የእግዚአብሔር መንግስት 2016 - free books. the kingdom of god.pdf ·...

51
የእግዚአብሔር መንግስት 2016 0 www.tlcfan.org በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

Upload: phungnga

Post on 14-Feb-2018

819 views

Category:

Documents


105 download

TRANSCRIPT

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

0 www.tlcfan.org

በመጋቢ ሊዮን ኢማኒኤል

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

1 www.tlcfan.org

የመጀመሪያ እትም

Copyright ©1998

የሁለተኛ እትም

REVISED 2016

መብቱ የተጠበቀ ነው፦

All rights Reserved to:

Bible Teacher Pastor Leon Emmanuel

FOUNDER OF KINGDOM CITIZENS MINISTRY

Permission is granted to copy and quote freely from this publication for non-commercial purposes.

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

2 www.tlcfan.org

ማውጫ

1. መግቢያ ................................................................................................ 3

2. መንግስት ምን ማለት ነው?. ............................................................... 4

3. የመንግስቱ ንጉስ .................................................................................. 9

4. የመንግስቱ ዜጎች .................................................................................. 20

5. የመንግስቱ ሕግ .................................................................................. 29

6. የመንግስቱ ግዛት. ................................................................................. 39

7. የመንግስቱ ሰራዊቶች ............................................................................ 45

8. ምድርና ሞላዋ ...................................................................................... 47

Copyright ©1998

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

3 www.tlcfan.org

መግቢያ

ሰው የእግዚአብሔርን መንግስት ወይም መንግስተ ሰማያትን ሲያስብ የሚኖረው

ግንዛቤ አለ። በዓለም ያሉ ሰዎች በሙሉ በአንድነት የሚስማሙበት ሃሳብ መልካም መንግስትና

ሥፍራ እንደ ሆነች ነው። ሁሉም ሰዎች መንግስተ ሰማያትን ሲያስቡ በአብዛኛው ተመሳሳይ

እይታ አላቸው። ይህም የለመለመች ስፍራ፣ የጽድቅ ስፍራ፣ የሚመች አስተዳደር፣ ከተማይቱ

የተሰራችበት ቁሳቁሶች፣ የመላአክትና የተለያዮ ነገሮች መገኘት......ወዘተ ናቸው። ይህንና

ይህን የመሳሳሉ ነገሮች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እንደሚገኙ ይገምታሉ። በመሆኑን

ሁሉም ሰዎች ውስጥ የተለያዮ ቅርጽ የያዘ ምስል በአዕምሯቸው ቢኖርም በአብዛኛው

በተመሳሳይ እይታ ሁሉም ይኖራሉ።

የእግዚአብሔር መንግስት ምን ትመስላለች? የእግዚአብሔር መንግስት ምን ማለት

ነው? በእርግጥም በእኛ አዕምሮ ተስሎ ያለው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው ዝምንድናው

ምን ያህል ነው? ሰለ እግዚአብሔር መንግስት ፍጹም ለሰዎች ልጆች የሚገባን ትምሕርት

ያሰተማረው ማነው? የእግዚአብሔር መንግስት ምን እንደ ምትመስል ሳናውቅ በቀጥታ

የመንግስቱን ወንጌል መስበክ እንዴት ይቻላል? የመንግስቱ ወንጌል አንባሳደር ወይም

የመንግስቱ መንጌል አብሳሪ ለመሆን እንዴት ይቻላል?

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎቱን ሲጀምር የእግዚአብሔር መንግስት ቀርባለችና

ንስሃ ግቡ በማለት ነበር። ከራሱ ይልቅ ያስተዋወቀው የእግዚአብሔር መንግስት ነው። ንስሃ

የመግባቱም አሰፈላጊነት ይቺን መንግስት ለመቀበል ወይም ለመውረስ ነው። ለመቀበል ደግሞ

የምንቀበለው ነገር ምን እንደሚመስል ማወቅ ተገቢ ይሆናል። በመሆኑም የመጀመሪያው

የቅዱሳን እውቀት ሊሆን የሚገባው ከንስሃ በኃላ የእግዚአብሔር መንግስት ማወቅና

መመልከትና ቀጥ ብሎ ወደ እርሷ መግባት ነው። በንስሃ አዕምሮ የምንቀበልው የመጀመሪያ

እውቀት የእግዚአብሔር መንግስት ነው። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ

አስተማሪዎች ፈጽሞ የተለየ ነው። ምክንያቱም እርሱ እግዚአብሔር በመሆኑና የሁሉ ብቸኛ

ጀማሪ በመሆኑ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ከእርሱ የሆነ በመሆኑ ነው። መንግስተ ሰማይም ከእርሱ

ወጣ እንጂ ኢየሱስ ከመንግስተ ሰማያት አልወጣም። ነገር ግን ለኛ የተሰጠችውና የምትሰጠው

መንግስት ግን የወጣችው ከመንግስተ ሰማያት ነው። እንዲያውም ልትመስል የገባው ልክ እንደ

መንግስተ ሰማያት ነው። “ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር.”

በእግዚአብሔር መንግስት እውቀትና ሚስጥር በማወቅ ደቀመዛሙርት ከሌሎች

አማኞች ይለያሉ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግስተ ሰማያትን በምድር ቋንቋ እንዲገባን

አመቻችቶ አስረድቶናል። ኢየሱስ ካስተማረው ምሳሌዎች ውጪ የእግዚአብሔር መንግስት

መረዳት በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህም መጽሐፍ የተዘጋጀው የእግዚአብሔር መንግስትን

ለማጥናት እንድነሳሳ ለማድረግ ሰለ መንግስቱ እውቀት መሰረት ለመጣል ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

4 www.tlcfan.org

መንግስት ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ የመንግስትን ወንጌል ስብዃል። ይህ የመንግስት ወንጌል የዘመን ፍጻሜ ከመምጣቱ በፊት በዓለም ሁሉ እንደሚሰበክ ኢየሱስ ተናግሯል። ይህ ደግሞ ታላቅ ሃላፊነትን በሰው ላይ ይጥላል። መጨረሻው እንዲመጣ የመንግስቱን ወንጌል መስበክ ከመንግስቱ ዜጎች የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው።

“ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” ማቴ24፥14

የመንግስት ወንጌል ማለት ምን ማለት ነው? ይህ የምንግስት ወንጌል ከደህንነት ወንጌል ጋር አንድ ነውን? በፍጹም አንድ አይደለም። (Gospel of salvation and Gospel

of the kingdom of God) ተብሎ በእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ተለያይቶ ግልጽ ሆኖ ተቀምጧል። ይህ ደግሞ ሁለቱ ወንጌሎች የተለያዮ መሆናቸውን ያሳያል። ነገር ግን ይህ የደህንነት ወንጌል የመንግስት ወንጌል አንዱ ክፍል ወይም አካል ነው። የደህንነት ወንጌል ሰዎች በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ዜግነትን እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ያተኮረ ወንጌል ነው። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የማይገነዘቡት ግን የመንግስቱ ወንጌል ከደህንነት ሁሉ ያለፈ መሆኑን ነው። ሰለዚህም ይህን እውነት በጥልቀት በትክክለኛ መንገድ ለመረዳት የእግዚአብሔር መንግስት በመጀመሪያ ከጀመረበት ተነስተን ልንመለከት ይገባል።

የእግዚአብሔር መንግስት የት ጀመረ? የእግዚአብሔር መንግስት የጀመረው በዘፍጥረት.1፥1 ላይ ነው። ይህንን ስንል ለሰው መገለጡን መታየቱን መታወቁን ነው።

“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።”

የእግዚአብሔር መንግስት እግዚአብሔር በሰማይም ሆነ በምድር የፈጠረውን ሁሉ የሚጠቀልል ነው። መንግስቱ ሰማይን ብቻ ሳይሆን ምድርንም የሚጠቀልል ነው። መንግስቱ የማይታየው ብቻ ሳይሆን ከማይታየው የወጣውንም ሁሉ የሚታየውንም ሁሉ የሚጠቀልል ነው። ስለዚህ እኛም ከመጀመሪያው ተነስተን ይህን ሁሉ ልንመለከት ይገባል። ምክንያቱም መጀመሪያ ታወቀ ማለት መጨረሻው በቀላሉ ታወቀ ማለት ነው። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በመጀመሪያ የመጨረሻን ይናገራልና ነው።

በነጻ ፍቃድ መጽሐፌ ላይ እንደጸፍኩት እግዚአብሔር በመፍጠር ባለመብትነት ሕግ የሁሉ ባለቤት ነው። የማይታየውም ሃገር ሆነ የሚታየው ግኡዙ አለም የወጣው ከማይታየው ነው። የዚህ ሁሉ ብቸኛ ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ሰለዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ምድርንና ሞላዋ የእግዚአብሔር እንደ ሆነች ደጋግሞ ይናገራል። እግዚአብሔር የሁሉ ባለቤት እንደ ሆነ ቃሉ ይነግረናል። እግዚአብሔር ግን ምድርን ለወደደው ሰው በግዛትነት ይሰጣል። ስለዚህም በምድር ላይ የሚሆነውን ሁሉ ለመቆጣጠር ባለ ሙሉ መብት እግዚአብሔር ግዛት የሰጠው ሰው ነው። ምድር የሰይጣን ፈጽሞ አይደለችም። በምድር ላይ ያሉ ማንኛም አይነት ፍጥረታት የሚኖሩበትን የአኗኗር ሕግ የሚያወጣው የፍጥረት ሁሉ ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

5 www.tlcfan.org

ሃጢያትና ሞት የእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ጣልቃ ገብተዋል መንግስቱን በክለዋል። ይህም ብከላ በመጀመሪያ በሰማይ በማይታየው ዓለም ከዛም በኃላ ደግሞ ምድርን በሚታየው ዓለም ነው። ይህ የብክለት ችግር ጊዚያዊ ችግር ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ጀምሮ ይህንን ችግር በእርሱ እይታ በሁሉ አዋቂነቱ ብቃት አይቶታል፣ አሰተካክሎታልና ነው። ነገር ግን ለእኛ ይህ የሃጢያት ብክለት ችግር በምድር ታሪክ መዝጊያ ላይ ፍጻሜን ያገኛል። ሃጢያትና ሞት ፈጽሞ ይወገዳል። ይህም የግል ሃጢያት የምንለው የደህንነት ወንጌል ሰምተን ከዳንን በኋላ የምንፈጽመው ነው። ከዛም እግዚአብሔር በትንቢት በነብያቶቹ በኩል እንደተናገረው በመጨረሻ የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሸፍናል። ሁሉ ነገር ይታደሳል። ሁሉ በክርስቶስ ይጠቀለላል።

እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት የሚታየውንና የማይታየውን የሚጠቀልል ነው። በመጀመሪያ ደረጃ እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መልካም እንደተባለ አስረግጠን ልናውቀው ልናምነው የሚገባ እውነት ነው። ደግሞም እግዚአብሔር ስራውን ወደ ፍፃሜ ሲያመጣው እጅግ መልካም ነው ብሎታል።

“እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ።” ዘፍ.1፥31

ምድር፣ እጽዋት፣ ድንጋይ፣ ውሃ፣ እንስሳት ሰው ሁሉ . . .የተፈጠረው በእግዚአብሔር እንጂ በስይጣን አይደለም። ስለዚህም ሁሉ እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር በጠቅላላው እጅግ መልካም የሆነ ፍጥረት ነው። መንግስቱ እጅግ መልካም ነገርን ሁሉ በሙላት የተሞላ ነው። ይህ እውነት በተለያዩ የእምነት ድርጅቶች ዘንድ ተቀባይነቱን አጥቷል። ይህም እምነት ከመጥፋቱ የተሳሳተ የሚታየው አለም ራሱ ክፉ ነው። መልካም የሆነው ሰማያዊው ብቻ ነው የሚል ትምህርትንም እንዲያስተምሩ አድርጓቸዋል።

ከዚህም አይነት መረዳት መበላሸት የተነሳ በጳውሎስ ዘመን የነበሩ ግሪኮች ታላቁ እግዚአብሔር እንዴት በሰው ስጋ ውስጥ መኖሪያ ሊያደርግ ይችላል? በማለት እውነቱን ለመቀበል ብዙዎች በዚያን ዘመን ተቸግረዋል። ምክንያቱም እነርሱ የሚያምኑት ግኡዙ ዓለም ክፉ እንደ ሆነ ስለ ሆነ ነው። ይህም ስህተት የመጣባቸው ሰለ ግዑዙ አለም ያላቸው ግንዛቤ የተሳሳተ ሰለሆነ ነው። ምክንያቱም እነርሱ እንደሚያምኑት ግዑዙ አለም ክፉ ስለ ሆነ መልካም የሆነ እግዚአብሔር እንዴት በክፉና እርኩስ በሆነው ውስጥ ሊያድር ይችላል የሚል መረዳት ነበር።

ዛሬም ይህንን ጥያቄ ደግመው የሚያነሱና የበዓለ አምሳን ልምምድ የመንፈስ ቅዱስ በሰው ልጆች ውስጥ ማደር የሚቃወሙ ብዙ ሃይማኖቶች አሉ። ይህም እንደ ጳውሎስ ዘመን ግሪኮች እርኩስ የሆነው ይህ ግኡዙ ሰው ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔር መንፈስ እንዴት ሊሸከም ይችላል የሚል ነው። ይህ ሁሉ ስህተት የመነጨው ጉኡዙ ዓለምና በውስጡ ያለው ፍጥረት እርኩስና ክፉ ነው የሚል አስተሳሰብ ሰዎች በመያዛቸው ነው። ይህ ደግሞ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ፈጽሞ የማይሄድ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

6 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር የፈጠረውን ይህን አለምና በውስጡ ያለውን እጅግ መልካም ነው ያለውን ክፉና እርኩስ ነው ብሎ ማሰብ ከእግዚአብሔር የሚያጣላ አይመስልምን? ወይም በእግዚአብሔር ስራ ጥልቅ ማለት አይሆንምን? የእግዚአብሔርን ፍጥረት እንዲህ ነው ልንልስ እኛ ማን ነን?

እንግዲህ መንግስትንና የመንግስትን ወንጌል ማወቅ ከፈለግን የሚታየው ግዑዙ አለም ክፉና ከሰይጣን እንዳልሆነ ልናውቅ በመጀመሪያ ደረጃ ይገባናል። ጉዑዙ ቁሳዊው አለምና መላው አለም መልካም ሆኖ በእግዚአብሔር የተፈጠረ ነው። ይህ ብቻ አይደለም የማይታየውን እግዚአብሔር ባሕሪ የማንጸባረቅን ችሎታን የተሞሉ ድንቅ ፍጥረቶች የተሞሉ ናቸው።

በእግዚአብሔር ስራ በጅማሬው ላይ ያለን መረዳት በታሪክ መጨረሻ ለሚኖረን እይታ ታላቅ አስተማጽዎ ያደጋል። በዘፍጥረት ላይ ያለን መረዳት በራዕይ ላይ ለሚኖረን እይታ ታላቅ አስተዋጽኦ አለው። እግዚአብሔር ራሱን በተለያያ ጊዜ በግዑዙ ፍጥረት ገልጿል። ለሙሴ በቁጥቋጦ፣ ለእስራኤል በዓለት ፣በበትር ፣ በሰማይ፣ በምድር፣ በተራራ፣ በበግ......ወዘተ።

“እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። 20-21 የማይታየው ባሕርይ እርሱም

የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ

እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።”

ሮሜ.1፥19-21

ሃጢያትና ሞት ቀንድመው ቢኖሩም በሰማይና በምድር መንግስቱ መልካከል ጣልቃ ገቢ ሃይሎች እንጂ በፍጥረት ጊዜ ከፍጥረት ጋር አብረው የተፈጠሩ አይደሉም። ሃጢያት ለታሪክ ሌላ መጠምዘዣ መንገድን አበጅቷል። ለዚህ ሃጢያት ብክለት ችግር ፍጻሜ ለማምጣት ጊዜ፣ ሰዓትና ዘመን በእግዚአብሔር ተመድቧል።

‘’ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥ የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል።

ዳን.9፥24

የታሪክ ግብ የመንግስቱን ወንጌል ተሰፋ ክፍል ሁሉ ይሸፍናል። ወንጌል የፍጥረትና እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለውን ግንኙነትና ህብረት ይነገረናል። የሃጢያትና የሞትን ችግር ምን እንደ ሆነ ይነግረናል። ደግሞ ችግሩን ለማስተካከልና ለማስወገድ እግዚአብሔር ያቀደውን መልኮታዊ እቅድንም ያሳየናል። እግዚአብሔርም በመጨረሻ ሁሉ እንዳለመው እንደሚሆንለት እንደሚሳካለትና ሁሉ ድል እንደሚያደርግ ይነግረናል። እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ለፈጠረበት አላማ ሆነው ይገለጣሉ ብሎ ያውጅልናል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

7 www.tlcfan.org

እቅዱ ከመጀመሪያ እንዳሰበው እንዲሁ ይፈጸማል ይቆማል። የእግዚአብሔር እቅድ ሊያፈርስ የሚችል ምንም አይነት ሃይል የለም ብሎ ራሱ በድል ያውጃል። ምድር የተፈጠረችው የእግዚአብሔር ክብር ለማንጸባረቅ ነው። እግዚአብሔር ይህንን እቅዱን መፈጸም ማከናወን ካልቻለ እግዚአብሔርን ራሱ ደካማ በቃሉ የማይጸና ሃጢያተኛ ያደርገዋል ማለት ነው። ምክንያቱም በዕብራይስጡ ሃጢያት ማለት “ካውታው” ‘’kawtaw’’ በግሪኩ “ሃርማትያ” ማለት ሲሆን ትርጉሙም ግብ ከመምታት መውደቅ ኢላማን መሳት ማለት ነው። እግዚአብሔር ግን ሃጢያትን አይሰራም አላማውን ፍጽሞ አይስትም።

ሃጢያትን በመንግስቱ ውስጥ እግዚአብሔርን እንደ አጋጣሚ አላገኘውም። ሁሉን አዋቂ ነውና በቀደመ እውቀቱ ሃጢያት በፈጠረው ሰይጣን አማካኝነት ጣልቃ እንደሚገባ ያውቃል። ደግሞም የሃጢያትንም ችግር አስወግዶ ሁሉን ለማስተካከል እግዚአብሔር ብቁ ስለሆነ ይህ የሚስተካከልበት እውቀትንና ዘመን በሃሳቡ ይዞ ነበር ሁሉ የጀመረው። እግዚአብሔር የምድርን ታሪክ ሆነ የፍጥረትን ታሪክ የሚዘጋው ሁሉን ነገር በማደስና ሁሉ ትትክክለኛውን ስፍራ እንዲይዝ ከመጀመሪያው በበለጠ ክብሩን በመመለስ ነው። (የሁሉ ነገር መታደስ የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ) ጳውሎስ በሌላ መልኩ ደግሞ እንዲህ ብሎ ሉቃስ በሐዋርያት ስራ ላይ እንዳስቀመጠልን አስቀምጦታ፦

“እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተናገረው፥ ነገር ሁሉ እስከሚታደስበት ዘመን ድረስ ሰማይ ይቀበለው ዘንድ ይገባልና።” ሐዋ.3፥21

“26 የኋለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው፤ 27 ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት

በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። 28 ሁሉ ከተገዛለት በኋላ ግን እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን

ላስገዛለት ይገዛል።’ 1ቆሮ.15፥26-28

እግዚአብሔር ሁሉ ደግሞም በሁሉ ይሆናል። ሞት ይሻራል ብሎ በግልጽ አስቀምጣል። ቀሪው ጥቅስ ደግሞ ይህን የእግዚአብሔርን ግብ በእቅዱ በምን እንዴት እንደሚፈጸም ያሳየናል። በዚህ ጥቅስ ውስጥ ብዙ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው ነገሮች አሉ። ነገር ግን ሁሉም እግዚአብሔር ከፍጥረቱ ጋር ያለውን ሕብረት በተለያየ መልኩ ያንጸባርቃል። በይበልጥም ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ሕብረቱን በጥልቀት ያሳያል።

የእግዚአብሔርን መንግስት ሁሉ ለማብራራት ከመጽሐፍ ቅዱስ ገጽ የበለጠ መጽሐፍን መጻፍ ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ በሕይወት ዘመናችን አንብበን የማንጨርሰው ይሆናል። ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ሰለ እግዚአብሔር መንግስትና የመንግስቱ ወንጌል ምንነት በጥቂቱ መንደርደሪያ መረጃን ለመስጠት ብቻ የተዘጋጀ ነው።

በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መረጃ መሰረት እግዚአብሔር ሁለት በተለያዩ መንገዶችና ዘዴዎች መንግስቱ እንዴት እንደሚያጸና አስተምሮናል። የመጀመሪያው መንገድ ለመውደቅ የተሰራ ሲሆን። ይህም ምን ነገር እንደ ጎደለ ለማሳወቅ የተጠቀመበት መንገድ ሲሆን።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

8 www.tlcfan.org

ሁለተኛው መንገድ ደግሞ በሁሉ ነገር ሙሉና ፍጹም ውጤታማ እንዲሆን የሚደረግበት መንገድ በጌታ የተመረቀ መንገድ ነው። እነዚህ የእግዚአብሔር ሁለት መንገዶች ወይም ዘዴዎች አሮጌው ኪዳንና አዲስ ኪዳን ተብለው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተቀምጠው እናገኛቸዋለን።

አሮጌው ኪዳን በሰዎች ላይ የእግዚአብሔርን አላማና እቅድ የመፈጸም ሃላፊነትን የሚጥል ኪዳን ነው። ይህም ሰው ይህን ሃላፊነት ሊፈጽም ስላልቻለ አሮጌው ኪዳን ውድቅ ሆኗል። አዲሱ ኪዳን ደግሞ ሃላፊነቱን ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያደርጋል። ይህም ኢየሱስ ሁሉን የእግዚአብሔር እቅድና አላማ ፈጽሞ በሟሟላት ፍጽምና ጽድቅን ለሁሉ በአዲሱ ኪዳን ሊያመጣ ነው። ይህም በእርሱ ደም የቆመ ኪዳን እንጂ እንደ አሮጌው ኪዳን በእንስሳት ደም አይደለም። የአዲስ ኪዳን ስራ ገና አልተጠናቀቀም። የእግዚአብሔር መንግስቱ ወንጌል በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የእግዚአብሔር እቅድና አላማ ወደ ፍጻሜ እንደሚመጣ ግን ተናግሯል ተስፋም ተገብቷል።

እንግዲህ መንግስት ምንድ ነው? መንግስትን መንግስት የሚያሰኘው ምንድን ነው?

ሰንል አንድ መንግስት ቢያንስ መንግስት ተብሎ ለመጠራት አምስት ነገሮችን መያዝ

ይኖርበታል። እነርሱም ንጉስ፣ ዜጋ፣ ሕግ፣ ግዛትና ሰራዊት ናቸው። እንግዲህ መንግስት

የእነዚህ ሁሉ ጥርቅም ማለት ነው። መንግስተ ሰማይ ስንል መንግስቱ የመጣበትን ሰፍራ

ለማመልከት ነው። መንግስቱ በሰማይ ተፈጽሟ። ስለዚህም ነው መንግስትህ ትምጣ

የምንለው። መንግስቱና ፍቃዱ በሰማይ ሆኗል ተፈጽሟል፣ ተጠናቅቋል። ነገር ግን

መንግስቱና ፍቃዱ በምድር እንዲፈጸም አሁን ድረስ እንጠባበቃለን እንጸልያለን።

የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች፣ ሕግ፣ ንጉስ፣ ግዛትና ሰራዊቶች አላት።

የእግዚአብሔርን መንግስት መንግስት የሚያሰኘው ደግሞ ይህን ሁሉ ይዞ መገኘቱ ነው።

ሌሎች መንግስታት ሁሉ ይህን ካላሟሉ መንግስት ሊባሉ ከቶ አይችሉም። የመጽሐፍ ቅዱስ

ታሪክ ሂደት የሚያሳየው ትንሽ የሆነችው የእግዚአብሔር መንግስት እድገትን ደረጃን ነው።

በኢየሱስ ምሳሌ እንደተተረከችው የሰናፍጭ ቅንጣት፦ ከትንሽ ቅንጣት ተነስታ

መንግስቱ ሁሉን የምታስጠጋና የምታስጠልል ታላቅ ዛፍ መሆንዋን የምናይበት ነው።

የእግዚአብሔርን መንግስት ለመረዳት እነዚህ አምስቱን በእግዚአብሔር ቃል መመልከት

ይገባናል። ከላይ እንዳየነው መንግስቱ እንዳትገለጥ ወይም ሰዎች ወደ መንግስቱ እንዳይገቡ

የሚያደርጉ ብክለቶችና ሃይማኖታዊ ወጎችና ስርዓቶች ሁሉ መወገድ አለባቸው።

መንግስት ማለት ይህን ሁሉ ከላይ የዘረዘርናቸውን ጠቅልሎ የያዘ ግዛት ወይም

አገዛዝ ማለት ነው። መንግስት ግዛት አለው ይህ ማለት ግን መንግስቱ በግዛት ብቻ የተወሰነ

አይደለም። መንግስቱ ሁሉን እስከሚወርስ የሚሰፋ የሚያድግ ነው። መንግስቱ የያዘቸውን

ከዚህ በመቀጠል በዝርዝር እንመለከታለን።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

9 www.tlcfan.org

የመንግስቱ ንጉስ

የእግዚአብሔር መንግስት ምድርንም ሰማይን የሚያጠቃልል ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር ምድርን ለሰው ልጆች እንዲገዟት ስልጣንን ሰጥቷል። የመጀመሪያው የምድር ንጉስ አዳም ነበር።

“27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና

የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” ዘፍ.1፥26

በዕብራይስጡን ቃል መሰረት ዘፍጥረት ላይ አዳም ሳይሆን ሰው የሚለውን ቃል ይጠቀማል። ይህም ግዛቱ ሰውን ሁሉ የሚጠቀልል መሆኑን የሚይሳይ ነው። ነገር ግን ሌሎቹ ሰዎች ሁሉ በዚህ በዘፍጥረት ላይ በተፈጠረው ሰው ውስጥ ሰላሉ ቢገዙም የሚገዙት ከእርሱ ጋር በመሆን ከመጀመሪያው ንጉስ ከአዳም በመማር ነበር። ይህ ሰው የተፈጠረው በስድስተኛው ቀን ነው። ሰለዚህ ምንም ሰው በምድር ላይ ገዢ ቢሆን የተፈጠረው ፍጥረት ሲፈጠር ምንም የእርሱ ስራ አልታከለበትም። ይህም ሰው የተቀበለው ገዢነት የምድር ባለቤት አላደረገውም ። እግዚአብሔር ግን እርሱ እንዳሰበው እንዳቀደው ሁሉ ግዛት ፈጥሮ በዚያ ላይ ሰውን ሾመው፣ ሰልጣን ሰጠው። የመጀመሪያው የምድር ንጉስ አደረገው።

ከእግዚአብሔር ሰው ግዛትን በመቀበሉ የምድር የመጀመሪያ ንጉስ እንዲሆን ያደርገዋል። እግዚአብሔር ግን ከአዳም ከፍ ያለ በአዳም ውስጥ ላሉት ሰዎች፣ ማለት የንጉስ ልጆች ስለሚሆኑ ነገስታት ሁሉ እግዚአብሔር ለሁሉ የነገስታት ሁሉ ንጉስ ነበር። ይህ ስንል በአዳም ውስጥ ያሉት የሰው ልጆችን ሁሉ የምድር ነገስታት በማድረግ ነው። እግዚአብሔር ለአዳም ስልጣንን በምድር ሁሉ ላይ በመስጠቱ እግዚአብሔር የምድር ባለቤትነት ስፍራውን አልለቀቀለትም።

አዳም ይገዛ የነበረው ከእግዚአብሔር በታች ነው እንጂ ከእግዚአብሔር በላይ አይደለም። ነገር ግን አዳም ሃጢያትን ሲሰራ ከእግዚአብሔር ተነጥሎ በራሱ ምድርን ሊመራን ሊገዛ ፈለገ ራሱን እንደ እግዚአብሔር ሊያደርግ ፈለገ። ይህም ምድርን ዳርቻ የራሱ ብቻ አድርጎ በመቁጠር ነው። በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ዙፋን ወይም አገዛዝ ከላዮ ገለበጠ። የእግዚአብሔር አገዛዝ ከላዩ አስወገደ። ይህ ግለኝነቱ ከሕይወት ጎዳና ወደ ሞት ወደ መበስበስ ጎዳና አወጣው። ይህ ሞት ደግሞ ግዛቱን ያሳጣዋል። ይህ እግዚአብሔር በቃሉ አስቀድሞ እንደተናገረው ተፈጸመበት። በእግዚአብሔር አሰራር የበላይ ከሌለን የበታችም አይኖረንም። የአዳም የበላይ እግዚአብሔር ነበር። እርሱን ባለመታዘዙንና በላዮ ላይ የእርሱን አገዛዝ ባለመቀበሉ የበታች ሆኖ ሊገዛለት የተሰጠውን ሁሉ አጣ።

“ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” ዘፍ.2፥17

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

10 www.tlcfan.org

በዚህ መጽሐፍ ላይ ዛፉ ምንን ይወክላል እያልን ብዙ ቃላትን ማብዛት አያስፈልገንም። ነገር ግን አዳም ያንን ፍሬ ሲበላ እግዚአብሔር አለመታዘዙን እናውቃለን። ወይም ሃጢያት በመስራቱ እግዚአብሔር ያወጣለትን ሕግ መተላለፉን ያሳያል። የአዳም ሃጢያት ወጤቱ ደግሞ መንፈሳዊ ሞት ነው።

አዳምና ሄዋን በእግዚአብሔር መልክ ሳይሆን በመልካቸውና በምሳሌያቸው ከዔደን ገነት ከወጡ በኋላ ልጆችን ወለዱ። ከሃጢያት በፊት በዔደን ልጅ ወልደው ቢሆን ኖሮ በመጀመሪያው እግዚአብሔርን በሚመስለው መልካቸው ልጆች ይኖራቸው ነበር። ነገር ግን አዳምና ሄዋን ሃጢያት ከሰሩ በኃላ ልጅ ወለዱ። ስለዚህም የወለዷቸው ልጆች በሃጢያተኛ ማንነታቸው መልክና ምሳሌ የተወለዱ ሰዎች ሆኑ። ስለዚህም ከአዳም ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሞትና መበስበስ እኛ ድረስ ሲወድ ሲዋረድ መጣ። ይህን ጳውሎስ በሮሜ.5፥12 ላይ በግልጽ ያስቀምጠዋል።

“12 ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ።”

ሞት የሰው ልጆች ድካም ወይም ካንሰር ነው። የመንግስቱ ወንጌል ይህን ሞት እንዴት ድል እንደምንነሳውና ሃጢያትን እንዴት መስራት እንደምናቆም የእግዚአብሔርን ችሎታና ብቃት ያስተምረናል። የእግዚአብሔር ቃል ይህ ለእኛ ለአማኞች ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠው ትልቅ እድል እንደ ሆነ ይናገራል።

“እርሱም (ኢየሱስ ክርስቶስ) የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።”

1.ዮሐ.2፥2

ሞትና ሃጢያት በንጉስ አዳም በውስጡ ባሉት ነገስታት ላይም ጭምር ችግርን ፈጥሯል። እንደ ፍጥረት መጀመሪያ ማንነቱ የማይሞት ዘላለማዊ ሆኖ ቢቀጥል ኖሮ የምድር ንጉስ ሆኖ በምድር ላይ ለዘላለም አዳም ይገዛ ነበር። ዘውደ መግስቱንም ለልጅ ልጅ ማስተላለፍም አያስፈልገውም ነበር። በውስጡ ላሉት ነገስታት ንጉስ ሆኖ ለዘላለም ይኖር ነበር።

ምድርን መግዛት በዋነኝነት የአዳም ስራ ይሆን ነበር። ናቡከደነዖር ይህን እድል ለጥቂት ዘመናት አግኝቶት ነበር። ይህም አገዛዝ ምድርንና በውስጡዋ ያለውን ሁሉ ከፍ ላለው ለእግዚአብሔር መንግስት ማስገዛት ነበር። ነገር ግን ልክ እንደ አዳም አይነት ሃጢያትን በመስራቱ ወደቀ። ስለዚህም ሌላ አዳም አስፈለገ። ይህም የመጀመሪያ አዳም ከጀመረበት ጀምሮ የሚከናወንለትና የሚሳካለት አዳም ነው። የመጀመሪያው አዳም ሊፈጽመው ያልቻለውን ሁለተኛው አዳም ሲመጣ ፈጸመው። ሁለተኛውና የመጨረሻው አዳም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የመጀመሪያ ማለቱ ከአዳም በፊት ማንም አለመኖሩን ሲያሳይ የሁለተኛና የመጨረሻው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ በመሆኑ ከእርሱ ውጭ የሆነ የነገስታት ንጉስ አንጠብቅም።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

11 www.tlcfan.org

‘’ 45 እንዲሁ ደግሞ። ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።

46 ነገር ግን አስቀድሞ ፍጥረታዊው ቀጥሎም መንፈሳዊው ነው እንጂ መንፈሳዊው መጀመሪያ አይደለም። 47 የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። 48 መሬታዊው

እንደ ሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥ ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው። 49 የዚያንም

የመሬታዊውን መልክ እንደ ለበስን የሰማያዊውን መልክ ደግሞ እንለብሳለን።’’ 1.ቆሮ.15፥45

አዳም በሃጢያት ምክንያት ስለ ሞተ መበስበስም ስለያዘው የገዢነቱ አክሊል ከትውልድ ወደ ትውልድ ለተመረጠ ንጉስ ይሸጋገር ዘንድ ተገባው። ሽግግሩ ቀጠለ ምክንያቱም ከዳም በኃላ ሰው ሁሉ ሞት ይዞታልና የንግስና አክሊል ከሰው ወደ ሰው ሊዘዋወር ተገባው። ደግሞም ቢነግሱም ፍላጎታቸው የራሳቸውን የልብ ፍላጎት እንዳልታዘዘው አባታቸው ያደርጉ ነበርና በእግዚአብሔር የተቀሰፉም ነገስትም ነበሩበት። ምክንያቱም አንድ ጊዜ በአባታቸው ያለመታዘዝ መርዝ ተመርዘዋልና ነው።

ሰዎች ከሃጢያተኝነት ባሕሪ የተነሳ በሰዎች ላይ መንገስን ይፈልጋሉ እንጂ በሰዎች ላይ እግዚአብሔርን ማንገስ አይፈልጉም። ከዚህም የተነሳ ፍቃዳቸውን ለማስፈጸም ሌሎችን ከመግዛት አልፈው ባሪያ ያደርጋሉ። ይህ አይነቱ አሰራር የሰው ልጆች መንግስት የመመስረት ምንጭ አድርጎታል። የሰው ልጅ መንግስት ምንጩ ውድቀት ነው። “...እርሱም ገዢሽ ይሆናል።” የእግዚአብሔር መንግስት ምድር ከውድቀት በፊት በነበረችበት ጊዜ ግን ሁለቱ አብረው ይገዟት ነበር። “ግዙአትም ብዙ ተባዙ ሙሏትም ...” ነበር የተባሉት። ከውድቀት በኋላ ግን ተቀየረ። አንድ ሰው በሌላው ሰው ላይ መግዛት ጀመረ። የእግዚአብሔር መንግስት ጀማሬ ከሰማይ ሲሆን የሰው መግስት ጅማሬው ደግሞ ከውድቀትና ካለመታዘዝ ነው።

አክሊላቸው ጠብቀው የራሳቸውን ፍቃድ ለማስፈጸም በብዙ ክርክርና ውጊያም ያለፉ

ነገስታት ሃያሌዎች ነበሩ። አክሊን በእንዲህ አይነቱ ውጊያ ያለ አግባብ መያዛቸው ብዙሃኑ

ለራሳቸው ጥቅም ብቻ ሲሉ ነበር። ዛሬም መምድር መንግስታት እንዲህ ናቸው። እንግዲህ

ሁሉ ግልጽ እንዲሆንልን በምድር ላይ የነገሱትን ንጉሶችና አነሳሳቸውን ከመጀመሪያው

እንመልከት።

ገዢ መሆን፣ ንጉስ መሆንና አገዛዝ በራሱ በመጀመሪያ ደረጃ የመወለድን መብት የሚጠይቅ ነገር ነው። የንጉስ ልጅ ካልሆንክ ልትነግስም ሆነ ንጉስ ልትሆን አትችልም። ሌላው ከንግስና ጋር አብሮ የሚሄደው ደግሞ ፍሬያማ መሆን ነው። ይህ ደግሞም የመብዛት መብትን የሚሰጥ ነው። መግዛትና መብዛት ያለ እግዚአብሔር ፍቃድ ከቶ የማይሆን ነገር ነው። ያቆብ ይህ ስለገባው ሚስቱን ልጅ ስትጠይቀው እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን ብሏታል። ይህ አባባሉ ዘር የሚሰጥ እንድትበዛ ፍቃድን የሚሰጣት የእግዚአብሔር ብቸኛ መብት እንደ ሆነ ሚስቱን አስተምሮ ለእኛም ትምህርት ጥሎልን አልፏል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

12 www.tlcfan.org

በዘፍ.1፥26 ላይ ለስው ልጆች የመብዛትን የመውለድን፣ የዘር ፍሬን የማግኘትን መብት የሰጠው እግዚአብሔር በግዛቱ ውስጥ በሚበዙት ትውልድ ላይ የእግዚአብሔር መግስትን በዜጎች እንዲበዙና መስፋት ለማምጣት ነው። አዳምና ሄዋን ሃጢያት ሳይሰሩ በፊት በእግዚአብሔር መልክ ልጅ ወልደው ቢሆን ኖሮ የተወለዱት ሁሉ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋና የእግዚአብሔርን መልክ የያዙ ይሆኑ ነበር። ይህም በመንግስቱ ውስጥ ያለ የመወለድ መብት ውጤት ነው።

አዳም ግን ሃጢያት በመስራቱ ሞት ሰለያዘው ንግስናው ብቻ ሳይሆን የልጅነት መብቱ የመብዛትም ብቃቱ ተወሰደ። ሃብቱ ከአዳም ወደ ልጁ ሴት ወረደ። አዳም ልብዛ ቢል የሚበዛው በሕይወት እስካለ ድረስ ነበር። ምክንያቱም ሞት ይዞታልና ነው። ልጁ ሴት ሲሞት ደግሞ ወደ ልጁ ወደ ኤኖስ አለፈ። ይህ ሁሉ እየሆነ ንግስናውና የልጅነት መብቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየወረደ ኖህ ጋር ደረሰ። ኖህ በጥፋት ውሃ በኩል የልጅነትንና የመግዛትን መብት ተቀበለ። ኖህም ደግሞ ይህን መግዛትና መብዛት ለሴም አቀበለ። ሴምም 600 ዓመት ኖረ።

‘’የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ።

11፤ ሴምም አርፋክስድን ከወለደ በኋላ አምስት መቶ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም።’’ ዘፍ.11፥10-11

ሴም አስር ትውልድ ያህል በሕይወቱ ዘመን አሳልፎ ሞተ። ዘፍጥረት 11ን በእግዚአብሔር የዘመን ቀመር አቆጣጠር ብናጠናው ሴም አብርሃምን አልፎ የኖረ የልጅነትና የንግስና ባለመብት ሰው ነው። ሴም በአብርሃም ዘመንም በሕይወት በመኖሩ ንግስናና የልጅነት መብቱ ለይሳቅ እንጂ ለአብርሃም አልደረሰውም ነበር። (የእግዚአብሔር ዘመን አቆጣጠር በሚለው መጽሐፌ ላይ ስለ ዘመን ቀመር በዝርዝር አስቀምጫለሁ ያንቡቡ)

ዘመኑን ስንቆጥር ሴም የሞተው ይሳቅ 110 አመት ሲሆነውና ያቆብ 50 አመቱ እያለ ነው። ስለዚህም የልጅነት መብት አብርሃምን አለፈው። የልጅነት መብት ለይሳቅ ተሰጠ። ይህም የሆነው ሴም ከሞተ በኋላ ነው። የልጅነት መብት የሚለው ነገር በቀጥታ ተጠቅሶ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘውም በይሳቅ ታሪክ ላይ ነው። ከዛም በመቀጠል ስለዚህ የልጅነት የመወለድ መብትን ያቆብና ዔሳው ሲጣሉበት እናገኛለን።

ያቆብ የዚህ የልጅነትና የገዢነት መብት ከአባቱ ከይሳቅ ወራሽ ሆነ። ነገር ግን ከስጋዊነቱ የተነሳ ያገኘው ከብዙ ትግል በኃላ ነበር። ከዛም በመቀጠል የልጅነት መብት ወደ ያቆብ ልጆች ወረደ። ያቆብ ግዛትንና መብዛትን ለበኩር ማስተላለፍ ቢገባውም በበኩሩ ልጁ በሮቤል ሃጢያት ምክንያት ንግስናን ከሮቤል ነጥቆ ለይሁዳ ሰጠው። ዘፍ.49

“3፤ ሮቤል፥ አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ፥ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።4፤ እንደ ውኃ የምትዋልል ነህ፤ አለቅነት ለአንተ አይሁን፤ ወደ አባትህ መኝታ ወጥተሃልና፤

አረከስኸውም፤ ወደ አልጋዬም ወጣ።”

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

13 www.tlcfan.org

‘’9፤ ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ ሴት አንበሳም አደባ፤ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል?

10፤ በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ፤

የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።11፤ ውርንጫውን በወይን ግንድ ያስራል፥ የአህያይቱንም ግልገል በወይን አረግ፤

ልብሱን በወይን ያጥባል፥ መጎናጸፊያውንም በወይን ደም። 12፤ ዓይኑም ከወይን ይቀላል፤ ጥርሱም ከወተት ነጭ ይሆናል።

ያቆብ የልጅነትን መብትና ፍሬያማነትን መብት ደግሞ ከይሁዳ ነጥሎ ለዮሴፍ ሰጠው። ይህም ይሁዳ ንግስናን ሲይዝ ዮሴፍ ደግሞ መብዛት መፍራትን ያዘ ማለት ነው። እዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ላይ ከአዳም ጀምሮ እስከ ያቆብ በአንድ ሰው ላይ ይተላለፍ የነበረው ንግስናና የልጅነት መብት ለሁለት ተከፈለ። ለሁለት ሰው ተሰጠ ይህ ራሱ የቻለ የታሪክ ለውጥን በሰው ልጆች ውስጥ አምጥቷል። ለክርስቶስም ዳግም ምጽዓት ቁልፍ ነው።

‘’22፤ ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፤ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።23፤ ቀስተኞች አስቸገሩት፥ ነደፉትም፥ ተቃወሙትም፤24፤ ነገር ግን ቀስቱ እንደ ጸና ቀረ፤ የእጆቹም ክንድ በያዕቆብ አምላክ እጅ በረታ፥ በዚያው በጠባቂው በእስራኤል ዓምድ፥ 25፤ በአባትህ አምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ፥ በጥልቅም በረከት ከታች በሚሠራጭ፥ በጡትና በማኅፀን በረከት።’’26፤ የአባትህ በረከቶች

ጽኑዓን ከሆኑ ከተራሮች በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፤ ዘላለማውያን ከሆኑ ከኮረፍቶችም በረከቶች ይልቅ ኃያላን ናቸው፤

እነርሱም በዮሴፍ ራስ ላይ ይሆናሉ፥ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነው (በይሁዳ) ራስ አናት ላይ።”

“1፤ የእስራኤልም በኵር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኵር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ

ብኵርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኵርና ጋር አልተቈጠረም። 2፤ ይሁዳም በወንድሞቹ መካከል በረታ፥

አለቃም ከእርሱ ሆነ፤ ብኵርናው ግን ለዮሴፍ ነበረ። 1.ዜና.5፥1-2

ይህ ሁሉ ይሁንና የይሁዳ መንግስት ገዢነት ጊዚያዊ ነበር። ይህም በእግዚአብሔር የተባለለት እውነተኛው ገዢ እስከሚመጣ ነው። ዘፍ.49፥10 ያኔ ያቆብ ሲናገረው በዛን ዘመን ለነበሩ ግር የሚያሰኝ እንደሚሆን አያጠራጥርም። ነገር ግን ጊዜ እያለፈና ትውልድ እያለፈ ሲመጣ ያቆብ በይሁዳ ሆነ በዮሴፍ ላይ ያደረገው ነገር ሚስጥሩ ሁሉ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። የመንግስቱ ንጉስ ጥላ ደግሞ እራሱ የእግዚአብሔር መቅደስም ነበር። ታቦቱና የምስክሩ ድንዃን የተተከለው በኤፍሬም ከተማ ነበር። ይህም ስፍራ ሴሎ በመባል ይታወቃል። ኢያሱ.18፥1 ከዛም በመቀጠል በኤሊቤትና በካህናቱ በሕዝቡ ሃጢያት ምክንያት ክህነቱ ስለ ረከሰ ታቦቱ ከሴሎ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ጽዮን ተራራ እንዲሄድ ተደረገ።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

14 www.tlcfan.org

“56 ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔርን ፈተኑት አስቈጡትም፥ ምስክሩንም አልጠበቁም፤ 57 ተመለሱም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ፤ 58 በኰረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቈጡት፥ በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት። 59 እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም እጅግ ናቀ፤ 60 የሴሎምን ማደሪያ ተዋት በሰዎች

መካከል ያደረገባትን ድንኳኑን፤ 61 ኃይላቸውን ለምርኮ፥ ሽልማቱንም በጠላት እጅ ሰጠ። 62 ሕዝቡንም በጦር ውስጥ ዘጋቸው፥ ርስቱንም ቸል አላቸው። 63 ጕልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፥ ቈነጃጅቶቻቸውም አላዘኑም፤ 64 ካህናቶቻቸውም በሰይፍ ወደቁ፥

ባልቴቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም።65 እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ 66 ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤ የዘላለምን ኀሣር ሰጣቸው። 67 የዮሴፍንም ድንኳን ተዋት፥ የኤፍሬምንም ወገን

አልመረጠውም፤ 68 የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥የወደደውን የጽዮንን ተራራ።”መዝ.78

ደግሞም ከካሕናቱ የተነሳ አሁንም የእግዚአብሔር ክብር ከሴሎ እንደ ተነሳ ከኢየሩሳሌም ተነሳ።

“1.ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። 2 በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር። እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 3 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ በዚህም ስፍራ አሳድራችኋለሁ። 4 የእግዚአብሔር መቅደስ፥

የእግዚአብሔር መቅደስ፥ የእግዚአብሔር መቅደስ ይህ ነው እያላችሁ በሐሰት ቃል አትታመኑ። 5 መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ ብታሳምሩ፥ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ

ብትፈርዱ፥ 6 መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም ባትገፉ፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፥ ክፉም ሊሆንባችሁ እንግዶችን አማልክት ባትከተሉ፥ 7 ከዘላለም እስከ ዘላለም

ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ። 8 እነሆ፥ በማትረቡበት በሐሰት ቃል ታምናችኋል። 9 ትሰርቃላችሁ፥ ትገድላላችሁ፥ ታመነዝራላችሁ፥ በሐሰትም ትምላላችሁ፥

ለበኣልም ታጥናላችሁ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ትከተላላችሁ፤ 10 መጣችሁም፥ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ። ይህን አስጸያፊ የሆነ ነገርን ሁሉ አላደረግንም

አላችሁ። 11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ አይቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። 12 ነገር ግን በቀድሞ ዘመን ስሜን ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፥ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ። 13 አሁንም ይህን ነገር ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ በማለዳም ተነሥቼ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥ 14 ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግሁ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት

ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ አደርጋለሁ። 15 የኤፍሬምንም ዘር ሁሉ፥ ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፥ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።16 እንግዲህም አልሰማህምና

ስለዚህ ሕዝብ አትጸልይ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፤ አትማልድላቸው።’’ኤር.7፥1-16

እግዚአብሔር ኢየሩሳሌም እንደ ሴሎ ተዋት እርሱም በአዲሲቷ ኢየሩሳሌም ሊያድር ወሰነ ይህም የእግዚአብሔር መቅደስ በደሙ የታጠብን መቅደሱ የሆንን እኛ ነን።

“16.የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? 17 ማንም የእግዚአብሔርን

ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።’’1.ቆሮ.3፥16

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

15 www.tlcfan.org

“19-20 ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?” 1.ቆሮ.6፥19

እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ማደሪያ ትቶ በእኛ ሊያድር ወደደ። ሰሙ በሴሎ በኢየሩሳሌም እንደተጠራ ሰሙ በእኛም እንዲጠራ ስሙም በግንባራችን ላይ ተጻፈ።

“3.ከእንግዲህም ወዲህ መርገም ከቶ አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉም ዙፋን በእርስዋ ውስጥ ይሆናል፥ ባሪያዎቹም ያመልኩታል፥ ፊቱንም ያያሉ፥

4.ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።’’ ራዕይ.22፥4

ስሙ የሚጠራበት መቅደስ ሆንን። በመጨረሻ የሴሎ የከበረ ትንቢት በሰው ልጆች ላይ መጣ። በምድር በተወሰነ ስፍራ ያለ መቅደስ ሳይሆን መቅደሱ ሰዎች ሆኑ። እነዚህ መቅደሶች ኢየሱስን ራስ ያደረጉ ሰዎች ሁሉ ናቸው። በአንድ ላይም ከእርሱ ጋር አዲስ ሰው የመንግስቱ ዜጎች በመባል ይታወቃሉ።

“13.አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። 14-15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤

ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም (ሰዋዊ) የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው

አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ 16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል

ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።” ኤፌ.2፥15

ይህ መቅደስ የመሰራቱ ፍጻሜው መቅደሱ የተመስረተበት ሐዋርያትና በነብያት መሰረትና የማዕዘኑ ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እነርሱም ኢየሱስን እንደ ማዕዘን ድንጋይ ራስ ያደረጉ ናቸው።

“19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም። 20 በሐዋርያትና በነቢያት

መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤ 22 በእርሱም እናንተ ደግሞ

ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።” ኤፌ.2፥20

ይህ መቅደስ የሚያድግና መሰራት እንደ ቀደሙት መቅደሶች የሚያስፈልገው ነው። ከሃሳባችን እንዳንወጣ ይህ የመንግስት ንጉስ የእግዚአብሔር መቅደስ እንዴት እንደሆነ ካላይ በዘረዘርኩት ለተረዳን ስለ መቅደሱ በዚህ እናብቃና ለሁለት ስለተከፈለው የልጅነትና የንግስና መብትና የመብዛት መብት ሃሳብ እንመለስ።

ይህ በያቆብ በኩል ተሰንጥቆ ለሁለት ተከፋፍሎ የነበረው ንግስናና ልጅነት በክርስቶስ በኩል መልሶ አንድ ሆኗል። ኢየሱስ ክርስቶስ ከይሁዳ ነገድ መጣ። በግልጽ አመጣጡ የዳዊት ዘር ይዞ ነበር። ይህም በማድረጉ የገዢነቱን የንግስናውን መብቱን አስጠበቀ ወይም ወረሰ። እርሱም ሞት ስለማይዘው ከዳዊት የተቀበለውን ንግስና ለዘላለም ለራሱ አጸና።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

16 www.tlcfan.org

ይህም ለመንግስቱ ንግስና ብቁ አደረገው። ኢየሱስ ሲወለድ ንጉስ ነበር። ይህ ደግሞ አባቱ ንጉስ እንደ ሆነ ያሳያል። ይህ ንግስናውን መውስዱ በመጀመሪያው ምጽዓቱ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን በሁለተኛ ምጽዓቱ ማለትም የኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምጸአት ደግሞ እንደ ዮሴፍ ሆኖ ይመጣል፣ ይመለሳል። ይህም የመወለድን መብት ጠቅልሎ ለመውሰድ ነው። ኢየሱስ ሁለቴ መጥቶ ይህን ሁለት ከአዳም ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን በያቆብ ለሁለት የተከፈለውን አንድ ሊያደርግ ነው። ያቆብ መግዛትን ለይሁዳ ልጅነትን ዮሴፍ ስለሰጠ የግድ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ይሁዳም እንደ ዮሴፍም መምጣት አለበት። ይህም በሕጋዊ መልኩ የሁሉ ወራሽ ለመሆን ነው። እንደ ይሁዳ መጥቷል አሁን እዲመጣና እንዲመለስ የምንጠባበቀው እንደ ዮሴፍ ነው። ስለዚህም በራዕይ ላይ እንዲህ የሚል ትንቢት ተጽፏል።

“11.ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። 12 ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ

ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ 13 በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም

የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።” ራዕይ.19፥11-13

“31.የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ፥ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት።” ዘፍ.37፥31

ልብሱም እንደ ዮሴፍ ልብስ በደም ተረጭቷል። ይህም ኢየሱስን ከዮሴፍ ጋር ያለውን ተዛምዶ ለማያያዝ ነው። የመጀመሪያንም መምጣት ማለት በመስቀል ላይ እንደ ይሁዳ ንጉስ መሞቱንም ውጤት ጠቅልሎ መምጣት ያሳያል። አመጣጡ ግን እንደ ዮሴፍ ነው። የኢየሱስ ዳግም ምጽዓት እጅግ በጣም አስፈላጊና ወሳኝ ነገር ነው። ይህን መሆኑ ስለሚያውቅ ሰይጣን ይህን ለማጥፋት ቃሉን ያለ ልክ መንፋሳዊ በማድረግ ኢየሱስ እንደመጣና ሌላ ዳግም ምጽአት የለም ብሎ ዛሬ ያስተምራል። በዚህ አይነት ስህተት ውስጥ ወድቃችሁ ያላችሁ በዚህ ቃል መመለስ እንዲሆንላችሁ ጸሎቴ ነው። በመጀመሪያው መምጣቱ የጀመረውን ስራ በዳግም ምጽአቱ ወደ ፍጻሜ ያመጣዋል። ዳግም ለሁለተኛ ጊዜና ለመጨረሻ ጊዜ ኢየሱስ ሳይመጣ የዮሴፍን የልጅነት መብት ተጠቅሎ አይወስድም። የልጅነት መብት በሙላትና ውርስ ሰው ፈጽሞ አንቀበልም።

ወደ ንግስናውና ገዥነቱ ስንመለስ ግን ኢየሱስ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጨረሻው አዳም ሆኖ ሲመጣ የመጣው ከይሁዳ ነገድ ነው። ይህም ከዳዊት ዘር ስለሆነ የምድር ሁሉ ንጉስ እንዲሆን ብቃትን ሙሉ በሙሉ መብትን ሰጥቶታል። በመጨረሻም ሁሉ ነገስታት ይገዙለታል። ይህም በግዴታና በጉልበት አይደለም። በደስታና በታላቅ ሃሴት ያገለግሉታል፣ ይገዙለታል። ኢየሱስ መቼም ቢሆን በግዴታ ሰው እንዲስግድለትና እንዲያመልከው አያደርግም። ይልቁንም ፍቅሩን በመግለጥ ምን ያህል ሁሉን እንደሚወዳቸው ያሳያል። ከዚህም ጥልቅ ፍቅሩና ምሕረቱ የተነሳ ሁሉ ያመልኩታል ይገዙለታል። ኢየሱስ የንግስና መብቱን በሕጋዊ መንገድ በሰማይም ሆነ በምድር አስከብሯል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

17 www.tlcfan.org

ነገር ግን ሁሉ ቢገዛለትም አሁን ባለንበት ዘመን ግን እግዚአብሔር አይናችንን ካልከፈተው በቀር ሁሉ እንደተገዛለት አናይም። ባሪዎቹም ነገሩን ቃሉም የሚለን ይህንን ነው። ስለዚህ እኛም ሆንን እርሱ ይህም መግስትና አገዛዝ መገለጥ እንጠባበቃለን።

“4 ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ። 5 አቤቱ፥ አሕዛብ

ያመስግኑህ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ።” መዝ.67፥4-5

ይሁንና ይህች ምድር በአሁን ወቅት የተለያዩ ነገስታትንና ገዢዎች እያስተናገደች ትገኛለች። ስለዚህ ሁሉ ከእግሩ በታች እስኪገዛለት ድረስ በቀኙ ተቀምጦ የሚያስገዛለትን አባቱን ይጠብቃል። የሰዓት ባለቤት ሰዓቱንና ዘመን የፈጠረው እግዚአብሔር አብ ነው።

የኢየሱስ ክርስቶስ የምድር ገዢነት በብዙዎች ከመጀመሪያ ጀምሮ ተገፍቶ ነበር። የመጀመሪያው የምድር ገዢ የሆነው እግዚአብሔርን ተቃዋሚ ናምሩድ ነበር። ይህም ንጉስ ሰውን ያሳመጸ ባቢሎን መንግስት የመሰረተ የባቢሎን ግንብም እንዲገነባ ያደረገ ሰው ነው። የመሲሁን መምጣት ጠንቅቆ የሚያውቅ ንጉስ እንደ ነበር ታሪክና ቀኖና መጽሐፍት ያናገሩለታል። ናምሩድ ግን ያን መሲ ለመሆን ስፍራውንም መውሰድ ፈለገ። ይህም የመጀመሪያው በታሪክ የመጀመሪያው አስቹ ክርስቶስ ምሳሌ ያደርገዋል።

ሴም በዚያን በናምሩድ ዘመን ነበር። ሴም ግን በዚህ ንጉስ ዘመን የባቢሎንን የናምሩድን አጋዛዝ ጥሎ ወጣ። ወደ ምዕራብ ከንዓን ርቆ ሄደ። በዛም ሳሌም የምትባልን ከተማ በዛ መሰረተ። ትርጓሜውም ሰላም ማለት ነው። በዚያም ሲወርድ የመጣውን እውነተኛ ንግስናውን ይዞ እስከ ይሳቅ ዘመን ቆየ። ይህም ሴም የመሰረተው ከተማ አሁን ኢየሩ-ሳሌም ነው። ኢየሩሳሌም አመሰራረቷ ገና እስማኤላዊያን ሳይወለዱና ሳይነግሱ ነው። በዚያም መንግስቱን በመልከ ጸጺቅ ስም ሰይሞ ተቀመጠ። ይህም የጽድቅ ንጉስ ማለት ነው።

እነዚህ ታሪካዊ የሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የእግዚአብሔር መንግስት አገዛዝና የሰው መንግስት አገዛዝ በአንድ ምድር ላይ የነበሩ ዘመን የሚያሳይ ነው። ናምሩድና የጽድቅ ንጉስ ሴም አሁን ላለንበት ዘመንና ለአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ጥላና ትንቢታዊ መልዕክት ያላቸው ፍቺ ያላቸው ታሪኮች ናቸው። አሁን ያለችው ሚስጥረኛዋ ባቢሎን ወይም ታላቂቱ ባቢሎንና አዲሲቷ ኢየሩሳሌም ግጭት በዚህ ዘመን የምናየው ለዚህ ነው።

ይህ በራዕይም ሆነ በዘፍጥረት በትንቢት የተቀመጠ እውነት ነው። ለባሪያዎቹ ለነብያት ሁሉ የምስራችን በትንቢት እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ሚስጥር ግን ይፈጸማል። ራዕይ.10፥7 ከሴምና ከናምሩድ ሁለት የተለያዩ ከሚቃረኑ መንግስቶች በኃላ ግዛት ለዳዊት ተሰጠ። ይህም መሲሁ የእርሱ የትውልድ ዘር እንደሚሆንን ዙፋኑም ከእርሱ በኃላ በዘሩ በክርስቶስ ኢየሱስ ለዘላለም እንደሚጸና ትንቢት እግዚአብሔር በመናገር ነበር ለዳዊት ጊዚያዊ መንግስትን እግዚአብሔር የሰጠው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

18 www.tlcfan.org

የዳዊት መንግስት በገዛ ልጁ በአቢሴሎም ችግር ገጥሞት ነበር። እርሱም እንደ ዳዊት ልጅነት መብቱ ዙፋን የሚገባው ስለመስለው ነው። አቢሰሎም ግን ልክ አልነበረም። ይህንንም የተስፋ ቃል ሊወርስ አልተገባውም ለዚህ ንግስና ብቁም አልነበረም።

ከሺ አመታት በኃላ የዳዊትን ዙፋን ለዘላለም ሊወርስ ኢየሱስ የዳዊት ልጅ የይሁዳ ነገድ ሆኖ መጣ። ይህም የተገባው የተነገረት ልጅና ዘር እርሱ ስለነበር ነው። አቢሴሎም ዳዊትን እንደ ተጋፋ ኢየሱስንም የተጋፉት አቢሰሎሞች የገዛ ልጆቹና ወገኖቹ ነበሩ። ንግስናውን ተግፉት እርሱን ከማንገስ ቀብረውት እራሳቸውን አነገሱ።

ይህ አሁንም ያለ ያላበቃ ጉዳይ ነው። ይህንንም ንግስናውን ያስተጓጎሉ ሃይማኖተኛ መሪዎች ጻፎችና ፈሪሳዊያን የአኪጦፌልን ምክር ስሚዎች ነበሩ። አኪጦፌል ደግሞ የአስቆርቱ ይሁዳ ጥላ ነው። ዳዊትም አቢሴሎም በተጋፋው ጊዜ ምንም እንኳን ንግስናው የእርሱ ቢሆንም ለንግስናው መዋጋት ቢችልም ለጊዜው ንግስናው ለቆ ሄዷል። ነገር ግን ዳዊትም ተመልሶ እንደ መጣ። ኢየሱስም ተመልሶ ይመጣል። ማራናታ!!

ዳዊት ዳግም ሲመጣ ያንጊዜ አቢሴሎም ይገደላል። የዳዊት ንግስና ይጸናል። በኢየሱስ ሁለተኛ ምጽዓት የሚቃወሙ መንግስታትና ነገስታት ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይፈጫሉ፣ ይወገዳሉ። በራሳቸው ፍቃድ ሰው ላይ እራሳቸውን የሾሙ የዘመኑ በአለም ዙሪያ ሁሉ የሚገኙ ጻፎችና ፈሪሳዊያን ይወገዳሉ።

እንዲሁ ዳዊት (ኢየሱስን ክርስቶስ) ዳግም ሲመጣ እንደ ዮሴፍ ይመጣል። ኢየሱስ ዳግም ሲመጣ የዳዊትን መንግስት በትረ መንግስትና ዙፋን አክሊ ያጸናል። እንደ የዮሴፍ ደግሞ የልጅነት መብትን ደግሞ በዳግም ምጽአቱ ያጸናል። በዚህም ምክንያት የመጀመሪያውን አዳም ማንነት በበለጠ ክብር ጠቅልሎ ሁለተኛው አዳም ይይዛል ይወርሳል።

የመጀመሪያው አዳም ከውድቀት በፊት በመወለድ መብት የእግዚአብሔር ልጅ ነው። ግዛ በመባሉ በትረ መንግስት የእርሱ ነበር። አዳም ያጣውን ሁለተኛውና የመጨረሻው አዳም ሁለቱንም ክብር ጠቅልሎ ይወስዳል። በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ገዢነቱንና ልጅነቱን ባጸና ጊዜ አንድ ንጉስ ብቻ አይኖርም። ነገር ግን ከሁለተኛው አዳም በመልኩና በአምሳሉ የሚወለዱ የበኩራት አይነት ልጆችም አሉ። እነርሱም የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋና የልጅነትና የንግስና ባለ መብት ባዳኛቸው በኢየሱስ የእግዚአብሔር ወራሽ ይሆናሉ። እነርሱ በእግዚአብሔር ቃል የመጀመሪያ ፍሬ የበኩር ልጅ አይነት ይሆናሉ።

“ለፍጥረቱ የበኵራት ዓይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።” ያቆብ.1፥18

ከክርስቶስ በታች ሆኖ የሚገዛ ማን ነው? በመጀመሪያው ትንሳኤ የማይበሰብሰውን አካል የሚቀበል ድል ነሺ ብቻ ፣ በእውነት ቃል ዳግም የተወለደ ታዛዝዥ አማኝ ባሪያ ብቻ ነው። እንግዲህ የእግዚአብሔር የመንግስቱ ንጉስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ደግሞ ከእርሱ ጋር አብረው የሚነግሱ ድል ነሺዎች ናቸው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

19 www.tlcfan.org

“26-27 ድል ለነሣውና እስከ መጨረሻም ሥራዬን ለጠበቀው እኔ ደግሞ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ በአሕዛብ ላይ ሥልጣንን እሰጠዋለሁ፥ በብረትም በትር ይገዛቸዋል፥ እንደ ሸክላ ዕቃም ይቀጠቀጣሉ፤

28 የንጋትንም ኮከብ እሰጠዋለሁ። 29 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።”

ራዕ.2፥26-29

“21 እኔ ደግሞ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥሁ፥ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ።

22 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።” ራዕ.3፥21-22

“4 ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥ ለአውሬውና ለምስሉም

ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ። 5 የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ

በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው። 6 በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ዳሩ ግን (የፊተኛውን ትንስኤ

የሚቀበሉ ድል ነሺዎች ሁሉ) የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።”

ራዕ.20፥4-6

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

20 www.tlcfan.org

የመንግስቱ ዜጎች

መጀመሪያ መንግስት ንጉስ እንዳለውና ንጉሱ ማን እንደ ሆነ በደንብ ካረጋገጥን ካየን የሚቀጠለው ሁለተኛ ደረጃ መንግስቱ ሊኖረው የሚገባው የመንግስቱ ዜጋዎችን ማንነት ማየት ነው። የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች አሏት። እነርሱም እግዚአብሔርንና በላያቸው የተሾመውን ንጉስ የሚያገለግሉ ዜጎች ናቸው። በአሁን ዘመን ሰው ባወጣላቸው ስም መሰረት ክርስቲያን በመባል ይታወቃሉ። ይሁንና ሁሉ ራሱን ክርስቲያን ብሎ የሚጠራ ሁሉ የመንግስቱ ዜጋ ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ልብን እንጂ አንደበትን አያይምና ነው። እምነትን እንጂ ሃይማኖትን አያውቅም ወይም አይቆጥርም።

የምንለውን ከሆንንና ከኖርን ትዕዛዙን ከጠበቅን በእውነት የክርስቶስ ተከታዮች ነን። እግዚአብሔር የምንወድ አማኞች ነን። ክርስቶስን ብቻ ከተከተለን በእውነት ክርስቲያኖች ነን። ነገር ግን እግዚአብሔርን መውደዳችን የሚታወቀው ትዕዛዙ በእኛ ዘንድ ካለች በእኛ ዘንድ የተከበረችና የምትደረግ ከሆነች በእውነት እግዚአብሔርን እንወዳለን።

“27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። 28፤ እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው። ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥

ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።”

የዜጋው ዋናው አስፈላጊነት የዘጥረትን 1፥28 የእግዚአብሔር ቃል ለመፈጸም ነው። ይህም ግዛቱን መግዛት፣ መሙላትና ማስተዳደር ነው። በጥቅሉ ፍሬያማ ለመሆንና ለመብዛትና ለመግዛት ነው። አዳምና ሄዋን በእግዚአብሔር መልክ ልጅን እንዲወልዱ እግዚአብሔር ይወድድ ነበር። ነገር ግን ሃጢያት ከመስራታቸው በፊት ምንም ልጅ አልወለዱም። መብዛት የሚለው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ በእነርሱ ተፈጻሚነትን አላገኘም። ከሃጢያት በኃላ ስለወለዱ የወለዷቸው ልጆች ከውድቀት ማንነታቸው መልክ እንጂ በእግዚአብሔር መልክ አምሳል አልነበረም። በገነት የሚወለድና ከገነት ውጭ የሚወለድ ልዮነቱ በ1.ቆሮ.15፥47-49 ባለው ላይ ተቀምጧል።

“47 የፊተኛው ሰው ከመሬት መሬታዊ ነው፤ ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። 48 መሬታዊው እንደ ሆነ መሬታውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው፥

ሰማያዊው እንደ ሆነ ሰማያውያን የሆኑት ደግሞ እንዲሁ ናቸው።”

ከዔደን ገነት ውጭ በአዳም አምሳል የተወለደ ሰው ሁሉ ምድራዊ ነው። ዘፍ.5፥1 ከውድቀት በፊት ልጅ ቢወለድ ኖሮ የተወለደው የእግዚአብሔር መልክን የያዘ መንፈሳዊ፣ ሰማያዊ ይሆን ነበር። ይህም ዜግነቱ ማንነቱ ነው። አዳም የሚለው ስም ትርጉሙ ምድራዊ ማለት ነው። ይህም የመጣው አዳማ ከሚለው የዕብራይስጡ ቃል ነው። ትርጉሙም ቀይ አፈር ወይም ምድር ማለት ነው። ጳውሎስ በመልክቱ የመጀመሪያውን አዳም ከሁለተኛው አዳም ለይቶ አስቀምጦልናል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

21 www.tlcfan.org

የመጨረሻው አዳም ክርስቶስ እንደ ሆነም ሳይጠቅስ አላለፈም። የመጀመሪያው አዳም የወደቀውን ምድራዊውን የሰው ማንነትና መልክ ሲያሳየን የሁለተኛውና የመጨረሻው አዳም ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መልክና ማንነት ያሳየናል።

እግዚአብሔር ከመጀመሪያም ብዛ ተባዛ ያለው ሰማያዊውን ሰው እንጂ ምድራዊውን ሰው የወደቀውን ሰው አይደለም። ነገር ግን ዛሬ በዝቶ ያለው ምድራዊው የወደቀው ነው። ነገር ግን ከኢየሱስ ትንሳኤ በኋላ ሰማያዊ ልጆች በእውነት ቃል መወለድና መብዛት ጀምረዋል። ስለዚህ የመንግስቱ ዜጎች ሰማያዊውን መልክ ሊይዙ የግድ ይገባል። ይህ የእግዚአብሔር ውሳኔ ትዕዛዝና ሕግ ነው። ይህም መልክ የክርስቶስ መልክ ነው። (የልጁ መልክ የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡት) ይህ ነው የልጅነት ሕብረት የመንግስቱ ዜግነት።

ልጅነትና የልጁን መልክ እንዴት አድርገው ሰዎች በሂደት እንደሚይዙ በመጽሐፍ ቅዱስ ተብራርቶ ተቀምጧል። ይህ ልጅነት እንዴት እንደሚያዝ በሶስቱ የእስራኤል በዓላት በግልጽ ተቅምጧል። ከዚህም የተነሳ ወደ ልጁ መልክ ወደዚህ ወደ ሰማያዊ መልክ የምንመጣበት ደረጃዎች ሶስት ናቸው ማለት እንችላለን። እነዚህ ሶስት በዓላት ሕዝበ እስራኤል ከግብፅ ወጥቶ ከንዓን እስከሚገባ ድረስ ባለው ጉዞ ውስጥ ከዘጸአት እስከ ኢያሱ ባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል። ይህም የእያንዳዳችንን ከሰው መንግስት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ ማንነት የምንሸጋገርበት የጉዞ ሕይወትና እድገት በግልጽ ያሳያል።

ሶስቱ በዓላት ሶስቱ የእድገቶቻችን ደረጃዎች ናቸው። ፋሲካ እስራኤል ግብፅን የሰውን አገዛዛ ወይም መንግስትን ጥሎ የወጣበት ነው። ይህ የማያምነው ሰው ወደ እምነት የሚጣበት ደረጃን ያሳያል። አለም ወይም ግብፅን መተው ነው። የመጀመሪያው በዓል ፋሲካን በዓል የሚያደርግን ማንኛውም ሰው የመንግስቱ ዜጋ ይሆናል። ይህ በእምነት በእግዚአብሔር በግ በኢየሱስ የመሰቀሉ ጽድቅ ስራ በደሙ በኩል በመቀበል ነው። ይህ ዳግም ውልደት ነው።

ሁለተኛው በዓል በዓለ አምሳ ነው። ይህም በዓል እግዚአብሔር በሲና ተራራ ወርዶ ሕጉን ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሰጠበት ቀን መታሰቢያ ነው። ይህም የሚያሳየው የመንግስቱን ዜጎች የሆኑ ሁሉ የመንግስቱ መሪዎች ለማድረግ የሚሰጥን መንግስታዊ ስልጠናን ያመለክታል። ይህ ስለጠና በምድረበዳ ለዜጎች የሚሰጠው መንፈሳዊ ብስለት በዜጎች ላይ ለማምጣት ነው። ደግሞም የእግዚአብሔርን ሕግ በልብ ላይ ለመጻፍ ነው። ከዚያም ዜጋው በእግዚአብሔር ሕግ በኩል መግዛት፣ መፍረድ፣ ሁሉ በጥበብ፣ በፍቅርና በምሕረት ማድረግን ፈጽሞ ከእግዚአብሔር ሕግ ይማራል። ይህ ከመንፈሳ አገዛዝ ስር ራስን ማስገባት ወይም በመንፈስ መታተም ነው።

መጨረሻም ሶስተኛው በዓል የዳስ በዓል ሲሆን ይህም በዓል ሕዝበ እስራኤል የምድረበዳውን ጉዞ ጨርሰው ወደ ከንዓን ወደ ተስፋይቱ ምድር የሚገቡበት ቀን ነበር። ሕዝበ እስራኤል በዚያን ጊዜ ለመግባት ዝግጁ አልነበሩም። ይህ ከእነርሱ በኃላ ለሚመጣው ትውልድ ትንቢታዊ መልክትን ጥሎ አልፏል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

22 www.tlcfan.org

እግዚአብሔር በምድረበዳ ዜጎቹን በመንግስቱ እንዴት መግዛትና መፍረድ እንደሚችሉ ካስተማረ በኃላ በዳስ በዓል ዘመን አዲሱን አካላቸውን በትንሳኤ ወርሰው ከእርሱ ጋር እንዲነግሱ ያደርጋቸዋል። የዳስ በዓል በእግዚአብሔር ልጆች መገለጥና የመጀመሪያው ትንሳኤ ፍጻሜን ያገኛል። እነርሱም ከክርስቶስ ገዥነት በታች ሆነው አብረውት ይገዛሉ ይነግሳሉ። ይህ አሮጌውን ድንኳን ጥሎ በአዲሱ ማደር ነው። ይህም ከሚበሰብሰው አካል ወጥቶ በማይበሰብሰው አካል መኖር ነው።

የመንግስቱ ዜጋ መሆን የሚጠይቀው በክርስቶስ በመስቀሉ ስራና በደሙ የማንፃት ሃይል ማመንን ብቻ ነው። ይህም በፋሲካ በዓል በግልጽ ታይቷል። መግዛትና ማስተዳደር ደግሞ መንፈሳዊ ብስለትን፣ መታዘዝን ለመማር ምድረበዳን ማቋረጥ ይጠይቃል። እግዚአብሔር ሕግን የሚያስተምረው ወይም የሚሰጠው በግብፅ ሳይሆን በምድረበዳ ነው። በደሙ ተዋጅቶ ከዓለም ለወጣ ለተጠመቀ ሰው እግዚአብሔር ሕጉ ያስተምረዋል። ይህ ሁለተኛ የዕድገት ደረጃ የእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ የምንማርበት ታላቅ ሃላፊነት የምንቀበልበትና በቃሉ መኖራችን ወይም አለመኖራችን የሚፈተንበት ደረጃ ነው። ዘዳ.8:2

የዚህ የሁለተኛ ደረጃ የመግስቱ ዜጋ እድገት በበዓለ አምሳ በግልጽ ውጤቱ ይታያል። ደግሞም የዳስ በዓልን ዜጋው ሲያደርግ ወደ ፍጻሜ ይመጣል። የዳስ በዓል የሚተነብየው የእግዚአብሔር ልጆችን መገለጥ ነው። ይህም የበሰሉ የመግስቱ ዜጎች በሙላት ወደ ልጁ መልክ ሲቀየሩ ነው። እነዚህ ሶስት የእድገት ደረጃዎች እምነት፣ መስማማት መታዘዝና ፍቅር በሚሉት ሊተኩ ይችላሉ።

ወደ ልጅነት የምናደርገው ጉዞ የሚጀምረው በእምነት ነው። ከዛም ወደ ሰዋዊ ማንነቱና ባሕሪው ለእግዚአብሔር ወደሚታዘዝበትና ወደ ሚገዛበት ደረጃ ይመጣል። ከዛም የእግዚአብሔር ድምጽ ወደ መስማትና በመንፈስ ወደ መመራት ይመጣል። ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር ለመግዛት ብቁ ይሆናል።

በእነዚህ በሁለቱ የመጀመሪያና የሁለተኛ የእድገት ደረጃ ጊዜያት በአማኙ ሕይወት በከፊል የሆነ የልብ ለውጥ ይደረጋል። ይህ መታዘዝን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራስን ማስገዛትና ያካትታል። ይህም የራሱ ፍቃድ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ሕግ ጋር አንድ ሆኖ ሲስማማ ነው። ነገር ግን አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መንገድና ፈቃድ በሕይወቱ በመታዘዝ ሲያጎለብት ከእግዚአብሔር ጋር መደመስማማት ያልፋል። ሰው ወደ መስማማት ገባ ማለት ያ ሰው ከእንግዲህ በኃላ አንድን ነገር እንዲሰራ አይታዘዝም። ምክንያቱም በባሕሪው ይህን ነገር ስላጎለበተ በውስጥ ፍላጎት አነሳሽነት ትክክለኛ የሆነው ነገር ከእግዚአብሔር በመስማት ስለሚያደርገው ነው። ስለዚህ የልጅነት ግቡ እምነት ወይም መታዘዝ ሳይሆን ከክርስቶስ አዕምሮ ጋር ፍጹም የሆነ agreement መስማማትን ማምጣት ነው። ይህም የዳስ በዓልን ልምምድ አሁን በማድረግ የሚፈጸም ነው። የመንግስቱ ዜጋ መሆን ከአንድ ምድራዊ ክርስቲያን ሃገር ዜጋ ከመሆን ፈጽሞ የሚለይ ነው። እስራኤል የመጀመሪያዋ መንግስትና ሃገር ነች።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

23 www.tlcfan.org

“ጕልበቴ ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነውማለሁ፥ የአባቴ አምላክ ነው

ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ።” ዘጸ.15፥2

“እነሆ፥ አምላክ መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፥ መድኃኒቴም ሆኖአልና በእርሱ

ታምኜ አልፈራም ትላለህ።” ኢሳ.12፥2

yeshu‛ah, yesh-oo'-aw , יׁשּועה

ይህ በዘጸ.15፥2ና በኢሳ.12፥2 ያለው መድኃኒቴ የሚለው ቃል ሕግ ስጪው ጌታ አዳኜ ሆነ ማለት ነው። ከዚህም የተነሳ ሕጉ ተስጥቷት ሕጉ ለሃገር መተዳደሪ በማድረጓ እስራኤልን አንደኛ የመንግስቱ ዜጋ የሞላባት ሃገር ያደርጋታል። ምንም እንዃን በሙሴ ዘመን ክርስቲያን የሚለው ስም ባይኖርም እኛ በዚህ ዘመን ያለን እነርሱን ክርስቶስን አውቀው ወይም ሳያውቁ ቢከተሉትም ክርስቲያኖች እንላቸዋለን። የመጀመሪያው ኪዳንም የጸናው በዚህ በክርስቲያን ዜጎች ወይም ሃገሮች ላይ ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔር ሕግ ሊጠብቁ በራሳቸው ቃል የገቡ ነበሩ።

“ሕዝቡ ሁሉ አንድ አፍ ሆነው። እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን ብለው መለሱ፤ ሙሴም

የሕዝቡን ቃል ወደ እግዚአብሔር አደረሰ።” ዘጸ.19፥8

ሰለዚህም ደህንነታቸውን በመታዘዛቸው አደረገ። ይህም የእግዚአብሔር ሕግ ከመጠበቅ እንዲወድቁ አደረጋቸው። በብሉይ ኪዳን ሰዎች ብቁ ስላልነበሩ ሕጉ ላላ ጉልበቱን አጣ። ሕጉ መንፈሳዊ ሰዎቹ ደግሞ ስጋዊ ነበሩና ነው። ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ሊደረግ አልተቻለም። የግድ እንደሚጠላው ለመታወቅ መግደል ነበረበት።

“እላችኋለሁና። ጽድቃችሁ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። 21 ለቀደሙት። አትግደል እንደ

ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። 22 እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤

ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።” ማቴ.5፥20-22

በአዲስ ኪዳን ግን ቀልድ የለም ሕግ ጠንክሯል ጸንቷል። እንድንጠብቅ የሚያስችል መንፈስና ጸጋ ስለወረደ ጽድቃችን ከጻፎችና ከፈሪሳዊያን ሊበልጥ የግድ ሰለሚገባው ነው።ጥላቻ በእራሱ በእግዚአብሔር መንግስት ትክክለኛ ስፍራውን አግኝቷል። ቁጣ ስድብ...ወዘተ። ሕጉ አሁንም አልተወገደም። የእግዚአብሔር ሕግን አሁን ስንጠብቅና ስንታዘዝ የልባችን ፍላጎትና በውስጣችን ያለው ነገር ሁሉ ይፈተናል ይጣራል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

24 www.tlcfan.org

ክርስቲያናዊ መንግስት እስራኤልን በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የመንግስቱን ሕግና ስርዓት በምድር ላይ ለማስፈጸም ተተቅሞባታል። ይህም ዜጎቹ በእግዚአብሔር ሕግ ሲኖሩ በነበረበት ወቅት ሁሉ ነው። እስራኤሎች በመቀጠል ሕዝብ በብዛት ካልተስማማበት ሕጉ በራሱ ስልጣን እንደሌለው ሕዝቧን ማስተማር ጀመረች። ይህም የሚያሳየው ሰው ሁሉ በገዛ መንገዱ ሊሄድ መፈለጉን ነው። ሕጉን በራሱ ፍቃድ መተርጎም መጀመሩን ያሳያል። የባሰው ደግሞ ነብያቱና ካህናቱ ሕጉን ያስተምራሉ የተባሉት ሳይቀሩ ቀጥተኛ የሆነው ግልጽ የሆነው ሕግ ይህን ማለቱ ነው እያሉ በገዛ መንገዳቸው ያጣሙሙት ጀመር።

ይህም ትምህርታቸው የሰዎች ወግ መሆኑ በክርስቶስ ከተገለጠ በኋላ ታውቋል። ይህም የእግዚአብሔር ሕግ በሰው አሰተሳሰብና መንገድ ተጣሞ ሲተረጎም የስው ወግ ሰርዓት የሃይማኖታዊ ሕግ ይሆናል። የእግዚአብሔር ሕግንም ጉልበት ያሳጣዋል።

“7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ።8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ

የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። 9 እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ

ንቃችኋል። ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።

11 እናንተ ግን ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥ 12 ለአባቱና

ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤ 13 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤

እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።” ማር.7፥8-13

Why do ye also transgress the commandment of God by your tradition? For God commanded, saying, Honour thy father and mother: and, He that curseth father or mother, let him die the death. But ye say, Whosoever shall say to his father or his mother,

It is a gift, by whatsoever thou mightest be profited by me; And honour not his father or his mother, he shall be free. Thus have ye made the commandment of God of none effect by your

tradition. Ye hypocrites, well did Esaias prophesy of you, saying, This people draweth nigh unto me with their mouth, and honoureth me with their lips; but their heart is far from me. But in vain they

do worship me, teaching for doctrines the commandments of men. Mat 15:3-9

“እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።” ቆላ.2፥8

ይህ የመጀመሪያ ትምህርት የአባቶች ወግና ስርዓት ሰዋዊ ሕግና የሰዋዊ መንግስት ሕግ ናቸው ሁሉንም በኢየሱስ ዘመን ተሽሯቸዋል። ማቴ.15፥2, ማር.7፥3,5,8,....ወዘተ። ካህናት መንፈሳዊ መሪዎችን ነን ባዮች መቅደሱን አረከሱት። ወደ ሌቦች ዋሻነት ቀየሩት። ኤር.7፥11 ይህም ካህናቱ የሰሩት ሰርተው የሚደበቁበት ሕዝቡም የሰራውን ሰርቶ እርስ በእርሱ በመሸፋፈን የሚያመልጥበት የሚደበቅበት ዋሻ ሆናቸው። ሕጉን የማይጠብቅ ሁሉ እርስ በእርሱ ይፈላለጋል፣ ይደባበቃል። ይህም በሰዎች ሁሉ ዘንድ የተሰወረው እነርሱ በወግና ሰርዓት በሰዋዊ ሕጋቸው ጉልበቱን ያሳጡት የእግዚአብሔር ሕግ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

25 www.tlcfan.org

“1 ስለዚህ፥ አንተ የምትፈርድ ሰው ሁሉ ሆይ፥ የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው በምትፈርድበት ነገር ራስህን ትኰንናለህና፤ አንተው ፈራጁ እነዚያን ታደርጋለህና። 2

እንደዚህም በሚያደርጉት ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን። 3 አንተም እንደዚህ በሚያደርጉ የምትፈርድ ያንም የምታደርግ ሰው ሆይ፥ አንተ

ከእግዚአብሔር ፍርድ የምታመልጥ ይመስልሃልን? 4 ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? 5 ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና... ....ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቍጣ ቀን ቍጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ። 6 እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ

ሥራው ያስረክበዋል፤ 7 በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ 8 ለዓመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቍጣና መቅሠፍት ይሆንባቸዋል። 9 ክፉውን በሚያደርግ ሰው ነፍስ ሁሉ መከራና ጭንቀት ይሆንበታል፥ አስቀድሞ በአይሁዳዊ

ደግሞም በግሪክ ሰው፤ 10 ነገር ግን በጎ ሥራ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናና ክብር ሰላምም ይሆንላቸዋል፥ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው። 11 እግዚአብሔር ለሰው

ፊት አያዳላምና። 12 ያለ ሕግ ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ያለ ሕግ ደግሞ ይጠፋሉና፤ ሕግም

ሳላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፤ 13 በእግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉት ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ ጻድቃን አይደሉምና። 14 ሕግ የሌላቸው

አሕዛብ ከባሕርያቸው የሕግን ትእዛዝ ሲያደርጉ፥ እነዚያ ሕግ ባይኖራቸው እንኳ ለራሳቸው ሕግ ናቸውና፤ 15 እነርሱም ሕሊናቸው ሲመሰክርላቸው፥ አሳባቸውም እርስ

በርሳቸው ሲካሰስ ወይም ሲያመካኝ በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ። 16 ይህም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ እኔ በወንጌል እንዳስተማርሁ በሰው ዘንድ

የተሰወረውን በሚፈርድበት ቀን ይሆናል።” ሮሜ.2

ሕዝበ እስራኤል በካህናቱ የስህተት ትምህርት ተበከሉ ሕጉን አቀለሉ። ከዚህም የተነሳ የተሰወረውን ወደ አደባባይ የሚያወጣውን እግዚአብሔር ባቢሎንን አምጥቶ ስለ በደላቸው ሕዝቡ ከየተደበቁበት እያወጣ ወደ ባርነት አጋዛቸው።

ይህ በተመሳሳይ ታሪክ በአዲስ ኪዳንም ተፈጽሟል። ኢየሱስ የኤርሚያስን ቃል በመጥቀስ ስለ መቅደሱ መፍረስ ስለ ኢየሩሳሌም መቅደስ መፍረስ ተናግሯል። ማቴ.21፥13 ከዛም ጌታ እንደተነበየው ከ40 ዓመት በኃላ የሮማ ወታደሮች መጥተው መቅደሱንና የክርስቲያን ከተማዋን አፈረሷት።

የክርስቲያን መንግስት ወይም ዜጋ ማለት የእግዚአብሔር ሕግ ደንብ የሚከተል መንግስት ማለት ነው። የእግዚአብሔር ሕግ እንደ መተዳደሪያ የማይጠቀም ሃገር የክርስቲያን የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ ሊባል ፈጽሞ አይችልም። የእግዚአብሔር መንግስት የአዲስ ኪዳንን እቅድ ይዞ ነው የተነሳው። በብሉይ ኪዳን የነበሩ ጥላዊ ታሪኮች በአንዳንድ ዘመን አካላቸውን ገልጠው አልፈዋል ገና በአካል የሚገለጥም ትንቢታዊ ጥላም አላቸው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

26 www.tlcfan.org

አዲሱ ኪዳን ግን በነብዮ ኤርምያስ እንደተተነበየው የሚከናወን ነው። ኤር.31፥31-34 ይህ ኪዳን በኢየሱስ በስጋ መገለጥና በመስቀል መሞት በደሙ በኩል ጸንቷል። የብሉይ ኪዳን ኪዳን በክርስቲያን ዜጎች ላይ በሰዎቹ ተግባርና ስራ ላይ የተመሰረተ ሃላፊነን ሰው ላይ የጫነ በውጭ የሆነ በቀለም የሆነ ሕግ ነበር። አዲስ ኪዳን ግን የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች ኑሮና ሕግ የተመሰረተው በልባቸው ላይ በእግዚአብሔር በመጻፍ ነው።

በሁለቱም ኪዳን ዜግነትን ለመቀበል መገረዝ የሚገባ ነው። በብሉይ በስጋ የሚሆን መገረዝ ሲሆን በአዲስ ኪዳን ደግሞ በልብ የሚደረግ መገረዝ ነው። በብሉይ ኪዳን ያለው በውጭ የሚታየው መገረዝ የውስጥን የሰውየውን የልቡን ምንነትን ማንነት አያንጸባርቅም ነበር። በአሁን ጊዜ አንድ አንድ የክርስቲያን ዜጎች ነን የሚሉ መገረዝን እንደ ዜጋ መሆኛ አድርገው የሚቆጥሩ አሉ። አዲሱ ኪዳን ግን ማንኛውንም ውጫዊ ነገር አስወግዶ ቀጥታ ወደ ውስጥ ወደ ልብ መገረዝ ነው ያመራው።

ጳውሎስ እንዳለ ትክክለኛ አይሁድ ወይም የመንግስቱ ዜጋ ማለት በውጭ በስጋ የተገረዘ አይደለም። በልብ የተገረዘ በውስጥ የሚደረግ ግርዘትን የተቀበለ ሁሉ ነው። ሮሜ.2፥28-29 ይህም የእግዚአብሔር መንግስት ዜግነት አሰራር ቀጥተኛነት ያስያል። ጳውሎስ በግልጽ እንደሚናገረው አንድ ሰው የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ ለመሆን የግድ የልብ መገረዝን ሊያደርግ እንደሚገባው ነው።

በእስራኤል ይህ የስጋ መገረዝ በጣም የጎላ ከመሆኑም በላይ አንድ ሰው የሃገሩን ዜግነት ለመቀበል በአሁን ዘመን እንኳን በቀጥታም ሆንው በተዘዋዋሪ የግድ መገረዙን በአካል ወይም በሃኪም መረጃ ማሳየት ይጠበቅበታል። እስራኤሎች የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ ተብለው አሁን የሚጠሩት በውጫዊ በስጋ መገረዝ እንጂ በውስጣዊ የልብ መገረዝ አይደለም። ይህ አይነቱም መገረዝ በአንድ ሕጻን ልጅ በስምንት አመቱ የሚከናወን የሸለፈት ማስወገድ ስርዓትና ሕግ ነው።

በስጋ እስራኤል ሆኖ የተወለደ የመንግስት ዜግነቱን ሊያጣ እንደሚችል የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል። ዘሌ.17፥1-7 ይህም እግዚአብሔር ያለውን ሕግ ካላደረገ ከዚህ ከእግዚአብሔር መንግስት ዜግነት ይወገድ ይቆረጥ ነበር። ነገር ግን በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ እውነተኛ የሃጢይት መስዋዕት ስለ ሆነ በእግዚአብሔር መንግስት ዜግነት ውስጥ የኢየሱስን ደም እግዚአብሔር ስሙን ወዳስቀመጠበት ያላመጣ አሁን ዜግነቱን ያጣል።

በብሉይ ኪዳን አንድ ሰው በግ አርዶ የበጉን ደም ወደ መቅደሱ የእግዚአብሔር ስም ወደሚጠራበት ስሙ ወዳለብት ካላመጣ ዜጋ መሆኑ ይቀራል። ከትውልዱ ይቆረጣል። በአሁን ዘመን በአዲሱ ኪዳን የእግዚአብሔር ክቡር ስሙ የተቀመጠበት ስፍራ ግንባራችን ወይም አዕምሮችን ነው። እርሱ በግንባራችን ስሙን ጽፏል። የእርሱ ቤተመቅደስም አድርጎናል። ስለዚህ ሕሊናችን በደሙ ልንረጭ ይገባል። ይህም ማለት ደሙን ስሙ ወዳለበት አመጣን ዜጎች ሆንን ማለት ነው። በጥቅሉ በመስቀሉ ስራ የማያምን ሁሉ የመንግስቱ ዜጋ አይደለም።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

27 www.tlcfan.org

ይህን ሕግ በተግባር እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ ስናደግር የመንግስቱ ዜጎች እንሆናለን። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መቅደስ በአዲስ ኪዳን ሰዎች ስለሆንን ነው። ደሙ ወደ እኛ ወደራሳችን የሚመጣው። የሚወጣውም አምኖ በመቀበል ብቻ ነው። ራዕይ.22፥4 ይህን በእምነት የማያደርግ ሰው ሁሉ የመንግስቱ ዜጋ አይደለም።

ሕግ መንፈሳዊ ነው። ሮሜ.7፥14 በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ጠንካራውን ስፍራ ይይዛል ደግሞም ለዘላለም ይጸናል። ነገር ግን በብሉይ ኪዳን እንደነበረው አስራርና አደራረግ አይደለም። አዲስ ኪዳን የገለጠው ሁል ጊዜም እውነት የነበረውን ነገር ነው። ነገር ግን በሙላት ወደ መረዳት ያልመጣውን እውነት ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት ዜግነት በስው ጥረትና ውጫዊ ስራ ሳይሆን በልብ የመገረዝ ስራ ነው። አዲስ ኪዳን ሁሉን ወደ ግልጽነት አደባባይ አውጥቶታል በስጋ መገረዝ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ ፈጽሞ አያደግም። የክርስቲያን ሃገር ዜጋ ስለተባልንና በስጋ ስለተገረዝን የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች አንሆንም። ልንሆንም ፈጽመን አንችልም። ደሙ ለዜግነታችን የመጀመሪያውን ስፍራ ይይዛል። ከደሙ የተነሳም ደግሞ እንገረዛለን ይህም ልባችንን ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ ለመሆን ትክክለኛ መስዋዕትንና የልብ መገረዝን እንደሚጠይቅ ተምረናል። ሰለዚህ ለዚህ ጅማሬ ሰዎች ሁሉ የግድ የፋሲካውን በግ የኢየሱስን ደም በመቅደሱ በር መቃንና ጉበን ላይ በእምነት ሊያደጉት ይገባል። ይህም እሊናቸውና ልባቸው ነው። ተረጭተው እግዚአብሔር ሕጉን በልባቸው እንዲጽፍ ልባቸውን ለእግዚአብሔር በእግዚአብሔር በራሱ ስራ ለማዘጋጀት በርን የሚከፍት ከሰው መንግስት ዜግነት ወደ እግዚአብሔር መግስት ዜግነት የሚያመጣ ነው። ይህ የማያደርግ ሁሉ የእግዚአብሔር መግስትም ሆነ የእግዚአብሔር እስራኤል አይደልም። ገላ.6፥16 የመንግስቱ ዜጋም ሆነ ወራሽ አይሆንም።

የኢየሱስን ደም ካልተቀበልን አድርግ እንደተባልነው ወደ መቅደሱ ካላመጣን ከአይሁድ እንኳን ብትወለድ የመንግስቱ ዜጋ ወይም አይሁድ አትሆንም። የእግዚአብሔር ሕግ እንደሚል ደሙን ወደ ቤተ መቅደሱ ያላመጣ ከመንግስቱ ዜግነት ይቆረጣል ይፋቃል።

በብሉይ ኪዳን የእስራኤል ዜጋ ለመሆን የሚፈልግ ሁሉ ይገረዝ ዘንድ ግድ ነበር። ይህም በስጋ የሚደረግ የቁልፈት ወይም የሸለፈት ማስወገድ ነው። አህዛብም እንደ ዜጋ አይቆጠሩም ነበር። ይህን ሁሉ ነገር እንዲያደርጉት እድል የሚሰጥ አልነበረም። በእግዚአብሔር መንግስት ዜግነት ግን የኢየሱስን ደም በመቅደሱ ላይ ካደረክ ምንም አህዛብ ብትሆን ዜጋ ትሆናለህ። በአዲሱ ኪዳን አህዛብም የዚህ ታላቅ እግዚአብሔር መንግስት ዜጋ የመሆን መብት ተቀብለዋል። ገላ.3፥28

ሁሉ የሰው ልጅ ሁሉ እኩል የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ የመሆን መብት አሁል በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉ ስራ በኩል አለው። ማንም ሰው የመንግስቱ ዜጋ ለመሆን የትውልድ ሃረግ ይቆጥርና ይዘረዝር ዘንድ ፈጽሞ አያስፈልገውም።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

28 www.tlcfan.org

ማንኛውም ሰው ከፋሲካ በዓል ጀምሮ እስከ መጨረሻው የዳስ በዓል እስከ እግዚአብሔር ልጆች መገለጥ ድረስ ያድግና ይጓዝ ዘንድ እግዚአብሔር በእኩልነት ለሁሉ ሰው ፈቅዷል። ለሁሉ እኩል እድልን ይህ ቸር እግዚአብሔር ዘርግቷል።

ሰለዚህ የክርስቲያን ሃገር ነዋሪ ስለሆንክ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ አትሆንም። በስጋ የሚደረግ መገረዝም ስላደረክ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ አትሆንም። የእግዚአብሔር መንግስት ዜጋ የምትሆነው የኢየሱስን ደም ከላይ እንዳየነው በሚገባው ስፍራ ስታመጣውና በእምነት ሰታደርገውና በልብህ ስትገረዝ ነው። የመንግስት ዜጋ የሚያደርግህ በመስቀል ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው። ነገር ግን ሕዝበ እስራኤል በእምነት በበራቸው መቃን ላይ በመቀባት ከሞት ወደ ሕይወት ከሰው መንግስት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ዜጋነት እንደተሸጋገሩ አንተም ልትሸጋገር አሁን ትችላለህ።

የሚያስፈልገው የፋሲካውን በግ ደሙን መቀበል ባደፈው ህሊናህ ላይ በእምነት ማድረግና ከሃጢያትህ ንስሃ ገብተንህ በደሙ በመንጻት ነው። ሃጢያት ምን እንደ ሆነ ካላወቅህ የእግዚአብሔርን ሕግ አንብብ። ሃጢያት በሕግ ይታወቃልና ነው። ሃጢያት ደግሞ ሕግ የለሽ ኑሮ መኖር ነው። ስለዚህ ይህ ሃጢያት ምን እንደሆነ የሚገልጥልንን የመንግስቱ ሕግ ደግሞ በሚቀጥለው ክፍል እንመለከተዋለን።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

29 www.tlcfan.org

የመንግስቱ ሕግ

የእግዚአብሔር የመንግስቱ ሕግ እግዚአብሔር የሰው ልጆች እንዲያደርጉ የተናገራቸውንና ያዘዛቸውን ሁሉና ከአፉ የወጣውን ቃል ሁሉ የሚያካትት ነው። ለንግሱ መታዘዝ ማለት ሕጉን መጠበቅ ማለት ነው። የመንግስቱ ሕግ እግዚአብሔር ራሱን ማንነቱን ባሕሪውን የሚያንጸባርቅበት ነው። ፍጽምና፣ የልጁን መልክ መምሰልና ሩጫ መጨረስ የሚባለውም የሚመዘነው በሕግ ነው። ሕግን የሚሰማ ሳይሆን የሚያደርጉትና የሚታዘዙት ሁሉ ብጹሃን ናቸው። ሮሜ.2፥13

የንጉሱን ባሕሪ ወይም ሕግን መተላለፍ ወይም በሕግ የለሽለት ሕይወት መኖር ሃጢያት ይባላል። በዕብራይስጡ ሃጢያት “ካታው” በግሪኩ ደግሞ “ሃርማቲያ” በመባል ይታወቃል። ትርጉሙም ኢላማን ወይም አላማን መሳት ወይም የፈለጉበት ግብ ላይ አለመድረስ ማለት ነው። ሮሜ.3፥23 ስለዚህ ሁሉ ሰው ይህን ግብ ወይም ኢላማውን ስቷል፣ግቡን ከመምታት ጎድሏል፣ ወድቋል ይለናል። ሁሉ ሰው የእግዚአብሔር የጽድቅ ባሕሪና ክብሩ ጎሎታል። ይህም በእግዚአብሔር የተፈጠረበትን አላማ መሳቱንም ያመለክታል።

የሕጉ አላማ ከሃጢየኞች ጋር ለመፋረድ ወይም ለመወቃስ ነው። እግዚአብሔር ሃጢያት ምን እንደሆነም ሕጉን በመጠቀም ለሃጢያተኛው ለማሳየት ነው። ሃጢያተኛ እስካለ ድረስ የሕግ መኖር የግድ ነው። ሕግን ለማይታዘዘው ማንኛው ሰው የራሱ የሆነ ቅጣት አለው። አንድ ሰው የአንድን ሰው መብት ቢነካ በሕጉ በኩል ቅጣቱን ይቀበላል። ነገር ግን በሕጉ በኩል የሚገባውን ከከፈለ ደግሞ የተለመደ ኑሮውን በንጽሕና ይቀጥላል። ጳውሎስ የሕጉን አላማ በጢሞቲዎስ ላይም አስቀምጦታል።

“8 ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሰራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፤ 9-11 ይኸውም፥ ለበደለኞችና ለማይታዘዙ፥ ለዓመጸኞችና ለኃጢአተኞች፥ ቅድስና ለሌላቸውና ለርኵሳን፥ አባትና እናትን ለሚገድሉ፥ ለነፍሰ ገዳዮችና ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለውሸተኞችም በውሸትም ለሚምሉ፥የብሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደ

ተሰጠኝ ወንጌል የሆነውን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደ ተሰራ እንጂ

ለጻድቅ እንዳልተሰራ ሲያውቅ ነው።”1.ጢሞ.1፥8-11

በመጀመሪያ ሃጢያት ወደ እዚህ አለም ከመግባቱ በፊት ሕግ በሰው ላይ በብዛት እንዲጫን አያስፈልግም ነበር። ነገር ግን ሰው ሃጢያት መስራት ሲጀምር ሕግ ትክክለኛ መንገድ ለማስያዝ የግድ በእግዚአብሔር ፍቃድ ውስጥ አስፈላጊ ሆነ።

በመጨረሻው በዚህ ባለንበት ዘመን እግዚአብሔር በሁሉ ሰው በእግዚአብሔር ቃል ወይም ሕግ በሙላት ይኖራል። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሁሉ በሁሉ ሲሆን ሕጉን በልባችን ላይ ፈጽሞ ስለሚጽፈውና በትእዛዛቱ እንድንሄድ ራሱ እግዚአብሔር ስለሚያደርገን ነው። ሰለዚህ ሕጉ ለዘላለም የማይቀየር የማይሻር የመንግስቱ ምሶሶ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

30 www.tlcfan.org

ሰው በልቡ ላይ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ሲጻፍበት በተፈጥሮው ከልቡ በእግዚአብሔር በኩል የሚገኘውን ሕግ መኖር ይጀምራል። ይህም ከመሆኑ የተነሳ ይህን አድርግ ወይም አታድርግ የሚለው ሰው ወይም ውጫዊ ሕግ አያስፈልገውም። ምክንያቱም እግዚአብሔር ከውስጥ ሆኖ በሕጉ መንገድ ይመራዋልና ነው።

የመጀመሪያው ሕግ የተሰጠው በዘፍ.2፥16-17 ላይ ነው። በዚያን ወቅት ከዚህ ሌላ ሰው ሌላ ሕግ አያስፈልገው ነበር። ይህን ስንል ግን ሁሉ የእግዚአብሔር ሕግ በልቡ በአዳም ውስጥ ቀደሞ ስለ ተጻፈ ነው እንጂ ሕግ ስለ ሌለ አይደልም። አዳም የእግዚአብሔር አምሳል ሊመጣ ላለው ለክርስቶስ አምስሉ ነበርና ነው። ሮሜ.5፥12

የእግዚአብሔር ሕግ የመንግስቱ ሕግ እግዚአብሔር ካለበት ጀምሮ ያለው ነው። አዳምና ሄዋን ይወድቁ ዘንድ ተገባቸው። ይህም የሰው ልጆች ውድቀት ከሆነበት ቀን ጀምሮ ሰው ሁሉ ሃጢያት ሲሰራ ብዙ የማይታወቀው የእግዚአብሔር ሕግ እየታወቀ መጣ። ይህ ማለት ደግሞ የእግዚአብሔር አዕምሮ መታወቅ ጀመር ማለት ነው። አዳም ባይወድቅ ኖሮ የእግዚአብሔር ባህሪ ምን እንደ ሆነ ለማወቅ ይከብደን ነበር። አዳምም ስላላወቀ ወደቀ። በእግዚአብሔር አምሳል ተፈጥሮ ሳለ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ሞከረ። ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር ሊያስተካክል ሞከረ። ይህም አዳም ማነነቱና እግዚአብሔርን በሙላት አለማወቁን የሚያመለክት ነው።

ከጥፋት ውሃ በኋላ እግዚአብሔር ለኖህ ሌላ ምድርን ለመግዛት የሚያስችለውን ሕግ ገለጠለት። ኖህ የምድር ንጉስ ተደርጎ ነበር። ይህ ንግስናም ከአዳም ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ ለእርሱ መጣ። ኖህ በዚያን ወቅት ንጹህና ንጹህ ያልሆኑትን እንስሳ ያውቅ ነበር። ምክንያቱም ይህ እውቀት ወደ መርከቡ የሚገቡትን ለመለየት በጣም አስፈላጊ ነበር። ዘፍ.7

ከውሃ መድረቅ በኋላ እግዚአብሔር ሌላ ሕግ ጨምሮ ገለጠለት። ዘፍ.9፥1-7 ይህም ከስጋ ጋር ደም እንዳይበሉ የሚለውን ነው። 9፥4 ምክንያቱም ደም ለሰው ምግብ ይሆን ዘንድ ስላልተፈጠረ ነው። ሌላው ሕግ ደግሞ ማንም ጎረቤቱን ቢገድል እርሱም እንዲገደል የሚል ነው። 9፥6 ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር ባሕሪ ከበፊት ይልቅ በኖህ ዘመን በይበልጥ ታውቆ ነበር። ከዛ በመቀጠልም የእግዚአብሔር ባሕሪ በሚሰጣቸው ሕጎች ከበፊት ይልቅ እየተገለጠ መጣ። አሁንም እንዲሁ ሕጉ የእግዚአብሔር ባሕሪና ማንነት በጥልቀት የሚገልጥ ነው። የእግዚአብሔር ሕግ ካልተገለጠና ካልተፈታ ባሕሪው ዛሬም አይታወቅም።

“4.ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፥ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም አህዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤5.አብርሃም ቃሌን

ሰምቶአልና፥ ፍርዴን ትእዛዜን ሥርዓቴን ሕጌንም ጠብቆአልና።” ዘፍ.26፥4-5

ከኖህ ቀጥሎም ዘፍ.26፥5 እንደሚናገር እግዚአብሔር አብርሃምን ሕጉንና ትዕዛዙን ስለ ጠበቀ እንደ ባረከው እናያለን። ይህ እንግዲህ ሕግ ከዘጸአት 20 በፊት እንደ ነበር በግልጽ ያስረዳናል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

31 www.tlcfan.org

ነገር ግን የአምስቱ መጽሐፍ ጸሃፊ ሙሴ ስለ ነበር። በዘፍጥረት ላይ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ብዙ ሊያሳያን አልፈለገም? ለምን? ምክንያቱም በሌሎቹ መጽሐፍት በዝርዝር የእግዚአብሔር ሕግ ስለተቀመጠው ነው። ሙሴ ነብይ ነበር። ዘፍጥረት የነብዮ ሙሴ የትንቢት መጽሐፍም ጭምር እንጂ ታሪክ ብቻ የያዘ አይደለም። ይህን ዘፍጥረት በሸመገለው አይን በሚለውና የሁሉ ነገር መታደስ የሚለውን መጽሐፌን ያነበበ በግልጽ መመልከት ይችላል።

እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሕግጋቱ ለአዳምም ተሰጥቶ ነበር ማለት ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ ቃየንና አቤል የእንስሳት መስዋዕትና የእህል መስዋዕትን ባላወቁ ነበር። አብርሃምም ሆነ ያቆብ ሕጉን ባልጠበቁ አስራታቸውንም ባላወጡ ነበር። ሴምም በመልከ ጸዴቅ ተመስሎ ለአብርሃም ባልተገለጠ ነበር። ሌላም ሌላም. . .ወዘተ።

አብርሃም የኖረበት መለኮታዊ ሕግና ትዕዛዛት ከዘጸአት.20 ጀምሮ የተዘረዘረው የእግዚአብሔር ሕግ ነበር። የአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ከተቆጠረለት በኋላ እምነቱ ሕያው መሆኑን በምልክት ያሳየው የመገረዝን ሕግና ትዕዛዛ በራሱና በልጆቹ ላይ በመፈጸም ነው። ሳይገረዝ አመነ ነገር ግን ካመነ በኋላ እንስከ ቁልፈቱ ወይም ሸለፈቱ ከእግዚአብሔር ጋር አልተጓዘም። ከስራ የተለየ እምነት የሞተ ስለሆነ የእምነት አባት አብርሃም እምነቱ በስራ ሕያውነቱን አጸና አሳየ። አብርሃም በእምነት ጸደቀ ወይም ጻድቅ ሆኖ በእግዚአብሔር ተቆጠረ።

አብርሃም ወደ ሙላትና ቅድስና የመጣው የእግዚአብሔር ሕግና ትዕዛዝ በመጠበቅ በስራ ነው። ምክንያቱም ከከላዳውያን ዑር ውጣ ሲለው ታዞ ወጥቷልና ነው። እምነቱ የታየው በዑር ሳይሆን ከዑር በመውጣቱ ነው። ልጅህን ሰዋ ሲባል ታዘዘ። ይህ ሰው ስላመነ ባለበት ቦታ የቆመ አማኝ ለልነበረም ነገር ግን ካለበት ስፍራ የተንቀሳቀሰ እምነት ያለ ስራ ሙት መሆኑ የገባው የእግዚአብሔር ባሪያ ነው። የአብርሃም እምነት በመታዘዙ ተረጋገጠ። የእኛስ? እናምናለን ብቻ ወይስ የእምነትን ፍሬ ስራ እንናደርጋለን?

ከአራት ትውልድ በኋላም ሙሴም ሕዝበ እስራኤልን እየመራ ወደ ሲና ይዟቸው መጣ። እግዚአብሔር በዛ ፍጹምና የተሟላን ለመንግስቱ ኑሮ የሚያበቃን የመንግስቱን ሕግን በሙላት በዝርዝር ሰጣቸው። ይህ ሕግ እግዚአብሔር ከሰው ጋር እና ሰው ከሰው ጋር ያለውን ፍጹም ሕብረት ለማስተካከልና ወደ ትክክለኛ መልኩ ለማምጣት የተሰጠ ነው። ይህ ሕግ የሚገባውን ፍርድ እየፈረደ ሁሉ በትክክል ይገዛና በጽድቅ ይበይን ያስተዳድር ነበር። መምድረበዳ የነበረችው የእግዚአብሔር መንግስት ወይም አግዛዝ በእግዚአብሔር ሕግ ውብ የሆነ ለሁሉ በቅንና በትክክል የምትፈድ ነበረች። ለሚመጣው መንግስት ጥላ ነበረች።

ሙሴ ሳይቀር ባለመታዘዙ የሚገባውን ፍርድ ተቀብሏ። ሕጉ አድሎን ፈጽሞ አያደርግም። ይህ ማለት ግን ሙሴ ስላልታዘዘ ጠፋ ወይም ደህንነቱን አጣ ማለት አይደለም። ይህ ቢሆን ኖሮ ከኤሊያስ ጋር ኢየሱስን ለማገልገል በተራራው ሊገለጠ አይችልም ነበርና ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

32 www.tlcfan.org

ሕግን አለመታዘዝ ወይም አለመጠብቅ እግዚአብሔር ከገባልን ተስፋና ወደ መንግስቱ ከመግባት ያጎድለናል እንጂ ደህንነትን አያሳጣንም። ምክንያቱም ደህንነታችን በእምነትና በእግዚአብሔር ስራ ላይ ብቻ የተመሰረተ ስለሆነ ነው። ጽድቅ በእምነት ብቻ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ስራ ብቻ የሚመጣ ነው። ንግስናና ወደ መንግስቱ መግባት ግን መታዘዝን ድል መንሳትን ይጠይቃል።

ሕጉ የሰው ስጋዊ ሃሳብና ምኞት በሌሎች ላይ ተጽኖ እንዳይመጣ ይገታ ነበር። ሕጉ ክፉን ከመልካሙ መለየት ብቻ ሳይሆን ፍርድንም ይዟል። ይህም የሌሎችን መብት ለሚነኩ ሁሉ የሚገባቸውን ፍርድ ይሰጣል። ፍርድ የተጎዳውን ሰው መብት ብቻ ሳይሆን የጎጅውንም መብት በሚገባ ይጠብቃል። ጳውሎስ ሰለ እግዚአብሔር ሕግ ሲናገር እንዲህ ነው ይለናል።

“ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት።” ሮሜ.7፥12

በመቀጠልም በቁጥር 14 ላይ ሕጉ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለን ይለናል። እኛስ እናውቃለን? ብዙዎች የእግዚአብሔር ሕግ ለስጋና ስጋዊ ነው ይላሉ። ነገር ግን ይህ ፈጽሞ የእግዚአብሔር ቃል የወጣ መረዳት ነው። እግዚአብሔር መንፈስ ነው። ዮሐ.4፥24 ሕጉም መንፈሳዊ ነው። ምክንያቱም መንፈስ ከሆነው ከእርሱ ወጥቷልና ነው።

የሕጉን ባለቤት አስተሳሰብ ያላወቀ ሰው ከእርሱ የወጣውን ሕግ ምንነት ሊያውቅ ፈጽሞ አይችልም። ልፍረድም ቢል በስጋዊ አዕምሮ እንጂ እንደ እግዚአብሔር ሕግ ሊፈርድ ከቶ ያለ እግዚአብሔር ሕግ እውቀት ማንም ሰው ሆነ አገልጋይ አይችልም።

ይህ አይነት እውቀት ለሕዝበ እስራኤል ከጊዜ በኋላ ችግር ሆኖባቸው ነበር። ስለዚህም ኢየሱስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ የሰራው አንድ ነገር ቢኖር በስጋዊ አዕምሮ የተረጎመውን ሕግ በመንፈስ መተርጎም ትክክለኛ የሕጉን መልክ ማምጣት ነበር። የተራራው ስብከቱ አንዱ ዋነኛ የምንለው ሕግን ያጸናበት በሰው ወግ የቀየሩትን ሕግ ለማስተካከልና ትክክለኛውን መልኩን ለማስያዝ ነው። ነገር ግን ከትንሳኤው በኋላም ለደቀመዛሙርቶቹ ሕጉን ተርጉሟል። እነርሱም ከዛ በኋላ የእግዚአብሔርን ሕግ መተርጎም እንዲችሉ አዕምሯቸውን ከፍቷል። ሉቃ.24

ሰው በሰው አስተሳሰብ ሕጉን ሲተረጉመው የእግዚአብሔር ሕግ መባሉ ይቀርና የሰው ባሕል፣ ወግና ሰርዓት ሃይማኖት ይባላል። ይህ እንግዲህ በሁሉ ስፍራ በምድር ላይ የምንተዳደርበትን ሕግን ሁሉ ይጨምራል። በቤተክርሲያን ብቻ ሳይሆን ይህ የሰው ስርዓት የምድር የዘመኑ መንግስታትም ሕግ በብዛት ሰዋዊ የሆነው እርሱ ነው።

ለምሳሌ ሌባ ሲሰርቅ በምድራዊ መንግስት ሕግ እስር ቤት 1-6 ዓመት ወይም እንደ ስርቆቱ ትልቅነት 10-15 አመት ይታሰራል። ከዚያም እስሩን ሲጨርስ ነጻ የሚል ወረቀትን ተቀብሎ ወደ ሕብረተሰቡ ይቀላቀላል። ይህም ከሕግ በታች በእስር የነበረው አሁን ከጸጋ በታች ሆነ ማለት ነው። በእግዚአብሔር ሕግ ግን ሌባ ሲያዝ የሰረቀውን ያህል ሁለት እጥፍ ለተሰረቀው ሰው ይከፍላል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

33 www.tlcfan.org

የሰረቀውን ንብረት ካወደመው ደግሞ ይህን ንብረት ዋጋውን በሁለት እጥፍ እስከሚከፍል ለተሰራቂው ስው ይሰራል ወይም ለሌላ ሰው ተቀጥሮ እየሰራ እዳውን ይከፍላል። ይህን እዳ እስከሚከፍል ከሕግ በታች ይሆናል። ልክ እዳውን ለተሰራቂው ሰው በሁለት እጥፍ ሲከፍል ከጸጋ በታች ይሆናል። ሕጉ የሰራቂውን መብትና ነጻነት ይጠብቅለታል። የተሰራቂምንም መብት በሁለት እጥፍ መክፈል ይጠብቅለታል። ሁለቱም ደስተኛ ወይም ከጸጋ በታች ይሆናሉ። የጌታ ሕግ ድንቅ ውብ ነው።

የምድር መንግስት ግን የተሰራቂውን መብት አይጠብቅም። መክፈል ካልቻለ ወይም እጁ ላይ ገንዘቡ ካልተገኘ ወይም መንግስት በእግዚቢት ሰበብ ከወረሰው ተሰራቂው ለዘላለም ሃብቱን የተሰረቀውን ንብረት ያጣል። ሰራቂውም ሰርቶ በመክፈል ፋንታ በእስር ቤት ቁጭ ይቀለባል። ደግሞ ከሌሎች ወንጀለኞች በሌላ ወንጀል ተመርቆና ዲግሪውን ጭኖ ይወጣል። ይህ ሌባ ምንም እንኳን እስራቱን ጨርሶ ቢወጣም በወንጀሉ ስለተቀጣ በምድር መንግስታት ሕግ መሰረት ስራ የማግኘት እድሉ የጠበበ ይሆናል። ስለዚህም የግድ ከሌሎች ወንጀለኞች የተማረውን በመተግበር ለዘላለም በወንጀለኝነት ስራው ይኖራል። ከዚህ የተነሳ የምድር መንግስታት ሕግ ራሱ ፈጽሞ ግራ የገባው፣ ፍቅርና ምሕረት የሌለው የሰራቂውን ሆነ የተሰራቂውን መብት የማይጠብቅ ነው። ለዚህ ነው የእግዚአብሔር መንግስት የምድርን መንግስታት ፈጭታ ማፍረስ ያለባት። ዳንኤል.2

የምድር መንግስታት ሕግና የቤተክርስቲያ ሕግ ከእግዚአብሔር ሕግ በጣም ስለራቀ ሰውን ያለ ልክ የማይገባውን እንዲያደርግ ሲገፋፋ ሲያስገድድ እስካሁን ድረስ ቆይቷል። በእግዚአብሔር ሕግ ግን ሰው የሚገባውን ፍርድ በትክክል ይቀበላል። በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ አድሎና ልዮነት የለም። በእግዚአብሔር ሕግ ውስጥ ፍጻሜ የሌለው ለዘላለም እስከ ዘላለም የሚቆይ የሕግ ፍርድ የለም። ዳንኤል በትንቢቱ እንዳለ ኢየሱስም በምድር በነበረ ጊዜ ደግሞ እንዳስጠነቀቀ አመጸኛው የእግዚአብሔር ሕግ እየሻረ በእግዚአብሔር መድረክ ሲቆም አንባቢው ያስተውል እንዳለ። እኛም እናስተውል!!!

ጻፎችና ፈሪሳዊያን ሕጉ ለራሳቸውና ለሃይማኖታቸው የሚመቻቸው መስመር አስይዘው በተሳሳተ መልኩ ለራሳቸው ጥቅም ተርጉመውታል። ማቴ.24 በሙሉ ያንብቡ። ይህ ቢበቃ ጥሩ ነበር። ነገር ግን ይህ በሰዋዊ አዕምሮ የተረጎመውን ከእግዚአብሔር ሕግ ጋር አብሮ እንኳን የማይሄደውን ሕጋቸውን የእግዚአብሔር ሕግ ነው እያሉ በየምኩራቡና በየፑልፒቱ አሁን ድረስ የዘመኑ ፈሪሳዊያ በአለም ዙሪያ ያስተምራሉ። አንባቢው ሰሚውም ያስተውል።

ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ሌላው ዋንኛ አላማ ሕጉ ምን ማለት እንደ ሆነ ሊያስረዳና ትክክለኛ ሃይሉን ሊያሳይም ጭምር ነው። ይህም እግዚአብሔር ሕጉን የሰጠበትን ትክክለኛ ልብ እንድናገኝ እንድናውቅ በምድር ኑሮው ወቅት አስተምሯል። ይሁንና ጻፎችና ፈሪሳዊያን ሕጉ እንደገና በራሳቸው አስተሳሰብ ለራሳቸው እንዲመች አድርገው ተርጉመውታል። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ሕግ ሃይል እንዳሳጣው ኢየሱስ በግልጽ ተናግሯል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

34 www.tlcfan.org

ኢየሱስ የመጣው የሕጉን ትክክለኛ ትርጉም እግዚአብሔር አስቀድሞ እንዳሰበው ሊያስተምረን ነው። አሁንም ባለንበት የመጨረሻ ቤተክርስቲያን ዘመን ብዙዎች በተመሳሳይ ስህተት ወድቀው እናገኛለን። ከዚህም የተነሳ ከእግዚአብሔር ሕግ ይልቅ ሰዋዊ ስርዓት ቤተክርስቲያንን ሞልቶ ይገኛል። ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር በሃሳብ ባልተስማሙበት መጠን ሕጉን ለራሳቸው በሚመች ሁኔታ አዕምሯቸውን በመጠቀም ይተረጉሙታል።

የጻፎችና ፈሪሳዊያን ስርዓተ ሕጎች ተብለው የሚታወቁት በአሁን ወቅት የአይሁድ ታልሙድ በመባልም ያታወቃሉ። ታልሙድ መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። ታልሙድ የሰዎች ሰርዓትና ወግ ሕግ በሰው አዕምሮ አነሳሽነት በወረቀት ሲንጸባረቅ ወይም ሲተረጎም ነው።

“5 ፈሪሳውያንም ጻፎችም። ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ ብለው ጠየቁት። 6 እርሱ ግን እንዲህ አላቸው። ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች። ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል

ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ 7 የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ በእውነት ትንቢት ተናገረ። 8 የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ ጽዋን ማድጋንም እንደ ማጠብ የሰውን ወግ ትጠብቃላችሁ፥ ይህንም የመሰለ

ብዙ ሌላ ነገር ታደርጋላችሁ። 9 እንዲህም አላቸው። ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል። 10 ሙሴ። አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ። አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና። 11 እናንተ ግን

ትላላችሁ። ሰው አባቱን ወይም እናቱን። ከእኔ የምትጠቀምበት ነገር ሁሉ ቍርባን ማለት መባ ነው ቢል፥ 12 ለአባቱና ለእናቱ ምንም እንኳ ሊያደርግ ወደ ፊት አትፈቅዱለትም፤

13 ባስተላለፋችሁትም ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ እንደዚሁም ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ። 14 ደግሞም ሕዝቡን ጠርቶ። ሁላችሁ እኔን ስሙ

አስተውሉም።”አለ ኢየሱስ። ማርቆስ.7፥5-9

በሰዎች ስርዓትና በእግዚአብሔር ሕግ መካከል ያለውን ልዮነት ከዚህ ጥቅስ በመነሳት በቀላሉ መመልከት እንችላለን። ኢየሱስ መልካም የሚናገረው ሰለ እግዚአብሔር ሕግ ብቻ ነው። ነገር ግን ስለ ሰዎችና ሽማግሎች ስርዓት የሚናገረው መልካምነት ፈጽሞ የለም። አንድ ሰው የእነዚህን የሁለቱን ልዮነት በደንብ ሊያጤን ይገባዋል።

ሐዋርያው ጳውሎስ ግልጽ አድርጎ ሕጉ እንዳልተሻረ አስቀምጦ አልፏል። ኢየሱስ ሕጉ የሚጠይቀውን የሃጢያት ዋጋ እንደ ሕጉ ለሁላችን ከፍሏል። ይህም ፍርድን የሚጠይቀውን የእግዚአብሔር ሕግ ቅጣቱን በመቀበል ሁሉን ወደ ፍጻሜ በማምጣት ሕግ ሰጪውንና ሕጉን በመፈጸም እግዚአብሔር አብን አርክቶታል። ትክክለኛ የጽድቅ ፍርድም በዚህ መልኩ እንደ እግዚአብሔር ሕግ ተከናውኗል።

ኢየሱስ ሕጉን በማስወገድ የመስቀልን ሞትን ሊያስወግድ ይችል ነበር። ሁሉንም ዝም ብሎ ይቅር ብያለው ማለት ይችል ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕግ ጥያቄ ለሟሟላት ሕጉ የሚጠይቀውን ሁሉ በመስቀል ላይ በመክፈል ሕጉ መፈጸም እንጂ መወገድ እንደሌለበት እግዚአብሔር ራሱ ቃሉንና ሕጉን አክባሪ እንደ ሆነ ማሳየት ነበረበት።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

35 www.tlcfan.org

ይህም ሕግ በመተላለፍ የሰራነው ሃጢያት የሚገባንን እዳ በሕጉ ለእኛ ተቀበለ። ከዚህም ከሕግ መታዘዙ የተነሳ እኛ የመስቀሉ ቃል ተጠቃሚዎች ሆንን። “የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የሚለው በአርያም ተሰማልን የመስቀሉ ቃልም ሃይላችንና ምሕረትና ደህንነት የምናገኝበት ብቸኛ ስራና ጉልበታችን ሆነልን።

ኢየሱስ በመስቀሉ ላይ የሆነውና የፈጸመው ሕጉ የሚጠይቀውን ፍርድ መደረግ መከፈል እንዳለበትና ለመክፈል በመስማማቱ ነው። በዚህም ሕግን መጠበቅ ተግባሩ የሰው ልጆችን ከሞት አዳነ። ሃጢያት መስራት ማለት ደግሞ ትዕዛዝን መተላለፍ ማለት ነው። ጳውሎስ ሃጢያት መስራትን ያወግዛል።

“14 ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና። 15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ

ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም።” ሮሜ.6፥14-15

ከሕግ በታች መሆን ማለት ምን ማለት ነው? አንድ ሰው ሃጢያት ስርቷል የሃጢያትን ዋጋ ሊቀበል ይገባዋል ማለት ነው። ምን ጊዜም ሰው በግል ሕይወቱ ሃጢያት ሲሰራ ከሕግ በታች ይሆናል። ይህም ስለ ሰራው ሃጢያት ነው። ይህ የሚያምነውንም የማያምነውንም ሰው ይጠቀልላል። የማያምኑትም ሁሉ በልባቸው እግዚአብሔር ያስቀመጠው ሕግ በውስጣቸው አለ። ሮሜ.2 ይህ ሃጢያት የሰራው ሰው የሃጢያቱን ዋጋ ሳይከፍል ወይም ንስሃ ሳይገባ ከሕግ በላይና ከጸጋ በታች አይሆንም።

ኢየሱስ በሕግ የሚጠየቀውን የሃጢያት ዋጋ ሲከፍል ሃጢያተኞች ነጻ ወጡ ከሕግ በላይ ከጸጋ በታች ሆኑ። ምክንያቱም ሕጉ የሚጠይቀው ሰለተከፈለ ነው። ከዚህም የተነሳ ሕግ ሃጢያተኛ የነበረውን አያሰጋውም። ምክንያቱም አሁን ከጸጋ በታች ሆኗልና ነው። ይህም የሆነው ሃጢያቱ ምንም ሆኖ ስላልተቆጠረ ሳይሆን ኢየሱስ ለሰራው ሃጢያት እዳውን ሰለከፈለለት ብቻ ነው። ሃጢያተኛው መክፈል ስላልቻለ ኢየሱስ ከፈለለት።

ይህ መሆኑ ግን ሃጢያት ሃጢያት መሆኑን አልቀየረውም። ሌባ አሁንም ቢሰርቅ ሃጢያተኛ ነው። መግደል አሁንም ሃጢያት ነው። ዝሙት አሁንም ሃጢያት ነው። ሃጢያት በምንም መልኩ በኢየሱስ የመስቀል ስራ ምክንያት ሃጢያት የመደረግ መብትን አላገኘም። የኢየሱስ መስቀል ሞት እንዳሳየው የሃጢያት ደሞዝ ሞት መሆኑን ነው።

መስረቅ፣ መግደል፣ ዝሙት ከክርስቶስ መስቀል ስራ በኋላ የጽድቅ ስራ አልሆነም። በብዙዎች አማኞች ዘንድ ግን መሰቀሉ ሃጢያትን የጽድቅ ስራ እንዳደረገው አድርገው የተቀበሉ ይመስላል። የፈለጋቸውን ሃጢያት እየሰሩ ምንም የማይሆኑ ይመስላቸዋል። ለዚህ ደግሞ ማባበያ ከጸጋው በታች ነኝ ይላሉ። ሃጢያት አሁንም ሃጢያት ነው። አሁን ቢሆን የሃጢያት ደሞዝ ሞት ነው። ኢየሱስ ሕግ የለሽ ኑሮ የሚኖሩትን በመንግስቱ ለመግባት ሲመጡ አላውቃችሁም እናንተ ሕግ የለሾች ብሎ ይመልሳቸዋል። መንግስት የሚመሰረተውና የሚጸናው በጸጋ ሳይሆን በሕግ ነው ስለዚህም መንግስቱ ሕግም አለው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

36 www.tlcfan.org

ምንንም አይነት መለኮታዊ ስራ መስራት፣ ታላላቅ ተዓምራት ማድረግ እግዚአብሔር ከመታዘዝ አይበልጥም። ይህ ሁሉ ድንቅና ታዓምር ማድረግ ወደ መንግስቱ ለመግባት ብቃትንም አይሰጥም። ዋንኛው ራሳችንን ልንጠይቅ የሚገባው ቅን ጥያቄ እግዚአብሔር እታዘዘዋለሁኝን? የሚል ጥያቄ ነው።

ሕጉ አሁንም ሆነ ወደፊት የእግዚአብሔር ባህሪ መገለጫ ሆኖ ለዘላለም ይኖራል። ሃጢያት ምን እንደሆነ አጉልቶ ያሳያል። የሚገባውንም ፍርድ አሁንም ይሰጣል። ኢየሱስ ለእኛ በመስቀል እዳችንን ሲከፍል ሕጉ እኛን ምንም እዳ አይጠይቀንም። በነጻ ይለቀናል። ምክንያቱም ኢየሱስ ሕጉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሁሉ ስለ ከፈለልን ነው። ስለዚህም አሁን በእርሱ ያመንን ሁሉ አዳም ከሰራው ሃጢያት ሕግ ተተያቂነት በታች ነጻ ወጥተን ከጸጋ በታች ሆነን ከሃጢያት ባርነት ነጻ ወጥተናል። ደግመን ግን በባርነት እንድንገዛ የእግዚአብሔር ፍቃድ አይደለም። አሁን ሃጢያት ብንሰራ መልሰን ከጸጋው ወድቀን ከሕግ በታች እንደምንሆን የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል። ሕጉም ለሰራነው ነገር የሚጠይቀን ዋጋ ይኖራል ማለት ነው። ጳውሎስ ጸጋ እንዲበዛ በሃጢያት ጸንተን እንኑርን? ሃጢያትን እናድርግን? አለና መልሱን በፍፁም!!!! በማለት አጋኖ ይመልስልናል። ሮሜ.6፥1,15

የመንገድ ፍጥነት ሕግ የተላለፈ ሹፌር ትራፍክ ፖሊስ ቅጣቱን እንደ ሕጉ ይሰጠዋል። ከዛም ሹፌሩ በመኪናው ሳያሳብብ ቅጣቱን ይቀበላል፣ ቅጣቱን ይከፍላል። ቅጣቱን ሊከፍለው ካልቻለ ከአቅሙ በላይ ከሆነ ያኔ ይህ ሹፌር ከሕግ በታች ይሆናል። መኪናውም ይታሰራል። ይህም ሕጉ የሚጠይቀውን እስከሚያሟላ ወይም እስከሚከፍል ነው። እንደ ምድር ሕግ ብናየው መክፈል ካልቻለ 30 ቀን እስር ቤት ይሄዳል። በ30 ቀን በዋስ ይወጣል ይህም ወይም አጎት፣ አባት ወይም ወንድም ከከፈለለት ከጸጋ በታች ይሆናል። ምክንያቱን ሕጉ የሚጠይቀውን ሌላው ዘመዱ ከፍሎሎታልና ነው። አሁን እዳው ስለተከፈለ ሕግ ከበታች ማድረጉን ትቶ በነጻ ይፈታዋል።

ነገር ግን ልጠይቃችሁ ይህ ሰው ከተፈታ በኋላ የፍጥነት ሕግን አሁንም ደጋግሞ ቢተላለፍ ዘመዶቹ ምን ያደርጋሉ? ዘመዶቼ ይከፍላሉ ብንል ቢከፍሉ እንኳን ዘመዶቹን ያኮራቸዋልን? በፍጹም አያከብርም፣ አያስደስትም። ልክ እንደዚሁ ብዙ ክርስቲያኖች ሕጉን መተላለፍ ምንም ነገር እንደማያመጣ ስለተማሩ እግዚአብሔርን እያሳዘኑ ያሉ ብዙዎች ናቸውም። ምክንያቱን ለእግዚአብሔር ሕግ መገዛት ተስኗቸዋልና ነው። ይህም ኢየሱስ እዳዬን ሁሉ ከፍሏል በማለት ነው። ይህ የልቅነት ሕይወት እግዚአብሔር ያለመታዘዝ ሕይወት እግዚአብሔርን ደስ አያሰኘውም።

“6 ስለ ሥጋ ማሰብ ሞት ነውና፥ ስለ መንፈስ ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው። 7 ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም ተስኖታል፤ 8 በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም።”ሮሜ.8፥6-8

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

37 www.tlcfan.org

ደግሜ እላለሁ ኢየሱስ ሃጢያትን ሕጋዊ ወይም የጽድቅ ስራ እንዲሆን አለደረገውም። ሃጢያት አሁንም ሃጢያት ነው። ሃጢያት አሁንም ቅጣት አለው። አማኞች አሁም ሃጢያትን የመስራት መብት የላቸውም። ማንኛው ስው ሃጢያት ቢሰራ በእግዚአብሔር ሕግ መሰረት የሚገባውን ዋጋ ይከፍላል። ይህ በአሁን ወይም በሚመጣው በመንግስቱ ዘመንም ነው። ዮሐንስ እንቅጩን ሲነግረን ሃጢያት ሕግ የለሽነት ነው የለናል።

lawlessness

ኢየሱስ በመንግስቱ ሲመለስ ብዙዎች ወደ እርሱ መጥተው ብዙ ነገር በስሙ እንደ ሰሩና ለመግባት ብቁ እንደሆኑ ራሳቸውን ብቁ አድርገው ሲናገሩ እናያለ። እነዚህ ሰዎች የዚህን ዘመንን አማኞች በብዛት ይመስላሉ። እርሱ ግን እንዲህ ይላቸዋል፦ “እናንተ ልቅ ኑሮን ሕግ እንደሌለው ሰው የምትኖሩ ሕግ የለሾች ከእኔ እራቁ” አላውቃችሁም ይላቸዋል።

lawlessness (Matt. 7:23)

እግዚአብሔር ሕግ የመንግስቱ ሕግ የተሰጠው የሕግ የለሽ የሰው ባሕሪን ለማስወገድ ሃጢያትን ገልጦ በሃጢያት ላይ ለመፍረድ ነው። እግዚአብሔር ሕግ የለሽ ኑሮን ችግር የሚያጠራበት ሁለት አይነት መንገድ አለው። የብሉይ ኪዳን መንገዱ ሕግን በሕግ የለሽ ኑሮ በሚኖረው ሰው ላይ በማጠንከር በሰውርም ሆነ በአደባባይ በሕዝብ መሃከል በመቅጣትና ሌላው ሕጉን እዲጠብቅ እንዲማር ማድረግ ነው። የአዲስ ኪዳን መንገድ ደግሞ በክርስቶስ የጸናው ሲሆን እንደ ብሉይ ኪዳኑ በውጭ ሃይል በመተቀም ሳይሆን ከውስጥ ከሚመነጭ በገዢውና አስተዳዳሪው በመንፈስ ቅዱስ ሃይል ሕጉን እንዲጠብቅ ማድረግ ነው።

የብሉይ ኪዳኑ መንገድ በከፊል ስርቷል። ነገር ግን ታሪክ እንደሚያሳየው ይህ ከፍራቻ የተነሳ የሚጠበቀው ሕግ ከሞላ ጎደል መጨረሻው ጥሩ እንዳልሆነ ወጤታማ እንዳልሆነ ስለታየ እግዚአብሔር ራሱ ይህን ኪዳን ስለደከመ ለውጦታል። ምክንያቱም ሰዎች አስተሳሰባቸው እየበሰለ በመጣ ቁጥር ሃጢያትን ተሰውረው ማድረግን ተማሩ ብዙ ሕግ ደግሞ ሃጢያተኛው ካልተያዝ አይፈርድም ነበር። ምክንያቱም በልብ ሳይሆን ከውጭ በቀለም የተፃፈ ነበርና ብዙዎችን ሃይለኛ ሯጭ ከመሆናቸው የተነሳ ምሕረትን በሩጫ ፍጥነት ተቀበሉ። ሮጠው መማጸኛ ከተማ ይገቡ ነበር። አሁን ግን ምሕረት ለሮጠ ወይም ለወደደ አይደለም። አሁንም ብዙ አቢያተክርስቲያናት የመማጸኛ ከተማ ናቸው። አንዱ ጋር ሃጢያት ሰርቶ ወደ አንዱ መመጸኛ ከተማ ሄዶ ይደበቃል። ቤተክርሲያን እንደ እግዚአብሔር ሕግ መፍረድ ተሰኗታል። ሰዎችን እንደ እግዚአብሔር ሕግ እንዲኖሩ አታስተምርም።

ከዚህም የተነሳ ነገስታት ሆነ መሪዎች በተለዋወጡ ቁጥር ሕጉን በተለያየ መልኩ ሊያጠነክሩት ሊያላሉት ሞከሩ የራሳቸውንም አይነት ፍርድ እንደ መሰላቸው በአዋጅ በማቆም አሁን ያለንበት የተራቀቀ ፍርድ ዘመን ላይ አምጥተውናል። ይህም አመፅን ለመቀነስ በሚል ሰበብ ነው። ይህ ሁሉ ቢሆንም አመጽ ደግሞ የዚያኑ ያህል በተለያየ ምድራዊ ጥበብ መጨመሩን ቀጥሏል። ሕጋቸው እንደውም የአመጽና የሃጢያት ማዳበሪያ ሆኖ ሃጢያት ፍሬን አፍርቶ ልጣጩ በየሜዳው ወድቆ ብዙዎችን ማዳለጡት ቀጥሏል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

38 www.tlcfan.org

አዲሱ ኪዳን ሕጉን ከውጭ ሆኖ በመቀያየር የተለያየ ፍርድ በየወቅቱ በማምጣት ሳይሆን። ያው የመጀመሪያውን የእግዚአብሔር ሕግ በመጠቀም ልባችንን ከውጭ በመጫን ሳይሆን እያባበለ ለልባች ሊናገረን ሕጉን በልባችን ሊጽፍ ወደሚያስተምረን ምድረበዳ ሕይወት እየተለማመጠና እያባበለ ያስገባናል። ለውጥንም ከውስጥ ከልባችን በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በመጀመር እስከ ውጨኛው አካላችን ይሰራል። ሕጉን በቀለም ሳይሆን በልባችን ላይ በመንፈስ ይጽፈዋል። ይህም ከእግዚአብሔር ባሕሪ ጋር እንድንመሳሰል ያደርገናል። ይህም ከእግዚአብሔር ጋር በልባችን መስማማት እንድናደርግ ነው።

ቃሉን ሕጉን በማንበብ የቃሉን ጸሃፊ የልብ ትርታ በማየት በመንፈስ በመመራት ስንረዳ የሚመጣና በፍቅር የሆነ ነው። ያኔ ሕጉ በኢየሱስ አይን እይታ ውስጥ መመልከት እንችላለን። በዚህ መልኩ የእግዚአብሔር ሕግ የእግዚአብሔርን ባህሪ በእኛ ውስጥ መገለጫ ይሆናል። ይህ የእግዚአብሔር ባህሪ የአማኙ ባሕሪ ይሆናል።

ውጫዊ ሕግ መጫን እግዚአብሔር የመረጠው መንገድ አይደለም። ነገር ግን በልብ የሚፃፍ ልብን የሚሰራ የሚገርዝ ሕግ ከውስጥ ተነስቶ የሚለውጥ የእግዚአብሔር መንገድ ነው። ሰው የሚያደርገው በልቡ ያለውን ነው። በልቡ ለውጥ የመጣለት ሰው ብጹህ ነው። ይህ የአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር የመረጠው መንገድ በኢየሱስ የመረቀው አዲሱ መንገድ ነው። ይህ መንገድ በምድር ላይ ጽድቅ እንዲቆም ያደርጋል። የመንግስቱ ሕግ ያኔ በመንግስቱ ዜጎች ልብ ላይ ይጻፋል።

እግዚአብሔር በአሁን ወቅት ቅሬታውን ጥሩ የመንግስቱ ዜጎች እንዲሆኑ የመንግስቱን ሕግ በማስተማር ላይ ይገኛል። ይህም ለመንግስቱ ግዛት የተዘጋጁ ለማድረግ ነው። እነርሱ ለሌሎች የጽድቅ ባሕሪን በማሳየት ምሳሌን ምስክር ሆነው ለክብሩ በሕዝቡ ፊት ይቆሙለታል። እግዚአብሔርን የሚያስደስቱ ልጆች ሆነው ይገለጣሉ። ፍጥረትም እነርሱን እስካሁን በናፍቆት ይጠባበቃል። እነርሱም ከእርሱ ጋር ሆነው በመንግስቱ ሕግ መሰረት ይገዛሉ።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

39 www.tlcfan.org

የመንግስቱ ግዛት

የእግዚአብሔር መንግስት የራሱ የሆነ ግዛት አለው። ይህም እግዚአብሔር የፈጠረውን ነገር ሁሉ አጠቃሎ ይይዛል። ይህ በስማይም ሆነ በምድር ያለውን ሁሉ ያጠቃልላል። እግዚአብሔር ባለቤቱ የሆነው ነገር ሁሉ የመንግስቱ ግዛት ክፍል ነው። ምድርን በመፍጠሩ እግዚአብሔር የባለቤትነት መብቱ የራሱ ብቻ ነው። ምድርም ሆነ ሰማይ የሚታየውም ሆነ የማይታየው የእግዚአብሔር ግዛቱ ናቸው።

በሙሴ ዘመን እግዚአብሔር ለእስራኤላዊያን የከንዓንን ምድር እንዲወርሱ ሲስጣቸው ሕዝቡ የምድሪቱ ባለቤቶች እንዳልሆኑ እግዚአብሔር ግልጽ አድርጎ ነግሯቸዋል። የምድር ባለቤትነትን መብት እግዚአብሔር ፈጽሞ ለሕዝቡ አልተሰጣቸውም። ነገር ግን በምድሪቱ ላይ እንዲነግሱና እንዲኖሩ ስልጣንን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀብለው ነበር። የምድሪቱ ባለቤት ግን እግዚአብሔር ነው። ይህን በዘሌዋውያን.25፥23 ላይ እናገኛለን።

“23.ምድርም ለእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ። 24.በርስታችሁም

ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ አድርጉ።”

በሌላ አማርኛ ሰዎች ምድርን የሚጠቀሙበት ስልጣን በእግዚአብሔር ሕግ የተወሰነ ነበር ማለት ነው። ይህን ሕጉን ለመጠበቅ እንቢ ቢሉ በምድሪቱ ላይ የተሰጣቸውን ስልጣን እንደ አዳም ያጣሉ ደግሞም ከምድሪቷም ይወገዳሉ። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግስቱ ሕግ ከላይ እንዳየነው ፈጽሞ አያዳላም አያመቻምችምና ነው። ዘሌ.26፥33

“33፤ እናንተንም ከአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፥ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፥ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ። 34፤ በዚያም በተፈታችበት ዘመን ሁሉ እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር ሳላችሁ፥ ምድሪቱ ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ በዚያም ጊዜ ምድሪቱ ታርፋለች፥ ሰንበትንም በማድረግዋ

ትደሰታለች።35፤ እናንተ ተቀምጣችሁባት በነበረ ጊዜ በሰንበቶቻችሁ አላረፈችም ነበርና በተፈታችበት ዘመን ሁሉ ታርፋለች።”

የእስራኤል በከነዓን ምድር ላይ በስልጣንና በገዢነት የመመላለስ መብት ሕጉን በመታዘዘው ላይ የተወሰነ ነበር። ሕዝቡ ግን ምድሪቱን እንደ ራሳቸው ንብረት በመቁጠራቸው ሕጉን አልታዘዙም ምድሪቱ የሚገባትን የሰንበት እረፍትን አልሰጧትም።

ስለዚህም እግዚአብሔር ከምድሪቱ ጠርጎ አስወጣቸው። ምድሪቱን በሕዝቡ ምክንያት በነገሱባት ሰዎች ምክንያት ያጣችውን ሰንበት እንድታደርገ ተደረገች። በመጀመሪያ ጠርጎ ከወረሷት ምድር ከከነዓን ያስወጣቸው የባቢሎን ንጉስን ንጉስ ናቡከደነዖርን በመጠቀም ነው። ከዛም በኋላ ደግሞ በመጨረሻው ዘመን በሮም መንግስት ነው። በንጉስ ናቡከበነፆር ከምድሪቷ ሲያስወጣቸው ይህንን የምድር ባለቤትነት መብቱን በድጋሚ ነግሯቸው ደግሞም ለወደደውም የመሰጠት መብቱን በነብዮ ኤርሚያስ በኩል እግዚአብሔር ገልጦላቸው ነበር።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

40 www.tlcfan.org

“5 ምድሪቱን በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ፤ ለዓይኔም

መልካም ለሆነው እሰጣታለሁ። 6 አሁንም እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባሪያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ይገዙለትም ዘንድ የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።”

ኤር.27፥5-6

ምድር የእግዚአብሔር ክብር እንድትገልጥ የተፈጠረች ናት። ይህም እግዚአብሔር ክብሩን የመግለጥ እቅዱና አላማው በፍጻሜ ወደ ክንውን ይመጣል። እግዚአብሔር በእቅዱና በዓላማው መቼም ቢሆን ወድቆ አያውቅም። የከንዓን ምድር ውርስና አገዛዝ ሚስጥር ወደፊት ሊፈጸምና ሊገለጥ ላለ ለታላቅ ፍጻሜ የከበረ ትንቢታዊ ጥላ ነው። ከንዓንን ሆነ ሕዝበ እስራኤል እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ሊያደግ ያለውን ለማሳየት የፈጠራቸው የእርሱ ሞዴሎች ናቸው። እግዚአብሔር የከነዓን፣ የአብርሃም፣ የይሳቅና የእስራኤል አምላክ ብቻም አይደለም። እርሱ እግዚአብሔር የምድር ሁሉ አምላክም ይባላል። ይህ ደግሞ የሰው ልጆች ሁሉ አምላክም ያደርገዋል።

“5.ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፥ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።” ኢሳ.54፥5

ብሉይ ኪዳን የመጀመሪያው እግዚአብሔር አላማውን ሊፈጽም የጀመረበት መንገድ ነበረው። ነገር ግን ይህን የከበረውን አማውን በመጀመሪያው አዳም መፈጸም እዳይችል ተደርጎ በራሱ በእግዚአብሔር በቀደመ እውቀቱ የተቀረጸ ነበር። ይህም ሰዎች ማንነታቸውን ማወቅ እንዲችሉና እንዲማሩ ለማድረግ ነው። “በተስፋ ስላስገዛው እንጂ በፍቃዱ አይደለም” ሰው በፍቃዱ ሳይሆን በራሱ በእግዚአብሔር በቀደመ እውቀቱና ፍቃዱ ተገዛ። ሮሜ.8፣ ኢዮ.12፥16 ፣ ዘፍ.3

ብሉይ ኪዳን ሃላፊነትን በሰው ላይ ይጭን ነበር። ይህም ሰው መንግስቱን ለማቆም የራሱ ጥረት ያስፈልገው ነበር። ዘጸ.19፥8 ይህ ደግሞ በስጋ የሆነ መደገፍን ያመጣል። እግዚአብሔር በስጋ መደገፍ ያለበት መንገድን አስወግዶ በእውነተኛ መንፈሳዊ ልምምድ የተሞላውን መንገድ ሊያመጣ የድሮው አካሄድ በአዲሱ ሊቀየር ተገባው።

በዚያን ዘመን መጀመሪያ እስራኤል ከዛም ይሁዳ ከዚህ ሁሉ ነገር በራሱ ጥረት ሰው ማድረግ ስላልቻለ ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር መንግስት በምድር ላይ ለማምጣት ሞክሮ አልቻለም። ሁሉ ወደቀ። ምክንያቱም ሕጉ መንፈሳዊ ነው። ነገር ግን እንጠብቀዋለን ብለው ቃል የገቡት ስዎች ግን መንፈስ ለዘላለም ያደራባቸው ስላልነበሩ ሕጉን መጠበቅ ተሳናቸውም። ሰው ሁሉ ከስጋና ሃጢያት የተነሳ ደካማ ስለነበረ ነው። ከዚህም የተነሳ ሕጉን በመተላለፉ ሕዝቡ ከግዛቱ እንደ እግዚአብሔር መንግስት አገዛዝ ሊገዛው ከተሰጠው ምድር ተወገደ። እግዚአብሔር ከዛ ዘመን በኋላ እራሱ ሃላፊነትን የሚወስድበትን አዲስን ኪዳን በደሙ አቆመ። ይህም ጌታ አስቀድሞ ሰው ያለ እግዚአብሔር ምንም መስራት እንደማይችል ካሳየ በኋላ ነው።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

41 www.tlcfan.org

አዲስ ኪዳን ያስፈለግው ጽድቅንና የእግዚአብሔር መንግስትን ግዛትና አገዛዝ በምድር ላይ ለማምጣት ነው። በአዲስ ኪዳን እግዚአብሔር ኪዳኑ ሲያደርግ እኔ አደርጋለሁ ስለዚህ እናንተም ከእኔ የተነሳ ታድርጋላችሁ አለን። ይህ ደግሞ ከብሉይ ኪዳን ፈጽሞ የተለየ ኪዳንና አሰራር ነው። በብሉይ እግዚአብሔር ኪዳኑን ከሰው ልጆች ጋር ሲያደርግ ያለው ያልኩትን ብታደርጉ እኔ አደርግላችኋለሁ ነበር። አዲሱን ኪዳን ልዩና ክቡር የሚያደርገው ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ችሎታ እንጂ በሰው ጥረት ላይ ያልተመሰረተ ሰለሆነ ነው። ይህም ሕጌን በልባችሁ እጽፈዋለሁ። እራሱ እግዚአብሔር ሊጽፍ ቃል ገባ። ደግሞ አለ ፦ በትዕዛዛቴም አስኪዳችኋለሁ። እግዚአብሔር ራሱ በእርሱ ትእዛዝ እንደሚያስኬደን ቃል ገባልን። ከእኛ የሚጠበቀው የልብ መዘጋጀት ብቻ ነው።

በመቀጠልም ይህ በእነርሱ የተፈጸመው የእግዚአብሔር ታሪክ ከአንድ ሃገር ከንዓን ከማውረስ ያለፈ ምድርን ሁሉ የሚያሰወርስ ጥላዊ ኪዳን ነው። እግዚአብሔር ይሁዳን ከከንዓን በኤርምያስ ዘመን ባስወገደ ጊዜ ሰዎቹ የሰባ አመት ባርነት ብቻ መስሏቸው ነበር። ከዛም ዘመን በኋላ ወደ ግዛታቸው የሚመለሱ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ለናቡከደነፆር በሕልም እንደገለጠለትና እንዳረጋገጠለት የወርቁ እራስ እርሱ ነበር። ዳን.2 ነገር ግን በሕልም የታየው ምስል እንደሚያሳየው ይህ ባርነት ከባቢሎንም አልፎ እስከ መጨረሻው ዘመን እንደ የሚቀጥል የሚያመልክት ነው።

ከዛም የይሁዳ የ70 ዓመት ባርነት ሲፈጸም ራሳቸውን በፋርስና በሜዶን ባርነት ስር አገኙት። እነዚህ ሁለት መንግስታትና ገዢዎች ሁለቱን የብር ክንዶችን የሚወክሉ ናቸው። ይህ ባርነት ቀጥሎ በግሪክ በመጨረሻም በሮም ከዛም ዳንኤል በሕልሙ የሮም መንግስት ደግሞ በትንሽ ቀንድ እንዴት እንደሚያከትም ይናገራል። ከዛም ከትንሹ ቀንድ በኃላ በተከፋፈሉ መንግስታትም ዘመን ፍጥረታዊው ባርነት ቢያበቃም መንፈሳዊ ባርነቱ አሁንም ቀጥሏል። ነገር ግን ባርነቱ በዓይን የሚታይ አይነት ባርነት አልነበረም።

“20.በራስዋም ላይ ስለ ነበሩ ስለ አሥር ቀንዶች፥ በኋላም ስለ ወጣው፥ በፊቱም ሦስቱ ስለ ወደቁ፥ ዓይኖችና ትዕቢት የተናገረ አፍ ስለ ነበሩት፥

መልኩም ከሌሎች ስለ በለጠ ስለ ሌላው ቀንድ እውነቱን ለማወቅ ፈቀድሁ። 21. እነሆም፥ ያ ቀንድ ከቅዱሳን ጋር ሲዋጋ አየሁ፥ 22. በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ

ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።”

ዳን.7፥8, 20-22

ይህም በፓፓል ሮም የኢቴሪያል ሮም ውድቀት ፍጻሜን አግኝቷል ይህም 476 A.D ከክርስቶስ ልደት በኋላ ነው። ዳንኤል በሕልሙ የመንግስታቱን መለዋወጥ ብቻ ሳይሆን በመጨረሻው ምድር ለቅዱሳኑ እንደምተሰጥ ይናገራል። ይሁንና ትንሹ ቀንድ ቅዱሳንን የተዋጋው በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ መሆኑን ይናገራ። ያኔ በኢየሱስ ዳግም ምጽዓት ረጅሙ የመንፈሳዊ ባርነት ዘመን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያበቃል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

42 www.tlcfan.org

ወደ አዲስ ኪዳን ቅዱሳን መጻሕፍት ስንመለስ ቅዱሳኑ ስልጣን እንደሚሰጣቸው ቃሉ ይናገራል። ይህም ስልጣን የሚሆነው በብሉይ ኪዳን መሰረት አይደለም። በአዲሱና በደሙ በቆመው በማይናወጥው አዲስ ኪዳን ሃይልና ብቃት ነው። እግዚአብሔር ባቢሎን የሞከረውን የሁሉን በአንድ መንግስት ስር የመሰብሰብ እቅድ እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መንገድ ሁሉን በመንግስቱ ስር በመሰብሰብ ይፈጽመዋል። በመጀመሪያ ድል ነሺዎችን ከዚያን በ8,000 ዓመት ጅማሬ መልካምን ክፉ ያደረጉት ይጠቀልላ። ይህን ዘመን ሁሉ ለፍርድ ከሚነሱበት ዘመን ነው።

ናምሩድ በዘፍጥረት.11፥4 ላይ ሞክሮት ያልተሳካለትን እግዚአብሔር በኪዳኑ በኩል ያቆመዋል። እግዚአብሔር ባቢሎንን ያስወግዳታል። ያኔም እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ባለቤትነቱ በፍጥረት ሁሉ ዘንድ ይታወጃል። ምስሉ የተፈጨው ድንጋዪ ከተራራ ተፈንቅሎ ሲመጣ ነው። የምድር መንግስታት ሰማቸው ተለዋወጠ እንጂ ፈጽመው ገና አልፈረሱም። ከተራራ ተፈንቅሎ የሚመጣው ሕያው ድንጋይ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በዳግም ምጽዓቱ ምስሉን ፈጽሞ የፈጨዋል። ምድን ፈጽሞ ግዝቱ ያደርጋታል።

ክርስቲያኖች ሆኑ የምድር ነግስታት የባቢሎንን መንፈስ በመመራት አንድ አለም፣ አንድ ኢኮኖሚና አንድ ሃይማኖት ለማቋቋም የሚጓዙት ጉዞ አሁን ተረድተውት ይሆናልን? ነገር ግን ይህ ፍጽሞ በሰው ጉልበት የማይሆን በሙከራ የሚቀር የሰው ጥረት ነው። ሰዎች ዛሬ ይህንን አይነት መንግስት ለማቆም የሰዎችን ድንበር ጥሰው ይገባሉ። እግዚአብሔር የሾማቸውንም ያዋርዳሉ። ይህ ሁሉ ያለ እግዚአብሔር ፍርድ የሚያልፍ በፊቱ ዝም ተብሎ የሚታለፍ ነገር አይደለም። ይህና በዓለም ዙሪያ ወደ ፊት የሚሆነው ነገር ብዙ አማኞችን ያስፈራቸዋል። ነገር ግን የእግዚአብሔር እቅድና አላማ የገባቸው አማኞች ግን በጣም በደስታ የተስፋውን ፍጻሜ ይጠባበቃሉ። ከእግዚአብሔር የሚሰማ በእርጋታ ይቀመጣል።

ይህ ሁሉ መንገድና የታሪክ ክንውን ግን የእግዚአብሔር የጠለቀውን የእቅዱን ሚስጥር መፈፀሚያ መንገድ እንደ ሆነ እናምናለን። እግዚአብሔር ባቢሎናዊያንን ንጉስ እንደ ባሪያው ያኔ እንደተጠቀመ ዛሬም እንዲሁ ነው። እርሱ የወደደውን ባሪያዬ ነው ይላል። ሁሉን አሳልፎ በእጁ ይሰጠዋል። ኤር.25፥6 እነርሱ በራሳቸው ሰርተው ሲጨርሱ እግዚአብሔር የቀረጸውን ደግሞ ወደ ሙላት ያመጣዋል። ስለ ምድር ገዢዎች እርሱ የሚለው ብዙ ነገር አለ። የሚደንቀኝ ግን በእነዚህ ጥቅስ ላይ የተቀመጠው ተሰፋ ቃል ነው። ራዕይ.11፥15 ሉቃ.12፥42-44 ኢየሱስ የማይጨቁን አገልጋይ ታማኝ አገልጋይ። የማይጨቁን ገዢ ስልጣን እንደሚሰጠው በግልጽ ይናገራል።

ታማኝ ባሪያ በዚህ ጥቅስ መሰረት እግዚአብሔር ባለው ሁሉ ላይ እንደሚሾመው ይናገራል። ይህ ማለት መሪ ለመሆን ያልበቁት ሰዎችን ሁሉ ይመሯቸዋል ማለት ነው። መሪነት የተሰጣቸው ሌሎችን በፍቅር በምሕረት ሰለገዙ ነው። ሌሎችን ስላላስጨነቁና በፍርድ አድሎን ስላላደረጉ ነው። ለዚህ ክብር በቂ የምንሆነ በዚህ ምድር በምንኖረው አኗኗር ማንነት የእለት ተዕለት ተግባራችን መሰረት በእግዚአብሔር ተፈትነን ነው። ዳንኤል እነዚህን መሪዎች የልዑሉ ቅዱሳን ይላቸዋል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

43 www.tlcfan.org

“27.መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል

ይታዘዙለትማል።28. የነገሩም ፍጻሜ እስከዚህ ድረስ ነው።” ዳን.7፥27

ይህ መንግስት የሚሰጣቸው የድንጋዮ መንግስት ምስሉን ፈጽሞ ሲፈጨው ነው። ይህንን በተመሳሳይ በራዕይ ላይ እናገኘዋለን። ራዕይ.5፥10 እነዚህ እነማን ቅዱሳን ናቸው? ብዙዎች ጺዮናዊ ክርስቲያኖች በመጨረሳው ጊዜ የሚቀየሩት አይሁዶች ናቸው ብለው ያምናሉ። አንዳዶች ደግሞ የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ሁሉ እንደ ሆኑ ያምናሉ። አንዳዶች ደግሞ144,000 ብቻ ናቸው ይላሉ።

የእግዚአብሔር ቃል ግን አዲስ ኪዳን አማኞች ሁሉ ብሎ አያስተምርም። ሁሉም ከላይ ያየናቸው ትክክለኛ መረዳት አይደሉም። ትክክለኛው በእግዚአብሔር መንግስት ግዛት የሚሰጣቸው ድል ነሺ አማኞች ብቻ ናቸው። እነዚህም ድል ነሺዎች በፋሲካና በበዓለ ዓምሳ ያለውን የእምነት እድገት ጉዞ በሚገባ የተወጡ ናቸው። እነርሱ ናቸው ከበዓለ አምሳ ወደ ዳስ በዓል በዓልን እንዲያደርጉ የተጠሩት። ይህ ደግሞ ትውልድና ዜግነት የሚጠይቅ ሳይሆን ስራን ተግባርን መንግስትን መታዘዝ ኑሮን የሚጠይቅ ነው።

ሰው ከአንድ ዘር ብቻ ሰለ ተወለደ ምንም አይነት ሰው ቢሆን መሪና ንጉስ ይሆናል ብሎ ማሰብ ትክክል አይደለም። ከእርሱ ጋር አብሮ ለመንገስ የእርሱን ባሕሪ ራሳችንን በማስለመድና ባሕሪውን መልበስ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ነው ጳውሎስ ክርስቶስን ልበሱ የሚለው። ለመንግስቱ ብቁ የሚያደርገውን ባሕሪ አንስቶ መልበስ የአማኙ ሃላፊነት መሆኑ አወቀን የተሰጠንን የእርሱን ባሕሪ ለማድረግ መነሳት ተገቢ ነው። ልብሱን ወይም ባሕሪውን ግን እግዚአብሔር በልጁ በኩል ሰጥቶናል።

እግዚአብሔር መሃከል ያለውን የጥል ግድግዳ ያፈረሰው አዲስን አንድ ሰው ይፈጥር ዘንድ ወዶ ነው። ኤፌ.2፥15 ይህ አዲስ ሰው ግን አንድ ሰው ብቻ አይደለም። ክርስቶስን ራስ ያደረጉ ብዙ ድል ነሺዎችን ሁሉ የሚጠቀልል ሰው ነው። ሁሉ አማኝ በፋሲካ ሊጸድቁ በበዓለ አምሳ ሊቀደሱ በዳስ በዓል ደግሞ ሊከብሩ ይገባቸዋል። እነዚህ ሁሉ እድገት ያለፉ የእርሱ አዲስ ፍጥረትና ድል ነሺዎች ናቸው። ከዚህም የተነሳ ለመጀመሪያው ትንሳኤ ግዛት ለሚሰጥበት ትንሳኤ ብቁ ይሆናሉ። ይህ የሚሻለው የመጀመሪያው ትንሳኤ ነው። (የሙታን ትንሳኤዎች የሚለውን መጽሐፌን ያንብቡ)

ጳውሎስ ይህን አዲስ ሰው በሐዋርያትና በነብያት መሰረት ላይ የተመሰረተ ኢየሱስን እንደማዕዘን ድንጋይ የያዘ ነው ይለዋል። ምንም እንኳን የተለያየ መገለጥ ከዚህ ጥቅስ ብንጎትትም ዋናው ቁም ነገሩ ከጌታ ጋር ያለው ሕብረትና መጣመር መገጣጠም የሚያሳይ ነው።

“4 ዙፋኖችንም አየሁ፥ በእነርሱም ላይ ለተቀመጡት ዳኝነት ተሰጣቸው፤ ስለ ኢየሱስም ምስክርና ስለ እግዚአብሔር ቃል ራሶቻቸው የተቈረጡባቸውን ሰዎች ነፍሳት፥

ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን ምልክቱንም በግምባራቸው በእጆቻቸውም ላይ

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

44 www.tlcfan.org

ያልተቀበሉትን አየሁ፤ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ። 5 የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው። 6

በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ

ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።” ራዕ.20፥6

ድል ነሺዎች የስንበት ወር እስኪያልፍ አንድ ሺ አመት እስኪፈጸም አብረውት ይገዛሉ። ይህም ስንበት የምንለው ከአዳም መፈጠር ጀምሮ ያለውን አንድ ሳምንት ይዘጋሉ። ከዛም ሁለተኛው የእግዚአብሔር ታላቁ ጉዞው ይጀምራል። ይህም ታላቁ ጉዞ ሁሉም ሙታኖች በማሳት ይጀምራል። ይህ ደግሞ ሁለተኛው ትንሳኤ ወይም መልካም ያደረጉና ክፉ ያደረጉ የሚነሱበት ትንሳኤ ነው። እነርሱም ሁለቱንም ወገኖች እንደ ስራቸው ይፈረድባቸዋል። የማያምኑ ሁሉ ለድል ነሺዎች ታልፈው ግዛት ሆነው ይሰጣሉ። ሁሉ ተንበርክከው ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፋቸው አስቀድመው ይመሰክራሉ።

“9 በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ 10 ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ 11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ

ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።” ፊሊ.2፥10-11

ይህ ደግሞ ያለ መንፈስ ቅዱስ የሚሆን አይደለም። ሰለዚህ መንፈስን ይቀበላሉ ማለት ነው።

“3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር። ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር። ኢየሱስ ጌታ ነው

ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ።” 1ቆሮ.12፥3

ይህ በዚያን ወቅት ለእነርሱ ሁለተኛው የፋሲካ በዓል ልምምድ ይሆንላቸዋል። ዘሁ።9፥6-7 ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አማኞች ይሆናሉ። በቀሪው ዘመን ግን ፍጻሜ እስኪመጣ በዓለ አምሳን በማድረግ ጽድቅንና ቅድስናን ከድል ነሺዎች ይማራሉ። ይህም የፍጥረት ኢዮቤልዮ እስኪሆን ድረስ የሚቀጥል ነው። ይህ ኢዮቤልዮ ሲሆን ደግሞ ፍጥረት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅ ነጻነትን ይቀበላሉ። ይህንንም ክብርና የእግዚአብሔር ነጻነት ይለማመዳሉ። የመንግስቱ ግዛት ሰማይና ምድርን በስጡ ያሉትን ሁሉ የሚጠቀልል ነው። ሰለዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ግዛት ነው። እርሱም ለወደደውና ለታማኝ ባሪያ ግዛትን ይሰጣል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

45 www.tlcfan.org

የመንግስቱ ሰራዊቶች

የእግዚአብሔር መንግስት ሰራዊቶች መላእክት ናቸው። መላእክት የሚለው ቃል የመጣው ከግሪኩ “አጊሎስ” ከዕብራይስጡ “ ማላክ” ከሚለው ቃል ሲሆን ቀጥተኛ ትርጓሜው መልክተኛ፣ መልክትን ተቀብሎ የሚያስተላልፍ፣ የሚላላክ ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ መላእክት የሚለውን ቃል ለሰዎችም ይጠቀመዋል። ራእይ.1፥20 ይህም የእግዚአብሔር መልክተኛ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው። ሌላው ደግሞ በቃሉ ውስጥ የእግዚአብሔር መለአክ ተብሎ በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው ኢየሱስ በስጋ ከድንግል ማርያም ከመወለዱ በፊት የሚገለጥበት ማንነቱ ነው። የሰማይ መላእክት ደግሞ እንደ ሚካኤል፣ ገብርኤልና ሱራፌል ያሉትን በሙሉ ይጠቀልላል። መላእክት “ማላክ” የሚለው ለአገልጋይ፣ መልክትን ይዞ ለሚመጣ ነብይ፣ አንዳዴም ለሰማይ መላእክትም ቃሉ ሲጠቀመው እናገኛለን። (ኢሳ.42:፥19)

በጥቅሉ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት በቂ የሆነ መረጃን ይሰጠናል። መላእክት እነማን ናቸው? ከየት መጡ? ስንት ናቸው? ምን አይነት አካል አላቸው ወይም በምን አይነት አካል ይገለጣሉ? ክንፍ አላቸው የላቸውም? ሁሉ መለአክቶች መልካም ናቸው አይደሉም? መላእክት ስንፍና አላቸው የላቸውም? መላእክት ለምን ተፈጠሩ? የት ይገኛሉ? የወደቁ መላእክት አሉ የሉም?… ወዘተ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ይመልሳል።

ኢየሱስ ስለ መላእክት በምድር በነበረት ወቅር አስተምሯል በመላእክትም ተገልግሏል። ስለዚህ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች የእግዚአብሔር መንግስት ሰራዊት ስለሆኑት ስለ መላእክት መሰረታዊ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል። መላእክት ቁጥራቸው ከመጠንና ከመታወቅ በላይ አላፋት ጊዜ አላፋት ነው። ዕብ.12፥22-23፣ ዳን.7፥10፣ ማቴ.26፥53 መላእክት ስም ስልጣንና የስልጣን ደረጃ አላቸው፣ የስራ መደብም አላቸው።

ቀዳሚውና የመንግስቱ ዜጎች የሆንን ልናውቀው የሚገባው ስራቸው እኛን የሚያገለግሉና ለማገዝ ከእግዚአብሔር መንግስት በእግዚአብሔር ስለእኛ የሚላኩ መሆናቸውን ነው። ዕብ.1፥14 ‘‘ቃሉን የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ‘‘ እንደሚል መላእክት ቃሉን እና እንደ ቃሉ የሆን ነገር ብቻ ይሰማሉ ያደርጋሉ።

መላእክት በእግዚአብሔር የተፈጠሩ ፍጥረቶች ናቸው። ነህ.9፥6፣ መዝ.148፥2,5,፣ቆላ.1:፥16-17 እግዚአብሔር ምድር ከመፍጠሩ በፊት ገነትንና በገነት ያሉት መላእክት ሁሉ ፈጥሯል። ኢዮ.38፥4-7 በቃሉ መሰረት ሁሉ መላእክት በአንድ ጊዜ በቃሉ ነው የተፈጠሩት። ስለዚህም በቁጥር አይጨምሩም ወይም አይቀንሱም። መላእክት የሚያገለግሉ መንፈሶች ናቸው። ፍጥረታዊ እንደኛ አይነት አካል የላቸውም። ማቴ.28፥2-4፣ ሉቃ.24፥37-39 ላይ ኢየሱስ መንፈስ አጥንትና ስጋ እንደሌለው በግልጽ ተናግሯል። ነገር ግን መላእክት ወደ በዘፍጥረት ወደ ምድር የሰው ልጆችን ለመጠበቅንና ለመጎብኘት ሲላኩ ጊዚያዊ አካልን እንደ ሰው የመልበስ ብቃትን ይቀበሉ ነበር። ዘፍ.18 ይህ ጊዚያዊ ኑሮ የመላእክትን ስንፍና ገልጧል። ስለዚህ በዝርዝር የወደቁ መላእክትና የእግዚአብሔር ፍርድ በሚለው መጽሐፌ ስላብራራሁ አሁን አልፈዋሁ።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

46 www.tlcfan.org

መላእክት በመጽሐፍ ቅዱስ በወንድ ጾታ የተገለጡ ቢሆንም ሴት መላእክት እንዳሉ በዘካርያስ.5፥9 ላይ እናገኛለን። ነገር ግን በቃሉ በብዛት እንደ ወንድ ተገልጠው እናገኛለን። ማር.16፥5 መላእክት አይሞቱም። ሉቃ.20፥36 ስለዚህ የእግዚአብሔር መንግስት ስራዊትን ልዮና ጠንካራ መሆኑን ያጎላዋል። መላእክት ምንም እንኳን ያለ ክንፍ መቀሳቀስ ቢችሉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ክንፍ እንዳላቸው ተጠቅሶ እናገኛለን። ይህ ክንፍ የሚለው በራሪ መንፈስ መሆናቸው ለማመልከት እንጂ ክንፍ አላቸው ማለት አይደለም ብለው የሚያምኑም አሉ።

መላእክት የመንግስቱን ዜጎች የሚጠብቁ ስራዊቶች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳየው ታሪክ የሚገኘው በ 2ኛ ነገ.6:፥17 ላይ ይገኛል። ይህን እውነትና ሚስጥር ለመመልከት ብላቴናው ግያዝ የግድ መንፈሳዊ አይኑ መከፈት ነበረበት። ማንኛውም የመንግስቱ ዜጋ እንደ ኤልሳዕ በእግዚአብሔር ስራዊቶች ይጠበቃል። ይህ ዜጋው በእግዚአብሔር የተሰጠው የዜግነት መብትና ብቃት ነው። ኤልሳዕ በዚያ ስፍራ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ መላእክቶቹ የሰዶምን ሰዎች እንዳሳወሩ ሰዎቹን አሳወሯቸው።

በአጠቃላይ የእግዚአብሔር መንግስት ስራዊቶች መላእክት ናቸው። ዳንኤል ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ የጸሎት መልስ ይዘው መጥተዋል። ለመንግስቱ ዜጎች በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን የተለያዮ አገልግሎትን ስጥተዋል። የመንግስቱን ዜጎች ከእስራት ፈተዋል። የመቃብሩን ድንጋይ በማንከባለል ሴቶቹ ወደ ውስጥ ገብተው ትንሳኤውን እንዲያዮ አግዘዋል ወዘት።

የእግዚአብሔር የመንግስቱ ስራዊቶች ብዙ ስራ ሲሰሩ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ እናገኛለን። ይህ መስረታዊ ትምሕርት ስለሆነ በጥልቀት አንገባም ነገር ግን ከሰሩት ስራዎች አንዳዶቹን ላስቀምጥ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ማምለክ ኢሳ.6:፥1-3፣ ራእይ.4ና5 መልእክትን ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች ማምጣት፣ መምራት ማቴ.1-2 ፣ሐዋ.8፥26፣ 10፥1-8 ምግብን ለሰው ልጅ መኖር የሚያስፈልጉት መስጠት ዘፍ.21፥17-20 ፣ 1.ነገ.19፥6፣ ማቴ.4፥11 ፣ጥበቃ ዳንኤል.3ና6 ፣ነጻ ማውጣት ሐዋ.5ና12 ፣ ማበረታታት ማጠንከር ሐዋ.5፥19, 27፥23-25፣ በሞት ጊዜ ወደ ገነት ለመውሰድ እንክብክቤ ማድረግ ማጀብ ሉቃ.16፥22፣ ሚስጥርን ይገልጣሉ፣ ያስተምራሉ፣ ህልም ይፈታሉ፣ ይቀጣሉ 2.ነገ.19፥20-34… ወዘተ። ለመሰረታዊ እውቀት እነዚህን ካየን ይበቃናል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

47 www.tlcfan.org

ምድርና ሞላዋ

የእግዚአብሔር መንግስት በድሮዋ ከንዓን ምድር ክልል ብቻ የተወሰነ አይደለም። ያ የብሉይ የአሮጌው ኪዳን ሊወድቅና ሊሻር የተገባው ኪዳን ተስፋ ነው። ነገር ግን ሊመጣ ላለው የእግዚአብሔር መንግስት የተለያይዮ ሚስጥራዊ ትምሕርቶችን በጥላነቱ ጥሎልን አልፏል። የእግዚአብሔር መንግስትና ግዛት ግን ምድና ሞላዋን የምታጠቃልል ናት።

ሕዝበ እስራኤል በፊት ከንዓንን ለመውረስ እንዲገቡ በእግዚአብሔር ሲታዘዙ ገብተው ለመውረስ የሚያስችላቸው እምነት አልነበራቸውም። 12 ሰላዮች ተልከው አስሩ መጥፎ ነገርን ተናገሩ። ይህንን አስሩ የተናገሩት ሕዝቡ ሁሉ አመኑ። እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ፍቃዱን በሙሴ በራሱ ትውልድ በኩል ሊፈስመው እንደሚፈልግ ለሙሴ ነገረው። ይህ የሙሴ ፈተናው ወቅት ነበር። ሙሴ ግን ይህን የእግዚአብሔርን የፈተና እቅድ አልተቀበለም። ባለመቀበሉም ፈተናውን አልፏል። ሌሎች እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባውን ቃል አጠፈ ብለው ይላሉ። ሰለ ምንስ ስምህ ይሰደብ፦ በማለት ለእግዚአብሔር ሃሳብ ሙሴ አቀረበ። ስለዚህ ጉዳይ እግዚአብሔር መልስን ሰጠ፦

“12፤ ከርስታቸው አጠፋቸው ዘንድ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ አንተም ከእነርሱ ለሚበዛና ለሚጠነክር ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው። 13፤ ሙሴም እግዚአብሔርን አለው። ግብፃውያን ይሰማሉ፤ ይህን ሕዝብ ከመካከላቸው በኃይልህ አውጥተኸዋልና፤ 14፤ ለዚችም ምድር ሰዎች ይናገራሉ። አንተ

እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ፊት ለፊት ተገልጠሃል፥ ደመናህም በላያቸው ቆሞአል፥ በቀንም በደመና ዓምድ፥ በሌሊትም በእሳት ዓምድ በፊታቸው ትሄዳለህ። 15፤ ይህን ሕዝብ እንደ አንድ

ሰው ብትገድል ዝናህን የሰሙ አሕዛብ። 16፤ እግዚአብሔር ይህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ

ገደላቸው ብለው ይናገራሉ። 17፤18፤ አሁንም፥ እባክህ። እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም

ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን። 19፤ ይህን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ካወጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ

ድረስ ይቅር እንዳልሃቸው፥ እባክህ፥ እንደ ምሕረትህ ብዛት የዚህን ሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል። 20፤ እግዚአብሔርም አለ። እንደ ቃልህ ይቅር አልሁ፤ 21፤ ነገር ግን እኔ ሕያው ነኛ በእውነት

የእግዚአብሔር ክብር ምድርን ሁሉ ይሞላል።” ዘሁ.14፥21

እግዚአብሔር ይህን በመናገር በምድር ላይ ያለውን አላማ ለሰው ልጆች በቃሉ አሳየ። ከንዓን ከእግዚአብሔር እቅድና አላማ ትንሿ ክፍል ነች። ከንዓን በክብሩ ለሞትሞላዋ ምድር ትንሽዬ ጥላ ነች። ይህን ለማድረግ እግዚአብሔር ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን በራሱ ማለ። መዝ.72፥19

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

48 www.tlcfan.org

be his glorious name for ever: and let the whole earth be filled with his glory

Psa 72:19

is the LORD of hosts: the whole earth is full of his glory

ይህ ነገር በኢሳያስ ራዕይ ውስጥ ኪሩቤሎች ሲናገሩት ተሰማ። ኢሳ.6፥3 በእነርሱ ዘንድ ሰዓት ስለሌለ ሁሉ እንደተፈጸመ አድርገው ተሞላለች ብለው ፍጻሜውን እያዮ ይናገሩ ነበር። ኢሳያስ ደግሞ ደግሞ ይህን እውነት ከእግዚአብሔር ተቀብሎ አስተላልፎልን አልፏል። ኢሳ.11፥9

the earth shall be full of the knowledge of the LORD,

የመጨረሻውን በዚህ ሃሳብ ቃል ትቶልን ያለፈው ጳውሎስ ነው።

“እያንዳንዱም ጐረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን። ጌታን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ

ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና።” ዕብ.8፥11

ሁላችን እንደምናውቀው ውሃ ባሕርን የሚሸፍነው መቶ በመቶ ነው። የእግዚአብሔር የማወቅ እውቀትም ምድርን የሚሸፍነው መቶ በመቶ ነው። በምድር ላይ የእግዚአብሔር ክብር የማይገለጥበት አንዲትም ስፋራና ሰው አይኖርም። በናቡከደነፆር የታየው ያ ያማረ ምስል ድንጋዮ ሲፈጨው አፈር ትቢያ ብቻ ነበር። አዳማዊ ስዋዊ ብቻ ነበር።

ውጩ ሲታይ የከበረ ጠንጋራ የሚመሰል ድንጋዮ ሲገልጠው ግን ውስጡ ያለው ተገለጠ። ያ ድንጋይ ይህን ማንነት ገልጦ ብቻ ሳይሆን ያቆመውን አፍርሶ በመንፈስ ንፋስ ተርጎ ድንጋዮ የእግዚአብሔር መንግስት ምድን ሁሉ መቶ በመቶ ሞላ። ድንጋዮ ምድን እስኪሞላ ድረስ አደገ። ይህ የእግዚአብሔር መንግስት አሰራር ሞዴል ነው። ዳን.2፥35,44

የሚያብረቀረቀውን ምስል ስፍራ በእግዚአብሔር መንግስት ሊተካ ጊዜው ቅርብ ነው። ይህም አምስተኛውና የመጨረሻው መንግስት ይሆናል ማለት ነው። የእግዚአብሔር መንግስት ማንኛውንም አይነት የተፅኖ መንግስት አስወግዳ ሕዝቡ ሁሉ የመንግስቱን ነፃነት እንዲቀበሉ ታደርጋልች። ይህ ይለንበት ዘመን ይህ ድንጋይ የምስሉን እግር እየፈጨ ያለበት ዘመን ነው። ይሁንና ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈጅ አናውቅም። ነገር ግን ዋንኛው የሚጠበቀው ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች መገለጥ ነው። ያኔ ፍጻሜው እንደመጣ እናውቃለን። እነርሱም ከእርሱ ጋር እንዲነግሱ በመጪው ዘመን ሞትን ድል የሚነሱ ናቸው። የምድርን ነግስታት ግልብጦ ድል ነሺዎችን በስፍራቸውን ያነግሳል።

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

49 www.tlcfan.org

ዳንኤል ምዕራፍ ሰባት ስለዚህ ክንውን በዝርዝር ያስቀምጣል። ዳንኤል ያየው ህልም ቀደም ብሎ ናቡከደነፆር ካየው ጋር የሚመሳሰል ነው። እርሱ ግን የተመለከተው በሚያብለጨልጭ ምስል ሳይሆን በተለያዮ አውሬዎች ተመሰለውን ያንኑ የሰው መንግስታት የሚያሳይ ነው። ሮም ከሆነችው ላይ የበቀለችው ትንሿ ቀንድ ፓፓል ሮም ካቶሊክን የምትወክል ሲሆን ያቺም የሮም መንግስት ማራዘሚያ ነች። ለዚህ ነው የሮም መንግስት አወዳደቅ በታሪክ እንኳን የማይታወቀው። ይህቺ ቀንድ ከቅዱሳኑ ጋር ተዋግታ ፍጻሜው እስኪመጣ አሸንፋለች። ሮም የክርስትና ማእከል ሆና በአሸኛፊነት የምትቆየው ስልጣን ለልዑሉ ቅዱሳን እስከሚሰጥበ ቀን ድረስ ነው።

ከደመና የመጣው ተመስሎ የተቀመጠው ከተራራ ተፈልቅሎ ከመጣው ድንጋይ ጋር ነው። ይህም የእግዚአብሔር መንግስት ነው። ክርስቶስ ራሱ ደግሞ የዚህ መንግስት ንጉስ ነው።

“21. እነሆም፥ ያ ቀንድ ከቅዱሳን ጋር ሲዋጋ አየሁ፥ 22. በዘመናት የሸመገለው እስኪመጣ ድረስ፥ ፍርድም ለልዑሉ ቅዱሳን እስኪሰጥ ድረስ፥ ቅዱሳኑም መንግሥቱን የሚወስዱበት

ዘመን እስኪመጣ ድረስ አሸነፋቸውም።” ዳን.7፥22

እንደሚናገር ቅዱሳኑም መንግስቱን ይወስዳሉ። ይህ ደግሞ ከራዕይ 20፥6 ጋር ይስማማል። በመጀመሪያው ትንሳኤ እድል ያላቸው ከእርሱ ጋር በመንግስቱ ይነግሳሉ። የእግዚአብሔር ልጆች ከኢየሱስ ክርስቶስ በታች ሆነው መንግስቱን ያስተዳድራሉ።

“27.መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥

ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል።” ዳን.7፥27

ይህ ነው የእግዚአብሔር መንግስት ትንቢት በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሲታይ። ይህ ሁሉ በምድር ያሉ ሁሉ ክርስቶስ የእነርሱ ንጉስ እንደሆነ ይማራሉ። በፍቅርና በእኩልነት ለእርሱ ይገዛሉ። ይህም አብረው በሚነግሱት ድል ነሺዎችም ጨምሮ ነው። መዝ.67 ሐጌ.2፥5-9 እንደሚናገር ይህ የእግዚአብሔር መንግስትና ኢየሱስ ክርስቶስ የሁሉ ሕዝብ ፍላጎት እንደሚያረካ ያሳያል። በክብርም እንደሚሞላ ይናገራል። የእግዚአብሔር ልጆች ሆነው ፣ የበኩራት አይነት ሆነው በመጀመሪው ትንሳኤ የሚገለጡት አብረውት የሚገዙት ድል ነሺዎቹ የመንግስቱ ነግስታትና ካህናት ናቸው። እርሱ ደግሞ የነግስታቱ ሁሉ ንጉስ ነው።

“18 ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ሥቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። 19 የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጠባበቃልና።

20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቶአልና፥ በተስፋ ስላስገዛው ነው እንጂ በፈቃዱ አይደለም።” ሮሜ.8፥19-21

የእግዚአብሔር መንግስት 2016

50 www.tlcfan.org

ምድርና ሞላዋ ይህን መገለጥ በመጠባበቅ ትገኛለች። ምድርም የእግዚአብሔርን የፍጥረት አላማ ለፍጥረት ትፈጽማለች። ስለዚህ የመንግስቱ ወራሽ ለመሆን የሚጠበቅብንን እናድርግ። በቃሉ ውስጥ ይህና ያንን የሚያደርጉ መንግስቱን አይወርሱም እንደሚል እናስተውል። የዳነ ሁሉ መንግስቱን እንደማይወርስ እናሰውል። ስለዚህ እግዚአብሔር ለመምስል ከአሁኑ ራሳችንን እናስለምድ።

ይህም ለመዳን ሳይሆን ወደ መንግስቱ ለመግባት ነው። ወደዚህ የእግዚአብሔር መንግስት አገዛዝና ግዛት ለመግባት አንድ አማኝ ድልመንሳት ይጠበቅበታል። ድልባይነሳ ግን ደህንነትን አያጣም። በመንግስቱ ውስጥ ግን የከፍታን ስፍራ አያገኝም። የመንግስቱ ተካፋይ የመሆን ወይም ያለመሆን መብቱንና ምርጫውን እግዚአብሔር የሰጠው ለእኛ ነው። ስለዚህ ሁሉን እንደ ቃሉ ማድረግን እንማር። እግዚአብሔርን በቀሪው ዘመናችን በንስሃ ተመልሰን እንታዘዝ። ሁላችን እንደክማለን እንወድቅማለን። ነገር ግን ውሻ ወደትፋቱ እሪያም ወደ ዳጡ እንደሚመለስ እኛም እንዳንመለስ እግዚአብሔር ይፈልጋል።

የጠፋው ልጅ በንስሃ ወደ አባቱ መገኘት ተመለሰ። በሩቅ ሃገር ልቅ በሆነ ሕይወት ለዘላለም ሊኖር አልወደደም። ይህ ዛሬ እንደዚህ ሩቅ ሃገር ኑሮ ኒወታችንን እየኖርን ያለን እንድንመልስ ትልቅ ምሳሌ ነው። የምድሩን አትርፈን የሰማዮንና የሚበልተውን ክብር ብናጣ ምን ይጠቅመናል። ስለዚህ ነው እግዚአብሔር የሚገስጸን የሚመክረን። ይህም ከእርሱ የመለኮታዊ ባሕሪ እንድንካፈል ነው። ዕብ.12 አንዱም በእግዚአብሔር መንግስት በሙላት መግባትና፣ መግዛት ነው። ጌታ አይምኗችንን ለሕጉ ፍቺ ይክፈተው። ማራናታ!!!

ሌሎች መጽሐፎቼን ለማግኘትና ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን ድረ ገጽ ይጫኑ ወይም ይጠቀሙ

www.tlcfan.org

......................................ተፈጸመ............................................