hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p d÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p hß 5 ß0 4 1//6...

16
ነፃነት አራተኛ ዓመት ቁ.84 ቅዳሜ 6 ህዳር 5 2007 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን! ዋጋው 7 ብር Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

Upload: others

Post on 11-Aug-2020

15 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

ነፃነትአራተኛ ዓመት ቁ.84ቅዳሜ 6 ህዳር 5 2007 የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን! ዋጋው 7 ብር

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

Page 2: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 842

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

በቀለ ኢተፋ (ለዚህ ጽኁፍ ሲባል ስሙ የተቀየረ) ስላሳለፋቸው የስር ቤት ቆይታዎች እና በመንግስት ሀይሎች ስለደረሰበት ስቃይ ሲያስብ አሁንም ድረስ አይኑን ጨፍኖ ራሱን ይነቀንቃል፤ “ይህ ሁሉ መከራ የደረሰብኝ ኦሮሞ በመሆኔ ብቻ ነው” ሲልም ይናገራል፡

፡ ባሳለፍነው ወር መጨረሻ የወጣው የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ውስጥ የተገለጹት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከዚህ ቢከፉ እንጂ አያንሱም ሲል በጠባሳ የተሸፈነ ጀርባና በድብደባ ብዛት መራመድ ያቃተውን ግራ እግሩን ዋቢ በማድረግ ያሳያል፡፡

ከኢትዮጵያ መንግስት ጋራ በተደጋጋሚ የሰብአዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ እሰጥ አገባ ውስጥ የሚገባው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባሳለፍነው ወር ባወጣው ሪፖርት ከ2003

እስከ 2004 ዓ.ም ብቻ ቁጥራቸው ከአምስት ሺህ (5,000) የሚልቁ የብሔሩ ተወላጆችን ገዥው መንግስት እንዳሰረና አሁንም በክልሉ ከፍተኛ ፍርሀት እንዲሰፍን እየሰራ መሆኑን በሪፖርቱ ያስረዳል፡፡ ይህ ሁነትም ባለፉት አመታት በተለያዩ እስር ቤቶች ላሳለፈው በቀለ ‹‹እውን ይህች ሀገር! ሀገሬ ናት?›› ብሎ እንዲጠይቅ አስገድዶታል፡፡

የኦሮሞ ፖለቲካ ዳገት

በ1940ዎቹ የኢኮኖሚ፣ የታሪክ እና ባህል እኩልነት ጥያቄዎችን አንግቦ የጀመረው የኦሮሞ ልጆች ጥያቄ በተበታተነ መልክ ቢጀምርም ይህንን ማህበራዊ እንቅስቃሴ ያጤኑት የብሔሩ ልሂቃን የሜጫና ቱለማ ራስ አገዝ ማህበርን በማቋቋም በተበታተነ መልክ የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ድርጅታዊ መልክ ለመስጠት ሞከሩ፡፡ ነገር ግን ሜጫና ቱለማ በባህል እድገት እና በማህበራዊ አገልግሎት ላይ፣ የተገደበ እንቅስቃሴ ስለሚያደርግ ለኦሮሞ

ሊሂቃን እንደ መገናኛ ስፍራ ጠቀማቸው እንጂ ወደ ፖለቲካዊ ስልጣን መዳረሻ መልህቅ ሊሆን አልቻለም፡፡ይኸው ማህበር በንጉሱ ላይ የመግደል ሙከራ አድርጎ በንጉሳዊው አስተዳደር ትእዛዝ ማህበሩ እንዲዘጋና የማህበሩ የጡት አባት ጀነራል ታደሰ ብሩም የቁም እስራኛ እንዲሆኑ ተወሰነ፡፡ የኦሮሞ ልጆችም ወደ ሁለተኛው የትግል ስልት ፊታቸውን አዞሩ፡፡

በሜጫና ቱለማ ማህበር ውስጥ

ይንቀሳቀሱ የነበሩ የከፍተኛ ትምህርት

ተቋም ተማሪዎች ጥያቄአቸውን ከፍ ባለ

ደረጃ በማንሳት “የኦሮሞ ጥያቄ የሚፈታው

ነፃ የኦሮሚያ ሪፐብሊክ በመመስረት ነው”

በሚል የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን መመስርት

ይፋአደረጉ፡፡ይህም ሁናቴ በወቅቱ “የብሄሮች

እኩልነትና ጭቆና የመደብ ልዩነት ሲጠፋ

አብሮ ይጠፋል” ከሚሉት ኃይሎች ጋራ

ከጅምሩ ከድርጅቱ ጋር በተቃራኒው

እንዲቆሙ ምክንያት ሆናቸው፡፡ነገር ግን

ይህ አይነት ሁናቴ ለድርጅቱ ውጫዊ

ተቀባይነት መሰናክል ቢሆንም የገዥዎች

ጭቆና ያስመረረው አብዛኛው ኦሮሞ

ድርጅቱን እንዳይቀላቀል አላገደውም፡፡

በዚህ መልክ የቀጠለው የድርጅቱ እንቅስቃሴ

እስከ ሽግግር መንግስት ድረስ ቀጠለ፡፡

በዚህም ወቅት ነበር ድርጅቱ በሰፊው

ኦሮሞዎች ልብ ውስጥ ሊገባ የቻለው፡፡

“Har’a waajiran oolee dhufa” (ጉለሌ

ባለው የኦነግ ጽ/ቤት ውዬ መጣው ማለት)

እንደ ክብር መታየት ጀመረ፡፡ ይህ አይነት

እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ያልፈለገው

ገዥው መንግስት የኦነግን ሰራዊት ካምፕ

በማስገባትና ትጥቅ በማስፋታት ከሽግግር

መንግስቱ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ይህ ድርጊትም

ለኦነግ ሰዎች የመጨረሻውን አማራጭ ብቻ

እንዲመለከቱ አስገደዳቸው፤ “ትጥቅ ትግል”

በመጋቢት 17 ቀን 1982 አዴት

ላይ በምርኮኛ ወታደሮች የተቋቋመው

ኦህዴድ በክልሉ ያለውን የብሔርተኝነት

ጥያቄ ለመመለስ እንዳልቻለ፣ የበታችነት

ስሜት ተሸካሚ መሆኑ ድርጅቱ ከጅምሩ

የራሳቸው ፖለቲካዊ አጀንዳ በሌላቸው ሰዎች

መመስረቱ እና የተአማኒነት ቅቡልነት (legit-

imacy) ችግር እንዳለበት አንድ ማሳያ ነው፡፡

ድርጅቱ በክልሉ ለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት

ጥሰቶች ጉዳይ አስፈፃሚ መሆኑ በክልሉ

ከትሮይ ፈረስነት የዘለለ ሚና እንዳይጫወት

አድርጎታል፡፡ ኦሕዴድ በክልሉ የሚያነሳቸው

ጥያቄዎች በቅድምና በኦነግ የተነሱና

ለተፈፃሚነቱ የተንቀሳቀሰባቸው ናቸው፡፡ ይህ

ሁናቴም ኦህዴድ ጥያቄዎቹን ለማስፈጸም

ከመንቀሳቀስ ይልቅ ኦነግን ከኦሮሚያ

ማስወጣትን የመጀመርያ ስራው አደረገው፡፡

የኦሮሞ ልሂቃን እዳ

ÇÓT© }cT

ለአምነስቲ

ኢንተርናሽናል

ቃላቸውን ከሰጡት

አብዛኛዎቹ የኦሮሞ

ተወላጆች የሰውነት

አካላቸው እየተቆራረጠ

ጭምር መከራ

እንደደረሰባቸውና

በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ

ማለፋቸውን ገልጸዋል፡

፡ሁነቱንም ያጠናቀሩት

የተቋሙ ተወካይ

ክሌይር ቤስተንም

“እጅግ ዘግናኝ” ሲሉ

ገልጸዋል፡፡

ምርኮኛው ኦህዴድ “

ወደ ገፅ 13 ይዞራል

Page 3: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

3ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

በእውቀቱ ስዩም በ “እንቅልፍ እና እድሜ” መፅሀፉ የሳለው የዋና ገጸ-ባህሪዋ አንድሮሜዳ አፍቃሪ አለ፡፡ እምባ የማይወጣው ደረቅ፤ ለእናቱ ሞት እንኳ የማይከፈት የእምባ ከረጢት ያለው፡፡ በእውነቱ ደረቅ ነበር፡፡ እድሜ ፒተር ቤንሰን ለመራችው የ “Amnesty International” ጥናት ቢያነብ ያለወትሮው የእንባ ጎርፍ ያስነሳ ነበር፡፡ “Because I Am Oromo” የሀገር ልጅ በሀገሩ ልጅ ላይ ቀርቶ በየትኛውም ስጋ ለባሽ ላይ ማድረጉ ያጠራጥራል፡፡ እምባ አልባው የበእውቀቱ ገፀ-ባህሪ ይህንን ባየ ጊዜ በህይወቱ ለሁለተኛ ጊዜ (አንዱ አንድሮሜዳ ቀብር ላይ ነበር) ፊቱን በመዳፎቹ መሀል ቀብሮ በተንሰቀሰቀ ነበር፤ እንባውን በዘራ ነበር፤ ሰው ኦሮሞ በመሆኑ ብቻ የደረሰበትን መጠን አልባ ጭካኔ ቢያይ፣ ደረቁ ሰው፣ በእውባው ብዛት ፊቱ ቦይ ያበጅ ነበር፡፡

እኔ እንደዚህ ገጸ ባህሪ የእምባ ድርቅ

የመታኝ ባልሆንም፣ ሆደባሻ ግን አይደለሁም፤ ሆደ ባሻ የደረገኝ የአምንስቲ ሪፖርት ነው፤ በርግጥ በተግባር የማውቀው የወገኔ ሰቆቃ፡፡በዚህ ወግ የአምንስቲ ኢንተርናሽል ሪፖርት ለመዳሰስ አልፈለግሁም፡፡ ሳምንት እና በቀጣዮቹ ጊዜያት መስመር በመስመር እየተከታተልን እንፅፋለን፡፡

ቻይና ነብር ያደነ ሰው በሞት የሚቀጣባት ሀገር ናት፤ የህወሀቷ ኢትዮጵያ ግን ኦሮሞ አዳኞችን ትሸልማለች፡፡ በነቀሉት ጥፍር፣ በሰበሩት እግር፣ ባፈረጡት ዓይን፣ ከጥቅም ውጪ ባደረጉት ጭንቅላት ልክ እድገት የሚያገኙ ህወሓቶችና ተባባሪዎቻቸው ከፍ ወዳለ ስፍራ የሚዛወሩባት ሀገር፡፡

ኦሮሞ ላይ ጥርጣሬ ማሳደር በሁለት ምክንያት ይመስላል፤ አንድም በ16ኛው መ/ክ/ዘ በነበረው የመስፋፋት ሂደት በጦረኝነት መሳሉ እና ዛሬም ድረስ በአፈ-ታሪክ መነገሩ፤ እንዲሁም የህዝቡ ቁጥር የበላይነት የእንዋጣለን ስጋት ማሳደሩ፡፡ በንጉሱ ዘመን “ኦሮሞሰግ” (OromoPhobic) የሆኑ ባለስልጣናት ነበሩ፡፡ ኦሮሞጠል የነበሩ ግለሰቦችም ነበሩ፡፡ ለኦሮሞ ብሄርተኝነትም እውቅና ለመስጠትአልፈቀዱም፡፡ ደርግም ቢሆን እውቅና ለመስጠት እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ የቆየ ከመሆኑም በላይ የኦሮሞ ብሄርተኝነት ማራመድ “ኋላ ቀርነት፣ ጠባብነት፣ አድሃሪናነት እና የሀገር አደጋ” አድርጎ ነበር የሚቆጥረው፡፡“ኢንስትሩሜንታሊስቱ”ህወሀትበበኩሉ ለኦሮሞ ብሄርተኝነት የሰጠውን እውቅና መጠቀሚያ ነው ያደረገው፡፡

እኛ ሰዎች ነን፤ የማስታወስ ጸጋ አለን፤ በዚህ ችሎታችን አዎንታዊነት፣ ዓለም ወደ ስልጣኔ ገስግሳለች፤ በአሉታዊ

ትውስታችን ደግሞ በአለም ላይ ጥፋቶችን አ ስመ ዝ ግ በ ና ል ፡ ፡ ህ ወ ሀ ት ኦ ሮሞ ላ ይ የሚያደርሰው ጥቃት ትውስታ ሲሆን፣ በጥፋት ነው ራሱን የሚገልጸው፡፡ በቂም በበቀል፡፡ ሰው እንደከብት ከባለፈው መነጠል አይቻልም፤ከብት በሚልዮን አመታት ለልጁ ያስተላለፈውትውስታየለም፤ ስለዚህ ላምቱም “እምቧ” ጥጃዋም “እምቧ” ከማለት በዘለለ ወደ ሌላቋንቋ፣ሳር ከመጋጥ ውጪ ምግብ ወደማብሰል አልተሸጋገሩም፡፡ሰው ግን እንደማሽን ባለፈውን ደምስሰህ ከዚህ ወደዚያ ጀምር አይሉትም፡፡

ሁሉም ባህል አለው፤ ትግሬው፣ አማራው፣ ጉራጌው…፡፡ ኦሮሞውም እንዲሁ፡፡ ስለዚህ ማንነቱን ማንፀባረቁ ወንጀል ሊሆን አይችልም፤ ወንጀሉ ራሱን፣ ማንነቱ የተመሰረተበትን እሴት እንዳይገልፅ መከልከሉ ነው፡፡ ኦሮሞ ማንነቱን ማንፀባረቁ፣ ለማንነቱ ቀናኢ መሆኑ ሰውነት ነው፤ ታሪካዊነት ነው፤ ታሪክ የሰው ሰውነት ነው፡፡ የማስታወስ ተፈጥሯዊ ፀጋ ነው፡፡ በማንም ዘንድ አለ፤ ለዚህ ነው ጀምስ ቦልድውድ “I’m human, thus nothing of human is alien to me” ማለቱን የምወድለት፡፡ “ሰው ነኝ! የሰው የሆነ ሁሉ እንግዳ አይሆንብኝም” እንደማለት፡፡

ታዋቂዋ አፍሪካ-አሜሪካዊት የስነ-ሰብዕ ተመራማሪ ቶኒ ሞርሰን “ትውስታ (Memory) ልክ እንደውሃ ነው፤ ሁል ጊዜ ወደምንጩ ለመመለስ ይጥራል” ያለችውን እውነታ ያስታውሷል፡፡ ወደ ማንነት ዞሮ መመልከት ሰውነት ነበር፤ በህወሀት ዘንድ ወንጀል ሆነ እንጂ፡፡(“ለመሆኑ ኦህዴድ የሚገርፈውን እና የሚገድለውን ለምን በህወሀት ስም ትፅፋለህ?” የሚል እንደማይኖር አውቃለሁ፤ ቢኖር እንኳ ነገሩ “ዋርዲያ ልገልበጥ?” የሚለውን ያስታውሷል፡፡ ካላሰለቸሁ ነገሩ እንዲህ ነው፤ ኩማ ደመቅሳ የደርግ ወታደር ሆኖ ወደ ኤርትራ ይዘምታል፤ እዚያም በሻዕብያ ተማርኮ የተሀድሶ እና የእስር ቤት መልክ ያለው ቦታ ይገባል፤ ታዲያ ሌሊት አስመራ ድርድር የተባለው አተኛኘት ስለነበር ከአንዱ ጎን ወደ ሌላ መቀየር ከባድ ነበር፤ የኩማ ፍርሀት ግን መጠን አልባ ነበር፤ ጎኑን መቀየር ፈልጎ “ዋርድያ ልገልበጥ?” ብሎ ይጠይቃል፤ ወርዲያውም “ተገልበጥ” ይለዋል፤ የኦህዴድ አመራር ይህ ነው፡፡ ለሁሉ ነገር የማራኪዎቹን ትዕዛዝ የሚቀበል፡፡በነገራችን ላይ ይህንን የነገረኝ አብሮት የተማረከና የታሰረ ሰው ነው፡፡)

በልጅነቴ አያቴ መስቀሊ ዳdhi ጥጆች መልሼ እንድመጣ ስታግባባኝ እንዲሁ በደረቁ አይደለም፤

“Saree tiyya! Jabbiloota san-neen ilaltee yoo dhufte waanan qopheessee si eegu hin beektu.” ትለኛለች፡፡

እኔ በበኩሌ “Maal naaf qopheesi-ta akkoo?” እላታለሁ፡፡

እርሷም በተራዋ “Waajabbilo” ትለኛለች፡፡

በቀላል አማርኛ “የኔ ቡችላ! ጥጆቹን አይተህ ብትመጣ ምን እንደማዘጋጅልህ አታውቅም” ትላለች፡፡

እኔም “አያቴ ባክሽን ምን ይሆን” እላታለሁ እጅግ ጓጉቼ፡፡

በ ተ ራ ዋ “ ዋ ጀ ብሎ ” ት ለ ኛ ለ ች ፡ ፡ እንግዲህ ሁሉ ነገር ያለው “ዋጀብሎ”

የሚለው ቃል ላይ ነው፡፡ “ዋጀብሎ” ቀጥታ ትርጉሙን ባላውቅም ለልጅ (እንደጥጃ ልጅ ለሆነ) የሚዘጋጅ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ነገር

ግን የማይነገር ነው፡፡ ያለመነገሩ በእንግሊዘኛው “Surprise” እንደሚባለው መሆኑ ነው፡፡ ታዲያ ዛሬ ማንም ሰው “ዋጀብሎ” የሚል ድምፅ ካሰማ ሰውነቴ ከፈቃዴ ውጪ የሆነ ሆርሞን ያመነጫል፡፡ሰውነቴ ሁሉ አፍንጫ እና ምላስ ይሆንብኛል፤ የማላውቀው ስሜት ይወረኛል፤ ምን ይሆን እላለሁ- ከ “ቂጣ መርቃ” ፣“ጭብጦ”፣ “እረድባ”… አማርጣለሁ፡፡ይሄን ስሜት መካድ እንደምን ይቻላል? ይህ እኔ ሳልፈቅድ ከነርቭ፣ ከሆርሞን እና ስነ-አዕምሮዬ ጋር የተጋመደ ሆኗል፡፡

ህወሀት እንዲህ አይነቱን ሰዋዊ መግቦት ነው አቁሙ የሚለው፤ የማይቻለውን፡፡እንዲህ አይነቱ የጋራ ተሰሞታዊ ጥርቅም ነው ወደ ብሄራዊ ማንነት የሚያድገው፡፡ብሄርተኝነት የሚለውን ስሜት ከሚሰጡ አንጓዎች አንዱ ይህ ነው፡፡ “ትውስታ (Memory) ልክ እንደውሃ ነው፤ ሁል ጊዜ ወደምንጩ ለመመለስ ይጥራል”

ዘውጌነትን በተመለከተ ከተቀመጡ ሶስት ንድፈ ሀሳቦች ሁለቱ (ፕሪሞርዲያል እና እንስትሩምንታል) ለዚህ ጭብጣችን ጠቃሚ ናቸው፡፡ ኤስማን ኤም. ጄ. የተባለው ተመራማሪ እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም “Ethnic Politics” በተባለ ጥናቱ ፕሪሞርዲያሊስቶቹ “ዘውጌነት የጋራ ማንነት ነው” ብለው እንደሚያምኑ ገልፆ “በታሪካዊ ሂደት ውስጥ ስር የሰደደ በመሆኑ እንደተፈጥሯዊ የሰው ለሰው ግንኙነት መያዝ አለበት” እንደሚሉም አክሎ ገልጧል፡፡እንስትሩመንታሊስቶቹ በበኩላቸው “ዘውጌነት በታሪካዊ እድገት ውስጥ የዘለቀ አይደለም፤ ይልቅ በቀላሉ የሚለመድና የሚቀየር ሀቅ ነው” እንደሚሉ አብራርቷል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም ድረስ ኦሮሞሰግነት (Oromophobia) አለ፡፡ የህወሀትም ችግር ይሀው ነው፡፡ በህወሀት መንደር ያለው የኦሮሞ ጥላቻ በዋናነት የኦሮሞ ብሄርተኝነት ስልጣን ወደመያዝ ሊያድግ ይችላል ከሚል ነው፡፡ ይህን ጭብጥ በተመለከተ በቀጣዩ እትም ሰፋ አድርገን እናየዋለን፡፡ በሌላው ዘንድ ያለው ደግሞ የተለመደው የበታችነቱ እንደምን አይቀጥልም የሚል ነው፡፡ ተስፋዬ ገብረአብ በቅርቡ በኦሮሞ አመታዊ ጥናት (OSA) ላይ ተጋብዞ ከተመለሰ በኋላ በነዚህኞቹ የሚታየውን ኦሮሞሰግነት በሚከተለው አንቀፅ ነበር የገለጸው፡-

ርግጥ ነው “ኦሮሞ” የሚለው ቃል ሲነሳ የሚረበሹ ወገኖች አሉ። ኦሮሞዎች “ኦሮሞ” የሚለውን ቃል እንዳያነሱ የማሸማቀቅ ተፅእኖ ለማድረግ አሁንም ድረስ ይሞከራል። በመኪናው ውስጥ የኦሮምኛ ዘፈን ከፍቶ የሚሄድ ሰው ካጋጠማቸው፣ “ይሄ ዘረኛ!” ይሉታል። ታክሲ ውስጥ ኦሮምኛ የሚናገር ሰው ሲሰሙ ተገላምጠው ያዩታል። ከደብተሮቻቸው በወረሱት አሸማቃቂና አስፀያፊ ስድብ ኦሮሞ ኦሮሞነቱን እንዲሸሽ ለረጅም ዘመናት ጥረት አድርገው ሳይሳካላቸው ቀረ። በርግጥ እነዚህ ሰዎች አማሮች አይደሉም። “ኢትዮ- አማሮች” ተብለው ይታወቃሉ። በኢትዮጵያዊነት እና በአንድነት ስም ለአንድ ወገን መብት መከበር የሚታገሉ ናቸው።

እውነት ነፃ አይደለም፤ ለነፃነትም

ዋጋ አለው፤ በአለም ታሪክ ብሩኖ ማርስ በሰም የተነከረ ቀሚስ ለብሶ ተቃጥሏል፤ ሶቅራጠስ ኦምሌት ጠጥቷል፤ ግብፃዊቷ ፈላስፋ በድንጋይ ተወግራለች፡፡ ማሞ መዘምር እና ታደሰ ብሩ አንገታቸውን ለገመድ ሰጥተዋል፤ ለኦሮሞ እውነት፡፡

እስር ቤቱም ለኦሮሞ አዲስ አይደለም፤ የመፅሀፍ ቅዱሱ ሰው (ወደ አፋን ኦሮሞ የተረጎመው) ኦኔስሞስ ነሲብ (አባ ገመቺስ) በዚያ ነበር፤ ቄስ ጉዲና ቱምሳ እዚያ ነበር፡፡ ዛሬ የተለየው በዚያ የሚገጥመው ዘግናኝ ኢሰብአዊነት ነው፤ የእስር ቤቶቹ ቋንቋ በቅርቡ ቀን የወጣለት “ኦሮምኛ” መሆኑ ነው፡፡ ከስየ አብረሃ ጀምሮ እስከታሰሩት ሰዎች መስክረዋል፤ ነጋሶ ጊዳዳ (ፒኤች.ዲ) ከፕሬዚዴንትነቱ ስልጣን ሲወርድ ሰላሳ አምስት ሺህ ኦሮሞ እስር ቤት እንደነበሩ መስክሯል፡፡ እኔም ስንት አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ … ጓደኞች ከጎኔ እንዳጣሁ ሳልቆጥር የኦሮሞ እንደሚከፋ አውቃለሁ፡፡

ስደቱም ለኦሮሞ አዲስ አልነበረም፤

የአፋን ኦሮሞ አባት ልንለው የምንችለው ሼክ በክሪ ሳጳሎ ህይወቱ ያለፈው ሶማሊያ ነው፡፡

ኦሮሞው ግን ማን ነው? ኢብሳ

ጉተማ በኮሌጅ ቀን ግጥሙ “ኢትዮጵያዊው ማን ነው?” ብሎ ነበር፡፡ ኦሮሞው ማን ነው? ብሎ መጠየቁም አይከፋም፡፡ ኦሮሞነትን በደም የሚቆጥር ካለ ለኔ ሞኝ ነው፡፡ ማንነት መንፈሳዊ መገለጫነቱ ነው የሚበዛው፤ በዚያ ባህል መሰራት ነው፡፡ ኦሮሞነት ከመወለድ ውጪ የሚገኝባቸውን “ሞጋሳ”፣ “ጉድፈቻ”፣ “ሀመቺሳ”፣ እና “ለለብሳ” የመሳሰሉ መንገዶች ስንቶቹን ወደ ኦሮሞነት አምጥቷቸዋል፡፡(ሀርበርት ሌዊስ እንደዚህ አይነቶቹ ሰላማዊ መጠቅለሎች የተሳኩት ከኦሮሞ የባህል አድማሳዊነት፣ የእኩልነት መርህ፣ እና ሙሉ በሙሉ የመቀበል ችሎታ የተነሳ ነው ይላል፡፡ ፕ/ር መኩሪያ ቡልቻ በበኩሉ “The Survival and Reconstruction of Oromo National Identity” ሲል በሰራው ትናታዊ ወረቀት “today it is impossible to differentiate between descendants of the once “proper” and assimilated Oromo groups.” (ዛሬ ላይ ሆነን የአንድን ኦሮሞ ሀረግ “ከትክክለኛ” ግንዱ ነው አሊያም ኦሮሞነትን ተቀብሎ [አሲምላንዶ ሆኖ] ነው በማለት መለየት አይቻልም” ይላል፡፡)

ከታላላቆቹ አባ ገዳዎች እንዳልመጡ፣ ከእልሀኛው ገመቹ ቀመርቲ፣ ከፈረሰኛው ኦርዶፋ ጨንገሬ እንዳልተዛመዱ ሁሉ፣ የአብቹን የመቶ ሰው ግምትነት ያልሰሙ ይመስል ምነው በማዕከላዊ ተሸበቡ?

ሳምንት ብሄርተኝነት የመንግስት ስልጣን ከመቆጣጠር አንጻር ያለውን ውል እና የህወሀት ግፎችን እናያለን፡፡

ሰለሞን ስዩም

“ኦሮሞ ስለሆንኩ” እና “ዋጀብሎ”ች

እስር ቤቱም ለኦሮሞ

አዲስ አይደለም፤ የመፅሀፍ

ቅዱሱ ሰው (ወደ አፋን ኦሮሞ

የተረጎመው) ኦኔስሞስ ነሲብ

(አባ ገመቺስ) በዚያ ነበር፤ ቄስ

ጉዲና ቱምሳ እዚያ ነበር፡፡ ዛሬ

የተለየው በዚያ የሚገጥመው

ዘግናኝ ኢሰብአዊነት ነው፤

የእስር ቤቶቹ ቋንቋ በቅርቡ ቀን

የወጣለት “ኦሮምኛ” መሆኑ ነው፡፡

Page 4: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

ርዕሰ አንቀፅፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ሐምሌ 2003 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡ፍኖተ ነፃነት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ስር የሚታተም በፖለቲካዊ፣በማህበራዊ፣ወቅታዊ ጉዳዮችና በመዝናኛ ላይየሚያተኩር ጋዜጣ ነዉ፡፡

ጋዜጣችን ሚዛናዊና ነፃ ጋዜጣ ሆኖ ማገልገል መርሁ ነዉ፡፡ ማንኛዉም ሀሳብና አመለካከት የሚስተናገድበትና የሚንሸራሸርበት እንዲሆን እንሻለን፡፡ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን አለዉ የሚባለዉኢህአዴግም በዚህ ሚዲያ አቋሙንናፖሊሲዉን ለማግለፅ ቢፈልግ መድረኩ ክፍት ነዉ፡፡

ዋና አዘጋጅ፡-ነብዩ ኃይሉአድራሻ፡-ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10የቤት ቁ.320ስልክ ሞባይል፡- 0911124769

አምደኞች፡-ዳንኤል ተፈራመምህር አበበ አካሉአስራት አብርሃምግርማ ሰይፉበቀለ ጎሹመምህር ደረጀ መላኩዳግማዊ ተሰማሪፖርተር እዩኤል ፍስሃ ዳምጠው

ህትመት ክትትል፡-ወንድወሰን ክንፈ

አከፋፋይ፡-ነብዩ ሞገስአሳታሚዉ፡-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)አድራሻ፡-አራዳ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁ. አዲስአታሚ፡- አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)

የዝግጅት ክፍሉ ስልክ፡-01 11249659ፖ.ሳ. ቁ. 4222ኢሜይል [email protected]@gmail.comandinet@ andinet.orgፋክስ ቁጥር ፡-+251-111226288

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 844 ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ዲዛይን እና ሌይአውት አብነት ረጋሳ 0913366064

ሰዎች በሀገራቸው የባለቤትነት ልዩ መብት

ይኖራቸዋል፤ ይህ መብት እንደ ተፈጥሯዊ

መብትም ነው የሚወሰደው፡፡ ይኸውም በሰብዓዊ፣

ዲሞክራሲያዊ (የመምረጥ፣ የመመረጥ

ሀሳባቸውን የማንፀባረቅ…) እና የመሳሰሉት

መብቶች ይገለጣል፡፡ እነዚህን መብቶች በጥንቃቄ

በማስከበርና በመከላከል ለዜጎቻቸው የምድር

ገነትነት ያክል የተመቹ ሀገራት ተፈጥረዋል፡፡

የዓለማችን የስልጣኔ መለኪያም ዜጎች ባላቸው

ነፃነት ልክ መመዘን ከጀመረ ከርሟል፡፡ ቀደም

ሲል በዚህ ረገድ የሚታሙ የአፍሪካ ሀገራት

እንኳ ወደዚህ መስመር ከገቡ ውለው አድረዋል፡፡

በነዚህ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎችም መብቶቻቸውን

በእጅጉ በማወቃቸው መንግስት የሚመሰርቱት

በነፃ ፍቃዳቸው ከመሆኑም በላይ በሀገራቸው

የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡ በህዝብ

ነፃ ፈቃድ የሚመረጡ መንግስታትም ከዚህ ሀሳብ

በታች ሆነው በአገልጋይነት ስሜት ይንቀሳቀሳሉ፡፡

አስገራሚው ቁምነገር ግን ከአፍሪካም ሆነ

ከምዕራብ አውሮፓ ውጪ ካሉ ሀገራት ይልቅ

የኢትዮጵያ ልጆች የመብት ጥያቄ ረዥም እድሜ

አስቆጥሯል፡፡ በኢትዮጵያ ለነፃነት የተከፈለው

ዋጋ ከፍ ማለቱ ምጸት የሚሆነው ትግሉ

በሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራት ከውጪ ከመጡ

ወራሪዎች ሳይሆን ከሀገራቸው ልጆች ጋር

መሆኑ ነው፡፡ ጭካኔውም በሀገራቸው ልጆች

መፈፀሙ ሁናቴውን እጅግ አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡

ከ1950ዎቹ ጀምሮ ተጠናክሮ የመጣው የመብት

ጥያቄ ተንፏቆ ተንፏቆ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ

ደግሞ መብት መጠየቅ ነውር ነው እንዳይባል

በወረቅት ላይ ተደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ

አገዛዝ በበኩሉ በአንድ በኩል ዴሞክራሲያዊ

መንግስታት የሚገዙበትን መርሆች በተለያዩ

አዋጆች ደንግጓል፡፡ ነገር ግን ይህ መንገድ

ህዝብን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት እንደሚያደርግ

የተረዳው ህወሀት/ኢህአዴግ በመጀመሪያ ወደ

ስልታዊ አምባገነንነት ነበር የዞረው፡፡ ቀጥሎ

ህገመንግስቱን እንዲሁም በወረቀት ላይ

የተደነገጉ ሌሎች ህጎችን የሚፃረሩ ህጎች ወደ

ማውጣት ነው የዞረው፡፡ የፀረ ሽብር ሕግ፣

የሚዲያና የመረጃ ነፃነት ሕግ፣ የመንግሥታዊ

ያልሆኑ ድርጅቶች ሕግ፣ የሲቪል ማህበራት

ሕግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ…ወ.ዘ.ተ

በሌላ በኩል ዜጎች እነዚህን ህጋዊ ሰብዓዊና

ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለመተግበር ሲሞክሩ

ከፍተኛ የሆነ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡

መደብደብ፣ መታፈን፣ መሰደድ እና መገደል

በኢትዮጵያ የለት ተለት ሁነት ሆኗል፡፡ ዛሬ

ኢትዮጵያ የዜጎቿ እስር ቤት ናት፡፡ ሰዎች

በያዙት አቋም ብቻ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት

ጥሰጦች ወደሚፈፀሙባቸው እስር ቤቶች

ይጋዛሉ፡፡ አንዷለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና

ሌሊሳ፣ ናትናኤል መኮንን የመከራ ገፈት

የሚጋቱት ባላቸው የፖለቲካ አቋም ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ደግሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር

የነበሩት ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ

እንዲሁም በሰሜን ጎንደር ምዕራብ አርማጭሆ

የአንድነት ፓርቲ አመራሮች አንጋው ተገኝ፣

አባይ ዘውዱ፣ እንግዳው ዋኘው፤ ከመተማ አቶ

በላይ ሲሳይ፣ አለባቸው ማሞፎገራ አቶ አለበል

ዘለቀ፣ ምዕራብ ጎጃም ደጋ ዳሞት ወረዳ አቶ

ጥላሁን አበበ ታስረው ወደ አሰቃቂው ማእከላዊ

ተወስደዋል፡፡በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ጋዜጠኛ

መሆን እጅጉን አደገኛ ስራ ሆኗል፡፡ “በፃፉት

ፅሁፍ አልከስም” ሲል የቆየው የህወሀት/

ኢህአዴግ መንግስት በሽብርተኝነት ከሶ ወደ እስር

ቤት ማጋዙ ሲበዛበት አሁን ደግሞ ጋዜጠኞችን

በግልጽ በፃፉት ፅሁፍ መክሰስ ጀምሯል፡

፡ ተመስገን ደሳለኝና ኤልያስ ገብሩ የቅርብ

ጊዜ አብነት ናቸው፡፡ ሰለሞን ከበደ፣ ዩሱፍ

ጌታቸው፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ…

ከዚሁ የመንግስት አቋም የተነሳ ነው እስር

ቤት ቤታቸው የሆነው፡፡ የመኢአድ፣ የሰማያዊ፣

ኦፌኮ… አባላት በእስር ቤት ቤታቸው ሆኗል፡፡

ህወሓት/ኢህአዴግ የዘር ማጥራት ስራም

እየከወነ ነው፡፡ አማሮችን ከተለያዩ የሀገሪቱ

አከባቢዎች ማፈናቀል ህጋዊ ስራው መስሏል፡

፡ “Because I am Oromo” በሚል በአምኒስቲ

ኢንተርናሽናል የወጣው ሪፖርት ህወሀት/

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ልጆች ኦሮሞ በመሆናቸው

ብቻ የሚሰቃዩባት ሀገር አድርጓታል፡፡

ህውሓት/ኢህአዴግ በመብታችን እንዲጫወት መፍቀድ የለብንም!!

Page 5: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

5ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

በጥርስና በጥፍር የሚደረግ ትግል እንዴት ይቁም?

በመጨረሻ ራሱ መጣ

አስራት አብርሃም

ግርማ ሠይፉ ማሩ[email protected]

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ/አንድነት አሳዛኙን የ2002 ምርጫ ውጤት ተከትሎ ፍራሽ አንጥፎ “ኢህአዴግ ምርጫ ዘረፈ” ከሚል መደበኛ ለቅሶ መውጣት አለብኝ ብሎ ቁርጠኛ ውሳኔ በመወሰን ውስጣችንን መፈተሸ ተገቢ አቅጣጫ ነው ብሎ በማመን፤ በእኛ በኩልስ የነበረው ችግር ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ አንስቶ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ይህን ያደረገው ነገሮችን ወደ ውጭ ከማላከክ በዘለለ ሙሉ ቁጥጥር ባለን በራሳቸን ላይ የውስጥ ፍተሻ ማድረግ ጠቃሚና ተገቢ ነው ከሚል እምነት የመነጨ ነበር፡፡ ይህ ማለት ግን የውጭ ጫናዎች በተለይም የኢህአዴግ አፈና የነበራቸውን ተፅዕኖ አሳንሶ ማየት እና የኢህአዴግን አፋኝነትን ዝቅ አድርጎ መመልከት አድርገው የሚውስዱ ሰዎች አይጠፉም፡፡ ዋናው ጉዳይ እና ቅድሚያ መሰጠት ያለበት የውስጥ ጥንካሬና ድክመትን

ማወቁ ነው የሚለው ነበር፡፡

በዚህም መነሻ አንድነት በተቃዋሚ ፓርቲዎች ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂናዕቅድ አዘጋጅቶ ለህዝብ ይፋ አድርጓል፡፡ይህም ሆኖ ግን ሪፖርተርን የመሰሉ ጋዜጦች ተቃዋሚዎችን በጅምላ የሚመሩበት አቅጣጫ የሌላቸው አድርገው መፈረጃቸውን አላቆሙም፡፡ ሌሎችም ቢሆኑ ይህን ተከትለው ከማስተጋባትና

ተቃዋሚዎችን በጅምላ ከመክሰስ ወደኋላ አላሉም፡፡ ለማንኛውም ፍረጃው እንደተጠበቀ ሆኖ አንድነት ያለፉትን አራት ዓመታት ጎዞውን ባስቀመጠው ስትራቴጂና አምስት ዓመት ዕቅድ መሰረት አድርጎ ቀጥሏል፡፡ የእቅዱ ማጠቃለያ ዘመንም ከምርጫ ሁለት ሺ ሰባት ምርጫ ጋር የሚገጣጠም ነው፡፡

ይህ የአምስት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ወደ ፊት እንደሚካሄድ ታሳቢ ተደርጎ የመጨረሻው ዓመት ሊኖረን የሚገባው ዋነኛ ስራ ምርጫን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ይታወቃል፡፡ ከዚህ አንፃር ገዢው ፓርቲ በጥርሱም በጥፍሩም ምርጫን ለማሸነፍ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን እግረ መንገዱን ደግሞ የተቃዋሚዎችን በተለይም ደግም የአንድነትን ጥርስ ማውለቅና ጥፍር ማዶልደሙን ተያይዞታል፡፡የጫወታውህግ በጥርስም በጥፍርም መጫወት የሚፈቅድ ከሆነ ተወዳዳሪዎች በተመጣጣኝ ጥርስም ጥፍርም ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በቦክስ ጫወታ ግጥሚያ የሚወጣው በኪሎ ነው፡፡አጫዋቹም/ዳኛውም ጫወታው ከመጀመሩ በፊት ቅድሚያ ሰጥቶ ማረጋገጥ ያለበት ይህን ጉዳይ ሁሉም ተወዳዳሪዎች ማሟላታቸውን ነው፡፡

አንድነት በዚህ ዓይነት የጥርስና የጥፍር ጫወታ ውስጥ ገዢው ፓርቲ ለማድረግ እንደሚፈልገው የተወዳደሪን ጥርስ ማርገፍና ጥፍር ማዶልዶም ተመጣጣኝ ምላሹ የገዢውን ፓርቲ ጥርስ ማርገፍና ጥፍር ማዶልዶም መፍትሔ ይሆናል ብሎ አያምንም፡፡ ለውድድሩ ጥርስም ጥፍርም አስፈላጊ ከሆነ የአንድነት ፓርቲ ጥርስና ጥፍር እንዳይጎዳ መጠበቅ ቅድሚያ ይሰጠው ነው፡፡ ይህ ነው በቁጥጥራችን ስር የሚገኘው እና ዋና ትኩረታችንን ሊወስድ የሚገባው እንዲሁም ተገቢ ጊዜ መስጠት አለብን የምንለው፡፡

ድሮ ልጅ ሆኜ መደባደብ አልወድም ነበር፣ ነገር ግን ገፍተው ከመጡብኝ፣ ተገደን የገባንበት ጦርነት እንዲሉ መንግስታት አልፎ አልፎ ተገድጄም ቢሆን መደባደቤ አልቀረም፣ ከዕለታት በአንዱ ቀን እንዲሆነ፣ ሀጎስ ከሚባል የጎረቤታችን ልጅ ጋር ተጣላንና መደባደብ ጀምር፤ ሁሌ እርሱ ነበር የሚያሸንፈኝ በዚያን ዕለት ግን አልቻለምና ወደ ጮኸ ከዚያ በኋላ የሆነው ነው አስገራሚው ነገር! የልጁ አባት የሚገላግል መስሎ መጥቶ እኔኑ በያዘው ዱላ ወገብ ወገቤን ይለኝ ጀመር፤ ወቅቱ ክረምት ስለነበር እኔ ብጮኽም ሰዎች ሳያገኙት ማሽላ ውስጥ ገብቶ ተደብቆ አመለጠ።

እኔ ያደኩበት አገባቢ የህወሀት ነፃ መሬት የነበረ በመሆኑ ጉዳዩ በህግ ተይዞ ሰውዬው ተከሶ ካህሳይ ወደ ተባለ የህወሀት ታጋይና የአከባቢው አስተባባሪ ጋር ቢቀርብም፤ እርሱ ልጆቹ ሲደባደቡ አግኝቼ አገላገልኩ እንጂ፣ አልመታሁትም ብሎ ማለ፤ ምስክርም ባለመኖሩ በግርግር አመለጠ፤ ከዚያ በኋላ እኔ አድጌ እርሱን የምመታበት ወቅት መጠበቅ ዋና ስራዬ ሆነ። በመሆኑም፤ ሁሌ ጠዋት ጠዋት ቁመቴ ምን ያህል እንደጨመረ ለማወቅ ከአንዱ ግንድ ጋር አለካካው ነበር፤ በነገራችን ላይ ይህ ሰው በ2002 ምርጫ ወደ ተንቤን በሄድኩ ወቅት የዓረና አባል ሆኖ አግኝቼው ብዙ ተጫውተናል፤ ሆኖም ድሮ ስለሆነው ጉዳይ አላነሳሁለትም።

የገዢውን ፓርቲ ጥርስ ለማርገፍና ጥፍሩን ለማዶልዶም የምናባክነው ጊዜ የራሳችን በመጠበቅ ብሎም በቁርጠኝነት ባለማስደፈር ቢሆን የበለጠ አዋጭ ነው ብለን እናምናለን፡፡

በገዢው ፓርቲ መንገድ የምንሄድ ከሆነ ግን ወደፊት ለሚደረግ ውድድር በሁለቱም ወገን የሚኖሩ ተወዳደሪዎች በድድ እና በዱልዱም ጥፍር የሚወዳደሩ ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ የጫወታውን ህግ መለወጥ የሚጠይቅ ይሆናል፡፡ በዛሬው የጥርስና ጥፍር ተምሳሌት ዋነኛ ወካይ ባህሪዎች በሁለቱም ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ነው፡፡ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎችን በተለይ የአንድነትን ጥርስና ጥፍር ላይ አደጋ አደረሰ ማለት በየደረጃው ያሉ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ላይ የሚወስዳቸው ቅጥ ያጡ ህገወጥ እርምጃዎች ማለቴ ነው፡፡ በአፀፋው አንድነት ይህን ያድርግ ሲባል ደግሞ በኢህአዴግ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ቅጥ ያጡ ሕገ ወጥ እርምጃዎች እንውሰድ ማለት ነው፡፡

የእነዚህ ድምር ውጤት ኢትዮጵያዊያንን በፖለቲካ አቋማቸው ከመጉዳት የሚተናነስ አይደለም፡፡ በዚህ ሁኔታ በተጎዳ ህዝብ ውስጥ ወደፊትም ቢሆን የተሻለ እና የሰለጠነ አማራጭ ይዞ በፖለቲካ መወዳደር ይቻላል የሚል እምነት አይኖርም፡፡ ለዚህም ነው ጉልበታችንን የኢህአዴግ አባላትን ለመጉዳት ወይም ለመበቀል ሳይሆን የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን አቅም በማሳደግ የአይደፈሬነት ስነልቦና ማዳበር መሆን ይኖርበታል የምንለው፡፡

በአንድነትበኩል የአባላቶቻችንን አቅም እናሳድጋለን ብለን ስንነሳ በዋነኝነት በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚደረግ ውድድር የሚመነጨው አንዱ ሀገር ወዳድ ሌላው ጠላት ነው ከሚል መንፈስ፣ ወይም

በግል በደረሰብን በደል በቁጭትና ለበቀል መሆን እንደሌለበትበማሰተማርነው፡

የፖለቲካፓርቲዎች የሚለያዩትበሚመርጡትየርዕዮተ

ዓለም፣ይህንለመተግበር በሚያወጡት ፖሊሲናየማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎች መሆኑን በማስረዳት በማስከተለም እነዚህ ልዩነቶች ሀገርን ሊጎዱ እንደሚችሉ ለህዝብ በማሳየት ህዝብ ለሚሰጠው ብይን ተገዢ ለመሆን ዝግጁ ሲኮን ነው፡፡ ይህን ልዩነታችንን ከጠባብ ቡድናዊ/የፓርቲ ወይም ሌላ ስብስብ ፍላጎት ከመነሳት “ሀገር ወዳድ እና የሀገር ጠላት” በሚል እንድንፈራረጅ ምክንያት ከሆነ የጋራ ሀገር እንዲኖረን እየሰራን ነው ማለት አይቻልም፡፡ኢትዮጵያ ሀገራችን ለሁሉም ፓርቲዎች የጋራ መኖሪያ ከመሆን በዘለለ የሁሉም ፓርቲዎች አባላት የሚኖሩባት ብቻ ሳትሆን ለልጅ ልጆች በተሻለ ደረጃ ልናስተላልፋት ትልቅ ራዕይ ሰንቀን የምንቀሳቀስ መሆኑ በሁሉም ዘንድ መታወቅ አለበት፡፡ ኢትዮጵያችን እንድትኖር እኛም በእርሷ እንድንኮራ በሁሉም ጎራ የተሰለፍን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለብን አውቀን

መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

በኢህአዴግ በኩል የሚገኙ አባላት ብሎም ከፍተኛ አመራሮች ጭምር የተቃዋሚ ፓርቲዎችን “ኪራይ ሰብሳቢ” ከሚል ቅጥ አንባሩ ከጠፋው ፍረጃ በላይ ግልፅ ሆኖ በወጣ መልኩ በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፍን ዜጎች በፍፁም ለሀገር ደንታ የሌለን አድርገው መሳል የተለመደና አስልቺ ፕሮፓጋንዳ ከሆነ ቆይቶዋል፡፡ ይህ በእውነቱ የኢህአዴግ በጥርስም በጥፍርም ለመጫወት እንዲመቸው የሌላውን ጥርስ ማርገፍና ጥፍር ማዶልዶሚያ ስትራቴጂው ነው፡፡

ወደ ገፅ 6 ዞሯል

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ፤ ኢህአዴግም በተላላኪዎቹ አልሆንልህ ሲለው ራሱ የሚመጣበት ሁኔታ ስላለ ነው ይህን ማስታወሴ! ባለፈው ጊዜ አንዳንድ ሰዎች በአንድነት ውስጥ ችግር ለመፍጠር በሞከሩበት ወቅት ኢህአዴግ በዚያ ግርግር ገብቶ ለማጋጋል ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ፓርቲውን ደህና አድርገው ያዳክሙልኛል ያላቸው ሰዎች አንድ ባንድ ሲመቱ፤ በተጠባባቂ ቦታ፣ በምርጫ ቦርድ ውስጥ ሰግስጎ አስቀምጧቸው በነበሩ ሰዎቹ በእኩል ምርጫ ቦርዱ ከተቋቋመበት አዋጅና መንፈስ ውጪ በሆነ መልኩ በአንድነት ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው ውዥንብር ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ ተሞክሯል።

የምርጫ ቦርዱ አዋጅ አንድን የፓርቲ ሰነድ ወደ ምርጫ ቦርድ ከገባበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ሰላሳ ቀናት ውስጥ ቦርዱ ለፓርቲው መልስ ካልሰጠ እንደተቀበለው ይቆጠራል የሚል በግልፅ ሰፍሮ እያለ፤ በምርጫ ቦርዱ ምክትል የፅህፈት ቤት ሀላፊ በአቶ ወንድሙ ጎላ በእኩል እንዲፃፍ የተደረገው ደብዳቤ ይህ አዋጅ በግልፅ የሚጥስ ነው። አዲሱ ህገ ደንብ ቦርዱ አይቶ ስላላፀደቀው ዶ/ር ነጋሶ በነበሩበት ጊዜ የነበረው ህገ ደንብ ነው የምናውቀው ተብሎ እንዲፃፍ የተደረገው ሆን ተብሎ ውዥንብር ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ምንም ዓይነት የህግ መሰረት የለውም፤ የአንድነት አዲሱ ህገ ደንብ በሀምሌ 17/2006 ወደ ምርጫ ቦርድ ገብቶ፤ ሀምሌ 25/2006 ቦርድ በሰነዱ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቆ፤ ወዲያው ሀምሌ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ተገቢው ማብራሪያ ከፓርቲው ተፅፎለት ተቀብሏል። ከዚያ በኋላ

ነሀሴ አልፎ፤ ጳጉሜ አልፎ፣ መስከረም አልፎ፣ ጥቅምት መጨረሻ ላይ አላየሁትምና አልተቀበልኩትም ማለት አይችልም፤ ቢያንስ ሰማኒያ ቀናት ያለፈው ጉዳይ በመሆኑ ፈጽሞ የሚያስኬድ ክርክር ነው የሚሆነው፤ እነርሱም ይሄ እንደማያስኬድ ሲረዱ ሌላ ማብራሪያ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፈዋል፤ ፓርቲውም ለዚህ ተገቢ የሆነ ማብራሪያ በድጋሜ ፅፎ አስገብቷል። ይህም ቢሆን ግን ቦርዱ በማንኛውም ጊዜ ማብራሪያ ቢጠይቅ ችግር የለውም፤ ከሚል ነው እንጂ ከዚህ በኋላ ስለህገ ደንቡ ህጋዊ መሆንና ያለመሆኑን ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር አይደለም። አንድነት አሁን ካለበት የተሻለ ምሽግ ወጥቶ አውላላ ሜዳ ላይ የሚገኝበት ሁኔታ አይኖርም። ምርጫ ቦርድ በአዋጁ ላይ በግልፅ የሰፈረውን የጊዜ ገደብ የማያከብር ከሆነ ሌላው ያከብራል ተብሎ ፈፅሞ አይጠበቅም፤ ስለዚህ አንድነት አሁንም ህጉን ተከትሎ መጓዝና በዚያ በህጉ ብቻ የሚጠበቅበትን ነገር ሁሉ ማሟላት ነው ያለበት። ከዚህ ውጪ ለሚመጣ ማንኛውም እጅ ጥምዘዛ በር መክፈትና ፊት ማሳየት የለበትም።

አንድነት እንደ ኢሪኮ ግንብ በተላለኪዎችና ዞምቢዎች ጩኸትና ጫጫታ የሚፈርስ መስሏቸው፤ ከሰንደቅ እስከ ኢቲቪ፣ ከሀገርቤት እስከ ዲያስፖራ ጫጫታና ውዥንብር ለመፍጠር ተሯሩጠዋል፤ ይኸው እነዚህ ሁሉ ፀደያቸው አልፎ፤ ክረምት እየገባላቸው፤ ከዚህ በኋላ ኢህአዴግ ግን እንደተለመደው ራሱ በቀጥታ ወደ አንድነት አይመጣም ብዬ አላስብም። በፈለገው መንገድ ይምጣ ትግሉ ግን ይቀጥላል፤

“ገበየው ቢሞት ተተካ ባልቻ፤

መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ፡፡”እንደተባለው፣ ጀግኖች

ቢታሰሩ፤ ሌሎች ጀግኖች እየተተኩ ትግሉ ይቀጥላል፤ አንድነትም ተተኪ በበቂ ሁኔታ የመፍጠሩ ስራ ጠንክሮ እየሰራበት ነው የሚገኘው፤ ስለዚህ ፈጽሞ የተተኪ ችግር አይኖርም። እስርቤቱ እስኪሞላና በቃኝ እስኪል ድረስ፤ አሳሪዎቻችንም እጃቸው ዝሎ፤ መግረፍ በቃን ብለው ከማሰርና ከመግረፍ የተሻለ መላ እስኪያመጡ ድረስ እኛ ትግሉን እንቀጥላለን፤ እነርሱ ማስር ኪሰራ እንጂ ትርፍ እንደሌለው እስኪያውቁ ድረስ ማሰራቸውን ይቀጥላሉ፤ በአንድ ነገር ላይ ግን እርግጠኛ መሆን ይቻላል፤ ይሄ ስርዓት አላፊ ጠፊ መሆኑን መታወቅ አለበት። ሌላው ይቅርና ሰው በላው የናዚ ስርዓትም ለሶስት ሺህ ዘመናት እንዲቆይ አድርገን ገንብተኗል ሲባል ቆይቶ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው ተንኮታኩቶ የወደቀው፤ በናዚ ማጎርያ ውስጥ የነበሩ፣ በህይወት የቀሩ፤ ስርዓቱ ተንኮታኩቶ ሲወድቅ በዓይናቸው አይቷል።

በህይወት ከዚህ ዓይነቱ ሁኔታ እንወጣለን ብለው ፈፅመው ያላሰቡ አይሁዶችና ሌሎች ግፉአን ህዝቦች በመጨረሻ ነፃ ወጥቷል። በዚያው ልክ ደግሞ ወንጀለኞቹ ከተደበቁበት ስርጫ ሁሉ እየተፈለጉ፤ ወደ ህግ ፊት ቀርበው የሚገባቸው ዋጋ አግኝቷል። ለሌላው መማሪያ ይሆኑ ዘንድ ተገቢው ቅጣት እንዲያገኙ ተደርጓል። ስለዚህ ማንም ቢሆን ወንጀል ከሰራ ፈፅሞ ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል መታወቅ አለበት።

Page 6: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 846

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ለአያሌ ዘመናት በፊውዳሎችና በመሬት ከበርቴዎች መዳፍ ስር ለቆየችው ኢትዮጵያችን የወንድማማቾቹን መንግስቱ ነዋይና ገርማሜ ነዋይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከትሎ አዲስ የፖለቲካ በር ተከፈተላት፡፡ እኒያ እቤት ውስጥ እንኳን አገዛዛቸው እንዳይተች መለኮታዊ ሃይል እንደተጎናፀፉና ቢታሙ እንኳን እንደሚሰሙ ዘለግ ላሉ አመታት የሰበኩት አባባ ጃንሆይ ህዝባቸውን ቀጥቅጠው ይገዙ ዘንድ አምላክ ያልቀባቸው መሆኑንና እንደማንኛውም ሁለት እግር እንዳለው ፍጡር መዋቲ ስለመሆናቸው፤ ዙፋናቸውም በለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ሊነቀነቅና ብሎም ከአሸዋ ክምር አንደተሰራ ቤት ተደርምሶ ሊፈርስ የሚችል ሰው ሰራሽ እንደሆነ ‹‹የታህሳስ ግርግር›› በመባል የሚታወቀው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አበሰረ፡፡

በንጉሱ ፊውዳላዊ አገዛዝ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉ የያኔ ለውጥ ፈላጊ ሃይሎች ለመቀጣጫ ተብሎ አንገታቸው በቀጭን ሲባጎ ታንቆ ቢንጠለጠለም የለኮሱት የዘመናዊ ፖለቲካ አስተሳሰብ፣ የለውጥ ናፍቆትና የጃጀውን የፊውዳል ስርዓት እድሜ የማሳጠር መንፈስ እንደ ለውጥ ፈላጊዎቹ በሲባጎ የሚታነቅ አልነበረም፡፡ መንፈሱ በበርካታ ኢትዮጵውያን ጎጆና ታዛ ብሎም ልብ ውስጥ ተቀመጠ፡፡ የወቅቱ ልሂቃንና ተማሪ ቤት በራፍ የረገጡ ወጣቶች በለውጡ ሽታ ታወዱ፡፡ ዜማዎች ሁሉ የጭቆና ቀንበርን የሚሰብሩ፣ የትውልዱን ተስፋ የሚያበስሩ ሆኑ፡፡ ተማሪዎች ንቅናቄ በመፍጠር የንጉሱን ስልጣን መነቅነቅ ያዙ፡፡

እነሆ ይህ የዴሞክራሲና የፖለቲካ ለውጥ ፍላጎት ከተጀመረ ድፍን 50 ዓመት ሆነው፡፡ ስለዴሞክራሲና ህዝባዊ መንግስት መቋቋም ከተጠየቀና ህዝብ የስልጣን ባለቤት ይሁን የሚለው ክቡር ጥያቄ ከተለኮሰ ያው የአንድ አዛውንት እድሜ ያዘ፡፡ ያኔ የለውጡ አካል የነበሩ ወጣቶች የአሁን አዛውንቶች በቁጭት እንደሚያስታውሱት ያልተደራጀው ንጉሱን የማውረድ ትግል መሳሪያ ባነገበው ወታደራዊ ሃይል ላይ በመውደቁ ኢትዮጵያችን ለአስራ ሰባት ዓመት ዋጋ ልትከፍል የግድ ሆነ፡፡ የዴሞክራሲ ስርዓት ናፍቆቱም በወታደራዊ መንግስት ተደቁሶ መሰረቱን ሳተ፡፡ “ጉልቻ ቢለዋወጥ...” ይሉት አይነት ሆኖ የገዥ ለውጥ እንጅ የጭቆናው ለውጥ ባለመምጣቱ ኢትዮጵያ አነባች፡፡

“ብሶት ወለደኝ” የሚለው ተረኛ ገዥም መሰረታዊ ተፈጥሮውና ይከተለው የነበረው ርዕዮተ አለም ከዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ አርባ ክንድ ቢርቅም ድንገት ለምኒልክ ቤተ መንግስት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች እንደቀራቸው በማወቃቸው፤ በተያያዥም አለምን ይንጣት ከነበረው የግራና ቀኝ አክራሪዎች ፍጥጫ ሚዛኑ ወደ ምዕራቡ አለም በማድላቱ ታጋዮቹን አሰላለፋቸውን እንዲያሳምሩ ግድ የሚላቸው ቀን ከተፍ አለ፡፡ ከእነ ዴሞክራሲ ጋር ትውውቅ ተጀመረ - “ዳሩ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ” ይሉት አይነት ቢሆንም፡፡

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ወደ ስልጣን ሲመጣ ቀልብ ለመሳብ ከቻለባቸው ጉዳዮች አንዱ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር የሚለው ነው፡፡ ዴሞክራሲው እንዲፈጠር ደግሞ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ዋነኛውን ስፍራ ይይዛል፡፡ ምርጫ

ቦርድ፣ ነፃው ፕሬስ፣ የሲቪክ ተቋማት ወዘተ፡፡

በተለይ ዴሞክራሲ ለባለፉት 50 አመታት የተጠየቀባት ግን በተግባር ያልተገኘባት፤ እንዲሁም ለሀገርና ለህዝብ

የሚጠቅሙ ክቡር ዜጎች በየጎዳናው የወደቁባት ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ መንግስት የመሆን ዕድል ላገኘ ፓርቲ ዴሞክራሲን ለማስፈን የሚጠበቅበት አጭር ስራ ገለልተኛ የዴሞክራሲ መገንቢያ ተቋማትን የመፍጠር ብቻ ይሆናል፡፡

የዚች ፅሁፍ አቅራቢ እነደሚያምነው እንደኢትዮጵያ ባለ ሀገርና ህዝብ ዴሞክራሲ በሂደት የሚጎለብት ሊሆን አይችልም፡፡አንባገነኖች ዴሞክራሲን እንደህፃን ልጅ ድሆ ድክድክ የሚል እንደሆነና በሂደት እንደሚጎረምስ የሚነግሩን ሆን ብለው ነው፡፡ቢያንስ እንኳ ገለልተኛ የሆነ ምርጫ ቦርድ የማቋቋም ቁርጠኝነት ሳይኖር፣ ነጻው ፕሬስ ላይ ያለው አፈና ተጧጡፎና የሲቪክ ተቋማት እንደ ዶሮ ረዘም ባለች ገመድ ታስረው እንዴት ዴሞክራሲያችን ሊያድግ ይችላል እንዲህ እያደረጉስ ዴሞክራሲ ሂደት ነው፣ እንደ ጨቅላ ህፃን ቀስ እያለ የሚያድግ ማለት ምን ማለትስ ይሆን ምፀት ካልሆነ በቀር፡፡

እሰቲ ከዚህ አብይ መንደርደሪያ ተመልሰን በጨረፍታም ቢሆን ምርጫና ምርጫ ቦርድን እንመልከት፡፡ ጥያቄም አንስተን እንሞግት፡፡እንዳለመታደል ሆኖ በምርጫና ምርጫ ቦርድ ብዙ ደስ የሚያሰኝ ትዝታ የለንም፡፡ምርጫ በደረሰ ቁጥርም ተቃዋሚውና ገዥው ፓርቲ ከሚነታረኩባቸው ጉዳዮች አንዱ የዚሁ ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ይሁንና በገለልተኛ ወገኖች ይቋቋም የሚለው ነው፡፡ ከምር ስለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የምንጨነቅ ከሆነ ገለልተኛ የሆነ ምርጫ ቦርድ ይቋቋም የሚለው አንኳር ጥያቄ መሰረታዊ ነው፡፡ ይህን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ ዴሞክራሲ የመገንባት ሂደቱን አንድ ርምጃ ማሳደግ ነው፡፡ኸረ እንዴውም ዋነኛው ሳይሆን አይቀርም፡፡

ኢህአዴግ ቦርዱ ገለልተኛ ነው እያለ ቢከራከርም በተጨባጭ ግን የሚነሱ ጥቄዎችን የሚመልስበት አቅም አላገኘም፡፡ ለምሳሌ እንኳ የቦርዱ ሰብሳቢ የሚሰየመው በተወካዮች ምክር ቤት ቢሆንም አቅራቢው ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆኑ ከተፅዕኖ እንዳይላቀቅ ያደርገዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመልምሎ የመጣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ገለልተኛ ለመሆን እንደሚቸገር መገመት ይቻላል፡፡

ውስጥ አዋቂዎች እንደሚጠቁሙት ደግሞ በተዋረድ የምርጫ ቦርድ ሃላፊነት ላይ የሚገኙ ግለሰቦች የፓርቲ ወገንተኝነት እንዳላቸው ይናገራሉ፡፡ የእናት ፓርቲያቸው ነገር እንደ ግመል ሽንት ወደ ኋላ እየጎተታቸው እንደሚቸገሩ ይታመናል፡፡ ስለዚህ የምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዱና አመራረጣቸው ገለልተኛ በሆነ መልኩ ይዋቀር ማለት ተገቢ ብቻ ሳይሆን አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡ ለባለፉት ሃምሳ ዓመታት የተዘመረለትን ህዝብን የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት የማድረግ ጥያቄ መመለስ እንደሆነም ልብ ይሏል፡፡

ሌላው ለቦርዱ ገለልተኛ አለመሆን የሚጠቀሱት የተቃዋሚ ፓርቲ ነን የሚሉ በተግባር ግን ተቃዋሚ የሚያስብል ተግባር ሲፈፅሙ የማይታዩ ፓርቲዎች ጉዳይ ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ ራሱ እንደጠቀሰው ከ75 በላይ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መንግስት ለመሆን ይፋለማሉ፡፡ ይፋለማሉ ይሰመርበት፡፡ ዋናው ጉዳይና ምርጫ ቦርድ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ማድረግ አለበት የምለው አብይ ነገር እነዚህ አያሌ ፓርቲዎች ፓርቲ መሆናቸውን የሚያሳይ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ጠቅላላ ጉባዔ የሚጠሩ፤ ምክር ቤት ያላቸው፤ ስራ አስፈፃሚ ያላቸው፤ ቢሮ የተከራዩ ወይም ያላቸው፤ አግባብነት ያለው የፖለቲካ

ፕሮግራምና ደንብ ያላቸው ስለመሆናቸው መረጋገጥ አለበት፡፡ ሀገር እንመራለን ብለው ምርጫ ላይ የሚሰለፉ ፓርቲዎች ማንነት እና አቋም ለህዝብ በግልፅ መነገር ይገባዋል ባይ ነኝ፡፡

የዚች ፅሁፍ አቅራቢዎ እንደሚስታውሰው ባለፈው አመት ሰንደቅ በተባለች አንዲት ጋዜጣ ላይ የተሰራ ዜና ምርጫ ቦርድ በነዚህ ፈቃድና ማህተም ብቻ ባላቸው ፓርቲዎች ክፉኛ መናደዱን እንዲሁም በአስቸኳይ ይህንን ካላሟሉ ፈቃዳቸው እንደሚነጠቅ በማስታወስ ደብዳቤ እንደፃፈላቸው የሚጠቅስ አይነት ዜና ነበር፡፡ ታዲያ ባለፈው ሳምንት ምርጫ ቦርድ የ2007ን ሀገርአቀፍ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ሲደርግ ስለነዚህ ፓርቲዎች አላነሳም፡፡የተፃፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም ምልሽ አልታወቀም፡፡እንደዚህ ሆኖ ግን እንዴውም‹‹ዋነኛ ተፋላሚዎች›› እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን ምርጫ ቦርድ የነዚህን ፓርቲዎች ጉዳይ አጣርቶ ይፋ ማድረግ አለበት፡፡ አለበለዚያ ገለልተኝነት ገደል ገባች ማለት ነው፡፡

እንደሚታወቀው ምርጫና ምርጫ ቦርድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፆች ናቸው፡፡ ቦርዱ ሲስተካከከል ምርጫውም ይስተካከላል፡፡ለባለፉት ጥቂት ሳምንታት የኢቲቪና የምርጫ ቦርድ ጭንቀትና ስራ የነበረው አንድነት ፓርቲ ነው፡፡ የሻይ ሲኒ ማዕበሏ የተፈጠረችው አንድነት ፓርቲ ምክር ቤቱ ከጠቅላላ ጉባዔ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን የለቀቁትን ኢ/ር ግዛቸው ሺፈራውን ለመተካ እጩዎችን አወዳድሮ ፕሬዘዳንት በመተካቱ ነበር፡፡ ሂደቱን ለመጠቀም ሦስት በአንድነት ፓርቲ የሚታወቁና ሌሎች የፓርቲው መዋቅር የማያውቃቸው ግለሰቦች በፈጠሩት ግንባር ስራ ለማስፈታት ሲራወጡ ቦርዱም በመግለጫ ተራወጠ፤ ኢቲቪም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ለ6 ጊዜ መላልሶ ዜና አደረገው፡፡

አጫጭር ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ አሉኝ፡፡ ቅሬታ አቀረቡ የተባሉ የዞን ሃላፊዎች በአንድነት ፓርቲ በኩል አይታወቁም እየተባለ ነው፡፡ ስለዚህ ሃላፊ ስለመሆናቸው ማረጋገጫው ምን ነበር ወረቀት ላይ አመራር ነን ስላሉ ይህንን መቀበል ይቻላል ወይም ጉዳዩ በህግም በታሪክም ያስጠይቃል፡፡ እነሆ ምርጫው ደርሷል፡፡ የትወናው መጠንና ስፋትም በዚያው ልክ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የምንፈልጋትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የመፍጠር ትግል ይቀጥላል፡፡ ትግሉ የሚቆመው ለውጥ ሲመጣ ብቻ ይሆናል፡፡

ዳንኤል ተፈራ

ምርጫና ምርጫ ቦርድ

ከገፅ 5 የዞረበጥርስና በጥፍር ....

ይህ መንገድ ግን ብዙ ርቀት የማያስኬድ ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም የሚበጅ ነው የሚል እምነት የለንም፡፡

በተቃዋሚ መስመር የተሰለፍን ሰዎች መካከልም ኢህአዴግን መሳደብ እንደ ዋና የትግል ስልት የተያዘ እስኪመስል ድረስ ጥግ እንደምንሄድ አምኖ መቀበል ስህተታችንን ለማረም ጉልዕ ድርሻ አለው፡፡ አንዳንዴም የሃሳብ ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ ከመግለፅ ይልቅ ስነምግባር በጎደለው ሁኔታ በተለይ የግለሰቦችን ስብዕና የሚነኩ አላስፈላጊ የቃላት ጫወታዎች እንዳሉ እንረዳለን፡፡ “ቅኔው ሲጠፋበት ቀረርቶ ሞላበት” የሚለው አባባል በሁለቱም ጎራ የመከራከሪያ ሃሳብ ድርቀት ምልክት ሊሆን ይቻላል፡፡ ይህንን ከመሰረቱ ለመቅረፍ ከላይ እንደተገለፀው አባላትን በስነምግባር መኮትኮት እና ዋነኛው የፓርቲዎች ልዩነት መሰረት መሆን የሚገባው የፖሊሲና የስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ እንዲያተኩሩ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ሲሆን በከፍተኛ ሀገራዊ መግባባት ስሜት መንቀሳቀስ ይቻላል የሚል ፅኑ እምነትን ይዳብራል፡፡

ምርጫ ቦርድ ራሱ

እንደጠቀሰው ከ75 በላይ

የተቃዋሚ ፓርቲዎች

መንግስት ለመሆን

ይፋለማሉ፡፡ ይፋለማሉ

ይሰመርበት፡፡ ዋናው

ጉዳይና ምርጫ ቦርድ

ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ

ማድረግ አለበት የምለው

አብይ ነገር እነዚህ

አያሌ ፓርቲዎች ፓርቲ

መሆናቸውን የሚያሳይ

ህጉ በሚፈቅደው

መሰረት ጠቅላላ ጉባዔ

የሚጠሩ፤ ምክር

ቤት ያላቸው፤ ስራ

አስፈፃሚ ያላቸው፤

ቢሮ የተከራዩ ወይም

ያላቸው፤ አግባብነት

ያለው የፖለቲካ

ፕሮግራምና ደንብ

ያላቸው ስለመሆናቸው

መረጋገጥ አለበት፡፡

ሀገር እንመራለን ብለው

ምርጫ ላይ የሚሰለፉ

ፓርቲዎች ማንነት እና

አቋም ለህዝብ በግልፅ

መነገር ይገባዋል ባይ

ነኝ፡

Page 7: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

7ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ፍኖተ ነፃነት፡- ከሰሞኑ በመላው ሀገሪቱ ከተጀመሪው የአንድነት አባላትና ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን የማሰር ዘመቻ ውስጥ ጎንደርም የሚጠቀስ ነው፤ ስለተፈጠረው ሁኔታ በዝርዝር ንገረን?

ጎንደር ላይ ከፍተኛ ዘመቻ ነው የተደረገው። ጥቅምት 25 ነው በያሉበት እየዞሩ የለቀሟቸው። ስለዚህ የዛ ሰሞን ከ25 -27 እኔ ወደ እዚህ እስክመጣ ድረስ የፀጥታ መኪና ነው ከተማዋ ላይ የሚታይ የነበረው። ይሄን ከያሉበት ለመልቀም ነው የተደረገው ሰላማዊ ታጋይ ናቸው። ከያሉበት ቦታ ነው ቤታቸው ደጃፋቸው እየተነቀለ እየጎተቱ እየደበደቡ ያወጧቸው።

ፍኖተ ነፃነት፡- ስማቸውን እየጠቀስክ ከእነ ሀላፊነታቸው ንገረን

ሰመረ በላይ አንቃው ተገኘ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ነው። እንግዳው ዋኘ የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ሀላፊ ነው። አባይ ዘውዱ የመንግስት ስራ ነበር የሚሰራው። በመንግስት ተፅእኖ ከስራ የተባረረው። በፓርቲው ግን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ነው። መተማ ላይ የተደረገው ደግሞ በላይነህ ሲሳይ ነው። የፓርቲው ሰብሳቢ ነው። እንደገና አንድ አባል አለ ተራ አባል ነው።

ፍኖተ ነፃነት፡- አባላቱን ሲይዝዋቸው ቤታቸውን እንደሚፈትሹ ሰምተናል፤ የእስር መያዣና ቤት እንዲፈተሽ የሚፈቅድ የፍርድ ቤት ማስረጃ ይዘው ነው የሚወስዷቸው?

የእስር ማዘዣ እንዳትልማ በህግ የሚመካ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአንድን ተቃዋሚ ሰላማዊ ፓርቲ አባል አፍነው አይሄዱም ነበር። ሌሊቱን ነው አፍነውት ያደሩ ቀድሞ በወጣ ቤቱ ሲከፈት እየዘሉ ነው እየደበደቡ ያወጧቸው። የእስር ማዘዣማ ቢሆንማ በሰዓት በማንኛውም ወቅት ጠይቀው መያዝ ይችሉ ነበር። ግን ያደረጉት እነሱ የጠበቁት በመሳሪያ ነው። የተለመደ መሳሪያ አለ ያንን መሳሪያ ደቅነው ገብተው እየደበደቡ በአፈሙዝም በምንም የያዟቸው እንጂ ምንም የተናገሩት ነገር የለም። ህጋዊ ነን ምናምን ያሉት ነገር የለም። ከፍተው ገቡ የፈለጉትን መረጃ ብለው የያዙትን መፅሀፍ ጠቅላላ እንዳለ የሚያነቡትን መፅሀፍ የወሰዱት ስለዚህ ህጋዊነትን የሚያመለክት እቃ ይዘው የመጡት ነገር ስለሌለ የፍርድ ቤት ወረቀትም ስለሌለ ቀጥታ በሀይል ነው ተጠቅመው እነሱን በቁጥጥር ስር ያደረጓቸው።

ፍኖተ ነፃነት፡- አባላቱ በሚታሰሩበት ሰዓት የአካባቢው ህዝብ አናስወስድም በሚል ከፖሊስ ጋር ጥያቄ ሲያቀርብ ነበር እና ያንንስ ሁኔታ እስቲ አስረዳኝ?

ህብረተሰቡ እንዳይሄዱ ጥረት አድርጎ ነበር። ከአሁን በፊትም እነ አባይ ተይዘው ነበር። በህብረተሰቡ ተፅእኖ ነው የተፈቱት። አሁን በ25 ሲያዙ ህብረተሰቡ አንሰድም ፖሊስ ነው መያዝ ያለበት እንጂ ፌደራል ፖሊስ እንዴት ይይዛችኋል። ፖሊስ የያዛቸው ህጋዊ ፖሊስ ነው ከዛ በኋላ በጉዳያቸው መጠየቅ ይችላሉ ያጠፉት ነገር ካለ። ካልሆነ ግን እኛ ዝም ብለን አንሰድም የሚል ነገር ነበር ተነስቶ የነበረው። ግን ህብረተሰቡ በሌለበት መንገድ ነው የወሰዷቸው። ከአውራጅራ ቀጥታ ወደ ሱዳን ጠረፍ ኮርባ ነው ያወጧቸው። ከኮርማ ወደዚህ ወዴት እንደወሰዷቸው አልታወቀም። ግን መምጣት የነበረባቸው ከአውራጅራ ወደ

ሶረቃ ቀጥታ ወደ ጎንደር ነበር። ከጠረፍ ወደ ጠረፍ ስለሆነ ያዞርዋቸው እንግዲህ እኛ የት እንዳሉ አናውቅም። ህብረተሰቡ ግን የበኩሉን አስተዋፅኦ አድርጎ ነበር። ምክንያቱም ልጆች በህብረተሰቡ ላይ ግፍና በደል የሚደርሰው ሁሉ በግምባር ስለሆነ ይጋፈጡ የነበሩት ህብረተሰቡም ከልቡ ነበር እንትን ይላቸው የነበረው። ስለዚህ ለምን ብሎ ነበር ግን ባልሆነ መንገድ ስለወሰዷቸው ተቃውሞ በዛ መልኩ ሊቀር ችሏል።

ፍኖተ ነፃነት፡- የታሰሩት አባላት አሁን ያሉበት ሁኔታ ይታወቃል። ቤተሰብ እንዲጠይቃቸው ተፈቅዷል?

በፍፁም ምንም የታወቀ ነገር የለም። እኔ በግሌ የራሴን የተቻለኝን ጓደኞቼም ስለሆኑ የትግል አጋሮቼም ስለነበሩ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ሞክሬያለሁ በፍፁም ያገኘሁት ነገር የለም። የትም እንዳሉ በህይወት ይኑሩ ይገደሉ የትም ይውሰዷቸው ምንም የታወቀ ነገር የለም። በቃ ከእዛ ቦታ አነሷቸው ቤታቸው ከወጡ በኋላ ወደ ሱዳን ጠረፍ ወደ ኮርማ ሄዱ። ከዛ በኋላ የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም።

ፍኖተ ነፃነት፡- የአካባቢው ህዝብ መንግስት በሚያደርሰው ተፅእኖ ምን አይነት ምላሽ ነው እየሰጠ ያለው?

ምላሹ ምንድን ነው በጠቅላላ ህዝባችን አንደኛ ጠረፍ ነው። በህገወጥ መንገድ ለሱዳን የተሰጠ መሬት አለ። በዛ ተቃውሞ አለ። ሁለተኛ ደግሞ የሚደርሰው ግፍና በደል አለ። አሁን ያለው ሁኔታ ከባድ ነው። ህዝብና መንግስት አንድ ናቸው ለማለት አይቻልም። ምክንያቱም ህዝብን ያላስተዳደረ ወይንም ህዝብን ያላረካ አስተዳደር ስለሆነ ያለ በሚሰጡት የመንግስት አገልግሎቶች ሁሉ ህዝብ እየተማረረ ነው ያለው። ምክንያቱም ህዝብ የደገፈው አካል ስላልሆነ የተቀመጠው ሁሌም በጉልበት ስለሆነ ያሉት አንደኛ ወደ ፍትህ ብትሄድም ወደ አስተዳደራዊ ሁኔታዎች ብትሄድም ሁሉም አማሮ የሚመጣበት ሰውን ተበድያለሁ ልክሰስ ከማለት ይልቅ በሀገር ሽማግሌ ሁኔታዎችን የሚፈታበት ተበድሎም ቢሆን አስታራቂ ሆኖ የሚገኝ እሱ ነው ብሎ የሚያምን በሱ ብቻ ነው መንግስትና ህዝብ የተመጣጠኑ ናቸው በቃ ሆድና ጀርባ ፈርተህም ቢሆን ልትቀርባቸው

ትችላለህ እንጂ እውነት ትክክለኛ ስራ ይሰራሉ ብለህ አይደለም የምትቀርባቸው። ምናልባት ሊበቀሉህም ይችላሉ። ጊዜ ለመጠበቅ ማለት ነው። ሊበቀሉም ይችላሉ ብለህ ፈርተህ ልትቀር የምትችልባቸው ነገሮች ሊኖር ይችላል። ህብረተሰባችን ደግሞ እንደዚህ አይነት አካሄድ ነው የሚሄድ ያለው። በእሱ ላይ የሚወሰድ እርምጃ ስላለ ፈርቶ ነው የሚቀርብ እንጂ እውነት በሚሰጠው አስተዳደራዊ ስርአት ወይም የፍትህ ስርአት

ረክቶ ሳይሆን ሊበቀሉም ይችላሉ። የብቀላ ስራ ስለሚሰሩ ሊበቀሉም ይችላሉ የሚል ነገር ስለሚሰማ በዛ ምክንያት ነው እንትን የሚለው እንጂ ምንም መንግስትና ህዝብ ተጣጥመው እየኖሩ አይደለም። መንግስት በሚሰጣቸው አገልግሎቶችም ረክቶ እየኖረ አይደለም። እንደገና ደግሞ ድንበር አካባቢ ያሉ መሬቶች ወደዛ ስለሄዱ እዛ ላይም ቅራኔ አለ። ህዝብም እያቀረበ ነው። መሬታችን አላግባብ ሄዷል። ከእርሻ ቦታችን ነቅላችሁናል። መሬታችን ይመለስ። የሀገራችን ዳር ድንበር ነው። እኛ የምናመርተው መሬት ነው እያለ ስለሆነ በዛም አልተጣጣመም። መንግስትም የህዝብን ጥያቄ መመለስ አልቻለም። በዛ ሆድና ጀርባ ናቸው። በተጨማሪም መንግስት ይሄ ብሎክ ብሎ የመሬት ስሪቱ ላይ የመሰረተው እንትን አለ። ያ ደግሞ ብዙ አርሶ አደሮችን አፈናቅሏል። ብዙ ንፁህ አርፈው መብላት የሚችሉ ወገኖቻችንን አፈናቅሏል። መሬት አልባ አድርጓቸዋል። አሁን ግፋ ቢል የሚያገኙት ብር የሰጡ ሰዎች ናቸው። ሀብታሞች። ከየትም ይምጡ የሚጠየቁትን ነገር ማድረግ ከቻሉ ይሰጣቸዋል። ድሃው ገበሬ ሰርቶ መብላት ልጅ ማስተማር ቤቱን መምራት የሚፈልግ ንፀህ ገበሬ ግን ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ ነው የሚውለው። ወደ ቀን ሰራተኝነት ተቀየረ ማለት ትችላለህ።

ፍኖተ ነፃነት፡- ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር ለሱዳን ተሰጠ የተባለው መሬት ኢትዮጵያኖች ከጥቂት ጊዜ በፊት ወረው የያዙት ነው እንጂ የኢትዮጵያ የነበረ መሬት ለሱዳን አልሰጠንም ብለዋል፡፡

የኢትዮጲያ ህዝብ የማንንም መሬት ወሮ የያዘበት ታሪክ ያለ አይመስለኝም። ግን ዳር ድንበሩን ያስጠብቃል። ለዳር ድንበሩ ሲል ይሞታል። አሁን የሚጠይቁት የዳር ድንበራችን ይከበር ነው። ምናልባት እነሱ

የሰጡት ለራሳቸው የስልጣን ጥቅም ሲሉ ነው። ትናንት የነበረው አሁን እስር ላይ ያለው ወንድሜ አባይ ዘውዴ የተናገረው ነገር አለ። የኢትዮጲያ መሬት በሱዳን እጅ ተይዞ የሚኖረው ህወሐት/ኢህአዴግ እስካለ ብቻ ነው ብሏል። እኔም ዛሬ እሱን ነው የምደግመው። ያ ማንኛውም ሰው አርሶት የሚኖረው ነው። ከብቱን የሚጠብቅበት ነው። ፍየሉን የሚያረባበት ነው። በጉን የሚጠብቅበትነው። ሁሉን ነገር የሚሰራበት ነው። ሰሊጥ የሚያፈስበት ነው። ስለዚህ የማንንም መሬት አይደለም ገበሬው ወሮ የያዘው የኢትዮጲያን መሬት ነው የያዘው። ትላንት የነበሩ የኢትዮጲያ ባለስልጣናት ወይም የሀገር መሪዎች አስከብረውት የነበሩት መሬት ነው። አሁን የተሰጠው። ስለዚህ ይሄ የእነሱ የተሳሳተ መግለጫ ስለሆነ ለስልጣን ሲሉ የሚያደርጉት ስለሆነ ይሄ ውሸት ነው። ሌላ ምንም ነገር የለውም። የሀገራችን መሬት ነው። የኢትዮጲያ መሬት አካል ነው።

ፍኖተ ነፃነት፡- በአካባቢው የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ተሰርተዋል። መንገድ ተሰርተዋል። ጤና ጣቢያ በአግባቡ ተሰርቷል የሚል ነገር ከመንግስት ይቀርባል።

መንገድ ተሰርቷል። ለምሳሌ አንድ ምሳሌ ልስጥህ ጎንደር የተሰራ አስፋልት አለ። እሱ አሁን እየተላጠ ባዶ ነው ያለ ገባህ ሊቀባ ይችላል ቅቡን ግን ቋሚነት የለውም። አሁን ይሄ አራት አመት ምናምን ነው ያገለገለው። ወደ ኮረኮንች መንገድነት ተቀይሯል። ይሄ ለምርጫ ተኮር የሚሰሩ ስራዎች እንጂ እውነት ለሀገር ላለ ህዝብ ይጠቅማል ተብለው የሚሰሩ ስራዎች አይደሉም ወደ ጤና ጣቢያው አካባቢ ልምጣልህ። ጤና ጣቢያው ላይ ግንቦች አሉ። ፎቆች ምናምኖች ተሰርተዋል። ውስጡ ባዶ ነው። ውስጡ የመድሀኒት ዘር የለም። በቂ ባለሙያ የለም። ሁሉ ነገሮች አሁን አድቨርት ነው። አሁን ኮንዶሚኒየም ምናምን የሚባል ነገር አለ። አድቨርት ይሰራልህና ተመሰረተ እንደዚህ አገልግሎት እየሰጠ ነው የሚባለው እንጂ ህብረተሰቡ አሁን ከመንግስት ጤና ጣቢያ ከመገልገል ይልቅ ወደ ግሉ ነው የሚሄድ። ከግሎች ነው የሚሄድ ምክንያቱም የፈለገው ነገር የለም። አሁን ልትመረመር ብትሄድ ፃፋ ፃፍ ያደርግልህና መድሀኒት የለም ይልሃል። ስለዚህ ይሄ ነው። በእርግጥ ግንቦች አሉ። ይገነባሉ የውስጥ እንትናቸው የለም። ሳይንሳዊም ሆነ የተለያዩ መድሃኒቶች ከቦታው የሉም።

ፍኖተ ነፃነት፡- በመጨረሻ ሊያስተላልፉት የሚፈልጉት መልእት ካለ

የማስተላልፈው መልእክት ለመላው ኢትዮጲያ ህዝብ ነው። ለሰሜን ጎንደር ህዝብ ብቻ ወይም ለአማራ ክልል ህዝብ ብቻ አይደለም። ለመላው ኢትዮጲያ ህዝብ የጋራ ችግር ነው ይሄ። የጋራ ጭቆና ነው። የአማራ ህዝብ ሲበደል የሚስቅ ኢትዮጲያዊ ካለ ፣ የትግራይ ህዝብ ሲጨቆን የሚስቅ ኢትዮጲያዊ ካለ የኦሮሞ ተወላጆች ሲሰቃዩ የሚስቅ ኢትዮጲያዊ ካለ ይሄ የዋህነት ነው። ሁላችንም ማንም ሰው ሲሰቃይ የጋራችን ነው ብለን ማሰብ አለብን። ለዘመናት አብረን የኖርነው ከአሁን በፊት እንደዚህ አይነት የስቃይ ዘመን ነበር ብዬም አላስብም። ምክንያቱም ኢትዮጲያዊነታችንን ሊያስረሳ የሚችል ክፉኛ በደል እየተፈፀመብን ስለሆነ ሁላችንም በአንድነት መቆም አለብን። ለነፃነት ለፍትህ የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል ለመደገፍ ከአንድነት ፓርቲ ጎን በመሰለፍ ያለውን ጭቆና በጋራ እናስወግድ

አቶ አወቀ ብርሃን ይባላል፤ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው፡፡ ከሰሞኑ በጎንደር አካባቢ ባሉ የአንድነት አመራሮች ላይ መንግስት የወሰደውን የእስር እርምጃ በማስመልከት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቶ ሲመለስ እሱም እንደትግል አጋሮቹ ሁሉ በመንግስት የደህንነት ሀይሎች ለእስር ተዳርጓል፡፡ ታጋይ አወቀ ብርሃን ከመታሰሩ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ከፍኖተ ነፃነት ጋር የሚከተለውን ቃለምልልስ አድርጓል፤ ተከታተሉን፡፡

በህግ የሚመካ መንግስት ቢሆን ኖሮ የአንድን ተቃዋሚ ሰላማዊ ፓርቲ አባል አፍነው አይሄዱም ነበር

አቶ አወቀ ብርሃን የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር ዞን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ

Page 8: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 848

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ፍኖተ-ነፃነት፡- የአንድ ምርጫ ዴሞክራሲያዊነት የሚለካው በምርጫ ሰሞን በሚኖረው ሁኔታ ብቻ አይደለም፡፡ አሁን የ2007 ዓ.ም ምርጫ 6 ወራት ብቻ ቀርተውታል፡፡ በነዚህ ሁሉ ጊዜያት ኢህአዴግ ሲገርፍ፣ ሲያሳድድ፣ እና ሲገድል ነበር የቆው፤ ተቃዋሚዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ምርጫው ትርጉም ይኖረዋል?

አቶ አስራት፡- ስለ ምርጫ 2007 ዓ.ም ሲነሳ ብዙ በቁምነገር ልናስባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ፡፡ በመጀመሪያ መመለስ ያለበት ጥያቄ አገራዊ ምርጫ ለምንና እንዴት መካሄድ አለበት የሚለው ሲሆን ሁለተኛ የምርጫ ሂደትና ውጤት እንዴት ይታያል ነው፡፡ በግልጽ እንደሚታወቀው ሁሉ በፓርላሜንታዊው ሥራዓቶች የፖለቲካ ፓርቲ የሚመሰረተውና የሚንቀሳቀሰው አብላጫውን የፓርላማ ወንበሮች በመያዝ ለብቻው መንግስት ለመመስረት ነው፡፡ ይህ ካልተቻለ ደግሞ ፈቃደኝነት ካላቸው ሌሎች ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ጋር ዲሞክራሲያዊ ብሄራዊ የጥምረት መንግስት ለመመስረት ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም ሁኔታዎች ካልተቻሉ ግን ፓርቲው ፓርላማ ሊያስገባቸው በቻለው አባላቱ አማካኝነት አገራዊና ሕዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የፓርቲውን አቋምና ዕይታ በማንፀባረቅ የበኩሉን ድርሻና ኃላፊነት መወጣት ይሆናል፡፡ ይህም ካልተሳካ ከፓርላማ ውጭ ሆኖ በተቃዋሚነት መታገል ነው፡፡

በመሠረቱ የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ዋና ዓላማ ሕዝብን የሥልጣኑና የአገሩ ባለቤት ማድረግ ነው፡፡ ከዚህ በመለስ የሚገኙ ለውጦችሳይናቁ ማለት ነው፡፡ እንዳልከው የምርጫ መኖር በራሱ የዴሞክራሲ መኖርን አያረጋግጥም፡፡ የምርጫ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን ሂደቱም በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ነገሩ ሁሉ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው አይደለም፡፡ የት ተፈጨ? እንዴት ተፈጨ?ማን ፈጨው? ወ.ዘ.ተ ጥያቄዎችም መጠየቅ አለባቸውና፡፡ ስለዚህ ምርጫ 2007 ዓ.ም አሻግረን ስናይ ምርጫ 1997 ዓ.ም እና ምርጫ 2002 ዓ.ም መለስ ብለን ማየት ያስፈልገናል፡፡ በአንፃራዊ መልኩ ምርጫ 1997 ዓ.ም ስናይ ጥቂት እውነታዎችን ማየት እንችላለን፡፡ የመድብለ ፓርቲ ስርዓትና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት በመጠኑም ቢሆን መልካም ነበር፡፡የዚህ መገለጫዎቹም የግሉ ነፃ ፕሬስ በጥሩ ሁኔታ ይሰሩ ነበር፡፡ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ታዛቢዎች ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ በፓርቲዎች መካከል ሳንሱር ያልተደረገባቸው ነፃ ክርክሮች በቴሌቪዥን ቀርበዋል፡፡ በአንፃራዊ መልኩ የድምፅ አሰጣጡ ሚስጥራዊነት የተጠበቀ ነበር፡፡ በሌላ በኩል በኢህአዴግ የተጠራው የሚያዚያ 29 ቀን 1997 ዓ.ም ሕዝባዊ ስብሰባና በቅንጅት የተጠራው የሚያዚያ 30 ቀን 1997 ዓ.ም ሕዝባዊ ስብሰባ ሲነፃፀር ሕዝብ ምን ያህል ለለውጥ የቆመና የኢህአዴግን ስርዓት እንደጠላውና እንደማይፈልገው ያሳየበት ነበር፡፡ በውጤቱም ተቃዋሚ ኃይሎች ቅንጅትና ህብረት ድል ያስመዘገቡበት ቢሆንም ኢህአዴግ መራሹ መንግሥት የሕዝብን ውሳኔ በኃይል ቀልብሶ ሥልጣኑን የተቆጣጠረበት ሁኔታን ፈጥሯል፡፡

ከምርጫ 1997 ዓ.ም ኢህአዴግ

የተማረው ነገር ቢኖር የኢህአዴግ መንግስት የመጨረሻ የሥልጣን ዋስትናው የሚመነጨው ከሕዝብ ድምጽ ሳይሆን ከጦር ኃይሉ መሆኑን ነው፡፡ ይህን መሠረት አድርጐ በመጠኑም ከፈት ወይም ገርበብ ብሎ የነበረውን የዲሞክራሲ በር ሙሉ በሙሉ በሚያሰኝ መልኩ መዝጋት ነበር፡፡

ፍኖተ-ነፃነት፡- ለዚህም የሚሆኑ ማሳያዎች ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ?

አቶ አስራት፡- አዎ፣ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያክል

1.በገዥው ፓርቲና በመንግስት መዋቅር መካከል ያለው ልዩነት ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም የዜግነት መብትን ወደ ኢህአዴግነት መብት ለወጠው፡፡

ኢትዮጵያውያን የሥራ ዋስትናቸው የዕድገት ዋስትናቸው የትምህርት ዕድል ወ.ዘ.ተ ማግኛቸው በዜግነትና በችሎታ ሳይሆን በኢህአዴግነት ሆነ፡፡ ለዚህም ነበር በ1997 ዓ.ም 760,000 የነበረው የኢህአዴግ አባላት ብዛት በ2002 ዓ.ም 5,000,000 የሆነው የአባላት ዕድገቱ 546% ነበረ፤

2.በመላ አገሪቱ የፍርሃት ድባብ እንዲሰፍን ተደረገ፤

3.መራጩን ሕዝብ 1ለ5 ጠረነፈ፤4.የዲሞክራሲ ስርዓት መገለጫ

የሆኑ ተቋማትና ሥርዓቶችን የሚያፈርሱ ሕጐችንና ደንቦችን ደነገገ፡፡ ለምሳሌ ያህል የፀረ ሽብርተኛ ሕግ፣ የሚዲያና የመረጃ ነፃነት ሕግ፣የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሕግ፣ የሲቪል ማህበራት ሕግን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በአጠቃላይ አሳውን

ለመግደል ውሃውን ማድረቅ እንደሚባለው ማለት ነው፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ሁኔታ ነበር የ2002 ዓ.ም አገር አቀፍ ምርጫው የተካሄደው፡፡ የመድብለ ፓርቲ እና የዴሞክራሲው ስርዓት ሙሉ በሙሉ በመጥፋቱ በውጤቱ ኢህአዴግ በ99.6% አሸናፊ ነኝ አለ፡፡ የምርጫውን ውጤት ሙሉ በሙሉ ዘረፈው፤ ነጠቀ፡፡

ፍኖተ-ነፃነት፡- በጉዳይ ላይ ነፃ ተቋማት የሰጡት ግምገማ ለአብነት ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ?

አቶ አስራት፡- ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አንድ አብነት የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ሪፖርት ነው፡፡ ልጥቀስልህ፡-

“. . . ምርጫው ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያላሟላ፣ በጫና የተካሄደ፣

ታዋቂው ፖለቲከኛ እና የአንድነት የቀድሞ ዋና ፀሀፊ አቶ አስራት ጣሴ ቀጣዩን ምርጫ በተመለከተ፣ አዲስ ስለተመሰረተው

ትብብር፣ አንድነትና መድረክ ስላሉበት የግንኙነት ሁኔታ፣ ስለምርጫ ቦርድና ፓርቲያቸው አንድነት የወቅቱ ውዝግብ

እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት ከባልደረባችን ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ መልካም ንባብ፡-

Page 9: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

9ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

እኩል የመጫዋቻ ሜዳ ያልነበረው፣ ገዥው ፓርቲ የተቆጣጠረውን የመንግሥት መዋቅርና የአገር ሀብት አለአግባብ ጥቅም ላይ ያዋለበት፣ የምርጫ ሂደቱም ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ቆጠራው ችግር የነበረበት፣ በአጠቃላይ ግልጽነትና ተኣማኒነት የጐደለው፣ ፉክክር ባልተደረገበት

የተካሄደ ምርጫ” ሲል ነበር የገለፀው፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ በአውሮፓ ህብረት የተጠቀሰውን የምርጫ ታዛቢዎችን ሪፖርት አስመልክቶ በወቅቱ የተናገሩት ሲጠቀስ ደግሞ

“ወረቀትና ቀለም ያለው ሰው የፈለገውን መለቅለቅ ይችላል፡፡ በወረቀት ላይ የተለቀለቀ ቀለም ሁሉ ግን ፋይዳ አለው ማለት አይደለም፡፡ ቆሻሻ መጣያ ባስኬት ውስጥ የሚጣል እንጂ ከዚህ በላይ ትኩረት የሚሰጠው አይደለም” ብለው ነበር፡፡

እንግዲህ እሳቸው ዛሬ በሕይወት ባይኖሩም የእሳቸውን ራዕይና እምነት እናስቀጥላለን በሚል ኢህአዴግ እየተመራን ወደ ምርጫ 2007 ዓ.ም እንገባለን ስንል ያለውን አደጋና ችግር ሙሉ በሙሉ እንረዳለን፤ እናውቃለንም፡፡ ሆኖም አንድነት እንደ ፓርቲ የምርጫ ፓርቲ ነው፡፡ ቢሮዎች ከፍቶ አባላት አደራጅቶ የሚንቀሳቀሰው በምርጫ ተሳትፎ የአገሪቱንና የሕዝብን እጣ ፈንታ ለመለወጥ ካልሆነም ለማሻሻል ነው፡፡ በመሆኑም በመርህ ደረጃ በምርጫ 2007 እንሳተፋለን ብለን አቅርበናል፡፡ለዚህም ተግተን እንሰራለን፡፡ በመሆኑም ምርጫ 2007 ዓ.ም ነፃ ፍትሀዊ ሕጋዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በሕዝብ ተቀባይነት ያገኘ እንዲሆን ኃላፊነት በተሞላው መንገድ ተግተን እንሰራለን፡፡ ሁሉም መንገድና ስልት ተሞክሮ ካልተሳካ ግን ዴሞክራሲያዊ ምርጫን “የእርሶዋም ሞከሩት” ስራ አድርገን አናየውም፡፡ ወይም ዲሞክራሲያዊ ምርጫን እንደ ታላቁ አገራዊ ሩጫ አናየውም፡፡ ይህም በመሆኑ በመጨረሻ ደቂቃም ቢሆን ከምርጫው እራሳችንን አናገልም ማለት አይደለም፡፡ ይህን አስተያየቴን ፓርቲዬ ሙሉ በሙሉ ላይጋራው ይችል ይሆናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ አንድ ቁምነገር አንስቼ ይህን ጥያቄ ብደመድመው እወዳለሁ፡፡ የብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የ2002 ዓ.ም ምርጫን አስመልክቶ ባለ 143 ገጽ ጥናት አሰጠንቶ ለፓርቲዎች አቅርቦ ነበር፡፡ ኢህአዴግን ጨምሮ 50 የፖለቲካ ፓርቲዎች መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም በግዮን ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ጥናቱን ገምግመው ባለ 14 ገጽ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የሪፖርቱ ቁልፍ መደምደሚያ የሚከተለው ነው፡፡ “የ2002 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ በዘመነ ኢህአዴግ ከተካሄዱ ምርጫዎች ሁሉ የከፋና የገዥ ፓርቲውን አምባገነንነት ያረጋገጠ ሆኖ አልፋል” ይላል፡፡

ፍኖተ-ነፃነት፡- በአሁኑ ወቅት ምርጫውን በተመለከተ ሊደረግ የታሰበ ጫና እንዲመራ የተመሰረ ትብብር አለ፤ እንደት ያዩታል?

አቶ አስራት፡-ትብብርለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ የሚለው አዲሱ ስብስብ ከጥቅምት 15 ቀን 2005 ዓ.ም አዳማ ላይ ከተመሰረተው የ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ የወጣ አካል ነው፡፡እኔ የ33ቱ ፓርቲዎችን ለረጅም ጊዜ በስብሳቢነት የማወቀው ስለሆነ በድፍረትና በልበሙሉነት ስለ ስብስቡ ለመናገር እችላለሁ፡፡ለስብስቡ ከፍተኛ አክብሮትና አድናቆት አለኝ፡፡ ከፍተኛ አገራዊና ሕዝባዊ ራዕይ ያለው ስብስብ ነው፡፡ከአንድነት ለዲሞክራሲና ፍትሕ ፓርቲ ጋር በትብብር ሲሰራ የቆዬ ነው፡፡ በብዙ አገራዊና ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫዎች አውጥተናል፤ ቃለምልልስ አደርገናል፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች አድርገናል፤ ሠላማዊ ሰልፎችን በአዲስ አበባና በክልሎች አካሂደናል፡፡ ከተወሰኑ ፓርቲዎች ጋር የውህደት ውይይት አድርገናል፡፡ በተወሰነ ደረጃም ከፍተኛ መግባባት ላይ ደርሰን ነበር፤ ምንም በመጨረሻ ሳይሳካ ቢቀርም፡፡ አንድነት ከስብስቡ ጋር አብሮ እየሠራ ነበር፤ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ በተፈጠረው ችግርና በኋላ ላይም በተደረገው የአመራር ለውጥ ምክንያት ክፍተት በመፈጠሩ የትብብሩ አካል ሆኖ ሳይፈርም ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ

እንደ እኔ እምነትና ተስፋ አንድነት በአጭር ጊዜ ውስጥ በጉዳዩ ላይ መክሮ ትብብሩን ይቀላቀላል ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለትብብሩ ያለኝ አቋም ሁሉም የአንድነት አመራርና አባላት ይጋሩታል ማለት ግን አይደለም፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- ሰሞኑን አንድነት እና መድረክ ውዝግብ ውስጥ ናቸው ተብሎ ተፅፏል፤ ለመሆኑ ያለው ሁኔታ ምን ይመስልል?

አቶ አስራት፡- የመድረክና የአንድነት ግንኙነት አስመልክቶ ብዙ ማለት ይቻላል፡፡ጥያቄው በአጭር ቃለምልልስ የሚዳሰስ አይደለም፡፡ መጻፍ ሊጻፍበት ይችላል፡፡ ሆኖም ለቀረበው ጥያቄ ከብዙ በአጭሩ መናገር ይቻላል፡፡

አንድነት ወደ መድረክ ሲገባ ብዙ ውድ ዋጋዎችን ከፍሏል፡፡ በፓርቲው ውስጥ አንጃ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ህዝብን ያሳዘኑ ድርጊቶችም ተከስተው ነበር፡፡ ሕብረ ብሔራዊ ፓርቲ በብሔረሰብ ከተደራጁ ፓርቲዎች ጋር ቅንጅት መፍጠር የለበትም የሚልም እምነት ተራምዶ ነበር፡፡ ሆኖም አብዛኛው አባላት አንድ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ እስከሆነ ድረስ በብሔረሰብ ቢደራጅም መብቱ ነው ብሎ ስለሚያምን ከዚያም ባሻገር ሁልጊዜ ተለያይቶና ተኮራርፎ መኖር ተገቢ አይደለም፤ ለአገሪቱ አንድነት ሰላምና ዕድገት ጐጂ በመሆኑ ይህን በመካከላችን የተፈጠረውን ልዩነትና ሸለቆ የአንድነት ድልድይ ፈጥሮ መገናኘት ያስፈልጋል በማለት መድረክን መሠረትን ተቀላቀልን ረጅም ጉዞም አብረን ተጉዘናል፡፡ ከእነ ውጣ ውረዱም ብዙ መልካም ውጤቶችንም አስመዝግበናል፡፡

ዛሬ አንድነት ፓርቲ ከመድረክ ቢወጣም በወቅቱ የመድረክ አባል መሆናችን ትክክልም ተገቢም ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ መድረክ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ጥሩ ጅማሮና ጐጆ በመሆኑ ነገም እንደገና እንገናኛለን፤ አብረን እንሆናለን ብዬ አምናለሁ፡፡ በእኔ እምነት አንድነት የወጣው ተገዶ እንጂ በፍቃዱ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው መድረክን አስመልክቶ አንድነት ኮሚቴ አቋቁሞ ግምገማ አካሄዷል፡፡ የኮሚቴውን አባልም ስለ ነበርኩ ሁሉንም በትክክል አውቀዋለሁ፡፡ በመድረክ ውስጥ የአንድነት ተወካይ ሆኜ ረጅም ጊዜ ስለ ሠራሁ መድረክን አውቀዋለሁ፡፡ ከእነ ብዙ ችግር ለመድረክ አደላለሁ፤የተለየም ፍቅር አለኝ፤ በዚህም ብዙ ጊዜ ትችትም ወቀሳም ደርሶብኛል፤ዛሬ ላይ ሆኜ ስናገር ግን ጥቅምት 29 ቀን 2007 ዓ.ም የተካሄደው 10ኛው የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ የአንድነት እግድ እንደገና እንዲቀጥል ማድረጉ እጅጉን አሳዝኖኛል፤ አቁስለኛልም፡፡ ድርጊቱም የፖለቲካ ደባ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔ ከጉባኤው እጠብቅ የነበረው ጉባኤው የ2007 ዓ.ም ምርጫ የቀረው በዛ ቢባል 7 ወራት ከመሆኑ አንፃርና ከምርጫ ቦርድ የምርጫ ሠሌዳ አንፃር ፓርቲዎች ምልክት የመውሰጃቸው ጊዜ ከህዳር 15 እስከ 30 ከመሆኑ አንፃር በልበ ሰፊነት ከአገራዊና ሕዝባዊ ራዕይና ተስፋ አንፃር አይቶ (ለአግድ የሚያበቃ ክፋት የለም እንጂ)መጠነኛ ስህተቶች ቢኖሩም እንኳን በአንድነት ላይ የተጣለው እግዳ ያነሳል የሚል ነበር፡፡ ሆኖም አለመታደል ሆኖ ጉባኤው ታሪካዊ ስህተት ፈጽሟል፡፡

1., አንድነት እንደ ፓርቲ አባላቱንና ደጋፊዎች አሳዝኖ በቴክኒክ ስህተት ወይም ምክንያት ብቻ ከምርጫ 2007 ዓ.ም እራሱን ማስወጣት ስለሌበት፣

2. .የአንድነት የ2007 ዓ.ም ምርጫ መግባት ወይም አለመግባት ከአባልነት በአገደው መድረክ በጐ ፍቃድ መሆን ስለሌለበት ጥቅምት 30 ቀን የተሰበሰበው የአንድነት ብሔራዊ ም/ቤት ከመድረክ አባልነት እራሱን ማግለል አማራጭ የሌለውን ክፉ ምርጫ መርጧል፡፡ በዚህም

ክፉኛ አዝኛለሁ፤ሆኖም የሕዝብና አገር ጉዳይ መቼም ረፍት ስለማይሰጠን ነገም ሆነ ተነገወዲያ ከዚያም ቢዘል በቅርብ ጊዜ ሁላችንም ወደ ህሊናችን ተመልሰን አገርን ለማዳን ሕዝብን ለመታደግ አብረን መስራትን እንጀምራለን ብዬ አምናለሁ፡፡ ዛሬም ቢሆን በማንኛውም መመዘኛ አንድነት ለመድረክ መድረክ ለአንድነት ያለው አክብሮትና መተሳሰብ ይበላሻል ብዬ አላስብም፤አላምንም፡፡ ለጊዜውም ቢሆን እንደ ፓርቲ እንደ ስብስብ ተለያየን እንጂ እንደ ሰዎች ግን ወንድማማችነታችን ጓደኝነታችን እንደ ወትሮ ሁሉ ይቀጥላል የሚል ሙሉ ተስፋና እምነት አለኝ፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- አንድነት ቀድሞውን ፕሬዚዴንት ኢ/ር ጊዛቸውን በሌላ አመራር ተክቷል፡፡ ፓርቲውን ፕሬዚዴንቱ በፈቃዳቸው ነው የለቀቁት ቢልም ምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ገጥማችኋል ተብሎ ይነገራል፤ ለመሆኑ ያለው እውነታ ምንድነው?

አቶ አስራት፡-በአንድነት ውስጥ በቅርብ ጊዜ በተደረገው የፕሬዝዳንትና የአመራር ለውጥ ምክንያት በብሔራዊ የምርጫ ቦርድና በአንድነት መካከል የደብዳቤዎች ልውውጥ መደረጉ እውነት ነው፡፡ ይህን አስመልክቶ በብዙሃን መገናኛ የሚዘገቡ ዘገባዎች ሕዝብን ማሳዘናቸውና ግራ ማጋባታቸውም እውነት ነው፡፡ በምሳሌነት ብጠቅስ ህዳር 3 ቀን 2007 የወጣው የሰንደቅ ጋዜጣ በፊለፊት ዓምዱ የዶ/ር መረራ ጉዲና ፎቶግራፍ ጐን “የአንድነት እና መድረክ ውዝግብ ቀጥሏል” ይላል፡፡ አንድነት ግን በጥቅምት 30 ውሳኔው ከመድረክ እራሱን ማግለሉን ሲገልጽ የአንድነትና መድረክ ውዝግብ መፈታቱን መቋጨቱን ነው የሚያውቀው፡፡ ዶ/ር መረራ ጉዲና በዚሁ ጋዜጣ ገጽ 3 ላይ አንድነት ከመድረክ ወጥቻለሁ ማለቱን አለመስማታቸውን ገልጸው እውነትም (አንድነት እንዲህ ዓይነት ውሳኔ አሳልፎ ከሆነ ጥሩ መሆኑን ተናግረዋል ይላል፡፡ እንዲህ ከሆነ የአንድነትና መድረክ ውዝግብ ቀጥሏል ማለት ጋዜጣውን ትዝብት ላይ የሚጥል ነው፡፡

የምርጫ ቦርድን ደብዳቤዎችና ከፓርቲው የተሰጡትን መልሶች ተመልክቻቸዋለሁ፡፡ በመሠረቱ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲው ማብራሪያ ነው የጠየቀው፤ ፓርቲውም ለጥያቄዎቹ መልስ ሰጥቷል፡፡ እርግጥነው ታህሳስ 19 እና 20 ቀን የተካሄደው የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤና የተሻሸለው ሕገ ደንብና ፕሮግራም ለምርጫ ቦርድ የተላከው ዘግይቶ ነው፡፡ ሆኖም ለምርጫ ቦርድ ከደረሰው ከ75 ቀናት በላይ ሆኖታል፡፡ በምርጫ ቦርድ ሕግ ደግሞ ቦርዱ መልስ መስጠት ያለበት በ30 ቀናት ነው፡፡ መልስ ካልተገኘ ደግሞ ሰነዱ ተቀባይነት እንዳገኘ ይቆጠራል፡፡ ሆኖም ከምርጫ ቦርድ ጋር በተደረገው ግንኙነትና ውይይት መሠረት ጉዳዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት እንደሚያገኝ ነው የማምነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ምርጫ ቦርድ የሚሰጠውን ውሳኔ መሠረት አድርጐ አንድነት ችግሮችን ፈቶ ወደፊት ለመራመድ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅትና መሰናዶ ስለአለው ምንም የሚያሳስብና የሚያስጨንቅ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡

አንድነት እንደ ፓርቲ ብዙ ተግዳሮቶችና ፈተናዎች ቢኖሩበትም ተስፋውና አቅሙም ታላቅ ነው፡፡ ጥያቄው ያለው አመራርና አባላቱ ችግሮችን ፈተው እንዴት ፓርቲውን ወደፊት ያራምዱታል የሚለው ነው፡፡ ይህ በተግባር ወደ ፊት የሚታይ ቢሆንም ፓርቲው ያለው ተስፋና አቅም ግን ትልቅ መሆኑን አምናሁ፡፡ለዚህም እግዚአብሄር ይርዳን እላለሁ፡፡

ፍኖተ ነፃነት፡- አመሰግናለሁ፡፡

አቶ አስራት፡- እኔም ዕድሉን ስለሰጣችሁኝ አመሰግናለሁ፡፡

ዛሬ አንድነት ፓርቲ ከመድረክ ቢወጣም በወቅቱ የመድረክ አባል መሆናችን ትክክልም ተገቢም ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

መድረክ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ጥሩ ጅማሮና ጐጆ በመሆኑ ነገም እንደገና እንገናኛለን፤ አብረን እንሆናለን ብዬ አምናለሁ፡፡

በእኔ እምነት አንድነት የወጣው ተገዶ እንጂ በፍቃዱ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው መድረክን አስመልክቶ አንድነት ኮሚቴ አቋቁሞ ግምገማ አካሄዷል፡፡ የኮሚቴውን አባልም ስለ ነበርኩ ሁሉንም በትክክል አውቀዋለሁ፡፡በመድረክ ውስጥ የአንድነት ተወካይ ሆኜ ረጅም ጊዜ ስለ ሠራሁ መድረክን አውቀዋለሁ፡፡ ከእነ ብዙ ችግር ለመድረክ አደላለሁ፤የተለየም ፍቅር አለኝ፤ በዚህም ብዙ ጊዜ ትችትም ወቀሳም ደርሶብኛል

Page 10: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 8410

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ከቤቴ ወጥቼ ብዙም ሳልጓዝ አንድ ረዘም

ያለ ሰልፍ ተመለከትኩ። ብዙውን ጊዜ

ግርግር ባለበት አካባቢ ማለፍ ባልወድም

ይህ ግርግር ግን ቀልቤን ሳበው። በርካታ

ወጣቶች ወረቀትና ካኪ ፖስታ ይዘው

እዚህም እዛም ይራወጣሉ። ይህን

የወጣቶቹን ሩጫ ጠጋ ብዬ ሳስተውል

የግርግሩ ምክንያት ተገለጠልኝ። በተንዳሆ

ስኳር ፋብሪካ የስራ ማስታወቂያ አውጥቶ

ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ። ብዙውን ጊዜ

የዚህ አይነት ግርግር መስሪያ ቤቱ የስራ

ማስታወቂያ ሲያወጣ ለመታዘብ ችያለሁና።

አይኔ ሰልፍ ይዘው ወደ ቆሙት ወጣቶች

ላይ እያማተረ ሳለ አንድ የማውቀው

ፊት አየሁ- የዩኒቨርሲቲ ወዳጄ ነው።

እንደተገረምኩ ፊቴ እንዳያሳብቅብኝ

በመስጋት ሰላምታ ሰጠሁት። ይህ ሁሉ

ሰው በዚህ መስሪያ ቤት ደጃፍ ላይ የተገኘው

አንድ የስራ ማስታወቂያ ወጥቶ እንደሆነና

ስራውም በአፋር ክልል ተንዳሆ እንደሆነ

አያይዞ አጫወተኝ። “ታዲያ አንተም

ልታመለክት ነው ወይ” ስል ጥያቄዬን

ሰነዘርኩለት፡፡ በአዎንታ ራሱን እየነቀነቀ

“እዛ መሄዱ ሳይሻል አይቀርም አለኝ።”

መልካም እድል ተመኝቼ ተለየሁት። ልጁን

ከተለየሁት በኋላም ቢሆን በአእምሮዬ

ይህ ሁሉ ወጣት ወደ እዛ ምቹ ያልሆነ

ሞቃታማ አካባቢ ለማምራት ለምን

ተገደደ? ፣ የወጣት ስራአጦች ቁጥር

ይህን ያህል የተበራከተበት ምክንያት ምን

ይሆን?፣ ይህ ሁሉ የተማረ ወጣትስ ስራ

ለማግኘት ይህን ያህል መሰቃየት አለበት

ወይ? ፣ መንግስት እውነት ለወጣቱ ደንታ

አለው? ፣ወጣቱስ በመማሩ ምን ተጠቀመ?

የሚሉና አያሌ ጥያቄዎች መመላለስ ያዙ።

ወጣት ስራ አጦች

መንግስት ለወጣቱ ስራ አጥነትን ከመቀነስ

አኳያ የተለያዩ ዘዴዎችን መንደፉን

ይናገራል። ከእነዚህም መሃል ወጣቱን

በተለያዩ የስራ መደቦች በማደራጀት ኮብል

ስቶን ድንጋይ ማንጠፍና የመሳሰሉትን

ስራዎች ፈጥሬያለሁ ሲል ይደመጣል።

ከዛም በተጨማሪ ወጣቱ የስራ አጥነት

ችግሩን ለመቅረፍ መንግስትን ብቸኛው

ፍትህ ሚኒስቴር ሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ባወጣው መግለጫ “ክስ መስርቼባቸዋለሁ” ባላቸው ፋክት፣ አዲስ ጉዳይ፣ ዕንቁ፣ ሎሚ፣ ጃኖ እና አፍሮታይምስ መፅሔቶች እና ጋዜጣ ላይ በፍርድ ቤት ክስ ሳይመሰረት በቅድሚያ በሚዲያ ማሳወቁ የነፃውን ፕሬስ አባላት ለማሸማቀቅ እና ከህትመት ለማስወጣት መሆኑ ድርጊቱ ያሳብቃል፡፡

ኢህአዴግ ነፃ ጋዜጠኞችን ማሳደድ ዋነኛ መርሆው አድርጎ በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ የጀመረው ከ1997 ዓ.ም ምርጫ ማግስት ጀምሮ የነበረ ሲሆን ይህም ዜጎችን መረጃ የማግኘት ህገ-መንግስታዊ መብታቸውን በመፃረር አፍኖ ለመግዛት የሚያደርገውን ኢ-ህገ-መንግስታዊ ድርጊቱን በአስቸኳይ እንዲያቆም ቢጠየቅም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የግሉ ፕሬስ አባላት ላይ አሁን ተመሰረተ የተባለው ክስ አንድነት በሚቃወመው የፀረ ሽብርተኛ ህግ የተቀነቀነ በመሆኑ የክሱ ውጤት ምን ሊሆን

አማራጭ አድርጎ መመልከት እንደሌለበት

በመንግስት በኩል ሲነገር እንሰማለን።

መንግስት በዚህ በኩል እንደ መፍትሔ

የሚያቀርበው ወጣቱ ስራ መፍጠር

እንዳለበት ነው። ብዛትን እንጂ ጥራትን

መሠረት ያላደረገ የትምህርት ፖሊሲን

የሚከተል መንግስት ባለበት ሀገር ወጣቱ

ስራ ፈጣሪ እንዲሆን መጠበቅ አስተዛዛቢ

ነው። ጥራቱን የጠበቀ የትምህርት ስርዓት

በሌለበት ሂደት ውስጥ አልፎ ስራ መፍጠር

ሳይሆን ስራም ተወዳድሮ ማግኘት አዳጋች

ነው። ምክንያቱም በርካታ ወጣቶች የይድረስ

ይድረስ ተምረው ከኮሌጅና ከዩኒቨርስቲ

ተመርቀው በሚወጡበት ጊዜ ስራ ቀጣሪዎች

በርካታ አማራጮች ይኖራቸዋልና። ከዛም

በተረፈ በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ

ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚታየው የስራ

ቅጥር ትክክለኛውን ሂደት ያላማከለ መሆኑ

ወጣት ስራ አጦች የሚገጥማቸው ሌላኛው

ተግዳሮት ነው። መንግስት ለወጣቱ ግድ

እንደሚሰጠውና የወጣቱን ችግር ለመቅረፍ

ተደጋጋሚ ሙከራ እያደረገ መሆኑን ቢገልፅም

ቃሉና ተግባሩ ለየቅል ናቸው። መንግስት

ወጣቱን የሚፈልገው፣ ወጣቱን ለራሱ

ዓላማ ለማዋል እንጂ የራሱ ሀገራዊ አላማ

ይዞ እንዲንቀሳቀስ በጭራሽ አይፈልግም።

የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለው የራሳቸውን

ዓላማ ቀርፀው የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ

የሀይል እርምጃ ይወስዳል። ለአብነት ያህል

በቅርቡ በዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ላይ የወሰደውን

የእስር እርምጃን ማንሳት ይቻላል። ወጣቶቹ

የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለው ተነስተው

ወጣቱንም ሆነ ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል

ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሞክረዋል። ሆኖም

በዚህ ድርጊታቸው የተበሳጨው መንግስት

እነሱን በሽብርተኝነት ከሷቸው በወህኒ

ቤት እያማቀቃቸው ይገኛል። መንግስት

ለወጣቱ ግድ እንደማይሰጠው ከዚህ በላይ

ማሳያ ማቅረብ የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም።

ስለወጣት ስራ አጥነት ይህን ያህል ካልኩ

ወጣቱ ይህን ችግር ለመቅረፍ ምን ማድረግ

እንደሚጠበቅበት የተወሰኑ የመፍትሔ

ሀሳቦችን በማንሳት ፅሁፌን ልቋጭ።

በእኔ እምነት ይህን ችግር ለመቅረፍ ዋነኛውን

መፍትሔ መስጠት የሚችለው ወጣቱ እራሱ

እንደሆነ ማመን ይኖርበታል። ከራሱ በስተቀር

በመንግስትም ሆነ በየትኛውም አካል ላይ

ተስፋ ማድረግ አይኖርበትም። ካመነ ደግሞ

ለሚያምንበት ነገር ዋጋ መክፈል ይኖርበታል!

ለውጡን ከፈለገ ለውጡ ያለመስዋትነት

እንደማይገኝ ማወቅ ይኖርበታል።

ለውጡን ለማስጀመር ደግሞ ወጣትነት

ሀይል መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል።

ወጣቱ ወጣትነት ሀይል መሆኑን ተገንዝቦ

በሀገሩ ጉዳይ ባይተዋር እንዲሆን ያደረገውን

ስርዓት መገዳደር አለበት። ድምጹን ከጫፍ

እስከ ጫፍ ማሰማት ይኖርበታል። የወጣቱ

ስራአጥነትም ሆነ ሌሎች ችግሮች ሊፈቱ

የሚችሉት የተረጋጋች ሀገርና ወጣቶቹን

ለመጥቀምም ሆነ በወጣቶቹ ለመጠቀም

የሚያስብ መንግስት ሲኖረን ነው። እናም

ወጣቱ በሀገሩ ተጠቃሚ እንዳይሆን

ያደረገውን እንቅፋት ማስወገድ ይኖርበታል።

እንቅፋቱ እንዴት ይወገድ?

እንቅፋቱ በሀገራችን የሚገኘው አምባገነናው

ስርአት ነው። ከላይ እንዳስቀመጥኩት ይህ

ስርአት እስካለ ድረስ ወጣቱ ከሀገሩ ተጠቃሚ

ሊሆን አይችልም። ሀገሪቷም ከወጣቶቿ

ተጠቃሚ ልትሆን አትችልም። እንቅፋቱን

ለማስወገድ የመጀመሪያው እርምጃ

ሊሆን የሚገባው መስዋትነት ለመክፈል

በአእምሮ ደረጃ ዝግጁ መሆን ነው። ለውጥ

ያለመስዋትነት አይገኝምና። ዝግጁ መሆን

ብቻውን ግን በቂ አይደለም። ከምንም

በላይ በውስጣችን ፅናት ሊኖረን ይገባል።

መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ እንድንሆን

የሚያደርገን ፅናት ነውና። ከዛም በተጨማሪ

ለራሳችን ችግሮች ከራሳችን ውጪ

መፍትሔ ሰጪ አካል እንደሌለ መገንዘብ

ይኖርብናል። ከላይ ባስቀመጥኳቸው

ነጥቦች ከተስማማን ቀጣዩና ዋነኛው ነገር

እንቅፋቱ በምን አይነት መንገድ ይወገድ

የሚለው ነው። በእኔ እምነት በምናምንበትና

ዋጋ ለመክፈል በተዘጋጀንበት የትግል መስክ

በመሳተፍ ማስወገድ ይቻላል ባይ ነኝ።

ዋናውና ወሳኙ ነገር ግን በምናምንበትና

መስዋትነት ለመክፈል በተዘጋጀንበት

የትግል መስክ ተሳትፎ በማድረግ እንቅፋቱን

ማስወገድ ነው። ስለሆነም እያንዳንዱ

ወጣት ኢትዮጲያዊ ራሱን ለትግል

ዝግጁ በማድረግ እንቅፋቱን በማስወገድ

የሀገሩ ባለቤት መሆን ይችላል እላለሁ።

ተስፋ ያጣው ወጣት

ጋዜጠኞችን ማሳደድ ይቁም! ኢቮላን መከላከል ይቅደም!

ዘካርያስ የማነብርሃን

እዩኤል ፍስሃ ዳምጠው

እንደሚችል ስጋት ያለን ሲሆን ጉዳዩ ከምርጫ መቃረብ ጋር በተያያዘ መልኩ ኢህአዴግ የሚያራምደው ‹‹ምርጫ መጣ ነፃ ፕሬስ ውጣ›› ዘመቻ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ከእዚህ የክስ መግለጫ በኋላ ማተሚያ ቤቶች ይደርስብናል ባሉት ጫና ምክንያት ማተም ባለመፈለጋቸው መፅሔቶችና እና ጋዜጦች ከህትመት ውጪ ሆነዋል፡፡

የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አዘጋጆችም ከሀገር ለመሰደድ በቅተዋል፡፡ ‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› እንደተባለው ይህ ሁሉ ማዋከብና አፈና ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ ወቅት የሚፈጽመው እንደለመደው ምርጫውን በአፈና ስር አድርጎ ያለውድድር በሕዝብ ድምጽ ለመቀለድ ነው፡፡

ይህ አገዛዝ የመረጃ ጠላት መሆኑ እና ነፃ አስተሳሰብን መርገጡ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ በየእስር ቤቱ ያጎራቸውን ጋዜጠኞች፣ ብሎገሮች፣ የፓርቲ አባላትና መሪዎችን እንዲፈቱ የእስረኞች ሰብአዊ መብት እንዲያከብር ሁሌ እንጠይቃለን፤ እስር መፍትሔ ስለማይሆን ለብሔራዊ መግባባት መንግስት ቅድሚያ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

Page 11: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

11ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ሁለቱ ተከራካሪዎች

አቤኔዘር ወደ ጐልማሳነት እያመራ ያለ ወጣት ነው፡፡ ገረሱም ወጣት ነው ግን ለጐልማሳነት ብዙ ይቀረዋል፡፡ ሁለቱም የተማሩ ናቸው፡፡ በሶሻል ሚዲያ ላይ ነው ያገኘኋቸው፡፡ ኢህአዴግ ነፃ ሚዲያውን ጨርሶ እየዘጋው በመሆኑ፣ የተማረው ሕዝብ ፊቱን ወደ ኢንተርኔት እያዞረ ነው፡፡

ገርሱ በዓለፉት ሥርዓቶች የብሄር ጭቆና ነበር፤ በተለይ ኦሮሞ ክፉኛ ተጨቁኖአል ባይ ነው፡፡ ኦሮሞ በኦሮሞነቱ፣ በባህሉ፣ በቋንቋውና በአጠቃላይም በማንነቱ እንዳይኰራ ተደርጐአል፤ ከዚህም በላይ በኢኮኖሚ ጥቅም፣ በሥልጣን ክፍፍል . . . አድልኦ ተደርጐበታል፤ ይላል -ገረሱ፡፡ አቤነዘርም እነዚሁኑ ታሪካዊ ክስተቶች ከሞላ ጐደል እውነት ናቸው ብሎ ተቀብሎ፣ ሌሎችም እንዲቀበሉት ይማፀናል፡፡ ሁለቱም ወጣት “ተከራካሪዎች” መፍትሄውንም በተመለከተ ተመሳሳይ አቋም አላቸው፡፡ መፍትሄውም ለእያንዳንዱ ብሔር የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን መስጠት ነው፡፡

አቤነዘርና ገረሱ ሁለቱም ብሩህ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች ናቸው፤ የንግግር ችሎታቸውም የሚደነቅ ነው፤ ግን የቀሰሙትን ዕውቀት በሚገባ የመረመሩት አይመስልም፡፡ በኢትዮጵያ ኦሮሞ ወይም አማራ የሚባል ንፁሕ ዘር የለም! ኦሮሞ አፍ መፍቻ ቋንቋው ኦሮምኛ የሆነ ማህበረሰብ ነው፡፡ አማራም አፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ የሆነ ማህበረሰብ ነው! አማራ የሚባል ንፁህ ዘር የለም! አማራ የአገው፣ የቤጃ፣ የኩናማ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ . . ክልስ ዝርያ ነው! እነዚህ የኢትዮጵያ ነገዶች እንደመሆናቸው፣ ሲካለሱ፤ ሲዋለዱ ሲዋሀዱ ዘራቸው ኢትዮጵያዊነት ይሆናል፡፡ኢትዮጵያዊነት ክልስ ዘር ነው፡፡ ዜግነት ብቻ አይደለም፡፡ በመሆኑም. ኢትዮጵያዊነት ዜግነትም፣ ዘርም ነው፡፡ በተመሳሳይ ኦሮምም የደቡብ ነገዶችና የአማራ ክልስ ዘር ነው በመሆኑም ዘሩ ኢትዮጵያዊነት ነው፤ እንደ አማራ ክልስ ዘር ነው፡፡

በኢትዮጵያ ብሔር አለ እንዴ? ኦሮምኛ የጋራ ቋንቋው (አፍ መፍቻ ቋንቋው) የሆነ ማኅበረሰብ አለ፤ ግን የሰፈረበትና የመኖሪያ አካባቢው መላ ኢትዮጵያ ነች! ኦሮሞ በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ በምዕራብ ኢትዮጵያ፣ በደቡብና በመሀል ኢትዮጵያ ሠፍሮአል! በመሆኑም፣ የኦሮሞ መኖሪያ አካባቢ ሕወሓት/ኢህአዴግ የከለለው ሰው ሰራሹ “ኦሮሚያ” ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ነች! ኦሮሞ የስታሊንን የመኖሪያ አካባቢ መሥፈርት ስለማያሟላ፣ ብሔር አይደለም! አራት ነጥብ! አማራ ዘሩ ኢትዮጵያዊነት ነው፤ መኖሪያ አካባቢው አድርጐ የሚቆጥረው መላ ኢትዮጵያን ነው፤ ስለዚህ ብሔሩ ኢትዮጵያዊ ነው! በኢትዮጵያ ብሄር አለ ከተባለ ኢትያዊነት ብቻ ነው! ሌሎቹ በሙሉ የቋንቋ ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ በተለይ አማራ፣ አንደኛ “አማራ” ተብሎ

መጠራት አይፈልግም፤ ሁለተኛ፣ “አማራ የሚባል የተለየ ክልል እንዲኖረው ፈልጐ አያውቅም፡፡ እንዴት ነው፣ ኢህአዴግ ትልቅ

በሆነ የቋንቋ ማህበረሰብ ላይ የማይፈልገውን ማንነት በግድና በጉልበት የሚጭንበት?

ጐልማሶችና አዛውንቶች ከእነ አቤነዘር የተለየ አመለካከት ነው ያላቸው፡፡ጥንት፣ ጥንት በድሮ ጊዜ ዛሬ ኢትዮጵያ እያልን በምንጠራው መልካምድራዊ አካባቢ፣ ነገዶች ተራርቀው ነበር የሠፈሩት፡፡ የሕዝብ ዕድገት አቀራረባቸው፤

ለመሬት፣ ለውሃ፣ ለእንስሳት፣ ለማገዶ፣ ወዘተ… ሲሉ እርስ በእርሳቸው ይጋጩ ጀመር! ያሸነፈው፣ ተሸናፊውን ያስገብረዋል፤ ሕዝብ ለመቀነስ ሲል ሊገድለውም ይችላል፤ ተሸንፎአላ! ባሪያም ሊያደርገው ይችላል፤ አሊያም፣ አሸናፊው ነገድ የበላይ ሆኖ በሰላም ይኖረዋል! ይህ እንግዲህ ከባሪያና

ከቅድመ ፊውዳሊዝም እስከ ፊውዳሊዝምና ፊውደቡርዥዋ ያሉትን ሥርዓቶች ያጠቃልላል፡፡ ነገዶች እርስ በእርሳቸው የሚጋጩት በኢኮኖሚ ሀብት ላይ ብቻም አይደለም፤ የግዛት ማስፋትና የሀገር ግንባታ ዓላማዎችም አሉ፡፡ ገረሱ የሚያወግዘው በእነዚህ ተፈጥሮአዊና ታሪካዊ ሥርዓቶች የተፈፀሙትን ግድያዎች፣ ጭቆናዎችና በደሎች ነው! የሰው ልጅ ከሕገ አራዊት ወደ ሕገመንግሥት በተሸጋገረበት ረጅም ዘመን ውስጥ የተፈፀሙትን በደሎች ማውገዝ ይቻላል፤ ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ላይ ሆኖ! ግን በዚያን ጊዜ ሌላ አማራጭ አልነበረም! ወደኋላ እንመልሰው ቢባል፣ ምንአልባትም ውጤቱ እንደገና መተላለቅ ሊሆን ይችላል! የኢትዮ ኤርትራን ጦርነት ማስታወሱ ብቻ ይበቃል!

ገረሱ አማራ በኦሮሞ ላይ ያደረሰውን ጭቆና ጠቅሷል፤ ታሪክ ስለሆነ መጥቀሱ ስህተት አይደለም፤ ይህን በአለበት አንደበቱ ለምን ኦሮሞ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን በሌሎች ማህበረሰቦች ላይ ያደረሰውን በደልና ግፍ አልጠቀሰም! የሕብረተሰብ ዕድገት ሕግጋት በሁሉም ማኅበረሰቦች ላይ ተፈፃሚ የሚሆኑ ናቸው፡፡ ከኦሮሞ ፍልሰት (ወረራ የሚሉትም አሉ) ቀደም ብሎ የአዳሎችና የአፋሮች ተራ አልነበረምን? ግራኝ መሐመድ በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ከመፈለጉ ሌላ፣ ግዛት በማስፋትና ሀገር በመገንባት ከምኒልክ በምንድን ነው የሚለየው? ንጉስ ጦና ምኒልክን ቢያሸንፉ ኖሮ፣ ምኒልክ ከሠሩት የተለየ ነገር ይሰሩ ነበርን? ወጣቶች እየተስተዋለ! የጐልማሶችና አዛውንቶች አካል ቢገረጅፍ፣ አእምሮአቸው የዛገ እንዳይመስላችሁ የሰው ልጅ ከሕገ አራዊት ወደ ሕገመንግስት በሚሸጋገርበት ዘመን ለተፈፀሙ በደሎች፣ በደሎቹን ከማቆም ሌላ የሚከፈል ካሣ ይኖራል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡

ወደ ዘር ጉዳይ ለአንድ አፍታ እንደገና ብንመለስ፣ አንድ ትልቅ ቁምነገር ወይም መሰረተሃሳብ እንገነዘባለን፡፡ ዘር በዘጠኝ ወር ይጠፋል ይባላል፡፡ አማራና ኦሮሞ ተጋብተው ልጅ ቢወልዱ፣ በልጃቸው የእነሱ ዘር ይጠፋል፡፡በዘጠኝ ወር ቋንቋ ተደቅሎ እስኪጠፋ በጣም ረጅም ጊዜ ይወስዳል፡፡ ይህ የሚያሳየው በኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ችግር የዘር ሳይሆን፣ የቋንቋ ልዩነት ነው፡፡ብዙ ቋንቋዎች ማወቅ ደግሞ ያስከብራል እንጂ አያዋርድም፡፡ገረሱ ተበድለናልና “ኦሮሚያ” ነፃ መውጣት አለበት የሚል መልክት ከማስተላለፍ ይልቅ፣ አሮምኛም (ከአማርኛ ጐን ለጐን) የመላ ኢትዮጵያ መግባቢያ ቋንቋ ሊሆን ይገባል ቢል፣ ለሰሚው ደስታን የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡

በስታሊንም ሆነ በሌኒን ትርጉም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብሔር የለም፡፡ ያሉት የቋንቋ ማህበረሰቦች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከዜግነት አልፎ፣ ዘር ሆኖአል፡፡ኢትዮጵያዊነት ክልስ ዘር ነው፤ አማራ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ወላይታ ኢትዮጵያዊ ነው፤ ወዘተ ዋለልኝ መኮንን ጐበዝ አብዮተኛ ነበር፤ ህይወቱንም በጀግንነት ለሚያምንበት ሰውቶአል፤ ግን የስታሊን እና የሌኒንን መርሆዎች በጥልቀት ሳይመረምር

ዘር በዘጠኝ ወር

ይጠፋል ይባላል፡፡ አማራና

ኦሮሞ ተጋብተው ልጅ

ቢወልዱ፣ በልጃቸው

የእነሱ ዘር ይጠፋል፡፡

በዘጠኝ ወር ቋንቋ ተደቅሎ

እስኪጠፋ በጣም ረጅም ጊዜ

ይወስዳል፡፡ ይህ የሚያሳየው

በኢትዮጵያውያን መካከል

ያለው ችግር የዘር

ሳይሆን፣ የቋንቋ ልዩነት

ነው፡፡ ብዙ ቋንቋዎች

ማወቅ ደግሞ ያስከብራል

እንጂ አያዋርድም፡፡ ገረሱ

ተበድለናልና “ኦሮሚያ” ነፃ

መውጣት አለበት የሚል

መልክት ከማስተላለፍ

ይልቅ፣

ያለፈውን የብሔር ጭቆና ታሪክ እንቀበል?

የጐልማሶችና የአዛውንቶች አመለካከት

ገረሱና አቤነዘር በስታሊን እና በሌኒን ቋንቋ ይጠቀማሉ

ነበር የተቀበላቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሁኔታ በጣም የተለየ ነው፡፡ እናም የብሄሮች የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል የሚለው መርህ ለኢትዮጵያ አይሰራም!

በቅደመ ፊውዳልና በፊውዳል ሥርዓት የማህበረሰቦች ላይ በደል መፈፀሙ ተፈጥሮአዊና የታሪክ ሐቅ ነው፡፡ ሀገሮች ሁሉ የተመሠረቱት በዚህ መንገድ ነው፡፡ጀርመን ሆነ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ ሆነ እንግሊዝ፣ ሩሲያ ሆነ ቻይና በዚሁ መንገድ ነው የተመሠረቱት፡፡ አቤኔዘር የኦሮሞ ጥያቄ የሚፈታው፣ ምርጫው ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሲተው ነው ይላል፡፡ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሳለ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እንዴት ብቻውን ሊወስን ይችላል? ኤርትራ የተገነጠለችው በወታደራዊ ኃይል እንጂ በኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ አይደለም፡፡ በኤርትራ ሕዝብ ይሁንታም አልተገነጠለችም፡፡ የኤርትራ ሕዝብ የኢትዮጵያ መሥራች (ያውም ግንባር ቀደም መሥራች) ሕዝብ ነው፡፡ እውነተኛ ነፃ ውሳኔ ሕዝብ ቢካሄድ፣ የኤርትራ ህዝብ ኢትዮጵያዊነቱን እንደሚመርጥ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡

በአቤነዘር አካሄድ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአለፉት ሥርዓቶች ስለተበደሉ፣ አንድ ላይ ተሰባስበውና ክልል ተሰጥቶአቸው እስላማዊ መንግስት ያቋቋሙ የሚለውንም ሃሳብ መቀበል ይቻላል ማለት ነው፡፡ እነ ጁሀር መሐመድ የሚሉት እኮ ይህንን ነው፡፡ ለማንኛውም ገረሱና አቤነዘር የሚሰጡት የመፍትሄ ሃሳብ ተመሳሳይ ስለሆነ፣ እንደ ተከራካሪዎች ልንወስዳቸው አንችልም፡፡አንደኛው ተቃራኒ ሃሳብ የሚያቀነቅን ሊሆን ይገባ ነበር፡፡ ገረሱ ስለ ወደፊቷ ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ መድረስ ያስፈልገናል ይላል፡፡በምንድን ላይ ነው የምንስማማው? እያንዳንዱ ማህበረሰብ የራሱን ዕድል በራሱ እንዲወሰን? እስከመገንጠል? በዚህ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ መስማማት የምንችለው በጉዳዩ ላይ ጥቂት የተማሩ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲወያይበት ነው፡፡ ነፃ ውይይት ለማድረግ ደግሞ በመጀመሪያ ራሳችንን እና ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢህአዴግ የአፈና ሥርዓት ነፃ ማድረግ ይኖርብናል! እዚህ ላይ በጋራ መታገል እንችላለን፡፡

ምሁራንና የተማሩ ዜጐች ብቻቸውን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ሊወሰኑ አይችሉም፤ አይገባቸውምም፡፡ በተለይ የብሄር ጥያቄ የሚባለው ጉዳይ፣ የብሄር ፌዴራሊዝም፣ ዲሞክራሲያዊ አሀዳዊነት እና የመሬት ስሪት ጉዳይ ሰፊው ህዝብ ከኢህአዴግ አፈና ነፃ ሆኖ ያለተፅዕኖ ሊወያይባቸው ይገባል፡፡የምሁራንና የተማሩ ዜጐች ሚና ስለ ጉዳዮቹ ገለፃ ማድረግና ማወያየት ይሆናል፡፡ በቂ ነፃ ሕዝባዊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ሕዝቡ በድምፅ ብልጫ ይወሰናል፡፡ ገረሱና አቤነዘር ለሰጡን መግለጫ አመሰግናለሁ፤ ግን ከኢህአዴግ አፈና ነፃ ሆኜ በጉዳዩ ላይ ድምፅህን ስጥ ብባል፣ የሁለቱንም ሃሳብና የመፍትሄ ሃሳብ አልመርጥም፡፡ ሃሳባቸውን ነፃ ሆነው በመግለጣቸው ግን ሁለቱንም ከልብ አከብራቸዋለሁ፡፡ ውይይታቸው (ክርክራቸው ለማለት እቸገራለሁ) እኔንም በጉዳዩ ላይ እንደገና በጥልቀት እንዳስብበትና ይህቺን መጣጥፍ እንዳቀርብ ስለገፋፋኝ፣ በድጋሚ ሁለቱንም አመሰግናለሁ፡፡ ወደፊት ውይይቱ በክርክር መልክ ቢቀርብ ይበልጥ ትምህርት ሰጪ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡

የገረሱና የአቤኔዘር ክርክር

በለጠ ጎሹ

Page 12: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 8412

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

ኢትዮጵያን በአገዛዝ ስልት ስር እያስተዳደረ የሚገኘው ገዢው ቡድን ህገመንግስቱን በመርገጥ የማያጠቃው፣ የማይጨቁነውና ለስቃይ የማይዳርገው አንድም የህብረተሰብ ክፍል አለ ብሎ ለመናገር አይቻልም፤ ሁሉንም በየደረጃው የገፈቱ ቀማሽ አድርጓቸዋል፡፡ ይህ መጣጥፍ ለማመላከት የሚሞክረው ግን ከሌላው ህብረተሰብ በተለየ ራሳቸውን ለመከላከል በማይችሉ እስረኞች ላይ እየደረሰ ስላለው መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፡፡

አገዛዙ በየትኛውም ደረጃ የሚተቹ ወይም በተደራጀ ሁኔታ የሚቃወሙ ዜጐችን ለማጥፋት፤ ኢህገመንግስታዊ “ህጎች” በማውጣት እንዲሁም የፖሊስና የደህንነት መዋቅሮችን እንደሚጠቀም የአሜሪካን የውጪጉዳይ መስሪያ ቤት እና ታዋቂ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት ሪፖርቶች አጋልጠዋል በተደጋጋሚ አጋልጠዋል፡፡ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ስውርና ይፋዊ እስር ቤቶች የዜጎቻችን የስቃይ ጩኸት ይሰማል፡፡ በተለይም በኦጋዴንና በኢሮሚያ ለቁጥር የሚታክቱ የህሊና እስረኞች ህገመንግስቱንና አለማቀፋዊ የእስረኞች አያያዝ ዝቅተኛ መለኪያዎችን ከምንም በማይቆጥረው ገዢ ቡድን ስቃይ እየተቀበሉ ይገኛሉ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት ከአንቀጽ 19 እስከ 21 ተጠርጥረው አልያም ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ያሉ ዜጐች ሊከበሩላቸው ስለሚገቡ ሰብአዊ መብቶች እና ሊፈፀሙባቸው ስለማይገቡ ኢሰብአዊ የአያያዝ መንገዶች በዝርዝር ሰፍሯል፡፡ በህገ መንግስቱ “ኢሰብአዊ አያያዝ ስለመከልከሉ” በሚል ርዕስ በአንቀጽ 18 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ “ማንኛውም ሰው ጭካኔ ከተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው፡፡” የሚልና በየትኛውም ሁኔታ የማይገሰስ መሰረታዊ የሰብአዊ መብት ጥበቃ አምድ ተቀምጧል፡፡ ይህ አንቀጽ “ማንኛውም ሰው” የሚል አፅንኦት የሰጠውም የትኛውም ሰው አመለካከት ወይም ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ አያያዝ ስር እንዲወድቅ የሚያደርግ ውጤት እንደማያስከትል የሚያረጋግጥ ነው፡፡ ገዢው ቡድን ግን እንደ ሌሎቹ ህገመንግስታዊ ዋስትና የተሰጣቸው መብቶች ሁሉ አንቀፅ አስራ ስምንት ያስረገጠውንም የሰብአዊ መብት ከለላ ከምንም ባለመቁጠር በተደጋጋሚ ሲደፈጥጥ ለመመልከት ችለናል፡፡

ገዢው ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማፈን ለመግዛት ያለውን ፍላጎት የሚቃወሙ ዜጎችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስር በመዳረግ ኢሰብአዊ በሆነና ጭካኔ በተሞላበት አያያዝ እንዲማቅቁ ያደረጋል፡፡ እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባው ኢሰብአዊና ጭካኔ የተሞላበት አያያዝ የሚያዙት በተደራጀ ሁኔታ አገዛዙን የሚቃወሙት ብቻ አለመሆናቸው ነው፤ በተለያዩ ደረቅ ወንጀሎች ተጠርጥረው ወይም ተፈርዶባቸው የሚያዙ እስረኞችም ተመሳሳይ ግፍ እንደሚፈፀምባቸው በእስረኞች ተጽፈው በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ላይ የተስተናገዱ አሳዛኝ የወህኒ ቤት የመብት ጥሰት ታሪኮችን እንደማሳያነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ይህን ድርጊት ግን ብሶ የሚፈፀመው በህሊና እስረኞች ላይ ስለመሆኑ አከራካሪነው፡፡ ፍኖተ ነፃነት ሐምሌ 2005 ዓ.ም በድምፅወ ምስል ጭምር ይፋ ያደረገችው ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ ላይ የደረሰው ሰቅጣጭ የስቃይ ታሪክ አንዱ ነው፡፡ (https://www.youtube.com/watch?v=6pTtPzqAVyg በዚህ ሊንክ የወጣት

ተስፋዬ ተካልኝን ቃለምልልስ መመልከት ይችላሉ) ተስፋዬ በወጣትነት ዕድሜው በማዕከላዊ የማሰቃያ ስፍራ በተፈፀመበት ኢሰብአዊ ድብደባ በመላ አካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ በፊኛው ላይ በደረሰበት ከባድ ጉዳትም ሽንቱን መቆጣጠር በማይችልበት ደረጃ ለዘላቂ ጉዳት ተዳርጓል፡፡ተስፋዬ ለእስር የተዳረገው በአመለካከቱ እንጂ በየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ተሳትፎ በማድረጉ አልነበረም፡፡ ይህ ወጣት የህገመንግስቱ አንቀጽ 18 የሚከለክላቸው ኢሰብአዊ ተግባራት በማዕከላዊ የማሰቃያ ስፍራ ለገባ የህሊና እስረኛ እንደማይከበሩ በተለያዩ ሚዲያዎች በሰጣቸው ቃለምልልሶች አስረግጦ ተናግሯል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 19 ንዑስ አንቀፅ 5 ደግሞ የሚከተለውን ይደነግጋል፡- “የተያዙ ሰዎች በራሳቸው ላይ በማስረጃነት ሊቀርብ የሚችል የዕምነት ቃል እንዲሰጡ ወይም ማናቸውንም ማስረጃ እንዲያምኑ አይገደዱም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡”

ከስድስት ወራት በፊት “በሽብር ድርጊት” ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት መንግስት ክስ የመሰረተባቸው የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞችን ጨምሮ በፀረሽብር ህጉ የተከሰሱ በርካታ ዜጎች፤ ፖሊስ በድብደባና በማሰቃየት በተቀበላቸው ቃል ላይ በግድ እንዲፈርሙ መደረጋቸውን በፍርድ ቤት ገልፀዋል፡፡ በምርመራ ወቅት የሚፈፀም ድብደባና ማሰቃየትን ተከትሎ መርማሪዎች በሚያዘጋጁት “የተጋገረ” ማስረጃ ላይ በማስፈረም ለፍርድ ቤት “በምርመራ የተገኘ ማስረጃ” በሚል የህሊና እስረኞች ሀሰተኛ ማስረጃ እንዲቀርብባቸው መደረጉ አንቀፅ አስራ ዘጠኝም በዢው ቡድን ጫማ ስር መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

የህገ መንግስቱ አንቀጽ 21 ንዑስ

አንቀጽ 1 “በጥበቃ ስር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብአዊ ክብራቸውን በሚጠብቅ ሁኔታዎች የመያዝ መብት አላቸው፡፡” ይላል፡፡ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ሰብአዊ ክብራቸውን የሚጠበቅላቸው ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ በሙስና ተከሰው በቃሊቲ ወህኒ ቤት ዘና ባለ ሁኔታ ታስረው የሚገኙ አንዲት የቀድሞ ታጋይ ጠባቂዎቻቸው በሚያመቻቹት ክፍል በማንኛውም ጊዜና ሰዓት በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ፣ ቡና ተፈልቶላቸው ፈታ እንዲሉ እንደሚደረጉ ሰምቻለሁ፡፡ በተቃራኒው ከታጋይ ኮረኔሏ ጋር ክፍል ትጋራ የነበረችው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ህክምና ተከልክላ ለስቃይ ተዳርጋለች፡፡ ርዕዮት ለማንፀሪያነት ተጠቀሰች እንጂ ሰብዓዊ ክብራቸውን በማይጠብቅ ሁኔታ የሚታሰሩ ዜጎች አዕላፍ ናቸው፡፡

በዚሁ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ታሳሪዎች ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው ከጓደኞቻቸው፣ ከሃይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሐኪሞቻቸው እና ከሕግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘት እንዲጎበኟቸውም ዕድል የማግኘት መብት አላቸው፡፡” ሲል ይደነግጋል፡፡ ይህ ድንጋጌ ለህሊና እስረኞች የተረት ያክል ነው፡፡ለማሳያነት ያክል ጥቂት እውነታዎችን ማንሳት በቂ ነው፡፡ አሸባሪው የፀረ ሽብርተኝነት ህግ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የታሰሩ የህሊና እስረኞች በተደጋጋሚ ይህ መብታቸው እንዲነፈግ ተደርጓል፡፡

የትውልዱ የፅናት ተምሳሌት እና የነፃነት አርበኞች የሆኑት ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው ውጪ እንዳይጐበኙ ለረጅም ጊዜ የፀና ክልከላ ተደርጐባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ብርቱዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት

አለሙም ላለፉት 15 ወራት ከእናትና አባቷ ውጪ በማንም እንዳትጎበኝ ተከልክላለች፡፡

በአሸባሪው ህግ ታስረው ያልተፈረደባቸው የህሊና እስረኞች ተሞክሮም ተመሳሳይ ነው፤ መንግስት በሃይማኖታቸው ጉዳይ እንዳሻው እጁን መክተቱን በመቃወም ህዝበ ሙስሊሙ ላነሳቸው ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ለማምጣት የተንቀሳቀሱት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትና የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞችም “በምርመራ” ላይ በነበሩበት ወቅት ይህ መብታቸው እንዲገፈፍ ተደርጓል፡፡

ከአራት ወራት በፊት በመአከላዊ ወንጀል ምርመራ እንዲታሰሩ የተደረጉት ወጣት ፖለቲከኞች ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሺዋስ አሰፋ እና አብረዋቸው የታሰሩት ወጣቶች ከቅርብ ቤተሰቦቻቸው ውጪ ማንም እንዳያገኛቸው ክልከላ ተጥሎባቸው ቆይቷል፡፡ ክልከላው የህግ ጠበቃቸውን አቶ ተማም አባቡልጉንም አካቶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው የእስረኞች አያያዝ ዝቅተኛ መለኪያ ደንብ (Standard minimum rules for the treat-ments of prisoners) እስረኞች ለጤና ጎጂ በሆነ ቦታ መታሰር እንደሌለባቸው፤ ጤናቸው የተጓደለ እስረኞች ህክምና የማግኘት መብት እንዳላቸው እንዲሁም ተላላፊ በሽታ ያለባቸው እስረኞች ከሌሎቹ ጋር ተቀላቅለው እንዲታሰሩ መደረግ እንሌለበት ያስቀምጣል፡፡ በኢትዮጵያ በሚገኙ እስር ቤቶች ግን ይህ እንደማይታሰብ በእነሃብታሙ አያሌው ላይ ከአንድ ወር በፊት እጅግ ኢሰብሰዊ በሆነና የገዢው ቡድን ፋሺስታዊነት የት ድረስ እንደዘለቀ በሚያሳይ መልኩ የደረሰውን በዋቢነት ማንሳት ብቻ ይበቃል፡፡

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው ወጣት ሀብታሙ አያሌው በማዕከላዊ በተፈፀመበት ድብደባ እንዲሁም እጅግ ቀዝቃዛ በሆነ ቦታ በመታሰሩ ለህመም በተዳረገበት ወቅት ተገቢ ህክምና ማግኘት ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት አንድ እግሩን ለማንቀሳቀስ ተቸግሯል፡፡ ለሳምንታት ብቻውን ጨለማ ክፍል ውስጥ መታሰሩ ሳያንስም ለአንድ ሳምንት መፀዳጃ ቤት እንዳይጠቀም ተከልክሏል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ም/ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ በዳንኤል ሺበሺ ላይ የተፈፀመውን ደግሞ እንመልከት፡፡ ዳንኤል ሺበሺ በሳንባ በሽታ ከታመመ ታሳሪ ጋር በአንዲት የታፈነች ክፍል ውስጥ ታስሮ ነበር፤ የታሰረበት ክፍል የታፈነ በመሆኑም በተደጋጋሚ ለተቅማጥ በሽታ ተዳርጓል፤ እሱም እንደ ሀብታሙ ሁሉ መፀዳጃ ቤት ተከልክሏል ፡፡

ከላይ የተመለከትናቸው ታሳሪዎች ላይ የሚደርሱ ኢሰብአዊ ድርጊቶች በኢትዮጵያ ህገመንግስትም ሆነ በአለም አቀፍ ስምምነቶች የተወገዙ ናቸው፡፡ የገዢው ቡድን ወንበርተኞች ግን ስልጣናቸውን ለማደላደል በፖለቲካ አመለካከታቸው የሚለዩዋቸውን ዜጎች ገርፈው፣ ህክምና ከልክለውና የተለያዩ ኢሰብአዊ ጥቃቶችን አድርሰው በሰው ስቃይ የሚደሰቱ አረመኔዎች በመሆናቸው ህገመንግስቱን ከጫማቸው ስር አደርገው ሀገር ይገዛሉ፡፡ የትኛውም አገዛዝ ሲወገድ ገዢዎችና ጀሌዎቻቸው ጭቁኞች ተሸክመውት የነበረውን ቀንበር በተራቸው እንደሚሸከሙም እንያስቡ የገዢነት እብሪታቸው አሳውሯቸዋል፡፡

ህገ መንግስቱ በወንበርተኞች ጫማ ስር

ነብዩ ሀይሉ

በኢትዮጵያ

ህገመንግስትም ሆነ

በአለም አቀፍ ስምምነቶች

የተወገዙ ናቸው፡፡የገዢው

ቡድን ወንበርተኞች ግን

ስልጣናቸውን ለማደላደል

በፖለቲካ አመለካከታቸው

የሚለዩዋቸውን ዜጎች

ገርፈው፣ ህክምና

ከልክለውና የተለያዩ

ኢሰብአዊ ጥቃቶችን

አድርሰው በሰው

ስቃይ የሚደሰቱ

አረመኔዎች በመሆናቸው

ህገመንግስቱን

ከጫማቸው ስር አደርገው

ሀገር ይገዛሉ፡፡ የትኛውም

አገዛዝ ሲወገድ ገዢዎችና

ጀሌዎቻቸው ጭቁኞች

ተሸክመውት የነበረውን

ቀንበር በተራቸው

እንደሚሸከሙም እንያስቡ

የገዢነት እብሪታቸው

አሳውሯቸዋል፡፡

Page 13: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

13ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

-የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞችን ጎብኝተዋል

በአንድነት ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ በላይ ፍቃዱ የሚመራና ከፍተኛ የአንድነት አመራሮችን ያካተተ ቡድን ህዳር 4 ቀን 2007 ዓ.ም በዝዋይ እስር ቤት የሚገኙትን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እና የአንድነት የምክር ቤት አባል የሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን ጎበኙ።

ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝንና አቶ ናትናኤል መኮንን ፊት ለፊት ተገናኝተው መነጋገራቸውን አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡ አቶ በላይ ተመስገን ደሳለኝ አሁንም በጥሩ የመንፈስ ልዕልና ላይ እንደሚገኝና ፅናቱ የሚያኮራ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል።

ወደ ዝዋይ ከሄዱት የአንድነት አመራሮች መሀከል የሆኑት የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት ም/አፈጉባኤ አቶ ፀጋዬ አላምረው የአንድነት ከፍተኛ አመራር አባል የሆነው አቶ ናትናኤል መኮንን በአዲሱ የፓርቲው አመራር ደስተኛ እንደሆነ መናገሩን ገልፀው “እኔ የሚጠበቅብኝን

የአንድነት፤ የሰማያዊ፤ የመኢአድ እና ሌሎች በርካታ ሰዎች ወደ ማእከላዊ መግባታቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡

ሰባት የአንድነት ፓርቲ አባላት ወደ ማእከላዊ ሲሸጋገሩ ከጎንደር አራማጨሆ አንጋው ተገኝ፤ እንግዳው ዋኘው፤ አባይነህ ዘውዱ ከመተማ አቶ በላይ ሲሳይ፤ አለባቸው ማሞ እንዲሁም ከፎገራ አለበል ዘለቀ፤ ጥላሁን አበበ ወደ ማዕከላዊ የተዘዋወሩ ሲሆን ገዢው ፓርቲ መጪው ምርጫ ማሰር መፍትሔ አይሆንም ይልቁንም ህዝቡን እያተራመሰ ያለው ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ነው፡፡ ወደ እርቅና መስማማት መሄድ ያልቻለው ኢህአዲግ ስልጣኑን አሁኑኑ ለህዝቡ ማስረከብ ይኖርበታል ስልጣን የህዝብ ነውና፡፡

ከጐንደር ወደ ማዕከላዊ የተሸጋገሩ የአንድነት አባላት ከትላንት በስቲያ ዕለት ህዳር 5 ቀን 2007 ዓ.ም ምሳ የገባላቸው ሲሆን በዛሬው እለት ግን ምሳ ለማስገባት ቢኬድም ከአንጋው ተገኝ በስተቀር ለሌሎቹ መኖራቸውን ለማረጋገጥ ፖሊሶቹ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ምግብ ለማስገባት ለሄዱት የአንድነት አባላት “ምግብ ማስገባትም አይቻልም” የሚል ምላሽም ተሰትቷቸዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላለፈ

ማዕከላዊ ላሉት የአንድነት አባላት ምግብ እንዳይገባ ተከለከለ

ተወጥቻለሁ እናንተ ትግሉን አጠናክራችሁ ቀጥሉ” የሚል መልዕክትም ማስተላለፉን ተናግረዋል፡፡ ልዩነታቸውን በውስጥ አሰራር መፍታት ሳይችሉ የአንድነት ፓርቲን ስም በአደባባይ የሚያጠፉ ግለሰቦች የእኛን የእስር ጊዜ ከማራዘም ውጪ የሚያመጡት ለውጥ የለም” ማለቱንም ተናግረዋል፡፡

“ጋዜጠኛ ተመስገን ህዝባዊ ትግሉ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት” የሚል መልዕክት ማስተላለፉንም የአንድነት አመራሮች ተናግረዋል፡፡ የህዝቡ የዴሞክራሲና የፍትህ ጥያቄ በትክክል እስኪመለስ ድረስ ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ በመክፈል ወደፊት ማስኬድ እንደሚገባም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በመልዕክቱ አስምሮበታል።

የአንድነት ፓርቲ ፕሬዚደንት አቶ በላይ ፍቃዱ ስለተመስገን ሲገልፁ “ተመስገን ደሳላኝ በእኔ እምነት የዚህ ትውልድ አርአያ ነው፤ እርሱ እየተጓዘበት ያለው መንገድ ያለምንም ጥርጥር ወደ ለውጥ የሚያደርስ ነው፡፡” ብለዋል።

ኦነግ እንደ ዳቦ ስም

ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ከፍተኛውን የሚይዘው የኦሮሞ ብሔር ባለፉት ሰላሳና አርባ አመታት በማያቋርጥ ትግል ውስጥ እንደሆነ ሲይግፍረይድ ፓውስዋንግ “The Oromo Between Past and Future” በተባለው ጽሁፋቸው ያትታሉ፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን በኦሮሚያ ያለውን እንቅስቃሴ ፓስዋንግ በሶስት ከፍለው ያስቀምጣሉ፤ የመጀመርያው ወገን “አሁንም የኦሮሚያ መገንጠል ለኦሮሚያ ጥያቄ መፍትሄ ነው” ብሎ የሚያምን ሲሆን ሁለተኛው ወገን ደግሞ “ኦሮሞ በኢትዮጵያ ትልቅ ብሄር በመሆኑ በአገሪቱ የስልጣን የበላይ መሆን አለበት” ብሎ የሚያምን ነው፤ ሶስተኛው ወገን ደግሞ “በዴሞክራሲያዊ አንድነት ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ጋር መኖር ይቻላል” አማራጭ መፍትሄ ያቀርባል፡፡ እነዚህን ሶስት የተለያዩ ጥያቄዎች የሚያነሱ የኦሮሞ ልጆች ግን በግዥው መንግስት የሚሰጣቸው መልስ ሁሉንም “ኦነግ ነህ” የሚል ነው፡፡ ይህም ዋናው ምክንያት ኦነግ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ያለው መታመን እጅግ ከፍተኛ መሆኑና በአንጻሩ ኦሕዴድ በተውሶ ብሔርተኞች (Feed Nationalists) መሞላቱ

መንግስት በክልሉ አንድ አይነት ችግር ሊነሳ ቢችል ለመቆጣጠር አያስችለኝም የሚል ስጋትን ስላሳደረ፣በዚህም ምክንያት በክልሉ የሚፈጸሙ ማንኛውንም አይነት እንቅስቃሴዎች በእንጭጩ ለመግታት ማንኛውም ሰላማዊ ግለሰቦች ላይ ሳይቀር ይህንን የዳቦ ስም ይለጥፋል፡

መርዶ ነጋሪው ሪፖርት

ባሳለፍነው ጥቅምት መጨረሻ “Because I am Oromo” (ኦሮሞ በመሆኔ) በሚል ርእስ የወጣው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በክልሉ በስፋት እየፈጸመ መሆኑን ማጋለጡና በተለይ ሪፖርቱ የጉዳዩ ሰለባ የሆኑ ከሶስት መቶ በላይ የምስክሮችን ቃል በምስል ጭምር መሰብሰቡ በተለያዩ የሚድያ ተቋማት ዘንድ ከመቼውም በላይ እንዲስተጋባ አድርጎታል፡፡ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል ቃላቸውን ከሰጡት አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ተወላጆች የሰውነት አካላቸው እየተቆራረጠ ጭምር መከራ እንደደረሰባቸውና በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ማለፋቸውን ገልጸዋል፡፡ሁነቱንም ያጠናቀሩት የተቋሙ ተወካይ ክሌይር ቤስተንም “እጅግ ዘግናኝ” ሲሉ ገልጸዋል፡

፡ ይህም ሁናቴ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ሪፖርቶችን ከማውጣት ባሻገር ለቆሙለት ተልእኮ በከፍጠኛ ሁኔታ የማቀንቀንና የመሞገት(Advocacy) ስራ እንዲሰሩ አድርጎአቸዋል፡፡ይህ የመሞገት ስራ በባህሪው ሪፖርቱን በሚገባ በማዳረስ በሚድያ፤ በፖሊሲ አርቃቂዎችና ፖሊሲ አውጭዎች ዘንድ ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግን ይጨምራል፡፡ይህ አይነት ሁናቴም ገዥውን መንግስት ከፍተኛ እርዳታ በሚሰጡ ምራባውያን ዘንድ በመጥፎ አይን እንዲታይ ያደርገዋል፡፡

ነገር ግን ገዥው መንግስት ይህንም ሪፖርት እንደ ቀደሙት ሪፖርቶች “የኒዮ ሊበራሎች ሪፖርት” ብሎ ከማጣጣል በክልሉ ያለውን ነባራዊ ችግር ለመፍታት እንደ ማንቂያ ደውል ሊጠቀምበት ይገባል፡፡ይህ የመብት ጥሰት ዘገባ በሀገር ውስጥ በተለያዩ አካላት ርእሰ ጉዳይ ተደርጎ ቢነሳም በቂ ውይይት ሲደረግበትና ተጨማሪ ትኩረት ሲሰጠው አለመታየቱ አሁንም የኦሮሞ ልሂቃንን እዳ ከፍ ያደርገዋል፡፡

የኦሮሞ ልሂቃን ሌላው እዳ ጥያቄዎቻቸውን እና ስሜቶቻቸውን ማጋባት አለመቻላቸው እና የአንድነት ሀይሎች በአንጻሩ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚደረሰው ግፍ በበቂው መጠን አለማንሳታቸው ትግሉን

የኦሮሞ…. ከገፅ 2 የዞረ ረጅም ርቀት ወስዶታል፡፡ በተለይም “የኦሮሞ ጥያቄ የሚፈታው ነፃ የኦሮሚያ ሪፐብሊክ በመመስረት ነው” የሚለው ሀልዮት በቀሪው ብሄረሰቦች ዘንድ በጥርጣሬ መታየቱና መገንጠል የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች መፍትሄ እንደማይሆን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ፤ መታየቱ በተለይም ቀደምት የኦሮሞ ፖለቲከኞች ይህንን ጥያቄ ወደ መሳቢያቸው መመለሳቸው ለኦሮሞ ልሂቃን ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ በር ከፋች ነው፡፡ በብሄሩ ልሂቃን የሚነሳው ሁለተኛው ጥያቄ “ኦሮሞ በኢትዮጵያ ትልቅ ብሄር በመሆኑ በኦገሪቱ የስልጣን የበላይ መሆን አለበት” የሚለው በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የሰፈነውን የአንድ ብሄር ጠቅላይነት (Hege-mony) በሌላ ከመተካት ውጭ ዴሞክራሲያዊ አማራጭ አድርጎ ማቅረብ አይቻልም፡፡ የኦሮሞ ልሂቃን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆን ያለበት በዴሞክራሲያዊ አንድነት ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄሮች ጋር ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዚህ ሀልዮት ደጋፊዎች መበራከትና ቀደምት የብሄሩ ልሂቃን ይህንን ሀሳብ ማቀንቀናቸው የኦሮሞ ልሂቃንን ሚና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በተስፋ እንዲጠብቅ ምክንያት ይሆናል፡፡ እስከእዛው ግን በቀለ ኢተፋ ጥቄዎቹን እና ጉዳቱን ተሸክሞ ይቆያል እንዲህ እያለ “እውን ይህች ሀገር! ሀገሬ ናት?”

ኦሮሞ በመሆኔ የሚል ዘመቻ እየተካሄደ ነው

በኦሮሞ ህዝብ ላይ በመንግስት የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የበይነ መረብ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፡፡ ዘመቻው በዋነኝነት በፌስ ቡክና በቲውተር እየተካሄደ ነው፡፡

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት ተከትሎ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የተጀመረው ይሄው ዘመቻ “ኦሮሞ ስለሆንኩ” የሚሪ መሪ ቃል ይዟል፡፡ ከዘመቻው የተሳተፉ ዜጐች የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ጽሁፎችን እና ምስሎችን ተጠቅመዋል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚያደርሰውን ግፈና ልክ ያጣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚተነትን ሪፖርት አውጥቶአል፡፡ በኦሮምያ ህገወጥ ግድያዎች ፤ቶርቸርና፤የጅምላ እስር፤ ስርአቱ የኦሮሞ ተወላጆችን ብቻ ለይቶ በጅምላ ማጥቃቱን መቀጠሉን ሪፖርቱ ዘርዝሮአል፡፡

በሪፖርቱ ከተጠቀሱት ነጥቦች አንደኛው በኦሮምያ ከመሬት ማካለል ጋር በተነሳው ግጭት አስመልክቶ የተጠቀሰው ነው፡፡ሪፖርቱ እንደሚለው ከሚያዝያ እሰከ ግንቦት በዘለቀው ግጭት ቁጥራቸው ከመቶ ሺዎች የሚልቁ የብሄሩ ተወላጆችን ለሞት፤ለስቃይና፤ለስር፤እንዲሁም ለጅምላ ስደት ዳርጎአቸዋል፡፡ እነዚህ ድርጊቶችም በክልሉ ስሱ የሆኑ ፖለቲካዊ ወጎችን ማንሳት ለከፍተኛ ቅጣት እንደሚዳርግ በክልሉ የሰፈነውን ህገወጥነት እንደሚያሳይ ጠቁሞአል፡፡

ከዚህ የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከተጠቀሱት ሁነቶች መካከል ተጠርጣሪዎች ከተያዙበት እለት ጀምሮ መደፈር፤ ከፍተኛ ቶርቸር ፤የኤሌክትሪክ ንዝረት፤አሰቃቂ የማሳቃያ ስልቶችን እንደሚጠቀሙባቸው ይገልጻል፡፡ከሁለት መቶ በለይ የድርጊቱ ሰለባ የሆኑ ሰወችን ቃል የሰበሰበው ተቋሙ፡፡አባትሽ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ደጋፊ ነው በሚል ምክንያት ብቻ ወደ ጦር ካምፕ በመውሰድ የጋለ ከሰል ሆዷ ላይ ጭምር በማስቀመጥ ያሰቃያት መሆኑን ገልጻለች፡፡ሌላው የድርጊቱ ሰለባ የሆነ መምህር ደግሞ መንግስት የሚቃወም ንግግር በክፍል ውስጥ ተናግረሀል በሚል ምክንያት ከፍተኛ ስቃይ እንደደረሰበት ተናግሯል፡፡

በኢትጵያ የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ተመራማሪ የሆኑት ክሌይር ቤስተን ስርአቱ በኦሮሞዎች ላይ የሚያደርሰውን ግፍ አውግዘዋለወ፡፡‹‹የኢትዮጵያ መንግስት በኦሮምያ ክልል ውስጥ ምንም አይነት ተቋውሞ የሚመስል ነገር ለማፈን የሚጠቀምበትን ጭካኔ የተሞላውን ዘግናኝ ግፍ ሰነዱ የሚጠቁም ነው ያሉት ክሌይር ቤስተን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተቃውሟቸውን በመግለጻቸው ብቻ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡››ሌላ የማፈኛ መንገድ ያለ ፍርድ ለረጅም ግዜ ማሰር ሲሆን ይህም ከብዙ ወራት እስከ ብዙ አመታት ሊደርስ እንደሚችል የገለጹት የተቋሙ ተወካይ ቃለ መጠይቅ ያደረጉዋቸው ሰዎች በቶርቸር ምክንያት የእጆቻቸውን ጣቶች፤ጆሮዎቻቸውን፤ጥርሶቻቸውን፤የሰውነታቸው አካላታቸው በእሳት መጠበሱን እንዲሁም መላው የሰውነት ክፍላቸው በጠባሳ መሞላቱን ተመልክተዋል፡፡በእስር ቆይታቸውም ወቅት እጅግ ከባድ ሁናቴ ውስጥ እንደቆዩና በከፍተኛ ቅዝቃዜ ውስጥ በመቆየታቸው የሰውነት አካለቸውን ለማዘዝ ተቸግረዋል ብለዋል፡፡

(Because I am Oromo) ኦሮሞ በመሆኔ በሚል ርእስ የወጣው የአምኒስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት በስፋት የጠቀሰው ሌላኛው ጉዳይ መንግስት የክልሉን ተወላጆች ለማሰቃየት የሚጠቀምበት ምክንያት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ደጋፊ ናችሁ የሚል መሆኑን ይገልጻል፡፡ እስርና እንግልቱ ከቤተሰብ አባላትን በርከት አድርጎ ማሰርንና ሴቶችን መድፈርን ያካተተ መሆኑን ቶርቸር ለመፈጸም የተለያዩ የመከላከያ ተቋማትን ለእስር ቤት እንደሚጠቀም ገልጾአል፡፡ ከ2003 እስከ 2004 ዓ.ም ብቻ ቁጥራቸው ከ አምስት ሺህ ባላይ የሚጠጉ የክልሉ ተወላጆች ለእስር እንደተዳረጉ ሌሎች በመቶወች የሚቆጠሩ በሰላም ተቃውሞአቸውን ያሰሙ ሰዎችን፤ እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ፤ሌላ በመቶወች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ባህላዊ ድርጊት ሲከውኑ የተገኙ ሰዎችን ማሰሩን የገለጸው ሪፖርቱ በነፃው የግል ሚድያና ፤የሰብአዊ መብት ተሟጓች ድርጅቶች ላይ ያለው ቀፍዳጅ ማእቀብ በመኖሩ ምክንያት እንጂ በሪፖርቱ ያልተካተቱ የብዙ ሌሎች አፈናዎች የመኖር እድል ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

ስርአቱ በክልሉ የሚፈጽማቸው የጅምላ አፈናዎች ፤ እስሮች ፤ ግድያዎች፤ በዚህ መጠን በሪፖርቱ መገለጹ በሀገሪቱ የሚፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰጦች ሀገሪቱ የደረሰችበት የሰብአዊ መብት አያያዝ የቁልቁለት ገዞ አመላካች ነው ሲሉ ብዙዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

Page 14: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 8414

ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

“ባለጌ ወንበር”

አበበ አካሉ ክብረት

በተለምዶ ባለጌ ወንበር ይሉታል፣ የመጠጥ ቤቱን ባልኮኒ ታክኮና ቁመቱን አዘልጎ መሸተኞችን የሚያፈናጥጠውን ወንበር፡፡

መቼም ይሄ ቁመተ መለሎ ወንበር ያለግብሩ ስም ወጥቶለት እንጂ የግዑዝ ነገር ባለጌ የለውም፡፡ የሰው ልጅ የራሱን ነውረኛ ባህሪ በወንበሩ ያላክክና ምስኪኑን ወንበር ባለጌ ሲል ይፈርጀዋል፡፡ ወንበሩም አስቀድሞ ባለጌ ተብሏልና ተቀማጩ ሁሉ ከወንበሩ ጋር ይደመራል፡፡ ወንበር የሚለው ስያሜ እማሬዳዊና ፍካሬያዊ ፍች አሉት፡፡ በእማሬያዊው ወይም በቀጥተኛ ፍችው መቀመጫ፣ ማረፊያ፣ ወግ መጠረቂያ፣ ሀሳብ መካፈያ . . . ነው፡፡ ወንበሩ ከእንጨት ከብረት አሊያም ከሌሎች ቁሳቁሶች ለሰው ልጅ መቀመጫነት እንዲመች ሆኖ በተለያየ ቅርፃ ቅርጽ ይሰራል፡፡

የወንበር ፍካሬያዊ ፍች /ከቀጥተኛ ፍች ጀርባ ያለው ምስጢራዊ ፍች/ ግን ሥልጣንን፣ ዳኝነትን፣ ፍርድንና ኃይልን . . . . አመልካች ነው የዚህ ፀሀፊም አላማ ከወንበር ፍካሬያዊ ትርጉም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡

ፈጣሪ የሰውን ልጅ በአምሳሉ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከፍጥረቱ መሀከል እየመረጠ ሕዝብን በቅንነት እና በታማኝነት ይመሩ ዘንድ በየዘመናቱ ወንበር ላይ ሰዎችን እየመረጠ ያስቀምጥ ነበር፡፡ የብዙዎቹም ታሪክ (በተለይም በብሉይ ኪዳን ዘመን) በስፋት ተተርኮ እናገኘዋለን፡፡

የግብፁ ፈርኦን የእስራኤልን ህዝብ ከአገዛዝ መዳፉ ላለማውጣት ፈጣሪውን ሲገዳደር እናያለን የተቀመጠበት ወንበር አባልጎት የአምላኩን ትዕዛዝ ባለመፈፀም ልቡን ማደንደኑ በተደጋጋሚ ዋጋ ሲያስከፍለው ተመልክተናል፡፡

ንጉሥ ሳኦልም የእስራኤል መሪ ሆኖ ከተቀባ በኋላ ወንበሩ ላይ ውሎ ሲያድር አምላኩን በብዙ ጉዳዮች አሳዝኗል፡፡ ይባስ ብሎ ከተሰጠው የምሪት አገልግሎት ውጪ በነብዩ ሳሜኤል እጅ መቅረብ የሚገባውን የእግዚአብሄር ቤትን መስዋዕት በራሱ ጊዜ ማቅረቡ የድፍረቱን ልክ ማለፍ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ፈጣሪውን በመገዳደሩ የተነሳ እግዚአብሄር በጠላቶቹ ፊት አሳልፎ ሲሰጠውና ከነ ልጆቹ የውርደት ሞትን ሲጎነጭ እንመለከታለን፡፡

ለመልዕክቴ ማዋዣ ይሆን ዘንድ ከዚሁ ከመፅሀፍ ቅዱስ የንጉስ ዳዊትን አሳዛኝ ድርጊት ላካፍላችሁ፡፡ ንጉስ ዳዊት ከንጉስ ሳይል የውድቀት ዋዜማ ላይ የእስራኤልን ህዝብ ለመምራት ለወንበሩ የተቀባ ንጉስ ነው፡፡ እግዚአብሄር “እነሆ ልቤ ያረፈችበት የእሴይ ልጅ . . .”ሲል ያሞካሸው ንጉስ ዳዊት፣ፈጣሪው ከበጎች የእረኝነት ሥፍራ አንስቶ ለንግስና የቀባው ንጉስ ዳዊት፣ ጦረኛውን ፍልስጤማዊጎልያድን በወንጭፍ እንዲገነድሰው ፈጣሪው ጉልበት የሆነው ንጉስ ዳዊት . . .እሱም በተራው ወንበሩ አባለገውና አሳዛኝ ድርጊት ፈፀመ፡፡እስራኤላዊያን በጦርነት ተጠምደው ባሉበትና ሠራዊቱ በጦር ሜዳ ግዳይ እየጣለ በሚወድቅበት ፈታኝ ወቅት ላይ የኦርዮን

ሚሰት ቤርሳቤህን አስነወራት ፈጣሪውከእስራኤል ቆነጃጅቶች መካከል በርካታ ሚስቶችንና ቁባቶችን ሰጥቶት ሳለ የኦርዮን ሚስት መመኘቱ እጅግ ያሳዝናል፡፡ንጉስ ዳዊት ይዝናናበት ከነበረው ሰገነት ላይ ሆኖ ቤርሳቤህ እርቃኗን ሆና ገላዋን ስትታጠብ ይመለከታል፡፡ ይህን ጊዜ የሠራ አካላቱ በፍትወት እሳት ጋየ፡፡ ወዲያውኑ ከአገልጋዮቹ አንድ ሰው ጠርቶ ወደ ቤተመንግስት አስመጣች ተገናኛት፡፡ እሷም አረገዘች፡፡ንጉሱም ማርገዟን ሲረዳ ኦርዮን ከጦር ሜዳ አስጠርቶት ከሚስቱ ጋር እንዲገናኝ ለማድረግ ሞከረ፡፡ሙከራው ግን አልተሳካም፡፡ኦርዮን አሻፈረኝ አለ፡፡ እስራኤል ከጠላቶቹ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቀ ባለበት በዚህ ቀውጢ ሰዓት የእኔ ክንድ ሚስቴን አያቅፍም በሚል በአላማው ፀና፡፡ ይህን ጊዜ ዳዊት በኦርዮን ላይ ሞትን ፈረደበት፡፡ የጦር አዛዡ ኦርዮን የተፋፋመ የውጊያ ግንባር ላይ ፊት ለፊት አላባከነም፡፡ ከኦርዮ ሞት በኋላ ግን ሚስቱን የራሱ ንብረት አደረጋት፡፡

ንጉስ ዳዊት እንዲህ አይነቱን አስነዋሪ ተግባር የፈፀመው ግን ወንበሩ ባለጌ ስለነበረ አይደለም፡፡ የባለገው ንጉሱ ራሱ ነው፡፡ ሥጋዊ ስሜቱን መግዛት ባለመቻሉ ስልጣኑን ተጠቅሞ በስራው በደል ፈጣሪውን ክፉኛ አሳዘነ፡፡ አምላኩም የቅጣት ብትሩን ሰነዘረበት፡፡ እሱም ማቅለብሶና ምድር ላይ ተንከባልሎ ከፈጣሪው ዘንድ ምህረትን ተማጠነ፡፡

የኢህአዴግ ባለጌ ወንበሮች

የእምዬ ምኒሊክ ወንበር ላይ በአፈሙዝ ኃይል የተቀመጠው ኢህአዴግ ላለፉት 23 ዓመታት አሳዛኝ አስነዋሪና የአገሪቱን ሉኣላዊነትና የዘመናት ታሪክ የተገዳደሩ እኩይ ተግባራትን ፈፅሟል፡፡ ዛሬም ቢሆን ከዚህ ድርጊቱ ባለመታቀብ በወንበሩ ተተግኖ አገሪቱን ወደ መቀመቅ እያወረዳት ይገኛል፡፡

የሕወሓት/ኢህአዴግ ፊታውራሪ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ወንበሩ ላይ ገና በቅጡ ሳይቀመጡ የአገሪቱን ሉኣላዊነት የሚመሰክረውን ሰንደቅ ዓላማ ከተራ ጨርቅ ጋር አመሳሰሉት፤ የሶስት ሺህ ዘመን ታሪኳን በመቶ አመት አስጠሩት፤ የሻዕቢያ ደቀመዝሙርነታቸው ከኢትዮጵያዊነታቸው ይበልጥ አክንፏቸው ኤርትራን በቀላሉ አስገነጠሉ፡፡ አገሪቱንም የባህር በር በማሳጣት ቅስም ሰባሪ ህፀፅ ሰርተው አለፉ፡፡

የአቶ መለስ የአገዛዝ ዘመን የወለደው የዘርና የጐሣ ፖለቲካ ለነገዋ ኢትዮጵያ እሾህና አሜኬላ መሆኑን ዛሬ ላይ ከሚታየው ነገር ተነስተን መናገር እንችላለን፡፡በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ለዘመናት ተከባብሮ የኖረው ህዝብ እርስ በርሱ ጦር እንዲማዘዝና የጎሪጥ እንዲተያይ በማድረጉ ረገድ ጉልህ ሚና የተጫወተው የ4ኪሎው ቤተመንግስት ወንበር ቢሆንም የባለገው ግን መቀመጫው ሳይሆን ተቀማጩ ነው፡፡

ከአቶ መለስ ህልፈት ማግስት ወንበሩ ላይ የተቀመጡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ቢሆኑ ለወንበሩ ጨዋነት እንዳልቆሙ የተመለከትነው ገና በስልጣናቸው ማለዳ ላይ ነበር፡፡ ለፈጣሪ የሚገባውን ዘላለማዊ ክብር ለአቶ መለስ በመስጠት እንደ ሳዖል አምላክን

በመገዳደር አገሪቱን መምራት መጀመራቸው የብዙዎችን ልብ ሰብሮ አልፏል፡፡

አቶ መለስ 21 ዓመታት ሙሉ በቀደዷቸው የስህተትና የጥፋት ቦዮች አንዳችም አቅጣጫ ሳይቀይሩ እንደሚፈሱ አስረግጠው ስለነገሩን እኛም ከአቶ ኃይለማርያም ምሬት ለውጥ አንጠብቅም፡፡

ላለፉት 23 ዓመታት በወንበሩ ላይ የባለጉት መሪዎቻችን ዛሬም ቢሆን ከልካይ የለባቸውም፡፡ ያሻቸውን ሲያደርጉም ሕሊናቸው አይወቅሳቸውም፡፡ ዜጎች ከቆሻሻ ገንዳ ውስጥ ከዝንቦች ጋር ተሰልፈው የዕለት ጉርሳቸውን ሲፈልጉ የባለጌው ወንበር ሹማምንት እጆቻቸውን እያስረዝሙ የአገሪቱን አንጡራ ሀብት በጠራራ ፀሀይ ይዘርፋሉ፡፡ የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በአደባባይ እየረገጡ ስለ ዴሞክራሲ ለማቀንቀን አንደበታቸውን የሚይዛቸው አንዳችም ኃይል የለም፡፡ ከትናንቱ ታሪካዊ ስህተት ለመማር ልባቸው ዝግጁ ባለመሆኑ ኤርትራን ባስገነጠለው እጃቸው ዛሬ ደግሞ ከአገሪቱ ሰሜናዊ ግዛት (ለጎንደር) የግዛት ክልል እስከ ደቡብ ጥግ የአገሪቱን የግዛት ክልል ቆርሰው ለሱዳን መንግስት በገፀ በረከትነት መስጠታቸው የሰሞኑ አንገብጋቢ አገራዊ አጀንዳ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ መቼም ብልግና ከዚህ በላይ መገለጫ ያለው አይመስለኝም፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሚሊዮኖችድምፅ ለነፃነት በሚል በወርሃ ሐምሌ መግቢያ በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሠልፍ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ለዞኑ ባለስልጣናት የሰልፉን ሂደት ለማሳወቅና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የፓርቲው አመራሮች በተንቀሳቀሱበት ወቅት ካጋጠሟቸው በርካታ ባለጌ ወንበሮች መሃከል የሰሜን ጐንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወንበር ዋነኛው ነበር፡፡

ሰውዬው አይናቸውን እያጉረጠረጡ “በምንም አይነት ሁኔታ ሰልፉ አይካሄድም፡፡” ሲሉ የፈረጠመ የስልጣን ክንዳቸውን ለማሳየት ሞከሩ፡፡ የፓርቲው ተደራዳሪዎችም የዋዛ አልነበሩምና ከሰውዬው ጋር ሙግት ገጠሙ፤ ይህን ጊዜ ትዕግስት የለሹ የአማራ ክልል ሹመኛ የታሪካዊውን የጐንደርን ህዝብ ቅስም የሚሰብር ንግግር አሰሙ፡፡ “ . . . እናንተ የጎንደርን ህዝብ አታውቁትም፣ የጐንደር ህዝብ ዱርዬ ነው አንድ እግሩን አርበኞች ግንባር አንድ እግሩን ከእናንተ ጋር በማድረግ የሚንቀሳቀስ ህዝብ ነው፡፡” ሲሉ በድፍረት ተናገሩ፡፡ ሕዝቡ በሙሉ ድምፁ መርጦናል የሚሉት የኢህአዴግ ሹማምንት የሚያስተዳድሩትን ህዝብ እጅግ በወረዱ ቃላት የመሳደባቸው ምክንያቱ ግዑዙ ወንበር ሳይሆን ሰዎቹ ናቸው፡፡

በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ከተማ ላከናወነው ምድር አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሠልፍ መነሻው ምክንያት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የአማራን ህዝብ ያዋረደ ስድብ መሆኑ የትናንት ትዝታችን ነው፡፡ ለአቶ አለምነው መኰንን ወንበር መባለግ ግን ተጠያቂው አንድ እና አንድ ገዢው ፓርቲ ነው፡፡ ያልተገራ አንደበት ያላቸውን አቅመቢስ ሰዎች ከሜዳ እያነሳ መሾሙ ውሎ አድሮ ዋጋ እንደሚያስከፍለው ኢህአዴግ ራሱ ልብ ሊል ይገባል፡፡

ላለፉት 23 ዓመታት

በወንበሩ ላይ የባለጉት

መሪዎቻችን ዛሬም ቢሆን

ከልካይ የለባቸውም፡

ያሻቸውንሲያደርጉም

ሕሊናቸው

አይወቅሳቸውም፡፡

ዜጎች ከቆሻሻ ገንዳ

ውስጥ ከዝንቦች ጋር

ተሰልፈው የዕለት

ጉርሳቸውን ሲፈልጉ

የባለጌው ወንበር

ሹማምንት እጆቻቸውን

እያስረዝሙ የአገሪቱን

አንጡራ ሀብት በጠራራ

ፀሀይ ይዘርፋሉ፡፡

Page 15: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

15ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም

የመድረክ መንገድ ለምን ሩቅ አላስኬደንም?

ይህ ገፅ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አቋሞች የሚስተናገዱበት ነው

መድረክ የተባለው የፖለቲካ ስብስብ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በብሔር የተደራጁና ህብረ ብሔር የሆኑ ፓርቲዎችን አንድ ላይ በማሰባሰብ የተዋቀረ፤ አዲስ የመተባበር መንገድ ይዞ የመጣና በመጠኑም ቢሆን ውጤት ያስገኘ ስብስብ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ይህ ስብስብ የተሻለ ጠንካራ አማራጭ ሆኖ እንዲገኝና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጥግና ጥግ የያዙትን አቋሞች እንዲቀራረቡ ለማድረግ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተገቢውን ድርሻ ተጫውተዋል፤ ከፍተኛ የሆነ ዋጋም ከፍሎበታል። አንድነት አሁንም ቢሆን በመድረክ ጉዳይ ላይ የነበረውን አቋምና የወሰዳቸው ውሳኔዎች ትክክልና ተገቢ ነበሩ ብሎ ያምናል። ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ያላት፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሰፈነባት፣ የተረጋጋችና በኢኮኖሚ የበለፀገች እንድትሆን ከተፈለገ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚያሳትፍ ፖለቲካዊ ስርዓት መፈጠር አለበት የሚለው የአንድነት ፅኑ አቋም ነው፤ በዚሁ እምነትና መንፈስም ነው ከመድረክ ጋር አብሮ ሲሰራ የነበረው። ነገር ግን መድረክ በአስተሳስብ፣ በአወቃቀርና በአሰራር ያልተሻገራቸው መሰረታዊ የሆኑ ችግሮች የነበሩት በመሆኑ፤ እነዚህ እጥረቶቹ የአንድነት አባላትና በጠቅላላ ለውጥ ፈላጊው የኢትዮጵያ ህዝብ በሚፈልጉት ቁመናና ደረጃ እንዳይገኝ አድርጎውታል።

በዚህ ምክንያት አንድነት ገና ከጠዋቱ መድረክ ከእነዚህ እጥረቶቹ እንዲያስተካክልና እንዲሻገራቸው ለማድረግ በፅናት ታግሏል፤ የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጦ በመድረክ የመዋቅርና የአሰራር ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ የሆነ የመስመር ትግል አድርጓል። መድረክ ከመጀመርያው ጀምሮ ህብረ ሔርና ብሔር ተኮር የሆኑ ድርጅቶች አንድ ላይ ያቀፈ በመሆኑ በተወሰነ ደረጃ ተፈጥሯዊ የሆኑ የፍላጎት መጋጨቶች ነበሩበት። ህገ ደንቡ ላይ በስብስቡ ውስጥ የታቀፉ ህብረ ብሔራዊ የሆኑ ፓርቲዎች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲንቀሳቀሱ፣ አባላት እንዲያደራጁና ፅህፈት ቤት እንዲከፍቱ የሚገድብ ነገር ባይኖርም፤ በተግባር፣ በእምነትና በአሰራር አንዳንድ የመድረክ አመራሮች አንድነት ላይ ገደብ በመጣል ወይም የተወሰነ አከባቢ ፓርቲ ነው የሚል የተዛባ አቋም በማራመድ በመድረክ አባል ፓርቲዎች መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት እንዳይኖር ምክንያት ሆኗል።

ከዚህም አለፍ ሲል እነዚህ የመድረክ አመራሮች አንድነትን የሚፈልጉት እነርሱ መሸፈን በማይችሉባቸው ከተሞችና የአማራ ክልል የሚባለው አካባቢ እንዲወክልላቸው እንጂ ህብረ ብሔራዊነቱን አምነው እንዳልተቀበሉት በግልፅ እየታየ የመጣ ሀቅ ሆኗል። በዚህም ምክንያት አንድነት ወደ ተለያዩ ክልሎች ለመግባት በሚሞክርበት ወቅት ከሌሎች የመድረክ አባል ድርጅቶች ተዳጋጋሚ ክስና ወቀሳ ሲደርስበት ነበር። ይህ የሆነበት ምክንያትም አንዳንዶቹ በሚፈልጉት መንገድ ኦሮሚያ በኦፌኮ፣ ትግራይ በአረና፣ ደቡብ በደቡብ ህብረት እንዲወከልና አንድነት ወደ እነዚህ አከባቢዎች መንቀሳቀስ ቢፈልግ የእነዚህ ድርጅቶች መልካም ፍቃድ እየጠየቀ እንዲሆን ነው። ይህ ደግሞ ከአንድነት ህብረ ብሔራዊነት፣ ፖለቲካዊ አቋምና ቁመና ጋር ፈፅሞ የሚሄድ ነገር አይደለም።

እርግጥ ነው፤ አንድነት አንዳንድ የመድረክ አመራሮች በግልፅ “አንድነት የከተማና የአማራ ፓርቲ ነው” የሚለውን አቋም ሲያራምዱ አብሮ ለመስራት ሲባል የእዮብን ትዕግስት በማሳየት በዝምታ አልፎታል። ነገር ግን ይህ አባባል በአንድነት ውስጥ በሀሳብና በአላማ ላይ አምነው ለተሰባሰቡበት፣ የተለያዩ የሀገራችንን ቋንቋዎች የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ላሉበት፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ቤት ለሆነው አንድነት ፓርቲ የሚመጥን አይደለም። አንድነት ከአመራሩ ጀምሮ እስከታች ያሉት አባላቱ ድረስ ያለው የብሔረሰቦች ስብጥር፤ ፖለቲካዊ እምነቱና አሰራሩ ፍፁም ህብረ ብሔራዊ እንደሆነ ማሳየት የሚችል ነው። በአቋም ደረጃም ከዚህ በላይ ገፍቶ በመሄድ አንድነት በተሻለ ሁኔታ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ቤት እንዲሆን ጠንክሮ እየሰራ ነው የሚገኘው።

ሌላው መድረክ ላይ ያለው መሰረታዊ ችግር ህገ ደንባዊ ነው። መድረክ በቅንጅትነት ጊዜ ያረቀቀውንና ሲሰራ የነበረውን ህገ ደንብ መሰረታዊ ለውጥ ሳይደረግበት ወደ ግንባር በመሸጋገሩ ስብስቡ እውነተኛ ግንባር እንዳይሆን አድርጎታል። ከዚህም ባሻገር የመድረክ ህገ ደንብ አሳታፊነት የሌለው፤ ዴሞክራሲያዊ ባህልና የአመራር ዳይናሚዝም ለማምጣት የማያስችል ህገ ደንብ ነው። በህገ ደንቡ ላይ ያሉት ችግሮች ብዙ ቢሆኑም፤ በዋናነት ግን የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፦

የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ አሳታፊ ያለመሆኑ በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ከየፓርቲው ከሚገኙ መሪዎች መካከል አስር አስር ሰዎች የሚወከሉበት የነበረ ከመሆኑም ባሻገር እነዚህ አስር አስር ሰዎችም በሚሰበሰቡበት ጊዜ ምንም ዓይነት ውሳኔ ማሳለፍ አይችሉም፤ ምክንያቱም በመድረክ ህግ ደንብ መሰረት ወሳኝ የሚባሉ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች የሚተላለፉት እያንዳንዱ ፓርቲ በሚይዘው አቋም ስለሆነ፤ በመሆኑም የፓርቲዎቹ አመራሮች ናቸው የሚወሰኑት እንጂ የጠቅላላ ጉባኤው አባላት አይደሉም፤ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተሰብስበው ፓርቲዋቻቸው ካስቀመጡት ውሳኔ ውጪ ምንም ዓይነት ውሳኔ መወሰን አይችሉም። በእውነቱ ከሆነ ምንም ዓይነት ስልጣን የሌለው ጠቅላላ ጉባኤ ባይሰበሰብም ምንም የሚያጎድለው ነገር የለውም፤ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ እንደዚያ ዓይነት ነው የነበረው።

ሌላው መሰረታዊ ችግር ደግሞ የመድረክ ሊቀመንበርና ሌሎች ምክትል ሊቃነመናብርት የሚመረጡት በብቃት ሳይሆን በዙር ለየፓርቲዎቹ በተራ የሚዳረስ በመሆኑ ብቃት ያለውና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነ አመራር ለማምጣት አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል። በዚህ ምክንያትም የግንባሩ መሪዎች ተብለው ከተመረጡ በኋላ ምንም ዓይነት ስራ ሳይሰሩ የሚወርዱና እንደገና ተመልሰው በሌላ ጊዜ መሪ ሆነው የመጡ ነበሩ፤ ይሄ በተደጋጋሚ የታየ ክስተት ነበር። ይህ ሁኔታ በመድረክ ውስጥ ምንም ዓይነት ተጠያቂነት የሌለው ስልጣንና ሃላፊነት እንዲኖር አድርጎታል፤ በዚያው መጠንም ትግሉን ጎድቶታል፤ ትግሉን በአግባቡ ለመምራትና ወደፊት ለማስኬድም አልተቻለም።

ከዚህም ባሻገር የአንድ የመድረክ መሪ የስልጣን እድሜ ስድስት ወር እንዲሆን

መደረጉ፤ (ግንባር ከሆነ በኋላ በብርቱ ጉትጎታ ወደ አንድ ዓመት ተደጎ ነበር) በመድረክ ውስጥ የተረጋጋና ዘላቂነት ያለው ስራ እንዳይኖር አድርጓል፤ ምንም ዓይነት ለውጥ ሳይኖር፣ ምንም ዓይነት ስራ ሳይሰራ በየጊዜው ተመሳሳይ ሰዎች ሊቀመንበርና ምክትል እየሆኑ የሚመረጡበትም ሁኔታ እንዲፈጠር ሆኗል፤ ይህም ሁኔታ በህዝብ ዘንድ ውዥንብር ከመፍጠር ውጪ የፈየደው ነገር አልነበረም። እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ አዳዲስ አመራር ወደፊት እንዳይመጣ፣ በህገ ደንብ ላይ ሊቀመንበር የነበረ ሰው ሲወርድ ምክትል ይሆናል የሚል አንቀፅ እንዲኖር በመደረጉ፤ በግንባሩ ላይ የአመራር ዳይናሚዝም ለመፍጠር እጅግ በጣም አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል።

በህገ ደንቡ ላይ ያለው ሌላ ችግር ደግሞ አዳዲስ ፓርቲዎች ወደ ግንባሩ ለመግባት ቢፈልጉ መንገዱ በጣም ጠባብና አስቸጋሪ እንዲሆን መደረጉ ነው። አንድ ፓርቲ መድረክን ለመቀላቀል ቢፈልግ የሁሉም አባል ፓርቲዎች ይሁንታ የሚያስፈልግ በመሆኑ በስብስቡ ካሉት ውስጥ አንዱ ፓርቲ ከተቃወመ መግባት አይችልም። በተግባርም ሲሆን የነበረው ይሄው ነው፤ በተደጋጋሚ ብዙ ፓርቲዎች የመድረክ አባል ለመሆን ቢያመለክቱም በአንድ ፓርቲ ምክንያት ውድቅ እንዲሆን እየተደረገ ስብስቡ እንዳይጠናከርና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የተቃውሞ ኃይል ወደ አንድ እንዳይሰባሰብ አድርጓል።

በመሆኑም አንድነት እነዚህ ችግሮች እንዲቀረፉና መድረክ እውነተኛ የትግል መስመር እንዲይዝ ለማድረግ በቃል ከመወትወት ባለፈ መልኩ፤ የጥናት ኮሚቴ በማዋቀር መድረክ ወደ ተሻለ አቅጣጫ ስለሚሄድበት ሁኔታ ጥልቀት ያለው ጥናት አዘጋጅቶ አቅርቧል፤ የመፍትሄ ሀሳቦችንም አስቀምጧል።

አንደኛ በመድረክ ውስጥ ያሉትን የህገ ደንብ ችግሮች በማሻሻል ስብስቡ አሳታፊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ማድረግ፤ ይህ እንዲሆን ደግሞ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥር ከፍ እንዲል ተደርጎ ከየፓርቲው ከአንድ መቶ በላይ አባላት እንዲወከሉ እንዲደረግ፤ የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ የመወሰን ስልጣን እንዲኖረው እንዲደረግ፤ የመድረክ መሪ አመራረጥ በብቃትና በችሎታ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ የተረጋጋና ዘላቂ የሆነ አመራር እንዲኖር ሊቀመንበሩና ስራ አስፈፃሚው በስልጣን የሚቆይበት ጊዜም እንዲረዝም፤ አዳዲስ ፓርቲዎች ለመቀበል የሁሉም ፓርቲዎች ስምምነት ያስፈልጋል የሚለው ቀርቶ 2/3ኛ ድምፅ እንዲሆን፤ መድረክ ብሔራዊ ምክር ቤት እንዲኖረው እንዲደረግ የሚሉና የመሳሰሉት እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆኑ ማሻሽያዎች አቅርቦ ነበር።

ሁለተኛው ደግሞ በፕሮግራም ላይ እልባት ያልተደረገባቸው፣ የርዕዮተ ዓለም፣ የፌደራሊዝም አወቃቀርና የመሬት ጉዳይ ተጨማሪ ውይይቶች በማድረግ ወደ ተሻለ መግባባትና አቋም እንዲመጣ፤ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ከተያዘ ደግሞ መድረክ ወደ ውህድ ፓርቲነት እንዲሸጋር በጥናቱ ላይ አንድነት ጠቋዋል። መድረክ ትክክለኛ ግንባር ወይም ውህድ ፓርቲ የማይሆን ከሆነ አሁን ያለው ህገ ደንብና

ፕሮግራም በቅንጅትነት ካልሆነ በስተቀር በግንባር ደረጃ የማያሰራ በመሆኑ፤ አንድም ወደ ቅንጅትነት እንዲወርድ፣ አልያም ትክክለኛ ግንባር እንዲሆን ወይም እንዲዋሀድ ነበር አንድነት ሀሳብ ያቀረበው።

የሚያሳዝነው ነገር አንድነት ተነሳሽነት ወስዶ ላቀረበው ጥናትና የመፍትሄ ሀሳብ በመድረክ በኩል የተሰጠው መልስ አዎንታዊ አልነበረም ብቻ ሳይሆን ከዚያ በፊት ከነበሩት ሌሎች ቁርሾዎች ጋር በማያያዝና አንድነት በመድረክ ላይ እምነት እንደሌለው በማስመል ሌላ ያለተፈለገ አቧራ ለማስነሳት ሞከሩ ነው። ከዚህም ባሻገር አንድ ጊዜ የፓርቲው ሊቀመንበር በመድረክ ላይ ያልሆነ ነገር ተናግራል፤ ይህን አስተባብሉ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከመድረክ ፍላጎት ውጪ ተንቀሳቅሳቸዋል በሚል ሰብብብ አንድነት ከመድረክ እንዲታገድ ነው የተደረገው። አንድነት አብሮ ለመስራት ከነበረው ፍላጎት የተነሳ እነዚህ ችግሮችን ሁሉ ችሎ በሊቀመንበሩ በኩል ተነገሩ የተባሉት ነገሮች ፓርቲው አቋም ያልወሰደባቸው በመሆኑ አይወክሉም ብሎ በመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቢያስተባብልም፤ በሚዲያ ነው ማስተባበል ያለባችሁ የሚል ግትር አቋም በመያዝ አንድነት እንዲታገድ ተደርጓል። በመሰረቱ በወቅቱ የተጣለው እግድ ፈፅሞ አግባብ አልነበረም፤ በኋላም ቢሆን አንድነት እግዱ አግባብነት የለውም በማለት እንዲነሳለት በደብዳቤ ቢጠይቅም፤ ከመድረክ የተሰጠው ምንም ዓይነት መልስ አልነበረም፤ ምናልባት ጠቅላላ ጉባኤው በድጋሚ አይቶ ይሄ ጉዳይ መፍትሄ ይሰጥበት ይሆናል በማለት አንድነት እስከመጨረሻ ድረስ በትዕግስት ጠብቋል። ነገር ግን ጥቅምት 29 ቀን2007 ዓ.ም. በተካሄደው የመድረክ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አንድነት አዲስ አመራር በተካበት ሰዓት እስኪ እግዱ እናንሳውና እድል እንስጣቸው፣ አብረን ነው ችግሩን መቅርፍ ያለብን ከማለት ይልቅ በአንድነት ላይ የተጣለው እግድ እንዲቀጥል መወሰኑ መድረክ በዚህ የምርጫ ወቅት ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ታሪካዊ የሆነ ስህተት ፈፅመዋል ብለን እናምናለን።

በምርጫ ቦርድ አዋጅ መሰረት በግንባር የታቀፉ ፓርቲዎች ምርጫ ላይ መወዳደርና የምርጫ ምልክት መውሰድ የሚችሉት በግንባሩ በእኩል በመሆኑ በዚህ ሰዓት አንድነት አውላላ ሜዳ ላይ እንዲቀር የሚያደርግ ውሳኔ ነው በመድረክ በኩል የተወሰነበት፤ በመሆኑም የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ጥቅምት 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ አንድነት ከመድረክ ግንባር አባልነት ራሱን በይፋ ማግለሉንና ከዚህ ጊዜ በኋላ አንድነት ራሱን ችሎ እንዲንቀሳቀስ ውሳኔ አስተላልፏል። አንድነት አሁንም በኢትዮጵያ ፖለቲካ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው የተቃውሞው ጎራ ወደ አንድ የተደራጀ ኃይል ሲሰባሰብና በአንድ ላይ ሲቆም መሆኑን ያምናል። አሁንም ቢሆን አንድነት ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በእኩልነት መርህና በጋራ ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ የመተባበርና አብሮ የመስራት አቋሙ ያልተቀየረ መሆኑ፤ የተቃውሞው ጎራ ወደ አንድ እንዲሰባሰብ አሁንም አንድነት በማንኛውም መልኩ ከሌሎች ሀቀኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመስራት ቁርጠኛ የሆነ አቋሙ በቦታው ላይ እንዳለ ማሳወቅ ይፈልጋል።

Page 16: Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ p Þ k÷ û º ......* p Hß 5 ß0 4 1//6 .k Á p D÷73 Õ pÛ Ø Ê` Õ Á ¹ 8 ^ _p Þ k÷ û º÷¼ 6 `0 Visit us :- ,

አራተኛ ዓመት ቅፅ 4 ቁ 84የኢትዮጵያ ህዝብ የሉዓላዊ ስልጣኑ ባለቤት እንዲሆን እንተጋለን!

ፍኖተ ነፃነት

Visit us :- www.fnotenetsanet.com, www.andinet.org

16ቅዳሜ ህዳር 6 2007 ዓ.ም