uôÈ^m Ö?“ t>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ ²?“...

4
uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ www.ephi.gov.et ²?“ ኢሕጤኢ ግንቦት 2012 pê 4 lØ` 3 ኢንስቲትዩቱ ከሳቶ ድርጅት ጋር በመሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእጅ መታጠቢያዎች በስጦታ አበረከተ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ (SATO Ethiopia) ያገኛቸው 50 እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋጋ የሚያወጡ የእጅ መታጠቢያዎች በስጦታ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አበርክቷል፡፡ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ይህንን የእጅ መታጠቢያ ለፖሊስ ኮሚሽኑ በስጦታ መስጠት ያስፈለገው በተለያየ ሁኔታ አባላቱ ከኮቪድ-19 ስራዎች ጋር ግንኙነት ስላላቸው በየመዳረሻቸው የእጅ ንፅህናቸውን መጠበቅ እንዲችሉ ለማገዝ ነው ብለዋል። አቶ አስቻለው አባይነህ አክለውም የፖሊስ አባላቱ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮቪድ-19 ዙሪያ እየሰራ የሚገኘውን ስራ በማገዝና መንግስት ያወጣውን የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማስተማርና በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ ከ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ በማስፈፀም እያበረከቱ ላለው አስተዋፅዖ ለማመስገንና በቀጣይም በአብሮነት መንፈስ ከጎናችን መሆናችሁን ለማሳየት፤ እንዲሁም ለሌሎች አጋር ድርጅቶች ማነሳሻ ይሆን ዘንድ ነው ብለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ነጋሽ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት በሽታው ወደ ሀገራችን መግባቱ ከተገለፀበት ጊዜ አንስቶ የተላያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን እና የተደረገው ድጋፍም ለተቋሙ እጅጉን ጠቃሚ መሆኑን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድጋፉ ችግር ከመቅረፉ በተጨማሪ ይህን ወቅት በአንድነትና በመተጋገዝ ለማለፍ እንደሚቻል የሚያሳይ ነው ብለዋል። . . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል በWaterAid Ethiopia ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ባለ አስር ሺ ሊትር 20 የውሀ ታንከሮችን፣ ቆሻሻን በአግባቡ ለመሰብሰብ የሚረዱ የቆሻሻ መሰብሰቢያዎች፤ 44,000 ባዮ ሃዛርድ ባጎችን ፤ 6000 የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎች /ሳኒታይዘር/ እና 1000 ፈሳሽ ሳሙናዎችን ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስረክበዋል፡፡ በተጨማሪም AMREF Health Africa ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የቆሻሻ መሰብሰቢያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጎአል፡፡ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስን /ኮቪድ 19 /ወረርሽኝ ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ የለይቶ ማቆያና ለይቶ ማከሚያ ማዕከላት መዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡ ለማዕከላቱም ህሙማንን ተቀብሎ ለማከም የሚያስችሉ ግብአቶች እየተሟሉ እንደሚገኙም ገልጸዋል

Upload: others

Post on 25-Jul-2020

8 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ ²?“ ኢሕጤኢ · የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ

uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚`¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ

www.ephi.gov.et

²?“ ኢሕጤኢ ግንቦት 2012 pê 4 lØ` 3

ኢንስቲትዩቱ ከሳቶ ድርጅት ጋር በመሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእጅ መታጠቢያዎች በስጦታ አበረከተ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ (SATO Ethiopia) ያገኛቸው 50 እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋጋ የሚያወጡ የእጅ መታጠቢያዎች በስጦታ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አበርክቷል፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ ይህንን የእጅ መታጠቢያ ለፖሊስ ኮሚሽኑ በስጦታ መስጠት ያስፈለገው በተለያየ ሁኔታ አባላቱ ከኮቪድ-19 ስራዎች ጋር ግንኙነት ስላላቸው በየመዳረሻቸው የእጅ ንፅህናቸውን መጠበቅ እንዲችሉ ለማገዝ ነው ብለዋል። አቶ አስቻለው አባይነህ አክለውም የፖሊስ አባላቱ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮቪድ-19 ዙሪያ እየሰራ የሚገኘውን ስራ በማገዝና መንግስት ያወጣውን የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማስተማርና

በኢሕጤኢ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቢሮ በየወሩ የሚዘጋጅ

ከ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገ

በማስፈፀም እያበረከቱ ላለው አስተዋፅዖ ለማመስገንና በቀጣይም በአብሮነት መንፈስ ከጎናችን መሆናችሁን ለማሳየት፤ እንዲሁም ለሌሎች አጋር ድርጅቶች ማነሳሻ ይሆን ዘንድ ነው ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሃሰን ነጋሽ በርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት በሽታው ወደ ሀገራችን መግባቱ

ከተገለፀበት ጊዜ አንስቶ የተላያዩ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን እና የተደረገው ድጋፍም ለተቋሙ እጅጉን ጠቃሚ መሆኑን በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ድጋፉ ችግር ከመቅረፉ በተጨማሪ ይህን ወቅት በአንድነትና በመተጋገዝ ለማለፍ እንደሚቻል የሚያሳይ ነው ብለዋል።

. . .ወደ ገጽ 4 ዞሯል

በWaterAid Ethiopia ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ባለ አስር ሺ ሊትር 20 የውሀ ታንከሮችን፣ ቆሻሻን በአግባቡ ለመሰብሰብ የሚረዱ የቆሻሻ መሰብሰቢያዎች፤

44,000 ባዮ ሃዛርድ ባጎችን ፤ 6000 የእጅ ንጽህና መጠበቂያዎች/ሳኒታይዘር/ እና 1000 ፈሳሽ ሳሙናዎችን ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

አስረክበዋል፡፡በተጨማሪም AMREF Health Africa ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የቆሻሻ መሰብሰቢያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጎአል፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህበርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ በሀገራችን የኮሮና ቫይረስን /ኮቪድ 19 /ወረርሽኝ ስርጭትለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ የለይቶ ማቆያና ለይቶ ማከሚያ ማዕከላትመዘጋጀታቸውን አመልክተዋል፡፡ ለማዕከላቱም ህሙማንን ተቀብሎ ለማከም የሚያስችሉ ግብአቶች እየተሟሉ እንደሚገኙም ገልጸዋል

Page 2: uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ ²?“ ኢሕጤኢ · የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ

ግንቦት 2012 pê 4 lØ` 3 Ñê 2

www.ephi.gov.et

ኦይልሊቢያ ኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ነዳጅ እና አንድ ሚሊየን ብር የሚያወጣ የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮች በአጠቃላይ ሁለት ሚሊየን የኢትዮጵያ ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስረክቧል፡፡ኢንስቲትዩቱም ቁሳቁሶቹን በመረከብ ለተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ መንግስት፣ በጤና ሚኒስቴር እና በኢንስቲትዩቱ ስም ምስጋና አቅርቧል፡፡

ኦይልሊቢያ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚረዱ የነዳጅ እና የእጅ ንጽህና መጠበቂያ ሳኒታይዘሮች ድጋፍ አደረገ

ለኮቪድ 19 መከታተያ እና ስልጠና ለመስጠት የሚያገለግሉ መተግበሪያዎች ይፋ ተደረጉ

. . .ወደ ገጽ 5 ዞሯል

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከሌሎች አጋር ድርጅት ጋር በመሆን ያዘጋጀው ሁለት የሞባይል መተግበርያዎችን (አፕሊኬሽኖችን) አገልግሎት ላይ ማዋሉን ገለጸ።ከሞባይል መትግበርያዎቹ የመጀመርያው የጤና ባሙያዎችን እውቀት ለማሳድግ የሚያስችል ሲሆን ሌላው ኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መለየት የሚያስችል ነው።

ኮቪድ-19ን ለመግታት እና ለመቆጣጠር ለሚሰሩ ባለሙያዎች የስራ መመሪያ ተሰጠ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለክልሎች በተለያየ ጊዜ የቴክኒክ፣ የገንዘብ፣ የቁሳቁስና የተለያዩ የግብዓቶች ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።በዚሁ መሰረት የኮቪድ-19 ቅድመ ዝግጁነት እና ምላሽ ለማጠናከር እና በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ችግሮች ላይ ለመስራት ይረዳ ዘንድ ለክልሎች ለሶስተኛ ዙር ድጋፍ ለሚሰጡ ከ80 በላይ ባለሙያዎች የስራ መመርያ ተሰጣቸው።

Page 3: uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ ²?“ ኢሕጤኢ · የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ

ግንቦት 2012 pê 4 lØ` 3 Ñê 3

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደ አዲስ አበባ ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የተሰሩ ስራዎችን እና የተወሰዱ እርምጃዎችን በሰፋት እና

የጤና ሚኒስትር ከተጠሪ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር በመሆን ኮቪድ-19ን የመከላከል ስራዎች ላይ መግለጫ ሰጡ”

በዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ዶ/ር ኤባ አባተ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸው ከሕብረተሰቡ ሲነሱ የነበሩትን የተለያዩ ጥያቄዎች

እና ሕብረተሰቡን ግራ ሊያጋቡ የሚችሉ ጉዳዮችን ግልጽ ለማድረግ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ሕብረተሰቡ ትኩረት በመስጠት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ገዳዮችንም በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡በሃገራችን በኮሮና በሽታ ከተያዙት 16 በመቶ (መግለጫው በተሰጠበት ወቅት የነበረ መረጃ) የሚሆኑት ሰዎች የውጪ ሐገር የጉዞ ታሪክ እና በሽታው ከያዛቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያልነበራቸው መሆናቸውን እና ከነዚህም ውስጥ 48 በመቶ የሚሆኑት በአዲስ አበባ መሆናቸውን ፣በተለይም በአዲስ አበባ በበሽታው የተያዙት ሰዎች 40 በመቶ የልደታ እና የአዲስ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን እና በቀጣይ በሽታውን ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት ከሁሉም አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመግታት በጤና ሚኒስቴር አና በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሕብረተሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይቶአል። የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማህበረሰቡን በይበልጥ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳ ዘንድ የኮቪድ-19 ምልክቶች፣ ስለመተላለፊያ መንገዶች፣ የመከላከያ ዘዴዎች አና ሌሎች ጠቃሚ ነጥቦችን በዝርዝር የሚያስረዳ ድረገጽ አስገንብቷል፡፡ ድረገጹ በሁለት ቋንቋ ማለትም በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ መረጃን የሚሰጥ ሲሆን በቅርብ በሌሎች ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፡፡ ይህንን መረጃ ለማህበረሰባችን እንዲደርስ በማጋራት የበኩልዎን አስተዋጽኦ

እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ይህንን ድህረገጽ ለመገንባት አስተዋጽኦ ያደረጉትን የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች እና በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉትን እውነት ኮሚኒኬሽን ሃ/የተ/የግ/ማህበር ባለሙያዎችን ከልብ ለማመሰገን

እንወዳለን፡፡

በኮቪድ-19 ዙርያ ሰፊ መረጃ የሚሰጥ ድህረገጽ ተገነባ

www.ephi.gov.et

Page 4: uôÈ^M Ö?“ T>’>e‚` ¾›=ƒÄåÁ ¾Qw[}cw Ö?“ ›=”e+ƒ¿ƒ ²?“ ኢሕጤኢ · የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሳቶ ኢትዮጵያ

Ñê 4

www.ephi.gov.et

ግንቦት 2012 pê 4 lØ` 3

ከገጽ 1 የዞረ. . . ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ

ሁዊይሳንግ ሲንግ የተሰኘ ድርጅት፣ ድሪም ኢትዮጵያ ቱርስ በተባለ ድርጅት አማካኝነት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) በልገሳ ተሰጠ። ድርጅቱ በአጠቃላይ የለገሰው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) 50 ሺህ ሲሆን 30ሺህ ማስክ ለጤና ሚኒሰቴር የቀረውን 20 ሺህ ደግሞ ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነው። ይህ ማስክ በስጦታ የተበረከተው COVID-19

ላይ እየሰሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች፤ ሆስፒታሎች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች እንደሁም ለኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች እንዲሆን ታስቦ ነው፡፡በተያያዘ ዜና ቴክዳታ የተሰኘ ሃገር በቀል ድርጅት አለማችንን ብሎም ሃገራችን ኢትዮጵያን እያስጨነቀ ለሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ሃገራዊ ጥሪ በብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ)

የሚያወጡ ምንም አይነት ፈሳሽ የማያሳልፉ ከፕላስቲክ የተሰሩ አልባሳት እና የቆሻሻ ማስወገጃዎችን (ባዮሃዛርድ ባግ) ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ ለሆኑ ሃኪሞችና ነርሶች ይገለገሉበት ዘንድ በልገሳ አበርክቷል፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሁለቱም ድርጅቶች ላበረከቱት ልገሳ እያመሰገነ በቀጣይም በአብሮነት እንሰራለን ብሏል፡፡

፡፡ በመሆኑም በዛሬው ዕለት በ WaterAid Ethiopia እና AMREF Health Africa የተደረጉ ድጋፎችም ለማዕከላቱ ጠቃሚ መሆናቸውን በመጥቀስ ድርጅቶቹም ለሌሎች

አርአያ የሚሆኑ ተግባራትንበማከናወናቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የድርጅቶቹ ተወካዮች በበኩላቸው በሀገራችን የኮሮና ቫይረስን

ለ መ ከ ላ ከ ል ና ለ መ ቆ ጣ ጠ ር የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑን እና ወደ ፊትም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ከ 62,000 ብር በላይ ግምት ያላቸው የሶላር መብራቶች ድጋፍ ተደረገ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢትዮጵያ ፓዎር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከ 62,000 ሺ ብር በላይ የሚያወጡ በሶላር እና በቻርጅ የሚሰሩ ሶላር ላንተርን / መብራቶች/ ለኢንስቲትዩቱ አስረከቡ፡፡የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ

ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ምላሽ መስጫ ስራዎች ጠቃሚ መሆናቸውን በመጥቀስ በተለይም የመብራት መቆራረጦች በሚገጥሙን ወቅት የሚሰሩ ስራዎች እንዳይደናቀፉ ከማድረግ አንጻር ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። አያይዘውም በርካታ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፎችን እያደረጉ እንደሚገኙ በመግለጽ ይህ የመተጋገዝና የመደጋገፍ ተግባራትን

ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ኢንደስትሪው በተለይም ለሌሎች አርአያ የሚሆኑ ተግባራቶችን በማከናወናቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡የኢንዱስትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ ኮ/ል ነገሰ ጫኔ ድጋፉን ባበረከቱበት ወቅት እንደገለጹት በሀገራችን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የቀረበላቸውን ጥሪ መሰረት በማድረግ ፈጣን ምላሽ እንደሰጡ በመጥቀስ ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ሁላችንም በምንችለውና ባለን አቅም ሁሉ መደጋገፉ ግድ የሚለን ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ኢንዱስትሪው በሀገራችን ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎችን ለመደገፍ ወደ ፊትም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (ማስክ) በልገሳ ተሰጠ