18/6/2007 - mudc.gov.et

73
/////072007 የመጀመሪያ ዕትም 18/6/2007 የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ የካቲት 2007 .አዲስ አበባ

Upload: others

Post on 04-Oct-2021

1 views

Category:

Documents


0 download

TRANSCRIPT

Page 1: 18/6/2007 - mudc.gov.et

ከ/ል/ቤ/ኮ/ሚ/ር 07፡2007

የመጀመሪያ ዕትም

18/6/2007

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

የካቲት 2007 ዓ.ም አዲስ አበባ

Page 2: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 2 of 73

ማውጫ

1. ወሰን ................................................................................................................................. 4

2. የስታንዳርድ ጥናቱ መነሻ ............................................................................................. 5

3. ትርጓሜዎች ..................................................................................................................... 8

4. የከተሞች ፈርጅ ............................................................................................................ 12

5. የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ................................................................................................. 13

6. ቆሻሻ ማጠራቀም .......................................................................................................... 20

7. ቆሻሻ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች .................................................................................... 24

8. ቆሻሻን ማስተላለፍ (የቆሻሻ ቅብብሎሽ) /Waste Transfer/ ................................... 27

9. የመንገድ፣ የህዝብ ቦታዎች እና የመናፈሻዎች ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ ....... 30

10. የገበያ ቦታዎች ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ................................................................. 39

11 መልሶ መጠቀም ........................................................................................................... 41

12 ቆሻሻን ማከምና ማዳን /Waste Treatment and Recovery/ ................................ 43

13 የቆሻሻ ማስወገጃ (ማከሚያ) ቦታ ................................................................................ 45

14 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ /Health Care Waste/ ...................................... 53

15. የፋይናንስ ጉዳዮች ........................................................................................................ 64

16. ተቋማዊ አደረጃጀት ...................................................................................................... 66

17 ሥራ አመራር ............................................................................................................... 68

Page 3: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 3 of 73

የአሕፅሮተ ቃላት መፍቻ

ይህንን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ለመተግበር የሚያግዝ ደጋፊ

መረጃዎችና የአሰራር መመሪያዎችን የያዘ ክፍል ሁለት ማኑዋል ተዘጋጅቶለታል፡፡

ማአድ፡- ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅት

ኢአጥባ፡- የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን

ተደቆአአ፡- የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ከልቤኮሚ፡-

ማቆአአ፡-

የከተማ ልማት፣ ቤቶች እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

የማዘጋጃ ቤታዊ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

መያድ፡-

ጥአኢ፡-

ደቆአአ፡-

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ዩ.ኤን.ኢ.ፕ/UNEP/፡- የናይትድ ኔሽንስ ኢንቫይሮመንታል ፕሮግራም

Page 4: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 4 of 73

1. ወሰን

ይህ አገር አቀፍ የከተማ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ማዘጋጃ ቤቶች

የህብረተሰቡን ጤንነትና የአካባቢውን ደህንነት ለመጠበቅ ወጤታማ፣ ተደራሽ እና ዘላቂ

የከተማ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችላቸው የአሰራር

ማዕቀፍ ነው፡፡

ይህ የስታንዳርድ ሰነድ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ አዋጅ ቁጥር 515/1999 በተደነገገው

መሰረት የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በህግ የተጣለባቸውን ኃላፊነት

በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ ነው፡፡

ይህ አገር አቀፍ የከተሞች ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ በሁሉም

የኢትዮጵያ ከተሞች ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የደረቅ ቆሻሻ ስራ አያያዝና አወጋገድ

ስርዓት ከዕቅድ እስከ ትግበራ እና አፈጻጸም ባለው ሂደት ውስጥ ቢያንስ ዝቅተኛዉ

መሰረታዊ የአገልግሎት ደረጃ ተፈጻሚ እንዲሆን ያግዛል፡፡

ይህ አገር አቀፍ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ጉዳዩ በቀጥታ

የሚመለከታቸው የክልል እና የከተማ መስተዳደር አካላት፡-

1. የህብረተሰቡን ጤንነት ለመጠበቅ ሁሉም የከተማ ኗሪዎች በቋሚነት እና

በአስተማማኝ ሁኔታ የቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ማግኘታቸውን

ለመረጋገጥ፣

2. የአካባቢውን ደህንነት ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ ቆሻሻን በአግባቡ ተይዞ፣

ተጓጉዞ መልሶ በመጠቀም እና መልሶ በማከም ወይም አግባብነት ባለው ሁኔታ

መወገዱን ለማረጋገጥ፣

3. ጥቃቅንና አነስተኛና ኢንተርፕራይዝ ተቋማት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

የስራ ዘርፍ ተሳታፊ እንዲሆኑ በማስቻል ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ

ጠቀሜታ ለማጠናከር እንዲቻል መወጣት የሚገባቸውን ኃላፊነቶች

ይዘረዝራል፡፡

በዚህ ሰነድ የተካተቱት ስታንዳርዶች በዋነኝነት ከላይ የተዘረዘሩትና ቅድሚያ

የሚሰጣቸው ተግባራት መፈጸማቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሲሆን የተለያዩ

ተጨባጭ ሁኔታዎችን በማገናዘብ በሁሉምነ ባራዊ ሁኔታዎች ተፈጻሚ ሊሆኑ

በሚችሉበት መልኩ የተቀረጹ ናቸው፡፡

Page 5: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 5 of 73

ይሁን እንጂ በስታንዳርዱ የተቀመጠው ዝቅተኛ የአግልግሎት ደረጃ መመዘኛዎች

እስከተሟሉ ድረስ የሚመለከታቸዉ ኃላፊዎች ከስታንዳርዱ ልቀው ለመሄድ ወይንም

አማራጭ እና ተስማሚ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ሊተገበሩ

እንደሚችሉ መገንዘብ ይገባል፡፡

2. የስታንዳርድ ጥናቱ መነሻ

የኢትዮጵያ ከተሞችን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን ስታንዳርድ ማሻሻል በሃገር

አቀፍ ደረጃ ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡

ኢኮኖሚያዊ እድገት ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን የሚያስከትል እና የከተማ ነዋሪዎች

የአሰፋፈር ጥግግትን የሚጨምር ሲሆን ይህ ሁኔታም የከተማ አገልግሎቶች ፍላጎትን

እንዲጨምር የሚያስገድድ ነው፡፡ ይህ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ

በሚዘጋጅበት ጊዜ የሀገሪቷ ከተሞች ተጨባጭ ሁኔታዎች እና ለየአካባቢው

የሚያስፈልጉ ነገሮች ታሳቢ ተደርገዋል፡፡

በዚህ ስታንዳርድ መሟላት የሚገባቸው ተጨባጭ ዝቅተኛ እና መሰራታዊ መስፈርቶች

ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ እነዚህን ዝቅተኛ ስታንዳርዶችን ለማስፈጸም የሚያግዙ

የተለያዩ አሰራሮችም ተብራርተዋል፡፡

ቆሻሻ ከህብረተሰቡ ፍጆታ የሚመነጭ እንደመሆኑ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላቸው

ከተሞች ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻ ያመነጫሉ፡፡ ስለሆነም አነስተኛ የህዝብ ቁጥር

ካላቸው ከተሞች የተለየና ለሁኔታቸው የሚመጥን የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት

እንዲኖራቸው ያስፈልጋል፡፡

በአንጻሩ የትልልቅ ከተሞች የኢኮኖሚ አቅም ከፍተኛ በመሆኑ የተሻሻለ እና የላቀ

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የፋይናንስ አቅም

በመኖሩ በትልልቅ ከተሞች ከትንንሽ ከተሞች የተለየ እና የተሻለ የአገልግሎት ደረጃ

እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በትልልቅ ከተሞች የተጎሳቀሉ እና የደቀቁ ቤቶች በሚበዙባቸው ሰፈሮች

እንዲሁም ከፕላን ውጪ ባሉ አካባቢዎች ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከተው

የስራ ክፍል ሁኔታው የሚያስከትለውን መሰናክል ከግምት ያስገባና ሁሉም ነዋሪዎች

Page 6: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 6 of 73

የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተገቢ የሆነ የደረቅ

ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት መስጠትይጠበቅባቸዋል፡፡

በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ ላይ አገራዊ ለውጥ እንዲመዘገብ መንግስት

አስፈላጊውን አመራር እና ድጋፍ መስጠቱን ይቀጥላል፡፡እንደ አስፈላጊነቱም ተጨማሪ

የፖሊሲ ማዕቀፍ ሰነዶች ከማዘጋጀትም በተጨማሪ በዘርፉ ያልተማከለ የዕቅድና

የትግበራ እርምጃዎችን ያበረታታል፡፡

ይህ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ከአገር አቀፍ ብሄራዊ ፖሊሲና

ሌሎች የህግ ማዕቀፍች እንዲሁም በክክልሎች እና በከተሞች ደረጃ እቅድ አተገባበር

ጋር ቁርኝት ያለው ሰነድ ነው፡፡ አጠቃላይ የሰነዶቹ ስብስብ እና አደረጃጀት ከዚህ

በታች ባለው ዲያግራም /ምስል/ የተገለጸ ሲሆን በነጭ ግራጫ ቀለም የተመለከቱት ገና

በመዘጋጀት ላይ ያሉት ሰነዶች ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም የተዘጋጁ ተያያዥ ሰነዶች

በነጭ የተመላከቱት ሲሆን አገር አቀፍ የፖሊሲ እና የህግ ማዕቀፍ ሰነዶች በጥቁር

ግራጫ ተመልክተዋል፡፡ በክልል እና በከተማ ደረጃ አተገባበርን የሚመለከቱ ሰነዶች

ደግሞ በነጠብጣብ ሳጥኖች ተቀምጠዋል፡፡

Page 7: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 7 of 73

የሚተገበሩት የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት (systems) ተፈላጊዉን

መሰረታዊ ዝቅተኛ የአገልግሎት ስታንዳርድ ለሟሟላት ይችሉ ዘንድ የሚከተሉትን

ወሳኝ ተግባሮች መከናወናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡

ሀ/ በመጀመሪያ ደረጃ በክልል/ከተማ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዕቅድ ውስጥ

በተገቢው ሁኔታ ማካተት፣

ለ/ በአዋጪነት ጥናት እና በድርጊት መርሃ ግብር ውስጥ ስራዎችን በጥልቀት

መዘርዘር፣

ሐ/ ስራዎችን በኮንትራት እና የአገልግሎት አፈጻጸም ዝርዝር /specifications/

መሰረት መተግበር፣

የፖሊሲ ማ

እቀፍ ሰ

ነዶች

ያልተማከለ የእቅድና ትግበራ ክንውኖች

የድርጊት መርሃ ግብር

የክልል/ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድ

የአዋጪነት ጥናት

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የህግ ማዕቀፎች

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ጋይድላይን/መመሪያ

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ስታንዳርድ

የፌደራል ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፖሊሲ

ብሄራዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ስትራቴጂ

ውልና የአገልግሎት መዘርዝር /specifications/ ዝርዝር

Page 8: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 8 of 73

እነዚህ ሰነዶች በጋራ “ያልተማከለ የእቅድና የአፈጻጸም መለኪያዎች” ተብለው የሚጠሩ

ሲሆን ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ጋር የተጣጣሙ መሆን

አለባቸው፡፡

የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች የደረቅ ቆሻሻ ስራ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት

በስታንዳርድ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አግባብ መሰረት ስለመፈጸሙ በየዓመቱ ለከተማ

ልማት፣ ቤቶች እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአመታዊ ሪፖርት ማሳወቅ

ይኖርባቸዋል፡፡

በሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች በሚቀርብ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት

መሰረት እንዲሁም ከትግበራ ከሚገኝ ልምድ በመነሳት ይህ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ስታንዳርድ ሊከለስ የሚችልበት ሁኔታ ታሳቢ ሊሆን ይገባል፡፡

3. ትርጓሜዎች

3.1. የድርጊት መርሃ ግብር፡-የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ግቦችን ለማሳካት

የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ወይም ባለድርሻ አካላት ሊወስዷቸው

የሚገቡ እርምጃዎችን የሚተነትን እና በስትራቴጂያዊና ታክቲካዊ የውሳኔ

አሰጣጥ ሂደት የሚዘጋጅ ተግባራዊ የአፈጻጸም ሰነድ ነው፡፡

3.2. የሚበሰብስ ማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ፡-በረቂቅ ህዋሳት ወይም በሌሎች ህይወት

ያላቸው ነብሳት አማካኝነት በውስን ጊዜ ውስጥ ሊበሰብስ የሚችል እና ወደ

ተፈጥሮ ማዳበሪያነት ሊቀየር የሚችል ቆሻሻ ነው፡፡

3.3. የከተማ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድ፡-የተሻሻለ የደረቅ ቆሻሻ

አያያዝና አወጋገድ ስራን ለመተግበር መከናወን ያለባቸውን ስራዎች

የሚተነትን ዝርዝር መረጃን የያዘ እና አሳታፊ በሆነ ሂደት በሚመለከተው

የከተማ አስተዳደር አካል የተዘጋጀ ሰነድ ነው፡፡

3.4. መሰብሰብ፡-በአመንጪዉ በቆሻሻነት የተፈረጁ ቁሶችን ከመነጩበት ቦታ

ከመሰብሰብ እና መጫን ጀምሮ እስከ ማከም፣ መልሶ መጠቀም ወይም ማስወገድ

ድረስ ያለዉ ሂድት ነዉ፡፡

3.5. ውል(ኮንትራት)፡-የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራን የሚመለከቱ

አገልግሎቶችን ለማቅረብ ወይምመ ለመቀበል በሁለት ወይም ከዛ በላይ ባሉ

Page 9: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 9 of 73

አካላት መካከል የሚደረግ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው አስገዳጅ የስምምነት

የጽሁፍ ሰነድ ነው፡፡

3.6. አግባብነቱን የጠበቀ የቆሻሻ ማስወጋጃ ቦታ፡-ማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻን

አግባብነት ባለው መልኩ እና አግባብነቱን በጠበቀ ቦታ ቆሻሻን የማስወገድ ስራ

ነው፡፡ ቆሻሻን በስሱ (ከ1 ሜትር ባልበለጠ ከፍታ) ቆሻሻው ሊደፋ በተዘጋጀው

ቦታ ላይ ከተደፋና ከተበተነ በኋላ በኋላ ወዲያውኑ በቡልዶዘር ይጠቀጠቃል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ተጨማሪ ቆሻሻ እየተነባበረና እየተጠቀጠቀ እስከ 3 ሜትር

ከፍታ ድረስ ይከማቻል፡፡ መጥፎ ሽታ እንዳይፈጠር እና በነፋስ ሃይል ቆሻሻ

እንዳይበትን የተደፋውንቆሻሻ በየቀኑ በአፈር በመሸፈን መጠቅጠቅ

ያስፈልጋል፡፡ የከርሰ ምድር ውሃ ብክለትን ለመከላከል ሁሉም ዘመናዊ የቆሻሻ

ማስወገጃ ቦታ በጥንቃቄ ተመርጦበአግባቡ መዘጋጀት አለበት፡፡ ከሚደፋው

ቆሻሻ የሚመነጭ ፍሳሽ /leachate/ ወደ ከርሰ ምድር በመስረግ ብክለት

እንዳይፈጠር ለማድረግ የቆሻሻ ማስወገጃው ቦታ በሚዘጋጅበት ወቅት ውሀ

ወደታች በማያሰረግ መልኩቦታውን መለሰን ይኖርበታል፡፡

3.7. የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች፡- ስራን ለማከናወን ወይም ስራውን

ለሌላ አካል ለማስተላለፍ በህግ የተደገፈ ስልጣን እና ኃላፊነት ወይም ውክልና

ያለው ማንኛውም ሰው ወይም ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ድርጅት ሲሆን

በኢትዮጵያ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ በተመለከተ የሚመለከታቸው

የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የሚባሉት ክልሎች እና ማዘጋጃ ቤቶች ናቸው፡፡

3.8. የአዋጪነት ጥናት:-የአንድን ዕቅድ፣ ቴክኖሎጂ ወይም የአሰራር ስልት

ተግባራዊነት ለመፈተሽ እና ለመወሰን የሚደረግ ጥናት ነው፡፡

3.9. ጋይድላየን(መመሪያ)፡-የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን ለማሻሻል

መወሰድ ያለባቸውን ውሳኔዎች እና ሂደቶች በመጠቆም አቅጣጫን የሚያሳይ

ሰነድ ነው፡፡

3.10. ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ፡-ማንኛውም ሙሉ ወይም ከፊል የሰው

ወይም የእንስሳት አካል፣ ደም ወይም ሌሎች የሰውነት ፍሳሾች፣ መድሃኒቶች፣

የፋርማሲ ውጤቶች፣ የህክምና አገልግሎት አነስተኛ መሳሪያዎች፣ የቁስል

መጥረጊያ ጥጥ እና መሸፈኛ ፋሻዎች፣ ስሪንጅና መርፌዎች ወይም ሌሎች

ስለታም ነገሮችን የያዘ ቆሻሻ ሲሆን በአግባቡ ተይዞ፣ ተጓጉዞ ካልተወገደና

ንክኪ ከተፈጠረ አደገኛ የሆነየሆነ ቆሻሻ ነዉ፡፡

Page 10: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 10 of 73

3.11. አደገኛ ቆሻሻ፡-ማናኛውም በፍሳሽ፣ በደረቅ፣ በጋዝ ወይም በዝቃጭ መልክ

የሚወገድ ቆሻሻ ሆኖ በሰው ልጅ ጤንነት፣ እና አካባቢ ደህንነት ላይ አደገኛ

የሆነ ወይም አደገኛ የመሆን ሰፊ ዕድል ያለው ቆሻሻ ማለት ነው፡፡

3.12. የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ፡- የተለያዩ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ስራ ስልቶች እና ሂደቶች በአንድ ላይ በተጣጣመ ሁኔታ፣

በመቀናጀት እና የየራሳቸውን አወንታዊ ሚና ሲጫወቱ ሊፈጠር የሚችል

ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ነው፡፡

3.13. ህግ፡-ከደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሕጎች፣

ደንቦች፣ መመሪያዎች ማለት ነው፡፡

3.14. የመንገድ ላይ ቆሻሻ፡-በየመንገዱ ወይም በክፍት ቦታዎች ላይ የተጣሉ

ወረቀቶች ፕላስቲኮች፣ ጣሳዎች፣ ጠርሙሶች እና ሌሎች ጥቅም አይሰጡም

ተብለዉ የተጣሉ ወድቅዳቂ ቆሻሻዎችን ያካትታል፡፡

3.15. መልሶ ጥቅም ላይ የሚውል ቆሻሻ የሚለይበት ማዕከል፡- ጥቅም ሊሰጡ

የሚችሉ ቆሻሻ በሰው ሀይል ወይም መካኒካል በሆነ ሁኔታ በማሽን ቆሻሻ

በአይነት የሚለይበት ማእከል ማለት ነው፡፡

3.16. ማዘጋጃ ቤታዊ ደረቅ ቆሻሻ፡-ከእያንዳንዱ መኖሪያ ቤት ወይም ህጋዊ ሰውነት

ከተሰጣቸው እና ከመኖሪያ ቤት ጋር ተመሳሳይነት ካላቸው ተቋማት

የሚመነጭ ቆሻሻ ነው፡፡

3.17. ፖሊሲ፡-መንግስት በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ር ዘርፍ ላይ ተጽእኖ

ለመፍጠር፣ ውሳኔ ለመወሰን እና እርምጃ ለመውሰድ እንዲሁም ለማስፈጸም

የሚያዘጋጀው ዕቅድ ወይም የድርጊት መመሪያ ነው፡፡

3.18. የማገገሚያ ቦታ፡-የሰው ሃይል ወይም ማሽን በመጠቀም ተመልሰው

አገልግሎት ላይ ሊውሉ የሚችሉ ነገሮች ከቆሻሻው የሚለዩበት ቦታ ነው፡፡

3.19. የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ አሰባሰብ፡-አመንጪው በቆሻሻነት የተጣሉ ቁሶችን

ከመነጩበት ቦታ ወይም ከቤት ለቤት በመሰብሰብ ወደ ማጓጓዣ በመጫን እና

በማጓጓዝ እስከ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ ወይም እስከ ሁለተኛ ደረጃ ቆሻሻ

መሰብሰቢያ ወይም ማቆያ ቦታ የማድረስ ሂደት ነው፡፡

3.20. መልሶ መጠቀም፡-በቆሻሻ አመንጪው ቆሻሻ ተብለው የተጣሉ ዕቃዎች

በመሰብሰብ እና ቆሻሻውን በአይነት በመለየት እና በፊዚካል፣ መካኒካል

Page 11: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 11 of 73

ወይም ኬሚካል ሂደት በመለወጥ ወደ ሌላ ጥቅም ሰጪ ምርትነት የመቀየር

ሂደት ነው፡፡

3.21. የክልል ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዕቅድ፡-የተሻሻለ እና ዘመናዊ የደረቅ

ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለመተግበር የሚያስችሉ ስራዎችን በመተንተን

የክልል የዘርፉ ኃላፊዎች ወይም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማዘጋጃ

ቤቶች ንቁ ተሳታፊ ሆነው የሚያዘጋጁት የእቅድ ሰነድ ነው፡፡

3.22. ደንብ፡-የህግ አስገዳጅነት ያለው የመንግስት ትዕዘዝ ወይም አዋጅ ነው፡፡

3.23. ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ፡-ቆሻሻ ለጤና ጠንቅ ያለመሆኑ

እስከሚረጋገጥ ድረስ ከአካባቢው ተለይቶ የሚከማችበት እና የአካላዊ፣ የስነ

ህይዎታዊ እና የኬሚካላዊ ሂደት ክትትል እየተደረገለት በእራሱ ተፈጥሮአዊ

ሂደት የሚበሰብስበት ወይም የሚከማችበት ቦታ ማለት ነው፡፡

3.24. ሁለተኛ ደረጃ ቆሻሻ አሰባሰብ፡-ቆሻሻ ከጊዜያዊ ማቆያ ቦታ ወደ መልሶ

መጠቀም ማዕከል ወይም የማስወገጃ ቦታ እስከሚደርስ ያለው የመሰብሰብ

የመጫን እና የማጓጓዝ ሂደት ነው፡፡

3.25. የቆሻሻ ገንዳ (ስኪፕ)፡-የቆሻሻ ማጓጓዣ ተሸከርካሪ ላይ ለመጫን ምቹ ሆኖ

የተዘጋጀ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ ክፍት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ

ነው፡፡

3.26. የቆሻሻ ገንዳ ማንሻ ተሸከርካሪ፡-ቆሻሻን በገንዳ ወደ ቅብብሎሽ ጣቢያ ወይም

ማስወገጃ ቦታ ለማጓጓዝ የሚያገለግል ተሸከርካሪ ሲሆን ተስፈንጣሪ ገንዳን

ለመጫን የሚያስችል መጫኛ እና ማውረጃ የተገጠመለት ተሸከርካሪ ነው፡፡

3.27. ዝርዝር መግለጫ (Speceification)፡-አንድ ነገር ለመገንባት ለመግጠም ወይም

ለመፈብረክ የሚያስፈልጉ የቁሳቁስ (ግብዓት) የልኬት እና የጥራት ደረጃ

መወሰኛ ዝርዝር መግለጫ ነው፡፡

3.28. ስታንዳርድ፡-የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራን ለማስፈጸም እና

የአገልግሎት ደረጃውን ለመወሰን እንዲሁም አፈጻጸሙን ለመገምገም

የሚያስችል የታወቀ የሚለካ ወይም ሊለካ የማይችል መስፈርት ነው፡፡

3.29. ስትራቴጂ፡-የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ግቦችን ለማሳካት እና

ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ዘዴዎችን ስልቶችንና አቅጣጫዎችን

በሳይንሳዊ መንገድ መንደፍ ነው፡፡

Page 12: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 12 of 73

3.30. ቅብብሎሽ፡-ቆሻሻን ከአንድ ንዑስ ክፍል ወደ ሌላኛው ማእከል የሚጓጓዝበት

እንቅስቃሴ ሲሆን አላማውም የትራንስፖርት ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ነው፡፡

3.31. የቅብብሎሽ ጣቢያ፡- ቆሻሻን ወደ መልሶ መጠቀም ማእከል፣ ወይም ማስወገጃ

ቦታ በትላልቅ ተሸከርካሪዎች ከመጓጓዙ በፊት ቆሻሻ ከቤት ለቤት እና

ከሁለተኛ ደረጃ የቆሻሻ ማጠራቀሚ ቦታ ተጓጉዙ በጊዜያዊነት የሚቀመጥበት

ቦታ ነው፡፡

3.32. ማከም፡-ህይወት ባላቸው ነገሮች እና በአካባቢ ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ

ማዘጋጃ ቤታዊ ወይም ከኢንዱስትሪ የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻዎችን ስነ

ህይዎታዊ፣ ኬሚካላዊ እና ሜካኒካል መንገዶችን በመጠቀም ባህሪያቸውን

በመቀየር ጎጂነት እና በካይነታቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲወገድ ወይም

እንዲቀንስ የማድረግ ተግባር ነው፡፡

3.33. ቆሻሻ፡-ጠቃሚነቱ ያበቃለት ዋጋ የማያወጣ ተብሎ የታመነ ከሚፈለገው

መጠን በላይ የተከማቸ ወይም ለተሟላ አገልግሎት ሊውል የማይችል

ማንኛውም ቁስ ነው፡፡

4. የከተሞች ፈርጅ

4.1 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች መሰረታዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ዝቅተኛው ስታንዳርድ በዚህ ሰነድ በተገለጸው መሰረት ተቀባይነት

ባለው ደረጃ መፈጸሙን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው

4.2 ለደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ አፈጻጸም ሲባል ከተሞች

በሚከተሉት ፈርጆች ተከፋፍለዋል፡-

ሀ) የሜትሮ ፖሊስ አስተዳደር፡- አዲስ አበባ ከተማ፣

ለ) የሪጂዮ ፖሊስ አስተዳደር፡-ድሬደዋ፣ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ ደሴና ኮምቦልቻ፣

ጅማ፣ አዳማ እና ሐዋሳ ከተሞች

ሐ) ፈርጅ አንድ ከተሞች፡-ከ100001-250000 ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች፣

መ) ፈርጅ ሁለት ከተሞች፡-ከ50001-100000 ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች፣

ሠ) ፈርጅ ሦስት ከተሞች፡-ከ20001-50000 ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች፣

ረ) ፈርጅ አራት ከተሞች፡-ከ10001-20000 ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች፣

ሰ) ፈርጅ አምስት ከተሞች፡-ከ2001-10000 ህዝብ የሚኖርባቸው ከተሞች፣

Page 13: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 13 of 73

4.3 የሚመነጭ ቆሻሻ እና የሚመነጭ ቆሻሻ አይነትን የሚመለከት ጥናት በመላ

ሀገሪቱ የሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶችን የሚወክል የናሙና መጠን ያለው መሆን

ይገባዋል፡፡እንደዚህ አይነት ጥናቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላቸው

አሰራሮች ጋር መጣጣም አለባቸው፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ አሰራሮች የሚከተሉት

ናቸው፡፡

i/ የአሜሪካ የቁሳቁስ ጥናት ሙከራ እና ፍተሻ ማህበረሰብ የማዘጋጃ ቤት ደረቅ

ቆሻሻ ወዘተ አወሳሰን የጥናት እና ሙከራ ስልት (ASTM - American

Society for Testing and Materials – Standard Test Method for

Determination of the Composition of Unprocessed Municipal Solid

Waste – D5231 -92 -2008);

ii/ ዩ.ኤን.ኤ.ፒ (UNEP)፡- የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ

ዕቅድ አዘገጃጀት መመሪያ ቅጽ 1 የወደፊት ትንብያን ያካተተ የቆሻሻ

አይነት አመዳደብ እና የመጠን አወሳሰን 2009 (UNEP–Developing

Integrated Solid aste Management Plan, Volume1, Waste

Characterisation and Quantification with Projections for Future

2009).

5. የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ

የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ሂደት ቆሻሻ አመንጪውን ከቆሻሻ ሰብሳቢው እና አጓጓዡ ጋር

የሚያገናኝ ነው፡፡ በተግባር ላይ የዋለው የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት አይነት ለዚሁ

ተስማሚ የሆነውን የማጓጓዣ ተሸከርካሪ ዓይነት የሚወስን ሲሆን የተሸከርካሪው አይነት

ደግሞ ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸውን የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች አይነት

ይወስናል፡፡

5.1 የሚመለከታቸው የዘርፉ ስራ ኃላፊዎች የአካባቢውን የመንገድ አመቺነት፣

የአካባቢዉን የቤቶች ጥግግት፣ የሚመነጭውን የቆሻሻ መጠን፣ አሁን ያለውን

የቆሻሻ አሰባበሰብ ልምድ፣ ሊገኘኝ የሚችል የቁሳቁስ አይነት፣ የቅብብሎሽ ጣቢያ

ለማቋቋም ወይም የቆሻሻ ገንዳ ለማስቀመጥ የሚያስፈልግ መሬት መኖር፣ ከቆሻሻ

ማስወገጃ ቦታ ያለውን ርቀት፣ የህብረተሰቡን የመክፈል አቅምና ፍላጎት እንዲሁም

አገልግሎቶቹን በተወሰነው ስታንዳርድ መሰረት ለመቀበል ያለውን ፍላጎት ያገናዘበ

Page 14: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 14 of 73

እና ከእነዚህ ሁኔታዎች ጋር ተስማሚ የሆነ የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት መምረጥ

ይኖርባቸዋል፡፡

የተቀናጀ ዲዛይን እና አፈጻጸም

5.2 በቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት ውስጥ ያሉ ሁሉም ተያያዥ አሰራሮች እርስ በእርስ

የሚቀናጁ እና የተጣጣሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ የቆሻሻ አሰባሰብ

ስርዓት ዲዛይን ትግበራን እና ቅንጅትን ታሳቢ ያደረገ መሆን ይገባዋል፡፡

5.3 የሚመለከታቸው የዘርፉየስራ ኃላፊዎች የተለያዩ አሰራሮችን መርጠው በማዋሃድ

መጠቀም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም በተለያየ የሀገሪቱ ከተሞች በተግባር ላይ የዋሉ

የተለያዩ ስልቶችን ይጨምራል፡፡የህዝብ አሰፋፈር ሁኔታ፣ የተሸከርካሪዎች

መገኘት፤ የትራፊክ ፍሰት ሁኔታ፣ የመንገድ ሁኔታ፣ የቦታው መልክዓምድር ሁኔታ

እና የህዝብ ጥግግት የመሳሰሉት ሁኔታዎች ተመራጭ የሆነውን የአሰራር አይነት

የሚወስኑ ምክንያቶቸ ናቸው፡፡

5.4 የማዘጋጃ ቤት ደረቅ ቆሻሻ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ መሰብሰብ አለበት፡፡ ይሁን

እንጂ የህዝብ ፍላጎትን ለማርካትና በህብረተሰቡ ላይ የጤንነት ስጋትን ለመቀነስ ፣

መጥፎ ሽታን ለመከላከል እንዲሁም ሌሎች በሽታ አምጪ ተ ህዋሳት ማለትም

የወባ ትንኝ፣ ዝንቦችንና ሌሎች አነስተኛ ነፍሳትን መፈልፈል ለመከላከል

በሚያስችል ድግግሞሽ እና ፍጥነት እንዲሁም የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች

ከመጠን በላይ ሞልተው ቆሻሻዉ ሳይንጠባጠብ ቆሻሻ በአግባቡ መሰብሰብ

አለበት፡፡

5.5 የሚመለከታቸዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ከተማውን በተለያዩ ዞኖች በመከፋፈል

እና ለየዞኖቹ የቆሻሻ ሰብሳቢ ቡድን እና ተሸከርካሪዎችን በመመደብ እንዲሁም

ቆሻሻው የሚነሳበትን የመንገድ ፍሰት በመወሰን ለቆሻሻ አሰባሰብ ሂደቱ የተመቸ

አሰራር በመፍጠር መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሁሉም የአገልግሎት

ዞኖች የተጠናከረ ክትትል እና ቅጥጥር በማድረግ የአካባቢውን ንጽህና ማረጋገጥ

አለባቸው፡፡

5.6 የቆሻሻ አሰባሰብ ቅልጥፍናን ውጤታማነት ለማረጋገጥ፣ የተሸከርካሪዎችን ምልልስን

ውጤታማ ለማድረግ እንዲሁም ወጪ ቆጣቢነትን ለማረጋገጥ እና የአገልግሎት

ሽፋንን ለማስፋት ይቻል ዘንድ የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች የቆሻሻ ሰብሳቢ

Page 15: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 15 of 73

ቡድኖች እና የመንገድ ጠራጊዎች የሚሄዱበትን የአሰራር ቅደም ተከተል

በመቀየስ እና በካርታ መልክ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸዉ፡፡

የቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት 5.7 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በራሳቸው መዋቅር ወይም ቆሻሻ

የመሰብሰብ ስልጣን በተሰጣቸው አካላት አማካኝነት የቤት ለቤት ቆሻሻን

የመሰብሰብ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ የአሰራር ስርዓት ሂደት

ጥቅም ላይ ሊውል የሚችሉ ቆሻሻ በየዓይነቱ ተለይቶ ወይም ሳይለይ ሊሰበሰብ

ይችላል፡፡

5.8 ቆሻሻን ከቤት ለቤት ለመሰብሰብ የተለያዩ አነስተኛ ተሸከርካሪዎችን መጠቀም

የሚቻል ሲሆን የእጅ ጋሪ፣ ባለሶስት እግር ብስክሌት፣ በአህያ የሚጎተት ጋሪ

ወይም ሜካናይዝድ ጋሪ አገልግሎት ላይ ሊውል ይችላል፡፡ለመሰብሰብ

የምንጠቀምባቸዉ ተሸከርካሪዎች ዓይነት የትራፊክ ፍሰት ብዛት እና የመንገድ

ሁኔታን በመሳሰሉ አካባቢው ሁኔታዎች የሚወሰን ይሆናል፡፡

5.9 በሌላ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር በፈርጅ 1 እና 2 ምድብ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች

ካላቸው ከፍተኛ የተሽከርካሪዎች ጭንቅንቅ እና ፈጣን የሆነ የትራፊክ ፍሰት

አንጻር ባለሞተር ሜካናይዝድ ተሸከርካሪ ቢጠቀሙ ይመረጣል፡፡

5.10 የቆሻሻ ገንዳ ማንሻ ያልተገጠመላቸው የቆሻሻ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች ጥቅም ላይ

በሚውሉበት ጊዜ የቆሻሻ ማጠራቀምያዉን በሰው ጉልበት ለማንሳት፣ ለማራገፍ

እና ለማውረድ ይቻል ዘንድ የቆሻሻው ማጠራቀሚያዉ የመያዝ አቅም ከ0.3

ሜትር ኪዩብ መብለጥ የለበትም፡፡

5.11 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ 1 ከተሞች ሁኔታዎች ከፈቀዱ ቆሻሻን

የሚጠቀጥቁ ዘመናዊ ተሸከርካሪዎችን መጠቀም እንደ አንድ አማራጭ ሊወሰድ

ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ አማራጭ ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ላሉ ከተሞች

እምብዛም ተመራጭ አይደለም፡፡

5.12 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ፣ በፈርጅ 1 እና 2 ከተሞች ቢያንስ በሳምንት 2 ጊዜ

ቆሻሻ ከቤት ለቤት መሰባሰብ ሲኖርበት በፈርጅ 3፣ 4 እና 5 ከተሞች ደግሞ

ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ መሰብሰብ አለበት፡፡

Page 16: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 16 of 73

5.13 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ቤት ለቤት ቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓትን

ተግባራዊ ለማድረግ ከአገልግሎት ሰጪዎች ጋር ውል ሲገቡ ወይም በልዩ ሁኔታ

የአገልግሎት ፈቃድ ሲሰጡ የአገልግሎቱን መጠን እና ተደራሽነት እንዲሁም

አገልግሎቱ በሚጠበቀው እና ተቀባይነት ባለው ስታንዳርድ ካልቀረበ ሊወሰዱ

የሚገባቸዉን የማስተካከያ እርምጃዎች በሚሠጠው ፈቃድ ወይም ውል ውስጥ

በግልጽ እና በማያሻማ ሁኔታ በማስፈር ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው፡፡

የመንገድ ዳር /Kerbside/ ቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት

5.14 የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች ቆሻሻ አመንጪዎች በመንገድ መታጠፊያ

(ኩርባ) ላይ በተወሰነ ጊዜ እና ሰዓት የሚያስቀምጡትን ቆሻሻ የማንሳት

አገልግሎት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በዚህ የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት በመንገድ ዳርቻ

ላይ ቆሻሻ የሚቀመጠዉ በተያዘለት ግልጽ የቀንና ሰዓት ፕሮግራም እንዲሁም

የቆሻሻ ማጠራቀሚያ እቃዎች በመጠቀም መሆን አለበት፡፡

5.15 በዚህ የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት ነዋሪዎች ከየቤቱ ወይም ከየሱቁ ቆሻሻውን

በማውጣት እና ወደ መንገድ ዳር በማምጣት እንዲተባበሩ ደውል ወይም ሌሎች

ድምጽ የሚያወጡ ዘዴዎችን በመጠቀም መቀስቀስ እና ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡

5.16 ሃድሮሊንክ ማንሻ (ክሬን) ያላቸውና ቆሻሻን የማይጠቀጥቁ ተሽከርካሪዎች

ቆሻሻን ከኩርባ አካባቢ እንዲያነሱ የማድረግ አማራጭ ከአካባቢው ሁኔታ አኳያ

መገምገም ይገባዋል፡፡ እነዚህን ተሸከርካሪዎች በመጠቀም ጎማ ያልተገጠመላቸው

እና እስከ 1 ሜትር ኪዩብ ይዘት ይዘት ያላቸውን ገንዳዎች አሽዋማ ቦታዎች

ጨምሮ በማንኛውም ቦታ ማንሳት እና መገልበጥ የሚቻል ቢሆንም ጠባብ

መንገዶች ባሉበት እና የክሬኑ ጫፍ ከላይ የሚያልፉ እንደ መብራት ያሉ

የመሰረተ ልማት ገመዶችን ሊነካ በሚችልበት አካባቢ ይህንን አማራጭ

መጠቀም አይገባም፡፡

5.17 የመንገድ ዳር ቆሻሻ አሰባበሰብ ስራዓት ተግባራዊ በሆነባቸዉ ሜትሮፖሊስ፣

ሪጂዮፖሊስ፣ ፈርጅ 1፣ እና ፈርጅ 2 ከተሞች ቆሻሻ ቢያንስ በሳምንት ሁለት

ቀን ከመንገድ ዳር መሰብበሰብ ሲኖርበት ፈርጅ 3 ፣ 4 እና 5 ከተሞች ደግሞ

ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ መሰብሰብ አለበት፡፡

Page 17: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 17 of 73

5.18 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ውል

በመግባት ወይም ልዩ የአገልግሎት ፈቃድ በመስጠት ከኩርባ ቆሻሻን የመሰብሰብ

አገልግሎት ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር የሚገባው ውል

ወይም የሚሠጠው ፈቃድ የሚቀርበውን አገልግሎት መጠን እና መሟላት

የሚገባውን መስፈርት የያዘ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም በአገልግሎት ላይ

ጉድለት ቢያጋጥም ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ በማያሻማ ሁኔታ ማካተት

አለበት፡፡

የጋራ ቆሻሻ አሰባበሰብ ስርዓት 5.19 የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች የጋራ ቆሻሻ አሰባበሰብ ስርዓትን ሊተገብሩ

ይችላሉ፡፡ በዚህ አይነቱ አገልግሎት የአካባቢውን ህብረተሰብ የጋራ የቆሻሻ

መጣያ ገንዳዎች የሚቀመጡበትን ቦታ እና በገንዳዎቹ መሀከል ሊኖር የሚገባው

ርቀት በከተማው በማዘጋጃ ቤት በሚዘጋጀው የሰፈር ልማት ፕላን መሰረት

መወሰን ይኖርበታል፡፡ ይሁን እንጂ በተቻለ መጠን ገንዳዎች ከመኖሪያ ቤት

ከ200 ሜትር ባልበለጠ ርቀት እንዲቀመጡ ይመከራል፡፡

5.20 የጋራ የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ከማናቸውም የመሰረተ ልማት መስመሮች ቢያንስ

በ4 ሜትር ርቀት ላይ መቀመጥ አለባቸው፡፡

5.21 የጋራ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ወጣ ገባ ባልሆነ ደረቅ መሬት እና በቂ

ብርሃን ባለበት ቦታ ላይ መቀመጥ አለባቸው፡፡

5.22 የጋራቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ለቆሻሻ ሰብሳቢ እና አጓጓዥ ተሸከርካሪዎች

አመቺ በሆነ እና በትራፊክ ፍሰት ላይ እንቅፋት በማይፈጥር ሁኔታና ቦታ

መቀመጥ አለባቸው፡፡

5.23 የጋራ የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ውስጥ የሚጠራቀመውን ቆሻሻ በየቀኑ ወይም

ቢያንስ በየሁለት ቀኑ በማንሳት ገንዳዎች ቶሎ ቶሎ ባዶ እንዲሆን ማድረግ

ያስፈልጋል፡፡

5.24 የጋራ የቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ከመኖሪያ ቤት ከ200 ሜትር ባልበለጠ ርቀት ላይ

እስከተቀመጡ ድረስ ነዋሪዎች ቆሻሻን ከየቤታቸው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎቹ

ወደአሉበት ቦታ በማምጣት በገንዳዎቹ ውስጥ መድፋት አለባቸው፡፡

Page 18: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 18 of 73

5.25 በትራፊክ ፍሰት መጨናቀቅ ወይም በቦታ ጥበት ምክንያት ገንዳዎቹ ከመኖርያ

ቤት ወይም ከሱቅ 200 ሜትር ባልበለጠ ርቀት ማስቀመጥ ካልተቻለ

የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት የቤት ለቤት ቆሻሻ አሰባሰብን ስርዓትን

በመተግበር ቆሻሻ ከመኖሪያ ቤት ተሰብስቦ የጋራ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ

እንዲጠራቀም ማድረግ ይገባቸዋል፡፡

5.26 በፈርጅ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ያሉ ከተሞች የተሻሻሉ ተሳቢ ያለውን የእርሻ ስራ

ተሸከርካሪ ማለትም ትራክተርን ለጋራ የቆሻሻ አሰባሰብ ስራ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

የጋራ መኖሪያ ህንጻዎች (የአፓርትመንት ህንጻዎች) 5.27 በጋራ መኖሪያ ህንጸዎች እና ፎቆች ስር ወይም አጠገብ ተሸከርካሪ ጎማ

የተገጠመላቸው የቆሻሻ ማጠራቀሚ እቃዎች በማስቀመጥ ቆሻሻ እንዲጠራቀም

እና እንዲሰበሰብ ሊደረግ ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት የህንጻው ነዋሪዎች ራሳቸው

ወይም በጥበቃዎች እና ጽዳት ሰራተኞቻቸው አማካኝነት ቆሻሻን ወደ

ማጠራቀሚያው በማምጣት ማጠራቀሚያ ውስጥ መክተት አለባቸው፡፡

5.28 የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹ እቃዎች ከማይዝግ ብረት መስራት ይኖርባቸዋል፡

የሚይዙት መጠንም ቢያንስ 1 ሜትር ኪዩብ ሆኖ ከአካባቢው የሚመነጨውን

ቆሻሻ ሙሉ በሙሉ ለመያዝ በሚያስችል ብዛት መቅረብ አለባቸው፡፡ በዚሁ

መልኩ የሚጠራቀመው ቆሻሻ ቢያንስ በሳምንት 2 ጊዜ መነሳት አለበት፡፡

5.29 በረጃጅም ፎቆች /ከአምስት ፎቅ/ በላይ ላይ በሚገጠሙ የደረቅ ቆሻሻ ማስወጋጃ

/Garbage Chut/ መስመሮች መዘርጋት ምክንያት ሊከሰት የሚችል የእሳት

አደጋን ለመከላከል እንዲሁም በአጠቃቀም ስህተት እና በማንሸራተቻ መስመሮች

የጽዳት ጉድለት ምክንያት የሚፈጠረውን ብክለት ለማስቀረት ሲባል በጋራ

መኖሪያ ህንጻዎች እና ረጃጅም ፎቆች የቆሻሻ ማንሸራተቻ ስልትን አለመጠቀም

ይመረጣል፡፡ ይሁን እንጂ (በኢትዮጵያ የህንጻ መመሪያ ቁጥር 5/2003 አንቀጽ

29 ንዑስ አንቀጽ 29.10 በሚፈቅደው መሰረት) የደረቅ ቆሻሻ ማስወጋጃ

የተገጠመለት ህንጻ ሲያጋጥምም በዕቃ ማንሸራታቸው ውስጥ ሊከተቱ የሚችሉ

ቆሻሻዎች (ትንንሽ ቆሻሻዎች) እና መከተት የሌለባቸውን ቆሻሻዎች (ትልልቅ

ዕቃዎች፣ የካርቶን ሳጥኖች ወዘተ) የሚገልጽ የአጠቃቀም መመሪያ እና ማብራሪያ

Page 19: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 19 of 73

ለህንጻው ነዋሪዎች መሰጠት አለበት፡፡ ተከታታይ የሆነ ክትትል፣ ጥገና፣ ቆሻሻ

የማንሸራተቻውን ጽዳት ግምገማ እና የማስተካከያ ስራ መሰራት ይኖርበታል፡፡

የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት ተግባር እና ኃላፊነት

5.30 ቆሻሻ አመንጪዎች ቆሻሻን ወደ ተወሰነው መሰብሰቢያ ቦታ የማምጣት ኃላፊነት

አለባቸው ይህም የህብረተሰቡ የጋራ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ፣ ኩርባ ወይም የቤት

ለቤት ቆሻሻ መሰብሰቢያ ቦታ ሊሆን ይችላል፡፡

5.31 ቆሻሻ አመንጪዎች ቆሻሻ እንዳይበተን በአግባቡ በማጠራቀም ማስረከብ ግዴታ አለባቸው፡፡

5.32 ቆሻሻ አመንጪዎች ቆሻሻውን ወደ የጋራ ማጠራቀምያ ገንዳ ካደረሱ በኋላ

ወይም ለመጀመሪያ ደረጃ ሰብሳቢዎች ካስረከቡ በኋላ የሚመለከታቸው አስፈጻሚ

አካላት ይህም ሲባል የተሰበሰበውን ቆሻሻን ወደ መልሶ መጠቀም እና ማከሚያ

ማዕከላት፣እንዲሁም ማስወገጃ ቦታ ለማድረስ የሚያስችል የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ

አያያዝና አወጋገድ ስርዓት አገልግሎት የመዘርጋት ኃላፊነት አለባቸው፡፡

5.33 የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ በቀን መሰብሰብ አለበት፡፡ ነዋሪዎችን ከድምጽ ብክለት

ለመከላከል እንዲሁም የነዋሪዎችን እና ሰብሳቢዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል

ቆሻሻን በምሽት (በሌሊት) መሰብሰብ መከልከል አለበት፡፡ ይሁን እንጂ

ሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ 1 የተመደቡ ከተሞች ቀን ላይ

የሚኖራቸው ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ቆሻሻን በመሰብሰብ ስራ ላይ ከፍተኛ

እንቅፋት የሚፈጥር ከሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ የምሽት (የሌሊት) ቆሻሻ አሰባሰብ

አገልግሎትን እንደ አማራጭ መጠቀም ይችላሉ፡፡

5.34 የጋራቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች የት መቀመጥ እንዳለባቸው ከመወሰኑ በፊት

የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች ህብረተሰቡ በውሳኔው መሳተፉን ማረጋገጥ

ይኖርባቸዋል፡፡ መጥፎ ሽታ፣ የውሾች፣ ድመቶች እና ሌሎች ቆሻሻ ተመጋቢ

እንስሳት መበራከት ስጋቶች እንዲሁም ገጽታንና የስነ ውበት ፍላጎቶችን ባገናዘበ

ሁኔታ ገንዳዎቹን በአመቺ ቅርበት እና ቦታ ለማስቀመጥ የነዋሪዎች ተሳትፎ

ወሳኝነት አለው፡፡

5.35 ሆን ተብሎ የሚደረግ የቆሻሻ ማቃጠል ተግባርን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል

የሚመለከታቸው ኃላፈዎች ተገቢውን የህግ ማስፈጸሚያ ስርዓት መዘርጋት

አለባቸው፡፡ቆሻሻን ማቃጠል ለጤና ጠንቅ የሆነ አደገኛ ጭስ ከመፍጠር

Page 20: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 20 of 73

በተጨማሪ የብረት ገንዳዎችን የመከላከያ ሽፋን በማቅለጥና የፕላስቲክ

ገንዳዎችን በማቃጠል ጉዳት ያስከትላል፡፡

5.36 ሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት በቀጥታ በሚተገብሩትም ሆነ በውል ወይም ልዩ

ፍቃድ በመስጠት የሚያስተገብሩት የቆሻሻ አሰባሰብ አገልግሎት በመደበኝነት

በአስተማማኝነት እና የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድን ተከትሎ

መተግበሩን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

6. ቆሻሻ ማጠራቀም

ቆሻሻ ማጠራቀም ማለት ቆሻሻ አመንጪዎች (መኖሪያ ቤቶች፣ ሱቆች ወዘተ..) ወይም

የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ቆሻሻን የሚያጠራቅሙበት ሆኖ ወደ ሚቀጥለው

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሰንሰሰለት ከመሻገሩ በፊት ያለው ሂደት ነው፡፡

የሚተገበረው የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት እንዲሁም የምንጠቀምባቸው የቆሻሻ አንሺ

ተሸከርካሪዎች መጠቀም የሚገባን የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃ ዓነት ይወስኑታል፡፡

6.1 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የእያንዳዱን አካባቢ ተጨባጭ

ሁኔታ ያገናዘበ ጥናት በማድረግ ለአካባቢው ተስማሚ የሆነና ከአጠቃላይ

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ ሰንሰለት ጋር የሚጣጣም የቆሻሻ

ማጠራቀሚያ ስርዓት መወሰን አለባቸው፡፡

6.2 ቆሻሻን ከመሰብሰብ አንስቶ እስከ መጨረሻው የስራ ደረጃ ባሉት ሂደቶች

ቆሻሻ ከመሬት ጋር ተደጋጋሚ ንክኪ እንዳይኖረው ለማድረግ ይቻል ዘንድ

የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ቆሻሻ በአግባቡና ተስማሚ በሆነ

የማጠራቀሚያ ገንዳ ተከማችቶ የሚጫንበትና የሚጓጓዝበት አሰራር

መተግበር አለባቸው፡፡

6.3 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች

ገንዳዎቹን ከሚያጓጉዙት ተሸከርካሪዎች የቆሻሻ ገንዳዎችን ከመጫንና

ከማውረድ ጋር ተስማሚ እና አግባብነታቸዉ የጠበቀ መሆናቸውን ማረጋገጥ

አለባቸው፡፡

6.4 በመንገድ ዳር የሚከማች ቆሻሻ ለማሰባሰብ ከፍተኛ ስራ የሚጠይቅ እና

ለዓይን አጸያፊ ከመሆኑም በላይ በንፋስ በመበተን የሚያቆሽሽ እና ቆሻሻ

ተመጋቢ የሆኑ እንስሳትን የሚስብ በመሆኑ የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ

Page 21: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 21 of 73

ኃላፊዎች ቆሻሻን በየመንገዱ ዳር ማከማቸት እንዲቀር ብርቱ ጥረት ማድረግ

አለባቸው፡

6.5 የአካባቢውን ህብረተሰብ ፍላጎት፣ በስራ ላይ ያለውን የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት

እንዲሁም ለዚህ ስራ የዋሉ ተሸከርካሪዎችን ከግንዛቤ በማስገባት እና

በተለያየ የቆሻሻ አሰባሰብ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን መሰረት በማድረግ

የተለያየ የቆሻሻ ማከማቻ (ማጠራቀሚያ) ዓይነቶችን በስራ ላይ ማል

ይቻላል፡፡

6.6 ሜካናይዝድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ዕቃ ማንሻ መጠቀም በማይቻልበት ሁኔታ

ሲሞላ ያለችግር በሰው ጉልበት ሊነሳ የሚችል እና ለአካባቢው ሁኔታ

ተስማሚ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

6.7 ሜካናይዝድ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ማንሻ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ

ከማይዝግ ብረት በፋብሪካ የተሰሩ እና በቀላሉ ሊነሱ የሚችሉ የቆሻሻ

ማጠራቀሚያ ገንዳ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከጠንካራ ፕላስቲክ የሚሰሩ

ገንዳዎች ለእሳት አደጋ ተጋላጭ ስለሆኑ እና በቀላሉ ስለሚቃጠሉ ለዚህ

አገልግሎት መዋል የለባቸውም፡፡

6.8 በሁሉም ከተሞች የጋራ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ዝቅተኛው መሰረታዊ የመዘጋጃ ቤታዊ ደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት ስታንዳርድ ነው፡፡ የቤት ለቤት ቆሻሻ ማንሳት እና የመንገድ መገንጠያ (ኩርባ) ዳር ቆሻሻ ማንሳት አገልግሎቶች በጋራ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከማቅረብ የላቁ የአገልግሎት ሰታንዳርዶች ናቸው፡፡

6.9 ዝቅተኛው መሰረታዊ የአገልግሎት ደረጃ (የጋራ ገንዳ) በስራ ላይ በሚውልበት ጊዜ ገንዳዎቹ ከመኖሪያ ቤቶች ከ200 ሜትር ባልበለጠ ርቀት መቀመጥ አለባቸው፡፡ ገንዳው በቅርበት መቀመጡ ያለአግባብ የሚጣል ቆሻሻን ለመቀነስ እና በየመንገዱ የቆሻሻ መዝረክረክን እንዲቀንስ ይረዳል፡፡

6.10 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች የሚቀመጡበት ቦታ የሚከተሉትን እሳቤዎች

ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡

ሀ/ የትራፊክ ብዛትን፣ ተሻጋሪ መብራትና የስልክ ገመዶችን ከግምት

ባስገባ ሁኔታ ለህብረተሰቡ እና ለቆሻሻ ሰብሳቢ ተሸከርካራች አመቺ

እና ተደራሽ በሆነ ቦታ ላይ ማስቀመጥ እና በዕቅድ ወቅት ታሳቢ

መሆን አለበት፡፡

Page 22: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 22 of 73

ለ/ ገንዳዎች በግልጽ በሚታይ ቦታ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ገንዳዎቹ

አቅራቢያ የመንገድ መብራት እንዲኖር በማድረግ ጭምር የተሻለ

ብርሃን እና ዕይታ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ሐ/ የህብረተሰብ ደህንነት፡-ሰዎች ወደ ገንዳዎቹ ለማድረስ ፈጣን የትራፊክ

ፍሰት ያላቸው ወይም የተጨናነቁ መንገዶችን ማቋረጥ የለባቸውም ፡፡

መ/ ከእንስሳትና ከአዕዋፋት ንክኪ መከላከል፡-ይህን ለማድረግ የቆሻሻ

ማጠራቀሚያ ክዳን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

6.11 የህብረተሰብ የጋራ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎችን የመያዝ አቅም ለመወሰን የሚከተሉት ምክንያቶች ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡

ሀ/ገንዳውን ከሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ አካባቢዎች የሚመነጨው የቆሻሻ መጠን፣

ለ/ በገንዳ ውስጥ የሚከማች የቆሻሻ አይነት፣ ሐ/ ከገንዳ ውስጥ የሚከማቸው ቆሻሻ የሚገለበጥበትና ገንዳው ባዶ በሚሆንበት ቀናት መካከል የሚጠበቀው ረጅም ጊዜ፣

6.12 የገንዳው አይነትና መጠኑ በቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓትና የተሸከርካሪ አይነት

መወሰን አለበት፡፡ ሜካኒካል የቆሻሻ ማንሻ ተጠቅመው ቆሻሻ የሚሰበስቡ

ተሸከርካሪዎች ጥቅም ላይ ሲዉሉ የገንዳው መጠን በቆሻሻ እቃ ማንሻው

ከፍተኛ ማንሳት አቅም ይወሰናል፡፡ የሰው ጉልበት በመጠቀም በሚደረግ

የቆሻሻ መሰብሰብ ሂደት በመሰብሰብና በመጫን እንዲሁም ገንዳውን ባዶ

በማድረግ ወቅት የሰዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የገንዳው መጠን ቢበዛ 0.6ሜ3

መሆን አለበት፡፡

ሳጥን 1፡ አስፈላጊ የገንዳ ስፋት መጠን ቀመር

ቀመሩ ፡ (ሀ X ለ + ሐ) X መ = ሰ

ሀ ═ የሚመነጨው የቆሻሻ መጠን (ሜ3 በሰው በቀን)

ለ ═ ገንዳዉን የሚጠቀሙ ሰዎች መ ═ የቆሻሻ አሰባሰብ ድግግሞሽ (ገንዳው ባዶ የሚሆንባቸው ረዥሙ የቀናት ብዛት ) ሐ ═ ከሌላ ምንጭ ተሰብስቦ የሚወገድ የቆሻሻ መጠን (ሜ3 በሰው በቀን) ሰ ═ የገንዳው መጠን በሜትር ኪዩብ

Page 23: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 23 of 73

6.13 ሜካኒካል የቆሻሻ ማንሺያ ያላቸው ተሸከርካሪዎች ስራ ላይ ከዋሉ በማይዝግ

ብረት የተሰሩት የጋራ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ቢያንስ የEN840

መስፈርትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ/ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳው ተፈላጊው የአፈፃፀም መስፈርትና

ለተመደበለት ክፍል የEN840 ምርመራ ማሟላት አለበት፡፡

ለ/ ገንዳው ተቀባይነት ያለው፣ ገንዳውን ለሚያነሳው ተሸከርካሪ ተስማሚ

እና የተሻሻለ ሆኖ መሰራት ይኖርበታል፡፡

ሐ/ገንዳው በተሸከርካሪ በሚነሳበት ወቅት ግጭት ቢፈጠር ጉዳት

እንዳይከሰትና የገንዳው ማንሺያ ከገንዳው እንዳይላቀቅ እጀታዎቹ

ጠንካራ ሆነው መሰራት ይኖርባቸዋል፡፡

6.14 የማህበረሰብን ጤንነትና የአካባቢን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ተንቀሳቃሽ

ያልሆነ ቋሚ የጋራ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ መጠቀም ክልክል ነው፡፡

የማይንቀሳቀስ የቆሻሻ የጋራ ማጠራቀሚያ ገንዳ ስንጠቀም ቆሻሻውን ለማጓጓዝ

በእጅ መነካካት ስለማይቀር በምንም መልኩ መፈቀድ የለበትም፡፡

6.15 ከፍተኛ የቆሻሻ ክምችት ባለበት አካባቢ አመቺ መሬት ማግኘት ካልተቻለ

የጋራ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎቹ የሚቀመጡበት ቦታ በኮንክሪት መገንባት

ይቻላል፡፡ ቢሆንም የሚሰራው የገንዳ ማስቀመጫ /Platform/ የሚከተለው

መስፈርት ማሟላት አለበት፡-

ሀ/ ለጥንካሬ እንዲያመች በግምት 15 ሴ.ሜ. ቁመት ከወፍራም የጠርዙ

ውፍረት (30 ሴ.ሜ. ቁመት x 30 ሴ.ሜ. ወርድ)፣

ለ/ ለተጨማሪ ጥንካሬና መሰንጠቅን ለመቌቌም በ1.25 ሴ.ሜ. ብረት

ኮንክሪት ስላቭ መደረግ አለበት፣

6.16 የቤት ለቤት ቆሻሻ መሰብሰብ ሜካናይዝድ በሆነ የቆሻሻ ማንሺያ ተሸከርካሪ

የሚከናወን ከሆነ ገንዳዎቹ ከማይዝግ ብረት ወይም ከጠንካራ ፕላስቲክ

መዘጋጀታቸው አለባቸው፡፡

ስለሆነም የቆሻሻ ማጠራቀሚው ገንዳ የሚከተለውን ዝርዝር መስፈርት

ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

ሀ/ የመያዝ አቅም፡-ከ120 -240 ሊትር

ለ/ መስፈርት፡- በEN840 ተቀባይነት ያገኘ

Page 24: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 24 of 73

6.17 የመንገድ መታጠፊያ አሰባሰብን በሜካናይዝድ የቆሻሻ ማንሺያ ተሸከርካሪ

የሚከናወን ከሆነ ገንዳዎቹ ከማይዝግ ብረት መሰራትና የሚከተለው ዝርዝር

መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

ሀ/ የመያዝ አቅም፡- >1,100 ሊትር

ለ/ መስፈርት፡- በEN840 ተቀባይነት ያገኘ

6.18 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ንፁህ ሆነው በቅደም ተከተል መደርደር

አለባቸው፡፡ እንዲሁም በየወሩ ፍተሻ ሊደረግላቸውና ሊፀዱ ይገባል፡፡የጋራ

ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ባለበት 10 ሜትር ሬዲያስ ያለ ሁሉም አካባቢ

ቢያንስ በሦስት ወር አንድ ጊዜ መፅዳት አለበት፡፡

7. ቆሻሻ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች

የቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሽከርካዎች ቆሻሻ በገንዳዎች ከተሰበሰበ በኋላ ወደሚቀጥለው

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሂደት ማለትም ወደ ቅብብሎሽ ጣቢያ፣ ቆሻሻ ማከሚያ

ጣቢያ ወይም ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ያጓጉዛሉ፡፡ የቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሸርካሪዎች

ስታንዳርድ ተግባር ላይ ባለው የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ

ነው፡፡

የተሸከርካሪ መረጣና ተስማሚነት

7.1 የቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሸከርካሪ ዓይነቶች ሲመረጡ በርካታ ምክንያቶች ግምት ውስጥ

ገብተው መሆን ይገባዋል፡፡ እነዚህም ምክንያቶች የሚመነጭ የቆሻሻ መጠን፣

የቆሻሻ ዴንሲቲ፣ የቆሻሻ አይነቶች፣ የትራንስፖርት ርቀትና የመንገድ ሁኔታ፣

የትራፊክ መጨናነቅ ሁኔታ፣ የመለዋወጫ ዕቃ ማግኘትና የጥገና ፋሲሊቲ መኖር

እና ከሌላው የኤኮኖሚ ሴክተር ጋር የሚያገናኝ የትራንስፖርት ስርዓት መኖር

ናቸው፡፡

7.2 የቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሸከርካሪዎች የመስራት አቅም በሚያጓጉዙት የቆሻሻ መጠን

በቶን በቀን ስለሚለካ ውጤታማነታቸውን በእቅድና ዲዛይን ወቅት ግንዛቤ ውስጥ

ማስገባት ያስፈልጋል፡፡

Page 25: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 25 of 73

7.3 አገር ውስጥ ጥገናቸውን ለማከናወን የሚቻለውን እና በሀገር ውስጥ በቀላሉ

መለዋወጪያ እቃቸው ለሚገኝ የተሸከርካሪ አይነቶችን ቻንሲን ቅድሚያ መስጠት

አስፈላጊ ነው፡፡

7.4 መደበኛ ጥገናና መለዋወጫ ዕቃ አቅርቦት ከነዋስትናው የሚገኝ ከሆነ እና

ሀይድሮሊክ የቆሻሻ ማንሺያ ተሸከርካሪ ከEN840 ገንዳ ጋር የሚጣጣም እና

ሊገጥም የሚችል ከሆነ እንዲሁም ተቀባይነት ካገኘ ሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ

እና በፈርጅ 1 ውስጥ ለሚገኙ ከተሞች መጠቀም ይቻላል፡፡ የተለዩ ቆሻሻን

የሚጠቀጥቁ ተሸከርካሪዎች/ኮምፓክተር ተሸከርካሪዎች ለቆሻሻ ማጓጓዢያ በፈርጅ

2፣ 3፣ 4 እና 5 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ባይጠቀሙ ይመረጣል፡፡

7.5 ቆሻሻን የሚጠቀጥቁ/ ኮምፓክተር ተሸከርካሪዎች በባለ ብዙ ፎቅ አፓርታማ አካባቢ

1ሜ3 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ አገልግሎት ላይ በዋለበት ሁኔታ መጠቀም

የሚቻልበት ሁኔታ አለ፡፡ ይሁን እንጂ ይህ መሆን የሚችለው የተስተካከለ ጥሩ

መንገድ ሲኖር ብቻ ነው፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ መሰብሳቢያና ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች

የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ መሰብሰቢያ ተሸከርካሪዎች የሰራተኞችን ጤንንትና ደህንነት

መርህ የተከተለእና ለሰራተኞች አመቺ እንዲሆን በሚያስቻል ሁኔታ ዲዛይን ተደርጎ

መሰራት አለበት፡፡

7.6 የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ መሰብሰቢያ ተሸከርካሪዎች መልሰው ጥቅም ላይ

የሚውሉና ሌሎች በአይነት ያልተለዩ የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ ለየብቻው በመለየት

የሚጭኑ መሆን አለባቸው፡፡

7.7 በእጅ የሚገፉ ጋሪዎች ቀጥ ያሉና በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ፣ ለመንገድ ደህንነት እና

የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚያንጸባረቅ ቀለም የተቀቡ፣ ቀላል ክብደት ያላቸው፣

ጠንካራና ሰዎች በቀላሉ የሚያንቀሳቅሷቸው ሆነው ዲዛይን መደረግ እና መሰራት

አለባቸው፡፡ እንዲሁም ጥቅም ላይ የሚውሉና ሌሎች በየአይነቱ ያልተለዩ ቅይጥ

የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻዎችን ለየብቻው ለያይተው መጫን የሚችሉ መሆን

አለባቸው፡፡

Page 26: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 26 of 73

7.8 በአህያ የሚጎተቱ ጋሪዎች በአግባቡ ዲዛይን የተደረጉና ከእንስሳሰቶቹ የመሸከም

አቅም ጋር የተጣጣሙ መሆን ይገባቸዋል፡፡ እንዲሁም የአህዮችን ጫና ለመቀነስ

በቀላሉ የሚያጔጉዙበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡

7.9 ሜካናይዝድ ባለሞተር የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻን የሚያሰባስቡ ተሸከርካሪዎች

በአገር ውስጥ መጠገን የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

ሁለተኛ ደረጃ ቆሻሻ መሰብሳቢያና ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች

7.10 የሁለተኛ ደረጃ ቆሻሻ መሰብሳቢ ተሽርካሪዎች ከፍተኛ አፈፃፀም ለማስመዝገብ

በቀላሉ የሚጠገኑና የመለወዋጫ ዕቃ አገር ውስጥ የሚገኝላቸው በመለየት

ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል፡፡

7.11 በአካባቢ መገኘት በመቻላቸው፣ በማዘጋጃ ቤት አቅም ሊገዙ መቻላቸው እና

የአገልግሎት ዘመን እንደ መስፈርት በመውሰድ በፈርጅ 2፣ 3፣ 4፣ እና 5 ውስጥ

የሚገኙ ከተሞች ተጎታች ያላቸዉ ትራክተሮችን መጠቀምን ግምት ውስጥ

ማስገባት አለባቸው፡፡

7.12 ባለተሳቢ ትክተሮች ለቆሻሻ ማጓጓዢያ ስራ ላይ በሚውሉበት ጊዜ በሃይደሮሊክ

የሚሰሩ፣ የተሸሻሉ እና በቀላሉ የሚጎተት አጭር የጭነት ቁመት እና 5ሜ3

የመጫን አቅም ካላቸው ተሳቢዎች ጋር መገናኘት አለባቸው፡፡

7.13 ቆሻሻ ሰብሳቢ ሰራተኞች ከትክሻቸው በላይ (የተለመደው 1.5 ሜትር ነው)

በተደጋጋሚ መሸከም አይጠበቅባቸውም፡፡ ይህም ቆሻሻ ወደ ጭንቅላታቸው

በመደፋቱ ምክንያት የሚከሰት የጤና ችግር እንዲሁም የወገብና የአንገት ጡንቻ

መዳከምን ያስወግዳል፡፡

7.14 የቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ሲታቀድ የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች

በከባድ ዕቃ ማንሺያ ማሽን መጠቀም ትኩረት ሊያደርጉበት የሚገባ ጉዳይ

ነው፡፡

7.15 ቀደም ብሎ የነበረ በገንዳ ማንሺያ ደረቅ ቆሻሻን የማንሳትና የማጓጓዝ ስራ

ተግባራዊነቱ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ሆኖም ግን የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ

ኃላፊዎች ወደፊት ሲያቅዱ እነዚህ ገንዳ ማንሺያ ተሸከርካሪዎች የበለጠ ክብደት

በሚሸከሙ ተሽከርካሪዎች በመተካት የኢኮኖሚ እድገቱ የሚፈልገውን አሰራር

ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል፡፡

Page 27: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 27 of 73

7.16 የተሻሻለ ቆልፎ የሚይዝ ቆሻሻ ገንዳ ማንሺያ (Hook-Lift) የተገጠመለት ያለው

ተሸከርካሪ መጠቀም እና ስራ ላይ ማዋል መታሰብ አለበት፡፡እንደዚህ ዓይነት

የቆሻሻ ማንሺያ ያላቸው ተሸከርካሪዎች በተሸከርካሪው የጎን ርዝመትና ቁመት

መጠን ገንዳዎችን ያለምንም እንቅፋት በማንሳት መጫን ስለሚችሉ የሚያነሱት

ገንዳ የክብደት መጠን ከሌላ ገንዳ አንሺ ተሸከርካሪ (Skip-Lift) በብዙ እጥፍ

ይበልጣል፡፡

7.17 ቆሻሻ በማጓጓዝ ስራ በተሰማሩ በሁሉም ተሽከርካሪዎች ላይ የአገልግሎት ሰጪው

ስምና የስልክ ቁጥር ግልጽ በሆነና በሚነበብ ሁኔታ መለጠፍ አለበት፡፡

7.18 ቆሻሻ በሚጓጓዝበት ወቅት እንዳይፈስ ወይም በንፋስ እንዳይበተን ውኃ

በማያሰርፅ ክዳን ወይም መረብ በበቂ ሁኔታ መሸፈን ወይም ሽፍን በሆነ

ተሸከርካሪ ወይም ገንዳ መጔጔዝ አለበት፡፡ የመረብ መሸፈኛ አገልግሎት ላይ

በሚውልበት ጊዜ ቆሻሻ በመረቡ ሾልኮ እንዳይዝረከረክ ለመከላከል የመረቡ

ቀዳዳ ከቆሻሻው ቅንጣት መጠን ማነስ ስለሚገባው ቀዳዳው 150 ሚ.ሜ. በ150

ሚ.ሜ. መብለጥ የለበትም፡፡ እንዲሁም ቆሻሻ በሚጓጓዝበት ወቅት መረቡ ወይም

የመሸፈኛው ማቴሪያል ከተሸከርካሪው ወይም ከገንዳው ጋር ተወጥሮ በጥብቅ

መታሰር አለበት፡፡

7.19 ቆሻሻ በመሰብሰብና በማጓጓዝ አገልግሎት ስራ ላይ የተሰማሩ ተሸከርካሪዎች

የበሽታ አምጪ ነፍሳቶችን መራባት እንዲሁም መጥፎ ሽታን ለመከላከል ሲባል

ቶሎ ቶሎ መፅዳት አለባቸው፡፡

7.20 አስተማማኝ የቆሻሻ አሰባሰብ አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የተሸከርካሪዎች

የጥገና ፕሮግራም ከመንገድ አመቺነት ጋር በማዛመድ ተመቻችቶ መዘጋጀት

አለበት፡፡

8. ቆሻሻን ማስተላለፍ (የቆሻሻ ቅብብሎሽ) /Waste Transfer/

ቆሻሻ መቀባበል ከአነስተኛ ቆሻሻ ማጓጓዣ ተሸከርካሪ /ከጋሪ ጀምሮ ተሳቢ ወዳለው

ትልቅ ተሸከርካሪ ድረስ ያለዉን የማስተላለፍ ወይም የመቀባበል ሂደት ያጠቃልላል፡፡

ይህ ሁኔታ ትናንሽ ቆሻሻ የሚያጓጉዙ ተሸከርካሪዎች ቆሻሻውን በፍጥነት እና በብዙ

ምልልስ አድርሰው ወዲያውኑ ወደ መስመራቸው እንዲመለሱ ስለሚያደርጋቸው

ከፍተኛ መጠን ያለው ቆሻሻ በከባድ ተሸከርካሪዎች ወደ ማከሚያ ጣቢያ ወይም

Page 28: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 28 of 73

ማስወገጃ ቦታ ሲያጓጉዙ ፍጥነታቸው እንዲጨምርና ቅልጥፍናን ይጨምራል፡፡

የቅብብሎሽ ጣቢያ ቦታ አመራረጥና የቅብብሎሽ ጣቢያው አይነት የሚወሰነው

በቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ወይም የቆሻሻ መከሚያ ቦታ አቀማመጥና መገኛ ሁኔታ

እንዲሁም ቆሻሻው ከሚመነጭበትና አጠቃላይ የቆሻሻ አሰባሰብ ተግባራዊ ስርዓት

መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

8.1 ቆሻሻን የመቀባበል ወይም የማስተላለፍ አሰራር ፍላጎትና እቅድ

ከክልሉ/ከተማው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድ ውስጥ መካተት

አለበት፡፡

8.2 ይሁን እንጂ የመጨረሻው የቆሻሻ ማስወገጃ/ማከሚያ ማእከል ከከተማው መሃል

በ23 ኪ.ሜ. ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ከሆነ የቅብብሎሽ ጣቢያ አስፈላጊ

አይደለም፡፡

8.3 የቅብብሎሽ ጣቢያው በከተማ ውስጥ ወይም ከከተማ ውጭ እንዲሆን

የሚወስነው የተዘጋጀለት ዲዛይንና አጠቃላይ የአሰራር ሁኔታው ነው፡፡

8.4 የቅብብሎሽ ጣቢያ ቦታ ለመምረጥ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመደረሱ በፊት

የሚመለከታቸው የዘርፉ ኃላፊዎች የአካባቢ ተፅእኖ ግምገማ ጥናት

መጠናቀቁና ከአካባቢው ኗሪዎች ጋር ምክክር መደረጉን ማረጋገጥ

አለባቸው፡፡

8.5 በሜትሮፖሊስ፣ ሪጂዮፖሊስና እና ፈርጅ 1 ወደ ትላልቅ ገንዳዎች ወይም

ተሸከርካሪዎች ቅብብል የሚደረግበት ወይም የሚተላለፍበት ቋሚ አገልግሎት

የሚሰጥ የቅብብሎሽ ጣቢያ በከተማው ውስጥ የማቋቋም አስፈላጊነትን

መገምገም አለባቸው፡፡

8.6 የቅብብሎሽ ጣቢያው አሰራር ዲዛይን የአሰራር ቅልጥፍናን የሚያስገኝና

ንፅህናን የሚያስጠብቅ መሆን አለበት፡፡

8.7 ወደ ቅብብሎሽ ጣቢያ የሚመጣ ቆሻሻ በጊዚያዊ አሰራር ምክንያት

ካልተስተጓጎለ በስተቀር በአንድ ቀን ውስጥ ወደ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ወይም

መልሶ መጠቀሚያ ጣቢያ መተላለፍ አለበት፡፡

8.8 በፈርጅ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ዉስጥ የሚካተቱት የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች በስምምነት

በሚወሰን የመሰብሰቢያ ቦታ ላይ የተገጠመ የቆሻሻ ማንሺያ ያለው ወይም

ገንዳ የሚያነሳ ተሸከርካሪን እንደ ቅብብሎሽ ጣቢያ የመጠቀም አማራጭን

ማጤን አለባቸው፡፡

Page 29: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 29 of 73

8.9 ቆሻሻን በሎደር ወይም በተመሳሳይ ማሽነሪ ከመሬት አንስቶ ለማስተላለፍ

ወይም ማሸጋገር በጊዜያዊነት ወይም በአደጋ ጊዜ ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት

ሊኖረው አይገባም፡፡

8.10 የትራፊክ መጨናነቅ ካላሳሰበ በስተቀር ቆሻሻ የማስተላለፍና የማጓጓዝ ስራ

በቀን መከናወኑን የሚመለከታቸው የስራ የዘርፉ ኃላፊዎች ማረጋገጥ

አለባቸው፡፡

8.11 የትራፊክ መጨናነቅ በሚከሰትበት ወቅት ቆሻሻ እንዲጓጓዝና ማስተላለፍ

ሌሊት እንዲሆን ሁኔታው ካስገደደ የአደጋ ተጋላጭነትና ጉዳት ለመቀነስ

በሌሊት ለሚደረግ እንቅስቃሴ የጤንንትና የደህንነት ሁኔታን በሚያስጠብቅ

መልኩ እንዲሁም አስፈላጊ ቁሳቁሶች በሚገባ መጠናከር አለበት፡፡

8.12 የአነስተኛ ቅብብሎሽ ጣቢያ መጠን በሳጥን 1 በተገለፀው የቆሻሻ ገንዳ

በሚይዘው መጠን ስሌት አግባብ የሚወሰን ሲሆን በተጨማሪም የገንዳዎቹ

ስፋት ሁለት እጥፍ የሚሆን ቦታ ቆሻሻውን ለሚያስተላልፉ ተሸከርካሪዎች

መንቀሳቀሻ እና ለተንቀሳቃሽ መሰላል ወዘተ... ያስፈልጋል፡፡

8.13 የቅብብሎሽ ጣቢያው የሚሸፍነው ዙሪያ መለስ ክልል/ራዲየስ የቅብብሎሽ

ጣቢያውን ሚያገለገሉ የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ ሰብሳቢ ተሸከርካሪዎች

በሚሸፍኑት ዙሪያ መለስ ክልል/ራዲየስ ይወሰናል፡፡

8.14 የቅብብሎሽ ጣቢያው ዓይነት፣ ዲዛይን፣ አቀማመጥ፣ የሚገኝበት የቦታ ሁኔታ

እና አገልግሎት ዙሪያ መለስ/ራዲየስ ክልል በአዋጭነት ጥናት መወሰን

ይኖርበታል፡፡

8.15 የቅብብሎሽ ጣቢያው ጠንካራ፣ ቋሚ የጥበቃ አጥርና በር፣ የመተጣጠቢያ

ፋሲሊቲዎች እንዲሁም መብራትና ውኃ ያለው ሊኖረው ይገባል፡፡

8.16 ሁሉም የቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያዎች፣ ፋሲሊቲዎችና ገንዳዎች ሁልጊዜ

በአግባቡ የተቀመጡ፣ የሚሰሩ እና ንፁህ መሆን አለባቸው፡፡ገንዳዎቹና

አካባቢው በወር አንድ ጊዜ ሊጸዳ ይገባል፡፡ በ20 ሜትር ዙሪያ ርቀት ላይ

ያለ አካባቢ በሁሉም አቅጣጫዎች በየሦስት ወሩ መፅዳትና ትግበራውም

መደበኛ ቁጥጥር ሊደረግለት ይገባል፡፡

Page 30: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 30 of 73

9. የመንገድ፣ የህዝብ ቦታዎች እና የመናፈሻዎች ቆሻሻ አያያዝ እና

አወጋገድ

አጠቃላይ

9.1 የማዘጋጃ ቤታዊ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት የመንገድ ጽዳትን፣

ከትናንሽ የመንገድ ዳር ቆሻሻ የሚጠራቀምያ እቃዎችን (ደስት ቢን) ዉስጥ

ቆሻሻን ማሰባሰብን፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎችን፣ መናፈሻዎች፣ የውሀ

መውረጃ ቦዮችን እና ተፋሰሶችን ማፅዳትን ያጠቃልላል፡፡

9.2 በከፍተኛ ደረጃ መንገዶችን ማጽዳትና የተበታተኑ ቆሻሻዎችን ማንሳት

አካባቢን ንፁህ ለማድረግና እግረኞች ቆሻሻ እንደመጣላቸው ከመበተን

ሊያግዳቸው ይችላል፡፡

9.3 ቆሻሻን በየአካባቢው ባልተገባ ሁኔታ መጣልን ለማውገዝ የነዋሪውን ህዝብ

ግንዛቤ ለማሳደግ የሚረዳ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ፕሮግራም

በመቅረጽ መተግበር ያስፈልጋል፡፡ ጥብቅ ክትትልና አስገዳጅ የማስፈጸሚያ

እንቅስቃሴዎችን በማስተዋወቅ ቆሻሻን ያለአግባብ ያለመጣል ዘመቻን

የሚደግፍ ስርዓት መተግበር ያስፈልጋል፡፡

9.4 የመንገድ ጽዳት፣ አደባባዮችና የህዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች ጽዳት በሰው

ጉልበት መከናወን አለበት፡፡ የመንገዱ ሁኔታ በሚፈቅድበት ሁኔታ ዋና ዋና

መንገዶች ላይ የሜካኒካል /ማሽን በመጠቀም/ የመንገድ ጽዳት ስራ ተግባራዊ

ሊደረግ ይችላል፡፡

9.5 ቆሻሻ በመኖሪያ ቤት ወይም በህዝብ ቦታዎች አጠገብ፣ በዋና መንገዶች እና

ውሀ መውረጃ ቦዮች እንዳይጣል የቆሻሻ አሰባሰብ ስርዓት በበቂ ምልልስ፣

በፍጥነት እና በአስተማማኝ ሁኔታ ሊተገበር ይገባል፡፡

9.6 ከውሀ መውረጃ ቦዮች እና ዲቾች የሚሰበሰብ ቆሻሻ እንዲደርቅ ወጥቶ በመንገድ

ዳር ላይ መቀመጥ ቢኖርበትም በ24 ሰዓት ውስጥ ተሰብስቦ መጓጓዝ አለበት፡፡

9.7 አፈር፣ አሸዋ እና ደለልና ሌሎች ቆሻሻዎችን በደስት ቢን ውስጥ ማስቀመጥ

ክልክል ነው፡፡

Page 31: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 31 of 73

የመንገድ ላይ ቆሻሻዎችን መሰብሰብ

9.8 የመንገድ ላይ ቆሻሻ በመጥረጊያ ተሰብስቦ በትናንሽ ክምር ከተቆለለ በኋላ

የእጅ ንክኪ ከቆሻሻው ጋር ሳይኖር በአካፋ ወይም ተመሳሳይ መሣሪያ በእጅ

ወደሚገፋ ጋሪ በመጫን መጓጓዝ አለበት፡፡

9.9 ለነዋሪው ህዝብ ጤንነት ሲባል ቆሻሻ በመንገድ ላይ ማቃጠል በጥብቅ የተከለከለ

ነው፡፡

9.10 የመንገድ ጽዳት ኃላፊነት ከመንገድ ላይ የተሰበሰበውን ቆሻሻ የሚያጓጉዙት

ተሸከርካሪዎች ከመድረሳቸው በፊት በሚጸዳው መንገድ አቅራቢያ የሚገኘውን

የቆሻሻ መጣያ ገንዳ እና የቅብብሎሽ ጣቢያን አካባቢን መጥረግ

ያጠቃልላል፡፡

9.11 የመንገድ ጽዳት የሚያከናውኑ ባለሙያዎች አነስተኛ የአባላት ቁጥር ባለዉ

ቡድን ተከፋፍለዉ መስራት አለባቸዉ፡፡እያንዳንዱ ቡደን የሚጠርገዉ

የመንገድ ርዝመት ተወስኖ መከፋፈል አለበት፡፡

9.12 የትራፊክ እንቅስቃሴ በራሱ የመንገዶችን መሀል ከቆሻሻ የጸዳ ስለሚያደርገው

በተደጋጋሚ መጸዳት እና መጠረግ ያለበት የመንገዱ ዳርቻ ነው፡፡

9.13 የመንገድ ጽዳት የሚያከናውኑ ባለሙያዎች /የመንገድ ጠራጊዎች/ በመንገድ

ዳር የሚቀመጡ የቆሻሻ ማጠራቀምያ እቃዎች (ደስት ቢኖች) ውስጥ

የሚቀመጥ ቆሻሻን መሰብሰብ ከመደበኛ ስራቸው አንዱ በመሆኑ በደስት ቢኖች

ውስጥ የሚጠራቀመውን ቆሻሻ በየእለቱ መሰብሰብ አለባቸው፡፡

9.14 በሰው ጉልበት የሚከናወን የመንገድ ጽዳት ከመኖሪያ ቤቶች እና ከንግድ

ቤቶች ቆሻሻን ከመሰብሰብ ስራ ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራ ከሆነ መንገድ

ጠራጊዎች የሚጠቀሙ በት የሚገፋ ወይም በእንስሳ የሚጎተት ጋሪ ሰፋ ያለ

መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም መንገድ ጠራጊዎቹ ወደ ቆሻሻ ማራገፍያዉ ቦታ

ተደጋጋሚ ጉዞ ማድርግ ሊኖርባቸው እንደሚችል መታወቅ አለበት፡፡

9.15 የሞተ እንስሳ መንገድ ላይ ሲገኝ የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ሪፖርት

እንደደረሳቸው በአንድ የስራ ቀን ውስጥ የሞተውን እንስሳ ከጠንካራ ፕላስቲክ

ከተሰራ ከረጠት ውስጥ በመክተት ወደሚፈለገው ቦታ ማጓጓዝ አለባቸው፡፡:

የሞተው እንስሳ በጣም ትልቅ ከሆነ እና ለማንሳት በማይመች ሁኔታ አካሉ

Page 32: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 32 of 73

ከፈረሰ የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በክሬን ወይም በሌላ መካኒካል

ማንሻ ባለዉ ተሽከርካሪ አማካኝነት እንዲነሳ ማድረግ አለባቸዉ፡፡

9.16 የተበላሹ መኪናዎች የቤት መገልገያ ቁሳቁሶች እና ሌሎች ትልልቅ ቆሻሻዎች

በብዛት በመንገድ ላይ ተጥለዉ ሲገኙ የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች በሁለት

የስራ ቀናት ዉስጥ ወደሚመለከተዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊ ሪፖርት ማድረግ

አለባቸዉ፡፡ የሚመለከታቸዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎችም ቆሻሻዉን በአግባቡ

የመሰበሰብ፣ የመጫን፣ የማከም ወይም የመስወገድ ከተቻለም ይህንን ለማድረግ

የሚያስፈልገዉን ወጪ በቅጣት መልክ ቆሻሻዉን በጣሉት ባለቤቶች

የሚሸፈንበትን አሰራር ተግባራዊ የማድረግ ሀላፊነት አለባቸው፡፡

9.17 በሚተገበረዉ የቆሻሻ አሰባሰብ ስርአት መሰረት የመንገድ ጠራጊዎች

የጠረጉትን ቆሻሻ በጋራ የቆሻሻ ማጠራቀምያ ዉስጥ ገንዳ ያሰባስባሉ ወይም

በቀጥታ ወደ ቅብብሎሽ ጣቢያ በማጓጓዝ በማጓጓዝ ያደርሳሉ፡፡

9.18 በስራ መጀመርያ እና መጨረሻ ሰአቶች ላይ በጉዞ የሚባክን ግዜን በመቀነስ

የመንገድ ጠራጊዎችን የአገልግሎት ብቃት ውጤታማ ለማድረግ የመንገድ

ጠራጊዎች ጋሪዎቻቸውን እና ሌሎች ለጽዳት አገልግሎት የሚጠቀሙበትን

ቁሳቁስ የሚያስቀምጡበት ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ ቦታ በአቅራቢዉ

መዘጋጀት አለበት፡፡

የጎርፍ መውረጃ ቦዮችን (ዲቾችን) ማጽዳት

9.19 የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እና የመንገድ ዳር ቦዮች በቅርበት የሚገኘውን

መንገድ ለማጽዳት በተመደቡ የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ከመንገዱ ጋር

በየቀኑ መጸዳትአለበት፡፡

9.20 የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ደረቅ ቆሻሻዎች እንዳይገቡ የሚከላለከል ወንፊት

በተገጠመላቸው የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች ላይ እንዲሁም የፍሳሽ ቦዮች

ውስጥ የሚጣለውን ደረቅ ቆሻሻ በየቀኑ በማጽዳት በአካባቢው ጎርፍ

እንዳይፈጠር የመከላከል ሃላፊነት አለባቸው፡፡

9.21 የትላልቅ እና ከባድ ጎርፍ ማሳለፍያ ቦዮች ጠረጋ በልዩ የባለሞያዎች ቡድን

ክሬን ወይም ሌላ አመቺ የሆነ ቆሻሻ ማንሻ መሳርያ በተገጠመለት ተሽከርካሪ

በመታገዝ ቢያንስ በአመት ሁለት ጊዜ የጽዳት ስራ መከናወን አለባት::

Page 33: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 33 of 73

9.22 ከፍተኛ መጠን ያለዉ ወይም ከባድ ቆሻሻ መሰብሰብ ሲኖርበት ሎደር ወይም

ተመሳሳይ ለከባድ ስራ የሚያመች የትላልቅ የመዛቅያ አካፋ እና ማጠራቀምያ

ባልዲ ያለዉ ተሽከርካሪ ተጠቅሞ ቆሻሻዉን ወደ ተሽከርካሪ በመጫን

መሰብሰብ ይቻላል፡፡

9.23 አስፈላጊ ሲሆን ከፍሳሽ ቱቦ የወጣ ቆሻሻ እስከሚደርቅ ድረስ በጊዜያዊነት

በመንድ ዳር ሊቀመጥ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ •መጥፎ ሽታን የተለያዩ ነፍሳት

መራባትን እና ቆሻሻ የሚመገቡ የተለያዩ እንስሳትን ለመከላከል ቆሻሻዉ በ24

ሰዓት ዉስጥ መሰብሰብ አለበት፡፡

የህዝብ ተሳትፎ

9.24 የከተማ ኗሪዎች በቤታቸዉ ፊትለፊት የሚገኙ መንገዶን እንዲጠርጉ

ማበረታታት ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ከመንገድ ጽዳት የተሰበሰበውን ቆሻሻ

በውሀ መውረጃ ቦዮች ውስጥ እንዳይጥሉ ማስተማር እና መከላከል አስፈላጊ

ነዉ፡፡

9.25 የከተማ ኗሪዎች የአካባቢቸዉን መንገዶችና ክፍት ቦታዎች አንዲያጸዱ የህዝብ

የጽዳት ቀን መመቻቸት አለበት፡፡ ይህም ለቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ

ተጨማሪ እገዛ የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ በኗሪዎች ዘንድ የባለቤትነት

ስሜት በመፍጠር አካባቢያቸውን በንጽህና እንዲጠብቁ ያበረታታል፡፡

የአገልገሎት ቅልጥፍና

9.26 የመንገድ ጽዳት ብዛት ባለዉ የሰው ኃይል ተሳትፎ ስለሚከናወንና ከዚህም ጋር

ተያይዞ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ስራ እንደመሆኑ በተማሩ ብቁ ባለሙዎች

በጥንቃቄና ሳይንሳዊ በሆነ የአመራር ሁኔታ መመራት አለበት፡፡

9.27 ለአንድ የመንገድ ጽዳት ሰራተኛ ወይም በመንገድ ጽዳት ላይ ተሳትፎ

ለሚያደርግ ሰው ሊሰጥ/ ሊያፀዳዉ የሚገባዉ የመንገድ ስፋት ወይም ርዝመት

ተለክቶ መታወቅ ይኖርበታል:: በመንገድ ጽዳት ተሳትፎ እያደረጉ ለሚገኙ

ሰዎች ወይም ቡድኖች ተሳትፎ ለሚያደረግ ቡድን ስራው በአግባቡ መከናወኑን

እንዲሁም የስራው ክፍፍል ተመጣጣኝ መሆኑን በቅርብ ሱፐርቫይዘሮች

አማካኝነት መከታተል እና በየጊዜዉ በመከለስ የስራዉን መጠን በአግባቡ

ለመወሰን ያስችላል፡፡

Page 34: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 34 of 73

9.28 በመንገድ ጽዳት የተሰማሩ ሰራተኞች ስራ ለመጀመር ወይም ለመፈረም

የሚቆዩበት ጊዜ እንዲሁም ወደ ስራ ቦታ ለመምጣት እና ለመሄድ

የሚያደርጉት ጉዞ የሚፈጀዉ ጊዜ በየጊዜዉ መከለስ አለበት፡፡ይህን

በማድረግም አላስፈላጊ ቆይታን እና በጉዞ የሚባክን ጊዜን በማስወገድ የስራ

ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ ያግዛል፡፡

ጤናና ደህንነት

የዲዛይንና የመሳሪያዎች ሁኔታ

9.29 የመንገድ ጽዳት ስራ በባህሪዉ አድካሚና ከፍ ያለ አካለዊ ብቃትን

የሚጠይቅ እንደመሆኑ በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች ሲመለመሉ አካላዊ

ብቃት እንደ አንድ መመዘኛ ከግምት ዉስጥ መግባት ይኖርበታል፡፡

9.30 ጤንነት፣ ደህንንት እና የስራ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ወጪን

ለመቀነስ ሁሉም ሰራተኞች ለፍጥነት እና ለቅልጥፍና አመቺ የሆኑ የእጅ

መሳሪዎቸ እና የእጅ ጋሪዎች ማግኘት አለባቸዉ፡፡

9.31 የመጥረጊያ መሳሪዎችና የእጅ ጋሪዎች (ስራ ላይ ከዋሉ)የቅርብ ሱፐርቫይዘሮች

ተስማሚነታቸዉን፣ አመቺነታቸዉን እና የመሳሪያዎቹን ሁኔታ በመደበኝነት

መፈተሽ አለባቸው፡፡ የሚመለከታቸዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የመንገድ ጽዳት

ሰራተኞች ስራቸውን በቅልጥፍና እና ጤንነትና ደህንንታቸዉን በሚስጠብቅ

ሁኔታ ለማከናወን በሚያስችሉ እና በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ትክክለኛ የስራ

መሳርያዎችን ማግኘታቸውን እና መጠቀማቸዉን ማረጋገጥ አለባቸዉ፡፡

የትራፊክ ደህንነት

9.32 የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች በስራ ወቅት ሊለብሱት የሚገባ ደማቅ እና

አንጸባራቂ ጃኬት ወይም ሰደርያ ሊሟላለቸዉ ይገባል፡፡

9.33 የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ሌሊት የሚሰሩ ከሆነ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል

ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ ቀይ አንጸባራቂ

መብራት በጋሪያቸዉ ላይ መለጠፍ አንዱ የጥንቃቄ እርምጃ ነዉ፡፡

9.34 የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ለአደጋ አጋላጭ በሆነ ሁኔታ በከፍተኛ ፍጥነት

የሚንቀሳቀስ ትራፊክ በሚያስተናግዱ መንገዶች ላይ በተለይም በመንገዶች

Page 35: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 35 of 73

አካፋይ ላይ በሚሰሩበት ወቅት የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች በስራ ላይ

መሆናቸዉን የሚሳይ ግልጽ የማስጠንቀቅያ የመንገድ ላይ ምልክት በማሳየት

አሽከርካሪዎችን ማስጠንቀቅ ይገባል፡፡

የግል ጤንንት እና ደህንነት መጠበቅያ መሳሪያዎች

9.35 የመንገድ ጽዳት ሰራተኞች ቢያንስ የሚከተሉት የራስ ጤንንትና ደህንነት

መጠበቅያ መሳሪያዎችን ማግኘት አለባቸዉ፡-

ሀ/ ጠንካራ የደህንንት ቦቲ ወይም ጫማ

ለ/ ባለማንገቻ ቱታ

ሐ/ ጠንካራ ጓንት

መ/ ከሩቅ የሚታይ አንጸባራቂ ሰደርያ

ሠ/ በጋሪ ላይ የሚገጠም ባትሪ (ለሌሊት ስራ)

ረ/ የአቧራ መከላከያ ጭምብል

ሰ/ ባርኔጣ ወይም ቆብ

9.36 የግል ጤንንትና ደህንነት መጠበቅያ መሳሪያዎች በየስድስት ወሩ ወይም

ቀድመው ከጥቅም ዉጭ ከሆኑ ከስድስት ወር በፊት በሚመለከተው የስራ ክፍል

ወይም ኮንትራት ወስዶ አገልግሎት በሚያቀርበው አካል መቀየር አለባቸዉ፡፡

9.37 የተሟላ የግል ጤናና ደህንንት መጠበቅያ መሣሪያ ለበሁሉም ሰራተኞች

መሟላታቸዉ እና መሳሪያዎቹን ዘወትር በስራ ወቅት መጠቀም አስፈላጊ የስራ

ላይ ግዴታ መሆን አለበት፡፡

የቆሻሻ ገንዳን መጫን

9.38 ቆሻሻን ከጋሪዎች ላይ በእጅ ማራገፍ ወይም ቆሻሻ ወደ ገንዳ ከመጫኑ በፊት

በእጅ እያወጡ መሬት ላይ መገልበጥ ለጤንነት ጎጂ ከመሆኑም በላይ የስራ

ቅልጥፍናን ስለሚቀንስ መበረታታት የለበትም፡፡

9.39 ትላልቅ መጠን ባላቸዉ የጋር ቆሻሻ መጣያ ገንዳዎች ከእንጨት ወይም ከብረት

የተሰራ መወጣጫ መሰላል ተጠቅሞ የእጅጋሪዎችን ቆሻሻ በቀጥታ ወደ

ገንዳዎች መገልበት ይገባል፡፡ሁለት ወይም ሶስት አነስተኛ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ

Page 36: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 36 of 73

እቃዎችን በአንድ ጊዜ በማንሳት በቀጥታ ወደ ገንዳዉ ለማራገፍ የሚያስችል

የተሻሻለ መወጣጫ መጠቀም የተሻለ አማራጭ ነዉ፡፡

የአደጋ ጊዜ ምላሽ

9.40 ማዘጋጃ ቤቶች በድንገተኛና አጣዳፊ ሁኔታዎች ወይም የመንገድ ላይ ቆሻሻን

በከፍተኛ ሁኔታ በሚጨምሩ እንደ ጎርፍ፣ ኃይለኛ ንፋስ፣ ባዛር፣ ፌስቲቫል ፣

የጎዳና ላይ ስብሰባ፣ የስፖርት ትርኢቶች እና ውድድሮች በሚከሰቱበት ወቅት

የሚመነጨውን ቆሻሻ በፍጥነት በማጽዳት ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ የሰው

ኃይል ለማሰማራት የሚያስችል አሰራር መተግበር ይኖርባቸዋል፡፡

9.41 የመኪና ግጭት ከተከሰተ በኃላ እንደ መስታዉት እና ፕላስቲክ የመሳሰሉ

የመኪና ስብርባሪ አካላትን ለማንሳት የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች ተጨማሪ የጽዳት

ሰራተኞችን ሊያሰማሩ ይገባል፡፡

9.42 ከባድ የመኪና አደጋን ተከትሎ ዘይት፣ ነዳጅ፣ ሞተር የሚያቀዘቅዙ ኬሚካሎችን

የመሳሰሉ ፈሳሾች በመንገዱ ንጣፍ ላይ ሊፈሱ ይችላሉ፡፡ ይህን አይነት ሁኔታ

ሲያጋጥም የሚመለከታቸዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እንደ አሸዋ እና ሰጋቱራ

የመሳሰሉ ፈሳሹን የሚመጡ ማቴርያሎችን በማቅረብ መንገዱ በፍጥነት

የሚጸዳበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለባቸዉ፡፡

የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀምያ/ደስት ቢን/

መገኛ/ማስቀመጫ ቦታ

9.43 የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እቃዎች ወይም ደስት ቢኖች •እግረኞች

በብዛት በሚተላለፉባቸዉ መንገዶች ዳር ቢያንስ በየ50 ሜትር ርቀት ላይ

በማስቀመጥ እግረኞች አላስፈላጊ ቁሳቁሶችን የሚጥሉበት ቦታ በቅርበት

እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ መልእክቶች

9.44 በመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀሚያ እቃዎች ወይም ደስት ቢኖች ላይ ቆሻሻን

በየቦታዉ መጣልን የሚያወግዙ መልዕክቶችን እንዲሁም ሰዎች ስለቆሻሻ

አጣጣል ወይም የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን ስራን በሚመለከት የሚቀርቡ

Page 37: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 37 of 73

መልዕክቶችን፣ ችግሮችን እና ቅሬታዎችን ለሚመለከተው አካል ደውለው

የሚያሳዉቁበት የስልክ ቁጥሮችን በግልጽ በሚታይ ሁኔታ መጻፍ

ያስፈልጋል፡፡

የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀምያ/ደስት ቢን/ ዲዛይን

9.45 የጥገና አስፈላጊነትን እንዲሁም የወደሙ ወይም በእሳት ወይም በአገልግሎት

ብዛት የተጎዱ የመንገድ ዳር የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች/ ደስት ቢን/ በሌላ

ለመቀየር እንዲቻል የማጠራቀምያዎቹ ሳምንታዊ ፍተሻ ማከናወን ይገባል፡፡

9.46 የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀምያ /ደስት ቢን/ የሚከተሉት ገጽታዎች አሉት፡-

i/ አመራረት ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሲባል የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀምያዎች ቢንስ ከ2 ሚ.ሜ ዉፍረት ካለዉ የማይዝግ ብረት መሰራት አለባቸዉ፡፡

ii/ የመያዝ አቅም ከ 80 – 120 ሊትር

iii/ ገጽታ ሀ/ ጽዱና በቀላሉ የሚታዩ መሆን አለባቸው፡፡ ለ/ ስለ አጠቃቀማቸዉ እና አካባቢያን በንጽህና ስለመያዝ

የሚያስገነዝቡ መፈክሮች መያዝ አለባቸው፡፡ ሐ/ በመናፈሻዎችና በህዝብ ቦታዎች አካባቢ አካባቢውን ውበት

በሚያጎናጽፍና እና ትንንሽ ልጆች እንዲጠቀሙባችዉ

በሚያበረታታ በውብና ማራኪ ዲዛይን ሊሰሩ ይገባል፡፡

iv/ ንፋስና ዝናብ

ሀ/ የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀምያዎች /ደስት ቢን/ በውስጣቸዉ

የተቀመጠዉ ቆሻሻ በንፋስ ኃይል እንዳይበተን የሚከላከል

ዲዛይን አሰራር ያለዉ መሆን አለበት፡፡

ለ/ የእንስሳትና አእዋፍ መዋያ እንዳይሆኑ እንዲሁም ዝናብ

አንዳይገባባቸዉ ማጠራቀምያዎቹ ሽፋን ወይም ክዳን

ሊደረግላቸዉ ይገባል፡፡

Page 38: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 38 of 73

ሐ/ የማጠራቀምያ•እቃዎቹ /ደስት ቢን/ ወለል ፍሳሽ በፍጥነት

ለማሳለፍ የሚያስችሉ ትንንሽ ቀዳዳዎች ያሉት መሆን

አለበት፡

v/ እሳት

የተጣሉ የሲጋራ ቁራጮች እሳት ሊፈጥሩ ስለሚችሉ የመንገድ ዳር

ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎች /ደስት ቢን/ ከፕላስቲክ የተሰሩ መሆን

የለባቸዉም፡፡

Vi/ የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን /ደስት ቢን/ ስለማራገፍ

ሰራተኞች ቆሻሻን ከማጠራቀሚያው ለማውጣት እጃቸዉን ወደ

ማጠራቀምያዉ ዉስጥ ከተዉ ማውጣት የለባቸዉም፡፡የቆሻሻ

ማጠራቀምያዎቹ /ደስት ቢን/ በቀላሉ ባዶ ለማድረግ በሚያስችል

ዲዛይን መሰራት አለባቸዉ፡፡ ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹ ሰራተኞች

በዕለታዊ የቆሻሻ ማንሳት ስራቸዉ ከቆሻሻ ጋር ቀጥተኛ የእጅ ንክኪ

እንዳይኖራቸዉ በሚያደርግ መልኩ መሰራት አለበት፡፡ስለዚህ የቆሻሻ

ማጠራቀምያዎቹ /ደስት ቢኖች/ ከሚከተለዉ በአንዱ መልክ መሰራት

ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ/ ቆሻሻዉን አንስቶ ለመገልበጥ የሚያስችል የዉስጥ ቅርጫት

ወይም ገንዳ ያለዉ፣ ወይም

ለ/ ማጠራቀሚያ እቃውን በቀላሉ ወደጎን ለመገልበጥ

በሚያስችል መልኩ እንዲንቀሳቀስ ሆኖ የተተከለ መሆን

አለበት፡፡

Vi/ ሽብርተኝነት

አልፎ አልፎ የመንገድ ዳር ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን/ ደስት ቢኖችን

አሸባሪዎች ለቦምብ መደበቅያነት ሊጠቀሙባቸዉ ይችላልሉ፡፡ እንደዚህ

አይነት ስጋት ጉልህ በሚሆንበት ወቅት የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎቹን

/ደስት ቢኖችን/ በፍሬም ተያይዞ በሚንጠለጠል እና ግልጽ ሆኖ

በዉስጡ የተቀመጠዉን ነገር በአይን ሊታይ በሚችል የፕላስቲክ

ከረጢት መቀየር ያስፈልጋል፡፡

Page 39: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 39 of 73

10. የገበያ ቦታዎች ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ገንዳዎች የሚቀመጡበት ቦታ

10.1 በገበያ ቦታዎች በተለይም ደግሞ በአትክልትና ፍራፍሬ ገበያዎች ከፍተኛ መጠን

ያለዉ ቆሻሻ ሰለሚመነጭ ትላልቅ ገንዳዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የገንዳዎቹ

መጠን ከ8 ሜትር ኪዩብ እስከ 20 ሜትር ኪዩብ ሆኖ ትክክለኛ መጠኑ

በአካባባዉ የትራፊክ ፍሰት ሁኔታ አመቺ የማስቀመጫ ቦታ መገኘት እና ከላይ

የሚያልፉ እንደ ቴሌ እና መብራት አይነት የመሰረተ ልማት ገመዶች ላይ

ተመስርቶ ይወሰናል፡፡

10.2 የቆሻሻ ማጠራቀምያ ገንዳዎች አስቀድሞ በተመረጠ ስትራቴጂካዊ አካባቢ

መቀመጥ አለባቸዉ፡፡ ቦታዉ ገንዳዎችን ለማስቀመጥና ተሽከርካሪዎችን

ለማስገባት አመቺና ሰፊ መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ገንዳዉ ለገበያ ስፍራዉ

ቅርብ እና በመጀመርያ ደረጃ ቆሻሻ አሰባሳቢዎች አማካኝነት ቆሻሻን በእጅ

ጋሪዎች ለመሰብሰብ እና ወደ ገንዳዉ ለማጓጓዝ በሚያስችል ቅርበት ላይ

መቀመጥ አለበት፡፡

10.3 ከላይ የሚሄዱ የመሰረተ ልማት ገመዶች ካሉና ገመዶቹን ማስወገድ የማይቻል

ከሆነ የቆሻሻ ማጠራቀምያ ገንዳ ማንሻ ያላቸዉ ተሽከርካሪዎችን ከመጠቀም

ይልቅ ባለመንጠቆ ማንሻ ያላቸዉ ወይም ክሬን የተገጠመላቸውዉ

ተሽከርካሪዎችን መጠቀም ይመረጣል፡፡

የመጀመርያ ደረጃ ቆሻሻ አሰባሰብ

10.4 ገበያዎች ትላልቅ ከሆኑና ቆሻሻ ማከማቻ ገንዳዉ ጋር ለመድረስ ሰፊ ርቀት

መጓዝ የሚያስፈልግ ከሆነ የእጅ ጋሪዎች በመጠቀም የመጀመርያ ደረጃ ቆሻሻ

የመሰብሰብ አገልግሎት ማቅረብ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡

10.5 የመጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ አሰባሰብ ተግባር ላይ በሚውልበት ወቅት የአገልግሎት

ክፍያዉ ከመደብር ባለቤቶች በቀጥታ መቀበል ወይም ደግሞ የመደብር

ባለቤቶች ለማዘጋጃ ቤት በሚከፍሉት የገበያ ቦታ ክፍያ በኩል ሊሰበሰብ

ይችላል፡፡

Page 40: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 40 of 73

10.6 የራስን ጤንነትን ለመጠበቅ እና አደጋ ለመከላከል ሲባል የመጀመሪያ ደረጃ

ቆሻሻ ሰብሳቢዎች ቆሻሻዉን ወደ ገንዳ ወይም ወደ ሌላ ማጠራቀሚያ ዕቃ

በእጃቸዉ በማሰባሰብ መጫን የለባቸውም፡፡

10.7 ማዘጋጃ ቤቱ ከብረት ወይም ከእንጨት የተሰራ ተንቀሳቃሽ መሰላል በማቅረብ

የእጅ ጋሪዎች በግፊት ብቻ ወደ ትላልቅ ገንዳዎች ቆሻሻ የሚገለብጡበት ዘዴ

መተግበር አለበት፡፡

የመሰብሰብ ድግግሞሽ

10.8 ከገበያ ቦታዎች የሚመነጭ ቆሻሻ በአብዛኛዉ ተፈጥሮአዊ (ኦርጋኒክ) የሆነ እና

በፍጥነት የመበስበስ ባህሪ ስላለዉ መጥፎ ሽታ እንዳያመጣ እና የተለያዩ

ነፍሳትና የእንስሳት መዋያ እንዳይሆን በመነጨበት ቀን ወዲያውኑ መሰብሰብ

አለበት፡፡

10.9 ከገበያ ቦታዎች የሚመነጨዉ በተፍጥሮአዊ ሂደት ሊበሰብስ የሚችል (ኦርጋኒክ)

ቆሻሻ በመሆኑና ከቆሻሻው የሚመነጭ ጥቁር ፍሳሽ ቆሻሻ (ሊቼት) የቆሻሻ

ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ውስጥ የሚሰረግ እና ከፍተኛ ዝገት እና ብልሽት

የሚፈጥር በመሆኑ ከብረት በተሰሩ ገንዳዎች ዉስጥ የሚጠራቀም ቆሻሻን በየቀኑ

በማንሳት እና ገንዳዎቹን ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ በቋሚነት በማጽዳት

የአገልግሎት ዘመናቸዉን ማራዘም ይቻላል፡፡

10.10 የትራፊክ ከፍተኛ መጨናነቅ ቆሻሻ በመሰብሰብ ስራ ላይ እንቅፋት

በሚፈጥርበት አስቸጋሪ ሁኔታ የገበያ ቦታዎችን ቆሻሻ የትራፊክ ፍሰት

በሚቀንስባቸዉ ሰዓቶች ማለትም ንጋትና አመሻሽ ላይ ማከናወን ይመረጣል፡፡

10.11 የገበያ ቆሻሻ እርጥበታማ እነዲሁም ከፍተኛ ክብደትና ብዛት ያለዉ ስለሆነ

የቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን ከመጠን በላይ ቆሻሻ እንዳይዙ እና ቆሻሻ ሰብሳቢ

መኪናዎችም ከመጫን አቅማቸዉ በላይ የሆነ ቆሻሻ እንዳይጭኑ መጠንቀቅ

አለባቸው፡፡

ጤናና ደህንነት

10.12 በገበያ ቦታዎች የሚሰማሩ መጀመሪያ ደረጃ ቆሻሻ ማሰባሰብ ላይ የተሰማሩ

ሰራተኞች እንደ ቦት ጫማ፣ ጓንት እና ባለማንገቻ ቱታ የመሳሰሉት ጤናና

Page 41: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 41 of 73

ደህንነት መጠበቅያ መሳሪያዎች ማግኘት አለባቸው፡፡ በተጨማሪም በስራ ወቅት

ደማቅ እና የሚያንፀባርቅ ሰደርያም መልበስ ይኖርባቸዋል፡፡

11 መልሶ መጠቀም

ጥቅም ላይ የሚውል ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ሂደት ውስጥ ባሉት የተለያዩ ደረጀዎች ውስጥ ሊተገበር ይችላል፡፡ መልሶ የመጠቀም

ስራ ቆሻሻውን የመሰብሰብ፣ የማጓጓዝ፣ የመሸጥ፣ የመለየት፣ የማፅዳት ወደ ሌላ ጥቅም

ወደሚሰጥ ነገር የመለወጥን ስራዎች ሁሉ የሚያካትት ነው፡፡ ከነዚህ የስራ ሂደቶች

ለአንዱ የሚቀረጹ ስታንዳርዶች በሁሉም ቀጣይ ስራዎች ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ

ስለሆነ ስታንዳርዶችን በመቅረጽ እና በመተግበር ወቅት አጠቃላይ የቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ስራ ሰንሰለቱን ታሳቢ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

11.1 የመልሶ መጠቀም አሰራር በንግድ መርህ መሰረት መተግበር አለበት፡፡ ይህም

የግብአት ቁሳቁሶችን፣ ፍላጎት እና አቅርቦትን እንዲሁም በጥሬ እቃዎች ገበያ

ውስጥ መልሶ ጥቅም ላይ ለሚውሉ ቁሳቁሶች አቅርቦት ያለውን ፍላጎት ያገናዘበ

መሆን አለበት፡፡

11.2 የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት መልሶ የመጠቀም ስራን ለማከናወን እና

ለመምራት የሚያስችል የህግ የማዕቀፍ መኖሩን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ የህግ

ማዕቀፉ መደበኛ ምዝገባን፣ የመልሶ መጠቀም ንግድ ስራ ፍቃድ አሰጣጥን፣

በግል የሚቋቋሙ የመልሶ መጠቀም ኢንተርፕሪነሮች፣ አስፈላጊ የአካባቢ ጥበቃ

ኮዶችን እንዲሁም ጤናና ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ ስታንዳርድ ያካትታል፡፡

11.3 የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት አገልግሎት ሰጪዎች የሚሠሩበት የክልል

ወሰን እስከታወቀ እና ቆሻሻ የመሠብሰብ ኃላፊነት እስከተሰጣቸው ድረስ

የመጀመርያ ደረጃ ቆሻሻ የመሰብሰብና ወደ መልሶ መጠቀም የመለወጥ ስራን

የመስራት ፈቃድ ሊሰጣቸዉ ይቻላል፡፡ ይህም ከአገልግሎት አቅራቢዎቹ ጋር

በሚደረግ የወርሀዊ ክፍያ ስምምነት የሚቀርብ አገልግሎት ሆኖ በተጨማሪ

ቆሻሻ ሰብሳቢዎቹ ከአከባቢዉ ከሚሰበሰበው ቆሻሻ ለመልሶ ጥቅም የሚውለውን

ቆሻሻ እና ቁሳቁስ የመሸጥ እና የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል፡፡

11.4 የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ስራ ላይ

ለተሰማሩ አካላት በአቅራቢያው በሚገኝ የቆሻሻ አገልግሎት መስጫ ውስጥ የስራ

Page 42: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 42 of 73

ቦታ በመስጠት እና በስራ አመራር ሂደታቸዉ ውስጥ በማካተት ድጋፍ ማድረግ

ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሰራተኞቹ የግል ደህንንት መጠበቅያ ቁሳቁሶችን

መጠቀማቸውን በማረጋገጥ እና ከክፍያ ነጻ የሆነ የጤና ምርመራ አገልግሎት

በማቅረብ የጤንነታቸዉን ሁኔታ እንዲከታተሉ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸዉ፡፡

11.3. የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት የተለያዩ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ

የማዋል ስራ ተነሳሽነት ማበረታት አለባቸው፡፡ ከመጀመሪያ ደረጃ (የቤት-

ለቤት) መልሶ መጠቀም ተግባር ጀምሮ መልሶ ጥቅም ላይ ሊዉል የሚችል

የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻን በተፈጥሮአዊ ሂደት ከሚበሰብስ ርጥበታማ ቆሻሻ

ከምንጩ መለየትን እና ግንዛቤን የማዳበር ስራ መስራት አለባቸው፡፡

11.4. በአይነቱ ያልተለየ የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻን መልሶ ለመጠቀም ከተፈለገ

ቆሻሻዉ ጠቅጥቆ በሚጭን መኪና መሰብሰብ የለበትም፡፡ምክንያቱም

መጠቅጠቅያዉ ብስባሽ ርጥበታማ ቆሻሻን ከደረቁ ቆሻሻ ጋር ስለሚደባልቀዉ

መልሶ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ቁሳቁሶችን ለመለየት አስቸጋሪ ከማድረጉም

በተጨማሪ ንፅህናው ያልተጠበቀ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

11.5. በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ አንድ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች

መልሶ የመጠቀም እና ከቆሻሻ ቀልዝ /የተፈጥሮ ማዳበሪያ/ የማምረት ስራ

ከከተማ አስተዳደሩ ይልቅ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ወይም በግል

ባለሃብቶች ቢከናወን ይመረጣል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋፋት የመልሶ መጠቀምና ቀልዝ /የተፈጥሮ

ማዳበሪያ /ማምረት ሥራ በማሽነሪ ከማከናወን ይልቅ የሰው ጉልበት መጠቀም

ይመረጣል፡፡

11.6. ሜካናይዝድ የመልሶ መጠቀምና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማዕከል የመገንባት ስራ

መጀመር ከተፈለገ ከአካባቢዉ ከሚሰበሰብ ቆሻሻ በቂ የግብአት አቅርቦት

መኖሩን እንዲሁም ለምርቱ በቂ ገበያ መኖሩን ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው

የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በቅድሚያ የአዋጭነት ጥናት ማከናወን አለባቸው፡፡

11.7. ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ የመለየት ሥራ በመኖሪያ ቤት ደረጃ ማከናወን

ከተፈለገ ንፅህናን ለማበረታታትና መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉ ማቴሪያሎች

ሳይቀላቀሉና ሳይበከሉ ተለይተዉ እንዲቀመጡ ለማድረግ ቡናማ ወይም

Page 43: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 43 of 73

ብርቱኳናማ የፕላስቲክ ማጠራቀሚያ ወይም ጠንካራ የፕላስቲክ ከረጢት

ለመኖሪያ ቤቶች ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡

11.8. የሚበሰብስ (organic) ቆሻሻን የመለየት ሥራ በመኖሪያ ቤት ደረጃ ማከናወን

ከተፈለገ ንፅህና ለማበረታታትና መልሰው ጥቅም ላይ የሚውሉ ማቴሪያሎች

ሳይቀላቀሉና ሳይበከሉ ተለይተዉ እንዲቀመጡ ለማድረግ አረንጓዴ የፕላስቲክ

ማጠራቀሚያ ወይም ጠንካራ የፕላስቲክ ከረጢት ለመኖሪያ ቤቶች ማቅረብ

ያስፈልጋል፡፡

11.9. ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ምርት የሚውል ተፈጥሮአዊ (organic) ቆሻሻ እንደ ገበያ

ቦታዎች፣ ምግብ ቤቶችና ሆቴሎች ከመሳሰሉ የተመረጡ አመንጭዎች

ተሰብሰብዉ ጥቅም ላይ ከማይውሉ ቆሻሻዎች (ለምሳሌ የመንገድ ጥራጊ) ጋር

ሳይደባለቁ ተለይተው መቀመጥ አለባቸው፡፡

11.10. በፈርጅ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች አነሰተኛ ቆሻሻን መልሶ

መጠቀም እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ የማምርት ስራ በአነስተኛ ደረጃ የሰውን

ጉልበት በመጠቀም መከናወን አለበት፡፡ ይህ ስራም በጥቃቅንና አነስተኛ

ተቋማት ቢከናወን ይመረጣል፡፡

11.11. በመልሶ መጠቀም ሥራ ሂደት የሚከሰት የጤንነትና የአካባቢ አሉታዊ

ተጽእኖን ለመከላከል የኤሌክትሪክና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ ዘይቶች፣

ኬሚካሎችና ሌሎች አደገኛ ማቴሪያሎችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ስራ ላይ

የሚመለከታቸዉ አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ

ሊያስከትሉ የሚችሉትን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችሉ መፍትሔዎችን

ማበጀት አለባቸዉ፡፡ በተጨማሪም የስራ ላይ ጤናና ደህንነት ጥበቃ

እርምጃዎችን በህግ ማዕቀፍ በማካተት ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸዉ፡፡

12 ቆሻሻን ማከምና ማዳን /Waste Treatment and Recovery/

ቆሻሻን ወደ ኃይል መለወጥ

12.1 የሚመለከታቸው አስፈጻሚ ኣካላት ከቆሻሻ ኃይል ለማመንጨት የሚቀርቡ

የፕሮጀክት ሀሳቦችን ለሚፈለገዉ አካባቢ ተስሚሚና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ

መሆናቸውን በአዋጭነት ጥናት መወሰን አለባቸው፡፡

Page 44: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 44 of 73

12.2 ከቆሻሻ ሀይል የማመንጨት የፕሮጀክት ሀሳቦች የቆሻሻ ይዘት ጥናትን ማካተት

አለባቸዉ፡፡እንደዚህ አይነት ጥናቶች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለዉ ዘዴን

በመከተል በዚሁ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስታንዳርድ ሰነድ ውስጥ

በተገለጸዉ መሰረት መካሄድ ይገባቸዋል፡፡

ባዮ ጋዝ

12.3 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ 1 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች

በተፈጥሮአዊ መንገድ ከሚበሰብስ የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ ባዮጋዝ የማምረት

ስራን ሊተገብሩ ይችላሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ፕሮጀክቶችን ከመተግበር በፊት

የተመረጠውን ቴክኖሎጂ ተስማሚነት እንዲሁም ለግንባታ፣ ለሥራ ማስኬጃና

ለጥገና የሚያስፈልገው ወጪ ምርቱ ከሚያስገኘዉ ገቢ ጋር ሲነፃፀር ያለውን

አዋጭነት በግልጽ የሚያሳይ ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡

12.4 ፈርጅ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ነባራዊ ሁኔታቸውን መሰረት

ባደረገ መልኩ ተግባረዊ ሊሆን የሚችል እና አዋጪ ሆኖ ካገኙት አነስተኛ

ደረጃ ያላቸው የባዮጋዝ ማምረቻዎችን በማቋቋም የሚበሰብሱ የማዘጋጃ ቤታዊ

ቆሻሻዎችን ወደ ባዮ ጋዝ መቀየር ይችላሉ፡፡

ከቆሻሻ የሚመረት ነዳጅ

12.5 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ 1 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ከማዘጋጃ

ቤታዊ ደረቅ ቆሻሻ ነዳጅ በማመንጨት ለሲሚንቶ ፋብሪካዎችና፣ ኢንዱስትሪ

የማሞቂያ ገንዳዎች እና ባጠቃላይ ለኢንዱስትሪ ግብአትነት ማቅረብ

ይችላሉ፡፡ ይሁን እና ይህን መሰል ፕሮጀክቶችን ለመተግበር የተመረጠውን

ቴክኖሎጂ ተስማሚነት እንዲሁም ለግንባታ፣ ለሥራ ማስኬጃና ለጥገና

የሚያስፈልገው ወጪ ምርቱ ከሚያስገኘው ገቢ ጋር ሲነፃፀር ያለውን አዋጭነት

በግልጽ የሚያሳይ ጥናት ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ከቆሻሻ የመነጨ

ነዳጅን ለኢንዱስትሪ ግብአትነት መጠቀም ልዩ የአካባቢ ደህንነት ቁጥጥር

ፈቃድ በማቅረብ መጠቀም እንደሚያስፈልግ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

Page 45: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 45 of 73

ቆሻሻን በከፍተኛ ሙቀት ማቃጠል

12.6 ከሆስፒታሎች እና ከሌሎች የህክምና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻዎችን

ለማከም ወይም ለማስወገድ አነስተኛ መጠን ያለው የቆሻሻ ማቃጠያ ፋሲሊቲ

መገንባት ታሳቢ መሆን አለበት፡፡

12.7 ቆሻሻ ማቃጠያ ፋሲሊቲ በሚገነባበት ወቅት ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀው

በካይ ጋዝ ለመቆጣጠር የሚያስችል እና ቆሻሻውም ከተቃጠለ በኋላ

የሚገኘውን አመድ የማስወገድ ሥራ ብክለትን በማያስከትል ሁኔታ በጥንቃቄ

መከናወኑን መቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ ከቆሻሻ ማቃጠያዎች የሚወጣ አመድ

ከፍተኛ መርዛማነት ስላለዉ በአግባቡ ተቀይሶ በተሰራ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ

መቀበር አለበት፡፡የማስወገጃ ቦታዉም የከርሰ ምድር ውሀ ብክለትን ለመከላከል

በሚያስችል ሁኔታ በድርብ ልስን መለሰን አለበት፡፡መርዛማነት ያለው

የተቃጠለ አመድ በተለይ ደግሞ ተደራርቦ ከተቀመጠበት ስፍራ የሚቦን አመድ

ለማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ በተሰራ ማስወገጃ ቦታ ላይ መደፋት የለበትም፡፡

12.8 የማዘጋጃ ቤታዊ ደረቅ ቆሻሻ ለማከም የእንፋሎት ማከሚያ ቴክኖሎጂን ሥራ

ላይ ለማዋል የሚቀርቡ የፕሮጀክት ሀሳቦች በገለልተኛ ተቋም ወይም ገለልተኛ

ተቋምን ወክለው በሚሰሩ ባለሞያዎች በዝርዝር እና በጥንቃቄ መፈተሽ

አለባቸው፡፡የተቋሙ ኃላፊነት የታሰበው ቴክኖሎጂ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው

ተግባራዊነት፣ የፕሮጀክቱ ባለቤቶች ወይም አስተዋዋቂዎች በማደግ ላይ ባሉ

አገሮች መሰል ፕሮጀክቶችን በተመሳሳይ ዓይነትና መጠን በመተግበር ያለቸው

ተሞክሮ ውጤታማነት እንዲሁም ለፕሮጀክቱ የታሰበውን ቴክኖሎጂ አዋጪነት

ጥናት በገለልተኝነት ማከናወንን ያጠቃልላል፡፡

13 የቆሻሻ ማስወገጃ (ማከሚያ) ቦታ

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ለመተግበር ሲታቀድ ከመጀመርያ እሰከ

መጨረሻ ያሉትን ስራዎች አስቀድሞ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ

ማዘጋጀት ለማንኛውም የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርአት የሚያስፈልግና የማይቀር

ተግባር ነው፡፡ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም ስራ በከፍተኛ ደረጃ ቢከናወንም እንኳ ጥቅም

የማይሰጡና የቆሻሻ የማስወገጃ በታ የሚፈልጉ የተወሰኑ ቆሻሻዎች መቅረታቸው ግድ

Page 46: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 46 of 73

ነው፡፡ ስለዚህም ሁሉም የከተማ አካባቢዎች ተፈላጊዉን ስታንዳርድ የሚያሟላ

የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ እንዲኖራቸው ማድረግ ክፍተኛ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡

የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች አይነቶች

13.1 የሚመለከታቸዉ የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሁሉም ከተሞች ቢያንስ የሚከተለዉን

ዝቅተኛ ስታንዳርድ የሚያሟላ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ያዘጋጁ መሆናቸውን

ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

ለሜትሮፖሊስ ከተማ የሚያስፈልግ የቆሻሻ ማስወገጃ ስታንዳርድ

ደረጃ 1 የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ (Class 1 Sanitary landfill)

ሀ/ ከተከማቸ ደረቅ ቆሻሻ የሚወጣውን ፍሳሽ /leachate/ ለመከላከል እና

ለማከም የሚስችል የኦክስዴሽን ኩሬ መስራት፣ ወዘተ፣

ለ/ ከማስወገጃ ቦታው የሚመነጨው ያልተብላላ ጋዝ በመሰብስብ ጥቅም ላይ

ለማዋል ወይም በነበልባል መልክ ለማስወገድ የሚያስችል የማከምያ

ስልት መዘርጋት፣

ሐ/ ቆሻሻ ወደ ከርሰ ምድር ውሃ እንዳይሰርግ ለመከላከል የማስወገጃ

ቦታውን በማያሰርግ ሁኔታ መለሰን እንዲሁም ተከታታይ የስርገት

ቁጥጥር ማድረግ፣

መ/ ቢያንስ ለ10 ዓመት ያክል እንዲያገለግል በቂና ስፋት እና ትርፍ ቦታ

ባለው አካባቢ ላይ ማስወገጃ ቦታውን መገንባት፣

ሠ/ ሥራውን በማስወገጃ ቦታው የሥራ አመራር እቅድ መሰረት

ማከናወን፣

ረ/ የማስወገጃ ቦታዉ ለስራ ደጋፊና ምቹ መገልገያዎች ተሟልተዉ

እንዲኖሩት ማድረግ፣

ሰ/ የቦታዉ አነስተኛ ተፈላጊ ስፋት የቆሻሻ ማስወገጃዉ የሚያርፍበት ቦታ

እና የዚህን 40% ያህል ለስራ ማከናወኛ እና ለሳይት አገልግሎትች

የሚያስፈልግ ስፋት ያለው መሆን አለበት፣

ሸ/ በቀን ከ251 - 500 ቶን ቆሻሻ የማስወገድ አቅም ያለው፣

ቀ/ ሙሉ ጎማዎች፣ የህክምናና ሌሎች አደገኛ ቆሻሻዎች፣ የኢንዱስትሪ

ቆሻሻዎች እንዲሁም የግንባታና ፍርስራሽ (ለመሸፈኛ እና ለምህንድስና

Page 47: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 47 of 73

ካልተፈለገ በስተቀር) በዚህ አይነቱ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ማስወገድ

በፍፁም መከልከል አለበት፡፡

ለሪጂዮፖሊስ እና ፈርጅ 1 ውስጥ ለሚገኙ ከተሞች የሚሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ስታንዳርድ

ደረጃ 2 የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ (Class 2 Sanitary landfill)

ሀ/ ከቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዉ ስር የተገጠመ እና ከቆሻሻዉ የሚወጣውን ጥቁር

ፈሳሽ /leachate/ መሰብሰብያ ቱቦ ያለዉ እና (እንደ አየሩ ጸባዩ የሚወሰን)

የጥቁር ውሀ /leachate/ ዝውውር እና ትነትን ለመቆጣጠር የሚያስችል

የመቆጣጠርያ ስልት ማበጀት፣

ለ/ ከቆሻሻ ማስወገጃው በታች የአየር መተላለፍያ እና የጋዝ ማስተንፈሻ

ቱቦዎችን በመግጠም የማስወገጃ ቦታዉ በከፊል አየር እንዲገባበትና

አንዲናፈስ በማድረግ መጥፎ ሽታን መቀነስ፡፡

ሐ/ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታው ጋዝ በመሰብሰብ በጥንቃቄ የማስተንፈሻ ፋሲሊቲ

እንዲኖር ማድረግ፣

መ/ መጠኑ እየጨመረ የሚሄድ እና ይዘቱ የሚቀያየር ቆሻሻን ለመጠቅጠቅ

የሚያግዙ ከባድ ማሽኖችን መጠቀም፣

ሠ/ ሥራው በማስወገጃ ቦታው የሥራ አመራር እቅድ መሰረት ማከናወን፣

ረ/ ቦታዉ ለስራ ደጋፊና ምቹ መገልገያዎች ተሟልተዉ እንዲኖሩት ማድረግ፣

ሰ/ የቦታዉ አነስተኛ ተፈላጊ ስፋት ማማስወገጃው የሚያርፈበት ቦታ እና

የዚህን 30% ያህል ለስራ ማከናወኛ እና ለሳይት አገልግሎትች

የሚያስፈልግ ስፋት ያለው መሆን አለበት፣

ሸ/ በቀን ከ131 – 250 ቶን ቆሻሻ ማስተናገድ የሚችል፣

ቀ/ ሙሉ ጎማዎች፣ የህክምናና ሌሎች አደገኛ ቆሻሻዎች፣ የኢንዱስትሪ

ቆሻሻዎች እንዲሁም የግንባታና ፍርስራሾች (ለመሸፈኛ እና ለምንድስና

ካልተፈለገ በስተቀር) በዚህ አይነቱ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ማስወገድ

በፍፁም መከልከል አለበት፡፡

Page 48: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 48 of 73

ለፈርጅ ሁለት ከተሞች የሚሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ስታንዳርድ

ደረጃ 3 ቁጥጥር የሚደረግበት የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ /Class 3 Landfill/

ሀ/ የማስወገጃ ቦታውን ድንበር ከሌላ ቦታ በገልጽ ለይቶ መከለል፣

ለ/በማስወገጃ ቦታዉ ክፍልፋዮች ውስጥ በየቀኑ የሚደፋውን ቆሻሻ ለመደልደል

እና በየጊዜው የሚጨምር የቆሻሻ መጠንን በአግባቡ ለማስተናገድ

እንዲቻል ብዛት ያላቸዉ ከባድ ተሽከርካሪዎችን መጠቀም፣

ሐ/ ቆሻሻ ሲወገድ በቆሻሻ ማስወገጃ ቦታውን በበቂ ሁኔታ መሸፈን፣

መ/ ቆሻሻ የሚራገፍበትን እና የማስወገድ ሂደቱ የሚከናወንበትን ቦታ

መለያየት፣

ሠ/ በአካባቢው የሚዘልቅ ወራጅ ውሃና ጎርፍ አቅጣጫን ለማስቀየርና

ከተከማቸ ቆሻሻ የሚመነጨውን ፍሳሽ /Leachate/ ብክለት እንዳያስከትል

የሚያስችል የተፋሰስ ስርዓት ማበጀት፣

ረ/ የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ዙሪያ መከለል፣ ቆሻሻ

በአካባበዊዉ መጣልን መከላከልን እና የጋዝ መተላለፍያ እና ማስተንፈሻ

የመሳሰሉ የኣካባቢ ደህንንት መከላከያ እርምጃዎችን መተግበር፣

ሰ/ ለሰራተኞችን ሥራ የሚያቃልል ምቹ እና ተስማሚ መገልገያዎችን

ማሟላት፣

ሸ/ የቦታዉ አነስተኛ ተፈላጊ ስፋት ማስወገጃ ቦታው የሚያርፈበት ቦታ እና

የዚህን 20% ያህል ለስራ ማከናወኛ እና ለሳይት አገልግሎትች

የሚያስፈልግ ስፋት ያለው መሆን አለበት፣

ቀ/ በቀን ከ51 –130 ቶን ቆሻሻ ማስተናገድ የሚችል፣

በ/ ሙሉ ጎማዎች፣ የህክምናና ሌሎች ኣደገኛ ቆሻሻዎች፣ የኢንዱስትሪ

ቆሻሻዎች እንዲሁም የግንባታና ፍርስራሾች (ለመሸፈኛ እና ለምንድስና

ካልተፈለገ በስተቀር) በዚህ አይነቱ የቆሻሻ ማስወገጃ ማስወገድ በፍፁም

መከልከል አለበት፡፡

Page 49: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 49 of 73

ለፈርጅ 3፣ 4 እና 5 ከተሞች የሚሆን የቆሻሻ ማስወገጃ ስታንዳርድ

ደረጃ 4 ቁጥጥር የሚደረግበት የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ /Class 4 Controlled Landfill/

1/ ጥገናና ቁጥጥር የሚደረግለት ቦታ ማቋቋም፣

2/ መጥፎ ሽታን ለመከላከል እንዲሁም ቆሻሻ በንፋስ ሀይል እንዳይበተን እና

እሳት እንዳይከሰት ለማድረግ የማስወገጃ ቦታው ቆሻሻ ከተደፋበት በኋላ

በአፈር መሸፈን፣

3/ ወደ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታው የሚመጡ ቆሻሻዎችን መከታተል፣ መቆጣጠርና

በአጠቃላይ የስራ ሂደቱን መከታተል፣

4/ እንደ ትራክተር ዓይነት ቀላል ማሽነሪዎች በመጠቀም ወደ ማስወገጃ ቦታው

የሚመጣ ቆሻሻን በአግባቡ ማስተዳደር፣

5/ የቦታዉ አነስተኛ ተፈላጊ ስፋት ማስወገጃ ቦታው የሚያርፍበት ቦታ እና

የዚህን 15% ያህል ለስራ ማከናወኛ እና ለሳይት አገልግሎትች

የሚያስፈልግ ስፋት ያለው መሆን አለበት፣

6/ በቀን ከ0 – 50 ቶን ቆሻሻ ማስተናገድ የሚችል፣

ሙሉ ጎማዎች፣ የህክምናና ሌሎች አደገኛ ቆሻሻዎች፣ የኢንዱስትሪ ቆሻሻዎች

እንዲሁም የግንባታና ፍርስራሾች (ለመሸፈኛ እና ለምንድስና ካልተፈለገ በስተቀር)

በዚህ አይነቱ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ማስወገድ በፍፁም መከልከል አለበት፡፡

13.2 የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ስፋት የቦታውን አቀማመጥ ጨምሮ በሚመነጨው የቆሻሻ

መጠን፣ የቆሻሻው ዓይነት፣ የቆሻሻው ጥግግት/ ደንሲቲ በቀን የሚስፈልገው የቆሻሻ

መሸፈኛ ብዛት፣ የቆሻሻ ማስወገጃውጥልቀት እንዲሁም በማስወገጃ ቦታው አዋሳኝ

ተዳፋት አንገል ይወሰናል፡፡ እንደ አንደ አጠቃላይ መመሪያ በጠፍጣፋ (ወጣ ገባ

ያልሆነ) የመሬት አቀማመጥ ላይ የሚገነባ የቆሻሻ ማስወገጃ የሚያስፈልገዉን

የመሬት ስፋት (በቆሻሻ የሚሞላዉን ቦታ እና ለስራ ማስኬጃና ተጨማሪ

አገልግሎቶች የሚያስፈልገዉን ቦታ ጨምሮ) ለመወሰን በዚህ ሰነድ ክፍል ሁለት

(የስራ ማንዋል) ሰነድ ውስጥ የቀረበውን የስሌት ዘዴ መጠቀም ይቻላል፡፡ ይሁንና

በዚህ ስሌት የሚገኘዉ የቦታ ስፋት ግምት የአዋጭነት ጥናት በሚካሄድበት ወቅት

ከአካባቢዉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተገናዝቦ እንደአስፈላጊነቱ መስተካከል አለበት፡፡

Page 50: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 50 of 73

የድርጊት መርሃ ግብር እና የአከባቢ ተፅእኖ ግምገማ

13.3 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ስታንዳርዱ እንዴት መተግበር

እንዳለበት በዝርዝር በሚያሣይ መልኩ እስከ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታው አገልግሎቱን

ሲጨርስ እስከ መዝጋት ወይም አገልግሎት ላይ ያለውን የማስወገጃ ቦታ ማሻሻል

ወይም አዲስ ለመገንባት መፍትሄ የሚያቀርብ የደርጊት መርሃ ግብር ማዘጋጀት

አለባቸው፡፡ እንዲሁም የሥራዎች አፈጻጸም የሚያሳይ ዓመታዊ ሪፖርት ለከተማ

ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር መላክ አለባቸው፡፡

13.4 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሥራ ላይ ያሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች

በህግ (የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዓዋጅ ቁጥር 299/1995 ወይም ደግሞ የክልል

ህግ) በተደነገገው መሰረት የተለያዩ የአከባቢ ተፅእኖ ግምገማ የተደረገላቸው

መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

13.5 አዲስ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ በሚመለከታቸው አካላት ሲወሰን የተካሄደ የዳሰሳ

ጥናት ተንተርሶ እና ከቀረቡት አማራጮች ቴክኒካዊ ፣ አከባቢያዊ፣ ኤኮኖሚያዊና

ማህበራዊ መመዘኛዎች ተጠቅመው ደረጃ በመስጠት መምረጥ ይገባቸዋል ፡፡

13.6 ስታንዳርድ የአከባቢ ተፅእኖ ግምገማ ውጤት መሰረት ከቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ

በታች ያለን የውሃ ምንጭ መከላከል አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት ቦታው ፍሳሽ

ቆሻሻ የማሳለፍ ተፈጥሮው ዝቅተኛ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

13.7 የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ዲዛይን ተደርጎ ፈቃድ በሚሰጥበት ጊዜ እስከ መጨረሻው

የመሬቱ መልክአ ምድር፣ አገልግሎት ሲጨርስ ለመዝጋት የሚያስፈልግ

ቴክኒኮች እንዲሁም የወደፊቱ የቦታው አደረጃጀት ተገቢው እንክብካቤ

ከተደረገለት በኃላ ያለው ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ መሆን አለበት ፡፡

13.8 አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች በሚመለከተው አካል

መርሃ ግብር ውስጥ ያልተካተቱ ከሆነ ቦታዎቹ በጥንቃቄ ተዘግተው የቴክኒክ

ስታንዳርድ በሚፈቅደው መሰረት የአከባቢ አደጋ ተጋላጭነት ደረጃ በመቀነስ

ቦታዎቹን በማደስ ለሌላ አገልግሎት ማዋል ይገባል፡፡

13.9 አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ የአከባቢ አደጋ ተጋላጭነት

ዳሰሳ ለብቻው ወይም የአከባቢው ተፅእኖ ግምገማ አካል ተደርጎ መጠናት

አለበት፡፡አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ የማስወገጃ ቦታዎች ቆጠራና የአከባቢ

Page 51: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 51 of 73

አደጋ ተጋላጭነት የዳሰሳ ጥናት በአገር አቀፍ ወይም ክልል ደረጃ ሊከናወኑ

ይችላሉ፡፡

የማስወገጃ ቦታ ስራ አመራር

13.10 የማስወገጃ ቦታ ዕለታዊ ሥራ የሚያከናውን ብቁና ልምድ ያለው የሰው ሃይል

መመደቡን የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች እርግጠኞች መሆን

አለባቸው፡፡ የቦታው ሥራ አስኪያጅ ቦታውን በብቃት ማስተዳደር የሚያስችለው

ሀብትና አስፈላጊ መሣሪያዎች ሊሟላለት ይገባል፡፡

13.11 የማስወገጃ ቦታው የስራ አንቀሳቃሾች እያንዳንድ ቦታ በተቀመጠለት ምድብ

ስታንዳርድ መሰረት እየተስተዳደረ ስለመሆኑ፣ የአሰራር እቅድ መነደፉን፣ በበቂ

ሁኔታ በሰው ሀይል የተደራጀ መሆኑ እና ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎቹ የሚሰሩ

ስለመሆናቸው እርግጠኞች መሆን አለባቸው ፡፡

13.12 የማስወገጃ ቦታዎች የስራ አንቀሳቃሾች ምንም ዓይነት የእሳት ቃጠሎ

እንደማይፈቀድ ማወቅ አለባቸው፡፡ቃጠሎ ቢያጋጥም እንኳ ለሚመለከተው

አካል ወዲያውኑ ማሣወቅ አለባቸው ፡፡

13.13 የቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሸከርካሪዎች ደህንነት ለመጠበቅ የማስወገጃ ቦታ ስራ

አንቀሳቃሾች ወደ ቦታው የሚውስዱ ቦታው ውስጥ ያሉ መንገዶች መጠገንና

መንከባከብ ይኖርባቸዋል ፡፡

13.14 ከቆሻሻ የሚመነጭ ፍሳሽ ውሀ /Leachate/፣ የነብሳት መራባት፣ በንፋስ ሀይል

የሚበተን ቆሻሻ እና ሽታ ለመቀነስ የቆሻሻው ማስወገጃ ቦታው ገፅታ

እንዳይበላሽ ቆሻሻ ከተደፋ በኋላ በየቀኑ ወይም ቢያንስ በየሶስት ቀኑ ከ15

ሴ.ሜ በማያንስ ጥልቀት በአፈር መሸፈን ያስፈልጋል፡፡

13.15 በመደበኛ ሥራ ሰዓት መደበኛ ያልሆኑ ከቆሻሻ ዉስጥ መልሶ ጥቅም ላይ

የሚዉሉ ቁሳቁሶችን የሚሰበስቡ ሰዎች ቁጥጥር በሚደረግበት ሁኔታ በተወሰነ

ቦታ መሰብሰብ እንዲችሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ቆሻሻን

ማስወገድ ሥራ እየተከናወነ ባለበት ሁኔታ ቆሻሻ እንዲሰበስቡ አይፈቀድም፡፡

13.16 ቆሻሻ በማስወገጃ ቦታ ስራ እየሰሩ የሚገኙ ሰራተኞቹ እና በቦታው ላይ ቆሻሻን

መልሶ የመጠቀም ሥራ የሚያከናውኑ ሰዎች መደበኛ የህክምና ምርመራ

Page 52: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 52 of 73

አግልግሎት በነፃ እያገኙ መሆናቸውን የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች

ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

13.17 ሁሉም በቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ የሚሰሩ ሰራተኞች እና ቆሻሻን መልሶ

የመጠቀም ስራ በመስራት የሚሳተፉ ሰራተኞች መሰረታዊ የጤና እና

የደህንነት መጠበቂያ ስልጠና መውሰዳቸውና እንደ ቦት ጫማ እና ጓንት

የመሳሰሉ የመከላከያ መሣሪያዎች ማግኘታቸው የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ

ኃላፊዎች ማረጋገጥ ይገባቸዋል ፡፡

13.18 በቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ስራን በቅልጥፍናና በአግባቡ ለመከናወን የሚያስፈልጉ

ስታንዳርዱን የሚያሟሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎች በበቂ ሁኔታ መቅረባቸውና

መጠገናቸው መረጋገጥ አለበት፡፡ የመሣሪያዎቹ ዓይነትና በእያንዳንዱ ማስወገጃ

ምድብ የሚከናወኑ ተግባራት እና የሚያስፈልግ ቁሳቁስ ከዚህ በታች ያለውን

ያጠቃልላል፡፡

ምድብ

የማስወገጃቦታ ሥራ አመራር

ዕቃ ማዘጋጀት ቆሻሻ

መበተንና መጠቅጠቅ

ክዳን ማልበስ

የቦታው መንገድ መስራትና መጠግ

ምድብ 1

LE-2, LE-4, LE-6 እና LE-9

LE–1 እና LE-4

LE-4, LE-5, LE-6,እና LE-4

LE-5, LE-6, LE-7 እና LE-10

ምድብ 2

LE-2, LE-4 እና LE-6

LE-1 እናLE- 4

LE-5, LE-6 እናLE-4

LE-5, LE-6 እና LE-7

ምድብ 3 LE -2 እናLE-3 LE-2 እና LE-3

LE-2 እናLE-3

LE-2 እናLE-3

ምድብ 4 LE-3 LE-3 LE-3 LE-3

LE-1-የማስወገጃ ቦታ ላይ ቆሻሻ

የሚጠቀጥቅ ማሽነሪ LE-6- ገልባጭ መኪና

LE-2- ተንቀሳቃሽ ሎደር LE-7- ግሬደር

LE-3- የእርሻ 4 ዊሕል ትራክተር ከነመገጣጠሚያው (ተሳቢ፣ ሎደር፣ መቧጠጫ ያለው)

LE-8-የተሸከርካሪ ክብደት መለኪያ ሚዛን

Page 53: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 53 of 73

LE-4- ተንቀሳቃሽ ሎደር LE-9- ኤክስካቫተር

LE-5- ፊቱ ላይ አካፋ የተገጠመለት ሎደር

LE-10-የውኃ ቦቴ መኪና

13.19 በፈርጅ 2፣ 3፣ 4 እና 5 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች በአነስተኛ ወጪ የማስወገጃ

ቦታ ለማስተዳደር 4 ዊሕል ተንቀሳቃሻ የእርሻ ትራክተር ከተለያየ

ተገጣጣሚዎች ጋር መጠቀም ግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡

13.20 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በሁሉም የማስወገጃ ቦታዎች ላይ

ከቆሻሻ የሚመነጨውን ጋዝ በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችል አሰራር

ተግባራዊ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

13.21 በሁሉም የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ቢያንስ ቢያንስ አገልግሎት ላይ ያልዋለ

ከማስወገጃ ቦታው የሚመነጨው ጋዝ ለማስወጣት የሚያስችል አሰራር ያለው

መሆኑን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፡፡

13.22 ኤኮኖሚያዊ አዋጭነት ካለውና ለታዳሸ የሀይል ምንጭ አገልግሎት መጠቀም

ሲቻል የማስወገጃ ቦታ ጋዝ መሰብሰብና ለገበያ መቅረብ አለበት፡፡

13.23 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ፣ እና በፈርጅ 1 ከተሞች የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች

የተሸከርካሪዎች ክብደት መመዘኛ ሚዛን የተገጠመላቸው ስለሚሆኑ ወደ ቆሻሻ

ማስወገጃው የመጣውን ትክክለኛ የቆሻሻ መጠን ማወቅ ይቻላል፡፡ በሌሎች

የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎችም ቢሆን አቅም እስከፈቀደ ድረስ ክብደት መመዘኛ

ሚዛን እንዲኖር ያስፈልጋል፡፡

14 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ /Health Care Waste/

ትርጓሜ

14.1 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ ከጤና ተቋማት፣ ከምርምር ተቋማት እና

ከተለያዩ ላብራቶሪዎች የሚመጩ ቆሻሻዎች ሲሆኑ በተጨማሪም ከቤት ውስጥ

ከሚወሰዱ የጤና እንክብካቤዎች (ዲያሊሲስ፣ ኢንሱሊን፣ መርፌ ወዘተ)

የሚመነጩ ቆሻሻን ያካትታል፡፡

14.2 ከ75% እስከ 90% ከጤና ተቋማት እንክብካቤ የሚወጡ ቆሻሻዎች አደገኛ

ስላልሆኑ ከአከባቢ ቆሻሻ ጋር መዋሃድ የሚችሉ ናቸው፡፡ አብዛኛው ከጤና ተቋም

Page 54: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 54 of 73

የአስተዳደር ቢሮ፣ ከቤት ንፅሕና እና የምግብ ዝግጅት ሥራዎች የሚመነጩ

ናቸው፡፡

14.3 የተቀሩት ከ10% እስከ 25% ከጤና ተቋማት የሚመነጩ ቆሻሻዎች አደገኞች

ስለሆኑ ለተለያ የሰው ጤናና የአከባቢ ደህንነት አደጋ ያጋልጣሉ፡፡ በመሆኑም

ቆሻሻዎቹ በተለምዶ አደገኛ የጤና ተቋማት ቆሻሻ ተብለው ይጠራሉ፡፡

14.4 የተሟላ ዝርዝር መረጃ በማይገኝበት ወቅት ከእያንዳንዱ የሆስፒታል አልጋ

በአማካይ 0.5 ኪ.ግ በቀን የበሽታ መንስኤ እና አስተላላፊ የሆኑ አደገኛ ቆሻሻ

እንደሚመነጭ ይገመታል ፡፡

አደገኛ የጤና ተቋማት ቆሻሻ

14.5 ሆስፒታሎችና ሌሎች የጤና እንክብካቤ ተቋማት ቆሻሻ በመያዝ፣ በማከምና

በማስወገድ እንቅስቃሴ ምንም አይነት የጤና ወይም የአከባቢ ጉዳት

እንደማይደርስ የማረጋገጥ እና የመንከባከብ ሀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው፡፡

14.6 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ በማመንጨትና በማስተዳደር የሚገኙ

ተቋማት ከርዕሱ ትርጓሜ እና ከተገቢው የአሰራር ሂደት ጋር እራሳቸውን

ማስተዋወቅ አለባቸው፡፡

14.7 አነስተኛ የህክምና ተቋማትን ጨምሮ ከሁሉም የጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ

ቆሻሻ አመንጪ ተቋሟት የሚከተሉት ተቋማትን ያካትታል፡፡

ሀ/ የሀኪሞች ቢሮ፣

ለ/ የጥርስ ክሊኒክ፣

ሐ/ የደረቅ መርፌ ህክምና መስጫ፣

መ/ የወገብና የመገጣጠሚያዎች የአጥንት ህክምና፣

ሠ/ የህመምተኞች ማገገሚያ ቦታ፣

ረ/ የአካል ጉዳተኞች ተቋማት፣

ከጤና ተቋማት ከሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ ጋር በተያያዘ ሊከሰት የሚችል አደጋ

14.8 ከጤና ተቋማት በሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ አማካኝነት የሚከሰት በሽታና አደጋ

በማስቀረት ተጋላጭነትን የሚጋብዙ ሁኔታዎችን መቀነስ የሚመለከታቸው የዘርፉ

የስራ ኃላፊዎች ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ከጤና ተቋማት የሚወጡ አደገኛ ቆሻሻ

ምክንያቱ በካይ ቁሳቁሶች፣ ስለታም እቃዎች፣ አደገኛ የኬሚካልና የፋርማሲ

Page 55: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 55 of 73

ውጤቶች እንዲሁም በአነስተኛ ደረጃ ቢሆንም መርዘኝነትና የጨረር ማቴሪሎች

በመኖራቸው ነው፡፡፡

ከጤና ተቋማት የሚመጭ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድ

14.9 አደገኛ የጤና ተቋማት ቆሻሻ በማመንጨትና በማስተዳደደር የሚሳተፉ አካላት

የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድን ለማሻሻል በሀገር አቀፍ ደረጃ፣ በክልልና በከተማ

ደረጃ የሚተገበር እቅድና ስትራቴጂ ማዘጋጀት አለባቸው ፡፡

14.10 የመንግስት መሥሪያ ቤቶች፣ሆስፒታሎች እና የተለያዩ የጤና ተቋማት ማእከላት

ከጤና ተቋማት ለሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድና ስትራቴጂ

ትግበራ የሚያስፈልግ ፋይናንስ መኖሩን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

ቆሻሻ መለየትና ማሸግ

14.11 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ የመለየትና በተገቢው መንገድ ለይቶ

የማስቀመጥ ሥራ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ቆሻሻው በመነጨበት የመጀመሪያ

ቦታ ላይ ነው፡፡

14.12 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻን አደገኛ እና አደገኛ ያልሆነ ቆሻሻን የመለየት

ስራ በተቻለ መጠን ቆሻሻው ከመነጨበት ቦታ መሆን አለበት፡፡ በአይነት

የተለዩት አደገኛና አደገኛ ያልሆኑ ቆሻሻዎች እንደተለዩ መከማቸትና መጓጓዝ

አለባቸዉ፡፡

14.13 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ በባለ ቀለም ፕላስቲክ ቦርሳ ወይም

ገንዳ ተለይተው መቀመጥ አለባቸው፡፡ የአፈፃፀም መመሪያው የሚከተሉትን

መጠበቅ ይኖርበታል፡፡

ሀ/ አጠቃላይ አደገኛ ከጤና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ያልሆነ ቆሻሻ

በአካባቢው ከቤት ለቤት ከተሰበሰበው ቆሻሻ ጋር በመቀላቀል መወገድ

አለበት፡፡

ለ/ ስለታም ነገሮች፡

i/ ቢበከሉም ባይበከሉም ሁሉም ስለታም ነገሮች አንድ ላይ በጋራ

መሰብሰብ አለባቸው፣

ii/ በማይቀደድና ክዳኑ በሚገጥም ገንዳ ውስጥ መቀመጥ አለባቸው፣

Page 56: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 56 of 73

iii/ ስለታም ነገሮች ብቻ ሳይሆን በውስጥ የሚይዙት ፈሳሸም እንዳይፈስ

የሚጠራቀሙበት ገንዳዎቹ ጠንካራና በቀላሉ የማይከፈቱ መሆን

አለባቸው፣

iv/ የስለታም ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ለመክፈትም ይሁን

ለመስበር የሚያስቸግሩ ዓይነት መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም

መርፌዎችና የፍሳሸ መምጠጫዎች ዳግሞ ጥቅም ላይ የሚውሉ

አይደሉም፣

ሐ/ የፕላስቲክ ወይም የብረት ገንዳ ካልተገኘ ወይም በጣም ከተወደደ ከካርቶን

(ወረቀት) የተሰራ ገንዳ መጠቀም ይመከራል (WHO/የአለም የጤና

ድርጅት/,1997)፡፡ ይህን መሰል የካርቶን ገንዳዎች የፕላስቲክ ንጣፍ

ያለቸዉም ጭምር ለማጠፍና፣ ለማሸግ እና ለማጓጓዝ ምቹ ናቸዉ፡፡

መ/ አደገኛ ቆሻሻን ለማጠራቀም የምንጠቀምባቸዉት ካርቶኖች እና ገንዳዎች

ላይ የዓለም አቀፍ አደገኛ በካይ እቃ ምልክት ሊደረግባቸዉ ይገባል፡፡

ሠ/ ከፍተኛ የበካይነት ባህሪ ያላቸው ቆሻሻዎች ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ወዲያውኑ

ስቴርላይዘር እና አውቶካሊቨር በመጠቀም ከጀርም ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ

ያስፈልጋል፡፡ስለዚህ ተገቢ በሆነ የቆሻሻ መያዢያ ከረጢት ማሸግ

ያስፈልጋል ማለት ነው ፡፡

ረ/ ከዋና ዋና ሆስፒታሎች ወይም ከምርምር ተቋማት የሚመነጩ መርዛማ

አደገኛ ቆሻሻዎች በጠንካራ፣ በማያፈስ እና በግልፅ አደገኛ መርዛማ

ቆሻሻ ተብሎ በተለየ ገንዳ ላይ መሰብሰብ አለባቸው፡፡

ሰ/ የኬሚካል ወይም የፋርማሲ መድሀኒት ቆሻሻ፡-

i/ አነስተኛ መጠን ያላቸው የኬሚካልና የፋርማሲ ቆሻሻዎች ከሌሎች

አደገኛ የህክምና ተቋማት ቆሻሻዎች ጋር አብረዉ መሰብሰብ አለባቸው፣

ii/ በርካታ መጠን ያላቸው በሆስፒታል ዋርዶች ወይም ክፍሎች

የተከማቹ፣ የተበላሹ ወይም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው

መድሃኒቶችና ተያያዥ ቁሳቁሶች በአግባቡ እንዲወገዱ ወደ መድሃኒት

ቤት መመለስ አለባቸው ፡፡

iii/ ሌሎች የፈሰሱ ወይም የተበከሉ መድሃኒቶች ወይም በማሸግ ወቅት

የቀሩ የመድሃኒትና ተያያዥ ቆሻሻዎች መድሃኒት ቤቱን ሊበክሉ

Page 57: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 57 of 73

ስለሚችሉ ወደ መድሀኒት ቤቱ ሳይመለሱ በትክክለኛዉ ገንዳ

ተከማችተው በመነጩበት ቦታ መቀመጥ አለባቸው፡፡

ሸ/ ከፍተኛ የኬሚካል መጠን ያለባቸው ቆሻሻዎች ኬሚካል በሚቋቋም ገንዳ

ውስጥ መታሸግ አለባቸው፡፡እንዲሁም በጥንቃቄ ተከማችተው በአግብቡ

በባለሙያ እንዲወገዱ ወደ ልዩ ማከሚያ ቦታ መላክ አለባቸው፡፡የኬሚካሉ

ምንነት ገንዳው ላይ በግልፅ መጻፍ አለበት፡፡ የተለዩ አደገኛ የኬሚካል

ቆሻሻ አይነቶች በአንድ ላይ መደባለቅ የለባቸዉም፡፡

ቀ/ ከፍተኛ የብረት ይዘት ያለው (እንደ ካድሚየም እና ሜርኩሪ) ቆሻሻ ለብቻው ተለይቶ መሰብሰብ አለበት፣

በ/ የፍሳሽ መድሀኒት መያዣ ከረጢቶች ወደ ቆሻሻ ማቃጣያ ቦታ ካልተወሰዱ በስተቀር ከአጠቃላይ የህክምና ተቋማት አደገኛ ቆሻሻ ጋር አብረዉ ሊሰበሰቡ ይገባል፡፡

ተ/አነስተኛ መጠን ጨረር አመንጪ ቆሻሻዎች (ለምሣሌ መምጠጫ፣

ለምርመራ አገልግሎት የሚውል መምጠጫ መርፌ ወይም የህክምና

መገልገያዎች) በብጫ ከረጢቶች ወይም ገንዳዎች በመሰብሰብ ወደ ማቃጠያ

ቦታ መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡

14.14 ሁሉም ባጠቃላይ አደገኛ ያልሆኑ ቆሻሻዎች ልክ ከቤት ለቤት እንደሚሰበሰበው

ቆሻሻ በተመሣሣይ ሁኔታ መያዝና በጥቁር ቦርሳ መሰብሰብ አለባቸው፡፡

14.15 ከስለታም ቆሻሻ በስተቀር ሌላ ዓይነት የጤና ተቋማት አደገኛ ቆሻሻ ስለታም

ቆሻሻ በሚቀመጥበት ገንዳ ውስጥ መቀመጥ የለበትም፡፡

14.16 ከአንድ ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ የሚውል የስሪንጅ መርፌ አገልግሎት ላይ

ሲውል ማሸጊያው ወደ አደገኛ ያልሆኑ ቆሻሻዎች በሚጠራቀሙበት ዕቃ

ሲጠራቀም መርፌውን ግን በቢጫው የስለታም ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ

ማጠራቀም ያስፈልጋል፡፡

14.17 ተስማሚ ገንዳዎች ወይም ከረጢቶች የተለያየ ዓይነት ቆሻሻ በሚመነጩት

ሁሉም አቅጣጫዎች ላይ መቀመጥ አለባቸው፡፡

14.18 የአሰራር ሂደቱን ለሰራተኞች ለማስታወስ ያክል በእያንዳንዱ የቆሻሻ

መሰብሰብያ ቦታ ላይ ቆሻሻውን በአይነት ለይቶ የማስቀመጥ መመሪያዎች

መለጠፍ አለባቸው ፡፡

Page 58: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 58 of 73

14.19 አደገኛ የህክምና ተቋማት ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሦስት አራተኛው ከሞላ

ተነስቶ በባዶ ገንዳ መቀየር አለበት፡፡

14.20 ቆሻሻን በመለያይት ጊዜ ስህትት ሲፈጠር ሰራተኞች ቆሻሻዉን ከረጢት

መይም ማጠራቀምያ በማዉጣት ወይም አንዲን ቆሻሻ የያዘ ከረጢት ሌላ ቀለም

ባለዉ ከረጢት ዉስጥ በመክትት ስህትቱን ለማረም መሞከር የለባቸዉም፡፡

14.21 አደገኛ ያልሆነ ቆሻሻ አደገኛ ከሆነ ቆሻሻ ጋር በስህተት ከተቀላቀለ

የተደባለቀው ቆሻሻ እንደ አደገኛ የጤና ተቋማት ቆሻሻ ታስቦ መስተናገድ

አለበት፡፡

ቆሻሻ በምንጩ ላይ መሰብሰብ፣ ማጓጓዝ እና ማከማቸት

መሰብሰብ

14.22 ነርሶችና የክሊኒክ ሰራተኞች የቆሻሻ ከረጢቶች 2/3ኛው ሲሞሉ በጥብቅ

መዘጋታቸው ወይም መታሸጋቸው ማረጋገጥ አለባቸው፣

14.23 ስስ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በራሳቸዉ አንገታቸው አካባቢ በመቋጠር መዝጋት

ሲቻል ጠንካራ ከረጢቶች ግን በራሱ የሚቆለፍ የፕላስቲክ ማሸግያ ሊኖራቸዉ

ይገባል፡፡

14.24 የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ከረጢቶች በወረቀት ማያያዣ ሽቦ (ስቴፕለር) መዘጋት

የለባቸውም፡፡

14.25 ስለታም ነገሮችን የያዙ የታሸጉ ቆሻሻ መያዣዎች ከሆስፒታል ዋርድ ወይም

መምሪያ ከመውጣታቸው በፊት በቢጫ በካይ የጤና ክብብከቤ ቆሻሻ መያዣ

ከረጢት ዉስጥ ታሽገዉ “በካይ የጤና ክብካቤ ቆሻሻ” የሚል ምልክት

ሊለጠፍባቸው ይገባል፡፡

14.26 ቆሻሻው በሚመነጨበት አከባቢ በብዛት መከማቸት የለበትም፡፡

14.27 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ የቆሻሻ አያየዝና አወጋገድ ዕቅድ መደበኛ የእለት

ተእለት የጤና ክብካቤ ቆሻሻ አሰባበሰብን ያካተተ መሆን አለበት፡፡

14.28 ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ በመሰብሰብ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች

የሚከተሉትን ምክረ ሃሳቦች እንዲከተሉ ይመከራል፡-

ሀ/ ቆሻሻ ቢያንስ በቀን አንድ ጊዜ አለዚያም እንደአስፈላጊነቱ ከአንድ ጊዜ

በላይ እየተሰበሰበ ወደ ተወሰነዉ ማከማቻ ቦታ መጓጓዝ አለበት፡፡

Page 59: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 59 of 73

ለ/ ቆሻሻ የያዙ ከረጢቶች ይዘታቸዉን የሚገልጽ ጽሁፍ ወይም ምልክት

በሆስፒሉ ወይም የሚመለከተዉ ዋርድ ሳይደረግባቸዉ መነሳት

የለባቸዉም፡፡

ሐ/ የሞላ የቆሻሻ መያዣ ከረጢት ወይም ማጠራቀምያ እቃ ወዲያዉኑ

በተመሳሳይ ባዶ ከረጢት ወይም ማጠራቀምያ መተካት አለበት፡፡

መ/ ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ በሚመነጭባቸዉ ሁሉም ቦታዎች

በቂ የቆሻሻ መያዣ ከረጢቶች እና ማጠራቀሚያ እቃዎች ተዘጋጅተዉ

መቀመጥ አለባቸዉ፡፡

ማጠራቀም

14.29 በጤና ክብካቤው ተቋም ወይም የምርምር ጣብያ ውስጥ ከጤና ተቋማት

የሚመነጭ ቆሻሻ የሚከማችበት ቦታ ተለይቶ መዘጋጀት አለበት፡፡

14.30 በተቋሙ ዉስጥ የሚመነጨዉን የቆሻሻ መጠን እና ቆሻሻዉ የሚሰበሰብበትን

ድግግሞሽ ታሳቢ በማድረግ በቂ ስፋት ያለዉ ቦታ፣ ክፍል ወይም ህንጻ ለቆሻሻ

ማጠራቀምያነት መዘጋጀት አለበት፡፡

14.31 ማቀዝቀዣ ያለው ማከመቻ ካልተጠቀሙ በስተቀር የጤና ተቋማት አደገኛ

ቆሻሻ የሚከማችበት ጊዜ (ከማመንጨት እስከ ማከም ያለው ጊዜ) ከ24 ሰዓታት

በላይ መብለጥ የለበትም፡፡

14.32 ህዋሳትን የያዘ መርዛም የህክምና ተቋማት ቆሻሻ ከሌሎች የህክምና ተቋማት

ቆሻሻ ተለይቶ ለዚሁ በተዘጋጀ አስተማማኝና ደህንነት ባለው ቦታ ላይ

መከማቸት አለበት፡፡

14.33 ራዲዮ አክቲቭ ጨረር የሚያመነጩ አደገኛ ቆሻሻ ጨረር አፈትልኮ ወይም

ፈንድቶ እንዳይወጣ በሚከላከል ገንዳ ውስጥ መከማቸት አለበት፡፡ የጨረር

ዝቃጭ በሚከማችበት ወቅት የጨረሩ ዓይነት፣ ቀን፣እና እንዴት መቀመጥ

እንዳለበት ዝርዝር የሚያስረዳ መግለጫ መያዝ አለበት፡፡

ቆሻሻን በመነጨበት ተቋም ዉስጥ መጓጓዝ (ሳይት ላይ ማጓጓዝ)

14.34 ከጤና ተቋማት የሚመነጩ ቆሻሻዎች በመነጩበት በሆስፒታሎች ወይም ሌሎች

የጤና ተቋሞች ክልል ውስጥ ሲጓጓዙ ጎማ ያለቸዉ ጋሪዎች፣ ገንዳዎች ወይም

ባለሞተር አመላለሾችን እና ተሳቢዎችን በመጠቀም መጓጓዝ አለባቸዉ፡፡ ለዚህ

Page 60: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 60 of 73

አገልግሎት የሚዉሉ ማጓጓዣዎች ከጤና ተቋማት የሚመነጩ ቆሻሻዎችን

ከማመላለስ በስተቀር ለሌላ አገልግሎት መዋል የለባቸዉም፡፡ በተጨማሪም

ማጓጓዣዎቹ የሚከተሉተን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸዉ፡-

ሀ/ ለመጫን እና ለማዉረድ የሚመቹ፣

ለ/ ሲጫንኑ ሲወርዱ የቆሻሻውን ከረጢት ወይም ማጠራቀምያ ሊቀድ፣

ወይም ሊጎዳ የሚችል ምንም ዓይነት ስለታም ጫፍ ወይም ጠርዝ

የሌላቸዉ፣

ሐ/ ለማፅዳት ቀላል እና አመቺ፣

14.35 ማጓዢያ ተሸከርካሪዎች ፅዱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ እንዲሁም በተገቢ ፀረ በካይ

ፍሳሽ በየቀኑ ከብክለት ነፃ እንዲሆኑ መደረግ ይኖርበታል፡፡

14.36 ሁሉም የታሸጉ የቆሻሻ ከረጢቶች በጉዞዉ መጨረሻ ላይ ያለምንም ጉዳት (እሽጉ

ሳፈታ) መድረስ አለባቸው ፡፡

ቆሻሻን ወደ ቆሻሻ ማስወገጃ /ማከሚያ/ ቦታ ማጓጓዝ

ደንብና የቁጥጥር ስርዓት

14.37 አደገኟ ቆሻሻ የሚያመነጩ የጤና ተቋማት ቆሻሻዉ ከተቋሙ ወጥቶ ከመጓጓዙ

በፊት ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ መታሸጉን እና ማጓጓዣዉ የቆሻሻውን ዓይነት

/ባህሪ የሚገልጽ ጽሁፍ የተለጠፈበት መሆኑን እና የሚጓጓዝበት ቦታ ፍቃድ

የተገኘለት መሆኑን የማረጋገጥ ሀላፊነት አለባቸው፡፡

14.38 የቆሻሻው ማጠራቀሚያ ገንዳ ወይም ከረጢት አስተሻሸግና የቆሻሻው ባህሪ

እንዲገልፅ የሚለጠፈው ፅሁፍ በሀገሪቱ የአደገኛ ቆሻሻ ማጓጓዥያ ህጎች መሰረት

መሆን አለበት፡፡

14.39 ከህክምና እና ጤና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻዋች የቁጥጥር ስትራቴጂ

ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማካተት አለበት፡-

ሀ/ ቆሻሻው ለማንሳትና ለማጓጓዝ የተፈቀደ ስለመሆኑ የሚገልፅ ማስታወሻ

ከሚመነጨበት ቦታ እስከ ሚወገድበት ቦታ ድረስ አብሮ መያያዝ

አለበት፡፡ በጉዞው መጨረሻ አጓጓዡ በማስታወሻዉ ላይ በተዘጋጀለት

ቦታ አስፈላጊዉን መረጃ በመሙላት ማስታወሻዉን ወደ ቆሻሻ

አመንጪው መመለስ አለበት፣

Page 61: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 61 of 73

ለ/ የትራንስፖርት ድርጅቱ በሚመለከተዉ የቆሻሻ ተቆጣጣሪ

ባለስልጣን መመዝገብ አለበት፡፡

ሐ/ ከጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ የሚይዙ፣ የሚያስተዳደሩ እና የሚስወግዱ ተቋማት ይህን ለመድረግ የሚስቸል ፈቃድ ከቆሻሻ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ማግኘት አለባቸዉ ፡፡

የማጓጓዥ ተሸከርካሪዎች ወይም ገንዳዎች

በቆሻሻ የሞሉ ከረጢቶችን በመነካካት የሚከሰት የጤና እና የአካባባ አደጋን

ለመከላከል የጤና ተቋማት ቆሻሻ የሚመነጭበት በግቢ (ሳይት) ውስጥ ከሚያመላልሱት

ማጓጓዣዎች በቀጥታ ወደ ቆሻሻ ሰብሳቢ ተሽከርካሪዎች መገልበጥ አለበት፡፡

14.40 ቆሻሻውን ወደ ሚፈለገዉ ቦታ ካደረሱ በኋላ ማጓጓዣዎቹ ተጸድተዉ እና

በተገቢው የብክለት ማስወገጃ ፈሻሽ ተረጭተዉ/ተወልዉለዉ ወደ ጤና ተቋሙ

መመለስ አለባቸዉ፡፡

14.41 ማንኛውም ከጤና ተቋማት የሚመነጭ ቆሻሻ ማጓጓዢያ ተሽከርካሪ የሚከተሉትን

የዲዛይን ዝርዝር ማሟላት አለበት፡፡

ሀ/ የገንዳው አሰራር ከተሸከርካሪው መጠን ጋር የሚስማማና የውስጥ ቁመትም 2.2 ሜትር መሆን አለበት፣

ለ/ ግጭት ካጋጠመ ጭነቱ እንዳይወድቅ ለመከላከል በአሸከርካሪው ክፍልና የመኪናው ሰውነት የሚያለያይ ማከፋፈያ ግድግዳ (በልክሄድ) መኖር አለበት ፡፡

ሐ/ ጭነቱን በጉዞ ወቅት እንዳይንቀሳቀስ ለማጓጓዝ የሚያስችል ማሰርያ ወይም ሌላ ስልት ሊኖርዉ ይገባል፡፡

መ/ በተሽከራካረዉ ልዩ የእቃ ማስቀመጫ ክፍል ዉስጥ ባዶ ፕላስቲክ ቦርሣዎች ፣ አመቺ የአደጋ የመከላከያ ልብሶች፣ የፅዳት መሣሪያዎች የሥራ ቁሳቁሶችና የብክለት መከላከያዎች ፈሳሸ መያዣ እነዲሁም ከቆሻሻ የሚወጣ ፈሳሽን ለማጽዳት የሚስቸሉ መሳሪዎች መቀመጥ አለባቸዉ፡፡

ሠ/ የተሽከርካሪው የውስጥ ቅብ በእንፋሎት /ሊፀዳ የሚችል እና የውስጥ ማዕዘኖቹም ዙሪያ ገጠም (የእንቁላል ቅርጽ ያላቸዉ) መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ረ/ ተሸከርካሪው የአጓጓዡን ስም እና አድራሻ መያዝ አለበት፡፡ ሰ/ አለም አቀፍ የአደገኛ ቆሻሻ ምልክት እና የአደጋ ጊዜ ስልክ ቁጥሮች

በተሸከርካሪው ወይም በገንዳው ላይ መለጠፍ አለባቸዉ፡፡ ሸ/ የጤና ተቋማትን ቆሻሻ የሚያጓጓዙ ተሸከርካሪዎች ወይም ገንዳዎች ለሌላ ዓይነት እቃ ማጓጓዢያ ትራንስፖርት አገልግሎት ሊውሉ አይገባም፡፡

Page 62: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 62 of 73

ሲጭኑና ሲያራግፉ ካልሆነ በስተቀር ሁልጊዜ ሊቆለፉ ይገባል፡፡ ቀ/ በቆሻሻ ማምረቻ ቦታ ላይ በቀላሉ የሚያነሱና ከአከባቢው ጋር

የሚስማሙ በልዩ ሁኔታ የተሰሩ ተሳቢዎች (አስፈላጊ ከሆነ ሙቀት

የሚቆጣጠሩ ሊሆኑ ይችላሉ) አገልግሎት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ በሌላ

ዓይነት አሰራርም በልዩ ሁኔታ ዲዛይን የተደረጉ ገንዳዎችና

ገንዳዎችን የሚሸከሙ ተሸከርካሪዎች መጠቀም ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን

ክፍት የቆሻሻ ማጓጓዥያ ገንዳዎችን ከጤና ተቋማት የሚመነጩ

አደገኛ ቆሻሻዎችን ለማጓጓዝ አገልግሎት መጠቀም አይቻልም፡፡

በ/ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ተሸከርካሪ መመደብ የማይቻል ከሆነ

በመኪና ላይ የሚጫኑ ትላልቅ ገንዳዎችን መጠቀም እንደ አማራጭ

ሊወሰድ ይችላል፡፡ ገንዳው በጤና ክብካቤ ተቋሙ ዉስጥ ተቀምጦ

ቆሻሻ ከተጠራቀመበት በኋላ በባዶ ገንዳ ይተካና በቆሻሻ የሞላዉ ገንዳ

በመኪና ተጭኖ ወደ ማስወገጃ ቦታ ይወሰዳል፡፡ ቆሻሻው ከ24 ሰዓት

በላይ የሚከማች ከሆነ ባለማቀዝቀዥ ገንዳ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ አገልግሎት የሚዉሉ ገንዳዎች የውስጥ ንጣፍ ልሙጥና ምንም

ነገር የማያሰርግ እንዲሁም ለማጽዳትና ከብክለት ነጻ ለማድረግ

የሚያመች መሆን አለበት፡፡

14.42 በተለያየ ቦታ ከሚገኙ አነስተኛ ምንጮች የሚሰበሰቡ ከጤና ተቋማት የሚመነጩ

አደገኛ ቆሻሻዎችን ለመሰብሰብ ከላይ የተዘረዘሩት የአሰባሰብ ሂደቶች

በተመሣሣይ ሁኔታ መተግበር አለባቸዉ፡፡

ከህክምናና ከጤና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻዎች አወጋገድ

14.43 ከህክምናና ጤና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻዎች የሚወገዱባቸው

የተለያዩ አማራጮች አሉ፡፡ በመሆኑም ተፈላጊዉን የአወጋገድ መንገድ

በአዋጭነት ጥናት ላይ በመመስረት አና አካባቢያዊ ሁኔታዎችን በማገናዘብ

መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ በተጨማሪም የሚከተሉት ጉዳዮች ታሳቢ መሆን

አለባቸዉ፡-

ሀ/ የሚታከም ወይም የሚወገድ ቆሻሻ መጠን፣

ለ/ መታከም ወይም መወገድ ያለባቸው የቆሻሻ ዓይነቶች፣

Page 63: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 63 of 73

ሐ/ በቂ ቦታ መኖር፣

መ/ የኢንቨስትመንትና ሥራ ማስኬጃ ወጪዎች፣

ሠ/ በማስወገድ ሂደት ሊከሰት የሚችል የአካባቢ ተፅእኖ፣

በእንፋሎት ኃይል ማምከን/አውቶክላቪንግ/

14.44 ከጤናና ህክምና ተቋማት የሚመነጩ አደገኛ ቆሻሻ ለማከም የእንፋሎት ኃይል

ተጠቅሞ ማምከን /Autocleviry/ እንደ አንድ ጠንካራ አማራጭ መወሰድ

አለበት፡፡ ቆሻሻው በእንፋሎት ሃይል ከአደገኛ በካይነቱ ነፃ ከሆነ በኋላ ከሌላው

የማዘጋጃ ቤታዊ ቆሻሻ ጋር አብሮ ሊሰበሰብና ሊወገድ ይችላል፡፡

በከፍተኛ ሙቀት ማቃጠል

14.45 ከህክምና እና ከጤና ተቋማት የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻ የእንፋሎት ኃይል

ተጠቅሞ ቆሻሻን ማምከን ተግባራዊ ሊሆን በማይችልበት ሁኔታ ከፍተኛ ሙቀት

ተጠቅሞ ማቃጠል ሌላዉ አማራጭ ነዉ፡፡

14.46 መርዛማ ካርቦን ሞኖኦክሳይድ እንዳይመረት እና፤ ተከትለዉ የሚወጡ አመድና

ቆሻሻ ውሃ እንዲሁም ሌሎች መርዛማ ንጥረ ነገሮች አከባቢውን እንዳይበክሉ

የማቃጠል ተግባሩ በአግባቡ በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር ተደርጎ መከናወን

አለበት፡፡

14.47 ቆሻሻን ማቃጠል አማራጭ ተመራጭ የሚሆነዉ የቆሻሻው የሙቀት መጠን

ቢያንስ 2000 kcal/kg (8370 kJ/kg) ሲደርስ ብቻ ነው፡፡ የበካይ ቆሻሻ የሙቀት

መጠን ከ4000 Kcal /kg በላይ ነው፡፡

14.48 የሚከተሉት ቆሻሻዎች መቃጠል የለባቸውም

ሀ/ የታመቀ ጋዝ መያዣ ጋኖች፣

ለ/ በርካታ የጨረርና ኬሚካል ይዘት ያለዉ ቆሻሻ፣

ሐ/ መዳብ፣ ብረት እና ፎቶግራፊክ ወይም ራዲዮግራፊክ ቆሻሻ (እንደ ራጅ

የመሳሰሉ)፣

መ/ እንደ ፓሊቪናይል ክሎራይድ(PVC) ዓይነት የኬሚካሎች ቅይጥ

ፕላስቲኮች፣

ሠ/ ከፍተኛ የሜርኩሪና የካድሚየም ክምችት ያላቸዉ ቆሻሻዎች (ባትሪ፣

ቴርሞሜትር፣ የሊድ ሽፋን ያለቸዉ አንጨቶች ወዘተ)፣

ረ/ የታሸጉ አምፑሎች ወይም ከፍተኛ ብረት ያላቸው አምፑሎች፣

Page 64: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 64 of 73

14.49 ከህክምና እና የጤና ተቋሞች የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻን በማቃጠል ለማስወገድ

ድርብ የማቃጠያ ክፍል እና ከፍተኛ አምቅ ሙቀትን የሚጠቀም ማቃጠያ

መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

14.50 ነጠላ በጡብ የተሰራ ማቃጠያ በሚያመነጨው አነስተኛ ሙቀት እና የማቃጠል

ብቃት በቂ ባለመሆኑ ምክንያት ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም፡፡

14.51 በነጠላ ጡብ የተሰራ ባለ አንድ ክፍለ ማቃጠያ በሚያመነጨው ሙቀት

አነስተኛ እና የማቃጠል ብቃቱም በቂ ባለመሆኑ ከህክምና እና የጤና ተቋሞች

የሚመነጭ አደገኛ ቆሻሻን ለማቃጠል ጥቅም ላይ ሊዉል አይገባም፡፡

14.52 ከማቃጠያው የሚወጣው ጭስ መጠን የአገሪቱን ስታንዳርድ የተከተለ መሆን

አለበት፡፡ የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎች ስታንዳርድ ካለስቀመጡ

የአሜርካና አውሮፓ ስታንዳርድ በማጣቀስ መጠቀም ይችላሉ፡፡

15. የፋይናንስ ጉዳዮች

15.1. የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች አጠቃላይ ለደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ አገልግሎት ማለትም ለስራ ማስኬጃና ሪፖርት የሚወጣዉን ወጪ

በግልጽ የሚሳይ የፋይናንስ ሥራ አመራር ስርዓት ማበጀት አለባቸው፡፡

15.2. የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር

በመቀናጀት በተመረጡ ማዘጋጃ ቤቶች የደርቅ ቆሻሻ አገልግሎት ፍላጎትን እና

ለአግልግሎቱ የመክፈል ፈቃደኝነትን የሚዳስስ ጥናት ማካሄድ አለበት ፡፡

15.3. የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር የወጪ መሸፈን አካሄድን

ለመከለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መቀናጀት ይኖርበታል፡፡ የቆሻሻ

አገልግሎት ክፍያ ከውሃ ቢል ጋር አብሮ የሚከፈልበት የአዲስ አበባና የአንድ

አንድ ማዘጋጃ ቤቶች ልምድም ኪዚሁ አንጻር በልዩ ሁኔታ መመርመር

አለበት፡፡

15.4. የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ወጪ በሚመለከታቸው አካለት ሲወሰን

መሰረት ማድረግ ካለበት ጉዳዮች መሀከል ዋናዎቹ አሁን አግልግሎቱን

ለመስጠት የሚወጣዉ ወጪ ግምት፣ ወደፊት የሚተገበሩ የአልግሎት

አማራጮች እና አነዚህን ለመተግበር የሚያስፈልገዉ ወጪ ናቸዉ፡፡

Page 65: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 65 of 73

15.5. የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ አገልግሎት ክፍያ በተመለከተ በአማካኝ

ከእንዳንዱ ቤተሰብ አመካይ ገቢ ከ1% በላይ መሆን የለበትም፡፡ የሚመለከተው

አካላት ለቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ የሚወጣውን ወጪ በተወሰነ መልኩ

መንግስት ከሚመድበው በጀት ድጎማ ማድረግ ቢቻልም ቢያንስ ግን

ለቆሻሻ የማሰባሰብ ስራ የሚውለውን የሥራ ማስኬጃና የጥገና ወጪ ከነዋሪው

ለጽዳት ተብሎ በሚሰበሰበው ገቢ አማካኝነት መሸፈን አለበት፡፡

15.6. የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች አነስተኛው መሰረታዊ አገልግሎት

ለሁሉም የከተማ ኗሪዎች የማዳረስ ግዴታ አለባቸው፡፡ አገልግሎቱ አስተማማኝ

ፋይናንስ እንዲኖረው ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት መዘርጋት

ያስፈልጋል፡፡

15.7. የሚመለከተው የስራ ኃላፊ ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ተቋማት የሚቀርብ የደረቅ

ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት (የንግድ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪ እና

ሌሎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የቆሻሻ አያያዝ

አያያዝና አወጋገድ) ሙሉ የአገልግሎት ክፍያ (የቆሻሻ ማስወገጃ ወጪንም

ያካትታል) ቆሻሻውን አመንጪዎቹ ተቋማቶቹ መሸፈን አለበት፡፡

15.8. ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ተቋማት የሚቀርብ የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት (የንግድ፣

የኢንዱስትሪ አንዲሁም ሌሎች ቆሻሻ አመንጪ ተቋማትን ጨምሮ) ሙሉ

የአገልግሎት ክፍያ (የቆሻሻ ማስወገጃ ወጪንም ያካትታል) በቆሻሻ

አመንጪዎች መሸፈን አለበት፡፡

15.9. የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ለደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ሥራ አገልግሎት ተብሎ የሚሰበሰቡ ክፍያዎች ለደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ሥራ ተግባራት እንጂ ለሌሎች የህዝብ አገልግሎቶችን ፋይናንስ

ለማደረግ መጠቀም የለባቸዉም፡፡

Page 66: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 66 of 73

16. ተቋማዊ አደረጃጀት

16.1 የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራን የሚያስተባብሩ አደረጃጀቶች በክልልና

ከተማ ደረጃ መቋቋም አለባቸው፡፡

16.2 የሚዘረጋዉ ተቋማዊ አደረጃጀት በሚመለከተው የዘርፉ የስራ ኃላፊ የደረቅ

ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎትን ለማቀድ እና ለደንበኞች ለማቀርብ

የሚያስቸል በቂ የሰዉ ኃይል እና በጀት ያለዉ መሆን አለበት፡፡

16.3 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የደረቅ ቆሻሻ ሥራውን በሃላፊነት

የሚመራ ቢያንስ አንድ ሰው ሊመድቡ ይገባል፡፡ ሀላፊነት የሚሰጠው ኦፌሰር

በድንጋጌ መሾም አለበት፡፡

16.4 በሜትሮፖሊስ፣ በሪጂዮፖሊስ እና በፈርጅ 1 ውስጥ የሚገኙ ከተሞች የደረቅ

ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ እቅድ የማቀድ፣ ውል የመዋዋል፣ አስፈላጊውን

ክትትልና ድጋፍ የማድረግ፣ ከህዝብ የጎንዮሸ ትስስር መፍጠር እና ለከተማ፣

ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ስታንዳርዱ መተግበሩን ሪፖርት ማድረግ ኃላፊነት ያለዉ በቂ እና ብቁ

ሰራተኞች የተዋቀረ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዩኒት ሊኖራቸዉ

ይገባል፡

16.5 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት/የግል

ባለሃብቶች በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት ውጤታማ ተሳትፎ

እንዲያደርጉ በአግባቡ ስልጠና ያገኙ ተገቢነት ያላቸው ሰራተኞች

መቀጠራቸውን ማረጋገጥ አለባቸዉ፡፡

16.6 ስልጠናው በዚህ ባይወሰንም የሚከተለውን ማካተት አለበት፡- የደረቅ ቆሻሻ

አያያዝና አወጋገድ ፍላጎት እና አገልግሎት መለየት፣ ትክከለኛ የስራ ውል

ማዘጋጀት፣ የጨረታ ሰነዶች መገምገም፣ አሸናፊ ማሳወቅ/ ውል መስጠት እና

አገልግሎቱ በተፈለገዉ ደረጃ መቅረቡን መቆጣጠር የመሳሰሉትን ማካተት

አለበት፡፡

16.7 ቢቻል ስልጠናዎቹ በብሄራዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የሙያ

ስታንዳርድ መሰረት በኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ፣ ትምህርትና ስልጠና

ፕሮግራም መሰረት መሰጠት አለባቸው፡፡

Page 67: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 67 of 73

16.8 በእቅድና በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ የሥራ ዲዛይን ህብረተሰቡ

ተነሳሸነት እና ተሳትፎ እንዲኖረዉ የሚመለከታው አካላት ከህዝብ ጋር

መወያየት ይኖርባቸዋል፡፡

16.9 የሚመከታቸው የስራ ኃላፊዎች መጠይቆችን የቡድን ዉይይቶችን እንዲሁም

የሰፈር ኮሚቴዎች በመጠቀም የህብረተሱን አስተያየት መቀበል አለባቸው ፡፡

16.10 በተለይ አገልግሎቱ የሚቀርብበት ጊዜ፣ የመሰብሰቢያ ቦታ፣ የሚሰበሰበው የቆሻሻ ዓይነት፣ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያን በሚመለከቱ ውሳኔዎችን ህዝቡ እንዲያውቃቸዉ መደረግ አለበት ፡፡

16.11 በአገልግሎት አቅርቦት የሚያጋጥሙ ችግሮች በተመለከተ ህዝቡ ቅሬታውን

የሚያሰመዝግብበት የህዝብ ቅሬታ መቀበያ ስርዓት መፍጠርና መተግበር

ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ይጠበቃል፡፡

16.12 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች አዲስና የተሻሻለ የደረቅ ቆሻሻ

አያያዝና አወጋገድ ሥርዓት ለመተግበር በሚያቅዱበት ጊዜ በአገልግሎት

አሰጣጥ የግል ባለሃብቶች የሚሳትፉበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ ማስገባት

አለባቸው፡፡ ይህን የሚመለከቱ ስልጠናዎቸም በከተማ ልማት፣ ቤቶችና

ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መዘጋጀትና መስጠት ሲኖርባቸዉ ስታንዳርድ ውሎች

ደግም በአገር አቀፍ መመሪያው መሰረት በከተሞችና /በአከባቢ መስተዳድሮች

ለአከባቢው በሚስማማ ሁኔታ ማዘጋጀት አለባቸው ፡፡

16.13 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች አዲስ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ አገልግሎት በሚያቅዱበት ጊዜ ህጋዊ ሰውነት ሳይኖራቸው የመልሶ

ጥቅም ላይ የሚዉል ቆሻሻን በማሰባሰብ ስራ ላይ የተሰማሩ አካላትን ድርሻና

ወደፊት ሊያበረክቱ የሚችሉትን ጠቃሚ አስተዋጽኦ ከግምት በማስገባት

ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ተገቢ ግምት ሊሰጡት ይገባል፡፡

16.14 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች አዲስ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት በሚያቀርቡበት ጊዜ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ወይም ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅት በአገልግሎት አቅርቦት እና አገልግሎት ክትትል እንዲሁም ግብረመልስ የሚኖራቸው የወደፊት ተሳትፎና ሚና ተገቢ ግምት ሊሰጡት ይገባል፡፡

16.15 በሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የሚተገበር የግሉ ሴክተር እና ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት ሊያሳትፍ

Page 68: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 68 of 73

የሚችል ሞዴል ውል እና/ወይም ስምምነት በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሸን ሚኒስቴር ሊዘጋጅ ይገባል፡፡

16.16 የሚመለከታቸዉ ኃላፊዎች የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት አቅርቦት ዉል በሚዋዋሉበት ጊዜ ስምምነቱ ልዩ መሣሪያዎችን ግዢና ተገቢ አጠቃቀም የሚያበረታታ ተመጣጣኝ የቆይታ ጊዜ ሊኖረዉ ይገባል፡፡ ዉሉ ለዚህ አገልግሎት የሚገዙ ተሽከርካሪዎች የአገልግሎት ዘመን ቢያንስ 5 ዓመት መሆን እንዳለበት ያገናዘበ ሊሆን ይገባል፡፡

16.17 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ውል የገቡባቸዉን ክፍያዎች ሣያጓትቱ ለመክፈል ወይም አገልግሎት አቅራቢዎች የአግልግሎት ክፍያን በወቅቱ ከማይከፍሉ ቆሸሻ አመንጪዎች ክፍያዉን ከነቅጣቱ በመሰብሰብ ድርሻቸዉን ለመዉሰድ የሚስችል የአሰራር ስልት እና ብቃት ሊኖራቸዉ ይገባል፡፡

16.18 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ውል የተገባለት አገልግሎት በአግባቡ

መቅረቡን ለማረጋገጥ ጥብቅና ፍትሃዊ አካሄድን የተሞላ ክትትል ማድረግ

አለባቸዉ፡፡ ይህም መልካም አፈፃፀምን ለማረጋገጥ የሚጣሉ ቅጣቶችንም

ያጠቃልላል ፡፡

16.19 ከተሞችን በተለያዩ አገልግሎት ዞኖች በመከፋፈል ለእያንዳንዱ ዞን የራሱ

የአገልግሎት አቅርቦት ውል እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይሁንና

ማዘጋጃ ቤቱ ቢያንስ በእንዱ ዞን አገልግሎቱን በራሱ መዋቅር በማቅረብ

በዘርፉ ያለውን የሞያ ክህሎት ለማዳበር ብሎም በትግበራ ወቅት የሚያጋጥሙ

ችግሮችን ለመረዳት እና መፍትሔ ለመስጠት የሚስችለዉን ሁኔታ መፍጠር

አስፈላጊ ነዉ፡፡

17 ሥራ አመራር

ጤና እና ደህንነት

17.1 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሰራተኛውን ከህመም እና ከአደጋ

የመከላከል የሰብአዊነት የአሰሪነት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ይህን ኃላፊነት

ለመወጣትም የመገልገያ መሳሪያዎች ዲዛይን ተስማሚነትና አመቺነት፣ የግል

ደህንነት መጠበቅያ መሳሪያዎች መሟላት፣ መደበኛ የጤና ምርመራና የክትባት

አገለግሎት እንዲሁም የመጸዳጃ ቤት እና የመታጠቢያ ቦታዎች መሟላት

ትኩረት ሊሰጣቸዉ ይገባል፡፡

Page 69: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 69 of 73

17.2 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሁሉም የሚከሰቱ አደጋዎችና

ክስተቶች የሚመዘገቡበትና የሚያጣሩበት የሪፖርት ስርዓት መዘርጋት

አለባቸው ፡፡

17.3 አደጋና ጉዳቶችን ለመከላከል ቆሻሻ ሰብሳቢ ሰራተኞች ቆሻሻን ከትከሻቸዉ

በላይ በሆነ ከፍታ እንዲያነሱ ወይም እንዲሸከሙ መደረግ የለበትም፡፡

17.4 ቆሻሻን በመጫን እና በማጓጓዝ ወቅት ቆሻሻ ሰብሳቢ ሰራተኞች በቆሻሻ

ሰብሳቢዉ መኪና ዉስጥ በተጫነዉ ቆሻሻ ላይ መቆም የለባቸዉም፡፡

17.5 በቁጥጥር የተደገፉ የጤና አጠባበቅ እና የደህንነት ስልጠናዎችን በመስጠት

የቆሻሻ አሰባሰብ እና አወጋገድ ሰራተኞች በስራ ወቅት እና ከስራዉ ባህሪ ጋር

በተያያዘ ሊያጋጥሟቸዉ የሚችሉ አደጋዎችን እና መንስኤዎቻቸዉን እንዲሁም

አደጋዎቹን ሊከላከሉ ወይም ሊቀንሱ የሚችሉባቸዉን መንገዶች በአግባቡ

አንዲገነዘቡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

17.6 በሁሉም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሂደቶች በሁሉም የስራ ደረጃዎች

ሴቶችና ወንዶች በእኩል ደረጃ እድሎችን የማመቻቸት እና ተሳትፏቸውን

የማረጋገጥ ስራ ይሰራል፡፡ ከፖሊሲ ጀምሮ ስራዎችን እስከ መምራት፣

በፋይናንስ፣ በእቅድ፣ በትምህርትና ግንዛቤ፣ ከህብረተሰብ ጋር ተቀናጅቶ

መሥራት፣ የሰፈር ቆሻሻ አሰባሰብ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም

የህዝብ ቅሬታዎችን ማዳመጥ ላይ በእኩል ደረጃ የወንዶችና ሴቶች ተሳትፎ

መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

ስልጠና

በእጅ የሚሰሩ ሰራተኞች ስልጠና (Training of Mnaula Workers)

17.7 ሁሉም በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ ላይ ተሳትፎ የሚያደርጉ

ሰራተኞች አግባብ ያለዉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፕሮግራም የተከታተሉና

አስፈላጊውን ፈተና ማለፋቸዉን የሚያረጋገጥ ሰርትፊኬት ያገኙ መሆን

አለባቸው፡፡

Page 70: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 70 of 73

17.8 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥራ

የተሰማሩ የመንግስት ወይም በግል ሴክተር ተቀጥረው የሚሰሩ ሁሉም

ሠራተኞች ጊዚያዊ ሰራተኞችን ጨምሮ የቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አገልግሎት

አሰጣጥ ላይ በአግባቡ ስልጠና መውሰዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ ስልጠናው

የሚከተለዉን ሊያካትት ይገባል፡-

ሀ/ ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ ሂደት- ማንሳት ፣የአቧራ ብነት ወደ መተንፈሻ

አካልት አንዳይገባ መከላከል ፣መንገድ ማቋረጥ ፣ሃይድሮሊክ ማንሻ

ወይም የጭነት መሣሪያዎች አጠቃቀም፣ የደህንነትና መከላከያ ልብስ፣

አሽከርካሪዎች ቆሻሻ ሰብሳቢ/አጓጓዥ ተሽከርካሪዎችን በሚያዞሩበት

ወይም ወደኋላ በሚሄዱበት ጊዜ ድጋፍ እገዛ ማድረግ ወዘተ...

ለ/ የስራ ፖሊስዎች፡- ለምሳሌ መሰብሰብ ያለባቸዉ የቆሻሻ ዓይነቶች

ሐ/ የግል ንጽህና እና መሰረታዊ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ አሰጣጥ

መ/ ከህዝብ መገናኛት እና መነጋገር/የግንኙነት ክህሎት፣

17.9 በስልጠና ፕሮግራም ላይ የተሳተፉ ሰራተኞች ምን እንደሚያስታውሱና

እንደተገነዘቡ ለማወቅ የመመዘኛ ፈተና መዉሰድ አለባቸው፡፡ አብዛኞቹ

ማንበብ እና መጻፍ የማይችሉ ሊሆኑ ስለሚችሉ ትክክለኛዉን መልስ

አንዲመርጡ የሚጠይቅ በቪዲዮ ወይም በፎቶግራፍ የተደገፈ የመመዘኛ

ፈተና ሊቀርብላቸው ይገባል ፡፡

የአሸከርካሪዎች ስልጠና

17.10 አሽከርካሪዎች ከላይ ከተገለፀው ስልጠና በተጨማሪ የሚከተሉትን ስልጠናዎች

መውሰድ አለባቸው፡

ሀ/ በየቀኑ ተሸከርካሪውን መፈተሽ እና ችግር ወይም ብልሽት

ሲያጋጥም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ማስተማር

ለ/ በተሽከርካሪዉ ላይ ጉዳት እና መጎሳቆል በማያስከትል መልክ

የማሽከርከር ዘዴ

ሐ/ ደህንነቱ የተጠበቀ ወደኋላ የመንዳትና የማዞር ዘዴ

መ/ በእርጥበታማና ጥብቅ ባለሆነ መሬት ላይ ማሽከርከር (ወደ

ማስወገጃ ቦታ ቆሻሻ ለማድረስ)

Page 71: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 71 of 73

ሠ/ በአደጋ ጊዜ፣ ብልሽት ሲያጋጥም ወይም ጎማ ሲተነፍስ መወሰድ

ያለባቸዉ እርምጃዎች፣

ረ/ የመገናኛ መሳሪያዎች አጠቃቀም (በመኪናዉ ላይ ካሉ)፣፣

ሰ/ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ አሰጣጥ

17.11 አሽከርካሪዎች የቆሻሻ ሰብሳቢውን ቡድን የማስተባበርና የመምራት ኃላፊነት

ጭምር ከተሰጣቸው ስለ ራሳቸው እና ስለ ቡድኑ መብቶችና ግዴታዎች

እንዲሁም ስለ ሪፖርት አደራረግ ስልጠና ማግኘት አለባቸዉ፡፡

ለመካኒኮች፣ ኤሌክትሪሺያኖች እና ለባለሙያዎች የሚሰጥ ስልጠና

17.12 ለእነዚህ ባለሞያዎች በስራ ላይ የሚሰጥ ስልጠና አስፈላጊ ነዉ፡፡ በተጨማሪም

አዲስ መሳሪያዎች በፈበረኩ አምራቾች የሚሰጥ ስልጠና መሳሪያዉ

ለሚያስፈልጋቸውና ለሚጠቀሙበት ሰራተኞች መስጠት፡፡

ለአመራሮች፣ መሀንዲሶችና ቴክኒሽያኖች የሚሰጥ ስልጠና

17.13 ባደጉና እያደጉ ባሉ አገሮች መካከል ያለ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ

ስራ ብዙ ልዩነቶች ስላሉት ሰልጣኙንና የሚሰራበት ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ

ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል፡፡

17.14 ስልጠና በራስ መተማመንን የሚያጎለብት መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም

የሰልጣኙ እውቀት በአመራር፣ አሰራር፣ ጥገና እና ከፍተኛ አፈፃጸም

ማስመዝገብ የሚያስችል መሆን አለበት፡፡

ደህንነት

17.15 ሁሉም አሽከርካሪዎችና የጉልበት እንዲሁም ሰራተኞች በደህንነት ጉዳዮች

የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መሳተፍ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ስልጠናውን ተገቢ

ክትትል ሊደረግበት ይገባል፡፡

17.16 ስልጠናው ቆሻሻ ሰብሳቢ ሰራተኞች የሚያጋጥማቸው የተለያዩ አደጋዎችን

በመከላከል ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፡፡ሰራተኞች መንገድ ሲያቋርጡ

የሚያጋጥም የትራፊክ አደጋ፣ተሽከራካሪዎቸን በማዞር ወይም ወደኋላ በመንዳት

ወቅት የሚያጋጥሙ አደጋዎች እና በተሽከርካሪዎች ላይ በተገጠሙ

Page 72: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 72 of 73

ከሀይድሮሊክ መሣሪያዎች ጋር በተተያያዘ በሚያጋጥሙ አደጋዎች ላይ

ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

17.17 በመንገድ ጽዳት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች አንጸባራቂ ልብስና የጣት/የዉስጥ

እግር መከላከያ ያላቸዉ የደህንነት ጫማዎች ማድረግ አለባቸው፡፡

ክትትል

17.18 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሁሉም የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ተግባሮች የተሟላ ክትትል የሚደረግባቸዉ መሆኑንና ክትትል

የሚያደርጉ ሰራተኞችን የስራ ውጤታማነት የሚያግዙ አስፈላጊ ቁሳቁሶች

መሟላታቸዉን ማረጋገጥ አለባቸዉ፡፡ይህም የግንኙነት ቁሳቁስ ማለትም

ሞባይል ስልክ፣ ትራንስፖርት ለምሳሌ ሞተር እና ሞተር አልባ ሳይክል

ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ቅልጥፍና

17.19 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ሰራተኞቻቸው እና የስራ

ተቋራጮች/ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊ ማነቃቂያዎች በመጠቀም

አፈፃፃማቸው ቀልጣፋ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከነዚህ

መካከል የክትትልና ግብረ-መልስ ስርዓት ማስተዋወቅ፣ስራ ተቋራጮች/ጥቃቅንና

አነስተኛ ተቋማት መካከል ውድድር ማካሄድ፣ የአፈፃፀም ማጣቀሻ መከተልና

በመረጃ የተደገፉ አፈፃጸሞችን ለህትመት ማብቃት፣

የህዝብ ግንኙነት ስራዎች

17.20 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች ነዋሪዎችና ባለሱቆች በደረቅ ቆሻሻ

አያያዝና አወጋገድ ትግበራ ላይ እና ክትትልና ድጋፍ ላይ የሚሳተፉበት

ስርዓት መቀየስ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አጠገባቸው ያለ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ

ገንዳ እንዲቆጣጠሩና ችግር ሲኖርም ሪፖርት ማድረግ አንዱ ተሳትፎን

የማበረታታት መንገድ ነዉ፡፡

17.21 የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች መልካም ገጽታን ለመገንባት ጠንካራ

የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን መስራት አለባቸዉ፡፡ ሰራተኞቻቸው ከህዝብ ጋር

እንዴት መነጋገር እንዳለባቸው በማሰልጠን፣ እንዲሁም ሁልጊዜ ንጹህ የደንብ

ልብስ ለብሰዉ እንዲታዩ እና የሚጠቀሙባቸዉ ተሽከራካሪዎችም ጭምር ንጹህ

Page 73: 18/6/2007 - mudc.gov.et

የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አሰባሰብና አወጋገድ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድ

Page 73 of 73

ሆነዉ እንዲታዩ በማድረግ ህብረተሰቡ ስለ አገልገሎቱ መልካም አስተየየት

አንዲኖረዉ ማድረግ አለባቸዉ፡፡

17.22 ቅሬታዎች በፍጥነትና በውጤታማነት መፈታት አለባቸው፡፡ ይህንን ለማሳካት

የሚመለከታቸው የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች የህዝብ ቅሬታ የሚፈታበት ስርዓት

ማዘጋጀትና መፈጸም አለባቸው፡፡ ይህም በስልክ፣ በፅሁፍ ወይም በአካል

የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመመዝገብ እና የመለያ ቁጥር በመስጠት የቅሬታ

አፈታት ሂደቱን እና የተወሰደውን የመፍትሔ እርምጃ ለመከታተል ያስችላል፡፡

.............................................///..............................................

ይህ ስታዳርድ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚኒ ካቢኔ ከፀደቀበት ከየካቲት 18 ቀን 2007 ዓ/ም

ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

መኩሪያ ኃይሌ

የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር