addis guday(1)

42
አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ƛ.ም

Upload: backback

Post on 27-Dec-2015

112 views

Category:

Documents


24 download

DESCRIPTION

mag

TRANSCRIPT

Page 1: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 2: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 3: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

8 የታፈኑ እውነቶች መጸዳጃ ቤት

48 አንድ ጉዳይ

ዳንኤል ክብረት29

46 ስፖርት አዲስ ጉዳይ

11 የአረንጓዴ ጉዳይ

4 ሰሞነኛ ጉዳይ

22 ማስታወሻ

15 ሃይማኖት

ሙስጠፋ ሓሚድ ዮሱፍ

ብርሃኔ ረዳኤ (ዶ/ር)

ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር)

26 ወንጀል

34 የወግ ማዕድ

‘ቃልቾቹ’

ጠላት ሳይኖር ምሽግኤ.ሲ.ቲልየር

ጣ’ል

37 ኤፍሬም እሸቴ

መስፍን ሀ/ማርያም

አበራ ብርሃኑ

44 ልቦለድ

17 ጤናማ ውበት

የካቲት 17 2004 ዓ.ም

ውዳሴና እንክብካቤ

ኮከብ አሳየ

ከተማን እንደ ዘአካል

የንግድ ትርኢቶችና ተግዳሮቶቻቸው

38 ቢዝነስ

“ስድስት ኪሎ ሲሞት አምስት ኪሎ መጠውለጉ አይቀሬ ነው”

18 ቃለ ምልልስ

ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)

ፕሪምየር ሊጉ ተወዳጅ እንጂ መሪ አልሆነም

30 ዐቢይ ጉዳይ

41 ጥበባት

የ9 ዓመት-80 ሺህ ብር-በ3 ወር

ደራሲው ለደራሲውስለ ድምጽ ብክለት

ቤቢ ሻወር

በዩኒቨርስቲዎቻችን የሠፈነው ተማሪነት? ጐሰኝነት? ብሔርተኝነት?

32 ሐራምቤ ሐራምቤበዕውቀቱ ሥዩም

“ራእየ ዮሐንስየዓለም መጨረሻ”

ስብሐት ገ/እግዚአብሔር

“ሁለተኛው ቀይ ሽብር ተፋፋመብን”ከሠማዕታቱ ቤተሰቦች አንዱ

ጽድቅ ለማን?

Page 4: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ሰሞነኛ ጉዳይ

Page 5: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 6: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 7: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

የታፈኑ እውነቶች

ማንም ከምንም አስቀድሞ ሊያውቀው የሚፈልገውና ነፍሱ የምትቃትትለት ጉዳይ ማንነት (Identity) ነው፡፡ ማንነትን አለማወቅ ወይም ማነኝ

ለሚለው ጥያቄ መልስ ማጣት ሰዎችን ከራሣቸው ጋር አጣልቶ ለገዛ ሕይወታቸው ጠላት ያደርጋቸዋል፡፡ ደረጃው ይለያይ እንጂ የማንነት ጥያቄ የሚያስከትለው ግለሰባዊና ማኅበራዊ ቀውስ ከፍ ያለ ነው፡፡

አንድ የማስኮሙኒኬሽን መማሪያ መጽሐፍ “Each of us enters the world with little or no sense of identity. We gain an idea of who we are from the ways others define us” ይላል፡፡ በግርድፉ ወደ አማርኛ ሲመለስ “እያንዳንዳችን ወደዚህች ዓለም ስንመጣ ማንነትን በተመለከተ የሚኖረን ስሜት ጥቂት ወይም ምንም ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ ራሳችን ማን ስለመሆናችን ፍንጭ የምናገኘውና የምናውቀው ሌሎች እኛን የሚገልፁባቸውን መንገዶች ተንተርሰን ነው” እንደማለት ይሆናል፡፡

የማንነት ጥያቄ ቀዳሚ የሰው ልጅ የዕውቀት ልኬት መስፈሪያ እንደመሆኑ ለዚህ አንገብጋቢ ጥያቄ ምላሽ ማግኘትም ግድ ይሆናል፡፡ ማንነትን በማጣት (Identity crisis) ውስጥ የገባ ሰው የራሱ ሕይወት ጠላት መሆኑም አይቀሬ ነው፡፡ ማንነት የሰው ልጅ ነፍስ ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ የሚያዳብረው ባህሪ ነው፡፡ አንድ ሰው ሰው ስለመሆኑ፣ መለያ ስም ያለው ስለመሆኑ፣ በቤተሰቡና በአካባቢው ስላለው ቦታ፣ የተፈጠረበት አካባቢ ባህልና ወግ የርሱም ጭምር ስለመሆኑ፣ ስለነዚህ ሁሉ መረጃ የሚያገኘው አጠገቡ ካሉ ሰዎች ነው፡፡ ይህን እውነት በማስረጃ ለማጠናከር የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች “ቀበሮ ወስዳ ጫካ ውስጥ ያሳደገቻትን ልጅ” እና “በአንድ ቤት ውስጥ በር ተቆልፎባት በጨለማ ውስጥ ለዓመታት የኖረችውን ህፃን” በምሳሌ ይጠቅሳሉ፡፡ ቀበሮ ያሳደገቻት

በዩኒቨርስቲዎቻችን የሠፈነውተማሪነት? ጐሰኝነት? ብሔርተኝነት?

ልጅ ሰው ስለመሆኗ አንዳች ግንዛቤ ያልነበራት በመሆኑ ከሰው አፈጣጠሯ በቀር አረማመዷ (በእጅና በእግር በመጠቀም) እንዲሁም አጯዋጩኋ ጭምር ከቀበሮዋ ሙሉ በሙሉ የተወረሰ ሆኗል፡፡ አመጋገቧም ከቀበሮዋ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህች ህፃን ሰው መሆኗንም ሆነ ማንነቷን አታውቅም፡፡ ማን እንደሚያሳድጋት ግን ታውቃለች— ቢያንስ ከቀበሮዋ ጋር በሚገባ ትግባባለችና፡፡ ጨለማ ቤት ውስጥ ያለችው ህፃንም በተመሳሳይ ቋንቋ ካለመቻሏ በላይ ለመናገርም አንዳች ሙከራ አታደርግም፡፡ ሰዎች ሲያገኟት ምንም ዓይነት ዕውቀት የሌላትና ማንነቷን በተመለከተ አንዳች ግንዛቤ ያልነበራት ሆና ነው፡፡ እንግዲህ ሳይንሱ እንደሚለው ሰው ስለራሱ ያለውን ግምትና አሁን ያለውን አስተሳሰቡን የሚሰጠው ማኅበረሰቡ እንጂ ራሱ አይደለም፡፡ እንዲያ ቢሆንማ የሰው ልጅ እንደተወለደ ስለራሱና ስለተዛማጆቹ የጠለቀ ዕውቀት ይዞ በመጣ ነበር፡፡

ሰው መሆንን እንዲሁም የተፈጠርንበት ማኅበረሰብን እንደራሳችን ታላቅ ሃብት አድርገን በዚህ ጥላ ውስጥ ራሳችንን መቅረፃችን የማንነታችን ትልቁ መገለጫ ነውና ይህ ሃብት ከሁሉም በላይ በእኛ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ለዚህም ነው ማንም አካል የማንነት ጥያቄን ካነሳ ጉዳዩን በቶሎ መቋጨት የማይችለው፡፡

አንድ ሀገር የአንድ ወጥ አስተሳሰብ ውጤት አይደለም— ሊሆንም አይችልም፡፡ ሰዎች እንግሊዛውያን ተብለው እንዲጠሩ ነጭ መሆንና ከዘር ማንዘራቸው ጀምሮ የዜግነት ክብር ተሰጥቷቸው በእንግሊዝ መሬት ላይ መወለዳቸው አይደለም ምክንያቱ፡፡ ነገር ግን ይህን መለያ ማንነት ያገኙት በመሬቱ ላይ በመኖራቸው፣ በመወለዳቸውና በአካባቢው ያለው ሰውም ‘እንግሊዛዊ መሆናቸውን’ እየነገራቸው ስላደጉ ብቻ ነው፡፡ እነርሱም የዚያን የአካባቢያቸውን ቋንቋ እየተናገሩና በእርሱ ባህልና ወግ ውስጥ እየኖሩ ያሉበትን ቦታ ‘ሀገሬ’ ብለው

መጥራታቸው ነው እንግሊዛዊ ያሰኛቸው፡፡ ለሌላውም ሀገር ይኸው ነው፡፡

የሰው ልጅ ከዚህም አልፎ ማንነቱን ከወል ወደግል ለመውሰድና ጥቂቶች ውስጥ ለመጠቃለልም ይፈልጋል፡፡ ይህ ደግሞ ቤተሰብ፣ ጐሣ፣ ማኅበረሰብ በእያንዳንዱ አባላቸው ላይ የሚፈጥሩት ከፍተኛ ተፅዕኖ ውጤት ነው፡፡ ሰው ከመሆን ሰውነት ባሻገር የኔና የጥቂቶች መለያ ነው ብሎ በማሰብ ጐሠኝነትና ቤተሰባዊነትን አጠንክሮ መያዝ የሰው ልጅ ባህሪ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ፍልስፍናና እውነታ የሰው ልጅ የቤተሰቡና የአካባቢው ውጤት ነው የሚለውን አስተምህሮ ለማ ስረገጥ የቀረበ ነው፡፡ በተለይ ከማንነት ጥያቄ ጋር የተያያዙ ታሪኮች በግጭትና በእልቂት የተሞሉ፣ ለሌሎች የፀብና የጥፋት ምክንያቶች በተለይም ለባለቤቱ ትልቅ የመነሻ ምክንያት የሚፈጥር በመሆኑ ከፍተኛ ጥፋት ያስከተሉ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ የማንም ሰው ማንነት፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ወግ በሌላው ዘንድ መከበር ይገባዋል የሚባልበት ዋነኛ ምክንያት ይኸው ነው፡፡ የተረገጠና የተናቀ የሚያስነሳው አብዮት ማብቂያ የለውምና፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ላለች ከ100 በላይ ቋንቋዎች ለሚነገሩባትና ከ80 ያላነሱ ብሔር ብሔረሰቦች ለሚኖሩባት ሀገር አንድነትን መፍጠር ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁሉም የተለያየ ቀለም ያለው እንደመሆኑ በጋራ ሲሆን ደግሞ ያ ልዩነቱ ውበት ይሆናል፡፡ እንዲያም ሆኖ ከኢትዮጵያዊነት ስሜት ይልቅ የብሔርተኝነት ስሜታቸው ጐልቶ የሚወጣባቸው— በብሔር፣ በጐሣና በእምነት ጐራ ለይተው ‘የኔ ይበልጥ የኔ’ እያሉ የሚፏከቱበትን መድረክ ያበዙ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ አሁን አሁን ይህ አስተሳሰብ ሀገራዊ እየሆነ የመጣ እስኪመስል ከተማሪ አስተማሪ፣ ከወንድ ሴት፣ ከህፃን አዋቂ ድረስ ተዛምቷል፡፡ ከሁሉ የከፋው ግን የዚህች

Page 8: Addis Guday(1)

� አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ሀገር የዕድገት መሠረት ይጣልበታል በሚባልበት ትምህርት ቤት ውስጥ የዘርና የብሔር ልዩነት ከቀለም በላይ ጉዳይ ሆኖ ዕውቀትና ዓላማ ‘ዱባና ቅል’ ሆነው መታየት መጀመራቸው ነው፡፡

የዘረኝነት ስሜት በከፍተኛየትምህርት ተቋማትትምህርት ቤቶች የአንድ ሀገር ዜጋ መቅረጫዎች

ናቸው፡፡ ዜጐች በዕውቀት በልፅገው ሀገራቸውን በአግባቡ እንዲያስተዳድሩ ለማስቻል ትምህርት ትልቁን መሠረት ይጥላል፡፡ ለግለሰብም ሆነ ለማኅበረሰብ እንዲሁም ለአጠቃላዩ የሀገር ዕድገት ትምህርት ወሳኙ ግብዓት ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ‘ትምህርት ድሮ ቀረ’ ወደሚባልበት ዘመን ልንሻገር እያኮበኮብን ያለን መስለናል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብቅ ጥልቅ ሲል ቆይቶ አሁን አሁን የተለመደ እየሆነ የመጣው የብሔር ግጭትና መቆራቆስ ነው፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜ በዩኒቨርስቲዎቻችን ውስጥ ከምን ሰማው የተማሪዎች ስነ-ምግባር መበላሸት ባሻገር በብሔር ግጭት የተፈጠሩ ችግሮች አሁን አሁን የወሬውን ርዕስ ወደዚህኛው ተራ እየቀየሩት ይገኛሉ፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዕውቀት ለመቅሰምና ይህቺን ሀገር ተረክቦ ለማስተዳደር በገቡበት ተቋም ውስጥ ጠባብነትንና የብሔር ፖለቲካን እያራመዱ ‘አማራ’— ‘ኦሮሞ’— ‘ትግሬ’ እያሉ መቧቀስን ልምዳቸው እያደረጉት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ተዋደው በሠላምና በፍቅር ብዙ ዓመታትን የኖሩ ህዝቦች ዛሬ የጐሪጥ መተያየታቸውና በመሃላቸውም መከለያ መስመር ማበጀታቸው የግንኙነቱንና የመማር ማስተማር ሒደቱን ጥላ አጥልቶበታል፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የግል መገናኛ ብዙሃን በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ብሔርን መሠረት አድርገው የተነሱ ፀቦችንና የተወሰዱ እርምጃዎችን ሲያቀርቡ ስናነብና ስናይ ቆይተናል፡፡ በስፖርት ሊደምቅ የሚገባው ዩኒቨርስቲ በፀብ ሲተራመስ፣ በቀለም ትምህርት ሊወጠር የሚገባው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በብሔርተኝነት ስሜት ሲናወጥ፣ በትምህርታዊ ውድድሮችና ፉክክሮች ጦፎ የተሻለ ብቃት ያላቸውን ተማሪዎች ለመምረጥ መትጋት የነበረበት ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች ድንገተኛ ፀብ ትምህርት ለሳምንትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ እያቋረጠ ቁልቁል ወደታች የማደጉ ነገር ግራ ያጋባናል፡፡ በርግጥም ይህ ችግር ከባድ መሆኑን አጥብቀን እንድናስብበትም ግድ ይለናል፡፡

ተማሪነት — ድሮና ዘንድሮዘመናዊ ትምህርት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት ዘመን

ሩቅ ባይሆንም በነበሩት ጥቂት አስርተ ዓመታትም ቢሆን የተመዘገቡት ለውጦች አንገት የሚያስደፉ አልነበሩም፡፡ በየወቅቱ የነበሩት ሥርዓቶች ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ለትምህርት የሰጡት ትኩረትና ትምህርትን የሀገር ዕድገት መሠረት አድርገው ማሰ ባቸው እንደየአፈፃፀማቸው ያስመሰገናቸው ነበሩ፡፡ አጼ ኃይለ ሥላሴ መኖሪያቸውን የለገሱት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 6 ኪሎ ካምፓስ) ንጉሡ ለትምህርት የነበራቸውን በጐ አመለካከት ከሚያሳዩት መገለጫዎች አንዱ ተደርጐ ይወሰዳል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ብዙ ናቸው፡፡ ደርግም በተመሳሳይ ‘መሃይምነት የጨለማ ጉዞ ነው’፣ ‘የማይፅፉ እጆች አይኖሩም’ ወዘተ በሚሉ መፈክሮች መሪነት የከፈተው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ አድናቆትን ካገኙለትና ከነችግሮቻቸውም ጭምር ቢሆን ከተወደሰለት ስኬቱቶቹ ትምህርትን የማስፋፋት አንዱ ተግባር ነበር፡፡

በዚህ መልክ የተስፋፋው የትምህርት ብልጭታ የዘመኑ ተማሪዎች የሀገር ፍቅር ስሜት እንዲኖራቸውና ሀገራቸውን እንዲያስቡም አድርጓቸው ኖሯል፡፡ ምንም እንኳን የቀድሞ ተማሪዎች የውጪ ሀገር ቋንቋ መማር ላይ ብዙ ጊዜያቸውን ቢያጠፉና ቀልብና ሙሉ ሰዓታቸውን የወሰደባቸው ሆኖ ስለሀገራቸው በጥልቀት ለመረዳት ጊዜ ቢያጥራቸውም የውጪውን ዕውቀት እንዳለ ሀገራቸው ውስጥ በመትከል ለቀኑበትና ለወደዱት የፈረንጅ ትምህርት በሀገራቸው ውስጥ መሠረት ለመጣል ያደረጉት ጥረት ግን መልካም ነበር፡፡ የድሮ ተማሪዎች መገለጫ የኢትዮጵያን የወደፊት ዓለም መቀየስ ነው፡፡ ያኔ “ኢትዮጵያውያን መኖር ያለብን እንዲህ ነው፣ የለም እንዲያ ነው” እያሉ መሟገት፤ መተቻቸት፣ መስማማት መለያየት ወዘተ ባህሪዎቻቸው ነበሩ፡፡ የፖለቲካ ፈላስፎችን መጽሐፍት እያነበቡ ‘የእገሌ ሃሳብ ከእገሌ ይልቅ ለኛ ይጠቅመናል፣ የለም ይጐዳናል’ የሚሉ መፍጨርጨሮች የድሮ ተማሪነት መልክ ናቸው ሊባሉም ይችላሉ፡፡

አለመታደል ሆነና ታዲያ ከዚህ ፍትጊያ መሃል ትልቅ ብርሃን አልተወለደም፡፡ ለሀገሬ አዋቂዋ እኔ ነኝ የሚለው የእኔነት፣ የባለቤትነትና የተቆርቋሪነት ትጋት ሌላ ድንቅ የድሮ ተማሪነት መገለጫም ሆኖ ይታያል፡፡ የድሮ ተማሪ ሌላው መልኩ በወቅቱ የነበረውን ማኅበራዊና አስተዳደራዊ መዋቅር መተቸቱ ነው፡፡ ራሱን ከላይ አውጥቶ የገዛ ህብረተሰቡን በተለይም የአስተዳደር ሥርዓቱን በማስተዋል ‘መልካምና ስህተት’ እያለ መተቸትም ልምዱ ነበር፡፡ የለውጥ ሃሳብ እንደ አቅሙ ያቀርብም ነበር፡፡ “ሃሳብና መርህ ከትምህርት ቤት ወጥቶ ለስርዓተ መንግሥት መሠረት ይኹን፣ ለህብረተሰብም ሕይወት ምቹነት ይዋል” የሚል የማይናወጥ አቋምም ነበረው፡፡ “አስተዳዳሪዎች ትምህርት ቤትን የሃሳባቸው መናኸሪያ፣ የልቅናቸው መገለጫ ከማድረግ ይቆጠቡ” ይልም ነበር፡፡ ጠቅለል አድርገን ስናየው የድሮ ተማሪ የሀገሩን መሪዎች ‘አት ንኩኝ’ ባይ ነበር፡፡

ዘንድሮ ግን ነገር ተለውጧል፡፡ ትምህርት ቤቶች የትውልድ ማፍሪያ ቦታዎች መሆን ሲገባቸው ሚናቸው በተቃራኒው ቆሟል፡፡ ከላይ የተገለፁት የተማሪነት መልኮች በአሁኑ የተማሪነት ሕይወት ተለውጠዋል፡፡ የድሮ ተማሪ “የኢትዮጵያ አናጢዋ፣ ሰዓሊዋ፣ ቀራጯ... እኔ ነኝ ባይ ነበር፡፡ “በተሰጠኝ ጐዳና አልጓዝም፣ ራሴ መንገድ አውጪ፣ ተጓዥም ራሴ ነኝ” የሚል አቋምም ያራምድ ነበር፡፡ ምንም እንኳን የኔ የሚለው ንድፈ ሃሳብ ኖሮት ባያውቅም ድሮ ተማሪነት ማለት የአንድ ሀገር ወሳኝ

ዜጋ መሆን ማለት የመሆኑ ግንዛቤ በሚገባ ሰርፆ ነበር ማለት ያስደፍራል፡፡ ዛሬ በራስ የመመራት ፍላጐት በዩኒቨርስቲዎቻችን አይታይም፡፡ በምግብ መተዳደር ነው የተያዘው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ብዙ ነው፡፡

ድሮ አነሰም በዛም የተማረው የውጭ ቋንቋ ችሎታ የውጪ ፀሐፍትን ጭላንጭል ለማግኘት የሚያወላዳ ነበር፡፡ ምናልባትም አብዛኛው ተማሪ ከጥንታዊው የኢትዮጵያ ትምህርት ጥቂት የቀማመሰ ስለሚሆን አዲሱን ዕውቀት የመቀበያ አቁፋዳውም የዚያኑ ያህል የሰፋ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ ያነበበውን የመግለጽ ያወቀውን የማስረዳት ኃይል አላጣም፡፡ አሁን ግን ነገሩ ሌላ ነው፡፡ ያ የንባብ ችሎታ ቢኖር እንኳን (የለም እንጂ!) የተመከርነው መከራ ልበ ሙሉነትን ከነደብዛው ፍቆ አጥፍቶታል፡፡ ስለዚህ የዘንድሮ ተማሪነት ከድሮ ፍፁም ተቃራኒ ለመሆን በቅቷል፡፡

ዘንድሮ ነገር ቢመረው የሚቃወም የለም፡፡ የተሰ ራለት ሥርዓት ማንም ቢሆን ቢችል እንዲወደው ባይችል ግን የወደደው እንዲያስመስል ይፈልጋል፡፡ ይህ ማዳመቅ ነው፡፡ ተማሪ የገዛ መንገዱን መጥረግ ሲያቅተውና በገዛ አስተሳሰቡ መማር ሲሳነው በሰው መንገድ መጐተትና የጠባብነት አስተሳሰብ ውስጥ ገብቶ መዳከር ዕጣው እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያ የሚለውን የወል ማሠሪያ ልክ ትቶ ውስጡ ያለውን ፍልጥ ተካፍሎ ማንነቱን በዚያ ላይ ለመጠምጠም እየጣረ ነው፡፡

ማነው ኢትዮጵያዊ?ዛሬ በዩኒቨርስቲዎቻችን የኢትዮጵያ አንድነት ጥያቄ

ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ጥልቅ ባህር ውስጥ እየጠለቀ ነው፡፡ ተማሪ በየብሔሩ የየራሱን ቆዳ ማዋደዱና ብሔሩ የሰፈረበትን መሬት ወርድና ቁመት በመለካት ‘የኢትዮጵያ ትልቁ— ከትልቁ ቀጥሎ አንደኛ፣ ከአንደኛው ቀጥሎ አንደኛ’ እያለ ቀዳሚ ለመሆን የመፈለግ ስሜት እየተጠናወተው ነው፡፡ ማኅበራዊ ድርጅቶች በሴት፣ በወንድ፣ በኃይማኖት፣ በደራሲ፣ በአንባቢ፣ በሠራተኛ፣ በአሠሪ ወዘተ ተከፋፍለው ከውህደታቸው ይልቅ ጐረቤትነታቸው ጐልቶ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ተማረው ‘በተቀየሰልህ ፍሰስ’ በሚለው ያልተፃፈ መርህ መሠረት ተሰልፎ በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ መንደር፣ ጐጥ፣ ማኅበር ፈጥሯል፡፡ እነዚህን ማኅበራትም የሥራ ማግኛ ወረቀቱን ለመውሰድ የሚያስችሉት መከታ አድርጓቸዋል፡፡ አንድ ተማሪ አስተማሪውን ሲከስ ስሙን መጥቀስ ብቻ አይደለም እያስፈልገው ያለው፤ ያለውን የንዑሣን ጐሣ ቡድን አባልነትም አብሮ መጥቀስ የማያዋጣ ሆኗል፡፡ ይህ ሲሆን ጉዳዩ ከፍ ብሎ ይሰማለታል፡፡ ተበድሏል ይባልለታል፡፡ ተጨቁኗል ይባልለታል፡፡ ታላቅ ችግር ነው ይኼ፡፡

ኢትዮጵያ ደግሞ የመታደል ወይም ያለመታደል ነገር ሆኖ የብዙ ንዑሣን ጐሣዎች ጥርቅም ናት፡፡ እንደማንኛውም ሀገር ሴትነት፣ ወንድነት፣ አፋርነት፣ ትግሬነት፣ ኦሮሞነት፣ አማራነት፣ ሙስሊምነት፣ ጴንጤነት፣ ተዋህዶነት፣ ዕውርነት፣ አንካሣነት፣ ስፖርተኝነት፣ ሸማኔነት… ከዚህ ዓይነት ውጪ ምን ጥርቅም ምን መለያ ሊኖር? ታዲያ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ይህን ንዑስነት ይዞ ‘ሰው ተብሎ’ ለመጠራት ያለመፈለግ አዝማሚያ ውስጥ የገባው ራሱን ከሌሎች ንዑሣን የበለጠ አድርጐ ለማሳየት ነው፡፡ ተማሪው

ሰው ተብሎ ከመጠራቱ በፊት በተጨባጭ ‘ንዑስ ሰውነቱ’ መጠቀስ አለበት ዘንድሮ፡፡ ዋናው ነገር ተማሪው የተሠራለትን ሸማ ሳያቅማማና ሳያራግፍ በመልበሱ ነው ችግር ውስጥ የገባው፡፡ ኢትዮጵያዊነት የጋራ አጀንዳ መሆን ሲገባው ከግንዱ ቅርንጫፉ ይበልጣል እያለ የሚሟገት

ከሆነ፣ የአንድ ብሔር አባልነቱን አጐልቶ ለማሳየት መነሳቱ ክፋት ባይኖረውም በዚያ የበላይነት ሌሎችን ለመጨቆን ሲፈልግ መታየቱ

‘ትምህርት ሆይ መውጊያሽ የት አለ?’ ብሎ ሳያስፀልይ አይቀርም፡፡ ኢትዮጵያ አቋቁመውኛል ብላ እንደ ሀገር የምትጠራቸው ብሔሮቿ ለየቅል ተከፋፍለው ስሟን ሲያስረሷት ማየቷ አያሳዝናት ይሆን? ሊያውም ነገ ከሚደግፏት ባለተስፈኛ ተማሪዎቿ መንደር ውስጥ?

ቀዳሚው ትምህርት ወይስ ብሔር?ናዝሬት ቴክኒክ ኮሌጅ (ዛሬ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ

ዩኒቨርስቲ) የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የሆነችው መቅደስ ከምትኖርበት አዲስ አበባ ወደ ናዝሬት እየተመላለሰች ነው የምትማረው፡፡ ለእረፍት ከወጣች በኋላ ወደ ካምፓሱ የተመለሰችው ከሁለት ቀናት በፊት ነው፡፡ ብዙም ሳትቀመጥ ወዲያው በማግስቱ ተመልሳ አዲስ

...ያኔ “ኢትዮጵያውያን መኖር ያለብን እንዲህ ነው፣ የለም

እንዲያ ነው” እያሉ መሟገት፤ መተቻቸት፣ መስማማት መለያየት

ወዘተ ባህሪዎቻቸው ነበሩ፡፡ የፖለቲካ ፈላስፎችን መጽሐፍት እያነበቡ

‘የእገሌ ሃሳብ ከእገሌ ይልቅ ለኛ ይጠቅመናል፣ የለም ይጐዳናል’ የሚሉ

መፍጨርጨሮች የድሮ ተማሪነት መልክ ናቸው ሊባሉም ይችላሉ...

Page 9: Addis Guday(1)

10 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

አበባ ገባች፡፡ እንዲህ በፍጥነት የመለሳት ጉዳይ ግን የአዲስ አበባ ናፍቆት ወይም አስገዳጅ ቤተሰባዊ ምክንያት አይደለም፡፡ ሁለት ተማሪዎች ቴሌቪዥን በሚመለከቱበት ወቅት በፈጠሩት ግጭት በግቢው ረብሻ ተነስቶ ስለነበር እንጂ፡፡ ታኅሣሥ 19 እና 20 2004 ዓ.ም ነው፡፡ የተማሪዎቹ ረብሻ መነሻ የብሔር ግጭት እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከትግራይ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ የኦሮሞ ክልል ተወላጅ የሆነ ሌላ ተማሪን በመስደቡ ነው ተብሏል— ረብሻው የተቀሰቀሰው፡፡ ይህ ከሆነ በኋላ የኦሮሞው ልጅ የትግራዩን ተማሪ በአጠና ነገር ስለፈነከተው በተቀሰቀሰው ረብሻ ቴሌቪዥኑም ተሰብሮ ትምህርትም ወዲያው እንዲቆም በመደረጉ ግጭቱን ለማርገብ ዩኒቨርስቲው የማስተካከያ እርም ጃዎችን ለመውሰድ ተገድዷል፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ በብሔር የተነሳ ፀብ ከፈጠሩት ተማሪዎች ሰው ደብድበሃል፣ ቴሌቪዥንም ሰብረሃል የተባለው ልጅ በዲሲፕሊን ግድፈት ተከስሶ በዩኒቨርስቲው ተባሯል፡፡ ይህ የሁለት ተማሪዎች ግጭት ትልቅ ጉዳይ ሆኖ ሳይሆን መነሻ ምክንያቱ ግን የብሔር መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ፍርሃትን መፍጠሩ ግን አልቀረም፡፡

ይህ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከትምህርት ይልቅ ብሔረተኝነትን ማቀንቀንና ዘረኝነትን የማዳበር ጉዳይ ስናነሳ በሌሎች አካባቢዎች ይህን መነሻ አድርገው የተቀሰቀሱ ግጭቶችንም መዳሰስ ለጉዳያችን ማጠናከሪያ ይሆናል፡፡

ሳምሶን ከሁለት ዓመታት በፊት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 4 ኪሎ ካምፓስ ተመርቆ በአንድ የመ ንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኝ ወጣት ነው፡፡ በተማሪነቱ ጊዜ በሚማርበት ካምፓስ ውስጥ የገጠመውን ነገር አይረሣውም፡፡

“አንድ ቅዳሜ ጠዋት soil engineering ትምህርት ነበረንና ክፍል ውስጥ ተገኝተናል፡፡ አስተማሪያችን የታወቁ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡ በትምህርታችን መሃል ሁለት ተማሪዎች ነጠላ አጣፍተው ወደክፍለ ገቡ— ዘግየት ብለው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን የመጡ ይመስለኛል፡፡ ፕሮፌሰሩ ታዲያ የአንድ ብሔርን ስም ጠቅሰው ደግሞ ‘ለ ‘እንትን’ ብሔር ሃይማኖት ጊዜያችሁን ታጠፋላችሁ’ በማለት በሁላችን ፊት ዘለፏቸው፡፡ ይህን ጊዜ ራሴን መቆጣጠር ባለመቻሌ ‘አርፈው ያስተምሩ’ አልኳቸው፡፡ ከዚያም ፊታቸውን እንኳን ወደኛ ሣያዞሩ ሰሌዳው ላይ ተተክለው ቀሩ፡፡ ጥቂት የቃላት ምልልስ ቢካሄድ ኖሮ የሚከተለው ነገር ከባድ ነበር፡፡ እኚህ የጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ፕሮፌሰር ከትምህርታቸውና ዕውቀታቸው ተሻግሮ የጠበበ የብሔርተኝነት አስተ ሣሠባቸው በማወቅ የታረቀ አይደለም፡፡ ይህን ያህል የብሔርተኝነት አስተሣሠብ አቀንቃኝ መሆናቸው በርግጥም ‘እርሳስ እንደቀራጩ ነው’ ያስብላሉ፡፡ ተማሪያቸውን በምን ይቅረጹት፣ በዘር፣ በዕውቀት ወይስ በብሔርተኝነት መንፈስ? ይህ ነው የጊዜው ጥያቄ” ብሏል፡፡

ተማሪዎች ብቻ ሣይሆን የመምህራን ብሔርተኝነትና ጠባብ አስተሣሠብ ዩኒቨርስቲዎችን የዕውቀት ሣይሆን የጸብና የግጭት መድረክ ለማድረግ የራሱን መርፌ የሚወጋ ችግር ነው፡፡ ተማሪዎች ኢትዮጵያዊ መሆ ናቸውን ብቻ ካሰቡ በቂ ነው፡፡ ነገር ግን ግለኝነትን ማራመድና ወደ አንድ ጥላ መሠባሠብን መልመድ ኋላ ላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የት ሊደርሱ ይችላሉ የሚለውን ጥያቄ ያስነሣል፡፡ እየታዩ ያሉት ምልክቶች የነገ ችግር መታያዎች ናቸው፡፡

ከጅማ ዩኒቨርስቲ በ2002 የተመረቀውና አሁን አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ አንድ የግል ባንክ ውስጥ በአካውንታንትነት የሚሠራ ወጣት የደረሰበትን ጉዳይ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡

“አንድ ቀን ምሽት ከጅማ ዩኒቨርስቲ ውጪ አምሽቼ ብቻዬን ወደ ካምፓስ ተመለስኩ፡፡ ዶርም አካባቢ ስደርስ የግሩፕ ፀብ ነገር አየሁ፡፡ ለመደባደብ እንዲያግዛቸው ዱላ፣ ብረት፣ መጥረቢያና ሌላም ነገር የያዙ ተማሪዎች እኔን አገኙኝ፡፡ በኦሮምኛ እያወሩ ወደኔ ቀረቡ፡፡ ሁኔታቸው ስላላማረኝ ልሮጥ ስል አንዱ በዱላ የግራ ትከሻዬ ላይ መታኝ፡፡ በአጋጣሚ የወደኩበት ቦታ ላይ መብራት ስለነበርና አብሯቸው የነበረ የማውቀው ልጅ ማን እንደሆንኩ ስለለየኝ በኦሮምኛ “ዲሲ ዲሲ- ኬኛ” አለና የመታኝን

ልጅ ሌላ ምት ከመሰንዘሩ በፊት አስቆመው፡፡ ‘ተወው ተወው የኛ ነው’ እንደማለት ነው፡፡ የመታኝ ልጅ ‘ለምን ከኛ ጋር አትሄድም፣ እኛንስ ለምን አታግዘንም?’ ብሎ አንባረቀብኝ፡፡ ‘ኦሮሞ ሆነህ አፋን ኦሮሞ አትናገርም ምንድነህ ታዲያ?’ ሲል አፈጠጠብኝ፡፡ ኦሮምኛ መስማት እንጂ መናገር እንደሚያዳግተኝ ተናግሬና ለመደባደብ እንደማልፈልግ ይቅርታ ጠይቄ ሸሸሁ፡፡

በማግስቱ ነገሩን ሣጣራ ማታ ካየኋቸው ልጆች አንዱ ከአንድ የደብረማርቆስ ልጅ ጋር ደብተሬን ወስደሃል በሚል ፀብ መፍጠራቸውንና ማታ ላይ በቡድን ሆነው ያንን ልጅ እየፈለጉት እንደነበር ተረዳሁ፡፡ ትምህርቴን በውጥረትና በፍርሃት ብጨርስም አሁን ሣስበው የዩኒቨርስቲ ትምህርትና የተማሪዎች አስተሣሠብ ወዴት እየተጓዘ እንደሆነ ግራ ገብቶኛል፡፡ ዩኒቨርስቲ መማር ከባድ ፈተና ነው እላለሁ ለራሴ፡፡ የብሔርተኝነት ስሜት በቢሮም በሌላም ቦታ ቢኖርም በትምህርት ተቋማት ውስጥ መግነኑ ግን አደገኛ ምልክት ነው እላለሁ በግሌ” ብሏል፡፡

ታመጣለህ?’ አለኝ፡፡ ቂም ይዞም ብዙ ሊጎዳኝ ሞክሮ ነበር፡፡ Handout የሰጠው ልጅ የሀገሩ ተወላጅ እንደነበር አውቄያለሁ፡፡ ዛሬ ዛሬ በበርካታ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በዘርና በብሔር እንዲሁም በሀገር ልጅነት ቡድን ፈጥረው የሚሠሩ መጥፎ ድርጊቶች መኖራቸውን ሣስተውል ነገሩ እጅግ ይከነክነኛል፡፡ የፖለቲካ ሥርዓቱ ያመጣው ችግር ይሆን ብዬም እጠይቃለሁ” ብሏል፡፡

በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በብሔር መደራጀት መብትን ለማስከበርና በተለይ ማንነትን፣ ባህልንና ታሪክን ለማወቅ የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ችግር ባይኖርባቸውም ተማሪውን ግን ከመደበኛውና ቀናው አስተሣሠብ ውጪ እያደረጉ ለተቃራኒ ድርጊት እየዳረጉት መሆኑ ግን በግልፅ ይታያል፡፡ ብዙዎች የዩኒቨርስቲ የብሔር ግጭቶች የዚህ አደረጃጀት ውጤት ናቸው ብለው እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡ የቱነው ችግሩ የሚለውን የሚመልሰው በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረገ አካል ነው፡፡ እየተፈጠረ ያለው አልባሌ አቅጣጫ ግን ከወዲሁ ትኩረትን እንደሚሻ ጥርጥር የለውም፡፡

ይህን ርዕስ ይዘን ስንሠራ ተሞክሮዋን ያካፈለችን ሠላማዊት አማረ የተባለች የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ ተማሪ ችግሩ ከወዲሁ እሣቤ ይሻል ትላለች፡፡ እንደ ሠላማዊት ገለፃ የካቲት 2000 ዓ.ም ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ተፈጥሮ የነበረው ግጭት አሣዛኝ መነሻ እንደነበረው ታስባለች፡፡

“በአንድ ዕለት 11 ሰዓት አካባቢ ንፋስ ለመቀበል ስንወጣ ግቢው ተተራምሶ አየን፡፡ ብዙም ሣንርቅ የተኩስ ድምፅ ሠማን፡፡ ከሁለትና ሦስት ቀናት በፊት ጥቂት ተማሪዎች በብሔር ግጭት መነሻ ፀብ መፍጠራቸውና ይኼ ተስፋፍቶ ዛሬ መክረሩን ተረዳን፡፡ ግቢው ሁሉ በድብድብ ተሞላ፡፡ የፀቡ ተዋንያን ለሁለት የተከፈሉ ናቸው፡፡ የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች፡፡ በሀገራቸው አጠቁን እያሉ የሚናገሩት የኦሮሞ ሴት እህቶቻችን ያስነሱት ግጭት ወንድሞቻቸውን ለፀብ ጋብዟቸዋል፡፡ በዚህ ግርግር ብዙ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ፡፡ በዚህ ወቅት ፖሊስ በየዶርሙ ፍተሻ ሲያደርግ የተገኘው ከተማሪ የማይጠበቅ ዱላ፣ ስለትና ሌሎች መሣሪያዎች ሁሉንም ያስደነገጡ ነበሩ፡፡ ያ ግርግር ለተከታታይ 5 ቀናት ሳይበርድ ቀጥሎ በመጨረሻ በአካባቢው ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት ቆሟል፡፡ በወቅቱ ፀቡን አባብሳለች የተባለች አንዲት ከኦሮሚያ የመጣች ተማሪና ሌሎችም እንደየጥፋታቸው ቅጣት ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህቺ ተማሪ ሌሊት በ 9 ሰዓት በፀጥታ አስከባሪዎች ከዶርሟ ተወስዳ ሻንጣዋን ይዛ እንድትባረር ተደርጓል፡፡ ፀቡ የተፈታበት መንገድ ግልፅነት የጐደለው ቢሆንም ተጨማሪ ግርግር ፍራቻ መሆኑን ግን ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ ‘በነገራችን ላይ…’ ትላለች ሠላማዊት በዩኒቨርስቲ ውስጥ ፀብን ለማብረድ የሚገቡ ወላጆችና ባለሥልጣናት ሁሉንም ተማሪ በአንድ ዓይን ማየትና ለማገላገል መጣር እንጂ ዘረኝነትን የሚያባብስ ተግባር መፈፀም የለባቸውም፡፡”

የነዚህ ሁሉ ችግሮች እናት የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አሁንም በዘርና በጎሳ ችግሮች እንደተተበተበ ነው የሚሉ አሉ፡፡ የአንድ ጎሣ ተወላጆች የሚማሩባቸውና የሚያስተምሩባቸው ዲፓርትመንቶች ለዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ የአደባባይ ምስጢር ናቸው፡፡ የእርሱ ብሔር ተወላጆች የሌሉበት እና የማያስተምሩበት ዲፓርትመንት የገባ ተማሪ መመረቁ አደጋ ውስጥ እንደሆነ የሚረዳው በመጀመሪያው ሴሚስተር ነው፡፡ ሳይባረር ዲፓርትመንት መቀየር ይኖርበታል፡፡ አለዚያ ቤተክርስቲያን እንደገባች ውሻ መካለብና መዋከብ ቀጣይ እጣው ይሆናል፡፡ ሀገር ይገነባሉ— እውቀት ያካፍላሉ— ትውልድ ይተካሉ ተብለው መምህራን እንዲሆኑ የተመደቡ በአብዛኛው ወጣት የሆኑ ምሁራን ከነሱ የማይጠበቅ የደካማ ሰው ስብዕና ተላብሰው ፊደል እንዳልቆጠረ ሰው ተማሪውን በጎሳና ብሔር እየከፋፈሉ ሲያቀርቡና ሲያርቁ— ሲያዳሉና ሲበድሉ ይውላሉ፡፡ ተማሪዎች በሃገሪቷ ባሉ 32 ዩኒቨርስቲዎች ተመድበው ከቀዬአቸው ርቀው እንዲማሩ የሚላኩት አዲስ ዕውቀት፣ ማኅበራዊ ትስስር፣ ሀገራዊ ራዕይና ወንድማዊ ፍቅርን በማዳበር ለሀገር እንዲተጉ በማሰብ መሆኑን ልብ ማለት የፈለጉ አይመስልም፡፡ በምትኩ ሁሉም የሚመስለውን ፍለጋ ይሻኮታል፤ ይዋከባል፡፡ ሁሉም በየጎጡ ተቦጣቡጦ ያገኘውን የትምህርት ማስረጃና መርጃ ከአቻው በስተቀር ከሌላው ጋር አይካፈልም፤ አይረዳዳም፣ አይግባባም፣ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለመፍጠር አይተጋም፡፡

...ዘንድሮ ነገር ቢመረው የሚቃወም የለም፡፡ የተሰራለት ሥርዓት ማንም ቢሆን ቢችል

እንዲወደው ባይችል ግን የወደደው እንዲያስመስል

ይፈልጋል፡፡ ይህ ማዳመቅ ነው፡፡ ተማሪ የገዛ መንገዱን መጥረግ

ሲያቅተውና በገዛ አስተሳሰቡ መማር ሲሳነው በሰው መንገድ መጐተትና የጠባብነት አስተሳሰብ

ውስጥ ገብቶ መዳከር ዕጣው እየሆነ የመጣ ይመስላል...

ሌላ በ2003 ዓ.ም ከሃዋሣ ዩኒቨርስቲ የተመረቀ አቤል የተባለ ወጣት (ስሙ የተቀየረ) በተማሪነት ጊዜው ደረሰብኝ የሚለውን ነግሮናል፡፡

“የሁለተኛ ዓመት ተማሪ ሣለን አንደኛውን ሜጀር ኮርስ የሚሠጠን መምህር የሃዋሣ አካባቢ ተወላጅ ነበር፡፡ በሁለተኛ ሴሚስተር ፈተና ሲቀርብ ለአንድ የዲፓርትመታችን ተማሪ የተለየ ጽሁፍ /Handout/ ሰጠው፡፡ ፈተናው በአብዛኛው ከዚህ ጽሁፍ ላይ የወጣ በመሆኑ ተማሪውና ያካፈላቸው ሰዎች ጥሩ ውጤት አመጡ፡፡ ይህን የሠማነው ግሬድ ሪፖርት ከተለጠፈ በኋላ ነበር፡፡ ወደ መምህሩ ቢሮ ሄጄ ውጤቴን እንዲነግረኝ ስጠይቀው የመጣሁበትን አካባቢ በስም ጠቅሶ ‘እናንተ ጉረኞች ናችሁ፡፡ አላሣይህም ምን

Page 10: Addis Guday(1)

11 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ዘአካል ማለት በአንድ ወይም በሌላ መልኩ የሚገለጽ ሰብሰብ ያለና የራሱ የሆነ አካል (የሚታይም የማይታይም) ያለው ህያው ማለት ነው— ኦርጋኒዝም የሚባለው ማለት ነው። ዘአካል ያድጋል፤ ይራባል። ሲተነኮስ ግብረ መልስ የመስጠት ባህርይም አለው። ዘአካሎች ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያደርጋቸው ግብአት (ምግብና ኃይል) ያስፈልጋቸዋል። እነዚህን ግብአቶች በአካባቢያቸው ከሚያገኟቸው ምንጮች ገቢ አድርገው ሲያበቁ በግንባንደት ሂደት (ሜታቦሊዝም) አካላቸውን እየገነኑ ወደ አካባቢያቸው ደግሞ ውጣት ይለቃሉ። ይህ ውጣት ጠጣር፡ፈሳሽ ወይም ጋዛማ ሊሆን ይችላል። ኃይልም ሊሆን ይችላል።ማንኛውም ከተማም ህይወት አለው። ካልሞተ።

እርግጥ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ላይሞቱ ይችላሉ— በመደበኛ ሂደት። የሚንፈራፈር ከተማ፤ የአልጋ ቁራኛ የሆነ ከተማ፤ ‘ካሉት በታች— ከሌሉት በላይ’ የሆነ ከተማ ግን አለ። ይኖራልም። ከተሞችን እንደ ዘአካል የማየት እሳቤ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው። ዘአካሎች እንደሚበሉ እንደሚጠጡ ሁሉ፤ ዘአካሎች ወደውስጥም ወደውጭም እንደሚተነፍሱ ሁሉ፤ ዘአካሎች ጠጣር ፈሳሽና ጋዛማ ውጣት እንዳላቸው ሁሉ ከተሞችም እንዲሁ ይሄ ሁሉ ነገር አላቸው። ለዝርዝሩ... አብረን እንቀጥል።

ግብአቶችውኃ ለአንድ ከተማ ወሳኝ ነው ማለት ወሳኝነቱን በደንብ

መግለጽ ላይሆን ቢችልም እንበለው። ውኃው ንጹህ መሆን አለበት። በቂ መሆን አለበት። የጥራትና የመጠን ብቃቱም በዘላቂነት የሚቀጥል መሆን አለበት። ማንኛውም ከተማ ለነዋሪዎቹ የሚሆን ምግብ

(የእንስሳት መኖ ወዘተን ጨምሮ) ጭራሽ ወይም በበቂ መጠን ስለማያመርት ከውጪ የሚያስገባው ጥሬና የተሰናዳ ምግብ እጅግ በርካታ ነው— የነዋሪ ምግብ ብለን እንጥራው? በቁመትም በስፋትም እያደገ ሲመጣ ከተማው ከመስፋቱና ወደላይ ከማደጉ ጋር የሚቆራኘው በከፍተኛ መጠን ጥቅም ላይ የሚውለው ሌላው አይነት ‘ምግብ’ ነው። ኢ-ነዋሪ ምግብ ብንለውስ? አይነቱ ብዙ ነው። እነዚህ የተለያዩ ምግቦች ከሞላ ጎደል ከከተማው ውጪ የሚገቡ ናቸው። ውኃውና የነዋሪና ኢ-ነዋሪ ምግቦች ወደከተማው

ገብተው በግንባንደት ሂደት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ለማድረግ ኃይል ያስፈልጋል። ለማሞቂያነት፤ ለማሽከርከሪያነትና፤ ለሰው-ሰራሽ ብርሃንነት ወዘተ የሚሆን ኃይል። ይህ ኃይል ወደከተማው የሚገባው እና/ወይም ጥቅም ላይ የሚውለው በሙቅ ውኃ ወይም እንፋሎት፤ በኤሌክትሪክ ወይም በነዳጅ መልክ ሊሆን ይችላል። ነዳጅ ስንልም የማገዶ እንጨት፤ የድንጋይ ከሰል፤ የተፈጥሮ ጋዝ፤ ነዳጅ ዘይት፤ ነዳጅ አረቄ፤ ባዮዲዝል፤ ባዮጋዝን ሁሉ ይጨምራል።ለከተማ ሕይወት የሚያስፈልጉት ከላይ የተጠቀሱት

ብቻ አይደሉም። አንድ ከተማ መረጃም ያስፈልገዋል። ድምጻዊ፤ አኃዛዊና ፊደላዊ እንዲሁም ምስላዊ መረጃ በበቂ ጥራት መጠንና ፍጥነት በከተማው መዳረስ አለበት። ማንኛውም ከተማ በበቂ ሁኔታም መተንፈስ አለበት።

አዎ በቂ አየር— በቂ ንፋስ ማግኘት አለበት። ጥራቱ የተጠበቀና ሙቀቱ የተመጠነ አየር፤ ፍጥነቱ ያልበዛም ያላነሰም ንፋስ ለከተማ ከተማነት አይተኬ ሚና አለው።ሰው ሰራሽ ያደለ ብርሃንና ጥላው በተለያዩ የከተማው

ክፍሎች ሲገኙ ህይወትን ይዘራሉ። ህይወትን ይቀጥላሉ፤ያስቀጥላሉ። ብርሃንና እና ጥላ የተለያየ የብርሃን መጠኖች ናቸውና የሚፈለጉበት ቦታና ጊዜ እስከታወቀ ድረስ ሁለቱንም በአግባቡ የሚጠቀም ከተማ የኔ በሆነ ቢያስብል አይገርምም።እንግዲህ ከተማ ሲባል የሚበላና የሚጠጣ ከሆነ፤

የሚተነፍስ ከሆነ፤ የሚያይ የሚሰማና የሚያነብ ከሆነ

ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር)

የአረንጓዴ ጉዳይ

- ከካናዳwww.akababi.org [email protected]

ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር)፤ በካናዳ የዩኒቨርስቲ ኦፍ ካልጋሪ የኢንቫይሮንመንታል ዲዛይን ተባባሪ ፕሮፌሰር፤ የአቴና ላይፍ ሳይክል አሰስመንት ቼር፤ የኢንስቲትዩት ፎር ሳስተይነብል ኢነርጂ ኢንቫይሮንመንት ኤንድ ኤኮኖሚ ፌለው፤ የባዮ ኤነርጂ ኢንተርናሽናል ማጋዚን ኤዲተር፤ የኢንደስትሪስ ፎር አፍሪካ ፋውንዴሽን አባል፤ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጉዳዮችና እና የኃይል አቅርቦትና ፍጆታ ጉዳዮች ላይ የረጅም ጊዜ ጸሐፊ ናቸው።

ከተማን እንደ ዘአካልእነዚህን ሥራዎች ያለምንም እንከን እንዲያከናውን የሚያደርገው ተገቢ የከተማ ክፍል (ክፍለ-አካል ወይም ብልት) ያስፈልገዋል ማለት አይደል? የከተማ ክፍለ-አካሎች አዎ ማንኛውም ከተማ ክፍለ-አካሎች ወይም ብልቶች

አሉት። የሚበላው ነዋሪና ኢ-ነዋሪ ምግብ ወደከተማው በአግባቡ እንዲደርሰውና በከተማው ውስጥ ከአንድ ክፍል ወደሌላ ክፍል እንዲጓጓዝ ወሳኝ የምግብ ማስተላለፊያ ሆነው የሚያገለግሉት መንገዳዊ ክፍለ-አካሎች ናቸው።መንገዶች ሰፊም ጠባብም፤ አስፋልት-ለበስ፤ ጠጠር-

ለበስ ወይም ሳር-ለበስ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደቦታው-እንደሁኔታው። ዋናው ቁም ነገር ያለው በትክክለኛው

ቦታ፤ ትክክለኛው የመንገድ አይነት፤ በትክክለኛው ስፋትና ርዝመት መገኘቱ ላይ ነው። ይህ በማይሆንበት ጊዜ አንድ ዘአካል ከደም ማስተላለፊያው ጋር በተያያዘ የሚያጋጥመው የጤና እክል እንዳለው ሁሉ ከተማም ከተማዊ ጤንነቱ ላይ እክል ይገጥመዋል— ለምሳሌ መንገዶች በበቂ ጥራትና ስርጭት በማይገኙበት ሁኔታ። በመንገዳዊ ክፍለ-አካሎች ስር ከየብሳማ መንገዶች ሌላ የባቡር መስመሮች፤ የአየር መስመሮች፤ አውሮፕላን ማረፊያዎች ወዘተን አካቶ ማየት ያስፈልጋል። ውኃንም ወደከተማዋ ጉሮሮና ወደተለያዩ የከተማው አቅጣጫዎች በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ ያልዛጉና የማያፈሱ እንዲሁም በበቂ ግፊት ማስተላለፍ የሚችሉ የውኃ ትቦዎች የግድ ያስፈልጋሉ። የኤሌክትሪክ መስመሮች የተለያየ የኤሌክትሪክ

ምንጮችን ከከተማው የተለያዩ ክፍሎችና ተጠቃሚዎች ጋር ማገናኘት የሚችሉ መሆን አለባቸው— መቼም ሁሌም። መረጃ ከያለበት መንዶቅዶቅ አለበት። መረጃ ከየቦታው በየቦታው ፏፏ ማለት አለበት። አዎ መረጃ ደኅንነቱ ተጠብቆና የተጠቃሚንም ደኅንነት አደጋ ላይ ሳይጥል መፍሰስ አለበት። ለዚህ ሁሉ የመረጃ ጎዳናዎችን ሌላ ወሳኝ የከተማ የደም ስር የሚባሉ አይነቶች ናቸው።ፋብሪካዎች፤ ህንጻ ግንባታ የሚከናወኑባቸው

ቦታዎችና ማሽነሪዎች ወዘተ ሁሉ የከተማ አስፈላጊና ኢ-ነዋሪ ምግቦችን ማብላሊያ ክፍለ-አካሎች ናቸው። እንደ ጨጓራና እንደ አንጀት ግብአቶችን የሚፈጩባቸውና የሚሰለቀጥባቸው። እነዚህ ብልቶች እንከን አልባ የሆኑላት ከተማ የታደለች ወይም የታገለች ነች። መኖሪያዎች፤ ቢሮዎች፣ ሆስፒታሎች ወዘተ የየራሳቸው ሚና የሚጫወቱ ሌሎች ክፍለ-አካሎች ናቸው።የውኃ ማጣሪያ ትክሎችና የቆሻሻ ቤተ-ውገዳዎች እንደነ

ኩላሊት ለጤናማው የከተማ ህይወታዊ ኑሮ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። ግን በደንብ መስራት አለባቸው። ልዩ እስትንፋስ ጭቃን ሰው አድርጓል። መደበኛ

እስትንፋም የመኖር ምልክት ነው። አዎ መተንፈስ ሕይወት ነው። የትንፋሽ ሀገሯ ደግሞ ሳንባ ነው። የከተሞች ሳንባ ደግሞ ለከተማው ስፋትና አቀማመጥ የሚመጥኑ በአግባቡ የተሰሩና የተያዙ ፓርኮች— አረንጓዴ ክልሎች— ናቸው። ከውኃ አካል ጋር የተዋሀደ፤ የአይነትና የብዛት ምጣኔ ካላቸው ዛፎችና አበቦች ጋር የተዋደደ ስርጭትና አያያዝ ያስፈልጋቸዋል— ፓርኮች— እስትንፋሰ ከተማ።

ውጣቶችአንድ ከተማ ቁሳዊና ኃይላዊ ግብአቶችን አስገብቶ

ሲያብላላ በግንባንደት ሂደት ጊዜ የሚፈጥራቸው ውጣቶች በርካታ ናቸው። እያንዳንዱ ክፍለ-አካል ሲገነባም ሆነ በስራ ላይ በሚውልበት ወቅት ስለሚያወጣው ውጣት ነው እያወራሁ ያለሁት። ከየፋብሪካው፤ ከየሆቴሉ፤ ከየሆስፒታሉ፤ ከየቤቱ የሚወጣው እጣቢ፤ የሽንት ቤት ቆሻሻ፤ ደረቅ ቆሻሻ ሁሉ የከተማውን ምንነት የመግለጽ ባህርይ አለው። በመጥፎ ሽታው ሲገለጽ ያላየው ማን አለ? ለእይታ አስቀያሚ መሆኑስ ላይ ማን ይጠራጠራል?

ከሁሉ በላይ ደግሞ ከውኃ ብክለት ጋር በተያያዘ የሰውን ህይወት ለሚቀጥፉ ተላላፊ በሽታዎች መንደርደሪያ ነው— እንደነዚህ አይነት ውጣት— በሥርዓት ካልተያዘ። ጭሳጭስም አለ— ከቤትም ከፋብሪካም ከሌሎችም

የሚለቀቅ ጋዛዊ ልቀት። በአይን ቢታይም ባይታይም በካይነቱ ግን የማያጠራጥር የጭስ አይነት ሁሉ ይወጣል። ቅሪታዊ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት በአይን ከማይታዩት ውስጥ ይመደባል። ፓርክ በፓርክ የሆነች ከተማ ውስጥ እንጨት

ሲማገድ የሚለቀቀው ካርቦንዳይኦክሳይድ በፓርኩና ከፓርኩ ውጪ ባሉ ዛፎች ወደውስጥ ስለሚማግ ከሞላ ጎደል ችግር-አልቦ ነው። ዛፎቹና ባልደረቦቻቸው ወደውስጥ የሚመጥጡት የከተማ ነዋሪዎች ወደ ውጪ ያስፈነጥሩትን ካርቦንዳይኦክሳይድ ጨምሮ ሲሆን በምትኩ ምን የመሰለ ኦክስጅን ለነዋሪዎቿ ጀባ ይላሉ። ከተማን እንደዘአካል ብናየውም የከተማው ሞትም

ሆነ ትንሳኤ የሚገለጸው ግን በክፍለ-አካሎቹ ደረጃ ነው— በሙሉ ከተማነቱ ደረጃ ሳይሆን። ማንኛውም የከተማ ክፍለ-አካል አስፈላጊ የእድሳት ሥራ እየተደረገለት ከቆየ በኋላ የአገልግሎት ጊዜው ሲያበቃ ወይም አዲስ ክፍለ-አካል በቦታው መተካት ሲፈለግ ይፈርሳል። ፈርሶ በተመሳሳይ ክፍለ-አካል ወይም በሌላ አይነት ክፍለ-አካል ሊተካ ይችላል። እያንዳንዱ ክፍለ-አካል ሲታደስም ሆነ ሲፈርስ የሚፈጠረው ቆሻሻም የማንኛውም ከተማ ዘአካላዊ ሕይወት መገለጫ ነው።

እና ምን ይጠበስ?ከተሞቻችንን ከላይ በተገለጸው የዘአካላዊ ሞዴል

አይን ስናያቸው አብረው የሚነሱ ጥያቄዎችና ጉዳዮች ይመጣሉ። ለመሆኑ ጤነኛ ከተማ በአገራችን አለ? የነዋሪና ኢ-

ነዋሪ ምግብ ማስተላለፊያ መንገዶች፤ የውሃ ማሰራጫ መስመሮች፤ የመረጃ ጎዳናዎች ያሉት፤ ቢኖሩትም በደንብ የሚሰሩለት ከተማ የትኛው ነው? የፈሳሽና የደረቅ ቆሻሻ አይጎዴ የሚደረጉበት ደረጃቸውን የጠበቁ ቤተ ውገዳዎች ያሏቸው ስንት ከተሞች ናቸው? አካላቸው ሽንት በሽንት ያልሆነባቸው በእንትን ያልተለቀለቁ ከተሞች የትኞቹ ይሆኑ? አንድ ከተማ የተበላሸ መንገድ፤ የሚያፈስ ወይም የሚቋረጥ የውኃ መስመር እያለው ሁሉም አማን ነው ብሎ ቁጭ ማለት አንድ የኛ ቢጤ ዘአካል ችግር ያለበት የደም ቧንቧና ወደውስጥ ደም የሚፈስበት ክፍለ-አካል እያለው ሁሉም ጤና ነው ብሎ ቁጭ የማለት ያህል ከባድነቱ ሊሰማን ይገባል።አንድ ከተማ ከጅማሮው አንስቶ በምን መልኩና

ፍጥነት ወዘተ ማደግ እንዳለበት የተቀመጠለት ነገር ከሌለ ሲጀመር የታመመ ከተማ ነው። መወገድ ይችል የነበረ፤ ግን ያልተወገደ በተለያዩ ክፍለ-አካሎቹ ላይ የሚገለጥ ህመም። ለማከምም ይቀል የነበረ፤ ግን ከማከሚያ ወጪው እጅግ ከፍተኛ መሆን አንጻር ከባድ የሆነ ሕመም።በዚህ እይታ ከከተሞቻችን ስንቶቹ ናቸው እየተ

ንፈራፈሩ ያሉት? ስንቶቹስ እያጣጣሩ ናቸው? ስንቶቹ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ፤ አነሰም በዛም የታመሙ ናቸው? ቢያንስ የመጨረሻው ጥያቄ መልስ ‘መ) ሁሉም’ የሚል መሆኑ አያጠራጥርም። እንደዛም ሆኖ ግን ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም (ዛፍም ቆርጠን ተስፋም ቆርጠን ስለማይሆንም ጭምር)። አዎ ከተሞቻችንን አንድ በአንድ ጤነኛ ዘአካሎች ማድረግ እንችላለን። የሚያስፈልገው እያንዳንዱ ከተማ የተለያዩ አብረው የሚሰሩ፤ የሚመጋገቡና የተሳሰሩ ክፍለ-አካሎች ያሉት ትልቅ ዘአካል አድርጎ የሚያይ የተቀናጀና የተጠና እውቅና የሚሰጥ አይናማ አሠራር ነው። የዚህ አሠራር አይናማነት አይን ያለው ደግሞ ብሌኑ ላይ ነው— እንደማንኛውም አይን። ብሌኑ ደግሞ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ነው። ጨረስኩ። ድኅረ ነገር— በዚህ ሳምንት የገባው ታላቅ ጾም ለበረከት

ያድርግልንና ወራቱ ከፈቀደልን ዘንድ ስለጾምና አካባቢ ጾሙ ከማለቁ በፊት እጽፍበት ይሆናል።

Page 11: Addis Guday(1)

12 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ዋና አዘጋጅ፡ ዮሐንስ ካሣሁን [email protected] አድራሻ፡- ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቀበሌ: 02 የቤት ቁጥር: አዲስ

ከፍተኛ አዘጋጆች፡ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ

ከፍተኛ ሪፖርተር፡ እንዳለ ተሺ

ሪፖርተር፡ ማጂ አሰፋ

ፎቶግራፍ፡ ኤፍሬም ሽፈራው

ክርኤቲቭ ዲዛይን፡ ዘሪሁን አሰፋ(ኩኩ)

ሌይአውት ዲዛይን፡ መስፍን አድነው

ኮምፒዩተር ጽሑፍ፡ ሮማን ጥላሁን ቤተልሔም ልሳነወርቅ

ሽያጭና ስርጭት፡ ተከተል ሻንቆ

ዓምደኞች መስፍን ሀብተማርያም ብርሃኔ ረዳኤ (ዶ/ር) ጌታቸው አሰፋ (ዶ/ር) ዳንኤል ክብረት ኤፍሬም እሸቴ ኮከብ አሳየ ብሩክ ደምሴ

አሳታሚ፡ ሮዝ አሳታሚ ኃ.የተ.የግ. ማህበር የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ፡-

አራዳ ክፍለ ከተማ ቀበሌ፡ 04/05 የቤት ቁጥር፡ 558/52 ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ ተፈራ የንግድ ማዕከል 6ኛ ፎቅ ስልክ፡ 251-11-155 55 27 / 251-911-69 80 59 ፋክስ፡ 251-11-111 96 23 / ፖ.ሳ.ቁ፡ 180703

ህዳር 1999 ዓ.ም ተመሰረተ

አታሚ፡ ብራና ማተሚያ ድርጅት አድራሻ፡- በጎተራና በወሎ ሰፈር መሀል ላይ የድሮ መኮድ ግቢ ውስጥ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበሌ: 04

E-mail: [email protected]: [email protected]

ርዕሰ አንቀጽ

የገበያና ሽያጭ ሥራ አስኪያጅ፡ ሲሳይ ቦጋለ

ከውልደት እስከሞት ያለው የሰው ልጅ ሕይወት የመጠየቅና የማወቅ፣ የመረዳትና የማስረዳት ሂደት ነው፡፡ የቱም የሰው ፍጡር ከእናቱ ማህጸን እስከ ምድር ማህጸን በትምህርት ላይ ነው፡፡ የተማረ ሁሉ ግን አያውቅም፡፡የሕይወትና የአካዳሚ እውቀት ሰውን ሙሉ የሚያደርጉት ቢሆንም ይበልጥ

ሙሉ የሚሆነው ደግሞ ያወቀውን በተግባር አውሎ ለውጥ ማምጣት ሲችል ነው፡፡ ለውጥ ደግሞ አንጻራዊ ነው፡፡ ፊደል ቆጥሮ፣ እውቀት ቀምሮ “ተምሯል” የሚባል ማንም ዜጋ መማሩና ማወቁ የሚለየው በእውቀቱ ሳይሆን በተግባሩ ነው፡፡ ይሁንና ግን እንዳለመታደል ሆኖ አወቁ የምንላቸው ሳያውቁ፣ የተማሩትም ያልተማሩ ሆነው የሚገኙበት አጋጣሚ ብዙ ነው፡፡ከሀገራዊ ስሜት ይልቅ ክልላዊ፣ ከሰውነት ይልቅ ጎሣዊነት ፈጥኖ የሚታያቸው፣

ከሠልፍ መሃል ተወላጃቸውን መምረጥ የሚቀናቸው፣ ተምረው ያልተማሩ ዜጎች ቁጥር ጥቂት አይደለም፡፡ እነዚሁ ተምረው ያልተማሩ ዜጎች ዩኒቨርስቲን በሚያህል የሰው ልጅ አዕምሮ ማበልጸጊያ ሥፍራ ገብተው ስለሙሉው ቤት በመጨነቅ ፈንታ በመኝታ ክፍላቸው አሊያም ስላረፉበት ስፍራ ብቻ ሲቆረቆሩ ሲታይ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የመማር ቢሆን እንኳ የማወቅ እንዳልሆነ መረዳት አያዳግትም፡፡በተለይም ፌደራሊዝም ሰፍኗል፣ የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል ተፈጥሯል

በሚባልበት ሀገር ዕውቀት አካባቢያዊ ጃኬትን አውልቆ የመጣል አቅም ሲያንሰው ማየት ችግራችንን በአትኩሮት እንድንፈትሽ የሚያስገድድ ሃቅ ነው፡፡ ዕውቀት በተግባር ተገልጦ መታየት ይኖርበታል፡፡ የሚታየው ተግባርም በራሱ የዕውቀትን እንጂ የጉድለትን መኖር የሚያመላክት ከሆነ ትምህርት ተሰጥቷል፣ የተማረም ተፈጥሯል ለማለት አያስደፍርም፡፡በተወሰነ መልኩ የብሔር ብሔረሰብ መብት ተረግጧል፤ ዜጎች በማንነታቸው

እንዲያፍሩ ተደርገው ተጨቁነዋል እንል በነበረበት ጊዜ እንኳ ያልታዩ ልዩነቶች ሲመጡ፣ መቀላቀል ጠፍቶ ገለልተኝነት ጎልቶ ማየት የትምህርት አሰጣጣችንን ብቻ ሳይሆን የብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች አያያዛችንንና የመብት አጠባበቃችንን እንድንፈትሽ የሚያደርግ ነው፡፡ፌደራሊዝምን በተቀበለችና “እስካሁን ከነበሩ ሥርዓቶች ሁሉ ብሔር ብሔረሰቦች

ተግባብተውና ተፋቅረው እየኖሩ ነው” ብላ ለዓለም በመለፈፍ ላይ የምትገኝ ሀገር “ተምረዋል” የተባሉት ዜጎቿ በጥቃቅን ጉዳይ ለሚነሱ አለመግባባቶች ከሰው ልጅነትም፣ ከኢትዮጵያዊነትም በላይ ከጎሳዊ መሰላቸው ጋር ሠልፍ ሲይዙ ማየት አንድ ሥፍራ ላይ የተሰራ ሥህተት መኖሩን የሚያሳይ ነው፡፡አንጋፋው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዳሁኑ “የገባ ሁሉ የተወሰነ ዓመት

ቆይቶ ይወጣበታል” እንደሚባለው ሳይሆን በተለይም በ1960ዎቹ አጋማሽ አካባቢ የጎሳ ሳይሆን የሀገር፣ የአካባቢ ኩርፊያ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ ርዕዮተ ዓለምና ፍልስፍናዎች ፍጭት የሚደረግበት፤ ወገንተኝነቱም ከተሻለው ሃሳብ እንጂ ከተወላጅነት እንደማይደመር በጊዜው የነበሩ ሁሉ የሚመሰክሩት ነው፡፡ በውይይትም ሆነ በተቃውሞ መልኩ ለሚገለጹ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ ልጆች ዘር ሳይለያቸው— ሃሳብ እያገናኛቸው በጋራ ሲወድቁና ሲነሱ፣ ሲታገሉና ውጤት ሲያመጡ ዛሬ ላለንበት ሁኔታ አብቅተውናል፡፡አዋቂ ነው የሚባል ሰው ከፊት ለፊቱ የሚመጣው ሰው ሰውነቱ እንጂ ተወላጅነቱ

ከየት እንደሆነ ሊቆጥር ከቶም አይችልም፡፡ ሰብዓዊ መብት የሰውን ልጅ በሰውነቱ ብቻ እንድናከብረው የሚያደርግ መርህ ነው፡፡ እዚሁ መሃል ሀገር በብዙ መልኩም በተሻለ የአደረጃጀትና የአገልግሎት ሁኔታ ላይ የሚገኘውና ቀዳሚው ዩኒቨርስቲ ውስጥ ታች ያሉት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በፋኩልቲ ደረጃ መምህራን በዘር ተደራጅተው ሲሳሳቡ ሲታይ፤ ልጅ ከማን ይማር? የሚያሰኝ ይሆናል፡፡ ይሁንና ተማሪው ቀርቶ መምህሩም አዋቂነቱ የሚለካው በተማረውና በሚያስተምረው ሳይሆን በተግባሩ እንደሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

መልዕክቶቻችሁ

መስለውኝ ነበረ

የበቁ የነቁ

ያወቁ የረቀቁ

የሰው ፍጡሮች

ለካ እነሱ ናቸው

ጥሬ ጨው…ጥሬ ጨው ጥሬ ጨዋዎች

መፈጨት-መሰለቅ-መደለዝ-መወቀጥ-

መታሸት-መቀየጥ

ገና እሚቀራቸው

“እኔ የለሁበትም!”

ዘወትር ቋንቋቸው።

ደበበ ሠይፉ

ጥሬ ጨው

ተግባር — የማወቅ መለኪያ

የሃገራችን ውዱ መንገድ እንደሆነ የተነገረለት የመስቀል አደባባይ-ቦሌ መንገድ ሥራ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በጊዜ መጀመሩ የሚያስመሰግን ነው፡፡ ይሁን እንጂ እየተተከሉ ያሉት የመልዕክት ማስተላለፊያ ሠሌዳዎች ለማን እና ለምን? የሚል ጥያቄ የሚያስነሱ ሆነውብኛል፡፡ “በመንገድ ሥራው የተነሳ ለሚደርስብዎ መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሎ በመጻፍ ሀገሬውንና ዋነኛውን የመንገዱን ተጠቃሚ ማሳሰብ እየተቻለ ይህን ማሳሰቢያ ጽፈው ለመስቀል የመረጡት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው፡፡ ይህ መልዕክት አቋራጭ መንገድን የሚጠቁም— የንብረት መውደምና የሞት አደጋን ሊያስቀር የሚችል ወሳኝ ነገር ቢሆን ሀገሬውን ውሃ በላው ማለት አይደለም? የራሷ ፊደል እና ቋንቋ ያላትን ሀገር መናቅስ አይደለም? ይህ ሳያንሳቸው ቻይናዊያኑ ባለማወቅም ይሁን በንቀት ወይንም በሌላ እነሱ ብቻ በሚያውቁት ምክንያት ሩዋንዳ ጋ የተመሠረተው ካምፕ የነሱ ማረፊያ መሆኑን ለማሳወቅ የገለጹበት መንገድም የሚያበሳጭ ነገር አለው፡፡ ከላይ በቻይንኛ ከሥር ደግሞ በእንግሊዝኛ ብቻ ነው የጻፉት፡፡ ለመሆኑ ቋንቋችን ምን ያህል ቢያሳፍራቸው ይሆን የቻይናዊያኑን ስራ የሚቆጣጠሩት ሀበሾች እርምት ተደርጎ በአማርኛ እንዲጻፍ ያላደረጉት? የሉዓላዊነት መደፈር ከዚህ መሰሉ ጥቃቅን፣ ነገር ግን ከማስተውለው ችግር እንደሚመጣ ልብ አላሉት ይሆን?ጌታቸው በላይ ከቦሌ-ሩዋንዳ

መልዕክቱ ለማን ነው?

Page 12: Addis Guday(1)

14 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

የኔ ሃሳብ

ከሰሞኑ የከተማችን የትራፊክ ፖሊሶች በተለይ ባለሞተሮቹ አንድም ሁለትም እየሆኑ ትርፍ የሚጭን ታክሲን በመቅጣት ሥራ ተወጥረዋል፡፡ አላፊ አግዳሚ ሹፌሮች

በምልክትና በመብራት መኖራቸውን የማያሳብቁባቸው ሥፍራ ላይ ሆነው ይጠብቁና በመደዳ አቁመው ይቀጧቸው ይዘዋል፡፡ አጋጣሚ ሆኖ የተሳፈርኩበት ታክሲ ትርፍ አልያዘ ኖሮ ከቅጣቱ ተረፈ፡፡ ውስጥ ያለነው ሰዎች ግን በሱ እድለኛነት ላይ ከተወያየን በኋላ አንድ ተሳፋሪ “የሀገሪቱ በጀት ላይ ከትራፊክ ቅጣት የሚሰበሰብ” የሚል ነገር አለ ሲሉ የውይይቱ አቅጣጫ ተቀየረ፡፡ እንዲህ የሚል ነገር በበጀቱ ላይ መኖሩን እርግጠኛ የሆነ ሰው ባይኖርም ትራፊኮቹ እንዲህ በርትተው የሚቀጡት ቢያንስ የቅጣት ኮታ ቢኖራቸው ነው በሚል ተሳፋሪው ተስማምቷል፡፡

ከታክሲ ከወረድኩ በኋላ ለምን ትርፍ ሰው የጫኑ ታክሲዎችን እና የመጠምዘዣ መብራት (ፍሬቻ) ያላበሩትን ብቻ እየለዩ እንደሚቀጡ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ኮታም ይያዝለት በጀት፤ የትራፊክ ቅጣት አላማ ከጥፋት እንዲመለሱ ማድረግ ከሆነ ታክሲ ብቻ ነው እንዴ የሚያጠፋው?

ትራፊኮች ኮታችሁንም ይሁን በጀታችሁን ህጉ በሚያዘው መልኩ በቶሎ ለመሙላት እና ኮኮብ ተብላችሁ ለመሸለም የምትችሉበትን ምስጢር ልንገራችሁ? ቀላል ነው፡፡ ከፍጥነት ልክ በላይ የሚያሽከረክሩትን ቅጡ፡፡ በየትኛውም መስመር፣ በየትኛውም ሠፈርና መንደር መኪናው ክንፍ እስክታወጣ የሚጠብቅ የሚመስል፣ ከራሱ ውጭ ለሌሎች ደህንነትና በሠላም ውሎ መግባት ግድ የሌለው አሽከርካሪ ሞልቶላችኋል፡፡ በቀን የዚህ አይነቱን ሺውን መቅጣት ትችላላችሁ፡፡ ያኔ በእጅ መጻፍ የማይታሰብ ስለሚሆን ተንቀሳቃሽ የቫት ደረሰኝ መቁረጫ ሊያስፈልጋችሁ ይችላል፡፡ ይሄ ጽሑፍ በተከበሩት (የእውነት አከብራቸዋለሁ) ትራፊኮቻችን ላይ ለመቀለድ የተጻፈ ከመሰልዎት ተሳስተዋል፡፡ በከተማና በሃገር አቀፍ ደረጃ ፍጥነት— ከፍጥነትም ልጓም የሌለው የሚመስል ፍጥነት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለማመልከትና ይህን ለማስቆም ትራፊኮቻችን እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ባለማየቴ ነው፡፡ በኩርባዎችና መዞሪያዎች ላይ ፍጥነታቸውን ሳይቀንሱ ከመኪናው ጋር አብረው የሚዞሩ፣ ረጋ ብለው እግረኛ ከማሳለፍ ይልቅ በጡሩምባ አስደንግጠው ማለፍ የሚቀናቸው ሁሉ ሊቀጡ ይገባል፡፡

ከተማውን በጭስ እየበከሉ አላፊ አግዳሚውን በሳል እያሰቃዩ የሚያልፉ አሮጌና እድሳት እርሙ የሆኑ

ዘካርያስ ኪሮስየሰዋሰው ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅሦስተኛ ዓመት ተማሪ፡፡

ዘካርያስ ኪሮስ

“ቅድስት አገር” እየተባለች የምትጠራው አገራችን ርኩሱን የግብረ ሰዶማዊያንን ጉባኤ ካስተናገደች ከወራት በኋላ፤ የሊዙ አዋጅ “የለዘዘ ነው” እየተባለ መተቸት በጀመረ ከቀናት በኋላ እንዲህ ሆነ፡፡

ሠላምን ለማስከበር ፀጥታን ለማስፈን ሕጋዊ እውቅና ከተሰጣቸው አካላት ውስጥ አንዱና ዋናው የፖሊስ

ሠራዊት ነው (የፌደራል፤ የአ/አ እና የክልሎችም)፡፡ እኛ ስንተኛ ሳይተኙ— በዓልን ከቤተሰቦቻችን ጋ ሆነን በየቤታችን ስናከብር እነሱ (ፖሊሶች) በየበረንዳው በፀሐይና በቁር (በብርድ) እያንገላቱ ይጠብቁናል (ከአምላክ በታች) ይበል ያሰኛል፡፡

የፖሊስ ተግባር የተቀደሰና የተባረከ እንደሆነ ሜክሲኮ ጋ ያለው የፌደራል ዋና መ/ቤት ሰሜን ሆቴል አካባቢ ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በአንድ ለእናቱ ቴሌቪዥናችን በፖሊስና ሕብረተሰብ እንዲሁም በአዲስ ፖሊስ የሚቀርቡልን አስተያየቶች የበለጠ ይሰብካሉ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን በእኔ ዕድሜ እንኳን ሳየው ፖሊስ ማስተካከል ያለበት ነገር ግን ያላስተካከለው ወይም ማስተካከል ያልፈለገው አንድ ደካማ ጐን አለው፡፡ “ምንድን ነው?” ማለታችሁ ግድ ነውና እነሆ! ምክንያተ ጺሂፍ ለዝንቱ ጦማርየዚህን ጽሑፍ ምክንያትን ካስረዳኋችሁ ነገሩ

ይገባችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአንድ ምሽት ላይ የመብራት ምሰሶ ተደግፌ መጽሐፍ እየነበብኩ ሳለ አንድ በዕድሜው ለጋ የሆነ ልጅ ከእጁ ላይ ደሙን እያዘራ ሲያልፍ ፖሊሶች አዩትና ጠሩት፡፡ “ምን ሆነህ

ቂሣሪያ ወደ ደብረታቦርነው !?” ሲሉም ጠየቁት፡፡ “ከሰው ተጣልቼ ስለነበር ተናጅዴ ራሴን በራሴ ነው አንዲህ ያ ደረኩት” የወጣቱ ልጅ መልስ ነበር፡፡ “እንዴት እራስህን በራስህ እንዲህ ታደርጋለህ?” አሉና አንደኛው በጥፊ ሌላኛው ፖሊስ ደግሞ በእርግጫ አጣደፉት፡፡ “ጉድ ጉድ…” በማለት (አማርኛው ጉድ) ከተሰበሰቡት ሰዎች አንደኛውን ወጣት ጠሩትና ደግሞ “ምናባህ ተገትረህ ታያለህ” አሉና እንኳን በሰው ላይ ቆዳዋ ‘ኤክስፖርት’ መሆን በጀመረላት ለአህያይቱ እንኳን የማይገባ ዱላቸውን አወረዱበት፡፡ መጽሐፍ ማንበቤን ትቼ ድርጊታቸውን እከታተል ስለነበር በመጨረሻ እንዲሄዱ ሲያዟቸው ቀድሞ ከእጁ ብቻ ደም ይፈሰው የነበረው ልጅ ከአፍንጫው የሚወጣውን ደም እያዘራ አንደኛው ወገቡን እያሻሸ ወደሚሄዱበት ሄዱ፡፡

ምን አልባት ይኸን ጽሑፍ የምታነቡ ሰዎች “ሌባ ይሆናሉ፤ እንደውም ደግ አረጉ” ልትሉ ትችሉ ይሆናል፡፡ ቢሆኑስ? መደብደብ ነው መፍትሔ!? እኔ ይኸን መልዕክት የማስተላልፈው ድርጊቱ ከቀን ወደቀን እየተባባሰ ስለሆነ ኋላ የማፈልገውን ውጤት እንዳያመጣ በመስጋት ነው፡፡

ማጅራታቸው ይሆን የሚመስለው? አንዲት ከውሻዋማ (ከውሽማዋ) የወለደች ሴት

ነበረች አሉ፤ ልጇ ከት/ቤት ሲመለስ ያልተጠበቀ ጥያቄ ይጠይቃታል፡፡ “እማዬ ጓደኞቼ አንተ አባትህን አትመስልም እያሉ ያበሽቁኛል እኔ አባዬን አልመስም እንዴ?” ብሎ ሲጠይቃት ጎንበስ አድርጋው ፀጉርንና ማጅራቱን እያሻሻች “ዝም በላቸው ልጄ ማጅራትህ ቁርጥ ያባትህን ነው የሚመስለው” አለችው ይባላል፡፡ በእውነቱ ከሆነ ቀደም ብዬ የገለጽኩላችሁ ደብዳቢ ፖሊሶች፤ ፖሊሶችን የሚመስሉት በማጅራታቸው ካልሆነ በስተቀር በጸባይ፣ በትዕግስት፣ በማመዛዝን፣ በመመራመር፣ አርቆ በማሰብ ግን በምንም ታሪክ የሚመሳሰሉ አልመሰል ብሎኛል፡፡

እንኳን አይደለም ሌብነትን እና ሌላም ወንጀልን ቀርቶ ሽብርተኝነትንም ቢሆን የእነአሜሪካ የጓንታናሞ አሰቃቂ የምርመራ ሂደት እንኳን አላቆም ብሎ ዓለምን እያመሰ ባለበት ዘመን ወንጀልን በዱላ እከላከላለሁ ማለት ዘበት ነው፡፡ ተደብደበው ታስረው የነበሩ የመቶ ብር ሰራቂዎች ሲፈቱ የመቶ ሺህ ብር ሌባ እየሆኑ እኮ ነው፡፡ ቃሪያ ጥፊ እየቀመሱና አጸያፊ ስድብ እየተሰደቡ ታስረው የተፈቱ የጋሪ ቀበኞች እኮ አውሮፕላን ለመጥለፍ እያወጠነጠኑ እንዳልሆነስ ማስተማመኛችን ምንድን ነው? ሴቶችን “ገላምጣችኋል” ተብለው የድብደባ ዓይነት የቀረበላቸው ታሳሪዎች ሲፈቱ ከሴት የተፈጠሩ መሆናቸውን የሚያጠራጥር ግፍ በሴቶች ላይ የሚፈጽሙ ከሆነ የያዝነው ተጨባጭ ሁኔታ አስጊ እንደሆነ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡

ቂሣርያ ወደ ደብረ ታቦርፖሊሶቻችን ከየመሥሪያ ቤታቸው የሚመጣውን

ሙገሳ ብቻ ሳይሆን መስማት ያለባቸው ሕብረተሰቡስ— ወንጀለኛውስ— የሕግ ታሪሚውስ— ቤተሰቤስ— በትራንስፖርት አብሬው የምሄደው ሰውስ— ልጆቼስ— ከምንም በላይ ደግሞ ህሊናዬስ ምንይለኛል? ብሎ መጠየቅ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ቸግሮት፣ ሱስ ሆኖበት፣ ታማሚ ሰው ኖሮት ለማሳከሚያ በሌላም በላሌም ምክንያት እኮ ሰው ሊሰርቅ ይችላል፡፡ ስርቆቱ ባይደገፍም ይኸን ሁሉ ደብድቦና አፀያፊ ስድብ ሰድቦ መከላከል ይቻላል እንዴ?

እንኳን ፖሊሶቻችን ክርስቶስ በቂሣርያ “ሰዎች እኔን ምን ይሉኛል?” ብሎ ጠይቆ የነበራቸውን የተለየ ግንዛቤ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ አሳይቷቸዋል፡፡ ስለዚህ ፖሊሶቻችን የምትሰሩልን መልካም ሥራ እንዳለ ሆኖ ይቺን ለሃያ አንደኛው ክፍለዘመን የማትመቸውን ዘሎ ሰውን መደብደባችሁን ትታችሁ ስለ ራሳችሁ የምትጠይቁበት ቂሣርያ፣ ስለ ትክክለኛ የፖሊስ መለያችሁን የምታሳዩበትን ደብረ ታቦታችሁን አብጁ፡፡

መኪኖች መቀጣት የለባቸውም ትላላችሁ? ከመኪናው አቅም በላይ አትክልትና ሌላም ሸቀጥ እየጫኑ መኪናው አጋድሎ እንፉቅቅ ሲጓዝ ትራፊኮቻችን መቅጣት አለባችሁ፡፡ የኋላ መብራታቸው የወላለቀና ሌላም አካላዊ አቋማቸው መኪና ተብለው በጎዳና እንዲፈሱ የማይፈቅድላቸውና በየመንገዱ እቃ እየጣሉ የሚሄዱት ሁሉ የትራፊኮቻችን የቅጣት ደረሰኝ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

ታክሲም ይሁን ሌላ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ትርፍ ጭኖ መጓዙ ብቻ ሳይሆን ቶሎ ቶሎ ተመላልሶ በትርፍ የሚያገኘውን ገንዘብ እያሰበ ሲከንፍ ከታየ እሱስ ለምን አይቀጣም? ችግሩ ትራፊኮቻችን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ መንገድ ላይ አይታዩም፡፡ ማን ያውቃል እነሱም በትርፍነት ተጭነው ቤታቸው ለመግባት ይጣደፉ ይሆናል፡፡

እዚህ ላይ የትራፊኮቻችንን ስህተቶች ሳላነሳ ባልፍ አዳላ ትሉኛላችሁ፡፡ በአብዛኛው ከምሽቱ 12፡30 በኋላ ነው ትርፍ መጫን የሚጀመረው፡፡ በአንዳንድ መስመሮችማ ብትወራረዱ ትራፊክ አታዩም፡፡ እኔ ግን ሳስበው ትራፊኮቹ ቀን ሲቀጧቸው የዋሉት ታክሲዎች ማታ በትርፍ ሰርተው ነገ ሲያዙ የሚከፍሉትን እንዲያዘጋጁ ወይንም ለዕለቱ ኪሳራቸው ማካካሻ እንዲይዙ ሲሉ ሆነብለው እያዩ እንዳላዩ የሚሆኑ ይመስለኛል፡፡

ትምህርት ሲሰጡም የእግረኛ ማቋረጫው (የሜዳ አህያው) የእግረኞች ርስተ ጉልት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በዚህ የተነሳም በርካታ እግረኞች መንገድ ሲያቋርጡ መኪና ሲመጣ ካዩ ወደ ዜብራው በእጃቸው ጠቆም እያደረጉ “የኛ ነው” በሚል መንፈስ ደረታቸውን ነፋ ያደርጋሉ፡፡ አንተ በመኪናህ እኛ በዜብራችን ማን ይመጣብናል ነው ነገሩ፡፡ ዜብራ ለእግረኛ ነው የተባለውን ብቻ የሰሙ በርካቶች ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ መኪና ግዑዝ አካል እንደመሆኑ (ራሱን በራሱ ስለማይመራ) እግረኞች ከማቋረጣቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው፣ በፍጥነት የሚመጣ መኪና በድንገት ፍሬን ይዞ ለመቆም ከ30 ሜትር በላይ ሊንሸራተት እንደሚችል እና የመሣሠሉት ሊነገ ራቸው ይገባል፡፡

ብዙዎቻችንን እንደሚያስማማው የከተማችን ወይንም የሀገራችንን የመኪና አደጋ ያባሰው ትርፍ መጫን ሳይሆን ፍጥነት ነው፡፡ ትርፍ መጫኑ ግን በቶሎ ፍሬን ይዞ እንዳይቆምና መኪናው ከቁጥጥር ውጭ እንዲወጣ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ዋናው የችግሩ ምንጭ ፍጥነቱ እያለ አደጋ አባባሹ ላይ እንዲተኮር መደረጉ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመ አስመስሎታል፡፡

ሡልጣን ከድርከአዲሱ ገበያ

ትርፍ የጫነ ብቻ ለምን ይቀጣል?ሡልጣን ከድር

Page 13: Addis Guday(1)

15 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ሃይማኖት

ስጦታ በሰዎች መካከል ያለንን ቅርርብና ጓደኝነት ይበልጥ ያጠናክራል፡፡ በፍቅረኛሞች መካከል ሲሆን ደግሞ ፍቅርን ያጣፍጣል ይጨምራልም፡፡ ፍቅርን ይጨምራል ስል ስጦታ በጓደኛሞች ወይም በፍቅረኛሞች መካከል የሚፈጸም ሙስና ነው ማለቴ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ከእኛ ከሰዎች መካከል አንዳንዶች የሌላው ወገንን ልብ ለማማለልና ይህን ወገን የራስ ለማድረግ ስጦታን እንደማማለያና መደለያ የሚጠቀምም አይጠፋም፡፡ ምን አለፋችሁ የስጦታ ትርጉሙና ዓላማው “ሕልም እንደፈቺው ነው” እንደሚለው ሀገረኛ ተረት እንደ ስጦታ ሰጪዎች ይለያያል፡፡ ከዚሁ ጐን ለጐንም ከአንድ ወገን የሚቀርብ ስጦታ ምን መሆን አለበት በሚለው ላይም ስጦታውን የሚቀበለው ሰውም እንደስጦታ ሰጪው የስጦታ አተረጓጐም ይለያያል፡፡ የአንድ ሰሞን ገጠመኜን ላውጋችሁና ለዛሬ

ወደተነሳሁበት አብይ ርዕሴ ላምራ፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በአንድ የስነ-ልቦና መጽሐፍ ላይ ስለ ስጦታና ስለ ስጦታ አሰጣጥ አንድ ነገር አነበብኩ፡፡ በመጽሐፍ ላይ ለምን ዓይነት ሰው ምን ዓይነት ስጦታ መሰጠት እንዳለበት ከነምክንያቱ ዝርዝር አድርጐ ከማስቀመጥ ባሻገር ስጦታው ከተሰጠ በኋላ ሊያመጣ የሚችለውንም ተጽዕኖ ልቅም አድርጐ ይናገራል፡፡ እኔም ይህን መጽሐፍ ካነበብኩ በኋላ በመጽሐፉ መሠረት ለአንድ ከልብ ለምወደውና ለማከብረው ወዳጄ አንድ አጋጣሚን ጠብቄ አንድ ቀይ ጽጌረዳ አበባና “you are a very special to me” የሚል የእንግሊዝኛ ጽሑፍ የሰፈረበት ካርድ ሰጠሁት፡፡ ግን የሚገርማችሁ ከላይ አነበብኩት ያልኳችሁ መጽሐፍ ላይ የሰፈረውና ስጦታውን ያቀረብኩለት ሰው ባጋጣሚ በሀሳብ አልተገናኙ ኖሯልና ስጦታውን በአግራሞትና በማድነቅ ተቀብሎኝ ከተመለከተው በኋላ “ይህንን ዓይነት ስጦታ እከሊት ለምትባለው የሴት ጓደኛህ ብትሰጣት ምንኛ ደስተኛ ትሆን?!” በማለት አስተያየቱን ሰጠኝ፡ ወዳጄ እኔ እንደ ሙስሊምነቴ ከትዳር በፊት

በተቃራኒ ጾታ ላይ ያለኝን አቋም ቢያውቅ ኖሮ ይህን ባላለኝ ነበር፡፡ ይሁንና ወዳጄ ይህን ዓይነቱን አስተያየት ሲሰጠኝ ስጦታው ከእኔ ለእርሱ እንደተሰጠ ስነግረው በስጦታው ላይ የነበረው አግራሞታዊና የማድነቅ ስሜት ባንዴ ወደ ብስጭት ተቀየረ፡፡ በአራድኛው ቋንቋ “ፋራ” ካለኝ በኋላ ስጦታውን ይዤ ለምፈልገው ሰው እንድሰጥ “ይህ ስጦታ በቁጥር ስህተት ምክንያት ከማይታወቅ ግለሰብ በስህተት እንደሚመጣ መልዕክት (SMS) አጭር የሞባይል ጽሑፍ ዓይነት በስህተት ወደእኔ ይዘኸው የመጣኸው ስጦታ ነውና የምትሰጠውን ሰው ማንነት በደንብ አስተካክለህ እወቅ እኔ “ቺክህ” አይደለሁም” ብሎኝ አረፈው፡፡ እኔም የስጦታውን መልዕክት ላስረዳው ብሞክርም ፈጽሞ ሊቀበለኝ ስላልቻለ ስጦታውን ለራሴው አበረከትኩት፡፡ ጥቂት ጊዜያት ካለፉ በኋላ ስለዚህ ክስተት ይኸኛውን ወዳጄን ሳጫውተው እንደርሱ ፍላጐት እኔ ለርሱ ስጦታ መስጠት ከፈለግኩ አሁን ወይም ደግሞ ወደፊት ሊጠቅም የሚችል ነገር እንጂ አንዴ ተነብቦ የሚተው ካርድ እንደማይፈልግ ገለጸልኝ፡፡ “የሚጠቅም ነገር” ሲል ምን ዓይነት መሆን ይኖርበታል በማለት ስጠይቀው ወዳጄ የሚፈልገው ዛሬ ገንዘብ ሊሆኑ ወይም ነገ ገንዘብ የሚገኝበትን መንገድ የሚያመለክቱ መጽሐፍት ቢበረከቱለት እንደሚመርጥ ነገረኝ፡፡ አይ አለመታደል የሰው ልጅ የሰውን ውስጣዊ ስሜትና ፍላጐት እንዲሁም የወደፊት ክስተቶችን በፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) እንዳያውቅ ተወሰነበት እንጂ ባይወሰነበት ኖሮ እንደ ዕድል ሆኖ ለወዳጄ ስጦታ ይሆን ዘንድ የጽጌረዳ አባባና የስጦታ ካርድ እንደው እንደዋዛ አይከስርም ነበር፡፡ ግን እኮ እኔ መጀመሪያውኑ ስጦታውን በንጹሕ አንደበት ወዳጄ ሳያውቀው የገዛሁት የወዳጄን ውዴታ በማግኘት ለመፅደቅ ፈልጌ እንጂ ለሌላ ባለመሆኑ ወዳጄ ያዘጋጀሁለትን ስጦታ ባይቀበለኝም በቅን ልቦና በማሰቤ ብቻ ከፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) ዘንድ እንደሰጠሁ ያህል

ጽድቅ ለማን?ይጻፍልኛል፡፡ የውስጤን የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው፡፡እኔ ስጦታ በመስጠት ለመፅደቅ ፈልጌ ስጦታዬን

ይዤ ሄድኩኝ፡፡ ወደ ወዳጄ ዘንድ፡፡ እንደው እናንተስ በሰዎች ሆነ በፈጣሪ ዘንድ ለመፅደቅ ምን ፈጽማችሁ ይሆን፡፡ ይህን እንዲያው ዝም ብዬ ጊዜ ለማጥፋት ወይም ደግሞ የተወሰኑልኝ የቃላት ብዛት ይሟሉልኝ ዘንድ አላነሳሁትም፡፡ የያዝነው ቁም ነገር ነውና ይህን ፈፅሞ አላደርገውም፡፡ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ሁላችንም ያመንበትን እምነቶች የምንከተል ነን፡፡ እንደየ እምነቶቻችን አስተምህሮ ሃጢአት መስራትና ሃጢአትን ለማሰረዝ (ለማሰረየት) ወደፈጣሪ መቃረብ እንዳለብን ሳናውቅ አንቀርም፡፡ ታዲያ የእኔ ጥያቄ መልካም ተግባራትን የምንፈፅማቸው እውን በድብቅም ይሁን በገሃድ የፈፀምናቸውን ሃጢአቶች ለማሰረይ (ለማሰረዝ) ብቻ ነውን? ካለ ሃጢያአት የፅድቅ ስራ (ቢር)፣ ካለቢር ሃጢአት የለምን? ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው፡፡ አብዛኞቻችን ደግሞ በፅድቅ (ቢር) ተግባራትና በሰብአዊ ተግባራት መካከል ያሉት ልዩነቶች ፈፅሞ አልገቡንም፡፡ ይህን ግልፅ ለማድረግ የሚከተሉትን እንመልከት፡፡ምሳሌ 1፡- በትዳር ዓለም ውስጥ ያሉ ነዎት፡፡ መቼም

በስራ ብዛት ምንም አብዛኛውን ጊዜዎን በስራዎ ተጠምደው ቢያሳልፉም በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ቢያንስ ከባለቤትዎ ጋር ምግብ መመገብዎ አይቀርም፡፡ እርስዎ ሆኑ የትዳር አጋርዎ በፍቅር ስሜት ውስጥ ሆነው አንድ ጉርሻ መጐራረስዎ አይቀርምና ይህን ጉርሻ ለብቻዎ በሚሆኑበት ወቅት የሚሰጠውን ጠቀሜታ ለብቻዎ ያስተንትኑ፡፡ በዓለማዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሕይወትዎ እንዲሁም ትዳርዎን ከአደጋ በመጠበቁ ረገድ ማለቴ ነው፡፡ምሳሌ 2፡- በመንገድ ላይ በመሄድ ላይ ሳሉ የሙዝ

ልጣጭ ወድቆ ቢያገኙ ከእለታት አንድ ቀን አዳልጦት በመውደቅዎ ምክንያት ምነኛ እንደተጐዱ ወዲያው እንደሚያስታውሱ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ታዲያ ይህን የሙዝ ልጣጭ እንደወደቀ ያልፉት ይሆን? እርግጠኛ ነኝ አያልፉትም፡፡ እርስዎም ሆኑ ሌላ መንገደኛ ወድቆ እንደርስዎ በጉዳት እንዳይሰቃይ በማሰብ ልጣጩን በማንሳት አርቀው ይጥሉታል፡፡ ይህንንም ያስተውሉ፡፡ምሳሌ 3፡- በአቅራቢያዎ አንድ ፀያፍ ተግባር ዘወትር

ሲፈፀም ይመለከታሉ፡፡ ይህን ፀያፍ (ነውር) ተግባር በፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) የተቸርዎትን ጉልበት ተጠቅመው ለማስወገድ አቅሞ (ጉልበትዎ) ውስን እንደሆነ አውቀዋል፡፡ ይህን ፀያፍ ተግባር በይሁንታ ለማለፍ ግን መንፈስዎ አልፈቀደም፡፡ ታዲያ ምን ያደርጉ ይሆን፡፡ አዎን በአቅምዎ ሊፈፅሙት የሚችሉት ተግባር ቢኖር ለአካባቢዎ የቀበሌ ባለሥልጣን የጉዳዩን አስከፊነት (ፀያፍነት) በመግለፅ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድ ዘንድ ሀሳብ መስጠት ነው፡፡ምሳሌ 4፡- ጐረቤትዎ ወይም ዘመድዎ በመሞቱ ልጆቹ

በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡ እርስዎም ይህን ጠንቅቀው እያወቁ የእርዳታ እጅዎን እንዳይዘረጉ አቅምም አይፈቅድ ይሆናል፡፡ ይሂዱና አብረው የአባትነት ወይም የእናትነት ፍቅር ያካፍሏቸውና በሕጻናቱ ፊት ሊፈጠር የሚችለውን ደስታና ገጽታ ያስተውሉ፡፡ምሳሌ 5፡- የተቸገረ ጐረቤት ወይም ዘመድ አለዎት?

ይህን የተቸገረ ጐረቤት ወይም ዘመድ በሚችሉት አቅም በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ ሲረዱት ምን ይሰማዎት ይሆን? ይህንንም ያስተንትኑ፡፡ሌሎች ምሳልዎችንም ማቅረብ ይቻል ነበር ለአሁኑ

በዚህ ይብቃን፡፡ ታዲያ እነዚህን ሁሉ ሊፈፅሙ የቻሉት ወይም ደግሞ ሊፈፅሙ የተነሳሱት እርስዎ ሃጢአትን በመስራትዎ ይመስልዎታልን? ወይስ ሰብአዊ ተነሳሽነት ኖሮዎት? ሃጢአት አልሰራሁም ወይም ሰብአዊ ተነሳሽነት የለኝም ካሉ ለምን ይሆን ታዲያ ይህን ሊፈፅሙ የቻሉት? መልሱን በመመለስ ይተባባሩኝ፡፡ሃጢአት (ፀያፍ) ተግባራት ሳይከናወን የፅድቅ (ቢር)

ተግባራትን መፈፅም እንግዲህ ይህን ከላይ የጠቀስኳቸውን ተግባራት ይመስላል፡፡ በራስ ተነሳሽነት የፈጣሪ አላህ (ሱ.ወ) ውዴታና ፍቅር ለማጐናፀፍ የሚረዳ ተግባር፡፡ አንድ ነገር ያስተውሉ መልካም የፅድቅ (ቢር) ተግባራትን ከፈፀሙ በፈጣሪዎ፣ በቤተሰብዎ፣ በአካባቢዎ በሚኖሩ ሰዎች፣ በወረዳዎና በአገርዎ ሰዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ከመሆን አልፈው የወዲያኛውን ዓለም (አኺራ) በድል ለመቀዳጀት ይችላሉ፡፡የፅድቅ (ቢር) ተግባርን ለይስሙላና ለይሉኝታ

የሚፈፅሙ ከሆነ በቀይ ካርድ ከእግር ኳስ ሜዳ እንደሚባረር የእግር ኳስ ተጫዋች ከወዲያኛው ዓለም ክብር በምድራዊ ዓለም ላይ ሳሉ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ውጭ ነዎት፡፡ የፅድቅ (ቢር) ተግባር ለመፈፀም ሲነሱ ሰብአዊነት የሚለውን የዘመኑ የሚዲያና የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ነን የሚሉትን ተቋማት ዘፈን አያቀንቅኑ፡፡ ግንኙነትዎን ከፈጣሪዎና ከፈጣሪዎ ጋር ብቻ ያድርጉ፡፡ አለዚያ የሚያከናውኑት ተግባራት ዳቦ ሰርቆ ፅድቅ እንደመፈለግ ያስደርግብዎታልና ይህን መሰሉን ከመፈፀም ይጠንቀቁ፡፡ በተለይ የሃይማኖት አባት ወይም መሪ ከሆኑና ይህ መሰሉን የአስመሳይነት ተግባር የሚፈፅሙ ከሆነ በምድርም በወዲያኛውም ዓለም (አኺራ) የተወገዙ ነዎት፡፡ ምክንያቱም ለሚመሯቸው ምዕመናን አብይ ምሳሌ መሆን የሚገባው ከርስዎ በስተቀር ማንም የለምና፡፡ ይህን ለማለት ያስደፈረኝ በአሁኑ ጊዜ በሙስሊሙ

ሕብረተሰብ የፅድቅ ተግባር ራሳቸውን ለማፅደቅ የሚፈልጉ አስመሳይ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች በሀገራችን እየበረከቱ በመምጣታቸው ነው፡፡ እነዚህ አስመሳይ መሪዎችና የሃይማኖት አባቶች በሰፊው ሕዝብ ላይ ለመፅደቅ፣ ዓለማዊ ሥልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሽርጉዱን ተያይዘውታል፡፡ የመፅደቅ ትርጉም በእነርሱ አተረጓጎም ከሃይማኖታዊ ዓለም ይልቅ ለምድራዊ ዓለም ጌቶች መሆን ይገባዋል ወደሚለው ማምራት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ የእነርሱ መፅደቂያ አልያም ደግሞ መርገፊያ መቼ ይሆን? በጣም የሚያጓጓ ጥያቄ ነው፡፡ ለአለማዊ ጥቅም መንፈሳዊ ፅድቅን መተው ምንኛ የሚያሳፍር ተግባር እንደሆነ ሲመክሩን እንዳልነበር አሁን ለራሳቸው ሲሆን ግን የምንላችሁን እንጂ የምንሰራውን አትከተሉ ብለው ማስተማር ጀመሩ፡፡ ይገርማል ጃል፡፡ አንዳንዱም የሃይማኖት መሪ ተብዬ በተከታዮቹ ምእመናን ላይ በፈፀመው የጀብደኝነት ተግባር የዓለማዊ ፅድቅ ሽልማት በቅርቡ ማግኘቱን ከኢንተርኔት ላይ ሳነብ እጅጉን ተገረምኩ ተደነቅኩም፡፡ በፅድቅ ፈንታ ኩነኔ (መዕሲያህ) የሚያሸልምና የሠላም አምባሳደር የሚያሰኝ ከሆነ እባካችሁ እኛንም አትርሱን ለማለት ቃጣኝ፡፡ ግን ግን ለምን ይሆን በሌላው ወገን ፅድቅ (ቢር) ተግባር የሃይማኖት መሪዎቻችን ለፃዲቅነት ለመብቃት የቻሉት? እኔ እንደማውቀውና ኢስላም እንደሚያስተምረው ፅድቅ ማለት በአላህ፣ በመላዕክት፣ በመለኮታዊ መጽሐፍት፣ በነብያት ማመንና ገንዘብንም ለሙት ሕጻናት፣ ለመንገደኞች፣ ለተቸገሩ ወገኖች መለገስ፣ ሰላትን (ስግደትን) በወጉ መፈፀም፣ ምፅዋትን መስጠት፣ ቃል ኪዳንን መጠበቅ፣ ትዕግስት ማድረግ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ታዲያ ከእነዚህ ተግባራት ውጭ በሌሎች ለመፅደቅ በሃይማኖት መሪዎች ነን ባዮቹ ሌላ መንገዶችና ዘዴዎች ለምን ተመረጡ? እውን ከሃይማኖት ማፈንገጥ ለተራው ሙእሚን ሳይሆን ለእነርሱ ያዋጣ ይሆን? መልሱን አብረን እንመልስ አበቃሁ ወሰላም፡፡

በሙስጠፋ ሓሚድ ዮሱፍ

የተመረጠ ርዕስ

ጽድቅና ኩነኔ(ከእስልምና ሃይማኖት አንጻር)

[email protected]

በዚህ የሃይማኖት አምድ የተለያዩ እምነት ተከታዮች በየእምነቶቻቸው ስላሉ ሀሳቦች ያነሳሉ፡፡ በተከታታይ ለሚቀርቡ ሃይማኖት ነክ ጽሑፎች ተመሳሳይ ርዕስ ተሰጥቶ ጸሐፊያን ከእየምነታቸው ድንጋጌ ተነስተው ጽሑፋቸውን ያቀርባሉ፡፡

ሙስጠፋ ሓሚድ ዮሱፍ በአለም አቀፍ ሕጐችና በሸሪዓ ሕግ ንፅፅራዊ ጥናት (ኮምፓራቲቭ ሎው) ኤል.ኤል.ቡ፣ በፊሎሎጂ ማስተርስ፣ የተለያዩ ኢስላማዊ መፅሐፍቶችን አዘጋጅ፣ ተርጓሚና አርታኢ፣ ኢስላማዊ ሕግን አስመልክተው ለሚነሱ የሕግ ጥያቄዎች አማካሪ ናቸው

Page 14: Addis Guday(1)

16 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 15: Addis Guday(1)

17 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 16: Addis Guday(1)

18 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

በቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

ቃለ ምልልስ

ከፅንሰ ሃሳቡ እንነሳና ዩኒቨርሲቲ ስንል ምን ማለታችን ነው?

እኔ እስከምረዳው ድረስና ብዙዎችም “ዩኒቨርሲቲ ማለት ምን ማለት ነው?” ለሚለው ጥያቄ በሰጡት መልስ ላይ እንዳገኘሁት የ20ኛው ክፍለ ዘመን የጀርመን ፈላስፋ የሆኑት ካርል ያስፐርስ “ዩኒቨርሲቲ ማለት የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለማወቅ ያለውን ፍላጐት ለማሟላት የሚያደራጀው ማዕከል ነው” ይላሉ፡፡ ይህም ማለት አካላዊ ብቃትን ለማግኘት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች (ጂም) እንደሚያስፈልጉ ሁሉ ዩኒቨርሲቲ የአእምሯዊ ብቃት ለማግኘት የተከለለ ስፍራ ነው፡፡ ታላቁ አርስቶትል “ሜታፊዚክስ” የተ ባለው ድርሳኑ ላይ ሲጀምር “ሰው በተፈጥሮው ለማወቅ ይፈልጋል” ይላል፡፡ በዚህ አባባል መጽሐፍ ቅዱስ “ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው” ከሚለው ጋር ዝምድና እናያለን፡፡ ሁለቱም አባባሎች የሰውን ልጅ ትልቅነት የሚያበስሩ ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የነገረ መለኮት (Theology) እና የፍልስፍናን የየቅል መንገድ ያመላክታል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ዩኒቨ ርሲቲ ስንል መመህርና ተማሪውን አቅፎ ይዞ እውቀትን ለመጐናፀፍ የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡

የትምህርትና የማወቅ ግንኙነት ምንድነው?ይህን ጥያቄ ለመመለስ መጀመሪያ ትምህርትን

በሁለት ሰፋ ባለመደብ እንክፈለው፡፡ የመጀመሪያው መደበኛ ያልሆነ (Elemental) ትምህርት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መደበኛ (Formal) ትምህርት ነው፡፡ እንግዲህ የሰው ልጅ በጠቅላላ የመጀመሪያውን (ኢ-መደበኛ) ትምህርት ስለሚያሟላ ሁሉም የሰው ልጅ የተማረ ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህ የትምህርት ዘርፍ ዋንኛዎቹ መምህራን ደግሞ ቤተሰቦቻችን ናቸው፡፡ የሁለተኛው (መደበኛ) ትምህርት በተደራጀና ጥያቄን ማዕከል በማድረግ የተለያየ የጥናት ዘርፍን እየወለደ ሆነ ተብሎ በተቀረፀ ስርዓት እውቀትን ለመጨበጥና ለማስተላለፍ የተዘረጋ መንገድ ነው፡፡

እውቀት ስንል ደግሞ በምርምር፣ በጥያቄ፣ በጥናት ላይ ተመስርቶ እነ አስተያየትን፣ እነ ግምትን፣ እነ መሰለኝን ተሻግሮ ወደ እርግጠኝነትና ወደ እውነታ የተጠጋ ሽግግር ነው፡፡ በመሆኑም ማንኛውም የትም ህርት ዘርፍ ተቀዳሚ ዓላማው እውቀት ለማጐናፀፍ ነው፡፡

ሚናቸውስ?... የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ምንድን ነው?ከመካከለኛው 20ኛው ክ/ዘመን እስካሁን ድረስ

የዩኒቨርሲቲን ሚና በሚመለከት ተቀባይነት ያገኘው ሃሳብ ዩኒቨርሲቲዎች ቢያንስ የሚከተሉትን ሦስት ዐቢይ ተግባራትን መፈፀም አለባቸው የሚል ነው፡፡ እነርሱም የመጀመሪያው እውቀትን ለመጨበጥ

ምርምር የሚካሄድበት፣ ሁለተኛው እውቀትን ለማሸጋገር የመማር ማስተማር ስርዓት

የሚካሄድበት እና ሦስተኛው ደግሞ የተገኘውን እውቀት ወደ ማኅበረሰቡ የሚደርስበት ስፍራ መሆኑ ነው፡፡ አንድ ዩኒቨርሲቲ ጤናማ ነው የምንለው እነዚህን ሦስት ሚናዎች አጣጥሞ ተግባራዊ ማድረግ ሲችል ነው፡፡

“ስድስት ኪሎ ሲሞት አምስት ኪሎ መጠውለጉ አይቀሬ ነው”

ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)

አመዛዝነው ከሚያስቡ፤ ያሰቡትንም የመናገር ድፍረት ካላቸው ምሁራን መካከል ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ በቃለ ምልልስ ቆይታችን የተረዳሁት እውነት ቢኖር ከምሁሩ ጋር ቃለ ምልልስ ማድረግ ማለት መጠየቅ ሳይሆን ማወቅ… ከሚያውቅ መምህር ሌክቸር የመውሰድ ያህል መሆኑን ነው፡፡

Page 17: Addis Guday(1)

19 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

የእነዚህ ሦስት ሚናዎች ተጣጥሞሽ መኖር አለበት ስንል ምን ማለት ነው?

ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ህልውና ሦስቱም ሚናዎች የማይተካኩ አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ ይህንንም ስንል የዩኒቨርሲቲው ግብ እውቀትን ብቻ ወይም የመማር ማስተማር ሂደትን ብቻ አሊያም ደግሞ እውቀትን የመተግበሪያ ማዕከል ብቻ አድርገን ነጣጥለን ከወሰ ድነው ለዩኒቨርሲቲው ሕይወት ችግር ያመጣል፡፡

እየተነጋገርን ያለነው በሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አካሄድ ዙሪያ ስለሆነ እነዚህ ሦስቱ ሚናዎች ምን ያህል ተጣጥመው እየሄዱ ነው ብለህ ታምናለህ?

ልጅ ቴዎድሮስ ይሄ ጥያቄ ወሳኝ እና ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚጠይቅ ነው፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ የአንድ ሀገር መንግስታዊ ፖሊሲና የትምህርት ፖሊሲ የተቀራረበ ግንኙነት አላቸው፡፡ በመሆኑም ስለ ኢትዮጵያ የትምህርት ፖሊሲ በምናወራበት ጊዜ ስለመንግሥት ፖሊሲም እያወራን ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ሀገሪቱን የሚያስተዳድረው መንግሥት “ተቀዳሚ አጀንዳዬ ልማት ነው” ብሎ ስለተነሳ ማንኛዎቹም ተቋማት የልማት አገልጋይ መሆን አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡

ወደ ትምህርት ዘርፍ በምንሄድበት ጊዜም ያንኑ የልማት ጥሪውን ይዞ ይቀርባል፡፡ በመሆኑም ቀደም ሲል ከዘረዘርናቸው ሚናዎች ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ ድርሻውን ብቻ እንዲያካሂድ ስለሚፈለግ ሌሎቹ የዩኒቨርሲቲ ተግባራት ላይ ትልቅ አሉታዊ ጫና ይፈጥራል፡፡ እኔ እስከምረዳው ድረስ ይህ ተግባርን ብቻ ማዕከል ያደረገ አካሄድ የሚከተሉትን ችግሮች ያመጣል፡፡

መጀመሪያ ዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ መሆን አለበት በሚባል ጊዜ የ70/30 ፖሊሲ አስቀምጧል፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ባልዳበረበት ሀገር “በጀቴን ለእነሳይንስና ኢንጂነሪንግ ነው የማወጣው” ማለቱ በራሱ ችግር የለውም፡፡ ሆኖም ግን በዚህ አካሄድ ከሁለት አቅጣጫ ችግር ይመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ለሳይንስና ኢንጂነሪንጉ ዘርፍ 70 በመቶውን እጅ መስጠቱ ሳይሆን ችግሩ 30 በመቶ እጅ የተሰጣቸው ዘርፎች ምንም አገልግሎት አትሰጡም በሚል የተጣበበ መስፈርት እንዲጠወልጉ መደረጋቸው ነው፡፡ አንዲት እናት ከወለደቻቸው አምስት ልጆች ሦስቱን ለይቼ እወዳለሁ ማለት መብቷ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እወዳቸዋለሁ ያለቻቸውን ሦስት ልጆች በአግባቡ እየመገበች ሁለቱን እንዳሻችሁ ካለች ግን ጥያቄው የቁጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ ሁለቱ በህይወት እንዳይኖሩ እያደረገች መሆኑም ጭምር ነው፡፡ በ70/30 ፖሊሲ እየተካሄደ ያለው ሁኔታም ይህን ይመስላል፡፡ የቁጥር ክፍፍሉ ሳይሆን ለሁለቱ ልጆች ምን እየተደረገ ነው? ነው ጥያቄው፡፡

የነገረ ሰብ ትምህርት (Humanities፣ Social Science) የመሳሰሉት ትምህርቶች በሳይንስ፣ በቴክ ኖሎጂ እና በኢንጂነሪንግ ጥናት ዘርፍ ለሚሳተፉ ተማሪዎች የድርሻቸውን ክሂሎት ያካፍላሉ፡፡ እን ደውም ከዚህ አኳያ የ20ኛው ክ/ዘመን ተደጋጋሚ ጥናት እንደሚያሳየው በነገረ ሰብ ጥናት ጥሩ መሠረት ያላቸው ሰዎች በየትኛውም የሳይንስና ምርምር ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በዚህ የተነሳም ነው እንደኔ እምነት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ስድስት ኪሎ ሲሞት አምስት ኪሎም መጠውለጉ አይቀሬ ነው፡፡

ትምህርት ዕውቀት ለጋሽ ነው፡፡ እውቀት ደግሞ በመሠረታዊት ችግር ፈቺ ነው፡፡ ስለዚህ በተለይም የደሃ ሀገር መንግሥት ችግር ፈቺ የትምህርት ስርዓት ላይ ቢያተኩር ስህተቱ የቱ ጋር ነው?

ይህንን ጥያቄ ለመመለስ በዋንኛነት የተዘገበው ስርዓተ ትምህርት ሳይንስ ነው፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ ስለ ሳይንስ ባህሪ ሁለት ነገሮች እንበል፡፡ አንደኛ ሳይንስ እንደማንም ስርዓት እውነትን ለመጨበጥ የሚካሄድ ምርምር ሲሆን ከዚያ አኳያ ስናየው የራሱ ግብና ተልዕኮ ያለው ጥናት ሆኖ ይገኛል፡፡ የ400 ዓመት የዘመናዊ ሳይንስ ታሪክ እንደሚነግረን ትልልቆቹ የሳይንስ ውጤቶች በቀጥታ ችግርን ለመፍታት ከሚል መነሻ የተገኙ አይደሉም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የሳይንስ ግኝቶች ሄዶ ሄዶ በተዘዋዋሪ መንግድ ችግር ፈቺ ሆነው ለዓለማችን ስልጣኔ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

በሌላ በኩል የችግርና ድህነት ጥያቄ ተደጋግሞ ይነሳል፡፡ ስለ ድህነት በምናወራበት ጊዜ ፊት ለፊት የምናየው ቁሳዊ ብቻ ሳይሆን አእምሯዊና መንፈሳዊ ድህነትንም ያካትታል፡፡ እንደህዝብ ማህበረሰባዊ ጉዳያችን ላይ ለመወያየት፣ ሂስ ለመደራረግ፣ በተለያየ ዘርፍ ያሉንን ሀሳቦች ለማበልፀግ የስነሰብ የጥናት ዘርፍ (ትያትር፣ሥዕል፣ሙዚቃ፣ሥነጽሑፍ፣ቋንቋ፣ፍልስፍና ወዘተ) ወሳኝ ድርሻ አላቸው፡፡

አሁን ለምሳሌ ሀገራችን በ2015 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፋለች ሲባል ውድድሩ የኢኮኖሚያዊና ቁሳዊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የመንፈሳዊ ሃብት ውድድር አይደለም፡፡ ገባህ የምልህ?... “በስነጽሑፍ በዚህ ዓመት እዚህ እንደርሳለን” ሲባል ሰምተሃል? “በትያትር፣ በሲኒማ ፕሮዳክሽናችን ጥራት፣ በስነግጥም አቀራረባችን…” ሲባል ሰምተሃል? ውድድሩ ቁሳዊ በሆኑ ነገሮች ብቻ ነው፡፡ ሀገር ደግሞ በዚህ ብቻ አታድግም፡፡ አሜሪካኖቹ የተሻለ የትምህርት ተቋም መገንባት የቻሉት ከጀርመን የሳይንስና ቴክኖሎጂን ጠቃሚነት፣ ከራሳቸው ደግሞ ሥነጽሑፍና ፍልስፍናን የመሰሉ የስነሰብ አስተምህሮዎችን ወስደውና አቻችለው ስርዓተ ትምህርታቸውን መቅረፅ በመቻላቸው ነው፡፡

የተማረ ሰው (ምሁር) የምንለው ምን ዓይነቱን ነው?የተማረ ሰው ማለት ክህሎት ያለው ማለት ብቻ

አይደለም፡፡ ከዓመት ዓመት በስልጠና ውስጥ የኖረ እና ያነበበ ሰው ማለትም አይደለም፡፡ ሚዛናዊ የሆነ፣ መጠየቅ የሚችል፣ ሁኔታዎችን ማገናዘብ የሚችል… ወደ ኋላ ሄዶ ስነጽሑፎችን ያነበበ፣ ትንሽ ታሪክም ለማወቅ የተጋ… ታሪክ ወሳኝ ነው ቴዎድሮስ፡፡ የሮማ ትልቁ የህግ አስተማሪ ሴሰሮ ምን ይላል? “ከመወለዳችን በፊት ያለውን ታሪክ ካላወቅን ዕድሜ ልካችንን ሕፃን ሆነን እንቀራለን” ይላል፡፡ አሁን በትምህርት ላይ የምታየው የይድረስ ይድረስ አቀራረብ በራሳቸው የማይተማመኑ እና የተቀባይነት መንፈስ የተጠናወታቸው ዜጐች ይወጣሉ፡፡ የዝቅተኝነት መንፈስ፣ በራስ የመተማመን አቅም የጐደላቸው ዜጐች ማፍራቱ አይቀርም፡፡ አሁን ያለው ከትምህርት

ይልቅ ስልጠናና ማዕከል ያደረገ አቀራረብ እንደሆነ እነግርሃለሁ፡፡ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ባለቅኔ እና ሃያሲ ጆርጅ ኢለየት ያሉትን እናንሳ፡፡ እሳቸው እንዳቀረቡት አውሮፓና አሜሪካ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ትምህርትን ለሁሉም ዜጐቻቸው ተደራሽ ለማድረግ ፖሊሲ ቀርፀው ተንቀሳቅሰው ነበር፡፡ በመሆኑም የዘመቻው ተልዕኮ ተሳክቶ በሀገራቸው የነበረውን የመጀመሪያ ደረጃ ማይምነት ድል በመንሳት ፕሮጀክቱ ተጠናቀቀ፡፡ “ሆኖም ግን…” ይላሉ ጆርጅ አሊየት “ፖሊሲው የተመረኮዘው ሽፋን (ቁጥር) እንጂ ጥራት ላይ ስላልነበር ወዲያው አይበገሬ የሆነው ሁለተኛ ደረጃ ማይምነት ብቅ አለ፡፡ ሁለተኛው ዙር ላይ የመጣው ማይምነት ከጋዜጣ ርዕስ በላይ የማያነቡ፣ የታሪክና የስነጽሑፍ መጣጥፎችን የማይፈልጉ፣ ከስፖርትና ከአልባሌ ወሬዎች ውጭ መወያየት የማይሹ፣ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ በአጠቃላይ ፀረ-ቀለም የሆኑ ዜጐችን አውሮፓና አሜሪካ አፈሩ” ይላሉ፡፡ ከዚያም ሃሳባቸውን ሲደመድሙ የመጀመሪያውን ማይምነት ማሸነፍ ቀላል ነበር፡፡ ሁለተኛውን ማሸነፍ ግን በእጅጉ ከባድ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

የመጀመሪያው ደረጃ ማይምነት ተሸካሚ የነበሩት ልጆችን መለወጥ ቀላል የሆነው አለማወቃቸውን የሚያውቁ ስለሆኑ ተማሩ ሲሏቸው የሚማሩ ስለሆኑ ሲሆን የሁለተኛውን ማይምነት አስቸጋሪ ያደረገው ምክንያት ተምራችኋል፣ አውቃችኋል ተብለው የተለያየ የትምህርት ደረጃ የአዋቂነት ምስክር ወረቀት ወይም ዲግሪ ስለተቀበሉ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ አንድ ሰው ታውቃለህ ተብሎ እውቂያ በጽሑፍና በሰነድ ከቀረበለት በኋላ እንደገና ተማር ማለቱ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

እኔ ግን ጆርጅ ኢሊየት የጠቀሷቸው ከጋዜጣ ርዕስ በላይ የማያነቡ፣ ከስፓርትና አልባሌ ጉዳዮች ውጭ መወያየት የማይፈልጉ ወጣቶች በዩኒቨርሲቲው የበዙ ይመስለኛል፡፡ ከሃገራዊ ራዕይ የሌላቸው፣ በ1960ዎቹ አጋማሽ እንደነበሩት የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ሀገራዊ ፓሊሲዎች፣ ከዓለም አቀፍ ፓለቲካዊ እና ፍልስፍናዊ ጉዳዮች የራቁ ከሃገር ብሔር ሰፍቶ የሚታያቸው ጥቂት እንዳልሆኑ እረዳለሁ፡፡ ይህን የምን ጉድለት ነው ብሎ ማሰብ ይቻላል?

እንደምታውቀው ሀገራችን የትራንስፎርሜሽን ፕሮጀክት አለ፡፡ ይህ ሊተገብር የታሰበው ትራንስፎርሜሽን ቁሳዊ ጉዳይ ላይ ብቻ የተመረኮዘ ነው፡፡ ይህ አገላለጽ ሰፋ ያለውን የትንስፎርሜሽን ትርጉም አያካትትም፡፡ ይህንንም ስንል የሞራል ትራንስፎርሜሽን፣ የእውቀት ትራንስፎርሜሽን፣ የስነውበት ትራንስፎርሜሽን፣ የፍልስፍና ትራንስ ፎርሜሽን ወዘተ እንዳለ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ይህን ገፀ ብዙ ትርጉም ወደተማሪዎቹ ጋር ለማድረስ የተ ጠናከረ የስነሰብና የሶሻል ሳይንስ ትምህርት ትኩረት ስላልተሰጠው ተማሪዎቹ ሊያገኙት የሚገባውን ሰፋ ያለ የታሪክ አመለካከት፣ ጠለቅ ያለ ፖለቲካዊ ግንዛቤ፣ ሊኖር የሚገባ ከክልላዊ መንፈስ የዘለለ ብሔራዊ ስሜት ለመጨበጥ ሲሳናቸው ይታያል፡፡ አንድ ዩኒቨርሲቲ የገባ/የገባች ተማሪ የቀረበላቸውን የትምህርት ገበታ ጨርሰው ዲግሪ ሲያገኙ በዲግሪው ከተሰየመው የትምህርት ዘርፋቸው ሌላ ከአካባቢያቸው “ትክክል ነው” ብለው ይዘው የመጡትን ሃሳብ ፈትሸው የሚያራግፉበት፣ ሰፋ ያለ የአመለካከት ልምድ አድማስ የሚቀስሙበት፣ ያለማስረጃ ያለመቀበልን ልምድ የሚያካብቱበት፣ ሳይመረምሩ የችኮላ ዳኝነት ላይ የማይደርሱበት የአእምሮ ፈለግ የሚያስይዛቸው ሊሆን ይገባል የሚል እምነት አለኝ፡፡

ቀደም ሲል ያልካቸው መንፈሳዊ ዕውቀቶች እንደቁሳዊው እውቀት በዳቦ ምርት፣ በመንገድ ሥራ እና በኤሌክትሪክ ማመንጨት ዓይነት የሚለካ አይሆንም፡፡ መንግሥት ደግሞ በፈጣን ሁኔታ “ለማደግ” ቁሳዊው ሀብት ላይ ቢያተኩር እንደምን ይፈረዳል?

እስከሚገባኝ መንግሥት ለሀገርና ለማህበረሰብ ይጠቅማሉ ብሎ የሚያከናውናቸው ተግባራት አሉ፡፡ እነዚህም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የምግብ አቅርቦት፣ መንገድን የመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች መሥራት ሥራው ነው፡፡ ይህ የመንግሥት ተቀዳሚ ሥራ እንደሆነ ማንኛችንም እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት አካባቢ ስንገባ መምህር ነንና የትምህርት ሁኔታ ያገባናል የምንለው ነን “የለም— ለማህበረሰቡ የሚያስፈልገው ይህ ብቻ አይደለም፡፡

በአሁኑ ጊዜ ትምህርት ተሽሮ ስልጠና የሚሰበክበት

ወቅት ላይ እንገኛለን...

Page 18: Addis Guday(1)

20 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ሌላም አስፈላጊ ጉዳይ አለ” ብሎ ማስታወስ እኛ ጋር ነው ያለው፡፡ እኛ በዝምታ ልክናችሁ ካልናቸው በእነሱ በኩል ሥራቸውን እየሠሩ ነው፡፡ አንድ ዩኒቨርሲቲ ከውጭ የሚመጣ ሃሳብ የሚፈተሽበት ነው ካልን መንግሥት የያዘውንም አቅጣጫ የመመርመር የሞራል ኃላፊነትም አለብን፡፡ በመሆኑም ሳንፈትሽና ሳንመረምር የምንቀበለው ፖሊሲ እንደ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ያለብንን ኃላፊነት እንዳልተወጣን ያስገነዝባል፡፡

እዚህ ላይ በአንድ ወቅት ማይናርድ ሃቸንስ (R.Maynard hutchens) በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንዲህ ብለው ነበር “ሁልጊዜ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከቄሣር (መንግሥትን ቄሣር ነው የሚሉት) ተፅዕኖ በመጣ ቁጥር አብዛኛዎቹ የዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች ሮጠው የቄሣርን ካምፕ ይቀላቀላሉ፡፡ የተቀሩት ደግሞ ‘እኛ የለንበትም’ ብለው አንገታቸውን ደፍተው ያልፋሉ” ይላሉ፡፡ ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ አብዛኛዎቹ የቄሣርን ካምፕ ተቀላቀሉ ማለት ባንችልም ብዙዎቹ ዝምተን መምረጣቸውን ግን መረዳት አያስቸግርም፡፡

አንድ በሌላ ሙያ ባንተ ደረጃ ያሉ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ መምህር ለቃለ መጠይቅ ሳነጋግራቸው ርዕስ ጉዳዩን ከጠየቁኝና ከመለስኩላቸው በኋላ “ያልከው በሙሉ ልክ ነው፡፡ ግን እውነቱን ልነግርህና ስለምፈራ ቃለመጠይቅ አልሰጥህም” ብለውኛል፡፡ ግልጽነታቸውን ባደንቅም ብዙ ዎችም ያመኑበትን መነጋገር ላይ እንዲሁ ናቸውና የግል ህሊና ነፃነት የሌላቸው መምህራን እንደምን የመንግሥትን መመሪያ ለመመርምርና ስህተቱን በድፍረት ሊጠቁሙት ይችላሉ?

ከዚህ ገጠመኝ ትረካህ ማንኛውንም ዩኒቨርሲቲ በሚመለከት አንድ በጣም ወሳኝ ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን፡፡ ይኸውም የአካዳሚ ነፃነት ጥያቄ ነው፡፡

ላቋርጥህና ለመሆኑ አካዳሚያዊ ነፃነት ምን ማለት ነው?የአካዳሚ ነፃነት ማለት ማንኛውንም መምህር

ያለበትን ኃላፊነትና ተልዕኮ በሚወጣ ጊዜ ምንም ዓይነት ጫና እንዳይደርስበት የሚከላከል የህግና የሞራል መርህ ነው፡፡ ተልዕኮ በምንል ጊዜ በዋንኛነት ማኅበረሰባዊ ተልዕኮ (ልማት፣ኃይማኖት፣ ባህል…) ሳይሆን፣ ፖለቲካዊ ተልዕኮም ሳይሆን ለእውነት ብቻ ተጠሪ የሆነ መንገድን የሚከተል ነው፡፡ እውነትን በመከተል ላይ የተመሠረተው የአካዳሚ ነፃነት አንፃራዊ ሳይሆን ለመምህሩ ልክ እንደ ሰብአዊ መብት የሚታይ ፍፁማዊ የሆነ ነው፡፡

ወደ መምህሩ ልመልስህና እሳቸውም ሆነ ብዙዎች ያልከውን (እንደ ሰብኣዊ መብት የሚታየውን) የአካዳሚ ነፃነት በገለፅከው መንገድ ሊጠቀሙበት ያልቻሉት ለምን ይመስልሃል?

ይህን ጥያቄ በቀጥታ ከመመለስ በ1960ዎቹ ራስል ከርክ (Russell Kirk) የተባሉ የአሜሪካ ፈላስፋ ‘Academic Freedom’ በሚለው መጽሐፋቸው እንዳሉት “አንዳንድ መምህራን የአካዳሚ ነፃነት የሚባለው ነገር አእምሯቸው ላይ የሚመጣው የራሳቸውን የንዋይ ጥያቄ በሚመለከት ሲሆን፣ የፈለጉትን ርዕዮተ አለማዊ ጥምቀት (Indoctrination) ተማሪው ላይ እንዳይጭኑ ሲጠየቁ፣ በተጨማሪም የተማሪ መብት አክብሩ ሲባሉ ነው፡፡”

እንደ ራስል አቀራረብ የአካዳሚ ነፃነት ሁኔታ ከመምህራኑ የሚመነጨውን ጉድለት የሚያሳይ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የነፃነት መነፈግ ጉዳይም እንደሆነ መዘንጋት የለበትም፡፡ ከላይ እንዳልከው አንድ ዩኒቨርሲቲ የራሱ ዓላማና ግብ አለው፡፡ መንግሥት

የራሱን ዓላማና ግብ ዩኒቨርሲቲውን ሲያሸክመው ትልቅ የአካዳሚያዊ ነፃነት ጥሰት ይሆናል፡፡ ወደ እኛ ሀገር መለስ ስንል ከዚህም በተጨማሪ በጣም አሳሳቢ እየሆነ የመጣው ዩኒቨርስቲው በተለይም ድህረ ምረቃን በሚመለከት ማንን በተማሪነት አወዳድሮ እንደሚቀበል ውሳኔው የዩኒቨርሲቲው ሳይሆን የሌላ አካል መሆኑ በእጅጉ አካዳሚያዊ ነፃነትን ይጋፋል፡፡ ልክ መንግሥት በኃይማኖት የቀኖና ትምህርት ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ ሁሉ የዩኒቨርሲቲ ካሪኩለም ላይም ገብቶ “ይህን ተማሩ… እነ እገሌን አስተምሩ…” የሚለው አሰራር የአካዳሚ ነፃነትን የሚጋፋ ይሆናል፡፡ ጥያቄውን ለማጠቃለል በተለያዩ ግላዊና ማህበራዊ ሰበቦች መምህራኑ በአደባባይ ጥያቄ ማንሳትም ሆነ ለጥያቄ መልስ መስጠት እንደማይፈልጉ መረዳት ይቻላል፡፡

ከዚሁ ከትምህርት ጉዳይ ጋር በተያያዘ በመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አካባቢ እንደ ባህል የተያዘ የስልጠና ስርዓት ተዘርግቷል፡፡ ቀላል የማይባል ገንዘብ የሚፈስባቸው እነዚህ ስልጠናዎች የሚፈለገውን ለውጥ እያመጡልን ይመስልሃል?

ከሁሉ አስቀድሞ መመልከት ያለብን በዚህ ሀያ ዓመት ውስጥ “ስልጠና” ከ “ከትምህርት” በላይ ትልቅ ስፍራ ተሰጥቶታል፡፡ ከዚህ በፊትም በሬዲዮ እንደተናገርኩት ልክ ኦሪት ተሽሮ ወንጌል የሚሰበክበት ዘመን እንደሚባለው በአሁኑ ጊዜ ትምህርት ተሽሮ ስልጠና የሚሰበክበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ስልጠና ሄዶ ሄዶ የትምህርት አንድ አካል ይሆናል እንጂ አጠቃላይ የሆነ የትምህርትን ዘርፍ የሚያሟላ ነገር ስላልሆነ ስልጠና ትምህርትን እንዲተካ ማሰቡ ራሱ ያስቸግራል፡፡ ትምህርት ስንል አእምሮን መኮትንኮት (Cultivate)፣ ማበልፀግ፣ ማረም የመሳሰሉትን የሚይዝ ሲሆን ስልጠና በሌላ መንገድ ክህሎትን ሙያን፣ መገንዘብን የመሳሰሉት የሚያስገኝ ነው፡፡ የልማት ፖሊሲ ሄዶ ሄዶ ቁጥርና አቅርቦት ላይ የመድረስ ፍላጐት ስላለው ከትምህርት ይልቅ አቋራጭ እና ብዙ ንዋይ አፍሳሽ ያልሆነውን ስልጠናን ይመርጣል፡፡ እንዲያውም ከስልጠና የመጣን ችግር ለመፍታት ወደ ትምህርት እንሂድ ከማለት ተጨማሪ ስልጠና መስጠት የተሻለ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡

የቁጥር ጥያቄ ከተነሳ አይቀር ባለፉት 20 ዓመታት አንድ ከነበረው ዩኒቨርሲቲ አሁን ሠላሳ ሁለት ደርሰናል፡፡ የቁጥሮቹ መብዛት በመንግሥትና በተለያዩ ወገኖች በተለያየ ትርጉሙ ሲገለፅም ይታያል፡፡ ከልማትና ቁጥር አንፃር የዩኒቨርሲቲዎቹን እየበዙ መሄድ እንዴት ታየዋለህ?

ደግሞ አንድ ቦታ ላይ መጀመርና በሂደት እያሻሻሉ መሄድ እንደሚገባ ይናገራሉ፡፡ ምን መልስ ትሰጣቸዋለህ?

ጥሩ ጥያቄ ነው፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በማን ኛቸውም ሁኔታ መስፈርቱን ሊያሟሉ የማይችሉ ቁጥራቸው በዛ ያለ ዩኒቨርሲቲዎች ገንብተናል ከምንል አቅማችን እንደፈቀደ መስፈርታቸውን የጠበቁ አነስተኛ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተን ብንንቀሳቀስ ውጤታማ እንሆናለን የሚል እምነት አለኝ፡፡ ተማሪዎች ቋሚ ሳይሆኑ በስርዓተ ትምህርት ኃላፊዎች ስለሆኑ ጥራት በጐደለው የትምህርት አካሄድ ካለፉ በኋላ መልሶ መጥራት አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ጥራት የሌላቸውን ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተን በሂደት እናሻሽላለን ከምንል ይልቅ ጥራት ያላቸው ተማሪዎችን አስተምረን በሂደት ቁጥራቸውን እየጨመርን ብንሄድ ይመረጣል ባይ ነኝ፡፡

እስካሁን ያነሳነው በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ያሉትን ነው፡፡ በሀገሪቱ እየበረከቱ ያሉት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየታየባቸው ያለው የትምህርት ጥራት መጓደል በጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት “ዲግሪ የሚያትሙ” ተብሎ እስከ መገለጽ የደረሰ ነው፡፡ እነሱን በአንድ ጥያቄ እናንሳቸው?

መንግሥት ይህን ጉዳይ በሚመለከት እየወሰደ ያለው እርምጃ የሚያስመሰግነው ነው፡፡ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሥራዬ ብዬ ባላጠናም በቅርብ የተከታተልኳቸው ሁለት የትምህርት ተቋማት ግን መዘጋት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ እንደውም ከሁለቱ አንዱ በጣም ከፍ ያለ ገንዘብ እያስከፈለ ለመንግሥት ሹመኞች የዲግሪ አቅርቦት አገልግሎት ላይ የተሰማራ ለመሆኑና በአንድ ዓመት ውስጥ ካልተሻሻለ እንደሚዘጋ ጥራትን ከሚመለከተው ክፍል ማስጠንቀቂያ እንደደረሰው በሚዲያ ሲገለፅ ሰምቻለሁ፡፡ በግል ይዞታ ስር 1ኛ ደረጃና ከዚያ በታች ያሉት በአንፃራዊ መልኩ በተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ ሲሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ግን እዚህ ግባ የሚባል ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል ማለት አይቻልም፡፡ የእነዚህ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ የማደል ተግባር በሚመለከታቸው ወገኖች በጥብቅ ሊታሰብበት የሚገባ ነው እላለሁ፡፡

እንግዲህ ወደ መደምደሚያው እየደረስን ይመስለኛል፡፡ እስካሁን የተወያየንባቸውን ሀሳቦች መንፈስ በሁለት ዓረፍተ ነገር ብናቀርበው የዛሬ መቶ ዓመት ካርዲናል ኒውማን እንዳሉት አንድ ዩኒቨርሲቲ የሚለካው በማንነቱ እንጂ በሚያመርተው መሆን የለበትም፡፡ በመሆኑም በመንግሥትም ይሁን በግል ይዞታ ስር ያሉት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እውነትን ለማግኘት ጥናት፣ ምርምር እና ፍተሻ የሚካሄድባቸው ብቸኛና የተከለሉ ተቋማት እንደሆኑ መታወቅ አለበት፡፡ በኔ እምነት የዩኒቨርሲቲዎቹ ቁጥር የበዛው ከዩኒቨርሲቲ አቅርቦት ፍላጐት ሳይሆን ከፖለቲካ ፍላጐት የመነጨ ነው፡፡

እስቲ በጉዳያችን መጨረሻ የስርዓተ ፆታን ጉዳይ አንስተን እንለፍ፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለሴቶች ስለሚሰጠው ማበረታቻ እናንሳ፡፡

ያንተን ባለውቅም እኔ በበኩሌ ማበረታቻው ጥሩ እንደሆነ ነው የሚታየኝ፡፡ ይሄን ሁሉ ማበረታቻም ተሰጥቶም የሴቶች ቁጥር በትምህርትም ሆነ በሥራ ትንሽ ነው፡፡

ማበረታቻው እስከመቼ መቀጠል አለበት?ገና ጊዜ ይፈጃል፡፡ አሜሪካኖቹም ለሴቶችና አናሳ

ብሔሮች የሰጡትን ማበረታቻ (Affirmative action) ገና አላነሱትም፡፡ እንደውም አሜሪካ ውስጥ ይህ ማበረታቻ መቅረት አለበት የሚለው ጉዳይ አልፎ አልፎ ስለሚነሳ በአንድ ወቅት ጉዳዩ የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደርሶ አንደኛዋ ዳኛ “እኔ በግሌ ማበረታቻው እንዲቀር እፈልጋለሁ፡፡ ግን አሜሪካ ለዚህ ዝግጁ አይደለችም” ነው ያለችው፡፡ እኔ ማበረታቻው መኖር እንዳለበት አምናለሁ፡፡ እሱ ላይ ችግር የለብኝም፡፡ የእኔ ችግር ይህ እየተባለም ዩንቨርሲቲው በዋንኛነት በወንዶች የበላይነት ቁጥጥር ስር እንደዋለ መቅረቱ ላይ ነው፡፡ ይህ የባህላችን የአመለካከት ነፀብራቅ ነው፡፡ የሚያስገርመው ባህልና ወግ ዘመናዊ ትምህርት ሳይበግራቸው የራሳቸውን አሻራና ተፅእኖ አስፍነው መቀጠላቸው ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ኃላፊነት ቦታ ላይ ሴቶች ምን ያህል ይኖራሉ?

ብዙ የሉም፡፡

ከ32 ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ሴት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች አሉ?

እኔ እስከማውቀው ምንም የለም፡፡

አመሰግናለሁ፡፡

ከሁሉም አስቀድሞ ካለን ከአንዱ በቀር ተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች መገንባታቸው አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ የሚነሳው ጥያቄ ግን እነዚህ 32 ዩኒቨርሲቲዎች በምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት? የሚለው ነው፡፡ ይሄንን ጥያቄ በቀጥታ ከመመለሴ በፊት ከአንድ መጽሐፍ ያነበብኩትን ልንገርህ፡፡ በ1960ዎቹ አሜሪካ ሀገር በተካሔደ አንድ ትልቅ የትምህርት ጉባኤ ላይ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተነስተው “አሁን አሜሪካ ውስጥ የዛሬ 30 ዓመት ከነበረን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቁጥር በላይ ዩኒቨርሲቲዎች አሉን” ብለው ሲናገሩ ሌላው ተሰብሳቢ የዩኒቨርሲቲ መምህር ተነስተው “አዎን በቁጥር እንዳልከው በፊት ከነበረን 2ኛ ደረጃ በላይ ዩኒቨርሲቲ ከፍተናል፡፡ ሆኖም ግን ይህም የሆነበት ምክንያት ከ2ኛ ደረጃ ትንሽ ከፍ ያሉ የትምህርት ተቋማትን እየከፈትን ዩኒቨርሲቲ የሚል ስያሜ ስለሰጠናቸው ነው” ብለው መለሱላቸው፡፡ የኔም አመለካከት ከዚሁ መንፈስ ብዙም የራቀ አይደለም፡፡ ይኸውም የሚሆንበት ምክንያት ሌላው የእጥረት ዝርዝር እንደተጠበቀ ሆኖ 32ቱን ዩኒቨርሲቲዎች በብቃት ሊሞሉ የሚችሉ መምህራን የሉም ብዬ ስለማምን ነው፡፡

በመንግሥት ወገን ያሉ ሰዎችም እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያየ መልኩ እጥረት እንዳለባቸው አይክዱም፡፡ ግን

“ሁለተኛው ዙር ላይ የመጣው ማይምነት ከጋዜጣ ርዕስ በላይ የማያነቡ፣ የታሪክና የስነጽሑፍ

መጣጥፎችን የማይፈልጉ፣ ከስፖርትና ከአልባሌ ወሬዎች ውጭ

መወያየት የማይሹ፣ በራሳቸው የማይተማመኑ፣ በአጠቃላይ ፀረ-ቀለም የሆኑ ዜጐችን...”

Page 19: Addis Guday(1)

22 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ማስታወሻ የጽጌረዳ ኃይሉ መታሰቢያ ገጽ

Page 20: Addis Guday(1)

23 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 21: Addis Guday(1)

24 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም(ቀጣዩን በገፅ 35 ላይ ይመልከቱ)

Page 22: Addis Guday(1)

25 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 23: Addis Guday(1)

26 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ከባልደረቦቿነፍሱን ይማርልንና አብርሃም ረታ ዓለሙ

ለመጀመሪያ ጊዜ ስለጽጌ ሲነግረኝ “ሥራዋን በፍቅር ትወዳለች፣ ታነባለች፣ ለመማር ዝግጁ ነች፣ ደፋር ነች፣ አትዋሽም፡፡ እነዚህን ካሟላችም አሪፍ ጋዜጠኛ ነች” ብሎን ነበር፡፡ ላለፉት አምስት ዓመታት አብርሃም ከመሠከረላት አንዱንም እንኳ አጓድላ አይቼ አላውቅም፡፡ እውነትም ጽጌ አሪፍ ጋዜጠኛ፣ ሁለገብ ዕውቀት ያላት አስተማሪዬ ነበረች፡፡

እንዳልካቸው ተስፋዬ

መቃብርሽ ልባችን ውስጥ ነውየኔ እና የጽጌረዳ ትውወቅ ከሮዝ መጽሔት ምስረታ

ይጀምራል፡፡ መስከረም 1999፡፡ አንዲት እንስት ጋዜጠኛ በምትክል ዋና አዘጋጅነት አብራን እንደምትሠራ ቢነገረኝም ለቀናት አልተያየንም ነበር፡፡ አንድ ዕለት ቢሮ እያለሁ አንዲት ቀይ ልጅ ገብታ ፀሐፊያችንን ካዋራቻት በኋላ ልትወጣ ስትል እኔ ማን እንደሆንኩ ነግራት ኖሮ ፊቷ በፈገግታ ተሞልቶ ወደ እኔ በመምጣት “… አለቃዬ እኔ ጽጌረዳ ኃይሉ እባላለሁ” ብላ ተዋወቀችኝ፡፡ ከዚያች ዕለት ጀምሮ ቅርርባችን ከሥራ ባልደረባነት ወደ ልብ ጓደኝነት እና ወደ ቤተሰብነት አድጓል፡፡ ጽግዬ የኔም የባለቤቴም የትንሿ ኩኩዬም ወዳጅ ነበረች፡፡

ቢሮ ውስጥ ላለነው ሁሉ እናታችን ነበረች፡፡ ብዙ ጊዜ ሳንነግራት ፊታችንን በማንበብ ብቻ መከፋታችንን ታውቅና አብራን መፍትሔ ለማግኘት ትጨነቅ ነበር፡፡ ለኔማ የልብ አውቃዬ ናት፡፡ ምንም ሳልነግራት ያስከፋኝን ነገር ታውቀው ነበር፡፡ “ሰውየው…” ብላ ከጀመረች አሳስቃ ልታረሳሳኝ ጀመረችኝ ማለት ነው፡፡

ጽግዬ በማንኛውም ሰዓት የማገኛት ጓደኛና አማካሪዬ ነበረች፡፡ ልቧና ስልኳ በተፈለጉበት ሰዓት ወዳጆቻቸውን ለማስተናገድ ክፍቶች ናቸው፡፡ ክፋት የሚባል አይቼባት አላውቅም፡፡ ስትበሳጭ እንኳን ያቺን ፈገግታዋን ከፊቷ ማራቅ ይከብዳት ነበር፡፡ ስለዚህ ፀባይዋ አንድ ወቅት ስንጨዋወት “… አባዬ በከፍተኛ ፍቅር ነው ያሳደገኝ፡፡ በዚህ የተነሳ ማንም ሰው ይጠላኛል— አይወደኝም ብዬ አስቤ አላውቅም…” ብላኝ ነበር፡፡ ይህ አመለካከቷ መጽሔቷን በተመለከተም ይሁን የግል ሥራዎቿን አስተያየት በምትቀበልበት ወቅት ይታይ ነበር፡፡

የምላት ነገር ሳይኖረኝ እንኳ እንዲሁ በነገር ልተነኩሳት እደውልላት የነበረችው ጽግዬ እንደዘበት “መጣሁ ዕቃ ተቀብዬ” እንደምትለኝ ዓይነት ማክሰኞ ማታ ወጥታ ላትመለስ ተለየችኝ፡፡

በአካል አጠገቤ ባትኖርም ሁልጊዜ በዙሪያዬ እንዳለች ይሰማኛል፡፡ ይህን ስሜት እፈልገዋለሁ፡፡ አማካሪዬ፣ የልብ ጓደኛዬን አፅናኜን ማጣት አልፈልግም፡፡ አብረን እንዲሁ እንደተጨቃጨቅን እናረጃለን እንባባል ነበር፡፡ እንደታላቅ የምላትን የምትተገብር፣ እንደ እህት ተንከባካቢዬ— አቀማጣዬ— አለሁ ባዬ፣ እንደ እናት ከሷ ይልቅ እኔን አስቀዳሚዬ ናትና እንድትርቀኝ ያውም በድንገት አለስንብት እንድትለየኝ አልፈልግም፡፡ አእምሮዬ ለዚህ አልተዘጋጀምና፡፡ “ያጣናቸው ወዳጆቻችን መካነ መቃብር ያለው መሬት ውስጥ ሳይሆን ልባችን ውስጥ ነው” የሚለውን የአንድ ደራሲ አባባል ቴዲ ነግሮኝ ነበር፡፡ ጽግዬ በልባችን ውስጥ ትልቅ ቦታ አለሽ፡፡ መቼም ቢሆን ለአፍታም ቢሆን አንቺን መዘንጋት የሚቻል አይደለም፡፡

የቢሮ ጓደኞቻችን የሚናፍቁትን ተረብና ብሽሽቃችንን ለመጀመር ቀና ብዬ ወደቦታሽ አማትራለሁ፡፡ ቦታሽ ውስጥ ባጣሽም ሁልጊዜ ልቤ ውስጥ አለሽ፡፡

ደግነትሽ፣ ቀናነትሽ እና የተቸገረ ሰው አይተሽ ማለፍ አለመቻልሽ የፈጣሪ እጆች በፍቅር እንዲቀበሉሽ ያደርጋሉ፡፡ ነብስሽን በአብርሃምና በይስሃቅ አጠገብ ያኑርልን፡፡

ዮሐንስ ካሣሁን

ይብላኝልን ለእኛእንባዬ በረጅሙ ይፈሳል… በረጅሙ! በብቸኝነት

ቤቴ ውስጥ ከልቤ ሞልቶ የተረፈው ሃዘን በእንባዬ በኩል እየወጣ ይመስለኛል፡፡ ለእንባዬ ከልካይ የለበትም፡፡ እኔም አልከለከልኩት፡፡ ይውረድ እስኪበቃው፡፡ ከአራስ ቤት መውጣት ላልቻለች… የአራስ ወግ ማየት ላልቻለች መልካም ሴት… ለአራስነቷ የተዘጋጀ ገንፎ፣ አጥሚት የአዘቦት ምግብ ለሆነባት ምስኪን ሴት እንባዬ ይፍሰስ፡፡ እንባ ከዓይን ሳይሆን ከልብ፣ በደም ስር በኩል የሚወጣ አይመስለኝም ነበር፡፡ ዛሬ ግን እያየሁ ነው፡፡ ይፍሰስ እምባዬ… በረጅሙ! ትኩስ ለቅሶ ነው ለእኔ፡፡

በዚህ መጠን ሃዘን ውስጤን የሰበረው ጊዜ የለም፤ አባትም ሞቶኝ ያውቃል፡፡ አሁን ግን ለምን እንዲህ ሆንኩ? ይቺ ትንሿ ልቤ ከሚበቃት በላይ በሃዘን ተሞልታለች፡፡ አሁን ግን በእምባዬ በኩል የተወሰነው

Page 24: Addis Guday(1)

27 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 25: Addis Guday(1)

29 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

‘ቆይ ግን አማርኛ እና እንግሊዝኛ እየቀላቀላችሁ ለምን ታወራላችሁ?’ የሚሉ ሰዎች በጣም ነው የሚያስገርሙኝ፡፡ አሁን እውነት ምክንያቱ ጠፍቷቸው ነው? ለመሆኑ ሊቅነት ምንድን ነው? መቀላቀል ማለት አይደለም እንዴ፡፡ ለመሆኑ ሳይቀላቀል የሚያተርፍ ነገር አለ?

ቆይ ቆይ ግን እነዚህ አጭበርባሪዎች ሙዝ እና ቅቤ፣ ሸክላ እና በርበሬ፣ ስኳር እና የሩዝ ድቃቂ የሚቀላቅሉት ለምን ይመስላችኋል? አንድ ነገር ካልተቀላቀለበት አያተርፍማ፡፡ ወሬ እንኳን’ኮ ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ከተወራ አያተርፍም፡፡ እስኪ ወሬ ሲጀመር እዩ፡፡ ስለ መንደራችሁ፣ ስለ ከተማችሁ፣ ስለ ገጠራችሁ ከአሥር ደቂቃ በላይ ካወራችሁ እንኳን የሚሰማችሁ የሚያያችሁ አታገኙም፡፡ ታድያ በመካከል «አሜሪካን ሀገር» የሚል ጣ’ል አድርጉበት ወደ እናንተ ያልተቆለመመ አንገት አታገኙም፡፡

እስኪ ጎበዝ ከሆናችሁ ስለ ቡና እና ጊዮርጊስ፣ መከላከያ እና ደደቢት፣ ሲዳማ ቡና እና ሐረር ቢራ ብቻ አውሩ? ራሳቸው ተጫዋቾቹ እንኳን በቅጡ አያዳምጧችሁም፡፡ ያን ጊዜ ታድያ አርሴናል፣ ማንቸስተር፣ ቼልሲ፣ ማድሪድ፣ ባርሴሎና ማለት ትጀምራላችሁ፡፡ መቀላቀል ያለ ነው ጎበዝ፡፡

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በስሙ ላይ ዴሞክራሲ የሚል ቃል ጣ’ል ያላደረገ ፓርቲ አይታችሁ ታውቃላችሁ? ድሮ ኮሌጅ ስንማር ዜር ፎር የሚባል ምግብ ነበረን፡፡ በወጡ ውስጥ ከሦስት ፍሬ በላይ ሥጋ የማይገኝበት፡፡ ለስሙ ሥጋ ወጥ ነው፡፡ ሥጋውን ግን ፈልገህ አታገኘውም፡፡ የኛም ዴሞክራሲ እንደ ዜር ፎር ወጥ ጣ’ል የተደረገ ስለሆነ ፈልጋችሁ አታገኙትም፡፡ ጣ’ል ማድረግ ያለ ነው ጎበዝ፡፡

በኛ ላይ ብቻ ዐቅም አግኝታችሁ የትችት መዓት ታወርዳላችሁ እንጂ እስኪ ሬዲዮውን እና ቴሌቭዥኑን ተከታተሉት፡፡ አዲስ ዐዋጅ ሲታወጅ፣ አዲስ መመሪያ ሲጸድቅ፣ አዲስ መዋቅር ሲሠራ ባለ ሥልጣናቱ፣ «ኤክስፐርቶቹ? ስለ ኢትዮጵያ ብቻ ነው እንዴ የሚያወሩት? ኧረ በጭራሽ፡፡ «ይህ ሕግ» ይሉላችኋል «ከእንግሊዝ የመጣ ነው፣ ከሆላንድ የተወሰደ ነው፣ ከአሜሪካ የተገለበጠ ነው፣ ከጃፓን የተሻለ ነው፣ ከኬንያ የሚመረጥ ነው» አይደል እንዴ የሚሉት፡፡ ካልተቀላቀለ አያዋጣማ፡፡

ፍትሐ ነገሥትን መጠቀም ከጀመረች ሰባት መቶ ዓመት ሊሞላት የደረሰች ሀገር የሕጎቿን ትክክለኛነት ለመግለጥ የእንጀራ አባት ፍለጋ አውሮፓ እና አሜሪካ መንከራተት ነበረባት? ደግሞስ አንድ ሕግ ምርጥ ሕግ ለመባል ከእንግሊዝ እና ከአሜሪካ፣ ከደቡብ አፍሪካ እና ከጋና የተሻለ መሆን አለበት? እኛ‘ኮ እንጀራን የወደድነው ከሕንድ ሩዝ እና ከጣልያን ፓስታ፣ ከኬንያ ኡጋሊ እና ከሜክሲኮ ሾርባ ጋር አወዳድረን አይደለም፡፡ በቃ በራሳችን መመዘኛ መዘንነው ወደድነው፤ አለቀ፡፡

ግን አየህ በዘመኑ ካልተቀላቀለ አያምርም፡፡ ስለዚሀ አትስረቅ የሚል ባህል ቢኖርህም አትስረቅ የሚለውን ሕግ ግን ከጃፓን መውሰድ የግድ ነው፡፡ ጣ’ል ለማድረግ፡፡

እንዲያውም ባይገርማችሁ የማይቀላቅሉ የአራዳ ልጆች ብቻ ናቸው፡፡ የራሳቸውን አማርኛ ይፈጥራሉ እንጂ እንግልጣር ከአማርኛ አይቀላቅሉም፡፡ በሀገራቸው ቋንቋ አሟልተው መናገር የሚችሉት አራዶች ብቻ ናቸው፡፡ ምን ዋጋ አለው ታድያ የፋራ ምልክት ሆነ፡፡ እነርሱም ቢጨንቃቸው ፋዘር እና ማዘርን መቀላቀል ጀመሩ፡፡ የሠለጠነ አራዳን ከፋራ አራዳ ለመለየት ያህል ጣ’ል ያደርጉባታል፡፡

ኧረ ቆይ እንዲያውም ምን እዚያ ድረስ አስኬደኝ፡፡ ባለፈው የጥምቀት በዓል ሲከበር እነማን ነበሩ ከጃንሜዳ በቀጥታ ሥርጭት ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው የነበሩት እነማን ናቸው? አንድም ፈረንጆች፣ አንድም ከፈረንጅ ጋር ወይ ኖረው ወይ ሠርተው የመጡ፣ አንድም

ዳንኤል ክብረት[email protected]

ጣ’ልየፈረንጅ ጓደኛ ኖሯቸው እርሱን ተከትለው መድረኩን መጠጋት የቻሉ አይደሉምን?

እኔ ስለ ጥምቀት በዓል ለመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መኖር በቂ አለመሆኑን፣ የኢትዮጵያን ዕድገት ለመገምገም ለዕድገቱ የሚሆን ግብር መክፈል በቂ አለመሆኑን፣ ስለ ኢትዮጵያን በሚገባ ለመግለጥ ከውጭ ወደ ውስጥ ማየት የግድ መሆኑን ያወቅኩት ያኔ ነው፡፡ በጋዜጠኛው አልፈርድም፤ ወዶ አይደለማ፡፡ ካልተቀላቀለ አያዋጣም ብሎ ነው‘ኮ፡፡ በአማርኛ ላይ እንግሊዝ፣ በሀገርኛ ላይ ዳያስጶራ ጣ’ል ሲደረግ ያምራል፡፡

እናንተ ልታርፉ አልቻላችሁም‘ንጂ የአራዳ ልጆች‘ኮ ይገባናል፡፡ ለመሆኑ በአማርኛ ወይንም በትግርኛ አለበለዚያም በኦሮምኛ ተናግሮ ሊቅ የተባለ ሰው ታውቃላችሁ፡፡ እርሱንማ ማንም ይናገረዋል‘ኮ፡፡ መወለድ ብቻ በቂ ነው፡፡ ምናልባት እዚች ሀገር በራስህ ቋንቋ መናገርህ ብሔረሰብህን ይገልጥ እንደሆነ እንጂ ዐዋቂነትህን አይገልጥም፡፡ ምን ብሔረሰብህን ብቻ የተወለድክባትን ጎጥ ነው የምታስመሰክረው፡፡

ስለዚህ መሐል መሐል ላይ እንግሊዝኛ ጣ’ል ታደርጋለህ፡፡ እናቶቻችን ሲናገሩ አልሰማህም፡፡ «ሽሮው ላይ ቅቤ ጣ’ል አድርጊበት፣ ፍርፍሩ ላይ ሥጋ ጣል አድርጊበት» ይላሉ‘ኮ፡፡ አየህ ዋናው ነገር ሽሮው ወይንም ፍርፍሩ ሳይሆን ጣ’ል የሚደረገው ቅቤው እና ሥጋው ነው ማለት ነው፡፡ ቅቤ እና ሥጋ ውድ ነዋ፡፡ ምግብ ቤት ገብተህ ቅቅል ወይንም ቀይ ወጥ ስታዝ ምንድን ነው የምትለው፡፡ «ማነህ አንተ አጥንት ጣ’ል አድርግበት» ትል የለም እንዴ፡፡

እኛም ታድያ በአማርኛ እና በኦሮምኛ መሐል እንግሊዝኛውን ጣል እናደርግበታለን፡፡ ቆይ አንድ ጉድ ላውጋ፡፡ አማርኛ እና ትግርኛ፣ አማርኛ እና ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና ሶማልኛ የሚችሉ ብዙ ወገኖች አሉ፡፡ በአማርኛ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ለወደፊቱ እኔ እንደሰማሁት አድርጋችሁ ስሙ፡፡ ቢሞቱ አማርኛን ከትግርኛ፣ አማርኛን ከኦሮምኛ፣ አማርኛን ከሶማልኛ ሲቀላቅሉ አትሰሙም፡፡ ለምን አትሉም? ያስበላላ፡፡ አያተርፍም፡፡ መካከል ላይ እንግሊዝኛ ጣ’ል ሲያደርጉ ነው የምትሰሙት፡፡ በአማርኛ ላይ ኦሮምኛ፣ በትግርኛ ላይ ሶማልኛ ጣ’ል ማድረግማ በሽሮ ላይ ድንች ጣ’ል እንደ ማድረግ ነው፡፡

መቀላቀል ልማድ ቢሆን ኖሮ አማርኛ እና ኦሮምኛ፣ አማርኛ እና ትግርኛ ሳይቀላቀሉ እንዴት ነው አማርኛ ከእንግሊዝኛ ጋር ካልተቀላቀልኩ ብሎ የሚያስቸግረው? ይሄ በየትኛውም የቅልቅል ባህል የሌለ ነው፡፡

ፈረንጅ ለዘር እንኳን በሌለበት የገጠር ከተማ የሚደረግ ሠርግ መጥሪያ አይታችኋል? በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ‘ኮ ነው የሚዘጋጀው፡፡ ታድያ ፈረንጅ ሲጋበዝ ግራ እንዳይገባው መሰላችሁ? ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ቀላል አይደለንም ነው ነገሩ፡፡

አሁን እናንተ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ትጠይቁ ይሆናል፡፡ ሁለቱን ቋንቋዎች በየራሳቸው ለምን አትናገሩም ትሉ ይሆናል፡፡ ሀገርኛውንም በሀገርኛ፣ ውጭኛውንም በውጭኛ፡፡ ችግሩ ይህ ጥያቄ የቤት ልጅ ጥያቄ መሆኑ ነው፡፡ ለነገሩ ጥያቄውን በጥያቄ መመለስ ይሻለኛል፡፡

ሽሮው ላይ ሥጋ ጣል ለምን ይደረጋል? ሙዝ ሻጭ ቅቤ አብሮ አይሰጥም፣ ቅቤ ሻጭ ግን ለምን ሙዝ ይቀላቅላል? ሸክላ ሻጭ በርበሬ ለምን አብሮ አይሰጥም? እስኪ መልሱልኝ?

ሽሮው እንደ ልብ ይገኛል፡፡ ሙዙንም ማግኘት ቀላል ነው፡፡ ሸክላውም ውድ አይደለም፡፡ በርካሹ ላይ ውድ ጣ’ል ይደረጋል እንጂ፣ በውድ ላይ ርካሽ ጣ’ል አይደረግም፡፡ አሁን መልሱ የገባችሁ ይመስለኛል፡፡

እንግሊዝኛው ውድ ሆነብን፡፡ subject + verb + object = sentence እየተባልን ሂሳብ እንጂ ቋንቋ ያልተማርን ሰዎች አሁን ጣ’ል ከማድረግ በላይ

እንግሊዝኛውን ከየት እናምጣው? እኔን ካላመናችሁ እነዚህ እንግሊዝኛን በአማርኛ መካከል እየደነጎሩ መከራ የሚያሳዩዋችሁን ዘመዶቻችሁን እስኪ በእንግሊዝኛ ብቻ ተናገሩ በሏቸው፡፡ መዝገበ ቃላት እያዩ እንኳን አንድ አንቀጽ አያወሯችሁም፡፡

ምን ሩቅ አስኬዳችሁ አወራራቸውን ወይንም በእናንተ ቋንቋ «ፕሮናውንሴናቸውን» አትሰሙልኝም፡፡ ልክ ለእንግሊዝ ፊልም የምንጃር ዜማ «ሳውንድ ትራክ» እንደመጠቀም እኮ ነው፡፡ የሰዎቹ ቃላት እንግሊዝኛ አነጋገሩ አማርኛ ይሆንላችኋል፡፡ ወይንም በቀላሉ በአራዳ ቋንቋ ለመግለጥ ፊልሙ እንግሊዝኛ የማጀቢያ ዜማው አማርኛ ይሏችኋል ይሄ ነው፡፡ ለነገሩ አንዳንዶች ይህ ልምድ ከሕንድ እና ከፓኪስታን የተወሰደ ነው የሚሉ አሉ፡፡

አሁን እኔ አንድ ሃያ የማይሞሉ የእንግሊዝኛ ቃላት አሉኝ፡፡ እነርሱን ሁሉ ለብቻ ከተናገርኳቸውማ ያልቃሉ፡፡ ከዚያ ምን ልሆን ነው፡፡ ያ «ማኑዋል» እያየ አውሮፕላን ሲያበርር የነበረ ጀብደኛ አየር ላይ ሲደርስ “ቀጣዩን በሚቀጥለው መጽሐፍ ይመልከቱ” እንዳለው እኔም ቀጣዩን መቼ ስሙኝ ልል ነው፡፡

ሞኝ አትሁኑ፡፡ ዛሬ አንድ ሦስቷን እንግሊዝኛ ጣ’ል ታደርጋላችሁ፡፡ ነገ ደግሞ አንድ ሦስቷን ጣ’ል እያደረጋችሁ ሊቅ እንደመሰላችሁ መኖር ስትችሉ ምን በእንግሊዝኛ አንጣጣችሁ፡፡ ጎበዝ ጥይት በአንድ ዙር መጨረስ ደግ አይደለም፡፡

አንድ ነገር ረስቼው «መሪጌታ ጉግልን» ታውቋቸዋላችሁ? መሪጌታ ጉግል የኛ ሠፈር ሰው ናቸው፡፡ በኛ አጥቢያ ማታ ማታ ያስተምራሉ፡፡ አልፎ አልፎም በየአዳራሹ ገለጣ ይሰጣሉ፡፡ መሪጌታ ጉግል ብለው ስም ያወጡላቸው አንድ የደብራችን ዜማ ዐዋቂ ናቸው፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው፡፡እኒህ ሰው አንድም ቀን ኢትዮጵያዊ የሆነ መጽሐፍ

ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሊቅ አድንቀው፣ የኢትዮጵያን ታሪክ አሞግሰው አያውቁም፡፡ የዚህ ምክንያታቸው ደግሞ ከኢትዮጵያ ዓይነተኛ መጻሕፍት፣ ከገድል እና ከስንክሳር፣ ከሊቃውንት እና ከምሁራን መጻሕፍት ይልቅ በኮምፒዩተራቸው ጎልጉለው የሚያገኙት ጉግልን ስለሚያምኑት ነው ይባላል፡፡ እና ታድያ የርሳቸው እንግሊዝኛ የጉግል እንግሊዝኛ በመሆኑ አንበውት እንጂ ሰምተውት አያውቁምና ሲናገሩት ስትሰሙ የማታውቁትን ግእዝ የጠቀሱ እንጂ እንግሊዝኛ ያወሩ አይመስላችሁም፡፡

እንግሊዝኛን ጣ’ል ማድረግ ለኤፍ ኤም ሬድዮ እና ለባለሥልጣን ብቻ ማንሰጠው ብለዋል መሪጌታ ጉግል፡፡ እናም በስብከታቸው ሳይቀር ከግእዝ ይልቅ እንግሊዝኛ ጣ’ል ያደርጉልናል፡፡ እኛም በሊቅነታቸው ተደንቀን አንገታችንን እንነቀንቃለን፡፡ አንዳንድ ሰዎች እንዲያውም ወደፊት በዚሁ ከተጉ በቅዳሴው ውስጥም እንግሊዝኛ ጣ’ል ሊያደርጉልን እንደሚችሉ በተስፋ እየጠበቋቸው ነው፡፡

መሪጌታ ጉግል እንደ ጉግል የሚያምኑት እና የሚወዱት የለም፡፡ አንድ ጥያቄ ሲጠየቁ «እስኪ ኮምፒዩተሬ ላይ አይቼ እነግራችኋለሁ» ይሉናል፡፡ እርሳቸው ኮምፒዩተር ላይ የሌለ ነገር ሁሉ በዓለም ላይ እንደሌለ ይቆጥሩታል፡፡ እንዲያውም ከሀገራቸው ይልቅ ውጭውን የሚናፍቁ፣ ከሀገርኛ ሊቃውንት ይልቅ የውጭዎቹን የሚያደንቁ፣ ኢትዮጵያን በውጩ መሣርያ ሊያርሟት የሚፈልጉ አያሌ ደቀ መዛሙርት አውጥተዋል መሪጌታ ጉግል፡፡

እና ጣ’ል ማድረግ እንኳን በኛ በዓለማውያኑ በነ መሪጌታ ጉግልም እየተለመደ ስለሆነ እኛን ለቀቅ ብታደርጉን፡፡ 30 ሺ ወገኖቻችን ካለቁበት የሰማዕታት 75ኛ ዓመት በዓል ይልቅ የቫለንታይን በዓል በሚደምቅበት ሀገር ተቀምጣችሁ እንግሊዝኛ ጣ’ል አታድርጉ ማለት ነውር ነው፡፡

Page 26: Addis Guday(1)

30 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ዐቢይ ጉዳይ

ዘውዳዊው ሥርዓት በወ ታደራዊው ቡድን ሥልጣኑን ሲቀማ የራሱ የወታራዊው ቡደን አባላትን ጨምሮ ብዙዎች የተመኙት ሀገር

የምትለማ፣ ሠላምና ዲሞክራሲ የሚሰፍን፣ ህዝቦችም በእኩል የጋራ መብት የሚኖሩባት ሀገር የምትመጣ አድርገው ነበር፡፡ የደርግ መንግሥት ተመስርቶ ሀገሪቱ ከቀዳሚው ሥርዓት መሠረታዊ ሊባል በሚችል የለውጥ ሥርዓት ውስጥ ስትገባ ግን ገና ከጥንስሱ የአዲሱ መንግሥት አመራርን ያልተቀበሉና ከመስከረም 1967 ዓ.ም ወዲህ ያለው መጪ አዝማሚያ ያላማራቸው፤ እንዲሁም የህዝቡ የዓመታት ጥያቄ በወታደራዊ ቡድን (ጁንታ) ሥር ተጠቃሎ መግባቱን የተረዱ ኃይሎች እያደገ ከሄደ አነስተኛ ተቃውሞ እስከ ነፍጥ ማንሳት፣ ከዱር እስከ መሃል ሀገር በመደራጀት ቀዳሚውን የደርግ መንግሥትም ሆነ የኋለኛውን የኢሠፓ መንግሥት ታግለዋል፡፡ ከአሲምባ የተነሳው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) 1968/69 የደርግ መንግሥትን በከተማ ትግል ለመጣል ቃታ ከሳቡ ፓርቲዎች መሃል አንዱ ነው፡፡

የደርግ መንግሥት በመጀመሪያዎቹ ሁለትና ሦስት ዓመታት ከኢህአፓ ጋር ባካሄደው የቀይ እና ነጭ ሽብር ትግል አንድ ትውልድ አልቋል፡፡ ይህንኑ ህዝባዊ አመፅ በኃይል ለማዳፈን ከመንግሥት ይደረግ የነበረው ምላሽ ፖለቲካ ጉዳያቸው ያልሆነ ዜጐች ጭምር ወገን በወገኑ ላይ ሊፈፅመው ይችላል ተብሎ በማይታመን ሁኔታ ተሰቃይተው አሰቃይቶ ሞትን የስቃያቸው መጨረሻ እንዲሆን አድርጓቸዋል፡፡ በዚያ ትግል ዛሬም ድረስ በሕይወት የተረፉና ለበርካታ አካላዊና ስነልቦናዊ ስቃይ ሰለባ የሆኑ ዜጐች፣ ያሏቸውን ልጆች ሁሉ ለሞት የገበሩና ሞትን እየፈለጉ ሳያገኙት ቀርተው ከሞተው በላይ ከቆመው በታች ሆነው የስቃይ ኑሯቸውን እየገፉ ያሉ ወላጆችና ቤተሰቦች አሁንም ከ36/37 ዓመት በኋላ ያልዳነ ጠባሳቸውን እያሻሹ አሉ፡፡

በ1960ዎቹ፣ ከዚያ በፊትና በኋላ ነፍጥ አንስተው ሥርዓቱን ከታገሉ የፖለቲካ ቡድኖች መሃል የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ግንቦት 1983 ዓ.ም የኢሠፓን መንግሥት ጥሎ የመንግሥት ሥልጣኑን ሲጨብጥ የአሸናፊነት መዶሻውን ያነሳው ኢሕአዴግ ይሁን እንጂ ለሥርዓቱ መሸርሸርና ኋላ ላይም መውደቅ ባለድርሻዎቹ ብዙዎች ናቸው፡፡ ኢሕአፓ ከእነዚህ ባለድርሻዎች አንዱ ነው፡፡ የፓርቲው ፖለቲካዊ ትግል በተለያዩ ወገኖች የተለያየ የ“ልክ” እና “ስህተት” አስተያየት ቢነሳበትም በዚያ ትግል በግራና በቀኝ በአንድ ትውልድ የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ልጆች አካላቸውን፣ ህልውናቸውን፣ ሕይወታቸውን ገብረዋል፡፡ የአንድ እናት ልጆች በግራና በቀኝ ነፍጥ አንስተው ለሀገርና ለህዝብ ይበጃል ላሉት ርዕዮተ ዓለም ወግነው ተታኩሰዋል፤ ቆስለዋል፤ ሞተዋል፡፡

ከግንቦት 1983 በኋላ ሀገር ተረጋግቶ ህዝቦችም ከነበሩበት የጦር አውድ አረፍ ብለው መረጋጋት ሲጀምሩ በ17ቱ የትግል ዓመታት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ላደረጉት

አስተዋፅኦ በተለያዩ ክልሎች የሰማዕታት ሀውልት ሲቆምላቸው በ1969/70 በቀይ ሽብር ለተሰዉ ሰማዕታት የሚሆን መታሰቢያ ደግሞ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ የመታሰቢያ ሙዚየም ቆሞላቸዋል፡፡

“ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ሲታገሉ በፖለቲካዊ አመለካከትና እምነታቸው ብቻ በደርግ መንግሥት ስለተጨፈጨፉ ሰማዕታት ዜጐቻችን ሁሉ መታሰቢያ እንዲሆን የተቋቋመው ቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም የሰማዕታቱን ቤተሰብ በመወከል በአንድ ሌሊት አራት ልጆቻቸውን በተገደሉባቸው እናት በወ/ሮ ከበቡሽ አድማሱ የካቲት 28/2002 ዓ.ም ተከፈተ” የሚል ጽሑፍ በመግቢያው ላይ የሚያስነብበው ይህ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም በይፋ ተመርቆ ከተከፈተ ሁለት ዓመታት የሆነው ቢሆንም በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ አንደኛው የበደል ዘመን ሲያልፍ ሌላ የበደል አሠራር በሙዚየሙ ዙሪያ መስፈኑን የሚናገሩ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች ቁጥር ብዙ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት እንዲሁም በሼክ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ የተለመደ ድጋፍ ወደ 11 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የተነገረው ይህ ሙዚየም ተገንብቶ ለአገልግሎት ሲበቃ ገና ከጥንስሱ የሙዚየም መገንቢያ ቦታ ከተገኘ በኋላ ግንባታው ለቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ያለ ጨረታ ከመሰጠቱ ጀምሮ በቅድመ ግንባታና በግንባታው ወቅትም ከፍተኛ ብክነቶች መከሰታቸው፣ ብክነቶቹና በደሎቹ የተፈጸሙት ሙዚየሙን እንዲመሩ ኃላፊነት በተሰጣቸው በጣት የሚቆጠሩ ወገኖች እንደሆነ በተለያዩ ጉዳዩ ያገባናል ያሉ ወገኖች አፍና ጆሮ ሲመላለስ የነበረ ሃቅ ነው፡፡

ይኸው ሃቅ ከግል ጉምጉምታ አልፎ የቀይሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር መስከረም 27/2004 በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ከኢ.ፌ.ድ.ሪ የበጐ አድራጐትና ማህበራት ኤጀንሲ ሁለት አባላት በተገኙበት ውይይት ተደርጐ አሉ የተባሉ ችግሮችን አጣርቶ የሚያቀርብ አጣሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ተወስኖ ጥቅምት 3/2004 ኮሚቴው ሊያጣራቸው ስለሚገቡ ጉዳዮች ከቦርዱ በተፃፈ ደብዳቤ አባላቱ ሥራቸውን እንዲጀምሩ ተገልጾላቸዋል፡፡

ይህ ኮሚቴ ሥራውን ለመጀመር መሠረት

የሆኑት ጉልህ ጉዳዮች በሙዚየሙ አጠቃላይ አስተዳደራዊና ፋይናንሳዊ የአሠራር ጉድለቶች መኖራቸው፣ በማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድና በሥራ አስፈፃሚውና በሥራ አስኪያጅዋ መካከል የማህበሩን ህገ-ደንብ የጠበቀ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የተላበሰ የሥራ ግንኙነት አለ መኖሩ፣ በሙዚየሙ ቅድመ ግንባታና አሠራር ምዝበራ ተካሂዷል የሚል አስተያየት መቅረቡ፣ የሠራተኞች ቅጥር የሀገሪቱን ህግና ደንብ ጠብቆ እንደማይፈፀም በመነገሩ፣ ማህበሩ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያስችል ሁኔታ ሊመራ፣ ሊስፋፋና ሊዳብር ሲገባው ይህ ባለመሆኑና ጭራሹን እየተዳከመና የአባላቱም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መምጣቱና ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ጉዳዮችን አጣርቶ ለጠቅላላ ጉባኤው እንዲያቀርብ መታሰቡ ነው፡፡

ይህ ኮሚቴ እንዲመሩ አምስት አባላት ማለትም አቶ ዓለምሸት ተስፋዬ፣ አቶ ኃ/መለኮት መዋዕል፣ አቶ መላኩ ለገሠ፣ ወ/ሮ ሆሳዕና ካሣሁንና ወ/ሪት ይርጋዓለም መንግ ሥቱ በጠቅላላ ጉባዔው ተመርጠው ጥቅምት 9/2004 ኮሚቴው በሙዚየሙ አዳራሽ ባካሄደው የመጀመሪያው ስብሰባ ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡ በሙዚየሙ እና ማህበሩ ዙሪያ የተካሄደው የማጣራት ሥራ የጽ/ቤቱን የገቢና ወጭ ደብዳቤዎችንና መዛግብትን፣ የሥራ አመራር ቦርዱን ቃለ ጉባዔዎች፣ የውጭ ኦዲተሮችን የሂሳብ ምርመራ ውጤቶች፣ ልዩ ልዩ ጥቆማዎችን፣ ሃያ ግለሰቦችን ቃለ መጠይቅ በማድረግና የ14 ሰዎችን አቤቱታና ጥቆማ በመቀበል እንዲሁም ከፋብሪካዎች የተገኙ ማስረጃዎችንም እንደተመለከቱ በመጥቀስ እሁድ የካቲት 11/2004 በሰማዕታቱ መታሰቢያ ሙዚየም ለጠቅላላ ጉባዔው ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከአምስቱ የኮሚቴው አባላት አቶ ዓለምሸት ተስፋዬ ከሦስት ስብሰባ በኋላ የተቀሩት አባላት ባላወቁት ምክንያት ሥራቸውን ቢያቆሙም በተቀሩት አባላት የማጣራት ሂደቱ ተከናውኖ ለሦስት ወራት የተሰጠው ሥራ አራት ወር ተኩል ፈጅቶ ሊቀርብ በቅቷል፡፡ ከ1996 እስከ መስከረም 2004 ከተያዙት ሰነዶች ውስጥ 288 ገጽ ያላቸው ቃለጉባዔዎችን፣ ከ20 ሰዎች የቀረቡ 85 ገጽ ያላቸው ቃለመጠይቆችን እና ልዩ ልዩ ሰነዶችን ያገላበጡበት ፍተሻ የሚያስረዳው

በማያጠራጥር ሁኔታ በሙዚየሙና ማህበሩ ዙሪያ ጥቅመኝነትና የአስተዳደር በደል አለመፈፀሙን የሚያስተባብል ሆኖ አልተገኘም፡፡ በዚያ ፈንታ አጣሪ ኮሚቴውና የጠቅላላ ጉባዔው አባላት (በሙሉ ማለት ይቻላል) በጥርጣሬ የተጠቀሱት በደሎች መፈፀማቸውን ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በዚህ የተነሳም አስተዳደራዊና ጥቅማዊ በደል አድርሰዋል፣ ህይወታቸውን ለህዝባዊ ዓላማ የሰጡ ሰማዕታት ቤተሰቦች በችግር እየተቆራመዱ ከሥራ አስፈፃሚው ጥቂት አባላት ጋር ባላቸው ግልፅ ያልሆነ ግንኙነት ሌሎች እንዲጠቀሙ አድርገዋል፤ ይባስ ብለው ትናንት ሰማዕታቱን ዛሬ በህይወት ያሉትን የትግሉ አባላት ሲገርፉና ሲያሰቃዩ አልፎ ተርፎም ሲያስገድሉ የነበሩ የመኢሶንና ኢሠፓ አባላት የበግ ለምድ ለብሰው የሥራ አስፈፃሚው አባል እንዲሆኑ በር ከፍተዋል ያሏቸውን በሙሉ ድምፅ ከኃላፊነታቸው አንስተዋቸዋል፡፡

እንደ አጣሪው ሪፖርት የሀገሪቱን ሕግ መሠረት ያደረገ ሠራተኛን የመቅጠር፣ የማረምና የማሰናበት አሠራር በማህበሩ ውስጥ አልነበረም፡፡ አግባብነት በሌለው የጓደኝነት ጥቆማ እና ምደባ ብቻ ቅጥር እንደሚፈፀም በመግለጽ በማህበሩ ውስጥ አራት ሠራተኞች ብቻ ጋዜጣ ላይ በወጣ ማስታወቂያ ሲቀጠሩ ምንም እንኳ የተለየ የሙያዊ ስልጠና የሚጠይቁ ባይሆኑም 27 ሠራተኞች ያለ አንዳች ወድድርና ማስታወቂያ መቀጠራቸው ተመልክቷል፡፡ በዚህ ረገድ አሁን ሙዚየሙን በሥራ አስኪያጅነት የሚመሩት ወ/ሮ እመቤት ከበደ የሙዚየሙ ሥራ አስፈፃሚ በነበሩት በወ/ሮ ዓይኔ ጽጌ አማካኝነት መጥተው እንደተቀጠሩ ቀጣሪም ተቀጣሪም ተጠይቀው በተፈረመ ቃል ጉባዔ መረጋገጡን ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

ሙዚየሙ ገና ከቁፋሮ ሥራ ጀምሮ በርካታ ምዝበራ እንደተካሄደበት የሚገልፀው ሪፖርት ላይ እንደሚታየው የሙዚየሙ ቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በቦታው ላይ የነበረው 31 መኪና ቀይ አሸዋ በስመ ተወጋጅነት እንደተሸጠና ገንዘቡ ገቢ እንዳልተደረገ፣ በዚሁ ቦታ የተገኘው በብዙ ኩንታል የሚገመት የግንባታ ፌሮ ብረት ከቦርዱ እውቅና እና ውሳኔ ውጭ በብር 78,000.00 (ሰባ ስምንት ሺህ) ተሸጦ ገቢ የተደረገው ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) እንደሆነ፣ በብር 70-80 ሺህ ብር ሊገዛ የሚገባው ባለ 1 ጋቢና ያገለገለ መኪናም በኮሚቴ

“ሁለተኛው ቀይ ሽብር ተፋፋመብን” ከሠማዕታቱ ቤተሰቦች አንዱ

Page 27: Addis Guday(1)

31 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

እንዲገዛ ከተወሰነ በኋላ አንድን አባል ከኮሚቴው በማስወጣት በብር 150,00.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) መገዛቱ ተመልክቷል፡፡

አጣሪ ኮሚቴው በሙዚየሙ ዙሪያ ከመረመራቸው ሰነዶች አንዱ የውጭ ኦዲተሮች የምርምር ውጤት ነው፡፡ በውጭ ኦዲተሮች የምርመራ ውጤት መሠረት የ1996 ዓ.ም የማህበሩ ሂሳብ አለመመርመሩ፣ የ1997 ዓ.ም የማህበሩ ገቢ በጥቅል ከመቀመጡ በስተቀር ስለሂሳቡ ዝርዝር ፍሰት የተሰጠ በቂ የሙያ ማብራሪያ አለመኖሩ፣ በ1998 ዓ.ም የወርሃዊ ሂሳብ ማስታወቂያ አለመሥራቱ፣ አንዳንድ ክፍያዎች ያለበቂ የሰነድ ማስረጃ እና ከሥልጣን እርከን በላይ በሆነ መልኩ ክፍያ መፈፀም፣ በወቅቱ የተሰበሰቡ ገንዘቦች በጊዜ ወደ ባንክ ገቢ አለመደረጋቸው፣ ከግንባታ ኮንትራክተሩ ጋር በተደረገው ስምምነት ተቋራጩ የሠራተኛ ጉልበትና ማቴሪያል ሊያቀርብ የተዋዋለ ሲሆን ለሲሚንቶ እና ለትራንስፖርት ብር 128,772.75 ከውል ውጭ ክፍያ መፈፀሙ፣ ውል ሳይደረግና ደረሰኝም ሳይቀርብ ለዋናው ጽ/ቤት ሊፍት (አሳንሰር) ማሰሪያ ብር 8,000.00 አለአግባብ መውጣቱ የኦዲተሮቹን የምርመራ ውጤት ምንጭ አድርገው ጠቅሰዋል፡፡

የካቲት 11/2004 በተጠራው አጠቃላይ ጉባዔ አንድ ተሳታፊ “ሁለተኛው ቀይ ሽብር ተፋፋመብን፣ ደርግ የመጀመሪያውን ቀይ ሽብር አድርጓል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አሁን ተካሄደብን” እንዲሉና ሌሎችም አባባላቸውን ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደረጋቸው የማህበሩ ምዝበራ በዚህ ብቻ ያበቃ አይደለም፡፡ በ2001 የሙዚየሙን ህንፃ የተወሰነ ክፍል ሻማ የመፃሕፍት መሸጫ ድርጅት እንዴትና ከማን ጋር ተወዳድሮ ሊከራይ እንዳልቻለ አለመታወቁ፤ እንዲሁም በቀጣዩ ዓመትም ሠራተኞች የወሰዱት ብድር ሳይወራረድ ተጨማሪ ብር መሰጠቱ፣ ለመንግሥት ገቢ መሆን ያለበት with hold tax ተቀናሽ ተደርጐ ለመንግሥት ሳይገባ መገኘቱ፣ ያለ ዋጋ ማወዳደሪያ (ፕሮፎርማ) ግዢ መፈፀሙ፣ ከለጋሾች የተገኘው ብር 112,258.82 ትክክለኛ የገቢ ደረሰኝ ሳይቆረጥለት መገኘቱ፣ ከካፌና ምግብ ቤት ኪራይ ገቢ ሊደረግ ከሚገባው ውስጥ ብር 39,950.20 ገቢ አለመሆኑ፣ ከለጋሾች የተገኘው ብር 112,258.62 ትክክለኛ የገቢ ደረሰኝ ሳይቆረጥለት መቅረቱና ሌሎች ከቀረቡ ሰነዶች ላይ ተሞልቶ የተሰበሰበው የማጣራት ሥራ ሙዚየሙና ማህበሩ በሰፋ ችግር እና በተወሳሰበ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አመላካች ነው፡፡ በዕለቱ በቀረበው ሪፖርት ላይ በሰማዕታቱ ስም ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ከመዚየሙ ግንባታ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ብዛት ያለው ኩንታል ሲሚንቶ ለግል ጥቅም መዋሉ ተመልክቷል፡፡ ምንም እንኳን ለሙዚየሙ ግንባታ ሲሚንቶ ገዝቶ ማቅረብ የተቋራጩ ቫርኔሮ ኮንስትራክሽን ሃላፊነት ቢሆንም በሰኔ ወር 2000 ዓ.ም በነበረው የሲሚንቶ እጥረት ሳቢያ ተቋራጩ በማህበሩ በኩል እንዲቀርብለትና የገዛበትን ገንዘብም ለማህበሩ እንደሚተካ በቁጥር 032/08/ በ10/6/08 በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል፡፡ ይሁንና የሰማዕታቱን አደራ እና ማህበሩን የግል መጠቀሚያው ላደረገው አመራር ይህ ሁኔታ የራስ ጥቅምን ለማዳበር የተሻለ ሁኔታን እንደፈጠረለት ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡

በቫርኔሮ ጥያቄ መሠረት ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ ከጉና የንግድ ሥራዎች፣ ከአምባሰል ን/ሥ/ድርጅት እና ከናሽናል ሲሚንቶ አ/ማህበር በድምሩ ከተገዛው 4,950 ኩንታል ሲሚንቶ መካከል 2,500 ኩንታል ሲሚንቶ የት እንደገባ አልታወቀም፡፡ ይኸው ሲሚንቶ የሙዚየሙ የወቅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ፍቅሩ በጥቁር ገበያ ይሸጥበታል ብለው በገለፁበት ደብዳቤ ላይ ባለው ዋጋ ብር 303.25 ሲባዛ ብር 758,125.00 /ሰባት መቶ ሃምሳ

ስምንት ሺህ አንድ መቶ ሃያ አምስት/ ምናልባትም ወዳልታወቀው ዋሻ ሳይገባ እንዳልቀረ ይገመታል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በዚሁ የመግዛትና የመተካት አሠራር ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ተገዝቶ ቀርቦ ለቫርኔሮ የተሰጠና ተቋራጩ ክፍያውን ፈፅሞ ገንዘቡ ግን ለማህበሩ ሳይተካ የቀረው 250 ኩንታል ስሚንቶ ብር 38,750.25 ሲደመርበት የት እንደገባ ያልታወቀውን ብር መጠን ወደ 796,875.25 ያደርሰዋል፡፡ አጣሪ ኮሜቴው አድራሻው ካልታወቀው ስሚንቶ ጋር በተያያዘ በወቅቱ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ የነበሩትን አቶ ዳንኤል ፍቅሩ ህግ በሚፈቅደው መሠረት እንዲጠየቁና ሁኔታውም እንዲጣራ ጠይቋል፡፡

አንዲት የጉባዔው ተሳታፊ ስለማህበሩ ሥራ አመራር አባል ወ/ሮ ዓይኔ ጽጌ ሲገልጹ በዘመነ ቀይሽብር ወንድማቸውን በትግሉ ቢያጡም እሳቸው ተቃራኒ ቡድን የነበረውን መኢሶንን ሲያደራጁ የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይ ምርጫ የተሰራጮች ማንነት በአግባቡ ተጠንቶ ሊመረጥ እንደሚገባ በአፅንኦት ጠይቀዋል፡፡

በቀይሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም በር ላይ ለጋሾች ለሰማዕታቱ ያላቸውን ክብር የሚገልፅበትና ማህበሩ በገንዘብ እንዳይደክም ሊያግዙ የሚችሉበት የልገሳ ማጠራቀሚያ ሳጥን አለ፡፡ በዚህ ሳጥን ውስጥም ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ለጉብኝት ከሚመጡት ቱሪስቶች ዶላር፣ ፓውንድ፣ ዩሮ፣ዶች ማርክና ሌሎች የዓለም ሀገራት ገንዘቦች በልግስና ይሰጣሉ፡፡ በአንድ ህጋዊ እውቅና ባለው ማህበርም ሆነ ህግ እንዲከበር በሚፈልግ የትኛውም ዜጋ አሰራር የውጭ ሀገር ገንዘብ ሊመነዘር የሚገባው ባንክ ሲሆን በግለሰብ ፍላጎት ብቻ በሚፈፀም አሠራር በጥቁር ገበያ (Black market) ተመንዝሮ ገቢ እንዲሆንና ይህን አሠራርም አጣሪ ኮሚቴው ሥራ አመራሩንና ቦርዱን ጠይቆ ሁለቱም አካላት ጉዳዩን እንደሚያውቁ እንደገለጹለት በሪፓርቱ ላይ አስፍሮት ይገኛል፡፡ በሪፖርቱም ላይ እንደታየውም ሆነ ከሌሎቹ ማህበሩን ባለቤት የለሽ በሚያስመስሉት አሠራሮች እነዚህ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ህግ ተጥሶ በጥቁር ገበያ የተመነዘሩት የማህበሩ ገቢ ከፍ እንዲል ታስቦ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡

የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ከሚያነሳቸው ጉዳዩች አንዱ መመሪያዎች እየተጣሱ በህግና ደንብ ሳይሆን ለግለሰቦች ፍላጎት መከበር እንደሚውሉ ነው፡፡ ማህበሩን እንዲመራ የተቋቋመ ቦርድ ቢኖረውም በሥራ አስፈፃሚው እና በአንዳንድ የቦርድ አባላት ተፅዕኖ ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ሥልጣን የአመራር ቦርዱ ይሁን የሥራ አስፈፃሚው በውል እንደማይታወቅ በመግለጽ በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ሥራ አስፈፃሚ የሚባል አካል እንደሌለ አትቷል፡፡ በእስካሁኑ አሠራር ከደንቡ ውጭ ሥራ አስፈፃሚው በቦርዱ

ውስጥ ተካቶ የሚሰበሰብ ሲሆን ይህም የቦርድ አባላት ለማህበሩ በሚጠቅም ብቻ ሳይሆን ከግለሰቦች ማንነት አንፃር አስተያየት እንዲሰጡና ውሳኔ እንዲያስተላልፉ እንዳደርጋቸው ያሳያል፡፡ ሪፖርቱ በማህበሩ ቦርድ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተሸፋፋነው ሰርገው ስለገቡ ግለሰቦች በገለፁበት ክፍል “የትናንት ገዳይና አስገዳዮቻችን— ገራፊና አስገራፊዎቻችን— የጅምላ ጭፍጨፋው የፋሺሽታዊ ደርግ የፖለቲካ አባላት የነበሩ የመኢሶንና የኢሠፓ እንዲሁም የመሰል የፖለቲካ ቡድን አባላት በግለሰብ ፍቃድና ጋባዥነት የአመራሩ ቦርድ አባል እንዲሆኑ መደረጉ አግባብነት የለውም” ብሎ ያምናል፡፡

አጣሪው “ቦርዱ የለየለት የይስሙላ ቦርድ ነበር” ካለ በኋላም የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ስለሆኑት ወ/ሮ ዓይኔ ጽጌ ሲገልጽም “ወ/ሮ ዓይኔ ጽጌ የሥራ አስፈፃሚ አባል ቢሆኑም ምን ጊዜም በቦርድ ስብስባ ላይ ይሳተፉ ነበር፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግ ላቀረብንላቸው ጥያቄ በጹሑፍ ሰፍሮ በፊርማቸው ባረጋገጡልን መሠረት ኢህአዴግን አምጥተሻል፣ መኢሶንን አምጥተሻል፣ ኢሕአፓን አምጥተሻል ብትሉኝም ማን ምን እንደሆነ ባላውቅም በራሳቸው ፍላጎት ይመጣሉ በራሳቸው ፍላጎት ይወጣሉ” እንዳሉት ከገለፀ በኋላ “በሙዚየሙ ውስጥ የታዩ ጉድለቶችና የተፈፀሙ ስህተቶችን ሁሉ እንደማያውቁና እሳቸውንም በፍጹም እንደማይመለከት ገልፀዋል” ይላል ሪፖርቱ፡፡ ሪፖርቱ ይህንን ገልጾ ብቻ ሳያበቃ “ስለሆነም ጉባኤው የመረጣቸው አመራሮች የተጣለባቸውን ታሪካዊ እምነትና አደራ መወጣት ስላልቻሉ ይህ ጉባኤ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መልሶ የመውሰድና የመሻር ሙሉ መብትና ሥልጣን አለው፡፡ ይህ እንዴትና መቼ ተግባራዊ መሆን እንዳለበት ጠቅላላ ጉባኤው ያውቃል የሚል እምነት አለን” በማለት ጠቅሷል፡፡

በሪፖርቱ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት አጣሪ ኮሚቴው ባቀረበውና ጠቅላላ ጉባዔው በተስማማው መሠረት የጉባዔው አካሄድ ፈሩን እንዳይስትና ህጋዊ አሠራርን እንዲከተል ለማድረግ መድረኩን በተባባሪነት የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተወካይ አቶ ልዑል የኋላ የመሩ ሲሆን ከውይይቶቹ በኋላም “ቀጣዮቹን የቦርድ አባላት ለማስመረጥ አስመራጭ አባላትን ከመጠቆማችን በፊት የቀረበው ሪፖርት ሪፖርታችን ነው ብሎ ጉባዔው በድምፅ ማፅደቅ ወይም መቃወም ይኖርበታል” ባሉት መሠረት መላው የጉባዔ አባላት ያለምንም ተቃውሞ በጭብጨባ መቀበላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ልዑል የኋላም ተቃውሞን በተመለከተ ’የሚታይ እጅ— የሚደመጥ ድምጽም የለም’ በማለት ጉባዔው ሪፖርቱን እንደራሱ ሪፖርት በሙሉ ድምፅ እንደተቀበለው አረጋግጠዋል፡፡

በጉባኤው የአጣሪ ኮሚቴውን ሪፖርት የማዳመጥና ማፅደቅ፣ የቀድሞውን ሥራ አስፈፃሚ እና ቦርድ የመሻርና አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ የመሾም ሂደት ላይ በርካታ የበደል ድምፆች ተደምጠዋል፡፡ “አንድ ግለሰብ እንዲህ ያለውን ብልሹ ሥራ ሲሰራ ዝም ብሎ የተመለከተው ቦርድም ሆነ ሥራ አስፈፃሚ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል” የሚለውን እና “ለዚህ ማህበር ገና ከጥንስሱ ሲደክሙ ከነበሩት አባላት መሀል ሁለቱ ያለ አግባብ በሥራ አስፈፃሚዋ የተባረሩ የሰማዕታት ቤተሰቦች እስካሁን በአስማት ይሁን በምን ባልታወቀ ሁኔታ ቤተሰቦቻቸውን ያኖሩት በቂ ሆኖ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ” የመሳሰሉት አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡

የጉባኤው አባት ችግሮቻቸውን አውርተውና በዳዮ ቻቸውን ኮንነው ብቻ አልተለያዩም፡፡ የበጎ አድራጎትና ማህበራት አጀንሲ ተወካዮችን በተለይም በእለቱ በተባባሪነት የተወሰነውን ፕሮግራም የመሩት አቶ ልዑል የኋላን፤ እንዲሁም “ሙስናን ይጠየፋል፣ የመጀመሪያው ሥራው ያደረገው በቀይሽብር የገደሉንን ወንጀለኞች ከያሉበት እያደነ ለህግ እንዲቀርቡ ያደረገ፣ ከውሻ ባነሰ አቀባበር አፅማቸው የትም የተጣለ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን በክብር እንዲቀበሩ ያደረገ፣ ከሊዝ ነፃ በሆነ መልኩ ይህን ያለንበትን ቦታ የሰጠን መንግስታችን ነው” ያሉትን የኤፌዲሪ መንግሥትን አመስግነዋል፡፡

የካቲት 11/2004 በተጠራው በዚህ ጠቅላላ ጉባዔ ቀደም ሲል በአባልነት ተመዝግበው የነበሩና በዕለቱ የተገኙት ሰባት ግለሰቦች በአዳራሹ እንዲገኙ ቢፈቀ ድላቸውም ጉባዔው አባላትን የማፅደቂያ ጉባዔ ስላልነበረ ሀሳብና አስተያየት እንዲሁም ድምፅ እንዲሰጡ አልተፈቀደላቸውም፡፡ በጉባዔው መጨረሻ ላይ የአመራር ኮሚቴ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ 7 አባላት ያሉት የአመራር ቦርድ፣ 3 የጉባኤ መሪዎች እንዲሁም የኦዲተር ምርጫ ተደርጎ ጉባኤው ተጠናቋል፡፡ ይኸው ቃለ ጉባኤ እና የአዳዲሶቹ ተመራጭ የቦርድ አባላትን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለበጎ አድራጎት ማህበራት ኤጀንሲ እና ለፍትህ ሚኒስቴር ሊላክ እንደተዘጋጀ ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

...በዚሁ የመግዛትና የመተካት አሠራር ከሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ተገዝቶ ቀርቦ ለቫርኔሮ የተሰጠና

ተቋራጩ ክፍያውን ፈፅሞ ገንዘቡ ግን ለማህበሩ ሳይተካ የቀረው 250 ኩንታል ስሚንቶ ብር 38,750.25

ሲደመርበት የት እንደገባ ያልታወቀውን ብር መጠን ወደ

796,875.25 ያደርሰዋል...

Page 28: Addis Guday(1)

32 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ያፍሪካ ነጂዎች ማለቴ መሪዎች፣ ለማይወዱትና ለማይወዳቸው ሕዝባቸው ሲሉ አዲስ አበባ ውስጥ ጉባኤ ባደረጉ ቀን፣ እኔ ቴሌቪዥን እያየሁ ነበር፡፡

መሪዎቹ ዱላ ቀረሽ ሙግት ያመጣሉ ብዬ ስጠብቅ እያንጐላጁና እየተኙ አዲሱን የጉባኤ አዳራሽ የጅምላ አልቤርጎ አስመሰሉት፡፡ ካሜራው የዝምባብዌ ፕሬዝዳንት ላይ ሲያነጣጥር ሙጋቤ፣ ሠርግ ያደሩ ይመስል ጠረጴዛው ላይ ተደፍተው ያንኮራፋሉ፡፡ ለነገሩ ማን የቀረ አለ? የሴኔጋሉ ተኝተዋል፤ የኬንያው ተኝተዋል፤ የሶማልያው ተኝተዋል፤ የኢትዮጵያዊ መሪ ግን ተኝተው አልታዩም፡፡ ምናልባት እሳቸው በተኙበት ሰዓት የካሜራ ባለሙያው ራሱ ተኝቶ ይሆናል፡፡ ነገሩ እንዲህ የሚቀጥል ከሆነ በመሪዎች ጠረጴዛ ላይ አምቦውሃና ብርጭቆ ብቻ ሳይሆን የታጠፈ ብርድልብስም ቢቀመጥላቸው ጥሩ ነው፡፡እኔ ራሴ ከመተኛቴ በፊት ከቤት ወጣሁ፡፡ የኮንደ

ሚንየማችን ሁለት ዘቦች በሞባይላቸው ውስጥ ካርድ ለመዶል እየሞከሩ እያቃታቸው “ገባልህ? ገባልህ?” ይባባሉ፡፡ ድሮ አንድ ፍሬ ልጅ እያለሁ ያየሁት ትዕይንት መጣብኝ፡፡ ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ከቤት ስወጣ ደጅ ላይ አያቴና አብሮ ዘማች ጓደኛው በመርፌ ቀዳዳ ክር ለማሾለክ እየሞከሩ “ገባልህ፣ ገባልህ?” ሲባባሉ አይቻቸው አልፋለሁ፡፡ ታዲያ ማታ ወደ ቤቴ ስመለስ በረንዳ ላይ የተቀመጠው አያቴ “አቸቸቸቸ ለትንሽ ሳትሁት!” ሲል አልፌው ወደ ቤት እገባለሁ፡፡ የዘመኑን ቴሌ ካያቴ መርፌ በላይ ምን ሊገልፀው ይችላል?!ከኮንደሚኒየማችን ወረድ ብዬ፣ ቀምቃሚዎች ከሞ

ቅታ በኋላ፣ “ጣቢያ ጠጅ ቤት” ብለው የሚያነቡትን “ጦቢያ ጠጅ” ቤትን ወደ ጐን ጥዬ፣ “እርሾ ክሊኒክ” በር ላይ የተገተረውን ማለቂያ አልባ ሠልፍ ጥሼ እሻገራለሁ፡፡ እርሾ ክሊኒክ በር ላይ የተገጠገጠውን ሠልፍ የተመለከተ ሰው ጤና እንደ ራሽን የሚታደል ይመስለዋል፡፡ ወደ አረብ አገር የሚሄዱ ምልምል ስደተኞች ልብ እና ኩላሊታቸውን እያስመረመሩ ነው፡፡ እዚህም እዚያም የሚታየው ተሻግሮ የሚሄድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ባገር ማን ቀረ?? ድሮኮ ወደ ውጭ አገር መሄድ በጣም ብርቅ ነበር፡፡ ብርቅ ከመሆኑ የተነሣ ብላታ ጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ የተባሉ ፀሐፊ “ውጭ አገር ሄጄ ነበር” የተባለ፣ ዜናም ጉራም የሚመስል መጽሐፍ አሳትመው ነበር፡፡ከአክሱም ሆቴል ፊትለፊት ያለውን አስፋልት

ለማቋረጥ ሳመነታ የቢሾፍቱ አንበሣ አውቶብስ በመርፌ ቁልፍ የተያያዘ የሚመስለውን ፉርጐውን እየጎተተ መጥቶ አጠቤ ቆመ፡፡ አውቶብሱ ውስጥ እንደታይታኒክ ሰማጮች ከሚተራመሱት ብዙ ፊቶች መካከል አንድ የማውቀው ፊት በመስኮቱ ብቅ አለና “በውቄ ምነው ወፈርህ! መጽሐፍ ከማሳተምህ በፊት አትበላም ነበርን’ዴ?” ብሎ ጮኸ፡፡ እጅግ ተናድጄ፣ የመልስ ምት ልሰጠው ስሰናዳ፣ አውቶብሱ አካባቢውን በወፍራም ጢስ የጠላ ቂጣ የተጋገረበት ማድ ቤት አስመስሎት ወደ ፊት ተሳበ፡፡ “ሄይ! ፈጠን ብለህ ተሻገር!” የሚል ድምጽ ከጐኔ

ሰማሁ፡፡ ዞር ስል ተንቀሳቃሽ የጦር መሣሪያ መደብር

ሐራምቤ ሐራምቤየተሸከመ የሚመስል ቡራቡሬ መለዮ ለባሽ ወታደር በክፉ ዓይኑ ይገለምጠኛል፡፡ እኔ ለወትሮው አስፋልት ሳቋርጥ ጅንን ብዬ፣ ሁለት እጆቼን በኪሴ ሸጐጬ፣ ለነፍሴ እንደማልሳሳ ላላፊ አግዳሚው እያሳየሁ ነው፡፡ አሁን ታዲያ የወትሮውን ለመድገም ስሞክር “ሮጠህ አትሻገርም ወይ?” አለ ወታደሩ “መጣሁልህ!” በሚል ዓይነት መሬቱን በከባድ መጫሚያው እየደቃ፡፡ ይኸኔ መሮጡም እንዳይቀር መጀነኑም እንዳይቀር እጄን በኪሴ ከትቼ ሮጥሁ፡፡በጣም ከመደናገሬ የተነሣ የቆመ ምኒባስ ጋቢና

ውስጥ ገብቼ ተደበቅሁ፡፡ ምኒባሱ ጉልበት ለጉልበት ትከሻ ለትከሻ በተቆላለፉ ተሳፋሪዎች ክፉኛ ተሞልቶ የጥንት የባርያ ንግድ መርከብ መስሏል፡፡“ተጠጋጉ! ተጠጋጉ!” ይላል ወያላው፡፡“ተጠጋግተናል!” አለ በሰው ኩሬ ውስጥ የሰመጠ

አንድ ተሳፋሪ፡፡“ተጠጋጋችሁ?”“አዎ!”“ጥሩ! አሁን ደሞ ተቃቀፉ!”ምኒባሱ የቆመበት ቦታ በጣም ይጠነባል፡፡“ሾፌር! የሕዝብ ሽንት ቤት በር ላይ መሰለኝ

ያቆምከን፡፡ ትንሽ ፈቀቅ ልትል ትችላለህ!” አለች አንዲት ሴትዮ፡፡ትሁቱ ሾፌር ትንሽ ወደ ፊት ፈቀቅ አለ፤ ግን

ሽታው አልጠፋም፡፡“ጀለሴ! ሽንት ቤቱን ከኋላ ጫንከው እንዴ?” የሚል

ድምጽ ተከተለ፡፡ አይ አዲስ አበባ! አዲስ አበባ ከምድር ወገብ ከፍ ብላ በምድር ብብት ላይ የተመሠረተች ከተማ ናት፡፡ በምኒባሱ የጋቢና መስታወት በኩል ወደ ውጭ ማየት ጀመርሁ፡፡ ቡራቡሬ ለባሽ ፌደራል ፖሊሶች እንደ አዲስ ትክል ሃውልት እዚም እዚያም ተገትረው ይታያሉ፡፡ እውነት ለመናገር ፖሊሶቹ ኢትዮጵያዊ ሁኖ የተወለደን ሁሉ በሚያኮራ መን ገድ ዙሪያ ገባውን በተጠንቀቅ ይጠብቃሉ፡፡ ያም ሆኖ፣ የመረብ ሱሪ የለበሱ ያዲስ አበባ ቆንጆዎች ባጠገባቸው ሲያልፉ ከዳበሳ በማይተናነስ ትኩረት ይሾፋሉ፡፡ በተለይ አንዱ ወታደር ጠመንጃውን እንደ ቆላ ከዘራ ተመረኩዞ በአልፎ ሂያጅ ቆንጃጅትን ተግቶ ከማየቱ የተነሳ ለጠለፋ እንጂ ለጥበቃ የተሠማራ አይመስልም፡፡ በርግጥ እኔም በኑሮዬ ጣልቃ ሴት አያለሁ፡፡ እንደዚህ ወታደር አልመዝምዤ ያየሁበት ቀን ግን ትዝ አይለኝም፡፡ ዘመዶቼ!! የዚህ ወታደር አስተያየትኮ ካድናቆት አልፎ የመስክ ጥናት የሚሉት ዓይነት ነው፤ “አቤት! አቤት! እኛ ወደ ካምፕ ከገባን በኋላ ደሞ እንዴት እንዴት ያሉት ተወልደዋል?” እያለ የሚተክዝ ይመስላል፡፡ አንዳንዱ ፌደራል ፖሊስ፣ ጥበቃ ሲሰለቸው በሬዲዮ መገናኛው መልዕክት የሚ ቀበል መስሎ ሸገር ሬዲዮ ያዳምጣል፡፡ አልፎ አልፎም በወኪቶኪው ደውሎ ዘፈን ይመርጣል፡፡ድንገት አካባቢው በማስጠንቀቂያ ነጋሪት ድበልቅልቁ

ወጣ፡፡ ከታንክ በስተቀር በብዙ የጦር መኪና የታጀበ ሊይመዚን አለፈ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆን አለ ባቸው፡፡ቀጥሎ፣ ባራት ሞተረኛ የታጀበ መኪና አለፈ፡፡

ሌሎቹ ያፍሪካ መሪዎች ይመስሉኛል፡፡ በመጨረሻ

ማንም ያላጀበው ቮልስ አለፈ፡፡ በዚህ ውስጥ ያለው የኤርትራው ልዑክ መሆን አለበት፡፡ይህንን ግምቴን አጠገቤ ላለው ሾፌር ሳጫውተው

“ሆሆ ወንድሜ ልኑርበት!” በሚል አስተያየት ገላ መጠኝ፡፡ አይ ቡካት! በየቦታው የሚቦካው ሰው መብዛቱ፡፡ ምን ነካን! ኧረ ምን ነካን! በቀደም ዕለት ማታ አዝማሪ ቤት ገባሁና “ተቀበል!” አልሁት አንዱን ባለማሲንቆ፡፡ባለማሲንቆው ለጥቂት ደቂቃ ትክ ብሎ በጥርጣሬ

ሲመለከተኝ ተቆዬ በኋላ “ከመቀበሌ በፊት ግጥሙ በምን ዙሪያ ያጠነጥናል?” ብሎኝ አረፈ፡፡አዝማሪ በደጃች ውቤ ዘመን መቅረቱ ያስቆጫል፡፡

ያኔ፣ አዝማሪ የሕዝቡን ቁጭት አውጥቶ ያንጐ ራጉራል፡፡ ሕዝቡም በአዝማሪው ግንባር ላይ፣ አሞሌ ጨው በመከስከስ፣ ደስታውን ይገልጣል፡፡ (በጊዜው አንድ አሞሌ ጨው በሁለት ያሜሪካ ዶላር ይመነዘር ነበር፡፡) በጊዜያዊ እገታ ሥር የነበረው ምኒባሳችን መንገዱን

እንዲቀጥል ተፈቀደለት፡፡ አንድ የኢትዮጵያ ባንዲራ ጥለት ያለበትን ያንገት ልብስ የጠመጠመ ፀጉራም ፈረንጅ ገብቶ አጠገቤ ተቀመጠ፡፡ ብዙ ሱቆችን፣ አለፍን፡፡ “…ማንደፍሮ፣ የቤትና የቢሮ እቃዎች መሸጫ፡፡ የሚያከሳ ሻይ ቅጠልም እንሸጣለን!” የሚል መፈክር ያለበትን ሱቅ አለፍን “ኤርታሌ ቡቲክ፣ ኮንደምም እንሸጣለን!” የሚል ማስታወቂያ ያለበትን የሰፈራችን ልብስ መደብር አስታወሰኝ፡፡ አንድ ቀን ጓደኛዬ ምዑዝ ኤርታሌ ቡቲክ ገብቶ “ኮንደም ፈልጌ ነበር” አለ፡፡ ባለ ቡቲኩ፣ በግማሽ ሐሳብ ውስጥ ሆኖ አንድ ፖኬት ኮንደም ለምዑዝ እያቀበለው “ከፈለግህ፣ መጋረጃው ውስጥ ገብተህ ልትለካው ትችላለህ!” አለው፡፡ሜክሲኮ አደባባይ ስንደርስ፣ አንድ ጠብደል እብድ

እርቃኑን ሶምሶማ እየሮጠ በጋቢናው በኩል ብቅ አለ፡፡ ከእፍረቴ የተነሳ መሬት እንደ ጋዳፊ ቱቦ ተከፍታ ብትውጠኝ በወደድሁ፡፡ ፈረንጁ ያገሬን እብድ እንዳያዬው ፀለየሁ፡፡ ወይኔ ሊያዬው ነው! ሊያየው ነው! ሊያየው ነው! ሊያየው ነው! አየው፡፡ What a hell is this (ምን ጉድ ነው?) አለ ፈረንጁ በድንጋጤ ወደ እኔ ዞሮ፡፡ አማኑኤል ሆስፒታል የጠበበው እብድ ነው ብዬ ያገሬን ገፅታ የሚያበላሽ ምላሽ መስጠት አልፈልግሁም፡፡ ስለዚህ እንግሊዝኛዬን እንደምንም ጠጋገንሁና “Well! you know, this is a gentleman from a newly discovered tribe አልሁት፡፡ አስከ ትዬም unlike most of African countries we don’t coerce people to put on clothes it they want to stay naked” ብዬ ተነተንሁለት (ሰውዬው በቅርቡ የተገኘ ጐሣ አባል ነው፡፡ ከብዙዎቹ ያፍሪካ አገሮች በተቃራኒ ሰዎች ልብስ እንዲለብሱ አናስገድዳቸውም ማለቴ ነው፡፡) ፈረንጁ ትንታኔዬ ስላረካው ኢትዮጵያ ያፍሪካ መቀ

መጫ የመሆኗን ጉዳይ አፀደቀ፡፡ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት ተመለስሁ፡፡ የኮንደሚኒየማችን

ዘበኛ በሞባይላቸው ላይ ካርድ ለማስገባት እየሞከሩ “አቸቸቸ! አሁን ለትንሽ” ሲሉ አልፊያቸው ገባሁ፡፡ ምሽቱም ቀጠለ፡፡

በዕውቀቱ ሥዩም[email protected]

Page 29: Addis Guday(1)

33 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 30: Addis Guday(1)

34 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 31: Addis Guday(1)

35 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ባህላዊ ዕውቀትም ይሁን ዘመናዊ ሳይንስ ያገቡ ሰዎች ከወንደላጤዎች የተሻለ ረጅም ዕድሜ እና ጤንነት እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡

“ከላጤዎች ጋር ሲነፃፀር ባለትዳሮች ጤናማዎችና እና ለረጅም ዘመን ለመኖር የታደሉ ናቸው” ይላሉ በካሊፎርነያ ዩኒቨርስቲ ሳይኮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ቴዎዶር ሮቤልስ፡፡ “ጥናቶች እንደሚያሳዩት ባለትዳሮች በተለይ ወንዶች ረዘም ላለ ዕድሜ ይኖራሉ፡፡ በልብ በሽታዎች የተነሳ የመሞት ዕድላቸው ከላጤዎች ሲተያይ ያነሰ ነው፡፡ ጤናማ ሰዎች ትዳር የመመስረት ፍላጎት አላቸው” በማለት ትዳር ጤናማ የማድረግ አቅም እንዳለው ይገልጻሉ፡፡

“የሚረዳዱና የሚተጋገዙ ጥንዶች ጤናማነታቸው ከግንኙነታቸው ጋር ተያያዥነት አለው” ይላሉ የኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ባልደረባዋ ዶክተር ጃኒስ ኪኮልት ግላሰር፡፡

ትዳር ለጤና በምክንያት የጥሩ ባህርይ ባለቤት ያደርጋል ጥንዶች በትዳር ሲጣመሩ በአደንዛዥ ዕፅ፣ በሲጋራ፣

እና በሌሎች ለጤና ጎጂ በሆኑ ነገሮች የሚደርሰባቸው ጉዳት እየቀነሰ ይሄዳል፡፡

“አብረው ለመኖር ሲስማው በፈቃደኝነትም ይሁን በትዳር አጣማሪያቸው ጉትጎታ ከነዚህ ሱሶች ስለሚታቀቡ ወይንም አወሳሰዳቸውን ስለሚቀንሱ የሚከሰት ነው” ይላሉ በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሳይኮሎጂስት እና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ክርስቶፈር ፍገንደስ፡፡

ማህበራዊ ግንኙነት“ባለትዳር ከሆንክ/ሽ እስከ አሁን ከፈጠርካቸው/

ሻቸው ግንኙነቶች በጣም መቀራረብ የሠፈነበት እንደሆነ ትረዳለህ/ሽ፡፡ ይህ ማለት በማንኛውም ወቅት የምትፈልገውን/ጊውን እገዛ እና ድጋፍ ሊያደርግልህ/ሽ የሚችል ሰው አለህ/ሽ ማለት ነው፡፡” ይላሉ ዶ/ር ጃኒስ፡፡

“በሌላ በኩል ደስተኛ ያልሆኑ ሰዎች ከማህበራዊ ኑሮ የተገለሉ ይሆናሉ፡፡ ይህም ወደ ድብርት ይመራቸዋል፡፡ የጤንነታቸውን ሁኔታም አይከታተሉም” ሲሉ በኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ ሳይኪያትሪስት የሆኑት ዶክትር ሱዴፕታ ቫርማ ይናገራሉ፡፡

ጤናማ ልምዶችን ያዳብራሉባለቤትዎ ጤናማ ልምዶችን እንዲያዳብሩ ሊረዱዎ

ይችላሉ፡፡ “ባለቤትዎ በእርስዎ ባህርይ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራሉ፡፡ ይህን መመገብ የለብህም/ሽም፤ አልኮል ቀንስ/ሺ ወዘተ የሚሉት ከዚህ በጎ ተፅዕኖ የሚመነጩ ናቸው” ይላሉ ዶክተር ቴዎዶር ሮቤልስ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በትዳራቸው ደስተኛ የሆኑ ሰዎች የዶክተሮቻቸውን ትዕዛዝ እንደሚያከብሩ አንድ ጥናት ይገልፃል፡፡

ከሚወዱት ሰው ጋር ለረጅም ጊዜ መኖርዎ ሌሎች የጤና ጠቀሜታዎችም አሉት፡፡ “አብዛኞቻችን ከፍቅረኞቻችን ጋር ለመዝናናት መኖራችን በጎ ጎን አለው፡፡ በትዳር ተጣምሮ መኖር ከሚያስገኘው ጋር ሲወዳደር ግን አነስተኛ ነው” ዶክተር ክርስቶፍር

“ከትዳር የምናገኘው ፍቅርና መተጋገዝ ለራሳችን የምንሰጠውን እንክብካቤ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ ይህ የሚሆነው የትዳር ተጣማሪያችን በኛ ደስተኝነት ላይ የማይተካ ሚና ስላለው ነው” በማለት ዶክተር ቫርማ የትዳር ጥቅም ከፍተኛ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ቀለበት ማጥለቅ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ የተሻለ ትዳር ማለት የተሻለ ጤና ማለት ነው፡፡ የልብ ቀዶ ጥገና ከተደረገላቸው በሽተኞች ውስጥ በጥሩ ትዳር ውስጥ ያሉት የመዳን ዕድላቸው ከሌሎቹ የተሻለ እንደሆነ ከ15 ዓመታት በላይ የተካሄደ አንድ ጥናት ያስረዳል፡፡ ፍቅርና ደስታ በራቀው ትዳር ውስጥ የሚኖሩ በሽተኞች የመዳን እና በቶሎ የማገገም ዕድላቸው

Fopp

ጎርደን ሞንትጎመሪ ስኮትላንድ ግላስኮ በሚገኘው የቨርጂን ሬከርድስ መደብር የአካባቢ ማኔጀር ሆኖ ሲሰራ የራሱን የአልበም መሸጫ ለማቋቋም በማሰብ ከገበያ ውስጥ በርካሽ ዋጋ አልበሞችን እየገዛ መሠብሠብ ጀመረ፡፡ ይህ በጎን ለመስራት ያሰበው ሥራ በአለቆቹ ስለተነቃበት ሁለት አማራጭ ተሰጠው፡፡ የግል ቢዝነስ ሃሳቡን መተው ወይንም የ3 ወር ክፍያውን ተቀብሎ ስራውን መልቀቅ፡፡ ለቀናት ካሰበበት በኋላ ነፃነቱ መረጦ ሥራውን ለቀቀ፡፡

ኮቨንትሪ በተሰኘው ስፍራ ከሠራተኛው መደብ ወላጆች የተገኘው ሞንትጎመሪ ከወላጆቹ ስምንት ልጆች ሰባተኛው ነበር፡፡ አባቱ የመንገድ ሠራተኛ ሲሆን ቤተሰቡ ሁሌም በዕዳ እንደተዘፈቀ ነበር፡፡

የ16 ዓመት ልጅ እያለ ቅዳሜ ቅዳሜ በHMV የሪከርድ መደብር በሽያጭ ሠራተኝነት ማገልገል ጀመረ፡፡ የሚገኘው ገንዘብ ከትምህርቱ በለጠበትና የሙሉ ሠዓት ሠራተኛ ሆነ፡፡ አባቷ ቤተሰቡን ጥሎ ሲሄድ ጎርደንም ቤት ተከራይቶ ወጣ፡፡

በየጊዜው ገንዘብ ያጥረው ስለነበርም ይህን ችግር ለመፍታት እድገት ማግኘት ዋናው ነጥብ እንደሆነ ያምን ነበር፡፡ የተለያዩ የሥራ ማስታወቂያዎች ላይ ሲያመለክት ከቆየ በኋላ የሚሠራት መደብር ማኔጀርና ረዳቱ በድንገት ስራ ለቀቁ፡፡ ጎርደንም በ17 ዓመቱ ተጠባባቂ ማኔጀር ለመሆን በቃ፡፡ አዲስ አለቃ ተሹሞ ከመጣ በኋላ ከጎርደን ጋር ሊጣጣሙ ስልቻሉ ስራ ለቆ በቨርጅን የሙዚቃ መደብር ተቀጠረ፡፡ በቀጣይ ጥቂት ዓመታትንም በሀገሪቱ በሚገኙ የቨርጂን መደብሮች እየተዘዋወረ ከሠራ በኋላ ወደ ማኔጀርነት አደገ፡፡

የራሱን መደብር ለመክፈት ሲል ስራውን ከለቀቀ በኋላ ተቆጭቶ እንደነበር ይናገራል፡፡ “ቨርጂን ሬከርድስ እያለሁ በሳምንት እስከ 200 ፓውንድ አገኝ ነበር፡፡ የራሴን ሱቅ ከከፈትኩ በኋላ በሳምንት 75 ፓውንድ ብቻ ሳገኝ ምነው ስራዬን ባለቀቅሁ ኖሮ ብዬ ነበር” ይላል፡፡

ደንበኛ ለማፍራት ሲልም ከድሮ ሙዚቃዎች ጎን ለጎን አዲስ የወጡ አልበሞችንም ከጎን በከፈተው ሱቅ መሸጥ ጀመረ፡፡

ለሁለት ዓመታት ከሥራ በኋላ ደንበኛ የሙዚቃ ሱቅ በመክፈት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኘት እንዳለበት ወሰነ፡፡ በዚህ መሠረትም ከአንድ የቻይና ሬስቶራንት ስር የሚገኝ ሱቅ በሊዝ ተከራየ፡፡

የፐንክ፣ ሶል እና ጃዝ ሙዚቃዎችን የሚሸጠው መደብር ትልቁ ስኬቱ ሆነ፡፡ በጥቂት ጊዜ ውስጥም ድሮ ከሚሸጠው በሦስት እጥፍ የላቁ አልበሞችን ለመሸጥ ቻለ፡፡

ነገር ግን በሊዝ የያዘው ቦታ ችግር አመጣበት፡፡ “ሱቅ ለማግኘት ተጣድፌ ስለነበር ሊዙ ሊያበቃ ስድስት አመት የቀረበው ቦታ ነበር የተከራየሁት፡፡ የሊዙ ጊዜ ሲያልቅ ቦታውን አድሶ ማስረከብ የኔ ግዴታ ነበር፡፡ ከላይ ያለው የቻይና ሬስቶራንት ሽንት ቤት ያፈስ ስለነበር ሱቁን በብዙ ገንዘብ አድሼ ብገነባም የውል ጊዜው ሲያልቅ ቀድሞ እንደነበረው አድርጌ ማስረከብ ስለነበረብኝ 40ሺ ፓውንድ አስወጣኝ፡፡ ባንክ ባያበድረኝ ከስሬ ነበር፡፡” ይላል፡፡ በግላስኮ ያገኘውን ስኬት በኤደንብራ ለመድገም አልሞ ሱቅ ቢከፍትም ለ15 ወራት ያህል ኪሳራ እንጂ ትርፍ አላገኘም ነበር፡፡ ቀስ በቀስ አንዱ ለሌላው እየነገረ ገበያ ሲደራለት ሌሎች ሦስት መደብሮችን ከፈተ፡፡

በ1990ዎቹ አጋማሽ ሌላ ችግር ተደቀነበት፡፡ “ባለቤቴ ወደ ኮቨንትሪ ተመልሳ ከወላጆቿ አቅራቢያ ለመኖር ስለፈለገች ወደዚያው ሄደን መኖር ጀመርን፡፡ ነገር ግን ስራዬን ቀነስ ለቤተሰቤ የምሠጠውን ጊዜ ጨመር እንዳደርግ ፈለገች፡፡ የዚህ አይነቱ ሥራ ከደም የተዋሃደ ስለሆነ ችግሮች እያፈጠጡ መጡ፡፡ ኋላም ተለያየን”፡፡ ይላል፡፡

ከባለቤቱ ሲለያይ ያለውን ሁሉ በማጣቱ እንደ ልጅነቱ አንድ ክፍል ቤት ተከራይቶ ለመኖር ተገደደ፡፡ በጊዜ ሂደትም ወደስራው ተመለሰ፡፡ አሁን ግን የቢዝነሱን አደጋ ለብቻው መጋፈጥ ስላልፈለገ ድርጅቱን FOPPን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በማድረግ 40 ከመቶ ድርሻውን ሸጠው፡፡ በ2006 FOPP በመላው እንግሊዝ 25 መደብሮች ነበሩት፡፡ ዓመታዊ ሽያጩም 38 ሚሊዮን ፓውንድ ይጠጋ ነበር፡፡ ችግርን በጥረቱ ከማምለጥ አልፎ ሚሊየነር ለመሆን የበቃው ጎርደን ሞንትጎመሪ ስራውን ለልጆቹ አስተላልፎ ጡረታ ለመውጣት ቢያስብም የስራ ፍላጎቱ እንደማያስችለው ይናገራል፡፡

ጎርደን ሞንትጎመሪMy big idea

ባለትዳር መሆን የተሻለ ጤንነት እንዲኖረን ያደርጋል?

ዝቅተኛ እንደሆነም ጥናቱ ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡ለዚህ የተሰጠው ዋነኛ ምክንያት መጥፎ ትዳር

ለከፍተኛ ጭንቀት የሚዳርግ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የበሽታ መከላከል አቅምን ክፉኛ ያዳክማል፡፡ በተለየ ሴቶች ለዚህ ዓይነቱ ጭንቀት ተጋላጭ ናቸው፡፡ በትዳር ላይ በሚጋጥም ጥላቻ (ያለ መወደድ ስሜት) ሴቶቹ ስሜተ ስስ መሆናቸው ለችግር አጋልጧቸዋል ይላሉ ዶክተር ጃኒስ፡፡

ዶክተር ጃኒስ እና የጥናት ቡድናቸው በምርመራ ክፍሎች ውስጥ ጥንዶች ባስቀመጡት ስውር ካሜራ ሲጨቃጨቁ ሁኔታውን በመቅረፅ ለማጥናት ሞክረዋል፡፡ “በክርክርና ባለመስማማት ወቅት ጥላቻን የሚያሳዩ ጥንዶች ጭንቀትን የሚያባብሱ ሆርሞኖች መጨመር ታይቶባቸዋል፡፡ የቃላት መቋሰሉ ከፈጠረው ህመም ለመዳንም ብዙ ጊዜ ይወስድባቸዋል” ብለዋል፡፡

ጠቅለል ተደርጐ ሲቀመጥ ከባድ የትዳር ችግር ያለባቸው ሰዎች የበሽታ መከላከል አቅም ሊዳከም ይችላል፡፡ የትዳር የጤናማነት ሁኔታ ወንዶችንም የጤና ችግር ሊያስከትልባቸው ይችላል፡፡

“በጥናታችን እንደደረስንበት ከሆነ ድብርት፣ አለቅጥ ክብደት መጨመር እና ከፍተኛ የደም ግፊት ደስተኛ ባልሆነ ትዳር ውስጥ በሚኖሩ ሴቶች ላይ ይታያሉ፡፡ ነገር ግን ወንዶች ትዳራቸው በሚፈጥርባቸው ብስጭት የአደንዛዥ ዕጾች ሱሰኛ ከሆኑ ተመሳሳይ የጤና ጉድለት ሊያገጥማቸው ይችላል” ሲሉ ዶክተር ቫርማ የችግሩን ስፋት ያስረዳሉ፡፡ እንደሳቸው እምነት ሁለቱም ፆታዎች ደስታ የራቀው ትዳር በሚያስከትላቸው አለመመቸቶች ይጠቃሉ፡፡ ይሁንና የሚያሳዩት የጉዳት መጠን ግን የተለያየ ነው፡፡

ብቸኞችአንድ ሰው ብቸኛ (single) ነው ሲባል ከሌሎች

ጋር የቅርብ ወዳጅነት መመስረት አይችልም ማለት አይደለም፡፡ ሌሎች ደግሞ ለፍቅር የሚሆናቸውን ሰው ባለማግኘታቸው ብቸኛ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ዋነኛው መፍትሔ ጥሩ ጓደኞችን ማፍራት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ሊያስቡልዎና ሊጠነቀቁልዎ እርስዎም ተመሳሳዩን ሊያደርጉላቸው ይችላሉ፡፡ ይህ ዓይነቱ ራስን በጥሩ ሰዎች መሃከል ማኖር ትዳራቸውን በፍቺ ለበተኑ ሰዎችም ይሠራል፡፡

ፍቺ ካለዕድሜ ከመሞት ጋር ተያያዥነት እንዳለውና በተለይ በወንዶች ላይ በስፋት እንደሚታይ የአሪዞና ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ዴቪድ ስባራ ይናገራሉ፡፡ “በዕድሜ በሰል ካሉ ሰዎች ውስጥ ከፍቺ በኋላ በደስታ የተሞላ ህይወት ሲመሩ የሚታዩ ይኖራሉ፡፡ ደስታ በራቀው ትዳር ውስጥ ካሉና ትዳርዎ እንዲሠራ የሚችሉትን ያህል ከለፉ በኋላ ተስፋ እንደሌለው ካወቁ ፍቺ ምክንያታዊና አምነን መቀበል ያለብን አማራጭ ይሆናል፡፡ ተፋትተው ደስተኛ ሆነው መኖር ከቻሉ ፍቺ የሚያመጣቸው ጐጂ ጐኖች ሊያሳስብዎ አይገቡም” ይላሉ ዶክተር ዴቪድ፡፡

ከፍቺ በኋላ ሴቶች ከወንዶች በተሻለ መልኩ ጥሩ ስሜት ሊሰማቸው ይችላል፡፡ “ላጤዎችን እና የጤናቸውን ሁኔታ ስናይ ሴቶቹ ከወንዶቹ በተሻለ ጤንነት ላይ ይገኛሉ፡፡” የሚሉት ዶክተር ክርስቶፈር ባለትዳሮች ወይንም አብረው የሚኖሩ ፍቅረኞች ለመስማማት በማይችሉበት ወቅት በአክብሮት ያለ ዘለፋ እንዲነጋገሩ ይመከራል፡፡ ጥላቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚንፀባረቅበት ክርክርና ጭቅጭቅ ለጤና ጉዳት ያጋልጣል፡፡ በተገቢው ሁኔታ መነጋገር ሲባል ማዳመጥ፣ መስጠት፣ ቅድሚያ መስጠት እና የተናጋሪውን ስሜት መረዳትን ያጠቃልላል፡፡ በሰው ልጆች ውስጥ ያለው ትልቁ ፍላጐት ለመወደድ መንሰፍሰፍ ሲሆን እውቅና ማግኘት ደግሞ ሌላው ነው፡፡ ይህን ካደረጉ “እያዳመጥኩህ/ሽ ነው” የሚል መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ይህ አይነቱ መተሳሰብ የትዳር ችግሮቻችሁን በቀላሉ ለመፍታት እና ለመስማማት ያስችላችኋል፡፡

Page 32: Addis Guday(1)

37 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

አሜሪካ ከመጣኹ ከሰማዃቸውና ካወቅዃቸው አዳዲስ ባህሎች መካከል በእንግሊዝኛው “Baby shower” የሚባለውና ሕጻናት ለመውለድ ዝግጅት ለሚያደርጉ ነፍሰ ጡሮች የሚደረገው የሥጦታ ባህል አንዱ ነው። “ሻወር” የተባለው ነፍሰ-ጡሯ ሥጦታዎች እንደ ዝናብ/ እንደ ውኃ እንደሚርከፈከፉላት ለማሳየት የተጠቀሙበት ቃል ነው። ስለ “ቤቢ ሻወር” ያነበብኳቸው ጽሑፎች እንደነገሩኝ ከሆነ በጥንቱ ዘመን ሥርዓቱ የሚዘጋጀው የመጀመሪያ ልጆች ሲወለዱ ሲሆን በዓሉ በዋነኝነት የሴቶች ብቻ ዝግጅት ነበር። ይሁን እንጂ በሒደት ቀጥለው ለሚወለዱ ልጆችም ቢሆን “ሻወሩን” ማዘጋጀቱ ቀጥሏል።

ይህ ለነፍሰ-ጡሮች የሚዘጋጅ ዝግጅት በቤተሰብ አባላት ሳይሆን በቅርብ ጓደኞች እና ወዳጆች የሚከናወን ሥርዓት ነው። ዓላማው አዲስ እንግዳ “ሕጻን” ለመቀበል ሽር ጉድ የሚሉ ወላጆችን ለመርዳት እና ወጪያቸውን ለመጋራት በሚል ይከወናል። ዝግጅቱን የቤተሰብ አባል አያዘጋጀውም፤ ምክንያቱ ነገሩ እንደ ልመና እንዳይታይ ነው። ይህንን ለማስቀረት እንግዲህ ማንኛውም ከቤተሰብ ውጪ ያለ የቅርብ ሰው፣ ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት ያዘጋጀዋል ማለት ነው።

ቀደም ባለው ጊዜ ይኸው “የቤቢ ሻወር” ዝግጅት ሕጻኑ ከመወለዱ አንድ እና ሁለት ወር ቀደም ብሎ ማዘጋጀት የተለመደ ጉዳይ ነበር። እናቲቱ ከመውለዷ ቀደም ብሎ ማዘጋጀቱ የሚያስፈልግበት ምክንያት እናቲቱ የምትገዛቸው ዕቃዎች ካሉ ድግግሞሽ እንዳይኖር፣ የገዛቻቸውም ካሉ በጊዜው እንድትመልስ እና ገንዘብ እንድታተርፍ ለማድረግ በማሰብ ነው። በእርግጥም ሥጦታዎቹ ለአንድ ሕጻን የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት የሚደረግ እንደመሆኑ ወዳጆች እና ጓደኞች በሚያቀርቡት ሥጦታ ወላጆች ለብቻቸው ለመሸፈን ቢሞክሩ ብዙ ወጪ ሊያስወጣቸው የሚችል የተለያየ ቁሳቁስ ማግኘት ያስችላቸዋል።

“ቤቢ ሻወር” የሚዘጋጅበት ቦታ የወዳጆች ቤት፣ ሬስቶራንት ወይም ቤተ እምነቶች ሆነው የቆዩ ቢሆንም በአሁኑ ዘመን ግን በማንኛውም መዝናኛ ቦታዎች፣ በመዝናኛ ፓርኮች እና ሰዎች ሊሰባሰቡባቸው ምቹ በሆኑ በማንኛውም ቦታዎች ይደረጋል። ተመራጩ ግን ዞሮ ዞሮ “ዝግጅቱን በሚያዘጋጁት ወዳጆች ቤት” ቢሆን ነው።

ዝግጅቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ታዳሚዎች ይጠራሉ። ጥንት ጥንት በዓሉ የሴቶች ብቻ እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን የነፍሰ-ጡሯ ባልም “ሥራ በማገዝ ሰበብ” ታዳሚ የሚሆንበት ሁኔታ አለ። እንደ ዋና እንግዳ ግን አይቆጠርም። በመካከል የወንዱን መገኘት ሴቶቹ እንደ ነውር ነው የሚያዩት።

የዝግጅቱ ወጪ “ሻወሩን” በምታዘጋጀው ወዳጅ የሚሸፈን ሲሆን ሌሎች ታዳሚ የነፍሰ ጡሯ ጓደኞች ደግሞ የተለያየ ሥጦታ በመያዝ ይመጣሉ። በተለይም የመጀመሪያ ልጅ እና የእናቲቱ የመጀመሪያ “ቤቢ ሻወር” ከሆነ ሥጦታው የዚያኑ ያህል ከፍ ያለ ግምት ይሰጠዋል። ሁለተኛ ልጅ እና ድጋሚ “ቤቢ ሻወር” በሚሆንበት ጊዜ ግን ሥጦታ አቅራቢ ወዳጆች ራሳቸው የመሰላቸውን ይዘው መምጣት ይችላሉ።

ቴክኖሎጂው ባደገበት በአሁኑ ዘመን ደግሞ የሕጻናት ዕቃ የሚያቀርቡ ድርጅቶችም አሠራራቸውን ለቤቢ ሻወር ባህሉ የተመቸ አድርገውታል። ለምሳሌ ያህል ነፍሰ ጡሯ ሴት የምትገዛቸውን ዕቃዎች ዝርዝር ካወጣች በኋላ ሥጦታ መስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ከዚያው ዝርዝር ላይ የራሳቸውን ፈንታ በመውሰድ እና በማዘዝ ቀላል በሆነ መንገድ ድግግሞሽን በማስቀረት እና ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት በመጠቀም ድካም ቀናሽ ዝግጅት ያደርጋሉ።

ቤቢ ሻወር

ኤፍሬም እሸቴ[email protected]://www.adebabay.com

- ከዩ ኤስ አሜሪካ፣ ሜሪላንድ

በጥንቱ ዘመን የሚወለደው ሕጻን ጾታ ቀድሞ ካለመታወቁ ጋር ቤቢ ሻወር ለማድረግ ምን ዓይነት ቀለም ያለው ዕቃ (ወንድ ከሆነ ቀይና ተመሳሳዮቹ፤ ሴት ከሆነች ሮዝ እና ተመሳሳዮቹ)፣ ለወንድ ይሁን ለሴት ልጅ የሚሆን መጫወቻ፣ ሱሪ ወይስ ቀሚስ የሚለውን ለመምረጥ ይቸገሩ ኖሯል። አሁን ግን (ከተወሰኑ ወላጆች በስተቀር) አብዛኛው የልጁን ጾታ ቀድሞ አውቆ፣ ተዘጋጅቶ ይጠብቃል። አዲሱ እንግዳ የሚያስፈልገው ነገር ቀድሞ ይዘገጃጅለታል። ይህ የቤቢ ሻወር ባህላቸው በተለይም ከመረዳዳት አንጻር ስንመለከተው በጣም ጥሩ ሆኖ አግኝቼዋለኹ። ከአንድ ብርቱ ሁለት መድኀኒቱ እንዲሉ ማለት ነው።

በነገራችን ላይ፣ ልክ እንደ ሕጻናቱ ሁሉ፣ ለአዳዲስ ተጋቢዎች እንዲጠቅም በሚል ሴቶቹ “ብራይዳል ሻወር” የሚባል ሙሽሪትን በገጸ በረከት የማንቆጥቆጥ ሥርዓት አላቸው። ለጊዜው ዕድሉ ገጥሞኝ ስላልተመለከትኩ ብዙ ልልበት አልችልም። በሌላ ጽሑፍ፣ ሴቶቹንም ጠይቄ ቢሆን፣ ላካፍላችሁ እሞክራለኹ።

ሐሳቤን ስቀጥል… በአገራችንም ቢሆን እንዲህ የመረዳዳቱ ባህል ጥሩ መሠረት አለው። በሠርግ እና በለቅሶ መደጋገፉ የተለመደ ነገር ነው። በእርሻ እና አረማ፣ ቤት በመሥራትና በጎጆ መውጣት መተጋገዙ የተለመደ ነው። ይህም ከብሔረሰብ ብሔረሰብ የተለያየ መልክ አለው። በደምሳሳው ግን መተጋገዙ እንዳለ እርግጥ ነው። ሕጻን ሲወለድ እንዲህ በኅብረት ተዘጋጅቶ መጠበቁ ላይ ስላለን ሰፊ ባህል የማውቀው የለም። ሲወለድ ከምናደርገው ዝግጅት ይልቅ ሲሞት ለቀብር የምናደርገው ይበልጣል ብል ከስድብ የሚቆጥርብኝን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቄዋለኹ።

ሞትም ቢሆን ከዚህኛው ዓለም ወደዚያኛው የምንሸጋገርበት ክቡር-ፍኖት ስለሆነ ሊከበር ይገባዋል። ኢትዮጵያውያን ለሙታን ክብር ቢሰጡ ያስመሰግናቸዋል እንጂ ሊያስወቅሳቸው አይገባም። ሰው ሞተ ማለት ጥቅም የሌለው ውዳቂ ቆሻሻ ሆነ ማለት አይደለም። ሰው ሊከበር የሚገባው ቆሞ ሲንቀሳቀስ ብቻ ሳይሆን ነፍሱ ከሥጋው ከተለየ በኋላም ቢሆን ጥሎ ስለሄደው አሻራ፣ በምድር ስለሠራው ሥራ ሊከበር ይገባዋል። ሙታንን ማክበር ለቋሚው የኑሮ ማጽናኛም ነው። ሙትን ማጎሳቆል ለኑሮ የሚኖርን ጣዕም አጥፍቶ ሰብዓዊ ርኅራኄን ያሳጣል።

ኤፍሬም እሸቴ በዩ ኤስ አሜሪካ፣ ሜሪላንድ ግዛት፣ ሲልቨር

ስፕሪንግ መኖርያውን ያደረገ ጸሐፊ ነው፡፡ በሃይማኖታዊ እና

ባህላዊ ጉዳዮች ላይ ጽሑፎችን እና መጻሕፍትን አበርክቷል፡፡

ቅዱስ መጽሐፍ “ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው” ካለ በኋላ “ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል” (መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ 3 ቁጥር 2 እንዲሁም ምዕራፍ 7 ቁጥር 1) ሲል “የሞተ-አረፈ” ይለናል። ይህ ማለት ግን ከእናቱ ማኅፀን በልቅሶ ወደዚህ ዓለም የመጣው ሕጻን ኑሮው ሁሉ በዕንባ የራሰ፣ በመከራ የታጀለ እንዲሆን ፍረዱበት ማለቱ እንዳልሆነ ግልጽ ነው።

አንዳንድ ጊዜ ለሙታን ክብር የምንሰጠውን ያህል ለቋሚው አለመጨነቃችን፣ በከተሞች አካባቢ ባሉ የመቃብር ሥፍራዎች የምናየው ዓይነት ብሔረ-ሙታንን፣ የመቃብር ሥፍራዎችን አለማክበራችን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ስሜት ያጭርብኛል። ባይሆን የጥንቱ መጽናኛችን የሚወለደውን ከቁብ ባንቆጥረውም ለሚሞተው ማዘናችን ነበር። አሁን ታዲያ ለሚወለደውም ሳንጨነቅ፣ ለሚኖረውም ሳንሳሳ፣ ለሚሞተውም ክብር ሳንሰጥ ስንታይ የሕይወት ትርጉማችን ግራ ያጋባል። የሰው ሕይወቱ ሲወለድ ያለው አቀባበሉ፣ ሲኖር ያለው ክብሩ፣ ሲሞት ያለው ሽኝቱ ነው። ሲወለድ “በዕድሉ እንዲያድግ ተፈርዶበት”፣ ሲኖር በገዢዎች ተረግጦ፣ ሲሞት አስከሬኑ እንኳን ክብር አጥቶ ከሆነ ኑሮው ከመ-እንስሳት መሆኑም አይደል?

ማንኛውም ጤናማ ማኅበረሰብና አገር ለሕጻናት፣ ለወጣቶች፣ ለሴቶች እና ለአረጋውያን በሚሰጠው ቦታ፣ ክብር እና አያያዝ ይታወቃል። ሕጻናቱን በጥሩ ሁኔታ የሚንከባከብ ከሆነ፣ ወጣቶች ያላቸው አካሄድ እና አኗኗር ትልቅ ግምት ተሰጥቶት በሚያስፈልጋቸው ሁሉ የሚያግዛቸው አገር ከሆነ፣ ሴቶች እና አረጋውያን እንደ ሁለተኛ ደረጃ ዜጎች የማይታዩ ከሆነ የዚያ ማኅበረሰብ ጉዞ በውስጡ ያሉትን ሰዎች ማንነት የሚንከባከብ ለመሆኑ መስተዋት ነው።

ልጆች ሆነን የምንጫወትባቸው ብዙ ሜዳዎች ነበሩን። ሣር ባይኖርባቸው እንኳን አቧራቸውን እያቦነንን የጨርቅ ኳሳችንን የጠለዝንባቸው ቁርጥራጭ መሬቶች ዛሬ ለመተንፈሻ እንኳን ቀዳዳ ሳያገኙ ቤቶችና ቅራቅንቦዎች ተገጥግጠውባቸዋል። ሕጻናት ከቤታቸው ቢወጡም የልጅነት መብታቸውን (መሮጥ፣ መንጫጫት፣ መጯጯህ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር መዛለል) ለማከናወን የሚያስችላቸው አንዳችም ቦታ አያገኙም። ሕንጻ መሥራት መልካም ቢሆንም የበሬ ግንባር የምታክል ክፍት የመጫወቻ ቦታ ለማግኘት ከከተማ ለመውጣት የሚያስገድድ ዓይነቱ ሥርዓት የለሽ የመሬት ሽሚያ ግን ለትውልድ አለማሰብ ነው። ቤቢ ሻወሩ እንኳን ቢቀር ሮጠው የሚያድጉበት ሠላማዊ መንደር ልንነፍጋቸው አይገባም።

ወደ ርዕሰ ጉዳያችን ልመልሳችሁና፣ አገር ቤት “ቫለንታይን ዴይ” ከየካቲት 12 የበለጠ መከበር እንደጀመረ ወዳጆቼ በፌስቡክም፣ በስልክም ነግረውኛል። “ቤቢ ሻወር” ደግሞ የሚያደማምቃት ኤፍ.ኤም፣ የሚያንቆለጳጵሳት መጽሔትና ዕድል ያገኘች ቀን የሚወለዱ አዳዲስ ሕጻናት ተንበሸበሹ ማለት ነው። የቴክኖሎጂ ብቻ ሳይሆን የባህል ሽግግርም አለ ማለት ይኸው አይደል? ከሆነ አይቀር መረዳዳትን የሚያጠነክረውን፣ በተለይም ምኑንም ምኑንም ለማያውቁ ሕጻናት የሚሆነው እንዲህ ያለውን የዘመናዊ “ማርያም በሽልም ታውጣሽ” ሥጦታ ብንጠቀምበት አይጎዳንም።

...አንዳንድ ጊዜ ለሙታን ክብር የምንሰጠውን ያህል ለቋሚው አለመጨነቃችን፣

በከተሞች አካባቢ ባሉ የመቃብር ሥፍራዎች የምናየው ዓይነት ብሔረ-ሙታንን፣ የመቃብር ሥፍራዎችን አለማክበራችን

እርስ በእርሱ የሚጣረስ ስሜት ያጭርብኛል። ባይሆን የጥንቱ

መጽናኛችን የሚወለደውን ከቁብ ባንቆጥረውም

ለሚሞተው ማዘናችን ነበር። አሁን ታዲያ ለሚወለደውም

ሳንጨነቅ፣ ለሚኖረውም ሳንሳሳ፣ ለሚሞተውም ክብር

ሳንሰጥ ስንታይ የሕይወት ትርጉማችን ግራ ያጋባል...

Page 33: Addis Guday(1)

38 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 34: Addis Guday(1)

39 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 35: Addis Guday(1)

40 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 36: Addis Guday(1)

41 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 37: Addis Guday(1)

42 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 38: Addis Guday(1)

43 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 39: Addis Guday(1)

44 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

ድርሰት - ኤ.ሲ. ቲልየርተርጓሚ - አንዳርጋቸው ቢምረው

ልቦለድ

በርካታ ደሴቶችን የያዘ በደቡብ ባህሮች አቅራቢ የሚገኝ ሥፍራ አለ፡፡ አርቺፔላጎ ይሉታል— ተጎራባች ደሴቶች እንደማለት ነው፡፡ የአየር ፀባዩ መልካም፣ መሬቱ ለም፣ እንዲሁም ባህሩ በዓሣ ሃብት የበለጸገበት አካባቢ ነው፡፡

ታዲያ በእያንዳንዱ ደሴት ላይ ዝርያቸው የተለያየ ሰዎች ይኖሩበታል፡፡ እነዚህ ሰዎች አቋማቸውና መልካቸው የተመሳሰለ ቢሆንም ወግና ባህላቸው ግን በጣም ይለያያል፡፡ አኗኗራቸውም እንዲሁ ለየቅል ነው፡፡ የሚያመሳስላቸው ነገር አለ ከተባለ ከአካባቢው መልክዐ ምድር ጋር ፍጹም የሚቃረን የአገነባብ ዘይቤ የሚከተለው የቤት አሠራራቸው ብቻ ነው፡፡

ለምሳሌ በአለታማ ኮረብታ ላይ የእንጨት ጎጆዎችን ይሰራሉ፤ በጫካ ቦታ ላይ ደግሞ ከአለት የተወቀሩ ቤቶችን ይገነባሉ፤ ምድረ-በዳ አካባቢን በመስኖ አትክልት በአትክልት ያደርጋሉ፡፡ ለምለም መሬትን በድንጋይ ጠብጥበው መናፈሻ ያደርጉታል፤ ንፋስ በሚበዛበት ጉድባ ላይ ድንኳን ይዘረጋሉ፤ ተክሎች በሚበዙበት ቦታ ላይ ግን ጠንካራና ጥብቅ ቤቶችን ይገነባሉ፡፡

በእርግጥ ከልዩነታቸው ውጭ ሁሉም በሠላም ይኖራሉ፡፡ አልፎ አልፎ በዓሣ ማስገሪያ ቦታና በስፖርት ማዘውተሪያዎች አካባቢ የሚነሳ ፀብ ቢኖርም ኃይለ ቃል ከመወራወር አልፈው አያውቁም፡፡ ሁሉም በራሱ አካባቢ ቢኖርም ለንግድ ሲባል አልፎ አልፎ መገናኘታቸው አልቀረም፡፡

ከነዚህ በርካታ ደሴቶች ውስጥ አንዷ በተለይም ምርጧ ቦታ እንደሆነች የምትቆጠረው ደሴት ለበርካታ ዓመታት ከሌሎቹ ተገልላ ኖራለች፡፡ ደሴቷ ጥሩ መሬት፣ በቂ የመጠጥ ውሃ፣ ሁለት ተፈጥሮ

የሰራቻቸው ወደቦች እና መልካም የአየር ንብረት ቢኖራትም ለምን ሰው እንደማይኖርባት በግልፅ የሚነገር ምክንያት የለም፡፡ በደሴቷ ሰማይ ወፍ አይዞርም፤ በምሽትም የሚታይ መብራት የለም፡፡ ዝም ጭጭ— ጸጥ እረጭ ያለች ስፍራ ነች፡፡

በርግጥ ድሮ እንዲህ አልነበረችም፡፡ ደሴቷ እንደሌሎቹ ደሴቶች ገበሬዎችና ዓሣ አስጋሪዎች ይኖሩባት ነበር፡፡ ነዋሪዎቿ ደማቅ ጀልባዎችን በመቅዘፍና የሚያስገርም የመጥለቅ ጥበብ በማሳየት የታወቁ ነበሩ ይባላል፡፡ ከመሸ በኋላ እንኳን መዋኘት የሚወዱ፣ የባህር ምግብ አዘውትረው የሚመገቡ፣ ጥሩ ወይን ጠማቂዎችና ቤታቸውን ለመጠበቅ የማይጨነቁ አይነት ሰዎች ነበሩ፡፡ ገና በልጅነታቸው የሚያገቡና በጣም አርጅተው የሚሞቱ እንደነበሩም ይነገራል፡፡

በአንድ ወቅት ግን ይሄን አኗኗራቸውን የሚቀይር ነገር ተከሰተ፡፡ ለምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት ገደሉን በድማሚት አፈራረሱና ግንብ መገንባት ጀመሩ፡፡ ድንበራቸውን በማጠር ብቻ አልቆሙም፡፡ ማጠናከር ፈልገዋልና የመጀመሪያው ግንብ ሲጠናቀቅ ሁለተኛውን ዙር ጀመሩ፡፡ ይኼኛው ግንብ ይባስ ብሎ የጠባቂዎች መመልከቻ ማማ ሁሉ ተጨመረበት፡፡ ሁለተኛ ግንብ ሲጠናቀቅ ደግሞ የሦስተኛው ዙር ሥራ ምሽግ ቁፋሮው ቀጠለ፡፡ የግንብ አጥሮች በበርካታ ዙሮች ስለተገነቡባት ደሴቲቱ ከሩቅ ስትታይ ለሠርግ የተዘጋጀ ኬክ መሰለች፡፡ የደሴቱቱ ነዋሪዎች ግን አጥር በማብዛትና የድንጋይ ካብ በመገንባት የተለከፉ ይመስል አራተኛውን አጥር ማጠር ጀመሩ፡፡

በሌሎቹ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ጎረቤቶቻቸው ለምን አራት ዙር አጥር ማጠር እንዳስፈለጋቸው

ሊገባቸው አልቻለም፡፡ ደሴቱቱን ለማጥቃት የዛተ ምንም አይነት ጠላት የለም፡፡ ከሌላው የዓለም ክፍልም ተወዳጇን ደሴት አጠቃለሁ ያለ ወራሪ ጦርም አልመጣም፡፡ ጠላት ቢመጣ እንኳን የመጀመሪያውን ዙር የግንብ አጥር መጣስ በራሱ ከባድ ከመሆኑም በላይ የሚቻል ነገርም አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው ነገሩ?

እርግጥ ነው የደሴቲቱ ነዋሪዎች ግንብ መገንባት ከጀመሩ አንስቶ ስሜታቸው እየተረበሸ መጥቷል፡፡ ምን እንደሚፈሩና ምንና ለምን እንደሚጠራጠሩ ባያውቁትም ምሽግ ሰሪዎቹ ከዕለት ወደ ዕለት የበለጠ እየፈሩና እየተጠራጠሩ መጡ፡፡ እንዲያውም ዘር የመዝራት፣ ከብት የማሰማራት፣ ልጆችን የመንከባከብና የመዝናናት ነገር እየተረሳ መጣ፡፡ ቅድሚያ የሚሰጠው ግንብ መገንባት ሆነ፡፡

ቀስ በቀስ ደሴቲቱ ፀጥታ እየሰፈነባት መጣ፡፡ እንደነገሩ የነበረው ንግድ ጭራሽ ተቋረጠ፡፡ ወደ ምርጧ ደሴት ለመሄድ የሚፈልግ ጠፋ፡፡ ብዙዎች ለመኖሪያነት እንዳልተመኟት ዞር ብሎ ሊያያት የደፈረ እንኳ የለም፡፡ በዚህ የተነሳ ውበትና ተወዳጅነት ሳይጎድላት ደሴቲቱ ከሌሎች የተለየች ሆነች፡፡ መገለጫዋም የዛጉ ትላልቅ የአጥር ሽቦዎችና የወየበ ግንብ ብቻ ሆነ፡፡

የሌሎቹ ደሴቶች ኗሪዎች ለደሴቲቱ መለወጥ የየራሳቸውን መላምት ያስቀምጣሉ፡፡ አንዳንዶቹ “የምርጧ ደሴት ነዋሪዎች ጊዜያቸውን በመገንባት ስለሚያሳልፉ የሚሸጡትና የሚለውጡት ስላጡ ተሰደዱ” ይላሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ “ ‘ምሽጉን’ በመገንባቱ ሂደት ብዙ ህዝብ ስላለቀ ነው ኗሪ አልባ የሆነችው” በማለት ሃሣባቸውን ይሰነዝራሉ፡፡ እንዲያውም “ይሄ ሁሉ ህዝብ ካለቀ በኋላ መገንባቱን ማቆም ሽንፈት መስሏቸው ነው መገንባቱን ማቆም ያልፈለጉት...” የሚሉም አልታጡም፡፡ ምሽጉን ለመገንባት ብዙ መሬት ስለፈጀባቸው የሚዘሩበት ማሣ ሊተርፋቸው አልቻለም የሚሉም አሉ፡፡ እንዲያውም ጥቂት ሰዎች “አራተኛው አጥር የሞቱ ሰዎች አጥንት ተፈጭቶና ተጋግሮ ነው የተገነባው…” እስከማለት ደረሱ፡፡ ምናልባት የደሴቲቱ ሰዎች ምሽግ በመስራት ስለተለከፉ ስራውን ማቆም አልችል ብለውም ይሆናል፡፡ ምንም ተባለ ምን ትክክለኛውን ነገር የሚያውቅ ሰው ግን ፈፅሞ አልተገኘም፡፡

አንድ ነገር ግን በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ይመጣል ተብሎ የተፈራው ጠላት ባይኖርም የደሴቲቱ ሰዎች ግን በገነቡት ግንብ ራሳቸውን አግተዋል፡፡ የሚበሉት የሚጠጡት እያጠረ ሲሄድም ለበርካታ ወራት ሲገነቡና ሲመሽጉ ይሰማ የነበረው ድምፅም ቀስ በቀስ ፀጥ አለ፡፡

An A-Z Of Possible Worlds የተሰኘ የጎበኘቻቸውን ሀገራት መሠረት ያደረገ መጽሐፍ ካሳተመች በኋላ እየታወቀች የመጣችው ኤሲ ቲሊየር በሙያዋ የዶክመንተሪ ፊልሞች ኤዲተር ናት፡፡ በማንቸስተር ዩኒቨርስቲ እንግሊዝኛን እና ፊሎዞፊን ካጠናች በኋላ ወደ ለንደን በመጓዝ የፊልም ኤዲተር ሆና መስራት ጀምራለች፡፡

ጠላት ሳይኖር ምሽግ

Page 40: Addis Guday(1)

46 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 41: Addis Guday(1)

47 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም

Page 42: Addis Guday(1)

48 አዲስ ጉዳይ የካቲት 2004 ዓ.ም