publisher: zehabesha llc · ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክ በሴንት ፖል ሚኒሶታ 1144...

16
መዲና ጋዜጣ በዘ-ሐበሻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሥር የምትታተም፣ በጋዜጠኝነት ሙያ ከ15 ዓመት በላይ ልምድ ባላቸው ጋዜጠኞች የምትዘጋጅ ወርሃዊ ጋዜጣ ናት:: የጋዜጣዋ ዋና ዓላማ እያዝናኑ ማስተማር፤ እያወቁ ማሳወቅ ነው:: በመዝናኛ፣ በፍቅር፣ በኪነጥበብ፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በውበት፣ በፋሽን እና በሳይኮሎጂ ጉዳዮች ዙሪያ የምታተኩር የመጀመሪያዋ የሚኒሶታ ጋዜጣ ናት:: "መዲና" ጋዜጣ በነጻ የምትከፋፈል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ እህት ስትሆን ሁልጊዜ በወሩ የመጀመሪያው ማክሰኞ ቀን ትወጣለች:: Publisher: Zehabesha LLC Publisher: Zehabesha LLC Medina/መዲና June 2012 volume 2 No. 4 ሰኔ 2004 2ኛ ዓመት ቁጥር 4 የ2012 የዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በዚህ ዓመት ጁን 20/12 ተከብሮ ይውላል። ይህን በማስመልከት በሚኒሶታ የትዊን ሲቲስ (ጥንዶቹ ከተሞች) የስደተኞች ቀን ጁን 16 ቀን 2012 በሚኒሃሃ ፓርክ (ወደ ገጽ 14 ይዞራል) $10 ገጽ 3 ገጽ 11 ገጽ 3 ገጽ 13 ገጽ 7 ገጽ 14 ገጽ 5 ገጽ 5

Upload: others

Post on 29-Oct-2019

50 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

መዲና ጋዜጣ በዘ-ሐበሻ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ሥር የምትታተም፣ በጋዜጠኝነት ሙያ ከ15 ዓመት በላይ ልምድ ባላቸው ጋዜጠኞች የምትዘጋጅ ወርሃዊ ጋዜጣ ናት:: የጋዜጣዋ ዋና ዓላማ እያዝናኑ ማስተማር፤ እያወቁ ማሳወቅ ነው:: በመዝናኛ፣ በፍቅር፣ በኪነጥበብ፣ በጤና፣ በሴቶች፣ በውበት፣ በፋሽን እና በሳይኮሎጂ ጉዳዮች ዙሪያ የምታተኩር የመጀመሪያዋ የሚኒሶታ ጋዜጣ ናት:: "መዲና" ጋዜጣ በነጻ የምትከፋፈል የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ እህት ስትሆን ሁልጊዜ በወሩ የመጀመሪያው ማክሰኞ ቀን ትወጣለች::

Publisher: Zehabesha LLC

Publisher: Zehabesha LLC

Medina/መዲና June 2012 volume 2 No. 4 ሰኔ 2004 2ኛ ዓመት ቁጥር 4

የ2012 የዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በዚህ ዓመት ጁን 20/12 ተከብሮ ይውላል። ይህን በማስመልከት በሚኒሶታ የትዊን ሲቲስ (ጥንዶቹ ከተሞች) የስደተኞች ቀን ጁን 16 ቀን 2012 በሚኒሃሃ ፓርክ (ወደ ገጽ 14 ይዞራል)

$10

ገጽ 3

ገጽ 11

ገጽ 3

ገጽ 13

ገጽ 7

ገጽ 14

ገጽ 5

ገጽ 5

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

Founded in December 2008 Publisher :-

ZeHabesha LLC ዋና አዘጋጅ:-

ሔኖክ ዓለማየሁ ደገፉ

Editor in chief:-

Henok A. Degfu e-mail:-

[email protected]

[email protected]

አዘጋጆች: ሊሊ ሞገስ፣ [email protected]፣ ሮቤል ሔኖክ፣

[email protected]፤ ቅድስት አባተ ፤ ዘላለም ገብሬ (ቺካጎ፤ )፤

Medina Newspaper Address:-

6938 Portland Ave, Richfield MN 55423

612-226-8326 ww.zehabesha.com

በዚህ ዓምድ ላይ እንድትሳተፉ እንጋብዛለን። ከተቃራኒ ጾታ የምትወዱትን እና

የምትጠሉትን አካፍሉን። በአድራሻችን ይጻፉልን።

መንፈሳዊ መዝሙር እና ስብከት የሚያዳምጠውን፤

ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት እናደርግ ብሎ የማይጠይቀውን፤

ጋብቻ ሲጠይቅ በቅዱስ ቁርባን ለማግባት የሚፈልገውን፤

ጾም ጸሎት የሚያደርገውን

ሲጋራ የማያጨሰውን፤

አፉ ጋን ጋን የማይለውን፤ በጊዜ እቤቱ የሚገባውን እወዳለሁ። ባገባውም እመርጣለሁ።

ያያት ሁሉ የምታምረውን፤

ሴት ሲያይ ሰውነቱን ሁሉ የሚቆላውን፤

የሚዋሸውን

ጉረኛውን፤

በ እውቀቱ ሳይሆን ባለው ነገር የሚመዳደቀውን

ቤተሰቡን የማይረዳውን፤

ሸሚዙን ሳይተኩስ ሰው ፊት የሚቀርበውን፤

ቤተክርስቲያን መሄድ የማይፈልገውን ነጭናጫ ወንድ በሕይወቴ ምድር ያስጠላኛል። ከ እንደዚህ ዓይነቱ ሰው ጋር ምንም ግንኙነት እንዲኖረኝ አልሻም።

ከስንዱ

ድህነቷን ረስታ እዚህ አሜሪካን ሃገር ሰለመጣች ብቻ አነጋገሯን ለውጣ አጉል ሞልቃቃ የቦሌ ልጅ ለመሆን የምትጥረው የማንነት ችግር ያለባትን፤

“የሃበሻ ወንድ ፍቅር አያውቅም” እያለች ከጥቁር ጋር የምትሄደውን፤

ፍቅር ሰጥቶ ፍቅርን መቀበል የ እውነተኛ ፍቅር መሠረት ሆኖ ሳለ ያፈቀራትን ወንድ እንደ ጅል የምትቆጥረውን ጥቅመኛ

ታማኝ ያልሆነችውን ሴት ላገባ አልፈልግም።

በስደት ላይ በወገኗ ደስ የሚላትን። የሃገሯን ልጅ ስታገኝ ልክ እንደቤተሰቧ የምታየውን አዛኝ፤

ሰው ሲቸገር ለመርዳት የምትጥረውን፤

ጠበቅ ያለ ጅንስ ወይም ጉርድ ቀሚስ የምታደርገውን፤

ከንፈሯ እንደ ወይን ሊፈርጥ የደረሰውን ቁመተ ለግላጋ

ብዙ እንዲነገራት የማትፈልገውን ብልህ

ሰው የጠፋ ዕለት ሰው ሆና በችግርም በመከራም ጊዜ አብራ የምትቆመውን ለትዳር እፈልጋታለሁ።

በዚህ ዓምድ ላይ እንድትሳተፉ እንጋብዛለን። ከተቃራኒ ጾታ የምትወዱትን እና የምትጠሉትን አካፍሉን። በአድራሻችን

ይጻፉልን።

ከሰራዊት

Welcome to Medina’s Community Calendar. Medina’s mission is simple: To contribute to the community in which we live! Medina newspaper offers free event listings for

churches, schools, community groups and other non-profit organizations. Do you have an event you'd

like to share with the rest of the Capital District, or the world, for that matter? You may submit your information in these ways:

email: [email protected]

6938 Portland Ave, Richfield MN 55423

ጁን 9 ቅዳሜ ጁን 8 የሚስቶቼ ባሎች የተሰኘ ትያትር እዚህ ሚኒሶታ ውስጥ ይታያል። ትያትሩ የሚታየው በሴንትራል ሃይስኩል

ነው። ከምሽቱ በ5:30 አዳራሹ ይከፈታል።

ጁን 9 በሬድ ሲ ክለብ ዲጄ ኤቲ የሙዚቃ ምሽት አለው።

ጁን 16 ከቀኑ በአንድ ሰዓት የጥንዶቹ ከተሞች (ትዊን ሲቲስ) የዓለም የስደተኞች ቀን በመኒሃሃ ፓርክ ይከበራል። በዚህ በዓል ላይ

የተለያዩ ሃገራት ባህሎችና ምግቦች ይቀርባሉ።

ጁን 16 ብሉሚንግተን ሞል ኦፍ አሜሪካ አጠገብ በሚገኘው ክራውን

ፕላዛ ሆቴል ድምዳዊ ጎሳዪ ተስፋዬ የሙዚቃሥራውን ያቀርባል። ትኬቱ በር ላይ $ 30 ነው ተብሏል።

ጁን በየሳምንቱ እሁድ ቲ ኤስ ፕሌስ ድምጻዊ ተሾመ አሰግድን ይዞ ይቀርባል።

ጁን በየሳምንቱ እሁድ ቲ ኤስ ፕሌስ

ለሙስሊሞች በሙሉ በሚኒሶታ ዳዋ ኢንስቲትዩት በማርች በሳምንቱ እሁድ ለመላው

እስልምና ተከታዮች ልዩ የትምህርት ፕሮግራም አዘጋጅቷል። በሚከተለው አድራሻ ይጠይቁ።

Minnesota Da'wah Institute (Islamic Da'wah Center)

478 University Ave W. Saint Paul, MN 55103

Telephone: 651.224.6726 or

651.224.6722 Email: [email protected]

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ጁን 19 ትወጣለች

የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ ሚኒሶታ በአህመድ ዋሴ አዘጋጅነት በየሳምንቱ እሁድ የሚቀርበውን የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ በኢንተርኔትም ጭምር ማድመጥ እንደሚችሉ ያውቁ ኖሯል?www.kfai.org ኦንላይን ላይ ማድመጥ ትችላላችሁ። እንደዚሁም ደግሞ በራዲዮ ለማድመጥ በሚኒያፖሊስ የምትኖሩ በ90.3 እንዲሁም በሴንፖል የምትኖሩ በ106.7 የሬድዮ ሞገዶች ላይ ዘወትር እሁድ ከአራት ሰዓት እስከ አምስት ሰዓት ድረስ ማድመጥ ትችላላችሁ።

የአረብኛ ቋንቋ ለመማር ዘወትር እሁድ ኢማም ሃሰን የሙስሊሞች ማ እከል ነጻ የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት አዘጋጅቷል። ትምህርቱ የሚሰጠው ጠዋት ከ10

ሰአት እስከ ቀትሮ 11 ሰዓት ድረስ ነው። ለበለጠ መረጃ በ(763)

560-2225 ይደውሉ። ወይም 6120 Brooklyn Blvd,

Brooklyn Center, MN 55429 አድራሻችን ይምጡና ይጠይቁ።

በጋው መጣ፤ ተማሪዎች ትምህርት የላቸውም። የት ወስጄ ላዝናና ብለው አስበዋል? ወተር ፓርክ ኦፍ አሜሪካ (ብሉሚንግተን የሚገኘው) በየቀኑ ክፍት ነው። ጥሩ የሆኑ

ዋጋዎችን ስላቀረቡ ለማዝናናት ጥሩ አጋጣሚ ይሆንላችኋል። ዋጋ ለመጠየቅ 952)

229-5753 ይደውሉ።

- ከሆሊላንድ ፊትለፊት ኮለምቢያ ሃይት ናሮቢ የተሰኘ ትልቅ ግሮሰሪና ምግብ ቤት ተከፍቷል። በዚህ ግሮሰሪና ዴሊ ውስጥ ክትፎ በጣባ ቀርቦላችኋል። ሄዳችሁ መርቁ።

- በበርከታ ሰርጎች ላይ ምግቦቿን የምትወዱላት የሬድ ሲ ሬስቶራንት ባለቤት ዘወትር ሃሙስ ምሳ ሰዓት ላይ ብፌ በ9.99$ አዘጋጅታለች። በብፌው ላይ ተወዳጁን ክትፎዬንም አዘጋጅቻለሁ ቅመሱልኝ ትላለች።

- ሚኒያፖሊስ ፍራንክሊን አቬንዩ ላይ የሚገኘው ሉሲ የኢትዮጵያውያን ሬስቶራንት ዘወትር ሃሙስ ክትፎ በቆጮ የሚበላበት ቀን ካደረገው ሰንብቷል። የኖቬምበር አራት ሃሙሶች ማለትም በ3፣ በ10፣ በ17 እና በ24 ክትፎ በቆጮ ለሚበሉ ነጻ የለስላሳ መጠጥ ያቀርባል።

ጁምአ (አርብ) እንዲሁም በሌሎች ቀናቶች በመስጂድ መስገድ ለምትፈልጉ፦ ኦማር ኢስላሚክ ሴንተር መስጂድ

አድራሻ፡ 912 East 24th Street, Minneapolis - ስልክ ቁጥር (612) 871-8275 አል ሁዳ መስጂድ

አድራሻ፦ 2534 Central Ave. NE Minneapolis, MN 55418 ስልክ ቁጥር፡ 612-782-3883

ከዳዊት ወርቁ ሀይ ጀለሶቼ! ዛሬ ሸፋፋ ወግ ይዤላችሁ ቀርቤያለሁ፣ . . .

እየተንሻፈፍኩ አወጋችኋለሁ፡፡ ፋሺን የሚለው ቃል ለመጀመርያ ጊዜ የተገኘው

በላቲን አገር ይኖሩ ከነበሩት አቶ ሽፋ ከሚባሉ ሰው ነው፡፡ አ ቶ ሽፋ ሸፋፋ ነበሩ ይባላል፡፡ በዚያ ላይ ሽፋሽፍቶቻቸው በጣም ጸጉር ይበዛባቸው ነበር አሉ፡፡

ታዲያ አቶ ሽፋ አንድ ጊዜ አንድ አልፎ ሂያጅ፣ “ሽፋ ሸፋፋ ስላላቸው!” በጣም ተናደው፣ ሊጨረግዱት ዱላ ቢመዙ፣ ዱላቸውን ተቀብሎ ስለፈነከታቸው፣ ጭንቅላታቸው በፋሻ ተጠቀለለ፡፡

ሽፋን የሰጧቸው ሚዲያዎችም በጊዜው ሰዉ ሁሉ መጠቅለልልስ ካልቀረ በፋሻ ልክ እንደ ሽፋ፤ እያለ እየተደባደበና እየተፈነከተ በፋሻ መጠቅለልን ፋሽን አደረገው ይላሉ፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮም ፋሽን ፋሻ ከሚለው ቃል መጣ ብለው ጥናቶች ያወሳሉ ወደ ቁምነገሩ ልምጣ . . . እናንተዬ፣ መቼም ዘንድሮ የፋሺን ኢንደስትሪው

የማሳየን ጉድ የለም፤ በተለይ በተለይማ የሴት እህቶቻችንን አልባሳትና አለባበስ፣. . . ቆይ ቆይ አንድ

ጊዜ፣ እኔ ምለው “ሴት እህቶቻችን” ነው ያልኩት ?. . . ይባላል እንዴ ?. . . አይባልም! . . . ግን ግን ብዙ ሚዲያ ላይ “ሴት እህቶቻችን” ይህን አርገው፣ ያን አርገው፣ “ሴት እህቶቻችን” እንዲህ ብለው፣ እንዲያ ብለው፣ “ሴት እህቶቻችን” በዚህ ወጥተው በዚያ ገብተው ሲባል ስለምሰማ ነው፤ . . . ቋንቋ ሲደኸይ ማለትም ይኼኔ ነው እንግዲህ፡፡ “ሴት እህቶቻችን”. . . ግሩም ቃል!!! . . . እኔ ምላችሁ ወንድ እህቶች አሉ እንዴ?. . .

. . . ወንድ እህቶች ካላችሁ እስቲ አንዴ እጃችሁን አውጡ . . . ሆቸጉድ! አሉ እማማ ወለቴ፡፡

እዚህ አገር ከሰነበቱ ምን የማይሰማ ነገር አለ ብላችሁ ነው?. . . “የቆየ ከሚስቱ ይወልዳል” እንዲሉ፤… እና ከማን ሊወልድ ነበረ ታዲያ? . . . ሌላ ቀን እንዲህ ባሉ ተረቶቻችን ላይ መዝመቴ አይቀርም፣

እናላችሁ የፋሽኑ ዓለም መላቅጡ እየጠፋበት ነው፡፡ አሁን አሁንማ አይኖችህ ምን ማየት ሰለቹ አትሉኝም?. . . የ“ሴት እህቶቻችን” ን የፋሽን ዓይነት፡፡ አለባበሳቸውን ጭምር፡፡ በተለይማ ይኼ ከእምብርታቸው በታች እንዲውል ሆነ ተብሎ የተሰራው ሱሪያቸው፤ በተቀመጠበት አልውል እያለ ሺ ጊዜ ወደ ላይ ሲስቡት ዳሌያቸውን ዳንስ ቢጤ እያስሞከራቸው መከራቸውን አበላቸውኮ፤

. . . ሰው በሚበዛባቸው ቦታዎች ውስጥ የሚጨናነቁትንስ መጨናነቅ ታዝባችሁልኛል? . . . በተለይማ ጎንበስ ብለው ቀና ሲሉ ጡት ማስያዣ ይሁን

ፓካውት አሊያም ካናቴራ እየጎተቱ “መቀመጫቸው” ን ለመሸፈን ሲታገሉ አቤት አንጀቴን ሲበሉት. . . አንዳንድ ጊዜማ እምባዬ ሳይቀር ደርሶ ባይኔ ግጥም ይላል፤ እኔን!. . . ምፅ!! . . . (lol)

በነገራችን ላይ “lol” የሚለውን ቃል ትርጉሙ ሳይገባኝ በፊት ምን ለማለት ፈልገው ነው፣ “ሎሌ” ነው ወይስ “አሎሎ” እያልኩ ስጨነቅ በኋላ ነው የአሜሪካዋ የፌስቡክ ወዳጄ “lots of love” ወይም “ laugh out loudly” ማለት ነው ብላ የገላገለችኝ፡፡ ምን ይደረግ . . .

እናላችሁ የተንሻፈፈው ፋሽን የሴቶቻችንን አለባበስ አንሻፎብን የኛንም ልብ እያንሻፈፈብን ነው፡፡ ማየት የምንመኛቸውን ያካል ክፍሎቻቸውን እየገላለጠ፣ በነፃ እያሳየን፣ ሲያልፍም ከኃጢያት ማጥ እየከተተን፣ ሲብስም ወንጀል አሰርቶ ዘብጥያ እያስወረደን፡፡ አሁንማ ግራ ገባንኮ፣ ጾም ጸሎት ይዘን ጥ ሩ ጊዜ ካምላካችን ጋር አሳልፈን ወጣ ስንል ዐይናችን . . . እንዴት ዐይነት ጣጣ ነው ጎበዝ! . . . ሙሴ ከሴትጋ ያመነዘረ ኃጢአት አደረገ ብሎ ሕግ ደነገገ፣ ይሁንና ኢየሱስ ማሻሻያ አደረገለትና ሴትን ያየ በልቡም የተመኘ አመነዘረ፣ ኃጢአትም አደረገ፤ አለ፡፡ በዚህ ዓይነት በየቀኑና በየሰዓቱ፣ በየደቂቃውና በየሰከንዱ ከስንቷ ጋር በልባችን እንደምናመነዝር አስቡት እንግዲህ!

ታዲያ ሁለቱን ሕጎች ለየት የሚያደርጋቸው በአካል እና በልብ ማመንዘሩ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በሙሴ ሕግ ኤች አይ ቪና .ሌሎች በግብረ ሥጋ የሚተላለፉ ተላላፊ በሽታዎች ሲተላለፉ፣ በክርስቶስ ሕግ ግን ይህ የለም፣ በልብ ስለ ሚመነዘር፡፡

እናላችሁ የፋሽኑ ዓለም ግራ እያጋባን ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ወዳጆቼ ሁሉ “ስክኒ ሱሪ” ሲለብሱ ባይ የነበሩኝን ሱሪዎች ሁሉ አውጥቼ ልብስ ሰፊው ቅባቱጋ ወስጄ “ቃሪያ” አስደረኳቸው፡፡

በነገራችን ላይ እነዚህ የመርካቶ ልብስ ሰፊዎች የተቀደደ ነፍስና የተሰበረ ልብ ሁሉ መስፋት ጀምረዋል የሚባል ጭምጭምታ አለ. . .

. . . “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” አሉ እማማ ወለቴ በኋላ አንደኛው “ሼባ ሙድ” ጀለሴ (ብዙ ጊዜ የወፍጮ ቤት ቋት የሚመስል

ሱሪ የሚለብስ) አይቶኝ፣ በሳቅ ጦሽ ብሎ አይፈነዳም? . . . በፍንዳታውም አካባቢው ስለተረበሸ፣ ባሸባሪነት ተጠርጥሮ፣ ባሻ አሸብር ባሜሪካ የተባለውን የመንግሥቱ ለማን መጽሐፍ በቃሉ እንዲወጣው ተፈርዶበታል . . . የታባቱ!! . . . ልለው አሰብኩና ተውኩት

እናላችሁ የፋሽኑ ዓለም ግራ ተጋብቶ ግራ እያጋባን ነው እላችኋለሁ፡፡ ደግሞ አይታችሁልኛል በስፖርት የፈረጠሙ ሰዎች እነ ቫንዳም ሸዋዚንገር ወዘተ. . . ዓይነት ሰዎች፣ የሚለብሱትን “ቦዲ ቲሸርት?” . . . አዎ እኛምጋ አንዳንዶች ቦዲ እንልበስ ብለው ቢሞክሩ በ ሽሮ ያበጠች ትንሽ ኳስ የመሰለች ሆዳቸው ፊጢጥ ብላ ብታስፎግራቸው የሚፈልጓት ሴትጋ ሲደርሱ ሆዳቸውን እንደ ሎሚ ይመጧታል፡፡

ባለፈው አብዲ የሚባል ጀለሳችን ዲዲ (ሴት እህቶቻችን... ወደ ገጽ 6 የዞረ)

ቤተክርስቲያኖች በሚኒሶታ ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክ በሴንት ፖል ሚኒሶታ

1144 Earl St, Saint Paul, MN 55106 651.771.7129 ደውለው በዚህ ወር ታዋቂዋ ዘማሪት ዘርፌ በዑራኤል ለተከታታይ 3 ቀናት በመቆየት ታገለግላለች። ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሴንት ፖል በአባ ዘራ ዳዊት የምትመራው ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በጁን ወር ያላት ሃይማኖታዊ መርሃ ግብር ምን ይመስላል?

አድራሻው የሚከተለው ነው፡ 678 Robert St S Saint

Paul, MN 55107። ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሴንት ፖል በጁን ወር ያላቸውን መርሐ ግብርና አቅጣጫ ለመጠየቅ በ651-771-1490 ለአባ ሃይለማርያም ከሌታ ይደውሉ። ደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ሚኒያፖሊስ ዘወትር ሐሙስ የትምህርት መርሃ ግብር አለ።

ለበለጠ መረጃ አድራሻ 4401 Minnehaha Ave. S Minneapolis, MN

55406 ወይም በስልክ (612)-721-1222 ይጠይቁ። የኢትዮጵያ ኢቫንጀሊካል ቤ/ክ ሴንትፖል 770 7th St E Saint Paul, MN 55106-5026 በጁን ወር ያላቸውን ፕሮግራም ለማግኘት በ(651) 772-0216 ይደውሉ።

ሞሪንሆ..... ከገጽ 10 የዞረ

አሁን በመጠኑም ቢሆን ያንን ሂደት ያለፍኩት ይመስለኛል፡፡ አሁን የማስበው በአንድ ክለብ ውስጥ ለረጅም ጊዜያት ያህል በመቆየት ታላላቅ ስኬቶችን ስለመቀዳጀት ብቻ ነው፡፡ ክለብ ደግሞ ሪያል ማድሪድ ነው፡፡ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢገጥሙኝ እንኳ በሳንቲያጎ በርናባው በመቆየት ታላላቅ ድሎችን ለመቀዳጀት ራሴን ዝግጁ አድርጌዋለሁ፡፡ አሁን በዕድሜም የመጎልበት ሁኔታ ስላለ ከፊቴ የሚገጥሙኝን ፈተናዎች እንደከዚህ ቀደሙ በጭቅጭቅና በንትርክ ሳይሆን በብልሀት ማለፍን ነው የምመርጠው፡፡ የዘንድሮውን የውድድር ዘመን ያለፍኩትም በዚህ መንገድ ነው፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ ተጋጣሚዎቻችንን እየረመረምን በመጓዝ ላይ ሳለንና እንዲሁም ላ ሊጋውን በሰፊ የነጥብ ልዩነት እየመራን እያለ ‹‹ዦዜ አበቃለት፡፡ ከክለቡ ይባረራል›› የሚሉ በርካታ አሉባልታዎች ሲወሩብኝ ነበር፡፡ ይሄ በጣም የሚገርም ነገር ነው፡፡ በየትኛውም ዓለም ብትሄድ ደካማ እንጂ ውጤታማ አሰልጣኝ ሲባረር አይቼ አላውቅም፡፡ ይሄ ታዲያ እንዴት እኔ ላይ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል? እኔ በጣም ብልጥ ሰው ነኝ፡፡ የሚገጥሙኝን ፈተናዎች እንዴት በብልሀት ማለፍ እንዳለብኝ በሚገባ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው ምንም ሳልረበሽ ዘና ብዬ በቻምፒዮንስ ሊጉ እስከ ግማሽ ፍፃሜ ለመጓዝና በላሊጋውም የድል ባለቤት ለመሆን የቻልኩት፡፡ ስለዚህ በዚህ ክለብ ውስጥ በሚመዘገቡ ድሎች ላይ በሙሉ የእኔ አስተዋፅኦ ላቅ ያለ ነው፡፡ የዛኑ ያህል ደግሞ ሽንፈት ሲገጥመንም ኃላፊነቱን ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ፡፡ ሁልጊዜም እንደምናገረው አሁንም የዓለማችን ምርጡ አሰልጣኝ ነኝ፡፡ ጥያቄ፡- እርስዎ እዚህ ክለብ ውስጥ በመቆየትዎ ምን ያህል ደስታ ይሰማዎታል? የክለቡ ጄኔራል ዳይሬክተር ሆዜ አንሂል ሳንቼዝና ክለቡስ ምን ያህል ደስተኛ ናቸው ብለው ያስባሉ?

መልስ፡- ይህ የቀሽም ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ክለብ እኮ አባቴ ወይም እናቴ አይደለም፡፡ ካልፈለጉኝ ታዲያ ለምን ያቆዩኛል? ለምን አያባርሩኝም? እንደዚህ አይነት ስራ እኮ በይሉኝታ የሚሰራ አይደለም፡፡ ክለቤ በእኔ ስራ ደስተኛ ሆኖ እኔ ግን በእነሱ ደስተኛ ካልሆንኩኝም ውሳኔዬ ተመሳሳይ ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ቀንም ሳላድር ነበር ጥዬ የምወጣው፡፡ ሁለታችንም ወገኖች ስለዚህ ጉዳይ ለረጅም ጊዜያት ስንነጋገር ቆይተናል፡፡ ከስምምነት ላይ ከደረስንም ቆይተናል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን ለሚዲያ ይፋ ማድረግ ስላልፈለግን ነው ዝምታን የመረጥነው፡፡ ይህ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ተጨዋቾችና ደጋፊዎችን አቅፎ የያዘ ቤተሰባዊ ክለብ ነው፡፡ ስለዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ ቀጣይ ጊዜያትም በእጅጉ የምደሰትባቸው እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ጥያቄ፡- በቀጣዩ የውድድር ዓመት ዋንኛ እቅድዎ ምንድነው? መልስ፡- ወደ ውድድሩ መግባት የምፈልገው ለሻምፒዮናነት የሚያበቃንን የቤት

ስራችንን ሙሉ ለሙሉ አጠናቅቄ ነው፡፡ ይህንን አቋሜን ለተጨዋቾቹ በሙሉ አስረግጬ ነግሬያቸዋለሁ፡፡ አንደኛውን ዋንጫ ከሌላኛው ማበላለጥ አልፈልግም፡፡ የምንካፈልባቸውን ውድድሮች በሙሉ በድል አድራጊነት መወጣት እፈልጋለሁ፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ዋነኛ ግቤ ይህ ነው፡፡ ምንም እንኳን ዘንድሮ የቻምፒዮንስ ሊጉን ዋንጫ ማንሳት ባንችልም ጥሩና ማራኪ እንቅስቃሴ ነበር ያደረግነው፡፡ ደጋፊዎቻችን በሙሉ በስራችን በእጅጉ እንደሚኮሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዚህም መነሻነት በቀጣዩ ዓመት በመላው ዓለም በርካታ አዳዲስ ደጋፊዎች እንደሚቀላቀሉን እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዓመት እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ የሆነውን የላ ሊጋውን ዋንጫ ለማንሳት የተጓዝንበት መንገድ ፍፁም ስኬታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ይህም ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ይህንንም በቀጣዩ ዓመት አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፡፡ አንድ ነገር ማሰብ ያለብን ሁሉም ክለቦች ወደ ውድድሩ የሚገቡት ዋንጫውን ለማንሳት ነው፡፡ ነገር ግን ያንን ማሳካት የሚችለው አንድ ክለብ ብቻ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ዘንድሮ እኛ ፈፅመነው አሳይተናል፡፡ ወደዚህ ክለብ ስመጣ ዋንኛ እቅዴ የነበረው ቢያንስ እስከ ሁለተኛው ሲዝን ድረስ የላሊጋውን ዋንጫ ማንሳት ነበር፡፡ በእቅዱ መሰረትም ዘንድሮ ይህንን ማሳካት ችያለሁ፡፡ በቀጣዩ የውድድር ዓመት ደግሞ ምን እንደሚከሰት አብረን የምናየው ይሆናል፡፡ ምንም በማይፈይዱን ጉዳዮች ላይ ጊዜያችንን ማቃጠል አንፈልግም፡፡ አንድና ብቸኛ የሚያስጨንቀን ጉዳይ ቢኖር በተሳተፍንበት የውድድር መድረክ ላይ በሙሉ በምን አይነት መልኩ የድል ባለቤት እንሆናለን? የሚለው ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ የክለቡን ታላቅ ታሪክ መጠበቅም በእኛ ላይ የተጣለ ኃላፊነት ነው፡፡ አሁን የአራት ዓመት ኮንትራት መፈረሜን ተከትሎ ትልቅ የቤት ስራ እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ፡፡ ስለዚህ የቤት ስራዬን ከወዲሁ ጀምሬያለሁ ማለት ነው፡፡ የቀጣዩ የውድድር ዓመት ዋነኛ እቅዴም የላሊጋውን ድል መድገምና በቻምፒዮንስ ሊጉም የሻምፒዮናንት ድልን መቀዳጀት ነው፡፡

ጥያቄ፡- እስከ 2016 ድረስ ጠንካራ ሆኖ መዝለቅ የሚችል ቡድን ይኖረኛል ብለው ያስባሉ? መልስ፡- በትክክል! ይህ ቡድን የወጣቶች ስብስብ ያለበት ነው፡፡ ምናልባት በጉዳትና

በአደጋ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከዕድሜ ጋር በተያያዘ ከ2016 በፊት ጫማውን የሚሰቅል አንድም ተጫዋች እዚህ ቡድን ውስጥ የለም፡፡ ያ ዘመን ሲደርስ ሁሉም በችሎታቸው ጫፍ ላይ የሚደርሱበት ነው የሚሆነው፡፡ በጣም ጥቂት ተጨዋቾች ደግሞ ምናልባትም ጫማቸውን ወደሚሰቅሉበት ጊዜ ሊቃረቡ ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡ በዛ ላይ ደግሞ አዳዲስ ተጨዋቾችም የሚመጡበት መንገድም ይኖራል፡፡ አሁን አሁን እኮ ተጨዋች መሸኘትና መቀበል አልያም ማቆየት ተራ ነገር ሆኗል፡፡ በተለይም ደግሞ የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሲከፈት እንደዚህ አይነት ነገሮችን መስማት የተለመደ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ዘንድሮ እኛን ይህ ነገር የሚያሰጋን አይመስለኝም፡፡ ቡድናችን በአስተማማኝ መሰረት ላይ የተገነባ ነው፡፡ በእርግጥ አንድ ሁለት ምርጥ ተጨዋቾችን እዚህ ስብስብ ላይ ጣል ማድረግ ዘንድሮ ካገኘነው 100 ነጥብ በላይ ሊያስጉዘን ይችላል ብዬ አምናለሁ፡፡ ዘንድሮ ይህንን በማሳካት አዲስ ሪከርድ ለመጨበጥ ችለናል፡፡ በቀጣይ ውድድር ዘመንም ይህንን እንደምንደግመው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ለአጭር ጊዜያት ብቻ ሳይሆን ለረጅም ዘመናትም ጭምር ሲታወስ የሚኖር ታላቅ ቡድን እንደገነባሁም ውስጤ

ያምናል፡፡

ከሊሊ ሞገስ

እየተበሳጩ ለምን የጤና ዋጋ ይከፍላሉ?

ንዴት በጣም ታላቅ የሆነ ስሜት ነው፡፡ በቅጡ ካልተያዘ ለተናዳጅም ሆነ ለሚወዷቸው የቅርብ ሰዎች አሉታዊ ተፅዕኖ ማምጣቱ አይቀርም፡፡ በሌላ በኩል ብስጭቱን በአግባቡ ማስተናገድና ምክንያቶቹን መረዳት ከተቻለ አዎንታዊ የሆኑ ለውጦችን ማምጣት እንደሚቻል አንዳንድ ጥናቶች ዘርዝረው ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን የተለያዩ ጥናቶች መሰረት አድርገን ለዛሬ ብስጩነት እና ጤና ያላቸውን ዝምድና እንቃኛለን፡፡

አካላዊ ተፅዕኖዎች ሰዎች በሚበሳጩበት ወቅት ሰውነት ‹‹የመሸሽ ወይም

የመጋፈጥ›› ምላሽ ስርዓትን ይጀምራል፡፡ ሰውነት ተመሳሳይ ምላሽ የሚሰጥባቸው ፍርሃት፣ መደነቅ፣ ጭንቀት እና ተያያዥ ስሜቶች በዚሁ ስርዓት ይስተናገዳሉ፡፡ በነዚህ ስሜት ወቅት አድሬናሊን የተሰኘው እጢ ሰውነታችንን በውጥረት ሆርሞኖች ያጥለቀልቀዋል፡፡ ከሆርሞኖቹ መካከል ዋነኞቹ ኮርቲሶል እና አድሬናሊን ናቸው፡፡ አዕምሮአችን ወደ ሆድ አካባቢ የሚልከውን ደም ይገድብና ወደ ጡንቻዎች እንዲሄዱ ያደርጋል፡፡ ይህም አካላዊ ምላሽ ለሚፈልግ ጉዳይ ሰውነታችንን ዝግጁ የማድረግ አላማ አለው፡፡ የልብ ምት እና የደም ግፊት ይጨምራሉ፣ የሰውነት ሙቀት ያሻቅባል፣ ቆዳችን ላብ ያመነጫል፡፡ አዕምሮም ንቁ ይሆናል አንክሮው ይጨምራል፡፡ ይህም አጠቃላይ ሰውነትን ለጦርነት እንደሚያዘጋጅ ወታደር ሰፊ ውጥረት ውስጥ ይከትተዋል፡፡

የጤና መዘዞቹ ያለመቋረጥ በውጥረት ሆርሞን ኬሚካሎች እና የሰውነት

ስርዓት ለውጦች ሰውነታችንን የመናጥ አቅም ያለው ያልተገራ ንዴት በተለያዩ የሰውነት ክፍል አካላት ላይ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ጥፋቶችን ያደርሳል፡፡ ያልተገራ ብስጭት የሚያቋርጥ ራስ ምታት ይሰጠናል፡፡ የሆድ ህመም እና ምግብ ለመፍጨት መቸገር እንዲሁም የጨጓራ ችግር በበርካቶች ይስተዋላል፡፡ እንቅልፍ ባይንዎ ሳይዞር የሚያድሩ ከሆነም በጣም የሚበሳጩ ሰው መሆንዎን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ብስጩ መሆን የደም ግፊትዎንም ይጨምራል፡፡ የልብ ድካም እና ስትሮክ ደግሞ በጣም ከበድ ያሉት የጤና ቀውሶች ናቸው፡፡ የቆዳ ችግሮችም እንዲሁ በሀይለኛው ሲበሳጩ ከሚፈጠር የሰውነት ውስጥ ለውጦች መነሻነት ሊከሰቱ

እንደሚችሉ የጥናት ውጤቶቹ ያመለክታሉ፡፡ የህክምናው ሳይንስ ሰዎች የንዴት ስሜት በተለይ ልብ ላይ ጫናው ከፍ ያለ በመሆኑ ‹‹ልቤን ያላችሁ ንዴት እና መጦፋችሁን በልክ አድርጉት›› ይላሉ፡፡ ጉዳቱን ለመግለፅም የጥናት ውጤቶቻቸውን ዋቢ ያደርጋሉ፡፡ 44 በልብ በሽታ እና ጤናማ ያልሆኑ ስሜቶች ላይ የተደረጉ ጥናቶች ላይ ትንታኔ የተሰራበትና ባለፈው ዓመት ጆርናል ኦፍ ዘ አሜሪካን ኮሌጅ ኦፍ ካርዲዮሎጂ የተሰኘው መፅሔት ላይ የሰፈረው ፅሑፍ እንዳረጋገጠው ንዴት እና ቁጠኝነት ለልብ ህመም ሁነኛ አባባሽ ምክንያት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በጥናቱ እንደታየው ምንም አይነት የልብ ህመም ታሪክ የሌላቸው ነገር ግን ሁል ጊዜ ብስጩ ሆነው የሚታዩ ሰዎች ከሰላማዊዮቹ አቻዎቻቸው በ10 በመቶ የበለጠ በልብ ህመም የመጠቃት ዕድል አላቸው፡፡ በዚህም ከሴቶች ይልቅ የወንዶች ልብ የበለጠ እንደሚጠቃ ተመልክቷል፡፡

በዕለት ተዕለት ህይወታችን በርካታ የሚያበሳጩን ጉዳዮች ሊገጥሙን ይችላሉና ጉዳዩ አይገጥምዎትም አይባልም፡፡ ነገር ግን ንዴቱን የሚገልፁበት መንገድ ከብስጭቱ ማዶ ሆነው ተረጋግተው ለማሳለፍ የሚያስችል ሳይሆን ይቀርና ራስዎን ከመጉዳት አልፈው የሌሎችን ሰላም ጭምር የሚነሱበት ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ‹‹ይህ ጤናማ አይደለም ለማንም አይበጅም›› ይላሉ የጥናት ባለሞያዎቹ፡፡ አንዳንዶች ንዴቱ ገንፍሎ ሰዎችን እንዲማቱ እና ጉዳት እንዲያደርሱ ዕቃዎችን እንዲሰባብሩ እና እንዲያጠፉ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ይህ ለጊዜው ንዴቱን በረድ ያደረገላቸው ቢመስላቸውም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቁጭት ውስጥ ሲገቡ እና ይቅርታ ሲጠይቁ መዋልን ያስገድዳቸዋል፣ እረፍትም ያጣሉ፡፡

ንዴት እንዲህ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጉዳት ሲያከስትል መጥፎ የመሆኑን ያህል ተሸፋፍኖ እና ተደብቆ ሲቀመጥም መዘዙ ብዙ ነው፡፡ መናደድ ስሜት መጥፎ ነው ብለው በማሰብ ሲቆጣጠሩት ሲሞከሩ ድንገት የፈነዳ ቀን ጥቃቱ በረክታል፡፡ ሳይገለፅ መቆየቱ ለድብርትና ጭንቀት እንዲሁም መሰል የአዕምሮ ችግሮች ሊመራ ይችላል፡፡ በተገቢው ጊዜና ቦታ በስርዓቱ ሳይገልፁት ቀርተው በልጆች፣ በእንስሳት ወይም ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት በሌለው ሰው ላይ በመግለፅ ችግሩን የሚፈጥሩም ጥቂት አይደሉም፡፡

ትክክለኛው ምላሽ ቱግ ማለት ወይስ ዝምታ?

እናስ ምን ይደረግ? ‹‹ንዴትዎን በጤናማ መልክ መግለፅ ይችላሉ!›› ነው የባለሞያዎች መልስ፡፡ ጥቂቶቹን ጤናማ የንዴት መግለጫ መንገዶች እነዚህ ናቸው፡፡ በተፈጠረው ሁኔታ

ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ ከመሰልዎት ከሁኔታው ለጊዜው ዞር ይበሉና ጥቂት ይረጋጉ፡፡ ነገር ግን የንዴትዎ መንስኤ የሆነውን ችግር ሳይውሉ ሳያድሩ ይፍቱት፡፡ የንዴት ስሜት ተፈጥሯዊ የሆነ ጤናማ ስሜት ነውና እንዴት እናደዳለሁ ብለው አያስቡ፡፡ የተበሳጩበትን ትክክለኛ ምክንያት ቁጭ ብለው ያስቡና ነጥለው ያውጡ፣ ቀድሞ የተከተሉት ችግሩን የመፍታት ዘዴ ትተው በሌላ ስትራቴጂ ለመፍትታ ይነሱ፡፡ ብስጭትዎት እንደ ረጅም ወክ፣ ሩጫ አሊያም ሌላ የስፖርት አይነት በመስራት ኔጌቲቭ ኢነርጂውን ቢያስወጡም ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡ ለአጭር ጊዜ በመፍትሄነት እነዚህን ሊጠቀሙ ቢችሉም ሁሉም ላይሰሩልዎ ይችላል፡፡ ስለዚህ የረጅም ጊዜ እና ቋሚ መፍትሄው የሚያናድዱዎትን ድንገት ቱግ የሚያደርጉዎትን ክስተቶች መዝግበው ይያዙና ለምን እና እንዴት ንዴት ውስጥ እንደከተተዎ ያስተውሉ፣ ከነዚህ ቆስቋሽ ሁኔታዎችም ይራቁ፡፡ ሰዎችን አሳማኝ የሆነ ንግግር ማድረግን እንዲሁም የቅራኔ አፈታት ጥበቦች ላይ ያንብቡ፣ ስልጠናም ይውሰዱ፡፡ እራስዎን ዘና ሊያደርጉ የሚችሉባቸውን እንደ ሜዲቴሽን አለዚያም ዮጋ ጥበቦችን ቢለምዱም ጥሩ ነው፡፡ እንደ ባለሞያዎቹ፡፡ ያለ ህይወትዎ ውስጥ የቆየ ጉዳይ ካለ የስነ ልቦና አማካሪ ዘንድ ቢደርሱ ጥሩ መፍትሄ ሊያገኙበት ይችላሉ፡፡ መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን መለማመድ በጣም ጥሩ ስሜትን ማስተንፈሻ ቀዳዳ በመሆኑም ይወደሳል፡፡

ንዴት በልጆች- ቁልፍ የመፍትሄ ስፍራ

አብዛኛዎቹ ግልፍተኛ ሰዎች ንዴታቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው እና ለከፍተኛ የጤና ጉዳት ሲዳረጉ የተመለከቱ

ባለሞያዎች የጀርባ ታሪካቸውን ለማወቅ

ጥረት ሲያደርጉ የተመለከቱ ባለሞያዎች የጀርባ ታሪካቸውን ለማወቅ ጥረት ሲያደርጉ ለዘመናት ቆይተዋል፡፡ ለዚህም ከተገኙ ውጤቶች መካከል በዋነኛነት ሰዎቹ በልጅነት ዕድሜያቸው ብስጭትን ሲያስተናግዱ የነበረበት መንገድ ችግር

ያለበት እንደሆነ መታወቁ ቁልፍ የጥናቶቹ ውጤት ነበር፡፡ ይህን መሰረት አድርገውም ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ንዴት ጠንካራ ትምህርትን መስጠት እነርሱም ምሳሌ ሆነው መገኘት አለባቸው ብለዋል፡፡

ልጆች ንዴታቸውን እንዲገልፁ ማበረታታት፣ ስሜቶቻቸውን በአክብሮት ማስተናገድ እና የችግር አፈታት ዘዴዎችን ማስተማር፣ ግልፅ እና አመኔታ ያለበት ግንኙነትን መሰረቶች ማሳወቅ ዋነኛ የወላጆች ኃላፊነቶች ሊሆኑ እንደሚገባቸው ይጠቁማሉ፡፡ ምክንያታዊ ንዴትን እና ጠብ የለሽ በዳቦ አይነት ግፊትን ለይተው እንዲያውቁ እና ሌሎችን ማጥቃት እንደሚያስቀጣቸው በተግባር ማሳየትም የወላጆች የቤት ስራ ነው ብለዋል አጥኚዎች፡፡

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

ኤፍሬም እሸቴ - ከሜሪላንድ ወደ ላስ ቬጋስ ስሔድ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። በመጀመሪያው ጉዞዬ ወደ ከተማይቱ የገባኹት በቀን ነበር። አሁን ደግሞ በማታ። አውሮፕላኑ

ለማረፍ ሲግደረደር፣ በግማሽ ክንፍ ከተማይቱን ሲዞር ላስ ቬጋስ ሰፊ ደረቷን ሰጥታ ተንጣልላ ትታያለች። በረሃማዋ የአሜሪካ ገነት፣ የቁማር ከተማ። በቀን ሲመለከቷት ዙሪያዋን ጭው ባለው በረሃ ውስጥ ተሰድረው በተሰለፉ የዓለት ኮረብቶች ተከብባለች። ሙቀት እንጂ ልምላሜ የሚባል ነገር የለባትም። ክሽን ብለው የተሠሩት መንገዶቿ በሌሎች ከተሞች ከማውቃቸው መንገዶች በተለየ መልኩ ሰፋፊዎች ናቸው። የላስ ቬጋስ ትንሽ የሚባለው ጎዳና የሌሎቹ ከተሞች ዋና መንገድ ሊሆን ይችላል። ደግሞም መልክዓ ምድሩ ለ….ጥ ያለ

ሜዳ ስለሆነ ሁነኛ ባለሙያ በደብተር ላይ ያሰመረው መስመር እንጂ በእውን ያለ መንገድ አይመስልም።

ላስ ቬጋስ የምትታወቀው በቁማሯ እና በመዝናኛዎቿ ነው። ከአውሮፕላን ወርጄ ወደ ዋናው መውጫ መንገድ ስጓዝ አንድ ማስጠንቀቂያ የሚመስል ማስታወቂያ ተሰድሮ ተመለከትኩ። "What happens in Vegas, Stays in Vegas” ይላል፤ “በቬጋስ የተደረገ ነገር (ምሥጢርነቱ) በቬጋስ ይቀራል” ይልና የምታነሣውን ፎቶም የሆነ የምታደርገውን ነገር ቴክስት እንዳታደረግ ሲል ያስጠነቅቃል። ከነጭራሹ አንዱ ማስታወቂያ “ወደ ኃጢአት ከተማ እንኳን በደህና መጡ” ይላል። የኔ አገር ሰው ቢያየው “በስማ …. ብ” ብሎ ሲያማትብ በዓይነ ኅሊናዬ ታየኝ።

“ለመሆኑ ስንት አበሻ ነው እዚህ አገር የሚገኘው?” አልኩ፣ እንደደረስኩ። “ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት ወደ 30 ሺህ ሰው ይኖራል ሲባል ሰምቻለኹ” ሲሉ መለሱልኝ - በከተማው የሚገኘው የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ካህን። ይኼ ሁሉ ኢትዮጵያዊ ቬጋስ ከተማ ውስጥ ይኖራል? አንዲት ትንሽ የኢትዮጵያ ከተማ ሕዝብ እንደማለት ነው። ያደግኹባት ሆለታ

ስንት ሕዝብ ይኖራት ይሆን ብዬ ስጎረጉር ያገኘኹት ወደ 26 ሺህ ነዋሪ እንዳላት ነው።

አብዛኛው ወንድ ኢትዮጵያዊ በታክሲ መንዳት ላይ የተሠማራ ነው። ያውም በቀን 12 ሰዓት። ከዚያ በታች መሥራት የሚባል ነገር የለም። አንድ ሺፍት የሚባለው 12 ሰዓት ነው። ታዲያ 12 ሰዓት ሙሉ ቬጋስ የታክሲ ተጠቃሚ አላት። ያውም ቱሪስት። “ስንት ታክሲ እንዳለ ታውቃለህ ኤፍሬም” አለኝ አንዱ ወዳጄ። “20 ሺህ ታክሲ ነው እኮ”። ያውም ጽድት ያሉ ታክሲዎች።

የታክሲ ሥራው ረዥም ሰዓት ለመሥራት የሚያስገድድ ቢሆንም የሚገኝበት ገንዘብ ጥሩ ስለሆነ በተለይ ወጣት ኢትዮጵያውያን ይስማማቸዋል። “ጥሩ ከሠራችሁ ስንት ታገኛላችሁ?” አልኩት ያንን ወዳጄን። “ዌል፤ ጎበዝ ሠራተኛ ከሆነ እስከ 4 ሺህ ዶላር ሊሠራ ይችላል። ሰነፍ የሚባለው ደግሞ መቼም ቢያንስ ቢያንስ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ዶላር ይሠራል”።

ሴቶቹ ኢትዮጵያውያን ከተማይቱን በሞሏት ቁማር ቤቶች በተለያየ መስክ ተሠማርተዋል። ቁማር

የከተማይቱ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ነው። በዓመት ከሰባት ሚሊዮን የማያንስ ቱሪስት ከመላው ዓለም የሚመጣባት ቬጋስ ቁማሯን እያጫወተች፣ በመጠጧ እያሰከረች፣ በአስረሽ ምቺው የጎብኚዋን ቀልብ ትሰውራለች። በዚህ እብደት ውስጥ የሚነሣ ፎቶ ቢኖር የሚስማማው ለጌጋስ ብቻ ያውም ለዚያ የአስረሽ ምቺው ወቅት እንጂ ለሌላ ጊዜ ላይሆን ይችላል። "What happens in Vegas, Stays in Vegas” እንዲል።

ገና ከአውሮፕላን ማረፊያ ሲደረስ የሚገኙት ዋነኛ ነገሮች የቁማር መጫወቻ ማሺኖች ናቸው። የቁማር ሱስ ያለበት ሰው ከዚያ ይጀምራል። ወይም ቬጋስን ተሰናብቶ ከመውጣቱ በፊት የማሳረጊያ ቁማር ይጫወታል። የቀረችው ተረፈ-ሳንቲም ብትኖር እዚያች አሟጦ እንዲሄድ ሁሉ ነገር ተዘጋጅቶላታል። ቁማር ከሲጋራና ከጫት የበለጠ አደንዛዥ መሆኑን ቲቪውም፣ ባለሙያውም ሁሌ ይናገራል። ምስክሩ ቬጋስ ነው።

ወደ ከተማዋ ስንዘልቅ አስፓልቱ ጽድት ብሎ ሳየው “ከተማችሁ በጣም ንጹህ ነው” አልኩት ወዳጄን። “እንዴ፣ በየማታው እየታጠበች እንዴት አትጸዳ?” ሲል

መለሰልኝ። ቁሽሽ ያሉ የዲሲ መንገዶች በዓይነ ኅሊናዬ መጡ። “ቆሻሻ መጣል ክልክል ነው፤ እስከ ሁለት ሺህ ዶላር ያስቀጣል” ይላል አንዱ ማስታወቂያ። ያበደ ታልሆነ ደፍሮ ቆሻሻ ወደ መንገድ አይወረውርም። ፖሊስ ወዲያው ከች ነው።

መቸም የአሜሪካ ፖሊስ ዋነኛ ሥራው የአገር መሪ ሲያልፍ ሕዝቡን በዱላ ወደ ጓሮ ማባረር አይደለም። ሥርዓት ከማስከበር ጀምሮ መንገድ ላይ መኪናህ ነዳጅ አልቆበት ቢቆም ወደ አንዱ ማደያ የሚያደርስ 2 ሊትር ዘይት እስከ መስጠት፣ አቅጣጫ እስከመጠቆም ድረስ ነው። “ሰላም ኦፊሰር” ብለው መጀመር ነው። “ሰላም ኦፊሰር፣ መንገድ ጠፍቶብኝ ነው። እንዲህ እንዲህ የሚባል ቦታ መሔድ ፈልጌ ነበር” ይሉታል። ሲመልስሎት “በዚህ አርገው፣ በዚህ ሔደው፣ በዚህ ታጥፈው” ያብራራል። “በሰላም ይንዱ” ብሎ ይሰናበታል።

በዚያ በረሃ ውስጥ እንዲህ የቱሪስት መዲና የሆነች ከተማ መገንባቱ ገረመኝ። የበረሃ የበረሃ እኛስ ስንት አልነበረን አልኩ በሆዴ። ለረዥም ዘመን በአፋር የተለያዩ ከተሞች የኖሩ ወዳጄ ሲነግሩኝ “ራሷ ዱብቲ ማለት ነው እኮ” ብለውኛል። ሙቀቱ - ዋዕዩ። በተለይም የበጋ ወራት እስከ 47 ዲግሪ ሴንትግሬድ የሚደርሰው ሙቀቷ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ያሰኛል። ውጪ መንገድ ላይ ሲሔዱ። ማን መንገድ ላይ ይሄዳል ታዲያ? ቶሎ መኪና ውስጥ ጥልቅ ነው። ከዚያም ቶሎ ወደ ሥራ ቦታ ወይም መኖሪያ ቤት ግብት። ሙቀቱ የሚታወቀው ከቤትም ከመኪናም ውጪ የመሆኛ አጋጣሚ ካለ ብቻ ነው። ከዚያ ውጪ በመኪናም በቤትም ያለው ማቀዝቀዣ አየሩን ገርቶታል። ውጪው ንዳድ-ቃጠሎ ይሁን እንጂ ውስጡ ግን ለስለስ ያለ አየር ነው። ቴክኖሎጂው ተፈጥሮውን ገርቶታል። “ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ሥር እናደርጋለን” ብለው ረሃብ በረሃብ ያደረጉን (ላስ ቬጋስ... ወደ ገጽ 6 የዞረ)

- ለሠርግ

- ለማንኛውም ድግስ

- እንግዳ ለመቀበል

- ለተማሪዎች ምርቃት - ለሽርሽር

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

1999 አዲስ አበባ እዚህ ቤት ሽርጉዱ ጦፏል፡፡ ዛሬ ማታ ትልቅ እንግዳ

ይጠበቃል፡፡ ሰሞኑን እናት ሌሊቱ አልነጋ ቀኑ አልመሽ ብሏቸው ነው የሰነበቱት፡፡ ያለፉት 13 ዓመታት እንዲህ እንደዋዛ ሲያልፉ ከልጆቻቸው የጎደለችው የመጀመሪያ ልጃቸው ናፍቆት ከልባቸው ሳይወጣ ኖሯል፡፡ አባትና እናት ካሏቸው 8 ልጆች ውስጥ የመጀመሪያ የሆነችው መቅደስ ወደ አሜሪካ የሄደችው የ20 ዓመት ወጣት ሳለች ነበር፡፡ ዲቪ ደርሷት ቤተሰቡን ተሰናብታ ከሄደች በኋላ ቤታቸው ጭር ብሎባቸው ነበር- ለወላጆቿ፡፡ ተጫዋች፣ የእናትና የአባቷን ስሜት ጠንቅቃ የምታውቅ፣ የቤቱ ምሰሶ የምትባል አይነት ወጣት ነበረችና ከቤት ስትርቅ ወላጆቿም ወንድምና እህቶቿም ትልቅ የብቸኝነት ስሜት ውስጥይ ነበር የገቡት፡፡ በጥቂት ዓመታት ልዩነት የተወለዱት የመቅደስ እህትና ወንድሞች በጊዜ ቦታ ቦታቸውን ለመያዝ አልተቸገሩም፡፡ ቤተሰቡ ለትምህርት በነበረው ከፍተኛ ክብርና አባት ዘወትር ሳይሰለቹ የልጆቻቸውን ውጤት ከስር ከስር የመከታተላቸው ነገር በጊዜ የትምህርት አስፈላጊነት በውስጣቸው እንዲሰርፅ አግዟቸዋል፡፡

መቅደስ አሜሪካ ከገባች በኋላ የመጀመሪያ ምርጫዋ የነበረው ወደ ትምህርት ቤት መግባት ነበር፡፡ ዋሽንግተን ከተማ ውስጥ የነበሩት የአጎቶቿ ልጆች ጋር ብታርፍም የትምህርት ዕድል ለማግኘት የነበሯትን አጋጣሚዎች በቸልታ ልታልፋቸው አልፈለገችም፡፡ በተለይም ገንዘብ ማግኘት ጀምራ የአሜሪካ ህይወት በዚያው ውጧት እንዳይቀር በማሰብ ወደ ካምፓስ እንድትገባ ግፊት ያደረገባት የተቀበላት የአጎቷ ልጅ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ጠቅልላ ወደ ትምህርት ቤት ገባች፡፡ አባቷም ቢሆኑ ይህንኑ መረዳት አላቃታቸውምና አበረታተዋታል፡፡ መቅደስ የጀመረችውን ትምህርት ቀጥላ እስከማስተርስ እና ዶክትሬት ዲግሪዋን እስክትይዝ ድረስ ከትምህርት ቤት አልወጣችም፡፡ ላለፉት 14 ዓመታት ህይወት ማለት ትምህርት ማለት ሆኖ ኖሯል ለርሷል፡፡ በትርፍ ጊዜዋ እየሰራች በጥሩ ተማሪነቷ የምታገኛቸውን የስኮላርሺፕ እድሎች እየተጠቀመች ሳታቋርጥ ተምራ የዶክትሬት ዲግሪዋን በህዝብ ጤና አስተዳደር ስትይዝ በሕይወቷ ልትደርስበት ያሰበችው ግብ መሳካቱን ነበር ያወጀችው፡፡ አሜሪካን ሀገር የብዙ ኢትዮጵያውያ ተምሳሌት የሆነችበትን ትምህርት ጥርስን ነክሶ የመማር ፅናት ፍሬ በማፍራት አሳይታለች፡፡ አንዴ ስራ ጀምሮ ገንዘብ ማግኘት ከተለመደ በኋላ ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ነገር ዘበት በሆነባት አሜሪካ ከሀበሾች ውስጥ ተጠቃሽ የሆነ ስኬት ለማስመዝገብም ችላለች- የተመረቀችው በከፍተኛ ማዕረግ ነበርና፡፡ ከዚህ በኋላ ለመቅደስ የአሜሪካ ህይወት ቀላል ነበር፡፡ ፕሮፌሽናል በመሆኗ ከማንም አሜሪካዊ እኩል ተፎካክራ የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ላይ ለመሰማራት እድል አላት፡፡ 14 ዓመት ያጠፋችበት ትምህርቷ አሁን በምታገኘው የዳጎሰ ገቢ ይክሳታል፡፡ በጊዜው ራሷን ከብዙ ነገር ከልላ የ34 ዓመት ወጣት እስክትሆን ድረስ ትምህርቷን ጓደኛዋና ሁለነገሯ አድርጋ ኖራለች፡፡ እናትና አባቷ ሁኔታውን ቢረዱትም ልጃቸው ትዳር የምትይዝበት ጊዜ ያለ እየመሰላቸው ይጨነቁ ነበርና ዘወትር ስለወደፊት ህይወቷ እያሰቡ ይጨቀጭቋትም ነበር፡፡ አላማዬ ብላ የተነሳችበትን መስመር ላለመሳት ወላጆቿን ጨምሮ ከብዙ አቅጣጫ የሚሰነዘርላትን አስተያየት ለጊዜው ችላ ከማለት ውጪ አማራጭ አልነበራትም፡፡ አሁን ግን እፎይ ብላለች፡፡ ሁሉም ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፡፡ ዝቃ የማትጨርሰው የዕውቀት ሀብት አፍርታለች፡፡ ሌላው ሀብት ደግሞ ይህን ስኬት ተከትሎ ይመጣል፡፡ ዶክተር መቅደስ የመጀመሪያ እቅዷ ለዓመታት የተለያየችውን ቤተሰቧን ማየት ነው፡፡ ዛሬ ማታ ትገባለች፡፡ ብዙ ዘመናት አልፈዋል፡፡ ትንንሽ ሆነው ጥላቸው የሄደችው እህትና ወንድሞቿ አድገው ትልቅ ሰው ይሆናሉ፡፡ ሁለቱን ወደ አሜሪካ ለመሳብና እዚያ እንዲኖሩ ለማድረግ ብትችልም አምስቱን ግን አይናቸውን ካየችው ይህንን ያህል ዓመት አልፏል፡፡ በተለያየ አጋጣሚ አሜሪካ እንዲገቡ ያደረገቻቸው አንድ ወንድሟና አንድ እህቷ ቤተሰቡን የመርዳት ኃላፊነት ጥላላቸው እሷ በሙሉ ልቧ በትምህርቷና በምርምር ስራዋ ላይ ተጠምዳ ቆታለች፡፡ አሁን ደግሞ ታግሰው የቆዩዋትን ቤተሰቧን ለመካስ ወጥናለች፡፡

ለማንኛውም ወደሀገሯ ልትበር ነው የመቅደስ ቤተቦች ይህቺን በታላቅ ክብር ወደ ቤተሰቧ

የምትመለስ ልጃቸውን አይን ለማየት ጓጉተዋል፡፡ አባትና እናቷ ወደዚያ ሄደው ሊያዩዋት የሚችሉበት ዕድል የነበራቸው ቢሆንም አባቷ ‹‹ተረጋግታ ትማርበት፤ እኛን ስታይ ልትጨነቅ ትችላለች›› ብለው የመሄድ ሀሳባቸውን ደጋግመው ሰርዘውታል፡፡ ብዙም አልተቃወመቻቸውም፡፡

የካ ክፍለ ከተማ መገናኛ አካባቢ የሚኖሩት የመቅደስ ቤተሰቦች ድሮም የተሻለ ኑሮ አላቸው ከሚባሉ ሰዎች ተርታ የሚመደቡ ነበሩ፡፡ አባቷ በአንድ የጣሊያን ድርጅት ውስጥ ይሰሩ በነበሩበት ጊዜ ገንዘብ አጠራቅመው የገነቡት ትልቅ መኖሪያ ቤት ዛሬ እንደ ወተት ላም የማይነጥፍ ገቢ የሚሰጣቸው ሆኗል- አንድ የውጪ ድርጅት ተከራይቶት በየወሩ ዳጎስ ያለ ገቢ ይሰጣቸዋል፡፡ በዚያ ገቢ የነበራቸው ሌላ መሬት ላይ አነስተኛ ቤት ቀልሰው መኖር ጀምረዋል፡፡ ውጪ ሀገር ያሉ ልጆቻቸውም የሚልኩላቸው ገንዘብ ለሁሉም ቤተሰብ የተሻለ ኑሮ ፈጥሯል፡፡ ለዚህም ነው ያለምንም ጭንቀት ልጆቻቸውን በመልካም ሁኔታ ያሳደጉት፡፡ አሁን የመቅደስ መምጫ ሲደርስ በርሷ ጭቅጭቅ ለድርጅት ያከራዩትን ቤት አስለቅቀው ከገቡበት 3 ወር ሆኗቸዋል፡፡ ቤቱን አድሰውና ሙሉ አዳዲስ ዕቃ አሟልተው ነው የገቡበት፡፡ ልጃቸውን ድል ባለ ድግስ የሚቀበሉትም በዚሁ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሰፊው ግቢ ዘበኛና ሁለት ሠራተኞችም ተቀጥረውለታል፡፡ የምትመጣውን ልጅ ለማየት ወላጆች ብቻ ሳይሆኑ ሠራተኞችና ዘበኛውም ጓጉተዋል፡፡

መጋቢት 8 ቀን 1999 ሌሊት የተጠበቀችው ዶክተር አዲስ አበባ ገባች፡፡ በሁሉም ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ በተለይም ላለፉት 14 ዓመታት በሰው ሀገር ብዙ መሰናክሎችን ተቋቁሞ ያለማንም አይዞህ ባይ መኖር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለምታውቀው ለመቅደስ ቤተሰቦቿን በሰላም ማግኘት ከደስታም በላይ አስለቅሷታል፡፡ ያቺ የ20 ዓመት ለጋ ወጣት በዕድሜው ላይ 14 ዓመታትን ጨምራ ትልቅ ሰው ሆና መምጣቷ- አባትና እናት ፀጉራቸውን ሽበት ወርሶትና ዕድሜው ተጫጭኗቸው ማግኘቷ- ወንድምና እህቶቿ ትልልቅ ልጆች ሆነው ማየቷ ሁሉም በየስሜቱ ልቡን የሚፈነቅለው ጉዳይ ነበር- የመለያየትን መራርነት ለሚያውቁት ለነዚህ ቤተሰቦች ያቺ ቀን በርግጥም ታላቅ የደስታ ቀን ናት፡፡ ቢያንስ በዓይነ ስጋ ለመገናኘት እድሉን አግኝተዋልና፡፡

በዚህ ቤተሰብ ተድላና ደስታ ነገሰ፡፡ በየዕለቱ ድግስ- በየዕለቱ የዘመድ አዝማድ ጉብኝት በየዕለቱ አዳዲስ ነገር በሞላበት ግቢ ውስጥ በልቡ ነገር ይዞ መጎንጎን የጀመረ አንድ ሰው ግን አልጠፋም- ዘበኛው፡፡

በ1980 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ከገባ በኋላ ከቀን ስራ ጀምሮ በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰልፎ ራሱን ለመርዳት ጥሯል- አይን አየሁ፡፡ ከጎጃም ደብረማርቆስ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ሲመጣ እዚህ ሀገር የሚያውቀው አንድ ሰው አገኘው የአባቱን የጥንት ጓደኛ ልጅ ብቻ ነው፡፡ እሱ ጋር ለጥቂት ቀናት ከተቀመጠ በኋላ ነበር ወዲያው አንድ ቤት ውስጥ ዘበኝነት ተቀጥሮ ሰራ የጀመረው፡፡ የሚሰራባቸው ሰዎች ውጪ ሀገር ጠቅልለው እስኪሄዱ ድረስ አብሯቸው ይኖሯል- ለ6 ዓመታት፡፡ ከዚያ ወዲህ ሲያገኝ ቀን ስራ እየሰራ- አንዳንዴም የትናንሽ ሱቆችና ድርጅቶች ዘበኛ ሆኖ እያገለገለ የአዲስ አበባ ህይወቱን ገፍቷል፡፡ እንደርሱ አነጋገር ጠብ ያለ ነገር ባያገኝም ላለፉት 19 ዓመታት አዲስ አበባ ውስጥ ሳያርፍ ሰርቷል፡፡

የዛሬ 3 ወር ግድም አንድ የሚያውቋቸው ሰው ለጥቂት ጊዜ ስራ ፈት ሆኖ ያዩትን አይንአየሁን ጠርተው አንድ ቤተሰብ ውስጥ ስራ ላስቀጥርህ ሲሉት አላቅማማም፡፡ የምግብና መጠለያ ጉዳይ ሳያሳስበው ገንዘቡን ብቻ እየቆጠረ የሚያስቀምጥበት ቤት ፈልጓል፡፡ ወዲህም የአዲስ አበባ የኑሮ ውድነት አማርሮታል፡፡ ሁልጊዜም ሀብታም የመሆን ምኞት ቢኖረውም ይህን ሀሳቡን የሚያሳካበት አጋጣሚ ግን አግኝቶ አያውቅም፡፡ ዕጣ ፈንታው ዘበኝነት የሆነ እስኪመስለው ድረስ እዚያው ላይ ተተክሎ ኖሯል፡፡ አሁንም የመቅደስ አባት አግኝተው ሲያነጋግሩት የሰራባቸውን ቦታዎችና አዲስ አበባ ውስጥ የኖረበትን ዘመን ነግሯቸው ደስተኛም ሆነው ነው የቀጠሩት፡፡ ተያዥ አስመጥተው፡፡

በቆይታው ስለቤተሰቡ ብዙ ያወቀው ነገር አለ፡፡ የቀጣሪዎቹ ሶስት ልጆች ውጪ ሀገር እንደሚኖሩና አንደኛዋ በቅርቡ ወደ ሀገሯ እንደምትመጣ የነገረችው ከቤተሰቡ ጋር ለ7 ዓመታት የኖረችው ሠራተኛ ናት፡፡ ዓይንአየሁ የዚህች

ትመጣለች የተባለች ዶክተር ጉዳይ አሳስቦታል፡፡ በዓይነ ህሊናው ከአሜሪካ ምን ያህል ሻንጣ ብር ይዛ እንደምትመጣ ነው የሚያስበው፡፡ መቼም የአሜሪካ ሀገር ዶክተር ሆና ሀብታም አይደለችም ማለት ይከብዳል ብሎ ነው ለራሱ ያሰበው፡፡ ለማንኛውም እሱም በተራው እስክትመጣ ድረስ ጓጉቷል- ሊያያት፡፡

ሌሊት በር ሲከፈት በሁለት መኪና ተጭኖ ወደ ቤት የገባውን ሻንጣ ሲያይ በጣም ተገርሞም ነበር፡፡ ምን ይዛ ብትመጣ ነው ይህ ሁሉ ሻንጣ ብሎም አስቧል፡፡ ከሰሞኑ ታዲያ ልቡ ገብቶ አልወጣ ያለውን ሀሳብ ይታገለው ይዟል፡፡ የልጅቷ መግባት አዲስ ስለሆነ ትንሽ እስክትቆይ ሀሳቡን ተግባራዊ ከማድረግ ለመቆጠብ አሰበ፡፡ ቀናት እየተቆጠሩ መቅደስ ሀገሯ ከገባች ሳምንት አለፋት ሲባል ግን ጥንስሱን ጀመረ፡፡ በነዚህ ቀናት መካከል ግን መቅደስ ለዚህ ሰው 100 ብር ሰጥታዋለች፡፡ ስትወጣና ስትገባ ተሽቆጥቁጦ ስለሚያስተናግዳት ያሳዝናታል፡፡ በልቧ የሆነ ነገር ልታደርግለትም አስባለች፡፡ ግና የሁለቱ ሆድ ልዩነት ባለው ሀሳብ ውስጥ መውደቁን አታውቅም፡፡

ዓይንአየሁ ወደቤተሰብ ስልክ ልደውል ብሎ ወጣና አንድ ስልክ ቁጥር መታ፡፡ ከዚህ ቀደም የቀን ስራ ሲሰራ የሚያውቀው ጓደኛው ነው፡፡ ይህ ጓደኛው ከሚሰራበት ቤት ገንዘብ ዘርፏል ተብሎ ተከስሶ ለ2 ወራት ከታሰረ በኋላ የተለቀቀና የቀን ስራ ሲሰራ ያገኘው ወጣት ነው፡፡ ባለሱቁ እንዳይሰማው ቀስ ብሎ የደወለበትን ምክንያት አስረዳው፡፡

‹‹የምሰራበት ቤት ልጅ ከአሜሪካን ከመጣች ሳምንት አልፏታል፡፡ ብዙ ዶላር ጭና የመጣች ይመስለኛል፡፡ 14 ዓመት አልፏታል አሉ ከሄደች፡፡ የሆነ ነገር ብናደርግ ምን ይመስልሃል?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ ጓደኛው በሁኔታው ተስማምቶ ከሰው ተማክሮ ሊጠብቀው ተነጋገሩና በማግስቱ ደውልልኝ ብሎት ተለያዩ፡፡

ዓይንአየሁ በማግስቱ ወደዚህ ጓደኛው ስልክ ሲደውል ያኛው ያሰበውን ገለጠለት፡፡ 4 ሌሎች ሰዎችን ይዞ እንደሚመጣና ሌሊት ወደቤት ገብተው እንደሚዘርፉ መነሻ ሀሳቡን ነገረው፡፡ ቀሪውን ፍቃድ ጠይቆ ወጥቶ እንዲነጋገሩ አሳሰበው፡፡ ዓይንአየሁ እንቅልፍ ሊወስደው ስላልቻለ በማግስቱ ነበር ‹‹...የታመመ ዘመድ አለኝ ለግማሽ ቀን ፍቃድ ስጡኝ...›› ብሎ የመቅደስን አባት ጠይቆ የሄደው፡፡ ያለጥርጥር ያሰበው እንደሚሳካ እርግጠኛ ነበር፡፡ እዚህ ቤት ያለእኚህ ሰው እንዲሁም በቅርቡ ከዩኒቨርሲቲ ከመጣው አንድ ወጣት በቀር ሌላ ወንድ የለም፡፡ ሁሉም ሴቶች ናቸው፡፡ ሌሎቹ ወንዶች ትምህርትና ስራ ላይ ናቸው፡፡ ስለዚህ በቀላሉ ቤቱን ለመድፈር ችግር አይኖርም ብሎ ነው ያሰበው፡፡

ከጓደኛው ጋር ተገናኝተው ሀሳባቸውን ሲወያዩም ያነሳለት ይህንኑ ነው፡፡ ሁለቱ ጓደኛሞች ቁጭ ብለው ንድፍ አወጡ- የዘረፋ ንድፍ፡፡ ማንም ለማንም ምስጢር እንዲያጋልጥ ተማማሉ፡፡

በዕለተ አርብ መጋቢት 21 ቀን ከምሽቱ 7 ሰዓት አራት ሰዎች ወደዚህ ግቢ እንደሚመጡ- ዘበኛው በጠጠር የግቢውን በር ሲመቱ እንደሰማ በር እንዲከፍት- ከዚያ የልጅቷ መኝታ ክፍል ድረስ ሄደው መስኮት ሰብረው እንደሚገቡ- ገጀራ እንደሚይዙና ልጅቷን ካገኙ በኋላ አስገድደው ገንዘብ ተቀብለዋት እንደሚሰወሩ ተነጋገሩ፡፡ በዚህ መሀል ዘበኛው ጥርጣሬ ላይ እንዳይወድቅ እሱም የተደበደበና ዘራፊዎች የጎዱት እንዲመስል በገመድ አስረውት አፉን በጨርቅ አፍነው ጥለውት እንደሚሄዱ ጭምር ዘዴ አወጡ፡፡ በደንብ ተመካክረው ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡ አይንአየሁ ከዚህች ዕለት ጀምሮ እንቅልፍ አላየም፡፡ በተቻለው መጠን በዚያን ቀን ዘረፋው በየትኛው መስኮት በኩል መፈፀም እንደሚገባው ያስብ ነበር፡፡ ሠራተኛዋን በድንገት አስመስሎ መቅደስ የምትተኛበትን ክፍልን ጠይቋት ነግራዋለች፡፡ ስለዚህ እሷ ያለችበትን ቦታ መስኮት ገንጥሎ መግባት ብዙም እንደማይቸገር አጥንቷል፡፡ ዘበኛው ቤት ተቀምጦ ይህንን ግቢ እንዴት መድፈርና መዝረፍ እንደሚቻል ይጠናል፡፡ እየተከፈለው- እየተቀለበ ታላቅ ወንጀል ድርጊት በልቡ ያውጠነጥናል፡፡

ያቺ ቀን ደረሰች፡፡ ገመድ ገዝቷል፡፡ የአቡጀዴ ንፁህ ጨርቅ

አዘጋጅቷል፡፡ ምሽቱን ሲቁነጠነጥ ቆየ፡፡ ቤተሰቡ ከምሽቱ 5

ሰዓት በፊት ወደ አልጋ አይሄድምና እሱም ሌሊት ላይ እንቅልፍ እንዳይጥለው ብሎ በተቀመጠበት ጥቂት አሸለበ፡፡ ሲነቃና ሰዓቱን ሲያይ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ሆኗልና የቪላ ቤቱ መብራት ጠፍቷል፡፡ ሠራተኞች የሚያድሩበት ክፍል መብራት ጠፍቷል፡፡ በግቢው የሚሰማ አንዳች ድምፅ የለም፡፡ ግብርአበሮቹ በተባለው ሰዓት መጡ፡፡ ምልክቱን ሰጡት፡፡ በሩን ሳይሰማ ቀስ ብሎ ከፈተው፡፡ አራቱም ጭንብላቸውን ያጠለቁት ግቢው ውስጥ ገብተው ነው፡፡ ግቢውን የደጅ መብራት አብርቶላቸው ነበርና ያለችግር የዘረፋ ማካሄጃቸውን አደራጁ፡፡ የመጀመሪያ ስራቸው በሰጣቸው ገመድ እሱን ማሰር ነበር፡፡ ሳያጠብቁ እጆቹን ወደኋላ አስረው ከእግሩ ጋር በገመድ ካገናኙት በኋላ የሰጣቸውን ጨርቅ አፉ ውስጥ ጨመሩት፡፡ ከዚያም ተሸክመው የማይቆረቁር ቦታ አጋደሙትና ወደ ውስጥ ገቡ፡፡

ሶስቱ ገጀራና ጩቤ ይዘዋል፡፡ ወደ ተጠቆሙበት መስኮት በዝግታ እርምጃ ተጠጉና በያዙት መፈልቀቂያ በመታገዝ ለመንቀል ሞክሩ፡፡ የሚቻል አልሆነም፡፡ ስለዚህ በዋናዋ በር በኩል ሰብረው ሊገቡ ተስማሙ... መስኮቱን፡፡ አንደኛው ጃኬቱን አውልቆ መስታወቱን ሲመታው ረገፈ፡፡ ወዲያው ተከታትለው ገቡ፡፡ ይህንን ድምፅ የሰሙት አባወራ ጆሯቸውን አቀኑ፡፡

ዘራፊዎቹ በቤቱ ውስጥ ቀስ እያሉ ወደ መኝታ ቤቱ ተጠጉ፡፡ ሁለቱ አንደኛውን ሁለቱ ደግሞ ሁለተኛውን መኝታ ለመክፈት ተከፋፈሉና ስራቸውን ጀመሩ፡፡ በዚህ መሀል ነበር ሰውዬው ማነው? ብለው ያንቧረቁት፡፡ ዘራፊዎቹ በሰውየው መንቃት ቢደናገጡም መመለስ ግን አልፈለጉም፡፡ ሰውየው በሩን በርግደው የገቡትን ሁለት ባልጭንብል ሰዎች ሲያዩ ጩኸታቸውን አቀለጡት፡፡ ይሄኔ የተኛው ቤተሰብና ሰርቪስ ቤት ያሉት ሠራተኞች ጭምር ነቁ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ወደመቅደስ መኝታ ቤት ያመሩት ሁለቱ ሌቦች ደግሞ እሷን ገንዘብ እንድታመጣ በገጀራ እያስፈራሩ ከቁም ሳጥኗ ያስቀመጠችውን 250 ዶላርና 3 ሺህ 560 ብር ብቻ አግኝተዋል፡፡ ሰውየው ጩኸታቸው በመጨመሩ ሌቦቹ በያዙት ገጀራ እጃቸውን ክፉኛ መቷቸው፡፡ ቤቱ በጩኸት ትርምስ ተናወጠ፡፡ የዘበኛውን ስም እየጠሩ የሚጮሁት የሰውየው ባለቤት አራቱም ሌቦች ግር ብለው ከግቢው ወጥተው ሲሄዱ በመስኮት እያዩ ነበር ድረሱልን የሚሉት፡፡ ጩኸቱን የሰማ ጎረቤት በሙሉ ግቢውን ወረረው፡፡ በገጀራ የተመቱት ሰው ወደ ሆስፒታል ተወሰዱ፡፡ ብዙዎች በገመድ ታስሮና ታፍኖ የተገኘው ዘበኛ በጣም አሳዝኗቸዋል፡፡

ፖሊስ በዚያው ሌሊት በስፍራው እንደደረሰ እስሩ የተጎዳናውን ዘበኛን ነበር ቀድሞ ያገኘው፤ ሁኔታውን ጠየቀው፡፡ የሆነውን ሁሉ ተናገረ፡፡ ዱብ ዕዳ እንደገጠመው በማልቀስ ነበር የሚገልፀው እንደደበደቡትም ጭምር፡፡

የዚህን ዘበኛ ወሬ ፖሊስ ሙሉ ለሙሉ አምኖ ግን አልተቀበለም፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ ቢያዝኑለትም ፖሊስ ግን የተለመደ ጥርጣሬውን ከርሱ ላይ አላነሳም፡፡ ከዚህም ቀደም የተካሄደ ተመሳሳይ ድርጊት ነበርና ዘበኛውን የዚያን ዕለት ሌሊቱን አስሮ አሳደረው፡፡ ዘበኛው ይህ ይሆናል ብሎ ስላልጠበቀ በጣም ደገነጠ፡፡

መርማሪ ፖሊሶች በተለያዩ መስቀለኛ ጥቄዎች ቀኑን ሲያጣድፉት ቢውሉም ብዙም ለመናገር የደፈረው ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን ብዙ ቴክኒክ ተጠቅመው የተቀነባበረውን ሴራ ደረሱበት፡፡ ዘበኛው በወንጀሉ ላይ የነበረውን ተሳትፎ አመነ፡፡ ያደረገውን ሁሉ ለፖሊስ ተናዘዘ፡፡

የመጀመሪያ ተያዥ የርሱ ጓዳኛ ወንጀለኞቹን ያደራጀው ሰው ነበር፡፡ ፖሊስ በ3 ቀን ውስጥ ሁሉንም በወንጀል ላይ የተሳተፉ ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ከተሰረቀው ገንዘብ ጥቂቱን ማስመለስ ቻለ፡፡ ፖሊስ ይህን ይጠረጥራል ያላለውና ታይቶ የማይታወቅ አዲስ ወንጀል ስልት ፈጠርኩ ብሎ የተኩራራው ሰው ወህኒ ቤት ሲወረወር በገጀራ የተመቱት የቤቱ ባለቤትም አገግመው ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡

በዝርፊያ፣ በድበደባና በአካል ላይ ጉዳት ማድረስ ተደራቢ ወንጀሎች የተከሰሱት 5 የዘረፋው ቡድን አባላት ወረዱ፡፡ ሀገሯ መጥታ ከቤተሰቧ ጋር የደስታ ጊዜ ለማሳለፍ የጓጓችው መቅደስ ለብዙ ቀናት በድንጋጤ ታማ ብትከርምም እየቆየ ግን ሁሉም ነገር ተረሳ፡፡ ምስጢረኞቹ ብዙም ልፋት ሳይጠይቅ የቋጠሩት የሌት ምስጢር በቀን ተፈታ፡፡

ጋዜጣችንን በየወሩ ይጠብቋት።

አቅራቢ፡ ታየ ዘሪሁን

የመንግስቱ ኃይለማርያም “ትግላችን” መጽሐፍም አለን

በአዲስ ማርኬት (ሴንት ፖል እና ሚኒያፖሊስ)፣ በሰላም ካፌ ሚኒሃሃ እና እንደዚሁም በሸጋ ሱቅ

ሚኒያፖሊስ (ሲደርና ፍራንክሊን ላይ) ያገኙታል።

የበለጠ መረጃ ከፈለጉ አሁኑኑ ይደውሉ፤ 612-226-8326

ለመጽሐፍ አንባቢዎች በሙሉ የዳንኤል ገዛኸኝ

“ሲዋን” የሲሳይ አጌና

“የቃሊቲው መንግስት”

የዶ/ር አክሎግ ቢራራ

“የመሬት ነጠቃና ቅርሚት” እንግሊዘኛ

መጽሐፍት በሚኒሶታ ገበያ ላይ ናቸው

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

ሜሮን ከሳቬጅ ሚኒሶታ

1 . ምን አላችሁ? ጎጆአችሁ በፀጋ ብቻ ሊቆም አይችልምና ገንዘብ

አቅም ያስፈልጋችኋል፡፡ እንደሚታወቀው ትዳር መመስረት እንደ አንድ ትልቅ ኢንቨስትመንት ስለሚቆጠር እንዲያው ተንደርድረው የሚገቡበት

አይደለም፡፡ በተቻለ መጠንም በወንዱም ሆነ በሴቷ በኩል በቂ ዝግጅት ሊኖረው ይገባል፡፡ በተለይም ሁለቱም በስራው ዓለም ውስጥ ያሉ ከሆኑ ይነስም ይብዛም የቋጠሯት ጥሪት ትኖራለች፡፡ ይህች የተቋጠረች ገንዘብ ደግሞ ለትዳራቸው መጠናከር የራሷ የሆነ የጎላ አስተዋፅኦ ይኖራታል፡፡ ባለ ገንዘቡ ታውቆ ሚስት ይፋ መሆን አለባት፡፡ ወይም ደግሞ ሚስት ገንዘቧን አፍስሳ ባል ግን ‹‹ከደሞዜ በቀር ሌላ የለኝም›› ብሎ መደበቅ አይኖርበትም፡፡ በዚህ ረገድ የበለጠ የሚጎዱት ሴቶች ናቸውና በሠርጉ ዋዜማ ‹‹ምን አለው?›› የሚለውን ሁኔታ ማወቅ አለባቸው፡፡

2 . እዳ ይኖርቦት ይሆን? እንግዲህ ለጋብቻ የቀረበው ባል ገበያው የደራለት ጎበዝ ነጋዴ ሊሆን ይችላል፡፡ በርካታ የሚከራዩ ቤቶች፣ ተንቀሳቃሽ መኪኖች፣ ከቤተሰቡ የወረሰው ‹‹እርጥባን›› መሆኑ ተስፋን ሊያለመልም

ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ የተማረ የተመራመረ ከኮሌጅ የተመረቀ ምሁር ባልም ያጋጥማል፡፡ እነዚህ የሚያጓጉ ሁኔታዎች ያሉት ሰው አማራጩ ሊበዛ ይችላል፡፡ ተመራጯ ሴት ደግሞ የራሷ ንብረት ያላት ትሆንና ‹‹የአቻ ጋብቻ›› ተብሎ ይሞጋገሳል፡፡ ሆኖም የባል ንብረት በተለያየ ምክንያት የተወሰነ እዳ ያለበት፤ ወይም ሙሉ በሙሉ በእዳ የተያዘ ሊሆን ይችላልና ሚስት የጋብቻ ውል ከመፈረሟ በፊት አስቀድማ ማወቅ ይኖርባታል፡፡ አሊያ ግን ባልበላችው እዳ እድሜ ልኳን ስትገፈግፍ ትኖራለች፡፡

3 . ገንዘብ ስለማስቀመጥ፡- ትዳር የሚበተነው በፍቅር እጦትና ባለመተማመን ብቻ አይደለም፡፡ መታመም አለ፤ ልጅ መውለድም ይኖራል፡፡ ልጆች የሚያድጉበት ገንዘብ ከወዲሁ

ካላመቻቹ በቀር ‹‹በእድሉ ይደግ›› የሚባለው አባባል ከአሁን በኋላ አይሰራም! ከዚህ በተጨማሪም ባልም ሆነ ሚስት አባወራ ሆነዋል ማለት ‹‹ባለህበት ሂድ›› ይራመዳሉ ማለት አይደለም፡፡ ሁለቱም ንግዳቸውንም ወይም የትምህርት ደረጃቸውን ማሻሻል ይፈልጋሉ፡፡ ለዚህ አላማ ግን የተቀመጠ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋልና ከወዲሁ መወሰን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለምሳሌ፤ ልጆቻቸው እስኪያድጉ ድረስ ሁለቱም ለተጨማሪ ትምህርት ገንዘብ ላለማውጣት ሊወስኑ ይችላሉ፡፡ ለጥቂት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በአንድ አጋጣሚ ጋብቻቸው ቢፈርስ ግን

ሁሉንም ነገር እንደአዲስ ለመጀመር ይገደዳሉ፡፡ አንዳንድ ባለትዳሮች ግን ገና ከመጀመሪያው በየወሩ ገንዘብ ተቀማጭ ለማድረግ ይወስናሉ፡፡ ይህ ባህል በእኛም ሀገር እየተለመደ መጥቷል፡፡ በእርግጥ ትዳራቸው ቢፈርስ የተጠራቀመው ገንዘብ እኩል ይካፈሉታል፡፡ ይህ ሁኔታ ግን ፍትሃዊ የማይሆንበት ጊዜ አለ፡፡ የተጠራቀመውን ገንዘብ በአብዛኛው ያበረከተችው ሚስት በምትሆንበት ወቅት ገንዘቡ እኩል ሲከፈል ትክክለኛውን ደረጃዋን አታገኝም፡፡ ስለዚህም ይህ ችግር እንዳይፈጠር አዲስ ትዳር መስራቾች ከወዲሁ መጠንቀቅ

አለባቸው፡፡ ሁለት አማራጭ ይኖራቸዋል፣ አንደኛው፣ በየወሩ ስንት ስንት እንደሚያስቀምጡ አስቀድሞ መስማማት ነው፡፡ ሁለተኛውና የተሻለው አማራጭ ግን ገንዘባቸውን ለየብቻ ማስቀመጥ ሲሆን በፍቺ ወቅት ሊፈጠር የሚችለውን መምታታት ያስቀራል፡፡

4 . ማን ይወስን? ባል ሆነ ሚስት የየራሳቸው የሆነ የገቢ ምንጭ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሚስተዋለው ግን በሁለቱም ገንዘብ ባለ በብቸኝነት ሲያዝበት ነው፡፡ በተለይም ትዳራቸው ከረምረም ሲል የባል ገንዘብ

ለብቻው፣ የሚስት ግን የጋራ እየሆነ ይመጣና ሴቷ በቀንበር ስር ትወድቃለች፡፡ ሚስት የቤት እቃ ይገዛ ስትል ባል ይህን ሐሳብ በመቃወም ገንዘብ ወደ ኪሱ የመጨመርና በተለያዩ መዋያዎች የመበተኑን ተግባር ሊያጧጡፈው ይችላል፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን ገና ከመጀመሪያው ጓደኞቹ ለቤት ወጪ እያንዳንዳቸው ምን ምን ያህል እንደሚያዋጡ ሊስማሙ ይገባል፡፡ በዚህ ሁኔታ የተዋጣው ገንዘብም በየትኞቹ ነገሮች ላይ መዋል እንዳለበት በጋራ ሊስማሙ ይገባል፡፡ ለየት ያለ ስምምነት ላይም መድረስ ይችላሉ፤ ለምሳሌ፣ የወር አስቤዛ ወጪዎች የሚወሰኑት በሚስት ብቻ ይሆናል ብለው መስማማት መብታቸው ነው፡፡

5 . ትዳር የጋራ ነው ውሳኔም የጋራ ነው፡- ታላቁ የሚስቶች ጭቆና የሚፈጠረው የቤተሰባቸው የገቢ ምንጭ አባወራው ብቻ በሚሆንበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ባልን ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ አድርጎ ሚስትን

ለ‹‹ወጭት ጥዶ አልቃሽነት›› ይዳርጋልና ይህ ችግር እንዳይፈጠር አዲስ ተጋቢዎች አስቀድመው ሊወያዩበት ይገባል፡፡ ቢቻል ውል ቢፈርሙ ይመረጣል፡፡ ለምሳሌም ‹‹ባል በወር ገቢው መቶ በመቶ በብቸኝነት የመወሰን መብት የለውም፤ በገቢው የሚገዙ ነገሮች በባልና ሚስቱ የጋራ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ብቻ ይሆናሉ›› የሚል ውል ከጊዜ በኋላ የሚመጣ የባሎች አጉል አመል በቀላሉ ሊቀረፍ ይችላል፡፡

- Engine

- Brakes

- Suspension

- Transmission

- Electrical

- Body

- Interior

More...

የመኪናዎን ዘይት ለማስቀየር ብዙ መቆም አያስፈልግዎትም፤ በቂ የሰው ኃይል ስላለን

ወዲያውኑ ቀይረን ውድ ጊዜዎን

እንቆጥብልዎታለን

የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውና

ጉልበቱ በ20$ ብቻ።

ይህ እድል አያምልጥዎ

- እነሆ ወሳኝና ጠቃሚ የባለሙያ ምክሮች

ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ያለው ስቃይ በተፈጥሮ ህግ

መሰረት ወዲያው የሚናጋ ባይሆን ኖሮ ዛሬ ላይ የመገኘታችን ሁኔታ አጠያያቂ ይሆን ነበር፡፡ ለዚህም ይመስላል ‹‹ምጡን እርሺው፤ ልጁን አንሺው›› የሚለው ሀገርኛ ብሂል የመነገሩ ምክንያት፡፡ እናትነት የርህራሄና የጥሩነት መገለጫ ተምሳሌት ነው፡፡ ይህ የመሆኑ ምስጢር እናትነት በመልካም ስሜቶች ድርና ማግ ብቻ የተሰራ በመሆኑ ሳይሆን ተፈጥሮአዊ በመሆኑ ጭምር ነው፡፡

ሁሉም እርግዝና በራሱ የተወሰነ አደጋ አለው፡፡ በተለይም እርግዝናው የመጀመሪያ ከሆነ ዘርፈ ብዙ የጤና መታወክ ብሎም የወሊድ አደጋ ይኖረዋል፡፡ በአጠቃላይ ነፍሰጡር ከሆኑ እናቶች 15 ከመቶ የሚሆኑት እርግዝና ህይወትን ለአደጋ የሚጥልና የባለሙያ የህክምና እርዳታ የሚሻ ነው፡፡

ከእነዚህ ውስጥ በወሊድ ወቅት ለእናቶች ሞት ምክንያት የሆኑና እርግዝናን በአሳዛኝ ሁኔታ እንዲደመደም የሚያደርጉ ህመሞች፣ ያለ ጊዜው የሚመጣ ምጥ፣ የእርግዝና ጊዜ የደም ግፊት፣ የእርግዝና ወቅት ስኳር በሽታ፣ የእንግዴ ልጅ ከማህፀን

ግድግዳ መላቀቅ (Placental abruption) ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ያለ ጊዜው የሚመጣ ምጥ (Premature labour):-

ማንኛውም ነፍሰጡር እናት ያለ ጊዜው ምጥ ሊይዛት ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ በማህፀን ህመም የሚሰቃዩ፤ የእንግዴ ልጅ አፈጣጠር መዛባት እንዲሁም ቀደም ሲል በነበረው እርግዝናቸው ያለ ጊዜው ልጅ ወልደው የሚያውቁ ሴቶች ለችግር ይበልጥ የተጋለጡ ናቸው፡፡

ፅንስ ሙሉ ተፈጥሯዊ እድገቱን አጠናቅቆ ወደዚህች ዓለም የሚመጣው ከአርባ ሳምንታት የማህፀን ውስጥ ቆይታ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን አልፎ አልፎ ምጡ አይሎ ፅንሱ የሚወለድበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ ያለ ጊዜው የተፈጠረ ምጥ የሚባለው ከ37ኛው ሳምንት ጀምሮ ሲያጋጥም ነው፡፡ ዘጠኝ ወር ከመሙላቱ በፊት የሚወለድ ህፃን በመጠኑም ቢሆን የፅንሱን የእድገት ደረጃ ባለማጠናቀቁ በሆስፒታል የቅርብ ክትትል ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሰውነቱ የሚገኘው የቢሊሩቢን (Bilirubin) ንጥረ ነገር ሙሉ በሙሉ ስለማይወገድ የፍሎረሰንት ወይም በተለምዶ ሙቀት ቤት መግባት ያሻዋል፡፡ አሁን የህክምና ሳይንስ በደረሰበት የእድገት ደረጃ ያለወቅቱ የመጣን ምጥ ማዘግየት የሚያስችል የህክምና ዘዴ አለ፡፡

በእርግዝና ወራት በቂ ውሃ አለመጠጣት ያለ ወቅቱ የመውለድ ሁኔታዎችን ይበልጥ ሊያባብስ እንደሚችል የቅርብ

ጊዜ ጥናቶች ይገልፃሉ፡፡ ስለሆነም በቂ ውሃ መጠጣት ጠቃሚ ነው፡፡ ከወሊድ ጊዜ አስቀድሞ የሚመጣ የምጥ ህመም (Premature labour) በእርግዝና ወራት አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ህመሞች አንዱ ነው፡፡ ከሰላሳ ሰባተኛው የእርግዝና ሳምንት በኋላ የህመም ስሜቶቹ ሲታዩ በጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ያለ ጊዜው የሚመጣ ምጥ የህመም ምልክቶች የሚባሉት፡-

- ሄድ መጣ የሚል የሆድ መጨምደድ - በወር አበባ መምጫ አካባቢ የሚሰማ አይነት ህመም

ሆድን ጭብጥ አድርጎ መያዝ - ከእንብርት በታች ወደ ታች የመውጋት ስሜት - መጠኑ የበዛ የጀርባ ህመም - መጠነኛ የደም መፍሰስ - የሆድ ውጋት፤ ማቅለሽለሽ - ብዛት ያለው ውሃ መሰል ወይም ወፍራም ፈሳሽ መውረድ

ያለ ጊዜው የመጣ ምጥ ምልክት በመሆኑ በአፋጣኝ የባለሙያ እርዳታ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ከላይ የተጠቀሱት የህምም ስሜቶች በትክክለኛው ወቅት የታዩ እንደሆነ የችግሩ አመላካች በመሆናቸው ህክምናዊ ክትትል በማድረግ ለቀጣዩ ምዕራፍ መዘጋጀት ነው፡፡

የእርግዝና ወቅት ደም ግፊትና የስኳር በሽታ፡- በእርግዝና ወራት የሚፈጠር የሆርሞን መዛባት የተነሳ

በሰላሙ ጊዜ ምንም አይነት የስኳር በሽታ ወይም ደም ግፊት የሌለባቸው ሴቶች በሚያረግዙበት ወቅት በሽታዎቹ መታየት ይጀምራሉ፡፡ ወደ ፊት የጤና ችግሮቹ በቋሚነት ሊታዩ እንደሚችሉ ወይም ከእርግዝና በኋላም ሊጠፉ እንደሚችሉ ጠቋሚ ስለሆነ የህክምና ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡

የእርግዝና ወራት የጤና ችግሮች የምንላቸው በአይነት የበዙ ናቸው፡፡ እርግዝናው በራሱ የሚያስከትለው ያልተለመዱ ሁኔታዎች ዘርፈ ብዙ በመሆናቸውም ነው፡፡ የነፍሰ ጡር እናቶች ሆርሞናዊ ለውጦች የሚፈጥሩት የጤና መቃወስ አካላዊ ብቻ አይደሉም- ስነ-ልቦናዊ ጭምር ናቸው፡፡ የምናነሳቸው ስነ ልቦናዊ ችግሮች በአዘቦት ቀናቶችም ያሉ ናቸው፡፡ ለአጭር ሰዓት ቢበዛ ለአንድ ሁለት ቀን የሚቆይ ድብርት፣ ጭንቀት በነገሮች ያለመርካት ስሜት በማንኛውም ሰው ላይ የሚያጋጥም የስሜት ለውጥ ነው፡፡ ነገር ግን በነፍሰጡር እናቶች ላይ የሚታየው የጥሩ ስሜትና ምቾት መጥፋት (ድብርት) እርግዝናው ምን ይዞ እንደሚመጣ በማሰብ ስለሚወለደው ህፃን ደህንነትና ፆታ በማብሰልሰል፣ ከማህበራዊ እንቅስቃሴ በመገደባቸው በመሳሰሉት የሚፈጠርም ችግር ነው፡፡ ከእርግዝና ጋር ተያይዘው ከሚያጋጥሙ ጭንቀት፣ ውጥ ረት፣ ድብርት፣ ደስተኛ አለመሆንና የመሳሰሉት ስነ-ልቦናዊ ችግ ሮች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ድብርት (Depression) በደ ንብ ጎልቶ የሚታይ እንከን ነው፡፡ (እርግዝና.. ወደ ገጽ 6 የዞረ )

ሴት... ከገጽ 2 የዞረ

የምትባለዋን “ቺክ” ለመጥበስ ፈለገና “ቦዲ” ገዛ፤ ይሁንና ቦዲዋ በድራፍት “የቦረጨች” ቦርጩን ስላሳበቀችበት “አብዲ መስሎ ዋለ ያበጠ ባልዲ” ብለው ቅኔ ተቀኝተውለታል የዲዲ አባት ጋሽ መሐዲ፡፡ ምነው ጋሼ መሐዲ መች ታይቶ ይታወቃል ያበጠ ባልዲ? አላችኋቸው?. . .

በሙከራው መከራውን እንዳየ የተረዱት ሐኪም ጢማም ግን ፣ በየሰከንዱ ሶስት ሶስት ጠርሙስ ድፍርስ ውኃ ቢጠጣ ያበጠ ሆዱ ሽው እንደሚል መክረውታል፡፡

ጀለሶቼ በሌላ ወግ እመጣለሁ፣ ነጋቲ፡፡© ዳዊት ወርቁ

ላስቬጋስ... ከገጽ 3 የዞረ

ሰዎች መፈክሩን ለቬጋሶች መመለስ አለባቸው። ዋነኛ ገቢዋ በቁማር እና በመዝናኛ ላይ የተመሠረተው

ቬጋስ እንግዶቿ ከመላው ዓለም ይጎርፋሉ። ቀን ከሌት የለ። የአዘቦት ቀን የለ፣ ሰንበት የለ። ሁሌም ብልጭ ድርግም የሚለው መብራቷ ፋታ የለውም። መቸም የመብራት ብዛት እንደ ቬጋስ አላየሁም። በመጀመሪያው ጉዞዬ ቀን ነው የገባኹት ብያችኋለሁ። በአሁነኛው ደግሞ እኩለ ሌሊት ላይ ነበር አውሮፕላናችን ያረፈው። ከተማይቱን ወደ ታች ሲመለከቷት በመብራት ትነድዳለች። “ክሪስማስ ነው የማስመስለው” ያለው የክበበው ገዳ ቀልድ ትዝ ይሏችኋል? ግማሽ ኪሎ ሥጋ ይዞ የሚፎክራት የሰካራም ፉከራው? ይልቅ “ክሪስማስ” የምትመስለው ቬጋስ ናት፤ በማታ ከአውሮፕላን ላይ ቁልቁል ስትታይ። መኪናው ውር ውር ሲል ቁልጭ ብሎ ይታያል።

“እንዴት ነው ያገራችን ሰው በቬጋስ?” ብዬ መጠየቄ አልቀረም። “ድሮ ጥሩ ነበር። የአገሬውም ሰው፣ ፖሊሱም በደህና ነበር የሚያዩን። አሁን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ስማችን እየተበላሸ ነው” አለኝ ታክሲ የሚነዳው አንዱ። “ምነው?” አልኩት። “ባክህ፣ አሁን አሁን የመጡ ልጆች መኪናውን እንዴት እንደሚነዱ ብታይ ይዘገንንሃል። ፖሊሶቹ ራሳቸው ‘የኔ ወንድም፣ ይህ አዲስ አበባ አይደለም’ ማለት ጀምረዋል። ኢትዮጵያዊ ከሆንክ እና ፖሊስ ካስቆመህ አይምርህም። በቃ ስማችንን እያበላሹት ነው። ብትነግራቸው ደግሞ አይሰሙህም። ባለጌ ስድብ ሊሰድቡህ ይችላሉ።” ቀጠለ ወዳጄ።

“እንዲያውም አንድ ገጠመኜን ልንገርህ። አንድ ቀን እንግዳ የምናገኝበት ቦታ ስሔድ ከፊቴ የቀደመ አንድ ታክሲ አይቼ አሳለፍኩት። እኔ ከኋላው ሄጄ ወረፋዬን ያዝኩ። ከዚያ ቅድሚያ የሰጠኹት ባለ ታክሲ፣ ፈረንጅ ነው፣ ከመኪናው ወርዶ መጣና ‘አንተም ከኢትዮጵያ ነህ?’ አለኝ። ‘አዎ’ ስለው ‘እንዴ እንደዚህ ጨዋ ሰዎችም አሉበት እንዴ?’ ሲል መለሰልኝ። ተናደድኩ። እዚህ ከተማ ታክሲ መንዳት ከጀመርኩ 10 ዓመት ሊሞላኝ እንደሆነ ገልጬ እኛ ኢትዮጵያውያን ጨዋና ሰው አክባሪዎች መሆናችንን ለማስረዳት ሞከርኩ። ሰውየው ያየው ለካስ የዚያ ተቃራኒ ነበር። ጫት እየቃሙ የሚነዱ አበሾች ብዙ ናቸው። ጫት እንደ አደንዛዥ ዕጽ ነው የሚታየው በቬጋስ ሕግ። ያስቀጣል። መቼ ፈርተው” አስረዳኝ - በረዥሙ።

በዓይነ ኅሊናዬ የአዲስ አበባ ታክሲዎች ትዝ አሉኝ። ብዙዎቻችን ጎበዝ መኪና ሾፌር የሚመስለን እንዲያ ነፍስ እና ሥጋ በድንጋጤ የሚለያየው ነጂ ሊሆን ይችላል። ከፊታቸው ያለውን ታክሲ ቀድመው ቦታ ለመያዝ መሽቀዳደም የሥራው አንዱ አካል ነው - በአዲስ አበባ። እዚህ ግን “ያልሰለጠነ ሰው ጠባይ” እንጂ የጉብዝና ምልክት አይደለም።

ያ ወዳጄ አንድ ሌላ ገጠመኝ ጨምሮ አጫወተኝ። ታክሲ ሥራ ላይ የማውቀው አንድ ፈረንጅ ነገረኝ ብሎ የነገረኝ ነው። ሰውየው ወደ ቬጋስ ከመምጣቱ በፊት በነበረበት ከተማ ውስጥ ይሠራበት በነበረበት ቦታ ኢትዮጵያውያንም ነበሩ። አንድ ቀን ሁነኛ ዕቃ ይጠፋና ለፖሊስ ይደወላል። ከዚያ ፖሊስ የካምፓኒውን በር በሙሉ ዘግቶ ሠራተኛው ከመውጣቱ በፊት

ቁጥጥር ለማድረግ ሲጀምር አንዱን ኢትዮጵያዊ መካከላቸው ያየዋል። “ከኢትዮጵያ ነህ?” ብሎ ከጠየቀው በኋላ “አንተ መውጣት ትችላለህ” ብሎ በመጀመሪያ አሰናበተው። “ኢትዮጵያውያን አይሰርቁም” የሚል ንግግርም እንደጨመረበት ፈረንጁ ለዚያ ለወዳጄ አጫውቶታል።

እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ የኢትዮጵያውያኑን ልብ በኩራት የሚሞላ ነው። ያ ወዳጄ “አሁን የመጡት ልጆች” የሚላቸው ታክሲ ነጂ ኢትዮጵያውያን “ይህንን ስም አናግተውታል” ባይ ነው። በዚያ አነዳዳቸው የሚያደርሱትም አደጋ ዘግናኝ እንደሆነ አጫውቶኛል። ማንኛውም የአዲስ አበባን የመኪና አደጋ ብዛት

የሚያስታውስ ሰው ይህ ወዳጄ ያለው ትክክል ሊሆን እንደሚችል ይገምታል።

የቬጋስ ወዳጆቼ ከተማውን እና የቱሪስት መስሕቦቿን ካስጎበኙኝ በኋላ ሳላየው መሔድ የሌለብኝ ሁለት ወሳኝ ቦታ እንዳለ ነገሩኝ። አንደኛው ከከተማዋ ለሁለት ሰዓታት በመኪና ተጉዘው ጭው ባለው በረሃ መካከል የሚገኘው የግብጾች ገዳም እንዲሁም ከቬጋስ 28 ማይል አካባቢ ስለሚርቀው ታዋቂው የ“ሑቨር ግድብ”።

ሲዖልም መንግሥተ ሰማያትም በአንድ ያሉበት ቦታ ላስ ቬጋስ ሳይሆን አይቀርም። ከነስሟ “የኃጢአት ከተማ”

እንደምትባል፣ “ወደ ኃጢአት ከተማ እንኳን ደህና መጡ” የሚል ጽሑፍ ማየት የተለመደ መሆኑን ላስታውሳችሁ። ወደ ቬጋስ የሚመጣ አብዛኛው ጎብኚ አቅሉን ለመሳት፣ የዕብደት ጫፍ ረግጦ፣ በኑሮ ድካም የናወዘ አዕምሮውን በዕብደት ምጥቀት ለማስከን ሽቶ ነው ይባላል። መዝናናትና ስክነት ከዕብደት ጫፍ ደርሶ በመመለስ ይገኝ እንደሆነ እነርሱ ያውቃሉ።

ሲዖሉ በስካሩ፣ በሴተኛ አዳሪው ጋጋታ እና በዚያ ትርምስ የሚታየውን ማለቴ ነው። በርግጥ ለቱሪስቱ ሲዖል ብሎ የሚነግረው የለም። ራሱም አስቀድሞ “ገነት” ብሎ ስለጠራው በዚያው ነው የሚረዳው። መሐል ከተማ የቁማሩን ታላላቅ ሕንጻዎች፣ ብልጭልጭ መንደሮች ለመጎብኘት ስንጓዝ ጎረምሶች በዕኩለ ቀን ስክር ብለው በግሩፕ እየተሳሳቁ ያልፋሉ። ካናቴራዎቻቸው ተከፋፍተዋል። በእጃቸው አልኮል ይዘዋል። በሌላ የአሜሪካ ከተማ ቢሆን የተከፈተ አልኮል ይዞ መሔድ በፖሊስ ያስቀፈድዳል። በቬጋስ ይሄ የተፈቀደ ነው።

ከመኪና ወርደን በእግራችን መጎብኘት ስንጀምር የማስታወቂያው ዓይነት ዓይን ያጥበረብራል። አብዛኛው ከተለያየ “ሾው” እና ሴተኛ አዳሪዎች ጋር የተገናኘ ነው። በደረቁ “ሴተኛ አዳሪ” አልኩት እንጂ ማስታወቂያዎቹስ አስውበው ነው ያቀረቡት። በእግራችን እየተዘዋወርን ጎበኘን። በሺህዎች የሚቆጠሩ ክፍሎች ያሏቸው ሆቴሎች አሸብርቀዋል። ደግሞ ጽዳታቸው። አስፓልቱ ሳይቀር በየቀኑ የሚታጠብባት ከተማ። ውጪ አገር፣ ፈረንጅ አገር የሚለውንና ድሮ በአዕምሮዬ የሳልኩትን አሜሪካ ያየኹት ቬጋስ ነው።

መንገዶቹ ሰፋፊዎች ናቸው። የመንደር ውስጥ መንገድ የሚባለው ባለ ሦስት ረድፍ መሔጃ፣ ሦስት ረድፍ መምጫ ሆኖ ሰፋፊ ጎዳና ነው። የላስ ቬጋስን የመንደር ውስጥ መንገድ እንግሊዝ አገር ብትወስዱት “ትልቅ የቀለበት መንገድ” የሚሆን ይመስለኛል። ጠባብ መንገድ ምሳሌ ሲባል የምትመጣብኝ ለንደን ናት። ሰዉ ሁሉ ከመኪና ከወረደ አልጋው ጫፍ ላይ የሚደርስባት፣ መሬት ውድ የሆነባት ከተማ። ቬጋስና ቴክሳስ የዚያ ተቃራኒ ናቸው።

ቬጋስ ውስጥ ለመዘዋወር ዋነኛው የትራንስፖርት መንገድ እግር መሆን አለበት። መኪና ከአንድ ሩቅ ቦታ ወደ ሌላ ሩቅ ቦታ ለመሔድ ካልሆነ በስተቀር ተመራጭ አይደለም። በተለይም “ሾው” ወዳለባቸው ሥፍራዎች ስንሔድ እግራችን ሊሰበር ምንም አልቀረውም። ከድካሙ የተነሣ። ወገባችን ሁሉ ተንቀጠቀጠ። ውኃው ሲጫወት፣ እሳተ ገሞራው ሲፈነዳ፣ የባሕር ላይ ዘራፊዎች ሲዋጉ የሚያሳዩ ድንቅ ድንቅ የውጪ ቲያትሮች ይታያሉ። ታዲያ ሰዓት ሰዓት አላቸው። አዘጋጆቹ ሆቴሎቹ ናቸው። በተለያዩ ሰዓቶች የሚካሄዱት ዝግጅቶች እንዳያመልጡን አስተናጋጅ ወዳጆቻችን እየመሩን መሮጥ ነው።

አንድ ቦታ ስንገባ ደግሞ የዓለም ታላላቅ ከተሞች በሙሉ ከነምናምናቸው መጥተው ቁጭ ብለዋል። ሮም በለው ፓሪስ በለው እንዲያው ከነመልክ አካላቸው እዚያ ያሉ ይመስላሉ። ግን ቤት ውስጥ ነው። ቀና ስንል ሰማዩ በከዋክብት አጊጦ ይታያል። ግን የእጅ ሥራ ነው። በጀልባ ብቻ የሚኬድባት የጣሊያኗ የፍቅር ከተማ ቬኒስ ቁጭ ብላለች። ጥንድ ጥንድ ሆነው በጀልባ የሚጓዙ ሰዎችም ይታያሉ። ትንሽ አለፍ ስንል ተራራ የሚመሳስሉ ቋጥኞች ተቆልለዋል። ነገር ግን ድንጋይ አይደሉም። የሰው ልጅ የእጅ ጥበብ ድን……ቅ ይላል።

በበነጋው ጠዋት ከዚህ “ከሲዖሉ” ወጣ ብለን ሌላኛውን ገጽ ለማየት ከቬጋስ እንብርት ሁለት ሰዓት ወደሚርቀው ጭውውው ያለ በረሃ መንዳት ጀመርን። ወደ ግብጽ ኦርቶዶክሶች ገዳም። በቅ/እንጦንስ ስም የተሰየመ ነው። ኔቫዳ በረሃ ላይ ገዳም፤ ያውም ከአፍሪካ የመጡ ሕዝቦች ገዳም። የማይታሰብ ነው። ምናልባት ግብጾች ለበረሃ ለበረሃ ሰሐራን ስላዩ ይሆናል። “ለውኃ ለውኃ ምናለኝ ቀኃ” አለ የጎንደር ሰው።

የአባ እንጦንስ ገዳም ከላስ ቬጋስም ከሎስ አንጀለስም እኩል ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። ከካሊፎርኒያ ለሚመጣውም፣ ከወዲህ ከቬጋስ ለሚሄደውም የሚመች መንገድ ነው። አስጎብኚያችን (ላስ ቬጋስ... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

Center for Multi- Services! Meet your Friendly & Experienced professionals!

Tax(all-year-round), Insurance, Mortgage Referrals, Residential &

Investment Real Estate Sales, Buying and Selling of Businesses,

Translation, Immigration Form, Resume, Notary Public etc.

BUDGET INSURANCE (A member of Wiser Insurance Group)

More Insurance Companies, More Price Choices!

[Auto. Home. Life. Health. Business. Commercial

(Various)]

Tel: 651 649 0644 / 651 209 6077 Fax: 651 649 0620 Bisrat (Bis) Alemayehu: [email protected]

Ephrem Negusse [email protected]

Asfaw B. Silga [email protected]

BISRAT ALEMAYEHU BISRAT ALEMAYEHU BISRAT ALEMAYEHU

& & &

ASSOCIATESASSOCIATESASSOCIATES

እርግዝና... ከገጽ 5 የዞረ

እርግዝና እና የድብርት ስሜት (Depression)

በእርግዝና ወራት የድብርት ስሜት በነፍሰጡር እናቶች ላይ ይበረታል ሲባል ምን አልባት ለአብዛኞቻችን ከብዶን ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሀሳቡ ሳይንሳዊ እውነታ ያለው ነው፡፡ ድብርት (Depression) የስሜት (mood) መዛባት ችግር ነው፡፡ በተለምዶ ዛሬ ደብሮኛል ስንል በዚያች ሰዓት የተሰማንን ደስ አለመሰኘት ስሜት ይሆናል፡፡ ትክክለኛው የድብርት መጫጫን ስሜት (Clinical Depression) ግን የሀዘን፣ የመናደድ፣ ተስፋ የመቁረጥ በአንድነት ተደምረው ከሁለት ሳምንት በላይ ሲቆዩ ነው፡፡ የመጫጫን ስሜቱ በረዘመ ቁጥር ማህበራዊ ግንኙነት ያበላሻል፡፡ በተለይም በእርግዝና ወራታቸው ወይም ከወሊድ በኋላ በብቸኝነት ለሚያሳልፉ ሴቶች ስሜቱ እጅግ ከባድ ነው፡፡ በሀገራችን ማህበራዊ ህይወት እጅግ የጠነከረ በመሆኑ እንጂ ይህ ሁኔታ ባልተለመደበት የምዕራቡ ዓለም ብዙዎች ራስን በራስ የማጥፋት ሙከራ እስከማድረግ ይደርሳሉ፡፡ የእርግዝናና የወሊድ ጊዜያት የቅርብ የቤተሰብ እንክብካቤና ፍቅር መለገሰን ይጠይቃል፡፡

እርግዝና ለብዙ ሴቶች እጅግ አስደሳች የህይወት ዘመን ገጠመኛቸው እንደሆነ ይታመናል፡፡ ቢሆንም ይህ ሁኔታ ሁሌም እውነት አይሆንም፡፡ እርግዝና ለአንዳንድ ሴቶች የፍርሃት፣ የጭንቀት፣ የሀዘንና ግራ የመጋባት እንዲሁም የድብርት ጊዜ ይሆንባቸዋል፡፡ ከ10-20 በመቶ የሚሆኑ ነፍሰጡር እናቶች በጤነኛ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው የእርግዝና ወራታቸውን ያሳልፋሉ፡፡ ከእነዚህ ግማሽ ያህሉ ከባድ የሚባል የድብርት መጫጫን (Clinical Depression) ውስጥ ያልፋሉ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ የጥናት ውጤት እንዳስገነዘበው ድብርት ከአራት ነፍሰጡር እናቶች ቢያንስ በአንዷ ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ችግሩ በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የሆርሞን መዛባት ምክንያት ከሚፈጠሩ ሌሎች የባህሪ ለውጦች ጋር የሚምታታ በመሆኑ እምብዛም ትኩረት እንዳልተሰጠው ጥናቱ ጨምሮ ይገልፃል፡፡ የሆርሞን መዛባት ብቻ ለስነ ልቦናዊ ችግሩ መፈጠር ዋስትና አይሆንም፡፡ ድብርትና ሌሎች የመንፈስ መረበሽ ሁኔታዎች ያረገዘችው ሴት አስቀድማ በምትመራው አስቸጋሪ ህይወት ይበልጥ የሚባባስም ነው፡፡

የእርግዝና ወራት የድብርት ስሜት ምልክቶች

- ለነገሮች ትኩረት አለመስጠት፣ የማስታወስ ችሎታ መቀነስ፣ መወሰን አለመቻል

- እንቅልፍ መተኛት አለመቻል - ራስን ከሌሎች የማግለል ፍላጎት ማሳየት - በትንሽ በትልቁ ማልቀስና መነጫነጭ - መጨነቅ - ራስን ዋጋ ቢስ አድርጎ መቁጠር፣ የጥፋተኝነት ስሜት

መሰማት - የምግብ ፍላጎት መቀነስ ናቸው፡፡ እነዚህ የመንፈስ ስሜት መረበሽ ሲያጋጥም በተቻለ መጠን

ከሰዎች ጋር ለመወያየት መሞከር ወይም የባለሙያ ምክር ማግኘት ጠቃሚ ነው፡፡

በአጠቃላይ ከእርግዝና ጋር ተያይዞ የሚፈጠር የመንፈስ መናጋት (ድብርት) በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ አንደኛው የቅድመ ወሊድ ድብርት ስሜት ሲሆን ሌላኛው የድህረ ወሊድ ድብርት ስሜት ናቸው፡፡

የቅድመ ወሊድ ድብርት

መንስኤዎች የቅድመ ወሊድ የእርግዝና ወቅት የድብርት ስሜት

መንስኤዎች በአብዛኛው ከኑሮ ውጣ ውረድ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡ በዋናነት ግን፡-

- ከትዳር ተጓዳኝ ጋር የሚፈጠር አለመግባባት - የግለሰቧ ጭንቀታም ባህሪ - ለመፀነስ ከተዳረጉ የህክምና ጥረቶች ውስብስብነት የተነሳ - ቀደም ሲል ሽል ጨንግፎ የሚያውቅ እንደሆነ በመፍራት - የተጨናነቀ አኗኗር - በቀደመ ጊዜ አስቸጋሪ የምጥ ሁኔታን ማሳለፍ ናቸው፡፡ ሌላው የቅድመ ወሊድ የድብርት ስሜት መንስኤዎች ውስጥ

መጠቃለል የሚገባቸው ሁለት ተጨማሪ መንስኤዎች ከቤተሰብ የተወረሰ የስነ አዕምሮ በሽታ እና ያልተፈለገ እርግዝና ናቸው፡፡

የድህረ ወሊድ ድብርት መንስኤዎች፡- ከወሊድ በኋላ የሚኖር የድብርት ስሜት (Restpartum

depression) በመባል ይታወቃል፡፡ ድህረ ወሊድ ድብርት በልዩ ልዩ ምክንያቶች እንደሚከሰት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የሚጠቀሰው በእርግዝና ወራት በከፍተኛ መጠን የሚገኙት የኦስትሮጅን (estrogen) እና የፕሮጅስትሮን (progesterone) ሆርሞን ከወሊድ በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቸውን መቀነስ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው የታይሮይድ (thyroid) ሆርሞን መጠን አነስተኛ መሆን ናቸው፡፡ የታይሮይድ ሆርሞን መጠን ማነስ፣ የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ የድካምና የድብርት መጫጫንን ያስከትላል፡፡ የድህረ ወሊድ ድብርት መንስኤዎች ሆርሞናዊ ለውጦች ብቻ ሳይሆኑ ውጫዊ ግፊቶች ጭምር ናቸው፡፡ ከወሊድ በኋላ የመንፈስ መረበሽ ሌሎች መንስኤዎች

- ከወሊድ በኋላ የአካል መድከም፣ የሰውነት ቅርፅ መበላሸት ያጋጥመኛል ብሎ መስጋት

- ከመደበኛ ስራ እርቆ በጓዳ ስራ ብቻ እንደታሰሩ ማሰብ - ሌላ የእነርሱን እንክብካቤ የሚፈልግ ህፃን

እንደተጨመረባቸው በማሰብ መጨነቅ፣ ይህንንም ለመወጣት አብዝቶ ማሰብ

- ጤናማ ያልሆነ ፅንስ መገላገል፣ የፅንስ በወሊድ ላይ መጥፋት (በህይወት ማለፍ)

- ረጅም ጊዜአቸውን ከፍቅር ጓደኛ ጋር ወይም ከጎረቤት ጋር ከማሳለፍ ይልቅ በልጅ እንክብካቤ በማሳለፋቸው የሚፈጠር ጥሩ ያልሆነ የበታችነት ስሜት ናቸው፡፡

የእርግዝና ወራት የድብርት ስሜትና ጉዳቱ

በወቅቱ ህክምና ካልተደረገ የመንፈስ መረበሹ በፅንሱም ሆነ በእናትየው ጤንነት ላይ ችግር ያስከትላል፡፡ በድብርት ለምትኳትን እናት ብቸኝነቱን መርሻ አልኮልና ሌሎች አደንዛዥ እፆች ይሆናሉ፡፡ የምግብ ፍላጎት ዝቅተኛ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ፅንሱ ሲወለድ አነስተኛ ክብደት እንዲኖረው እና ያለ ወራቱ እንዲወለድ ምክንያት ይሆናል፡፡

የእርግዝና ወራቶችን አስደሳችና ጤናማ ለማድረግ የሚያግዙ ጠቃሚ ነጥቦች

1. የቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል ማድረግ፡- የቅድመ ወሊድ ምርመራ ለእናትም ሆነ ለህፃኑ ጤንነት

እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ ወቅት በሚደረግ የህክምና ክትትል ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል፣ በሂደት የህፃኑን የማህፀን ውስጥ አቀማመጥ በማጥናት መደረግ ስለሚገባ ጥንቃቄ ራስን ለማወቅ ብሎም ደም ማነስ የደም ግፊት እና የስኳር በሽታ ከተፈጠረ አስቀድሞ እርምት ለመውሰድ ይረዳል፡፡

2. የተመጣጠነ አመጋገብ መከተል፡- ሴቶች ነፍሰጡር ስለሆኑ ብቻ ብዙ መመገብ የለባቸውም፡፡

ከዚህ ይልቅ ብዙ ሴቶች ቅሪት በሚሆኑበት ጊዜ ለመመገብ የማይፈልጓቸውን የምግብ አይነቶች በሌላ አይነት ምግብ ለመተካት መሞከር ተገቢ ነው፡፡ በአመጋገብ ዝርዝር ስር አትክልትና ፍራፍሬ መካተቱን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

3. የምግብ ዝግጅትን ንፁህ ማድረግ፡- አንዳንድ የምግብ አይነቶች በእርግዝና ላይ የጤና ችግር

ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ምግቦችን መጠናቸውን መቀነስ አልያም በደንብ ማብሰል አስፈላጊ ነው፡፡ ጥሬ ስጋ፣ ጥሬ አትክልቶችን አይመገቡ፣ ዓሳ የሚመገቡ ከሆነ በመጠኑ ያድርጉት፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ የዓሳ ዝርያዎች ከፍተኛ የሆነ የሜሪኩሪ ንጥረ ነገር ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ይህም ለሰውነት መርዛማ ይሆናል፡፡

4. በቂ ቫይታሚን ቢ (ፎሊክ አሲድ) መውሰድ፡- ፎሊክ አሲድ ወይም በሌላ ስሙ ቫይታሚን ቢ ለፅንሱ

አካላዊ እድገት መፋጠን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት በሰውነት በከፍተኛ መጠን ይፈለጋል፡፡ የቫይታሚን ቢ ማነስ ምናልባትም የነርቭ ችግር፣ ሲወለድም አካል ጉዳተኛ ሆኖ እንዲወለድ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ቫይታሚን ቢ ከዓሳ ዘይቶች፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ ማግኘት ይቻላል፡፡

5. መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- በእርግዝና ወራት ቀላል የሆኑ እንቅስቃሴዎችን

ማድረግ በምጥ ወቅት የሚፈጠርን የጡንቻ ህመም በአጠቃላይ አካላዊ ስቃይን ለመቋቋም ያስችላል፤ ጭንቀትንም ያስወግዳል፡፡ በተጨማሪም ውፍረትን ለማመጣጠን ይረዳል፡፡ ስለዚህ በእርግዝና ወራት ቀላል የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ቀለል ያለ መጠነኛ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግና ዮጋ ስፖርትን መስራት ጥሩ ነው፡፡ ልብ ይበሉ ከፍተኛ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚጠይቁ እንደ ዋና ያሉትን አይሞክሩ፡፡

6. አልኮል አለመጠጣት፡- አልኮል በሰውነት ህዋሳት በቀላሉ የመዋሀድ ፀባይ ስላለው

በቀላሉ ጽንሱ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችላል፡፡ ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ የፅንስ የማስታወስ ችሎታን ዝቅ ያደርጋል፡፡

7. የካፌይን ንጥረ ነገር አወሳሰድን ይቀንሱ፡- ካፌይን በሻይ፣ በቡና እና በአልኮል መጠጥ ውስጥ የሚገኝ

ንጥረ ነገር ነው፡፡ በብዛት ሲወሰድ ፅንስ በሚወለድ ጊዜ አነስተኛ ክብደት እንዲኖረው ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ብዛት ያለው ሻይና ቡና ከመጠጣት መታቀብ ያስፈልጋል፡፡

8. ሲጋራ አለማጨስ፡- የነፍሰ ጡር እናቶች ማጨስ ወይም ሌሎች አደገኛ እፆችንም

መጠቀም የፅንሱን ጤንነት በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል፡፡ ሲጋራ ድንገተኛ ውርጃን፣ ፅንስ በማህፀን ውስጥ እያለ መሞትን (Stillbirth)፣ የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅንና ችግሮችን ሊያስከትልበት ይችላል፡፡

9. በቂ እረፍት ማድረግ፡- በመጀመሪያዎቹና በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራቶች

የድካም ስሜት ይበዛል፡፡ በዚህ ወቅት እንቅልፍ ሊወስዶት ባይችል እንኳን እግርን ዘረጋግቶ ቢያንስ ለሰላሳ ደቂቃ እረፍት ማድረግ መልካም ነው፡፡

10. ከመርዛማ ኬሚካሎች መራቅ፡- የፅንሱንና የእናቶችን ጤንነት ሊጎዱ ከሚችሉ እንደ

ሜሪኩሪ፣ ሊድ፣ የተባይ ማጥፊያ ከመሳሰሉ መርዛማ ኬሚካሎች መራቅ ለእናትየዋም ለፅንሱም ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡

በተጨማሪም ድመትና ውሻ የመሳሰሉት የቤት እንስሳቶች የተለያዩ በሽታዎች ተሸካሚ ስለሚሆኑ አለመነካካት

ይመከራል፡፡ በመካከል በሐኪም የታዘዘ መድኃኒት ካለ ከመጠቀም በፊት እንደፀነሱ መግለፅና መድኃኒቱ በፅንሱ ላይ ሊያደርስ

የሚችለውን ጉዳት መጠየቅና መረዳት ይገባል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች ወደ ተግባር በመለወጥ የእርግዝና ወራቶችን ቀላልና አስደሳች ያድርጉ፡፡

እነዚህ እንክብካቤዎች ቢኖሩም እንኳን እርግዝና በራሱ የሚፈጥራቸው አካላዊና ስነ ልቦናዊ ለውጦች ይኖራሉ፡፡ በቀላሉ ብንነሳ እንኳን በቅሪትነት ወራት የሚፈጠር የሆርሞን መዛባት ነፍሰጡሮችን በቀላሉ ሲያበሳጭና ሲያስለቅስ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተለየ ሁኔታ በተለያዩ የእርግዝና ወራቶች ያልተለመዱ አካላዊ ለውጦች ያጋጥማሉ፡፡ ለውጦቹ ተፈጥሯዊና ጊዜያዊ በመሆናቸው ብዙ መጨነቅ አይገባም፡፡ እርግዝናው የመጀመሪያቸው ለሆኑ ሴቶች እነዚህን ለውጦች ማሳወቅ የሚፈጥርባቸውን ጭንቀት እንደሚያስወግድ ይታመናል፡፡

በቤተሰብ ደረጃ ሊወሰዱ የሚገቡ እርምጃዎች - ለነፍሰጡር እናቶች ከወሊድ በፊትና በኋላ በቂ ድጋፍ

መስጠት - የአባወራ የቅርብ ክትትልና ፍቅር መለገስ - ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ማበረታታት - የቤተሰብ ኃላፊነታቸውን መጋራት ሸክማቸውን ያቀላል፡፡ ጤናማ የእናትነት ጊዜ እመኛለሁ!

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

ከ ሮቤል ሔኖክ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከወጣት ድምፃውያን መካከል አንዱ ነው። በሕብረተሰባችን ውስጥ ገና በመጀመሪያ ስራዎቹ የብዙዎቹን ቀልብና ጆሮ

ስለሳበ ከአይን ያውጣህ ሁሌም እንደተባለ ነው - ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ። ይህ ተወዳጅ ድምጻዊ ወደ ሚኒሶታ በመምጣት የሙዚቃ ዝግጅቱን የፊታችን ጁን 16/12 በብሉሚንግተን ክራውን ፕላዛ ሆቴል ውስጥ ያደርጋል። በሶል ዲዛይን እና ፕሮሞሽን አማካኝነት የተዘጋጀውን የጎሳዬ ተስፋዬን የሙዚቃ ኮንሰርት በማስመልከት ከድምጻዊው ጋር መዲና ጋዜጣ በስልክ አጭር ቆይታ አድርጋ ነበር።

ለድምጻዊው በቅድሚያ ያቀረብንለት ጥያቄ የዛሬ ዓመት አካባቢ እዚህ ሚኒሶታ ይመጣል ተብሎ ፍላየር ሁሉ ተበትኖ ኮንሰርቱ ከመቅረቱ ጋር የተያያዘ ነበር።

“ሁሉ ነገር አልቆ ባለመምጣቴና በጉጉት ይጠብቁኝ የነበሩት አድናቂዎቼን በወቅቱ ከቤተሰብ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ድንገት በገጠመኝ ነገር በመሰረዙ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ቤተሰብ ላይ ችግር አጋጥሞኝ ሥራ ሊሰራልኝ አልቻለም፤ በወቅቱ እንደዚያ ያለ ስሜት ውስጥ ሆኜ ብመጣና ብሰራ አድናቂዎቼን እንደጠበቁኝ ላያገኙኝ ይችሉ እንደነበር ይሰማኝ ነበር። ስለዚህ በቀጥታ ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩኝ። በእግዚአብሔር ፍቃድ ነገር አሁን ተስተካክሏል።” ያለው ጎሳዬ “ጁን 16 /2012 በሚደረገው የሙዚቃ ኮንሰርት አንድም የሚኒሶታ አድናቂዎቼን ለማስደስተና ለመካስም ጭምር ነው” ብሏል።

ከጎሳዬ ምን አዲስ ነገር እንጠብቅ? በሚል ላቀረብለት ጥያቄ “እንግዲህ መደረኩ ላይ እንተያይ፤ ሕዝቡ ይምጣ እዚያ ላይ ይታያል ሁሉ ነገር” የሚለው ጎሳዬ “በቅርቡ ከማህሙድ አህመድ ጋር ነጠላ ዜማ ልትለቁ እንደሆነ ሰምተናል። ምን ያህል እውነት ነው? እውነት ከሆነስ ዘፈኑ በምን ዙሪያ የሚያጠነጥን ይሆን?” ብለን ጠይቀነዋል።

“የሰማችሁት እውነት ነው። ከአንጋፋው ድምጻዊ ማህሙድ አህመድ ጋር አንድ ቆንጆ ሥራ ሠርተን ጨርሰናል። ዘፈኑ በቪድዮም ጭምር በቅርቡ ስለሚለቀቅ አሁን እንዲህ ነው የሠራነው ብዬ ለመናገር ይከብደኛል። እንደ ሰርፕራይዝ ይሁንና ሕዝቡ ይጠብቀው። አድማጩም እንደሚወደው ተስፋ አለኝ”

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አርቲስቶች ጋር በጋራ በመሥራት ይታወቃል። ከሌሎች ድምጻዊያን ጋር እየተቀባበለ የሚሠራቸው ሥራዎችም ሁሌም ተቀባይነት እንዳገኙለት ነው። ለምሳሌ ያህልም ከኤፍሬም ታምሩ ጋር የሠራው “ባላገሩ” ዘፈኑ ይጠቀሳል። አሁንም ከማህሙድ ጋር የሚያቀርቡት ነጠላ ዜማ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል።

“ጎሳዬ... ከአለማየሁ ሄርጶ ጋር “ኢቫንጋዲ” አልበምን ሰርታችሁ ጥምረታችሁ በጣም ተወዶ ነበር። ያ ጥምረት ምን ላይ ደረሰ?” የኛ ጥያቄ ነበር። ጎሳዬም “ከአንድ ወር በፊት ስዊድን እና ኖርዌይ ሥራዎቼን ለሕዝብ ለማድረስ ሄጄ ነበር። ያን ጊዜ አሌክስን እዚያ ሄጄ አግኝቼው ነበር። ኖርዌይ ውስጥ ጥሩ ኑሮ እየኖረ ነው። ብዙ ተጨዋውተናል። ሆኖም ግን እርሱ በአሁኑ ወቅት ሙዚቃ እንዳቆመ ነው የነገረኝ።” ብሎናል።

ልክ እንደ ቴዲ አፍሮ ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ነጠላ ዜማዎቹን ድንገት እየለቀቀ የሚያዝናናን ጎሳዬን ስለ አንዳንድ ሥራዎቹ በተለይም በሃገራችን ስላለው ያላቻ ጋብቻ ስዘፈነው “ለታናሿ ልስጋ” ዘፈንና ባለፈው ዓመት ስለለቀቀው “ያስተፈሰ ልበ ስብ” ስለተሰኘው የሠርግ ዘፈንም ጠይቀነዋል።

“ለታናሿ ልስጋ የተሰኘው ዘፈን ትምህርታዊ ዘፈን ነው። በዚህ ዘፈን ላይ የአማኑኤል ይልማ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር። ሁልጊዜ የፍቅር ዘፈን ብቻ መዘፈን የለበትም። እንደዚህ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይም እየተፈለገ መዘፈን ይኖርበታል ከሚል ስሜት ተነሳስቼ ነው ለታናሿ ልስጋ የተሰኘውን ዘፈኔን የሠራሁት። በሃገራችን እንደምታውቀው ሴት ልጆች እድሜያቸው ለአቅመ ሄዋን ሳይደርስ እየተዳሩ ለበሽታ ይዳረጋሉ። ወደ ትምህርት ቤት ሄደው በመማሪያቸው ጊዜ የልጆች እናት በመሆን ወደ ኋላ ይቀራሉ። ይህን ስሜት ነው ለታናሿ ልስጋ ዘፈን ላይ የሠራሁት። ሕዝቡም በጣም ወዶታል። ሁልጊዜም ደግሞ ስለፍቅር ብቻ እየዘፈንን የትም አንደርሰም ከዚህ መንፈስ በመነሳትም ነው የሠርጉን ዘፈን የዘፈንኩት። ብዙዎቹ የሠርጉን ዘፈን ከመውደዳቸው የተነሳ እየተዳሩበት እንደሆነ እያየሁ ነው። ብዙ ጥንዶች በኔ ዘፈን ሲዳሩ ስመለከትም የሚሰጠኝ ደስታ ልዩ ነው። በአጠቃላይ ግን እነዚህ ሁለት ነጠላ ዘፈኖች ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ይገልጻሉ።”

“በሚኒሶታ ለጁን 16/12ቱ ኮንሰርት ብዙ አድማጮች ያንተን ኮንሰርት በጉጉት እየጠበቁ ነው። በከተማው ላይም እየተወራ ነው። ይህን ኮንሰርት በጉጉት ለሚጠብቁት አድናቂዎችህ ምን ትላቸዋለህ በዚህ አጋጣሚ?”

“በቅድሚያ ሁሌም ለማከብራቸው አድናቂዎቼ እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ለጁን 16ቱ ኮንሰርት በሰፊው ተዘጋጅተናል። ሕዝቡ ተደስቶ የሚሄድበትና የማይረሳ ምሽት እንዲያሳልፍ ነው ምኞቴ። በኮንሰርቱ ላይ እንገናኝ በልልኝ” ብሏል።

ስለጎሳዬ የበለጠ ግንዛቤ ታገኙ ዘንድ በዋሽንግተን ዲሲ ለሚታተመው ባውዛ ጋዜጣ በአንድ ወቅት ሰጥቶት የነበረውን ቃለ ምልልስ እነሆ ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል።

ጥያቄ፡ የዚህ ሃገርና የኢትዮጵያ አድማጮችን

ስታነጻጽራቸው ለየት ያለ ነገር አስተውለሃል? ጎሳዬ፡- አሜሪካ፣ ኢትዮጵያም፣ አውሮፓም፣ ሆነ አረብ ሃገር

ኖርን የኢትዮጵያውያን ደም እስካለን ድረስ አንድን ዘፈን በእኩል ስሜት ነው የምንቀበለው። እዚህ ነው የተወደደው እዛ ነው የቀዘቀዘው የሚል ነገር አልገጠመኝም ። በዚህ ላይ የኔ ስራ የተለያዩ ነገሮችን አካቷል ። ለምሳሌ ያህል ኦሮምኛና አማርኛ የተቀላቀለ ፤ ኦልዲስ የሚመስልና ከክራር ጋር የተቀነባበሩ ስራዎችን ስላካተተ በሁሉም ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።

ጥያቄ- ሃገር ቤት እያለህ ምን ምን አይነት ስራዎችን ትሰራ

ነበር ? ጎሳዬ፡ የሙዚቃ ስራዬን አስመልክቶ የራሴ የሆነ ናይት ክለብ

የለኝም። በሌሎች ቦታዎችም አልሰራም ። በዋናነት ከእጮኛዬ ጋር የግል ድርጅት አለን። እሱን አግዛታለሁ ።

የጎሳዬ የሙዚቃ ህይወት አሁን እስካለህበት ድረስ ከየት

ተነስቶ የት ደረሰ? ጎሳዬ፡- ልክ እንደ አብዛኛዎቻችን ያው ከትምህርት ቤት

ነው የጀመርኩት። በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ

ት/ቤት እንዲሁም በተለያዩ የሙዚቃ ክበቦች ለምሳሌ ያህል

መስታወት የሙዚቃና የቲያትር ክበብ፡ የክስታኔ ባንድና በመሳሰሉት ውስጥ እየሰራሁ በሸዋ ጌጥ ሆቴል

ውስጥ ናይት ክለብ ለአራት ዓመት ያህል ሰርቻለሁ። ከዚህ በኋላ ነው እንግዲህ ቴክ ፋይፍ ፡ኢቫንጋዲና አሁን ሳታማህኝ ብላ የሚሉት ስራዎቼ እየተቀባበሉ

የመጡት ማለት ነው። የመጨረሻውን ስራህን ለመጨረስ ስንት ዓመት ፈጅቶብህ

ነው የወጣው? ጎሳዬ ፡ አራት አመት አካባቢ።

አራት አመት በጣም የቆየህ አይመስልህም ?

ጎሳዬ ፡ እኔና አለማየሁ ሂርጶ(አሌክስ) ኢቫንጋዲን ስንሰራ በጣም ነው ተጠንቅቀንና ለፍተን የሰራነው ።

የአሌክስ አስተዋፆ ቀላል አልነበረም። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከአሌክስ ጋር ተነጋግረን ወደፊት ተገናኝተን በጋራ

አንድ ላይ እስክንሰራ ድረስ ተለያይተን መስራቱ ጥሩ መሆኑን ተስማምተናል። ኢቫንጋዲ ላይ የነበሩትን እነዛን

የአሌክስን ጥሩ ስራዎች ብቻዬን ሸፍኜ ስሰራ ጊዜ ያስፈልገኛል። በጠቅላላው ጉዳዩ ከጊዜው ጋር አይደለም። ትልቅ

ኃላፊነት እስከተጣለብኝ ድረስ ጥሩ ስራ መስራት አለብኝ ለዚህ ነው የቆየበት ምክንያት ከዚህ በተጨማሪም

አሌክስንም አንዳንድ ነገሮች አግዘው ነበር። በመጨረሻው ካሴትህ ውስጥ ምን ምን ለየት ያሉ ነገሮችን

ለማካተት ሞክረሃል? ጎሳዬ፡ እንደሚታወቀው ኢቫንጋዲ ለሳታማኸኝ ብላ ትልቅ

ምንጭ ነው። ሳታማሃኝ ብላ የሚለው በራሱ ሙዚቃውን ከሰጠኝ ልጅ እውነተኛ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው። ስሜት የሚነካና ትርጉም ያለው ስራ ነው። ኦሮምኛ በአማርኛውም እንደዚሁ ለየት ያለ ስሜት አለው። በሙዚቃው በኩል ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ። አቀናባሪዎቹ ብቻ ስምንት ናቸው። በተጨማሪ ቤዝ ጊታር ፡ክራር፡ማሲንቆ፡ ሳክስፎንና የመሳሰሉት የገቡ አሉ ። እነዚህን ሁሉ ስንደምራቸው አስራ ሁለትና አስራ ሶስት ሙዚቀኞች ተሳትፈዋል። ከነዚህም ውስጥ በዋናነት አበጋዝ፡ ኤልያስ መልካ ፡ ዳዊት ጥላሁን፣ ሁናንተ፡አማኑኤል ይልማ ፡ አሸብር፣ ሳሚ የሚባሉ ሙዚቀኞች ተሳፈዋል። በግጥምና ዜማው በኩል ጎሳዬ ፡ ሃብታሙ ቦጋለ፣

ታመነ መኮንን ፡ እራሴ በአብዛኛው እንዳለ አድምቄ ከዜማው በኩል እና ታምራት ደስታም እናትዬ የሚለውን ስራዎች አግዘውኛል ። ያው በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰግናቸው አላልፍም።

አንዳንድ በሙዚቃው አለም ላይ የሚገኙ አንጋፋ አርቲስቶች ሂስ ሲሰጡ በዚህ ዘመን ያሉ የወጣቶቹ

ስራ ለፈረንጆች እጅ ወደ ላይ ሳይባል እንደሰጠ ምርኮኛ ቀድመው እጃቸውንሰጥተዋል። ጥርት ያለውን ሃገረኛ

ስሜት ያላቸውን ስራዎች እየናፈቁን መተዋል። እነዚህ ስራዎች ባህላችን እያጠፉት ነው ይላሉ። አንተ በዚህ

ላይ ምን ያህል ትስማማለህ? ጎሳዬ፡- በዚህ በኩል ይህን ነገር እኔ ብዙም

አልስማማበትም። ምክንያቱም ሙዚቃ በራሱ ቋንቋ ነው ።ለምሳሌ አውሮፓውያን ወይንም አሜሪካዊያን የነሱን የሚመስል ስራ በአማርኛ ቀይጠን ብንሰጣቸው እንደውም ይህ

ስራ የኛን ሃገር ይመስላል ብለው ይስባቸዋል እንጂ ባሕላችንን እያጠፉ ነው ለሚለው እንግዲህ በኔ በኩል

በተቻለኝ መጠን ኦሮምኛ በአማርኛ ላሊበላ እያልኩ ድሬድሬ የሚለውን በራሳችን እስክስታና ከክራር ጋር

የተያያዙም በጣም ጥሩ ሃገረኛ ስሜት ያላቸውን ስራዎችን ሰርተናል። የቱ ጋር እንደ ጎደለ ባይገባኝም ይህ ነገር

ለምሳሌ ላቲኖች ወደ ዓለም ሙዚቃ የገቡት ከተሰሩ ሙዚቃ ጋር እያመሳሰሉ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሃገራችንም

በድሮ ጊዜም ቢሆን አንጋፋዎቹ ድምፃዊያን ሳይቀሩ ከሱዳን ሜሎዲ እየወሰዱ የሚሰሩበት አጋጣሚም ነገር።

በኛ በወጣቶቹ ላይ ብቻ ተተኮረ እንጂ ድሮም ያለ ነገር ነው አዲስ ነገር አይደለም።

ጥርት ያለው ባህላችን ከዘመናዊ ሙዚቃ ጋር ቢሰራ ኖሮ ይሄኔ የት በደረስን ነበር። በቀጥታ የውጪውን ስራ በመኮረጅ

ስም በማጥፋት ላይ የሚገኙም አሉም ይላሉ? ጎሳዬ ፡ ባይሆን እዚህ ላይ እደግፋቸዋለሁ። በኔ በኩል

የሃገራችን ሙዚቃ ከዘመናዊው ጋር ተቀላቅሎ ቢሰራ ምን ያህል ሊጣፍጥ እንደሚችል ያሳየሁበት ስራዎች

አሉኝ ። በሌላ በኩል አሁን ጎሳዬን ወስደህ ሙሉ በሙሉ ፍፁም የባህል የሆነ ሥራ ሥራ ብትለው ምናልባት የሱ ችሎታ ላይሆን ይችላል። ለሱ የተሰጡ ሰዎች አሉ። ይህንን ሃላፊነታቸውን

ጠብቀው ይዘው የሚሔዱ አርቲስቶች እንዳሉ ተስፋ አደርጋለሁ። በመጨረሻው አልበምህ ላይ ላይ ለብሰህ ስለተነሳኽው

ቲሸርትህ እንምጣ ሃሳቡን ማን አመነጨው?

ጎሳዬ፡- (ረጅም ሳቅ) ለመሆኑ ቲሸርቴ እዚህ አገር

መጥቷል? (እረጅም ሳቅ) አንድ ወዳጄ እዚህ ሃገር ላይ

ያለኝን ልንገርህ «የጎሳዬ በነጭ ወይም በጥቁር ምስል ላይ ያለው ያንተ ቲሸርት ሰማንያ ብር ገባ መቶ ብር ገባ ሲሉኝ ምንም ትርጉም ሳይሰጠኝ አለፈ አለኝ። ይሄውልህ ቲሸርቱ ማለት በሁሉም የሃገራችን ክፍል በተለይ የገጠሩ ወጣቶች በሙሉ የሚያደርጉት ደረቱ ላይ ሸንተረር ሸንተረር ኖሯቸው የተለያዩ መልክ ያላቸው ቲሽርቶች ናቸው። አወካቸው ወይ ስለው እነሱን ነው እንዴ ብሎ ተገረመ። የቲሸርቱ ሐሳብ የመነጨው አንድ ወቅት ላይ እቤት ቁጭ ብዬ ቴለቪዥን እያየሁ ሳለ የአንድ ብሔረሰብ አኗኗራቸውና የለቅሶ ስርዓታቸው

እንዴት እንደሆነ የሚገልፅ ስነ-ስርዓት ላይ ሳስተውላቸው ወዲያው መርካቶ ለሚገኘው ጓደኛዬ ስልክ አነሳሁና ይሔንን ልብስ እፈልገዋለሁ ። ይህ በኔና በአንተ ብቻ የሚቀር ይሁን ብዬው ፈልጎ አገኘልኝ።

ስንት ነው ስለው 28 ብር አለኝ። በል እንግዲያው በአረንጓዴ በቀዩም በሰማያዊውም ግዛልኝ። በሱ ፓስተር መስራት አለብኝ አልኩት ።ይህ ልብስ ሁሉም ሰው ስለሚለብሰው መለያችን እየሆነ መጥቷል።

“እንዴት አሰብከው?” ሲለኝ እሱን ይዘህ ስትመጣ

ይነገርሃል” አልኩት። ይዞ ሲመጣልኝ በተለያዩ

ሚዲያዎች ላይ እንደገለፁት ”ወደ ሰሜናዊ ኢትዮጵያ

ስሄድ ላሊበላዋን ፡ ወደ ምስራቅ ድሬ. . . ድሬ ፡ ወደ ምእራብ እቫንጋዲ ፤መካከለኛውን ደቡብና ወደ

ምስራቁን የሚገልጽልኝ ኦሮሞ ናት እሷ (ኮያባቦ) ብያለሁ። ይህን ሁሉ የሃገሬን ክልል ለጠራሁበት ስራ

የ500 እና የ600 ብር ሸሚዝ አደርጌ ምስሌ ፖስተር ላይ ቢወጣ ምንም ትርጉም አይሰጠኝም ብዬ ስላስብኩ ነው።

ከዚህ በፊት ጓደኛህ 28 ብር የገዛውን ቲሸርት እኔ

እስከማውቀው 12ብርም ሲሸጥ አውቀዋለሁ። ለመሆኑ አንተ ፖስተር ከሰራህበኩት በኋላ ስንት ብር ገባ ሲባል

ነው የሰማኸው? ጎሳዬ ፡ አሁን ወደ መጨረሻዎቹ ላይ መቶ ሃያ ምስት ብር ገባ ሲባል በጣም ነው የቆጨኝ ይሄኔ በኮንቴነር አስመጥቼ ብሸጠው ትልቅ ቢዝነስ ውስጥ ገብቼ ነበር።

የጎሳዬ ልጅ ወደፊት የት ነው የሚያድገው? አንዳንድ አርቲስቶች ወደዚህ ወደ አሜሪካ እያመጡ ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ እያየናቸው ነው። ጎሳዬ ፡ አዲስ አበባ። እኔና ባለቤቴ የግል ድርጅት ስላለንና በሌሎችም ምክንያቶች ኢትዮጵያ ላይ ነው መኖር የምንፈልገው ስለዚህ ልጄም ሃገሬ ነው የሚያድገው።

ድርጅታችሁ ምን አይነት ድርጅት ነው? ጎሳዬ ፡ ከኬሚካል ድርጅቶች ጋር የተያያዘ ስራ ነው የምንሰራው። እስቲ ስለ ባለቤትህ ትንሽ አንዳንድ ነገር በለኝ ። በአንተ

ሙያ ላይ አስተዋፆ ታደርግልሃለች? ጎሳዬ ፡ በነገራችን ላይ እጅግ በጣም ጠንካራ ፤ ጎበዝና የስራ

ሰው ናት።በተጨማሪም ጥሩ የቤት ዕመቤት የሆነች ባለቤት ነው ያለችኝ። እኔም እጅግ በጣም ነው

የማከበራትና የምወዳት ። በኔም ሙያ በኩል ከምጠብቀው በላይ ነው አስተዋፆ እያደረገችልኝ ያለችው። ለምሳሌ ያህል

በቅርቡ ሳታማሃኝ ብላ የሚለውን ካሴት ሳዘጋጅ በፕሮሞሽኑ በኩል ከሙዚቃ ቤቱ ውጪ የእኔን ፖስተርና ፍላየር እያሰራች በሁሉም ቦታዎች ላይ እያስበተነች በጣም ትልቅ ሚና ተጫውታለች ላመሰግናት እወዳለሁ ።

በሕይወቴ ላይ የኔ ጠንካራና ደካማ ጎን ይህ ነው የምትለው

አለህ? ጎሳዬ ፡ መቼም ሰው እስከሆንክ ድረስ ጠንካራም ደካማም

ጎን ይኖርሃል። በርግጥ ደካማ ጎንህን ላታስተውለው ትችላለህ። ጠንካራ ጎኔ ነው የምለው በየቀኑ ስራዬን አስባለሁ። ሁል ጊዜ በአይምሮዬ ውስጥ ዛሬ ጥሩ ስራ ሰርተሃል ብሎ አድናቆት ለሰጠኝ ሕዝብ ነገ ከነገ ወዲያ ምን ሰርቼ ላስደስተው የሚል ነገር አለ። ሌላው ይቅርና እኔና አንተ እንኳን ቻው ቻው ተባብለን ከተለያየንበት ጊዜ ጀምሮ ሌላ የፈጠራ ስራ ላስብ የምችልበት ጊዜን ነው ለራሴ የምሰጠው። ስለ ራሴ ይህን ያክል ነው።

አንተም ሆንክ ባለቤትህ የወደፊት ዓላማችሁ ምንድነው? ጎሳዬ ፡ እኔም ባለኝ ሙያ ከሷም በምትሰራው ስራ ትልቅ

ደረጃ ላይ ደርሰን ሃገራችንን በጥሩ ስም ማስጠራትእንፈልጋለን

። በተረፈ አባወራነቱም መጥቷል (ሳቅ) በተለይ እንደምታውቀው በዚህም በሃገራችንም በርካታ

ወጣቶች በተለያዩየሞያ መስኮችና ባንተ የሞያመስክ የተሰማሩ ወገኖቻችን አሉ ። እነዚህ ከአንተ ምን ሊማሩ ይችላሉ ። ምን

የምትላቸው ነገር አለ ? ጎሳዬ ፡ በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ሰው ጠንካራ ለመሆንና

ትልቅ ደረጃ ላይ ለመድረስ እያሰብን መጣር አለብን።ሃገራችንም ገብተን ስማችን በጥሩ ጎን እንድናስጠራ በተለይ ከጦር በላይ እያስፈራራን ከመጣው ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ራሳችንን ጠብቀን

መዋጋት ይኖርብናል።

Facts About Gossaye

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

ለፈገግታ አለቃ ገብረሀና የማይለመድ ለምደው ማታ ማታ ሰራተኛቸው ጋ ብቅ ሳይሉ አያድሩም ነበር። አንድ ቀን ሰራተኛቸው ጋ አምሽተው ቆይተው ቀስ ብለው ተደብቀው ገብተው ይተኛሉ። ትንሽ እንደቆዩ እንደገና ያምራቸውና ቀስ ብለው ምንም ሳያሰሙ

እራቁታቸውን ሊሄዱ ሲነሱ ወ /ሮ ማዘንጊያ

ነቄ አሉና «አንቱ ወዴት ኖት በዚህ

በጭለማ» ብለው ወይዘሮ ማዘንጊያ

ሲጠይቋቸው። «ቆዪ እስኪ አንዴ ውዳሴ

ማርያም ደግሜ ልምጣ» አሉ። «ታዲያ ውዳሴ ማርያም እራቆት ተኩኖ ነው

የሚደገም?» «ምን ላድርግ? እራቁቴን ሆኜ

እንኳን ብትሰማኝ» ብለው እርፍ። **** ***** **** አንድ የሚኒልክ መኮንን ስልብ ነበሩ ይባላል። መኮንኑ አንድ የጀግንነት ስራ ይሰሩና ሙሉ ትጥቅ ከነልብሱ ይሸለማሉ። አለቃን

ያገኟቸውና “አለቃ እንዴት ነው?”

“አላማረብኝም” ይላሉ።አለቃም መልሰው “አይ አስተታጠቅ አይ አለባበሥ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ አይ ጎራዴ”

ይላሉ። ሌሎች መኳንንት መኮንኑን አለቃ ምን አሉህ? ይሉታል አደነቁኝ አይ አስተታጠቅ አይ ጎራዴ አሉኝ

ይላል።መኳንንቱም ምን አደነቁህ ሰደቡህ እንጂ ስልብ ስለሆንክ ጎራዳ ነህ - አይ ጎራዴ -የኔ ጎራዳ ነው ያሉህ ብለው ሲነግሩት አለቃን ካልገደልኩ ብሎ በገላጋይ ነው አለቃ የተረፉት ይባላል፡፡ *** **** **** አንድ ቀን የሙላ ነስረዲን ጓደኛ እድሜውን ጠየቀው ሙላም አርባ አንድ አመት ሲል መለሰ። ጓደኛው

በመገርም ምነው ሙላ የዛሬ ሁለት አመትም አርባ አንድ ብለኸኝ አልነበረም እንዴ « ሲል ተናገረ። ሙላም «

ትክክል፤ አየህ እኔ በቃሌ የምጸና ሰው ነኝ « በማለት መለሰለት

ምርጥ አባባሎች ታሪኳ ከሴንት ፖል

- በዓለም ከፍተኛ መራራ ነገር ቢኖር ራዕይ አባል ሆኖ መፈጠር ነው።

- ባልና ሚስት በጋራ የሚተነፍስ ሳንባ ባይነራቸውም በጋራ የሚጓዝ የትዳር ሰንሰለት አላቸው።

- በዓለም ትልቁ ውርደት ከመስራት የሰው እጅ ማየት ነው።

- በአንድ ዛፍ የሚዘሉ ጉሬዛና ጦጣ አብረው ቢውሉም ተቃቅፈው አይተኙም።

- በኢላማህ የማትተማመን ከሆንክ ወደ ነብር አትተኩስ።

- በዛሬ ደስታ ብቻ የሚፈነድቁ ሰዎች ውብ አበባ ከተቀጠፈ መጠውለጉን የሚዘነጉ ናቸው።

- በፍቅር የተነሳ ልብ በፍቅር ይሰክናል።

- ብርቱካን መጨመቁን ቢያውቅ ውሃ አይዝልም ነበር።

- ብቃት የሚመጣው በውጥረት ሳይሆን በተግባር ምጥቀት ነው።

- ለማመን እንጂ ላለማመን ምክንያት አያስፈልግም::

- መልከመልካም ሴት ባየህ ጊዜ ተፈጥሮን አድንቅ እንጂ የዝሙትን መንፈስ አይሰማህ' ዝሙት ከደካማ መንፈስ የሚመንጭ

ሲቸግርህ የጎረቤትህን ንብረት ሸጠህ መጠቀም የምትችልባት የደደሆ ቀበሌ በአፋር ክልል

ከአዲስ አበባ በ270 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር አዋሽ ፈንታሌ በከሰም ዙሪያ ካሉት ቀበሌዎች አንዷ የደደሆ ቀበሌ ናት። ይህች ቀበሌ 750 አባወራዎች ይገኙበታል። በአካባቢው ነዋሪ የሆኑት መምህር ኑሪስ መሐመድ እንደሚናገሩት በቀበሌዋ የተቸገረ ሰው የለም። አንድ ነዋሪ ከተቸገረ እንኳን የሌላውን አፋር ንብረት እንደራሱ ሊጠቀምበት ይችላል። ገንዘብ ቢያስፈልገውም የሌላውን አፋር ንብረት እንደራሱ በመውሰድ ሸጦ ሊጠቀም ይችላል።

ይህ ባህል በቀበሌዋ ውስጥ የተቸገረ ሰው እንዳይኖር ያደረገ ባህል ቢሆንም አንዳንዶች ሠርተው እንዳይበሉ የራሳቸውን ንብረት ማፍራት እንዳይችሉ የሚያሰንፍ ነው።

የተቸገረ ሰው የሌላውን ከብትና ሌሎች ንብረቶች ሲወስድ ማንም የማይጠይቀው ቢሆንም ነገር ግን ሸጦ ያገኘውን ገንዘብ ላልተገባ አላማ ካዋለው በዐዳው (ኢረና በሚባል ባህል) ቅጣት ይጣልበታል። ኢረና የሚባለው የቅጣት ባህል የወሰደውን ከብት ሸጦ ያገኘውን ገንዘብ ጫት በመቃምና አልባሌ ለሆኑ ነገሮች ካዋለው የሚጠየቅበት ሥርዓት ነው። ሆኖም ግን ያገኘውን ገንዘብ ጋብቻ የሚፈፀምበት ከሆነና ለተመሳሳይ በጐ ዓላማ ካዋለው አይጠየቅም።

የኢረና የቅጣት ሥርዓት የቀበሌዋ ሕዝብ እንዲሰበሰቡ ከተወከሉት ኮሚቴዎች አንዱ ማለዳ ላይ ከፍታ ቦታ ላይ ሆኖ የስብሰባ ጥሪ ያስተላልፋል። «... ቅጣት ስላለ ሁላችሁም እንድትገኙ የምትቀሩ ከሆነ የእናንተም ከብት ይታረዳል» የሚል መልዕክትም ያስተላልፋል። ይህንን ጥሪ የሰማ የአካባቢው ነዋሪ በሥርዓቱ ላይ አይቀርም። በሥርዓቱ ላይ ሽማግሌዎችም ይታደሙበታል።

በጥሪው መሠረት የቀበሌዋ ሕዝብ ከተሰበሰበ በኋላ አጥፊውን ይዘው እንዲያቀርቡት የተመደቡት ወጣቶች ለተሰበሰበው የመንደሩ ሕዝብ ጥፋቱን በዝርዝር ያስረዳሉ።

አጥፊው ካለው ከብት ተመርጦ ይታረድበታል። ይህ የማይሆን ከሆነ ሌላ አማራጭ ቅጣት ይጣልበታል። ሁለት እጁ ወደ ኋላ ይታሠርና እንጨት ላይ ይሰቀላል። አልያም በሦስተኛ አማራጭ ቅጣት ይቀጣል፤ ንብረቶቹ ተሸጠው ገንዘቡን እንዲከፍል ይደረጋል።

ይህ ቅጣት ከተከናወነ በኋላ ሌሎች የተጣሉ ግለሰቦች ካሉ በዚሁ አጋጣሚ ዕርቅ እንዲፈጽሙ ይደረጋል። ያጠፋው ግለሰብም በገንዘብ ቅጣት ይቀጣል። በመጨረሻም የተሰበሰበው የቀበሌዋ ሕዝብ ሥጋ እየበላ ይጨዋወታል። የታረደው ሥጋም ለማንም አይላክም፤ ወደ ቤትም አይገባም። የቅጣት ሥርዓቱ በሚከወንበት ግራር ሥር ይጠናቀቃል። ምንጭ፡ የአፋር ባህልና ቱሪዝም መጽሔት

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

እውን 2012 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት የኅልፈተ

ዓለም ዘመን ሊሆን?! ነገ ፤ ወደፊት፣ በተጨባጭ ሁኔታ ሊከሠት ስለሚችለው

የፕላኔታችን ዕጣ -ፈንታ፣ የሥነ ፍጥረት ጠበብት ፣ በእርግጥ በአጭርና በረጅም ጊዜ ስለሚሆነው፤ ምናልባትም ስለለሚያጋጥመው፤ አሥፈሪ ሁኔታ ሊያሳምን የሚችል መላ- ምት ማቅረብ ይችላሉ ወይ? የሥነ-ቴክኒክና የማኅበራዊ ኑሮ መስተፋጥናዊ ለውጦች ስለወደፊቱ መጻዔ-ዕድል ለመተንበይ

፤የሳይንቲስቶች፤ መነሻ ምክንያቶች ምን ይሆኑ? በዛሬው ሳይንስና ኅ ብ ረ ተ ሰ ብ የ ም ን ዳ ስ ሰ ው ጉ ዳ ይ ይ ሆ ና ል ። ወደ ሳይንስ ጠበብት መላ-ምቶች ከማምረታችን በፊት እስቲ ተንባዮችም ሆኑ ሙዋርተኞች ካሉት በጥቂቱ እናንሳ። እ ጎ አ ታኅሳስ 21 ቀን 2012 ዓ ም፣ በጥንታናውያኑ የማዕከላዊው አሜሪካ ነባር ተወላጆችና የጥንት ስልጣኔ ባለቤቶች፣ ማያዎች ትንቢት መሠረት፣ ዓለም በውሃ ተጥለቅልቃ ትጠፋና እንደገና አዲስ ህይወት ይጀመራል። ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 3114 ዓመተ ዓለም፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕላኔታችን በውሃ ተጥልቅልቃ የጥፋት ውሃ ሰለባ እንደነበረች የማያዎች ትረካ ያስረዳል። እንደማያዎች እምነት፣ ፍጥረተ ዓለም (ዩኒቨርስ በተለያዩ ዘመናት ፣ ዑደታዊ ጥፋትና ድኅነት የሚፈራረቅበት መሆኑ እንደተፈጥሮ ህግ የሚታይ ጉዳይ ነው። ምንም እንኳ፤ የትንቢቱ መያዝ አለመያዝ አነጋጋሪነቱ እንዳለ ቢሆንም፤ የማያዎች ሥልጣኔ፤ የሂሳብና የሥነ ፈለክ ምርምር ችሎታቸው የሚያስደንቅ እንደነበረ ነው የሚነገረው። የዘመን አቆጣጠራቸው የጨረቃን ዑደት መሠረት ያደረገና ፣ 23 ሴኮንድ ድረስ ፍጹም ትክክለኛነት የሚንጸባርቅበት ነበረ። የማያዎች የቀን መቁጠሪያ ያለፉትን 5000 ዓመታት በትክክል የሚቃኝና፣ ስሌቱ በዚህ ረገድ ያልተዛባ መሆኑ ነው የሚመሠከርለት። የማያዎች ትንቢት፤ ዓለም፣ በጥፋት ውሃ፤ በእሳትና በሚያሳቃዩ አጋንንት መከራ እንደሚደርስበት ነው የሚገልጸው። በአያሌ ዘመናቱ ጥንታዊ ሥልጣኔአቸው ፤ ማያዎች፤

በፒራሚድ ፣ በአብያተ-መንግሥት፣ በሃውልትና በመሳሰለው ሥራቸውም የታወቁ ነበሩ።

በታኅስስ ወር 2005 ፤ ወይም እ ጎ አ ታኅሳስ 21 ቀን 2012 ዓ ም ፣ ማያዎች እንደተነበዩት ዓይነት ጣፋት ይደርሳል ካሉት መካከል እ ጎ አ ከ (1503 -1566) የኖረው መድኃኒት ቀማሚ፤ ሀኪምና ኮከብ ቆጣሪ Michel de Nostredame ወይም ኖስትርዳመስ ይገኝበታል። ኮከብ ቆጠራን አስመልክቶ በስንኞች በደረደረው ግጥም ላይ እ ጎ አ በ 2003 እና 2022 ዓ ም መካከል እጅግ አስከፊ የአየር ንብረት መዛባት እንደሚያጋጥም ተንብዮአል።

በ 2012 ዓ ም፤ 3ኛውና የመጨረሻው የዓለም ጦርነት እንደሚካሄድና ፣ ጦርነቱ ካከተመ በኋላ፣ ፍጹም ሰላም ይሠፍናል ነው የሚለው ፤ ኖስትራዳመስ! በፍጥረተ ዓለም አዳዲስ ክስተቶች አጋጥመው ፣ ለፕላኔታችን በመጀመሪያ ጥፋት፣ በኋላም ድኅነት እንደሚያስገኙ ያትታል። ያ ከመሆኑ በፊት ግን መሬት የተፈጥሮ አቅዳዊ ሂደትን ባዛባ መልኩ በራሷ ዛቢያና በፀሐይ ዙሪያ የምታደርገው መሽከርከር እንደሚናጋ ፤ የሰሃራ ምድረ በዳ ሳይቀር እጅግ አስከፊ ማጥለቅለቅ እንደሚያጋጥመው፤ የሰሜንና ደቡብ ዋልታዎች የበረዶ ተራሮች ይቀልጣሉ። በደቡብ አውሮፓና ፣ ጥቅጥቅ ያሉ ደኖች በሚገኙባቸው፣ሞቃት ሃገራት፣ብርቱ የድርቅ አደጋ እንደሚያጋጥም፤ በኮሎኝና ቦን አቋርጦ የሚያልፈው የራይን ወንዝ እንኳ የሚፈስበትን አቅጣጫ እንደሚለውጥ ፤ በኢጣልያ አዳዲስ ባህሮች እንደሚፈጠሩ፣ ሲሲሊ፣ ማርሴይ አካባቢ ያለው

የፈረንሳይ ግዛት፤ እንዲሁም ብሪታንያ እንደሚሰጥሙም (ውቅያኖስ እንደሚውጣቸው)ነው የኖስትራዳመስ ትንቢት የሚያወሳው።

በ 2012 ጎርጎሪዮሳዊው ዓመት ፣ (ማለትም በታኅሳስ ወር 2005) በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ ተደራራቢ ጥፋት ቢያጋጥም ፣ ተንባዮች ራስን ለማዳን ፣ በዓለም ዙሪያ 5 አካባቢዎችን የጠቀሱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አምባዎች ይገኙበታል። ይህ ሁሉ እንግዲህ ትንበያ ምናልባትም ሟርት ልንለው እንችል ይሆናል።

ሳይንስን እንመርኮዝ የሚሉት ወገኖችስ ምንድን ነው የሚሉት?

«2020 እፁብ ድንቅ ዘመን ይሆናል፤ በህክምናው ዘርፍ የሚደረጉ ምርምሮች፣ እርጅናን በእጅጉ ለመግታት የሚያስችል ይሆናል። 100 ዓመት የሆናቸው ሰዎች፤ በዚያ ዕድሜ ፣ህይወትን

የሚያጣጥሙ እንጂ የሚያማርሩ አይሆኑም። በ 2010 ( እ ጎ አ)በማስተዋል ይበልጥ አስተዋይነትን የሚያጎናጽፉ ክኒኖች ገበያ ላይ ይውላሉ፤ በአነዚህ ክኒኖች እርዳታ ሁሉም ምጡቅ ዕውቀት ገብዪ ይሆናል። ባክቴሪያንም ሆነ ተኀዋሲን መፍራት ተገቢ አይሆንም ። እ ጎ አ ከ 2000 ዓ ም አንስቶ ክትባት መሰል፤ መርፌ መስጠት ተጀምሯል። ማንኛውም በጤንነት ላይ እክል ለመፍጠር የሚዳዳውን ሁሉ፤ በዘመናዊ ህክምናና መድኃኒት አስቀድሞ መከላከልም ሆነ ማስወገድ አዳጋች አይሆንም። (www.dw)

1. ኪስ /Kiss/ የሚለው ቃል ከጥንታዊው የእንግሊዝኛ ቋንቋ Lyssan የመጣ ሲሆን፣ መነሻው ደግሞ በጀርመንኛ Kussijanan ወይም Kuss የሚለው ቃል ነው፡፡ ይህም በመሳሳም ወቅት የሚደመጠውን ድምፅ ይወክላል፡፡

2. አንዲት ቻይናዊት ፍቅረኛዋ በጆሮዋ ውስጥ ምላሱን አስገብቶ ሲስማት የጆሮ ታምቡር በመበጠሱ መስማት የተሳናት ልትሆን ችላለች፡፡ ይህንንም ሮይተርስ የዜና አውታር ዲሴምበር 8 ቀን 2008 ‹‹The kiss of Deaf Chinese Man Ruptures Girlfriends Eardrum›› በሚል ርዕስ ዘግቦት ነበር፡፡

3. ስለመሳሳም የሚያጠና ሳይንስ ፊሌማቶሎጂ /Philematology/ ይባላል፡፡

4. Kiss my Ass የሚለው የስድብ ቃል የተጀመረው ከ1705 አንስቶ ነው፡፡

5. ከንፈሮች ከጣቶች በ100 እጥፍ የበለጠ ስሜታዊ ናቸው፡፡ ብልቶች እንኳ የከንፈሮችን ያህል ስሜትን አይጭሩም፡፡

6. ወደ ሁለት ሶስተኛ የሚሆኑ ሰዎች በሚሳሳሙበት ወቅት ጭንቅላታቸውን ወደ ግራ ዘመም የማድረግ ልማድ አላቸው፡፡ አንዳንድ ምሁራን ይሄን ልማድ በማህፀን ውስጥ እያሉ የጀመሩት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

7. ከጁላይ 5 እስከ 6 ቀን 2005 የለንደን ጥንዶች በመሳሳም የዓለምን ሪከርድ ጨብጠዋል፡፡ እነዚህ ፍቅረኛሞች በተጠቀሰው ቀን ለ31 ሰዓታት፣ 30 ደቂቃዎችና 30 ሰከንዶች ያለማቋረጥ ተሳስመዋል፡፡ ይህም ረጅሙ መሳሳም ተብሎ በጊነስ ተመዝግቦላቸዋል፡፡

8. በመሳሳም ወቅት በጣም ጠቃሚው ጡንቻ አርቢኩላሪስ ኦሪስ (Orbicularis Oris) የሚባለው ሲሆን፣ እሱም ከንፈሮችን የሚያፍታታ ነው፡፡

9. በፍሬንች ኪሲንግ ወቅት በፊታችን ላይ ያሉት 34ቱም ጡንቻዎች ይሳተፋሉ፡፡

10. የወንድም ሆነ የሴት ከንፈሮች ከሴት ብልት ከንፈር ጋር ይመሳሰላሉ፡፡

11. ‹‹French Kiss›› የሚለው ሐረግ እንግሊዝኛ ቋንቋን የተቀላቀለው ወደ 1923 ገደማ ነበር፡፡ ያኔ ፈረንሳዊያን ለወሲብ ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡ ለማሳየት ሲባል የተቀመጠ ሐረግ ነው፡፡ በፈረንሳይ ይህ አሳሳም የምላስ ወይንም የመንፈስ አሳሳም ተብሎ የሚቀመጥ ሲሆን፣ ምክንያቱ ደግሞ በትክክል አሳሳሙ ከተከናወነ የሁለቱ ተሳሳሚዎች ነፍስ ወደ አንድ እንደሚገጥም ስለሚታመንበት ነው፡፡

12. በስነ ፅሑፍ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ስለመሳሳም የተፃፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1500 በታተመው The Four Vedic Sanskrit የተሰኘ መፅሐፍ ነበር፡፡

13. ሮማዊያን መሳሳምን በሶስት ክፍሎች መድበውታል፡፡ አንደኛው፡- Osculum ሲሆን የጉንጭ ለጉንጭ መሳሳም ነው ሁለተኛው፡- Basium ሲሆን ከንፈርን መሳም ነው ሶስተኛው፡- Svolium ሲሆን ጥልቀት ያለውን መሳሳም ይገልፃል፡፡ 14. በጥልቅ ፍቅር ውስጥ የሚከናወን መሳሳም በደቂቃ 6.4 ካሎሪ

ያቃጥላል፡፡ በመሆኑም 26 ካሎሪን ለማቃጠል ወይ አምስት ደቂቃ በእግር መጓዝ አልያም ለአራት ደቂዎች መሳሳም ያስፈልጋል፡፡

15. ሴት ልጅ በመሳሳም ብቻ የስሜት እርካታ ላይ ልትደርስ

ትችላለች፡፡

ትንኝ የሚያወጣላት

ነው የሚመስለው እኮ!

ድሮግባ..... ከገጽ 15 የዞረ

ትክክለኛውን የእሱን ምትክ ያገኛሉ ወይ? የሚለው ነው›› በማለት ስለድንቅ ብቃቱ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የቡድን ጓደኛው ፍራንክ ላምፓርድ በበኩሉ ‹‹እሱ እውነተኛ ጀግና ነው›› ሲል አድናቆቱን ችሮታል፡፡ በ2006 እና በ2009 የዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጨዋች ተብሎ ለመመረጥ የበቃው ዲዲዬ ድሮግባ ከሜዳ ውጪ ያለው ህይወቱም በስኬት የተሞላ ነው፡፡ በምግባረ ሰናይ ስራዎች ላይ በሰፊው የሚሳተፍ ሲሆን 11 አባላት ያሉት የአይቮሪኮስት የእውነት አፈላላጊና እርቅ ኮሚ ሽን አባል ነው፡፡ በቀጣይ ህይወቱስ ምን ይገጥመው ይሆን?

Happy Ending! አይቮሪኮስታዊው ከከብ ዲዲዬ ድሮግባ በቼልስ መውጫ

በር ላይ ቆሟል፡፡ ይህ ለበርካታ የክለቡ ደጋፊዎች ለማመን የሚያስቸግር ነገር ቢሆንም እሱ ግን በአቋሙ እንደሚፀና በግልፅ ተናግሯል፡፡ አሁን የሚጠበቀው ነገር ቀጣይ ማረፊያው የት ይሆናል? የሚለው ብቻ ነው፡፡

የአፍሪካዊው ጀግና በስምንት ዓመት የስታምፎርድ ብሪጅ ቆይታው ሶስት የፕሪሚየር ሊግ፣ ሁለት የካርሊንግ ካፕ፣ አራት የኤፍ.ኤ ካፕ እና እንዲሁም አሁን በስተመጨረሻ አንድ የቻምፒዮንስ ሊግ በድምሩ አስር ዋንጫዎችን ለመሳም ችሏል፡፡ ለእሱ ታላቅ ዝና መቀዳጀት የዦዜ ሞውሪኖ ሚና በእጅጉ ላቅ ያለ ነው፡፡ በ2004 ከፈረንሳዩ ማርሴይ ክለብ በ24 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቼልሲ ያመጡትም እሳቸው ናቸው፡፡ የፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ስንብት ተከትሎ እሱም ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ በወቅቱ ገልፆ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በኋላ ላይም በውሳኔው መፀፀቱን በመግለፅ ይቅርታ ጠይቋል፡፡ ነገር ግን ሰውዬው ባለውለታው ናቸውና ይሄንን ቢያደርግ ማን ሊፈርድበት ይችላል? አሁን ግን ያን ጊዜ የተናገረውን ተግባራዊ በማድረግ ሰማያዊውን ማሊያ ለማውለቅ ከጫፍ ደርሷል፡፡

የድሮግባ መልቀቅ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በእጅጉ እንደሚጎዳው እሙን ነው፡፡ ጉዳዩን ዘግይቶ ቢያሳውቅም ውስጥ ውስጡን ግን አስቀድሞ ሲወራ ቆይቷል፡፡ እሱ ራሱም በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ወደ ሌላ ክለብ በመሄድ አዲስ ህይወት ለመጀመር እንደሚችል በይፋ አስታውቋል፡፡ በቻምፒዮንስ

ሊግ ፍፃሜ ወሳኟን የአቻነት እና የአሸናፊነት የፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ካሳረፈ በኋላ ሜዳው መሀል ቆሞ ሁለት እጆቹን በማውለብለብ ለደጋፊያቸው ሰላምታ ማቅረቡም ለስንብቱ ፍንጭ የሰጠበት ሂደት እንደሆነ ተናግሮለታል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ለእሱ የተለየ ፍቅር ያላቸው አድናቂዎቹ የሆኑ የተወሰኑ የቼልሲ ደጋፊዎች አይናቸው በእምባ ሲሞላ ማስተዋሉን የዴይሊ ሜይል ጋዜጣ ዘጋቢ ተናግሯል፡፡ በእርግጥም በዛ ጨዋታ ሰማያዊዎቹን ከሞት ታድጎ ታሪካዊ አድርጓቸዋልና የልብ አፍቃሪዎቹ ይሄንን ስሜት ቢያሳይ ምንም ላይገርም ይችላል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይ የድል ባለቤት ለመሆን መቻሉ ብቻ ሳይሆን በ2008 ሞስኮ ላይ በዚሁ ውድድር ፍፃሜ ላይ የቀይ ካርድ ሰለባ በመሆን ቡድኑን ላስከፈለው መስዋዕትነትም አስፈላጊውን ካሳ መክፈሉን ማረጋገጡ ብቻውን የደስታውን ጥግ ከፍ ሊያደርገው ችሏል፡፡

ለመሆኑ በድሮግባ መልቀቅ ቼልሲ ውስጥ ማን ተጠቃሚ ይሆን? ብዙዎቹ ጣታቸውን በመቀሰር ላይ ያሉት ወደፈርናንዶ ቶሬስ ነው፡፡ ስፔናዊው አጥቂ በ50 ሚሊዮን ፓውንድ ሂሳብ ከሊቨርፑል ወደ ቼልሲ ከተዘዋወረበት ጊዜ አንስቶ የሚጠበቅበትን ያህል ውጤታማ መሆን አለመቻሉ ድብርት ውስጥ ከትቶት ቆይቷል፡፡ ከዚህም ሌላ ቤንች ላይ ለመቀመጥ መገደዱ በራሱ የፈጠረበት ትልቅ ተፅዕኖ እንዳለ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲናገር ቆይቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በመጪው ክረምት የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ሊሸጥ እንደሚችል ሲነገር ቆይቷል፡፡ አሁን ግን የድሮግባ መሄድ እርግጥ ከሆነ እሱ በስታምፎርድ ብሪጅ እንደሚቀየርና የአይቮሪኮስታዊውን ሚና እንደሚወጣ በመነገር ላይ ነው፡፡ ቶሬስ በመጀመሪያው የውድድር ዘመን አጋማሽ ደካማ አጀማመር ቢያሳይም በኋላ ላይ ግን ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየትና ጎል ማስቆጠርም ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ድሮግባ መልቀቁ እርግጥ የሚሆን ከሆነ እሱ በስታምፎርድ ብሪጅ በመቆየት የእሱን ቦታ እንደሚተካ እርግጥ ይሆናል የሚሉ አስተያየቶች መደመጥ ጀምረዋል፡፡

የድሮግባ መውጣትና መውረድ በ2004/05 የውድድር ዘመን 16 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ

ቼልሲ ከ50 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ረድቶታል፡፡ በካርሊንግ ካፑ ፍፃሜም ኳስና መረብን ማገናኘት ችሏል፡፡ በ2006/07 በአንድ የውድድር ዓመት 30 ጎሎችን

በማስቆጠር ከኬሪ ዲክሰን በመቀጠል የመጀመሪያው የቼልሲ ተጨዋች ለመሆን ችሏል፡፡ በካርሊንግ ካፕ ፍፃሜ አርሴናልን ሲያሸንፉ ሁለት እንዲሁም በኤፍኤካፕ ማንቸስተር ዩናይትድን በመርታት የድል ባለቤት ሲሆኑ እንዲሁ አንድ ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ የተመረጠውም በዚህ ዓመት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በ2007/08 የሆዜ ሞውሪንሆ ስንብት ተከትሎ እሱም ክለቡን የመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን መፀጸቱን በመግለፅ ክለቡን ይቅርታ ጠይቋል፡፡ በካርሊንግ ካፕ ቼልሲ በቶተንሀም ቢሸነፍም እሱ ግን ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡ በዛ ሲዝን በማንቸስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ኔማንያ ቪዲችን በክርኑ በመማታቱ አነጋጋሪ ሆኖ ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የቀ ድሞው የሊቨርፑል አሰልጣኝ ራፋ ቤኒቴዝ በበኩላቸው ሆን ብሎ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ይወድቃል በማለት ት ችታቸውን ሰንዝረውበት ነበር፡፡ በፍፁም ቅጣት ምት በማንቸ ስተር ዩናይትድ ተረትተው የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ባጡበት ጨዋታ በቀይ ካርድ መሰናበቱም ሌላው ተጠቃሽ ነገር ነው፡፡

በ2008/09 በበርንሌይ በተሸነፉበት የካርሊግ ካፕ ጨዋታ በተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ላይ ሳንቲም በመወርወሩ የሶስት ጨዋታዎች ቅጣት ሊጣልበት ችሏል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ በባርሴሎና ተሸንፈው ከውድድሩ በወጡበት ግጥሚያ በካሜራ እይታ ውስት ሊገባ ችሏል፡፡

በ2009/10 ከቼልሲ ጋር የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ በግሉም በ29 ጎሎች ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ ጨርሷል፡፡

በ2010/11 በወባ በሽታ መጠቃቱ ቢገለፅም በቶሎ ሊያገግም ችሏል፡፡ በሀገሩ አይቮሪኮስት የተቀሰቀሰው የርስ በርስ ጦርነት አብቅቶ ሰላም ይሰፍን ዘንድ የተጫወተውን ከፍተኛ ሚና ተከትሎ በታይም መፅሔት ምርጫ ከዓለማችን 10 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ አድርጎ ሊያካትተው ችሏል፡፡

በ2011/12 በዌምብሌይ በተካሄደው የግማሽ ፍፃሜ ጎል አስቆጠረ፡፡ በፍፃሜውም እንዲሁ ሊቨርፑል ላይ ጎል አገባ፡፡ በዚህም በአራት ኤፍ.ኤ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ጎል በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጨዋች ለመሆን በቅቷል፡፡

ሞሪንሆ..... ከገጽ 15 የዞረ

መሆን አለብኝ የሚል ውሳኔ ላይ እንድደርስ አድርጎኛል፡፡ በዛ

ላይ ደግሞ በእኔና በስራዬ ላይ ያላቸው እምነት በዚህ ክለብ እንዳልርቅ ተፅዕኖ አሳድሮብኛል፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ሁልጊዜም እንደምናገረው ከስራዬ ጋር በተያያዘ የተለየ ስሜት እንዲሰማኝ እፈልጋለሁ፡፡ ከክለቡ እንደምለቅ በሰፊው ሲወራ ነበር፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሁሉ ተራ አሉባልታዎች መሆናቸውን ማሳየት ነበረብኝ፡፡ ይህ ክለብ ታላቅ ነው፡፡ እርግጥ ነው እንደማንኛውም ተቋም አልያም ግለሰብ ጥቂት ችግሮች አሉበት፡፡ ይህ ግን የእኔ ራስ ምታት አይደለም፡፡ ፊርማዬን ያኖርኩበት ዋና ምክንያት ክለቡ ታላቅነቱን ጠብቆ እንዲኖር ስለምፈልግ ብቻ ነው፡፡ ሁልጊዜም እንደምናገረው አሁንም እኔ ልዩ ሰው ነኝ፡፡ አጭር አቅጄ ብዙ መተግበር ነው ፍላጎቴ፡፡ ይህንን ደግሞ ላለፉት ሁለት ዓመታት ተግባራዊ ሳደርገው ቆይቻለሁ፡፡ ስለዚህ በአሸናፊነቴ ለመዝለቅ ምንም የሚያግደኝ ነገር የለም፡፡ ስለወደፊቱ እያሰብን ገና ብዙ እንሰራለን፡፡ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት የማድሪድ ሀያልነት በማንም እንደማይደፈርም እርግጠኛ ነኝ፡፡

ጥያቄ፡- ይህንን ማሳካት የቻልኩት በእኔ ልዩ ስራ ነው ብለው ያስባሉ?

መልስ፡- እና ታዲያ አንተ ሰርተህልኝ ነው? (በቁጣ)፡፡ እርግጥ ነው ሁላችንም እርስ በርስ መተማወቃችንና መግባባታችን ሸክሙን አቅልሎልናል፡፡ ሁሌም እንደምናገረው ይህ ቡድን በወጣቶች የተዋቀረ ሲሆን ወደ ፊት ገና በርካታ ታላላቅ ድሎችን የመቀዳጀት እድሎች አሉት፡፡ ስብስቤ እንደሌሎች ክለቦች በጨዋታ ዘመናቸው የመጨረሻ ዓመት ላይ በሚገኙ ተጫዋቾች የተዋቀረ አይደለም፡፡ ይህ ክለብ ማህበራዊ ትስስሩ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ወደዚህ ክለብ የመጣ ማንኛውንም ተጨዋች ከቀጣዩ ቀን ጀምሮ ራሱን የክለቡ ቤተሰብ አንዱ አካል አድርጎ ነው የሚቆጥረው፡፡ እንደዚህ አይነት ማህበራዊ ትስስር ደግሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሰብከውን እንድታሳካ ይረዳሀል፡፡ እንደ አሰልጣኝነቴ ደግሞ ሁልጊዜም ማደግና መሻሻል እፈልጋለሁ፡፡ በተለያዩ ሀገራትና በተለያዩ ክለቦች ውስጥ በመዘዋወር የተለያዩ ልምዶችን የመቅሰም ፍላጎት አለኝ፡፡ ይህን የማደርገው ግን የምሔድበት ቦታ ለእኔ ተስማሚ መሆኑን ሳረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ ሁልጊዜም ለመማር ዝግጁ መሆኔ ነው የዓለማችን ምርጡ አሰልጣኝ እንድሆን የረዳኝ፡፡ በእርግጥ (ሞሪንሆ... ወደ ገጽ 2 የዞረ)

ሜሮን ከሳቬጅ ሚኒሶታ በጋብቻና ፍቺ ዙሪያ መማክርት የሆኑት የስነ ልቦና

ጠበብት ሚስተር ጌራይ ቻፕማን አንድ ደንበኛቸው ባለቤቱ ሁልጊዜ አንድ የማይገባውን ጥያቄ እንደምታቀርብለት ይናገራሉ፡፡ ጥያቄውም ‹‹እኛ የበለጠ ቅርርብ ያስፈልገናል፡፡ የሚገባንን ያህል ቅርብ አይደለንም›› ትለኛለች ይላል፡፡ ያክልና ደንበኛው ‹‹ምን እያለችኝ እንደሆነ አላውቅም፤ እንደማስበው ጥሩ ትዳር ነው ያለን›› በማለት ግራ ስለገባው ይናገራል፡፡ ለደንበኛቸው ግራ የገባው ነገር ምንነት በትክክል ያጤኑት ሚስተር ቻፕማን ሁሉን አቀፍ የሆነ አምስት በትዳር ውስጥ መኖር ያለባቸውን የመቀራረብ ጎኖች በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡ እነዚህ አምስቱ የሰው ልጅ በትዳር የሚጋራቸውና ሁለቱ ሰዎች በአንድ ጭንቅላት እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው ነገሮች ናቸው፡፡ እነሱም ምሁራዊ፣ ማህበራዊ፣ ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ መቀራረብ ናቸው፡፡ የሚስተር ጌራይ ቻፕማን ትንታኔ የሆኑትን አምስቱን በትዳር መኖር የሚገባቸውን መቀራረብ፤ በፍቅር ግንኙነት ያለውን ሚና እንዲሁም እነዚያን የመቀራረብ ጎኖች እንዴት ልማዳዊ ማድረግ እንደሚቻል የጠቆሙትን አቅጣጫ እንደሚከተለው አዘጋጅተነዋል፡፡

በትዳር መስተጋብር ትልቅ ጠቀሜታ ያላቸውና ሚስተር ጌራይ የዘረዘሩዋቸው አምስቱ የመቀራረብ ጎኖች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1 . ምሁራዊ ቅርርብ ይህ የረቀቁ ምሁራዊ ሀሳቦችን መወያየት ማለት አይደለም፡፡ ትልቁ ቁም ነገር እሳቤ/ሽ/ን መወያየት ነው፡፡ ስለ ምግብ፣ ስለ ፋይናንስ (ገንዘብ)፣ ጤና፣ ወንጀል፣ ስራና ፖለቲካ እሳቤዎችን ሊሆን ይችላል፡፡

በዕለቱ ሂደት ወደ አዕምሮዋቸው የመጣውን እሳቤ እርስ በእርስ ግልፅ በማድረግ መወያየት መቻል ነው፡፡ መሰል ውይይት በማድረጋቸው ሀሳባቸውን መለዋወጥ፣ መማማር የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ስለሚችሉ ባለትዳሮች ልዩነታቸውን በማጥበብ ቅርበታቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡ ያም ብቻ አይደለም ምሁራዊ ቅርርብ ጥንዶቹ ስለሚያወሩት ጉዳይ ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በብዙ ነገሮች የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል፡፡

2 . ማህበራዊ ቅርርብ በህይወት ዙሪያ ስለሚያጋጠሙ ነገሮች /ጉዳዮች/ ጊዜን ሰጥቶ መነጋገርና መወያት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ክስተቶች ውስጥ በጋራ ያሳለፉዋቸው፣

ሌሎቹ በተለያዩ ጊዜ የተፈጠሩና በግልጽ ንግግር የተጋሩዋቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የህይወት አብዛኛው ጊዜ የሆነ ነገር ማድረግን የሚያካትት ነው፡፡ ጥንዶቹ ነገሮችን በጋራ ከፈፀሙ ውጤቱ በቡድን (በቅንጅት) የመስራትን ብቻ ሳይሆን የመቀራረብ ስሜትን ማሻሻል ነው የሚሆነው፡፡ ይህ የሚሆነው በውይይት /

ንግግር/ ሂደት ቅርበቱ የአብሮነት /የአንድነት/ መንፈስን የሚፈጥር በመሆኑ ነው፡፡

3 . ስሜታዊ ቅርርብ ስሜቶች በአምስቱ የስሜት ህዋሶቻችን አማካይነት ለሚያጋጥሙን ነገሮች በቅፅበት (ሳናስብ) የምንሰጣቸው ምላሾች ናቸው፡፡ የእሳት አደጋ መኪና

በዋናው መንገድ አቅጣጫ ሲበር ብመለከት የመረበሽ ስሜት ይፈጠርብኛል፡፡ ባለቤቴ እጄን ስትነካኝ የፍቅር ስሜት ይኖረኛል፡፡ መሰል ምላሾቻችን መጋራት በትዳር ህይወት ስሜታዊ ቅርርብ እንዲገነባ ያደርጋል፡፡

4 . መንፈሳዊ ቅርርብ ብዙ ጊዜ በትዳር ትኩረት የሚሰጠው ነገር ግን በቅርርብ ላይ ከፍተኛ እገዛ ያለው መንፈሳዊ አንድነት ነው፡፡ በዝርዝር የእምንት ጉዳዮች ዙሪያ

መስማማት አይጠይቅም፡፡ ይልቁንም ተጓዳኞቹ በውስጣቸው እየሆነ ያለውን እርስ በእርስ ለመነጋገር (ለመንገርና ለመስማማት) መሻት ነው የሚያስፈልገው፡፡ በተጨማሪም ስለ መንፈሳዊ እውነታ መወያየት ዋና ግቡ መስማማት ብቻ ሳይሆን ግንዛቤን ማግኘት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቅርርቡን ጥብቅ ያደርገዋል፡፡ በሌላ አነጋገር ባለ ትዳሮች በስራ፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ያጋጠሙንን ክስተቶች ውሎዋቸውን ሲጋሩ ጥልቅ

ስሜታቸውን እርስ በርሳቸው ይገልፃሉ፡፡

5 . አካላዊ (ወሲባዊ) ቅርርብ ለዘላለም ያቆየውና ወንዶችና ሴቶች የተለያዩ መሆናቸውን ወሲባዊ ቅርርብ ማድረግን የተለመደ አድርጎታል፡፡ ብዙ ጊዜ የባል ትኩረት በአካላዊ ነገሮች

ማለትም እይታ፣ መነካካትና ወሲባዊ ንቃት ላይ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሚስት ወደ ወሲባዊ ቅርርብ የምትገባው የበለጠ ፍላጎቷን በጠንካራ ግንኙነት ላይ በማድረግ ነው፡፡ እናም የመፈቀር፣ የመደነቅና የመንከባከብ ድርጊቶች ሚስትን ወደ ታላቅ ሐሴት ያመጣታል፡፡ ስለዚህም አካላዊ (ወሲባዊ) ቅርርብ እነዚህን ልዩነቶች በአግባቡ በመረዳት ምላሽን መስጠት ማለት ነው፡፡

እንግዲህ እነዚህ አምስቱ የመቀራረብ ጎኖች በትዳር መካከል ጥሩ ፍቅር ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የጓደኝነት መንፈስ እንዲዳብር ፍቅርም እንዲለመልም ትልቅ ሚና ያላቸው እሴቶች ናቸው፡፡

በትዳር ጥብቅ ቅርርብን እንዴት መለማመድ ይቻላል? በትዳር ፍቅር ትልቅ ቦታ እንዲኖረው የጓደኝነት

መንፈስ ማበብ አለበት፡፡ የጓደኝነት መንፈስ ደግሞ ከጥልቅ መቀራረብ የሚመነጭ ሲሆን ተጓዳኞቹ ከማስመሰል ይልቅ ራሳቸውን ሆኖ መገኘት ያስፈልጋቸዋል በመቀራረብ ሂደት ወደ አንድነትና ጥልቅ ግንኙነት በመገባት በልዩነቱ መደሰት ማለት እንጂ ልዩነቱን ማጥፋት አይደለም፡፡ ሴቶችና ወንዶች የተለያዩ መሆናቸውን በመገንዘብ እነዚያን ልዩነቶች ለመልካም እንኳን ቢሆን ለማጥፋት መነሳት የለባቸውም፡፡ ስለሆነም ልዩነቶችን በሚገባ መገንዘብ፣ ተቆርቋሪ በመሆንና ስሜታዊ አንድነትን ለመፍጠር በሚደረግ ጥረት ቅርርብን መላመድ ይቻላል፡፡

በትዳር ጥብቅ ቅርርብ እንዳይኖር የሚያደርገው ምንድነው?

ሁላችንም ለራስ ክብር ከፍተኛ ዋጋ የምንሰጥ ፍጡር ነን፡፡ እናም ለራሳችን ብቻ ትኩረትን ስንሰጥ መኖር የሚገባውን ቅርርብ እናጣለን፡፡ መሰል ባህሪይ ጥብቅ መቀራረብን ብቻ ሳይሆን ፍቅርንም ይሸራርፋል፡፡

የራስ ወዳድነት ተቃራኒው አንድና አንድ ብቻ ነው፡፡ እሱም ፍቅር ነው፡፡ ፍቅር በትዳር አጋር ሁለንተናዊ መልካምነት እንዲያተኩር ያደርጋል፡፡ ስለዚህ ባል የሚስትን ሚስትም የባልን እሳቤዎችን፣ ስሜቶችና ፍላጎቶች ለማድመጥ ጊዜ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ለማድረግና ውስጣዊ ስሜትን ለመጋራት ተነሳሽ መሆን ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው የማይመቻቸውን ነገርም ቢሆን ለመፈፀም ፍላጎት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ይህንን የሚያደርጉት በቃ ለእርስ በእርሳቸው እንክብካቤን ለማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ ጥብቅ ቅርርብን የሚያዳክሙ ነገሮችን በራስ ዙሪያ ብቻ ከማሽከርከር የተጓዳኝን ፍላጎት፣ ስሜት፣ እሳቤ፣ ውጥን፣ እምነትና ግንዛቤ ለመጋራት ለመማማር ጊዜና ቦታ መስጠት አስፈላጊ ይሆናል ማለት ነው፡፡

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

(በወንዶች ብቻ የሚነበብ) ከፍቅረኛችሁ ጋር ስለመኝታ ቤት ምስጢራችሁ

ተወያይታችሁ ታውቃላችሁ? ስንፈፅመው የማይከብደን በግልፅ ለማውራት ግን ዳገት የሚሆንብን አንድ ጉዳይ ካለ የመኝታ ቤት ምስጢር ነው፡፡ ብዙዎቻችን ይሄን ጉዳይ ልናነሳው አንወድም፡፡ ፍቅረኛህ የወሲብ ስሜቷ ቢቀንስ ወይንም ብትቀዘቅዝብህ ምን ታደርጋለህ? ምስጢር ሆኖ እንዲቀር ከመረጥክ ውጤቱ እስከመለያየት ሊያደርስ ይችላል፡፡ እናስ ምን ይሁን? መፍትሄው በእጅህ ነው፡፡

‹‹አንተና ፍቅረኛህ ማናቸውንም ጉዳዮች በግልፅ የምትነጋገሩ ከሆነና በተቀረው ግንኙነታችሁ ሁሉ ደስተኛ ከሆናችሁ ያለምንም ሀፍረት ስለ መኝታ ቤት ምስጢራችሁ (ወሲብ) መነጋገር አሁኑኑ ጀምሩ›› ይላሉ አሜሪካዊው የስነ ልቦናው ባለሙያ ክሊፎርድ ሳጀር፡፡

ፍቅር መስራት እንደምትፈልግ ጠይቃትና ምላሿን ተመልከት፡፡ አሉታዊ ከሆነ አትቆጣ፣ ለምን እንደማትፈልግ ጠይቃት፡፡ በጥያቄህ ልትደናገጥ ትችላለች፡፡ ግን ደግሞ ጉዳዩ በመነሳቱም እፎይ ልትል ትችላለች፡፡ በእርግጥ አደገኛ ጠርሙስ ይሆናል የከፈትከው እናም ላፈጠጡ እውነቶች ራስህን አዘጋጅ፡፡ ይሄኔ ለምን የወሲብ ስሜቷ እንደቀነሰ ትረዳለህ፡፡ እርሷ ጉዳዩን ለመወያየት ፈቃደኛ ካልሆነችስ? ሳትሰለች ጉዳዩ እንዴት ለሁለታችሁም ደስታ ወሳኝ እንደሆነ አስረዳት፡፡ በፍቅራችሁ መሀል አንድም እንቅፋት እንዲኖር እንደማትሻም ንገራት- ያኔ ታሸንፋታለህ፡፡

ባልታወቀ ምክንያት እንደቀድሞው ከፍቅረኛህ ጋር ፍቅር መስራት አቁመሃል እንበል፡፡ በዚህም የተነሳ ፍቅራችሁ ቀዝቅዟል፤ እንደቀድሞው ፍቅር ለመስራት ብንሞክር ሁሉም ነገር ወደ ቦታው ይመለሳል ልትል ትችላለህ፡፡ እሷ ደግሞ ከወሲብ በፊት ነገሮች ወደቀድሞው ቦታቸው መመለስ አለባቸው ትላለች፡፡

ይሄኔ ምን ታደርጋለህ? ‹‹ስለወሲብ ህይወታችሁ ውይይት በተነሳ ቁጥር በንትርክ

የሚቋጭ ከሆነ ሶስተኛ ሰው ያስፈልጋችኋል›› ይላሉ ሴክስ ትራፒስቷ ሔለን ክሮህን፡፡ ‹‹ግን ውሽማ ማለት አይደለም›› ሲሉም ይቀልዳሉ፡፡ ‹‹ወሲብ ብዙ ጊዜ ሁለተኛው ችግር ነው ሌላ የማይነሳ ጉዳይ አለ›› የሚሉት ክሮህን፣ ነጥቡ ችግርን ለይቶ ማወቅ ላይ ነው ይላሉ፡፡ ‹‹ችግሩ ለቤት ጉዳይ የሰጠኸው አነስተኛ ጊዜ አሊያም አይንህን ሌሎች ሴቶች ላይ መጣልህ ሊሆን ይችላል›› ሲሉም ያስረዳሉ- ቴራፒስቷ፡፡

ለአፍላ የፍቅራችሁ ስሜት ስጦታዎች ታጎርፍላት ይሆናል፣ እራት ትጋብዛታለህም፣ በየሰዓቱ ስልክ ትደውል ነበር፣ አድናቆትህ እንደ ጉድ ነበር፡፡ እሷም በምላሹ ፍቅር ለመስራት ፈቃደኛ ነበረች እንበል፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ትኩረትህ ወደ ስራ ሆነ፡፡ ለልጆችህ ማስተማሪያ ገንዘብ ማጠራቀም፣ በማህበራዊ ጉዳዮች መታሰር መጣ፡፡ ግን አሁንም ትወዳታለህ፡፡ እሷ ግን መወደድህን የምታውቅበት መንገድ ስለሌለ የወሲብ ስሜቷ ይቀንሳል፡፡ ይሄኔስ ምን ማድረግ አለብህ?

አንድ የቆየ ቀልድ አለ፡፡ ‹‹አንዱ አንዲት ሴት ካንተ ጋር ወሲብ መፈፀም እንድታቆም ምን ታደርጋለህ›› ተብሎ ሲጠየቅ፣ ‹‹አገባታለሁ›› ብሏል፡፡ ነገሩ ግን እንደዛ መሆን እንደሌለበት

ልታውቅ ይገባል፡፡ የተበላሸውን ግንኙነት ለማስተካከል እሷ ሳታስበው በጊዜ

እቤት ገብተህ እራት አዘጋጅ፡፡ በጓደኞችህ ፊት እቀፋት፣ ሳማት፡፡ ከዚህ ሁሉ የትዳር ዓመታትም በኋላ ‹‹ንግስትህ›› እርሷ እንደሆነች በአደባባይ አሳይ፡፡ የተዋወቃችሁ ሰሞን የምትሰሩትን አይነት ፍቅር እንደ አዲስ ጀምሩት፡፡ መናፈሻ ውስጥ ርካሽ አልቤርጎ ተከራይታችሁ ወይም ከከተማ ወጣ ብላችሁ ያን መልካም የፍቅር ጊዜ አስታውሱ፡፡ አሁንም የምትፈቀር፣ ልዩና ማራኪ መሆኗን በተግባርህ አሳያት፡፡ ይሄን የምታደርገው ግን ሁልጊዜ እንጂ ፍቅር መስራት ሲያሰኝህ ብቻ አይደለም፡፡

ሴት ልጅ እንደወለደች የወሲብ ስሜቷ ሊቀንስ ይችላል፡፡ የጡት ወተት የሚያመርተው ፕሮላክቲን የተባለው እጢ መጨመር ከምክንያቶቹ አንዱ ነው፡፡ የስነ ልቦና አማካሪ የሆኑት ካሬን ክሌይማን እንደሚሉት ‹‹ሴት ከወለደች በኋላ ስለሰውነት ክፍሎቿ የተወነባበደ አዲስ ስሜት ሊፈጠርባት ይችላል›› ድካም፣ ጭንቀት፣ ዳግም አረግዛለሁ የሚሉ ስጋቶች ከወሲብ ስሜት ያራርቃታል፡፡ በእርግጥ ብዙዎቹ ሴቶች ልጅ ከወለዱ በኋላ ባለው ከ4-6 ወር ጊዜ ውስጥ ወሲብ መፈፀም ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ግን በስሜትም ሆነ በአካል ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ለመሆን ረዘም ያለ ጊዜ ያሻቸዋል፡፡ እናም ለሚስትህ ጊዜ ስጣት፡፡ ግን ደግሞ ራቃት ማለት አይደለም›› ይላሉ ክሌይማን፡፡ ‹‹ሁሌም አዋራት፣ እቀፋት፣ አሻሻት፣ ሳማት›› ዋናው ነገር ይላሉ ባለሙያዋ እራሷ ‹‹አንዳች ችግር አለብኝ አንዴ?›› የሚል ስሜት እንዳይፈጠርባት ማድረግ ነው፡፡

ሴቶች ከመደቡት የተነሳ የወሲብ ስሜታቸው ሊቀንስ

ይችላል፡፡ ሐኪሞች ሴቶች የመደበት ስሜት ውስጥ እንደገቡ ከሚያውቁበት ምልክቶች አንዱ የወሲብ ስሜት መቀነስ ነው፡፡ ፍቅረኛህ (ሚስትህ) በድብርት ስሜት መያዟን ከተረዳህ የመጀመሪያ እርምጃህ በሚያፅናና ስሜት ድብርት ውስጥ መሆኗን ማሳወቅ ነው፡፡ ከዚያስ? እንደምታፈቅራትና ሁሌም ከጎኗ እንደሆንክ በልበ ሙሉነት ንገራት፡፡ ምንም ነገር ካላስደሰታትና ድብርቱ ከበረታ ወደ ሐኪም እንድትሄድ ገፋፋት፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሳታውቀው ስለውፍረቷ በንቅፈት አስተያየት ሰንዝረህ ይሆናል፡፡ ‹ቦርጭሽ በዝቷል፣ መቀመጫሽ ሰፍቷል... ወዘተ› በሚሉ አስተያየቶች ሰውነቷን እንድትጠላው አድርገሃል? እንዲያ አድርገህ ከሆነ የዘራኸውን ነው ያጨድከው፡፡ ሰውነቷ እንደሚያስጠላ እየነገርካት እንዴት የወሲብ ስሜት ይኖራታል? አሁን አካሄድህን አስተካክል፡፡ ተወዳጅና ተፈላጊ መሆኗን ደጋግመህ ንገራት፡፡

በጣም የሚያስገርመው ጥንዶች ለዓመታት ሁለቱም ወገኖች ደስታን የሚያገኙበት ወሲብ እየፈፀሙ ሊኖሩ መቻላቸው ነው፡፡ አንደኛቸው ሌላኛው እርካታ እያገኘ እየመሰላቸው ይቀጥላሉ፡፡ ይሄ ከባድ አደጋ ነው፡፡ ሁላችንም የራሳችንን እርካታ ፍለጋ ስለምናተኩር፣ ወሲብ ሰጥቶ የመቀበል ጨዋታ መሆኑን እንዘነጋዋለን፡፡ ሁሌም የፍቅረኛህ እርካታ ላይ ስታተኩር ያንተም የወሲብ እርካታ እየተሻሻለ እንደሚመጣ ባለሙያዎች ይመሰክራሉ፡፡ ፍቅር መስራት ከመጀመራችሁ በፊት ስለፍላጎቷ ጠይቃት፡፡ እንዴት? ምን እንደምትፈልግ በግልፅ ትነግርህ ዘንድ ሁኔታዎችን አመቻችላት፡፡ ያኔ እኩል ትሞቃላችሁ፤ እኩል ትቀዘቅዛላችሁ መልካም የፍቅር ጊዜ!!

Telba (Ethiopian flaxseed beverage)

Telba is a healthy and refreshingly creamy bev-

erage. Be careful how much you drink, though.

Telba is a mild laxa-

tive.

4 to 6 servings

Ingredients Flaxseed -- 1 cup

Water -- 6 cups

Honey -- 1 to 2 table-

spoons

Method Heat a cast-iron

skillet over

low heat. Add the flaxseed and dry

roast it in the skillet, stirring, for about

5-10 minutes. Remove from heat and

set aside to cool.

Place the toasted flaxseed in a spice grinder

and grind to a powder. Sift through a

medium-mesh sieve into a bowl.

Add the water to the flaxseed, stir and let

set for about 10-20 minutes to allow

solids to settle out.

Strain into a pitcher, add honey and chill

before serving.

Variations Telba Firfit: Mix telba with broken up pieces of

injera bread and heat. Serve as a sidedish.

Toasted, unhulled barley and sunflower seeds

are sometimes added to telba for additional

flavor.

ከማርታ ፔድሪኒ

የህልበት አሰራርየህልበት አሰራር

ስንቶቻችን እንሆን ህልበትን የምናውቀው? በጾም ግዜ የሚበላ ምግብ ነው።

ህልበት የሚሰራው ከባቄላ፣ ምስር እና የበቀለ አብሽ ዱቄት ነው። (ህልበት እና ስልጆ አንድ አይደሉም ይለያያሉ)

መጀመሪያ ዱቄቱ ሲዘጋጅ 3 ኬሎ ...የተከካ ባቂላ እሩብ ከሎ በደምብ የተከካ ምስር እሩብ ኬሎ የበቀለ አብሽ እነዚህ ሲፈጩ የህልበት ዱቄት ይሆናሉ። አሰራሩ መጀመሪያ በንጹህ ድስት 2 ኩባያ ውሀ እንጥዳለን።

ከዚያ ውሀው እስኪፈላልን ድረስ በንጹህ ሳህን 4 የጠረጴዛ ማንኪያ የህልበት ዱቄት በአንድ ኩባያ ቀዝቃዛ ውሀ እንበጠብጠዋለን። ...ከዚያ ውሀው ሲፈላ የበጠበጥነው ቀስ እያልን እየጨመርን ማማሰል ... ወፈር እስኪል ድረስ እናማስለዋለን። በደምብ ሲበስል ልክ እንደሽሮ ... አውርደን በሌላ እቃ ገልብጠን እናቀዘቅዘዋለን ...ከዛ ሰፋ ባለ ሳህን ላይ አድርጎ እስኪኮረፍ እና መልኩ እስኪቀየር (ነጭ ) እስኪሆን ድረስ በደምብ ይመታል። ይመታል ያኔ ለምግብነት ሲዘጋጅ በደምብ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት እና ቃርያ አድርገን እናዋህደዋለን።

ቂቤ ለማንጠርቂቤ ለማንጠር አራት መአዘኖቹን የዳቦ ቅቤዎች (ጨው የሌለበትን)

ከሱፐርመርካቶ መግዛት። ከዛ ቅቤውን በተገኘው ቅመም (ጥቁር አዝሙድ, ኮሰረት, ኮረሪማ ... ይበቃል) መለወስና ከሁለት እስከ ሶስት ቀን ማስቀመጥ። በለስላሳ እሳት ማንጠር እና ማጥለል። የቅቤ ቅመም ከሀገር ቤት የምታስመጡ ከሆነ ግን ተቀላቅሎ የተፈጨው ጥሩ ነው። ለማንኛውም የተፈጨው ከሌላችሁ ኮረሪማውን (የተፈለፈለ) መቼም የቡናም ብረት ምጣድ ወይም ማንከሽከሻ አታጡም በሱ ትንሽ እሳት ሳታበዙ አመስ አመስ ካደረጋችሁ በኃላ አውጡትና በቡና መፍጫ በደንብ ጠራርጋችሁ ትፈጩታላችሁ። ከዛ አራት መአዘኑን የዳቦ ቅቤ ጋር ቀላቅለሽ ያው በለስላሳ እሳት ማንጠር ነው።

እዚህ የቂቤ ቅመም የት እንደሚገኝ ልጠቁማችሁ እወዳለሁ። ይህንን ማንም የሚያውቀው ሰው እንደሌለ አውቃለሁ። ህንዶች ቤት ታገኛላችሁ። ኮረሪማ፣ ጥቁር አዝሙድ፣ ... ወዘተ ... ከፈለጋችሁ። ኮሰረት ግን የሚገኝ አየመስለኝም።

ለወቅታዊ መረጃ

Zehabesha.com

ሕመም የትኛውም አካል ላይ ሲከሰት ያሰቃያል። የሕመም ትንሽ የለውም። ይሁንና አንዳንዴ ሕመምን ከሕመም የማበላለጥ ሃሳብ ይሰጣል። «እንደ ጣት ቁስል አትነ ዝንዘኝ» የሚለው የጣት ቁስለትን ጥዝጣዜ ያመለክታል። ይህን የጠቀስኩት ብዙውን ጊዜ ከእግር ጣትና እጅ ላይ የሚከሰተውን ሕመም ምንነት መከላከያና ሕክምና ወዘተ የተመለከቱ መረጃዎችን ለመስጠት አስቤ ነው። - ስለ «ጋንግሪን። »ስለ ጋንግሪን ማብራሪያ የሰጡን ዶክተር ሄለን ይፍጠር ይባላሉ። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔ ሻሊስት ሐኪምና በስኳር ሕመም ትምህርትና ጥናት ላይ የሚገኙ ምሁር ናቸው።

ጥያቄ፡- ጋንግሪን ምንድን ነው? ዶክተር ሄለን፡- ጋንግሪን ወደ አማርኛ ሲመለስ በደም እጥረት

የሞተ የሰውነት ክፍል እንደማለት ነው። አንድ የሰውነት ክፍል ደም አጥሮት ምግብና ኦክስጅን አልደርሰው ብሎ ሲጠቁር ሕይወት አልባ ሆኖ ሲሞት ጋንግሪን ተፈጥሯል ማለት ነው።

ጥያቄ፡- የጋንግሪን መነሻ ወይም መከሰቻ ምክንያቶች ምን ምን ናቸው?

ዶክተር ሄለን፡- አንደኛ በተለያዩ አደጋዎችና ምክንያቶች የደም ዝውውር ቢቋረጥ ያ ዝውውሩ የተቋረጠበት የሰውነት ክፍል ጋንግሪን ይፈጥራል።

ሁለተኛ የልብ ችግር ያለባቸው ሰዎች ደም ይረጋና ከልብ ወደ ደም ሥሮች ይሄዳል። ትንሽም የረጋች ደም ብትሄድ መተላለፊያ ትዘጋለች። ይህች የረጋች ደም የዘጋችው የደም ሥር ይመግበው የነበረው የአካል ክፍል ጋንግሪን ይፈጥራል። በደም ምግብና አየር እጥረት ምክንያት ይሞታል።ሦስተኛ በደም ሥር ጥበት ጋንግሪን ይፈጠራል። በረጅም ጊዜ የመጣ የስኳር ሕመምተኞች፣ የደም ግፊት ችግር ያለባቸውና የደም ቅባት ከፍ ያለባቸው ሕሙማን የደም ሥራቸው ሊጠብ ይችላል። ደም ሥራቸው ላይ ቅባት እየተጋገረ ጠቦ በመጨረሻ የደም መተላለፊያ ይዘጋል። ደም ከተቋረጠበት አካል በታች ያለው ሰውነት ጋንግሪን ይፈጠርበታል።

አራተኛው ምክንያት ኢንፌክሽን ነው። የሰውነት ክፍል ኢንፌክሽን ፈጥሮ ሲያብጥበትና በባክቴሪያ ሲጠቃ በደም ሥር ደም አይደርሰውም። የምግብ ዑደቱ ስለሚቋረጥ ጋንግሪን ይፈጠራል ይሞታል።

ጥያቄ፡-የጋንግሪን ሕመም በዘር ይተላለፋል? ዶክተር ሄለን።- በተወሰኑ የደም ስር ችግሮች (እንደ ስኳር ባሉ) በዘር የሚመጣ ችግር በጣም አነስተኛ

ነው። ነገር ግን ስኳር ሕመም ሳይኖርም በማጨስና በሌላም ምክንያት የደም ዝውውርን መዝጋት ጋንግሪን ሊያመጣ ይችላል። ዋና መነሻዎች የሚባሉት ረዥም ዓመት የቆየ የደም ግፊት፣ የስኳርና የደም ቅባት (ኮሌስትሮል) ችግሮች የደም ሥር ጥበትና መዘጋት ናቸው።

ጥያቄ፡- ጋንግሪን በአገራችን ምን ያህል ችግር እያደረሰ ነው? ዶክተር ሄለን፡- የጋንግሪን ሕመም የሚከሰትባቸው ሰዎች ከሃምሳ ከመቶ በላይ የስኳር ሕመም ያለባቸውና

በስኳር ሕመም መያዛቸውን የማያውቁ ናቸው። የእግር ቁስለት ያጋጠማቸውና በጋንግሪን የታመሙ ሲመረመሩ ስኳር ሕመምተኛ ሆነው ይገኛሉ። የዓይንና የነርቭ ችግር አጋጥሟቸው ሲመረመሩም ስኳር ሕሙማን ሆነው ይገኛሉ።በዓለም አቀፍ ደረጃ ከስኳር ሕሙማን ከአሥራ አራት እስከ ሃያ አራት ከመቶ ቢያንስ አንድ ጊዜ የእግር ቁስለት ያጋጥ ማቸዋል። ከእነዚህም ሃያ አምስት ከመቶው በቁስለቱ ምክንያት የእግር መቆረጥ ያጋጥማቸዋል። በአገራችንም ከሕክምና ክትትልና ስኳርን ከመቆጣጠር ባህል እንዲሁም ስኳርንና የእግር ቁስለትንም ሆነ ጋንግሪንን ቀድሞ ከመከላከል ዝቅተኛነት የተነሳ እርግጡን መናገር ባይቻልም ከዓለም አቀፉ ተሞክሮ እንደ ሚበልጥ ይገመ ታል። በጥናት ባይሆንም በየቀኑ የሚታየው ይህ ነው። በአገራችን ምልክት የማያሳየው 2ኛው ዓይነት ከሰላሳና አርባ ዓመት በኋላ የሚከሰተው የስኳር ሕመም እየተስፋፋ ነው። የእግር ቁስለትና የጋንግሪን በሽታም በዚያው መጠን የሕሙማኑን ጉዳት እያባባሰ ነው።

ጥያቄ፡- የጋንግሪን በሽታ መከላከያ ምንድን ነው? ዶክተር ሄለን፡- ዋናው መከላከያው የስኳርን ሕመም መኖር አለመኖር ቀድሞ ተመርምሮ ማወቅ ነው።

2ኛው ዓይነት የስኳር ሕመም (ከጉልምስና ዕድሜ ጀምሮ የሚከሰት) ምልክት የለውም። በቅድሚያ መመርመር። የደም ግፊት ካለም ቀድሞ መመርመር። የሚያጨሱ የልብ ችግር ያለባቸው ክብደታቸው ከፍ ያለና በዘር የስኳርና የግፊት ችግር ያለባቸው ቀድመው መመርመር አለባቸው።

ስኳር ከተገኘ ሕክምናውን በሚገባ መከታተል፣ ግፊትና የደም ቅባትን መቆጣጠር፣ ማጨስን ማቆም፣ ለእግር ጥንቃቄ ማድረግ ጋንገሪንን ቀድሞ መከላከል ነው።

ጥያቄ፡- የጋንግሪን ሕመም ሕክምናው ምንድን ነው? ዶክተር ሄለን፡- ጋንግሪን የሞተ የአካል ክፍል ላይ የሚከሰት በመሆኑ መወገድ ብቻ ነው ሕክምናው። እጅና

እግር ላይ የሞተ አካል ዝም ከተባለ ይስፋፋል። ወደ ሌሎች አካባቢዎች ይሠራጫል። ለከፍተኛ ሕመምና ሞት ይዳርጋል። በምግብና ኦክስጅን እጥረት የሞተ አካል በመሆኑ ማስቀጠል አይቻልም። እንዳይፈጠር መከላከል እንጂ ጋንግሪን ከተፈጠረ ያ የተፈጠረበት አካል ሕይወት አልባ ስለሆነ የትም አገር ቢኬድ ተቆርጦ ነው የሚወጣው።

ጥያቄ፡- ጋንግሪን በእግርና በእጅ ላይ ብቻ ነው የሚከሰ ተው? ዶክተር ሄለን፡- ብዙውን ጊዜ በእግርና እጅም ላይ ይከሰታል። እጅና እግር ላይ የሚወጣው ነው «ጋንግሪን»

የተባለው። ሆኖም በሌላ የሰውነት አካልም የደም ዝውውር ቢቋረጥ ጋንግሪን ሊፈጠር ይችላል። ጥያቄ፡- ብዙ ጊዜ በእግር ላይ የሚከሰት ከሆነ ለእግር የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈ ልጋል? ዶክተር ሄለን፡- አዎ! ለእግር የተለየ ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የነርቭ ችግር የደም ሥር ጥበት ከተከሰተና የስኳር

ሕመም ካለ በየቀኑ እግርን ማየት በዓመት አንድ ጊዜ እግርን መመርመር ያሻል። « የደም ዝውውሩ ጥሩ ነው አይደለም በእግሩ ላይ ያለ ስሜት ቀንሷል? የእግር ቅርጽ ለውጥ አለ?» የሚሉት ይመረመራሉ። ቁስል የነበረበት ከሆነም መታወቅ አለበት። ከእነዚህ አንዱ ችግር ካለ ለቁስለትና ለመቆረጥ እንዳይ ጋለጥ መከላከል ይገባል። ግለሰቡ በየቀኑ እግሩን ማየት አለበት። በላይ፣ በታች ፣በጣቶቹ መሐል ስሜት መኖሩን ለውጥ መከሰቱን ልብ ማለት አለበት። በየቀኑ ማታ መታጠብ ማድረቅና ደርቆ ተሰነጣጥቆ ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር እንደሎሽን ያሉ ቅባቶችን መቀባት ይመከራል፡፡ ጥፍሩን ሲቆርጥ በምላጭ በሰንጢ ሳይሆን በጥፍር መቁረጫ መሆን አለበት፡ አቆራረጡ በቀጥታ (አግድም) ነው፡፡ ጎንና ጎኑን በሞረድ ማስተካከል ይበቃል። ይህ አቆራረጥ ለሁሉም ሰው ጥሩ ነው።

ሌላው ጥንቃቄ የጫማና ካልሲ ነው። ስልሳ ከመቶው የእግር ቁስለት በስኳር ሕሙማን ላይ የሚከሰተው ከጫማ ጋር በተያያዘ ነው። አዲስ ጫማ ይጠባል፤ ብዙ ይኬድበታል፤ እግር ይላጣል ፤ ውሃ ቋጥሮ ችግሩ ይጀምራል። ጫማ ማሠሪያ ያለው፣ ጫፉ ሹል ያልሆነና ብዙ ሙቀት የማይፈጥርና የሚመች መሆን አለበት። ሴቶች ባለተረከዝ ጫማና ክፍት ጫማ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው መተው አለባቸው። በቤትና በየትኛውም ቦታ በባዶ እግር መሄድ ክልክል ነው። ካልሲም የጥጥና ጫፉ ተቀዶ ጣትን ለጫማ ፍትጊያ የማያጋልጥ መሆን አለበት።

ጥያቄ፡- ጥፍርን ገባ ብሎ መቁረጥ ለጋንግሪን እንደሚያጋልጥ የሚነገረው እውነት ነውን? ዶክተር ሄለን፡- ጥፍርን በመቆረጥ ብቻ ጋንግሪን ሊመጣ ይችላል ማለት አይደለም። የእግርና የእጅ መቁሰል

ወደ ጋንግሪን የሚሄደው አስቀድሞ የስኳር፣ የደም ስር ጥበትና መሰል የጤና ችግር ነው። በሽታ የመከላከል አቅማቸው ከሌላው ያነሰ ነውና በትንሽ ክፍተት ኢንፌክሽን ይፈጥርና ባክቴሪያ ይይዝና ቶሎና በቀላሉ የማይድን እብጠት ይፈጠራል። በተለይ የስኳር ሕሙማን ከጥፍሩ ጋር የተያያዘውን ሥጋ ከነኩ በቀላሉ ለችግሩ ይጋለጣሉ።

ጥያቄ፡- የእግር ቁስለት ወደ ጋንግሪን ተቀይሮ ሙት ወይም ሕይወት አልባ የሆነበት ሰው ጣቱ ወይም እግሩ መቆረጥ እንዳለበት ሲነገረው ምን ይመልሳል?

ዶክተር ሄለን፡- ሰውኛ ነው። ማንም ሰው አካሉን ማጣት አይፈልግም። ማንም ሰው ቶሎ አይቀበለውም። በጣም የታመመ ወይም ሕይወቱ አደጋ ላይ የሆነ ካልሆነ በቀር ወዲያው አይስማማም። « የሚሆን ነገር ሞክሩልኝ እንጂ!» ይላል።

ጥያቄ፡- ውሳኔያችሁን አልቀበል ብሎ የሚሄድ አለ? ዶክተር ሄለን፡- እንቢ ብሎ በጊዜ ሳይስፋፋ ይቆረጥ ተብሎ ጥሎ ሂዶ ብሶበት የሚመጣ አለ። አማራጭ

ሲያጣ ነው የሚስማማው። እኛ ግን ቆስሎ ጠቁሮ ከሞተ መመለስ አይቻልም። ሌላ ሕክምና የለውም ብለን እናስረዳለን።

ጥያቄ፡- የአሁኑ መልዕክትዎ ምንድን ነው? ዶክተር ሄለን፡- ቀድሞ መከላከል። ስኳርን መመርመር፤ ቁስለት ከተከሰተ በባለሙያ መታከም ነው። የደም

ስር ጥበትንና የሚሞት አካልን በሌላ ደም ስር ደም እንዲያገኝ የሚያደርጉ አዳዲስ ሕክምናዎች አሉ። ቁስለት ሲኖር በቅባት፤ በሎሚ... ከማለት ቀድሞ መታከም ይገባል። ቁስለቱ ተባብሶ ሆስፒታል እስከሚተኙ መጠበቅ ችግሩን ያበዛዋል።

ጥያቄ፡- አመሰግናለሁ!

ዶክተር ሄለን ፡- እኔም አመሰግናለሁ!

አንዳንድ ጊዜ ከዘመናዊ የህክምና ዘዴ ውጪ የሚከናወኑ የሀገረሰብ (ተፈጥሯዊ) የህክምና ዘዴዎች ለሰው ልጅ ጤና እያበረከቱ ያሉትን አስተዋፅኦ መመርመር አስፈላጊ ነው፡፡ ጠቃሚ ሆነው ሲገኙ ማበረታታት ጉዳትም ካላቸው ለተጠቃሚው ያለውን እውነታ በሳይንሳዊ መረጃ አስደግፎ ማቅረቡ ተገቢ ነው፡፡ ለዛሬም አንድ የሀገረሰብ ህክምና ወደ ሚሰጥበት ስፍራ በማምራት በህክምናው ያገኙትን ጥቅም መጠየቅ ጀመርኩ፡፡

‹‹...ለአስር ዓመታት በከባድ የጀርባ ህመም እሰቃይ ነበር፡፡ አሁን ይመስገነው ይህን ህክምና ከጀመርኩ በኋላ ትልቅ ለውጥ አለኝ››

አንድ ተጠቃሚ ካይሮፕራክቲስ ህክምና ያስገኘለትን ውጤት እንዴት እንዳገኘው በጠየኩት ጥያቄ የሰጠኝ ምላሽ ነበር፡፡

ወደሌላኛው የአገልግሎቱን ተጠቃሚ ተመሳሳይ ጥያቄ አሻገርኩላት፡፡ በነጠላ ተሸፍና የነበረ ፊቷን ለመግለጥ እየሞከረች ‹‹...ዛሬ እዚህ ቆሜ ስትመለከተኝ ነገሮች ሁሉ ቀላል ሊመስልህ ይችላል፡፡ ለዓመታት

ወገቤን ጎንበስ ካልኩበት ነቃ ለማድረግ ትልቅ ፈተና ነበረብኝ፡፡ ያልሞከርኩት ህክምናም ሆነ ፀበል አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን

ለውጥ አላገኘሁበትም፡፡ ...አሁን በሰው በሰው ሰምቼ ይህን ህክምና መከታተል ጀመርኩ፡፡ እንደምታየኝ እንደፈለኩ ጎንበስ ቀና ማለት

እችላለሁ፡፡›› ለእኔ ለማሳየት ያህል ከመሬት ጎንበስ ብላ አንዲት ጠጠር አነሳች፡፡ እውነትም ያለ ምንም ችግር መንቀሳቀስ ትችላለች፡፡ ይህ የእኔ የእማኝነት ቃል ነው፡፡ ስለ ህክምናው ውጤታማነት ብዙ ምስክር ማፈላለግ አላሻኝም፡፡ ከዚህ ይልቅ በቀጥታ ስለዚህ ታምረኝ የህክምና ዘዴ የሚያወሱ መረጃዎችን ማገላበጡን ተያያዝኩት ብዕሬንም አነሳሁ፣ በተረዳሁት መጠን ለእናንተ ለማጋራት ወሰንኩ፡፡

የህብረ ሰረሰር አጥንትን መሰረት ስላደረገው የካይሮፕራክቲስ ህክምና መፅሐፍ ውስጥ ስለዚሁ የህክምና ዘዴ ተፅፎ የሚገኘውን ፅሑፍ ያስታውሰናል፡፡ ጥንታዊ ግብፃውያን እንዲሁም የዘመናዊ ህክምና አባት ተብሎ የሚጠራው አርስጣጥሊስም የጀርባ አጥንት መሰረት ያደረገው ህክምና ያከናወኑ እንደነበረ ጥንታዊ መዛግብቶች ያመለክታሉ፡፡

ህክምናው ታሪካዊ ጉዞውን አጠናቆ ደግሞ በዘመናዊ መንገድ ተግባራዊ የሆነው እ.ኤ.አ በ19ኛው ክፍለ ዘመን በአሜሪካን ሀገር ነው፡፡

ዘዴውን ደግሞ ለዓለም ያስተዋወቀው በትውልድ ካናዳዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊ የሆነው ዳንኤል ዴቪድ ፓልመር ነው፡፡ ፓልመር በ1895 የካይሮ ፕራክቲስ ህክምናን በጥቅም ላይ እንዲውል ሲያደርግ ስለ ህክምና ምንም እውቀት ያልነበረው ባለግሮሰሪ ነበር፡፡ በኋላም የማግኔት ሞገድ በአካል ላይ በማሳረፍ ፈውስ የሚሰጥ እንደ እሱ አጠራር ‹‹ህመምተኛን በእጅ በማሸት የፈውስ ኃይልን ወደ በሽተኛ ማሰራጨት›› የሚለውን የህክምና እምነቶችን ዘዴን በበርሊንግተን ማስተዋወቅ ቻለ፡፡ ከዚህ ሌላ የተለያዩ እምነቶች ተከታይ ነበር፡፡ ፓልመር የሰው ልጅ የጭንቅላት ቅርፅ የስብዕናው እና የእውቀት መጠኑ መገለጫ እንደሆነ የሚሰብክ አመለካከት እንዲሁም መንፈሳዊነት (Spiritualism) እና የህይወት አይመረመሬነት (Vitalism) ፍልስፍናዎች በከፍተኛ ሁኔታ ይሳብ ነበር፡፡ ቫይታሊዝም (Vitalism) ፍልስፍና ህይወት ያለው ነገር ህይወት ከሌለው ግዑዝ የሚለይበት የህይወት ብልጭታ (spark of life) በውስጡ መያዙ ነው፡፡ የሚል ሲሆን ይህም ከቻይና አኩፓንክቸር ህክምና መሰረት የሚያደርግበት ቻይ (Chi) ከህንዱ ፕራና (Prana) ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡

ካይሮፕራክቲክ (Chiropractic) የሚለው ቃል ከግሪክ ቋንቋ የተወሰደ ቃል ነው፡፡ ካይሮ ማለት እጅ ሲሆን ‹‹ፕራክቲክ›› ማለት ደግሞ መስራት ወይም ማከናወን የሚለውን ትርጓሜ ይሰጣል፡፡ ጠቅለል ባለ አገላለፅ በእጅ ብቻ የሚከናወን ህክምና የሚለውን ትርጓሜ ይሰጠናል፡፡ በሙያው የሰለጠነ ሰው ደግሞ ካሮፕራክተር (Chiropractic) በመባል ይታወቃል፡፡ ከትርጓሜው እንደምንረዳው የህክምና ዘዴው ትኩረት የሚሰጠው በሙያው በሰለጠነ ሰው እጅ የጀርባ አጥንት (አከርካሪን) አሽቶ በማስተካከል ፈውስን ለህመምተኛው ማስገኘት ነው፡፡ ህክምናው በመጠኑም ቢሆን ከሀገርኛው የስብራት ወጌሻ አሰራር ጋር የሚዛመድ ይመስላል፡፡ የእኛ ወጌሻ ይህ አይነቱን እሽታ የሚያከናውነው ለአጥንት ስብራትና ውልቃት ሲሆን ካይሮፕራክቲስ ግን ለሁሉም ህመሞች ነው፡፡

ካይሮፕራክቲስ የዘመናዊ

የህክምና አካል ባይሆንም እንደማንኛውም አማራጭ (complemntary medicine) ወይም የሀገረሰብ የህክምና ዘዴዎች ለብቻው አንዳንዴም ከዘመናዊ ህክምና ጋር በጣምራ በበርካታ ሀገሮች ጥቅም በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በዩናይትድስቴት የዘመናዊ ህክምና አካል ያልሆኑ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘታቸው ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተፈቀዱ በአይነት የበዙ የሀገረሰብ ህክምና ዘዴዎችና በባህላዊ መንገድ የተቀመሙ መድኃኒቶች ይገኛሉ፡፡ ካይሮፕራክቲስም ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በ2002 እ.ኤ.አ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳሳየው ከአጠቃላይ ወጣት አሜሪካዊያን መካከል ሃያ ከመቶ የሚገመቱት ካይሮፕራክቲስን በህይወት ዘመናቸው ቢያንስ አንድ ጊዜ ተጠቅመው ያውቃሉ፡፡ ጥናቱ ከዚህ በተጨማሪ በከፍተኛ ደረጃ ከሚዘወተሩ አስር ልዩ ልዩ የሀገረሰብ ህክምናዎች አንዱ ካይሮፕራክቲስ እንደሆነ አክሎ ገልጿል፡፡ ከተጠቃሚዎቹም አብዛኞቹ በከባድ የጀርባና የመገጣጠሚያ ህመም የሚሰቃዩ ናቸው፡፡

የካይሮፕክቲስ ፍልስፍና ካሮፕራክቲስ በራሱ ሳይንሳዊ ባይሆንም እንኳን የህክምና ዘዴው

መሰረት የሚያደርግበት የአሰራር ፍልስፍና አለው፡፡ ዘመናዊ ህክምና (Conventional medicine) የበሽታዎች መንስኤ በሽታ አስያዥ ጀርሞች፣ የሆርሞኖች መዛባት፣ የዘርውርስ (genetic disorder) ግድፈት፣ የሰውነት ስነ ህይወት አሰራር እንደሚያውኩ ይገልፃል፡፡ የካይሮፕራክቲስ ግን ከዚህ ፍፁም የተለየ ነው፡፡ የህክምና ዘይቤ ፈላስፋ ፓልመር ስለ በሽታዎች አመጣጥ ያስቀመጠው ንድፈ ሀሳብ (ቲዎቺ) ‹‹የማንኛውም ህመም መንስኤ የጀርባ አጥንቶች (የጀርባ አጥንት የተሰራው ከበርካታ፣ ቁርጥራጭ አጥንቶች መሆኑን ልብ ይበሉ) አገጣጠም መዛባት/መዛነፍ የሰውነት ጤናማ ስነ ህይወታዊ አሰራርን ያስናክላል፡፡ ሰውነትም በተፈጥሮ እራሱን በራሱ ከህመም እንዲያገግም የሚያስችለውን ስርዓት ያውቅሳል›› ይላል፡፡ በማከልም ስለ ቲዎሪው ሲያብራራ ‹‹የተዛነፉ የጀርባ አጥንቶች በውስጣቸው የሚያልፉትን የነርቭ ህዋሳት ስለሚጫኑ ወደ ሰውነት የሚሰራጨውን የነርቭ ሞገድ ፍሰት በማቃወስ ጤናን ያውካሉ›› በማለት ያትታል፡፡

በህክምናው ቲዎሪ መሰረት በአጥንቶች አቀማጥ መዛባት የተከሰተውን ህመም የጀርባ አጥንቶችን አቀማመጥ በማስተካከል ያለ ምንም የመድኃኒት እንክብልና የቀዶ ህክምና ፈውስን ማስገኘት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ጠቀል ብለን የካይሮፕራክቲስ ፍልስፍና ሲጠና ‹‹ህይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ በቁስ ሊገለፅ የማይችል የማይመረመር (vitalism) ናቸው የሚለውን ፍልስፍና የሚያራምድ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ በዚህም እሳቤ ሙያው እራሱን የቻለ እንዲመስል አስችሎታል፡፡ ነገር ግን ካይሮፕራክቲስ ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ነገሮች ቁስ አካላዊ (materialistic) መንገድ መግለፅ/መዳሰስ ይችላሉ›› የሚለውን ንድፈ ሀሳብ ያንፀባርቃል፡፡ አቀራረቡ ሳይንሳዊ ይዘት ያለው ይመስለዋል፡፡ ከእነዚህ ቲዎሪዎች ሳቢያ በብዙ ሀገራት ተመራጭ ሆኖ ለዘመናት እንዲዘልቅ አስችሎታል፡፡

የካይሮፕራክቲስ አስተምርኦት በውጪው ዓለም ማንኛውም ካሮፕራክተር ወደ ስራ

ከመሰማራቱ አስቀድሞ እውቅና ካለው ኮሌጅ መቅሰም ይጠይቃል፡፡ ባለሙያዎቹ ሐኪሞች ሳይሆኑ እራሱን በቻለ የስልጠና ዘርፍ የሚሰለጥኑ ናቸው፡፡ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ትኩረት የሚሰጣቸው፡-

- ጤና ከአካባቢያዊ ተፅዕኖ እና ከአኗኗር ሁኔታ ጋር ያለውን ግንኙነት መረዳት - ሌሎች በጤና ላይ

አሉታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ የሰውነት

አወቃቀር

(Structure) እና ተግባራት

(function) ማወቅ - የጀርባ አጥንትና የአንድ ሰው

ጤና የተያያዙ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይህን በሚቆጣጠሩት የነርቭ ህዋሳት

ላይ ማተኮርን - የበሽተኛውን ምቾት የሚቀንሱ አሰራሮች መቀነስ ላይ ያተኩራል፡፡ ህክምናው በሆርሞን መዛባት የሚመጡ የእንቅርት በሽታ በፓራሳይት የሚመጡ የአሜባ (ካይሮፕራክቲክ... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

በደም እጥረት የሞተ የሰውነት ክፍል

ከዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

ማሳሰቢያ በመዲና ጋዜጣ ላይ የሚቀርቡ የጤና ዘገባዎች ለግንዛቤ ነው እንጂ የዶክተር ሥራ ውስጥ ለመግባት አይደለም።

የትኛውም ህመም ሲሰማ ወደ ሃኪም እንዲሄዱ እንመክራለን።

የኦርቶዶክስ ዕምነት መዝሙሮችን እና ስብከቶችን ለማዳመጥ kidase.org

በሚኒሶታ ነዋሪ የሆነው ወጣት የገነባው ይኸው ድረ ገጽ መዝሙራትን ስብከቶችን

እና ወቅታዊና መንፈሳዊ ዜናዎችን ያቀርባል።

ትርጉም እና ቅንብር በቅድስት አባተ ዛሬ የብዙ ወንዶች ችግር ሆኖ እየመጣ ስላለውና

የብዙዎችንም ትዳር ለፍቺ እስከመዳረግ ስላደረሰው ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን (ወይም የወንድ ልጅ ብልት በተራክቦ ጊዜ በሚፈለገው መልኩ ብቁ ያለመሆን ችግር) እናነሳለን፡፡ ይህ ችግር እንዴት ይከሰታል? በምንስ ምክንያት ይመጣል? የብዙ ወንዶች ችግርስ ለምን ሆነ? ትዳርን እስከማፋታትስ እንዴት ሊደርስ ቻለ? እንዴትስ መከላከል ይቻላል? የሚሉትን ተመሳሳይ ጉዳዮች በስፋት እናያለንና አብረን እንዝለቅ፡፡

ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን ምንድን ነው?

ስንፈተ ወሲብ /Impotence/ በሚል ጥቅል መጠሪያ በአንድነት ብዙ ጊዜ እናንሳው እንጂ ስንፈተ ወሲብ ‹‹የወሲብ ፍላጎት አለመኖር፣ ለተራክቦ ፍቃደኛ አለመሆን›› የመሳሰሉትንም የሚያጠቃልል ነው፡፡ ነገር ግን አሁን እያነሳን የምንመጣው በህክምናው አጠራር ‹ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን› ወይም የብልትን በአግባቡ መወጠር ያለመቻል ችግር ራሱን በቻለና በተለየ መልኩ የሚገለፅ የወንዶች ከባድ ችግር ነው፡፡ እንደ አንድ የስንፈተ ወሲብ የመከሰት ችግር ግን ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን በመባል የሚታወቀውና የወንዶች ብልት በሚፈለገው መልኩ አለመነሳሳትም ሆነ፤ በጊዜ ተነስቶ ቶሎ መሟሸሽ፤ ወይም በተገቢውና ቀጣይነት ባለው መልኩ መወጠር ወይም መቆም ያለመቻል ችግር ሲሆን ለወንዶች የወሲብ አፈፃፀም ስንፈትም ሆነ በተራክቦ ድክመት አንዱና ዋነኛው ችግር ነው፡፡ ይህ ችግር የሚመጣው ለብልት መወጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከሚያደርጉ የብልት ደምስሮች ጋር በተያያዘ የሚከሰት ነው፡፡ በዓለማችን ላይ አሁን አሁን ችግሩ እየሰፋ የመጣ ሲሆን ህክምናውን ለመውሰድ ከሚመጡት ሰዎች ከሚገኘው መረጃ በተጨማሪ ችግራቸውን አምቀው ይዘውት ያለ ወንዶች ቁጥር በአጠቃላይ ከሁለት መቶ ሚሊዮን በላይ ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ ከሌሎቹ ወንዶች በተለየ ከዕድሜ አንጻር ከ40 ዓመት በላይ የሆናቸው በአምስት ፐርሰንት እንደዚሁም ከ65 ዓመት በላይ የሆናቸው ወንዶች ደግሞ ከ15-25 ፐርሰንት ከሌላው በበለጠ የመጠቃት ዕድል አላቸው፡፡

ይህ ችግር ለወንድ ልጅ ትልቅ ራስምታት የሚሆን ቢሆንም በጊዜው በቂ ግንዛቤ ከመያዝና ህክምናን ከማግኘት አንጻር ሊታከምና ሊቀረፍ የሚችል ነው፡፡

ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን በምን ምክንያት ይከሰታል?

ስለ ችግሩ መነሻ ምክንያት ከሚሆኑት ጋር አስቀድመን በተያያዘ መልኩ ልናነሳው የሚገባ ነገር አለ፡፡ ይህም የወንድ ልጅ ብልት በሚገባው መልኩ እንዲነሳሳና እንዲቆም ላያደርጉት የሚችሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው? የሚሉ ነገሮችን አያይዘን ልናነሳ ያስፈልጋል፡፡ የወንድ ልጅ ብልት እንደ ስፖንጅ ስስ በሆኑ ህብረህዋስ /Spongy tissues/ የተሞሉ ባለሁለት ቻምበር የሆኑ ኮርፓራ ካቪርኖሳ /Corpora cavernosa/ የሚባሉ ክፍሎች አሉት፡፡ እነዚህ ህብረ ህዋሳት ደግሞ ጡንቻዎችን፣ የተለያዩ ክፍተቶችን፣ ቬይኖችንና አርተሪዎችን የመሳሰሉ ደምስሮችን የያዙ ናቸው፡፡ በሽንትም ሆነ ለወንድ ልጅ ዘር መውረጃ የሚሆነው ዩሬትራም /Urethra/ በቻምበሮች መካከለኛ ክፍል የሚያልፍ ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁሉ ክፍሎች በወንድ ልጅ የብልት በብቃት መነሳሳት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለብልት መነሳሳት መነሻ የሆኑት ስሜት ቀስቃሽ ነገሮች የሚወሰን የአንጎላችን መነሳሳት በተመለከተ በሚኖረው ምላሽ ወይም በሁለቱም የተቀናጀ ሂደት ነው፡፡ ከአንጎላችን ጀምሮ በብልት አካባቢ እስካሉ ነርቭ ሴሎች ጭምር በሚሰጡት ምላሽ የኮርፖራ ካቪቲኖሳ ጡንቻዎች ዘናና ለቀቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ በዚህም ጊዜ ደም በቀላሉ እንዲዘዋወርና ያሉትን የብልት ደምስሮችና ክፍት ቦታዎች በደም እንዲሞላ ያደርጋል፡፡ በብዛት እየሞላ የሚመጣው ደምም በጡንቻዎቹ ላይ ከፍተኛ ግፊት መፍጠር ይጀምርና ብልት እንዲቆም ያደርጋል፡፡ የሚዘዋወረው ደም የፍሰቱና የግፊት መጠን እየቀነሰና የብልት አካባቢ ጡንቻዎችም መሟሸሽ ሲጀምሩ የብልት የመነሳሳትም ሆነ ተነቃቅቶ የሚቆይባቸው ደቂቃዎች ከላይ ከጠቀስነው ሂደት ጋር የተያያዘ ይሆናል፡፡ ይህም ከወሲብ በፊትም ሆነ በወሲባዊ ተራክቦ ጊዜ ሊታይ የሚችል ነው፡፡

ከዚህም ጋር በተያያዘ ለኢሬክታይል ዲስፈንክሽን ምክንያት ናቸው ተብሎ የሚጠቀሱ ምክንያቶች በአጠቃይ ስናያቸው አካላዊና የአዕምሮ ወይም የስነ ልቦና ችግር ውስጥ ሁሉንም ከተናቸው ልናያቸው እንችላለን፡፡

አካላዊ የችግሩ መነሻ ምክንያቶች የወንድ ልጅ ብልት በሚፈለገው መልኩ እንዳይነሳሳና

እንዳይቆም ከሚያደርጉ ችግሮች መካከል አንዱ አካላዊ በሆነ መልኩ የምናየው ሲሆን ይህም የኩላሊት ህመም፣ የስኳር ህመም፣ የደም ስር መጥበብ፣ የልብ ህመም፣ የነርቭ መጎዳት የመሳሰሉትን ህመሞች የሚያጠቃልል ሲሆን በተጨማሪም የአልኮልና የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆችን ተጠቃሚ መሆን፣ ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረትና እንቅስቃሴ አልባ የህይወት መርህ የመሳሰሉትም በዚህ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ ይህ አካላዊ የሆነው የችግሩ መነሻ ለወንድ ልጅ ብልት አለመነሳሳት ከ75 እስከ 80 ፐርሰንት ያለውን ድርሻ ይወስዳል፡፡ አካላዊ ከሆኑት የችግሩ መነሻዎች መካከል ዋና ዋናዎቹን እናያለን፡፡

1. የስኳር ህመም የስኳር ህመም አንደኛውና ሁለተኛው በመባል የሚታወቅ

ሲሆን ሁለቱም ለስንፈተ ወሲብ የማጋለጥ ፀባይ ሲኖራቸው በወንድ ልጅ ላይ የበለጠ የብልት መቆም ችግር በማስከተል ስንፈተ ወሲብ ውስጥ ይከቱታል፡፡ ተፅዕኖ ከሚያደርሱበት መልኩ አንዱ የብልት ደም ስሮችን የማጥበብ ባህሪይ በማሳየት ነው፡፡ ይህም በብልት መነሳሳት አስተዋፅኦ ያላቸው ቀጫጭን ደምስሮች በበቂ ሁኔታ በደም እንዳይሞሉ በማድረግ የብልት ደም ስሮችም ሆኑ በዙሪያው ያሉ ጡንቻዎችን በቂ የግፊት ኃይል እንዳያገኙ በማድረግ ብልት እንዳይነሳሳ ያደርጋል፡፡ ሌላው ደግሞ የስኳር ህመም በደመስሮቹ ዙሪያ የሚገኙ ወሳኝ የሆኑ የነርቭ ሴሎችን በመጉዳቱ ነው፡፡ ይህም በየቅፅበቱ ለብልት ደምስሮች በደም ለመሞላትም ሆነ በዙሪያው ያሉ ደም ስሮች በቂ የሆነ የግፊት ኃይል እንዲያገኙ የሚያደርጋቸው የነርቭ ትዕዛዝ ወይም መልዕክት እንዳይኖር በማድረጉ የብልት በበቂ ሁኔታ መነሳሳት ላይ እንቅፋት ይፈጥርበታል፡፡ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩትም የስኳር ህመም ከ35 እስከ 40 ፐርሰንት ለሚደርሰው ኢሬክታይል ዲፈንክሽን ተጠያቂም ነው፡፡

2. የልብና የሳንባ ህመም ልባችንም ሆነ ሳንባችን በወሲባዊ ተራክቦ ወቅት ከፍተኛ

ጫና ያለባቸው ሲሆን በዚህም ልክ እንደ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሁሉ በቂ አየርም ሆነ የኃይል አቅርቦት ሰውነታችንም ሆነ የብልት ሴሎች ሁሉ አየርም ሆነ የኃይል አቅርቦት

ሰውነታችንም ሆነ የብልት ሴሎች እንዲያገኙት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ሳንባ በቂ አየር በማሰገባት እንደዚሁም ልባችን ደግሞ ከሳንባ ኦክስጅን ከአንጀት የምግብ መፍጫ የመጨረሻ ሂደት ውስጥ አስተዋፅኦ ከሚያደርጉት ግድግዳዎች ግሉኮስን ተቀብለው በደም አማካኝነት ለጡንቻዎች የሚያሰራጭ ነው፡፡ በእነዚህ አካላት ላይ የሚደርሱ ህመሞችም ሰውነታችንም ሆነ የብልት ሴሎቻችን በቂ የሆነ የኃይል አቅርቦትም ስለማያገኙ ድክመት ውስጥ ይገባሉ፡፡ የብልት ሴሎችም ለዚህ ተጋላጭ በመሆናቸው መነሳሳትም ሆነ መቆም ባለመቻላቸው ስንፈተ ወሲብ ውስጥ እንዲገባ ያስገድዳል፡፡

3. የጉበት ህመም ጉበት በማንኛውም አጋጣሚ ከተጎዳ አጠቃላይ የሰውነት

ሂደቶች ላይ ትልቅ ችግር መፍጠሩ ስለማይቀር የብልት ሴሎችም ተጎጂ ይሆናሉ፡፡ በተለይም ስር የሰደደው የጉበት ህመም አይነት ደግሞ የበለጠ የወሲብ ስሜትን በመጉዳት የወንድ ልጅ የብልት መነሳሳትን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የወሲብ ፍላጎትንና ስሜትን ሊያወርድ የሚችል ነው፡፡

4. የደም ግፊት ህመም የደም ግፊት ህመም በተለይም ከታማሚው ጋር ለረዥም

ጊዜ እየቆየ ሲሄድ በብልት ውስጥ ያሉና ለብልት መቆም ትልቁን ሚና የሚጫወቱትን ቀጫጭን ደም ስሮችን በማጥበብ በወሲብ ወቅት ለሚፈጠር በከፊልም ሆነ ከነጭራሹ ከመጀመሪያው ለብልት መነሳሳት ችግር ተጠያቂ ነው፡፡

5. የጀርባ አጥንቶች ጉዳት የጀርባ አጥንቶች በተለይም ከወገብ በታች ባሉ አከርካሪ

አጥንቶችና የነርቭ ሴሎች ላይ የመመታት ወይም በመውደቅም ቢሆን አደጋ ከተከሰተ ከእነዚህ አካባቢ በመነሳት ወደ ብልት በሚጓዙ ነርቮች ላይ ጉዳት በማምጣት ከጥቅም ውጪ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ ብልት ለመነሳሳት የሚያስችሉት ነርቮች በመጎዳታቸው መነቃቃት አይችልም፡፡ በወሲብ ወቅትም ትልቅ ድክመት ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፡፡

6. የኮሌስትሮል መብዛት በሰውነታችን ውስጥ የደማችን የቅባትነት ሁኔታን

የሚያመለክተን ኮሌስትሮል ብለን የምንጠራው ከደም ዝውውር ጋር ያለው ግንኙነት የጠበቀ እንደመሆኑ መጠኑን ከሚፈልገው በላይ ከሆነ የደም ስሮች እንዲጠቡ ያደርጋል፡፡ በዚህም የብልት ቀጫጭን ደምስሮችም እንዲጠቡ በማድረግ የሚኖራቸውን ጤናማ የሆነውን የደም ዝውውር ያውካል፡፡ ብልትም በደምስሮቹ ጥበት የተነሳም የመወጠር አቅሙንም ሆነ ኃይሉን እያጣ ይመጣል፡፡ ለካንሰርም ሆነ የዕጢ ችግር ተብሎ የሚደረግ የቀዶ ጥገና በብልት ነርቮች ላይ በሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ የተነሳ ብልትን ሊያነሳሱና እንዲቆም የሚያደርጉ ነገሮች

ሁሉ እንከን እንዲያገኛቸው በማድረግ ኢሬክታይል ዲስፈንክሽን ያስከትላል፡፡

7. የብልት አካባቢ ጉዳቶች በተለያዩ አጋጣሚ በአደጋ፣ በግጭት ወይም ከስራ ቦታ

ፀባይ የተነሳ እንደዚሁም በህክምናም ሆነ በሌላ ሁኔታ ለጨረር ነገሮች የብልት ሴሎች የተጋለጡና የተጎዱ ከሆነ መነሳሳትም ሆነ ለረዥም ጊዜ መቆም ይሳነዋል፡፡ ይህም በዙሪያው ባለውና ለመነሳሳት ወሳኝ በሆኑት ቀጫጭን ደምስሮችና ነርቭ ሴሎች መጎዳት ምክንያት የወንድ ልጅ ብልት ለመነሳሳት አይችልም፡፡

8. ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለተለያዩ ህመሞች ለምሳሌ

ለስኳር፣ ለልብና ለደም ግፊት ፊት ከማጋለጡም በተጨማሪ ለስንፈተ ወሲብም ምክንያት ይሆናል፡፡ ብዙውን ጊዜ ይህ የሚሆነው ከመጠን በላይ ውፍረት ያላቸው ሰዎች በደማቸው ውስጥ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን በደማቸው ውስጥ ስለሚኖር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች በሙሉ የደም ስሮችን እንደሚያውከው ሁሉ የብልት ደምስሮችንም እንዲጠቡ በማድረግ ብልት በበቂ ሁኔታ እንዳይቆም ያደርጋል፡፡

9. የኩላሊትና የሽንት ቧንቧ ህመሞች በኩላሊትም ሆነ በሽንት ቧንቧ ላይ የሚፈጠሩ ህመሞች

ከወንዶች ብልት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በማስከተል ለብልት አለመነሳሳት ምክንያት ይሆናሉ፡፡ በተለይም ተያያዥ የሆኑ የትቦዎች ግንኙነት ላይ የደም ስሮችም ስላሉዋቸው የአንዱ አካል መታወክ በሌላው ላይም ተፅዕኖ ስለሚፈጥር ብልትንም የችግሩ ሰለባ እንዲሆን በማድረግ በበቂ ሁኔታ እንዳይቆም በማድረግ ስንፈተ ወሲብ ውስጥ ሊከት ይችላል፡፡

10. የአስፈላጊ ምግቦች እጥረት ምግብ በተለይም የተመጣጠኑ ምግቦች ሰውነታችን

ለሚያደርጋቸው ማንኛውም እንቅስቃሴዎች ለሚያስፈልገው ጉልበትና ኃይል እንደዚሁም የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ሚናን መጫወታቸው ሀቅ ነው፡፡ ታዲያ ወንድ ልጅም የብልቱ ሁኔታ በበቂ በአስፈላጊ መነሳት ውስጥ እንዲገኝ የተመጣጠኑ ምግቦች በተለይም ሞቅ ያሉ ምግቦች፣ ትኩስ የሆኑ ምግቦች፣ የሚያቃጥሉ እንደዚሁም በካርቦሃይድሬትና በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦች የበለጠ ተመራጭ ነው፡፡ ታዲያ የተመጣጠኑ ምግቦች ብልትን በአንዴ እንዲነሳሳ ከማድረግም በላይ ሰውነታችን ብልት እንዲነሳሳ መነሻ የሚሆኑ ስሜት ቀስቃሽ ለሆኑ ነገሮች በበቂ ሁኔታ መልስ እንዲሰጥ ጭምር የሚያደርግ ነውና ከምግብ አንፃር የሚኖሩ እንከኖች መፍትሄ እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ የአንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ተከታታይና በህይወት ውስጥ ሁልጊዜ ሊተገበር የሚገባው ነው፡፡

11. መድኃኒቶችና የአጠቃቀማችን ችግሮች

ለተለያዩ ህመሞች የሚታዘዙና የሚወሰዱ መድኃኒቶች ተያይዞ ሊመጣ ከሚችለው የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል አንዱና ዋናው ለስንፈተ ወሲብ ማጋለጣቸው ነው፡፡ ለዚህም በወንድ ልጅ ላይ የብልት የመነሳሳት ስሜትን በማውረድ የሚገለፅ ይሆናል፡፡ በተለይም ለድብርትና ለደም ግፊት የሚታዘዙ መድኃኒቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የመድኃኒቶች ይህን መሰል ተፅዕኖ ክትትል የሚፈልግ ሲሆን መድኃኒቶቹ ተወስደው ሲያልቁ ችግሩም ሊቀንስ ይችላል፡፡ የመድኃኒቶቹን በተደጋጋሚ የመጠቀም ሁኔታ ግን ችግሩን ሊያባብሰው ይችላል፡፡

12. እንቅስቃሴ አልባ ህይወት ማዘውተር ከትንሽ የእግር ጉዞ ጀምሮ እስከተለያዩ ስፖርታዊ

እንቅስቃሴዎች ድረስ የሰውነታችን የተለያዩ ስርዓቶች በተለይም የደም ዝውውር ስርዓት የተስተካከለ ሂደት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ይህን እንቅስቃሴ አልባ ህይወት መምራት ደግሞ የተስተካከለ የደም ዝውውር ባለመኖሩ ምክንያት የብልት የደም ዝውውርን ደካማ እንዲሆን በማድረግ በሚፈለገው ጊዜና ሁኔታ መነሳሳቱና መቆሙ እንዳይኖር ያደርገዋል፡፡

13. ዕድሜና የልምምድ ዝግጁነት ዕድሜ በህይወት ውስጥ የተለያዩ ነገሮች ነፀብራቅ ሆኖ

ይታያል፡፡ ከእነዚህም ለምሳሌ ከጉልምስና በፊት ወንዶች የብልታቸው ደምስሮችና ነርቮች እንደዚሁም ጡንቻዎች በደንብ ስለማይዳብሩ በደንብ ብልትን የማነሳሳትም ሆነ የመቆም ደረጃ ላይ አይገኙም፡፡ ከጉልምስና ዕድሜ በኋላ

በተለይም ከ16 እስከ 22 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ብልት በደንብ መነሳሳትና መቆም

ቢጀምርም ለወሲባዊ አመለካከቶች ሁሉ አዲስና የመጀመሪያ የሚኮንበት ጊዜ ስለሚሆን ቶሎ ዘር ማፍሰስና የስሜት መውረድ ይታያል፡፡ ተያይዞም የብልት ቀጣይነት ያለው ወይም ለረጅም ደቂቃ

ተነሳስቶ መቆም አይችልም፡፡ ከጎልማሳነት ዕድሜ በኋላ በበቂ ሁኔታ ብልት መነሳሳትና

መቆም የሚችል ቢሆንም ከ40 ዓመት በኋላ ግን የመነሳሳትና ለረጅም ደቂቃ የመቆየት ብቃቱ እየወረደ ይመጣል፡፡ በተለይም ከዕድሜ ጋር ተያይዘው የሚመጡ እንደ ደም ግፊት፤ የደም ስር መጥበብ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ካሉ ችግሩ እየተባባሰ ሊመጣ ይችላል፡፡ የብልት ጡንቻዎችም ሆኑ ደምስሮች ዕድሜ ሲገፉ ብቃታቸውም እየወረደ ስለሚመጣ ብልትም በብቃት መነሳሳትና መቆም አይችልም፡፡ በሌሎች የታችኛው የዕድሜ ክፍሎች ሁኔታው የዕድሜን ተፈጥሯዊ ሁኔታ በተከተለ መልኩ ይዘው የሚታዩ ናቸው፡፡

ሌላው በቂ የልምምድና የዝግጁነት ሁኔታ ከወሲባዊ የስሜት መነሳሳትም ሆነ ከወሲባዊ አፈፃፀም ጋር ሊኖር ያስፈልጋል፡፡ ይህም ጊዜውን ጠብቆ የብልት መነሳሳትና መቆም እንዲኖር ያደርጋል፡፡ በተለይም ከሚያፈቅሩትና ከሚወዱት ሰው ጋር አብሮ እየተላመዱና የተለያዩ አስደሳች ጊዜዎችን ማሳለፍ በመካከላቸው ድብርትና መተፋፈርን በማስወገዱ ወንድ ልጅም ብልቱ በሚጠበቀው ጊዜ ሲነሳሳና ሲቆም ምንም ማለት እንዳልሆነ መገንዘብን ይፈጥራል፡፡ ይህም ለቀጣዩ ቀናትም ብልት በቀላሉና ያለጭንቀት እንዲነሳሳ ያደርጋል፡፡

14. የአንደንዛዥ ዕፆችና የአልኮል ሱሰኛ መሆን ብዙውን ጊዜ ለመነቃቃት ተብለው የሚወሰዱ አደንዛዥ

ዕፆችና የአልኮል መጠጦች ስሜትን ከማነቃቃት ጋር ጊዜያዊ የሞቀ ስሜትን ይፍጠሩ እንጂ የወሲባዊ ግንኙነትን በማዳከም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ወደ ብልት የሚሄደው የደም ስሮች እንዳይነቃቁ ብልት የመወጠር ብቃቱን በማጣት በቀላሉ እንዲልፈሰፈስ ያደርጋሉ፡፡ እንደዚሁም ልክ እንደ ሲጋራ አይነቶችም የደም ውስጥ ኮሌስትሮልን በመጨመር ለልብ ህመምም ሆነ ለአጠቃላይ የደም ዝውውር እንከን በመፍጠር የብልትን የመነሳሳት ብቃትን በማውረድ ወንዱን ስንፈተ ወሲብ ውስጥ ይከቱታል፡፡

ስነ ልቦናዊ የችግሩ ምክንያቶች ለወንድ ልጅ ብልት በሚፈለገው መልኩ አለመነሳት

ከአካላዊ ችግሮቹ በተጨማሪ ስነ ልቦናዊ የሆኑ መነሻ ምክንያቶችም አሉት፡፡ ይህ ስነ ልቦናዊ ምክንያትም ከ20 እስከ 25 ከሚሆነው ምክንያቶች መካከል ዋና ዋናዎቹን ጠቅለል ባለ መልኩ እናያቸዋለን፡፡

ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ ድብርት፣ ለራስ ዝቅተኛ ግምት መስጠትና ጫና እነዚህ አጠቃላይ የስነ ልቦናዊ ችግሮች መገለጫ ሲሆኑ ለስንፈተ ወሲብ መፈጠር አይነተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የወንድ ልጅ ብልት በሚፈለገው ሁኔታና ጊዜ አለመነሳትና በመፍጠር ለወሲብ ብቁ እንዳይሆን ያደርገዋል (ሽ.ሽ.ሽ.ሽ.ሽ... ወደ ገጽ 14 የዞረ)

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

Photo Source ourpleasure.wordpress.com

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

ላስቬጋስ... ከገጽ 6 የዞረ

ወዳጃችን ተፈራ ተበጀ መኪናዋን እያሽከረከረ የሚመቸውን አስፓልት ሲጋልብበት ቆይቶ ልንደርስ ጥቂት ሲቀረን ዋናውን አስፓልት ትቶ በጥርጊያ መንገድ ታጥፎ ወደ በረሃው ገባ። የውጪውን ሙቀት ለማወቅ ከመኪናው መውረድ አይጠይቅም። እንዲሁ በዓይን ሲያዩት ያስታውቃል። ዋዕዩ።

ወደ ገዳሙ ስንታጠፍ “Saint Antony Monastery” የሚል ቅስት/ ጽሑፍ በቀስት አቅጣጫ ያመለክታል። ወደ ገዳሙ ስንዘልቅ የገዳሙ መሥራች አባት የነበሩት ብፁዕ አቡነ ካራስ ሥዕል ከሩቅ ይታያል። ሱዳን ተወልደው፣ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተመርቀው፣ ምንኩስናን መርጠው፣ አሜሪካ መጥተው፣ እዚህ በረሃ ላይ ይህንን ገዳም መሥርተው ከዚያ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2002 ከዚህ ዓለም ድካም በሞት እንደተለዩ ታሪካቸው ያትታል። መቃብራቸውም እዚያው አለ። ይጎበኛል።

መምጣታችንን ያወቁት ገዳማውያኑ ወደኛ መጡ። አንድ ወጣት ግብጻዊ፣ ነጭ ቀሚስ ለብሶ ሊያስጎበኘን መጣ። አረብኛ ወዙ ባልለቀቀው እንግሊዝኛ ለምንጠይቀው ምላሽ ሰጠን። ለነገሩ የቬጋስ ወዳጆቻችንም ብዙ ጊዜ ወደ ገዳሙ ስለሚመላለሱ ሌላ አስጎብኚም አላስፈለገንም። በመጀመሪያ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገብተን ከተሳለምን በኋላ አካባቢውን ሁሉ ማየት ጀመርን።

በአንድ በኩል መጻሕፍት፣ ሲዲዎች፣ ዲቪዲዎች፣ ሌሎች ንዋየ ቅድሳት የሚሸጡበት ሱቅ አላቸው። እንደ ሙዚየም የሚጎበኝ የመሥራቹ አባት መካነ መቃብር እና የቅዱሳን አጽሞች የሚገኙባቸው ቤቶችም አሉ። ሥዕሎቻቸው፣ መስቀሎቻቸው ሁሉ በሥርዓት በሥርዓት ተሰድረው ተቀምጠዋል። ከቬጋስ ግርግር፣ ከአሜሪካ ኑሮ ትርምስ ወጥቶ ፍጹም መንግሥተ ሰማያዊ ጸጥታ የሰፈነበት ቦታ በቅርብ ርቀት ማግኘት በራሱ ይደንቃል። ኢትዮጵያውያን የቬጋስ ክርስቲያኖች ወደ ገዳሙ ብዙ ጊዜ ይጓዛሉ። ለመንፈሳዊ ሕክምና።

ከዋናው ቤተ ክርስቲያን አምስት መቶ ሜትር ያህል ርቆ አንድ ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ቆሟል። አስጎብኚ ወዳጆቻችን “ይህ ተአምራዊው የሙሴ ጸሊም (የኢትዮጵያዊ ቅዱስ የሙሴ፣ ጥቁሩ ሙሴ/ Moses the Black የሚባለው) ቤተ ክርስቲያን ነው” አሉን። ገዳሙ የቅ/እንጦንስ ነው። የርሱ ቤተ ክርስቲያን ትንሽ ሆኖ የቅ/ሙሴ ይህንን ያህል ግዙፍ የሆነበት ምክንያት ደግሞ በራሱ የሚደንቅ ታሪክ ነው። ውስጡን ለማየት፣ ታሪኩን ለመስማት ተጓዝን።

ወደ ውስጥ ከመግባታችን አስቀድሞ ትልቁ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ያለች “መቃኞ”/ የሥዕል ቤት ገብተን ጸሎት አደረግን። ከዚያ ወደ ትልቁ ቤተ ክርስቲያን ገባን። ትልቅነቱ አራት ኪሎ ካለው ከቅ/ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብዙም አይተናነስም። ሥዕሎቹ በሚገርም ውበት ተስለዋል። ቋሚዎቹ እና ከጣራው ሥር በመስመር የተገጠገጡት ማስዋቢያ እንጨቶች በወይን ዘለላ ቅርጽ የተፈለፈሉ፣ ከግብጽ ድረስ የመጡ ጣውላዎች ናቸው። መቅደሱ በካህናተ ሰማይ ሥዕሎች ተውበዋል። እኛ በጎበኘንበት ወቅት የውስጡ ሥራ ተጠናቆ የማስዋብ ሥራ ላይ ነበሩ።

ከሕንጻው ወጥተን ወደ ጓሮ ስንዞር አንድ ሐውልት ቆሟል። ለዚህ ቤተ ክርስቲያን መሠራት ምክንያት የሆነ ተአምር የተፈጸመበት ቦታ ላይ የቆመው ይህ ምልክት ጻድቁ ሙሴ በተአምራት ተገልጾ በግልጽ የታየበት እንደሆነ አስጎብኚዎቻችን ገለጹልን። አጠገቡ ያለች አንዲት ዛፍም ቅዱሱ በተገለጸ ጊዜ ለተአምሩ እማኝ እንዲሆን በጣቱ የነካትና፣ የሚፈውስ ቅዱስ ቅብዓት የፈለቀባት ሲሆን በወቅቱ ከፈለቀው ዘይት/ ቅብዓት ለእማኝነት በገዳሙ ተቀምጧል። በዚህም ተአምር መነሻ ራእዩ በተገለጸላቸው ክርስቲያኖች አማካይነት ይህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሊገነባ ችሏል። ጻድቁ ሙሴ በ አራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረ ቅዱስ ሲሆን የኖረውና ያረፈው በግብጽ ነው።

ያንን ቀን በገዳሙ ስንዘዋወር፣ ጸሎት ስናደርግ፣ ኃላም ከመጻሕፍት መሸጫው ገብተን የምንፈልጋቸውን መጻሕፍት፣ መንፈሳዊ ዲቪዲዎችና ሲዲዎች እንዲሁም መስቀሎች ስንገዛ ቆይተን በምሳ ሰዓት ወደ መመገቢያ አዳራሻቸው ገባን። በኩሽና የሚሠሩት ምእመናን የምንበላውን የምንጠጣውን ሰጥተው አስተናገዱን። የከፈልነው ነገር አልነበረም። መርዳት የምንፈልገው ነገር ቢኖር ኋላ በባንክ ልናደርግላቸው እንደምንችል ወረቀቶቹ ያመላክታሉ። እኛም አድራሻችንን ሰጥተን፣ ገዳሙ የሚያዘጋጀውን መጽሔት በፖስታ እንዲልኩልን ስማችንን አስፍረን ወደ መጣንበት ተመለስን። እየተገረምን። ላስ ቬጋስ - ሲዖልና ገነት ይሏል እንዲህ ነው።

ማንም ገዳሙን ያየ ኢትዮጵያዊ መንፈሳዊ ቅናት ቢጤ መሰማቱ የግድ ነው። “እነዚህ ግብጻውያን በቁጥር ከእኛ አነስተኛ ሆነው እንደዚህ ሲሠሩ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በቁጥር በዝተን ሳለ አንድ ገዳም እንኳን የሌለን ምን ሆነን ነው?” ማለቱ አይቀርም። “አብራችሁ ብሉ እንጂ አብራችሁ ሥሩ” ማን አለንና? ስለዚህም በየሔድንበት ከቁጥራችን ጋር የሚመጥን አሻራ ሳንተው፣ ሁሌም አዲሶች እንደሆንን፣ እንደተበታተንን፣ የማይረባ የታዳጊ አገር ፖለቲካ ይዘን እንደተናተፍን ይኸው ዘመን ጥሎን ይሄዳል። በውስጤ ይኼንን እያመላለስኩ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያደርገው ራሴን እየወቀስኩ፣ ከራሴ ጋር እየተጫወትኩ ወደ ቬጋስ ተመለስኩ።

አስተያየታችሁን ደግሞ በኢ-ሜይል [email protected] ብትልኩልኝ ደስታውን አልችለውም።

የካይሮፕራክቲክ... ከገጽ 12 የዞረ

እና የጃርዲያ በሽታ እንኳን በአከርካሪ አጥንቶች (spin) መዛባት (alignment) እንደተፈጠረ ያቀርባል፡፡ በዚህም ከዘመናዊ ህክምና የሚያርቀው ዋና ነጥብ ነው፡፡

ህክምናው እንዴት ይከናወናል ባለሙያው ህመሙ እንዴት እንደጀመረው ከታካሚው

ታሪክ በመጠየቅ ይረዳል፡፡ በማስከተልም የተወሰነ የአካል እንቅስቃሴ (ህብለ ሰረሰር ላይ በማተኮር) ለማሰራት ይሞክራል፡፡ ሌሎች ተጨማሪ የራጅ ምርመራ ሊያካትት ይችላል፡፡

በህክምናው የክትትል ወቅት አንድ ወይም የተለያዩ የካይሮፕራክቲስ እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ ይህም ህመሙ በሚሰማበት ቦታ በእጅ በማሸት፣ በመገጣጠሚያ አካባቢ ጫና ጫን በማድረግ፣ መገጣጠሚያን በመዘርጋትና በመጠኑ በመለጠጥ የሚከናወን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፈውስ ለማስገኘት የሚከናወነው ካይሮፕሮክቲስ ተጨማሪ ቴክኒኮችንም ሊያጠቃልል ይችላል፡፡

- ህመም በሚሰማበት አካባቢ ማሞቅ ወይም በረዶ ማስቀመጥ

- የኤሌክትሪክ ንዝረት ማነቃቂያ መጠቀም - በቂ እረፍት - መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ - የአመጋገብ፣ ክብደት ቅነሳና ሌሎች የአኗኗር ዘይቤ

ለውጥ ላይ ምክር መቀበል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ምግብ ሊታዘዝ ይችላል፡፡

የህክምናው ጎጂ ጎኖች ህክምናው የጉዳት ሁኔታ የሚወሰነው እንደ

ካይሮፕራክቲስ አይነትና ባለሙያዎች ሁኔታ ይወሰናል፡፡ ሊያስከትላቸው የሚችላቸው ጉዳቶች ተብለው የሚታወቁት ጊዜያዊ የራስ ምታት፣ መጠነኛ ድካም፣ ህክምናው የሚደረግለት የአካል ክፍል መጠነኛ የህመም ስሜት ናቸው፡፡ የካይሮፕራክቲስ ህክምና ዋና ጉዳቶች የሚባሉት፡-

1. የአከርካሪ አጥንቶች መዛነፍን ለማወቅ በሽተኛው

በተደጋጋሚ ለራጅ ጨረር መጋለጡ 2. ህክምናው ፀረ ክትባት አቋም ያለው መሆኑ በቲዎሪው

መሰረት የማንኛውም ህመም መንስኤ የአከርካሪ መዛነፍ ነው ብሎ ማመኑ

3. በበሽታ ጀርም ለሚመጡ ህመሞች ፈውስ መስጠት አለመቻሉ፡፡

ሕክምናውን መውሰድ የማይችሉ እነማን ናቸው? - በተዋስያን በሚመጡ በሽታዎች የተጋለጡ ሰዎች ተገቢ

የሆነ መድኃኒት በመውሰድ ፈውስ ማግኘት እየቻሉ በዚህ እንዳይጠቀሙ ይመከራል

- ከባድ የቁርጥማት ህመም (Arthritis) ያለባቸው - የአጥንት መሳሳት ችግር ያለባቸው (Osteo poresis

patient) ናቸው፡፡ ከዘመናት ጉዞ በኋላ ካይሮፕራክቲስ በሌላ መልክ ብቅ

ብሏል፡፡ ከሚከተሉት የህክምና ፍልስፍና መሰረት ባለሙያዎቹ በሁለት ተከፍለዋል፡፡

1. ቀጥተኛ ካይሮፕራክተር (straight chiropractor)፡- እነዚህኞቹ የህክምና ዘዴው መስራች የሆነው የፓልመርን ንድፈ ሀሳብ ብቻ በመተግበር ህመምን ለመፈወስ የሚጥሩ ናቸው፡፡

2. ቅጥ ካይሮፕራክተር (mixer chiropractor)፡- እነዚህ ደግሞ የፓልመርን ንድፈ ሀሳብ ከዘመናዊ የህክምና ንድፈ ሐሳብ በማዋሀድ የሚሰሩ ናቸው፡፡ አንዳንዴም አስፈላጊውን ምርመራ አድርገው ወደ ዘመናዊ ህክምና ለተጨማሪ ክትትል ይልካሉ፡፡

ካይሮፕራክቲስ መፍትሄ የሚያስገኝላቸው የትኞቹ በሽታዎች ናቸው?

‹‹የሁሉም በሽታዎች መነሻ የጀርባ አጥንት አቀማመጥ መዛነፍ ነው›› የሚለውን እሳቤ ተመልክተን ገዳይ ወደሆኑት የሳንባ፣ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ የወባ በሽታ፣ ካንሰርና ሌሎች በሽታዎች ፊታችንን ስንመልስ ንድፈ ሐሳቡ የዋህነት የተቀላቀለበት ይመስላል፡፡ እውነት ነው የግልና የአካባቢ ንፅህናን ባለመጠበቅ የሚከሰቱ የሆድ ህመሞች የትራኮማ በሽታ በጀርባ አጥንት መዛባት ብቻ የተከሰተ ነው ብሎ ለማሰብ ቀርቶ ለማለም ይከብዳል፡፡ የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በካይሮፕራክቲስ ሊረዱ ከሚችሉ ህመሞች መካከልም፡-

1. የጀርባ አካባቢ ህመም 2. የአንገት ዙሪያ ህመም 3. የሽንጥና የወገብ አካባቢ ህመሞች እንደሆኑ

ይገለፃል፡፡ ለራስ ምታትም (ማይግሬን) ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ይታመናል፡፡

ሽ.ሽ.ሽ.ሽ.ሽ... ከገጽ 13 የዞረ

ማለት ነው፡፡ ታዲያ በእነዚህ የስነ ልቦና ችግሮች ውስጥ ለብልት አለመነሳሳት ተጠያቂ የሚያደርጋቸው ነገር ሲምፖተቲክ የሚባለውን የነርቭ ስርዓት የበለጠ እንዲነቃቃ የሚያደርጉት ሲሆን ይህ የነርቭ ስርዓት ደግሞ የበለጠ ተነቃቅቶ መስራቱ ሰውነታችን የማይፈልገው ሲሆን በወሲባዊ ተራክቦ ጊዜ ዘር ቶሎ እንዲፈስ የሚያደርግና የብልት መነሳሳትን ከመጀመሪያው የተዳከመ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በአጠቃላይ ከላይ የጠቀስናቸው የስነ ልቦና መገለጫ ችግሮች ከገንዘብ/ከቢዝነስ፣ ከኢኮኖሚያዊና ከማህበራዊ ህይወታችን ጋር በተያያዘ በየዕለቱ ችግር የሚያደርሱብን እንደመሆናቸው ወሲብ ነክ ስለሆኑት ህይወታችን ጊዜ እንድንሰጥ ውስጣዊ ስሜታችንን ስለማያነሳሱት ወንድም ልጅ የችግሩ ተቋዳሽ ይሆናል፡፡ ምናልባትም የብልቱ ፈጽሞ መነሳሳትን በዚህ ምክንያት የሚያጣ ሲሆንና ይህን የስንፈተ ወሲብ ህይወት እየለመደው ሲመጣ የብልቱ ስራ ምን እንደሆነ እስኪረሳውም ድረስ ችግሩን ሊያባብስበት ይችላል፡፡

የመልካም ፍቅር እጦት ከትዳር በፊትም ሆነ በኋላ ለጥሩና ቀጣይነት ላለው

ግንኙነት በፍቅር ውስጥ ያሉ ወንዱም ሴቷም መልካም ፍቅር እየተሰጣጡ መቆየት የግድ ያስፈልጋል፡፡ ታዲያ ይህን የመሰለ መልካም ፍቅር የጎደለው የግንኙነት ህይወት የወሲባዊ ህይወትንም ጣእም ያሳጣዋል፡፡ ፍቅር ከሌለና ብጥብጥና ክርክር ወይም መወዛገብ ባለበት ህይወት ውስጥ ወሲባዊ ተነሳሽነት ይጠፋል፡፡ በዚህ አይነት የቀዘቀዘና የሞተ ፍላጎት ውስጥ ደግሞ የወንዱን ብልት ለማነሳሳት ይቸግራል፡፡ መነቃቃት ቢችልም እንኳን ቶሎ ይቀዘቅዛል፡፡ በአጠቃላይ

ለብልት አለመነሳሳት ወይም ለኢሬክታይል ዲስፈንክሽን አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ችግሮች ተወራራሽና ሳይነጣጠሉም በአንድ ሰው ላይ ሊታዩ የሚችሉ ናቸው፡፡ ሁለቱም ተደራራቢ በሆነ መልኩ የችግሩ ተጠቃሽ ምክንያቶች ይሆናሉ፡፡

አጠቃላይ ምርመራዎቹ ምን ይመስላሉ? ኢሬክታይል ዲስፈንክሽንን የተለያዩ ድምር የምርመራ

ውጤቶችን ባማከለ መልኩ ልንመረምር የምችለው፡፡ እነዚህም፡-

1. የተጎጂው የታሪክ ምርመራ ይህም ግለሰቡ ስለ ወሲብ ያለው አመለካከትና ተያያዥ

ችግሮች እንዳሉት እንደዚሁም በተለያዩ ህመሞች መጠቃት አለመጠቃቱንና የአልኮልም ሆነ የአደንዛዥ እፅ ተጠቃሚ መሆን አለመሆኑን የማወቅ ቀዳሚ የምርመራ ደረጃ ነው፡፡ የወሲብ ፍላጎት መኖር አለመኖሩን በመጠየቅና በማረጋገጥ የሽንት መሽናት ችግሮችና የሆርሞኖች መዛባት የመሳሰሉት ከብልት አለመቆምም ጋር ተያያዥ ሊሆኑ የሚችሉ ችግሮች እንደዚሁም የነርቭ መቃወስም መኖር አለመኖሩን በመጠይቆች ለማወቅ መሞከር እንደመነሻ ጠቋሚ ምርመራ ይሆናል፡፡

2. የስነ ልቦናና ሌሎች ምርመራዎች ስነ ልቦናዊ ምርመራዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን ያካተተ ሆኖ

የቅርብ የፍቅር ጓዳም ካለች የዚህ ምርመራ አካል ልትን ትችላለች፡፡ በህይወት ውስጥም ሆነ በወሲባዊ ተራክቦ ጊዜ የሚፈጠሩ አጠቃላይ ስነ ልቦናዊ ችግሮ ካሉአ ነዛን መለየት የሚያስችል ምርመራ ይሆናል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የብልት መቆም ችግር ከስነ ልቦና ይሁን ከአካላዊ ችግሮ እንደመጣ ለመለየት ብልት በምሽት ወይም በሌሊት የእንቅልፍ ጊዜ አልያም በብልት ላይ በሚገጠም መሳሪያ መለየት ይቻላል፡፡ በራሳችን ችግሩን ለማወቅ ለምሳሌበእንቅልፍ ወቅት ብልት ለተወሰነ ደቂቃ የሚቆም ከሆነ ከአከላዊ ይልቅ የስነ ልቦና ችግሮች እንደመነሻ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ የበለጠ ለመለየት ደግሞ የችግሩን አጀማመር ማወቅ ተቢ ነው፡፡

3. ሔሞይናሚክ ሞኒተሪ ይህ ምርመራ በብልት በኩል በመርፌ መልኩ እንደ

መድኃኒት ሆኖ የሚሰጥ ሲሆን ይህም የብልትን ሴሎች አነቃቂ መድኃኒት በመሆን የብልትን የመነሳሳትና ቶሎ የመሟሸሽ ጥንካሬና ኃይልን ያሳውቃል፡፡ ከዚህም ጋር በመታገዝ እንደ ቀጣይ ምርመራ ከአልትራሳውንድ ጋር በመጠቀም የብልትን የደም ዝውውር ሂደት ለመጠቆም ይረዳል፡፡

4. ፔናይል አርተሪዮግራም ይህ የመሳሪያ ምርመራ ሲሆን የብልት ደምስሮች በተለያዩ

አደጋዎች ወይም ችግሮች መዘጋት ወይም መጥበብ አለመጥበባቸውን ለማረጋገጥ የሚደረግ ምርመራ ነው፡፡

ህክምናዎቹና መከላከያው ኢሬክታይል ዲስፈንክሽንን አስቀድሞ መከላከል

ከተጠቀሱት መነሻ ምክያቶች በመነሳት እንደ ጫት መቃምና የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚነትን በመተው ለተለያዩ ህመሞቻችን አሰፈላጊውን መፍት በመውሰድ እንደዚሁም ደስተኞች የሚያደርግንንና የማያጨናንቀን የሕይወት መርህ በመከተልና በመሳሰሉት አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡

1. ስነ ልቦናዊ ህክምና ይህ ህክምና ለብልት አለመነሳሳት ምክንያት የሆኑ ስን

ልቦናዊ ችግሮን ለምሳሌ የሆኑ ስነ ልቦናዊ ችግሮን ለምሳሌ ድብርት፣ ጭንቀት፣ ውጥረትና ፍርሃት የመሳሰሉት እንዲቀረፉ ማድረግ ነው፡፡ እንደዚሁም ከፍቅረኛዎ ጋር ጥሩ የሆነ ደስተኛና መተሳሰብ ያለበት ግንኙነት እንዲፈጠር ማድረግ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ወደ ወሲባዊ የስሜት መነሳሳትም ሆነ እርካታን የሚያደናቅፉ ችግሮች እንዳይኖሩ መፍትሄ መስጠት ላይ ያተኩራል፡፡

2. የመድኃኒት ህክምናዎች ይህ የመድኃኒት ህክምና ለብልት አለመቆም ምክንያት

ሊሆኑ የሚችሉ ህመሞችን ለይቶ ከማከም ጀምሮ በቀጥታ የችግሩ ሰለባ የሆኑትን የብልት ደም ስሮን በዙሪያው ያሉ ነርቭ ሴሎችን ማከም ያጠቃለለ ነው፡፡ እንደዚሁም ለብልት መነሳሳት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉና ለዚሁ አላማ የተሰሩ እንደቪያግራ ያሉ መድኃኒቶችን መጠቀምንም ይጨምራል፡፡

ሁሉም ግን ከተሟላ ምርመራና ከሐኪም የቅርብ ክትልል ጋር ሊፈፀሙ የሚገባቸው ናቸው፡፡

3. ቫኪውም ዲቫይስ ይህ ህክምና የተለያዩ ቫኪውሞችን በመጠቀም በቂ የሆነ

ደም ወደ ብልት ደም ስሮች እንዲገባ የሚያግዝ መካኒካል የሆነ መሳሪያ ነው፡፡ ይህም እንደ አይነቱ ብልት በበቂ ሁኔታ ከተነሳሳ በኋላ የሚነቀል ወይም እንደ ጎማ ነገር በብልት ላይ የተደረገ በወሲባዊ ግንኙነትም ጊዜ የሚኖር ሊሆን ይችላል፡፡

4. ቀዶ ጥገና የብልት የመቆም ችግር በደምስሮች ምክንያት ከፍተኛ

የመለወጥ ሁኔታ የሚያሳይ ችግር ውስጥ ሲገባ ቀዶ ጥገና ህክምናው ይፈፀማል፡፡ ቀዶ ጥገናው መሰረት የሚያደርገው ወደ ብልት ደም የሚያመጡ አርተሪዎችን ለማስተካከል ወይም ከብልት ሌሎች ከፍተኛ የደም መጠን ይዘው የሚወጡ ቪይኖችን ለማስተካል አለበለዚያም ብልት እንዲቆም የሚያደርግ መሳሪያ ለመግጠም የሚደረግ ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ ጤናማ የሆነ የብልት መነሳሳት እንዲኖር አጠቃላይ የሰውነታችን ጤንነትንም መጠበቅና የኑሮ ዘይቤያችን አስደሳች በሆኑ ነገሮች እንዲታጀቡና ጥሩ የፍቅር ቅርርብም እንዲኖር ማድረግ የወንዶች ትልቅ የህይወት የቤት ስራቸው ይሆናል፡፡ ኢሬክታይል ደስፈንክሽንም በማንኛውም የዕድሜ ክልል ቢከሰትም ታሞ መዳም እንደሚቻል ልናውቅ ይገባል፡፡ ወንዶችም ለችግራችሁ ሁሉ ግንዛቤን በማግኘት መፍትሄ እንድታገኙ እመኛለሁ፡፡ ሰላም ቆዩ!!

የስደተኞች ቀን... ከገጽ 1 የዞረ

የ2012 የዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን በዚህ ዓመት ጁን 20/12 ተከብሮ ይውላል። ይህን በማስመልከት በሚኒሶታ የትዊን ሲቲስ (ጥንዶቹ ከተሞች) የስደተኞች ቀን ጁን 16 ቀን 2012 በሚኒሃሃ ፓርክ እንደሚከበር አቶ ይስሃቅ ቱራ በተለይ ለመዲና ጋዜጣ ገለጹ። ጁን 16 ቀን 2012 ከቀኑ 1 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ

በሚከበረው በዚህ የጥንዶቹ ከተሞች (ሚኒያፖሊስ-ሴትፖል) የስደተኞች ቀን ላይ የተለያዩ ሃገራት ስደተኞች በመገኘት ባህላቸውን እና ምግቦቻቸውን ያሳያሉ። “የስደተኞች ቀን እንዲከበር ያስፈለገበት ምክንያት ብዙ ስደተኞች ከሚኖሩባቸው የአሜሪካ ከተሞች መካከል ሚኒሶታ ግንባር ቀደሙን ትይዛለች። በመሆኑም ከተለያየ ሃገርና ባህል የመጣውን ስደተኛ ከሌላው ስደተኛ ጋር የባህል ልውውጥ በማድረግ ለማስተዋወቅ ነው ይህ በዓል በየዓመቱ የሚደረገው” ያሉን አቶ ይስሃቅ “በስቴታችን በተለያዩ ቦታዎች ተበትነው የሚኖሩት ከ100ሺህ በላይ ስደተኞች ይህን ልዩ ቀን በደስታ ያከብሩታል” ብለዋል። በዲቪ ሎተሪና በትምህርት የመጡትን ሳይጨምር በስደት

ሚኒሶታ ከገቡት ከ100 ሺህ ሚኒሶታ ውስጥ ከሚኖሩት ስደተኞች ውስጥ የሞንግ፣ የሶማሊያና የላይቤሪያ ስደተኞች ቅድሚያውን ይይዛሉ። ወደ ሚኒሶታ ከ1979 እስከ 2010 ድረስ 5 ሺህ 398 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መጥተዋል። በ2010 ወደ ሚኒሶታ በስደት የመጡት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 104 መሆኑም ታውቋል። የ2011 ስታትስቲክስ እስካሁን አልወጣም። በ2010 ወደ ሚኒሶታ መጥተው መኖር የጀመሩት የኤርትራውያን ቁጥር 35 ነው። በሚኒሶታ ጁን 16 በመኒሃሃ ፓርክ በሚከበረው በዚህ ታላቅ

በዓል ላይ የመዝናኛ ዝግጅት፣ የባህል ሾው፣ ምግብ በነጻ ይቀርባል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን የባህል ልብሶቸውን ለብሰው በሥፍራው እንዲገኙም ተጋብዋል።

አውሮፓ..... ከገጽ 14 የዞረ

በስቶክሆልም ከተማ ስዊድን በሌላኛው ግማሽ ፍፃሜ 3ለ2 ለማሸነፍ ችላለች፡፡ የፍፃሜን ግጥሚያ ጀርመን በቀላሉ ለማሸነፍ ትችላለች የሚል ግምት ነበር፡፡ ነገር ግን ፒተር ሽ ማይክል፣ አምበሉ ካርሎ አልሰን፣ ጆን ዬንሰን፣ ኪም ሺልፎርትና ብሪያን ላውድሩፕን የያዘው የዴንማርክ ቡድን የማይበገር በመሆኑ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫውን ድል ለመቀዳጀት ችሏል፡፡

1996 የጀመርኖች ወርቃማ ጎል የሶቪየት ህብረት፣ የቺኮዝላቪያና የዩጎዝላቪያ መበታተንን

ተከትሎ 47 አገሮች የውድድሩ የማጣሪያ ዘመቻን ለመጀመር ችለዋል፡፡ በእንግሊዝ አዘጋጅነት የተካሄደ ዩሮ 96 ለመጀመሪያ ጊዜ 16 ቡድኖችን ያሳተፈ ውድድርም ጭምር ነው፡፡

በአሰልጣኝ ቴሪ ዜናብልስ የተመራው የኢንግላንድ ብሔራዊ ቡድን እስከ ግማሽ ፍፃሜው ለመዝለቅ ቢችልም ከጀርመን ጋር ያደረገው ግጥሚያን ለ120 ደቂቃ 1ለ1 ካጠናቀቀ በኋላ በመለያ ምት 6ለ5 ተሸንፎ ለፍፃሜው ግጥሚያ ሳይደርስ ቀርቷል፡፡

በሌላው ግማሽ ፍፃሜ ቼክ ሪፐብሊክ ሳይጠበቅ ፈረንሳይን በተመሳሳይ 6ለ5 ውጤት በመለያ ምት ለማሸነፍ ችላለች፡፡

በዌምብሊ ስቴድየም በጀርመንና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል የተደረገው የፍፃሜ ግጥሚያ እስከ 95ኛ ደቂቃ ድረስ 1ለ1 ከዘለቀ በኋላ በጭማሪ ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባራዊ የሆነው የጎልደን ጎልን ኦሊቨር ቤርሆፍ በማስቆጠር ለጀርመኖች የ2ለ1 ድል አስገኝቶላቸዋል፡፡

ቼክ በጨዋታው 59ኛው ደቂቃ በፓትሪክ በርገር ጎል 1ለ0 መምራት ችላ በ73ኛው ደቂቃ የጀርመኖችን የአቻነት ጎልን ያስቆጠረው ቤርሀፍ ነው፡፡

2004-የግሪካውያን ተአምር በጀመርናዊው አሰልጣኝ ኦቶ ወሀጋል የተመራው የግሪክ

ብሔራዊ ቡድን የውድድር ተሳትፎውን በጀመረው የውድድሩ አዘጋጅ ፖርቹጋልን በፖርቶ ከተማ በተደረገው የመክፈቻ ጨዋታ 2ለ1 በመርታት ይሁን እንጂ ይህ ብቻውን ግሪክ እስከ ፍፃሜው ግጥሚያ ለመዝለቅ ትችላለች የሚል ግምትን አልፈጠረም፡፡

ነገር ግን የግሪካውያን ተአምር በዩሮ 2004 መንገሱን ገፍቶበታል፡፡ በሩብ ፍፃሜው ፈረንሳይን እንዲሁም በግማሽ ፍፃሜው ቼክ ሪፐብሊክን 1ለ0 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት በማሸነፍ ከውድድሩ ውጪ አድርጋቸዋለች፡፡

ከዛም በሊዝበን ከተማ በተደረገው የፍፃሜ ግጥሚያ ፖርቹጋልን ለ2ኛ ጊዜ 1ለ0 በማሸነፍ ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር በቅታለች፡፡

ከግሪካውያን ተአምር ባሻገር ዩሮ 2004 የሚታወሰው በውድድሩ ታሪክ ፈጣኗ ጎል የተቆጠረችበት በመሆኑ ነው፡፡

የራሽያው ዲማትሪ ክሪቼንኮ ቡድን ከግሪክ ጋር ባደረገው የምድብ ማጣሪያ ጎል ያስቆጠረው ጨዋታው በተጀመረ 68 ሴኮንዶች በኋላ ነበር፡፡

2008-ስፔናውያን የ44 ዓመታት ትዕግስት መቅረፍ የስፔን ብሔራዊ ቡድን በ1964 የአውሮፓ ሻምፒዮናን

አስተናግዶ የዋንጫውን ሽልማትን ካገኘበት ጊዜ አንስቶ ሌላ የትልቅ ኢንተርናሽናል ውድድር የዋንጫ ድል ሳይኖረው ዘልቋል፡፡

ይህንን ከ44 ዓመታት የዘለቀ ትዕግስቱን ግን ኦስትሪያና ስዊዘርላንድ በጋራ ባዘጋጁት ዩሮ 2008 ከውድድሩ ተሳታፊ ቡድኖች አቻ የማይገኝለት ማራኪ ፉትቦልን በማበርከት ጭምር ሊቀርፈው ችሏል፡፡

ስፔን ለራሽያ፣ ከስዊድንና ከግሪክ ጋር ያደረገችው ሁሉንም የምድቧ ግጥሚያዎች በድል ካጠናቀቀች በኋላ በሩብ ፍፃሜው ጣሊያንን በመለያ ምት 4ለ2 በመርታት ከውድድሩ አስወጥታታለች፡፡

በግማሽ ፍፃሜው ስፔን ራሽያን 3ለ0 እንዲሁም ጀርመን ቱርክን 3ለ2 በማሸነፍ በቪዮና ከተማ ለተደረገው ፋይናል ተገናኝተዋል፡፡ በፍፃሜው ግጥሚያ ፈርናንዶ ቶሬስ በ33ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠራት ጎል ስፔን ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር በቅታለች፡፡ ስፔን ከጀርመን /ዩሮ 96/ ወዲህ በውድድሩ ግጥሚያዎች ሽንፈት ሳይገጥማት ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት የበቃችበት ተደናቂ አጋጣሚም ተፈጥሮለታል፡፡

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

1960 ፈረንሳይ- በሶቪየት እጅ የገባው የመጀመሪያው ዋንጫ ዩሮፒያን ኔሽንስ ካፕ በሚል ተቀፅላ በፈረንሳይ አዘጋጅነት የተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ብዙም ትኩረት አልተሰጠውም ነበር፡፡ በዚህም 17 አገሮች ብቻ ከውድድሩ በተደረገው የማጣሪያ ዘመቻ ተሳትፈዋል፡፡ ጠንካራ የፉትቦል አገሮች የሆኑት እንግሊዝ፣ ጣሊያንና ምዕራብ ጀርመን ላለመሳተፍ መወሰናቸውም ውድድሩን ውበት አልባ አድርጎታል፡፡ የመጀመሪያው ውድድርን በዋንጫ ድል ለማጠናቀቅ ትችላለች የሚል የቅድሚያ ግምት የተሰጣት ስፔን ነበረች፡፡ በታሰበውም መልኩ በደርሶ መልስ መልክ ይካሄድ የነበረው የውድድሩ ዘመቻዋን እስከ ሩብ ፍፃሜው ለማዝለቅ ችላለች፡፡ ነገር ግን በሩብ ፍፃሜው የመጀመሪያው ጨዋታ ከሜዳው ውጪ ከሶቪየት ህብረት አቻ ከተለያየች በኋላ የመልሱ ግጥሚያን በአገሯ ሳታደርግ ቀርታለች፡፡ ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ በዛን ወቅት የነበሩት የስፔን አምባገነን መሪ ጄኔራል ፍራንሶ የሶቪየት ህብረት ቡድን ወደ አገራቸው እንዳይገባ በመከልከላቸው ከዚህ አጋጣሚ ተጠቃሚ በመሆን ሶቪየት ህብረት በግማሽ ፍፃሜው ቼኮዝላቪያን 3ለ0 ከረታች በኋላ በፍፃሜው ዩጎዝላቪያን 2ለ1 በማሸነፍ የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ 3ኛው፡- 1968 አዘጋጅ፡- ጣሊያን የዋንጫው ባለድል፡- ጣሊያን በ1964 የስፔን የሜዳዋ ጣፋጭ ድል የስፔን አምባገነን መሪ ጄኔራል ፍራንሶ ሶቪየት ህብረትን ወደ አገራቸው አላስገባም ካሉበት አራት ዓመታት በኋላ ስፔን ባዘጋጀችው 2ኛው ዩሮፒያንስ ኔሽንስ ካፕ የፍፃሜ ግጥሚያ ግን ሶቪየት ህብረትን በፍፃሜው ግጥሚያ ለመፋለም ፈቃደኛ ሆናለች፡፡ በፋይናሉ ድል ቀንቷት ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር ተቀዳጅታለች፡፡ በ2ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የተሻለ ቁጥር ያላቸው ማለትም 29 አገሮች በማጣሪያው ዘመቻ ተሳትፈዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በዝነኛው ሰር አልፍ ራምስ የተመራው የኢንግላንድ ብሔራዊ ቡድን ይገኝበታል፡፡ ነገር ግን ኢንግላንድ ከውድድሩ ውጪ የሆነች ገና በመጀመሪያው ዙር በፈረንሳይ 6ለ3 በሆነ አጠቃላይ ውጤት በመረታት ነው፡፡ ስፔን ለፋይናሉ የደረሰችው አየርላንድ ሪፐብሊክን በሩብ ፍፃሜው በአጠቃላይ 7ለ1 እንዲሁም በግማሽ ፍፃሜው ሀንጋሪን 2ለ1 ለመርታት ከቻለች በኋላ ነው፡፡

በ1968 የጣሊያን የሪፕሌይ ድል ለ3ኛ ጊዜ በ1968 በጣሊያን አዘጋጅነት በተደረገው ውድድር በዛን ወቅት የአውሮፓ ፉትቦል ማህበር አባል ከነበሩት 33 አገሮች ውስጥ አይስላንድና ማልታ ብቻ በማጣሪያው ዘመቻ አልተሳተፉም፡፡ የውድድሩ ተሳታፊ ከነበሩት 31 አገሮች ውስጥ ምዕራብ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ የዩሮፒያን ኔሽንስ ካፕ ተሳታፊ ሆናለች፡፡ በውድድሩ ከተደረጉት ታላላቅ ፍልሚያዎች ውስጥ እንግሊዝና ስፔን በሩብ ፍፃሜው የተገናኙበት ይገኝበታል፡፡ እንግሊዝ በዌምብሌ የተደረገው የመጀመሪያው ጨዋታን በቦቢ ቻርልተን ብቸኛ ጎል 1ለ0 ለማሸነፍ ችላለች፡፡ ስፔን በማድሪዱ ከተማ በተደረገው የመልሱ ግጥሚያ በኢማንቺዬ ጎል 1ለ0 በማሸነፍ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ማርቲን ፒተርሰን ኖርማን ሀንተር ባስቆጠሩት ተጨማሪ ጎሎች 3ለ1 በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ለማድረግ ወደ ውድድሩ አዘጋጅ ጣሊያን ተጉዛለች፡፡ በግማሽ ፍፃሜው ዩጎዝላቪያ እንግሊዝን 1ለ0 ጣሊያን ደግሞ ከሶቪየት ህብረት ጋር 0ለ0 ተለያይታ በእጣ ለማሸነፍ በመቻሏ ዩጎዝላቪያና ጣሊያን ጁን 8/1968 በሮም ከተማ በተደረገው የፍፃሜ ግጥሚያ ተገናኝተዋል፡፡ ፋይናሉ 1ለ1 በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ በድጋሚ እንዲደረግ ተወስኗል፡፡ ከሶስት ቀናት በኋላ በፋይናሉ ሪፕሌይ ጣሊያን ዩጎዝላቪያን 2ለ0 በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር በቅታለች፡፡

በ1972-የጀርመኖች ሙሉ የበላይነት ከ33ቱ የአውሮፓ ፉትቦል ማህበር አባል አገሮች ውስጥ አይስላንድ ብቻ ለ4ኛ ጊዜ በቤልጅየም በተደረገው

ውድድር አልተሳተፈችም፡፡ 32ቱ ተሳታፊ አገሮች እያንዳንዳቸው አራት ቡድኖችን በያዙ ስምንት ምድቦች

ተከፍለው ማጣሪያቸውን ካደረጉ በኋላ የምድብ አሸናፊዎቹ በሩብ ፍፃሜ የደርሶ

መልስ ፍልሚያ ተገናኝተዋል፡፡ በእንደዚህ አይነቱ ፎርማት በተደረገው ውድድር ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ

ፋይናሉ ድረስ በአሰልጣኝ ሄልሙት ቫኦን የተመራው የምዕራብ ጀርመን ቡድን ሙሉ የበላይነትን ይዞበታል፡፡ ፖል ብራይትነር፣ ጌርቾ ሙለርንና ፍራንስ ቤከንባወርን

የመሳሰሉት ዝነኞችን ያቀፈው የጀርመን ቡድን የምድብ ማጣሪያውን የቅርብ ተፎካካሪው የነበረችው ፖላንድን በአራት ነጥቦች በመብለጥ በመሪነት ካጠናቀቀ በኋላ በሩብ ፍፃሜው እንግሊዝን በደርሶ መልሱ አጠቃላይ ውጤት ካስወጣቻት በኋላ በግማሽ ፍፃሜው ቤልጅየምን 2ለ1 በመርታት ወደ ፍፃሜው ግጥሚያ ተሸጋግሯል፡፡ በብራሰልስ ከተማ በተደረገው ፋይናል ጀርመን ሶቪየት ህብረትን 3ለ0 በመርታት ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብርን ተቀዳጅታለች፡፡ በ1976- የቺኮች ገድል የ1976 የአውሮፓ ሻምፒዮና ከዛ በፊት ከተደረጉት ውድድሮች የበለጠ ልዩ ትኩረትን ስቦ ነበር፡፡ ለዚህ ዋነኛ ምክንያቱ አራት ቡድኖች ማለትም ቼኮዝላቪያ፣ ሆላንድ፣ ጀርመንና ዩጎዝላቪያ ጠንካራ አቋምን ይዘው ያደረጉት ውድድር በመሆኑ ነው፡፡ ቼኮዝላቪያ በምድብ ማጣሪያው በዌምብሊ ስቴድየም በእንግሊዝ 3ለ0 ብትሸነፍም በመልሱ የ2ለ1 ድልን በመቀዳጀት ምድቡን በመሪነት ለማጠናቀቅ ችላለች፡፡ በውድድሩ ግማሽ ፍፃሜ ቼኮዝላቪያ ሆላንድን

3ለ1 እንዲሁም ምዕራብ ጀርመን ዩጎዝላቪያን 4ለ2 በመርታት በቤልግሬድ ከተማ ለተደረገው የፍፃሜ ግጥሚያ ደርሰዋል፡፡ ፋይናሉን 2ለ2 በሆነ ውጤት ቢያጠናቅቅ ቼኮዝላቪያ 5ለ3 በሆነ ውጤት በመለያ ምት በማሸነፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡ (የአውሮፓ.... ወደ ገጽ 16 የዞረ)

ሆ ዜ ሞውሪኖ ኢንተር ሚላንን ተሰናብተው ወደ ሪያል ማድሪድ ካመሩ እነሆ ሁለተኛ ዓመት ሞላቸው፡፡ ራሳቸውን ‹‹ልዩው ሰው›› እያሉ

የሚጠሩት እኚህ ሰው አሁንም በስኬት መንገድ ላይ መረማመዳቸውን ቀጥለዋል፡፡ በ2011 ማዮርካ፣ ሊቫንቴ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ፣ ሲቪያ እና ባርሴሎናን በመርታት ከ18 ዓመታት ቆይታ በኋላ ማድሪድን ለንጉሱ ዋንጫ ባለቤትነት ሲያበቁት ዘንድሮ ደግሞ የቻምፒዮንስ ሊግ ባለድል ለመሆን በቅተዋል፡፡ በእነዚህ ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በርካታ ለቁጥር የሚያዳግቱ ሪከርዶችን ለመጨበጥም ችለዋል፡፡ ሞውሪኖ ገና በመጀመሪያ ሲዝን የላንቲያን በርናባው ቆይታቸው በፊፋ ምርጫ የዓመቱ ኮከብ አሰልጣኝ ሆነው ሲመረጡ የጣልያኑ ጋዜጣ ዲሎ ስፖርት ደግሞ ‹‹የዓመቱ ምርጥ ሰው›› ሲል ሰይሟቸዋል፡፡ አይ.ኤች.ኤፍ.ኤች.ኤስ ተባለው የስፖርት ተቋምም እንዲሁ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሲል ሰይሟቸዋል፡፡ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ድረ ገፅም ተመሳሳይ ክብር አጎናፅፏቸዋል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመንም ይህኑ አጠናክረው በመቀጠል በላ ሊጋው በርካታ ሪከርዶችን በመስበር የድል ባለቤት ለመሆን ችለዋል፡፡ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ነጥብ ለመሰብሰብ ሲችሉ 121 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍም አዲስ ሪከርድ መያዝ ችለዋል፡፡ ካደረጓቸው 38 ጨዋታዎች መካከል 32ቶን ማሸነፍ ችለዋል፡፡ በዚህም በማድሪድ ታሪክ ብዙ ጨዋታዎችን በማሸነፍ አምስተኛው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል፡፡ ከ2002/03 የውድድር ዓመት በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ በቻምፒየንስ ሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመታት ግማሽ ፍፃሜ ለመድረስ ችለዋል፡፡ በድምሩ ሰውዬው ወደላንቲያን በርናባው ካመሩበት ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ 117 ጨዋታዎችን አድርገው 322 ጎሎችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

አወዛጋቢው ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ዦዜ ሞውሪኖ በሪያል ማድሪድ የላሊጋውን ዋንጫ እንደሚያነሱ አስቀድመው ቢያረጋግጡም በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ላይ ግን ከክለቡ ሊለዩ እንደሚችሉ ሲወራ የሰነበተው አስቀድሞ ነበር፡፡ ይሁንና በዚህ ሳምንት አጋማሽ ከስፔን ዋና ከተማዋ ክለብ ጋር እስከ 2016 የሚያቆያቸውን አዲስ ኮንትራት ፈርመዋል፡፡ ከፊርማ ስነ ስርዓቱ በኋላም ተከታዩን ቃለ ምልልስ በክለቡ ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ ሰጥተዋል፡፡

ጥያቄ፡- እስከ 2016 ድረስ የማድሪድስታ አባል መሆንዎን በፊርማዎ አረጋግጠዋል፡፡ ይህን ማሳካት ምን አይነት ስሜት ነው የሚሰጠው?

መልስ፡- በጣም የደስተኛነት ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ እንደዚህ አይነት

ስሜት በውስጤ ባይኖር ኖሮ ፊርማዬን አላኖርም ነበር፡፡ ማድሪስታ መሆን የሚሰጠው የደስታ ስሜት ልዩ ነው፡፡ ፊርማዬን ማዋሌ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለክለቡ ፕሬዝዳንት ሆሌ አንሄል ሳንቺዝና ለቦርዳቸውም ጭምር ነው፡፡ እነሱ በእኔ ላይ ላላቸው ከፍተኛ እምነት እኔም እስከ 2016 ድረስ ባሳንቲያጎ በርናባው በመቆየት የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ከግብ ማድረስ እንደሚጠበቅብኝ ራሴን ስላሳመንኩኝ ነው ፊርማዬን ለማሳረፍ የፈቀድኩት፡፡ ከስኬታማው የማድሪድ ቡድን አባላት መካከል አንዱ መሆን ትልቅ ደስታ ነው የሚያጎናፅፍህ፡፡ እዚህ ውሳኔ ላይ በመድረሴ መላው የቡድን ተጨዋቾቼ እንደሚደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በእኔ ዙሪያ በርካታ ነገሮች ሲወሩ ቆይተዋል፡፡ ተጫዋቾቼም ደጋግመው ስለጉዳዩ ይጠይቁኝ ነበር፡፡ እኔ ግን የትም እንደማልሄድ ደግሜ ደጋግሜ ስነግራቸው ቆይቻለሁ፡፡ አሁንም ያንን ነው ተግባራዊ ያደረግኩት፡፡ በዚህም ደስተኞች ሆነዋል፡፡ በዚህ ውሳኔዬ ውስጥ የባለቤቱና የልጆቼ ሚና ላቅ ያለ ሲሆን እነሱም በጣም ተደስተዋል፡፡

ጥያቄ፡- ኮንትራትዎን እስከ 2016 ድረስ ለማራዘም ምን አነሳሳዎት? መልስ፡- እዚህ ውሳኔ ላይ እንድንደርስ ምክንያት የሆነኝ ዋናው ቁልፍ ነገር

በክለቡ ውስጥ ያለው ፕሮጀክት ነው፡፡ በተለይ ፕሬዝዳንቱ ትልቅ ፕሮጀክት ለመገንባት የያዙት እቅድ እኔም የዚህ አካል (ሆዜ ሞውሪንሆ... ወደ ገጽ 10 የዞረ)

ቼ ልሲ የቻምፒየንስ ሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን ተከትሎ በብሪታኒያ ምድር ደስታው

አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በባየር ሙኒክ ላይ ለተቀዳጀው ከፍተኛ ድል ትልቅ አስተዋፅኦ በማበርከት የአንበሳውን ድርሻ የያዘው ደግሞ ዲዲዬ ድሮግባ ነው፡፡ አይቮሪኮስታዊው ኮከብ በስታምፎርድ ብሪጅ ቆይታው ከዚህ ቀደም በቻምፒዮንስ ሊጉ ሶስት ጊዜ ለግማሽ ፍፃሜ ሲደርስ አንድ ጊዜ ደግሞ ለፍፃሜ መቅረብ ችሏል፡፡ አንድ ጊዜም እንዲሁ ሩብ ፍፃሜ ድረስ ተጉዟል፡፡ ዘንድሮ ደግሞ አምስት ጊዜ ሞክሮ ያልተሳካለትን ዋንጫ ማሳካት ችሏል፡፡ በእሱ ከፍተኛ ጥረትም ሰማያዊዎቹ ዋንጫውን ከፍ አድርገው ማንሳት ችለዋል፡፡

በሙኒኩ አልያንዝ አሬና በተካሄደው የዘንድሮው ሲዝን የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ድሮግባ ወደ ጨዋታው መጠናቀቂያ ላይ በግሩም ሁኔታ የአቻነቷን ጎል በግንባሩ ገጭቶ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ይህም የሮቤርቶ ዲሚቲዎችንና የልጆቻቸውን የሜዳ ላይ ህይወት ያራዘመች ሆናለች፡፡ አሸናፊውን ለመለየት የሚያስችለው የፍፁም ቅጣት ምት ሲሰጥም የመጨረሻዋንና ወሳኟን ጎል ከመረብ በማሳረፍ ታሪኩን በወርቃማ ቀለም ለመፃፍ ችሏል፡፡

የአይቮሪኮስቱ ኮከብ ብዙ ጊዜ በወሳኝ ጨዋታዎች ላይ በክለብም ሆነ በብሔራዊ ቡድን ደረጃ የፍፁም ቅጣት ምት ገድ

የለውም፡፡ ዘንድሮ ግን ይህ ተቀይሮ ታሪክ መስራት ችሏል፡፡ በባህሪው ሳቢያ ቡድኑን ዋጋ ሲያስከፍልም ይታይ ነበር፡፡ በ2008 ፍፃሜ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ሲጫወቱ በቀይ ካርድ በመውጣቱ ሰማያዊዎቹን ለሽንፈት ዳርጓቸዋል፡፡ በአወዛጋቢ ሁኔታ በባርሴሎና ተሸንፈው ከውድድር በወጡበት የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታም በተመሳሳይ መልኩ በካሜራ ፊት

የሰራው ብልግና አይረሳም፡፡ ከሊቨርፑል ጋር በመለያ ምት ተሸንፈው ከውድድር በወጡበት ዓመትም እንዲሁ ፔናሊቲ በመሳት ዋጋ አስከፍሏቸው ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ግን አሁን ታሪክ ሆነዋል፡፡ እሱም በመልካም ጎኑ ታሪክ መስራቱን ቀጥሏል፡፡ አጥቂው በማይዋዥቅ አቋሙ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ በመጥቀም ላይ ይገኛል፡፡ በቼልሲ ማሊያ ለፍፃሜ በቀረበባቸው ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ ዘጠኝ ጎሎችን ማስቆጠሩም ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው የሚሆነው፡፡ ከእግርኳሰ አንፃር ካየነው እድሜው ገፍቷል ሊባል ቢችልም እሱ ግን ገና እንደ አፍላ ጎረምሳ አሁንም በጥሩ አቋም ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ለዚህም የረዳው ጠንካራ ልምምድ መስራቱና በፀሎት የተጋ ሰው መሆኑን ነው የሚናገረው፡፡ በአሊያንዝ አሬና የቻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ ድሮግባ የሰራውን ገድል ቢቢሲ የገለፀው ‹‹አጨራረሱ በሚያምር ልብ ሰቃይ ቴአትር ላይ የተሳተፈ ዋና ገፀ ባህሪ ይመስል ነበር›› በማለት ነበር፡፡ በዚህ ወሳኝ የፍፃሜ ጨዋታ አስገራሚ የጭንቅላት ኳስ በማስቆጠር ሰማያዊዎቹን ለአቻነት ሲያበቃቸው የመጨረሻዋን

ወሳኝ የፍፁም ቅጣት ምትም ወደጎልነት በመቀየር ቼልሲን በ107 ዓመት ታሪኩ የመጀመሪያው የሆነለትን የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን እንዲስም አስችሎታል፡፡ የዝውውር መስኮቱ ሊከፈት መቃረቡን ተከትሎ በእሱ ዙሪያም የተለያዩ ወሬዎች እየተናፈሱ ይገኛሉ፡፡ ያቺ የፍፁም ቅጣት ምትም በቼልሲ ማሊያ የመጨረሻ ኳስና ጎሉ እንደሆነችም ተወርቶበታል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ጥያቄ የቀረበለት ተጨዋቹም ‹‹ለወደፊቱ ብዙ ራዕይ ያለኝ ሰው እንደሆንኩ አምናለሁ፡፡ ሁልጊዜም አብዝቼ እፀልያለሁ፡፡ ወደዚህች ምድር ስመጣ የተፃፈልኝ የራሴ የሆነ ራዕይ አለኝ፡፡ ይህ ቡድን አስገራሚ ቡድን ነው፡፡ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ ስላደረገልኝ ሁሉ አመሰግነዋለሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ስለቀጣይ የኳስ ህይወቴ ምንም ማለት አልችልም›› የሚል የተድፈነፈነ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ዲዲዬ ድሮግባ በቻምፒዮንስ ሊግ ላይ ጎል በማስቆጠር እንግዳ አይደለም፡፡ የመጀመሪያ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታውን ያደረገው በሴፕቴምበር 2003 የማርሴይ ተጨዋች በነበረበት ወቅት ነው፡፡ በወቅቱ በሪያል ማድሪድ 4ለ2 በተሸነፉበት በዚህ የመጀመሪያ የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታው ጎል ማስቆጠር ችሎ ነበር፡፡ በድምሩም እስከዛሬ ድረስ 75 የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎችን አድርጎ 39 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል፡፡ በመጨረሻ የወርቅ ሜዳሊያውንም በአንገቱ አጥልቋል፡፡ በቀድሞው አሰልጣኝ አንድሬ ቪያስ ቦአስ ጊዜ በመጀመሪያው የውድድር ዘመን ክለቡን ለመልቀቅ ተቃርቦ ነበር፡፡ አሁን እዛ ውሳኔ ላይ ባለመድረሱ በበጎ መልኩ ነው የሚያየው፡፡ አሁን ግን ከክለቡ መለያየቱ የተቃረበ ይመስላል፡፡

የ34 ዓመቱ አይቮሪኮስታዊ አጥቂ በስታምፎርድ ብሪጅ ለስምንት ዓመታት ያህል ቆይቷል፡፡ አሁን ግን በመውጫው በር ላይ ቆሟል፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ አሁን አጥብቆ የሚፈልገው ቢሆንም እሱ ግን ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ አዲስ ህይወት ለመጀመር እንደሚፈልግ የቅርብ ሰዎች በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡ የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተከላካይና የአሁኑ የሰንደርላንድ አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ተጨዋቹን በተመለከተ ሰሞኑን ለቢቢሲ ሬዲዮ ፋይቭ ላይ አስተያታቸውን ሲሰጡ ‹‹ዲዲዬ ድሮግባ ላለፉት ስምንት ዓመታት በፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ አጥቂ ሆኖ የቆየ ነው፡፡ ነገር ግን የዘንድሮው የውድድር ዓመት የመጨረሻ የፕሪሚየር ሊግ ቆይታው ይመስለኛል፡፡ ቢሆንም ግን አሁን ባለው አቋም የትም ሄዶ በድንቅ ብቃቱ መጫወት ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ አሁን ትልቁ ጥያቄ የሚሆነው ቼልሲዎች (ድሮግባ.... ወደ ገጽ 10 የዞረ)

በሊሊ ሞገስ

የእስካሁኑ የዩሮ

ሻምፕዮና አዘጋጆችና አሸናፊዎች

1ኛው 1960 አዘጋጅ፡- ፈረንሳይ የዋንጫው ባለድል፡- ሶቭየት ህብረት 2ኛው፡- 1964 አዘጋጅ፡- ስፔን የዋንጫው ባለድል፡- ስፔን 3ኛው፡- 1968 አዘጋጅ፡- ጣሊያን የዋንጫው ባለድል፡- ጣሊያን 4ኛው፡- 1972 አዘጋጅ፡- ቤልጂየም የዋንጫው ባለድል፡- ምዕራብ ጀርመን 5ኛው፡- 1976 አዘጋጅ፡- ዩጎዝላቪያ የዋንጫው ባለድል፡- ቼኮዝሎቫኪያ 6ኛው፡- 1980 አዘጋጅ፡- ጣሊያን የዋንጫው ባለድል፡- ምዕራብ ጀርመን 7ኛው፡- 1984 አዘጋጅ፡- ፈረንሳይ የዋንጫው ባለድል፡- ፈረንሳይ 8ኛው፡- 1988 አዘጋጅ፡- ምዕራብ ጀርመን የዋንጫው ባለድል፡- ሆላንድ 9ኛው፡- በ1992 አዘጋጅ፡- ስዊድን የዋንጫው ባለድል፡- ዴንማርክ 10ኛው፡- 1996 አዘጋጅ፡- እንግሊዝ የዋንጫው ባለድል፡- ጀርመን 11ኛው፡- በ2000 አዘጋጅ፡- ቤልጅየምና ሆላንድ የዋንጫው ባለድል፡- ፈረንሳይ 12ኛው፡- በ2004 አዘጋጅ፡- ፖርቹጋል የዋንጫው ባለድል፡- ግሪክ 13ኛው፡- በ2008 አዘጋጅ፡- ኦስትሪያና ስዊዘርላንድ የዋንጫው ባለድል፡- ስፔን

የአውሮፓ አገሮች ሻምፒዮና በ1960 በፈረንሳይ አዘጋጅነት ሲጀመር ያንን ያህል ልዩ ትኩረት አልተሰጠውም ነበር፡፡ በተለይም በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ የፉትቦል አገሮች በተለይም እንግሊዝና ጀርመን በመጀመሪያው ውድድር የመሳተፍ ፍላጎትን አላሳዩም፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የአውሮፓ ሻምፒዮና ከዓለም ዋንጫ ቀጥሎ የፕላኔታችን ትልቁ የፉትቦል ውድድር ነው፡፡ በሰኔ ወር በፖላንድና በዩክሬን አዘጋጅነት የሚደረገው ዩሮ 2012 ለመጨረሻ ጊዜ 165 ቡድኖችን የሚያሳትፍ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ከቀጣዩ ማለትም ከአራት ዓመታት በኋላ በፈረንሳይ አዘጋጅነት ከሚደረገው ዩሮ 2016 ጀምሮ ውድድሩ 24 ቡድኖች የሚያሳትፍ እንዲሆን በአውሮፓ ፉትቦል ማህበር ተወስኗል፡፡ በዚህ መልኩ በርካታ ቡድኖችን እንዲያሳትፍ ተደርጎ እየሰፋ የሄደው የአውሮፓ ሻምፒዮናን የዋንጫ ድልን ለመቀዳጀት የቻሉ በርካታ ዝነኛ ቡድኖች ታይተውበታል፡፡ እስካሁን የዚህ ውድድር የዋንጫ ድልን የተቀዳጁት ቡድኖች ከዚህ በታች ባለው መልኩ ተዳስሰዋል፡፡

የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን

Jackso

n st

Rice S

t.

Pennsylvania Ave.

Medina/መዲና June 2012 volume 1I No. 4 ሰኔ 2004 ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፬

የሃገር ቤት ቅመማ ቅመሞች

ጧፍ የሃበሻ ልብሶች የሃበሻ ነጠላዎች ጀበና እና ሸክላ

ድስቶች

ክትፎ በጣባ በባህላዊ መቀመጫ

የኬተሪንግ አገልግሎት ለማንኛውም ድግስ

ባህላዊ የስጦታ እቃዎች

ባህላዊ የስጦታ እቃዎች

Injera Bucher shop Groceries Coffee Spices Gift items Calling cards Kitfo

እንጀራ የበግ፣ የዶሮ፣ የበሬና የፍየል ሥጋ ቅመማ ቅመም ቡና የስጦታ እቃዎች የስልክ ካርድ ሌሎችም ክትፎ

ትኩስ የበሬ ሥጋ፣ ሽንኩርት፣ የፊት ቅባቶች፣ የሙዚቃና የመዝሙር ሲዲዎችን አሉን

በተለይ የኮለምቢያ ሃይትስ፣ ፍሪድሊና ኒውብራይተን አካባቢ ነዋሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ በአቅራቢያችሁ ግሮሰሪና ክትፎ ቤት ተከፈተላችሁ

2518 Central Avenue Northeast Minneapolis, MN 55418 (In front of Holy land Market)

612-354-4419 or 702-349-8012

አውሮፓ..... ከገጽ 15 የዞረ

በ1980 - ቦሩሜንጋ ቁልፍ ተዋናይነት የውድድሩ የፍፃሜ ጨዋታዎች ስምንት አገሮች ለመጀመሪያ

ጊዜ ተሳትፈውበታል፡፡ ጣሊያን ለ2ኛ ጊዜ የማስተናገድ እድልን በማግኘት

የመከጀመሪያዋ አገር በሆነችበት በዚህ ውድድር በምድብ አንድ ቤልጅየም፣ ስፔን፣ ጣሊያንና እንግሊዝ ሲመደቡ በምድብ ሁለት ጀርመን፣ ሆላንድ፣ ቼኮዝላቪያና ግሪክ ይገኙ ነበር፡፡ በዛን ወቅት በነበረው ደንብ መሰረት ሁለቴ የምድብ አድማቂዎች ቤልጅየምና ጀርመን በሮም ከተማ በተደረገው ፋይናል ተገናኝተዋል፡፡

ጀርመን የፍፃሜውን ግጥሚያ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ ለአውሮፓ ሻምፒዮንነት ክብር በቅታለች፡፡ በውድድሩ ካርል ሄንዝ ሩሚንጋ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ቁልፍ አስተዋፅኦን ለማበርከት ችሏል፡፡

1984- የፈረንሳይ የመጀመሪያው የዋንጫ ድል በሚሽል ፕላቲን ዋነኛ ተዋናይነት የሚመራው የፈረንሳይ

ብሔራዊ ቡድን በ1980ዎቹ በአውሮፓ ውጤታማ ፉትቦል

ከነበራቸው ቡድኖች አንዱ ነበር፡፡ በተለይም የ1982ቱ የዓለም ዋንጫ በድል ለማጠናቀቅ

ተቃርቦ በግማሽ ፍፃሜው በጀመርን በመለያ ምት ተሸንፎ ከውድድሩ በመውጣት አላማውን ለማሳካት ሳይችል ቀርቷል፡፡ ይህ ፈረንሳይ ከሁለት ዓመታት በኋላ ራሷ ያዘጋጀችው ዩሮ 84ን በዋንጫ ድል የማጠናቀቅ የቅድሚያ ግምት እንዲሰጣት ምክንያት ሆኗታል፡፡

በታሰበውም መልኩ ፈረንሳይ የውድድሩ እጅግ ጠንካራ ቡድን መሆኗ ተመስክሮለታል፡፡ ከፕላቲን ባሻገር ፈረንናንዴዝ፣ ዣን ቲጋናና አሊን ጂሬስን የመሳሰሉት ዝነኞችን የያዘው የፈንሳይ ቡድን በግማሽ ፍፃሜ ፖርቹጋልን 3ለ2 ሲረታ ስፔን ዴንማርክን በመለያ ምት 5ለ4 በማሸነፍ በፍፃሜው ግጥሚያ ተገናኝተዋል፡፡

በፓሪስ ከተማ በተደረገው ፋይናል ፈረንሳይ በፕላቲኒና በቤሌኔ ጎሎች ስፔንን 2ለ0 በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የትልቅ ኢንተርናሽል ውድድር የዋንጫ ሽልማትን አንስታለች፡፡

1988-የቫንባስተንና የራይ ካርድ ማጅክ ሆላንድ በ1974 እና በ1978 የዓለም ዋንጫዎች በተከታታይ

ለፍፃሜ ከደረሰች በኋላ በኢንተርናሽናል ፉትቦል ስኬታማ

ለመሆን ተስኗት ነበር፡፡ ነገር ግን በአሰልጣኝ ሩኒስ ሚሼል በመመራት በጀርመን የተዘጋጀው የዩሮ 88 ውድድር በዋንጫ ባለቤትነት ለማጠናቀቅ ችላለች፡፡

የኤሲሚላኑ አጥቂ ማርኮ ቫንባስተን ሙሉውን ሲዝን በቁርጭምጭሚት ጉዳት ለማሳለፍ ቢችልም ለዩሮ 88 ውድድር በጥሩ ጤንነት ሆኖ በመድረስ ሆላንድ ኢንግላንድን 3ለ1 በረታችበት የምድብ ማጣሪያ ሀትሪክ ሰርቷል፡፡

በግማሽ ፍፃሜው ሆላንድ ከአዘጋጅዋ ጀርመን ጋር በሀምቡርግ ከተማ ተገናኝታ ሉተር ማቲያስ ባስቆጠራት ጎል 1ለ0 ተመርታለች፡፡ ነገር ግን በሮናልድ ኪዮመን ፍፁም ቅጣት ምትና በማርኮ ቫንባስተን 2ኛ ጎል ለፍፃሜው ደርሳለች፡፡ በሌላው ግማሽ ፍፃሜ ሶቪየት ህብረት ጣሊያንን 2ለ0 አሸንፋለች፡፡ በሙኒክ ከተማ በተደረገው የፍፃሜ ግጥሚያ የውድድሩ ኮከብ በሆኑት በሩድ ጉሌትና ማርኮ ቫንባስተን ጎሎች ሆላንድ 2ለ0 በማሸነፍ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለትልቅ ኢንተርናሽናል ውድድር የዋንጫ ድል በቅታለች፡፡

በ1992-የዴንማርካውያን አስገራሚ ገድል በስዊድን አዘጋጅነት የ1992ቱ የአውሮፓ ሻምፒዮና

የተካሄደው የምስራቅ አውሮፓ የለውጥ አብዮት ባሰፈነበት

ማግስት ነበር፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ዴንማርክን ተጠቃሚ አድርጓታል፡፡

ምክንያቱም የዩሮ 92 ተሳትፎን ያገኘችው ዩጎዝላቪያ በምስራቅ አውሮፓ ከተቀሰቀሰው አብዮት ሳቢያ በመበታተኗ በምትኳ እንድትገባ በአውሮፓ ፉትቦል ማህበር ስለተፈቀደላት ነው፡፡

አሰልጣኝ ሪቻርድ ሞለር ኔልሰን ለዕረፍት ተበታትነው የነበሩት ተሰላፊዎች በማሰባሰብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጠንካራ ቡድን በማዋቀር በጀመሩት ውድድር ዴንማርክ ሳይጠበቅ እስከ ፍፃሜው ድረስ ለመዝለቅ ችላለች፡፡ ዴንማርክ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ስዊድን፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ጋር በመጫወት ውድድሩን ስትጀምር በምድብ ሁለት ሆላንድ፣ ጀርመን፣ ስኮትላንድና ራሺያ ይገኙ ነበር፡፡

ከምድብ አንድ ስዊድንና ዴንማርክ እንዲሁም ከምድብ ሁለት ሆላንድና ጀመርን ወደ ግማሽ ፍፃሜው ተሸጋግረዋል፡፡ በጎተንበርግ ከተማ በሆላንድና በዴንማርክ መካከል የተደረገው ግማሽ ፍፃሜ 2ለ2 በሆነ ውጤት በመጠናቀቁ በመለያ ምት ዴንማርክ በማሸነፍ ለፍፃሜው ግጥሚያ ደርሳለች፡፡

ጀርመን በበኩሏ (የአውሮፓ.... ወደ ገጽ 14 የዞረ)