550099 ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ...

10
ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው፡፡ 62ዓመት .67 መስከረም 2007 .የጋዜጣው ዋጋ 8.00 ብር ለውጭ ሀገር እጥፍ ይሆናል 550099 Ext.47 1283 ይህ ጋዜጣችን የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት፣ ሥርዓትና ባሕል፣ ታሪክና ዜና የሚያትም ስለሆነ ዜና ቤተ ክርስቲያን ተብሎ ተሠየመ፡፡ ፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በፒያሳ አካባቢ በተለምዶ ዘውዲቱና መንበረ መንግሥት ተብለው በሚጠሩ ሕንጻዎች መካከል ባለው ቦታ ሊሠሩ ለታቀዱ ሁለት ዘመ ናዊ ፎቆች ነሐሴ 19 ቀን 2006/ረፋዱ ላይ የመሠረተ ድንጋይ አኑረዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተ ዳዳርና ልማት ድርጅት በራሱ አቅም ለሚያስ ገነባቸው ለእነዚህ መንታ ሕንጻዎች ሥራ የመሠረተ ድንጋይ ማኖር ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ኮንታ ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤ ቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት የበላይ ኃላፊ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደ ረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክር ስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና በሥሩ የሚገኙ አህጉረ ስብከት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓት ርያርኩ በላኩት የጽሑፍ አቤቱታ በሕክምናና ለተጐዱ አብያተ ክርስቲያናት የገንዘብ ርዳታ ማሰባሰብ በሚሉ ምክንያቶች ከሀገር ቤት ወደ ሰማን አሜሪካ የሚሄዱ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ አንቀበልምከሚሉ የስም አብያተ ክርስቲያናት በመወገንና የቅዱስ ሲኖዶስን የው ግዘት ቃል በመጣስ ራሳቸውን ስደተኛው ሲኖዶስእያሉ ከሚጠሩ አካላት ቤተ ክርስቲያን፣ በመገኘት ባረፉበት ቤት ሳይ ቀር ቅስናና ዲቁና በመስጠት የሀገረ ስብከቱንና የምእመናንን ሰላምና አንድነት በማናጋት ችግር መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፊርማ ሐምሌ 17 ቀን 2006/ በቁጥር / /162/06 በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተጻፈው ደብዳቤ ውስጥ - ዘመንና ጊዜ ሐዘንና ትካዜ መቼም መች የማይለውጠው፣ አምላከ ዓለም ዓለምን በባ ሕርይ ዕውቀቱ ፈጥሮ የሚገዛ፣ ኋላም በረቂቅ ሥልጣኑ የሚያሳልፈው ኀያሉ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ያለ ፍጡር ሁሉ ይለወጣል፡፡ ለው ጥና መለወጥም ሕገ ተፈጥሮ የመሆኑን ያኽል ሁል ጊዜ ለሁሉም ተፈላጊ ነው፡፡ እንዲህ ከመሆኑ የተነሣም ነው እንደ መልአከ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ሰባኬ ሕይወት ወመድ ኀኒት የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከላይ ከመሪ ርእሱ ቀጥለን ለመነሻነት የጠቀ ስነውን ቃለ ትምህርት ወሐድሱ ልበክሙ ልቡ ናችሁን በነፍስ ዕውቀት ዐድሱ በማለት በጥዑም ልሳኑ ለዓለም ያስተላለፈው፡፡ ዘመን አልፎ ዘመን ሲመጣ በዘመናት የሚመ ላለሰው ፍጥረት ሁሉ እያረጀ ስለሚሔድ እን ደገና ዐዲስ ሆኖ መገኘት ተገቢው ይሆናል፡፡ ደገኛው ሐዋርያ ከላይ የተጠቀሰውን ቃል አን ብቦ፣ ተርጒሞና አራቆ እንዳለው የሰዎች ልብ መታደስ ሲባል፡- ይህን ኃላፊ ዓለም ብቻ ልብ ውልቅ እስኪል አለመውደድ፣ እግዚአብሔር የሚወደውን አስቦ መልካሙን መሥራት፣ ሐሰትና ሸፍጡን ትቶ እውነቱን፣ ሐቁን መር ምሮ መመስከር፣ አለማወቅን፣ በነፍስ ዕውቀት መለወጥ፣ ሰቅለ በእንቲኣነ ወበመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ ጽንዕነ ቤዛነ - ስለ እኛ ተሰቀለ፥ በመስቀሉም ጽናችን፥ ቤዛችን፥ ድኅነታችን ተደረገልን» (ሃይ. አበው እልመስጦ አግያ (41) 1ጴጥ. 224) መስቀል የሚለው ጥሬ ቃል «ሰቀለ» ከሚ ለው ግዕዛዊ ግሥ የወጣ ዘር ሲሆን ትርጕሙም መስቀያ፥ ማንሻ ማለት ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰ ቀለበት አራት ክንፍ ያለው ዕንጨትም ስሙ «ሐዋርያ መስቀል»«መጾር መስቀል» ይባላል። ወደ ገጽ 4 ዞሯል ወደ ገጽ 4 ዞሯል ወሐድሱ ልበክሙ= ልባችሁንም ዐድሱሮሜ.12.2 ወደ ገጽ 5 ዞሯል ወደ ገጽ 8 ዞሯል ወደ ገጽ 7 ዞሯል ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ የደብሩን ሰፊ የይዞታ ቦታ በሕጋዊ መንገድ በባለቤትነት በማስከበራቸውና የጥፋት ምሽግ ማለት የሌባ ዋሻ፣ የቀማኛ መናገሻ የነበረውን ጫካ አስመንጥረው ቦታው የደብሩ አስተዳዳሪ የልማት አርበኛ ተብለው አውቶሞቢል ተሸለሙ፡፡ ከደንነት ወደ ለምነት ተለውጦ ዘርፈ ብዙ የሆኑ የልማት ተግባራት እንዲከናወኑበት በማድረግ የደብሩን ገቢ በማሳደጋቸውና መልካም አስተዳደርን በማስፈናቸው የደብሩ ካህናትና ሠራተኞች የሽልማት ኮሚቴ አቋ ቋመው ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ጭምር በማስተባበርና ወርሐዊ ደመወዛቸውን በሙሉ በማዋጣት ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን የሚያከ ናውኑበት አውቶሞቢል መኪና ገዝተው ሸልመዋቸዋል፡፡ ቅዱስነታቸው የመሠረተ ድንጋዩን ባኖሩበት ወቅት

Upload: others

Post on 11-Nov-2020

13 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡

መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው፡፡

62ኛ ዓመት ቊ.67 መስከረም 2007 ዓ.ም የጋዜጣው ዋጋ 8.00 ብር ለውጭ ሀገር እጥፍ ይሆናል 550099 Ext.47 1283

ይህ ጋዜጣችን የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን እምነትና ትምህርት፣ ሥርዓትና ባሕል፣ ታሪክና ዜና የሚያትም ስለሆነ ዜና ቤተ ክርስቲያን ተብሎ ተሠየመ፡፡

ብ ፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣

ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ

ሃይማኖት በፒያሳ አካባቢ በተለምዶ ዘውዲቱና

መንበረ መንግሥት ተብለው በሚጠሩ ሕንጻዎች

መካከል ባለው ቦታ ሊሠሩ ለታቀዱ ሁለት ዘመ

ናዊ ፎቆች ነሐሴ 19 ቀን 2006ዓ/ም ረፋዱ ላይ

የመሠረተ ድንጋይ አኑረዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያኒቱ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተ

ዳዳርና ልማት ድርጅት በራሱ አቅም ለሚያስ

ገነባቸው ለእነዚህ መንታ ሕንጻዎች ሥራ የመሠረተ

ድንጋይ ማኖር ሥርዓት በተካሄደበት ወቅት ብፁዕ

አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ

አስኪያጅና የወላይታ ኮንታ ዳውሮ አህጉረ

ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና

ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ፣ የቤ

ቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት

የበላይ ኃላፊ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ የተደ

ረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በ ኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክር

ስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና በሥሩ

የሚገኙ አህጉረ ስብከት ለብፁዕ ወቅዱስ ፓት

ርያርኩ በላኩት የጽሑፍ አቤቱታ በሕክምናና

ለተጐዱ አብያተ ክርስቲያናት የገንዘብ ርዳታ

ማሰባሰብ በሚሉ ምክንያቶች ከሀገር ቤት ወደ

ሰማን አሜሪካ የሚሄዱ አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት

“የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ አንቀበልም” ከሚሉ

የስም አብያተ ክርስቲያናት በመወገንና የቅዱስ

ሲኖዶስን የው ግዘት ቃል በመጣስ ራሳቸውን

“ስደተኛው ሲኖዶስ” እያሉ ከሚጠሩ አካላት

ቤተ ክርስቲያን፣ በመገኘት ባረፉበት ቤት ሳይ

ቀር ቅስናና ዲቁና በመስጠት የሀገረ ስብከቱንና

የምእመናንን ሰላምና አንድነት በማናጋት ችግር

መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡

በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የዋሽንግተን ዲሲና

ካሊፎርኒያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፊርማ

ሐምሌ 17 ቀን 2006ዓ/ም በቁጥር ሀ/ስ/162/06

በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ

ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ

ሃይማኖት በተጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ፡-

ዘመንና ጊዜ ፣ ሐዘንና ትካዜ መቼም መች

የማይለውጠው፣ አምላከ ዓለም ዓለምን በባ

ሕርይ ዕውቀቱ ፈጥሮ የሚገዛ፣ ኋላም በረቂቅ

ሥልጣኑ የሚያሳልፈው ኀያሉ እግዚአብሔር

ብቻ ነው፡፡

በዚህ ዓለም ያለ ፍጡር ሁሉ ይለወጣል፡፡ ለው

ጥና መለወጥም ሕገ ተፈጥሮ የመሆኑን ያኽል

ሁል ጊዜ ለሁሉም ተፈላጊ ነው፡፡

እንዲህ ከመሆኑ የተነሣም ነው እንደ መልአከ

ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ሰባኬ ሕይወት ወመድ

ኀኒት የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ

ከላይ ከመሪ ርእሱ ቀጥለን ለመነሻነት የጠቀ

ስነውን ቃለ ትምህርት ወሐድሱ ልበክሙ ልቡ

ናችሁን በነፍስ ዕውቀት ዐድሱ በማለት በጥዑም

ልሳኑ ለዓለም ያስተላለፈው፡፡

ዘመን አልፎ ዘመን ሲመጣ በዘመናት የሚመ

ላለሰው ፍጥረት ሁሉ እያረጀ ስለሚሔድ እን

ደገና ዐዲስ ሆኖ መገኘት ተገቢው ይሆናል፡፡

ደገኛው ሐዋርያ ከላይ የተጠቀሰውን ቃል አን

ብቦ፣ ተርጒሞና አራቆ እንዳለው የሰዎች ልብ

መታደስ ሲባል፡-

ይህን ኃላፊ ዓለም ብቻ ልብ ውልቅ እስኪል

አለመውደድ፣

እግዚአብሔር የሚወደውን አስቦ መልካሙን መሥራት፣

ሐሰትና ሸፍጡን ትቶ እውነቱን፣ ሐቁን መር

ምሮ መመስከር፣

አለማወቅን፣ በነፍስ ዕውቀት መለወጥ፣

ተ ሰቅለ በእንቲኣነ ወበመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ

ጽንዕነ ቤዛነ - ስለ እኛ ተሰቀለ፥ በመስቀሉም

ጽናችን፥ ቤዛችን፥ ድኅነታችን ተደረገልን» (ሃይ.

አበው እልመስጦ አግያ (4፥1) 1ጴጥ. 2፥24)

መስቀል የሚለው ጥሬ ቃል «ሰቀለ» ከሚ

ለው ግዕዛዊ ግሥ የወጣ ዘር ሲሆን ትርጕሙም

መስቀያ፥ ማንሻ ማለት ነው። ጌታችን መድኃኒታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን የተሰ

ቀለበት አራት ክንፍ ያለው ዕንጨትም ስሙ

«ሐዋርያ መስቀል»፥ «መጾር መስቀል» ይባላል።

ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ወደ ገጽ 4 ዞሯል

ወሐድሱ ልበክሙ= ልባችሁንም ዐድሱሮሜ.12.2

ወደ ገጽ 5 ዞሯል

ወደ ገጽ 8 ዞሯል ወደ ገጽ 7 ዞሯል

የ ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ

ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን

ጽጌ አበበ የደብሩን ሰፊ የይዞታ ቦታ በሕጋዊ

መንገድ በባለቤትነት በማስከበራቸውና የጥፋት

ምሽግ ማለት የሌባ ዋሻ፣ የቀማኛ መናገሻ

የነበረውን ጫካ አስመንጥረው ቦታው

የደብሩ አስተዳዳሪ የልማት አርበኛ ተብለው አውቶሞቢል ተሸለሙ፡፡ ከደንነት ወደ ለምነት ተለውጦ ዘርፈ ብዙ

የሆኑ የልማት ተግባራት እንዲከናወኑበት

በማድረግ የደብሩን ገቢ በማሳደጋቸውና

መልካም አስተዳደርን በማስፈናቸው የደብሩ

ካህናትና ሠራተኞች የሽልማት ኮሚቴ አቋ

ቋመው ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ጭምር

በማስተባበርና ወርሐዊ ደመወዛቸውን በሙሉ

በማዋጣት ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን የሚያከ

ናውኑበት አውቶሞቢል መኪና ገዝተው

ሸልመዋቸዋል፡፡

ቅዱስነታቸው የመሠረተ ድንጋዩን ባኖሩበት ወቅት

Page 2: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 2

ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ

እየታተመ በየወሩ ይወጣል፡፡

ዋና አዘጋጅ፡- መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ

ም/አዘጋጅ፡- ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር

መስከረም 2007 ዓ.ም

የ ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳዳርና ልማት ድርጅት ባለፈው ነሐሴ ወር ፒያሳ በሚገኙ ዘውዱቱና

መንበረ መንግሥት ሕንጻዎች መካከል ባለው ቦታ ሊያሠራቸው ላቀዳቸው መንታ ሕንጻዎች በቅዱስ

ፓትርያርኩ መሠረት እንዲጣል ማድረጉ ድርጅቱ ከአስተዳደር ሥራው በተጨማሪ በተጨባጭ ወደ

ልማት ተግባር መሸጋገሩን ፍንጭ የሚያሳይ ብሩህ ምልክት ነው፡፡

በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጀት በቸርችል ጐዳና እየተገነባ ያለው ባለዘጠኝ ፎቅ ዘመናዊ ሕንጻም

የግንባታውን ሐሳብ ከማመንጨት ጀምሮ የግንባታው ሂደት እየተመራ ያለው በቤቶችና ሕንጻዎች

አስተዳደርና ልማት ድርጅት በመሆኑ ለዚህ በጎ ሥራቸው የድርጅቱ አመራሮችና ሐሳብ አፍላቂዎች

ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ከሁሉ በላይ እነዚህ የልማት እንቅስቃሴዎች መንግሥት የተወረሱ ቤቶችን

ለቤተ ክርስቲያንዋ መመለስ ከጀመረበት ካለፉት ሃያ ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወኑ

በመሆናቸው ድርጅቱ በተግባር ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ እነዚህ

አዳዲስ የልማት ጅምሮችን ስናይ በድርጅቱ በኩል በቀጣይነት ሊተገበሩ የታቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች

በሥራ ተተርጒመው ልናይ እንችላልን የሚል የተስፋ ጭላንጭል እንድናይ አድርጎናል፡፡

የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳዳደና ልማት ድርጅት ጠንካራ ጐን ሆኖ ያየነው ሌላው ተግባር በቅርቡ

በደርግ መንግሥት በግፍ ተወርሰው የነበሩ ሕንጻዎችን ለማስመለስ በተደረገው ጥረት የላቀ አስተዋጽኦ

ላበረከቱ ሦስት ግለሰቦች ዕውቅና የሰጠበት አካሄድ ነው፡፡ ጠንካራ ጐኑ ለሦስቱ ሰዎች ሽልማት መስጠቱ

አይደለም፡፡ የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት

በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዳሉት የሽልማቱ ዋና ዓላማ ተሸላሚዎቹ ባገኙት ሽልማት ይጠቀማሉ

ማለት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችን የእነዚህን አባቶች ውለታ ያልረሳች መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡

የዚህ ዓይነቱ አሠራር ተሸላሚዎችን ከማስደሰት ባለፈ አሁን በሥራ ያሉና ለወደፊቱ የሚመጡ

አዳዲስ ሠራተኞችን በሥራቸው ይበልጥ እንዲተጉ ስለሚያግዛቸው ጥቅሙ መንታ ነው፡፡ በዚህ

አጋጣሚ የእነዚህን ግንባር ቀደም አባቶችን ውለታ በማስታወስ ለሽልማት እንዲበቁና ስማቸው

በክብር እንዲወሳ ያደረጉ የድርጅቱ አመራሮች አርቆ አስተዋይነታቸውን ያሳያል እንላለን፡፡

ድርጅቱ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሠራሩን በማሻሻል ላይ ቢገኝም ሥር

የሰደዱና እርምት የሚያሻቸው ደካማ ጐኖችም አሉት፡፡ ለአብነት ያህል ድርጅቱ ሕንጻዎችና ቤቶችን

በማደስና በመንከባከብ በኩል እንደዚሁም በሥሩ ያሉ ለመኖሪያና ለንግድ የሚሆኑ ቤቶችን የሚያከ

ራይበት አሠራር በዋናነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ ድርጅቱ ከኪራይ ፍትሐዊነት ጋር በተያያዘ ያሉበትን

ድክመቶች ለሌላ ጊዜ እናቆየውና ለአሁኑ በጨረፍታም ቢሆን የእድሳቱን ጉዳይ እናንሣ፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በ1994ዓ/ም በመስከረም፣ በጥቅምትና በታኅሣሥ እትሞቹ ድርጅቱ

በዚህ በኩል የነበረበትን በሙስና የታጠረ ችግር በማስረጃ በማስደገፍ ተከታታይ ምርመራዊ ዘገባዎችን

ማቅረብዋ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ዘገባዎች መነሻነት በተደረገው ማጣራት በወቅቱ መሻሻሎች ታይተው

የነበረ ቢሆንም አሁን ድረስ ከእድሳት ጋር የተያያዙ ችግሮች በተደጋጋሚ ሲስተዋሉ እናያለን፡፡

ብዙዎች ሕንጻዎችና መኖሪያ ቤቶች (የንግድ ቤቶቹ በተከራዮቹ በየጊዜው ስለሚታደሱ ነው)

ተገቢው እድሳትና እንክብካቤ ስለማይደረግላቸው እናት አባቱ እንደሞቱበት እጓለ ማውታ ሕጻን

ተጐሳቁለውና ለተለያዩ ብልሽቶች ተዳርገው ይታያሉ፡፡ በአንዳንድ ሕንጻዎች ላይ ተደረጉ የሚባሉ

“እድሳቶችም” ተከስተው የነበሩ ብልሽቶችን ያልፈቱ፣ የነበሩ ችግሮችን ያባባሱ፣ ለይስሙላ የተከናወኑ

“ሙስና ሙስና የሚሸት” አሠራር የተስተዋለባቸው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ያሰሙባቸውና እያሰሙባቸው

ያሉ ናቸው፡፡ የአንዳንድ ሕንጻዎች አሳንሱሮች /ሊፍቶች/ (ለምሳሌ የመንበረ መንግሥት) በብልሽት

ምክንያት ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው ሳያንስ በተቆጣጣሪ አካል እጦት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ

በመሆናቸው በሕንጻዎቹ መወጣጫ ደረጃዎች ለመውጣትና ለመውረድ የፈለገ ሁሉ የግድ አፍን

ጫውን ሸፍኖ መሄድ አለበት፡፡

ነዋሪዎችን አስተባብሮና አደራጅቶ የሕንጻዎችን ድህንነት ማስጠበቅ እየተቻለ በየሕንጻዎች

የሚገኙ የጋራ መጠቀሚያ አካባቢዎች /መኪና መቆሚያ፣ ልብስ ማስጫ ወዘተ/ የቆሻሻ መጣያ እስከ

ሚመስሉ ድረስ ይዞታቸው ተለውጦ ይታያል፡፡ የፍሳሽ ማስወገጃዎችና የዝናም ማውረጃ ቱቦዎች

ጉዳይማ ባይነሳ ይሻላል፡፡ ሌላው ከቤቶቹ ደህንነት አንጻር ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ሆኖ ያገኘነው የቤት

አመልካቾችን አፍ ለማስያዝ ወይም የባለሥልጣናትን ቊጣ ለማስታገስ በሚመስል መልኩ አንዱን

ቤት ለሁለትና ለሦስት ሸንሽኖ በመሰጠቱ በቤቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ነው፡፡ በዚህ የተነሣ

የምግብ ማብሰያውን ወደ መኖሪያ ቤትነት፣ የእንግዳ ማረፊያውን /ሳሎንን/ ወደ ማዕድ ቤት የተለወጡበት

በነበረው ቤት ውስጥ ከሕግ ውጭ በሆነ መንግድ ተጨማሪ ክፍሎች በመሥራት ሁኔታ እንዳለ

ታዝበናል፡፡ በተለይ ሳሎንን ለምግብ ማብሰያነት መጠቀም የቤቱን መልክና ቅርጽ ከማበላሸት አልፎ

የሕንጻውን ውሳጣዊ ይዘት ስለሚጐዳ የቤቱን የአገልግሎት ዕድሜ ሊያሳጥር እንደሚችል

ከባለሙያዎች ጠይቀን ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ችለናል፡፡

እዚህ ላይ ከእድሳት ጋር በተያየዘ ለተከሰቱና ለሚከሰቱ ችግሮች ቤቶችን ከሚያስተዳድረው

ድርጅት በተጨማሪ በጀት የሚፈቅደው አካልና ጉዳዩን በበላይነት ይመሩት የነበሩ የምህንድስና

ባለሙያዎች ጭምር ኃላፊነት ያለባቸው ይመስለናል፡፡ በጥቅሉ ቤተ ክርስቲያናችን የዛሬ ብቻ ሳይሆኑ የነገ

ተስፋዎቿ የሆኑትን ሕንጻዎች በአግባቡ ለመጠቀም ካስፈለገ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንዳሉት

“ሕንጻዎችን አድሰንና ተንከባክበን” መያዝ አለብን፡፡ የሕንጻዎቹ የእድሳት ወጪን ለማቃለልና

ዘለቄታዊ መፍትሔ ለማግኘት ከተፈለገ ደግሞ መንግሥት በሀገሪቱ የሚሠሩትን መንገዶች ለመጠገን

ሲባል የመንገድ ልማት ፈንድ እንዳቋቋመ ሁሉ በሁሉም ተከራዮች ላይ ለእድሳት በሚል የተወሰነ መጠን

ጨምሮ መያዝና ነዋሪዎች ቤቶቻቸውን በሥርዓት የሚይዙበት የተጠና ስልት ማበጀት ያስፈልጋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ነዋሪዎች የተከራይቱን ቤት በሚገባ መያዛቸውንና አለመያዛቸውን በተወሰኑ

ወራቶች እየሄዱ ቊጥጥር ማድረግ፣ ተከራዮች የተከራዩትን ቤት ለቀው ሲሄዱ ጥብቅ ቊጥጥር

አድርጎ መረከብ፣ እስከ አሁን በአግባቡ እየተሠራበት ያልሆነ ነገር ግን ለቀጣይ መዘንጋት የሌለበት

ጉዳይ ነው እንላለን፡፡

ከ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በሆነ አሠራር

በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ሐመረ ኖኅ

ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ

በመልአከ ኪዳን ታደሰ ሲሳይ በማይመለከታቸው

አካላት ተወስዶ የነበረው ከኃላፊነት የመሻር

እርምጃ ውድቅ ሆኖ መልአከ ኪዳን ታደሰ

ሲሳይ ወደ ቀድሞ ቦታቸውና ክብራቸው እንዲመለሱ

መደረጉን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ

ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው

ሀገረ ስበከት ጽ/ቤት ለሚመለከታቸው ሁሉ

በሚል እ.አ.አ ጁላይ 14 20014 ባሰራጨው ደብዳቤ

አስታውቋል፡፡

በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሀገረ ስበከቱ ሊቀ ጳጳስ

ፊርማና ማኅተም የተሰራጨው ይኸው ደብዳቤ

በመሠረቱ አንድን ካህን ከሥልጣነ ክህነቱም

ሆነ ከደረጃው የመሻር ብቸኛ መብት ያለው የሀገረ

ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና ከቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑ

እየታወቀ የማይመለከታቸው አካላት የዚህ ዓይነት

እርምጃ መውሰዳቸው ሕገ ወጥ አመራርና ሕገ

ቤተ ክርስቲያንን የሚቃረን በመሆኑ ጥቂት ግለሰቦች

ተነሳሽነት መልአከ ኪዳን ታደሰ ሲሳይን ለመሻር

የተወሰደው እርምጃ ሕጋዊነት የሌለው መሆኑ

ጠቅሷል፡፡

Page 3: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 3 መስከረም 2007 ዓ.ም

ከ ሳቴ ብርሃን ተሰማ በመዝገበ ቃላት መጽሐ

ፋቸው “ወጣት” የሚለውን ቃል ሲተነትኑ

“ገና የሚያድግና የሚረዝም ልጅ፣ ከአሥራ

አምስት ዓመት እስከ ሠላሳ ዓመት ድረስ ያለ

ልጅ ወጣት ይባላል” ብለው በዕድሜም ጭምር

ሲወስኑት “ጎለመሰ” የሚለው ደግሞ “በአእምሮ፣

በትምህርት፣ በዕውቀት አደገ” በማለት ገልጸ

ውታል፡፡ (የአማርኛ መዝገበ ቃላት፡ 1951፡ ገጽ

960 እና 2034)

አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ግን “ወሬዛ”

የሚለው አቻ የግእዝ ቃል ሲተረጉሙ “ጎልማሳ፣

ጎበዝ፣ ለጋ ወጣት፣ ከአሥራ አምስተ ዓመት

በላይ የሆነ…” ካሉ በኋላ “ውርዙት” ን ደግሞ

“ሕፃንነት፣ ጎልማሳነት፣ ጉብዝና፣ ዐፍላ” በማ

ለት የዕድሜ ገደብ ሳያደርጉ ከአሥራ አምስት

እስከ ጉልምስና ያለው የዕድሜ ክልል በማካ

ተት ተርጉመውታል፡፡ (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ፡

ገጽ.403-404)

ከዚህ መረዳት የሚቻለው ከአሥራ አምስት

ዕድሜ ጀምሮ እስከ ጎልማሳነት የሚገኝ የዕድሜ

ክልል የወጣትነት ዘመን ሲባል በዚህ የዕድሜ

ክልል የሚፈጸሙ ድርጊቶች ሁሉ ደግሞ የወጣ

ትነት ታሪክ፣ የወጣትነት ተሳትፎ፣ የወጣትነት

አስተዋጽኦ… ተብሎ ሊጠቀስ እንደሚችል

ነው፡፡

የወጣትነት ዘመን (ዕድሜ) መንፈሳዊም

ሆነ ዘመናዊ ትምህርት ተምረው ዕውቀት የሚገ

በዩበት፣ የቀድሙ አባቶችን ታሪክ የሚያጠኑበት፣

ሀገራዊ ማንነታቸውን የሚለዩበት፣ በሥነ ቋን

ቋና በፍልስፍና የሚመራመሩበት፣ በኪነ ጥበብ

የሚካኑበት፣ በሥነ ሥልጣኔ የሚራቀቁበት በአጠ

ቃላይ በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ ዘርፍ ትው

ልድ በሚታነጽበት የዕድሜ አካል ነው ማለት

ይቻላል፡፡

በዚህ የወጣትነት ዘመን የቀድሞ አባቶች

ያከናወኗቸውን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ሀገራዊ

ታሪኮች በጥንቃቄ አጥንቶ ክብር በመስጠት ይኸው

ታሪክ እንዳይጠፋ ወይ እንዳይበረዝ ነቅቶ የሚጠ

ብቅበት ብቻ ሳይሆን በትናንትናው ታሪክ መሠ

ረትነት በወቅቱ የሚገኙትን ነባራዊ ሁነታዎችን

እንደግብአት ተጠቅሞ ወገን አኩሪ የሆነ የራስን

(የትውልድን) ታሪክ የሚሠራበት፣ ሀገር የሚገ

ነባበት፣ ማኅበረሰብ የሚገለገልበት፣ የሀገር ሉዓላ

ዊነት የሚረጋገጥበት፣ የታሪክ ቅብብሎሽ ገሀድ

የሚሆንበት እጅግ ወሳኝ የሆነ የዕድሜ ክልል

ነው፡፡

ይህ እውነት ለመሆኑ መዝገበ ቃላት ሳያስ

ፈልገው የሀገራችንና የቤተ ክርስቲያናችን ጥንታዊ

ታሪክ፣ እንዲሁም ይህንኑ ያልተቋረጠ ታሪክ

የወለዳቸው የታሪክ ማኅተሞቻችን የሆኑ ቅርሶ

ቻችንን መገንዘብ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡ በሀገ

ራችን የሚገኙ የታሪክ ምዕራፎች በጥንቃቄ የመረ

መርን እንደሆነ በዚህ የዕድሜ ክልል (በወ

ጣትነት) የተሰሩ ሥራዎች ለጠቅላላ ብሔራዊ

ታሪካችን ምሰሶዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይ

ሆንም፡፡

እዚህ ላይ በዋናነት ለመግለጽ የተፈለገው

ይኸው የዕድሜ ክልል በአግባቡ ከተጠቀምንበት

መንፈሳዊ ሆነ ማኅበራዊ (ሀገራዊ) ሥራዎች

በተሳካ ሁኔታ ለመሥራት አስኳል የሆነ የዕድሜ

ደረጃ መሆኑን ልብ ማለት እንደሚያስፈልግ ነው፡፡

ስለሆነም ይህንን የዕድሜ ክልል አለአግባብ

እንዳይባክንና አንዴ ካለፈም ልንተካው ስለማ

ንችል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባን የእግዚ

አብሔር ቃል ሁሌም ቢሆን ይመክረናል፣ ያስተ

ምረናል፡፡

“አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥

በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በል

ብህም መንገድ ዓይኖችህም በሚያዩት ሂድ ዳሩ

ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ

እንዲያመጣህ እወቅ”መጽ. መክ. 11፡9

“የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት

ፈጣሪህን አስብ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም

ዓመታት ሳይደርሱ፣ ፀሐይና ብርሃን ጨረቃና

ከዋክብትም ሳይጨልሙ፥ ደመናትም ከዝናብ

በኋላ ሳይመለሱ… ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ

እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ”መጽ.

መክ. 12፡1-7 እንዲል

የመስቀል በዓልና የወጣቶች ሚና...

ሀገራዊ ገጽታው

ሀገራችን ኢትዮጵያ የክርስትናው የምስራች

በኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ጌታ ባረገበት ዓመት

የሰማች ቢሆንም ምስጢራትን መፈጸም የሚያ

ስችለውን ሙሉ ክህነት (ጵጵስና) ገንዘብ አድርጋ

በብሔራዊ ደረጃ የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሆኑ

የተረጋገጠ ግን በ4ኛው ክ/ዘመን እንደሆነ ግልጽ

ነው፡፡ ከዚህ ታሪካዊ እውነታ የተነሳ ክርስትና

በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ ሲደረግ የመስቀል ደመራ

በዓልም አብሮ በብሔራዊ ደረጃ በአደባባይ የሚ

ፈጸም ታላቅ የክርስትና ሃይማኖት መገለጫ የሆነ

በዓል ነው፡፡

የመስቀል በዓል አከባበር ዘመን እየተሻገረ

ሲመጣ በዓሉን የወለዳቸው ልዩ ልዩ ባሕላዊ

ሥነ ሥርዓቶች በመኖራቸው በተለይ በወጣቱ ዘንድ

እጅግ የሚናፈቅና የሚወደድ በዓል እንዲሆን

አድርጎታል፡፡ ምክንያቱም ወጣቶች የመስቀል

በዓል ምክንያት በማድረግ በአንድነትና በሕብረት

እየተገናኙ ደስታቸውን የሚገልጹበት፣ ማኅበራዊ

መስተጋብራቸውን ይበልጥ የሚያጸኑበት፣ ቤተሰባዊ

ፍቅራቸውን አጠናክረው በአንድነት የሚሰባ

ሰቡበት፣ ለሥራ ከራቁበት ቦታ ወደ ትውልድ

ቦታቸው ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋራ የሚገ

ናኙበት... ወዘተ ጥንታዊ ሥርዓትን የተከተለ

በዓል በመሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ከላይ በጥቂቱ የተገለ

ጹትንና ብዙ ያልተጠቀሱትን የመስቀል በዓልን

ምክንያት በማድረግ የሚከናወኑ ማኅበራዊ እሴ

ቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ በዋናነት የሚያስተባብሩ

ወጣቶች ናቸውና ነው፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል አከባበርም እንዲሁ

የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ሚና ያላቸው ወጣቶች

ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ለደመራው የሚያገለግል

እንጨት ከየቦታው በመሰብሰብና ደመራውን

በመትከል፣ ሕብረተሰቡን በመቀስቀስና በመስቀል

በዓል አከባበር በሚችለው ሁሉ ተሳታፊ እንዲሆን

በማድረግ፣ ችቦ በማዘጋጀት እና ትውፊቱ ጠብ

ቀው በማብራት፣ የደመራውን አከባበር ሥነ

ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ

የፀጥታ ሥርዓትን በማክበርና በማስከበር እንዲሁም

የመስቀል ደመራ ቦታዎችን በማጽዳት በኩል

ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱት ወጣቶች

ናቸው፡፡ ይህ የወጣቶች እንቅስቃሴ በመላ ሀገሪቱ

በገጠርም ይሁን በከተማ የሚፈጸም ሲሆን እንደየአ

ከባቢው ሁኔታ መለስተኛ የሆነ የአፈጻጸም ዘይቤ

ልዩነት ሊኖር ቢችልም ይህንን በዓል የማይከ

በርበት አካባቢ ግን የለም ማለት ይቻላል፡፡

በወጣቶች መሪነት በመላ ሀገራችን የሚተገ

በረው የችቦ ማብራት ሥነ ሥርዓትም ቢሆን ይህ

የመሰቅል በዓላችን የወለደው ክርስቲያናዊ ባህል

ሲሆን ክርስቲያናዊ ትርጉሙም የመስቀልን ብርሃ

ንነት ለመግለጽ ነው፡፡ በጨለማ ወይም ለዓይን

ያዝ ሲያደርግ ችቦው መለኮሱ ደግሞ በጨለማ

ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ አማናዊ ብርሃን በመስቀል

አማካኝነት ማግኘቱን ለማመሳጠር የተደረገ የአ

በው አስተማሪ ባህል መሆኑ ልብ ማለት ያስፈ

ልጋል፡፡

ስለሆነም በገጠርም ይሁን በከተማ በዚህ

ተመሳሳይነት ባለው የመስቀል ደመራ በዓል ወጣ

ቶችን በአንድነት ተሰባስበው በከፍተኛ ሁኔታ

ያደምቁታል፤ ያከብሩታል፣ እንዲከበርም የበኩላ

ቸውን ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡

የመስቀል በዓል ድምቀትና የሰ/ት/ቤቶች ሚና…

ሀገር አቀፋዊ እይታ

“ሰንበት ት/ቤት”፡- ቤተ ክርስቲያናችን በሕግ

በሥርዓት በቃለ ዓዋዲ የመሠረተችው የሕፃናትና

የወጣቶች ተቋም ነው፡፡ ሰ/ት/ቤት ሕፃናትና ወጣ

ቶች የቤተ ክርስቲያኗን አጠቃላይ ትምህርተ

ሃይማኖት ማለትም ዶግማና ቀኖና፣ ሥርዓትና

ሕግ፣ ታሪክና ባህል… የሚማሩበትና የአባቶ

ቻቸው አደራ የሚረከቡበት ተቋም ነው፡፡

ወጣቶች በሰ/ት/ቤት ውስጥ በመሰባሰብ

በትምህርትና በመዝሙር የሚሰለጥኑበትና የአባ

ቶቻቸውን ፈለግ ተከትለው የሚያገለግሉበት ሕይ

ወት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም የሰ/ት/ቤት ወጣቶች

መዘምራን የቤተ ክርስቲያን የአደባባይና የንግስ

በዓላት በማድመቅ በኩል ከፍተኛ ሚና እየተ

ጫወቱ መሆኑን በሁሉም ዘንድ የሚታወቀ

ነው፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በሁሉም ሰ/ት/ቤቶች

ዘንድ በከፍተኛ ናፍቆትና ፍቅር እየተጠበቀ

በየዓመቱ የሚከበር በዓል ነው፡፡ ለዚህ በዓል

ድምቀትም ሰ/ት/ቤቶች ቢያንስ ከአንድ ወር

ያላነሰ ጊዜ ወስደው ሁለገብ ዝግጅት ያደርጋሉ፤

ይህ ማለትም የመስቀል በዓል ሊገልጹ የሚችሉ

የቅዱስ ያሬድ መዝሙሮች በመለየት፣ ይህንን

ጥንታዊ የክርስትና በዓላችን ሊገልጹ የሚችሉ

ልዩ ልዩ ትያትሮችና ትርኢቶች በመድረስ…

ሁሉንም አባላት እንዲያጠኑትና በተግባርም

እንዲለማመዱት በማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት

ያደርጋሉ፡፡

የመስቀል ደመራ በዓል በሚከበርበት ዕለትም

በየአጥቢያቸው በመገኘት የአገልግሎት ዩኒፎር

ማቸውን ለብሰው በፍጹም መንፈሳዊ ሥነ ሥር

ዓት መዝሙር እየዘመሩ ደመራ ወደተተከለበት

ቦታ ሲጓዙ በዓሉ በመንፈሳዊ የአገልግሎት ድባብ

እንዲታጀብ በማድረግ የበዓሉ ጅማሬ ያበስራሉ፡፡

በበዓሉ ቦታ ተገኝተው በተፈቀደላቸው የጊዜ

መጠን አባቶቻቸው ሊቃውንትን ተከትለው ያሬዳዊ

ዝማሬ (ወረብ) በማቅረብና በመዝሙር የታጀቡ

ልዩ ልዩ ሀገራዊና መንፈሳዊ እሴት የተላበሱ ትር

ኢቶችንና ድራማዎችን በማሳየት በዓሉ እንዲ

ደምቅ የድርሻቸውን ይወጣሉ፡፡ በዚህም የመስቀል

በዓል ድምቀት የካህናት፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስ

ቲያን፣ የሰ/ት/ቤት ወጣቶች እና የምዕመናን አገል

ግሎት አጠቃላይ ድምር ውጤት ነው ያሰኙ

ታል ማለት ነው፡፡

ይህ የሰ/ት/ቤቶች ዓመታዊ ከፍተኛ አገል

ግሎት በመላ ሀገሪቱ የሚተገበር ተልዕኮ ሲሆን

በተለይ የአኅጉረ ስብከት መቀመጫ የሆኑ

ከተሞች ላይ ግን ሰ/ት/ቤቶች በጋራ ሆነው የሚፈ

ጽሙት አገልግሎት በመሆኑ በሁሉም መመዘኛ

እጅግ ያማረና የሠመረ መሆኑ በዓሉ ከሚከበርበት

ስፍራ ተገኝቶ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

የወጣቶች ሕብረ ቀለማዊ አገልግሎት

በመስቀል አደባባይ

የመስቀል ደመራ በዓል በተለይ በመስቀል

አደባባይ የሀገራችን ርዕሰ ብሔር፣ ብፁዕ ወቅዱስ

ፓትርያርክ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣

ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አምባ

ሳደሮችና በርካታ ቱሪስቶች እንዲሁም በርካታ

ቁጥር ያላቸው ምዕመናን በተገኙበት የሚከበር

ታላቅ በዓል ስለሆነ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድ

ባራት ሰ/ት/ቤቶችም ይህንን መሠረት በማድረግ

ለአንድ ወር ያህል ከፍተኛ ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡

ከሁሉም ሰ/ት/ቤቶች ተውጣጥተው አምስት

አቅጣጫዎች ተለይተው ሁሉንም ሊያማክሉ

የሚችሉ ቦታዎች ተመርጠው ማለትም የምሥራቅ

ክፍለ ከተማ በታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም

ገዳም፣ የምዕራብ ክፍለ ከተማ በደብረ ገሊላ

ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል፣ የሰሜንክፍለ ከተማ

በምስካየ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም፣ የደቡቡ

ክፍለ ከተማ በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ

ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ

ከተማ በአቃቂ ስታድየም በመገኘትየመዝሙርና

የትርኢት ጥናትና ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ የመዝሙር

ጥናቱ በተቻለ መጠን አምስቱንም ክፍለ ከተሞች

በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም አንዱ ክፍለ ከተማ

ቢያንስ ሁለት ወይም ሦስት የሀገራችን ቋንቋዎች

እንዲያጠኑና እንዲዘምሩ ይደረጋል፡፡

መዝሙሩን በሚገባ ማጥናታቸውን ሲረጋገጥ

በተመደበላቸው የመስክ ስፍራ ተገኝተው የትርኢት

ሥራውን ያጠናሉ፡፡ እዚህ ላይ መግለጽ የም

ፈልገው ነገር ዘመኑ ዘመነ ክረምት እንደመሆኑ

መጠን በአብዛኛው ጊዜ ዝናብ ይዘንብባቸዋል፤

ካልሆነ ደግሞ ጭቃ ሁሌም ቢሆን አይጠፋም፡፡

ይሁን እንጂ ወጣቶች ከላይ እንደተገለጸው

ይህንን በዓል እጅግ በናፍቆት ስለሚጠብቁት

“እንዴት አድርገን የመስቀል በዓላችንን እናድምቀው”

በማለት ለበዓሉ ድምቀት ይጨነቃሉ እንጂ

አንድም ጊዜ ስለስለዝናቡ ሆነ ስለጭቃው

አስበው አያውቁም፡፡

በዚህ መልኩ ከተዘጋጁ በኋላ መስከረም 16

ቀን ከጥዋቱ ጀምረው የመጨረሻ ዝግጅታቸውን

ካጠናቀቁ በኋላ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ሲሆን በአ

ምስቱ የጥናት ቦታዎች የሚገኙ መዝሙርና ትርኢት

አቅራቢዎችን ጨምሮ የሁሉም አድባራትና

ገዳማት ሰንበት ት/ቤት መዘምራን በተለያዩ

ሕበረ ቀለማት የተዋቡ ዩኒፎርማቸውን ለብሰው

በሥርዓት ተሰልፈው በልዩ የመዝሙር አገል

ግሎት በሁሉም የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ወደ

መስቀል አደባባይ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ጊዜ

የሚፈጥሩት ሕብረ ቀለማዊ አገልግሎት ከልብ

ለሚገነዘብ ሰው የበዓሉን ፍጹም ሃይማኖታዊነት፣

ታላቅነትና ጥንታዊነት ብቻም ሳይሆን ይህ የመ

ስቀል በዓላችን በሀገራችንና በሕዝባችን ዘንድ

ምን ያህል ሥር የሰደደና ከፍተኛ ስፍራ እንዳለው

የሚያስረዳና የሚያረጋግጥ ማኅተም ሆኖ ያገ

ኘዋል፡፡

መሰቀል አደባባይ ከገቡ በኋላም በተመደ

በላቸው ቦታ በመቆም እጅግ ማራኪ በሆነ ዘይቤ

በመዘመር በዓሉን ያደምቃሉ፡፡ የደመራ የጸሎት

መርሐ ግብር እስኪፈጸም ድረስ በሰልፍ ከቆሙ

በኋላ ለአንድ ወር የተዘጋጁበትን አገልግሎት

በወጣላቸው መርሐ ግብር መሠረት አቅርበው

የመስቀል በዓሉ የተሟላ ድምቀት ይሰጡታል፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ይኸው የወጣቶች ሕብረ

ቀለማዊ አገልግሎት ጥንታዊና ታሪካዊ የሆነ

የመስቀል በዓላችን በዩኔስኮ ለመመዝገብ የራሱ

የሆነ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተ በወቅቱ በተደ

ጋጋሚ ከቀረበው ዶክመንተሪ ፊልምና ከተሰጠው

መግለጫ እንዲሁም ይኸው የወጣቶች አገል

ግሎት ቦታው ድረስ ተገኝቶ በመመልከት መረዳት

ይቻላል፡፡

በመስቀል በዓል የሚቀርቡ ትርኢቶችና

ይዞታቸው

ከላይ እንደተገለጸው በተለይ የአዲስ አበባ

ገዳማትና አድባራት ሰንበት ት/ቤቶች በመስቀል

አደባባይ በመገኘት በየዓመቱ የመስቀል ሊገልጹ

የሚችሉ በርካታ ትርኢቶች አቅርበዋል፤ እያቀ

ረቡም ይገኛሉ፡፡ ትርኢቶቹ በየዓመቱ የሚቀርቡት

አዳዲስ ሲሆኑ ዘመኑን ሊዋጁ የሚችሉት ወቅ

ታዊ ሁኔታን መልእክቶች ማዕከል ያደረጉ ሆነው

የሀገራችን መልካም ገጽታና የቤተ ክርስቲያናችን

ትውፊት እንዲገልጹ ታስበው የሚዘጋጁ ናቸው፡፡

ለምሳሌ፤

ኢትዮጵያን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያና መጽሐፍ

ቅዱስ (ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር

ትዘረጋለች /መዝ.68፡31/) እንዲል፣ ኢትዮጵያና

ክርስትና፣ ኢትዮጵያና ዓባይ፣ ኢትዮጵያና የዘመን

ወደ ገጽ 5 ዞሯል

Page 4: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 4 መስከረም 2007 ዓ.ም

ከገጽ 1 የዞረ

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ...

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የሁለቱንም ሕን

ጻዎች የመሠረተ ድንጋዮችን ካኖሩ በኋላ ባስተ

ላለፉት አጭር አባታዊ መልእክት እስከ አሁን

ቤተ ክርስቲያናችን እየተጠቀመችባቸው ያሉ

እነዚህ የምናያቸው ሕንጻዎች ለኛ አስተላልፈውልን

የሄዱት የቀድዎቹ ነገሥታት፣ መኳንንትና ባለሥ

ልጣናት ናቸው እኛ በተራችን እነሱ የተውልንን

ተንከባክበን መጠበቅ አድሰን በሚገባ መያዝ

አለብን፡፡ከዚህ ጐን በተራችን ለቀጣዩ ትውልድ

የሚተርፍ ሌላ አዲስ ሥራ ሠርተን የማለፍ

አደራና ግዴታ አለብን፡፡ በዚህ መሠረት የኛ

ጸሎት ዛሬ መሠረታቸው የጣልንላቸው ሕን

ጻዎች በታሰበው ሰዓት በጥራትና በፍጥነት

ተሠርተው እንድናይ እግዚአብሔር እንዲያበቃን

ነው፡፡ ዛሬ መሠረት ከጣልናቸው በተጨማሪ

ተጨማሪ ሕንጻዎችና ተቋማትም ልንገነባ ይገ

ባል ብለዋል፡፡

ከቅዱስነታቸው ቃለ በረከት አስቀድሞ አቶ

ተስፋዬ ውብሸት የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳ

ደርና ልማት ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ስለሚ

ሠሩት ሕንጻዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ

በገለጻቸው አዲስ የሚሠሩ ሕንጻዎች ይዘታቸውና

ገጽታቸው በቦታው ካሉ ጥንታውያን ሕንጻዎች

አሠራርና መልክ በማይቃረን መልኩ በከተማው

መስተዳደር ፈቃድ በጥናትና በጥንቃቄ የሚገነቡ

መሆናቸውን አስታውቀው በዘውዱቱ ሕንጻ

ግቢ የሚሠራው ሕንጻ ባለ አራት ፎቅ ሆኖ

ከሥር ሱቆች፣ አርት ጋላሪና መኪና ማቆሚያ ያካተተ

መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመንበረ መንግሥት አቅ

ጣጫ የሚገነባው ዘመናዊ ሕንጻ እንደ መጀመ

ሪያው ሕንጻ ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ቦታ

ያለው ሆኖ እንደሚሠራ ዋና ሥራ አስኪያጁ

ተናግረዋል፡፡ በዘውዲቱ ሕንጻ ግቢ በሚሠራው

ሕንጻ ከሱቆች በተጨማሪ እያንዳንዳቸው 240

ሜትር ስ£ር ስፋት ያላቸው 8 ባለ ሦስት መኝታ

ክፍሎችና 176 ሜትር ስ£ር ስፋት ያላቸው 4

ባለሁለት መኝታ ክፍሎች ይኖሩታል፡፡ በመንበረ

መንግሥት ግቢ የሚገነባው ሕንጻ በበኩሉ

በውስጡ 121ና 130 ሜትር ስ£ር ስፋት ያላቸው

8 /ስምንት/ መኖሪያ ቤቶች ይኖሩታል፡፡

ሁሉም ቤቶች በውስጣቸው ከሚይዙዋቸው

የመኝታ ቤቶችና ሳሎናች በተጨማሪ ዘመናዊ

ማዕድ ቤት የሠራተኞች መኝታ ቤት፣ መታ

ጠቢያና ሽንት ቤት ያካተቱ በአጠቃላይ አንድ

ዘመናዊ የከተማ ቤት ሊያሟላቸው የሚገባውን

ሁሉ የሚያሟሉ መሆናቸውን ከአቶ ተስፋዬ

ውብሸት ገለጻ ለማወቅ ችለናል፡፡

ከመሠረተ ድንጋይ የማኖር ሥነ ሥርዓት በኋላ

ቅዱስነታቸው በቸርቸል ጐዳና በተለምዶ ባንኮ

ዲሮማ እየተባለ ከሚጠራው የቤተ ክርስቲያናችን

ሕንጻ አጠገብ እየተገነባ ያለውን ባለዘጠኝ ፎቅ

ዘመናዊ ሕንጻ ግንባታን ጐብኝተዋል፡፡ በወቅቱ

ከባለሞያዎች ገለጻ ለማወቅ እንደተቻለው ግንቦት

3ዐ ቀን 2005ዓ/ም ግንባታው የተጀመረው ይህ

ሕንጻ ሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ/ም ለማጠናቀቅ

የጊዜ ሰሌዳ ተይዞለታል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሕንጻውን የግንባታ

ሂደት እየተዘዋዋሩ ከጐበኙና በሚመለከታቸው

አካላት የተደረገላቸውን ገለጻ ካዳመጡ በኋላ

የሕንጻው ግንባታ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ እንዲ

ሠራና የሚመለከታቸው አካላትም ጥብቅ ቊጥ

ጥርና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው አባታዊ

መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የቅዱስነትዎ መልእክትና ሐዋርያዊ ጒዞ

ታላቅ ድጋፍ ሆኖን በአገልግሎታችን ውጤታማ

ሆነን ባለንበት በአሁኑ ሰዓት በቅርቡ በልዩ ልዩ

ምከንያት ወደ ሰሜን አሜሪካ የመጡ ብፁዓን

አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖደስ አባላት

ከአህጉረ ስብከቱ ጋር ግንኙነት በመፍጠር የመ

ጡበትን ጉዳይ ማከናወን ሲችሉ፣ ከእናት ቤተ

ክርስቲያናችን የቀረበላቸውን የሰላምና የአንድነት

ጥሪ ወደ ጎን ትተው የኢትዮጵያን ቅዱስ ሲኖዶስ

አንቀበልም” ከሚሉ የስም አብያተ ክርስቲያናት

ጋር ወግነው መታየታቸው ከዚያም በላይ ራሳ

ቸውን ስደተኛ ሲኖዶስ እያሉ ከሚጠሩ ጋር

የቅዱስ ሲኖዶስን የውግዘት ቃል ጥሰው በእነርሱ

ቤተ ክርስቲያን በመገኘት፣ አልፎ ተርፎ በእን

ግድነት ባረፉበት ቤት ቅስና እና ዲቁና እንዲ

ሁም የማዕረግ ስም በመስጠት፣ ቀደም ሲል ቅዱስ

ሲኖዶስ በፈጠሩት ችግር ምክንያት ወደ ሀገር

ቤት እንዲገቡ ውሳኔ አስተላልፎባቸው እምቢተኛ

ሆነው ከቀሩት ሊቀ ጳጳስ ጋር ያለ ሀገረ ስብከቱ

ዕውቀና በአንድ ላይ ሆኖ አዲስ ሕንጻ ቤተ

ክርስቲያን መባረካቸው፣ ይህንና ይህን የመሳ

ሰለውን ድርጊት ብፁዓን አባቶች በመፈጸማቸው

የአህጉረ ስብከታችንን ሰላምና አንድነት በእጅጉ

አናግቶታል የፍትሕ መንፈሳዊም ሕግ እየተጣሰ

ይገኛል የሚል ሰፍሮ ይገኛል፡፡

ከዚህም በላይ የእነዚህ ጥቂት አባቶች ሕገ

ወጥ ድርጊት #ሕዝቡ በእናት ቤተ ክርስቲያኑና

በቅዱስ ሲኖዶስ ያለውን አመኔታ እየሸረሸረና

በአበያተ ክርስቲያናት መካከል መለያየትን እያስ

ከተለ በመሆኑ ለችግሩ ትኩረት ተሰጥቶት ዘለቄታ

ያለው መፍትሔና ውሳኔ ያገኝ ዘንድ በታላቅ አክ

ብሮት እንጠይቃለን” በማለት ደብዳቤው የጉዳዩን

አሳሳቢነት ይገልጻል፡፡

በተመሳሳይ ከምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ

ሀገረ ስበከት በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አሰ

ኪያጅ በሊቀ ማእምራን ለይኩን ተስፋ ፊርማ

ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተላከው የአቤቱታ

ደብዳቤ “በሕክምና ሽፋንና በመሳሰሉ ምከን

ያቶች ወደ ሰማን አሜሪካ የሚመጡ አባቶች

ከቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ውጭ በሆነና

ፍትሕ መንፈሳዊ በሚቃረን መልኩ ፡-

ከገጽ 1 የዞረ

የሰሜን አሜሪካ አህጉረ...

ያለ ሀገረ ስብከታቸው የክህነት ማዕርግ በመ

ስጠት

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክር

ስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተናል ብለው

በአደባባይ ቤተ ክርስቲያንን ክደው ከተለዩ

ወገኖች ጋር በገንዘብ ልመና ሽፋን በጋራ

አገልግሎት መስጠታቸው፣ ማረፊያቸውን

ከእነዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ከሚቃወሙ ወገ

ኖች በማድረግ የሚሉና ሌሎች ክንውኖችን

በመጥቀስ የእነዚህ አባቶች ድርጊት በቅዱስ

ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ታይቶ ዘላቂ ውሳኔ

እስኪያገኝ ድረስ በቅዱስ ፓትርያርክና በቋሚ

ሲኖዶስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በሕገ ወጡ

አሠራር ላይ ጊዜያዊ እገዳ እንዲደረግ በታላቅ

አጸንዖት እናሳስባለን ይላል፡፡

የዋሽንግተን ስቴት ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በቤተ

ክህነቱ ሊቀ ካህናት መልአከ ኃይል ቆሞስ አባ

ዘመልአክ ተክሉ ፊርማ ለሰሜን አሜሪካ ካሊ

ፎርኒያ ሀገረ ስብከት የተላከው የአቤቱታ ደብ

ዳቤም ከላይ ከጠቀስናቸው ለብፁዕ ወቅዱስ

ፓትርያርኩ ከተላኩ የድረሱልን ጥሪ ጋር ተመ

ሳሳይ ይዘት ያለው ነው፡፡

ይህንን ደብዳቤ ልዩ የሚያደርገው ችግር

ፈጠሩ ያላቸውን አባቶች ስም፣ ከነማን ጋር ምን

እንደሠሩና ድርጊቶቹ መቼና እንዴት እንደተረፈሙ

ሂደቶችን በግልጽ ማስቀመጡ ነው፡፡ ወደ

ቅዱስ ፓትርያርኩ የተላኩ የአቤቱታ ደብዳ

ቤዎች ሁሉ በፎቶግራፍ ጭምር የተደገፉ

ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዜና ቤተ ክርስቲያን

በደረሰው በፎቶግራፍ የተደገፈ ጥቆማ አንዳንድ

የቤተ ክርስቲያን አለቆች በግል ሥራ ወደ ሰሜን

አሜሪካ ከሄዱ በኋላ ቤተ ክርስቲያናችንን

ከሚቃወሙ ወገኖች ጋር በማበር ማለትም

አብረው አገልግሎት በመስጠትና ገንዘብ በማሰ

ባሰብ ከቆዩ በኋላ ተመልሰው ከነበሩበት የኃላ

ፊነት ደረጃ ሥራቸውን መቀጠላቸውን የሚያሳይ

ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች “ሁለት ባላ ተክል አንዱ

ሲሰበር በአንዱ ተንጠልጠል የሚለውን የወላ

ዋዮች መርህ የሚከተሉ ባለሁለት ቢላዋዎች ዓይ

ነቶች ይመሰላሉና የሚመለከተው አካል ሊያስ

ብበት ይገባል እንላለን፡፡

አቶ ተስፋዬ ውብሸት አዲስ ስለሚሠራው ሕንጻ ገለጻ ሲያደርጉ

ከዚህ መካከል ለሁለት ጌታ የሚገዛው ማን ነው?

Page 5: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 5 መስከረም 2007 ዓ.ም

ከክሕደት፣ ከኑፋቄ ከባዕድና የራስ አምልኮ

ወጥቶ እውነተኛውን ኃያል አምላክ ወደማ

ወቅና እርሱን ብቻ ወደ ማምለክ መለወጥ፣

ከትዕቢት ወደ ትሕትና ፣

ከርኲረሰት ወደ ንጽሕና ፣

ከጠማማነትና አልታዘዝ ባይነት ወደ ቅንነት፣

በአለፈው ዘመን ያደረገውን ሀኬት ስሕተትና

በደል ራስን መውደድ ሁሉ በልቡናው መር

ምሮና በንስሓ ጠበል ተጠምቆ ለማስወገድና

ቆርጦ ለመነሣት በዐዲስነት ተዘጋጅቶ መም

ጣት መሆኑን አጥርቶ የሚያስገነዝብ ታላቅ

ምስጢር ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ኤፌ.4.23 እስከ

ፍጻሜው ስንመለከተው ከልቡና የማይጠፋና

የማይረሳ ትምህርት እናገኛለን፡፡

በወደ ርእሰ ነገራችን ዋና አካል እንመለስና

በየክፍለ ዓለማቱ በብዙ ስልትና ቀመር በበ

ቂም፣ ያለበቂም አመክንዮ የዘመን መለወጫ

ቀንና ሥነ በዓል እንዳለ ይታወቃል፡፡ ኢትዮ

ጵያችንም እንደ መልካም ጋሜ በራሷ ላይ

በቀል በሆነችው ጥንታዊት፣ ብሔራዊትና

ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርታዊ

ጥበብ እየተመራች በየዓመቱ የዘመን መለ

ወጫ በዓልን #ዐውደ ዓመት$ ብላ በበቂና

ተስማሚ አመክንዮ በመሠየም ታላቅ

መንፈሳዊ ደስታን ይዛ ታከብራለች፡፡

ይህን ከ365 ቀናት ከሩብ ጉዞ በኋላ በየዐ

መቱ የሚመጣ የፀሐይ ዓመት መለወጫ ዐቢይ

በዓል ከምስጢር ጌጥ አስማምታ ቅዱስ ዮሐንስ

እያለች በጸሎት በምስጋና ታከብራለች፡፡

ሰው የሚሠራበት ምክንያቱን የሚሠራለት

ባለቤቱን ማወቅ ይገባዋልና ዘመን መለወጫን

ቅዱስ ዮሐንስ ያለችው ያለምክንያት አይደለም፡፡

በሊቃውንት እንደሚታወቀው ዮሐንስ

ማለት ፍሥሐ ወሐሤት ፍጹም ደስታ ማለት

ነው፡፡ አበው ስምን መልአክ ያወጣዋል፡፡

እንዲሉ ዮሐንስ ብሎ የሰየመው ገና ከመፀነሱ

አስቀድሞ መልአከ እግዚአብሔር ቅዱስ

ገብርኤል ስለሆነ ስሙ ሥራውን የሚገልጠው

ሆኖ አል፡፡ ይኸውም እንዲህ ነው፡፡ ወይቤሎ

መልአክ ኢትፍራህ ዘካርያስ እስመ ተሰምዐ

ጸሎትከ ቅድመ እግዚአብሔር ወብእሲትከኒ

ኤልሳቤጥ ትወልድ ለከ ወልደ፡፡ ወትሰምዮ

ስሞ ዮሐንስ መልአኩም እንዲህ አለው ዘካ

ርያስ ሆይ! አትፍራ፣ ጸሎትህ በእግዚአብሔር

ፊት ተሰምቶልሀልና ፡፡ ሚስትህ ኤልሳቤጥም

ወንድ ልጅን ትወልድልሀለች፡፡ ስሙንም ዮሐንስ

ትለዋለህ፡፡ ብሎት ሲያበቃ ተድላ ደስታ ይሆን

ልሀል፣ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡

እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና፡፡

$በማለት የስሙን ትርጓሜ በሚሠራው ግብርና

በሚኖረው ዐላማ አስቀድሞ አበሠረው፡፡

እንዲህም በመሆኑ ቅዱስ ዮሐንስ የዘመናት

መለወጫ ምልክት ዐዲስ ነቢይና ሐዋርያ ሆኖ

ለብሉይና ለሐዲስ ኪዳን መልካም መሸጋ

ገሪያ በመሆን በዐዋጅ ነጋሪነት ተነሥቶ የእግ

ዚአብሔርን መንገድ ጥረጉ፣ አስተካክሉ፡፡

ጎዳናው ሁሉ ይሙላ፣ ተራራውና ኮረብታውም

ሁሉ ዝቅ ይበል፡፡ ጠማማውም ይቅና፣ ሰርጐጥ

ጓጣውም ለጥ ያለ ምቹ ሜዳ ይሁን፡፡ በማለት

የሰው ሁሉ ሰውነት መለወጥ እንዲገባው

የነፍስና ሥጋ ደስታ ቃልን በዐዲስ መንፈስ ለሕ

ዝብ ለውጥን ዐዲስነትን አስተምሮ ሕዝብና

እግዚአብሔር አምላክ ከቀድሞው በተለወጠ

ሁኔታ የሚገናኙበትን የትሕትና የንጽሕና

ቀጥተኛ መንገድ በቃል ብቻ ሳይሆን በግብር

ገልጾ ለዓለም ሕዝብ በሙሉ ዕጽፍ ደስታን

ዐዲስ መንፈሳዊ መሪ በሆን አበሠረ& አጽን

ቶም ዐወጀ፡፡

መቼም ሰው ሁሉ ልዩ ልዩ ሥራ ተሠርቶበት

ያረጀው ዘመን ተሰናብቶ ለዐዲስ ሥራ ዐዲስ

ዘመን ሲመጣ ለሥጋም ለነፍስም ከዚህ የሚ

በልጥ ደስታ የለውም፡፡

ከገጽ 1 የዞረ

ዘመነ ሐዲስ በቅዱስ ዮሐንስ

በዚህ ምክንያት ዘመነ ሐዲስ በቅዱስ ዮሐንስ

በብሉይና በሐዲስ መሸጋገሪያ ድልድይ ስም

ተሰይሞና የደስታ ቀን ሆኖ እየተገኘ በየዓ

መቱ ዐዲስ እየሆነ በዐዲስ ዝግጀት እነሆ!

ይከበራል፡፡

የዘመናት ባለቤት ቸሩ አምላክ ስንኳን ከዘ

መነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና

ጠብቆ አደረሰን፡፡ እያለች እናት ቤተ ክርስ

ቲያን መልካም ምኞቷን ከቃለ በረከት ጋር

ለልጆቿ ታስተላልፋለች፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የዘመን አቆጣጠራችንና ወቅቱም መሠረትና ጥንታዊነት ያለው አኩሪ

ሆኖ ይገኛል፡፡

ይኸውም በአጭሩ ሕዝበ አምላክ ይባሉ ከነ

በሩት ከእስራኤል የተገኘ ነው፡፡ ቀድሞ ዘመ

ናቸውን በመስከረም ይለውጡ ነበርና ነው፡፡

ይህም ሊሆን የቻለው ደግሞ እኛ ኢትዮጵ

ያውያን ከእስራኤል ከጥሎ ሕገ ኦሪትን የተቀ

በልን የታወቅን ሕዝቦች ሆነን ከመገኘታችን

የተነሣ ነው፡፡

ከዚህም ጋር ኢትዮጵያ ዘመኗን ዘመን ሐዲስ

በቅዱስ ዮሐንስ እያለች ለመጥምቀ መለኮት

ውለታ የዘለዓለም መታሰቢያ በማድረግ በመስ

ከረም ወር መጀመሪያ ቀን ያደረገችበት ሌላም

በቂ ምክንያት አለ፡፡

ይኸውም በሀገራችን ከዘመነ መለወጫችን

ቀደም ያሉት ወራት ታቹ ውሃ፣ ላዩም ውሃ

የሞላበት ከመሆኑ የተነሣ ዘመድ ከዘመዱ

እንደልብ የማይገናኝበት የክረምቱ ወቅት

አልፎ ፣

የተለያየው ወገን የሚገናኝበት፣

የተራራቀው የሚቀራረብበት፣

ጨለማው ተገልጦ የፀሐይ ብርሃን ጐልቶ የሚታ

ይበት፣

አዝመራው ከበረድ ድኖና አብቦ ፍሬው

በተስፋ የሚጠበቅበት ወር በመሆኑ ነው፡፡

ይህም የአበው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን

ታላቅ ጥበብና አስተዋይነት የሚያሳይ ነው፡፡

በመሆኑም አሁንም ለወደፊትም በባሕረ

ሐሳብ /በሐሳበ ባሕር/ የዘመን መቊጠሪያ

ስልታችን ጸንተን የበዓላትና አጽዋማት ቀና

ትን እያወጣን ለሕዝቡ በማወጅ ዐውደ

ዓመቱን ስናከብር እንኖራለን፡፡

ይኸውም ዐውድ ዙሪያ፣ ክብ ከዓመት እስከ

ዓመት ማለት ሆኖ፣

ዐውደ አበቅቴ 19 ዓመት ጨረቃና ፀሐይ

የሚገናኙበት ፣

ዐውደ ዕለት ሙሉ ሰባት ቀን፣ ከእሑድ

እስከ ቀዳሚት፣

ዐውደ ወርኅ ሠላሳ ቀን ከመባቻ እስከ አመ

ሠላሣ ያለው፣ ደግሞም፣

ዐውደ ወርኅ 359 ቀናት የጨረቃ ዓመት፣

ዐውደ ዓመት 365 ቀናት ከሩብ ማለትም

ከ6 ሰዓታት የፀሐይ ዓመት ደግሞም ፣

ዐውደ ፀሐይ ጥንተ ዕለት ረቡዕና ወንጌላዊው

ማቴዎስ የሚገናኙበት 28 ዓመት ፣

ዐውደ ቀመር ዕለተ ሠሉስና ወንጌላዊ ማቴዎስ

የሚገናኙበት 532 ዓመት ሆኖ አበቅቴው አልቦ

ነው፡፡ ይህም ሒሳብ፣ መቁጠሪያ ስፍር ነው፡፡

ዘመን ብዛቱ ዘመናት ወይም አዝማን ሆኖ

ዓመት ዓመታት፣ ጊዜ ወራት በየስሙና በየክፍሉ

ማለት ነው፡፡

የቃሉ ምንጭም በዕብራ በሱር፣ ዝማን በዐረ፣

እንደ ግእዙ ዘመን /ዘማን/ የሚለው ቃል ነው፡፡

ዓ/ም ዓመት ዘመን፣ ብዙ ቀን የዕለታት

ድምር፣ ዐውዳቸውና ቀመራቸው፣ በየሦስት

ወሩ አራት አክፋል፣ ወይም 12 ወራት ያሉት፣

ማለት ጸደይ፣ ክረምት፣ መጸው፣ ሐጋይ

የሚባሉት ናቸው፡፡

ዓመተ ዓለም ከጥንተ ፍጥረት ከአዳም ጀምሮ

ያለውና የሚኖረው መላው የዓለም ዕድሜ ነው፡፡

ዘመነ ሥጋዌ፣ በኩነቱ ቃለ አብ ወቃለ መን

ፈስ ቅዱስ በስምና ግብሩ ወልድ ሥጋ ሆኖ

ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና ከተፈ

ጸመላት እመቤታችን ድንግል ማርያም ተፀንሶ

ከተወለደበት ዘመን ወዲህ ያለው ዘመን

ነው፡፡ ይህም ዓመተ ምሕረት ይባላል፡፡ ያለ

ጥርጥር ነውም፡፡ ይህን ሁሉ ያነሣነው

ታዲያ ለዋዛ አይደለም፡፡

ስንዱዋ እናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ቤተ ክርስቱያን ታዲያ በዚህ የዘመን አቆጣጠር

ዘዴ እየተጠቀመች፣

በዓላት የሚከበሩበት፣

የሕግ አጽዋማት የሚገቡበትና የሚወጡበት

ቀን ሳይሳሳትና ሳይዛነፍ መስመሩን ይዞ ከት

ውልድ ወደ ትውልድ ተጒዞ እንዲደርስ አድ

ርጋለች፡፡ በመሆኑም በዘመነ ሐዲስ፣ ቅዱስ

ዮሐንስ $በዓል ዕለት በየዓመቱ፣ በየቤተ

ክርስቲያኑ አለቃው ወይም የባሕረ ሐሳብ/

የሐሳበ ባሕር/ ሊቁ ከላይ በገለጽነው ስልት

እየተጠቀመ አጽዋማት የሚገቡበትን ዐበይት

በዓላት የሚከበሩበትን ቀን ለሕዝበ ክርስቲያኑ

ከትምህርት ጋር ያውጃል፡፡

በዚህ ጊዜም ስንዴ፣ ዘቢብና ዕጣን ቀርበው

ይጸለይባቸዋል፡፡ ዋና ምክንያቱም በምድሪቱ

የተዘራውና የሚዘራው አዝመራ፣ የተተከለውና

የሚተከለው አተክልት ውሃ ሳይጠርገው፣

በረድ ሳይመታው፣ አንበጣና ተምች ሳይ

በላው፣ /ብርድ /አመዳይና ድርቅ/ ሳያገኘው

ፍሬ እንዲያፈራ፣ ለሀገር ለወገን ሕይወት

በረከት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር እንዲ

ፈቅድና ይባርከው ዘንድ በሩቅ ታስቦ ነው፡፡

አራቱ ወንጌላውያንም በቋሚነት በቅዱስ

ዮሐንስ የተሰየመውን የዘመን መለወጫ በየአራት

ዓመቱ እየተለዋወጡ በማዕርግ ዘመነ ማቴዎስ፣

ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ፣ ዘመነ ዮሐንስ

ወንጌላዊ እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡

ምስጢራዊ ምክንያቱም የዓለም መድኀኒት

ጌታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ በዚህ ዓለም እየተ

ዘዋወረ ያስተማረውን ትምሀርት፣ ያደረ

ገውን ተአምራት መንክራትና ኀይላት፣ የሠራ

ውን ትሩፋት፣ ለአዳምና ዘሩ ካሳ ይሆን

ዘንድ የተቀበለውን መከራና ሞት ዘርዝረው

ለዓለም ስላሳወቁና ጽፈው ለቅድስት ቤተ

ክርስቲያን ስለአስረከቡ ለተጋድሏቸው ለታላቅ

ውለታቸው መታሰቢያ፣ ማስታወሻ ይሆን

ዘንድ ተጠንቶና በሊቃውንት ተወስኖ ነው

ይገባልም፡፡ መቼም የቅዱሳንን ክብርና ውለታ

መርሳትና ማጥፋት አክባሪው እግዚ አብ

ሔርን መካድ፣ ምቀኝነትና ራስንም ከባለታ

ሪክነት የማውጣት ክፉ አለመታደል ነው፡፡

ይሁንና፡-

ወንጌላውያኑ ገጸ ብእሲ ማቴዎስ፣ ገጸ አንበሳ

ማርቆስ፣ ገጸ ላህም ሉቃስ፣ ገጸ ንስር ዮሐንስ፣

ተብለው የተጠሩበት ምስጢርም በመጀመሪያ

በእግዚአብሔር ዘንድ ባላቸው የሕያውያን

ፍጥረታት ውክልና የተነሣ ነው፡፡ ከዚህም በላይ፣

አምላክ ሰው፣ ሰውም አምላክ ሆነ፣

ጣዖታት እንዲጠፉ፣ የወንጌልን ጥቅምና የእግዚ

ብሔርን አምላክነት ኃያልነት ጨክነው በማስ

ተማራቸው፣

መድኀኒታችን በተቀበለው መከራ ቀንድ እያ

ለው እንደማይዋጋ ላም ወሰን በሌለው ትዕ

ግሥት በመሥዋዕት ነት ዕዳ መክፈሉን፣

ንስር ወደላይ አየር ወጥቶ ቊልቊል ሲመ

ለከት ዐይኑ የጠራ ስለሆነ የሥጋ ቅንጣት

ልትሰወረው አትችልም፣ በዚህም አንጻር

ባሕርየ መለኮትን አምልተው አስፍተው ሰው

የሆነው አምላክ ጌታችን መድኀኒታችን በቅድ

ምና የነበረ ያለና የሚኖር የባሕርይ አምላ

ክነቱን በሚገባ ገልጠው ለዓለም ስለአስተማሩ

የተሰጣቸው የግብራቸው መግለጫ የማዕርግ፣

የሽልማት ስም እንደሆነ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል የዘመነ ሐዲስ፣ በቅዱስ ዮሐንስ

የሚገኘውና ዐውደ ዓመት የሆነው ዘመን

መለወጫ በዓል፡፡ እንቊጣጣሽምእየተባለ

በሕዝቡ ዘንድ ይታወቃል በተድላ ሥጋ

በተድላ ነፍስ በፍጹም ደስታ ይከበራል፡፡

የዚህም ምክንያቱ ከሀገራችን ታሪክ ጋር የተ

ያያዘ ከየት መጣ/ደራ/ አለው፡፡ይህውም

እርሷ የምትመራት የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ፣

የሕዝቡንም አኗኗር ለማስገንዘብ፣ ዝናው

ወደ ገጽ 7 ዞሯል

ከገጽ 3 የዞረ

የወጣቶች ተሳትፎ...

አቆጣጠርዋ፣ የአፍሪካ መዲናነትዋ የሚገልጹ

ልዩ ልዩ ትርኢቶች፣ ወቅታዊ የልማት እንቅስቃሴ

የሚያሳዩ ትርኢቶች ይቀርባሉ፡፡

ቤተ ክርስቲያንን በተመለከተ፤ የኢትዮጵያ

ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ የክርስትና አመጣጥ ታሪክ፣

የአክሱምና የታቦተ ጽዮን ታሪክ፣ የላሊበላ ጥንታ

ውያን አብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፣ የጥንታ

ውያን ገዳማና አድባራት የአሠራር ጥንታዊ

ጥበብ፣ የብራና መጻሕፍት ጥበብ፣ የቅዱስ ያሬድ

ታሪክ፣ ዜማዎችና የዜማ ምልክቶች፣ የአብነት

ት/ቤቶችንና ተማሪዎቻቸው እንዲሁም የመማር

ማስተማር ሂደት፣ የመስቀል ኃይልና ክብር ሊገልጹ

የሚችሉ የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች፣

የግማደ መስቀሉ ታሪክ… እነዚህንና መሰል ትምህ

ርቶችን በማቀነባበር ለዓለም በቀጥታ ስርጭት

በሚተላለፍ መርሐ ግብር ይዘው በመቅረብ ለመ

ላው ዓለም መልእክታቸውን ያስተላልፋሉ፡፡

ማጠቃለያ

ከላይ እንደተገለጸው ይህ የመስቀል በዓላችን

በሀገር አቀፍ ደረጃ በብዙ ሚልዮን የሚቆጠር

አማኝ አደባባይ ላይ ወጥቶ በፍጹም መንፈሳዊ

ሥነ ሥርዓት የሚያከብረው ክርስቲያናዊ በዓል

ነው፡፡ በመሆኑም ይህ በዓል አሁን ከሀገራችን

አልፎ የዓለም ህዝብ በዓል በመሆን ከማይታዩ

የዓለም ቅርሶች ውስጥ በክብር ተመዝግቦ

ይገኛል፡፡ ይህ እውን ሊሆን የቻለው በወጣቱ

ከፍተኛ ተሳትፎ መሆኑ እሙን ነው፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ክርስቲያናዊ በዓላችን በዩኔስኮ

ማስመዝገቡ በቻ በቂ አይደለም፡፡ ከዚህም

በላይ አሁንም የመስቀል በዓላችን ጥንታዊ ታሪኩ፣

የአከባበር ሥርዓቱና ትውፊቱ ተጠብቆ ለት

ውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ አኳያ ያለባችሁ

ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑ አውቃችሁ ለልጆቻችሁና

ለወንድሞቻችሁ ይህንኑ ጥንታዊና ያልተበረዘ

የመስቀል በዓላችንን ምንነት በአግባቡ በማተማርና

በተግባርም እንዲለማመዱት በማድረግ ትውልዳዊ

አዳራችሁን ልትወጡ ይገባል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ቅዱስ ጳውሎስ “ዘመኑን

ዋጁ” (ኤፌ.5፡16) በማለት እንዳስተማረን ዘመኑ

የቴክኖሎጂ ዘመን እንደመሆኑ መጠን እናንተ

ወጣቶች ደግሞ ለቴክኖሎጂ ቅርቦች ስለሆ

ናችሁ ዘመኑ በሚፈቅደው የቴክኖሎጂ ሂደት

ተጠቅማችሁ የዚህ የመስቀል በዓላችን ታሪክ፣

ባህልና የአከባበር ትውፊት በተመለከተ ለመላው

ዓለም የማስተዋወቅና የማስተማር ግዴታችሁን

ለመወጣትም አሁን በተጀመረው አዲሱ የሰንበት

ት/ቤቶች አደረጃጀት አጠናክራችሁ በመቀጠል

በተፋጠነና በተደራጀ መልኩ ከሀገርም አልፎ

ዓለም አቀፍ ትስስር ፈጥራችሁ መንቀሳቀስ ዘመኑ

የሚፈቅደው ተልዕኮአችሁ መሆን ይገበዋል

እላለሁ፡፡

የሰ/ት/ቤት መዘምራን ወጣቶች እስከ አሁን

እያደረጋችሁ ያለውን ተሳትፎ እጅግ የሚያ

ስመሰግን ቢሆንም አሁንም የበለጠ መሰል

የአደባባይና የንግስ በዓላቶቻችንን በቅዱስ ያሬድ

ዝማሬ በማድመቅ ሌሎችም የቤተ ክርስቲያናችን

በዓላት በዩኔስኮ ተመዝግበው ዓለም አቀፍ

ክበርና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያለንን አገልግሎት

ይበልጥ ተደራሽና አሳታፊ ማድረግ ለነገ የማ

ይባል ተልዕኮአችሁ መሆን ይገባዋል እያልኩ

አገልግሎታችሁ ግን በመዝሙር ብቻ ሳይወሰን

በሁለገብ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊና ልማ

ታዊ መርሐ ግብሮች ተሳትፎ በማድረግ ጊዜያ

ችሁን፣ ጉልበታችሁንና ዕውቀታችሁን ሰጥታችሁ

እናት ቤተ ክርስቲያናችሁን ይበልጥ ተጠና

ክራችሁ እንድታገለግሉ አደራ ጭምር ሳሳስብ

መልካም የመስቀል ደመራ በዓልም እንዲሆ

ንላችሁ በመመኘት ነው፡፡

በመምህር ሙሴ ኃይሉ

Page 6: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 6 መስከረም 2007 ዓ.ም

የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክር

ስቲያን የመስቀል በዓልን በቤተ ክርስ

ቲያን በማሕሌትና በቅዳሴ ከማክበር አልፋ

ከሕፃን እስከ አዋቂ፥ ከንጉሥ እስከ እረኛ፥

ከባላባት እስከ ሠራተኛ፥ በአጠቃላይ ሁሉም

የኅብረተሰብ ክፍል በተገኙበት በአደባባይ

የምታከብር ብቸኛ የዓለማችን ቤተ ክርስቲያን

ናት።

የመስቀል በዓል አከባበር በኢትዮጵያ

ሌላው ልዩ የሚያደርገው አከባበሩ በሺሕ

ለሚቆጠሩ ዓመታት ይዘቱ፥ ውበቱና ድም

ቀቱ ሳይቀንስ፥ ሥርዓቱ ሳይፋለስ፥ ከትው

ልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ መቆየቱ ነው።

ለዚህ ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶ

ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የወንጌል ትም

ህርት በሕዝቡ ዘንድ እንዲሠርጽ ከማድረግ

ጎን ለጎን የመስቀል በዓል አከባበር ሥርዐት

የሕዝቡ ባህልና ትውፊት አንድ አካል አድ

ርጋ መያዝ በመቻልዋ ነው።

አንዳንድ ያልገባቸው (ዕውቀቱ የሌላ

ቸው) ሰዎች የመስቀል በዓል ባህላዊ በዓል

ብቻ እንደሆነ አስመስለው ይናገራሉ። ጥቂ

ቶች ደግሞ ሆን ብለው የበዓሉን መንፈሳዊ

ገጽታ በመሸፈን ባህላዊ ጎኑን ከሃይማኖታዊ

መሠረቱ ነጥለው ለማሳየት ይሞክራሉ።

ይሁን እንጂ የመስቀል በዓልን ጨምሮ በዕንቍ

ጣጣሽ፥ በጥምቀትና ልደት በመሳሰሉ ብሔ

ራዊ በዓላት የሚስተዋሉ ባህላዊና ትው

ፊታዊ ሁነቶች በሙሉ ምንጫቸውና መሠረ

ታቸው ሃይማኖታዊ ነው። በመሆኑም በእነ

ዚህ ዓበይት በዓላት በሕዝቡ ዘንድ የሚ

ከወኑ ማኅበራዊና ባህላዊ ሥነ ሥርዓቶችን

ከሃይማኖት ነጥሎ ለማሳየት መሞከር ወተትና

ውኃ ከተደባለቀ በኋላ ለመለየት ከመሞከር

ጋር እኩል ነው።

የሌሎቹን በዓላት ሁኔታ ለጊዜው እናቆ

የውና አሁን ወደተነሣንበት የመስቀል በዓል

ጉዳይ እንመለስ። የመስቀል በዓል መለያውና

አርማው የደመራ ሥርነ ሥርዓት ነው። የዚህ

ሥነ ሥርዓት መነሻው ደግሞ ንግሥት እሌኒ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰ

ቀለበትን መስቀል ለዘመናት ተቀብሮ ከጠ

ፋበት ቦታ ለማግኘት ካደረገችው መንፈሳዊ

ተጋድሎ በቀጥታ የተያያዘ ነው።

ንግሥት እሌኒ ከኢየሩሳሌሙ ሽማግሌ

መምህር ኪራኮስ ባገኘችው ጥቆማ መሠረት

መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለይታ ለማወቅ

ደመራ ካስደመረች በኋላ በደመራው ላይ ዕጣን

በመጨመር በእሳት ለኮሰችው። ከዚያ በኋላ

ከደመራው የወጣው ጭስ ሽቅብ ወደ ሰማይ

ከወጣ በኋላ ተመልሶ እንደ ጦር ቁልቁል

በመውረድ አንዱ ተራራ ጫፍ ላይ አረፈ።

በዚህ ምክንያት መስቀሉ የት እንደተቀበረ

ታወቀና ጢሱ ባመለከተበት ቦታ ተቆፍሮ

ሊወጣ ቻለ።

ኢትዮጵያውያን የመስቀል በዓልን በአደ

ባባይ፥ በየዐምባውና ተራራ ላይ ደመራ እየ

ደመሩ የሚያከብሩት ይህንን የንግሥት እሌኒን

ደመራ መነሻ በማድረግ ነው። ሌላው በአብ

ዛኛው የኢትዮጵያ አካባቢዎች ደመራ የሚደ

መረው በተራራ አናት፥ በጉብታዎችና በከፍተኛ

አካባቢዎች ላይ ነው። የዚህ ምክንያቱ፦

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመ

ስቀል ላይ ተሰቅሎ ለሰው ልጅ ቤዛ የሆነው

በቀራንዮ ተራራ በመሆኑ አበው ያንን ለማ

ዘከር የዘረጉት ሥርዓት ነው።

ከደመራው ሥርዓት ሳንወጣ ማውሳት

ያለብን ተጨማሪ ትውፊት አለ። ኢትዮጵ

ያውያን የመስቀል ደመራው ተቀጣጥሎ በደ

መራው መሀል የተተከለው ቀጥ ያለ ዕንጨት

ሳይወድቅ አይንቀሳቀሱም። በሌላ አገላለጽ

የደመራውን የመጨረሻ የአወዳደቅ ሁኔታ

በጕጕት ነው የሚጠብቁት። ምክንያቱም ኢትዮ

ጵያውያን ደመራው የወደቀበት አቅጣጫ

አዝመራው ያምራል፥ ዘመቻ ካለ ይቀናል፥ ሰላም

ይሰፍንበታል ብለው ስለሚያምኑ ነው።

ይህም ከባዶ ተነሥቶ የመጣ ባህል አይ

ደለም። ንግሥት እሌኒ ከደመረችው ደመራ

የወጣው ጭስ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ

እንደ ጠቆመ ሁሉ ደመራው የወደቀበት አቅ

ጣጫም በተመሳሳይ ሰላምና በረከት ያድር

በታል ከሚል እሳቤ የመጣ ነው።

ይህ ብቻ አይደለም፥ ደመራው የሚቀ

ጣጠለው ከተጸለየበትና ከተባረከ በኋላ በመ

ሆኑ ምእመናን ለበረከት አመዱን እየቆነጠሩ

በግንባራቸው ላይ መስቀለኛ ምልክት ያደ

ርጋሉ። የምዕራብ ሸዋ ምእመናን ከቃጠሎ

የተረፈውን የተለበለበ ዕንጨት ወደየቤታቸው

በመውሰድ ለበረከት በቤታቸው አጥር ላይ

ይስጉታል። ጉራጌዎች ከደመራው ቃጠሎ

የተረፈውን ትርኳሽ የተቀደሰ ነው በማለት

ሰብስበው በቤተ ልሔም ያስቀምጡታል።

የደቡብ ትግራይና የዋግ ሕምራ ምእመናን

በበኩላቸው ደመራው ረመጥ ላይ እሬት በመ

ጥበስ ይረግጡታል። ይህን የሚያደርጉት

ከተለያዩ ሕመሞች ይፈውሰናል ብለው ስለሚ

ያምኑና ስለሚድኑበትም ነው። አመዱንም

ወደየቤታቸው ወስደው በከብቶቻቸውና ፍየሎ

ቻቸው በረትና ጋጥ ይበትናሉ። በተመሳሳይ

በትግራይ በረመጡ ላይ አደይ አበባን በመ

ጥበስ ከቍርጥማት ሕመማቸው ለመፈወስና

ለመከላከል ሰውነታቸውን ያሹበታል።

ኢትዮጵያውያን ስለ መስቀል በዓል የነበራ

ቸውና ያላቸው መንፈሳዊ ዕውቀት የጠለቀ

መሆኑን የሚያሳዩ ተጨማሪ ተግባራትም አሉ።

ለምሳሌ በአብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባ

ቢዎች መስቀል የዕርቅና የሰላም በዓል ሆኖ

ነው የሚከበረው። ከመስቀል በፊት በሀገር

ሽማግሌዎችና ዳኞች ጥረት ለዕርቅ እምቢ

ብለው የቆዩ ጥለኞች ሳይቀሩ በዚህ ጊዜ ይታ

ረቃሉ። በመሆኑም በእነዚህ አካባቢዎች

ምን ይሁን ምን በመስቀል ለዕርቅ እምቢ

የሚል ሰው አይገኝም። ይህም ሰዎቹ ጌታችን

መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለ5500 ዓመ

ታት በሰውና በፈጣሪ መካከል ተገንብቶ

የቆየውን የጠብና የጥል ግንብ በመስቀል ላይ

ተሰቅሎ በማፈራረስ በመስቀሉ ሰላምን ያመጣ

መሆኑን በማመን የሚፈጽሙት መሆኑን

ልብ ማለት ያሻል።

ከደመራ በተጨማሪ ለመስቀል በዓል

ዋዜማ ልጆች ችቦአቸውን እያበሩ በየቤቱ

ይጨፍራሉ። አባ ወራውም በመስቀል ዕለት

ወደ ደመራው ከመሄዱ በፊት ልጆቹን ሰብ

ስቦ ችቦ በማብራት ማጀቱን፥ እልፍኙን፥ ጐተ

ራውን፤ የከብቶች፥ የፍየሎች፥ የበጎችና

የበቅሎ ዎችን በረትና ጋጥ በችቦው ብርሃን

ይተረኩሳል። አባወራው በዚህን ጊዜ ከሚደ

ረድራቸው ግጥሞች መካከል መስቀል ብርሃን፥

መስቀል ሰላም መሆኑን የሚያመለክቱ፥ ድርቅና

በሽታ እንዲጠፉለት ለእግዚአብሔር የሚያመለ

ክትባቸው የጸሎት ስንኞችን የቋጠሩ ናቸው።

በሆያ ሆዬ ወቅት ሕፃናትም ሆኑ አዋቂ

ዎች ከሚደረድሯቸው ግጥሞች ብዙዎች

መስቀል የብርሃን ተምሳሌት፥ የሰላም አርማ

መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ለአብነት ያህል

እረኞች በየቤቱ እየሄዱ ሲጨፍሩ

ከሚያሰሙዋቸው ግጥሞች መካከል፦

ሆያ ሆዬ ... ሆያ ሆዬ

ክፈት በለው በሩን የጌቶችን

የኔታ እገሌ የሰጡኝ ሙክት

ግንባረ ቦቃ ባለ ምልክት

የሚለውን ስናይ በተለይ በመስቀል ዕለት

በስጦታ የሚሰጠው ሙክት ግንባረ ቦቃ

(በግንባሩ ላይ ነጭ ያለበት) መሆን እንዳለበት

ያሳያል። በተመሳሳይ አባወራው ችቦውን

አብርቶ በቤቱ ውስጥና ውጭ በሚዞርበት

ጊዜ ከሚያሰማቸው የግጥም ስንኞች መከካል፦

አረሬ አረሬ መስቀል በራ ዛሬ

የጎመን ቶፋ ውጣ የገንፎ ቶፋ ግባ

ትዃን ውጣ ቍንጫ ግባ

በብርሃን ገዳይ በመስቀል ገዳይ

የሚል ይገኝበታል። ይህም መስቀል የብርሃን

ምንጭና ተምሳሌት ብቻ ሳይሆን መስቀል

የችግርና የጠላት ማስወገጃ መንፈሳዊ መሣሪያ

መሆኑን ያመለክታል።

ገበሬዎችም ቢሆኑ ለእንስሳዎቻቸው ስም

ሲያወጡ ግንባራቸው ነጭ የሆኑትን ለበሬ

መስቀል፥ ለላም መስቀሌ እያሉ ነው የሚጠ

ሯቸው። ለእንስሳት ብቻ ሳይሆን ኢትዮ

ጵያውያን በመስቀል በዓል ዕለት ለተወለደ

ወይም ክርስትና ለተነሣ ልጅ ወልደ መስ

ቀል (የመስቀል ልጅ)፥ ገብረ መስቀል (የመ

ስቀል አገልጋይ)፥ ብርሃነ መስቀል (የመ

ስቀል ብርሃን) እያሉ ይሰይሙዋቸዋል። እነዚህ

ሁሉ የስያሜ አሰጣጦች ኢትዮጵያውያን ለመ

ስቀል ያላቸውን ክብር ማሳያዎች ናቸው።

የመስቀል በዓል አከባበር በኢትዮጵያ ልዩና

ደማቅ እንዲሆን ከሚያደርጉት ምክንያ ቶች

አንዱ የተፈጥሮ ሁኔታ ነው። ወቅቱ የጨለማው

(የክረምት) ጊዜ አልፎ ዕፀዋትና አዝርዕት

የሚያብቡበትና የሚያፈሩበት፥ እንስሳት እሸት

ሣር እየነጩ፥ የጠራ ውኃ እየጠጡ የሚቦ

ርቁበት፥ በአጠቃላይ ምድር በአበቦች የምታ

ጌጥበት፥ ሰማይ የደመና ቡሉኮ ውን (ጋቢ

ውን) ጥሎ ቀን በፀሐይ፥ ሌሊት በከዋክብትና

ጨረቃ ማጌጥ የሚጀምርበት፥ አዕዋፋትና

እንስሳት እንደልባቸው መንቀሳቀስ የሚጀ

ምሩበት በመሆኑ ኢትዮጵያውያን የመስቀል

በዓልን የሚያከብሩት በተፈጥሮ ውበት

ታጅበው ነው።

ይህ ብቻ አይደለም በመስቀል በዓል

የበዓሉ መለያና ማድመቂያ ሆኖ የሚያገለግለው

ዐደይ አበባም የሚያብበው በዚህ ወቅት ነው።

በውበቷ የሰው ዓይንን የምትማርክ፥ የመስቀል

በዓልን ለማድመቅና ለማክበር ከእግዚአብሔር

የተላከች የምትመስለው የመስቀል ወፍም

በዚህ የመስቀል በዓል ሰሞን የምትታይ ብርቅዬ

ወፍ ናት። በነገራችን ላይ የዐደይ አበባም

ሆነ የመስቀል ወፍ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ

እግዚአብሔር ለዚህች ሀገር ያበረከታቸው

ገጸ በረከቶች ናቸው።

እንደዛሬው ዘመናዊ የመገናኛ አውታሮች

ባልተዘረጉበት ጊዜ በክረምቱና በወንዝ ሙላት

ምክንያት ተለያይተው የከረሙ ቤተሰቦች የሚገ

ናኙበት፥ ነገሥታትና አገረ ገዢዎች ተበታትኖ

የከረመውን ሠራዊታቸውን በማሰባሰብ ወታ

ደራዊ ሰልፍ የሚያሳዩበት፥ አዳዲስ ዐዋጆች

የሚታወጁበት፥ የሀገር ሽማግሌዎች ተሰብስበው

የሚመክሩበት ወቅትም ነው፥ መስቀል። ከሁሉ

በላይ በመስቀል በዓል ልጆች የመስቀል

ብርሃን ተምሳሌት የሆነውን ችቦአቸውን

እያበሩ «ሆያ ሆዬ» የተሰኘውን ባህላዊ ጭፈራ

የሚጨፍሩበት፥ አዲስ እሸት የሚቀመስበት

የዓመቱ የተስፋና የብሩህ ፋና ምልክት

በዓል ነው።

የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባ

ቢዎች በድምቀት የሚከበር በመሆኑ በዚህ

ሰሞን ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ሀገር ጎብኚ ባለበት

የኢትዮጵያ ክፍል ሆኖ የበዓሉ ሥነ ሥርዓት

ተካፋይ ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ በዓለ መስ

ቀል በተለየና በደማቅ ሥነ ሥርዓት የሚከ

በርባት ብቸኛ የዓለማችን ሀገር ብቻ ሳትሆን

ጌታ የተሰቀለበት መስቀል (ቀኝ እጁ ያረ

ፈበት) የመስቀል ቅርጽ ባለው የግሸን ዐምባ

ላይ በመስቀልኛ ሕንጻ ቅርጽ በተሰራው ቤተ

ክርስቲያን ውስጥ በክብር ተቀምጦ የሚገ

ኝባት ሀገረ እግዚአብሔር ጭምር ናት።

Page 7: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 7 መስከረም 2007 ዓ.ም

ወደ ገጽ 9 ዞሯል

7

በ ደርግ መንግሥት ኢፍትሐዊ እርምጃ ተወ

ርሰው የነበሩ የቤተ ክርስቲያንዋ ሕንጻዎች

በተደረገው እልህ አስጨራሽ ሂደት መረጃን

በማሰባሰብ፣ የጠፉ ሰነዶችን ከየቦታው በማፈ

ላለግ፣ የዓይን ምስክር በመሆን ሌት ተቀን በመ

ሥራት የላቀ አስተዋጽኦ ያበረቱ ሦስት ግለሰቦች

ነሐሴ 19 ቀን 2006ዓ/ም በተደረው ሥነ ሥርዓት

ከቤቶችና ሕንጻዎች ልማት ድርጅት የተዘጋጀ

ላቸውን ሽልማት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢት

ዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወእጨጌ ዘመንበረ

ተክለ ሃይማኖት እጅ ተቀብለዋል፡፡

በቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት ድር

ጅት አማካኝነት በመንበረ ፓትርያርክ አዳራሽ

በተካሄደው ሥነ ሥርዓት እያንዳንዳቸው ካባና

የእጅ ሰዓት የተሸለሙት፣

1. አቶ ታደለ ገ/መስቀል

2. መምሬ ተዘራ ወርቁ

3. ሊቀ ካህናት ኃይለሥላሴ ዘማርያም ናቸው፡፡

ደርግ ቤቶችንና ሕንጻዎችን የወረሰው ሕጋዊ

አሠራር በተከተለ መንገድ ሳይሆን ድንገትና በጉልበት

ስለነበር መንግሥት የቀድሞውን ፓትርያርክ የብፁዕ

ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስና የቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄ

ተቀብሎ የቤተ ክርስቲያን ቤቶችና ሕንጻዎች

እንዲመለሱላት በፈቀደበት ጊዜ የተወረሱት

ቤቶች ብዛት ዓይነትና የሚገኙበት ቦታ በትክክል

ለማወቅ አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር፡፡ በመ

ሆኑም አንዳንድ የአዲስ አበባ መስተዳድርና የመን

ግሥት ኪራይ ቤቶች ድርጅት አመራሮች ሕን

ጻዎቹ የናንተ ለመሆናቸው የሚያሳይ ካርታና

ሕጋዊ ሰነድ ካላመጣችሁ እያሉ በቢሮክራሲያዊ

አሠራር ሂደቶችን ለማጓተትና ብሎም ለማደናቀፍ

በሚሞክሩበት ወቅት ከላይ በስም የተጠቀሱት

ግለሰቦች ቤቶችን በመለየትና ማስረጃዎችን በማጠ

ናከር የማይተካ ሚና ነበራቸው፡፡

በዚህ ሂደት በተለይ የአቶ ታደለ ገብረመስቀል

ድርሻ የላቀ እንደነበር ሁሉም በጋራ የሚስማማበት

ጉዳይ ነው፡፡ መምሬ ተዘራ ወርቁ እና ሊቀ ካህናት

ኃይለሥላሴ ዘማርያም ግን ዛሬም ድረስ ያልተ

መለሱ ቤቶች ለማስመለስ በሚረደረገው ጥረት

ተሳትፎአቸውን እንደቀጠሉበት ይገኛሉ፡፡

ከገጽ 5 የዞረ

ዘመነ ሐዲስ በቅዱስ ዮሐንስ

የገነነው የንጉሠ እስራኤል ሰሎሞንን ጥበብ

በቅርብ ተመልክታ የዐይን ምስክር ለመሆን

ንግሥተ ሳባ/ንግሥተ አዜብ/ በጒብኝት ወደ

ኢየሩሳሌም መሔዷ በቅዱስ መጽሐፍ በባለቤቱ

በአድናቆት ተጠቅሶና ተመዝግቦ ይገኛል፡፡

1ኛ ነገሥ.10.1-10 ማቴ12.42

ጒብኝቷን ከፈጸመች በኋላ ንግሥተ ሳባ /አዜብ/

ለአቀረበችለት ብዙ ሸቱና ልዩ ልዩ በረከተ ገጽ

አጻፋ አድርጐ ሰሎሞን እጅግ ብዙ ዕንቊ

ለጣጣሽ፣ /ለጉዳይሽ/ ብሎ ሰጣት፡፡ ንጉሥ ሰሎ

ሞን በንግሥተ ሳባ በከፍተኛ ደረጃ እንደተደሰተና

ለደስታውም ማረጋገጫ ዐያሌ እንቊዎችን ሸልሞ

ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ እንደ ሸኛት ዜናው አስቀድሞ

በኢትዮጵያ በሁሉም የሕዝብ ወገን ዘንድ በቅብ

ብል ተሰማ፡፡

ንግሥተ ሳባም አንድ ዓመት ቆይታና የመልስ

ጒዞዋን ፈጽማ ከመናገሻ ከተማዋ በገባች ጊዜ

እንደ ሕጉ እንደ ወጉ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱም በእል

ልታ ደስታ በተመላው ሥርዐት አክብሮ በታላቅ

በክብር ተቀበላት፡፡ይልቁንም ሕፃናትና ልጆች

አበባና የተለያየ የዕፀዋት ለምለም ቅጠል ይዘው

እየፈነደቁ ሰሎሞን ዕንቊለጣጣሽ የሰጠሽ በዓመትሽ

ስንኳን ደኅና መጣሽ እያሉ በመዘመር፣ በመዝፈን

ደማቅ አቀባበል አድርገውላት ነበር፡፡ጊዜውም

እንደዚሁ የመስክረም ወር እንደነበር በታሪክ

ይታወቃል፡፡

ስለዚህ ያ መልካም ድርጊት መልካም ልማድ፣

በቆይታው የሀገር ባህል ሆኖ ይኸውና ከጊዜ

ያችን ደርሷል፡፡

በዚህ መሠረትነት ዘመነ ሐዲስ በቅዱስ

ዮሐንስ በማለት ያወሳነው የዘመን መለወጫ

ዐውደ ዓመት በሚከበርበት ዕለት ሕፃናትና

ልጆች ወደ ዘመዶቻቸውና ጐረቤቱ መኖሪያ

እየሔዱ እንቊጣጣሽ በየዓመቱ ያምጣሽ/ስንኳን

ደኅና መጣሽ/ እያሉ በመጨፈር የአበባና የለምለም

ግጫ ሣር በረከተ ገጽ ይሰጣሉ፡፡ ተቀባዮቹም

በየደረጃቸውና ማዕርጋቸው ከዕንቊ ጀምሮ ልዩ

ልዩ ንጹሓን እንስሳትና ገንዘብ ለጣጣችሁ/

ለጉዳይ-ችግራችሁ/ ይሁን፡፡ በማለት ለሕፃናቱና

ልጆቹ ይሰጧቸው እንደነበር በትውፊት የታወቀ

ነው፡፡ በጊዜያችንም ሕፃናትና ልጆች በየጾታቸው

በተናጠል ወይም አንድነት ሆነው ለጣጣቸው

ስጦታ እንዲያኙ አበባ ወይም እርጥብና ለምለም

ግጫ ይዘው እንቊጣጣሽ እያሉ እያጨበጨቡ

በተለይ ልጃገረዶች እታሟቸውን ይዘው እየመቱ

በመዝፈን በየቤቱ ይዞራሉ፡፡ ተቀባዩም የቻለውን

ያኽል የገንዘብ ስጦታ ያደርግላቸዋል፡፡ በዚህ

ምክንያት እንቊ ለጣጣሽ የነበረው ሁለት ቃል

ይኸው በዘመን ብዛት ተለውጦ እንቊጣጣሽ

ሊባል ችሏል፡፡

እንግዲህ የበዓሉ መንፈሳዊና ባህላዊ መልክና

ይዘቱ፣ ምስጢርና አጥጋቢ ምክንያቱ ይህ ከላይ

የታተተው ሆኖ እያለ የተገኘውን በረከት ዐብሮ

ከመብላት፣ ከመጠጣት፣ ድኾችን ከመጐብኘት፣

ለዐዲስ ሥራ ለለውጥና መሻሻል ለልማትና እድገት

ዐዲስ የተለወጠ ዕቅድ ለማውጣት ከመዘጋጀት

በስተቀር ከዚህ የወጣ ሰይጣናዊ ግብር የሚያ

ስከፍል አጒል ጐን ፈጸሞ የለውም፡፡ ለበዓሉ

የሚታረዱ የእንስሳትንና የአዕዋፍን የጸጉርና

የላባ ቀለም የሚያስመርጥ ጣጣ ፈንጣጣ በኋላ

በባዕድ ተጽዕኖ በችግር ጊዜ ወደ ውዲቱ ሀገራ

ችን ሠርጐ የገባ የአምልኮ ባዕድ ርዝራዥ ነው፡፡

ስለሆነም በንጽሐ ነፍስ ቢቀር በንጽሐ ሥጋ ሁሉን

ለማወቅ ጸጋ የታደለው ዐዲሱ ትውልድ እንደ

ዘመኑ ልቡናውን በጥበብ ዐድሶ ይህን ከዐውደ

ዓመቱ ሥነ በዓል ዐላማ ውጭ የሚፈጸም ጐጂ

ልምድ እርግፍ አድርጐ ሊተወው ይገባል፡፡ እንደ

አመንጭው ዲያብሎስ አምዘማዝጐና አንቆጫቁጮ

ወዲያ ሊጥለው የሚገባው ነው፡፡

ለዓመቱ ይበለን

ተርፎ ከሚቀር ዕድም አይንፈገን፡፡

ሊቀ ትጉሃን ኀይለጊዮርጊስ ዳኘ በመምሪያ ሓላፊ ማዕርግ

የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ምክትል ኃላፊ

መስቀል ጌታ በተሰቀለበት አምሳል ከዕንጨት፥

ከብረት፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከወርቅ፥ ከዕብነ

በረድ፥ ከሌላም የከበረ ማዕድን እየተሠራ ከአበው

ሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ ቄሶች በሙሉ በእጃቸው

የሚይዙት፥ ክርስቲያኖችም የሚሳለሙትና በአንገ

ታቸውም የሚያሥሩት፥ ሴቶችም በቀሚሳቸው

የሚጠልፉት፥ በግንባራቸውም የሚነቀሱት ሁሉ

ስያሜው መስቀል ነው።

የጽሑፉ ዋና ሐተታ

መስቀል በሃይማኖታዊ ይዘቱ በቤተ ክርስ

ቲያናችን ከፍተኛ ክብር ያለው ነው። መስቀል

በነቢያት ዘንድ ትንቢትና ምሳሌ አለው። በትን

ቢት «ሐረገ ወይን ኮነ መድኃኒትየ ዘእምሐሢሦን

ይትገዘም ወበጎልጎታ ይተከል» (መሓ. 3፥10

ትርጓሜ)

«ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ

ከመ ያምስጡ እምገጸ ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ»

- ለሚፈሩህ፥ ለሚያመልኩህ የአጋንንት ማሸ

ነፊያ ምልክት የሚሆን በመስቀል ምልክት ማማ

ተብን፥ ስመ ሥላሴ መጥራትንም ሰጠኻቸው

(መዝ. 59፥4-5)

የኖኅ መርከብ የተሠራችበት ዕንጨት የመስቀል

ምሳሌ ነው። ኖኅ ወደ መርከብ ከነቤተሰቡ

ገብቶ ከጥፋት ውኃ ድኖአል። ወደ መርከቡ

ያልገቡ ግን በጥፋት ውኃ ተደምስሰዋል። «ወይቤሎ

እግዚአብሔር ለኖኅ አመ አይኅ ግበር ታቦተ

በዘትድኅን እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል

ይእቲ።» (ቅ/ያሬድ)

የአሮን ተአምራታዊ በትርም የመስቀል ምሳሌ

ናት። የአሮን ተአምራታዊ በትር በፈርዖንና

በመኳንንቱ ፊት በተጣለች ጊዜ ዕባብ ሆናለች፤

የግብፅ አስማተኞችም እያንዳንዳቸው በትራቸውን

በጣሉ ጊዜ የእነርሱም በትሮች ዕባብ ሆነው

ነበር። የአሮን በትር ግን የአስማተኞቹን ሁሉ በትሮ

ቻቸውን ለቃቅማ ዋጠቻቸው፤ እነርሱም

በሃፍረት ሸሹ ይላል። (ዘፀ. 7፥9-13)

ሁልጊዜ እንደሚነገረውም መስቀል በብሉይ

ኪዳን የመቅጫ፥ የርግማንና የውርደት ምልክት

ነበር። (ዘዳ. 21፥23፤ 2ቆሮ. 5፥21፤ ገላ. 3፥13)

ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት

በኋላ ግን የመንፈሳዊ ነፃነታችን አዋጅ የተነገ

ረበት ሰላማዊ ዙፋን ነው። (መዝ. 2፥6)

የመስቀልን ሃይማኖታዊ ይዘት በ3ት ከፍሎ

ማየት ይቻላል።

1. ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው ሃይማ

ኖታዊ ትርጕም

2. ከአማንያን ክርስቲያኖች አንፃር ሲታይ

3. መስቀል በቅዱስ ዕፅነቱ ሲታይ፥ የሚሉ ሲሆኑ፥

እነዚህም በእያንዳንዳቸው ሲተነተኑ እንደሚ

ከተለው ይቀርባሉ፦

መስቀል የጌታችንና የመድኃኒታችን

የኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ነው

መስቀል፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ

ሰው ልጅ ሕይወት ሲል ከጎልጎታ እስከ ቀራንዮ

አደባባይ ከዚያም እስከ ርደተ መቃብር የደረ

ሰበት ጽኑ መከራ በሙሉ «መከራ መስቀል» ይባ

ላል። ለሰው ልጆች ግን ሕይወት ሰጪ ነው።

የመስቀል ምሥጢራዊ ትርጕሙም መከራ ማለት

ነው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በበረት መወለዱ፥

በጨርቅ መጠቅለሉ፥ በብርድ መንከራተቱ

ሁሉ መስቀል ነው።

ወደ ግብፅ ተሰዶ እኛን ከስደተ ነፍስ መመ

ለሱና ሰይጣንንም ከሰዎች ልቡና ማሳደዱ

ትልቅ መስቀል ነው።

ጻድቀ ባሕርይ ሲሆን በአይሁድ ዘንድ ኃጥእ፥

ጊጉይ፥ ሰአሬ ሰንበት መባሉም መስቀል ነው።

መፍቀሬ ኀጥኣን አርከ መጸብሐን መባሉም ምስ

ጋና ይድረሰውና መስቀል ነው።

ከገጽ 1 የዞረ

መስቀልና ሃይማኖታዊ ይዘቱ

ወደ ገጽ 9 ዞሯል

Page 8: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 8 መስከረም 2007 ዓ.ም

የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ

ክርስቲያን ለሌሎች አድባራት በመልካም

አርአያነት የሚጠቀሰውን አሁን በመካሄድ

ላይ ያለውን ዘርፈ ብዙና መጠነ ሰፊ

የልማት ተግባር ሊያከናውን የቻለው የደ

ብሩ አስተዳደር ከአገልጋዮች ካህናት፣

በሥራ ላይ ካለው ከሰበካ ጉባኤውና ከልማት

ኮሚቴው አባላት ጋር ሰምና ወርቅ ሆኖ

በመሥራት እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ፣ እንደ

አንድ ልብ መካሪ በመሆን በጠቅላይ ቤተ

ክህነትና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ድጋፍ

ሰጭነት ከአዲስ አበባ መስተዳድር የይዞታ

ማረጋገጫ ካርታ አስወጥቶ የቦታውን ክብር

ለማስጠበቅና የጥፋት ምሽግነቱን ለማስቆም

በቅድሚያ ዙሪያውን በአጥር ማስከበር

አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአጥር ግንባታ

ፈቃድ በማስወጣት የልማት ሥራውን

ጀምሮ በርካታ የጥበቃ አባላትን በመ

ቅጠር፣

1. የደብሩን ዳር ድንበር ከወራሪ ለማዳን፣

2. መካነ መቃብሩን ከሌቦች ለመታደግ

ሌቦችን በመያዝ ለሕግ አስቀርቦ እያስ

ፈረደ በ2 በ3 ዓመት እሥራት በማስ

ቀጣት፣

3. የሌቦች መጠቀሚያ የነበረውን አፀዱንና

ሳሩን አስከብሮ በመጠቀም በየዓመቱ

ከብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በላይ

ለደብሩ ገቢ በማስገኘት፣

4. ቀደም ሲል የቦታው አንጋፋ ካህናትና

ሠራተኞች የተከሏቸውን የባሕር ዛፍ

ደኖች እንዲጠበቁ በማድረግ፣ ከዘራፊዎች

የተረፉት በሁለት ጊዜ ሽያጭ ከብር

200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ ብር)

በላይ ለደብሩ ገቢ በማስገኘት፣

5. የቤተ ክርስቲያኑ ቦታ ደንጋያማ በመሆኑ

ለቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈልጦ የተረ

ፈው አቹማ ደንጊያ የቀን ሐፋር፣ የሌሊት

ቁር ሲፈራረቅበት ወደ አፈርነት ከመ

ቀየሩ በፊት ተፈልጦ የቆየውንና ሳይፈለጥ

በመሬት ውስጥ የነበረውን ደንጊያ

በመሸጥ የሚገኘው ገቢ ለቤተ ክርስ

ቲያኑ አገልጋዮች ካህናትና ለደብሩ ሠራ

ተኞ ወቅታዊ ችግር መቅረፊያ ሆኖ

መቆየቱና ሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ

ተሹመው አስከመጡበት ጊዜ ድረስ

የደብሩ ካህናትና ሠራተኞ ወርሐዊ

ደመወዝ ብዙውን ጊዜ በብድር ይከፈል

እንደነበረም ተገልጿል፡፡

ከዚህም የተነሣ የደብሩ አስተዳደርና ሰበካ

ጉባኤ በ2006 የበጀት ዓመት ዕቅዱ የደብሩን

ችግር ለአንደየና ለመጨረሻ ጊዜ ቀርፎ

ለመጣል ባደረገው ከፍተኛ ጥረትና መጠነ

ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ በደብሩ ሰፊ ይዞታ

የተለያዩ የልማት ተግባራትን በመዘርጋትና

በመተግበር ቦታውን ለተወሰነ ጊዜ ለአልሚ

ድርጅቶችና ባለሀብት ግለሰቦች በማከራየት

በወር ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ

ብር) ለማስገባት አቅዶ ዕቅዱን ተግባራዊ

በማድረግ፣

1. የጊዜው ሁኔታ እየታየ በየሦስት ዓመቱ

የሚታደስ፣

2. ተዋዋዮቹ ድርጅቶች ወይም ባለሀብት

ግለሰቦች ለልማት ሥራ ለሚከፍቱት

ተቋም ወይም ለሚሠሩት ቤት ያወጡት

ወጭ ለደብሩ ከሚከፍሉት ወርሐዊ

ኪራይ የማይታሰብ፣

3. ተዋዋዮቹ ድርጅቶች ወይም ባለሀብት

ግለሰቦች የተዋዋሉበትም ሆነ የተኮ

ናተሩበት የጊዜ ገደብ ሲያልቅ ከተን

ቀሳቃሽ ንብረት በስተቀር የከፈቱትን

የሥራ ተቋም ወይም የሠሩትን ቤት

ለደብሩ በነጻ አስረክበው (ሰጥተው)

ሊለቁ (ሊሄዱ) ሕግ በሚፈቅደው መሠ

ረት የውል ሰነድ አዘጋጅቶ ወደ ሠላሳ

ከሚጠጉ የተለያዩ ድርጅቶችና ባለ

ሀብት ግለሰቦች ጋር በመፈራረም ለደብሩ

በወር ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ

ብር) የሚያስገኘው የልማቱ ሥራ ለተመ

ልካች ዕፁብ ድንቅ በሚያሰኝ ሁኔታ

በየዘርፉ በመጧጧፍ ላይ ይገኛል፡፡

በገቢ (በገንዘብ) እጥረት ምክንያት

ደብሩ ሳያከናውናቸው በቁም ቀሪ የነበ

ሩትም ተግባራት ሁሉ በየደረጃውና

በየመልኩ በመከናወን ላይ ናቸው፡፡

ይህም በመሆኑ ከአጥሩ ጋር ተያይዞ

ያለው የቤተ ክርስቲያኑ ዋና መግቢያ በር

ወይም አርክ የአስተዳደሩ ጽ/ቤትና ሌሎ

ችም ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች በመገ

ባደድ ላይ ሲሆኑ የቤተ ክርስቲያኑ ማስተር

ፕላንም በባለሙያዎች ተሠርቶ ስለተ

ጠናቀቀ ከጥቅምት አንድ ቀን 2007 ዓ.ም.

ጀምሮ ግቢውን የማስዋብ ሥራ ለመሥ

ራትና ቀጣይ ሥራዎችንም ለማከናወን ደብሩ

ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡

በአጠቃላይ የቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ

ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ይህን በመሰለው

ዘርፈ ብዙና መጠነ ሰፊ የልማት ተግባሩና

የላቀ ውጤቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተ

ዳደር በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት በኅብ

ረተሰብእ ተሳትፎ ልማት ኤጀንሲ ሰርተ

ፍኬት ተሰጥቶታል፡፡ ጠቅላይ ቤተ ክህነትና

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትስ እንዲህ ላሉት

ልማታዊ አድባራት ሰርተፍኬትና የማበረታቻ

ሽልማት መስጠት የሚጀምሩት መቼ ነው?

እንደዜና ቤተ ክርስቲያን እምነት መንግ

ሥት በምርት ዕድገታቸው ብልጫ ላሳዩ

አርሶ አደሮችና አምራች ድርጅቶች ድጎማ

ከማድረጉ ባሻገር የማበረታቻ ሽልማትና

ሰርተፍኬት እንደሚሰጥ ሁሉ ጠቅላይ ቤተ

ክህነትና የአዲስ አበበ ሀገረ ስብከትም

በራሳቸው ብልሃት አቅም ፈጥረው ለልማት

ሥራ ለሚንቀሳቀሱና ውጤት ለሚያሳዩ አድ

ባራትና ገዳማት ድጎማ ለመስጠት የአቅም

እጥረት ቢኖርባቸውም ራሳቸውን በራሳ

ቸው ለመሸለም ሲዘጋጁ ልዩ ልዩ ትርጉም

መስጠታቸውንና ማቅማማታቸውን ትተው

በየሽልማቱ መድረክ እየተገኙ መሸለምና

ማበረታታት ይገባቸዋል፡፡

ጠቅላይ ቤተ ክህነትና የአዲስ አበባ

ሀገረ ስብከት ማቅማማትና ርምጃ መውሰድ

የሚገባቸው ራሳቸውን ለመቻልና ለሌላ

ውም ለመትረፍ በሚፍጨረ ጨሩትና

ሠርተው በሚበሉት አድባራትና ገዳማት

ላይ ሳይሆን የቦዘነ ጉልበትና የተንጣለለ

ቦታ እያላቸው ቦታቸውን እያስወሰዱ ለዝንተ

ዓለም የጸሎተ ፍትሐት ገንዘብ እየተጠባበቁ

በሚኖሩትና የሙዳየ ምጽዋት ሳጥን እየሰበሩ

የእግዚአብሐርን ገንዘብ በመዝረፍ ሳይሠሩ

በሚበሉት አድባራትና ገዳማት ላይ እንጂ

ሠርተው በሚጠቀሙትና በሚጠቅሙት

አድባራትና ገዳማት ላይ አይደለም፡፡

ጌታችንም እኮ ርምጃ የወሰደው ወርቁን

በቀበረው በዚያ በሰነፉ ባለመክሊት እንጂ

ትርፋማዎቹን ባለመክሊቶችማ ሾሟቸዋል፡፡

‹‹ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋል፤ ላለው ይጨ

መርለታል፤ ለሌለው ግን ያንኑ ያለውን

ይወስዱበታል›› የሚለውም የቅዱስ መጽሐፍ

ቃል ይህንኑ የሚያጠናክር እንደሆነ ሊዘነጋ

አይገባውም፡፡

ስለዚህ እንዲህ እንደ ቦሌ ደብረ ገነት ቅዱስ

ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ያሉት ልማታዊ

አድባራትና አለቆች ሊመሰገኑና ሊበረታቱ

ይገባቸዋል፡፡ በተለይም እንደ ሊቀ ማእ

ምራን ጽጌ አበበ መልካም አስተዳደርን ያሰፈ

ኑትና ሠርተው ማሠራት የሚችሉት ትርፋማ

አለቆች በደብሩ ካህናትና ሠራተኞች መዋጮ

ይቅርና በደብሩ ገንዘብም ቢሆን ‹‹ኦ ገብርኄር

ወምእምን ዘበህዳጥ ምእመነ ኮንከ ባዕ

ውስተ ፍስሐሁ ለእኪእከ ዲበ ብዙኃ እሠይ

መከ›› ማለት አንተ በጥቂቱ የታመንክ አገልጋይ

በብዙ ላይ እሾምሃለሁና ና ወደ ጌታህ ደስታ

ግባ ተብሎ ሊመሰገንና ሊሸለም ይገባዋል፡፡

እንኳን ተሠርቶ ምንም ነገር ሳይሠራ ባለፉት

ሃያ ዓመታት ለልማት ሥራ ሊውል በሚገባው

በአድባራቱ ገንዘብ አልባሌ ሰዎች ለግላቸው

ሲሸላለሙበት እንደኖሩ የመንበረ ፓትርያርክ

የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ይመሰክራል፡፡

የሽልማቱ ሥነ ሥርዓት የተከናወነው

ነሐሴ 22 ቀን 2006 ዓ.ም. ሲሆን በሥነ

ሥርዓቱ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ

በመሆን ተገኝተው የአውቶሞቢሉን መኪና

ቁልፍ ለሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ ያስረከ

ቧቸው መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ

የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን

አስተዳዳሪ ናቸው፡፡

በዚሁ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ

ለሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ የሥራ ባል

ደረቦች ለሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ

መንበር ለመቶ አለቃ ተክለሃይማኖት ነገሠና

ለሌሎች አባላት፣ ለደብሩ ዋና ጸሐፊና

ምክትል ጸሐፊ፣ ለሂሳብ ሹሙና ለቁጥጥር

አገልግሎት ኃላፊ ለአገልግሎታቸው ማበረታቻ

የገንዘብና የቁሳቁስ ሽልማት የተደረገላቸው

ሲሆን የደብሩ ዋና ጸሐፊ ቀሲስ ጌታሁን

ወልደ አብ የተሰጣቸውን የ15000.00 /

አሥራ አምስት ሺህ ብር/ የገንዘብ ሽልማት

ለደብሩ የልማት ሥራ ማጠናከሪያና ማስ

ፋፊያ መልሰው ለግሰዋል፡፡

መልአከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ የመኪና

ቁልፉን ካስረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር

ሽልማት የጽኑእ ፍቅርና የሥራ ውጤት መግ

ለጫ መሆኑን ጠቅሰው ሊቀ ማእምራን ጽጌ

አበበ ለዚህ ዓይነቱ ሽልማት የበቁት በእው

ቀታቸው፤ በመልካም አስተዳዳሩነታቸውና

ሠርቶ በማሠራት ክሂሎታቸው መሆኑን

በማስገንዘብ ወደፊትም ባገኙት የሞራል

ድጋፍ በመበረታታት ለቤተ ክርስቲያን

የበለጠ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚተጉ

ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም ተሸላሚው ሊቀ ማእምራን

ጽጌ አበበ ባደረጉት ንግግር የተደረገላቸው

ሽልማት የደብሩ ካህናትና ሠራተኞች እንዲሁም

የሰበካ ጉባኤና የልማት ኮሚቴው አባላት

የፍቅር መግለጫ መሆኑን አውስተው እግዚ

አብሔር ባስቻላቸውና አቅማቸው በፈቀደ

መጠን የተጣለባቸውን እዳ ለመክፈል

ከአለፈው በበለጠ አገልግሎት ለመስጠት

እንዲተጉ ሽልማቱ እንደሚያበረታታቸውና

እንቅልፍ እንደሚነሳቸው በመግለጽ የደብሩ

ካህናትና ሠራተኞች ላደረጉላቸው ሽልማትና

አክብሮት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ቀደም ሲልም የደብሩ የልማት ኮሚቴ

ሊቀ መንበር አቶ ካሱ በርሄና የልማቱ ዋና

ጸሐፊ አቶ አለበል ከበደ በተከታታይ ባደ

ረጉት ንግግር ሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ

ባላቸው ሰፊ መንፈሳዊ ዕውቀት ለምእመናን

በሚሰጡት አርኪ ትምህርት፣ በአስተዳደር

ክሂሎት፣ በሥራ ብቃትና ትጋት፣ ብሎም

ከደብሩ ካህናት፣ ከሰበካ ጉባኤውና ከልማት

ኮሚቴው አባላት ጋር በሚያደርጉት መግባ

ባትና መናበብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ደብሩን

የልማት አርአያ ለመሆን እንዳበቁት፤ እሳ

ቸውም ለሽልማት እንደበቁና ያለእሳቸው

ደብሩ ከዚህ ዓይነቱ እመርታ ላይ ሊደርስ

የማይችል እንደነበረ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ለሽልማቱ ድጋፍ ሰጭ የሆነ

ቅኔና መዝሙር በደብሩ ካህናትና የሰንበት

ት/ቤት ዘማርያን ቀርቧል፡፡

ከገጽ 1 የዞረ

የቦሌ ደብረ ገነት...

ሊቀ ማእምራን ጽጌ አበበ ከተሸለሟት መኪና ጋር

Page 9: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 9 መስከረም 2007 ዓ.ም

ከገጽ 7 የዞረ

በደርግ ተወርሰው የነበሩ...

ከገጽ 7የዞረ

መስቀልና ሃይማኖታዊ ይዘቱ

ጨርቅ መታጠቁ፥ ግንድ መሸከሙ፥ የአይሁድን

ስድብና ፌዝ መታገሱም ትልቅ መስቀል ነው።

በአጠቃላይ ስለ እኛ የተቀበለው ፀዋትወ

መከራ ሁሉ መስቀል ነው። ቅዱስ ጳውሎስም

ከዚህ በመነሣት «እስመ ነገረ መስቀሉ እበድ ውእቱ

በኀበ ኅጉላን ወበኀቤነሰ ለእለ ድኅነ ኃይለ እግዚ

አብሔር ውእቱ» - የመስቀሉ ነገር (የክርስቶስ

መከራ የመቀበሉ ነገር) ለሚጠፉት ሞኝነት

ነው፥ ለእኛ ለምናምን ግን የእግዚአብሔር

ኃይል ነው» ይላል። (1ቆሮ. 1፥18)

አያይዞም በገላትያ መልእክቱ በአብርሃም

አባትነትና በግዝረታችን እንድናለንና የክርስቶስ

ሞት ምንም አያደርግልንም ለሚሉት ቢጽ ሐሳ

ውያን ላይ «ወአንሰ ሐሰ ሊተ ኢይዜኀር ዘእንበለ

በመስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ» - እኔስ በጌታችን

በኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀል እንጂ በሌላ

አልመካም ብሎአቸዋል። (ገላ 6፥14)

ሐዋርያው በኤፌሶን መልእክቱም «ገብረ

ሰላመ በመስቀሉ» - ክርስቶስ ሰላምን፥ ነፃነትን

በመስቀሉ አደረገ ብሎአል (ኤፌ. 2፥15-17)።

እነዚህ ከዚህ በላይ የተመለከትናቸው የጌታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀልን ከሚያስታውሱ

መካከል ናቸው።

በዚህም መሠረት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን

የክርስቶስን ቤዛነት በመስቀል የተፈጸመውን

መከራ ለምእመናን ሕይወት መሆኑን በማመን፡

መስቀል ኃይልነ

መስቀል ጽንዕነ

መስቀል ቤዛነ

መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ

ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ

ድኅነ» እያለች ትዘምራለች፥ ትጸልያለች።

ይህ የክርስቶስ መከራ ዘወትር በልብ የሚታሰብ

እንጂ በዓይነ ሥጋ የሚታይ አለመሆኑንም «አኮ

ከመ ይትረአይ አላ ከመ ይትኀለይ ውእቱ ዝንቱ

መስቀል» (መጽሐፈ ኪዳን)። ስለዚህ የጌታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማሙንና ሞቱን እያሰብን

እንደ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ከልብ ልንጸና

ይገባል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድም

መድኃኒት ስለሆነው ስለጌታ መስቀል (ሞት)

ሲናገር «ዝንቱ መስቀል በአማን ዕጸበ ያቀልል ...

ኃይልነ ወጸወንነ ወሞገስነ - ይህ መስቀል

ሞገሳችን፥ ኃይላችን፥ መጠጊያችን የሆነ በእው

ነት ጭንቅን ያቀላል» ብሎታል፤ አያይዞም «በመ

ስቀሉ ኃይል መድኃኒትን አደረገ፥ አጋንንትን

አሳደደ፥ ሙታንን አስነሣ፥ የታሠሩትንም ፈታ»

ይላል።

እንዲሁም «በመስቀሉ አርኀወ ገነተ» - በመ

ስቀሉ ገነትን ከፈተ አለ። በተጨማሪም «መድኃ

ኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉና በቃሉ

ሰላምን አደረገልን፥ የተበተነውንም በመስቀሉ

አንድ አድርጎ ሰበሰበን፥ ሕይወትም ሆነን» ብሎ

አል።

«መስቀል ለምናምን ለእኛ ረድኤትና ሕይወት፥

ለአይሁድ ግን ስደት ነው» በማለት ምሥጢሩንም

አብራርቶ ዘምሯል።

መከራ መስቀልና አማንያን ክርስቲያኖች

መከራ መስቀል በክርስቲያኖች ዘንድ ሲታይ

የሚለውና በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ንኡስ

ክፍል ክርስቲያኖች በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

አዳኝነት በፍጹም ልባቸው አምነው ከበቁ

በኋላ፦

በሐዋርያነት ወንጌልን በመስበክ እስከ ሞት

መድረስ

በሰማዕትነት በዓላውያን ነገሥታት ፊት ልዩ

ልዩ ፀዋትወ መከራ በመቀበል መመስከር

በተባሕትዎ በበረሓ ወድቆ ደንጊያ ተንተርሶ፥

ጤዛ ልሶ፥ ዋሻ ዘግቶ ፀብአ አጋንንትን ግርማ

ሌሊትን ሳይሣቀቁ መኖር ራሱ መከራ

መስቀል መሆኑን ቅድስት ቤተ ክርስ

ቲያናችን ታምናለች።

ከማመንዋም በመነሣት ተጋድሎአቸውን

ታነሳሣና በመጨረሻውም «ወኵሎሙ ለባስያነ

መስቀል - እነዚህ ሁሉ መከራ መስቀልን እንደ

ሸማ የለበሱት ናቸው» ትላቸዋለች። (በቅዳሴ)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም

ለዚህ ጉዳይ ርእስ ሰጥቶ «ዘኢያጥብአ ወዘኢነሥአ

መስቀለ ሞቱ ወዘኢተለወ ድኅሬየ ኢይደሉ ሊተ

- ጨክኖ ነፍሱን ከሥጋው የሚለይበትን መከራ

ተቀብሎ በመከራው ካልመሰለኝ የእኔ ደቀ መዝ

ሙር ሊባል አይገባውም» ብሎታል (ማቴ. 10፥38)።

እንዲሁም በማርቆስ ወንጌል 8፥34-36 ላይም

«እኔን ማገልገል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፥

መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ» በማለት አስረ

ድቶአል። እዚህ ላይ ማስተዋል ያለብን መስቀሌን

ተሸክሞ ይከተለኝ፥ አላለም፤ መስቀል ያለው

አማንያን የሚቀበሉት መከራ ነው እንጂ፤ የጌታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀል አለመሆኑን

ለመግለጽና በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑንም

በቃሉ አስረድቶናል።

እንዲህ ስለሆነም የእነ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ

ጴጥሮስ ቁልቁል መሰቀል፥ የእነ ብርሃነ ዓለም

ቅዱስ ጳውሎስ በሰይፍ መመታት፥ የእነ መክብበ

ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጋዝ መመገዝ

(መነተፍ)፥ አጠቃላይ የቅዱሳን ሁሉ ልዩ ልዩ

ጸዋትወ መከራ መቀበል፥ መከራ መስቀል ይባላል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ከዚህ በመነሣት

ነው «ወኵሎሙ ለባስያነ መስቀል» ያለቻቸው።

በዘመናችንም ስለ እውነተኛ ሃይማኖት ብለው

በሕይወታቸው ላይ መከራ መስቀል የሚሸከሙ

አሉ? የሉም? መልሱ፦ እንደ ነቢዩ ኤልያስ

መልስ እንዳይሆንብን፤ ይኖራሉ ስለመኖራቸው

ማወቅ የሚችለው ግን «ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ

በርትዕ» የሆነው እውነተኛው የቅዱሳን አምላክ

ብቻ ነው።

መስቀል በቅዱስ ዕፅነቱ ሲታይ

«ወበእንተ ኃጣውኢነ ውእቱ ተሰቅለ ዲበ

ዕፅ በሥጋሁ - ስለእኛ ኃጢአት እርሱ በሥጋው

በዕንጨት (በዕፅ) ላይ ተሰቀለ» ይለናል።

(1ጴጥ. 2፥24) በዕፀ መስቀል ላይ በአፈሰሰው

ክቡር ደሙ ሰላምን አደረገ ብሎአል።

አንዳንድ የዕፀ መስቀል ትርጕም ያልገባቸው

ሰዎች፦

በመጽሐፈ ኪዳን «እንዲታሰብ እንጂ እንዲታይ

አይደለም» ይላልና፥ እንዴት የሚታይ መስቀል

ትይዛላችሁ ይላሉ። ከላይ እንደ አተትነው

የሚታሰብ እንጂ የሚታይ አይደለም የተባለው

ምስጋና ይድረሰውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

መከራ እንጂ ስለ ዕፀ መስቀል አለመሆኑን

ለሚጠራጠሩ በደንብ ልናስረዳቸው ይገባል።

ዕፀ መስቀሉን አክብረንና ከልብ አፍቅረን

ስለምንስመውና ስለምንሳለመውም በውል

ትርጕሙን ሳይረዱ፥ የአባታችሁ ደም የፈሰ

ሰበትና የሞተበትን መሣሪያ እንዴት ትሳለ

ሙታላችሁ፥ ታከብሩታላችሁ ይላሉ። ያለማስ

ተዋላቸው እንጂ ሲጀመር ጀምሮ በመስቀል

ላይ የሞተው ማን ነው? በመስቀል ላይ

የሞተውማ መርገማችንና የጥንተ ጠላታችን

የዲያብሎስ ኃይል የተሻረበት መሆኑ ቅዱሳት

መጻሕፍት ያስረዳሉ።

እነዚህ አፅራረ መስቀል ግን ቢያውቁማ ኖሮ

ዕፀ መስቀሉን የምናከብረው ጌታችን መድኃኒታችን

ኢየሱስ ሊቀ ካህናት ሆኖ ያገለገለበት መቅደሱ

ነው። «ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ ወመሥዋዕተ

ሥሙረ - ተመሳሳይ የሌለው የሠመረ መሥዋዕት

ሆኖ ራሱን ለአባቱ መሥዋዕት ያሣረገበት ነው

(ቅዱስ ኤፍሬም)። በግ ሆኖ ስለእኛ ራሱን

ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሠዋበት ምሥዋዕ

(መንበር) በመሆኑና ቅዱስ ደሙም ስለፈ

ሰሰበት፥ መርገማችንም ስለተሻረበት እናከብረዋለን።

ከዚህ የበለጠ ሊከበር የሚገባውም ነው፤

ሊከበርም ይገባዋል።

እነዚህ ባለመታደል በዕፀ መስቀሉ ላይ የሚጠ

ራጠሩት ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ እያለ

ያጋልጣቸዋል «እስመ ብዙኃን እለ የሐውሩ

ሑረተ ካልአ ዘከመ እብለክሙ ዘልፈ ወይእዜኒ

ገሃደ እነግረክሙ ከመ እሙንቱ ጸላእቱ ለመ

ስቀለ ክርስቶስ» - ዘወትር እንደምነግራችሁ በልዩ

አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና አሁንም የክር

ስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደሆኑ በግልጥ

እነግራችኋለሁ። (ፊልጵ. 3፥18-19)

የጽሑፉ ዓምድ ያጥረናል እንጂ ስለ መስቀል

ሁለመናው ሃይማኖታዊ ይዘቱና ምሥጢራዊ

ክብሩ መነሻ በማድረግ ያልጻፈ ሐዋርያ፥ ያላብራራ

ሊቅ የለምና ብዙ መጻፍ ይቻል ነበር። ከጊዜ

አኳያ ግን፦

1ኛ) መስቀል ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለው

ግንኙነት

2ኛ) መስቀል ከአማንያን ክርስቲያኖች አንፃር

ሲታይ

3ኛ) መስቀል በቅዱስ ዕፅነቱ ሲታያ፥ በሚሉ

በሦስቱ ርእሶች የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን

መሠረት በማድረግ ከዚህ በላይ አትተን

አቅርበናል።

ስለዚህ መስቀል በሃይማኖታዊ ይዘቱ ስናየው

መስቀል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

ጠላት ዲያብሎስን ድባቅ የመታበት ቅዱስና

ልዩ የድል መንሻ የሃይማኖት መሣሪያችን ነው።

እነዚህ በመስቀል ላይ የሚጠራጠሩ ግን የቅዱስ

መስቀል ገባሬ ተአምርነቱን ካለማመናቸው የተነሣ

ዕፅ ሲሆን እንዴት ይህን ያህል ተአምር ያደርጋል

ይላሉ። አልገባቸውም እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ

ተራ ግዑዝ ዕቃ የሆኑ ብዙ ተአምር እንደ አደረጉ

በመጽሐፍ ተጽፎአል። ለምሳሌ፦

የሊቀ ነቢያት ሙሴ በትር ቀይ ባሕርን ከፍሏል፥

(ዘፀ. 14፥21)

የነቢዩ ኤልያስ መጠምጠሚያ የዮርዳኖስን

ወራጅ ውኃ አቁሞአል፥ (2ነገ. 2፥19)

የብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ሰበን (ልብስ)

ጋኔን አውጥቶአል፥ (የሐዋ. ሥራ 19፥11-20)

የሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ ጥላ ብዙ

ሕሙማን ፈውሶአል። (የሐዋ. ሥራ 5፥15-

16)

ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ

ቀሚስም ለ12 ዓመት ይፈስ የነበረውን ደም

አቁሞአል። ምስጋና ይግባውና የተቸነከረበትና

በደሙ ፈሳሽነት ያጠበው ቅዱስ ዕፀ መስቀልም

ዕውር ቢያበራ፥ ሙት ቢያስነሣ፥ ሕሙማንን ቢፈ

ውስ የሚያስደንቀው የት ላይ ነው? ሲሉአቸው

መልስ የላቸውም። በሁሉም ዘንድ ተአምር በማ

ድረግ የሚሠራው ራሱ አምላክ ነውና በሚደረገው

ተአምረ መስቀልም ልናምን ይገባል። እነዚህ

በመስቀል ላይ የሚጠራጠሩም በቀና ልቡና

ሊያምኑ ይገባል። እንደሚሉት ዕፅ ቢሆንም

አምላካዊ ኃይል ያለበት ስለሆነ ይህን ገባሬ

ተአምርነቱ ከልብ ሊገነዘቡት ይገባል እንላለን።

ማጠቃለያ

መስቀል የሲኦል መሠረት የተናወጠበት፥

ሰውና እግዚአብሔርንም ለዘመናት ለያይ

ቶአቸው የነበረው የጠብ ግድግዳ የተናደበት፥

ሞት ድል የሆነበት፥ የትንሣኤ መንገድ

የተከፈተበት ልዩና ቅዱስ የሆነ የድል አርማና

መሣሪያ ነው።

ስለዚህ መስቀል ለምእመናን የነፃነታቸው፥

የዕርቃቸውና የሰላማቸው ልዩ ምልክት በመሆኑ

ለመስቀል ልዩ ክብርን ይሰጣሉ፤ ይሰግዱለታልም።

ማንኛውንም ተግባር ማለት ጸሎትን፥ ምግብን፥

ጉዞን ከመጀመራቸው በፊትና ከጨረሱም በኋላ

በትእምርተ መስቀል ያማትባሉ። በፈተና፥ በኀዘንና

ክፉ ሐሳብ በሕሊናቸው በተፈጠረ ጊዜም ሁሉ

በከበረ ደሙ የቀደሰው ጌታቸውም በመስቀሉ

ኃይል ሊያደርግላቸው እንደሚችልም በመታመን

ይህን ያደርጋሉ።

መስቀል ሕይወትን ሊያጠፉ በተነሡ ጠላቶች

ቢዘጋጅም ቅሉ በእርሱ አዲስና ዘለዓለማዊ

ሕይወት ተዘጋጅቷል። «እምከመ ተለዓልኩ

እምድር እስህብ ኵሎ ኀቤየ» - ከምድር ብቅ፥

ከሰማይ ዝቅ ብዬ በተሰቀልኩ ጊዜ ሁሉን ወደ

እኔ እስባለሁ በማለት ራሱ ባለቤቱ ጌታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደገለጸው በመስቀሉ

የሰውን ልጅ ወደራሱ አቅርቦታል። በተመሳሳይ

መንፈስም በመስቀልህ በፈጸምከው መሥዋ

ዕትነት ወደ ባሕርይ አባትህ (ወደ እግዚአብሔር

አብ) አቀረብከን፥ ከእርሱም በአንተ አማካይነት

ዕርቅና ሰላምን እንድናገኝ አደረከን።

በዚህም መሠረት፡

መስቀል የክርስቲያኖች ተስፋ ነው

መስቀል የሙታን ትንሣኤ ነው

መስቀል የዕውራን መሪ ነው

መስቀል ትንቢተ ነቢያት ነው

መስቀል ስብከተ ሐዋርያት ነው

መስቀል ክብረ ሰማዕታት ነው

መስቀል የጻድቃን ሞገስ ነው

መስቀል የመነኰሳት ጽሙና ነው

መስቀል የደናግል ንጽሕና ነው

መስቀል የቤተ ክርስቲያን መሠረትና ጉልላት

ነው

መስቀል የዓለም መረጋጋትና ሰላም ነው።

ለሁሉም የዓለም መድኃኒት ጌታችን መድኃ

ኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኃይለ መስቀሉ

ይጠብቀን፤ አሜን።

አቅራቢ

ርእሰ ደብር መሐሪ ኃይሉ

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ሽልማቱን ከሰጡ

በኋላ የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆ

ኑትን ሕንጻዎች ለማስመለስ ወጥተው ወርደው

ተጨባጭ ውጤት ላስገኙ ለእነዚህ አባቶች መሸ

ለም ተገቢ ነው፡፡ እናንተ የዛሬ ተሸላሚዎችም

ለቤተ ክርስቲያናችሁ ላበረከታችሁት የላቀ አስተ

ዋጽኦ እግዚአብሔር ይባርካችሁ በማለት ሸላሚው

ድርጅትንና ተሸላሚዎችን ባርከዋል፡፡

በሽልማቱ ሥነ ሥርዓት መጀመሪያ አቶ ተስፋዬ

ውብሸት የቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደርና ልማት

ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ባሰሙት ገለጻ

በአሁኑ ጊዜ የቤተ ክርስቲያናችን የጀርባ ዐጥንት

በመሆንና በዓመት ከሃያ ስድስት ሚሊዮን ብር

በላይ ለቤተ ክርስቲያናችን ገቢ በማስገኘት ያሉ

ሕንጻዎችን ለማስመለስ በተደረገው እንቅስቃሴ

ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አባቶች እውቅና

የምንሰጥበት ቀን ነው ካሉ በኋላ ሽልማቱ በገን

ዘብ ሲተመን እዚህ ግባ የማይባል ቢሆንም የሽል

ማቱ ዋና ዓላማ ቤተ ክርስቲያናችን የእነዚህን

አባቶች ውለታ ያልረሳች መሆንዋን የሚያመለክት

በመሆኑ ትርጒሙ ታላቅ ነው ብለዋል፡፡

Page 10: 550099 Ext.47 1283 · 2014. 9. 29. · ሠናይ እገሪሆሙ ለእለ ይዜንዉ ሠናየ ዜና፡፡ መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት

ዜና ቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ 10 መስከረም 2007 ዓ.ም

የ ዐባይንና የኢትዮጵያን ትስስር ለማወቅ

አንዱና ዋናው ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዐባይ የምታስተ

ምረውን ትምህርት መመርመር ነው። ዐባይ

በመጽሐፍ ቅዱስ፥ በሊቃውንት ትምህርት፥

በታሪክና በትውፊት ከፍተኛ ትኩረት የተሰ

ጠው ወንዝ ነው። ይህ ጽሑፍ የዐባይንና የኢት

ዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን

ትስስር የሚያትት አጭር ጽሑፍ ነው።

ዐባይ በመጽሐፍ ቅዱስ ከተጠቀሱ ዐራት

ታላላቅ ወንዞች አንዱ ነው

«ዐባይ» የሚለው የግእዝ ቃል ታላቅ ማለት

ነው፤ ቃሉ የወንዙን ታላቅነት የሚያመለክት

ሲሆን፥ ወንዙ በታላቅነቱ በኢትዮጵያዊው ስሙ

ዐባይ ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ «ግዮን»

ተብሎ የሚጠራው ከዐራቱ አፍላጋት (ወንዞች)

ሁለተኛው ወንዝ ዐባይ (ግዮን) የኢትዮጵያ

የተፈጥሮ ስጦታ ሆኖ ከእግዚአብሔር እንደ

ተሰጠን ከመጽሐፍ ቅዱስና ከታሪክ መረዳት

እንችላለን።

ዐራቱ አፍላጋት የሚባሉት ኤፌሶን፥ ግዮን፥

ጤግሮስና ኤፍራጥስ ናቸው። ከቅዱሳት መጻሕፍት

ስለ ዐባይ (ግዮን) በመግለጽ ቀዳሚት የሆነችው

ኦሪት ናት። በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 2 ቍጥር

11-14 እንደሚከተለው ተጽፎ ይገኛል። «ወንዝም

ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም5 (ዔደን) ይወጣ

ነበር፤ ከዚያም ለዐራት መዓዝን ይከፈል ነበር።

የአንደኛው ወንዝ ስም ኤፌሶን ነው፤ እርሱም

ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፤

የዚያች ምድር ወርቅ ጥኑ ነው፤ በዚያም የሚያበራ

ዕንቍና የሚያብረቀርቅ ዕንቍ አለ። የሁለተኛው

ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን

ምድር ሁሉ ይከብባል (ያጠጣል)። የሦስተኛውም

ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሶር ላይ

የሚሄድ ነው። ዐራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ

ነው።»

ከዚህ ንባብ የሚከተሉትን ነጥቦች መገንዘብ

ይቻላል፤ እነዚህም፦

አንድ ወንዝ ከዔደን ገነት ይመነጫል

ይህ ወንዝ ለዐራት ይከፈላል

ኤፌሶን የኤውላጦንን ምድር፥ ግዮን የኢት

ዮጵያን ምድር፥ ጤግሮስ የአሶርን ምድር

ዞረው የሚያጠጡ ሲሆን አራተኛው ወንዝ

ኤፍራጥስ በየትኛው የምድራ ችን አካባቢ

እንደሚፈስስ አልተገለጠም።

የአንድምታ ትርጓሜ መምህራን ይህን ንባብ

ሲተረጕሙ የኤፌሶን ወንዝ የሚያጠጣው «ምድረ

ኤውላጦን» ምድረ ጽርእ እንደሆነ፥ ኢትዮጵያን

የሚከብበው የግዮን ወንዝ ዐባይ እንደሆነ፥ ጤግ

ሮስም የፋርስን ሀገር ዞሮ የሚያጠጣ እንደሆነ፥

በኦሪቱ ገጸ ንባብ በየትኛው የዓለማችን አካባቢ

እንደሚፈስስ ያልተገለጠው የኤፍራጥስ ወንዝ

ደግሞ ህንድን ዞሮ የሚያጠጣ ወንዝ እንደሆነ

ገልጸዋል።

ግእዝ በግእዝ የተዘጋጀው ትርጓሜ ኦሪት

ደግሞ «እምኤፌሶን ወየሐውር ውስተ ዐረብ

ወየዐውድ መንገለ ሰሜን ወይሰቅያ ለምድረ

ህንድ ወቦ እለ ይቤሉ ባሕረ እልጎንድ ውስቴቱ

ዕንቍ ወግዮንኒ ውእቱ እልኔል (ዘውእቱ ኔል)

ወይዌጥን እምሥራቀ አዜብ ወይሰቅዮሙ ለኢት

ዮጵያ ወለግብፅ ወይበጽሕ እስከ ባሕረ ዐረብ

ወጤግሮስኒ ይዌጥን እምድረ አርመን ሉዓላዊ

ወየኀልፍ በፋርስ ወይበጽሕ እስከ ባሕረ አዜብ

ወዝንቱ ፈለግ ደቂቅ ወረቂቅ ወኤፍራጥስ ይዌጥን

እምነ አርመን ታሕታዊ ወይበጽሕ እስከ ባሕረ

ባስራ ወይክዑ ማዩ እስከ አዜብ ወእሎንቱ

ክልኤቱ አፍላጋት ይንእሱ እምእልክቱ ክልኤቱ

አፍላጋት» ወደ አማርኛ ሲመለስ፦ «አንደኛው

ወንዝ ከኤፌሶን (ኤፌሶን) ነው፤ ወደ ምዕራብም

ይሄዳል፤ ወደ ሰሜንም ይመለሳል፤ የህንድንም

ምድር ያጠጣል፤ እስከ ሕንድ ባሕርም ይደርሳል

(ወደ ሕንድ ባሕር ይገባል)፤ «ባሕረ ሕንድ»

ማለት ባሕረ እልጎንድ ነው የሚሉ አሉ፤ በዚህ

ወንዝ ሸለቆም ዕንቍ ይገኛል። ግዮን የተባ

ለውም እልኔል (ኔል) ነው፤ ከአዜብ ምሥራቅ

ተነሥቶ ኢትዮጵያንና ግብፅን አጠጥቶ ወደ

ምዕራብ ባሕር ይገባል። ጤግሮስም ከላይኛው

አርመን ተነሥቶ በፋርስ ያልፍና እስከ አዜብ

(ደቡብ) ባሕር ይደርሳል (ከደቡብ ውቅያኖስ

ይጨመራል)፤ ይህም ወንዝ ትንሽና ቀጭን

ነው። ኤፍራጥስም ከታችኛው አርመን ተነሥቶ

እስከ ባስራ ባሕር ይደርሳል፤ ውኃውም እስከ

አዜብ ይፈስሳል፤ እነዚህ ሁለት ወንዞች (ጤግ

ሮስና ኤፍራጥስ) ከሁለቱ ወንዞች (ከኤፌሶንና

ግዮን) ያንሳሉ» ማለት ነው ይላል።

ግእዝ በግእዝ ትርጓሜ ኦሪት ስለ ዐባይ

ሦስት ነጥቦችን ግልጽ አድርጎልናል፤ እነዚህም፦

1. በመጽሐፍ ቅዱስ ግዮን፥ በግእዝ ዐባይ የሚ

ባለው ወንዝ «እልኔል» ወይም ኔል ተብሎ

እንደሚጠራ ያሳያል፤ እልኔል ወይም ኔል

ማለት ደግሞ ናይል ከሚለው የዐባይ ስም

ጋር አንድ ነው። እልኔል (ኔል) ማለት ቀለም

ማለት ሲሆን ጥቁር ዐባይ ጥቁር ኔል፥ ነጭ

ዐባይ ደግሞ ነጭ ኔል ተብለው ይጠራሉ።

2. ዐባይ ኢትዮጵያንና ግብፅን የሚያጠጣ ወንዝ

ነው፤ በእርግጥ ዐባይ የሚያጠጣ ቸው

የአፍሪካ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ከ10 ያላነሱ

ናቸው፤ በዋናነት ግብፅ፥ ሱዳንና ኢትዮጵያ

በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሀገራት ናቸው፤ ይህ

የሚያመለክተን ደግሞ ግብፅ ዐባይ የእኔ

ብቻ ነው ብላ አንድ በመቶ እንኳን

በማታመነጭበት ውኃ ብቻዋን መጠቀም

ስትፈልግ ዐባይ ከኢትዮጵያ እንደሚመነጭ

የሚያውቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ቤተ ክርስቲያን መምህራን ግን «ዐባይ ኢትዮ

ጵያንና ግብፅን ያጠጣል» ብለው ለሁለቱም

ሀገራት ጥቅም የሚበጅ ትምህርትን ሲያስ

ተምሩ የኖሩ መሆኑን ነው። ይህም ለግብፅ

ሊቃውንት አስተማሪ የሆነ ተግባር ነው

የሚል እምነት አለን።

3. ዐባይና ኤፌሶን ከጤግሮስና ከኤፍራጥስ

የሚበልጡ ታላላቅ ወንዞች ናቸው። ግዮን

በኢትዮጵያውያን ዘንድ ዐባይ ተብሎ የተጠ

ራበት ዋና ምክንያት የዚህን ወንዝ ታላቅነት

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ

ክርስቲያን መምህራን ሲያስተምሩ ስለኖሩ

ነው፤ ይህም የወንዙን ታላቅነት በመረዳት

ነበር። ስለዚህ የዐባይ ወንዝ በኢትዮ

ጵያውያን ልብ ውስጥ ታላቅ ቦታ እንዲ

ኖረው ለማድረግ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ

ሚና መጫወቷን ያሳያል።

ዐባይ ውኃ ብቻ ሳይሆን ወተትም ነው

የሥነ ፍጥረትን ነገር በስፋት የሚናገረውና

አክሲማሮስ ተብሎ የሚታወቀው መጽሐፍ

ዐራቱ አፍላጋት (ኤፌሶን፥ ግዮን፥ ጤግሮስና ኤፍ

ራጥስ) እንደ መስቀል ተመሳቅለው ገነትን ያጠ

ጣሉ (ከምሥራቅ የሚመነጨው ወደ ምዕራብ፥

ከምዕራብ የሚመነጨው ወደ ምሥራቅ፥ ከሰሜን

የሚመነጨው ወደ ደቡብ፥ ከደቡብ የሚመ

ነጨው ወደ ሰሜን እየፈሰሱ ገነትን ያጠጣሉ)።

በገነት ሳሉ ኤፌሶን ወይን፥ ግዮን ወተት፥

ጤግሮስ መዓር፥ ኤፍራጥስ ደግሞ ዘይት ናቸው።

ወደዚህ ዓለም ሲመጡ ንጹሕ ውኃ ይሆናሉ።

ወደዚህ ዓለም መጥተው ግዮን የኢትዮጵያ

ውኃ ናት፥ ኢትዮጵያን ዙራ ታጠጣለች፤ ኤፌሶን

የአንጾኪያ ውኃና ናት፥ አንጾኪያን ዙራ ታጠጣለች፤

ጤግሮስ ደግሞ የቁስጥንጥንያ ውኃ ናት፥ በቁስ

ጥንጥንያ ትዞራለች ይላል። እንደ አክሲማሮስ

ገለፃ፦

ሀ) ኦሪቱ «ኤውላጦን» ያለው ፈለገ ኤፌሶን የሚፈ

ስስበት ሀገር አንጾኪያ

ለ) ኦሪቱ «አሶር» ያለው ፈለገ ጤግሮስ የሚፈስ

ስበት ሀገር ቁስጥንጥንያ

ሐ) በኦሪቱ ባይገለጥም የኤፍራጥስ ወንዝ

የሚፈስስበት ሀገር ሮም ሲባሉ

መ) ግዮን የተባለው ዐባይ የሚከብባትና የሚያ

ጠጣት ሀገር ኢትዮጵያ መሆንዋ በግልፅ

ተቀምጧል (ተጠቅሷል)።

እንደ አክሲማሮስ አገላለጥ ዐራቱ አፍላጋት

ውኃ ብቻ ሳይሆኑ «ወይን፥ መዓር፣ ወተትና

ዘይት» ናቸው፤ ይህም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን

መምህራን ዘንድ ለእነዚህ ዐራት ታላላቅ ወንዞች

ያለውን ክብር ያሳያል። ትርጓሜ ወንጌልም በተመ

ሳሳይ መልኩ ፈለገ ወይን የተባለው ኤፌሶን

የማቴዎስ ወንጌላዊ፥ ፈለገ ሀሊብ የተባለውን

ግዮን የማርቆስ ወንጌላዊ፥ ፈለገ መዓር የተባለውን

ጤግሮስ የሉቃስ ወንጌላዊ፥ እንዲሁም ፈለገ

ዘይት የተባለውን ኤፍራጥስ የዮሐንስ ወንጌላዊ

ምሳሌዎች እንደሆኑ ይናገራል። ይህም ማለት

እግዚአብሔር በእነዚህ ዐራት አፍላጋት ዓለምን

በምግበ ሥጋ እንደሚመግብ ሁሉ በአራቱ ወንጌላ

ውያን ዐራት ክፍል ሆና በተጻፈች ቅድስት

ወንጌል ዓለምን በመንፈሳዊ ሕይወቱ የሚ

መግብ መሆኑን ለመግለፅ ነው። አንድ ወንጌል

በዐራት ወንጌላውያን ተከፍላ እንደተጻፈች ሁሉ

አንድ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር የሚመነጭ

ወንዝ ለዐራት ተከፍሎ ዓለምን ተዘዋውሮ

ማጠጣቱን (መመገቡን) መምህራኑ ይገልጣሉ።

ዐባይ የብርሃን ወንዝ ነው

በቅዳሴ አትናቴዎስ ስለ ዐራቱ አፍላጋት

የተጻፈው እንዲህ ይላል፦ «የገነት ጠባቂዋ መልአክ

ሆይ፥ ገነትን የሚያጠጡ የብርሃን ወንዞችን

ግዮንንና ኤፌሶንን፥ ጤግሮስንና ኤፍራጥስን

እናያቸው ዘንድ ተወን፤ ከምዕራብ ወጥቶ

በምሥራቅ ያለውን ያጠጣ ዘንድ ወደ ምሥራቅ

የሚሄድ አለ፤ ከምሥራቅ ወጥቶ በምዕራብ

ያለውን ያጠጣ ዘንድ ወደ ምዕራብ የሚሄድ

አለ፤ ከሰሜን ወጥቶ በደቡብ ያለውን ያጠጣ

ዘንድ ወደ ደቡብ የሚሄድ አለ፤ ከደቡብ ወጥቶ

በሰሜን ያለውን ያጠጣ ዘንድ ወደ ሰሜን

የሚሄድ አለ።» የአንድምታ ትርጓሜ ሊቃውንት

ይህን ሲተረጕሙ «ነቅዑ (መመንጫው) ከእግዚ

አብሔር እግረ መንበር ሥር ነው፤ ከገነት ከአንድ

ዕፀ ሕይወት ሥር መንጭቶ በሥውር ወደዚህ

ዓለም ይመጣል፤ በዚህ ዓለም ለዐራት ተከፍሎ

ዓለምን ዞሮ ካጠጣ በኋላ ወደ ውቅያኖስ ይገባል»

ይላሉ። ስለ ዐራቱ አፍላጋትና ስለ ዐባይ ወንዝ

ይህን ሁሉ ሐተታ ካየን አሁን ደግሞ ይህ

ትምህርት በኢትዮጵያውያን አእምሮ የሚፈጥረውን

መልእክት እንመልከት።

ይህ ሁሉ ሐተታና ትምህርት በኢትዮጵያውያን

አእምሮ ላይ ስለ ዐባይ ወንዝ

የፈጠረው ተፅዕኖ ምንድን ነው?

ይህ ትምህርት ኢትዮጵያውያን የዐባይን

ውኃ እንዲያለሙትና እንዲጠቀሙበት ይረዳል

ወይስ እንዳያለሙት ይከለክላል? የሚለውን

ጥያቄ ከዚህ ላይ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል። ይህን

ጥያቄ በሁለት መልክ መመለስ ይቻላል፤ ይኸ

ውም ኢትዮጵያውያን መምህራን ስለ ዐባይ

ሲያስተምሩትና ሲያትቱት የኖሩት ትምህርት

በአንድ በኩል ስለ ዐባይ ውኃ (ወንዝ) ታላቅ

የእግዚአብሔር ስጦታነት በማስተማር ኢትዮ

ጵያውያን ውኃው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው

ሀብት (ጸጋ) እንደሆነ እንዲያስቡ (እንዲያምኑ)

ያደርጋል፤ ከዚህ አንጻር የባለቤትነትን ስሜት

ይፈጥራል፤ ታላቅ ስጦታ ከእግዚአብሔር ያገኘን

መሆኑን በማስተማር መልካም አስተሳሰብን ያዳ

ብራል ማለት እንችላለን። ትምህርቱ ዐባይ

ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ግብፅንም የሚያጠጣ

መሆኑን በግልፅ ስለሚያስረዳ ውኃው ፈጣሪ

ከኢትዮጵያ እስከ ሜዲትራኒያን ባሕር ድረስ

ለሚኖሩ የተፋሰሱ ሀገራት ሕዝቦች የተሰጠ

ስጦታ ስለሆነ በጋራ መጠቀም ይቻላል የሚለውን

በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ የምታራምደውን

የጋራ ተጠቃሚነት መርሕ ይደግፋል። ከዚህም

የተነሣ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ የዐባይ

ውኃ የብቻችን ነው ብለው አስበው (ተናግረው)

እንደማያውቁ ደፍረን መመስከር እንችላለን።

ይህ በጎ ነገር ከሐተታው ሊወሰድ የሚገባው

ቁም ነገር ነው ማለት ይቻላል።

በሌላ በኩል ደግሞ ለወንዙ መንፈሳዊ

ትርጕም በመስጠት ወደ ምድር በምሥጢር

የመጣ፥ ከእግዚአብሔር መንበር (ዙፋን) ሥር

የመነጨ፥ በገነት ሳለ ሀሊብ (ወተት) የነበረ፥

ወደዚህ ዓለም ሲመጣ ግን ንጹሕ ውኃ የሆነ

ነው በማለት ከቁጥጥር ውጭ የሆነና ሰዎች

ገድበው ሊጠቀሙበት፥ ኢትዮጵያውያንም ሀገራ

ቸውን ሊያለሙበት የሚችሉት ወንዝ ሳይሆን

ከሰው አእምሮና ቁጥጥር ውጭ የሚኖር ወንዝ

አስመስሎ ማስተማር ትክክል አይደለም። ይህም

ኢትዮጵያ ውኃውን ማልማት በነበረባት ጊዜ

አልምታ እንዳትጠቀምበት አድርጓል ብለው

የሚያስቡ ምሁራን አሉ። አንዳንዶችም ዐባይ

በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንዲህ ዓይነት መንፈሳዊ

ወንዝ ተደርጎ እንዲታሰብ ያደረጉት ግብፃውያን

ጳጳሳት ናቸው፤ ምክንያቱም ደግሞ ከዘመነ

ዛጕዌ ጀምሮ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት

ዐባይን ለመገደብ አስበው ስለነበር የግብፅ

ነገሥታት በግብፃውያን ጳጳሳት በኩል ይህን አሳብ

ማደናቀፍ ስለፈለጉ ነበር ይላሉ። ይህ አስተሳሰብ

ዐባይ ከአሁን ቀደም ልማት ላይ እንዳይውል

ግብፅ በግብፃውያን ጳጳሳት በኩል የኢትዮጵያን

ቤተ ክርስቲያን ተጠቅማ በኢትዮጵጵያ ላይ

ተጽዕኖ ስታደርግ ነበር የሚል መልእክት ያለው

ይመስላል። ሆኖም ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት

ከተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም ከኦሪት

ዘፍጥረት ያገኙትን ትምህርት መነሻ አድርገው

ይህን ሐተታ ጻፉ እንጂ ከግብፃውያን ጳጳሳት

ያገኙትን ነገር ሳይመረምሩ በትምህርታቸው

ያካተቱት አይደለም። እንዲያውም ግብጻውያን

ጳጳሳት የሀገራችንን ቋንቋ የማያውቁ፥ ለባሕላችን

ባዕድ (እንግዳ) ስለነበሩ በትምህርት በኩል

ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ያለምንም ተፅዕኖ

ይንቀሳቀሱ እንደነበር ይታመናል። ስለዚህ

ሁለተኛው አስተሳሰብ ተቀባይነት ያለው አይሆ

ንም፤ ምክንያቱም ዐራቱ ወንዞች በአንድ

ወንዝነት ከገነት ይመነጫሉ፤ ከዚያም ለዐራት

ይከፈላሉ፤ ሁለተኛው ወንዝ ግዮን (ዐባይ) ነው

የሚለው ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት

ነውና።

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ፥ ከትርጓሜ

መጻሕፍትና ከሊቃውንት ትምህርት የተገኙትን

መረጃዎች መሠረት በማድረግ የዐባይ ወንዝ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

እንዴት እንደሚገለፅ የሚከተለውን ድምዳሜ

መስጠት ይቻላል።

1. ዐራቱ አፍላጋት (ኤፌሶን፥ ግዮን፥ ጤግሮስና

ኤፍራጥስ) ከገነት በአንድ ወንዝነት መንጭተው

ለዐራት በመከፈል ይህን ዓለም እንሚያጠጡ

በኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 2 ቍ. 10 ተረጋ

ግጧል።

2. ከዐራቱ ወንዞች ሁለተኛው ወንዝ ግዮን

(ዐባይ) ኢትዮጵያን ዙሮ የሚያጠጣ መሆኑ

በዘፍጥረት ምዕ. 2 ቍ. 13 ተገልጧል።

3. ዐባይ የፈጣሪ ስጦታና የልዩ ልዩ መንፈ

ሳውያት ምግብናት (መግበቶች) ምሳሌያዊ

መግለጫ ሆኖ በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃ

ውንት ይገለጣል።

4. የዐባይ ወንዝ ምንም እንኳን ከኢትዮጵያ

የሚንመነጭ ቢሆንም ከኢትዮጵያ ጀምሮ

እስከ ግብፅ ድረስ ላሉት የተፋሰሱ ሀገራት

ሁሉ እንጂ የኢትዮጵያ ወይም የሌላ አንድ

ሀገር ብቻ ሀብት እንዳይደለ ቤተ ክርስቲያን

ከትንት ጀምሮ ስታስተምር ኑራለች።

5. ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ኦሪት ዘፍጥረትን

መሠረት በማድረግ ስለ ዐራቱ አፍላጋ ትም

ሆነ ስለ ዐባይ የሚሰጡት መንፈሳዊና ምሥ

ጢራዊ ሐተታ የዐባይ ወንዝ እንደ ማንኛ

ውም ወንዝ ውኃ አለመሆኑን አያመለክትም።

ስለዚህ ለዐባይ ወንዝም ሆነ ለዐራቱ አፍ

ላጋት የተሰጠውን መንፈሳዊ ትጕርም እንደ

ፈለጉ አሉታዊ መልእክት እንዲይዝ ማድረግ

ጽንፈኛ አስተሳሰብ ይመስላልና ቤተ ክርስ

ቲያንን አይገልጥም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ

ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ዐባይ የኢት

ዮጵያና የተፋሰሱ ሀገራት ሕዝቦች እንዲ

ጠቀሙበት ከፈጣሪ የተሰጠ ታላቅ ስጦታ

እንደሆነ ታምናለች። የኢትዮጵያ መን

ግሥት በዐባይ ላይ እየገነባ ያለውን ታላቁን

የኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ የሕዳሴ ግድ

ብም በአላት አቅም ሁሉ ትደግፋለች።

እግዚአብሔር ሀገራችን

ኢትዮጵያን ይጠብቅ!

በመጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር