ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/wudassie...

17
ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩማቴ 2641ቅድሥተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽየማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ሉቃ 142

Upload: others

Post on 17-Nov-2020

10 views

Category:

Documents


3 download

TRANSCRIPT

Page 1: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ” ማቴ 26፥41።

ቅድሥተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ሉቃ 1፥42

Page 2: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

2

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

መክስተ አርዕስት

• ጸሎት ዘዘወትር…………………………………………………………….3

• ውዳሴ ማርያም……………….……………………………………………5

• የሰኞ ውዳሴ ማርያም…….…………………….…..…………..………….…………….5

• የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም…………………………………….………….…………….6

• የረቡዕ ውዳሴ ማርያም………………………….…………….………….…………….8

• የሐሙስ ውዳሴ ማርያም……………………………………..………….…………….9

• የዓርብ ውዳሴ ማርያም……………………………………….……..…….………….11

• የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም……………………………………..……………………….12

• የእሁድ ውዳሴ ማርያም………………………………….....…………….…….…….14

• ይዌድስዋ………………………………….....…….……….…….…….15

Page 3: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

3

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

የዘወትር ጸሎት

በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትእምርተ መስቀል ፊቴን እና ሰውነቴን ሦስት ጊዜ አማትባለው።

፩፤ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማፀንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለው፣ በዚች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለው ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።

፪፤ አቤቱ እናመስግንሃለን አቤቱ እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን። አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመስግናለን። ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበትም ሁሉ ላንተ ይገዛል የአምላኮች አምላክ የጌቶች ጌታ የንጉሦችም ንጉሥ አንተ ነህ። የሰጋም የነፍስም ፈጣሪ አነተ ነህ። እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራለሃን።

፫፤ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን። የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል። አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋናም ለዘለዓለሙ አሜን።

፬፤ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ፤ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ በሃሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ፤ ላንቺ ሰላምታ ይገባል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ፀጋን የተመላሽ ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታን ለምኝልን ኃጢአታችንን ያስተሰርይልን ዘንድ አሜን።

የሃይማኖት ጸሎት

፭፤ ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ፥ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለርሱ ምንም ምን የሆነ የለም ስለኛ ስለሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፣ ደግሞ ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን

Page 4: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

4

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ተለይቶ ተሰሣ፣ በቅዱሳን መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደሰማይ ዐረገ። በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፣ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብ ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው። ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ክብርት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ።

፮፤ አሸናፊ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ። ምስጋናህም በሰማይ በምድር የመላ ነው። ክርስቶስ ላንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ እንሰግድልሃለን ወደዚህ ዓለም መጥተህ አድነኸናልና።

፯፤ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለው /3 ጊዜ በል/። አንድ ሲሆን ሦስት ሦስት ሲሆኑ አንድ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለው አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለው፣ ዓለምን ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እስገዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው ኃይላችን መስቀል ነው የሚያፀናን መስቀል ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው፣ መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው፣ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን፣ ድነናለም።

፰፤ ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል። /3 ጊዜ በል/ አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል። ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ፣ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ እንዳያሳፍረን፣ ስሙን ለማመስገን ያነቃን ዘንድ፣ እርሱንም በማምለክ ያጸናን ዘንድ፣ እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጊልን፣ ኃጢአታችንንም አስተሥርዩልን በጌታችን መንበር ፊት ጸሎታችንን አሳርጊልን፣ ይህንን ኅብስት ላበላን ይህንንም ጽዋ ላጠጣን፣ ምግባችንንና ልብሳችንንም ላዘጋጀልን፣ ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሠልን፣ ክቡር ደሙን ቅዱስ ሥጋውን ለሰጠን፣ እስከዚችም ሰዓት ላደረሰን ለእሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍፁም ምስጋና ይገባል፣ ለወለደችው ለድንግም ምስጋና ይገባል፣ ለክቡር መስቀሉም ምስጋና ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱና በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።

፱፤ እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

Page 5: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

5

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

፲፤ አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የማርያም ጸሎት፤ ማርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል። የባሪያይቱን መዋረድ አይቷልና። እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል። እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና ስሙም ቅዱስ ነው። ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ነው ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ ትዕቢተኞችን በታተናቸው ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው። የተራቡትንም በቸርነቱ አጠገባቸው ባለጠጎችንም ቦዶ እጃቸውን ሰደዳቸው ምሕረቱን እንዲያስብ እስራኤል ባርያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩም እስከዘለዓለሙ ድረስ እንደተናገረው።

ውዳሴ ማርያም

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና።

፩፤ ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ ከድንግል ያለወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና አዳነን።

፫፤ ከይሲ (ዲያብሎስ) ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ጻርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት፤ ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ ሰው የሆነና በኛ ያደረ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ክብሩንም ለአባቱ አንደ እንደመሆኑ ክብር አየን። ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ነቢዩ ኢሳያስ በመንፈስ ቅዱስ የአማኑኤልን ምሥጢር አየ ስለዚህም ሕፃን ተወለደልን ወልድም ተሰጠን ብሎ አሰምቶ ተናገረ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ ሰው ሆይ ፈጽመህ ደስ ይበልህ እግዚአብሔር ዓለሙን ወዶታልና አንድ ልጁንም የሚያምንበት ሁሉ እስከ ዘለዓለም ፈጽሞ ይድን ዘንድ አሳልፎ ሰጥቷልና ልዑል ክንዱን ሰደደልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ የነበረው የሚኖረው የመጣው ዳግመኛ የሚመጣውም ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ያለመለወጥ ፍጹም ሰው ሆነ። አንዱ ወልድ በሥራው ሁሉ አልተለየም የእግዚአብሔር ቃል መለኮት አንድ ነው እንጂ ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ የነቢያት ሀገራቸው ቤተልሔም ሆይ ደስ ይበልሽ ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ በአንቺ ዘንድ ተወልዷልና። የቀድሞውን ሰው አዳምን ከምድር (ከሲኦል) ወደ ገነት ይመልሰው ዘንድ፤ አዳም ሆይ መሬት ነበርክና ወደ መሬት ትመለሳለህ ብሎ የፈረደበትንም የሞት

Page 6: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

6

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ፍርድ ያጠፋለት ዘንድ፤ ብዙ ኃጢአት ባለችበት የእዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱፤ የሰው ሁሉ ሰውነት ደስ ይላታል በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰውም እርሱ በሚፈቅደው እያሉ አሰምተው ንጉሥ ክስርቶስን ከመላእክት ጋር ያመስግኑታል። የቀድሞውን እርግማን አጥፍቷልና የጠላትን ምክሩን አፈረሰበት ለአዳምና ለሔዋን የዕዳ ደብዳቤያቸውን ቀደደላቸው በዳዊት ሀገር የተወለደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምንና ሔዋንን ነፃ አደረጋቸው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፤ በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታበራ እውነትኛ ብርሃን ስለሰው ፍቅር ወደ ዓለም የመጣህ ፍጥረት ሁሉ በመምጣትህ ደስ አለው አዳምን ከስህተት አድነኸዋልና ሔዋንንም ከሞት ጻዕረኝነት ነፃ አድርገኻታልና የምንወለድበትን መንፈስ (ረቂቁን

ልደት) ሰጠኸን ከመላእክት ጋርም አመስገንህ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ማክሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም

ምስጋና፤

፩፤ የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ የንጽሕናችንም መሠረት እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን። ሰው ከሆነ በኋላም ፍጹም አምላክ ነው ስለዚህም በድንግልና ወልደችው። ድንቅ የሆነ የመወለድዋ ችሎታ የማይመረመር ሊነገር የማይቻል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ በእርሱ ፈቃድ በአባቱ ፈቃድ በመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ መጥቶ

አዳነን። በድንግልና ፍጽምት የሆንሽ ማርያም ሆይ የድንግልናሽ ምሥጋናና ክብር ታላቅ ነው። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና። ያዕቆብ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ የእግዚአብሔር መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያያት መሰላል አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ ሙሴ በነደ እሳት ሳትቃጠል ያያት ዕፅ አንቺ ንሽ ይኸውም መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው የመለኮቱ እሳትነት ሥጋሽን አላቃጠለውም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ዘር ያልተዘራባት እርሻ አንቺ ነሽ የሕይወት ፍሬ ከአንቺ ወጣ። ዮሴፍ የዋጃትና የከበረ ዕንቁን ያገኘባት ሣጥን አንቺ ነሽ ይኸውም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው በማኅፀንሽ አደረ በዚህ ዓልምም ወለድሸው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ የመላእክት ደስታቸው የሆነ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። የነቢያት ዜናቸው ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ቢሆን ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። የዓለም የሰው ሁሉ ደስታ የሆነ የመልአኩን ቃል ተቀብለሻልና ደስ ይበልሽ። ዓለምን ሁሉ የፈጠረ ጌታን የወለድሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ። የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ

Page 7: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

7

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ይበልሽ። ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግበውን እሱን ጡትሽን አጥብተሽዋልና ደስ ይበልሽ። የሕያዋን (የጻድቃን) ሁሉ እናታቸው ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ። ትለምኝልን ዘንድ ወደ አንቺ እናንጋጥጣለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ

ምሥጢር (ተዋህዶ) በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በልዩ ልዩ መልክ የፈጠረ የርሱን የገናንነቱን ነገር ፈጽመን መናገር አይቻለምና ዝም እንበል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፱፤ ወደ ደብረሲና የወረደ ለሙሴ ሕግን የሰጠ የተራራውን እራስ በጽጋግ በጢስ በጨለማና በነፋስ የሸፈነ ፈርተው የቆሙትንም በነጋሪቶች ድምፅ የገሠፀ የአብ አካልዊ ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፤ በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ ይኸውም ወደ አንቺ የወረደው ነው። ሰውን የወደደ እርሱ ያለመለወጥ ባንቺ ሰው ሆነ። እንደ እኛ በሚናገር ሥጋ ፍጹም ሆኖ አምላክ በመንፈስ ቅዱስ በማህፀኗ አደረና ፍጹም ሰው ሆነ። አዳምን ያድነው ዘንድ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ በሰማያት (በሰማያዊ መዓርግ) ያኖረው ዘንድ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት ወደ ቀድሞው ቦታው ይመልሰው ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፩፤ የድንግልን ገናንነቷን ሊናገሩት አይቻልም። ጌታ መርጧታልና። የሚቀርበው በሌለ ብርሃን ውስጥ የሚኖር እርሱ መጥቶ አደረባት ዘጠኝ ወር በማኅፀንዋ አደረ የማይታይና የማይመረመር (ታይቶ የማይታወቅ) እርሱን በድንግልና ወለደችው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፪፤ ነቢዩ ዳንኤል ያየው ያለ እጅ ከረጅም ተራራ የተፈነቀለው ያ ደንጊያ ከአብ ዘንድ የወጣው ቃል ነውና መጥቶ ያለ ወንድ ዘር ከድንግል ተወልዶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፲ ፫፤ እንደ ንጹሕ ጫፍ ሆንሽ የሃይማኖትም መገኛ ነሽ የቀናች የቅዱሳን አባቶቻችን ሃይማኖታቸው ነሽ። አምላክን የወለድሽና በድንግልና የታተምሽ ንጽሕት ሆይ የአብን ቃል ወለድሽልን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን መጣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፬፤ የከበርሽ ጌታን የወለድሽ ሆይ የማይታይ ቃልን የተሸከምሸው የብርሃን እናቱ አንቺ ነሽ። እሱን ከወለደሽው በኋላ በድንግልና ኖረሻልና በፍጹም ምስጋና ያገኑሻል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፭፤ የአብ ቃል እናቱ ንጽሕት ድንግል ሆይ ስለአንቺ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው፤ ኪሩቤል ለሚሸከሙት ንጉሥ ዙፋኑ (ማደሪያው) ሆንሽ፤ የተከበርሽ ሆይ እናመሰግንሻልን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ መልካሟ እርግብ ሆይ ስምሽን በልጅ ልጅ እንጠራለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፮፤ እናትና ገረድ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ። የታቀፍሽውን መላእክት ያመሰግኑታል ኪሩቤልም በፍርሃት ይሰግዱለታልና ሱራፌልም ያለማቋረጥ ክንፋቸውን ዘርግተው የሚመሰገን ንጉሥ (የክብር ባለቤት) ይህ ነው፤ በይቅርታው ብዛት የዓለምን

ኃጢአት ያስተሰርይ ዘንድ የመጣው ይህ ነው ይላሉ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

Page 8: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

8

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ረቡዕ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምስጋና፤

፩፤ የምድር ሁለተኛ የሆንሽ ሰማይ ሆይ የሰማይ ሠራዊት (መላእክት) ንዕድ ነሽ ይላሉ። ድንግል ማርያም የምስራቅ ደጅ ናት። ሙሽራዋ ንጹሕ የሆነ ንጽሕት የሠርግ ቤት ናት። አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ አላገኘምና አንድ ልጁን ላከው በአንችም ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ትውልድ ሁሉ አንችን ብቻ

ያመሰግኑሻል። የእግዚአብሔር ሀገር (ከተማ) ሆይ ነቢያት ድንቅ ድንቅ ነገርን ተናገሩልሽ፤ ደስ የተሰኙ የጻድቃን ማደሪያ ሆነሻልና የምድር ነገሥታት ሁሉ በብርሃንሽ ይሄዳሉ። ሕዝቡም ሠራዊቶቻቸውም በብርሃንሽ ይሄዳሉ፤ ማርያም ሆይ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑሻል። ካንቺ ለተወልደውም ይሰግዱለታል ያገኑታልም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ የዝናብ ውሃ የታየብሽ የእውነት ደመና አንቺ ነሽ። አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይል ጋረደሽ፤ ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር የአብን ልጅ ቃልን የወለድሽልን መጥቶም ከኃጢአት አዳነን። ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርክ መልአኩ ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው ወደእኛ የመጣ የጌታን ልደት ነገርከን ለድንግል ማርያም ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሰርካት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ጸጋን አገኘሽ መንፈስ ቅዱስ አደረብሽ የልዑል ኃይልም ጋረደሽ (ጸለለብሽ) ማርያም ሆይ በእውነት ቅዱሱን ወለድሽ ዓለምን ሁሉ የሚያድን መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ አንደበታችን የድንግልን ሥራ ያመስግናል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዳዊት አገር ከእርስዋ ስለተወለደ አምላክን የወለደች ማርያምን ዛሬ እናመስግናት አሕዛብ ኑ ማርያምን እናመስግናት። እናትና ድንግል ሁለቱንም ሆናለችና። ርኩሰት የሌለብሽና የአብ ቃለ መጥቶ ካንቺ ሰው የሆነ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ፣ ነውር የሌለብሽ ፍጽምትና ጉድፍ የሌለብሽ ሙዳይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለቀደመ ሰው አዳም ሁሉተኛ አዳም የሆነ የክርስቶስ ማደሪያው የምትናገሪው ገነት ሆይ ደስ ይበልሽ። ከአባቱ ያልተለየ አንድ እሱን የተሸከምሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። በክብር ጌጥ ሁሉ ያጌጠ እርሱ መጥቶ ሰው የሆነብሽ ንጽሕት የሠርግ ቤት ሆይ ደስ ይበልሽ። የመለኮት እሳት (ባሕርይ) ያላቃጠለሽ ዕፀ ጳጦስ ሆይ ደስ ይበልሽ። በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን ሰማያዊ መለኮትን በሥጋ የተሸከምሽ ገረድና እናት ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ። ስለዚህ ንጹሓን ከሆኑ መላእክት ጋር በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኝተን እናመስግን በሰማይም ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ዕርቅ ይሁን እንበል ክብርና ምስጋና ጌትነት ያለው እርሱ አንችን ወድዋልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ከቅዱሳን ክብር የማርያም ክብር ይበልጣል፣ የአብን ቃል ለመቀበል በተገባ ተገኝታለችና። መላእክት የሚፈሩትን ትጉሆች በሰማይት የሚያመሰግኑትን ድንግል ማርያም በማኅፀንዋ ተሸከመቸው። ይህች ከኪሩቤል ትበልጣልች፣ ከሱራፌልም ትበልጣልች ከሦስቱ አካል ለአንዱ ማደሪያ ሆናለችና። የነቢያት ሀገራቸው ኢየሩሳሌም

Page 9: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

9

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ይህች ናት። ለቅዱሳን ሁሉ የደስታቸው ማደሪያ ናት። በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው። በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ሰው ሆኗዋልና። ኑ ይህን ድንቅ እዩ። ስለ ተገለጠልን ምስጢር ምስጋና አቅርቡ። ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና። ቃል ተዋህዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለት እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ ነቢዩ ሕዝቅኤል ስለ እርስዋ መሰከረ ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ ምሥራቅ አየሁ አለ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱፤ ኆኅትም ደጅም መድኃኒታችንን የወለደች ድንግል ናት። እርሱን ከወለደች በኋላ እንደ ቀድሞ በድንግልና ኖራለችና። መጥቶ ምሕረት ከሌለው ጠላት እጅ ያዳነን ጌታን የወለጅሽ ሆይ የማኅፅንሽ ፍሬ የተባረከ ነው፥ አንቺ ፍጽምትና የተባረክሽ ነሽ የእውነት አምላክ በሆነ በክብር ባለቤት ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና በምድር ላይ ከሚኖር ሁሉ ይልቅ ገናንነትና ክብር ለአንቺ ይገባል። የአብ ቃል መጥቶ በአንቺ ሰው ሆነ። ከሰው ጋርም ተመላለሰ። መሓሪ ይቅር ባይ ሰውን ወዳጅ ነውና በልዩ አመጣጡ አዳነን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ሐሙስ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም

ምስጋና፤

፩፤ ርኵሰት የሌለባት ድንግል ማርያም ሙሴ በበረሃ በነደ እሳት ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ያያት ዕፅን ትመስላለች፤ የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆኗልና፣ እሳተ መለኮቱ (የመለኮቱ ባሕርይ) አላቃጠላትምና ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሰውም ቢሆን መለኮቱ አልተለወጠም በዕውነት አምላክ ነውና በዕውነት አምላክ የሆነ እርሱ መጥቶ አዳነን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፪፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ሁላችን እናገንሻልን። ይቅርታሽ ለሁላችን ይሆን ዘንድ ነውና።

፫፤ ሔዋን እንጨት በልታ ባደረገችው ዓመፅ በባሕርያችን ያደረ የቀድሞው እርግማን በእርስዋ የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የሁላችን መመኪያ ናት። ስለ ሔዋን የገነት ደጅ ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን። ከዕፀ ሕይወት እንበላ ዘንድ አደለን። ይኸውም እኛን ስለመውደድ መጥቶ ያዳነን የክርስቶስ ክብር ሥጋው ክብር ደሙ ነው። ስለ እርሷ ድንቅ ሆኖ የሚነገረውን ይህን ምሥጢር ማወቅ የሚቻለው ምን ልቡና ነው? መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማት

Page 10: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

10

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር አንድ ብቻ የሆነ አምላክነቱ ሳይለወጥ ከዓለም በፊት የነበረ የአብ ቃል ከአብ ዘንድ መጥቶ ልዩ ከሆነች እናቱ ሰው ሆነ። ከወለደችውም በኋላ ድንግልናዋ አልተለወጠም። ስለዚህ አምላክን የወለደች እንደሆነች ታወቀች። የእግዚአብሔር የጥበቡ ስፋት ምን ይጠልቅ? በጻእር በምጥ በልብ ጋር ትወልድ ዘንድ የፈረደባት ማኅፀን የሕይወት መገኛ ሆነች ከባሕርያችን እርግማንን የሚያጠፋልንን ያለ ወንድ ዘር ወለደችልን። ስለዚህም ሰውን የምትወድ ሆይ ክብር ላንተ ይገባል፤ ቸርና የሰውነታችን መድኃኒትም ነህ እያልን እናመስግነው። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፬፤ ያለ ወንድ ዘር አምላክን የወለደች ድንግል የማኅፀንዋ ሥራ ምን ይደንቅ? ለዮሴፍ የታየው መልአኩ ከእርሷ በመንፈስ ቅዱስ የሚወለደው ያለ መለወጥ ሰው የሚሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው ብሎ መስክሯልና። ማርያም የዚህ ደስታ ዕፅፍ የሆነ እርሱን ወለደችው። መልአኩ ልጅ ትወልጃለሽ ስሙም አማኑኤል ይባላል አላት። ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው። ዳግመኛ ወገኖቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ኢየሱስ ይባላል። በችሎታው (በኃይሉ) ያድነን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለም ክብር ይግባውና ሰው የሆነ እርሱን አምላክ እንደሆነ በተረዳ ነገር አውቀነዋልና። ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወልዱም ንግልናዋን አልለወጠውም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ሕማም ተወለደ። ሰብአ ስገል ሰገዱለትም አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት ንጉሰም ነውና ወርቅ አመጡለት ስለእኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነ ሞቱም ከርቤ አመጡለት። ቸር ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው ። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፭፤ ከአዳም ጎን አንዲት ዐፅም ማንሣት ምን ይደንቅ? ከእርሱ ሴትን ፈጠረ የሰው ፍጥረትንም ሁሉ ፈጠረ። ጌታ የአብ ቃል ተሰጠ። ከልዩ ድንግልም ሰው ሆነና አማኑኤል ተባለ ስለዚህ ሁል ጊዜ እርስዋን እንለምን፣ ከተወደደ ልጅዋ ታማልደን ዘንድ። በቅዱሳንና በሊቃነ ጳጳሳት ዘንድ ቸር ናት ደጅ የሚጠኑትን ወልዳላቸዋልችና ለነቢትም ትንቢት የተናገሩለትን ወልዳላቸዋለችና ለሐዋርያትም እስከ ዓለም ዳርቻ በስሙ ያስተማሩለትን ወልዳላቸዋለችና ሰማዕታትና ምዕመናንም የተጋደሉለትን የጥበቡ ጸጋ ብዛት የማይታወቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርስዋ ተወልዷልና የይቅርታውን ብዛት መርምረን እንወቅ (እንገፈልግ) መጥቶ አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፮፤ እግዚአብሔር የባሕርይህን ፍሬ በዙፋንህ አኖራለው ብሎ ለዳዊት በእውነት ማለ እይጸጸትም። ጻድቅ እርሱ ዳዊት ክርስቶስ በሥጋ ከእርሱ እንዲወለድ ባመነ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል ማደሪያ ፈልጎ ያገኝ ዘንድ ወደደ ይህንንም በታላቅ ትጋት ፈጸመ። ከዚህም በኋላ እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ብሎ በመንፈስ ቅዱስ አሰምቶ ተናገረ። ይህቺውም አማኑኤል እኛን ለማዳን በሥጋ ይወልድባት ዘንድ የመረጣት የያዕቆብ አምላክ ማደሪያ ናት። ዳግመኛም ከነቢያት አንዱ ሚክያስ አንቺ የኤፍራታ ክፍል የሆንሽ ቤተልሔም ከይሁዳ ነገሥታት መሳፍንት አገር አታንሺም ወገኖቼ እሥራኤልን

Page 11: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

11

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

የሚጠብቃቸው ንጉሥ ካንቺ ይወጣልና፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከቸር አባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ምስጋና ስለተገባው ስለ ክርስቶስ ባንድ መንፈስ ቅዱስ ትንቢት የተናገሩት የነዚህ የሚክያስና የዳዊት ነገር ምን ይረቅ? ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፯፤ ለእስራኤል የነገሠ ዳዊት ጠላቶቹ በተነሡበት ጊዜ ከቤተልሔም ምንጭ ውኃ ይጠጣ ዘንድ ወደደ የጭፍሮቹ አለቆች ፈጥነው ተነሡና በጠላቶቹ ከተማ ተዋግተው ሊጠጣ የወደደውን አመጡለት። ጻድቅ ዳዊት ግን ጨክነው ሰውነታቸውን ስለ እርሱ ለጦርነት ለሞት አሳልፈው እንደ ሰጡ ባየ ጊዜ ያን ውኃ አፈሰሰ ከእርሱም አልጠጣም ከዚህ በኋላ ለዘለዓለም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በዕውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ እግዚአብሔር አፈሰሱ። ስለ መንግሥተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ። እንደ ይቅርታህ ብዛት ይቅር በለን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

፰፤ ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ መዋረዳችንን አይቶ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ባሕርዩን ዝቅ አደረገና መጥቶ በድንግል ማኅፀን አደረ። ከብቻዋ ከኃጢአት በቀርም አንደኛ ሰው ሆነ፤ ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩለት በቤተልሔም ተወለደ። ፈጽሞ አዳነን ወገኖቹም አደረገን። ቅድስት ሆይ ልምኝልን።

ዓርብ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም

ምስጋና፤

፩፤ ከሴቶሽ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረክ ነው ያለርኵሰት

አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ እውነተኛ ፀሐይ ከአንቺ ወጣልን (ጌታ

ተወለደልን) በክንፈ ረድኤቱም አቀረበን። እርሱ ፈጥሮናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፪፤ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ የብርሃን እናት ነሽና አንችን ብቻሽን

በክብር በምስጋና እናገንሻለን። ፫፤ የተባረክሽ አንቺ ከመላእክት ትበልጫለሽ ከደቂቀ አዳምም ትበልጫልሽ ከድቂቀ አዳምም ትበልጫለሽ። ከአሳቦች ሁሉ ትበልጫልሽ ገናንነትሽን መናገር የሚቻለው ማነው አንቺን የሚመስል የለምና። ማርያም ሆይ መላእክት ያገኑሻል ሱራፌልም ያመሰግኑሻል። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ አድሮ የሚኖር ጌታ መጥቶ በማኅፀንሽ አድሮአልና። ሰውን የሚወድ ወደ እርሱ አቀረበን፣ ክብር ምስጋና ያለው እርሱ የእኛን ሞት ተቀብሎ የእርሱን ሕይወት ለእኛ ሰጠን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፬፤ የደናግል መመኪያቸው አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ

የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ከዓለም በፊት የነበረ እርሱ ሰው ሆኖዋልና ከአንቺ ተወልደ ሥጋችንን ነሣ (ተዋሐደ) መንፈስ ቅዱስንም ሰጠን። በቸርነቱ ብዛት መሳዮቹ አደረገን ጸጋንና ክብርን ከተቀበሉ ብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫልሽ አምላክን የወለድሽ ማርያም ሆይ ልዑል እግዚአብሔር ያደረብሽ (የከተመበሽ) ረቂቅ ከተማ ነሽ። በኪሩቤልና በሱራፌል ላይ የሚኖረውን ጌታን በመኻል እጅሽ ይዘሸዋልና። በቸርነቱ ብዛት ሥጋዊ ፍጥረትን ሁሉ የሚመግብ እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ። ይኸውም ሁሉን

Page 12: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

12

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

የሚያድን አምላካችን ነው። ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል። እንሰግድለትን እናመስግነው ዘንድ እርሱ ፈጥሮናና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፭፤ ድንግል ማርያም የሽቱ መኖሪያና የሕይወት ውኃ ምንጭ ናት። የማኅፀንዋ ፍሬ

ሰውን ሁሉ አድኖአልና። ከእኛም እርግማንን አጠፋልን። በመካከለችንም ሆኖ በስቀሉ አስታረቀን በልዩ ትንሣኤውም ሰውን ዳንመኛ ወደ ገነት መለሰው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ ንጽሕት ድንግል ማርያም የታመነች አምላክን የወለደች ናትሽ። ለሰዎች ልጆችም የምሕረት አማላጅ ናት። ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ክርስቶስ ለምኝልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ድንግል ማርያም በቤተመቅደስ አሰምታ ትናገር ነበር። መልአኩ ቅድስት ድንግል ሆይ ሰልምታ ይገባሻል ብሎ አክብሮ ከነገረኝ ነገር በቀር ምንም ምን ሌላ የማውቀው እንደሌለኝ እግዚአብሔር ያውቃል አለች። የማይቻለውን ቻልሽ የማይወሰነውንና ምንም ምን የሚወስነው የሌለውን ወሰንሽ። በክብር ሁሉ ላይ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ምስጋናሽ ይበዛል ክብርሽ ፍጹም ነው። የአብ ቃል ማደሪያ ሆነሻልና የክርስቲያን ወገኖች ምእመናንን የምትሰበስቢያቸውና ማሕየዊ የሚያድኑን ለሆኑ ለሥላሴ ሰጊድን (መሰገድን) የምያስተምሪላቸው ሰፊ መጋረጃ ሙሴ ያየውን የእሳት ዓምድ የተሸከምሽ አንቺ ነሽ። ይኸውም መጥቶ በማኅፀንሽ ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ሰማይና ምድር ለማይወስኑት የታመንሽ አንቺ ነሽ። ከምድር ወደሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ ብርሃንሽ ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል። ቅዱሳን በፍጹም ደስታ ያዩት ኮከብ ካንቺ የተወልደ ምሥራቅ አንቺ ነሽ። አንቺ ማርያም ግን ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ የሚል ቃልን ሰማሽና መጥቶ ያዳነን የፍጥረት ሁሉ ገዥ የሆነ ንጉሥን ወለድሽልን። መሐሪ ነው፣ ሰውንም ወዳጅ ነው። ስለዚህ ማርያም ሆይ የተባረክሽ ነሽ፣ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ እያልን መልአኩ ገብርኤል እንዳመሰገነሽ እናመሰግንሻለን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

ቅዳሜ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምስጋና፤

፩፤ ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ። ጌታን በመኻል እጅሽ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደሽ ነሽ። ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልም ብለው እየጮኹ ካንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ። ባለሟነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ። እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ።

፫፤ ግርማ ያለሽ ድንግል ሆይ ገናነትሽን እናመሰግናለን እናደንቃለን። እንደ መልአኩ ገብርኤልም ምስጋና እናቀርብልሻለን የባሕርያችን መዳን በማኅፀንሽ ፍሬ ተገኝቷልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

Page 13: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

13

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

፬፤ እንደ ሠርግ ቤት ጉድፍ የሌለብሽ ነሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና። የልዑል ኃይልም ጸልሎሻልና። ማርያም ሆይ ለዘለዓለም የሚኖር መጥቶ ከኃጢአት ያዳነን የአብ ልጅ ቃልን በእውነት ወለድሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፭፤ ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ (ዘር) አንቺ ነሽ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና። ከአብ የተወለደ ከዓለም በፊት የነበረ አንዱ ቃል ራሱን (ባሕርዩን) ሰወረ ካንቺም የተገዥን (ሰውን) አርአያ ነሣ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ አምላክን ያለርኵሰት የወለድሽው ሆይ የምድር ሁለተኛ ሰማይን ሆንሽ፣ እውነተኛ ፀሐይ ካንቺ ወጥቶልናልና። እንደነቢያት ትንቢትም ያለዘርና ያለመለወጥ ወደልሽው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ከተለዩ የተለየች የተባልሽ የኪዳን ጽላት ያለብሽ የተሰወረ መና ያለበት የወርቅ መሶብ ያለብሽ ደብተራ ድንኳን አንቺ ነሽ። ይኸውም መና የተባለው መጥቶ በድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረው የእግዚአብሔር ልጅ ነው። የአብ ቃል በርስዋ ሰው ሆነ መጥቶ ያዳነን የባሕርይ ንጉሥን በዓለም ውስጥ የወደችው የሚናገር በግ የክርስቶስ እናቱ ገነት ደስ ይላታል ለዘለዓለም የሚኖር የአብ ልጅ እርሱ መጥቶ ከኃጢአት አድኖናልና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፰፤ የንጉስ ክርስቶስ እናቱን ተባልሽ እርሱን ከወለድሽ በኋላም በድንግልና ኖርሽ። ድንቅ በሆነ ምሥጢርም (ተዋህዶ) አማኑኤልን ወለድሽው ስለዚህም ባለመለወጥ አጸናሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፱፤ እግዚአብሔር በላይዋ ተቀምጦባት ያዕቆብ ያያት መሰላል አንቺ ነሽ በሁሉ በኩል የማይመረመር እርሱን ተፈትሖ በሌለበት ማኅፀንሽ ተሸክመሽዋልና። እኛን ስለማዳን ካንቺ ሰው በሆነ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማላጅ ሆንሽን።ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲፤ የተባረክሽና ንጽሕት የሆንሽ አዳራሽ ሆይ እነሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ሁሉ በይቅርታው ብዛት ያድን ዘንድ ካንቺ ወጣ (ተወለደ) ፈጽመን እናመስግነው። ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፩፤ ያለርኩሰት ድንግል የሆንሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ የዓለም ሁሉ መክበሪያ ንጽሕት ጽዋ ነሽ። የማትጠፊ ፋና ነሽ የማትፈርሽ መቅደስ ነሽ። የቅዱሳን መደገፊያቸው (መጠጊያቸው) የማትለወጪ የሃይማኖት በትር ነሽ፣ ቸር አዳኛችን ወደ ሆነ ልጅሽ ለምኝልን ፈጽሞ ይቅር ይለንና ይምረን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

Page 14: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

14

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

በሰንበተ ክርስቲያን እfhድ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ምስጋና፤

፩፤ ከሴቶሽ ይልቅ ተለይተሽ የተባረክሽ ሆይ የተወደድሽ ተባልሽ። ከተለዩ የተለየች በውስጧም የኪዳን የሕግ ጽላት ያለባት የምትባይ ሁሉተኛ ክፍል አንቺ ነሽ ኪዳንም በእግዚአብሔር ጣቶሽ የተጻፉ ዓሥሩ ቃላት ናቸው። ያለመለወጥ ካንቺ ሰው የሆነ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደገኛ ስሙን መጀመሪያ ስሙን አስቀድሞ በየውጣ ነገረን፣ ለአዲስ ኪዳንም አስታራቂ ሆነ። በከበረ ደሙ ፈሳሽነት ወይም መፍሰስ ያመኑትንና ንጹሓን የሆኑትን ወገኖች አነጻቸው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፪፤ ሁል ጊዜ ንጽሕት የሆንሽ አምላክን የወለድሽ እምቤታችን ሆይ ሁላችን ስለዚህ እናገንሻለን ሰውን በሚወድ በጌታ ዘንድ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ እንለምንሻለን ወዳንቺም እናንጋጥጣልን።

፫፤ ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረፀ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትና ያለመለወጥ ሰው የሆነ የእግዚአብሔርን ቃል ይመስልልናል። ይኸውም መለውጥ የሌለበት ንጹሕ መለኮት ነው። ከአብ ጋር የተካከለ ነው ለንጽሕት በራሱ አበሠራት። በልዩ ጥበብ ያለ ወንድ ዘር እንደ እኛ ሆነ መለኮቱን አዋሕዶ ያለ ርኵሰት ባንቺ ሰው ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፬፤ በእግዚአብሔር ሥዕል የተሣሉ ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደስ አንቺ ነሽ። ንጽሕት ሆይ ያለመለወጥ ካንቺ ሰው የሆነው ቃል ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልንና አበሳችንን የሚደመስስልን ሆነ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፭፤ የተሠወረ መና ያለብሽ የንጹሕ ወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ መናም ከሰማይ

የወረደውና ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የሚያድለው ኅብስት ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፮፤ ሁል ጊዜ ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ ይኸውም ፋና የዓለም ብርሃን ነው። ጥንት ከሌለው ብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው። ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ እውነተኛ አምላክ ነው። ያለ መለወጥ ከአንቺ ሰው የሆነው ነው። በመምጣቱም (ሰው በመሆኑም) በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለምንኖር ለእኛ አበራን በልዩ የጥበቡ ምሥጢር በሥጋዌ የልቦናችንን እግር ወደ ሰላም መንገድ አቀናልን። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፯፤ ቡሩክ ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ የወርቅ ማዕጠንት አንቺ ነሽ ፍሕም የተባለውም ኃጢአትን የሚያስተሠርይና በደልን የሚደመስስ ነው። ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነና ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያሳረገ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፰፤ የእግዚአብሔርን ቃል የወለድሽልን መልካሟ ርግብ ማርያም ሆይ ደሽ ይበልሽ።

ከዕሴይ ሥር የወጣሽ መዐዛሽ ያማረ አበባ አንቺ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

Page 15: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

15

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

፱፤ ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበረች ያለ ዘር ሰው ሆኖ ያዳነን እውነተኛ አምላክችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ሆይ አንቺ እንደርሷ ነሽ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፲፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ከቅዱሳን ሁሉ ይልቅ ትለምኝልን ዘንድ ላንቺ ይገባል። አንቺ

ከሊቃነ ጳጳሳት ትበልጫለሽ ከነቢያትም ከመምህራንም ትበልጫለሽ። ከሱራፌልና ከኪሩቤል ግርማ የሚበልጥ የመወደድ ግርማ አለሽ። በእውነቱ የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ። ለሰውነታችንም ሕይወትን የምትለምኝ ነሽ። ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምኝልን ፤ እርሱን በማመን በቀናች ሃይማኖት ያጸናን ዘንድ ይቅርታውንና ምሕረቱን ይሰጠን ዘንድ በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን።

፲ ፩፤ ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከልጇ ከወዳጇ ከ እንዲሁም ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋራ ለዘለዓለሙ ይኑር፤ አሜን።

ይዌድስዋ መላእክት

፩፤ መላእክት ማርያምን በመንጦላዕት ውስጥ ያመሰግኗታል፤ ሐዳስ ጣዕዋ ላንቺ ምስጋና

ይገባሻል እያሉ። መልአክ ማርያምን ቃልን ተቀበይው አላት ካንቺ ዘንድ ይመጣልና በማኅፀንሽም ያድራል። እንዴት ከድሀ ቤት አደረ እንደ ምስኪን ከሰማያት ወርዶ የርስዋን ባሕርይ ባሕርይ አድርጎ ተወለደ?

፪፤ በ፮ኛው ወር ገብርኤል መልአክ ከእግዚአብሔር አብ ዘንድ ተላክ ካንዲት አገር ናዝሬት ገሊላ ከምትባል ለዮሴፍ እጮኛ ከሆነች ከድንግል ዘንድ። የዚች የድንግል ስሟ ማርያም ነው መልአኩ ወደ እርስዋ ገብቶ እንዲህ አላት ደስታ ይገባሻል እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ሰው ሆኗልና ከሴቶች ይልቅ አንቺ ቡርክት ነሽ። ከቃሉ አነጋገር አይታ ደነገጠች እንዲህም አለች እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ ይደረግልኛል? መልአክ እንዲህ አላት ማርያም ሆይ አትፍሪ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አግኝተሻልና እነሆ ትፀንሻለሽ ትወልጃልሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ እርሱም ታላቅ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል እግዚአብሔር አምላክም የዳዊት ያባቱን ዙፋን ይሰጠዋል እርሱም በያዕቆብ ወገን ለዘላለሙ ይነግሣል መንግሥቱም አያልፍም፤ ማርያምም መልአኩን እንዲህ አለችው ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል እንዘ ኢየአምር ብእሴ መልአኩም እንዲህ አላት፤ መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅሻል የልዑል ኃይልም ያድርብሻል ይህ የሚወለደው ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ ነው እነሆ ኤልሣቤጥ ካንቺ ወገን የምትሆን ከሸመገለች ካረጀች በኋላ ፀነሰች ልጅም አገኘች እነሆ ይህ ስድስት ወር ሆነ መካን ሲሏት ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ማርያምም መልአኩን እንደ ቃልህ ይደረግልኝ እኔ ለእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ አለቸው።

፫፤ መልአኩ ገብርኤል ማርያም ድንግል ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል አላት።ክብር ምስጋና ይድረስሽ

ወላዲተ አምላክ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

Page 16: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

16

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን

ቅድስት ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

የመለኮት ማደሪያ ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

የተሸለምሽ ድንኳን ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

የመላእክት እኅት የሕዝቡ ሁሉ እናት ነሽና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

የሁሉ እመቤት ማርያም ክብር ምስጋና ይጋባሻል፣

የሁሉ ሰላም ማርያም ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

ልዑል ማደሪያው ትሆኝ ዘንድ መርጦሻልና ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

በወርቅ የተሸለምሽ የርግብ ክንፍ በብር ያጌጥሽ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

ጎኖችሽ በወርቅ አመልማሎ የተሸለሙ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

የምሥራቅ ደጃፍ የብርሃን እናቱ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

ከፀሐይ ሰባት እጅ የምታበሪ ክብርሽ ከአድባራቱ ሁሉ ከፍ ከፍ ያለ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፣

ማርያም ሆይ ከተመረጡ የተመረጥሽ ከተከበሩ የተከበርሽ ላንቺ ክብር ምስጋና ይገባሻል፤

ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ለምኝልን ያድነን ዘንድ ከአባቱ ምስጋና ከቅዱሳን መላእክቶቹ ጋር በመጣ ጊዜ ጻድቅንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ባቆመ ጊዜ እኛን ከሰማዕት እንጢፋኖስ ከመጥምቁ ዮሐንስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ከሰማዕታትም ጋር ያቆመን ዘንድ ለምኝልን ለዓለመ ዓለም አሜን፤ ለዘለዓለሙ ይቅር ይበለን።

የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና፤ እነርሱም ተቀበሉት፥ ከአንተም ዘንድ እንደ ወጣሁ በእውነት አወቁ፥ አንተም እንደ ላክኸኝ አመኑ።እኔ ስለ እነዚህ እለምናለሁ፤ ስለ ዓለም አልለምንም ስለ ሰጠኸኝ እንጂ፤ የአንተ ናቸውና፤የእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው የአንተውም የእኔ ነው፤ እኔም ስለ እነርሱ ከብሬአለሁ። ከዚህም በኋላ በዓለም አይደለሁም፥ እነርሱም በዓለም ናቸው፥ እኔም ወደ አንተ እመጣለሁ። ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ

በስምህ ጠብቃቸው።ዮሐ 17፥8-12

Page 17: ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ ቴ 26 41debretsioneotc.org/Wudassie Mariam.pdf“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸዩ” ቴ 26፥41። ቅድሥተ

፳ ፻ ፳ -2020

17

ደብረ ጽዮን ቅድስት ድንግል ማርያም ፖርትላን ኦሪገን