brochure amharic final - the compass...? éñ ó y l / 3 d æ ¬ l Ò / q æþ d wÞ \ â e l q _ t...

2
ተጨማሪ ምክሮች 1. በቤት ውስጥ የአጎበር እጥረት ካለ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ሁልጊዜ በአጎበር ውስጥ መተኛት አለባቸው። 2. በማንኛዉም አጋጣሚ ያገኛችሁትን ወባን ለመከላከል የሚያስችሉ ትክክለኛ መረጃዎች ወይም ክህሎቶች ለቤተስቦቻችሁ እና ለጓደኞቻችሁ አካፍሉ። 3. በትምህርት ቤት ውስጥ ወይም በማኅበረሰቡ አማካኝነት በሚሰጡ የጤና እንክብካቤ ፕሮግራሞች ተሳተፉ። የወባ በሽታ ምንድን ነው? የወባ በሽታ በጥገኛ ተሕዋስያን አማካኝነት የሚመጣ ለሞት የሚያደርስ በሽታ ነው። እነዚህ ተሕዋስያን ፕላዝሞዲየም ተብለው የሚጠሩ ባለ አንድ ህዋስ ፍጥረታት ሲሆኑ ወደ ሰው ደም ውስጥ የሚገቡት አኖፊሊስ በምትባለው ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ነው። የወባ በሽታ ተሕዋስያን በግለሰቡ ጉበትና ቀይ የደም ህዋሳት ውስጥ በመግባት ይራባሉ። የወባ በሽታ ምልክቶች የወባ በሽታ ምልክቶች ከሁለት እስከ ሶስት ቀናት እየቆዩ በተደጋጋሚ ሊታዩ የሚችሉ እንደ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ማላብ፣ ማንቀጥቀጥ ፣ ራስ ምታት፣ የመገጣጠሚያ ቁርጥማት፣ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ናቸው። በማንኛውም ሰው ላይ እነዚህ ምልክቶች ከታዩ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባል፡፡ ÕpÛĜØ IJÜ.¹ à!¤.5ع -ķ`¤ Õċ Č[F 8o0 Federal Democratic Republic of Ethiopia Ministry of Health

Upload: others

Post on 06-Aug-2020

2 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: Brochure Amharic Final - The Compass...? éñ ó y L / 3 D æ ¬ l Ò / q æþ D wÞ \ â E L q _ t î D / B L ¬Ü ] Û _ D ×ã Î / l Ò / æ î ? g D lÞ 2 G /ñ a g ó l Ï äð

ተጨማሪ ምክሮች1. በቤት ውስጥ የአጎበር እጥረት ካለ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና ከ5 ዓመት

በታች የሆኑ ህፃናት ሁልጊዜ በአጎበር ውስጥ መተኛት አለባቸው።

2. በማንኛዉም አጋጣሚ ያገኛችሁትን ወባን ለመከላከል የሚያስችሉ

ትክክለኛ መረጃዎች ወይም ክህሎቶች ለቤተስቦቻችሁ እና

ለጓደኞቻችሁ አካፍሉ።

3. በትምህርት ቤት ውስጥ ወይም በማኅበረሰቡ አማካኝነት በሚሰጡ

የጤና እንክብካቤ ፕሮግራሞች ተሳተፉ።

የወባ በሽታ ምንድን ነው?የወባ በሽታ በጥገኛ ተሕዋስያን አማካኝነት የሚመጣ ለሞት

የሚያደርስ በሽታ ነው።

• እነዚህ ተሕዋስያን ፕላዝሞዲየም ተብለው የሚጠሩ ባለ

አንድ ህዋስ ፍጥረታት ሲሆኑ ወደ ሰው ደም ውስጥ

የሚገቡት አኖፊሊስ በምትባለው ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት

ነው።

• የወባ በሽታ ተሕዋስያን በግለሰቡ ጉበትና ቀይ የደም ህዋሳት

ውስጥ በመግባት ይራባሉ።

የወባ በሽታ ምልክቶች የወባ በሽታ ምልክቶች ከሁለት እስከ ሶስት ቀናት እየቆዩ

በተደጋጋሚ ሊታዩ የሚችሉ እንደ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ

ማለት፣ ማላብ፣ ማንቀጥቀጥ ፣ ራስ ምታት፣

የመገጣጠሚያ ቁርጥማት፣ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

ናቸው። በማንኛውም ሰው ላይ እነዚህ ምልክቶች ከታዩ

በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ ይገባል፡፡Federal Democratic Republic of EthiopiaMinistry of Health

Federal Democratic Republic of EthiopiaMinistry of Health

Page 2: Brochure Amharic Final - The Compass...? éñ ó y L / 3 D æ ¬ l Ò / q æþ D wÞ \ â E L q _ t î D / B L ¬Ü ] Û _ D ×ã Î / l Ò / æ î ? g D lÞ 2 G /ñ a g ó l Ï äð

ራስን ከወባ በሽታ መጠበቅ ይቻላል?

አዎ ይቻላል፡፡ ወባ በተደጋጋሚ በሚከሰትበት አካባቢ የምንኖር ከሆነ ፤

አጎበር ሁልጊዜ እና በአግባቡ መጠቀም አለብን። አጎበሩም፦

• በፀረ ወባ ኬሚካል የተነከረ መሆን አለበት

• ምንም ቀዳዳ የሌለው፥ ካለዉ ደግሞ በአግባቡ መሰፋት አለበት

• በመተኛ ወይም ፍራሻችን ዙሪያ አጎበሩ ተዘርግቶ መጠቅጠቅ

አለበት፡፡

ቤትን በፀረ ወባ ኬሚካል ማስረጨት ፤ ከተረጨ በሗላ የቤት

ግድግዳን ለ6 ወር አለመለሰን ወይም ቀለም አለመቀባት፤

በመኖሪያ ቤቶች በር እና መስኮቶች ላይ እንደ ወንፊት ያለ መከለያ

ማድርግ፤ ቤት ዉስጥ በቂ የአየር ዝውውር እንዲሁም በቂ ብርሃን

እንዲኖር ማድረግ

የወባ ትንኞች በብዛት ከሚገኙበት ጥሻ፤ ረግረጋማ የሆነ አካባቢና

ለትንኝ መራቢያነት አመቺ የሆኑ የታቆሩ የውኃ ጉድጋዶች ካሉ

በደንብ መድፈን/ ማፋሰስ

የወባ በሽታ ከሰዉ ወደ ሰው እንዴት ይተላለፋል?

አንድ ሰው አኖፊሊስ በምትባለው ሴት ትንኝ ቢነደፍ ወባ

ሊይዘው ይችላል። ስለዚህ ሁል ጊዜ በአጎበር ውስጥ መተኛት

አለብን።