ የቤተሰቦች የእጅ መታጠቢያ ሲሆን በአመቺ ስፍራ በቤት ውስጥና ከቤት ውጪ በቀላሉ ሊሰራ ይችላል፡፡

እቴ ብርቱካን፡-ትክክል ነው ውዴ ! የዉሃ ቆጣቢ እጅ መታጠቢያእጃችሁንለመታጠብና መመረዝን ለመከላከል የሚረዳ እጅግ ጠቃሚ መሣሪያ ነው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አሁን አካሄዳችንን ለወጥ ብናደርገው ምን ይመስላቸዋል?እስቲ ለ6 ወር ህጻን፣ ወፍራም ገንፎ ስለመመገብ ለአማቷ ለማሳመን ስለምትሞክር አንዲት እናት የተዘጋጀ ድራማ እናዳምጥ፡፡ በድራማ ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዴት እንደሚነጋገሩ አስተውሉ፡፡

ለምለም:- (ከህጻን ጋር እየተጫወተች) ውቧ ልጄ! ኦኦኦ-ኦኦኦ! ማን እንደመጣ አየሽ አያትሽ እታለም

እታለም፡- እንዴት ነሽ ለምለም? የልጄ ልጅ እንዴት ናት?

SFX: ህጻንኗ ማልቀስ ትጀምራለች እታለም: እርቧት መሆን አለበት

ለምለም፡- (ተነስታ ህጻኑን ትይዘዋለች) አዎ፤ በእርግጥ የምግብ ሰዓትዋ ነው፡፡ እስቲ የምትበላውን ላሰናዳላት እጄን ታጥቤ ምግቧን እስካዘጋጅላት ይይዙልኛል?

እታለም፡- ህጻኑን ያባብላሉ : “ሚጡዬ ሚጡዬ…የእኔ ሸጋ”

Page 139: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

139

SFX: የእጅ መታጠብ፡ የቁም ሳጥን በር፣የወጥ ቤት እቃዎች-- ድምጽ

እታለም፡- ምንድነው! (በመገረም) ለምለም፤ ህጻኑን የምትመግቢው ይሄን ዓይነት ምግብ ነው እንዴ?

ለምለም፡- አዎ፤ ምን ችግር አለው ?

እታለም፡- እንደኔ ልምድ ከሆነ፣ በዚህ እድሜ ያሉ ህጻናት ፈሳሽ ነገር ነው መውሰድ ያለባቸው፡፡ ምንድነው ይሄ ያዘጋጀሽላት?

ለምለም፡- ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወፍራም ገንፎ ጀምሬላት ነበር፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እንቁላልና ጥቂት ቅቤ በመጨመር ከለስላሳ ወፍራም ገንፎው ጋር ደባልቄ ማሰናዳት ጀምሬአለሁ፡፡

እታለም፡- እንቁላል፣ ወፍራም ገንፎ? ህጻኗ ይሄን እንዴት ትውጠዋለች? ገና ጥርስ እንኳን አላወጣች ትንሽ ቆይተሽ ስጋም አበላታለሁ እንዳትይኝ ሆሆ!

ለምለም : እታለም፤ እንቁላሉ የተፈጨ ነው፤ ህጻኗ እንዲህ መብላት ተስማምቷታል፡፡ አዎ ዛሬ እኮ ሥጋ ስሌለኝ ነው እንጂ ምግቧ ውስጥ እጨምርላታለሁ፡፡

እታለም፡ ምን ሚጡ ይሄን ለመብላት ገና አልደረሰችም፤ በጣም ሕጻን ናት እኮ… ለመሆኑ ይሄን ነገር ከየት ነው ያመጣሽው?

ለምለም የአንድ ሺህ ቀናት እናቶች አባል ነኝ፤ በተጨማሪም ለማህበረሰብ ውይይትና በአካባቢያችን የ ጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ከሚሰጡት ቁሳቁሶች ለመማር ዘወትር የሚገናኙ የእናቶች ቡድን አባል ነኝ፡፡ ልጄን እንደዚህ ያለ ምግብ ማብላት ትክክል እንደሆነ የተማርኩትም እዚያ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት እኔና ግዛው ልጃችንን እንዴት ማሳደግ እንዳለብን በጋራ በመወያየት ለመወሰን እየሞከርን ነው፡፡

እታለም፡- (ያጉረመርማሉ) ከእኔ ይልቅ የእነሱን ምክር ትቀበያለሽ? እኔ እኮ ባለቤትሽን ጨምሮ ልጆች በማሳደግ የብዙ ዓመት ልምድ ያለኝ እናት ነኝ፡፡ ግዛውን ጥሩ አድርጌ ነው ያሳደግሁት፡፡ ጥሩ ሆኖ አላደገም እንዴ? እመኚኝ ለልጅ ልጄ የሚሻላት ምን እንደሆነ በደንብ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡

ለምለም፡- እታለም -- የእርስዎን እውቀት አልተጠራጠርኩም ፤ ግን…

እታለም:- ስሚ፤ ህጻኗ ገና ጥርስ እንኳን አላበቀለችም፤ እንኳንስ እንቁላል ወይም ስጋ ቀርቶ ወፍራም ምግቦችን ማኘክ አትችልም፡፡ እንዲህ ያሉ ውድ ምግቦችን ህጻን ልጅ ላይ ማባከን አያስፈልግም ሆ ድርቅ አትበይ የምነግርሽን እህ ብለሽ ስሚ፡፡ የማወራውን ነገር ጠንቅቄ አውቃለሁ!

ለምለም፡- ልጆችዎትን በደንብ እንዳሳደጉ አውቃለሁ፡፡ አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡፡ ግዛው ካደገበት ጊዜ የተለየ ነው፡፡ ይሄ መረጃ አልነበረም፡፡ የተማርነው ትምህርት ስለእናቶችና ህጻናት የዘወትር ምግባችን ላይ ኮከብ ምግቦችን ስለማከል ነው፡፡

እታለም፡- (ድምጻቸውን ከፍ አድርገው) ኮከብ ምግቦች! ሆሆ ጉድ እኮ ነው እናንተ ወጣቶች የማታመጡብን ነገር የለም? ስለ ህጻናት ምን የምታውቂው ነገር አለ? ይሄ እኮ ገና የመጀመሪያ ልጅሽ ነው፡፡ እኔ ግን ሦስት ልጆች ወልጄ አሳድጌአለሁ፡፡

Page 140: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

140

የእግር ኮቴ ድምጽ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማል

ግዛው፡- እንደምን አረፈዳችሁ፤ ምን ሆናችኋል፤ ሰላም አይደለም እንዴ?

እታለም፡- ልጄ እንኳን መጣህልኝ፡፡ ይህቺ ሚስትህ ስለህጻናት አመጋገብ ሁሉን ነገር እንደምታውቅ ነው የምታስበው፡፡ ታምናለህ? ሚጡን እንቁላል ከወፍራም ገንፎ ጋር ልታበላት ስትል ነው የደረስኩት፡፡

ግዛው፡- እማዬ አትናደጂ፡፡ ጥቂት ስጋም አምጥቼላታለሁ፡፡

እታለም፡- ስጋ… በጣም እኮ ውድ ነው፤ ይህቺ ሴት ገንዘብህን እያባከነችው ነው፤ እሺ ገንዘቡን እርሳው፤ ለልጅህ አታስብም? ሚጡ ገና የስድስት ወር ህጻን ናት፤ እንቁላል ወይም ስጋ መብላት አትችልምትታመማለች፡፡

ግዛው:- ኧረ አስብላታለሁ እማዬ፤ ለልጄ ጥሩውን ነገር ነው የምፈልገው፡፡ ለምለም እንቁላልና ስጋ ግዛ አለችኝ ፤ገዛሁ፡፡

ለምለም፡- አመሰግንሃለሁ ውዴ! ትክክል ነው ያደረግከው፡፡ ልጃችን ህይወቷን በጥሩ ሁኔታ ልትጀምር ይገባታል፡፡ ሁላችንም ጤናማ፣ ጠንካራና ብሩህ አዕምሮ ያላት ሆና እንድታድግ እንፈልጋለን፡፡ አይደለም እንዴ?

እታለም፡- ምን ትላለች እኔም ቢሆን ለልጅ ልጄ ጥሩውን ነው የምፈልገው፡፡ ግዛው፤ አየሃት ድፍረቷን፡፡ ስማ፤ እዚህ የመጣሁት እረዳችኋለሁ ብዬ በማሰብ ነው፤ ምክሬ ተሰሚነት ከሌለው ግን ወደ ቤቴ እመለሳለሁ፡፡

ለምለም፡- እታለም፤ እባክዎ እንደዚያ አይበሉ፡፡ ለእርስዎ ትልቅ ክብር ነው ያለኝ፡፡ ለምክርዎትም ትልቅ ግምት አለኝ፡፡ ነገር ግን ያስተማሩኝ ትምህርት በጥናት የተደገፈ ሲሆን በሚጡ እድሜ ላይ የሚገኙ ሕጻናት እንቁላልና ስጋም ቢሆን በደንብ እስከተፈጨ ድረስ መብላት እንደሚችሉና ጠንካራ ጤናማና ብሩህ ሆነው ለማደግ አስፈላጊውን የምግብ ንጥረ ነገር እንደሚሰጣቸው ነው፡፡

እታለም፡- ወቸ ጉድ! ሚስትህ የምትለውን ብቻ ስማልኝ! አስሬ ይሄን ነገር ትደግመዋለች፡፡ ግዛው፤ አንተ በሚጡ እድሜ ሳለህ እንቁላል ወይም ስጋ የሚባል ነገር አላበላሁህም፡፡ ግን ጤናማ ነህ፡፡ የሆኖ ሆኖ አንተ ነህ አባወራው፤ እንቁላሉንና ስጋውን የምትገዛው አንተ ነህ፤ ስለዚህ በዚህ ጉዳይ ላይ መወሰን አለብህ፡፡

ግዛው:- እ…እ…ትንሽ ግራ ገብቶኛል፤ እኔ ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም፡፡ ለምለም እንቁላልና ስጋ ግዛ አለችኝ፤ገዛሁ፡፡

እታለም፡- ትሰማኛለህ ግዛው፤አንተ ነህ የቤቱ አባወራ፤ በእንዲህ ያለ ትልቅ ጉዳይ ላይ እሷ እንድትወስን እንዴት ትፈቅድላታለህ፡፡ እናትህን መስማት አለብህ፤ ሚስትህ ህጻኗን በወፍራም ምግቦች አፍና ከመግደሏ በፊት አሁኑኑ ወስን! ሚጡ እንቁላልና ስጋ መመገብ ማቆም አለባት፡፡

ለምለም፡- ግዛው፤ ለልጃችን ስጋውን ባልኩህ መሰረት በመግዛትህ አመሰግንሃለሁ፤ ነገር ግን እኔ የተማርኩትን ብትካፈል ኖሮ፣ ከሚስትህና ከቤተሰብህ ጋር እንዴት መወያየትና መወሰን እንዳለብህ ትማር ነበር፡፡ አሁንም ግን አልረፈደም፡፡

Page 141: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

141

ግዛው:- ለምለም፤ እናቴ እንድትበሳጭ አልፈልግም፡፡ ለሚጡ እንቁላል ወይም ስጋ ማብላት ማቆም ሳይኖርብን አይቀርም፡፡ እናቴ የሚሻለውን ነገር ታውቃለች፡፡ በእኒህ ጉዳዮች ላይ የብዙ ዓመት ልምድ ያላት ትልቅ ሴት ናት፡፡

ለምለም፡- እሺ በቃ አንድ ሃሳብ አለኝ፡፡ ነገሩን በቅጡ አላስረዳሁት ይሆናል፤ነገር ግን የመጀመሪያ አንድ ሺህ ቀናት የድጋፍ ቡድናችንን የሚመሩት እማማ ታደለች ሁላችንንም ሊያነጋግሩን ይችላሉ፡፡ ቢያንስ ይሄን እድል ስጡኝ?

ግዛው:- እማዬ ምን ትያለሽ?

እታለም:- ታደለችን አውቃታለሁ፤ እሷም የልጅ ልጆች አድርሳለች፤ሁለት ልጆች ወልዳ ለቁም ነገር ያደረሰች ናት፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደምትል መስማት እፈልጋለሁ፡፡

ለምለም: ይሄን እድል ስለሰጣችሁ አመሰግናለሁ…አሁን ሄጄ እጠራቸዋለሁ፤ ቅርብ ነው ቤታቸው፡፡

SFX: የደውል ድምጽ ይሰማል

አያ ሙላት፡- የፈጣሪ ያለህ! እንዴት ያለ ታሪክ ነው! እንዲህ ነው ታሪኩ የሚያልቀው? ሚጡስ- -እነሱ ሙግታቸውን እስኪጨርሱ ምንም ምግብ አልበላችም እኮ! ወይ ጉድ

እቴ ብርቱካን፡-እባክህን ተረጋጋ ፤ሙላት፡፡ ስሜትህን ተረድቼዋለሁ፡፡ የታሪኩ ማለቂያ ይሄ አይደለም፤ እስካሁን ያለውን ሂደት እንድንወያይበት ፈልጌ ነው፡፡ ውድ ወዳጆቼ፤ የለምለምንና ቤተሰቧን ታሪክ ሰምታችኋል፡፡ የለምለም ባለቤትና እናቱ ለህጻኗ ስጋ ይሰጣት አይሰጣት በሚለው ላይ ሲሟገቱ ነበር፡፡ እስቲ ስለሰማነው ለመነጋገርና ለመወያየት ጊዜ እንውሰድ፡፡

አስተባባሪ፤ ተሳታፊዎች በእነዚህን ሦስት ጥያቄዎች ዙሪያ እንዲወያዩ ያድርጉ፡፡

1. ለምለም (የሚጡ እናት)፣ አባቷ እና ሴት አያቷ የተነጋገሩበትን መንገድ በተመለከተ ምን ታስባላችሁ?

2. የአነጋገራቸው ሁኔታ ለማሻሻል ምን ማድረግ ይገባቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ?

3. ለእያንዳንዳቸው ምንስ ምክር ትለግሷቸዋላችሁ?

አስተባባሪ፤ እባክዎን ቴፑን ያጥፉና ተሳታፊዎች በእነዚህ ሦስት ጥያቄዎች ዙሪያ እንዲወያዩ ያድርጉ ስትጨርሱ እባክዎ ቴፑን መለሰው ይክፈቱት፡፡

SFX: : የደውል ድምጽ ይሰማል

ብርቱካን፡- እንኳን በደህና መጣችሁ! ሁላችሁም ስለለምለም፣ እታለምና ግዛው ሁኔታ እንዲሁም የእንቡጥ ህጻናቸውን ወፍራም ገንፎ አመጋገብ በተመለከተ ሃሳባቸውን ያቀረቡበትን አኳኋን የመወያየት እድል እንዳገኛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

እስቲ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባላት እንዴት እንደተነጋገሩ እንመልከት፡

ግዛው ትንሽ ግራ ተጋብቶ ነበር፤ ትንሽ ፈዘዝም ብሏል፡፡ እናቱን ማናደድ ስላልፈለገ ለእሳቸው ወግኖ ነበር የቆመው፡፡ የእንስሳትን ገጸባህሪ ወክሎ ስለመወያየት በተማርነው መሰረት፤ ግዛውን ከእንስሳት ገጸባህርይ አንጻር ካየነው፣ በአብዛኛው

Page 142: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

142

የአህያን ባሕርይ ነው ያንጸባረቀው፡፡ ቸልተኛና ዝምተኛ በመሆን፡፡ እናቱ ትክክል ይሁኑ አይሁኑ እርግጠኛ ባይሆንም የእሳቸውን ሃሳብ ተቀብሏል፡፡ ሚስቱ፤ የልጃቸው እንቁላልና ወፍራም ገንፎ እንዲሁም ሥጋ መመገብ ለአካሏና ለአዕምሮ እድገቷ ወሳኝ መሆኑን ብታስረዳውም አልሰማትም፡፡ እናቱ ህጻኗ እንቁላልና ሥጋ መብላት የለባትም ያሉትን ግን ለመቀበል እያቅማማ ነው፡፡

አያ ሙላት፡- እታለምስ (አያትየውን) ደግሞ እንመልከት፡፡ ለምለም እንቡጥ ህጻናትን የተፈጨ ስጋና እንቁላልን መመገብ ስላለው ጠቀሜታ ልታስረዳቸው ስትሞክር ከመበሳጨታቸውም በላይ የመናቅ ስሜት ተሰምቷቸዋል፡፡ እታለም ከእምነታቸው ንቅንቅ የማይሉ በመሆናቸው እሷ ያለችውን ስህተት ነው ብለው አምነዋል፡፡ እንደውም ለምለም በሳቸው ሃሳብ የማትስማማ ከሆነ፣ የልጃቸውን ቤት ለቀው ለመውጣት እስከማስፈራራት ደርሰዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ከልጃቸው እንዲሁም ከሚስቱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያበላሽባቸው ነበር፡፡ በባልና ሚስቱ መካከልም ውጥረት ሊፈጥር ይችል ነበር፡፡ እታለም ሲበዛ ጠብ ጫሪ ነበሩ፡ ሁኔታቸው እንደ አንበሳ ገጸ ባህሪ ነበር፡፡ እንደ አንበሳ ስንተውን ምን እንደሚከሰት ሁላችንም እናውቃለን፡፡ የማንንም ሃሳብ አንሰማም፤ ዝም ብለን እንጮሃለን!

እቴ ብርቱካን፡ ለምለም ደግሞ እስኪ እንመልከት፡፡ ክብሯን የጠበቀች፤ ትእግስተኛና መለኛ ነበረች፡፡ አማቷ ጠብ ጫሪ ሆነው ቢያስፈራሯትም እሷ ግን አክብራቸዋለች፡፡ ባለቤቷ ለእናቱ ወግኖ ቢቆምም እሷ ግን የነበረበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ተረድታ ታግሳዋለች፡፡ ሁሉንም የሚያስማማ የጋራ መፍትሄ በመፈለግም መለኛነቷን አስመስክራለች፡፡ ለምለም በእርግጥም ራሷን መያዝ ችላበታለች፡፡ እንደ /ማርና ውሃ/ጉሬዛ ነበር የሆነችው ማርና ውሃ ጣፋጭ ናቸው፤ በደንብ ይዋሃዳሉ፤ ከሚፈጥሩት ጥምረትም ብዙ መልካም ነገሮች ይወጣቸዋል፡፡

አያ ሙላት፡- ለምለም ተቻችሎ በጋራ ለመኖር ዋጋ ትሰጣለች፡፡ የአማቷ እምነት የተፈጠረበትን ሁኔታ ታውቃለች፤ ትረዳለች፡፡ አማቷ በራሳቸው መንገድ የቆሙና እምነታቸውን ባለፈ የህይወት ልምዳቸው ላይ የመሰረቱ አዛውንት ሴት ናቸው፡፡ ምንም እንኳን ለምለም ስለ እንቡጥ ህጻናት አመጋገብ ባላት እውቀት ቅንጣት ባትጠራጠርም እንዲሁም ለልጇ ባለ ሦስት ኮከብ ምግቦችን መመገቧም ትክክል እንደሆነ ብታውቅም አማቷን ልታፋጥጥ አልፈለገችም፡፡

ሃሳቧን ለማስረዳት በትህትና በትግስት እንዲሁም በአክብሮት መናገርን መርጣለች፡፡ ባለቤቷንም በተመለከተ የነበረበትን አጣብቂኝ ሁኔታ ተረድታለታለች፡፡ ለእናቱ ብሎ ሊቃወማት ሲወስን በንዴትና በቅናት ስሜት አልመለሰችለትም፡፡ ውሳኔው ስሜታዊና በአብዛኛው በህጻናት አመጋገብ ዙሪያ ባለው የእውቀት ማነስ ላይ የተመሰረተ እንደሆነ አውቃለች፡፡ ለዚህም ነው ሁሉንም የሚያግባባ መፍትሄ ለማቅረብ የመረጠችው፡፡

እቴ ብርቱካን፡-አንድ ነገር በእርግጠኝነት እናውቃለን፡፡ ሴት አማቶች የልጅ ልጆቻቸውን ይወዳሉ፤ጥሩ ጥሩውን ብቻ ነው የሚመኙላቸው፡፡ ሁሌም ከጎናችን ያስፈልጉናል፤ እውቀታቸውን እንሻለን፡፡ ከአማቶችና ከባሎች ብዙ ድጋፎችን ማግኘት የምንችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ እውቀታቸው ከወቅቱ ጋር የማይሄድ

Page 143: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

143

ከሆነ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኛ ወይም ሌላ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት እናቶች ቡድን በመጋበዝ፣ ከአማቶቻች ጋር እንዲወያዩ ማድረግ እንችላለን፡፡ ለምለም ያደረገችውም ይሄንኑ ነው፡፡

እንደ ለምለም መሆን የምትችሉበት አንዳንድ መንገዶች ምንድን ናቸው? የተማርነውን መረጃ ማካፈል እንችላለን - የመጀመሪያዎቹ 1000 ቀናት ቁሳቁሶችን ለሰዎች ማሳየት እና በአክብሮትና በትህትና ማነጋገር፡፡ እነሱም የመጀመሪዎቹ አንድ ሺህ ቀናት አማቶች ሲሆኑ እኛ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ አንድ ሺህ ቀናት እናቶች ነን፡፡ ሁላችንም እንቡጥ ህጻናቶቻችን ብሩህ አዕምሮ ያላቸው፣ ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉ እንሻለን፡፡ የተፈጨ ስጋ፣ ዓሳና አትክልት በመመገብ፣ በየቀኑ የዳበረ የምግብ ንጥረ ነገር ማግኘታቸውን ማረጋገጥ፣ የምንሻውን እውን ያደርግልናል፡፡

እቴ ብርቱካን፡-እሺ፡፡ ቀሪውን የድራማ ክፍል በመጪው ክፍለ ጊዜያችን እንቀጥለዋለን፡፡ እናንተም የእኔን ያህል በድራማው ቀጥሎ ምን እንደሚሆን ለማወቅ እንደጓጓችሁ አውቃለሁ፡፡

ማግኘትና የመግዛት

አያ ሙላት፡- አስተባባሪ ይሄንን ጨዋታ ለመጫወት ተሳታፊዎችን በአራት ቡድን ይከፋፍሉ፡፡ ለእያንዳንዱ ቡድን ‘’ገቢ ማግኘትና የመግዛት’’ የተሰየመውን ጨዋታ ማለትም የመጨዋወቻ ሰሌዳና 56 የገንዘብ ካርዶች ይስጧቸው፡፡ ጨዋታን ለመጫወት የቡድኑ አባላት በመጨዋወቻዉ ሰሌዳ ዙሪያ መቀመጥ ይችላሉ - መሬት ወይም ወንበሮች ላይ፡፡

በጨዋታው ሰሌዳ ዙሪያ ያሉት የተለያዩ የቤትና የግብርና ቁሳቆሶች እንዲሁም ኮከብ ምግቦች ከነዋጋቸው በዝርዝር ተቀመጠዋል፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች ቤተሰቦች የሚገዟቸው ናቸው፡፡ በሰሌዳው መሀከል ላይ ክብ ዙሪያ ውስጥ ገንዘብ የሚቀመጥበት ሲሆን እንዲሁም ቤተሰቦች ያመረቱትን እህል የሚሸጡበት የገበያ ማዕከልን ይወክላል፡፡

1. ጨዋታውን ለመጫወት በየቡድኑ የተካፋፈሉ ተሳታፊዎች ተራ በተራ ምርቶቻቸውን ገበያ በመውሰድ ለሽያጭ በማቅረብ የምርታቸውን የሽያጭ ዋጋ መጠን በገንዘብ መልክ ይወስዳሉ፡፡ ሸጠው ባገኙት ገንዘብ ተሳታፊዎች በሰሌዳው ዙሪያ ከሚገኙ የቤትና የግብርና ቁሳቁሶች መርጠው የሚፈልጉትን ይገዛሉ፡፡

2. የመጀመሪያው ተጫዋች ተራቸውን ከጨረሱ በኋላ የገንዘብ ካርዶችን ወደነበረበት በመመለስ ተራውን ለሚቀጥለው ተጫዋች ይለቃሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጫዋች ምርቶቻቸውን ሸጠው ባገኙት ገቢ የገንዘብ ካርድ በመውሰድ እንደፊቱ የሚፈልገትን ሰሌዳው ላይ የተደረደሩ ቁሳቁሶች መግዛት ይችላሉ፡፡ የቀሩት ተሳታፊዎች ጨዋታውን ይመለከታሉ፤ ተራቸውም ሲደርስ እንደበፊቱ ጨዋታውን ይቀጥላሉ፡፡

3. ሁሉም ተሳታፊዎች ተራ በተራ ከተጫወቱ በኋላ እያንዳንዱ የቡድን አባላት ተጫዋቾች ባገኙት ገንዘብ ምን እንደሸመቱበት በትኩረት ይወያዩበት እና

Page 144: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

144

የምርጫቸውን ምክንያት ይወያዩበታል፡፡

አስተባበሪ ተሳታፊዎች ምን አይነት ምግቦችን ለንግስት ንቦቻቸው እንዲሁም ለእምቡጥ ልጆቻቸው እንደገዙ እየተዘዋወሩ ይመልከቱ፡፡ በተጨማሪም የትኛዎቹን የቤት ቅሳቁሦች እንደገዙ ይመልከቱ፡፡

በዚህ አዝናኝ ጨዋታ ላይ የትኞቹ ቁሳቁሶችና ኮከብ ምግቦችን ቤተሰቦች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ውይይት ያድርጉ፡፡ ምርጫቸው አቅማቸውን ያገናዘበ መሆኑንና የትኞቹን ምርቶች ሸጠው ቅድሚያ ለኮከብ ምግቦች ግዢ እንዲያውሉ አሳስቧቸው፡፡

ማዘጋጀት፣ ሳይበላሽ ማቆየትና ማስቀመጥ

ማረፍ ማገዝና መብላት

እቴ ብርቱካን፡-ስለእንቡጥ ህጻናት ተጨማሪ ምግቦች አዘገጃጀት ተጣጣፊ በራሪ ወረቀትና የትንሽ እንቡጥ ህጻን ፖስተርን አሰራጩ

መወያየትና በጋራ መወሰን

እቴ ብርቱካን:ባልና ሚስቶች ያገኙትን መረጃና የተማሩትን ነገር በተመለከተ ለባለቤቶቻቸው ያካፍሏቸው፡፡ ሌሎች እንዴት በውሳኔ አሰጣጣችን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ መማር ይገባናል፡፡ ለምሳሌ፡- ለሚስት፤ ባለቤትሽ የእንቡጡ ህጻን የአመጋገብ ምርጫዎችሽን ይደግፋል ወይ? አማትሽ ትደግፍሻለች? አንዳንዴ በጣም የሚያስቡልን ሰዎች ተገቢውን ምክር ላይሰጡን ይችላሉ ወይም ደግሞ እንቡጥ ህጻናቶቻችን ጤናማና ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉ የሚያግዘንን ውሳኔ አይደግፉ ይሆናል፡፡. ባልና ሚስቶች በእነዚህ ክፍለጊዜያት የተማራችሁትን የመግባባት ክህሎቶች በመለማመድ እነዚህን ፈተናዎች እንዴት እንደምትወጡት በግልጽ መነጋገር ይኖርባችኋል፡፡ እናም እንደ ጉሬዛ ወይም ማርና ውሃ መግባባታችሁን ለማረጋገጥ ሞክሩ፡፡

ጠይቁና አግኙ

ያለፈውን ክፍለ ጊዜ መከለስ

ወደ ቤት የሚወስዱ ቁሳቁሶችና የቤት ሥራዎች

እቴ ብርቱካን፡-እድሜው ከ6-7 ወር የሆነ ህጻን ላለው ለእያንዳንዱ ተሳታፊ ወደቤት የሚወሰዱ የልምምድ ቁሶችን አንድ አንድ ያከፋፍሉ፡፡ እነዚህን ቁሳቁሶች እቤታቸው ወስደው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲወያዩበት ንገሯቸው፡፡ ለእንቡጥ ህጻናት ወፍራም ገንፎና የተፈጩ ምግቦችን ከብዙ ባለኮከብ ምግቦች ጋር ማዘጋጀትን ያስታውሳቸው ዘንድ ግድግዳቸው ላይም መስቀል አለባቸው፡፡

Page 145: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት

145

መዝጊያ

1. የእንቡጥ ወላጆች የእንቡጥ ስቲከር ቤታቸው ይውሰዱ፤ምን እንደሆኑም ለሌሎች ያስረዱ፤

2. “ተጨማሪ ምግቦች” የሚለውን መዝሙር ለህጻን ልጆቻችሁ ዘምሩላቸው፤ ለቤተሰባችሁም አስተምሩት፤

3. የትንሽ እንቡጥ ተጨማሪ አመጋገብ ፖስተሩን ቤታችሁ ውሰዱና ከቤተሰብ ጋር ተወያዩበት፤

4. ወፍራም ገንፎ ሠርታችሁ ለስላሳ ምግቦችን ለመፍጨት ሞክሩ፤እናም ህጻኑን በቀን ከ2-3 ጊዜ መግቡ (ከ6 ወር በኋላ ላለሆኑ ህጻናት)፤ጡት ማጥባቱንም ቀጥሉ

5. ህጻናትን ንጽህናው በተጠበቀ አካባቢ አስቀምጡ

6. ለትላልቅ ልጆች ስለ ህጻናት አይነ ምድር አወጋገድና ሌሎች የመታጠብ ልማዶች አስተምሩ

አያ ሙላት፡- እንዴ! ይሄ የምሰማው ምንድን ነው? የምናውቀው አይመስልም? ተጨማሪ ምግቦች መዝሙር ነው! ይሄን ግሩም ስብሰባ ለማጠናቀቅ እንዴት ያለ ግሩም መንገድ ነው! የአንድ ሺህ ቀናት የስድስተኛው ስብሰባችንን!እስቲ ተጨማሪ ምግቦች የሚለውን የተጨማሪ አመጋገብ መዝሙር እንደገና እንዘምረው!

SFX; ተጨማሪ ምግቦች መዝሙር

እቴ ብርቱካን፡-እንዴት ደስ የሚል ሸጋ መዝሙር ነው! አዎ፤ ሁሉም መዝሙሮችና አብረን ያሳለፍናቸው ስድስት ክፍለ ጊዜያት በእጅጉ አርክተውኛል፡፡ ቀጣዩን ክፍለ ጊዜ በጉጉት ነው የምጠብቀው፡፡

አያ ሙላት:- እሺ አስተባባሪ፤ ቀጣዩ ክፍለ ጊዜያችን መቼ እንደሆነ ለተሳታፊዎች ይንገሯቸው፡፡ ውድ ተሳታፊዎች እንደገና እስከምንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑ፡፡

እቴ ብርቱካን:-ደህና ሰንብቱ፡፡ በቀጣዩ ክፍለ ጊዜ በሰላም ያገናኘን፡፡

Page 146: Save the Children - gtn-learning.org all in one...ዘር፣ ችግኝ፣ እቡጥ እና አበባ በአንድ ጻን እድገት ይ በዩ አንድ ሺ ቀናት ውስጥ የታዩበት