የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር...

23
ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13 2004 ዋጋ 7፡00 ብር ‹‹በማህከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት ጠ/ሚኒስትር መለስ የቅንጅት እስረኞች .. ህገ-መንግስቱን ለመጠበቅ በገቡት ቃል መሠረት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አቀረቡ። በህወኃት ማህከላዊ ኮሚቴ አክራሪ ስብስቦች በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ ቀረበ። እርምጃው ‹‹ከአሜሪካ ሚዲያዎችና ከአሜሪካ ኮንግረስ የሚሰጡ አሉታዊ አስተያየቶች ተፅዕኖ ውጤት ነው›› የሚል ትችት ሊመጣ እንደሚችልም ተጠቆመ። ከረጅም ፍትጊያ በኋላ ጠ/ሚኒስትር መለስ የማዕከላዊውን ኮሚቴ ይሁንታ አገኙ…›› በ ገፅ 5 በ ገፅ 18 በ ገፅ 16 ሕዝቡን እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ ነፃ ሊያወጣው አይችልም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ? ስልጣን እማልፈልግ ለእስር እማልቸኩል ከጠሀዩ መንግስት እሰራለሁ እኩልአቋራጩን የመረጡ ዊክሊክስ የሚባለው ቱሪናፋ ኬብል ጠላፊ በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና ሌሎች ፖለቲከኞች ያወሩትን ማጋለጡ እኛም ያወራነውን አንድ ቀን ገሀድ ማውጣቱ አይቀርም ሲሉ አንዳንድ ተንበርካኪ ካድሬዎች ቦክተው አስቦክተውናል። ዊክሊክስ ሆይ ደግሞ አፍሪካ መጣህ? ጎሽ እስቲ ለ‹‹ሽብር›› ሲያሴሩ ስለተያዙም ሰዎች መረጃውን አንድ ቀን እንደምታደርሰን እንጠብቃለን። “ሂትለሮችን” ዊኪሊክስ በዚህ ዙሪያ ይፋ ያደረገውን መረጃ ይከታተሉ እውነት ግን “ይህ አገር የማነው?” አቶ ሽመልስ ተረጋግጧል ያሉት ‹‹ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት››፤ በሕጉ አተረጓጎም ላይ ብዥታ እንዳለ ጥያቄ ማቅረብንም የማያካትት ከሆነ ምኑ ላይ ነው የተረጋገጠው ታዲያ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ለመሆኑ መደንበርም፣ መፍራትም፣ መተቸትም … እንዴት ሽብር ይሆናል? በ ገፅ 3 በ ገፅ 12 በ ገፅ 14 ኢትዮጵያውያን ማን ያቁማቸው? ሽብር እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩትን ጋዜጠኞች ሁኔታ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) ተወካዮች በአካል ተገኝተው እንደጎበኙ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ህብረት (ኢብጋህ) አስታወቀ። ዋና ጽህፈት ቤቱ በቤልጂየም ብራሰልስ ያደረገው ይኸው ፌዴሬሽን ልኡካኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልክበት ዋንኛ ዓላማ ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና አውሮፓውያን ጋዜጠኞች የሚደረግላቸውን አያያዝና የታሰሩበትን ትክክለኛ ምክንያት ማጣራት ሲሆን፣ ተወካዮቹ እስረኞቹንም ጭምር አግኝተው ሊያነጋግሩ እንደሚችሉ መንግስት ፈቃደኝነቱን አሳይቷል። በጉብኝቱ ወቅት በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ያለውን አጠቃላይ ድባብ ለመገንዘብ እንዲረዳ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማትንና ጋዜጠኞችን፣ የእስረኞችን የታሰሩ ጋዜጠኞች በዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች ፌደሬሽን ልኡካን እንዲጎበኙ መንግስት ፈቀደ የሲፒጄ ልኡካን አልተፈቀደላቸውም

Upload: others

Post on 22-Apr-2020

14 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ በውስጥ ገፅ

4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13 2004 ዋጋ 7፡00 ብር

‹‹በማህከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት ጠ/ሚኒስትር መለስ የቅንጅት እስረኞች .. ህገ-መንግስቱን ለመጠበቅ በገቡት ቃል መሠረት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አቀረቡ። በህወኃት ማህከላዊ ኮሚቴ አክራሪ ስብስቦች በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ ቀረበ።

እርምጃው ‹‹ከአሜሪካ ሚዲያዎችና ከአሜሪካ ኮንግረስ የሚሰጡ አሉታዊ አስተያየቶች ተፅዕኖ ውጤት ነው›› የሚል ትችት ሊመጣ እንደሚችልም ተጠቆመ። ከረጅም ፍትጊያ በኋላ ጠ/ሚኒስትር መለስ የማዕከላዊውን ኮሚቴ ይሁንታ አገኙ…››

በ ገፅ 5

በ ገፅ 18

በ ገፅ 16

“ሕዝቡን እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ ነፃ ሊያወጣው አይችልም”

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?

“ስልጣን እማልፈልግ ለእስር እማልቸኩልከጠሀዩ መንግስት እሰራለሁ እኩል”

አቋራጩን የመረጡ ዊክሊክስ የሚባለው ቱሪናፋ ኬብል ጠላፊ በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና ሌሎች

ፖለቲከኞች ያወሩትን ማጋለጡ እኛም ያወራነውን አንድ ቀን ገሀድ ማውጣቱ አይቀርም

ሲሉ አንዳንድ ተንበርካኪ ካድሬዎች ቦክተው አስቦክተውናል። ዊክሊክስ ሆይ ደግሞ

አፍሪካ መጣህ? ጎሽ እስቲ ለ‹‹ሽብር›› ሲያሴሩ ስለተያዙም ሰዎች መረጃውን አንድ ቀን

እንደምታደርሰን እንጠብቃለን።

“ሂትለሮችን”

ዊኪሊክስ በዚህ ዙሪያ ይፋ ያደረገውን መረጃ ይከታተሉ

እውነት ግን “ይህ አገር የማነው?”

አቶ ሽመልስ ተረጋግጧል ያሉት ‹‹ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት››፤ በሕጉ አተረጓጎም ላይ ብዥታ እንዳለ ጥያቄ ማቅረብንም የማያካትት ከሆነ ምኑ ላይ ነው የተረጋገጠው ታዲያ? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ለመሆኑ መደንበርም፣ መፍራትም፣ መተቸትም … እንዴት ሽብር ይሆናል?

በ ገፅ 3 በ ገፅ 12 በ ገፅ 14

ኢትዮጵያውያን

ማን ያቁማቸው?

ከሽብር እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩትን ጋዜጠኞች ሁኔታ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (IFJ) ተወካዮች በአካል ተገኝተው እንደጎበኙ የኢትዮጵያ

መንግስት መፍቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ህብረት (ኢብጋህ) አስታወቀ።

ዋና ጽህፈት ቤቱ በቤልጂየም ብራሰልስ ያደረገው ይኸው ፌዴሬሽን ልኡካኑን ወደ ኢትዮጵያ የሚልክበት ዋንኛ

ዓላማ ከሽብርተኝነት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና አውሮፓውያን ጋዜጠኞች የሚደረግላቸውን አያያዝና የታሰሩበትን ትክክለኛ ምክንያት ማጣራት ሲሆን፣ ተወካዮቹ እስረኞቹንም ጭምር አግኝተው ሊያነጋግሩ እንደሚችሉ መንግስት ፈቃደኝነቱን አሳይቷል።

በጉብኝቱ ወቅት በሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ያለውን አጠቃላይ ድባብ ለመገንዘብ እንዲረዳ አንዳንድ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማትንና ጋዜጠኞችን፣ የእስረኞችን

የታሰሩ ጋዜጠኞች በዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች ፌደሬሽን ልኡካን እንዲጎበኙ መንግስት ፈቀደየሲፒጄ ልኡካን አልተፈቀደላቸውም•

Page 2: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

የኢትዮጵያ ሕዝብ እየተፈፀመብን

ያለውን ደባ ይረዳልን‹‹ … የዓለም ሰላም ጠበቃዎች፣ የጋዜጠኞች መብቶች አስከባሪዎች፣ የዴሞክራሲ ሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ነን ለሚሉትና በውጭ ሀገር የተቃዋሚዎች

አፈ ቀላጤዎች በመሆን በማገልገል ላይ ለሚገኙ አንዳንድ ኃይሎች ሳይንበረከክ፣ መንግሥት የአመፅ ጥሪ የሚያቀርቡትን ኃይሎች ሀይ ሊላቸው ይገባል … ››

T’@Í=”Ó ›?Ç=}` Ç©ƒ ŸuÅ

ª“ ›²ÒÏõì<U TV

(›É^h ¾ካ ¡/Ÿ kuK? 03/04 ¾u?.l 1540)

U/ª“ ›²ÒЋ ›u?M ¯KT¾G<¨<wgƒ �Â

›²ÒÏ አናኒያ ሶሪ

Ÿõ}— ]þ`}a‹ ›?MÁe Ñw\

c<^õ›?M Ó`T�ናፍቆት ዮሴፍ

ኮፒ ኤዲተርƒ°Óeƒ ¨”ÉS<

¯UÅ™‹ታዲዎስ ጌታሁን ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን

SpÅe õeNደሳለኝ ስዩም

iÁß“ Te�¨mÁ }hK cÃñ

Ó^ò¡e ›?Ç=}` ’w¿ Seõ”

(0911 18 09 33)E-Mail:[email protected]

የማስታወቂያ ክፍሉ ስልክ0911629281

¾´Óσ ¡õK< eM¡eM¡:- ®911 62 92 78 0923 02 88 91 ®911 62 92 82 0911 65 30 13

þ.X.l [email protected]://www.awramba.com

›d�T>¨<ብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ

ኃላ/የተ/የግል/ማህበር

ር ዕ ሰ አ ንቀፅ

ማን ምን አ ለ

2

የካቲት 2000 ዓ.ም ተመሠረተ

አውራምባ ታይምስ፡- በብሉ ኤርዝ ጀነራል ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግል/ማህበር ስር የሚታተም፤ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር፤ በንግድ ሚኒስቴር በቁጥር 020/2/6572/2001 የተመዘገበ ሳምንታዊ ጋዜጣ ነው፡፡

አድራሻ አራዳ ክፍለከተማቀበሌ 13/14

የቤት ቁጥር 467ከአራት ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወደው መንገድ

ከራስ አምባ ሆቴል አለፍ ብሎ በሚገኘው

አቤኔዘር እንግዳ ማረፊያ ግቢ ውስጥ

አታሚ፡-

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ክ/ከተማ፡- አራዳቀበሌ፡- 17የቤት ቁጥር፡- 984

‹‹እስክንድር በንጽህናው፣ በኢትዮጵያዊነቱ ለህዝብና ለአገር ሲሟገት ለህዝብ ነፃነት እየጮኸ መታሰሩ ያኮራኛል። እስክንድር በተደጋጋሚ ‘ለአገርና ለህዝብ መታሰር፣ ለህዝብ እየታገሉ መሞት ጻድቅነት ነው’ ይላል። በዚህ እኔም አምንበታለሁ። በጣም የሚያሳዝነው በልጃችን ላይ የተፈጠረው ተፅእኖ ነው››

ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል /የአቶ እስክንድር ነጋ ባለቤት/እስክንድር በመታሰሩ በኑሯችሁ ወይም በኑሯችሁ ላይ ጫና ይኖራል? ተብሎ ከፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

ለቀረበላቸው ጥያቄ ከሰጡት ምላሽ የወሰደ።

‹‹… እኛ አቅምም፣ ጉልበትም የለንም። በህጋዊ መንገድ ትግላችንን ቀጥለናል። ኢህአዴግ ግን ህጋዊው መንገድ የጠፋበት ይመስላል።››

ተባባሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ‹‹ራሳችሁን በምን መልኩ ልታዩ አስባችኋል?›› በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ

የሰጡት ምላሽ።

ካላይ የሰፈረው ጥቅስ የተወሰደው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ.ም ለንባብ ከበቃው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ገፅ 3 ነው። ምንጣፍ የሚያክለው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከርዕስ አንቀፁ ጎን ‹‹የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሲጋለጡ›› በሚል ርዕሥ ባሰፈረው ሰፊና ረዥም ሀተታ ይህቺኑ አውራምባ ታይምስን ጨምሮ፣ ፍትህ እና የአንድነት ፓርቲ ልሳን የሆነው ‹‹ፍኖተ ነፃነት›› ጋዜጣ ላይ በተለየ መልኩ ጣቱን ቀስሯል።

አዲስ ዘመን፣ “በተለያዩ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ዜጎች ነፃ አስተያየታቸውን የሚሰጡበት” አምድ ነው በሚል ሰበብ ያሰፈረው ረዥም ሀተታ በጳጉሜ ወር 2003 ዓ.ም፣ ‹‹በአጠቃላይ ማለት ይቻላል ብዙዎቹ የግል ፕሬሶች ከርዕስ አንቀፃቸው ጀምሮ በሁሉም አዋጆቻቸው ያሰፈሩት የ2004 ዓ.ም የአመፅና የመንግስት ግልበጣ ዘመን እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል›› ሲል ይከሳል።

አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደመጫኛ በረዘመውና ቅጣምባሩ በጠፋበት ረዥም ሀተታው፣ መንግሥት አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ‹‹ሀይ እንዲል›› ያሳሰበው፣ ጋዜጣችን በባለፈው ሳምንት

ዕትሟ ‹‹አስደንጋጩ አዋጅና አፈፃፀሙ›› በሚል ርዕስ ለንባብ ካበቃችው ዘገባ አስረጅ ይሆነኛል በሚል ነቅሶ በማውጣት ነው።

ዘመን ‹‹የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች ሲጋለጡ›› በሚል ርዕሥ አንድነት ፓርቲን፣ የፓርቲውን ልሳን ‹‹ፍኖተ ነፃነት›› ጋዜጣ፣ እንዲሁም በማያፈናፍን ሜዳ በነፃ መንፈስ ነፃ መረጃን ለህዝብ በማቅረብ ላይ የሚገኙትን ‹‹ፍትህ›› እና ‹‹አውራምባ ታይምስ››ን ለመክሰስ ይረዳው ዘንድ መነሻ ያደገው፣ መንግስት በሽብር ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን የ29 ሰዎች ጉዳይ መነሻ በማድረግ ነው።

እንደ እውነቱ ከሆነ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አጓጉል ክስ ለአውራምባ ታይምስ አዲስ አይደለም። አዲስ ዘመን፣ አውራምባ ታይምስ ጋዜጣን ከዚህ ቀደም እስኪታክተው ድረስ በማይጨበጥ ክስ ሲያዥጎደግድበት እንደነበረ የአደባባይ ምስጢር ነው።

የ ጋ ዜ ጣ ች ን ን ባልደረቦች በሀገር ክህደት፣ በሻዕቢያ ተላላኪነት ወዘተ በውጭ ኃይሎች ወኪልነት ሲጠረጥር፣ ሲያስጠረጥር ነበር። አልተሳካለትም እንጂ።

የአዲስ ዘመን ክስ ያሻውን ያህል ቢከመር፣

እኛ ግን አልደነገጥንም፤ አንደነግጥምም። ከዚያ ይልቅ መንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ አይረቤ ውንጀላውን እንዲያቆም ወደ ፍ/ቤት ነው የሄድነው። ፍ/ቤቱ አቤቱታችንን አይቶ ተገቢውን ውሳኔ ባይወስንም፣ ወደ ፍርድ ቤት መሄዳችን በራሱ ለሀገሪቷ ሕግ ምን ያህል ተገዢዎች እንደሆንን የሚያመላክት ነው። መረጃ የመቀበልና የመስጠት መብታችንን የምናከብረው እና የምናስከብረው በሕግ እና በሕግ ጥላ ሥር ብቻ ስለመሆኑ ከበቂ በላይ ማረጋገጫችንም ነው ብለን እናምናለን።

አሁንም ሆነ ወደፊት ተግባራችንን የምንወጣው በሕግ ጥላ ሥር ብቻ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን። መንግሥት ያወጣውን የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግንም በተመለከተ ጠንቅቀን እናውቃለን። ፓርላማ በአሸባሪነት የፈረጃቸውን ድርጅቶች ጉዳይ መዘገብ አቁመናል። ምክንያቱም ለሕግ ተገዢዎች ነንና። ይሁን እንጂ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በጥሬው መቃኘትና ስለሂደቱም የመዘገብና የመናገር መብት አለን።

አዎ፤ በሽብርተኝነት ተጠረጠሩ ማለት ሽብርተኝነታቸው ተረጋገጠ ማለት አይደለም። የተጠረጠሩት ሰዎች አስኪፈረድባቸው

ድረስ ቢያንስ በመርህ ደረጃ ነፃ ሰዎች ናቸው ብለን እናምናለን። የሀገሪቱም ሕግ የሚለው ይህንኑ ነው። ታዲያ አዲስ ዘመን፣ በሽብርተኝነት ስለተጠረጠሩ ሳይፈረድባቸው ስለተጠርጣሪዎቹ መዘገብን ወንጀል አድርጎ እኛ ላይ ጣቱን የሚቀስረው በምን ሎጂክ ነው?

ቀድሞ ነገር የአዲስ ዘመን የጠርጣሪነት (Skepticism) ፍልስፍና ከየት የመጣ ነው? እኛ እስከምናውቀውና ከታሪክ እንደተረዳነው የጠርጣሪነት ፍልስፍና እጅና እግር የሌለው መሆኑን ነው። ጠርጣሪነት ለተጨበጠ፣ ለረቀቀ ዕውቀት ቦታ የማይሰጥ ያለፈበት ፍልስፍና ነው። ሌላው ቀርቶ የስሜት ህዋሳትን መረጃ እንኳ መረዳትና መገንዘብ አይፈልግም። እኛ ደግሞ እጅና እግር ለሌለው የጠርጣሪነት ፍልስፍና የምንበረግግ አይደለንም።

ይህንን የምንለውና በእምነት የምንናገረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በአዲስ ዘመን በኩል እየተሴረብን ያለውን ደባ እንዲገነዘብልን ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

‹‹…መቶ ብር ከኪሴ አወጣሁና አንድ ጊዜ በነፃ አስተምሬሃለሁ፤ አሁን ግን መክፈል አለብን፤ ለሌኒንን ፅሁፍ ካላመጣሁልህ መቶ ብር ታገኛለህ፤ ካመጣሁ ግን መቶ በር ትከፍላለህ ብለው አሻፈረኝ ብሎ በስህተቱ ፀና››

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ፕ/ር ገብሩ ታረቀኝ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ከዚህ ቀደም ለፃፉት ፅሁፍ ምላሽ ‹‹የአስተሳሰብን ሕግ ካልጠበቅን ለመግባባት ያቅተናል›› በሚል ርዕስ በዚሁ

ጋዜጣ ላይ ከፃፉት ውስጥ የተወሰደ።

Page 3: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004 3

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የፖለቲካ አየር ላይ ያጠላው የሽብር ዜና እና ፍርሀት ብቻ ይመስላል። ለዚህም ነው መሰል ባለፈው

ቅዳሜ እኩለ ሌሊት እንቅልፍ ትቼ ይህችን ፅሁፍ ለመሞነጫጨር የተነሳሁት፡፡ ያለወትሮዬ በውድቅት ሌሊት ተነሳሁና ቴሌቪዥኔን ከፈትኩ። በአጋጣሚ ሆኖ አቶ ሽመልስ ከማል ሰሞኑን ስለታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ጋዜጠኞች ማብራሪያ እየሰጡ ነው። ከጎናቸው ም/ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል እጃቸውን አጣምረው ይታያሉ። ቀደም ሲል በጋዜጣችን የተዘገበ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን፤ ስለ መግለጫው ይዘት በቂ መረጃ ቢኖረኝም፤ አይኖቼን በአቶ ሽመልስ ላይ ተክዬ ‹ማስጠንቀቂያቸውን› በጥሞና ከመከታተል አልቦዘንኩም፡፡ አቶ ሽመልስ መነፅራቸው ከፍና ዝቅ እያደረጉ ማብራሪያቸውን ቀጥለዋል። ‹‹…ከፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመሆን በአገራችን የሽብር መረብ በመዘርጋት የሰላማዊ ዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ ለመጣል ሲያሴሩ…›› በዚህች አገር ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አልገባህ አለኝና ተነስቼ መስኮቴን ከፈትኩት፡፡ ምንም አዲስ ነገር የለም። እንኳን ጦርነትና ሽብር ምንም የሚሰማ ነገር የለም፡፡ ከተማዋ ፀጥ ረጭ ብላለች።

በእርግጥ ከርቀት የኡራኤል ቤተክርስቲያን ካህናት የሚያሰሙት የ‹‹ሠዓታት›› ያሬዳዊ ዜማ በጆሮዬ ይንቆረቆራል፡፡ የሚያሸብር መርዶ እያሰማኝ ያለው ቴሌቭዥኔ ብቻ ነው፡፡

ተመልሼ ተቀመጥኩ፡፡ አቶ ሽመልስ ማብራሪያቸውን አላቆሙም። በፖሊስ ሊብራሩ የሚገባቸው በርካታ ቴክኒካል የመረጃ ነገሮችን እየዘረዘሩ ነው። ቀጠሉና ‹‹አንድ ሰው በፖለቲካ አቋሙና ሀሳቡን በነፃነት በመግለጹ የተነሳ የሚታሰርበት ሁኔታ የለም›› አሉ፡፡ አዎ! እዚህ ላይ በመርህ ደረጃ እንስማማለን። አቶ ሽመልስ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡- ‹‹…በዚህ አዋጅ የሚደነብሩት … ሽብርተኛ ለመሆን ፍላጎት ያላቸው ብቻ ናቸው›› በማለት በሕጉ አተረጓጎም ላይ ብዥታ እንዳለ አድርጎ ጥያቄ ማቅረብም እንደማይቻል ገለጹ፡፡ ምን እያሉን እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ንግግራቸው ከሕግ ባለሙያና በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ ከነበረ ሰው የሚጠበቅ ሆኖ ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ምክንያቱም ከላይ ተረጋግጧል ያሉትን ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በሕጉ አተረጓጎም ላይ ብዥታ እንዳለ ጥያቄ ማቅረብንም የማያካትት ከሆነ ምኑ ላይ ነው የተረጋገጠው ታዲያ? የሚል ጥያቄ ስለሚያስነሳ፡፡ ለመሆኑ መደንበርም፣ መፍራትም፣ መተቸትም … እንዴት ሽብር

ይሆናል? ለወትሮው ‹‹ልማታዊ›› የነበረው ኢቲቪ መርዶ ነጋሪ ስለሆነብኝ ዘጋሁትና ተንቀሳቀሽ ኮምፒውተሬን ከፍቼ አንዳንድ ድረ-ገጾችን መጎብኘት ጀመርኩ። አንዱ በፌስ-ቡክ የአጭር መልእክት መለዋወጫ (chat) በኩል ‹‹ዳዊት ለምን አገሩን ለቃችሁላቸው አትወጡም?›› አለኝ። ምላሽ አልሰጠሁትም። ቀጠለና ‹‹ሁሉም ሰው እንዴት ሽብርተኛ ይባላል? በዚህ አይነት ሽብርተኛ የማይባለው ምን አይነት ሰው መሆን አለበት ማለት ነው?›› ሲል ጠየቀ።

እውነት ለመናገር ይህ ከባድ ጥያቄ ነው። መመለስ ያለበትም በሁለት አይነት መንገድ ነው፡፡ በጸረ-ሽብር አዋጁና በአቶ ሽመልስ ትርጓሜ፡፡ በአዋጁ መሠረት ከሆነ ሽብርተኛ ላለመባል የፖለቲካ፣ የኃይማኖትና የአይዲዮሎጂ አቋሙን ለማራመድ በመንግስት ላይ ተፅዕኖ አለመፍጠር… ወዘተ ነው። ነገር ግን ቀደም ብዬ በሰማሁት የአቶ ሽመልስ ማብራሪያ መሠረት ከሆነ ሽብርተኛ ላለመባል አለመደንበር፣ አለመፍራትና ‹‹አዋጁ ችግር አለበት›› ብሎ አለመተቸት ነው። ሆኖም ለጥያቄ አቅራቢው ወዳጄ እንዲህ ብሎ ምላሽ መስጠትም በሽብርተኛነት ላለማስፈረጁ በእርግጠኝነት መናገር ስለማይቻል ምላሽ መስጠቱን ትቼ በቀጥታ ወደ ድረ-ገጾች አመራሁ፡፡ ከሁሉም ለየት ባለ መልኩ በአዲስ ነገር ድረ-ገፅ ላይ ያየሁት ርዕስ ግን ይበልጥ ትኩረቴን የሚስብ ሆኖ አገኘሁት። (መቼም እንቅልፍ የሚታሰብ አይደለም)

በድረ-ገጹ ላይ ‹‹የተለመዱትን ተጠርጣሪዎች እሰሩ›› የሚል ርዕስ የተሰጠው የመስፍን ነጋሽ መጣጥፍ ጎላ ብሎ ይታየኛል። በመሰል ስጋት ለስደት ተዳርጎ ዛሬ በሰሜን አውሮፓዊቷ ስዊድን የሚገኘው መስፍን፣ በዚህ ሰዓት ምን ሊል እንደሚችል እያሰብኩ ከፈትኩት። መስፍን በተመጠኑ ቃላት ሀሳቡን ግሩም በሆነ ሁኔታ የመግለፅ ተሰጥኦ ተችሮታል። ከባልደረቦቹ ጋር ጋዜጣውን ዘግቶ ሊሰደድ ጥቂት ሳምንታት ሲቀረው ‹ይህ አገር የማነው?› በሚል ርዕስ ልብ የሚነካ መጣጥፍ አስፍሮ ነበር፡፡ እኔም ከሁለት አመት በኋላ በርዕስነት እንድጠቀምበት ያስገደደኝ ያኔ በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እንደጻፈው የሚያስረግጡ አስደንጋጭ ስሜቶች እየተፈጠሩ መስለው ስለታዩኝ ነው፡፡

መስፍን ‹‹አገሪቱ በሽብርተኞች የተሞላች እስክትመስል ድረስ የሚያዙ “ሽብርተኞች” ዜናና ጉዳይ መነጋገሪያ እየሆነ ነው። ለመሆኑ መንግሥት ይህን ያህል “ሽብርተኞችን” መያዝ ከቻለ፣ ያልተያዙት “ሽብርተኞች” ስንት ይሆኑ?›› ይለናል በአዲሱ መጣጥፉ፡፡ አያይዞም ‹‹… ደርግ ተቃዋሚዎቹን ያጠፋልኛል ያለው ፖሊሲ “ከሕወሃትና ከሻእቢያ ጋራ በማንኛውም መንገድ

ይገናኛሉ፣ የአማጽያኑን ሐሳብ የመደገፍ አዝማሚያ ሊኖራቸው ይችላል” ያላቸውን ግለሰቦችና ቡድኖች ማሰርና መግደል ነበር። በመጨረሻ ውጤቱ ይህ ፖሊሲ እነሕወሓትን የሚጠቅም፣ ደርግን ደግሞ ከሕዝብ ፈጽሞ የሚነጥል ነበር፤ አቶ መለስም በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎችን ከኦነግና ግንቦት 7 ጋር በማያያዝ እንደ ደርግ አሳን ለማጥፋት ባህሩን የማድረቅ ፖሊሲ እየተከተሉ ነው ይላል። አንዷለም ከመታሰሩ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ተጨዋውተን ነበር፡፡ አንዷለም በቁጭት የተናገራት ዓረፍተነገር በመስፍን መጣጥፍ ቃል በቃል ተደግማ ሳያት ግን በእጅጉ ተደንቄአለሁ፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው ‹‹ቀደም ሲል ደርግ “የተለመዱ ተጠርጣሪዎች” ነበሩት። በአገሪቱ ለሚያጋጥሙ ማናቸውም ችግሮች ተጠርጣሪዎቹ እነዚሁ አካሎች ነበሩ። በሬዲዮ፣ በኢቲቪ፣ በአዲስ ዘመን፣ በፓርቲ ልሳን፣ በቀበሌ ስብሰባ…በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚወገዙት እነርሱው ነበሩ። ዛሬም የማውገዣ ቦታዎቹና ተቋማቱ እንኳን አልተቀየሩም። የውግዘቱ ይዘትና ቋንቋም እንዲሁ። የይዘት ሳይሆን የቃላት ለውጡን በምሳሌ እናስታውስ። ኢምፔሪያሊዝም ወደ ኒዎ ሌበራሊዝም፣ ሕወሃት/ሻእቢያ ወደ ኦነግ/አብነግ/ግንቦት 7፣ ተገንጣይ/አስገንጣይ ወደ ጠባብ/ትምክህተኛ፣ አልበሽር ወደ ኢሳያስ..ተቀይረዋል።›› አዎ! መስፍን እንደሚለው አምባገነኖች ከታሪክ ለመማር ስለማይችሉ ታሪክን እየደገሙ ሳይመስላቸው ታሪክን ይኖራሉ።

ለስድብ የተጉ ጥንዶች ዛሚ የተሰኘው ኤፍ ኤም ሬዲዮ በየሳምንቱ ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› የተሰኘ ፕሮግራም አለው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ ማን ሊታሰር እንደሚገባው፣ ማን መሰደድ እንዳለበት የሚቦካበት፤ እንዲሁም መንግስትን ሊያስቆጣ የሚችል ሀሳብ የሚሰነዝሩ ግለሰቦች ጨዋ ባልሆኑ ቃላት የሚዘለፉበት መድረክ ነው፡፡ አንዱአለም እና እስክንድር ከመታሰራቸው ከጥቂት ሰዓታት በፊት የዚሁ ክብ ጠረጴዛ ታዳሚያን ሰዎቹ መታሰር እንዳለባቸው ከስምምነት ላይ ደርሰው ነበር የተለያዩት፡፡ ባለፈው ረቡዕ ደግሞ እነዚሁ ታዳሚያን በአውራምባ ታይምስ መዘጋትና በአዘጋጆቹ መሰደድ ዙሪያ ትንቢታዊ ስምምነት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡

ከአምስት አመታት በፊት ‹‹ኢፍቲን›› የምትባል አፍቃሬ መንግስት ጋዜጣ ሲያሳትሙ የነበሩትና ብዙም ድምፃቸው ሳይሰማ ቆይቶ ሰሞኑን በዚሁ ፕሮግራም ላይ የቀረቡት አቶ ዘሪሁን ተሸመ፤ ከትዳር/ፖለቲካ አጋራቸው ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ጋር በመሆን በአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ መዘጋትና በእኛ

በአዘጋጆቿ መሰደድ ዙሪያ የ‹ውሳኔ ሀሳብ› የሚመስል ትንቢታዊ ቃል አስተላልፈዋል። ጋዜጣዋ እንድትዘጋ የሚያደርግም ሆነ እኛን የሚያሳስር ምንም አይነት ወንጀል አለ ብዬ አላምንም። ፈጣሪና ኢህአዴግ ይሁን ካሉ ግን መቼስ ምን ይደረጋል።

አገር ክህደትን እና ስለላን በተመለከተም በዚሁ ፕሮግራም ሲቦካ ነበር፡፡ በመሰረቱ አስተዳደጋችንና ኢትዮጵያዊ ጨዋነታችን አይፈቅድም ብቻ ሳይሆን፣ ለአሜሪካ ቅርበት ያለው ማን እንደሆነ በሁላችንም ፓስፖርት ላይ ያለው ዜግነት ገለጥ ተደርጎ ቢታይ ይበልጥ አሳማኝ ይመስለኛል። ‹ኢትዮጵያዊ› የሚለውን ዜግነት ተጠይፎ ሌላ ዜግነት የደረበ ሰው በምን አይነት ሥነ-አመክንዮ የአውራምባ አዘጋጆችን ዜግነትና የአገር ፍቅር ስሜት ጥያቄ ውስጥ ለመክተት ሞራል እንደሚኖረው አይገባኝም፡፡ (ይህንን ስል ግን አገራቸውን የሚወዱ ለኢትዮጵያ እድገትና መሻሻል ደፋ ቀና የሚሉ አያሌ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥና በውጭ መኖራቸውን ዘንግቼው አይደለም። የአገር ፍቅር ስሜት ፓስፖርት ላይ ባለ ዜግነት መመዘን አለበት ብዬ ባላምንም፤ የዜግነትና የአገር ፍቅር ሂሳብ እናወራርድ ከተባለ ግን እውነታው ይኸው ይመስለኛል)

በተለይ ከጥቂት አመታት በፊት በረባሶና ቁምጣ ለብሰው ‹‹ወያኔ እንዲህ ለብሶ ነው ምንሊክ ቤተመንግስት የገባው፤ እንደሱ ለብሰን በመሰለፍ ካላባረርነው ውጤታማ አንሆንም›› በማለት በዋሽንግተን ዲሲ ጎዳናዎች የተቃውሞ ሰልፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች፤ ዛሬ ‹‹ከአቶ መለሰ በላይ እኛ ነን ለሕወሓት ተቆርቋሪ›› ብለው ቢደነፉ ትርፉ ትዝብት ነው፡፡ ስድብ የእውቀት መለኪያ አይደለም፡፡ ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ለስድብ ይተጋል? የፀያፍ ቃላት ‹‹ሱሰኛ›› መሆንስ ለማን ነው የሚጠቅመው? ስደት ሰለቸን ብለው ለእህል ውሀ የተንበረከኩ ሰዎች ሌሎች እንዲሰደዱ መካሪ የሚሆኑት በምን አይነት ሎጂክ ነው?

አውራምባ ታይምስ የአገሪቱን ሕግና ስርአት አክብራ የምትሰራ ጋዜጣ ነች። ነገር ግን ‹‹እኛም እንደ ጋዜጠኛ አርጋው ውስጥ አዋቂዎች ነንና ዘግታችሁ ተሰደዱ›› ከሆነ መልእክታቸው፣ እሱኑ ያሳውቁንና የምንወስነውን እንወስናለን፡፡ እንጂ ከመሬት ተነስቶ ያንንም መንቸፍ፣ እዚያም ላይ ሥም መለጠፍ፣ ያንንም ማቡካት፣ ሌላውን ማነካካት ምን የሚሉት ዕውቀት የወለደው ‹‹እምነት›› ነው? የሚጠቅመውስ ማንን ነው? የሚጠቀመውስ ማነው? በዚህም የተነሳ ነው ‹‹ይህች አገር የማናት?›› ብለን ለመጠየቅ የተገደድነው፡፡ እንደእኛ እምነት ከሆነ ይህቺ አገር የእኛ ናት፡፡ የተወለድንባት፣ በተወለድንባት ቅፅበት የዜግነት ክብር የተጎናፀፍንባት፣ ያደግንባት፣ የተማርንባት፣ የምንሰራባት፣ መከፋቷ የሚያስከፋን፣ ደስታዋ የሚያስደስተን፣ ክብሯ የሚያስከብረን፣ ውርደቷ ውርደት የሚሆንብን የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም ሀገራችን ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያ ብቻ ናት፡፡ በማንም በምንም የማትለወጥ፣ በማንም በምንም የማትተካ፣ አምሳላችን ከአፈሯ የተቀረፀባት ውድ አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ ታዲያ ዛሬ ከመሬት ተነስተው ጣታቸውን የሚቀስሩብን ሰዎች እነማን ናቸው? ከእኛ የበለጠስ ኢትዮጵያዊ የሚሆኑት እንዴትና በምን መመዘኛ ነው?

እውነት ግን “ይህ አገር የማነው?”

በዳዊት ከበደ

ስድብ የእውቀት መለኪያ አይደለም፡

፡ ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ለስድብ ይተጋል?

የፀያፍ ቃላት ‹‹ሱሰኛ›› መሆንስ ለማን ነው

የሚጠቅመው? ስደት ሰለቸን ብለው ለእህል ውሀ

የተንበረከኩ ሰዎች ሌሎች እንዲሰደዱ መካሪ

የሚሆኑት በምን አይነት ሎጂክ ነው?

Page 4: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

የትምህርት ጥራት

ጀምበር ልትወጣ ይሆን?

ፊ ቸ ር4

በማለት ሁኔታውን ይተቻሉ። የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት

ኤጀንሲ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር የሆኑት አቶ ታረቀኝ ገረሱ ግን፣ የትምህርት አስተዳዳር ውስብስብ መሆኑን፣ የጥራት ጉዳይ ጊዜ እንደሚወስድና በስርዓቱ አፈፃፀም ላይ ችግር እንዳለ ይናገራሉ። በተጨማሪም፣ ‹‹ኤጀንሲው ከተቋቋመ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሰራው ሥራ ሲገመገም በጣም ጥሩ ሲሆን ሳይዘገይም በሚችለው አቅምም እየሰራ ነው። የመንግስቶቹ በሂደት መገምገማቸው አይቀርም። ጅምሩም ያንን የሚያመላክት ነው። ከውጭ ሀገራት መጥተው በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቋማትም አሉ። መመሪያ ለእነሱም እያተዘጋጀ ነው›› ብለዋል። በሂደትም በመንግስት የትምህርት ተቋማት የጥራት ደረጃ ላይ ግምገማ ተደርጎ የተቀመጠውን አነስተኛ መስፈርት ማሟላት የማይችሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች ከተገኙ ከመዘጋት እንደማይተርፉ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰሩ ለአውራምባ ታይምስ ያስረዳሉ። ሆኖም ግምገማው በተቋማቱ ላይ መቼ እንደሚደረግ አውራምባ ታይምስ በተደጋጋሚ ለአቶ ታረቀኝ ጥያቄ ብታቀርብም፣ ትክክለኛውን ጊዜ እና የጊዜውን ቅርበትና ርቀት ለመጠቆም መልስ አልነበራቸውም። ከላይ እንደተጠቀሰው ኤጀንሲው

ግምገማውን ያከናወነው 10 መስፈርቶችን መሠረት በማድረግ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን፣ በግምገማው ሂደት ላይ የኤጀንሲው የአካዳሚክ አደረጃጀት ደረጃውን በጠበቀ ሙያዊ ድጋፍ መታገዙን ጥያቄ ውስጥ የሚከትቱ ወገኖች አሉ። ለዚህ ጥያቄ አቶ ታረቀኝ ምላሽ አላቸው። የግምገማ ሂደቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በሙያቸው ያዳበሩ ባለሙያዎች መሆናቸውንና ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሌሎች የግል ተቋማት ማሕበር አባላት ጋር በእያንዳንዱ ነጥብ ላይ ተወያይተዋል። ሂደቱም ምንም አይነት ችግር ሳይኖረው በሙያዊ አካሂድን በሟሟላት አሳታፊ እንደነበረ አቶ ታረቀኝ ቢገልፁም፣ ባለድርሻ አካላት የነበራቸው ተሳትፎ አነስተኛና በገደብ የታጀበ መሆኑን ገልፀው ነበር።

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግዳሮቶች

ተቋሞቹ በርካታ ተግዳሮቶች እንዳሉባቸው ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡ የመምህርነትና የሕግ ትምህርት ስልጠናዎች በግል ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች እንዳይሰጡ መታገዳቸው ይታወሳል። ‹‹ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ ሰልጣኞች በመንግስት መ/ቤቶች እንዳይቀጠሩ›› የሚል ግድምድሞሻዊ አነጋገር በሰዎች ዘንድ ሲነገር የሚደመጥ ሲሆን ለእነዚህ የግል ተቋማት መንግስት ሊያደርግላቸው ከሚገቡ ነገሮች መካከል በዋነኝነት የባንክ ብድርን ማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ግለሰቦች ቅሬታ ነው። እንዲሁም በዘርፉ ለግንባታ የሚሆን የመሬት አቅርቦት በቀላሉ ስለማይገኝም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የሄደው የህንፃ ኪራይ ዋጋ የተቋማት ባለቤቶችን ክፉኛ አማሯቸዋል። ለኪራይ የሚወጣው ገንዘብም ለትምህርት ጥራት እንዳይውል አሉታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠሩም ባሻገር ከቀረጥ ነፃ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና መለዋወጫዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት አለመግባታቸው ባልታየበት ሁኔታ የተካሄደው የብቃት ደረጃ የግምገማ ሂደት አስቸጋሪ መሆኑን ለዘርፉ በጣም ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች ተናግረው ነበር።

በትምህርት አዋጁ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች

በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 መሠረት ከላይ የተጠቀሱትን የተቋማት ደረጃዎችን ለማግኘት መሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች በአዋጅ በግልፅ የተቀመጠ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ደረጃ ስለማግኘት በሚለው አዋጅ አንቀጽ 18 ሥር የዩኒቨርስቲን ስያሜ ለማግኘት ከሌሎች መስፈርቶች በተጨማሪ የሚከተሉትን መመዘኛዎች ማሟላት አለበት ይላል። በተራ ቁጥር 2 ሥር “has a record of at least four consecutive years in graduating students in a degree Programme after being accredited as a university college, or college institute” ይላል። ትርጉሙም አንድን ተቋም ዩኒቨርስቲ ብሎ ለመሰየም በዩኒቨርስቲ ኮሌጅነት ወይም በኮሌጅነት ወይም በኢንስቲትዩትነት እውቅና ካገኘ በኋላ ቢያንስ ለአራት ተከታታይ ዓመታት ተማሪዎችን በዲግሪ ፕሮግራም ወይም መርሀ-ግብር ያስመረቀ መሆን አለበት ማለት ነው። በተራ ቁጥር 4 ሥር ‹‹አግባብነት ባላቸው

የተለያዩ መስኮች ምርምር የሚያደርግና በተቋሙ የታተሙ የምርምር ውጤቶች ያሉት የምርምር ውጤቱን ለተጠቃሚው የሚያስተላልፍበት መንገድ ያመቻች›› ይላል። (ሰረዝ የተጨመረ) በተራ ቁጥር 5 ሥር ደግሞ ‹‹ለሥራው አስፈላጊ የሆኑና ለደረጃው የሚመጥኑ የማስተማሪያ መሳሪያዎች፣ ክፍሎች፣ ቤተ-መጽሐፍት፣ ቤተ ሙከራዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫ መማሪያዎች ያሉት›› ሲል አስፍሯል። ደረጃውን የሚመጥኑ የአካዳሚክ ሰራተኞችን ለምን እንዳልተጠቀሱ ግልጽ ባይሆንም። እነዚህን ግልጽና የሚለኩ መመዘኛዎች (objective criteria) አንድን ተቋም ዩኒቨርስቲ ብሎ ለመሰየም ዓይነተኛና ተገቢ መመዘኛዎች ናቸው። ሌሎች በተጨማሪ የሚጠቀሱ ቢኖሩም። እነዚህን የሚመዘኑና የሚለኩ መለኪያዎችን

መንግሥት የሚያቋቁማቸው ዩኒቨርስቲዎች ባለመሟላታቸውና በአጭር ጊዜ ውስጥም ሊያሟሉት እንደማይችሉ በማመኑ በሚመስል መልኩ የዩኒቨርስቲ ደረጃ ትምህርት ጥራትን ለመናድ የሚያስችል ሌላ የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 650/2001 ማውጣቱንና በተሻሻለው አዋጅ ውስጥ አንድ ንዑስ አንቀጽ መጨመሩን አቶ አስራት ይናገራሉ፡፡የዩኒቨርስቲ ደረጃን ስለመስጠት በሚለው

በዚህ አዋጅ አንቀጽ 11 ሥር በተራ ቁ.2 መሠረት ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 351/1995 ላይ የዩኒቨርስቲነትን ስያሜ ለማግኘት የተቀመጡትንና በዚህ ጽሑፍ

እገዛና ክትትል እየተሰጣቸው ብቃታቸው ወደሚፈልገው ደረጃ ሊመጡ እንደሚችሉ የሚታመንባቸውና ደረጃ በደረጃ እየተጠናከሩ የሚሄዱ ተቋማት ውስጥ ተመድበዋል። የትምህርት ጥራትና አግባብነትን ለማረጋገጥ የጎላ ጉድለት ያለባቸው ተቋማት፣ ግን ደግሞ ውስጣቸው ተነፃፃሪ ልዩነት የሚታይባቸው ተቋማት ምድባቸው ‹‹ሐ›› ነበር። በዚህ ስርም፣ ‹‹ሐ1›› የጎላ ጉድለት ቢኖርባቸውም በተወሰኑ ቁልፍ መለኪያዎች በአንፃራዊነት የተሻለ ይዞታ ስላላቸው በአጭር ጊዜ መሻሻል እድል ይኖራቸዋል ተብሎ የሚታሰቡና ስልጠና የሚቀጥሉ፣ ነገር ግን ማስተካከያ እርምጃ መካሄዱ በአጭር ጊዜ ውስጥ በኤጀንሲው ሲረጋገጥ እንደ ተቋም የመቀጠል ዕድል የሚሰጣቸው ናቸው። እንዲሁም፣ ‹‹ሐ2›› ካለባቸው መሰረታዊ ጉድለት አኳያ በስርዓቱ መቀጠል የማይገባቸው በሚል ተመድበዋል። የተቋማቱን ብቃት ለመገምገም ዘጠኝ

ቁልፍ የብቃት መለኪያዎች ሥራ ላይ ውለዋል። እነዚህም የተቋሙ የአመራር ስርዓት፣ የአካዳሚክ ፕሮግራምና አደረጃጀታቸው፣ ስርዓተ ትምህርት፣ መምህራን፣ የተማሪዎች ምዘና ስርዓት፣ የተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባና ሪከርድ አያያዝ ስርዓት እና ድጋፍ አገልግሎት፣ የትምህርት አገልግሎት መስጫ ከባቢና ሕንፃ ምቹነት፣ የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓት እና የምርምር ባጀት፣ አስተዳዳርና ውጤቶች ናቸው። የተቋማቱ ዋነኛ ተግባር የመማር ማስተማር ሥራ በመሆኑ ከፍተኛ ድርሻ ለመማር ማስተማር ተሰጥቷል። በዚህ መሠረት አነስተኛውን የመመዘኛ

መስፈርት ያሟሉና እንዲቀጥሉ የተፈቀደላቸው 57፣ በጊዜ ገደብ እንዲቀጥሉ የተፈቀደላቸው 13 እና የተቀመጠውን አነስተኛ መስፈርት ያላሟሉትና በድግሪ መርሃ ግብር ማስተማር የማይችሉ አምስት ተቋማት ናቸው። ይኼንን ጉዳይ ተከትሎ የኢትዮጵያ የግል

የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ማህበር የሥራ አመራር ቦርድ በቅርቡ በሂልተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በወቅቱም የማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር አረጋ ይርዳው፣ ‹‹አነስተኛውን የመመዘኛ መስፈርት አላሟሉም›› በሚል ፕሮግራማቸው እንዲዘጋ የተደረጉ ተቋማት ጨርሶ አለመዘጋታቸውን እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል። ‹‹የተዘጋው ተቋማቱ የሚሰጡት የዲግሪ ፕሮግራም እንጂ ጠቅላላ ተቋሙ አይደለም። አንድ ተቋም የቴክኒክና ሙያ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን አጣምሮ መስጠትና ከተዘጋው የዲግሪ ፕሮግራም በስተቀር ያሟሉትን ትምህርቶች መቀጠል ይችላል።››

‹‹እርምጃው ዘግይቷል››ምንም እንኳን ኤጀንሲው የወሰደው

የብቃት ግምገማና የደረጃ አሠጣጥ እርምጃ ቢዘገይም ጥሩ መሆኑን የሚናገሩት የዘርፉ ባለሙያና የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አስራት ጣሴ ናቸው። ነገር ግን፣ ኤጀንሲው የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን በመተው በግሎች ላይ ብቻ ያደረገው ግምገማና እርምጃ ተገቢ አለመሆኑን ያስረዳሉ። አያይዘውም ‹‹የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን የመቀበል አቅማቸው 18 በመቶ ሲሆን የተቀሩት 82 በመቶ እውቀት ፈላጊዎት የሚማሩት በመንግስት ተቋማት ውስጥ ነው። ይኼ ብዙሃኑን የያዘው በቅድሚያ መገምገም ሲገባው ወደኋላ መጎተቱ ተገቢ አይደለም። የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በብዙ የጥራት ችግሮች ተተብትበዋል።››

ዊሊያም ሴይንት የተባሉ ምሁር ‹‹Higher Education in Ethiopia: The Vision and its challenges›› በተሰኘ ፅሁፋቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ራሳቸውን ነፃነት በተገደበ፣ በወግ አጥባቂ ምሁራዊ ዝንባሌ የተቀየደ፣ የትምህርት ጥራት እየዘቀጠ የሚገኝ፣ የጥናት እና ምርምር ውጤቱ የተዳከመ እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የምሁራን ማሕበረሰብ ጋር ያለው ቁርኝት ውስን ሆኖ ይገኛል›› ብለው ነበር። እኚሁ ምሁርም እንደ ኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የቅበላ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ እንደሚጥር ሀገር የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ ፈተና እንደሚሆንበት ይናገራሉ። በአንድ ወቅትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስነ-ትምህርት ኮሌጅ የሚገኙ መምህር ‹‹መንግስት በሁለት ትይዩ ጎዳናዎች እየተጓዘ ነው። በአንድ በኩል ስለትምህርት ጥራት ያነሳል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የትምህርት ጥራትን ገደል የሚከቱ እርምጃዎችን ይወስዳል›› ሲሉ ከስሰው ነበር። ነሐሴ 30/2003 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት

አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ለአንድ ዓመት ያህል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የብቃት ደረጃ ለመለየት ተቋማቱን በመገምገም የመጨረሻውን ውጤት ለመገናኛ ብዙሐን ይፋ አደረገ። መንግስት በግል የከፍተኛ ትምህርት

ተቋማት እየተሰጠ ባለው ትምህርትና ስልጠና ላይ የጥራት ችግር መኖሩን በመገንዘብ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ አቅጣጫ ማስቀመጡን ተከትሎ ችግሩን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የጥራት ማረጋገጫ የአፈፃፀምና የእውቅና አሰጣጥ መመሪያዎችን በነሐሴ ወር 2002 ዓ.ም አውጥቶ ነበር። በዚሁ መሠረት የግል የከፍተኛ ትምህርት

ተቋማትን የጥራት ደረጃ ለመገምገም የብቃት መለኪያዎች ተዘጋጅተው በተቋማቱ ላይ አጠቃላይ ግምገማ ተካሄደ። በተደረገው ግምገማ የተገኘው ውጤትም ተጠናቅሮ ለኤጀንሲው ቦርድ በመቅረብ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ውሳኔ መሰጠቱን በነሐሴ ወር ኤጀንሲው በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

የብቃት ግምገማ ሒደቱየወጣውን መመሪያ ተከትሎ የተቋማቱን

ብቃት ለመለካት የጥራት መመዘኛዎች ተዘጋጅተው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲወያዩበት ከተደረገ በኋላ ማሻሻያዎች ታክለውበት የኤጀንሲው ቦርድ አፀደቀው። ከዚያም የሚመለከታቸው ተቋማት በቅድሚያ እንዲያውቁት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ኤጀንሲው ያስረዳል። ይህንን ሥራ በብቃት ለማካሄድ ከኤጀንሲውና ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጣ የባለሙያዎች ቡድን ተቋማቱ ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ክልሎች ተሰማርተው የመስክ ግምገማ በማከናወን በመመዘኛው መሠረት ዝርዝር ግምገማ ማካሄዱንና በሂደቱም ከተቋማቱ የተለያዩ አካላት መረጃዎች መሰብሰቡን ከኤጀንሲው የተገኘው መረጃ ይዘረዝራል።

የብቃት አመዳደብ ይዘትና መለኪያዎቹ

በመደበኛ መርሃ ግብር ስልጠናዎችን ሲሰጡ የነበሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሂደት ተካትተው፣ ግምገማው ሲካሄድ መሠረታዊ ይዘቱ የእውቅና አሰጣጥ ሂደቱን ተከትሎ ተቋማቱ ስልጠናውን በሚሰጡባቸው ዋና እና ቅርንጫፍ ካምፓሶች ላይ አትኩሮ ማካሄድ የኤጀንሲው ዕቅድ ነበር። በዚህ መሠረት በአጠቃላይ 75 ተቋማት በካምፓስ ደረጃ የብቃት ግምገማው ተካሂዶባቸው፣ 57 አነስተኛ የጥራት መለኪያዎችን ያሟሉ እና 18 ደግሞ ያላሟሉ ተቋማት ተለይተዋል። በጥናቱ ላይ በ2002 የትምህርት ዘመን

መጨረሻና በ2003 ዓ.ም የእውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው ተቋማት አልተካተቱም። ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል፣ ብቃትና ዝግጁነት ያላቸው በምድብ ‹‹ሀ›› እና በምድብ ‹‹ለ››ደግሞ

የተጠቀሱትን ሦስት የሚለኩና ተጨባጭ መመዘኛዎችን ወደ ጎን የሚያደርግና በግልጽም ተፈፃሚነታቸውን የሚያፈርስ ነው። በአዋጅ ቁጥር 350/2001 አንቀጽ 11 ተ.ቁ

2 ሥር የሚከተለው ሙያ ተፅፎ ይገኛል። ‹‹… አንድ ተቋም የዩኒቨርስቲ ስያሜና ደረጃ ይዞ እንዲቋቋም ታስቦ ከሆነና ያለው የሀብት አቅርቦት፣ ተቋማዊ እቅድና ራእይ ሲታይ የታሰበው ተቋም (ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት የሚለኩና ተጨባጭ መስፈርቶችን) ተቀባይነት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊያሟላ ይችላል ብሎ ሚኒስትሩ ሲያምን ተቋሙ ዩኒቨርስቲ ሆኖ መቋቋም ይችላል›› ይላል። (ሰረዝ የተጨመረ)‹‹ከተሻሻለው አዋጅ አንድ ዋና ቁም

ነገርን መመልከት ይቻላል።›› የሚሉት አቶ አስራት ዩኒቨርስቲዎች ሲቋቋሙ ለደረጃው የሚገቡትን መስፈርቶች በማሟላት ሳይሆን በፖለቲካ ውሳኔ፣ ለፖለቲካ ፍጆታና ጥቅም ጭምር እንደሚውሉ እና ዩኒቨርስቲዎችን የመክፈት ውሳኔዎችም ግብታዊ መሆናቸውን ያስረዳሉ። ይህንን ሃሳብ የሚጋሩ ሌላ ባለሙያም በአንድ ወቅት ላይ ‹‹በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች እየተሰጠ ያለው የትምህርት ጥራት ደረጃ፣ የተማሪ እና የአስተማሪ ብቃት መካተቱ “ዩኒቨርስቲ” ብሎ ለመጥራት የማያስችል ነው›› ይላሉ። አገሪቱን የሚታደግ ተማሪ ሳይሆን በከፍተኛ ፍጥነት ‹‹የተማረ የሚመስል ግን ያልተማረ ትውልድን›› የመፍጠር ጥድፊያ የተያዘ ይመስለላል፡፡›› ሲሉ አዳዲስ ዩኒቨርስቲዎችን የመክፈት ችኮላውን ተችተው ነበር።

ያልተዳሰሰው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገመና

በግል የከፍተኛ የትምህርት የተቋማት ውስጥ አሉ የሚባሉት በርካታ ችግሮች በመንግስት አቻዎቻቸው ዘንድ በባሰ መልኩ እንደሚገኝ በስፋት ይገለፃል። ‹‹የመንግስት ተቋማት ይሻላሉ›› የሚባለው በአንድ ነገር ሰፊ ቦታን ከመያዛቸው በስተቀር በብዙ ችግሮች የተተበተቡ መሆናቸውን አውራምባ ታይምስ በስም የማይጠቅሳቸው አንድ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህር ያስረዳሉ። ለአንድ አመት ገደማ ያህል ሰፊ ግምገማ በማድረግ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የብቃት ደረጃ ማውጣት ብቻውን ተፈላጊውን ግብ እንደማያመጣም ሃሳቦች ይሰነዘራሉ፡፡ በ2002 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው

ስታትስቲክስ መሠረት በመንግስት ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የመምህራን ቁጥር 11,238 እንደነበረ ይገለፃል፡፡ከእነዚህም ውስጥ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው 50.8 በመቶ፣ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 40.3 በመቶ እና ፒ.ኤች.ዲ ያላቸው 8.9 ነበሩ፡፡ ከዚህ በሚቃረን መልኩም የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ተቋማቱ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው መምህራንን 10 በመቶ፣ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 60 በመቶ እና ፒ.ኤች.ዲ ድግሪ ያላቸውን 30 በመቶ መያዝ እንደሚገባቸው ይደነግጋል። ‹‹እነዚህ ቁልጭ ያሉ ችግሮች በመጀመሪያ ካልተፈተሹ ምን ማለት ነው?›› በማለት የሚጠይቁት አቶ አስራት፣ ‹‹ጥረት አልባ በሆነና ዓላማ በጎደለው አካሄድ መንግስት ለትምህርት ጥራት ተገቢውን ቦታ አልሰጠም›› በማለት ይተቻሉ። መንግስት በአሁን ወቅት በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን የሚጠቅሱ ወገኖችም በዚህ ጉዳይ ላይ መንግስት በሚወስደውና ሊወስደው በሚችለው እርምጃ ላይ ሙሉ እምነት የላቸውም፡፡ ምክንያታቸውም ኢህአዴግ የተለያዩ ነገሮችን ለማሻሻል

በኤልያስ ገብሩ

ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው ስታትስቲክስ

መሠረት የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው መምህራን

50.8 በመቶ፣ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 40.3

በመቶ እና ፒ.ኤች.ዲ ያላቸው 8.9 ነበሩ፡፡ ከዚህ

በሚቃረን መልኩም የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ

ተቋማቱ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው መምህራንን

10 በመቶ፣ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው 60 በመቶ

እና ፒ.ኤች.ዲ ድግሪ ያላቸውን 30 በመቶ መያዝ

እንደሚገባቸው ይደነግጋል

Page 5: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

5ጀምሮ የመተው ባህሪ አለው በማለት ነው። ‹‹እንዲያውም በተወሰኑ ነገሮች የግሎቹ ይሻላሉ›› የሚሉት ከላይ የተጠቀሱት መምህር፣ ጥቂት የማይባሉ ተማሪዎች የተመደቡበትን የመንግስት የትምህርት ተቋም ለቅቀው በግላቸው ለመማር ወደ ግል ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጀች ፊታቸውን የሚያዞሩት በዋነኛነት በጥራት ችግር ምክንያት መሆኑን ምስክርነት ለአውራምባ ታይምስ ይሰጣሉ። ምንም እንኳን የጥራት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲው ብቃታቸውን ገምግሞ ደረጃዎችን ያወጣው በግሉ ዘርፍ ላይ ቢሆንም የመንግስቶቹ ሊፈተሹ እንደሚገባ የመምህሩ አስተያየት ነበር፡፡‹‹በአካዳሚክ ትምህርት ‹ኤ› ከማምጣት

ይልቅ በኢህአዴግ መመዘኛ ‹ሲ› ማምጣት ይሻላል›› እየተባለ በሚገለፀው አነጋገር የሚስማሙት እኚሁ መምህር በርካታ ተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ማጣታቸውንና ተለፍቶ የሚገኝ የትምህርት ውጤትም (Grade) ዋጋ የሚያጣበት ሁኔታ ቀላል እንደማይባል እንዲህ በማለት ያስገነዝባሉ፡- ‹‹የኢህአዴግ የትምህርት ስርዓት ውጤታማነቱን እያጣ ነው፡፡ ሰው ዋጋ የሚያደርገው አካዳሚክ ዕውቀትን ሳይሆን የፖለቲካ ነፀብራቅን ሆኗል። አካዳሚክ ትምህርት የራሱ የሆነ ምቹ ከባቢ ይፈልጋል። አሁን ባለው ሁኔታ ተማሪም ሆነ አስተማሪ አልምጧል››በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

ውስጥ ካሉ ችግሮች መካከል በመምህራንና ተማሪዎች ዘንድ እንግሊዘኛ ቋንቋን በተገቢው ሁኔታ በመግለፅ መግባባት አለመቻል፣ የመምህራን የዕውቀት ደረጃና የማስተማር ብቃት አነስተኛ መሆንና አንጋፋ ስም ያላቸውን ዩኒቨርስቲዎች ስም ላለማጣት ሲባል በምርምርና በሌሎች ምክንያቶች ብዙ ብር ለማግኘት ሲሉ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚኖሩ አንጋፋ መምህራን ተሰግስገው መገኘታቸው ይጠቀሳል። በተጨማሪም፣ ብዙ ተማሪዎች ያለፍላጎታቸው የሚማሩትን ትምህርት የቀጣይ ህይወታቸው ዓላማ አድርገው አለመውሰድ፣ ውድድር አለመኖር፣ የተምሳሌታዊ ምሁራን ድርቅ፣ የሱሰኝነት ችግር ውስጥ መግባት፣ የተማሪና አስተማሪ ግንኙነት ድንበሩን ማለፍ፣ ቁጥራቸው ትንሽ ያልሆኑ ሴት ተማሪዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በወሲብ ንግድ ላይ መሰማራት ሌሎች ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው፡፡ በመምህራኖች ዘንድም የአዕምሮ ፍልሰት ከፍተኛው ችግር ነው፡፡ ለዚህም የውጭ የትምህርት ዕድል፣ ዝቅተኛ ክፍያ፣ የሥራ ዋስትና አለመረጋገጥ… በችግርነት ይገለፃሉ፡፡ ከሶስት ዓመት በፊት ትምህርት ሚኒስቴር

ካወጣው የድረ-ገፅ ፅሁፍም ትምህርት ብቻውን ተነጥሎ የሚከናወን ሳይሆን ከምርምር ከሙያዊ ተግባርና ከልማት ጋር ተስተጋብሮ ለኅብረተሰቡ ሁለንተናዊ እድገት ተገቢውን አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት ያስረዳል። ይኼም ፅሁፍ፣ ‹‹የሀገራችን የትምህርት

ሁኔታ በዓላማ፣ በይዘት፣ በአቀራረብ በሥርጭትና በሂደት፣ እንዲሁም በውጤት ሲታይ ተማሪዎች ተገቢውን ትምህርት ቀስመው የችግር ፈቺነት ባሕርይንና ችሎታን እንዲያጎለብት አስችሎአቸዋል ለማለት አያስደፍርም። የሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል ተገቢውን ባህል በማዳበር ሳይንስና ቴክኖሎጂን በህብረተሰቡ አስርጾ አካባቢያቸውን ለመንከባከብ፣ ለማልማትና ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ተሳትፏቸውን ለማጠናከር እንዲያስችላቸው ያደረገው አስተዋጽኦና በከፍተኛ ትምህርት በሳል ችግር ፈቺ ምሁራንን በማፍራትም ሆነ ለሕዝብ ጥቅምና ለሀገር እድገት የሚጠበቀውን ያክል የጥናትም ሆነ የምርምር ውጤት ጎልቶ አልታየም።›› ይላል፡፡

የትምህርትና የፖለቲካ ትስስር

በመንግስት ላይ ከሚነሱ ትችቶች መካከል ትምህርትና የትምህርት ተቋማትን ለፖለቲካ ፍጆታ በመጠቀሙ ላይ ነው፡፡ በዚህ ሀሳብ የሚስማሙት አቶ አስራት በዘርፉ ተደጋግሞ የተነሳው አደጋ የመምህራን አመራረጥና መለኪያው የፖለቲካ መስፈርት መሆኑን ያስገነዝባሉ እንዲህ በማለት፡- ‹‹ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ተቋማት ድረስ ብዙ መምህራን የሚመለመሉት በፖለቲካ መስፈርት ነው። በባለፈው በደርግ ስርዓት ውስጥም ትምህርቱ ከሶሻሊዝም ርዕዩተ ዓለም ውጪ አልነበረም። አሁንም ቢሆን ትምህርትና ተቋማት በፖለቲካውና በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዮተ -ዓለም የተቃኙ ናቸው›› ከዚህም በላይ መንግስት ዩኒቨርስቲ መክፈትን እንደ ፖለቲካዊ አፍ የማዘጊያ ስልት ተጠቅሞ የፖለቲካ ድጋፍና ታማኝነትን እንደማግኛ መሳሪያ እየተገለገለበት ነው የሚሉም በርካቶች ናቸው፡፡ለትምህርት ጥራት ነፃ የሆኑ ተማሪዎች፣

ነፃና ብቁ መምህራን፣ በፖለቲካ ያልተቃኘ ንፁህ የስርዓተ-ትምህርት ምህዳር፣ ያልተሟሉ የትምህርት መሳሪያዎች፣ ላቦራቶሪዎች፣ ሰርቶ ማሳያዎች እና ነፃና ብቁ የአስተዳደር ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጉ ለችግሩ በመፍትሄነት ሃሳቦች ተሰንዝረዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም ለመምህራን ኑሮን ያገናዘበ ተገቢ ክፍያ፣ የተለያዩ ጥቅማጥቅሞች፣ መኖራያ ቤቶች፣ የጤና ኢንሹራንስ … ሊሟላላቸው ይገባል።

ጉዳዩ፡- ውስጣዊ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የፖለቲካ እስረኞችን ሊለቁ ነው (በአምባሳደር ዶናልድ ያማሙቶ

ተዘጋጅቶ በጥብቅ ምስጢር የተያዘ) የቅንጅት የፖለቲካ እስረኞችን

ለማስፈታት ፕ/ር ኤፍሬም ይስሀቅ ሲያደርጉት የቆዩት የማቀራረብ ዲፕሎማሲ ጁን 22 ቀን ጉልህ ምዕራፍ ላይ ደረሰ። ከፍተኛው ፍርድ ቤት በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ናቸው ካለ ከሁለት ሳምንት በኋላ 21ዱ የቅንጅት አመራር አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ላቀረቡት የምህረት ቅድመ ሁኔታ ተገዥ በመሆን ‹ጥፋተኝነታቸውን› አምነው ፊርማቸውን አኑረዋል። በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር ያሉት የተቀሩት 40 እስረኞች እና የመገናኛ ብዙኃን አባላትም ጭምር ሰነዱን ፈርመዋል። (ሁለቱ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች (ዳንኤል በቀለና ነጻነት ደምሴን ለማለት ነው) በፊርማው ሳይስማሙ ህጋዊ ክርክር ሊቀጥሉ ወስነዋል፤ ቀጠሮዋቸውም ጁላይ 12 ነው) የህወኃት ማህከላዊ ኮሚቴ በጁን

23 ስብሰባው እስረኞችን ለመልቀቅ በጠ/ሚኒስትሩ የቀረበውን ሐሳብ በቅሬታ ቢያፀድቀውም ይፋ የሚሆንበት ጊዜ ግን ከ2 ሳምንት በኋላ እንዲሆን ግዴታ ጥሏል። ይህ የጊዜ ክፍተት ለህወሓት አክራሪዎች (hardliners) እንዲሁም በጠ/ሚኒስትሩ የሚቀርብን ማንኛውም ጉዳይ ለሚቃወሙት በቅንጅት ውስጥ ላሉ አባላት ስምምነቱን ‹በጥልቀት እንዲመረምሩ› ተጨማሪ ጊዜ ይሰጣል።

የሀገር ሽማግሌዎች ስምምነት ለማምጣት እየጣሩ ነው

ፕ/ር ኤፍሬም በቅርቡ ወደኢትዮጵያ የመጡበት ጉዳይ ጁን 13 ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው (ከቀድሞው የሚያዚያ ጉብኝታቸው ጊዜ አንስቶ በእስር ላይ ከሆኑት) ከቅንጅት መሪዎች ጋር ስለሚደረገው ድርድር እና እስረኞችን ነፃ ለማውጣት ማሟላት ስለሚጠበቅባቸው ሁኔታዎች ለመወያየት ነበር። ጠ/ሚኒስትሩም እስረኞቹ ‹‹መንግስትን በሕገ-ወጥ መንገድ የመቀየር ሙከራ አድርገናል›› የሚል የይቅርታ ደብዳቤ በየግል ከፈረሙ ተፈተው ነፃነታቸውን ያገኛሉ በሚል ተስማምተዋል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የደብዳቤው ቋንቋ አከራካሪ ሆኖ ቢቆይም የቅንጅት እና የህወኃት መሪዎችን ሊያስማማ የሚችል

ቋንቋ በመፈለግ ረገድ ፕሮፌሰሩ እና የአገር ሽማግሌዎች ሲደክሙ ቆይተዋል። ጁላይ 18 በዋለበት ሳምንት ፕሮፌሰሩ በቃሊቲ እስር ቤት ከቅንጅት መሪዎች ጋር ደብዳቤውን በመፈረም ረገድ ስለ ውሳኔያሳቸው ሲመክሩ በርካታ ሰዓታትን አሳልፈዋል። ጁን 22 ቀን ደግሞ 21ዱም የቅንጅት መሪዎች ሰነዱን ለመፈረም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። የመሪዎቹ እርምጃ የተቀሩትን 40 እስረኞች እና የመገናኛ ብዙኃን አባላት ጨምሮ ጁን 25 በተመሳሳይ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ እና ፊርማቸውን እንዲያኖሩ አድርጓል። ይሁንና ሁለቱ የሲቪል ማህበረሰቡ ተወካዮች ህጋዊ ሂደቱን እንጂ ፊርማውን አልመረጡም። ቀጠሮአቸውም ጁላይ 12 ነው።

የመለስ የድፍረት እርምጃ ገና በርካታ ፈታኝ ሥራ የቀረ ቢሆንም

ፕ/ር ኤፍሬም ጁን 22 መልካሙን ዜና ለጠ/ሚኒስትር መለስ አበሰሩ። በኢህአዴግ ማህከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ወቅት (ሰኔ 23) ጠ/ሚኒስትር መለስ የቅንጅት እስረኞች ስህተታቸውን በማመን እና ህገ-መንግስቱን ለመጠበቅ በገቡት ቃል መሠረት እንዲፈቱ የሚጠይቅ የውሳኔ ሀሳብ አቀረቡ። በስብሰባው ጊዜ ጠ/ሚኒስትር መለስ ከራሳቸው የህወኃት ማህከላዊ ኮሚቴ አክራሪ ስብስቦች በኩል የቅንጅት አመራሮችን የመፈታት ሀሳብ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀረበበት። ቢከሰሱም ገና ያልፈተረደባቸውን እስረኞች መፍታት የህግ ጥሰት እንደሆነም በአክራሪዎቹ ተጠቆመ። በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት ይሄን እርምጃ ያደረገው ‹‹ከአሜሪካ የመገናኛ ብዙኃን እና ከአሜሪካ ኮንግረስ በሚሰጡ አሉታዊ አስተያየቶች የተነሳ በተፅዕኖ ነው›› የሚል አንድምታ ሊመጣ እንደሚችልም ተጠቆመ። ከረጅም ፍትጊያ በኋላ ጠ/ሚኒስትር መለስ የማዕከላዊውን ኮሚቴ ይሁንታ አገኙ፤ ግን ይሄን ለማሳካት የገጠማቸው ፈተና ህወኃት የአንድ ሰው አዛዥነት የሚንፀባረቅበት ነው ተብሎ እንደሚታመነው እንዳልሆነ ያሳየ ነው።

እና መች ይፈቱ?የህወኃት ማዕከላዊ ኮሚቴ የቅንጅት

እስረኞችን መፈታት እንዲያፀድቅ ለማስቻል የኢትዮጵያው ከፍተኛ ፍ/ቤት ጥፋተኛ ሆነው በተገኙት ሰዎች ላይ ውሳኔ (ጁላይ 9) መስጠቱ ቀዳሚ መሆን እንዳለበት ጠ/ሚኒስትሩ ተስማምተዋል። ከዚህ በኋላም ፊርማ ያኖሩ እስረኞች የሚፈቱበት እና የኢትዮጵያ መንግስትም መግለጫ የሚሰጥበት ሂደት ይከተላል። ጠ/ሚኒስትሩ ፕ/ር ኤፍሬምን በዚያ ወቅት በኢትዮጵያ እንዲገኙና የአገር

ሽማግሌዎችም የእስረኞቹን መፈታትንና መቻቻልን በተመለከተ መግለጫ እንዲሰጡ ጠይቀዋቸዋል።

አስተያየት፡- ቀጣዮቹ 10 ወሳኝ ቀናትከውሳኔው እና ቀጥሎ ከሚመጣው

የእስረኞች መፈታት በፊት ያሉት መጪ ሁለት ሳምንታት በቋፍ ላይ የሚገኙ ናቸው። የህወሓት አክራሪዎች የቅንጅት እስረኞችን መፈታት እንዲስማሙ ግፊት በማድረግ ጠ/ሚኒስትር መለስ በጣም ወሳኝ (ለዚያውም የፖለቲከ ህይወታቸውን የሚፈታተን አደጋ ያለበት) ምርጫ ወስደዋል። በህወኃት ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች ይህን ውሳኔ ለማጠፍ የሚችሉበትን አጋጣሚ ቢያገኙ እንደሚጠቀሙበት ጥርጥር የለውም። ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የሚደመጡ አሉታዊ አስተያየቶች ይበልጡን ከአሜሪካ ኮንግረስ የሚደመጡቱ፤ ስምምነቱን የሚያደናቅፍ እና የኢትዮጵያን ሰላምና መረጋጋትን እንዲደፈርስ ሊያደርጉም ይችላሉ። በፕ/ር ኤፍሬም እና አቻ የአገር ሽማግሌዎች ከፍተኛ ጥረት እና በጠ/ሚኒስትር መለስ የተወሰደ አጣብቂኝ የተሞላበት የፖለቲካ እርምጃ አማካኝነት የተገኘው ይህ እመርታ /break through/ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው ተቃውሞ የደረሰውን ጉዳት በመጠገን ረገድ ጉልህ ሚና አለው። የአሜሪካ ኮንግረስ ተወካይ ፔይን

አቅርቦት የነበረውን በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረውን አዋጅ እንዲያዘገይ በማድረግ ረገድ ኤምባሲው እና ዲፓርትመንቱ በተጫወቱት ሚና የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ምስጋናውን አቅርቧል። በአሜሪካ የሚገኙ የቅንጅት አክራሪዎች ግን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር የሚደረግ ማንኛውም ስምምነት ነቃፊ ናቸው። ለአምባሳደሩ ከሚደርሱት ስድብ አዘል ከሆኑ የስልክ ንግግሮች እና የኢ-ሜይል መልዕክቶች መረዳት የሚቻለው አሜሪካ የሚገኙት የቅንጅት አክራሪዎች የእስረኞቹ በእስር መቆየት ጠ/ሚኒስትሩን ለማጥቃት የተሻለ መንገድ እንደሆነ የሚያስቡ ናቸው። የእነሱን መፈታት የኢትዮጵያን መንግስት የሚቃወሙበትን ሌላ መንገድ እንዲፈልጉ ያስገድዳቸዋልና።የተግባር ጥያቄዲፓርትመንቱ ይህን ጉዳይ

በተመለከተ ለሚቀርቡለት ማንኛውም ጥያቄዎች ቀድሞ የተስማማንበትን ቋንቋ በመጠቀም መልስ መስጠቱን እንዲቀጥል ፖስት (Post) ይጠይቃል። በተጨማሪም እስረኞቹ ሲፈቱ ዲፓርትመንቱ የሚከተለውን መግለጫ እንዲሰጥ ፖስት ይጠይቃል። ዶናልድ

ያማሙቶ

የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?

ዊኪሊክስ በዚህ ዙሪያ ይፋ ያደረገውን መረጃ ይከታተሉ

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተለያዩ የጥራት ችግሮች ቢኖርባቸውም ዕውቅና ለማግኘት በሚሉ ደንቦች ተፈትሸው እውቅና እንደሚያገኙና ቁጥጥር እንደሚደርግባቸው ይገለፃል፡፡ የመንግስቶቹ በብዙ ችግሮች ቢተበተቡም በነፃነት የተለቀቁ በመሆናቸው የማይደፈሩና የማይጠየቁ መሆናቸውን በዘርፉ ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች አስተያየት ይሰጣሉ። በጥራት ደረጃቸው ዝቅተኝነት ምክንያት በዘንድሮው ዓመት በድግሪ መርሃ ግብር እንዳያስተምሩ ለታገዱት አምስት የግል ተቋማት ትምህርት ሚኒስቴርና ኤጀንሲውን ተጠያቂ የሚያደርጉ ወገኖች አሉ፡፡ ይኼንን ሃሳብ ሲያጠናክሩም፣ ‹‹ተቋሞቹ እስኪሞቱ ድረስ መጠበቁ በቂ ክትትል እየተደረገባቸው አለመሆኑን የሚያሳይ ነው›› ብለዋል፡፡ በማያያዝም፣ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በቅርቡ የተወሰደው እርምጃ ስህተትን ስለማቆም ሳይሆን ስህተትን ስለመቅጣት መሆኑን ይጠቁማሉ፡- ባቡር ሃዲዱን ስቶ ከመገልበጡ በፊት ሃዲዱን እንዳይስት ሌት ተቀን መስራት ተገቢ ነው የሚል ምክር በመለገስ፡፡ ሆኖም ‹‹በመንግስት የትምህርት ተቋማት ውስጥ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት አለ የሚባለው አሉባልታ ነው›› የሚሉት አቶ ታረቀኝ፣ ኤጀንሲያቸው ከአዋጅ በመነሳት መስፈርቶችን እንደሚያስፈፅም፣ በዚህ ላይም ተማሪዎች ውሳኔ እንደሚሰጡበት እና የተማሪዎችና የመምህራኖች አካዳሚክ ነፃነት የተጠበቀ በመሆኑ ችግር አለመኖሩን ተናግረዋል።

የሥርዐተ-ትምህርቱ የእዝ-አመራር በዩኒቨርስቲዎች

ከላይ እንደተገለፀው በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በመንግስት የሚደረግ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት በወሬ ደረጃ ከማንሾካሾክ ባለፈ በግልፅና በስፋት የመነጋገሪያና የመወያያ አጀንዳ መሆን ከጀመረ ሰነባብቷል። በርካታ መምህራኖች ከከፍተኛ ደረጃ ት/ቤት አንስቶ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ በአባልነት ተመልምለው ስርዓቱ በሚከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ርዕዩተ ዓለም ተጠምቀው ሙያቸው የሚያስፈልገውን አካዳሚክ ነፃነት በማጣት ዕውቀትን ለተማሪዎቻቸው እየመገቡ እንደሚገኙ ይገለፃል። ብዙ ተማሪዎችም የኢህአዴግ አባል ድርጅት ፓርቲ አባላት መሆናቸውና ይኼም በትምህርት ቅበላቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማምጣቱ የሚናገሩ ወገኖች አሉ። አንዳንዴም በተቋሞቹ ውስጥ በአባል ድርጅት አመራሮች አማካኝነት የዕዝ አመራር በመኖሩ ሳቢያ መምህራኖች መንግስትን የሚተች አስተምርሆት ወይም አስተያየት ለተማሪዎቻቸው መስጠት አደጋ አለው፡፡ ይህን መሰል ነገር ከተናገሩ ከቀናቶች በኋላም፣ ‹‹ባለፈው የተናገርከውን አስተካክል›› የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር ከአመራሮች እንደሚለገሰው ለአውራምባ ታይምስ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህር ያስረዳሉ። ቢሆንም በትምህርት ተቋሞቹ ውስጥ የኢህአዴግ አባልነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ስሜት እያጣ መሆኑም ይነገራል፡፡

የመፍትሄ ሃሳቦችየትምህርት ሚኒስቴር ድረ-ገፅ መረጃም

የትምህርት ችግሮች መንስኤዎች ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በሀገራችን ትክክለኛ የትምህርት ፖሊሲ አለመኖር ትምህርት በዓላማው፣ በይዘቱ፣ በመማር -ማስተማር ሥነ-ዘዴው፣ በሥርጭቱ፣ በአደረጃጀቱ፣ በአስተዳደሩ፣ በፋይናንስ፣ በምርምሩ፣ በድጋፍ ሰጪዎች ወዘተ የብቃት ማጣት ውጤቶች መሆናቸውን ዘርዝሮ ነበር፡፡ በመሆኑም፣ በአሁኑ ወቅት በግልና በመንግስት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ላሉት በርካታ ችግሮች አፋጣኝ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ብዙዎች የሚስማሙበት ጉዳይ ነው። መንግስት ተግባራዊ እያደረገ ያለው የትምህርት ፖሊሲ ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ የሲቪክ ማህበራትና ሌሎች በውይይት ተሳታፊ ሆነው በድጋሚ ሊፈተሽ እንደሚገባም በመፍትሄነት ይቀርባል፡፡ ‹‹የትምህርት ጥራት ከዴሞክራሲ ስርዓት

ተነጥሎ ሊታይ አይችልም። መንግስት ትምህርትና ተቋማቱን ከፖለቲካና ከካድሬዎች ነፃ ማድረግ አለበት›› በማለት ሌላ የመፍትሄ ሃሳብ የሚያቀርቡት የከፍተኛ ትምህርት ባለሙያ የሆኑት አቶ አስራት፣ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ካልተከበሩ፣ እንዲሁም መንግስት ተጠያቂ ካልሆነ የትምህርት ስርዓት ብቻውን በጥራት ሊወጣ እንደማይችል ያስገነዝባሉ፡፡ በተጨማሪም፣ በዘርፉ ያለው የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት መስተካከል እንደሚገባው፣ ተማሪዎችና መምህራኖች አካዳሚክ ነፃነት ማግኘት እንዳለባቸው፣ ተቋማቱ ዕውቀት የሚገበይባቸው እንጂ የፖለቲካ ማራመጃ ሜዳ መሆን እንደሌለባቸው፣ የትምህርት ሥራ ሙያ እንጂ ፖለቲካ አለመሆኑ፣ እንዲሁም በመልካም ተምሳሌትነት ሊጠቀሱ የሚገቡ የልሂቃን /Elite/ ት/ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች ሊፈጠሩ እንደሚገባ ችግሮቹን ለመቅረፍ በመፍትሄነት ቀርበዋል፡፡ ትምህርት በዋናነት መፍትሄ ሰጪ ዕውቀት ካላስጨበጠና ችግር ፈቺ መሳሪያ ካልሆነ ለብዙሃኑ እንደሚታደል መሰረታዊ ሸቀጥ ካየነው አደጋው የከፋ የሀገር እድገት እንቅፋት ከመሆን የዘለለ ሚና እንደማይጫወት የባለሙያዎች አስተያየት ነው፡፡

Page 6: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 20046 ኮመንትሪ

“ዴሞክራታይዜሽን ሰዎች የሚፈልጉትን ያውቃሉ፤ እናም ሳይሸራረፈ ለዘለቄታው ሊያገኙት ይገባቸዋል የሚል ንድፈ-ሃሳብ

ነው።”ኤች. ኤል. ሜንክን

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ እግጅ ምስኪን ሰዎች፣ መንግሥታቸው ምሳሌያዊውን እንጀራ በምሳሌያዊው ጠረጴዛ ላይ እስካኖረላቸው ድረስ የሚገዛቸው የመንግሥት አይነት እምብዛም ግድ አይላቸውም የሚለው ገለፃ እንዲሁ ተጨባጭነት የሌለው ሀቅ ነውን? እንዲሁም፣ በመሰል ሀገሪት ያሉ ያን ያህል ያልደኽዩ ሰዎች ከምስኪኖቹ በበለጥ የዴሞክራሲ ጉዳይ ያሳስባቸዋል የሚለውስ?አህጉሪቱን የዴሞክራሲያዊ አብዮቶች

እያጥለቀለቋት ከመሆኑ አንፃር፣ ከላይ በርዕስነት የተጠቀምኩት ጥያቄ የግዴታ መነሳት ያለበት ሆኗል። እንደ ሀገሪቱ ተቃዋሚዎች ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ጭረት ብቻ የሚጠባበቅ ጭራሮ ሆኗል ሲሉ ይሞግታሉ። ግን ያ ሙግታቸው እንዲሁ ቀቢፀ-ተስፋ ብቻ ነውን? “የተቃዋሚ ፓርቲዎች (ምርጫው) ኢ-ፍትሃዊ ነው እያሉ ከአሁኑ ውንጀላ በመሰንዘር ላይ ይገኛሉ፤ የህዝቡም መንፈስ በምንም መንገድ በ1997 ምርጫ ጊዜ እንደነበረው የጋለ አይደለም” ሲል አንድ የአልጃዚራ መጣጥፍ በባለፈው ምርጫ ወቅት [2002 ዓ.ም] ለተከታታዮቹ እድርሶ ነበር። (እንደተጠበቀውም በ2002 ገዥው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር - ኢህአዴግ - ሥልጣን ተቆጣጠረ።)

የኢትዮጵያ አልቦ ዴሞክራሲበአሁኑ ወቅት በኦክስፎርድ

ዩኒቨርስቲ የከፍተኛ ደረጀ ትምህርት ተማሪ የሆነው እና እስከ 2009 ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ ይታተምና ይሰራጭ፣ እንዲሁም በስፋት ተነባቢና ጠንካራ የመንግሥት ተቺ የነበረው አዲስ ነገር ጋዜጣ - በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ውጪ በድረ-ገፅ ሥራውን ቀትሏል - ኤግዚኩቲቭ ኤዲተር የሆነው አብይ ተክለማርያም፣ በ2009

የሰው ልጅ ሰው ስለሆነ፣ አፈጣጠሩ ተራራና ወንዝ ከተፈጠረበት አግባብ ወጣ ያለና ፍፁም የተለየ በመሆኑ ክብር ይገባዋል።

ይህ ዓይነቱ ክብር አንዳንዶች ገንዘብ በመርጨት ከሚያገኙት ሰው ሰራሽ ክብር እጅግ የራቀና የተራቀቀ፣ በመጨረሻ በምስጥ እና በአፈር አጣብቂኝ ውስጥ ከሚሰነቀር ፈራሽ ስጋ የተገኘ ገንቢ ክብር ነው - የሰው ልጅ የተሰጠው።

ሰዎች ሰው በመሆናቸው ብቻ ከሚያገኙት ክብር በተጨማሪ፣ ምድር ላይ ሲኖሩ በሚሰሩት መልካም ሥራ የሚያገኙት በሜዳሊያና በኒሻን የታጀበ ክብር አለ።

አንዳንድ ጊዜም በየአካባቢው (በየሀገሩ) በሚኖረው የአስተሳሰብ ዝቅጠት የተነሳ፣ በሚመለከተው አካል እና በማኅበረሰቡ ተገቢው እውቅና ያልተሰጣቸው፣ ክብራቸውን ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚያውቅላቸው ባለ ብዙ ክብር የሆኑ ሰዎች አሉ።

አንድ ሰው ስለራሱ መብት ሲከራከር ቢታይ ድርጊቱ ይበል

ያሰኛል እንጂ አያስገርምም። የሚያስገርመው ያ ሰው ከራሱ አልፎ ተርፎ ለሌሎች መብት ለመከራከር አጀንዳ ይዞ ሲመጣ ነው። ለራስ መከራከር ግዴታ ሲሆን ለሌሎች መከራከር ግን ውዴታ ነው። በአንዲት ውዴታ ብዙ ሰው ለማዳን መነሳት ደግሞ በእርግጥ ከክብሮች ሁሉ የላቀውን ክብር ያስገኛል። በተለይ ደግሞ ይህ ነው የሚባል ለቀቅ ያለ ነፃነት በሌለበት ሀገር ውስጥ ከራስ አልፎ ለሌላው መከራከር ‘ሜዳሊያ አልባ ጀግንነት’ ነው። ክብር የሚለካው አንድ አካል (መሥሪያ ቤት) በሚሰጠው ሜዳሊያ ብቻ ሳይሆን በማኅበረሰቡ ጭብጨባም ጭምር ነው።

ብዙዎች፣ በመረጡትና መንፈሳቸው እጃቸውን ይዞ ወደ መራቸው መስክ ሔደው ስለወገናቸው ተከራክረዋል። ብዙ ዓይነት የመከራከሪያ መስኮች አሉ። ሁሉም በየራሳቸው የባህርይ መጠን፣ ወርድና ስፋት ልክ ከበድ የሚል ፀባይ ቢኖራቸውም፣ የፖለቲካን መስክ ያህል የፅጌሬዳ እህት ኩባንያ የመሰለ ባህርይ የላቸውም። ‹‹አምሳለ ፅጌሬዳ›› ወይም የፅጌሬዳ እህት ኩባንያ ነው - የፖለቲካው መስክ።

ፅጌሬዳንም ሆነ ሥልጣንን /ፖለቲካን ሳይነኳቸው (ከሩቅም ሆነ ከቅርብ) ሲያዩዋቸው በጣም ያምራሉ። ሥልጣን ላይ ለመቀመጥም ሆነ ፅጌሬዳን ለመቅጠፍ ግን ከመወጋትም አልፎ ደም እስከመፍሰስ (እስከ መስጠት) የማድረስ መስዋዕትነት ሊጠይቅ ይችላል። ጠይቆም በተግባርም ሆነ በዶክመንታሪ ፊልም ታይቷል።

በዛ ላይ መስኩ (የፖለቲካው) ከሌላሙ መስክ በእጅጉ የሚለይበት የባህርይ ክብደት አለው። ልጁን በውጭ ድርጅት እርዳታ የሚያስተምር ሰው፣ በልጁ ስም የሚሰራውን ሸፍጥ ለማጋለጥ ግብግብ የሚፈጥረው ከአንድ የመያድ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋር ነው።

በፖለቲካው መስክ የሚሰራውን ሸፍጥ ለማጋለጥ የሚነሳ ሰው (ተከራካሪ) ግብግብ የሚፈጥረው፣ ታሪክ፣ የጦር ጄት፣ ፖሊስ ጣቢያ፣ ፍርድ ቤት . . . ካለው (ከያዘ) መንግስት ጋር ነው።

ከዚህ አንፃር የፖለቲካ መስክ የታንክ፣ የቦምብ፣ ሚሳየል … እሳቶች ተባብረው የሚነዱበት ‘አምሳለ ገሀነም’ ነው።

ዓይኑ እያየ፣ ጆሮው እየሰማ እዚህ እሳት ውስጥ ገብቶ

ለሌላው (ወገኖቹ) የሚከራከር ሰው ደግሞ ‘ኀብረተሰባዊ ጀግና’ ነው። ማኅበረሰቡም እንዲህ ላሉት ጀግኖች በግልፅ ሊያጨበጭብ ይገባል።

ምክንያቱም፣ ማኅበረሰቡ ለራሱ የሚከራከሩለትን ሰዎች የማያበረታታና የማያመሰግን፣ እንዲሁም ተገቢውን ክብር ማይሰጥ ከሆነ፣ በጊዜ ሂደት ስለወገናቸው የሚከራከሩ ሰዎች ሊጠፉና ሊነጥፉ ይችላል።

የተከራካሪ እጦት፣ በተለይ ደግሞ አያሌ ፖለቲካዊ ችግሮች ላሉበት ኅብረተሰብ፣ ቁጥሮችና ፎቶዎች ሊገልፁት ከሚችለው በላይ አስፈሪ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል።

አንድ ዓይነት ብቻ የፖለቲካ አሰፋፈር አሊያም አስተሳሰብ፣ በምንም ተዓምር ለአንዲት ሀገር ያውም ለብዙ ሚሊየን ህዝብ ይበቃል ተብሎ አይመከርም።

የሀገሪቱን የፖለቲካ መስክ የሚቆጣጠሩት ሰዎች በሁሉም ዘርፍ ‘ምቹ’ ቢሆኑ እንኳ፣ ሊቀናቀናቸው የሚገባ የማኅበረሰብ ጠበቃ (ተከራካሪ) ሊኖር ይገባል። ምክንያቱም፣ ምቹ የሆነ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ … መዋቅር በሌላና በከፍተኛ ደረጃ ምቹ በሆነ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መዋቅር ሊለወጥ ይችላል።

ውድድር የሚካሔደው ደግሞ በጥሩና በመጥፎ ወይም በጠንካራና በደካማ ሰዎች /አስተሳቦች መሐል ብቻ አይደለም። ጠንካራና ጠንካራ ሰዎችንም ሆነ አስተሳሰቦችን በማወዳደር እጅግ ጠንካራ አስተሳብ … ማግኘት እንደሚቻል መታመን አለበት። እጅግ ጠንካራ ሰው፣ አሰራር፣ አስተሳብ የሚገኘው ደግሞ በፖለቲካውም ሆነ በሌላው

መስክ ሰላማዊ ተቀናቃኞች ሲኖሩ ብቻ ነው።

እነዚህ ተቀናቃኞች ብቅ ብቅ የሚሉት ደግሞ በማኅበረሰቡ ሁነኛ ግፊት ነው። በተለይ በተለይ ለረዥም ዘመናት በውስብስብ ችግሮች ለተቃኙ የአፍሪካ ሀገራት፣ ከሰለጠኑ ሀገራት የበለጠ የማኅበረሰብ ተከራካሪ ያስፈልጋቸዋል።

ምንም እንኳን የአፍሪካ ሀገራት ከተተበተቡበት አርበ ሰፊ እና ሁለንተናዊ ችግር አኳያ ሲታይ ቁጥራቸው ይነስ እንጂ፣ ለጥቅስ የሚበቁ የማኅበረሰብ ተከራካሪዎች በየሀገራቸው ተነስተዋል።

ብዙ ዓመታት ሥልጣን ላይ ከመቆየታቸው የተነሳ ራሳቸውን እንደ አማልክት የሚያዩ እና መንበራቸው በመላዕክት እንደሚጠበቅ ለማሳመን ስብከት የጀመሩ ሰዎችን ለመቀናቀን ወደ ፖለቲካው መስክ መምጣት ከባድ ነው። ክብደቱ ደግሞ ከእስር አንስቶ እስከ ሞት ድረስ ባሉት ፈተናዎች ሁሉ ይመዘናል።

ጥቂት የማይባሉ አፍሪካውያን በየሀገራቸው ያለው የፖለትካ መስክ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ እያወቁ፣ ለማኅበረሰባቸው ሲሉ ታስረዋል፣ ተሰቅለዋል።

እውነት ለመናገር፣ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ለማኅበረሰብ ተከራካሪ ሆኖ ከመንግስት መንገድ ወጣ ማለት፣ መስቀል ይዞ ወደ ቀራንዮ ለመሔድ ቆርጦ መነሳት ነው። ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ብዙዎች በየሀገራቸው ተሰቅለዋል። እናም፣ “ክብር ለወገናችሁ መብቶች ለምትከራከሩ ሁሉ ይሁን”።

ውስጥ በተደረገ አንድ ቃለ-መጠይቅ፣ ከ1991 አንስቶ ኢትዮጵያን የገዟት ጠ/ሚኒስትር መለስ፣ የዴሞክራታይዜሽን ወሬን በመተው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል ወደሚሉት አጀንዳቸውን በመለወጥ ሂደት ላይ እንደሆኑ አመላክቶ ነበር። የዚሁ ቃለ-መጠይቅ ተከታይ በሆነ በ2010 ውስጥ በተደረገ ሌላ ቃለ-መጠይቅ፣ ‹‹መንግሥት ወደ ዴሞክራሲ ሽግግር እያደረገ ነው የሚለውን ማስመሰል ለመተው ወሰኗል። ቀድሞም ቢሆን ሽግግሩ ባለበት የሚረግጥ ነበር የሚል ስሜት ነበረን። አሁን ደግሞ ጭራሽ የኋሊት እያዘገበመ ነው። … እናም አሁን በጣም ውጤታማ የሆነ መሪ ገፅታ ለመከሰት እየተጣጣሩ ነው፤ ይህም ማለት የፈለ አምባገነን ቢሆኑ እንኳን፣ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ልማት እያመሁ ነው እንደማለት ነው›› ሲል ተናግሮ ነበር።በተጨማሪ፣ ልክ ጠ/ሚኒስትር

መለስ ዋነኛ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ አጋርነትን ከአውሮፓና አሜሪካ ወደ ቻይና ባዞሩበት ወቅት፣ በተመሳሳይ ‹‹በርድኬጅ›› የተሰኘ ዴሞክራሲ አስተዋወቀው ነበር፤ ያም በፖለቲካው ላይ ጠንካራ ውይይት ማካሄድን የተመለከተ ነበር። ያ በስፋት በሀገር ውስጥ ባይካሄድ እንኳን በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተተግብሯል። አቶ መለስ፣ “እንደ ዴ.አር.ሲ [ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ] አይደለንም - እንደ ቻይና እንጂ” ነበር ያሉት። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዋና ኃላፊ የሆኑት በረከት ስምኦን በቅርቡ በቻይና ካደረጉት ጉብኝት በኋለ የኢትዮጵያ ፕሬስ “ልማታዊ ጋዜጠኝነት”ን ሊተገብር ይገባል እስከማለት ድረስ ሄደው ነበር። በሌላ አገላለፅ፣ አግባብነት ያለው የጋዜጠኞች አስተዋጽኦ፣ ለመንግሥት ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች እንደ አጨብጫቢነት ሲሰሩ ነው ማለት ነው።ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋን ለማልማት

እየተሳናት እንዳይደል ማንም ባይሞግትም፣ የመንግሥት ፈጣንና ውጤታማ [የኢኮኖሚ ዕድገት] የተባሉት ግን እጅግ ለክርክር የሚጋብዙ ናቸው። በ2010 ውስጥ

እንዲህ ሲል አብይ ተናግሮ ነበር፡- “. . . ኢኮኖሚያዊ ፍትህ የዴሞክራሲ ዋልታ ነው - ወይም መሆን አለበት ተብሎ ይገመታል።” ሆኖም ግን በጣም የተለመደውን የኢኮኖሚ ኢ-ፍትሃዊነት መለኪያን (“ጂኒ ኮ’ፍሸንት”) ስንመለከት የልኬቱ ዝቅተኛነት የሚያረጋግጥልን ኢትዮጵያ ፍትሃዊ፣ በጣም ድሃ ወይም ሁለቱንም መሆኗን ነውን?ስለዚህም፣ አቶ መለስ ስለኢኮኖሚው

ትክክል ናቸው ተብሎ ቢወሰድ እንኳን፣ ያ የሚያሳየው ቀደም ሲል ሀገሪቱ እየተጓዘችበት ነበር ያሉት ጎዳና - የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ - በእርግጥም አስፈላጊነት የነበረው መሆኑን የሚጠቁም ነው። ሆኖም፣ የዴሞክራሲ አስፈላጊነት ፍላጎት አለ ብሎ ማለት ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲን ተርበዋል ማለት አይደለም። እንዲሁም፣ ቢፈልጉ እንኳን፣ ዴሞክራሲን ለመጠየቅ ይደፍራሉ ማለትም አይደለም።የኢትዮጵያ መንግሥት በህዝቡ ላይ

የቅርብ ክትትል የሚያደርግ ሲሆን ይህ ደግሞ በተለይ በሀገሪቱ ባሉ መንደሮች ኑዋሪ ገበሬዎች ላይ የጠነከረ ነው። ያለፈውን ምርጫ መንግሥት ‘በማሸነፉ’ ምክንያት በአሁኑ ወቅት ቀበሌዎች፣ ወይም አካባቢያዊ ምክር ቤቶች በመዳፎቹ ሥር በመሆናቸው ኢህአዴግ በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍሎች የፈቀደውን ማድረግ ተችሎታል። እንዲሁም በአቶ መለስ የተጀመረ ሀገር አቀፍ የስለላ መረብ አለ። ጥብቅ የፕሬስ ገደቦችና በሁሉም መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (መያዶች) የሚደረጉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን የሚከለክለው የቅርብ ጊዜው አዋጅ ተግባራዊ መሆናቸው የሚያሳዩት ከአዲስ አበባ በስተቀር በመላ ሀገሪቱ የመንግሥት ቁጥጥር መፈናፈኛ የሚያስጣ ደረጃ መድረሱን ነው። ብርቱ የመገንጠል ንቅናቄዎች ባለባቸው እንደ አጋዴን ባሉ ክልሎች ቁጥጥሩ ሙሉ በሙሉ ነው።ሌላው ይቅርና እንደ ኢትዮጵያ ባለች

አንዲት የተቀፈደደች ሀገር ውስጥ የ‹‹ህዝቡ ሰሜት›› ምን እንደሚመስል ፍንጭ ማግኘት በራሱ እጅግ አስቸጋሪ ነው። ስሙ/ሟ እንዳይጠቀስ በፈለገ/ች

የአዲስ አበባ ጋዜጠኛ ከሆነ፣ ገዥው ፓርቲ እስከ ቤተሰብ ድረስ ማኅበረሰቡን ይከታተላል። ዛሬ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ለሚያምኗቸው፣ የቅርብ የቤተሰብ አባል ካልሆነ በስተቀር ስለፖለቲካ ትንፋሽ እንኳን አይደሉም። በተለይ ጠንካራ ፉክክር በነበረባቸው ክልሎች ከጋዜጠኞች ጋር የተገናኙ ወይም ለኢህአዴግ ተወካዮች ድምፃቸውን ያልሰጡ መራጮች የበቀል እርምጃ የሚደርስባቸው ሲሆን፣ እንደ ምግብ ዕርዳታ ያሉ መሰረታዊ ጥቅሞችንም እስከመከልከል ድረስ በደል ይደርስባዋል።በከተማዎችስ? በተለይ ደግሞ በአዲስ

አበባ ውስጥ? የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ያለበት ደካማ ሁኔታ የሚያሳስበው አንድስ እንኳ አለን? ለምሳሌ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች? ምርጫዎችን ተከትሎ የፓርላማ መቀመጫቸውን ላለመውሰደ ከወሰኑበት 97 አንስቶ፣ ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ተሳትፎ ጠፍተዋል ማለት ይቻላል። ከጥር-የካቲት 2011 ድረስ በሀገሪቱ

ዋና መዲና አዲስ አበባ በነበረኝ የአንድ ሳምንት ቆይታ ወቅት ጋዜጠኞችን ብቻ ሳይሆን የታክሲ ሹፌሮችን፣ በእድሜ የገፉ ዜጎችን፣ አስተናጋጆችን፣ ድንገት ሱቆች፣ ሆቴሎች እና በሕዝብ ማመላለሻዎች ውስጥ ያገኘሁዋቸውን፣ እና በርካታ ከፍተኛ የትምህርት ደረጃ ያላቸውን ጨምሮ፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ ሰዎችን በመጠየቅ ለዚያ ጥያቄው የሆነ ምላሽ ለማግኘት ሙከራ አድርጌ ነበር።ብዙዎቹ ጋዜጠኞች የኢትዮጵያ

ዴሞክራሲ የሚያሳስባቸው መስላሉ። ነገር ግን ይህን የሚያሳስባቸውን የዴሞክራሲ ጉዳይ የሚመለከቱት በተለየ መንገድ ነው። የዳያስፖራ ድረ-ገጾች (እንደ አዲስ ነገር፣ ኢትዮጵያን ሪቪው ያሉት) የመንግሥትን አፈና በመቃወም ጠንካራ ተከታታይ ትችቶችን ይሰነዝራሉ። በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የሥርጭት ሚዲያዎች ልክ እንደ ኢንተርኔቱ ሁሉ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው ያሉት። ከለየላቸው የመንግሥት አቀንቃኝ

ጋዜጦች (አዲስ ዘመን) አንስቶ ከፍተኛ ጥንቃቄ እስከሚያሳዩት ድረስ የተለያዩ የህትመት ሚዲያዎች በሀገሪቱ ይገኛሉ። እንዲሁም፣ መንግሥትን አበክሮ የሚተች ቢያንስ በአንድ ጋዜጣ በሀገሪቱ ውስጥ ይገኛል - የዳዊት ከበደ አውራምባ ታይምስ።

ሁለት ጥልቅ ውይይቶች በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ላይ

ስለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ በይበልጥ የተወሳሰበና አስደማሚ ምላሸ ያጋጠመኝ የተናጠል ቃለ-መጠይቆችን ካደረግኋቸው ሁለት የአዲስ አበባ ኑዋሪዎች ነበር። ሁለቱም በጣም የተማሩ፣ የተሳካላቸው ሙያተኞች ሲሆኑ በእውቀት የበሰሉና አሁን ጡረታ የወጡ ናቸው። በ70ና 79 የዕድሜ ከልል ላይ የሚገኙት እነዚህ አዛውንቶች በኢትዮጵያ የተማሩ የሚባሉትን የሚወክሉ ናቸው ማለት ይቻላል። ለጥያቄው ፍጹም ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ምላሾችን ነበር የሰጡኝ። እውነተኛ ባልሆነው ስማቸው ‹‹ገብሬ›› እና ‹‹ሔኖክ›› እያልኩ እጠቅሳቸዋለሁ።አቶ ገብሬ የዳያስፖራ አባል ሲሆኑ፣

ቀንደኛ የመንግሥት ደጋፊ ናቸው። በሀገሪቱ የሰብዓዊ መብቶች ችግር አለ ብለው አያምኑም። ድህነትን ማስወገድ ይቀድማል ከሚለው የመንግሥት አቋም ጋር በተስማማ መልኩ፣ መንግሥት የሰብዓዊ መብቶችን /የዴሞክራሲን/ ጉዳይ በተመለከተ በአጠቃላይ እጅግ በጣም የተዋጣለት ሥራ እየሰራ ነው የሚል ዕምነት አላቸው። በሌላ አገላለፅ፣ ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈላጊ ነው ብለው አያስቡም ማለት ነው።በዝርዝር እንዳጫወቱኝ የግል

ታሪካቸው ከሆነ፣ ወጣት ሳሉ ከጠባብ የብሔር አስተሳሰብ ጋር በተያያዘ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም ተባረዋል። አቶ ገብሬ ትምህርታቸውን አጠናቀው በውጭ ሀገር ቤተሰብ ከመሰረቱ በኋላ ልክ ወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ሥልጣን እየተረከበ በነበረበት ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ። በኋላም

በታዲዎስ ጌታሁን

ክብር ለወገናችሁ መብቶች ለምትከራከሩ ሁሉ ይሁን

በሮን ሲንገር

“የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የሚያሳስበው ማን ነው?

የዴሞክራሲያዊ አብዮቶች ማዕበል አሕጉሪቱን እያጥለቀለቁ እንደመሆናቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የአብዮቶቹን ማዕበል የመቀላቀል ጉጉት ምን ያህል ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለዴሞክራታይዜሽን ማውራት ያቆሙ ነው የሚመስሉት። ግን ሕዝቡ ምንድን ነው የሚያስበው?

በ ገፅ 21

ብዙ ዓመታት ሥልጣን ላይ ከመቆየታቸው የተነሳ ራሳቸውን እንደ አማልክት የሚያዩ እና መንበራቸው በመላዕክት እንደሚጠበቅ ለማሳመን ስብከት የጀመሩ ሰዎችን ለመቀናቀን ወደ ፖለቲካው መስክ መምጣት

ከባድ ነው። ክብደቱ ደግሞ ከእስር አንስቶ እስከ ሞት ድረስ ባሉት ፈተናዎች ሁሉ ይመዘናል

Page 7: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

7

የ አቤቶ ወግአቤ ቶክቻው[email protected]

ኮመንትሪ

ይገርማል። መስከረም መጥባቱን፣ አዲስ ዘመን መግባቱን አውጀን ሳናበቃ ጊዜ በተለመደ ሩጫው አግለብልቦ የወሩ አጋማሽ አቅራቢያ አደረሰን። በአደይ መዐዛ ተመስሎ ያወደን የመታደሰ ጠረን፣ የለመለመ መስክ መልክ ይዞ ከፊታችን የተዘረጋው የእድልና የተስፋ መንፈስ ግን ተኩስነቱ ገና አልበረደም። ወላጆች፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎችና ሌሎች የኑሮ ውድነት ሰለባዎች የእንቁጣጣሽ የዞረ ድምር አወራርደው አልጨረሱም።

ተያይዞም ተማሪዎች ቦርሳዎቻቸውን ሸከፍከፍ፣ እርሳሶቻቸውን ቀረፅረፅ፣ የደንብ

ልብሶቻቸውን ተኮስኮስ አድርገው ለሌላ የትምህርት ዓመት ይንደረደሩ ጀምረዋል። የጡሩምባ ጩኸት፣ የደወል ቅጭልጭልታ፣ የአዋቂነትን ቁጥር ለመሻገር ጓጉተው የሚቁነጠነጡ ህፃናት ሰላምታ እና ጫጫታ አየሩን ሊሞሉ ተቃርበዋል።

እስኪ አንዱን ቀን ከውጣ ውረድዎ ሰዓት ሸራርፈው ያስተርፉና ወደ አንዱ ትምህርት ቤት ጎራ ይበሉ። ልጅዎትን አስከትለው እስከ አሁን ሄደው ካልሆነ ማለቴ ነው። ሁለተኛ ደረጃዎች ላይ ቢያተኩሩ እመርጣለሁ። በሩን አልፈው ወደ ግቢው መኃል ከዘለቁ ወዲያ ዙሪያ ገባውን ይቃኙ። ስኬት-ተኮር መፈክሮችን፣ አነቃቂ ጥቅሶችን፣ ደንቦችን እያነበቡ ይራመዱ። የመማሪያ ክፍሎችን ግድግዳዎችና መቀመጫዎች ከፈተሹ ግን የሚመለከቱት ከማነቃቃትና ተስፋ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማስከፋትና ማስቆዘም ሊያዘነብል ይችላል። የትምህርት-ጠል ትውልድ አርማዎችና አቋም መግለጫዎችን ማየት ብዙም አይገድም። በየስፍራው ተከትበውና ታትመው ተመልካች ላይ ይሳለቃሉ።

‹‹ትምህርት በኛ ይብቃ፤ ትውልድ ይዳን!››፣ ‹‹ለማያልቅ ትምህርት የሚያልቅ እድሜህን አትፍጅ!›› ዝነኛ ምክሮች ናቸው። እውቀት ለሚሰበክባቸው፣ ብርሃን ለሚረጭባቸው፣ ጥበብ ለሚደረስባቸው መቅደሶች የሚባለው በእውነቱ ምስጋና እንጅ ጥላቻ ነበር? ከአረፍተ ነገሮቹ ቅርፊት ስር ትምህርት ቤቶችን እንደማያመልጧቸው ማኅበረሰባዊ ወህኒዎች የሚቆጥር የአስተሳሰብ አስኳል መዋለሉን ለማስረገጥ አስረጂዎቻችን ራሳቸው ፅሁፎቹ

ናቸው።በእርግጥ ታዳጊዎች በእድሜ-

ወለድ ጀብደኝነት ስለሚጠቁና አትኩሮትን ለመስረቅ ባልተገባም አካሄድ ረጅም ርቀት መጓዝ ስለማይሳናቸው በየክፍሉ በሚያሰፍሩት ኃሳብ ሁሉ ያምኑበታል ብሎ መደምደም ይቸግራል። ሆኖም ዋናው ፍሬ ነገር ከላይ የጠቃቀስኳቸውን የመሳሰሉ ፌዘኛ አስተያየቶች ውለው ሲያድሩ ወደ ብርቱ እምነትነት ካደጉ መዘዛቸው ይከፋልና እናርማቸው ማለቱ ላይ ነው። በጥቃቅንነት ከረጢት ሸብበን ፊት የነሳናቸውና ክብደታቸውን ያልተረዳንላቸው ደቃቅ ድርጊቶች የገዘፉ አመለካከቶችን የመቅረፅ አቅም አያጡም።

ከመምህራኑም መካከል ቅዱስ ስራቸውን ወደማንቋሸሽ የሚያደሉ አይጠፉም። ትኩስ የመስከረም ፀሀይን እየማጉ አይኖቻቸው ግን መታከትን የሚያስነብቡ፣ ተጨማሪ ዓመት ከተማሪዎች ጋር ማሳለፍን እንደውርደትና ውድቀት አስበው ለራሳቸው ማስተባበያ የሚደረድሩ አስተማሪዎች ትውልድን እንደምን በአግባቡ ሊያንፁ ይቻላቸዋል? ሰንደቅ ዓላማ ሲሰቀል እየተጥመዘመዙ፣ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ከስልኮቻቸው ጋር እየተጨዋወቱ የአገር ፍቅርን መስበክ ይሆንላቸዋል?

በአካል ግዝፈት የሚመጣጠኑ ተማሪዎችና መምህሮቻቸው ትከሻ ለትከሻ ተገጫጭተው እንደጓደኛ ሲቃለዱ ይስተዋል ይዟል። በመካከላቸው ሲኖር የምናውቀው ርቀት ሲጠብ፣ ድንበር አካላዩ መስመር ሲፋቅ እየታዘብን ነው። የሚደንቀው መምህራኑ ሸጋ አመላቸውና የዳበረ ስብዕናቸው ሊኮረጅ የሚገባው

አወያዎች መሆናቸው እየቀረ በተቃራኒው የተማሪዎቻቸው አምሳያትን መምረጣቸው ነው። እንዲመሯቸው የሚጠብቋቸውን ታዳጊዎች ከብበው ማሽቃበጣቸው ነው።

ጉዳዩ በግል ትምህርት ቤቶች ሳይብስ አይቀርም። እዚያ ልዩ ዋጋ የሚያስገኘውን ተወዳጅነት ለመሸመት ኮስታራነት አያዋጣም። ቀደም ባለው ጊዜ ከአስተማሪነት ጋር ይያያዙ የነበሩ ባህርያት - ቁም ነገረኛነት፣ ስርዓት ወዳድነት፣ ደንብ አክባሪነት፣ መርህ አጥባቂነት - ማራኪነታቸውን አጥተዋል። አመክንዩው ‹‹ዘመኑ ተቀይሯል፤ የዛሬ ጊዜን ልጆች በፍቅር እንጂ የምትገዛቸው፤ ካመረርክባቸው አይሰሙህም›› የሚል ነው። ከላይ ከላይ ሲገረምሙት ቁልፍ እውነት ያዘለ አባባል ቢመስልም፣ ሀቁ ግን መወናበድ የፈጠረው ተልካሻ ሰበብ መሆኑን ነው። የተማሪዎች አቅም ዳብሯል። በመረጃ በየደቂቃው ይሞላሉ። የወላጆቻቸው ምጣኔ ሀብታዊ ከለላ ደንድኗል። መምህራኑ በአንፃሩ በሞያቸው ደረታቸውን የሚነፉበት ወቅት ጥሏቸው ነጉዷል። የልበ-ሙሉ ታዳጊዎቹን ቀልብ እንደምን እንደሚይዙ ግራ ተጋብተዋል።

በዘመናዊነት ስም የተምታቱት ግን እነርሱ ብቻ አይደሉም። አንዳንድ ‹ስልጡን ነን› ባይ ወላጆችም አሉ። የምዕራባውያንን ባህል ጠልቀው ሳይመረምሩ እፍታውን በጨረፍታ ጨልፈው ከመሰረታዊው የአስተዳደግ መርሆ ያፈነገጡ።

ለህፃናት የሚሰጠው እንክብካቤና ልጆች የሚያድጉበት አግባብ ከወትሮው በእጅጉ ተለይቷል። እነ‹‹ልጅ ያቦካው›› ታሪክ ወደመሆን ተቃርበዋል። ይገባቸውማል።

በደሳለኝ ስዩም

ነገር ግን ለልጆች ነፃነት መስጠት ማለት እንዳሻቸው እንዲሆኑ መረን መልቀቅ አይደለም። ፍላጎታቸውን ማሟላትና የሻቱትን ሁሉ እንዲጨብጡ መፍቀድ ለየቅል ናቸው። ፍቅር መለገስ ለጊዜውም ቢሆን ህመም ከሚፈጥሩት ጨዋነትን መተግበርና በስራ ለመትጋት መነሳሳት ሊከለክል አይገባውም።

እንደሚባኝ ዘመን የቱንም ያህል ቢቀያየር፣ ዓለም በስልጣኔ ብትተኮስ፣ የምድር ስሬት ቢገለባበጥ የመልካም መምህርና የጥሩ ወላጅ መሰረታዊ መለኪያዎች ዘላቂና ሁለንተናዊ ናቸው። በቀጣዩ ትውልድ ሰናይና እኩይ የሚባሉ ንፍቀ ክበቦች እንዳሉ ማሳወቅ፤ ሁልጊዜም ወደበጎው እንዲያዘምሙ በቃላትም በተግባርም ማሳየት፤ መዳረሻው አዘቅት ከሆነው የጨለማ መንገድ ተጠብቀው የብርሃንን ጎዳና እንዲመርጡ የማስተዋልን ፀጋ ማስተዋወቅ። ሌላው ነገር ሁሉ ተከታይ ነው።

አልታደልንም መሰለኝ ፍሬያችንን ጥለን ለገለባ እንማልላለን። መልካም ሁነቶች ስንቀስም እንኳ ሥርና ግንዱን ትተን ቅርፊቱን እንጎትታለን። ልንመስላቸው የምንጋጋጥላቸው ምዕራባውያን ለህፃናት ሰፊ ነፃነትን ሲሸልሙ ጎን ለጎን ግዴታዎቻቸውን የማይታለፉ ወሰኖቻቸውን ቁልጭ አድርገው ባያሳዩ፣ በትምህርት ተቋሞቻቸው ተማሪዎች ከአስተማሪዎቻቸው ተጠግተው እውቀት የሚቃርሙ ጥመኞች እንዲሆኑ ባይደክሙ ስቴፈን ሀውኪንጎች፣ ቢል ጌትሶች እና ኦባማዎች ይኖሯቸው ነበር?

ልጆቻቸው አናታቸው ላይ እስኪወጡ ያረመሙ ወላጆችን ባየሁ ጊዜ የተሰማኝ ስሜት ከዚህ ብዙም አይርቅም።

ከ“ዘመኑ ተቀይሯል” ባሻገርበቃልኪዳን ይበልጣል

ዛሬም የሰዎች የምሬት መንስኤ አቅጣጫውንና መልኩን እየቀያየረ ከህዝቡ ጋር ይኖራል። ምንም ያህል ሰሚ ባያገኙም ሰዉ ከማማረርና ከመጠየቅ ያልቦዘነባቸው ብዙ ማኅበራዊ ጣጣዎች አሉ።

ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ያረጁ ቤቶች መፍረሳቸው እንደሚቀጥል በሬዲዮ ሲነገር ሰማሁ። ልብ በሉ፤ አሁን እኔ የሚያስደነግጠኝ የአረጁ ቤቶች መፍረስ አይደለም። ሀገር ብትሰለጥን፣ ከተማዋ ብትዘምን፣ ኑሮው ቢሻሻል ለአንድ ዜጋ የሀሴት ምንጭ እንደሆነ የታወቀ ነው።

ባለፈው ዓመት ቤቶች ሲፈርሱ ከአንድ ቤት ስንት አባወራ አለ የሚል ስሌት የተሰራ አይመስለኝም። በሌላ አባባል ለቤቱ ባለቤት ከሚሰጥ ምትክ ውጭ ተከራይተው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የት ይገባሉ የሚል ቅድመ ዝግጅት አልተደረገም ይመስለኛል።

በዚህ ምክንያት የአራት ኪሎ መፍረስ ከካዛንችስ እስከ ሽሮ-ሜዳ፣ ከፒያሳ እስከ ፈረንሳይ ለጋሲዮን የቤት መወደድን

አስከትሏል። /አጥንቼው አይደለም፤ ቤት ለመከራየት በጠቀስኳቸው አካባቢዎች ስጠይቅ አክርዮች የሚሰጡኝ ምክንያት ነው።/

የቤት እጥረት ብዙ ችግር እየፈጠረ ይመስለኛል። ግለሰቦች ቤቶችን /ለዚያውም ግብር የማይከፍሉበት/ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ ያከራያሉ። ተከራዮችም ቤት በማይመስል ደሳሳ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ አማራጭ አሳጥቷቸዋል።

ይህ የቤት እጥረት ችግር ደግሞ ልጆች ላላቸው፣ ትዳር ለመሰረቱ ተከራዮች ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማስተዋል ይቻላል። የአከራይን ግላዊ ባህርይ ችሎ ከአቅም በላይ የሆነ ኪራይ ተከፍሎ ልቀቅ ሲባል እቃ አጓጉዞ ወዘተ መኖር የራስ-ምታት ነው። በነገራችን ላይ ይሄ በሀገሪቱ ኢኮኖሚም ሆነ የሥልጣኔ ጉዞ የራሱ የሆነ ተፅዕኖ ያለው ይመስለኛል።

አንድ ዜጋ ሰርቶ ሊያመርት ወይም በጥሩ ሁኔታ ሊያገለግል የሚችለው በተርጋጋ ማኅበራዊው ኑሮ ውስጥ ሲኖር ነው። ከስራ ውሎ የሚገባበት

ወይም አድሮ የሚወጣበት ቤቱ የራስ-ምታት መንስኤ ከሆነ ይህ ሰራተኛ ውጤታማ ሊሆን አይችልም።

ለምን እንደሆነ ባይገባኝም አከራዮችም የተከራይን ችግር ለመፍታት አይደለም ለመስማትም ጆሮ ዳባ ልበስ ይላሉ። ዜጎችና ዜጎች መተሳሰብ ማጣታቸው እውነት የእድገት ምልክት ይሆን እንዴ?

አዲስ አበባ ውስጥ የቤት ፈላጊው ቁጥር እለት በእለት እየበዛ ነው። የከተማው የቤቶች ግንባታ ደግሞ ከፈላጊው ብዛት ጋር የሚመጣጠን አይደለም። ኮንዶሚኒየም ቤት ከዓመታት በፊት የተመዘገቡ እስከ ዛሬ ያልደረሳቸው አሉ። ይህ ብቻ አይደለም፤ አሁን የቤትን ጉዳይ አናስተናግድም የሚሉ ማስታወቂያዎች በየወረዳ አስተዳደሩ በር ላይ ተለጥፎ ማየት የተለመደ ሆኗል።

ለኮንዶሚኒየም ቤት ምዝገባ የለም። የቀበሌ ቤት የለም። ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት የሚቻልበት ሌላ መንገድ አልተፈጠረም። ችግሩ ግን እለት በእለት እየተባባሰ ነው። በነገራችን ላይ ይህን የምፅፈው እንዲሁ አይደለም። ራሴን ማሳያ አድርጌ ማቅረብ እችላለሁ። ከወርሃዊ ገቢዬ 62% (ስልሳ ሁለት በመቶ) ለቤት ኪራይ እከፍላለሁ። ከዚህ በሚተርፈኝ ገንዘብ ኑሮዬን እየመራሁ ነው በዘመነ ትራንስፎርሜሽን ውስጥ አለሁ የምለው? (ያስቃል ወይስ ያሰገርማል?)

መ ን ግ ስ ት መፍትሄዎችን በብዛት መቀየስ ያለበት ይመስለኛል። በጋራ ተደራጅተው ለሚመጡ /በመስሪያ ቤት፣ በሙያ፣ በእድሜ ወዘተ/ የቤት መስሪያ ቦታዎች እያዘጋጀ ቢያቀርብ፣ በመለስተኛ ዋጋ

ለኪራይ የሚቀርቡ ቤቶችን በብዛት ቢሰራ ችግሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቅረፍ የሚችል ይመስለኛል።

በነገራችን ላይ፣ ስለሕግ ወይም ስለደንቡ የማውቀው ዝርዝር ጉዳይ ባይኖርም፣ አንድ ዜጋ በራሱ ሀገር ላይ ሊኖርበት የሚችልበት ቦታ ማጣት ያለበት አይመስለኝም። አቅሙን ባመጣጠነ፣ ፍላጎቱን በተመረኮዘ ሁኔታ መጠለያ ሊያገኝ ይገባዋል። መሬት ኃብት ነው ቢባልም፣ ኃብትነቱ ለሕዝብ እንጂ ለመንግሥት ብቻ አይደለም። አዎ፤ መንግሥት በታላቅ ቁልፍ ዘግቶ የሚጠብቀው፣ እየቀነጠሰም አቅም በማይችል ዋጋ የሚሸጠው ነገር መሆን የለበትም።

የኅብረተሰቡን አቅም ያመጣጠነ፣ ቢያንስ ለአንድ ቤት ማረፊያ የሚሆን ቦታ ማቅረብ የመብት ጉዳይ ይመስለኛል።

ሌላው፡-አሁን ድረስ ማባሪያ

ያጣው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች እንደ ልብ አለመገኘት ነው። ዋጋው ደግሞ እያደር ይቆለላል።

የአዲስ አበባ ከተማ የትራስፖርት ፍላጎት ከዕለት ዕለት ሲጨምር ነው የምናየው። በየጊዜው አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ቢገቡም፣ የነዋሪውን ፍላጎት ማሟላት አልቻሉም። አሁንም ታክሲ ላይ መጋፋት፣ መራገጥ የተለመደ ነው።

አንዳንዶችን ለመግፋትና ለመርገጥ የምናባክነውን ጉልበት ለምን በእግራችን አንሄድበትም ብለን እንወስንና ደግሞ ሌላ ችግር ይገጥመናል።

ከታክሲ አተረፍናት ያልናት ሳንቲም የሰው ብርጭቆ ሰብረን ካሳ እንከፍላታለን። ለመሆኑ የሚኖረን አማራጭ

ሰላም ለእናንተ ይሁን! ይህ ከዚህ በታች

የሰፈረው ቃል በአንድ ቀደም ባለ መጽሐፍ ውስጥ የተፃፈ ነው - በ1986። እና እንደ ትንቢት አየሁት ወይስ የዛሬውን ብሶቴን ለመፃፍ መነሻ አደረግሁት?

“ … ነጋ ጠባ ሰልፍ ነው። መበደበኛ ሥራ ሰልፍ ነው ማለት ይቻላል። ሰልፈኞች ጩኸው፣ ጩኸው ሲደክማቸው ይበተናሉ። ከሁሉም ያስደነቀኝ ሰልፍ ታዲያ የምዕራብ አዲስ አበባ ህዝብ ተሰልፎ ያቀረበው ጥያቄ ነበር። ጥያቄውም፣ ‹‹መቀበሪያ ቦታ አጣን፤ ይሰጠን›› የሚል ነበር። … እንግዲህ ሁሉም ሞቱን አውቆ ለአስከሬን ማስቀመጫ ቦታ ይጠይቃል። እኔ ለአንገቴ ማስገቢያ ጎጆ የምቀልስበት ቦታ አጣሁ ብዬ ስበሳጭ፣ ለካ ለአስከሬን መጣያም ሶስት ክንድ መሬት ይቸግራል።”

(ቅሌት) አንዳርጌ መስፍን፤ ገፅ 148

ቀደም ብዬ እንደጠቀስሁት፣ ይህ መጽሐፍ የታተመው በ1986 ዓ.ም ነው። ከአስራ ሰባት ዓመት በፊት ማለት ነው። ዛሬስ?

“ በ ገፅ 18

አንዳንድ ምሬቶች

መንግስት መፍትሄዎችን በብዛት መቀየስ ያለበት ይመስለኛል። በጋራ ተደራጅተው ለሚመጡ /በመስሪያ ቤት፣ በሙያ፣ በእድሜ ወዘተ/ የቤት መስሪያ ቦታዎች እያዘጋጀ ቢያቀርብ፣ በመለስተኛ ዋጋ ለኪራይ

የሚቀርቡ ቤቶችን በብዛት ቢሰራ ችግሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ መቅረፍ የሚችል ይመስለኛል።

በአካል ግዝፈት የሚመጣጠኑ ተማሪዎችና

መምህሮቻቸው ትከሻ ለትከሻ ተገጫጭተው እንደጓደኛ

ሲቃለዱ ይስተዋል ይዟል። በመካከላቸው ሲኖር

የምናውቀው ርቀት ሲጠብ፣ ድንበር አካላዩ መስመር

ሲፋቅ እየታዘብን ነው። የሚደንቀው መምህራኑ

ሸጋ አመላቸውና የዳበረ ስብዕናቸው ሊኮረጅ

የሚገባው አወያዎች መሆናቸው እየቀረ በተቃራኒው

የተማሪዎቻቸው አምሳያትን መምረጣቸው ነው

Page 8: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 20048 ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 9: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

9

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 10: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 200410

p Ç T@ S ´ “ —

‹‹ህዝቡ እንዲያውቅልን የምንፈልገው፣ የጣቢያው ኃላፊዎች በእነ መቲ ላይ የዲስፕሊን እርምጃ መውሰዳቸውን ነው››ሰይፉ ፋንታሁን

‹‹እኔ መገለባበጥን የማውቀው በጅምናስቲክ ካልሆነ በቀር ልምዱም፣ ችሎታውም አስተዳደጌም የሚፈቅድልኝ አይደለሁም››ተቦርነ (ተወልደ) በየነ

እንደመነሻአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል፣

በአዲሱ ዓመት የመድረክ ቲያትሮችንና ፊልሞችን፤ እንዲሁም ለህትመት የሚቀርቡ መፅሐፎችን አበርክቶ ለማበረታት እና ለማገዝ የበኩሏን ሚና ለመጫወት አቅዳለች። በዚህም መሰረት በወር ሁለት ፊልሞችን፣ አንድ ቲያትር እና አንድ መፅሐፍን በሂሳዊ ዕይታ በመቃኘት ከተደራሲያን እና ከኪነጥበብ ሙያ ጋር የምትቆራኝበት አምድ መድባለች። እነሆ በ2004 ዓ.ም ለዕይታ ከበቁ ፊልሞች መሀል በቀዳሚነት የምንዳስሰው ‹‹ሰውየው›› የተሰኘውን ፊልም ነው።

ሰውየውከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደአሸን እየፈሉና

ለተመልካች ዕይታ እየቀረቡ ካሉ ፊልሞች አንዱ፣ በሸዋፈራሁ ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው ‹‹ሰውየው›› የተሰኘው ፊልም ነው። የፊልሙ ደራሲ አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝ

ነው። ድርሰቱን ወደ ፊልም ፅሁፍ (script) የለወጠው አክሊሉ ኃ/ማርያም ሲሆን፣ አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝን ጨምሮ፣ ሽመላሽ ለጋስ፣ ፀደይ መስፍን፣ ይገረም ደጀኔ፣ ወለላ አሰፋ፣ ኤርምያስ ሙሉጌታ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ ሔኖክ ብርሃኑ እና ሒወቴ ብርሃኑ ተውነውበታል።

የፊልሙ ታሪክ ዋነኛ ጭብጥየፊልሙ ዋና ነገረ ጉዳይ ወይም ማጠንጠኛ

ሀብት ነው። የዚያ ሀብት ባለቤት ደግሞ ‹‹ሰውዬው›› ነው። ሰውዬው ሀብቱን ከየትና እንዴት አመጣው? ከሀብቱ በስተጀርባ ያለው ምስጢር ምንድነው? ምስጢሩን ለመጠበቅ ምን ተግባር ፈፀመ? ለምን? ወዘተ። እነዚህ መጠይቆች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ያገኙበት ፊልም ነው። በአጭሩ የፊልሙ ዋነኛ ጭብጥ ‹‹ከእያንዳንዱ ሀብት በስተጀርባ አንድ ወንጀል አለ›› የሚለውን ብሒል መሠረት ያደረገ ነው ማለት ይቻላል። ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ በ10 ሰዓት

በዮፍታሄ ሲኒማ፣ ቅዳሜ በ10 ሰዓትና እሁድ በ12 ሰዓት በእምቢልታ ሆቴል፣ ማክሰኞ በ12 ሰዓት፣ ሐሙስ ከምሽቱ 2.40 እና አርብ በ8 ሰዓት በዓለም ሲኒማ፣ እንዲሁም በሌሎች ሲኒማ ቤቶች በመታየት ላይ የሚገኘው ‹‹ሰውየው›› ፊልም የ1 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ጊዜ የሚፈጅ ነው።

የፊልሙ ዘውግ‹‹ሰውየው›› ፊልም ልብ አንጠልጣይ

(suspense) ተብለው ከሚፈረጁ የፊልም ዘውግ የሚመደብ ነው። ይህ ፊልም 1.35 ደቂቃ በሚፈጅ ጊዜ ውስጥ፣ የ20 ዓመት ታሪክን ጠቅልሎ የያዘ ነው። ፊልሙ በ3 ደቂቃ ውስጥ ተመልካቾች የታሪኩን ሴራ እንዲጨብጡ በማድረግ ረገድ ተሳክቶለታል። የታሪኩን መዋቅር በመገንባት፣ ሴራውን በፍጥነት በማቀጣጠል እና በማጦዝ ረገድ የተመልካችን ህሊና ሰቅዞ መያዝም ችሏል። ለዚህ አባባል አብነት የምናደርገው ይህንን ሂሳዊ ግምገማ ያቀረበው ፀሐፊ ማክሰኞ ምሽት በዮፍታሄ ሲኒማ በተገኘበት ወቅት ታድመው የነበሩ ተመልካቾች በሙሉ እስከ ፍፃሜው ድረስ ትንፋሻቸውን ሰብስበው በፅሞና ‹‹ሰውየው››ን መከታተላቸውን ነው። ይህ ደግሞ ለፊልሙ

ልብ አንጠልጣይነት ከበቂ በላይ ምስክርነት ይሰጣል ብሎ ያምናል። የፊልሙ ጥራት (የካሜራ አጠቃቀም) እና

የድምፅ ግብአት ከሞላ ጎደል መልካም ነው ማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ ተገቢው ጥንቃቄ ተደርጎበታል ማለት የሚስችል አይደለም። ምክንያቱም አንዳንድ ቦታዎች ላይ የተዋናዮቹ ንግግር በወጉ አይደመጥም። ምነው ቢሉ? ፊልም ማለት ድምፅና ምስል እኩል ህብር የሚፈጥሩበት ጥበብ ነው። ከዚህ አንፃር ስንመዝነው በፊልም ጥበብ ውስጥ ሹክሹክታ እንኳን የጩኸት ያህል (እኩል) በተመልካች ዘንድ መደመጥ አለበት ማለት ነው። በ‹‹ሰውየው›› ፊልም ውስጥ ግን ጥቂት ቃለ-ተውኔቶች በወጉ የሚሰሙ አልሆኑም። ይህም ብቻ አይደለም፤ የፊልም ህብራዊ ውጤት የሰመረ ይሆን ዘንድ ወሳኝነት እንዳለው የሚነገርለት (sound track) የመሸጋገሪያ ሙዚቃ ስሜት በሚሰጥ መልኩ የተቀናበረበትም አይደለም። እንዲያም ይባል እንጂ ‹‹ሰውየው›› ፊልም

የሰከነ እና አንዳች ቁምነገርን የሚያስጨበጥ ሀሳብን መሰረት ያደረገ፣ ሴራው በሚገባ የተወሳሰበ፣ የታሪኩ ጡዘት እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ልብን የሚያንጠለጥል፣ አጨራረሱ እፎይታ የሚሰጥ (Happy ending)እና የሚስደስት፣ የተዋጣለት ሥራ መሆኑን መካድ አይቻልም። ይህም የሀገራችን የፊልም ጥበብ ከትርኪምርኪና ከአጓጓል አስቂኝ ተብዬ ሥራ ወጣ እያለና እየሰከነ መሄዱን አመላካች ነው ብዬ አስባለሁ። በመልካም ጅምርነቱም ሊወደስ ይገባል።

‹‹ሰውየው›› በእርግጥም …‹ሰውየው› በእርግጥም አዲስ ነገርን አሳይቷል

ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ‹‹ሰውየው›› ተብሎ ለፊልሙ ስያሜነት የተመረጠውን እና አቶ ክፍሉ የተሰኘውን ዋና ገፀ ባህርይ ወክሎ የተጫወተው አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ነው።ሸዋፈራሁ ደሳለኝ በኪነ ጥበበ አፍቃሪዎች

ዘንድ አስቂኝ ገፀ ባህርይ በመጫወት የሚታወቅ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። እንዲያውም አንዳንዶች ‹‹ካለማሳቅ በስተቀር ትወና አያውቅም እንዴ?›› እያሉ ሲነቅፉትም ይሰማ ነበር። የቃለ-ተውኔቱ አሰነዛዘሩ፣ የፊቱ ገፅታ ወዘተ ሁሉ ሳቅ-በግዴ የሚያመጡ ነበሩ። ‹ሰውየው› ፊልም ላይ ግን ሸዋፈራሁ ደሳለኝ ሰዉን አጓጉል ለማሳቅ መጣደፉን እና ተንቀዝቃዥ እንቅስቃሴውን ወዘተ እርግፍ አድርጎ በመጣል ችሎታውን አሳይቶበታል። በእርግጥም አርቲስት ማለት ሁሉንም አይነት ገፀ ባህርይ የሚችል ነው (ሰናዩንም እኩዩንም) የሚለውን ዕውነት በገሀድ ማሳየት ችሏል። አልፎ አልፎ የፊቱ ገፅታ ላይ የአስቂኝ ባህርይ ተፅዕኖ ሽው ቢልበትም፣ የሰከነ እና መረር ያለ ገፀ-ባህርይ መጫወት እንደሚችል ያሳየበት፣ ትወናውን በአሸናፊነት የተወጣበት ሥራ ነው። ከዚህ ሌላ በ‹‹ሰውየው›› ፊልም ውስጥ የተሳተፉት (Actors) ተዋንያን በጥቅሉ የተሰጣቸውን ገፀ ባህርያት በመጫወት ረገድ የተዋጣላቸው መሆናቸውን አለመመስከር ንፉግነት ነው። ሆኖም ግን ፊልሙ ፍፁም የተዋጣለትና እንከን የለሽ ነው ማለት አይቻልም። ምነው ቢሉ፣

በቀላሉ ሊታረሙ የሚችሉ፣ በመጠነኛ ትኩረት ሊነቀሱ የሚገባቸው ጥቃቅን ህፀፆች ያስተናገደ መሆኑ በደካማ ጎንነት የሚታዩ ናቸው።

የፊልሙ ደካማ ጎኖችፊልም፣ አንዳች ታሪክ ላይ የሚመሰረት

የሰው ልጆች ህይወትን ማሳያ የኪነጥበብ ዘርፍ ነው። ያንን ታሪክ ከመነሻው እስከመድረሻው የሚያጓጉዙት ደግሞ ገፀ ባህርያት ናቸው። እነዚህ የገሀዱ ዓለም ውክልና የሚሰጣቸው ገፀባህርያት ታዲያ ተዓማኒነት ይኖራቸው ዘንድ ግድ ነው። ተዓማኒነት ፈርጀ ብዙ ሁነቶች ያሉት ነው። በገፀ ባህርያቱ የእርስ በእርስ ግንኙነት፣ በዕለት ተዕለት ተግባራቸውና ድርጊታቸው ወዘተ ሁሉ ምክንያታዊ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ከዚህ አንፃር ‹‹ሰውዬው›› ፊልም መጠነኛ ድክመት የታየበት ነው ማለት ይቻላል። ለምሳሌ ያህል ኤደን የተሰኘችውን ገፀ-ባህርይ የወከለችው ተዋናይ (ፀደይ መስፍን) የኋላ ኋላ ፍቅረኛ ያደረገችውን ወሰን የተባለውን ገፀባህርይ (ይገረም ደጀኔ) የተዋወቀችበት ሁኔታ ፍፁም የሚያሳምን አይደለም። ከእሷ የኋላ ታሪክ አኳያ በአንድ ሰው የመርጋት ዝንባሌ የሌላት መሆኑ በአፅንኦት ተነግሮናልና። ሆኖም ግን ፍቅረኛዋን የቀረበችበት ስልት፣ ያንን ሰው በግድ ወደ ፊልሙ ታሪክ ውስጥ ጎትቶ ለማስገባት የተደረገ ነው የሚመስለው። በአጭሩ አቀራረቧ አያሳምንም። ነገር ግን በፊልሙ አጠቃላይ ታሪክና ልብ አንጠልጣይነት የተነሳ ይህ ድክመት በተመልካች ዘንድ ቦታ ያልተሰጠው (የማይሰጠው) መሆን ችሏል፤ ወይም ተሸፍኗል። ይሁን እንጂ በየትኛውም ታሪክ ውስጥ የሚቀረፁ ገፀ ባህርያቶች ወደ ታሪኩ ሲገቡም ሆነ ሲወጡ (ሲለዩ) ተዓማኒነት ሊኖራቸው ግድ ነው።ከዚህ ሌላ በፊልሙ ታሪክ ውስጥ በቅድመ-

ንግርነት የተመረጠው ስልት ከሌላ የጥበብ ሥራ ተፅዕኖ ያልተላቀቀ መሆኑ በደካማ ጎንነት ሊጠቀስ ይገባል። ቅድመ ንግር የታሪኩ ሂደትና መደምደሚያን (ፍፃሜን) ከዋናው ታሪክ ጋር ተዛምዶ በሌለው ተግባር ወይም ክስተት(ግለ-ጨዋታ፣ ውርርድ፣ ገጠመኝ ወዘተ) አማካኝነት አስቀድሞ መናገር ወይም መጠቆም ነው። ‹‹ሰውየው›› ፊልም ለቅድመ ንግርነት የተጠቀመበት ዘዴ ካርታ ጨዋታን ነው። በገመና ድራማ አቶ ለይኩን እና ሉሲ (አባትና ልጅ እንደሆኑ ልብ ይሏል) ቼዝ በመጫወት በድራማው ታሪክ ውስጥ የሚገጥማቸውን ውድቀትና ስኬት አስቀድመው ለተመልካች ይጠቁሙ እንደነበር ያስታውሷል። በ‹‹ሰውየው›› ፊልም ውስጥ ካርታ ጨዋታ ነው ለቅድመ-ንግርነት የተመረጠው። ይህንን ዓይነቱን ጨዋታ ማንኛውም ሰው፣ በየትኛውም ቦታና ሁኔታ ሊጫወተው የሚችል ቢሆንም፣ የገፀ ባህርያቱ የዘወትር ልምድ መሆኑ በሚገባ አልተገለፀም። በፊልሙ መነሻ ካርታ ሲጫወቱ የምናያቸው ገፀባህርያት ጨዋታው የዘወትር ልምዳቸው መሆኑን በአፅንኦት ማሳየት የሚያስችሉና የሚያሳምኑ በርካታ አጋጣሚዎችን መጠቀምም ይቻል ነበር። እነዚያን መልካም አጋጣሚዎች አለመጠቀም የጎላ ባይባልም ራሱን የቻለ ድክመት ነው። ከዚህ በተጨማሪ በፊልሙ መጨረሻ አካባቢ

የሚታየው ፍጥነትም ሊታሰብበት ይገባ ነበር ባይ ነኝ። እርግጥ ነው፤ ፊልም በድርጊት የሚገለፅ፣ እንቅስቃሴና ፍጥነት የሚያይልበት ጥበብ ነው። በሌላ አነጋገር፣ በንግግር ቁጥብ መሆንን፣ በድርጊትና በእንቅስቃሴ ፍጥነት ታሪክን አጉልቶ ማሳየት ማለት ነው። ይሁን እንጂ ከመጠን በላይ የሆነ ፍጥነት ለቅስፈት እንደሚዳርግ የሚካድ አይደለም። ‹‹ሰውየው›› ፊልም በታሪኩ ፍፃሜ ድርጊትን ወይም ሁኔታዎችን በአናት በአናቱ እያከታተለ ያሳየበት ፍጥነት የፊልሙን እድሜ የቀጨ ከመሆኑ ባሻገር፣ የታሪኩን ፍሰትና ተዓማኒነት አጠራጣሪ አድርገታል።ከዚህና ከዚህ መሰል ጥቃቅን ግድፈቶች ውጪ

በአጠቃላይ ፊልሙን ስንመዝነው፣ በጠንካራ የታሪክ መሰረት ላይ የተገነባ፣ አስተማሪና አዝናኝ፣ ከሁሉም በላይ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ በልብ አንጠልጣይነት የተሳካለት መሆኑ አሌ የሚባል አይደለም። ለዚህም ነው የፊልሙ ታዳሚያን በፍፁም ፅሞና እና ካለ አንዳች ኮሽታ እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ፊልሙን የተከታተሉት። ይህም የተመልካችን መንፈስ ማሸነፍ የቻለ ፊልም ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው። ለማንኛውም የ‹‹ሰውየው››ን ፊልም ዳሰሳ የምንቋጨው ቀሪውን አስተያየት ለፊልም አፍቃሪያን በመተው ነው።ቸር ክራሞት!!

“ሰውየው”ን

በጨረፍታ

በፊልሙ መጨረሻ አካባቢ የሚታየው ፍጥነትም ሊታሰብበት ይገባ ነበር ባይ ነኝ። እርግጥ ነው፤ ፊልም በድርጊት የሚገለፅ፣ እንቅስቃሴና ፍጥነት

የሚያይልበት ጥበብ ነው። በሌላ አነጋገር፣ በንግግር ቁጥብ መሆንን፣ በድርጊትና በእንቅስቃሴ ፍጥነት ታሪክን አጉልቶ ማሳየት ማለት ነው።

ይሁን እንጂ ከመጠን በላይ የሆነ ፍጥነት ለቅስፈት እንደሚዳርግ የሚካድ አይደለም።

የፊልሙ ርዕስ፡- ሰውየው የፊልሙ ደራሲ፡- ሸዋፈራሁ ደሳለኝ የፊልም (script) ፅሁፍ፡- አክሊሉ ኃ/ማርያም የፊልሙ ዳይሬክተር፡- ሸዋፈራሁ ደሳለኝ የፊልሙ ዘውግ፡- ልብ አንጠልጣይ ፊልሙ የሚፈጀው ጊዜ፡- 1 ሰዓት ከ35 ደቂቃ

በንፍታሌም

Page 11: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

11

p Ç T@ S ´ “ —አ ፍታ1

ቢጢቆ ልበልሽ ስናፍቅሽ?ደስ ባለሽ እና በተመቸሽ ጥሪኝ ሁለቱም መጠሪያዎቼ ናቸው ማለት ይቻላል። እስከ ዛሬ ቢጢቆን እያስታወሱ በእሷ የሚጠሩኝ አሉ።

ከአስር ዓመት በፊት በኢቴቪ ይተላለፍ የነበረውን አካፑልኮ ቤይን ቦሌ ት/ቤት ከጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ ጋር [የፋና ብሮድካስቲንግ ባልደረባ ነው] ትተርኩ ነበር። አይደል?አዎ ታስታውሽዋለሽ? [እኔ መረጃውን አግኝቼ ነው። በጣም አዳማጭ እንደነበራችሁ ሰምቻለሁ።]

ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር ስትገናኚ በየትኛው ስራሽ ያስታውሱሻል?በመድረክ ሥራ ብዙዎች የሚያስታውሱኝ በ‹‹እግዜር ጣት›› ቲያትር ነው። በቴሌቪዥን ደግሞ ቢጢቆን (ያልተኬደበት መንገድን) ነው በብዛት የሚያስታውሱት። አሁንም መድረክ ስወጣ ተመልካቾች ቢጢቆ እያሉ ይጠሩኛል። ይህ ሥራ በሰው አዕምሮ ውስጥ ተቀርጾ የቀረው ሳይካበድ ቀለል ተደርጎ በመሰራቱ ይመስለኛል።

ብዙ ጊዜ የሞልቃቃ፣ ነገረኛና የቡና ቤት ሴትን ገፀ-ባህሪያትን ወክለሽ ትጫወቻለሽ፡፡ ተውኔቱ ቢለያይም የአንቺ አተዋወን [የአፍ እንቅስቃሴሽ ሳይቀር] ይመሳሰላል። ለምንድን ነው?ምንም የተለየ ነገር የለውም፡፡ ለነዚህ ገፀ-ባህሪያት ‹‹ትሆናለች›› ተብዬ ስለምመረጥ ነው። እነዚህ ገፀ-ባህሪያት ያሉባቸውን ተውኔቶች የሰራኋቸው በብሔራዊ ቴአትር ነው። ሌላው ነገር የገፀ-ባህሪያቱ እድሜ ተመሳሳይ ነው። ለምሳሌ ባቢሎን በሳሎንና ደመ-ነፍስን ብትመለከቺ ሁለቱም ተመሳሳይ እድሜ ያላቸው ናቸው። በብሔራዊ ቴያትር ውስጥ የእነዚህን ገፀ-ባህሪ እድሜ ልወክል የምችለው እኔ ነኝ። እንዲህ አይነት ተውኔት ከመጣ ለእኔ ነው የሚሰጠኝ፤ ከእድሜ አንፃር ማለቴ ነው።

በተለይ ደመ-ነፍስና ባቢሎን በሳሎን ላይ የአተዋወን መመሳሰል ጎልቶ ይታያል አንቺስ አይምታቱብሽም?ለእኔ አይመሳሰሉብኝም። በደንብ አድርጌ እጫወታቸዋለሁ። ሁለቱን ገፀ-ባህሪያት የሚያመሳስላቸው ሞልቃቃነታቸው ነው እንጂ አንዷ የቡና ቤት፣ ሌላዋ ደግሞ የቤት ልጅ ናቸው። ሰው እንደሚመሳሰሉ የሚገምተው ሁለቱ ቲያትሮች በተከታታይ በአንድ ሳምንት ውስጥ መሰራታቸው ነው።

በቀጣይ በተለየ ገፀ-ባህሪ ራስሽን ለመፈተን አስበሻል?እነዚያን አይነት ገፀ-ባህሪያት ብቻ የምሰራው ግድ ስለሆነብኝ ነው። ጨርሶ እንደነዚህ ማለትም የሞልቃቃ፣ ነገረኛና የቡና ቤት ሴት ገፀ-ባህሪዎችን ባልሰራ ነው ደስ የሚለኝ።

ለምን?ምክንያቱም ሰው በአንድ አይነት ገፀ-ባህሪ ይለምድሽና ያንን ብቻ የምትችይና ለሌላ ገፀ-ባህሪ የማትመቺ አድርጎ ይወስድሸል። ይሄ በስራሽ ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል። ከላይ ከጠቀስናቸው ገፀ-ባህሪያት ወጣ ያሉ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃሁ እኮ! ለምሳሌ መርዛማ ጥላ ላይ በጣም የተለየች ገፀ-ባህሪ ናት። በጣም የምታሳዝን፣ አካል ጉዳተኛ የሆነችና በእንጀራ አባቷ የተደፈረች ናት፡፡ ይህንን ሁሉ አጣምራ የያዘች ካራክተር ናት።‹‹አዳብና›› ላይ ያለችዋም እንደዚያው አሳዛኝ ናት። አሁን ዋናው ችግር ባቢሎን በሳሎንና ደመ-ነፍስ በተከታታይ በአንድ ሳምንት መታየታቸው ነው፡፡ የሆነ ሆኖ ወጣ ያሉትንም ባህሪያት መስራት እችላለሁ ለማለት ነው።

በአዲስ ዓመት ዕለት የአስታጥቃቸው ይሁን ድርሰት የሆነን አጭር ድራማ አዘጋጅተሽና ተውነሽ በብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ተመልክተንሻል። ወደ አዘጋጅነቱ ዳርዳር እያልሽ ነው?እስካሁንም እንዲህ አይነት እድል ስላላጋጠመኝ ነው እንጂ ፍላጎቱ ነበረኝ። በአሁኑ ሰዓት በብሔራዊ ቴአትር ብዙ አዳዲስና አሪፍ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው። አሁን አሁን ንድፈ ሀሳብ አቅርበሽና ተፈትነሽ ካለፍሽ ማዘጋጀት ትችያለሽ፡፡ ከዚህ በፊት አቅምም ችሎታም ቢኖርሽ የአዘጋጅነቱ እድል በተወሰኑ ሰዎች እጅ ብቻ ነበር ያለው፡፡ አሁን እሱ ቀርቶ ጥሩ ጊዜ መጥቷል በቢ.ፒ.አር ጥናት አቅምና ችሎታ ካለ ተወዳድሮ መስራት ይቻላል። እኔም የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆን ተወዳድሬ ነው ድራማውን ያዘጋጀሁት። በቀጣይም

የአዘቦት ቀን ተውኔቶች ለማዘጋጀት እወዳደራለሁ። ሌሎች ተዋንያንም ለማዘጋጀት ተወዳድረው ያለፉ አሉ።

ገንዘብ የማይከፈልሽ ቢሆን በኪነ ጥበብ ውስጥ ትቆዪ ነበር?ይህ የህልውና ጥያቄ ነው። የምንወሻሸው ነገር አይኖርም። ሰው ሲኖር ቢያንስ ለመሰረታዊ ነገሮች ማሟያ ገንዘብ ያስፈልገዋል። ሌላ ተጨማሪ ስራና ገቢ ሳይኖረኝ ሁሌ ቲያትርና ፊልም እየሰራሁ ገንዘብ ከሌለ እንዴት እኖራለሁ? ሌላውን ተይውና ከቤቴ እዚህ ለመምጣት የትራንስፖርት ገንዘብ ያስፈልገኛል፡፡ [እዚህ የምትለው ቆይታውን ያደረግበት በብሔራዊ ቴአትር ግቢ ውስጥ ከአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም ጋር በምትጋራው ቢሮዋ ውስጥ ነው] ቋሚ ስራ ብለሽ ስትሰሪ ገንዘብ ማግኘት አለብሽ፡፡ የፈለግኩት ገብቶሻል አይደል? በቃ መኖር አለብኝ። ሌላ ቋሚ ሥራና ገቢ ኖሮሽ ለፍቅሩና ለፍላጎቱ ብለሽ የምትሰሪው ስራ ይኖራል። ግን ከመስራት መኖር ይቀድማል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚማርክሽ መልከ-መልካም ወንድ ማን ነው?አይ … ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ነገሮችን አስቤያቸው

አላውቅም። ግን ደግሞ ድንገት ፊልም ላይ አይተሻቸው ደስ የሚሉሽ አክተሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ‹‹ይሄ ቁመናው፣ መልኩ ለፊልም በጣም ይመቻል›› ብለሽ አድንቀሽ ከዚያ በኋላ የማታስታውሻቸው አሉ አይደል? ከዚያ ውጪ አዕምሮዬ ውስጥ ተቀርጾ የቀረ እከሌ ብዬ ልጠራው የምችለው መልከ-መልካም ሰው ለጊዜው አላስታውስም። ያ ማለት ግን መልከ መልካም ወንዶች የሉም ለማለት አይደለም።

ቶዮታ ኮሮላ- ሀች ባክ መኪና እንደምታሽከረክሪ አውቃለሁ። የትራፊክ ህግ ጥሰሽ ተቀጥተሽ ታውቂያለሽ?አዎ! እንደማንኛውም ሰው እኔም እሳሳታለሁ። አንድ ሁለት ጊዜ ተሳስቼ ተከስሼ አውቃለሁ።

ጥፋቶችሽ ምን ምን ነበሩ?አንደኛውን እንኳን የኔ ጥፋት ነው ማለት አልችልም። ምክንያቱም ቀኙ መስመር የእሱ ስለነበር ደርባኛለች ብሎ ክላክስ ነፍቶ ነው ለትራፊክ ያስያዘኝ። የከፋ ነገር አላደረስኩም። ምንም ይሁን ምንም የእሱ መስመር ስለነበረ ነው። ሌላው ደግሞ የማስቆሚያ መብራት ከበራ በኋላ መቆም ሲገባኝ ሄደሻል ተብዬ ነው። በነገራችን ላይ በጣም የሚያስተምሩሽ ጥሩ ጥሩ ትራፊክ ፖሊሶች አሉ።

ሰበብ ፈልገው የሚቀጡ ትራፊክ ፖሊሶችም እንዳሉ ይነገራል አጋጥሞሻል?ኦኦ… [በጣም እየሳቀች] እኔ እስካሁን ያጋጠሙኝ ጥሩዎች ናቸው፡፡ ሰበብ ፈላጊዎቸ አላጋጠሙኝም [ከዚህ በኋላ ህግ ብትጥስ ትራፊኮች እንዳይጨክኑባት የምትለማመጥ ትመስላለች።] በተቻለኝ መጠን የምነዳው በጣም ተጠንቅቄ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ብዙ ጥፋት ሰርቼ አላውቅም።

ታላቁ የአባይ ግድብ የሚገነባው በየትኛው ክልል እንደሆነ አስታውሺኝ?እኔ ሄጄ ባላየውም የሙያ አጋሮቼ ሄደው ጎብኝተውታል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተገነባ እንዳለም አውቃለሁ። አንድ ቀን ሄጄ እንደማየው ተስፋ አደርጋለሁ። እኔ እድለኛ ነኝ የምልበት አጋጣሚ ምን መሰለሽ ባቢሎን በሳሎንን ይዘን ባህር ዳር ሄደን በነበረበት ጊዜ አባይን ከመነሻው ጀምሮ ለማየት ችያለሁ። መነሻውን ብቻ ሳይሆን ከጣና ጋር እንዴት እንደሚቀላቀል ሁሉ ነው ያየሁት፡፡

“የሞልቃቃ፣ ነገረኛና የቡና ቤት ሴት

ገፀ-ባህሪዎችን ባልሰራ ደስ ይለኛል”ስናፍቅሽ ተስፋዬ

ወደ ሰባት ያህል የመድረክ ሥራዎች ላይ ተውናለች፡፡ ኢቴቪ 2 ይተላለፍ በነበረው ‹‹ያልተኬደበት መንገድ›› ተከታታይ ድራማ ላይ ‹‹ቢጢቆ›› የተሰኘችን ገፀ-ባህሪ ወክላ ከተጫወተች በኋላ ‹‹ቢጢቆ›› መጠሪያዋ ሆኗል። ‹‹ከመስራት መኖር ይቀድማል›› የትለው ስናፍቅሽ ተስፋዬ አንዳፍታ ከናፍቆት ዮሴፍ ጋር ቆይታ አድርጋለች።

አንድ ሰው ዜግነቱን ሊነጠቅ የሚችለው መቼ ነው? አንቺ ለምሳሌ ኢትዮጵያዊት ነሽ ዜግነትሽ ሊገፈፍ የሚችለው መቼ ይመስልሻል?መቼም [ተጠራጠረች] ምናልባት ከአገር ስትወጪ ይሆን? አ…አ… ይሄም አይሆንም። ምክንያቱም ከአገር ውጪ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ አይደል እንዴ?

በሚገባ!ስለዚህ አንቀጽ ጠቅሼ ባልናገርም ወንጀለኛ እንኳን ብትሆኚ በዜግነትሽ ትዳኛለሽ እንጂ ዜግነትሽ የሚገፈፍበት ሁኔታ አለ ብዬ አላምንም። [በጣም ትክክል! ሀሳብሽን ለማጠናከር የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት፣ አንቀጽ 33 የዜግነት መብቶች በሚል ርዕስ ስር፤ ቁጥር አንድ ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ኢትዮጰያዊት ከፈቃዱ/ዷ ውጪ ዜግነቱን/ቷን ሊገፈፍ እንደማይችል ይደነግጋል።]

ቆይታችን እዚህጋ ይብቃ… ስናፍቅሽ እንግዲህ ስናፍቅሽ ደውይልኝ [ሳቅ]ሊበቃም ይገባል። ብዙ አፋጠጥሽኝ እኮ! ሌላ ጥያቄ አልመልስልሽም እሺ! [በጣም እየሳቀች]… እሺ ስትናፍቂኝ ደውልልሻለሁ። [የሚያምረውን ሳቋን ለቀቀችው፤ በረዥሙ።]

የምንወሻሸው ነገር አይኖርም። ሰው ሲኖር ቢያንስ ለመሰረታዊ ነገሮች ማሟያ

ገንዘብ ያስፈልገዋል። ሌላ ተጨማሪ ስራና ገቢ ሳይኖረኝ ሁሌ ቲያትርና ፊልም

እየሰራሁ ገንዘብ ከሌለ እንዴት እኖራለሁ? ሌላውን ተይውና ከቤቴ እዚህ

ለመምጣት የትራንስፖርት ገንዘብ ያስፈልገኛል

ሙሽራዋ ቀረች

በአቤል አለማየሁ

250 የሚሆኑ እንግዶች ተጠርተዋል። ዱር ዱር ባንድ ትልልቅ ስፒከር ሰድሮ ሙዚቃውን ለማቅረብ እየተሰናዳ ነው። የአዳራሽ አስዋቢዎች መሰናዷቸውን ጨርሰው አዳራሹን አስጊጠውታል። ህዝቡ እየተንጠባጠበ ቢሆንም መምጣት ጀምሯል። ሙሽራዋ ግን በመጥፊቷ መደናገጥ ተፈጠረ። ለሰውም በስልክ እና በሩ ድረስ ሲመጡ ተነግሮ አዳራሹ ተዘጋ፤ ይህ ከትላንት በስቲያ መገናኛ በተለምዶ 24 ቀበሌ ከሚባለው ሰፈር የሚገኘው ወረዳ 5 ወጣቶች ማዕከል አዳራሽ የተፈጠረ አስገራሚ ክስተት ነው።

ስምንት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ አሜሪካ የኖረው ዳውድ መሀመድ ወደ አዲስ አበባ ከመጣ አስር ቀን አልሞላውም፤ የአጎቱ ልጅ ከሆነችው ‹‹ንማ›› ከተባለች ወጣት ጋር በትዳር ለመቆራኘት። ጥንዶቹ አንድ ሳምንት ሙሉ አብረው እያደሩ አሳልፈዋል። ረቡዕ ምሽትም አብረው አድረው እስከ ሀሙስ ጠዋት ሰላማዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ምንጮች ይገልፃሉ።

ታዳሚው አዳራሽ ከተጠራበት 12 ሰዓት በፊት በባህላቸው መሠረት ሙሽሪት ‹‹ሻሽ የማሰር›› ፕሮግራም ስለምትከውን የምትይዘውን የተሽሞነሞነ አበባ ይዘው፣ የቪዲዩ ካሜራ ባለሙያዎች ቤት ከደረሱ በኋላ ነው። ከሰዓታት በፊት ፀጉር ቤት ስትዋብ የነበረችውን ሙሽራ የበላ ‹‹ጅብ›› አልጮህ አለ። ድንጋጤው የሁሉ ሰው ሆነ።

ሙሽሪት ወደ የት እንዳቀናች የታወቀው የዚያው ሰፈር የላዳ ታክሲ ሾፌር ሌሊቱን ወደ ጅጅጋ ለመጓዝ ትኬት ለመቁረጥ እንደሸኛት ከተናገረ በኋላ ነበር። ሙሽራው ስላልተረጋጋ ምንም መናገር አልፈለገም። እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ሙሽሪት እንደወሰደችው ባይረጋገጥም ዳውድ መጠኑ ያልታወቀ ብር ጠፍቶታል።

ሃቄ ስፖርት ለሜሪጆይ ድጋፍ ለገሰ

ሃቄ ንግድና ኢንዱስትሪ ኢንተርፕራይዝ 13 ሺህ ብር የሚገመቱ የተለያዩ ነባር የአልባሳት ምርቶቹን ለሜሪጆይ የልማት ተራድኦ ድርጅት በትናንትናው እለትበድጋፍ መልክ ሰጠ። ድጋፉንም የኢንተርፕራይዙ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሀኑ ሀቄ ለሜሪጆይ የልማት ተራድኦ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ለሆኑት ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ አስረክበዋል፡፡ 30ኛ የምስረታ በአሉን መስከረም 27/2004 ዓ.ም እንደሚያከብር የሚገልፀው የኢንተርፕራይዙ መግለጫ፣ ከዚህ በተጨማሪ በሜሪጆይ ድርጅት ከሚረዱ ሕፃናት መካከል የአራት እና የ12 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ወንድምና እህት ሕፃናትን ባሉበት ድርጅት ስር እንዳሉ በቋሚነት ወርሃዊ ወጪያቸውን ለመሸፈን ቃል ገብቷል።

የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ

71ኛ ዓመት ልደት ይከበራል

የክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ 71ኛ ዓመት የልደት በዓል መስከረም 17 ቀን 2004 ዓ.ም በብሄራዊ ትያትር አዳራሽ እንደሚከበር አዘጋጅ ኮሚቴው አስታወቀ። ሀሙስ ጠዋት በብሄራዊ ቴአትር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ‹‹ሕዝብ ጀግና የሚላቸው በየትኛውም ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች ከሞቱም በኋላ የራሳቸው ቀን ተሰጥቷቸው እንዲታወሱ የአርቲስቱ ልደት መከበር በር ይከፍታል›› ተብሏል። በዕለቱ የጥላሁን አድናቂዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የገለፀው አዘጋጅ ኮሚቴው የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ድግሶች እንደሚቀርቡም ጨምሮ ገልጿል። የአርቲስቱ ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኖች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ ዘፈኖቹን የማሰባሰብ፣ ዶክመንተሪ ፊልሙ የማዘጋጀት እና የሀውልት ሥራ እንቅስቃሴው የማከናውኑ ተግባር በሂደት ላይ መሆኑን በዕለቱ የተናገሩት የአርቲስቱ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ብዙ፣ የተገለፁት ነገሮች ሲጠናቀቁ ለሚዲያ ይፋ እንደሚያደረጉ ገልፀዋል።

Page 12: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 200412አንድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ‹‹ሰሞንኛ›› የሚለውን ቃል፣ ‹‹ከዕሁድ እስከ ዕሁድ የሚያገለግል ሰው›› ሲል

ይተረጉመዋል። እኔም የሰማሁትን ላሰማዎ፣ ያየሁትን ላሳይዎ፣ ትጉ ሰሞነኛ አገልጋይዎ መሆንን ወደድሁ።

ሰ ሞ ነ ኛ

ከወጋየሁ ታምራት

እንዴት ሰነበታችሁ ወዳጆቼ? … እኔ ሰሞነኛ አገልጋይዎ እርስዎን ለመድረስ ከላይም ከታችም

የቃረምኩትን የወግ ቁርጥ ልቆርጥ ቢላዋ እያፋጨሁ ነው። ቁርጥን በወግ እንቃመሰው እንጂ አራት ኪሎ፣ ጊዮርጊስ፣ ልደታና የመሳሰሉት አካባቢማ ሄደን ቢላዋ ማፋጨት ከተውን ከርመናል። እኔማ ይሄ ቀይ እና ነጭ ነገር ስሙም ጠፍቶኛል። ስሙ ስጋ ነበር ስጋት? ወደ ፊት የሚወለዱ ህፃናት ‹‹ድሮ እኮ ስጋ እንበላ ነበር›› ብንላቸው የሚያምኑኝ አይመስለኝም። እንደ አያያዙ የስጋ ዋጋ ንሮ ለመብላት ሳይሆን ለማየት የምንሽቀዳደምበት ቀን እንዳይመጣ ዱአ ማድረግ ነው።ስጋችንን ቦርቡረው ገብተው

የሚያሰጉን ጉዳዮች ጨምረዋል። የታክሲ ዋጋ መጨመር አንዱ ምክንያት ነው። ይህንን በኋላ ላይ ተመልሰን ነካ ነካ እያደረግን እነሆ በረከት እንባባላለን። ይቅርታ ‹‹በረከት›› የሚለውን ስጦታ ብላችሁ አንብቡት። ልክ ነኛ! እኒህ የታች ሰፈር ልጆች ልማታዊነትን ይልመዱት ብዬ ‹‹ኧረ ሎተሪ’ንኳ አዙሩ›› ብላቸው ነገር ማዞር ጀመሯ! ለነገሩ ቢያዞሩትም መልሰን ቦታው ላይ ማስቀመጥ ስለተማርን ችግር የለብንም። እኔምለው ግን የእኛ ሰፈር ልጆች የጨለምተኝነታቸውን ሂስ በመስከረሟ ፀሀይ አወራርደው ስልቅጥ ሳያደረጉ አይቀርም ወይም ደግሞ ፉገራ ጀምረዋል። አሃ! አልሰሙም’ንዴ የገጠሙትን? ቆዩኝማ… ስልጣን እማልፈልግ ለእስር

እማልቸኩል

ከጠሀዩ መንግስት እሰራለሁ እኩል የኑሮ መላው ገብቷቸው

ይሆን? እንዴት ግን? ብላቸው ‹‹የኑሮ አቋራጩን ባነንነው›› ብለውኛል። የግጥማቸው ኪናዊ ለዛው እንደቡና ደጋፊዎች ገራሚ አይደል? የወደቀን ገንዘብ ያገኘ እንደሚያነሳው ጨዋታንም ጨዋታ ያነሳው የለ? ቡናዎች ሻምፒዮን በመሆናቸው በተሸለሙት ብር መጠን ቅር መሰኘታቸው ለእኔም ስለተጋባብኝ ይመዝገብልኝማ! ዋንጫ በልተው ከፍተኛው 21 ሺህ ብር ከተሸለመ ዋንጫ ቢያጡ ኖሮ 21 ሺህ ብር ያስከፍሏቸው ነበር ባዮችን ሰምቻለሁ። ‹‹አባይ ተጀምሯል። ቡና ዋንጫ

በልቷል።…›› የሚለውን ዜማ … አንዱ ቱሪናፋ ‹‹አባይ ይገደባል፣ መንግስት ይገደዳል›› ልንል ነው አለኝ። ከማስገደድ መለመን አይሻልም? ብለው ልመናን ከአገራችን እናጥፋ ብለው ከጠ/ሚኒስትሩ ፎቶ ጋር መስቀል አደባባይ ሰቅለውታል አለኛ! አሃ! ልመናን ቻው ብንለው የማይቀር አበልጃችን ነው መች ይቀራል? ብለው ልጁ ዋዘኛ እንዳይመስልዎ! የተቀዋሚ መንፈስ ከነከራማዎቹ

“ስልጣን እማልፈልግ ለእስር እማልቸኩልከጠሀዩ መንግስት እሰራለሁ እኩል”

አቋራጩን የመረጡ

‹‹አባይ ተጀምሯል። ቡና ዋንጫ በልቷል።…›› የሚለውን ዜማ … አንዱ

ቱሪናፋ ‹‹አባይ ይገደባል፣ መንግስት ይገደዳል›› ልንል ነው አለኝ።

ከማስገደድ መለመን አይሻልም? ብለው ልመናን ከአገራችን እናጥፋ

ብለው ከጠ/ሚኒስትሩ ፎቶ ጋር መስቀል አደባባይ ሰቅለውታል አለኛ!

በ ገፅ 18

Page 13: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

እ ን ግ ዳ

13ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

Page 14: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

እ ን ግ ዳ

14

ዓ ለም አቀፍ

በሱራፍኤል ግርማ

ሴት ልጅን መምታትና መስደብ ነውር በሆነባት ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ያልተለመዱና እጅግ አሰቃቂ የሆኑ ጥቃቶች እየተበራከቱ መጥተዋል። ከአሰቃቂነቱ የተነሳ በአገር አቀፍ ደረጃ የመነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በካሚላት ላይ የተፈፀመው የአሲድ ጥቃት ከኢትዮጵያውያን አዕምሮ ሳይጠፋ የሶስት ልጆች እናት በሆነችው ትዕግስት መኮንን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ተፈፅሞ፣ ወጣቷ ከብዙ ስቃይ በኋላ ማረፏ የብዙዎችን ልብ ያደማ ነበር።

አሁን ደግሞ ከጥቂት ቀናት ወዲህ ሌሎች የሚረብሹ ዜናዎች አየሩን ተቆጣጥረውታል። የቀድሞ ባለቤቷ ሁለቱንም ዓይኖቿን በስለት ወግቶ ያፈሰሰባት የወጣት አበራሽ ኃይላይ ጉዳይ እና በወለጋ መንዲ ነዋሪ በሆነችው ቤቴል አዲሱ ላይ የተፈጸመው ተጨማሪ የአሲድ ጥቃት፣ ‹‹ወደየት እየሄድን ነው?›› የሚለው ጥያቄ እንዲነሳ ያስገድዳል።

የእንደነዚህ ዓይነት አሰቃቂ ጥቃቶች መበራከትም ‹‹የኢትዮጵያዊነት ዕሴት›› እየጠፋ ለመምጣቱ ማሳያ መሆኑ እየተገለፀ ነው።

ምክንያቱ ምንድን ነው?የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በሴቶች

ላይ ስለሚፈፀሙ ጥቃቶች በ2008 (እ.አ.አ) ባከናወነው ጥናት ለጥቃቶቹ መንስዔዎች ያላቸውን ዘርዝሯል፡፡ በጥናቱ መሠረት በአመዛኙ በቅርብ ሰዎቻቸው በተለይም በትዳርና በፍቅር አጋሮቻቸው ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶች የራሳቸው ገቢ የሌላቸው ናቸው፡፡

ጥናቱን ያከናወነው ማኅበር የሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር የሆኑት ዜናዬ ታደሰም ለአውራምባ ታይምስ እንደገለፁት፣ ከእንደዚህ ዓይነት ጥቃቶች በስተጀርባ ሴቷ ለወንዱ ተገዢ እንድትሆን መፈለግና ‹‹እንዴት ከእኔ ተሻለች?›› የሚል ቅናት አለ።

ምንም እንኳን በርካታ ጥናቶችና በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች የኢኮኖሚ ሁኔታን ለጥቃቶቹ በምክንያትነት ቢያስቀምጡም፣ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች የሆነችው የትነበርሽ ንጉሴ፣ ‹‹ይሄ የተሳሳተ አስተያየት ነው። በአሁኑ ሰዓት ‘ኮ ጥቃት እየደረሰባቸው ያሉት የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ሴቶች ናቸው›› በማለት ለእንደዚህ ዓይነት ጥቃቶች ዋና መንስዔ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የሞራል ዝቅጠት መሆኑን ታስረዳለች፡፡

መጥበቅ የሚያስፈልገው

የሕግ ማዕቀፍበየጊዜው የሚስተዋሉትን አሰቃቂ ጥቃቶች ተከትሎ

ወደ አዕምሮ፣ ‹‹ለሴቶች የሚያደርግ የሕግ ከለላ የለም እንዴ?›› የሚል ጥያቄ መምጣቱ አይቀርም። ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ወገኖች የሚገኘው መልስም፣ ‹‹አዎ፤ የኢትዮጵያ ሕጎች ለሴቶች በቂ ጥበቃ የሚሰጡ አይደሉም›› የሚል ነው።

በሕግ ባለሙያዋ ዜናዬ ታደሰ ገለፃ መሰረት፣ ምንም እንኳን የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚመለከት ድንጋጌ ቢኖርም፣ ድንጋጌው ያስቀመጠው ቅጣት ሥርዓተ-ጾታን ከግምት ውስጥ ያስገባ ካለመሆኑ በላይ፣ ሳይጋቡ በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ያሉ ጥንዶችን እና የተፋቱ ሰዎችን አይመለከትም።

በሴቶች ላይ ጥቃት ባደረሱ ወንጀለኞች ላይ የሚበየነው የቅጣት ማነስ የሚያሳስባቸው የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዳይሬክተር፣ ‹‹የሚጣሉት ቅጣቶች ኅብረተሰቡን የሚያሰተምሩና ሴቶችን ከጥቃት የሚከላከሉ አይደሉም›› ይላሉ። በማያያዝም፣ ‹‹የቤት ውስጥ ጥቃት›› የሚለው ትርጓሜ ሌሎች ዓለም አቀፍ ሰነዶች በሚተረጉሙት መልኩ ግድያን አካቶ አሰቃቂነቱን እንዲያስገነዝብ ሆኖ ሊቀመጥ እንደሚገባም ያስገነዝባሉ።

ከቅጣት ማነስና ከሕግ ክፍተት ባሻገር የፍትሕ ሥርዓቱ የገንዘብ አቅማቸው በፈረጠመ ወንጀለኞች ቁጥጥር ሥር መውደቁን የሚናገሩም ጥቂቶች አይደሉም። በሥርዓተ-ጾታ ላይ ዕውቀትና ልምድ ያላቸው ዳኞች በአሻጥር ከቦታቸው እንዲነሱ እየተደረገ መሆኑን የምትናገረው የትነበርሽ፣ ‹‹እዚህ አገር ‘ኮ በርካታ ፋይሎች በብርጭቆ ነው የሚዘጉት›› ስትል ትዝብቷን ታካፍላለች።

ከመብት ተሟጋቾቹና ከሕግ ባለሙያዎቹ በተጨማሪም፣ ‹‹ዋነኛ የሥራ ኃላፊነቴ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው›› የሚለው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ የህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮም፣ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚያደርሱ ወንጀለኞች የሚበየንባቸው ቅጣት በቂ አለመሆኑን ያምናል፡፡

ትኩረት የተነፈገው ዛቻምንም እንኳን በማንኛውም ግለሰብ ላይ አደጋ

ለማድረስ በመግለፅ መዛት በሕግ የሚያስቀጣ ወንጀል ቢሆንም፣ አሁን ባለው ሁኔታ በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው የሕግ ባለሙያዎች ያሳስባሉ፡፡ እንደባለሙያዎቹ አባባል፣ አሰቃቂ ጥቃት ከተፈፀመባቸው ኢትዮጵያውያን መካከል በቁጥር የሚያመዝኑት ከጥቃቱ በፊት ሲደርስባቸው የቆየውን ተደጋጋሚ ዛቻ ለፖሊስ ቢያመለክቱም፣ ይህ ማመልከቻቸው ግን በሚመለከተው አካል ተገቢው ትኩረት አልተሰጠውም፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ መንግሥት ምን እየሰራ እንደሆነ ለማወቅ ከሚመለከታቸው አካላት አንዱ ለሆነው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ የህፃናት እና የወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ጥያቄ አቅርበን ነበር፡፡ በቢሮው የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰሎሞን ወ/ገብርኤል፣ ‹‹አሁን ‘ኮ ብዙ ጥሩ ነገሮችን እያየን ነው። በሕጉ ላይ የተቀመጡት ነገሮች በፖሊስ እና በሌሎች የፍትሕ አካላት ተግባራዊ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።›› የሚል ምላሽ ሰጥተውናል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሕይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቆ የሚደርስባቸውን ዛቻና ማስፈራሪያ በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢያደርጉም፣ ስለማስፈራራቱ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻሉ ከለላ ሊያገኙ እንደማይችሉ የሚናገሩት የሕግ ባለሙያዎች፣ ‹‹በተደጋጋሚ ቢያመለክቱም ጉዳት ሳይደርስባቸው በፊት የሚጠብቃቸው አካል የለም›› ይላሉ።

ከወራት በፊት፣ ባለቤቷ ባደረሰባት ከፍተኛ ድብደባና የአሲድ ጥቃት ሕይወቷ ያለፈው ትዕግስት፣ ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት ያለችበትን ሁኔታ አሳሳቢነት ለፖሊስ በተደጋጋሚ ብታስታውቅም የሚሰማት እንዳልነበር ወንድሟ ዮሀንስ ታደሰ በቁጭት ያስታውሳል።

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ከተለመዱት ጥቃቶች ለየት አድርጎ ማየት እንደሚያስፈልግ የሚያሰገነዝቡት ወ/ሮ ዜናዬ፣ በፖሊስ ላይ የሚስተዋለው በቤት ውስጥ ጥቃት ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት ያለመፈለግ አካሄድ ሊገታ እንደሚገባ ያሳስባሉ።

ከዚህ በተጨማሪ፣ ፖሊስ በማስረጃ ሳይቀር ተደግፎ የሚቀርብለትን የማስፈራራት ወንጀል ከማስቆም ይልቅ ‹‹ይኼ የቤተሰብ ጉዳይ ነው፤ እናንተው ፍቱት›› በማለት ኃላፊቱን ከራሱ ላይ ለማውረድ የሚያደርገው ሙከራ እጅግ አደገኛ ውጤት የሚያስከትል መሆኑ አስተያየታቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያዎች የሚስማሙበት ነጥብ ነው።

‹‹ለሚከሰቱት አሰቃቂ የሞትና የአካል ጉዳት መነሻው ዛቻ ነበር›› በማለት አስተያየቷን ለምትሰነዝረው የሕግ

ባለሙያና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቿ የት ነበርሽ፣ ዛቻን በወንጀልነት ለፈረጀው ሕግ ፖሊስ ዕውቅና አለመስጠቱ የሚያበሳጭ ነው።

አወዛጋቢው የዋስትና መብትና

የቅጣት ማቅለያየኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ

የሆነችው አበራሽን ሁለት ዓይኖች በስለት በመውጋት ያፈሰሰው ተጠርጣሪ፣ ረቡዕ መስከረም 10 ቀን 2001 ዓ.ም ፍ/ቤት ቀርቦ በነበረበት ወቅት በስፍራው የነበሩትን ባስገረመ አኳኋን የ‹‹ዋስትና መብቱ›› እንዲከበርለት ጥያቄ አቅርቦ ነበር - ባይሳካለትም።

ግለሰቡ በቀድሞ ባለቤቱ ላይ በቃላት ለመግለፅ የሚከብድ ጉዳት አድርሶ ‹‹ንብረቴን እንዳስተካክል ዋስትና ይከበርልኝ›› ማለቱን በራሱ እንደሌላ ጥቃት የቆጠሩት አልጠፉም።

ምንም እንኳን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ የህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰሎሞን ወ/ገብርኤል ቢሮው ባከናወነው ሥራ አማካኝነት በጾታ ጥቃት የሚከሰሱ ሰዎች ዋስትና እንዳያገኙ መደረጉን ቢገልጹም፣ ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቆይታ ያደረጉ ባለሙያዎች ግን በዚህ አይስማሙም።

በሴቶች ላይ ጥቃት ፈፅመው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ተከሳሾች የዋስት እና መብታቸው ተከብሮላቸው ከእስር ሲለቀቁ የመጀመሪያ ተግባራቸው ማስረጃ ማጥፋትና መሰወር እንደሆነ የሚያስገነዝቡት የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዳይሬክተር፣ ለዚህም በምሳሌነት የሚያስቀምጡት በአስገድዶ መድፈር ተጠርጥረው ከሚያዙት መካከል ቅጣት ተፈፃሚ የሚሆነው በጣም ጥቂቶቹ ላይ ብቻ መሆኑን ነው።

ሌላው አከራካሪ ጉዳይ የቅጣት ማቅለያ ነው፡፡ ተከሳሾች ወንጀሉን ከፈፀሙ በኋላ ያለማንም አስገዳጅነት እጃቸውን በመስጠታቸው እና በድርጊቱ ‹‹መፀፀታቸውን›› በመግለፃቸው ብቻ ሊበየንባቸው ይገባ የነበረው ቅጣት እንዲቀል የሚደረግበትን ሂደት የሚኮንኑት ወ/ሮ ዜናዬ፣ ‹‹የቅጣት ዓላማ አጥፊን መቅጣት ብቻ አይደለም። ሌሎችን ለማስተማር ጭምር ነው። በመሆኑም ተከሳሾች ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ ቅጣት ሊያገኙ ይገባል›› ሲሉ ይሞግታሉ።

የትዕግስት ‘ገዳይ’ ያለመያዙ አንደምታ

በትካዜ ተውጦ፣ “ገና ድሮ በተደጋጋሚ ለፖሊስ ስናመለክት የሚሰማን ብናገኝ ኖሮ ይኼ ሁሉ ነገር

አይፈጠርም ነበር” ሲል በተደጋጋሚ የሚደመጠው የትዕግስት ታናሽ ወንድም፣ የተጠርጣሪው አለመያዝ በሟች ቤተሰብ ላይ ያስከተለው ተፅዕኖ ከባድ መሆኑን ይናገራል።

በወጣቷ ላይ ከተፈፀመው ወንጀል ባሻገር የዋና ተጠርጣሪው አለመያዝ ለቤተሰቧ የእግር እሳት ሲሆን፣ ወትሮም ከእናታቸው ጋር ሲጣላ የሚሸበሩት የሟች ሕፃን ልጆች ‹‹እኛም ላይ አሲድ ይደፋብናል›› በሚል ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን ለመረዳት ከዮሐንስ ጋር ጥቂት ደቂቃዎችን መቆየት በቂ ነው።

ከተጠርጣሪው ወንጀለኛ በላይ ተጠርጣሪውን የሸሸገ ሰው አሊያም ማኅበረሰብ ድርጊት አሳፋሪ እንደሆነ አፅንኦት የምትሰጠው የትነበርሽ፣ ‹‹እኛው ላይ ጥቃቱ እየተፈፀመ እንዴት እኛው እንደብቃለን?›› ስትል ትጠይቃለች። የትነበርሽ በማከልም፣ ከለከፋ ጀምሮ ያሉትን ጥቃቶች ኅብረተሰቡ እንዲያወግዝ እና እንዲከላከል ጥሪዋን አቅርባለች፡፡

ትዕግስትን በአሲድ አቃጥሎ ገድሏታል ተብሎ የተጠረጠረው አለመያዝ ለሌሎች ተመሳሳይ ጥቃት ፈፃሚዎች የልብ-ልብ ሊሰጥ እንደሚችል ሲገለፅ የቆየ ሲሆን፣ የተፈራውም አልቀረም ገና ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ጥቂት ወራትን ያስቆጠረችው የ21 ዓመቷ ቤቴል አዲሱ ከጥቂት ቀናት በፊት የተመሳሳይ ጥቃት ሰለባ ሆናለች፡፡

ጥቃቶቹ ለምን ትኩረት ተነፈጋቸው?ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ስለሴቶች መብቶች

መከበር የሚሟገቱና አሰቃቂ ጥቃቶች ሲፈፀሙ የሚያወግዙ ድምጾች በርክተው ይሰሙ ነበር። ሆኖም እነዚያ ድምጾች ዛሬ ‹‹ሙሉ በሙሉ የሉም›› በሚያስብል ደረጃ ቀንሰዋል። ለ‹‹ድምጾቹ›› መታፈን በዋና ምክንያትነት የተቀመጠው ደግሞ ከሁለት ዓመታት በፊት ፀድቆ ተግባራዊ መሆን የጀመረው አወዛጋቢው የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማኅበራት አዋጅ ነው።

ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቆይታ ባደረጉ አስተያየት ሰጪዎች መሠረት፣ በአዋጁ የተነሳ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› ሆነው የተመዘገቡ ድርጅቶች እንደበፊቱ ገንዘብ ከውጪ አገራት ማሰባሰብ ባለመቻላቸው ምክንያት በየጊዜው የሚደርሱ አሰቃቂ ጉዳቶችን ለማውገዝ የንቅናቄ ሥራ ማከናወን አልቻሉም። ጉዳት ለደረሰባቸውም፣ የሕግና ሌሎች የተለያዩ ድጋፎችን ለማቅረብ ከፍተኛ ጋሬጣ ሆኖባቸዋል - አዋጁ።

የተዘረዘሩት ችግሮችም ባፋጣኝ እስካልተፈቱ ድረስ፣ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ ‹‹ነገ በእኔ ላይ ይፈጸም ይሆን?›› በሚል ታላቅ ሥጋት ተሸብበው ኑሮአቸውን መግፋታቸው አይቀሬ ይመስላል። እናም፣ በርካቶች፣ የኢትዮጵያውያን ‹‹ሂትለሮች›› መቆሚያ መቼ ይሆን? ሲሉ ደግመው ደጋግመው መጠየቃቸውን አላቆሙም፡፡

ኢትዮጵያውያን

ማን ያቁማቸው?“ሂትለሮችን”ተጠየቅ

Page 15: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

15

በናፍቆት ዮሴፍ

ከወር በፊት፣ ዕለተ ቅዳሜ፣ ለወጣት ዘላለም መልካም የሚባል አልነበረም። በዚያ የሳምንት መጨረሻ ቀን፣ አየር ልቀበል ብሎ ከሰፈሩ አዲሱ ገበያ እስከ ሰሜን ሆቴል ድረስ በታክሲ ከመጣ በኋላ በእግሩ መጓዝ ይጀምራል። ማዕከላዊ አካባቢ ወረድ ብሎ ሶራአምባ ሆቴል አጠገብ ሲደርስ፣ አንድ ጎስቆልቆል ያለ ወጣት ስቆመውና፣ ‹‹እባክህ እርዳኝ›› ሲል ይማፀነዋል። ወጣት ዘላለምም በትህትና፣ “ምን ልረዳህ?” ብሎ ተጠጋጠጋው። ‹‹የመጣሁት ከደቡብ አካባቢ ነው። ከተማውን ፍፁም አላውቅውም። እባክህ የሎተሪ አስተዳደር መሥሪያ ቤትን ታሳየኝ?›› በማለት ጠየቀው። ‹‹ራሱን ከተማ እንደያማያውቅ ፍፁም የገጠር ሰው አድርጎ የተላበሰው ገፀ-ባሕሪ ተዋጥቶለታል›› የሚለው ዘላለም፣ ለጥያቄው በቅዳሜ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳዳር እንደማይሰራ በማስረዳት በነጋታው ሰኞ ግን ምናልባት መ/ቤቱን ሊያሳየው እንደሚችል ነግሮት ጉዞውን ይቀጥላል።

ይሁን እንጂ ብዙም ሳይርቅ ባለሎተሪው ስለሎተሪ ምንም እንደማያውቅና በሎተሪው እድለኛ ሆኖ እንደሆነ እንዲያይለት አንድ “ሎተሪ” ከኪሱ አውጥቶ ያሳየዋል። ሎተሪው ፈጣን እንደነበረና ሶስተ ተመሳሳይ ምስሎች በካርዱ ላይ ከተገኙ፣ በሽልማት ሳጥኑ ውስጥ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን የሚያሸልም እንደነበር እና በሎተሪው ላይ ሶስት ተመሳሳይ ምስሎችና የገንዘቡ መጠን በሚገለፅበት ቦታ ላይ 25 ሺህ ብር እድለኛ እንደሆነ መመልከቱን ዘላለም ያስታውሳል። ‹‹ይህን ባየሁበት ቅፅበት ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርሁበት ወቅት በስርቆሽ ስሙ የገነነና በከተማዋ የማውቀው ረሺድ [ስሙ ተቀይሯል] የተባለ ሰው በድንገት በአጠገባችን አለፈ።’’ ሲል ሁኔታውን በግርምት የሚያስታውሰው ዘላለም፣ ልክ ረሺድን እንደተመለከተ “ሌባና የሚሰረቅ ነገር እንደማግኔት ይሳሳባሉ እንዴ?” የሚል ሀሳብ ብልጭ ይልበታል። ሆኖም ወዲያው ሀሳቡን ገፍቶት ትኩረቱን ወደ ባለሎተሪው አዞረ።

ረሺድና ባለሎተሪው ቆመው እየተነጋገሩ ሳለ፣ ባለሎተሪው ረሺድን ይጠራውና ሎተሪውን ከዘላለም ጋር አብረው እንዲያዩለት ይጋብዘዋል። ‹‹ልጁ ሌባ ስለሆነ ይሰርቀዋል ብዬ በማሰብ አትጥራው ብየው ነበር። ግን ጠራውና መጣ። እኔንም ሰላም አለኝ” ሲል የነበረውን ውይይት በምልሰት ያወጋኝ ዘላለም፣ በኋላም ረሺድ ሎተሪውን አይቶ ትከሻውን ቆንጠጥ እንዳደረገው ያስታውሳል። ረሺድ፣ “ሎተሪውን እንውሰድበት” ሊለው እንደፈለገ መገንዘቡን የሚናገረው ወጣቱ፣ በመጨሻም ባለሎተሪው፣ ‹‹እየመሸብኝ ስለሆነ ወይ ሎተሪ ቤቱን አሳዩኝ፣ ካልሆነም መሳፈሪያ እና የተወሰነ ገንዘብ ስጡኝና እናንተ ሰኞ ወስዳችሁ አሳዩት›› ሲል አማላይ የመደራደሪያ ሐሳብ ያቀርባል።

በዚህ ወቅት ረሺድ፣ ‹‹ገንዘብ ስጠውና አሰናብተው›› ብሎ ዘላለምን ቢመክረውም፣ ዘላለም በወቅቱ ምንም ገንዘብ በኪሱ አለመያዙን ለረሺድ ይነግረዋል። ‹‹ልጁን ይዘህ እዚሁ ጠብቀኝ። ገንዘብ ይዤ ልምጣ ብሎኝ ሲሄድ፣ እሱ ከሚወስደው ብዬ ውድ ተንቀሳቃሽ ስልኬን ሰጥቼው ሎተሪውን ይዤ ወደ ቤቴ ሄድኩኝ›› የሚለው ዘላለም፣ በነጋታው እሁድ ከወንድሙ ጋር ሎተሪውን ሲመረምሩት 25ሺህ የሚለው የሽልማት የገንዘብ መጠን በስቲከር የተጣበቀ እንጂ ሎተሪው ያስገኘው እድል አለመሆኑን ተገነዘበ።

ከዓመታት በፊት ሰዎች በሎተሪ የሚታለሉበት ሌላ መንገድ ነበር። አሁንም አለ። አጭበርባሪዎች ሎተሪ እንደደረሳቸው፣ ነገር ግን መታወቂያ እንደሌላቸው በመግለጽ የማያውቋቸው ሰዎች ሄደው ‘የሽልማት ገንዘቡን’ እንዲያወጡላቸው፣ ግን ያን ገንዘብ ይዘው እንዳይጠፉባቸው መያዣ እንዲሰጧቸው ይጠይቃሉ። የዋሆቹም የአንገት ወርቃቸውን፣ ስልካቸውን እና ይመጥናል ብለው ያመኑትን እቃ ለአጭበርባሪ ሰጥተውና ባዶ ሎተሪ ይዘው ወደ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳዳር ለመሄድ መንገድ ጀምረው ዘወር ሲሉ ከመቅፅበት ሰዎቹ ይሰወራሉ።

አሁን አሁን ደግሞ አይነቱንና ይዘቱን ቀይሮ፣ በስቲከር ከፍተኛ የገንዘብ መጠን በሚገልፁ ቁጥሮች ሰዎች የሌባ ሲሳይ እየሆኑና በአተርፍ ባይ አጉዳይነት

ባዶ እጃቸውን እየቀሩ ይገኛሉ። ምንም እንኳን ጥፋቱ በሁለቱም ወገን የሚከሰት ቢሆንም፣ በተለይ የአጭበርባሪዎቹ ስልት ግን የሰዎችን አዕምሮ መስለብ መቻሉ ጉዳዩን የተወሳሰበ አድርጎታል።

ወጣት ዘላለምን ምን እርምጃ ወሰድክ ስንል ጠይቀነው ነበር። ‹‹ያው መጭበርበሬን ያወቅሁት በሁለተኛው ቀን ነው። ከዚያም ላዛሪስት አካባቢ በሚገኘው ጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ሄድኩ። የሚሰማኝ አጣሁ። ፒያሳ ነው የተጭበረበርከው፤ ፒያሳ ሂድ አሉኝ። ገዳም ሰፈር ያለው ፖሊስ ጣቢያም እኔን እንዳጭበርባሪ ቆጥሮኝ የሚሰማኝ አጣሁ” የሚለው ዘላለም፣ በዚህም ተስፋ ሳይቆርጥ ራስ ደስታ ሆስፒታል አካባቢ ያለው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በደሉን መናገሩን ገልጾ፣ “እሁድ በመሆኑ ምንም ልንረዳህ አንችልም” ብለው እንደመለሱት፣ በዚህም ማዘኑን ይናገራል። ‹‹ቅዳሜና እሁድ ወንጀል አይሰራም ተብሎ አይታሰብም እንዴት!? እሁድ ነው አናናግርም ይሉኛል? ያውም ወንጀለኛውን አውቀዋለሁ እያልኩ እየጮህኽሁኝ!›› በማለት በፖሊስ ላይ ያደረበትን ቅዋሜ በአግራሞት ይጠይቃል።

‹‹አገሪቱ በአጭበርባረዎች እየተሞላች ነው። እኛ የተማርን ነን የምንለው ይህን ያህል ከተጭበረበርን፣ ሌላው እንዴት ሊሆን ነው?›› ሲል የሚጠይቀው፣ 80ሺህ ብር አተርፋለሁ ብሎ የ13ሺህ ብር ቶሺባ ላፕቶፕ ‘የተበላው’ የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነው ወጣት ተጭበርባሪ ነው። በሙያው ላለፉት አራት ዓመታት ማገልገሉን ያጫወተኝ ይህ መምህር፣ ‹‹እኔ ይህን ታሪክ ስነግርሽ በራሴ በጣም እያፈርኩ ነው። ብቻ ሁሉም ቀናት ጥሩ አይሆኑም፤›› ነበር ያለኝ በፀፀት ከንፈሩን እየነከሰ።

ከሁለቱም ተበዳዮች እንደሰማሁት፣ የተጭበረበሩበት መንገድ በእጅጉ ይቀራረባል። አጭበርባሪዎቹ የሚቀርቧቸው ስለምንም ነገር ምንም እንደማያውቁ አድርገው በሚተውኑት ተውኔትና ሰዎችን ለማሳመን ባላቸው ብቃት እንደሆነ ይህ ስሙ እንዲጠቀስበት ያልፈለገ ወጣት መምህር ይናገራል። ‹‹ታሪኩን የምነግርሽ ሰዎች እንዲማሩበት እንጂ በእኔ ደረጃ እንዲህ መጭበርበር እጅግ አሳፋሪ ነው›› ይላል - እጅግ በመቆጨት።

ወጣት ዘላለምም በበኩሉ፣ ‹‹ወደ ሶስቱም ፖሊስ ጣቢያዎች ስሄድና ይሄን ስነግርሽ ሞባይሌን ዳግም አገኘዋለሁ ብዬም አይደለም። ደግሞም እስካሁንም አልገዛሁም። ግን ያልተናገሩ ግን በርካታ የተጭበረበሩ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታሁ። እናም ሰዎች ከእኔ መማር አለባቸው” ሲል ይመክራል።

የዛሬ 50 ዓመት፣ ማለትም በ1954 ታህሳስ 29 ቀን፣ የተቋቋመውና የመጀመሪያውን መደበኛ ሎተሪ ለገበያ ያበቃው ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር፣ በ50 ዓመት የሥራ ቆይታው እጅግ በርካታ ዜጎችን እድለኛ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ እሙን ነው። ዘንድሮም ታህሳስ 28 ቀን 2004 50ኛ የልደት በዓሉን ለማክበርና እግረመንገዱንም የተለያዩ የማሳወቅና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ለመስራት 6 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የማስታወቂያ እና የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ይናገራሉ።

ለአቶ ቴዎድሮስ ተጭበረበርን ስላሉ ሰዎች ጉዳይ ጥያቄ አንስተንላቸው፣ ‹‹እኛ ጋር አልፎ አልፎ የሚመጡ ተበዳዮች የሚያቀርቡት አቤቱታ መታወቂያ የለኝ፤ ሎተሪ ቤት ሄዳችሁ አውጡልኝ፤ እስከዚያው ግን እንድንናምናችሁ እያሉ ወርቅም፣ ብርም ሆነ ሌላ ነገር ይዘርፉ እንደነበር ከ20ና 25 ዓመታት በፊት የሚታወቅ ነው። አሁን አንቺ ያልሺው ፈጣን ሎተሪን በስቲከር እያጣበቁ ማጭበርበርን እንሰማለን እንጂ እኛ ጋር አቤቱታ መጥቶ አያውቅም›› ሲሉ እንደዘላለም አይነት የመጭበርበር አቤቱታ አጋጥሟቸው እንደማያውቅ አብራርተውልናል። ይሁን እንጂ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተለያዩ ዘዴዎች ኅብረተሰቡን የማሳወቅና የማስተማር ሥራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

እነዚህን መጭበርበሮች ለማስቀረት አስተዳደሩ ምን አይነት መንገዶችን ይጠቀማል ሲል ዝግጅት ክፍላችን ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹መጭበርበሩ ብዙ ስላልሆነ ገፍተን አልሄድንበትም›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ መስመር የሚጀምረው ከነጥብ ነውና ጉዳዩ ትኩረት የሚያሻው እንደሆነ ተጭበርበርን ያሉ ወገኖች ይናገራሉ።

‹‹እኔ ሞባይልና ላፕቶፕ የተወሰደባቸውን ‘ተበዳይ’፣ ወሳጆቹን ደግሞ ‘አጭበርባሪ’ ለማለት እቸገራለሁ›› የምትለው ወጣት ወይንሸት፣ ‹‹ለምሳሌ ባለ ሞባይሉ አተርፋለሁ ብሎ እንጂ ባለሎተሪውን ለመርዳት ብሎ ስልኩን ሰጥቶ እንዳልሄደ እርግጠኛ ነኝ›› ስትል ምክንያቷን ታስቀምጣለች። “እነዚህ ሰዎች ትክክለኛ ቢሆኑ ኖሮ እዩልን ብለው ሲሰጧቸውው፣ ‘ይህን ያህል ብር ደርሶሀል፤ ሄደህ ውሰድ’ ብለው ማመላከት ሲገባቸው ለማትረፍ አይደል እንዴ ላፕቶፑን በ80 ሺህ ብር የተጭበረበረ ሎተሪ የቀየረው›› ስትል ትሞግታች። ‹‹እኔ የማደንቀው ኅብረተሰቡ ከእኛ ይማር ብለው ችግሩን መናገራቸውን እንጂ ከተበዳይነት አንፃር አልመለከተውም፤ ምክንያቱም እባብ የልቡን አይቶ እግር ነሳው ነው ነገሩ›› በማለት ሀሳቧን ታጠቃልላለች።

በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳዳር የማስታወቅና ግንኙነት አስተባባሪው የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ነዋይም ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ምንም ጥፋት እንደሌለበት ገልፀው፣ “ሌላው ቀርቶ እጣ ሲወጣ እንኳን ከኢ.ቴ.ቪ ጋር በመተባበር በቀጥታ ስርጭት እንደሚያሰራጭ፣ በተለያዩ መንገዶች ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንደሚፈጥር፣ እንዲሁም ሎተሪዎች ማታ ከወጡ አዟሪዎች ማውጫውን በጠዋት አውቶቡስ መናኸሪያ ድረስ ይዘው በመሄድ እስከ ክልል ድረስ እንደሚያሰራጩ፣ በዚህም ኅብረተሰቡ በትክክለኛው መንገድ የሎተሪ አወጣጡን እንዲያውቅ እያደረገ ነው።” ሲሉ አብራርተዋል። ‹‹ምን መሰለሽ፤ አሁን አንቺ ያነሳሻቸው ጉዳዮች የተፈፀሙት የተማሩ ያውም ድግሪና ማስተርስ ባላቸው ሰዎች ላይ ነው። አንድ ሰው የከተማ ነዋሪ ሆኖ መታወቂያ የለኝም ሲል ሌላው እንዴት አይጠረጥርም? ሁሉም ዜጋ መታወቂያ የማግኘት መብት እንዳለው እኮ ይታወቃል›› በማለት ሰዎች ለራሳቸው ጥንቃቄ ካላደረጉ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳዳር እያንደንዱን ዜጋ የመጠበቅ ሥራ እንደማይሰራ ገልፀዋል።

ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ባልደረባ የሆኑ ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክተው ለአውራምባ ታይምስ በሰጡት አስተያየት፣ በአሁኑ ሰዓት እጅግ በርካታ የሚጭበረበሩ ነገሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ጠቁመው ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ጩልሌዎቹ

በዚህ ወቅት ረሺድ፣ ‹‹ገንዘብ ስጠውና

አሰናብተው›› ብሎ ዘላለምን ቢመክረውም፣

ዘላለም በወቅቱ ምንም ገንዘብ በኪሱ

አለመያዙን ለረሺድ ይነግረዋል። ‹‹ልጁን ይዘህ

እዚሁ ጠብቀኝ። ገንዘብ ይዤ ልምጣ ብሎኝ

ሲሄድ፣ እሱ ከሚወስደው ብዬ ውድ ተንቀሳቃሽ

ስልኬን ሰጥቼው ሎተሪውን ይዤ ወደ ቤቴ

ሄድኩኝ›› የሚለው ዘላለም፣ በነጋታው እሁድ

ከወንድሙ ጋር ሎተሪውን ሲመረምሩት 25ሺህ

የሚለው የሽልማት የገንዘብ መጠን በስቲከር

የተጣበቀ እንጂ ሎተሪው ያስገኘው እድል

አለመሆኑን ተገነዘበ።

አልተናገራችሁም እንጂ ከእናንተ ዘንድ መፍትሄ አለ። ደግሞስ ከናንተ ዘንድ መላ ጠፍቶ ያውቃልን? ከምር ዕድል ብታገኙ እና የእውነት ከልብ ብንሰማችሁ ኖሮ በልቦናችሁ ጓዳ ተሰውረው ያሉት ህልቆ-መሳፍርት ምስጢራትና ጥበባት ተገልጠው ምንኛ ህይወታችንን ባደሱት ነበር! በጨዋ አስተዳደግ ታንፃችሁ፣ በስነ ምግባርና ሃይማኖት ፀንታችሁ፣ በማህበራዊ ኑሮ ዘዴ ጎልብታችሁ፣ ልጅ ወልዶ እስከማሳደግ ባለ ልዩ ፀጋ ተክናችሁ፣ ህይወትን ለማጣፈጥ የእንስትነት ቅመማችሁን እነሆ ብላችሁ ይህቺን አስቸጋሪና ፈታኝ ምድር ወደምድራዊ ገነትነት ባትለውጧት እንኳ ዕለት-በለት ተናፋቂና አጓጊ ምቹ ስፍራ አድርጋችኋታል። ምስጋና ለእናንት ለኢትዮጵያውያን እንስቶች!

ታዲያ ይሄን ሁሉ ስጦታ እና በረከት እኛ ወንዶች ፍቅርን ተገን አድርገን ለየብቻችን በግል እንደባል፣ በቤተሰብ ውስጥ ደግሞ እንደአባት፣ ልጅ፣ ወንድም በነፃ እያገኘን ማር-ማር የሚል ህይወታችንን ስንኮመኩም፤ በአንፃሩ በጋራ አገራዊ ህይወታችን እንደማህበረሰብ ስንኖር ግን እነዚህን የመልካም እንስት እና እናቶች በጎ ምግባራት ብሎም እሴቶች ልንካፈል አልቻልንም። ምናልባትም ከተመሰቃቀለ እና የእናቲቱን መልካም ተፅዕኖ (ወይ በሞት በመለየት አሊያም ሚና በመንፈግ) ካጣ ቤተሰብ የተወለደ ምስኪን እና መካሪ የለሽ ወጣት ሃይ የሚለው ጠፍቶ በልቡ እብሪትን፣ ማን-አለብኝነትን፣ ጥላቻን፣ እና መራዥ ነገሮችን ሁሉ አጭቆ፤ ሰፈሩን የሚያርበደብድ፣ ማሕበራዊና መንፈሳዊ ደንቦችን የሚጥስ፣ የእንስቶቻችንን እና እናቶቻችንን በጎ ነገር ሁሉ ወደጎን የሚገፋ ‹እኔ-ወንዱ!› እያለ የሚፎክር አምባገነን ከመሃላችን በቅሎ ይሆናል። ሰላሙን አጥቶ ሰላማችንን የሚነሳ ዓይነት! እንዲህ ዓይነቱም አምባ-ገነን ነው የእናቶቻችንን አንደበት ለጉሞ የልባቸው ብርሃን በጋራ ህይወታችን ላይ ሳይገለጥ በጭለማ እንድንኖር የሚፈረድብን።

ለርሱ የሰውነት ብቸኛ መለኪያ በሆነው ህገ-ጉልበት እና መራሄ-ጡንቻ እኩዮቹን ብሎም ጎበዛዝቱን ሁሉ እያንበረከከ በፍርሃትና በሽብር አንቀጥቅጦ መግዛት፣ ታፍሮ እና ተፈርቶ መኖር የህይወት ዓላማው ነው። በዚህም የሰፈር አውራነቱን አውጇል። ብዘዎችም በፍርሃት ይርበደበዱለታል። ነገር ግን እናቶቹ የሚሆኑ አዛውንት እንስቶች በልቡ ያለውን ስር የሰደደ የብቸኝነት ስሜት፣ የሰው ፍቅር ረሃብ፣ የ‹ሌሎች አይወዱኝም› የበታችነት ስሜት፣ አፍቅሮ እና አምኖ የመከዳት ቅጥ-ያጣ ፍራቻ፣ ብሎም እንደጓደኞቹ መልካም እና ጤናማ ቤተሰብ ስላላጋጠመው የሚሰማውን ጥልቅ ሀዘን ጥላቻ እና የአውዳሚነት ስሜት ይህንንም ለማካካስ የሚያደርገውን የታላቅነት ዘመቻ ሁሉ አንድ ባንድ አብጠርጥረው ያውቁለታል። በልባቸውም ስለሱ ማዘናቸው አይቀርም። እንዲህም ሆኖ ግን እነርሱም የድርሻቸውን ይፈሩታል። ሁሉም ግን አይደሉም። በኢትዮጵያ የ400 ዓመታት ታሪክ ውስጥ እንኳ አንዲት ልበ-ሙሉ እንስት እጅግ ጨካኝና ልበ-ደንዳና የሚባለውን አፄ ተገዳድራ አሸንፋዋለች-በጥበብና በፍቅር።

ያደረሰባትን ግፍ እና በደል አውጥታ በድፍረት በመናገሯ አፄ ቴዎድሮስ ህሊናው ተወቅሷል፤ ልቡ ተፀፅቷል። ይህች መላ ቤተሰብዋን በአፄው እጅ ያጣች ምንትዋብ የተባለች እንስት የልቧን ስብራት በይፋ ለመግለፅ በመቻሏ አፄው ተፀፅቶ ቀለብ እየሰፈረ ለማኖርና በሄደበት ሁሉ እየሄደች በቅኔ እስክትወቅሰው ድረስ ይቅርታዋን ሊማፀን ግድ ሆኖበታል። ያው የበደላት በደል የአባት፣ ወንድሟ፣ እና ባሏ ሞት ሆነና ነው እንጂ በሌላ እንደንብረት ባለው ቢሆን ሰባ-ሰባት እጥፍ በካሳት ነበር - የቋራው ካሳ። በአፄው የተጠቃች እንስት ይህች ብቻ ግን አልነበረችም። ሆኖም የሌሎቹንም ጭምር እንባ-አባሽ እና ጥቃት-መላሽ ሆና የተከራከረችው ይህችው ምንትዋብ ነበረች። ታዲያ እሷም ለዚህ ይመስላል፡-

‹‹አንጥረኛው ብዙ ከንጉሱ ቤት ባላልቦ አደረጉት ይህን ሁሉ ሴት››

ስትል ለመሰሎቿ በድፍረት የተቀኘችው።

የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ ስለምን ትፈራላችሁ?ስለልጆቻችን እንደምትሉ ማንም አይጠራጠርም። ‹ጎሽ ለልጇ ስትል

ተወጋች!› አይደል ተረታችሁስ? ባይሆንማ ኖሮ መቼም ልጇ ሰላሳ እና አርባ ዓመት እስኪሞላው/ት ድረስ ከጉያዋ ስር ወሽቃ ቤቷ የምታኖር ሲበዛ ደግ-እናት ባላየን ነበር። አዎ ይህች ኢትዮጵያዊት እናት ስለልጆቿ ስትል የማትሆነው የሌላት አንጀቷ ማይችል ሰፍሳፋ ናት።

ምናልባትም በዘመኗ ከ‹ማይከሰሰው ንጉስ› እስከ ‹ማይንኳሰሰው ጠቅላይ-ጌታ› ድረስ ብዙ ልጅ-በላ ስርዓቶችን አልፋ እንዲሁም ገብራ እዚህ የደረሰች ምስኪን መፃጉዕ ትሆናለች። የዚች እናት ትከሻ በአምባገነን አባት ቀንበር የጎበጠም ይሆናል። ወይ ደግሞ ከልጆችዋ መሃል አልቃና ብሎ አግድሙን የሚሄድ ልጅ አይጠፋትም ኖሯል። በዚህ ሁሉ ላይ ደግሞ የድህነት አሰቃቂ ኑሮ የልጅነት መልኳን አደብዝዞ፣ የአፍላነት ኃይሏን አንጠፍጥፎ ዕድሜዋ ሳይገፋ ያስረጃታል። አዬ-እናት ዓለም ጠኑ!

ታዲያ ይህች ኢትዮጵያዊት እናት ይህን ሁሉ ችላ እየኖረች አንዳቸውም ልጆቿ ከጎኗ ለደቂቃም ባይለይዋት ለአፍታም ባይርቋት የምትመርጥ የልጅ ስስታም ናት። እንኳን ሰው በክፉ ዓይኑ እንዲያይባት ቀርቶ እሷ ራሷ እንኳ በሙሉ ዓይኗ የማታያቸው የስስት-ዓይን ትራፊ ልጆቿን አንዳች እንዲነካቸው አትፈቅድም። አትፈቅድም እንኳ ባይባል አትወድም። ነገር ግን ሳትወድ በግድም ቢሆን ልጆቿን ለሞት፣ ለስደት፣ ለእስር፣ ለአፈና፣ ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለሰቆቃ፣ ለድህነት፣ ለእንግልት፣ ለፍርሃት አሳልፋ መስጠቷ አልቀረም።

ሁሉን አሳምራ እያወቀች እንዳላወቀች ሆና በልቧ ለመያዝ የተገደደችው ኢትዮጵያዊት እናት ይህን የመረጠችበት ምክንያት አላት። ቤተሰቧን በእቅፏ ሰብስባ አንዳቸውም ሳይጎሉባት ለመኖር ነው - ደግ ቀን እስኪወጣ። ታዲያ ይሄ ተናፋቂ ደግ ቀን መምጫው እየራቀ ሲሄድ የክፉ ቀናቶች ቀንበርም እየጠበቀ ሲመጣ ቢያንስ ቢያንስ አሁን ያለው ጦርነት-አልባም ሰላም-አልባም ሁኔታ እንዲቀጥል ያስመኛል-ለእናት። ልጆቿ ብቻ በህይወት ይኑሩላት እንጂ። አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊ እናቶች ሁሉን ነገር በፀጋ ተቀብለው ‹በሰላም› ለመኖር የሚመኙትም ለዚህ ነው። ህይወት በተመኙት ብቻ አይሆንምና በአገሪቱ ውስጥ የሚዘረጋው የፖለቲካ ሥርዓት አካሄድ በእያንዳንዷ እናት ቤት ተራ-በተራ ከተፍ ይላል። የፈሩት ይደርሳል እንዲል ብሂሉ። እንደምርጫና ፍላጎታቸው ቢሆን ግን ፖለቲካ የሚባል ነገር በደጃቸውም ባያልፍ ይሻሉ። ካለፈው አንገፍጋፊ የህይወት ልምዳቸው ያዩት ነገር ቢኖር ፖለቲካ የልጆቻቸውን ደም ለመጠጣት ያሰፈሰፈ የእብድ ጋኔን የሚጋልበው የዛር ፈረስ መሆኑን ነው። የቅርብ-ሩቅ ትዝታቸው የሚያስታውሳቸው ጉዳይ ቢኖር ደግሞ የደረሱ ልጆቻቸው እንደአውሬ እየታደኑ እሬሳቸው ለአሞራ መጣሉን፣ እርማቸው መከልከሉን፣ ቀብራቸው መታገዱን፣ አስከሬናቸው መቸብቸቡን፣ እና ገዳያቸው መሾም መሸለሙን ነው። ጭንቅ-ጥብብ ያላቸው ምስኪን ኢትዮጵያውን እናቶች፡-

‹‹መላኩ ተፈራ የእግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ ከእንግዲህ አልወልድም››

ሲሉ ሰቀቀናቸውን የተቀኙትስ ለዚሁ አይደል?

ፍርሃታችሁ ምን ወለደ?‹‹ፈሪ-ለናቱ›› እንደምትሉኝ አውቃለሁ። ለናቱ ምን? የሚለው ነው

ለመመለስ ከባዱ። ፈሪ ለናቱ ልጅ ብቻ ከሆነ ግን ይህ አነጋጋሪ እና ጉድለት ያለበት ነው። ፈሪ ልጅ እናቱን የሚጦራት፣ ወግ-ማዕረግ የሚያሳያት፣ ውለታዋን የሚከፍላት የልጅ ልጆች አያት የሚያደርጋት መቼ ነው? ይህንን ሁሉ የልጅነት ድርሻውን ለመወጣትስ አሁን ባለው አያያዝ እና ሁኔታ እውነት ይቻለዋል? ህሊናውን ሳያቆሽሽ፣ ነብሱን ሳይሸጥ፣ ክብሩን ሳያጎድፍ፣ የራሱንና የቤተሰቡን ህይወት ለመቀየር የሚችል ጠንካራ ልጅ ስንት ይገኛል? ደግሞስ ልጅ አምላክ አድሎት

እናት - ኢትዮጵያውያን

ዝም አትበሉ!

ል ዩ ቅኝት

በአናንያ ሶሪ

በ ገፅ 20

Page 16: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 200416

የሰሞኑን የእስር ሂደቶች ፓርቲው እንዴት ነው የሚመለከተው?በተለያዩ ጊዜያት እንደገለፅነው፣ ፓርቲያችን ለፍትህና ለዴሞክራሲ ይታገላል፤ ሕገመንግስቱ ያጎናፀፈንን መብቶች በመጠቀም መታገላችንን እንቀጥላለን። ትግላችንም ሰላማዊ መሆን እንዳለበት እናምናለን። በእኛ አመለካከት የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚና የብሔራዊ ም/ቤቱ አባላት፣ እንዲሁም የሌሎች ታጋዮች መታሰር የሚያመለክተው ጠንካራ ተቃዋሚዎችን የማጥፋት መንገድ መያዙን ነው። የእኛን ድርጅትንም ሆነ ሌሎች ለሰላምና ለዴሞክራሲ የሚታገሉ ድርጅቶችን የማዳከሚያ ሥልት ነው።

የታሰሩትን ሰዎች ስናያቸው ወጣቶች ናቸው። በጣም ጠንካራ ታጋዮች ናቸው። እነሱን በማሰር ድርጅቱን የሚያዳክሙ ሊመስላቸው ይችላል።

“እስሩ ወደ እኛም ሊመጣ ይችላል” የሚል ሥጋት በሌሎች አመራሮች ላይ አለ እንዴ?ለምን እንፈራለን? የምንፈራበት ምክንያት የለም። እኛ በግልፅ እንደምንናገረው ሰላማዊ

ታጋዮች ነን። ሰላማዊ ትግላችንን መንግስት አጣሞ በመተርጎም ሊያስረን ይችላል። ግን ይሄ አያስፈራንም። ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ ለመብቱ እንዲታገል የማያቋርጥ ጥሪ እናደርጋለን። ይሄንን ለሽብር እንደማነሳሳት ከቆጠሩት ምንም ማድረግ አይቻልም። ገና ለገና ያስሩናል ብለን ከትግላችን አንስተጓጎልም።

የታሰሩት ሰዎች የምር አሸባሪ ላለመሆናቸው ምንድን ነው ማረጋገጫችሁ?ልጆቹን [የታሰሩትን] እናውቃቸዋለን እኮ። እሁን ለምሳሌ አንዷለም እንኳንስና አሸባሪ ሊሆን ይቅርና ከሰላማዊ ትግል ውጪ የሚያስቡ ወገኖችን በጣም ነው የሚኮንነው። ነፍጥ አንስቶ የመሳሪያ ቃታ ለመሳብ ይቅርና ከሰዎች ጋር በፍቅር ስለመኖር የሚሰብክ ትሁት ልጅ ነው። ናትናኤልና … ቢሆኑም በአንድነት ሰላማዊ አካሄድ ከልብ አምነው የሚንቀሳቀሱ ልጆች ናቸው። ለዚህ ነው ንፅህናቸውን የምንመሰክረው።

እርስዎ ቀደም ባሉት ጊዜያት የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ነበሩ። ኢህአዴግን በደንብ እንደሚያውቅ ሰው እነዚህን እርምጃዎች እንዴት ያዩዋቸዋል?

ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ተናግሬዋለሁ … የኢህአዴግ አስተሳሰብ የተቃኘው በነማኦ እና በነስታሊን መንገድ ነው። ስለዚህ ተቀናቃኞቹን ሁሉ

በማጥፋት ነው የሚያምነው። በምንም ጉዳይ ላይ ከእሱ ውጪ ትክክለኛ ሐሳብ ያለው አካል ያለ አይመስለውም። “እኔ ይቺን አገር ካልመራሁ ትበታተናለች” የሚል እኮ ነው። እራሱን በዚህ

መልኩ ተመልክቶ ብቻ ቢያበቃ ጥሩ ነበር ግን ሌሎቹን ተቃዋሚዎቹን ደግሞ በፀረ-ሰላምነት፣ በሽብርተኛነት በመፈረጅ እንዲጠፉ ያደርጋል።ከምንም በላይ ደግሞ በ1993 ዓ.ም ግንባሩ በግልፅ እንዳስቀመጠው፣ “አገሪቷን ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለማሰለፍ የግድ ቀጣዩቹን 20 እና 30 ዓመታት በገዢነት መቀጠል አለብኝ” ብሏል። ስለዚህ ይህንን “ዕቅዱን” ሊያጨናግፉ የሚችሉ ወገኖችን ለመከላከል ከቀየሳቸው ዘዴዎች ውስጥ አንዱ የሰሞኑ ዓይነት ዘመቻዎች እና ቀፍዳጅ ሕጎች ዋንኞቹ ናቸው።

የአባሎቻችሁ መታሰር በፓርቲያችሁ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?እርግጥ ነው በአባሎቻችን መታሰር አዝነናል። ነገር ግን የእስሩ ምክንያት

ስለሚገባን ራሳችንን አጠናክረን በመቀጠሉ ላይ ነው ያተኮርነው። ከምንም በላይ ደግሞ ድርጅታችን በተወሰኑ ሰዎች ላይ ብቻ የተደገፈ ስላልሆነ የታሰሩት

አባሎቻችን ይሰሩት የነበረውን ሥራ ሌሎች አባሎች እንዲሸፍኑት አድርገናል። በሌላ በኩል ግን ምንም እንኳን እስሩ የታቀደው እኛን ለማሸማቀቅና ለማዳከም ቢሆንም እኛ የሚደርስብንን ጫና ይበልጥ ለመቋቋም የሚያነቃቃ እና የሚያጠናክር አድርገን ወስደነዋል።

በአንድ በኩል የሚያጠናክራችሁ እንደሆነ እየለፃችሁ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አባሎቻችሁ እየታሰሩ ነው … ይሄ በሰላማዊ ትግል ተስፋ አያስቆርጥም?ይሄ እርምጃ በሰላማዊ ትግል ተስፋ ሊያስቆርጥ አይገባም። እንዲያውም አባሎቻችን በቆራጥ ሰላማዊ ታጋይነታቸው መታሰራቸው ለሌሎች አርዓያ በመሆን የሚያበረታታ ነው።

በቅርቡ ፓርላማው በአሸባሪነት አምስት ድርጅቶችን ሰይሟል፤ ይሄ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ያስከተለው …አዎ፤ ውሳኔው አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደገውን ጥረት ያጨናገፈና በር የዘጋ

ነው። የትጥቅ ትግልን እንደአማራጭ ይዘው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ወገኖችን ወደ ሰላማዊ ጎዳና ለመመለስ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ‹‹አሸባሪ›› ብሎ መፈረጁ

ተገቢ አይደለም።በመሰረቱ እኮ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ከሰፈነ

የትጥቅ ትግልን እንደአማራጭ የሚያራምዱ አይኖሩም። ስለዚህ መንግሥት ሰላማዊ ታጋዮችን ማሰሩ በሰላማዊ ትግል ተስፋ ለቆረጡ ወገኖች ጥሩ ማሳመኛና መከራከሪያ ከመሆኑ ውጪ ለአገሪቱ የፖለቲካ ችግሮች መፍትሄ አይሆንም።

የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ሲፀድቅ በፅኑ ተቃውማችሁ ነበር። የዛኔ የፈራችኋቸው ነገሮች አሁን እየተስተዋሉ ናቸው?በትክክል። አዋጁ በብዙ መንገድ በሕገመንግስቱ የተደነገጉትን ሰብዓዊ መብቶች እንደሚጥስ በማስገንዘብ ነበር የተቃወምነው። ለምሳሌ፤ በግል እኔ ላይ ቁርሾ ያለው ሰው ‹‹ሽብርተኛ ነው›› ብሎ በመጠቆሙ ብቻ ልታሰር እችላለሁ። መንግስት በፈለገው መንገድ አጣርቶ አንድን ሰው በሽብርተኛነት ለመፈረጅ

“ሕዝቡን እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ

ነፃ ሊያወጣው አይችልም”ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

ሰሞኑን መንግሥት በአሸባሪነት የጠረጠራቸውን ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፖለቲከኞች ማሰሩ ይታወሳል። በዚህ ጉዳይ እና በሌሎች ተያያዥ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ፣ ሱራፍኤል ግርማ ከቀድሞ የኢፌዴሪ

ፕሬዝዳንት እና ከወቅቱ የአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)ሊቀ-መንበር ከሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር ቆይታ አድርጓል።

እ ን ግ ዳ

Page 17: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

17

መረጃና ማስረጃ ሳይኖረው ሲቀር የተከሰሰው ሰው ነው ማስረጃ በማቅረብ ራሱን ነፃ ማውጣት ያለበት። ይሄ እንግዲህ የመንግስትን ኃላፊነት ወደ ግለሰቡ ማላከክ ነው። ሌላው የጠረጠሩትን ሰው እስር ቤት ሲያስገቡ በተፋጠነ ፍርድ ውሳኔ እንዲያገኝ ከማድረግ ይልቅ ለረዥም ቀናት (እስከ አራት ወር) እስር ቤት አቆይተው ምርመራ ያካሂዳሉ። መጀመሪያ ካሰሩ በኋላ ነው መረጃና ማስረጃ የሚያሰባስቡት። ከዚህ በተጨማሪ የሕገ ወንግስቱን አንቀጽ 19 በመጣስ ታሳሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸውና ከሕግ አማካሪዎቻቸው እንዳይገናኙ ይከለክላሉ።

ውጪ አገራት ከሚገኙና በአሁኑ ሰዓት በአሸባሪነት ከተሰየሙ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች ጋር እርስዎም ሆኑ ሌሎች የፓርቲዎ ሰዎች ቀደም ባሉት ጊዜያት ወዳጅነት ነበራችሁ። አሁን ባለው ሁኔታ ከእነዛ ፖለቲከኞች ጋር ከፖለቲካ ሥራ ውጪ ባሉ የግል ጉዳዮች ላይ እንዳትነጋገሩ አዋጁ ይከለክላል? የግለሰብን ነፃነት ከመዳፈር አንፃር . . .እንበልና ከዶ/ር ብርኃኑ ነጋ ጋር ዘመድ ብንሆንና ስለጤንነታችን፣ ስለቤተሰብ መረጃ ከተለዋወጥኩኝ “ከሽብርተኛ ጋር መረጃ ተለዋውጧል” ብለው ያስሩኛል። አሁን እንግዲህ የኦነግ ከፍተኛ አመራር የሆነው አቶ ሌንጮ ለታ የስጋ ዘመዴ ነው። የልብ ጓኛዬም ነበር። እና አሁን ለእሱ በኢ-ሜይል ሰላምታ ብልክለት እንኳን ከማሰር ወደኋላ አይሉም። ይሄ እንግዲህ ሰብዓዊ መብትን በግልፅ የሚጥስ ነው።

አዋጁ መግቢያ ላይ፤ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ እንዲወጣ ያስፈለገው በሥራ ላይ ያሉት ሕጎች ሽብርተኛነትን በቢቂ ሁኔታ መከላከል ስላላስቻሉ መሆኑ ተገልጿል። እውን በሥራ ያሉት ሕጎች ሽብርተኛነትን ለመከላከል ብቁ አልነበሩም?በመሠረቱ ከሆነ በሥራ ላይ ያሉት ሕጎች በጣም ጥብቅ (ቀፍዳጅ) ከመሆናቸው አንፃር ሽብርተኛነትን መከላከል አያቅታቸውም ነበር። ዋናው ነገር ኢህአዴግ ተቃዋሚዎቹን ይፈራል። የተቃውሞ ትግልን ለማዳከምና ዜጎችን ለማስደንገጥ ሲል የፈጠረው ነገር ነው።

አድነት ፓርቲ ከዚህ በኋላ ንፅህናቸውን የሚመሰክርላቸው አባላቱንም ሆነ ሌሎች “የፖለቲካ እስረኞችን” ለማስፈታት ምን እያረገ ነው? እንዲሁም በየክልሉ ላሉ አባሎቹ ምን ከለላ ነው የሚያደርገው?እኛ ለአባሎቻችን ምንም ዓይነት ዋስትና መስጠት አንችልም። በፕሮግራማችን አምነውና ሕገ-ደንቡን ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ አባሎቻችን ዋና ዓላማቸው ትግሉን ማጠናከር እንጂ ስለራሳቸው መጨነቅ አይደለም። ፓርቲያችንን የሚቀላቀሉ ሰዎች እንዲያውቁት የምናደርገው በመጀመሪያ ደረጃ ትግል ውስጥ ሲገቡ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ሊከፍሉ እንደሚችሉ ማስገንዘብ ነው።ይኼንን አውቀው ነው እኛ ጋር የሚገቡት እንጂ ከለላ ፍለጋ አይደለም። ከለላ ፈልጎ የሚመጣማ ቀድሞውኑ ታጋይ አይደለም ማለት ነው። ይኸ ሲባል ግን ታጋይ አባሎቻችንን ለአደጋ አጋልጠን ዝም ብለን አንጥላቸውም። በተቻለን መጠን የታሰሩ ሰዎች እንዲፈቱ፣ ወከባና እንግልት የሚደረስባቸውን ለመታደግ እንንቀሳቀሳለን። አሁን ሰሞኑን የታሰሩብንን አባሎች ለማስፈታት ግብረ-ኃይል አቋቁመናል። ግብረ-ኃይሉ በሕጋዊ፣ በሰብዓዊ እና በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በሕዝብ ግንኙነት እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ነው።

“ዓላማችን የኢትዮጵያን ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ነው” ትላላችሁ። ግን አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ይኸን እንዴት ነው የምታሳኩት?ያሉትን ወቅታዊ ችግሮች በጋዜጣዊ መግለጫዎችና በሌሎች መንገዶች እየለፅን ነው። ኹኔታዎቹን ስንገልፅ ሕዝቡ ደግሞ ከችግሩ ለመውጣት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ አለበት። ሕዝቡ ራሱ ለመብቱ፣ ለነፃነቱና ለዴሞክራሲ ካልታገለ የእኛ ሥራ ብቻውን ውጤት ሊያመጣ አይችልም። ሕዝቡን እግዚአብሔር ከሰማይ ወርዶ ነፃ ሊያወጣው አይችልም። ሕዝቡ የተነፈገውን መብቱን ለማስከበር ራሱ መታገል አለበት።እኛም ይኼን ለማሳካት የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወንን ነው። በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናት ያደጉ ባለሙያዎችን እየጋበዝን ውይይት እያደረግን ነው። ቀስ ብለን ደግሞ ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ለማካሔድ አቅደናል። የአባላት ምልመላና የፓርቲ ማደራጀት ሥራም በከፍተኛ ሁኔታ እያከናወንን ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ መግለጫዎችን ከመስጠት ባለፈ ሌሎች ሰላማዊ የተቃውሞ ሥልቶችን አትጠቀሙም። ምንድን ነው ምክንያቱ?ሌሎቹን ሥልቶች መጠቀም ግድ የሚለን ደረጃ ላይ አልደረስንም ብለን ስለምናስብ ነው። ምክንያቱም ከምርጫ 97 በኋላ የሆነውን ነገር ማንም ኢትዮጵያዊ ያስታውሳል። ከዛ እንደገና መሪያችን ብርቱካን ሚደቅሳ ታሰረች። እንዲሁም የውስጥ ችግሮች ነበሩብን። እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት እየሞከርን የምርጫው ጊዜ ደረሰ። በአንድ በኩል ከኢህአዴግ የሚመጡብንን ችግሮች ስንከላከል፣ በሌላ በኩል እነዚህን የውስጥ ችግሮች ለመፍታት ስንንቀሳቀስ ነው የቆየነው።ከዚህ በኋላ ነው ሁሌ ኢህአዴግ ላይ ለድክመቶቻችን መንስኤ ጣት ከመቀሰር ወደ ራሳችን መመልከት የጀመርነው። ከዚህ አንፃር የመጀመሪያ ግምገማ አካሂደን በግምገማው ውጤት መሰረት የሥራ አስፈፃሚውን አባላት አቀያይረናል። 18 የነበረውን የሥራ አስፈፃሚ አባላት ቁጥር ወደ 13 እንዲቀነስና ወጣቶች ወደ አመራር እንዲመጡ ተደርጓል።ወደ ጥያቄህ ስመለስ … ሌሎች ሰላማዊ የትግል

አካላት “መቼ ነው መንግስትና ተቃዋሚዎች ልዩነታቸውን አጥብበው ወደ ውይይት የሚመጡት?” የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው። የእናንተ ፓርቲ በዚህ ረገድ ምን እየሰራ ነው?በአንድነትም ሆነ በመድረክ በኩል ከሁለት ዓመት በላይ ነው “ወደ ውይይት እንምጣ” የሚል ጥሪ ለገዢው ፓርቲም ሆነ ለመንግስት ስናቀርብ የቆየነው። እኛ ነገሮች እንዲካረሩ አንፈልግም። በዚያው ልክ ደግሞ ነገሮች እንዳይካረሩ በመስጋት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሲጣሱ እያየን ዝም አንልም።ከመብት ጥሰቶች ባሻገር አስከፊ የሆነ ድህነት ሕዝቡን እያሰቃየ ነው፤ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት በየቀኑ እየጨመረ ነው። እነዚህ ችግሮች ደግሞ ጊዜ ሳይሰጣቸው ሊፈቱ የሚገባቸው ናቸው። ለችግሮቹም መፍትሔ ለመፈለግ ኢህአዴግ ‹‹ለሁሉም መፍትሔው እኔ ጋር ብቻ ነው ያለው›› የሚለውን ነገር መተው አለበት። እኛ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ጥሪ እያቀረብን ነው። ግን ሊሰማን ፍቃደኛ አልሆነም።

ሥልቶችን ለምሳሌ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ የረሐብ አድማ፣ ቤት ውስጥ መቀመጥ ወዘተ ወደ ማድረጉ የምንመጣው ያሉብንን የቤት ሥራዎች ከጨረስን በኋላ ነው። አሁን ለምሳሌ ሰላማዊ ሰልፍ ዝም ተብሎ አይወጣም - አደገኛ አካሄድን የሚከተል ገዢ ፓርቲ ባለበት አገር ሰልፍ ቢጠራ የሚሆነውን ነገር ማሰብ ይከብዳል። ሰርጎ ገቦቹን በማስገባት ሆን ብሎ ሰላማዊውን ሰልፍ ሊያውክና አቅጣጫውን ሊያስቀይስ ይችላል። ስለዚህ ይህንን አስቀድሞ ለመከላከል ብዙ ቅድመ ዝግጅቶችን ይጠይቃል። ሌሎች ፓርቲዎችም በጋራ ሰልፍ እንድንጠራ ጥያቄ አቅርበውልን ነበር። ግን እንዳልኩህ ጉዳዩ ትልቅ ኃላፊነትን የሚጠይቅና በጥንቃቄ መያዝ ያለበት ስለሆነ ጥያቄያቸውን ለጊዜው አልተቀበልነውም። በተጠቀሱት ምክንያቶች አስገዳጅነት ነው እንጂ ከኑሮ ውድነቱ፣ ከሥራ አጥነቱና ከፖለቲካዊ ቀውሶቹ አኳያ በአሁኑ ሰዓት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራት ይቻል ነበር።

ከሰላማዊ ትግል ውጪ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ የምትኮንኑት ኢትዮጵያ ውስጥ እስካላችሁ ድረስ መተግበር ስለማትችሉት ነው ወይስ የምር የትጥቅ ትግልን ስለማታምኑበት ነው?የትጥቅ ትግልን አናምንበትም። ምክንያቱም የትጥቅ ትግል ሲባል ቀላል ነገር አይደለም፤ የሰው ሕይወትን ይቀጥፋል። የአገር መሠረተ-ልማትን ያወድማል። ከዚህ ባሻገር የጠብመንጃ አስከፊነት የሚያሳዩ ሁለት ተሞክሮዎችን በኢትዮጵያ ማንሳት ይቻላል። አንዱ የወታደራዊው መንግስት ጠብመንጃ ይዞ አገሪቱን 17 ዓመታት ቀጥቅጦ ገዝቷል። በወቅቱ ደርግ በሰላማዊ መንገድ ሥልጣኑን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ባለመሆኑ በትጥቅ ትግል ሊወርድ ችሏል። ደርግን በኃይል ያስወገደው ኢህአዴግም ደግሞ በተራው ጠብመንጃ በመያዝ የሕዝቡን መብት እንዳሻው እየረገጠ ይገኛል። ሥልጣኑንም ያለ አግባብ ሲጠቀም ቆይቷል።ስለዚህ እነዚህ ሁኔታዎች የሚያሳዩት ነገር በመሳሪያ ኃይል ሥልጣን ላይ የሚመጡ ድርጅቶች ፍፁም ኢ-ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆኑ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እነሱም ከሥልጣን መውረድ የሚፈልጉት ወደ ሥልጣን በመጡበት አኳኋን ነው።

አሁን ነገሮች በጣም እየከረሩ ናቸው። አንዳንድ ገለልተኛ

አሁን ያለው ሁኔታ ለተቃዋሚዎች ፈታኝ መሆኑን የሚገልፁ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ በአንፃሩ ደግሞ ተቃዋሚዎች አብረው በመስራት ራሳቸውን የሚያጠናክሩበት መልካም አጋጣሚ ተደርጎም እየተወሰደ ነው … የመድረክ ጉዳይ ከምን ደረሰ?አሁንም በውይይት ላይ ነን። በቅርብ ጊዜ ውይይቱ ተጠናቆ ውጤቱን ይፋ እናደርጋን።

ግንባር ነው የሚሆነው ወይስ ውህድ ፓርቲ?በአንድነት በኩል ያለው ሐሳብ “ብንዋኻድ ጥሩ ነው” የሚል ነው። ሌሎች ደግሞ ግንባር መሆኑን የሚፈልጉ አሉ። ዞሮ ዞሮ በጥንቃቄ እየሰራነው ነው። እያንዳንዱ ድርጅት የየራሱ ተሞክሮ፣ ፕሮግራም እና ርዕዮት-ዓለም ስላለው በችኮላ የሚሆን አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ አሁን ካሉት የመድረክ አባል ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎች ድርጅቶች ፕሮግራማችን የሚመቻቸው ከሆነ መድረኩን እንዲቀላቀሉ በሩን በይፋ ክፍት አድርገነዋል። ከዚህ በተጨማሪ በአገሪቷ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመድረክ አባላት ባይሆኑም ከሌሎች ጋር ተባብረን ለመስራት ሁኔታዎችን እያስተካከልን ነው።

እስኪ አሁን ወደ እርስዎ ልምጣ … “ዶ/ር ነጋሶ ሕብረ-ብሔራዊነት በሚያራምደው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ውስጥ ከገቡ በኋላ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚያደርጉትን ትግል ትተዋል” የሚል አስተያየት እየተደመጠ ነው። ምን ምላሽ አለዎት?አንድነት ፓርቲ የገባሁበትን ሂደት መለስ ብለን ስናየው … የመድረክ መስራች አባል ነኝ። እና መድረኩ ሕጋዊ ዕውቅና አግኝቶ ሲመዘገብ አንድ ሰው እንደግለሰብ አባል መሆን አይችልም። የግድ የፓርቲ አባል መሆን አለበት። እኔ ደግሞ በወቅቱ የፓርቲ አባለ አልነበርኩ። ስለዚህ የግድ አንዱ ፓርቲ ውስጥ መግባት ነበረብኝና አንድነትን መረጥሁ። አንድነትን የመረጥሁበት ምክንያት ፕሮግራሙ በጣም ስለተመቸኝ ነው። ፓርቲው ለግለሰብ መብቶች የሚታገለውን ያህል ለቡድን መብቶች መከበርም እንደሚታገል በፕሮግራሙ ላይ ሰፍሯል። ርዕዩት-ዓለሙ ሊበራል ዴሞክራሲ ቢሆንም ከሶሻሊዝምና ከኮንሰንሰስ ዴሞክራሲ የተቀበለው አለ ይላል። እንደገና ደግሞ የአገሪቱን የፖለቲካ ችግሮች በጠብመንጃ ሳይሆን በሰላም መፍታት አለብን። ይሄ ካልሆነ ጉዳዮቹ ላይ ሕዝቡ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ነው የሚለው።ለምሳሌ የፌዴራሊዝምና የሕገመንግስት ጥያቄዎች ላይ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ በሕዝበ-ውሳኔ እንዲፈቱ ነው አቋሙ የሚፈልገው። አንድነትም ውስጥ ሆኜ ለኦሮሞ ሕዝብ መብቶች እታገላለሁ። ለኦሮሞ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የጭቆና ሰለባ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን በመሉ እታገላለሁ። ስለዚህ አንድነት ውስጥ በመግባት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ መከበር እያደረኩት ያለው ትግል በቀጥታ ለኦሮሞም ሆነ ለሌላው ሕዝብ እስከሆነ ድረስ ‹‹ትግሉን ትቷል›› አያሰኝም።

በአንድነት በኩል ያለው ሐሳብ

“ብንዋኻድ ጥሩ ነው” የሚል ነው።

ሌሎች ደግሞ ግንባር መሆኑን የሚፈልጉ

አሉ። ዞሮ ዞሮ በጥንቃቄ እየሰራነው

ነው። እያንዳንዱ ድርጅት የየራሱ ተሞክሮ፣

ፕሮግራም እና ርዕዮት-ዓለም ስላለው

በችኮላ የሚሆን አይደለም።

Page 18: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

“ስልጣን እማልፈልግ ...

18

ሴት

ሴየሐሙራቢ ሕግ ሆይ

… የት ነህ?

በመቅደስ ፍስሐ [email protected]

‹‹አስተውሎ የሚራመድ ብዙ ርቀት ይጓዛል›› የሚለው አባባል፣ አባባል ብቻ ሆና የቀረበት ዘመን። ራስ ወዳድ ሰው የነገውን ውጤት እንደምን ያስተውላል? ለእሱ ጊዜያዊው እርምጃው ጋርዶታልና ማስተዋል አይሆንለትም። ‹‹ሰው›› የተባለው ፍጥረት ‹‹ሰው›› ለመባሉ የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ካላሟላ ከ‹‹እንስሳ›› በምን ይለያል?

በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከቀን ወደ ቀን በጣም ‹‹ዘመናዊና ሥልታዊ›› በሆነ መልኩ (አሳፋሪ በሆነ መንገድ) እየተሻሻለ ነው። አስገድዶ ደፈራ፣ ድብደባ፣ የአሲድ ጥቃት …

አዲሱ የተወሰኑ ወንዶች ሴትን የማጥቂያ መንገድ ነው - አሲድ። በእሱ ይብቃ ብለን ጉሮሮአችንን ሳናሳርፍ በቅርቡ የቀድሞ ባለቤቱ በሆነችው አበራሽ ኃይላይ በምትባል የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ ሴት ላይ አይን የማጥፋት ‘ወንጀል’ በመፈፀም ጉድ አሰኘን። አይን በማጥፋት ብዬ አቀለልሁት ይሆን? አይን ጎልጉሎ በማውጣት ብለው ይሻላል።

ፀፀት የለም። ሀፍረትም ሆነ ጥፋተኝነት አልተሰማውም። ማን አለብኝነት የተቀላቀለበት ይህ አይነት ጥቃት ቀጥሎ ወደየት ይሄዳል አንለውም - ምክንያቱም ከዚህ የገዘፈ ጥቃት ከየት ይመጣል? ይሄን ሰይጣናዊ ድርጊት ሰይጣን ራሱ ማወቁን እጠራጠራለሁ።

ይሄ ጥቃት - በፊልሞች ላይ ከምንመለከተው አይነት ጭካኔያዊ ትዕይንት /Horror/ እንኳ ወጣ ይላል። ምክንያቱም በፊልም ዓለም እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች የአስተሳሰብ ችግር፣ አለያም ትክክለኛ ‹‹ሰው›› ከምንለው ፍጥረት ወጣ ያለ ተፈጥሮን የተላበሱ ናቸውና ለሌላ ጥቃት እንጂ ለፀፀት ጊዜ የላቸውም።

ሴቶች እንዲህ ያለውን ጥቃት ለማድረስ የ‹‹እናትነት›› ባህሪያቸው አይፈቅደውም። የእነሱ የመጨረሻ እርምጃ ‹‹ጥሎ መሰደድ›› ነው የሚሆነው። በቅርቡ እንኳ በኢራናዊ ጓደኛዋ የአሲድ ጥቃት የደረሰባት ሴት በተመሳሳይ መንገድ በእሱ ላይ ጥቃቱን እንድታደርግ ቢፈረድላትም ‹‹አይሆንም›› በማለት ምህረቷን ሰጥታ ሩህሩህነቷ እስከምን ድረስ እንደሆነ አሳይታዋለች።

ሌላኛው ‘ወንጀል’፤ መስከረም 4 ቀን 2004 ደግሞ ቤቴል አዲሱ ለምትባል ሴት አዲሱ ዓመት በዓሲድ እንድትቀበለው ምክንያት የሆናት ሰው ተብሎ የተጠረጠረው - የፍቅር ጓደኛዋ ነው።

ዛቻና ማስፈራሪያውን ለማስቀረት በሚል ወደሚመለከተው አካል ድምጿን ብታሰማም ጆሮው የሰነፈው አካል ዛሬ አሲድ ባንገበገበው ድምጿ ኡኡ ስትል ከወለጋ አዲስ አበባ ቢሰማ ዋጋ ቢስነት ነው።

እንዲህ ያስብላል - የሐሙራቢ ሕግ ሆይ የት ነህ? ከክርስቶስ ልደት በፊት የባቢሎናውያን ሕግ እንዲህ ነበር። አይን ላጠፋ ዓይን ይጥፋ፤ ጥርስ ላወለቀም እንዲያው ጥርስ ይውለቅ። እንዲያ የማናስብ ብዙዎች ነን - ግራ ጉንጫችንን ስንመታ ቀኙን ደግመን መስጠት የምንፈልግ። የድርጊቱ አስከፊነት ጎላ ሲል ግን የባቢሎናውያኑን ንጉስ፣ የሐሙራቢውን ሕግ የማንመኝ አለን ይሆን? አሲድ ለደፋ አሲድ።

አሲድ በአሁን ሰዓት የሴቶች፣ የእህቶች፣ የእናቶች ስጋት ሆኗል። ‹‹እንዲህ ከምትሆን ቢገላት ይሻላል›› እንል ይሆናል። ይህቺ ሴት እውን በህይወት አለች? አይመስለኝም። የሰው ልጅ በደረሰበት መጥፎ ጥቃት እንደምን ነገን ያስባል። ነገን ማሰብ ያልቻለ ሁሉ እንደሞተ ቢቆጠር አያስማማን ይሆን?

ብዙው ማሕበረሰብ ከወራት በፊት የአሲድ ሰለባ የሆነችውን ትዕግስትን እያሰበ ‹‹ተገላገለች›› አለ። የእሷ ስቃይ ያበቃ ቢመስለንም የእኛ ጥቃት “ምዕራፍ አንድ … ሁለት” እያለ መሄዱን እንደምን መገንዘብ አቃተን?

የአሲድ ጥቃቱ በዚህ የማያበቃ ይመስላል። በሚዲያ መነገሩ፣ በጋዜጦች መፃፉ ለጥቃቱ ፈፃሚዎች አበረታች እስኪመስል ድረስ አሁንም ቀጥሏል። ሴቶቻችን ዋስትና ያጡበት ዘመን ላይ የደረስን እስኪመስለን አሳስቦናል።

የአንድ ሰው ጥፋት ምንም ይሁን ምን አሲድ ሊሆን ይገባል? ይሄንን ጥቃት በሴቶች ላይ ብቻ በተደጋጋሚ መፈፀሙ፣ ‹‹ወንዶች (የተወሰኑት ማለቴ ነው) ምን ነካቸው? ሰብዓዊነት የሚባል ነገር አልተፈጠረባቸውም እንዴ?›› ብለን እንድንጠይቅ ያደርጋል።

ውስጣቸው እንጥፍጣፊ የምታህል ስብዕና የሌላቸው፣ የቅርቡን እንጂ የሩቁን በማያስቡ ደፋርና ጨካኝ ማንነት ባላቸው ግለሰቦች የተሞላች አገር ለትውልድ ከማስከረባችን በፊት ኬላ ሊበጅለት ግድ ነው።

ከዚህ ቀደም ለደረሰው ጥቃት ይበል የሚያሰኝ እርምጃ ያለመውሰዳችን ውጤት ዛሬ ላይ እየታየ ነው። የእያንዳንዳችንን በር አንኳኩቶ የመጣ ቀን ብንጮህ ምን ዋጋ ይኖረዋል? ከንቱ የደንቆሮ ጩኸት ነው።

ድርጊቱ አሳሳቢ ነው፤ አስደንጋጭ ነው። ከአንድ ‹‹ክቡር›› ከምንለው ፍጥረት የማይጠበቅ ማን አለብኝነት ነው።

በትላንትናው እለት በሸራተን አዲስ ‹‹አሁን በዓይኔ መጣህ›› በሚል መሪ ቃል የጥቃት ሰለባ የሆኑት እህቶቻችን ‹‹መፍትሄ›› እንዲበጅላቸው አንድ ፕሮግራም በላሊበላ አዳራሽ ተከናውኗል።

እንባ ምንን መልሶ ያውቃል? እናቶች ያለቅሳሉ፤ እህቶች ያነባሉ፤ ሴቶች ይጮሃሉ። ነገር ግን ሰሚ የለም። በዚያ አዳራሽ የነበረው እንባ የእንስቶቹን ጥቃት ማቆም ቢችል የትናንቷ ቀን ቅዱስ ነበረች።

በሰራው ጥፋት የሚፀፀት እንዴት መልካም ሰው ነው? አበራሽ ኃይላይን ብርሃን ያጨለመው የቀድሞ ባለቤቷ ‹‹ንብረቶቼን እንድሰበስብ የዋስ መብቴ ይከበር›› ብሏል። አጀብ የሚያሰኝ ነው።

ማስተዋል ከየት አለች? ሰብዓዊነትስ? የነገውን ውጤት አለማገናዘብ የገብጋባነት፣ የራስ ወዳድነትና የአለአስተዋይነት ምልክቶች ናቸው። ለዚህም ነው የንጉስ ሐሙራቢ ሕግ ሆይ ወዴት ነህ? ማለታችን።

ምንድን ነው? የታክሲ ዋጋ አሁንም ይጨምራል። የገቢ መጠናቸው እምብዛም ለውጥ የማያሳይ ብዙ ሰራተኞች ደግሞ አሉ። እኒህ ሰዎች ምን ይሁኑ?

ከፍ ሲል እንዳልሁት ነፃ የሆነ የእግረኛ መንገድ ማግኘትም ይቸግራል። ከብሔራዊ ሜክሲኮ፣ ከሜክሲኮ ልደታ፣ ቄራ፣ ጎፋ፣ ሳር ቤት፣ ወዘተ፤ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፤ ወደመገናኛ፣ ሃያ ሁለት . . . ነፃ የእግረኛ መንገድ

አንዳንድ ምሬቶች...አይናፍቃችሁም?

በራሳችን ሀገር በእግራችን መዘዋወር የተከለከልንበት ጊዜ ስለሆነ ያሳዝናል። ከላይ እስከ ታች በሸቀጣ ሸቀጥ ግጥም ብሎ ይሞላል። ሰዉ በየት ይለፍ?

ይህ ቸልተኝነት ካልሆነ በስተቀር የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ይህንን ነገር ለማስተካከል አቅም ያጣሉ ብዬ አልገምትም። በእውነት አስበውበት ከተንቀሳቀሱ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ነፃ የአግረኛ መንገድ እናገኝ ነበር።

ደግሞ ሌላ፡-‹ ‹ ይ ቅ ር ታ ፤

የደወሉላቸውን ደንበኛ አሁን ማግኘት አይችሉም።›› ይህ ድምፅ ያላስበረገገው የከሰሞኑ ሞባይል ተጠቃሚ ስንት ይሆናል?

ኢ ት ዮ - ቴ ሌ ኮ ም እድገትን ያመጣል ሲባል ዘመናዊ ኔት-ወርክን በማስፋፋት ነው ብዬ አስብ ነበር። እድገቱ ግን የቃል፤ ማለትም፣ ‹ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ናቸው› ከሚለው ወደ ‹አሁን ማግኘት አይችሉም›።

ኢ ት ዮ - ቴ ሌ ኮ ም ሲቀጥል፡-

በየቀኑ ሲም ካርድ

ግዙ እያለ የፅሁፍ መልዕክት ይልካል። በእርግጥ ይህ መልዕክት ዋጋ አይከፈልበትም ይሆን? አጋጣሚው ስለተገኘ ደምበኛን ማሰልቸት ኢትዮ-ቴሌኮምን አያስመሰግነውም፤ ጥርት ያለ ኔት-ወርክ መዘርጋት ግን ያስጨበጭብለት ነበር።

ከዚህ በላይ የፃፍኳቸው ምሬቶች ናቸው። ሌሎችም ብዙ የምናማርርባቸው ጉዳዮች አሉ። ግን ማማረራችን ምሬት ብቻ ነው፤ ሰሚ የለውም። አሁን ግን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ መጽደቅ ወዲህ የግል ጋዜጦች በመንግሥት እየተነበቡ ስለሆነ ዛሬ ያነሳናቸው ምሬቶች መፍትሄ ያገኛሉ።

በላዩ ላይ ሰፍሯል። እናም ወዳጄን ለምንድነው

የምታስገድዱት? ብለው ባዋጣነው መዋጮ፣ በገዛነው ቦንድ የአባይ ግድብ እንዲሰራ ነዋ! አለኝ። ይሄን ጊዜ ኡፍፍፍ... ስል ተንፍሻለሁ። ነው ይሄ ወዳጄ ሀሳቡ ሌላ ሆኖ ካድሬ ጓደኛውን ጠርጥሮኝ እጥፍ ብሎ ይሆን? ሳይሆን እንዳልቀረ የተረጠርኩት ‹‹እናንተኮ እናታችሁ አንድ ናት። የገረመኝ የመነፅራችሁ አንድ መሆን ነው። ገደሉን ሜዳ፣ ረሀቡን ጥጋብ፣ ወዘተ… ወዘተ እያደረጉ ነው የሚያሳያችሁ ቀናችሁን …›› ብሎኝ ላሽ አይልም? ሰኔ ሰላሳ ነው? ሳልለው ቀረሁ ‹‹ኧረ ሳቄ ናልኝ›› አለች ጄኔፈር ሎፔዝ። እውነቷን ነውኮ ከድርጅቴ ይነጥለኝ አንዳንዴ ሳቅ ይጠፋል። ቀናችንን…. ግን እኛ እንጠቀምበታለን፤ ገና ሦስት ዲጂት እናድጋለን።ሳልረሳው ልንገራችሁማ ይኸው

ልጅ ከእኛ ድርጅት አባል ጋር በቅርቡ በትዳር ተሳስሯል። አንድ ምሽት ደወለልኝና ‹‹ምንድን ነው በየቀኑ እንገማገም ትለኛለች›› አለኝ። ሌላስ? ‹‹የወደ ፊት እቅዳችንን ስናወራ ‘ለአምስት ዓመቱ የትዳርና የኑሮ እቅዳችን ከእኛ ብቻ ሳይሆን ከጎረቤቶቻችን ብዙ ይጠበቃል!’ ትለኛለች። ጎረቤቶቻችን በእኛ ትዳር ምን አገባቸው?›› ሌላስ ‹‹ልማታዊው ትዳራችን በዚህ ዓመት ሁለት ዲጂት እድገት ማሳየት እንዳለበት እወቅ ትለኛለች›› ሲለኝ ታዲያ እቺን የመሰለች ትራንስፎርም ያደረገች ሚስት ማግኘት መታደል አይደለምን ብለው? በረዥሙ ተንፍሶ ኮስተር ብሎ ‹‹ሚስት ሳይሆን ኢቴቪን ያገባሁ

ነው የመሰለኝ›› ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመው። በሉ ፀረ ትዳር ኃይሎች መሀከላችሁ ገብተው እንዳይለያይዋችሁ ግለ ሂስ በማካሄድ ቤታችሁን አፅዱ ብያለሁ። ወዳጆቼ ደግሞ የመስቀል በዓል

ከች አለች አይደል? ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ ብያለሁ። በዘመን መለወጫ በዓል ኪሳችሁ ፀዳ ያለችባችሁ ከእኔ ጎረቤት ተሞክሮ ውሰዱ ወላዲቴን! በዓመት ያሉት በዓላትን እጣ አስገብተው የወጣለት በዓል እንደ ነገሩ ይከበራል፤ እና ታዲያ ዘንድሮ እድለኛው ዘመን መለወጫ ነበር። እኒህ ወዳጆቼን ለገና አግኝታችሁ እንኳን ለገና በዓል አደረሳችሁ ብትሏቸው ‹‹ገና የቱ?›› ብለው ሊጠይቋችሁ ይችላሉ። ‹‹ዘይገረም ሻሸመኔ!›› አሉ እኒያ ሴትዮ!ኑሮ መናሩን አንዱ ያሳየኝ ህፃናት

ለአዲሱ ዓመት የሰጡኝ የመልካም ምኞት መግለጫ አበባ (ወረቀት) ሰልቫጅ መሆኑ ነው። በደጉ ጊዜ የተሰጡትን በሁለተኛው ቀን ሄደው ሰብስበው ለቀጣዩ ዓመት እንደሚዘጋጁ ነግረውኛል። ይህችን ተሞክሮ ታች ሰፈር መውሰድ ደግ ነው ብዬ አንዱን ተላከኝ ብለው ‹‹ታች ሰፈር በ6 ወር አንድ ጊዜ ነው የምሄደው አለኝ›› የገረመኝ ምክንያቱ ነው ያለምክንያት የታክሲ ዋጋ በመጨመሩና በአቅም ማነስ አለኝ። የታክሲ ዋጋ ለመጨመሩም መንግስት ላይ አይኑን አፍጧል። [ሰው እጁን መንግስት ላይ መጠቆም ይወድ ነበር ይሄ ደግሞ አፍጣጭ ነው]። እርግጥ ነው መንግስታችን ለህዝብ የቆመ… ብዬ ተናግሬ ሳልጨርስ በቃህ! አለኝ... ‹‹ድጎማውን አነሳችሁ። ዝም አልን፣ ጭራሽ ነዳጅ እየቀነሰ

ባለበት ወቅት የታክሲ ዋጋ ጨመራችሁ። ከ80 ሚሊየን ህዝብ ጥቂት የታክሲ ባለንብረቶች ችግር በድንገት የገባችሁ የፈራችሁት ነገር አለ እንዴ?›› ሲል ሳቅኩበት የምን ፍርሀት? እኛጋ ፍርሀት አይታወቅም ብለው ተቀኘብን።እየነገርናቸው እያረጉት ዋዛ ደስ ከሚሰኘው የተከፋው በዛ አለኛ! ሆሆይ! ብሶት እንዲህ

ገጣሚ ያረጋል’ንዴ? ለማንኛውም እንዲካሄድ የመንግስታችን አቋም አብስትራክት ሆኖባችሁ ነው እንጂ አንድና አንድ ነው። በፍትህ ላይ መሠረቱን የጣለ፣ በልማታዊነት ላይ ኮለኑን የገነባና ከሙስና የፀዳ ቱንቢ በመጣል ፊኒሽንጉን ለማሳመር ሶምሶማ በመሮጥ ላይ ነው ብለው ነገር መምዘዙን ስለማያቆም ብዬ ተውኩት እሎታለሁ። [ውድ አንባቢያን አሁን የዜና

ሰዓታችን የደረሰ በመሆኑ ከዜናው በኋላ ተመልሰን እንደገና እናወጋለን።]ጤና ይስጥልኝ ዜና እናሰማለን፤

ምክንያቱም ከማን እናንሳለን። በሀምሌ ወር በአገራችን የነበረው የዋጋ ግሽበት 39.2 በመቶ የነበረ ቢሆንም እድሜ ለመንግስታችን በነሐሴ 40.6 መድረሱን ያዩ ግሽበቱ መጨመር እንጂ መቀነስ ያላሳየው መንግስት ይህም እድገት መስሎት ሊሆን ይችላል ብለው እንደገመቱ ለሪፖርተራችን ሹክ ብለውታል። ዊክሊክስ የሚባለው ቱሪናፋ

ኬብል ጠላፊ በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና ሌሎች ፖለቲከኞች ያወሩትን ማጋለጡ እኛም ያወራነውን አንድ ቀን ገሀድ ማውጣቱ አይቀርም ሲሉ አንዳንድ ተንበርካኪ ካድሬዎች ቦክተው አስቦክተውናል። ዊክሊክስ ሆይ ደግሞ አፍሪካ መጣህ? ጎሽ እስቲ ለ‹‹ሽብር›› ሲያሴሩ ስለተያዙም ሰዎች መረጃውን አንድ ቀን እንደምታደርሰን እንጠብቃለን። ይህን ከነገርከኝ ባለመርገፍ ጃንጥላ

ከነነብሴ አውስሀለሁ ያሉት ወ/ሮ እየተፈለጉ ሳይሆን አይቀርም ተባለ። በተያያዘ ዜና ‹‹መንግስት ሽብርተኞችን ማሰር የቀበቶ ማሰር ያህል ቀሎታል›› ሲሉ ያሸሞሩ ግለሰብ ምን ለማለት እንደፈለጉ እንዲያስረዱ ከእለታት በአንዱ ቀን ይጠራሉ ተብሎ ተገምቷል። ለማንኛውም ከዜናው

ተመልሰናል። በሞቴ ሳልረሳው ላውራውማ ሰው ግፍ አይፈራም? ወይስ ግፈኛ በአቋራጭ ገነት ይገባል ተባለ? መሰለኛ! የአየር መንገዷን የበረራ አስተናጋጅ አይኗን ያወጣው ‹‹ሰው›› ነገር አላሳዘናችሁም? ይኸው በሚስትና ባል መካከል ሽብር አንግሷል። ሌላም ሴት አሲድ ተደፍቶባት የካቲት 12 ሆስፒታል ተኝታለች የሚለውን ወሬም አውራምባ ታይምሶች ነግረውኛል። የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በሀሳብ ደረጃ ያለን ሽብር ብቻ ሳይሆን እየተፈፀመ ያለውንም ሊያተኩርበት ይገባል ያሉኝ አሉ። ‹‹ሰዉ አገሩ ላይ ቅሬታ እንዲገባው ያደረገው የዴሞክራሲ መታጣቱ ብቻ ሳይሆን የአደጋውም አይነት እየሆነ መጥቷል›› የሚሉ አስተያየቶችን ዋ! እያልንም ቢሆን እየሰማን ነው። ታይቶ የማይታወቅ 15

አትሌቶች ከሞዛምቢክ በዚያው ጠፉ መባሉንም በማሳያነት እየቀረበ ነው። በኤርትራ አትሌቶች እና ተጨዋቾች ሲሳለቁ የነበሩ ኤፍ ኤሞች የእኛም አትሌቶች ለምን እንደጠፉ እውነተኛውን ምክንያት ይነግሩናል ብለን ባንጠብቅም፣ እንጠብቃለን። ለማንኛውም አቶ ሽመልስ

ከማል ‹‹እስክንድር የሚባል ጋዜጠኛ አላውቅም›› እንዳሉት ሁሉ እኔንም ‹‹አንተን ብሎ ወግ ጠራቂ›› የሚለኝ መጥቶ ብዕሬን ካልያዘው ሳምንት እንገናኛለን። ሰላም እና ጤና ከሁላችን ጋር ይሁን!

ቤተሰቦች እንዲሁም የህግ ባለሙያዎችንና የመሳሰሉትንም ማነጋገር እንዲችሉ ኢብጋህ የማስተባበር ሥራ እየሰራ እንደሚገኝና አቅም በቻለ መጠንም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የሚችሉ የመንግስት ባለስልጣናትም ከተወካዮቹ ጋር ተገናኝተው እንዲወያዩም ለማድረግ እቅድ መያዙን ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ ጠቁሟል፡፡

በቅርቡ ከሽብር ተግባራት ጋር በተያያዘ ፖሊስ የጠረጠራቸውን ሰዎች በሚያስርበት ጊዜ ጋዜጠኞችም ጭምር ለእስር መዳረጋቸው በተቀሩት ጋዜጠኞች ዘንድ ሥጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ የብሔራዊ ጋዜጠኞች ህብረትም የጉዳዩን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ

በማስገባት ለጉዳዩ የማያዳግም እልባት ለመስጠት እንዲቻል ከሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጋር ተባብሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

‹‹ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የተለሳለሰ አቋም ይዟል፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ጋዜጠኞች ሲታሰሩና የፕሬስ ነጻነት አደጋ ላይ ሲወድቅ ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠት ተቆጥቧል›› ተብሎ ሲተች የቆየው ‹‹ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን››፤ ተወካዮቹ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ቢፈቀድላቸውም፣ በጋዜጠኞች ላይ በሚደርሰው እንግልትና እስር የተነሳ መንግስትን በፅኑ የሚተቹ የጋዜጠኞች መብቶች ተሟጋች

ተቋማት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን ሁኔታ ለማየት እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም፡፡

‹‹ሲፒጄ›› የተሰኘው የጋዜጠኞች መብቶች ተሟጋች ቡድን የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ቶም ሩድስ፣ የቡድኑ ወኪሎች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ለአውራምባ ታይምስ አረጋግጠዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ የፖለቲካና የሰብዐዊ መብት አያያዝ ለማጥናት ከመንግስት ፈቃድ አግኝተው ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩት የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ወኪሎች ጥናታቸውን ሳያካሂዱ መባረራቸው ይታወሳል፡፡

የቡድኑ አባላት በመንግስት የተባረሩበትን

ምክንያት ‹‹ስላለው ሁኔታ የመንግስት ባለስልጣናትን ካነጋገርን በኋላ የታሰሩ ጋዜጠኞች ቤተሰቦችንና ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን ማነጋገር በመጀመራችን ነው›› በማለት ገልፀው ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላት መባረር ባሻገር፣ ለቡድኑ መረጃ የሰጡ የመድረክ አመራሮችም መታሰራቸው የሚታወስ ነው፡፡

የአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ልኡካን ከአንድ አመት በፊትም ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሲሚንቶ ፋብሪካዎችንና ሌሎች መሰል የመሰረተ ልማት ተቋማትን ጎብኝተው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡

የታሰሩ ጋዜጠኞች በዓለምአቀፍ ...

Page 19: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

“አሁን በአይኔ መጣህ” ጸረ-ጥቃት ዘመቻ ተጀመረ“እየተሰራ ያለው ሥራ ፍፁም ፈሪነትን የሚያንፀባርቅ ነው››

ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ

‹‹አገራችን ውስጥ እምቢኝ፣ አሻፈረኝ የሚያሰኙ ብዙ ችግሮች አሉብን። ጫንቃችን ጥቃትን መሸከም የለበትም››አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ

‹‹እኛ አገር አንድ ወንጀለኛ የፈለገውን አድርጎ በሰላም መኖር እንደሚችል ያምናል”

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

19ዜናዎች

በናፍቆት ዮሴፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ለመጣው

በሴቶች ላይ ለሚፈፀሙ አሰቃቂ ጥቃቶች መንግሥት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ የሚያሳስብ ግልፅ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሊቀርብ ነው። ትላንትና ረፋዱ ላይ፣ ‹‹አሁን በአይኔ መጣህ›› በሚል መርህ የፀረ-ጥቃት ዘመቻ በሸራተን አዲስ ሆቴል፣ ላሊበላ አዳራሽ፣ በተካሄደበት ወቅት ለዘመቻው ስኬታማነት የድጋፍ ፊርማ ተሰብስቧል።

በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች እኛንም ይመለከተናል በማለት በተሰባሰቡ ተቆርቋሪዎች በተዘጋጀው በዚህ የጸረ-ጥቃት ዘመቻ ጉባዔ፣ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ሰዎች ቤተሰቦች፣ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ተወካዮች፣ የሴት ማኅበራት ቅንጅት ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ሥራ አስኪያጅ እና በርካታ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

እስከዛሬ በአሲድ፣ በገጀራ እና በመሳሰሉ መሣሪያዎች የተፈፀሙ አሰቃቂ ጥቃቶች አሁን ዓይነታቸውን ቀይረው፣ ሁለት ዓይን ጎልጉሉ እስከ ማውጣት መድረሱንና ይህም ከፍተኛ ቁጣን መቀስቀሱን የሴት ማኅበራት ቅንጅት

በሱራፍኤል ግርማ በወለጋ መንዲ ነዋሪ በሆነች ወጣት

ላይ እስካሁን ከተፈፀሙት የአሲድ ጥቃቶች ጋር ተመሳሳይነት ያለው ጥቃት ተፈፀመ። ጥቃቱ የተፈፀመባት ወጣት ቤቴል አዲሱ የምትባል ሲሆን፣ ጉዳቱን ያደረሳት ደግሞ የቀድሞ ፍቅረኛዋ የነበረ ግለሰብ መሆኑን እና ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር መሆኑን ቤተሰቦቿ ለአውራምባ ታይምስ አስታውቀዋል።

ጥቃት የደረሰባት የ21 ዓመቷ ወጣት የቀድሞ ፍቅረኛዋ ከነበረው ግለ-ሰብ ጋር መጣላቷን ተከትሎ በጦር መሳሪያ ጭምር ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርስባት እንደነበር ያስታወችው እህቷ ለምለም አዲሱ፣ ‹‹እንደዚህ ዓይነት ነገር ያደርጋል ብለን ባንጠብቅም ‹ከዚህ ከተማ ካልወጣች እገድላታለሁ› ሲል ነበር›› ብላለች፡፡ ሐሙስ መስከረም 4 ምሽት 2፡30 ላይ ከቤቷ ጠርቶ አሲዱን እንደደፋባት የገለፀችው የሰለባዋ ታላቅ እህት፣ ጩኸቱን የሰሙ ሰዎች

የዩጋንዳ ፍ/ቤት ለአማፂያኑ መሪ ምሕረት እንዲሰጥ አዘዘ የዩጋንዳ ሕገ-መንግስታዊ ፍ/ቤት፣ ‹‹ሎርድስ ሬዚስታንስ አርሚ›› የተባለውን የአማፂ

ቡድን በጦር አዛዥነት ሲመራ የቆየውና አሁን በእስር ላይ የሚገኘው ቶማስ ክዌሎ ምህረት እንዲደረግለት ትዕዛዝ አስተላለፈ። ሐሙስ ዕለት በፍ/ቤቱ ችሎት የተሰየሙት አምስቱም ዳኞች፣ የቀድሞ ወንጀላቸውን በማመን

ድርጊታቸውን ላወገዙ ሌሎች አማፂያን ምሕረት እንደተደረገው ሁሉ ቶማስ ክዌሎም ተመሳሳይ ዕድል ሊሰጠው እንደሚገባ ገልፀዋል። ሆኖም ከአማፂ በድኑ የጦር አዛዦች በዩጋንዳ ዓለም አቀፍ ወንጀል ፍ/ቤት በመቅረብ የመጀመሪያ

የሆነው ቶማስ ክዌሎ ምሕረት እንደማይገባው የሚሞግቱ የሕግ ባለሙያዎች አልጠፉም። ምሕረቱን የተቃወሙት የሕግ ባለሙያዎች በመከራከሪያ ምክንያትነት ያስቀመጡትም ተከሳሹ በወንጀሉ መፀፀቱን የገለፀው በ2009 እ.አ.አ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መሆኑን ነው። ‹‹ሎርድስ ሬዚስታንስ አርሚ›› በዩጋንዳና በአጎራባች አገራት ውስጥ የሚንቀሳቀስ አማፂ

ቡድን ሲሆን፣ የቡድኑ መሥራችና መሪ የሆነው ጆሴፍ ኰኒ በዓለም አቀፍ የወንጀል ፍ/ቤት ተፈላጊ ነው። (ምንጭ አሶሽየትድ ፕሬስ)

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ በ‹‹ዳይመንድ ጦርነት›› ሰዎች እየሞቱ ነው

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሚገኙ የዳይመንድ ማምረቻ ቦታዎችን መቆጣጠር በፈለጉ ሁለት ታጣቂ ቡድኖች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ40 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተዘገበ። በአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ መሠረት ግጭቱ የተቀሰቀሰው መስከረም አንድ ላይ ሲሆን፣ የሞቱት ታጣቂዎች ‹‹የዴሞክራቲክ ኃይሎች ለአንድነት›› እና ‹‹የፍትሕና ሰላም አርበኞች ጉባዔ›› የተባሉ ቡድኖች አባላት ናቸው። የዴሞክራቲክ ኃይሎች ለአንድነት ከሮንጋ ጎሳ የተውጣጡ ታጣቂዎች ያቋቋሙት ቡድን

ሲሆን፣ ‹‹የፍትሕና ሰላም አርበኞች ጉባዔ›› ደግሞ የሮንጋ ጎሳ ተቀናቃኝ የሆኑ የጎውላ ጎሳ አባላት የመሰረቱት ነው። ዋንኛ የዳይመንድ ማምረቻ በሆነችው ብሪያ ግዛት ግጭቱ መከሠቱን የዘገበው አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፍራንኮይስ ቦዚዜ ለብሔራዊ ሸንጎው ‹‹ማንም ሁለቱ ጎሳዎች ወደ ግጭት እንዲያመሩ አልቆሰቆሰም፤ እኔም ብሆን ተጠያቂ አይደለሁም›› ማለታቸውን አስነብቧል።

በሴኔጋል ሊካሄድ የታቀደው ሰልፍ ተሰረዘየሴኔጋል ገዢ ፓርቲ በአገሪቱ ሊካሄዱ የታቀዱ ፖለቲካዊ ሰልፎችን በሙሉ እንዳገደ

አስታወቀ። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሰልፍ ለማድረግ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው ውሳኔውን ይፋ ያደረገው ገዢው ፓርቲ፣ የብሔራዊ ሸንጎው ሁለተኛ ሰው የሆኑት ዲያዋር ቱሬን ሞት በምክንያትነት ማቅረቡን የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል። የሴኔጋል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የሚባለው ገዢው ፓርቲ ለጋዜጠኞች በላከው የፋክስ መልዕክት

‹‹አጠቃላይ የፖለቲካ ክበቡን በነካው ሐዘን ምክንያት ፓርቲው ማናቸውንም ዓይነት የፖለቲካ ሰልፎች በተለይም ለመስከረም 23 ቀን 2011 ቀጠሮ ተይዞለት የነበረውን መሰረዝ አስፈላጊ ሆኗል›› ይላል። ለመስከረም 23 ቀን 2011 (እ.አ.አ) ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ባለፈው

ሰኔ 23 ላይ የተካሄው ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ተከታይ ሲሆን፣ ሰልፉም የተዘጋጀው ‹‹የሰኔ 23 ንቅናቄ›› በሚባል ቡድን መሆኑን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘግቧል። ምንም እንኳ ገዢው ፓርቲ የተቃውሞ ሰልፉ መታገዱን ቢያስታውቅም የ85 ዓመት አዛውንቱ

ፕሬዝዳንት አብዱላዬ ዋዴ ከስልጣን እንዲወርዱ ጥሪ የሚያቀርበው ተቃዋሚ ቡድን ቃል አቀባይ ለአሶሽየትድ ፕሬስ ‹‹ሰልፉ በታቀደለት ጊዜ ይካሄዳል›› ብለዋል።

ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የበረራ አስተናጋጅ በሆነችው ወ/ሮ አበራሽ ኃይላይ ላይ የተፈፀመውና እጅግ አሰቃቂ የተባለው ይህ ጥቃት እጅግ እንዳሳዘናቸው የተናገሩት ወ/ሮ ሳባ፣ ‹‹አበራሽ ያለ ወንጀሏ ለዘላለም ታስራለች። ጥቃቱ ሲደርስባት እጇን ወደ ኋላ ታስራና አንገቷ በጫማ ተረግጦ በነበረበት ወቅት ያጋጠማትን ብቸኝነት አስቡት›› በማለት ተጠቂዋ ጥቃቱ በደረሰባት ወቅት ያደረባትን ስሜት ምስል ከስተው ባስረዱበት ወቅት አዳራሹ በለቅሶ ተሞልቶ ነበር።

የዘመቻው ዓላማ የተጎጂዎቹን ስቃይ ለመካፈልና መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳሰብ እንደሆነ ያስታወሱት ወ/ሮ ሳባ ገ/መድህን፣ ከወራት በፊት የአሲድ ጥቃት ተፈፅሞባት ከብዙ ስቃይ በኋላ ሕይወቷ ያለፈው የትዕግስት መኮንን ገዳይ [ተብሎ የተጠረጠረው] ግለሰብ አለመያዙ እንደሚያንገበግባቸው በመናገር፣ ‹‹[ለወንጀሉ ተጠርጣሪ] ኅብረተሰቡ ሽፋን ባይሰጠው ኖሮ ለፍርድ ይቀርብ ነበር›› ሲሉ ቁጭታቸውን

በውኃ አጥበው ወደ ህክምና ቦታ እንደወሰዷት ተናግራለች።

ቤቴል አዲሱ በአሁኑ ሰዓት ሕክምናዋን እየተከታለችበት በሚገኘው የካቲት 12 ሆስፒታል ያገኘናቸው የሕክምና ባለሙያዎች እንደገለፁልን ከሆነ በፊቷ፣ በግንባሯ፣ ግራ ዓይኗ፣ ደረቷ ላይና ሁለቱም እጆቿ ከፊትና ከኋላ በኩል ቃጠሎ ደርሶባታል። በአሲዱ የተቃጠለው የሰውነቷ ክፍልም ከአጠቃላይ ሰውነቷ 24 በመቶ ነው።

በሕክምና ባሉመያዎቹ ገለፃ መሠረት፣ ሰውነቷ ላይ የተደፋውና ወደ ውስጥ የዘለቀው የአሲድ መጠን ምን ያክል እንደሆነ አለመታወቁና የሞቱ ህዋሳትን ከቁስሉ ላይ ለማስወገድ አዳጋች በመሆኑ የጉዳቱ መጠን ከባድ ሆኗል፡፡ በዚህም የተነሳ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን ዓይኗን ለማከም አልተቻለም።

ተጎጂዋ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2003 ዓ.ም መመረቋን የተናገሩት ቤተሰቦቿ፣ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ በመሆኑ ለልጃቸው ዕርዳታ ይደረግ ዘንድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተማፅኖ፣ አቅርበዋል።

ተናግረዋል።እስከዛሬ በቢላዋ ቆርጠው፣ በጥይት

ደብድበው የሴቶችን ሕይወት የቀጠፉ ወንጀለኞች የሚጣልባቸው ፍርድ ፍፁም ተመጣጣኝ ባለመሆኑ፣ ጥቃቱ እየተባባሰ መምጣቱን የጠቆሙት ደግሞ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር መስራች አባል ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ናቸው። ‹‹የግድያ ወንጀል በየትኛውም የዓለም ሥፍራ የሚፈፀም ቢሆንም፣ በሌሎች ዓለማት ፍቅረኛውን (ሚስቱን) የገደለ ወንጀለኛ ራሱን ይገድላል ምክንያቱም ማምለጫ ቀዳዳ እንደሌለው ያውቃልና›› ያሉት ወ/ሮ መዓዛ፣ ‹‹እኛ አገር ግን አንድ ወንጀለኛ የፈለገውን አድርጎ በሰላም መኖር እንደሚችል ያምናል፡፡ ለዚህም አበራሽ ላይ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ፣ ‘ንብረቴ በየቦታው ስለተበታተነ እንድሰበስብ በዋስ ልቀቁኝ› ማለቱ የዚህ ውጤት ነው›› ሲሉ እንደ ወ/ሮ ሳባ ያደረባቸውን የቁጭት ስሜት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ጌታቸው ደግሞ በበኩላቸው ጉዳዩ እጅግ እንዳንገበገባቸው ገልፀው፣ አየር መንገዱ ድርጊቱን እንደሚያወግዝ

ተጨማሪ የአሲድ ጥቃት ተፈፀመ

እና አበራሽ ለሚያስፈልጋት ማንኛውም እርዳታ ከጎኗ እንደሚቆም ቃል ገብተዋል።

ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኢየሱስ ወርቅ ዛፉ ድርጊቱን ከሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ማንበባቸውን አስታውሰው፣ ‹‹ለመሆኑ ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈፀመው ሰው ነው?›› የሚል ጥያቄ አንስተዋል። ‹‹አገራችን ውስጥ እምቢኝ፣ አሻፈረኝ የሚያሰኙ ብዙ ችግሮች አሉብን። ጫንቃችን ጥቃትን መሸከም የለበትም›› ያሉት አቶ ኢየሱስ ወርቅ፣ ድርጊቱን ለማውገዝ እና ለማስቆም በሚደረገው ትግልና ዘመቻ እስከመጨረሻው እንደሚሰለፉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የፀረ-ጥቃት ዘመቻውን መድረክ በመምራት ላይ የነበሩት ወ/ሮ ሰሎሜ ታደሰ፣ ‹‹ይህ ድርጊት የኢትዮጵያዊ ወንዶች መገለጫ አይደለም›› ካሉ በኋላ፣ ‹‹የሀገራችን ወንዶች የሚታወቁባቸው በርካታ ገድሎች አሉ፡፡ እየተሰራ ያለው ሥራ ግን ፍፁም ፈሪነትን የሚያንፀባርቅ ነው›› በማለት አውግዘውታል፡፡

‹‹የአበራሽ ዓይን ሲጎለጎል የእኛም ዓይን አብሮ ተጎልጉሏል፤ የእኛ ሀዘን በ‹እግዚአብሔር ያፅናችሁ› የሚረሳ ሳይሆን፣ የዘላለም ነው። በእኛ የደረሰ አይድረስባችሁ›› በማለት እንባቸውን እያዘሩ የተናገሩት የተጠቂዋ አጎት የሆኑት አቶ አስመላሽ፣ ታዳሚውን በእንባ አራጭተውታል። አቶ አስመላሽ አክለውም፣ “መንግሥት ከእኛው አብራክ የወጣ እንደመሆኑ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል የሚል እምነት አለኝ” በማለት በመንግሥት ላይ ያላቸውን ፅኑ እምነት ተናግረዋል፡፡

Page 20: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004ጤና20

በኤልያስ ገብሩ[email protected]

እ.አ.አ ሰኔ 2000 የለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሮፌሰር የሆኑት ሰሚን ዛኪ እና አንድሪው ባርቴላ ለምርመራ ፍቃደኛ የሆኑ የ11 ሴቶችን እና የስድስት ወንዶችን የአዕምሮ አንጎል ክፍል በሕክምና መሳሪያ ስካን (በኤሌክትሮ ማግኔት በመጠቀም ምስል ማንሳት) አደረጉ። 17ቱም ሰዎች ከስድስት እስከ 12 ወራት ጊዜ ውስጥ ከተቃራኒ ጾታ ጋር በፍቅር መክነፋቸውንና መውደቃቸውን የሚናገሩ ነበሩ። በጥናቱ ወቅትም ግለሰቦቹ የሚያፈቅሯቸው ሰዎችና ከጾታቸው ጋር ተመመሳይ የሆኑ የቅርብ ጓደኞቻቸውን ፎቶግራፍ በማቀያየር እንዲያዩ ተደርጎ ነበር። በወቅቱም ግለሰቦቹ የፍቅረኞቻቸውን ፎቶግራፍ በሚመለከቱበት ወቅት በአንጎላቸው ውስጥ የሚገኙ አራት ወሳኝ ክፍሎች መነቃቃታቸውን ሳይንቲስቶቹ በጥናት ደረሱበት። ሁለቱ ክፍሎች የሚገኙት በጣም በላቀው ሰረብራል ኮርቴክስ በሚባለው የአዕምሮ ክፍል ውስጥ ነው። ይኼም በጣም ለጠለቀ ስሜት ኃላፊነትን ይወስዳል። እንዲሁም ፊት ለፊት ባለው የአዕምሮ ክፍል ውስጥ ተደራርበው የሚገኙት ቃጫ መሰል የነርቭ እስሮች በጣም ለላቀ የደስተኝነት ስሜት ምላሽ ይሰጣሉ። ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ በጥልቁ እና በጥንታዊው የአዕምሮ ክፍል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ተደጋጋሚ ልምድን በመፈለግ ለሱሰኝነት ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። … የምርምር ጥናቱም ሰዎች ፍቅር ውስጥ ሲገቡ ድብርት ሳይዛቸው ለምን እንደሱስ የጠለቀ የደስተኝነት ስሜት እንደሚሰማቸው አብራርቷል።

ሶስት ዓይነት ስሜታዊነትበአሜሪካ ኒውጀርሲ ሩትገርስ ዩኒቨርሲቲ

የሰው ዘር አጥኚ (አንትሮፖሎጂስት) የሆኑት ዶ/ር ሄለን ፊሸር፣ የአዕምሮ አንጎል ክፍልን ስካን በማድረግ ፍቅር በየትኛው ቦታ እንደሚገኝ በማመላከት ፈር ቀዳጅ ሥራ መስራታቸው የሚገለፅላቸው ባለሙያ ናቸው። ምንም እንኳን የዶክተሯ ጥናት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኝ ቢሆንም፣ በአዕምሮ ውስጥ ሦስት ዓይነት ጠንካራ ስሜቶች መኖራቸውን የጠቆሙበት ሁኔታ ነበር። እነዚህም ጠንካራ የወሲብ ፍላጎት ወይም አንድን ነገር በጣም አጥብቆ መሻት (lust)፣ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ ጥልቅ የስሜት መነቃቃት (infatuation) እና

በፍቅር ስሜት መጣመር (attachment) ናቸው። እያንዳንዱ ጥልቅ ስሜትም የራሱ የሆነ የአዕምሮ ወስጥ የኬሚስትሪ እንቅስቃሴ አለው። ይኼም ግለሰቡ ከአንድ ሰው ጋር በሚጣመርበት ጊዜ አዕምሮን የማንቃትና የማብራት ሚናውን ይወጣል። በሥነ-ሕይወት (Biology) ሂደት

መሠረት ደግሞ ሦስቱ የፍቅር ስሜት መገለጫዎች የውልደት ቀጣይነትን በሰዎች ዘንድ ለማረጋገጥ ወሳኝ ተግባራትን ይጫወታሉ። በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኘው ጠንካራ የወሲብ ፍላጎት (lust) በውጫዊ አካል እይታና ያለንግግር የሚደረግ ፆታዊ መሳሳብ ነው። በዶ/ር ሄለን አገላለፅ መሠረት ደግሞ ለአጭር ጊዜ በሚቆይ ጥልቅ ስሜት መነቃቃት (infatuation)፣ አንድን ሰው በፍቅር ወደነው ወደ አዕምሯችን ካስገባነው በኋላ ለማውጣት የማንችልበት ደረጃ ተደርጎ ይገለፃል። በዚህ ወቅት አዕምሯችን ትኩረት የሚያደርገው በወደድነው ሰው መልካም ባህሪያት ላይ እንጂ መጥፎ/ አሉታዊ ባህሪውን ወይም ልምዱን መመልከት አይፈልግም። ‹‹በኢንፋቹዌሽን ወቅት አዕምሯችን

ከመረጥነው የፍቅር አጣማሪ ጋር ጥምረት መመስረት የሚያስችለን ሲሆን ስሜቱም በጣም አስገራሚ ኃይል አለው። ለምሳሌ፣ አንድ የሚወዱት ሰው ትኩረት ከነፈግዎት ወይም ዝቅተኛ ግምት ከሰጥዎት አደጋኛ ሁኔታ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ጉዳዩ ሥር ከሰደደ ደግሞ መጨረሻው የግድያ ወንጀል ሊሆን ይችላል።›› ሲል ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

ኬሚካሎቹሆኖም በዚህ ደረጃ ከፍተኛ ኃይል

ያላቸው የአንጎል ውስጥ ኬሚካሎች

ተረጭተው በጣም በላቀ የደስተኝነት ስሜት ውስጥ ሰዎችን ያስቀምጣሉ። ዶፓማይን የተባለው የአንጎል ኬሚካል ደህና የመሆን ስሜትን ይሰጣል። ፌናይል ታይናማይል የመደሰት ስሜት ደረጃን በጣም ከፍ ያደርጋል። ሴሮቶኒን የተባለው ኬሚካል ደግሞ ስሜታዊ መረጋጋትን ይፈጥራል። ኖርፓይን ፍራይን ደግሞ ማንኛውንም ነገር ለማድረግ የሚያስችል ስሜትን የመፍጠር አቅም አለው። የወሲብ ሱሰኛ የሆነ ሰው በኢንፍቹዌሽን ደረጃ ላይ የሚፈጠሩ ሆርሞኖች /የኬሚካል ርጭቶች ያሉት ሲሆን ግለሰቡም ይኼ የስሜት ደረጃው በቋሚነት አብሮት ለዘለቄታው እንዲኖር ፍላጎቱ ነው። ነገር ግን፣ ይኼ ደረጃ ዘለቄታዊነት ስለሌለው ስሜቱ በአጭሩ ጊዜ ውስጥ መቆሙ አይቀሬ ነው። ከሦስት እስከ 12 ወራት በሚቆየው በዚህ ወቅት ሰዎች በተሳሳተ ሁኔታ ‹‹ፍቅር ነው›› ብለው ይገልፁታል። በተጨማሪም፣ በሥነ-ሕይወት ተፈጥሯዊ ሽወዳ መሠረት ሁለቱ ጥንዶች በፍቅር ዓለም እስከመጨረሻው ለመዝለቅ ዋስትና የማግኘት ስሜት ይሰማቸዋል። የዚህ ደረጃ አደገኝነትም ፍቅረኛሞቹ ለወሲብ ያላቸው ተነሳሽነት ያለእንከን የተጣጣመ መሆኑን እንዲሰማቸው የማሳመን አቅም አለው። ነገር ግን፣ ሁለቱም ለወሲብ ያላቸው ተነሳሽነት (ፍላጎት) የተለያየ መሆኑን የሚረዱት የኢንፍቹዌሽን ደረጃ ሲያበቃ ወይም ትክክለኛው የአብሮነት ጥምረታቸው ሲጀምር ነው። እውነተኛው ነገር የኢንፋቹዌሽን ደረጃ

ቦታን በሚረከብበት ጊዜ ደግሞ ከጥንዶቹ መካከል አንዱ አንዱን ለመተው ይገደዳል፣ ወይም ሁለቱም ‹አይንህን/ሽን ለአፈር› ይባባላሉ። … ወይም ወደ ሦስተኛው የፍቅር ስሜት ደረጃ ተሻግረው የጋራ የመተባበር ጥምረትን ይመሰርታሉ፣ ይገነባሉ። በዚህ አካሄድም፣ ፍቅራቸው

እስከ መጨረሻው ምዕራፍ ድረስ ተጉዞ ልጅ ወልደው በማሳደግ ላይ ያላቸው ዓላማ አንድ እንደሚሆን የዘርፉ ምሁራን ይመክራሉ። በፍጥነት እያደጉ በመጡት ዘመናዊ

የቴክኖሎጂ የሕክምና መሳሪያዎች አማካኝነት የአዕምሮ አንጎል ክፍልን በማንሳትና በመከታተል ላይ ያተኮሩ በርካታ የምርምር ጥናት ውጤቶች በሴቶችና በወንዶች አዕምሮ ውስጥ የሚገኙትን የፍቅርና የጥልቅ ስሜት ቦታዎች ለማወቅ እንደሚረዳ ዶ/ር ሄለን ያስረዳሉ። ከላይ የተገለፁትን ሦስት የፍቅር ስሜት ደረጃዎች በአግባቡ መረዳት የኢንፋቹዌሽን ደረጃን በቀላሉ ለመገንዘብና በዚህም ሳቢያ ሊከሰቱ ከሚችሉት አሉታዊ ችግሮች ላለመዳረግ ሰዎችን ዝግጁ ያደርጋል።

በፍቅር የሚወድቀው ማን?

ፍቅር በተለይም ለወንዶች ግራ የሚያጋባ እውነት መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ። ወንዶች የአይን ብሌናቸው በቴስቴስትሮን ሆርሞን ስሜት የተሞላ በመሆኑ የሴቶችን ውጫዊ አካል በቀላሉ ተመልክተው በቀላሉ በፍቅር ምርኮ ውስጥ ይወድቃሉ። በኢንፋቹዌሽን ደረጃ ላይ ወንዶች የቴስቴስትሮን ሆርሞናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ ስለሚል የጀመሩት የግንኙነት መንገድ ወደ ላይ፣ ወደታች ወይም ወደ ጎን እንደሚወስዳቸው በትክክል አውቀው መናገር አይችሉም። ነገር ግን፣ ይኼ በሴቶች ላይ ተቃራኒ ሆኖ ተገኝቷል። ለምሳሌ፣ ትናንት ምሽት እኩለ ሌሊት ላይ በጣም ደስተኛ የነበረች ሴት በነጋታው ደስታና ማራኪነት ላትገኝ ትችላለች። ምክንያቱም በሴቶች አዕምሮ ውስጥ የጥልቅ ስሜታቸው ማዕከላዊነትና ምክንያታዊነት በላቀ መልኩ የተያያዙ በመሆናቸው በቴስቴስትሮን ሆርሞን ምክንያት ከስሜት ቁጥጥር ውጪ አይወጡም። ስለዚህ፣ ሴቷ በአጠገቧ ያለው ወንድ ትክክለኛ አጣማሪዋ መሆን አለመሆኑን በቀላሉ ማወቅ ትችላለች። ብዙ የፍቅር ግንኙነቶች የሚቋጩት በሴቶች የመሆኑ ምስጢር አንዱ ይኼ ነው። በርካታ ወንዶችም፣ ‹‹ይኼ እንዴት ሊሆን ቻለ?›› በማለት ራሳቸውን በመጠየቅ ግራ ይጋባሉ።ሴቶች ከወንዱ ለመለየት ወይም ለመራቅ

በሚፈልጉበት ጊዜ በተረጋጋና በሰላማዊ

መንገድ ድርጊቱን በመከወን የሚደርስባቸው የለም። ለዚህም ነው ሴቶች ፍቅረኛቸው ለነበረ ሰው የመጨረሻ የመሰነባበቻ ደብዳቤ በሚፅፉበት ጊዜ የደስታ ፊት ያለው ስዕል/ምስል የሚልኩት፣ ወይም እሱን ሁሌም እንደሚወዱት የሚገልፁለት፡- በዘዴ።

ፍቅርን መግለፅ ለማን ይከብዳል?

‹‹እወድሃለሁ/አፈቅርሃለሁ›› ማለት በጭራሽ የሴቶች ችግር አይደለም። የሴቶች አዕምሯዊ አወቃቀር በራሳቸው ዓለም ውስጥ ሆነው በተሟሉ አነስተኛና ጥልቅ ስሜቶች፣ ተግባቦቶችና ቃላቶች የተሞሉ ናቸው። ሴት ልጅ ደስ የሚል የፍቅር ስሜት ሲሰማት፣ በወንዶች ስትፈለግ፣ እሷም ወንድን ስታከብርና ስታፈቅር ለራሷ ይታወቃታል። ከትክክለኛው ወንድ ጋር በትክክል ስትጣመር ያኔ በፍቅር ትወድቃለች። ነገር ግን፣ ወንዱ በትክክል ፍቅር ምን ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለም። ለዚህም ነው ወንዱ በእይታ በሴቷ መማረኩንና ለአጭር ጊዜ በሚቆየው ጥልቅ የፍቅር ስሜት ውስጥ መግባቱን ከእውነተኛ ፍቅር አንፃር ለመለየት ግራ የሚጋባው። ወንዱ የሚያውቀው ነገር እጁን ከእሷ ላይ ማንሳት አለመቻሉን ሲሆን፣ ‹‹ይኼ ፍቅር ይሆን!?›› በማለት ራሱን ለመጠየቅ ይገደዳል። ‹‹አዕምሮው በቴስቴስትሮን ሆርሞን በመሞላቱ ሳቢያም በማንኛውም ጊዜ ለወሲብ ዝግጁ ስለሚሆን ትክክለኛውን ነገር ማሰብ ይሳነዋል።›› ይላሉ ዶ/ር ሄለን። ወንዱ በፍቅር መውደቁን የሚረዳው ግንኙነት ከጀመረ ከተሰወኑ አመታት በኋላ፣ ወዳለፉ ጊዜያቶች በጥሞናና በአንክሮ በመመልከት ነው።ሴቶች ፍቅር የሌለበትን ግንኙነት

የመረዳት ችሎታም አላቸው። ብዙ ወንዶች ደግሞ ቃል የመግባት ፍርሃት እንዳለባቸው ይገለፃል። ለወንዶች፣ ‹‹እወድሻለሁ/ አፈቅርሻለሁ›› ብሎ መናገር በቀሪ ሕይወታቸው ላይ ከፍ ያለ ጫናና ዱብእዳን መፍጠር ስለሚመስላቸው ቃሉን ይፈሩታል። ይኼንን መስመር ያለፈ ወንድ ግን፣ ለማንኛውም ሰው በማንኛውም ቦታ መናገርን ይደፍራል። ብዙ ወንዶችም የፍቅር ቃላትን ከተናገሩ በኋላ በሴቶች ወሲባዊ እርካታ ላይ የሚጨምረውን ሁኔታ ንቁ ሆነው አያስተውሉትም።

ፍቅር የት ነው ያለው?ፍቅር በተለይም ለወንዶች ግራ የሚያጋባ እውነት መሆኑን መረጃዎች ያስረዳሉ።

ወንዶች የአይን ብሌናቸው በቴስቴስትሮን ሆርሞን ስሜት የተሞላ በመሆኑ የሴቶችን

ውጫዊ አካል በቀላሉ ተመልክተው በቀላሉ በፍቅር ምርኮ ውስጥ ይወድቃሉ።

ጥሩ ልብ ካልሰጠው እና ታታሪ ካልሆነ በምኑ ተፍጨርጭሮ ኃብት ያካብታል? ወላጆቹ እንኳን ለመነሻ የሚሆን ጥሪት ሊያወርሱት ይቅርና ከእጅ-ወደ-አፍ በሆነ ኑሮ የሚያስተዳድሩበትን ገቢ እንኳ በቅጡ ማግኘት የተሳናቸው ምስኪን ድሆች ናቸው።

በአገሪቱ ካለው አስከፊ እና ስር የሰደደ ጉስቁልና የተነሳም ጎበዛዝቱ ሁሉ ስደትን መርጠዋል። በአውሮፓ አገራት የተሻለ ሕይወት ለማግኘት ናፍቀው በየመን፣ ሊቢያ፣ ሱዳን እና ቱኒዚያ በኩል በታንኳ ወደተስፋቸው ምድር ለመግባት እንደኳተኑ ህይወታቸው ያለፈውን አያሌ ወጣት ኢትዮጵያውያን ባህር ይቁጠራቸው። ይህንን ‹‹እድል›› ተብዬም ያላገኙ ወጣቶች ለወንጀለኝነት እና ሱሰኝነት ተደርገው መክነዋል። እነዚህ ሁሉ ውስጥ የሌሉበት ደግሞ ከመራር ድህነት በመነጨ የባህሪ መራርነት ተበርዘው ማህበረሰባቸውን መልሰው የሚያጠቁና የሚያደሙ እኩይ ሴረኛ ፍጥረታት ሆነዋል። በዚህም እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የሚሄድ የተንኮል፣ የአሻጥር እና የደባ ወላፈን ባጠቃላይ ማህበረሰቡ ላይ በመለኮስ የማህበራዊ መስተጋብር ግንኙነቶችን ጨርሶ ለማጥፋት እና አገሪቱን እለት-በእለት በአዳኝ ታዳኝ ፍልሚያ የምትኖር የአውሬዎች ጫካ እያደረጓት ነው። በሂደቱም በፊት ለፊት፣ በግልፅ በመነጋገር የማያምን፣ ካብ ለካብ የሚሄድ እባብ ትውልድ እየገነቡ ነው። ገሚሶቹም በብረት የሚያምኑ ጨካኞች እና እናንተኑ አስጨንቀው ከመኃረባችሁ ውስጥ ንዋይ የሚፈለቅቁ የልጅ ቀማኞች ሆነውባችኋል። ‹ላም እሳት ወለደች፤ እንዳትልሰው ፈጃት፣ እንዳትተወው ልጅ ሆነባት› መሆኑ ነው።

የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ፡- የሴት ልጆቻችሁም ህይወት ከዚህ ብዙ ያልተለየ ነው። ከእናንተው ጓዳ ሳይወጡ ዲቃላ የሚታቀፉት ቢበዙም ለመኖር ያህል ውር ውር የሚሉትም በአገራቸው ተስፋን አጥተዋል።

እኔ የምለው ግን፡- ከአረብ

አገራት አሰቃቂ የጉልበት ብዝበዛና የውርደት ኑሮ የተረፉት ሴት ልጆቻችሁ በየጎዳናው ጥጋጥግ ላይ ለሽያጭ ሲቀርቡ ልባችሁን የኃዘን ስለት አይወጋውምን? የእናንተን ጎስቋላ ኑሮ ለመለወጥ ሲሉ ከፎቅ የተወረወሩ፣ በሙቅ ውሃ የተቀቀሉ፣ ያለምግብ ለሳምንታት በርሃብ የተቀጡ፣ ያለእንቅልፍ ለቀናት በባርነት ስራ የናወዙ፣ ይህም አልበቃ ብሎ በአሳዳሪዎቻቸው ወንዶች ልጆች በየተራ የተደፈሩ፣ ይህን ሁሉ ችለውም በደምና ወዛቸው የቋጠሩትን ጥሪት በግፍ ተከልክለውና ፓስፖርታቸውን ተቀምተው ለአደባባይ ወሮበላ የተጣሉ፣ በዚህም ለአረብ አገራት ፖሊሶች መጫወቻነት ተላልፈው የተሰጡ፣ በየእስር ቤቱ ታጉረው እንደአውሬ በጭለማ የሚኖሩ፣ በለስ ከቀናቸውም ያለሙሉ አካል አልያም ያለሙሉ አዕምሮ የአገራቸውን አፈር ለማየት የሚበቁ አካላቸው የጎደለ እና አዕምሮአቸው የተቃወሰ የልጆቻችሁ እድል ፈንታ፣ እጣ ፈንታም ከእነርሱ ጋር ያልነበረ ልጆቻችሁ ደግሞ ሙቅ እና ህያው ሳይሆን ቀዝቃዛና በድን አስክሬናቸውን የተረከባችሁ እናቶች ሆይ፡- ይህ ሁሉ የልጆቻችሁ መከራና ስቃይ እውነት እናንተ በህይወት እያላችሁ የሆነ ነውን? ‹‹ጎሽ ለልጇ ስትል ተወጋች!›› የሚለው አባባል ተረት ብቻ ሆኖ ቀርቶ ይሆን እንዴ? እሱ እሺ ያሻውን ይሁን፤ ግን ይሄ ሁሉ መከራ፣ ግፍ፣ ስደት፣ ስቃይ፣ እብደት እና መስዋዕትነት ለምን? እኮ ምን ለማግኘት? ግዑዙን ቤት ቀለም ለመቀባት!? አግዳሚውን የእንጨት ወንበር ሶፋ ለማድረግ!? የቆርቆሮውን በር በብረት ለመለወጥ ብቻ!? ቤቱን የአሻንጉሊት እና የብርድልብስ ክምር ለማድረግ (ጎረቤት ይሄን ስላሟላ እኛም እንዳይቀርብን)!? ወይ ገላችን ወይ ምላሳችን ኑሯችንን ማሳበቁን ላይተው የአልባሳት እና የጌጣጌጥ መሰረተ-ኃብታም መስለን ለመታየት!? ኧረ! እንዲህ ያለውን ግብዝነትስ ከወዴት አመጣነው? ኢትዮጵያዊ ኩራትንስ የቱ ጅብ በላው? በፍቅር ለወደቅንለት እና ‹ዘመናዊነት› ለሚባል ምዕራባዊ ጣኦት

ስንል የልጆቻችንን አፍላ የጉብዝና ወራት በመሰዊያው ስር እያቀረብን ስንገብር እና ጭዳ ስናደርግ እስከመቼ እንዘልቀዋለን? የምንኖረውስ ለምድራዊ ተድላና ምቾት ብቻ ነውን? ምቾት እና ተድላ ለማግኘት መሻቱ ባይነቀፍም ይህንን ለማግኘት ግን ራስን ማጣት፣ ልጆችን አሳልፎ መስጠት ምንኛ ከንቱ ነው! ይህንን ፍላጎታችንን በገዛ አገራችን ላይ ማሳካት ያቃተንስ ስለምን ምክንያት ነው? ለዚህም ይመስላል ከያኒው፡-

‹‹ሰው ችግር ቢያስጨንቀው ካገሩ ተሰደደ

ሆድ ይፍጀው ብሎ ሄዶ አይለምዱትን ለመደ

በሰው አገር ላይ ሆኖ ወርቅ እንኳን ቢታፈስ

ደርሶ የህሊና እዳ ነው ትልቅ ሆኖ ማነስ››

ማለቱ።ልጆቻችሁ ከዓይናችሁ ሳይርቁ፣

በባዕዳን ፊት ሳይሸማቀቁ ሰብዓዊና ዜጋዊ ክብራቸው ተጠብቆ በተወለዱበት አገር ላይ ዘርተው ለመቃም፣ ወልደው ለመሳም፣ ሰርተው ለመጠቀም ያልቻሉትና የድህነትን ቀንበር ሰብረው በደንብ ቀና ብለው ለመራመድ ከእነርሱ በኩል የቀረው ነገር ከቶ ምን ይሆን? ያልፈነቀሉትስ ድንጋይ በእውነት ይገኛልን? ታዲያ ከዚህ ሁሉ ትዕግስት አስጨራሽ ፈተናና ግብግብ ወዲያ፤ ስደትን ከግር-እስከራሱ አብጠርጥረው ካዩ በኋላ እጃቸው አመድ-አፋሽ የሆነባቸው ከርታታዎች ሁሉ አንድ አብይ ጥያቄ ማንሳታቸው አይቀሬ ነው። አሁን ስለሌላው ዓለምም ግንዛቤ አግኝተዋልና አወዳድረው፣ አነፃፅረው፣ አመዛዝነው፣ ግራ-ቀኝ አይተው ‹‹ለሌሎቹ አገራት መሠረታዊ የህልውና ማቆያዎች (እንደምግብ፣ መጠለያ እና አልባሳት ያሉ) ሁሉ ለአገሬ ህዝብ የቅንጦት ተራራ የሆኑበት፣ እውነት ይሄን ያህል ኢትዮጵያ ምስኪን ያጣች የነጣች ድሃ ሆና ነውን?›› ይላሉ። ከዓመት እስከዓመት የሚራቡ፣ የሚታረዙ፣ የሚለምኑ እና

በበሽታ የሚማቅቁ አያሌ ኢትዮጵያውያን ህይወት ሊቀየር እና ሊፈወስ ያልቻለውስ በተፈጥሮአዊ ምክንያት ወይስ በሰው ሰራሽ ጥፋት ነው? ከዚህ አስቀያሚና የተዋረደ ህይወት ለመውጣት አምላክ የሰጠንን የገዛ ህሊናችንን እና ነፃ ውሳኔያችንን ተጠቅመን የጋራ አገራችንን በጋራ እናድናት ወይስ የመለኮትን እገዛ እና ተራዳዒነት እየተጠባበቅን በአርምሞ እንቀመጥ?

የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ፡- ለዚህ መልሳችሁ ምን ይሆን? የአገር ካስማ ቤተሰብ ነው። የቤተሰብ መሰረቱ ደግሞ እናንተ ኢትዮጵያውያን እናቶች ናችሁ። ታዲያ ከጎጆአችሁ እስከ አደባባዮቻችሁ ድረስ የዘለቀውን ያለመተማመን፣ ክርክር፣ በደል፣ አመፃ፣ ግፍ፣ አፈና፣ እስር፣ ቁርሾ፣ በቀል፣ አምባገነንነት፣ ሙስና፣ ውጥረት፣ እንዲሁም የጥላቻ ልዩነት ለማስታረቅ እና ለማስማማት ብሎም በፍቅር አብሮ ለመኖር ብልሀታችሁን እና ጥበባችሁን እንደእንዝርታችሁ በማሾር የእርቅ ፈትል ማሰናዳትና አገሩን ሁሉ የፍቅር ሸማ ማልበስ ኧረ እንደምን ተሳናችሁ?

በፍርሃት ሳይሸማቀቁ፣ ለጉልበተኛ ሳያደገድጉ በነፃነት የሚኖሩ እውነት ተናጋሪ ነፃ ልጆችስ ማፍራት እንዴት አቃታችሁ?

ከፍራቻ-ቅኔ ወደ ፍቅር-ወኔአሁን በዚህ ዘመን ኢትዮጵያን

የሚያስፈልጋት የፍራቻ ቅኔ ሳይሆን የፍቅር ወኔ ነው። የፍቅር ሁሉ ምንጭ ደግሞ እናንት የኢትዮጵያ እናቶች ናችሁ። ስለዚህ በተገዢም ሆነ በገዢ ጎን ያላችሁ ኢትዮጵያውያን እናቶች ስለፍቅር ስትሉ ከፍርሀታችሁ ውጡ። የነበላይ ዘለቀ፣ የነመንግስቱ ነዋይ፣ የነጥላሁን ግዛው፣ የነዋለልኝ መኮንን፣ የነማርታ፣ የነሙሴ፣ የነአኖሌ እናት ዝምታ ይበቃናል።

በ1988 ዓ.ም የልጆቻችሁ የስነምግባር መቃወስ አሳስቧችሁ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ያሰማችሁ የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ፡- አሁንም በዚህ ዘመን ሊያሰጋችሁ የሚገባ ነገር አለ። ይኸውም ልጆቻችሁ የገቡበት የሱሰኝነት፣ የዝሙት፣ የስካር፣ የመዳራት ብሎም ግራ የመጋባት፣ የቀቢፀ-ተስፋ ህይወት ነው። ይህንን ደግሞ ለመቀየር አዲስ ራዕይ እና ህልም ወጥኑ። የተዋረደ ህይወት ቀንበርን

ለማፍረስ እናንተም ፈርታችሁ ልጆቻችሁን አታስፈራሩ። የአመፃ ሳይሆን የፍቅር ልጆችን ፍጠሩ፤ ገዳይን ሳይሆን ስለፍቅር የሚሰዉትን አድንቁ-ዘክሩ። ‹ሴት የላከው ሞት አይፈራም! ቀርቶ ሴት የላከው እርቅ አይፈራም!› ይሁን ብሂላችሁ። ይህም እንዲሆን ባሎቻችሁን በፍቅር አንፁ፤ በመልካም አንደበትም ገስፁ። መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናትና የመልካም ሚስት ምግባር ይታይባችሁ። ከንግስተ ሳባ፣ ተዋበች፣ ጣይቱ፣ ትምህርት ቅሰሙ።

አቴቴ ዱብራ ኦሮሞ ለምለም ሳር ይዛ፤ የቀዬው አድባር የሆኑ እናቶች ነጠላቸውን አጣፍተው ለእርቅ ይውጡ። የእናት ኢትዮጵያውያን አንደበቶች ሰላምን ይዘምሩ፤ ፍቅርን ይስበኩ! ልጆቻቸውንም ያስታርቁ። የእርቅ በጎ መንፈስ በአየሩ ላይ ይናኝ-ጠፈሩንም ይሙላው! የፍቅራችን ድርሳን በየምኩራቦቻችን ላይ ይነብነብ! ያኔ እንኳንስ እንቦቃቅላ ልጆቻችን ሳር ቅጠሎቹም ጭምር ከእኛው ጋር ያሸበሽባሉ። በፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን በልባዊ ፍቅርም እንተሳሰር! ዳግም ቃልኪዳን እንግባ፤ የእርቅ ቀለበት እንሰር!

ወይዛዝርት እና ባልቴቶች፣ እናቶችና መበለቶች፣ ቆነጃጅት እና የደረሱ ሴት ልጆች ሁሉ ፀአዳ ልብሳቸውን ለብሰው የሰላም ዘንባባና እርግቦች ይዘው ስለፍቅር እየዘመሩ ወደከተማይቱ አደባባዮች ይትመሙ። እናት ኢትዮጵያውያን ይናገሩ! እኛም ትንፍሽ ሳንል በፅሞና እናዳምጣቸው። የሚናገሩትን ሁሉ በጥንቃቄ በልቦናችን እንመዝግብ። በቅን ልቦና እየተደመምን እንስማቸው። እነርሱም የልባቸውን ይተንፍሱ። ያኔ ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ ፈውሳችንን እናገኛለን። ህመማችን ይድናል፤ ቁስላችን ይደርቃል፤ አጥንታችን ይለመልማል። ነፍሳችን ሃሴት ታደርጋለች። እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንን እስክንል ድረስ እንዋደዳለን-በንፁህ ፍቅር ተፋቅረን እንደህፃናት ልጆች እንቦርቃለን። አንገት-ላንገት ተቃቅፈን በሃሴት እናነባለን፤ ስለፍቅር ከልብ ይቅር ተባብለናልና! አሁን አምላክም በርግጥ ከኛ ጋር ይሆናልና! በዚህ ጊዜ ፊታችን የሚቆም አንዳች ምድራዊ ኃይል አይኖርም። ሁሉ ለፍቅር ሰግዷልና! ፍቅር-አምላክም አሸንፏልና!

እናት - ኢትዮጵያውያን . . .

Page 21: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

21

በአብዱ መሐመድ

ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ የሀገር መሪዎችና በተለያዩ መስኮች ለስኬት የበቁ ስመጥር ግለሰቦች፣ የፍቅር መግለጫ የሆነውን የሩካቤ ሥጋ ግንኙነት በማዋረድ በወሲብ ቅሌት መዘፈቃቸው በተደጋጋሚ ይደመጣል።

ፖለቲከኞችና መሪዎች ከፍተኛ ኃላፊነት ተሸክመዋልና ይህ አይነቱ ቅሌት ምናልባት በሥልጣን ዘመናቸው ያበረቷቸው የጎሉ አስተዋፅኦዎች ካሉ እነዚያ አስተዋፅኦዎች ጥርጣሬ ውስጥ የሚወድቁት እና የሚሸረሸሩት ገመናቸው እንደተጋለጠ ወዲያው ውሎ ሳያድር ነው።

መሪዎቹ ቅሌቱን የሚፈፅሙት በፖለቲካ ፍላጎትና በጥቅም በዙሪያቸው በሚገኙ ወዳጆቻቸው አስተባባሪነትና ከለላ በመሆኑ ምክንያት ተግባራቸው ተሸፋፍኖ የመቅረቱ ዕድል የጎላ ቢሆንም፣ እውነታው አንዴ አፈትልኮ ከወጣ ዓለምን የሚያዳርሰው በሽርፍራፊ ሰኮንዶች ውስጥ ነው። ለኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ዕድሜ ይግባውና!

የታይም ዘጋቢ ናንሲ ጊብስ ባለሥልጣናትን ምንድን ነው እንደ አሳማ የሚያደርጋቸው? (“Sex. Lies. Arrogance. What Makes Powerful Men Act Like Pigs?”) በማለት ባቀረበው የጥናት መረጃና ምላሽ ጽሑፉ ቀዳሚ ያደረገው፣ በስመጥር መሪዎች እና ፖለቲከኞች የተፈፀሙ የወሲብ ቅሌቶችን በዋቢነት የሰፈረበትን የታሪክ አሻራ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሶስተኛው ፕሬዝዳንት የነበሩት ቶማስ ጀፈርሰን የመጨረሻ ባለቤታቸውን (ማርታ ጀፈርሰን) ይዘው ወደ ኋይት ሀውስ የዘለቁት፣ በመኖሪያቸው በሰራተኛነት ታገለግላቸው ከነበሩት ከቀዳማዊ እመቤት ማርታ ጀፈርሰን እህት ሳሊ ሄሚንግስ በምስጢር ሰድስት ልጆችን ወልደው ነበር።

ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ. ኬኔዲ የባሪያ አሳዳሪ ሥርዓት እንዲወገድና የሴቶች መብቶች እንዲከበሩ ይሟገቱ የነበረው፣ ከቤተመንግስታቸው ውጪ የዕረፍት ጊዜያቸውን በሚያሳልፉባቸው ደሴቶች ከውቧና ስመጥሯ አርቲስት ማርሊን ሞንሮ እና በተደራጀ ወንጀል/ውንብድና እጁ ነበረበት የሚባለው የቺካጎው ‘ጋንግስተር’ ሳም ጂያናካና ፍቅረኛ ከነበችው ጁዲዝ ካምፕቤል ኤግዝነር ጋር አንሶላ እየተጋፈፉ ነበር - ተብሎ ይጠረጠራሉ። ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን በኋይት ሀውስ ከሞኒካ ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ነበራቸው በተባሉበት ወቅት ገና የሥልጣን ዘመናቸው አልተጠናቀቀም ነበር፤ ያም ማለት፣ የአሁኗን የዩ.ኤስ. አሜሪካ ስቴት ሴክሬታሪ፣ የቀድሞዋ የሀገሪቱ ቀዳማዊ እመቤት ሂላሪ ክሊንተን እዛው በቤተመንግሥታቸው አብረዋቸው ነበሩ።

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በመቃወም የሚታወቁት ሴናተር ላሪ ክሬይግ፣ ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው ኢቫንጀሊካል ፓስተር ቴድ ሀጋርድ፣ በአሜሪካ ሴኔት የሥነ-ምግባር ኮሚቴ አባልና የኔቫዳ ሕግ አርቃቂ ጆን ኢንሳይን ማዕረጋቸውንና ሥልጠናቸውን ተገፈው ወህኒ የወረዱት በወሲብ ቅሌት ነበር።

የፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ቅሌት ምስጢር እንዳፈተለከ እውነቱን አውጣ ብለው በመሟገት ቀዳሚ የነበሩት የጊዜው አፈ-ጉባኤ ኒውት ጊንግሪች የኋላ ኋላ ራሳቸውም ከአንዲት ስታፍ ጋር በተመሳሳይ ቅሌት ተዘፍቀው ተገኝተዋል።

ስመጥሩ የፊልም አክተር አርኖልድ ሽዋዚንገር እ.አ.አ በ2003 የካሊፎርኒያ ገዥ ለመሆን ሲወዳዳር ‹‹ፕሪዳተር›› የተባለውን ፊልሙን ጨምሮ መሪ ተዋናይ ሆኖ በሰራባቸው ፊልሞቹ፣ ከእርሱ ጋር አብረን ተኝተናል፣ አንሶላ ተጋፈናል ያሉ የተወሰኑ ሴቶችና ሞዴሎች (ሴቶች) ለሥልጣኑ አይመጥንም፣ አይመረጥ የሚል ተቃውሞ አቀረቡ።

ከሽዋዚንገር ጎን ቆማ ተቃውሞውን ያጣጣለችው ባለቤቱ ማርያ፣ ‹‹ከፈለጋችሁ እሱን ስም የሚያጠፉትን፣ ከሰላሳ ዓመት በፊት ለአምስት ሰኮንዶች የተገናኛቸውን ሰዎች አዳምጡ። እኔን የምታዳምጡ ደግሞ ባለቤቴ ለትዳሩ ታማኝና አፍቃሪ መሆኑን ቅንጣት አትጠራጠሩ›› በማለት ሥልጣን እንዲይዙ ከፍተኛውን ሚና ተጫወቱ።

የእርሳቸውና የቤተሰባቸው ከአገዛዙ የተደረገው ሽሽት እጅግ አስቸጋሪ ነበር። በአሁኑ ወቅት እርሳቸውና ከእርሳቸው ጋር ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸው የዳያስፖራ ጓደኞቻቸው በገጠሪቷ ኢትዮጵያ በርካታ የትህርት እና የግብርና ፕሮጀክቶችን ስፖንሰር ያደርጋሉ።በውይይታችን ወቅት ለአህዛብያውያን (ለእንደ’ኔ ላሉት) ራሳቸውን በራሳቸው የሾሙ አጥማቂ

አይነት ነበር የሚመስሉት። እንደ አቶ ገብሬ ከሆነ ራሳቸውን አፍቃሬ-ዴክራሲ የሚሉ በጭፍን የብሔር ጥላቻ የሚመሩ ሰዎች ናቸው። ሥልጣን በትግሬ እጅ ሆኖ መመልከት አይፈልጉም። አሁንም እንደ እርሳቸው አባባል፣ የብሔር ጥላቻው ስለምን አቶ መለስ በአዲስ አበባ ውስጥ ሕዝባዊ ድጋፍ እንደሌላቸው፤ ስለምን ከትግራይም ባሻገር በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ሕዝባዊው ድጋፍ ሊኖራቸው እንደቻለ ምክንያቱን የሚያብራራ ነው።ሀገሪቱን በገዟት ገዢዎች አላግባብ የተበዘበዙትን አብዛኞቹን ገበሬዎች ሕይወት አቶ መለስ

ለውጠዋል። በገብሬ ግምት ብቸኞቹ ጥሩ የተቃዋሚ መሪዎች - ሁለት ናቸው - አሁን የፓርላማ አባላት አይደሉም። በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ያለውን ተቃውሞ በተመለከተ መንግሥት በምስራቅ በኩል በኦጋዴን ክልል ውስጥ ነዋሪዎችን ጋዜጠኞች እንዳያነጋግሯቸው የጣለውን ጥብቅ ክልከላ አግባብነት ያለው ነው ሲሉ ይከራከራሉ፤ የጦር ቀጠና ነውና ጋዜጠኞቹ ጥበቃ ሊደግላቸው አይችለም በማለት።ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ነፃነት አላቸው ለሚለው አቶ ገብሬ ያን ያህል ትኩረት ያልሰጡበት

ምክንያት ምናልባት ለአቶ መለስ ካላቸው ከፍተኛ አክብሮት የተነሳ ሊሆን ይችላል። ሰዎች ሊጎትቷቸው ከፈለጓቸው መሰሎቻቸው ላይ ጉድፍ እንዳገኙ ነው የሚሉት አቶ ገብሬ፣ አቶ መለስ አንዱ የአፍሪካ ምርጥ መሪ ሆነው ሳለ ስለምን እንዲህ አበክረው ይተቻሉ? ሲሉ ይጠይቃሉ። በኢትዮጵያ የብሔር ፌዴሬሽን አካል ስለሆነችው ሌላኛዋ መረጋጋት ስለሌለበት ክልል በተመለከተ፣ እዚህ ግቡ በማይባሉ፣ አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የነፃነት ተቃውሞዎች ካልሆኑ በስተቀር፣ አንድም ኦሮሞ በመሰል ተቃውሞዎች አይሳተፍም ማለት ይቻላል፤ ውሱን ቁጥር ካላቸው ፅንፈኛ አንጃዎች በስተቀር።‹‹ስለዚህ እዚህ ማን ነው ጠንከራ ተቃዋሚ?›› አልኳቸው አቶ ገብሬን። ‹‹ደርግ እንዲመለስ የሚፈልጉ ሰዎች፤ የደርግን መሪ መንግስቱ ኃ/ማርያምን [አቆላምጠው]

‹‹መንጌ›› ሲሉ የሚጠሩ።›› ሲሉ መለሱልኝ።‹‹ብዙ ናቸው?›› ብዬ ተከታይ ጥያቄ ስሰነዝር፣ ‹‹በጣም ብዙ ናቸው፤ ማንኛውንም የታክሲ ሹፌር ጠይቅ!›› ሲሉ መለሱልኝ።አቶ ገብሬ መንግሥት ቴሌኮሙኒኬሽንን በብቸኝነት መያዙን በከፊል ይቃወማሉ፤ 19

ዓመታት ከአሁኑ የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ በቂና ረዥም ጊዜ እንደሆነ የሚያምኑት አቶ ገብሬ፣ ለዚህም በኋላ ላይ በአንድ ዝነኛ የፈረንሳይ ኮንሰልታንሲ የተቀየረውን ደካማ የድርጅቱን አስተዳደር ተጠያቂ ያደርጋሉ።እንደ አቶ ገብሬ ማብራሪያ ከሆነ፣ የአቶ መለስ የፖለቲካ ሕይወት ጅማሬ በማርክሲስት

ርዕዮተ-ዓለም የተቃኘ የነበረ ሲሆን፣ በኋላም ብዙም ሳይቆዩ ትክክለኛውንና ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ጎዳና መከተል ጀመሩ፤ በተለይም የገበያ መር ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች። ፖሊሲዎቹም ተጨባጭ እድገት እንዳስገኙ አቶ ገብሬ ይመሰክራሉ። ተመሳሳይ ትችትና መከላከያ ቻይናን አስመልክቶ ማንሳት ይቻላል፤ በቻይና በካፒታሊስት ዲክታተርሺፕ አማካኝነት በርካታ ሰዎች ከድህነት ተመንጭቀው ወጥተዋል። በአንተ ላይ እምነት ያላቸውን ሰዎች ህይወት ከመለወጥ የበለጠ ወሳኝነት ያለው አንዳች ነገር አለን? ይላሉ - አቶ ገብሬ።በ2010 ውስጥ ይህ ከነፃነት ወደ ልማት የተደረገ የአጀንዳ ለውጥ በጥብቅ የተያዘ ይፋዊ

የኢትዮጵያ ፓርቲ መስመር ሆነ። አቶ ገብሬን የለየላቸው የመንግስት አቀንቃኝ አድርጌ ነበር የወሰድኻቸው። ሆኖም ግን እርሳቸውም የተወሰኑ የራሳቸው እይታ የሆኑ ትችቶች ነበሯቸው፤ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት፣ መንግሥት አፈና ሊፈፅም እንደሚችል የሚያውቁ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ነበሩ። ለምሳሌ፡- ከግብር ጋር በተያያዘ፣ እጅግ ከባድ ፍርድ የተሰጠበትን አንድ የሙስና ጉዳይ በተመለከተ አቶ ገብሬ እንዲህ ይላሉ፡- “ኢትዮጵያውያን ጉቦ መክፍል እንጂ ግብር መክፈል አለመዱም፤ ስለዚህም መንግሥት በቅጣት ላይ ሳይሆን፣ በማስተማር ላይ ማተኮር አለበት።” እንዲሁም አንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለተወሰኑ የብሔር ቡድኖች ብቻ የሥራ ቅጥር መፈፀማቸውን የሚያውቁት እውነታ ሲሆን፣ ይህንንም ይኮንኑታል።ካለዴሞክራሲ ልማት፣ በተለይ በሙስና፣ ይደናቀፋል የሚለውን በተመለከተስ? መንግሥት

እጅግ በርካታ የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ እያከናወነ መሆኑንና በአዲስ አበባ አጎራባች አካባቢዎችም እየተገነቡ ያሉ ቤቶችን መጎብኘታቸውንም ያወሱኝ አቶ ገብሬ፣ አያይዘውም ብዙ አዳዲስ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታዎችም እየተጧጧፉ መሆናቸውንና በመላ ከተማዋም ትላልቅ አዳዲስ የንግድ ሕንፃዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቆሙኝ። እርግጥ ነው እኔው’ራሴ በአዲስ አበባ ያለውን የሕንፃዎች ግንባታ ኤቻለሁ።አቶ ገብሬ እንደሚስማሙት፣ የተወሰኑት ለእነዚህ ፕሮጀክቶች የሚውለው ገንዘብ የሚመጣው

በደርግ ወታደሮች እና በሥርዓቱ የመጨረሻዎቹ የሥልጣን ዘመናት በደርግ ባለሥልጣናት ተከማችቶ፣ አሊያም ተመዝብሮ ከነበረ ገንዘብ ነው። የመንግሥት አመለካከት፣ ‹‹ይሁን፤ በዚህም ተባለ በዚያ ዶላሩን ከሀገሪቱ ማስወጣት አይችሉም፤ እናም የሆነ መልካም ነገር ሊሰራ ይችላል›› የሚል ነበር።አቶ ገበሬ ከነገረኝ በአብዛኛው የተረዳሁት ምንድን ነው፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ነገሮች እንዴት

እንደሚከወኑ፣ ሕይወት እንዴት ምስቅልቅል ያለች እንደሆነች እና ፖለቲካዊ መርሆዎች ሊጠበቁ የማይቻሉ ቅንጦቶች መሆናቸውን ነው። ሆኖም እርሳቸው ግን የራሳቸው መርሆዎች አሏቸው። በከተማዋ በመኪና እየተዘዋወርን በነበርንበት ወቅት በአዲስ አበባ ፅዱ አለመሆን በተለይ ደግሞ ቢልቦርዶችን ተችተዋል። እንዴት ያሉ ቪዥዋል አርቲስቶች እያሉን?›› ሲሉ ይጠይቃሉ።ከገብሬ ጋር ከሁለት ሳምንታት በላይ አብረን በቆየንባቸው ጊዜያት የሚጋጩ የፖለቲካ

አመለካከቶቻችንን እያነሳን እርስ በእርስ እስከመበሻሸቅ ድረስ የደረስ ጓደኛሞች ሆነን ነበር። ገብሬ ስለሀገራቸው ካላቸው ያልተለመደ ሀሳብ እጅግ የገረመኝ ለዴሞክራሲ ደንታቢስ የመሆናቸውን ያህል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሀገሪቱ ሕዝብ እና በአጠቃላይ ለሀገራቸው ያላቸው ጥልቅ እና የተቆርቋሪነት ሥሜቱ በአንድነት የመጣመራቸው ጉዳይ ነበር።ለሌኛው ለረዥም ሰዓት ያወጋሁአቸው ሁለተኛው ተወያዬ የሆኑት አቶ ሔኖክ፣ ከአቶ

ገብሬ በበለጠ የተወሳሰበ እይታን ነበር ያቀረቡልኝ። የሚያገኟት የጡረታ ገንዘብ ምንም እንኳን አነስተኛ ብትሆንም፣ በአዲስ አበባ ጥሩና ደስታ የሰፈነበት ኑሮ ይኖራሉ። አቶ ሄኖክ አይደለም ለዴሞክራሲ፣ በአጠቃላይ ፖለቲካ የሚባል ነገር ፍላጎታቸው እንዳያደል በተደጋጋሚ አጫውተውኛል።እኚህ እጅግ ተግባቢ ሰው ለፖለቲካ አቋማቸው እንደምክንያትነት ያቀረቡልኝ በኢትዮጵያ

ውስጥ ፖለቲካ (እንደ ሃይማኖት) ቤተሰብን ከቤተሰብ፣ ጓደኛን ከጓደኛ የሚያለያይ መሆኑን ነበር። ይህን ካሉኝ በኋላ የፖለቲካ (እና ሃይማኖት) ውይይቶች እንዲሁ ዙሪያ ጥምጥም የመሽከርከር አዝማሚያ እንዳላቸው አወጉኝ። ከሙያቸው አንፃር ብቻ ራሳቸውን ገድበው በመግለፅ እውቀቱና ፍላጎቱ የለኝም በሚሉ ምክንያቶች ከፖለቲካ አስተያየቶች የተቃቡበትን ምክንያት አብራሩልኝ።የሄኖክ አቋም፣ ስለምን በርካታ ኢትዮጵያውያን ጀርባቸውን ለፖለቲካ ይሰጣሉ ለሚለው

እንደ ምሳሌ አድርጌ ነበር የወሰድኩት ምክንያቱም እንደዛ አለማድረግ በጣም አደገኛ አድርገው ይወስዱታልና ነው። የተናገሯቸው እና ያደረጓቸው በርካታ ነገሮች ግን እንደ አመለካከታቸው ቀላል አለመሆናቸውን ነበር የሚጠቁሙት።‹‹የፖለቲካ አቋሜ እንደዚህ የሆነው እንግልትን በመፍራት አይደለም፤ ወይም ተመሳሳዩን

በመፍራት አይደለም። በተአምር! በሕይወቴ ታስሬ አላውቅም።›› ሁለቱንም በጠየኳቸው ወቅት፣ አቶ ገብሬ ብዕሩ ለመንግሥት የማይመለሰው ዳዊት ከበደ ማን መሆኑን እንኳን አያውቁም፤ አቶ ሔኖክ ግን ጋዜጠኛ ዳዊትን እንደሚያውቁት ነገሩኝ። የኢትዮጵያን ታሪክ በተመለከተ አቶ ሔኖክ የፊውዳል ሥርዓት በአንድ ወቅት በሀገሪቱ ውስጥ እንደነበር አስታውሰውኛል - ምንም እንኳን ያ ግልፅ የሆነ እውነታ ቢሆንም።አቶ ሔኖክን ስለፖለቲካ ያላቸውን አቋም ሙሉ በሙሉ አምኜአቸው ለመቀበል ያንገራገርሁበት

አንዱ ምክንያቴ በሆነ የአዲስ አበባ ሬስቶራንት ሳለን ያጋጠመኝ ክስተት ነበር፤ ከአዲስ አበባ ከመልቀቄ አንድ ምሽት ቀደም ብሎ አብረን ማዕድ በተጋራንበት በዚህ ሬስቶራንት፣ ምግባችንን እየተጠባበቅን ሳለ ወደ ዋሌታቸው እጃቸውን በመስደድ ከጋዜጣ ተቆርጦ የወጣ ጭምድድ ያለች አንዲት ወረቀት አወጡ። የእስክንድር ነጋ እና የባቤቱና የወንድ ልጁ ምስል ያረፈባት ነበረች ወራቷ። በወቅቱ ከእስክንድር ነጋ ጋር ‹‹ትውውቅ›› እንዳላቸው ነበር የገለፁልኝ። ያቺን ቁራጭ ወረቀት አቶ ሄኖክ በስጦታ መልክ ሰጡኝ። ከዚያ በኋላ ባሉት ወራት ተመሳሳዩን ፎቶግራፍ በበርካታ የመንግሥት ተቺ ድረ-ገጾች ላይ አይቻለሁ። አፍቃሬ ዴሞክራሲ በሆኑ ኢትዮጵያውያን መካከል ምሳሌ ተደርጎም የተወሰደም መሰለኝ።በአጠቃላይ ሲታይ፣ እነዚህ ሰዎች የነገሩኝ እያንዳንዱ ነገር አንፃራዊ ነው። እንዲሁም ሁሉም

የተማሩ ከተሜዎች ናቸው፤ እናም ከአብላጫው የኢትዮጵያ ሕዝብ - ከገበሬው - አባል ለሆነ አንድ ሰው ይህን ጥያቄዬን አላነሳሁም። ቢሆንም ማንም ሰው ቅልብጭ ያለ ምላሽ አለው ብዬም አላስብም። አይደለም ስለዴሞክራሲ፣ በአጠቃላይ ስለፖለቲካ ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌለው አንድ በጣም የተማረ የአዲስ አበባ ኑዋሪ ጡረተኛ ከተናገረ፣ በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል የሚኖር አንድ ገበሬ፣ እንደው ከነአካቴው ድፍረቱን ካገኘ ማለት ነው፣ ምን ሊለኝ ይችላል?

(ሮን ሲንገር፣ ከ1976 እስከ 2008 ድረስ በኒው ዮርክ ውስጥ ባለ አንድ ተቋም ለ44 ዓመታት ያህል በመምህርነት ያገለገለ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ፣ በተለይ ናይጄሪያን በተመለከቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባሕላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተከታታይ ጽሁፎችን በማቅረብ ይታወቃል።)

ሎስ አንጀለስ ታይምስ በመኖሪያቸው የምትገኝ ህፃን ከእርሳቸው የተወለደች ናት ስለሚባለው ጉዳይ ጥያቄ ሲያቀርብላቸው፣ “በፍፁም ስህተት ነው። ከአሥር ዓመት በላይ በቤቴ በሰራተኛነት የምታገለግል ሴት ከሌላ የወለደቻት፣ ነገር ግን እንደ ልጄ ተንከባክቤ የማሳድጋት ናት” አሉ።

ይህ ሁሉ ከተባለና የካሊፎርኒያ የሥልጣን ዘመናቸው ከተጠናቀቀ በኋላ ባለፈው ግንቦት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡና ክስ ሳይመሰረትባቸው በራሳቸው አንደበት የሰራተኛቸው ልጅ የአብራኬ ክፋይ ናት ብለው ራሳቸው ላይ መሰከሩ።

የቀድሞ የፈረንሳይ የገንዘብ ሚኒስትርና የፈረንሳይ ሶሻሊስት ፓርቲ መሪ የነበሩት ዶምኒክ ስትራውስ ካን - ዲ.ኤስ.ኬ - ፣ እ.አ.አ በ2007 የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዳይሬክተር ሆነው የተመረጡት የቀረበባቸውን የወሲብ ቅሌት ያጣጣሉላቸው ባለቤታቸው ድጋፍ ታክሎበት ነበር።

የወሲብ ጥቃት ፈፅመውብኛል በማለት በስትራውስ ላይ በ2007 ክስ የመሰረተችው ሁለተኛ ሚስታቸው አኒ ማንሶሬት ከሌላ የወለዷት የ31 አመቷ ጋዜጠኛ ትሪስታኒ ባኖን ‹‹የጡት መያዣዬን፣ ጂንስ ሱሪዬን . . . አውልቀው የወሲብ ጥቃት ፈፅመውብኛል›› አለች። ይሁንና አሁን እንደገና ያንቀሳቀሳቸውን ክስ እናቷ አኒ ማንሶሬት በወቅቱ ባሳደሩባት ግፊት ምክንያት ማቋረጧን አስታወቀች።

ሶስት ሚስት አግብተው መፍታታቸውን የሚያውቁት አኒ ሲንክሊየር (የዶምኒክ ስትራውስ አራተኛ ባለቤት) የትሪስታኒ ባኖንን ክስ ውድቅ በማድረግ ‹‹በባሌ ላይ የሚቀርበውን የወሲብ ቅሌት ክስ ለአንድ ሰኮንድ እንኳን የማምንበት አእምሮ ወይም ጥርጣሬ የለኝም›› አሉ።

ፈፅመዋል ተብሎ የቀረበባቸው የወሲብ ቅሌት ተድበስብሶ የዓለም አቀፉን የገንዘብ ተቋም ዋና ሥልጣን የተረከቡት ስትራውስ፣ አንዲት የተቋሙ ሰራተኛ (ፒሮስካ - ትውልደ ሀንጋራዊ)፣ “የወሲብ ጥያቄያቸውን ባለመመለሴ የሚገባኝ ዕድገትና የሥራ መደብ አጥቻለሁ” የሚል ክስ መሰረተችባቸው››። ይህንን ክስ፣ “የወሲብ ጥያቄ አላቀረብኩም። ነገር ግን የሚገባትን የሥራ ድርሻና ዕድገት ባለመስጠቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ” በማለት ተሸጋግረው አለፉት - ዲ.ኤስ.ኬ።

ሆኖም እ.አ.አ ግንቦት 14 የቀድሞ የወሲብ ቅሌታቸውን የተመለከተ መረጃ እንዲደርሰን ያደረገ ዜና በዓለም ሚዲያዎች ተሰራጨ፤ የኒው ዩርክ ከተማ ዕምብርት በሆነችው ማንሀታን በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ የምትሰራ አስተናጋጅ፣ ዲ.ኤስ.ኬ ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመውብኛል በማለት ክስ መመስረቷና

ዳይሬክተሩም በዕለቱ በኒው ዮርክ አየር ማረፊያ ለጉዞ እንደተሰናዱ በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ የሚገልፅ ነበር። ዲ.ኤስ.ኬ በቀረበባቸው ክስ በነፃ ቢሰናበቱም በፈቃደኝነት የፈፀምኩት ነው በማለት ቤተሰባቸውን የፈንሳይን ህዝብ ይቅርታ የጠየቁት ባለፈው ሳምንት ነበር።

ስለመሪዎች የወሲብ ቅሌት ሲነሳ ሳይጠቀስ የማይታለፈው እንደ ዲ.ኤስ.ኬ በወሲብ ቅሌት ተደጋጋሚ ዘገባ የሚቀርብባቸው የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዩ ቤርሎስኮኒ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች የ17 ዓመት ወጣት በገንዘብ አማለው ወሲብ ፈፅመዋል በሚል ክስ እንደተመሰረተባቸው ነው።

አርቲስቶችና ምሁራን ዝናቸውንና ኃብታቸውን በመንተራስ የሚፈፅሙት የወሲብ ቅሌት ተዘርዝሮ የሚያልቅ ባይሆንም፣ ማይክ ታይሰን (እ.አ.አ በ1992) እና የሆሊውድ የፊልም ዳይሬክተር ሮማን ፓላኒስኪ እ.አ.አ በ1997 በፈፅሙት የአስገድዶ መድፈር ዘብጥያ መውረዳቸውና ታይገር ዉድስ ከሁለት ዓመት በፊት በትዳሩ ላይ የፈፀመው የወሲብ ቅሌት በዓለም አቀፍ ሚዲያ ከፍተኛ ትኩረት ከተሰጣቸው መካከል ሳይጠቀሱ የሚታለፉ አይደሉም።

ናንሲ ጊብስ የመሪዎችን የወሲብ ቅሌት ላስነበበበት ጥንቅሩ ከላይ የሰፈረውን ርዕስ ርዕስ የመረጠ አሳማ በተፈጥሮው የወሲብ ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑና ወሲብ ሲፈፅም የዕርካታ ጣሪያ ላይ ለመድረስ ከ20-30 ደቂቃ እንደሚቆይ የሚገልፀውን ሳይንሳዊ መረጃ በመንተራስ ነው።

መሪዎችስ ለሚለው ጥያቅ የሥነ-ልቦና ተመራማሪዎች ‹‹ሴክስ ኤንድ ፓወር›› በሚለው መፅሀፍ ያቀረቡት የጥናት መረጃ እንደሚያመለክተው፣ መሪዎች ወሲባዊ ቅሌት ውስጥ በመግባት ሥህተት ውስጥ የሚገቡት ሥልጣን አማራጮችን ስለሚያሰፋና በራስ የመተማመን ስሜት ስለሚፈጥር ነው። ይህ በራስ የመተማመን ስሜት የወሲብ ስሜትና ፍላጎትን የሚያቀጣጥልና የማን አህሎኝነት ሥዕል በአእምሮ የሚፈጥር ነው። ይህ ፍላጎት ዕውቅናና ሥልጣን እያደገ ሲሄድ የመወስለት ዕድልም ዚያኑ ያህል ያድጋልና ፍላጎቱ ገደቡን እያጣ ይሄዳል።

ይህ ፍላጎት እንዲያድግ፣ እንዲጠናከር ከተፈቀደለት ለመቋቋም የሚያስቸግር ግፊት ያሳድራል። ድርጊቱንም ወደ መፈፀም ሊያደርስ ይችላል። ወደ አእምሮአችን በሚገባውና በምናደርገው ነገር መካከል በጣም የተቀራረበ ዝምድና ስለሚፈጥር አብዛኛውን ጊዜያቸውን ከህብረተሰቡ ተነጥለው የሚያሳልፉ መሪዎች በወሲብ ቅሌት ውስጥ እንዲዘፈቁ የሚያደርግ ጫና ይፈጠርባቸዋል።

በህክምናው ዘርፍ ‹‹በኢቮልሽነሪ ባዮሎጂ›› ተመራማሪዎች የቀረበው ምላሽ የሰው ልጅ ብዙ አማራጮች ካገኘ በአማራጮቹ እየተጠለፈና የአእምሮአችን ራስን የመቆጣጠር ሥርዓት እየተዳከመ እንዲሄድ የሚያደርግ መሆኑን ነው። እንዲሁም፡- እውቅናና ሥልጣን ከታከለበት፣ አእምሮአችን ለሰው ልጅ የሚሰጠውን አድናቆት እና ለስብዕናው ሙገሳን የመስጠት ሞራሉ እየወደቀ በተቃራኒው ደግሞ የራሱን ተፈላጊነት አጉልቶ በሚያሳይ ጀብደኝነት እየተጠለፈ ይሄዳል። ሥልጣን የሥሜትን የወሰን ልክ በማሳጣት አእምሮን ስለሚመርዝ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ራስ ወዳድነት ይፈጠራል፤ እናም ንፁህ ህሊና ይዞ ለመኖር የሚደረገውን ጥረት ያመክናል። በዚህም የተነሳ ከሥነ-ምግባርና ከጨዋነት ውጪ የሆኑ ድርጊቶችና የወሲብ ቅሌቶች እንዲፈጠሩ ያደርጋል። ይህንንም ለመከላከል መሪዎች ተከታታይ የሥነ-ልቦና ምክርና ሕክምና ማግኘት እንዳለባቸው ይመክራሉ - ተመራማሪዎቹ።

ህክምናው ያስፈለገው መሪዎች በተጣለባቸው ኃላፊነት ከህብረተሰቡ ተነጥለው ስለሚኖሩና ይህም በውጪው ዓለም ይፈፀማል በሚባለው ወሲብ ነክ መረጃ ስለሚጎመጁ በውስጣቸው በሚፈጠር የነርቭ፣ የጡንቻና የስሜት ጫና ክብራቸውን ወደሚያዋርድ ስህተት እንዳይገቡ ለማድረግ የሚያስችል ምክር ስለሚለግስ ነው። ከመሪዎች የሚፈለገው የተፈጠረባቸውን የስሜት ጫና በገሀድ አውጥተው ለሥነ-ልቦና ምሁራንና ለግል ሀኪሞቻቸው መንገር ነው።

መሪዎችን ለወሲብ ቅሌት የሚዳርጉ የሥነ-ልቦና ችግሮች

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በመቃወም

የሚታወቁት ሴናተር ላሪ ክሬይግ፣

ተመሳሳይ አቋም የነበራቸው ኢቫንጀሊካል

ፓስተር ቴድ ሀጋርድ፣ በአሜሪካ ሴኔት

የሥነ-ምግባር ኮሚቴ አባልና የኔቫዳ ሕግ

አርቃቂ ጆን ኢንሳይን ማዕረጋቸውንና

ሥልጠናቸውን ተገፈው ወህኒ የወረዱት

በወሲብ ቅሌት ነበር።

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ...

Page 22: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 200422

ከዴጉ መልስ ህዝቡ በ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተገኘውን ውጤት እንዴት እንደተረዳው

ታዘቡ?በዴጉ ውጤት ሳቢያ ህዝባችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ተደስቶ ልበ ሙሉ ሆኖ አልተቀበለንም። በውጤቱ እንደተከፋም እርግጠኛ ነኝ። በቅርብ ያለን አስልጣኞችም በውጤቱ ከማንም በላይ የምንከፋ እና የምንቆጭ መሆኑን እንዲታወቅ እፈልጋለሁ። እንደገባን ያገኙኝ ጋዜጠኞች፤ [እነሱም የህብረተሰቡ ክፍል ናቸውና] ሲጠይቁኝ ብስጭት ወስጥ ገብተው ነበር። እነሱ ተበሳጭተው፣ እኔ በውጤቱ ተበሳጭቼ መጥቼ በምን አይነት ስሜት ልናወራ እንደምንችል ማንም ሰው ሊረዳው ይችላል። እኔም ስሜታዊ ሆኔ ስለነበር የምመልሳቸው መልሶች ህዝባችንን ሊያስቀይም ይችል ይሆናል። እንቅልፍ ሳንተኛ ረዥም ጉዞ ስላደረግን ድካምም ስለነበር ልናገር የፈለግኩትን በአግባቡ መግለፅ አልቻልኩም። በየሚዲያው እና በህዝቡ ዘንድ ሲነገር ስሰማ በእኔ ላይ ሀዘኔታ እንዳለ ገብቶኛል። ስናገር የማስታውሰው ‹‹ሕዝባችን ወርቅ ይፈጋል›› ሲሉኝ ‹‹ወርቅማ አምጥተናል። ነገር ግን ህዝባችን አልማዝም ቢኖር አልማዝ ማምጣት አለባችሁ ይላል›› ያልኩትን ነው። ለማሳሰብ የፈለግኩት አልማዙን ለማምጣት ብዙ መስራት እንዳለብን ነው። ንግግሬ በአሉታዊ መልኩ ተተርጉሞ ከሆነ የኢትዮጵያ ህዝብን በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ። ውድድሩ ላይ የአልማዝ ሽልማት ካለ አልማዝም ማምጣት አለብን። በክፋት የመለስኩት መልስ አለመሆኑ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ። [ምላሻቸው ‹‹አንድ ወርቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ማለት ነው›› ተብሎ ከጋዜጠኞች ጥያቄ ሲቀርብላቸው ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብማ ከወርቅም በላይ አልማዝ ከተፈጠረ የአልማዝ ሜዳሊያን ይጠብቃል›› ብለው መመለሳቸው በመገናኛ ብዙሐን ላይ መገለፁ ህዝብን እንደመናቅ መቆጠሩን ታሳቢ ያደረገ ነው።]

በውጤቱ ደስተኛ መሆንዎን ገልፀው ነበርና በጥቅሉ ይህን ያልኩት በድካም ውስጥ ስለነበርኩ ነው። ትክክትል

አይደለሁም እያሉ ነው?አዎ! በአንድ ወርቅ ብቻ መወሰናችን እኔንም አላስደሰተኝም። እኔም እንደ ሕዝባችን ብዙ ወርቆችን ማምጣት እፈልጋለሁ። ጥረታችንም ይሄ ነበር። ‹‹ውጤቱ ጥሩ ነው›› ያልኩበት ምክንያት የምንመካባቸው የታመሙ አትሌቶቻችን ለዚህ ውድድር ባይደርሱልንም እስከ ዛሬ ድረስ ተነጥቀን በማናውቀው የወንዶች 10 ሺህ በአዲስ አትሌት ወርቅ ስላመጣን፣ ከመሰረት ውጪ ያሉት ነሐስ ያመጡ አትሌቶችም አዲስ ስለሆኑ ነው። እስከ ስምንተኛ የወጡ አትሌቶችም በቀጣይ ጊዜያት ወርቅ እንደሚሻሙ ሙያዊ አስተያየት ነው የሰጠሁት። በጥቅሉ አስተያየቴ አዲስ ልጆች ይዘን ተሰልፈን ያመጣነው ውጤት አስደስቶናል ለማለት ነው። በእርግጥ በጣም የምንረካው ወርቅ ሲመጣ ነው። ያመጣናቸው ነሐሶችም ብሩህ ተስፋ የፈነጠቁ ናቸው። አጠቃላይ ውጤቱ ግን እንደሚያንስን አልካድኩም።

‹‹ወርቅ የጠበቅነው በወንዶች 10 ሺህ እና በሴቶች 5 ሺህ ነበር›› ማለትዎ ያስከፋቸው አሉ። [ይህን ብቻ ካሰብን

አልሰራንም ነበር ከሚል ስሜት ነው።]በሴቶች 5 ሺህ መሰረትን ጠብቀን ነበር። ገንዘቤ እየተሻሻለች የመጣች እና ጥሩ ብቃት ላይ ስለነበረች በእሷም ቢሆን መጥፎ ውጤት ይመጣል አላልንም ነበር። እንዲህ ስንል በቁጥብነት ነው። ኬኒያውያኖቹ ማሳይ እና ቺሩየትን በአሁን ሰዓት ሴት ነኝ ያለች ልትቀድማቸው አትችልም። ጊዜያቸው ነው፤ የብቃታቸው ጫፍ ላይ ደረሰዋል። ምናልባት ጥሩነሽ ጤናማ ብትሆን የምትቋቋማቸው እሷ ነበረች። ዓለምም ለአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት የሰጠው ለእነሱ ነው። መሰረት ደፋር በ10 ሺህ ልትቋቋማቸው ትችላለች ብለን ነበር፤ አልተሳካም። ይህ የእኛ አለመስራት ሳይሆን እንዳልኩህ የእነሱ ጊዜያዊ ብቃት ከፍ ማለት ነው።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች ላይ ጥርጣሬያቸውን የሚያሳድሩ ሰዎች በውጤቱ ደስተኛ መሆንዎን መናገርዎ አምነውበት ሳይሆን ቦሌ ላይ

እርስዎን ‹‹አጋፍጠው›› የሄዱትን አመራሮች ለመከላከል የተናገሩት (እነሱ በሉ ያልዎትን) መሆኑን የሚናገሩ አሉ። ንግግሩ የራሴ አቋም ነው። የተናገርኩት ቴክኒካዊ ጉዳይ ነው። ወርቅ ማግኘት እና መታጣቱን አስመልክቶ መናገር የራሴ ስራ ነው። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስልጠና ውስጥ የሚገባበት ሁኔታ የለም። የማንንም ሀሳብ ለማንፀባረቅ ወይም ፌዴሬሽኑን ለመከላከል የተናገርኩት አይደለም።

ተሳታፊዎች ብዙዎቹ ወጣቶች ናቸው መባሉን የማይስማሙበት አሰልጣኞች አሉ። [ወጣት የሚባለው በአትሌቲክስ ከ20 በታች በመሆኑ አትሌቶች ከዚያ እንደሚሻገሩ በመጠቆም] እንደዚህ አይነት አስተያየቶች ከአሰልጣኝ ከተነሱ በጣም የሚያሳዝን እና የሚያሳፍር ነው። እኛ የዕድሜን ጉዳይ ምንቆጥረው በብቃት እና በውጤት ነው። አንድ አትሌት ብሔራዊ ቡድን መጥቶ ውጤት ማምጣት ደረጃ ከገባ በኋላ ዓለም ሻምፒዮና ላይ ተወዳድሮ ሜዳሊያዎች ውስጥ የሚገባበትን ጊዜ እናያለን። ለዚህ አራት/አምስት ዓመት ያስፈልገዋል። በእነዚህ ጊዜያት ደብቀን ከመጋረጃ ጀርባ አስቀምጠን እያሰለጠንን አምስት ዓመት ሲሞላው ብቅ አድርገነው አዲስ ስም እንደትሰሙ አናደርግም። ይሄ አትሌት በአገር ውስጥ፣ በአፍሪካ ደረጃ፣ በዓለም ዙሪያ በሚካሄዱ ውድድሮች እየወዳደረ ራሱን ብቁ አድርጎ ወደ አምስት ዓመት ሲቃረብ ወርቅ የመሻማት ደረጃ ላይ ይደርሳል።

እኛ እድሜን የምንቆጥረው በዚህ ነው። ሰው ግን እድሜው ከወጣትነት ካለፈ በኋላ የአትሌቱን ዕድሜ ይቆጥራል። ለምሳሌ ኃይሌን እንውሰድ… ኃይሌ አሁን እድሜው 38 ነው። እስካሁን ግን የዓለም ሪከርድ እየሰበረ ነው። እንደሚሰጡ አስተያየቶች ከሆነ ‹‹ኃይሌ ይውጣ በቃው!›› እንደ ማለት ነው። አቅም እና ውጤት እስካለው፣ ሰዎች በውጤት ገፍትረው እስካላስወጡት ድረስ ለምን በቃህ ይባላል?

አንድ እድሜው 30 የደረሰ አትሌት አምስት ዓመት ስለሰራችሁበት ወጣት ይባላል?

30 ዓመት ሞልቶት አራት/አምስት ዓመት አሰልጥነነው ውጤታማ ከሆነ ወጣት ነው የምንለው። ለውጤቱ እንጂ የ30 ዓመትን አትሌትን ወጣት ነው ለማለት አይደለም። ወጣት/ጀማሪ ነው ስንል ውጤት ያመጣበትን ጊዜ ቆጥረን እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ኢማና መርጋን ውሰድ … ብ/ቡድን ከገባ አራት ዓመቱ ነው። በእነዚህ ጊዜያት ቤት ተዘግቶበት ሲሰለጥን የነበረ አይደለም። ከአፍሪካ እስከ ዓለም ዙሪያ ተወዳድሯል፤ ዳይመንድ ሊግን ጨምሮ። ሜዳሊያ ውስጥ የገባው ዘንድሮ ስፔን ላይ የዓለም አገር አቋራጭ ውድድር ላይ ነው፤ ወርቅ አግኝቷል። ዴጉ ላይ ነሐስ አምጥቷል። ከሁለት ዓመት በፊት በበርሊን የዓለም ሻምፒዮና ወቅት የወጣው አራተኛ ነበር። እየሰለጠነ፣ እየተሻሻለ መጥቷል። ኢማናን የቆየ፣ የነበረ ሰው ነው ልንለው አንችልም። አምስት ዓመት አሰልጥነን ውጤት እንዲያመጡ ካላደረግን በድንገት ‹‹ብቅ›› አድርገን ‹‹አትሌት አገኘን›› ልንል አንችልም። የት አይተናቸው?

ብ/ቡድን ውስጥ የሚሰጠው ስልጠና ወቅቱን ያገናዘበ አለመሆኑ ጥያቄ ይነሳበታል። ከአምስት የወንድ የማራቶን ተወዳዳሪዎች ውስጥ ሦስቱ እና ሌሎች አትሌቶች ዴጉ ላይ ማቋረጣቸው በማሳያነት እንደሚቀርብ በአትሌቲክስ ውጤት መጥፋት ዙሪያ ባለፈው ሳምንት በፋና የስርጭት ማዕከል በተካሄደ ውይይት ላይ ተገልጿል። የስልጠናው ደረጃ

መለኪያው ምንድን ነው?ስልጠናው ሊለካ የሚችለው በትምህርት ነው። ትምህርት ደግሞ ሳይንስ ነው። ሳይንስ የተማረ ሰው ምን አይነት ልምምዶች እንደሚሰጥ እና መቼ እንደሚሰጥ ያውቃል። ማንም ሰው ‹‹ልምምዱ ልክ አይደለም›› ካለ ይህን ላለበት ማሳያ ማቅረብ አለበት።

የአትሌቲክሱን ሳይንስ ያልተማረ ሰው በዘርፉ ውጤት ሲጠፋ እና አትሌቶች እያቋረጡ ሲወቱ ማየቱ ብቻ

ስልጠናው ላይ ጥያቄ ለማንሳት በቂ ምክንያት ሊሆነው አይችልም?

ውድድር አቋርጦ ለመውጣት የሚቀርቡ ብዙ ምክንያቶች አሉ። በውድድር መሀከል ውጋት ይይዝሀል፣ የጡንቻ መሸማቀቅ ይኖራል። የተለያዩ ውስጣዊ ችግሮች ሲያጋጥምህ አቋርጠህ ልትወጣ ትችላለህ። በሳይንሱ እና በህክምናው የተካኑ አገሮች አትሌቶች አቋርጠው ይወጣሉ። ‹‹የእኛ አትሌቶች ለምን አቋረጡ?›› ልንል አንችልም። ወድድር አቋርጦ መውጣት የልምምድ ደካማነት ማሳያ አይደለም።

ስልጠናው ከዘመኑ ጋር የተራመደ ነው እያሉኝ ነው?ወደ ፌዴሬሽን የገቡ ሰልጣኞች ሳይንሱን በደንብ የተካኑ ናቸው።

ለዚህ ማሳያ ሊገልፁልኝ ይችላሉ?እስከዛሬ ድረስ እየታገልንባቸው የምንገኘው የወንድ እና የሴት አምስት እና አስር ሺህ ሜትር ሩጫ ነው። እዚህ ላይ ከጨመርን ማራቶንን ነው። ፌዴሬሽነ ውስጥ ያሉ ምሁሮች ግን ተሰባስበው ልጆቹን ለማብቃት ዘጠኝ ወር ጥረት አድርገዋል። በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ 36 አትሌቶች ያሳተፍን ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ነባሮቹ ስድስት ወንድ እና አራት ሴቶች (10) ናቸው። ይህን ያህል ወደ ውጤት እንዲመጣ ያደረገው ምሁሩ ባግባቡ መስራቱን የሚያሳይ ነው። [ሞዛምቢክ- ማፑቶ ላይ በተካሄደው 10ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ተካፋይ ለነበረው የልዑክ ቡድን ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በግዮን ሆቴል በተካሄደ የእራት ግብዣ እና የሽልማት ስነ-ስርዓት

ስ ፖ ር ትአቤል ዓለማየሁ

ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ ስድስት ወርቅ፣ አስር ብር፣ 12 የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘት የዴጉውን ውጤት ቀውስ ማካካሻ እና ለለንደን ኦሎምፒክ ማስተማመኛ እንደማይሆን ገልፀዋል።]3 ሺህ መሰናክል ውድድር በሴትም በወንድም በቁጥር ከአንድ በላይ አልነበረንም። አሁን ግን እስከ ሦስት ማሰለፍ ችለናል። በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይ በወንዶች ሦስቱንም ሚዲያዎች ያገኙት አዲስ ልጆች ናቸው። በዚሁ ውድድር የኦሎምፒክ ሚኒማ (ዝቅተኛ ሰዓት) ማምጣት ችለዋል። በ1500፣ በ800 ሜትር ብዙ ለውጦች አሉ። ፋንቱ ሜጌሶ እና መሀመድ አማን የዚህ ማሳያዎች ናቸው። ይህ ሁሉ የምሁር ውጤት ነው። [መሀመድ ከዴጉ በኋላ ጣሊያን ላይ በተደረገ የ800 ሜትር ሩጫ ለረዥም ጊዜያት ያልተሸነፈውን ኬኒያዊውን ዴቪድ ሩዲሺያን ማሸነፍ ችሏል። በርቀቱ ዴጉም ላይ የፍፃሜ ተፋላሚ ነበር።]

እርስዎ ይህን ይበሉ እንጂ ምሁር ያልሆኑ ወደ ዴጉ የኢትዮጵያን ብ/ቡድን በአሰልጣኝነት መርተው የሄዱ

መኖራቸው ይነገራል። በማራቶን አሰልጣኝነት የሄደው ሃጂ አዴሎ (የአትሌቶች ማናጀር) ለዚህ ዋና ተጠቃሽ ነው።

በፌዴሬሽን አሰልጣኞች ብቻ ስራውን እንወጣዋለን ካልን መንገዱን እናጠበዋለን። አትሌት የትም ይሰልጥን ኢትዮጵያዊ እስከሆነ ድረስ መጥቶ ተወዳድሮ ለአገሩ ውጤት ማስመዝገብ ይችላል። ማናጀሮች ብቃት ካላቸው እና ስልጠናውን በአግባቡ የሚሰጡ ከሆነ ያሰልጥኑ። ፌዴሬሽኑ ግን ስልጠናው በተገቢው ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን፣ ግለሰቡ ለማሰልጠን ብቁ መሆኑን ክትትል የማድረግ ስራ አለበት። በርግጥ እስካሁን ክትትል ባናደርግም ከዚህ በኋላ ግን ይህንን የምናጠራው እና የምንከተለው ይሆናል። ውጤቶች ለምን እንዳልመጡም የምንገመግመው ይሆናል።

ያላቸው የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆንን በመጥቀስ ከብ/ቡድን እንዲርቁ የተደረጉ አሰልጣኞች እያሉ ማናጀሮች

በአሰልጣኝነት ሲመደቡ ግርታን አይፈጥርም?

አሰልጣኞቹ በጣም የተማሩና ያወቁ ናቸው።

የትምህርት ደረጃ አላቸው?ሊኖራቸውም፣ ላይኖራቸውም ይችላል። ብቁ

አለመሆኑን ወርደን መፈተሽ አለበን።

ማስረጃቸውን ካላያችሁ ታዲያ በምን መስፈርት ነው እንዲያሰለጥኑ ያደረጋችሁት?

ይኸውልህ ማናጀሮች የሚሰሩት ቢዝነስ ነው። አትሌቱም ቢዝነስ (ውድድር) የሚያመጣለት ማናጀሩ ስለሆነ ‹‹እኔጋ መጥተህ ካልሰራህ ውድድር አልክህም›› ስለሚለው ስልጠናው ችግርም ቢኖርበት መፈፀም ግዴታው ነው። ሰልጣኞቹ እንዳይጎዱ የሰውየውን የማሰልጠን ብቃት መገምገም ያለበት ፌዴሬሽኑ ነው። አንድ ውጤት ላይም እንደርሳለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን።

ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞች እና የትምህርት ደረጃቸው መልካም ነው የሚባሉ አሰልጣኞችን አጣምሮ መሄድ

ለለንደን ኦሎምፒክ እንደ አጭር ጊዜ መፍትሄ እየተቀመጠ ነው። እዚህ ላይ የግልዎን ሀሳብ ቢገልፁልኝ? [በርግጥ ይህ ጥያቄ የሚመለከተው የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ አካላት

ቢሆንም]አሰልጣኞች ይምጡ አይምጡ ማለት እኔን አይመለከተኝም። እንዳልከው የአመራሮቹ ስራ ነው። እኔ ፌዴሬሽኑን ትቼ ወጥቼ ነበር። የግድ ደግሞ መጥቼ ልስራ አላልኩም። በግሌ ስልጠናውን ስሰራ ነበር፡፡ አንድም ቀን ስልጠናውን ትቼ ፌዴሬሽን ካልገባሁ ብዬ ለየሚዲያው መግለጫ ሰጥቼ አላውቅም። ፌዴሬሽኑ ከፈለጋቸው መጥተው የሚሰሩበት ሁኔታ ሊኖር ይችላልብዬ እገምታለሁ። የራስን ጥቅም እያዩ አተካሮ ውስጥ መግባትን ግን ተገቢ አይደለም።

በዴጉ በግል ጥረቱ ለኢትዮጵያ ብቸኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘው ኢብራሒም ጄይላን ሁለት ዓመት ያህል ጃፓን ውስጥ ተቀምጦ ለሆንዳ ካምፓኒ ይሮጥ ነበር። [ሚኒማም

ያመጣው እዚያው ነው።] በዓለም ሻምፒዮና ውጤት ካስመዘገበ በኋላ አሰልጣኙ ‹‹እዚህ ያደረስነው እኛ ነን›› ብለዋል። ትክክል አይመስልዎትም? ኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች በኢብራሒም ውጤት ላይ ድርሻ አልባ

እንደሆናችሁ ብናገር ምላሽዎ ምን ይሆናል?ኢብራሒም በወጣቶች የዓለም ሻምፒዮና ላይ በ10 ሺህ ሜትር ያሸነፈ አትሌት ነው። በ16ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወቅትም በ10 ሺህ ሜትር ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያምን ተከትሎ በመግባት የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል። እዚህ አገር ሲሰራ የነበረ ልጅ ነው። ክለብ ፈልጎ ውጪ አገር (ጃፓን) ይሰለጥን ነበር። የትም ይሰልጥን ክሬዲቱን ማንም ይውሰደው ብቃቱ እስካለው እንቀበለዋለን። ኢብራሒም ውጤት እንዳለው አይተን ህዳር ላይ ብ/ቡድን ልምምድ ስንጀምር ብንጠራውም የመጣው ሰኔ አካባቢ ይመስለኛል፤ መጣና ተቀላቀለ። ሁለት ወር ያህል ከእኛ አትሌቶች ጋር በሚገባ ሰርቷል። የስራው ውጤት የእኛ ነው፣ የጃፓኖች ነው ብለን ሽሚያ ውስጥ አንገባም። ጃፓናዊያን እሱን አሰልጥነው ካወጡ ጃፓኖችንም ማውጣት አለባቸው። የጃፓን አትሌቶች ደግሞ በረዥም ርቀት ላይ የት እንዳሉ ሁላችንም የምናውቀው ነው። የትኛው ስልጠና ለዚህ እንዳበቃው የሚገምተው ልጁ ራሱ ነው።

ዘላቂነት ባለው መልኩ በውጤታማ መም ላይ እንድንጓዝ የሚያቀርቡት የመፍትሄ ሃሳብ አለ?

መንግስት፣ ህዝብ፣ ሙያተኛና ፌዴሬሽን ተረባርቦ ለስፖርቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ይገባል። ምንም ምቹ ነገር በሌለበት ሁኔታ እየተሰራ ነው። ለልምምድ ያለን አንድ መም (track) ነው፤ እሱም ቢሆን ለውድድር እንጂ ለልምምድ የሚሆን ባለመሆኑ አትሌቶችን ለጉዳት እየዳረገ ነው። ኢትዮጵያን የሚያህል በርካታ አትሌቶችን የምታፈራ አገር ቀጣይነት ያለው ተመጋጋቢ የአትሌቲክስ ስርዓት የላትም። አትሌቱ ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናቶች እያደረጉ የሚሰሩ ሐኪሞች ኖረውት፣ ምቹ ላብ መተኪያ ምግቦች ተዘጋጅተውለት የሚሰራ አይደለም። ኬኒያውያን ግን ይሄ ሁሉ ተሟልተውላቸዋል። ሁሉም ያገባኛል ብሎ ለስፖርቱ ሊሰራ ይገባል። አትሌቶች በብዛት የሚፈልቁበትን መንገድ ለማመቻቸት

‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብን በጣም ይቅርታ እጠይቃለሁ››ዶ/ር ይልማ በርታ

/የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ/ዶ/ር ወልደ መስቀል ማን ነበረና ነው ለእሱ ወረቀቴን የማመጣው?•

የራስን ጥቅም እያዩ አተካሮ ውስጥ መግባት ተገቢ አይደለም•

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆኑት ዶ/ር ይልማ በርታ ከ13ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መልስ የሰጡት አስተያየት መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። በዚህ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኢትዮጵያን የሚያህል በርካታ አትሌቶችን

የምታፈራ አገር ቀጣይነት ያለው

ተመጋጋቢ የአትሌቲክስ ስርዓት የላትም።

አትሌቱ ሳይንሳዊ የሆኑ ጥናቶች እያደረጉ

የሚሰሩ ሐኪሞች ኖረውት፣ ምቹ ላብ

መተኪያ ምግቦች ተዘጋጅተውለት የሚሰራ

አይደለም። ኬኒያውያን ግን ይሄ ሁሉ

ተሟልተውላቸዋል። ሁሉም ያገባኛል ብሎ

ለስፖርቱ ሊሰራ ይገባል።

Page 23: የቀድሞ ቅንጅት መሪዎች እንዴት ከእስር ተለቀቁ?ethioforum.org/wp-content/uploads/2011/09/Awramba-Times... · 2012-11-25 · አዲስ ዘመን ጋዜጣ

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

አውራምባ ታይምስ 4ኛ ዓመት ቁጥር 186 ቅዳሜ መስከረም 13/ 2004

ለመረጃ ቅርብ ይሁኑ

23

}SdeK¨< Ÿ}c\ ð×” ¾h¨` ¨<H TVmÁ U`„‹ ÃÖ”kl ƒ¡¡K—¨<” ¾w^²=M

¾h¨` ¨<H TVmÁ ÃÖkS<

Brazmart International General Trading Plc. Address!- •Urail Alem Brehan Plaza 1st Floor #106 1. ›<^›?M u?} ¡`e+Á” ›”vu= ¯KU w`H” ýL³ 1— öp u=a lØ` 1062. Ku< ›Åvvà òƒ Kòƒ dS<›?M I”íuT”—¨<U ¾vD”vD“ ¾h¨` u?ƒ �n ዎ ‹ SgÝ“ �”Ç=G<U u¾I”í SX]Á SÅwa‹ ÁÑ–<�M::

c=Ѳ< ƒ¡¡K— ¾w^²=M U`ƒ SJ’<” Á[ÒÓÖ<! Tel. 251-11 552 -6011 /12 Fax 251-11-5526012

ሰፋ ብሎ ውሃየሚያወርድ

ምቾት እናጥራት ያለው

ከበቂ መለዋወጫ ጋር

ለጥንቃቄዎ የተመሳሰሉትን

ይለዩ

በፌዴሬሽኑ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ውጤት ያመጣሉ ብለን የምንጠብቃቸው ብዙ ወጣት አትሌቶች አሉን። በጥራት እንድናመጣቸው ከፍተኛ ስራ ያስፈልጋል። እስከ ብራዚል ኦሎምፒክ (2016) ድረስ ቀጣይ እቅዶቻችን የተቋቋሙ ፕሮጀክቶችን እና የተለያዩ ቦታ ያሉ ክለቦችን እየጎበኙ ማገዝና፣ ጠንክሮ መስራት ነው። ከሕዳር ጀምሮም ይህንኑ ለመስራት ብዙዎቻችን እንንቀሳቀሳለን፡፡ አትሌቶቹ የሚፈሩበት ሁኔታን ካመቻቸን ለብራዚል ኦሎምፒክ አዳዲስ ውጤታማ አትሌቶች ይኖሩናል የሚል ራዕይ አለን። ከመም ጀምሮ ያሉ በቂ ረጂ መሳሪያዎች ሊሟሉ ይገባል። ሁሉም ባለ ድርሻ አካል ‹‹ለአትሌቲክስ እድገት ምን አደረግኩኝ?›› ብሎ ሊጠይቅ ይገባል። በተቆርቋሪነት ከተነሳን በጋራ ብዙ ስራ መስራት እንችላለን።

ሳምንት ከአውራምባ ታይምስ ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉትን የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ካሱ ዓለማየሁ በተደጋጋሚ ጊዜ በተለያየ መድረክ እርስዎን አስመልክተው ትችት ይሰነዝራሉ። በውድድር ሰሞን ብቻ ታይተው የሚጠፉ አሰልጣኝ ናቸው፣ አንድም አትሌት አፍርተው ሳያውቁ ነው እዚህ የደረሱት…ልክ ነህ። በተደጋጋሚ ጊዜ ስለ እኔ ያነሳል። እኔም እንዲህ አይነት መድረክ አግኝቼ ነገሮቹን ለማጥራት አልቻልኩም። እኔ ትምህርቴን አጠናቅቄ ከቼኮዝሎቫኪያ ከመጣሁ 30 ዓመት ይሆነኛል። ያኔ እሱ አትሌት ነበር። ከዚያ ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው ወደ ክለብ አሰልጣኝነት የመጣው። እኔ ግን ከእሱ በፊት ብዙ አትሌቶችን ከእሱ በላይ አፍርቼ ለታላቅ ውጤት ያበቃሁ ነኝ። እነ ኃይሌን፣ ወርቁ ቢቂላን ያመጣኋቸው እኔ ነኝ።

ኃይሌን አሰላ ላይ በነበረው የኢትዮጰያ አየር መንገድ ፓይለት ፕሮጀክት ውስጥ ከአቶ ንጉሴ ሮባ ጋር በመሆን እንዲካተት እንዳደረጉ አንስቼላቸው አልተስማሙበትም። ‹‹ለመደጋገፍ ተብሎ የሚወራ ወሬ ነው›› ሲሉ ጥያቄዬን

ውድቅ አድርገውታል።የአንድን ሰው ስም ለማጥፋት ከተነሳህ ማንኛውንም ነገር ልትል ትችላለህ። አትሌቶችን መልምለን ፕሮጀክቱን ያቋቋምነው እኔ እና ንጉሴ ሮባ ነን። እየሄድኩ እከታተል ነበር። ሁለት ዓመት ከቆዩ በኋላ ውድድር አድርገን ኃይሌን፣ ወርቁ ቢቂላን ለንደን ላይ የጠፋ ካሳ የሚባል አትሌትን ያስመጣኋቸው እኔ ነኝ። በወቅቱ የማሰለጥነው 5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ነበር። ዱቤ ጀሎንም ያመጣሁት እኔ ነኝ።

ዱቤ ያን ያህል ሊወራለት የሚችል ውጤታማ የነበረ አትሌት አይደለም።

እነ አብርሃም፣ አዲስ አበበን ያመጣኋቸው እኔ ነኝ። አንድ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ከኬጂ አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ያድርስ የሚባልበት ሁኔታ የትኛውም አገር የለም። በየድርሻው ያለው የተለያየ አስተማሪ ነው፤ ቅብብሎሽ ነው። ስልጠናም ይሄ ነው። እሱም (ካሱ) ቢሆን አትሌቶችን ከየት ነው የሚያመጣቸው? አዲስ አበባ ሰዎች ያመጧቸውን አይደል እየነጠቀ የሚያስገባው? ገጠር ሄዶ ነው መልምሎ ያመጣቸው? እየተዋወቅን የማይሆን ነገር ባንናገር ጥሩ ነው። አትሌቶችን

በ2,045,496 (ሁለት ሚሊየን፣ አርባ አምስት ሺህ፣ አራት መቶ ዘጠና ስድስት) ብር የዝውውር ሂሳብ ቅ/ጊዮርጊስን ለቅቆ የግብፁን ዋዲ ደግላ የተቀላቀለው ሳልሃዲን ሰይድ የቀድሞ ክለቡ ያለ ምንም የመሸኛ ፕሮግራም ስላሰናበተው ማዘኑን ገለፀ። ከካይሮው ክለብ ጋር የሦስት ዓመት የኮንትራት ውል ፈፅሟል። የአሶሳው ልጅ ምዕራብ አውሮፓ ከሚገኘው ከሶከር ዛሬ

ኤዲተር ኤርሚያስ አማረ ጋር በስልክ ባደረገው አጭር ቆይታ ላይ እንደገለፀው አዲሱ ክለቡ ከመሀል ከተማው ወጣ ብሎ ከሚገኘው ስታዲየሙ አቅራቢያ አፓርትመንት ላይ ‹‹ስቱዲዮ›› ቤት እና መኪና ሰጥተውት ልምምዱን በአግባቡ አጠናክሮ እንደቀጠለ ተናግሯል። ‹‹የፊርማ ገንዘብ አልሰጡኝም። ደመወዜ በወር አስር

ሺህ የአሜሪካ ዶላር ነው። ክለቡ የስድስት ወር ቀድሞ ደሞዝ ይከፍላል፤ የስድስት ወር ቅድሚያ ደመወዝ ስልሳ ሺህ ዶላር ተቀብያለሁ›› የሚለው ሳልሃዲን የሦስት ዓመት ኮንትራት ከክለቡ የተሰጠው ሲሆን ደመወዙ በሁለተኛው ዓመት ወደ 11ሺህ፣ በሦስተኛው ህመት 13 ሺህ ዶላር እንደሚሆን የውል ሰነዱ ላይ ማረፉን ጠቁሟል። የትራንስፖርት፣ የምግብና የቤት ኪራይ ወጪው ‹‹በክለቡ ይሸፈናል›› ብሏል። በ2002 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ ቅ/ጊዮርጊስ እና ደደቢት

ሰበታ ላይ የጥሎ ማለፍ የፍፃሜ ጨዋታ ሲያደርጉ ዋና ዳኛውን ዓለም አቀፍ አርቢትር ባምላክ ተሰማን በመማታቱ የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ቅጣት ከተጣለበት በኋላ ግንቦት 30/ 2003 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባስገባው ደብዳቤ ላይ በጥፋቱ መፀፀቱን ገልጾ ‹‹አንድ ዓመት የተቀጣሁት ቅጣት በቂ ነው። ቀሪው የስድስት ወር ቅጣት በምህረት ይነሳልኝ›› ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ሰምቶ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኔ 9/2003 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በይቅርታ እንዲነሳለት ውሳኔ ማሳለፉ የሚታወስ ሲሆን ተጨዋቹም ይህንን (ተጠናቀቀውን) ዓመት ‹‹የመከራ ዘመን ነበር›› ብሎታል። ‹‹በዓመቱ በጣም ተጎድቻለሁ ለዚህ በመድረሴ አምላኬን አመሰግናለሁ›› ሲል ጨለማው ወቅት ማለፉን ለድረ ገፁ ጠቁሟል። ጥቅምት አጋማሽ ላይ በሚጀመረው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ

የሚጫወት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ተጨዋች የሚሆነው ሳልሃዲን ሰይድ ከታች ጀምሮ ላሳደገው የሙገር ሲሚንቶ እና ለእውቅና ላበቃው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ምስጋና አቅርቧል። የፈረሰኞቹ ደጋፊዎችን ‹‹በተቸገርኩኝ ጊዜ ከጎኔ ሆነው አበረታትተውኛል። በጣም አመሰግናቸዋለሁ›› ብሏል። ‹‹አይን ውስጥ›› እንዲገባ ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ የሽኝት

ዝግጅት ስላላደረገለት ቅሬታ እንደተሰማው ገልጿል። ‹‹ሳልገልፀው የማላልፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ ትንሽ እንኳን መሸኛ ሳያደርግልኝ መቅረቱን ነው። በዝምታ ስለሸኙኝ በጣም ከፍቶኛል›› የሚለው ሳልሃዲን ወደ ቡናማዎቹ (ኢትዮጵያ ቡና) ዳግመኛ የተመለሰው ታፈሰ ተስፋዬ ወደ የመን ሊግ ሲዛወር በደንብ መሸኘቱን አስታውሶ እሱ ግን ይህ እድል ስላልገጠመው አዝኗል። ‹‹ቅዱስ ጊዮርጊስ ለእኔ ቢበዛ እስከ ሃምሳ ሺህ ዶላር አውጥቷል። ከእኔ ሽያጭ ግን 120 ሺህ ዶላር አግኝቷል። ክለቡን በሁሉም ነገር ጠቅሜ

በዝምታ መሸኘት አልነበረባቸውም።››ጉዳዩን አስመልክተን ያነጋገርናቸው የቅዱስ ጊዮርጊስ

ኮምዩኒኬሽን እና ማርኬቲንግ ኃላፊ አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ሳልሃዲን የጉዞ ሂደት ለማጨረስ ወጣ ገባ ይል ስለነበር ክለቡ፣ ደጋፊዎችና ግለሰብዎች መሸኛ ማድረግ ፈልገው ምቹ ጊዜ አለማግኘታቸውን ‹‹የጊዜ መጣበብ እንጂ ሳናስብ ቀርተን አይደለም›› በማለት ለአውራምባ ታይምስ ገልፀዋል። ከኢትዮጵያ ብ/ቡድን ጋር ከኮናክሪ እንደተመለሰ በቶሎ ወደ ግብፅ መሄዱም የሽኝት ፕሮግራም ለማዘጋጀት ጊዜ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል። ሳልሃዲን ወደ ካይሮ ካቀና በኋላ ለሦስት ጊዜያት ያህል እንደደወለላቸው የገለፁት አቶ ዘካሪያስ አንድም ጊዜ ግን ቅሬታውን እንዳልገለፀላቸው ተናግረዋል።ለዝውውር ያስከፈለው ሒሳብ ኢትዮጵያዊው ውድ

ተጨዋች ያደረገው አጥቂው በሰርቢያ እንደተመለከተው ሁሉ ከግብፅ ተጨዋቾችም ኢትዮጵያዊያን በእግር ኳስ ክህሎት የተሻለ እንደሆኑና አጨዋወታቸው ግን ፈጣን መሆኑን፣ መገናኛ ብዙሐን ለአገር ውስጥ እግር ኳስ የሚሰጡት ሽፋን የላቀ በመሆኑ መገረሙን፣ 11 እና 17 ቁጥር መለያን ማጥለቅ ፈልጎ በተጨዋቾች ስለተያዘ ውደድሩ ሲጀመር 21 ቁጥርን ሊሰጡት እንደሚችል ከሶከር ዛሬ ድረ-ገፅ ኤዲተር ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ጨምሮ ገልጿል። በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ኮናክሪ ላይ በጊኒ አንድ ለዜሮ በተሸነፈችበት ጨዋታ የጉልበት ጉዳት ስላጋጠመው ወደ መደበኛ ልምምዱ ከመመለሱ በፊት ጅምናዚም ውስጥ እየሰራ የሚገኘው ሳልሃዲን ሰይድ አዲሱ ቡድኑ ዋዲ ደግላ ከተመሰረተ አስር ዓመት ያልደፈነ ሲሆን ባለፈው ዓመት ሊጉን በ12ኛነት አጠናቋል።

አፍርቻለሁ። ዛሬ ግን ቦታዬ እዚያ አይደለም። ልጆቹ ከፍተኛ ደረጃ ሲደርሱ የሚያሰለጥናቸው ከፍተኛ አሰልጣኝ ነው። ከእኔም በላይ ሌላ ካለ ለእሱ አቀብዬ ያሰለጥናቸዋል። ሂደቱ ይሄ ነው። በዚህ ሂደት የማያምን ሰው ካለ አካሄዱ የተሳሳተ ነው። ፌዴሬሽን ተመርጦ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲያሰለጥን የተመረጠ ሰው ወርዶ ክለብ ማሰልጠን አይችልም። ሁለት ቦታ መስራት በመንግስትም ክልክል ነው፤ በብ/ቡድን ቅጥር ሆነው ክለብ መስራት አይፈቀድም። ክለብ ውስጥ የሚሰሩ አሰልጣኞች እኛጋ መጥተው በተባባሪነት የሚሰሩበት ሁኔታ ግን አለ። ቋሚ ስራዬን ጥዬ ክለብ ወርጄ ላሰለጥን እንዴት እችላለሁ? እንዲህ የሚሉ ሰዎች ያልገባቸው ናቸው። በአትሌቶች መሀከል ብዙ ጊዜ ችግሮች ይፈጠሩ የነበሩትም የክለብ አሰልጣኞች ሲመጡ ወደ ክለባቸው አትሌት ይሳባሉ፣ እኛን አግለው እነሱን ይመክራሉ የሚል ነው። ብሔራዊ ቡድን የሚሰራ ሰው ታች ወርዶ የማይሰራው አቅቶት ሳይሆን ሁኔታዎቹ ስለማይፈቅዱለት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። ሁሌም ይሄን የሚያነሱ ሰዎች ህዝቡን እንዳያሳስቱ ብዬ ነው። የእኛ ኃላፊነት ብቁ አትሌቶችን አሰልጥኖ ለዓለም ዓቀፍ ውጤት ማብቃት ነው። አሁን እኔ ያለሁበትን ቦታ (የኢትዮጰያ ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ) ለመውሰድ የሚፈልግ ሰው ካለ ያለበት መማር ነው። ከተማረ ቦታውን የሚከለክለው የለም። ሳይማሩ ከውጪ ሆኖ መተቸት፣ የሰውን ስም ማጥፋት ትክክለኛ አካሄድ አይደለም። በጣም የሚያሳዝነው የሚተቹኝ ሰዎቹን ከማክበር በስተቀር ነክቻቸው አላውቅም። ባሉበት ደረጃ ከፍተኛ ስራ እንደሚሰሩ አውቃሁ። ዛሬ አንተ ጥያቄውን ስላነሳህልኝ እንጂ ስማቸውንም ማንሳት አልፈልግም። የሚመሰክርልኝ ስራዬ እንጂ ሰዎች ሊሆኑ አይችሉም። ፋጡማ ሮባ፣ ገዛኸኝ አበራና እልፍነሽ ዓለሙ እኔ ያሰራኋቸው አትሌቶች ናቸው።

ከሁለት ሳምንት በፊት በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ እንግዳ የነበሩት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ እርስዎን ፔዳጎጂስት

ነው እንጂ የስልጠና ትምህርቱንት አምጣ ብለነው ማምጣት አልቻለም የሚል አንድምታ ያለው ንግግር ተናግረዋል።

የቃላት ፍጭቱን ለማክረር ሳይሆን ነገሮችን ለማጥራት ነው ይሄን ጥያቄ ያነሳሁት።

ፔዳጎጂስት ነው ሲል ምን ማለት እንደፈለገ እሱን ብትጠይቀው ደስ ይለኛል። አብረን ሰርተናል፣ አብረን በልተናል፣ ጠጥተናል። 30 ዓመት ያህል አብረን ስንቆይ ይሄ ነገር የተነገረበት ጊዜ የለም። ዛሬ ለምን እንደተነሳ ይገባኛል። በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አልፈልግም ነበር። እንደውም ስለ እሱ ብዙ መዘርዘር እችላለሁ፤ በጣም ብዙ፡፡ እሱ እኔ የተማርኩበት ትምህርት ቤት አልሄደም። እኔ ግን እሱ የሄደበት ትምህርት ቤት ሄጄ ብዙ የማውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ እሱ እንዲህ አለ ብዬ ግን አልናገራቸውም። እኔ የተማርኩት ቼኮዝሎቫኪያ - ቻርለስ ዩኒቨርሲቲ ነው። እሱ የተማረበትን ሲስተም ባላውቀውም የምስራቅ አውሮፓ አገሮች አንድ አይነት የማስተማር ሂደት አላቸው። [ዶ/ር ወ/መስቀል የተማሩት ሃንጋሪ ነው] ትምህርት ቤቴ የሚያስተምረው ጠቅላላ የሰውነት ማጎልመሻ (Physical Education) ትምህርቶችን ነው። ስፖርተኛ ከሆንክ ሁሉንም መማር አለብህ፡፡ እዚህ አገር የእኛ ዩኒቨርሲቲዎች ይህንኑ

እየተከተሉ ነው። ፊዚዮሎጂ፣ ባዮሎጂ፣ ባዩ ሜካኒክስ፣ ፊዚክስ ታጠናለሀ። በዓለም ላይ ያሉ የስፖርት አይነቶች ምንም አይቀሩህም ሁሉንም ትማራለህ፡፡ በተጓዳኝ ደግሞ አንዱን መርጠህ ስፔሻላይዝ ታደርጋለህ። እኔ ድሮም በትምህርት ቤት ደረጃ አትሌት ስለነበርኩ የመረጥኩት አትሌቲክስን ነው። አምስት ዓመት ተምሬያለሁም። የመመረቂያ ፅሁፌም የፃፍኩት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አትሌቲክስ ላይ ነው። ዶክትሬቴን ስቀጥል የተለያዩ ጥናቶችን የሰራሁ ሲሆን መጨረሻ ላይ የሰራሁት ፅሁፍ ፔዳጎጂ ላይ ነው። ፔዳጎጂስ (የማስተር ጥበብ) የሁሉም የበላይ ነው። ሁሉንም ነገር መስራት ይችላል። ‹‹Doctor of Athletics Coaching›› የሚባል የለም። እኛ ትምህርት ቤት ቅድም ያልኩህን የትምህርት ዓይነት ገፍቶ መውጣት የሚያቅታቸው ሰዎች ወደ ስልጠና (Coaching) ሄደው ለሁለት ግፋ ቢል ለሦስት ዓመት ቢማሩ ነው። ስልጠና የተማረ ሰው ብቻ አሰልጣኝ እንደማይባል ግንዛቤው እንዲኖር እፈልጋለሁ። የሚያሰለጥነው የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ትምህርቶችን በአግባቡ የሰራ ሰው ነው። ዛሬም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተምረው ይሄንኑ ነው። ተማሪዎቼም ዛሬ አብረውኝ እየሰሩ ነው። በትምህርቴ ብዙ የሰራሁበት እና የምሰራበት እንጂ የማፍርበት አይደለም። ሌላው ጋዜጣውን ሳነብ ዶ/ር ወ/መስቀል ‹‹እሱ ረዳት ዶክተር ነው›› ብለዋል። ረዳት ዶክተር የሚባል ነገር የለም። ቀረችኝ ያሉትን ዶክትሬት እንግዲህ መቼ ሄጄ እንደምሰራውም አላውቅም። [እየሳቁ] የሰውን ስም ጠርቶ እንዲህ ብሎ መናገር በጣም ያሳፍራል። ‹‹ወረቀቱን አምጣ ብለነው አላመጣም›› ብሏል ማን ነበረና እና ነው ለእሱ የማመጣው? ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርቴ እውቀና ባይሰጥ ኖሮ እስከዛሬ ድረስ ልሰራም አልችልም ነበር። አስፈላጊ ከሆነ ግን የትምህርት ማስረጃዎቼን ዶክትሬቴን፣ ማስትሬቴን ለማንም ማሳየት እችላለሁ። ለጋዜጣ ሄዶ ውሸት መንገር አሳዛኝ ነው። ትንሽ ዶክተር የሚባል ነገር የለም። እስቲ ተመልከት እንደዚህ ተብሎ ይወራል?

በመጨረሻበዴጉው ውጤት ሕዝባችን በጣም እንደተቆጨ አውቃለሁ። ጥሩ የተሰሩን ነገሮች ባያስደስቱም መልካም ጎናቸውን ስህተቶችን በመተራረም ሚዛናዊ የሆነ ወቀሳን የምንፈልገው ነው። ኃላፊነቱን ስንረከብ አገራችን የሚወክሉ በርካታ አትሌቶችን እናፈራለን ብለን ነው። አሁንም ቢሆን ተስፋ የሚያስቆርጠን ነገር የለም። መንግስታችንም፣ ህዝባችንም ትንሽ ጊዜ ይስጠንና በጥሩ አትሌቶች ተጥለቅልቀን አገራችንን እናስከብራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ለለንደን ኦሎምፒክ ዘጠኝ ወር ይቀራል፤ ቀላል ጊዜ አይደለም። የታመሙ አትሌቶች ድነው ከተመለሱ፣ ያሉትም ከተጠናከሩና ከህመም ነፃ መሆን ከቻሉ የተሻለ ውጤት ይመጣል የሚል እምነት አለኝ። በተረፈ ባለፉት ጊዜያት ከድካም እና ከቁጭት ስሜት የተናገርኳቸው ነገሮች ህዝቡን አስቆጥቶ ተቀይሞኝ ከሆነ በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ድካም እንደነበረብኝ የማውቀው ብዙዎቹ የተናገርኳቸውን ነገሮች አሁን አለማስታወሴ ነው።

የ38 ዓመቱ ኅይሌ ገ/ሥላሴ ነገበ38ኛው የበርሊን ማራቶን ላይ ይሮጣል

ነገ በጀርመን በርሊን በሚካሄደው 38ኛው የበርሊን ማራቶን ላይ የ38 ዓመቱ የርቀቱ የሪከርድ ባለቤት ኅይሌ ገ/ሥላሴ ይሮጣል። በሴቶች የ38 ዓመቷ ኢሪና ሚኪቴንኮ እና ፓውላ ራድክሊፍ ፉክክር ትኩረት አግኝቷል። እንደ ሌትስራን ድረ-ገፅ ፀሐፊ ዴቪድ ሞንቲ ገለፃ ከሆነ

የ38 ዓመቶቹ ኃይሌ እና ጀርመናዊቷ ሚኪቴንኮ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ካጋጠማቸው ጉዳት ጋር ሲታገሉ ስለ ነበር ወጥ አቋማቸው ላይ መገኘት ያልቻሉ ሲሆን ነገ ግን የተሻለ ነገር እንደሚሰሩ ገምቷል። በበርሊን ማራቶን 2007 እና በ2008 የዓለም ሪከርድ

በማሻሻል ያሸነፈው ኀይሌ ገ/ሥላሴ በጉልበቱ ጉዳት ኒው ዮርክ ማራቶን ላይ አቋርጦ ከወጣ በኋላ የማራቶን ውድድር ያላካሄደ ሲሆን በየካቲት ወር ሊወዳደርበት በነበረው የቶኪዮ ማራቶን ላይ በልምምድ ላይ በመውደቁ ከውድድር ውጪ እንደነበር ይታወሳል። በኦስትሪያ የግማሽ ማራቶን አድርጎ ማሸነፉም ይታወሳል።ከ20 ቀን በፊት በስፔን ማድሪድ በስፖርት የላቀ

አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሰዎች የሚሰጠውና ልዑል ኦስተሪየስ ፋውንዴሽን የሚያጀጋጀውን የስፖርት አዋርድ ከቀድሞው የሪያል ማድሪድ ኮከብ ራዑል ጎንዛሌዝ ጋር የመጨረሻ እጩ ሆኖ ቀርቦ በማሸነፍ 50 ሺህ ዩሮ የተሸለመው ኀይሌ ገ/ሥላሴ 2፡03.59 በሆነ ሰዓት የርቀት የሪከርድ ባለቤት ሲሆን እ.አ.አ ጥቅምት 13/1974 ዓ.ም በተጀመረው የበርሊን ማራቶን ላይ 38ኛ መድረክ ነገ ያሸንፋል የሚል ከፍተኛ ግምት አግኝቷል። ከኬንያዊው ፓትሪክ ማኩ ጠንካራ ፉክክር እንደሚገጥመውም ተገልጿል። አሸናፊዎቹ አትሌቶች እያንዳንዳቸው 40 ሺህ ዩሮ፣

እንዳስመዘገቡት ፈጣን ሰዓት ጉርሻ እንዲሁም መጠኑ ያልተገለፀ የመግቢያ ክፍያ (Appearance Fee) ያገኛሉ።

ሳልሃዲን ሰይድ

በቅ/ጊዮርጊስ ላይ ቅሬታውን ገለፀ‹‹በዝምታ ስለሸኙኝ በጣም ከፍቶኛል›› •

‹‹የጊዜ መጣበብ እንጂ ሳናስብ ቀርተን አይደለም›› ክለቡ•