ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/head start...ለመግባት ዝግጅት ላይ...

20
የታይትል/Title I & የልጆች ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች ዲቪዥን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ፣ ሮክቪል፣ ሜሪላንድ MONTGOMERY COUNTY PUBLIC SCHOOLS, ROCKVILLE, MARYLAND ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start የ 2019–2020 መምሪያ መፅሐፍ/HANDBOOK Child’s Name: _____________________________________________________________ Pre-K/Head Start Family Service Worker assigned to child’s class: __________________________________________________ Telephone Number for Family Service Worker: 240-740-4530 ወላጆች ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች፦ Amharic

Upload: others

Post on 05-Nov-2020

6 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

የታይትል/Title I & የልጆች ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች ዲቪዥን

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ፣ ሮክቪል፣ ሜሪላንድ MONTGOMERY COUNT Y PUBLIC SCHOOLS, ROCKVILLE, MARYLAND

ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድስታርት/Head Start

የ 2019–2020 መምሪያ መፅሐፍ/HANDBOOK

Child’s Name: _____________________________________________________________

Pre-K/Head Start Family Service Worker assigned to child’s class: __________________________________________________

Telephone Number for Family Service Worker: 240-740-4530

ወላጆች ማወቅ የሚገባቸው ነገሮች፦

Amharic

Page 2: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

ራእይ

ለእያንዳንዱና ለማንኛውም

ተማሪ እጅግ የላቀውን ህዝባዊ

ትምህርት በማቅረብ መማርን

እናበረታታለን።

ተልእኮ

እያንዳንዱ ተማሪ በኮሌጅ

እና በሥራ መስክ ውጤታማ

እንዲሆን/እንድትሆን፣

በአካደሚክስ፣ ችግር

የመፍታት ዘዴ/ ብልሃት

ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ

ስሜት ክህሎቶች ይኖሩታል/

ይኖሯታል።

ዋና ዓላማ

ሁሉንም ተማሪዎች የወደፊት

ህይወታቸው እንዲዳብር/

እንዲበለጽግ ማዘጋጀት፡፡

ዋነኛ እሴቶች

መማር/እውቀት

ግንኙነቶች

አክብሮት

ልቀት

ፍትኃዊነት/ሚዛናዊነት

Board of Education የትምህርት ቦርድ

Mrs. Shebra L. Evans ወ/ሮ ሸብራ ኤል. ኢቫንስ President ፕሬዚደንት

Mrs Patricia B. O’Neill ወ/ሮ ፓትሪሻ ቢ ኦኔይል Vice President ም/ፕሬዚደንት

Ms. Jeanette E. Dixon ሚስ ጃኔት ኢ. ዲክሰን Dr. Judith R. Docca ዶ/ር ጁዲት አር. ዶካ Ms. Karla Silvestre ሚ/ስ ካርላ ሲልቨስትሪ

Mrs. Rebecca K. Smondrowski ወ/ሮ ርብቃ ኬ. ስሞንድሮውስኪ Ms. Brenda Wolff ሚስ ብረንዳ ዎልፍ Mr. Nathaniel Tinbite አቶ ናትናኤል ትንቢተ Student Member የተማሪ አባል

Montgomery County Public Schools (MCPS) Administration የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አስተዳደር

Jack R. Smith, Ph.D. ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር) Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ

Monifa B. McKnight, Ed.D. ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. መክናይትም/ሱፐርኢንተንደንት

Maria V. Navarro, Ed.D. ማሪያ ቪ. ናቫሮ የትም/ዶክተር Chief Academic Officer የአካደሚ ዋና ኃላፊ

Kimberly A. Statham, Ph.D. ኪምበርሊ ኤ. ስታተም (ዶ/ር) Chief of School Support and Improvement የትምህርት ቤት ድጋፍ እና መሻሻል ዋና ኃላፊ

Andrew M. Zuckerman, Ed.D. አንድሪው ኤም. ዙከርማን (ዶ/ር) Chief Operating Officer ዋና የሥራ ኃላፊ

850 Hungerford DriveRockville, Maryland 20850www.montgomeryschoolsmd.org

Page 3: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

ሜሪላንድ MARYLAND ድረ-ገጽ፡- www.montgomeryschoolsmd.org

850 Hungerford Drive ♦ Rockville, Maryland 20850

ኦገስት 2019

ውድ ወላጅ/ኣሳዳጊ፡-

እንኳን ደስ ኣለዎት! ልጅዎ በሚቀጥለው ፎል ወደ ቅድመ መዋእለ ህጻናት ወይም ሄድስታርት ፕሮግራም ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት ምዕራፍ እያመራችሁ ነው። የልጅዎን የመጀመሪያ ት/ቤት ተሞክሮ ደስተኛና ስኬታማ እንዲሆን ከእርስዎ ጋር አብሮ ለመሥራት በጉጉት እንጠብቃለን። ታዳጊ ተማሪዎቻችንን ለትምህርት ቤት ዝግጁነት ለማዳበር እና ለ 21 ኛው ክፍለዘመን ስኬታማ፣ እና ውጤታማ የሆኑ ዜጋዎች ለማዘጋጀት የዳበረ/የበለጸገ እና የተሟላ የቅድመ ትምህርት ልምድ መቀበል አለባቸው ብለን እናምናለን። ከፍተኛ ጥራት ያለው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቅድመ መዋለ ሕጻናት እና ሄድስታርት/Head Start ፕሮግራሞች በሀገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ምርጥ ከሚባሉት መካከል በስፋት የሚታወቅ ሲሆን፣ ተማሪዎች በኮሌጅ እና በሥራ ላይ ስኬታማ ለመሆን በአካዴሚያዊ፣ ፈጠራዊ ፕሮብሌም አፈታት፣ እና ማህበራዊ ስሜታዊ ክህሎቶችን ለማረጋገጥ የትምህርት ቤት ዲስትሪክት ራዕይ ለማሳካት አመርቂ ግስጋሴ የሚያሳዩበት ነዉ።

እባክዎን ስለ ልጅዎ ቅድመ መዋለ ሕጻናት ወይም ሄድስታርት/Head Start ክፍል ማንኛቸውም ጥያቄዎች ካለዎት ለምድብ ት/ቤትዎ ያቅርቡ የልጅዎ የቅድመ መዋለ ሕጻናት ወይም የሄድስታርት/Head Startከ ተሞክሮ ከ MCPS ጋር ጠንካራ አጋርነት ለመገንባት ከብዙ ተሞክሮዎች የመጀመሪያው እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።

ከማክበር ሰላምታ ጋር

Jack R. Smith, Ph.D. ጃክ አር. ስሚዝ (ዶ/ር)Superintendent of Schools የት/ቤቶች ዋና ተቆጣጣሪ

JRS:MVN:EJL:spa

Page 4: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት
Page 5: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

i

A BC ቅድመ መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ማዉጫ

Rocking Horse Road Center

4910 Macon Road, Rockville, MD 2085

240-740-4530

TTY: 301-230-5462 ፋክስ፡- 301-230-5401

ቅድመ መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ተቆጣጣሪ . . . . . . . . . . . Verna Washington/ቨርና ዋሽንግቶን

ሂሳብ ሰራተኛ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Gloria Diaz/ግሎሪያ ዳያዝ

የት/ቤት ሬጅስትራር/School Registrar . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ስማይል ሶሪያ/Smil Soria

የመረጃዎች(ዳታ) ስርአት ኦፐሬተር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Gyungae Kim/ግዩንጌ ኪም

የአስተዳደር ጸሐፊ/Administrative Secretary . . . . . . . . . . . . . . ካርይን ስትይን/Caryn Stein

Karim Quintanilla

ከሪም ቊይንታኒላ

A BC የልጆች እድገት እና ትምህርት ሠራተኞች . . . .240-740-4530

የትምህርት ስፔሻልስት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Melisha Creef/መሊሻ ክሪፍ

Louise Tolin/ሎዊስ ቶሊን

Nakeya Stephens-Chukwudebe/ናኬያ ስቲቨንስ-ቹክዉዴብ

የፕሮግራም ድጋፍ መምህርት/Program Support Teacher . . . . . . . . . ሶናሊ ሞዛ/Sonali Motha

Susan Dowling/ሱዛን ዶውሊንግ

ሳይኮሎጂስቶች/Psychologists . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .ማሪሳ ሴንሰ/Marissa Senese

Julie Shields/ጁሊ ሼይልድስ

Sara McKeen/ሳራ ማኪን

Victoria Willingham/ቪክቶሪያ ዊሊንግሃም

የንግግር/ቋንቋ ፓቶሎጅስትካረን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . ነልሰን/Karen Nelson

Joe Ann Robinson/ጆ አን ሮቢንሰን

Lynne Teoman/ላይን ቴዎማን

Page 6: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

ii

A BC የጤና አገልግሎት ሰራተኛ 240-777-1553

የጤና አገልግሎት ማናጀር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Beka Urgessa/ቤካ ኡርጌሳ

የጥርስ ሀኪም . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .Lesley Konigsburg/ሌስሊ ኮንስበርግ

Teresa Soodak/ቴረሳ ሱዳክ

Cindy Xander /ሲንዲ ዛንደር

ነርሶች ሚና አሊባዲ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Mina Aliabadi

Boris Senatorov/ሴናቶሮቭ ቦሪስ

Rubina Mason/ሩቢና ማሶን

Renee McNevin/ረኔ ማክኔቪን

Kimberly Muhammed/ኪምበርሊ ሙሃመድ

Nomvuyo Qubeka/ኖምቩዮ ኩቤካ

Simone Roberts/ሲሞኔ ሮበርትስ

የጤና ረዳቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Norma Davis/ኖርማ ዴቪስ

Teresa Hock/ተሬሳ ሆክ

Cheryl Pyle/ቼሪል ፓይል

Eligibility Specialist/የብቃት ስፔሻሊስት . . . . . . . . . Wond Workalemahu/ዎንድ ወርቃለማሁ

A BC የወላጅ፣ ቤተሰብ፣ እና የማህበረሰብ

ተሳትፎ ሰራተኛ . . . . . . . . . . . . . . . . 240-740-4530

የማህበራዊ አገልግሎቶች ልዩ ባለሙያ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Lisa Conlon/ሊዛ ኮንሎን

የማህበራዊ ስረተኞች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Annette Harris/አኔት ሀሪስ

Renée Foster/ረኔ ፎስተር

}የወላጅ፣ ቤተሰብ፣ እና የማህበረሰብ

ተሳትፎ/በጎ ፈቃደኛ ስፔሻሊስት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .Beverly Brown/ቤቨርሊ ብራዎን

የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኞችMaral Abkarian/ ማራል አብካርያንStella Anderson/ ስቴላ አንደርሰንJazmina Begazo/ ጃዝሚ ቤጋዞTeresa Delgadillo/ ቴሬሳ ዴልጋዲሎAna Diaz/አና ዲያዝDamara Dockery/ ዳማራ ዶክሪMichelle Dove/ ሚሼል ዶቭ

Reyna Escamilla/ ሬንያ ኤስካሚላRosa Escobar/ ሮዛ ኤስኮባርEsperanza Flores/ ኤስፔራንዛ ፍሎሬስShelby Foreman/ ሼልቢ ፎርማንDeborah Garcia/ ዴቦራ ጋርሲያRosa Hardy/ሮዛ ሀርዲTerri Harris/ቴሪ ሀሪስ

Tamar Hill/ (ታመር ሂል)Samira Hussein/ ሳሚራ ሁሴንTheresa Huynh/ ተሬሳ ሃይነVicki Johnson/ ቪኪ ጅንሶንNuha Khalaf/ኑሃካላፍPatty Marroquin/ ፓቲ ማሮኩይንRuth Meininger/ ሩት ሜንንጀር

Milena Parra/ ሚሌና ፓራ Amabilia Reyes/ አማቢላ ሬይስDaniela Rodriguez/ ዳኒዬላ ሮድሪጌCesiah Ventura/ ሴሲያ ቬንቱራJeannette Zepeda Escobar/ ጃኔት ዜፒዳ እስኮባር

Page 7: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

iii

A BC

ማውጫ

የፕሮግራም ቅየሳና አስተዳደር . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

ተማሪዎችን ለስኬት ማዘጋጀት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

የፖሊሲ ምክር ቤት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

የፖሊሲ ምክር ቤት መማክርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 1

የፖሊሲ መማክርት ሀላፊነቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

የልጅ እድገት እና ትምህርት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

አይነተኛ የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ቀን . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

ስለ ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት እና ሄድስታርት ፕሮግራሞች/MCPS Pre-K እና Head Start Programs መታወቅ ያለባቸዉ ሌሎች ነገሮች . . . . . . . . . . . . 2

ምግቦች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 2

የመስክ ጉዞዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የግል ደህንነት . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ንግግር/ቋንቋ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ልብስ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

ክትትል . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የቤት ጉብኝቶችና የወላጅ-መምህር ስብሰባዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

የበረዶ ቀኖች ወይም አስቸኳይ ሁኔታዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 3

በቅድሚያ መለቀቂያ ቀኖች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

አካል ጉዳተኛ/ስንክልና ያላቸዉ ልጆች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

እንግሊዝኛ ተማሪዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

የጤና አገልግሎቶች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 4

ወላጅ፣ ቤተሰብ፣ እና የማህበረሰብ ተሳትፎ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 5

በጎ-ፈቃደኞች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

መጓጓዣ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

የወላጅ/ማእከል ኮሚቴ ስብሰባዎች . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 6

ሌላ መረጃ/ኢንፎርሜሽን

ተቀዳሚ Head Start . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

የልጅ እንክብካቤ . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት ሙከራ ፕሮግራም (Pre-K+) . . . . . . . . . . . . . . . . . . 7

በቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድስታርት ብዙውን ጊዜ አገልግሎት ላይ የሚዉሉ ቃላት . . . . . . . 8

የ 2019–2020 ካላንደር/Calendar . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . 9

Page 8: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት
Page 9: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

1

የፕሮግራም ቅየሳና አስተዳደር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)፣ከወላጆች/ሞግዚቶች በጋራ እና ከማህበረሰቡ ባለድርሻ አካላት፣ የካውንቲውን የመንግስት አስተዳደር፣ እና የስቴት እና የአካባቢ ኤጀንሲዎችን ጨምሮ በጋራ ትብብር፤ ለእያንዳንዱ ልጅ ከፍተኛ ጥራት ያለው የልጅነት እድሜ ልምምድና ቁልፍ የሆነ የእድገትና የትምህርት ጠንካራ መሠረት የሚፈጥር፣ በእያንዳንዱ ተከታታይ የክፍል ደረጃ ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ ወደ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እያደጉ በሚሄዱበት ጊዜ የአካደሚና የግል የህይወት መከናወን እንዲኖራቸዉ የሚያስችል የቅድመ መዋዕለ ህጻናት እና ሄድስታርት ፕሮግራሞችን ያቀርባል/ይሰጣል። በቅርቡ የተሻሻለው የሞንትጎመሪ ካውንቲ/Montgomery County የትምህርት ቦርድ ፖሊሲ IEA፣ የቅደመ ልጅነት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት አወቃቀር፣ የካውንቲውን፣ የክልል፣ እና የፌደራል ሀብቶችን ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር ውጤታማ በሆነ መልኩ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ፍላጎት ያላቸዉን ህፃናት ለመለየት እና በእያንዳንዱ የልጆች እድገት ደረጃ ከቤት፣ ከሕጻን እንክብካቤ ወይም ከቅድመ ትምህርት ወደ ቅድመ መዋዕለ ህፃናት፣እንደ አግባቡ፣ እና ከአንዱ አንደኛ ደረጃ ክፍል ወደ ሌላው፣ የተማሪን እድገት፣ ሽግግር፣ አቀማመጥ እና የፕሮግራም ዘላቂነትን ለማመቻቸት፣ትናንሽ ልጆች እና ቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጓቸው አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለማቋቋም የቦርዱን ቁርጠኝነት በዝርዝር ያቀርባል።

ቦርዱ ከወሊድ ጀምሮ እስከ 5 ዓመት እድሜ ድረስ ያሉ ህጻናትን ለመደገፍ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ከሚገኙ የህዝብ እና የግለሰብ ወኪሎች ጋር በመተባበር፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ/Montgomery County የቅድሚያ እንክብካቤ እና የትምህርት ስልታዊ ስትራቴጂክ ፕላን እንደተቀመጠው ለአንደኛ ደረጃ ትም/ቤት ስኬታማነት ያዘጋጃቸዋል። MCPS በተጨማሪ ከመወለድ እስከ 8 አመት ድረስ ላሉ ህጻናት፣ በቤት እና በትምህርት ቤት በተመሰረቱ ፕሮግራሞች እና በሌሎች መስኮች እና በማዕከላዊ ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ የማጣሪያ ምርመራ፣ ቅድመ ጣልቃ ገብነት እና የልዩ ትምህርት አገልግሎቶችን ይሰጣል። ለልጆች በስፋት አገልግሎቶች የሚሰጡት ባላቸው ፍላጎት መሠረት በተለያየ ደረጃ ስለ ንግግር/ቋንቋ፣ የመስማት/ማዳመጥ፣ የማየት፣ የሰውነት መገጣጠሚያ/orthopedic እና የእድገት ዘገምተኝነትን ጨምሮ በተለያየ አይነት ፍላጎቶች ሲሆን ነገር ግን በዚህ ብቻ አያበቃም።

በ MCPS፣ የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት/ሄድስታርት/Head Start ሱፐርቫይዘር/ተቆጣጣሪ፣ የድጋፍ መስፈርቶችን አፈጻጸም ከፖሊሲ ምክር ቤት፣ከማህበረሰብ የተግባር/አክሽን ኤጀንሲ፣ ከክልል III ቢሮ፣ እና ከ MCPS ጋር ያስተባብራል/ታስተባብራለች። ይህ ቡድን የባለአነተኛ ገቢ ቤተሰቦችን እና የቅድመ-ት/ቤት ልጆቻቸውን ፍላጎቶች ለማሟላት አገልግሎት ከሚያቀርቡ ሌሎች ወኪል ድርጅቶች ጋር ግንኙነቶች በተጨማሪ ተንከባክቦ ይይዛል። የቅድመ መዋዕለ ህጻናት /ሄድስታርት ወላጆችን ፍላጎት ለማገዝ፣ ተቆጣጣሪው/ዋ የፕሮግራሙን ግብ፣ አላማ፣ እና ውጤቶች ይመረምራል//ትመረምራለች፣ ይገመግማል/ትገመግማለች እናም ያሻሽላል/ታሻሽላለች።

ተማሪዎችን ለስኬት ማዘጋጀት የ MCPS ቅድመ መዋዕለ ህጻናት /ሄድስታርት ክፍል ለህጻናት ለትምህርት ዝግጁነት ድጋፍ ሰፋ ያሉ አገልግሎቶች ይሰጣል። ለትምህርት ቤት ዝግጁነት ማለት ልጆች በትምህርት ቤት ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችላቸዉ ክህሎቶች፣ ችሎታዎች እና አመለካከቶች ይኖሯቸዋል ማለት ነው። ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጆች የመጀመሪያ እና በጣም አስፈላጊ መምህራን ናቸዉ። ወላጆች/አሳዳጊዎች፣ መምህራን፣ የፕሮግራም ሰራተኛ አባላት፣እና ሌሎች የቤተሰብ እና የማህበረሰብ አባላት ሁሉም ልጆችን ለትምህርት ቤት በሚያዘጋጁበት ወቅት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

የመመርያ ምክር ቤት እያንዳንዱ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለ "Pre-K/Head Start programs" ለፖሊሲ ካውንስል የወላጅ/ሞግዚት ተወካይ ይመርጣል። ልዑካን/ተወካይ ሌሎች ወላጆች/አሳዳጊዎችን የማሳወቅ እና የእንቅስቃሴ እቅድ እንዲያወጡ ይሠራሉ። አዳዲስ መኮንኖች በዲሴምበር ይመረጣሉ ቦታቸውንም በጃንዩወሪ ይይዛሉ።

የፖሊሲ ምክር ቤት የወላጅ/አሳዳጊ ልዑካን በየወሩ በ 7 00 ፒ.ኤም.፣ በ Rocking Horse Road Center የስብሰባ አዳራሽ፣ 4910 Macon Road, Rockville, MD 20852 ውስጥ ይገናኛሉ። ስብሰባዎች በሴፕቴምበር መጨረሻ ወይም በኦክቶበር መጀመርያ ላይ በመተዋወቂያ/ስልጠና ክፍልጊዜዎች ይጀምራሉ። የበጀት ሰብሰባ የሚካሄደው በኦክቶበሩ ስብሰባ ነው፣ መደባኛ የወር ስብሰባዎች ደሞ ከዚያ በኋላ በየወሩ ሶስተኛ ሀሙስ ይካሄዳሉ።

የመመርያ ምክር ቤት መኮንኖችየመምርያ ምክርቤት የተመረጡ መማክርት የየወሩን ስብሰባዎች አጀንዳ አስቀምጠው ለጠቅላላ አባላት የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባሉ።

ሊቀመንበር

ምክትል ሊቀመንበሮች (2)

ገንዘብ ያዥ

የዘገባ ፀሀፊ

የግንኙነት ፀሀፊ

የህብረተሰብ የተግባር/Action ቦርድ ተወካዮች (2)

የሜሪላንድ ስቴት ሄድስታርት ተወካዮች (2)

የማእከልዎ የመመርያ ምክር ቤት ተወካይ፡-

____________________________________

ቴሌፎን ቁጥር፡- ________________________

ማእከልዊ የመምሪያ ምክር ቤት ተለዋጭ፡-

____________________________________

ቴሌፎን ቁጥር፡- ________________________

Page 10: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

2

የመመርያ ምክርቤት ተወካዮች ከኪሳቸው ለሚያደርጓቸው ወጪዎች ከወላጅ እንቅስቃሴ ገንዘብ/Parent Activity Fund ይከፈላሉ። ምክር ቤቱ በጀቱን በየአምቱ ያስተካክና የመተኪያውን መጠን ይወስናል። ሁሉም ወላጆች /አሳዳጊዎች በፖሊሲ ካውንስል ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ እና እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ቢሆንም፣ ድምፅ መስጠት የሚችሉት ተመራጭ ተወካዮች ብቻ ናቸው።

የፖሊሲ ምክር ቤት ከቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት/ሄድስታርት (Head Start) አገልግሎት ዙሪያ ጋር የተያያዙ ፣እንደ ማህበራዊ አገልግሎቶች፣ ትምህርት፣ የአካል ጉዳት አገልግሎቶች፣ እና ጤና የመሳሰሉ ተግባራትን የሚያቅድ እና የሚተገብር ንዑስ ኮሚቴዎች አሉት። ሌሎች ንኡስ ኮሚቴዎች ከፕሮግራም አመራር ጋር በተዛመዱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ።

የመመርያ ምክር ቤት ሀላፊነቶች• ለወላጅ እንቅስቃሴው ገንዘብ/Parent Activity Fund በጀት ያዘጋጃል

• በፕሮግራም ግምገማዎች ይሳተፋል

• በልጅና ቤተሰብ አዋጅ ድንጋጌ አፈፃጸም ይደግፋል።

• ከተጋባዥ ተናጋሪዎች ጋር ፕሮግራሞች ያደራጃል።

• የቤተሰብ ሽርሽሮችና ክውነቶች ያስተናግዳል

• የፕሮግራም በጀት እና የፕሮጀክት ሀሳብ ዝግጅት ያግዛል

• በአገልግሎት አካባቢ ኮሚቴዎች ያገለግላል

• የልጆች ምልመላ ላይ ያግዛል

የልጅ ብልፅግናና ትምህርትልጆች በቅድመ-መዋዕል ሕፃናት/ሄድ ስታርት ፕሮግራም ዉስጥ በጣም ይጫወታሉ። ጨዋታ የልጆች ስራ ነው፤ ይህ ነው የመማርያ ዘዴአቸው። ልጆች በመዋዕለ ሕጻናት ውስጥ ለስኬት ሲዘጋጁ፣ የሚከተሉትን ያከናውናሉ ፦

• ትናንሽና ትላልቅ ጡንቻዎችን ያዳብራል/ታዳብራለች

• ተረቶችን ያዳምጣል/ታዳምጣለች መፃህፍትንም ይመለከታል/ትመለከታለች።

• ቀለም መቀባት፣ መሳል፣ እና መፍጠር

• በሳይንስ ቁሳቁሶች ዳሰሳ ማድረግ

• የቤት (ትያትር) መጫወት እና ታሪኮችንና መዝሙሮችን/ዘፈኖችን መጫወት

• ማዳመጥ፣ መጨፈር፣ መጽፈን፣ እና ሙዝቃ መስራት

• የስራ እንቆቅልሽና የጨዋታ ግጥሚያዎች

• ስሞችን፣ ቀለሞችን፣ እና ቁጥሮችን መለየት

• መጋራትንና መተባበርን መማር

የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ክፍል የልጆችን ስሜታዊ፣ የአእምሮ/የአስተሳሰብ፣ ማህበራዊ፣ እና አካላዊ እድገትን ያበረታታል።

የተለመደ የቅድመ መዋለ ህጻናት/ሄድስታርት የመጀመሪያ ቀን• መክፈቻ፡- የመስተንግዶ መዝሙር/ዘፈን

አየር የቀን መቁጠሪያ

• መላ የማንበብና የመፃፍ ብሎክ፡- መፃህፍትና ታሪኮች

መዝሙሮች/ዘፈኖችና የቤት ምቶች ፊደል Amharic

• አነስተኛ የማንበብና የመፃፍ ብሎክ፡- የቃል ቋንቋ

ስለህትመት ፅንሰሀሳቦች ድምፃዊ ንቃት የፊደል እውቀት

• ማእከላዊ ጊዜ፡- የትያትር ጨዋታ የማንበብና የመፃፍ ማእከሎች ብሎኮች—በመደገፍያዎች/

props የበለፀጉ የሂሳብ ትምህርት/ማቀነባበርያዎች/

manipulatives የሳይንስ ፕሮጀክቶች ማብሰል

• የሂሳብ ብሎክ፡- የቁጥር ፅንሰሀሳቦች በያይነት መለያየትና ቅርፀቶች

• ከቤት ውጭ ጨዋታ፡- አካላዊ መንቀሳቀሻ

ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች

• ምሳ

ስለ MCPS ቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድስታርት ፕሮግራሞችን በተመለከተ ሌሎች ማወቅ ያሉባቸው ነገሮች

ምግቦችየ Head Start ልጆች በየእለቱ የቤተሰብ ወጪ የሌለበት የት/ቤት ምሳ ያገኛሉ። የቁርስ ፕሮግራሞች ያሏቸው ት/ቤቶችም፣ ትምህርት አስቀድሞ የሚጀመር ከሆነ ለHead Start ልጆች ቁርስ ሊያቀርቡ ይችላሉ።

በክፍል ውስጥ የማብሰል እና የመቅመስ እንቅስቃሴዎች ለቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ልጆች ከሌሎች ልምዶች ጋር አዳዲስ እና የተመጣጠኑ ጥሩ ምግቦችን ያቀርባል። ወላጆች /ሞግዚቶች ከልጆች ጋር ለማቀድ እና ምግብ እንዲያዘጋጁ ለመርዳት ተጋብዘዋል።

እንደ በጎ ፈቃደኛ አገልጋዮች ወይም ጎብኚዎች፣ የሄድስታርት ወላጆች /ሞግዚቶች ወደ ት/ቤት ሲመጡ በክፍል ውስጥ ከልጆቻቸው ጋር ምሳ እንዲጋሩ ይጋበዛሉ።

Page 11: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

3

የመስክ ጉዞዎችየመስክ ጉዞዎች የልጆችን ባህላዊ ተሞክሮዎች ያስፋፋሉ፣ አድማሳቸውን ያሰፋሉ፣ እናም የራሳቸውን አካባቢ ግንዛቤ ይጨምራሉ።

የግል ደህንነትየደህንነት ሥርዓተ ትምህርት አካል እንደመሆኑ፣ ልጆች ለአዋቂዎች "አልፈልግም/አይሆንም" የማለት ፍቃድ መስጠትን ጨምሮ፣ የግል የደህንነት ቴክኒኮችን እንዲማሩ ፣እና ልጆች ደህንነታቸዉ ስጋት ላይ መሆኑ ሲሰማቸው ለሚያምኑት አዋቂ እንዲናገሩ ማበረታታት። የማጎሳቆል እና ቸልተኝነት ጉዳዮችን ሠራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች ሪፖርት እንዲያደርጉ የሜሪላንድ ስቴት ሕግ እንደሚጠይቅ ወላጆች/ሞግዚቶች ማወቅ አለባቸው።

ንግግር/ቋንቋየቅድመ መዋዕለ ሕጻናት /ሄድስታርት (Pre-K /Head Start Unit) ክፍል የንግግር ስፔሻሊስቶች/ፓቶሎጅስቶች እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች/ሳይኮሎጅስቶች የለጋ-የልጅነት /early-childhood ትምህርት ልዩ ስልጠና አላቸው፤ ለልጆች እና ለቤተሰቦች አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

ልብስየጨዋታ ልብሶች ለቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት Pre-K/Head Start ተገቢ ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ልጆች የሆኑ ነገሮችን ያፈሳሉ፣ይረጥባሉ ወይም በልብሳቸዉ ላይ የሆነ አደጋ ሊፈጠር ይችላል። ንጹህ ልብሶች አስፈላጊ ሲሆን እንዲቀርብ ወላጆች/አሳዳጊዎች የተማሪ ስም የተጻፈበት/የተለጠፈበት ቅያሪ ልብሶችን እንዲልኩ ይጠየቃሉ። የዝናብ ልብሶች፣ቦት ጫማዎች፣ ጓንቶች፣ እና ሌሎች ዓይነት ልብሶችም ከሌሎች ጋር መደባለቅን ለመከላከል የልጅዎ ስም ለምልክት እንዲኖርባቸዉ ያስፈልጋል።

ክፍል ውስጥ መገኘትተማሪዎች በየቀኑ ት/ቤት መከታተል እና በሰዓቱ መድረስ አስፈላጊ ነዉ። እያንዳንዱ/ዷ ልጅ ከቅድመ-መዋዕለ ህፃናት /ሄድስታርት ተሞክሮ የበለጠ ጥቅም ለማግኘት አዘውትሮ መገኘት /መከታተል አስፈላጊ ነው። ዘወትር ወደ ት/ቤት መሄድ እና በሰኣት መገኘት ልጅዎ ስለ ትም/ቤት ስለሚያ/ምታዳብረው አስተሳሰብ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። ስለ ት/ቤት ኣወንታዊ ኣቋም እና የተሟላ ክትትል በሚመጡት ኣመታት ይክሳል።

ልጆች በሰዓቱ ት/ቤት ሲደርሱ፣በቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ዉስጥ የተሻለ የትምህርት እና ማህበራዊ ተሞክሮ አላቸው። ልጅዎ ከታመመ/ች፣ ት/ቤት ይደዉሉ እና ለመምህር መልዕክት ያስቀምጡ/ያኑሩ። ልጅዎ መመለስ ሲችል/ስትችል፣ የቀረ/ችበትን ምክንያት በመግለጽ ማስታወሻ በልጅዎ ይላኩ። እባካችሁ የልጃችሁን መምህር ወይም የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኛ ስለ ማንኛውም የልጅዎ ህመም ወይም አስቸኳይ ሁኔታ ምንጊዜም እንዲያውቁ አድርጉ። ልጅዎ በወር ውስጥ 3 ቀናት ወይም ከዚያ በላይ ከቀረ/ች፣ ቀኖቹ ተከታትለው ወይም ሳይከታተሉ ቢሆንም፣ በቤተሰብ የአገልግሎት ሰራተኛ ክትትል ይካሄዳል። የእርስዎ ልጅ 10 ወይም የሚገልጥ ተከታታይ ቀኖች ትምህርት ላይ ካልተገኘ/ች፣ እና በህመምህ ምክንያት መቅረት ካልሆነ ልጅዎ ከፕሮግራሙ ይወጣል/ትወጣለች።

የቤት ጉብኝቶች እና የወላጅ-መምህር ስብሰባዎችበ "Head Start እና Pre-K Pilot (Pre-K+) ለሚገኙ ተማሪዎች፣ የእርስዎ ልጅ መምህር/ት እና ፓራኢጁኬተር ሴፕቴምበር ላይ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ቤትዎን ይጎበኛሉ። ለ "Pre-K" ተማሪዎች፣ የልጅዎ አስተማሪ እና ፓራኢጁኬተር በትምህርት ቤት ወይም በቤት የቤተሰብ ጉብኝት ያደርጋሉ። የ "Head Start እና Pre-K Pilot (Pre-K+)" ቤተሰቦች ፌብሩወሪ ላይ ሌላ የቤት ጉብኝት ያገኛሉ። በተጨማሪ፣ ሁለት ስብሰባዎች ይኖሯችኋል—አንድ በኖቨምበር እና አንድ በጁን። ወላጆች/አሳዳጊዎች በሌላ ጊዜ ከልጃቸዉ መምህር ጋር ለመገናኘት ለት/ቤቱ ደዉለዉ ቀጠሮ መያዝ ይችላሉ።

የቤት ውስጥ ጉብኝቶች እና ከልጅዎ መምህር ጋር ስብሰባዎች ስለ ልጆችዎ መረጃ ለመለዋወጥ ጥሩ እድል ይሰጣሉ። ይህ ቀጣይነት ያለው መግባባት/ግንኙነት በቤት እና በት /ቤት መካከል ዘለቄታዊ አጋርነትን ያመጣል። እንደዚህ ኣይነቶቹ ትብብሮች ከተፈጠሩ፣ ልጃችሁ ለሚያስደስትና ለስኬታማ ተሞክሮ የበለጠ እድል ይኖረዋል/ይኖራታል።

የበረዶ ቀኖች ወይም አስቸኳይ ሁኔታዎችየአየር ጠባይ መጥፎ ሲሆን፣ የMCPS ት/ቤቶች ሙሉውን ቀን ሊዘጉ ይችላሉ ወይም የትምህርት መጀመርያ በሁለት ሰአት እንዲዘገይ ሊደረግ ይችላል።

• የትምህርት መጀመርያ በሁለት ሰአት እንዲዘገይ ከተደረገ፣ የጥዋት ቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድስታርት ክፍሎች አይኖሩም። የከሰአት በኋላ ትምህርቶች እንደተለመደው ይካሄዳሉ።

• በመጥፎ የአየር ፀበይ ምክንያት ት/ቤቶች ቀድመዉ ከተዘጉ፣የጥዋት ቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድስታርት ልጆች ቀደም ብለዉ ወደ ቤት የሚመለሱ ሲሆን፤ የከሰዓት በኋላ ቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድስታርት ክፍሎች አይኖሩም።

• ት/ቤት ሙሉውን ቀን ከተዘጋ፣ ወይም ት/ቤት አስቀድሞ ከተዘጋ፣ ሁሉም የምሽት እንቅስቃሴዎች ወድያውኑ/በአውቶማቲክ ይሰረዛሉ፣ እናም የመመርያ ምክርቤት ስብሰባ ወይም የአዋቂ ትምህርቶች አይኖሩም።

የትምህርት ቤት መዘጋቶች መረጃ በአካባቢ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች፣ በ MCPS የኬብል መስመሮች (Channel 34 on Comcast, 36 በ Verizon ላይ እና በ RCN ኬብል 89 ላይ)፣ እና በ MCPS ድረገጽ (www.montgomeryschoolsmd.org) ይሰራጫል። እንዲሁም መረጃ በ MCPS ቲዊተር አካዉንት (twitter.com/MCPS)፤የ MCPS ፌስቡክ አካዉንት(www.facebook.com/mcpsmd/) እንደሚያገኙ፤እና እንዲሁም MCPS በ Connect-ED ♦በወላጆች /አሳዳጊዎች በተሰጠ የድንገተኛ ጊዜ ቁጥሮች እና የኢሜል አድራሻዎችን የሚጠቀም የመደወያ እና የኢ-ሜል መላኪያ ስርዓት♦ መልዕክት ይልካል። እንዲሁም፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ/Montgomery County የማንቂያ ስርዓት የጽሁፍ/ቴክስት እና የኢሜል መልእክቶችን ለመቀበል መመዝገብ ይችላሉ (www.montgomeryschoolsmd.org/emergency/alertmcps.aspx)።

Page 12: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

4

በድቅድሚያ መለቀቂያ ቀኖችቅድመ-መዋለ-ህፃናት/ ሄድስታርት ክፍሎች በቀደም ብሎ መለቀቂያ ቀናት በተለየ ሁኔታ መርሀግብር ተይዞላቸዋል። የልጃችሁ መምህር የመልቀቂያ ሰአቶችን ያስታውቋችኋል። በተጨማሪ፣ እነዚህ አስቀድሞ መልቀቂያ ቀኖች ከመድረሳቸው በፊት ማሳሰቢያ ይላካል።

ኦክቶበር 4ኖቨምበር 8 እና 27

ጃኑዋሪ 24ፌብሩዋሪ 28ማርች 27

ጁን 15 (ለተማሪዎች የመጨረሻው ቀን)

የአካል ጉዳተኛ/ስንክልና ያላቸዉ ልጆችሄድስታርት በፌደራል ገንዘብ የሚካሄድ ፕሮግራም ነዉ። የአካል ጉዳተኛ /ስንክልና ያላቸዉ ልጆች ከምዝገባ ቦታዎች/መቀመጫዎች ከመቶ እጅ አስሩን እንዲይዙ ያዛል። አካል ጉዳተኛ/ስንክልና ያላቸዉ ልጆች የቅድመ-መዋዕለ ህጻናት /ሄድስታርት መማሪያ ክፍሎችን ስንክልና ከሌላቸው ጋር የጋራሉ (የማካተቻ ሞዴል/inclusion model) እናም የቅድመ-መዋዕለ ህጻናት/ሄድስታርት ልጆች የሚያገኟቸዉን ሁሉንም አገልግሎቶችና መብቶች ያገኛሉ። የመማሪያ ክፍል እንቅስቃሴዎች እና ልምዶች አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜና ቦታ ሁሉ የአካል ጉዳተኛ ልጆችን በሚያሳትፍ መልኩ እንዲስተካከሉ ይደረጋል።

ሁሉም ልጆች አንድ ላይ የሚማሩበት እና የሚያድጉበት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን፣ ወላጆች / ሞግዚቶች፣ አስተማሪዎች፣ እና ልጆች በማካተቻ ሞዴል/inclusion model ይደሰታሉ። ስለ ልጃቸው እድገት ከወላጆች/አሳዳጊዎች ለሚነሱ ጥያቄዎች የሰራተኛ አባላት መልስ ይሰጣሉ። በተጨማሪም፣ የሰራተኛ አባላት ለወላጆች/ለአሳዳጊዎች ልጃቸዉ እርዳታ በሚያስፈልጋቸው በተለየ አካባቢ የሚያግዝ/የሚረዳ የቤት ውስጥ እንቅስቃሴዎች ይሰጣሉ። ልጆች በተለያዩ የእድገት ዘርፎች የማጣሪያ ምርመራ ይደረግላቸዋል (ትምህርታዊ የንግግር፣ ዓይን፣ ጥርስ እና መስማት።) በማጣሪያ ምርመራው መሰረት፣ የትምህርት ስንክልና ከተጠረጠረ፣ የግላዊ የትምህርት ፕሮግራም (IEP) ቡድን (ለምሳሌ፣ መምህራን፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና የት/ቤት ስነ-ልቦና ባለሙያ፣ ልዩ አስተማሪ፣ የንግግር ፓቶሎጂስት፣ ነርስ፣ ወዘተ) ተጨማሪ ምዘናዎች/ምርመራዎች እንደሚያስፈልጉ ለመወሰን ይገናኛሉ። ሌሎች ተጨማሪ ምዘናዎች/ምርመራዎች ከተመከሩ/ከተወሰኑ፣ ትምህርት ቤቱ ለምርመራዎቹ የወላጅ /የአሳዳጊ ስምምነት ማግኘት አለበት።

አንዴ ምርመራዎቹ እና ግምገማዎቹ ከተጠናቀቁ በኋላ፣ የ IEP ቡድን አንድ የትምህርት ስንክልና እንዳለ መወሰን አለበት፣ ከሆነም፣ የትኛው የፌዴራል የትምህርት ስንክልና ኮዶች የተማሪዉን /ዋን ስንክልና እንደሚገልፅ ይለያል። አንዴ የትምህርት ስንክልና መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ፣ እና የ IEP ቡድን ስንክልናዉ በተማሪው/ዋ መማር ላይ ተፅእኖ ማሳደሩን ከወሰነ፣ ተገቢ ግቦች እና የልዩ ትምህርት አገልግሎቶች ላይ ዉይይት ይደረጋል።

ተፈላጊ አገልግሎቶች በቅድመ-መዋዕል ህጻናት/ሄድስታርት ፕሮግራም ወይም በሌላ የ MCPS ፕሮግራሞች በኩል

ሊቀርቡ ይችላሉ። ልጅዎ በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት/ (Pre-K/Head Start) የመማሪያ ክፍል ሊቀርብ ከሚችል የበለጠ የልዩ ትምህርት አገልግሎት ወይም በ MCPS ከሚቀርቡ አገልግሎቶች የተለየ የሚፈልግ/የምትፈልግ ከሆነ፣ የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ሰራተኛ የተወሰነዉን/የተመከረዉን አገልግሎቶች ወላጆች/አሳዳጊዎች እንዲያገኙ ይረዳሉ።

በልጅዎ እድገት ውስጥ ሊያዩዋቸው የሚገቡ ነገሮች፦

• ንግግርና ቋንቋ፡- ልጅዎ በግልጽ መናገር እና ቋንቋን መረዳት ይችላል?

• እውቅና/Cognitive፡- የእርስዎ ልጅ ከሌሎች .. ልጆች እኩል በተመሣሣይ መማር እና እድገት ይታይበ(ባ)ታል? እንደሌሎቹ በዕድሜ እኩዮች?

• ግርድፍና ረቂቅ እንቅስቃሴ/Gross and Fine Motor፡- ልጅዎ "ገልጃጃ" ነው/ናት ወይም ልጅዎ በእጁ/ጇ በመጠቀም በብሎክ ለመጫወት ወይም በወረቀት ላይ ለመጫር ችግር አለበት/ባት ወይ?

• ማህበራዊ/ስሜታዊ ልጅዎ ከሌሎች ልጆችና ጎልማሶች ጋር ይስማማልን/ትስማማለችን?

• ማሳሰብያ፡- ልጅዎ ዕድሜያቸው ካሉ ከሌሎች ልጆች ይልቅ በእርጋታ ቁጭ የማለት ወይም ትኩረት የመስጠት ችግር አለበት/ባት ወይ?

• ማዳመጥ/መስማት ወይም ማየት፡- ልጅዎ መጽሐፍትን ወይም ቴሌቪዥን ሲመለከት/ስትመለከት ዓይኑን/ኗን በከፊል ይጨፍናል/ትጨፍናለች ወይ? ልጅዎ ለአካባቢው/ዋ ድምጽ በአግባቡ ምላሽ ይሰጣል/ትሰጣለች ወይ?

የልጅዎን እድገት በተመለከተ ስጋት ካለዎት፣ ለአስተማሪዎ ያሳውቁ፣ ወይም ለቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ክፍል በ 240-740-4530 ይደውሉ።

የእንግሊዘኛ ተማሪዎችበፌደራል እና በስቴት መስፈርቶች መሠረት፣ የሁሉም ቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/የሄድስታርት/Head Start ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች የሜሪላንድ የቤት ውስጥ ቋንቋ ቅኝት በ MCPS ፎርም 560-24 ላይ፣ የአዲስ ተማሪ መረጃ፣ በምዝገባ ጊዜ ያጠናቅቃሉ። ልጅዎ በቤት ውስጥ ስለሚናገረው/ስለምትናገረዉ ቋንቋ መረጃ ይሰጣል። ትምህርት ቤቶች በአመቱ መጀመርያ ላይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሌሎች ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL) አገልግሎቶች ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግና ተማሪዎችን ለመለየት ይህንን መረጃ ይጠቀማሉ። በማጣሪያ ውጤቶቹ ላይ መሰረት በማድረግ፣ ተማሪዎች በቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት የትምህርታቸው ፕሮግራም አካል ሆኖ የ ESOL አገልግሎቶችን ይቀበላሉ። የማጣሪያ ውጤቶች ለኢሚግሬሽን ጉዳይ ጥቅም ላይ አይውሉም።

የጤና አገልግሎቶችለቅድመ-መዋለ ሕጻናት/ሄድስታርት (Head-Start) እንደ ቅድመ ሁኔታ፣ ሁሉም ተማሪዎች አካላዊ ምርመራ፣ የስቴትና የፌድራል ተፈላጊ ክትባቶች፣ የደም ምርመራና

Page 13: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

5

የጥርስ ምርመራ ማድረግ አለባቸው። ልጅዎ አካላዊ ምርመራ እና ክትባቶች ለመቀበል የጤና እንክብካቤ ምንጭ ከሌለው/ከሌላት፣ እነዚህን አገልግሎት ማግኘት እንዲ(ድት)ችል እባክዎን የልጅዎ አስተማሪ፣ የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኛ፣ ወይም የት/ቤቱ ነርስ እንዲያውቁ ያድርጉ። ለስቴት እና ለአካባቢ የጤና እና የአመጋገብ ፕሮግራሞች፣ በሚከተሉት ቦታዎች በሚገኙ የብቁነት እና የድጋፍ አገልግሎቶች ጽ/ቤት (OESS) ለቤተሰብዎ ፋይናንሳዊ ድጋፍ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፦

12900 Middlebrook RoadGermantown, MD 20874 . 240-777-3591

1401 Rockville PikeRockville, MD 20852 . . . 240-777-3120

8630 Fenton StreetSilver Spring, MD 20910 240-777-3066

4910 Macon RoadRockville, MD 20852 . . . 240-740-4430

በሞንትጎመሪ ካውንቲ/Montgomery County የጤና ማዕከሎች እና በ Rocking Horse Road Center (4910 Macon Road, Rockville) በሚገኝ የ MCPS የጤና አገልግሎቶች ማእከል የሚሰጡ ሁሉም ክትባቶች ለቤተሰቦች በአነስተኛ ወጪ ይቀርባሉ። እባክዎን ልጀዎ የወሰዳቸውን ክትባቶች ማስረጃ በሚገባ ይያዙ።

በትምህርት አመት ውስጥ ልጅዎ የጥርስ፣ የመስማት፣ የማየት፣ የቁመት እና የክብደት ምርመራዎች/መለኪያዎች ይቀበላል።

ልጅዎ በትምህርት ቀናት በሃኪም የታዘዘ ወይም ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ተግዝቶ የሚወሰድ መድሃኒት የሚያስፈልገው/የሚያስፈልጋት ከሆነ ፈቃድ ባለው/ባላት የህክምና ባለሙያ መድሃኒት የታዘዘበትን እና MCPS ቅጽ 525-13 ተሞልቶ ለት/ቤት መሰጠት አለበትበሃኪም የታዘዘ መድሃኒት ለመስጠት ፈቃድ መስጫ ቅጽ በልጅዎ ት/ቤት እና በ MCPS ድረገጽ ላይ ይገኛል፦ www.montgomeryschoolsmd.org/departments/forms/pdf/525-13.pdf). በሐኪም የታዘዘ መድሃኒት በመድሃኒት በባለሙያ በተገቢዉ ምልክት ተደርጎበት በዋናዉ/በመደበኛ መያዣ ወደ ትምህርት ቤት መምጣት አለበት። ያለሃኪም ትእዛዝ የሚወሰድ ከመደርደሪያ ላይ የሚገዛ መድሃኒት በተመረተበት ኦርጅናል እቃ ላይ በትክክል የተከደነ እና የታሸገ መሆን አለበት። MCPS ቅጽ 525-14፣ Anaphylaxis ያለበት/ያለባት ተማሪ ድንገተኛ እንክብካቤ/እርዳታ፣ epinephrine auto-injectors ለመጠቀም ህጋዊ ፈቃድ ባለው/ባላት የህክምና ባለሙያ ተመራጭ የማዘዣ ፎርም (www.montgomeryschoolsmd.org/departments/forms/pdf/525-14.pdf)። ሁሉም ዓይነት መድኃኒት በወላጅ/በሞግዚት አማካይነት ለት/ቤት በእጅ መሰጠት አለበት። ልጃችሁ የሆነ የጤና ችግር፣ በተለይ ኣስቸኳይ እርምጃ የሚጠይቁ እንደ ኣስማ፣ የስኳር በሽታ፣ ኣዙሮ የሚጥል፣ ወይም የተባይ ንድፊያ ወይም የምግብ ኣለርጂ ካለው/ካላት እባክዎን ለርእሰመምህር እና ለት/ቤቱ ነርስ ያስታውቁ።

ወላጅ፣ቤተሰብ፣እና የማህበረሰብ ተሳትፎየሄድስታርት ፕሮግራም እያንዳንዱ በፌደራል ብቁ የሆነ ቤተሰብ ከተሰየመ/ች የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ሰራተኛ አባል ጋር የቤተሰብ የሽርክና ስምምነት (FPA) ማዘጋጀት እንዳለበት ይጠይቃል። FPA የቤተሰብ ሀይሎችና ፍለጎቶችን ለመወሰንና ቤተስቦች ግላዊ ግቦቻቸውን እንዲመቱ የሚያግዝ ሂደት ነው።

የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ሰራተኞች ከሌሎች የማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር አጋርነት መመስረት እና እንደ ሥራ/ቅጥር፣ መኖሪያ ቤት፣ ምግብ፣ልብስ፣የቤተሰብ ማንበብና መጻፍ፣ የቤት ውስጥ ብጥብጥ፣እና የአደንዛዥ እፅ መጠቀም ላሉ የድጋፍ አገልግሎቶች ወላጆች/ሞግዚቶችን ከመገልገያዎች ጋር ያገናኛሉ። በቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት እና በማህበረሰብ ድርጅቶች መካከል አገልግሎቶችን ለማስተባበር እና የጥረቶችን ማባዛት/ድግግሞሽ ለማስወገድ ቤተሰቦች FPA ን እንዲያጠናቅቁ ይበረታታሉ።

የማኅበረሰብ ሪሶርስ መረጃ እና ድጋፍ ለልጅዎ ክፍል በተመደበው/ችዉ የቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኛ በኩል ይቀርባል። በ 240-740-4530 ያግኙዋቸዉ። እያንዳንዱ ቤተሰብ ወቅታዊ እና የወደፊቱን ፍላጎቶች ለማገዝ የማህበረሰብ ሪሶርስ መመሪያ ይቀበላል። የድንገተኛ እና የችግር ጊዜ ጣልቃ ገብነትን ጨምሮ፣ ሁለቱም የግል እና የቤተሰብ ምክር፣ በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ማህበራዊ ሰራተኞች/social workers በኩል ይቀርባል። ሁሉም መረጃ በሚስጢር ይያዛል።

በየወሩ፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች በልጆቻቸው ትምህርት ቤት ውስጥ የወላጅ/አሳዳጊ የትምህርት ዎርክሾፕን ለማዘጋጀት/ለማቀድ የቤተሰብ አገልግሎት ሠራተኛና የማስተማር ቡድንን እንዲረዱ ይጋበዛሉ። ርእሶች የልጅ ዕድገት እና ብልጽግና፣ ጤና፣ የአመጋገብ እና የምግብ ደህንነት፣ የወላጅ/አሳዳጊዎች በት /ቤት ዝግጁነት ተሳትፎ፣ ቋንቋ እና ማንበብና መፃፍ እና የግል ደህንነትን ያካትታሉ።

ከፍተኛ ጥራት ያለው ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ፕሮግራም ለማግኘትን ልጆች/ወላጆች/ሞግዚቶች እና ሰራተኞች ከፍተኛውን ጥቅም እንዲያገኙ ችሎታቸውን፣ እውቀታቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን ማካፈል አለባቸው. በፕሮግራሙ ላይ የሚሳተፉ ወላጆች/አሳዳጊዎች መማር እና ማጋራት አስፈላጊ መሆናቸውን ለልጆች ያሳያሉ። ወላጆች/አሳዳጊዎች በሚከተሉት መንገዶች ይሳተፋሉ፦

ስለ ፕሮግራሙ ምንነትና እንቅስቃሴ አወሳሰን ላይ በሚከተሉት መንገዶች ማገዝ—

• በፖሊሲ ካውንስል ስብሰባዎች ላይ የመሀከል ተወካይ የሚሆን/የምትሆን አንድ ወላጅ/አሳዳጊ መምረጥ፣

• የመመርያ ምክር ቤት ስብሰባዎች መከታተል፣

• የማእከል ስብሰባዎች ማደራጀትና ማካሄድ፣

• ማዕከሉ እና መርሃግብሩ ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲሰራ የማገዣ መንገዶች ማቀድ፣

Page 14: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

6

• በመርሃግብሩ በጀት እና በፕሮጀክት እቅድ ላይ መስራት፣ እና

• በአመታዊ ፕሮግራም ግምገማ ማገዝ።

በመማርያ ክፍል እንደ በጎ-ፈቃደኛ፣ ተመልካች፣ ወይም የሚከፈለው ሰራተኛ ሆኖ መስራት—

• መማርያ ክፍል በመጎብኘት፣

• የመስክ ጉዞዎችን አጃቢ-ተቆጣጣሪ በመሆን፣

• በመማርያ ክፍል አዘውትሮ በጎ-ፈቃደኛ በመሆን፣

• እንደ ረዳት መምህር፣ ተለዋጭ ረዳት መምህር፣ የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኛ፣ ወዘተ ሆኖ መቀጠር።

ለወላጆች/አሳዳጊዎች የሚከተሉትን የሚያካትት እንቅስቃሴዎችን ማጎልበት፦

• የቤተሰብ እንቅስቃሴዎች ማቀድና ማካሄድ፣

• ከካውንቲና ከበጎ-ፈቃደኛ ድርጅቶች ጋር ማህበረሰቦችን ለማሻሻል መስራት፣

• በማህበረሰብ መገልገያዎች መጠቀም፣

ከቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ሰራተኛ ጋር በመተባበር፣ የሚከተሉትን በማካተት ከልጆቻቸው ጋር ቤት ዉስጥ መሥራት፦

• ልጆች እንዲማሩ የሚያበረታቱ ጨዋታዎችን ወይም እንቅስቃሴዎችን በቤት ውስጥ መጠቀም፣ እና

• ስለ ልጅ ብልፅግና በተማሯቸው ቴክኒኮች መጠቀም።

በጎ-ፈቃደኞችየወላጅ/ሞግዚት በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ተሳትፎ በጣም አስፈላጊ እና የሚበረታታ ነው። ወላጆች/አሳዳጊዎች በክፍል ውስጥ በመጎብኘት፣በመጠበቅ፣ እና በመርዳት ልጆቻቸውን እና ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርትን ይደግፋሉ። በተጨማሪም፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች የመስክ ጉዞዎች በመሄድ፣ ፕሮግራሙን ለማሻሻል አስተያየቶችን በመስጠት፣ እና የክፍል ውስጥ ቁሳቁሶችን በቤት ውስጥ በማዘጋጀት ያግዛሉ። እንደ አንድ መደበኛ በጎ-ፈቃደኛ ሆነው ማገዝ ከፈለጉ፣ ከልጅዎ መምህር ጋር ይወያዩና ከሳምንት በየትኛው ቀን በመማርያ ክፍል በጎ-ፈቀደኛ ለመሆን እንደሚቻልዎት ፕሮግራም ያድርጉ። የቀን ሰአቶች ካጠሩ፣ ከቤት ሆነው ማገዝ ስለሚችሉባቸው ሌሎች መንገዶች ተወያዩ። ለተጨማሪ መረጃ ለቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ክፍል በ 240-740-4530 ይደዉሉ።

የበጎ ፈቃደኞች በሙሉበመደበኛነትትምህርት ቤቶችን እና ተማሪዎችን የምትደግፉ እና የመስክ ጉዞዎች ላይ የምትሳተፉ፣ በአውታረ-መረብ ላይ የሚሰጠውን “Recognizing and Reporting Child Abuse and Neglect.” ስልጠና ማጠናቀቅ ይኖርባችኋል። ስልጠናዉ በእንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ቻይንኛ፣ ኮሪያኛ፣ እና ቪዬትናምኛ በ MCPS ድረገጽ፣ www.montgomeryschoolsmd.org ላይ ይገኛል። ስልጠናውን ሲጨርሱ፣ የመጠናቀቂያውን የምስክር ወረቀት ማተም እና ለልጅዎ ትምህርት ቤት መስጠት አለብዎት። ሁሉም በጎ ፈቃደኞች በእያንዳንዱ የእንቅስቃሴ መጀመሪያ እና

ማብቂያ የጎብኚ አስተዳደር ስርዓት (VMS) በመጠቀም፣ ት/ቤቱ ህንጻ ውስጥ ሲገቡ እና ሲወጡ መፈረም እና ሁልጊዜ የእራስዎን የበጎ ፈቃደኛ መታወቂያ መለያ ስም ያለበትን መጠቀም እንዳለብዎት ያስታዉሱ።

ለመማርያ ክፍል በጎ-ፈቃደኛ ከመሆንዎ በፊት የሳምባ ነቀርሳ (TB) ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። የTB ምርመራ ለማድረግ፣ እባክዎን በልጅዎ ት/ቤት ነርስ ይደውሉ።

መጓጓዣ/ትራንስፖርትወላጆች/ኣሳዳጊዎች ወደ ኣውቶቡስ ጣቢያ/ማቆሚያ መንገድ ላይ፣ ኣውቶቡስ ጣቢያ/ማቆሚያ ላይ፣ እና ከኣውቶቡስ ጣቢያ/ማቆሚያ ወደ ቤት ለልጆቻቸው ሃላፊነት ኣለባቸው። እባክዎ ልጅዎች ጥዋት ጥዋት ወደ አውቶቡስ ያድርሱ በያንዳንዱ ሰአት በኋላ ደሞ አውቶቡሱን ያግኙ። የአውቶቡስ መርሃግብሮች ግምታዊ ናቸው እናም በአየር ሁኔታ፣ ትራፊክ፣ እና የተማሪ ለውጦች ምክንያት ሊለያዩ ይችላሉ። ከመደበኛ መድረሻ ሰዓት ቢያንስ ከአምስት ደቂቃ በፊት በአውቶቡስ ማቆሚያ ላይ መገኘት በጣም ጥሩ ነው። አውቶቡሱን ማግኘት የማይችሉ ከሆነና ሌላ ሃላፊነት የሚሰማው አዋቂ እንዲተካዎ ከመረጡ (ለምሳሌ፣ የልጅ እንክብካቤ አቅራቢ፣ አያት)፣ እባክዎ የልጅዎን መምህር ወይም ረዳት አስተማሪን በፅሁፍ ያስታውቁ። ለአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ የትምህርት ቤት ስልክ ቁጥር በሞባይል ስልክዎ ወይም በሌላ ምቹ ቦታ ያስቀምጡ/ይያዙ።

እርስዎ ወይም የእርሶ ተወካይ ልጅዎን ካላገኙ፣ ወደ ትምህርት ቤት ይመለሳሉ። እርስዎ ወይም ተወካይዎ ከአውቶቡሱ ልጅዎን ለመቀበል ሶስት ጊዜ ካልቻላችሁ፣ የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኛ ጋር መገናኘት አለብዎት። ችግሮቹ ከቀጠሉ፣ የመጓጓዣ መብቶች ሊቋረጡ ይችላሉ። በተጨማሪም፣ የአውቶቡስ ላይ የባህሪ ችግሮች የአውቶቡስ መብቶችን ሊያቋርጡ ይችላሉ።

የወላጅ/ማእከል ኮሚቴ ስብሰባዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች፣ የማስተማሪያ ሰራተኞች፣ እና የቤተሰብ አገልግሎት ሰራተኞች ተባብረው መረጃ ሰጪ እና አዝናኝ የሆነ የወላጅ/አሳዳጊ ስብሰባ ለማቀድ ይሠራሉ።

በትምህርት ቤት ውስጥ በሚካሄደዉ በወላጅ /አሳዳጊ የማዕከል ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ እንዲሳተፉ ልጅዎ ግብዣዉን ወደ ቤት ያመጣልዎታል/ታመጣልዎታለች። ቦታ ካለ ከልጆዎ ጋር አብረው በአውቶቡስ መሳፈር ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ፣ የሕጻናት እንክብካቤ ይቀርባል።

እያንዳንዱ የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ክፍል ሁሉም ወላጆች/አሳዳጊዎች የሚገኙበት አንድ የማዕከል ኮሚቴ አላቸው። የማእከል ኮሚቴው በሚከተሉት ምክንያቶች በትምህርት ሰአት በየወሩ ይሰበሰባል፡-

• ወላጆች /አሳዳጊዎች እንዲተዋወቁ ማገዝ፣

• ስለ ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ክፍል የበጎ ፈቃደኞች እና የመስክ ጉብኝቶች ውሳኔዎችን መስጠት፣ እና ለተማሪዎች በጣም የተሻለውን ፕሮግራም በማቀድ መርዳት፣

Page 15: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

7

• በትምህርት ቤትና በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ሄድስታርት ፕሮግራም መካከል የሁለትዮሽ /የሁለት አቅጣጫ ግንኙነት ማድረግ፣

• ከ እና ወደ መመርያ ምክር ቤት ቅሬታዎችና መርጃዎች መላክ/መቀበል፣

• የማእከል ስራዎችን ማካሄድ እና በሚከተሉት ላይ መረጃ መጋራት -

» ልጆች እንዴት እንደሚያድጉና እንደሚደረጁ

» ልጆች እንዲማሩ ለመርዳት አስደሳች መንገዶች

» አልሚ ምግቦችን ለማዘጋጅት የምግብ ዶላሮችን ማብቃቃት

» እደጥበባትና ክህሎቶች

» ልጆችን መኖርያ ቤት ውስጥ እንዲማሩ ማገዝ

ቅድመ መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት የቤተሰብ ፕሮግራም ነዉ። የርስዎን እርዳታ በመማርያ ክፍል፣ በፖሊሲ ምክር ቤት፣ እና በሙሉው ፕሮግራም እንፈልገዋለን።

A BC ሌላ መረጃ

ቀዳሚ ሄድስታርት/Head Startቀዳሚ ሄድስታርት/Head Start እድሜአቸው ከወሊድ እስከ 3 አመት የሆኑ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች አስደናቂ ፕሮግራም ነው። ፕሮግራሙ ከሄድስታርት/Head Start ጋር ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ አገልግሎቶች እና የተወሰኑ ልዩ የሆኑትን ለቀዳሚ ሄድስታርት/Early Head Start ያቀርባል። ለማመልከት፣ ቤተሰቦች እርጉዝ ወይም እድሜአቸው 26 ወሮች ወይም ከዚያ በታች የሆኑ ልጆች ያሏቸው መሆን አለባቸው።

ስለ ፕሮግራሙ ተጨማሪ መረጃ የሚያገኙበት እነሆ፦

በጌተርስበርግ/Gaithersburg እና በላይኛዉ ካዉንቲ/Upcounty አካባቢ፦ ለቤተሰብ አገልግሎቶች Inc፣ ቅድመ ሄድስታርት በ 301-840-3272 ይደዉሉ።

በስልቨር ስፕሪንግ እና ራክቪል አካባቢ/Silver Spring and Rockville areas፦ ለ Reginald S. Lourie ማዕከል፣ ቅድመ ሄድስታርት በ 301-891-1900 ይደዉሉ።

በላንግሊ ፓርክ/ስልቨር ስፕሪንግ አካባቢ/Langley Park/Silver Spring areas፦ ለ CentroNía፣ ቅድመ ሄድስታርት በ 301-543-8040 ይደዉሉ።

የህፃናት እንክብካቤየልጅ እንክብካቤ ሰጪ የሚፈልጉ ወላጆች/ኣሳዳጊዎች ወደ LOCATE መደወል ይችላሉ፡- የሕፃናት እንክብካቤ በስልክ ቁጥር 1-877-261-0060፣ ወይም ቻይልድሊንክ 240-777-4769 በነፃ እርዳታ ፈቃድ ያለው የሕጻናት እንክብካቤ አቅራቢ ለማግኘት፣ የትምህርት እድሜ መርሃ ግብር፣ የሰመር ካምፕ፣ ቅድመ ትምህርት፣ እና/ወይም የመሰናዶ ት/ቤት ፕሮግራም። LOCATE፣ እንደ የእንክብካቤ

ሰኣቶች፣ ቦታ፣ የልጆች ብዛትና እድሜ፣ እና የልጅ እንክብካቤ ዋጋ በመሰሉ፣ የያንዳንዱን ቤተሰብ ፍላጎቶች ላይ በመመስረት አገለገሎት ሰጪዎችን ይለያል። ይህ ኣገልግሎት በበርካታ ቋንቋዎች ሊደረስበት ይቻላል።

LOCATE በትምህርት ቤቱ የአገልግሎት ክልል ውስጥ ወይም አጠገብ የሚገኙትን አቅራቢዎች ለይቶ ማወቅ ይችላል። በተጨማሪ፣ ኣማካሪዎች መልካም-ኣይነት ፕሮግራሞችን ስለ መለየት ጥቆማዎች እና ወላጆች/ኣሳዳጊዎች ትክክለኛ ፕሮግራም ለልጃቸው እንዲመርጡ ለማገዝ ለክትትል ቀላል የሆኑ ጥቆማዎች ይሰጣሉ። ማፈላለግ/LOCATE፡- Child Care በሜሪላንድ ትምህርት መምርያ Child Care ጽ/ቤት የፀደቁ የቤተሰብ የልጅ እንክብካቤ ኣቅራቢዎችንና የልጅ እንክብካቤ ማእከሎችን ሁለቱንም ይለያል።

ወላጆች/ኣሳዳጊዎች የሚከተሉትን ጠባዮች የሚያንፀባርቁ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ፕሮግራሞች ማግኘት ኣለባቸው፡- ሰራተኛው/ዋ የልጆቹን እድገታዊ ፍላጎቶች ይገነዘባል/ትገነዘባለች፤ ፕሮግራሙ የተለያዩ ትምህርታዊ ቁሳቁሶች፣ ኣቅርቦቶች፣ እና ከተገልጋዮች እድሜዎች ጋር ኣግባብ ያላቸው ግጥሚያዎች ኣሏቸው፤ ወላጆች/ኣሳዳጊዎች መልካም ኣቀባበል ኣላቸው ይሳተፋሉም፤ መርሃግብሮችን፣ ፖሊሲዎች፣ሂደቶች እና ፕሮግራሞችን በሚመለከት ሰራተኛው/ዋ ከት/ቤት ፔርሶኔል ጋር ኣብሮ/ራ ይሰራል/ትሰራለች።

የስቴትና የካውንቲ ህጎች ከ8 አመት በታች የሆኑ ልጆች ሁልጊዜ በወላጅ/ኣሳዳጊ፣ የልጅ እንክብካቤ ኣቅራቢ፣ ወይም ቢያንስ 13 አመት እድሜ ያለው/ያላት የህፃን ሞግዚት ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ ይጠይቃሉ። ወላጆች/ኣሳዳጊዎች ስለ ልጅ እንክብካቤ መረጃዎች መስመር ላይ በ www.marylandfamilynetwork.org መፈለግ ይችላሉ።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ/Montgomery County ጤና እና የሰብአዊ አገልግሎቶች በኩል ለህጻን እንክብካቤ ለመክፈል የገንዘብ እርዳታ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ፦ የሠራተኛ ቤተሰብ ድጋፍ (WPA) 240-777-1177 ይደዉሉ። ቅጂው እርስዎ ብቁ መሆንዎን ለመወሰን እንዴት እንደሚቻል ጨምሮ አጠቃላይ መረጃ ይሰጣል። የሜሪላንድ ስቴት የልጆች እንክብካቤ ድጎማ ፕሮግራም ለልጆች እንክብካቤ ክፍያ ብቁ ለሆኑ ሰራተኛ ቤተሰቦች ድጋፍ ያደርጋል፤ ወደ 1-866-243-9796 ይደውሉ።

ቅድመ መዋዕለ ህፃናት የሙከራ ፕሮግራም (Pre-K+)ይህ ሙሉ ቀን የሚካሄድ የ Pre-K ፕሮግራም ገንዘብ የሚገኘው ከሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት "Maryland State Department of Education (MSDE)" ነው። ፕሮግራሙ በሰባት የተመረጡ ኤለመንተሪ ትምህርት ቤቶች 160 የአራት-ዓመት እድሜ ተማሪዎችን ያገለግላል፦ ዌለር ሮድ (Weller Road)፣ ቤል ፕሬ (Bel Pre)፣ ጁአን ለለክ አት ብሮድ ኤከርስ (JoAnn Leleck at Broad Acres)፣ ዋሽንግተን ግሮቭ (Washington Grove)፣ እና ክሎፐር ሚል (Clopper Mill)። መጓጓዣ እና ምሳ ይቀርባል። የቤተሰብ ገቢ ከድህነት ደረጃ 300 በመቶ ወይም በታች መሆን አለበት። ቤተሰቦች እንደ ሄድስታርት ተሳትፎ ተመሳሳይ የድጋፍ አገልግሎቶች እና እድሎች ያገኛሉ።

Page 16: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

8

A BC ብዙ ጊዜ በቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ ሄድስታርት ጥቅም ላይ የሚዉሉ ቃላት

ACYFለልጆች፣ ወጣቶች፣ እና ቤተሰቦች አስተዳደር—የሄድስታርት ፕሮግራምን የሚቆጣጠር የፌደራል ኤጀንሲ።

የህብረተሰብ ተወካይከፖሊሲ ምክር ቤት ጋር የሚያ(ምታ)ገለግል፣ ነገር ግን የአሁን ቅድመ መዋዕለ ሕጻናት/ ሄድስታርት ተማሪ ወላጅ/አሳዳጊ ያልሆነ/ች፤ በአብዛኛው ቀደም ብለው በፕሮግራሙ ውስጥ ልጆች የነበሯቸዉ ወይም የአንድ ድርጅት ተወካይ ወይም የካውንቲ ወኪል የሆነ/ች።

ስርአተትምህርትየልጆችን ትምህርት የሚደግፍ የማስተማር መዋቅር።

የቤተሰብ ሽርክና ስምምነት (FPA)ከቤተሰብ አገልግሎት ስራተኛቸው ድጋፍ ተጨምሮበት፣ የቤተሰብ ግቦች ለማስቀመጥና ለክትትልና ለአፈፃፅም እርምጃዎች ያሉት የፅሁፍ ፕላን ለማዳበር፣ አንድ የቤተሰቦች እድል።

እርዳታ/Grant/በቀረበው የፅሁፍ ሀሳብ እንደተገለፀው፣ የHead Start ን ፕሮግራም ለማንቀሳቀስ የሚሰጥ ገንዘብ።

እርዳታ ተቀባይ ወኪል ድርጅትየ Head Startን ፕሮግራም ለማንቀሳቀስ ከACYF የሚሰጠውን ገንዘብ የሚቀበል ወኪል ድርጅት—የሞንትጎመሪ ካውንቲ የማህበረሰብ ትግባሬ ወኪል ድርጅት/Montgomery County Community Action Agency።

ተወካይ ድርጅትለቅድመ መዋለ ሕጻናት/ሄድስታርት ፕሮግራም የዕለት ተዕለት ስራ ሀላፊነት ያለበት ድርጅት —የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ/Montgomery County Public Schools።

የፖሊሲ/መመርያ ካውንስልለቅድመ-መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ፕሮግራሞች ፖሊሲን በማዘጋጀት የሚረዱ የወላጅ/ማዕከል ኮሚቴ ተወካዮች።

የፌዴራል ግምገማበፌደራል መንግስት በየሶስት አመት የሚከናወን የቅድመ-ሙአለህፃናት/Head Start ፕሮግራም ግምገማ።

ለትምህርት ቤት ዝግጁነትአንድ/ዲት ልጅ ለት/ቤት ስኬታማነት የሚያስፈልጉ ክሂሎቶች፣ ችሎታዎች፣ እና አቋሞች አሉ(ሏ)ት።

ራስን መገምገምየፕሮግራም ራስን የመገምገም ሂደት በወላጆች/አሳዳጊዎች እና ሰራተኞች በየዓመቱ ይካሄዳል።

የቅድመ መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት TOT መስመር፦ 240-740-4580

ስለ ልጃቸው ባህሪ ወይም እድገት ጥያቄ ወይም አሳሳቢ ጉዳይ ሲኖርባቸው ለቅድመ መዋዕለ ህፃናት/ሄድስታርት ወላጆች/አሳዳጊዎች እንዲጠቀሙ ልዩ የስልክ መስመር አለ። የፕሮብለሞች አያያዝ ላይ ልዩ አስተያየቶች/ሃሳቦች ሲያስፈልጉ

ይደውሉ። የ TOT መስመር ከሰኞ እስከ ዓርብ፣ ከጠዋቱ 8 30 a.m. እስከ 5:00 p.m. ይሠራል።

Page 17: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

9

A BC የ 2019 የቀን መቁጠሪያ

ጁላይ 4 የነፃነት ቀን — ት/ቤቶችና ቢሮዎች ዝግ ናቸዉ

ኦገስት 26፣ 27፣ 28፣ 29፣ 30

የመምህራን የሙያ ቀን

ሰፕተምበር 2 የወዛደር ቀን — ት/ቤቶችና ቢሮዎች ዝግ ናቸዉ

ሴፕቴምበር 3 (K–12) የመጀመሪያው የትምህርት ቀን

ሴፕቴምበር 3፣ 4፣ 5፣ 6 ሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) የቤት ጉብኝት

ሴፕቴምበር 9 & 10 በቅደምተከተል የሚከፈቱ Head Start፣ Pre-K፣ እና Pre-K Pilot (Pre-K+) ተማሪዎች

ሴፕተምበር 11ለሄድስታርት፣ ቅድመ መዋዕለ ህፃናት፣ እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) ሁሉም ተማሪዎች የመጀመሪያ ቀን

ሴፕቴምበር 30 ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም

ኦክቶበር 3 የመምርያ ምክር ቤት—መተዋወቂያ—7 PM Rocking Horse Road Center

ኦክቶበር 4 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ኦክቶበር 9 ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም

ኦክተበር 11 የ Head Start የወላጅ መተዋወቂያዎች ያልቃሉ

ኦክተበር 16የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) አስተማሪዎች ስልጠና —የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) ተማሪዎች ክፍል አይኖርም

ኦክተበር 17 የመምርያ ምክር ቤት—ስልጠና—7 PM Rocking Horse Road Center

ኦክቶበር 24 የቅድመ መዋዕለ ህፃናት መምህራን ስልጠና—ለቅድመ መዋዕለ ህፃናት ተማሪዎች ትምህርት የለም

ኦክቶበር 24 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Center

ኦክተበር 31 የቅድመሙዓለህፃናት/Prekindergarten መግለጫ ይጠናቀቃል

ኖቬምበር 7 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 Rocking Horse Road Center

ኖቬምበር 8 ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ኖቨምበር 11 የወላጅ - መምህር ኮንፈረንሶች— ለ Pre-K፣ Pre-K+ እና ሄድ ስታርት ተማሪዎች ት/ቤት አይኖርም

ኖቨምበር 12 የወላጅ - መምህር ኮንፈረንሶች— ለ Pre-K፣ Pre-K+ እና ሄድ ስታርት ተማሪዎች ት/ቤት አይኖርም

ኖቨምበር 19የልጅ እድገት እና መዳበር ወላጅ/ሞግዚት ስብሰባ—6:30 እስከ 8:30 p.m. Rocking Horse Road Center

ኖቬምበር 21 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center

ኖቨምበር 27 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ኖቨምበር 28 እና 29 ታንክስጊቪንግ/Thanksgiving— ት/ቤቶች እና ጽ/ቤቶች ዝግ ናቸው

ዲሰምበር 5የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) አስተማሪዎች ስልጠና —የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) ተማሪዎች ክፍል አይኖርም

ዲሰምበር 5 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 Rocking Horse Road Center

ዲሰምበር 6 የክረምት መብራቶች ክውነት

ዲሴምበር 9-13 ብሔራዊ የሄድስታርት የወላጅ ማሰልጠኛ ኮንፈረንስ

ዲሴምበር 11ቋንቋ እና መሠረተ ትምህርት ወላጅ/ሞግዚት ስብሰባ —6:30 እና 8:30 p.m.

Rocking Horse Road Center

ዲሰምበር 12 የቅድመ መዋዕለ ህፃናት መምህራን ስልጠና—ለቅድመ መዋዕለ ህፃናት ተማሪዎች ትምህርት የለም

ዲሴምበር 13 የክረምት መብራቶች ክውነት

ዲሰምበር 19 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center

ዲሴምበር 23፣ 24፣ 25፣ 26፣ 27፣ 30 31

የዊንተር/የክረምት እረፍት-ለተማሪዎች እና ለመምህራን ት/ቤት ዝግ ይሆናል፣ ዲሴምበር 24 እና 25 ጽ/ቤቶች ዝግ ይሆናሉ።

Page 18: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

10

A BC የ 2020 የቀን መቁጠሪያ

ጃንዋሪ 1 አዲስ ዓመት የመጀመርያ ቀን—ት/ቤቶች እና ጽ/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጃኑዋሪ 2 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 Rocking Horse Road Center

ጃንዋሪ 15 የአባትነት ተግባር/Fatherhood Activity—6:30 PM Rocking Horse Road Center

ጃኑዋሪ 16 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center-

ጃኑዋሪ 20 የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር/Dr. Martin L. King፣ Jr. ቀን—ት/ቤቶች እና ጽ/ቤቶች ዝግ ናቸው

ጃኑዋሪ 24 ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ጃኑዋሪ 27 የመምህራን የሙያ/ፕሮፌሽን ቀን፣ ለተማሪዎች ት/ቤት አይኖርም

ፌብሩዋሪ 5የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) አስተማሪዎች ስልጠና —የሄድስታርት እና ቅድመ መዋዕለ ህፃናት ሙከራ (Pre-K+) ተማሪዎች ክፍል አይኖርም

ፌብሯሪ 6 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 Rocking Horse Road Center

ፌብሩዋሪ 12 የቅድመ መዋዕለ ህፃናት መምህራን ስልጠና—ለቅድመ መዋዕለ ህፃናት ተማሪዎች ትምህርት የለም

ፈብሩዋሪ 17 የፕረዚደንት ቀን—ት/ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸዉ

ፌብሩወሪ 18፣ 19፣ 20፣ 21

ሄድስታርት እና Pre-K Pilot (Pre-K+) የቤት ጉብኝት—ለ ሄድስታርት እና Pre-K Pilot (Pre-K+) ክፍል አይኖራቸውም

ፌብሩወሪ 20 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center

ፌብሩዋሪ 28 ሁሉም ተማሪዎች ቀደም ብለው የሚለቀቁበት ቀን

ማርች 5 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 – Rocking Horse Road Center

ማርች 19 ፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center

ማርች 24ስለ ጤና እና ስነምግብ የወላጅ/ሞግዚት ስብሰባ—6:30 እስከ 8:30 p.m.

Rocking Horse Road Center

ማርች 27 ኣስቀድሞ መለቀቂያ ቀን ለሁሉም ተማሪዎች፤ የሩብ ኣመት ፕላን መጨረሻ

ማርች 29–ኤፕሪል 2 ናሽናል ሄድስታርት ኮንፈረንስ/ስብሰባ

ኤፕረል 2 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ—6:30 Rocking Horse Road Center

ኤፕሪል 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ 13

የስፕሪንግ እረፍይ-ለተማሪዎች እና ለመምህራን ት/ቤት አይኖርም፣ ጽ/ቤቶች ኤፕሪል 10 እና 13 ዝግ ይሆናሉ።

ኤፕረል 16 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ—7 PM Rocking Horse Road Center

ኤፕረል 21 ስለ ግል ደህንነት የወላጅ/ሞግዚት ስብሰባ —6:30 to 8:30 p.m. Rocking Horse Road Center

ኤፕረል 25 ዓመታዊ የጤና ኤግዚቢሽን በዓል

ኤፕረል 28 ለተማሪዎችና ለመምህራን ትምህርት የለም

ሜይ 7 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ —6:30 Rocking Horse Road Center

ሜይ 21 የፖሊሲ ካውንስል ወርሃዊ ስብሰባ —7 PM Rocking Horse Road Center

ሜይ 25 ሜሞሪያል ዴይ/Memorial Day— ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ናቸው

ጁን 4 የፖሊሲ ካውንስል ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ —6:30 PM Rocking Horse Road Center

ጁን 15ለተማሪዎች ት/ቤት የመጨረሻ ቀን፤ ሁሉም ተማሪዎች አስቀድመው የሚለቀቁበት ቀን

ቅድመ ሙዓለህፃናት/ሄድስታርት የበጎፈቃድ እውቅና/አድናቆት ዝግጅት

ጁን 16 የመምህራን የሙያ ቀን

በአደጋዎች/አስቸኳይ ሁኔታዎች ምክንያት የትምህርት ዓመቱ የሚደናቀፍ ከሆነ እና ትምህርት ቤቶች ሦስት ወይም ይበልጥ ቀኖች ከተዘጉ፣ በ 2020 የትምህርት ቀኖችን ማካካሻ ይሆናሉ ትብለው የተያዙት ቀኖች የሚያካትቱት ጁን 16 - 22፣ ኤፕሪል 6፣ ኤፕሪል 7 እና ጃኑወሪ 27 ናቸው።

Page 19: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት
Page 20: ቅድመ-ሙአለህፃናት/ሄድ ስታርት/Head Start...ለመግባት ዝግጅት ላይ በመሆኑ/ኗ እርስዎና ቤተሰብዎ ወደ ሌላ የህይወት

ሮክቪል፣ ሜሪላንድ ROCKVILLE, MARYLAND

ህትመት፦ Department of Materials Management for the Division of Early Childhood Programs and Services/Prekindergarten/Head Start Unit

ትርጉም፡- በቋንቋ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል • የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት Language Assistance Services Unit • Office of Communications

0059.20ct • Editorial, Graphics & Publishing Services • 8/19 • 2,00Copyright © 2019 Montgomery County Public Schools, Rockville, Maryland

የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) የፀረ-መድሎ መግለጫ MCPS Nondiscrimination Statement

የሞንጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ዘርን፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ የዘር ሃረግ፣ የብሔር ማንነት፣ ኃይማኖት፣ የስደተኝነት ሁኔታ፣

ጾታ፣ ስነ-ጾታ፣ የጾታ ማንነት (gender identity)፣ የጾታ አገላለጽ (gender expression)፣ የጾታዊ ግንኙነት ዝንባሌ/ምርጫ (sexual

orientation)፣ የቤተሰብ/የወላጆች የኑሮ ደረጃ/አቋም/ሁኔታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ እድሜ፣ ድህነት፣ እና የማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ አቋም፣

ቋንቋ፣ የአካል ወይም የአእምሮ ጉዳተኝነት፣ በህገመንግስት ጥበቃ የተደረገላቸው ሁኔታዎችን ባህሪያትን ወይም ተዛማጅነት ያላቸውን

(affiliations) መሠረት ያደረገ ሕገ-ወጥ አድሎ/መድሎ ይከለክላል። መድሎ ወይም አድሎአዊነት፤ በሕብረተሰባችን ለረዥም ጊዜ

እኩልነትን፣ ፍትሕ፣ አብሮነት፣ሁሉን አቀፍነትን፣ ለመፍጠርና ለማሳደግ/ለመንከባከብ፣ ሲደረግ የቆየ ትጋትን ይሸረሽራል/ያበላሻል።

አድልዎ የሚከተሉትን የተወሰኑ ምሳሌዎችን ያካትታል፦ጥላቻ፣ ሁከት፣ ደንታቢስነት፣ ወከባ፣ ማስፈራራት፣ ማሸማቀቅ፣ ንቀት፣ ወይም

ማጥቃት። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ደምብ/Policy ACA ስለ ጸረ-መድሎ፣ ፍትህ፣ የዳበረ

ባህል ይመርምሩ። ይህ መመርያ እያንዳንዱ ተማሪ አስፈላጊ/ተፈላጊ መሆኑ(ኗ)ን፣ በተለይም የትምህርት ውጤቶች የሚረጋገጡት በምንም

ዓይነት ግለሰብ ባለበት(ባለባት) ምክንያት ወይም ይሆናል ተብሎ የሚገመት ግላዊ ጠባዮች የሚተነበዩ አለመሆናቸውን የቦርዱን እምነት

ያረጋግጣል። ፖሊሲው በቅድሚያ መወሰድ ስላለባቸው የፍትህ እርምጃዎች የተዛባ አመለካከትን፣ ማረጋገጫ የሌላቸው የማዳላት/ልዩነት

አፈጻጸሞችን የሚያስከትሉትን አሉታዊነት፣ የትምህርት እና የሥራ መቀጠር እኩልነትን የሚያሰናክሉ መዋቅራዊ እና ድርጅታዊ አሠራር

ደንቃራዎችን በተለይ ያስገነዝባል።

በMCPS ሰራተኛ* ላይ ስለደረሰ መድሎዎ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ለማቅረብ

በMCPS ተማሪዎች ላይ የአድልዎ ጥያቄዎች ወይም ቅሬታዎች ካላችሁ*

የሰራተኛ ተሳትፎ እና የሥራ ግንኙነት ጽ/ቤትየአፈጻጸም እና የክትትል/የምርመራ መምሪያ Department of Compliance and Investigations 850 Hungerford Drive, Room 55Rockville, MD [email protected]

Office of the Chief of StaffStudent Welfare and Compliance850 Hungerford Drive, Room 162Rockville, MD 20850240-740-3215COS–[email protected]

* ክትትል፣ ቅሬታ/ስሞታ፣ ወይም ስንክልና ላለባቸው ተማሪዎች አመቺ ስፍራ ለመጠየቅ፤ ወደ ልዩ ትምህርት ተቆጣጣሪ ጽ/ቤት፣ የቅሬታ ሰሚና መፍትሔ ሰጪ ን/ክፍል በ ስልክ ቁጥር 240-740-3230 ሊቀርብ/ሊመራ ይችላል። ለሰራተኞች መገልገያዎች ወይም ማሻሻያዎች በሚመለከት የሚቀርቡ ጥያቄዎች ወደ Office of Employee Engagement and Labor Relations, Department of Compliance and Investigations/ የሰራተኛ ተሳትፎ እና የስራ ግንኙነት የአፈጻጸም እና የክትትል (የምርመራዎች) መምርያ፣ ስልክ፦ 240-740-2888 ሊመሩ ይችላሉ። በተጨማሪ፣ አድሎአዊነት ቅሬታዎች ለሌሎች ኤጀንሲዎችም ፋይል ሊደረጉ ይቻላል። እነርሱም፦ the U.S. Equal Employment Opportunity Commission, Baltimore Field Office, City Crescent Bldg, 10 S. Howard Street, Third Floor, Baltimore, MD 21201, 1-800-669-4000, 1-800-669-6820 (TTY); ወይም U.S. Department of Education, Office for Civil Rights, Lyndon Baines Johnson Dept of Education Bldg., 400 Maryland Avenue, SW, Washington, DC 20202-1100, 1-800-421-3481, 1-800-877-8339 (TDD), [email protected], ወይም www2.ed.gov/about/offices/list/ocr/complaintintro.html.

ይህ ሠነድ ካስፈለገ በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ከእንግሊዝኛ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አማራጭ ቅርፀት ሊገኝ ይችላል። በአካል

ጉዳተኝነት ስለሚኖሩ አሜሪካውያን ደንብ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት/MCPS Department

of Communications በስልክ ቁጥር፦ 240-740-2837፣ 1-800-735-2258 (ሜሪላንድ ማዞሪያ)፣ ወይም [email protected].

የምልክት ቋንቋ ትርጉም የሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም የንግግር ትርጉም/ምልክት አገልግሎት ለማግኘት የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/

ቤቶች የትርጉም አገልግሎት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-1800, 301-637-2958 (VP) ወይም MCPSInterpretingServices@

mcpsmd.org መገናኘት ይችላሉ። የሞንጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS)፤ ወጣት ስካውቶችን (ወንድ/ሴት) እና ሌሎችም

የሚመለከታቸውን ወጣት ቡድኖችን በእኩል ያስተናግዳቸዋል።

ጁላይ 2019