(612) 341-4373 ze-habesha newspaper / february 2015 no. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ...

24
Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 612-226-8326 / [email protected] Voice of Ethio-Americans የካቲት 2007 ቅጽ VI ቁጥር. 71 [email protected] ዕውነት ያሸንፋል በውስጥ ገጽ፦ ዘጠኛው ስቃይ (የወንጀል ታሪክ) .... ባለቤት የሌለው ምድር... ፍየል ብትሰርቅ ሌባ ተብለህ ትታሰራለህ፤ ሃገር ብትሰርቅ ትነግሳለህ.. ለጤናማ ጉበት 9 አማራጮች ታክስዎን የሚሰራልዎ የረዥም ዓመታት ልምድ ያለው አክሎግ ነው አፕል ጋራዥ Apple Auto Repair - Engine - Brakes - Suspension - Transmission - Electrical - Body - Interior More... የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን $25 ብቻ የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃው እና ጉልበቱ በ20$ ብቻ። ለነብሰ ጡር የማይራራ ዱላ ሥጋ ለጤና ምን ይጠቅማል? ስለሊቨርፑልና አሰልጣኙ ገጽ 16 ላይ ገጽ 18 ላይ ገጽ 21 ላይ በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ ዶ/ር ሲራክ ኃይሉ 3601 Minnehaha Ave, Mpls, MN55406. ዮሐንስ፡ 6513343029 ሸጋ እንጀራ፣ ግሮሰሪና መጋገሪያ Shega Foods የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ ወደ ሸጋ ይደውሉ ሸጋ 100% የጤፍ እንጀራን ከየሱቁ ይጠይቁ በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች ሁሉም ይገኛሉ 2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406 (612) 341-4373 900 American Blvd E Ste 206, Bloomington, MN 55420 የትዝታው ንጉሥ የማህሙድ አህመድ ና የጃኪ ጎሲ የሚኒሶታ ኮንሰርት በጉጉት እየተጠበቀ ነው ስለማህሙድ አህመድ ተሰምተው የማይጠገቡ መረጃዎ የኢትዮ-አሜሪካውያን ድምጽ ሰኔና ሰኞ ገጠመ እንደሚባለው ቅዳሜና ቫለንታይን ተገጣጥመዋል። የዘንድሮው ቫለንታይን ደይ በሚኒሶ ታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የት እንደሚያከብሩት ከወዲሁ ያወቁ ይመስላል። ገና የትዝታው ንጉሥ ማህሙ ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል። ቫለንታይን ደይ ቅዳ ሜ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሲከበር ማህሙድም በሚኒያፖሊስ ከጃኪ ጎሲ ጋር ደምቆ ያመሻል። ይህን ትልቅ የሙዚቃ ድግስ በሚኒሶታ ከሶል ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ያቀረበላችሁ ናዲ ፕሮሞሽን ለዘሐበሻ እንደገለጸው ይህን ትልቅ ኮንሰርት እውን ለማድረግ የወጣው ወጪ ከፍተኛ ነው። እንደናዲ ፕሮሞሽን ገለጻ ፌብሩዋሪ 14 የትዝታው ንጉስ ማህሙድ አህመድ እና የጃኪ ጎሲ የሙዚቃ ኮንሰርት የሚደረገው ሚኒያፖሊስ Muse Event Center ሲሆን አድራሻውም 107 3rd Avenue North, Minneapolis, MN 55401 ነው። ስለዚህ ኮንሰርት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥሮች 6124237009 /6127016276 / 2063531937 መደወል ይቻላል። ይህን የሙዚቃ ኮንሰርት በዲጄ የሚያጅበው ዲጄ ሶል; የሙዚቃ ባንዱም ዛየን ባንድ መሆናቸው ታውቋል። ጥቂት ዘመን ስለማይሽረው ማህሙድ አህመድ ሚኒሶታ መምጣቱን በማስመልከ ት የተዘጋጀ) ዝነኛውና ዘመን የማይሽረው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር በሚኒያ ፖሊስ የፊታችን ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ያቀርባል። ይህን በማስመልከት ለሚኒሶታ አንባቢዎችና ኮንሰርቱን በጉጉት ለሚጠብቁት ወገኖች የድምፃዊውን የ ሙዚቃ ሕይወት በጥቂቱም ቢሆን ላስቃኛቸው ነው። “አዲስ ነገር አመጣሁ : ራሴን ለወጥኩ ብዬ እንደ ጀምስ ብራውን አፌን እያጣመምኩ ስዘፍን አይቶ በሁኔታዬ ተናዶ ጥላሁን ገሰሰ በጥፊ መትቶኛል” ማህሙድ አህመድ ነበር ይህን ያለው :: በአንድ ወቅት የጀምስ ብራውን ዝና በአለም ላይ በናኘበት ወቅት የሱን ስታይል ለመከተል ብሎ ራሱን ባጣበት ወቅት የሙያ አባቱ የሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ ለመገሰጽ ሲል እንደመታው ገልጿል :: የትዝታው ንጉሥ የሚል የአድናቂዎቹ የቁልምጫ ስም የተሰጠው ተወዳጁ ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ እንደ አውሮፓውያን ቀመር ሜይ 8 ቀን 1941 በአዲስ አበባ እጅግ የአራዶች ሰፈር በሚባለው አሜሪካ ጊቢ ተወለደ :: እናቱ ጥሩ የጉራጌ ባለሙያና የቤት እመቤት ሲሆኑ አባቱ ሼክ እንደነበሩ ማህሙድን በአካል አግኝቼው ባነጋገርኩበት ወቅት ገልጾልኛል :: በተለይም አዲስ አበባ በነበርኩበት ወቅት በማሳትማት ጋዜጣ አማካኝነት ለተለያዩ ጊዜያት በሀገር ፍቅር ትያትር ቤትም ሆነ በፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ሙዚቃ ቤቱ አግቼው ብዙ አውርቼው ነበር :: (ማህሙድ ... እባክዎ ገጽ 15 ይመልከቱ) አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ሳይቀናቸው ተመለሱ በምሽትና በድብቅ ሀሙስ ምሽት ጃንዋሪ 29/2015 ዓ.ም ሚኒሶታ የገቡት የሕወሓት ተላላኪው ባለስልጣን አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን መከናነብ የጀመሩት ገና ከአውሮፕላን ከወረዱ ጀምሮ ነበር:: አባዱላ የሕወሓት ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን እመራታለሁ፤ የኦሮሞ ሕዝብ መሪ ነኝ እያሉ በርከት ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች በሚኒኖሩባት ሚኒሶታ ከኤርፖርት የተቀበሏቸው ጥቂት የሶማሌ ተወላጆች ናቸው:: እነዚህ የሶማሊያ ተወላጆች አባዱላን ከተቀበሉ በኋላ ብሎሚንገተን በተሰኘው የሚኒሶታ ከተማ ሆቴል ያሳረፏቸው ሲሆን እንደዚህ ቀደሙ የወያኔ ተላላኪዎች ሲመጡ ፖስተር ተለጥፎ (አባዱላ... እባክዎ ወደ ገጽ 6 ዞሯል)

Upload: others

Post on 26-Mar-2020

25 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 612-226-8326 / [email protected] Voice of Ethio-Americansየካቲት  2007                        ቅጽ    VI      ቁጥር.  71              [email protected] ዕውነት ያሸንፋል

በውስጥ  ገጽ፦  ዘጠኛው  ስቃይ  (የወንጀል  ታሪክ)....  ባለቤት  የሌለው  ምድር...  ፍየል  ብትሰርቅ  ሌባ  ተብለህ  ትታሰራለህ፤  ሃገር  ብትሰርቅ  ትነግሳለህ..  ለጤናማ  ጉበት  9  አማራጮች

ታክስዎን የሚሰራልዎ የረዥም ዓመታት ልምድ ያለው አክሎግ ነው

አፕል  ጋራዥ  

Apple Auto Repair- Engine- Brakes- Suspension- Transmission

- Electrical- Body- InteriorMore...

የመኪናዎን ዘይት ካለቀጠሮ እንቀይራለን

$25ብቻ

የዝናብ መጥረጊያዎን ለማስቀየር እቃውእና ጉልበቱ በ20$

ብቻ።

ለነብሰ ጡር የማይራራ ዱላ

ሥጋ ለጤና ምን ይጠቅማል?

ስለሊቨርፑልና አሰልጣኙ

ገጽ 16 ላይገጽ 18 ላይ ገጽ 21 ላይ

በሥራ  ቦታዎ  አደጋ፣  የመኪና  አደጋና  የስፖርት  ጉዳት  ከደረሰብዎት  እና  ካጋጠመዎ  እውቅ  ካይሮፕራክተር  ከፈለጉ  ወደ  ካይሮፕራክቲክ  ክሊኒካችን  ይምጡ

ዶ/ር  ሲራክ    ኃይሉ

3601 Minnehaha Ave, Mpls, MN55406. ዮሐንስ፡-­ 651-­334-­3029

           ሸጋ  እንጀራ፣  

ግሮሰሪና  መጋገሪያ

Shega Foods

የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ

ወደ ሸጋ ይደውሉ

ሸጋ  100%  የጤፍ  

እንጀራን  ከየሱቁ  

ይጠይቁ

በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች ሁሉም ይገኛሉ

2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406(612) 341-4373

900 American Blvd E Ste 206, Bloomington,

MN 55420

የትዝታው   ንጉሥየማህሙድ  አህመድ  ና  የጃኪ  ጎሲ  

የሚኒሶታ  ኮንሰርት  በጉጉት  እየተጠበቀ  ነው

ስለማህሙድ  አህመድ

ተሰምተው  የማይጠገቡ  መረጃዎች

የኢትዮ-አሜሪካውያን  ድምጽ

ሰኔና ሰኞ ገጠመ እንደሚባለው ቅዳሜና ቫለንታይን ተገጣጥመዋል። የዘንድሮው ቫለንታይን ደይ በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የት እንደሚያከብሩት ከወዲሁ ያወቁ ይመስላል። ገና የትዝታው ንጉሥ ማህሙድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል። ቫለንታይን ደይ ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ሲከበር ማህሙድም በሚኒያፖሊስ ከጃኪ ጎሲ ጋር ደምቆ ያመሻል።

ይህን ትልቅ የሙዚቃ ድግስ በሚኒሶታ ከሶል ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር ያቀረበላችሁ ናዲ ፕሮሞሽን ለዘ-­ሐበሻ እንደገለጸው ይህን ትልቅ ኮንሰርት እውን ለማድረግ የወጣው ወጪ ከፍተኛ ነው። እንደናዲ ፕሮሞሽን ገለጻ ፌብሩዋሪ 14 የትዝታው ንጉስ ማህሙድ አህመድ እና የጃኪ ጎሲ የሙዚቃ ኮንሰርት የሚደረገው ሚኒያፖሊስ Muse Event Center ሲሆን አድራሻውም 107 3rd Avenue North, Minneapolis, MN 55401 ነው። ስለዚህ ኮንሰርት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥሮች 612-­423-­7009 /612-­701-­6276 / 206-­353-­1937 መደወል ይቻላል። ይህን የሙዚቃ ኮንሰርት በዲጄ የሚያጅበው ዲጄ ሶል; የሙዚቃ ባንዱም ዛየን ባንድ መሆናቸው ታውቋል።

ጥቂት  ዘመን  ስለማይሽረው  ማህሙድ  አህመድ  ሚኒሶታ  መምጣቱን    በማስመልከ

ት  የተዘጋጀ)

ዝነኛውና ዘመን የማይሽረው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር በሚኒያፖሊስ የፊታችን ፌብሩዋሪ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ያቀርባል። ይህን

በማስመልከት ለሚኒሶታ አንባቢዎችና ኮንሰርቱን በጉጉት ለሚጠብቁት ወገኖች የድምፃዊውን የሙዚቃ ሕይወት በጥቂቱም ቢሆን ላስቃኛቸው ነው።

“አዲስ ነገር አመጣሁ : ራሴን ለወጥኩ ብዬ እንደ ጀምስ ብራውንአፌን እያጣመምኩ ስዘፍን አይቶ በሁኔታዬ ተናዶ ጥላሁን ገሰሰ

በጥፊ መትቶኛል” ማህሙድ አህመድ ነበር ይህን ያለው :: በአንድ ወቅት የጀምስ ብራውን ዝና በአለም ላይ በናኘበት

ወቅት የሱን ስታይል ለመከተል ብሎ ራሱን ባጣበት ወቅት የሙያ አባቱ የሙዚቃው ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ

ለመገሰጽ ሲል እንደመታው ገልጿል :: የትዝታው ንጉሥ የሚል የአድናቂዎቹ የቁልምጫ

ስም የተሰጠው ተወዳጁ ድምጻዊ መሀሙድ አህመድ እንደ አውሮፓውያን ቀመር

ሜይ 8 ቀን 1941 በአዲስ አበባ እጅግ የአራዶች ሰፈር በሚባለው አሜሪካ

ጊቢ ተወለደ :: እናቱ ጥሩ የጉራጌ ባለሙያና

የቤት እመቤት ሲሆኑ አባቱ ሼክ እንደነበሩ

ማህሙድን በአካል አግኝቼው ባነጋገርኩበት

ወቅት ገልጾልኛል :: በተለይም አዲስ አበባ በነበርኩበት

ወቅት በማሳትማት ጋዜጣ አማካኝነት ለተለያዩ ጊዜያት በሀገር ፍቅር

ትያትር ቤትም ሆነ በፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ሙዚቃ ቤቱ አግቼው ብዙ

አውርቼው ነበር :: (ማህሙድ ... እባክዎ ገጽ 15 ይመልከቱ)

አባዱላ  ገመዳ  በሚኒሶታ  

ሳይቀናቸው  ተመለሱበምሽትና በድብቅ ሀሙስ ምሽት ጃንዋሪ 29/2015 ዓ.ም ሚኒሶታ የገቡት የሕወሓት ተላላኪው ባለስልጣን አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ቅሌትን መከናነብ የጀመሩት ገና ከአውሮፕላን ከወረዱ ጀምሮ ነበር::አባዱላ የሕወሓት ተላላኪ ሆነው የኢትዮጵያን እመራታለሁ፤ የኦሮሞ ሕዝብ መሪ ነኝ እያሉ በርከት ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች በሚኒኖሩባት ሚኒሶታ ከኤርፖርት የተቀበሏቸው ጥቂት የሶማሌ ተወላጆች ናቸው:: እነዚህ የሶማሊያ ተወላጆች አባዱላን ከተቀበሉ በኋላ ብሎሚንገተን በተሰኘው የሚኒሶታ ከተማ ሆቴል ያሳረፏቸው ሲሆን እንደዚህ ቀደሙ የወያኔ ተላላኪዎች ሲመጡ ፖስተር ተለጥፎ (አባዱላ... እባክዎ ወደ ገጽ 6 ዞሯል)

Page 2: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 2

Page 3: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 3

Page 4: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 4

Masinqo Night.2

የማስንቆ ምሽት 2ዝነኛዋ

ማሪቱ ለገሰከግዛቸው ተክለማርያም ጋር

ከማስንቆ በተጨማሪበዋሽንትእና ክራርልዩ ምሽት

በራስ ያሳልፋሉ

ቅዳሜ ማርች 14Saturday

March 14, 2015ቀኑን ይያዙ

Ras Lounge2516 7th Street West, Saint

Paul, MN 55116Phone:(651) 698-6407

Page 5: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 5

ለምን  ራስ  በኢትዮጵያውያን  እና    

ኤርትራውያን  ተመራጭ  ሬስቶራንት  ሆነ?

እጅ  የሚያስቆረጥም  

የጾም  እና  

የፍስክ  ምግቦች

ከረምቡላን  እና  ፑልን

የያዘ  ብቸኛው  

የወገን  ባር  በመሆኑ

በየወሩ  ምርጥ  ዘፋኞችን  

እና  ታዋቂ  ዲጄዎችን

ይዞ  መገኘቱ

ከደንበኞች  ጋር  የቤተሰብ  

ያህል  የሚቀራረቡት  

ሠራተኞቻችን

ራስ  ቁርጥ

ዘወትር  ሐሙስ፣  አርብ

ቅዳሜና  እሁድ

ራስ  ወዲያው  የታረደ  

ቁርጥ  ሥጋ

ከጠንክርአዋዜ  ጋር  ይዞ  ቀርቧል

ስፖርት

የእንግሊዝ፣  የስፔን  

እና  የአሜሪካ  ሶከር

ና  ፉትቦል  ጨዋታዎችን  

17  በላይ  ቲቪዎች  

እናሳያለን

ድግስ  

አስበዋል?

ሠርግ፣  ልደት፣  ምርቃት፣  

የግል  ፓርቲ  አለብዎት?  ቦታ  

አጣሁ  ብለው  ተቸግረዋል?  

ራስ  የተንጣለለ  የታችኛው

 ላውንጁን  ያከራያል።  ይም

ጡና  ካለምንም

 ጭንቅንቅ  ይዝናኑበት

በምግቦቻችን  ጥራትና  በዋጋችን  ተመጣጣኝነት  የሚወዳደረን  ሬስቶራንት  የለም

የእረፍት  ቀንዎን  በሙዚቃና  ስፖርት  ጨዋታዎች  

እየተዝናኑ  ተወዳጁን  ቁርጥ  ይመገቡ

ራስ  ለታላቁ  አብይ  ጾም  

እየዘጋጀ  ነው

ቅዱስ  ቫለንታይን

ደይን

በራስ  ያሳልፉ

የምሽት ጨዋታበራስ ላውንጅ እንደተወደደ የቆየ ምርጥ የመዝናኛ ምሽት በየወሩ አንድ ጊዜ -­ የዚህ ወር ፌብሩዋሪ 2, 2015 ነው

Page 6: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 6

Ze-Habesha Newspaper is

Legally Registered in state of

Minnesota - USA

Founded in December 2008

Publisher :-

ZeHabesha LLC

ዋና  አዘጋጅ:-    

ሔኖክ  ዓለማየሁ  ደገፉ    

Editor in Chief:-

Henok A. Degfu e-mail:- [email protected]

[email protected]

አዘጋጆች:-­  ሊሊ  ሞገስ፣  [email protected]

ቅድስት  አባተ  

 አማካሪ፡-  ዶር  ዓብይ  ዓይናለም  

Zehabesha LLC

6938 Portland Ave,

 Richfield  MN  55423    

612-226-8326 www.zehabesha.com

www.facebook.com/zehabesha

www.twitter.com/zehabesha

“Journalism can never be silent: that is

its greatest virtue and its greatest fault. It

must speak, and speak immediately, while

the echoes of wonder, the claims

of triumph and the signs of horror are

still in the air.”

Henry Anatole Grunwald

በሚኔሶታ -­ አሜሪካ የተቋቋመ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ጋዜጣ ነው። ጋዜጣው ዓላማው የማህበረሰባችን የወቅታዊና ሚዛናዊ መረጃ መገኛ መሆን ነው።

ዘ-­ሐበሻ ከማንኛውም ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ድርጅት፣ ጎሳ፣ ያልወገነ፣ ነጻ ጋዜጣ ነው፡፡

ዓብይ  መልዕክት

ከቴዲ ጸጋ

ውብ፤ ቆንጆ፤ ማራኪ የተባሉ ውበት ገላጭ ቃላቶች ውበቷን ለመግለፅ አቅም አልነበራቸውም፡፡ የወጣለት ቆንጆ ናት! ምንም የሚወጣላት እንከን የለም? ብዙዎች በፍቅር ተነድፈው ተማርከውላታል፤ አቅላቸውን እስኪስቱ ወደዋታል፡፡ ሊያገኛት የታደለ ግን አንድም ሰው የለም! ከላይ ጀምሬ ያሞገስኳት ሲፈን ትባላለች፡፡ የሲፈን ውበት ውጫያዊ ብቻ ውስጣዊም እንጂ አይደለም! እነሆ ትምህርቷን አጠናቃ ወደ ሥራ ዓለም ከገባች ድፍን አስራ ስምንት ወራቶችን አስቆጥራለች፡፡ እስከ አሁን ከምታገኘው ወርሃዊ ደሞዟ ግማሽ ያህሉን ከእሷ ውጪ ጧሪ ለሌላቸው እናቷ በመላክ የልጅነት ግዴታዋን እየተወጣች ነው፡፡ በመስሪያ ቤቷ የምታየውን ብልሹ አሠራ ር፤ የባለሥልጣናት በጉቦና ሙስና መጨማለቅ ሁሌም ውስጧን እንደ አስቆጣት ነው፡፡

በዚህ የክፋት መንገድ ላለመጓዝ የምታደርገው ጥረት ደግሞ ዘወትር ያኰራታል! ይሄም ጥረቷ ነው በግምገማ ወቅት ደረቷን ነፍታ የሥራ ባልደረቦቿ ላይ የምታየውንና የምትሰማውን ሥልጣንን ተገን በማድረግ የሚደረግ ብልግና ፊት ለፊት ለመቃወም ድፍረት የሰጣት፡፡

ሲፈን አትፈራም! የኦህዴድ አመራሮችን ላይ መረጃዎቿን አንድ በአንድ እያቀረበች የሂሳ ናዳ ስታጎርፍባቸው በድፍረት ነው፡፡ ‹‹ጣልቃ አይገቡብን!፤ በእኛ ጉዳይ በቀዳሚነት የሚመለከተው እኛን ነው!፤ እኛ ጉዳዩን አይተን የራሳችንን ውሳኔ ከወሠንን በኃላ ነው ወደ አጋር ድርጅቶች ማስተላለፍ ያለብን፤ አሁን ያው አሠራር ግን በአይነቱም በይዘቱም ከዚህ ለየት ያለነው፡፡

በእኛ ጉዳይ ሌሎች እየወሰኑልን ነው፡፡ ለምን ይሄ ይሆናል?›› ኦህዴድ አቅም ስለሌለው ነው? እንዴት የሀገሪቱን ግማሽ ህዝብ የያዘ ድርጅት፤ በተለይም የወከለው ህዝብ ድጋፍ የሌለውን ድርጅት ሊፈራ ይችላል?

ይሄን የማስተር ፕላን ጥያቄ ተከትሎ የተወሰደውን እርምጃ ብቻ ሳይሆን አይደለም እንደ ድርጅት ኦህዴድ ከተቋቋመ በኃላ የነበሩትን ጣልቃ ገብነቶች በሙሉ ነው፡፡ እናንተ እነሱን የምትፈሯቸው ደኅንነቱ፣ ፖሊሱ፣ መከላከያው፣ በእጃቸው ስላለ ነው) ወይስ ሁላችሁም በሙስና ስለተጨመላለቃችሁ እንዳያስሯችሁ ሰግታችሁ ነው? ወይስ እንደሚባለው አብዛኛዎቻችሁ የኦህዴድ ባለሥልጣኖች፤ የዘር ግንዶቻችሁ ከኦሮሞ ስለማይመዘዝ ነው) በእነሱ እጅ ተጠፍጥፋችሁ ስለተሰራችሁ ነው፡፡ ቁርጠኝነት አጥታችሁ የወከላችሁትን ህዝብ እምነት እንዳይጥልባችሁ ተላላኪ የሆናችሁት?

ስለዚህ እናንተ እራሳችሁን አርሙ! እኛም ራሳችንን እናርም! ህወሃት የትግራይ ህዝብ አደራ እንዳለበት ሁሉ እኛም የኦሮሞ ህዝብ አደራ አለብን! ለእዚህ ህዝብ በትጋት መስራት አለብን!፤ ታሪካችን ን አድሰን ከህዝብ ጋር ታርቀን የምንሰራበት ሰዓት አሁን ነው፡ ፡ይሔ ካልሆነ፤ ግን ችግሩ የከፋ ይሆናል፡፡ ህገ-­መንግሥቱ የሰጠንን መብት ተጠቅመን በትጋት መስራት አለብን›› ብላ ንግግሯን ስትቋጭ የሚጠሏት ሰዎች ሁሉ ሳያውቁ ቤቱን በጭብጨባ ቤቱን አናወጡት፡፡ በዕለቱ መድረኩን የመራው ግለሰብ ቁጣው ነዳደ፤ በንዴት ደም ስሮቹ ተገታተሩ፤ እንደተናደደ ስብሰባውን ጨርሶ ወጣ! ከ ኦህዴድ ግምገማ በኃላ ከዕለታት በአንዱ ቀን ሲፈን እንደ ወትሮዋ የቢሮዋን በር ከፍታ ስትገባ አንድ ልጅ እግር ተከትሏት ገባ፡፡ ሰላምታ ሳያቀርብላት በእጁ የያዘውን ደብዳቤ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦላት በፍጥነት ወጣ፡፡ ፖስታውን አንስታ ቀዳ ማንበብ ጀመረች፡፡ ደብዳቤውን አንብባ እንደጨረሰች በመተከዝ ውስጥ ሆና ከወትሮው በተለየ እናቷን አሰበች፡፡

‹‹ለእውነት የማልሆነው ነገር የለም!›› ስትል በለሆሳስ አወራች፡፡ ስታ

“ፍየል  ብትሠርቅ  ሌባ  ተብለህ  ወህኒ  ትወርዳለህ

ሃገር  ብትሠርቅ  ግን  ንጉሥ  ትሆናለህ”ወራ ማንም የሰማት አልነበረም! አዝናለች! ያዘነችው በእስር ቤት የምታሳልፈውን የመከራና የስቃይ ወቅት በማሰብ አይደለም! በእርግጥ የእናቷ ጉዳይ ሁሌም እንዳሳሰባት ነው፡፡ ዛሬ ግን በፅኑ ያሳሰባት ያሳደጋት የኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ ነው! ‹‹ማነው ለዚህ ህዝብ በ

ታማኝነት ሊቆም የሚችለው? ማነው ህዝቡን ከመመዝበር የሚቆጠበው? መቼ ነው የእዚህ ህዝብ መብት የሚከበረው?

መቼ ነው የዚህ ህዝብ ግፋና መከራ ገደብ የሚያገኘው? የዚ

ህን ህዝብ መብት የጠየቀ ሁሉ ‹‹ኦነግ›› ተብሎ እጅና እግሩ ታስሮ ወደ ጨለማ ቤት መወርወር ከጀመረ አመታቶች ተቆጥሯል፡፡ እኔም በተቻለኝ መጠን ይሄን እኩይ ተግባር ለመዋጋት አስቤ ስታገል ይሔው ወደ ማይቀርልኝ እስር ቤት ለመግባት መንገድ ላይ ነ

ኝ!›› ብቻዋን ስታወራ ሳታውቀው ፊቷ በዕንባ እየታጠበ ነበር፡፡ እያለቀሰች መሆኑን ያወቀችው ፊት ለፊት ባለው መስታወት ራሷን ባየች ጊዜ ነው! ያ ውብ ፊቷ ጉበት መስሏል፡፡

የደብዳቤውን አንኳር መልዕክትድጋሚ ለማሰላሰል ሞኮረች ‹‹እውድሻለሁ! ጥያ

ቄውን በአግባቡ አቅርቤልሽ ነበር፡፡ አንቺ ግን ልትረጂኝ አልቻልሽም፡፡ ስለምወድሽ እንዳጣሽ ስለማልፈልግ እንዳትታሰሪ ብዙ ታግዬልሻለሁ፡፡ አንቺ ባይገባሽም እኔ በፍቅርሽ ብዙ ብዙ ተጐድቻለሁ፡፡ ከአሁን በኃላ ግን መጎዳት አልፈልግም፡፡ ያንቺ መታሰር ሰላምን የሚሰጠኝ ይመስለኛል፡፡

ምናልባት ስንራራቅ እረሳሽ ይሆናል እኔና አንቺ እንድንራራቅ ብዙ ነገር ምክሬያለሁ፤ መስሪያ ቤት ለመቀየር ድርጅቱን በደብዳቤ ጠይቄያለሁ፡፡ ድርጅቱ ግን ሊፈቅድልኝ አልቻለም፡፡ ስለዚህ ከአንቺ ጋር ለመራራቅ ያለኝ ብቸኛው አማራጭ ጋሻ፣ ከለላ ሆኖ ሲከላከልልሽ የነበረውን ክርኔን ከላይሽ ላይ ማንሳት ነው!›› አስባ ስትጨርስ ተገረመች እያዘነችም ቢሆን ሳትወድ በግድ ጥርሶቿን አፈገገች፡፡ ከአራት ወራት በኋላ ሲፈን በተፈበረከላት ወንጀል በውሸት ተፈርዶባት ቤቷ ቃሊቲ ሆነ፡፡

እውነትን መናገር ለህዝብና ለሀገር ጥቅም መታገል ባደጉት ሀገራትና እያደጉ ባሉት ሀገራት ሲያሽልም

በእኛ ሀገር ግን ሲፈንን እስረኛ አደረጋት፡፡ ምዕራባውያን ስለሌባ ሲተርቱ “ፍየል ብትሠርቅ ሌባ ተብላህ ወህኒ ትወርዳለህ አገር ብትሠርቅ ግን ንጉስ ትሆናለህ” ይሉ ይሄ ነው።

አባዱላ  ገመዳ  በሚኒሶታ  ሳይቀናቸው  ተመለሱከገጽ 1 የዞረስብሰባ እንደሚጠራው ለአባዱላ የወያኔ ተላላኪዎች ያደረጉት ነገር የለም:: ምክንያቱም ከዚህ ቀደም ፖስተር ተለጥፎ የአባይ ቦንድ ስብሰባ ተጠርቶ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት ተቃዋሚዎች ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይልቁንስ በቴክስት መልክት ብቻ በስልክ የወያኔ ኔትወርኮች ብቻ እንዲጠራሩ የተደረገና ሌላው ሕዝብ የአባዱላን ስብሰባ እንዳይሰማ ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ይህ ቴክስት መልዕክት ለኢትዮጵያን ደረሰ::ኢትዮጵያውያኑ ልክ እንደሕወሓት ተላላኪዎች ድምፃቸውን ሳያሰሙ በቴክስት መልዕክት የተጠራሩ ሲሆን ስብሰባው የሚደረግበት ሂልተን ሆቴል ተገኝተዋል:: አባዱላ ገመዳ ከአንዲት ሴት ጋር ሁለተኛ ፎቅ ላይ ቁጭ ብለው ወደታች በአንደኛው ፎቅ በኩል የሚገቡትን ሰው እየተመለከቱ; አጠገባቸው ያለችው የትግራይ ተወላጅ የሆነች ሴት የሰውን ማንነት የምትነግር ይመስል ለባለስልጣኑ ትጠቁማለች:: በዚህ መሃል የዘ-­ሐበሻ አዘጋጆችም ሲገቡ ሴትየዋ ለአባዱላ በጥቆማ ስታሳይ የዘ-­ሐበሻ አዘጋጆች ተመልክተዋል:: የዘ-­ሐበሻ አዘጋጆች ወደ ስብሰባው ሊገቡ ሲሉ እንደተለመደው የተከለከሉ ሲሆን ስብሰባውን ያዘጋጀው አካል ከ30 በላይ የሚቆጠሩ ፖሊሶችን በመቅጠር ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል:: አንድ ፖሊስን በሚኒሶታ ለአንድ ዝግጅት በሰዓት መንግስት ከሚከፍለው በተጨማሪ ዝግጅት አዘጋጁ ከ$50 ዶላር ያላነሰ የሚከፍል ሲሆን የሕወሓት መንግስት ለነዚህ የአሜሪካ ፖሊሶች ለ6 ሰዓታት ለ እያንዳዳቸው $300 ዶላር በአጠቃላይም ለፖሊስ 9 ሺህ ዶላር አውጥቷል:: ይህም በኢትዮጵያ ብር ሲመነዝር 180 ሺህ ብር መሆኑ ነው:: ለአዳራሽ በትንሹ ከ2 ሺህ ዶላር በላይ, ለሶማሌ ታክሲ ሾፌሮች በሰዓት ከ60 ዶላር በላይ እንዲሁም ለአባዱላ እና ለተላላኪዎቻቸው የሆቴል አዳር ከ150 ዶላር በላይ የወጣበት ይኸው የሚኒሶታ ስብሰባ ካለስኬት የተጠናቀቀ ሲሆን በስበባው የተገኘው ሕዝብም ከ25 ሰው እንደማይበልጥ በውስጥ ጉዳዩን እንዲከታተሉ የላክናቸው ምንጮች አስታውቀዋል::የሕወሃት መንግስት ተላላኪው አባዱላ ገመዳ በሚኒሶታ ስብሰባ እንዲያደርግ ግማሽ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር ያጠፋ ሲሆን ያተረፈው ጥፋትን ብቻ ሳይሆን አባዱላ ገመዳ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ስድበንም ጭምር ነው:: በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሂልተን ሆቴልና በተለያዩ አባዱላ በሄዱባቸው የኢትዮጵያ ሬስቶራንቶች በመገኘት አባዱላን በሰብ አዊ መብት ረገጣ, በአፋኝነት, በአምባገነንነት, በሙስና እና በግድያ ወንጀሎች ሲናገሯቸውና በርሳቸው ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ሲያሰሙባቸው ውለዋል:: በአጠቃላይ የሕወሓት መንግስት የዲያስፖራ ሳምንት በኦሮሚያ አከብራለሁ ብሎ ስብሰባ የጠራበት የአባዱላ ስብሰባ ከትርፉ ኪሳራው አመዝኗል:: ኢትዮጵያውያኑም በሚኒሶታ በተቃውሞ ሲያሸብሩት ውለዋል:: አባዱላ ገመዳ ዛሬ በሚኒሶታ የደረሰባቸው ቅሌት ነገ በሲያትል እንደሚደገም ይጠበቃል:: በሲያትል ያሉ ኢትዮጵያውያን የአባዱላን የህወሃት ተልኮ ለማክሸፍ እየተጠባበቁ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: አባዱ

ላ በሚኒሶታ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ የደረሰባቸውን የተቃውሞ ውርደት ቪድዮ በዘ-­ሀበሻ ድርድረ ገጽ ይመልከቱ።-­ See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38630#sthash.0NznliNY.dpuf

Page 7: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

ፖለቲካ ኢኮኖሚ አሜሪካ ማኅበረሰብ

(ዳዊት ከበደ ወየሳ)ሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለዚህ አካባቢ እኩል ግንዛቤ ይኖረው

ይችላል:: በመሆኑም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ስለዚህ አካባቢ ታሪካዊ ዳራ ማሳየት አስፈላጊ ሆኗል:: እናም በታሪክ መንኮራኩር ትንሽ ወደኋላ መሄድ ሊኖርብን ነው::

ይህ የሰሜን አውራጃ ከጥንት ጀምሮ ቤጌምድር ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን በራሱ መሪዎች ይተዳደር የነበረ ስፍራ ነው:: በደርግ ዘመን ስሙ ተቀይሮ ስሜን ጎንደር ሲባል በወቅቱ ከፍተኛ ክርክር የተደረገ ቢሆንም; ቀስ በቀስ ቤጌምድር መባሉ ቀርቶ ስሜን ጎንደር የሚለውን ስያሜ ይዞ ዘልቋል:: ይህ የቤጌ ምድር ክልል በሰሜን ከኤርትራ ጋር በመረብ ወንዝ, ከትግራይ ጋር ደግሞ በተከዜ ወንዝ ተፈጥሮአዊ ድንበር ሰርቶ ይተዳደር ነበር:: አጼ ቴዎድሮስ ይህንን ስፍራ በፍቅር እንጂ በጦርነት አሸንፈው አልገዙትም:: ላዩን ሁመራ እና ወልቃይትን ካልሆነ በቀር ወደ አርማጭሆ ዘልቆ የአካባቢውን ህዝብ ያስገበረ መንግስት የለም:: እዚህ ህዝብ ውስጥ ዘልቆ የፖለቲካ ስራ የሰራ አካል ቢኖር መጀመሪያ ኢዲዩ ከዚያ በኋላ ደግሞ ኢህዴን የተባለው የኢህአፓ ሁለተኛ እርከን አመራር ብቻ ነው:: ከዚያ ውጪ ራስ ሚካኤል ስሁልም ሆኑ አጼ ዮሃንስ የተከዜን ወንዝ ሲሻገሩ -­ ከትግራይ ወጥተው ቤጌምድር መግባታቸውን ያውቁት ነበር::

የድሮውን ታሪክ ካነሳን ካልቀረ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የአክሱማዊት ገዢ የነበረው ንጉሥ ኢዛና -­ በአውደ ነገሥቱ ከ4ሺህ በላይ የሚቆጠር ሰራዊቱ የ”ቤጃ”ን ምድር መቆጣጠሩ ተጽፏል:: ወደ መካከለኛው ዘመን ስንሻገር በ1530ዎቹ ንጉሥ ልብነ ድንግል ለፖርቱጋል ንጉሥ ደብዳቤ ሲጽፉ “ቤጌምድር” ድረስ ግዛታቸው መሆኑን ገልጸው ነበር:: ከዚያ በኋላ በነበረውም ታሪክ ቢሆን በ18ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ ላይ እስከ1788 ድረስ የየጁው ራስ አሊ አስተዳድረውታል:: እንዲህ እንዲህ እያልን ዘመነ መሳፍንትን አልፈን በአጼ ቴዎድሮስም ሆነ አጼ ዮሃንስ ወይም አጼ ምኒልክ ዘመን ቤጌምድር ራሱን የቻለ ግዛት ሆኖ ቆይቷል::

በራስ ኃይሉም ሆነ, ራስ መንገሻ አቲከም ወይም ራስ ወልደጊዮርጊስ አቦዬ ዘመን ቤጌምድር የትግራይ ክልል የሆነበት ወይም እንዲሆን የተጠየቀበት የታሪክ አጋጣሚ የለም:: ሌላው ቀርቶ ራስ ወልደጊዮርጊስ አቦዬ በንግሥት ዘውዲቱ ዘመን በ1909 ዓ.ም.የንጉሥነት ዘውድ ሲጭኑ -­ ቤጌምድር ራስ ገዝ ክልል መሆኑ ታውቆለት ነበር:: በነደጃዝማች አያሌው ብሩም ሆነ በነ ክፍሌ ዳዲ ሲተዳደርም ቤጌምድር ነበር -­ ስያሜው::

እስከ ቡያ ድረስ, በሃከርን ጨምሮ አብደራፊ የቤጃዎች ምድር እንጂ ሱዳንም ትግራይም ሆኖ አያውቅም:: የጎንደር ነገሥታት ለሰራዊታቸው እህል እና ከብት እስከፈለጉት ድረስ የሚጫንላቸው ከዚሁ የቤጃ ምድር (ቤጃ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች መጠሪያ የነበረ ነው) ወይም ከቤጌምድር ነበር:: ጣልያን አካባቢውን ሲቆጣጠር -­ ማይጨው ድረስ ዘምተው የወጉትን እነደጃች ጎላን ራስ ጎላ ብሎ መልሶ የሾመው ወልቃይት እና ጠገዴን በጸብ ሳይሆን በፍቅር ለመግዛት ካለው ፍላጎት በመነሳት ነው::

በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን በ1943 ዓ.ም. በነጋሪት ጋዜጣ

ጭምር -­ በአዋጅ ቤጌምድር በወቅቱ ከነበሩት 13ቱ ጠቅላይ ግዛቶች ውስጥ አንደኛው ነበር: (ነጋሪት ጋዜጣ 1943/1 አንብብ)::

ጠቅላይ ግዛት ከሆነ በኋላ ጎንደርን ዋና ከተማው አደረገ:: በተለይ ሁመራ መልማት ሲጀምር የወልቃይት እና ጠገዴ ህዝብ ጭምር የትራክተር እና ዘመናዊ የእርሻ መሳሪያ ባለቤት ሆኖ አካባቢውን ማልማት ጀመረ:: በዚያን ወቅት የመሃል አገሩም ሆነ የጎንደር እና የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወደ ቤጌምድር ተሻግረው አካባቢውን አልምተዋል:: በሱዳን በኩል መሃዲ ሉግዲ ተራራን ሲወጣ -­ ወይም በኤርትራ በኩል ጀብሃ መረብን ተሻግ ሮ ሲመጣ -­ ሁሉም በአማራው እና በትግራይ በተለይም በወልቃይት ህዝብ እየተቀጡ ተመልሰዋል:: ነገር ግን ከመቆየት ብዛት አካባቢው የቤጃዎች መሆኑ ቀርቶ በትግራይ ሰዎች እጅ ወደቀ:: ቤጌምድርመባሉ ቀረና “ምዕራብ ትግራይ” የሚል ስያሜ ተሰጠው::

ሌላ ተጨማሪ ነገር እዚህ ላይ ማከል ያስፈልጋል::ከቤጌምድር በታች ያሉ ሰዎች የቤጃዎችን ምድር “ስሜን” እያሉ መጥራት ያዘወትሩ ነበር:: (በኋላ ላይ North ለሚለው አቻ ፍቺ -­ አማርኛ ሰሜን የሚለውን ቃል የተዋሰው ከስሜን ነው):: ነገሮችን የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?) በሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ “ገ’ጨው” በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል:: ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱአሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል:: የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት -­ አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው -­ በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው::

ሰሞኑን ግጭቱ ከመባባሱ በፊት የአማራው ህዝብ ተዋጊዎች -­ ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር:: ሆኖም የህወሃት ወታደሮች አካባቢውን ለቅቀው ባለመሄዳቸው በተለይ በማይ’እምቧ በርካታ የህዝባዊ ወያኔሃርነት ትግራይ -­ ህወሃት አባላት ሞተዋል:: በወያኔዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ያስደነገጣቸው እና ወደ አርማጭሆ ያመሩት ሌሎች የህወሃት አባላት -­ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ጦርነት ሲያደርጉ ነበር የከረሙት:: በዚህ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ ነበር:: አሁን የመከላከያ ሰራዊት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከሰፈረ በኋላ ግን ጦርነቱ ለጊዜው ጋብ ብሏል:: ሆኖም ሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች -­ ማለትም የህወሃት እና ብአዴን አመራሮች ውስጥ ውስጡን እየተናቆሩ ናቸው::

ህወሃት በድንበር ጉዳይ ካደረጋቸው የአገር ውስጥ ጦርነቶች ይሄኛው ጠንከር ያለ ነው:: ከዚህ ቀደም የህወሃት ወይም የትግራይ ታጣቂዎች የአማራውን መሬት ሲወስዱ -­ ህዝቡ “በህግ አምላክ” ብሎ እየጮኸ ከመሞት ውጪ ብዙ ምርጫ አልነበረውም:: አሁን ግን እየጮኸ ሳይሆን ጥይት እያጮኸ መሞትን የመረጠበትን አጋጣሚ ለማየት እየበቃን ነው:: አሁን የደረንበትን የቅርቡን ታ

ሪክ እንዳየነው ከሆነ -­ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የአማራውን ህዝብ ከሁመራ እና ጠለምት: ከበየዳ, ከወልቃይት, ከድብ ባህር, ከአብደራፌ, ከብራዋድያ, ከሻግኔ እና ላሄን እያፈናቀሉ መሬቱን ለቀድሞ የወያኔ ወታደሮች ሲሰጡ ቆይተዋል:: በአካባቢው የአማራው መሬት ብቻ አይደለም የተወሰደው:: ወንዶቹን እያፈናቀሉ: ያንገራገረውን እየገደሉ ሚስቶቻቸውን እና ሴት ልጆቻቸውን በሙሉ ነው ነጥቀው የወሰዱት::

ባለቤት የሌለው መሬት -­ ቤጌምድር! በደምሳሳው እንለፋቸውና ወደ ደርግ ዘመን እንሻገር:: በደርግ ዘመን ከሁሉም የአገሪቱ ግዛቶች ይልቅ በአዲሱ ወታደራዊ አስተዳደር “አንገዛም” ብሎ መጀመሪያ የሸፈተው የቤጌምድር ህዝብ ነው:: አብዛኛውም ህዝብ በኢዲዩ ፓርቲ ስር በመሰባሰብ በነራስ መንገሻ ስዩም መሪነት የትጥቅ ትግል ያደረገው እዚህ ምድር ላይ ነው:: የኢህአፓ ሰራዊት ከትግራይ አሲምባ ከወጣ በኋላ የመጨረሻ ምሽጉን ያደረገው ጠለምት, በለሳ እና አርማጭሆን የመሳሰሉ የቤጌምድር ስትራቴጂ ቦታዎች ላይ ነው::

የአካባቢው ህዝብ ከማዕከላዊ መንግስት የራቀ በመሆኑ ህጋዊ ገንዘብ ጥቅም ላይ ያልዋሉባቸው የገጠር አካባቢዎች ጭምር ነበሩ:: እስከቅርብ ዘመን ድረስ በተለይ በአርማጭሆ የባርያ ንግድ ሙሉ ለሙሉ አልጠፋም ነበር:: በኋላ ላይ ኢህዴን አካባቢውንሲቆጣጠር ብዙ ባሮች ነጻ ወጥተዋል:: ቤጌምድር እውቅና ተነፍጎት -­ የመንግስት አስተዳዳሪዎች በግድ እየተጫኑበት በሺዎች የሚቆጠሩ የግል ትራክተሮች እና እህል መሰብሰቢያ መሳሪያዎች ዝገው እና አፈር በልቷቸው የቀሩት በተለይ በደርግ ዘመን ነበር:: የግል እርሻዎች በ”መሬት ላራሹ” አዋጅ ሲወረሱ የቤጌምድር ሰዎች ለክብር እና ለአፈራቸውን ደማቸውን ገበሩ -­ ብዙዎች ሰማዕት ሆነው በትግል ሜዳ ህይወታቸው አለፈ:: የተቀሩት ወደ ሱዳን ተሰደዱ:: አገሩ ያለ አራሽ እና ያለባለቤት ቀረ:: ይህ ግን እዚያው የቀሩትን ጭሰኞች -­ በተለይም ተከዜን ተሻግረው ሁመራ ላይ እገዛ ያደርጉ የነበሩትን የትግራይ ሰዎች ጠቀማቸው:: በመሬት ላራሹ አዋጅ የትግራይ ሰዎችን ተጠቃሚ አደረገ:: ቆይቶ ደግሞ ቤጌምድር የሚለው ስያሜ በመቀየሩ ታሪካዊ ስህተት ተሰራ::

ነገሮችን ለማጠቃለል ያህል -­ በደርግ ዘመን ቤጌምድርስያሜው ተቀይሮ ስሜን ጎንደር ሲባል ብዙ ውዝግብ ተነስቶ ነበር:: ሆኖም በወቅቱ ጎንደርን ያስተዳድር ለነበረው ሻለቃ መላኩ ተፈራ “ቤጌምድር” የሚለውን ስያሜ መሰረዝ በጣም ቀላሉ ነገር ነበር:: ነገሩ የሆነው በቤጌምድር ሰዎች “አልገዛም” ባይነት ነበር:: በወቅቱ የቤጌምድር ስያሜ እንዲቀር በመደረጉ -­ ህዝቡ ሰሚ የሌለው ተቃውሞ አድርጎ ነበር:: ግን የአካባቢው ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ለደርግ ያልተገዛ በመሆኑ -­ የአገሩን ሽማግሌዎች ጆሮ ሰጥቶ የሚሰማቸው አላገኙም:: እናም ቤጌምድር የሚለው ስም ያለ አዋጅ እና ያለ ህግ ቀስ በቀስ ከህዝቡ ጆሮ እና ህሊና እየጠፋ መጣ::

የዚህ አካባቢ ህዝብ... ቀን ጠብቆ የሚጥል እና የሚያነሳ ለመሆኑ -­ የአጼ ቴዎድሮስን ነገር ምሳሌ በማድረግ -­ እንግሊዛዊው ሄንሪ ብላንክ የጻፈውን መግለጹ አሰልቺ ይሆናል እንጂ እውነትነት ያለው ነው የሚመስል:: በራስ አሊ ያኮረፈው የቤጌምድር ህዝብ -­

አጼ ቴዎድሮስ ለስልጣን ከመብቃታቸው በፊት ፍቅር ነበሩ::ንጉሡም የቤጌምድር ባላባቶችን አክብረው ነው የቀረቧቸ

ው:: ንጉሠ ነገሥቱ ቤጌምድር ላይ ደብረ ታቦር ከተማን ሲገነቡም ሆነ ላስታን አልፈው ሸዋ ድረስ ሲዘልቁ ቤጌምድሮች አብረዋቸው ነበሩ:: በኋላ ላይ ግን ኩርኩም ሲበዛባቸው ለአጼ ቴዎድሮስ መገበር አቁመው ንጉሡ እንዴት እንዳዳከሟቸው ሄንሪ ብላንክ በዝርዝር ይተነትናል::

“ታሪክ ራሱን ይደግማል” እንዲሉ በደርግ ያኮረፈው የዚህ አካባቢህዝብ -­ ኢህዴን እና ህወሃትን ጋሻ ሆኖ መክቶላቸዋል:: ለስልጣንም በቅተዋል:: ሆኖም በዚህ ህዝብ ላይ ነው ዳግም ግፍ እና በደል እየተፈጸመ ያለው:: የህዝቡን መሬት ህወሃት መውሰዱ ሳያንስ ለሱዳን እየሸነሸነ በመስጠት ላይ ነው::

በሚገርም ሁኔታ ወደትግራይ የተከለለው የቀድሞው የቤጌምድር መሬት አሁንም ድንበሩን ሉግዲ ተራራ አድርጎ ወደ ሱዳን የሄደ መሬት እንደሌለ ይነገራል:: ወረድ ብሎ አማራውንና ሱዳንን የሚያገናኘው ድንበር ግን በህወሃት ታጣቂዎች አጋፋሪነነት ከአርማጭሆ ማዶ ባህረሰላምን ይዘን ጣያ, ሽንፋ, ከአቡጢር እስከ አብደራፊ ድረስ ለሱዳን ተሰጥቷል:: ሱዳን በ1956 ነጸ እንደወጣች የጠየቀቻቸውን መሬቶች (በጋምቤላ በኩል ጠይቃ ከነበረው መሬት በቀር) ሌሎቹን አንድ በአንድ እያገኘች ያለች ይመስላል::

ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ ቤጌምድር እንደ አንድ ጠቅላይግዛት ወይም ክፍለ አገር ስም እና ማንነቷን እንድታጣ; በውስጧ የነበሩት ወረዳ እና አውራጃዎች ያለ ጠያቂ እንዲበታተኑ በመደረጋቸው ነው:: ህዝቡ በታሪኩ ቀርቶ በስሙ እንኳን እንዳይኮራ ሆኗል:: ወንዶቹን አባረው አስረው እና ገድለው; ሴቶቻቸውን ወስደው ከነሱ የሚወለዱት ልጆች አዲስ ማንነት እንዲያበጁ እየተደረጉ ነው::

ወደድንም ጠላን -­ ስሙን ብቻ ሳይሆን ዘሩን የማጥፋት ዘመቻ ተደርጓል -­ በዚህ ህዝብ ላይ:: አሁን በቀደም.... የትጥቅ ትግሉ አብቅቶ ኢህአዴግ አገሪቱን ሲቆጣጠር -­ ህወሃት የቤጌምድርን ግዛት “ምዕራብ ትግራይ” ብሎ ሰየመው:: ከደርግ ጋር ሲዋጉ የነበሩ በጣም ብዙ ሺህ የሰራዊቱን አባላት የጡረታ ገንዘብ ከፍሎ መሬቱን ከዳር እስከዳር ሸንሽኖ ሰጣቸው:: ወልቃይት ጠገዴ እና ጸለምት ጭምር በህወሃት ሰራዊት ተወሰዱ:: አሁን የመስፋፋቱ ነገር እየገፋ መጥቶ የራስ ዳሽን ተራራን አንደኛውን ወገን ጭምር ጠቀለሉት:: የቀድሞው ስሜን አውራጃ -­ የቀድሞው ቤጌምድር ቀስ በቀስ በህወሃት ሰዎች ቁጥጥር እየዋለ መጥቶ አርማጭሆ ድረስ ዘለቀ:: በዚህ ጉዳይ ከህወሃት ሰዎች ጋር ስንነጋር “ህዝቡን እንጂ መሬቱን ለምን ታያላቹህ” ይሉናል:: ‘ነባሩን ህዝብ እያጠፉት አዲሱን ሰፋሪ በግድ ተቀበሉ’ -­ አይነት አባባል የቀድሞው የህወሃት አባል አቶ ገብሩ አስራት ጭምር ደግመውልን -­ አንገታችንን የደፋንበት አጋጣሚ አለ::

ዛሬ በስሜን የአማራ ክልል እየታየ ያለው የመተራመስ አደጋ አርማጭሆ ሲደርስ ከጥይት ጩኸት ጋር እንስማው እንጂ የህዝቡ ብሶት እና አቤቱታ -­ ለቅሶ እና እግዚኦታ ማስተጋባት ከጀመረ በጣም ብዙ (ባለቤት... እባክዎ ወደ ገጽ 19 የዞረ)

ባለቤት  የሌለው  መሬት  

ታክስዎን  የረዥም  ዓመት  ልምድ  

ባለው  አክሎግ  አስፋው  ያሰሩ

900 American Blvd E Ste 206, Bloomington, MN 55420

የመከላከያ ሰራዊት በትግራይ እና አማራ ተዋጊዎች መካከል ሰፈረ (ከዚያስ?)በሰሜን ጎንደር, አርማጭሆ አውራጃ ልዩ ስሙ “ገ’ጨው” በተባለው ስፍራ የመከላከያ ሰራዊት ከትላንት ጀምሮ እንዲሰፍር ተደርጓል:: ማዶ እና ማዶ ሆነው እየተዋጉ ባሉት የትግራይ ወታደሮች እና በአማራ ህዝብ መካከል መከላከያ ሰራዊት ከሰፈረ በኋላ ጦርነቱአሁን ለጊዜው ጋብ ብሏል:: የቀድሞ የህወሃት ወታደሮችን ሁመራ ላይ በማስፈር አካባቢውን ለራሱ ያደረገው ህወሃት -­ አሁን ደግሞ በአርማጭሆ መስፋፋት በመጀመሩ ነው -­ በአካባቢው ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ጋር ግጭቱ የተቀሰቀሰው::ሰሞኑን ግጭቱ ከመባባሱ በፊት የአማራው ህዝብ ተዋጊዎች -­ ህወሃት በአጭር ጊዜ ውስጥ አካባቢውን ለቅቆ እንዲወጣ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር:: ሆኖም የህወሃት ወታደሮች አካባቢውን ለቅቀው ባለመሄዳቸው በተለይ በማይ’እምቧ በርካታ የህዝባዊ ወያኔሃርነት ትግራይ -­ ህወሃት አባላት ሞተዋል:: በወያኔዎቹ ላይ የደረሰው አደጋ ያስደነገጣቸው እና ወደ አርማጭሆ ያመሩት ሌሎች የህወሃት አባላት -­ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ጦርነት ሲያደርጉ ነበር የከረሙት:: በዚህ ጦርነት የሞቱት ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም የተኩስ ልውውጡ ከፍተኛ ነበር:: አሁን የመከላከያ ሰራዊት በሁለቱ ወገኖች መካከል ከሰፈረ በኋላ ግን ጦርነቱ ለጊዜው ጋብ ብሏል:: ሆኖም ሁለቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች -­ ማለትም የህወሃት እና ብአዴን አመራሮች ውስጥ ውስጡን እየተናቆሩ ናቸው::ህወሃት በድንበር ጉዳይ ካደረጋቸው የአገር ውስጥ ጦርነቶች ይሄኛው ጠንከር ያለ ነው:: ከዚህ ቀደም የህወሃት ወይም የትግራይ ታጣቂዎች የአማራውን መሬት ሲወስዱ -­ ህዝቡ “በህግ አምላክ” ብሎ እየጮኸ ከመሞት ውጪ ብዙ ምርጫ አልነበረውም:: አሁን ግን እየጮኸ ሳይሆን ጥይት እያጮኸ መሞትን የመረጠበትን አጋጣሚ ለማየት እየበቃን ነው:: አሁን የደረንበትን የቅርቡን ታሪክ እንዳየነው ከሆነ -­ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) የአማራውን ህዝብ ከሁመራ እና ጠለምት: ከበየዳ, ከወልቃይት, ከድብ ባህር, ከአብደራፌ, ከብራ ዋድያ, ከሻግኔ እና ላሄን እያፈናቀሉ መሬቱን ለቀድሞ የወያኔ ወታደሮች ሲሰጡ ቆይተዋል:: በአካባቢው የአማራው መሬት ብቻ አይደለም የተወሰደው:: ወንዶቹን እያፈናቀሉ: ያንገራገረውን እየገደሉ ሚስቶቻቸውን እና ሴት ልጆቻቸውን በሙሉ ነው ነጥቀው የወሰዱት::

Page 8: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 8እንመካከር

የኢሳያስ ከበደ ምላሽ፦ ያለፈውን የሕይወትህን ምዕራፍ ያልተፈቱ ችግሮቹን ይዘህ ወደፊት መራመድ አትችልም!

ውድ አንባቢያችን ትዳርህ በዚህ አይነት ሁኔታ መፍረሱ ያሳዝናል፡፡ አሁን ምክር መጠየቅህ መልካም ቢሆንም ትዳርህ ከመፍረሱ በፊት የባለሙያ ምክር አግኝተህ ቢሆን ኖሮ ትዳርህን ከመፍረስ ማዳን የምትችልበትን አማራጮች ማግኘት እንደምትችል እገምታለሁ፡፡ ሃያ አምስት ዓመት የኖርክበት የጋብቻ ግንኙነት ፈርሷል፤ ይህ ግን የአንተ የህይወትህ መጨረሻ አይደለም፡፡ በአዲስ ጎዳና ወደፊት መቀጠል ትችላለህ፡፡ የወደፊት ህይወትህ መልካም እንዲሆን ደግሞ ልታደርጋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህን ነገሮች አብረን እንመልከት!

ራስህን እወቅ፡፡ በዚህ በጻፍክልኝ ደብዳቤ ውስጥ የቀድሞ ሚስትህን በሚገባ ኮንነሃታል፡፡ ለትዳርህ መፍረስ መንስኤው እርሷ እንደሆነች በዝርዝር ለመግለፅ ሞክረሃል፡፡ የእርሷ ባህሪይ መልካም እንዳልሆነ በተለያዩ ምሳሌዎች አስረድተሃል፡፡ በአንተ አገላለፅ እርሷ ገንዘብ ወዳድ፣ ብልጣ ብልጥ፣ በጣም ራስ ወዳድ፣ ተነጫናጭ፣ ክፉ፣ ንፉግ፣ ገንዘብ አባካኝ፣ ምስጋና ቢስ፣ አሽሙረኛ፣ ተሳዳቢ፣ ራሷን የማታርም፣ ግትር... ናት፡፡

ከአንድ ነገር በስተቀር ስለእርሷ አንድም መልካም ነገር አልተናገርክም-­ ‹‹የመዝለል ባህሪይ ስለሌላት›› የሚል ሐሳብ ብቻ ጠቅሰሃል፡፡ ያውም እርሷን ከማግባትህ በፊት የነበራት ባህሪይ ነበር፡፡

ስለራስህ ግን ብዙ መልካም የሆኑ ነገሮችን ተናግረሃል፡፡ ቀና መሆንን የምትመኝ፣ የሚስትህ መካሪ፣ ሚስትህን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የምትቀበል፣ እርቅ ፈላጊ፣ በልጆችህ ዘንድ ተወዳጅ፣ ደግ (ራስህን የማትወድ)፣ ስለትዳርህ መፍረስ ፀፀት የማይሰማህ... እንደሆንክ ገልፀሃል፡፡

ከባህርይ አንፃር የቀድሞ ሚስትህንና ራስህን የገለፅክበት መንገድ ስለአንተ ማንነት የሚናገረው መልዕክት አለው፡፡ አንድ ጣትህ ወደ እርሷ፣ ሶስቱ ግን ወደ አንተ የሚያመለክቱ መሆናቸውን ማስታወሱ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ምናልባት አንተ ያላወከው የማንነትህ ክፍል ያለ ይመስላል፡፡ ሌላውን ሰው ብዙ የሚኮንን ሰው፣ ሌላውን የሚኮንንበትን ነገር አብዝቶ አድራጊ እንደሆነ ይታሰባል፡፡

ስለዚህ የወደፊቱ ግንኙነትህ ቀና እንዲሆን የራስህን ባህሪይ በደንብ መቃኘቱና የአንተ ባህሪይ በትዳር ግንኙነት ላይ የሚኖረ

ውን አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ መለየት ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ያለፈውን የትዳር ግንኙሀትን መርምር፡-­ በዚህ ስር በርካታ ሐሳቦችን እንቃኛለን፡፡ (1) የባልና ሚስት ሚና፡-­ የትዳር ግንኙነት በትንሹ የሁለት

ሰዎች ግንኙነት ነው፡፡ ለግንኙነቱ ግንባታና ስኬት ባልና ሚስት የሚጫወቱት ሚና ይኖራል፡፡ ከሚና አንፃር ሲታይ ያለፈው የትዳር ግንኙነትህ በአብዛኛው አንተ ዋና ተዋናይ ስትን ባለቤትህ ግን ምን አይነት ሚና እንደነበራት ግልፅ የሆነ ነገር አልተጠቀሰም፡፡

አንዱ የአንተ ሚና የነበረው የሚስትህን ባህሪይ ማስተካከል ነው፡፡ ለመሆኑ አንተ ሚስትህን እንዴት አድርገህ ለማስተካከል ኃላፊነት ወሰድክ? ሰው እኮ እንደ ድንጋይ ተጠርቦ ወይም እንደ እንጨት ተልጎ አይስተካከልም፡፡ እርሷን የማስተካከል ነገር ያልተሳካልህ ለዚህ ነው፡፡ እርሷ ራሷን ታስተካክላለች እንጂ አንተ አታስተካክላትም፡፡

ሰው የጠባይ ለውጥ ማምጣት የሚችለው በራሱ ሲወሰን ብቻ ነው እንጂ አንድ ሰው ሌላውን ከውጭ ሆኖ ማስተካከል አይችልም፡፡ የጠባይ ለውጥ ሞተሩ የሰው አዕምሮና ውስጣዊ መነሳሳቱ ነው፡፡ ከውስጥ የሆነ የጠባይ ለውጥ ስኬታማ፣ ቀጣይነት ያ

ለውና ውጤታማ ይሆናል፡፡ ከውጭ ማድረግ የሚቻለው ለጠባዩ ለውጥ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ስራ ማከናወን ነው፡፡ ስለዚህ የቀድሞ ሚስትህ እጮኛህ በነበረችበት ጊዜ ‹‹በሂደት አስተካክላታለሁ›› በሚል እሳቤ እርሷን ማግባትህ አዋጪ አልነበረም፡፡ በእርግጥ መነጫነጭ የእርሷ ትክክለኛ ጠባይ መሆኑን አውቀህ ካገባሁት ለማስተካከል ማሰብ ብቻ ሳይሆን ካልተለወጠችም ከእርሷ ጋር እኖራለሁ በሚል እሳቤ ቢሆን የተሻለ ነበር፡፡

አሁንም ቢሆን አዲስ ግንኙነት ለመመስረት ካሰብክ በቀላሉ ሊለወጥ የሚችልና የማይችለውን ጠባይ መለየቱ ጠቃሚ ነው፡፡ ከአንተ ጋር የማይጣጣም ጠባይ ያላትን ሴት ‹‹አስተካክላታለሁ›› በሚል እሳቤ ብቻ ሳይሆን ‹‹ካልተለወጠችም ይህን ጠባይዋን ችዬ እኖራለሁ›› በሚል እሳቤ ማግባቱ ለግንኙነቱ ቀጣይነት በጎ አስተዋፅኦ አለው፡፡

ሌላው ከደብዳቤህ መንፈስ አንተ የቤቱ አለቃ ትመስላለህ፡፡ የምታደርጋቸውን ነገሮች ሚስትህን እያማከርካት የምታደርግ አይመስልም፡፡ በኑሯችሁ ውስጥ የቀድሞ ባለቤትህ ተሳትፎ አነስተኛ ይመስላል፡፡ አንተው ታስባለህ፤ አንተው ትወስናለህ፡፡ ባልና ሚስት በኑሯቸው ውስጥ (በልጆቼ... እባክዎ ወደ ገጽ 19 የዞረ)

በልጆቼ  እናት  የተነሳ  ሴቶችን  ሁሉ  ጠልቻለሁ፤  ምን  ይሻለኛል?ዕድሜዬ 42 አካባቢ ሲሆን በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ውስጥ በመምህርነት 25 ዓመት አገልግያለሁ፡፡ ቤተሰብም መስርቼ 2 ወንድ ልጆች አፍርቻለሁ፡፡ ምንም አይነት ሱስ የለብኝም፡፡ ባለቤቴ መምህርት ስትሆን በጣም ገንዘብ ወዳድ፣ ብልጣ ብልጥ እና በጣም ራስ ወዳድ ነች፡፡ ገና ሳላገባትም ምክንያቱ ባልታወቀ ነገር መነጫነጭ ልማዷ ነው፡፡ ነገር ግን ሌላ የመዝለል ባህሪ ስለሌላት በሂደት አስተካክላታለሁ በሚል እ

ሳቤ አገባኋት፡፡ ያሰብኩት አልሆን ብሎ በዚህ ጠባይዋ የተነሳ ከባለቤቴ ጋር እሳትና ጭድ ከሆንን እነሆ 10 ዓመታትን አስቆጠርን፡፡ እኔ ቀና መሆንን ስመኝ እሷ በተቃራኒው ክፉ እና ንፉግ መሆንን ትመርጣለች፡፡ የቅራኔው መነሻ ይህ ነው፡፡ የእኔ አብሮ አደግ ጓደኛዬ በስጦታ በሰጠኝ 25,000 ብር ሱቅ ከፍቼ ስሰራ እሷ እኔ እየለፋሁ በማመጣው ገንዘብ ምክንያት እየፈለገች በትንሽ በትልቁ ገንዘቤን መጨረስ ትፈልጋለች፡፡ ይልቁንም ብላ የእኔ ማደግ እያበሳጫት ቤት ውስጥ ዘወት

ር እየተነዛነዘች እረፍት ትነሳኝ ጀመር፡፡ ይህንንም ጉዳይ በየጊዜው ቁጭ አድርጌያት ለመምከር ብዙ ለፍቻለሁ፡፡ ነገር ግን ምላሿ አሽሙር እና ሰብዕናን በመንካት ስለሆነና ራሷን የማታርም መስላ ስለታየችኝ ምክሬን እርግፍ አድርጌ እሷነቷን ተቀብዬ መኖር መረጥኩ፡፡ ይህም ሰላማዊ ዝምታዬ ክፋት አድርጋው ደግሞ መቁጠር ጀመረች፡፡ ይባስ ብላ... በተደጋጋሚ ከአቅሜ በላይ ብር እየጠየቀችኝ አልችልም ስላት ገንዘቡን ካልሰጠኸኝ... አልፈልግህም... እያለችኝ ሰብዕናዬን እየነካች ህይወቴን ምሬት ውስጥ ከተተችው፡፡ እኔም ትዳሬን ብ

ዬ ለልጆቼ መኖር ስላሰብኩ በጣም እየተበሳጨሁ መኖር ጀመርኩ፡፡ ይህ በዚህ እንዳለእያበሳጨችኝ የቻልኳት የልጆቼ እናት እኔ ሳላውቅ ፍርድ ቤት ከሳኝ የፍርድ ቤት ወረቀት እምሰራበት መስሪያ ቤት ድረስ ሰዎቹን አብራ ይዛ የክስ ወረቀቱን ሰጠችኝ፡፡ ይህ የሆነው እንግዲህ ሁለታችንም አንድ ቤት እያደርን እየበላን መሆኑ በጣም ያ

ስገርማል፡፡ ይህም ሆኖ በውስጤ በጣም አዝኜ 25 ዓመት የለፋሁበት ትዳር ከሚፈርስ ብዬ የሚያውቋትን ሰዎች ሁሉ ሰብስቤ አደብ እንድትገዛ ባስጠይቃትም እፋታለሁ ብላ አሻፈረኝ በማለቷ በፍርድ ቤት ውሳኔ ትዳራችን ፈርሷል፡፡ እኔም ራስ ወዳድ ስላልሆንኩ ያለኝን ንብረት ሁሉ በፈቃደኝነት ሰጥቻት አሁን ሌላ ሀገረ በስደት ስራ ላይ እገኛለሁ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ምንም አይነት ፀፀት አይሰማኝም፡፡ ብዙ ስለቻልኩ፡፡ አሁን ሁለቱ ወንድ ልጆቼ የእናታቸውን ክፋት እና ነዝናዛነት ስለተረዱ ይልቁንም እኔ ከእንግዲህ እንዳልበሳጭ ይመክሩኛል፡፡ እንዲያውም ለእነሱ ብዬ ዘመኔን ሁሉ እንዳቃጠልኩ እና ብዙ ዋጋ እንደከፈልኩ ይነግሩኛል፡፡ ልጆቼ እኔን ስለተረዱ ይህ ይበልጥ ያስደስተኛል፡፡ ነገር ግን አሁንም እናታቸውን ማክበር እንዳለባቸው ግን እነግራቸዋለሁ፡፡ እኔ ግን ዳግም ወደ ሲኦል መመለስ አልፈልግም፡፡ የባለቤቴን ፊት ዳግም ማየት አልፈልግም፡፡ አሁን በእሷ የተነሳ ሴቶችን ሁሉ ጠልቼ አላምንም፡፡ ምን አድርግ ትሉኛላችሁ? ቻለው ሆዴ... ነኝ፡፡

የምወደው  ወንድሜን  የገደለው  

ሰው  ወይስ  በሽታ?

“በጭንቀት  እየተሰቃየሁ  ነው፤

 መፍትሄውን  ጠቁሙኝ”ስለሁሉም ነገር እጨነቃለሁ፡፡ ትንንሽ ነገሮች እንኳ ያሳስቡኛል፣ ያስጨንቀኛል፣ ያበሳጨኛል፡፡ ለመተኛት አልጋዬ ላይ ስወጣ ከአ

ንዱ ጉዳይ ጭንቀት ወደ ሌላኛው ጉዳይ ጭንቀት ስመላለስ እንቅልፌን አጣለሁ፡፡ አንዳንዴ ስጨነቅ አድሬ ይነጋብኝና ተነስቼ ወደ ስራ እሄዳለሁ፡፡ ከቤተሰቦቼ አንዱ የሆነ ነገር ሲያማክረኝ ‹ባክህ ከጭንቀቴ ላይ ጭንቀት አትጨምርብኝ› ብዬ እጮህባቸዋለሁ፡፡ ሥራ ገብቼ ትኩረቴን መሰብሰብ ያቅተኛል፡፡ የማታ ትምህርት ጀምሬ ጭንቀቴ ሲበዛብኝ አቋረጥኩት፡፡

በመጀመሪያው ሴሚስቴር ጥሩ ውጤት አምጥቼ በሁለተኛው ሴሚስተር ሳቋርጠው ያላዘነብኝ ሰው የለም፡፡ መተዌን ሳስበው እጨነቃለሁ፤ እናደዳለሁ፡፡ ሁሌም መቆጣት ስለሆነ ማንም ደፍሮ አይናገረኝም፡፡ እናቴ ብቻ ነች የምትነግረኝ፡፡ እሷን ደግሞ መናገር አልችልም፡፡ ሁሉም ግን እንደሚያዝንብኝ ይገባኛል፡፡

አንዳንዴ በነገር ወጋ ያደርጉኛል፡፡ ብዙ ነገሮች አስቤ በተግባር የማውለው ግን ጥቂት ነው፡፡ አስቤ፣ አስቤ አንዳንዴ ፍርሃት፣ ፍርሃት ይለኛል፡፡ አንዴ በሬዲዮ አንድ የኤሌክትሪክ ፖል ወድቆ ሰው ገደለ የሚል ዜና ሰማሁ፡፡ ከዛን ጊዜ ጀምሮ ከመስሪያቤታችን ግቢ ያለው ፖል ቢወድቅ እኮ እኔ ላይ ነው የሚወድቀው ብዬ በተደጋጋሚ በማሰቤ ቀና ስል በመስኮቱ ፖሉን ካየሁት ስፈራ እውላለሁ፡፡

ሰዎችን ሳወራ የሆነ ነገር ካሉ በጣም ስለሚያሳስበኝ እንደድሮው ከሰዎች ጋር ማውራት አያስደስተኝም፡፡ ዝምተኛና ብቸኛ ሆኛለሁ፡፡ ይሄ ሁኔታዬ ደግሞ መልሶ ያስጨንቀኛል፡፡ ለዚህ መዓት መፍትሄ ይኖራችሁ ይሆን?

እኔ ነኝውድ ጠያቂያችን ከፅሑፍህ እንደተረዳነው ያንተ ችግር ጭንቀት ነው፡፡ ጭንቀትና ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ችግሮች በጣም የተለመ

ዱና በብዛት የሚከሰቱ የአዕምሮ ህመም አይነቶች ናቸው፡፡ የተለያዩ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት እስከ 31 በመቶ የሚሆኑ የዓለማችን ህዝቦች በህይወታቸው ውስጥ ቢያንስ አንዴ የጭንቀት ችግር ያጋጥማቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ጭንቀት እንደ ችግር አይታይም ወይም ቢታም ተገቢው ህክምና አያገኝም፡፡ በነገራችን ላይ ጭንቀት የዕለት ተዕለት ኑሮአችን አካል ነው፡፡ ጭንቀት ችግር የሚሆነው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ማስተጓጎል ሲጀምር ነው፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች የጭንቀት ችግር (Anxiety disorder) ብለው የሚሉት ችግር ምልክቶችን በሚገባ ዘርዝረው አስቀምጠዋል፡፡ የመጀመሪያው ምልክት የጭንቀት መጠኑ የበዛ (excessive) መሆኑ ብሎም ከፍራቻ (fear) ስጋት (worry) እና ነገራትን ማስወገድ (avoidance) ጋር የተያያዘ እንደሆነ ነው፡፡ ሌላኛው ምልክት ደግሞ ጭንቀቱ በማህበራዊ ህይወታችን፣ በስራችን ወይም በሌሎች የህይወት ዘርፎቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት (significant distress) ወይም መስተጓጎል (impairment) ሲፈጥር ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ግለሰቡ መጨነቁ ምንም ዋጋ እንደሌለው አምኖ እያለ ጭንቀቱን ማቆም አለመቻሉ ነው፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ደግሞ የጭንቀት ሁኔታው ቢያንስ ለአራት ሳምንታት የቀጠለ መሆኑ፣ ተደጋጋሚ የሰውነት መወጣጠር መኖሩ፣ በሁኔታዎች በፍጥነት የመናደድ ሁኔታ በተደጋጋሚ መታየቱ እና ለመተኛት መቸገር የጭንቀት ችግርን ለመለየት የሚያስችሉት ምልክቶች ናቸው፡፡

በፅሑፍህ ላይ የነገርከን ምንም ነገር ስለሌለ በመጀመሪያ ጭንቀትህ የተፈጠረው በሌሎች አካላዊ ወይም አዕሯዊ ህመሞች አለመሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ የስነ ልቦና ባለሙያዎች እንደሚነግሩን እነ ስኳር፣ ልብድካምና የመሳሰሉ ስር የሰደዱ ህመሞች እና ከዚህ በፊት ያጋጠሙ የጭንቀት ችግር፣ ስሜት የመቀያየር ችግር (Mood disorder) ወዘተ (ጭንቀት... እባክዎ ወደ ገጽ 11 የዞረ)

የ28 ዓመቱ ወንድሜ ምንም አይነት ጠላትም ሆነ ሱስ አልነበረበትም፡፡ ይሁን እንጂ ድንገት ከጓደኞቹ ጋር እንዳለ መሞቱንና በድንገትም አምቡላንስ ተጠርቶ ወደ ሆስፒታል እንደወሰዱት ሆኖም ሆስፒታል እንደደረሰ መሞቱን ሰማን፡፡ ምንም እንኳን በመሞቱ ምክንያት የልብ ችግር ሊሆን እንደሚችል ቢነግረንም ሬሳውን ግን በሆስፒታል አስመርምረን በሰው ተመቶ እንዳልሞተ ቢያረጋግጡልንም ሊዋጥልን አልቻለም፡፡ ምናልባት መድሃኒት ሰጥተውት ሊሆን ይችላል በሚል እየከነከነን ይገኛል፡፡ በጣም የምወደውና ያሳደገኝ ወንድሜ በመሆኑ ከልብ አዝናለሁ፡፡ በእንዲህ መሰል ችግር በድንገት የሚሞቱ ሰዎች ያሉ በመሆኑም በዚህ ዙሪያ ሃሳብ ብትሰጡኝ ብዬ ነው ደብዳቤ መፃፌ፡፡ አመሰግናችኋለሁ፡፡

ሰለሞን ነኝየዶ/ር ዓብይ ዓይናለም ምላሽ፦ ውድ ጠያቂያችን በቅድሚያ

እግዚአብሔር ያጥናህ ልንልህ እወዳለን፡፡ ወንድምህ በለጋ ዕድሜው በዚህ መልኩ መሞቱ አሳዛኝ ነው፡፡ ሆኖም አንተ እንዳልከው እንዲህ መሰል ያልታሰቡ ድንገተኛ ሞቶች በተለይ በአሁኑ ወቅት ከዘመናዊ በሽታዎች መስፋፋት ጋር እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ለጥያቄህ ቅድሚያ ሰጥተነዋል፡፡

ድንገተኛ ሞት ማለት ምን ማለት ነው? ምክንያቶቹስ? ለድንገተኛ ሞት የሚያጋልጡ በሽታዎችና ሁኔታዎች ምንድናቸው? ከመከሰታቸው በፊት አውቆ እንዳይከሰቱ የመከላከያ ጊዜስ ይኖራቸው ይሆን? ወዘተ የሚሉት ጥያቄዎች በደብዳቤው ውስጥ የቀረቡ ይመስላሉ፡፡

በአጭሩ ልዳስሳቸው እሞክራለሁ፡፡ ድንገተኛ ሞት ማለት በአንፃራዊ መልኩ ጤነኛ የነበረ ሰው በድንገት ራሱን ሲስትና ለህልፈተ ህይወት ሲዳረግ ማለት ነው፡፡ አንድ ሰው በድንገት ሞተ ለማለት ድንገተኛ የህመም ስሜት (ለምሳሌ የልብ ውጋት) ከተሰማው

ጀምሮ በአንድ ሰዓት ጊዜ ውስጥ ለሞት ሲዳረግ ነው፡፡ ሆኖም አንዳንድ ፓቶሎጂስቶች ይህን ጊዜ እስከ 24 ሰዓት ሊያራዝሙት ይችላሉ፡፡ ማለት ሰውየው በጤንነት ከታየበት ጊዜ ጀምሮ ሞቶ እስከ ተገኘበት ጊዜ ድረስ ≤ 24 ሰዓት ከሆነ ድንገተኛ ሞት ልንለው እንችላለን፡፡ ይህ ሲሞት የነበረው ሁኔታ ላልታወቀ ሰው ነው፡፡

ውድ ገመችስ እንግዲህ እንዲህ አይነቱ ሞት በብዙ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ዋነኛው መንስኤ ግን ልብ ድካም ነው፡፡ የተለያዩ የልብ በሽታዎች ለድንገተኛ ሞት ያጋልጣሉ፡፡ ለምሳሌ የልብ ምት መዛባት፣ የልብ ጡንቻዎች መወፈር ወይም መሳሳት፣ በደም ዝውውር ዕጦት የልብ ህዋሶች ድንገተኛ ሞት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ በልብ በሽታዎች አማካይነት የሚከሰት ሞት ያልተጠበቀና ድንገተኛ ወይም በሽታው ስር እየሰደደ ሄዶ የማይቀለበስበት ደረጃ በመድረሱም ሊሆን ይችላል፡፡ ግማሽ ያህሉም በድንገት የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ምናልባት ወንድምህ ከአሁን ቀደም እንደደም ግፊትና ስኳር የመሰሉ ተዛማጅ ህመሞች ያሉበት አይመስለንም፡፡ አንተም አልገለፅክም፡፡

ጥናቶች እንደሚጠቁሙት በአሜሪካ ብቻ በዓመት እስከ 30,000 ድንገተኛ የልብ ድካም ምቶች ይከሰታሉ፡፡ በእንግሊዝ ደግሞ እስከ 100,000 ድንገተኛ የልብ ድካም ምቶች ይከሰታሉ፡፡ በድንገተኛ የልብ ድካም የመሞቱ ነገር ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ አብሮ የሚያድግ ነው፡፡ ማለትም ከ20 ዓመት በፊት የመከሰት ዕድሉ ከ30 በመቶ በታች ሲሆን ከጎልማሳነት ዕድሜ ጀምሮ ግን እየጨመረ በመሄድ 80 በመቶ ይደርሳል፡፡ ከልብ ህመሞች መሀል የልብ ደም ቧንቧዎች መጥበብና የሚያስከትለው ችግር ትልቁን ድርሻ (80 በመቶ) ይወስዳል፡፡ ለዚህም ነው ለልብ ደም ስር ጥበት አጋላጭ ሁኔታዎች ያለባቸው ሰዎች ላይ የሞቱ አደጋም እየጨመረ የሚሄደው፡፡ (ወንድሜን... እባክዎ ወደ ገጽ 11 የዞረ)

Nuru Dedefo, ESQ.Attorney at Law & Counselor

- Car Accidents- Work place Injuries- Immigrations- Family Law- Criminal LawIf you have lega l issues, you

need a lawyer who fights for your rights. Nuru Dedefo

fights for your rights.

If you have questions, Contact Nuro Dedefo Law Firm at:

3989 central Ave, NE, Columbia Heights, MN 55421

(763)-781-5254 (office), (612-559-0489) Cell(763)-781-5279 Fax

Page 9: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 9

ከግንባታዎች ጋር ተያይዞ እየደረሰ ያለው አደጋ አሳዛኝ እየሆነ ነው፡፡ ይኼ አደጋ በሦስት ነገሮች ምክንያት እየደረሰ ያለ ይመስለኛል፡፡ የመጀመሪያው ግንባታዎች ሲከናወኑ ተገቢ የሆነው ቅድመ፣ጊዜና ድኅረ ግንባታ ጥንቃቄ ስለማይወሰድ ነው፡፡ ታላላቅ ክሬኖች አገር ደርምሶ የሚሄድ ቋጥኝ አንጠልጥለው እየታዩ፣ በሥራቸው ሰውና መኪና እንዲያልፍ ይደረጋል፡፡ ለግንባታ ሠራተኞች በቂ የሆነ የአደጋ መከላከያ ሥልጠናና መሣሪያ አይሰጣቸውም፡፡ አማራጭ መንገዶችና የእንቅስቃሴ ቦታዎች ቀድመው ስለማይዘጋጁ ግንባታና ኑሮ ጎን ለጎን ይካሄዳል፡፡ መታጠር ያለባቸው ሳይታጠሩ፣ መሸፈን ያለባቸው ሳይሸፈኑ፣ መከደን ያለባቸው ጉድጓዶች ሳይከደኑ፣ ምልክት መደረግ ያለባቸው ቦታዎች ላይ ሳይደረጉ ግንባታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም የተነሣ በተገቢ ጥንቃቄ ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ሕይወቶች ይቀጠፋሉ፣ አካል ይጎድላል፣ ንብረት ይወድማል፡፡

ግንባታዎች በመንደሮች መካከል ሲከናወኑ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ሕጻናት የሌሉበት መንደር ይመስላል፡፡ በየቦታው ጉድጓዱ አፉን ከፍቶ ማየት የተሳናቸውን ሊውጥ አሰፍስፏል፤ አረጋውያንን ‹እስኪ ትዘልና› ይላል፡፡ ሕጻናትን ዋኝተው እንዲያልፉበት ይጋብዛል፡፡ በዊልቼር ለሚጓዙ፣ በከዘራ ለሚራመዱ፣ በክራንች ለሚታገዙ ቦታ የለውም፡፡

አንድ ግንባታ ከመከናወኑ በፊት የሚገነባው አካል በሚያስገባው የጨረታ ሰነድ ውስጥ የቅድመ ጥንቃቄ አሠራሮቹ አብረው እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ግን ለጨረታ ሰነድ ማሟያነት ይውላሉ እንጂ ተከታትሎ የሚያስፈጽማቸው አያገኙም፡፡ በእነዚህ የጨረታ ሰነዶች ላይ ለግንባታ ሠራተኞችና ለነዋሪዎች ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች ይገለጣሉ፡፡ ነገር ግን የሚቀሩት መደርደሪያ ላይ ነው፡፡ አንድን የግንባታ አካባቢ ገንቢው ሲረከብ የርክክብ ሥነ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ ከዚያ በኋላ አካባቢው የገንቢው አካባቢ ነው፤ በዚያ አካባቢ ለሚደርሰው ጉዳትም ተጠያቂው እርሱ ነው፡፡ ኢንሹራንስ እንዲገባ የሚደረገውም ለዚህ ነው፡፡ ነገር ግን አስፈጻሚው አካል ተከታትሎ ለማስፈጸምና በሕጉ እንዲመራ ለማድረግ የዐቅምም የሙስናም ችግር ያለ ይመስላል፡፡

አንድ ግንባታ ሲከናወን የአደጋ መከላከያ ወጭ ከግምት መግባት አለበት፡፡ በአንድ በኩል ከግንባታው ጋር ቀጥታ ስለማይያያዝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ወጭው ከፍተኛ ስለሚሆን ተጫራቾች የአደጋ መከላከያ ወጭን ይተውታል፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ያልፉታል፡፡ የመንግሥት ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ደግሞ እንደ ወጭ መቀነሻ አማራጭ ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ ምክንያትም ጆሮ ጭው የሚያደርግ አደጋ በየቀኑ መስማት የየዕለት ሰበር ዜናችን ሆኗል፡፡ ለዜጎች የሚገነባ ግንባታ ዜጎችን ያለ ፍላጎታቸው ይቀጥፋል፡፡

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ያሉን ነባር መንገዶችና ሕንጻዎች ያረጁ፣ በሚገባ ያልተገነቡና አሁን የሚደረጉ ግንባታዎች ለሚያስከትሉት ጫና ቀድመው ያልተዘጋጁ መሆናቸው ነው፡፡ በጣልያን ዘመን በተሠሩ ቤቶች ጎን፣ የጥገና ጊዜያቸውን ጠብቀው በማይጠገኑ ሕንጻዎች አጠገብ፣ እንደነገሩ ሲጠጋገን በኖረ ድልድይ ዳር፣ የፍሳሽ ማስወገጃዎች ተጠርገውና ተስተካክለው በማያውቁበት ከተማ ውስጥ ነው ግንባታዎች እየተከናወኑ የሚገኙት፡፡ መሬት አርዕድ አንቀጥቅጥ ማሽኖች፣ አስገምጋሚ ዶዘሮች፣ ሕንጻ ነቅንቅ ቁፋሮዎች፣ ጆሮ በጥስ የመሣሪያ ጩኸቶች፣ ግድግዳ ሰንጥቅ የድንጋይ ናዳዎች ናቸው በየአካባቢዎቻችን እየተከናወኑ ያሉት፡፡ ቤቶቻችንና ሕንጻዎቻችን፣ መንገዶቻችንና ድልድዮቻችን ለእነዚህ አዳዲስ ክስተቶች ታስበው የተዘጋጁ አይደሉም፡፡ መዓት ነው የወረደባቸው፡፡ አርማጌዶን የደረሰ እስኪመስል ድረስ አካባቢያችን ይደረመሳል፣ ይገመሳል፣ ይንቀጠቀጣል፣ በየቀኑ ይለዋወጣል፡፡ የኛ ሠፈር ግን ለዚህ አልተዘጋጀችም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥናቶች አብዛኞቹ ነባር ቤቶች ከደረጃ በታች የሆኑ ወይም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆናቸውን ገልጠዋል፡፡ ይህ እየታወቀ ግን ግንባታዎች ሲከናወኑ ሊደረመስ የሚችል ቤት፣ ሕንጻ ወይም ግንብ፣ ሊናድ የሚችል ገደል፣ ሊወድቅ የሚችል ድልድይ፣ ሊሰምጥ የሚችል ጉድባ፣ ሊሰነጠቅ የሚችል ግድግዳ መኖር አለመኖሩ ተለይቶ ጥንቃቄ ሲደረግ አ

እንደሰው  ወይስ  እንደ  እንስሳ?

ከዳንኤል ክብረትDanielkibert.com

ይታይም፡፡ አንድ ‹ዳምጠው› መኪና ሲያልፍ ቤቶቻችን ጎንደርኛ እየጨፈሩ ያጅቡታል፡፡ ቆይተውም በዘፈኑ ብዛት ልባቸው ጠፍቶ በዚያው ይወድቃሉ፡፡

ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ የማሳወቅ ግዴታችንን ስለማንወጣ ነው፡፡ መንደር ለውጥ፣ ምድር አንቀጥቅጥ ግንባታ ሲከናወን ኅብረተሰቡ(በተለይም በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከተው የአካባቢው ነዋሪ) በበቂ ሁኔታ እንዲያውቀውና የራሱን ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኃላፊነቱን የሚወጣ አካል ያለ አይመስልም፡፡ በመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ከመስጠት ያለፈ ግዴታ እንዳለም ተዘንግቷል፡፡ በሌላው ዓለም አካባቢን የሚለውጥ ግንባታ ሲደረግ የሠፈሩ ሰው ዝርዝር ጉዳዩ ተጽፎ በየቤቱ ይሰጠዋል፡፡ ተሰብስቦም እንዲወያይ ይደረጋል፡፡ ሐሳቡን ያቀርባል፡፡ ግንባታው ለነዋሪውም ሆነ ለገንቢው ችግር በማይፈጥር መንገድ እንዲከናወን የጋራ መግባባት ላይ እንዲደረስ ይሞከራል፡፡ ማኅበረሰቡ ሊያከናውናቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ይነገሩታል፡፡ ተቃውሞ ካለውም በምክንያት እንዲያስረዳ ይደረጋል፡፡ አሳማኝ ከሆነም ፕሮጀክቱ ይስተካከላል፡፡ እንዲያም ሲል ይቀራል፤ ፕሮጀክቱ የሚሠራው ለእርሱ ነዋ፡፡ በዚህ የተነሣም ዕድገት እሴት(asset) እንጂ ዕዳ(liability) አይሆንበትም፡፡

ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በድሬዳዋ ከተማ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተወያዩ ጊዜ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያቀረቡት ጥያቄ እዚህ ላይ ሊጠቀስ ግድ ይላል፡፡ ከባቡሩ መንገድ ጎን ለእግረኛ የተሠራው ድልድይ ክፍት ድልድይ አይደለም፡፡ ከላይ ጣራ መሰል ነገር አለው፡፡ ነገር ግን ይኼ ድልድይ ሲሠራ ግመሎችን እንዲያሳልፍ ሆኖ አልተሠራም፡፡ ለምን? አሉ ሽማግሌዎቹ፡፡ በወቅቱ ሌላ ምላሽ ቢሰጣቸውም ምክንያቱ ግን እነርሱን ያላሳተፈና ሐሳብ ያልሰጡበት ግንባታ መከናወኑ ነው፡፡ አያውቁም ተብሎ ነው የሚታመነው፡፡ ያነሡት ሐሳብ ግን ሕዝብን የማያሳትፍና ይሁንታ ያልሰጠበት ሥራ ሁሉ ከሪፖ

ርት ያለፈ ዋጋ እንደሌለው ያሳየ ነው፡፡ ድልድዩ ችግራቸውን ከመፍታት ይልቅ ራሱ ችግር ነው የሆነባቸው፡፡

መኖሪያ ማለት ጣራና ግድግዳ ብቻ አይደለም፡፡ አካባቢም ጭምር ነው፡፡ ለብዙ ዘመናት የኖረበት ወይም እኖርበታለሁ ብሎ የሚያስበው አካባቢ በአንድ ማለዳ ተለውጦ ሲጠብቀው፣ ለነዋሪው ሕመም እንጂ ደስታ አይፈጥርለትም፡፡ አስቀድሞ የማወቅ፣ ለሚመጣው ለውጥ የመዘጋጀት፣ ለውጡ ለሚያስከትለው አሉታዊ ነገር ጥንቃቄ የማድረግ፣ ለውጡን በሚችለው ሁሉ የማገዝና ለውጡም ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ከሆነ እስከማስቀረት የሚደርስ መብት ሊኖረው ይገባል፡፡ አንድ ነገር ‹መልካም ነው› ማለትና ‹ተቀባይነት አለው› ማለት ይለያያሉ፡፡ መልካም ነገሮች መልካም ሆነው እንዳይቀጥሉ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ የሕዝብ ተቀባይነት ማጣት ነው፡፡ የመንግሥት አንዱ ኃላፊነት መልካም ነው ብሎ ያመጣው ነገር ሕዝባዊ ተቀባይነት እንዲኖረው የመሥራት ግዴታ ነው፡፡ የማስረዳት፣ የማሳወቅና የሕዝቡን ሐሳብ የመቀበል ግዴታ፡፡

ግንባታዎች በሚከናወኑበት አካባቢ መረጃ ሰጭ ምልክቶች የሉም ማለት ይቻላል፡፡ ምን እየተከናወነ ነው? ለተዘጋው መንገድ አማራጩ ምንድን ነው? መኪኖች በየት ይታጠፉ? እግረኞችስ በየት ይለፉ? ምን ጥንቃቄ ይደረግ? የሚገነባው ግንባታ አካባቢውን እንዴት ይቀይረዋል? ከፍታው፣ ጥልቀቱ፣ ስፋቱ ምን ያህል ነው? ገደል ነው ሜዳ? ውኃማ ነው ደረቅ? ዋሻ ነው ግልጥ? ከላይ የሚወድቅ ነገር አለ ወይስ የለም? በአካባቢው መኪና ማቆም ይቻላል አይቻልም? ከስንት ሰዓት እስከ ስንት ሰዓት ግንባታው ይከናወናል? ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም ነው፡፡ ‹‹ምን አስቸኮላችሁ፤ እዚያው ሲደርስባችሁ ታውቁታላችሁ›› የተባለ ይመስላል፡፡ በአካባቢው የሚገኙ አደጋ የሚያስከትሉ ነገሮችን እንኳን የሚያመለክት ምልክት በሚገባ አይኖርም፡፡ በዚህ ም

ክንያት ገደል የሚገቡ መኪኖችንና ሰዎችን እያየን ነው፡፡ በሰሞኑ እንኳን ከግንባታ ጋር የተያያዙ አሰቃቂ ዜናዎችን እየሰማ

ን ያለነው እነዚህ ሦስት ነገሮች ስለተዘነጉ ይመስለኛል፡፡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አስቀድሞ የሚነግራቸው በማጣታቸው የትምህርት ቤት አጥር ሥር ተቀምጠው የነበሩ ተማሪዎች በመንገድ ግንባታ ንዝረት ግንቡ ተደርምሶ መዓት ወረደባቸው፡፡ ሰኞ ዕለት ደግሞ አፍንጮ በር አካባቢ በአሮጌ ማዕድ ቤት ውስጥ ሲሠሩ የነበሩ አዳጊ ልጆች በአካባቢያቸው እየተካሄደ ያለው ነገር ምን እንደሚያስከትል ስላልተነገራቸው አንዷ ለሞት አንዷም ለጉዳት ተዳረጉ፡፡ ለምን? አሁን እየገነባን ያለነው ግንባታኮ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ግንባታ አይደለም፡፡ ከአኩስም ዘመን ተነሥተን እንኳን ብናሰላ ከሁለት ሺ ዘመን በላይ በግንባታ ላይ አሳልፈናል፡፡ እንዴት እንደ አዲስ ገንቢ ስሕተቱ የግንባታውን ያህል ይሆናል? በዓለም ላይ እኛ የመጀመሪያዎቹ ገንቢዎች አይደለንም፡፡ ከቀደሙት ልንማራቸው፤ ተምረንም ልንተገብራቸው የሚገቡ ነገሮች ሞልተው ተርፈው እንዴት በ21ኛው መክዘ የ1ኛው (ቅልክ) ስሕተት ይሠራል?

እንደ እኔ የሚመለከታቸው አካላት እነዚህን ነገሮች ቢያደርጉ አደጋውን መቀነስ፣ ከዚያም አልፎ ማስቀረት የሚቻል ይመስለኛል፡፡

1. የሚቻለው ቅድመ፣ ጊዜና ድኅረ ግንባታ ጥንቃቄዎችን ማድረግ፡፡ ወጭ ለመቆጠብ ወይም ደግሞ ጉዳዩን ለማፋጠን ሲባል የጥንቃቄ ነገሮችን መዝለልና መቀነስ ቀርቶ፣ ልማዳዊ በሆነው መንገድ መሥራት አብቅቶ፣ አደጋው ቀድሞ ከመከላከል ይልቅ ለአደጋው ዜና አዘጋገብ መጨነቅ ተወግዶ የሚቻለው ጥንቃቄ ሁሉ መደረግ አለበት፡፡ ‹ማስተዋል ይጋርድሃል፣ ጥንቃቄም ይጠብቅሃል› እንዲል መጽሐፉ፡፡

2. የአካባቢው ነዋሪና ተጠቃሚ ስለ ግንባታው እንዲያውቅ፣ ዐውቆም እንዲዘጋጅ፣ ሐሳብም እንዲሰጥ በዝርዝር ማወያየት፣ መረጃውን በየቤቱ መስጠት፤ ሐሳቡን መቀበልና ተግባቦትን መፍጠር

3. በቂና ግልጽ ምልክቶችን በአካባቢው መጠቀም፡፡ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡና አደጋዎችን የሚያመላክቱ ምልክቶችን በአካባቢው ሕዝብ ሊመለከት በሚችልበት ቦታ ማስቀመጥ

4. ማኅበረሰቡ ጉዳዩን እንዲከታተል ማኅበረሰብ ዐቀፍ ኮሚቴ ማቋቋምና ችግሮች ከመድረሳቸው በፊት ከነዋሪውና ከሚመለከታቸው ጋር እንዲሠራ ማድረግ

5. ግንባታዎቹ እየተከናወኑ ያሉት በሕዝብ መካከል ነውና የሕዝቡን እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ከዲዛይኑ ጀምሮ መሥራት፡፡ ከተማዋን በባቡር ምክንያት በአራት ክፍለ ከተማ ከፍለን ያንንም በአጥር ከልለን፣ ዘላችሁ አታቋርጡ ማለት በጆሮ ግንድ በኩል አዙራችሁ ጉረሱ እንደማለት ነው፡፡ አንድ ሰው ከመነሻው ምን ያህል ተጉዞ ነው መንገድ ማግኘት ያለበት?የሚለው ነገር የታወቀ ዓለም ዐቀፍ ደረጃ አለው፡፡ ሰው በጠባዩ አጭር መንገድ ይፈልጋል፡፡ ይህንን የሰው ጠባይ በአጥር ብቻ ለማስቀረት ከመታገል ከዲዛይኑ ጀምሮ ዓለም ዐቀፍ ደረጃዎችን ተጠቅሞ ማሰቡ አደጋዎችን ያስቀራቸዋል፡፡

6. ብዙ ጊዜ ዓመታት በዓላቸውን ሲያከብሩ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ ሲያደርጉ ብቻ በመገናኛ ብዙኃን ስማቸውን የምንሰማቸው የሞያ ማኅበራት(የአርክቴክቶች፣ የሲቪል መሐንዲሶች፣ የሕንጻ ተቋራጮች፣ ወዘተ) ተገቢው ቦታና ሥልጣን ተሰጥቷቸው የግንባታዎችን ሂደት እንዲከታተሉ፣ የንሥር ተመልካችነት(watch dog) ኃላፊነትን እንዲወጡ ቢደረግ፤

እንዴው በአጠቃላይ ግን የግንባታ ሂደታችንን እኛም ከአክሱም በፊት የምንገነባው፣ ቻይኖችም ከቻይና ግንብ በፊት የሚሠሩት ባንመስል መልካም ይመስለኛል፡፡ ቅንዥላቶቻችን በዐጸደ ነፍስ ሆነው ይገረሙብናል፤ ‹አሁን እነዚህ የኛ ልጆች ናቸው?› ይሉናልና፡፡

ስድስቱ  የሸለብታ  (ናፕ)

ጥቅሞችከዶ/ር ሆኒሊያት ቱፈር

1) ንቃትን ይጨምራልድካም እየተሰማዎ የሚሰሩት ሥራ ውጤታማነት ስለማይኖረው ለትንሽ ደቂቃ ሸለብ አድርገው በነቃ አእምሮ ወ

ደ ሥራዎ ቢመለሱ ይጠቅማል፡፡2) የሥራና የትምህርት የማስታወሻ ችሎታን ያዳብራልሸለብታ የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡ ከባድና ው

ስብስብ ሥራዎችን በትኩረት እንድንሰራ ይረዳል፡፡3) አዕምሮ በሥራ ብዛት እንዳይወጠር ይረዳል

የምንሠራው ሥራ ብዛት ካለው ዕረፍት እየወሰድን ከሠራን ውጤታማ ውጤታማነት እንጨምራለን፡፡ ለ30 ደቂቃ ሸለብ ካደረግን በአዲስ አዕምሮ ወደ ሥራ መመለ

ስ ይቻላል፡፡4) የፈጠራ ችሎታን ያዳብራል

ዕረፍት ያደረገ አዕምሮ አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠር ችሎታ ይኖረዋል፡፡

5) ጤናማ እንድነሆን ያደርጋልሸለብታ ለአዕምሮ ዕረፍት የሚሰጥ ሲሆን ሕመም የመከላከል አቅምን ይጨምራል፤ጭንቀት እና ፍርሃትን ይ

ቀንሳል፡፡6) ጥሩ ስሜትን ይፈጥራል

ሸለብታ በእንቅልፍ ውስጥ ሴሮቶኒን የሚባል ንጥረ ነገር እንዲመነጭ ስለሚያደርግ የእንቅልፍ ስሜት እንዲሁም

የምግብ ፍላጎታችን እንዲስተካከል ያደርጋል፡፡እባክዎን ለወዳጆችዎ ያካፍሉ!

የአፍዎን  ጠረን  ለመቀየር

5  ዘዴዎች1) የአፍዎን ንጽህና በሚገባ ይጠብቁ፡-­ ጥርስዎን ቢያንስ በቀን ሁለት ጊዜ ማጽዳት እንዳለብዎ ይወቁ ከተቻለ ከምሳ በኋላም ለማጽዳት የጥርስ ብሩሽና የጥርስ ሳሙና በቦርሳዎ በመያዝ ጥርስዎን ያፅዱ፡፡ እንዲሁም የጥርስ ብሩሽዎን በየ3ወሩ መቀየር እንዳለብዎ አ2) ፈሳሽ በብዛት ይውሰዱ፡-­ ውሃን መጠጣት በአፍ ውስጥ እርጥበትን ሰለሚፈጥር በብዛት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ ከስኳር ነፃ ሆኑ ማስቲካዎችና ከረሜላዎች መውሰድ በአፍ ውስጥ (Saliva) ምራቅ እንዲመነጭ በማድረግ በአፍ ውስጥ የቀሩ ምግብና ባክቴሪያዎችን እንዲያጥብ ያደርጋል፡፡3) ሲጋራን ማጤስ ማቆም፡-­ ሲራጋ ማጤስ ለመጥፎ የአፍ ጠረን መኖር ምክንያት ስለሚሆን ማቆም ይኖርብዎታል፡፡4) የሚወስዱትን ምግብ ወይንም መድኃኒት መጥፎ የአፍ ጠረን እንደሚያመጣብዎ ካወቁ ወደጥርስ ሐኪምዎ በመሄድ ማሳየት ተገቢ ነው፡፡5) የጥርስ ሐኪምዎን በዓመት አንዴ እንዲያይዎት ማድረግ እንዲሁም በሕክምና የታገዘ ባለሙያዊ የጥርስ ዕጥበት በዓመት አንድ ጊዜ ማድረግ መጥፎ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

የሙዝ  7  የዜና  በረከቶች

1. የደም ግፊት እና የልብ ህመም ተጋላጭነትን ይቀንሣል2. የምግብ መፈጨት ሂደትን ያፋጥናል3. መደበትን ይቀንሣል4. አጥንታችንን ያጠነክራል5. ሃይል ይሠጣል6. በወር አበባ ጊዜ የሚከሠትን ህመም ይቀንሣል7. የጨጓራ ቁስለትን እንዳይከሰት ይከላከላልጤና ይስጥልኝ

ጤናዳም  መጽሔት

መጣችልዎ

በቅርብ  ቀንበመላው  አሜሪካና  ካናዳ

           ሸጋ  እንጀራ፣  

ግሮሰሪና  መጋገሪያ

Shega Foods

የፍስክ እና የጾም ምግቦችን ቱጎ አድርገው ለመውሰድ

ወደ ሸጋ ይደውሉ

ሸጋ  100%  

የጤፍ  እንጀራን  

ከየሱቁ  ይጠይቁ

በሸጋ ግሮሰሪ፡ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ከየትኛውም ሱቅ የማያገኟቸው የሃገር ቤት ባህላዊ እቃዎች፣ ጤፍ፣ የስልክ ካርድ፣ መጽሐፍት፣ ሲዲዎች፣ ሁሉም ይገኛሉ

2111 E Franklin Ave, Mpls, MN 55406(612) 341-4373

የባህል  አልባሳት

 በብዛትም  

በጥራትም  ይዘናል

Page 10: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 10

እያወቅን እንድንመርጥ የሚያስችሉ ጉዳዮችበወንዶች ዓይን የሚገቡ ሴቶች ልጅ እግር የሆኑ እና በሳል

የሆኑ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ቀጭን ወገብ ያላቸው፣ ሞላ ያሉ፡፡ ስስ ከንፈር እና ለስለስ ያለ የፊት ገፅታ ያላቸው ሴቶች ወንዶችን ይማርካሉ፡፡ ሴቶች ደግሞ ጀግና የሆኑ ወንዶች ይማርኳቸዋል፡፡ጡንቺስት የሆነ፣ ሰፋ ያሉ ትከሻ ያለው፣ ጥርት ያለ የቆዳ መልክ ያለው እና ጎልቶ የሚታይ የወንድነት ባህሪ ያለው፣ ወንዳወንድ የፊት ገፅታ የተላበሱ ወንዶች እንደሚማርኳቸው የቅርብ ጊዜ ጥናት አሳይቷል፡፡

በአጠቃላይ እነዚህ የወንድ ገፅታዎች ጥሩ የወሲብ ብርታት እና ጥሩ ዘረመል ያለውን ወንድ ያመለክታሉ፡፡ በተጨማሪም ሴቶች ሀብት ባላቸው ወንዶች ወይም ሃብትን ለማምጣት ብቃት ባላቸው ወንዶች ይማረካሉ፡፡ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች እውቀት/የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ተጓዳኝ ቅድሚያ ይሰጣሉ፡፡ ውበት፣ አዕምሮ እና ሀብት አለማቀፋዊ ነገሮች ናቸው ማለት ነው፡፡

በምንም የኑሮ መመዘኛ ከማንመጣጠናቸው ሰዎች ጋር (Su-­permate) በፍቅር ልንወድቅ አንችልም፡፡ በመካከለኛ ኑሮ የሚኖር አንድ ሰው ከአቅም በላይ ከሆነ ሰው ጋር ለመገናኘት እቅዱ ቢኖረው መግቢያ መውጪያው ይጠፋበታል፡፡ ምክንያቱም ከእንደነዚህ አይነት ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመስረት ለጥቂት ሰዎች ካልሆነ በስተቀር ለአብዛኞቹ አስቸጋሪ ነውና፡፡ በምርጫ መሀል የፍቅር ጣልቃ ገብነት መኖር ጥቅ እዚህ ላይ ነው፡፡ በጥንዶች መሀል የፍቅር መኖር ጥቅሙ በተጠናከረ ኃይል ልጁን ለማሳደግ ብቻ አይደለም ከማንመጣጠን ሰዎች ጋር ጊዜያችንን እና ጉልበታችንን ከማባከን ለመቆጠብም ጭምር እጂ፡፡ ስለዚህ ሰዎች በውበት፣ በጭንቅላት ብስለት እና በአኗኗር ዘይቤ ከራሳቸው ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ ሰዎች ጋር በፍቅር ለመውደቅ ያዘነብላሉ፡፡

ሳናውቅ ፍቅረኛን የምንመርጥባቸውእስካሁን የተመለከትናቸው ሰዎች ውጫዊ ኑሮአችንን በመ

መልከት ተማርከው የሚሆናቸውን ሰው ለመምረጥ የሚያስወስኗቸውን ነገሮች ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከላይ እንደተገለፀው በገሃድ የሚታይ ባይሆንም ወሳኝ የሆነ መጠቆሚያ ነው፡፡

ስለዘረመል እና የጓደኝነት ምርጫን አመላክቶ በተካሄደው ጥናት መሰረት በተገኘው አመርቂ ውጤት እያንዳንዳችን ለአንድ የተወሰነ የዘረመል ስብስብን ላካተተ ሰው ፍላጎታችን እንደሚያርፍ አሳይቷል፡፡ ይኸውም MHC (histocompatability complex) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን በሽታ አምጪ ህዋሶችን በመከላከል ረገድ አይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ሁለት ጥንዶች ውስጥ ያለው የMHC አይነት የተለያየ ከሆነ የሚወልዷቸው ልጆ ጤናማዎች እና በሽታን የመከላከል ብቃታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ሰዎችን የመምረጥ ዝንባሌያችን የሚጨምረውም ከዚሁ ልዩነት በመነሳት ሲሆን በአጋጣሚ የሚጣመሩ ጥንዶች ተመሳሳይ የሆነ MHC የሚ

ኖራቸው ሁኔታ ዝቅተኛ ነው፡፡ የተለያዩ MHC ያላቸው ሰዎች እንዴት ነው ሊገናኙ የሚችሉ

ት? ይህ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ግልፅ ባይሆንም ሽታ ወሳኝ የሆነ የመጠቆሚያ መሳሪያ ነው፡፡ ሰዎች ጓደኞቻቸውን በማሽተት ለይተው ይመርጣሉ፡፡ ጥናትም እንደሚያሳየው የተለያዩ MHC ያላቸው ሰዎች በለበሱት ልብስ ሽታ እርስ በርስ ይሳሳባሉ፡፡ ይህንን ነው የፍቅር ኬሚስትሪ ብለን የምጠራው፡፡

ብዙ ፍቅሮች ታስቦባቸው የተካሄዱ ሳይሆን በተለያየ አጋጣሚ የሚፈጠሩ ናቸው ይላል ሳይንስ፡፡ ድንገተኛ ፍቅር ወይም በድንገት በተፈጠረ አጋጣሚ የተነሳ ወደ ፍቅር፣ ወደ ግንኙነት አልያም ወደ ጋብቻ ሊያመራ ይችላል፡፡ ይሄ ደግሞ ተፈጥሯዊ ከሆነ ስሪታችን ጋር የሚሄድ ነው፡፡ እንደተመራማሪዎች ገለፃ ከሆነ በድንገት በሚደረጉ የስሜት መሳሳቦ የተነሳ ልጆች ሊወለዱ ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ እንስሳት ላይም ጭምር ነው፡፡ ለምሳሌ በአይጦች ላይ፣ በዓሣዎች ላይ፣ በጥንቸሎች ላይ፣ እንዲሁም በዝንጀሮዎች ላይ የተደረገው ጥናት ያሳየው ድንገተኛ መዋደድና በአጋጣሚ ወደዘር መቀላቀል የማዘንበል ሁኔታ የታየ ክስተት ሲሆን ይህም በሰውነታችን ውስጥ ካለው ተፈጥሯዊ ማግኔት ጋር የተገናኘ ነው ይላሉ ባለሙያዎቹ፡፡

አንድ ሰው አጠገቡ ካሉ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር ላይፋቀር ይችላል፣ ለሌላ ሰው ቆንጆ የሆነች ሴት ለዚህ ሰው ቆንጆ ላትሆን ትችላለች፡፡ ምክንያቱም ደግሞ በውስጣችን ያለው የፍቅር ማግኔት ከመከፈቱና መዘጋቱ ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ የፍቅር ማግኔት ሜጀር ሂስቶኮምፓቲቢሊቲ ኮምፕሌክስ በመባል የሚጠራ ሲሆን በአጭር መጠሪያውም ‹‹MHC›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ የ‹‹MHC›› ዘርም ‹‹HLA›› በመባል የሚጠራውን ማለትም (Human Leukocyte Antigen›› የተባለና በነጭ የደም ሴል ላይ የሚገኝን ፕሮቲን ያስገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ፕሮቲን ዋና ስራ በሽታ መከላከል ይሁን እንጂ በተለይ አፍንጫችን ውስጥ የሚገኘውን ልዩ የጠረን መለያ ክፍል ባህሪ የመቅረፅ አቅም አለው ይላሉ ባለሙያዎች፡፡

በአፍንጫችን ውስጥ ቬሮሞናሳል በመባል የሚጠራ የሽታ ወይም የጠረን ማዕከል ያለ ሲሆን ይህም የጠረን ማጣሪያ ቦታ አንድን ተቃራኒ ፆታ ሳቢ ወይም የማይስብ መሆንና አለመሆኑን የምንለይበት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ምግብ ጥሩ መሆን አለመሆኑን ወይም ጤናማ መሆን አለመሆኑን የምንለይበት ትልቁ መንገድ ጠረኑ ነው የሚሉት ባለሙያዎች አንድም ሰው የአንድን ተቃራኒ ፆታ መስህብነት የሚያረጋግጠው በጠረን ነው ይላሉ፡፡ እነዚህ ልዩ የፍቅር ጠረኞችን የሚሸከሙ ኬሚካሎች በልዩ ስማቸው ‹‹ፌርሞንስ›› በመባል ይጠራሉ፡፡

በዚህ ዙሪያ ባለሙያዎች የተለያዩ ጥናቶችን አድርገዋል፡፡ ከዚህም አንፃር አንዲት ሴት ለፍቅርም ሆነ ለወሲብ የበለጠ የምትሳበው ከእሷ ጋር (ድንገት... እባክዎ ወደ ገጽ 13 የዞረ)

ትዝብት  ከአሜሪካ

መብረቅ  እና  ጥንቃቄውብዙ ሰዎች በመብረቅ አደጋ ደርሶባቸው እንደተጎዱና ከፍተኛ አደጋ እንደደረሰባቸው ከዚህም አልፎ እንደ ሞቱ እንሰማለን፡፡ የመ

ብረቅ የብርሃን ብልጭታ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ሁኔታ የሚያስተጋባው ድምፁ ጭምር ሰዎችን ሊያስደነግጥና ሊያሸብር ይችላል፡፡ መብረቅ በከፍተኛ ድምፅና የብርሃን ብልጭታ መታየት ሲጀምር መሬት በራሷ ስበት የኤሌክትሪካል ፊልድ አማካኝነት ከብረቁ ጋር በከፍተኛ ሁኔታ የማግኔታዊ የቻርጆች መሳሳብ ስለምትፈጥር ይህ የመሳሳብ አጋጣሚ በጨመረ ቁጥር መብረቅ ወደ መሬት በቀላሉ የመውደቅና ከፍተኛ አደጋ የማድረስ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

ብዙውን ጊዜ በመብረቅ አደጋ ከሚደርሱ አካላዊ ጉዳቶች ውስጥ በብዛት የሚታየው የሰውነት ቆዳ በተለይም የፊትና ጭንቅላት አካባቢ መቃጠል ነው፡፡ ይህ የሰውነት መቃጠል ወይም መንደድ ከውጭ የሰውነታችን ክፍል ባሻገር ወደ ውስጥም በመግባት ትላልቅ የምንላቸው የሰውነታችን አካሎች የማቃጠል ወይም የማንደድና ከጥቅም ውጪ የማድረግ ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ከእነዚህ የውስጠኛው ተጋላጭ ክፍሎች መካከል የአንጎላችን ክፍሎች፣ ልባችን፣ ሳንባና ጉበታችን ይጠቀሳሉ፡፡ ይህ ችግር ከሚፈጠርበት ዋናው ምክንያት የኤሌክትሪክ ቻርጆች የፍሰት መጠን መለያየትና የሚፈጥሩት የኃይል መዛባት ነው፡፡

የአሜሪካ  ጉዳይ

ፒያሣ ገበያ ሲመጡ ምንም እንደማያጡ ይተማመኑ

ድንገት  የሚያፈቅረን  ማግኔት  

የት  ይገኛል?

ማንን  ላፍቅር  ያላችሁ  ይህንን  አንብቡ

ከሮቤል ሔኖክ

ሁልጊዜ የሚስማማቸውን የፍቅር ሰው ለማግኘት ከራሳቸው ጋር የሚመክሩና ከተፈጥሮ ጋር የሚሟገቱ ሰዎች ጥቂት አይደሉም፡፡ በቅፅበት እይታም የሚመለከቱትን ሰው ‹‹ምነው የእኔ ቢያደርገው በሚል የምኞት መንሰፍሰፍ ላጤነታቸውን የሚኮንኑም ጥቂት አይደሉም፡፡ ግን ሊስማማን የሚችለውን ሰው አይተን ብቻ እንዴት መምረጥ እንችላለን? የሚለው ሃሳብ ፈጥኖ የሚታሰብ አይሆንላቸውም፡፡ የሚስማማን ሰው በቅፅበት መለየት በእርግጥም መታደል ነው፡፡

ጓደኛን መምረጥ በህይወታችን ውስጥ ከምንወስዳቸው ውሳኔዎች ሁሉ በእጅጉ የጠነከረ ነው፡፡ የእኔ ብለን ከልባችን የምናስበውን ሰው ለማግኘት ያለንን ጉጉት ከግብ ለማድረስ ስንል የምናፈሰው ነዋይ አንዳንድ የጥንድ አፈላላጊ ድርጅቶችን እና ዓለም አቀፍ የመረጃ ልውውጥ አገልግሎቶችን በቢሊዮን ዶላር ገንዘብ እያንቀሳቀሱ አድርጓቸዋል፡፡

ይሁንና ይህ ብቻ እርካታ አልሰጠንም፡፡ ለምሳሌ ዓለም አቀፍ (internet) የመረጃ ልውውጥ አገልግሎቶች በመጠቀም ጓደኛ ለማፈላለግ የሚንቀሳቀሱ 900 ሰዎች ላይ በ2005 እ.ኤ.አ ጥናት ተደርጎ ነበር፡፡ በዚህም ጥናት መሰረት ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ 75 በመቶ የሚሆኑት የሚፈልጉትን ሰው አላገኙም፡፡ የሚስማማንን ሰው ለመምረጥ የምንጠቀምባቸው ዘይቤዎች ገና በጨለማ ውስጥ ያሉ ይመስላል፡፡

ጓደኛን ለመምረጥ የምንጠቀምበት ዘዴ ከምንም በላይ ውስብስብ ነው፡፡ ለመምረጥ የምንጠቀምባቸው መንገዶችም በሁለት አይነት መልኩ ይገለፃሉ፡፡ ልቦናችን/ህሊናችን እያወቀው ለመምረጥ የምንጠቀምባቸው ዘይቤዎች እና ሳናስበው ወይም ከህሊናችን/ከዕውቅናችን ውጪ ሆነን የምንጠቀምባቸው ዘይቤዎች ናቸው፡፡ ህሊናችን እያወቀው... የምንጠቀምባቸው ዘይቤዎች በጣም ጥቂቱ ክፍል ሲሆን የተቀረው ይህ ነው ብለን መግለፅ የማንችለው ማግኔታዊ ባህሪ የተነሳ የሚፈጠር ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ፍቅር በቃላት ሊገለፅ የማይችል ድንቅ ኬሚስትሪ ነው የሚል ድምዳሜ ውስጥ እንድንገባ ያደርገናል፡፡

ሰውነታችን ኤሌክትሪካዊ ፍሰት ያላቸው ቻርጆችን የያዘ ሲሆን ይህ ገላችን ልክ አንድ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ገመድ ወይም ሽቦ መያዝ ከሚችለው ወይም ከአቅሙ በላይ የሆነ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ፍሰት ሲመጣበት ከመቃጠል እንደማያመልጥ ሁሉ ሰውነታችንም ሊይዘው ከሚችለው የቻርጅ መጠን በላይ የቻርጅ ፍሰት ሲመጣበት ይቃጠላል፡፡

በዚህም ምክንያት የተነሳ ሰውነታችን ከመብረቁ በሚወርድበት ከፍተኛና ከአቅሙ በላይ በሆነ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ፍሰት የተነሳ ውጫዊም ውስጣዊም የሆነ የመቃጠል አካላዊ ጉዳት ይደርስበታል፡፡ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ፍሰቱም ከሰውነታችን የመሸከም አቅም በላይ እየሆነ ሲሄድ በቅፅበት የመሞት ዕድላችን የሰ

ፋ ይሆናል፡፡ ታዲያ በዚህ የመብረቅ መከሰት ከሌሎቹ የሰውነታችን ክፍ

ሎች በተለየ ሁኔታ በቀላሉ ሊጎዱና ከፍተኛ አደጋ ላይ ሊጥሉን የሚችሉ የትኞቹ ናቸው ብለን ስንጠይቅ ከላይ ካነሳነው ምክንያት ጋር በማያያዝ እናገኛቸዋለን፡፡ ቆዳችን ፊት ለፊት ወይም ከላይ እንደመገኘቱና የኤሌክትሪክ መልዕክቶችን የሚያስተላልፍበት ነርቮችን በብዛት እንደመያዙ ለመብረቅ ጉዳት በቀላሉ ተጋላጭ ሊያደርገው ይችላል፡፡

ነገር ግን ለቅፅበታዊ አደጋ ብሎም እስከ ሞት ሊያደርሰን የሚችለው የመብረቅ አደጋ በልባችንና በአንጎላችን ላይ በተለይም የነርቭ ስርዓታችንን (centeral nervous system) በጨመረ መልኩ ሲያጠቃ ነው፡፡

ልባችንም ሆነ የነርቭ ስርዓታችንን በጨመረ መልኩ የሚገኘውን አንጎላችንና ነርቭ ሴሎቻችን ከሌሎቹ የሰውነታችን ክፍሎች በተለየ ለመብረቅ አደጋ የተጋለጡበትን ምክንያትም በሰውነታችን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ተሸካሚና የኤሌክትሪክ መልዕክት አስተላላፊ በመሆናቸው ነው፡፡ ይህ ተፈጥሯቸው ደግሞ ከመብረቁ ከሚመጣው የኤሌክትሪክ ቻርጅ ጋር በሚፈጥረው የመሳሳብ ሁኔታ የተነሳ ድንገት የመብረቁ የኤሌክትሪክ ቻርጅ

ሲጨምር ልባችን፣ አንጎላችንም ሆነ የነርቭ ስርዓታችን ቻርጁን የመሸከም አቅም ስለሌላቸው በቀላሉ ይጎዳሉ፡፡

እነዚህ የሰውነታችን ክፍሎች ደግሞ በህይወት ለመቆየታችንና ለማንነታችን በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ እነሱ ከተጎዱ ደግሞ መላ ሰውነታችን ተጎድቷል፡፡ እኛም ሞተላን ማለት ይቻላል፡፡ በብዛት የፊታችንና የጭንቅላታችን ክፍል ተጎድቶ የሚታየው ደግሞ አንጎላችንም ሆነ አብዛኛው የነርቭ ስርዓታችን በላይኛው የሰውነታችን ክፍል ወይም በጭንቅላታችን አካባቢ መገኘቱ ነው፡፡

ይህ አካባቢ ደግሞ ከፍተኛው የሰውነታችን የኤሌክትሪክ ቻርጅ ፍሰት የሚካሄድበት በመሆኑ ከመብረቁ ከሚመጣው የኤሌክትሪክ ቻርጅ ጋር ብዙ ቁርኝት ይፈጥራል ማለት ነው፡፡ በአጠቃ

ላይ በእነዚህ ቦታዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ ቀለል ያለ ወይም ለርዥም ጊዜ ስቃይ ውስጥ እየከተተ የሚያቆይ አለበለዚያም ወዲያውም ይሁን ከጊዜያቶች በኋላ የሚመጣ ሞት ይሆናል፡፡

ስለዚህም መብረቅ በብዛት በሚፈጠርበት ወቅት በተለይም ኃይለኛ የዝናባማ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግባቸው ከሚገባን ነገሮች መካከል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ቻርጅ የመሸከምና የማስተላለፍ አቅም ካላቸው እንደ ዛፎች፣ የኤሌክትሪክ ሽቦዎችና የውሃ አካላት በዝናብና መብረቅ በሚታይበት ጊዜ መራቅ ተገቢ ነው፡፡

እንደዚሁም መብረቅ በሚበዛበት ሰዓት ለረዥም ሰዓት በቤት ውስጥ በስልክ መነጋገርን ማቆም ከነጭራሹ በስልክ ባንነጋገርም መልካም ነው፡፡ ይህ ግን ኃይለኛ የዝናብና የመብረቅ መከሰት በሚኖርበት ጊዜ ለማለት ነው፡፡ እንደዚሁም አደገኛ የመብረቅ አመጣጥን ካየን ቴሌቪዥኖችንና ኮምፒውተሮቻችንን መዝጋት ይገባል፡፡

ምክንያቱም እነዚህ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከመብረቁ የኤሌክትሪክ ቻርጅ ጋር በሚፈጥሩ የመሳሳብ ሁኔታ ለሌላ አደጋ ሊያጋልጡ ይችላሉና፡፡ በአጠቃላይ ቅድሚያ ለራሳችን እየሰጠን ክረምቱም መብረቁም በመልካም እንዲያልፍ ይሁንልን፡፡

Page 11: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 11

አጋፔ  /ፍቅር/  በቤት  ውስጥ  

እርዳታ  ሰጭ  ድርጅት

Agape Home Care Agencyፍቅር ይታገሳል፣ ቸርነት ያደርጋል፣ አይቀናም፣ አይመካም; አይታበይም፣

ፍቅር ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል፣ ያለውን ሁሉ ይሰጣል በመስጠቱ ይደሰታል።አጋፔ /ፍቅር/ በቤት ውስጥ እርዳታ ሰጭ ድርጅት (Agape Home Care Agency) አላማችን

በቤት ውስጥ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው አዛውንቶች የሃኪም ወረቀት ማስረጃ ያላቸው በአማርኛ፣የኦሮምኛ እና የትግርኛ ወዘተ... ተናጋሪዎች ራሳችሁ ባቀረባችሁ የቤተሰብ አባል

በማሰልጠን ወይንም በብቃት በሰለጠኑ በድርጅቱ ሰራተኞች በፍቅርና በአክብሮት ሊያገለግላችሁ ዝግጁ ነው

ለጊዜው የምንቀበለው Insurance Medical Assistance (MA)

ስልክ ቁጥራችን 612-384-6513 ቅድስት ታዬ ገምታ ብላችሁ ደውሉልን

Email: [email protected]

በወንጌል  አማኞች  የምርጦቹ  7000  ቤተክርስቲያን  

ሜኔሶታ  

ይሙጡ-  እግዚአብሔር  ያየሎትን  የክብር  ፍፃሜ  ይገናኙ!!!!

      Come  On  &  Meet  Your  Glorious  Destiny!

                መጋቢ  አበባየሁ  አበበ

        Family  Life  Educator  and  Councilor

 መደበኛ  ፕሮግራሞቻችን  ፡-  

 ዘወትር  እሁድ  ከ4፡00pm-7፡00pm  አምልኳና  በእረኝነት  ፀጋ  የትምህርት  ግዜ  

(መዝ  23)  

 ዘወትር  ረብዕ  ከ5፡00pm-7፡00pm  አምልኳና  የእግዚአብሔር  ቃል  ጥልቅ  

ሚስጢር  ልዩ  የትምህርት  ግዜ  (ሮሜ  16፣25)  

 ዘወትር  ቅዳሜ  ከ4፡00pm-7፡00pm  የፀሎት  ፣  ልመናና  የምልጃ  ልዩ  ግዜ  

 በተለያዩ  የሕይወት  ጉዳዮች  ላይ፣  በተለይም  በትዳርና  በቤተሰብ  ህይወት  ላይ  መፀሐፍቅደሳዊና  

ሞያዊ  ምክሮችን  (Counseling)  እንሰጣለን።  

አድራሻችን  ፡-  የአምልኮ  ስፍራችን  1697 Lafond Ave, Saint Paul, MN,55104 ቢሮአችን  1821  University  Ave.  S-229,  Saint  Paul,  MN,55  104  (የቀድሞ  የኢትዮጵያ  ኮሚኒቲ  ቢሮ  የነበረው)  

 ድህረ  ገፃችን  www.unique7000church.com  651-276-5798/651-239-6076/763-219-6143

ወንድሜን... (ከገጽ 8 የዞረ)

ወንዶች ከሴቶች በአራት እጥፍ ለሞት ሊጋለጡ ይችላሉ፡፡በተለይ ደግሞ አጫሾች፣ ጠጪዎች፣ ከመጠን በላይ ወፍራ

ም የሆኑ ሰዎች፣ የስኳር ህሙማንና ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የደም ግፊት ያለባቸው ሰዎች ለድንገተኛ የልብ ድካምና ሞት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው፡፡

ስለዚህም እነዚህና ሌሎች ሁኔታዎች እንዳይከሰቱ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ከተከሰቱም ተገቢውን ህክምናና ክትትል ማድረግ ብልህነት ነው፡፡ በተጨማሪም ከ20-­25 በመቶ የልብ ደም ስር የመጥበብ በሽታ (CHD) መኖሩ ሳይታወቅ በድንገት የሚከሰት ምት የመጀመሪያው ክስተት ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዘሆነም ለዚህ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ማስወገድ በጣም ልናተኩርበት የሚገባና በእኛ ቁጥጥር ስር ያለ እርምጃ ነው፡፡ አንዳንዴ ከቁጥጥራችን ውጭ የሆኑ በሽታዎችና ክስተቶች ሊከሰቱ የሚችሉበትን አጋጣሚ መቼም መገመት አይቻልም፡፡ ብዙ አልሞና ረጅም ራዕይ ሰንቆ ላይ ታች ሲሉ እንደወጡ መቅረት ልናስወግደው የማንችለው ዕጣ ፈንታችን ሊሆን ይችላል፡፡ ፈጣሪ በጥበቡ ይጠብቀን ከማለት ውጪ ሌላ ምን ማለት ይቻላል፡፡

እዚህ ላይ አሳዛኝ ተመሳሳይ ክስተቶችን ማስታወስ ይቻላል፡፡ ፍየ የተባለው ካሜሮናዊ ዓለም አቀፍ እግርኳስ ተጨዋች ሀገር ሰላም ብሎ እግርኳስ እየተጫወተ ስለነበር ድንገት ሜዳ ውስጥ ለ

ህልፈት የተዳረገው፡፡ እዚሁ ሀገራችንም ተመሳሳይ አሳዛኝ ክስተት አሳልፈናል፡፡ ይኸውም የታዋቂው ጀግና አትሌታችን ቀነኒሳ በቀለ እጮኛ የነበረች አትሌት በልምምድ ላይ እያለች ነበር ድንገት ህይወቷ የተቋጨው ያውም በእጮኛው ፊት ከህሊና የማይጠፋ አሳዛኝ ክስተቶች ናቸው፡፡ ነፍሳቸውን ይማርና በእርግጠኝነት የሞቱበት ምክንያት ይሄ ነው ብሎ እቅጩን መናገር ያዳግታል፡፡

ምክንያቱም ለዚህ የፖቶሎጂ ውጤት ሌሎችም ምርመራዎች ያስፈልጉናል፡፡ ሆኖም ግን ከሁኔታዎች መገመት እንደሚቻለው መንስኤው የልብ ድካም የመሆን ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ በተለይም የተሰኘው የልብ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ በመፋፋታቸው (አብሮ ሊወለድ ወይም በሂደት ሊከሰት ይችላል) የሚከሰተው ችግር በወጣትነት ዕድሜ በተለይም በስፖርተኞች ላይ ይከሰታል፡፡

ላልተጠበቀ ድንገተኛ ሞት በማጋለጥ የአምባሳውን ድርሻ የሚወስደው የልብ በሽ ስለሆነና ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ልንከላከለውም ስልምንችል ይበልጥ ትኩረቴን እሱ ላይ ላድርግ እንጂ ሌሎች የድንገተኛ ሞት መንስኤዎችም እንዳሉ መዘንጋት የለበትም፡፡ ለምሳሌ ድንገተኛ የመኪና ወይም በሰው የመደብደብ አደጋ፣ ድንገተኛ መመረዝ በምግብ ሆነ በመድሃኒት ሊሆን ይችላል፡፡ ትንተና፣ የተፈጥሮ አደጋዎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንግዲህ የአንተ ወንድም በሐኪሞች የተጠረጠረው እንዲሁ ሲሆን በሌላ ሰው የመሞት ሁኔታ እንዳልደረሰበት የተደረገለት የሬሳ ምርመራ ይህን አሳይቷልና ጉዳዩ ከላይ ከዘረዘርናቸው የልብ ህመም ክስተቶች ጋር የሚሄድ ነው ብለን እናስባለን፡፡ ለማንኛውም ከድንገተኛ

ሞት ሁላችንንም ይሰውረን እያልኩ በዚሁ ልሰናበት፡፡

ጭንቀት... (ከገጽ 8 የዞረ)አሁን ላለው የጭንቀት ችግር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፡፡ ከእነዚ

ህ በተጨማሪም ለረዥም ጊዜ ብቻን መኖር (loneliness)፣ መጥፎ የአስተዳደግ ሁኔታ (Adverse parenting) እና በልጅነት ጊዜ የደረሱ ከፍተኛ ድንጋጤ የሚፈጥሩ ክስተቶች ለጭንቀት ችግር እንደሚያጋልጡ ባለሙያዎቹ አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም እነዚህን መለየቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ምክንያቱም የችግሮችህ ምንጮች እነዚህ ነገራት ከሆኑ ለእነሱ የሚሰጠው የመፍትሄ አቅጣጫና ለጭንቀት ችግር የሚሰጠው የመፍትሄ አቅጣጫ የተለያየ ስለሆነ፡፡ በመሆኑም ቀጥለን የምንሰጥህ የመፍትሄ አቅጣጫ በእነዚህ ምክንያቶች የመጣ ከሆነ ብዙ የሚያግዝህ ስለማይሆን ችግርህን እንደገና ፃፍልን ወይም በአካባቢህ ያሉ ካውንስለሮችን አነጋግር፡፡ ያንተ ችግር በእነዚህ ምክንያቶች ያልወጣ ከሆነ ግን ቀጥለን የምንጠቁምህን የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተግብራቸው፡፡

የመፍትሄ አቅጣጫዎችውድ ጠያቂያችን በፅሑፍህ ላይ ከጠቀስካቸው ነገሮች ተ

ነስተን ያንተ ችግር አጠቃላይ የጭንቀት ችግር (Generalized Anxiety Disorder) ተብሎ የሚጠራው የጭንቀት ችግር አይነት ነው፡፡ ይህ ችግር ደግሞ የሚመጣው ከተሳሳቱ የአስተሳሰብ ሂደቶች (faulty thoughts) ነው፡፡ ስለሆነም እነዚህን የተሳሳቱ አ

ስተሳሰቦን መለየቱ የመጀመሪያ መፍትሄ ይሆናል፡፡ ምንም እንኳ የተለያዩ አይነት የተሳሳቱ የአስተሳሰብ ሂደቶ

ች ቢኖሩም ከአንተ ሁኔታ ጋር ይያያዛሉ ያልኳቸውን ዋና ዋና ሂደቶች ልጠቁምህ፡፡ አንደኛውና ባንተ ፅሁፍ ላይ በግልፅ የሚታየው አዕምሮን ማንበብ (mind reading) የሚባለው ሲሆን ይህም ሰዎች ስለኛ የሚያስቡትን አውቃለሁ የሚል አስተሳሰብ መያዝ ማለት ነው፡፡

ለምሳሌ አንተ ሁሉ እንደሚያዝንብኝ አውቃለሁ የሚል አስተሳሰብ ይዘሃል፡፡ ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው ምክንያቱም ሁሉም ስለሚፈሩኝ አይነግሩኝም ካልክ በኋላ እንዴት እንደሚፈሩህ እወቅ ብትባል የምትመልሰው አዕምሮአቸውን አንብቤ ነው የሚሆነው፡፡ አዕምሮን ማንበብ ደግሞ እንዲሁ እንደቀላል የሚቻል አይደለም፡፡

ሁለተኛው ደግሞ ሁሉም ወይም ምንም አይነት አስተሳሰብ (all none thinking) የሚባለው ነው፡፡ ይህም ማለት ሁሉም ነገሮች እንደፈለግነው እንዳሰብነው መሆን አለባቸው ካልሆኑ ግን ሁሉም አልተሳኩልኝም ብሎ ማሰብ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጅ ምሉዕ ስላልሆነ ሁሉንም እንደፈለገው እንዳሰበው ማድረግ አይችልም፡፡ ይልቁንም ካሰባቸው ውስጥ አንዳንዱ ይሳካሉ፣ አንዳንዱ ደግሞ አይሳካም፡፡ ስለሆነም ይህንን አስተሳሰብ የያዙ ሰዎች የተሳሳቱ አስተሳሰብ ይዘዋል ይባላል፡፡

ነገሮችን ወደ ራስ ማዞር (personalization) የሚባለው ደግሞ ሌላኛው (ጭንቀት... እባክዎ ወደ ገጽ 12 የዞረ)

Page 12: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 12

ጭንቀት... (ከገጽ 11 የዞረ)

የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ ማለት ከእኛ ጋር ተያያዥነት የሌላቸውን ነገራት ሁሉ ከራሳችን ጋር የማያያዝ ሁኔታ ነው፡፡ ለምሳሌ በመንገድ እየተጓዝን ሰዎች ሲስቁ በእኔ ነው የሳቁ ብሎ ማሰብ ነገሮችን ወደ ራስ የማዞር አስተሳሰብ ነው፡፡ ጠያቂያችን ሆይ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት የመጀመሪያ ተግባርህ ጊዜ ወስደህ እላይ የጠቀስኳቸውንና ሌሎችንም የተሳሳቱ አስተሳሰቦችህን መፈተሽ ነው፡፡ እስኪ እራስህን ይህንን ጥያቄ ጠይቅ፡፡ ‹‹ለመሆኑ አንድ ሰው እንዴትስ ሆኖ ስለሁሉም ነገር ሊያስብ ይችላል?›› መልሱ ደግሞ ወደ ቀጣዩ ተግባር ይመራሃል፡፡

ቀጣዩ ተግባር ደግሞ አንተ ልታስብባቸውና መፍትሄ ልታመጣባቸው የምትችላቸውን እና ማሰብህ ለውጥ ሊያመጣባቸው የማይችሉ ጉዳዮችን ነጥለህ በፅሑፍ ማስፈር ነው፡፡ ለምሳሌ ስለ ዓለም ሙቀት መጨመር ስታስብ ብታድር ልታመጣ የምትችለው የመፍትሄ አቅጣ አለ? ስላቋረጥከው ትምህርት አስበህ ልታመጣ የምትችለው የመፍትሄ አቅጣጫ አለ? እንደዚህ እያደረክ ልታስብባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን (area of concern) አይተህ አስቀምጥ፡፡ ልታስብባቸወ የማይገቡ ጉዳዮችንም ለይና ለብቻ አስቀምጥ፡፡ ልታስብባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን አንድ በአንድ እያነሳህ በጥልቀት በማሰብ የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጥላቸው፡፡

ለምሳሌ ስለ ትምህርት ጉዳይ አንተን ወክዬ ባስብልህ የማስቀምጠው የመፍትሄ አቅጣጫ ትማርበት የነበረው ትምህርት ተቋም ሄደህ የዊዝ ድሮል ፎርም መሙላትና በቀጣዩ ዓመት ትምህርትህን እንደገና ካቋረጥክበት መቀጠል ይሆናል፡፡ ቀጣዩ ተግባርህ የመፍትሄ አቅጣጫዎን ወደ ተግባር ለመቀየር መንቀሳቀስ ነው፡፡ ያን እንዴት እንደምትከውን ከመጠቆሜ በፊት አንድ ነገር ላንሳና የመፍትሄ አቅጣጫ ልጠቁምህ፡፡ በአዕምሮአችን ውስጥ ያሉ ሃሳቦ ተያይዘው ስለሚቀመጡ (schema ይባላሉ) አንድ ጉዳይ አንስተህ ለማሰብ ስትሞክር ሌሎች ሃሳቦች አብረው ተከታትለው በመምጣት ትኩረትህን ሊቀይሩ ይችላሉ፡፡

በዚህ ጊዜም ማድረግ ያለብህ በመጀመሪያ ትኩረትን ወደ ምትፈልገው ሃሳብ ለማድረግ መጣር፣ ይህ ሲከብድህ ደግሞ ማሰቡን ትተህ የተለያዩ የመፍታቻ መንገዶች (relaxation techin-­iques) መጠቀም፡፡ ለምሳሌ ከተቀመጥክበት ተነስተህ እጅና እግርህን እጥፍ ዘርጋ በማድረግ ማንቀሳቀስ ወይም ከዚህ በፊት ያዝናኑህ የነበሩ ነገሮች ማከናወን (ለምሳሌ ወክ ማድረግ፣ ሻይ ቤት ሄደህ ሻይ ቡና ማለት፣ ፊልም ማየት፣ ወዘተ)፡፡ በዚህ አለ በዚያ ሌሎቹ ሃሳቦች መተው ጭንቀትህን ሲጨምሩብህ ትኩረትህን ወደ ሌላ አቅጣጫ መቀየሩ በጣም ጠቃሚ ተግባር ነው፡፡

አሁን ደግሞ አስበህ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጥክባቸውን ጉዳዮ እንዴት መከወን እንዳለብህ ልጠቁምህ፡፡ አጠቃላይ የጭንት ችግር ያለባቸው ሰዎች ችግራቸው እየተባባሰ የሚሄደው በአ

ዕምሮአቸው ብዙ ነገራትን ያስቡና ወደ ትግበራው ሲመጡ የቱን ትተው የቱን እንደሚተግብሩ ስለሚያስጨንቃቸው ነው፡፡ ለዚህ የመጀመሪያው መፍትሄ የሚያስቡባቸውን ጉዳዮ ብዛት መቀነስ ሲሆን ቀደም ብዬ የጠቀስኳቸውን ተግባራት በመከወን ጉዳዮን መቀነስ ትችላለህ፡፡ ያም ሆኖ ግን ለእነዚህ ጉዳዮ ያስቀመጥካቸው የመፍትሄ አቅጣጫዎች በራሳቸው ብዙ ይሆኑና ወደ ጭንቀት ሊመልሱህ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ መፍትሄው ተግባራቱን በዝርዝር በወረቀት በማስፈር ባላቸው ጥቅም (importance) እና አስቸኳይነት (urgency) መሰረት በቅደም ተከተል ማስቀመጥ (prioritization) አለብህ፡፡ ከዛም ሳምንታዊ እቅድ ታወጣና በጣም አስፈላጊና አስቸኳይ የሆኑትን በመጀመሪያው ሳምንታዊ እቅድህ ታስገባቸውና ለመተግበር ትሞክራለህ፡፡ በቀጣይ ሳምንት እቅድህ ደግሞ በመጀመሪያው ሳምንት ያላሳካቸሃቸውንና በቅደም ተከተልህ መሰረት ሌሎች ተግባራትን አካተህ ለመተግበር ትሞክራለህ፡፡

በዚህ ሁኔታ ስትቀጥል የሚያስጨንቁህን ነገራት በሙሉ መፍትሄ ወስደህባቸው ጭንቀትህን መቀነስ ትችላለህ፡፡ በስተመጨረሻ አንድ ነገር ልበልህና ፅሑፌን ላጠናቅቅ፡፡ አጠቃላይ የጭንቀት ችግር ለብዙ ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች ነገሮችን ማድረግ እችላለሁ የሚል እምነታቸው (self efficacy) ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ይመጣል፡፡ አንተ በዚህ ችግር ምን ያህል እንደቆየህ ባትነግረንም ይህ እምነትህ እንደቀነሰ መገመት እንችላለን፡፡ ነገሮችን ማድረግ እች

ላለሁ የሚል እምነትን ለመጨመር ሁለት መንገዶች አሉ፡፡ አንደኛው ሁሉንም ነገራት መከወንን በአንዴ በመጀመር በአንዴ እምነታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ (Boost) ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ እምነታችንን ቀስ በቀስ የማሳደግ ሁኔታ ነው፡፡ አንተ የፈለከውን መንገድ መምረጥ ትችላለህ ነገር ግን ሁለተኛው በአብዛኛው ውጤታማ ስለሆነ እሱን መጠቀምህ የተሻለ ነው ባይ ነኝ፡፡ በነገርህ ላይ አንድ ትንሽ የሆነች ተግባር እንኳ ማድረግ አለብኝ ብለህ ወስነህ ስትተገብራት ማድረግ እችላለሁ የሚለው ስሜትህ ሲለወጥ ታስተውላለህ፡፡

ለምሳሌ ሁሌ ወደ ስራ ስትሄድ ማስቲካ የመግዛት ልምድ ኖሮህ ነገ መግዛት የለብኝም ብለህ ወስነህ ሳትገዛ ስራ ከሄድክ ማድረግ እችላለሁ የሚለው እምነትህን አድጎ ሌሎችንም ነገራት አደርጋለሁ ብዬ ከተነሳሁ አደርገዋለሁ የሚል እምነት ይፈጥርብሃል፡፡ በመሆኑም ቀላል ከሚባል ተግባራት በመጀመር ቀስ በቀስ ሁሉንም ተግባራት የመከወን እምነትህን አጎልብት እያልኩ የዛሬ ፅሑፌን በዚህ አጠቃለልኩ፡፡

መልካም የለውጥ ጊዜ!

ጤናአዳም  መጽሔት  በቅርብ  

ቀን  በመላው  አሜሪካና  ካናዳ

Page 13: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 13

ድንገት.... ከገጽ 10 የዞረ

የሚመሳሰል ዘር ካለው ጋር ሳይሆን ከእሷ ዘር ጋር የማይመሳሰለውን ነው፡፡ አንድ ወንድም በተመሳሳይ መልኩ አንዲትን ሴት ውብ አድርጎ እንዲመለከታት የሚያደርገው ወይም እንዲሳብባት የሚያደርገው ከእሱ የሰውነት ዝርያ ማለትም (MHC Gene) ጋር የማይመሳሰለውን ነው፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ሴት/ወንድ ከእሱ ጋር የማይመሳሰል ዘር ከያዘ ሰው ጋር በድንገት ሳያስበው በፍቅር ሊወድቅ፤ ወደ ወሲብ ውሳኔ ውስጥ ሊያመራ፤ ወደ ጋብቻ ሊቀጥል አልያም ልጅ የመውለድ አጋጣሚንም ሊፈጥር ይችላል፡፡

በዚህ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከሆነ በአጋጣሚ ተመሳሳይ ዝርያ ካለው ወንድ ጋር የፀነሰች ሴት ሳታውቀው ፅንሱን ታስወርደዋለች፡፡ ሰውነቷ ፅንሱን አይቀበለውም፡፡ ምክንያቱም ተመሳሳይ ዘር ካለው ወንድ የተፀነሰ በመሆኑ፡፡ እንዲሁም በሰው ሰራሽ የአረባብ ዘዴ የተፈጠሩ ሽሎችም ከተመሳሳይ ‹‹MHC gene›› ካላቸው የወንድና የሴት ዝርያ የተፀነሱ ከሆኑ ወደ ፅንስነት ማደግ አይችሉም ወይም በራሳቸው ይመክናሉ፡፡ ይህንንም ሆን ብለው ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው ስፐርምና ዕንቁላሎች እንዲዋኻዱ ተደርገው ውጤቱን በተመለከቱ ተመራማሪዎች ታይቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር የተለያዩ ሴቶች የወንዶችን ቲሸርት ተሰጥቷቸው እንዲያሸቱና የየትኛው ቲሸርት ባለቤት የሆነ ወንድ የበለጠ እንደሚማርካቸው በተደረገው ጥናትም ሁሉም ማለት ይቻላል የሚማረኩበት ወንድ ከእነሱ የተለየ ዝርያ ያለውን ነው፡፡

እንደተመራማሪዎቹ ገለፃም ሴቶችም ሆኑ ወንዶች የተቃራኒ ፆታ ሰዎ ዝርያ ከእነሱ ጋር የተለየ መሆኑን የሚወስኑት ሳያውቁት

ቢሆንም ይህን መሰል ከእውቅናቸው ውጭ የሆነ ውሳኔ እንዲፈጠር የሚያደርገው የአፍንጫቸው ልዩ የዝርያ ማጣሪያ ጣቢያ ሲሆን ውሳኔውን ሳያውቁት የሚያስተላልፈውም ደግሞ ውስጠኛው አዕምሯቸው ነው፡፡ ሰውነታችን ይህን የሚያደርገው ይላሉ ሳይንቲስቶች የተለያየ ዝርያ ያላቸው ተቃራኒ ፆታዎች የሚፀንሷቸው ልጆች የሰውነት በሽ መከላከያ አቅማቸው ከፍተኛ በመሆኑ ሳቢያ ረጅም ዕድሜ ስለሚኖሩ ሲሆን ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው ወላጆች ግን የሚወልዱት ልጅ የሚኖረው የበሽታ መከላከያ አቅም ደካማ ስለሚሆን ዕድሜው ስለሚያጥር ነው ይላሉ፡፡

መጥፎ ፍቅር የሚፈጥሩ አጋጣሚዎችበአጠቃላይ ተፈጥሯዊ በሆነ የስሜት ምላሻችሁ የምትወስኑ

ትን ውሳኔ ተቀበሉት፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው የሚከሰቱ ሁኔታዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ የእርግዝና መቆጣጠሪያ እየተጠቀሙ ያሉ ሴቶች የወንድ ምርጫቸው ከራሳቸው MHC ጋር ተመሳሳይነት ያለውን ነው፡፡ ስለዚህ መድሃኒት እየጠተቀሙ ያሉ ሴቶች በዘረመሉ ረገድ የማይስማማቸውን ወንዶች የመምረጥ አደጋ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ስለዚህ የእርግዝና መከላከያ መድሃኒት ከመውሰዳቸው በፊት የጠረን መረጃ ቢጠቀሙ ከሁሉ የበለጠ ተመራጭነት አለው፡፡

ሁለተኛ ምሳሌ ደግሞ ከሴቶች የወር አበባ ወቅት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ የመማረክ ወይም ያለመማረክ ሁኔታ ከወር አበባ ዑደት ጋር ሊለዋወጥ ይችላል ይላሉ ባለሙያዎች፡፡ ወንዶች የሴቶች ሽታ ማራኪ የሚሆንላቸው የማህፀን እንቁላላቸው ዝግጁ በሆነበት ወቅት ነው፡፡ የፍቅር ስሜት ውስጥ የሚገቡትም በዚህ ወቅት ነው ይባላል፡፡

በተጨማሪም ወሲብ መፈፀም ጓደኛችሁን የምትመርጡበ

ት መንገድን ሊያወሳስበው ይችላል፡፡ ወሲብ ከፈፀምን በኋላ አዕምሮአችን ኦክሲቶሲን የተባለ ሆርሞን ያመነጫል፡፡ ይህም ሆርሞን ሞ ያለ የጓደኝነትን ስሜት የሚፈጥር ፍቅር እንዲኖረን እና ልጅ የማሳደግ ጥሩ መንፈስ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ከተቃራኒ ፆታ ጋር፡፡

ይህ ማለት እንግዲህ በጥድፊያ የሚፈፀም ወሲብ ሙሉ በሙሉ ለእናንተ ከማሆን ሰው ጋር በፍቅር እንድትወድቁ ከፍተኛ ግፊት ውስጥ ሊያስገባችሁ ይችላል፡፡ ይህም ማለት ተፈጥሯዊውን ‹‹MHC›› ዘራችሁ እንድትወስኑ ያሳስታችኋል፡፡

ማህሙድ.... ከገጽ 15 የዞረለማይክሮሊንግ ኮሌጅ ለማዘዋወር በቅቷል :: ማህሙድ ሙ

ዚቃ ቤትንም ያየን እንደሆን ያው እንደድሮው እንዳለው ነው :: ቀለሙ እንኳ አልተቀየረም :: ከዛሬ 20 አመት በፊት የነበሩት ካሴቶች እንደተደረደሩ አሉ :: በትዳር በኩልም ያው ነው ::

ኑሮውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ማህሙድ በአሁኑ ወቅት እንደማናጀርም እንደሚስትም ሆና የምታግዘውን ፈጣሪ ሰጥቶታል። በሉ እንግዲህ ይህን ታላቅ ድምፃዊ ፌብሩዋሪ 14 በሚኒሶታ ስለሚመጣ በቫለንታይን ደይ ከምንወደው ሰው ጋር ኮንሰርቱን በመታደም ለዚህ ታላቅ ድምፃዊ ፍቅራችንን እንድናሳይ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ጉበትዎን.... ከገጽ 16 የዞረ አካላት የመላክ ስራን ስለሚሰራ፣ ቅባት የተጫናቸው ምግቦ

ች ሲበዙ ጉበትም ላይ ጫና ይበዛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ጉበትን በስብ የመሸፈን ጉዳትም የቅባት ነክ ምግቦች ተጨማሪ ችግር ሆ

ኖ በባለሙያዎቹ ይነሳል፡፡ ይህም የጉበትን ጤና የሚጎዳ በመሆኑ ጥንቃቄን ይሻል፡፡ ቅባታማና ከፍተኛ ካሎሪ ያላቸውን ምግቦች ከመውሰድ መታቀብ እንዲሁም ምግብን የተመጣጠነ ማድረግ አስፈላጊ የሚባሉ ናቸው፡፡

7. የስኳር ምጣኔየደም ውስጥ ስኳር መጠንን በሚገባ ለመቆጣጠር ጥረት ማ

ድረግ ከተቻለ፣ የስኳር ህሙማን በተለይም ለቅባታማ ጉበት ህመም የመጋለጥ ዕድላቸው ዝቅተኛ ይሆናልና ለስኳር ህመም የሚደረግን ክትትልና አስፈላጊ ህክምናዎች እንዲሁም ጥንቃቄዎች መተግበር ያስፈልጋል፡፡

8. የግፊት ምጣኔን ማስተካከልየቅባታማ ጉበት አንዱ መንስኤ ከፍተኛ ደም ግፊት ነውና

ለህመሙ የሚደረጉ ህክምናዎች የመከላከያ ስልቶችን ይተግብሩ፡፡

9. አጠቃላይ የጤና ምርመራን ያድርጉአጠቃላይ የጤና ምርመራን ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ማድ

ረግ፣ በርካታ የጤና ችግሮችን ቀድሞ ለማወቅና አስፈላጊ የህክምና ክትትል ለማድረግም ወሳኝ ነው፡፡ ይሁንና ይህ ልምድ በብዙዎቻችን ዘንድ የዳበረ ባለመሆኑ፣ ጉበትን ጨምሮ በርካታ ቁልፍ አካላቶቻችን ጉዳታቸው ከከፋ በኋላ ህክምና ስንጀምር ችግሩን በጊዜ የመቅረፋችን አጋጣሚ በእጅጉ አናሳ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ጉበትን ጨምሮ የበርካታ አካላቶቻችንን ደህንነት ለማወቅ፣ በየጊዜው የሚደረግ ምርመራ የሚመከረው ይህን መሰል ጉዳቶችን ለማስቀረት ነው፡፡ የጉበትን ጤና ለማወቅ የሚረዱ በርካታ የደም ምርመራ አይነቶች ያሉ በመሆኑ፣ እነዚህ ምርመራዎች ከአጠቃላዩ ምርመራ ጋር ተዋህደው እንዲሰሩ ባለሙያዎቹን መጠየቅዎን መዘንጋት የለብዎትም፡፡ ለጉበት ጤናዎ ወሳኝ ነውና፡፡

Page 14: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 14

Page 15: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

ኪነጥበብ የጤና  ሞግዚት ስፖርት ወንጀል/ፍቅር

ማህሙድ አህመድ... ከገጽ 1 የዞረበወቅቱ እግር መርቶዎት ወደ ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ብቅ

ሊሉ ከቻሉ የሀገር ፍቅር መዝናኛ ክበብ አልያም ከረምቡላ ቤቱ ውስጥ ማህሙድ አህመድን አያጡትም :: ለምን ይሆን ? መሄጃ አጥቶ አይደለም :: ያደገበት ቤት በመሆኑ ሀገር ፍቅርን ለአንድ ደቂቃ እንኳን አያምናትም :: ብዙ ጊዜውን ከከረምቡላ ጨዋታ ውጭ ከጥንት ጓደኞቹ ጋር በመጨዋወት ያሳልፋል ::

‘’ቤተሰቦቼ ደሀ ነበሩ :: የሚያኖራቸው ገቢ ጥቂት ስለሆነና እኔንም ለመርዳት ስለማይችሉ ጎዳና የወጣሁት ገና ሕጻን እያለሁ ነበር :: ቀን ቀን ሊስትሮ እየሰራሁ ራዲዮ አዳምጥ ነበር :: በዛ ራዲዮን የጥላሁን ገሰሰን እና የሌሎችን ሙዚቃዎችን ስሰማ በጣም እመሰጥ ነበር :: በራድዮ የሰማሁዋቸውን ሙዚቃዎች ጫማ እየጠረግኩም አቀነቅናቸው ነበር ::’’ የሚለው የትዝታው ንጉሥ ወደ ሙዚቃው አለም እንዴት እንደተሰማራ ያጫውተናል :: ይህ የሆነው በ 1953 ነው :: የሙዚቃ ክህሎቱ እያደገ ሲመጣም ቀን ቀን የጫማውን ማታ ማታ የናይት ክለብ ሥራውን ጀመረ :: በአሪዞንያ ክለብ መዝፈን ሲጀምር ማህሙድ የሚከፈለው ክፍያ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም ቀን ያወጣለት ይህ ሥራው ነበር ::

ከድህነት መነሳቱን የማይደብቀው ማህሙድ እንደዛሬ ዘመን ዘፋኞች አይደለም :: የዛሬ ዘመን ዘፋኞች በብዛት የመጡበትን ማህበረሰብ የዘነጉ ቢሆኑም እሱ ግን ዛሬ በሀብት ተንደላቆ እ

የኖረ እንኳ ድህነቱን ስለማይረሳ ብቻ እኔ የማውቃቸው 17 አረጋውያንን በወር በወር እየቆረጠ ያኖራል :: እነዚህ ረጂ አልባ አረጋውያን የማህሙድ ተጧሪዎች ሲሆኑ ክፉ እንዳይነካው ሁልጊዜ ይጸልያሉ ::

ከአሪዞንያ ክለብ እየሰራ ለዚህ ያበቁት ካፒቴን ግርማ ሀድጉ በሙያው እጀግ ያበረታቱን እንደነበረና ወደ ሹፌር ክለብም እንዲዘዋወር በሩን እንደከፈቱለት የሚናገረው ማህሙድ ካፒቴን ግርማን ሁልጊዜ ያመሰግናል :: ‘’ቤተሰቦቼ ሙያዬን ባልደገፉበት ወቅት አጠገቤ የነበሩት ብቸኛው ሰው እሳቸው ናቸው ‘’ ያለኝ ማህሙድ በ 1963 አሁም ዘመኑ እንደ አወሮፓውያን አቆጣጠር ነው የመጀመሪያውን ነጠላ የሙዚቃ ሥራውን ለሕዝብ አደረሰ :: ዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ሕዝብ ልብ ውስጥ የብሄራዊ መዝሙር ያህል የማይረሳው

‘’ካንቺ በቀር ሌላ ብሞት አልመኝም : ግን እስካሁን ድረስ አላወቅሽልኝም ‘’ የሚለው ሙዚቃው የመጀመሪያው እና አይኑን የገለጠችለት

ሥራው ናት :: ይህች ሙዚቃ በሸክላ እንዲታተም አምሀ ሪከርድስ እና ከሊፋ ሪከርስ ትልቁን ሚና የተጫወቱለት ሲሆን ማህሙድንም ተፈላጊነቱን ጨምራለታለች ::

አንጋፋው ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ (ነብሱን ይማረውና ) የዛሬይቱ ኢትዮጵያ በተባለው ጋዜጣ ላይ ጥያቄና መልስ የሚያስተናግድባት ‘’አንድ ለመንገድ ‘’ የምትል አምድ ነበረችው :: በዚህ አም

ድ ላይ አንዱ (ዷ ) ጠያቂ ‘’ከሀገራችን ዘፋኞች ውስጥ አፈ ሰፊ ዘፋኝ ማን ነው ?’’ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ‘’ከማህሙድ አህመድ ጋር እንዳታጣይኝ ‘’ የሚል መልስ በመስጠቱ ከጋዜጠኛው ጋር ማህሙድ እንደ አይጥና ድመት ይተያይ ነበር የሚል ወሬ ይሰራጭ እንጂ ወሬው ከወሬ አያልፍም :: ጳውሎስ ለመዝናናት የመለሰውን መልስ ማህሙድም ተዝናንቶበት አልፎታል ::

ጤና ይስጥልኝ !!... ያቆምኩት ስለማህሙድ አህመድ የመጀመሪያ ሥራ ካንቺ በቀር ሌላ ብሞት አልመኝም አውርቼ ነው :: እስኪ ልተብትብ የዛሬውን ::

‘’ሁልጊዜ ልቤ እንዳለቀሰ ነው ‘’ የሚለው ማህሙድ አህመድ በሚኖረው ኑሮ ደስተኛ እንዳለሆነ ያስቀምጣል :: ለዚህም ምክንያቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ያልተመጣጠነ የሀብታም እና የደሀ ኑሮ ልዩነትን በመመልከት ነው ::

‘’የመጀመሪያ ሸክላዬን ካወጣሁ በኍላ በራዲዮ ሲለቀቅ አስተያየት የጠየቅኩት ከጥላሁን ገሠሠ ነው :: ጥላሁን የሙያ አባቴም አስተማሪዬም ነው :: ከምንም በላይ ሁሉም ነገሬ ነው :: ጥላሁን ገና ብዙ እንደሚቀረኝና የአሁኑ ስራዬ ግን አጥጋቢ እንደሆነ መከረኝ :: ጥሩ ነገር ተሰማኝ :: ዘፈኖቼ በተለይም ካንቺ በቀር ሌላ በሕዝብ እየተወደደች ስትመጣ አይቤክ ባንዶች ቀጠሩኝ እና ከእነርሱ ጋር እሰራ ጀመር :: የእነ ካሳ ተሰማን እና የጥላሁን ዘፈኖችን እያስመስልክ እዘፍን ነበር ::

‘’የአባይ ውሀ ሞልቶ ይፈሳል ቦይ ለቦይ

አንቺ እንደምን አለሽ እኔ እንዳለሁ አለሁ ‘’ የምትለው ብርቱካኔ የተሰኘችው ዘፈን የተወሰድችውም ከዛው ነው ::’’ ይለናል ማህሙድ ::

ከተለያዩ ባንዶች ጋር የሰራው ማህሙድ አህመድ በሥራው ስኬታማ ከመሆኑ ሌላ በፈረንሳይ እና በሌሎችም ሀገራት ሲዲዎቹ በብዛት በፈረንጆች ጭምር ይወደዱለታል :: በክራር የዘፈናቸው ዘፈኖቹ በተለይም የትዝታው ንጉሥ እንዲሰኝ እንዳደረጉት የሚያምነው ማህሙድ አሁንም ገና ወጣት እንደሆነና ራሱን ከዘመኑ ጋር እያስኬደ መዝፈን እንደሚፈልግ አስታውቆአል ::

‘’የአሁኑ ዘመን ዘፋኞች በጣም ደስ ይላሉ :: በየእለቱ አዲስ ነገሮችን እየፈጠሩ ይመጣሉ :: ስራዎቻቸውን አደንቃለሁ ‘’ የሚለው ማህሙድ በአንድ ወቅት በፈርጥ መጽሄት ‘’ቴዲ አፍሮ እና እጅጋየሁ ሽባባው ጂጂ የዘመኑ የሙዚቃ አብዮተኞች ናቸው ? ወይ ‘’ በሚል ለቀረበለት ጥያቄ ሳያንገራግር ‘’አዎን ‘’ ብሏል :: ‘’ቴዲ አፍሮ መሽለም አለበት ‘’ የሚለው ማህሙድ አድናቂው እንደሆነና ከጂጂ ጋር በመሆን የሙዚቃችንን ደረጃ ወደ አንድ ምእራፍ ለውጠውታል ሲል ይመስክራል ::

በዘፈኑ ዘርፍ እጅግ የተሳካለት ማህሙድ በግል ሕይወቱ እና በንግዱ ዘርፍ የተዋጣለት አልሆነም :: በጉለሌ አካባቢ ‘’ካራራ ሎጅ ‘’ የሚል ሆቴል ከፍቶ የነበረ ሲሆን (ጉራጌ እንኳ የንግድን ነገር ያውቅበት ነበር ) ማህሙድ ግን ከሰረ :: ያን የመሰለ ሆቴል ዘግቶ ዛሬ ቦታውን (ማህሙድ... እባክዎ ወደ ገጽ 13 የዞረ)

በኢትዮጵያ  መንግስት  በጥብቅ  የሚፈለጉ  3  አርቲስቶችከሮቤል ሔኖክእንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመ

ግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።

ዛሬ ዛሬ ደግሞ ላለፉት 23 ዓመታት ሃሳባቸውን በነጻነት ከሚገልጹት ጋዜጠኞች ባልተናነሰ በመንግስት ጥርስ እየተነከሰባቸው የሚገኙት የጥበብ ባለሙያዎች እየሆኑ ነው።

እንደሚታወቀው በስደት ዓለም ከ150 በላይ ጋዜጠኞች እንዳሉ ሁሉ ዛሬ ቁጥራቸው በዛ ያሉ አርቲስቶችም በስደት ይህንን ስርዓት በመሸሽ በስደት ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ መንግስት እንደታላቁ እስክንድር ነጋ አስሮ ለማሰቃየት ከሚፈልጋቸው ታላላቅ አርቲስቶች መካከል 3ቱ ዋነኞቹ ሲሆኑ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ገና መንግስት እያጎበጎበባቸው በመሆኑ የ3ቱን ገድል አሳይቻችሁ የሁለቱን እንስት አርቲስቶችን ማንነት አስተዋውቃችኋለሁ።

1ኛ. ታማኝ በየነብዙዎች እንደስሙ ነው ይሉታል። አክቲቪስት ሆኗል ከአር

ቲስትነቱ በተጨማሪ። አላሙዲ ካደረገለት በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገልኝ ይበልጣል በሚል ዛሬም ድረስ የያዘውን አቋም ባለማዋዠቅ ይህን ተራ መንግስት ማንነቱን በማጋለጥ ላይ ይገኛል። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ “የሕዝብ ልጅ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ታማኝ በየነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አንባገነን ስርዓት ከዚህ አርቲስት ጎን ፎቶ የተነሳ፣ የታየ፣ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው የሚል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል። ታማኝ በየነ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ክብርን ያገኘ በመሆኑና ክብሩንም ለገንዘብም ይሁን ለታይታ ያልቀየረ በመሆኑ ብዙዎች የሚያከብሩት ሲሆን የሕወሓት መንግስት ይህን ታላቅ አርቲስት በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የማፈነቅለው ድንጋይ የለም።

ታማኝ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆን በግሉ በሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በነፃነት እያጋለጠ ዘረኛውን ስርዓት እርቃኑን እያስቀረው ሲሆን በተለይም መንግስትን የሚያጋልጠው ራሳቸው የመንግስት ባለስልጣናት በሚሰጡት እርስ በእርሱ በሚጣረስ በቪድዮ የታጀበ ቃለምልል መሆኑ በብዙሃን ዘንድ ተወዳጅነትን በሥርዓቱ ዘንድ ደግሞ ለመታሰር ከሚፈለጉ 3ቱ አርቲስቶች መካከል አንዱ ሆኗል።

2ኛ. ፋሲል ደመወዝአርቲስት ፋሲል ደመወዝን የማውቀው አዲስ አበባ ስድስት

ኪሎ የሚባል ሰፈር በተለምዶው ሸለቆ የሚባል አካባቢ ነው። በሸለቆ አካባቢ ሲራመዱ ፋሲል ሙዚቃ በመለማመድ ላይ እያለ የሚያሰማውን እንጉርጉሮ ማድመጥ የተለመደ ነው። ይህ ታላቅ ድምፃዊ የጎንደር መሬት ለሱዳን ተላልፎ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መን

ግስት በተሰጠበት ወቅት “አረሱት” የሚል ዘፈን ካወጣ በኋላ በስር ዓቱ ሰዎች ወፌ ላላ ተገርፏል። ፋሲል ታዝሎ እስኪሄድ ድረስ በዚህ ፋሽስት መንግስት የተገረፈ ከመሆኑም በላይ የዳነው በህክምና ብቻ ሳይሆን በጸበልም ጭምር ነው።

ፋሲል ደመወዝ አሁን ሰሜን አሜሪካ ከመጣ በኋላ ‘እንቆል

ሽ” በሚለው አልበሙ ‘ያውላችሁ’ የሚል ዘፈን ያወጣ ሲሆን በዚህም ዘፈኑ ሃገሪቱን ካለምንም ተቀናቃኝ በአፓርታይድ ስርዓት ለሚመሩት ሰዎች “ሰው አስተዳደራችሁን እና በደላችሁን ጥሎ ጥሏችሁ እየሄደ ነው” ሲል ነግሯቸዋል። ፋሲል ደሞዝ በአሁኑ ሰዓት በሕወሓት አስተዳደር ከሚፈለጉ ዋና አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው።

3ኛ. ክበበው ገዳኮሜዲያን ነው። በጣም ይወደዳል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ

ም ይቀልዳል -­ ክበበው ገዳ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ

እሱን የሚያል ኮሜዲያን አለ ብሎ ለመናገርም ይከብዳል ይላሉ በሙያው ውስጥ ያሉ ሰዎች እና ባለሙያዎች። ክበበው ገዳ በማንኛውም ማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ በመቀልድ ይታውቃል። ይህ ኮሜዲያን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የተለያዩ የኮሜዲ ሥራዎችን አቅርቦ ተመልሷል። የዘንድሮው ግን ለጉድ ነው። የ

ሥርዓቱን ሰዎች በእጅጉ እስቆትቷል።ባለፈው ኦገስት 2014 ላይ ክበበው ገዳ በዳላስ የኢትዮጵያ ኮ

ሚዩኒቲ በዓል አስተናጋጅነት ትልቅ በዓል ላይ ተገኝቶ ነበር። ይህ ኮሜዲያን አሁን ባለው የኢትዮጵያውያን ነባራዊ ሁኔታ ዙሪያ በርካታ ቀልዶችን አቀረበ። በተለይም አሁን ባለው ስርዓት ዙሪያ ልክ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ኮሜዲያን በመሪዎቻቸው እንደሚቀልዱት ሁሉ ቀለደ። የሕዝቡን ብሶትም በቀልዱ አሰማ። ስለሟቹ ጠ/ሚ/ር፣ ስለሟቹ ፓትሪያሪክ፣ አሁን ስላለው የመንግስት አካሄድ በቀልድ አዋዝቶ አቀረበ። ለዚህ ኮሜዲያን ከሕዝብ የቀረበለት አድናቆትን ቢሆንም ከ ስርዓቱ ግን የቀረበለት ማስፈራሪያና ዛቻ

ነው። እንደውም ‘ሃገርህ ትገባታለህ” የሚሉ ዛቻዎች ከስርዓቱ ደርሶታል። ክበበው ሙያውን ተጠቅሞ ባስተላለፈው መልዕክት ከኢትዮጵያ መንግስት ተላላኪዎች የሚደርስበት ማስፈራሪያ ሃገርህ ብትገባ አለቀልህ የሚል ብቻ ሳይሆን አሁን ባለበት ሃገር ሳይቀር እንደማይለቁት የሚገልጹ ናቸው።

ማነህ ባለሳምንት?ሜሮን ጌትነትና አስቴር በዳኔ።ሁለቱም ሴት አርቲስቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደ

ርሰውን የሴት ልጅ ተጽ ዕኖ ተቋቁመው አደባባይ የወጡ ሴቶች። ሁለቱም ያመኑመትን ይናገራሉ። ሁለቱም በተለይ ሃገር ቤት ካሉ አርርቲስቶች የሚለዩበት ነገር አላቸው። እነዚህ አርቲስቶች ስለ እውነት እውነትን ስለመሰከሩ ዛሬ በ ሥ ር ዓቱ ሰዎች እየተነከሰባቸው ያለውን ነገር አብረን እያየነው ነው።

Page 16: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 16

ጉበትዎን  ጤናማ  የሚያደርጉ  9  ወሳኝ  ነጥቦች

የሥጋ  ነገር!!!  ይጠቅመናል?  ወይስ  ይጎዳናል?ከኢሳያስ ከበደየሰው ልጅ ስጋ መብላት የጀመረው መቼ ነው? አዳምና ሔዋ

ን በገነት ሳሉ ምን ነበር የሚመገቡት? ሲወርድ ሲዋረድ እኛ ጋር የደረሰው የእነርሱ ዘር አመጋገቡ እንዴት ነው? የአመጋገብ ለወጡ ወደ ስጋ ማድላቱ ምን አተረፈለት? ምንስ አጎደለበት? እነዚህንና መሰል ጥያቄዎችን እያነሱ ምላሽ መፈለግ ወደ እውነታው ያመራናል፡፡ የዚህ ፅሑፍ የትኩረት አቅጣጫም ይኸው ነው፡፡

የሥጋ አይነቶችከመልካቸው ተነስተን ቀይ እና ነጭ ብለን መክፈል እንችላ

ለን፡፡ ቀይ ስጋ የሚባሉት የበሬ፣ የበግ፣ የፍየል እና የዓሳማ ሲሆኑ ነጭ ስጋ የሚባሉት ከዓሳ እና ዶሮ የሚገኙት ናቸው፡፡ እኛ ግን በተለምዶ ጮማ ስጋውን ነጭ፣ የሚታይ ጮማ የሌለውን ቀይ ስጋ እንለዋለን፡፡

በሌላ አከፋፈል በፋብሪካ ተቀነባብረውና ታሽገው የሚሸጡ አሉ፤ በቀጥታ ከቄራ የሚመጡ አሉ፡፡ ሌላም እንጨምር፣ ሳር እየጋጡ ካደጉ እና ከሳር ውጭ የሆነን ነገር እየተቀለቡ ከደለቡ ከብቶች የሚገኙ የሥጋ አይነቶች አሉ፡፡

ከጤና አኳያ ነጭ ከቀይ ሥጋ በእጅጉ ይመረጣል፡፡ ከቄራ በትኩሱ የተገኘ ሥጋ በኬሚካል ታሽቶና ታሽጎ ከሚሸጠው ሥጋ ይሻላል፡፡ ሣር እየጋጠ ካደገ ከብት የሚገኝ ሥጋ ፉርሽካ (በሰው ሰራሽ ሆርሞንና ፀረ ተህዋስያን ታጅቦ) ሲቀለብ ከነበረ ከብት ከሚገኝ ሥጋ ይሻላል፡፡ በምጣኔ ሀብት ባደጉ ሀገራት ሁሉም አይነት የሥጋ አይነቶች በስም ተለይተውና ደረጃ ወጥቶላቸው ነው ገበያ የሚወጡት፡፡ ሸማቹም ለጤና የሥጋ አይነቶች ከፍ ያለ ክፍያ ይፈፅማል፡፡

ሥጋ የፕሮቲን እና የሌሎች ንጥረ ነገሮች ምንጭ ነው

የተሟላ የአሚኖ አሲዶችን ስብጥር በመያዙ ግሩም የፕሮቲን መገኛ ነው፡፡ ዕድሜያቸው ከ19-­50 የሆኑ ወንዶች በቀን 55 ግራ፣ በዚህ ዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ደግሞ በቀን 36 ግራም ፕሮቲን ጤናቸው ተጠብቆ ለመሰንበት ያስፈልጋቸዋል፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ትልቁ ቁም ነገር የፕሮቲን ምንጭ ስጋ ብቻ አለመሆ

ኑን ነው፡፡ የለውዝ እና የጥራጥሬ ዘሮች፣ ወተትና ተዋፅኦዎቹ እንዲሁም እንቁላል ሁነኛ የፕሮቲን አቅራቢዎች ናቸው፡፡

ከዚህም አልፎ ስጋ የብረትና የዚንክ ማዕድናት፣ ቫይታሚን ቢ 12ን በመለገስ ይታወቃል፡፡

ቀይ ስጋ እና የጤና መዘዞቹ፡-­ከከብቶች የሚገኘው ሥጋ ማዘውተር ለልብና ደም ስሮች በ

ሽታዎች፣ ለነቀርሳ፣ እንዲሁም ለሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ እንደሚያጋልጥ በተለያዩ ሀገራት፣ ጊዜያት እና አጥኚዎች የተደረጉ ጥናቶች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው፡፡

ነቀርሳ (ካንሰር)የከብቶች ሥጋን ማዘውተር ለደንዳኔ፣ ለፊንጢጣ፣ ለጡት፣

እና ለፕሮስቴት ነቀርሳዎች ያጋልጣል፡፡ ቀይ ስጋዎችንና በጭስ የታጠኑ የስጋ ዘሮችን ያዘወተሩ ሰዎች በትልቁ አንጀት (ደንዳኔ) ነቀርሳ የመጠቃት ዕድላቸው ከ20-­30 በመቶ ጨምሮ ተገኝቷል፡፡ በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ዘሮች ለምሳሌ Mortedella, Salami,

Hotdogs, Sausage, Bologna, Bacon... ሲዘወተሩ ደግሞ የደንዳኔ ነቀርሳ ተጋላችነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ በሳንባ ካንሰር የመ

ያዝ ዕድላቸው በ16 በመቶ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት በዴንማርክ በተደረገ ተመሳሳይ ጥናት የዓሳማ ስጋ ማዘውተር በፊንጢጣ ነቀርሳ የመጠቃት አደጋን ጨምሮ ተገኝቷል፡፡

ከሀገርቫርድ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ቀይ ስጋን የሙጥኝ ያሉ ወጣት ሴቶች በከፍተኛ ሁኔታ ለጡት ነቀርሳ ሲዳረጉ በዚሁ ልምድ ያሉ ወንዶች ደግሞ ፈጥኖ የሚሰራጨው አይነት የፕሮስቴት ነቀርሳ ሰለባ ሆነዋል፡፡ አስገራሚው ግኝት ከቀይ ስጋ ምትክ በሳምንት ከሶስት ጊዜ በላይ ወንዶቹ ዓሳ ሲመገቡ በዚህ አደገኛ ነቀርሳ የመለከፍ ዕድላቸው በ50 በመቶ መቀነሱ ነው፡፡

በጋለ ብረት ላይም ይሁን በሚነድ እሳት ላይ በከፍተኛ ሙቀት ማንኛውም አይነት ስጋ ሲጠበስ ነቀርሳ በማምጣት የሚታወቁት Heterocyclic amines ይፈጠራሉ፡፡ ከዚህ አኳያ ዝና እያተረፈ የመጣውን የሸክላ ጥብስ እና የግሪል ጥብስ አደገኛነት ልብ ይሏል፡፡ በተለይ በእሳት ብዛት የጠቆረው የስጋ ክፍል የአደገኛ ንጥረ ነገሮቹ የዕዝ ጣቢያ ነው፡፡

የልብ እና የደም ስር በሽታዎችየከብት ስጋ እንኳን ሰብቶ ጮማው ተነስቶለትም ቢሆን በ

ጎጂ ስቦች (ሃይድሮጅን ጠገብ) የተመላ ነው፡፡ በመሆኑም ለኮሌስትሮል ሰውነተ ውስጥ መመረትና በደም ስሮች የውስጥ ግድግዳ ዙሪያ መለጠፍ መንስኤ እንደሚሆን ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፡፡ በቅርቡ በተደረገ የጥናቶች ጥናት ቀይ ስጋ እና በፋብሪካ የተቀነባበረ ስጋ አዘውታሪዎች ለድንገተኛ የአንጎል ዝለት ይበልጥ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

ሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታበፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ውጤቶችን የሚያዘወትሩ ሰዎች

በሁለተኛው አይነት የስኳር በሽታ የመያዝ አዝማሚያቸው ከማያዘወትሩት አንፃር ሲመዘን ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ጥሬ ስጋና መዘዞቹየቁርጥ ሥጋ ባለበት አጀቡና ትርምሱ ጉድ ያስብላል፡፡ ሰው

ሳይደማመጥ በየበኩሉ ያወራል፡፡ የድምፅ ብክለቱ ጣራ ሊነካ ይደርሳል፡፡ ደግነቱ ጮማ ያለበት የሥጋ ቁርጥ ከቢላዋ ጋር ሲቀርብ የሚያወራም የሚያደምጥም አለመኖሩ ነው፡፡ እንደዚያ በጋለ ስሜት ሲጨዋወቱ (የሥጋ... እባክዎን ወደ ገጽ 20 የዞረ)

ከቅድስት አባተ

ጉበት በሰውነታችን ትላልቅ ከሚባሉት አካላት በሁለተኛነት የሚመደብ ሲሆን፣ እጅግ ወሳኝ የሆኑ የመርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት የማስወገድ፣ ቫይታሚን እና አስፈላጊ ቅባቶችን የማዘጋጀት እንዲሁም ለክፉ ቀን የምንጠቀምበትን የኃይል ምንጭ አጠራቅሞ የማስቀመጥም ጥቅሞች አሉት፡፡ ከሌሎች አካላት አንጻር ጉበት ቻይ ነው ሊባል ይችላል፡፡

የተለያዩ ጉዳቶች ቢገጥሙት፣ ራሱን የሚጠግንበት ተፈጥሯዊ ሂደቶች ያሉት በመሆኑ በርካቶች ጥንቃቄን ሲያጎድሉበትና ለከፋ ጉዳት ሲጋለጡም ይስተዋላል፡፡ ለዚህም ይመስላል በርካታ ባለሙያዎች ጉበትን ከክፉ አደጋ ሊጠብቁ የሚችሉ ጤናማ የኑሮ ዘዬዎችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸው ውስጥ አካትተው እየመከሩ የሚገኙት፡፡ በሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንዲሁም በማዮክሊኒክ ባለሙያዎች ከቀረቡት የጥንቃቄ ስትራቴጂዎች መካከል ለዛሬው በጣም ጥቂቶቹን እናነሳለን፡፡

1. የሰውነት ክብደትዎን ይቆጣጠሩከልክ ያለፈ ክብደት ለተለያዩ የጤና ችግሮች ስለማጋለጡ

በደንብ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ ችግሮች መካከል የጉበት ጉዳት አንዱ መሆኑን የሚያስታውሱ ብዙ አይደሉም፡፡ አዎን! ከፍተኛ ቅባት በሰውነት ሲከማች ጉበትም በቅባት የመሸፈን እና ስራውም የመስተጓጎል አደጋ ይገጥመዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከአልኮል ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ የጉበት ፀር እየሆነ ያለው ይህ ከፍተኛ ክብደት ሲሆን በርካታ የቴና ባለሙያዎች ጉዳዩ አሳስቧቸው በተለያዩ መንገዶች ትምህርት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡በተለይም የቅባታማ ጉበት ክስተትን በሚገባ ለመቀነስ ቢያንስ የሰውነት ክብደትን በ10 በመቶ መቀነስና አዘውትሮ እንቅስቃሴ ማድረግ ጥሩ መላ ነው፡፡2. ፍራፍሬና አትክልቶችን ወዳጅ ያድርጉ

ለጉበት ሥራ መቀላጠፍ ወሳኝ የሆኑ የማዕድን ቫይታሚን ግብአቶችን በሚቻልዎ መጠን በምግብም እንዲያካትቱ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡ ለምሳሌ በካሮት ውስጥ የሚገኘው ካሮቲን፣ በወተት ውስጥ ያለው ካልሲየምና እንደ ሙዝ ባሉት ፍራፍሬዎች ው

ስጥ የሚገኘው ማግኒዚየም፣ በብርቱካን ውስጥ የሚገኘው ቫይታሚን ሲ እና መሰል አትክልትና ፍራፍሬዎች ለጉበት ጤና ጥሩ ናቸውና በሚቻልዎ መጠን ቢያዘወትሯቸው መልካም ነው፡፡ እንዲሁም በተለይ የቫይታሚን ኢ ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች የቅባታማ ጉበት ክስተትን የመቀነስ ዕድሉ አላቸው፡፡በተጨማሪም

ቡና ውስጥ የሚገኘው ካፌይን የጉበትን የቅባት ክምችት አቃጥሎ የሚያበረታታ በመሆኑ በመከላከያነት ይመከራል፡፡

3. ጥንቃቄ ከጎደለው ወሲብ ይታቀቡ

በግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ጉዳይ ሲነሳ በቀዳሚነት በርካቶችን ሲያሳስብ የኖረው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ከፀረ ኤች.አይ.ቪ መድሃኒት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ፍርሃቱ ጋብ ያለ ቢመስልም አሁንም ድረስ በዓለም አቀፍ ችግርነት ይነሳል፡፡ ሰዎች በወሲብ ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚመከረው፣ ለኤች.አ

ይ.ቪና ሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ብቻ ሳይሆን ጉበትንም ከጉበት ቫይረስ ለመጠበቅ ነው፡፡ በጥናቶች እንደታየው የጉበት ቫይረስ ቢ እና ሲ በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ በሚኖር የፈሳሾች ልውውጥ የሚተላለፉ በመሆኑ፣ የጉበት በሽታ ካለበት ሰው ወደ ሌላ

ኛው የመተላለፍ ዕድል እንዳለው ልብ ሊሉት ያስፈልጋል፡፡ ከኤች.አይ.ቪ በብዙ እጥፍ የበለጠ የመተላለፍ አቅም ያለው ቫይረስ በመሆኑ፣ ፍቅረኛዬ ወይም የትዳር አጋሬ ከኤች.አይ.ቪ ነፃ ስለሆነ/ች ሌላ ስጋት የለብኝም የሚል መዘናጋት ውስጥ እንዳይገቡ ሲሉ የሀርቫርድ ተመራማሪዎች ያሳስባሉ፡፡

4. ክትባት ይውሰዱየጉበትን ጤና ለመጠበቅ ከሚረዱ ጉዳዮ አንዱ ክትባት ላላ

ቸው የጉበት ቫይረስ አይነቶች ክትባት ቀድሞ መውሰድ ነው፡፡ በተለይ በበርካቶችየሚፈራውና ከተለያዩ የውጪ ሀገር ጉዞዎች እስከማሳገድ ድረስ የሚደርሰው፣ የሄፖታይተስ ቢ ቫይረስ የቅድሚያ ክትባቱ በአንዳንድ የጤና ተቋማት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ይህንን ቀድሞ መውሰድ ሌላው የጉበትን ጤና ማረጋገጫ ስልት ነው ሲሉ ባለሙያዎቹ ያስረዳሉ፡፡

5. ሲጋራና አልኮል የጉበት ፀር ናቸውሲጋራ ማጨስ ከሳንባ ካንሰር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለ

ው ይታወቃል፡፡ ስጋቱ በሳንባ ላይ አይቆምም፡፡ ጉበትም በሲጋራ ምክንያት ለጉበት ካንሰር የመጋለጡ ዕድል ከፍተኛ ነው፡፡ በተደጋጋሚ እንደሚባለው መጠን ያለፈ ተደጋጋሚ የአልኮል ጠጪነት፣ የጉበት ህዋሳትን በመግደል ለከፍተኛ ጉዳት የሚያጋልጥ በመሆኑ፣ ባለሙያዎቹ ልዩ ትኩረት እንዲያደርጉ በማሳሰብ ላይ ይገኛሉ፡፡

አልኮል በሁለቱም ፆታዎች አንድ አይነት ችግር በማስከተል ቢታወቅም፣ ሴቶች ግን ለአልኮል አሉታዊ ተፅዕኖ የበለጠ የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ ስለሆነም በተለይ የመጠጥ ብርጭቆ የሚደፍሩ ሴቶች ጠንቀቅ ይበሉ ብለዋል ባለሙያዎች፡፡

6. ቅባታማ ምግቦችን አይዳፈሩቅባት ነክ ምግቦች በዋናነት በለብና በየደም ቧንቧ ህመሞች

የመጠቃት ዕድልን በብዙ እጥፍ እንደሚያሳድጉ ይታወቃል፡፡ የጥቃቱ አንዱ አካል የሚሆነው ደግሞ ጉበትም ጭምር ነው፡፡ ጉበት ለሰውነት አስፈላጊ የሆነ ምጥን ኮሌስትሮል ከማዘጋጀት በተጨማሪ በሀሞት ፈሳሽ አማካኝነት ቅባትን የማሟሟትና ወደ የተገቢው የሰውነት (ጉበትዎን... እባክዎን ወደ ገጽ 13 የዞረ)

Page 17: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 17የጤና  ሞግዚት አዘጋጅ፦ ዶ/ር ዓብይ ዓይናለም

ኢቦላ*  የዘመናችን  እንቆቅልሽ  -  (ስለቫይረሱ  የተሟላ  የባለሙያ  ትንታኔ

እንደ ጎርጎሮሳውያን የጊዜ ቀመር ነሐሴ 26/1976 የቀድሞዋ ዛየር የአሁኗ ኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ውስጥ በአካባቢው ህዝብ ኢቦላ እየተሰኘ ከሚጠራው ወንዝ በስተደቡብ 60 ማይልስ ርቃ በምትገኘው ያምቡኩ ሰፈር ውስጥ እንዲህ ሆነ፡፡

ከዚህ ቀን አስቀድሞ ማለትም ከነሐሴ 10-­22 ድረስ የቆየ በአንድ ማባሎ ሎኬላ በተሰኘ መምህር ኢቦላ ወንዝ አቅራቢያ ጉብኝታዊ ጉዞ ተደርጎ ነበር፡፡ ማባሎ ሎኬላ ጉዞውን አጠናቆ ከተመለሰ በኋላ ‹አገር አማን ነው› ብሎ ብርቱ ሰልፍ የሆነችውን ህይወት ለማሸነፍ ተፍ ተፍ ማለቱን ቀጠለ፡፡ ነሐሴ 26 ቀን ግን የሎኬላ ህይወት ድንገተኛ ራስ ምታት፣ ትኩሳትና የሰውነት መቆረጣጠም አጀባት፡፡

ማሳሰቢያበዘ-­ሐበሻ የጤና አምዶች ላይ የሚወጡ ጽሁፎች በሙሉ ለማስተማሪያነት እና ግንዛቤ ለመስጠት እንጂ እንድትታከሙበት አይደለም። ሁልጊዜም ቢሆን አንድ ህመም ሲሰማ ወደ ዶ/ር ጋር በመሄድ

በዶ/ር ትዕዛዝ እንድትታከሙ አደራ እንላለን።

የግጥም  ጉባዔ

የአብርሃም ረታ የዛ ዘመን ስንኞችከአልን፣ ተባልን ይባላል ከሚለው መጽሐፉ የተወሰዱ

ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራእንደ ሆ ቺ ሚኒ እንደ ቼ ጉቬራ

* * *ሃይ ዘራፍ እያሉ እያረረ አንጀቴ

እኔስ አልረባሺም ወልደሽ ተኪ እናቴውስኪውም ይንቆርቆር ጮማውም ይቆረጥ

እማዬ እኔና አንቺ ሽሮ እናሯሩጥ* * *

ዮሜሳን ለሆዴ ማን ይገዛልኛልእንቆቆ እየጋቱ ዶሮ ማታ ይሉኛል

* * *እኔ ልኮራመት እኔ ከሰል ልምሰልስቀሽ አታስቂኝ የደላሽ ይመስል

* * *የእምዬ ልጅ ሙቺ ዉሃ ጉድጓድ ገብተሽላንቺ ሳጥን ገዝቶ ማንም ሰው አይቀብርሽ

* * *በስምንተኛው ሺ ሲመሽ ተወልጄ

ጅቡን ጋሼ እላለሁ ተኩላውን ወዳጄ* * *

ባንዲት ሉክ ጀምሬ አቤቱታስንት ዓመት ልኑር ስንገላታ

በሸንጎ ስወጣ ስወርድአለቀ ስንቄ በመንገድ

አንተ የበታች ሹም መዝገብ ቤት ያለኸውዶሴዬን ወደታች አርገህ የቀበርከውእንዲታይ ነው እንጂ ወደበላይ ቀርቦ

እንዲኖር አይደለም መዝገብ ቤት አጣቦ* * *

ይሄዳል ወታደር ይሄዳል ወታደር ይሄዳል ተራምዶእየወረደበት ቦንብ እንደበረዶ

* * *ወዘት በይ ልቤ እንደጀበናአልወጣልሽም የጦር ባፈና

* * *የፍየል ወጠጤ ትከሻው ያበጠ ልቡ ያበጠበት

እንዋጋ ብሎ ለነብር ላከበትየማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለችልጆቿም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች

* * *ሃቻምናም እሮሮ ዘንድሮም እሮሮዝም ነው ፀጥ ነው እሮሮን ዘንድሮ

* * *ማርክስና ኤንግልስ ሌኒንም እያሉ

በእቅፍሽ ልውል ስል ክንድሽ እያፈነኝበካባሽ ላጌጥ ስል ክሳዱ እያነቀኝ

መናገሩን ፈቅደሽ በቀቀን ሁን ያልሺኝባባትህ ተውና በኔ ስም ማልልኝ

ብለሽ የገረፍሺኝ ብለሽ የዘለጥሺኝምዬም አልጠቀምኩሽ እምቢም ብል ላተዪኝ

ምናለበት ነበር ያንቺ ልጅ ባልሆንኩኝ* * *

ለኩርማን እንጀራ ለስሙኒ ጠጅሄደ አሉ ሰፈራ ይህ የወሎ ልጅ

* * *ጨረቃና ኮኮብ ዛሬም እንዲያው ናቸው

ደርግና ኢሰፓ ባይለዋውጧቸው* * *

ወይ አልተጣላነ አልተደባደብነሰተት ብለው መጥተው ቤት አፍርሱ አሉነ

ወንዱም አላረሰ ሴቱም አላረሰእንደ ጥንብ አሞራ ቤት እያፈረሰ

* * *ደርሶ ማንጎራጎር ልማዱ ነው ደሃእየቀዘቀዘው የሚጠጣው ውሃ

* * *እሞታለሁ ብሎ ሰው ምነው ማዘኑ

ቅጠል አይበጠስ ካልደረሰ ቀኑ* * *

እበላለሁ ጮማ እጠጣለሁ ጠጅእኔን ያስለቀሰኝ የድሃው ራብ እንጅ

* * *ታርሶም ተሸምቶም ይበላል እንጀራእንደምነሽ ጥቃት የሞት ባልንጀራ

* * *ያላግባብ የሆነ ብዙ ጉድለት ቢያውቅም

ሰው እርጥብ ነውና መቼም ነዶ አያልቅም* * *

አለቅሳለሁ ባይኔ ሳዝን በወዳጄእንደ ሰማይ ኮኮብ እየራቀኝ ከጄ

* * *ብለነው ብለነው ካልሆነ ነገሩ

ብርና ወንድ ልጅ የትም ነው ሀገሩ* * *

ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታላገር ብልጽግና ለወገን መከታ

በወቅቱ የነበሩት ሐኪሞች ‹‹ወባህ ተመልሳብህ ነው›› ብለው ክሎሮኩይን የተሰኘውን መድሃኒት ሰጡት፡፡ የተሰጠው መድሃኒት ግን የሎኬላን ጤና እንደቀድሞው ማድረግ ተሳነው፡፡ መስከረም 1 ቀን ‹‹ትኩሳቴ አደብ አልገዛልኝ ብሏል›› ብሎ ሎኬላ ወዳከሙት ሐኪሞች ተመለሰ፡፡ ከአራት ቀን በኋላ ደግሞ የሎኬላ ህይወት መወሳሰብ ጀመረች፡፡ ከሰውነቱ ቀዳዳዎች ደም መጉረፍ ጀመረ፡፡ ትውከት፣ አጣዳፊ ተቅማጥ፣ ደረቱን ሰቅዞ የያዘ ውጋትና ከፍተኛ የሆነ ራስ ምታት ያናውጠው ጀመር፡፡ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ራሱን ማወቅ ለሎኬላ እየከበደው መጣ፡፡ መስከረም 8 ቀን ሎኬላ ለሐኪሞቹ እንቆቅልሽ እንደሆነ ላይመለስ በያምቡኩ ሰፈር ግብዓተ መሬቱ ተፈፀመለት፡፡

ከእርሱ ሞት በፊት የቀደሙ ሌሎች ሞቶች ተመዝግበው ነበር፡፡ ለምሳሌ ነሐሴ 28 ቀን በተመሳሳይ ምልክቶች የመጣና ሰፈሩ ከሎኬላ አጠገብ የሆነ ሰው ዳግም አልታየም፡፡ አንድ ዩምቤ ንጎንጎ የተባለችና ሎኬላ ተኝቶ ከነበረበት ሆስፒታል የነበረች ወጣት ከሆስፒታሉ በሰላም ወጥታ ከጥቂት ቀናት በኋላ ተመሳሳይ ምልክት አሳይታ በአንድ ቀን ሎኬላን ቀድማው ሞተች፡፡ እህቷ ደግሞ ሁለት ቀን ዘግይታ መስከረም 9 ቀን ተከተለቻት፡፡

የሎኬላ መዘዝ በቀላሉ የሚለቅ ሆኖ አልተገኘም፡፡ የሎኬላን አስከሬን የገነዙት ሚስቱ፣ እናቱና እህቱም ደግሞ ትንሽ ቀን ቆይተው አፈርን ለበሱ፡፡ በወቅቱ የነበሩት የጤና ባለሙያዎች የሞት መዝገቡን ከመሙላት ባሻገር የበሽታውን ምንነት ተረድተው እንዲህ ነው ብለው ለማስረዳት የደፈሩ አልነበሩም፡፡

በ1935 ዓ.ም በቤልጂየም የወንጌል መልዕክተኞች የተመሰረተው የያምቡኩ ሆስፒታል ወረርሽኙ የተቀሰቀሰበት ሰዓት 120 አልጋዎች ያሉት ሲሆን 17 የጤና ባለሙያዎች ነበሩት፡፡ የሚገርመው ነገር ይህ ሆስፒታል ለወረርሽኙ መስፋፋት ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ በየቀኑ ለተመላላሽ ታካሚዎች የሚመደብ አምስት መርፌ ነበር፡፡ ይህ መርፌ ተቀቅሎ ወደ ፍፁም ንፅህና ሳይደርስ ድጋሚ ለሌሎች መውጊያ ይውል ነበር፡፡ ስለዚህ አንዱ የተዋገበት ሌላው ይወጋበት ስለነበር በመጀመሪያ የመስከረም ወር ሳምንት የተመዘገቡት ዘጠኙ ህመምተኞች በሆስፒታሉ ሰራተኞች መርፌ ተወግተው ነበር፡፡

በአጠቃላይ ከመስከረም 1 እስከ ጥቅምት 24 ባሉት ቀናት ውስጥ በበሽታው ከተጠቁት 318 ሰዎች ሁለት መቶ ሰማኒያው መትረፍ አልቻሉም፡፡ ሆስፒታሉ ካለው 17 ሰራተኞች አስራ አንዱ ለኢቦላ መስዋዕት ሆኑ፡፡ በዚህም ምክንያት ሆስፒታሉ ተዘጋ፡፡

በሽታው ስርጭቱን ቀጥሎ ዋና ከተማዋን ኪንሻሳንም ስላደረሰ ነገሩ እየተጋጋለ መጥቶ ቤተ መንግሥት ስለገባ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኪንሻሳንና ያምቡኩን የስጋት ቀጠና ብለው ፈረጁና ማንም መውጣትም ሆነ መግባት ፈጽሞ የመሆኑን አወጀ፡፡ የዓለም የጤና ድርጅትና ሌሎች ሀገራት በንስር ዓይን ጉዳዩን ቦታው ድረስ መጥተው አጣሩ አበጠሩ፡፡

የሚገርመው ነገር ይህ ወረርሽኝ ኮንጎ ከመከሰቱ ሁለት ወራት ቀደም ብሎ በሱዳን ግዛት ስር ያሉትንና ከያምቡኩ ከተማ 825 ኪሎ ሜትር ርቀው የሚገኙትን ማሪዲንና፣ ኤንዛራ የተባሉትን ከተሞች አስጨንቆ ብዙ አልጋዎችን ወደ ቃሬዛነት ለውጦ ነበር፡፡

ነገር ግን የኮንጎው ውጤቱ በጣም አስከፊ ነበር፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት በ1978 ዓ.ም ያወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው ኮንጎን ያደቀቃት የኢቦላ ወረርሽኝ መነሻው የሱዳን ሳይሆን አይቀርም ይላል፡፡ ምክንያቱም በወቅቱ ሁለቱ ጎረቤት ሀገሮች የንግድ ለውውጥ ያደርጉ ስለነበር በሽታው ከዚያ ሳይመጣ አልቀረም፡፡

ኢቦላን ማን አስጠለለው?የኢቦላ ቫይረስ በሎኬላ ጀምሮ መላ ኮንጎን ከማሸበሩ በፊት ኢ

ቦላ የት ነበር? ለምን ከዛ በፊት አልታወቀም? የሳይንቲስቶች አልመለ

ስ ያለ ጥያቄ ነው፡፡ ኢቦላ መኖሪያውን ለማወቅ በዘርፉ የተሰማሩት ባለሙያዎች ያለ የሌለ ኃይላቸውን ተጠቅመው ምርመራቸውን ቢቀጥሉም እርግጠና ሆነው መናገር አልቻሉም፡፡ ይሁን እንጂ የኢቦላ ቫይረስን ፍራፍሬን ተመራጭ ምግባቸው ባደረጉ የሌሊት ወፎች ውስጥ ማግኘት ችለዋል፡፡ ታዲያ ቫይረሱ እነርሱን አንዳች ጉዳት ሲያመጣባቸው አልታየም፡፡

ወደ ሰው፣ ቺምፖንዚና ጉሬላ ወዘተ... የመሳሰሉትን የዱር እንስሳዎችን ካገኘ ግን የተለመደ ጉዳቱን ማስከተሉ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ

ቫይረሱ በሁለት መንገድ ወደሰው ዘር ሊደርስ ይችላል፡፡1. ለእነዚህ ሀገራት በተለይ ምዕራብ አፍሪካ አካባቢ የሌሊት

ወፎች የዶሮ ወጥን የሚያስንቅ ምግባቸው ነው፡፡ ለምሳሌ በጋና ከ100,000 በላይ የሚሆኑ የሌሊት ወፎች ከየጥቅጥቅ ጫካው እየታደኑ የምግብ ገበታ ላይ ይሞሸራሉ፡፡ እነዚህ ሀገራት ከማኛ ጤፍ በላይ የሌሊት ወፎች ጉዳይ ትልቁ ፀሎታቸው ነው፡፡

ምክንያቱም አድኖ መብላት ለጥቂቶቹ ምንም እንኳን ሲቀማጠሉ የሚያደርጉት ቢሆንም ለብዙሃኑ ግን ለመኖር መሰረታቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ቫይረሱ እሳት ውስጥ በሚገባ ጊዜ የመሞት ዕድል ያለው ቢሆንም በአደን ጊዜ ያለ ምንም መከላከያ ሽፋን የሚያድኑት ሰዎች የሰውነት አካላቸው መጫጫር ወይም ንክሻ ስለሚያጋጥመው ቫይረሱ ወደ ሰውነት የመግባት ዕድል ያገኛል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ የ2014

ዓመተ ምህረትና ከ7500 በላይ የሆኑ ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት ያበቃው የኢቦላ ቫይረስ ከጊኒ ሀገር ሲጀመር የሌሊት ወፍን ከበላው የሁለት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ ህፃኑ ትንሽ ቆይቶ ሞተ፡፡ ያስታመመችው ወላጅ እናቱ ደግሞ ጥቂት ቆይታ ተከተለችው፡፡

2. ሌላኛው የመተላለፊያ መንገድ ደግሞ ከሌሊት ወፎች የተሰደደው ቫይረስ ሰዎች ለምግብነት የሚጠቀሟቸውን እንስሳት ለምሳሌ ቺምፖንዚን፣ ጎሬላን፣ ዝንጀሮን፣ አጋዘንን የመሳሰሉትን ካጠቃ ነው፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ እንስሳት የሚወጣው ፈሳሽ፣ ደም እንዲሁም ስጋ

ቸው ለቫይረሱ መኖሪያ እንደመሆኑ መጠን እነዚህን እንስሳት የሚመገቡ ሰው ኢቦላን ወደ ህይወቱ ይጋብዛል፡፡

ኢቦላ ቫይረስ ታሪኩን ‹‹ሀ›› ብሎ ሲጀምር እነዚህን ሁለት መንገዶች ሳይጠቀም አልቀረም ተብሎ በዓለም ጤና ድርጅት ተዘግቧል፡፡ ለምሳሌ ሱዳን ላይ ኢቦላ ስሙ ሲናኝ ጥቃቱን የጀመረው ኤንዛራ በተሰኘችው ሀገር ከነበረ የጥጥ ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው በሚሰሩ ሶስት ሰዎች አማካኝነት ነበር፡፡ እነዚህ ሰራተኞቹ የነበሩበት ክፍል ጣራው በሌሊት ወፎች ያጌጠ ነበር፡፡ ስለዚህ ምናልባት ኢቦላን እነዚህን ሰዎች ያገኘው ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ነው ተብሏል፡፡

የኮንጎው ኢቦላ ስናየው ደግሞ ማባሎ ሎኬላ በ10 ቀን ጉብኝቱ ውስጥ በመንገዳቸው ላይ የተገዛውን አጋዘን በልቶ ነበር፡፡ ምናልባት በዚህ አጋጣሚ በቫይረሱ ተይዞ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌላኛው ደግሞ ከሱዳን ገባ የሚል ነው፡፡ ነገሩ ትንሽ ውጥንቅጡን ያጣ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ኢቦላ በአሁኑ ወቅት ለዓለማችን ትልቅ ስጋት ሆኗል፡፡

የኢቦላ ቫይረስን ስሙን ማን አወጣለት?አንድ ቀን ምሽ የምሁራን ጉባኤ በአሜሪካ ኬንታኪ ውስጥ ተደረ

ገ፡፡ ይህም ቫይረሱ ስም ይውጣለት ተብሎ ነው፡፡ አንዱ ሊቅ ተነሳና ‹‹ያምቡኩ›› አለ፡፡ ከሌላ ጠርዝ ተቃውሞ ተነሳ፡፡ ‹‹ከተማዋን ማግለል ይሆንብናል›› አለ፡፡ ሌላ ሃሳብ መጣ ‹‹ለምን ‹ኮንጎ ሪቨር ቫይረስ› አንለውም?›› አለ፡፡ እዛው የሚገኝ የዓለማችን ጥልቅ ወንዝ ነው፡፡ ይኼኛው ስም ደግሞ በሌላ ቫይረስ ተይዟል ተባለ፡፡ የመጨረሻ አማራጭ ተብሎ የተያዘው ያምቡክ ለተሰኘችው ትንሽ ከተማ በጣም ቅርብ የሆነውን ወንዝ ካርታ ላይ መፈለግ ተጀመረ፡፡ ኢቦላ የተሰኘ ወንዝ ተገኘ ትርጉሙ ደግሞ ‹‹ጥቁር ወንዝ›› ማለት ነው፡፡ በዚህ ኢቦላ ቫይረስ ተባለ፡፡ በኋላ ሲጣራ ግን ካርታው ስህተት ስለነበር ነው እንጂ ለከተማይቱ የሚቀርብ ሌላ ወንዝ ነበር ተባለ፡፡ ግን አንዴ ስለተሰየመ ‹ኢቦላ› የሚለው ስም ዛሬ ከወንዝነቱ ይልቅ ቫይረስነቱ ገኖ ወጥቷል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ አይነቶችየኢቦላ ቫይረስ ፊሎቪሪዲ ከተሰኘው የቫይረሶች ቤተሰብ ሲመ

ደብ በቅርፁ የሚመሰለው በ1967 ዓ.ም በጀርመን የተገኘው ማርበርግ ሲሆን ምንጩ ደግሞ ከአፍሪካ ተጭኖ ወደ ጀርመን ማርበርግ ከተማ የገባው ዝንጀሮ እንደሆነ ታውቋል፡፡ እንደውም ሱዳንና ኮንጎ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ በሽታ ዜጎች ሲያልቁ ማርበርግ ቫይረስ ነው ተብሎ ተወርቶ ነበር፡፡ ቅሉ ግን በቅርፁ ይምሰለው እንጂ ይህ ማርበርግ ሳይሆን አዲስ ቫይረስ ነው ተባለ፡፡ በኋላም ኢቦላ ተባለ፡፡

የኢቦላ ቫይረሶች አምስት አይነቶች ሲሆኑ የሱዳኑ፣ የዛየሩ፣ የኡጋንዳው፣ የኮትዲቯሩና የፊሊፒንሱ ተብለው ይከፈላሉ፡፡ በቅርቡ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የሆኑትን ጊኒን፣ ላይቤሪያንና ሴራሊዮንን በእንባ ሸለቆ ውስጥ የከተታቸው የዛየሩ ዝርያ መሆኑን ምሁራኑ ገልፀዋል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ ከእንስሶች ወደ ሰው ሊመጣ የቻለበት መንገድ ከላይ ተገልጿል፡፡ ቀጣዩ ደግሞ ከሰው ወደ ሰው እንዴት ይተላለፋል የሚለው ይሆናል፡፡

የኢቦላ ቫይረስ ከበሽታው የሚመጣውን ደም፣ ፈሳሽ /ለሀጭ፣ ምራቅ/፣ እንዲሁም በግብረ ስጋ ግንኙነት ሊተላለፍ ይቻላል፡፡ ይህ ማለት በሽተኛው ይጠቀምበት ወይም ይተኛበት የነበረው ዕቃ በበሽተኛው ፈሳሽ የተበከለ ከሆነ እነዚህን ነገሮች መንካት ለበሽታው ያጋልጣል፡፡ ሌላው ኢቦላ አስገራሚ የሚያደርገው ሰውዬው ከሞተ በኋላ በቀብሩ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው አስከሬኑን የዳሰሱ ሁሉ ለዚህ በሽታ መጋለጣቸው ነው፡፡ ኢቦላ የምትወዱትን ሰው አስከሬኑን እንኳን እንድትሰናበቱ የማያደርግ የዘመናችን ጭራቅ በሽታ ነው፡፡ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በአሁኑ ሰዓት የኢቦላ በሽታ የገደላቸውን ሰዎች አስከሬን የሚቀርብ ልዩ ግብረ ኃይል አቋቁመዋል፡፡

የኢቦላ በሽተኛ ከዳነ በኋላ በሽታውን አያስተላልፍም ማለት ደሙ ንፁህ ነው፡፡ ነገር ግን በወንድየው የዘር ፈሳሽ ውስጥ እስከ ሶስት ወር ሊቆይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ቫይረሱን ሊያስተላልፍ ይችላል ማለት ነው፡፡

አንድ ደስ የሚል ነገር ልንገራችሁ፡፡ የኢቦላ ቫይረስ በትንፋሽ አይተላለፍም፡፡ በትንፋሽ የሚተላለፍ ቢሆን ዓለም ይሄኔ በኢቦላ ጎርፍ ትታጠብ ነበር፡፡ (ኢቦላ... እባክዎን ወደ ገጽ 20 የዞረ)

በማድነቅ.... ከገጽ 18 የዞረ

አድናቆቶች የሰዎችን የፈጠራ ክህሎትና የሥራ አፈፃፀም ይጨምራል፡፡

3. አድናቆትን መናገር በተግባርም ማሳየትአድናቆት ሁሌም በፅሑፍ ወይም በቃል ብቻ የ

ሚገለፅ መሆን የለበትም፡፡ አድናቆትን በተለያዩ መንገዶች መግለፅ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፣ አንድን የሥራ አጋር ለአዲስ ሠራተኛ የክህሎት አማካሪ እንዲሆን ማድረግ ምን ያህል ስለ እሱና ስለ ስራው ቦታ እንደምንሰጥ ያሳያል፡፡ ፈጣን የስራ አፈፃፀም በሚኖርበት ወቅት አድናቆታችሁን የምሳ ግብዣ በማድረግ መግለፅ በተግባር የታጀበና የማይረሳ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በሉ፣ ወደ እኔ ግድምም አንድ ምሳ እንዳለባችሁ አትርሱ፡፡

4. የአድናቆት ክልልን ማስፋትበጣም ጠንካራ ሠራተኛ፣ ጎበዝ ተጨዋች፣ ልዩ ክ

ህሎት ወዘተ አላቸው የምንላቸው ሰዎች ከሞላ ጎደል አብዛኛውን ጊዜ አድናቆት ሲቸራቸው እናያለን፡፡ ምናልባትም ይህ የተነሳሽነታቸው አንዱ ምስጢር ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የአድናቆት ወላፈን ያላገኛቸውም ብዙ ሰዎች እንዳሉ አንዘንጋ፡፡ እነዚህን ሰዎችም የአድናቆታችሁ ክልል ውስጥ ማስገባት መቻል እስከ አሁን ያልታዩ ለውጦችን የማምጣት ብቃታቸውን ሊያወጣ ይችላል፡፡ ማን ያውቃል? ወደ ቀጣዩ የዕድገት ደረጃ ለመሸጋገር ውስጣቸው የሚሻው ያቺንትንሽ ‹‹አበጀህ!›› የምትለውን ግፊት ብቻ ይሆናል፡፡

ጉርሻ፡-­ አድናቆት የተለያዩ መስተጋብሮቻችንና ግንኙነቶቻችን የሚያጠናክር ብሎም የሚያለመልም ሸጋ ተግባር መሆኑ እንዳለ ሆኖ፣ የሆነ ነገርን ምላሽ ጠብቀን አድናቆትን መስጠት ከውስጣችን ልናወጣው የሚገባ አጉል ጠባይ ነው፡፡ አድናቆት በመስጠት ብቻ ተደሰቱ፣ አድናቆታችሁ በእናንተ እና በአካባቢያችሁ ባሉ ሰዎች መካከል በሚኖረው በጎ ተፅዕኖ አመስጋኝና ደስተኛ ሁኑ፡፡ አበጃችሁ! ሸጋ ሰው!

Page 18: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 18የወሩ  ታላቅ  ዜና

ለነብሰ  ጡር  እንኳን  የማይራሩ

የፖሊስ  ሰደፎችከሃብታሙ ምናለ

ሰላማዊ ትግል ስንል ያለምንም ጎጂ ሳሪያ ማንኛውንም ጨቋኝ የሆኑ ችግሮችን የምናስወግድበት ትልቅ የትግል ስልት ነው፡ ፡ታዲያ ይሄንን የትግል ስልት የተቀላቀሉ ፓርቲዎች ገዢውን ፓርቲ የሚያደርገውን ሕገ-­ወጥ ሥራዎችን ለመታገል ወደ ትግል ሜዳ የሃሳብ ትጥቆችን ብቻ ታጥቀው ሲገቡ፡፡ ገዢው መንግሥት ደግሞ ከነ ሙሉ የጦር ሜዳ ትጥቁ ሜዳው ላይ ኩታውን ደርቦ ጭንብሉን አድርጎ ጠበቃቸው፡፡ ታዲያ በሃሳብ ሞግቶ ሊጥል ያልቻላቸውን ሰዎች በዱላ በመቀጥቀጥ ለመጣል ጥረት ማድረግ ከጀመረ ቆየ፡፡ ለዚህም ማሳያ እንኳን በቅርቡ ሰማያዊ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በትብብር ሊያደርገው የነበረውን ‹‹ሰላማዊ ሰልፍ›› በመፍራት ፖሊሶችን ፓርቲው ጽ/ቤት ድረስ በመላክ አባላቱን እስኪበቃቸው ድረስ በዱላ ቀጥቅጠው ጥለዋቸው ሄዱ፡፡ ቀጠለና ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም አንድነት ፓርቲ ተቃውሞ ለማድረግ ባዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ሰላማዊ ትግል የመረጡ አባላት ላይ ከባድ ዱላ አሳረፈባቸው፡፡

ባለፈው እሑድ ያጋጠመኝን ላጫውታችሁ አራት ኪሎ አካባቢ ጠዋት ብገኝም ፖሊሶች ወደ ቀበና ሰው ማለፍ እንደማይቻል ገለፁ፡፡ መንገዱን እስኪከፍቱት ስጠብቅ ቆየሁ፣ ሲሰለቸኝ ጊዜ ወደ ስራ ባልደረቦቼ ስደውል ዋና የሚሊየን ድምፅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ስለሺ ሓጎስ ሰልፉን ለመበትን በመጡት ፖሊሶች ተደብድቦ ምኒሊክ ሆስፒታል እንዳለ ተነገረኝ፡፡ ወደ ሆስፒታሉ በማምራት ግቢው ውስጥ ስገባ በየወንበሩ ተኝቶ የሚያቃስት፤ የታመሙትን ለመተባበር የሚሯሯጡ ወጣቶች፤ ‹‹ጨካኝ መንግሥት!›› የሚል ሰው ብቻ ነው ያለው፡፡

የማየው ግራ ቢገባኝ ወደ ድንገተኛ ክፍል አዘገምኩ፡፡ በሚዘገንን ሁኔታ ስለሺ ፊቱ በጣም አብጦ፤ እጁ ተሰብሮ አየሁ፡፡ እሱ ግን እንኳን የተመታ ሰው ሲመታም ያየ አይመስልም! እሱን አዋርቼ ወደኃላ ስመለከት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች በየወንበሩ ተኝተው ያቃስታሉ፡፡ አንድ ሴት ግን ከሁሉም በተለየ ከፊት ለፊት አይቻት ሁኔታዋ ስቦኝ ምን ሆና ነው) ብዬ ጠየኩኝ ‹‹በዛሬው ሰልፍ ላይ ፖሊሶች ደብድበዋት ነው!›› አሉኝ -­ ከእግር እስከ እራሴ ወረረኝ፡፡

ወደ እሷ ስጠጋ በጉንጫ ላይ እንባዋ መንታ መንታ ሆኖ ይወርዳል፡፡ ወደእሷ ብጠጋም አይኗን ግርግዳ ላይ ተክላ ታነባዋለች! አይዞሽ ብዬ ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኃላ ከተቀመጠችበት ለመነሳት ጣረች እኔም እጄን ዘረጋሁላት ግን አልቻለችም!

‹‹ተወው በቃ፣ እዚሁ ልቀመጥ›› አለች፡፡ ጥያት መሄድ አልፈለኩም፣ ‹‹የስንት ወር ነፍሠ ጡር ነሽ?›› አልኳት፡፡

‹‹ሰባት ወር ሆኖኛል›› አለች፡፡ ‹‹እንዲህ ሆነሽ እያዩሽ መቱሽ)›› አልኳት፡፡ ‹‹መቱኝ ብቻ? ደጋግመው ነውየቀጠ

ቀጡኝ፡፡ ከሁሉም የገረመኝ፣ ሆዴን አንድ ሴት ፖሊስ ደጋግማ ስትመታኝ ነበር›› ስትለኝ ራሴን ልስት ምን ቀረኝ!

ይሄ የተካሄደው በኢትዮጵያውያን ነው) እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን እንዲህ አልነበርንም! እንኳን እርጉዝ ላይ ማንኛውንም ሴት ላይ እጃችንን ማንሳት አንወድም! ታክሲ ውስጥ ነፍሰ-­ጡር ስናይ እኮ ከተቀመጥንበት ተነስተን የሚመቻትን ወንበር ለእሷ የምንለቅ፤ ምግብ ቤት ስንበላ ያምራት ይሆን ብለን ባናውቃትም እንድትበላ በአክብሮት የምናሳትፍ፤ ሰልፍ የሚኖርባቸው ቦታዎች ላይ ቅድሚያ የምንሰጥ አልነበርን፡፡ ታዲያ ይሄ የአውሬ ባህሪ ከየት አመጣነው) ነፍሰ-­ ጡር የሆነችን መደብደብ በእዛ ላይ ከፍተኛውን ድብደባ የተፈፀመባት ህመሙን በሚቋደሱት ሴት ፖሊስ መሆኑ አያስደነግጥም) ሴት ፖሊሶ ሆዷን እንደመታቻት ስትናገር የሰሙ በሆስፒታል ውስጥ የሚሰሩ እናቶች እያነቡ ‹‹እመብርሃን ይቅር ትበላት!›› ይላሉ እያዘኑ፡፡ እኔ ግን ከዚህ በላይ ይሄን ግፍ ሰምቼ መቋቋም እንደማልችል ሳውቅ በርሬ ወጣሁኝ፡፡

ውጪም የሚያነክሱ፤ ወገባቸውን በእጃቸው እያሻሹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በዊልቸር እየገፉ ይወስዳሉ፡፡ ለሚያያቸው ሰው ሁኔታው ልብን ይነካል፡፡ ‹‹ሌሎችስ የት አሉ?›› ብዬ ጠየኩኝ፡፡ ከዚህ በላይ አይቶ መቋቋም የሚችል አቅም እንደሌለኝ እያወኩ፡፡አንዱ ተነሰቶ ና ላሳይህ አለኝ እየሄድን ሳለ በሰልፉ ላይ ነበርክ) አልኩት፡፡

አዎ አለኝ፡፡‹‹የተፈጠረውን ንገረኝ›› አልኩት፡፡‹‹እኔ ብዙም አልተመታሁም፡፡ ግን ገና ከበር እንደወጣን የዱላ ናዳ አወረዱብን፡፡አባሎቻችንን አስተኝተው ሲደበድቧቸውና ደማቸው ሲፈስ ሳይ እንደ እብድ ነው ያደረገኝ! ለመግደል በሚመስል ሁኔታ ነ

ው የሚማቱት፡፡ በዚያ ላይ የመጡት ፖሊሶች ብዛት ያላቸው ሲሆኑ አንድ ሰው ለአምስት ፖሊስ ይደርሳቸዋል፡ ፡ብቻ አሰቃቂ ነው›› አለኝ ውስጡ እልህ በተቀላቀለበት ቁጣ፡፡ወዲያውም መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች ወጣቶች አገኘቸው፡፡

ጉዳቱ መጠነኛ ነው ያልኩት ካለው ነባራዊ ሁኔታ እንጂ መንቀሳቀስም የማይችል ነበር፡፡ በዕለቱ ከአመራር እስከ አባሎች ድረስ ተደብድበዋል! ሰላማዊ ትግል ማለት እንዴት ነው) እራሱ መንግሥት ቢያስረዳን ጥሩ ነው፡፡ ሰልፍ መውጣት መቃወም ሰላማዊ ካልሆነ ታዲያ ምንድን ነው) እኔን ስላልገባኝ የሚያስረዳኝ ካለ ለመረዳት ዝግጁ ነኝ፡፡

ያለበለዚያ ‹‹እንደ ነጻው ፕሬስ በአደባባይ ነጻ ትግልን በመግደል ግባተ ቀብሩን በመፈጸም ይሻላል›› ከሁሉ የሚያሳፍረው በማታ የኢብኮ የሁለት ሰዓት ዜና ላይ ‹‹አድማው ሕገ-­ወጥ ስለሆነ ለመበተን ስንሞክር ተመትቻለሁ›› የሚል አንድ የፖሊስ አባል በዜና ዘገባው ቀርቦ የለመደውን የፌዝ ጨዋታውን አሳየ፡ ፡በዜናው

ም ‹‹ምንም ጉዳት አልደረሰም፣ በሁለት ፖሊስ ላይ ግን ጉዳት ደርሷል፡፡›› ብሎ ሲያቀርብ ኢብኮ ጉዳትን የሚለካው በኢህአዴግ አባላት የጉዳት መጠን ነው እንዴ? ጣቢያውን እንተወው፣፣ እነዚህ ፖሊሶችን የወለዷቸው የኢትዮጵያውያን እናቶች ማኅፀን እንጂ የኢህአዲግ የፕሮፖጋንዳ ክፍል ነው እንዴ) ያነሱት ዱላ የእነሱ ወንድም ላይ ቢሆንስ) ነፍሰ-­ጡሯ ላይ የተፈፀመው በእራሳቸው ሚስት ላይ የተደረገ ቢሆን?) ምን ይሰማቸው ይሆን? ነገ እኮ አንድ ልጃቸውን ሲደበድብ የከረመ ፖሊስ ወድቆ የኢትዮጵያውያን እናቶች ቢያዩ፡-­ ደረታቸውን እየደቁ ‹‹ልጄ እኔን እኔን›› እንደሚሉ ቢያውቅ ምን አለበት! የእነዚህን እናቶች ከልጆቻችው እኩል የሚያለቅሱላችሁ ልጆቻቸውን እህል ውሃ በማያሰኝ ዱላ መፈነካከት፣ መደብደብ፣ አንገት ማስደፋት ለምን ፈለጋችሁ”? እባካችሁ ኢትዮጵያውያንነታችሁን አትርሱት! እኛ የእናንተ! እናንተም የእኛ! መሆናችንን አትዘንጉ!

መልካሙን ሁሉ በሰላማዊ ትግል ለተጎዳችሁ!!!

       በማድነቅ

ውስጥ  ያለ  የደስታ  ምንጭ

ከሮቤል ሔኖክ-­-­-­-­-­-­-­-­

ስኬታችን መሬት ቆንጥጦ ከሚቆምባቸው ነገሮች መካከል አንዱ ስኬታማ ግንኙነት ነው፡፡ ወደ ስኬታማ ግንኙነትና መስተጋብር የሚወስደን አንዱ ጥርጊያ መንገድ ደግሞ ከሰዎች ጋር የምናደርገው የስሜት እና ሃሳብ ልውውጥ ነው፡፡ እስቲ ለደቂቃ ያሳለፍነውን የ2014 ዓ.ም በምናብ ገረፍ ለማድረግ ሞክሩ፡፡ ከአንዳድ ሰዎች ጋር ሃሳብ ተለዋውጣችሁ ስትጨርሱ በውስጣችሁ ታላቅ የተነሳሽነት ስሜት የተፈጠረበት በተቃራኒው ደግሞ ከትንሽ ጊዜ ቆይታ በኋላ ክብድ ያለ ስሜት ያደረባችሁ ጊዜ ይኖራል፡፡ ስኬታማ ሰዎች አንዱ ቀዳሚ ባህሪያቸው በመስተጋብር ውስጥ ሌሎች ሰዎችን የመገንባትና የማጠናከር ችሎታ ነው፡፡

ሰዎችን የምንገነባበትና የምናጠናክርበት አንድ መንገድ ደግሞ አድናቆትን መቸር ነው፡፡ ሰዎችን በማድነቅ ውስጥ የማይታይ ግን የሚቀጣጠል ኃይል አለ፡፡ ይህ ኃይል በእናንተም ሆነ በግንኙነታችሁ ውስጥ ይቀጥላል፡፡ እስቲ አንድ ሰው ስለ አንተነትህ ወይም ስለ ተግባርህ ለአንተ ወይም ለሌላ ሰው አድናቆት በተሞላበት መልኩ ሲናገር የሰማህበትን ጊዜ አስታውስ፡፡ ምን አይነት ስሜት ተሰማህ? ከዛ ሰው ጋር የሚኖርህስ ግንኙነት ምን ይመስላል?

ምናልባትም በዚህ የማድነቅ እሳቤ ውስጥ ብልጭ ያለብህ ጥያቄ ወይም እይታ ይኖራል፣ ምናልባትም በሽንገላ ሰበብ ወይም ተቀባይነት ለማግኘት በመፈለግ ብቻ የአድናቆትና የሚያወርዱ ሰዎች በምናብህ ውል ብለው ይሆናል፡፡ እኔም በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ትዝ የሚሉ ኩነቶች ስለመጡብኝ ነው፡፡ ‹‹እገሌ እኮ ሲደልል ተወኝ፣ ዛሬ ድለላ አብዝተሃል አባው...›› የምንልባቸው ጊዜ ትዝ ብለውኝ ነው፡፡ እነዚህና መሰል ሁኔታዎችን በተለያዩ የግንኙነት መስመሮች ላይ እንዳሉ እሙን ነው፡፡ እዚህ ጋር እያጋራኋችሁ ያለሁት ከዛ የተለየውንና በቅንነት በሰዎች ላይ የምናያቸውን በጎና አዎንታዊ ጠባያት ማድነቅና ማመስገን ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ሰዎችን አትሸንግል ብሎም አትዋሻቸው፡፡ ትክክል አይደለም የምትለውን ጠባይ ካየህባቸው እንዲያስተካክሉት አስታውሳቸው፤ ወይም ንገራቸው... ሸጋ ሰርተዋል ብለህ ካሰብክም አድናቆትህን መቸር አትዘንጋ፡፡ ይህን ካልን ዘንዳ አንድ አንድ የአድናቆት ጥቅሞችንና መንገዶችን እንመልከት፡፡

የአድናቆት ጥቅሞች በጥቂቱአድናቆት ሰዎች እያደረጉ ያሉትን ጥረት እንዲቀጥሉበት ያበረታታል፤ አንዱ የሰውነት ባህ

ሪያችን አድናቆት የሚያስቸሩ ተግባራትን ለመከወን መጣራችን ነውና፡፡ በዙሪያችን የሚገኙ በጎ ነገሮችን ማስተዋል እና ማድነቅ የደስተኛነት ስሜትን ከመቆስቆ

ሱ ባሻገር በህይወታችን በጎ ነገሮች የሚከሰቱበት ፍጥነት በአትኩሮታችን አማካኝነት እንዲያሻቅብ ያደርጋል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አዕምሮአችን እግረ መንገዱን የአትኩሮ ልምምድን ስለሚያደርግ ነው፡፡ አድናቆት በተቀባዩ ብቻ ሳይሆን በሰጪውም እንዲሁም በአካባቢው ላይም አዎንታዊ ስሜትን ይፈጥራል፡፡

ሌላው ሳይንሳዊ አግራሞትን የጫረው ግኝት፣ በአድናቆት ጊዜ የአድናቆት ሰጪውም ሆነ ተቀባዩ አንጎልና ሰውነታቸው ውስጥ የደስታ የመታደስ ስሜት እንዲሰራጭ የሚያደርጉ የሆርሞን (የሰውነት ኬሚካሎች) ለውጥ መካሄዱ ነው፡፡

ትክክለኛ አድናቆትን የመስጠት ጥበብ ሁነኛ የማህበራዊ መስተጋብር ክህሎት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች አድናቆት መስጠት ከባድ ይመስላቸዋል፡፡ ለምሳሌ፣ ያደጉበት አካባቢ አድናቆትን የመስጠት ክሂል ያልዳበረበት ሊሆን ይችላል፤ አልያም አንዳንዶች ስለራሳቸው ባላቸው ዝቅተኛ አመለካከት አድናቆትን ከመስጠት ይቆጠባሉ፡፡ ሲያስቡትም ይሸበራሉ፡፡

አድናቆትን የመስጠት ስሜት ጭራሹን የማይሰማህ ከሆነ ይህ ስሜት ከየትና እንዴት እንደመጣ ለማወቅ መሞከር ቀዳሚ ተግባርህ ይሁን፡፡ ምክንያቱም ያወክ እንደሆነ የእርምት እርምጃዎቹ ቀላል ይሆናሉ፡፡

ሁሌም አድናቆትን ፊት ለፊት መግለፀ አይጠበቅብህም፡፡ በስልክ ፅሑፍ መልዕክት ወይም በመደወል ሲቀጥልም የሚደነቀው ሰው ባልተገኘበት ቦታ ጭምር ስለ ሥራው ጥንካሬ ያለንን አድናቆት ለሌሎች ሰዎች ማጋራት አንዱ መንገድ ነው፡፡

አድናቆትን የመስጠት ጥቅም ዘርፈ ብዙ ሆኖ ሳለ የሚሰጥበት መንገድ ለሚኖሩን መስተጋብሮች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖ ወሳኝነት አላቸው፡፡ ግንኙነቶችን ለማሳደግና የግል ክህሎታችንን ለማጠናከር የሚረዱ ነጥቦችን እናንሳ፡፡

1. ቀጥተኛና ጠቋሚ አድናቆትአብዛኛውን ጊዜ ‹‹ጥሩ ሥራ ነው!›› ወይም ‹‹ጥሩ ተጫውተሃል›› የሚሉ አድናቆተችን እ

ንሰማለን፡፡ እንደዚህ አይነት አድናቆቶች የራሳቸው ቦታ ያላቸው እና ከምንም የተሻሉ ቢሆኑም አድናቆቱ ቀጥተኛና እንቅጩን መናገር ሲችል እውነተኛነቱ በትክክል የታየ አድናቆት መሆኑ እንዲጎላ ያደርገዋል፡፡

ለምሳሌ ‹‹በጨዋታው ላይ ያሳየኸው የአመራር ክህሎትና ተስፋ ያለመቁረጥ ስሜት በውስጤ ተነሳሽነት እንዲፈጠር ስላደረገ አመሰግናለሁ›› በማለት ተግባሩንና የተግባሩን ተፅዕኖ በመናገር የመልዕክቱን ጥንካሬ ማጉላት ይቻላል፡፡

2. አድናቆትን ማዘውተርአድናቆትን ባዘወተርን ቁጥር ሰዎች የዕድገት መንገዳቸውን ለማስተዋል ይረዳቸዋል፡፡ ይ

ህ በሰራው ዓለምና በአስተዳደር ዘርፍ ላሉ ሰዎች ሁነኛ ስልት ነው፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን ‹‹ሎሳዶ (3ለ1)›› የተሰኘ በአድናቆትና ገንቢ አስተያየት ላይ የሚያተኩር ሚ

ዛናዊ ንፅፅራዊ አመለካከት አለ፡፡ ይህም መስተጋብራዊ ቀመር እንደሚያስረዳው ለእያንዳንዱ አሉታዊ ወይም ይሄ ቢስተካከል በሚል ለምንሰጠው አስተያየት ሶስት አዎንታዊ ወይም አድናቆታዊ አስተያየቶችን የመስጠት ልምድን ያበረታታል፡፡ በተለያዩ የሥራ ቦታ ጥናቶች ላይ እንደሚታየው በጎ አስተያየቶችና (በማድነቅ... እባክዎ 17 የዞረ)

SUB-SAHARAN AFRICAN YOUTH and FAMILY SERVICES (SAYFSM)

Lakkoofsa bilbilaa፡ (651)644-­3983, (651)644-­1470, (612)554-­5676የስልክ ቁጥር፤ (651)644-­3983, (651)644-­1470, (612)554-­5676

SAYFSM Dhaaba Hawaasummaa namoota dhalootan Afrikaanota

ta’aniifi tajaajila garaagaraa kan laatudha.-‐Daddarbaa Vayirasii HIV/AIDS to’achuudhaafi dhaabni kun (﴾SAYFSM)﴿ barnoota fayyummaa barsiisa, Kondomii raabsa, akkasumas qorannaa

dhiigaa tola hojjeata-‐Qorannaan dhiigaa kun namoota leenjii ga’aa fi ragaa ogummaa qa-

baniin raawwatama

-‐Namnni fedha qoratamuu qabu waajjira SAYFSM keessatti yookiin bakka abbaan dhiimmaa itti amanetti qoratamuu danda’a-‐Namni nubiratti (﴾SAYFSM)﴿ qoratamu icitiin odeeffannoosaa sadarkaa cimaatti eegama.****************************************************************************

SAYFSM Dhaabbata MNsure wajjin walii galuudhan namoota In-

shuuraansii fayyaa hinqabneefi gargaarsa iyyannoo barreessuu laataHanga ammaatti jiraattota Minnesota tiifi gargaarsa heddu kennee jiraOdeeffannoon abbaan dhimmaa himatu hundi icitiidhaan eegamaMNsure tti iyyannoo galfachuu yoo barbaaddan beellama otuu hin qa-

batin yeroo gabaabaa keessatti dhimma keessan xumurattu

* SAYFSM በትዉልድ አፍሪካዊያን ለሆኑ ግለሰቦች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ሰብአዊ ድርጅት ነዉ፤* የ HIV/AIDSን ስርጭት ለመግታት ድርጅቱ (SAYFSM) ኮንዶም ያድላል፣ የጤና ትምህርትና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፣ ነጻ የደም ምርመራ ያከናዉናል፤* የደም ምርመራዉ በቂ ስልጥና ባላቸዉና ችሎታቸዉ በተመሰከረላቸዉ ባለሙያዎች ይከናወናል፤* HIV ለመመርመር ፍላጎት ያለዉ ማንኛዉም ግለሰብ በድርጅቱ በጽህፈት ቤት ወይንም ባለጉዳዪ ባመነበት ቦታ ምርመራዉ ሊከናወን ይችላል* በ SAYFSM ምርመራ የሚደረግለት ግለሰብ ሚስጥራዊ መረጃዉ በከፍተኛ ደረጃ ይጠበቃል። ***************************************************** SAYFSM ከMNsure ጋር በመተባበር የህክምና እንሹራንስ ለሌላቸዉ ግለሰቦች የማመልከቻ ቅጽ በመሙላት ሁኔታዉ በፈቀደ መሰረት እንሹራንስ እንዲያገኙ እርዳታ ያደርጋል* እስከ አሁን ድረስ ለብዙሃኑ የሚኒሶታ ነዋሪዎች በርካታ አገልግሎት ሰጥቷል* ባለጉዳይ የሚሰጠን መረጃ በሚስጥር ይጠበቃል* በ MNsure ድረግጽ (web site)የማመልከቻ ቅጽ ለመሙላት ከፈለጉ ያለቀጠሮ ጉዳይዎን በአጭር ጊዜ ዉስጥ ይፈጽማሉ

1885 University Ave. W #297 St. Paul, MN 551 04 Phone: 651-644-3983

ሳይኮሎጂ  

Page 19: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 19

በሊሊ ሞገስ

ቤት ውስጥ በቀላሉ ማዘጋጀት የሚችሉት ተፈጥሯዊ የፊት ቆዳ ማፅጃዎች፤ የሚከተሉት ሲሆኑ ቆንጆ ቆዳዎን በኬሚካል ከሚያቃጥክሉ በእነዚህ ተፈጥሯዊ ነገሮች በመጠቀም በተለይም የፊት ቆዳን ማጽዳት ይቻላል።

ዕንቁላልቅባታማ የሆነ ቆዳ የተለያዩ ችግሮች ሊጋለጥ ይችላል፡፡ ለ

ምሳሌ እንደ ብጉር የማያምር ገፅታን ሊፈጥር ይችላል፡፡ ስለሆነም ዕንቁላልን መጠቀም በፊት ቆዳ ላይ ያለን አላስፈላጊ ቅባት ያስወግዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ንፁህ እና ለስላሳ የፊት ቆዳን ይፈጥራል፡፡

አዘገጃጀት እና አጠቃቀምበጥንቃቄ የዕንቁላሉን ነጩን ክፍል ለይቶ በማውጣት ለስላ

ሳ እንዲሆን በደንብ መምታት፣ በመቀጠልም አፍና ዓይን አካባቢን በመተው ሌላውን የፊት ክፍል በሚገባ መቀባት እና እስኪደርስ ድረስ መጠበቅ፣ በመጨረሻም በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ፊት የተዋበ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ሎሚ፣ ማርና ለውዝአዘገጃጀት እና አጠቃቀምአንድ ሎሚ መጭመቅ እና ከአንድ የሻይ ማንኪያ ማርና ከአ

ንድ የሻይ ማንኪያ የለውዝ ዘይት ጋር በአንድነት ማዋሃድ፡፡ በመቀጠልም በፊት ቆዳ ላይ በመቀባት ማሸት (ማሳጅ ማድረግ) ከግማሽ ሰዓት በኋላ ለብ ባለ ውሃ ፊትን መታጠብ የሞቱ የቆዳ ህዋሳትን ከፊት ቆዳ ላይ ለማስወገድ ይረዳል፡፡

ማርና የተፈጨ አጃበጣም ምርጥ የሆነና በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ የማርና የተ

ፈጨ አጃን ውህድ በየቀኑ ለ15 ደቂቃ ያህል የፊትን ቆዳ በመቀባት (ማስክ ማድረግ) ፊትን ያማረ እና የፀዳ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡

ማር ፊትን በማፅዳትና በማለስለስ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ አጃ በሌላ በኩል ደግሞ ቆዳን ‹‹exfoliate›› በማድረግ የፊትን ቆዳ ንፁህ እና ያማረ ያደርጋል፡፡

የሎሚ ጭማቂሎሚ ሁሉም ሰው በቀላሉ እና በብዛት ሊያገኘው የሚችለው

የፍራፍሬ አይነት ሲሆን የሚሰጠውም ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በሎሚ ውስጥ የሚገኘው 6 በመቶ ያህሉ ሲትሪክ አሲድ ሎሚን ኮምጣጣ ጣዕም እንዲኖረው አድርጓል፡፡ ሎሚ በውስጡ ቫይታሚን ሲ፣ ካልስየም፣ ፎሌት፣ ቫይታሚን ቢ1፣ ቫይታሚን ቢ2፣ ቫይታሚን ቢ3 እና ቫይታሚን ቢ5፣ አይረን፣ ዚንክ፣ ፎስፈረስ፣ ፖታሺየም በተጨማሪም ስኳር እና ፋይበር ይይዛል፡፡ የሎሚ ጭማቂው በቆዳ ላይ የሚገኙ አላስፈላጊ የሆኑ ቅባታማ ቆሻሻዎችን በጥሩ ሁኔታ ያስወግዳል፡፡

በተለያዩ ጊዜ ፊት ላይ የሚወጡ ብጉር እና መሰል ነገሮች የቆዳን ውበት ያደበዝዛሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ችግሮች በሚያጋጥሙ

በት ጊዜ የሎሚ ችማቂን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ያህል ተቀብቶ በመቆየት እና በመጨረሻም በመታጠብ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ ሎሚ የሞቱ የቆዳ ህዋሳትን በማስወገድ የፊት ቆዳ ደማቅ እና ፅዱ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ይህ ነው የማይባል ትልቅ ጠቀሜታ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ስቲም ማድረግ (Steaming)

ስቲም ማድረግ በብዙ የዓለማችን ክፍል እጅግ በጣም የተለመደ የቆዳን ውበት መጠበቂያ ሁነኛ መንገድ ነው፡፡ የፊት ቆዳን ስቲም ማድረግ የተለያዩ የቆዳ ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል፡፡ በየጊዜው ስቲም ማድረግ በቆዳ ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመቀነስ የፊት ቆዳን የፈካ እና ያማረ ያደርጋል፡፡

የምግብ ጨውጨው ምግብን ማጣፈጥ ብቻ ሳይሆን የፊት ቆዳንም ማሳመ

ር ይችላል፡፡ ጨው የባክቴሪያ ጠላት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ልዩ ልዩ ‹‹ኢንፌክሽኖችን›› ሊቀንስ ይችላል፡፡ ነገር ግን የምግብ ጨው ቆን ደረቅም ሊያደርግ ይችላል፡፡ የምግብ ጨውን ለፊት ቆዳ ተስማሚ እንዲሆን ለማድረግ ከተፈገለ ከትንሽ የወይራ ዘይት ጋር መቀላቀል እና ለአስራ አምስት ደቂቃ ያህል ውህዱን የፊት ቆዳ ላይ በማሸት፤ በመጨረሻም መታጠብ፡፡ ቆዳ ላይ ያሉ የሞቱ ህዋሶችን ለማስወገድ ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የፊት ቆዳን በጣም ንፁህ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የሴቶች  ጤና/Womens Health

ቤት  ውስጥ  በቀላሉ  ማዘጋጀት  የሚችሉት  ተፈጥሯዊ  የፊት  ማጽጃዎች  

ባለቤት.... ከገጽ 7 የዞረአመታት ተቆጥረዋል:: ይህ የሰሜን ኢትዮጵያ የርስ በርስ ጦ

ርነት ለጊዜው በመከላከያ ሰራዊት ቢሰክን እንኳን ሙሉ ለሙሉ የሚቆም አይነት አይሆንም:: ወደፊት ይህ አካባቢ ጥይት ሳይሰማበት በሰላም ይኑር ከተባለ -­ የህወሃት ህገ ወጥ መስፋፋት መቆም ይኖርበታል:: እስካሁን የወሰደውን መሬት ለታሪክ ፍርድ ትተን “ለምን?” ብለው የመብት ጥያቄ በመጠየቃቸው የታሰሩትን መፍታት -­ ለሞቱት የደም ካሳ መክፈል ይኖርበታል:: ከጥንትም ቢሆን -­ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመን ጭምር ቤጌምድር -­ በፍቅር ካልሆነ በቀር በግድ እና በጦርነት ተገዝቶ አያውቅምና ልብ ያለው ልብ ይበል!

ከላይ በታሪካዊ ዳራው ለማሳየት እንደሞከርነው ቤጌምድር (ቅማንትንም መጨመር ይቻላል) በአማራው እና በትግራይ ህዝብ ሲለማ ቆይቷል:: ህዝቡ በጋብቻ እና በቋንቋ እርስ በርሱ የተሳሰረ ነው:: ችግር እየተፈጠረ ያለው -­ መሬቱም ሚስቱም ጠመንጃ በያዙ የህወሃት ሰዎች መነጠቁን ሲቀጥል ነው:: ስለሆነም ስሜን ጎንደር ወይም ቤጌምድር ላይ እርቅ እና ሰላም እንዲመጣ የህወሃት ሰራዊት በህገ ወጥ መንገድ መስፋፋቱን ማቆም አለበት:: ስለተገደሉት ነዋሪዎች “ይቅርታ” መጠየቅ አለበት:: በአካባቢው ዘላቂ የሆነ ሰላም ማምጣት ካስፈለገ ደግሞ ይህ በኢትዮጵያዊነቱ ፍጹም ኩራት ያለው ህዝብ -­ (ሰሜን ወይም ምእራብ ሳይባል) ከመረብ በታች ከተከዜ ወዲህ ያለው ህዝብ ቢያንስ ራሱን እንዲያስተዳድር እድል ሊሰጠው ይገባል:: ይህ ካልሆነ ግን ስሜን ላይ የተጀመረው የአማራው እና የትግራይ የግዛት ጦርነት -­ የግዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በማናቸውም ዘመን መልኩን ሊቀይር እንደሚችል -­ በውድም ሆነ በግድ የምንቀበለው እውነት ነው::

በልጆቼ... ከገጽ 8 የዞረበሚደረገው ነገር ተመጣጣኝ ተሳትፎ የማይኖራቸው ከሆ

ነ ድምፁ ያልተሰማው አካል መነጫነጩ አይቀሬ ነው፡፡ መነጫነጭ የሚመጣው ያልተመቸ ነገር ሲኖር ነው፡፡ ባለቤትህ ቢመቻት ኖሮ የምትነጫነጭና አንተንም ሰላም የምትነሳህ ይመስልሃል? እርሷ ስትነጫነጭ እርሷን ከመኮነን ይልቅ ያልተመቻት ነገር ምን እንደሆነና እንዴት ቢሆን እንደሚመቻት ብትጠይቃት ኖሮ መፍትሄውን ታገኝ ነበር፡፡

በተለይ ‹‹የእኔ ማደግ እያበሳጫት ቤት ውስጥ ዘወትር እየነዘነዘችኝ እረፍት ትነሳኝ ጀመር›› የሚለው ሐሳብ ገርሞኛል፡፡ ሁለት ሆናችሁ ማደግ ነበረባችሁ እኮ፤ አንተን እርሷ እኮ እንደ አንድ ሰው ናችሁ-­ ባልና ሚስት ናችሁ፡፡ በዚህ አባባል መሰረት አንድነታችሁ በትዳራችሁ ውስጥ በተግባር እየታየ አልነበረም፡፡ እርሷን ጥለሀት አንተ ብቻህን ስታድግ መበሳጨቷ ተገቢ አይመስልህምን? አንተ ራስህን በእርሷ ቦታ ብታስቀምጥና እርሷ አንተን እንዲህ ብታደርግ ተመሳሳይ ነገር የማይሰማህ ይመስልሃል?

የትዳር ግንኙነት ሰላማዊና ዘላቂ የሚሆነው ባልና ሚስት በኑሯቸው ውስጥ እኩል ተሳታፊ ሲሆኑ ነው፡፡ አንዱ ለሌላው ዕድገት መልካም ነገር ሲያደርግ፣ የሁለቱም ፍላጎት እርካታ እንዲያገኝ ጥረት ሲደረግ ቅንዓትና መጎዳት ላይኖር ይችላል፡፡

ስለዚህ ወደ ፊት ትዳር ለመመስረት የምታስብ ከሆነ ሚስትህን በኑሮህ ውስጥ እኩል ተሳታፊ አድርጋት፡፡ የሁለታችሁም ድምፅ እኩል መሆን አለበት፡፡ ለሁለታችሁ ኑሮ ዕድገት ሁለታችሁ አብራችሁ መነጋገር፣ ማቀድ፣ መተግበርና መገምገም ይኖርባችኋል፡፡በ‹‹እኔነት›› ፋንታ ‹‹እኛነት›› መንገስ ይኖርበታል፡፡ በትዳር ግንኙነት ውስጥ እኔነት በእኛነት ውስጥ ይዋጣል፣ ይህም በኃይል ሳይሆን እያንዳንዱ በገዛ ፈቃዱ ራሱን ለጋራ አላማ በመስጠት የሚመጣ ውጤት ነው፡፡

(2.) የገንዘብ አጠቃቀም፡-­ ገንዘብን ማጣትም፣ ማግኘትም የትዳር ግጭት መንስኤ የሚሆንበት ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ በአንተ የቀድሞ የትዳር ህይወት ውስ ገንዘብ ማግኘትህ ከሚስት ጋር የነበረውን ግንኙነት እንዳበላሸ ገልፀሃል፡፡ ገንዘብን በስጦታ ማግኘት መልካም ነገር ነው፤ በመሰረተ ሐሳብም የአንተ ገንዘብ ይባላል፡፡ በስጦታው ገንዘብ ንግድ ጀመርክ፡፡ እንግዲህ አንዱ ራስህን መጤቅ ያለብህ ነገር በዚህ ገንዘብ ይህን አዲስ ስራ ስትጀምር ባለቤትህን አማክረሃት ነበር ወይ? በደብዳቤህ ውስ በአብዛኛው አንተ እርሷን ስትመክራት እንጂ የእርሷን ምክር ስትሰማ ወይም ስትፈልግ አትታይም፡፡ በጋራ ምክክር ያልተጀመረ ስራ ምንም ያህል ትርፋማ ቢሆን የትዳር ጓደኛን ላያረካ እንደሚችል እወቅ፡፡

ይህ ብቻ ሳይሆን ከንግዱ የሚገኝ ትርፍ/ገንዘብ ደግሞ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የጋራ ስምምነት አልነበረም፡፡ ንግዱንና ገንዘቡን በሙሉ የተቆጣጠርከው አንተው ራስህ ነበር፤ ባለቤትህ ከጨዋታ ውጭ ነበረች፡፡ እርሷ ጠያቂ/ለማኝ አንተ ሰጪ ነ

ህ፡፡ ለኑሮ እርሷ ገንዘብ ስትጠይቅህ፣ አንተ እርሷን ገንዘብ ወዳጅ /አባካኝ/ የአንተ ዕድገት ተቀናቃኝ እንደሆነች ቆርጠርካት እንጂ ‹‹ንብረቱ የጋራችን፣ አጠቃቀሙም በወል ስምምነት ላይ የተመሰረተ ይሁን›› የሚል መርህን አልተከተልክም፡፡ ስለዚህ ባለቤትህ አንተ ከእርሷ ይልቅ 25 ሺ ትርፉን አብልጠህ እንደምትወድ ገምታ ከአንተ እንደ ተለየች ማሰብ ይቻላል፡፡

የቀድሞ ባለቤትህ መምህርት ናት፤ ስለዚህ ኑሮን በእቅድ መምራት አታውቅም ማለት ያስቸግራል፡፡ የመምህርነት ስራ ከዕቅድ፣ ትግበራ፣ ክትትልና ግምገማ ጋር ቁርኝት አለው፡፡ በንግዱ ስራና በገንዘብ አጠቃቀሙ ላይ እርሷን ብታሳትፋት ኖሮ ትዳሩም ንግዱም አይፈርስም ነበር፡፡

ስለዚህ ለወደፊቱም በኑሮ ውስጥ በተለይ ደግሞ በገንዘብ አጠቃቀም ዙሪያ ከትዳር ጓደኛህ ጋር ተነጋገር፤ ለቤተሰባችሁ የገንዘብ አጠቃቀም መመሪያ/ደንብ ይኑራችሁ፡፡ በእቅድና በበጀት ላይ መሰረት ያደረገ አጠቃቀም ካላችሁ፣ በገንዘብ ላይ የመጋጨታችሁ ዕድል ይቀንሳል፡፡

(3.) የግጭት አፈታት፡-­ በትዳር ግንኙነት ውስጥ ግጭት አይቀሬ ነው፡፡ የግጭቱ መጠንና አይነት ይለያይ እንደሆነ እንጂ በሁሉም ትዳር ውስጥ ግጭት አለ፡፡ ግጭት መኖሩ አይቀሬ ቢሆንም ግጭት እንዳይመጣ ወይም እንዳይበዛ ለማድረግ እያንዳንዱ የመከላከል ስራ መስራት ይችላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ባልና ሚስት ግጭት ሲከሰት አብሮ በመነጋገር መፍታትና ከክስተቱ ለወደፊት በጎ ነገር መማር ይችላሉ፡፡ በሁሉም ትዳር ውስጥ ግጭት ቢኖርም ሁሉም ትዳር አይፈርስም፡፡ ልዩነት የሚያመጣው የግጭት አያያዙ ነው፡፡ ብስለት ባላቸው ባለትዳሮች መካከል ግጭት ሲከሰት ግንኙነታቸውን ከማፍረስ ይልቅ ግጭቱን ለትምህርታቸው ይጠቀሙበታል፡፡

በአንተ የቀድሞ የትዳር ግንኙነት ውስጥ ግጭት ነበር፡፡ አንተ የግጭቱ መንስኤ ምን እንደሆነ ከባለቤትህ ጋር ከመነጋገር ይልቅ መንስኤው እርሷ እንደሆነች በማሰብ እርሷን መምከር ወይም መኮነን ነበር፡፡ ግጭቱ እንዲከሰትና እንዲባባስ አንተም ድርሻ እ

ንዳለህ ያሰብክ አይመስልም፡፡ ስለዚህ እርሷን ለማከም ብዙ ጥረት አድርገሃል፡፡ ነገር ግን ራስህን አላከምክም፣ ስለሆነም በሽታው አልተፈወሰም፡፡ በመጨረሻ ላይ ትዳራችሁን ገደለ፡፡

‹‹ዳግም ወደ ሲኦል መመለስ አልፈልግም›› የሚለው አባባልህ ገርሞኛል፡፡ በእርግጥ ሰዎች ወደ ሲኦል ይሄዳሉ እንጂ ሲኦል ወደ ሰዎች አይመጣም፡፡ የትዳር ሲኦልን የመረጥከው አንተው ነህ፣ ትዳርህን ሲኦል ያደረከው አንተው ነህ እንጂ ሌላ ሰው ትዳርህን ሲኦል አላደረገውም፡፡ የአንተው ማንነት፣ አስተሳሰብና ድርጊትህ የትዳር ግንኙነትህ የስቃይ ስፍራ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አሁን ትዳርህ ስለፈረሰ፣ በአካል ከቀድሞ ባለቤትህ በመራቅህ ከሲኦል የወጣህ መስሎሃል፡፡ ነገር ግን አሁንም በልብህ ውስጥ ጥላቻ፣ ቂምና በቀል ሞልተዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ የቀድሞ ባለቤትህ ፊት ማየት አትፈልግም፡፡ ምናልባት ሌላው ሲኦል ደግሞ በአንተው ውስጥ ሆኖ እያሰቃየህ ሊሆን ስለሚችል በህጋዊ መንገድ የትዳራችሁ ፋይል እንደተዘጋ ሁሉ አንተም ያለፈውን የህይወት ፋይልህን ዘግተህ አዲስ ምዕራፍ ብትጀምር መልካም ነው፡፡ የቀድሞ ባለቤትህ አሁን ሚስትህ አይደለችም፤ ነገር ግን የውድ ልጆችህ እናት ናት፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ፍፁም መለየትና ፊቷን ላለማየት የምትችልበት ሁኔታ ላይፈጠር ይችላል፡፡ ዓይንህ በማየት ባያመጣትም፣ ያልተፈወሰው የህይወትህ ገጽ በትውስታ ያመጣታል፡፡ ስለዚህ እንደ ባልና ሚስት ሳይሆን ባላችሁበት ቦታ እንደ አባትና እናት ሆናችሁ ለልጆቹ የወደፊት ዕድገት መልካም ነገር ብታደርጉ የተሻለ እንደሆነ አስባለሁ፡፡

(4.) የፍቺ ውጤቶችን አስተውል፡-­ ሃያ አምስት ዓመት የቆየህበትን ትዳር ማፍረስ ቀላል አይደለም፡፡ የትዳሩ እርካታ ምንም ቢሆንም ባለትዳር ነበርክ፡፡ ፍቺ የህይወትን አቅጣጫ ግራ ያጋባል፡፡ በተለይ ድንገት የተከሰተ ፍቺ ያስደነግጣል፡፡ የህይወትህ ጉዞ ያለጨልማል፣ ስለተቃራኒ ጾታም አሉታዊ አስተሳሰብ እንዲኖር ያደርጋል፡፡

ከቀድሞ ባለቤትህ የተነሳ ሴቶችን ሁሉ እንደጠላህ ተናግረሃል፡፡ ይህ ለጊዜው የሚጠበቅ ምላሽ ነው፣ ከቆየብህ ግን ጤናማ

ወዳልሆነ ጠባይ ይሻገራል፡፡ በመሰረቱ ወንዶች ሁሉ እንደ አንተ እንዳልሆኑ፣ ሴቶችም ሁሉ እንደ ቀድሞ ባለቤትህ አይደሉም፡፡ ሴቶች ሁሉ የሚመሳሰሉበት ነገር ቢኖራቸውም፣ ልዩነት አላቸው፡፡ የቀድሞ አነዳድህ ካልተለወጠ በስተቀር ወደፊት አንተን የሚያውቁ ሴቶች በአንተ የትዳር መኪና ላይ ላይሳፈሩ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡

በህይወት ጎዳና ላይ መልካም ነገር እንዳለ ሁሉ ክፉ ነገርም ያጋጥማል፡፡ ጤናማ አዕምሮ ያለው ሰው ፍቺን አስቦ ትዳርን አይመሰርትም፡፡ ፍቺ ግን በግል ስህተት ወይም በውጫዊ ጫናዎች ሊከሰት ይችላል፡፡ የአንተ ትዳር ከላይ በተጠቀሱ ምክንያቶች ፈርሷል፡፡ አሁን ያለህ አማራጭ ሳታገባ መኖር ወይም እንደገና ማግባት ነው፡፡ ሁለቱም አማራጮች የየራሳቸው ጥቅምና ተግዳሮ አላቸው፡፡ ግን ለሁለቱም አማራጮች መሰረታዊ መነሻ መሆን ያለበት የቀድሞ ህይወትህን መፈወስ ነው፡፡ ያለፈውን የህይወትህን ምዕራፍ ያልተፈቱ ችግሮችን ይዘህ ወደፊት መራመድ አትችልም፡፡ ለህይወት ትልቅ ሸክም ይሆኑና ጉዞህን ያሰናክላሉ፡፡ ስለዚህ የማያስፈልጉ ኮተቶችን (ትክክለኛ ያልሆኑ እሳቤዎችን፣ ክፉ አስተሳሰቦችን፣ የቂምና በቀል ስሜትን ወዘተ...) አራግፋቸው፡፡ ካለፈው ክፉ የህይወት ገጠመኝ በጎ ነገሮችን ለመማር ሞክር፡፡ ከስህተትህ በሚገባ ከተማርክ ተመሳሳይ ስህተት ላትፈፅም ትችላለህ፡፡

ለህይወትህ ውድቀትና ስኬት ኃላፊነት የማትወስድ ከሆንክ፣ ‹‹ሰው እንዲህ አደረገኝ›› እያልክ የምትኮንን ከሆንክ ወደፊትም ለውጥ አታመጣም፡፡ አንተ ስለራስህ የምታስበውን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ስለአንተ የሚሉትንም አድምጥ፣ ትክክለኛ የሆነውን ተቀበልና አስተካክል፡፡

ሊቨርፑል.... ከገጽ 24 የዞረ

የማጥቃት እንቅስቃሴዎችን ለማስጀመር ረዥም ኳሶችን የሚጥል እና ወደፊት በመገስገስ የማጥቃት እንቅስቃሴውን የሚያግዝ ተከላካይ ሊሆን ይችላል፡፡

ከማርቲን ስከርትል በሌላኛው አቅጣጫ የሚጫወተው ማማዱ ሳኮ ነው፡፡ ፈረንሳዊው ረዘም ላለ ጊዜ ከስኳዱ ርቆ ቆይቷል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ከክለቡ ጋር የፈጠረው አለመግባባት (ከኤቨርተን ጨዋታ ውጪ በመደረጉ) እና ያጋጠመው ጉዳት ናቸው፡፡ ሮጀርስ በተከላካይ መስመሩ ሳኮን ለመጠቀም የተገደዱት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቡድኑን የተቀላቀለው ዴያን ሎቨረን በመጎዳቱ ነበር፡፡ የቀድሞው የፒኤስጂ ተጨዋች አልፎ አልፎ ስህተቶችን የሚፈፅም ቢሆንም እስካሁን ባለው ሂደት የሊቨርፑል ምርጡ ተከላካይ እርሱ ነው፡፡ አቋሙ ጥሩ ከመሆኑ የተነሳ ሎቨረን ከጉዳት ሲመለስ እንኳን ቦታውን ሲነጥቀው አልቻለም፡፡ ሳኮ እና ቻን ውጤታማ በመሆናቸው ከስከርትል ትከሻ ላይ ጫና ቀንሷል፡፡

ሮጀርስ ብራድ ጆንሰን ወደ ቡድኑ የቀላቀሉት ሲሞን ሚኞሌን እንዲተካ ነበር፡፡ ነገር ግን አሰልጣኙ ለቤልድየማዊው የመውጫውን በር ሊያሳዩት አልቻሉም፡፡ የቀድሞው የሚድልስብራ ተጨዋች ብዙም ሳይቆይ ተጎዳ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን የሚኞሌ አቋም እጅግ የወረዳ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ሳምንት ወዲህ መሻሻል አሳይቷል፡፡ ምስጋናውን ሊወስዱ የሚገባው በአማካይ ክፍሉ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ያለው ሉካስ እና የሊቨርፑል የተከላካይ መስመር ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ወደ 3-­4-­2-­1 የተደረገው ሽግግር በርካታ ተጨዋቾችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ ሉካስ በአሁኑ ቡድን ውስጥ የማይተካ ተጨዋች ሆኗል፡፡ ብራዚላዊውም ቢሆን እያበረከተ ያለው ድንቅ ግልጋሎት እስከ ውድድር ዘመኑ ፍፃሜ በአንፊልድ እንደሚያቆየው ያምናል፡፡ በአሁኑ ወቅት በጉት ላይ የሚገኘው አዳም ላላና ይህኛው ፎርሜሽን ምቾት እደሚጠው ተናግሯል፡፡ በውድድር ዘመኑ መጀመሪ አካባቢ ሜዳ ውስጥ የሚያደርገው ጥረት ፍሬ ቢስ የነበረው ፊሊፕ ኩቲንሆ ከዓለማችን ምርጥ አጥቂዎች እንደ አንዱ መጫወት ጀምሯል፡፡ የፈጠራ ብቃቱ ግሩም ነው፡፡ ከአጥቂ ጀርባ በመሆን ሚናውን በአግባቡ በመወጣት ላይ ነው፡፡ ለቡድን ጓደኞቹ ተከላካይ ሰንጣቂ ኳሶችን ያሾልካል፡፡

የዤራርድ እንቆቅልሽ አሁንም አልተፈታም፡፡ ነገር ግን አዳም ላላና በመጉዳቱ ሊቨርፑልን በቅርቡ እንደሚለቀቅ በመነገር ላይ ያለው የቡድኑ አምበል ለጊዜውም ቢሆን በሚመርጠው የአጥቂ አማካይ ሚና የመጫወት ዕድል ያገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ጆርዳን ሄንደርሰን ይበልጥ ውጤታማ በሚሆንበት የሜዳው ክፍል የሚጫወትበት አጋጣሚ ይፈጠርለታል፡፡

ከስህተቱ የሚማር እና ጥፋቱን ለማስተካከል የሚጥር ሰው ክብር እና አድናቆት ይገባዋል፡፡ ይህ መርህ በሁሉም መስኮት ይሰራል፡፡ ታዲያ ሮጀርስ ምስጋና አይገባቸውም?

EMNT MultiCultura l Service

እምነት መልቲካልቸራል ሰርቪስ* የኢሚግሬሽን ፎርሞችን መሙላት* ውክልና መጻፍ

*የአማርኛና ትግርኛ ጽሁፍና ትርጉም ሥራበተጨማሪም

ፍቺ በስምምነት ፎርሞችን እንሞላለን

Address: 1821 University Ave. W. Suite S-­121 Saint Paul, MN 55104

በተለመደው ስልክ ይደውሉልን

651-494-7067

Page 20: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 20

ሥጋ.... ከገጽ 16 የዞረ

የነበሩ ጓደኛሞች የተኮራረፉ ይመስል ድንገት ዝም ይላሉ፡፡ በፍፁም ትኩረት ቁርጡን ያወራርዳሉ፡፡ እንዲያውም አንዳንድ የከተማችን ወይዛዝርት በዚህ መካናቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ጮማ ያልገባበት ቁጥር ያወራረደ ግለሰብ የመተዳደሪያ ደንቡን እንደጣሰ ነው አሉ የሚያስቆጥረው፡፡

ዋጋው እያሻቀበ፣ ኪስ እየተፈታተነ የሚገኘው ክትፎም ቢሆን በባህሉ የሚፈቀደው ወይ ጥሬውን ወይም ለብ ለብ ተደርጎ እንዲበላ ነው፡፡ በዚያም ላይ በቅቤ መጥለቅለቅ እና በሚጥሚጣ መታሸት ይኖርበታል፡፡

እነዚህ ወገኖች እጆቻቸውን በሳሙና ሙልጭ አድርገው ታጥበው ነው መታጠብ የማይሆንለትን ስጋ በጥሬው የሚወስዱት፡፡ እንግዲህ ልብ በሉ! ከብቱ ሲታረድ፣ ሲበለት፣ መኪና ላይ ሲጫን፣ ከመኪና ሲወርድ፣ ሥጋ ቤቱ መስቀያ ላይ ሲሰቀል፣ በቆራጩ ሲቆረጥ ዝምቦችና ተሕዋሲያን ዝም ብለው በትዝብት የሚያልፉት ይመስላችኋል?

እስኪ በዚህ ዙሪያ በከተማችን ዙሪያ በጥሬ ሥጋዎች ላይ ያተኮሩ 3 ጥናቶችን ላካፍላችሁ፡፡ ጥናቶቹ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ ከ2003-­2007 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት የተሰሩ ናቸው፡፡ ቀዳሚው ጥናት 24 ያዲሳባ የገበያ አዳራሾች የፈተሸና 300 የጥሬ ሥጋ ናሙናዎችን በላቦራቶሪ የመረመረ ነበር፡፡ Salmonela የተባሉ አደገኛ ተህዋስያን በ14.7 በመቶ ናሙናዎች ተገኝቷለ፡፡ በሁለተኛው ጥናት ተመራማሪዎቹ 738 የጥሬ ሥጋ ናሙናዎችን መርምረው ከበሬ ሥጋ 8 በመቶ፣ ከበግና ፍየል ሥጋ 2.5 በመቶ የደም ተቅማጥና የደም መመረዝ የሚያስከትለውን ስሙ Escherchia coli የተባለ ተህዋስያን ለመለየት በቅተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 22.6 በመቶዎቹ ለሶስትና ከዚያም በላይ መድሃኒቶች አይበገሬ ናቸው፡፡ የመጨረሻው ጥናት 540 ናሙናዎችን መርምሮ ሙቀት መቋቋም የሚችለውንና ለአደገኛ ተቅማጥ የሚዳርገውን campylobacter jejuni ተህዋስያን በ21.7 በመቶ የዶሮ ሥጋ፣ በ10.5 በመቶ የበግ ሥጋ፣ በ8.5 በመቶ የአሳማ ሥጋ፣ በ7.6 በመቶ የፍየል ሥጋ፣ እና በ6.2 በመቶ የበሬ ሥጋ ናሙናዎች ለይተዋል፡፡ እነዚህ ብርቅዬ የሀገራችን ምሁራን በመጨረሻ እንዲህ ሲሉ መከሩን፡፡ ሥጋ ስትመገቡ በአግባቡ በስሎ ይሁን፤ የግል እና የሥጋ ንፁህና ከከብት ማርቢያ ቦታ እስከ ገበያ ድረስ ይጠበቅ!

ሥጋ በልነት እና ሃይማኖትእንደ ሥጋ ከእምነት ጋር የተቆራኘ ምግብ ያለ አይመስለኝም፡

፡ ለዚህም ይመስላል የሃይማኖት አባቶችን ቄራ ድርጅቶች ውስጥ መመደብ ያስፈለገው፡፡ አንድ ሰው እንደሚከተለው ሃይማኖት አስተምህሮ ስጋ ሊመገብ፣ ላይመገብ ወይም ሊመርጥ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሙስሊሞች ሃላል ያልሆነ ስጋ አይበሉም፡፡ ከብቱ እስኪታረድ ድረስ በህይወት መቆየት ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡ ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ከብት በራሱ ከሞተ አርደው አይበሉትም፡፡ አይሁዶች ደግሞ ስጋው ኮሸር ካልሆነ አይፈልጉትም፡፡ ይህም ማለት ከብቱ እስኪታረድ ድረስ በህይወት መቆየት ብቻ ሳይሆን ራሱን ሳይስት መጠባበቅ ስለሚኖርበት በቄራዎች የሚከናወነውን የቅድመ እርድ ራስ ማሳት ግብር አጥብቀው ይቃወማሉ፡፡ ቀዳሚት ሰንበትን አክባሪ አድቬንቲስቶች አብዛኛዎቹ ‹‹ሥጋ ለምኔ›› እፅዋት በል ናቸው፡፡ የሂንዱ እምነት ተከታዮች የከብትና የዶሮ ሥጋ አይመገቡም፡፡ የኦርተዶክስ ተዋህዶ፣ የእስልምና እና የአይሁድ እምነት ተከታዮች የአሳማ ስጋ እንዳይነኩ ሐይማኖታዊ ክልከላ አለባቸው፡፡

ዓሣ የፆም ወይስ የፍስክ ምግብ?ይህ ጥያቄ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ከረጅም ጊዜያት አንስቶ

ሲያወዛግብ የቆየ ነው፡፡ እስካሁንም እልባት ያገኘ አይመስልም፡፡ በተወሰኑ ቦታዎች ካልሆነ በስተቀር ሆቴሎች በፍስክ ወራት የዓሣ ምግቦችን አያዘጋጁም፤ ለምን ብትሏቸው ‹‹በቃ ፆም አልገባም!›› ብለው ሊገረምሟችሁ ሁሉ ይችላሉ፡፡ በእነርሱ አመለካከት ዓሣ እንደ ቃሪያ፣ ሽንኩርት፣ ሰላጣ የመሳሰሉት ሁሉ የዕፅዋት ተዋፅኦ ነው ማለት ነው፡፡ ዓሣን በፆም ለመመገብ ምንም አይነት የሐይማኖት መሰረት በአሁኑ ጊዜ የለም፡፡

በ1985 ዓ.ም በዋለው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ዓሣ የሥጋ ዘር ነው፣ ስለሆነም በፆም ወራት መበላት የለበትም ብሎ ከዚህ በፊት የነበረውን ውሳኔ አጽንቶ አስተላልፏል፡፡ ባለምግብ ቤቶች ከዚህ አኳያ የዓሳ ምግብ አቅርቦታቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጤናማ የሥጋ ምርጫዎችየስነ ምግብ ባለሙያዎች ነጭ ብለው የሚጠሯቸው የሥጋ ዘ

ሮች በልክ ከተወሰዱ ለጤና ይበጃሉ፡፡ ዓሣ በኦሜጋ 3 ስብ የበለፀገ በመሆኑ ለልብና ደምስሮች ደህንነት ሲባል በሳምንት ሁለት ቀናት መመገብ እንዳለብን የሚያስገነዝብ መመሪያ አለ፡፡ በተለይ ቅባታዎቹ እንደ ሳልመን፣ ቱና፣ ሰርዲን... ወዘተ የመሳሰሉት ዝርያዎች ለልብ ዘብ በመቆም የሚስተካከላቸው የለም፡፡

ዶሮ ከዓሣ ቀጥሎ በጤናማ የሥጋ ምንጭነት ይታወቃል፡፡ ሆኖም በቀዶው ውስጥ የተከማቸ ጮማ ስላለ ይህን ማንሳት እንጂ መመገብ የለብንም፡፡ ታዲያ በሳምንት ከሁለት ቀናት በላይ ዶሮንም ቢሆን መመገብ ለጤና አስፈላጊ አይደለም፡፡ የዶሮና ዓሣ ሥጋዎች በጭስ ከታጠኑ፣ በጨው ከታጀሉ፣ ወይም በከፍተኛ የሙቀት ኃይል ከተጠበሱ ጠቃሚ መሆናቸው ቀርቶ ጎጂ ይሆናሉ፡፡ እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

ቀይ ሥጋን አስመልክቶ የተሰጠ ብያኔዓለም አቀፉ የነቀርሳ ምርምር ተቋም የቀኝና የግራውን ክርክ

ር ካዳመጠ በኋላ የሚከተለውን ብያኔ አሳልፏል፡፡ ሥጋ ሳይበሉ መኖር ይቻላል፤ መብላት ለሚፈልጉ ግን በሳምንት ቢበዛ ግማሽ ኪሎ ይሁን! ይህም በቀን 71 ግራም ቀይ ሥጋ ማለት ነው፡፡ ላመል ካልሆነ በስተቀር ይህችን የምታክል ሥጋ ብትቀርም አይቆጭ፡፡ በከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎ therefore ብለው የሚጠሩትን ስጋ ጣል ጣል ወጥ አስታወሰኝ፡፡

ኢቦላ.... ከገጽ 17 የዞረ

የኢቦላ በሽታ ምልክቶችአንድ ሰው ከኢቦላ በሽተኛ ጋር ቢነካካና በቫይረሱ ቢጠቃ የ

በሽታው ምልክት ከ2-­21 ቀን ውስጥ ይታይበታል፡፡ በሽታው ሲጀመር ከወባ፣ ከታይፎይድ አጀማመር የተለየ አይደለም፡፡ በኢቦላ የተጠቃ ሰው ድንገተኛ የሆነ ራስ ምታት፣ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት፣ ድቀት፣ የጡንቻ መቆረጣጠም፣ የጀርባ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ ትኩሳት፣ ተቅማጥ፣ ደረቅ ሳልና የጉሮሮ ህመም በመጀመሪያው ሳምንት ያሳያል፡፡ ከዚያ መዘዙ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ደም በአፍ በአፍንጫ ይመጣል፡፡ ደም የተቀላቀለበት ተቅማጥ፣ በሴቶችም ከማህፀን ደም መፍሰስ ይኖራል፡፡ ቆዳ ላይ ቀይ ሽፍታ ይወጣል፡፡ የደም መፍሰሱ መጠን እየበዛ ሲመጣ የሰውነት ፈሳሽ እየተመናመነ ይሄዳል፡፡ ሌሎችም ተያያዥ ችግሮች አ

ብረው ስለሚኖሩ በሽታው ለህልፈተ ህይወት ያጋልጣል፡፡ በኢቦላ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ይሞታሉ ተብሎ ይገመታል፡፡

እንዴት ይታወቃል?አጀማመራቸው ላይ ከኢቦላ ጋር የሚያምታቱ ብዙ በሽታዎ

ች አሉ፡፡ ነገር ግን ምልክቱ እየገፋ ሲሄድ ኢቦላ ጭምብሉ እየወለቀ ይመጣል፡፡ይሁን እንጂ በዛም ደረጃ ቢሆን ከኢቦላ ጋር የሚመሳሰሉ በሽታዎች አሉ፡፡ ስለዚህ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ከደም ወይም ከሌሎች ሰውነታችን ካሉ ፈሳሾች የቫይረሱን አንቲጂን ወይም የአር.ኤን.ኤ ቅደም ተከተል ተፈልጎ ሲገኝ ነው፡፡ እውነቱን ለመነጋገር በሽታው እኛ ሀገር ቢከሰት ይህን አይነት ምርመራ ሊያደርጉ የሚችሉ ሆስፒታሎች እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡

አንድ መሰረታዊ ነገር እዚህ ጋር እንድታውቁ እወዳለሁ፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ በራስ ምታትና ትኩሳት ተይዞ ቢመጣ ኢቦላ ብለን አንናገርም፡፡ ምክንያቱም ኢቦላ የኢትዮጵያውያን በሽታ አይደለም፡፡ ይህንን ለመረዳት ቀላል ምሳሌ ልስጣችሁ፡፡ አንድ ቀዝቃዛ ቦታ ውስጥ የሚኖር ሰው ራስ ምታት፣ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ብሎኛል ብሎ ቢመጣ ወባ እንደዚህ ያደርጋል ተብሎ ወባ አለብህ ቢባል ከእውነት የራቀ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም ወባ የቆላ በሽታ ስለሆነ ነው፡፡ ነገር ግን ሰውዬው በቅርቡ ቆላ አካባቢ ተጉዞ ከሆነ ወባን መጠርጠሩ ብልህነት ነው፡፡

ስለ ኢቦላ ቫይረስም የምናገረው ይህንኑ ነው፡፡ አንድ ሰው አጣዳፊ የሆነ ራስ ምታትና ትኩሳት ስለያዘው ብቻ ኢቦላ ነው ብለን ሽብር አንነዛም፡፡ ዳሩ ግን ሰውየው የሚኖርበትና የመጣበት ቦታ የመጀመሪያው ጥያቄያችን ነው፡፡ ሰውየው ከሱዳ፣ ከኮንጎ፣ ማሊ፣ ላይቤሪያ፣ ሴራሊዮን፣ ጋቦን፣ ጊኒ፣ ሴኔጋል የመሳሰሉት ለኢቦላ ቫይረስ ማህፀን የሆኑ ሀገራት ከሆነ የመጣው ኢቦላን በበሽታ መዝገባችን ውስጥ ቀዳሚ ስፍራን ያገኛል፡፡

አልያም ደግሞ በዚህ ምልክት ሆስፒታል መጥቶ ወደ ኋላ ላይ አልቆም ያለ ተቅማጥ፣ ትውከት እንዲሁም ቀያይ ሽፍታዎችና ከተለያየ የሰውነት ክፍሎች የደም ማፍሰስ ካጀበው ኢቦላን የምንጠረጥርበት ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል፡፡ አለበለዚያ ግን ወፍ በበረረ፣ ዘንግ በተወረወረ ቁጥር ‹‹ኢቦላ ይሆን?›› ብለን በስጋት የምንኖርበት ምክንያት የለም፡፡ ምክንያቱም ‹‹ኢቦላ›› የኢትዮጵያውያ በሽታ ስላልሆነ፡፡

ኢቦላ መድሃኒት አለው ወይ?የለውም! የ2014 የኢቦላ ወረርሽኝ ከ20,000 በላይ የሆኑ አ

ፍሪካውያንን ያጠቃቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ7,500 በላይ የሚሆኑት አሁን እዚህች ምድር ላይ የሉም፡፡ ሌሎች ደግሞ ከአስጨናቂ ማገገም በኋላ ከኢቦላ የተረፈ ህይወታቸውን ለማስቀጠል ዳግም መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡

ኢቦላን ከአጣዳፊነቱ በተጨማሪ ለተመራማሪዎቹ የጎን ውጋት ያደረገው ስርዓት የሚያስይዘው መድሃኒት መታጣቱ ነው፡፡ እርግጥ ነው የህክምና ጠበብት ብዙ ያላጠናቀቋቸው የቤት ሥራዎች በየቤተ ሙከራ ብርጭቆዎቻቸው ውስጥ እየጠበቋቸው ነው፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያጎላው ዳግም በየጊዜው እየተቀላቀሉን ያሉት አዳዲስ በሽታዎች ቁጥራቸው እየበረከተ መምጣቱ ነው፡፡ የኤች.አይ.ቪ ቫይረስን መድሃኒት ሳናገኝ የኢቦላን ቫይረስ መድሃኒት አምጡ መባላችን ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፡፡ ወይ እንቅርቱን፣ ወይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፡፡ ወይ እንቅርቱን፣ ወይ ጆሮ ደግፉን መምረጥ ግዴታችን ነው፡፡ ለእኔ ጠዋት እንደተነሳን ፊታችንን ከመታጠባችን በፊት ስለ ኢቦላ ብናስብ መድሃኒቱ በእጃችን የሚገባበትን ፍጥነት የሚጨምር ይመስለኛል፡፡ በእርግጥ የዓለም የጤና ድርጅት የወከላቸው ምሁራን ህክምና በዓይናቸው እንቅልፍ ካዩ ሰነበቱ፡፡ ኢቦላን የሚፈታ መፍትሄ ስራይ በመፈለግ ራሳቸውን ወጥረዋል፡፡ ምን ላይ ደረሱ የሚለውን መጨረሻ ላይ እገልፃለሁ፡፡ ለማንኛውም አሁን ባለን እውቀት የኢቦላ ቫይረስ ያጠቃው ሰው ቢመጣ ‹‹ምን ልናደርግለት እንችላ

ለን?›› የሚለውን ነገር በአጭሩ ላስቀምጥ፡-­ከላይ እንደገለፅኩት ያለምንም መድሃኒት የኢቦላን ቫይረስ በ

ተጋፈጥንበት ሆስፒታል አንድ የኢቦላ በሽተኛ ቢመጣ የሚከተለው እርዳታ ሊደረግለት ይችላል፡፡

1. ህመምተኛውን ለብቻው ነጥሎ ማስተኛትበሽተናው ከማንም ሰው ጋር እንዲገናኝ አይፈቀድለትም፡፡

ሊያየው የሚችለው ተገቢውን መከላከያ ሽፋን ባለሙያው የሚያሻሽለው የጤና ባለሙያውን ብቻ ነው፡፡

2. ምልክት ተኮር ህክምና ይደረግለታል፡፡ ይህም ማለት ህመምተኛው እያጣ ያለውን ፈሳሽ መተካት ነው፡፡ ኢቦላም ህመምተኛውን የሚገልበት አንዱ መንገድ ብዙ የሰውነት ፈሳሽ እንዲያጣ በማድረግ ነው፡፡ ስለዚህ የሚወጣውን ፈሳሽ መተካት ህመምተኛውን ሊታደገው ይችላል፡፡

3. እንዲሁም ኦክስጅን በመስጠት የኢቦላ ህመምተኛውን ለመታደግ ጥረት ይደረጋል፡፡ ይሁን እንጂ እንዲህም ሆኖ የሚተርፉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ስለዚህ ኢቦላን ለማዳን ከመድክም ይልቅ መከላከል ተመራጭ ነው፡፡

ኢቦላን መካለከል ይቻላል ወይ?አዎ! የኢቦላን ታሪካዊ አመጣጥ ስናጤው በአንድም ሆነ በ

ሌላ መንገድ ሰዎች ከዱር እንስሳት ጋር ባደረጉት ንክኪ ነው፡፡ የስርጭቱ ምክንያት ደግሞ በበሽታው ከተጠቃ ሰው ጋር ባለ ንክኪ እንደሆነ መረዳት ተችሏል፡፡ ስለዚህ ኢቦላን ለመከላከል ከተፈገለ፡-­

1. በበሽታው ከተጠቃ ሰው ጋር ፈጽሞ ንክኪ አለማድረግ፤ 2. የራስን የግል ንፅህና መጠበቅ3. እኛ ሀገር ላይ የተለመደ ባይሆንም አድነን የምንለባቸው

ምግቦች ላይ ጥንቃቄ ማድረግበመጨረሻም ‹‹እንደው ባደረገልን!›› የሚያሰኝ ዜና ከዓለም

የጤና ድርጅት እየተሰማ ነው፡፡ እንደዓለም የጤና ድርጅት ዘገባ መሰረት በ2015 መጨረሻ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ክትባቶች ይመረታሉ ተብሏል፡፡ የተገኙት ክትባቶች ሙከራ ላይ ሲሆኑ ሁለተኛው ክትባት ደግሞ አሜሪካ ቀጥሎም አውሮፓ፣ አፍሪካ ላይ ይታያል ተብሏል፡፡

ዶ/ር ማሪ ፖል የተባሉ የድርጅቱ ባለስልጣን ምንም እንኳን ኢቦላ አሁን በተከሰተበት ቦታ ላይ የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም ቀጣይ ላይ የሚነሱ ወረርሽኞችን ለመከላከል ተስፋ የተጣለበት ክትባት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ጽሑፌን ከመደምደሜ በፊት አንድ ሃሳብ ላንሳ፡፡ ‹ኢቦላ› የኢትዮጵያውያን በሽታ አይደለም ብዬ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን ሃሳቤን አለወጥኩም፡፡ ግን ምን ማለት እንደሆነ መሰረታዊ ትርጉሙን ማሳወቅ እፈልጋለሁ፡፡ አለበለዚያ ጽሑፌ ሃዲዱን የሳተ ባቡር ነው የሚሆንብኝ፡፡

ኢቦላ የኢትዮጵያውን በሽታ አይደለም ስል ኢቦላ ከበሽዎች ስርጭት አንፃር ስንመለከተው ኢትዮጵያ ለበሽታው ማህፀን አይደለችም ማለቴ ነው፡፡ ይህ ማለት የህዝቡ አኗኗር፣ አመጋገቡ፣ የእንስሳቱ ዝርያ ወዘተ ለበሽታው መፈጠር አመቺ አልነበረም ማለት ነው፡፡ እንዲያማ ባይሆን ኢቦላ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ይፈነጭ ነበር፡፡ ይህ ማለት ሀገራችን የኢቦላን ጉዳይ ‹ጆሮ ዳባ ልበስ› ብላ ተጠቅልላ ትተኛ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ አንድ ሽማግሌ ሰውዬ ነበሩ፡፡ ጊዜው ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ነው፡፡ ታዲያ ‹‹ጀርመኖች ኮሚኒስቶችን ያድናሉ› ሲሉኝ ኮሚኒስት ባለመሆኔ ደስ አለኝ› አሉ፡፡ ‹‹በቀጣዩ ጊዜ ሰፈራችን መጥተው አይሁዶችን ሲፈልጉ አይሁድ ባለመሆኔ ፈጣሪን አመሰገንኩኝ፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ መጥተው ሴቶችን ሲወስዱ ወንድ በመሆኔ ኮራሁ›› ትንሽ ቆይተው ደግሞ ‹‹ህፃናትን ሲማርኳቸው ሽማግሌ በመሆኔ ለመጀመሪያ ጊዜ በዕድሜዬ ርዝማኔ ጮቤ ረገጥኩ፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ መንደራችን መጡ፡፡ ሲመጡ እኔ ብቻ ነበር የቀረሁት፡፡ ምርጫ በማጣታቸው እኔኑ ወሰዱኝ›› አሉ፡፡ ኢቦላም እንደዚሁ እንዳያደርገን ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ ኢቦላን ለመከላከል ሀገራችን

ቁርጠና አቋም ልትይዝ ይገባል፡፡ ‹ሠርገኞቹ ሲመጡ በርበሬ ለመቀንጠስ› የምንሮጥ ከሆነ ታላቅ የሆነ ሰቆቃ ለትውልዱ ማትረፋችን አይቀርም፡፡ ለማንኛውም ፈጣሪ ሀገራችንን ዳሯን እሳት መሃሏን ገነት ያድርግልን፡፡ ሰናይ ጊዜ ተመኘሁላችሁ፡፡

ሉክ ሸው.... ከገጽ 21 የዞረ የሚጠቁሙ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ያሳፈለውን አስገራሚ ጊዜ መለስ ብሎ እንዲቃኝ ሲጠየቅ ‹‹የማይ

ታመን ነው፡፡ ነገሮች የተከናወኑት በፍጥነት ነው፡፡ አጋጣሚውን በተለየ መንገድ መመልከት አልፈልግም፡፡ ማተኮር የምፈልገው በእግርኳሱ ላይ ነው፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ነገሮችን መመልከት ያስደንቃል፡፡ ሆኖም ላለፈው ነገር ያን ያህል ትኩረት መስጠት አያስፈልግም፡፡ ወሳኙ መጪው ጊዜ ነው፡፡ ተደራራቢ ጨዋታዎች በጣም በፍጥነት ይመጣሉ›› የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

የ2014ቱ የዓለም ዋንጫ ምን መልክ ነበረው? ‹‹የማይታመን ነው፡፡ በዚያ ዕድሜ በዓለም ዋንጫ ላይ መሳተፍ ያስደንቃል፡፡ ብዙ ተምሬያለሁ፡፡ በተለይ ከእነ ሌይተን ቤይንስ ጋር መጫወት ጠቅሞኛል፡፡ በልምምድም ሆነ በጨዋታ ላይ የሚራውን በአንክሮ እከታተል ነበር፡፡ ከወርልድ ክላስ ተጨዋቾች ጋር መጫወት ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡›› በማለት ሾው ንግግሩን ይቀጥላል፡፡ ‹‹በተለይ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ስትሆን በአንተ ቦታ የሚጫወቱ ተጨዋቾች ምን እንደሚሰሩ መመልከት ትፈልጋለህ፡፡ እንደ መታደል ሆኖ እኔ ቤይንስን አግኝቻለሁ፡፡ ከምርጦቹ የግራ መስመር ተከላካዮች አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም እርሱን መመልከት እና ከእርሱ ጋር መወያየት ትልቅ ስሜት ይሰጣል፡፡ አስደሳች ነው››

የተቀላቀለው ክለብ ምን ያህል ግዙፍ እንደሆነ የተገነዘበው በኋላ ላይ ነው፡፡ ‹‹ፊርማህን እስክታኖር ድረስ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ አታውቅም፡፡ በመላው ዓለም ያለው የደጋፊዎች ብዛት እና ሁሉም ነገር ያስገርማል፡፡ የገጠምናቸው ቡድኖችም ቢሆኑ ትልልቆች ነበሩ፡፡ በ18 ዓመትህ እንደ ሪያል ማድሪድ እና ኢንተር ሚላንን የመሳሰሉ ቡድኖች መግጠም የማይታመን ስሜት ይፈጥርልሃል፡፡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጋሬት ቤልን በተቃራኒ መግጠም አስደሳች ነው፡፡ በአሜሪካ ያደረግናቸው ጨዋታዎች እጅጉን ጠቅመውኛል፡፡››

ቫን ገል ከሳውዛምፕተን ያስፈረሙት ተከላካይ የአካል ብቃቱን ማሳደግ እንዳለበት የተናገሩት በጁላይ መጨረሻ ኢንተርን ከመግጠማቸው በፊት ነበር፡፡ በንጋታው ሾው የአሰልጣኙ አስተያየት ትክክል መሆኑን አመነ፡፡ ‹‹ሁኔታውን ግልፅ ማድረግ እፈልጋለሁ፡፡ ምናልባት አንዳንድ ሰዎች ንግግሩን በተሳሳተ መንገድ ተረድተውት ይሆናል፡፡ እንደሚመስለኝ አሰልጣኙ ያንን ያለው ሊረዳኝ ፈልጎ ነው፡፡ አሁን ሁኔታው እልባት አግኝቷል፡፡ አጋጣሚው በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት የተፈጠረ ነው፡፡ አሁን ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡››

ቫን ሃል በተደጋጋሚ የዩናይትድን ቅርፅ ለዋውጠዋል፡፡ በተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ሶስት የመሀል ተከላካዮችን ተጠቅመዋል፡፡ በአንዳንዶቹ ደግሞ የተከላካይ መስመሩን ከአራት ተጨዋቾች አዋቅረዋል፡፡ ሾው የክንፍ ተከላካይ (wing back) ሆኖ ተጫውቶ ያውቃል? ‹‹በሳውዛምፕተን የመስመር ተከላካዮች ወደፊት ተጠግተው እንዲጫወቱ የሚደረግበት ወቅት ነበር፡፡ ምናልባት በእነዚያ አጋጣሚዎች እንደ ዊንግ ባክ ተጫውቼ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የዊንግ ባክ ሚና ይዤ ተጫውቼ አላውቅም›› ካለ በኋላ ይበልጥ በማጥቃት ሂደት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል ይናገራል፡፡ ‹‹ሁልጊዜም ትምህርት እንደቀሰምኩ ነው፡፡ በተለይ በተለያዩ ፎርሜሽኖች ውስጥ ሚናዬን በአግባቡ ለመወጣት ጥረት እያደረግኩ ነው፡፡ ምናልባት ወደፊት የክንፍ ተጨዋች እንድሆን ይጠቅመኝ ይሆናል››

ለዝውውሩ ስለወጣው 30 ሚሊዮን ፓውንድ ሲጤቅ ሾው በግድየለሽነት ትከሻውን ይነቀንቃል፡፡ ‹‹ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀልኩ ተጨዋች ነኝ፡፡ ዕድሜዬ ከግምት ሊገባ አይገባም፡፡ እንደ ማንኛውም ተጨዋች ሁሉ ለመልመድ ጥረት ማድረግ አለብኝ፡፡ የዕድሜዬ 28 አልያም 19 መሆን ልዩነት አይፈጥርም፡፡ ቡድኑን እስከተቀላቀልክ ድረስ አሰልጣኙ እንደሚፈልገው መጫወት አለብህ፡፡ እውነቱ ያ ነው፡፡ ወላጆቼ ያሳደጉኝ በስነስርዓት አንፀው ነው፡፡ ለመኮፈስ እና ለመታበይ አይዳዳኝም፡፡ የተረጋጋሁ እና ማሳካት በምፈልገው ነገር ላይ የማተኩር ተጨዋች ነኝ፡፡›› ሾው ይማርበት የነበረው የሱሬይ ራይደንስ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር የሆኑት ሄይዲ ስቶን ‹‹በመምህራኖቹም ሆነ አብረውት ይማሩ በነበሩ ተማሪዎች የሚወደድ፡፡ ትኩት እና ቁጥብ፡፡ ከእብሪት የፀዳ›› ሲሉ ገልፀውታል፡፡ ሾው ይህንን ሲሰማ ተደሰተ፡፡ ‹‹በተለይ ያንን የተናገሩት መምህራኖቼ መሆናቸው ያኮራል፡፡ አሁንም ድረስ ከተወሰኑት ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለኝ፡፡ ወደ ድሮ ትምህርት ቤቴ ሄጄ መጎብኘት እፈልጋለሁ፡፡ አሁን ለደረስኩበት ደረጃ መድረስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡ በእነርሱ እገዛ የፈጠርኩት መልካም መሰረት ባይኖረኝ ኖሮ ይሄኔ በችግር ውስጥ ነበርኩ፡፡››

በስምንት ዓመቱ የተቀላቀለው ሳውዛምፕተን የመጀመሪያ ፕሮፌሽናል ጨዋታውን ያደረገው በ16 ዓመቱ ነው በጃንዋሪ 28 ቀን 2011 ከሚልዎል ጋር በተደረገ የኤፍኤካፕ ጨዋታ ላይ፡፡ ‹‹አስታውሳለሁ፡፡ በዕለቱ ተሰልፌ የተጫወትኩት በግራ ክንፍ ላይ ነው›› ሲል ሾው በ77ኛው ደቂቃ ጄሰን ፐንቺዮንን ተክቶ ወደ ሜዳ በመግባት ስላደረገው ጨዋታ መናገሩን ይጠቅሳል፡፡ ‹‹ምንጊዜም ቢሆን ወደ ሚልዎል ተጉዞ መጫወት አስቸጋሪ ነው፡፡ በጨዋታው ተሳትፎ ያደረግኩት ለ20 ደቂቃዎች ብቻ ቢሆንም እጅግ ደክሜ ነበር፡፡ ለተሰለፍኩት ቦታ እንግዳ ነበርኩ፡፡ በዚያ ላይ ከፍተኛ የአካል ብቃት የሚጠይቅ ስፍራ ነው››

በኖቬምበር 2012 ከስዋንሲ ሲቲ ጋር በተደረገ ግጥሚያ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ሲያደርግ ጥቂት እንግሊዛውያን ተጨዋቾች ብቻ ያሳኩትን ድል አጣጥሞ ነበር፡፡ በ2011 በፈረንሳይ የተዘጋጀውን ከ16 ዓት በታች ቡድኖች ውድድር ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር አሸንፏል፡፡ ከኡራጓይ ጋር በተደረገው የምድብ ማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ ሾው ኳስ እና መረብ አገናኝቷል፡፡ ‹‹የፍፁምቅጣት ምት ነበረች፡፡ ኳሷ ስለመግባቷ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ አግዳሚውን ገጭታ ወደ መስመሩ ነጠረች፡፡ ነገር ግን ውድድሩን ማሸነፋችንን እርግጠኛ ነኝ››

ዩናይትድ በዚህ የውድድር ዘመን ፕሪሚየር ሊጉን በአሸናፊነት የማጠናቀቅ ዕድሉ የተመናመነ ነው፡፡ ከመሪው ቼልሲ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ 12 አድጓል፡፡ ሾው ግን ተስፋ የቆረጠ አይመስልም፡፡

‹‹ፕሪምየር ሊጉን ማሸነፍ እንፈልጋለን፡፡ እያንዳንዱን ጨዋታ በተናጥል እያየን መጓዛችንን እንቀጥላለን፡፡ ከሚቀሩን ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ እንሰበስባለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ›› ይላል፡፡

ዘጠነኛው.... ከገጽ 22 የዞረ ነው ሲላት ‹‹እንዲያ ከመሰለህ አዎ›› አለችኝ ብሏል፡፡ ይህ ደ

ግሞ ለታገሰ ‹‹ዘጠነኛው ስቃይ ነው›› ተናደድኩ ይላል፡፡ ለፖሊሱም የነገረው ይህንኑ ነው፡፡

‹‹ይህንን ቃል ስትናገረኝ ወረረኝ፤ ያቃጠልኩት ዕድሜ ቆጨኝ፡፡ በወጣትነቴ ስንት ዕድል ነበረኝ፡፡ ዛሬ ብቻዬን አልኖርም ነበር፡፡ በዓይኔ ባላይም የካደችኝ መሆኑን ሰውነቴ ነግሮኛል፡፡ ይህን ደግሞ ማረጋገጥ አያስፈልገኝም፡፡ ከዚህ በኋላ የማላውቀው ስሜት በውስጤ ገባ፡፡ ሰይጣን አሳሳተኝ፡፡ ስለዚህም ገደልኳት››

ታገሰ ይህቺን ወጣት የገደላት ፍራሹ ስር ደብቆት በነበረው ጩቤ ነው፡፡ ዘጠኝ ጊዜ የተለያዩ የሰውነቷ ክፍል ላይ ወግቷታል፡፡ ደሟ ያንን አልጋ ሙሉ በሙሉ ደም ሸፍኖታል፡፡ ታገሰ ‹‹የዘለዓለም ፍቅረኛዬ›› ያላትን ሴት ሲያብሰለስለው በነበረው ውሳኔ በጩቤ ከገደላት በኋላ ለፖሊስ እጁን ሰጠ፡፡ ያደረገው ነገር ትክክል ባይሆንም ሌላ ምርጫ አልነበረኝም ብሏል፡፡ ፍፁም የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑን ግን ልቦናው ያውቃል፡፡ ታገሰ ወደ ወህኒ ቤት ሲወርድ ግን ፖሊስ ጋር የሰጠው ቃል በአፉ ውስጥ አልነበረም፡፡ ይልቅስ ለቅሶ ፀፀትና ናፍቆት እያንገላቱት ነበር፡፡ ‹‹እሷን ከምገድል ራሴን ገድዬ ቢሆን ምንኛ ጥሩ ነበር›› ብሏል፡፡

በቋንቋ የተነሳ መንጃ ፈቃድማውጣት ተቸግረዋል?

G lob a l Transla tion & Interpreterበቋንቋ የተነሳ የኮምፒውተር ፈተናውን ማለፍ ተስኖዎታል?

በዚህ የተነሳ መኪና መንዳት አልቻሉም? እንግዲያውስ መፍትሄው እኛ ጋር አለ፤

አስተምረን ወስደን እናስፈትንዎታለን።

Tajajila Afaan

Oromoos Nikennina !

ልብ ይበሉ የእርስዎን ቋንቋ እንናገራለን24 0 0 Minnehaha Avenue Suite - 2 0 4

Minne a polis, MN 554 0 4

(612) 275-0970በተጨማሪም የትርጉም ድርጅታችን የፍርድ ቤት ጉዳይ ሲኖርብዎ ወይም በማንኛውም ሰዓት

የትርጉም ሥራ ሲያስፈልግዎ ክፍት ነው።

ኩፍኝ (measles) በዓለም ዙሪያ በየቀኑ 400 ሕጻናትን ይገድላል። በጣም የሚዛመት እንዲሁም ከአንዱ አህጉር ወደ ሌላው አህጉር በቀላሉ የሚተላለፋ ነው። ነገር ግን ራስዎን እና ቤተሰብዎን ከበሽታው ለመጠበቅ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አለ –ክትባት ይውሰዱ።

ከአገር ውጭ የሚጓዙ ከሆነ፤ እርስዎም ሆኑ ልጆችዎ የኩፍኝ (measles)፣ የጆሮ ደግፍ በሽታ (mumps) እና የጉድፍ (rubella) (ኤም.ኤም.አር/MMR ተብለው የሚጠሩት) ክትባቶቻችሁ መወሰድ በሚገባቸው ጊዜ መወሰዳቸውን ያረጋግጡ። ልጆች ከ6 ወር ዕድሜ ጀምሮ የኤም.ኤም.አር/MMR ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ሌላው በተጓዥዎች አማካኝነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመዛመት ላይ የሚገኝው ተላላፊ በሽታ ፖሊዮ ነው። ፖሊዮ ሽባ የሚደርግ (እጅ ወይም እግር ማንቀሳቀስ የሚከለክል)፤ አንዳንዴም ሜኔንጃትስ (የጭንቅላት እና የአከርካሪ ኢንፌክሽን) የሚያስከትል በሽታ ነው። ሽባነቱ በአካል ውስጥ ከተሰራጨ ሰው

ዬው መተንፈስ ሊያቆም ይችላል። የፖሊዮ በሽተኞች ቁጥር መጨመር የዓለም ጤና ድርጅት

(World Health Organization) ባለሥልጣናትን አሳስቧቸዋል። ፖሊዮ የሚገኝበት አገር ውስጥ ከአራት ሳምንት በላይ የሚቆዩ ሰዎች፤ ወደ እዚያ አገር ከመጓዛቸው በፊት መከተብ አለባቸው ብለው ይመክራሉ። ፖሊዮ ወደ ሚገኝበት አገር የሚጓዙ ሰዎች የጤና ባለሙያን በማነጋገር ቀደም ብለው የወሰዱትን ክትባት መቀስቀሻ የሚሆን ክትባት መውሰድ ይኖርባቸው እንደሆን እንዲሁም ልጆቻቸው ለጉዞው የሚፈለገውን የክትባት መጠን በሙሉ ወስደው እንደሆነ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል።

እነኝህ በሽታዎች እርስዎን እና ቤተሰብዎን አያጠቁም ብሎ ማሰብ ቀላል ሊሆን ይችላል። አንድ የሚኒሶታ እናት እነኝህ በሽ

ታዎች ምን ያህል አደገኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጉዞ ባደረገችበት ወቅት ተረድታለች። ጉዞ ከማድረግዋ በፊት ዶክተሩ ቤተሰብ ለመጎብኘት ወደ ኬንያ ስለሚሄዱ ልጅዋ ከመደበኛው ጊዜ አስቀ

ድሞ የኤም.ኤም.አር/MMR ክትባቱን አንዲወስድ አዝዞ ነበር። ልጅዎ እንዲከትብ ፈለገች፤ ነገር ግን ልጅዋ ተኛ። ተመልሰው እስኪመጡ ድረስ ይቆይለት ብላ ወሰነች። ቤተሰብ ለመጎብኘት ብቻ ስለሆነ የሚሄዱት ብዙ ችግር ያለበት አይመስልም።

ወደ ቤት የተመለሱበት ቀን ልጅዋ ሳል፣ የንፍጥ መዝረክረክ፣ እና እንባ ያዘለ ቀይ ዓይን የመሳሰሉ –የጉንፋን ምልክቶች ታዩበት። ከዚያም ትኩሳት ያዘው እንዲሁም በጣም ደከመ። ወደ ዶክተር ወሰደችው፤ እናም ቫይረስ እንደሆነ ተናግረው የቅ

ርብ ክትትልም ይደረግለት አሉ። ሳሉም እየባሰ እንዲሁም የትኩሳቱ መጠን እየጨመረ ሲመጣ መልሳ ወደ ዶክተር ወሰደቸው። የዚህን ጊዜ ኒሞኒያ ስለነበረው ሆስፒታል አስተኙት። ዶክተሮቹ

ም ተጨማሪ ምርመራ አደረጉና የብቻ ክፍል ውስጥ አስገቡት –ኩፍኝ ይዞት ነበር።

ልጅዋ መተንፈስ ስለተቸገረ የመተንፈሻ ማሽን አደረጉለት። በአፉ፣ በአፍንጫው እና በክንዶቹ ላይ ቱቦ ተደርጎለት ነበር። ምንም ማድረግ እንደማትችል ሆኖ ተሰማት። ዶክተሮቹ ልጅዋ ሊሞት ይችላል ብለው አስጠነቀቅዋት። ለሦስት ሳምንት ማሽን ለልጅዋ ሲተነፍስ አየች።

ይህ ትንሽ ልጅ ከሞት ተረፈ፤ እናቱ ግን ስቃዩን ፈጽሞ አትረሳም። በሽታውም በአውሮፕላኑ ውስጥ ወደ ነበሩ ሌሎች ሰዎች እና ክትባት ያልተከተቡ የቤተሰቡ አባላትም ላይ ተዛምቷል። ከሃገር ውጭ ለሚሄዱ ሁሉ “እርስዎ ወይም ቤተሰብዎ የሚያስፈልጋችሁን ክትባት ሁሉ መከተባችሁን እርግጠኛ ሁኑ” እያለች ትነግራለች።

ጉዞዎን ጤናማ ለማድረግ፤ ስለ ጉዞዎ፣ ክትባትዎችዎ እና በሚጓዙበት ወቅት ጤነኛ ሆነው የሚቆዩባቸው መንገዶችን አስመልክተው ከጤና ባለሙያዎ ወይም ዶክተርዎ ጋር ይነጋገሩ።

በዓለም  ዙሪያ  ጉዞ  ለማድረግ  ዕቅድ  አለዎትን?  ክትባት  መውሰድዎን  አይዘንጉ

Page 21: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 21ስፖርት

ባለፈው ሜይ ወር ነው፡፡ አርሰናል የኤፍኤ ዋንጫን አገኘ፡፡ ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ የተገኘ ድል ነበር፡፡ ከዚህ ድል ቀደም ብሎም በዘንድሮው የቻምፒዮንስ ሊግ የሚያሳትፈውን ደረጃ ማግኘቱን አረጋገጠ፡፡

ከእነዚህ ሁለት ትልልቅ ድሎች ማግስት ለአርሰናል ደጋፊዎች ቃል ተገባላቸው፡፡ ቡድናቸው በአንድ ደረጃ እንደሚሻሻል ተነገራቸው፡፡ ‹‹አንድ ደረጃ መሻሻል›› የተባሉት ደግሞ በፕሪሚየር ሊግ መፎካከርን ነው፡፡ ነገር ግን እስካሁን አልተሳካም፡፡ ይበልጥ አስከፊው ነገር በዚህ የውድድር ዘመን የመሳካት ዕድሉ ጠባብ መሆኑ ነው፡፡ ታዲያ የሚላከው መቼ ነው? አርሰናልስ ከፕሪሚየር ሊጉ ልሂቃን ተርታ የሚሰለፈውስ መቼ ነው? ይህ ጥያቄ በዚህ ወቅት መነሳቱ ትክክል የሆነውስ ለምን ነው? በቅርቡ የሚወጡ ዜናዎች አርሰን ቬንገር ክርስቲያን ቢዮሊክን ከሌጂያ ዋርሳው ማስፈረማቸው ያረጋግጣሉ፡፡ እንዲያውም ፕሮፌሰሩ አማካዩን ማንቸስተር ሲቲን በገጠመው ስኳድ ውስጥ እንደሚያካትቱት ሲዝቱ ነበር፡፡ አዲስ የተገዛ ተጨዋች የስኳድ አባል ቢሆን አያስገርምም፡፡ ዣቢ አሎንሶ ለባየርን በፈረመ በሰዓታት ውስጥ በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ ገብቶ ተጫውቷል፡፡

የቬንገርን የተለየ የሚያደርግባቸው ቢዬልክ ገና 17 ዓመቱ መሆኑ ነው፡፡ እንደተለመደው ቬንገር በጃንዋሪ በርካሽ ዋጋ የወደፊቱን ተጨዋች ገዝተዋል፡፡ በዝውውሩ አንድ ጥሩ ተጨዋች ገዝተው የቡድኑ ጥልቀት የሚያጠናክሩበት ዕድል አላቸው፡፡ እስካሁን ግን ይህንን እድል አልተጠቀሙበትም፡፡ ይባስ ብሎ ሚኬል አርቴታ እና ማቲዩ ዴቡሺ ለሶስት ወራት ወደ ሜዳ አይመለሱም፡፡ ስለዚህ አሁን ያለው ቡድን በተለይ በአማካይ እና በተከላካይ ክፍሉ በጥልቀት አስተማማኝ አይደለም፡፡ ችግሩ አሳሳቢ የሚሆነው ለረጅም ዘመናት ከቬንገር ጋር አብሮ የኖረ መሆኑ ነው፡፡

በጃንዋሪ የተገዛው ቢዬሊክ የተከላካይ አማካይ መሆኑ ትንሽ ምፀታዊ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የተከላካይ አማካይ ቦታ ቡድኑ ሊሸፍነው ያልቻለው ትልቁ ክፍተቱ ነው፡፡ ጄልቤርቶ ሲልቫ ቡድኑን ከለቀቀ ወዲህ ቦታው ‹‹ባዶ›› ሊባል የሚችል ነው፡፡ ምናልባት ለአንድ የውድድር ዘመን ማቲዩ ፍላሚኒ ጥሩ ነገር አበርክቷል፡፡ ታዲያ ቬንገር ወዲያውኑ ተፅዕኖ የሚያሳድር ታዳጊ ላይ ገንዘባቸውን ማፍሰስ ለምን ፈለጉ? ብዙዎቹ ግምት መስጠ

ትን አቁመዋል፡፡ ምክንያቱም ቬንገርን ለመረዳት ከባድ ሆኗልና፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ሰውዬው ራሳቸው የሚሰሩትን አያውቁም እየተባለ ይተቻሉ፡፡ ብዙዎች በዚህ ጉዳይ ከቬንገር በተቃራኒ እየቆሙ ነው፡፡ አንድ የአርሰናል ደጋፊ በፌስቡክ ገፁ ላይ ያሰፈረው ፅሑፍ ብዙዎችን የሚያስማማ ይመስላል፡፡ በብቃቱ

የተመሰከረለት የተከላካይ አማካይ አልገዙም፡፡ ኦሊቪዬ ዢሩ እና ዳኒ ዌልቢከን የመሳሰሉ አጥቂዎች ለዋንጫ እንድንፎካከር ያደርጉናል ብለውም ያምናሉ፡፡

‹‹ለዓመታት የቬንገር ዝውውር ወጣት፣ በአካል ብቃቱ ያል

ጠነከሩ፣ በቴክኒኩ የበለፀጉ፣ በትልልቅ ጨዋታዎች በቀላሉ ኳስ የሚነጠቁ ተጨዋቾች ላይ አተኩሯል፡፡ በያዝነው የዝውውር መስኮት ልምድ ያለውን ሉካስ ፖዶልስኪን በውሰት ሰጥተናል፡፡ የእኛ ኮከብ ተጨዋች (አሌክሲስ ሳንቼዝ ማለት ነው) ያለውን ሁሉ እያሟጠጠ ነው፡፡ ምርጦቹ ተከላካዮቻችን በጨዋታ በአካል

ብቃቱ በኩል ብቁ የመሆን እና ራሳቸውን 100 በመቶ ለቡድናችን አሳልፈው የመስጠት ችግሮች ይነሳባቸዋል፡፡ የቡድናችን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ተደጋጋሚ ስህተቶች እየመራ ነው፡፡ ከቋሚ 11 ውጭ ሊሆን እየተዘጋጀ ያለ ይመስላል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ሊያሳስ

ባችሁ አይገባም፡፡ በአሁኑ ወቅት ቬንገር የ17 ዓመት ብቃቱ ያልተረጋገጠ ፖላንዳዊ አማካይ ሊገዙ እየተደራደሩ ነው፡፡ በቃ! ጠዋት ከመኝታችሁ ስትነሱ የሚያጋጥማችሁን የደካማነት ሽታ አትወዱትም?›› ሲል ተሳልቆ ‹‹ቬንገር ይውጡ›› በሚል መልዕክት ፅሑፉን አጠናቋል፡፡

የውድድር ዘመኑ ከተጀመረ ወዲህ በትዊተር፣ በፌስቡክ እና አርሰናልን ብቻ የሚመለከቱ የደጋፊ ድረገፆችን ብትከታተሉ ደጋፊዎቹ ምን ያህል እንደተሰላቹ መረዳት አያዳግትም፡፡ ከሁሉም በላይ የሚገርመው የእንግሊዝ እግርኳስን የሚከታተለው ሁሉ የሚያየውን የኢምሬትስ ገበና ቬንገር እስካሁን አለመመልከታቸው ነው፡፡ የለንደን ኢቪኒንግ ስታንዳርድ ጋዜጠኛው ጀምስ ኦሌይ ቬንገር ‹‹አርሰናል በጃንዋሪ ተጨዋች ማስፈረም አያስፈልገውም›› ማለታቸውን አስነብቧል፡፡ ተከላካይ ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንዲጀምሩ ሊያደርጋቸው የሚችለው የሎሮ ኮቬዮልኒ ጤንነት አስተማማኝ ካልሆነ ብቻ መሆኑን መናገራቸውም ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል፡፡ ታዲያ ይህን የሚያዩ በቬንገር ቢናደዱ ይገርማል፡፡

በአጭሩ ቡድኑ ለዋንጫ ሳይሆን ቬንገር ‹‹እንደ ዋንጫ ይቆጠራል›› ላሉት የፕሪሚየር ሊጉን አራተኛ ደረጃ ማግኘት መታገሉን ይቀጥላል፡፡ እጄ የተባለ የአርሰናል ደጋፊ ቡድኑ ከሊቨርፑል ጋር ተጫውቶ አቻ ከተለያየ በኋላ የሰጠው አስተያየት መድፈኞቹ ለምን አራተኛ ደረጃ በላይ እንደማይጓዝ በግልፅ ያሳያል፡፡

‹‹አርሰናል ለአራተኛ ደረጃ የሚጫወት ቡድን ነው›› ይላል ኤጂ፡፡ ‹‹ምክንያቱም ላለፉት ዓመታት ቡድን ሲገነባ እና ሲሰራ የነበረው ለአራተኛነት እንዲፎካከር ብቻ ነው፡፡ ለቅፅበት አስብበት እስኪ፡፡ አሁን ክለቡ እየተከተለው ያለው ሞዴል ለቢዝነስ አዋጪ ነው፡፡ ሁልጊዜም አራተኛ ሆነህ ስትጨርስ ምን ታገኛለህ? በቻምፒዮንስ ሊጉ እንድትሳተፍ ያደርግሃል፡፡ በምድብ ውድድር ደግሞ ከፍተኛ ገንዘብ ያገኛል፡፡ ወደ ጥሎ ማለፍ ዙሩ ሲገባ ደግሞ የሚገኘው ገንዘብ ይጨምራል፡፡ በየዓመቱ በቻምፒዮንስ ሊግ ስትሳተፍ የክለቡ ክብር ከፍ ስለሚል ባለተሰጥኦ ተጫዋቾችን ለማስፈረም አይገኝም፡፡ ከሁሉም በላይ የሚያረጋግጣቸው ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው በቻምፒዮንስ ሊጉ በተከታታይ መሳተፍ ክለቡ ለማሸነፍ ያለበትን (አርሰናል... እባክዎ ወደ ገጽ 23 የዞረ)

4!?  -  አርሰናል  ለዋንጫ  ወይስ  ለአራተኛ?

ባለፈው የውድድር ዘመን በመጨረሻው የፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ኒውካስል ሲገጥም ማንቸስተር ሲቲ ጣጣውን አጠናቅቆ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ እንደሚያነሳ ሁሉም ሰው እርግጠኛ ነበር፡፡ ነገር ግን ምናልባት ዌስትሃም ተአምራዊ በሆነ መንገድ ሲቲን ቢያሸንፍ እና ሊቨርፑል ኒውካስልን ቢረታ በሚል እሳቤ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ በአንፊልድ እንዲቀመጥ ተደርጎ ነበር፡፡ እንደታሰበው ያልተጠበቀ ነገር አልተከሰተም፡፡ ሆኖም ቀዮቹ ለዋንጫ ይህን ያህል ሲቀርቡ ከረዥም ዓመት በኋላ የመጀመሪያቸው ነበር፡፡ በእርግጥ 14 ወይም 15 ተጨዋቾችን የያዘው ስኳድ አሸናፊ ለመሆን በርካታ ገንዘብ ከሚያፈሱ ቡድኖች ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረጉ ተጨዋቾቹ እና አሰልጣኙ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡

ያንን የተመለከቱ ደጋፊዎች በዚህ የውድድር ዘመን የተሻለ ነገር ለማየት ጓጉተው ነበር፡፡ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ልዊስ ሱአሬዝ ክለቡን ለቅቆ ቢጓዝም የሜርሲ ሳይዱ ቡድን ደጋፊዎች የውድድር ዘመኑ ውጤታማ እንደሚሆን ጠብቀው ነበር፡፡ በእርግጥ በዚህ የውድድር ዘመን ቡድኑ ለዋንጫ ይፎካከራል ያለ አልነበረም፡፡ ነገር ግን እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዞ ያጠናቅቃል የሚለው ግምት አይሎ ነበር፡፡ ሆኖም ከሴፕቴምበር አጋማሽ እስከ ኖቬምበር

መጨረሻ አካባቢ የተማገበው ውጤት የሚያበሳጭ ነበር፡፡ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

በደረጃ ሰንጠረዡ ከወገብ በታች ለሚውተረተር ቡድን የአንድ ተጨዋች በጉዳት መራቅ እንደምክንያት መቅረብ ይቻላልየተፈጠረው ችግር ምን እንደሆነ ለማብራራት የ

ሚሞክሩ በርካታ ምክንያቶች ቀርበዋል፡፡ የዳንኤል ስተሪጅ ጉዳት፣ በራሂም ስቴርሊንግ ላይ ከመጠን ያለፈ ጥገኛ መሆን፣ አሰልጣኙ ስቲቨን ዤራርድን ሮጀርስ ደካማ የማስተዳደር ብቃት ከምክንያቶቹ መካከል ጎልተው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ (ሊቨርፑል... እባክዎ ወደ ገጽ 24 የዞረ)

ይህን አምድ ሊሊ ሞገስ ከአፕል ቫሊ ና እና ዳኒ ከሚኒያፖሊስ ያዘጋጁታል

ሉክ ሸው ‹‹ለምሳ መሄድ እችላለሁ?›› ብሎ ጠየቀ፡፡ ይህንን ሲል ሰባት ሰዓት ለመሆን የቀረው አንድ ደቂቃ ብቻ ነበር፡፡ እንግሊዛዊው ተከላካይ ለልዊስ ቫን ሃል ያለው ክብር ያስገርማል፡፡ ሆላንዳዊውም ቢሆኑ ለስነ ስርዓት ከፍተኛ ግምት ይሰጣሉ፡፡ በእርሳቸው ደንብ መሰረት የተወሰኑ ደቂቃዎችን አርፍዶ ወደ ልምምድ መምጣት ያስወግዛል፡፡ በመጪዎቹ አስር ዓመታት የእንግሊዝ እና የዩናይትድ የግራ መስመር ተከላካይ እንደሚሆን የሚጠበቀው ተከላካይ አሁንም ድረስ ሰው አክባሪ ነው፡፡ ወደ ቤቱ ለመሄድ የሚጠይቀው እንኳን በትህትና ነው፡፡ ይህን መሰሎቹ አጋጣሚዎች የታዳጊዎች የተሟላ ሰብዕና ይጠቁማሉ፡፡ ባለፉት ጥቂት ወራት ፈጣን እመርታ ያደረገበትን ምክንያትም ያብራራሉ፡፡ አሁን ለሚገኝበት ቦታ ያበቃው ያልተጠበቀ አውሎ ነፋስ ነው፡፡

ሾው ወደ ብራዚል በተጓዘው ቡድን ውስጥ የተካተተው ኮልን ከምርጫ ውጪ አድርጎ ነው፡፡ በመጨረሻው የምድብ ማጣሪያ ከኮስታሪካ ጋር በአቻ ውጤት ሲለያዩ ተሰልፎ ተጫውቷል፡፡ ይህም ከማይክል ኦውን ቀጥሎ በዓለም ዋንጫ የተሳተፈ በዕድሜ ትንሽ እንግሊዛዊ ተጫዋች አድርጎታል፡፡ ወደ ዩናይትድ ያደረገው ዝውውር የተጠናቀቀው በጁን 27 ነው፡፡ ከዚያም ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የቡድኑን የቅድመ ውድድር ዝግጅት ለመቀላቀል ወደ ሎስ አንጀለስ በረረ፡፡ ቫን ሃል የአካል ብቃቱን ለማሳደ

ግ ጠንክሮ መስራት እንደሚኖርበት የጠቆሙት በዚያን ወቅት ነው፡፡ ያለ አልበቃ ብሎ የውድድር ዘመኑ ከመጀመሩ በፊት የታፋ ጅማት ጉዳት አጋጠመው፡፡ በዚህም ምክንያት ለዩናይትድ የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋ

ታውን ለማድረግ እስከ ሴፕቴምበር 27 ለመጠበቅ ተገደደ፡፡ በዕለቱ ዩናይትድ ዌስትሃምን በኦልድ ትራፎርድ 2-­1 አሸነፈ፡፡ ከዚያ በኋላ የተከሰቱ ሌሎች ጉዳዮችም ተከላካዩ እስካሁን ባለው ሂደት በ11 ጨዋታዎች ብቻ ላይ መሳተፍ እንዲችል ገድቦታል፡፡ ነገር ግን አሁንም ቢሆን የተጫዋቹን ተሰጥኦ ጎልቶ እንዲወጣ ያደረጉት የመከላከል እና የማጥቃት ክህሎቱ አብረውት መኖራቸውን (ሉክ ሸው... እባክዎ ወደ ገጽ 20 የዞረ)

የሊቨርፑል  ዕጣ  ፈንታና  

የሮጀርስ  ሚና

“ማን.  ዩናይትድ  ምን  ያህል  ትልቅ  እንደሆነ  

የምታወቀው  ከተቀላቀልከው  በኋላ  ነው”

-  ሉክ  ሸው

Page 22: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 22

ቅንብር በኢሳያስ ከበደበቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ወን

ጀል ምርመራ ክፍል ህንፃ ውስጥ በሚገኝ አንድ ደብዘዝ ያለ ብርሃን ያለው ክፍል ውስጥ ተቀምጧል፡፡ አሮጌ ጠረጴዛና ወንበር እንዲሁም ጥቂት ፋይሎች የተደረደሩበት የመጽሐፍ መደርደሪያ መሰል ነገር ጠበብ ያለውን ክፍል ለብቻቸው ይዘውታል፡፡

በተሰበረው የመስኮት መስተዋት በኩል ቀዝቃዛ አየር ይገባል፡፡ ታገሰ እና መርማሪ ፖሊሱ ፊት ለፊት ተፋጥጠዋል፡፡ በእንጨት ጠረጴዛው ላይ የተዘረጋው አረንጓዴ ቀለም ያለው የተከሳሽ ቃል መቀበያ ፎርም ላይ አቀርቅሮ የሚጽፈው መርማሪ ፖሊስ ታገሰ የሚናገረውን ነገር በሙሉ ይመዘግባል፡፡ አልፎ አልፎ ቀና እያለ ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡

የተረበሸ ስሜቱ እያስታወቀበት ነገር ግን የተረጋጋ ለመምሰል እየሞከረ ቃላቱን በቀስታ ከአፉ እየጎተተ የሚያወጣቸው ታገሰ እዚህ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘበትን ምክንያት ይተርካል፡፡ ይህ የ38 ዓመት ጎልማሳ በሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ነው የተያዘው፡፡ የተጠረጠረበትን ወንጀል ደግሞ በራሱ የእምነት ቃል ትክክል መሆኑን አረጋግጧል፡፡ መርማሪ ፖሊሱ በወንጀል ሕግ ቁጥር 25 መሰረት የእምነት ክህደት ቃሉን በፍርድ ቤት ከማፅደቁ በፊት እዚህች ጠባብ ክፍል ውስጥ በተከሳሹ ስም በተከፈተ ፋይል ታሪኩን እያሰፈረ ነው፡፡

ግንቦት 22 ቀን 1997 ዓ.ም፡፡ ከተማዋ ከምርጫ ቀውሱ ወሬ ገና አላገገመችም፡፡ የአብዛኛው ህዝብ የወሬ ርዕስ ምርጫው በሆነበት የአብዛኛው ህዝብ የወሬ ርዕስ ምርጫ በሆነበት የአብዛኛው ፖሊስ ትኩረትም በዚህ ጉዳይ ላይ ባረፈበት በዚያ ወር ታገሰ በፖሊስ እጅ ወድቋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የዘጠኝ ዓመት ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ገድሏል መባሉ ነው፡፡

‹‹ዘጠኝ ዓመት ዘጠኝ ጊዜ ተሰቃይቻለሁ፡፡ ከዘጠነኛው ስቃይ በላይ የሚሸከም ልብ አልነበረኝም›› ይላል፡፡ ታሪኩን ለመርማሪው እየነገረው ነው፡፡ የተወለደው ከአዲስ አበባ ከተማ አዋሳኝ ቀበሌ አንዷ በሆነችው ዛሬ ግን በከተማው ውስጥ በተካተተችው ቂሊንጦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ነው፡፡ ወደ መሀል ከተማ የገባው ደግሞ በ1988 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ ነው፡፡ ወደዚህ ያመጣው ምክንያት እንጀራ ፍለጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በአጎቱ በኩል ተፈልጎ የተገኘለትን የጥበቃ ስራ ለመስራት የአባቱን ሞፈርና ቀንበር ለታናሽ ወንድሙ አስረክቦ ቂሊንጦን ለቀቀ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የከተማ ልጅ የሆነው፡፡

አማርኛ ለመግባባት ያህል ብቻ የሚናገረውና ከተማውን እምብዛም የማያውቀው ታገሰ ጅማ ከአካባቢው ለመላመድ አልተቸገረም፡፡ ቀጣሪዎቹ ሰዎ ኦሮሞዎች መሆናቸው በቀላሉ ለመግባባትና ቀስ እያለም የከተማውን ህይወት ለመልመድ አስችሎታል፡፡ ባይተዋርነቱ ሲቀንስና ቀለል ሲለው አገሩ ሳለ የሚታወቅበትን ዘፈን ማንጎራጎር ጀመረ፡፡ ‹‹ምናለ ጥምቀት በመጣና የታገሰን ድምፅ በሰማን›› ይሉኝ ነበር ይላል ስለ ጓደኞቹ ሲናገር፡፡ በእርግጥም አሳዛኝ ቅላፄ ባለው ድምፅ የኦሮምኛ ዜማውን ሲያንቆረቁረው ጆሮን ለመያዝ ኃይል ነበረው፡፡ ከቀናት በኋላ በራሱ ቴፕ እየዘፈነ የቀዳውን ድምፁን በካሴት ማጠራቀምም ጀምሮ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ አሰሪዎ ወጣ ሲሉ በር ላይ ተቀምጦ የሚያንጉራጉራትን ዜማ አጥብቃ የምትናፍቅ ሴት የተፈጠረችው ከሩቅ አልነበረም-­ ከዚያው ከግቢው እንጂ፡፡ የቤት ሠራተኛዋ፡፡ ታገስ ለአራት ዓመታት በዚያ ቤት ሲቆይ የዚህች ሴት ወዳጅ መሆኑን እንኳን ያወቀበት የገመተም አልነበረም፡፡ ልጁ ዘለግ ያለ ቁመናውና ፈርጠም ያለ ሰውነቱ ለጥበቃ ስራ ‹የሰጠ› ነው ያስብለው እንጂ ድምፁ ደግሞ በሌላ ወገን የማረካት ሴት አለች፡፡ ስራ በጀመረ በ6ኛው ወር ነበር መግባባት የቻሉት፡፡ እሱም ይህን ዘፈኑን እንደምትወድለት ስለሚያውቅ ባለቤቶቹ በሌሉት ወቅት ሲያንጎራጉርና የልጅቷን ልብ ሲያሸፍት ይውላል፡፡ የሚያዜመውን ነገር ቋንቋውን ሰምታ ረዳት ባትችልም የሆነ የሚያሳዝን ቅላፄ እንዳለው ግን ደጋግማ ትነግረዋለች፡፡ ታገሰ የጥበቃ ቤቱ ውስጥ በነበረችው ትንሽዬ ቴፕ ሁለቱ ቁጭ ብለው ሲያወሩ ደጋግሞ ቀርፆታል እንደምትወደው ነግራዋለች፡፡ እንደሚወዳት ነግሯታል፡፡ የሚዘፈነው ለእርሷ ብቻ እንደሆነም ጭምር፡፡ ይህ ድምፅ ለእርሷ ስጦታ ነው፡፡ የታገሰ ስጦታ፡፡

ትርጎን የወሎ ልጅ ናት፡፡ ሐይቅ አካባቢ ነው የተወለደችው፡፡ አዲስ አበባ ከመጣች ቆየት ብላለች፡፡ ከዚህ ቀደምም በሁለት ሶስት ሰዎች ቤት ተቀጠራ ሰርታለች፡፡ አሁን ከታገሰ ጋር ያገናኛት ቤት የገባችው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም ለቤቱ ግን የኖች የቤተሰቡ አባል ነው የምትመስለው፡፡ አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው በዚህ መኖሪያ ቤት ብዙ ጊዜ እሷና ዘበኛው ታገሰ ብቻ የሚውሉባቸው ቀናት ብዙ ናቸው፡፡ ነጋዴው አባወራ ከባለቤታቸው ጋር ወደ ሱቃቸው ሲሄዱ ልጆቹ ደግሞ ወደ ትምህርት ቤ

ታቸው ያዘግማሉ፡፡ ቤቱ አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር ቀን ላይ አይከፈትም፡፡ እንደተዘጋ በግቢው ውስጥ የሁለት ሰዎች ፍቅር እንደነገሰ ይውላል፡፡ ትርንጎና ታገሰ የሚለያያቸው ቅዳሜና እሁድ ነው፡፡ ያ እንደማይተዋወቁ እንደማይነጋገሩ እንደማይግባቡ ሆነው ሁለቱን የፈተና ቀን ከዓይንና ከጥርጣሬ ለመውጣት በመታገል ያሳልፉታል፡፡ ሁለት ቀን መታገሳቸው አምስት ቀን ያለስጋት ለመጫወታቸው መስዋዕት ናት፡፡ አንድም ሰው ሌላ ግንኙነት አላቸው ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡

ትርንጎ ብዙ ጊዜ የምሽት ስራ ትወዳለች፡፡ ይህን የምታደርገው ሌሊቱ ገፋ ሲል ታገሰን ለመጎብኘት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥርላት ነው፡፡ ይህን ሐሳብ ያመጣው ራሱ ቢሆንም የሌሊቱን ጨለማ ተግና ያቺን የዘበኛ ቤቱን በፍቅር አሟሙቃት የምትመለሰው ትርንጎ ግን ምን ማድረግ እንዳለባት ታውቃለች፡፡ አንዲት ከፉ ቀን መጥታ እስክታጋልጣቸው ድረስ ሁለቱ ጥንዶች ፍቅራቸውን ከብርድልብስ ከጣራና ግድግዳው ውጪ ለማንም ሹክ አላሉም ነበር፡፡

የቤቱ ወይዘሮ አንዲት ለነ ታገሰ የተረገመች በነበረችበት ዕለት ከምሽ 5፡30 ላይ አድርገውት በማያውቁት ሁኔታ ትርንጎን ፈለጓት፡፡ ተኝታ ይሆናል ብለው በማሰብ እንዳያስደነግጧት ብለው ወደምትተኛበት ሰርቪስ ክፍል ሄደው አንኳኩ፡፡ በሩ ክፍት በመሆኑ ውስጥ አለመኖሯን ለመመልከት አልተቸገሩም፡፡ በፍፁም ወ

ደ ሌላ ቦታ ትሄዳለች ብለው ባለመጠርጠራቸው ሲያጧት ደንግጠው ነበር፡፡ የጥሪያቸውን ድምፅ ታገሰ ጥበቃ ቤት ውስጥ ተኝታ የሰማቸው ትርንጎ እየተንደፋደፈች በጨለማ ውስጥ ወደ ሰርቪስ ክፍሏ ስትጣደፍ ወይዘሮዋ ወደበረንዳው ሲመጡ እኩል ተገጣጠሙ፡፡ የምትሰጠው ምክንያትና በዚህ ሰዓት ከክፍሏ ወጥታ የነበረችበትን ቦታ ለመናገር የደረደረቻቸው ውሸቶች ወይዘሮዋን አላሳመኗቸውም፡፡ በዚህ ወቅት ነው ‹‹ከነገ ጀምሮ ጨርቅሽን ጠቅልለሽ ውጪ›› ብለው ያዘዟት፡፡

ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግ አላመነቱም፡፡ ‹‹ነገ ተባብረሽ ቤቴን ታስፍሪዋለች እኔ በሌለሁበት እስከ ዛሬ ያደረግሽውን ነገርም አላውቅም›› በማለት ከቤት እንድትወጣ ጨከኑባት፡፡ ይህ ለታገሰ የማይጋፋው ጭንቀት ጣለበት፡፡ እሱም ተረኛ ተባራሪ እንደሆነ እየገመተ ባለበት ወቅት ወይዘሮዋ ስለድርጊቱ ሰብደውትና አስጠንቅቀውት እንዳይለመደው ነግረው ተዉት፡፡ እሱ ፍፁም ያሰቡት ነገር ልክ አይደለም ብሎ ቢናገርም ከማስጠንቀቂያ ያለፈ ቅጣት ሳይጣልበት ቀኗን ተሻገራት፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ አካሉ ግቢ ውስጥ ቢሆንም ልቡ ግን ከትርንጎ ጋር ተሻግሮ ጠፋ፡፡

ከ2 ወራት በኋላታገሰ ከዚህ በላይ መቆየት አልቻለም፡፡ ይህቺን ልጅ የወደ

ደበት መንገድ ሌላ ማንንም መውደድ የሚችልበት መንገድ አይደለም፡፡ ዘወትር ስለርሷ እያሰበና እየተጨነቀ መኖሩ ፋይዳ እንደሌለው አውቋል፡፡ ስለዚህም ከዚህ ቤት ወጥቶ ትርንጎን መፈለግ እንዳለበት ወሰነ፡፡ ግን የት እና እንዴት እንደሚፈልጋት ማወቅ አልቻለም፡፡ ይህ በሆነበት አንድ ቀን ግን ያልጠበቀው ክስ

ተት ተፈጠረ፡፡እንደተለመደው የቤቱ ባለቤቶች ወደ ስራ ሄደዋል፡፡ ቤቱም

ኦና ሆኗል፡፡ አዲስ የተቀጠረችው ሰራተኛ ከዚህ ዘበኛ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖት ቀድሞ ተነግሯት ስለነበር በምግብ ሰዓት ምሳ እና እራቱን ጣል አድርጋለት ትመለሳለች እንጂ ብዙም ንግግር የላቸውም፡፡

ታገሰም ቢሆን ቀና ብሎ አይቷት አያውቅም፡፡ ለዚህች አዲስ ሴት ቀርቶ በዓለም ላይ አሉ ለተባሉ ቆነጃጅት እንኳን ገፁ የሚበራ አይመስለውም፡፡ በዚህች ቤቱ ውስጥ ያለርሱና ያለሰራተኛዋ ማንም በሌለበት ሰዓት ስልክ ተደወለ፡፡ የባለቤቶቹ ስልክ፡፡ ሰራተኛዋ እንደወትሮ እመቤቷ የደወሉ መስሏት ነበር ያነሳችው፡፡ ከወዲያኛው ጫፍ አንዲት ሴት ታገሰን እንደምትፈልግ ተናገረች፡፡ ሰራተኛዋ አንዳች ጥያቄ ሳታበዛ ታገሰን ጠራችው፡፡ ግራ ተጋባ፡፡ ስልክ ይፈልግሃል ሲባል ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ አንድ ሁለት ቀን የቤቱ ባለቤት ደውለው ትዕዛዝ ቢጤ ነግረውት ያውቃሉ፡፡ ከእሳቸው ሌላ የሚደውል አይኖርም ብሎ ፈጠን ፈጠን እያለ ወደ ሳሎኑ ገባ፡፡ ስልኩን ሲያነሳውና የደወለችው ሴት ትርንጎ ነኝ ስትለው ግን ማመን አልቻለም፡፡ ትርንጎ እዚህ ቤት በዚህ ሰዓት ማንም እንደማይኖር ታውቃለች፡፡ ለዚህ ነበር የደወለችበት አወሩ፡፡ በጣም ጠቂት ወሬ፡፡ በማግስቱ መምጣት ከቻለ ዑራኤል ቤተክርስቲያን በር ላይ እንደምትጠብቀው ገለፀችለት፡፡ ደስ አለው፡

፡ ወትሮም ከዚህ ቤት ለመውጣትና እሷን ለመፈለግ የነበረው እቅድ አሁን ሳይለፋ ቤቱ ድረስ መጥቶለታል፡፡ እንደ ዕድል የቆጠረው ደግሞ የትም ሳይሄድ እሷ እራሷ ያለችበትን ማሳወቋ ነው፡፡ ቀድሞ ከስራ ባለመልቀቁ ተደሰተ፡፡

ምሽት ላይ ቆረጠ፡፡ ፈቃድ እንደሰጡት ሊጠይቅ ካልሆነም ደግሞ ጥሎ ሊሄድ፡፡ አሰሪው ሲመጡ በማግስቱ ወደ ቤተሰቡ ለራሱ ጉዳይ መሄድ እንደሚፈልግ ነገራቸው፡፡ አልተቀበሉትም፡፡ ቤቱን የሚጠብቅ ሰው ስለማይኖር ሰው በሚኖርበት ዕለት መሄድ እንደሚችል ነበር የነገሩት፡፡ እሱ ግን አልተስማማም፡፡ ሰውዬው ‹‹የተናገርኩትን ተናግሬያለሁ በቃ!›› በሚል አይት ጥለወት ገቡ፡፡

ነጋ፡፡ ታገሰ ሌሊቱ ግራ ገብቶት ነው ያለቀለት፡፡ ማለዳው አልመጣህ ብሎት ነው የነጋለት፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ታዲያ ሊነጋጋ ሲል የቀሰቀሱት እኚያ ሰውዬ ናቸው፡፡ አሰሪው ወደ ስራ ሲሄዱ ለምን ይህ ያህል ሰዓት ተኝቶ እንደሚያረፍድ አስጠርተው በስድብና በቁጣ ገሰፁት፡፡ ይህቺ ቃል ‹ሆድ ለባሰው› ታገሰ የመጨረሻው ሆነች፡፡ እሳቸው ባላሰቡት መንገድ ቤቱ ውስጥ ያለችውን አነስተኛ ሻንጣ አንስቶ ልብሱን ከታተተ፡፡ በኋላ አሰናብቱኝ አላቸው፡፡ አባረሩት፡፡ ሄደ፡፡ በዚያ ማለዳ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲደርስ ልቡ ፍርሃት ፍርሃት እያለው ነበር፡፡ በፊት ለፊት በር ላይ ቆሞ እሷን በዓይኑ ይማትር ጀመር፡፡ ሳያስበው ከኋላው መጥታ ያዝ አደረገችው፡፡ ከዚያ በኋላ የነበራቸው ጓዜ ለሁለቱም ምን ያህል እንደሚዋደዱ ያሳየ ነው፡፡ ‹‹በእግራችን መገናኛ እስክንደርስ ድረስ ነው ያወራነው፡፡ ምን ያህል መንገድ እንደተጓዝን እንኳን አላወቅንም›› ይላል ታገሰ ለፖሊስ ሲናገር፡፡

ተለያዩ፡፡ እሱም ወደዘመዱ ቤት እሷም ወዳረፈችበት የአክስቷ ቤት፡፡ ከዚሁ ቀን በኋላ ያለውን ጊዜ ግን ሁለቱን ጥንዶች የሚለያያቸው ነገር አልነበረም፡፡

ከዓመታት በኋላሁልጊዜ እሁድ እሁድ ሳይገናኙ ቀርተው አያውቁም፡፡ ታገሰ

ከዘበኝነት ወጥቶ የቀን ስራ መስራት ከጀመረ በኋላ በየዕለቱ ትርፍ ጊዜ አለው፡፡ ትርንጎ ግን ያው በሰው ቤት ስለምትሰራ ሁሌም ከእሁድ በቀር የዓመት ፈቃድ የላትም፡፡ ስለሆነም ከእሁድ በቀር ከታገሰ ጋር ለመገናኘት ዕድሉ የለም፡፡ ፍቅረኞቹ ላለፉት 6 ዓመታት ያሳለፉት በርቀት ፍቅር ነው፡፡ ተገናኝተው ለማውራት ያለቻቸው ቀን ይህቺ ብቻ በመሆኗ እሁድን እንደነፍሳቸው ነው የሚሰስቷት፡፡ አብረው ለመኖር ግን የትርንጎ ፈቃድ አልተገኘም፡፡ እስካሁን ድረስ ታገሰ ቤት ተከራይቶ አብረው እንዲኖሩ ቢለምናትም በጄ አላለችም፡፡ ይህ ደግሞ የታገሰን አዕምሮ ወደ ሌላ ሃሳብ መርቶታል፡፡ ይህቺ ሴት ሌላ በፍቅር የምታስበው ሰው አለ ማለት ነው ብሎ፡፡ ድምፀ መልካሙ ታገሰ በድምፁ ያሸነፈው ልብ በሌላ ሰው የተጠለፈበት ስለመሰለው ተናዷል፡፡ አብረው ለመኖር ደጋግሞ ሲጠይቅ የምትሰጥ ምላሻም እርሱ በሚፈልገው መልኩ ባለመሆኑ ደስታ ርቆታል፡፡ ወደፊትም አጋጣሚ ቢፈጠርላት ከእርሱ ለመለየት ቀን የምትጠብቅ አድርጎ ሳላት፡፡ ፈርዶበት ቅናት ላዩ ላይ ሰፈረ፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም በመካከላቸው የነበረው ግንኙነት ሻከረ፡፡

በአጓጉል ፀባዩ የሚጨቀጭቃትን ይህንን ሰው ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡ ብስጭቷ ገንኖ ወጥቷል፡፡ አልፎ አልፎ ትናገረዋለች፡፡ ያቺ ስንት ነገር የሚያሳልፉባት እሁድ በየሳምንቱ የጭቅጭቅ ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ ትርንጎን ቅር አሰኝቷታል፡፡ ታገሰ ያለመፈለግ ስሜት ከተሰማው ቆይቷል፡፡

‹‹ያለፉትን ዓመታት ሙሉ ለእርሷ ስል ብዙ መስዋዕትነት እንደከፈልኩ ታውቃለች፡፡ ከስራ ወጥቼ ተንከራትቻለሁ፡፡ ሰርቼ የማገኘውን ነገር ሁሉ ለእርሷ አስፈላጊ ነገር በመግዛት ገንዘቤን አጥፍቻለሁ፡፡ ቤት ተከራይ ብላኝ ተከራይቻለሁ፡፡ የቤት ዕቃ ግዛ ብላኝ በአቅሜ መጠን ገዝቻለሁ፡፡ ትርንጎ የተቀጠረችው ሀብታም ቤት ስለሆነ እዚያ ያየችው ነገር እንዲሟላላት የፈለገች መስላለች፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ግን እኔን ለማዘናጋት እንጂ እንደማታገባኝ ታውቃለች፡፡ በተለይ እኔን አጃጅላ ሌላ ሰው እንደፈለገች ገብቶኛል›› ብሏል ለፖሊስ ሲናገር፡፡

የዚህ ሰው ልብ በፍቅረኛው ላይ አምርሯል፡፡ አለችኝ የሚለው ነገር ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ ለመጣው ጉዳይ መሰረት እንደሆነበት ይገልጻል፡፡ ላለፉት 8 ጊዜያት የቋጠርኳቸው ቂሞች በርሷ ታይተውኛል የሚለው ይህ ‹አፍቃሪ› የትርንጎ ሀጢያት ናቸው የሚላቸውን ነገሮች ዘርዝሮ ተናግሯቸው ነበር፡፡

‹‹ስልክ ደውይልኝ ስላትም-­ ያለሽበት ቤት ስልክ ልደውል ስላትም እሺ አትልም፡፡ ፍቅረኛ እንዳላት እንዲታወቅ አትፈልግም፡፡ እንደር ስላት ‹አዳር ፈቃድ ላንተ ብዬ ያለባህዬ አልወስድም› አለችኝ፡፡ እኔ ለእርሷ ብዬ ስንት ነገር ስሆን እሷ ለእኔ ብላ ማደር አልፈለገችም፡፡ አንድም ቀን እወድሃለሁ አላለችኝም፡፡ እኔ ስጠይቃት ብቻ ነው የምትመልስልኝ፡፡ ቤቴ ነይ ስላት ሁለት ቀን ብቻነው የመጣችው፡፡ ‹ያላገባሁት ወንድ ቤት ለምን እሄዳለሁ› አለችኝ፡፡ ይህም በእኔ ላይ አለመተማመኗን መሰከረልኝ፡፡ ዘመዷን እንድታስተዋውቀኝ ስጠይቃት እምቢ አለች፡፡ ታፍርብኛለች ማለት ነው፡፡ ከእኔ ሌላ ሰው ማፍቀር ትችያለሽ ወይ ብዬ ስጠይቃት ‹ሰው እኮ ነኝ› አለች፡፡ ከእኔ ስትለይ ግድ የላትም ብዬ አሰብኩ፡፡ የእኔን ቤተሰብ ላስተዋውቅሽ ስላት ‹ይቅርብኝ› ያለችኝ ስለምትንቀኝ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አገር ቤት እያለች ያገባችውንና አምልጣው የመጣችውን ባሏን ሁለት ቀን አነሳችብኝ፤ ትፈልገዋለች ማለት ነው፡፡ እነዚህ ስምንት ነገሮች ለዓመታት የቆየበትን ፍቅር ንደውብኝ ኪራ ደርሶብኛል፡፡ ያቃጠልኩት ጊዜ ቆጭቶኛል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ላናግራት ወስኜ ቤቴ ይዣት ስሄድ ግን ያ ዕለት ያላሰብኩት ሆነብኝ›› ብሏል፡፡ እነሆ ዘጠነኛ ስቃይ ያለውን ታሪክም ተናገረ፡፡

ግንቦት 19 ቀን 1997 ታገሰና ትርንጎ ቤት ተቀምጠዋል፡፡ ዛሬ ይዟት የመጣው አን

ድ ጥያቄ ሊጠይቃት ነው፡፡ ‹‹ትፈልጊኛለሽ አትፈልጊኝም?›› የሚል፡፡ እፈልግሃለሁ ካለች እንድታገባው፤ አልፈልግህም ካለች ትታው እንድትሄድ ነበር ውሳኔው፡፡ ቀትር ላይ ነው በሰበብ ያስመጣት፡፡ ለቅሶ አለብኝ ብላ ፍቃድ ጠይቃ ነው የመጣችው፡፡ እዚያች ሳሳ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ብዙ ሳይቆዩ ወሲብ እንዲፈፅሙ ጠየቃት፡፡ ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ ምክንያቱም ደግሞ እሱ እንደሚናገረው ‹‹አረግዛለሁ›› የሚል ነው፡፡ እሱ ግን በሌላ ተርጎሞታል፡፡ አልፈልግህም ማለትሽ (ዘጠነኛው.. እባክዎ ወደ ገጽ 20 የዞረ)

ፍቅርና  ወንጀል

ዘጠነኛው  ስቃይ  -  እውነተኛ  የወንጀል  ታሪክ

ከጃንዋሪ 1 ቀን 2015 -­ ኤፕሪል 15 ቀን 2015

Page 23: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    71 Page

ገጽ 23

ተኩስ በ$25 ብቻ

በቅርቡ ከሃገር ቤት መጥታ በሳሎናችን ሥራ የጀመረችው ስታይሊስት በከተማው በአዳዲስ የሹሩባዋ ዲዛይኗ

ብዙ እየተወራላት ነው፤ መጥተው ይጎብኟት

አርሰናል... ከገጽ 21የዞረ

ጫና ይቀንሳል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ለታላላቆቹ ክለቦች በቀላሉ እና በከፍተኛ ዋጋ ተጨዋቾችን እንድትሰጥ ያደርግሃል፡፡

‹‹ምን ያህል ምርጥ ተጨዋቾችን ለታላላቅ ክለቦች አርሰናል ሸጠ? እነዚህ ተጨዋቾች ሲለቁ ከክለቡ ጋር ዋንጫ እንደሚያገኙ እና ክለቡ የዋንጫ ከራማ እንደሌለው መናገር ነው፡፡ ወደ አርሰናል የሚመጡት ክለቡ ትልቅ ክለብ ስለሆነ ነው፡፡ ከዚያ ለጥቂት ዓመታት ይጫወቱ እና ‹‹ለአርሰናል የተጫወተ›› በሚል ስማቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡

ወደ ታላላቆቹ ክለቦችም ዋንጫ ለማሸነፍ ያመራሉ፡፡ አርሰናልም ትርፍ ለማግኘት ይሸኛቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አርሰናል የሚያስበው ስለገንዘብ ብቻ ነው፡፡ ይህም በቅርቡ የሚቀየር አይመስልም›› ሲል ኤጄ አስተያየቱን ያጠናቅቃል፡፡

የኤጄ አስተያየት አንድ ነገር ያሳያል፡፡ አርሰናል ለምን ከአራተኛ በላይ ሆኖ ለመጨረስ አላማ የለሽ የሆነው ለምን ነው? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ ይህን ለማብራራት አራተኛ ማለት አውሮፓ ለመግባት የሚበቃ፣ በእንግሊዝ ከትልልቆቹ ክለቦች ጋር አብሮ የሚያስጠራ ደረጃ ማግኘት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ትርጉም አይሰጥም፡፡

አርሰናል ሶስተኛ ወይም ሁለተኛ ሆኖ ቢጨረስስ? ደጋፊዎ ከቡድኑ የሚጠብቁት ውጤፍ ከፍ ያላል፡፡ ተጨዋቾቹም የተሻለ ነገር ለማግኘት ጫናው ከፍ ይላል፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ አርሰናል አሁን ከሚያወጣው ውጪ በላይ ገንዘብ ማፍሰስ አለበት፡፡ በዝውውር ገበያውም ከእነ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ሲቲ ጋር መፎካከር ይኖርበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለዋንጫ የሚፎካከር ቡድን ከሆነ አርሰናል ተጨዋቾችን ለ

ትርፍ መሸጡን ያቆማል ማለት ነው፡፡ ይህ እውነት ሆነም አልሆነ የሚገርም መላምት ይመስላል፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ የትኛውም መላምት ወደጎን ሊባል አይችልም፡፡

እነዚህ ሁሉ ግን ቲዮሪዎች ናቸው፡፡ መሬት ላይ ወዳለው እውነት እስኪ እንመለስ፡፡ የአርሰናል ስኳድ ከቼልሲ፣ ሲቲ እና ዩናይትድ ጋር ሲነፃፀር ለዘንድሮ ብቻ ሳይሆን ለቀጣዮቹ የውድድር ዘመናትም ከአራተኛ በላይ ሆኖ በመጨረስ ይቸገራል፡፡ እውነታው ለአርሰናል ደጋፊዎች ያሳምማል፡፡

ሆኖም ከቅርብ የውድድር ዘመናት ወዲህ የተጫዋቾችን ዝርዝር መመልከት እውነታውን ያሳያል፡፡ አርሰናል ከምርጦቹ ቡድኖች ቀጥሎ ያለምርጥ ሆኗል፡፡ የአርሰናልን ምርጥ 11 ብንወስድ አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ ሚሱት ኦዚል እና ሎሮ ኮሺየልኒ ብቻ በሌሎቹ ለዋንጫ በሚፎካከሩት ቡድኖ ውስጥም በቋሚነት የመጫወት ዕድል ያገኛሉ፡፡

የተወሰኑ ጥቂቶች ደግሞ ምናልባት የመፎካከር ዕድል ያገኙ ይሆናል፡፡ የሌሎቹ ተቀናቃኝ ቡድኖች ተጨዋቾች ግን አብዛኞቹ በአርሰናል በቋሚነት የመጫወት ዕድል ያገኛሉ፡፡ በቃ! ነገሩ ያን ያህል ቀላል ነው፡፡

ነገሩ አርሰናል ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች ማጣቱ አይደለም፡፡ ድክመቱ አርሰናል በቁልፍ ቦታዎች ላይ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች ማጣቱ እና ጥልቀት የሌለው መሆኑ ነው፡፡ የመድፈኞቹ ተቀናቃኞች ምርጥ 11 ብቻ ሳይሆን ተጠባባቂዎቻቸውም ከአርሰናል ተቀያሪ ተቸዋቾችም በጥራት ይልቃሉ፡፡

በአጠቃላይም የተሻሉ ተጨዋቾችን ይዘዋል፡፡ የአርሰናል ተቀናቃኞች ለዋንጫ ለመፎካከር የተገነቡ ናቸው፡፡ የሰሜን ለንደኑ ቡድን ግን ከእነርሱ የተረፈውን ለመቀራመት የተሰራ ይመስላል፡፡ ይህ እውነታም ያሳምማል፡፡ በእርግጥ እንደዚህ መሆን አ

ልነበረበትም፡፡ክለቡ አሁን በመልካም የፋይናንስ ጤንነት ላይ ይገኛል፡፡ በ

ዓለም ሀብታም ክለቦች መካከል አንዱ ነው፡፡ ‹‹በትክክለኛ አቅጣጫ እየተጓዘ ያለ›› የሚለውም ከክለቡ ስም ጋር አብሮ ይነሳል፡፡

ሆኖም ይህ መንገድ አርሰናልን ባለበት እንዲቀጥል ያደርግ እንደሆነ እንጂ ደጋፊዎቹ የሚያስቡት ቦታ ላይ ክለቡን አያደርሰውም፡፡ እውነታው ፕሪሚየር ሊጉ ላለፉት ዓመታት ገንዘብ ለሚያወጡ ክለቦች የሚያደላ መሆኑ ነው፡፡

ዋንጫ ለማሸነፍ ህልም ያለው ክለብ ገንዘብ በገፍ ማፍሰስ አለበት፡፡ ይህን ደግሞ ትልቁን የባለቤትነት ድርሻ የያዙት ስታን ክሮኤንክ፣ ቦርዱ እና ቬንገር መስማት አይፈልጉም፡፡

በርካታ ገንዘብ በማውጣት ወደ ፕሪሚየር ሊግ ተፎካካሪነት መመለስ አይሹም፡፡ እንደ አርሰናል ያለ ‹‹ሀብታም›› ክለብ ገንዘቡን አውጥቶ ለዋንጫ ከመፎካከር ይልቅ ባንክ ቤት ማስቀመጡ አስገራሚ ነው፡፡ ይህ እግርኳስ እንጂ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት አይደለም፡፡ ባለፉት ዓመታት ክለቡን ለቅቀው የወጡ ተጨዋቾች የተናገሩትን ‹‹የተሻለ ነገር ፍለጋ›› ያጠናክራል፡፡ አርሰናል ዋንጫ ለመውሰድ የተዘጋጀ አይመስልም፡፡

ከአርሰናል የለቀቁትን ተጨዋቾች አስታውሷቸው፡፡ ለብሔራዊ ቡድኖቻቸው በቋሚነት ይጫወቱ የነበሩ፣ ባለተሰጥኦዎች ናቸው፡፡ የክለቡ ታሪካዊ ተጨዋቾች ቲዮሪ ሆንሪ ክለቡን የለቀቀው ቻምፒዮንስ ሊግ የማሸነፍ ጥሙን እንደማያረካለት ስላወቀ ነው፡፡ እግርኳስ በየደቂቃው እየተለወጠ ነው፡፡ ክለቦች፣ አሰልጣኞች እና ባለቤቶችም የለውጡ አካል መሆን አለባቸው፡፡ አርሰናል ግን ይህን አላደረገም፡፡

ግምት ውስጥ ያስገባውም አይመስልም፡፡ ለቢዮሊክ 2 ሚሊዮን ፓውንድ ከሚከፍል ለስፖርቲንግ ሊዝበን 25 ሚሊዮን

ፓውንድ ከፍሎ ቡድኑን በፍጥነት የሚያሻሽለውን ተጨዋች መግዛት የተሻለ ይሆን ነበር፡፡ በክለቡ ያለው አስተሳሰብ ግን ይህ ነው፡፡ በለንደን ክሎኒይ የልምምድ ማዕከል የመሳ... መስኮቶች አሻግሮ በማየት ከጠቂት ዓመታት በኋላ እንዲህ ሊፈጠር ይችላል ብሎ የሚያስብ እንጂ ለአሁኑ የሚጠቅመውን የሚያደርግ አልተገኘም፡፡

ለማጠቃለል አርሰናል ከአራተኛነቱ ተላቅቆ ለዋንጫ ይፎካከራል ማለት አሳማኝ አይሆንም፡፡ በቅርብ ጊዜ ውስጥም የሚሳካ አይመስልም፡፡ ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ለውጥን የሚፈልገው ከሌለ ደግሞ አይመጣም፡፡ በአርሰናል ደግሞ ይህ ለውጥ መጥቶ ማየት የሚፈልግ ያለ አይመስልም፡፡

ክለቡ ትልቅ ገቢ ያገኛል፡፡ በቻምፒዮንስ ሊጉ ይሳተፋል፡፡ ይህ ደግሞ ለክለቡ ባለስልጣናት ከበቂ በላይ ነው፡፡ ሌሎች ክለቦች ሊጉን ለማሸነፍ ወይም አውሮፓን ለመቆጣጠር ሲያልሙ አርሰናል ትርፌን እንዴት ማሳደግ እችላለሁ በሚል ስራ ተጠምዷል፡፡ የቲኬት ዋጋ እንጨምር ወይስ? እያሉ መጠየቃቸውም አይቀርም፡፡

እግርኳስ ቀላል ነው፡፡ ለማሸነፍ ከፈለግክ ከሁሉም የበላይ የሚያደርግህ የተለየ መንገድ ፈልገህ አንደኛ መሆን ነው፡፡ የአርሰናል ተቀናቃኞ ይህን ያደርጉታል፡፡ አርሰናል ግን ዝም ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ በቅርቡ የሚቀየር አይመስልም፡፡

የጤና መረጃዎችን ለማግኘት

tenaadam.comይግቡ፤ አለመታመም ጤንነት አይደለም

Page 24: (612) 341-4373 Ze-Habesha Newspaper / February 2015 No. 71 ... · ድ አህመድ ከወጣቱ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ጋር ይመጣል ሲባል ብዙዎች ቀኑ ረዝሞባቸዋል።

February 2015 I volume VII I No. 71  የካቲት  7  I    ቅጽ    VII  I      ቁጥር.    717 Page

ገጽ 24

በሥራ ቦታዎ አደጋ፣ የመኪና አደጋና የስፖርት ጉዳት

ከደረሰብዎት እና ካጋጠመዎ እውቅ ካይሮፕራክተር

ከፈለጉ ወደ ካይሮፕራክቲክ ክሊኒካችን ይምጡ

እርሶ የሺ እንጀራን ካልቀመሱ ደንበኞቻችንን ለምን እንደሚመገቡት ይጠይቋቸው፤

የኛ የጥራት ምስክሮቻችን ደንበኞቻችን ናቸው

ሊቨርፑል.... ከገጽ 21 የዞረሮጀርስ የፕሪሚየር ሊጉ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው የተመረ

ጡት ባለፈው የውድድር ዘመን መጨረሻ ነው፡፡ ነገር ግን ከስድስት ወራት በኋላ ሰዎች በእርሳቸው ላይ ተቃውሞ ማሰማት ጀመሩ፡፡ ‹‹ብሬንዳን ሮጀርስ ምርጥ አሰልጣኝ ናቸው ብሎ እንዲያስብ በማድረግ ልዊስ ሱአሬዝ ዓለምን አታለለ›› የሚል እና መሰል ፅሑፎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መነበብ ጀመሩ፡፡ ወቀሳዎቹ ምክንያታዊ ያልሆኑ ናቸው፡፡ እንደ እነዚያ አይት ‹‹የፌዝ›› ፅሑፎችን በገፃቸው ላይ ለጥፈው ‹‹ላይክ›› አልያም ‹‹ሪትዊት›› እንዳደረግላቸው የሚፈልጉ ሰዎች የአዕምሮ ደረጃም ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ያም ቢሆን የሰዎቹን ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ቸል ማለት አይቻልም፡፡ ቡድኑ ከአቅም በታች ሲንቀሳቀስ አሰልጣኙ በተገቢው መንገድ ሊወቀስ ይገባል፡፡

ሊቨርፑል ከዲሴምበር 14 (ሊቨርፑል በኦልድ ትራፎርድ በማንቸስተር ዩናይትድ የተሸነፈበት ጨዋታ) ወዲህ ጥሩ እመርታ አሳይቷል፡፡ ለዚህ ውጤታማነቱ ምስጋና ሊቸራቸው የሚገባ አንድ ሰው ቢኖሩ ብሬንዳን ሮጀርስ ናቸው፡፡ እስቲ ስለ ብሬንዳን ሮጀርስ በመጠኑ እናውጋ፡፡ አሰልጣኙ አንዳንድ ጊዜበሚያበሳጭ መልኩ ግትር ይሆናሉ፡፡ ሃሳቦቻቸው ግን ለዘብተኛ ናቸው፡፡ ወደ ማርሲሳይድ የመጡት የስዋንሲን ፍልስፍና ይዘው ነው፡፡ ስዋንሲ የባርሴሎና አይነት በአጭር ቅብብል ላይ የተመሰረተ ጨዋታን በመተግባሩ ይወደስ ነበር፡፡ የዌልሱ ቡድን በአብዛኛው አሸናፊነቱ

ን የሚያረጋግጠው ከጨዋታ ብልጫ ጋር ነበር፡፡ ሰሜን አየርላንዳዊው በተመሳሳይ መንገድ በሊቨርፑል ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አስቡ፡፡ ነገር ግን በተፈጥሮ ፈጣን ሯች የሆኑ ተጨዋቾችን በያዘው ስብስብ ያለሙትን ማሳካት አልቻሉም፡፡ የጆ አለን በአማካይ ክፍሉ መኖር ብቻ በቀዮቹ ቤት በኳስ ቁጥጥር ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን ለመተግበር በቂ አልነበረም፡፡ ዳንኤል ስተሪጅ እና ፊሊፕ ኩቲንሆ ቡድኑን ሲቀላቀሉ እና ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ ሰብረው ሲገቡ አሰልጣኙ ሃሳባቸውን ቀስ በቀስ በመቀየር ቡድናቸው ፈጣን እግርኳስ እንዲጫወት አደረጉ፡፡ ቀዮቹም ከአጀማመራቸው እጅግ በተሻለ መንገድ የውድድር ዘመኑን አጠናቀቁ፡፡ ነገሮችም መልካ መሰሉ፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን በሊቨርፑል መለያ የሆነው እግርኳስ በመላው አውሮፓ እውቅናን አገኙ፡፡

ቡድኑ ከመከላከል ወደ ማጥቃት የሚያደርገው ፈጣን ሽግግር፣ የጨዋታው ፍጥነት እና የሚተገብረው የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ለተመልካች አስደሳች ነበር፡፡ ቡድኑ ይህን ሲያደርግ በበርካታ አጋጣሚዎች የተከላካይ መስመሩን ለጥቃት ያጋልጥ የነበረ ሲሆን የሊቨርፑል የማጥቃት እንቅስቃሴ እና የሱአሬዝ እና ስተሪጅ መኖር ቡድኑ ከተጋጣሚዎቹ በላይ ጎል እያስቆጠረ ጨዋታዎችን በአሸናፊነት እንዲወጣ ረድቶታል፡፡

ሱአሬዝ ወደ ባርሴሎና አመራ፡፡ ስተሪጅ ተጎዳ፡፡ ሮጀርስ በፊት መስመር ማሪዮ ባሎቴሊ ኦሊያም ሪኪ ላምበርትን ለመጠቀም ተገደዱ፡፡ በዚህ ምክንያት ሊቨርፑልን ውጤታማ ያደረገው ስታይል አላስፈላጊ ሆነ፡፡ ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ የቀዮቹ አሰ

ልጣን ተመሳሳይ ዘይቤ ላይ ሙጢኝ አሉ፡፡ እንደተጠበቀው ውጤት ራቃቸው፡፡ ከአንድ ወር ገደማ በፊት የ41 ዓመቱ አሰልጣኝ አሁን በያዙት ስብስብ ውጤታማ ሊያደርጋቸው የሚችለውን መንገድ ቀየሱ፡፡

ባለፈው የውድድር ዘመን ይጠቀሙበት የነበረውን 3-­4-­2-­1 በተለየ መንገድ መጠቀም ጀመሩ፡፡ አሁን በሚተገብሩት ሲስተም ከአጥቂዎቻቸው መካከል አንዱም ውጤታማ እንደማይሆን ተገንዝበዋል፡፡ ባሎቲሊ እና ላምበርት ቦታ እየቀያየሩ የሚጫወቱ አጥቂዎች አይደሉም፡፡ ቅልጥፍና ይጎላቸዋል፡፡ የማጥቃት እንቅስቃሴውን ያቀዘቅዛሉ፡፡

ይህን የተረዱት ሮጀርስ ስቴርሊንግ የሐሰተኛ ዘጠን ቁጥር ሚናን እንዲወጣ አደረጉ፡፡ ከፋቢዮ ቦሪኒ ጋር የነበራቸውን ልዩነት ፈቱ፡፡ ከሰንደርላንድ ጋር በተደረገው ጨዋታ ጣልያናዊው በስቴርሊንግ ቦታ አሰልፈው አጫውተዋል፡፡ ካሏቸው አማራጮች ፈጣኑ እርሱ ነው፡፡ ፊሊፕ ኩቲንሆ እና አዳም ላላና ከእርሱ ኋላ የ10 ቁጥር ሚናን ይዘው ተሰለፉ፡፡ ከእነርሱ ጀርባ ሁለቱ የመሀል አማካዮ ጆርዳን ሄንደርሰን እና ሉካስ ሌይቫ ቦታቸውን ያዙ፡፡ ከእነዚህ ተጨዋቾች አጠገብ ሁለቱ ዊንግ ባኮች ቦታ ቦታቸውን ያዙ፡፡

የማጥቃት ባህሪን የተላበሰው አልቤርቶ ሞሮኖ እና ላዛር ማርኮቪች ለሚናው ሁነኛ ዕጩዎች ናቸው፡፡ ሰርቢያዊው ከሰንደርላንድ ጋር በተደረገው ግጥሚያ በቀኝ መስመር ተሰልፎ ጥሩ ተንቀሳቅሷል፡፡ ነገር ግን ዤራርድ ተቀይሮ ሲወጣ ከቦሪኒ ጀርባ ያለ

ውን ስፍራ ያዘ፡፡ ሊቨርፑል ቦርንማውዝን ሲገጥም ማርኮቪች የግራ ዊንግ ባክ ሆኖ ተጫውቷል፡፡ ለመጀመሪያዋ ጎል መቆጠር ምክንያት የሆነችውን ኳስ አመቻችቶ ያቀበለው እርሱ ነው፡፡ ሁለተኛውን ጎል ደግሞ በስሙ አስመዝግቧል፡፡

ለሊቨርፑል ውጤታማነት ቁልፍ ሚና በተጫወተው ሶት ተጨዋቾችን በያዘው የተከላካይ መስመር ማርቲን ስከርትል የመሀሉን ስፍራ ይይዛሉ፡፡ ከእርሱ በስተቀኝ ኡምር ቻን ይሰለፋል፡፡ ጀርመናዊው በተጨዋችነት ዘመኑ ከግብ ጠባቂ እና አጥቂ ውጪ በሌሎች ስፍራዎች ተጫውቷል፡፡ በዚህም ሁለገብነቱን አስመስክሯል፡፡ ከበርንሌይ ጋር ሲጋጠሙ ሮጀርስ በእረፍት ሰዓት ኮሎ ቱሬን አስወጥተው በምትኩ አምርቻንን አስገብተዋል፡፡ ውሳኔው ድንቅ ነበር፡፡ ከዚያች ቅፅበት ጀምሮ ቀዮቹ ኳስን ከኋላ መስርተው መጫወት ጀመሩ፡፡ የኢንግስ፣ ቦይድ እና ባርነስ ተፅዕኖም ቀነሰ፡፡ በዚህ የውድድር ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ የሊቨርፑል የኋላ መስመር አስተማማኝ መሰለ፡፡ ኤምሮቻን ለኋላ መስመሩ መረጋጋትን አጎናፅፏል፡፡ የተጋጣሚ ቡድን አጥቂዎች ጫና እያሳረፉበት እንኳን በራሱ የፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ኳስን በደረቱ አብርዶ ወደ መሀል ሜዳ መጠለዝ ይችላል፡፡ ይህን መሰሉ አጨዋወት የሊቨርፑል ደጋፊዎች በተከላካይ መስመራቸው ሲመለከቱ ከነበረው ፍፁም የተለየ ነው፡፡ የተከላካይ መስመሩ በቀላሉ በጫና ውስጥ የሚወድቅ እና ተጋላጭ ነበር፡፡ ቻን ተፈጥሯዊ የመሀል ሜዳ ተጫዋች በመሆኑ ኳስ እግሩ ስር ስትሆን ምቾት ይሰማዋል፡፡ ወደፊት (ሊቨርፑል.. እባክዎ ወደ ገጽ 19 የዞረ)