ልሳነ ህዝብ -...

14
ሲገቡ አንዱን ተሸካይ አንዱን የበሰበሰ የሚል ስም በመስጠት ለዘመናት ሌበረከተላቸው አስተዋፅኦ ዜሮ በመስጠት በአካልም በመንፈስም ከጥቅም ውጭ ያደርጉታል። በዚሁ የተካነው መለስ ዜናዊ ነበር ጥቂት አሻንጉሊቶች በራሱ ምስል ቀርፆና ቦታ አስይዞ ሲያልፍ በልቡ ገና የሱ ልጅም ነገ ባንዳች መንገድ ወደ ስልጣን መጥታ አገሪቱን እንደአባቷ ወዳሻት መንገድ ትነዳታለች የሚል ህልም እንዳለመ ወደ መቃብር መውረዱ የታወቀ ነው። አሁንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ነቀርሳ የሆነው የወያኔ ዘረና አስተሳሰብ ከስሩ ተነቅሎ በህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ካልተተካ ግለሰቦች በራሳቸው ችግር እያፈነገጡና በቂ መቋቋሚያ እየተሰጣቸው ከወያኔ ስለወጡ መርዘኛው አስተሳሰብ ተሻሻለ ወይም ጸለወጸ ማለት አይደለም። እንደውም የጠገቡትን አስወግዶ የተራቡትን በማምጣት አገሪቱን ለከፋና ለረቀቀ ሙስና ያጋልጣታል። ስለዚህም የኢትዮጵያ ሀዝብ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንጂ በወያኔ አራዳነት ሊሸወድ አይገባም። አቋሙን በየጊዜው በመለዋወጥ የሚታወቀው ዓባይ ፀሃዬ ከወያኔ ቡድን ተሰናበተ ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ ወያኔ የሚፈልገውን ለመሾም የጠላውን ካካ የነካው እንጨት የሚያደርግበት አደገኛ መሳሪያው ግም ገማ ይባላል። በመጀመሪያ ግም ሆነ ያው ግም ነገር ደግሞ ሰሰለሚሸት ገማ የሚል ቅፅል ሰጡት። መሰረታዊ የአማርኛ ትርጉሙ ላማሳት ሳይሆን ረቂቅ በሆነ መንገድ ሂስ ግለ ሂስ የሚለውን መርክሰ ሌኒናዊ ሀረግን አሳጠርን ብለው ጥቂት ተንኮለኞች ግም ገማ በማለት ሃረጉን ወዳንድ ቃል አመጡት። የወያኔ ግም ገማ ከዚያ የባሰም አደገኛና የመሪዎቹ ሴረኛነትና ተበቃይነትን የሚያመለክት ነው። ቅንነት የሌላቸው ሰዎች በነፃነት ትግል ስም ጠመንጃ አንግተው አራት ኪሎ ከገቡ ነኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱ ሆድ እና ጀርባ አድርገው አንድነቱን ወደ እርስ በርሰ መጣራጠርና ጥላቻ እንዲለወጥ መርዘኛ ፖለቲካቸውን ረጭተውበታል። ታሪክ ነገ እያንዳንዱን በድሆች ደም የቀለደ ሁሉ ለፍርድ ባደባባይ ራቁታቸውን እንደሚያቀርባቸው የማይታለፍ ሃቅ ነው። አምባገነኖች የመጨረሻዋን የሽንፈት ፅዋ እስኪጎነጩ ድረስ ደህና ነን ብለው ሌሎችን ብቻ አይደለም የገዛ ራሳቸው ህሊናንም ለማታለል ወኔው ያላቸው ድፍን ሰዎች ናቸው። አምባገነኖች አሳፋሪ ስብእናቸው አንዱ የሌሎችነ አመለካከት ማንቋሸሽና ራሳቸውን እንደ ሊቀ ቃውንት የማሰቡ አባዜ ነው። ሰሞኑን እርጅናና ህመም አላላውስ እስኪላቸው ድረስ ባቅም ማነስ ምክንያት ጡረታ የወጡት መሪዎቻቸውን በመተካካት ቦታ ለቀቁ እያለ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀት ያመላከተ መግለጫ ሲሰጡ ማየት ያሳፍራል። ተካካት ከመቃብር ባሻገር አለመሆኑ መልካም ቢመስልም እነማንን ነው የተኩት? የነሱን ጥቅም የሚያስከብሩና ቡራኬያቸውን የሚቀበሉ የራሳቸው ፎቶ ኮፒዎች ወይስ ብቃት ያላቸው ተራ ዜጎች? የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዘናጋት ሲሉ የወጠኑት ይህ ተራ የሆነና የተለመዱ ማጥራት፣ መተካካት፣ ግም ገማ ወዘተ በሚሉ የማታለያ ቃላት የተለበጡ የወያኔ እርስ በርስ መበላላት ህዝቡ ከነሱ ቀድሞ ያውቃቸቃቸዋል። የትግሉ ሂደትም በነዚህ ተራ የማታለያ ቃላት ላፍታም ቢሆን ሊደናቀፍ አይችልም። ዓባይ ፀሃዬ መጣ ስብሃት ነጋ ወጣ የሚለወጥ ነገር የለም አምባገነን ስርዓቱ ነው አወቀ ዲንሳ /ለልሳነ ህዝብ/ አምባገነን ማንም ይምራው ማን አምባገነን ነው። ሰዳም ሁሴን በልጁ በኡዳይ ወይም በቋሳይ ቢተካ ኖር የበሰ ስርዓት እንጂ የተሻለ ሊመጣ እንደማይችል መተንበይ ቀላል ነበር። የሊቢያው መሪም እንደዚሁ። ወያኔም መለስ ቢሄድ በሌሎች አደገኛ መሪዎች ተተክቶ አፈናውንና ጭፍጨፋው ተጠናክሮ ቀጠለበት እንጂ የተለየ ለውጥ አልመጣም፡ እኛም አልጠበቅንም። መርዝ ከሚተፋ እባብ ጭንቅላት ላይ መርዝ እንጂ ሌላ መልካም ነገር ሊወጣ ስለማይችል ያ እባብ ሌሎችንም እየነደፈ ለአደጋ ሳያጋልጥ እራሱን ካልገደሉት የእባብን ጭንቅላት መርዝ እነዳያመነጭ አድርገን እናፀዳዋለን የሚለው የወያኔ ዓይነቱ ግምገማ እንኳንስ ከማህበራዊ ከተፈጥሮ ሳይንስም ጋር እጅግ የሚጣረስ የማይሆን አስተሳሰብ ነው። ዓባይ ፀሃዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ ዕቁባይ ወዘተ የዚሁ አምባገነንና ዘረኛ የሆነ አስተሳሰብ አራማጅ ቡድን አባላት / components/ እንጂ አስኳሎቹ አይደሉም። ወያኔዎች በጥቅምና በውስጣዊ ፍጭት ውስጥ ከነፀብራቅ መፅሄት የተወሰደ By Samuel Gebru Fantaye ለኃይለማርያም ደሳለኝ የተጻፈ ሽሙጥ ይህን ለሕዝብ ጆሮ ብሎ መጻፉ በራሱ ሰቅጣጭ ቢሆንም አንዳንዴ ስቆ ለማለፍም መጋራት ይበጃል እናም ለሳቸው እንዲህ ብ ዬ ብነግራቸው ጥሩ ነበር ያልኩትን ለናንተም አካፍላለሁ። አቶ ሐይለማርያም ሆይ ስለ እርስዎ ማፈራችን እስ ከመቼ ይቀጥላል? ገና መናገር ሲጀምሩ ስቅቅ ይለኛል። ተናግረው ሲያበቁ ሙሉ ሰው መሆንዎንም ማመን ያቅተኛል። እንዲያውም አሁን አሁንማ መለ ስ ጀምሮ በወጉ ያልጨረሰው አሻንጉሊት ይመስሉኛል። መለስ ኮርጀን ገልብጠን ቢል ያምርበታል መገልበጥም መኮረጅም ማስመሰልም ማድበስበስም የክብር የዶክትሬት ዲግሪ የሚያሰጠው ብልጥ ሰው ነው በቃ ሞላጫ አራዳ የሚሉት አይነት ነው። እርስዎ እግዜር ሲፈጥርዎ የሞኛ ሞኝ ገጽታ የየዋህ ሰው ቆዳ ይዘው የመገለባበጥ ችሎታው ሳይኖርዎት እንደልብ የሚዘግኑት የቃላት ቀረጢት ሳይዙ ጋዜጠኛ ፊት ቀርበው በማትረባ ጥያቄ ላብ ላብ ሲ ሎት ማየት እንዴት አሳዛኝ እንደሆነ ቢያውቁ ደግ ነፀብራቅ አንደኛ ዓመት ቁጥር 4 ጥር 19 www.netsebraqm.wordpress.com Netsebraq Magazine |First Year Vol. 4 19 ነበር። በሚናገሯቸው ቃላት የእውቀትዎ ልክ ብቻ ሳይሆን የማስተዋል ብቃትዎ የብልጠትዎ መጠን ፍንትው ብሎ ይታያል እናም ያ ሳፍራል። እውነቴን ነው የምሎት በጣም ያሳፍራሉ። እኚህ ሰው እንኳን የተ ማሩ በትምህርት ቤት በኩል ያለፉ አይመስልም እያሉ ሰዎች ቢያወሩስ እን ዴት ይፈረዳል? አረ ጥሩ አይደለም ለመሆኑ መልሰው ቃለመጠይቅዎን ሲመለከቱ ምን ይሰማዎታል? ምናልባት እኮ የቢቢሲን ጋዜጠኛ ልክ ልኩን ነገር ኩት ይሉ ይሆናል ቂ ቂ ቂ … የቂል ነገር። እውነቴን ነው የምሎት እርስዎ ድንገተኛ መገጣጠም ካልሆነ በቀር ፖለቲካ በደረሰበት ሊደርሱ አይገባም ነበር። “አህያም ቢሆ ን በኔ ያመነ ኢሕአድግ ይሆናል” እንዳለው ጌታመለስ እርስዎም እንደዚያ ሆነው ጠቅላይ ሆኑና የውርደት ቀንዎ መሽቶ በነጋ ቁጥር መሳቀቃችን በዛ። ታድያ ከመለስ መማር ሲገባዎ የብልጦቹ ብልጥ የመሰሪዎች መሰሪ ከሆነ ሰ ው ልኮርጅ ብለው እማይሆን ገደል ላይ ተንጠለጠሉብንና ተሳቅቀን አለቅን… አረ ለ እርስዎ በጣም አፈርን። “ብልጥ የእለቱን ብልህ የአመቱን” የሚል አባባል ባስኮርጅዎ አስበው መናገር ይጀምሩ ነበር … ወይ አለመተዋወቃች ን! አንዳርጋቸው በኤርትራ መሬት ሊገደል ‘አንገረብና ቄሱ’ ሲዶልቱ የርስዎን ይሁንታ የጠየቀ የለም። ተይዞ አዲስ አበባ ሲመጣ እርስዎ የሚያውቁት ነገር አልነበረም። የአንድ ጊቢ የጥበቃ ሰራተኛ ወጪና ገ ቢውን የማየት እድል አለው የቤት ሰራተኛ ደግሞ ጓዳ ጎድጓዳውን የማወቅ እድል አላት እርስዎ ከነዚህ ከአንዳቸው እንኳ ያነሱ ሰው መሆንዎን ለመ ገንዘብ ያለመቻልዎ ለምን? ለነገሩ ስሜትዎን ገድለው ሰብዕናዎን ሽጠው መዳን በመለስ ነው ብለየሚያድሩ ስለሆነ ግድ የሎትም። እኔ ግን ስለ እርስዎ ግድ ይለኛል። መዋረድ ይብቃዎ! መጫወቻስ መሆን ምን በወጣዎት ለየትኛው ዓለም? ከንግዲህ ይህ አለም ፍጹም ቤቴ አይደለም ብለው የዘመሩ ሰው አይደሉም እንዴ? ማን ያውቃል እሱም ከፈረንጆች የተኮረጀ መዝሙር ስለሆነ ይሆናል የዘመሩት። እውነት እውነት እሎታለሁ በኢየሱስ ስጋና ደም እንጂ በድሃ ደም ታጥበው ዘለዓለማዊ ህይወት አያገኙም። እኔ እንደሰማሁት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሕንድ ድረስ ዘልቀው ተምረዋል ኮሌጅ ውስጥም ሰርተዋልና ኩረጃ የሚያፍሩበት እንጂ የሚመጻደቁበት ነገር አይደለም። አሁንማ ሳስበው እነ ካራቱሪን ከሕንድ ያመጡትና ባለመሬት ያደረጉት የኮረጁበትን ውለታ ለመክፍል ይሆን እንዴ? ማለት ጀምሬአለሁ። ቃል በቃል ገልብጠን ወሰድን ብሎ መለስ ሲናገር ቦታ ይመርጣል። እነዚያ እሱ ፈገግ ሲል በሳቅ የሚፈርሱ ሲቆጣ የሚያለቅሱ የፓርላማ አባላት ፊት ስለተናገረው ትክክል የሆነ ይመስል ሲመጻደቁበት ፈረንጆቹ ራሳቸው “ ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ የወያኔ ሹም ሽር ጥገናዊ ለውጥ ነው። መለስ ሰርቶ ያልጨረሰው አሻንጉሊት ልሳነ ህዝብ ድምፅ ለተነፈጉት የቆመ ልሳን መስከረም 2/2015 ቅፅ 2 ቁጥር 13 በዚህ ዕትም 1. የወያኔ ሹም ሽር 2. ስርአቱ አምባገነን ነው 3. ርዕዮተ ዓለም 4. ከታሪክ ማህደር 5. ዜና 6. መጣጥፎች ስብሐት ነጋ ይባላል። ከወያኔ መስራቾች አንዱ ሲሆን በባህሪው ደፋርና ለሌሎች ክብር ምንም ስሜት የሌለው፣ ሰውን አፉን በከፈተ ቁጥር በጣም የሚያሳዝንና እራሱን የአዋቂዎች ቁንጮ አድርጎ የሚያይ ሰው ነው። በግሉ በየምሽቱ ሰክሮ ተደግፎ ቤቱ የሚገባና ለዓድዋ ሰዎች ብቻ የተለየ ጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ በአድሏዊ ባህሪው የታወቀ አደገኛ ሰው ነው። እሱ የመራው ትእምት የተባለ የወያኔ ድርጅት ለሙስናና ለከፍተኛ ኪሳራ ተጋልጧል። የመለስ ወዳጅና ደጋፊ ስለነበር ብቻ እስካሁን በማእከላዊ ኮሚቴነትና በተለያዩ ስልጣናት ቆይቷል። አሁን በቃው። ዓባይ ፀሐዬ ከወያኔ የመጀመሪያ ሰዎች አንዱ ነው። በጣም ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዕውቀት አላቸው ከሚባሉት የወያኔ ሰዎች አንዱ ነው። የማሌሊት ህገ ደንቦችን ከመለስ ዜናዊ በበለጠ እሱ እንዳረቀቃቸው ይነገራል። በባህሪው ወላዋይና ግልፅ አቋም /የጀርባ አጥንት/ የሌለው በመባል ይታወቃል። ወያኔ ለሁለት በተሰነጠቀበት ወቅት ከተቃዋሚዎች ጋር ስብሰባ ጥሶ ከወጣ በኋላ ወዲያውኑ መሸነፋቸውን እንዳወቀ ይቅርታ ጠይቆ ወደ ስልጣኑ ተመልሷል። እንደ አቦይ ስብሃት የሚታወቅበት ሙስናና ጎጠኝነት ባይኖረውም ወላዋይና አቋመ ቢስ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የማይበጅ ከነመለስ ዜናዊ ጋር በመሆን ከሻዕቢያ ጋር በመደራደር ያገራችንን መሬት አሳልፈው ከሰጡት አንዱ ነው። ከነኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተደረገው የትግራይ ትግርኚ ውል ከፈረሙት አንዱ ዓባይ ፀሃዬ ነው።

Upload: dobao

Post on 10-Mar-2019

228 views

Category:

Documents


1 download

TRANSCRIPT

ሲገቡ አንዱን ተሸካይ አንዱን የበሰበሰ የሚል ስም በመስጠት ለዘመናት ሌበረከተላቸው አስተዋፅኦ ዜሮ በመስጠት በአካልም በመንፈስም ከጥቅም ውጭ ያደርጉታል። በዚሁ የተካነው መለስ ዜናዊ ነበር ጥቂት አሻንጉሊቶች በራሱ ምስል ቀርፆና ቦታ አስይዞ ሲያልፍ በልቡ ገና የሱ ልጅም ነገ ባንዳች መንገድ ወደ ስልጣን መጥታ አገሪቱን እንደአባቷ ወዳሻት መንገድ ትነዳታለች የሚል ህልም እንዳለመ ወደ መቃብር መውረዱ የታወቀ ነው። አሁንም ለኢትዮጵያ ህዝብ ነቀርሳ የሆነው የወያኔ ዘረና አስተሳሰብ ከስሩ ተነቅሎ በህዝባዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ካልተተካ ግለሰቦች በራሳቸው ችግር እያፈነገጡና በቂ መቋቋሚያ እየተሰጣቸው ከወያኔ ስለወጡ መርዘኛው አስተሳሰብ ተሻሻለ ወይም ጸለወጸ ማለት አይደለም። እንደውም የጠገቡትን አስወግዶ የተራቡትን በማምጣት አገሪቱን ለከፋና ለረቀቀ ሙስና ያጋልጣታል። ስለዚህም የኢትዮጵያ ሀዝብ ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል እንጂ በወያኔ አራዳነት ሊሸወድ አይገባም።

አቋሙን በየጊዜው በመለዋወጥ የሚታወቀው ዓባይ ፀሃዬ ከወያኔ ቡድን ተሰናበተ

ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ ወያኔ የሚፈልገውን ለመሾም የጠላውን ካካ የነካው እንጨት የሚያደርግበት አደገኛ መሳሪያው ግም ገማ ይባላል። በመጀመሪያ ግም ሆነ ያው ግም ነገር ደግሞ ሰሰለሚሸት ገማ የሚል ቅፅል ሰጡት። መሰረታዊ የአማርኛ ትርጉሙ ላማሳት ሳይሆን ረቂቅ በሆነ መንገድ ሂስ ግለ ሂስ የሚለውን መርክሰ ሌኒናዊ ሀረግን አሳጠርን ብለው ጥቂት ተንኮለኞች ግም ገማ በማለት ሃረጉን ወዳንድ ቃል አመጡት። የወያኔ ግም ገማ ከዚያ የባሰም አደገኛና የመሪዎቹ ሴረኛነትና ተበቃይነትን የሚያመለክት ነው። ቅንነት የሌላቸው ሰዎች በነፃነት ትግል ስም ጠመንጃ አንግተው አራት ኪሎ ከገቡ ነኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ እርስ በርሱ ሆድ እና ጀርባ አድርገው አንድነቱን ወደ እርስ በርሰ መጣራጠርና ጥላቻ እንዲለወጥ መርዘኛ ፖለቲካቸውን ረጭተውበታል። ታሪክ ነገ እያንዳንዱን በድሆች ደም የቀለደ ሁሉ ለፍርድ ባደባባይ ራቁታቸውን እንደሚያቀርባቸው የማይታለፍ ሃቅ ነው። አምባገነኖች የመጨረሻዋን የሽንፈት ፅዋ እስኪጎነጩ ድረስ ደህና ነን ብለው ሌሎችን ብቻ አይደለም የገዛ ራሳቸው ህሊናንም ለማታለል ወኔው ያላቸው ድፍን ሰዎች ናቸው። አምባገነኖች አሳፋሪ ስብእናቸው አንዱ የሌሎችነ አመለካከት ማንቋሸሽና ራሳቸውን እንደ ሊቀ ቃውንት የማሰቡ አባዜ ነው። ሰሞኑን እርጅናና ህመም አላላውስ እስኪላቸው ድረስ ባቅም ማነስ ምክንያት ጡረታ የወጡት መሪዎቻቸውን በመተካካት ቦታ ለቀቁ እያለ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀት ያመላከተ መግለጫ ሲሰጡ ማየት ያሳፍራል። ተካካት ከመቃብር ባሻገር አለመሆኑ መልካም ቢመስልም እነማንን ነው የተኩት? የነሱን ጥቅም የሚያስከብሩና ቡራኬያቸውን የሚቀበሉ የራሳቸው ፎቶ ኮፒዎች ወይስ ብቃት ያላቸው ተራ ዜጎች? የኢትዮጵያን ህዝብ ለማዘናጋት ሲሉ

የወጠኑት ይህ ተራ የሆነና የተለመዱ ማጥራት፣ መተካካት፣ ግም ገማ ወዘተ በሚሉ የማታለያ ቃላት የተለበጡ የወያኔ እርስ በርስ መበላላት ህዝቡ ከነሱ ቀድሞ ያውቃቸቃቸዋል። የትግሉ ሂደትም በነዚህ ተራ የማታለያ ቃላት ላፍታም ቢሆን ሊደናቀፍ አይችልም።

ዓባይ ፀሃዬ መጣ ስብሃት ነጋ ወጣ የሚለወጥ ነገር የለም አምባገነን ስርዓቱ ነው አወቀ ዲንሳ /ለልሳነ ህዝብ/ አምባገነን ማንም ይምራው ማን አምባገነን ነው። ሰዳም ሁሴን በልጁ በኡዳይ ወይም በቋሳይ ቢተካ ኖር የበሰ ስርዓት እንጂ የተሻለ ሊመጣ እንደማይችል መተንበይ ቀላል ነበር። የሊቢያው መሪም እንደዚሁ። ወያኔም መለስ ቢሄድ በሌሎች አደገኛ መሪዎች ተተክቶ አፈናውንና ጭፍጨፋው ተጠናክሮ ቀጠለበት እንጂ የተለየ ለውጥ አልመጣም፡ እኛም አልጠበቅንም። መርዝ ከሚተፋ እባብ ጭንቅላት ላይ መርዝ እንጂ ሌላ መልካም ነገር ሊወጣ ስለማይችል ያ እባብ ሌሎችንም እየነደፈ ለአደጋ ሳያጋልጥ እራሱን ካልገደሉት የእባብን ጭንቅላት መርዝ እነዳያመነጭ አድርገን እናፀዳዋለን የሚለው የወያኔ ዓይነቱ ግምገማ እንኳንስ ከማህበራዊ ከተፈጥሮ ሳይንስም ጋር እጅግ የሚጣረስ የማይሆን አስተሳሰብ ነው። ዓባይ ፀሃዬ፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ ዕቁባይ ወዘተ የዚሁ አምባገነንና ዘረኛ የሆነ አስተሳሰብ አራማጅ ቡድን አባላት /components/ እንጂ አስኳሎቹ አይደሉም። ወያኔዎች በጥቅምና በውስጣዊ ፍጭት ውስጥ

ከነፀብራቅ መፅሄት የተወሰደ By Samuel Gebru Fantaye ለኃይለማርያም ደሳለኝ የተጻፈ ሽሙጥ ይህን

ለሕዝብ ጆሮ ብሎ መጻፉ በራሱ ሰቅጣጭ

ቢሆንም አንዳንዴ ስቆ ለማለፍም መጋራት

ይበጃል እናም ለሳቸው እንዲህ ብ ዬ ብነግራቸው

ጥሩ ነበር ያልኩትን ለናንተም አካፍላለሁ። አቶ

ሐይለማርያም ሆይ ስለ እርስዎ ማፈራችን እስ

ከመቼ ይቀጥላል? ገና መናገር ሲጀምሩ ስቅቅ

ይለኛል። ተናግረው ሲያበቁ ሙሉ ሰው

መሆንዎንም ማመን ያቅተኛል። እንዲያውም

አሁን አሁንማ መለ ስ ጀምሮ በወጉ ያልጨረሰው

አሻንጉሊት ይመስሉኛል። መለስ ኮርጀን ገልብጠን

ቢል ያምርበታል መገልበጥም መኮረጅም

ማስመሰልም ማድበስበስም የክብር የዶክትሬት

ዲግሪ የሚያሰጠው ብልጥ ሰው ነው በቃ ሞላጫ

አራዳ የሚሉት አይነት ነው። እርስዎ እግዜር

ሲፈጥርዎ የሞኛ ሞኝ ገጽታ የየዋህ ሰው ቆዳ

ይዘው የመገለባበጥ ችሎታው ሳይኖርዎት

እንደልብ የሚዘግኑት የቃላት ቀረጢት ሳይዙ

ጋዜጠኛ ፊት ቀርበው በማትረባ ጥያቄ ላብ ላብ

ሲ ሎት ማየት እንዴት አሳዛኝ እንደሆነ ቢያውቁ

ደግ ነፀብራቅ አንደኛ ዓመት ቁጥር 4 ጥር 19

www.netsebraqm.wordpress.com

Netsebraq Magazine |First Year Vol. 4

19 ነበር። በሚናገሯቸው ቃላት የእውቀትዎ ልክ

ብቻ ሳይሆን የማስተዋል ብቃትዎ የብልጠትዎ

መጠን ፍንትው ብሎ ይታያል እናም ያ ሳፍራል።

እውነቴን ነው የምሎት በጣም ያሳፍራሉ። እኚህ

ሰው እንኳን የተ ማሩ በትምህርት ቤት በኩል

ያለፉ አይመስልም እያሉ ሰዎች ቢያወሩስ እን

ዴት ይፈረዳል? አረ ጥሩ አይደለም ለመሆኑ

መልሰው ቃለመጠይቅዎን ሲመለከቱ ምን

ይሰማዎታል? ምናልባት እኮ የቢቢሲን ጋዜጠኛ

ልክ ልኩን ነገር ኩት ይሉ ይሆናል ቂ ቂ ቂ …

የቂል ነገር። እውነቴን ነው የምሎት እርስዎ

ድንገተኛ መገጣጠም ካልሆነ በቀር ፖለቲካ

በደረሰበት ሊደርሱ አይገባም ነበር። “አህያም

ቢሆ ን በኔ ያመነ ኢሕአድግ ይሆናል” እንዳለው

ጌታመለስ እርስዎም እንደዚያ ሆነው ጠቅላይ

ሆኑና የውርደት ቀንዎ መሽቶ በነጋ ቁጥር

መሳቀቃችን በዛ። ታድያ ከመለስ መማር ሲገባዎ

የብልጦቹ ብልጥ የመሰሪዎች መሰሪ ከሆነ ሰ ው

ልኮርጅ ብለው እማይሆን ገደል ላይ

ተንጠለጠሉብንና ተሳቅቀን አለቅን… አረ ለ

እርስዎ በጣም አፈርን። “ብልጥ የእለቱን ብልህ

የአመቱን” የሚል አባባል ባስኮርጅዎ አስበው

መናገር ይጀምሩ ነበር … ወይ አለመተዋወቃች ን!

አንዳርጋቸው በኤርትራ መሬት ሊገደል

‘አንገረብና ቄሱ’ ሲዶልቱ የርስዎን ይሁንታ

የጠየቀ የለም። ተይዞ አዲስ አበባ ሲመጣ እርስዎ

የሚያውቁት ነገር አልነበረም። የአንድ ጊቢ

የጥበቃ ሰራተኛ ወጪና ገ ቢውን የማየት እድል

አለው የቤት ሰራተኛ ደግሞ ጓዳ ጎድጓዳውን

የማወቅ እድል አላት እርስዎ ከነዚህ ከአንዳቸው

እንኳ ያነሱ ሰው መሆንዎን ለመ ገንዘብ

ያለመቻልዎ ለምን? ለነገሩ ስሜትዎን ገድለው

ሰብዕናዎን ሽጠው መዳን በመለስ ነው

ብለየሚያድሩ ስለሆነ ግድ የሎትም። እኔ ግን ስለ

እርስዎ ግድ ይለኛል። መዋረድ ይብቃዎ!

መጫወቻስ መሆን ምን በወጣዎት ለየትኛው

ዓለም? ከንግዲህ ይህ አለም ፍጹም ቤቴ አይደለም

ብለው የዘመሩ ሰው አይደሉም እንዴ? ማን

ያውቃል እሱም ከፈረንጆች የተኮረጀ መዝሙር

ስለሆነ ይሆናል የዘመሩት። እውነት እውነት

እሎታለሁ በኢየሱስ ስጋና ደም እንጂ በድሃ ደም

ታጥበው ዘለዓለማዊ ህይወት አያገኙም። እኔ

እንደሰማሁት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሕንድ ድረስ

ዘልቀው ተምረዋል ኮሌጅ ውስጥም ሰርተዋልና

ኩረጃ የሚያፍሩበት እንጂ የሚመጻደቁበት ነገር

አይደለም። አሁንማ ሳስበው እነ ካራቱሪን ከሕንድ

ያመጡትና ባለመሬት ያደረጉት የኮረጁበትን

ውለታ ለመክፍል ይሆን እንዴ? ማለት

ጀምሬአለሁ። ቃል በቃል ገልብጠን ወሰድን ብሎ

መለስ ሲናገር ቦታ ይመርጣል። እነዚያ እሱ ፈገግ

ሲል በሳቅ የሚፈርሱ ሲቆጣ የሚያለቅሱ የፓርላማ

አባላት ፊት ስለተናገረው ትክክል የሆነ ይመስል

ሲመጻደቁበት ፈረንጆቹ ራሳቸው “

ቀጣዩን በገፅ 2 ይመልከቱ

የወያኔ ሹም ሽር ጥገናዊ ለውጥ ነው።

መለስ ሰርቶ ያልጨረሰው አሻንጉሊት

ልሳነ ህዝብ ድምፅ ለተነፈጉት የቆመ ልሳን

መ ስ ከ ረ ም 2 / 2 0 1 5 ቅ ፅ 2 ቁ ጥ ር 1 3

በዚህ ዕትም

1. የወያኔ ሹም ሽር 2. ስርአቱ አምባገነን ነው 3. ርዕዮተ ዓለም 4. ከታሪክ ማህደር 5. ዜና 6. መጣጥፎች

ስብሐት ነጋ ይባላል። ከወያኔ መስራቾች አንዱ ሲሆን በባህሪው ደፋርና ለሌሎች ክብር ምንም ስሜት የሌለው፣ ሰውን አፉን በከፈተ ቁጥር በጣም የሚያሳዝንና እራሱን የአዋቂዎች ቁንጮ አድርጎ የሚያይ ሰው ነው። በግሉ በየምሽቱ ሰክሮ ተደግፎ ቤቱ የሚገባና ለዓድዋ ሰዎች ብቻ የተለየ ጥቅም እንዲያገኙ በማድረግ በአድሏዊ ባህሪው የታወቀ አደገኛ ሰው ነው። እሱ የመራው ትእምት የተባለ የወያኔ ድርጅት ለሙስናና ለከፍተኛ ኪሳራ ተጋልጧል። የመለስ ወዳጅና ደጋፊ ስለነበር ብቻ እስካሁን በማእከላዊ ኮሚቴነትና በተለያዩ ስልጣናት ቆይቷል። አሁን በቃው።

ዓባይ ፀሐዬ ከወያኔ የመጀመሪያ ሰዎች አንዱ ነው። በጣም ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዕውቀት አላቸው ከሚባሉት የወያኔ ሰዎች አንዱ ነው። የማሌሊት ህገ ደንቦችን ከመለስ ዜናዊ በበለጠ እሱ እንዳረቀቃቸው ይነገራል። በባህሪው ወላዋይና ግልፅ አቋም /የጀርባ አጥንት/ የሌለው በመባል ይታወቃል። ወያኔ ለሁለት በተሰነጠቀበት ወቅት ከተቃዋሚዎች ጋር ስብሰባ ጥሶ ከወጣ በኋላ ወዲያውኑ መሸነፋቸውን እንዳወቀ ይቅርታ ጠይቆ ወደ ስልጣኑ ተመልሷል። እንደ አቦይ ስብሃት የሚታወቅበት ሙስናና ጎጠኝነት ባይኖረውም ወላዋይና አቋመ ቢስ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የማይበጅ ከነመለስ ዜናዊ ጋር በመሆን ከሻዕቢያ ጋር በመደራደር ያገራችንን መሬት አሳልፈው ከሰጡት አንዱ ነው። ከነኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የተደረገው የትግራይ ትግርኚ ውል ከፈረሙት አንዱ ዓባይ ፀሃዬ ነው።

“To catch the reader's attention, place an

interesting sentence or quote from the story

here.”

መለስ ሰርቶ ... ከገፅ ፩ የዞረ

“This guy must be dumb” እንደሚሉ እርግጠኛ ነኝ። የቢቢሲን ጋዜጠኛ አንተንም ቢሆን ዋጋህን እሰጥሃለሁ ብለው ሲናገሩ ከፊትዎ የሚያዩት ጋዜጠኛ ያ የሚፈሩት ኦባንግ ነው ብለው የጠረጠሩ ይመስላል። ሀኪሙም ከህክምና ስራው ውጪ ፖለቲካ ከነካ አልቀውም ሲሉ እርስዎ ማህበራዊ

ሳይንስ (አስተዳደር፣ ፖለቲካል ሳይንስ ወይም ሕግ)

ተምረው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑ ይመስላል። ከደናቁርት ጋር ውለው ደነቆሩ እንዳልል ከዚህ የተለየ ሰው መሆንዎን አስረጂ አላገኘሁም። እንደ ማነጻጸርያ የፀረ ሽብር አዋጅ ሃሳቡን ከእንግሊዝ ተውሰን ከሀገራችን ሀኔታ ጋር አገናዝበን ይህንን አደረግን ቢሉ ትንሽ አለ አይደለም ግርማ ሞገስ የሚባል ነገር እሱን ጨመር ያደርግሎት ነበር። ፈረንጆቹን ስለፈራን እነሱ ያሉትን ብቻ ተጠቀምን ሲሉ ዝቅ ያደርጎታል። እንዴት ሆኖ ነው የእንግሊዙን ስለገለበጡ ትክክል ነን ሊሉ

የሚችሉት? የእንግሊዝ ስለገለበጡ አፈፃጸሙ

አተረጓጎሙ አተገባበሩ ሁሉ ትክክል ይሆናል

ያለውስ ማን ነው? ይህ አባባልዎ እርስዎን

ያለውድድር ከቂልነት ወደ ጅልነት የሚወስድ የአገላለጽ ስልት ነው። መለስ ይህን ሰምቶ ሊተርቦት ቢፈልግ ሊል የሚችለውን ሳስብ ሳቄ ይመጣል።

ነፀብራቅ አንደኛ ዓመት ቁጥር 4 ጥር 19

www.netsebraqm.wordpress.com Net-

sebraq Magazine |First Year Vol. 4 20

ከአማርኛ ተረት ኮርጆ “ሲሉ ሰምታ ዶሮ በገመድ

ታንቃ ሞተች” ይሎት ነበር መድረክ ላይ።

የሌላውንማ እንዴት ብዬ እፅፈዋለሁ። እኔ ግን በኩረጃ ስለማላምን አዲስ ተረትና ምሳሌ ፈጥሬ

“እንደ መለስ በሞከረ ምላሱ ተሳሰረ” እላለሁ። ሕገመንግስቱ ከካናዳ ተኮርጆ፣ የፀረ ሽብር አዋጁ ከእንግሊዝ ቃል በቃል ተገልብጦ እርስዎ ራስዎ

ከመለስ ተኮርጀው እንዴት ይዘልቁታል? ለምን

የተደላደለ ኑሮን ደግሞ ከአንዱ የበለጸገ ሀገር የማትኮርጁልን ቂ ቂ ቂ በእርስዎ የቂል መልስ የፈጣሪዎን የመለስን አጭበርባሪነት እያጋለጡ ነውና የወያኔ ሰይፍ እንዳይከትፍዎ በጣም እፈራለሁ። ጌታ

(የርስዎን ጌታ ባላውቅም) ብቻ ጌታ ይጠብቅዎ። ብዬ ምክሬን እጨርስ ነበር።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ኤክስፐርት በካናዳ የፖለተቲካ ጥገኝነት ጠየቁ ሪፖርተራችን በቶሮንቶ ከተማ ሊያገኛቸው ያደረገው ሙከራ አልተሳካም ከልሳነ ሀዝብ ዘጋቢ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የሴቶች ዴስክ ኤክስፐርት ወ/ሮ ማለፊያ ገሰሰ ለስራ ጉዳይ በተጓዙበት ካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነት ማመልከቻ ማቅረባቸው ከቶሮንቶ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል። ወ/ሮ ማለፊያ በእግር ኳስ ፌደሬሽኙ ያለውን ሙስና አጥብቀው ይቃወሙ እንደነበርና አንዳንድ ጊዜም በጋዜጠኞች ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ያልተለባበሰ መልስ በመስጠት ይታወቃሉ። ወ/ሮ ማለፊያ በአዲስ አበባ ከተማ የየካ ክፍለ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ አባል እንደነበሩና የሰማያዊ ፓርቲ ዓላማን በማሰራጨት በኩል ከፍተኛ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበርና ለአጭር ጊዜም ታስረው እንደነበር ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ወ/ሮ ማለፊያ ገሰሰ በካናዳ ያቀረቡት የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ከስራ ቦታቸው ጋር በተገናኘ ይሁን ከሰማያዊ ፓርቲ አባልነታቸው ጋር የታወቀ ነገር የለም። የሰሜን አሜሪካው ዘጋቢያችን ሰሞኑን

ቶሮንቶ ካናዳ ለስራ በተጓዘበት ወቅት ሊገኛቸው ያደረገው ጥረት አልተሳካለትም። በቀጣይ ወ/ሮ ማለፊያን ካገኘናቸው ቃለ ምልልሳቸውን ይዘን እንደምንቀርብ ቃል እንገባለን።

ወጣቱ ከባለቤቱ ጋር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠየቀ ፍየል ወዲያ ሄደ ቅዝምዝም ወደዛ በዱላ ተዳኘ ፍቅር እንደ ዋዛ ፍየሏም አትሞትም ቅዝምዝሙም ያልፋል በትግስት ላሰበ ሆድ ካገር ይሰፋል ቀን ቢረዝምም እንኳ ፍትህ ይበየናል በኛ መስዋእትነት ነገ ጥሩ ይሆናል በየሸንተረሩ ፍቅር ይዘፈናል የተተነበየው ያ ኢንተርናሲዮናል። በማለት ይህችን ጠሊቅ መልእክት ያላት ግጥም የፃፈው የአዲስ አበባው አዛርያ ለማ የዛሬ 3 ዓመት በፑሽኪን አደራሽ ካቀረባት በኋላ የተቸረው ሙገሳና ምስጋና ብዙም አላስደሰተውምም አላስገረመውምም። እንደሱ አገላለፅ በድንገት የሚመጡለት አጫጭር ግጥሞች ከመፃፍ በስተቀር እራሱን በማንኛውም ጊዜ እንደ ገጣሚ እንደማያይ ሲናገር ታዳሚው በሙሉ የበለጠ እንዲወደው ምክንያት ነበር። ያኔ አንዳንዴ ጠብ አጫሪ ሰዎች ምን ለማለት እንደፈለገ አብራራልን ሲሉት ዓላማቸው የገባው ይመስል “የግጥም ትርጉም እንደየአንባቢው አረዳድ ስለሚለያይ ለናንተ በገባችሁ መንገድ መረዳት እንጂ ለግጥም ትርጓሜ መስጠት በራሱ ኪነጥበባዊ ዋጋውን ያሳንሰዋል። የግጥም ውበቱ አንዱ እኮ ምን ማለት ነው ብሎ ማሰብ ነው ብሎ ነበር”። ይህ ኢትዮጵያዊ ወጣት የሰማያዊ ፓርቲ አባል ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ እንቅስቃሴ ያደርግ እንደነበርም ይታወቃል። ከምርጫው ጋር በተያያዘም በፖሊስ ታስሮና ተሰቀይቶ ከተፈታ በኋላ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የበረራ አስተናጋጅ ከነበረችው ባለቤቱ ጋር ካገር መጥፋቱን ሰምተን ስናፈላልገው በቶሮንቶ ካናዳ አግኝተነው ከሰሜን አሜሪካ ዘጋቢያችን ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡ የአዛርያ ለማ ቃለ ምልልስ በቀጣይ እትማችን ይዘን እንቀርባለን። በተመሳሳይ ዜና የአዲካ ኤቨንትስና ፕሮሞሽን ኩባንያ ባለ አክሲዮንና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ ዘለቀ ከነቤተሰባቸው በካናዳ የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቃቸው ከታማኝ ምንጮቻችን የደረሰን ዘረባ ያስረዳል። አቶ አሸናፊ ዘለቀ ባገራችን ስመ ገናና ከሆኑ ፕሮሞተሮች አንዱ መሆናቸው ይታወቃል። ቀደም ሲል የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በማካሄድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ታዳሚ ያስተናገዱ ሲሆን ቴዲ ጃ ያስተሰርያል የሚለውና አስራ ሰባት ርፌ የሚባለው ዘፈን በመድረኩ በመጫወቱ አቶ አሸናፊ ከመንግስት ሰዎች ጋር መቃቃር ላይ ደርሰው እስከ መታሰር የሄደ ቅጣት እንደደረሳቸው ይታወቃል። በቅርቡም በሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ፕሮሞሽን ላይ በመሳተፋቸው ታስረው በዋስ እንደተፈቱ የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ። አቶ አሸናፊ ለምን የፖለቲካ ጥገኝነት እንደጠየቁ ያገኘነው መረጃ የለም። ስለሳቸው የሚያውቅ ካለ በ [email protected] ቢፅፍልን ምስጋናችን የላቀ ነው።

ቀልዶች አንደኛው ውሸታም፤

“የኔ አባት በርሻው ቦታ ላይ አውሮፕላን

የሚያህል ጥቅል

ጐመን አምርቶ አንደኛ ወጣ፡፡

ሁለተኛው ውሸታም፤

“የኔም አባትኮ በጋራዣችን ውስጥ ትልቅ አፍሪካን

የሚያህል

ብረት ድስት አምርቶ ተሸለመ፡፡”

አንደኛው ውሸታም፤

“እንዴት! አፍሪካን የሚያህል ብረት ድስት ምን

ያደርግላቸዋል?

ብሎ ጠየቀው፡፡

ሁለተኛው ውሸታም፤

“ታዲያ! ያንተ አባት ጥቅል ጐመን በምን

ይቀቀላል ሲል

መለሰለት፡፡”

እሷ: ስንጋባ ጫት መቃምህን ታቆማለህ. እሱ: እሺ እሷ: ሲጋራም ማጨስ አትችልም እሱ: እሺ እሷ: የሰካራም ሚስት እንድባልም አልፈልግም ስለዚህ መጠጥም ማቆም አለብህ እሱ: እሺ እሷ: ኧ!!! ...ሌላ ደሞ ምን ነበር?? አዎ! እያመሸህ መግባት አትችልም እሱ: እሺ እሷ: እም...ሌላ? ሌላ? ምንድነው የረሳሁት??? ሌላ የምትተወው ነገር ምን ነበር??? እሱ: አንቺን ማግባት ሚስት አምሽታ ወደቤት እየገባች ነው ... ወድያው የመኝታ ቤቷን ከፍታ ስትገባ አልጋዋ ላይ ሁለት የተኙ ሰዎችን ትመለከታለች፤ አራት እግሮች ከብርድ ልብሱ ስር ወተው ይታያሉ ከዝያም ወድያውኑ አጠገቧ ያለውን ዱላ አንስታ ከብርድ ልብሱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱን ሰዎች ባላት ኃይል መደብደብ ትጀምራለች ..ወድያው መደብደቡን ታቆምና ወደ ሳሎን ቤት ስትሄድ ባሏ ሶፋ ላይ ቁጭ ብሎ ጋዜጣ ያነብ ነበር ከዝያም ባልየው " hi darling...ቤተሰቦችሽ መተዋሉ የኛ መኝታ ቤት ተኝተዋል ሰላም አልሻቸው ..? ሲላት ሚስት በድንጋጤ እራሷን ስታ ወደቀች :: "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉ" Love In A Digital Age ጎግዬ አስጎግዬ ያን ሰሞን ያጣኋት አወይ አጋጣሚ CHAT ላይ አገኘኋት

ADD ያረኳትን ልጅ አምናና ካቻምና አየኋት FACEBOOK ላይ ያቻትና ያቻትና ONLINE አየናት ሲሉኝ ትላንትና FACEBOOK LOGIN ብዬ አጣኋት ሄድኩና አገኛት እንደሆን TWITTER ላይ ሄድኩኝ አይኔ እንደናፈቃት ሳላያት አደርኩኝ YOUTUBE ገብቼ SEARCH አድርጌ አጣኋት TODAY እንደ ድንገት FACEBOOK ላይ አየኋት ጎግዬ አስጎግዬ ዛሬ አጊንቻታለሁ CHAT አድርጊው በሏት እኔ እሻላታለሁ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 2

የህዝብ ቁጣ

የሰሞኑ ምርጥ ካርቱኖች

ከታሪክ ማህደር "ሻቢያ" ታሪካዊ ጠላት ወይስ ወቅቱ ግድ የሚለው(ስልታዊ)ወዳጅ ? ሻቢያ እባብ ሊሆን ይችላል ! አዋቂዎች ግን “ከእባብ መርዝ” መድሃኒት ይሠራሉ! ( አክሊሉ ስዩም አውስትራሊያ) ለዚህ ጽሁፌ "ርዕስ" እንዲሆን የመረጥኩት ሻቢያ ታሪካዊ ጠላት ወይስ ወቅቱ ግድ የሚለው(ስልታዊ)ወዳጅ ? የሚለው አንድና አንድ ብቻ መልስ የሚሻ ጥንድ ጥያቄ የወቅቱ አንኳር መወያያ ጉዳይ እንደሆነ ብዙዎች የምትስማሙ ይመስለኛል።(የሃገር ቤቱን በውል ባላውቅም ቢያንስ ቢያንስ በውጭው ዓለም ያለው ኢትዮጵያዊ በዚህ ጉዳይ እየተወያየ መሆኑን ከሳይበር ውሎዬ ተረድቻለሁ)። ጉዳዩ፦ የብዙዎቻችንን ቀልብ የሳበው በተለይ ፕ/ሬ ኢሳያስ አፈወርቂ ለኢትዮጵያን ሪቪው አዘጋጅና ለአርበኞች ግንባሩ ጋዜጠኛ የሰጡት ቃለ መጠይቅ ይፋ ከሆነ በኋላ ይመስለኛል፡፤ ከዚያ ቀደም ባሉ ግዚያት በተለይ ኤልያስ ክፍሌ የወያኔን ዘረኛና ኢ-ዲሞክራሲያዊ አገዛዝ ለማሰወገድ የተያዘው ትግል ያለ ሻቢያ ድጋፍ ውጤታማ አይሆንም! እስከ ማለት የደረሰበትና ሻቢያን በማወደስ በተደጋጋሚ ሲያስነብበን የነበረው ጥሁፋ ጥሁፍ ከተለመደው "አፍቃሪ-ሻቢያ" አቋሙ ጋር በማያያዝ ብዙም ቁብ የሰጠው እንዳልነበር አስታውሳለሁ፡፤ይህን ጽሁፍ አቅራቢ ጨምሮ። ይሁንና ኤልያስና ሌላው ጋዜጠኛ ኤርትራ መዲና አስመራ ዘልቀው ከፕ/ሬ ኢሳያስ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉበት የምስል(ቪድዮ) ዘገባ ለእይታ ሲቀርብና ወዲያውም ደግሞ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ አስመራ መሄዳቸው በዚሁ በአቶ ኤልያስ ድህረ-ገጽ ሲሰማ ..እንዴት ነው ነገሩ ? ማለታችን አልቀረም። አዎ! የፕ/ሬ ኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ከተደመጠ በኋላ በቃለ መጠይቁ ይዘት ላይ አስተያየት መሰንዘር የተጀመረው በዛው ቅጽበት ነበር። በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እምነት በኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠየቅ ዙሪያ ይሰነዘሩ የነበሩት አስተያየቶች በሁለት ተከፍለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው። አንደኛው ክፍል፦ ለጋዜጠኞቹ የውዳሴ ናዳ አዥጎድጉዶ፤ ፕ/ሬ ኢሳያስንም አመስግኖ፤ ባጠቃላይ ሁሉንም እንደ ወረደ መቀበሉን በበርካታ አራት ነጥቦች ከሽኖ ካረጋገጠ በኋላ ፤ (ድሮ በኤለመንተሪ ሳለን ከንዳ ስንባል መዳፉችን ከፊታችን በቆመው ተሰላፊ ትከሻ ላይ እንደምንለጥፈው አይነት) ከአቶ ኤልያስ ኋላም ባይሆን ጎን መሰለፉን ለማሳወቅ ግዜ ያላጠፋው ክፍል ነው። ለዚህ ጎራ የጥልዬን "ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም ፍቅሬ ፍቅሬ በዛ እኔ አላማረኝም ..." የሚለውን መካሪ ዜማ መርጬ ወደ ቀጣዩ ላምራ። ሁለተኛው ክፍል፦ ቃለ-መጠይቁ በሙሉ ውሸት ነው። ኢሳያስ ብሎ ሊኢትዮጵያ አንድነት ተጨናቂ ?..ሊሆን ቀርቶ ሊታስብም የማይችል..! ማጭበርበሪያ ፕሮፓጋንዳ ነው። ኤልያስም የምናውቀውን የሻቢያ ቅጥረኝነቱን በተጨባጭ ያረጋገጠበት ድርጊት ነው ብሎ ለማጣጣልና ለመኮነን ግዜ ያላጠፋው ክፍል ነው፡፤ ይህ ክፍል ሻቢያ ከወያኔ ጋር ወዳጅ በነበረበት ወቅት በሃገራችንና በሕዝባችን ላይ የፈጸመውን በደል ከታሪክ ማህደር እየመዘዘ እንደ አዲስ እንባ ሊያራጭ የሚዳዳው፤ በአንባቢም ላይ የቁጭትና የበቀል ግርሻ ሊከምር የሚጥር የሚመስል ነው። እነኚህ አስተያየት ሰጭዎች ሻቢያን የሃገራችን ታሪካዊ ጠላት በማለት ይፈርጃሉ፡፤ የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ ለዚህ ጎራም " ወደ ኋላ ሄደሽ በሃሳብ ከማለም...ቀኑ እንዳይመሽብሽ ትናት ዛሬ አይደለም" የሚለውን የሙሉቀን መለሰን ....መርጧል። ሁለቱም ካልጣሙህ አንተስ በኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ዙሪያ ያለህ አስተያየት ምንድነው? እንደምትሉኝ እገምታለሁ። ይሁንና በቃለ መጠይቁ ዙሪያ የሚኖረኝ ወይም ያለኝ አስተያየት ለተነሳሁበት ጭብጥ ብዙም ጠቃሚ ስላልሆነ ኢሳያስ የተናገረው ከልቡ ነው፤ ከአንገቱ ነው፤ ወደ ማለቱ አልገባም ። ምክንያቱም በኔ እምነት ከአንድ ቃለ መጠይቅ ተነስቶ ስለ ሻቢያ ወቅታዊ ምንነት ለመናገርና እንደ አቋም ለመያዝ አስቸጋሪ ነው። ስለሆነም ለግዜው ፕ/ሬ ኢሳያስን የልብዎን ባናውቅም እንዳፍዎ ያድርገው ብዬ ማለፉን መርጫለሁ። በዚሁ አጋጣሚ ጋዜጠኞቹም ሥራቸው ብስልም ይሁን ጥሬ ግዜ የሚለየው ሆኖ ቢያንስ ቢያንስ አስመራ ድረስ ዘልቀው ይህን ዘገባ ማጠናቀራቸው ሊያስመሰግናቸው ይገባል እላለሁ፡፤ ይሁንና በቃለ ምልልሱ ላይ አስተያየት ከመስጠት ልቆጠብ እንጂ፦ ስለ ሻቢያ ወቅታዊ ማንነት አልያም "ሻቢያ" ታሪካዊ ጠላት ወይስ ወቅቱ ግድ የሚለው

(ስልታዊ)ወዳጅ ? በሚለው ጥያቄ ላይ ምንም አመለካከት ወይም አስተያየት የለኝም ማለቴም

አይደለም። አለኝ። የኔ አስተያየትና አቋም ግን ከላይ ከተጠቀሱት የነጭና ጥቁር ያህል ልዩነት ከሚታይባቸው አመለካከቶች የተለየ ምናልባትም ከሁለቱ ጋ በከፊል የሚስማማ ነው። የግድ ቀለም ስጠው ካላችሁም ግሬይ የሚባል አይነት ነው።(የነጭና ጥቁር ድብልቅ ግሬይ ወይም አመድማ መሆኑን ልብ ይሏል) ሁለቱም ክፍሎች (ጸረ- ሻቢያና ውገነ-ሻቢያነትን የሚያራምዱት) መሰረታዊ አላማቸው አንድ ነው። ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ሃገር የሆነውን ወያኔን በትግል ማስወገድ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዜ ሊሰጠው የማይገባ ችግር መሆኑን ያምናሉ! አምነውም ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ ሳንዘነጋ፤- ይህ የጋራ አላማ ወደ ተግባር እንዴት ይለወጥ በሚለው የአካሄድ ወይም የስልት ጥያቄ ላይ ግን ከሰማይና ከምድር የተራራቁ የሚመስሉ ልዩነቶች ተንጸባርቀውባቸዋል። በዚህ ጠሃፊ እምነት ይህም ጤነኛና የሚጠበቅ ነው። የሃሳብ ልዩነት የሌለበት እንቅስቃሴ የቆመ አልያም የሞተ እንቅስቃሴ ነውና። አሁንም በዚህ ጽሁፍ አቅራቢ እምነት ሁለቱም ወገኖች የሚታይባቸውን የቅራኔ ጓዝ እንደተጫኑም ቢሆን የተፈጠረውን ልዩነት እንዴት ማስወገድ ይቻላል? ሊወገድ ካልቻለም ቢያንስ እንኳ እንዴት ሊጠብ ይችላል ? ለሚለው ወቅታዊ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እራሳቸውን ከግትርነት አውጥተው በጨዋ ደንብ ለመወያየት ፈቃደኝነቱ እንዲኖራቸው ይጠበቅባቸዋል። ሁሌም በተደጋጋሚ የሚነሳውን "በልዩነቶቻችን ቀዳዳ ጠላት እንዳይገባ" የሚለውን ታላቅ ምክር ዛሬም እናነሳዋለን።አዎ በልዩነቶቻችን በአንደኛው ጎራ ሁሌም ጠላት መለጠፉ አይቀሬ ነው፡፤ ከላይ በተቀመጡት በወቅቱ ልዩነቶች በአንደኛው ደጃፍ ወያኔ መለጠፏን የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም። ይሁንና ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ ፈቃደኝነቱ እስካለ ድረስ እነኚህን ተለጣፊዎች ከመሃል መንጥቀን ለማውጣት አይከብድምና ብዙም አያሰጋንም። እነኚህን አሾልቀው የገቡ ጠላቶች (የወያኔ ካድሬዎች) ከእውነተኛው ኢትዮጵያዊ የምንለያቸው የሃሳብ ልዩነቱ ቢቻል እንዲወገድ አልያም እንዲጠብ በሚደረግ እንቅስቃሴና ውይይት ላይ ከአቋማቸው ፈቅ ላለማለት በሚያሳዩት የአክራሪነት ባህሪ ነው። ዛሬም የሻቢያን በደል ከፊታችን እያመጡ ፡ የወደብ አልባነታችንን ቁጭት እየጫሩ፤ በትግራይ ያለቁትን ሕጻናት እያነሳሱ እንባ ሊያራጩ ሲጥሩ የምናያቸው ብዙዎቹ የወያኔ ካድሬዎች መሆናቸው አትጠራጠሩ። ለሕዝብ መብትና ነጻነት በሚጮሀው ወገን መካከል የሃሳብ ልዩነቶች በተፈጠሩ ቁጥር፡ ወያኔ ይጠቅመኛል ባለቺው የልዩነት ስንጥቅ ተሸንቅራ ልዩነቱን ለማስፋት ስለመትጋቷ ልንጠቅሰ የምንችለው ብዙ ልምድ አለን። ሌላው ቀርቶ፦ በምርጫ 97 ማግስት ቅንጅት ምክር ቤት ይግባ - አይግባ በሚለው የሃሳብ ልዩነት ላይ የወያኔ ካድሬዎች እራሳቸውን የቅንጅት ደጋፊ አድርገው በመቅረብ፤ ቅንጅት ምክር ቤት መግባቱ እንድሚጠቅመው ባገኙት መድረክ ሁሉ ሲደሰኩሩ እንደነበር ማስታወሱ ይበቃ ይመስለኛል። ዛሬም ከላይ በተጠቀሱት ወቅታዊ የሃሳብ ልዩነቶች "ኤርትራን ወይም ሻቢያን" በታሪካዊ ጠላትነት ከፈረጀው ጎራ የወያኔ ካድሬዎች መለጠፋቸው የሚያጠያይቅ አይደለም የምለው ከዚሁ ልምድ በመነሳት ነው።ስለዚህ ሁሌም ማሰብ ያለብን በልዩነቶቻችን ቀዳዳ የገባውን ጠላት ለመለየት የምንችለው ከግትርነት ወጥተን ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ ስንፈቅድ ብቻ መሆኑን ነው። እንግዲህ ከላይ በስፋት እንዳየነው ወቅቱ ግድ ያላቸው ልዩነቶች የተፈጠሩት፦ በሻቢያ ታሪካዊ ማንነትና ወቅታዊ ማንነት ላይ ተመስረተው በሚሰነዘሩ ሃሳቦች ላይ ነው። በአጭሩ የሃሳብ ልዩነቱ እንብርት "ሻቢያ" ታሪካዊ ጠላት ወይስ ወቅቱ ግድ ያለው(ስልታዊ)ወዳጅ ? ለሚለው ጥያቄ የሚሰጡት የተለያዩ ምላሾች ናቸው። በሻቢያ ወቅታዊ ማንነት ዙሪያ የሚነሱት አስተያየቶች የነጭና የጥቁር ያህል ጉልህ ልዩነት ይሏቸው ናቸው፡፤ የኔ ደግሞ አመድማ ወይም ግሬይ ነው ብያለሁ፡፤ ከሁለቱም በከፊል የሚስማማ፤ ከሁለቱም በከፊል የማይስማማ፡፤ ላስረዳ፦ በመጀመሪያ የሻቢያ ወቅታዊ ማንነት ጉዳያችን ሆኖ የሚያወያየን በአንድና አንድ ምክንያት ነው። “ወያኔን ከሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድ ለሚደረገው ትግል አጋዥ ሊሆን ይችላል አይችልም ?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው። በአጭሩ ሻቢያ ይጠቅመናል ወይስ አይጠቅመንም? የሚለውን ለመወሰን ነው የሻቢያን ማንነት መመርመር ያስፈለገው፡፤ ካለፈው ታሪኩ

በመነሳት ሻቢያ መርዝ ነው! ሻቢያ እባብ ነው! ሊታመን የማይችል አካል ነው። የሚሉትን አስተያየቶች እኔም አምንባቸዋለሁ! አዎ ሻቢያ መርዝ ነው ! ሻቢያ ሊታመን አይገባውም! ሻቢያ እባብ ነው። ነገር ግን የእባብ መርዝ በህክምና ጠበበት ስሪንጅ ሲያዝ መድሃኒት እንደሚሆን ሁሉ መርዘኛው ሻቢያ በጥንቃቄ ከተያዘ ከወቅቱ በሽታ(ወያኔ) ፈውስ ልናውለው እንችላለን እላለሁ። አዋቂዎች ከእባብ መርዝ መድሃኒት ይሰራሉና። አባባሌን ዘርዘር አድርጌ ለማቅረብ ያህል። ዛሬ ለሃገራችን ሕልውና አስጊ የሆነው ወቅታዊው በሽታ ወያኔ እንጂ ሻቢያ አይደለም። በርግጥ ሻቢያ ካለፈው ባህሪው ስንገመግም አደገኛነቱን መጠራጠራችን አይቀርም፡፤ መጠራጠር ብቻም አይደለም በሻቢያ ውስጥ አሁንም ጎጂና ድብቅ መርዝ እንደሚኖር መገመት ይቻላል፡፤ ይህ መርዝ በርግጥ አያያዙን ካላወቅንበት ሊጎዳን ይችላል፡፤ ይሁንና አያያዙን ካወቅንበት ግን ልንጠቀበት እንደምንችል ፍንጮች ታይተዋል። በሌላ በኩ ሻቢያ የወያኔ ወቅታዊ ጠላት መሆኑ የኛ ተመራጭ ወዳጅ ለመሆን የሚያስቸለው ወይም በቀጥታ የሚያስመርጠው አይደለምና ፤ የፕ/ሬ ኢሳያስን ቃለ መጠይቅ ሰምተው ያድናቆት ከበሮ ከሚደልቁት ወገኖች ጋ የማልስማማውም በዚህ ነው፡፤ ይሁንና ለጋራ ጥቅም በውስን ጉዳዮች ላይ ከሻቢያ ጋር አብሮ መስራት መሞከሩን እደግፋለሁ፡፤ በርግጥ የማንጠራጠረው እንደ ሻቢያ ደም ያልተቃባነው ወዳጅ ቢገኝ ኖሮ ዛሬ ስለ ሻቢያ የቆጥ-የባጡን ባላወራን ነበር። ነገር ግን ምንም ቀዳዳ ያለመኖሩ አስቸጋሪ ምርጫ ውስጥ ከቶናል። ከሻቢያ ጋር አብሮ መስራት በፍጹም የሚሞከር አይደለም የሚሉት ወገኖች እሺ አይሆንም ካላችሁ አማራጭ ሰንዝሩ ሲባሉ፦ ቄሱም ዝም….መጽሃፉም ዝም! …ሆነ። ከዝምታው የምንረዳው ደግሞ ከሻቢያ ጋር ከመስራት ይልቅ ወያኔ ሕዝባችንንም ሃገራችንንም አቅልጦ እስኪጨርስ ፤ እኛም በየአደባባዩ ሻማ እያቀለጥን ብንቆይ ይሻላል ብለው መምረጣቸውን ነው፡፤ እዚህ ላይ እንግዲህ ልዩነቶች የግድ ካሉ ሁሉም ባመነበት(ሳይጎነታተል) የነፍስ ወከፍ ወይም የድርጅት ወከፍ ምርጫ አቋም ይዞ መንቀስቀሱን ተገቢ ያደርገዋል። ሌላው ቀርቶ፦ ምንም እንኳ የፕ/ሬ ኢሳያስ ቃለ መጠይቅ ይዘት ነጭ ነው፡ ጥቁር ነው የሚለው የአመለካከት ልዩነት መሃላችን ቢኖርም ። ቃለ መጠይቁ በመደረጉ ብቻ የወያኔን ጓዳ መረባበሹንና እራስ ምታታ እንደለቀቀባቸው ማየት በመቻላችን ይህን ጉዳይ ወዲያውኑ አጥላልቶ ማስወገዱም ለጠላቶቻችን ራስ ምታት መድሃኒት እንደ ማቀበል ያህል የዋህነት ስለሚሆን የሆዴን በሆዴ ብለን በፕሮፓጋንዳነቱ ብቻ እንኳ ልንጠቀምበት መሞከር ብልህነት ይመስለኛል። ከዚህ በተጨማሪ በድጋሚ አስምሬበት ለማለፍ የምሻው፦ ይህ በሻቢያ ዙሪያ ያለው አቋም ተቀዋሚ ድርጅቶች በነፍስ ወከፍ የፈለጉትን አቋም ይዘው የሚንቀሳቀሱበት እንጂ በዚህ ዙሪያ ወይም በሻቢያ ወቅታዊ ማንነት ላይ ሁሉም በአንድ አመለካከትሥር ይሰባሰቡ የሚል እምነት ሊኖር እንደማይገባ ነው። ቢሆንልን ጥሩ ነው። ነገር ግን ወቅቱ የትግል ወቅት ነውና የትግል አቅጣጫና ስልት ልክ እንደ ብሄራዊ-አጀንዳዎች ሊወሰዱ አይገባም ለማለት ነው፡፤ ይህ ማለት፦ ከሻቢያ ጋር መስራትን የመርጠ አካል ወይም ድርጅት ከሻቢያም ሆነ ከየትኛውም የውጭ ሃይል ጋር ሊኖረው የሚችለው ግንኙነት በድርጅቱ መርህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት እንጂ ብሄራዊ ወይም አገራዊ ግንኙነት ተደርጎ ሊዌድ አይገባውም፡ ማለት ነው። በሻቢያ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና የሚሰጡ አስተያየቶች ሁሉ በዚሁ መልክ መታየት አለባቸው እላለሁ፡፤ ግንቦት 7 ንቅናቄ ከሻቢያ ጋር መስራት ያዋጣል ብሎ ካመነ፤ የራሱን ጥንቃቄ ወስዶ ቢንቀሳቀስ፦ ሌላው ደግሞ ሻቢያን አላምንም ካለ እንደዛው የሚያምነውን አካልና አቅጣጫ መርጦ ቢንቀሳቀስ ወደ ዋናው ዓለማ በሚደረገው ጉዞ ላይ እንቅፋት የሚፈጥር አይሆንም። ዛሬ በሻቢያ ዙሪያ የተነሳው የሃሳብ ልዩነት ትናት በሰላማዊ ትግልና በትጥቅ ትግል ዙሪያ ከተነሳው ልዩነት ያነሰ አንድምታ እንጂ የበለጠ የልዩነት አድምታ የለውም ፡፤ እያንዳንዱ ተቃዋሚ ያዋጣኛል የሚለውን ስልት እንጂ የሚመርጠው፤- አላስፈላጊ መስዋእትነት ከፍሎ ልፋቱ ከንቱ እንዲቀር አይሻምና ከማንም የበለጠ ለራሱ ስልት እራሱ ያስባል ብለን ሃላፊነቱንም እምነቱንም መስጠት አለብን እላለሁ፡፤ የኛ ሃላፊነት አካሄዱ ትክክል ነው ለምንለው ወገን የሚቻለንን ድጋፍ ማድረግ ብቻ ነው። ሰላም ለሃገራችንና ለሕዝባችን አ.ስ ሰኔ 2001 ዓ.ም በማይቀረው የህዝቦች ነጻነት ዋዜማ ተጻፈ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 3

እናገኘዋለን።ፀሀይ ያሞቀው የውሸት ቋንጣ።ነገር ግን ስለታሰሩት ያለው እውነታ ሌላ ነው። በፀለምት፣ ወልቃይት ፀገዴ፣በቃሊቲ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዴዴሳ ፣ብርሸለቆ እና ዝዋይ የንፁህ ኢትዮጵያውያን ደም እምባ በምድሪቷ ላይ ድምፁን እያሰማ ይገኛል። እስር ቤቶቹ ሁሉ በጋዜጠኞች እና ሀገር ሊቀና የሚችል እውቀት ባካበቱ ምሁራን ታጭቋል። ስለዚህ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን ናቸው። የታሰሩት ሁሉም ናቸው! ከሁሉም ናቸው! ለሁሉም ናቸው። በሀገራችን ላይ ማንኛውንም ነገር በቀናነት ለማድረግ መብት ከሌለን ሀገር አልባ ነን ወይም ታስረናል ማለት ነው። በእስር ቤት ውስጥ አርፈህ ከተቀመጥህ ትበላለህ፣ ትተኛለህ ፣ትፀዳዳለህ ሌላ ትርፍ እርምጃ ለማድረግ ሀሳብ እንዳለህ ከተነቃብህ ፊደል ያልቆጠሩ የወያኔ ስልጡን ገራፊዎች ይገለብጡሀል። በከተማ ውስጥ ሰለተቀመጥህ ነፃ ነህ ማለት አይደለም አሊያም ነፃ መሆንህን ማረጋገጥ ካስፈለገህ እውነቱን በአደባባይ ቆመህ ተናገር ያን ጊዜ የት እንዳለህ ይገለፅልሀል። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ታስራለች ብለን የምንናገረው። የእኛም መለያየት ወያኔ እየቆመረ እንዲቀጥል አስችሎታል። በወያኔ ግዞት ውስጥ በስቃይ ስላሉት ስናስብ ወደ አዕምሮአችን የሚመጡት ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይስ ግለሰቦች? ከታሰሩት ውስጥ የነማን ይፈቱ? የየትኞቹ የብሔር ነፃነት ታጋዮች አሊይስ የቱ ተቃዋሚ ፓርቲ? ቀደምት የነበረው ወይስ መጤው? ለማን አቤት እንበል? መልሱ ግራ የሚያጋባ አይደለም። ለኢትዮጵያውያን ነው መሆን ያለበት። በአንድነት፣ በመጣመር፣በመያያዝ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ለአንድ አላማ መሰለፍ። ከቶውንም ኢትዮጵያዊ ባርያ ሆኖ አያውቅም። ሀገራችን በጄኔቫ የዓለም መንግሥታት ማህበር ጠቅላላ ስብሰባ ላይ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር መስከረም28 ቀን 1923 የመንግሥታቱ ማህበር ሃምሳ ሰባተኛዋ አባል ሆና መመዝገቧ በይፋ ታወጇል ።በዓለም መንግሥታት ማህበር መድረክ የክብር ቦታ ተሰጣት።ታዲያ ዛሬ ላይ ቆመን ይህንን የዚያን ዘመን ጀግንነት ስናስታውስ በፍፁም ቅንነትና የዋህነት የተሞላ ዕምነታቸውንና ተስፋቸውን ስናነብ የደማቸው ጩኽት እያስተጋባብን ማናችን የዚህ ዘመን ትውልድ ነን የዜግነት ግዴታን ቢያንስ ከእነሱ በተሻለ ለመወጣት የሞራል ብቃት ያለን? ዳር ድንበር የተጠበቀበት ከፋሺስቶች ጉልበት በላይ የተጎለበተበት ያንን የመሰለ ለጥቁሩ ህዝብ ኩራት ሆኖ ወራሪው በተራው ያፈረበት እና ያጎነበሰበት ክንድ አሁንም በአንድነት አዲሱ ትውልድ ወያኔን ድባቅ ለመክተት ሊቀሰቀስ ይገባል። ለፋሺስት ፀጉረ ልውጥ ወታደር ያልተበገረ ወኔ አሁንም በአንድነት በታላቅ እንቢተኝነትን እና አመፅ የተሞላ ትግል ያሻዋል። እንሔድብት ዘንድ ወያኔ አንጋዶ ያሰመረልን መስመር አሰናከለን፣በተነን፣ለየን እንጂ ለእድገት አላራመደንም።ስለዚህ በአንድነት በቁጣ እንነሳ እንታገን። ድምፃችን ይሰማ!!! ለአንዱ ብቻ አይደለም ለሁሉም ፍትህ እና ነፃነት ይገባል። ሰሜኑ ፣ ደቡቡ፣ ምዕራቡ እና ምስራቁ በየክልሉ ያለው የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ሲደመር ነው ኢትዮጵያ የሚባለው።ስለዚህም ለሁሉም መጮህ አለበት። የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች ሁሉም ይፈቱ። በአንድነት ለአንድ ትግል ለአንዲት ኢትዮጵያ እንቁም። ወያኔ ኢትዮጵያን ሊለቅ ይገባል።ሀገርን ቀምቶ በህዝብ ከርሰ ልብ ውስጥ ያለውን ሰላም ስርቆ ደስታን ወደ ሀዘን የለወጠውን የኢትዮጵያ ጠላት ለመፋለም የጀግና ልጅ ሆይ ተነስ ከወያኔ ረገጣ ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣት ያባቶችህ ወኔ እና አደራ ይጥራህ። ድል ለኢ ት ዮ ጵ ያ ህዝብ !!!! እናቸንፋለን!!! Biniam Gizaw Norway

ፍትህ እና ርትዕ ለሁሉም በኢትዩጵያ ውስጥ ከሁለት አስርት አምታት ወዲህ በህዝብ ላይ በጣም እየተንሰራፋ ስለሚገኘው የዘረኝነትን ተህዋስ ሳስብ በአንድ ወቅት በእስራኤል ያሉ አይሁዳውያን ያደረጉት አድሎ እና ወገናዊነት በአዕምሮዬ ይመጣል። ሁሉም ለፈለጉት ብቻ ነበር ጥብቅና የቆሙት።የሌላውን ሀዘን እና መከራ ከመጤፍ ሳይቆጥሩት በርባን!በርባን!በርባን! እያሉ በንጉሱ በር ላይ የራሳችው ወገን ብቻ እንዲፈታ አቤቱታቸው ታልቅ ነበር። ኢየሱስን አሳልፈው ለፍርድ ሰጥተውት የራሳቸው ወገኔ የሚሉት እንዲፈታ በታላቅ አድማ ድምፃቸውን ያሰሙ ነበር። በዚያን ጊዜ በርባን የሚባል ታወቂ እስረኛ ነበራቸውና መፈክራችው ሁሉ እሱን የሚያወሳ ነበር። በወቅቱ ፈራጅ ወደሆነው ቀርበው አድሎ የተሞላበት ጥያቄያቸውን አቀረቡ ገዥውም ጥያቄውን ከሰማ በኋላ እንዲህ አላቸው፥ ከሁለቱ ማንኛቸውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁ አላቸው? እነርሱም በርባንን አሉ። ይህ ነው አድሎ። ይህ ነው መለያየት። ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? አሁን የደረስንበትም ዘመን ይህንን መስሏል ። ሁሉም ቢጤዬ ለሚለው ለራሱ ፈርጆ ማድላቱ እና ለታሰረበት ሲጮህ የሌላውን ወገን አልባ መሆን ማታሰርና መንገላታት በስራህ ያውጣህ ጆሮ ዳባ ልበስ ካለው የአንድነት እና የመቀባበል ልብ ጠፍቷል ማለት ነው። እንግዲያስ ትግሉ ለማን ነው?ለግለሰብ?ለፓርቲ?ለብሔራችን? ወይስ ለኢትዮጵያ ? ሚዛኑን ሳታዳሉ ምላሽ ስጡብት ። ተለያይቶ በየሰፈራው ለራስ ወግኖ እታገላለሁ ማለቱ የወያኔን እድሜ ቢያረዝም እንጂ ለኢትዮጵያ ምንም አይበጃትም።ወያኔ ለራሱ ብቻ ወግኗልና 23 አመታት አስቆጥሮ ሀገሪቷን ወደሚቀጥለው ረመጥ ይዞ 24 ለማለት የብቀላ አየሩን ወደውስጥ እየሳበ ነው። ሌላ የጨለማ ጉዞ። እርስ በርሷ የምትለያይ መንግስት አትጸናም እንደተባለ ኢትዮጵያን በሁሉ አቅጣጫ ሸንሽኗት ይገኛል። ጎሳው፣ ክልሉ ፣ ብሔሩ፣ ፖለቲካው፣ የእምነት ተቋማቱ፣ ሚዲያው ወ.ዘ.ተ. . . በሌላውም የኢትዮጵያ ጉዳይ ሁሉ ይህ አስከፊ የወያኔ የመለያየት መርዝ እንደ ተስቦ በሽታ በምድሪቷ ላይ ተረጭቷል። ማምከኛው ደግሞ አንድነት ብቻ ነው። የተባበረ ክንድ! ወያኔ ኢትዮጵያን በአንድነቷ ሊገዛት ስለማይችል ከሰሜን አንስቶ ደቡብ ድረስ ከምስራቅ ጀምሮ እስከ ምእራብ ገንጥለህ እና ለያይተህ ግዛ በሚለው መርሁ ትውልዱ ቤተሰብ ሆኖ ሳለ እርስ በእርስ እንዳይቀባበል የጎጠኝነት እና የባይተዋርነት መንፈስ እየዘራበት ይገኛል። ውጤቱም ደግሞ እየተስተዋለ ነው። ይህን ለሚያህሉ አመታቶች በአንባገነንነት ምድሪቷን ሲመዘብር እና ወያኔ የራሱን ሆድ ሲያጠረቃ ከተጠቀመባቸው የውንብድና እና የማጭበርበርያ ስልቶቹ መሀል አንደኛው ኢትዮጵያውያንን እንደ ቅርጫ አጥንት መከትከት እና መቆራረጥ ነው። እናም ይህ የመለያየት መተት እና አዚም ብዙዎችን ለያይቶ ለኢትዮጵያዊነት ሳይሆን ለፓርቲ፣ ለግለሰብ፣ ለክልል፣ ለጎሳ ፣ ለእምነት ቤት፣ ወ.ዘ.ተ. . . ዘብ መቆም ብዙ ቦታ እየተስተዋለ የመጣ ጉዳይ ሆኗል ። ይህም በየስፍራው ያለው ልዩነት ወያኔን በግፍ አገዛዙ እስካሁን እንዲዘልቅ አግዞታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጭቆና አገዛዝ የነዳዳቸው ታጋዮች ጥቂቶች አይደሉም ። በገዢው ቡድን የኢትዮጵያ ጠላት ወያኔ አማካይነት ደብዛቸው እና ስማቸው የጠፉት በብዙ ሺህ ይቆጠራሉ። ለአመታት ያህል በአሰቃቂ ሁኔታ ከታጎሩበት እስር በነጻ እንኳን ቢለቀቁ የአዕምሮ፣ የአካል፣ ህሙም ሆነው አሊያም ከተቀበሉት ሰቆቃ አንጻር በመሀላ ወያኔን አትድረስብኝ አልደርስብህም በማለት በአይነ ቁራኛ የሚጠበቁ ይሆናሉ። ወያኔ ስላሰራቸው ሲናገር ወንጀልኞችን እና አሸባሪዎችን እንጂ ማንንም ጋዜጠኛም ሆነ የፖለቲካ እስረኛ የለኝም ማለቱን ከእውነታው ጋር ሲነጻጸር አንገት የሚያስደፋ ውሸት ሆኖ

የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት

ለትግራይ ሰው! በፍቃዱ ሃይሉ

ትግራይ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ መሬቷ ላይ የተጻፈባት ክልል

ናት፡፡ ብዙዎች ‹‹የኢትዮጵያ ራስ ናት›› የሚሉት ለዚህ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ 3000 ዓመት የሚያደርሰው

የአክሱም ስልጣኔ አሻራውን ትቶ የሄደው በትግራይ ክልል፣

አክሱም ከተማ ነው፡፡ ከአረቦች ተቀድቷል የሚባለውን የንግስተ

ሳባ ታሪክ ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚባለው መጽሐፍ ተርጉመው

ለዚህ ትውልድ ያኖሩልን የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡

ሌላው ቀርቶ ህብረ-ብሄራዊ ቅርስ የሆነንን የሳባ ፊደል ለመላው

ኢትዮጵያዊ ያወረሱት የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡

ከኢትዮጵያዊነት ቀለሞች አንዱ የሆነው ያሬዳዊው ዜማ

የተቀዳው ከትግራይ ምድር ነው፡፡ እነዚህና ሌሎች

ያልጠቀስኳቸው እውነታዎች ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚኮራባቸው

ናቸው፡፡

ኢትዮጵያዊነት በትግራይና በሌሎችም ህዝቦች አኩሪ ታሪክ፣

ባህልና ስርዓት ተገምዶ የተፈጠረ ማንነት ነው፡፡ ይሁን እንጂ

ነገሥታት በመጡና በሄዱ ቁጥር ለራሳቸው ጥቅም አንዱን ወገን

ከጎናቸው በማሰለፍ ሌላውን ወገን ያጠቁ ነበር፡፡ የአሁኑ

የሀገራችን ገዢዎችም፣ ይህንን ስልት እየተጠቀሙ በስጋና መንፈስ

የተገነባውን ህብረታችንን ሊያፈርሱብን ከጫፍ ደርሰዋል፡፡ የዚህ

ጽሁፍ ዓላማ ለዚህ እኩይ ተግባር ትግራዋዮች ተባባሪ

እንዳይሆኑ መጠየቅ ነው፡፡

እንደሚታወቀው አምባገነኑን ደርግ ለመጣል በተደረገው ትግል

የትግራይ ህዝብ የከፈለው መስዋዕትነት ቀላል አይደለም፡፡ ይሁን

እንጂ ደርግን ተክቶ ስልጣን የያዘው ሕወሓት ቃል የገባውን

ዴሞክራሲ እና ነጻነት ማምጣት ከብዶታል፡፡ እንዲያውም መልሶ

ከደርግ ያልተናነሰ አምባገነን ሊሆን ተቃርቧል፡፡ ይህ አልበቃ

ብሎት በትግራይ ህዝብ ስም የጥቂት ግለሰቦችን ጥቅም እያካበተ

ነው፡፡ በዚህም የከፋፍለህ ግዛ ስልቱ በትግራይ ህዝብ እና

በሌሎቻችን መካከል የቅራኔ ግንብ እየገነባ ነው፡፡ እኔ የመሐል ሀገር ሰው ነኝ፡፡ የመሐል ሀገር ሰው በሕወሓት ከፋፍለህ ግዛ ስልት ምን ያክል እንደተሸወደ አይቻለሁ፡፡ እኔም

የችግሩ ሰለባ ነኝ፡፡ ቀጣዩን በገፅ 5 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 4

በአፋኙና ጨቋኙ የወያኔ መንግስት ምክንያት የተሸበቡ የኢትዮጵውያን ልሳኖች

እንደተዘጉ አይቀሩም። ስለነሱ የሚናገርላቸው፣ አቤት የሚልላቸውና

የሚያስተጋባላቸው ልሳን አለ። ይህንንም ልሳን የህዝብ እንጂ የማንንም እንዳልሆነ

ላማሳየት ልሳነ ህዝብ በድረ ገፁ በየወሩ የማያወጣው ጋዜጣ ነው።

ልሳነ ህዝብ በፖለቲካ ፓርቲነትም ሆነ በማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ መድረክ ላይ

የማይሳተፍ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም ብቻ የቆመ የዲሞክራሲና የፍትህ መድረክ ነው።

ማንም ሰው አመለካከቱን በነፃነት መግለፅ የተፈጥሮ ልግሱ ነው በማለት የተነሳ

መድረክ ነው።

ሕወሓት በትግራይ ስም እየነገደ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ

በህወሓት ስም መልካም ገጽታው እየጎደፈ ነው፡፡ ይህ ግን

መቀጠል የሌለበት ታሪክ ነው፡፡ የትግራይ ህዝብ፣ በተለይ

የትግራይ ወጣቶች ይህንን ታሪክ ከሌላው ሕዝብ ጎን ቆመው

ማስቆም አለባቸው፡፡ የትግራይ ህዝብ ለጭቆና እምቢ ባይነት

ሕወሓት በሚል ስም ራሳቸውን ለሚጠሩት ሽፍቶችም

መዋል አለበት፡፡

ኑ! እምቢ አልጨቆንም እንበል፡፡

ናይ ማእኸል ሃገር ሰብ መልእኽቲ ንህዝቢ ትግራይ

በፍቃዱ ኃይሉ (ከቂሊንጦ ለነገረ ኢትዮጵያ)

ትግራይ ናይ ኢትዮጵያ ዕዙዝ ታሪኽ ዝሰፈረላ ክልል እያ፡፡

አባዝሓ “ናይ ኢትዮጵያ ርእሲ እያ” ንድሕሪት 3000 ዓመታት

ዘብፅሕ ስልጣነ ኣኽሱም አስር ገዲፋ ዝኸደ አብ ክልል

ትግራይ ከተማ አኽሱም እዩ፡፡ ካብ የዕራብ ተቐዲሑ ዝበሃል

ናይ ንግስተ ሳባ ታሪኽ “ክብረ ነገስት” አባ ዝበሃል መፅሐፍ

ተርጐሞም ነዚ ወለዶ ዘንበሩልና ሊቃውንቲ ትግራይ

እዮም፡፡

ካሊእ ተሪፋ ሕብረ – ብሄራዊ ሓድጊ ዝኾነና ናይ ሳባ ፊደል

ንኹሉ ኢትዮጵያ ዘውረሱ ሊቃውንቲ ትግራይ እዮም፡፡ ካብ

ኢትዮጵያ ዊነት ቀለማት ጣደ ዝኾነ ያሬዳዊ ዜማ

ዝተቐድጣሐ ካብ ምድሪ ትግራይ እዩ፡፡ እዚኦምን ካልኦት

ዘይፀራሕክፎም ሐቅታት ኩሎም ኢትዮጵያውያን

ዝሕበንሎም እዮም ኢትዮጵያውያን ዝሕበንሎም እዮም፡፡

ኢትዮጵያዊነት አብ ትግራይን ካልኦት ህዝብታት ዘሐብን

ታሪኽ፣ ባህልን ስርዓት ተላሒፁ ዝተፈጠረ እንታይነት እዩ፡፡

ይኹን እምበር ሃፄያውያን ብዝመፅሉን ብዝኸድሉ ጊዜ

ንዓርሶም ረብሓ ሓደ ወገን አብ ጎኖም ብምስላፍ ንኻልእ

ወገን ይሃስዩ ኔሮም፡፡ ናይ ሕዚ ገዛእቲ ሃገርና እዚ ሜላ

እናተጠቐሙ ብስጋን መንፈስ ዝተሃነፀ እንታይነትናን

ሕብረትና ንኸፍርሱ ኣብ ጫፍ በፂሖም እዮም፡፡

ናይዚ ፅሑፍ ዕላማ ነዚ ሕሱም ተግባር ትግራዎት ተሓባበርቲ

ንኸይኾኑ ንምሕታት እዩ፡፡

ከምዝፍለጥ ውልቀ መላኺ ደርጊ ንምግርሳሳ አብ ዝተኻየደ

ገድሊ ህዝቢ ትግራይ ዝኸፈሎ መስዋእትነት ቀሊል

ኣይኮነን፡፡ ይኹን እምበር ንደርጊ ተኪኡ መዚ ዝጨበጠ

ሕ.ወ.ሓ.ት ዝአተዎ ቃልን ዲሞክራሲን ነፃነት ምምፃእ

ካሊድዎ እዩ፡፡ ማሕልፎ ካብ ደርጊ ዘይንእስ ውልቀ መላኺ

ክኽውን ቀሪቡ ይርከብ፡፡ እዚ እንተይነኣሶ ብሽም ህዝቢ

ትግራይ ናይ ሒደት ውልቀ ሰባት ረብሓ እናኣከበ እዩ፡፡

ኣነ ናይ ማእኸል ሃገር ውልቀሰብ እየ፡፡ ናይ ማእኸል ሀገር

ሰብ ብናይ ሕ.ወ.ሓ.ት ከፋፊልካ ግዛእ ሜላ ክንደይ ዝኣክል

ከምዝተሸወደ ሪእዩ እዩ፡፡ ኣነውን ናይዚ ፀገም ኣካል እየ፡፡

ናይ ማእኸል ሃገር ሰብ አብ መንጎ ሕ.ወ.ሓ.ት ካልእ መማረፂ

ንኸይሕዝ ጌርዎ እዩ፡፡

ሕ.ወ.ሓ.ት ናይ ጨቆንቲ ጉጅለ እዩ፡፡ ሓደ ጨቋኒ ጉጅለ ድማ

እናመረፀ ኣይብድልን፡፡ ንመዙን ረብሕኡ ዘይተመቸወ ኹሉ

ዝብድል እዩ፡፡

ስለዚ ናይ ሕ.ወ.ሓ.ት ጭቆና ኣብ ህዝቢ ትግራይ እውን

ዝተርፍ ኣይኮነን፡፡ ኣነ /ናይ ማእኸል ሃገር ሰብ/ ህዝቢ

ትግራይ ምስ ሕ.ወ.ሓ.ት ዝተሓባበር ይመስለኒ ዝነበረ በዚ

ስርዓት ተረባሒ ስለዝኾነ ይመስለኒ ኔሩ፡፡ ተጋግየ፡፡ ለካ

ዝተፈጠረና ጥርጣረ ፍርሒ እዩ፡፡

ምስ ደቂ ትግራይ ብግልፂ እንተንዛተ ዝተገንብኩዎ እዚ እዩ፡፡

ደቂ ሰባት ትግራይ ንሕ.ወ.ሓ.ት ዝመርፁ ዝመስሉ ካልእ

ዝኣምንዎ ብዘይ ምርካቦም እዩ፡፡ ርግፅ‘የ ጭቆና ኾነ ሓርነትን

ሓደ ሂብካ ንኻልእ ዝዕገት አይኮናን፡፡

ኢትዮጵያ ኩላህና ብሕብረት እንነብረላ ሃገር ስጋዕ ዝኾነት

ጊዜ ህዝቢ ትግራይ ሓራ ወፂኡ ካልእ እንተይወፀ

ኣይተርፍን፡፡ እቲ ካልእ እናተጨቆነ እንተኾይኑ ድማ ህዝቢ

ትግራይ እውን እናተጨቆነ እዩ ማለት እዩ፡፡ ግን

ከምዝተገንዘብክዎ እዚ ሓቂ ኘሮፓጋንዳ ሕ.ወ.ሓ.ት ሸፊንዎ

ይደረስ ለትግራይ .... ከገፅ 4 የዞረ

የመሐል ሀገር ሰው ትግራዋይ ሁሉ የሕወሓት አባል

ይመስለዋል ቢባል የተጋነነ ውሸት አይደለም፡፡ የፖለቲካ

ቅሬታ ያለው የመሐል ሀገር ሰው ትግራዋዮች ፊት ችግሩን

አያወራም፡፡ ሁሉም አንድ ናቸው ብሎ ይፈራል፡፡ ታዲያ

በዚህ የመሐል ሀገር ሰው ሊወቀስ አይገባም፡፡ ምክንያቱም

የሕወሓት ፖሮፖጋንዳ ሰለባ አድርጎታል፡፡ ሕወሓት ራሱን

የትግራይ ሕዝብ ወኪል አስመስሎ ያቀርባል፡፡ በደል እና

ጭቆና የበዛበት የመሐል ሀገር ሕዝብ፣ ሕወሓት የጨቆነው

የትግራይ ህዝብ የጨቆነው ይመስለዋል፡፡

በዚህ ጉዳይ ከብዙ የትግራይ ልጆች ጋር ካወራሁ በኋላ ሌላ

ነገር ተገለጸልኝ፡፡ ለካስ ትንሽ የማይባሉ የትግራይ ልጆቹ

የመሐል ሀገር ሰው ይጠላናል ብለው ያስባሉ፡፡ የመሐል

ሀገር ሰው በሕወሓት እና በትግራይ ሕዝብ መሐል ያለውን

ልዩነት መረዳት ባለመቻሉ፣ የትግራይ ሰው በፍራቻ

ከሕወሓት ሌላ አማራጭ እንዳይዝ አድርጎታል፡፡ ሕወሓት

የጨቋኞች ቡድን ነው፡፡ አንድ ጨቋኝ ቡድን ደግሞ

እየመረጠ አይበድልም፡፡ ለስልጣኑ እና ለጥቅሙ

ያልተመቸውን ሁሉ ይበድላል፡፡ ስለዚህ የህወሓት

ጨቋኝነት ለትግራይ ሕዝብም የሚቀር አይደለም፡፡ እኔ

(የመሐል ሀገር ሰው) የትግራይ ህዝብ ከህወሓት የተባበረ

የሚመስለኝ በስርዓቱ ተጠቃሚ ስለሆነ ይመስለኝ ነበር፡፡

ተሳስቻለሁ፡፡ ለካስ የእኛ ጥርጣሬ የፈጠረው ፍራቻ

ነው፡፡ከትግራይ ልጆች ጋር በግልጽ ስንነጋገር የተረዳሁት

ይህንን ነው፡፡ የትግራይ ሰዎች ሕወሓትን የሚመርጡ

የሚመስሉት ሌላ የሚያምኑት ባለማግኘታቸው ነው፡፡

እርግጥ ነው፣ ጭቆናም ሆነ ነጻነት ለአንዱ ተሰጥቶ ለሌላው

የሚነፈግ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ሁላችንም በህብረት

የምንኖርባት ሀገር እስከሆነች ድረስ፣ የትግራይ ህዝብ ነጻ

ወጥቶ ሌላው ሳይወጣ አይቀርም፡፡ ሌላው እየተጨቆነ

ከሆነ ደግሞ የትግራይም ህዝብ እየተጨቆነ ነው ማለት

ነው፡፡ እንደተረዳሁት ግን፣ ይህንን ሐቅ የሕወሓት

ፕሮፖጋንዳ ሸፍኖታል፡፡

ልክ የመሐል ሀገር ሰዎች የትግራይ ሰዎችን ሁሉ በሕወሓት

አባልነትና ደጋፊነት እንደሚጠረጥሯቸውና እንደሚፈሯቸው

ሁሉ፣ የትግራይ ሰዎችም የመሐል ሀገር ሰዎች ከህወሓት ጋር

ቀይጠው ያጠቁናል ብለው ይጠረጥራሉ፤ ወይም ይፈራሉ፡፡

ይህ በመካከላችን ትልቅ የፍርሃት ግድግዳ ፈጥሯል፡፡

ግድግዳውን በመተማመን ማፍረስ ደግሞ የእኔና የእናንተ

ኃላፊነት ነው፡፡

ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ ሽፍቶቹ፣ ወያኔዎች እና የትግራይ

ህዝብ የተለያዩ ናቸው ይላል፡፡ ወያኔዎቹ የነጻነት ታጋዮች

ናቸው፡፡ ሽፍቶቹ ደግሞ በነጻነት ታጋዮቹ ስም የሚነግዱት

የአሁኖቹ ጨቋኞች (ሕወሓቶች) ናቸው፡፡ ዮናስ በላይ

የትግራይ ህዝብ የሽፍቶቹ ተባባሪ እንዳልሆነ የጻፈውን

ከልቤ ተቀብየዋለሁ፡፡ የትግራይ ህዝብ የሽፍቶቹ ተባባሪ

ካልሆነ አሁን ብዙዎቻችን እያደረግን ያለነውን የነጻነትና

የዴሞክራሲ ጥረት (ትግል) ይቀላቀላል ብዬ ተስፋ

አደርጋለሁ፡፡ በእርግጥም ብዙ ትግራዋይ የነጻነት ታጋዮች

ዛሬም አሉ፡፡ ነገር ግን ትግላቸው ከመሐል፣ ከምዕራብ፣

ከምስራቅና ደቡብ ሀገር ሰዎች ጋር መቀናጀት አልቻለም፡፡

እዚህ ጋር ከብዙ በእስር ከሚሰቃዩ የትግራይ ልጆች

መሀከል አብርሃ ደስታን መጥቀስ ይኖርብኛል፡፡ አብርሃ

የትም ቦታ የሚደረግ ጭቆና ይሰማኛል ብሎ የሚታገል

ታጋይ፣ ምሁርና ምክንያታዊ የሐውዜን ልጅ ነው፡፡ አብርሃ

ከማንም በላይ በትግራይ እና በመሐል ሀገር ሰው መካከል

ያለውን አለመተማመን የሰበረ ሰው ነው፡፡ አብርሃ በኃይለኛ

ብዕሩ ሕወሓትን ሲተች የተመለከቱ የመሐል ሀገር ሰዎች

‹‹ለካስ ትግራዋዮችም ህወሓትን ይቃወማሉ››

አስብሏቸዋል፡፡ ይህንን ሰው ግን ለነጻነት ታግያለሁ

የሚለው ሕወሓት በመቃወሙ አስሮታል፡፡ አሁን በቃሊቲ

ማረሚያ ቤት ጠያቂ ተከልክሎ፣ በጥብቅ ክትትል

እንደወንጀለኛ ታስሯል፡፡ በትግራይ ልጆች መስዋዕትነት

ስልጣን ላይ የወጣው ሕወሓት በስልጣኑ ከመጡበት

ለትግራይ ልጆችም እንደማይመለስ አብርሃ ደስታ ማሳያ

ነው፡፡

እዩ፡፡

ናይ ማእኸል ሃገር ሰባት ንደቂ ትግራይ ከም አባልነትን

ደጋፍነት ሕ.ወ.ሓ.ት ከም ዝጥርጥርዎምን ከምዝፈርሕዎም

ኩሉ ደቂ ትግራይውን ናይ ማእኸል ሃገር ሰባት ምስ

ሕ.ወ.ሓ.ት ጨፍሊቆም ከየጥቅዑና ኢሎም ይጠራጠሩ ወይ

ይፈርሑ፡፡ እዚ አብ መንጎና ግብዕ መንደቕ ፍርሓት ፈጢሩ

እዩ፡፡

እዚ መንደቕ ብምትእምማን ንምግ ሃስ ድማ ናተይን

ናታትኩም ሓላፍነት እዩ፡፡

ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ ሸፋቱ፣ ወያነን ህዝቢ ትግራይ

ዝተፈላለዩ እዮም ይብል፡፡ ወየንቲ ንሓርነት ተጋደልቲ

እዮም፡፡ ሸፋቱ ድማ ብሽም ተጋደልቲ ሓርነት ዝነግዱ ናይ

ሕዚ ጨቆንቲ /ሕ.ወ.ሓ.ት/ እዮም፡፡ ዮናስ በላይ ህዝቢ

ትግራይ ናይ ሸፋቱ ተሓጋጋዚ ተዘይኮይኑ ሕዚ ኩላህና /

አብዝሓ እናገበርናዮ ዘለና ኣብ ፃዕሪ /ቃልሲ/ ሓርነትን

ዲሞክራሲ ይፅምበር ኢለ ተስፋ እገብር፡፡ ርግፅ‘ዩ ብዙሓት

ተጋሩ ተጋደልቲ ሓርነት ሉሚውን አለው፡፡ ኮይኑ ግን

ቃልሶም ምስማእኸል ምዕራብ፣ ምብራቕን ደቡብ ጠቂ ሰባት

ክዋደድ አይከኣልን፡፡

ኣብዚ ምስ ብዙሓት ማእሰርቲ እናተሳቐዩ ካብዝርከቡ መንጎ

አብርሃ ደስታ ክፀርሕ ይግብኣኒ አብርሃ ኣብዝኾነ ቦታ

ዝካየድ ጭቆና ይስምዓኒ ኢሉ ዝቃለስ ተጋዳላይ ምሁርን

ምክንያታዊ ወዲ ሐውዜን እዩ፡፡ ኣብርሃ ልዕሊ ኹሉ ኣብ

መንጎ ደቂ ሰባት ማእኸል ሃገርን ትግራይ ዘሎ

ዘይምትእምማን ዝገሃስ ውልቀ ሰብ እዩ፡፡ ኣብርሃ በቲ ሓያል

ብዕሩ ንሕ.ወ.ሓ.ት እንትነቅፍ ዝረአዩ ደቂ ሰባት ማእኸል

ሃገር “ለካ ተጋሩ እውን ንሕ.ወ.ሓ.ት ይቃወሙ እዮም” ክብሉ

ጌርዎም እዩ፡፡ ንሓርነት ተቓሊሰ እየ ዝብል ሕ.ወ.ሓ.ት ግን

ነዚ ውልቀ ሰብ ኣሲርዎ እዩ፡፡ ብዚ እዋን ኣብ ቃሊቲ

ቤትህንፀት ዝሓቶ ተኸልኪሉ ብፅኑዕ ክትትል ከም ገበነኛ

ተኣሲሩ ይርከብ፡፡

ብመስዋእትነት ደቂ ትግራይ ኣብስልጣን ዝወፀ ሕ.ወ.ሓ.ት

ብስልጣኑ ንዝመፀ ንደቂ ትግራይ እውን ከምዘይምለስ

አብርሃ ደስታ መርአያ እዩ፡፡

ሕ.ወ.ሓ.ት ብሽም ትግራይ እናነገደ እዩ፡፡ ሕዝቢ ትግራይ

ብሽም ሕ.ወ.ሓ.ት ፅቡቕ መንፅሩ እናጠፍአ እዩ፡፡ እዚ ግን

ክቕፅል ዘይብሉ ታሪኽ እዩ፡፡ ህዝቢ ትግራይ፣ ብፍላይ

መናእሰያት ትግራይ እዚ ታሪኽ ምስ ካልእ ሕዝብታት ጎኒ

ብምስላፍ ደው ከብሎ ይግባእ፡፡

ህዝቢ ትግራይ ንጭቆና እምቢ ማለት ሕ.ወ.ሓ.ት ብዝብል

ሽም ዓርሶም ንዝፅውዑ ሸፋቱ እውን ክውዕል አለዎ፡፡ ንዑ! እምቢ ኣይንጭቆንን ንበል!

ለፈገግታ

የውሸታሞች ሙግት አንደኛው ውሸታም፤ “የዛሬ 10 ዓመት አባቴ በህንድ ውቅያኖስ ላይ በመርከብ ሲንሣፈፍ የእጅ ሰዓቱ ወድቆበት ከ10 ዓመት በኋላ ሲመለስ በዋና ውኃ ውስጥ ገብቶ ሲፈልግ ሰዓቱ ምንም ሳይሆን እየሠራ አገኘው ይለዋል” ሁለተኛው ውሸታም፤ “ይገርምሃል የኔም አባት በዚሁ ውቅያኖስ ላይ ሲንሳፈፍ ወድቆ ከ10 ዓመት በኋላ ምንም ሳይሆን በሕይወቱ ዋኝቶ ወጣ፡፡” አንደኛው ውሸታም፤ “እንዴት ያንተ አባት ሳይሞቱ ውኃ ውስጥ ሊኖሩ ቻለ፡፡ደግሞስ ምን እየሠሩ ይሕን ያህል ዓመት ቆዩ” ብሎ ይጮህበታል፡፡ ሁለተኛው ውሸታም፤ “ውኃ ውስጥ እንኳን ሳይሆን አሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ነው የቆዬው፣ ብቻ አንዳንድ ጊዜ ያንተን አባት ሰዓት እንዳይቆም እየወጣ ይሞላ ነበር ሲል መለሰለት፡፡

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 5

በህብረተሰቡ ውስጥ እንዲነ ዙ ስለሚያደርግ፣ እንደዚህ

ዐይነ ቱን የ ስልጣኔ ጠንቅ ጥልፍልፍ ሁኔ ታ መረዳቱ

እጅግ አስፈላጊ ነ ው። ዛሬ በአገ ራችንም ሆነ በብዙ የ

ሶስተኛው ዓለም አገ ሮች ያለው ተጨባጭ ሁኔ ታ

የሚያረጋግጠው እነ ዚህ አገ ሮች እንደህብረተሰብ

ወደማይታዩበት ደረጃ ዝቅ ብለው ማንም የሚፈነ ጭባቸው

ሆነ ዋል። ቤተሰብ መመስረት፣ አገ ርን ገ ንብቶ ለመጭው

ትውልድ የሚሆን በጥሩ እሴት ላይ የ ተመረኮዘ

ህብረተሰብና ማህበረሰብ መመስረት የ አንድ ህዝብ የ

ኑሮው ዓላማ ሆነ ው የ ማይታዩበት ሁኔ ታ በአገ ራችንም

ሆነ በብዙ የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮች በጉልህ ይታያሉ። የ

ዚህ ሁሉ ችግር አንድም፣ ህብረ-ብሄር፣ ህብረተሰብ፣

አጠቃላይ ባህልና ህብረተሰቡን የሚያስተሳስር በሳይንስና

በቴክኖሎጂ ላይ የ ተመሰረተ ኢኮኖሚያዊ ዕድገ ት አስፈላጊ

መሆናቸውን ካለመገ ንዘብና በጭንቅላት ውስጥ

ካለመቋጠር የ ተነ ሳ ሲሆን፣ ሌላም የፖለቲካ ትርጉምን

በተጣመመ መልክ መረዳትና ህብረተሰብን ማከረባበቻ

መሳሪያ አድርጎ በመውሰድ ዘለዓለማዊ ውዝግብ

እንዲፈጠር ከማድረግ የመነ ጨ የ ተሳሳተ ግንዛቤ ነ ው።

እንደዚህ ዐይነ ቱ አመለካከት ስልጣንን በጨበጠው ኃይል

ብቻ እንደፈሊጥ ተወስዶ ተግባራዊ የሚሆን ነገር ሳይሆን፣

ራሳቸውም ለዲሞክራሲ እንታገ ላለን የሚሉ ኃይሎችም

ከፍተኛ ችግር እንዳለበቻው እንገ ነ ዘባለን።

ከመጀመሪያውኑ በግልጽ የ ማያስቀምጧቸው መሰረታዊ ነ

ገ ሮች ስለሚኖሩ እንዳጋጣሚ ስልጣን ላይ በሚወጡበት

ጊዜ በድሮው መልክ የሚቀጥሉበት ሁኔ ታ ይታያል። የ ገ

ቡትን ቃል-ኪዳን ተግባራዊ እንዳያደርጉ ይሳናቸዋል።

ዓለም አቀፋዊ በሆኑ ኢንስቲቱሽኖች እየ ተጠለፉ በራሳቸው

ሌላና ውስብስብ ችግር ፈጣሪዎች ይሆናሉ። የመጨረሻ

መጨረሻም ጨቋኝና ጦርነ ት ፈልፋይ ይሆናሉ። የ ዚህ

ሁሉ ችግር ከምን የመነ ጨነ ው ? የ አንድን ህብረተሰብ የ

ችግር ምንጭ በቅጡ የመረዳት ችግር ! አንድን አገ ዛዝ

በድፍኑ ከመወንጀል ይልቅ ለምን ችግር ፈጣሪ ይሆናል?

የሚያስገድዱትስ ነ ገ ሮች ምንድናቸው? ብሎ ራስን መጠየ

ቅና መልስ ለመስጠት መሞከር ሁሉም ሊያቀርበው

የሚችለው ጥያቄ ባይሆንም፣ አንድ ምሁር ባይነ ኝ የሚል

ሰው ማቅረብ ያለበት ጥያቄና መልስም ለመስጠት

መዘጋጀት ያለበት ጉዳይ ነ ው። በተለያዩ ጊዜ ስልጣን

የሚይዙ ኃይሎች የሚሰሩትም ስህተት ሆነ ጥሩ ስራ

ከህብረተሰቦቻቸው ዕድገ ት ሁኔ ታ ጋር የ ተያያዘ ነ ው።

ማንኛውም አገ ዛዝ ከህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈልቅ ስለሆነ

አስተሳሰቡና ድርጊቱ በህብረተሰቡ የ ማቴሪያልና የመንፈስ

ዕድገ ት ሁኔ ታ ሰፋ ባለ ወይም በጠበበ የ ምሁር መሰረት

መልክ መገ ኘት የሚወሰን ነ ው። ማንኛውም አገ ዛዝ

ከጊዜና ከአካባቢ ወይም ከቦታ ውጭ ስለማይታይ

አስተሳሰቡና ድርጊቱ በጊዜና በቦታ የሚወሰኑ ናቸው ማለት

ነ ው። ይህም ማለት በአንድ የ ተወሰነ ወቅት የሚኖረው የ

ምርት ኃይሎች ዕድገ ትና፣ በምርት ኃይሎች ዕድገ ት የ ተነ

ሳ የ ህብረተሰቡ መተሳሰርና ያለመተሳሰር ጉዳይ በስልጣን

ላይ ያለውን ኃይል እንደየሁኔ ታው እንዲያስብ ወይም

እንዳያስብ፣ ጥሩ ስራ እንዲሰራ ወይም ደግሞ ስራው ሁሉ

ተንኮል የ ተሞላበትና ለህብረተሰቡ ደንታ የ ሌለው

እንዲሆን ያስገድደዋል። በዚህ ላይ ለራሱ ለጥቅሙሲል

የሚታገል የነቃ የ ህብረተሰብ ክፍል መኖርና ያለመኖር፣

በአገ ዛዙ ላይ ጫና ማድረግ መቻልና አለመቻል በአንድ የ

ተወሰነ ወቅት ያለን አገ ዛዝ አስተሳሰብም ሆነ ድርጊት

እንደየሁኔ ታው ይወስናል። ከዚህም ባሻገር፣

ህብረተሰብአዊ መተሳሰር እንዲኖር በየ ጊዜው ከሁኔ ታዎች

ጋር የሚጓዙ ኢንስቲቱሽኖች መቋቋምና መሻሻል፣ እንዲሁም

ደግሞ ኢንስቲቱሽኖች በየ ጊዜው የሚከሰቱ የ ህዝብን

ችግሮች መፍታት መቻልና አለመቻል በአንድ አገ ዛዝ

አስተሳሰብ ላይ ተፅ ዕ ኖ ይኖራቸዋል። በሌላ አነ ጋገ ር፣ የ

አንድን ህብረተሰብ የ ማቴርያልና የዕውቀት መሰረት ሳያገ

ናዝቡ ዝም ብሎ በጭፍን የሚሰነ ዘር ውንጀላ አንድን

ህብረተሰብ የዕውነ ተኛው ነፃነት ባለቤት ሊያደርገው

አይችልም። ለምሳሌ በጠባብ አመለካከት የ ተወጠሩ

ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ከመቶና ከሁለት መቶ ዐመታት

በፊት ይገዙ የነ በሩ የ ኢትዮጵያን ነ ገ ስታትን በጭፍኑ

ሲወነ ጅሉ በጥያቄ መልክ የ ማያቀርቧቸውና መልስ

የሰው ልጅ ዕድገ ት በቆየው ግንባታ ላይ አዲስ የመቀጠል

የ ትውልድ ሂደት ነ ው። ይህ በአብዛኛው የሚታየው

ታዲያ በሳይንስና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ነ ው። በማህበራዊ

ህይወትና በኑሮ ልምድ ላይ የ ተቀጣጠለ የመረጃ

መለዋወጥ ባህላችን እምብዛም የጎላ አይደለም።

አብዛኛውን ጊዜ ለአዲሱ ትውልድ እንቅፋት የሚሆነ ው

አሮጌው ትውልድ ላይ ቀድሞ ደርሶበት የነ በረ የ

ህይወትና የኑሮ ሳንካ ነ ው። ለምን ? አላፊው ትውልድ

በህይወት ጉዞ ላይ ሳለ እግረ-መንገ ዱን መጪው ትውልድ

መንገ ዱን እንዲያቃናለት ጥርጊያውን ሊያሳምርለት ይገ

ባል። ጉድባውን ባይደለድል እንኳን አመላካቾችን

በማኖር፣ „እዚህ ዕድሜና ኑሮ ላይ እንዲህ ያለ የ ህይወት

ሳንካ አለ“ ማለት ይገ ባዋል። እኔ በዚች መጽሐፍ

ማከናወን የ ፈለግኩት ይሄንን ተግባር ነ ው።“ * „ፈተና“

ከሚባለው ከወይዘሮ አስቴር ሰይፈ መጽሀፍ የ ተወሰደ

ጥቅስ! መግቢያ አንድ ህዝብ ለነ ፃ ነ ት፣ ለዕኩልነ ትና

ለብልጽግና በሚያደርገው ትግሉ፣ የ ትግሉ መሰካትና

ያለመሳካት ሊወሰን የሚችለው በምሁሩ ንቃተ-ህሊና

ስፋትና ጥንካሬ፣ እንዲሁም ድክመት ነ ው። የ አንድን

ህዝብ ብሶት በደንብ አዳምጦና ተረድቶ፣ እንዲሁም ደግሞ

ተጨባጭ ሁኔ ታዎችን አንብቦ የ ህዝቡን የ ትግል

አቅጣጫ ፈር ለማሲያዝ አንድ ምሁር የሚመራበት የ

ትግል ዘዴ መኖር አለበት። ለትግሉ መሳካትም በሳይንስ የ

ተፈተነ ና ሁኔ ታውን በደንብ ሊተነ ትን የሚያስችል የ

ቲዎሪ መሳሪያ መኖር አለበት። እየ ወደቀ የ ተነ ሳውንና

እዚህ የ ደረሰውን በተለይም የ አውሮፓውን ስልጣኔ ና የ

ካፒታሊዝምን ዕድገ ት ስንመለከት በየ ታሪኩ ወቅት ብቅ

ያሉ፣ በከፍተኛ ዕውቀት የ ተካኑ ፈላስፋዎችና

ሳይንቲስቶች ዕ ልክ የሚያስጨርስ የ ጭንቅላት ስራ

ባይሰሩ ኖሮ፣ የ አውሮፓውም ሆነ ጠቅላላው የዓለም

ማህበረሰብ እዚህ ዐይነ ቱ የ ዕድገ ት ደረጃ ላይ መድረስ

ባልቻለ ነ በር። እንደሚባለው በሳይንስ ላይ ባልተመረኮዘ

ቲዎሪ የ አንድ ህዝብ የነፃነት ጥምና የ ስልጣኔ ፍላጎት

ተግባራዊ ለመሆን ስለማይችል ነ ው። አንድን ሁኔ ታ

በሳይንስ መነ ጽር ለማንበብ መሞከርና፣ እንዲሁም ህዝብ

እንዲገ ነ ዘበው ለማድረግና፣ ከዚያም በመነ ሳት

ትክክለኛውን የ ትግል አቅጣጫ እንዲይዝ ማድረግ

እንደቅንጦት ወይም የ አካዴሚሺያን ቅብጠት ሆኖ መታየ

ት የ ለበትም። እስከዛሬ ድረስ በተለይም የ ሶስተኛው

ዓለም ተብለው በሚጠሩት አገ ሮች ውስጥ የ ተካሄደው

በመሳሪያ የ ታገ ዘ ዕ ልህ አስጨራሽ ውጣ ውረድ የበዛበት

ትግል አመርቂ ውጤት ማምጣት ያልቻለው፣ ለነ ፃነ ት

እንታገ ላለን ብለው መሳሪያ አንግበው የሚነ ሱ

ኃይሎችም ሆነ ፣ ወይም ደግሞ በሰላም መንገድ እንታገ

ላለን የሚሉ ከመጀመሪያውኑ ሳይንሳዊ መርህን

እንደመመሪያ አድርገው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸውና

ባለመፈለጋቸው ነ ው። እንደዚህ ዐይነ ቱ በቲዎሪና

በሳይንስ ላይ ያልተመረኮዘና፣ ከውስጥ በግልጽ ክርክር የ

ማይደረግበት የ ትግል ዘዴ የመጨረሻ መጨረሻ አምባገ ነ

ናዊ ባህርይ ይይዛል። በብዙ የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮችም

ዛሬ የሚታየው የኑሮ መመሰቃቀልና የ ህዝቦች የሰቆቃ ኑሮ

የሚያረጋግጠው ከመጀመሪያውኑ የ ቱን ያህል በቲዎሪና

በሃሳብ ዙሪያ ትግል ያልተካሄደ መሆኑን ነ ው። በሳይንስ

የ ተፈተነ የ ትግል መሳሪያ ቲዎሪ አስፈላጊነ ቱ እንዲያው

አንድን ጨቋኝ አገ ዛዝ ከመጣል አንጻር ብቻ መታየ ት የ

ለበትም። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ጨቋኝ የሚባለው አገ ዛዝ

ለምን እንደዚህ ዐይነ ቱን የ አገ ዛዝ ስልት 1 ለመከተል

እንደተገ ደደ ለመረዳት ሲሆን፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ፣

አገ ዛዙ በዘመኑ የ አዋቀራቸውን የመንግስት አውታሮች፣ የ

ጣለውን ባህልን አፍራሽና ሃሳብን በታኝ የ ሆኑ በተለያዩ

መልክ የሚገለጹ ክስተቶችን በሙሉ ለመመርመርና እነ

ሱን አሰወግዶ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ የመንግስት

አውታር ለመዘርጋትም ነ ው። ምክንያቱም፣ እንደዚህ

ዐይነ ቱ አገ ዛዝ የፖለቲካ ስልጣንን መጨበጥ የ

ህብረተሰብን ችግር መፍቻና ሰላምን የሚያሰፍን አድርጎ

ከመረዳት ይልቅ የ ራሱን ጥቅም ተግባራዊ ማድረጊያ

መሳሪያ አድርጎ ስለሚወስድ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የ

ህዝብን አድማስ የሚያጠቡ፣ በማይረቡ ነ ገ ሮች ላይ

ጭንቅላቱ እንዲጠመድና ርስ በርሱ እየ ተጠላለፈና እየ

ተጣላ እንዲኖር የሚያደርጉ አልባሌ ነ ገ ሮችን

ለመስጠት የ ማይችሏቸው መሰረታዊ ጉዳዮች አሉ።

በማንኛውም ምሁር ነ ኝ ባይ መቅረብ ያለባቸው መሰረተ-

ሃሳቦች አሉ። ከሁለትና ከሶስት መቶ ዐመታት በፊት የ

ኢትዮጵያ ህዝብ በምን ሁኔ ታ ውስጥ ይኖር ነ በር? ራሱን

ለማሽነ ፍ ሲል በምን ተግባሮች ላይ ተሰማርቶ ይኖር ነ

በር? ርስ በርሱስ እንዴት ይገ ናኝ ነ በር? ከገዢው መደብና

ሌላ ከፍ ብለው ከሚታዩ የ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የነ

በረውስ ግኑኝነ ት ምን ይመስል ነ በር? ከተፈጥሮስ ጋር የነ

በረው ግኑኝነ ት እንዴት ነ በር? በተፈጥሮ ውስጥ የሚገኙ

ነ ገ ሮችንስ አውጥቶ ቅርጻቸውን ለውጦ ለመጠቀም

የሚመካባቸው መሳሪያዎችስ ምን ይመስሉ ነ በር? ህዝቡን

ሊያሰተሳስሩ የሚችሉ ልዩ ልዩ ኢንስቲቱሽኖችስ ነ በሩ

ወይ? ካሉስ ምን ይመስሉ ነ በር? በህብረተሰቡ ላይ

የሚኖራቸው አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅ ዕ ኖ ምን

ይመስል ነ በር? እነ ዚህንና ሌሎች አያሌ ጉዳዮችን

የመመርመሩ ጉዳይ በመሰረቱ ቢያንስ ለፖለቲካ ነፃነት እታገ

ላለሁ በሚለው የ ህብረተሰብ ኃይል ትከሻ ላይ፣ በተለይም

ደግሞ በምሁሩ ላይ የ ወደቀ ጉዳይ ነ ው። 2 ያለፈውን

አርባ ዐመት፣ በተለይም ደግሞ የሃያ ዐመቱን ትግል ካለብዙ

ጭንቀት ስመረምር የ ማገ ኘው ሁለት አጭር መልሶች

ናቸው። አንደኛው፣ የ አገ ራችን ምሁር፣ እኔ ንም ጨምሮ

ጥያቄ የመጠየ ቅ ባህል የ ለንም። ሁለተኛ፣ የ ተለያዩ

ህብረተሰቦችን የ ማነ ጻጸር(Comparative Studies)

ልምድ የ ለንም፤ ወይም ደግሞ በዚህ ዐይነ ቱ የ አሰራር

ስልት በመጠቀም የ ህብረተሰባችንን ችግር ለመረዳት

በፍጹም አንጥርም። እንደሚታወቀው በህብረተሰብ ሳይንስ

ውስጥ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የ ሆኑ ህብረተሰቦችን የ

ማነ ጻጸሩ ጉዳይ የ ተለመደ ሳይንሳዊ አሰራር ዘዴ ነ ው።

የለም በዚህ መልክ መስራት አያስፈልገ ንም፣ እኛ የ ራሳችን

አንድን ህብረተሰብ የ ምንመረምርበት መሳሪያ አለን ካልን

ደግሞ እሱን ውጭ አውጥተን መወያየ ትና መከራከር

አለበን። ወይም ደግሞ የለንም ካልንና አያስፈልገ ንም ብለን

ግትር ያለ አቋም የ ምንወስድ ከሆነ ለምን ትምህርት ቤት

እንደሄድንም ግልጽ አይደለም ማለት ነ ው።

እንደሚታወቀው ማንኛውም ልጅ ትምህርት ቤት

የሚላከው እንዲያውቅ፣ አውቆ እንዲመራመርና ትምህርት

ቤት የ ገ ነ ባለትን ህዝብ መልሶ በማስተማር ጤናማ

ህብረተሰብ ለመመስረት ነ ው። በመሰረቱ ትምህርት ቤት

የሚላክና ከአንድ ዕውቀት ጋር የሚጋጭ ካልተማረው ጋር

ሲወዳደር የ ተሻለ ኢንፎርሜሽን ያለውና፣ የ ማመዛዘን

እንዲሁም ደግሞ አንድን ነገር በቀላሉ በመረዳት ጥያቄ

በማንሳት መልስ ለመስጠት የሚችል ነ ው ተብሎ

ይገመታል። ይሁንና ትምህርት ቤት ተልኮ ትምህርቱን ያገ

ባደደ በሙሉ አንድ የ ህብረተሰቡን ችግር ለመመርመር

የሚያስችለውንና፣ ተጨባጭ ሁኔ ታዎችን በቅጡ እንዲረዳ

የሚያደርጉ የመመርመሪያና የመተንተኛ መሳሪያ ቀስሞ

ይወጣል ማለት አይደለም። አንዳንዶች ያለውን ተጨባጭ

ሁኔ ታ እንደተሰጠና(given)፣ መለወጥም እንደሌለበት ተገ

ንዝበው ኑሮአቸውን በዚያው ሲገ ፉበት፣ ሌላው ደግሞ

ፍትሃ ዊ አስተዳደር ካልሰፈነ ና ድህነ ትም ስር የ ሰደደ

ከሆነ ይህ ሁኔ ታ ለምን እንደተፈጠረ በመመራመር

ለለውጥ የሚዘጋጅ አለ። ከዚህ ባሻገር ግን አንድ ተማርኩ

የሚል ግለሰብም ሆነ በቡድን የ ተደራጀ ከአርቆ አሳቢነ ት

ይልቅ እልከኛና ችግር ፈጣሪ የሚሆንበት ሁኔታም አለ።

ስራው ሁሉ ወደ ተንኮልና ህብረተሰብን ማከረባበት ደስ

የሚለውና በዚህ እየ ተዝናና የሚኖር አለ። ይህ ዐይነ ቱ

ኃይል የ ጭንቅላት ችግር ስላለበት ምክንያቱን በቅጡ

ማጥናትና መልስ ለመስጠት መሞከር በተለይም

በጭንቅላት ሳይንስ የ ሰለጠኑ ሰዎች ተግባር ነ ው። ያም

ሆነ ይህ፣ የመማር ትርጉሙ ስልጣኔ ን ከማምጣት ውጭ

መታየ ት የ ሌለበት ጉዳይ ስለሆነ ፣ ትምህርት ገበያ ላይ

ውለው የኋላ ኋላ ስልጣን ሲጨብጡ ችግር ፈጣሪዎች

ከሁኑ ለምን እንደዚህ ዐይነ ት ሁኔ ታ እንደሚከሰት

መመርመር ያስፈልጋል። ከላይኛው አጭር ሀተታ በመነ ሳት

ህብረተሰቦችን የ ማነ ጻጸሩን ጉዳይ ትንሽ ቢሆንም ቆም

ብለን እንመርምር። የ ዛሬይቱ ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት

ቅርጽ ከመዋቀሯ በፊት ከመቶ ወይም ከሁለት መቶ

ዐመታት በፊት ብቅ ያሉ ነ ገ ስታት

ቀጣዩን በገፅ 7 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 6

ርዕዮተ ዓለም ትንታኔ ውስብስቡ የአገራችንና የዓለም ሁኔ ታ፣ እንዲሁም ግራ የ ተጋባው የ ትግል ዘዴያችን ! ፈቃዱ በቀለ

ታዎች በአገ ራችንም ሆነ በሌሎች የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮችም

ተስፋፍተው እንደሚገ ኘ የ ታወቀ ጉዳይ ነ ው። የ እንደዚህ ዐይነ

ት ታሪክን በዕውቀት መነ ፅር ለመመርመር ያለመቻል ሁኔ ታ `ለነ

ፃ ነ ታችን` እንታገ ላለን በሚሉ እንቅስቃሴዎች ብቻ ሳይሆን፣

ራሳቸውም ለኢትየ ጵያ አንድነ ት እንታገ ላለን በሚሉ ኃይሎች

ሲስተጋብ ይሰማል። „በዚያች አገ ር ላይ ብዙ በደል ተፈጽሟል“ ፣

„ከባንዲራው በስተጀርባ ብዙ ደባ ተካሂዷል“ የሚለው በደንብ

ያልተጠናና ግንዛቤ ውስጥ ያልገ ባ አጉል አነ ጋገ ር ራሳችንን

እንዳንጠይቅና በአዲስ መንፈስ ተነ ሳስተን አዲስና የ ተቀደሰ

ተግባር እንዳንሰራ የሚያግደን ነ ው። የ አንድን ህብረተሰብ ታሪክ

አስቸጋሪና ውስብስብ ጉዞ በደንብ ሳይመረምሩ የ ተወሰኑ

ኃይሎችን ለመሸንገል ሲባል የሚሰነ ዘሩ አረፍተ-ነ ገ ሮችም ሆኑ

ፅንሰ-ሃሳቦች ከማንኛውም ምሁራዊ አስተሳሰብ የ ራቁና ሃ ላፊነ ት

የ ጎደላቸው ናቸው። አንድ ህብረተሰብ ዘለዓለሙን እየ ተፋጠጠና

እየ ተፋጨ እንዲኖር የሚያደርጉ ናቸው። ማንኛውም የ ዚህም ሆነ

የ ዚያኛው ብሄረሰብ አካል የ ሆነ ግለሰብ ቁጭ ብሎ እንዲያስብ

የሚያደርጉት አይደሉም። ታሪክን እንዳይሰራና፣ ታሪክ ሊሰራ

የሚችለው በግለሰቦችና በአንድ ህብረተሰብ ጥረት መሆኑን እንዲገ

ነ ዘብ የሚያደርጉት አይደሉም። በአጭሩ ይህንንም ሆነ ያንን

ብሄረሰብ መሸንገል ለማንም አይጠቅምም። ወደ ንዑስ አርዕስቱ

ልምጣና፣ እስከዛሬ ድረስ ጠምዶ የያዘንን አባዜ ለመረዳት የ

እኛንም ሆነ የ ህብረተሰብአችንን አእምሮ ለስለስ የሚያደርግ፣

በሰፊውና በጥልቀት እንድናስብ፣ እንዲሁም ደግሞ ሎጂክንና

ዲያሌክቲክን የ ምርምር መሳሪያ ለማድረግ ከመጀመሪያውኑ

በህብረተሰብአችን ውስጥ ስላልተስፋፉ እየመላለስን ስህተት

እንድንሰራ እንገ ደዳለን። የ ህብረተሰብአችንን ችግር ዲሞክራሲ

በመኖሩና ባለመኖሩ ብቻ ልንረዳው በፍጹም አንችልም።

ምክንያቱም አንድ ሰው ዲሞክራት ከመሆኑ በፊት አእምሮውን

ከማንኛውም ዕቡይ ፀ ባይ፣ ወይንም ኋላ-ቀር ከሆኑ አስተሳሰቦች

ማጽዳት ስላለበትና፣ ህብረተሰብንም ለመገንባት ቆራጥ እርምጃ

መውሰድ ያለበት ጉዳይ ስላለ ነ ው። ከላይ በተዘዋዋሪም ለማሳየ

ት እንደሞከርኩት፣ ከሪናሳንስና ከዚህ ጋር የ ተያያዙ ተጨባጭም

ሆኑ የሚሰሙግን ደግሞ ሊዳሰሱ የ ማይችሉ ነ ገ ሮች

በአውሮፓው ምድር ቀስ በቀስ እያሉ ባይስፋፉ ኖሮ ስለ

ኤንላይተንሜንት ማውራት በፍጹም አይቻልም ነ በር። የ

ኤንላይተንሜንት እንቅስቃሴ ከመኖሩ በፊትና የሰውን ልጅ

አስተሳሰብ በአዲስ መልክ ከማዋቀር በፊት ስለሊበራሊዝም

ማውራት በፍጹም ባልተቻለ ነ በር። ከዚያ በኋላ ልዩ ልዩ የ

ህብረተሰብ ኃይሎች ሲያብቡና እንደ መደብ `ሲደራጁ`

ኢንስቲቱሽናዊ የጥገ ና-ለውጥ እንዲኖር በፍጹም የ ሞናርኪ አገ

ዛዝ ላይ ግፊት ሲያደርጉ ይህንን መቋቋም ያልቻለው የ ነ ገ ስታት

አገ ዛዝ ሳይወድ በግድ ለአዳዲስ የ ህብረተሰብ ኃይሎች ቦታውን

እንዲለቅ ተገ ደደ። በዚህ ብቻ አላበቃም። የ ምዕ ራብ አውሮፓ

አገ ሮች በህብረ-ብሄር ከተዋቀሩና የ ኢንዱስትሪ አብዮት ማካሄድ

ሲጀምሩ ይህ በራሱ አዳዲስ ተቃዋሚ ኃይሎችን ማፍራት ጀመረ።

በኢንዱስትሪ አብዮት የ ተነ ሳ ከተማዎች በህዝብ ብዛት ጥቅጥቅ

ማለት ሲጀምሩ፣ ይህ ሁኔ ታ የሶሻል ጥያቄዎችን አስነ ሳ። በአንድ

በኩል የድሮውን ስርዓት የሚናፍቁ፣ ዕድገ ት ሲባል ተፈጥሮን

የሚቀናቀን መሆን እንደሌለበት የሚያመለክቱ፣ በሌላ ወገ ን ደግሞ

ከመሬት ተፈናቅሎ ወደ ኢንዱስትሪ ሰራተኛነ ት የ ተለወጠውና

ከማሽን ጋር መታገ ል የ ጀመረው ጥያቄዎችን ማንሳት ጀመሩ።

አዲሱ የ ከበርቴ መደብ በቀላሉ ዝም ብሎ በፋብሪካው ውስጥ

ተቀጥሮ የሚሰራውን ወዝአደር መበዝበዝ እንደማይችል ትግል

ጀመሩ።በዚህ መልክ እየ ተስፋፋና ስር እየ ሰደደ የመጣው ትግል

ይበልጥ የ ምሁራዊነ ት ባህርይ በመያዝ ህብረተሰብ በሌላ

መልክም መደራጀት እንዳለበት አመለከቱ። በአጭሩ በዚህ መልክ

ነ ው በአውሮፓው ማህብረሰብ ውስጥ ችግሮች ብቅ ሲሉ እነ ሱን

ሳይሸሹ በመመርመርና አማራጭ በማቅረብ አገ ርን መገንባት የ

ተያያዘው። ይህ ዐይነ ቱ ህብረተሰብአዊ እንቅስቃሴ ከሁለት መቶ

ዐመታት በኋላም በሌላ መልኩ ተከስቷል። ከሰላሳ ዐመታት በላይ

ጀምሮ በብዙ አንዳንድ የ አውሮፓ አገ ሮች በሌላ 4 መልክ እየ

ተደገመ ነ ው። የግሪን/አረንጓዴው/ ፓርቲ እንቅስቃሴ ከሰላሳ

ዐመት በፊት የ ማይታሰበውን ያህል ዛሬ ራሱን የ ቻለ ኃይል ሆኖ

ተደላድሎ ይገ ኛል። በህብረተሰብ ውስጥም ስር የ ሰደደ ነ ው።

ዛሬ ደግሞ የ ፒራተሪ ፓርቲ በየ ቦታው ብቅ በማለትና

በመደራጀት ወደፊት ሊታለፍ የ ማይችል ኃይል እየ ሆነ

በመምጣት ላይ ነ ው። ይህ ሁሉ በትግል የሚገ ኝ ነ ው።

ምንግዜም የ ጭንቅላትን ስራ በማስቀደም ነ ው። ምንጊዜም ቢሆን

ከአመፅ ይልቅ ህብረተሰብአዊ ችግሮችን ለመፍታት ዕውቀትን

ማስቀደምና እንደህብረተሰብአዊ ኃይል ሆኖ ለመውጣት በብቃት

በመደራጀት ነ ው። በራስ ላይ ከፍተኛ ዕምነ ትን በማሳደር ነ ው።

ዲሞክራሲ ከላይ ወደታች በአንድ የገዢ ኃይል የ ተወረወረበት የ

ታሪክ ወቅት አልነ በረም። ሀቀኛ ዲሞክራሲ በአመጽ የሚገ ኝ

ሳይሆን በከፍተኛ ምሁራዊ እንቅስቃሴ በመታገዝና ግፊት

በማድረግ ብቻ ነ ው። እዚህ ላይ የ ተለያዩ የዲሞክራሲ ዐይነ

ቶችን ሳናገ ናዝብ ማለት ነ ው። ያም ሆነ ይህ አፄ ኃይለስላሴ

ስልጣን እስከያዙ ድረስ የነ በረውን የ አገ ራችንን ሁኔ ታ

ስንመረምር - የ አፄ ምኒ ልክን የዘመናዊነ ት ፖሊሲ ወደ ጎን

በመተተው- እስከዚያን ጊዜ ዘመን ድረስ የ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ

በአማዛኙ አስተሳሰቡን ወጥረው በያዙ በግብርና ኢኮኖሚና፣

በርዕዮተ-ዓለም ደረጃ ደግሞ በክርስትናና በእስላም ሃ ይማኖት

ይተዳደር ነ በር። በፊዩዳሉ ኢኮኖሚ በአንድ በኩል፣ በሌላ ወገ ን

ደግሞ እዚህና እዚያ ተሰበጣጥረው በሚገኙ ሌሎች ምርታዊ

ትንታኔ ... ከገፅ 6 የዞረ

እንደየሁኔ ታው ግዛታቸውን ለማስፋፋትና ሌላውን ህዝብ ገባር ለማድረግ በአብዛኛው ይጠቀሙ የነ በረው ኃይልን ነ በር። ሃ ይማኖትንም ለማስፋፋት እንደዚሁ ኃይል ወሳኝ ሚናን ተጫውቷል። በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ በአነ ሳሱ አንድ ቦታ ላይ ረግቶ የ ኖረ አገ ዛዝ በፍጹም አለነ በረም። አገ ዛዞች ውስጣዊ-ኃይል ሊያገኙ፣ ሊስፋፉና ሊያድጉ የሚችሉት

ከሌሎች ክልሎች ጋር በኃይልም ሆነ በንግድ ወይም ደግሞ

በጋብቻ አማካይነ ት የ ተጠቃለሉ እንደሆን ብቻ ነ ው። እንደዚህ

ዐይነ ቱ አገ ዛዝን የ ማስፋፋትና የ ማጠናከር ጉዳይ በተለይም

በሮማውያን አገ ዛዝ ዘመን የነ በረና፣ በኋላ ደግሞ ከአስረኛው

ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ፊዩዳሊዝም ብቅ ሲልና ሲስፋፋ በአውሮፓ

ቀሳውስትና ነ ገ ስታት ዘንድ የ ተለመደ ነ በር። በተለይም የ

አውሮፓ ሞናርኪዎች ሃ ይማኖትን ለማስፋፋት ሲሉ

አልቀበላቸውም ያለውን ሁሉ እስከመስቀልና ቋንጃ እስከመቁረጥ

የ ደረሱበት ጊዜ እንደነ በር በታሪክ ማህደር ተመዝግቦ ይገ ኛል።

እንደዚሁም ገ በሬውን በጉልበት ማስገ በርና፣ ከባላባቱ ፈቃድ

ሳያገኝ እንዳያገ ባና ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ

በአውሮፓ ውስጥ የለመደ የ አገ ዛዝ ዘዴ ነ በር። ከሌሎች

አህጉሮች ይልቅ ህብርተሰብአዊ ግጭቶችና ጦርነ ቶች በብዛት የ

ተካሄደው በአውሮፓ ምድር ነ ው። እንደሚባለውና እንደሰማነ

ው ሳይሆን አውሮፓ በደምና በአጥንት የ ተገ ነ ባ አህጉር ነ ው።

በነ ጻ ገበያ አማካይነ ት እንዲያው በስምምነ ት ላይ የ

ተመሰረተና እዚህ የ ደረሰ አይደለም። በዚያውም መጠንም እንደ

አውሮፓው አህጉር ከፍተኛ ምሁራዊ እንቅስቃሴ የ ተካሄደበት፣

የ ሳይንስ ግኝቶች የ ተፈጠረበትና በኋላም በንግድ መስፋፋትና

በዕደ-ጥበብ ማበብ የ ከበርቴው መደብ ብቅ ያለበት ሌላ አህጉር

በፍጹም የ ለም። ይሁንና ብዙ ዕውቀት ተስፋፍቶም በጦርነ ት የ

ዘፈቀና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ የ ተገ ደለበትና የ

ተሰቃየ በት እንደ አውሮፓ አህጉር የመሰለ፣ ሌላ አህጉር በፍጹም

የለም ማለት ይቻላል። የ ኢትዮጵያን የ ህብረተሰብ ታሪክ

በአጭሩ ከላይ ከተዘረዘረው የ አውሮፓው የ ህብረተሰብ አገ ነ

ባብ ሁኔ ታ ጋር ስናወዳድረው ውሰጥ-ኃይሉ በጣም ደካማ ሆኖ

እናገ ኘዋለን። ይህም የ ሆነ በት ምክንያት ምናልባትም የ

ኢትዮጵያ ህብረተሰብ በጣም ተሰበጣጥሮ የነ በረና እንደ

ህብረተሰብ ለመገ ንባትና አንዱ ከሌላኛው ጋር ተፎካካሪ ለመኖር

ብዙ መጓዝ ይኖርበት ስለነ በር ይሆናል። በተጨማሪም የ ፊዩዳሉ

ስርዓት እንደ አውሮፓው ውስጠ-ኃይል ለማግኘት ከውጭ

የሚመጣ አዲስ አስተሳሰብና የ አኗኗር ስልት ዕድል

አላጋጠመውም። በመሆኑም እንደ አውሮፓው የ ፊዩዳል አገ ዛዝ

የ ትላልቅ ቤተክርስቲያናትና የመኖሪያ ቤቶች የመገንባት ዕድል

አላጋጠመውም። የ ህዝቡን አትኩሮና ተሰባስቦ እንዲኖር

የሚያደርጉት የመንደር አቆራቆሮች በኢትዮጵያ የ ፊዩዳል ስርዓት

የ ተለመደ አልነ በረም። በተጨማሪም የ ኢትዮጵያው የግዛት

አመሰራረትና መንግስታትን ወደ ታሪካዊ ስራ እንዲያዘ ነ ብሉ

ለማድረግ የ ነ በረው ምሁራዊ እንቅስቃሴ ከአውሮፓው ጋር

ሲወዳደር ምንም አልነ በረም ወይም እጅግ በዝቅተኛ ደረጃ የሚገ

ኝ ነ በር ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ይቻላል። ለዚህ ደግሞ የ

ክርስትና ሃ ይማኖት የ በላይነ ትን ይዞ መቆየ ትና፣ ይህ ርዕዮተ-

ዓለም ከፍልስፍና ጋር ለመጋጨት አለመቻልና አለመታደስ የ አገ

ዛዙንም ሆነ የ ህዝቡን አስተሳሰብ ቆልፎ ሊዝይና፣ ወደ ውስጥ

ለውጥ 3 እንዳይመጣ አግዷል ማለት ይቻላል። ስለሆነ ም

በአማዛኙ፣ የ ኢትዮጵያ አገ ዛዝ ታሪክ በዕደ-ጥበብ ማበብና

መስፋፋት፣ በውስጥ ንግድ መዳበር፣ በገንዘብ ልውውጥ

አማካይነ ት ህዝባዊ መተሳሰር መኖርና፣ በመንደሮችና

በከተማዎች ቁርቆራ በፍጹም ሊታማ የሚችል አይደለም።

እንደዚሁም ኤስቴቲክስና ህዝቡን ከተፈጥሮ ጋር የሚያገ ናኙትና

ተፈጥሮን እየ ቃኘ ራሱም ፈጣሪም እንዲሆን የሚያስችሉት

ዕውቀቶች ሊዘረጉ አልቻሉም። በዚህም ምክንያት በተለያዩ የ

ታሪክ ወቅት ብቅ ያሉ አገ ዛዞችም ሆነ ህዝቡ ችግርን ለመፍታትና

መረጋጋትን ለመፍጠር ኃይልን ቢያስቀድሙበፍጹም የሚያስደንቅ

አይደለም። የ አስተሳሰብ አድማሳቸውም ውስን ስለነ በር

በጉልበት የሚይዙትን ግዛቶች በምን መልክ ማዋቀር

እንዳለባቸውና፣ ቤተሰብአዊና ህብረተሰብአዊ አገ ነ ባቦች አንድ

ላይ ተያይዘው መሄድ እንዳለባቸው በቅደም ተከተል መወሰድ

ያለባቸውን እርምጃዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሏቸው የ

ቲዎሪ መሳሪያዎች አልነ በራቸውም። በሌላ አነ ጋገ ር፣ በየ ታሪክ

ወቅት የ ተነ ሱት ነ ገ ስታት በህዝብ ላይ ጉዳቶች ቢያደርሱም

ሆን ብለውና አውቀው ያደረጉት ጉዳይ አልነ በረም። ማንኛውም

አገ ዛዝም ሆነ ግለሰብ ራሱን እስኪያገ ኝ ድረስና፣ የሚሰራውን

ስራ ሁሉ ለማመዛዘንና ወደፊትም ስህተት እንዳይሰራ ብዙ ውጣ

ውረዶችን ማለፍ አለበት። ማህበረሰብአዊና ህብረተሰብአዊ

ባህርይ ለማግኘት እያንዳንዱ አገ ዛዝም ሆነ ግለሰብ ጭንቅላቱ

በተሻሉና በአዳዲስ ዕውቀቶች መታደስ አለበት። በዚህ መልክ የ

ህብረተሰብን አገ ነ ባብ ችግርና ውጣ ውረድ ሳያገ ናዝቡ የ

ዛሪይቱ ኢትዮጵያ በአመጽ ብቻ ነ ው ልትያያዝና እዚህ ደረጃ ላይ

ለመድረስ የ ቻለችው ብሎ ድርቅ ማለትና፣ በዚህ ዐይነ ቱ

አመለካከት ብዙ ሁኔ ታዎችን ያላገናዘበ አጻጻፍም ሆነ አነ ጋገ ር

መሰንዘር አብሮ ለመስራትም ሆነ ወደፊት አገ ርን ለመገ ንባት

ከመጀመሪያውኑ እንቅፋት ይሆናል። በኛ አገ ር ብቻ ሳይሆን፣ በየ

ጊዜው መታደስ ካለበት ዕውቀት አለመኖር የ ተነ ሳ ህብረተሰብን

የሚያመሰቃቅሉ፣ አንድ ህዝብ ዘላለሙን እየ ከነ ፈ እንዲሄድ

የሚያደርጉና፣ ህብረተሰብንም ሆነ ተፈጥሮን የሚያናጉ ሁኔ

ክንውኖችና በከብት እርባታ መሀከል የ ተቆላለፈ ግኑኝነ ት የ ተነ

ሳ የ ምርት ሃ ይሎች ሊያድጉ አልቻሉም። በዚህ ላይ የ ክርስትና ሃ

ይማኖት ከሌሎች ሃ ይማኖት ነ ክ ካልሆኑ አምልኮቶች ጋር

በመቆላለፍ የ ህዝባችንን የ ማሰብ ኃይል ይወስን ነ በር። ይህም

ማለት በእንደዚህ ዐይነ ት የኑሮ ሁኔ ታ ውስጥ የሚገ ኝ

ህብረተሰብ ከውስጥ የ አእምሮ ተሀድሶ ካላደረገ ና፣ የ አሰራርና የ

አኗኗር ዘዴውን እንዲለውጥ የሚያስችሉትን የ ቴክኖሎጂ መሻሻል

እስካላደረገ ድረስ ኑሮው ተደጋጋሚና አሰልቺ ከመሆን አልፎ

በቀላሉ ለማንኛውም አደጋ የሚጋለጥ ይሆናል። በተለያየ ጊዜያት

ባወጣሁት ጽሁፍ እንዳመለከትኩት በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በተለይም

በአስትሮኖሚ ግኝት አማካይነ ት ነ ው በአውሮፓ ምድር የ

ካቶሊክ ሃ ይማኖት የ በላይነ ቱን ሊነ ጠቅ የ ቻለው። በአገ ራችን

ግን ይህ ዐይነ ቱ ምርምርና መጋፈጥ ባለመኖሩ ነ ው ነ ገ ሮች ሁሉ

በሃ ይማኖትና በፊዩዳላዊ መነ ጽር አመለካከት መታየ ት የ

ቻሉት። ትላንትም ዛሬ አስተሳሰባችን፣ አጻጻፋችንና ነ ገ ሮችን መገ

ምገ ም፣ እንዲሁም አንድ ሰው ለየት ያለ አስተሳሰብ ይዞ ሲወጣ

ሽምቅቅ ማለት የሚያረጋግጠው የ ቱን ያህል ነ ገ ሮችን በድሮው

ዐይነ ት እንደምንመለከት፣ እንደምናስብና እንደምንረዳ ነ ው። በተጨማሪም ይህ የሚያረጋግጠው የ ቱን ያህል የባህል ተሃድሶ

እንዳላደረግንና ለማድረግም ዝግጁ እንዳልሆን ነ ው። ዘመናዊነ ት

(Modernization) ያመጣው ጠንቅ ! በመጀመሪያ ደረጃ

በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ጸሀፊዎች ዘመናዊነ ት የሚለው ጽንሰ-

ሃሳብ በተሳሳተ መልክ ይቀርባል። በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ

ለውጥና(Transformation) ዘመናዊነ ት የነ በሩ ነ በሩ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ተራማጅ ወይም የ ህብረተሰብን ለውጥ አርማ

ይዘው የ ተነ ሱ የግሪኩ ሶፊስቶች(Sophists) ናቸው። በሁለተኛ

ጊዜ፣ ከፍተኛ ህብረተሰብአዊ ለውጥና ዘመናዊነ ት በሬናሳንስ

አማካይነ ት ነ ው ሊገ ኝ የ ቻለው። ከዚህ ስንነ ሳ ዘመናዊነ ትና

ህብረተሰብአዊ ለውጦች፣ -ህብረተሰቦች በዚያው ረግተው ይቁሙ

ካልተባሉ በስተቀር- የ ታሪክ ግዴታና አስፈላጊም ናቸው።

አስፈላጊነ ታቸውም፣ አንድም፣ የሰው ልጅ የ ማሰብ ኃይል

ስላለውና ለውጥን ሰለሚፈልግ፣ ሌላም በለውጥ አማካይነ ት ብቻ

በቁጥር እያደገ ና እየጨመረ የሚመጣውን ህዝብና ፍላጎቱን

ማሰተናገድና ማሟላት ስላለበት ነ ው። በጥንታዊ ባህላዊ ኖርሞች

የ ተጠመደ ህብረተሰብ አዳዲስ ችግሮች ሲፈጠሩ ጥያቄ

ለማንሳትና መልስ ለመስጠት ይቸግረዋል። ስለዚህም አንዳንድ

የነቁ ግለሰቦች ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ደጋግሞ በመጠየ ቅ

ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ ይጠቁማሉ። ከተለያዩ ምሁሮች የ

ተለያዩ አስተሰሳቦች በመፍለቅ ምሁራዊ ትግል ይደረጋል። ቀስ

በቀስም እንደ ኃይሎች አሰላለፍ አንደኛው አስተሳሰብ በማሸነ ፍ

የለውጡ መንገድ ይዘጋጃል ማለት ነ ው። በዚህም ምክንያት

በአውሮፓ ምድር ውስጥ ከአስተሮኖሚና ከሌሎች ሳይንሳዊ

ግኝቶች፣ የ ፍልስፋና ምርምር መስፋፋት፣ የ ግጥምና የ ሊትሬቸር

ማበብ፣ እንዲሁም የ ክላሲካል ሙዚቃና በተወሰነ የጂኦሜትሪ

ቅርጽ የ ቤት አሰራርንና ልዩ ልዩ የመናፈሻ ቦታዎችን መስራትና

ህዝብን በአንድ የ ተወሰነ ና ስርዓት ባለው መልክ እንዲሰበሰብ

ማድረግ ልዩ ዐይነ ት ዘመናዊነ ት ነ ው። አንድ ህብረተሰብ

ካለሳይንስና ካለቴክኖሎጂ አብዮትና እንዲሁም ጭንቅላትን

በሚያድስ ዕውቀት ለውጥ ካላመጣ ወደ መተረማመስና ወደ

መከረባበት ያመራል። ስራው ሁሉ ጦርነ ት ይሆናል። ስርዓት

ያለው ኑሮ ለመገንባት በፍጹም አይችልም። በውጭ ኃይሎች

በቀላሉ ይጠቃል። ስለዚህም ስለዘመናዊነ ትና ስለህብረተሰብአዊ

ለውጥ በምናውራበት ጊዜ ነ ገ ሩን ሰፋ አድርገ ን መመልከት

ይኖርብናል። ከ1940ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ በተለይም በአሜሪካን

ሶስዮሎጂስቶችና ኢኮኖሚስቶች ለሶስተኛው ዓለም አገ ሮች ተብሎ

የ ተዋቀረውን የ ሞደርናይዜሽን ፕሮግራም ጠጋ ብለን ስንመለከት

ግን የ የ አገ ሮችን ልዩ ልዩ ልምዶችና የ አኗኗር ስልቶች

በማጥናትና ከዚያ በመነ ሳት የ ተነ ደፈ ፕሮግራም ሳይሆን፣

በተለይም የ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝምን ተፅ ዕ ኖ ከማስፋፋት

ጋር የ ተያያዘ፣ ሁለ-ገብ ሳይሆን የ ተወሰነ ህብረተሰብን ክፍል

ለመጥቀምና፣ በዚያ አማካይነ ት ስር- ነ ቀል ዕድገ ት እንዳይኖር የ

ታቀደ ልዩ ሴራ ነ ው ማለት ይቻላል። ይህ በተወሰኑ የ አሜሪካን

ሶስዮሎጂስቶች የዳበረው አስተሳሰብ በመሰረቱ ኤምፔሪሲዝም

በሚባለው በቀጥታ በሚታዩ ነ ገ ሮች ላይ የ ተመሰረተ አስተሳሰብ

ሲሆን፣ ከዚያ 5 ተሻግሮ በመሄድ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ የ

ሰፈነ ውን የ ኃይል አሰላለፍ፣ የፖለቲካና የመንግስት አወቃቀር፣ የ

ምርት ኃይሎች ዕድገ ትንና የ ምርት ግኑኝነ ትን ሁኔ ታና፣ እነ ዚህ

ነ ገ ሮች አንድ ላይ በመያያዝና በመጣመር በአጠቃላይ

ህብረተሰብአዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገ ት ላይ ስለሚኖራቸው

አሉታዊ ተፅ ዕ ኖ ወደ ውስጥ በመግባት አይመረምርም። የ አንድን

ህብረተሰብ አወቃቀር በዘመናዊነ ትና በኋላቀርነ ት በመክፈልና፣

ከዚህ በመነ ሳት ያለውን የ ኢኮኖሚ ዕድገ ት ችግር በልዩ የ ምዕ

ራቡ የ ፍጆታ አጠቃቀምና የ ተወሰነ አሰራር ስልት ለመቅረፍ

እንደሚቻል ያመለክታል። እነ ዚህ ሶስይሎጂስቶች ይህንን

አመለካከት በብዙ የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮች ሲያስፋፉና

ተቀባይነ ት እንዲኖረው ሲያደርጉ፣ በቲዎሪያቸው ውስጥ

ያላከተቷቸው ለዕውነ ተኛ ነ ጻነ ት ጠቃሚና ለኢኮኖሚ ዕድገ ት

የሚሆኑ ሌሎች ብዙ መሰረተ-ሃሳቦችና ልምዶችን ከቁጥር ውስጥ

አላስገ ቡም። በመጀመሪያ ደረጃ፣ በእነ ሶክራተስና ፕላቶ

የዳበረውን፣ ዕውቀት ሊፈልቅ የሚችለው ከሚታዩ ነ ገ ሮች

ሳይሆን በማሰብ ኃይልና ከተጨባጭ ሁኔ ታዎች ርቆ በመሄድ ነ

ው የሚለውን ከቁጥር ውስጥ አላስገ ቡም።

ቀጣዩን በገፅ 8 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 7

ህዝቦች መሞትና መሰቃየ ት እንዲሁም መሰደድ ምክንያት ሊሆኑ

በቅተዋል። በተጨማሪም የመንግስት መኪናውና ቢሮክራሲው

ለውጭ ሰላዮች ክፍት በመሆን አንድ አገ ዛዝ ማድረግ ያለበትን

ህብረተሰብአዊና የ አገ ር ግንባታ ተግባር እንዳያካሂዱ ታግደዋል።

በዚህም ምክንያት በተለይም አብዛኛዎቹ የ አፍሪካ መንግስታት የ

ዚኽኛው ወይም የ ዚያኛው የውጭ ኃይል ተቀጥያ በመሆንና፣

በሚያስፈልግበትም ጊዜ የመንግስት ግልበጣ የሚካሄድባቸው

መድረኮች በመሆን የ ታሪክ ግዴታቸውን እንዳይወጡ ተደርገ

ዋል። መረጋጋት የ ማይታይባቸውና፣ እንዲያውም ለታዳጊ

ትውልድ መጥፎ ምሳሌ በመሆን የ አገ ርንና የ ህብረተሰብን

ትርጉም በማበላሸት የሰው ልጅ ማድረግ ያለበትን ታሪካዊ ስራ

እንዳይሰራ በቀጥታ እንቅፋት ሆነ ዋል። በሳይንስና በቴክኖሎጂ

ላይ የ ተመሰረተ ሰፊ ገበያና ሰፋ ያለ ህብረተሰብአዊና ባህላዊ

እንቅስቃሴ እንዳይካሄድና እንዳይዳብር መሰናክል ሆነ ዋል። ይህ

ዐይነ ቱ አሰራር እንደተፈጥሮ ህግ ተደርጎ በመወሰዱ የ አገ ዛዝ

ለውጥ በሚደረግበት ጊዜ ሁኔ ታው በድሮው መልክ ይቀጥላል።

በተጨማሪም ስለመንግስት ምንነ ትና ሚና በቲዎሪ ደረጃ እንደ

አውሮፓው ምሁራን በሰፊው ውይይትና ክርክር ስለማይካሄድ

ስለመንግስት የሚኖር ግንዛቤ ተዳፍኖ እንዲቀር ይደረጋል።

በተለይም ከውጭ በሚናፈስ የ ተሳሳተና ከሳይንስ ጋር የ

ማይጣጣም ጥራዝ ነ ጠቅ አባባል በመወናበድና መንግስትን እንደ

አምላክ በመቁጠር፣ አባዛኛዎች ምሁራን ስለመንግስት ምንነ ት

እንዳይጠይቁ ታግደዋል። የ አውሮፓን ምሁራንን ከኛ ጋር ሲነ ፃ ፀ

ሩ የሚለያቸው፣ ስለመንግስትም ሆነ ስለግለሰብ ሚና፣ እንዲሁም

ስለህብረተሰብ ዕድገ ት ያላቸው ግንዛቤ በጣም ይለያል። ይህንን

ለመረዳት አሁንም በአናሎጊ እንመልከት። በአውሮፓ ምድር

ውስጥ የመንግስት ሚና በብዙ መልክ ተገ ልጿል። ከእነ ሶክራተስ/

ፕላቶንና እስከሬናሳንስ ድረስ የነ በረው የመንግስት ግንዛቤ፣

መንግስት የ አንድን የ ህብረተሰብ ኃይል ጥቅም ብቻ አስጣባቂ

ሳይሆን የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍል ጥቅም አስጠባቂ መሆን

አለበት የሚል ነ በር። በፕላቶን ዕምነ ት ፖለቲካና ስነ -ምግባር

በአንድነ ት በመጣመር ለአንድ አገ ዛዝ የ ህዝብን ርዕይ ተግባራዊ

እንዲያደርግ በር ይከፍቱለታል። ስለሆነ ም በዚህ የ አስተሳሰብ

ክልል ውስጥ ያልተደራጀ የመንግስት መኪናና አገ ዛዝ አድልዎን

የሚያስፋፋና ቀስ በቀስም ወደ ዘራፊነ ት የሚያመራ ይሆናል። ይህ

ከሆነ ደግሞ የ ህብረተሰብ ኖርም በመናጋት አንድ ህዝብ ስርዓትና

ጥበብ ያለው ኑሮ ሊገ ነ ባና፣ በሰላምና በመከባበር ሊኖር

አይችልም። የ ጀርመንን ክላሲኮችም ይህንን መሰረት በማድረግ

ጥበባዊ መንግስት በምን መልክ መዋቀር እንዳለበትና ተግባሩስ

ምን መሆን እንዳለበት በሰፊው ጽፈዋል። ካፒታሊዝም በአሸናፊነ

ት ከወጣ ከ18ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ግን የመንግስት ሚናና

ትርጉም እነ ፕላቶን በፈለጉትና ትክክል ነ ው ባሉት መስመር

ሊዋቀር አልቻለም። በተለይም የሊበራሊዝም አስተሳሰብ ሲስፋፋ

የ እነ ፕላቶንና የ ሌሎች ክላሲኮች የመንግስት ቲዎሪ እየ ተገ ፈተረ

በአዲሱ የ ኃይል አሰላለፍ ፍላጎት ሊዋቀር ቻለ። ይሁንና ግን

በሊበራሎች ዕምነ ት መንግስት የ አንድን ህብረተሰብ ክፍል ብቻ

ጥቅም አስጠባቂ ሳይሆን እንደሪፌሪ ነ ው። መንግስት የህግ የ

በላይነ ት እንዲከብር የሚያደርግ እንጂ አድልዎ የሚያደርግ

አይደለም ይሉናል። በሊበራሎች ዕምነ ት እያንዳንዱ አገ ር እንደ

ህብረተሰብ የሚታይ አይደለም። አንድ አገ ር ግለሰቦች የ የ

ራሳቸውን ጥቅም፣ ካፒታሊስቱ ትርፍን፣ ሰራተኛው ደግሞ ገቢውን

ከፍ ለማድረግ የሚታገ ሉበት መድረክ ነ ው። የ እያንዳንዱ

ግለሰብ አርቆ አስተዋይነ ት በራሱ የጥቅም ዙሪያ ብቻ

የሚሽከረከር እንጂ ከጠቅላላው የ ህብረተሰብ ጥቅም ጋር

የሚያያዝ አይደለም። በመሆኑም የሰው ልጅ ማህበራዊና

ህብረተሰብአዊ አይደለም የሚል አደገ ኛ አመለካከት ያስፋፋሉ።

ይህ አመለካከታቸው ተጨባጩን የ ህብረተሰብ ዕድገ ት ታሪክ፣

በተለይም ደግሞ የ ካፒታሊስትን ህብረተሰብ ተጨባጭ ሁኔ ታ

ይጻረራል። መንግስትም ሪፌሪ ሳይሆን የ ካፒታሊዝምን ዕድገ ትና

መስፋፋት እንዲሁም የ ቴክኖሎጂ ምጥቀትን በቀጥታም ሆነ

በተዘዋዋሪ የሚደግፍና የሚያግዝ ነ ው። ስለሆነ ም እንደየሁኔ

ታው በተለያየ መልክ የሚገለጸውን የ ከበርቴ መደብ በመደገ ፍና

በመደጎም በአሸናፊነ ት እንዲወጣና በዓለም ገ በያ ላይም ተወዳዳሪ

እንዲሆን የሚያደርግ ነ ው። በተጨማሪም የውስጥ ገበያ

እንዲስፋፋ የ ከተማዎችን ዕድገ ት በማፋጠንና በልዩ ልዩ የመገናኛ

ዘዴዎች እንዲተሳሰሩ በማድረግ የ ካፒታልንና የ ሌሎች ሀብቶችን

ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በፍጥነ ት እንዲሽከረከሩ ያግዛል። በሌላ

አነ ጋገ ር የመንግስት ፖሊሲዎች በሙሉ ከቴክኖሎጂው ፍጥነ ት

ጋር የሚጓዙ ብቻ ሳይሆኑ፣ መንግስት ራሱ በሁሉም አቅጣጫዎች

ንቁ ፖሊሲዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለአጠቃላይ ህብረተሰብአዊ

ሀብት መፈጠር ዐይነ ተኛ መሳሪያ ሊሆን ችሏል። በሌላ ወገ ን ግን

በየ ጊዜው ብቅ በሚሉ አዳዲስ የ ነ ቁና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነ ት

በሚሰማቸው ኃይሎች የ ተነ ሳ የ ካፒታሊስት መንግስት የ አንድን

ህብረተሰብ ክፍል ጥቅም ብቻ አስጠባቂ እንዳይሆን

የሚታገድበትም ጊዜ አለ። ስለዚህም የ ተቀረውም የ ህብረተሰብ

ክፍል ተጠቃሚ እንዲሆንና ህብረተሰብአዊ ሚዛን እንዳይናጋ

በማሰብ በልዩ ልዩ የ ኢኮኖሚ መሳሪያዎች የሶሻል መስክንና የ

ባህልን እንቅሳቃሴ ይደጉማል። በዚህ መልክ ገንዘብ በኢኮኖሚው

ውስጥ እንዲገ ባ በማድረግ የ ዕቃዎችንና የ አገ ልግሎትን በፍጥነ

ት መሽከርከር በተዘዋዋሪ ያግዛል ማለት ነ ው። ይህ ዐይነ ቱ

ድጎማና በሶሻል መስክ ውስጥ መሳተፍ እንደ ኃይል አሰላለፉ

ተለዋዋጭ ነ ው። በአጠቃላይ ሲታይ ግን የመንግስት በልዩ ልዩ የ

ኢኮኖሚ ዘርፎችና በባህል እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ

ትንታኔ ከገፅ 8 የቀጠለ

ከዚህ ጋር ተያይዞ፣ የ ተሳሳተ አመለካከትና በተሳሳተ አመለካከት

ላይ የ ተገ ነ ባ አስተዳደር ሊያስከትል የሚችለውን ዕኩልነ ትን

የሚጻረርና የ የ ግለሰቦችን ዕውነ ተኛ ነፃነት የሚገ ፍና ለገዢዎች

የሚያመችን ትምህርትና ርዕዮተ-ዓለም አልመረመሩም።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ብዙ የ ምዕራብ አውሮፓ አገ ሮች እንደ ህብረ-

ብሄር መንግስታት ባለተዋቀሩበትና፣ አገ ሮች በክልል

ባልተወሰኑበት በጨለማው ዘመን ይገኙ የ ነ በሩበትን ሁኔ ታና፣

ከዚያ ለመውጣት ሲሉ የ ግዴታ በሬናሳንስ አማካይነ ት

መውሰድ የ ተገ ደዱትን ሁለ-ገብ የግንባታ ስትራቴጂ በፍጹም

አላጤኑም። በሶስተኛ ደረጃ፣ አንዳንድ የ አውሮፓ መንግስታት

እንደ ህብረ-ብሄር ከተቋቋሙከ16ኛው ክፍለ- ዘመን ጀምሮ

ተግባራዊ ያደረጉትን የመርካንትሊስት ሁለ-ገብ የ ማኑፋክቱር፣ የ

ከተማዎችና የ ካናል ሲይስተም ግንባታዎችን በፍጹም አላገ

ናዘቡም። በአራተኛ ደረጃ፣ ሌሎችን ነ ገ ሮች ሁሉ ትተን፣ ብዙ የ

ምዕራብ አውሮፓ መንግስታት በሁለተኛው ዓለም ጦርነ ት የ ተነ

ሳ ኢኮኖሚያቸው ከተከሰከሰ በኋላ እንደገ ና መልሰው

ለመገንባት የ ወሰዱትን በመንግስት የ ተቀነ ባበረና የ ተደገ ፈ

ሁለ-ገብ የ ኢኮኖሚ ፖሊሲና ልምድ ዘመናዊ ብለው ከሚጠሩት

ለሶስተኛው ዓለም በተዘጋጀው ቲዎሪያቸው ውስጥ በፍጹም

አላካተቱም። የ ነ ዚህ የዘመናዊ ቲዎሪ አራማጆች ዋና ዓላማ

ከሁለተኛው ዓለም ጦርነ ት በኋላ የ ተቋቋመውን የ ኃይል

አሰላለፍና ይሰበክ የነ በረውን የነፃ ንግድና ገበያ በዓለም አቀፍ

ደረጃ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሲሆን፣ በዚያውም

በተለይም የ አሜሪካንን የ በላይነ ት በየ ቦታው ለማረጋገጥና በየ

አገ ሮቹ ውስጥ ዕውነ ተኛ የ ሆነ ሁለገብ የ ኢንዱስትሪ አብዮት

እንዳይመጣ ከመጀመሪያውኑ መሰናክል ማዘጋጀት ነ በር። ስለሆነ

ም በአሜሪካንና በተቀረው የ ምዕ ራብ አውሮፓ ካፒታሊዝም

ግፊትና የ በላይነ ት የ ተነ ሳ በብዙ የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮች

ሸቀጦችን እያመጡ በየ አገ ሩ ገበያ ላይ የሚያራግፍ የነ ጋዴ የ

ህብረተሰብ ክፍል እንዲፈጠር ሁኔ ታውን አመቻቹ። ዕድገ ቱና

አስተሳሰቡ በዚያው ብቻ እንዲቀር ሆኖ ተዘጋጀ። ሰፋ ያለ

ምሁራዊ እንቅስቃሴና በባህል የ ተገ ነ ባ የ ከበርቴ መደብ

እንዳይፈጠር መሰናክል ደቀኑ። በህብረተሰብ ግንባታ ታሪክ

ውስጥ እንደተረጋገ ጠው ሰፋ ባለ የ ኢንዱስትሪ አብዮት

አማካይነ ት ብቻ ነ ው በሁሉም አቅጣጫ የሚያስብ ምሁራዊ

እንቅስቃሴ ሊዳብርና፣ ፈጣሪና ተወዳዳሪ የ ሆነ የ ከበርቴ መደብ

ደግሞ መፈጠር የሚችለው። ከዚህም ሌላ ይህ ዐይነ ቱ በውስን የ

ካፒታሊዝም ሎጂክ ላይ የ ተመሰረተውና ለሶስተኛው ዓለም

ተብሎ የ ተዘጋጀው የ ሸቀጣ ሸቀጥ ኢኮኖሚ ተግባራዊ

እንዲሆንና ሁለ-ገብ ህብረተሰብአዊ ዕድገ ት እንዳይካሄድ

የመንግስት መኪናም ዘመናዊ በሚል ሽፋን ስር መዋቀር ነ

በረበት። ስለሆነ ም ቢሮክራሲያዊ መዋቅሩና ሌሎች የመንግስት

መኪናዎች በአንድ በኩል አዲሱን ኤሊት እንዲጠብቁና

እንዲከላከሉ ሆነ ው ሲዋቀሩ፣ በሌላ ወገ ን ደግሞ በተለይም

ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ሰርጎ ለመግባት እንዲያመቹ ሆነ ው

ተዘጋጁ። ምክንያቱም ቀላል ነ ው፤ ማንኛውንም ህብረተሰብዊ

እንቅስቃሴና ለለውጥ የሚደረግ ትግልን በእንደዚሁ ዐይነ ቱ

የመንግስት መኪና ነ ው ማኮላሸት የሚቻለው። ስለዚህም አገ ርን

ለመጠበቅ ተብሎ የ ተዋቀረው የ ሲቪልና የሚሊተሪ እንዲሁም

የ ደህንነ ት ቢሮክራሲ በመሰረቱ የ አገ ዛዙንና የውጭ ኃይሎችን

ጥቅም የሚያስጠብቅ እንጂ ለህብረተሰቡ አጠቃላይ ዕድገ ት

እንዲያመች ሆኖ የ ህብረተሰቡን ፍላጎ ት በማካተት ከታች ወደ

ላይ የ ተደራጀ አይደለም። ከታች ወደ ላይ ሰፋ ካለ ምሁራዊ

እንቅስቃሴ ጋር እየ ተነ ፃ ፀ ረ ያልተዋቀረ በመሆኑ በንቃተ-

ህሊናው ደካማነ ት አንድ ዐይነ ት ህዝባዊ እንቅስቃሴ በሚነ

ሳበት ወቅት ወደ ጨፍጫፊነ ት ይቀየ ራል። በተለይም አንድ

ወጥ አገ ዛዝ በሰፈነ በትና የ ተደራጀ የ ሲቪክ ማህበር በሌለበት

ህብረተሰብ ውስጥ በአሜሪካን ሎጂክ የ ተዋቀረ የ ሲቪሊና

የሚሊታሪ ቢሮክራሲ ወደ ፋሺሽትነ ት ይለወጣል ማለት ነ ው።

ይህ ዐይነ ቱ ሁኔ ታ በብዙ የ ላቲናን የ አፍርካ አገ ሮች ታይቷል።

ከዚህም ባሻገር ይህ ዐይነ ቱ የመንግስት ቢሮክራሲ ከኢኮኖሚው

መሰረትና ስፋት ጋር እየ ተነ ፃ ፀ ረ የ ተዋቀረ ባለመሆኑ

ህብረተሰብአዊ ሀብትን መጣጭ ነ ው። እንደሚታወቀው አንድ

አገ ር የ ራሷ የመሳሪያ ኢንዱስትሪ ከሌላትና፣ መሳሪያ ከውጭ የ

ምታስመጣ ከሆነ የ አገ ር ውስጥ ሀብት ወደ ውጭ ይፈሳል።

ከዚህም ባሻገር ለመሳሪያ ግዢ የሚወጣ ወጪምርታማ ስላልሆነ

ና የ ምጣኔ ሀብትን ስለሚጋራ በኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተጽዕ

ኖ ይኖረዋል ። በዚህ መልክ የ አሜሪካንን ጥቅም ለማስፋፋት

ሲባል የ ተኮተኮተውና የ ተጠናከረው የመንግስት የመጨቆኛ

መሳሪያና ቢሮክራሲ አገ ርን ለመግንባት ማገ ልገ ያ ከመሆን

ይልቅ ከረዥም ጊዜ አንፃ ር ጦርነ ትን ፈልፋይ እንዲሆን

ተደርጓል። የመንግስት ሚና ወደ መጨቆኛ መሳሪያነ ት ተቀንሶ

እንዲታይ በመደረጉ፣ ከውጭ ትዕ ዛዝ ተቀባይና ጦርነ ትን

የሚያካሂድ እንዲሆን ተደርጓል። በዚህም የ ተነ ሳ መንግስታዊ

ፖሊሲዎች አጠቃላይ ህብረተሰብአዊ ዕድገ ትን ከማምጣት

ይልቅ ሀብት አባካኝ በመሆን ህብረተሰቡ ስርዓትና ዓላማ ይዞ

ኑሮውን እንዳይመራ አግደውታል። 6 በመሆኑም የ ተወሰነ ው

ተማረ የሚባለው የ ህብረተሰብ ክፍልና መንግስታት የ

ተወሳሰበውን የ ካፒታሊዝምን ዕድገ ትና የ ልዩ ልዩ

ኢንስቲቱሽኖችን የ ሻጥር አሰራር ጠጋ ብለው ለመመርመር

ባለመቻል በየ ታሪክ ወቅት ብቅ ያሉትን አወናባጅ የ ኢኮኖሚ

ፖሊሲዎች በማስተጋባትና ተግባራዊ በማድረግ ለብዙ ሚሊዮን

የባህል ዕድገ ት ነ ፅብራቅ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።

ከጭንቅላት ተሃድሶ ጋር የ ተያያዘ ነ ው። የ ህብረተሰብንና የ አገ

ርን ትርጉም በሚገ ባ ከመረዳት ጋር የ ተያያዘና፣ በዚህም አማካይነ

ት ብቻ አንድ ህብረ-ብሄር በቋሚ መሰረት ላይ ጸንቶ ሊቆይ

ይችላል ብሎ በማመንም የሚደረግ ንቁ ተሳትፎ ነ ው። ይህ

አመለካከት ከአሜሪካን ይልቅ በምዕ ራብ አውሮፓ ውስጥ ከፍተኛ

ተቀባይነ ት ያለውና እንደ ባህል የሚታይ ነ ው። ይሁንና ግን

በጥልቅ ሲመረመር፣ በተለይም 7 ባለፉት ሰላሳ ዐመታት የ

ካፒታሊስት መንግስታት በአጠቃላይ ሲወሰዱ በተለያዩ የ ፊናንስና

የ ቀረጥ ፖሊሲዎች አማካይነ ት ሀብትን ከዝቅተኛው የ

ህብረተሰብ ክፍል ወደ ከፍተኛው በማስተላለፍ ሀብታሙን

የበለጠ ሀብታም አድርገውታል። በሁሉም አገ ሮች ህብረተሰብአዊ

መዛባቶች በመከሰታቸው፣ በተለይም ለቀኝ ኃይሎች አመቺ ሁኔ

ታዎች በመፈጠር ጥላቻ እየ ተስፋፋ ነ ው። ስለሆነ ም በአገ

ራችንም ሆነ በብዙ የ ሶስተኛው ዓለም አገ ሮች በተፈጠረው

ያለተስተካከለ ዕውቀትና ህብረተሰብአዊ ተሃድሶ አለመኖር የ ተነ

ሳ፣ በአንድ በኩል የመንግስት ሚና ሊጣመም ችሏል፤ ድርጊቱ ሁሉ

ወደ ጦርነ ት ተቀንሷል፤ በሌላ ወገ ን ደግሞ በተሳሳተ ፖሊሲ

በመጠመዘዝና በመመራት ህብረተሰብአዊና የ አካባቢ መዛባት

ሊፈጠር ችሏል። በአገ ራችንም ሆነ በሌሎች የ ሶስተኛው ዓለም

አገ ሮች በየ ጊዜው ስልጣንን የሚጨብጡትን የዕውቀት ደረጃ

ስንመለከት ይህንን ሁሉ ችግር ለማየ ት የ ማይችሉ ብቻ ሳይሆኑ፣

ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር የባሰ ችግርን በመፍጠር

ችግሮች እንዲደራረቡ የሚያደርጉ ሆነ ዋል። ከዚህ ሁኔ ታ ብቻ

በመነ ሳት ነ ው ከ1950 ዓ.ም መጀመሪያ ጀምሮ በአገ ራችን ምድር

የ ተፈጠረውን ሁኔ ታና እዚህና እዚያ ብቅ ያሉትን የ ህብረተሰብ

ኃይሎች አስተሳሰብና ድርጊታቸውን መረዳት የ ምንችለው።

አብዛኛውን ጊዜ በዘልማድ አነ ጋገ ር አፄ ኃይለስላሴ ዘመናዊነ ትን

ያስገ ቡና ኢትዮጵያን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ያስተዋወቁ መሪ

ናቸው እየ ተባለ ይነ ገ ራል። ይህ ዐይነ ቱ አነ ጋገ ር የ ናፍቆት

ይሁን የ ሌላ አመለካከት እየ ተመላለሰ ሲስተጋባ ይሰማል። የ ዚህ

ሁሉ ችግር አሁንም ቢሆን የ ኢትዮጵያን ዕድገ ት በየ ኢፖኩ እየ

ወሰዱ ከህብረተሰብ ሳይንስና(Sociology) ከፍልስፍና፣ እንዲሁም

ከሳይኮሎጂ አንጻር የሚመረምሩ ምሁራን ፍላጎ ት አለመኖር ነ

ው። የብዙዎቻችን አጠቃላይ ዕውቀት(Generalist) የ ነ ገ ሮችን

ዕድገ ት በተናጠል እየ ወሰድን እንዳንመረምርና እንዳንመዘግብ

አግዶናል። በተጨማሪም ያለን ህብረተሰብአዊ ኃላፊነ ትና ንቃተ-

ህሊና ደካማ በመሆኑ የ አገ ዛዙን ድክመትና የ ህብረተሰብአችንን

ችግር በጽሁፍም ሆነ በሌሎች ነ ገ ሮች በሰፊው ማሳየ ት

አልቻልንም። ስለሆነ ም አፄ ኃይለስላሴ ለህብረተሰብአችን ዕድገ

ት ያደረጉትን አስተዋጽዖ በጥሞና የ ሳይንስ መነ ጽር፣ በተለይም

ለንጉስ ናፋቂዎችና የ ሳቸውን ስራ ለሚያጋንኑት ማስረዳት የ

ማይቻልበት ሁኔ ታ ተፈጥሯል። የሰው ልጅ ሚናና ዕኩልነ ት

በማይታወቅበት በእንደኛው ባለው ህብረተሰብ ውስጥ ተውልደው

ያደጉ ውጭ አገ ርም ሰላሳና አርባ ዐመት ያህል ከኖሩ በኋላ አንኳ

ከ1940ዎቹ መጨረሻ አንስቶ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ያለውን የ

ህብረተሰብአችንን ያልተስተካከለ ዕድገ ት ሲያስረዷቸው ነ ገ ሩን

እንደስድብና አገ ዛዙን እንደመናቅ አድርገው ነ ው የሚቆጥሩት።

ያም ሆነ ይህ የ አፄው ዘመናዊነ ት ፖሊሲ አጠቃላይና(Holistic)

የ ተስተካከለ ዕድገ ትን ያመጣ አይደለም። በህብረተሰቡ ውስጥ

ግልፅ ያሰራር ስልትና ክፍፍል(Division of Labour) እንዲፈጠር

ያደረገ አይደለም። የ ሳይንስና የ ቴክኖሎጂ ዕምርታ እንዲኖር

መንገድ ለመክፈት የሚያስችል ፖሊሲ አለነ በረም። የ ኢኮኖሚ

ፖሊሲው እጅግ የ ተሰበጣጠሩና ውስጠ-ኃይላቸው ደካማ የ ሆኑ

አጠቃላይ ሀብትን ለመፍጠር የ ማያስችሉ የ ኢኮኖሚ ሁኔ

ታዎችንና ግኑኝነ ቶችን የ ፈጠረ ነ ው። ይህ ዐይነ ቱ የ

ተሰበጣጠረና ውስጠ-ኃይሉ ደካማ የ ሆነ የ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ

ከሶስዮሎጂ አንፃ ር መንፈሱ ያልረጋና ህብረተሰብአዊ ኃላፊነ ትን

ሊቀበል የ ማይችል የ ህብረተሰብ ክፍል ብቅ እንዲል አድርጓል።

የሚሙለጨለጭ፣ አታላይ፣ሌላውን በእግዚአብሄር አምሳል የ

ተፈጠረውን አምሳያውን የሚንቅ፣ በቀላሉ ለውጭ ኃይል

የሚያጎበድድና፣ አገ ሩንም ለመሸጥ የ ተዘጋጀ፣ ፈጣሪ ያልሆነ ና

በቀላሉ የሚታለልን የ ህብረተሰብ ክፍል በአገ ራችን ውስጥ ብቅ

ሊል ችሏል። ይህ አንደኛው ሲሆን፣ የ አፄው ያልተጠና የ

ኢኮኖሚ ፖሊሲ ፊዩዳሊዘምን በአዲስ መልክ ሲያጠናክር፣

እዚያው በዚያው ደግሞ ከዚህም ከዚያም ብቅ ያለ፣ ይህንን ሆነ

ያንን እወክላለሁ የሚል ንዑስ ከበርቴ የብሄረሰብ እንቅስቃሴ

ሊፈጠርና፣ በአሜሪካንና በእንግሊዝ ኢምፔሪያሊዝም አገ ሮችን

በማዳካም ስትራቴጂ ውስጥ በመጠቃለል፣ ምክርና ርዳታ

በማግኘት ለህብረተሰብአዊ ትርምስ ምክንያት ሆኗል። በአናሎጊ

ስንመለከት፣ የ አውሮፓው ካፒታሊዝም የብሄረሰብን አመለካከት

በመደምሰስ፣ ህብረተሰቡን በመበወዝና፣ ስራ ለመፈለግ ሲል

ከክልሉ ወጥቶ ወደሌላ ቦታ የሚሄድ ከሌላው ጋር በመጋባት

ብሄረሰቡ የ ጣለበትን መጋረጃ በመበጣጠስ፣ ከብሄረሰብ ይልቅ

ብሄራዊ ባህርይ እንዲወሰድና ብሄራዊ ባህልን ባህሉ እንዲያደርግ

ተገዷል። የ ካፒታሊዝም ውስጣዊ-ኃይል(Dynamism) በቡድንና

በዘመድ አዝማድ መደራጀትንና መሰበሳብን በመበጣጠስ በዕምነ

ትና በዕውቀት ላይ እንዲሆን አድርጓል። ስለሆነ ም በካፒታሊዝም

ዕድገ ት ውስጥ ህብረተሰቦችና የፖለቲካ ፍልስፍና አረማመድ ልዩ

ዐይነ ት ባህርይ ነ ው ያላቸው ማለት ይቻላል።

ቀጣዩን በገፅ 9 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 8

የሚያረጋግጠው የ ቱን ያህል ከበርቴያዊ ውይይት ወይም ደግሞ የ ፕላቶን ዲያሌክቲካዊ የውይይት ዘዴ፣ ጥያቄን የ ማቅረብና ለመመለስ የመሞከር ባህል ከሰውነ ታችን ጋር ያልተዋሃ ደ መሆኑን ነ ው። ኩሙኒ ካቲቭ ከሆነ የ አነ ጋገ ር ስልትና በውይይት የ ማሳመን ልምድ አለመኖር፣ በጋርዮሽና ተደራጅቶ ለመስራት ዝግጁ ከመሆን ወደ አፍራሽነ ት ማምራት፣ በራስ ላይ ዕምነ ት ከማሳደርና ርስበርስ በግልጽ ከመወያየ ት ይልቅ የብሄራዊ አጀንዳችንን የውጭ ኃይሎች እንዲፈቱልን እነ ሱን መማፀ ን የሚያረጋግጠው አንድ የ ተከበረች አገ ር ለመገንባት ገ ና ያለተዘጋጀን መሆናችንን ነ ው። ስለዚህም የ የ ካቲቱ አብዮት መክሽፍ፣ ደም መፋሰስና ህብረተሰብአዊ እሴቶች መበጣጠስና የ ህዝባችን ህሊና መረበሽና አቅጣጫውን ማጣት በቀላል ነ ገ ሮች በጥቁር/ ነ ጭ በመሳል የሚገለጹ አይደለም። የብዙ ዐመታትን የ ጭንቅላት ስራ የሚጠይቁ ናቸው። ያም ሆነ ይህ ከ1940ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ በዘመናዊነ ት ስም የ ተካሄደውን ህብረተሰብአዊ መመሰቃቀል መረዳት የሚቻለው፣ በአንድ በኩል በጊዜው የ ነ በረውን ዕውቀትና የ ምሁር ብስለትም ሆነ ድክመት ከቁጥር ውሰጥ ያስገባን እንደሆን ነ ው። በተጨማሪም በንጉሳዊ አገ ዛዝ የ ተወቃረው የ ሲቪልና የሚሊተሪ ቢሮክራሲ አገ ርን ለመገንባት መቻልና ወይም አለመቻል፣ እንዲሁም ደግሞ ከማንኛውም የ አገ ርን አንድነ ት ከሚያናጋ ሴራ ለመጠበቅ ብቃትነ ት ያለው ወይም የ ሌለው መሆኑን ስንገነ ዘብ ብቻ ነ ው። ከዚህም ስንነ ሳ የ ምንጠይቃቸው ጥያቄዎች፣ የ ምሁሩ ኃይልም ሆነ ቢሮክራሲው የ ቱን ያህል የ ተወሳሰበውን የዓለም ሁኔ ታና፣ በተለይም የ አሜሪካኖችን አሻጥር የ ተረዱና፣ ስትራቴጂያዊ ጥናቶች በማካሄድ በጥንቃቄ መወሰድ ያለበትን እርምጃ መውሰድ የሚችሉ ነ በሩ ? በጊዜው የ ዓለምን ፖለቲካና በአካባቢው የሚካሄደውን የጂኦ ፓለቲካ እሽቅድምድም የሚያጠና ኢንስቲቱሽን ነ በር ወይ? ስለሆነ ም ህብረ-ብሄርንና(Nation-State) ህብረተሰቡን በጠንካራ መሰረት እንዳይገ ነ ባ የሚደረገውን የ ውጭ 9 ኃይሎችን ግፊትና አሻጥር የሚከታተልና የሚያውቅ የ ምሁር እንቅስቃሴ ነ በር ወይ? ወይስ አገ ዛዙና ቢሮክራሲው ግብታዊ የ ፊዩዳል ፖለቲካ በመከተል አገ ራችንን ያሰጠቁ ነ በር ወይ? ብለን በማንሳት በጊዜው የነ በረውን አጠቃላይ አስተሳሰብና የፖለቲካ ሂደት መገ ምገሙ የ አገ ራችንን አስቸጋሪ ጉዞ እንድንረዳ ያስችለናል። በመሆኑም፣ የ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም የ በላይነ ትን ከተቀዳጀ ጀምሮ ደካማ አገ ሮች በጠንካራ መሰረት ላይ እንዳይገ ነ ቡና፣ ህዝቦቻቸውም የ ሰላም ኑሮ እንዳይኖሩ የሚሸርበው ተንኮል በጊዜው ለብዙዎች ግልጽ እንዳልነ በር መረዳት ይቻላል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነ ት ማለቂያ በኋላ ባለፉት ስድሳ ዐመታት ዓለም እፎይ ያለችበት፣ በተለይም እንደኛ ያሉ ደካማ አገ ሮች እፎይ ብለው ኃይላቸውንና ሀብታቸውን በማጣመር አገ ር ለመገንባት የ ተነ ሱበትን ወቅት ያገናዘበ በጣም ጥቂት ነ ው ብል አልሳሳትም። ጦርነ ት ማካሄድና፣ አንዱ ሌላውን በማጥፋት ብቻ ለመኖር የሚቻል ተደርጎ እንደተፈጥሮ ህግ ሆኖ በተወሰደበት ዓለም ውስጥ፣ ከትላንት በስቲያ በኮሙኒዝም ስም አገ ሮችን ማሰስ፣ በዛሬው ወቅት ደግሞ በአሸባሪነ ት ስም በየ ቦታው ጦርነ ት በመቀስቀስ አገ ሮችን ማመስና ህዝቦች በጋራ በመነ ሳት በሳይንስና በቴክኖሎጂ ላይ የ ተመሰረተ ጤናማና ጥበባዊ አገ ር እንዳይመሰርቱ የ ተደረገ በትን ሁኔ ታ፣ በተለይም ለፖለቲካ ስልጣን እንታገ ላለን በሚሉት ጭንቅላት ውስጥ ሰርጎ የገባ ጉዳይ አይደለም። በዚህ መልክ የ ተቀነ ባበርውን የ እንግሊዝና የ አሜሪካን ፕሮጀክት፣ ጠቅላላው ሰለጠንኩ የሚለው የ ምዕራቡ ዓለምም በተለያዩ መሳሪያዎችና የረቀቁ ዘዴዎች እንደሚያግዝና ዕድገ ታችንና በሰላም መኖራችንን የሚቀናቀኑ ኃይሎች ብዙ እንደሆኑ ለብዙዎቻችን ግልጽ የ ሆኑ አይመስለኝም። በሌላ አነ ጋገ ር አሜሪካና እንግሊዝ ብቻቸውን አይደለም ጦርነ ት የሚያካሂዱት። የነጩዓለም ሲጮህ በአንድ ጊዜ ነ ው። የሚዶቅሰንም ክንዱንም በማጣመር በአንድ ላይ ነ ው። እኛ ደካሞች ደግሞ የ ተለያዩ ተንኮሎችን እየ ፈጠርንና ርስባራሳችን እየ ተጠላለፍን ሁኔ ታውን እናመቻችላቸዋለን። አልፎም ተርፎም በስለላ ተግባር እንተባበራቸዋለን። ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ እንዲሁም ለብሄራዊ ነፃነት እታገ ላለሁ የሚለውን ግለሰብም ሆነ ድርጅት አሳልፈን በመስጠት ለማስመታት እንሞክራለን። የሃሳብ መጋጨት ተናውጦን፣ ራስን ለማግኘት ባለመቻልና የ ቀና ስራ ላለመስራት በጠባብ የሃሳብ ክልል ውስጥ በመሽከርከር ችግር ስንፈጥር እንታያለን። በዘመናዊነ ት ስም የገባውን ጥቅላላውን የ ተበላሸ የ አሰራር ስልትና የ ዛሬውንም የ ኢህአዴግ/የ ወያኔ የ ትርምስ ፖለቲካ መገንዘብ የ ምንችለው ከአጠቃላዩ የ ኢምፔሪያሊስት ፕሮጀክት ነ ው። ከዚያ በፊት ግን አንዳንድ መሰረተ-ሃሳቦችን እንመልከት። የኒዎ-ሊበራሊዝም ዓለም አቀፋዊ ፕሮጀክትና ውጤቱ! አብዛኛዎች የ ምዕ ራብ አውሮፓ አገ ሮች ኢኮኖሚያቸውን መልሰው ከገ ነ ቡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነ ት በኋላ የ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በተለይም በኢኮኖሚ መስክ ተወዳዳሪ ያጋጥመዋል። በጊዜው ምዕራብ ጀርመንና ጃፓን በተለይም በውጭ ንግዳቸው አሜሪካንን ይቀድማሉ። ይህ ሁኔ ታና አሜሪካን

ትንታኔ ... ከገፅ 8 የቀጠለ

አሁንም ወደኛ አገ ር ስንመጣ፣ በአገ ር ደረጃ ከመደራጀትና ብሄራዊ አጀንዳ ይዞ ከመንቀሳቀስ ይልቅ ነ ገ ሮችን በጠባቡ በመረዳትና በጠባብ አስተሳሰብ በመወጠር ነ ገ ሮችን ሁሉ በሎጂክና በዲያሌክቲክ መነ ጽር ማየ ት የ ማይቻልበት ሁኔ ታ ሊፈጠር ቻለ። እኔ ብቻ ነ ኝ የ ተጨቆንኩ፣ የ ተበደልኩ በማለትና በማጋነ ን የ አንድን ህብረተሰብ ዕድገ ት በሳይንስ መነ ጽር ለመመርመር የ ማይቻልበት ሁኔ ታ ተፈጠረ። በዚህ መልክ ደግሞ ነ ገ ሮች ሁሉ በዝቅተኛ ወይም በበላይነ ት ስሜትነ ት እየ ተገ ለጹ ለውይይትና ለክርክር አመቺ እንዳይሆኑ ተደረጉ። ይህ የ ተወሳሰበ ሁኔ ታና የ ኛ ደካማ ዕውቀትና ማንኛውንም ነገር በጠባቡ መመልከት በተለያየ መልክ የሚገ ለጹ፣ ጭቁን ህዝቦችን እናግዛለን የሚሉ፣ 8 በመሰረቱ ግን ሰላዮችና የ አገ ራችንን ዕድገ ትና ሰላማዊ ኑሮና በጋራ ግንባታ መንቀሳቀስ የሚቀናቀኑና ለዝንተ-ዓለም ተመጽዋች ሆነ ን እንድንኖር የሚያደርጉ ኢምፔሪያሊስታዊ ኃይሎች መሳሪያ በመሆን ርስ በርስ እንድንበጣበጥ ሆነ ። ይህ አስቸጋሪ የ ህብረተሰብአችን ዕድገ ት በብሄረሰብ ተወካዮች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን፣ ራሳቸውም ለብሄራዊ ነ ፃ ነ ትና ለአንድነ ት እንታገ ላለን የሚሉትን አስተሳሰባቸውን ያቀፈና በዕውቀትና በዕምነ ት ደረጃ እንዳይደራጁ ያደረገ ነ ው። ስለዚህም ነ ው የ የ ካቲቱ አብዮት በወንድማማችና በእህትማማች፣ ነገር ግን ደግሞ ለአንድ ዓላማ እንታገ ላለን በሚሉ ቡድኖች መሀከል የርስበርስ መተላለቅ እንዲኖር ያደረገው። „አብዮት ካለደም መፈሰስ አይሰምርም“ እየ ተባለ በብዙ መቶ ሺህ ህዝብ እንዲገ ደልና እንዲሰቃይ ዛሬም እንዲሸማቀቅና ለነ ጻነ ቱ እንዳይታገ ል የ ተደረገው ግለሰብአዊነ ትንና ቀና ዕምነ ትን ከራስ ጋር ለማዋሃድ ባለመቻሉ ነ ው። የየካቲቱ ሁኔ ታ ዛሬም ይታያል። ዕውቀትንና ዕምነ ት ሳይሆን ግለሰቦችን ማወደስና በጭፍን መመራት፣ ቡድናዊ ስሜትን ማጎ ልበስና ለጋራ ዓላማ ለመታገ ል ያለመቻል፣ ከዕውነ ተኛና ስልጣኔ ይልቅ በማይታወቀው ሊበራሊዝምና የገበያ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ ክልል መሽከርከርና፣ የ ሌላውን አስተሳሰብ ማፈንና ሌላውን ለማጥፋት መታገ ል የ ቱን ያህል ከፊዩዳል ባህርይ እንዳልተላቀቅን ነ ው የሚያረጋግጠው። በኮምፒዩተርና በኤንተርኔ ት ዓለም እያለን አሁንም ቢሆን እዚያው በዚያው የድሮውን ቡድናዊና ግልጽ ያልሆነ አሰራር እያራመድን እንገ ኛለን። ይህ በራሱ ለዕድገ ት ፀ ር መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። በኢትዮጵያዊነ ት ስሜት ሊጋረድ የሚችል አይደለም። ከዚህ በመነ ሳት ነ ው የ አብዮቱን ምስቅልቅል ሁኔ ታ መረዳት የሚቻለው። ሁላችንም የ ሶሻሊዝምና የ ኮሙኒዝም ውጤቶች አልነ በርንም። ሁላችንም የ ኢትዮጵያ ፊዩዳል ስርዓትና የ አሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም ውጤቶችና፣ የ አሜሪካንን እሴት(Value) ናፋቂዎች ነ በርን። አሁንም ያለን አለን። የለም እንደዚህ ዐይነ ቱ በተወሰነ ወቅት ብቅ ያለ ርዕዮተ-ዓለምና የ ኢኮኖሚ ግኑኝነ ት እኛን የሚመለከት አይደለም የ ምንል ከሆነ ልዩ ፍጡሮች ነ ን ማለት ነ ው። በሶስዮሎጂና በሳይኮሎጂ ልንገ ለጽ የ ማንችል፣ መጥፎም ሆነ ጥሩ ነገር ሲስፋፋ ልንቀበልና ልንለወጥ የ ማንችል፣ እንደተፈጠርን የ ቀረን ነ ን ማለት ነ ው። ለነ ገ ሩ ስዎች ስለሆን የ አስተሳሰብ ለውጥ እናመጣልን፣ ወይንም ደግሞ ጥያቄ ውስጥ ሳናገባ እንቀበላለን። በሌላ ወገ ን ደግሞ የ አንድ ሰው አስተሳሰብ ለውጥና አንድን ነገር መቀበል ከሰውነ ት ጋር ማዋሃድ ሁለት ሶስት ትውልድን ይጠይቃል። አንድ ሰው በአንድ ርዕዮተ-ዓለም ለመመራትና ዕምነ ት እንዲኖረው የ ጭንቅላት ለውጥ ያስፈልገ ዋል። ለዚህ ነ ው የ የ ካቲቱን አብዮት አራማጆች፣ በተለይም የ ደርግን መሪዎች በሶሻሊዝምና በኮሙኒዝም ስም ማማትና መወንጀል የ ማይቻለውና ስህተትም የሚሆነ ው። ሶሻሊስቶች ወይም ኮሙኒስቶች ስለሆኑ አይደለም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ወጣትንና ሌላውንም የጨረሱት። ስለሶሻሊዝም የ ተጻፉ መጽሐፎችም ውስጥ ሰውን በመግደልና በመጨፍጨፍ ብቻ ነ ው አዲስ ህብረተሰብ መመስረት የሚቻለው የ ተባለበት ቦታ የ ለም። በርዕዮተ-ዓለም የሚምሉትንና የሚገ ዘቱትን ድርጊታቸውንም የ ምንረዳው የ ፈለቁበትንና የ አደጉበትን የ ህብረተሰብ አወቃቀርና፣ ከዚያ ጋር ተያይዞ በትምህርት ዓለም የ ቀሰሙትንና በአገ ራችን የ ተስፋፋውን ውስን የ ካፒታሊዝም ስልተምርት ስንረዳ ብቻ ነ ው። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ትንተናና አነ ጋገ ር ሳይንሳዊ አይደለም። አንድን ህብረተሰብ ደግሞ ከሳይንስ አንፃ ር መመርመር ካልቻልንና ችግሩን ካልተረዳን መፍትሄ መስጠት አንችልም። በመወንጀልና በተራ ቃላት ድርደራ፣ ወይም ደግሞ በጥላቻ ላይ ተመርኩዘን የ ምናራግበው ወሬ ሌላ ህብረተሰብአዊ ቀውስን ጋባዥ ይሆናል። ስለሆነ ም የ ደርግንና የ ተቀሩትን ተራማጅ ነ ን የሚሉትን ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች ባህርዮችና ድርጊቶች፣ እልከኝነ ትና አልበገ ርም ባይነ ት፣ ከውይይት ይልቅ በጠበንጃ ትግል ማመንና ችግርን በኃይል ለመፍታት መሞከር፣ መፎከር፣

በቬትናም የሚያካሂደው ጦርነ ት በአንድ በኩል የ ዶላርን በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዛት መስፋፋት ሲያስከትል፣ በዚያው መጠንም የ አሜሪካን የ ወርቅ ክምችት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ እየ ተሟጠጠ ይመጣል። በብሬተንስ ውድስ ስምምነ ት አሜሪካን ዶላርን በወርቅ ለመለወጥ የገባውን ስምምነ ት ወደ ስድሳዎች ዐመታት መጨረሻ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ የ ማይችልበት ሁኔ ታ ይፈጠራል። በዚህም የ ተነ ሳ ከ1944 ዓ.ም ጀምሮ ይሰራበት የ ነ በረው ዶላርን በወርቅ የመቀየሩ ግዴታ በፕሬዚደንት ኒክሰን አስተዳደር በ1971 ዓ.ም እንዲቀር ይደረጋል። በ1973 ዓ.ም ተለዋዋጭ የ ከረንሲ ገበያ በመፍጠር ካፒታል ካለምንም ገ ደብ ሊንቀሳቀሰ የሚችልበት ሁኔ ታ ይፈጠራል። በዚህ ላይ በ1973/1974 የ ተከሰተው የ ዘይት ዋጋ መናር የ ምዕራብ አውሮፓን ኢኮኖሚዎች ቀውስ ውስጥ ከቶት ነ በር። ስለሆነ ም ብዙ መንግስታት እንደቀድሞው በኬኒያኒዝም ላይ የ ተመሰረተ የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ለማካሄድ የ ማይችሉበት ሁኔ ታ ይፈጠራል። በኒዎ-ሊበራሊዝምና በነ ፃ ንግድ አራማጅነ ት የሚመራው የ እነ ፕሮፌሰር ሚልተን ፍሪድማን ፍልስፍና ከአሜሪካና ከምዕራብ አውሮፓ አልፎ ዓለም አቀፋዊ የሚሆንበት ሁኔ ታ ይዘጋጃል። በ1980ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ለሶስተኛው ዓለም የ ኢኮኖሚ ዕድገ ት ያመቻል የሚባል የመዋቅር መስተካከያ(Strucctural Ad-justment Program) ተዘጋጅቶ ይቀርባል። ፕሮግራሙን የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ይደረጋል። በተለይም ፕሮግራሙን እንዲቀበሉ በብዙ የ አፍሪካ አገ ሮች ላይ ግፊት ይደረጋል። ይህ የኒዎ-ሊበራሊዝም የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ ከሆነ ከጥቂት ዐመታት በኋላ በየ አገ ሮች ውስጥ አዲስ የ ሀብት ክፍፍልና የ ኃይል አሰላለፍ ይፈጠራል። በማኑፋክቱር ላይ ከተመሰረተ የ ኢኮኖሚ ዕድገ ት ይልቅ የንግድ እንቅስቃሴና የ ኤክስፖርት መስኩ እየ ተጠናከረ ይመጣል። በዚያውም መጠን አገ ሮች የባሰውኑ በዕዳ እየ ተበተቡና፣ ዕ ዳቸውን ለመክፍል ሲሉ አዳዲስ አንጀት አጥብቅ ፓሊሲ(Austerity Program) እንዲከተሉ ይገ ደዳሉ። በዚህም ምክንያት የ ተነ ሳ የውስጥ ገበያን በጠንካራ መሰረት ገ ንብቶ የ ተስተካከለ ኢኮኖሚ በአገ ር ደረጃ ከመገንባት ይልቅ የ ተዛባ ሁኔ ታ ይፈጠራል። በዚህ ዐይነ ቱ የኒዎ-ሊበራል ፕሮጀክት በተለይም ከሰሀራ በታች ያሉ የ አፍሪካ አገ ሮች በአንድ በኩል ገ በያቸውን ለውጭ የ ፍጆታ ዕቃ ክፍት ሲያደርጉ፣ በሌላ ወገ ን ደግሞ ኢንዱስትሪዎቻቸው እየተመቱባቸው መጡ። በዚህ መልክ በዓለም አቀፍ የ ታወቁት ግብጻዊው የ ኢኮኖሚ ምሁር ፕሮፌሰር ሳሚር አሚን እንዳሉት አፍሪካ ብቻ ሳትሆን ዓለም በጠቅላላው ወደ ኒዎ-ሊበራል የመገበያያ መድርክነ ት ተለወጠች። 10 ይህ በእንደዚህ እንዳለ፣ በምስራቅ አውሮፓና በቀድሞው የ ሶቭየ ት ህብረት ውስጥ አዲስ ሁኔ ታ ይፈጠራል። በፕሬዚደንት ጎ ርባጆብ የ ተቀደደው ፕርስትሮይካ ሶቭየ ት ህብረትን እንድትሰነ ጣጠቅ በሩን ይከፍታል። የ ኮሙኒስት አገ ሮች መበታተንና አዲስ ዓለም አቀፍ የፖለቲካና የ ኃይል አሰላለፍ መከሰት የ አሜሪካን ካፒታሊዝም በአሸናፊነ ት እንደወጣ ተደርጎ ይተረጎማል። የ ዓለምም ህዝብ ከእንግዲህ ወዲያ በሊበራሊዝምና በነ ፃ ገበያ አማካይነ ት ብቻ ህልሙና ምኞቱ ተግባራዊ እንደሚሆንለትና እንደሚጠናቀቅለት ይበሰራል። የ ታሪክ ወይም የ ርዕዮተ-ዓለም መጨራሻዋ ደረሰ ተብሎ በነ ፉኩያማ ይተረጎማል። ልክ ሄገል የ ፕረሽያ መንግስት በጀርመን ምድር በአሸናፊነ ት ሲወጣ የ ምፈልገውን አገ ኘሁ ብሎና የ ታሪክን ድምዳሜ በዚያው ገድቦ እንደተነ ተነ ው ሁሉ፣ ፉኩያማም የ ኮሙኒዝምን መከስከስና የ አሜሪካንን ካፒታሊዝም በአሸናፊነ ት መውጣት የዓለም ህዝብ ደስታ መግለጫ አድርጎ ተረጎመው። ከዚህ የ አሜሪካን ፕሮጀክት ውጭ የዓለም ህዝብ የሚንቀሳቀስበት ሌላ የነ ጻነ ት ፕሮጀክት የለም ተብሎ ተነ ገ ረን። ስለሆነ ም፣ ራሷን እንድታገ ል በተገ ደደችው ራሽያና በተቀረው የ ምስራቅ አውሮፓ አገ ሮች የኒዎ-ሊበራሊዝም ፕሮጀክት መሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ተደረገ ። ይህ ሾክ ቴራፒ(Shock Therapy) በመባል የሚታወቀው ፖሊሲ ተግባራዊ ሲሆን፣ ጥቂቱን የሚያደልብበትና አብዛኛውን ህዝብ ደግሞ ወደድህነ ት የሚገ ፈትርበት ሁኔ ታ ተፈጠረ። በዚህ የኒዎ-ሊበራል ፕሮጀክት በመመካትና አዲስ የ ተፈጠረውን ደካማ የፖለቲካ ሁኔ ታ ተገ ን በማድረግ በተለይም የ ራሽያ ህልውና ጥያቄ ውስጥ መግባት ጀመረ። የ አሜሪካንና የ እንግሊዞች ፕሮጀክት አዳዲስ ኃይሎችን በመጥቀም እንዴት አድርገው የ ራሺያን የጥሬ ሀብት ለመዝረፍና ጠቅላላው ኢንዱስትሪዋን ለመምታትና የ ሶስተኛው ዓለም ሁኔ ታ መፍጠር እንደሚችሉ ስትራቲጂ ይቀይሳሉ። በእርግጥም እነ ፕሬዚደንት ዬልሲንና ወጣት ኢኮኖሚስቶች የ ተከተሉት የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ራሽያን ሙሉ በሙሉ ጥገ ኛ የሚያደርጋትና ወደድህነ ት በመገ ፍተር ህልውናዋን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነ በር። በዚህ ላይ አንዳንድ የድሮው በሶቭየ ት ህብረት ክልል ውስጥ የነ በሩ ፌዴራል መንግስታት ነ ፃ ከወጡ በኋላ በሰሜን አትላንቲክ የ ጦር ካምፕ ውስጥ መጠቃለልና ራሽያን ለመክበብ የ ተወሰደው እርምጃ የ ራሽያን የጂኦ ፓለቲካ ሁኔታና የውስጡን የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ የሚያናጋ ነ በር። ወደ ገፅ 10 ይዞራል

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 9

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 10

ትንታኔ ... ከገፅ 9 የዞረ

ይህ የ አሜሪካንና የ እንግሊዝ ኢምፔሪያሊዝም ሻጥርና ድርጊት ግን ቀስ በቀስ በፕሬዚደንት ፑቲን ሊከሽፍና ስትራቴጂክ ቦታዋን መልሳ እንድታገ ኝ ሆናለች ። ይሁንና ግን አሁንም ቢሆን አሜሪካን ራሽያን ከውጭ በመክበብና፣ ከውስጥ ደግሞ አንዳንድ የ ሲቪክ ማህበራትንና በቅራኔ ዎች አያያዝ የሚሰራውን ስህተት በመጠቀም ፖለቲካዊ ትርምስ እንዲፈጠርና ለሱ የሚስማማ ለስለስ ያለ አገ ዛዝ እንዲመጣ የ ውስጥ ለውስጥ እንደሚሰራ ግልጽ ነ ው። የ ሰሞኑ የ ዱማ ምርጫና የ ምዕራቡ ዓለም፣ በተለይም የ

ኦባማ አስተዳደር ጣልቃ-ገብነ ት የሚያረጋግጠው አሜሪካ

የ ቱን ያህል ራሽያ ውስጥ የ አገ ዛዝ ለውጥ እንዲመጣ

እንደሚፈልግ ነ ው። በተለይም እንደራሽያ ያሉ ታላላቅ አገ

ሮች ውስጥ ባለው ገ ና ባልሰከነ የ ኃይል አሰላለፍና፣ ንቃተ-

ህሊናው የ ዳበረ የ ከበርቴ መደብ በሌለበት አገ ር፣

በተለይም ደግሞ የ ሲቭክ ማህበሩና የፖለቲካ ፓርቲዎች ገ

ና ብዙም የ ምዕራቡን ዓለም የ ሻጥር ፖለቲካ በደንብ ማገ

ናዘብ በማይችሉበት ሁኔ ታ ውስጥ ተራ የ ፓርሊሜንተሪ

ምርጫ ማካሄድና ስልጣን መልቀቅ ራሽያ ያላትን ኃይል

ሊያዳክመው ይችላል። ይህ ማለት ግን ህልውናዋን የ ማይጎ

ዳና ለሁሉም የሚያመች ዲሞክራሲያዊ ሂደት ተግባራዊ

አይሁን ማለቴ አይደለም። ብሄራዊ ስሜት የሚዳብርበትና፣

የ ተለያዩ የ ህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ጠላት የ

ማይተያዩበት አዲስ የፖለቲካ ባህል ቢፈጠር ህብረተሰብአዊ

ሚዛን ጠብቆ የ ውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነ ት መቋቋም

ወይም በከፍተኛ ደረጃ መቀነ ስ ይቻላል። በሌላ ወገ ን ግን

ባሸናፊነ ት ወጣ የ ተባለለት ጎሎባል ካፒታሊዝምና የ

አሜሪካን እሴት በተለይም ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ቀስ በቀስ

ግን ደግሞ በእርግጠኝነ ት ቀውስን እየ ተከናነ በ ይመጣል።

የ ዶት ኮም ቀውስና በብዙ የ ኤሺያ አገ ሮች የ ደረሰው የ

ኢኮኖሚ መናጋት የሚያረጋግጠው የ ቱን ያህል የ ግሎባል

ካፒታሊዝምን ውስንነ ት ነ ው የሚያሳየው። ግሎባላይዜሽን

በከፍተኛ ደረጃ መሰበክ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ

እንደታመነ በት የዓለም ህዝብ ወደ ብልጽግናና እኩልነ ት

አላመራም። ቀጣዩን በገፅ 11 ይመልከቱ

አትሌቱ እስካሁን የት እንዳለ አይታወቅም የዓረና ትግራይ ደጋፊ ነበር ወያኔ ዓረናዎችን በጣም ነው የሚፈራቸው በማራቶን ሩጫ አገራችንን ካስጠሩት ወጣት አትሌቶች አንዱ አብርሃ አማረ በቅርቡ ለውድድር ወደ ካናዳ ከተጓዘ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱና አለመመለሱ አልታወቀም። በአዲስ አበባ ያለው የልሳነ ህዝብ ዘገጋቢ እንደገለፀው አብርሃ የዓረና ትግራይ ደጋፊ እንደነበርና በዚሁ ምክንያትም በአዲስ አበባ ከተማ የሰራው የግል ቤቱ በመንግስት ሰዎች ካለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖለቲካ ውሳኔ ብቻ ተቀምቶ ለአንድ የወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣን ስንደተሰጠ ለማረራገጥ ችሏል። አብርሃ በዚሁ ፖለቲካ ተሳትፎወ ምክንያት በፖሊሰ ቁጥጥር ስር ውሎ እንደነበረና ከእስር ቤት ከወጣ በሁዋላ ደስተኛ እንዳልነበር ከቅርብ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አብርሃ ሙሉ እራሱ የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ ምክንያት ዓረና ትግራይን መደገፉ ከማንኛውም ተቃዋሚ በላይ ወያኔዎችን እንደሚያናድዳቸው ይታወቃል። አትሌት አብርሃ ሙሉ በበርካታ ኢንተርናሽናል ውድድሮች የአገራችንን ባንዲራ አንግቦ ለክብራችን የሮጠ ኢትዮጵያዊ ሲሆን በ2008 በቫሌንሺያ ፣ በ2009 ፖላንድ ዋርሶውና በሳን አንቶንዮ አሜሪካ፣ 2011 በግራን ካናሪያ ስፔንና በ2011 ሉብጂ ሉብጃና 1ኛ በመውጣት በሁለቱም አገሮች የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል። በ2014 በቻይና ተወዳድሯል። በመጨረሻ በ2015 በቶሮንቶ ካናዳ ከወዳደረና ውድድሩን በ2ኛነት ከካጠናቀቀ በሁዋላ ወዴት እንደገባ ሳይታወቅ ቀርቷል። አንዳንድ ሰዎች አትሌቱ ከመንግስት ጋር ከነበረው ግጭት

በመነሳት ምናልባት ወደዳገር ቤት ተመልሶ በወያኔ

ደህንነቶች ታፍኖ ሊሆን ይችላል ሲሉ አንዳንዱ ደግሞ

ምናልባት ወዳገር ቤት ሳይመለስ ቀርቶ ይሆናል ይላሉ።

ወያኔ እንደ የዓረና ትግራይ ደጋፊና አባላት የሚያስፈሩት

ያህል ምንም ነገር አያስፈራውም፡፡ ወያኔ ሙሉ በሙሉ

ይደግፈኛል እያለ የሚመካበት የትግራይ ህዝብ እንደካደው

ሲያውቅ በተጠርጣሪ የትግራይ ሰዎች ለይ የሚያደርሰው

ቅጣት ከባድ ነው። ምናልባት አትሌት አብርሃ ሙሉንም

መቀጣጫ ለማድረግ ሲል አፍኖት ሊሆን ይችላል። ስለ

አትሌቱ ዕውቀት ያላችሁ ታዳሚዎቻችን

[email protected] ላይ ኢሜይል እንድትልኩልን

በትህትና እንጠይቃለን። አትሌታችን ሰላም እንዲሆንም

እንመኝለታለን።

የሚል እጅግ ጨካኝ የሆነ አስተያየት ሰማሁኝ! በእውኑ

ጠቅላይ ሚኒስትራችን አንድ ሰው የሚባሉ ናቸውን…? ለነገሩ

ባለፈው ጊዜም እኚያ አቦይ ስብሀት “ፋጢመት ሞተች

አልሞተች ዘሪሁን ሞተ አልሞተ መለስ ሞተ አልሞተ እኛ

ምን አገባን” አይነት ነገር ሲናገሩ በሰማሁ ጊዜ በእውነቱ

ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከእኛ በቀር አንድ እንኳ አሳቢ ሰው

እንደሌላቸው ተረድቻለሁ።

ኧረ ስለ እትዬ ሚሚ ካነሳን አይቀር የምንቀደው አለን…

እማማ ሚሚ በኤፍ ኤም ራዲዮናቸው ላይ “ጠቅላይ

ሚኒስትሩ ቢሞቱም ግዴየለም” ከሚለው ጨካኝ ንግግር ጋር

አብረው የዘመድ አንጀት ሆኖባቸው ነው መሰል “ደግሞም

ሀገር ውስጥ ያለው ህዝብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤና

እየፀለየላቸው ነው!” ብለው ሆድ አስብሰውኛል። እሜቴ

ሚሚ ልብ አላሉም እንጂ በውጪ ያለውም ኢትዮጵያዊ

እንዴት በአንድ በአንድ እግሩ ቆሞ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ

እንደሚፀልይ ቢመለከቱ ይደነቁ ነበር። የምሬን ነው

የምልዎት በርካታ በውጪ ሀገር የሚገኝ ኢትዮጵያዊ

ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ትልቅ ፀሎት እያደረገ ነው።

እርግጥ ነው የአብዛኛው ሰው ፀሎት እርሳቸው ድነው

የበደሉትን ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ለንስሀ ሞት እንዲበቁ

መሆኑን ሰምቻለሁ። (እኔ እንደሆንኩ የሰማሁትን መደበቅ

አይሆንልኝም።)

ወደ እትዬ ሚሚ ስንመለስ “ክብ ጠረቤዛ” የሚል አንድ

ፕሮግራም አላቸው። እርሱን ፕሮግራም አልፎ አልፎ

ለማዳመጥ እድሉ ገጥሞኛል። አንድ ግዜ ቁጭ ብዬ ስሰማ

አንዱ ወዳጄ ሰማኝና ምን አለኝ መሰልዎ… ይሄ ፕሮግራም

“በማሽካካት እና በጫጫታ የተሞላ በመሆኑ አንዳንድ ጊዜ

ክብ ጠረቤዛ ነው ክብ ባንኮኒ ብዬ እጠራጠራለሁ።”

ብሎኛል የምር ግን እኔ ራሴ ፕሮግራሙን ሳዳምጥ በተለይ

አንዳንድ ጊዜ በገደል ማሚቶ የታጀበ ሳቅ እና ሁካታውን

ሳዳምጥ ይሄንን ሰፈር የት ነበር የማውቀው…? ብዬ አይኔን

ጨፈን አድርጌ አስባለሁ… ትዝ ሲለኝ ለካስ ቺቺኒያ እና

ካዛንቺስ ነው….! የብርጭቆው ኳኳታ የለም እንጂ በእውነት

“መሸታ” ቤቶቻችንን ትውስ ያደርጋል!

በነገራችን ላይ እነ እማማ ሚሚ ሲበሳጩ የሚናገሩትን

አያውቁትም እየተባሉ ይታማሉ። ባለፈው ጊዜ ሙስሊም

ወንድምና እህቶቻችን ላይ ሲያደርጉ የነበረው ዘለፋ እና

ስድብ የቀለጠው መንድር ድራማ ላይ እንኳ የለም።

ብዙ ግዜ ሚዲያ ላይ ያለ ሰው ለብዙሃኑ ህብረተሰብ ስሜት

እና እምነት ይጠነቀቃል። ማህበረሰቡ ውስጥ የአመለካከት

ችግር አለ ብሎ እንኳ ቢያምን የሚሰራውን “ስህተት” ቀስ

ብሎ በተለያዩ የኪነጥበብ ዘዴዎች እና ለዛ ባላቸው

አቀራረቦች ለማረቅ ይሞከራል እንጂ እንደነ እትዬ ሚሚ

“የጉራንጉር ሰፈር ስድብ” እየተሳደቡ መውረግረግ እንኳንስ

ሚዲያ ላይ እና ሜዳ ላይም ቢሆን ከጨዋ ልጅ የማይጠበቅ

ነውር ነው።

ከሁሉ የገረመኝ እማማ ሚሚ ሙስሊም ወንድሞቻችንን

እና መንግስትን ለማሸማገል የሞከሩ ግለሰቦችንም በዜሮ

ማባዛታቸው ነው። “የምን ሽምግልና ነው!? ሽምግልና

የሚባል ነገርማ የለም!” ብለው ከእርሳቸው የሚጠበቅ

(ታይፕ ግድፈት የለውም “የሚጠበቅ” ነው ያልኩት)

ከእርሳቸው የሚጠበቅ አሳዛኝ ንግግር ሲናገሩ ሰምቼ፤

ሽምግልናን የሚያጥላላ እንደምን ያለ እርኩስ መንፈስ

ተጠናወታቸው!? ብዬ ክፉኛ አዘንኩላቸው! ቢችሉ ራሳቸው

ሽማግሌ ሆነው ማስማማት ሲገባቸው ሽምግልናማ “የለም”

ማለታቸው እጅግ አስደናቂ ነው! ስማቸው ሚሚ ቢሆንም

ዕድሜያቸው ለሽምግልና በቂ ነበር። ለነገሩ ለሽምግልና

ዕድሜ ሳይሆን መሰጠት ያስፈልገዋል።

በዚሁ ፕሮግራም ላይ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴሩ አቶ

ጁነዲን ሳዶ ላይ እነ ሚሚ ክፉኛ ተሳልቀውባቸው ሲያበቁ

“ዛሬ ነገ ሳይሉ ከስልጣናቸው በራሳቸው ፈቃድ እንዲለቁ”

እንደሚመክሩ እንዲሁም ፖሊስም በአስቸኳይ

“እንዲቀፈድዳቸው” ከጣራ በላይ እየተሳሰቁ ሲጠይቁ ነበር።

እኔ የምለው ድሮ በደርጉ ጊዜ መንግስቱ ኃይለማሪያም

ጓደኞቻቸው ላይ ሞት እየፈረዱ አብዮት ልጆቻን ትበላለች

እየተባለ ይነገር ነበር። አሁንም ኢህአዴግ ነብሴ ቁልፍ ቁልፍ

የሆኑ እና በአብዮታዊ ዴሞክራሲ አምነው የተጠመቁ

ግለሰቦች እና ድርጅቶች በራሱ በአብዮታዊ ዲሞልራሲ ክፉኛ

ጥቃት እየተሰነዘረባቸው ነው።

ታድያ ይሄ ነገር “አብዮታዊ ዴሞክራሲም ልጆቿን ትበላለች”

ያስብለን ይሆን!?

ኢትዮ ቻናል የተባለው ወሳኝ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ደቀ

መዝሙር ራሱ ይኸው በቅርቡ ክፉኛ ጥቃት ደርሶበት

ላልተወሰነ ጊዜ ጋዜጣውን ብቻ ሳይሆን ሳምሶን ማስታወቂያ

ድርጅትም ሊዘጋ መሆኑን ሰምተን አዘነናል።

ሳምሶን ማስታወቂያ ድርጅት እና ኢትዮ ቻናል ጋዜጣን

የሚያሳትመው ዜድ አሳታሚ ድርጅት ሁለት አመት ሙሉ

የመንግሰት ግብር ሳይከፍሉ ቁጭ ብለው በመገኘታቸው

ባለቤቶቹ ከታሰሩ በኋላ ለዋስትና ሁለት መቶ ሺህ ብር

“ሆጭ” አድርገው ከፍለው ነው የተለቀቁት።

አቶ ሳምሶን ሲናገሩ “ግብር አለመክፈል በኔ አልተጀመረም

የታሰርኩት ከበስተጀርባው ሌላ ነገር ኖሮ ነው” ሲሉ ቅሬታ

አሰምተዋል። ወይ ጉድ! “ጉድ ሳይሰማ መቼም የጠቅላይ

ሚኒስትሩ ፍፃሜ አይታወቅም” አቶ ሳምሶን ምን ነካቸው?

ምንስ ከጳጳሱ የሚበልጡ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ሰባኪ ቢሆኑ

ግብርን ያህል ነገር ለሁለት አመታት ሳይከፍሉ መቆየት ነውር

አይደለም እንዴ!? እዝች ጋ አንድ የተባረከ ወዳጄ የነገረኝን

ልንገርዎትማ… “ኢትዮ ቻናል ነፃ ጋዜጠኝነት ሲባል ከግብር ነፃ

መስሏት ነው እንዴ ይሄንን ያህል ጊዜ ግብር ያልከፈለችው?”

ሲል ጠይቆኛል። ጋሽ ሳምሶን ምን ልመልስለት? ደሞስ

ከጀርባው ሌላ ነገር አለ ማለት ምን ማለት ይሆን? የእኛ ሰዎች

ቅኔ መቼም ብዙ ነው! የታሰርኩት በግንቦት ሰባት ሴራ ነው…

ይበሉና እስኪ ያስቁኝ!

ለማንኛውም ፍርድ ቤት ቀርበው ዋናውን ቅጣት እስኪያገኙ

ድረስ ሁለት መቶ ሺህ ብር ዋስትና አስይዘዋል። ላልተወሰነ

ግዜም “ተወዳጇን” ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ገበያ ላይ አናያትም

ማለት ነው።

የሆነ ሆኖ ግን አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆቿን እየበላች ያለበት

ሁኔታ ነው ያለው። (“ያለበት ሁኔታ ነው ያለውን” ለኢቲቪ

ብቻ ማን ሰጠው!?)

የአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤትን ፖሊስ በሽብር ወንጀል

እንደጠረጠራቸው ተናግሯል። እነ እሜቴ ሚሚ እንዳሉት

ከሆነ ደግሞ አቶ ጁነዲንም የሚቀርላቸው አይመስልም። እኒህ

ሰውዬ ዋና ከሚባሉት የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆች አንዱ

ናቸው።

በጥቅሉ እንደሚወራው ከሆነ… ከአቶ መለስ እና ከህውሃት ጋር

የስጋ ዝምድና የሌለው ማነኛውም የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጅ

የመበላት ዕጣ ፈንታ አለው…! እንዴት አይነት ርሃብ ቢገባ

ነው…? ብሎ ማሽሟጠጥ አይገባም።

በመጨረሻም 1

ርዮት አለሙ

የርዮት አለሙ መፅሀፍ አሁን ገና ደረሰኝ። “የኢህአዴግ ቀይ

እስክርቢቶን” ሽፋኑ ላይ ተመለከትኩት። ልጅቷ መምህርትም

አይደለች…!? እናም በመምህርኛ ኢህአዴግዬ ዴሞክራሲ

የሚለውን ኤክስ አድርጎ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ሲል

ታሳየናለች። መድብለ ፓርቲ የሚለውንም በቀይ እስክርቢቶ

ሰርዞ አውራ ፓርቲ ብሎ ይተካል። ነፃ ፕሬስ የሚለውን ደግሞ

“በልማታዊ ሚዲያ” ያስተካክለዋል። ኢትዮጵያዊነት

የሚለውንስ…? የኢህአዴግ እስክርቢቶ ምን ጣጣ አለው

“ጎሰኝነት” ብሎ “ያስተካክለዋል” ታድያ ከዚህ ሁሉ የደነቀኝ

ምን መሰልዎ…!? የእጅ ፅሁፉ! ኢህአዴግ ማስተካከያውን

ሲፅፍ ቃላቱን ብቻ ሳይሆን ፊደል አጣጣሉንም ውልግድግድ

አድርጎ መሆኑ በጣም አስቆኛል። የራሱ የሆኑትን እነ

“አብዮታዊ ዴሞክራሲ” እንኳን በጥሩ የእጅ ፅህፈት

አያሰፍራቸውም። ትለናለች ርዕዮት!

በእውነቱ ሽፋኑ ብቻ ብዙ ነገር የሚናገር መፅሐፍ ስል

አድንቄያለሁ። እስቲ ደግሞ ገብቼ አነበዋለሁ! እጅሽን

ቁርጥማት አይንካው ብለን እንመርቃታለን!

... ቀጣዩን በገፅ 11 ይመልከቱ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 11

ትንታኔ....ከገፅ 10 የዞረ የጥሬ-ሀብትን መዝረፍና የ ገ ንዘብንም ሆነ ሌላ ተንቀሳቃሽ ካፒታልን በፍጥነ ት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በማንቀሳቀቀስ ብዙ የ ሶስተኛውን ዓለም አገ ሮች መቀመቅ ውስጥ ነ ው የ ከተታቸው። በአንድ አገ ር ውስጥና አካባቢ የ ተተከሉ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ጀምረው ለጥቂት ዐመታት ከተንቀሳቀሱ በኋላ የ ሰራተኛ ዋጋ ውድ ነ ው በሚል እየ ተነ ቀሉ ሌላ ቦታዎች በመውሰድ ተስፋ አግኝቶ ቤተሰቡን ማስተዳደር የ ጀመረውን ሰራተኛ እንደገ ና ወደድህነ ት ዓለም እንዲወረወር ይደረጋል። ከዚህ ጋር ተያይዘው ተግባራዊ የ ተደረጉት የ ሞነ ቴሪ የ ኢኮኖሚ ፓሊሲዎች በሙሉ በየ አገ ሮች ውስጥ የ ተዛባን ሁኔ ታንና በሀብት መባለግን ነ ው ያስከተሉት። በሌላ አነ ጋገ ር፣ እነ ፉኩያማ እንደሰበኩት የዓለም ማህበረሰብ በሊበራሊዝምና በካፒታሊዝም አማካይነ ት ነ ጻነ ቱንና ህልሙን ዕውን ሊያደርግ አልቻለም። በተለይም የ ፋይናንስ ካፒታሊዝም ማደግና ከቁጥጥር ውጭ መውጣት በተጨባጭ የ ኢኮኖሚው ዘርፍና የ ትርፍ ትርፍን ለማካበት ገ ንዘብን በተለያዩ የ ፊናንስ ፕሮዳክቶች አማካይነ ት እዚያው በዚያው በማሽከርከር በሚካሄደው ክንዋኔ ልዩ ነ ት እንዲፈጠር ሆነ ። የ ፋይናንስ ካፒታሊዝምን የ በላይነ ት ለመግታት በየ ጊዜው የሚወሰዱት ያልተሟሉ እርምጃዎች የበለጠ ጥንካሬ እየ ሰጡትና መንግስታትንም በዕዳ በመተብተብ ወደ ማናጋት ደረጃ የ ደረሰበት ሁኔ ታ በግልጽ ይታያል እንጂ የ ተዳከመበት ሁኔ ታ በፍጹም አይታይም። ምክንያቱም በየአውሮፓ ከተማዎች፣ በተለይም በብርሰልስና በዋሽንግተን የ ተቀመጡት ሎቢስቶች ህጉን አርቅቀው ስለሚሰጧቸው ይበልጥ ለመጠናከር ችሏል። በተለይም አሁን በግሪክ፣ በጣሊያን፣ በስፔይና በፖርቱጋል እየ ታየ ያለው በዕዳ መተብተብና የ ፋይናንስ ካፒታል እነ ዚህ አገ ሮች ጥብቅ የ ሆነ የ ባጀት ፖሊሲ እንዲያካሂዱ መገ ፋፋት የሚያመለክተው በዚህ መልክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለፋይናንስ ካፒታል የሚያመች ዓለም አቀፋዊ አገ ዛዝ(Global Governance) ለመመስረት ነ ው። የ የ አገ ሮች ብሄራዊ 11 ነፃነት በመናድና በራሳቸው በመንግስታት መወሰድ ያለበት የ ህብረተሰብ ፖለቲካ ቀርቶ፣ ምን ዐይነ ት የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማካሄድ እንዳለባቸው ዋሽንግተንና ለንደን ወይም ብርሰልስ ይወሰናል ማለት ነ ው። የ ፋይናንስ ካፒታሊዝም በማበጥና፣ ፓርቲዎችንና መንግስታትን በተዘዋዋሪ ፖሊሲያቸውን ለሱ እንዲስማማ እንዲያወጡ በማድረግ በአጠቃላይ ሲታይ ካፒታሊዝምን በአስቸጋሪ ሁኔ ታ ውስጥ እንደከተተው በግልጽ ይታያል። ባለፉት ወራት ዎል ስትሪትን መያዝ(Occupy Wallstreet) በማለት ከአሜሪካን ተነ ስቶ ወደ ምዕራብ አውሮፓ ከተማዎች የ ተስፋፋው ሰላማዊ ሰልፍና ግብግብ የሚያመለክተው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች በፋይናንስ ካፒታል የ ደረሰባቸውን ብሶት ለማሰማትና ቁጥጥር እንዲደረግም ነ ው። ፕሬዚደንት ኦባማም ከሶስት ዐመት በፊት ለምርጫ ውድድር ሲቀርብ „አዎን ይቻላል“ ብሎ ለአሜሪካን ህዝብ ብቻ ሳይሆን „ለዓለም ህዝብም ተስፋ የ ሰጠውን“ ተግባር ላይ ማዋል ያልቻለው፣ በአንድ በኩል በፋይናንስ ካፒታል ማበጥና በፓርቲዎች ላይ የ በላይነ ት እንዳለው የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ ወገ ን ደግሞ የሚሊታሪና የ ኢንዱስትሪው ኮምፕሌክስ የ ኦባማን መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነ ት ብቻ እንዲያካሄድለት ግፊት ስለሚያደርግበትም ነ ው። ከዚህም በመነ ሳትና በዎል-ስትሪት ሰዎች የ ተሰገ ሰገው የገንዘብ ምኒስተሩና የ ኢኮኖሚ አማካሪዎቹ፣ እንዲሁም የ ፊዴራል ሪዘርቡ ሃ ላፊ ቤርናንኪ አሁንም በኒዎ-ሊበራል አጀንዳቸው በመግፋት ኦባማ ፍቱን የ ሆነ የ ስራአጡን ቁጠር በከፍተኛ ደረጃ ሊቀንስ የሚያስችል የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እንዳይከተል አድርጎታል። ከዚህም በላይ አሜሪካ ራሱ በሚሰብከው የነፃ ገበያና የነፃ ንግድ ፍልስፍናው ገበያውን ልቅ በማድረጉ ወደ ውስጥ ስትራቴጂክ የ ኢንዱስትሪ ዘርፎቹም ሆነ የ ፍጆታ አምራች ኢንዱስትሪዎቹ በጣም እየ ተዳከሙበት ነ ው። የ አሜሪካን ገ በያ በቻይናና በሌሎች የ ሩቅ ምስራቅ ኤሺያ የ ኢንዱስትሪ ውጤቶች በመወረር ኤኮኖሚው እየ ተዳከመና የ ስራአጡም ቁጥር እየጨመረ እንዲመጣ ተገድዷል። በዚህም ምክንያት በቀላሉ ሊወጣው የ ማይችለው የ ማህበራዊና የባህል ቀውስ ውስጥ ወድቋል። ሰሞኑን ታትም በወጣ የዓለም አቀፍ ሄራልድ ትሪቡን ላይ በሰፊው እንደተነ ተነ ው፣ አሜሪካ ልክ እንደሌሎች የ ላቲን አሜሪካን አገ ሮች ዕጣ ሊደርሳት እንደሚችል ነ ው። ይህም ማለት የድረግን ትራፊክ የሚቆጣጠሩ ቡድኖች፣ በተለይም ትላልቅ ከተማዎችን በቁጥጥራቸው ስር ማድረግ እንደሚችሉና ከፍተኛ የ ሆነ ህብረተሰብአዊ ቀውስ እንደሚመጣ ነ ው። በዚህ ላይ ለተወሳሰበ የ ጦር መሳሪያ የሚወጣው ወጪና ለጠቅላላው የመከላከያ ኃይል የሚፈሰው በጀት በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ መዛባት በማስከተል ወደፊት ሊወጣው የ ማይችለው ሁኔ ታ ውስጥ እየ ከተተው ነ ው። ይህ በዚህ እንዳለ፣ በኢኮኖሚ ድጎማው ሳይሆን በሚሊታሪውና በፖለቲካው ጥንካሬ በመነ ሳት በተለይም እንደኛ ያሉ ደካማ አገ ሮችን በሱ የ ጦርነ ት ስሌት ውስጥ ማካተት ቀላሉ መንገድ ሆኖ አግኝቶታል። በኢኮኖሚ መስክ ደግሞ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ የስራ ድርሻን በመውሰድ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገ ሮችን

የ ኢህአዴግን የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ውስጣዊ ይዘት በሚመለከት

ከኒዎ-ሊበራሊዝም ሁኔ ታ በመነ ሳትና በመተንተን የ ተሰጠ

መግለጫ ወይም ትንተና የ ለም። የ ኢህአዴግ የ ኢኮኖሚ

ፖሊሲ ስምና ውስጣዊ ባህርይ ምን እንደሚመስል ካልታወቀ

ደግሞ ምን ዐይነ ት ትግል ማካሄድና ምንስ አማራጭ

ለመስጠት እንደሚቻል በጣም አስቸጋሪ ይሆናል። አንድን አገ

ዛዝ በአምባገ ነ ንነ ት ስምና ዲሞክራሲ ባለመኖሩ፣ ወይሞ

ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ግልፅ የ ሆነ አሰራር የለም ብሎ

መፈረጁ ብቻ አይበቃም። በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያለ የ

ረዥም ጊዜ ታሪክ ያለውንና በስልጣኔ ጥማትና በዲሞክራሲ

እጦት የሚሰቃይን ህዝብ በሶስት መፈክሮች ብቻ መሸንገ ልና

የ ስልጣኔ ውንም ጎዳና ማሳየ ት አይበቃውም። የ አገ ራችንን

የ ተወሳሰበ ችግርና፣ በአገ ዛዙና በውጭ ኃይሎች መሀከል

ያለውን የ እከክልኝ ልከክልህ የ ጥቅም መተሳሰር ለመተንተን

ከአምባገ ነ ን ባህርይው፣ ከመደብለ ፓርቲና ዲሞክራሲ እጦት

ባሻገር ሄዶ መተንተን ተገቢ ነ ው። ያም ሆነ ለማንኛችንም

ግልጽ እንዲሆን፣ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ከሁለት ዐመት

በኋላ መከተል የ ጀመረው በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት

(IMF) ተዘጋጅቶ የ ቀረበለትን የ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ነ ው።

ፓሊሲውን ያላያችሁ ካላችሁ ማሳየ ት ይቻላል። በስምምነ

ቱና በፖሊሲው መሰረት፣ 1ኛ)የ ኢትዮጵያ የ ውጭ ገንዘብ

ከዶላር ጋር ሲወዳደር በደርግ ዘመን 2.05 ብር በአንድ ዶላር

ይመነ ዘር የነ በረው፣ ከኢህአዴግ ጋር በተደረሰው ስምምነ ት

5 የ ኢትዮጵያን ብር በአንድ ዶላር እንዲመነ ዘር ይደረጋል።

ይህ ኢኮኖሚስቶች ዲቫልዌሽን የሚሉት ገ ንዘብን ዝቅ የ

ማድረግ ፖሊሲ በኒዎ- ሊበራሎች ዕምነ ት ወደ ውጭ

የሚላክ ምርትን በብዛት እንዲሸጥ ያደርጋል ተብሎ

ይታመንበታል። እንደዚህ ዐይነ ቱ ፖሊሲ ደግሞ በተለይም የ

ኢንዱስትሪ ምርትን በጥራት አምርተው ለማይልኩ አገ ሮች

እንደፍቱን መሳሪያ ሊሆን እንደማይችል ከብዙ አገ ሮች ታሪክ

የ ምንማረው ሀቅ ነ ው። ወደ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔ ታ

ሲመነ ዘር በገንዘብ ቅነ ሳው የ ተነ ሳ የ አገ ሪቱ የንግድ ሚዛን

መሻሻል ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ እየ ተዛባ ነ ው የመጣው።

በዚያው መጠንም ዕዳዋ ሊጨምር ችሏል። በጊዜው ከውጭ

በሚመጡ ዕቃዎች ላይና በመለዋወጫ ዕቃ ጥገ ኛ በሆኑ

ኢንዱስትሪዎች ላይ የ ማምረቻ ዋጋ ከፍ በማለቱ ለግሽበት

ምክንያት ሆኗል። 2ኛ) በስምምነ ቱ መሰረት ኢትዮጵያ የ አገ

ሯን የውጭ ንግድ መገበያያ ለውጭ ካፒታልና ዕቃዎች ክፍት

ማድረግ አለባት። ይህም ሌላው የኒዎ-ሊበራሎች ዕምነ ት

ሲሆን፣ አንድ አገ ር ገ በያዋን ክፍት ካደረገ ች ለኢኮኖሚ

ዕድገ ት አመቺ ሁኔ ታን ትፈጥራለች። ኢንቬስተሮች

በመምጣትና መዋለ-ነ ዋይ በማፍሰስ የስራ መስክ ሊከፍቱ

ይችላሉ። የስራ መስክ ሲከፈት፣ ገ ቢ የሚያገ ኘው የመግዛት

ኃይሉ ከፍ ይላል ይሉናል። የ ዚህንም ውጤት የ ተከታተልንና

የ ምናውቅ ያለን ይመስለኛል። ይህ ሁለተኛው ፖሊሲ

በተግባር ሲመነ ዘር በርካሽ ዋጋ የሚያመርቱ እንደቻይናና

ህንድ የመሰሉ አገሮች የ አገ ራችንን ገበያ በቀላሉ መውረርና፣

ወደ ውስጥ ደግሞ ብዙ ተመሳሳይ ምርት የሚያመርቱ

ኢንዱስትሪዎችን መምታት ችለዋል። 3ኛ)በመንግስት ቁጥጥር

ስር የነ በሩ ኢንዱስትሪዎች፣ ባንኮች፣ የመድህን ኩባንያዎችና

ሌሎች መደብሮች ወደ ግል መዘዋወር አለባቸው። ይህን

ፕራይቬታይዜሽን ይሉታል። አሁንም በኒዎ-ሊበራሎች ዕምነ

ት የመንግስት ጣልቃ ገብነ ት ለኢኮኖሚ ዕድገ ት ጠንቅ

ስለሚሆን፣ ቁልፍ የሚባሉ የ ኢኮኖሚው ዘርፎች ከመንግስት

ቁጥጥር ውስጥ መላቀቅ አለባቸው። የኒዎ-ሊበራሎች ዋናው

ችግር የ የ አገ ሮችን የ ኢኮኖሚ ሁኔ ታና አወቃቀር ከታሪክ

አንጻርና ከግሎባል ካፒታሊዝም ሁኔ ታ በመነ ሳት ትንተና

ለመስጠት አለመቻል ነ ው። የ ህብርተሰብን የ ዕድገ ት

ታሪክና የባህል ሁኔ ታ በፍጹም ከግምት ውስጥ አያስገ ቡም።

በእነ ሱ ዕምነ ት አሜሪካንና የ ተቀረው የ ካፒታሊስት አገ

ሮች የሚሰራበት የ አሰራር ዘዴ ካለምንም ችግር በሁሉም አገ

ሮች ተግባራዊ መሆን ይችላል። ስለሆነ ም፣ በተወሳሰበ የ

ማቲማቲክስ ሞዴሎችና ከመንግስት በተሰጣቸው

ስታትስቲክስ ብቻ በመደገ ፍና በመነ ሳት የ አንድን አገ ር ሁኔ

ታ ከዳር እስከዳር እየ ተዘዋወሩ ሳያጠኑ በሚያቀርቡት

`ትንተና` ብዙ ፖለቲከኞችንና ምሁራን ነ ን ባዮችን ያሳስታሉ።

13 በዚህ የ ተሳሳተ ምክርና ፖሊሲ ምክንያት የ ተነ ሳ በቀላሉ

በመንግስት ቁጥጥር ስር የነ በሩ ሀብቶች በኢህአዴግ

ካድሪዎችና በአቶ መለስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርገ ዋል።

ቀሪውን በቀጣይ እትም ይዘን እንቀርባለን

ሃሳባችሁን በ [email protected] ላኩልን እናስተናግዳቸዋለን።

በግሎባል ካፒታሊዝም የአስተሳሰብና ድህነ ትን የመፈልፈል

መዳፍ ውስጥ እንዲወድቁ በማድረግ ልዩ የፖለቲካና የ

ኢኮኖሚ ሁኔ ታ ተፈጥሯል። በተለይም በአገ ራችን የ ሰፈነ

ው በጣም ደካማ የ ምሁር እንቅስቃሴ የ አሜሪካን

ኢምፔሪያሊዝም በአገ ራችን ውስጥ ገብቶ የ ፈለገውን

እንዲፈተፍት ሁኔ ታውን አመቻችቶለታል። የነቃ የ ሲቪክ

ማህበረሰብ በሌለበት አገ ር ውስጥ የውጭ ኃያላን

መንግስታት እንደልባቸው ሰርገው በመግባት የ ጭቆና ሁኔ

ታዎችን ያዘጋጃሉ ማለት ነ ው። ሀብት እንዲዘረፍ ሁኔ

ታውን ያመቻቻሉ። ዕድገ ት እንዳይመጣ ያግዳሉ። ሰፊው

ህዝብ አቅመቢስ እንዲሆን ያደርጋሉ። ዲሞክራሲያዊ

መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲገ ፈፉ፣ በተለይም በስልጣን

ላይ ላሉት ልዩ ልዩ የ ጭቆና መሳሪያዎችን ያቀብላሉ፤

ምክርም ይሰጣሉ። ለነ ሱ የሚያመች ልዩ ዐይነ ት የ ኃይል

አሰላለፍ በመፍጠር ትግሉን አስቸጋሪ በማድረግ የ ጭቆና

ዘመኑንም ያራዝማሉ። የ ወያኔ ን ፓለቲካና ጥንካሬ

እንዲሁም የ ሀብት ዘረፋና ድህነ ትን መፈልፈል ከዚሁ፣

በተለይም የ እንግሊዝና የ አሜሪካን ግሎባል ካፒታሊዝም

ፕሮጀክት ነ ጥሎ ማየ ት ስህተት ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገ

ኛ የፖለቲካ አካሄድም ነ ው። ግሎባል ካፒታሊዝምና የ

ወያኔ አጀንዳና የፖለቲካ ትርምስ ! ወያኔ ን በአብዮታዊ

ዲሞክራሲና በሶሻሊዝም ስም የሚወነ ጅሉትን ስሰማና ሳነ

ብ፣ ፈረንጆች እንደሚሉት በአንድ ዐይኔ አለቅሳለሁ፣

በሌላው ደግሞ እስቃለሁ። ሁላችንም ቢሆን ወያኔ እንዴት

እንደተፈጠረ በትክክል አናውቅም። መልስ ሊሰጡን

የሚችሉት በአጠናነ ሱ ላይ የ ነ በሩና ለተወሰነ ም ጊዜ

አብረው የ ታገ ሉና ራሳቸውን አግለው ከወጡት ነ ው።

ይሁንና እነ ዚህም ቢሆኑ በእነ መለስ ጭንቅላት ውስጥ

ገብተውና ድርጊታቸውን ተከታትለው የ ወደፊት

ፕሮጀክታቸው እንደዚህ ነ ው ብለው የ ተሟላ ስዕል

ሊሰጡን አይችሉም። እኔ ም በቦታው ብሆን ኑሮ ቀደም

ብዬ መተንበይ አልችልም ነ በር። በተለይም ደግሞ የ እነ

ሌኒንን መጽሀፍ የሚደግምና ኢምፔሪያሊዝምን እዋጋለህ

የሚል ሰውና ድርጅት፣ በኋላ 180 ዲግሪ ተገ ልብጦ የ

ኢምፔሪያሊስትን ፕሮጀክት ተግባራዊ ያደርጋል ብሎ

ከመጀመሪያውኑ መናገር ያዳግታል። አንድን ግለሰብና

ድርጅት በድርጊቱ ብቻ ነ ው መመዘንና ትንተና መስጠት

የሚቻለው። ከዚህም በመነ ሳት ነ ው ለዲሞክራሲና ለነ ፃነ

ት እታገ ላለሁ የሚልን ግለሰብንም ሆነ ድርጅት የፖለቲካ

ትንተና ትክክል መሆኑንና አለመሆነ ኑ መመርመርና የ ራስን

ፍርድ መስጠት የሚቻለው። 12 ብዙዎችን የ ተቃዋሚ

ኃይሎች ትክክለኛ የ ፓለቲካ ትንተና ለመስጠት ያገ ዳቸው

በእኔ እምነ ት ከሶስት ምክንያቶች በመነ ሳት ነ ው።

አንደኛ፣ የ ኢህአዴግ አወቃቀር አንድ ወጥ ስለሆነ ና፣

ከውስጥ ፓርቲውን የሚቆጣጠረው ደግሞ በማርክሲስት-

ሌኒንስት ርዕዮተ-ዓለም የሚመራ ነ ው ተብሎ ስለታመነ ና፣

ከላይ ወደታች የ ተዘረጋ የ ስልጣን እርከን ስላለ፣ በዚህም

ምክንያት አገ ዛዙ የሚያራምደው የ አብዮታዊ

ዲሞክራሲያዊ ፖሊሲ ነ ው የሚል ነ ው። ሁለተኛው

ምክንያት፣ በደርግ ዘመን የ ሰፈነ ውና በሶሻሊዝም ስም የ

ተካሄደው ጭፍጨፋና ህብረተሰብን ማከረባበት ብዙዎችን

የ ሰከነ ና በጥናት ላይ የ ተመረኮዘ ትንተና እንዲሰጡ

አላስቻላቸውም። በሶስተኛ ደረጃ፣ አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ

ኃይሎች በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም አማካይነ ት በዓለም

አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ

ትክክል ነ ው ብለው ስለሚያምኑና፣ ከነ ፃ ገበያ ባሻገር ሌላ

አማራጭ የ ሌለ ስለሚመስላቸው አሜሪካንን እንደቅዱስ

ኃይል ነ ው የሚመለከቱት። ስለሆነ ም በአቶ መለስ ዜናዊ

የሚመራው መንግስት በሚያካሄደው የ ኢኮኖሚ ፖሊሲና

በአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በተጠነ ሰሰውንና በሚሰበከው

የኒዎ-ሊበራል ኢኮኖሚ ፖሊሲ መሀከል ግኑኝነ ት የ ለም።

ከዚህ የ ተሳሳተ ግምትና አመለካከት በመነ ሳት ብዙዎቹ የ

ተቃዋሚ ኃይሎች ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የ

ተከተላቸውንና ተግባራዊ የሚያደርጋቸውን የ ኢኮኖሚ

ፓሊሲዎች የሚመለከቱት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና

ከዓለም ባንክ አገ ሮችን ከማድኸየ ት ፕሮጀክት ውጭ ነ

ው።በብዙዎቹ ዕምነ ት የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም

ባንክ አደረጃጀት በቀጥታ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነ ት

መፈጸሚያ በኋላ የ ተፈጠረውን የ ኃይል አሰላለፍና የ

ሶስተኛውን ዓለም አገ ሮች በአዲሱ የዓለም የስራ-ክፍፍል

በማካተት ቀጭጨው እንዲቀሩ ከማድረግ ጋር የሚታይና

የሚያያዝ አይደለም። እስከማውቀው ድረስ ከተቃዋሚ

ድርጅቶች ወይም ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 12

ወያኔ አባይ ወልዱን እንደገና መረጠ

ሕወሃት ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቀሌ ሲያካሂድ

የከረመው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ አባይ ወልዱን ሊቀመንበር

አድርጓል።ሕወሓት በኢትዮጵያ ዋናውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ

ስልጣን የተቆጣጠረው፣በአገሪቱ እየደረሰ ላለው ሰብዓዊና

ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ ግንባር ቀደም ተጠያቂ፣ በስም ፌዴራሊዝም

የሚቀልደው ሌሎችን ድርጅቶች እንደ አሽከር በማየት የራሱ

ታዛዥ በማድረጉ አልፎ አልፎ በኢህአዴግ ውስጥ የጉምጉምታ

መነሻ የሆነው ድርጅት ማን ሊቀመንበሩን ይይዛል የሚለው

የስልጣን ሽኩቻ በመቀሌና የአዲስ አበባ ቡድን በሚል ውስጥ

ውስጡን ከጉባዔው በፊት በይፋ በጉባዔው ሂደት የተስተዋለ

ሲሆን የመቀሌው ቡድን አስቀድሞ እንደተዘገበው አባይ ወልዱን

የወቅቱ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ሊቀመንበር ለማድረግ

የጀመረው ትግል በበላይነት ተጠናቋል። የክልሉን ፖለቲካ ትኩሳት

በቅርበብ የሚከታተለው አምዶም ገ/ስላሴ በተደጋጋሚ ለህብር

ሬዲዮ የስልታን ሽኩቻውን አስመልክቶ በሰተው ቃለ ምልልስ

ሁለቱም ቡድን በየበኩሉ እስከ ቀበሌ ካድሬ ከጉባዔው በፊት

ሲያደራጅ ቆይቷል። አንዱ የአንዱን ቡድን ደጋፊ ለመጣል

በልብነትና አልፎ አልፎም በአረና ወገንተኝነት ሲከሱ ቆይተዋል።

የአባይ ቡድን ከፌደራለል እነ በረከትን ከብአዴን የያዘ ሲሆን ወ/ሮ

አዜብን በሕወሓት ስራ አስፈጻሚ ውስጥ ማስመረጡ ቀድሞም

ሲባል እንደነበረው <<የመለስ ራዕይ የመለስ ራዕይ >> የሚለው

መዝሙሩን አጠናክሮ የሚወጣ መስሏል።በጉባዔው በአንደኝነት

ከአንድ ሺህ ድምጽ በላኢ አግኝተው የተመረጡት ዶ/ር

ደብረጽዮን የሳቸው ሳይሆን የአባይ ቡድን ገኖ የሠጣበት ፖሊት

ቢሮ ተመርጣል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ም/ሊቀመንበር ሆነዋል። ሰውዬው በፌዴራሉ

ከፓርቲው ቀጥሎ በግለሰብ ደረጃ ከፍተኛ ስልጣን ያለው ሲሆን

ለስም ከተቀመጡት አቶ ሀይለማርያም በታች ባብዛኛው

የሚያሽከረክር የነበረው በአንድ ለአምስት አደረጃጀት እነ አባይ

ወልዱ መቀሌ ላይ በጉባዔው የዘረሩት የአዲስ አበባ የሕወሓት

ቡድን ነው። አዲሱን የስልጣን ድልድል የሀይለማሪያም የደህነት

አማካሪ አለቃ ጸጋዬ በርሄን ጨምሮ እነ አባይ ጸሐዬን ከድርጅቱ

የፖለቲካ ስልጣን በ<<ክብር>. አሰናበትኩ ብሏል።

አስቀድሞ በተሳታፊነት እግራቸውን አስገብተው በጉባዔው

የድምጽ ስልጣን የተሰጣቸው ከአዲስ አበባው ቡድን ጀርባ

የተሰለፉት እነ ስብሃት እና አርከበ መቀሌው ቡድን በአብዛኛው

ማንበብ መጻፍ ጭምር የማይችሉ የጉባዔ ተሳታፊዎችን በአንድ

ለአምስት ጠርንፎ ያሰበውን አሳክቷል።

አባይ ወልዱን መልሶ የድርጅቱ ሊቀመንበር ያደረገው ሕወሓት

ለሕወሓት እና ለድርጅቱ ስራ አስፈጻሚነት ዘጠኙን መርጧል።

1) ኣባይ ወልዱ”ኣባይ ደራ” ሊቀ መንበር 2) ዶክተር ደብረፅየን ገ/

ሚካል ምክትል ሊቀመንበር 3) ጌታቸው ኣሰፋ 4) ዶክተር ኣዲስ

ኣለም ባሌማ 5) ፈትለወርቅ ገ/ዝሄር(ሞንጀሪኖ) 6) ኣለም

ገብረዋህድ 7) በየነ መክሩ 8) ዶክተር ቴድሮስ ኣድሓኖም

9) ኣዜብ መስፍን ኣባላት ሁነው ተመረጡ።

ሕወሓት ከቀደሙ አመራሮችና አባላት መካከል የፖሊት ቢሮ

አባላት መካከል አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አቶ አባዲ ዘሞ፣ አቶ ቴድሮስ

ሐጎስና አቶ ፀጋይ በረኼ በመተካካት ሸኝቷል፡፡ ወ/ሮ ሮማን ገብረ

ሥላሴ፣ አቶ ተወልደ ብርሃን በርኼና አቶ ተክለወይኒ አሰፋ

በፈቃዳቸው ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ለቀዋል፡፡ ለማዕከላዊ

ኮሚቴ አባልነት 50 አባላት ታጭተው 45 አባላት የተመረጡ

ሲሆን፣ የአቶ ዓባይ ወልዱ ባለቤት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ክንደያ ገብረ ሕይወት

ሳይመረጡ ከቀሩት አምስት አባላት መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በተካሄደው 11ኛው የሕወሓት ጉባዔ

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ከተመረጡት ውስጥ አቶ

ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነ ማርያምና አቶ ገብረ መስቀል

ታረቀ ሳይቀጥሉ ቀርተዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አሰፋ፣ ዶ/ር አዲስ

ዓለም ባሌማና ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር አዳዲስ

አባላት ሆነው ገብተዋል፡፡

በጉባዔው አስቀድሞ በተሳታፊ ውስጥ ከገቡ በሁዋላ

ባለድምጽ ከሆኑት በመተካካት ቀድሞ ተሸኝተው

ከነበሩት መካከል አቶ ስብሃት ነጋ ከዚህ ቀደም አቶ

መለስ እሳቸውን ከሕወሓት ፖሊት ቢሮ አሰኝተው

ሚስታቸውን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ሲያስመርጡ <<ሕወሓት>>

ቀሚስ ለብሷል ድርጅቱን ቀሚሱን ማስወለቅ አለብን የሚል

የውስጥ የፖለቲካ አግቦ በየደረሱበት ሲያንጸባርቁ ይሄው

ለአደባባይ መብቃቱ ይታወሳል። አቶ ስብሃት በሕወሓት የተንኮል

ሴራ በግንባር ቀደምትነት ቀያሽና አስፈጻሚነት ተደጋግመው

የሚጠቀሱ ሲሆን የመቀሌው ቡድን ወ/ሮ አዜብን ጭምር ይዞ

የጠሉትን የአባይ ቡድን ዛሬም በቀሚስ ለባሽነት ይክሰሱት

አይታወቅም። የአዲስ አበባው ቡድን <<ትግራይ አለማችም>>

<<ትግራይ መጭ ተጠቀመች ለእድገት እንቅፋቱ ያልተማረውና

ሌባው የአባይ ብድን ነው የሚል ቅስቀሳው በጉባዔው ላይ

በተወሰነ ደረጃ መንጸባረቁን የሚናገሩ ወገኖች አባይ ወልዱ አንድ

ለአምስት አስቀድሞ ከተነገረው ውጭ አልሰማም በማለት

ተልዕኮውን የተወታ መስሏል።የሕወሓት መሪዎች የስልጣን ሽኩቻ

አገሪቱ ከዚህ አመራር ተጨማሪ አደጋ እንጂ ለውጥ እንደማይመጣ

አመላካች ሲሆን አቶ ሀይለማሪአምን በአሻንጉሊትነት ለማስቀጠል

የወሰነው ሕወሃት የመቀሌው ቡድን ስኬት ሀሳቡን ያስለውጠዋል

በቀጣዩ ወር የሚታይ ይሆናል።

በአዲሱ ምርጫ መሰረት የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 2. ወ/ሮ አዜብ መስፍን 3. ወ/ሮ

ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር(ሞንጆሪኖ) 4. አቶ ጌታቸው አሰፋ አቶ

አባይ ወልዱ(የመቀሌው ቡድነን) መሪና ዶ/ር ደብረጽዮን የአዲስ

አበባው ቢድን መሪ 5. አቶ አባይ ነብሶ 6. ዶ/ር ቴድሮስ አድሓኖም

7. ወ/ሮ አረጋሽ በየነ 8. ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ 9. አቶ በየነ ምክሩ

10. አቶ ኪሮስ ቢተው 11. ዶ/ር አብርሃም ተከስተ 12. ወ/ሮ ያለም

ፀጋይ 13. ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም 14. አቶ ሀዱሽ ዘነበ 15. አቶ

ተወልደብርሃን ተስፋዓለም 16. አቶ ሚኪኤለ አብርሃ 17. አቶ

ተወልደ ገ/ፃድቃን 18. አቶ ጎይትኦም ይብራህ 19. አቶ ጎቦዛይ ወ/

አረጋይ 20. አቶ አባይ ወልዱ 21. ዶ/ር ገ/ህይወት ገ/እግዚአብሄር

22. አቶ ተስፋአለም ይሕደጐ 23. አቶ ሀጐስ ጎደፋይ 24. አቶ

ዓለም ገ/ዋህድ 25. አቶ እያሱ ተስፋይ 26. አቶ ሃይለ አስፍሃ 27.

አቶ አፅብሃ አረጋዊ 28. አቶ ብርሃነ ፅጋብ 29. ወ/ሮ ሙሉ ካሕሳይ

30. አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም 31. አቶ ዳንኤል አሰፋ 32. አቶ

ጌታቸው ረዳ 33. አቶ ሃፍቱ ሀዱሽ 34. አቶ ገ/መስቀል ታረቀ 35.

አ/ሮ ዘነበች ፍስሃ 36. አቶ ኢሳያስ ገ/ጊዮርጊስ 37. ወ/ሮ ኪሮስ

ሃጐስ 38. አቶ ሽሻይ መረሳ 39. አቶ ብርሃነ ገ/የሱስ 40. አቶ

ኢሳያስ ታደሰ 41. አቶ ነጋ በርሀ 42. አቶ ማሙ ገ/እግዚአብሄር 43.

አቶ ተኽላይ ገ/መድህን 44. ወ/ሮ ቅድሳን ነጋ 45. አቶ ይትባረክ

አመሃ ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቀድሞ በህብር ሬዲዮ ህወሓት

መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዘገብንበት

ወቅት የህወሓት ታዣዥ የሆኑት የብአዴንና የኦህደዴድና የዸህዴግ

አመራሮችን ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማሰባሰብ

ሲሚክሩ ተስተውሏል። ህወሓት በ1993 ለሁለት የተከፈለ ሲሆን

የአቶ መለስ ቡድን ከባድመ መልስ ሊዘምትበት ተነሳውን ቡድን

አንጃ የሚል ስም ለጥፎ ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት

ውስጥ አቶ አባይ ጸሐዬ ይቅርታ ጠይቀው ሲመለሱ አቶ ገብሩ

አስራትን ጨምሮ ተባረው የቀሩ እንደ አቶ ስዬ በሙስና ታስረው

የወቱ ነበሩ።

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ተከፍሎ የነበረ ሲሆን

ጠላቶቻችን ብሎ የፈረጀው ሌላው የኢትዮጵአ ሕዝብ ስልታን

ሊያገኝ ይችላል በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ፈቶ አብሮ በክልልና

በፌዴራል ዋና ዋናውን ስልታን ተቆጣጥሮ የቆው ሀይል

ለዘንድሮውም ክፍፍል ተመሳሳይ <<ሽምግልና>> ሊአካሂድ ይችል

ይሆናል።

www.hiberradio.com

ዓባይ ወልዱ የአሁኑ የወያኔ መሪ ሲሆን ነባር ታጋይ ነው።

እዚህ ግባ የሚባል ፖለቲካዊም ሆነ ማህበራዊ እውቀት

የለውም። የሱ ጠንካራ ጎን ተደርጎ የሚወሰደው ቡስና ውስጥ

አልገባም ስለሚባል ነው። የረባ ቤትና ልብስ እንኳ የለውም።

ከዚህ ሌላ እሱ ከሚያስበው የተገደበ ዓለም ውጭ ሌላ ዓለም

ለማወቅ ምንም ፍላጎት የሌለው የትግራይን ህዝብ እንደ ክፉ

እንጀራ ኣበት በማፈንና በማሰቃየት ህዝቡን ወደ መሃል አገር

አንዲፈናቀል እያረገ ያለ የደደረ ልብ ያለው የክልል ፕረዚደንት

ነው።

የትግራይ ህዝብ ያልታደለ ህዝብ ነው። ከመጀመሪያው ያ

እንደ ህፃን ልጅ የሚንተባተበው ገብሩ አስራት የሚበላውንና

የሚጠጣውን ሳይቀር ሊቆጣጠረው የሚሞክርበት ስርዓት

ዘርግቶ ለስቃይና ለመከራ አጋለጠው በአንፃሩ ደግሞ

ትግራይን በሙስና ባገር ደረጃ የአንደኝነት ደረጃ እንደትይዝ

አድርጓት ነበር።

በመቀጠል ደግሞ ከእጅ አይሻል ዶማ እንደሚባለው ሃለቃ

ፀጋይ በመባል የሚታወቀው እጅግ በጣም ደካማ ሰው ስልጣን

ተሰጠውና ህዝቡን ወደ ልማት ሳይሆን ወደ ቁልቁለት መርቶ

ሲበቃው አቆመ።

አሁን ዓባይ ወልዱ ይኸውና ህዝቡን ይጫወትበታል።

ያልሰራውን ግብር እንዲከፍልና ያልቻለው የፖለቲካ ጠላት

እንዲባል የሚያደርገው ይህ እንኳን ሊመራህ ልትመራው

እንኳ የማይመች ፍትረት ፕረዚደንት አደረጉለት።

በዙሁ ደካማ አመራር ምክንያት በርካታ የትግራይ ባለሃብቶች

በቅርቡ ወደ መሃል አገር እየሸሹ እነደሆኑ ይታወቃል። ባሁኑ

ጊዜ ትግራይ ውስጥ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ግሽበት ተፈጥሯል።

ዓባይ ወልዱ ሃቀኛ ነኝ ብሎ ስለሚያስብ የሱ ሃቀኛ መሆን

አለመሆን ግን ህዝቡን እንጀራ እንደማይጋግርለት ለመገንዘብ

ነጋሪ የሌለውና ማስተዋሉም የተሳነው ደካማ ሰው ነው።

ከልሳነ ህዝብ ዘጋቢ

አዜብ መስፍን አሁንም የድራማው ተወዋናይ መሆንዋ

አያስገርምም። በሷ ስም በየፈረንጅ አገሩ የታጨቀው

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት እሷን አክብሮ በመያዝ ብቻ ነው

ሊገኝ የሚችለው። ያ የወያኔ ቡድን ለልጅ ልጅ የሚተርፍ

ሃብት ባከማቹ ባለስልጣናት የተሞላ ስለሆነ አዜብ ታማኟ

ግምጅ ቤት ናት። ይህች ሴት አራዳ ናት ለጊዜው መልካም

መስላ የሚያስፈልጋትን ትሰበስብና አንድ ቀን አሜሪካ

በገዛቻቸው ቪላዎች ገብታ ገንዘቧን ኢንቨስት እያደረገች

ተንፈላሳ ካልኖረች እናን ታዘቡን። ያ ሁሉ አዞ እንባ ምን

ማለት እንደሆነ ነገ ራሱ ጊዜ ያሳየናል።

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 13

አባይ Vs ስብሃት ኔትዎርክ – (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ) ዛሬም (እንደወትሮው) አንድ ቀሽም አስተያየት ልስጥ! በህወሓት ዉስጥ ያለው የሃይል አሰላለፍ እያየን ነው። ስብሃት ነጋ የሚዘውረው ቡድን አንሰራርቶ የፖለቲካ የበላይነቱ የሚቆጣጠርበት ዕድል ሊኖር ይችላል (መላምት ነው፣ ከውዲሁ በዚህ ጉዳይ እርግጠኛ መሆን አይቻልም)። የስብሃት ነጋ ኔትዎርክ ህወሓት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ የትግራይ ህዝብ ጠፍሮ ሲገዛና ሲያሰቃይ የነበረ ነው። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን በሆነ ዉስጣዊ አለመግባብት ምክንያት የስብሃት ኔትዎርክ እየተመናመነ መጣ። አቶ አባይ ወልዱ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት ከሆነ በኋላ ኔትዎርኩ በሌሎች ተተካ። ይባስ ብሎ ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ አቶ አባይ ወልዱ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነ። ከዚህ ግዜ ወዲህ ስለ አባይ ወልዱ ባህሪ መጥፎነትና የፖለቲካ ብቃት ማነስ በሰፊው ይወራ ጀመር። እኔ የሌሎች የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያህል የአባይ ወልዱ የተሟላ መረጃ የለኝም። እንደሌሎቹም በሓሳብ ክርክር ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም። (መለስ፣ ስብሃት፣ ስዩም፣ አባይ ጸሃየ፣ አርከበ፣ ቴድሮስ ሓጎስ፣ ፀጋይ በርሀ … ብዙዎቹ በደንብ አቃቸዋለሁ)። አባይ ወልዱ ግን በደንብ አላውቀውም። አንድ ግዜ ብቻ በሆነ አጋጣሚ ተገናኝተን ብዙ አውርተን ነበር (አብርሃ ደስታ መሆኔን ሳያውቅ ማለት ነው)። ያኔ እንዳየሁት ትህተኛ (humble) ይመስላል (በአንድ ግዜ የሰው ባህሪ ለመገምገም ቢከብድም)። ስለዚህ ስለ የአባይ ወልዱ ፖለቲካዊ ብቃትና የግል ባህሪ ጥሩነት ወይ መጥፎነት መመስከር አልችልም። ቁልፍ የሚባል የህወሓት ስልጣን ለባለቤቱ መስጠቱ ግን እንደማንኛውም ሰው ገርሞኛል። ይህ እንዳለ ሁኖ ስለ አባይ ወልዱ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ። አባይ በህወሓት ካድሬዎች አይወደድም። አባይ የአምባገነንነት ባህሪ እንዳለውና የፖለቲካ ብቃት እንደሚያንሰው ለህዝቡ እንዲደርስ ተደርጓል። ማነው ስለ አባይ መጥፎነት የሚያወራ ቢባል መልሱ የህወሓት ካድሬዎች መሆናቸው ግልፅ ነው። ለምን? አባይ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር ከመሆኑ በፊት ቁልፍ የህወሓት ኔትዎርክ ተቆጣጥረው የነበሩ ካድሬዎች የስብሃት ነጋ ታማኞችና ዘመዶች ነበሩ። ትግራይ ሙሉ ተቆጣጥረውት ነበር። አባይ ወልዱ የነሱ ዘመድ አይደለም። አባይ ስልጣኑ ከጨበጠ በኋላ የስብሃት ታማኝ ኔትዎርከኞች ስጋት አደረባቸው። ስጋታቸውም የህወሓት ኔትዎርከኞች ቀስ በቀስ ይቀየራሉ፤ ቁልፍ የሆኑ የስልጣን እርከኞችም ከስብሃት ታማኞች ወደ አክሱም ተወላጆች ይሸጋገራሉ የሚል ነበር። የስብሃት ህወሓቶች አንድ ሰው ከስልጣን ለማውረድ ወይም ስልጣን ለመስጠት ሲፈልጉ ስለሰውየው የፈጠራ ወሬ (የሚያዋርድ ወይ የሚያስወድስ) ለህዝብ ይነዛሉ። በቂ ኔትዎርክ ስላላቸው እነሱ የፈለጉትን ወሬ ከህዝብ ለማድረስ አይቸገሩም። እነሱ የፈልጉትን ሰው ወደ ስልጣን ለማውጣት ስለሰውየው ጥሩ ነገር ያወራሉ፤ ካልፈለጉት ደግሞ ስሙን ያጠፉታል። በዚህ መንገድ ስልጣን ወደ አክሱም ተወላጆች እንዳይሸጋገር በመስጋት የአባይን ስም ከማጥፋት አልቦዘኑም። አባይ ብቃት አለው ወይ የለውም ለሚለው ሰው ትክክለኛ ግንዛቤ የለውም። በትክክልም አባይ የቀድሞው የኔትዎርከኞቹ ማንነት በተቻለ መጠን ቀይሮታል። እንደፈሩት አልቀረም። ነገር ግን የአባይ ኔትዎርክ እግር ሳይተክል ፈተና ገጥሞታል። የስብሃት ኔትዎርክ እንደገና የሚያንሰራራበት ዕድል እያገኘ ይመስላል። ለትግራይ ህዝብ (በኔ እምነት) ከስብሃት ኔትዎርክ የአባይ ኔትዎርክ በብዙ እጥፍ ይሻላል። ምክንያቱም የአባይ ኔትዎርክ ከሞላ ጎደል ለዘብተኛ ነው። የስብሃት ግን መርዘኛ ነው። ትግራይ በተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ስር የወደቀችበት ምክንያት በስብሃት ኔትዎርክ ነው። (አሁን አባይም ተመሳሳይ ነገር የጀመረ ይመስላል)። ምናልባት ስብሃት ከተሳካለትና ትግራይን መልሶ ከተቆጣጠረ አደገኛ ስለሚሆን የሽግግሩ ግዜና አጋጣሚ ተጠቅሞ ዓረና ፓርቲ የህወሓት አመራር አባላት በማሳመን በህወሓት ዉስጥ ህቡእ የዓረና አባላት የሚፈሩበት መንገድ መመቻቸት አለበት። ህወሓትን ማሸነፍ የምንችለው ወደ ህወሓት ዘልቆ በመግባት ነው። ህወሓት ዉስጡ ስለበሰበሰ ፓርቲው ዉስጥ ገብቶ ኔትዎርኩን መቆጣጠር ያን ያህል የሚከብድ አይሆንም። It is so!!!

አንዳርጋቸው ፄ አሁንም እስር ላይ ነው፡ ያ ያልታጠቀና ለመከላከል አቅም ያልነበረው ሲቪል ሰው በየመን መንግስት እርዳታ ከአውሮፕላን ማረፊያ አፍኖ የወሰዳቸው መንግስት ልክ በጦር ሜዳ ላይ ግዳይ እንደጣለ ጀግና ጧት ማታ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ሲለፍፍ መስማት አሳፋሪና አሳዛኝ ነበር። የወያኔ ህልም በአሻንጉት ዳኛዎቹ በአንዳርጋቸው ላይ ያስወሰነው የሞት ፍርድ ለመፈፀመ ከመጓጓቱ የተነሳ ካድሬዎቹ ሬሳ የሸተተው ጀጅብ ሆነው ነበር፡፡ የእንግሊዝ መንግስት ምስጋና ይግባውና ወየያኔዎቹ በመማስጠንቀቂያ ቀልባቸውን ገፎ አንዳች ዓይነት እርምጃ በዜጋዬ ላይ እንዳትወስዱ በማለት አፋቸውን አስይዟቸዋል።

የፀሃፊዎች ጥቅሶች ከአዲስ አድማስ የተወሰደ ስለታሪክ) - ሰው የህይወት ታሪኩን ለሌላ ሰው የተናገረ ዕለት ነው ታሪክ የተወለደው፡፡ አልፍሬድ ዲ ቪጅኒ - ጀግና ፈፅሞ የታሪኩ ኮከብ አይደለም፡፡ ማሪሊም ማንሶን - ዩኒቨርስ የተሰራው ከአቶሞች ሳይሆን ከታሪኮች ነው፡፡ ሙርየል ፋክይሰር - ያልተነገረ ታሪክን በውስጥህ እንደመሸከም ያለ ስቃይ የለም፡፡ ማያ አንጄሉ - ሁሉም የየራሱ የህይወት ታሪክ ጀግና ነው፡፡ ጆን ባርዝ - የሰው ልጅ በቆዳ የተለበጠ ታሪክ ነው፡፡ ፍሬድ አሌን - ልብ ወለድ ፎቶግራፍ አይደለም፤ የዘይት ቅብ ሥዕል ነው፡፡ ሮበርትሰን ዲቪስ - ሁሉም ግሩም ታሪኮች አስር በመቶ እውነት ናቸው፡፡ ኮሎኔል ዴኒስ ፋኒንግ - ህብረተሰብን የሚገዙት ታሪክ ተራኪዎች ናቸው፡፡ ፕሌቶ - እያንዳንዱ የምፈጥረው ታሪክ እኔን ይፈጥረኛል፡፡ የምፅፈው ራሴን ለመፍጠር ነው፡፡ ኦክታቭ ያ ኢ. በትለር - እውነቱን ለማወቅ የሁለቱንም ወገኖች ታሪክ ማግኘት አለብህ፡፡ ዋልተር ክሮንኪት - እያንዳንዷ ሴት የራሷ ታሪክ ባለቤት መሆን አለባት፡፡ ያለበለዚያ ሁላችንም የዝምታው አካል ነን፡፡ ዛይናብ ሳልቢ - አገራትና ቦታዎች ታሪክ፣ ተረክና ባህል አላቸው። ሞሼ ሳፍዲ - ይሄን ታሪክ በፊት ሰምታችሁት ከሆነ አታስቁሙኝ፡፡ ምክንያቱም ደግሜ ልሰማው እሻለሁ፡፡ ግሮውቾ ማርክስ /ገብረክርስቶስ ደስታ / ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አእላፍ ሌሊት ሚሊዮን መሰለኝ ፍቅሬ አንችን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ። እኔ እወድሻለሁ የሰማይ መሬቱን የባህር ስፋቱን የዓለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል እንደ ፅጌ-ረዳ እንደ አደይ አበባ እንደ ሎሚ ሽታ፡፡ እንደ እጣን ጢስ እንጨት፣ እንደ ከርቤ ብርጉድ፣ እኔ እወድሻለሁ፣ አበባ እንዳየ ንብ፡፡ እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደሚያስሰው ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው ማር ወለላዬ ነሽ ከረሜላ ስኩዋር አማርኛ አይበቃ፤ ወይ ጉድ! ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር፣ እኔ እወድሻለሁ እንደማታ ጀንበር። እንደ ጨረቃ ጌጥ፣ እንደ ንጋት ኮከብ፣ እኔ እማልጠግብሽ ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፣ ስወድሽ፡፡ ጡት እንዳየ ህፃን ወተት እንዳማረው ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ህይወቴ ነው። ጣይ እንዳየ ቅቤ ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው፣ አፈር መሬት ትቢያ ውሃ እንደሚበላው፣ ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ብዙ ሺህ ዘመናት እልፍ አእላፍ ሌሊት ውድ እወድሻለሁ፣ ዐይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ ስወድሽ ስወድሽ እኔ እወድሻለሁ።

ሃሳባችሁን በ [email protected] ላኩልን እናስተናግዳቸዋለን።

አረማሞ ተደባልቆ በቃይ ሲናር አረማም ሲዘራ ካልዘሩ ምርጥ ዘር አክሞ ገለባ ነው ትርፉ ቀን ቆጥሮ ለከርሞ፡፡ ሙግት ያኮረፈ ሌሊት …መንጋቱን የረሳ ውስጤ እያደመጠ …የነፍሴን ጠባሳ እርምጃ ውልክፍክፍ …ጉዞውም የአንካሳ የጨለማ ሙግት …የንጋት ወቀሳ፡፡ ጀንበሩ ወልደዮሐንስ (ከኒዮርክ ቡፋሎ) * * * “አንተ” - ማለት!... “አንተ” ማለት፡- ብዙ ነህ! ብዙ - ብዙ! … የብዙ - ብዙ! “አንተ” ማለት …. አገር ነህ፣ አገር ከነጉዝጓዙ፡፡… ያገር ጉዝጓዙ… አቤትና አቤት … አቤት! ብዛቱ፡… ጂባው፣ አጐዛው - ጀንዴው - ቁርበቱ፡፡… ተራራው - ሸለቆው - ዱሩ፣ እንኮይ - መስኩ፣ መብሰክሰኩ…፤ እሾህ አሜኬላው - ቆንጥሩ… ባንድ ሌማት እሬት! ምሬት! የአጋም ፍሬው --- ጣዝማ ማሩ፣ ደግሞም፡- አድባር! አውጋር! … ያለ መጣፍ፣ አማኝ - እምነት በመጣፍም ያለ መጣፍ፡፡… መቼም - ሰው “አገር ነውና” አገርም “ሰብዓ ምርቱ” ታሪክ - ቋንቋ - ባህል - ቀኖናውና - ትውፊቱ፣ እሱ ነው! የማንነትህ እትብቱ፡፡… ከእኒህ - መነቀል… ማለት፡- ከሥር - መመንገል! ካናት - መቃጠል! ከእግር - መመንቀል! ማለት ነው፣ አገር እንደ ሰው!! ሰማህ!? (ወንድዬ ዓሊ) ለጠላት መንበርከክ ለባዕዳን ዓለም ታሪክን መለወጥ በሰው ሰራሽ ቀለም አሳልፎ መስጠት ብሄራዊ ጥቅም ወገንን መበደል በጥላቻ በቂም በፍፁም!! የህዝባችን ባህል አልነበረም መይሳው ዮሐንስ በታሪክ ሲዘከር አንገቱን የሰጠ ለሀገሩ ክብር በአጥንቱ ያጠረ ዳር ድንበር በደሙ የፃፈ የታሪክ ማሕደር። ዛሬ በባዕድ ተደፈረ ፍትሕ በሐሶት ተቀየረ የወላጅ አደራ ተሰበረ ወገን ታጣ የጠነከረ

ልሳነ ህዝብ ቅፅ 2 ቁጥር 13 ገፅ 14

መቀነትሽን አጥብቂ

(የኮተቤው የሻው ተሰማ)

የዕድሜሽን ተውሳክ-ተቀጥላ፣ በመሐፀንሽ ስትቋጥሪ፣

ያበሳሽን ቀነ ገደብ፣ ስትቀንሽ- ሰትደምሪ፣

በትኩስ-በበራዱ፣ ቃር ማቅለሽለሽ… ስትጀምሪ፣

ዶሮ መረቁ ቢያርብሽ፣ ወጡ በቅመም ባይጥም፣

‹ቅሪት ያምራታል› ተብሎልሽ፣ ለደንታሽ ደንታ ባይሰጥም፣

ፍሪዳ ባይጣልልሽ፣ ዕድል ባይጥፍሽ ለቅልጥም፤

አቅበጥብጦ ሲያስፋሽክሽ…፣ ሲያስመልስሽ የበላሽው፣

ቃሪያ ጎመኑ… ውል ሲልሽ ያኔ ነበር የጀመርሽው፡፡

ከባጥ በላይ ፅኑ ፍዳ፣ በልጅ ስቃይሽን መቁጠር፣

በኪነ ጥበቡ ትንግርት፣ ቅጥያሽ ሆኜ ስፈጠር፡፡

በመዓልት-ሌሊት ተራክቦ፣ ሲኳኳል የአዋርኅ ቀመር፣

ቀናትን ሣንምት ውጧቸው፣ ሣምታትን ዘጠኝ ወር፣

በወርኀ ማዕዶት ሽግሽግ፣ ለዓመት ሦሰት ወር ሲቀር፣

እንደ ልሳኑ ስያሜ፣ ‹ቅሪት› ነበርሽ ቀደም ሲል፣

ነፍስ ስዘራ ስጠራቀም፣ ከ‹ፅንሰነት› ተብዬ ‹ሽል›፣

ከደምሽ ደም እየሞላሁ፣ እድገቴን ባንቺው ሳሻሽል፣

በዚያ የሸክም ወራት፣ ሲያበራይሽ የልብ ጋር፣

ነፍስሽ ሕቅታን ስትቃዥ፣ ተሠርታ በሞት አውታር፣

ላይ ቅጽበት እፎይታ አጥተሸ፣ ሲያባዝትሽ ሰቀቀኑ፣

በብጽዓት እየማለድሽ፣ በምልጃ በጧፍ- በጣኑ፣

ነገ የሰማይ ያህል- እየመጠቀ ቀኑ፣

ቁም ስቅልሽን እያሳየሁ፣ ‹ነፍሰጡር› ሆነሽ ተጦሬ፣

ባፍንጫሽ እያስቃተትሁ፣ ልክ ዘጠኝ ወር ቆጥሬ፣

በመጣሁ-ቀረሁ ሕማማት፣ የቀናት ለጠፍ ደምሬ፣

የአራስ ቤት ወግ ላሳይሽ፣ ስበቃ ለምስልሽ ፍሬ፤

ደሜን ከደምሽ በመድፈቅ፣ አጥንቴን ካጥንትሽ አጋጥሜ፣

‹የምጥ ማርያምን› ሲማልድ፣ ምጥሽን ሲያምጥ አዳሜ፣

አስደግድጌው እንደ ጃን፣ ወንድ ሴቱን አስቁሜ፣

ኮኮቤ ሲቃናልኝ- ፍካሬው ሲያምር ሕልሜ፣

በሽርት ውሃ ብሥራት-መርዶ፣ ተሸጋገርኩ ለሌላ ዕድሜ፡፡

…..

የጣረ ሞት ምሥል ጉሙ፣ ሲገፈፍ ጥቁር ጨለማ፣

የአራስ ጥሪ ወጉ አይቀርም፣ ልብሽ ሐሴት ሲያሰማ፡፡

የደም ካሣ በልቶ ላይጠግ፣ አካል እም አካልሽ ደማ፣

ተቀጥላ ላበቀልሽ፣ ጥሪት ሀብትሽን የሚሻማ፣

አንባረቅሽ አሉ በዕልልታ፣ ገምገም ዙሮ እስኪሰማ፡፡

አንቺማ ምን ታደርጊው፣ የወረስሽው ነው ከእናትሽ፣

በጅማትሽ ድር ተደርቶ፣ የተማገ በሕይወትሽ፡፡

እንደ ተወጠርሽ ቃተሸ ተርገብግበሽ መሞትሽ፡፡

ግትሽን ብገጠግጠው፣ ወሸሽ ተመጦ እስኪደማ፣

ጆሮሽ መዝሙሬን እንጂ፣ ማንቋረሬን እንዳልሰማ፣

ፍዳን እንደበረከት መታረዝን እንደሸማ፣

ችጋርን እንደሲሳይ፣ ጥምን እንዳልተጠማ፣

አሜን ይሁን እንድትይው፣ ልብሽ እንዳያቅማማ፣

ታቻችይው ዘንድ ቸሮሻል፣ በረበበብሽ ግርማ፡፡

ደግሞ እኮ!…

ከጽንስ እስከ ሕርስ ቀን፣ መልክ ያጣው ስቃይሽ አንሶ፣

ከዳዴ እስከ ድክድክ፣ በደግሞ ባናት ተመልሶ፣

ከጉንፍሽ እስከ ጀርባሽ፣ አካሌ አካልሽን ዳሶ፤

ጽዱው ገላሽ ሲበሸቅጥ፣ በምናምኔ ርሶ፣

ሥቄ ስጫወት ፈክተሸ፣ ሳለቅስ ሆድሽ ተላውሶ፤

ስንፎለፎል ተፍነክንከሽ፣ ሲከፋኝ አንጀትሽ ጨሶ፣

አጸፋን መመለስ እንጂ፣ እንደ ቅጥንብሬ ጣጣ፣

ሆድሽ ከሁዳድ ሰፍቶ፣ ብሶት የማይቆጣ፣

የንባብ-ትርጓሜው ሰምና ወርቅ፣ ምሥጢሩ ጠፋኝ ጨርሶ፣

የማልሽው ኪዳን ምንድነው፣ በ´ናትነትሽ ደርሶ?

ይመጡንሻል ቃላቱ፣ ብልሽ ‹እምዬ እናቴ›

የመልኬ ምሥል መቅረጫ፣ ራሴን ማያ መስተዋቴ?

ሳትበይው ከምትከፍይው፣ ከዘጠኝ ወር ሸክም ዕዳሽ፣

ከጭንቅ አጥቢያ እስከ ማግስት፣ ከምጥ ዋይታ ምሬት

ፍዳሽ፡፡

ሥጋሽ አልቆ-ጥላሽ ቀርቶ፣

ደስታዬ እያረካ፣ ትኩሳቴ ሲጎዳሽ፣

ገላሽን ችፌ በጣጥሶት፣ እከክ አንፍሮት ቆዳሽ፣

ፊትሽ መጋፊያ መስሎ፣ አንድ ቀን እንኳን ሳይጸዳሽ፡፡

ሌሊት ቁንጫ ግጦሽ፣ መዓልት በቅማል ተልተሸ፣

በጥም አጎዶ ከስለሽ፣ በጠኔ ጣር ተላግተሸ፡፡

የእርሜን እንጥፍጣፊ፣ ለኔ ወተትሽን ግተሸ፡፡

ራስሽን ለኔ መግበሽ፣ አንቺን አሮብሽ ጎመን፣

የዘጠኝ ወር ሸክም ፍዳው፣ ሳይበቃሽ የምጡ ጣመን፣

የሐሩር ንዳድ አንፍሮሽ፣ ጽልመት አውሮሽ ዳፈን፡፡

ደቂቁ ሊቅ ተብዬ፣ ትሩፋትሽ ሰው እንድሆን፣

የዋተትሽበት ምሥጢር፣ መስታወቴ ምን ይሆን?

አይ አንቺ እምዬ እናቴ፣

አንድ ሆነሽ ምዕልፍቴ!

ሥገጠግጠው ሥጋሽን፣ እስኪነጥፍ የወረርሽ ጠል፣

በጀርባሽ አሞላቀሽ (አሟቅለሽ) ስትውይ፣ ትከሻሽ

እሲከገነጠል፡፡

ጭኖችሽን ዱካ አድርጌ፣ በደረትሽ ስንጠላጠል፣

አንቺ በለፋሽበት፣ እኔ ደልቶኝ ስቀማጠል፡፡

ለግብርሽ የሚመጥን መስታወቴን ማ` ልበል?

ለዚህ ወለታሽ አጸፋ እናት ይልሻል አገሩ፣

እኔም እናቴ ብልሽ፣ መች ሊመጥንሽ ዳሩ፡፡

ለማንም ባልቴት እንስት፣ ከተቸረ እንደዋዛ፣

ኅብረ ቀለሙን አወይቦ ካደረገብኝ ደብዛዛ፣

አሕዛብም ብሆን-አዋማ፣ ሰልሳላ ማተቤን በጥሼ፣

እንደ ናቡከደነፆር፣ ሣር ብበላ አጎንብሼ፤

‹እናት› ብዬ አልጠራሽም ከሌሎች ጋር ደምስሼ፡፡

አንችነትሽ ምጥቅ ነው፣ እናት ከመባል ይልቃል፣

የግብርሽ ስንክሳር-ዚቁ፣ በስያሜ መች ያልቃል፡፡

ግን ታዲያ መስታወቴ፣…

ምናብሽን ፍቅር ቸፍችፎበት፣ ንቁ አእምሮሽ ዶለዶመ፣

ነገን መተንበይ ተስኖት… ግምት በውስጥሽ ጨለመ፡፡

ያበው ተረት አልሰማሽም፣ የያቀበሉን ሊቀባበሉ፣

የዛሬ ልጆች ሠልጥነው፣ ‹ምሳሌ› ይሉታል አሉ፡፡

ስለናትና ልጅ ፍቅር፣ አብጠልጥለው ሲተርቱ፣

ለኔ አስመስለው ፈርደው፣ አንቺን ለይስሙላ ´ረቱ፡፡

የናትና ልጅ ፍቅር፣ እንደ ጀማ ውሃ ሁሉ፣

ከታች ወደ ላይ አይፈስም፣ ከላይ ወደ ታች እንጂ አሉ፡፡

ሲያጎርፍም ሆነ ሲጎድል፣ ከላይ አያቋርጥም፣

ከታች ያለው ግን ተቀብሎ፣ ያጸፋ መልስ አይሰጥም፡፡

ሲያፈስ ይኖራል እስከ ሕልፊት፣ የላይ ከበላይ ተቀብሎ፣

የላይኛው ሞልቶት ተርፎት፣ የታች አያውቀም ጎሎ፡፡

ያለ የሌለው አሟጦ፣ የላይ ለበታች ይሰጣል፣

የታችኛው ጉግማንጉግ ግን፣ ተቀብሎ ያሰምጣል፡፡

ከላይ ነውና አድራሻሽ፣ አንቺም እንደ ጀማ ውሃ፣

የቤዛነትሽ ወሮታ፣ የተለገሰሽ አምኃ፣

ጠፍቶሽ ከሆነ ምሥጢሩ፣ ነገ ቢመለስ ብለሽ፣

ጉድ ተቀብጥረሻል እሙ፣ የማን ያለህ ትያለሽ!?

ያኔ ሳነሆልልሽ፣…

በኮልታፋው ልሳኔ፣ በጥዑም አንደበቴ፣

ልቦናዬ ቂም ሳይደቅል፣

በፍቅርሽ ፍቅር ላበቅል፣

ጠርቼ አልጠግብም ነበር፣ ስምሽን መስታወቴ፡፡

ሲያልፍ ተረት ይመስላል፣

አንቺን ብቻ እንደምወድ፣ እንደምጦር ስገዘት፣

ቃሌ ስለታም ነበር፣ ያላጠቆረው ዝገት፡፡

ትንቢትን በጨቅላ ምናብ፣ በኩሸት-ግነት ከስቼ፣

እንደመድረክ መነባንብ፣ ስተርክ አስፋፍቼ፤

ሆድሽ ብሽ እንዳይለው፣ እህል-ውሃውን አስማምቼ፣

ምች እንዳይጋረፍሽ፣ የድባብ ምጽላል ገዝቼ፤

ቆፈን እንዳይጎዳብኝ፣ ፀሐይ በሰፌድ አግብቼ፤

‹እጦርሻለሁ› እል ነበር፣ የቅዱሳን ስም ጠርቼ፡፡

መስከረም በቀልድ አይጠባም፣

ከፈጩበት የጋፉበት፣ የመሰልሽበት ተስፋ፣

ከምድር ላቆየሽው ብድር፣ አቁረሽ ከሆነ አጸፋ፣

የደቀንሽውን ቋት አብሽው፣ዱቄት ሳይሞላ ተደፋ፤

እንደማምንሽ ባላመንሽኝ- ምነው ድራሼ በጠፋ፡፡

የፍቀርሽ ማጠንት ያጠነው፣ የልቤ ፀዓዳው ቀፎ፣

ያዳም-ሄዋን ግብር ሆነና፣ ያለቦታው ተሸክፎ፣

በአካል ዘ`ማካሉ ላይ፣ የናርዶስ ሽቶ አርከፍክፎ፣

እማኝ-ውል ሰሚ… ጠርቶ፣ የገባልሽን ቃል ገድፎ፤

ለባዕድ ጽጌ ሆኗል፣ ከሄዋን ሥር ተወትፎ፡፡

ሰው አፈር ነው ታጥቦ አይጠራም፣ ከክፋት ድቤ ተደባልቆ፣

ከትስብእት ባህርዬ ይልቅ የአውሬነቴ ባሕርይ ልቆ፤

እጅሽ ሲያጥር ዐይቼ፣ ውስጤ በንዋይ ቀልጦ፣

እንደ ሸንኮራ መጥጬ፣ ተንገፈገፍኩሽ እንደ ፌጦ፡፡

እናም እምዬ እናቴ፣

አንድ ሆነሽ ምዕልፊቴ፡፡

ያነጣጠርሽው ስቶ፣ ያቀባበልሽው ከሽፎ፣

ራዕይሽ ቅዠት ሆኖ፣ ከሚቀር ጥላሽን ገፎ፣

በሸንጎ ዐውድ ከሚጥለኝ፣ ልብሽ ፀፀት አትርፎ፣

አምሳለ እንጎቻ ከንፈርሽ፣ ከሚስም እኔን አቅፎ፣

ሲሳይ ወመድኅን ጡትሽ፣ ትን ባለኝ ተወትፎ፡፡

ወይ በጨነገፍኩልሽ፣ ውሃዬ በቀረ ሰፍፎ፡፡

ለሰሚው ግራ ነገር፣

ወይ አይበላ ጥሞ፣ ወይ አይደፋ አጸይፎ፤

ግራ አጋብቼሽ ከምቀር፣ እጅ- እጅ እንዳለ ገንፎ፣

ወስላታው ልቤ በነደለ፣ በማንጉርጥ ተቦትርፎ፡፡

አንቺም ምርኩዝሽን ባመንሽ፣ ይራዳሽ ነበር ደግፎ፡፡

ለነገሩማ እምዬ አንቺው ባንቺው ስትፈርጂ፣

የቁም-ስቅልሽን ያየሽው፣ መቼም ፈርዶብሽ እንጂ፣

እኔ በዕድሜ ድርብ ሳሻቅብ፣ አንቺ ቁልቁል ስትወርጂ፤

ባራት እግርሽ ስትቆሚ፣ በሦስት እግርሽ ስትሔጂ፣

ለጉሮሮሽ ደጅ ሰጠኝ፣ ለ`ህል-ውሃ ስትማልጂ፤

የዶሮ ሙቀት ሲያተኩሽስ፣ በነፋስ ሽውታ ስትበርጂ፤

የቅድሙን አሁን ረስተሸ፣ ወግ ደርሶሽ ስትጃጂ፤

ዕድሜ ግዳይ ሲጥልሽ፣ እንድጦርሽ ነው ስታረጂ?!

ድንገት እንድህ የሆንሽው፣

ንቁ አእምሮሽ ሲነሆልል፣ ንስር ዐይኖችሽ ሲጨልሙ፣

ከራራው ጅማትሽ ሲረግብ፣ እጅ `ግሮችሽ ሲካክሙ፣

እንዳቀፍሽኝ አስተኝቼ፣ እንዳጠባሽን መግቤ፣

ጦሬ እንድቀብርሽ ይሆን፣ እንዲራራልሽ ልቤ

…እምዬ…

ጠግቦ ባደረም ይሁን፣ ወይ ተርቦ በዋለ፣

አልጋ በተለወጠ፣ ወይ ዘመን ባጋደለ፣

ተበልጦ.. ልጁን ዘንግቶ፣ ሆድሽ ለሆዱ እንዳላለ፣

ልብሽ እንዳልሾከተ፣ ግብርሽ እንዳልታጎለ፣

ትልቅ-ትንሹ ዋቢሽ ነው፣ ከኔ ነው የጎደለ፡፡

ዶሮና ጫጩቷ ልብ ይሏል፣

ጩ -ጩ- ጩ- ጩ- ጩ- ጩ- እያሉ፣

በክንፏ ተከልለው፣ ያፏን ነጥቀው እንዳልበሉ፣

ራሳቸውን ባካል፣ ብልጥ ሲሉ

በየፊናቸው ኮብልለው፣ ትተዋት ኮበለሉ፡፡

ወላድ ይፍረደነኝ ብለሽ ባይዋጥልሽም ቅሉ፣

ባንቺ ልቀት፣ በኔ ድቀት፣ ፍች አያገኝም ቃሉ፤

ለኔ በዝቶ ላንቺ ያንሳል፣ እናትና ልጅ መባሉ፡፡

እንግዲህ መስታወቴ፣

ምኞትሽ አልቦ ሆኖ፣ የመሐን ዕድል ካስቸረ፣

እንደ ሸኮኮ ጸሎት፣ ፍጻሜው ካላማረ፣

ሆድሽን ሆድ አስብሽው፣ ልጄን ብለሽ አትነፍርቂ፣

ውላጅሽ ገደል ይግባ፣ መቀነትሽን አጥብቂ፡፡

(የሻው ተሰማ፣ የጥቁር አፈር ትሩፋ፣ ገጽ 79-87)