pulse crops special irrigation program first draft

27
ግግግግ ግግግግግ ግግግግ ግግግግግግግ ግግግግግግግ 2004 .ግ ግግግግ ግግግግግ ግግግግግ ግግግግ ግግግግግ ግግግግ ግግግ(ግግግግግግ ግግግ)

Upload: shiffam12922

Post on 15-Oct-2014

155 views

Category:

Documents


10 download

TRANSCRIPT

Page 1: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ግብርና ሚኒስቴር

ግብርና ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት

በ2004 ዓ. ም በመስኖ በመጠቀም የጥራጥሬ ሰብሎች ለማልማት የቀረበ ዕቅድ( የመጀመሪያ ረቂቅ)

አዲስ አበባ

መስከረም 2004 ዓ.ም.

Page 2: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

I. አጠቃላይ ገፅታ

በ 2002/03 ምርት ዘመን በተነፃፃሪነት ከሚመረቱት የምግብ ሰብሎች በሃገር ውስጥ እና በወጭ ገበያ ተፈላጊነታቸው ከፍተኛ የሆኑት የጥራጥሬ እህሎች ከአጠቃላይ የምግብ እህሎች በመሬት ሽፋን 10.8

በመቶ እና የምርት መጠናቸውም በ 8.2 በመቶ እንደሆነ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ስለዚህ በነዚህ ሰብሎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ በመረባረብ ምርት እና ምርታማነታቸውን በማሳደግ በአገር ውስጥ እና በወጭ ገበያ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቃል፡፡

ሰንጠረዥ 1፡- በ 2002/03 ምርት ዘመን በዋና ዋና ሰብሎች የተሸፈነ መሬት እና የተገኘ ምርት

ተ.ቁ ሰብል የመሬት ስፋት የተገኘ ምርት

በ ሺህ ሄ/ር በመቶኛ በሺህ ቶን በመቶኛ

1 ብርዕ እና አገዳ 9690.73 77.9 17761.33 74.52 ጥራጥሬ 1357.52 10.8 1953.19 8.23 ቅባት 774.52 6.1 634 2.64 አትክልት እና ፍራፍሬ 181.32 1.1 894.24 3.75 ስራስር 516.33 4.1 2610.37 11.0

ጠቅላላ 12520.42 100 23853.13 100ምንጭ፡- ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ 2003 አመታዊ የሰብል ትመና

በጥራጥሬ ሰብሎች መከላከል ያለውን የመሬት ሽፋን ለመለየት በሰንጠረዥ 2 ውስጥ ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በዚሁም መሰረት ባቄላ ቦሎቄ እና ሽምብራ ከ 1 ኛ እስከ 3 ኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡ ይሁን እንጂ የአገር ውስጥ ፍላጎትን እንኳን ለማርካት በቂ ባለመሆኑ ምርትን በብዛት እና በጥራት በማምረት የማስፋት እስትራቴጂን

በመጠቀም እና የሸማቾችን እና የአምራቾችን ትስስር በማጠናከር ቀጣይ እና ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር መፍጠር ይቻላል፡፡

ሰንጠረዥ 2፡-2002/03 ምርት ዘመን በጥራጥሬ ሰብሎች የመሬት ስፋት እና የተገኘ ምርት

ተ.ቁ ሰብል የመሬት ስፋት ደረጃ የተገኘ ምርት

Page 3: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ሄክታር በመቶኛ ኩንታል በመቶኛ

1 ባቄላ 459,183.51 33.83 1 ኛ 6,977,983.87 35.732 አተር

203,990.64 15.034 ኛ

2,570,314.09 13.163 ቦሎቄ 237,366.39 17.49 2 ኛ 3,402,795.18 17.424 ሽምብራ 208,388.62 15.35 3 ኛ 3,228,388.27 16.535 ምስር 77,334.22 5.70 6 ኛ 809,517.33 4.146 ጓያ 131,043.99 9.65 5 ኛ 2,009,485.58 10.297 አኩሪ አተር 11,261.12 0.83 9 ኛ 158,244.22 0.818 አብሽ 14,670.04 1.08 7 ኛ 179,052.29 0.929 ግብጦ 14,284.15 1.05 8 ኛ 196,154.18 1.00

ጠቅላላ 1,357,523 100.00 19,531,935 100ምንጭ፡- ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ 2003 አመታዊ የሰብል ትመና

ከዚህ በላይ የተገለፁት ሰንጠረዦች በ 2002/03 ምርት ዘመን በመኸር ወቅት በዝናብ የተመረቱ ሲሆን ይህንንም ከ 2003/04 ምርት ዘመን ጋር ለማነፃፀር እንዲቻል የቀረቡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ የ 2003/04

ምርት ዘመን የጥራጥሬ አመራረትም የአገር ውስጥ እና የውጭ ገበያን ፍላጎት የሚያሟላ ሆኖ አይታይም፡፡

የግብርና ልማት በዝናብ እና በመስኖ የሚለማ ሲሆን እስከ አሁን በአገራችን በስፋት የሚለማው ዝናብን በመጠቀም ነው፡፡ ሆኖም ግን በዓለም የዓየር መዛባት ክስተት የዝናብ አስተማማኝ አለመሆን እየጎላ በመምጣቱ እና መሬታችንንም በዓመት ከ 2 እስከ 3 ጊዜያት ማልማቱ ተገቢ በመሆኑ ለመስኖ ትኩረት

ተሰጥቶት ተገቢው የግብርና ልማት እንቅስቃሴ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በ 2003/04 ምርት ዘመን በአራቱ ዋና ዋና ክልሎች በመኸር ወቅት ----- ሄ/ ር ማሳ፣ በቅሬተ ውሃ------ ሄ/ር ማሳ በጥራጥሬ ሰብሎች የተሸፈነ ሲሆን በቀጣይም በአነስተኛ የመስኖ ልማት ---------- ሄ/ ር ማሳ

እንደሚሸፈን እና ከዚህም ------------- ኩ. ል ምርት እንደሚገኝ ይጠበቃል፡፡

II. ዓላማ

የጥራጥሬ ሰብልን በዝናብና በመስኖ በማልማት፡-

የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮችን በመጠቀም የጥራጥሬ ምርት ከእጥፍ በላይ በማሳደግ ለአገር ውስጥና

ወጭ ገበያ የሚሆን ምርት ማስገኘት፣

Page 4: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ጥራጥሬን በማምረት ሂደት አርሶ አደሩ የላቀ የቴክኖሎጂ ጥንቅሮችን በሥራ ላይ ለማዋል እንዲችል የምርት

ግብዓት አቅርቦትንና የቴክኒክ እገዛን ለማሟላት፣ የምርት ጥራትና መጠን ለማሳደግ አስፈላጊውን ሁኔታ

ከወዲሁ በማመቻቸት አርሶ አደሩ የምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፣

III. የሚጠበቅ ውጤት

በ 2004 ዓ.ም. የጥራጥሬ ሰብልን በመስኖ ለማልማት የተያዘ የማሳ ስፋት 50434 ሄ/ ር ነው፡፡ ይህ ዕቅድ

የደቡብ ክልል ባለማቀዱ የተነሳ ክልሉን አይጨምርም፡፡ በመሆኑም ዕቅዱ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲታይ በቂ

ባለመሆኑ፡-

አሁን በሌላ ሰብሎች በተለይ በአትክልት የተሸፈነው ለጥራጥሬ ሰብል ተስማሚ የሆነው በጥራጥሬ

ሰብል በመተካት፣

ከዚህ በፊት በመስኖ ያለማና መልማት የሚችል ለጥራጥሬ ሰብል ተስማሚ የሆነ መሬትን በማልማት፣

አሁን የታቀደውን 50434 ሄክታር በዚህ ሰነድ በተከለሰው መሠረት ወደ 241,248 ሄክታር

ለማሳደግ ቢሠራ አሁን ያለውን የጥራጥሬ የማሳ ስፋት ማሳደግ ይቻላል፡፡

በዚሁ መሠረት በአራቱ ክልሎች በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች አሁን በዕቅድ ከያዙት የማሳ

ስፋት በተጨማሪ በሚከተለው መንገድ ዕቅድን ከልሶ የጥራጥሬን የማሳ ስፋት መጨመር ይቻላል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በመስኖ ሊለማ የታቀደ መሬት 364066 ሄ/ ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የአገዳና ብርዕ

ሰብሎች 135,800 ሄ/ ር (37.3%) ፣ ለጥራጥሬ ሰብሎች በተለይ ለቦለቄ ሰብል 5,200 ሄ/ር

(1.4%) እና በሌላ ሰብሎች የሚሸፈን 223,066 ሄ/ ር (61.3%) ነው፡፡

ዕቅዱን በተቻለ መጠን በመከለስ ከብርዕና አገዳ ሰብል የማሳ ስፋት 7.3% እና ከሌሎች 11.3%

በመቀነስ ክልሉ ከያዘው ከቦሎቄ ሰብል ልማት የማሳ ሽፋን ጋር የጥራጥሬ ሰብል የማሳ ስፋት ወደ

18.6% ከፍ ይላል፡፡ ይህ በመቶኛ የተገለፀው አኀዝ በሄክታር ሲገለጽ ክልሉ በመስኖ ሊያለማ ያሳየውን

364,066 ሄ/ ር ሳይነካ በሚከተለው መንገድ በሠንጠረዥ ተገልጧል፡፡

ሠንጠረዥ 3 በ 2004 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በመስኖ የሚለማማሳ ስፋት በሄ/ር

የሰብል ዓይነትየተያዘ/ የታቀደ የመሬት ስፋት

(ሄ/ር) የተከለለው የመሬት ስፋት

(ሄ/ር) ብርዕና አገዳ 135,800 109,220

Page 5: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ጥራጥሬ 5,200(ቦሎቄ) 72,813

ሌሎች 223,066 182,033

ጠቅላላ 364,066 364,066

ምንጭ፡- ከክልል በስልክ ከተገኘ መረጃ የተጠናቀረ 2004 ዓ.ም.

በአማራ ክልል በ 2004 ዓ.ም. ሰብሎችን በመስኖ ለማልማት 680,000 ሄ/ ር በዕቅድ የተያዘ ሲሆን

ከዚህ ውስጥ 34,384 ሄ/ ር ለጥራጥሬ ሰብል ልማት ሲውል ቀሪው/ ሌላው 645,616 ሄ/ ር

ለሌሎች ሰብሎች ይውላል፡፡

ከዚህ በመነሳት በተደረገው ክለሳ ከጥራጥሬ ሰብል ልማት ከሚውለው ማሳ ውጭ ከሆነው ከ 645,616

ሄ/ ር ውስጥ 43,206 ሄ/ ር በመቀነስ ለጥራጥሬ ሰብል በተለይ የተያዘላቸውን ዕቅድ በ 3 እጥፍ በማሳደግ

ለምስር፣ ሽምብራና ባቄላ ሰብል ልማት ላይ ለማዋል ተሞክሯል፡፡

ሠንጠረዥ 4 በ 2004 ዓ.ም. ም በአማራ ክልል በመስኖ ልማት የሚለማ የማሳ ስፋት

ተ.ቁ የጥራጥሬ ዓይነትየተያዘ/የታቀደ

የመሬት ስፋት (ሄ/ር)

የተከለሰው የመሬት ስፋት (ሄ/ር)

የተጨመረው (ልዩነት) ሄ/ር

1. ምስር 5,374 16,122 10,748

2 ሽምብራ 15,390 46,170 30,780

3 ባቄላ 839 2,517 1,678

4 አተር 113 113 -

5 ቦሎቄ 1,316 1,316 -

6 አኩሪ አተር 60 60 -

7 ጓያ 10,703 10,703 -

8 ማሾ 539 529 -

9 ለውዝ 60 60 -

ንዑስ ድምር 34,384 77,590 43,206

10 ሌሎች 645,616 602,410 -

ጠቅላላ ድምር 680,000 680,000 43,206

ምንጭ፡- ከክልል በስልክ ከተገኘ መረጃ የተጠናቀረ 2004 ዓ.ም.

በትግራይ ክልል በ 2004 ዓ.ም. በመስኖ የሚለማ የማሳ ስፋት 217,000 ሄ/ ር ሲሆን በዚሁ

መሠረት ለአገዳና ብርዕ፣ ለጥራጥሬ ሰብሎች 45% ከዚህ ውስጥ 5% ለሽምብራ ሰብል ልማት፣

ለአትክልት 40% ፣ ለፍራፍሬ 8% ፣ ለቅመማቅመም 7% ተይዟል፡፡

Page 6: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ከዚህ በመነሳት ዕቅዱን መከለስ በማስፈለጉ ለጥራጥሬ ሰብል 20% ፣ ለብዕርና አገዳ ሰብል 35%፣

ለአትክልት 30% ፣ ለፍራፍሬ 8% እና ለቅመማቅመም 7% ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህንንም

በሚከተለው ሠንጠረዥ ማሳየት ተችሏል፡፡

ሠንጠረዥ 5 በትግራይ ክልል በ 2004 ዓ.ም. በመስኖ የሚለማ የማሳ ስፋት

ተ.ቁ የሰብል ዓይነትየተያዘ/የታቀደ

የመሬት ስፋት (ሄ/ር)

በ%የተከለሰው

የመሬት ስፋት ሄ/ር

በ%

1 ጥራጥሬ 10,850 5 43,400 20

2 ብርዕና አገዳ 86,800 40 75,950 35

3 አትክልት 86,800 40 65,100 30

4 ፍራፍሬ 17,360 8 17,360 8

5 ቅመማቅመም 15,190 7 15,190 7

ጠቅላላ 217,000 100 217,000 100

ምንጭ፡- ከክልል በስልክ ከተገኘ መረጃ የተጠናቀረ 2004 ዓ.ም.

በደቡብ ክልል በ 2004 ዓ.ም. በመስኖ የሚለማ ማሳ 291,146 ሄምር ሲሆን ከዚህ ውስጥ

ለበቆሎ 120,000 ሄ/ ር (41%) ፣ ለፍራፍሬ 25,339 ሄ/ ር (9%) እና ለአትክልት 145,807 ሄ/ር

(50%) በዕቅድ ተይዟል፡፡

ሆኖም ግን ክልሉ ለጥራጥሬ ሰብል ልማት በዕቅድ ባለመያዙ ከበቆሎ 6% እና ከአትክልት ማሳ ልማት 10%

በአጠቃላይ ለጥራጥሬ 16% በመወሰን ለመስኖ ልማት ለማዋል ጥረት ተደርጓል፡፡ ይህም በሚከተለው

ሠንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 6 በደቡብ ክልል በ 2004 ዓ.ም. በመስኖ የሚለማ የማሳ ስፋት

ተ.ቁ የሰብል ዓይነትየተያዘ/የታቀደ

የመሬት ስፋት (ሄ/ር)

በ%የተከለሰው

የመሬት ስፋት ሄ/ር

በ%

1 በቆሎ 120,000 41 101,901 35

2 ፍራፍሬ 25,339 9 25,339 9

3 አትክልት 145,807 50 116,458 40

4 ጥራጥሬ - - 47,448 16

ጠቅላላ 291,146 100 291,146 100

ምንጭ፡- ከክልል በስልክ ከተገኘ መረጃ የተጠናቀረ 2004 ዓ.ም.

Page 7: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

በአጠቃላይ በአራቱ ክልሎች በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች በመስኖ የሚለማ የጥራጥሬ

ሰብሎች ማሳ በሄ/ ር በሚከተለው ሠንጠረዥ ይገለጻል፡፡

ሠንጠረዥ 7 በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች በ 2004 ዓ.ም. በመስኖ የሚለማ የማሳ ስፋት

ተ.ቁ ክልል በጥራጥሬ ሰብል የማሳ

ስፋት በሄ/ር በሁሉም ሰብሎች በመስኖ

የሚለማ ማሳ (ሄ/ር)በ%

1 ኦሮሚያ 72,810 364,066 23.4

2 አማራ 77,590 680,000 43.8

3 ትግራይ 43,400 217,000 14.0

4 ደቡብ 47,448 291,146 18.8

241,248 1,552,212 100

ምንጭ፡- ከክልል በስልክ ከተገኘ መረጃ የተጠናቀረ 2004 ዓ.ም.

IV. ለመስኖው ልማት አስፈላጊ የሚሆነው የዘር እና የማዳበሪያ ምንጭ ለዚህ ግብ መሳካት የግብዓት አቅርቦት ወቅቱን ጠብቆ ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ይደረጋል፡፡ በዚህም መሰረት በአሁኑ ወቅት በፌደራል ስር ከሚገኙ የዘር ማበዣ ድርጅትች እና የምርምር ማዕከላት እንዲሁም በክልል ደረጃ

ሊገኙ የሚችሉ የዘር ምንጮች እና ከብሄራዊ የአፈር መርመራ ላቦራቶሪ የሚጠበቀው የህየው ማዳበሪያ መጠን የሚከተለው ነው

ሀ/ በዘንድሮው የምርት ወቅት ከሚሰበሰበው ምርት ውስጥ የዘር ምጭነት ሊያገለግል የሚችል ምርት ከአርሶ አደሮች በወረዳዎች አማካኝነት ክልሎች የሚሰበስቡት( ለግዜው መጠኑ የማይታወቅ)፣

ለ/ በኢትዮጲያ ምርጥ ዘር ድርጅት ስቶር ውስጥ ካለፈው የክረምት ወቅት ያደረ 468.57 ኩንታል ምርጥ ዘር እና ከክረምቱ የምርት ወቅት ይገኛል ተብሎ የሚጠበቅ 25886 ኩ. ል ምርጥ ዘር( በአብዛኛው ለቀጣዩ

የ 2004/2005 የክረምት ወቅት በዘርነት የሚቀርብ)፣ሐ/ በደብረዘይት፣ በመልካሳ እና በቁሉምሳ የግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩቶች እና በዙሪያቸው በሚገኙ አርሶ

አደሮች እና ዘር አባዦች እጅ የሚገኝ 3586 ኩ. ል ዘር፣መ/ በብሄራዊ የአፈር ምርመራ ላቦራቶሪ በኩል ተዘጋጅቶ ለክልሎች እንደሚቀርብ ታሳቢ የተደረገ-------ኪ.ግ

ህየወ ማዳበሪያ

በፌደራል ስር ከሚገኙ የዘር አምራች ድርጅቶች እና ምርምር ማዕከላት የሚገኝ የዘር መጠን በየሰብሉ እና ዝርያው ተዘርዝሮ ቀጥሎ ባሉት ሰንጠረዦች ቀርቧል

ሰንጠረዥ 7 ፡ በኢትዮጲያ ምርጥ ዘር ድርጅት መጋዘን ውስጥ የሚገኝ እና ከ 2003 የክረምት ወቅት የተላለፈ የዘር መጠን

ተ.ቁ የሰብል አይነት ዝርያ መጠን በኩንታል ምርመራ1 ሽምብራ ሻሾ 272 አተር ተገኘ 15.5

አዲ 18.353 ምስር አለማያ 286.52

Page 8: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

4 ቦሎቄ አርገኔ 103.26 ባቄላ ቡለጋ 18ድምር 468.57

ምንጭ፡- ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በስልክ የተገኘ መረጃ መስከረም 2004 ዓ.ም.

ሰንጠረዥ 8 ፡ ከግብርና ምርምር ማዕከላት እና ከማህበራት እጅ ያለ የዘር መጠን

ተ.ቁ ግ/ም/ማ የሰብል አይነት ዝርያ መጠን በኩንታል ምርመራ1 ደብረ ዘይት ምስር አለማያ 10

2 በደብረዘይት ምርምር ማዕከል በኩል ማህበራት

ሽምብራ አረርቲ 400 ደብረ ዘይት በአቶ አምሃ (0911362780) እጅ የሚገኝ

ሽምብራ አረርቲ 1500

ሽምብራ ሀርቡ 20

ምስር አለማያ 1200

3 መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል(200 ኩ.ል)

ቦሎቄ አዋሽ 1

አዋሽ መልካ

ናስር

ድንቅነሽ

450 በመኸር ከተዘራው የሚጠበቅ ምርት

4 መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በኩል ማህበራት(250 ኩ.ል)

5 ቁሉምሳ ምርምር ማዕከል አተር ማርቆስ 2.1

አተር አዲ 0.7

አተር ተገኘች 0.7

አተር መገሪ 1

ባቄላ መሳይ 1.8

ባቄላ ሞቲ 0.6

ድምር 3586.9 1

በተጨማሪም በቁሉምሳ ምርመር ማዕከል ድጋፍ በማህበራት እና በገበሬዎች የሚባዛ በማሳ ላይ ያለ ባቄላ 300 እና አተር 100 ኩንታል እንደሚገኝ ይጠበቃል፡

ምንጭ፡- ከግብርና ምርምር ማዕከላት በስልክ የተገኘ መረጃ መስከረም 2004 ዓ.ም.

1

Page 9: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ሰንጠረዥ 9፡- በኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በኩል በመኸር ከተዘራው የሚጠበቅ ምርት

ተ.ቁ የሰብል አይነት ዝርያ መጠን በኩንታል ምርመራ1 ሽምብራ አረርቲ 3225

ሻሾ 300ማርዩ 1680

2 አተር ተገኘ 16673 ምስር አለማያ 44254 ቦሎቄ አዋሽ መልካ 1818

አዋሽ 1 5132ሜክሲካን 358

5 አኩሪ አተር ኢቲ 26796 ባቄላ ሲ.ኤስ 20.ዲኬ 3542

ደጋጋ 1060ድምር 25886

ምንጭ፡- ከኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት በስልክ የተገኘ መረጃ መስከረም 2004 ዓ.ም.

V. የታቀደውን ግብ ለማሳካት መከናወን የሚኖርባቸው ተግባራት በፌደራል ደረጃ

በመስኖ ጥራጥሬ ለማልማት ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ አደሮች መለየታቸውን እና ለድጋፍ በሚያመች መልኩ መሰባሰባቸውን መከታተል ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን ድጋፍ መስጠት፣

የአርሶ አደሩን ግንዛቤ ለማስፋት በብዙሃን መገናኛ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን በመስኖ የጥራጥሬ ልማት ጠቃሚነት ላይ ተገቢ ሥራ መሥራት

የመሬት ዝግጅት እና የመስኖ አውታሮች ጥገና በአግባቡ መከናወኑን በመከታተል ላጋጠሙ ችግሮች ወቅታዊ መፍትሄ መስጠት፣

በመስኖ በመጠቀም የጥራጥሬ ልማት ለማከናወን የሚረዱ የአሰራር መመሪያዎችን ለክልሎች ማቅረብ ከዚህ በፊትም በጥራጥሬ ሰብሎችን በመስኖ ከማልማት አንፃር የተቀመሩ ምርጥ

ተሞክሮዎች ካሉ ለክልሎች ማስተላለፍ፣

ክልሎች ከአርሶ አደሮቻቸው እና ከምርጥ ዘር ኢንተርፖራይዞቻቸው ከሚሰበስቡት ዘር በተጨማሪ በፌደራል ደረጃ ካሉ ዘር አባዦች እና ከምርመር ማዕከላት ሊቀርቡ የሚችሉ የዘር እና የህየው ማዳበሪያ ግብዓቶችን ለክልሎች ማቅረብ እና ቀበሌ ደረጃ መድረሱን ማረጋገጥ፣

በመስኖ በሚለሙ ሰብሎች አመራረት እና በተለይም ለጥራጥሬ ሰብሎች የመስኖ አጠቃቀም ዙሪያ የክልል እና የዞን ባለሙያዎችን ከኢትዮጲያ ግብርና ምርምር ጋር በመተባበር የተግባር ስልጠና መስጠት፣

የሰብሎቹን የአዝመራ ሁኔታ በመስክ በመገኘት በመከታተል ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣

Page 10: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

በክልል ደረጃ

ከፌደራል የዘር እና የአፈር ምርመራ ላቦራቶሪዎች የሚልኩትን ግብዓቶች ወደ ወረዳ፣ ቀበሌዎች እና ለተጠቃሚዎች ሳይዘገይ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እጅ

መድረሱን ማረጋገጥ የመስኖ አውታር ባለባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙትን አርሶ አደሮችን እና

ወረዳዎችን በማስተባበር የመስኖ አውታሮች በወቅቱ እንዲጠገኑ ማስደረግ፣ ችግር ያለባቸውን የመስኖ አውታሮች በመለየት ማደስ

የመስኖ አውታር ባለባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ውስጥ በመስኖ የጥራጥሬ ሰብሎችን ለማልማት ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ አደሮችን በመለየት ለድጋፍ በሚያመች መልኩ እንዲሰበሰቡ ወረዳዎችን ማስተባበር፣ በትግበራ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ተከታትሎ መፍትሄ መስጠት

ከግብርና ሚኒስቴር የሚላከውን በመስኖ በመጠቀም የጥራጥሬ ልማት ለማከናወን የሚያስችሉ የአሰራር መመሪያዎችን በክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውል በሚችል መልኩ

በማዘጋጀት ለወረዳዎች እና ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ማድረግ፣ በክልሉ ከዚህ ቀደም የተሰበሰቡ እና የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከፌደራል ከሚላከው ጋር በማገናዘብ እና የክልሉን ተጨባጭ

ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለልማት ሰራተኞች እና ወረዳዎች እንዲተላለፍ ማድረግ፣

በመስኖ አጠቃቀም እና አያያዝ፣ መስኖን በመጠቀም ሊለሙ የሚችሉ የጥራጥሬ ሰብሎችን አለማም አያያዝ ዙሪያ ከግብርና ሚኒስቴር የሚሰጠውን ስልጠና ለወረዳ ባለሙያዎች እና ለልማት ሰራተኞች ማስተላለፍ፣

የመሬት ዝግጅት እና የሰብል ልማት ስራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መከናወናቸውን ማረጋገጥ እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት በየደረጃው እንዲፈቱ እንደየድርሻው ለባለድርሻዎች ማቅረብ

የተባይ እና የበሽታ ከስተቶች በወረዳ ደረጃ አስቀድሞ አሰሳ እንዲካሄድ በማድረግ የሚፈለጉ ድጋፎችን ለግብርና ሚኒስቴር እና ለግብርና ምርምር ማዕከላት ማቅረብ

ወረዳዎች እና የመስኖ ልማት ያላቸው ቀበሌዎች ደረጃ

የመስኖ አውታር በሚገኙባቸው ቀበሌዎች የሚገኙ አመራሮችን በመርሃ ግብሩ ላይ በማስገንዘብ ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን እንደ ፍላጎታቸው በጥራጥሬ ሰብል ልማት ላይ እንዲሰማሩ በማደራጀት

እና በማስተባበር ለመስኖው ስራ ዝግጁ በማድረግ የመስኖ አለማም ክህሎታቸውን ለመጨመር የተግባር ስልጠና ከክልሎች ጋር በመሆን ለአርሶ አደሮች እና ለልማት ሰራተኞች መስጠት፣

የልማት ሰርተኞችን፣አርሶ አደሮችን፣የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮችን በማስተባበር የመስኖ ቦይ እና አውታሮች ጠረጋ እና ጥገና ማድረግ እንዲሁም የክረምቱ አዝመራ እንደተሰበሰበ የሚኖረውን

የሰብል ቅሪት ባስወገድ መሬቱን በአፋጣኝ ለመስኖ ልማት ዝግጁ ማድረግ፣

ከፌደራል እና ከክልል የሚቀርብ ዘርን እና ከአፈር ምርመራ ላቦራቶሪዎች የሚላኩትን ህየወ ማዳበሪያ ለተሰባሰቡት አርሶ አደሮች ማድረስ እና አጠቃቀሙንም ማስገንዘብ እንደ አስፈላጊነቱም

አርሶ አደሮቹ በሚጠቀሙበት ወቅት አስፈላጊወን ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ፣ አርሶ አደሮቹም የደረሳቸውን ግብዓቶች በአግባቡ መተግበራቸውን ማረጋፈጥ እና በጥራጥሬ ሰብሎቹ

የተሸፈነውን መሬት ስፋት እና ጥቅም ላይ የዋለ ግብዓት መጠን መረጃ ለክልል ማስተላለፍ፣

Page 11: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ከክልል እና ከግብርና ሚኒስቴር የሚደርሳቸውን የአተገባበር መመሪያዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች በመጠቀም አርሶ አደሮች በአግባቡ የሰብል ልማት ስራውን እንዲተገብሩ ማድረግ እና በቅርበት

በመከታተልም አርሶ አደሮቹን መደገፍ፣

በመስኖ በተለዩ ቀበሌዎች በመስኖ ለማልማት ከተለዩት ማሳዎች ውስጥ ምንም ማሳ በሰብሎቹ ሳይሸፈን እንዳልቀረ ማረጋገጥ እና ያልተዘሩ ማሳዎችንም በመለየት በወቅቱ በአዝመራ መሸፈን፣

በልማቱ ላይ የገጠሙ ችግሮችን በመለየት ለክልል ማስተላለፍ፡፡

በመስኖ ልማቱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የተባይ እና የበሽታ ከስተቶችን የልማት ሰራተኞችን እና አርሶ አደሮችን በማስተባበር አሰሳ ማካሄድ እና ከወትሮው የተለየ የተባይ ወይም የበሽታ ክስተት ካለ

የሰብል ጥበቃ ማካሄድ እና የክልል ድጋፍ የሚሹትንም በመለየት ለክልል ማቅረብ፣

በሬድዮ የሚተላለፉ የግብርና ልማት ስራዎችን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልዕክቶች በወቅቱ ለልማት ሰራተኞች እና ለአርሶ አደሮች ማስተላለፍ

Page 12: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ሰንጠረዥ 10 ፡ በፌደራል ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት የግዜ ሰሌዳ

ተ.ቁ የሚከናወን ተግባር የሚከናወንበት የግዜ ሰሌዳ

ጥ ህ ታ ጥ የ መ ሚ ግ ሰ

1 የመሬት ዝግጅት እና የመስኖ አውታሮች ጥገና በአግባቡ መከናወኑን በመከታተል ላጋጠሙ ችግሮች ወቅታዊ መፍትሄ መስጠት፣

X X X X

2 በመስኖ ጥራጥሬ ለማልማት ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ አደሮች መለየታቸውን እና ለድጋፍ በሚያመች መልኩ መሰባሰባቸውን መከታተል ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን ድጋፍ መስጠት፣

X X X X

3 በመስኖ በመጠቀም የጥራጥሬ ልማት ለማከናወን የሚረዱ የአሰራር መመሪያዎችን ለክልሎች ማቅረብ ከዚህ በፊትም በጥራጥሬ ሰብሎችን በመስኖ ከማልማት አንፃር የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎች ካሉ ለክልሎች ማስተላለፍ፣

X

4 ክልሎች ከአርሶ አደሮቻቸው እና ከምርጥ ዘር ኢንተርፖራይዞቻቸው ከሚሰበስቡት ዘር በተጨማሪ በፌደራል ደረጃ ካሉ ዘር አባዦች እና ከምርመር ማዕከላት ሊቀርቡ የሚችሉ የዘር እና የህየው ማዳበሪያ ግብዓቶችን ለክልሎች ማቅረብ እና

ቀበሌ ደረጃ መድረሱን ማረጋገጥ፣X X X X

5 በመስኖ በሚለሙ ሰብሎች አመራረት እና በተለይም ለጥራጥሬ ሰብሎች የመስኖ አጠቃቀም ዙሪያ የክልል እና የዞን ባለሙያዎችን ከኢትዮጲያ ግብርና ምርምር ጋር በመተባበር የተግባር ስልጠና መስጠት፣ X

6 የሰብሎቹን የአዝመራ ሁኔታ በመስክ በመገኘት በመከታተል ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፣

X X X X

ሰንጠረዥ 11፡- በክልል ደረጃ ለሚከናወኑ ተግባራት የግዜ ሰሌዳ

Page 13: Pulse Crops Special Irrigation Program First Draft

ተ.ቁ የሚከናወን ተግባር የሚከናወንበት የግዜ ሰሌዳ

ጥ ህ ታ ጥ የ መ ሚ ግ ሰ

1 ከፌደራል የዘር እና የአፈር ምርመራ ላቦራቶሪዎች የሚኩትን ግብዓቶች ወደ ወረዳ፣ ቀበሌዎች እና ለተጠቃሚዎች ሳይዘገይ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እጅ መድረሱን ማረጋገጥ

X X X X

2 የመስኖ አውታር ባለባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኙትን አርሶ አደሮችን እና ወረዳዎችን በማስተባበር የመስኖ አውታሮች በወቅቱ እንዲጠገኑ ማስደረግ፣ ችግር ያለባቸውን የመስኖ አውታሮች በመለየት ማደስ

X X X X

3 የመስኖ አውታር ባለባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ውስጥ በመስኖ የጥራጥሬ ሰብሎችን ለማልማት ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ አደሮችን በመለየት ለድጋፍ በሚያመች መልኩ እንዲሰበሰቡ ወረዳዎችን ማስተባበር፣ በትግበራ ላይ

ለሚያጋጥሙ ችግሮች ተከታትሎ መፍትሄ መስጠት

X X X X

4 ከግብርና ሚኒስቴር የሚላከውን በመስኖ በመጠቀም የጥራጥሬ ልማት ለማከናወን የሚያስችሉ የአሰራር መመሪያዎችን በክልሎቹ ተጨባጭ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውል በሚችል መልኩ በማዘጋጀት ለወረዳዎች እና ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ማድረግ፣ በክልሉ ከዚህ ቀደም የተሰበሰቡ እና የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከፌደራለ

ከሚላከው ጋር በማገናዘብ እና የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለልማት ሰራተኞች እና ወረዳዎች እንዲተላለፍ ማድረግ፣

X

5 በመስኖ አጠቃቀም እና አያያዝ፣ መስኖን በመጠቀም ሊለሙ የሚችሉ የጥራጥሬ ሰብሎችን አለማም አያያዝ ዙሪያ ከግብርና ሚኒስቴር የሚሰጠውን ስልጠና ለወረዳ ባለሙያዎች እና ለልማት ሰራተኞች ማስተላለፍ፣

X

6 የመሬት ዝግጅት እና የሰብል ልማት ስራዎች ወቅታቸውን ጠብቀው መከናወናቸውን ማረጋገጥ እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት በየደረጃው እንዲፈቱ እንደየድርሻው ለባለድርሻዎች ማቅረብ

X X X X X X X

7 የተባይ እና የበሽታ ከስተቶች በወረዳ ደረጃ አስቀድሞ አሰሳ እንዲካሄድ በማድረግ የሚፈለጉ ድጋፎችን ለግብርና ሚኒስቴር እና ለግብርና መርመር ማዕከላት ማቅረብ

X X X X X X X